አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


....የውስጤን ሥቃይና የሕሊናዬን ሰፊ ጠባሳ ጠልቀው ያላዩ የቅርብ
ዘመዶቻችን «ዛሬማ ተበላሽቶ፣ የሱ ነገር እንዲህ ሆኖ ቀረ፡፡ ያየህይራድን የመሰለ
አንበሳ አባት እያለው ወግ ማዕረግ ያለማየቱ...» እያሉ ያጉመተምታሉ፡፡ ከቤት
ውጪ ማደሬ ያለ ማቋረጥ በመዘውተሩ ሁኔታውን መላው ቤተሰብ ከዳር እስከ
ዳር ዐወቀ፡፡ ደግማ ደጋግማ እናቴ እያፈረች፣ እኅቴ በተለይም የእናቴ
ምስጢረኛና የቅርብ ጓደኛ ወይዘሮ አማረች መኝታ ቤት ድረስ እየገቡ፣ ተው
ደግም አይደል የትልቅ ሰውና የጨዋ ልጅ እንዲህ አይደለም፡፡ እናትህ ብታለቅስ
ታደርስብሃለች» እያሉ ለወጉ ያህል ገሠጹኝ፡፡

እኔን የምመክራትና የምዳኛት ወደ ፊትም ሆነ ወደ ኋላ የማስኪዳት እኔው ራሴ ብቻ በመሆኔ የእነርሱን ምክር ሁሉ እንደሚያልፍ የበረዶ ውሽንፍር
ቆጠርኩት። በጠቅላላ መጻሕፍቶቼንና ልብሶቼን ውስጥ ውስጡን አንድ በአንድ
እግዥ ጨረስኩ፡፡ ከሁለትና ከሦስት ቀን አዳር በኋላ ወደ ወላጆቼ ቤት ስገባ ዘና
ብሎ የሚያናግረኝ ሰው አልነበረም፡፡

አባቴም ከቤት ውጪ በተደጋጋሚ ማደሬንና እንደ እናቴም አባባል «መዛተሌን» ቀስ በቀስ ሰማ።

«አግባ! ትዳር ንብረት ያዝ፣ እንደ ማንም የባለጌ ልጅ ሰፈር ለሰፈር
እትልከስከስ፣ ጎጆ ያስከብራል፣ ትዳር ግርማ ሞገስ ነው ያልኩህ ለዚህ ብዬ ነበር፡፡ያለበለዚያ ግን አካለ መጠን ከደረሰ ጐረምሳ ጋር ምን ያታግለኛል» ብሎ
ከነከተቴው ችላ አለኝ፡፡

ዋል አደር ብሎም «አደጋ ብቻ እንዳያገኘው እንጂ ልቡ መለስ
ሲልለትና ያበጠው ልቡ ሲሟሽሽ እንዳረጀች ውሻ ክትት ይላል» አለና ይብሱኑ ስለ እኔ የነበረውን 'አለና የለም ወይ?” እርግፍ አድርጎ ተወ፡፡

የሐሳቤ ተፃራሪ የሆነው አባቴ እንደ አህያ ሬሳ ቢጠላኝም ቅር አላለኝ፡፡ እኔ ግን «ይህ ነው ለሰው ልጅ የሚሰጠው ታላቅ የመኖር ጸጋ ብዬ ከጥላቻው ውስጥ ብርታትና እፎይታ የተሸለምኩ መሰለኝ።
ወደ ወላጆቼ ቤት ባሰኘን ጊዜ ገብቼ ባስፈለገኝ ሰዓት ውልቅ ማለት
ለመድኩ፡፡ እንደ ምኞቴ ሳልዘጋጅና ሳላስበው፣ የኑሮዬንም አዝማሚያ በሚገባ ሳላቅድ ድንገት ባለትዳር በመሆኔ ኑሮ በመጠኑ ተደናገረኝ። ሆኖም ትዳራችን የተመሠረተው በጽኑ ፍቅር ላይ በመሆኑ ፍላጎቴና ጉጉቴ ሁሉ ነጋ ጠባ
ለመሻሻልና አስደሳች ለውጥ ለማግኘት ሆነ። ወትሮ በቀላሉ ደንግጦ ይበረግግ
የነበረው አእምሮዬ የድፍረትና የወኔ ካፈያ ተርከፈከፈበት።

የየወዲያነሽን ቀኝ እጅ ያዝ አደርግና «ዛሬ ምን ያስፈልገናል?» ስላት ዐይን ዐይኔን እያየች እና የኮቴን አዝራሮች በጣቶቿ እየጠራረገች «ካለህማ....ያህል ይበቃኛል» ብላ ገንዘብ ስትጠይቀኝ የትዳርን አያያዝና አመራር ቀስ በቀስ
ለመድነው። በየወዲያነሽ በኩል የተቸገርኩበት ጉዳይ ቢኖር፡ ስትተኛም ይሁን ስትነሣ ስትበላም ይሁን ስትጠጣ አረ ተው ጌታነህ፡ ኧረ ተው! እረ ተው
ልጄን አሳየኝ? ሞቶም እንደሆነ ቁርጡን ንገረኝ ባይኖር ነው እንጂ ቢኖርግ
መቼ እንዲህ ዝም ትለኝ ነበር?» እያለች ስለምትጨቀጭቀኝ ነበር፡፡ ምንም እንኳ
አንዳንድ ነገርን አገላብጠው የማያዩ ቀባጣሪዎች «ጨካኝ አረመኔ ነች» እያሉ
እንደሚያሟትና ወደ ፊትም እንደሚያባጥሏት እያሰብኩ ለጊዜው ብበሳጭም እኔ ከማንም ይበልጥ የእኔዋን እና ቅኗን የወዲያነሽን አሳምሬ ስለማውቃት አባባላቸው ሁሉ ከወሬ እንኳ የነፈሰበት ተራ ወሬ ነው ብዬ እንደ ቤት ጉድፍ ጠራርጌ ጣልኩት።

ያን በማሕፀኗ ዘጠኝ ወር ሙሉ ተሽክማ በስንት የኑሮ ሥቃይ እና ውጣ ውረድ የወለደችውን ልጅዋንና አካሏን ለማየት እያለቀሰች ብታስቸግረኝም
የእናትነት ወጓ በመሆኑ ምንም ቅር አላለኝም፡፡

አንድ ቀን እሑድ ጥዋት ለቁርስ እንደ ተቀመጥን ሳላስበውና
የሚያጋጥመኝን ሳልጠራጠር ከኪሴ እንድ ትንሽ ሰማያዊ ማኅደር አወጣሁ፡፡
በውስጡ የነበሩትን ልዩ ልዩ ሥዕሎች ተራ በተራ ስመለከት የወዲያነሽም
እጅዋን ትከሻዬ ላይ ጣል አድርጋ ትመለከት ነበር፡፡ የልጃችንን ሥዕል ኣየት
እንዳደረገች «ይኸውና» ብላ ባስደንጋጭ ሁኔታ ጮኸች፡፡ ከእጄ ላይ መንጭቃ
ደረቷ ላይ ለጠፈችው።

እነዚያ በእንባ ተኮትኩተው ያደጉት ዐይኖቿ የእንባ ኩልልታ እንጠፈጠፉ፡፡ ሥዕሉን ጠረጴዛው ላይ ወርውራ እግሬ ላይ ዘፍ አለች፡፡ እግሬን ባላት ጠቅላላ ኃይል ቁልቁል ጨምድዳ ስለ ያዘችው ጎትቼ ማላቀቅ አቃተኝ።

«ብዙ ሥቃይና መከራ ያየሁበት፣ ተንገላትቼ የተንከራተትኩበት የበኸር
ልጂ ነውና አለበት ድረስ ወስደሀ እሳየኝ፡፡ እናት አባትሀም ቤት ከሆነ ከሩቅ
ልየው:: ዐይኑን አይቼና ኣንድ ጊዜ ስሜው ልሙት!» ብላ ጫፈ ድልዱሙን
ጥቁር ጫማዩን ዕንባ አርከፈከፈችበት። የምይዘውና የምለቀው ጠፋኝ፡፡ ቁርጡን
ለማወቅ ቆርጣ መነሣቷን ስላወቅሁ ኣበይ ተነሽ ልብስሽን ቀያይሪና እንሂድ!
እይተሽው ለመመለስ እንጂ ይዘነው መምጣት አንችልም» አልኳት። እግሬን
ሳትለቅ አሻቅባ እያየች «እኔም ይዤው ልምጣ አልልም፣ ዐይኑን ብቻ አንድ ጊዜ
ልየው፣ በሕይወት መኖሩን ብቻ ልይ!» ብላ የልቧን አውጥታ ተናገረች።

በጉንጫ ላይ የሚንኳለለው ትኩስ እንባ የልቤን የፍቅር ወለል ቦረቦረው።ተነሥታ ወደ ጓዳ ስትገባ አረማመዷ እንኳ አሳዘነኝ። የባዕድ ሀላፊ አግዳሚ ያህል
እንኳ የማይተዋወቀችን እናትና ልጅ እንዴት አድርጌ እንደማስተዋውቅ ጭንቅ
ጥብብ አለኝ፡፡ እማምዬ እያለ በእናቱ ክንዶች ላይ ያልተዘናከተን' አልቅሶ
ያልተባበለን ሕፃን፣ ዐይኑ አይቶ ሕሊናው ያልመዘገባትን፣ አልቅሶም ይሁን በማቅ
ተንከትክቶ ዕቅፏ ላይ ያልተዘረገፈን ልጅ እንዴት አድርጌ እማማዬ እማማ
ለማሰኘት እንደምችል አጀማመሩም ሆነ አፈጻጸሙ ስማይን መቆንጠር መስሎ
በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ልብሷን ቀይራ ብቅ አለች፡፡ ኣጭር ዞማ ጸጉሯ በሚያምር ሐምራዊ ሻሽ ሽብ ተደርጓል፡፡ ኣጠገቤ መጥታ ቆም ካለች በኋላ በል አታጓጓኝ ይኸው መጣሁ! እንሂድ! » ብላ አሰፈሰፈች፡፡

የረሳችውን ሕፃን፡ ልጅሽ ይኸ ነው ብዬ ሳሳያት፣ ኣቅፋው በደስታ ስታለቅስ እና የልጁም በሁኔታው መደናገጥ ገና ከሩቁ አሽቆጠቆጠኝ፡፡

«የምንሄድበት ቦታ እኮ በጣም ሩቅ ነው» አልኳት፡፡ ግድ የለህም ስለ መንገዱ ሰማይ ጥግ ይድረስ፣ እንሂድ ብቻ' » ብላ ቆርጣ መነሳቷን ወደ በሩ በመራመድ ገለጸች፡፡ ከአስራ አምስት ደቂቃ ጉዞ በኋላ በታክሲ ዕጓለ ማውታ ግቢ ደረስን። ለሁለተኛ ጊዜ ከሴት ጋር ያዩኝ የድርጅቱ ዘበኞችና ሌሉች ሠራተኞች እርስ በርሳቸው በመተያየት ተጎሻሽሙብኝ፡፡
ሕፃናቱ ሁሉ ልዩ ልዩ ቅርዕና መልክ ያላቸው መጫወቻዎችና አሻንጉሊቶች ይዘው በምድረ ግቢው ሜዳ ላይ እንደ እውድማ ዳር ጥሬ ፈስሰዋል፡፡ ኳስ እያንከባለለ የሚጫወተውን፣ ጅዋጅዌ የሚገፈትረውን፣ ወለሉ ላይ
በተሽከርካሪዎቿ እየተገፋች የምትሽከረከር መኪና ይዞ ራን ራን ጵጵ! ቢብ! የሚለውን፣ ሜዳ መኻል እየተሯሯጡ ድብብቆሽ የሚጫወቱትን ሁሉ አየናቸው::

ለጊዜው ልጃችንን ስላጣሁት ዐመዴ ቡን አለ፡፡ እጄን ኮት ኪሴ ውስጥ
ወሽቄ ከቤት እንደ ወጣን የገዛሁለትን ከረሜላ ማሻሸት ጀመርኩ፡፡ የየወዲያነሽ
ዐይኖች በተስፋ ብርሃን ተከበቡ። የናፍቆት ጎተራቸው አፉን ከፈተ። የጉጉቷ ጥም ተንሰፈሰፈ። ዐይኖቿን ቅርብና ሩቅ ድረስ እየላከች ኣየች፡፡ ሰውነቷ የሚንቀጠቀጥ መሰለ። ውሪ ብጤ ሩጭሩጭ እያለ ባጠገቧ ባለፈ ቁጥር ዐይኖቿ እግሮቹን ተከትለው ይጓዙና በዚያው ፈዝዘው ይቀራሉ፡፡

በመኻሉ አንድ አጠር ጠበብ ያለች ነጭ ሱሪ የታጠቀና ዐመድማ ሹራብ
የደረበ ድምቡል ያለ የሚያምር ልጅ ዝንጉርጉር ቢራቢሮ በግራ እጁ ይዞ
እያንደፋደፈና እፍ እያለባት ከፊት
👍3
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሀያ_ሦስት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...አሮጊቷ ሠራተኛችን ነጋ ጠባ እየታመሙ መውደቅ መነሣት ስለ
በዛባቸው «እስኪ በጠበሉም በምኑም ልሞካክረው» ብለው ከሔዱ ወሩ ተጋመሰ::በእርሳቸው እግር እንዲት ልጅ እግር ሠራተኛ ተካን፡ የወዲያነሽም ያሳለፈችው ችግርና መከራ ቁጣና ግልምጫ ረሃብና እርዛት ሁሉ ከአእምሮዋ ላይ የማይደመሰስና የማይረሳ የኑሮ ትምህርት አስጠንቷታል። በዚሁ የተነሣ አዲሷን ሠራተኛችንን በርኅራኄና በደግነት ታያታለች። በትምህርትም ረገድ ከቀን ወደ
ቀን በመበርታቷ በእርሷ ላይ ያለኝ ተስፋ እንደ አበባ እምቡጥ በየጊዜው ይፈነዳ
ጀመር። የደመወዜ ከፍ ማለት የቤታችንን ዕቃዎች በአዳዲስ ምርጥ ቁሳቁሶች
ለመተካት ረዳ፡፡ ለውጥ የኑሮ መስተዋት ነው። የየወዲያነሽ መልክና ውበትም
የቀድሞ ደረጃውን ሊይዝ ስንዝር ታህል ቀረው፡፡ በክርክርና በውይይት
እንድትመራና እንድታምን ያደረግሁት ጥረት ከጊዜው ሁኔታ ጋር እየተቀራረበ
የሚራመድ የልፋት ውጤት እስገኘልኝ። ጸጉሯ እንገቷ ላይ እየተገማሸረ
የቀሚሷን እንገትያ መዳሰስ ጀመረ፡፡ ዕድሜዋ ኻያ ሰባት ገደማ በመድረሱ
ደርባባና ጐዝጉዝ ያለች ወጣት ሆነች፡፡ እንዲያውም በምኗም በምኗም በከፍተኛ
ምቾትና ድሎት ካደገችው እኅቴ ይልቅ የእኔዋ የወዲያነሽ በእጅጉ ላቀች፡፡

የውብነሽ የንግድ ሥራ ትምህርቷን ጨርሳ ከንግድ ትምህርት ቤት
ከተመረቀች ሦስት ወር ዐለፋት፡፡ ነገር ግን መስከረም ሲጠባ ሥራ ትጀምሪያለሽ
ተብላ ቦዝና ከረመች፡፡ አባቴ ከግሼን ማርያም በተመለሰ በሳምንቱ በደኅና ደሞዝ ሥራ ጀመረች።

አንድ ቀን እሑድ ከቀኑ አምስት ሰዓት ገደማ ላይ እኔና የወዲያነሽ በእግራችን ወደ አፍንጮ በር ስናዘግም ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ደረስን።
በቤተ ክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረትና አካባቢ እጅግ በጣም ብዙ ሕዝብ ተሰብስቧል።
በሕዝቡ መኻል እየተጋፋን ወደ ሰሜን አቅጣጫ ስንጓዝ የኅዳር ማርያም መሆኗ
ትዝ አለኝ፡፡ ሕዝቡ እየተግተለተላ ወዲያ ወዲህ ሲሔድ ድንጋዩ የተፈነቀለበት
ቁጫጭ መስሏል፡፡ የወዲያነሽ ግንባሩን በጥንግ እንደ ተመታ ገነኛ ቀጥ ብላ
ቆመች፡፡ የቀኝ እጀን ይዛ ወደ ኋላ እየጎተተች «ጌትዬ ጉድፈላልህ! የዛሬን
አውጣኝ! » ስትል ትንፋሿ በድንጋጤ ወደ ውስጥ ሠረገ፡፡

ከወደፊታችን አንዳች አደጋ የመጣ መስሉኝ አፍጥጬ ተመለከትኩ፡፡
አገር አማን ነበር፡፡ ለካስ ነገሩ ወዲህ ኖሯል፡፡ ከፊት ለፊታችን ትንሽ ራቅ ብሎ
አንድ ቀጠን ረዘም ብለው ጥቁር ሱፍ የለበሱና አሽከር ያስከተሉ የቀይ ዳግ
አዛውንት ወደ እኛ ሲመጡ አየሁ። አባቴ ነው።

የወዲያነሽ እጅ በዱላ የተመታ ይመስል ተዝለፈለፈ። የበደነ አካል የያዝኩ መሰለኝ፡፡ እጅዋን ለቅቄ ወደ ጎን ገፋኋት። አልራቀችም፡፡ ከአባቴ በስተጀርባ እናቴና እኅቴ አንዲት ነባር ሠራተኛ አስከትለው ይከተላሉ፡፡የወዲያነሽ ትንሽ ፈንጠር ብላ በግራ ጎናቸው ዐልፋ ሄደች። በከዘራ በጥፊና በክርን ደብድበው ካባረሯት ወዲህ እናቴንና እህቴን ስታያቸው የመጀመሪያ የመጀመርያ ጊዜዋ ነበር።

ሁለት እጆቼን ወደኋላዩ አድርጌ ልምጥ ብዬ እጅ ነሳሁ፡፡ እሱ ግን ሌላም እላለ። «እንተ ከሃዲ! ወይኔ ያየህ ይራድ! የማታ ማታ እንዲህ ታደርገኝ?
በቁሜ ቀብረኸኝ ትሄድ? አዝኘብሃለሁና ወላዲተ አምላክ በዕለተ ቀኗ ትመስክር
አይቀናህም!! እንዲሁ አውታታ ሆነህ ትቀራለህ! በል ሒድ!» አለና ከእግር
እስከ ራሴ በጥላቻ ግርምሞኝ ሄደ፡፡

ከአባቴ በስተጀርባ ቆማ የነበረችው እናቴ ዐይኔን ከማየት ብላ ከሠራተኛዋ ጋር ታወራ ነበር። ነጭ ጋቢ የለበሰችው የውብነሽ በፍርሃት ዐይኗን እያቁለጨለጨች ጨበጥ አድርጋኝ ወደ እነርሱ ተመለሰች፡፡ ሆድና ጀርባ ሆነን
እነርሱ ወደ ደቡብ እኛ ወደ ሰሜን ተጓዝን፡፡ የወዲያነሽ ምን አሉህ?' እንኳ ብላ አልጠየቀችኝም፡፡ እኔም አላነሣሁላትም፡፡ የወጣንበትን ጉዳይ ፈጽመን ወደ ልጃትን ዘንድ ሄድን፡፡

ከዚያ ቀደም በወሰድንለት የመላያ እርሳሶች እየተጠቀመ በአንድ መስመር አልባ ወረቀት ላይ የምታምር ሰማያዊ አበባ ሥሉ ቅጠሎቿን አረንጓዴ ቀለም እየቀባ ሲያሳምራት ቀስ ብለን ከበስተጀርባው ቆመን አየን።እኔና የወዲያነሽ እርስ በርሳችን ተያየን፡፡ ፊቱን ወደ ምዕራብ አዙሮ በመቀመጡ ለመጥለቅ የጥቂት ጊዜ ጉዞ ብቻ የቀራት ፀሐይ ብርሃኗን በስላች ለቃ በነጩ ወረቀት ላይ ደማቅ ቦግታ ፈጥራለች። ዐይኖቹ እንዳይጎዱ ሠጋሁ፡፡ ከበላዩ እንደ ታቦት ድባብ ጉፍ ብሉ ቅርንጫፎቹን በቅጠሎች ፤ያሳመረው የባሕር ማዶ ተክል ለሰስ ባለው የምሽት ነፋስ ይወዛወዛል።ከበስተጀርባችን ባላው መሬት ላይ ያረፈው የዛፍ ጥላ በውዝዋዜ እየተመራ በቅርንጫፎቹና በቅጠላ ቅጠሎቹ ሥዕል ይሥላል። አንድ ሉክ ገለጠ። አራት ረዘም ረዘም ያሉ የተሰናሰሉ ተራሮች በተጉበጠበጡ መስመሮች ተያይዘው ቡናና ጥቁር ቀለም ተቀብተዋል፡፡ ዕጫፍ ጫፋቸው ላይ ሁለት ሁለትና አልፎ ልፎም ሦስት ዛፎች ጉች ጉች ብለዋል። ከተራሮቹ እግር አንሥቶ እስከ ወረቀቱ የታች ጠርዝ ድረስ አረንጓዴና ቀይ፣ ቢጫና ሰማያዊ መስመር
ከወዲያ ወዲህ ተመሳቅለው ጭራሮ መሰል ውስብስብ መረብ ጥረዋል።
ከየተራራው መኻል ላይ ደግሞ እየተጥመዘመዙ የሚወርዱ ደማቅ ሰማያዊ መስመሮች አሽቆልቁለዋል። ጅረቶች መሆናቸው ነው፡፡

እኔና እርሷ ደረቁ ፀደይ አፈር ላይ እግሮቻችንን ዘርግተን ተቀመጥን። ጋሻዬነህ በሁለታችን መኻል ፊቱን ወደ እኛ አዘሮ በመቀመጡ ሁለታችንም በወሬና በጥያቄ ተሻማነው። ዐልፎ ዐልፎ ኮልተፍ ይላል፡፡ ፀሐይ ያላትን ሙቀትና ብርሃን ዘክዝካ የጨረሰች ይመስል ቀስ በቀስ ሙቀትና ብርሃን እየነፈገች ከተራራው በስተጀርባ ተሰወረች። ዳግማኛ የማትመለሰዋ ቀንም አብራ ለዘልዓለም ጠለቀች። ሕፃናቱና ከፍ ከፍ ያሉት ልጆች ሁሉ ወደ መኝታ ክፍላቸው የሚዝብት ጊዜ በመድረሱ ልጆች ሁሉ ሊገቡ ነው፡ልሂድ እኔም» ብሎ በየተራ አየን። ያመጣንለትን ዕቃ በቀኝ እጁ ዐቅፎ
የሥዕል ደብተሩንና እርሳሶቹን በግራ እጁ ጨብጦ ተነሣ፡፡ እኛም ጉንጩን
ስመን ተለየነው:: ከዚያን ዕለት ወዲህ ስለ ልጃችን ጉዳይ ሐሳብ ገባን፡፡ከእኛው ጋር ቢሆን ለአስተዳደጉ እንደሚበጅ ስንወያይበት ሰነበትንና ከእጓለ
ማውታ ልናወጣው ተስማምተን ዝግጅቶች ጀመርን።

በዚህ መኻል የዘመዶቼን ሁኔታ ለማወቅ ስለ ጓጓሁ እስኪ የሚባለውን ልስማ በማለት ከሩቅ ዘመዶቼ ውስጥ ጠንቃቃውን መርጬ አንድ ቀን ወደ
ቤት ይዤው መጣሁ፡፡ እንግዳዩ እንግዳዋ በመሆኑ አንጀት በሚያርስ አኳኋን ተቀብላ አስተናገደችው፡፡ ለመሄድ ሲነሣም የእንግዳ ወጉ ሁነኛ ጥቂት ልሸኝህ ብዩው አብረን ወጣን፡፡ ሳይታወቀን ብዙ ተጓዝን፡፡ በጨዋታችን መኻል«መቼም ስለዚህ ጉዳይ ወላጆችህ ምንም አልሰሙ፣ ሰምተዋል እንዴ?» ብሎ ጠየቀኝ፡፡

ለካስ አንድ ቀን እነጉልላት ቤት በእንግድነት እንደተቀመጠ እኔና
ጉልላት ስንነጋገር አንዳንድ የቃላት ፍንጣሪ ወሬ ሰምቶ ኖሯል። «አዎ እስከ
ዛሬ ድረስ አልሰሙም ያም ሆነ ይህ መስማታቸው አይቀርም የእኔ ውሳኔ ግን
አይለወጥም» ብዬ ሐተታ ሳላበዛ ዝም አልኩ፡፡ “ታዲያ ነገ ጧት አባትህ
ባድራጎትህ ተናደውና ተበሳጭተው ከዚህ ሁሉ ሀብት ንብረታቸው ላይ ቢነቅሉህስ?» አለኝ፡፡ “ይኸ ቀላል ጉዳይ ነው። ሁልጊዜ ሰዎች ሸምጥጠው ያወረዱትን ፍሬ መመገብ የለብኝም፡፡ እኔም በድርሻዬ መሽምጠጥና የመሽምጠጥን ልፋት ማየትና መቅመስ አለብኝ፡፡ ዛሬ ተወዝፈ ነገ በሚወረስ ነገር አልተማመንም፡፡ እሱ ያፈራውን ንብረትና ሀብት ያህል እኔም በዘዴና በቆራጥነት ከሠራ አገኘዋለሁ። ከዚያ በኋላ እኔም በፈንታዩ አውራሽ ሆንኩ ማለት ነው፡፡ ይህ ነው
👍31
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


....ያች በየጊዜው የምትጠገነውና የማያዘልቅ የገንዘብ መፍጃ ዕድሳት
የሚደረግላት የጉልላት ቮልስዋገን እየተንገጫገጨች መንቆርሰሷ አልቀረም፡፡
አውላላ ሜዳ ላይ ታጋልጠኛለች በማለት ሆዱን ቅር ያለው ዕለት በታክሲና በእግሩ መሔድ ይቀናዋል። አንዳንድ ቀን ተገፍታም ይሁን በበርቺ በርቺ
ተንቀሳቅሳ መሽከርከሯ ስለማይቀር እየተንገራገጨችም ቢሆን ይነዳታል፡፡
መንገድ ላይ ቀጥ ባለች ቁጥር ደግሞ ከየትም ለቃቅሞ ያገዛቸውን ልዩ ልዩ
መፍቻዎች፣ የብረታ ብረት ቅባት ካጠገበ አሮጊ ከረጢት ውስጥ ይዘከዝክና
ለማጠባበቅ ወደ ሞተሯ ይገሠግሣል። ምን ያደርጋል ታዲያ! ያን ውስብስብና
ቁልፍልፍ የብረት ቁልል ሲያይ “አሁን ደግሞ የትኛው ይሆን? ምን ዐይነት
ፍርጃ ነው! » ይልና አንዱን መፍቻ ወርውሮ እንቺ ቅመሽ ይላታል። በዚያው
ደግሞ ሌላ ዕቃ ይቀለጠምና ከናካቴው እንደ አበያ በሬ ለጥ ትላለች፡፡

ከተማዉ ውስጥ ያሉት ሽቃዮች የተሰናከለች ተሽከርካሪ አነፍንፈው ማግኘት ይችሉ ይመስል ወዲያውኑ እንደ ጉንዳን ይከቧታል። እሺ ካለች አለች፡
አለበለዚያም በምንጭሯ አስጎትቶም ይሁን ከወደ ጅራቷ አስጠምዞ አንዱ ጋ
አስጠግቷት ይሔዳል። ለገፉለትም ሆነ ለሳቡለት ሰዎች ስለት እንዳለበት ሰው
የሚሰጠውን ሰጥቶና ኣንጀቱን አሳርሮ በእግሩ ሲንገላወድ የነቀሉት ጭሰኛ
ይመስላል፡፡

እንድ ሰሞን ጥርሱን ነክሶ ስላሳደሳት የመኪና ወጉ ደርሷት ደኅና ስትሽከረከር ሰነበተች። እሱም ሠጋር በቅሉ ላይ እንደ ተቀመጠ የዱሮ መኳንንት ውስጧ ገብቶ ጉብ ይላል፡፡ የወዲያነሽ ጋር ሽርሽር ለመሔድ አስበን ስለ ነበር መኪናውን እንዲሰጠኝ ጠየቅሁት፡፡ 'ውሰድ አለ ቃሉን
ሠፈር አድርጎ በደኅንነቷ እየተመካ፡፡ «በዚህ ሰሞን ውቃቢ ቀርቧታል፡፡
እንዳጋጣሚ ግን በመሏ መጥቶ እንዱ ጋ ቀጥ ብላ ጉድ ካደረገችህ የራስህ
ጉዳይ ነው የለሁበትም!» ብሉኝ ቅዳሜ ማታ ወሰድኳት።

እኔና የወዲያነሽ ከንጋቱ አስራ አንድ ሰዓት እንደሆነ ለሁለታችን የሚበቃ ጥቂት ለስላሳ መጠጥና ምግብ ጭነን ከአዲስ አበባ ውጪ ወደ ጎጃም መንገድ ሰማንያ አምስት ኪሎ ሜትር ያህል ተጓዝንባት፡፡ ምንም እንከንና ጉድለት ሳያጋጥመን ካሰብነው ቦታ እስክንደርስ ድረስ መኪናይቱን እያቆምኩ ባሻገር የሚታዩትን ተራሮችና ኮረብቶች ለጥ ያሉ ለምለም ሜዳዎችና የሽልጥልጥ ሸንተራራማ ገደሉች እያየን፡፡ ምቹ ቦታና መዝናኛ ነው ብዬ ከገመትኩት ሥፍራ ላይ እንደ ደረስኩ የመንገዱን ዳር አስይዤ አቆምኳት፡፡ያ ብዙ ቦታ ላይ በንዝረት የሚገጫገጨው ልል የብረታ ብረት ክፍል ጊዜያዊ ጸጥታ አገኘ። የመኪናይቱ ሙቀት ቀስ በቀስ ቀነሰ። የውስጧ ሞቃት አየር
በመስኮት በኩል በሚገባው ቀዝቃዛ አየር የተገፋ ቦታ ይለቃል፡፡ የመኪናይቱ
ፊት ወደ ሰሜን በመዞሩ በስተምሥራቅ በኩል ባለው መስኮት በከፍተኛ
ፍጥነት እየተግለበለበ የሚገባው አየር በትይዩው መስኮት እየተዥጎደጎደ
ይፈተለካል። የመኪናይቱ መሪ በስተግራ በኩል በመሆኑ የወዲያነሽን እየዳበሰ
የሚመጣው አየር ከላይዋ ላይ የለሰለሰ የሽቶ መዓዛ ያመጣና አወድወድ አድርጎኝ ይከተለባል። ባለፈው አየር እግር የሚተካው አየር ይክሰኛል። በእኔ በኩል ያለውን በር ከፍቼ እግሬን ወደ ውጪ ዘርግቼ ራሴን በየወዲያነሽ ጭን
ላይ አሳረፍኩት፡፡ አንጋጥጬ ስመለከታት አዘቅዝቃ አየችኝ፡፡ አዝራሮቼ በተከፈቱበት በኩል ቀኝ እጅዋን አሾልካ ደረቴን ስትደባብሰኝ የፍቅራዊ ደስታ ሰመመን አጥለቀለቀኝ፡፡ ጋደም እንዳልኩ ዐይኖቼ ተንገረገቡ፡፡ ዐሥራ አምስት ደቂቃ ያህል ቀ-ም እንዳደረግሁ ወደ ከተማ በሚያዘግም የጭነት መኪና ድምፅ ባንኜ ነቃሁ፡፡ ጥቂት ምዕራፎች ወደፊት ነዳሁ።
እንደገና ከመንገድ ገለል አድርጌ አቆምኳት። ሠላሳ ርምጃዎች ያህል
ወጣ ብዬ ስለ ነበር አንዳንድ አጫጭር ቁጥቋጦዎች በመኪናይቱ ተቀለጣጠሙ ጎማው የተሽከረከረባቸው በዚያው ሲቀሩ በመኪናይቱ ሆድ የተለመሰሉት ግን በመጠኑ ጎበጥበጥ ብለው ቀኑ፡፡ ከፊት ለፊታችን ጥቅጥቅ ያለ አጋምና ብሳና ድግጣና ምሥርች ዐልፎ ዐልፎ ኮርች በቅሉ አካባቢውን አይደፈር መሳይ ግርማ አልብሶታል። ወደ ዱሩ የምታስኬደው ቀጭን መንገድ ባረንጓዴ ወረቀት ላይ የተሰመረች ግራጫ መስመር ትመስላለች፡፡በዚቹ መንገድ በኩል ይዣት ልግባ ይሆን ይቅርብኝ እያልኩ ሳመነታ'
ስፈራና ስጠራጠር ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ፡፡

አንድ ውሳኔ ለመወሰን ጫካውን አፍጥጬ ስመለከት ጥቂት ራቅ
ብሎ አንድ አፈርቻና ሦስት አራት ያህል ዝንጉርጉር እንስሳት ከጫካው ውስጥ ተከታትለው ብቅ አሉ፡፡

ለጊዜው ልብ ብዬ ባለማየቴ ደንገጥ አልኩና «ምንድናቸው?» አልኩ።
እጅዋን ትከሻዬ ላይ ጣል ያደረገችው የወዲያነሽ «ፍየሉች ናቸው» አለችኝ፡፡
«እኔስ ሌላ ነገር መስለውኝ» ብዩ ነገሩን ወዲያ ወዲህ እምታታሁ፡፡ ደግነቱ
ስሜቴን ስላላወቀችብኝ ዝም አለች። ጥሎ አይጥሌ ሲረዳኝ አንድ እረኛ ብዙ
ፍየሎች እያንጋጋ ከጫካው ውስጥ ብቅ አለ፡፡ ከመኪና ወጥተን የየወዲያነሽን
እጅ ያዝ አድርጌ እንደቆምኩ እረኛው አጠገባችን ደረሰ። ደረቱ ላይ ሰፋ-ሰፋ
ያለ ኪሶች ያለባት የአቡጀዲ እጀ ጠባብ ለብሷል። የሁለቱም ኪሶቹ አፍ አደፍደፍ ብሎ ጠቁሯል። ሁለት ፍየሎች ተነጥለው ወደ ሌላ አቅጣጫ ስለሄዱ እነሱን ለመመለስ ነይ እሪያ!» ብሎ ወደ ኋላ ተመለሰ፡፡ ልብሱ ከበስተኋላው ቂጡ ላይ ድልህ የነካው ጋቢ መስሏል።

ከጉልበቱ በታች ያለው ሙጭርጭር በደረቀ ጭራሮ የተጠረገ የረገጥ ቤት መስሏል፡፡ በግራ ብብቱ ቀጠን ያለች ብትር አጣብቆ ይዟል። ዋሽንቱን በእጁ ውስጥ እያንከባለለ ያሻሻታል። ፍየሎቹ እየቀነጣጠቡ በአጠገባችን አለፉ፡፡ እረኛውም ከኋላ ከኋላቸው ከተፍ አለ። ልብሱ ላይ ዐልፎ ዐልፎ ጨጎጊት ተጣብቋል። አጋም ሲቃቅምበት የዋለው ከንፈሩ ጠቋቀሯል። እንኩታ ሲቸችግ የዋለ መስሏል።

ለስለስ ባለ ድምፅ "አንተ ልጅ ና እስኪ አንድ ነገር ልጠይቅህ አልኩት፡፡ ነባር ፍርሃት ሳይሆን የጥርጣሬ ፍርሃት በፊቱ ላይ እየታየ በዝግታ መጥቶ ቆመ ወደ ጫካው እያመላከትኩት በዚ ጫካ ውስጥ መንገድ አለ እንዴ?ብዬ ጠየኩት? 'አዎ' ብሎ ባጭሩ መለሰልኝ፡፡

«እንግዲያውማ እዚ ቅርቡ መናፈስ ይቻላል፣ አስቸገሩኝ አትበለኝና አንድ ነገር ልለምንህ ነው? ይህን የመብል የመጠጡን ነገር ተወው፡ ነጭ
ሺልንግም እጨምርልሃለሁ ይቺን መኪና ትጠብቅልኛለህ አልኩት።

«ፍየሎቼን ማን ያግድልኛል?» ብሎ መለሰልኝ፡፡ ጓደኛም የለህ እንዴ?
ካለህ ፍየሎቻችሁን ተራ በተራ እየመለሳቹ መኪና ትጠብቁልኛላችሁ» ከማለቴ ጓደኛስ አለኝ» አለኝ፡፡ “ሒድ በል ጥራውና ና » ብዬ በትሕትና አዘዝኩት፡፡ በቀጭኗ መንገድ ወደ ጫካው ወስተ ሄደ፡፡ ወደ ጉድጓድ እንደሚገባ ሰው ጭንቅላቱ ቁልቁል ስለ ወረደች አካባቢው ተዳፋት
እንደሆነ ገባኝ፡፡ ከየወዲያነሽ ጋር የሚረባ ወሬ እንኳ ሳናወራ ጥጆችና ጊደሮች
እየነዱ ከተፍ አሉ፡፡ በመጀመሪያዉ ልጅና በሁለተኛው ልጅ መካከል ትንሽ
የመልክ ልዩነት እንጂ በአለባበስና በአረማመድ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሁለተኛ
ልጅ ፊቱ ሰልከክ ብላ መጠጥ ያለች ነች፡፡ አፍንጫው ሰልካካ ፀጉሩ ጥቁር
ለስላሳ ነው፡፡ ቆሸሽ ባለችው የእጀ ጠባቡ ኪሶች ኣካባባና እጅጌዎቹ ላይ ልዩ
ልዩ አዝራሮች ተተክለዋል። ሁለቱም ግራና ቀኝ ቆመው እንጠብቅላችኋልን አሉ፡፡

«እንግዲህ አደራችሁን ስመለስ የማደርግላችሁን አታውቁትም አልኩና መኪናይቱን ከፍቼ ምግብና መጠጥ የያዘውን መጠነኛ የእቃ ሻንጣ
አወጣሁ፡፡

ደስ እንዲላቸውኛ በሚያጓጓ ተስፋ እንዲጠብቁልኝ በማሰብ ሁለት
ሁለት ዳቦና አንዳንድ ብርቱካን
👍2
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...እንደ ረጂም ነጭ ጭራ የዕንጨት ሽበት ያንጠለጠሉ ዛፎች በብዛት ይታያሉ፡፡ የማዶውን ትቼ አጠገቤ ስመለከት ትልልቅ ጐለጐሎች የሞተች
የእባብ ራስ (ትል) ጉማጅ አግኝተው ከፊትና ከኋላ በመተጋገዝ እያንከባለሉና
እየገፉ ሲወስዷት አየሁ። ሕይወት እና ኑሮ የከባድ ትግል ውጤት ናቸው::የቦታው ቁልቁለታማ ስበት ከጉልበታቸው በላይ በማየሉ አምልጣቸው ተንከባለለች፡፡ የት እንዳረፈችና እንደገባች ስላጧት ተቅነዘነዙ። እንደ ፈሪ መርዶ ነጋሪ ዙሪያውን ዞሩ። በፍለጋ ብዛት አገኟት፡፡

ተፈጥሮ ለታካች ከማዕዷ አታጎርስምና እንደገና በትግል ይዘዋት መንገድ ቀጠሉ ፍጻሜያቸውን ለማወቅ በዐይኖቼ ተከተልኳቸው:: በአንዲት ሰፊ ደረቅ ቅጠል ሥር ከነግዳያቸው ተሸጎጡ፡፡ የእንሱ ጉዳይ በዚያው አከተመ።

የየወዲያነሽ አእምሮ ምን እንደሚያስብና እንደሚያሰላስል ባላውቅም አካባቢውን በፈገግታ ትመለከተዋለች። ድንገት ሳታስበው ክንዷን ሳብ አድርጌ
«የወዲያ! ይኸ አካባቢ ደስ አይልም እንዴ? አልኳት፡፡ በአድናቂ ስሜት ፈገገ
አለች።

ሻንጣውን ከጐኗ ሳብ አድርጋ ትውስብሳቢውን ተረተረችው:: አምስት
ብርቱካኖች አውጥታ እንደ ምፅዋት መቀበያ ሰጣ በተን ባለው ነጠላዋ ላይ
አስቀመጠች:: እናት ነች የልብ ከውቃ:: መላጥ ጀመርኩ፡፡ እሷም ተያያዘችው:: እርሷ ገና ልጣ ሳታጋምስ እኔ ለእሷ ሦስት ጊዜ ለራሴ ሁለቴ ጎረስኩ፡፡ አንዷን የብርቱካን ፍንካች አፌ ውስጥ እያንከላወስኩ «የወዲያ ደስ አላለሽም መሰል ይህ አካባቢ?» ብዬ እንደገና ጠየቅኋት። በጠይሙ ፊቷ ላይ
ፈገግታዋ እየተዘናከተ «እንዴት ብዬ ልንገርህ?» ብላ በእጅዋ የያዘቻትን
ፍንካች ሰለከከች። እኔ ሁለተኛዬን በልቼ ልጨርስ ስል እርሷ ሁለተኛይቱን
ልጣ ፈረካከሰቻት። «እንካ እስኪ ይቺን ቅመሳት ጌትዬ?» አለችኝ።

“አ!” ብዬ ተቀበልኳት። ከእጅዋ ላይ ተጨማሪ ጣዕም ፈልቆ ብርቱካኑ ውስጥ የገባ ይመስል ያጎረሰችኝ ጣፈጠኝ። ስውጥ አይታ ደገመችኝ። ቁልቁል ሸኘኋት፡፡ በድጋሚ ስትዘረጋ «ተይ ተይ በቃኝ! አንቺ ጉረሻት» አልኳት። እጅዋን እንደ ዘረጋች «ይቺን ብቻ ጌትዬ ስሞትልህ?» ስትለኝ ካንገት በላይ እየተግደረደርኩ ተቀበልኳት። ሆዴ ብቻ ሳይሆን ሕሊናዬም ጠገበች፡፡ ደመናኑን በረጅም መጥረጊያ ሙልጭ አድርገው የጠረጉት ይመስል ሰማዩ ጸጥ ያለ ባሕር መስሏል። ምንም እንኳ በሰማዩ ላይ ደመና ባይታይ ፀሐይዋን ለማየት የቻልነው ገላጣው ቦታ ላይ በመቀመጣችን ነበር፡፡

እኩለ ቀን ሊሞላ አንድ ሰዓት ብቻ ቀርቶታል። ኃይለኛውን የበጋ ሐሩር የቀነሰልን ግን ከአካባቢው የሚነፍሰው የለስላሳ አየር ሽውታ ነበር፡፡
ከነበርንበት ሥፍራ ተነሥተን ጥቂት ርምጃዎች ወደ ጎን አለፍ ብለን ከአንድ
ቁጥቋጦ ሥር ተቀመጥን፡፡ የቁጥቋጦው ቅጠል የላይ ገጽ በጣም ደማቅ አረንጓዴ ሆኖ ወበቅ እንዳቃጠለው የከበርቴ ፊት
በስተጀርባው ግን ግርጣት ያይልባታል።
ወዛም እንደ ቀድሞ ገዳይ ጎፈሬ የተቸመቸመው ድፍን አረንጓዴ ቅጠሏና
ደርበብ ያለው ቁመቷ ታይቶ የማይጠገብ የውበት ፀጋ አልብሷታል፡፡

የወዲያነሽ አንዷን ጎበጥ ብላ መሬት ለመንካት አንድ ክንድ ያህል የማይቀራትን ቅርንጫፍ እንደ ተቀመጠች ተንጠራርታ ሳበቻትና ለጋ ጫፉን ቀለጠመቻት፡፡ በቀኝ እጅዋ ይዛ ግራ እጅዋ ላይ ስትጠበጥባት ጥቂት ቅጠሎች ረገፉ፡፡

አንዷን በጥቃ ተስተካክለው በሰቀሉት ጥርሶቿ እየነካከሰች በሳቻት።
ቅጠሊቱን ከእጅዋ ላይ መንጭቄ ወረወርኩና «ምን ዐይነቷ ናት እባካችሁ?
እስኪ አሁን ምኑን አውቀሽው ነው? ምናልባትስ መርዘኛ ቅጠል ቢሆን?»
አልኩና ከአንጀት ያልመጣ ቁጣ ተቆጣሁ፡፡ ሣቅ ብላ ትንሿን ጣቴን ያዘችና
«መጥፎ ቅጠል መሰለህ እንዴ? እኔ እኮ ዱሮውንም ቢሆን አውቀዋለሁ፡፡
አንተ አታውቀውም መስል? ደደሆ እኮ ነው:: ምን ያደርጋታል ብለህ ነው?
አለችኝ።

አለማወቄን ለመሰወር ያህል ነው እንዴ? እኔ እኮ ከረሳሁት ቆይቻለሁ» አልኳት ቀድሞዉንም ቢሆን የማላውቀውን ቅጠል፡፡ እንደማላውቀው አውቃብኛለች፡፡ አሁንም ያንኑ ቅጠል በጥሳ በጥርሷ
ወጋጋችው። እኔም ለመቅመስ ያህል አራት አምስቱን ቅጠል አጎርኩት።
ምራቄ ከአፌ ውስጥ በመዘውር ተቀድቶ የተወሰደ ይመስል አፌ ኩበት ሆነ፡፡
ምላሴ ደረቀች። ላንቃዬ እንደ ተወቀረ ወፍጮ ሞዠቀኝ። ውስጥ ውስጡን
ጉዴ ፈላ፡፡ እንዳይታወቅብኝ ወሬም የለ ምንም የለ፣ ዝም አልኩ፡፡ዳግመኛ ሌላ ቅርንጫፍ ጎትቼ እመጣለሁ ብላ ስትንጠራራ ጠርዙ ጉልበቷ ላይ ያደረው ቀሚሷ እስከ ጭኗ ተስቦ አሻቀበ፡፡ የወንድነት ንቁ ፍላጎቴ በጠይሙ ውብ ገላዋ ዙሪያ ተንከራተተ፡፡ እጄን ዘርግቼ ለስላሳ ገላዋን ዳበስኩት፡፡ መላ ሰውነቴ ብው ብሎ ጋለ፡፡ ከተቀመጥኩበት ተነሣሁ የወዲያነሽንም አፈፍ ኣድርጌ አስነሣኋት። እኔ ወደ ምዕራብ እርሷ ወደ
ምሥራቅ እያየን ፊት ለፊት ቆምን፡፡ ትከሻዋን ይዤ ደረቴን ወደ ደረቷ
አስጠጋሁት። አቀፈችኝ፡፡ አቀፍኳት። ከልብ ተሳሳምን።

ነፋስ እንደ መነጫጨረው የድርቆሽ ክምር ጸጉሯን በታተንኩት፡፡ ያ ከጥቂት ወራት በፊት አንገቷ ላይ ደርሶ የነበረው ጸጉሯ አድጎ ትከሻዋን ያስሳል፡፡ ጫፍ ጫፉ ተቆልምሞ በመጥመዝመዝ እጆቹን ሽቅብ እንደ ዘረጋ ባሕታዊ ወደ ላይ አንጋጧል። ከከንፈሯ ወረድ ብዩ ያን ካፊያ እንደ መታው ጓሚያ እንኮይ የተውለከለከውን አንገቷን ባፍና በአገጬ አድፈጠፈጥኩት።

እጅ ለእጅ ተያይዘን ከቁጥቋጦይቱ ውስጥ ወጣን፡፡ አካባቢውን ለማየት ስለ ፈለግን አንድ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ወጥተን መንገድ ፈለግን፡፡ የወዲያነሽ የለበሰችው ገብስማ ቀሚስና የደረበችው ቢጫ ሹራብ፣ የአካባቢው ዕፅዋት ልምላሜ፣ ምግብ የያዝንበት ቀይ ሻንጣ፣ የታጠቅሁት ሰማያዊ ሱሪና የለበስኩት ሽንብራማ ኮት፣ ባንድነት ሆነው የውበት ሽማ በመዘርጋት በቅልቅል ኀብረ ቀለማቸው አእምሮዬን ስላረኩት ታላቅ ሰብኣዊ ኩራት ተሰማኝ፡፡ ሹራቧንና ነጠላዋን አጣጥፌ ሻንጣ ውስጥ ከጨመርኩ በኋላ ቁልቁለቱን ተያያዝነው:: በጫካው ውስጥ ለውስጥ የሚያስኬደው መንገድ ቡችሎች እንደ ጎተቱት አንጀት የተጥመዘመዘ በመሆኑ በረጂሙ አግድም እንሔድና እንደ ገና ደግሞ ተመልሰን ከነበርንበት ቦታ ግርጌ እንደርሳለን፡፡ልዩነቱ ትንሽ ዝቅ ማለታችን ብቻ ነበር። አንዲት አፈመለከት ቅርፅ ያላት ትንሽ ቢጫ የሐረግ አበባ አገኘሁና ቀጥፌ ዘረጋሁላት፡፡ እጅዋ በድካም እንደ
መዝለፍለፍ እየቃጣው ተቀበለችኝ። መለስ ብዪ «የወዲያ! ያቺ ፀሐይና ይኸ
ቁልቁለት አዛሉሽ መሰል?» አልኳት። «ብዙ ሄጄ ስለማላውቅ ነው መሰል»
ብላ ደማ ፈገግታ አሳየች፡፡

ጥቂት ዝቅ እንዳልን ጆሮዎቼ የመልካም ተስፋ ድምፅ ሰሙ:: ለእኔም ለእርሷም አንጀት የሚያርስ እፎይታ ነበር። ከፊት ለፊታችን ከወደ ጋራው ጥግ ካሉት ትላልቅ የድንጋይ ቋጥኞች ሥር በከፍተኛ ፍጥነት እየተውዘገዘገች የምትወርድ ፏፏቴ ኣየን፡፡

በፏፏቴው ዳርና ዳር ያለው አለት በጥቁርና ጓያ መስል መልኩ
በጣም ይማርካል። ከወንዚቱ ዳርቻ የበቀሉት ዛፎች ቅርንጫፎቻቸው እንደ
ደጋን ጎብጦ ቅጠሎቻቸው ወራጅዋ ውሃ ውስጥ ተዘፍቆ በውሃይቱ ግፊት
ከወዲያ ወዲሀ ይነቃነቃሉ፡፡ ከሸለቆው ውስጥ የትኛው ቦታ ላይ እንደምትመነጭ አይታይም። ኩልል ብሎ የጠራው ውሃ የድንጋዩን መልክ ተጋርቶታል። ወራጂቱ ውሃ ድምፅ ሳታሰማ ጥቂት አግድመት ታገድምና ጥግ ይዞ ጠርብ የመሰለ ድንጋይ ሲያጋጥማት ፏፏቴ ቢጤ ፈጥራ ትፈጠረቃለች።

በፏፏቴው ማረፊያ ዙሪያ የእንዶድ አሪፋ የመሰሉ ነጭ የውሃ ንፍሥሪ ኳሶች ይንሳፈፋሉ፡፡ የጥበትና የስፋታቸው መጠን የተለያየ ቢሆንም
👍42😁1
A:
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


....እሑድ ከሰዓት በኋላ.….ስለ ለጎ ሐይቅ ከተማና አካባቢዋ ኣንድ ባንድ ካወራችልኝ በኋላ የሕሊናዋን ትዝታ ወደ ደሲ መልሳ ስለ በርበሬ ገንዳ ሙጋድ፣ ዳውዶ ገራዶ፣ ሆጤ፤ ሶሳ፣ አዘዋ ገደል ሰኞ ገበያ…. ነገረችኝ፡፡ «ቆየኝ ደግሞ ሥራዬን ጨርሼ ልምጣና አወራልሃለሁ» ብላ ካልጋው ጫፍ ላይ ሸርተት ብላ ሔደች፡፡ ከግማሽ ሰዓት በኋላ ሥራዋን አጠናቃ ከተፍ አለች::ነጣ ያለ ቦላሌና ሰማያዊ ሸሚዝ ለብሼ አልጋው ላይ በጀርባዬ ተንጋልዬ
የጋሻዬነህን ሥዕል አንጋጥጬ ስመለከት ደረሰች፡፡ ሲሠውረኝ አላየችብኝም፡፡
ትከሻዬ ሥር ጣል አድርጌ ተኛሁበት፡፡ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጣ በሆዴ
ላይ እጂን አሻግራ በመመርኮዝ ከደረቷ ዘንበል አለች፡፡ ትከሻዋ ላይ የነበረችው ባለ አረንጓዴ ጥለት ያንገት ልብስ ተንሸራተተችና የተዘረጋችውን እጅዋን ሸፈነቻት፡፡ ከደረቴ በታች የሆዴ አካባቢ በድንኳን ውስጥ ያላ ነጭ አግዳሚ መቀጫ መሰለ፡፡

ያን በሆዴ ላይ ዐልፎ አልጋው ላይ እንደ ካስማ የተተከለውን እጅዋን በቀኝ እጄ እያሻሽሁ ምናልባት ቅር ይላት ይሆን? በማለት ስፈራ ስቸር ከቆየሁ በኋላ የወዲያ፣ አንድ ነገር ብጠይቅሽ ቅር ይልሻል?» አልኳት፡፡ አሽቆልቁላ ዐይን ዐይኔን ትክ ብላ እያየች ምንስ ነገር ብትጠይቀኝ ምን ብዬ እቀየማለሁ? ስል ጠይቀኝ ልንገርህ? ብላ አቀማመጡዋን አመቻቸች።

ለሁለት ደቂቃ ያህል ውስጥ ውስጡን ሐሳቢን አንቀረቀብኩ፡፡ እንግዲህ
ያለችውን ትበል አልኩና «የወዲያ! ለምን አስታወስከኝ ኣትበይና፣ እናትና
አባትሽ ሲሞቱ የስንት ዓመት ልጅ ነበርሽ?» አልኳት። ፈገግታዋን የቅሬታ
ደም ስለ በረዘው ፊቷ ፈዞ የክረምት ዋዜማ መሰለ፡ ውስጥ ውስጡን ራሴን
«ጌታነህ! የተዳፈነ የኅዘን ረመጥ ጫርክ፣ ያንቀላፋ ኀዘን ቀሰቀስክ» ብዩ ወቀስኩ፡፡ ደቂቃዎች ሠገሩ። ትንሽ ፈነከነክ ብላ «ምነው ምን ነካሀና ኖረሀ ኖረህ ጠየቅኸኝ?» ብላ ፊቷን የትካዜ ዐመድ ነሰነሰችበት፡፡ ካኣሁን አሁን ትጀምራለች በማለት አሰፍስፌ ጠበቅሁ፡፡ ያን እንደ አተር እምቡጥ እበጥ ብሎ የቆየ የታች ከንፈሯን በላይኛው ውብ ጥርሷ ረመጠጠችው። አንድ ጊዜ
አፈትልኮ የተነገረን ሐሳብ መልሶ መዋጥ የማይቻል በመሆኑ ችሎታዩ ከዝምታ ሊያልፍ አልቻለም። እየር ስትስብና ስታስወጣ ከፍና ዝቅ የሚለውን
ደረቷን በመመልከት ላይ እንዳለ «አባቴ ሲሞት አንዲት ፍሬ ልጅ ነበርኩ
አሉ፡፡ ትንሽ ትንሽ እንደ ሕልም ትዝ ይለኛል፡፡ እናቴም አባትሽ ከልጆቹ
ሁሉ አንቺን ይወድሽ ነበር፡፡ ሳይንት እሚባል አገር ካሉት ዘመዶቹ መኻል
የሚወዳትን አክስቱን ስለምትመስዪ የእርሷ ነገር ሆነበትና 'የወዲያነሽ የወዲያ
ሰው ብሎ ስም አወጣልሽና የወዲያዬ የወዲያነሽ አልንሽ ብላ ነገረችኝ። ልጅ
ስለ ነበርኩ ሁሉንም ኣላስታውስም እንጂ አባቴ ብዙ ጊዜ ታሞና ማቆ ማቆ
ነው የሞተው። የሞተ ዕለት ሰዎች ሁሉ ሲያለቅሱ አይቼ እኔም ትንሽ
አልቅሻለሁ፡፡ ሞት ምን እንደሆነ ስለማላውቅ ሄዶ የሚመለስ እንጂ በዚያው የሚቀር አይመስለኝም ነበር፡፡ ሬሳውን በአልጋ ይዘው ከቤት ሲወጡ ምንም ስላልመሰለኝ ጉድሮዬን እያዘናፈልኩ ከመንደሩ ልጆች ጋር እቦርቅ ነበር፡፡
ታናሽ እኅቴ እማዋይሽ ክርስትና የተነሣች ዕለት መጥተው የነበሩት ቄሶች ራሱ የቀብሩም ዕለት መጥተው ስለነበር ለደስታ የመጡ እንጂ ለሌላ ነገር
የመጡ አልመሰለኝም። እያደር ግን ዋል አደር ስል ዕንጨት ለቀማም ይሁን
ዋርማ ይዤ ጅረት ስወርድ ጓደኛቼ እንደ ቀልድ 'አንቺዬ ማሳዘኗ' አንድ ቀን እኮ የሞቱት የዚች አባት ናቸው” እያሉ ሲያንሾካሽኩ እየሰማሁ ግራ ግብት ይለኝ ነበር። አባቴ ከሞተ በኋላ እዚያው አገር ቤት ከእናቴና ከእኅት ወንድሞቼ ጋር ቆየሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን የእናቴ ታላቅ እኅት ከአገር ቤት ወደ ከተማ ይዛኝ መጥታ ትምህርት ቤት አስገባችኝ ብላ ዝም ስላለች ያ በኀዘን ጉም ተሸፍኖ የቆየው ዐይኔ ቦግ ብሎ ወደ የወዲያነሽ ዐይኖች ተወረወረ፡፡እንባዋ እንደ አሸንዳ ጠፈጠፍ እየተንከባለለ በጉንጯ ላይ ተንኳለለ፡፡ ልብሴ ላይ የተንጠባጠበውን ዕንባዋን ደረቁ ሸሚዜ እንደ ግንቦት አፈር ጠጣው፡ የደቀነችውን ወሬ ለመጨረስ እንባዋን ካባበሰች በኋላ «አሁንም ቢሆን እነዚያ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ትዝ ይሉኛል። እነ የሻረግ፣ ዘነበች፡ አሚናት፡
ይመር፣ አያሌው፣ ገበያነሽ፣ ሰኢድ ኧረ ስንቱ ስንቱ... እክስቴ ከልጆቹ ሁሉ እኔን መርጣ የወሰደችኝ የረጋች ልጅ ነች፣ ደስ ትለኛለች» ብላ ነበር። ሁለት ሦስት ጊዜ ላግባ ባይ መጥቶ ሲጠይቅ ቆይ እስኪ ጥቂት ተምራ ነው ነፍስ ትወቅ» ብላ እምቢ አለቻቸው፡፡

እኔና እርሷ ብቻችንን ተቀምጠን በምናወራበት ጊዜ ግን፡ ያም የሸማኔ ልጅ ነው፣ ያኛው መናጢ ዘረ ድሃ ነው፣ የዚያኛውም እናት ዘር ማንዘሯ ሸክላ ሠሪ ነው የጠዳ የጨዋ ልጅ እስኪመጣ ሰጥ ብለሽ ትምርትሽን ተማሪ» ትለኝ ነበር፡፡ አክስቴ ከምላሷና ከንዝንኳ በስተቀር ሆዷ ባዶ ነው::ባልዋ አይዋ ዘለቀ አንድ ሲናገሩ ሁለትና ሦስት ነበር የምትመልስላቸው:: ችለው ችለው አንድ ቀን የተነሡ ለታ ግን ቀሽልደው ቀሽልደው ሲለቋት ውሃ ውስጥ የገባች አይጥ ትሆናለች። እሷ ታዲያ የሳቸውን እልክ በኔ ላይ ነበር የምትወጣው::

«አንቺ መድረሻ ቢስ ግንባረ ነጭ» ብላ ከጀመረች በርበሬ ሳታጥነኝና በጥርሷ ሳትበተብተኝ እንገላገልም፡፡ «አፈር ብይ! አፈር ያስበላሽ! ያባትሽን ቀን ይስጥሽ» ስትለኝ ግን አይመኙ ነገር ያስመኘኝ ነበር። ለጎ-ሐይቅ በሔድኩ በአራተኛው ዓመት አገር ቤት ወረርሽኝ ገባ ተባለና እናቴ በጠና ታመመች።ያኔውኑ ትምህርት ቤት በመዘጋቱ ካልሔድኩ ብዬ አገር አመስኩ፡፡ ቢሉኝ ቢፈጥሩኝ እዚያቹ ከናቴ
ጋር እሞታታለሁ እንጂ እይደረግም ብዬ
አስቸገርኩ፡፡ በማይረባው ነገር ሁሉ ካክስቴ ጋር መነታረኩ መሮኝ ስለ ነበር
ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ከፊቷ ገለል ብዬ እፎይ ማለት ፈልጌ ነበር። ወሬ
አበዛሁብህ መሰል? ላሳጥርልህ፣ እናቴ ቡሄ በዋላ ልክ በሳምንቱ ሞተች። ያን
እለት የሆንኩትን አኳኋን ግን ባትሰማው ይሻላል። እናቴ ፀሐይነሽ አማረ ትባል ነበር። ከዘመዶቻችን ጋር ዕርባዋን አውጥቼ ትምህርት ቤት የተከፈተ
በሳምንቱ ከዚያቹ ከአክስቴ ጋር ወደ ከተማ ተመለስኩ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ወደ
አገር ቤት አልተመለስኩም» ብላ ጋደም አለች፡፡ ያ የቀድሞ ውበታዋም ርዝማኔውን ሊይዝ ጥቂት የቀረው የሴትነቷ ግርማ የሆነው ዞማ ጸጉሯ በአንገቷ ዙሪያ በተንተን ብሎ ተነሰነሰ። ድንገት
ቀና ብላ እግሯን ኮርምታ ተቀመጠች፡፡ «አልጨረስኩልህም እኮ» ብላ
ቀጠለች። በበኩሌ የሕይወቷ ምሬት አንገፍግፎኝ ነበር፡፡» ያክስቴ ባል ዘኃ
ነጋዴ ነበሩ። ከደሴ ዘኃ ያመጡና፣ ከሐይቅ ደግሞ አንጋሬና ቆዳ ይዘው
ይመለሳሉ። የኋላ ኋላ ግን ደሴ መሬት ገዝተው ቤት ስለሠሩና ንብረት ስላበጁ ሁላችንም ወደዚያው ሄድን። ደሴ ወይዘሮ ስሒን ትምህርት ቤት አምስተኛ ክፍል ገባሁ፡፡ ያነዩ ገና ዐሥራ አራት ዓመቴ ነበር፡፡ አክስቴ ውሃ ቀጠነ፣ ጪስ በነነ፣ እያለች ስለምትነዛነዝ ይብስ እሳትና ጭድ ሆንን። እልህ ማብረጃ አረገችኝ፡፡ ስወጣም ስገባም ስድብና ዱላ ሆነ፡፡
ለጊዜውም ቢሆን ሌላ የሚያስጠጋኝና የምገባበት ዘመድ ስላልነበረኝ ያለችውን ብትል ታግሼ ዝም አልኩ፡፡ እንደ ምንም ብዬ ተፍጨርጭሬ ሰባተኛ ክፍል እንደ ገባሁ ከነከተቴው ሒጂልኝ! ውጪልኝ! ዐይንሽን ላፈር! ማለት አመጣች። ንግግሯ ሁሉ አንገሸገሸኝ፡፡ የዓመቱ ትምህርት ባሳር በመከራ ካለቀልኝ በኋላ ብሞትም ልሙት ብዩ ቆርጬ ተነሣሁ አንድ ቀን
ጎረቤታችን የነበሩ አንድ የጦር
👍7
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


በሐሰት ተገንብቶ በተለበጠ አካባቢ ሁሉ አንድ ግለሰብ ብቻውን ተገንጥሉ ልዩ ትክክለኛ አካባቢ ለመፍጠር ከፍ ያለ ችግር ያጋጥመዋል።ሁሉም በየበኩሉ የየራሱን የኑሮ ማሳ እያዳበረ በሚያርስበትና በሚያዘምርበት
ትክክለኛ ዓላማና ግብ ማምራት እንጂ፣ ይኸ እንዲህ ነው፣ ያኛው እንዲያ
አካባቢ፣ የራስን ዶማ እና መሣሪያ ይዞ በመቀላቀል ቀስ በቀስ ወደሚመኙት
ነው እያሉ መጃጃል ወደፊት መራመድ ሳይሆን ወደኋላ ማፈግፈግ ነው:: ልክ
ያልሆነው ነገር ሁሉ ወለል ብሎ ቢታየኝም በግል ስክበው የሰነበትኩት
አስተሳሰብ ለጊዜውም ቢሆን በአካባቢዬ አሮጌ ልማድ ተዋጠ።

ባለሁበት ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ተርፎታል፣ ሞልቶታል፣ እየተባለ ነገር ግን ዝቅ ብሎ መታየትን የመሰለ አሳሳቢ ነገር የለምና የአካባቢን አስተያየትና ግምት ለመለወጥ ሲባል የሚደረግ ልዩ ልዩ ጥረት አንድም ፈጽሞ መውደቂያ ወይም ለጊዜው ቀጥ ብሎ መቆሚያ ሊሆን ይችላል፡፡ ግላዊ ስምና ክብርን ለመጠበቅና ለማስከበር ሲባል የሚደረግ የስግብግብነት ውጣ ውረድ ሁሉ በሰው ሕይወት ውስጥ ትልቅ የሥቃይ ሸክም ነው::

በግል ሀብት ጥሪት ፍላጎት የቆሰለና የበለዘ ሕሊናን ለማንጻትና ለማዳን የሚደረግ ጥረት መሪርና አድካሚ ነው:: ከቤተሰቦቼ የሚደርስብኝን ትችትና የወጪ ገቢ ሐሜት ለመከላከል ያህል የሕሊናዬን ዓላማ ቅንጣት ታህል ችላ ብዪ ሕይወት ኣልባ ተራ ስሜን ለማዳን ስል አንዲት የተለየች የሐሳብና የተግባር ዘመቻ ጀመርኩ። ሌሎችን ለመምሰልና ላይ ላዩን እኩል ሆኜ ለመታየት ስል አንዲት ባገልግሎት ላይ ከዋለች አራት ዓመት ያህል ያለፋት ቮልስዋገን መኪና ከስንት የደላላ ንትርክ በኋላ ገዛሁ፡፡ በክፍያው ላይ እኔና ጉልላት ተረባረብንበት፡፡ የጠንቃቃ ሰው ንብረት ስለ ነበረች በየጊዜው በመሰናከል አላስቸገረችኝም፡፡

ኑሮዬን መለስ ብዬ እያየሁ «የሕይወት ቀላል ፍቺ ይህች ትሆን? ወይስ ራስን የማታለያ ስሕተት» እያልኩ ማሰብ አዲሱ ልማዱ ሆነ፡፡ መስሎ መታየትና በጉራ ተኮፍሶ መወጣጠርን ከዚህም ከዚያም ቀሠምኩ፡፡ አንዳንድ ቀን ያን መበስበሱ እየታወቀ ቀለም እንደተቀባ ግንድ ላይ ላዩን ያሽበረቀ አስመሳይ ኑሮዬን መለስ ብዬ ሳየው ጎምዛዛ ኀዘን ይስማኝና በረጅሙ እተክዛለሁ። በሳምንት አንድና ሁለት ቀን እያመሽሁ መግባትና ሳይበዛም
መጠጥ መጎንጨትን ኣዘወተርኩ፡፡ አንድ ቀን እሑድ ከጧቱ ሁለት ሰዓት የወጣሁ ጥምብዝ ብዬ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ተኩል ገባሁ።

የወዲያነሽ ያጋጠማትን ያልታሰበ ችግር ችላ «አይ ጌትዩ! ስንቱን ለፈለፍከው ! መንጋት አበይለው ነጋ» አለችኝ ሰክሬ በገባሁ ማግሥት አብረን ቁርስ ስንበላ፡፡ ከዚያ በመጥፎ ልማዳዊ እምነት ተበክሎ ካደገው ልቦናዩ ምን አስነዋሪ ነገር ወጥቶ ይሆን በማለት በጣም ሠጋሁ፡፡ ከጎኔ ተነሥታ በስተጀርባዬ ቆመች፡፡ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ሁሉ ፊት ለፊቴ ባለው የቁም ሳጥን መስታዋት እመለከት ነበር። እሷም ይህችኑ ብልሃቴን ደርሳበት ኖሮ በመስተዋቲቱ ውስጥ ስታየኝ ዐይን ለዐይን ተጋጨን። የያዝኩትን
የእንቁላል ጥብስ ለመጉረስ አፈን ከፈት ላደርግ ሣቄ አመለጠኝና ተንከተከትኩ፡፡ እጄን ስባ ጎረሰችብኝ፡፡ 'ጌትዬ” አለችኝ ጉርሻዩን ቀምታ የልቧን ካደረሰች በኋላ፡፡ «ይኸው ዛሬ አምስተኛህ መሆኑ ነው መሰል ካንተ አላውቅምና ለምኑም ለምኑም ቢሆን ጥሩ አይደለም። ጌታነህ ሰክሮ እንዲህ አለ መባል ደግሞ አንዳች የሚያህል ነውር ነው። በዚያ ላይ ውርደቱ? ቅሌቱ... ጌትዬ አፈር ስበላልህ! ባንዲት እንጨት ስሔድ አትጠጣ፡ መቼም
ይኸን ጉድህን ጋሼ ጉልላት ኣልሰማም እንጂ ቢሰማማ....» ብላ አዘኔታና
ምክሯን አደባልቃ ከነገረችኝ በኋላ የተዳፈረችኝ ስለ መሰላት ሳይታወቃት
ትከሻዬን በግንባሯ ጠረግ ጠረግ እድርጋ ልትሸሽ ስትል እጅዋን ይዤ
አስቀረኋት፡፡

«ለመሆኑ ክፉ ነገር ተናገርኩ እንዴ? ሆድ ያባውን... የሚሉት ነገር ነበረበት?... አልኳት።

«የተናገርከው ሁሉ ምኑም አልገባኝ። እነዚያኑ ቤተሰቦችህን ስትሰድብና ስታጥላላ ነው ያደርከው:: እኔንም አይዞሽ በርቺ ድሉ ያንቺ ነው፤ ያባትሽ ስም አሸናፊ ነው እንቺም አሸናፊ ትሆኛለሽ እያልክ
ስታጫውተኝ አመሽህ» ብላ እጅዋን ነጥቃኝ ወደ ጓዳ ገባች፡፡
የገዛ ስሕተቴን ለማስተባበል ሳይሆን ለማመኻንት ያህል ከጓዳ መለስ
እንዳለች «ትላንትም በል በል ብለው፣ አጠጥተውኝ ነው እንጂ ከእንግዲህ
ወዲህ መጠጥ በረበት ኣልዞርም» አልኳትና ወደ ሥራዬ ሄድኩ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከሌሊቱ አብዛኛውን ክፍል በሐሳብ ስገላበጥ አሳለፍኩት፡፡ እሑድ ጧት ከቁርስ በኋላ ሽር አልኩ። ሰበሰቡ ላይ ቆም ብዬ የወዲያነሽን ጠራኋት።
ከወደ ውስጥ ከተፍ አለች፡፡ የምትለውን ለመስማት ያህል 'አይቆርጡን አይፈልጡን ነይ እስኪ ወላጆቼ ቤት ይዤሽ ልሂድ? እኔ እያለሁ ምንም
እትሆኚ» አልኳት፡፡

ከልቤ ስለ መሰላት ክው ብላ ደነገጠች፡፡ «እንዲህ ንገረኝና ይለይልኝ
እንጂ! እጄን ይዘህ አስገድለኛ! እንኳንስ ካንተ ጋር አብሬ እዚያች ቤት
ገብቼላቸውና መንገድ ላይ ያዩን ይሆን እያልኩ አካላቴ ይበጠቃል። ምን
ቅብጥ ልጄ! ይልቅስ ሂድ ይቅናህ!» ብላ በእርሷ አስተሳሰብ የልቧን ተናግሬ
እንዳበቃች መንገድ ገባሁ፡፡ ጠምዛዛው መንገድ ከዐይኗ እስከ ሰወረኝ ድረስ
የአጥር ግቢውን በር ተደግፋ በዐይኖቿ ሸንችኝ፡፡ መኪናዬን ከቀበና ድልድይ
በላይ አቁሜ በእግር ቀጠልኩ። የወላጆቼን ቤት ከረገጥኩ ሦስት ወር ያህል አልፎኝ ስለ ነበር በዱሮው ዘበኛ በአቶ በየነ ምትክ ሌላ ሰው ተቀጥረዋል።
አጠር ብለው ከወደ ዐይናቸው ላም ያሉ ጸጉረ ገብስማ ሽማግሌ ናቸው::
አያውቁኝም። ለመግባት ፍቃድ ጠየቅሁ። ደረታቸውን ለረፋዷ ፀሐይ ሰጥተው
ማንን ነው የምትፈልገው? ጌቶችና አሜቴ እንደሁ ቤተስኪያን ሊስሙ እንደ
ኤዱ አልተመለሱም፡፡ ቆየት ብለህ ተመልሰሀ ናና ነግሬልህ ትገባለህ» ብለው ፊታቸውን አዙረው ችላ አሉኝ፡፡ ቸልታቸው ስላበሳጨኝ ልጃቸውስ የለችም
እንዴ? እሷም ካለች ያው ነው» ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ በጥፊ የመታኋቸው ያህል
ብው ብለው ተናደዱ፡፡ «እንዴ! እንዴ! መች አበድኩና! አንተ ስለ እኔ
እንጀራ ምንቸገረህ! የዋዛ ቤት መስሎሃል! እዚች ቦታም አያውሉኝ!» አሉና ነገሩኝ፡፡ ቀባጥሬም ሆነ ማንነቴን አስረድቼ መግባት ስላልፈለግሁ ደጅ ደጁን እያልኩ ለመቆየት ወሰንኩ፡፡ በዚያው አካባቢ መለስ ቀለስ ስል የውብነሽ ባዘቶ የመሰለ ነጭ ጋቢ ለብሳ ስትመጣ አየኋት።አመጣጧ በእኔው ኣቅጣጫ ስለ ነበር ቆሜ ጠበቅኋት። ከሩቅ የጀመረው ፈገግታዋ አጠገቤ ስትደርስ ተራውን ለውብ ጥርሶቿ ለቀቀ፡፡ ከጋቢው ሥር እጅዋን ብቅ አድርጋ ጨበጠችኝ፡፡ ስሜቷን ለመሸንገል ያህል ሳምኳት፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዘን ሽማግሌው ኣጠገብ ደረስን፡፡ ቀና ብለው ከእግር እስከ ራሴ አዩኝ። ይኸ ደግሞ የማን ነው? በሚል አስተያየት እየገረመሙኝ አልፈናቸው ገባን፡፡

በምድረ ግቢው ያሉት አበቦችና አትክልቶች በጣም ያማሩ መሰለኝ፡፡
ከየውብነሽ ጋር እያወራሁ ዐይኖቼ ካትክልቶቸ ላይ አልተነቀሉም፡፡ እነዚያ
ምን ጊዜም ሌላ መሄጂያና መግቢያ የሌላቸው የሚመስሉት ነባር ሠራተኞች
ናፍቆትን በሚገልጽ ፈገግታ እጅ ነሡኝ፡፡ ውስጥ ውስጡን ግን ዛሬ የጌቶች
ልጅ ከየት መጡ?” እንደሚሉ ታወቀኝ፡፡ አንደኛዋ ሠራተኛ እማማ ወለተሩፋኤልማ በወላጆቼ ቤት ውስጥ ከ30 ዓመታት በላይ አገልግለዋል፡፡ እኔ ግን ገና ከልጅነቴ ጀምሮ አልወዳቸውም ነበር፡፡ ኣብሮ ከመኖር ብዛት የተነሣ
እናትና አባቴ እንደ "ገረድ አያዩዋቸውም፡፡
👍4
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


እናቴም የአባቴን አኳኋንና ለዘብተኛ አነጋገር በመከተል እንደ ወትሮዋ አልተቆጣችኝም

ከየውብነሽ ጋር መገናኘቴን ቀጠልኩ። አባቴ ስለ እኔ ያለውን አስተያየት እምብዛም እንዳልለወጠው አጣራሁ፡፡ እናቴም የእኔን ደጅ ደጅ ማየት ችላ እንዳለችውና እንኳን ከዚያች ከመናጢ ገረድ ጋር አብሮ ያልታየና ስማችንን ያላስጠፋው እንጂ የኋላ ኋላ መመለሱና ልብ መግዛቱ አይቀርም፡፡ እኔም ለጊዜው ንድድ ያለኝ ከገረድ ጋር መዋልና መልከስከሱ ነበር፣ ሌላ ሌላውስ ግድ የለም” ማለቷን የዋህ ተመስዩ ከየውብነሽ ሰማሁ፡፡

ያም ሆነ ይህ አንድ ቀን የእኔንና የየወዲያነሽን ጉዳይ ይፋ ለማውጣት ቆርጬ በምነሣበት ጊዜ ንትርክና ከባድ የቤተሰብ ውዝግብ እንደሚያጋጥመኝ በእርግጠኝነት ወለል ብሎ ታየኝ፡፡ ካለፈ አገደም ከሥራ መልስ በምሳ ሰዓት ወደ ወላጆቼ ቤት እየሄድኩ የሻከረ ሆዳቸውንና
አስተያየታቸውን ደረጃ በደረጃ ለመለወጥ ጥሩ ጥረት አደረግሁ፡፡ ተደጋጋሚ
ሙከራዩ ትንሽ የለውጥ ፍሬ አሳየ፡፡ በተለይም ከእናቴ ጋር የማደርገው ወሬና
ጨዋታ ሁሉ አስደሳች ቅርርብ ፈጠረ፡፡ ትንሽም ፊቷ በኀዘን የሚጠወልግና
የጠራራ ቅጠል የምትመስለው ደህና እደሪ ብዬ ለመሄድ በምነሣበት ጊዜ
ነበር።

አንድ ቀን ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ከየውብነሽ ጋር መኝታ ቤቷ ውስጥ
ተቀምጠን ሞቅ ደመቅ ያለ መሬ ስናወራ «አንተ ጌታነህ» አለችኝ፡፡ ዐይኖቿ
የትዝታዋን ክብደት ለማስረዳት እየቦዙ ያነዩ ዱሮ ከዚያች ከገረዳችን ጋር
እንዲያ ስትሆን አባባ ያየኛል፣ ይሰማብኛል ብለሀ አልፈራህም?» ብላ
ታላቅነቴን በማክበር የኃፍረት ሣቅ ሣቀች። ምናልባት አንዳንድ ያልሰማሁትን
ነገር ታሰማኝ ይሆናል በማለት ልበ ግልጽ
ተመስዩ «እንዳልታይና እንዳይሰማብኝ ያልሠራሁትና ያልፈጸምኩት ዘድ አልነበረም። አንቺንም በጣም እፈራሽና እጠራጠርሽ ነበር» አልኩና አልጋዋ ላይ ጣል ያደረገችውን የሰነበተ ጋዜጣ ማገላበጥ ጀመርኩ። አንገቷን ወደ ቀኝ ሰበር አድርጋ የማገላብጠውን
ጋዜጣ እየተመለከተች ግን እኮ እያደር እንዳፈቀርካትና ከወዲያ ወዲህ
እየተመላለሰች በምትሠራበት ጊዜ ዐይኖችህ አብረዋት እንደሚዋትቱ ኣሳምሬ ዐውቅ ነበር፡፡ ከእንጀራ አቅም እንኳ ሌላ ሰው ሲያቀርብልህ ደስ አይልህም ነበር። እሷም የዋዛ ሾላካ አልነበረችም ! ኋላማ ልናባርራት አቅራቢያ
አረማመዷና አነጋገሯ፣ ጸጉር አሠራሯና አለባበሷ ሁሉ በጣም ተሻሽሉ ነበር፡፡
እኔ ከሁሉም ከሁሉም የማይረሳኝ ጠባይዋና ሲያዝዋት እሺ ባይነቷ ነው፡፡ ምን ይሆናል፣ ያ መሳይ መልክ ያለ ቦታው ቀረ፡፡ እሷ የተማረች ሆና ውጪ
ውጪውን ብናገኛት ኖሮ... እኔ ግን እስከ ዛሬ ድረስ ስለ እሷ አንዳችም ወሬ
ሰምቼ አላውቅም» ብላ አጠናቀቀች። የወሬ ከረጢቷን መፍታቷ ስለ ታወቀኝ
ለጊዜው ውስጣዊ ብስጭቴን ኣፍኜ ባናነሣው ይሻላል ያለፈው አልፏል እንጂ
ብሳሳትም ባልሳሳትም ከዚህ ቤት ስታባርሯት እርጉዝ ነበረች። ቀስ ብላችሁ
ሹክ ብትሉኝ ኖሮ እንደምንም አንዱ ጋ አስጠጋትና ትወልድ ነበር፡፡

ይኸንዬ እኔን አባብዬ” ሲል አንቺን ደግሞ ”እቴቴ' እቴ ሸንኮሬ 'እት -አይገኝ” ይልሽ ነበር» አልኳት፡፡ የአሁኑን የ'ወዲያነሽን ሕይወትና ኑሮ የማታውቀዋ እኅቴ ከሁሉም ከሁሉም በጣም የሚያሳዝነኝ» ብላ ቀጠለች፣
«ያነዪ አንተ ወደ ሥራ ወጣ ከማለትu እማዬ በአባባ ከዘራ ታፋ ታፋዋን'
ጀርባ ጀርባዋን ስትደበድባት ኩርምት ብላ ስትደበደብ የወረደባት የዱላ መዓት ነው፡፡ በመጨረሻ የተሰነዘረው ዱላ መኻል እናቷ ላይ በማረፉ ደሟ በጸጉሯ ውስጥ እየተንጀረጀረ ትከሻዋ ላይ ተንጠፈጠፈ፡፡ ነፍስ ይዟትም ይሁን ያሰበችውን እንጃ ከዘራውን ይዛ እለቅም በማለቷ እኔም እናቴን የተዳፈረችብኝና ግብግብ የምትገጥማት ስለመሰለኝ ሁለት ጊዜ በጥፊ አላስኳት።

«እሷ ግን ቀና ብላ አይታ፣ አንቺም? አንቺም? ጨክነሽ ትመቺኝ የውብነሽ? ኣይ ድኃ መሆን!” ያለችኝ ዛሬም አንጀት አንጀቴን ይበላኛል፡፡»
«እሷ ግን በጣም የተንገበገበችውና ያለቀሰችው ከቤት በመባረሯና
በመደብደቧ ሳይሆን እንተን ሳትሰናበትሀና ሳታይህ በመሔዷ ነበር። ከሥራ ስትመለስ መንገድ ላይ ጠብቃ እንዳታግባባሀና በሴት እንባዋ እንዳታታልልህ ከዚህ አካባቢ ያባረርናት በዘበኛ ነበር» ብላ ያን ዚያ ቀደም አሳርሮ
ያከሰለኝን መራራ ነገር እንደገና ጋተችኝ፡፡ የየወዲያነሽ መከራና እንግልት
ሁሉ ከተቀበረበት የትዝብት መቃብር ወጥቶ ነጭ ዓፅሙ ፊት ለፊቴ ተገተረ፡፡ ሌላ ተጨማሪ ነገር በመስማት አንጎሌን ማጥመልመል ስላልፈለግሁ
«ነገ አራት ሰዓት ላይ ዕጓለ ማውታ ስለምሔድ አብረን እንሂድ። ከዚያ በኋላ
ደግሞ ሌላ የማማክርሽ ጉዳይ ስላለ ቀደም ብለሽ ቀበና ድልድይ አጠገብ
ጠብቂኝ ብያት ወጣሁ፡፡

በማግሥቱ እሑድ እኅቴና ባለቤቴ ዕጓለ ማውታ እንዳይገናኙብኝ፡ የወዲያነሽን «እንግዳ ይዤ እመጣለሁና ተዘጋጅተሽ እንድትጠብቂኝ፡ ከዚያ በኋላ እንሔዳለን» ብያት ከቤት ወጣሁ፡፡ መኪና መግዛቴን መላ ቤተሰቦቼ ስላልሰሙ የውብነሽ የምትጠብቀኝ በእግር እንጂ በመኪና ይመጣል ብላ አልነበረም፡፡ ጥቂት ደቂቃዎች ዘግየት ብዬ ቀጠሮእችን ቦታ ስደርስ የውብነሽ ተረከዘ ሹል ጫማ አድርጋ ከጉልበቷ ትንሽ ከፍ ያለ ቀለመ ብዙ የፈረንጅ ቅድ ቀሚስና ነጭ ሸሚዝ ለብሳ ቡናማ ኮረጆዋን አንግታ ድልድዩ አካባቢ ስትጠብቀኝ አገኘኋት። መኪና አጠገቧ ደርሳ በመቆሟ ባለ መኪናውም እኔ መሆኔን ባለማወቋ ፊቷን በቁጣ ከሰከሰች፡፡ እንዳንድ የጎዳና ሴቶች
ለመግደርደር ሲሉ የሚያሳዩት አኳኋን ትዝ አለኝና የየውብነሽ አድራጎት አሣቀኝ፡፡ ወዲያው ወጣ ብዬ ወደ እርሷ ተራመድኩ። ከመኪና ወጥቶ ወደ
እርሷ የሚራመደው ሰው ታላቅ ወንድሟ መሆኑን ስታውቅ የአድናቆት ሣቅ
ሣቀች፡፡

«መኪና ገዛሁ እንዳትለኝ አለችኝ፡፡ «አዎ ገዛሁ እኔም ወጉ ይድረሰኝ ብዬ ገና ሁለተኛ ወሯን መያዟ ነው» አልኩና እየተሣሣቅን ተጨባበጥን፡፡
«የውቤ፣ ይቺንም ታድያ ቤተሰብ እንዳይሰማ፣ እንድ ቀን ሁሉንም ነገር
አጠራቅሜ አቀርበዋለሁ፡፡» «ሌላ ደግሞ ምን የሚነገር አለህ?» ብላ አየችኝ፡፡
«እኔ ገና ብዙ የሚነገር ነገር አለኝ» ብያት መኪና ውስጥ ገብተን መንገድ
ቀጠልን፡፡ በአሥራ አምስት ደቂቃ ውስጥ አግድመት ቁልቁለቱን ጨርሰን
ሕፃናት ማሳደጊያ ድርጅት ደረስን፡፡ ለምለሙ መስክ ላይ ትላልቅና ትናንሽ
ልጆች እንደ ጥሬ ፈስሰው ልዩ ልዩ ጨዋታዎች ይጫወታሉ። ከትንንሾቹ
ልጆች መኻል አንድ የግራ ዐይኑ የጠፋችና በዐይን አር የተጨማለቀች
ሰማያዊ ቁምጣና ትከሻው ላይ የተጣፈች እሷኑ መሰል ኮት የለበሰ ልጅ
በሩጫ መጥቶ ጨበጠኝ፡፡ የጋሻዬነህ ጓደኛ ነው:: ከኪሴ ከረሜላ ኣውጥቼ ሰጠሁት። የውብነሽ በድንጋጤ አፏን ከፍታ «ምነው ምን ሆነ? ዐይኑን ምን ነካው? ደኅና አልነበረም እንዴ !?» አለችኝ፡፡
«ይህ እኮ ያ ከዚህ ቀደም ያየሽው የጓደኛዬ ልጅ አይደለም፣ ይኸ ጓደኛዉ ነው:: አሁን ሮጦ ይጠራልናል» አልኩና የደነገጠውን ስሜቷን በደስታ
አደስኩት:: ከረሜላውን ልጦ ጎረሰና ተለይቶን ሔደ። እምብዛም ሳይቆይ
ጋሻነህን ይዞት መጣ፡፡ አንዲት በጣም የጠወለገች ነጭ አበባ ይዞ ነበረ።
እጆቼን ከብብቱ ሥር አስገብቼ በማንሣት ጉንጮቹን ስስም ሁሉም ነገር
ጥሉኝ ጠፋ፡፡ የውብነሽ ቀበል ብላ አገላብጣ ሳመችው:: ቀድሞውንም የሙት ልጅ ነው ብዬ ነግሬያት ስለ ነበር በርኅራኄ ተመለከተችው:: አላስችል ስላላት ዕንባ ተናነቃት። መሐረቧን አውጥቃ ዐይኖቿን አበሰች። «ለመሆኑ ያባቱ ዘመዶች እየመጡ ይጠይቁታል እንዴ?» አለችኝ፡፡ ልጅ ያለው መሆኑን የሰማ አንድም
👍2
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል

...አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ ለተለመደው የሥራ ጉዳይ ሳይሆን ለግላዊ ጉዳዩ ወደ አለቃዬ ጽሕፈት ቤት ገባሁ፡፡ በመጠኑ ግልጽ ሆኖ መናገር ፈቃድ በማግኘት በኩል ነገሩን የሚያፋጥንልኝ ስለ መሰለኝ ያጋጠመኝን ጉዳዬ ቀነጫጭቤ በሾላ በድፍን ዘዴ አስረዳሁ፡፡ ንግግሬን እንደ ጀመርኩ የወዲያነሽ ጆሮዬ ላይ ለጠፍ ብላ የምታበረታታኝ መሰለኝ፡፡

አለቃዩ አንደበቱን አለስልሶና የዝቅተኝነትን ስሜት በሚገልጹ ቃላት ተጠቅሞ የሚጠይቃቸውን ሰው ስለሚወዱ ጆሮአቸውን አቁመው ሰሙኝ::
የጉዳዩን አሳሳቢነትና መደረግ የሚገባውን ውጣ ውረድ ሁሉ ከኑሮ ልምዳቸው ስላወቁልኝ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ እያመለከትኩ ለመሔድ እንደምችል ካንዳንድ ግዴታዎች ጋር ነገሩኝ፡፡ አዎ ጌታነህ ከባድ ግዴታ ያለብኝ ሰው ነኝ።

የመጀመሪያዋን ቃታ ሳብኩ! ማመልከቻዪን ለዕጓለ ማውታው የበላይ
ባለሥልን ለማቅረብ የሐሳቤ ዝግጅት ተጠናቀቀ። የእኔንና የባለቤቴን
የግንኙነት መነሻ፣ የወላጆቼን የአመለካከት አቋም፣ እንዲሁም የልጃችን
ሕይወት ለምንና እንዴት ለዚያ ዕጓለ ማውታ እንደበቃ ተንትኖ የሚያስረዳ
ጽሑፍ ማዘጋጀት እንዳለብኝ ከየወዲያነሽ ጋር ተነጋገርንበት።

ማታ ከት/ቤት መልስ ግራና ቀኝ ተቀምጠን ሐሳብ ለማቀነባበር
ተፍጨረጨርን፡፡ ከጉዳዩ አፈጻጸም ጋር በጣም ተፃራሪ የሆነ አቋም ቢኖረኝም ሁኔታውን ሁሉ ተቋቁሞ ሌላ አመቺ ሁኔታን መፍጠር ግን የማይቀር ግዴታ ሆነ፡፡ በመጠኑ ሞጫጭሬ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ገደማ ለወጉ ያህል ጋደም አልኩ።ቁንጫውን ለማራገፍ እንደሚንደባለል ውሻ አልጋዩ ላይ መንከባለል እንጂ እንቅልፍ በማጣቴ ሁለት ሰዓት ያህል ቆይቼ ተነሣሁ፡፡ አካባቢዬ ጸጥ በማለቱ ሐሳቤን በቅደም ተከተል ለማስፈር ውጫዊ ችግር አልገጠመኝም፡፡ ምንም እንኳ የእኔና የወዲያነሽ የሕይወት ገድል በሁለትና በሦስት ገጽ ጽሑፍ ተዘርዝሮ የማያልቅ ቢሆንም መቆነጻጸሉ ግን የግድ አስፈላጊ ነበር፡፡ የወዲያነሽ በወላጆቼ ቤት ውስጥ ሠራተኛ ሆና ማገልገሏን፣ በእርግዝናዋ
ወራት ከቤት መባረሯን፣ የእኔን ማንነትና ያረገዘችውም ከእኔ እንደ ነበር፣
በችግርና በእጦት ተንገላታ ልጅዋን በጭካኔ ሳይሆን በአስገዳጅ የኑሮና የጊዜ ሁኔታ አሳዳጊ እንዲያገኝ ብላ ጥላው መጥፋቷን፣ ከዚያም በወንጀለኛነት ተይዛ አምስት ዓመት መታሰሯን፡ ልጁም በድርጅቱ አማካይነት በማደግ ላይ መሆኑን በልክ በልኩ አሳምሬ ጻፍኩ፡፡ በተጨማሪም እኔና የልጄ እናት በነበረንና ባለን እውነተኛ ፍቅር ትዳር መሥርተን ኣብረን በመኖር ላይ
መሆናችንን አከልኩበት። ቀላል በሆነ አገላለፅ የተቀነባበረ ማመልከቻ
ተዘጋጀ፡፡
በመጨረሻም ድርጅቱ ይህን እስከ ዛሬ ድረስ በጥንቃቄ ያሳደገልንን ልጅ በሕጋዊ መንገድ አስረክቦን ልጃችንን ማሳደግ እንችል ዘንድ የሚጠይቅ ማለፊያ መደምደሚያ አደረግሁለት። ረቂቁን ገልብጬ ስጨርስ ሰማይና መሬት ተላቀቀ። የወዲያነሽ ከእንቅልፏ ነቃች፡፡ አልጋውና የተቀመጥኩበት ወንበር አፍና አፍንጫ ነበሩ። መለስ ብዬ ስመለከታት ካንገቷ ቀና ብላ በድንጋጤ ታስተውለኛለች፡፡ እጆቿን በትከሻዬ ላይ አሳልፋ ጣቶቿን ደረቴ ላይ አንጠለጠለቻቸው። የተበታተነው ጸጉሯ አንገቴ ላይ ሲኩነሰነስ በጣም
እንደ ተጠጋችኝ አወቅሁ፡፡ ተቀምጬ በማደሬ አካላቴ ዝሏል፡፡ የወዲያነሽን
ሐሳብ ላይ ጣልኳት፡፡ በቀኙ ትከሻዬ ላይ ደፋ አለች። በአንገቴ ሥር የተጋደመውን ክንዷን እየደባበስኩ «እንግዲህ አንድ ጊዜ ጀምሬዋለሁ፣ ፍጻሜውን ሳላይ ፊቴን አላዞርም» አልኩና ጽሑፉን አነበብኩላት። የሐሳብ ሰመመን ይዟት ነጎደ። የጻፍኩትን ማመልከቻ ሳጣጥፍ በአእምሮዬ ውስጥ
የተረገዘው ፍላጎቴ ዕለተ ልደቱ እንደ ደረሰ ታወቀኝ፡፡ ውጤቱን በግምት ሳሰላስል የወዲያነሽ ከአልጋው ላይ ወረደች፡፡
ቁርሴን በልቼ ከቤት ስወጣና መኪና አስነሥቼ ስሔድ የማልመለስ ስለ መሰላት ዐይኖቿ ከላዪ ላይ ሳይነቀሉ ተለይቻት ሔድኩ።

ማመልከቻዬን ለባለ ሥልጣኑ ከማቅረቤ በፊት መኪናዬ ውስጥ ሁለት ጊዜ ወጣሁት። የድፍረት ወኔ አጥለቀለቀኝ፡፡ አረማመዴ ጎምላላ ሆነ።አንኳኩቼ ስገባ መላ ሰውነቴ ተሟሟቀ። ማመልከቻዬን ሳቀርብ በሐተታው ርዝመት እንጂ በዘረዘርኩት ከፊል ምስጢር ቅንጣት ታህል አላፈርኩም፡፡አያሳፍርማ!! እንዲያውም ማቀርቀሬና መደንገጤ ቀርቶ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማቅረብ ተዘጋጀሁ፡፡ ለሦስት ደቂቃዎች ያህል ታሪኩን ያላንዳች እንቅስቃሴ
አነበቡት። የታሪኩ አነሳና አካሔድ ስላስደነቃቸው ራሳቸውን ይነቀንቁ
ጀመር፡፡ ስሜታቸውና ሁኔታቸው ስላፍነከነከኝ የተስፋ ምጥ አጣደፈኝ፡፡
የሚያስደንቅ ዐረፍተ ነገር ሲያጋጥማቸው ንባባቸውን እያቋረጡ ስለሚመለከቱኝ የምትወጂውን ታሚያለሽ እንደ ተባለች ፈሰሰ ሁለመናዬ በደስታ ተነከረ፡፡ ሁለቱን ገጾች ጨርሰው ሦስተኛዉን ሲጀምሩ ወረቀቱን አጠፍ አድርገው ጠረጴዛውን በሁለት ክንዳቸው ተመረኮዙ። ከእግር ጥፍሬ እስከ ራስ ጸጉሬ ተመለከቱኝ። እንደገና ደግሞ «ልጄን በችግርና በሥቃይ ከመግደል ይልቅ ምናልባት ርኅሩኅ አሳዳጊና ሰብሳቢ ቢያገኝ ብዩ ብዙ ሕዝብ ከሚተላለፍበት መንገድ
ላይ በጨርቅ ጠቅልዩ ጣልኩት» የሚለውን የእናትየዋን አነጋገር ጽፌው ስለ ነበር ጮክ ብለው አነበቡት።

ምንም እንኳን እሷን ለመርዳትና ልጀንም ለማሳደግ ሙሉ ችሎታ ቢኖረኝም ከቤት የተባረረችው በሌለሁበት ጊዜ ስለነበርና ኋላም አድራሻዋን ለማግኘት ባለመቻሌ ይህ የአንድ ትውልድ የመጥፎ ልማድ ድርሻ ሊደርስብን ቻሏል የሚለውን ሐተታ በቀዳሚው የድምፅ ሁኔታ ደገሙት። አንብበው ከጨረሱ በኋላ ላቀረቡልኝ ጥያቄ የተብራራ ኣጥጋቢ መልስ ሰጠሁ፡፡ ጥያቄ በሚያቀርቡበትና መልስ በሚሰሙበት በሚያደርጉት ከፍተኛ ጥንቃቄ የጦር ስልት እንዳይበላሽበት የሚከታተልና የውጊያ ስልት ሚዛን የሚቆጣጠር የጦር አበጋዝ ይመስላሉ፡፡ መልሶቼን ሁሉ እያጣጣሙ ተራ በተራ ዋጧቸው::

ለእርሳቸው የአንድ ጉዳይ ተራ ውጥን ቢሆንም፡ ለእኔ ግን አንድ አነስተኛ የትግል ምዕራፍ ነበር፡፡ ሙሉ ተስፋ በማይሰጥ ሁኔታ ቀጠሮ ተቀብዩ ወጣሁ፡፡

ጉዳዩ በቀላሉ የማይፈጸም በመሆኑ ድርጅቱ ጥያቄውን አብላልቶ ከአንድ ውሳኔ ላይ ለመድረስ በጉዳዩ ላይ አተኮረበት።

ደጅ ደጁን ፍሬ ሐሳብ የሚያቀብለኝና በጎደለ የሚሞላልኝ ጉልላት ነበር፡፡ በየቀጠሮው ቀን ስቀርብ የሚጠብቀኝ ጥያቄ ከዕለት ወደ ዕለት እንደ
ስንቅ ሟሸሸ፡፡

አነጣጥሬ የለቀቅሁት የሰላም ቀስት ዒላማውን መታ፡፡ ልክ ባሽመቅሁ
በኻያ አንደኛዉ ቀን የድርጅቱ ደንብ እና ሌላውም ሕግ በሚፈቅደው መሠረት ልጁን የምረከብበት ቀን ተነገረኝ፡፡ ባለቤትህን ይዘህ እንድትቀርብ
ተብዬ ስለ ነበር የወዲያነሽን ተነሽ አልኳት፡፡ ዶፍ እንደ ወረደበት የፍየል
ግልገል አካላቷ ተሽማቀቀ፡፡ ልማደኛ እንባዋ አትንካት ሲል ተንቆረዘዘ፡፡
አስታራቂ ሐሳብ ስላልነበረ ተረታች፡፡ «እንዴት ብዩ ከሰው ፊት እቀርባለሁ?
ያለፈውን አድራጎቴን ሁሉ ቢጠይቀኝስ ምን እመልሳለሁ? ይቺ ጨካኝ
አረመኔ ቢሉኝስ ምን እላለሁ? አንተን እንዳልኩህ ነው የምላችው?» ብላ
በሥጋት ጠየቀችኝ። እእምሮዋ ተናውጦ እንዳይናጋ የፈጸምሽው ሁሉ በወቅቱ
ባጋጠመሽ አስገዳጅ ሁኔታ የተደረገ ተራ ድርጊት እንጂ ይህን ሁሉ አጓጉል
ስያሜ የሚያሰጥ ባለመሆኑ አታስቢ» ብዩ ካግባባኋት በኋላ ሄድን።

በመንገድ ላይና ድርጅቱም ጽሕፈት ቤት ከመግባታችን በፊት በጣም ስለ አበረታታኋት አራት የድርጅቱ ባለሥልጣኖች በተሰበሰቡበት ክፍል ውስጥ ለጥያቄዎቻቸው ሁሉ መልስ እንድትሰጥና ሐሳቧንም ያላንዳች ግፊት
እንዲሰሙ ጥያት ወጣሁ፡፡ በአስተዋይነቷ ስለምተማመን ምን
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሰላሳ


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...ጉልላት ሙሽራ ይዞ እንደሚመለስ ሚዜ በደስታ ብዛት ከወዲያ ወዲህ ይዞራል፡፡ እኔ ግን እምብዛም አያሌ ለውጥ የሚገኝበት ሕይወትና የኑሮ አካባቢ እንደማይጠብቀው ስለማውቅ አልፈነደቅሁም፡፡ በአካባቢው የነበሩት
ሰዎች ሁሉ እኔንና የወዲያነሽን «እንኳን ደስ ያላችሁ! እሱንም እንኳን ለዚህ
እበቃው!? እያሉ መልካም ምኞታቸውን ገለጹልን፡፡ የወዲያንሽ ከፍተኛ ደስታ
ስላጥለቀለቃት የሚፈጸመውንና የሚነገረውን ሁሉ የምትከታተልና
የምታዳምጥ ኣትመስልም፡፡ የድርጅቱ ተወካይ ባለሥልጣን ጋሻዬነህን ጎንበስ
ብለው ካነሡ በኋላ በወዳጅነት ፈገግታ ተዝናንተው «ለቁም ነገር የሚበቃና
የተባረከ፣ እናት አባቱን አክባሪ ጧሪ ቀባሪና አስመስጋኝ ልጅ እንዲሆንላችሁ
እመኛለሁ» ብለው ጋሻዬነህን ለየወዲያነሽ አስረከቧት፡፡ የጋሻዬነህ እጅ
በየወዲያነሽ አንገት ዙሪያ ተጠመጠመች ጉልላት ከአበባ ወደ አበባ ለቀሠማ
እንደምትዘዋወር ንብ ሰውን ሁሉ ይዞረዋል። የወዲያነሽ ሰውነቷ እየተንዘፈዘፈ የደስታ እንባ አነባች፡፡ የንጋት ፀሐይ ጨረር እንዳረፈበት የባቄላ አበባ
የሚያስደስተው ጥርሷ ፍልቅቅ ብሎ በመታየት የውስጣዊ ደስታዋ ምስክር
ነበር፡፡ ደስታና ትዝታ ተቃረጧት፡፡ «ቀስ በቀስ ደስታዬ ውስጥ ውስጡን
እንደ እሳተ ገሞራ ፍል እየተንሸከሽከ ሰውነቴን አሞቀው፡፡ የወዲያነሽ
ጉጉትና ምኞት ተፈጸመ፡፡ ወዴት እንደሚወሰድ የማያውቀው ጋሻዬነህም
ከእናቱ ትከሻ ባሻገር ወደ ኋላ እየተመለከተ የስድስት ዓመታት መኖሪያውን ለቅቆ ወጣ፡፡

ጋሻዬነህን ይዘን ወደ ቤት ስንገባ ቀደም ብለው ወሬውን የሰሙት ሦስት ወራት ያህል የቅርብ ጎረቤቶቻችን በሙሉ ደስታ ተቀበሉን፡፡ የወዲያነሽ ጋሻዬነህን አቅፋ ፊት ለፊቴ ተቀመጠች። ጋሻዬነህ ግራ ገባው። በማያውቀው አዲስ አካባቢ በመገኘቱ ተጨነቀ፡፡ ዐይኖቹ ተቅበዘበዙ፡፡ የቤቱ ዕቃና በዙሪያው ያሉት ሰዎች ሁሉ አዲስ ስለ ሆኑበት ቀስ እያለ በፍርሃት ዐይን አያቸው። የለበሰው ነጭ ልብስና የእናቲቱ አረንጓዴ ቀሚስ በአንድነት ሲታዩ በቄጠማ መኻል የበቀለች ነጭ አበባ መሰሉ፡፡ የተደረገው ውጣ ውረድ ሁሉ
አስደሰተኝ፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ለሚመጡት የጎረቤት ሰዎች ከወዲያ ወዲህ እያሉ ጠላ የሚቀዱት ጉልላትና ሠራተኛችን ነበሩ፡፡ የወዲያነሽማ ከተቀመጠችበት የምትነሣ አትመስልም ነበር፡፡ የሰው ሁሉ ዐይን በእናትና ልጅ ላይ አረፈ። «እንኳን ለዚህ አበቃሽ! እንኳን ደስ ያላችሁ፣ እሰየው እሰይ» እያሉ የሚስሙን የሰፈሩ ሰዎች ደስታችን ደስታቸው ሆነ። ጋሻዬነህ
መላ ቅጡ ጠፋው። ከእናቱ ተቀብዬ ስታቀፈው ከጭልፊት አምልጣ ከጭራሮ
መዝጊያ ሥር እንደምትሸጎጥ ጫጩት ደረቴ ላይ ተለጠፈ፡፡ ዐሥር ሰዓት
ገደማ ጉልላት፣ እኔና የወዲያነሽ እንዲሁም የቤታችን አዲሱ 'ሰው' ብቻ
ቀረን፡፡ የቤቱን ወለል ለመንካት የፈራ ይመስል ከእኔና ከእናቱ ዕቅፍ
አልላቀቅ አለ። ካፈናት የደስታ ሲቃ ጋር ትንሽ በትንሽ ስለ ተለማመደችና
የጎጆ ነገር በመሆኑ የወዲያነሽ ጉድ ጉድ አለች፡፡ ጋሻዬነህንም በእጅዋ ይዛ
ከመኝታ ቤት ወደ ትልቁ ክፍል ከዚያም ወደ ውጭና ወደ ግቢው እየወሰደች
አዝናናችው፡፡ በፍርሃት ተሳስሮ የቆየው ሰውነቱ በመፍታታቱ በፊቱ ላይ
የፈገግታ ጮራ ታየ፡፡ የቤቱን ውስጥ ዕቃዎች አንድ በአንድ እያየ መደባበስ
ጀመረ፡፡

ከዚያም ዐልፎ ”እማማ” እያለ ጥያቄ ማቅረብ ቀጠለ፡፡ ከሁሉም ከሁሉም እማሚ የምትለዋ ቃሉ ልቤን በደስታ ዘርፍ አሳመረቻት፡፡ የጉልላትን ዐመል የምታውቀዋ የወዲያነሽ ወፍራም ሻይ አቀረበችለት፡፡ የሚፈልገውን ያህል ስላላነቃቃው ጋደም አለ፡፡ የጋሻዬነህ አእምሮ ከአካባቢው ጋር ተላምዶ ፍርሃቱ በመቃለሉ ብቻውን በሰበሰቡ ላይ መሯሯጥና ዕንጨቱን እያሻሽ መጫወት ጀመረ፡፡ ትዎትም ትም እያደረገ በፍጥነት በሚራመድበት ጊዜ አንገቴን እርሱ ወዳለበት ቦታ አስግና «ቀስ! ቀስ እያልክ እንዳትወድቅ፣ ረጋ ብለህ ነው መጫወት! እያልኩ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት በመብቃቴ ያባትነት ኩራት ተሰማኝ፡፡ ድንገት እግሩ ከእግሩ ጋር ተጋጭቶ ወይም አንሸራቶት ሲወድቅ «አይዞህ! የኔ አንበሳ! » ብዬ ላነሳው በመሮጤ አንጎሌ
በደስታ ሰከረ፡፡ የዕለቷ ፀሐይ ግዴታዋን ጨርሳ ስትሰናበት ጉልላትንጰለመሸኘት ወጣሁ፡፡

የዚያች የጋግርታም መኪናው ሞተር ፍዳችንን አሳየን። «ሙክት ሲያጡ ወጠጤ አርደው ድግስን ይወጡ» ሆነና የእኔዋን ይዞ ሔደ፡፡ ቀኑም ሆነ ምሽቱ እንደዚያ ዕለት አጥሮብኝና ፈጥኖብኝ አያውቅም፡፡ ጊዜ የሚጨበጥ ግዙፍ ኣካል ቢሆን ኖሮ ይለይልን ነበር፡፡

አዲስ መዐድ ! በቀዳሚ ትግልና ድል ያጌጠ መዐድ! ከነጠላ ወደ ስሉስ አካላት የተሸጋገረ መዐድ! ያቺ የሁለት ቀን የወንደላጤነት ቤቴ ቀደም ሲል በየወዲያነሽ ዛሬ ደግሞ ጋሻዬነህ ደምቃ ምሰሶዋ ወፈረ።ለመጀመሪያ ጊዜ በመዐዳችን ዙሪያ ሦስት ማእዘን ሆነን ተቀመጥን። የተስፋዬ ዘለላ ተጨባጭ ፍሬ አፈራ፡፡ የመከራ ቀንበሯ ገና ያልተሰበረው የወዲያነሽ፡አረሠብሩህ ተስፋ ያለውና የሥቃይ ፍሬ የሆነው ጋሻዬነህ፣ ያን ሁሉ የኑሮ ኮረኮንች አልፈውና፡ ከፊት ለፊት ያለውን ጉራንጉራም የሕይወት ወጣ ገባ
እና የኑሮ ጭጋግ ከእኔ ጋር አብሮ ለመጋፈጥ ተገናኘን፡፡

ሕሊናችን በደስታ በመሞላቱ ሆዳችን ጠገበ፡፡ ችግር የተፈጠረው መኝታ ላይ ነበር፡፡ እኔ በበኩሌ ወደ እኔ ዞሮ አቅፌውና አቅፎኝ እንዲተኛ ስፈልግ፣ እናቱ ደግሞ «ኧረ ምን ሲደረግ አንተ እኮ አምስት ዓመት ሙሉ እስኪበቃህ አይተህ ጠግበኸዋል» ብላ አሻፈረኝ አለች፡፡ ወዲያ ብል ወዲህ ብል ተሸነፍኩ፡፡ ካንገት በላይ እሷን ያናደድኩ መስሎኝ ወደ ግድግዳው ዞሬ ተኛሁ፡፡ ዝም ብላ በመተኛት ፈንታ ቀስ እያለች ከልጅዋ ጋር ወሬዋን ቀጠለች፡፡ ትኩስ የአባትነት ቅናት አላስተኛ ስላለኝ ያለ ምክንያት መገላበጥና ማካክ አበዛሁ፡፡ የልጅዋን እጅ ባንገቷ ዙሪያ ጠምጥማ የናፍቆት ጥማቷን የምታረካዋ የወዲያነሽ «እባክህ አርፈህ ተኛ! አሁን ምን ሆንኩ ብለህ ነው
የምትገላበጠው?» አለችኝ፡፡ «አማረብኝ ብለሽ ነው? ጠቦሽ እንደሆነ ልነሣና
ልውረድ፣ አበዛሽው! » አልኩና ፍቅራዋ ቅናቴ ስለ ገነፈለብኝ «አምጪ!
አይቻልም፣ መተኛት ያለበት በእኔና በአንቺ መካከል ነው! » ብዩ አስገዳጅ
ቃላት ተናገርኩ፡፡ ከት ብላ ስቃ ጋሻዬነህን በላይዋ ላይ አሳልፋ በመካከላችን
አስተኛችው፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ የሁለታችንን ክንዶች ተንተርሶ ሲተኛ ለውጡ ምን ስሜት እንደ ፈጠረበት ለማወቅ ጓጓሁ፡፡ ሙያዩ ባለመሆኑ አቃተኝ፡፡ የብልጠቴ ብልጠት ባፍንጫው በኩል የምትወጣዋን ትንፋሹን ለማዳመጥ ስል ራሱን ወደ እኔ ኣስጠጋሁት:: ጧት ግን በዕለቱ ሥራ ምክንያት ማልዳ በመነሣቷ ከጋሻዬነህ ጋር ሰፊ ልፊያና ጨዋታ ቀጠልኩ። አንዳንድ ጊዜ ወደ እኛ ዘንድ ትመጣና «በል ይውልህ! በዚህ አያያዝማ ምኑን ተነሣኸው?» ትልና ወደ ሥራዋ ትመለሳለች:: ቆየትየት ብላ ደግሞ ትመስስና «እኔ ምኑም ምኑም አልተሠራልኝም እንዳፈቀዳት አድርጋ ትሥራው:: የእናንተ ጨዋታ ናፈቀኝ» በማለት አልጋው ጫፍ ላይ እረፍ ብላ እሽቆልቁላ ትመለከተን ነበር፡፡

ያም ሆነ ይህ የጋራ ቀንዲላችን ፏ ብሉ በራ፡፡ የእኔና የወዲያነሽ የአንድነት እና የጋራ ችቦ ተንቦለቦለ፡፡ ነበልባሉ እንዳይጠፋኛ ፍሙ እንዳይከስም ፍቅራችን የነዳጅ ኃይል ሰጠው:: የሳምንቱ ቀናት እንደ ነባር አመጣጣቸው ተራ በተራ ለዘለዓለም ባለፉ ቁጥር የጋሻዬነህ ሕይወት ለውጥ ማግኘቷን ቀጠለች፡፡ «እማማዩና አባባዬ» የሚሉት ቃላት ቀስ በቀስ ተዋሐዱት፡፡ ጠባዩን ለማስተካከልና ለማረቅ እዚህ ግባ የሚባል
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...ምን ብዬ እንደምጀምር ቸገረኝ፡፡ ቁርጤን ለማወቅና የምትመልስልኝን ለመስማት ያለመጠን ጓጓሁ። ከመኪናይቱ ውስጥ የመውጣት ፍላጎት ቢኖረኝም በዚያች ወቅት ረዳቴ ስለ መሰለችኝ ሙጢኝ አልኳት፡፡ ያወራነው ተራ ወሬ ሁሉ የአንጎል መርዝ ሆኖ ተሰማኝ፡፡ በመኪናይቱ ውስጥ የነበረው ሞቃት አየር እንዳይወጣ የተገዘተ ይመስል ወበቁ ፈጀን፡፡ ተነጋገርንና ከመኪናይቱ በስተምሥራቅ ኻያ እርምጃ ያህል ርቀን ተቀመጥን፡፡ እንደ ክረምት ደመና የጠቆረና የከበደ ሐሳብ አእምሮዩ ውስጥ ማንዣበቡን ቀጠለ።

ከአንድ አስፈሪ የኑሮ ገጽታ ጋር ጔተፋጠጥኩ፡፡ የጠወለገው ፊቴና በዝምታ
የተለጎመው አፌ በውስጡ አንድ ነገር እንደሚፈራገጥ ያስረዳል፡፡ ዝምታ
የሁኔታ ምልክት ነው፡፡ ጎንበስ ብዩ እንዲት እንጓ ሠርዶ አነሣሁ፡፡ አንድ
ጫፏን በፊት ጥርሴ ኣኘክሁት። የውብነሽ ዝምታዬ ስላሳሰባት «ምን ሆነሃል?
ምነው ዝም አልክ? ለዚህ ለዚህማ እዚያው እቤትህ አትጎለተውም ነበር?
ወንደላጤነት ሰለቸህ እንዴ? በጨለማ ተጻፍኖ የሚጠብቅህ ቤት አስጠላህ
መሰል?» አለችና የጥያቄ ጋጋታ አቀረበች፡፡
አነጣጥሬ መሳት ስላልፈለግሁ ከጥርጣሬና ካልባሰ ሐሳብ እንድርቅ
ፈገግ አልኩ፡፡ «ምንም አልሆንኩ እንድ ችግርና ሐሳብ ቢያጋጥመኝማ ኖሮ
እነግርሽ ነበር፡፡ እኔ የምፈራው አንቺን ሳይሆን እኔኑ ራሴን ነው። ውድቀቴንም
ሆነ ትንሣኤዬን የማፈልቀው እኔው ነኝ፡፡ ያም ሆነ ይህ ዛሬ በእኔና በአንቺ
እንድ ትልቅ ጉዳይ ያውም ሥርና ግንድ ያለው ቁም ነገር ይወጠናል።
የያዝኩትና የተለምኩት የሕይወት ጥርጊያ የልማትም ይሁን የጥፋት ፈር የሚይዘው ከእንግዲህ ወዲያ ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ ለመኖርና አካባቢዩን ለመምሰል ስል በምርም በቀልድም ባያሌው አታልያለሁ፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ግን
በቃኝ፡፡ ዘወትር ከማነጣጠር አንድ ቀን መተኮስ አለብኝ። ሐሳቤ ቢስማማሽም
ባይስማማሽም፣ ዘላቂ ሰላምንና ፍቅርን ቢፈጥርም ባይፈጥርም፣ ቢያቀራርበንም
ቢያራርቀንም ዛሬ ግን ይለይለት ብዩ ላብራራልሽ ቆርጬ ተነሥቻለሁ።
ሕይወቴን በማያቋርጥ የጨለማ ኦና ውስጥ ማዴፈን ስለማልፈልግ የብርሃን
ጭላንጭል ፍለጋ በምወጣበት ጊዜ እንደምትከተይኝና ረዳቴ እንደምትሆኝ
ርግጠኛ ነኝ፡፡ ጋን በጠጠር ይደገፋል ይባላል ብዬ ሐሳቤን ለማቀነባበር እና
በጥንካሪ ለመቀጠል ጥቂት ዝም አልኩ። ብዙ ሰው የራሱን ክብርና ዝና ለመጠበቅና ለማስከበር ሲል በኣካባቢው መጥፎ ባሕልና ልምድ የተለያየ በዴል
ይፈጽማል፡፡ በአሁኑ ዘመን በምድራችን ላይ አጥቂና ተጠቂ፣ የበላይና የበታች፡
ኃይለኛና ደካማ የሌለበት አካባቢ ይገኛል ብዬ አልገምትም፡፡ የጥቃት አፈፃፀሙ
ግን ያንዱ ካንዱ የተለየ ይሆናል፡፡ የእያንዳንዱ ሰው እስተሳሰቡና ዝንባሌው
ይለያይ እንጂ ኑሮን በየግል ዐይኑ ይመለከታታል፡፡ አስጨናቂና አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ሰው ሁሉ ኑሮን በጋራ ዐይን የሚያይበት ጊዜ ደግሞ ይመጣል።
እናቴም ትሁን ወይም ሌላ ሰው በየዋህነት በቂና ትክክለኛ ምክንያት ነው
ብለው ባመኑበት ሁኔታ ተነሳሥተው ቢበድሉኝና ክፉ ነገር ቢፈጽሙብኝ ነገር
ግን ስሕተታቸውን ዐውቀው ካረሙ በጥፋታቸው ደረጃ መጠን ይቅርታ
አልነፍጋቸውም፡፡ የቅርብ ዘመዱ እንዳይጠቃበት ብሎ የሩቅ ወገኑን የሚያጠቃና የሚያሳድድም አለ፡፡ ራስ ወዳድነት ካጠቃው የኑሮና የሕይወት አባዜ የፈለቀ ድርጊት፣ የመፍትሔው አቅጣጫ ሌላ ነው። ስንዴ ስጥ አጠገብ ያረፈችውን ርግብ ገና ለገና ጠቅ ጠቅ ታደርግ ይሆናል በማለት በድንጋይ እንከነችራት የለ? በትምህርት ወይም በትክክለኛ የሕይወት ልምድ ያልበሰለ ሕሊና የሚሰጠው መፍትሔና ውሳኔ በስሕተትና በጥፋት የተሞላ ሊሆን ይችላል። የበሰለ ሰፊ ሕሊና ግን የሚሰጠው ውሳኔ ለምንና እንዴት እንደተሰጠ ጉዳዩን በቅድሚያ
አጢኖ ይመረምራል። ባልበሰለና ከመጥፎ እምነት ባርነት ነጻ ባልወጣ ሕሊና ላይ የሚወሰድ ማናቸውም ርምጃ በአጥጋቢና ፍትሐዊ ምርምር ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይገባል።» አልኩና እንደነገሩ ከዚህም ከዚያም አያይዤ ሰፊና ያልተጣራ የሐሳብ ዝብዝብ ካቀረብኩ በኋላ ዝምታ ጎራ ውስጥ ገባሁ፡፡ ዕቃ እንደ ጣለ ሰው ኪሴን መፈተሽ ጀመርኩ፡፡ የተናገርኩት ሁሉ ዝብርቅርቅ ያለና ግራ የሚያጋባ ስለ ሆነባት «የዛሬውስ ደግሞ የጉድ ነው፣ የተናገርከው ሁሉ አማርኛ አልመስል አለኝ፡፡ ምን ለማለት እንደ ፈለግህ ኣልገባኝም፡፡ ካልግባኝ ደግሞ መልስ ለመስጠት…» አለችና ንግግሯን ሳትጨርስ ጎንበስ ብላ ትናንሽ ጠጠሮች ለቅማ ያዘች። ሐሳቤን የምሰቀስቅበት የምክንያት ስንጥር በማጣቴ ሐሳቤ አእምሮዬ ውስጥ በጻዕር ተያዘ፡፡ በጻዕር አልኩ! እንዲያውም ሊበክት ተቃረበ። በቁሜ ተርበተበትኩ። መጀመር የመጨረስን ያህል ምንኛ አስቸጋሪ ነው? ድንገት እንደ ፈነዳ እሳተ ገሞራ የሐሳቤን ረመጥና አመድ ቋቅ አልኩት።

«በወላጆቻችን ቤት በሠራተኛነት ተቀጥራ በማገልገሏና ሠርታ በማደሯ አላፍርባትም ለወደፊትም አላፍርም» ብዬ በልበ ሙሉነት ጀመር ሳደርግ
ዐይኖቿ በድንጋጤ ቦዙ፡፡ ቀጠልኩ፡፡
የምወድሽ እኅቴ በመሆንሽ ምስጢሬን
በመሐላ አላስጠብቅሽም። በእኔ ላይ የደረሰና የሚደርስ መከራ ሁሉ ያንቺም
በመሆኑ የመከራዩ ቀንበር ተጋሪ ነሽ። እስከ ዛሬ ይህን ጉዳይ ካንቺ በመደበቄና
ሳላዋይሽም በመቅረቴ እንደ ክፉ ሰው ትቆጥሪኝ ይሆናል። ጉዙ የዋለ
መንገደኛ ሲርበው ስንቁን ይፈታል' ነውና እኔም ምቹና ትክክለኛው ጊዜ
ሲደርስና ሐሳቤ አብቦ በሚያፈራበት ወቅት ምስጢሬን ላካፍልሽ በመወሰኔ
ይኸው ዛሬ ልገልጽልሽ ነው። ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ለተናገርኩት ሐሰት
ሁሉ የእኅትነት ልቦናሽ ንጹሕ ይቅርታ አይነፍገኝም» ብዬ የሚቀጥለው
ንግግሬን ሐሳብ ለማቀነባበር ያህል ትንፋሼን ዋጥኩ። ሁለተኛዉን ምዕራፍ
ከፈትኩ። ሐሳቤን ባጭሩና በቀላሉ ለማስረዳት ስል ብዙውን የኑሮ እና የችግር ውጣ ውረድ በጥቂት ቃላት ኣጠቃለልኩት፡፡

«ከስድስት ዓመታት በፊት ያውም ይበልጣል፡ በወላጆቻችን ቤት ውስጥ
ስትሠራ የነበረችው የወዲያነሽ ብዙ ሥቃይና መከራ አሳልፋለች። ዕርጉዝ ሆና
መባረሯንም ታስታውሻለሽ፡፡ ከእኛ ቤት ተባርራ ከሄደች በኋላ ልጅ ወልዳ
በመጣሏ በወንጀለኛነት ተይዛ አምስት ዓመት ተፈረደባት። ተጥሎ የተገኘው ልጅ
አሳዳጊና ሰብሳቢ ባለማግኘቱ ለዕጓለ ማውታ ተሰጠ። አሁን ግን የእስራት ጊዜዋን ጨርሳ ከወህኒ ቤት ወጥታለች፡፡ በከባድ ችግርና በኑሮ ውጣ ውረድ በመጐሳቆሏ መልኳን እንኳ ለይቶ ስላላወቃት የገዛ አባታችን በአሁኗ ባለቤቴ ላይ አምስት ዓመት እሥራት ፈርዶባት ነበር፡፡ ሕግ የጥፋተኝነት ማረሚያ እና የኃይል ሚዛን
መለኪያና መሳያ መሣሪያ በመሆኑ የሆነው ሆኗል። የገዛ ልጄን የሙት ልጅ ነው እያልኩ በመናገሬ በርህራሄ ዐይን እንድታይው አድርጌአለሁ። አስፈላጊ ተንኮልና የልብ ማራራቂያ ዘዴ ነበር። ለየወዲያነሽ ያለኝ ፍቅር ጽኑ በመሆኑ ከወህኒ ቤት እንደ ወጣች ውድና ፍቅርት ባለቤቴ ብዬ ከእርሷ ጋር ጐጆ ወጥቻለሁ፡፡የሁለታችን የፍቅር ፍሬ የሆነውና ዕጓለ ማውታ ውስጥ ያደገው ልጃችን አሁን ከእኛ ጋር እየኖረ ነው:: ከትናንት ወዲያ በመንገድ ላይ እርሷን የምትመስል ሴት ከሩቅ አየሁ ያልሽኝም የልጀ የጋሻዬነህ እናት የማፈቅራት የኑሮ ጓደኛዬ የወዲያነሽ ነች፡፡ ባጭሩ ላጠቃልልሽ፡፡ ሦስታችንም በአንድ ላይ በመኖር ላይ ነን» ብዬ ለዓመታት በምስጢር እየቋጠርኩ ያጠራቀምኩትን ሐሳብ በደቂቃዎች ውስጥ
ዘረገፍኩላት። አንድ ግዙፍ ሽክም የተራገፈልኝ ያህል በጣም ቀለለኝ፡፡ በአካባቢዩ ያለው ነገር ሁሉ ደምቆና ፈክቶ ታየኝ፡፡ የተጠራቀመ
👍5
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል

....ወደ ወላጆቼ ቤት በሔድኩ ቁጥር መኪናዬን የማቆማት ከአካባቢው
እርቄ ነበር። በሩን እንዳንኳኳሁ ወዲያው ተከፍቶልኝ ገባሁ። በአሁኑ ጊዜ እኔና
ያ ቤት ማንና ምን መሆናችንን ዘበኛው አሳምረው አውቀውታል። ምድረ ግቢው ውስጥ ያሉት የኮክ ዛፎች፣ ኮባዎችና ሌሉቹም አትክልቶች ሁሉ የቀድሞ
ውበታቸውን የተጎናጸፉ መስለው ታዩኝ። እንድ ጊዜ ቆም ብዩ ዙሪያውን ካየሁ
በኋላ በቀጥታ ወደ ቤት ገባሁ። መመላለሱንና ወጣ ገባ ማለቱን አዘውትሬው ስለነበር ፍርሃትም ሆነ ኃፍረት አልተጠጉኝም፡፡ እሑድ እሑድ ባለነገር እንግዳ ስለማይበዛ ከአባቴ እጅ ያንዱ መልአክ መልክአ እንቶኔ አይታጣም፡፡ ግባ ስል የአባቴ ነጭ ጋቢ ቤቱን ተጨማሪ ውበት ሰጥቶታል። እናቴ የለበሰቻት ወሃ ሰማያዊ ጥለት ያላት ቀሚስ ከሩቅ ሲመለከቷት ጭጋግ የጋረደው ሰማይ ትመስላለች።

የውብነሽ በጊዜው ስለ እኔ በምታወራው ወሬ የወላጆቼ ሸካራ ስሜት ለስልሶ ውጥረቱ በመላሳቱ መሠረታዊ አስተሳሰባቸው ሳይሆን ተራ ዕለታዊ
አስተያየታቸው በመጠኑ ተለውጧል፡፡ ሁለቱም በፈገግታ ተቀበሉኝ፡፡ በሕሊናዩ
ውስጥ የለውጥ ጮራ ጨረረ፡፡ በአቀባበላቸው የተዝናናው ሕሊናዩ እጅ አነሣሰንና ሰላምታ አሰጣጤን አሳመረው:: መምጣቴን በድምፄ ያወቀችው የውብነሽ የቤት ውስጥ ቀላል ልብስ ለብሳ ከጐኔ ተቀመጠች፡፡ በውስጤ የተጠነሰሰውን ዓላማና እምነት አባቴ ፊት በዐይነ ሐሳብ አቀረብኩት። የእኔ ለጋ እምነትና የአባቴ
ግብዝ ሐሳብ ተፋጠጡ፡፡ የእኔዋ ሐሳብ በዳመራ ነበልባል ውስጥ ዘሎ ለማለፍ
እንደሚፈልግ ሰው ስትዘጋጅና የአባቴ ግትርነት በፈሪዎች መካከል እየተጎማለለ
እንደሚያሳግድ ጀግና ተኮፍሶ ታየኝ፡፡ እናቴ ፈቷን ፈታ አድርጋ ለስስ ባለ
የእናትነት ድምዕ «አረ ዛሬስ አምሮብሃል እሰየው! አባትህ እንዳለው ልብ ልትገዛ
ነው መሰል? እየተመላለስክ መጠየቁንም ሥራዬ ብለህ ይዘኸዋል፡፡ ታዲያ እንዲህ
እንዳማረብህና ሙሽራ እንደ መሰልክ ወደ ቤትህ ናና እንደ ዱሯችን ተቻችለን
አብረን እንኑር፡፡ ዕድሜ ላባትህ እንጂ ምን ጠፍቶ! ለወግ ለማረጉ ነው እንጂ
አንተም ራስህን ችለሃል። ከእንግዲህ ልጅነት የለም። እኛም እኮ እያደር...»
አለችና ንግግሯን ሳትደመድም የተገረፈ ልጅ እንደምታባብል እናት አቆላመጠችኝ

እባቴ ወለድ ለመቀበል እንዳሰፈሰፈ አራጭ ዐይን ዐይኔን እያየ መልክአ
ጊዮርጊሱን ወደ ጋቢው ውስጥ ሸጎጠና «የውብነሽማ የእኅትነቷንም እንደሆነ
አላውቅም፡፡ ነጋ ጠባ "አገኘሁት” ነጋ ጠባ እንዴት ናችሁ ብሏል፥ እንዲህ
አድርጎ፤ እንዲህ ፈጥሮ እያለች ጥሩ ጥሩህን ታወራለች እኔስ ጉቦ ሰጥተሃታል
ልበል?» አለና ያቺን በሐሰት ተጀቡና በጉቦ የምትፌጸም ነገር ሳይታወቀው
ተናግሮ ሣቀ። በእናቴ መሪነት የሚረባ የማይረባውን ስናወራ ጥቂት ደቂቃዎች
ከቆየን በኋላ አባቴ ያቺው የወንጀለኛ መቅጫ መጽሐፉ ትዝ ስላለችው ወደ
መኝታ ቤት ገባ። ግልግል አልኩ በውስጤ። ያጠራቀምኩትን ድፍረት ቀስ በቀስ ልጠቀምበት በመፈለጌ ከናቴ ጎን ተቀመጥኩ፡፡ በእኔና በእናቴ መካከል ያለው የፍቅር ገመድ በየወዲያኒሽ የተነሣ ተገዝግዞ ላላ እንጂ ፈጽሞ ባለመበጠሱ
እንደገና ለማጥበቅ አያዳግትም፡፡ እስኪ ዛሬ እንኳ እንዲህ ጠጋ ብለህ
አጫውተኝ' የእናት ወጉ ይድረሰኝ ብላ ባሸበሸበው ፊቷ ላይ ፈገግታ
ረጨችበት። ፊቷ በመጠኑ ሽብሽብ ከማለቱ በስተቀር ወዝና ሙላቱ ባለመቀነሱ መልኳ እንደ ወጣት ሴት ባይማርክም አዲስ ርጥብ ሥጋ ትመስላለች፡፡ አንገቷን ወደ ጎን ዘንበል አድርጋ ዐይን ዐይኔን እያየች እስኪ አፈር ስበላልህ ንገረኝ፡፡ ወዲያ ወዲህ ቢሉት ምንም መላ የለው፡፡ ከእኔ ከእናትህ የምትበልጥብህና አይዞህ አይሀ የምትልህን አግኝተህ እንደሆነም አትደብቀኝ፡፡ ኧረ መቼ ነው ጓዝህን
ጠቅልለህ የምትመጣው?» አለችና ከመጀመሪያው በበለጠ ትኩር ብላ ተመለከተችኝ፡፡

ከዚያች ከምወዳትና እንደ ነፍሴ ከምሳሳላት ከየወዲያነሽ ጋር ትዳር
ይዤ ንብረት መሥርቻለሁ። ምን የመሰለ ታይቶ የማይጠገብ ወንድ ልጅ ወልደናል። እሷንም በቅርብ ጊዜ ይዣት እመጣለሁ። አስታርቃችኋለሁ” ብዬ ልንገራትና ለእኔ አንድ ግልግል፣ ለእርሷ ደግሞ ያልታሰበ መርዶ በማርዳት
'ጉዷን ልየው ይሆን?” በማለት ገና ያልበሰለና ከገለባ የቀለለ ሐሳብ አሰብኩ፡፡ ላቀረበችው ጥያቄ መልስ የምትጠባበቀዋ እናቴ በግራ እጅ ጣቶቿ አፏን እየተመተመች «በል እንጂ ንገረኝ? ምነው ሰምተህ ዝም አልክ?» ብላ ጥያቄዋን ደገመች። የጠየቀችኝን ትቼ ያሳለችኝን ጀመርኩ፡፡

«ለጠየቅሽኝ ጥያቄ መልስ ከመስጠቴ በፊት አንድ ነገር ብለምንሽ እሺ
ትይኛለሽ ወይ? አዎን ካልሽ እና ከማልሽልኝ እኔም ለጥያቄዎችሽ ሁሉ ደስ
በሚያሰኝ ሁኔታ እመልስልሻለሁ» ብዪ አዲስ ነገር ደቀንኩ፡፡
የእመ ብርሃን ያለህ! ደግሞ የምን ማይልኝ አመጣህ? እኔ እናትህ
ባልምልልህስ እንዴት ብዬ እንቢ እልሃለሁ፡፡ ካንተ ከልጂ የምሰስተው ምን ነገር አለና ነው?» ብላ የመሳቢያ ሐሳቧን አቀረበች፡፡ የአንደበቷ መላላት መንፈሴን
ሽምጥ ለማስጋለብ ረዳኝ፡፡ «ኧረ ለመሆኑ እኔ የምለምንሽንና የምጠይቅሽን ሁሉ
ዐይንሽን ሳታሺ ትፈጽሚልኛለሽ ወይ? ብዬ አዝማሚያዋን ለማወቅ በየዋህ መሰል አቀራረብ ስሜቷን ለመረዳት ጓጓሁ፡፡

«ልጄ ሙት አልልህም! የምትለኝን ሁሉ ባስፈለህ ጊዜ አደርግልሃለሁ፡፡ አንተ ልብ ግዛልኝ እንጂ፣ አንተን መንፈስ ቅዱስ ይጠጋህ እንጂ ለምን ባጉቼስ
አይሆንም» አለችና የልብ ልብ ሰጠችኝ፡፡ «ለመሆኑ» ብዬ ስጀምር ያን ምንም
ያልነበረበትን የቀሚሷን ጫፍ ልክ አቧራ እንደ ነካው እስመስዬ አራገፍኩና
ይህን አድርጌያለሁ፣ ይህን ፈጽሜያለሁ፣ ይህን አጥፍቻለሁ፣ የተጣሉ ወይም
የተኳረፉ ሰዎች አምጥቼ ታረቁልኝ እላለሁና፣ ታረቂልኝ ብዬ ብጠይቅሽ እሺ
ትይኛለሽ ወይ?» አልኩና ዙሪያ ጥምጥም ሄድኩ፡፡

እኔ ልሙትልህ! የምትጠይቀኝን ሁሉ እፈጽምልሃለሁ፡፡አንተ ደግሞ
በበኩልህ አባት እናቴ ቤት ብለህ ተመለስልኝ፡፡ በስተርጅና ወግ ማዕረግ አሳየኝ» ብላ ገና በመቀጠል ላይ እንዳለች ፋታ ሳልሰጥ «ምንጊዜም ብለምንሽና የፈለግሁትን ይዤ ብቀርብ ሳትቀያሚና ሳታሳፍሪ ትቀበይኛለሽ ወይ? ብዬ ውስጥ ውስጡን ለመጪው ጥቅሜ አደባሁ፡፡

የውብነሽ ጣልቃ ገብታ ወሬያችንን ባለማጨናገፏ ተደሰትኩ፡፡

«ታማኙን ወዳጄን አቡዩና!» ብላ በእምነት ፈረሷ ላይ አፈናጠጠችኝ::
«እኔ በበኩሌ ከጥቂት ቀናት በኋላ አንድ በጣም ድንቅ የሆነ ነገር ኣምጥቼ
አሳይሻለሁ» አልኩና ወደ የውብነሽ መለስ አልኩ፡፡ ልብ ለልብ በመተዋወቃችን በዐይናችን ተሣሣቅን፡፡ «እሰየው ተመስገን! አቡዩ ያውቃሉ! ምንጊዜም ረዳቴና ሰሚዩ ናቸው» ብላ እጄን ስባ ሳመችው:: ኃይለኛ ንፋስ በሌለበት ሰማይ ላይ እንደምትንሳፈፍ የማለዳ አሞራ አእምሮዬ በደስታ ተንሳፈፈች። አዝመራው ካማረልኝ የተግባር እርሻዪን ጀምሬያለሁ። የውብነሽ የወሬያችን ተካፋይ ለመሆን በመፈለጓ «አሁንስ እኔንም አስጎመዣችሁኝ የአሁኑ ፍቅራችሁስ ያጓጓል። ምነው እኔ አንድ ነገር ስለምንሽ ዓመት ሙሉ ታስደገድጊኛለሽ?» አለችና ለእኔ
የተሰጠኝን የተስፋ ቃል ሆን ብላ አጋነነችው፡፡

«አንቺ ምን ቸገረሽ ልጀ? እኔ ለስንቱ ታቦት እንደ ተሳልኩ የት አየሽና? ተማጥኜ ተማጥኜ ነው አሁንም ቢሆን ለዚህ የበቃልኝ፡፡ አንቺ ደግሞ በእኔና በልጄ መኻል ምን ጥልቅ ኣደረገሽ? የሚጠይቀኝን ሁሉ አደርግለታለሁ»
ካለች በኋላ ከደረቷ ውስጥ የምታምር አረንጓዴ መሓረብ ኣውጥታ ምንም
ጉድፍ ያልነበረባትን አፍንጫዋን ጠረገቻት፡፡

ነገር አቃኝልኝ ያልኳት ይመስል
👍3👏2
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...እናቴ ደረጃው ላይ ቆማ «አደራ በጊዜ እንድትመለሺ... ይኽ ወጣ ወጣ..» አለቻትና ተመልሳ ገባች። የቀኑ ሞቃት አየር እንደ ብረት ምጣድ ያሰማትን መኪና ከፍተን በቀጥታ ጉዞ ጀመርን፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከቤቴ አጥር በር አጠገብ ስንደርስ በደከሙ ዓይኖቹ ትናንሽ ፊደሉች እንደሚያነብ ዓይነ ደካማ ሽማግሌ፣ የውብነሽ በድንጋጤና በመገረም ዐይኗን ተክላ አየችኝ፡፡

«ያንተ ነገር እኮ አይታወቅም፡ ደረስን ልትለኝ እኮ ይሆናል» ብላ ወረቱ እንደ ረከሰበት ነጋደ ዐይኗ ቃበዘ፡፡ እጆቿ ተወራጩ፡፡ ቁልቁልም ሽቅብም
ወሰደቻቸው:: መጨረሻዋን ለማየት በጸጥታ ተቀመጥኩ፡፡ ቃላቷ በድንጋጤ
እየተቆራረጡ «እንዴት ብዩ ዐይኗን አየዋለሁ? ስንገናኝ ምን ምን ልበላት? በዚያ በሥቃይና መከራዋ ጊዜ ሳልጠይቃትና የት ገባች ሳልላት ኖሬ አሁን እንዲህ ብቅ ስል ምን ትለኛለች? ወይኔ ዛሬ 0ፈር በበላሁት!» አለችና ያንን ምድረ በዳ የሆነ ዐይኗን አቁለጨለጨችው::
«ይልቅ ነይ እንሒድ! እንዳንድ ጊዜ እዚህ ድረስ እየመጣች
ስለምትቀበለኝ አጉል ቦታ ላይ እንዳታገኝኽና ይብሱን እንዳትርበተበቺ ብዩ ከመናገሬ ጋሻዬነህ ከወደ ቤት «እባብዪ መጣ አባባ መጣ! » እያለ ሲጮህ ተሰማ፡፡ እናቱ ደግሞ በዚያች ቀጠን ብላ ቃናዋ በሚማርክ ድምጺ ና! ና
ተመለስ! ተው ትወድቃለህ! » እያለች ስትጣራና ስታስጠነቅቅ ሰማን። የውብነሽ
ማንቁርቱን እንቀው ዐይኑን እንዳስፈጠጡት ሰው አይኗ ፈጠጠ። የየወዲያነሽን ድምፅ ከሰማች ድፍን ስድስት ዓመት ኣልፏል። የውብነሽን ለማበረታታት ያህል
«አይዞሽ አትፍሪ! » ባለቤቴ እኮ ክፉ ሰው አይደለችም፡፡ ገና ገባ ስንል አንገቷ
ላይ ተጠምጥመሽ ሳሚያትና ኃፍረትሽን አስወግጂ፡፡ እንደገና ደግሞ ሳሚያት።
በእርሷ በኩል ሁሉንም ነገር በይቅርታ ትታዋለች፡፡ ከትናንት ጀምራ በጉጉት ነው
የምትጠባበቅሽ» አልኩና ከዚህም ከዚያም እምታትቼ እበረታታኋት፡፡ መለስ
ያለውን የአጥር በር ከፍተን ገባን።

ጋሻዬነህ ሰብሰቡ ሳይ ዝንጉርጉር ኳስ እያንከባለለ ይጫወት ነበር፡፡ ኳሱን
ጥሉ እየሮጠ መጥቶ አጠገቤ እንደደረሰ እጁን ዘረጋ፡፡ ቅብል ብዬ ታቀፍኩት፡፡
የየውብነሽ አእምሮ ያለ የሌለ ኃይሉን ፍርሃትን ለመቋቋሚያ አዋለው:: ዐይኖቿ
እንኳ በሚገባ ማየት የሚችሉ አይመስሉም ነበር፡፡ ቀይ ዳማ ፊቷ ከረመጥ የወጣ ካራ መስሎ ለሥቃይ መግለጫ ትሆን ዘንድ የተቀረፀች የመብ ሐውልት መሰለች፡፡ ወደ ቤት ገባ እንዳልን የወዲያነሽ ከወደ ጓዳ ወጣች፡፡ ባለ ወይን ጠጅ ጥለት ሽንሽን ቀሚስና ብሩህ እረንጓዴ እጀ ጉርድ ሹራብ ለብሳለች፡፡ ጸጉሯን በቀላሉ ጐንጉናና የቤት ውስጥ ቀላል ጫማ እድርጋ ወደ እኔ ስትመጣ
ከበስተጀርባዬ ያለችውን የውብነሽን ከወደ ጎኔ በኩል ኣየቻት። «እውይ የውብነሽ! አቤት የውቧ !» ብላ እጅዋን እስከ ትከሸዋ ከፍ ኣድርጋ ተንደርድራ
አንገቷ ላይ ተጠመጠመች። የየውብነሽ ኮሮጆ በድንጋጤም ይሁን ከደስታ ብዛት
አምልጧት ወደቀ፡፡ እንስቼ ወንበር ላይ አስቀመጥኩት። ተቃቅፈው ሲሳሳሙ
ልክየለሽ ደስታ አጥለቀለቀኝ፡፡ የምሆነው መላቅጡ ጠፋኝ፡፡ የየወዲያነሽ አለባበስ
እንደ ነገሩ ቢሆንም ደስ አለኝ እንጂ አልተከፋሁም። ጎን ለጎን ተቀምጠው
«ደኅና ነሽ ወይ?» እየተባባሉ በሣቅና በፈግታ ሲጠያየቁ ምንጊዜም በቃላት
እቀናብሬ ልገልጸው የማይቻለኝ ደስታ ተሰማኝ፡፡ ጋሻዬነህ ጭኔ ላይ አስቀምጬ
ፊት ለፊታቸው ጉብ አልኩ፡፡ ደቂቃዎች እየፈነጠዙ ተግተለተሉ፡፡ የየውብነሽ
ፍርሃትና ድንጋጤ ሙልጭ ብሎ ከላይዋ ላይ በመጥፋቱ ያለቻትን ፈገግታ ሁሉ
ሞጣጥጣ አወጣቻት። ጋሻዬነህ ከጭኔ ላይ ወርዶ ወደ እናቱ ሲሔድ የውብነሽ
አገላብጣ ሳመችው። ዐይን ዐይኑን እያየች «እንኳን ለዚህ አበቃችሁ እኔንም
እንኳን ይህን ለማየት አበቃኝ» ብላ ኣንስታ አቀፈችው::

የወዲያነሽን፡ ስለ የውብነሽ እንግድነት ይህን ይህን እንድታዘጋጂ ብዬ አልነገርኳትም። ደስ የሚያሰኘውንና መቅረብ የሚገባውን ነገር ሁሉ
ስለምታውቀው ይህን እንድትሠሪ ያንን እንዳትረሺ ማለት አላስፈለገኝም፡፡
የወዲያነሽ ንብ ነች! የውብነሽ አሁንም


አሁንም የማርያምን ጽዋ እያስቆሙ
እንደሚስሙ ሕፃናት የጋሻዬነህን ጉንጭ ደጋግማ ሳመች። ከሥቃይ በኋላ የሚገኝ
እውነተኛ ድል ከድሉች ሁሉ የበለጠ ድል ነው። የወዲያነሽ ግልጽና ቅን ከመሆኗ
የተነሣ ከየውብነሽ ጋር በምትነጋገርበት ጊዜ ሁሉ ካንጀቷ ስለምትሥቅና ፈገግ
ስለምትል አኳኋኗና አቀራረቧ ሁሉ የየውብነሽን ልብ ማረከው፡፡ ቀድሞም ቢሆን የውብነሽና የወዲያነሽ በጣም ይዋደዱ ስለነበር አሁን ከጥቂት ዓመታት በኋላ ሲገናኙ ፍቅራቸው ከትዝታቸው ሰታቴ ገንፍሎ ወጣ፡፡ የሁለቱ መግባባትና አዲስ ግንኙነት መጀመር ለእኔ አንድ ታላቅ የትግል ምርት ነበር። በእኅቴና በባለቤቴ መካከል ያለው ጋሻዬነህም በሁለት የሚያማምሩ አበቦች ዙሪያ እንደምትዞር የመስቀል ወፍ ይማርካል። የወዲያነሽ ከሁለታችን ተለይታ ወደ ጓዳ ገባች፡፡

በጋሻዬነህና በአክስቱ እንዲሁም በእኔ መካከል ውብ ትዝታው እስከ መቼም የማይረሳ ወሬ ቀጠለ፡፡ ጊዜ እንደ አበደ ውሻ ተክለፈለፈች። መሰለኝ እንጂ አትረዝም አታጥር! የወዲያነሽ ከሠራተኛይቱ ጋር በመረዳዳት ምግብና
መጠጥ አቀረቡ። ከግምቴ በላይ ሆኖ በማግኘቴ በአቀራረቧ ረክቼ ባይኔ ጠገብኩ፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ እኔ፤ ባለቤቴና እኅቴ በአንድ ማዕድ ዙሪያ ቀረብን፡፡ ድሉ ግን የእኔና የየወዲያዩ ነበር፡፡ ምንም እንኳ የውብነሽን ያ በአእምሮዋ ውስጥ
ተዳፍኖ በመጥፎ ትዝታ የሚጫረው ያንድ ቀን ስሕተቷ እያጸጸተ አንገቷን
እንድትደፋ ቢታገላትም እጅግም ስላላጠቃት ጨዋታው ደራ፡፡ የወዲያነሽ
በተደጋጋሚ ስታጎርሳት ቀጥ ያለ ዓቀበት ዘልቆ እፎይ እንዳለ መንገደኛ ተደሰትኩ፡፡ የውብነሽም በሌላ በኩል ብድር የምትመልስ ይመስል «ይቺን ብቻ
ጋሻው» እያለች ለጋሻዬነህ ታጎርሳለች፡፡
የማዕዱ ጣጣ ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ፡፡ እንደ ልብ
እንዲጠያየቁና እንዲጫወቱ ነጻነት መስጠቴ ነበር፡፡ ተቆርጦ እንደ ወደቀ የጥድ ዕንጨት ተዘረርኩ እንጂ እንቅልፍስ በዐይኔም አልተኳለ፡፡

የፈለግኸውን ነገር ብትጠይቀኝና አድርጊልኝ ብትለኝ እፈጽምልሃለሁ፡
የፈለግሁትን ሰው አምጥቼ ታረቁልኝ ብል እታረቅልሃለሁ ብለሽኛልና በይ
እንግዲህ እንደ መሐላሽና እንደ ቃልሽ ፈፅሚልኝ ብዬ እናቴን ሳስገድዳት እሺ
ብላ የወዲያነሽ ጋር ትታረቅልኛለች ወይ?» የሚለው ሓሳብ አንጎሌን በሥጋት
ሹል ወስፌ ዉቀዉቀው። ሌሎችም ተመሳሳይ ጥያቄዎች ደረደርኩ፡፡
እናቴ በአስገዳጅ ምክንያቶችና ሁኔታዎች ተገፋፍታ እሺ ብትለኝና ከባለቤቴ ጋር ብትታረቅልኝ የአባቴን ጉዳይ እንዴት ልወጣው እችላለሁ? የሚለው ሐሳብ ደግሞ የባሕር ላይ ኩበት አደረገኝ። ይህ ጉዳይ በእናቴ በኩል ቢደርሰው ይቀላል ወይስ በቀጥታ በእኔ አማካይነት? ይሁን ፈጽሞ ያላወቀውንና ይደርሳል ብሎ ያልጠረጠረውን ነገር ከሥር ከመሠረቱ አብራርቶ ለማስረዳት ቀላሉ ዘዴ ምንድነው? እያልኩ ራስን በራሲ በሐሳብ ቢላዋ ዘለከልኩት።

በቀላል ሐሳብም ሆነ በጊዜያዊ መግባባት ከአባቴ ይልቅ እናቴ ቅረብ
ስለምትለኝ በመጀመሪያ በእናቴ በኩል ያለውን ወደ ፍጻሚ ማድረስ አለብኝ
የሚለው ሐሳብ አመዘነ፡፡ በሐሳብ አዞሪት ውስጥ ተዘፍቄ ብቅ ጥልቅ በማለት ላይ
እንዳለው የውብነሽ ጋሻዬነህን
ስትገባ ከአሳቢ ተናጠብኩ፡፡
አልተንቀሳቀስኩም፡፡ ጎንበስ ብላ ጫማውን ካወለቀችለት በኋላ በላዩ ሳይ አሻግሬ አልጋው ላይ አስቀመችው::

ትንሽ ጎበጥ ብላ በሁለት እጅዋ አልጋውን በመመርኮዝ
👍3🥰1