#የወንበር_ፍቅር
ስንት ወንበር ክፍት እያለ - ለሚያስብ ሰው የሚስማማ
ለሰውነት ማይጎረብጥ - ለህሊናም የማይገማ፤
አንድ ወንበር ላይ ሙጭጭ ብለን - ለመቀመጥ ስንጋፋ
ሰው በሰው ላይ ተመርኩዞ - ቦታ እያለ ምቾት ጠፋ።
🔘ሙሉቀን🔘
ስንት ወንበር ክፍት እያለ - ለሚያስብ ሰው የሚስማማ
ለሰውነት ማይጎረብጥ - ለህሊናም የማይገማ፤
አንድ ወንበር ላይ ሙጭጭ ብለን - ለመቀመጥ ስንጋፋ
ሰው በሰው ላይ ተመርኩዞ - ቦታ እያለ ምቾት ጠፋ።
🔘ሙሉቀን🔘
#ለኀጥአን_የመጣ
#ክፍል_አራት
#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ
#በኢስማኤል_ቤህ
#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው
እንደርስበታለን ብለን ከገመትነው ስዓት በፊት ማታሩ ጆንግ ደረሰን፡፡ ስለ ቤተሰቦቻችን ምንም ዜና የለም። በተስፋ ከመጠበቅ እና ደህንነታቸውን ከመመኘት ውጪ ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም::
አማጺዎች ከ ማታሩ ጆንግ ሃያ ኪሎ ሜትር እና ከዛ በላይ በምትርቀው ሱምብያ ከተማ መሰፈራቸውን ሰማን። ቀጥሎ አማጺዎች ደብዳቤ እንደላኩና ደብዳቤው የነሱም መምጣት፤ ስለ
እኛ እየታገሉ እንደሆነ እና የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እንደሚፈልጉ ያትታል። መልዕክተኛው ወጣት ነው፡፡ ሰውነቱ ላይ የአማጺዎችን ስም እና አጸርሆተ ቃል ማለትም (አአግ
አብዮታዊ የአንድነት ግንባርን ተነቅሷል። ከአውራ ጣቱ ውጪ ሁሉንም ጣቶቹን ቆርጠውበታል። አውራ ጣት በብዙ ሰወች
የተለመደ የፍቅር ምልክት ነበር።
መልዕክቱ እንደደረስ ሰዎች ወደ ጫካ መሸሸግ ጀመሩ። የካሊሎ ቤተሰብ ግን እንድንቆይ እና ስንቅ ይዘን እነሱን
እንድንከተል ጠየቁን። ቆየን፡፡
ያ ምሽት በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የከተማን ህይወት የሚሰጠው የሰዎች መኖር እና መንፈሳቸው እንደሆነ ተረዳሁ። የሰዎች አለመኖር ከተማውን አስፈሪ አደረገው። ድቅድቅ ጨለማ እና ከባድ ጸጥታ! የዶሮዎች እና የወፎች ዝማሬ
እንኳ የለም። ጨለማ ፈጥኖ መጣ፤ ጨረቃም የለችም። አየሩ ከብዷል፡፡ ተፈጥሮ ራሷ የሚመጣውን የፈራች ትመስላለች።
ሰዎች ለሳምንት ያህል ተሸሸጉ። አማጺዎች ግን አልመጡም።በኋላ ሌላ መልዕክተኛ ላኩ፡፡ መልዕክተኛው ታዋቂ የካቶሊክ ካህነ ነበር፡፡ ከማስፈራራት ውጪ ካህኑን ምንም አላደረጉትም።
ቃሉን ተቀብሎ ህዝቡ ወደ ጫካ ተመልሶ ገባ። አስር ቀናት አለፉ አማጺዎች ግን አልመጡም፡፡ ነዋሪው ወደ ከተማ መመለስ ጀመረ። ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ፤ ሰዎች ወደ ዕለት ተዕለት
ኑሯቸው ተመለሱ፡፡ አምስት ቀናት በሰላም አለፉ፡፡
በመጨረሻ አማጺዎች ሲመጡ ቀላል የተኩስ ድምጽ ሰማን፡፡
ጅኒ የር፣ታሉ፣ ካሎኮ፣ ገብሬላ፣ ካሊሎ እና እኔ ቤት ውስጥ ነበረን
"ሰማቹህ?” ብለው ጠየቁ። ወታደሮች ናቸው የተኮሱት ወይስ ሌላ አካል እያልን በማሰብ ደርቀን ቆምን።
ከደቂቃዎች በኋላ ሶስት ጊዜ ተተኮሰ። አሁን ሁላችንም ፈራን።ከተማው ጸጥ ረጭ አለ። ተኩሱ ሲቀጥል። ሁሉም ተደናገጠ።በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ ሰዎች መጮህ እና ወደ ተለያዩ
አቅጣጫዎች መሮጥ ጀመሩ። ሰዎች ተገፋፉ፣ አንዱ በአንዱ ላይ ወደቀ የወደቁ ሰዎችን ረግጦ ያልፋል። እናቶች ልጆቻቸውን አጡ፤ ቤተሰብ ተለያየ፤ የከተማው ነዋሪዎች ለዘመናት
የለፉበትን ጥሪት ትተው ሮጡ። ልቤ በፍጥነት ይመታል።
ወደ ማታሩ ጆንግ ለመግባት ሁለት መንገዶች አሉ።የመኪና መንገድ እና በወንዙ በማቋረጥ :: አማጺዎች ግን በየብስ በኩል እያጠቁ ሲገሰገሱ ሰዎች ወደ ወንዝ እንዲሮጡ ተገደዱ። ብዙ
ሰዎች በፍርሃት ወንዝ ውስጥ ገቡ። እስኪደክማቸው ድረስ ዋኙ:: ወታደሮቹ በቁጥር መበለጣቸውን ሲያውቁ ቀድመው ነበር ከተማውን ለቀው የወጡት :: ህዝብ ሁሉ የተመመበት
አንድ ማምለጫ መንገድ ብቻ ነበር፡፡ ተከተልናቸው። መንገዱ ጭቃ ነበር፡፡ ጭቃ የያዛቸውን አካል ጉደተኞች ማንም
አልረደቸውም፡፡ ማንም ሊረደቸው የሚፈልግ የራሱን ህይወት አደጋ ላይ ይጥላል፡፡ አማጺዎቹ ወደ ሰው መተኮስ ጀመሩ። ሰው ከተማውን ለቆ እንዲወጣ አልፈለጉም። ነዋሪውን በተለይ
ሴቶችን እና ህጻናትን ምሽግ በማድረግ ከመከላከያ ጥቃት መዳን ይፈልጋሉ፡፡
እንደምንም ግን ወደ ማምለጫው መንገድ ስንዳረስ አማጺዎች ቀጥታ ወደ እኛ መተኮስ ጀመሩ። ሁሉንም የመሳሪያ አይነቶች ተጠቀሙ።ጥይት አዘነቡ፤ ሮኬት ና መትረየስ ተኮሱ ቦምብ ወረወሩ። እኛ ምንም አላመነታነም:: መያዝ የከፋ እንደሚሆን እናውቃለን፡፡ ከተያዝን እንመለመላለን : በጋለ ጩቤ አእግ
ብለው ደስ ያላቸው ቦታ ላይ ይጻፉብናል። ስለዚህ ማምለጥ ግድ ነው። ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ሳናርፍ በፍጥነት ሮጥን::
አማጺዎች ተስፋ ቆርጠው ወደ ማታሩ ጆንግ ተመለሱ። እኛ ግን መሮጣችንን ቀጠልን፡፡
ለብዙ ቀናት ስድስታችን ጅኒየር ታሎ ካሎኮ፣ ገብሬላ፣ ካሊ እና እኔ በቀጭን መንገድ ጥቅጥቅ ባለ ጫካ መሃል ተጓዝን፡፡ሁላችንም ሃሳብ ላይ እንመስላለን። ማውራት የለም፤ መሄድ
ብቻ:: ስለ ቤተሰቦቼ ደግሜ ላያቸው እችላለሁ ብየ አሰብኩ፡፡ማልቀስ ፈለኩ በጣም ስለ ራበኝ ግን አቅም አልነበረኝም ::
በተተወ መንደር ውስጥ ባዶ መሬት ላይ ተኛን።በሚቀጥለው ቀን ሙዝ፣ብርቱካን እና ኮኮናት ዛፍ በሚገኝበት መንደር አለፍን፡፡ ሙዙ ጥሬ ስለሆነ ቀቅለን ነበር የበላነው። ከዛ ትንሽ ብርቱካን እና ኮኮናት በላን። በቂ ምግብ ግን ማግኘት
አልቻልንም። ከቀን ቀን ረሃባችን እየተባባሰ መጣ። ስለዚህ ወደ
ማታሩጆንግ ተደብቀን በመግባት ምግብ መግዣ ገንዘብ ማግኘት አለብን፡፡ ከዚህ ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ አልነበረንም።
በመንገዳችን ጸጥ ረጭ ባለ በተከዳ ከተማ ስናልፍ አስክሬን፣የተበላሸ ምግብ ፣ የእንጨት ስራዎች፣ ልብስ እና ሌሎች
እቃዎች በየቦታው ወድቆ አየን። አስክሬን ተቆራርጦ እጅ፣ እግር እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በየቦታው ወድቋል። ይሄን ሳይ አዞረኝ፤ አቅለሸለሸኝ። የነ ካሊሎ ቤት በከተማ እንዳሉ ሌሎች
ቤቶች በሩ ተሰብሯል ተቃጥሏል። የጥይት ቀዳዳ በበሩ በኩል ሲታይ ስታር ቢራ እና ሲጋራ መጠቅለያ ደግሞ ድጃፍ ላይ ወድቋል።
ገንዘቡን ባስቀመጥኩት ቦታ ሳይነካ አገኘሁት። ገንዘቡን ካልሴ ውስጥ ከትቼ ወደ ረግረጉ ወረድን፡፡ አማጺዎች ባህር ዳርቻው አካባቢ ማማ ላይ ወጥተው ይጠብቁ ስለነበር መንፏቀቅ ነበረብን፡፡ ከመካከላችን አንድ ልጅ ትልቅ ቦርሳ አንግቶ ስለነበር ጠባቂዎች አይትውት ተኩስ ከፈቱ።ከጠባቂዎች እስክንርቅ
ድረስ በፍጥነት ሮጥን።አመሻሽ ላይ ብዙ ሰዎች ያሉበት መንደር ውስጥ ገባን፡፡
ገንዘብ ስለያዝን ምግብ ይሸጡልናል የሚል ተስፋ ነበረን።
ነገር ግን አንዳንዶቹ ለክፉ ጊዜ ምግብ መቆጠብ ስለምንፈልግ አንሸጥም ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ ያለ ምንም ምክንያት አንሸጥም አሉ። ራሳችንን ወቀስን፡፡ የጦርነት ወቅት እንዲህ ተለዋዋጭ
ነው። ማንም አይቆጣጠረውም፡፡ ነገሮችን በፍጥነት መረዳትና
የመትረፌያ መንገዶችን መቀየስ ነበረብን። ያን ምሽት አማራጭ
ስላልነበረን ሰዎች ወደ መኝታ ሲሄዱ ምግብ ሰርቀን በላን::
ምግብ እና ውሃ ሳናገኝ ብዙ ስለቆየን
ጉሮራችን ተንቃቃ፣ ሆድ ቁርጠትም ተሰማን። ከንፈራችን ተጣበቀ መገጣጠሚያችንም ዝሏል። ምግብ የት እንደምናገኝ ግራ ገባን። በመጨረሻ ረሃብ ወደ ማታሩ ጆንግ እንደገና
መለሰን።
የበጋ ወቅት ስለ ነበር ሳር ቅጠሉ ቢጫ ሁኗል። በሳር መሃል እየሄድን ድንገት አማጺዎች መጡብን። ገብሬላ ላይ ሽጉጥ ደቀኑ፤ እኔ ላይ ደግሞ ጩቤ ሰነዘሩ፡ "ደንግጧል" ብሎ ከት ብሎ
ሳቀ፡፡ አልፈን ወደመጣንበት መንደር መለሱን፡፡ አማጺዎቹ እጅጌ ጉርድ ቲሽርት፣ ጂንስ ጃኬት እና ሱሪ ለብሰዋል እና አዲዳስ ጫማም ተጫምተዋል። እጃቸው ላይ ውድ ስዐቶች አስረዋል።
ሁሉም በጉልበት የተቀሙ ወይም የተዘረፍ ናቸው።
ፈራሁ! እጆቼ እና እግሬዎቼ ተንቀጠቀጡ።አማጺዎች ትንሽም እንኳ ለመንቀሳቀስ ከሞከርን እንደሚገሉን ዝተዋል።ከጓደኞቼ እንዱ ወይም ወንድሜ ቢንቀሰቀስ ለማምለጥ ቢሞክርና ቢገሉንስ ብየ ሰግቻለሁ።
በአቅራቢያው ወዳለ መንደር ስንደርስ የመንደሩን ነዎሪዎች ሴቶች ህጻናት ሳይሉ ሁሉንም አሰለፉ። መጀመሪያ ካሊሎ
ቀጥሎ እኔን እና ሌሎች ወንዶችን መረጠው ወደ ፊት እንድንመጣ አዘዙ።
"ጠንካራ ወታደሮችን እንፈልጋለን” በማለት ጅኒየር

👍1
ን ጨመሩ። እኛ እየመራን ሌሎች ሰዎች ተከትለው እንዲሄድ
ታዘዘ፡፡ ከዛ አንድ አማጺ ወደ እኛ ዙሮ " እነዚህን ሰዎች ገላችሁ ነው እኛን የምትቀላቀሉት:: ደም እንድትለምድ እና ጠንካሮች እንድትሆኑ ነው ይሄን እንድታደርጉ የምናስገድዳችሁ ።” አለ
ድንገት የተኩስ ድምጸ ተሰማ፡፡ አማጺዎቹ
በመከለል ለተኩሱ መልስ መስጠት ጀመሩ። የተሰበሰበው ህዝብ በሙሉ መሮጥ ጀመረ። ሮጥኩ : ጓደኞቼ እና ወንድሜ ተከትለውኛል። አማጺዎቹ ለቀው መሄዳቸውን ካረጋገጥን በኋላ ወደ መንደሩ ገብተን አደርን።
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ

#የባንዲራ_ነገር
በኔ አይነቷ ምስኪን አገር -
የባንዲራችን ቁጥር ብዛት - ከልብሶቻችን በለጠ
የኔ አይነቱ ከንቱ ፍጡር -
ለባንዲራ ያለው ፍቅር - ወደ ሸሚዝ ተለወጠ።
ምን አይነት ነው ባንዲራችን? -
ምንድን ነው የኛ መለያ?
ምን አይነት ነው የአገሬ አርማ? -
ቀለሟ ምን ነው የኢትዮጵያ?
የልጅ ልጆቼን የሚያግባባ ፣ አያቶቼን የሚያከብር
የትላንትን የአገር ፍቅር ፣ ከነገ ጋር ሚያስተሳስር፣
ሁሉንም ኢትዮጵያውያን፣ በሙሉ ድምፅ የሚያስማማ
ምን አይነት ነው ባንዲራችን? -
ምን አይነት ነው የአገሬ አርማ???
ተረኛ ስፊዎች ሁሉ -
በፍላጎቶቻቸው ልክ ፣ቀደው ሰፍተው እየሰጡን
በቀለም ብዛት አነሁልለው ፣የባንዲራ ፍቅር አሳጡን፡፡
🔘በሙሉቀን🔘
💚 💛 ❤️
በኔ አይነቷ ምስኪን አገር -
የባንዲራችን ቁጥር ብዛት - ከልብሶቻችን በለጠ
የኔ አይነቱ ከንቱ ፍጡር -
ለባንዲራ ያለው ፍቅር - ወደ ሸሚዝ ተለወጠ።
ምን አይነት ነው ባንዲራችን? -
ምንድን ነው የኛ መለያ?
ምን አይነት ነው የአገሬ አርማ? -
ቀለሟ ምን ነው የኢትዮጵያ?
የልጅ ልጆቼን የሚያግባባ ፣ አያቶቼን የሚያከብር
የትላንትን የአገር ፍቅር ፣ ከነገ ጋር ሚያስተሳስር፣
ሁሉንም ኢትዮጵያውያን፣ በሙሉ ድምፅ የሚያስማማ
ምን አይነት ነው ባንዲራችን? -
ምን አይነት ነው የአገሬ አርማ???
ተረኛ ስፊዎች ሁሉ -
በፍላጎቶቻቸው ልክ ፣ቀደው ሰፍተው እየሰጡን
በቀለም ብዛት አነሁልለው ፣የባንዲራ ፍቅር አሳጡን፡፡
🔘በሙሉቀን🔘
💚 💛 ❤️
#ያልገባኝ
ለምድራዊ ስልጣን - ከሞት ለማያስጥል
ለማያጠግብ ንዋይ- ከምስጥ ለማይከልል፣
ውል በሌለው ምኞት - እየተደለለ
እንዴት ሰው ይኖራል - ሰው እየገደለ!!???
🔘በሙሉቀን🔘
ለምድራዊ ስልጣን - ከሞት ለማያስጥል
ለማያጠግብ ንዋይ- ከምስጥ ለማይከልል፣
ውል በሌለው ምኞት - እየተደለለ
እንዴት ሰው ይኖራል - ሰው እየገደለ!!???
🔘በሙሉቀን🔘
#ማን_ልበላት?
አያችኋት ያቺን - ከሰው ተነጥላ?
መልኬ ይኼውላችሁ - ስሜ ይቆይ ብላ፡፡
አትረዝም፣አታጥር
አትቀላ፣አትጠቁር ፤
ክሽን ያለ ቁመት ፣ ክሽን ያለ ከለር
በጣም የምትስብ ፣ በጣም የምታምር
አያችኋት ያቺን?
አትወፍር፣አትቀጥን
አትዘገይ፣አትፈጥን
የአይኖቿ ብርሐን ፣ ፅልመትን የሚያሸሽ
ለአይን የምታሳሳ ፣ ቢነኳት ምትቆሽሽ፡፡
አይችኋት ያቺን ?
ብዙም ዝም ያላለች ፣ ብዙም ማታወራ
ብዙም የማትደፍር ፣ ብዙም የማትፈራ
የማትንቅ ፣ ግን ኩሩ
የውበት ድንበሩ፡፡
ያቺን አያችኋት?
ስሟን ባላውቀውም - ስም እንዳወጣላት
ምናልባት
ምናልባት
እሷን የሚመጥን - ስም ከተገኘላት
ውቧን ማን ልበላት???
አያችኋት ያቺን - ከሰው ተነጥላ?
መልኬ ይኼውላችሁ - ስሜ ይቆይ ብላ፡፡
አትረዝም፣አታጥር
አትቀላ፣አትጠቁር ፤
ክሽን ያለ ቁመት ፣ ክሽን ያለ ከለር
በጣም የምትስብ ፣ በጣም የምታምር
አያችኋት ያቺን?
አትወፍር፣አትቀጥን
አትዘገይ፣አትፈጥን
የአይኖቿ ብርሐን ፣ ፅልመትን የሚያሸሽ
ለአይን የምታሳሳ ፣ ቢነኳት ምትቆሽሽ፡፡
አይችኋት ያቺን ?
ብዙም ዝም ያላለች ፣ ብዙም ማታወራ
ብዙም የማትደፍር ፣ ብዙም የማትፈራ
የማትንቅ ፣ ግን ኩሩ
የውበት ድንበሩ፡፡
ያቺን አያችኋት?
ስሟን ባላውቀውም - ስም እንዳወጣላት
ምናልባት
ምናልባት
እሷን የሚመጥን - ስም ከተገኘላት
ውቧን ማን ልበላት???
#ለኀጥአን_የመጣ
#ክፍል_አምስት
#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ
#በኢስማኤል_ቤህ
#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው
በቡድን መሆናችን እንድንተጋገዝ እና ችግርን በጋራ እንድናልፍ ቢረዳንም ሰዎች እኛን ሲያዩ ይፈሩ ጀመር። በእኛ
እድሜ ያሉ ታዳጊዎች በአማጺዎች ተገደው ይገድሉ ያቆስሉ ነበር። ስለዚህ ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን ለመጠበቅ ሲሉ እኛን ለመጉዳት ጥረዋል። እኛም ጥግጥጉን ይዘን መንደሮችን ማለፍ
ጀመርን። የጦርነት አንዱ መዘዝ ይሄ ነው። ሁሉም ሰው መተማመን ያቆማል፣ ጸጉረ ልውጥ ሰው በሙሉ እንደጠላት
ይቆጠራል። የሚያውቁህ ሰዋች እንኳ ሲያቀርቡህ ሲያወሩህ በጥንቃቄ ነው::
በአንድ መንደር ስናልፍ ገብሬላን የምታውቅ ሴትዮ አክስቱ ወደ ሰላሳ ኪሎሜትር የምትርቅ መንደር ውስጥ እንዳለች ነገረችው: አቅጣጫውን ጠቁማን ጉዞ ጀመርን።
የአዝመራ ወቅት እየተቃረበ ነበር፡፡ የመጀመሪያ ዝናብ ዘንቧል መሬቱ ረስርሷል፡፡ ወፎች በማንጎ ዛፍ ላይ ቤታቸውን ይሰራሉ፡፡ ጠዋት ጠዋት ጤዛ ይታይ ነበር። አጎቴ በዚህ ወቅት
ነው መሞት ምፈልገው እያለ ይቀልድ ነበር። ፀሐይ ቀድማ ወጥታ በሰማያዊው ሰማይ ላይ ትታያለች።
የካማቶር ነዎሪዎች ሁሉም ገበሬ ናቸው። ማገዝ የግድ ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከግብርና ጋር ተገናኘን። የመጀመሪያ
ስራችን የነበረው ማሳ ማጽዳት ነበር፡፡ ቅጠላቸው የተቆላለፈ የወይን ዛፎችን መቁረጥ በጣም አስቸጋሪ ነበር። ሶስት ስዓት የሚፈጀውን ሶስት ቀን ቆየንበት።
ከዛ ዘራን።
ለሶስት ወራት ያህል በካማቶር በእርሻ ስራ ላይ ብንቆይም ልለምደው አልቻልኩም። የተመቸኝ ከስዐት እረፍት ላይ ለዋና ወደ ወንዝ የምንወርድበት ጊዜ ብቻ ነበር። ስራው ለፍቶ መና
ነበር። ምክንያቱም አማጺዎች ሲመጡ ትተነው እንሮጣለን ሰብሉ በአረም ይዋጣል ወይም እንስሳት ይበላል::
አንድ የአማጺዎች ጥቃት ግን ይባስ ብሎ ከወንድሜ ጋር አለያየኝ። ትልቅ ወንድሜን ጅኒ የርን ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት
ያን ጊዜ ነበር።
ጥቃቱ የደረሰው በአንድ ለሊት ድንገት ነበር። ስለ አማጺዎች መድረስ ምንም ወሬ አልተሰማም :: ከየት መጡ ሳይባል
መንደራችን ገቡ።
ከምሽቱ ሁለት ስዐት አካባቢ ህዝቡ የቀኑን የመጨረሻ ጸሎት እያደረገ ነበር። ኢማሙ ብዙ እንደሚቆይ ይታወቃል፡፡ በህዝቡ ፊት ለፊት ሁኖ ረዥም የሱራ ጸሎት ያደርሳል። የአማጺዎችን
መግባት ሲሰማ ከኢማሙ በስተቀር ሁሉም መስጊዱን ጥሎ ሄደ። አማጺዎች ኢማሙን ብቻውን አግንተው ህዝቡ በየት
በኩል እንደሄደ ጠየቁት፡፡አልመለሰላቸውም፡፡ እጁን እና እግሩን
አስረው አቃጠሉት።
የአማጺዎች ጥቃት ሲጀምር ጅኒ የር እና ጓደኞቼ ቤት ውስጥ ነበሩ። እኔ ግን ደጃፍላይ ነበርኩ። ድንገት ተኩስ ሲጀምር
ፌቴን ሳላዞር ሩጬ ጫካ ውስጥ ገባሁ።አንድ ዛፍ ስር ብቻየን
አደርኩ። ሲነጋ ካሎኮን አገኘሁት። መንደሩ መሃል ላይ የኢማሙ የተቃጠለ አስክሬን ተጥሏል፤ ቤቶች ተቃጥለዋል
ህይወት የሚባል የለም:: በጥቅጥቁ ደን መኋል ጅኒ የር እና ጓደኞቻችንን ፈለግን
ግን ልናገኛቸው አልቻልንም።
የምናውቃቸው ሰዎች አግኝተን ለሁለት ሳምንታት ያህል ከነሱ ጋር በረግረጉ አካባቢ ተደበቅን። ሁለት ሳምንት ሁለት ወር ሆነብኝ፡፡ ስለእነ ጅኒየር አስባለሁ። አምልጠው ይሆን? ሁሉንም እያጣሁ ነው፦ቤተሰቦቼን፣ጓደኞቼን። በፍርሃት ውስጥ መኖር ሰለቸኝ:: ሞትን የምጠብቅ መስሎ ተሰማኝ። መንደሩ መልቀቅ ሰላም ወደ ሚገኝበት መሄድ እንዳለብኝ ተሰማኝ:: ቆረጥኩ። ካሎኮ ግን ፈራ፤ በረግረጉ መቆየትን መረጠ።
ጠዋት ሁሉንም ተሰናብቼ ወደ ምዕራብ መጓዝ ጀመርኩ።በኪሴ ከያዝኩት ያልበሰለ ብርቱካን ውጭ ሌላ ምንም
አልያዝኩም:: ለስድስት ቀናት ያገኘሁትን እየበላሁ ተጓዝኩ።
በስድስተኛው ቀን ሰው አገኘሁ፡፡ የአንድ ቤተሰብ አባላት እየዋኙ ነበር። ሰላምታ ሰጠኋቸው፡፡ አልመለሱልኝም። ልብሴን አውልቄ ወደ ወንዙ ገባሁ፡፡ " ከየት ነው የመጣሃው ወዴት እየሄድክ ነው?” ሲል ጠየቀኝ።
ከማታሩ ጆንግ ነኝ ወዴት እንደምሄድ ግን አላውቅም” ስል መለስኩለት። ቀጥየ "ወደ ቦንቴ ለመሄድ አቋራጩ መንገድ የቱ
ነው” ስል ጠየቁ፡፡ ቦንቴ ስላማዊ ቦታ ነው ይባላል። በባህሩ በኩል እንድሄድ እና ሰዎችን እንድጠይቅ ነገረኝ።
ብዙ የተቃጠሉ መንደሮችን እያለፍኩ ተጓዝኩ፡፡ በመንደሮቹ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሰዎች ከአዋቂ እስከ ህጻናት አየሁ።አይናቼን ለመጨፈን ሞከርኩ ግን አልቻልኩም። በመጨረሻ ደነዘዝኩ።
ብዙ ስጓዝ ውየ ራሴን ጥቅጥቅ ያለ ጫካ መሃል አገኘሁት።ከቆምኩበት ጫካ
ሰማዩን እንዳላይ በረጃጂም ዛፎች
ቅርንጫፎች እና ቅጠሎች ተጋርድዋል፡ እንዴት እዚህ ጫካ እንደገባሁ እንኳ አላውቅም። ለሊቱ ሲቃረብ ረጂም ቅርንጫፍ ካለው አንድ ዛፍ ላይ ወጥቼ አደርኩ።
በሚቀጥለው ቀን ከጫካው ለመውጣት ወሰንኩ። በጉዞየ በአንድ ትልቅ አለት ላይ የሚወርድ ፏፏቴ አየሁ። በዳርቻው
ትንሽ ለማረፍ ወሰንኩ። ግን ብዙም አልቆየሁም። ወደ ሃሳብ ከምገባ ብየ ጉዞየን ቀጠልኩ። ቀኑን ሙሉ ተጓዝኩ። ዙሬ ዙሬ በመጨረሻ ራሴን ትናንት ማታ ካደርኩብት እዛው ቦታ ላይ
አገኘሁት፡፡ እንደጠፋሁ አመንኩ። ስለዚህ ራሴን ማደላደል አዲሱ ቤቴን ማመቻቸት ጀመርኩ። ቅርንጫፎች ላይ ቅጠሎችን
ጨመርኩ።አካባቢውን ዙሬ ቃኘሁ። ምንም እንኳ ብጠፋ እና ብቻየን ብሆንም ለጊዜው ይሄ ቦታ ሰላማዊ ነው።
የፏፏቴው ጥግ ባልበሰሉ ፍራፍሬዎች ተሸፍኗል። አንዱን ቆርጬ በላሁ። መራራ ነው:: ነገር ግን ረሃብ ያስታግሳል።
ስለዚህ ወደ አስራ ሁለት የሚሆኑ ፍሬዎችን በላሁ። ከተወሰኑ ስዓታት በኋላ ገላየን ለመታጠብ አሰብኩ። ልብሴ ቋሽሽዋል፣የሰውነቴም ሽታ ተቀይሯል። መጀመሪያ በንጹህ ውሃ ቀጥሎ
በእንዶድ ገላየን ታጠብኩ ልብሴንም አጠብኩ።
አስቸጋሪው ነገር ብቸኝነት ነበር። ብቻህን ስትሆን ብዙ ታስባለህ ላቸማሰብ ሞከርኩ ግን አልቻልኩም፡፡ ወደ ጭንቅላቴ የሚመጡትን ሁሉንም ሃሳቦች ለመከላከል ወሰንኩ ብዙውን
ጊዜየን ሃሳብን በመዋጋት ማለትም ስለ ወደፊት ህይወቴ ማሰብ፡
ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ የት ናቸው የሚሉ ሃሳቦችን በመሸሽ አሳልፍ ነበር።
ይሄን ሳደርግ ራሴ ከመቼውም በላይ የጠነከረ መስለኝ። ሃሳቦቹ በህልሜ ይመጣሉ በማለት መተኛት ፈራሁ::
በጣም ትንሽ እያለሁ አባቴ የሚለው አባባል ነበር " በህይወት እስካለህ የተሻለ ቀን እንደሚመጣ እና መልካም ነገር እንደሚሆን ተስፋ አለ። እጣ ፈንታቸው መጥፎ የሆነ ደግ ጊዜ
የማይመጣለቸው ሰዎች ግን ይሞታሉ።”በጉዞየ ስለዚህ አባባል
አስብ ነበር፡፡ እነዚህ ቃላቶች ወደፊት እንድሄድ እንድገፋ አበረቱኝ፡፡
በረሃብ ደክሜ እያዘገምኩ ስሄድ በእኔ የእድሜ ክልል ያሉ ህጻናት አጋጠሙኝ። ስድስት ነበሩ፤ ከስድስቱ ሶስቱ አልሃጂ፣
ሙሳ እና ኬን ማታሩ ጆንግ በሚገኘው ሴንትያል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አብረውኝ ተምረዋል። እጃችንን በመጨባበጥ ሰላም ከተለዋወጥን በኋላ ወደየት እየሄዱ እንደሆነ ጠየቅኳቸው፡፡ በቦንቴ ወረዳ ወደ ምትገኝ የል ወደ ምትባል ሰፈር እየሄዱ እንደሆነ እና የል በ ሴራሌዮን መከላከያ ኃይል የሚጠበቅ
አስተማማኝ ሰላም ያለበት አካባቢ እንደሆነ ነገሩኝ። ተከተልኳቸው::
እንደገና የሰባት ህጻናት ቡድን፡፡ ሰዎች እኛን ሲያዩ ይጮሃሉ ይሮጣሉ። እንደአውሬዎች ተቆጠርን፡፡ ቦታ የሚያመለክተን አቅጣጫ የሚጠቁመን ሰው አልነበረም። ከስድስት ቀናት ጉዞ
በኋላ አንድ ሽማግሌ ሰው አገኘን። የመንደሩ ሰው እኛን ሲያይ ሩጦ እንደጠፋ እሱ ግን መሮጥ እንደማይችል ነገረን። ከየት እንደመጣን እና ወዴት መሄድ እንደምንፈልግ ነገርነው፡፡
ለተወሰኑ ቀናት ከእሱ ጋር

እንድንቆይ ጠየቀን። ምግብ ስጠን። ከበላን በኋላ ወደ የል የሚወስደውን አቅጣጫ በምርኩዙ ምድር ላይ ስሉ አሳየን።
ኦና የሆነውን መንደር አልፈን ከወጣን ከቀናት በኋላ አንድ ጥዋት ከትልቅ ማሽን የሚወጣ ሚመስል ከፍተኛ ድምጽ ሰማን።
አንዴ ከአስፓልት መንገድ ላይ ብረት ሲወድቅ፣ መብረቅ መንከባለል። እነዚህ
ሲያንጎዳጉድ፤ መንከባለል አሁንም
ድምጾች በሙሉ ጆሮችን ደረሱ። ወዲያው ወደ ጫካው በመግባት ተደበቅን። ተያየን። ማንም መልስ የለውም። ኬን መንፏቀቅ ጀመረ። ተከተልነው:: ቦታውን ከቃኘ በኋላ
" ውሃ ነው፤ ብዙ ውሃ እና አሽዋ::”
እና ድምጹ ምንድን ነው?” አለ አልሃጂ።
የማየው ነገር ውሃ እና አሽዋ ብቻ ነው።
አትላንቲክ ውቅያኖስ ነበር፡፡ የምንሰማው ድምጸ ዳርቻው በማዕበል ሲናጥ የሚፈጠር ነበር። የውቅያኖስ የተወሰነውን ክፍል አይቼ አውቃለሁ፡፡ የዚህን ያህል ሰፊ ዳርቻ ግን አይቼ
አላውቅም:አይኔ ከሚደርስበት ጥግ በላይ ዳርቻው ተዘርግቷል።
በሩቅ ሲታይ በእጀጉ ሰማያዊው ቀለም የያዘው ሰማይ በአግድሞሺ ወርዶ ውቅያኖሱን የነካው ይመስላል።
ወደ ውቅያኖሱ ቀረብን፤ በአሽዋው ጥግ ተቀምጠን ውቅያኖሱን ተመለከትን ተደጋጋሚ ማዕበል እያየን ተደነቅን።
ሁሉን ረስተን መሯሯጥ ጀመርን፤ አሽዋው ለይ ትግል ገጠምን ከዛ ደግሞ የእጅ ኳስ እግር ኳስ ያልተጫወትነው ጭዋታ የለም። ልባችን በሐሴት ተሞላ። ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ችግራችንን ያየነውን መከራ ሁሉ ረሳን፡፡ በቀጣዩ ቀን ንጋት ላይ ጉዞችንን ቀጠልን። ረፋድ ላይ

❤2👍1
#እንዲህ_አይነት_ሰው_አይታችኋል?
ጥርስ እያለው - የማይስቅ
ሐሳብ እያለው
የማይጠይቅ፤
አፍ እያለው - ማያወራ
እጅ እያለው - የማይሰራ::
ዝም ብሎ
አይኑ ብቻ ሚንቀዋለል
በአውራ ጎዳና ሚንገዋለል፧
እንዲህ አይነት ሰው አይታችኋል?
ጤነኛ መሳይ - ግን ያበደ
ብቸኛ ፍጡር - የተካደ፤
መንገደኛን በአይኑ ሲከተል
ህዝብ ቆጣሪ የሚመስል፤
እንዲህ አይነት ሰው አይታችኋል?
ስሜት ያለው የማይመስል
በሰው አሽሙር ልቡ ማይቆስል፤
እሾህና አስፓልት የማይመርጥ
እግሩ የትም የሚረግጥ፤
ማዶ ማዶውን እያየ
ከገሃዱ ዓለም የተለየ፤
እንዲህ አይነት ሰው አይታችኋል?
ጥርስ እያለው - የማይስቅ
ሐሳብ እያለው
የማይጠይቅ፤
አፍ እያለው - ማያወራ
እጅ እያለው - የማይሰራ::
ዝም ብሎ
አይኑ ብቻ ሚንቀዋለል
በአውራ ጎዳና ሚንገዋለል፧
እንዲህ አይነት ሰው አይታችኋል?
ጤነኛ መሳይ - ግን ያበደ
ብቸኛ ፍጡር - የተካደ፤
መንገደኛን በአይኑ ሲከተል
ህዝብ ቆጣሪ የሚመስል፤
እንዲህ አይነት ሰው አይታችኋል?
ስሜት ያለው የማይመስል
በሰው አሽሙር ልቡ ማይቆስል፤
እሾህና አስፓልት የማይመርጥ
እግሩ የትም የሚረግጥ፤
ማዶ ማዶውን እያየ
ከገሃዱ ዓለም የተለየ፤
እንዲህ አይነት ሰው አይታችኋል?
#ለኀጥአን_የመጣ
#ክፍል_ስድስት
#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ
#በኢስማኤል_ቤህ
#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው
የተጠጋጉ ጎጆ ቤቶችን ተመለከትን። ከመንደሩ ስንደርስ ማንም የለም። ከእኛ ተደብቀው ነበር። ብዙም ሳይቆይ አሳ አጥማጆች መጥረቢያ፣ ጦር እና መረብ ይዘው ወጡ። ምንም ማድረግ
አልቻልንም። ባለንበት ደርቀን ቆምን።
እንግዲያውስ "እባካችሁ እኛ ልንጎዳችሁ አልመጣንም፧ መንገደኞች ነን”ብለን ጮህን።አሳ አጥማጆች በሰደፍ መተው ጣሉን፡፡ ከበላያችን ላይ ተቀምጠው ካስሩን በኋላ ወደ አለቃቸው ወሰዱን። ብዙ ጥያቄዎች ጠየቁን። ከየት እንደመጣን፣ የት እንደምንሄድ እና
ለምን ይሄን አቅጣጫ እንደመረጥን ተጠየቅን፡፡ በመጨረሻ እጅ እና እግሮቻችንን ፈተው ከመንደራቸው አባረሩን። ጫማችንን ግን አልሰጡንም::
ብዙ ከተጓዝን በኋላ ነበር አሳ አጥማጆቹ ምን እንደቀጡን የገባን፡፡ ፀሐይ ስትወጣ 120 ዲግሪ ሆነ። ምንም ምንጠጋበት
ዛፍ እንኳ አልነበረም፡፡ ፀሐይዋ አሽዋው ላይ ስታርፍ በጣም ሞቀ፤ ግለት ሆነ። በባዶ እግር አሽዋ ላይ ተራመድን።
እግሮቻችንን ቆሰሉ። ደነዘዝን።በመጨረሻ አንድ ጎጆ ቤት ላይ ደረስን፡፡ ወደ ውስጥ ገብተን ተቀመጥን፡፡ የቤቱ ባለቤት ብዙም
ሳይቆይ መጣ። በሩ ላይ ቆሞ ተመለከተን እና ጉዳታችንን ሲያይ ፊቱን ዙሮ ሄደ፡፡
ከትንሽ ቆይታ በኋላ ሳር ይዞ መጣ። እሳት አያያዘ ከዛ ሳሩን በጥቂቱ እሳቱ እንዲለበለብ ካደረገ በኋላ ሳሩን ወደ እግሮቻችንን አስጠጋው:: ሙቀቱ ስቃያችንን አስታገስልን።ቀጥሎ የተጠበሰ አሳ ሾርባ፣ ሩዝ እና ውሃ ይዞ መጣ እና
ፊታችን ላይ አስቀምጦ እንድንበላ ጠየቀን፡፡ እንደገና ወቶ ሄደ፤
ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ተመለሰ። የምንተኛበትን ምንጣፍ አሳየን፤ ከመተኛታችን በፊት እግሮቻችንን የምንቀባው ቅባት ሰጠን።
በሚቀጥለው ቀን ስም አልባው እንግዳ ተቀባይ ሰው ምግብ ይዞልን መጣ። ፊቱ ላይ ያለው ፈገግታ እየተሻለን እንደሆነና እሱም ደስ እንዳለው ነገረን።
በጎጆው ለሳምንት ቆየን።እንግዳ ተቀባዩ ጥዋት እና ማታ ምግብ ይሰጠናል።ጥርሱ ነጭ በረዶ ይመስላል ከወገብ በላይ ሁሌም ራቁቱን ነው ልብስ አይለብስም።አንድ ቀን ስሙን ጠየቁት።ምን ይጠቅምሀል ብለህ ነው። እንደዚሁ ይሻለናል ለደንነታችን አለኝ።
በሚቀጥለው ቀን አመሻሽ ላይ ወደ ውቅያኖስ ይዞን ወረደ።እግራችንን እንድንነክር ነገረን።ጨዋማ ውሃ ከስቃይ እንደሚያስታግስ እና ከቲታኖስ እንደሚጠብቀን ገገረን።
በሁለት ሳምንት ውስጥ ከህመማችን አገገጀምን።አንድ ጠዋት ግን ሽማግሌ ሴትዮ ከእንቅልፋችን ቀስቅሳ መሄድ እንዳለብን ነገረችኝ።የአስተናጋቻችን እናት ነበረች።መንደሩ ስለኛ እንደሰማና ሊይዙን እየመጡ እንደሆነ ነገረችን።የተጠበሰ አሳ እና ውሃ ሰታን 'ልጆቼ መፍጠን አለባችሁ ጸሎቴ ከናንተ ጋር ነው" አለች።
ፈጥነን ከአሳዳጆቻችን ማምለጥ አልቻልንም አስራ ሁለት ነበሩ። አሸዋ ላይ ጥለው እጆቻችንን አሰሩ።ወደ መንደሩ መልሰው አለቃቸው ፊት አቀረቡን።
እናንተ ህፃናት ትናንሽ ሰይጣናት ሁናችኋል። አሁን ግን ወደተሳሳተ መንደር ነው የመጣችሁት አለ። እንደእናንተ ላለ ሰይጣኖች እዚህ ጋር ይበቃል።
ልብሳችሁን አውልቁ ብሎ አዘዘ አለ ስም አልባው አስተናጋጃችን እና እናቱ በ ህዝብ መሃል ነበሩ። በአለቃው መቆጣት ስለ እኛ ሲሳቀቁ እና ሲከፉ አየሁቸው። ልብሴን
ሲያወልቁ የራፕ ካሴት ከኪሴ ወደቀ። አለቃው ካሴቱን መረመረ እና የካሴት መጫወቻ እንዲመጣ አዘዘ፡፡
መጥቶ ሙዚቃው ተከፈተ። አለቃው ጠራኝ እና እንዴት እንደምንደንስ ማሳየት ጀመርኩ። ሞቴን ሳስብ መዳነስ ከበደኝ፤
ምቱም ጠፋብኝ፡፡ አለቃው ግን መረጋጋት ጀመረ። ልጆች መሆናችንን አወቀ። በድንገት ጓደኞቼ እንዲፈቱ አዘዘ። አለቃው ለህዝቡ ስህተት እንደሆነ እና ልጆች መሆናችንን እና ራሳችንን
ለማትረፍ እንደመጣን ተናገረ::
አለቃው ነጻ እንዳደረገን እና በፍጥነት አካባቢውን ለቀን እንድንወጣ ነገረን።
በጉዞየ ከሚረብሽኝ አንድና ዋናው ነገር ጉዞው የት እና መቼ እንደሚቋጭ አለማወቄ ነው፡፡ ይሄ ጥያቄ አዕምሮየን፣ ሰውነቴን እና ስሜቴን በጉዞየ ሁሉ ሲጎዳ ቆይቷል። በህይወቴ ምን እንደምሰራ ወደ የት እንደማመራ አላውቅም:: በየጊዜው እንደገና እንደምጀምር ይሰማኛል። አሁን የህይወቴ ዋና አላማ መትረፍ
ብቻ ነው። ለትንሽ ጊዜም ቢሆን እራሳችንን በምግብ እና በንጹህ
ውሃ ለማስደስት እንሞክር ነበር። በተለያዩ ስሜቶች ከመዋለል መከፋት ቀላል ነበር፡፡ ወደፊት መግፋት እንዳለብኝ አወቅኩ።
የባሰ አለ ብየ ስላሰብኩ አልተካፋሁም።
ጉዞችን ደመና እንደሽፈናት እና ለመውጣት እንደምትፍጨረጨር ጨረቃ መስሎ ታየኝ፡፡ ጨረቃዋ በመጨረሻ ትወጣለች ለሊቱንም ሙሉ ብርሃንዋን ትሰጣለች::
አንድ ቀን ሰኢዱ ”ብዙ ቀን ሰዎች ሊገድሉን ሲመጡ አይኖቼን ጨፍኜ ሞትን ጠብቄለሁ። እስከአሁን አልሞትኩም::
ሞትን በተቀበልኩ ቁጥር ግን አንድ አካሌ እንደሞተ ይሰማኛል። ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሙሉ ለሙሉ እንድምሞት ይሰማኛል። ያኔ
ባዶ ስውነቴ ብቻ አብሮችሁ ይጓዛል። ከአሁኑ በላይ ዝምተኛ ይሆናል" አለ። አይኖቼ እንባን አቀረሩ፤ ግንባሬም ሞቀ። የሰኢዱ ን ቃላቶች እያሰብኩ እስኪነጋ ድረስ መተኛት አልቻልኩም::
ጉዞችን አስቸጋሪ ቢሆንም አንዳንዴ ለትንሽ ደቂቃ ቢሆንም መዝናናት እንሞክራለን። አንድ ቀን አንድ መንደር ስንደርስ ሰዎች ለአደን እየተዘጋጁ ነበር። አብረናቸው እንድናድን ጋበዙን፡፡ ከአደን በኋል ምግብ ለሚያዘጋጁ ሴቶች ውሃ በመቅዳት አገዝን፡፡
ምሽት ላይ ሁሉም መንደርተኛ ወደ መንደሩ ተመለሰ፡፡ምግቡ ወደ መንደሩ አደባባይ ወጣ፡፡ ለሁሉም በስሃን ታደለ።
ከምግቡ በኋላ ከበሮ መምታት ተጀመረ:: ሁላችንም እጅ ለ እጅ ተያይዘን ክብ ሰርተን በጨረቃ ብርሃን መዳነስ ጀመርን።
በመሃል የት እንደመጣን ስለእኛ ታሪክ እንድናካፍል ተጠየቅን፡፡ቆይቶ ዳንሱ ቀጠለ።
ሲነጋ ውሃ እና መንደርተኛው የሰጠንን የተጠበሰ ስጋ ይዘን ጉዞችንን ቀጠልን፡፡ "የአባቶቻችሁ አምላክ ይከተላቹህ" ብለው ሸኙን።
ፀሐይዋ ስታዘቀዝቅ ወደ አንድ ልዩ መንደር ደረስን። መንደር ለማለት ይከዳል:: አንድ ትልቅ ቤት አንድ ኪሎ ሜትር ራቅ ብሎ ደግሞ ጭስ ቤት ብቻ ነበር የሚገኘው:: አማጺዎች በቀላሉ
ሊይዙት የሚችሉት ሰፈር" ብሎ ጅማህ ሳቀ።
ሰው መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ሰፈሩን ሙሉ ዙረን አየነው:: የወይራ ዘይት ሲመረት እንደነበር ምልክቶች አሉ።
ወንዙ ላይ ሳር የበቀለብት ታንኳ አለ። ወደ ትልቁ ቤት ተመልሰን ይዘነው የመጣነውን የተጠበሰ ስጋውን እና ውሃ አስቀመጥን።
ብዙም ሳይቆይ መሸ እና ከጓደኞቼ ጋር ተኛን፡፡ የሊሊቱ አጋማሽ እስከሚደርስ ግን እንቅልፍ አልወሰደኝም። ሴት አያቴን
አስታወስኩ:: "እንደ እሳት እኮ ነው ያደግከው: ስም የወጣልህ ቀን እንደ ትናንት ትዝ ይለኛል" ትላለች :: ሰፊ ድግስ ተደግሶ በግ ዶሮ ታርዶ ከተበላ ከተጠጣ በኋላ ኢማሙ ፊት ቀርቤ "ኢስማኤል ተብሎ ይጠራ እንዳለ እና ታዳሚው እንዳጨበጨበ ከዛም ጭፈራ እልልታ እንደነበረ ትነግረኛለች...

ፖሊስና እርምጃው በግንቦት 30 ፣ 2ዐዐ5 እትሙ በምስራቅ ሸዋ መቂ ከተማ ውስጥ ፣ አንድ ግለሰብ ጅብ አጥምዶ ፤ ከማጥመዱም በአህያ በሚጎተት ጋሪ ጭኖ ሲዘዋወር በመገኘቱ ፣ “ እናሰሳትን፣ በማንገላታት ” ክስ መታሰሩን ነግሮናል።
ሰውየው ፣ “ጅቡን ከነነፍሱ ያጠመድኩት እየተፋፋመ ያለውን የፀረ ሙስና ትግል መቀላቀሌን ለማሳየት ነው” ካላለ ትንሽ በቁጥጥር ሥር ሳይቆይ አይቀርም : :
“እንሰሳትን በማንገላታት” የሚለው ክስ ፣ እንግልቱ በየትኛው እንስሳ ላይ እንደተፈጸመ አጥርቶ ባይገልጽም ፣ እንደኔ በዚህ ጉዳይ ዋነኛው
የእንግልት ሰለባ አህያው ነው : :
መደበኛ የሽክም እንግልቱን ተዉት ፡ : ይህ አህያ ታሪካዊ አዳኙን ከነነፍሱ ተሸክሞ ሲዞር ፣ “ካሁን አሁን ዘነጠለኝ፤” እያለ መሳቀቁ ብቻ ከባድ የሥነ ልቦና እንግልት አይደለም?
ይሄንን ጅቦችን ተሸክመው ሲሄዱ የኖሩ ፣
ምስኪን አህዮች ሁኑ ጠንቅቀው ያውቃኩ
ወጣም ወረደ ክሱ ጅቡን የእንግልቱ ተጠቂ አድርጎ ያቀርበ መሆኑን፤
ከሰማን ፣ “ድሮም የኛ ሕግ ለጅቦች ያዳላል" ማለታችን የማይቀር ነው
🔘ሕይወት እምሻው🔘

#ክፍል_ሰባት
#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ
#በኢስማኤል_ቤህ
#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው
ጥዋት ስንነሳ ስጋው ተበልቶ አገኘን። ማን እንደበላው ግራ ገባን። መጀመሪያ ራስ በራሳችን ተጠቋቁመን ነበር። በኋል ግን ውሻ ሆኖ አገኘነው አልሀጂ በጣም ተናዶ ውሻውን ካልደበደብኩ ብሎ ተከላከልነው፡፡ ውሃችንን ይዘን ጉዞችንን
ቀጠልን፡፡ ቀትር ላይ ያገኘነውን ፍራፍሬ ለመብላት ሞከርን።እስከ ማታ ድረስ በመካከላችን ምንም አይነት ንግግር
አልነበረም። ምሽት ላይ ለማረፍ ወሰን።
አልሃጂ "ውሻውን መግደል ነበረብኝ" አለ።
ለምን? አልኩ እኔ
እኔን ተከትሎ “ምን ትርጉም አለው? የሱ መሞት ምን ያደርግናል" አለ ሞሪባ፡፡
አልሃጂ " ያለንን ብቸኛ ምግብ ነዋ የበላብን። ጥሩ ስጋ ይሆን ነበር።
"አይመስለኝም! ደግሞ ማዘጋጀቱ አስቸጋሪ ይሆን ነበር አልኩ።
ሙሳ ደግሞ ውሻውን ቢገድለው ኖሮ እበላው ነበር አለ። አባቴ ማሌዥያውያን ውሻ እንደሚበሉ ነግሮኛል።አልሃጂ ገድሉት ቢሆን ንሮ በልቼ እሞክረው ነበር። አባቴን እንደገና ሳገኘው የውሻ
ስጋ እንደሚጥም እና እንደማይጥም እነግረው ነበር አለ፡፡ጉዞችንን ማታ ለማድረግ ወሰን፡፡ ቀን ምግብ እንፈልጋለን
ተራ ይዘን እንተኛለን፡፡ ማታ ጨረቃዋ ምትከተለን ይመስላል።ሲነጋ ትጠፋ እና በሚቀጠለው ቀን እንደገና መታ መንገዳችንን ትመራለች።
አንድ ቀትር ላይ ኦና በሆነ መንደር ዉስጥ ምግብ ስንፈልግ ቁራ ከየት እንደመጣ ሳይታወቅ ከሰማይ ወደቀ። አልሞተም ነገር ግን መብረር አልቻለም፡፡ ያልተመደ ነገር ነበር፤ ምግብ ግን ፈልገን ነበር። ላባዋን ስንነጭ ሞሪባ ምን ቀን እንደሆነ ጠየቀን። ማንም ሚያውቅ አልነበረም::
"ዛሬ የባዕል ቀን ነው" አለ ኬን እየሳቀ፡፡ "የፈለጋችሁትን ቀን ልትሰይሙት ትችላላችሁ::"
" የቁራው መውደቅ የእርግማን ምልክት ነው መብላት የለብንም" አለ ሙሳ።
"እንግዲህ የእርግማን ምልክት ከሆነ እኛም እርጉማን ነን፡፡ ስለዚህ በደንብ አድርጌ ነው ምበላው:: የፈለከውን ማድረግ ትችላላህ" አለ ኬን፡፡
ብዙም ሳይቆይ ማታ ሆነ፡፡ ከባድ ጸጥታ! ንፋሱ እና ደመና አንድ የሚጠብቁት ነገር ያለ ይመስል መንቀሳቀሳቸውን
አቆሙ:: ለሊቱ በጣም ጨለማ ነበር። ጫካ ላይ አልነበርንም ጨለማው ግን ለመተያየት አስቸጋሪ ነበር። ሶስት ሰዎች ወደ እኛ ሲመጡ አየን፡፡ በዛፎች መሃል ተደብቀን ማየት ጀመርን።እኛ በመጣንበት አቅጣጫ ሄዱ፡፡ ከተደበቅንበት እየተጠራራን መውጣት ጀመርን። ሰኢድ ግን ሊነሳ አልቻለም። በፍርሃት ደነዘዘ ሊንቀሳቀስ አልቻለም:: በመጨረሻ ኬን ተሸክሞት ድልድዩን ተሻገርን፡፡
ድልድዩን እንደተሻገርን ሰኢድ አስነጠሰ፡፡ ኬን አስቀመጠው እና አስታወከ፡፡ በኋላ " መናፍስት ነበሩ አይደል ማታ ያየናቸው" አለ፡፡
ሁላችንም ተስማማን፡፡
“ራሴን ስቼ ነበር። አሁን ደህና ነኝ እንሂድ" አለ፡፡ እኩለ ቀን ሲሆን አንድ ትልቅ መንደር ደረስን። ገበያ ነበር የሚመስለው:: ሰዎች ያዜማሉ ይጨፍራሉ ልጆች ውርውር
ሲሉ የምግብ ሽታ:: ወደ መንደር ቀስ ብለን ገብተን እንጨት ላይ ተቀመጥን።
ሰዎች አዩን አንዳንዶቹ ከዚህ በፊት የምናውቃቸው ይመስላሉ::
እጃቸውን እያውለበለቡ ሰላም አሉን፡፡ አንድ ሴት ወደ እኛ መጥታ አውቅሃልሁ አለችኝ፡፡ አኔ ግን ላውቃት አልቻልኩም::
ጅኒየር እኔን እየፈለገ መጥቶ እንደነበረ እና እናቴን አባቴን እና ትንሽ ወንድሜን ከሚቀጥለው መንደር እንዳየቻቸው
ነገረችኝ፡፡ ከዛ መንደር ብዙ የማታሩ ጆንግ ሰው አለ እናንተም ዘመዶቻችሁን ልታገኙ ትችላላችህ አለች ወደ ጓደኞቼ ፊትዋን
ዙራ።
ወዲያው ለመሄድ ፈልጌ ነበር ነገር ግን በቀጣዩ ቀን ለመሄድ ተስማማን፡፡ በዛ ላይ ሰኢድ እረፍት ያስፈልገዋል::
ወደ ወንዝ ወርደን ዋኘን ድብብቆሽ ከተጫወትን በኋላ ድስት ሙሉ ሩዝ ሰርቀን በላን፡፡
ያን ምሽት መተኛት አልቻልኩም::
አልሃጂ "ውሾቹ ቀሰቀሱኝ” አለ
እኔ እንኳን ከመጀመሪያው አልተኛሁም አልኩ፡፡
ቤተሰቦችህን ለማየት ጓጉተሃል አይደል አለ አልሃጂ። "እኔም አለ እየሳቀ፡፡ ውሻወቹ ጩሀት ግን አልተለየብሁም?”
ትንሽ ቆይቶ መንደርተኛው ነቃ:: እኔ እና አልሃጂ ሁሉንም ከእንቅልፍ ቀሰቀስና ቸው:: ሰኢድ ሊነሳ አልቻለም:: "ተነስ
መሂድ አለብን" እያልን በጣም አንቀሳቀስነው። ሊነሳ ግን አልቻለም:: እንደገና ራሱን ስቶ ይሆን አልን። አንድ ትልቅ ሰው መጥቶ ውሃ አፈሰሰበት። ሰዒድ አልተንቀሳቀስም። ሰውየዋ
ፊቱን አዙሮ ትንፋሹ አዳመጠ። ቀስ ብሎ " ከዚህ መንደር የምታውቁት ሰው አለ ብሎ ጠየቀን፡፡ አናውቅም ብለን መለስን።
ኬንን ወስዶ በጆሮው አንድ ነገር ነገረው:: ኬን ማልቀስ ጀመረ። ሰዒድ ጥሎን እንደሄደ አወቅን፡፡ ሁሉም ማልቀስ ጀመሩ እኔ ግን ለደቂቃዎች ደንዝዥ ነበር። ኬን እና ትልቁ ሰውየ የመቃብር ሳጥን አምጥተው የስዒድን አስክሬን ሳጥኑ ውስጥ አስገቡ።በነጭ አንሶላ ተጠቅልሎ በእንጨት ሳጥን ውስጥ ከጠረጴዛ ላይ
ተቀመጦ ጸሎት ማድረግ ተጀመረ። ሰሙን እየጠራ ጸሎት ማድረግ ሲጀመር እንባየ ከፊቴ ላይ ኮለል ብሎ መፍሰስ ጀመረ።የስዒድን ትቶን መሄድ ማመን አልቻልኩም፡፡ ራሱን እንደሳተ
እና እንደሚመለስ ለማስብ ስጀምር ወደ መቃብር አስገቡት።እንባየ መሬት ላይ ተንጠባጠበ።
ከቀብር ስነ ስርዐቱ በኋላ ብቻችንን ቀረን። አንድ ነገር እንደሚጠብቅ ሰው ለስዓታት በመቃብሩ ቦታ ተቀመጥን። በጣም ልጆችን ነበርን። ከኬን በስተቀር ከአስራ ሶስት አመት በታች! ኬን ሶስት አመት ይበልጠናል። ምሽቱ ሲቃረብ
ከመቃብር ስፍራው ተንቀሳቀስን።
ሰዒድ ያለው አንድ ነገር ትዝ አለኝ " አንድ አካሌ እንደሞተ ይሰማኛል ::"
ሲነጋ የቀብር ስነ ስርዐቱ እንዲፈጸም የረዱንን አመስገን።ከመካከላቸው አንድ "የት እንዳረፈ ሁሌም ታውቃላችሁ አለ"።
በስምምነት ራሳችንን ነቀነቅን፡፡ ወደዚህ መንደር የመመለስ እድላችን አንስተኛ ነው:: ነገን አናውቅምና። ጓደኛችንን ጥለነው እየሄድን ነው" እናቴ እንደምትለም "የዚህ አለም ጊዚያዊ ሩጫውን ጨረሰ”::
ለሊቱን ሙሉ በጸጥታ ተጓዝን። ለትንሽ ደቂቃ ስናርፍ ሞሪባ ራቅ ብሎ ከተቀመጠ በኋላ ማልቀስ ጀመረ። ራሱን ለመቆጣጠር በቅጠሎች መጫወት ጀመረ።ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ጉዟችንን ቀጠልን።
"መንደሩ ስንደርስ እናቴን ጥብቅ አድርጌ ነው ማቅፋት” አለ አልሃጂ።
ሁላችንም ሳቅን፡፡
ወደ መንደሩ ስንቃረብ ቤተሰቦቻችንን እንደምናገኛቸው ተሰማኝ፡፡ ፈገግታየ አልተቋረጠም። የቡና ዛፎች ደኑን መተካት ጀምረዋል። በቡናው ተቃራኒ መለስተኛ የሙዝ እርሻ አለ፡፡ ከኛ
ተሻግሮ አንድ ሰው ያልበሰለ ሙዝ ሲቆርጥ አገኘነው::
ሰላም ዋሉ?" አለ ኬን።
ሰውየው ጎር ጋስሙ ይባላል። ወንደላጤ ነው:: ሰዎች ትልቅ ሰው አይደል ለምንድን ነው የማያገባው:: የግድየለሽ ኑሮ
የሚኖረው" ይላሉ። ምንም መልስ አይሰጥም::
ጋስሙ ፈገግ አለ። ያዙ አለን ሙዝ።
“አባትህ እና እናትህ ሁሌም ስለ አንተ ያወራሉ ይጸልያሉ” አለ ወደ እኔ ዙሮ።" አሁን ሲያዩህ በጣም ነው ደስ ሚላቸው" አለኝ።መንደሩ ተራራ ላይ ነው አለኝ እና መሮጥ ጀመርኩ። መንገዱ አዙሪት ነበር፡፡ ጫፍ ላይ ስንደርስ ደክሞን ተቀመጥን፡፡
ከተራራው ስወርድ የጥይት ተኩስ ተሰማ።ሰዎች መጮህ ማልቀስ ጀመሩ:: ሙዙን ጥለን በዛፎች መሃል ተሸሸግን።
በመጨረሻ አቆመ ሁሉም ነገር ጸጥ ረጭ አለ። ጋስሙን ወደ መንደሩ መሄድ እንደምፈልግ ስነግረው እጆቼን ያዘኝ፡፡ እጄን አስለቅቄ ወደ ታች ሮጥኩ፡፡ መንደሩ ስደርስ ሁሉም ነገር ተቃጥሏል። የት ጀምሬ እንደምፈልጋቸው

አላውቅም። ጋስሙ እና ጓደኞቼ ተከትለውኝ ነበር። የሚቃጠለውን መንደር ቁመን
መመልክት ጀመርን። ጋስሙ እየተንቀሳቀሰ ማየት ጀመረ፡፡ እኛ
በቆምንበት ተቃራኒ ጋስሙ ጩሆ ሲያለቅስ ሰምተን ሮጥን።ከሃያ በላይ ስዎች በጥይት ተደብድበው ወድቀዋል፡፡ አብዛኞቹ ወጣት ወንዶች ነበሩ። ቤተሰቦቻችንን ሁሉም ቦታ ዙረን ፈለግናቸው ልናገኛቸው ግን አልቻልንም፡፡
በጣም አዘንኩ። ጋስሙን ሰላም ለማለት ባንቆም፤ ተራራው ላይ ባናርፍ ቤተሰቦቻችንን ባየናቸው ብየ ተቆጨሁ። ተናደድኩ።ከጋስሙ ጋር ተናነቅኩ። በኋላ ጓደኞቼ ገላገሉን። ከዛ እነሱም ንትርክ ውስጥ ገቡ እርስበርሳችንን መደባደብ ጀመርን። ጋስሙ የማንም ጥፋት አይደለም ሲል እንደገና ለጠብ ተነሳሁ። ብዙም ሳይቆይ የሰዎች ድምጽ ሰማን። ወደ ቡናው እርሻ ሩጠን በመሄድ
ተደበቅን፡፡
ከአስር የሚበልጡ አማጺዎች ነበሩ። ልብሳቸው በደም ጨቅይቷል። አማጺዎቹ መሬት ላይ ተቀምጠው ማሪዋና
እያጨሱ ካርታ መጫወት ጀመሩ።
አንዱ “ዛሬ ሶስት መንደሮችን አቃጠልን" ሲል።ሌላው
“በትንሽ ስዓታት ሶስት መንደር ማቃጠል ደስ ይላል። ከዚህ መንደር ደግሞ ማንም የተረፈ የለም ሁሉንም ነገር ነው
ያቃጠልነው:: ኮማንደር እንደሚኮራብን ተስፋ አለኝ" አለ።
አንዱ ወደ ቡና ቅጠሉ ሲመጣ የቡና ቅጠሎቹ ድምጽ ተሰማ።
አማጺዎቹ ጨዋታቸውን አቁመው እሱን ለመሸፈን በሁሉም ቦታ ሮጡ። ሁላችንም አንዴ ተነስተን ሮጥን።ጋስሙ ፊት
ለፊታችን ነበር። የት እንደሚሄድ ስለሚያውቅ ሁላችንም ተከተልነው። ለስዓታት ሮጥን፡፡ ተኩሱ ቀጥለ። ጋስሙ ተኩሱ እንዳይደርስብን እሱ ከኋላ ካትሮ እኛ ከፊት መሮጥ ጀመርን።
ብዙም ሳይቆይ ጋስሙ ማልቀስ ጀመረ። ተንከባለለ። በጥይት ተመቶ ነበር። ብዙ ደም መፍሰስ ጀመረ። አልሃጂ እና እኔ
ቲሽርቱን አወልቀን ደሙን ለማቆም ሞከርን፡ አልቻልንም! እጁ ቀዘቀዘ ደሙ መፍሰሱን ቀጠለ። ምንም አላልንም። ምን እንደሆነ አውቀናል።
አልሃጂ የጋስሙን አይኖችን ከደናቸው::
የመታሁት ጸጸተኝ፡፡ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። የምታዘቀዝቀው ፀሐይ ጋስሙን ይዛው ሄደች።

#የክረምት_ግጥም
እትትትትትትት - ብርዱ እንዴት አይሏል
አየሩ ቀዝቅዞ - ሰውነቴ ግሏል።
በተወደደ እንጨት- ከሰል በጠፋበት
መብራት ሲፈልጉት - በማይገኝበት።
እንዳይቀዘቅዘን - እንዳይሰማን ብርድ
ነይ እሳት እንፍጠር
ነይ እሳት እናንድድ።
እትትትትትትት - ብርዱ እንዴት አይሏል
አየሩ ቀዝቅዞ - ሰውነቴ ግሏል።
በተወደደ እንጨት- ከሰል በጠፋበት
መብራት ሲፈልጉት - በማይገኝበት።
እንዳይቀዘቅዘን - እንዳይሰማን ብርድ
ነይ እሳት እንፍጠር
ነይ እሳት እናንድድ።