አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የባንዲራ_ነገር

በኔ አይነቷ ምስኪን አገር -
የባንዲራችን ቁጥር ብዛት - ከልብሶቻችን በለጠ
የኔ አይነቱ ከንቱ ፍጡር -
ለባንዲራ ያለው ፍቅር - ወደ ሸሚዝ ተለወጠ።
ምን አይነት ነው ባንዲራችን? -
ምንድን ነው የኛ መለያ?
ምን አይነት ነው የአገሬ አርማ? -
ቀለሟ ምን ነው የኢትዮጵያ?
የልጅ ልጆቼን የሚያግባባ ፣ አያቶቼን የሚያከብር
የትላንትን የአገር ፍቅር ፣ ከነገ ጋር ሚያስተሳስር፣
ሁሉንም ኢትዮጵያውያን፣ በሙሉ ድምፅ የሚያስማማ
ምን አይነት ነው ባንዲራችን? -
ምን አይነት ነው የአገሬ አርማ???
ተረኛ ስፊዎች ሁሉ -
በፍላጎቶቻቸው ልክ ፣ቀደው ሰፍተው እየሰጡን
በቀለም ብዛት አነሁልለው ፣የባንዲራ ፍቅር አሳጡን፡፡

🔘በሙሉቀን🔘

💚 💛 ❤️