አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ማን_ልበላት?

አያችኋት ያቺን - ከሰው ተነጥላ?
መልኬ ይኼውላችሁ - ስሜ ይቆይ ብላ፡፡

አትረዝም፣አታጥር
አትቀላ፣አትጠቁር ፤
ክሽን ያለ ቁመት ፣ ክሽን ያለ ከለር
በጣም የምትስብ ፣ በጣም የምታምር

አያችኋት ያቺን?

አትወፍር፣አትቀጥን
አትዘገይ፣አትፈጥን
የአይኖቿ ብርሐን ፣ ፅልመትን የሚያሸሽ
ለአይን የምታሳሳ ፣ ቢነኳት ምትቆሽሽ፡፡

አይችኋት ያቺን ?

ብዙም ዝም ያላለች ፣ ብዙም ማታወራ
ብዙም የማትደፍር ፣ ብዙም የማትፈራ
የማትንቅ ፣ ግን ኩሩ
የውበት ድንበሩ፡፡

ያቺን አያችኋት?

ስሟን ባላውቀውም - ስም እንዳወጣላት
ምናልባት
ምናልባት
እሷን የሚመጥን - ስም ከተገኘላት
ውቧን ማን ልበላት???