አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሁለት


#በክፍለማርያም

ፍፁም ከመምህር ፍቃዱ ጋር በሻይ ሰዓት ቁጭ ቡለዉ እያወሩ መምህር ፍቃዱ
"እዚህ ግቢ ዉስጥ ደግሞ ከወጣት ሴት ተማሪወች ጋር እንዳትታይ"
ፈገግ እያለ እና ፍፁምን ጀርባዉን መታ መታ እያረገ ነገረዉ
"ለትምህርት ቤቱም ለኛም ስም መጥፍያ ነዉ እንደማይክእዚህች ከሚማሩት ተማሪወች ጥቂት የእድሜ ልዩነት
ቢኖርህ ነዉ"
እንደ ምክርም እንደ ተግሳፅም እየቃጣዉ።

ፍፁምም በንግግሩ ቢከፋም ላለማስቀየም የዉሸት ፈገግ አለለት መስማማቱን ለመግለፅ በሚመስል መልኩ።
ቤዛዊት ጎበዝ ከሚባሉት ተማሪወች ተርታ አትመደብም
መሀል ላይ ያለች ቢሆንም በወሬ እና በመረበሽ የሚስተካከላት የለም ግን የፍፁም ክፍለ ጊዜ ደርሶ
ሲያስተምር ፀጥ ረጭ ብላ ትኩረትዋን ሰብስባ
ትቀመጣለች ጉዋደኞችዋ ሁሉ ታዝበዋታል በተለይ ትዕግሥት
"አረ የኛ ጎበዝ ተማሪ ከትምህርቱ ነዉ ከአስተማሪዉ ፍቅር የያዘሽ "
እያለች ትስቅባታለች።
ቤዛዊትም ጉዋደኛዋ ስታሾፍባት ኮስተር ብላ
"ምን አገባሽ"
ከማለት ዉጪ ሌላ መልስ አትመልስላትም
የልቧን ስሜት ግን ትሰማዋለች ፍፁምን ሰዓት ሳትጠይቀዉ
በፊት ገና የትምህርት ቤቱ በር አካባቢ ተማርካ ነበር።
ምኑ እንደሳባት ባታዉቅም ፀጉሩ በስርአት የተከረከመ
ጠይም መልኩ ላይ ለሰዉ የማይታይ ለእስዋ ግን የታያት
እና የተነበበላት የሆነ ነገር አለ ግን አስተማሪዬ ይሆናል
ብላ አላሰበችም ሰዓት የጠየቀችዉም ሆን ብላ ነበር።
መምህር ፍፁም እያስተማረ ተማሪወችን በአይኑ
ይከታተላል በመሀል ለእሱ በድንገት እስዋ ግን ሆን ብላ
የቤዛዊት አይኖች ቀጥታ ከአይኖቹ ጋር ተገናኙ የቤዛ አይኖች ሁለቱም ገርበብ ብለዉ እያዩት ቢሆንም
ቀኝ አይንዋ ብቻዉን ተዘግቶ ተከፈተ ቤዛዊት የምታረገዉን እያየ
"ምን መሆንዋ ነዉ" አለ በልቡ
ማስተማሩን ግን ቀጠለ ድጋሜም በድንገት ሲተያዩ ጠቀሰችዉ
ያልጠበቀዉ ነገር ስለሆነ ሁለት አይነት ስሜት ተሰማዉ
የመ'ፈለግ ስሜት በተቃራኒዉ የመናቅ መፈለጉን ሲያስብ
ከሙያዉ ስነ ምግባር ጋር የሚጋጭ መሰለዉ መናቁን
ሲያስብ ቤዛን እንደ ጋጠ ወጥ ተመለከታት ክፍለጊዜዉ
ሲያልቅ ለብቻዋ ጠርቶ ሊቆጣት እና ሊያስጠነቅቃት አስቦ ነበር ።

ግን እንደ አስተማሪ መሆን አቃተዉ ተወዉ ምንም አላላትም።
ከትምህርት ቤቱ እንደወጣ ቀጥታ ወደ ቤቱ አመራ ተከራይቶ የሚኖርበት ቤት ጠባብ ብትሆንመ ዉበት አላት
አልጋዉ በስርዓት ተነጥፎዋል መደርደርያዉ ዉስጥ
ያሉት መፅሀፎቹ በወግ በወጉ ተቀምጠዋል
ለማብሰያነት የሚጠቀምባቸዉ እቃወች ታጥበዉ
በአንድ እረድፍ ተስተካክለዉ ተቀምጠዋል በአጠቃላይ
ቤቱን በፅዳት ይዞታል።
ጥቂት ጋደም ካለ ብኃላ ማንበብ ያለበት መፅሀፍ
እንዳለ ሲያስታዉስ መተኛት ፈልጎ ስለ ነበር
ቅፍፍ እያለዉ ከአልጋዉ ተነስቶ ከመደርደርያዉ
የሚፈልገዉን መፅሀፍ መርጦ ወንበር ላይ ተቀመጠ።
እያነበበ ሳያቀዉ ሀሳቡ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ አይን ይታየዋል
አይኑን ሲከተል የቤዛዊት ፊት ታየዉ እየጠቀሰችዉ ነዉ
አንድ አይንዋን ብቻ ጭፍን አርጋ ስታበራዉ አፍዋ በትንሹ ተከፍቶ ከፊት ያሉት የሚያምሩት ጥርሶቿ ይታያሉ ጉንጮ ላይ
ሳትስቅ እራሱ ፈገግታ አለ ሁሉ ነገርዋ ደስ ይላል
ይሄንን እያሰበ በድንገት ማንበብን እንደረሳዉ ሲገባዉ
"ምን ነካኝ!!ምን ሆኜ ነዉ ስለሷ የማስበዉ
ከአሁኑ ማስቆም አለብኝ" ብሎ መፅሀፉን ዘጋዉ።
"ቤዛዊትን ነገ ስርዓት እንድትይዝ እነግራታለሁ" እያለ
ብቻዉን እያወራ በዛዉ እንቅልፍ አሸንፎት ወደ አልጋዉ አመራ ለነገ ቀጠሮ እየያዘ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#ፍቅር_እንደ ...

የሻማ መብራት ነው
ፍቅር እያልኩሽ
አንቺ ግን የአምፖል ነው
ብለሽ ተቆጣሽ
ቁጣሽን በመፍራት
ድንገት ተጨንቄ
ከመቅረዝ ላየሁት
እኔስ ምን አውቄ
አፍታ እንኳ ሳንቆይ
ሳይጠፋ መብራት
ጨለማ ተዋጥን
አላፊው አግዳሚው እፍ እፍ እንዳሉት፡፡

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
#የአባይ_ልጅ_አይጥማው

መሰረት የሚሆን ቢጠፋ እንኳ ድንጋይ
ሀገር ጥሎ ሽሽት እንዲቀር ከአባይ
እያንዳንዱ አካሌ ተነስቶ ከኔ ላይ
አጥንቴ ተለቅሞ ካፈሩ ተማግሮ
ጅማቴ ተመዞ እሱን አጠንክሮ
በቀጠነው ደሜ ስጋዬ ተቦክቶ
ካጥንቴ ማገር ላይ ልስኑ ተመትቶ
ነፍሴም ተሰውቶ ከጦር ከዘመቻ
“ የአባይን ልጅ ጠማው " አያሰማኝ ብቻ !!!

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
#ፍቅርን_በትወና

በየትያትር ቤቱ
በየፊልሙ ደጃፍ
ምስላችን ባይኖርም
ስማችን ባይጻፍ
በየ ቲቪው መስኮት
ኑ እዩን ! ባንልም
ፊልማችን ሲመረቅ
ታዳሚ ባይኖርም
እኛው ብንገኝም
ፍቅርን እንድንተውን
ድርሰቱን ሲሰጠን
ከሆሊውድ ደጃፍ
ከቦሊውድ ጓሮ
በጠፍ በጨረቃ
ዞሮ ተዟዙሮ
የተሻሊተዋኝ
ቢያጣ ተቸግሮ
ነበር የመረጠን
አንቺን ከኔ ጋራ
ገቢሩ እንዲፈጸም
ፍቅርን እንድንሰራ፡፡

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሶስት


#በክፍለማርያም

በነጋታዉ ፍፁም ማስተማሩን እንደጨረሰ
ቤዛዊትን የመምህራን ቢሮ እንድትመጣ አዟት ከክፍል ወጣ ከበሩ ወጥቶ ጥቂት እርምጃወች እንደተራመደ።

"ቲቸር" የሚል ድምፅ የሰማ ስለመሰለዉ ዞረ ቤዛዊት ናት
"ፈለግከኝ ነበር"
ፈጠን ፈጠን እያለች ስታወራ ትንፋሽዋም ቁርጥ ቁርጥ ይላል።
ፊትዋ ላይ ምንም የጥፋተኝነት ስሜት የለም እንደዉም ምን ሊለኝ ይሆን የሚል ጉጉት አድሮባታል
"ትላንት ምንም ያረግሽዉ ነገር የለም?"
መቆጣት ፈልጎ ቢኮሳተርም አልቻለበትም
ቤዛዊት ለማስታወስ ሌባ ጣትዋን አፍዋ ላይ አስቀምጣዉ የአይኖችዋን ብሌኖች ወደ ቅንድብዋ ላከቻቸዉ
"እ ምንም አላስታዉስም .......የጠቀስኩክ ግን"
አለችና አንጠልጥላ ተወቸዉ
ፍፁም እስዋ ይሄን ስትል ድፍረትዋ ገርሞት
ለይምሰል ተኮሳትሮ እያያት ነዉ ቤዛዊት ካቆመችበት ቀጠለች
"ስለ ጠቀስኩኩ ተናደክ ከሆነ ይቅርታ ቲቸር አይለመደኝም
ለርዕሰ መምህሩ አሳልፈህ ከሰጠሀኝ ቀጥታ ነዉ
የሚያባርረኝ ሌላ ጥፋትም አለብኝ እባክህ እዉነት አይለመደኝም ቲቸር ሳላስበዉ በስህተት ነዉ"
እያለች እንደ መለመን እጆችዋን እያርገበገበች ተጠጋችዉ
"ቆይ ቆይ" አለና ፍፁም እንደ ማሰብ ብሎ
ድጋሜ በደንብ ተመለከታት
እድሜዋን ሲገምት 20 አመት ቢሆናት ነዉ ግን
ቁመት ስላላት ትልቅ ትመስላለች የለበሰችዉ የዬኒፎርም
ቀሚስ በጣም አሳጥራዉ ከጉልበትዋ ከፍ ብሎ ታፋዋን
በከፊል ያሳያል ሰዉነትዋም ሞላ ያለ ነዉ ትከሻዋ ላይ በቅርብ የተተኮሰ የሚመስለዉ ፀጉርዋ ተመችቶት ተኝቷል
ጆሮዋ ፍፁም የሚላትን ለመስማት ቀስራቸዋለች
አይኖችዋ እንዲያዝንላት እየተለማመጡት ነዉ።
ድምፁን ጎርነን አርጎ
"ሁለተኛ እንዳይለመድሽ እኔ አስተማሪሽ እንጂ እኩያሽ አደለሁም!.."
አዉርቶ ሳይጨርስ ይቅርታ እንዳረገላት ስታዉቅ
ደስ ብሎዋት አቀፈችዉ ወድያዉ
"በጣም ይቅርታ ቲቸር"
ብላዉ እየሳቀች ወደ ክፍልዋ እየተመለሰች
ስታቅፈዉ ሳያስበዉ ስለሆነ ደንግጦ ነበር
ግልፅነትዋን ግን ስለወደደላት ዝም አላት
ጥቂት እንደተራመደች ግንስሟን እንደማያዉቀዉ እየሆነ
"ማን ነሽ ቤዛዊት?"
"አቤት"
አለችዉ በቅርብ እርቀት ላይ ሆና
"ይሄ ያረግሽዉን ቀሚስ ቀይሪዉ ላንቺ ሳይሆን
ገና ለተወለደ ህፃን ልጅ ነዉ የሚሆነዉ"
ፈገግ እያለ ነበር የነገራት
"እሺ ፍፄ"
ብላዉ ከፊቱ እርቃ ሄደች
እስዋን ቆሞ ለየት ያለ ባህሪ ነዉ ያላት ብሎ ስትሄድ
በተመስጦ እየተመለከታት መምህር ፍቃዱ ከጀርባዉ መጥቶ
"ከዚች ቀዉስ ጋር ደግሞ ምን አነካካክ?"አለዉ
"ቀዉስ?ምን ለማለት ነዉ ያዉ አስተማሪዋ አደለሁ እንዴ" መለሰለት በልቡ እንዴትቀዉስ ይላታል እያለ።
ፍቃዱ ስለ ቤዛዊት የሚያዉቀዉን መናገር ቢፈልግም
ክፍል የሚገባበት ሰአት ስለደረሰ
"ዛሬ አርብ አደል ማታ አንድ ሁለት እያልን እነግርሀለዉ ስለልጅቷ"
ብሎት ተለያዬ
ከተቀጣጠሩበት ሆቴል ስለ ቤዛዊት መስማትም ስለፈለገ
ቀድሞ የተገኘዉ ፍፁም ነበር።
ፍቃዱ እንደመጣ ወድያዉ ምግብ አዘዙ
ምግቡ ቀርቦ በልተዉ ከጨረሱ በኋላ ቢራ አዘዉ እየጠጡ
ፍቃዱ አዲስ ስለገዛዉ መፀሀፉ ማዉራት ጀመረ።ፍፁም አቁዋርጦት ስለ ቤዛዊት ሊጠይቀዉ አለና
"ምን ይለኛል ቡኀላ ወደዳት ብሎ ከስራ ቢያስተጎጉለኝስ
ደግሞ እኔ እራሴ ምን ሆኜ ነዉ ትኩረት የምሰጣት
መቼስ አልወደድኩዋትም"
ሳይታሰበዉ ድምፅ አዉጥቶ ሳቀ
"ምን የሚያስቅ ነገር ተገኘ ጃል ብቻህን የምትፍነከነከዉ
ለኛም አካፍለና እንወቀዉ"
ብሎ ፍቃዱ ሲያፋጥጠዉ
"መጠጥ ስለማልችል ነዉ ሁለት ጠጣሁ በቃ መሳቅ ነዉ"
የኔ ተፈጥሮ ብሎ መለሰለት ድጋሜ እየሳቀ።
ትንሽ የፍቃዱን የማያልቅ ወሬ ከሰሙ በኃላ ፍፁም
"እየመሸ ስለሆነ ወደየ ቤታችን እንሂድ ሌላዉ ደግሞ
ቅድሞ እነግርሀለዉ ያልከኝን ሳትነግረኝ....?
አለዉ ምን ይለኝ ይሆን በሚል ስሜት እያየዉ
ፍቃዱም ሰአቱን አይቶ
"ሳናስበዉ መሸ እዉነትህን ነዉ እንንቀሳቀስ
ሂሳብ በኔ ግብዣ ነዉ "
ብሎ ከፍሎ ተነሳ ሳይመልስለት
ከሆቴሉ በር እንደወጡ ሊለያዬ ቻዉ ተባብለዉ
በየ መንገዳቸዉ ሊሄዱ ሲሉ ፍቃዱ ማዉራት ጀመረ።
"ቤዛ ነዉ ቤዛዊት የሚሎት የታወቀ የሀብታም ልጅ ናት
ግን የሚያሳዝነዉ ትንሽ አይምሮዋ ደህና አይመስለኝም
አንድ አመት አቋርጣ ነበር ዘንድሮ ትንሽ አገግማ ነዉ እንጂ መማር የጀመረችዉ"አለዉና
"ቤት መግባትህን ደዉለህ አሳዉቀኝ"ብሎት ሄደ።
ፍፁም በእግሩ ወደ ቤቱ እየሄደ ከልቡ ለቤዛ ማሰብ ጀመረ
" ምን አይነት ህመም ይሆን ምስኪን እንኩዋንም ጠዋት
ክፉ ነገር አልተናገርኩዋት ግን እኮ ምንም የሚያማት
አትመስልም "
እያለ ቤቱ ደረሰ።
ለሊቱን በአብዛኛዉ እንቅልፍ እስኪወስደዉ ድረስ
ቤዛዊትን ከጭንቅላቱ አላወጣትም ስለስዋ በጣም ሲያስብ እና ስለስዋ የማወቅ ጉጉት አድሮበት ሲገላበጥ
ለሊቱ እንደምንም ነጋለት።
በጠዋት ተነስቶ ተጣጥቦ ቁርሱን በልቶ ከጨረሰ በኃላ መፅሀፍቶቹን ቦርሳ ዉስጥ ከቶ አነገበዉ እና በሩን ቆልፍ ወጣ
የግቢዉ መዉጫ በር ጋር ሲደርስ ሰዉ አይቶ ቆመ
ቤዛዊት የእግር ጥፍርዋ ድረስ የሚደርስ ዩኒፎርም ቀሚስ ለብሳ ቆማ እየጠበቀችዉ ነበር ቀይሪ ስላላት አዲስ መግዛትዋን ልታሳየዉ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍4
#አውቃለሁ_አታውቂም!

ክንፉ የተሰበረ፣ የታከተው መንፈስ፣
እንደ ክረምት ስማይ ፣ በእጦት ብልጭታ፣ ሲታረስ፣
.............................ሲመታ፣
ልብሽ ጽኑ ድጋፍ፣ እንዳጠነከረኝ፤
ፍቅርሽ አዲስ ምእራፍ፣ ገልቦ እንዳስጀመረኝ!
ታውቂለሽ?! ..

ድፍን ባል ለሊት፣
የብርሀን ሸማ፤
ጭር ባላ ውድቅት፣
ያሬዳዊ ዜማ፤
መሆንሽን
..............ታውቂያለሽ?!
አውቃለሁ አታውቂም!

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘

የካቲት፣ 2011፤ አዲስ አበባ፡፡
#ጸሉቴ_ስለቴ

ጸሎቴ፤
ስለቴ፣ . . .
ለአንድ ጊዜ ብቻ፣ የለሊት ወፍን ክንፍ
የጨለመን ዘመን፣ ሰንጥቆ 'ሚያሳልፍ፡፡
እንደየኖህ መርከብ፣ እንደመሴ በትር፤
ከዘመን ደንቃራ፣
ከገገር ፉከራ፣
ከመንጋ ገጀራ፣
ፍጡራንን ሁሉ፣ ጠብቆ 'ሚያሻግር፡፡
የሆነ ምትሀት!
የሆነ ብልሀት!
..............ፈጣሪ ቢያድለኝ!
ጸሎቴ፤
ስለቴ፣
እንደህጻን ትንፋሽ፣ ሳያነቃ ከእንቅልፍ ፣
እንደንጋት ዝናብ፣ ህልም ሳያዛንፍ፤
በዛሬዬ ስፍር - ለነገ እንድበቃ፤
ሽንቁሬን ደፍኜ - ሰው ሆኜ እንድነቃ፧
የሆነ ምትሀት።
የሆነ ብልሀት።

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘
#ከብጽእና_ጸብ
.
‹‹ብጹእ ናቸው›› ሲል ወንጌሉ ፤
ሳያይ ያመነውን ሁሉ ፤
ሳያዩ አምኖ መገኘት ፤
ሳይሰፈሩ መመላት፣
ሳይፈተኑ ማለፍ አይነት፤
...........................ቢመስልም፤
የሚታየውን፣
ዶፍ
ጎርፍ፣ . , ከማመን፤
ለወና ሰማይ መመነን፤
. ........................ አይቀልም?

ግና
ሁለቱን ምን ለየው?!
አንደኛው መጸየፍ፣
ሌላው ግብዝነት፤
ዞሮ ዞሮ ሽንፈት!

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘

ሰኔ፣ 2012
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አራት


#በክፍለማርያም

ቤዛዊት የፍፁምን ከቤቱ መዉጣት በጉጉት እየጠበቀች ስለነበር
ገና ስታየዉ ፊትዋ በደስታ በራ።
"ቤቴ እዚህ መሆኑን እንዴት አወቀች እዉነትም ፍቃዱ እንዳለኝ
ያማታል ማለት ነዉ"
ጭንቅላቱ ብዙ ጥያቄ እየጠየቀዉ ፈራ ተባ እያለና ሰዉ መኖሩን
ለማየት አቅራብያዉን እየቃኘ ተጠጋት።

"ፍፄ አየህዉ ቀሚሴን አሁን ትልቅ ሰዉ አልመስልም"
እያለች በሁለቱንም እጆቿ ቀሜስዋን ይዛ አንዴ በቆመችበት አንዴ ዞረች።
ቀሚስዋ ከመርዘሙ የተነሳ ጠርዝ ጠርዙ ከመሬት አፈር ስቧል

"እንዴት ቤቴን አወቅሽዉ?"

አላት የህመምዋን ስሜት ስላላወቀ ድምፁን ለስለስ አድርጎ
"ትላንት ወደ ቤት ስትገባ ስከተልህ ነበር ስጠራህ አልሰማሀኝም
እየፈጠንክ ስለምትራመድም ልደርስብህ አልቻልኩም" ትንሽ ትንፋሽ ሰብስባ
"ክፍል እንዳይረፍድብን አብረን እንሂዳ"ብላ እጁን በእጆችዋ
ያዘቻቸዉ።

ሊያስለቅቃት አልሞከረም እጅዋ ይለሰልሳል ተጠጋግተዉም
ሲሄድ በየአንዳንዱ እርምጃዉ ቤዛዊት የተቀባችዉ ልዩ መአዛ
ያለዉ ሽታ እያወደዉ ነዉ።
አይምሮዉ ሰሞኑን እስዋን እያሰበ ስለነበር ባልጠበቀዉ ሰዓት
ከጎኑ ስላገኛት እጅዋን ከእጁ ጋር ስለተያያዘ አጋጣሚ ሳይሆን
እኔና እስዋን ሊያገናኘን ከላይ የተፃፈ ነዉ አለ።

ለእስዋ ያለዉን ስሜት ከዚ በላይ መቆጣጠር አልቻለም
በምንም ሁኔታ ዉስጥ ባላወቀዉ ህመምዋም ቢሆን ከጎንዋ ሊሆን ሊወዳት እና ሊረዳት በልቡ ቃል ገባ።
ሳይተዋወቁ ተግባቡ
ሳያወሩ አብረዉ ሆኑ
እጅ ለእጅ ተያይዘዉ ወደ ትምህርት ቤቱ አቅርያቢያ ሲደርሱ የሰወች አይንን ፈርቶ እጇቹን ቀስ ብሎ ከስዋ እጇች አለያያቸዉ
ይህን ስታይ ቤዛዊት መሀል መንገድ ላይ ቆመች
"እንደሌሎች ሴቶች ስላልሆንኩ እንደወደድኩህ ስላወክ
ሰዉ ፊት ከኔ ጋር ላለመታየት ነዉ"
ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ነገረችዉ።

ከዚህ በፊት አይቷት እንደማያዉቅ ፊትዋ ተለዋዉጧል
ተናዳለች ደስ የሚሉት ጉንጮቿ ፍም ሆነዉ ቀልተዋል አይንዋ እንባ እንደማቅረር ብለዋል እንደዚህም ሆና
ዉበትዋ አልቀነሰም ስሜትዋ ወድያዉ እንደሚቀያየር ታዘበ
ፍፁም አሳዝናዋለች ልብንም አሸንፋዋለች
ድምፁ እየተንቀጠቀጠ
"ቤዚ እዉነት ንገረኝ ካልሽኝ እኔም ሰሞኑን ስላንቺ ሳስብ ነበር
አሁንም እጅሽን የለቀኩት ሌሎች አስተማሪወች እና ተማሪወች
አይተዉን ሌላ ስም እንዳይሰጡን ነዉ ከክላስ በኋላ እኔ ሰፈር
ቅድም የጠበቅሽኝ ቦታ ጠብቂኝ እናወራለን እሺ"

አላት በለሰለሰ ድምፅ በእጆቹ ትከሻዋን ነካ ነካ እያደረገ
ይሄን ሲላት ወደ መጀመርያዉ ደስታዋ ተመለሰች
መላ ፊትዋ ፈገግ አለ አይን አይኑን እያየች
"እወድሃለሁ እሺ የቡሀላዉን ቀጠሮ እንዳትረሳዉ"
አለችዉና ቀድማ ወደክፍለ ለመግባት ጥላዉ ሄደች ።
ፍፁም ምን አይነት የፍቅር ህይወት ዉስጥ ሊገባ እንደሚችል
እና ስለ ቤዛዊት የጀርባ ህይወት ሳያጠና ስለስዋ የሰማዉን
የህመምዋን ምንነት ሳያጣራ ለእስዋ መሸነፉ አልዋጥ እየለዉ
ነገር ግን ነገሮች እና ሁኔታወች ሳያስበዉ እንደተለዋወጡ
እንዴት ስለስዋ ከማሰብ አልፎ መዉደድ ዉስጥ እንደገባ
ግራ የመጋባት ስሜት ዉስጥ ሆኖ ወደ ትምህርት ቤቱ ግቢ ዘለቀ።

ክፍለ ጊዜዉ ደርሶ ለማስተማር የማስተማርያ መፀሀፎቹን
ይዞ ወደ እነ ቤዛዊት ከፍል ገብቶ ማስተማር ጀመረ በየ መሀሉ ከቤዛዊት ጋር ሲተያዬ እሱ እንደማፈር እያለ
አንዳንድ ቃላቶችን በትክክል መጥራት አቅቶት
በተደጋጋሚ ለማስተካከል ሲሞክር ከቤዛዊት በቀር
የክፍሉ ተማሪ እንዳለ መሳቅ ጀመሩ
እሱም የቤዛ አይን እንዳንተባተበዉ ሲገባዉ ጥቂት አብሮዋቸዉ ስቆ
"በቃ በቃ ትንሽ ተዝናንተናል አሁን ሁላችሁም ወደ ትምህርቱ"
ማስረዳቱን ቀጠለ።

ቤዛዊት እሱን ላለማየት ወረቀት አዉጥታ መፃፍ ጀመረች
ማስተማሩን ጨርሶ ሲወጣ ተከትላዉ የፃፈችዉን ወረቀት ሰጠችዉ።
ወደ መምህራን ማረፍያ ገብቶ ቤዛዊት ፅፋ የሰጠችዉ
ወረቀት ምንሊል እንደሚችል እያሰበ ወንበር ላይ በፍጥነት ተቀምጦ ሁለቴ የታጠፈዉን ወረቀት በጉጉት መግለጥ ጀመረ።....

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
ሃገርን ለማቆም እነሱ ሲወድቁ
ወቶ አደር ለመሆን ወኔን ሲሰንቁ
ባልተመቸ እንቅልፍ ድንጋይ ሲንተራሱ
ይህንን አስታወሱ.....
ኢትዮጵያን ብለው ነው መኖርን የረሱ
💚 💛 ❤️
🔘 ሄኖክ አባይነህ🔘ሐጠ
እልፍ አእላፍ ሞተው እልፍ አእላፍ ቆስለው
በትውልዶች ልብ ውስጥ የድል ሰንደቅ ተከለው
ያቆዩልን ክብር ኢትዮጵያዊ ዓርማ
በአጥንትና ደም የታተመ ፊርማ
ቃልኪዳን የያዘ የአደራ ንብረት ነው
ዘመን የማይሽረው ወራሪ የማይደፍረው።
💚 💛 ❤️
🔘ቴዎድሮስ አበበ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አምስት


#በክፍለማርያም

....መግለጥ ጀመረ..ወረቀቱ ላይ በጥቁር እስኪርቢቶ የተሳለ የልብ ቅርፅ
ምልክት ይታያል መሀሉ ላይ ልቡን አቁዋርጦ የሚያልፍ የጦር
ምልክት በቀይ እስኪርቢቶ የተንጠባጠበ የሚመስል የሚፈስ ደም
የሚመስል ነጠብጣብ ጨምራበታለች ወደታች ማየቱን ሲቀጥል
በትልቁ የተፃፈ
"ልቤን ሰጥቼሀለዉ አትጉዳኝ"
ፍፁም ደነገጠ
"ምን አስባነዉ"
ገና ተዋወቅን እንጂ መጎዳዳት ዉስጥ መች ደረስን ደሞ በወረቀት
ስዕል መሳል ምን የሚሉት ነዉ ሲል እያሰበ ከጀርባዉ መምህር ፍቃዱ ሲመጣ ወረቀቱን ጨምድዶ ኪሱ ዉስጥ ከተተዉ።

ፍቃዱም
"አቶ ፍፁም ዉሎ እንዴት ይዞሀል"
ብሎ አጠገቡ ወንበር ስቦ ተቀመጠ።
ፍፁም ደፈር ብሎ
"ባለፈዉ ስለጀመርክልኝ ስለ ቤዛዊት ታሪክ ቀጥልልኝ"
አለዉ ለመስማት ሰፍ ብሎ
"ቤዛዊት የምታሳዝን ልጅ ናት ዉበትዋን እንደምታየዉ
ቆንጆ ናት ቤተሰቦቿም ከተማዉ ዉስጥ በንግድ ስራ ።የታወቁ ከበርቴወች ናቸዉ "
ፍቃዱ አየር እየሳበ ማዉራቱን ቀጠለ
"ለቤተሰቧ ሁለተኛ ልጅ ስትሆን አንድ ታላቅ እህት አላት
እኔ እስከማዉቀዉ የታወቀ ሳይኸኮሎጂስት ጋር
ህክምና ስታረግ እንደነበር ከዚህ ቀደም አብራት ከምትማር
ተማሪ ጋር ተጣልታ ወላጅ አምጪ ብለናት
ከወላጆችዋ እንደሰማሁት ከሆነ ካደገች በሆላ
በምን እንደጀመራት በማይታወቅ የአይምሮ መታወክ
እና የስሜት መለዋወጥ እንዳለባት
እንደ ተስተካከለች ነግረዉን እና ከሀኪሙ የተሰጠ
ወረቀትም አሳይተዉ ነዉ ትምህርትም የጀመረችዉ
እና በሀሪዋ እንደምታየዉ ለየት ያለ ነዉ ከዚህ በላይ አላዉቅም"
ብሎት ወደ ሌላ እርዕስ ገባ።
ፍፁም ባላወቀዉ ታሪኳ በሰዉ ወሬ ብቻ ቤዛዊትን ማራቅ አልፈለገም እንደዉም ስለስዋ በሰማ ቁጥር
ቀስ በቀስ ፍቅሩ እየጨመረበት ነዉ።
ቁጭ ባለበት የቤዛ መልክ አይምሮዉ ላይ ታየዉ
ፊትዋ አነስ ያለ የቆንጆ ህፃን ልጅ መልክ ነዉ
ፊትዋ ላይ ጠዋት ስትናደድ ካየዉ አስተያየት ዉጪ
ፈገግታ አይለያትም ስትስቅ በሁለቱም ጉንጯ
ጎርጎድ የሚሉ የዉበት ማድመቅያወች የብይ ጉሬ የሚመስሉ ይታያሉ
ከንፈርዋ ጎበዝ ሰዓሊ የሳላቸዉ ነዉ የሚመስሉት
ጥርሷቿ ንጣታቸዉ ብርሀን የማንፀባረቅ ሀይል አሏቸዉ
ቁመቷ በጣም እረጅም ባትባልም ከሱ ቁመት ብዙም አታጥርም
ሰዉነትዋ ሞላ ያለ ነዉ በየመንገዲ አብረዉ ሲመጡ
አንገቱን እያዞረ ሲያያት የነበረ ብዙ ሰዉን ተመልክቷል
ይህን እያሰበ ምንም ይፈጠር ከጎንዋ ሆኜ የሚመጣዉን በፀጋ እቀበላለሁ ሲል ለራሱ ቃል ገባ።

ፍቅር የሰዉን ችግር አይቶ አይርቅም ይረዳል እንጂ
ፍቅር በሰዉ ህመም አይስቅም ያስታምማል እንጂ
ፍፁም ከተቀጣጠሩበት ቦታ ቆማ ከጠበቀችዉ
የቤቱ መግቢያ በር ፊት ለፊትተ ቆሞ እየጠበቃት ነዉ።
ሰዓቱን አስሬ ያያል ቀረችበት መንቆራጠጥ ጀመረ
አጠገቡ የሚገኝ ድንጋይ ላይ ቁጭ አለ
ቤዛዊትን መዉደዱ እርግጥ መሆኑ አሁን ገባዉ
"ምን ሆና ይሆን የቀረችዉ "
እያለ መጨነቅ ጀመረ ሰአቱን ሲመለከት እየመሸ ነዉ
ብዙ ተቀምጦ ከተጨነቀ በኃላ እያሰበ እና እያዘነ ወደ ቤቱ ገባ።
ቤት ገብቶ መፅሀፍ ለማንበብ ገፅ እየገለጠ የቤቱ በር ተንኳኳ
የቤት ኪራይ ለካ ደርሷል እረስቼዉ እያለ ኪሱ ዉስጥ
ያሉትን ብሮች ለአከራዩ ለመክፈል እየቆጠረ በሩን ከፈተዉ።
ቤዛዊት ፊትዋ በእንባ እረጥቦ ፊት ለፊቱ ቆማለች
"ምን ሆነሽ ነዉ የምታለቅሽዉ"
እየተንተባተበ ጠየቃት
መልስ ሳትሰጠዉ ገፍትራዉ እንደራስዋ ቤት ወደ ዉስጥ ገባች
እና የሱ አልጋ ላይ ቁጭ አለች።
ምን እንደሆነች ለመስማት አጠገቡዋ ተቀምጦ አቀፋት
"አትነግሪኝም ቤዚ"
"ከቤት አንተ ጋር ልመጣ ስል አትወጪም ብለዉኝ ተጣልቼ
አሁን እራሱ ተደብቄ ጠፍቼ ነዉ የመጣሁት ቀጠሮህን ለማክበር"
ስታወራ አሁንም እንባዋ እየፈሰሰ ስለሆነ የእሱም አንጀት አልቻለም
በሀዘን ተላወሰ በሁለቱም እጇቹ ጉንጯቿን
አቁዋርጠዉ የሚፈሱትን የእንባ ዘለላወቿን እየጠረገ
አባ'በላት ወድያዉ ማልቀስዋን አቁማ
"ናፍቀሀኝ ነበር"
አለችዉ
ከአልጋዉ ተነስቶ ዉሀ እንድትጠጣ እየሰጣት
"እንዴት በጥቂት ቀን ወደድሽኝ"
አላት አይኖችዋን በፍቅር እያያቸዉ
"ገና መጀመርያ ትምህርት ቤት በር ጋ ቆመክ ነዉ
አይኔን የሳብከዉ ልቤን ደሞ..."
አለችና ሳትጨርሰዉ ሳቀች አጠገቧ ቁጭ ብሎ አሱም ሳቀ
ትንሽ የሆድ የሆዳቸዉን ካወሩ በኃላ ሰዓቱን ሲያይ በጣም
እየመሸ ስለሆነ የእስዋ ቤተሰቦች እንዳይጨነቁ በማሰብ
ፍፁም እንዉጣ ብሏት እጅ ለእጅ ተያይዘዉ ሊሸኛት ወጡ።
መንገዱ ጨለም ያለ ስለነበር ትከሻዋን በእጆቹ አቀፋቸዉ
የየሷም እጇች ወገቡን አቅፈዉት እያወሩ ወደሷ ቤት አመሩ
ቤቷ በር ጋር ደርሰዉ መለያየት ከብዷቸዉ እየተያዩ
የእነ ቤዛዊት ቤት በር ተከፍቶ የቤዛዊት አባት ወጥተዉ
አይናቸዉን በቤዛዊት እና ፍፁም ላይ ተከሉት።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍3
አትሮኖስ pinned «#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #በክፍለማርያም ....መግለጥ ጀመረ..ወረቀቱ ላይ በጥቁር እስኪርቢቶ የተሳለ የልብ ቅርፅ ምልክት ይታያል መሀሉ ላይ ልቡን አቁዋርጦ የሚያልፍ የጦር ምልክት በቀይ እስኪርቢቶ የተንጠባጠበ የሚመስል የሚፈስ ደም የሚመስል ነጠብጣብ ጨምራበታለች ወደታች ማየቱን ሲቀጥል በትልቁ የተፃፈ "ልቤን ሰጥቼሀለዉ አትጉዳኝ" ፍፁም ደነገጠ "ምን አስባነዉ" ገና ተዋወቅን…»
#አራዳ_ላይ_ብቻ

ሰባ ነገስታትን ፥ ሲያስጨንቅ የነበር
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ
“ፒያሳ" በሚሏት ፥ በአራዶች ሀገር
የቢራ ቆርኪ ላይ ፥ ምስሉ ታትሞ
የጠርሙስ ልብ ላይ
ድራጎኑን ሲገል ፥ እያየሁት ቆሞ
“አራዳነት ማለት
አፅድቆ ማርከስ ነው” ፥ እላለሁ ባ'ርምሞ፡፡
ደግሞ
ደግሞ
ደግሞ
እዛው አራዳ ላይ
ፒያሳ አደባባይ
ሚሔድ የሚመስል ፥ የማይሔድ ፈረሱ
ሁሌ እዛው ቦታ….
ስሔድ የማላጣው ፥ ሚኒሊክ ንጉሡ
ሀውልቱ ታትሞ
ከፈረሱ ጋራ ፥ እያየሁት ቆሞ
“አራዳነት ማለት
“ሲሔዱ መቆም ነው” ፥ እላለሁ ባ'ርምሞ።
ደግሞ
ደግሞ
ደግሞ
እዛው አራዳ ላይ
ፒያሳ ላይ ያለ ፥ ሌላው አደባባይ
ነቅለው የተከሉት ፥ የእምነት አቡኑ
“አትገዙ” ብሎ!
ገዝቶን ያለፈ ፥ ጴጥሮስ ካህኑ
በሰንሰለት ታስሮ
ከመትረየስ ጋራ ፥ እያየሁት ቆሞ
“አራዳነት ማለት…
ፈቺውን ማሰር ነው” ; እላለሁ ባ'ርምሞ፡፡

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ስድስት


#በክፍለማርያም

...አይናቸዉን ቤዛዊት እና ፍፁም ላይ ተከሉት ፍፁም አባትዋ እንደሆኑ ደመ-ነብሱ ነግሮታል
ልቡ ትንሽ መምታት ጀምራለች አቅም አጊንቶ ቢሮጥ
ደስተኛ ነበር እንዴት
"በሯ ድረስ አብሬያት መጣሁ ከመጣሁስ
ለምን እስዋን አስገብቼ አልተመለስኩም"
እያለ እራሱን እየወቀሰ ደርቆ ቀረ።

ቤዛዊት አባትዋን ስታይ ምንም አልመሰላትም
እንደዉም እንደሌሉ ቆጥራቸዉ ፍፁምን ለከንፈሩ የቀረበ ቦታ ስማዉ
"ደህና እደር"
ብላዉ አባትዋን ከቁብ ሳትቆጥር ገፍትራቸዉ ወደ ቤትዋ ገባች።
ፍፁም ከቆመበት ወደ ቤቱ ለመመለስ ጥቂት እንደተራመደ
ኮቴ ስለሰማ አንገቱን በቀስታ አዞረዉ የቤዛዊት አባት
በራቸዉን ዘጋ አርገዉ እየተጠጉት ነዉ።

"ስማ ማነህ አንዴ ቁም"
ድምፃቸዉ እንደ አካላቸዉ ወፈር ያለ ነዉ ያስፈራል።
"እንዴት ብትደፍረኝ ነዉ ልጄን ከቤትዋ አስጠፍተህ
ወዳንተ ማምጣትህ ሳያንስ ቤቴ በር ጋ የምትስማት ውሻ ይመስል"
ቀጠሉ ማዉራት
"ማን እንደሆንኩ አላወከኝም የማንም ወጠጤ
መቀለጃ አደለሁም"
እያሉ ፊቱን በአትኩሮት አዩት።
እሱም ፍርሀት እና የወንድነት ወኔ እየታገለዉ አያቸዉ
አባትዋ ወፍራም አጠር ያሉ ሲሆኑ ሆዳቸዉ በምቾት
ከሰዉነታቸዉ ገዝፎ ይታያል ፀጉራቸዉ ሉጫ ሲሆን
ዉበታቸዉ እሱ ብቻ ነዉ።
አይናቸዉ ድፍርስርስ ያለ ነዉ ያስፈራል
የአፍንጫቸዉ ስፋት የከንፈራቸዉ ዉፍረት
የጥርሳቸዉ መበለዝ ከጉንጫቸዉ እና ከአካላቸዉ
ዉፍረት ጋር የሚያስፈራ ነገር ግን ግርማ ሞገስም አላቸዉ።
በጣም ተጠግተዉ ካዩት በኃላ
"ዉርጋጥ ሁለተኛ ከልጄ ጋር እንዳላይህ"
ብለዉ የለበሱትን ገዋን በግራ እጃቸዉ ገለጥ አርገዉ
ለሱ ያልታየዉን ነገር ለማሳየት ሞክረዉ መልሰዉ እያስተካከሉት
እየተበሳጩ ጥለዉት ወደቤታቸዉ ገቡ።
ፍፁም ቤቱ ገብቶ ማንበብ አልቻለም ተቁነጠነጠ
የሚያረገዉ ሲጠፋዉ አልጋዉ ላይ በጀርባዉ ተዘረረ።
አባትዋ ያሉትን ነገር በንዴት ማብሰልሰል ጀመረ
እኔን ዉርጋጥ ለነገሩ ዱርዬ መስያቸዉ ይሆናል
ሁሉም አባት ለልጁ ጥሩ ሰዉ ነዉ የሚመርጠዉ
እያለ እያሰበ ገልጠዉ ያሳዩት ነገር አሁን ታየዉ
የቤዛዊት አባት በግራ ታፋቸዉ ሽጉጥ ይዘዉ ነበር።
ፍርሀት ወድያዉ ወረረዉ
ስለ ቤዛዊት ግልፅነት የዋህነት እና ፍቅር ሲያስብ ግን
ቀስ እያለ ፍርሀቱ እየለቀቀዉ ልቡ በድፍረት ወኔ ተሞላ
ወድጃታለሁ ወዳኛለች ከኔ እና ከእስዋ ዉጪ የሚያገባዉ
ማንም የለም ብሎ እየተገላበጠ እንቅልፍ አሸለበዉ።
ጠዋት የትምህት ጊቢዉ ዉስጥ ገብቶ
ቤዛዊትን አይንዋን ለማየት እያሰበ ክፍለ ጊዜዉ ሳይደርስ
ወደ እነቤዛዊት ክፍል ገብቶ አየት አርጎት ሌሎች
ተማሪወችም ሲያፈጡበት
"ይቅርታ ለካ ክፍለጊዜዬ አደለም "
ብሎ ሲወጣ
ቤዛዊት እና ጉዋደኛዋ ትዕግሥት ተያይዘዉ ወጡ
አጠገቡ ደርሰዉ ቤዛዊት በቅፅበት ጉንጩን ስማዉ
"ተዋወቃት ትዕግሥት ትባላለች ጉዋደኛዩ ናት"
አለችዉ ቤዛዊት ወደ ጉዋደኛዋ እያሳየችዉ።
በልቡ እኔም ላያት መሄድ አልነበረብኝም
እስዋም እኔን ትምህርት ቤት ዉስጥ ልትስመኝ አይገባም
ደሞ ለጉዋደኛዋ ስለኔ እና ስለእስዋ ማን ንገሪ አላት
እንዴት አታገናዝብም እያለ በጣም እየተናደደ
የተዘረጋዉን የትዕግስት እጅ ጨብጦ ወደ ቢሮዉ አመራ።
ቢሮዉ ሊደርስ ጥቂት እርምጃ ሲቀረዉ ወፍራም አጠር ያሉ ሰዉዬ
አብሯቸዉ ጠብደል ያለ ወጣት ከጎናቸዉ በተጠንቀቅ ቆሞ
ከመምህር ፍቃዱ ቆመዉ እያወሩ ነዉ ።
እንደመደበቅ እየቃጣዉ ጥጉን ያዘ የሚያያቸዉ
የቤዛዊትን አባት መሆኑን እየተጠራጠረ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
አትሮኖስ pinned «#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ ፡ #ክፍል_ስድስት ፡ ፡ #በክፍለማርያም ...አይናቸዉን ቤዛዊት እና ፍፁም ላይ ተከሉት ፍፁም አባትዋ እንደሆኑ ደመ-ነብሱ ነግሮታል ልቡ ትንሽ መምታት ጀምራለች አቅም አጊንቶ ቢሮጥ ደስተኛ ነበር እንዴት "በሯ ድረስ አብሬያት መጣሁ ከመጣሁስ ለምን እስዋን አስገብቼ አልተመለስኩም" እያለ እራሱን እየወቀሰ ደርቆ ቀረ። ቤዛዊት አባትዋን ስታይ ምንም አልመሰላትም እንደዉም እንደሌሉ…»
#የትውልዴ_ድርሳን - 2

ለየመፈክሩ - እንደወነጨፈ፤
ለየነጋሪቱ - እንደተሰለፈ ፤
ባንዲራ ሲያዳውር - ባንዲራ ሲፈትል፤
ባንዲራ አውርዶ - ባንድራ ሲሰቅል ፤
ሰንደቁን ታቅፎ፣ ከጎጡ ጫፍ ሰቅሎ ፤
የሌላውን ሰንደቅ፣ እረግጦ - አቀጣጥሎ ፤
እንደተቆላ ዘር - በየወደቀበት እየበሰበሰ፣ ማጎንቆል ተስኖት፣
ፍሬውን ሳይተካ፤
አያጸድቅ - አያድን፣ የንፉግ ድርጎውን - መብቱን ሲያለካካ ፤
በ‹‹እኔ ይበልጥ ፣ የ«እኔ ይበልጥ እየተፋጠጠ ፤
በገዢው መዳፍ ላይ፣ ሙዝ ሆኖ ተላጠ፡፡

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘

ጥቅንት፣ 2012 ፤
#የትውልዱ_ድርሳን - 3

ቀረርቶው ጥላቻ ፣
ፉከራው ጭካኔ፣ ሽለላው ድንፋታ፤
መንፈሱ የታሰረ፣ አካሉ የተፈታ::
ልቦናን አስሮ፣ ለወስፋቱ ፈራጅ ፣
የገዛ ወንድሙን ፣ እንደሙክት አራጅ::
ፍቅሩ ያንዳፍታ፣
ህብረቱ ያንዳፍታ፣ የሳፋ ላይ ብቅል፤
መጽኛ ስር የነሳው ፣ መለምላሚያ ቅጠል፡፡

እድሩ የፈረሰ፣
አሟሟቱ ምጸት፣ መሾ ያነወረው ፤
በቁሙ የሞታ፣ ቀባሪ የቸገረው ፤
በጅምላ አሳቢ፣
በመንጋ ተዋጊ፣
የ'ራሱ ባላንጣ፣ ተስፋ የቆረጠ ፤
ሰብኣዊ ሚዛኑን፣ ለጎሳው የሸጠ፡፡

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘

የካቲት፣ 2011፣ አዲስ አበባ፡፡
#የተከፈተ_በር

የቤታችን በሩ፣
ከፍተሽው እንደሄድሽ፣ ዛሬም አልተዘጋም
የነበረኝ የለም፣ ለቀማኛ አልሰጋም
እምቢ ካልሽ እምቢ ነው፣ ፅኑ ነው ያንች ቃል
እንደማትመለሽ፣ አእምሮየ ያውቃል።

ግን አልፈርድበትም፣ ልቤ ቢያመነታ
ምኞት በሞላው ቤት፣ እውቀት የለው ቦታ።
ተስፋ አይቆርጥም ደግሞ
ልቤ ህልሙን ያምናል
ይለኛል ደጋግሞ፣
“ትመለስ ይሆናል
ትመለስ ይሆናል
ትመለስ ይሆናል።”

እኔም በምላሹ፣ ልቤን ፊት ሳልሰጠው
እንዲህ እለዋለሁ፣ ተስፋ ላስቆርጠው
“ጠጠር ላይቀቀል፣ አልማዝ ላይከለስ
በደመና ራስጌ፣ ጎጆ ላይቀለስ
እኔም አልሻሻል፣ እሷም ኣትመለስ።

ሰማይ ሰም ይመስል፣ ሲንጠባጠብ ቀልጦ
የረር ፈልሶ ቢሸሽ፣ ቢከተል እንጦጦ
ባሕሮች ቢከስሙ፣ ምድር ብትናወጥ
እሷም አትመለስ፣ እኔም አልለወጥ።

በዙሪያየ ያለው ጸጋ ብዙ ነበር
ግና ክንፍ አብቅሎ
ፍቅርሽ ጥሎኝ ሲበር
ከኔ ጋር የቀረው
የተቆለፈ ልብ፣ የተከፈተ በር።

🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘