አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አውቃለሁ_አታውቂም

ስላለፈው ዘመን
መርሳት የተሳነው መከረኛ ልቤን
ባንቺነትሽ ጥጋት
ሴት እየመዘነ የከሰረው ቀልቤን

ያለመሆን ህመም
በመሆንሽ ላይድን ሰርክ እንደባዘነ
በአመታት ስሌት
ከስቃዩ ሳይሽር መንፈሴ እንዳዘነ

አውቃለሁ አታውቂም
አለማወቅ ጠቅሞሽ ላየወጠቅመኝ ማወቄን
ሳታውቂ ባወኩት
የመታመን ብሶት እኔ መሳቀቄን፡፡

ግን እንዴት ላገግም
የህመሜ ምክንያት ሆኖ መዳኒቱ
ስቃዩ በዛብኝ
ልችለው አልቻልኩም ግራ ገባኝ እቱ፡፡

ለዛ ነው ሁል ጊዜ
የጀመርኩት መንገድ ደርሶ ላያደርሰኝ
በዛሬው ዓለሜ
ነገን ብናፍቅም አምና እየታወሰኝ
መኖር የታከተ
ሰቀቀናም ልቤ መሞቻውን ናፍቆ
አመታት ያለፉት
በመኖር እሳቤ ከመሞት እርቆ፡፡
1👍1
#አውቃለሁ_አታውቂም!

ክንፉ የተሰበረ፣ የታከተው መንፈስ፣
እንደ ክረምት ስማይ ፣ በእጦት ብልጭታ፣ ሲታረስ፣
.............................ሲመታ፣
ልብሽ ጽኑ ድጋፍ፣ እንዳጠነከረኝ፤
ፍቅርሽ አዲስ ምእራፍ፣ ገልቦ እንዳስጀመረኝ!
ታውቂለሽ?! ..

ድፍን ባል ለሊት፣
የብርሀን ሸማ፤
ጭር ባላ ውድቅት፣
ያሬዳዊ ዜማ፤
መሆንሽን
..............ታውቂያለሽ?!
አውቃለሁ አታውቂም!

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘

የካቲት፣ 2011፤ አዲስ አበባ፡፡