#ያው_እንደኛው_ናቸው
በሰማይ አዋፋት፣ አይዘሩም አያጭዱም
አገር አቆራርጠው፣ ሲራራ አይነግዱም
ግን ከኛ ኑሮ ምን ልዩ አረጋቸው?
ለእፍኝ እድሜ ሲባል፣ የሳር ጎጆ ማልማት
ሞላሁ ለማይል ሆድ፣ እህል በመሻማት
ያው እንደኛው ናቸው።
ያለም ከበርቴዎች
በፈጣን ጀታቸው፤ ሰማዩን ቢገምሱም
ርካታ ካለበት፣ ቀድመውን አይደርሱም
ሻርክ ተፈናጠው፣ ከባህር ቢጠልቁም
መንኰራኩር ጋልበው፣ ከጠፈር ቢመጥቁም
እኛን ከሚያሰጋን፣ አንድ ርምጃ እይርቁም።
የምድሪቱ ጌቶች
ለሰው ዐይን ሞልተው
ትልልቅ ቢመስሉም፣
በኩራት ተነፍተው
ተራራ ቢያከሉም፣
ከተሸከሸኩ፣ አንድ እፍኝ አይሞሉም።
ፍትወትና ፍራት፣ የሚጎትታቸው
ያው እንደኛው ናቸው፣
ባለስትንፋስ ሁላ፣ ቢታይ ተመንዝሮ
በቁመት አይበልጥም፣ ጎልያድ ከስንዝሮ
ለየቅል መሳዩ፣ ያው ነው ዞሮ ዞሮ።
በሰማይ አዋፋት፣ አይዘሩም አያጭዱም
አገር አቆራርጠው፣ ሲራራ አይነግዱም
ግን ከኛ ኑሮ ምን ልዩ አረጋቸው?
ለእፍኝ እድሜ ሲባል፣ የሳር ጎጆ ማልማት
ሞላሁ ለማይል ሆድ፣ እህል በመሻማት
ያው እንደኛው ናቸው።
ያለም ከበርቴዎች
በፈጣን ጀታቸው፤ ሰማዩን ቢገምሱም
ርካታ ካለበት፣ ቀድመውን አይደርሱም
ሻርክ ተፈናጠው፣ ከባህር ቢጠልቁም
መንኰራኩር ጋልበው፣ ከጠፈር ቢመጥቁም
እኛን ከሚያሰጋን፣ አንድ ርምጃ እይርቁም።
የምድሪቱ ጌቶች
ለሰው ዐይን ሞልተው
ትልልቅ ቢመስሉም፣
በኩራት ተነፍተው
ተራራ ቢያከሉም፣
ከተሸከሸኩ፣ አንድ እፍኝ አይሞሉም።
ፍትወትና ፍራት፣ የሚጎትታቸው
ያው እንደኛው ናቸው፣
ባለስትንፋስ ሁላ፣ ቢታይ ተመንዝሮ
በቁመት አይበልጥም፣ ጎልያድ ከስንዝሮ
ለየቅል መሳዩ፣ ያው ነው ዞሮ ዞሮ።
#ቀላውጦ_ማስመለስ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
"እኔ ገንዘብሽን አልፈልገውም፡፡ ለምትፈልጊው ሰው ስጪው።ለኔ ግን ለጥያቄዎቼ መልስ ስጪኝ፡፡ ያኔ በመጨረሻ የእናትነት ፍቅርሽን ያለስስት እንደቸርሽኝ በልቤ እፅፍልሻለሁ።" አልኳት የተቃጠለ ውስጤን እና የሚለበልብ ትንፋሼን ለመደበቅ በለዘበ
አነጋገር። ከእርሷ ጠብታ ፍቅር እንደማላገኝ ገብቶኛል፡፡ ቢያንስ ግን ጭንቅላቴ ውስጥ የሚርመሰመሱ
ጥያቄዎቼን እንድትመልስልኝ ተስፋ አደረግኩ፡፡ በስልችት ከንፈሯን ወደጎን
ከፈት አድርጋ አሽሟጠጠች።
"አባቴ ማነው? ከማን ነው የወለድሽኝ?"
“ሰይጣን ነው። አባትሽ ጭራቅ ነው::" ተመሳሳይ መልስ ከዚህ በፊትም መልሳልኛለች። ከሰይጣንነቱ፣ ከጭራቅነቱ ያለፈ አታብራራልኝም። የገባኝ ነገር አባቴ ማንም ይሁን ማን
በድሏታል፡፡ በምሬት ትጠላዋለች።
"እሱ ለበደለሽ በደል ለምን እኔን አስከፈልሽኝ? ለምን ከዳሽኝ?
እኔ ምን በበደልኩሽ ነው የበቀል ጅራፍሽን እኔ ላይ ያጮህሽው?"
ድምፄ እየጨመረ ሲሄድ ጥያቄዎቼ የማይረቡ እንደሆኑ ሁሉ ፊቷ በንቀት ሲሸረድደኝ ዘለሽ ተከመሪባት የሚል ስሜት ተፈታተነኝ።
"ለማንም የማይበጁ ጥያቄዎችሽን.. ብላ እስክትጨርስ መታገስ አቅቶኝ አዞረኝ፡፡ አነቅኳት፡፡ የእጄ ፍጥነት ከቁጥጥሬ
ውጪ ነበረ።
"ከቋጥኝ የከበደ በደልሽን ለመቻሌ ቢያንስ መልስ ይገባኛል፡፡መልሺልኝ፡፡ መልሺልኝ አባቴ ማን ነው?" እጆቼ አንገቷ ዙሪያ ሲከሩ የፊቷ ደምስሮች ተወጣጠሩ።
አላውቀውም።" አለችኝ ከእጄ ለማምለጥ እየሞከረች፡፡ እውነቷን
አው ያለችኝ፡፡ እውነቷን መሆኑን ለማወቅ ዓይኗ እና ድምፀቷ በቂ ነበር፡፡ ሴትየዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከውስጧ ስታወራ
ሰማኋት። አላውቀውም።በሚለው ቃሏ ውስጥ ምስጢራት እንደታጨቁ ሁሉ በመላው ሰውነቴ ፊደሎቹ ተሰራጩ፡፡ በሩ
ተከፍቶ ሰው ገባ፡፡ ካላወቀችው ሰይጣን ነው የምትለኝ ማንን እንደሆነ ልጠይቃት
ምላሴ ጫፍ ላይ ቃላቶቹ አንገዋልላቸዋለሁ።ለመተንፈስ ስትንፈራገጥ ነው ያደረግኩት የገባኝ ግርግር ተፈጥሮ ሁከት ደራ።ክፍሉ መሀል ተገትሬ ዘመዷቿ የመሰሉኝ ሰዎች ሲጯጯሁ እሰማለሁ እየደነፉብኝም ይመስለኛል ፖሊስ ሊጠሩም ሲንደፋደፉ፡፡
ከደራው ብጥብጥ አይሎ ጆሮዬ በአንድ ድምፅ ተደፍኗል።
አላውቀውም ሌላ ድምፆች የሚሾልኩበት ቀዳዳ የለም።የአክስቴ የስድብ ናዳዎች ሾልከው ሊገቡ ሲገፋፉ በተደፈነው ጆሮዬ የሚሰርጉ ፊደላትን ስገጣጥም ስድብ ወይ እርግማን
መሆኑን እጠረጥራለሁ።እየገፈታተሩ ከተኛችበት ክፍል ሲያስወጡኝም የሚሉትን አልሰማቸውም። በገፈታተሩኝ
ውክቢያ ፍጥነት እየተራመድኩ ከሆስፒታሉ ወጣሁ። መኪናዬን
ያቆምኩበትን ማስታወስ አልቻልኩም።
ቁልፉን በጣቴ እያሽከረከርኩ አራት እርምጃ በማትሞላ ቦታ ደጋግሜ በፈጣን
እርምጃ እመላለሳለሁ።መኪናዬን የቱጋ ነበር ያቆምኩት? ምንም እያሰብኩ አይደለም፡፡ ጭንቅላቴ ውስጥ የመቃብር ቦታ የመሰለ ረጭታ ነው የሚሰማኝ መኪናዬን ትቼ ለምን ታክሲ ተሳፈርኩ? ለታክሲ ነጂው በየትኛው ደቂቃ የቤቴን አድራሻ ነግሬው ነው ደጄ ላይ የጣለኝ? ምንም ቃል መተንፈሴን አላስታውስም።
መኪናሽስ?" ይለኛል ተፈሪ የአጥሩን በር እንደከፈተልኝ በሌባ ጣቴ እያሸከረከርኩት ያለሁትን የመኪና ቁልፍ እና ያመጣኝን
ታክሲ እያፈራረቀ እያየ። አልመለስኩለትም፡፡ የአጥሩ በር ቁልፍ
እጄ ላይ እያለ ለምን መጥሪያ ተጫንኩ? በቀጥታ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ።ልብሴን አውልቄ እዚያና እዚህ ወርውሬ መታጠቢያ ቤት ገባሁ:: በቁሜ ውሃው እላዬ ላይ ሲፈስ ምን ያህል
እንደቆየሁ እንጃ፡፡ ተፈሪ መኝታ ቤት ሲያወራ ይሰማኛል። ምን እንደሚል አልሰማውም፡፡ ለአስራ ስድስት
ዓመት በቆየ ትዳራችን በድምፁ ብቻ ሲፈልገኝ አውቀዋለሁ።በምንም ስሜት ሆነ በየትኛውም ሰዓት ልብሴን አውልቄ ካየኝ እንዲህ ያደርገዋል፡፡ ያን ድምፁን እጠላዋለሁ:: በክረምት የሚጮሁ ብዙ እንቁራሪቶች ፂፂስታ ይመስለኛል። እንደዛ
ሲያወራ ስሰማው ጆሮዬን ይበላኛል። በጣቴ ጆሮዬን ደጋግሜ እኮረኩራለሁ። እላዬ ላይ ሰፍሮ ላቡንና የወንዴ ፈሳሹን
እስካላንጠባጠበ እንደ ቆስለ ውሻ ማላዘኑን አያቆምም።ሙሉ ቀን የመሰለኝን ያህል ሰዓት ከውሃው ስር ቆሜ ብሰነብትም ተፈሪ ማላዘኑን አላቆመም።እየተንጎራደደ መሆኑን ድምፁ
የሚመጣበት አቅጣጫ ያስታውቃል። ፀጉሬና ገላዬ የተሸከመውን ውሃ እያራገፍኩ ወደ መኝታ ቤት መጣሁ። ቆሞ እየቀላወጠ ያየኛል። መጨቃጨቁ ልቤን ዝቅ ከማድረግ ያለፈ ፋይዳ እንደማይኖረው አውቃለሁ፡፡አይተወኝም:: መገላገል ነው አቋራጩ መንገድ፡፡ አልጋው ላይ እየተሳብኩ በጀርባዬ ተጋድሜ እግሬን ከፈትኩለት፡፡
አንዳንዴ ሳስበው እንኳን ትንፋሽ ኖሮኝ እየሰማ ሞቼ እግሬ ተከፍቶ ቢያገኘኝ በድኔ ላይ ሰፍሮ መወዛወዙን የሚያቆም
አይመስለኝም፡፡ እየገለፈጠ ልብሱን አወላልቆ ከላዬ ሆነ። ስልት የሌለው ውዝዋዜ ከቦርጩ እየታገለ ይወዛወዛል፡፡ በኮርኒሱ ላይ አምፓሉን ከምትዞር ትንኝ ጋር ዓይኖቼ አብረዋት ይዞራሉ።
ለአፍታ ዓይኔን ነቅዬ ስመለስ ወደኋላ ተመልሳ ይሁን ዞራ መጥታ በአምፓሉ ዙሪያ ከነበረችበት ወደ ኋላ መጥታ አገኛታለሁ እስካሁን አልጨረሰም ሰውነቴ ላይ የተንጠባጠበው ላቦቱ ሰውነቱና ሰውነቴ ሲነካካ የሲኦል ማስጠንቀቂያ ደወል የሚመስለኝን ድምፅ ይፈጥራል፣ ሰውነቴ በላቡ ሲጠባበቅ ላቡን የቀመስኩት ይመስል አፌን ጨው ጨው ይለኛል ሁሌም እንዲህ ነበርን።እሱ ተወዛዋዥ እኔ የውዝዋዜው መድረክ፡፡ አለቀ! አስራ ስድስት ዓመት። ዛሬ ግን
በተለየ ሰለቸኝ እንዲወርድልኝ ናፈቅኩ፡፡ መልሼ ዓይኖቼን ወደ አምፖሉ እልካለሁ። የምትዞረዋ ትንኝ የለችም:: ዙሯን ጨርሳ ወይም ሰልችቷት ሄዳለች።የእኔም መንገድ እንደትንኟ ይመርለኛል ዙር መዞር ፤ አንድን መንገድ እየደጋገሙ መርገጥ፡፡ ዓለም ራሷ ክብ አይደለች? ኑረትም እንደዛው መሰለኝ። አንድ ዒላማ ላይ መሽከርከር፡፡ ሽክርክሪቱ ያው ቢሆንም ሁሉም ሰው የሚሽከረከርበት መሃለኛ ነጥብ አለው።የታደሉት የሽክርክሪታቸው መሃለኛ ነጥብ ስህተት መሆኑ ሲገባቸው ወይም ሲሰለቻቸው አልያም ተስፋ ሲቆርጡ ዒላማቸውን ይቀይሩትና አዲስ ሽክርክሪት ይጀምራሉ።
ኡፍፍፍፍ እስካሁን አልጨረሰም? ዛሬ ደግሞ የላቦቱ ብዛት!
እናቴን ቀብሬያት ነው የመጣሁት!" ስለው ራሴን ሰማሁት።ውስጤ ወንድነቱ ሲሟሽሽ ተሰማኝ፡፡ አፍጦ እንደ እብድ እያየኝ ከላዬ ላይ ኩምሽሽ ብሎ ወደ ጎኔ ወደቀ።በስመአብ ወወልድ መቼ ሞተች? ለምን አልነገርሽኝም? እንሂድ እንዴት አትይኝም?"የጣር በሚመስል ቀሰስተኛ ድምፅ ጠየቀኝ፡፡
“ቅድም ሞተች፡፡ እናት የለኝም:: ቀብሬያታለሁ።” ስለው ግራ ተጋብቶ በድንዙዝ ስሜት ከተጋደመበት ተነሳ።
"መች ሞታ ነው? ቄሱ የመጡት የእናትሽን ሞት ሊያረዱሽ ነው? የት ነው የተቀበረችው?"
"እኔ ልብ ውስጥ!" ስለው ጤነኛ አልመስልኩትም። ብዙ ጥያቄ አከታትሎ ጠየቀኝ፡፡ አልመለስኩለትም፡፡ ጭራሹኑ ያልሰማሁት ይበልጣል፡፡ አወላልቆ እንደፍየል በጠጥ የበታተነውን ልብሱን
እየሰበሰበ ትቶኝ ወጣ፡፡ለምን ያህል ሰዓት
እንደዛው እንደተጋደምኩ ለማወቅ ብሞክር እሩቅ ሆነብኝ፡፡ አስባለሁ:: ምን
እንደማስብ ውሉን አልይዘውም:: ለራሴ እየደጋገምኩ "እናት የለኝም።አባቴም አይታወቅም::" እላለሁ። ቃሌን አላመንኩትም:: እደጋግማለሁ:: የአባቴን
ማንነት ማወቅ ያለመቻሌ በተወሰነ መልኩ እረፍት መሰለኝ፡፡ ሌላ ፍቅር ፍለጋ
መፋተጉ አቁሳይ ሊሆንብኝ ይችላል:: ፍፁም ሊገባኝ አልቻለም።እናቴ ስላልተቀበለችኝ ዓለም ሁላ ያልተቀበለኝ ርካሽ እንደሆንኩ እየተሰማኝ አንገቴን የምደፋው ለምን ይሆን? የሷ ጥላቻ የዓለም ሁሉ ጥላቻ ሆኖብኝ የተፈጥሮ ሁሉ

👍2
ልብ ጥላቻ እንዳቆረብኝ የሚታወቀኝ ለምንድነው? ፍጥረት ሁሉ ለሷ አሸብሽቦ
የማይፈልገኝ አላስፈላጊ ፍጡር መሆኔ በርትቶ የሚጠዘጥዘኝ እንዴት ይሆን?
እንድትሞትልኝ የምፈልገው ዘመዶቼ እና እራሷም ጭምር እንደሚያስቡት ስለምጠላት አይደለም፡፡ በተቃራኒው ነው።ስለምወዳት ነው:: ካለእርሷ ትርጉም ያለው ቀን ስለማልችል ነው፡፡ የሽክርክሪቴ መሀለኛ ነጥብ እሷ ናት።
የምስቅልቅሌ ሁሉ ቁልፍ እሷ ናት:: የጣዕም አልባ ውሎዬ ጨው የእሷ ፍቅር ነው:: በፍጥረት ሁሉ ላይ ለያዝኩት ቂም
ማስተሰርያ የእሷ እቅፍ ነው:: መኖር የምጀምረው እንደገና በፍቅሯ ስትወልደኝ ነው:: እሷ ግን በፍፁም ያን አታደርግም፡፡
በፍፁም!!! ዘመኗ በረዘመ ቁጥር እሷን መዞሬን አላቆምም፡፡
እሷም እንድጠላት ልቤን መቧጠጧን አታቆምም። በሰበረችኝ መጠን ራሴን ችዬ መቆም የማልችል ደካማ እሆናለሁ:: መደገፍ የምፈልገው ግን እሷኑ ይሆናል፡፡ ከእሷና ከመረረ ጥላቻዋ ውጪ እወድቃለሁ። ማነኝ? ከየት መጣሁ? የማን ዘር ርጭት ነኝ?
ካልፈለገችኝ ለምን ዘጠኝ ወር ሙሉ በሆዷ ተሸከመችኝ? ከምን ብፈጠር ነው አምጣ የወለደችኝን ልጇን ከነደሜ ጥላኝ የሄደችው?
💫ይቀጥላል💫
Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

👍1
#ቀላውጦ_ማስመለስ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሦስት
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
በእርግጥ እናቴ እሷ መሆኗን እስካወቅኩበት ቀን ድረስ እናትና አባቴ ሞተውብኝ ከሩቅ ሀገር አምጥተው የሚያሳድጉኝ ጥያቄ አልባ
ቀኖች የነበሩኝ ህፃን ነበርኩ:: አባባ የምለው አሳዳጊዬ እግዚአብሔርን በመፍራቱና በደግነቱ ትንሿ ያደግኩባት የገጠር ከተማ ድፍን ነዋሪ የመሰከረለት፣ ሚስቱ የምትኮራበት፣ ልጆቹ የሚመፃደቁበት፣ እኔን ጨምሮ ቤቱ የምንኖር አገልጋዮቹ የምንመካበት ሰው ነበር፡፡ በልጅነቴ ውስጥ ያለው አሳዳጊዬ ይህ ነው፡፡ የልጅነትን ቡረቃ ተሰናብቼ መብሰልና ህልም ማለም ስጀምር ለክብሩ እንጂ ለእኔ ግድ ከሌለው አያቴ ጋር ተዋወቅን፡፡በእርግጥ በቸርነታቸው ከሚያሳድጉኝ መልካም አሳዳጊዎቼን
ላሳዩኝ በጎነት በልቤ የማመሰግን፣ ለውለታቸው ክፍያ በአቅሜ
የማገለግል አገልጋያቸው እንጂ ለጎደለው
የማማርርበት መብትም ሆነ ይገባኛል የምለው አንዳች ያልነበረኝ ትንሽዬ ልጅ ነበርኩ። ቢቆጡኝ፣ ቢሰድቡኝ፣ ቢያንቋሽሹኝ ትምህርት፣ ቢሰድቡኝ ትምህርት እንድማር ሳይፈቅዱልኝ ከማንበብና መፃፍ የዘለለ ባላውቅም፣ እንደልጅ ለመጫወት ባይፈቅዱልኝ
መሄጃ የለሽ ወላጅ አልባ ህፃን ለሚያሳድጉ ደግ አሳዳጊዎቼልክ ነገር መሆኑ ነበር የሚገባኝ፡፡
በአስራ አራት ዓመቴ ገደማ ለአዲስ ዓመት መለወጫ በዓል ሁሉም ቤተሰብ ተሰብስቧል። አክስቴና እሷ ከአዲስ አበባ ነበር የመጡት:: ሴትነቴ ያበበበት ወቅት ነው።የሰፈራችን ጎረምሶች
በአጠገቤ ሲያልፉ ቂጤን ገፍተር፣ ያጎጠጎጠ ጡቴን ቆንጠር እያደረጉ ያሽኮረምሙኛል፡፡ አመሻሹን ከብቶች ከሜዳ ይዤ ስመለስ ችፍ ያለው የሰንሰል ተክል አጠገብ አዳነ ቆሟል። ጎትቶ
ወደራሱ አስጠጋኝ፡፡ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም:: ጡቴን እንዳስነካው ያባብለኛል። ብዙ አላስለምነውም:: ሲነካካኝ ደስ ስለሚለኝ እፈቅድለታለሁ።
"እረፍ አዳነ ቤት ሁሉም አሉ። እየጠበቁኝ ነው ልቀቀኝ" ብዬው ነበር አልሰማኝም። እንደሌላ ቀኑ አላባበለኝም:: ወደ ሰንሰሉ
ውስጥ ይዞኝ ገባ፡፡ ከላዬ የለበስኩትን ልብስ ወደ ላይ ሰብስቦ ጡቴን ሲነካካኝ የምከለክልበት አቅምም ምክንያትም ከዳኝ። ሳሩ ላይ አጋድሞኝ ጡቴን በአፉ ሙሉ እየጎረሰ ሲተፋው እያቃሰትኩ
ነበር። ድንገት አቁሞ ሲበረግግ የጨፈንኳቸውን ዓይኖቼን ገለጥኳቸው።ያየሁትን ደግሜ ላለማየት ዓይኖቼን ጨፈንኳቸው። መልሼ አጮልቄ አየሁ። ከተጋደምኩበት ሆኜ ሳየው ጋሼ (የአባባ ብቸኛ ወንድ ልጅ) ከሰማይ ላይ ተወርውሮ የተንጠለጠለ መስሎ ዓይኑን ጎልጎሎ አፍጥጦብናል። አዳነ ፓንቱ እስኪቀደድ እግሬ አውጪኝ ብሎ ሲሮጥ ጋሼ ማጅራቴን ጨምድዶ ይዞኝ ወደቤት ገባ። በቤቱ ጣራ ስር ያሉትን ሁሉ
በጩኸቱ ስብስቦ እንደ ክፉ ወንጀለኛ ፊትለፊታቸው አቆመኝ፡፡የት እንዳገኘኝ እና ምን ስሰራ እንደነበረ በሚዘገንን ፀያፍ ቃል ለሁሉም ተናግሮ እንዳበቃ ተራ በተራ የምላሳቸውን መርዝ ተፉት። እሷ ምንም አልተናገረችም።ዓይኖቿ ውስጥ የነበረው መፀየፍ ግን ከእነርሱ ስድብ በላይ ህመም ነበረው።የሚያውቁትን ስድብና ቁጣ ሁላ ጨርሰው ፀጥ ሲሉ ወደ ጎዳ ገባሁ።እሷም ሲጋራዋን ልታጨስ ወደ ውጪ ወጣች።ጋሼም ተከተላት።በጎሮ በር አድርጌ ወጣሁ።ልሰማቸው ፈልጌ ባይሆንም ሲጯጯሁ ይሰማኛል። የመደናቆራቸው መንስኤ እኔ መሆኔን ሳውቅ ጆሮዬን ጥዬ መስማት ጀመርኩ፡፡
እንቺ የወረወርሻትን ዲቃላ እድሜ ለአባቴ በይ አሳደግንልሽ፡፡ እሷ ይዛብን የምትመጣውን ዲቃላ ማን ሊሸከምልሽ ነው?ካንቺም ብሶ እንዳለማች ቆጥረሽ ዝም ትያታለሽ? ባንቺ ነው የወጣችው! ገና ቂጧን ሳትጠርግ በየሳሩ ትሸረሙጣለች፡፡ ከዚህ በኋላ እግሯን እየጠበቅኩ የከፈተችውን እግሯን አልገጥምም።ከፈለግሽ ወስደሽ የምታደርጊውን አድርጊያት:: " ከእውነታው እኩል የመረጣቸው ፀያፍ ቃላት አስደነገጡኝ፡፡ የሰማሁት
እውነት መሆኑን መቀበል አቃተኝ፡፡ እሷ አትመልስለትም።አጎቴ አንዴ እህቱን አንዴ እኔን እየሞለጨ ደቂቃዎች አለፉ፡፡
ደጋግሞ ከተናገረው እሷ እናቴ መሆኗን እና ለእነሱ ጥላኝ እንደሄደች ገባኝ፡፡
"እናቴ አንቺ ነሽ? አባባ አያቴ ነው?" አልኩኝ ተኮራርፈው ሳሎን እንደተቀመጡ ሁሉም ነብር እንዳየ ጥንቸል ዓይናቸው
ተጎልጉሎ ጆሮአቸው ቆመ።የመለሰልኝ የለም፡፡
ውጪ ያወራችሁትን እንዳለ ሰምቻለሁ::" አልኳቸው፡፡
እና የሰማሽ እንደው ምን ይሁን? እኔ እናትሽ አይደለሁም ስትለኝ እናቴ መሆኗን ስሰማ ተንሰራፍቶ የነበረውን
ብልጭታ ደስታ በተነችው:: አጠገቧ ተጠግቼ እጇን ስይዛት መንጭቃ ገፈተረችኝ፡፡ እናቴ መሆኗን ሳላውቅም በፊት ይዣት አውቃለሁ፡፡ እንደዚህ አስጠልቻት አይቻት አላውቅም፡፡ እነ አባባ ጋር የምትመጣው ከስንት
ዓመት አንዴ ቢሆንም የምትለብሳቸው ልብሶች፣ ሲጋራ አጫጫሷ፣ ቁመቷ፣ አካሄዷ...
ባየኋት ቁጥር እንደርሷ መሆን የምመኝላት ነበረች::ስትመጣ እንግዳ ሲመጣ እንደማደርገው እግሯን የማጥባት እኔ ነበርኩ፡፡ ከስንት ዓመት አንዴ ለአዲስ ዘመን መለወጫ ስትመጣ
አዲስ ልብስ እቤት ላለነው ሁሉ ስትገዛ ለእኔም ገዝታልኝ ታውቃለች:: እንደዛ ቀን በጥላቻ አመናጭቃኝ አታውቅም።
በእርግጥ የምትፈልገውን ነገር ልታዝዘኝ ካልሆነ በቀር በፍቅር ወይ በክብርም አናግራኝ ማወቋን አላስታውስም፡፡
በደስታ፣በተስፋ እና ግራ በመጋባት መሃል ዋለልኩ:: በጥያቄ መዓት ተበታተንኩ፡፡ ተራ በተራ አፍ አፌን ብለው አባረሩኝ፡፡
ዓይኗን እንኳን መልሼ ሳላየው ተመልሳ ወደ አዲስ አበባ ሄደች።
ባልገባኝ ምክንያት ከዚያን ቀን በኋላ ከአባባ በቀር ሁሉም ያመናጭቀኝ ጀመር። ለምን የስጋቸው ክፋይ መሆኔ
እንዳሳፈራቸው ግራ ተጋባሁ:: ምንስ ቢሆን ደግሞ የእኔ ጥፋት ምኑ ላይ ነው? ከቀናት በኋላ አባባን እያለቀስኩ እውነቱን
እንዲነግረኝ ጠየቅኩት። የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ሳለች ከሆነ ጎረምሳ ጋር ተጣልታ ከባድ ጉዳት ስላደረሰችበት አስር ወር ተፈርዶባት መታሰሯን ነገረኝ። ማንም የተፈጠረውን አያውቅም፡፡ ሊጠይቋት ሲመላለሱ ማናቸውንም ለማግኘት ፈቃደኛ አልነበረችም። ፍርዷን ጨርሳ ወደ ቤት ስትመለስ መንገድ ላይ ነበር ምጥ የጀመራት:: ማናቸውም ማርገዟን ሳያውቁ እቤት እንደደረሰች ወለደችኝ፡፡ አባቷ ወግ አጥባቂ እና
ክብሩን ወዳድ ስለነበረ ተዋረድኩ ብሎ ያዙዙኝ ልቀቁኝ አለ፡፡
(ይሄን ሲነግረኝ በቁጭት ነበር) አንዲትም ቀን አላደረችም፡፡ለማንም ምንም ሳትል ከነደሜ ጥላኝ ጠፋች:: ከቤተሰቦቿ ጋር
መልሳ ስትገናኝ አድጌ በእግሬ ድክ ድክ እል ነበር። ሁሉም በዲቃላነቴ ደስተኛ ስላልነበሩ እናቴ መሆኗን እንዳላውቅ
የሰጠችው ማስጠንቀቂያ ተስማማቸው:: አብዛኛዎቹ የቤት አገልጋዮች እንደሚጠሩት ከስሜ የማስከትለው የአባባን ስም ነው:: የእኔ መወለድ ሌላ ሴት እንድትሆን እንዳደረጋት አባባ ሲነግረኝ ለቤተሰቡም ሆነ ለእናቴ ክፉ እጣ እንደሆንኩ ደጋገመልኝ እናቴ እኔን ከመውለዷ በፊት ከወንድ ልጁ ይልቅ በራስ መተማመኗ የሚያስተማምነው፣ ጎበዝ ተማሪ ስለነበረች ቤት ተከራይቶላት ከተማ የሚያስተምራት መኩሪያው፣ ትልቅ
ቦታ ትደርስልኛለች ብሎ የሚመካበት የዓይኑ ማረፊያ፣ ማንም ደፋር ቀና ብሎ የማያያት ጉልበተኛ እና ደፋር እንደነበረች
በትካዜ ፊቱ ደብዝዞ አወራኝ፡፡ እኔን ከወለደች በኋላ ጠፍታ ስትመለስ የማያውቋት ሌላ ሴት ሆና መምጣቷን ጨመረልኝ፡፡
"አባባ አባቴ ማን ነው?" አልኩት:: ምናልባት አባቴ ልጁን በፍቅር ክንዱን ሊዘረጋልኝ ይችላል ብዬ እያሰብኩ፡፡
"አናውቀውም:: ከእርሷ ውጪ የሚያውቅ የለም:: ስለአንቺም ሆነ ስለአባትሽ ጥያቄ ሲነሳባት ጣረሞት እንዳየ ሰው
ትንፈራገጣለች::” አለኝ፡፡
አባባ ከነገረኝ ያልተሟላ ታሪክ

በመነሳት እናቴ የሴት ልጅ ዶክተር፣ ኢንጂነር፣ ሊቅ........ መሆን በሚደንቃት ትንሽዬ
መንደራቸው ከእኩዮቿ በተለየ ከህፃንነቷ ጀምሮ ዩንቨርስቲ ገብታ በማዕረግ የመመረቅ ህልም የነበራት የመንደሯ ፈርጥ ነበረች:: ህልሟን ለመጨበጥ መንገዷን ስታገባድድ እኔ በመንገዷ ገባሁ:: እኔን ለመውለድ ምን ዓይነት ስቃይ እንዳለፈች ከእሷና ከፈጣሪ ውጪ አውቃለሁ የሚል ባይኖርም ለእናቴ የሳቋ
ሞት፣ የተስፋዋ መቁረጥ፣ የብርታቷ መድቀቅ፣ ግብ አልባ መናኛ ሴት የመሆኗ ጅማሬ እኔ መሆኔ ገባኝ፡፡ እኔን ተጠያቂ የሚያደርገኝ ግን የትኛው ድርጊቴ ነው? ከአባባ ጋር ካወራሁ በኋላ የበፊቷን ራሴን መሆን አቃተኝ፡፡የሚያሳዩኝ ጠጠር ንቀት
ቋጥኝ ያክልብኛል። ከቤተሰብ እንደአንዷ ሊቆጥሩኝ ያለመቻላቸው እንደ ተራራ የገዘፈ ጥላቻ ይሆንብኛል። እየታየ
የመጣ ሴትነቴን ተከትሎ ከሰፈሩ ጎረምሳ ሁላ ጋር ባልዋልኩበት እያጋደሙኝ የሚለጥፉብኝ ፀያፍ ስድብ አንገቴን ወደ መሬት ቀለበሰው:ፈ። አባባጋ አዘውትሮ የሚመላለስ የቡና ነጋዴ ሊያገባኝ
ሲጠይቃቸው ሸክማቸውን እንደገላገላቸው ቆጥረው ሳይነግሩኝ ተስማሙ። ደስ ይበለኝ ወይ ልዘን ግድ
አልሰጣቸውም:: በራሴ ላይ እንኳን ስልጣን የሌለኝ መሆኔን ሲመሰክሩልኝ የጉዳዩዋ ባለቤት ሳላውቅ በእኔ ልዋጭ ከብትና ገንዘብ ተሰጣቸው። በተለመደ ቀኔ ውስጥ እቃ አድርሺ ተብዬ ያልተለመደ ትዕዛዝ ታዘዝኩ:: አንድ ቀን ከአባባ ጋር የሄድንበት የሰውየው ዘመዶች ቤት ነበር፡፡ ሰውየው ጋ በተላኩበት ይዞኝ ወደ አዲስ አበባ መጣ። ከማላውቀው ሰው ጋር አልተኛም
ባልኩኝ እንደጥጋበኛ ተቆጥሬ ጉንጩ በጥፊ ቀላ፡ ከተፈሪ ጋር መኖር በጀመርኩ በቀናት ውስጥ ጠፍቼ አባባ ጋር ተመለስኩ፡፡መጠለፌን ስነግራቸው ሳቁብኝ፡፡ በስሜቴ፣ በገላዬ፣ በወደፊቴ፣
በፍላጎቴ እነሱ ከጀርባዬ ተስማምተው መጨረሳቸውን የሰማሁት ይሄኔ ነበር።
የተሰበረ መንፈሴን መጠገኛ አጣሁ:: ይባስ ብሎ አቶ ተፈሪ ለአባባ ወቀሳ መላኩን ስሰማ ራሴን፣ ሴት መሆኔን፣ ሰው
መሆኔንም ጠላሁት፡፡የተበደልኩ እኔ የሚደራደሩት እነሱ።ያለፍላጎቴ እንደደፈረኝ ለአባባ ህመሜን በእንባ መንገሬ ለእሱ የካሳ ምንጩ መሆኑ ደግሞ የማይድን ድንዝና በልቤ ውስጥ
ረጨብኝ፡፡ ልጅነቴ ሳያሳሳው የፈነጨብኝ እኔ የሚካሱት ቤተሰቦቼ፣ የተበደልኩ እኔ አቤቱታው የሚሰማው የሱ፣የተሰበርኩ እኔ ስለደፈረኝ እኔ የምሸለመው ለሱ:: ለደንብ ያህል ሽማግሌ ተሰብስቦ በፈጣሪ ቃል፣በባህልና ወግ፣ በትህምክታቸው እና በእርባና ቢስነቴ እያመኻኙ በደሌን እንኳን ሳይሰሙ እኔው
ለተበደልኩ ይቅርታ መጠየቅ ግዴታዬ ሆነ፡፡ እናቴስ ልጇን የክዳችኝ ምንም ይሁን ምን ምክንያት ሊኖራት ይችላል ብዬ ላስብ ምናልባትም ክፉ ስለሆነች ነው ብዬም ልመን እንዴት ከቤተሰቤ ሁሉ ለለቅሶዬ ጆሮ የሚሰጥ አንድ አጣለሁ? እዚህኛው የጥያቄ ወለል ላይ ስቆም ነው የሽክርክሪቴ መሀለኛ ነጥብ እሷ መሆኗ የተገለጠልኝ፡፡........

#ምህረትህን_መልበሴን
"ባዝኖ! ባዝኖ! ባዝኖ!
ዋትቶ! ዋትቶ! ዋትቶ!
በጭጋጋማው ቀን
በደመናው ሞቶ
'ርቃኑን ተቀብሯል"
ብለው ያወራሉ
ም'ረትኸን መልበሴን
የማያውቁ ሁሉ።
"ባዝኖ! ባዝኖ! ባዝኖ!
ዋትቶ! ዋትቶ! ዋትቶ!
በጭጋጋማው ቀን
በደመናው ሞቶ
'ርቃኑን ተቀብሯል"
ብለው ያወራሉ
ም'ረትኸን መልበሴን
የማያውቁ ሁሉ።
#ቀላውጦ_ማስመለስ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራት
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
እኔ ለተበደልኩ ይቅርታ መጠየቅ ግዴታዬ ሆነ፡፡ እናቴስ ልጇን የክዳችኝ ምንም ይሁን ምን ምክንያት ሊኖራት ይችላል ብዬ ላስብ ምናልባትም ክፉ ስለሆነች ነው ብዬም ልመን እንዴት ከቤተሰቤ ሁሉ ለለቅሶዬ ጆሮ የሚሰጥ አንድ አጣለሁ? እዚህኛው የጥያቄ ወለል ላይ ስቆም ነው የሽክርክሪቴ መሀለኛ ነጥብ እሷ መሆኗ የተገለጠልኝ፡፡
የታየኝ ጭላንጭል ብልጭታ እናቴጋ መሄድ ነበር፡፡ እናቴ መሆኗ ባያራራት እንኳን ሴት መሆኗ ለስሜቴ ቅርብ
ያደርጋታል ብዬ አመንኩ፡፡ በግዳጅ ተመልሼ ከገባሁበት የተፈሪ ቤት ጠፍቼ እናቴን ለማግኘት ሻንጣዬን ይዤ ወጣሁ። የህይወቴ ሰንካላ ሽክርክሪት መጀመሪያው ይህ ጉዞዬ መሆኑ የገባኝ
ሰነባብቶ ነበር፡፡ ተደብቄ ከአጎቴ ማስታወሻ ደብተር ላይ የገለበጥኩት የቤቷ ስልክ ቁጥር ላይ ደወልኩ፡፡ የነፃነቴ ቁልፍ፣የምስቅልቅሌ ፍቺ፣ የኑረቴ አዲስ ምዕራፍ፣ ዳግም ውልደቴ እሷ መሆኗን እየቃዠሁ በጉጉት ተሰቅዤ አገኘኋት። ከቅዠቴ ለመንቃት ደቂቃዎች በቂ ነበሩ፡፡ ያገኘችኝ ቦታ ጥላኝ አልሄደችም:: ወደ ቤቷ ወሰደችኝ፡፡ ባሏና የእንጀራ ልጇ መሆናቸውን ከነገረችኝ ወንዶች ጋር የቅብጠት ኑሮ ነበር የምትኖረው። ያላቸው ትስስር ጥብቀት ምን ያህል የተገመደ መሆኑን ባላውቅም አብሯት በሚኖረው የእንጀራ ልጇ ቀናሁ።
ስለእናቴ ልጠይቀው ተመኘሁ። ግን እድሉን አላገኘሁም።በእርግጥ ልጇ መሆኔን ለአንዳቸውም መንገሯን
እጠራጠራለሁ።ልጁ አብሯቸው ቢኖርም ብቸኛ ይመስላል፡፡ቤታቸው ውስጥ ለጊዜው ትኩረት ልሰጠው ያልፈለግኩት የሆነ ልክ ያልሆነ ነገር እንዳለ ተሰምቶኛል፡፡
ምን ልታደርጊ መጣሽ?" ስትለኝ ፊቷ ላይ የነበረው መሸከክ ቢያስደነግጠኝም ምክንያቴን እስክነግራት ነው
ብዬ ራሴን አበረታሁ። የሆንኩትን ሁሉ ከዓይኔ የሚፈሰውን እንባና የአፍንጫዬን ንፍጥ በእጄ አይበሉባ እየሞዠቅኩ ነገርኳት።
"እና? እከክሽን እያከክሽ ከመኖር አይሻልሽም? ወይስ እድሜ ልክሽን በየአውድማው ከጎረምሳ ጋር እየተላፋሽ መኖር ነው የምትፈልጊው? ዝቀሽ የማትጨርሺው ሀብት ላይ ስለጣለሽ
ልታመሰግኚው ሲገባ አባቴን የምትኮንኚው ምን አድርግ ብለሽ
ነው?" ነበር ለለቅሶዬና ለብሶቴ መልሷ። ከዚህ በላይ ልትሰማኝ አንድ ደቂቃ አላባከነችም። በሚቀጥለው ቀን ተመልሼ ባሌ ያደረጉት ተፈሪጋ ለመሄድ እንድስናዳ ነገረችኝ፡፡
"እርሺው እኔ እስከዛሬ እናትሽ እንዳልነበርኩ ሁሉ ከዚህ በኋላም
እናትሽ ልሆን አልችልም።ሰበብ እየፈለግሽ ልታገኚኝ እንዳትሞክሪ።" የሚል ማስጠንቀቂያ አከለችበት። የተሰማኝ ስሜት አልነበረም።ምክንያቱም ደንዝዣለሁ። ከተቀመጥኩበት
ለመነሳት ሰውነቴ እንደወትሮው የሚታጠፍ የሚዘረጋ እስከማይመስለኝ በድኛለሁ። በጠዋት የቀሰቀሰችኝ የትራንስፖርት ገንዘብ ሰጥታኝ ከቤቷ ልታሰናብተኝ ነበር፡፡ለቀናት የማደርገውን ሁሉ የማደርገው አስቤ አልነበረም።
መላው አካሌ ከጭንቅላቴ ጋር እየተማከረ መንቀሳቀሱን እንጃ፡፡ ራሴን ከተፈሪ ጋር ያለኝን ኑሮ እያለማመድኩት አገኘሁት።ብቸኛው ፍቅርን ሊያሳየኝ የሚሞክር ፍጡር እሱ ነው።እውነቱን ነው ግን? እያልኩ አስባለሁ። ስለ ወለደችኝ ሴት ከማሰብ የላቀ የምሰራው የዛሬም ሆነ የነገ እቅድ ስላልነበረኝ እሱ የሚያቅድልኝን ውሎ እውላለሁ። መኪና መንዳት መማር፣የምግብ አሰራር ስልጠና ሙያ መሰልጠን፣ ከጓደኞቹ ሚስቶች
ጋር ተማክሮ ገዝቶ በሚያመጣልኝ ልብስና ጫማ ራሴን ለእርሱ ማስጌጥ፣ ፀጉሬን መሰራት እንዳለብኝ አሳስቦኝ በወጣ ቀን ጠዋት የራስ ቅሌን ለፀጉር ሰሪዎቹ እጅ መስጠት፣ ሊተኛኝ ፈልጎ ሲያላዝን በጀርባዬ ተጋድሜ እግሮቼን መክፈት፣በስራ ሰበብ ሲወሰልት ያደረ ቀን በጠዋት ገዝቶ የሚመጣው በግ መስራት.....(አይነግረኝም።አውቃለሁ።
እንደማውቅ ያውቃል።መፀፀቱን አያቆምም።መወስለቱንም እንደዛው። ከሌላ ሴት ጋር ማደሩን ማወቄ ግድ አይሰጠኝም ነበር፡፡ ምናልባት ለእርሱ ግድ ስለሌለኝ አልያም ለራሴ ግድ
ስለሌለኝ ወይ ደግሞ በሆነች የሀሳቤ ጥግ ሌላ ሴት ለመፈለጉ ምክንያት የራሴ መበደን መቀበሌ ይሆናል የዓመታት ባሌ ከሌላ ሴት ጋር በማደሩ ለሚሰማው ፀፀት ማስተሰሪያ የበግ ደም ማፍሰሱን መቀበሌ።)
በራሷ ጭንቅላት የምታስብ ሴት መሆኔ ጠፍቶ በተፈሪ ባወጣልኝ የእለት መመሪያ የምንቀሳቀስ ሮቦት ለመሆን የፈጀብኝ
ጥቂት ወራት ነው። ተፈሪ በስራው ምክንያት ከከተማ እስካልወጣ ድረስ ቀላል ግልፅ እና ተመሳሳይ የአስራ ስድስት ዓመት ውሎ...
የሚወደውን ምግብ ማብሰል፣ ሱቅ ወጥቶ የሚያስፈልግ ነገር መገዛዛት፣ እሱ እንድሆንለት የሚፈልጋትን ንፁህና ዘናጭ ሴት ሆኜ መጎለት፣ እላዬ ላይ ራቁቱን
እየተወዛወዘ መቼ ልጅ እንደምወልድለት ሲነዛነዝ መስማት፡፡
በራሴ ጭንቅላት የማደርገው ብቸኛ ነገር ለእናቴ ስልክ እየደወልኩ በስልኩ ሞገድ ድንዛዜን ማጨድ ብቻ ነው:: የተለየ
ነገር ከአፏ እንዲወጣ በመናፈቅ ሳልታክት ደውልላታለሁ።ከሚቆጠሩ ቃላት የዘለለ አታናግረኝም። ለምጠይቃት ጥያቄ
መልስ አትመልስልኝም። ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ባሏ ነኝ ያለ ሰውዬ በዚያ ስልክ እንደማላገኛት ነገረኝ፡፡ ደጋግሜ ብደውልም መልሱ ተመሳሳይ ነበር፡፡ የሆነ እለት እንደአበደ ሰው ተነስቼ
ቤቷ ሄድኩ፡፡ ከቤቷ ከወጣች መሰንበቷን ባሏ የነበረው ሰው እየተነጫነጨ ነገረኝ። የት መሆኗን ሊነግረኝ አልፈለገም ከብዙ ወራት በኋላ በተለመደ ውሎዬ መሃከል ያልተለመደ ስልክ ጥሪ አስተናገድኩ፡፡ አባባ ነበረ። ድምፁን ስሰማ እስከዛ ቀን ድረስ ደህንነቴ ወይ ምቾቴ ግድ ሰጥቶት ደውሉልኝ አለማወቁን እረስቼ ናፍቆቴን ገለፅኩለት: የአቧራ ብናኝ ያህል ግድ
አልሰጠውም:: የእናቴ ባል ስለሞተ ለቅሶ እንድደርስ ነገረኝ። ሟች ባሏ ድጋሚ እሷን ለማየት ምክንያት ስለሆነኝ መሞቱ
አስፈነደቀኝ፡፡ ከተፈሪ ጋር ለቅሶ ለመድረስ ሄድን፡፡ ዘመዶቼ ለቅሶውን የነገረኝ አባባን ጨምሮ ማንም ያለመምጣታቸው
አስገረመኝ፡፡ ድንኳኑ ውስጥ ለሟች ባሏ አምርራ ስታለቅስ ሳያት ድፍርስርስ ያለ ስሜት ተሰማኝ፡፡ ለባሏ ስትነፋረቅ ሳያት
ቅናት አነደደኝ፡፡ ለደንዳና ልቧ የሰጠሁት አንዱ ማስተባበያዬ ፉርሽ ሆነብኝ፡፡ ለአፍታ ተፈጥሮዋ ድንጋይነት እንደሆነ ሳምን መሰንበቴ ተሰረዞ ሌላ ነገር የገባኝ መሰለኝ፡፡ ሴትየዋ ከኔ ውጪ
ላለ ሰው ልቧ ስጋ እና ደም ነው ብዬ አሰብኩ፡፡ የሟች ልጅ ነው ያለችኝ ወጣት በአባቱ ሞት ያዘነ አይመስልም። እንደታዛቢ ለቀስተኛውን ይገረምማል:: አመሻሹን የለቅሶ ግርግር ሲበርድ
ጠብቄ ባገኘኋት ስንጣቂ አጋጣሚ ተጠቅሜ እያቀፍኳት ምን ያህል እንዳዘንኩ የልቧ በራፍ ያስጠጋኛል
ብዬ በተለማመድኳቸው ቃላት ነገርኳት። ለደቂቃ በእውነታ የሌለሁ የምቃዥ መሰለኝ፡፡ መልሳ አቅፋኝ አመሰገነችኝ፡፡ ካገባሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ከተፈሪ ጋር እንደቅርብ ሰው ስለእርሷ እቅፍ
ንዝረት አብራራሁለት:: ከድንኳኑ ይዤው ወጥቼ ስለእኔ የማያውቀውን ታሪክ በደስታ እየፈነደቅኩ ነገርኩት፡፡ በደሜ
የሚንቀለቀለው እሳት የገባው መሰለኝ:: ባይገባውም ግድ አልነበረኝም። እናቴ ባቀፈችኝ በዛች ደቂቃ ዓለም ቀጥ ብላ
የተፈጥሮ ዑደቶች “ሀ” ብለው አዲስ ቀመር መቀመር እንደጀመሩ ነው የተሰማኝ፡፡ ደስታዬ የተጋባበት መሰለ። ወደ ድንኳኑ ስንመለስ ጨለማው ውስጥ የሳቅ ድምፅ የሰማሁ መሰለኝ፡፡ ምን አስቤ እንደሆነ አላውቅም ተፈሪን በቆመበት ትቼው ወደ ሰማሁት ድምፅ ተራመድኩ፡፡ እናቴ ናት፡፡ ቅድም የነፍስ አባቷ መሆኑን ሲያወሩ ከሰማሁት ሰው ጋር ጨለማው ውስጥ እየተላፉ ይሳሳቃሉ። የነፍስ አባቷ አፉን ድንቅፍ እንኳን አይለው ከሟች በመገላገላቸው የጀመሩትን የድብቅ ፍቅር

ያለሰቀቀን ሊኮሞክሙ መሆኑን ሲናገር ስሰማው ከዛ በላይ መቆም እንደሌለብኝ ተሰማኝ፡፡ ሴትየዋ ማን ናት? ለሞተው ባሏ
የምታለቅሰው የውሸቷን ነበር?
በሚቀጥለው ቀን ከጠዋት ይልቅ ለለሊት በቀረበ ሰዓት በመኝታ ቤቷ ከተፈሪ ጋር አንድ ላይ ልታናግረን እንደምትፈልግ
መልዕክት የተነገረኝ እስከዛሬ መተኛቴን ከማላስታውሰው ጣፋጭ እንቅልፍ ተቀስቅሼ ነው።
"አቶ ተፈሪ በሃዘኔ ከጎኔ ለመገኘት ስለመጣህ ከልቤ አመሰግናለሁ:: ከዚህ በኋላ ብትቆይ ደስተኛ አልሆንም::
ሚስትህን ይዘህልኝ ወደ ቤትህ ተመለስ፡፡" ይሄን ስትናገር
ከተፈሪ ጎን መቆሜን ሆነ ብላ ረስታዋለች:: ተፈሪ ቃል ከአንደበቱ ለማውጣት የሚያስችል መረዳት አልገባውም። ዓይኑን እያቁለጨለጨ ያያታል፡፡
''በሀዘንሽ ከጎንሽ መሆኔ የቱጋ ነው ሀጢያቱ?" አልኳት:: እንባዬ
ከመጀመሪያው ፊደል እኩል ከዓይኔ እያመለጠ፡፡ ሆን ብላ አልሰማችኝም::
'ቁርስ እንዲያዘጋጁልህ ነግሪያለሁ:: ሰላም ግባ!” ብላ ለሰላምታ
እጇን ዘረጋችለት እኔ እዛ እንደሌለሁ ሁሉ ዓይኗን ከእርሱ ላይ ሳትነቅል:: ለተዘረጋ እጂ አፀፋውን በመመለስ ምትክ እኔን
በህፃን ግራ መጋባት ያየኛል። ዓይኖቿ እኔ ላይ እንዲያርፉ በተዘረጋ እጁና በተፈሪ መሃከል ገብቼ ቆምኩ። እጇን ልትሰበስብ
ስታሸሽ መንጭቄ ያዝኳት፡፡
"በሃዘንሽ ላፅናናሽ መምጣቴ ምንድነው ጥፋቴ? ቆይ ይሄን ያህል ምንድነው ያደረግኩሽ?" አልኳት እጇን ተጭኜ እንደያዝኳት እየታወቀኝ፡፡ ዓይኖቿን ዓይኖቼ ውስጥ በጥልቀት ዘፈቀቻቸው።
"አንድ ነገር ልንገርሽ፡፡ እስከዛሬ ድረስ አንቺ ያመጣሽብኝን ያህል ለመፅናናት የከበደ ሀዘን ገጥሞኝ አያውቅም:: ያኔ መፅናናት ከቻልኩ ዛሬ አፅናኝ አልፈልግም:: ካላየሁሽ እፅናናለሁ::" ብላኝ እንዳደነዘዘችኝ እጇን መንጭቃኝ በቁምኩበት ጥላኝ ወጣች።
የሆነ ነገር ማለት እፈልጋለሁ። ግን አልቻልኩም:: ተፈሪ እጄን ይዞ መኪናችን ድረስ ግራ የገባው ቁጥር አልባ ጥያቄ እኔን ይሁን እሷን ወይም ራሱን እየጠየቀ አደረሰኝ፡፡ ይህ አጋጣሚ የቀየረው ተፈሪን ብቻ ሆነ፡፡ ከእናቴ ጋር ያለኝን ውስብስብ
ሊፈታ መታገል ጀመረ:: በእኔ ፈንታ አዘውትሮ ሊያገኛት ታተረ ከለቅሶ በኋላ የቀድሞ ቤቷን ትታ ማንም ሊነግረን
ወዳላወቀው ቦታ መሄዷን አወቅን፡፡ ተፈሪ ከብዙ መፍጨርጨር በኋላ ተስፋ ቆርጦ ሁሉንም ባለበት ተወው:: ከድንዛዜዬ
የለዘብኩ የመሰለው ቀን ከእናቴ ውጪ መኖር እንደምችል ሊያስረዳኝ ይሞክራል፡፡ ዓለም በብዙ ደግ ልብ ባላቸው መልካም ሰዎች መሞላቷን ይዘበዝብልኛል፡፡
በድጋሚ እናቴን እንዳያት ያስቻለኝ አጋጣሚ የሴት አያቴ ሞት ነበር። አያቴ ከጭካኔና ከመርዛም ቃላት የተሻለ የተወችልኝ ትዝታ ባይኖርም በመሞቷ አዘንኩ፡፡ እናቴ ለያዥ ገናዥ አስቸግራ ስታለቅስ ሳያት አልዋጥልሽ እያለኝ በትዝብት አፈጥባታለሁ፡፡ ላናግራት ስሞክር ትሸሸኛለች:: አልያም
በእናትነቷ ተስፋ ቆርጬ እንድተዋት አንጀት የሚቆርጡ ቃላት ትነግረኛለች::
"አንቺ ማለት ማስታወስ የማልፈልገው ሳስታውሰው ሚጥሚጣ እንደነዙበት ቁስል የሚያቃጥል ንዳድ ያለው ትዝታዬ ነሽ፡፡.....

#የማለዳ_ራእይ!
ናፍቆትሽ ፀናብኝ
ብየ ስልክልሽ
‘አይዞህ ' አይባልም
መከሰት ነው እንጂ በገሀድ ወይ በህልም !
ካጨሽ አሰናብቺ
ትዳር ካለሽ ፍቺ
ለኔ ለምመኝሽ ሁሉን ነገር ስጪ
የህሊና ቀጪ
የልቦና ስሜት
ይሉንታና ሀሜት
ያገር ሰው ሽሙጥም
ከምኞቴ አይበልጥም ::
ተሊቀመላኩ
ክንፍ ተበድረሽ
ነፋስ ቀድመሽ በረሽ
ባለሁበት አገር
እንደ ሸዋዚንገር
ብረት ለበስ ጡንቻ
ባንድ ርግጫ ብቻ
የቤቴን በር ሰብረሽ
ዐይነ ርግብሽ ወድያ
ቀሚስሽ ወደ ላይ
ወደኔ በጥድፍያ
ወዳልጋው በዝላይ
በጀርባየ ሁኘ
ከእግሮቼ መካከል የጠላ ምልክት
አንቺ ጆሮ ሆነሽ
እኔ ሎቲ ሆኘ-ተጣጥሞ ስክት !
እንዲህ እያሰበ ገላየ ሲቸገር
መጣሁ ትያለሽ ስል
“አይዞህ “ ብሎ ነገር፤
የማለዳ ራእይ፤ ምኞቴን በማመን
በገሀድም ይሁን፤ ወይም በሰመመን
አሳትፊኝ አልሁ እንጂ
ከገላሽ በረከት፤ ከሙቀት ከለዛው
የቃል ምፅዋትማ ሞልቷል በየታዛው!
🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
ናፍቆትሽ ፀናብኝ
ብየ ስልክልሽ
‘አይዞህ ' አይባልም
መከሰት ነው እንጂ በገሀድ ወይ በህልም !
ካጨሽ አሰናብቺ
ትዳር ካለሽ ፍቺ
ለኔ ለምመኝሽ ሁሉን ነገር ስጪ
የህሊና ቀጪ
የልቦና ስሜት
ይሉንታና ሀሜት
ያገር ሰው ሽሙጥም
ከምኞቴ አይበልጥም ::
ተሊቀመላኩ
ክንፍ ተበድረሽ
ነፋስ ቀድመሽ በረሽ
ባለሁበት አገር
እንደ ሸዋዚንገር
ብረት ለበስ ጡንቻ
ባንድ ርግጫ ብቻ
የቤቴን በር ሰብረሽ
ዐይነ ርግብሽ ወድያ
ቀሚስሽ ወደ ላይ
ወደኔ በጥድፍያ
ወዳልጋው በዝላይ
በጀርባየ ሁኘ
ከእግሮቼ መካከል የጠላ ምልክት
አንቺ ጆሮ ሆነሽ
እኔ ሎቲ ሆኘ-ተጣጥሞ ስክት !
እንዲህ እያሰበ ገላየ ሲቸገር
መጣሁ ትያለሽ ስል
“አይዞህ “ ብሎ ነገር፤
የማለዳ ራእይ፤ ምኞቴን በማመን
በገሀድም ይሁን፤ ወይም በሰመመን
አሳትፊኝ አልሁ እንጂ
ከገላሽ በረከት፤ ከሙቀት ከለዛው
የቃል ምፅዋትማ ሞልቷል በየታዛው!
🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
#ቀላውጦ_ማስመለስ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
እባክሽ ተይኝ! ሳይሽ የሚሰማኝ እንደዛ ነው። እርሺኝ፡፡" አለችኝ የእናቷን ለቅሶ አብቅታ ልትመለስ የተነሳች እለት። የምትናገረኝ ሁሉ ለምን ተስፋ እንደማያስቆርጠኝ አይገባኝም።
ከዓመታት በኋላ ስለእርሷ በማሰብ መታተሬን ለማቆም በምታገልበት ወቅት ነው ታማ መተኛቷንና ልታየኝ መፈለጓን
በመልዕክተኛ የላከችብኝ፡፡
አመሻሽ ላይ ታክሲ ተሳፍሬ ሆስፒታሉ ደጅ የሄድኩት የመኪና ማቆሚያው ጋር የተውኩትን መኪና ለመውሰድ ነበር፡፡ ራሴን ያገኘሁት እናቴ የተኛችበት ክፍል ውስጥ ነው።ማንም የለም። ተመልሼ ዓይኗን የማየት ምንም ሀሳብ በጭንቅላቴ አልነበረም፡፡እዛ ስላየችኝ እንዳልተገረመች ሁሉ የተለየ ገፅታ አላሳየችኝም።
ከለመድኩት በተለየ ዓረፍተ ነገር አልነበረም አፏን ያላቀቀችው።
"ደሞ ምን ቀርቶሽ መጣሽ?"
አልመለስኩላትም። እዚህኛው የስሜት ወለል ላይ ቆሜ ለሷ ያለኝ ስሜት ፍቅር ይሁን ጥላቻ ተዳቅሎብኛል፡፡ ምናልባት
እሷን እየወደድኳት በመሰለኝ ጊዜ ሁሉ ራሴን አጥብቄ እየወደድኩ ይሆናል፡፡ በሷ ፍቅር የእኔን የመኖር መሰረት ላመጣል ይሆናል ፍቅሯን የሙጥኝ ያልኩት:: መራርነቷ ቀደምስሬ ትኩስ ደም ሆኖ ሲያግለኝ አካሌ የተወጣጠረ አይነት
ስሜት ተሰማኝ፡፡ ተራራ የሚያክል ምክንያት ቢኖራት እንኳን በዕድሜ ቁጥሯ የሰናፍጭ ታክል ቅንጣት መራር አስተዋፅኦ
ያላበረከትኩ እኔን ለመጥላት እና ቀኖቼን በጥላቻ ለማመሳቀል በቂ እንደማይሆን እያሰብኩ የሆስፒታሉ አልጋ ላይ ተኝታ ሳያት
"ከእሷ ሰንሰለት ራሴን ነፃ ማውጣት አለብኝ፡፡" አልኩት ራሴን::
ያሰብኩትን ባሰብኩ ቅፅበት እጅና እግሬ ለመተግበር ተዘርግተዋል፡፡ የማደርገውን ነገር ውጤት ለማሰላሰል የተረፈ
ስንዝር ክፍተት ጭንቅላቴ ውስጥ አልተረፈም።ጭንቅላቴ በብስጭት በፈላ ደም ብቻ የተሞላ ይመስለኛል፡፡
ያደረግኩት ነገር ሀጢያት ይሁን ፅድቅ ግድ አልነበረኝም።ፅድቅና ሀጢያትን ከህሊናዬ ውጪ የት ተማርኩት? ህሊናዬ
የቸረኝ ትልቁ ስጦታዬስ_ዘብራቃ ቀኖችን ብቻ አይደል?ላደረግኩት ድርጊት ስም መለጠፍ አላሻኝም:: ብቻ ግን
የሆስፒታሉን ቅጥር ጊቢ ለቅቄ ስወጣ መቼ እንደሳቅኩ የማላስታውሰውን ድምፅ ያለው ሳቅ ሳቅኩ: በመኪናዬ መስኮት
እየገባ ጉንጨን እየዳበሰ እና ፀጉሬን እየገለበ ከሚያባብለኝ ንፋስ
ጋር እየተጫወትኩ እቤት ስደርስ ተፈሪ ሳሎን ተቀምጦ በቴሌቭዥን ተከታታይ የአማርኛ ድራማ እያየ ነበር።
በደመነፍስ ወይም ለእርሱ ብዬ ያደረግኩት ነገር አልነበረም።ልብሴን አወላልቄ ስጨርስ የእርሱን የሚቀጥል እርምጃ አልጠበቅኩም:: ያለማቋረጥ እየፈገግኩ መሆኔ ይታወቀኛል።
በሁኔታዬ ግራ መጋባቱን ሳይደብቅ የራሱን ልብሶች በመግፈፍ አገዘኝ፡፡ ግራ ቢጋባም ልብሴ ወልቆ ካየኝ ምክንያትና ድርጊት ለማሰብ የሚተርፍ ጭንቅላት እንደማይኖረው አውቃለሁ።በራሴው የውዝዋዜ ስልት አብረን ጮቤ ረገጥን፡፡ ሳቃስት ራሴን መስማቴ መልሶ አስፈገገኝ።
"መቼ ነው ልጅ የምንወልደው? ልጆች እንዲኖሩን እፈልጋለሁ::" የተለመደ ውትወታውን ከወንድ ርጭቱ እና
ከረዥሙ ትንፋሹ ጋር ደምሮ ጠየቀኝ።
በፍፁም እናት መሆን አልፈልግም በፍፁም ልጅ አይኖረኝም።" ለመጀመሪያ ጊዜ መለስኩለት ፈ።
ለምን? ለምን? ከኔ መውለድ ነው የማትፈልጊው ?"
"አይደለም።እናት ምን እንደሆነች አላውቅም እናት መሆን የምችል አይመስለኝም:: እናት የማልሆነውን ልጅ ወደዝህች ምድር ማምጣት አልፈልግም::" መልሴ አጥጋቢ ሆኖለት ይሁን ደስታውን ላለመበረዝ ርዕሱን መቀየር ፈለገ፡፡
"የዛሬው ነገር ማለቴ የማላውቃት ሴት የሆንሽበት ሚስጥር ምንድነው?" ሲለኝና የበር መጥሪያው ሲጮህ አንድ ሆነ፡፡
“ነፃነቴን አገኘሁ::" አልኩት ልብሶቼን እየለባበስኩ፡፡የሚቀጥለውን ጥያቄ ከአፉ ላይ አስቀርቶት ልብሱን እንደነገሩ
ደራርቦ በር ሊከፍት ወጣ፡፡
"ወይዘሮ ማህሌት አጥጋቢ በወይዘሮ ወለላ አጥጋቢ ነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል::" አለ ተፈሪን አጅበውት ወደ ቤት ከዘለቁት ሶስት ፖሊሶች አንደኛው ወደ ፊት ጠጋ ብሎ፡፡
ስህተት መሆን አለበት። በጭራሽ እሷ ሰው አትገድልም:: ከኔ ጋር ነበረች። ስህተት ነው::" ይላል ተፈሪ ተራ በተራ ፖሊሶቹን እያየ:: ወደእኔ ዞሮ ማረጋገጫ ይጠብቃል።
ስህተት አይደለም:: ገድያታለሁ:: እራሴ ነኝ የገደልኳት፡፡ አንቄ ነው የገደልኳት:: ለፖሊስ ደውዬ ያሳወቅኩትም ራሴ ነኝ!"
ካደረግኩት በላይ ፀፀት እንደሌለብኝ እንዲታወቅልኝ የተናገርኩት ነበር፡፡ በመጠኑም እንደ አብሪ ትል ብልጭ እያለ
የጭንቅላቴ ክፍል ከፀፀት ነፃ የተናገርኩት ይመስለኛል።
እጆቼ በብረት ካቴና ተቆልፈው ወደ እስር ቤት እየተወሰድኩ እየተሰማኝ ያለው ወደ ነፃነት ዓለም እየሄድኩ እንደሆነ ነው።
የሰው ልጅ ዓለሙ ያለው ጭንቅላቱ ውስጥ መሆኑ የገባኝ በጭንቅላቴ ማሰብ ስጀምር ነው።ወደ ሚታየው ዓለም ተርጉሞ የሚኖረው በጭንቅላቱ የሰራውን ዓለም መሆን አለበት።ጭንቅላቴ ውስጥ አዲስ የተገነባው ዓለም ነፃነት ያለበት እና
ጥያቄ አልባ ሲሆን የእስር ቤቱ መሬት ከተፈሪ ሶፋ በላይ እንደተመቸኝ አይነት እና በዙሪያዬ የማየው ሁሉ ድሎት ሳለ
በውስጤ ያረጀው ዓለም ጥቀርሻነት ሳቅ ከፊቴ እንዳሸሽብኝ አይነት:: በእርግጥ በሚዳስሰው ዙሪያችን የራሳችንን ዓለም
መገንባት ረዥም ዕድሜን እንደሚፈጅ ሁሉ በጭንቅላታችን ውስጥም ጥቃቅን መሰረቶችን መጣል ሳይቀር የረዥም ጊዜ
ድልዳል ነው:: ገዳይ መሆንም ጭምር!!!! ዳኛው የእስር ዓመቴ ሀያ ዓመት መሆኑን በሞዶሻቸው ጠረጴዛውን በኩርኩም
ነርተው ሲያውጁ በነፃ ያሰናበቱት ወንጀለኛ ገፅታ ነበር ፊቴ ያጋለጠው።የምጓጓለት ቀሪ ኑሮ የለኝምና ነው:: የታሰርኩ ሰሞን ተፈሪ በየእለቱ ይጠይቀኝ ነበር። ሁሉም ሰላም እንደሆነ እና ከወህኒው ጊቢ ማዶ የሚያጓጓኝ የኔ ዓለም እንደሌለ አምኜ እንደደረስ ጎረምሳ በፉጨት ቀኖቼን እየተለማመድኩ ሳለ
ከዓመታት በፊት ያየሁት የእናቴ የእንጀራ ልጅ ከሌላ አንድ ወንድ ጋር እና ሁለት ሴቶች ጋር ሊጎበኘኝ መምጣቱ ከመገረም
በላይ የማይታመን ነገር ሆነብኝ፡ አጠገባቸው ደርሼ ከመቆሜ ከሴቶቹ ጋር ተደጋግፈው በቆሙት አቋቋም ጥንድ ጥንድ መሆናቸው ገባኝ፡፡ ያልገባኝ ምን ሊሰሩ እንደመጡ ነው፡፡....

👍4
#የባይተዋር_ገድል
በቁም መስተዋት ፊት መቆምኸ ሲጨንቅህ
የቁም መስታወቱ፣"ሰውነትህ የታል?" ብሎ ሲጠይቅህ
ግድግዳው ላይ ያለች፣የገደል ማሚቱ ዝም ማለት ፈርታ
ሳሎንህን ስትሞላው ዝምህን አብዝታ
ሕልም የቀላቀለ፣የዝናብ ነጠብጣብ፣ ጣራህን ሲመታ
ከመስኮትኸ ማዶ፣የለሊት ወፍ ሞታ
የጊዜ ስውር ክንድ
የጓሮህን ዋርካ ያላገር ሲያስቀረው
በለሊት ወፍ ምትክ፣ክንፍ ያወጣ ሌሊት ጎጆህን ሲዞረው
መርሳት የሚሉት፣የኑሮ ገባር ወንዝ፣ አልጋህን ሲገምሰው
"መንሳፈፍስ ይቅር፣ መስጠም ያቅተዋል ሰው?"
ሲያሰኝህ እድልህ
ያኔ ይጀምራል የባይተዋር ገድልህ
🔘በውቀቱ ስዩም🔘
በቁም መስተዋት ፊት መቆምኸ ሲጨንቅህ
የቁም መስታወቱ፣"ሰውነትህ የታል?" ብሎ ሲጠይቅህ
ግድግዳው ላይ ያለች፣የገደል ማሚቱ ዝም ማለት ፈርታ
ሳሎንህን ስትሞላው ዝምህን አብዝታ
ሕልም የቀላቀለ፣የዝናብ ነጠብጣብ፣ ጣራህን ሲመታ
ከመስኮትኸ ማዶ፣የለሊት ወፍ ሞታ
የጊዜ ስውር ክንድ
የጓሮህን ዋርካ ያላገር ሲያስቀረው
በለሊት ወፍ ምትክ፣ክንፍ ያወጣ ሌሊት ጎጆህን ሲዞረው
መርሳት የሚሉት፣የኑሮ ገባር ወንዝ፣ አልጋህን ሲገምሰው
"መንሳፈፍስ ይቅር፣ መስጠም ያቅተዋል ሰው?"
ሲያሰኝህ እድልህ
ያኔ ይጀምራል የባይተዋር ገድልህ
🔘በውቀቱ ስዩም🔘