አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ኗሪ_አልባ_ጎጆዎች

#አያቶች!
በባዶ መስክ ተመራምረው
ጥበባቸውን
ዕድሜአቸውን
ገብረው
የጎጆ ንድፍ ሲያበጁ
አረጁ
ዘመናቸውን ፈጁ

#አባቶች!
መላ ዘመናቸውን
ጎጆ በመቀለስ አሳለፉ
ሳይኖሩበት አለፉ

#ልጆች!
ጎጆውን ለመውረስ ሳይከጅሉ
እንዲህ አሉ
"ያ'ባቶቻችን ጎጆ
ይሁን ባዶ ይሁን ኦና
በ'ኛ ቁመት
በ'ኛ መጠን
አልተቀለሰምና።"

🔘በውቀቱ ስዩም🔘