አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ባለ_አንካሳ_ልብ_ሯጭ

ቅልጥም ለማደደን ቅቤ ከምጠጡ
ጋሬጣን ለማምለጥ ጫማ ከምትመርጡ
የልብ ወጌሻ አምጡ፣
አንካሳ ልብ ያለው ምን በእግሩ ቢሮጥም
ቢያባርር አይዝም ቢሸሽ አያመልጥም።
#ጎሠሣ_ሰላም

ማጭድ ይሆነን ፣ ምንሽር ቀለጠ
ዳሩ ብረት'እንጂ ልብ አልተለወጠ
ለሣር ያልነው ስለት ፣ እልፍ አንገት ቆረጠ።
#የበረሐ_ጠኔ

በረሐ ላይ ቆሜ ጠኔ ሲያደባየኝ
ቆሞ ሲያመሰኳ ግዙፍ ግመል ታየኝ፤
ሰውነቴ ደክሞ ሆዴ እየተራበ
እጄ መጣፍ ገልጦ ቃሉን አነበበ
"ካመሰኳ ብላው" ይላል የፊተኛው
"ሽኾናው ክፍት ይሁን" ይላል ሁለተኛው፤
የፊተኛው ት'ዛዝ በፍፁም ተሳክቷል
ግመሉን አየኹት ቅጠል ያመሰኳል
ሽኾናውም ቢሆን
አሸዋው ሸፍኖት
ጥልቅ አቧራ ውጦት
ካ'ይኔ ቢሰወርም
ክፍት እንደ ኾነ አልጠራጠርም።
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አስራ_ስድስት (የመጨረሻ ክፍል)


#በሜሪ_ፈለቀ

...ሰላም?” አልኩኝ የማውቀው ፊት ላይ አፍጥጬ።ብዙም ደቂቃ አላባከኑም ወንዶቹ ወንድሞቼ መሆናቸውንና ሴቶቹ
ፍቅረኞቻቸው መሆናቸውን ሲነግሩኝ አልጋ ላይ ሆኜ እየቃዠሁ አለመሆኔን ደጋግሜ ራሴን ስጠይቀው:: ለምን ነበር ወንድሜ መሆኑን እንዳውቅ ያልፈለገችው? ይህቺ ሴትዮ በስንቱ ነው
የምትበድለኝ? ስትሞት ጥያቄዬ ሁሉ አብሯት የሞተና ከዚያ በኋላ መቼም የማያስጨንቀኝ መስሎኝ ነበር፡፡ ነገር
ግን በተቃራኒው ሆነ፡፡ ሞታም ይኸው ግራ እያጋባች ታቀውሰኛለች።
ከተለያየ ወንዶች የወለደቻቸው ሁለት
ወንድሞች አሉኝ፡፡ ምናልባት ሌሎችም ይኖሩ ይሆናል፡፡ምክንያቱም እነርሱም እህት እንዳላቸው ያወቁት ስለገደልኳት
ነው። ሴትየዋ ማን ነበረች? ምንስ ነበር ትርፏ?

ብዙ ዓረፍተ ነገሮች ሳያባክኑ የተረዳሁት ለእነርሱም ጥሩ እናት እንዳልነበረች ነው። ከፍቅራቸው ገዝፎ ጥላቻና መከፋታቸው
ይታያል። ክልሱ ወንድሜ (ኪሩቤል) በተሻለ ፍቅር ነበረው። ስለገደልኳትም ማዘኑን አልደበቀኝም። ታላቃቸው ነኝ
ኪሩቤልን በሶስት ዓመት እበልጠዋለሁ። ቅዱስን በአስራ አንድ ዓመት።
እየተቅለበለበች የምታወራው የቅዱስ ፍቅረኛ በምሰማው ነገር እየተሰማኝ የነበረውን ስሜት ውል መያዝ
እንዳልችል ታስፎርሸኛለች፡፡ የራሷንም የእርሱንም ደምራ በሚቅበጠበጠው መላ አካሏ እየታጀበች የምታወራው እርሷ
ናት። አንዲትም ቃል ሳልተነፍስ የመጠየቂያ ሰዓቱ አልቆ ከመግባቴ በፊት ኪሩቤል እግሩ ስር አስቀምጦት የነበረውን ካርቶን እየሰጠኝ ይሄ አንቺ ትፅፊላት የነበሩት ደብዳቤዎች ናቸው። ከአጠገቧ ተለይቷት አያውቅም። ሆስፒታል እንኳን አብረዋት ነበሩ።
ያንቺ መሆኑን ያወቅነው ከሞተች በኋላ
ነው። ለነዚህ ደብዳቤዎች ፍቅር እንደነበራት አውቃለሁ። እያነበበች
ትንሰቀሰቅ ነበር። ምናልባት የምትፈልጊው ከሆነ ብለን ነው።"
አለኝ፡፡ የነገረኝ ነገር እኔ ውስጥ የሚፈጥረውን ውስብስብ ሳይረዳ፡፡

"ከእኔ ከልጇ በላይ አንቺ የምትፅፊላት ደብዳቤ ትርጉም ነበረው።ማን መሆንሽን ሳላውቅ ብዙ ጊዜ ቀንቼብሻለሁ::" አለ እስካሁን ከንግግር የተቆጠበው ቅዱስ፡፡ በስልክ ላገኛት ባለመቻሌ እቤቷ የሄድኩ ጊዜ ባሏ ነበረ የፖስታ አድራሻዋን የስጠኝ፡፡ ታንብበው አታንብበው እንኳን ሳላውቅ በየወሩ እፅፍላት ነበር፡፡ አንዳንዴ
ባታነበው እንኳን የውስጤን እየተነፈስኩ ስለሚመስለኝ መፃፌን አላቆምም ነበር። ስለእርሷ ለመርሳት መሞከር በጀመርኩ ጊዜ ከጥቂት ዓመታት በፊት ነው መፃፌን ያቋረጥኩት፡፡ተሰናብተውኝ ከሄዱ በኋላ ምን ማሰብና የቱን ማመን እንዳለብኝ
ግራ ተጋባሁ። ትወደኝ ነበር? ትጠላኝ ነበር? ትፀፀት ነበር? የትኛው ነበር ልኩ? የምታሳየኝ ጥላቻ ወይስ የደበቀችኝ ፀፀት?ለቀናት በጥቅጥቅ የጥያቄ ጫካ ውስጥ ተቅበዘበዝኩ። ጠፋሁ። መውጫው የማይገኝ ሆኖብኝ ባተትኩ። ማን ነበረች ይህቺ ሴትዮ?

ኪሩቤል አዘውትሮ መምጣቱን በቀጠለ መጠን ስለእርሷ የሚነግረኝ ነገር ሌላ የማላውቀው የእርሷ ገፅታ ነው።ሁሌም
በመጣ ቁጥር በሞቷ እናቱን እንዳሳጣሁት ይወቅሰኝ ስለነበር
በአንዱ ቀን የበደሌን ግዝፈት ልከምርለት አፌን ለማላቀቅ ተገደድኩ፡፡ የረጋ ቀልብ ያላት ፍቅረኛው በእንባዬ ጠብታ ልክ
እንባዋን እያፈሰሰች ስትሰማኝ እርሱ በጭንቀት ሲንቆራጠጥ ቆይቶ ምንም ቃል ሳይተነፍስ ሄደ፡፡ ለወቀሳው የመጨረሻ ቀን ሆነ፡፡ በፍቅረኛው ተገዶ የሚመጣ የሚመስለኝ ቅዱስ አልፎ
አልፎ ቢመጣም እርሷ ታወራለታለች እንጂ በዝምታ ሰዓቱን ጨረሶ ነበር የሚሰናበተኝ። በቃላት ባይናገረውም አምርሮ እንደሚጠላት መደበቅ አይችልም።የሁሉም ዑደት አንድ ጫፍ ላይ ገተረኝ ማናችንም ሴትየዋን አናውቃትም ልናውቃትም አንችልም። እንቆቅልሽ ነበረች:ፈ።ከነእንቆቅልሿ ተቀብራለች።ይሄን እያሰብኩ የእስር ቤት ቀኖቼን ልረሳት እራሴን እመክራለሁ፡፡ ወንድሞቼ እና ፍቅረኞቻቸው ሲመጡ ወጥቼ ሳገኛቸው ስለእነርሱ የሚሰማኝን ስሜት እፈትሻለሁ። በየእለቱ ተፈሪ ሊጎበኘኝ ሲመጣ አግብቶ እንዲወልድ እነግረዋለሁ።የታሰርኩ ሰሞን በየእለቱ፣ ጊዜው ሲገፋፋ በሁለት ቀን፣ ሲዘገይ
በሳምንት፣ ከራርሞ በወር፣ ሰነባብቶ ጭራሹኑ ቀረ።

ከእያንዳንዱ ክፋት ጀርባ መሪር በደል አለ እያልኩ አስባለሁ።ጥያቄው የሚሆነው በደልን ይቅር ያለ በጎነት የለም ወይ?
የሚለው ነው። ኖሮ ያውቅ ይሆናል፡ በደልን ይቅር ለማለት የሚያስችል ትልቅ በጎነት የሚፈጥር ፍቅር የሚጠይቅ
ይመስለኛል። የገባኝ በዛ መጠን በልቤ የተንሰራፋ መልካምነት መፍጠር የሚችል ከተበደልኩት ልቆ የሚገዝፍ ፍቅር የለኝም። እናቴን ልገድልበት የቻልኩበትን ቅፅበት ሳስብ በሰውኛ ምክንያት
ከመግመድ አይሎ ቅፅበታዊ ስሜት መላው አካላችንን የሚያዝበት አጋጣሚ መኖሩን ነው። ከታሰርኩ ከብዙ ወራት
በኋላ ጠየቂ እንደመጣልኝ ፖሊሷ ነገረችኝ፡፡ ከወንድሞቼ አንዳቸው እንደሚሆኑ እያሰብኩ ስወጣ ፖሊሷ የጠቆመችኝ ያለዛሬ አይቼ የማላውቀው ትልቅ ሰውዬ ነው።

"አላውቅህም!" አልኩት እንደሚሰማኝ ሳረጋግጥ፡፡

“እኔን ማወቅሽ አይደለም እዚህ ያመጣኝ ማወቅ የምትፈልጊውን ነገር እኔ ማወቄ ነው።” ያለኝ በትክክል አልገባኝም፡፡

"እኔ ማወቅ የምፈልገው ነገር የለም።" አልኩት ከሚቀጥለው መልሱ በኋላ ትቼው ልሄድ ራሴን እያሰናዳሁ።

"እናትሽን አውቃታለሁ፡፡ እንዴት እንዳረገዘችሽም አውቃለሁ።"
አለ ስሜቴን ከፊቴ ላይ እየበረበረ::
"ማወቅ አልፈልግም። ጥያቄዬን ከእርሷ ጋር አብሬ ገድዬዋለሁ።" ብዬው እየሸሸሁ መሆኔ እየታወቀኝ ጥዬው ለመሄድ ዞርኩ፡፡

"ከማን እንደወለደችሽስ ማወቅ አትፈልጊም?" ቀጥ አልኩ።ምንም ያህል ብታገል አባቴን ለማወቅ የሚላወሰውን ፍላጎቴን መገደብ አቃተኝ። ተመልሼ አጠገቡ ደረስኩ።

"እናትሽን በአንቺ እጅ ተገድላ መሞቷን ስሰማ የነበራችሁን ግንኙነት ማጣራት ጀመርኩ። ላንቺ፣ ለእናትሽ፣ ለራሴ
ማናችንን ነፃ እንደሚያወጣ ባላውቅም እውነቱን ልነግርሽ እንደሚገባ ወሰንኩ።" መጨማደድ የጀመረ ግንባሩን እያኮራመተ ይለጥጣል፡፡ የወሬ ማጀቢያው ትዕግስቴን እየተፈታተነው ነበር፡፡

ቀጥታ መልሱን ንገረኝ አባቴ ማን ነው?"

"እናትሽ እስር ቤት ውስጥ ተደፍራ ነው ያረገዘችሽ፡፡ ቁጥራቸው የማይታወቅ ጠባቂዎች ናቸው የደፈሯት። የማንኛው ልጅ መሆንሽ አይታወቅም፡፡ በወቅቱ እዛ ፖሊስ ነበርኩ፡፡ ስናገኛት ራሷን አታውቅም ነበር፡፡ ለወራት ስትታከም ቆይታ ነው
የዳነችው። ከባድ ስቃይ ብታልፍም የአካል ቁስሏን ድናለች።ከዛን ዕለት በኋላ ክንፏን የተሰበረች ወፍ ሆነች:: ......"

ማውራቱን ቀጥሏል... ጥዬው ገብቻለሁ።

💫ተ..ፈ..ፀ..መ💫

Like 👍 #Share እያደረጋቹ ይሄ ቢያልቅ ሌላ እንጀምራለን ግን የናንተ አስተያየት ወሳኝ ነው ስለ ድርሰቱ ስለ ቻናላችን ምን ይጨመር? ምን ይቀነስ? ያላችሁን አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን። አመሰግናለው🙏
👍5
#ሞኝ_ፍቅር

ለ'ሱ
ሰው ብቻ አይደለችም
ጠፈር ናት ባ'ካሏ
መሬት ናት በነፍሷ
ዕድሜ ልኩን ቢሮጥ
አያመልጥም ከ'ሷ።
#የነቢይ_ህልውና

#ትላንት
"ነብይ ባ'ገሩ አይከበርም"

#ዛሬ
ነብይ ባ'ገሩ አይኖርም

#ነገ

ነብይ አይፈጠርም
#ልረሳሽ_እየጣርኩ_ነው

በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
መጋረጃው ሲውለበለብ፥ ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ
ዋርካው በቅጠል ጽዋ
ውሀ ሲያቁር ክሕዋ
የምድርን ጉሮሮ ሊያርስ
መሬት ፍጥረትን ስትጸንስ
በዚህ ሁሉ ጸጋ ማሀል፥ ያንችን መሄድ ስተምነው
ኢምንት ነው ምንም ነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው፤

መጣ መጣ መጣ፥ የዝናቡ ኮቴ አየለ
ክረምት የፍጥረት መሲሕ፥ በቀጠሮው ክተፍ ከስሱ የጉም አይነርግብ፥ ውብ ገጽሽን ሸፋፈነው
የርጥብ አፈር ርጥብ ሽታ፥ ውብ ሽቶሽን አዳፈነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው፤

የዝናቡ ኮቴ ይደምቃል
እንደብሰል ሾላ ፍሬ፥ አሮጌው ሰማይ ይወድቃል
እንኳን የእግርሽ ኮቴ፥ ጎዳናሽም ታጥቦ ያልቃል፤
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው
👍1
#የገንዘብ_ቦርሳው


#ድርሰት_አንቶን_ቼኾቭ

አንድ መልካም የማለዳ እለት ነው።ሶስት ተዘዋዋሪ ዘፋኞች በባቡር ሃዲድ ላይ ሲጓዙ የገንዘብ ቦርሳ ወድቆ አገኙ። ስሚርኖቭ፣ፖፖቭና ባላባይኪን ቦርሳውን ከፍተው ሲመለከቱ ከደስታቸው
ብዛት የሚሆኑትን አጡ። ተፍነከነኩ፡ በጣምም ተገረሙ፡፡ ለካስ በቦርሳው ውስጥ 20 ኖቶች፣ ስድስት የሁለተኛ ዕጣ አሸናፊ የሎተሪ ትኬቶችና የሶስት ሺ ሩብል ገንዘብ ነበሩበት። በመጀመሪያ ከፈት አድርገው ሲመለከቱ “ወንዳታ” ብለው በጋራ ጮኹ።ከዚያም ሐዲዱ
ጥግ ላይ ባለ ጉድባ ሆነው በደስታ መደመማቸውን ቀጠሉ፡፡

ለመሆኑ ለእያንዳንዳችን ስንት ይደርሰናል?” ሲል ስሚርኖቭ ገንዘቡን እየቆጠረ ጠየቀ፡፡ “ያንተ ያለህ! አምስት ሺ አራት መቶ አርባ አምስት ሩብል! ወገን! ከዚህ ሁሉ ገንዘብ በኋላ ብንሞትም አይቆጭ!"

ባላባይኪንም ቀጠለ። “እኔ በበኩሌ ለራሴ አይደለም የተደሰትኩት” አለ“ለእናንተው ለምወዳችሁ ወንድሞቼ ነው በደስታ ያበድኩት።የገንዘብ ቦርሳው
ከእንግዲህስ ወዲያ እየተራባችሁ በባዶ እግር መኳተን አከተመለት።
ወደ ሞስኮ አቀናለሁ።ከእንግዲህስ ወዲያ እንደ አሚና እየዞርኩ አልዘፍንም ቄንጠኛ ሰው እሆናለሁ:: ባለ ሀሩን ክብ ባርኔጣና ልዩ የሆነውን የኦፔራ ባርኔጣም እገዛለሁ።እንደኔ ሽክ ማለት ለሚወድ
ሰው አመዳዩ የሀር ባርኔጣም አስፈላጊ ነው።

በነገራችን ላይ የዛሬዋን እለት ማከበር አለብን። እየበላንና እየጠጣን መደስት ያስፈልገናል፡፡ ደግሞም ለሶስት ተከታታይ ቀናት በቀዘቀዘ ምግብ ተቆራምደን ነው የቆየነው። ከእንግዲህ በኋላ ለየት ያለ ነገር ማድረግ ይኖርብናል አይመስላችሁም!?”

ትክክል ነው ወገኖቼ!” ሲል ስሚርኖቭ በቀረበው ሀሳብ ተስማማ፡፡
“ብዙ ገንዘብ ኖሮን የምንበላው ግን ከሌለን ምን ይፈይዳል የእኔ ውዶች? ወንድም ፓፓቭ! መቼም አንተ ከመሃከላችን ወጣት ስለሆንክ ከቦርሳው ገንዘብ ውሰድና እባክህ ሮጥ በል፡ አደራህን የእኔ መልአክ እዚሁ ቅርባችን ነው መንደሩ፡፡ ተመልከት!
መጠምዘዣው ላይ ነጭ የቤተክርስቲያን ጉልላት ይታይሃል? ትልቅ መንደር ነው፡፡ እዚያ ሁሉም ነገር ይገኛል። አንድ ጠርሙስ ቮድካ ግዛ፣ ትልቅ የእሪያ ስጋ፣ ሁለት ዳቦና ሰርዲንም ጨምርበት። እኛ
እዚህ እንጠብቅሃለን የእኔ ጌታ! የእኔ ተወዳጅ...”

ፖፖቭ እንደተባለው ገንዘቡን ተቀብሎ ለመሄድ ተዘጋጀ:: ስሚርኖቭ
እንባ ባቀረረ አይኑ እቅፍ አድርጉ ሶስቴ አገላብጦ ሳመው፡፡ እያማተበም
በምድር ላይ ያለ መልአክና ነፍስ የሆነ ሰው አድርጐ አሞጋግሰው፡፡
ባላባይኪንም ከስሚርኖቭ ባልተናነሰ አቅፎት ዝንተ ዓለማቸውን በጓደኝነት እንደሚቆዩ አድርጐ ፍቅሩን ገለፀለት፡፡ ሁለቱም እጅግ ስሜትን በሚነካ ሁኔታ አቅፈው እያሻሹት ወደ መንደሪቱ ሸኙት..
ፖፖቭም “አቤት! እንዴት ያለ ደስታ ነው!?” እያለ እግረመንገዱን
በሀሳብ ኳተነ።

“ከእንግዲህስ ወደ ትውልድ ሀገሬ እበራለሁ፡፡ ጓደኞቼን ስብስቤ አንድ
የግሌን ትያትር ቤት እገነባለሁ:: እዚህ ላይ ግን መታወቅ ያለበት
እም፣ ግን እኮ ተካፍዬ የማገኘው ገንዘብ ለምን ይሆናል? አንድ ደህና ክዳን ቤት እንኳ አይሰራልኝም፡፡ ቦርሳው ግን እንዳለ የእኔ ከሆነ ይህ ሌላ ጉዳይ ነው ምን የመሰለ ትያትር ቤት አቆምበታለሁ፡፡ ለእኔም ክብር ይሆነኛል፡ እንዲያው እውነቱን እንናገር ቢባል ስሚርኖቭና
ባላባይኪን ተዋናይ የሚባሉ ናቸው? እነሱን ብሎ ተዋናይ! ተሰጥኦ
የሚባል ነገር ያልፈጠረባቸው አሳሞችና ጡንቻ ራሶች ናቸው።ደደቦች! እነሱ እጅ ገንዘቡ ከገባ በዋዛፈዛዛ ያባክኑታል፡፡ እኔ ከሆንኩ ግን ለተወለድኩባት ኮስትሮም ከተማ ጥቅም አውላለሁ። ዘላለማዊ
ቅርስ አኖራለሁ ..አንድ ሀሳብ መጣልኝ ቦርሳውን ለራሴ ማስቀረት አለብኝ፡፡
ቀጥሎ የማደርገውን እኔ አውቃለሁ። በምገዛው ቮድካ ውስጥ መርዝ
እጨምራለሁ፡፡ እነሱ ወዲያው ይሞታሉ፡፡ ከዚህም በኋላ ሀገሬ ሩሲያ አይታ የማታውቀው ትያትር ቤት ይኖራታል፡፡ ማነው እሱ? ማከ-ማጐን ሳይሆን አይቀርም እንደተናገረው “ዓላማ ግብን ያመቻቻል”ብሎ ነበር። አዎን! ማከማጐን ታላቅ ሰው ነበር፡፡”
እግረ መንገዱን ፖፖቭ ከራሱ ጋር በሚመካከርበት ጊዜ ጓደኞቹ
ስሚርኖቭና ባሳባይኪንም ተቀምጠው ያወጋሉ።
“ጓደኛችን ፖፖቭ ደህና ጉርባ እኮ ነው” አለ ስሚርኖቭ አይኑ እንዳቀረዘዘ፡፡ “እወደዋለሁ። ችሎታውንም በሚገባ አደንቅለታለሁ፡፡በእሱ ላይ ፍፁም ፍቅር ነው ያለኝ። ግን ምን ያደርጋል? ይህ ገንዘብ አጥፊው ነው፡፡ ይጠጣበታል ወይም ነጋዴዎች ያታልሉትና ገንዘቡን የትም በትኖ ይመለሳል። ወጣትም በመሆኑ የገንዘብ መያዢያ ጊዜው አይደለም፡፡ በሀሳቤ ትስማማለህ የእኔ ወንድም
“አዎ!” ሲል ባላባይኪን በሀሳቡ መስማማቱን ለመግለጽ ስሚርኖቭን
አቅፎ ሳመው።ቀጠለናም "ለምኑ ነው ለዚ ውርጋጥ ገንዘብ የሚያስፈልገው ?
ካንተ ጋር ግን መካፈላችን የተለየ ጉዳይ ነው እኔና አንተ የቤተሰብ ኃላፊዎችና የሰከንን ሰዎች ነን ገንዘብ ብዙ ነገር ያደርግልናል።”

ዝምታ በመሃከላቸው ሰፈነ

“ስማኝ ወንድሜ?! ለረዥም ሰዓታት የዚህን ውርጋጥ ነገር እያወጋንና እየተፈላሰፍን መቆየት የለብንም። የገዛውን ዕቃ ተረክበን እንግደለው! ከዚህ በኋላ ለእኔና ላንተ ስምንት ሺ ሩብል ይደርሰናል ማለት ነው። እንግደለውና ሞስኮ ከተማ ውስጥ ፖፖቭን የባቡር
ፉርጐ በልቶት ሞተ እያልን እናስወራለን። እርግጥ ነው እኔም ብሆን እወደዋለሁ፣ አከብረዋለሁ። ከሁሉም በላይ ግን የኪነ ጥበብ እሴት ትበልጥብኛለች፡፡ በግልጽ ካየነውም ተሰጥኦ የለሽና እንደዚህ
እንደተነጠፈ የባቡር ሐዲድ የደነዘ ልጅ ነው::”

“ምነው ጃል?! ምን ማለትህ ነው?” ሲል ስሚርኖቭ ደንግጦ በአባባሉ አለመስማማቱን ገለፀለት፡፡ “ይህን የተቀደሰና ሀቀኛ ወጣት እንዲህ ስታጣጥለው ትንሽ አታፍርም
በእርግጥ በሌላ መልኩ
ብንገድለው በወንድማዊነት የሚሆን ነገር ነው::”ስመለከተው፣ በግልፅም ለመናገር አንተ የማትረባ አሳማ ስትሆን እሱ ግን ክብሩን የጠበቀ እብድ፣ አዋሻኪና ሀሜተኛ ነው እንኳ እኛኑ ያስመሰግነናል እንጂ ሌላ ትርጉም አያሰጥብንም።ስለዚህ ወንድሜ፣ የእኔ ብስል፤ ምን የሚያስቀይም ነገር ይኖራል
ብለህ ታስባለህ? ሞስኮ ከተማ ስንደርስ የሰውን ልብ የሚነካ የሀዘን
መግለጫ ፅፈን በጋዜጣ እንዲታተም እናደርግለታለን። ይህም ቢሆን በወንድማዊነት የሚሆን ነገር ነው
የተወራው መፈፀም አለበት

ፖፖቭ ከተላከበት መንደር የገዛውን ሁሉ ይዞ እንደተመለሰ ይጠብቁት የነበሩት ጓደኞቹ አይናቸው እንባ እንዳቀረረ አንገቱ
ላይ ፡፡ተጠመጠሙ:: አገላብጠው ሳሙት። ለተወሰኑ ሰዓታትም
ስለ ታላቅ ተዋናይነቱ እያወሱ አደነቁት፡፡
በድንገት ግን ተጠቃቅሰው አፈርድሜ አስጋጡት:: ፖፖቭ ሞተ፡፡ወንጀሉ እንዳይደረስባቸው አስከሬኑን ጐትተው የባቡር ሐዲዱ ላይ ጣሉት ያስገዙትን ምግብና መጠጥ ተከፋፍለው በመልካም ቃላት እየተሞጋገሱ ተመገቡ። የፈፀሙትም ወንጀል ለቅጣት እንደማያደርስ እረግጠኞች ነበሩ:: ዳሩ ግን ምግባረ ሰናይ መከበሩ፣ ምግባረ እኩይ ደግሞ መቀጣቱ መቼም የታወቀ ነገር ነው::
መርዝ .... ፖፖቭ ገዝቶ ባመጣው ቮድካ ውስጥ የጨመረው መርዝና ከላዩ ላይ የተጐነጨለት ቮድካ ስራውን መስራት ቀጠለ።
ጓደኛሞቹ ጨርሰው ለመጠጣት አልቻሉም:: ትንፋሻቸው ተቋረጠ፤
እነሱም ባቡር ሐዲዱ ላይ እንደተጋደሙ ቀሩ:: ከአንድ ሰዓት በኋላ አሞራ በላያቸው ላይ አንዣበበ።

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
አትሮኖስ pinned «#የገንዘብ_ቦርሳው ፡ ፡ #ድርሰት_አንቶን_ቼኾቭ አንድ መልካም የማለዳ እለት ነው።ሶስት ተዘዋዋሪ ዘፋኞች በባቡር ሃዲድ ላይ ሲጓዙ የገንዘብ ቦርሳ ወድቆ አገኙ። ስሚርኖቭ፣ፖፖቭና ባላባይኪን ቦርሳውን ከፍተው ሲመለከቱ ከደስታቸው ብዛት የሚሆኑትን አጡ። ተፍነከነኩ፡ በጣምም ተገረሙ፡፡ ለካስ በቦርሳው ውስጥ 20 ኖቶች፣ ስድስት የሁለተኛ ዕጣ አሸናፊ የሎተሪ ትኬቶችና የሶስት ሺ ሩብል ገንዘብ ነበሩበት። በመጀመሪያ…»
#ከምነቴ_ጋር_ቀረሁ

አውቃለሁ!
አታምኝም በማምነው
ያንደኛው ሰው መንገድ፣ ለሌላው ገደል
ቢቀና ጎዳናው፣ ቢወለወል አስፋልት
አብሮ ከማያልም፣ አብሮ መሄድ ልፋት
ያንደኛው ሰው እግር፣ ለሌላው እንቅፋት

ባልጮህ ባደባባይ
ምኩራብ ባልገነባ፣ መዝሙር ባላሰማ
ከጥላየ በቀር፣ ባይኖረኝ ተከታይ
በቃል ወይ በዜማ
ተገልጦ ባይታይ
በልብ ተጠንስሶ፣ ባይን የሚገነፍል
እኔም እምነት አለኝ፣ ዋጋ የሚያስከፍል።

“እምነት ተስፋ ፍቅር” ”
መች ባንድ ላይ ሁኖ
ለሰው ልጅ ይሰጣል
በምነቱ የፀና፣ ድንገት ፍቅሩን ያጣል
ፍቅርሽን ሸኝቼው፣ ተስፋየን አባረርሁ
ከምነቴ ጋር ቀረሁ።

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#ስኬት

የህይወት ሩጫ የህይወት ዳገቱ
ተሮጦ ተሮጦ ሲመጣ ስኬቱ
ጨለማ ተገፎ ሲወጣልን ፋና
ህይወት ተስተካክላ መንገዱ ሲቀና
ያ ነው ቂማ ማለት ያኔ ነው ምርቃና

በስኬት መካደም ጠዋት የጀበና፡፡

🔘በፋሲል ሃይሉ🔘
#በር_እና_ሽንቁር

የፍላጎት ቤቱ ፣ የምኞት ማደርያው
እያደር ሲለጠጥ፣ ግድግዳና ጣርያው
ኗሪው ገላው ሰፋ፣ጎጆውም ገዘፈ
ለበር የታሰበው፣ ሽንቁር ሆኖ አረፈው።

🔘በፋሲል ሃይሉ🔘
#ፈገግታ_ነው_የሚቀድመኝ

የድሜ ነፋስ በገላየ ተረማምዶ ኮበለለ
ልቤን ክንዴን እያዛለ
ያቀፍኩትን እየቀማ፣ የያዝኩትን እያስጣለ።

እድል በኔ ጨከነ ስል፣ በምረት እጅ ደባበሰኝ
አንቺን ነጥቆ ከቅፌ ላይ፣ በትውስታ ደሞ ካሰኝ።

አስታወሰኝ
አስታወሰኝ

ወድያው ታይቶ፣ ጠፊ ኩርፍያሽ
ገራም ሳቅሽ፣ ልዝብ ልፍያሽ
ያለም ዘፋኝ የማያውቀው
የግልሽ ዳንስ ውዝዋዜ
ትውስ ትውስ ባለኝ ጊዜ
ከግር ጥፍሬ
እስከ ጠጉሬ
ደስታ ነው የሚያቀልመኝ
ያንቺን ነገር ባሰብሁ ቁጥር፣ ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ።

በሰጠሽኝ ጸጋ መጠን፣ የሰራሽኝ ጉድ አያልቅም
እኔ ባንች ትዝታ እንጂ፣ በተራቢ ቀልድ አልስቅም
ማፍቀር ማለት ለካ ፍቺው፣ መጃጃል ነው አውቆ ፈቅዶ
ከገደል ላይ መወርወር ነው፤ ተጨፍኖ በራስ ፈርዶ፡፡

እፈቀርኩሽ በየቀኑ፣ ተጃጃልሁኝ ደጋግሜ
ከገደል ላይ ተከስክሼ ፣ ሞተ ሲሉኝ አገግሜ
ያጥንቶቼን ርጋፌ እንደዛጎል ለቃቅሜ
እንደ ቆሎ፣ ጥርሴን ቅሜ
ያደረኩሽ ሲደንቀኝ፣ ያደረግሺኝ ሲገርመኝ
እፍረት ፀፀት አይደለም፡ ፈገታ ነው የሚቀድመኝ

አውቃለሁኝ ጊዜ ሂዷል፣ ታሪካችን ተጠቅልሏል።
በሄድንበት ጎዳና ላይ፤ የመለየት ዝናብ ጥሏል
በርምጃችን ምልክት ላይ፣ ረጃጅም ሰርዶ በቅሏል
ብቻ ሙሾ ቢደረደር፣ የሆነውን ላይለውጠው
ለንባየማ ፊት አልሰጠው።

ያሳሳምሽ ለዛ ቀርቶ፣ እንደ እንጎቻ እሚጥመኝ
የነከሽኝ የቧጨርሽኝ፣ አገርሽቶ ቁስሉ ሲያመኝ

ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ!!

🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
👍21
#ሴቷ_እመቤት

#በብርክቲ

ይህን አጭር ድርሰት የላከችልኝ የቻናሉ ተከታታይ ናት እናንተም አንብቡና አስተያየታችሁን በ @Bruktiaug ላይ አድርሷት ሌሎችም የራሳችሁ ፅሁፍ ካለ ላኩልኝ እያየን እናስተናግዳችኋለን።
----------------------------------------------------

"አቤት የኔ እድል እግዚኦ....!! አሁን እኔም ቆሜ እሄዳለሁ? እበላለሁ? እጠጣለሁ? እስቃለሁ? ኧረ ለስንቱ ቆየሁት መድሀኒያለም ኧረ በቃሽ በለኝ"
ፀሀይ ሁለት እጆቿን ጭንቅላቷ ላይ አድርጋ የእምባ ዶፍ ታወርዳለች።የልብ ስብራቷን መደበቅ ተስኗት ለቀናት; ለወራት; ብሎም ለአመታት አምቃ የያዘችው የማይጠፍ ቁስል ከአቅም በላይ ሆኖባት ሳታቋርጥ ትንሰቀሰቃለች።ሳግ እየተናነቃት ሽንፈትን የማይቀበለው ማንነቷ ሲይዛት በእንባ ታጅባ ፈገግ ለማለት ትሞክራለች። ወ/ሮ ሰብለም አይኖቿን ወደ መሬት አቀርቅራ የምትለውን ከመስማት ውጭ አንድም ቃል አልተነፈሰችም። ምንስ ልትል ትችላለችና? ፀሀይ አምቃ የያዘችውን መከራ ፀጥ ብሎ ከመስማት ውጭ ምንም ልታደርግላት የምትችለው ነገር አልነበረም።
"ሰብልዬ አስታሞ መቅበር ምነኛ መታደል መሰለሽ። ሰው አስታሞ ሲቀበር ሳይማ ቅናት ነው የሚለቅብኝ።ምናለ ትንሽ ቀን የሆነ ምልክት ቢያሳዩኝና አንዴ ከህክምናው አንዴ ከፀበሉ ይዤ በዞርኩ እላለሁ።ቢይንስ መልፍቴ ህመሙን ይቀንሰው ይሆን? እህህ!! ኧረ እንደው ቢጨንቀኝ ነው።" ፀሀይ እንባ የሞሏቸውን አይኖቿን ከዚያ እዚ እያንከራተተች "ሰብልዬ እናቴን እንዴት እንዳጣኋት ታውቂያለሽ? አንድም ቀን የህመም ምልክት ሳላይባት ምስኪኗ እናቴ በእርጎ አብልታ ስማ መርቃ ተከራይቼ ወደምማርበት ከተማ ሸኝታኝ በሳምንቱ እናትሽ ሙታለች ነይና ቅበሪ ተብሎ ሰው ተላከብኝ"

"አህህ እናትዬ እኔን.. እኔ አፈር ልብላልሽ" ሰብለ እናትነትን ታቃለችና ከልቧ አለቀሰችላት። የሰብለን ልብ መሰበር ያየችው ፀሀይ አይኖቿ እንባ ቋጥረው ፈገግ አለችና አይ ሰብልዬ የኔ ጉድ እንዲ በቀላሉ የሚያበቃ መስሎሻል።

"አባቴ ደግሞ....."
ገና ሳትጀምረው ጉሮሮዋን ዝግት አድርጎ አንደበቷን አሳሰረው።እንደምንም ተነፈሰችና ስቅ ስቅ ብላ አለቀሰች።
"አባቴ ...ለንግድ ስራ ወደ ከተማ በሄድኩበት ዛሬ አንዳትቀሪ ቤት መጠሽ ነው 'ምታድሪው ብሎ ለሰው ላከብኝ።እኔም በጊዜ ስራየን ጨርሼ ምግብ እንኳ ሳልቀምስ ጉዞ ጀመርኩ። እንዳሁኑ መኪና አልነበረም ወደ ቤት በእግሬ እየሄድኩ እያለ ልደርስ ትንሽ ሲቀረኝ አንድ የሰፈር ሰው መጣና 'ኧረ ፀሀይ ኧረ ጩሂ ኧረ ጩሂ' አለኝ። ምንነቱን ሳላውቅ ልቤ ስለተረበሸብኝ እየጮኩ ወደ መንደር ገባሁ። ምንድን ነው ኧረ ምን ሆናችሁ ስላቸው........"
ፀሀይ ትንፍሿ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ; ሳግ እየተናነቃት
" አባትሽ ሙቷል አሉኝ።.......
ሙቷል።.......
ቀለል አድርገው ሙቷል አሉኝ ሰብልዬ። ከእናት በላይ የሆነው አባቴ... የምሳሳለት...ከጠላት እንደ ወንድ ሳልተኛ የምጠብቀው አባቴ ጠዋት አይቼው ማታ ስመጣ ሞቶ ጠበቀኝ።"

ከንፈሮቿን በቁጭት እየነከሰች እንባዋን ትዘረግፈዋለች።
"አረርኩ። ከሰልኩ። አበድኩ። ግን ምን አመጣለሁ? ፈጣሪ አንዴ ይሁን ያለውን እኔ በምን አቅሜ እታገለዋለሁ?

"ከዛ ሰብልዬ ቤተሰቦቸን የጨረሰውን ሀገር አያሳየኝ ብዬ ብን ብዬ ጠፍሁ። ያኔ የኔ የምለው አይቼ የማልጠግበው የልጅነት ትዳሬ አብሮኝ ነበርና በሱ የማይቻለውን ቻልኩት። ቀስ በቀስ ቀልብ እየገዛሁ መጣሁ። መከራው ባይቀልልኝም ተላምጀው አብሬ መኖር ጀመርኩ። የውስጤን በውስጤ ይዤ ዋጥ አደረኩት።"

ፀሀይ ሽፋሽፍቷ ረግፈው ያለቀውን አይኖቿን በእጆቿ ይዛ በረጅሙ ተነፈሰች። .....ወደ መሬት አቀርቅራ በሀሳብ ጭልጥ አለች።

"ላያስችል አይሰጥ ፀሀይዬ እኔ እንግዲ ምን ላድርግልሽ ?" ሰብለ የተናገረችው ለሷም ቢሆን ዋጋ ቢስ ስለሆነባት ብዙ ሳትቀጥልበት ዝምታን መረጠች። ከረጅም የጭንቀት ዝምታ በኋላ ፀሀይ ካቀረቀረችበት ቀና አለችና
"ከዛ እርም የለኝ ምንም ቤተሰቦቼን ቢነጥቀኝ ወንድሞቼንና እህቶቼን ለማን ብዬ እተዋለሁ ብዬ በወጣሁ በብዙ አመቴ ተመልሼ ወደ ትውልድ ሀገሬ ዘመድ ጥየቃ ገባሁ። ከዘመዶቼ ጋር ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍኩ። ከብቸኛዋ ከእናቴ ልጅ ጋር የሆዴን ስቃየን ብሶቴን ሁሉ አወራሁ። እስከዛሬ ባለመምጣቴ ስንቱ ቀረብኝ ብዬ ሳልጨርስ መቼስ የተረገምኩ አደለሁ ለጥየቃ ሂጄ በተመለስኩ በሁለት ሳምንቱ 'ነይ ብቸኛዋ የእናትሽ ልጅ ሞታለች ' ብለው አረዱኝ።"
ፀሀይ ሰቅሰቅ ብላ አለቀሰች።

"አይቻታለሁ እኮ ደህና ነበረች። የተቀቀለ እንቁላል እህቴ ሳትበላ ሄደች ብላ ከተሳፈርኩበት መኪና ድረስ ሮጣ መጣ አብልታኛለች። ሰብልዬ ምንም አልሆነችም ነበር እኮ...... እንገናኛለን ብላኝ ነበር።"
" እህህህ" ፀሀይ አላስችል ቢላት ህመሙ ቢበረታባት ተነስታ ወዲያ ወዲህ ማለት ጀመረች።
"አየሽ ሰብልዬ ከስቃይ ላይ ስቃይ ከመከራ ላይ መከራ ያከናንበኛል። እንደው ምን ሰርቸ ይሆን እንዲ 'ምፈተነው? እንደው ምን በድዬ ነው? አልሰረኩ ጉልበቴን አንጠፍጥፌ አፈር ድሜ በልቼ ነው ምኖረው....አልገደልኩ የሰው ሀቅ አልበላሁ" ፀሀይ እጆቿን እያወናጨፈች የሆዶን ታወራለች።
"ምናለ ደግሞ በዚህ በቃሽ ቢለኝ ሆ!" እንደ መሳቅ አለችና
" አንች የተረገምሽ ብቻሽን ቅሪ ነው መሰለኝ የ ሁለት ልጆቼን አባት;ሁሉን ያየሁበትን ; ፈጣሪን ተመስገን የምልበት ብቸኛውን ምክንያቴን ትንሽ እንኳ ጉብታ በሌለበት መንገድ መኪና በላብኝ። ይመጣል ብዬ ከልጆቸ ጋር ስጠብቀው በወጣበት ቀረ። ደጉ ባሌ በእናትና አባቴ እንኳ የማልቀይረው ባሌ ብቻዬን ትቶኝ ሄደ። ተሰቃይተን ተምረን አድገን እንቁላል ሽጦ ትልቅ ደረጃ የደረሰው ባሌ እፎይ ብሎ ጠግቦ በሚበላበት ጊዜ መኪና ወሰደብኝ። ልጆቹን ናፍቆ ድካም እንኳ ሳይለቀው ወደ ቤቱ ሲመጣ ሳይደርስ በዛው ቀረ።......."ኧረ ያሁኑ ባሰኝ ሰብልዬ" ፀሀይ ምርር ብላ አለቀሰች።
"የገጠር ክንድ ለክንድ በሚባለው ነበር የተጋባነው። ገና በልጅነታችን...። አንድ ላይ ሆነን ቤተሰብ እየረዳን ትምህርታችንን ልንማር...። የምንኖርበት ገጠር ስለሆነ ወደ ሌላ ከተማ ሂደን ዶርም ተከራይተን ነበር የምንማረው። ሰብልዬ አንድ ቀን ቤተሰብ ሳያግዘን ነው የተማርነው። አንድ ዩኒፎርም ለሁለት እየለበስን; ቅዳሜና እሁድ እየነገድን ነበር ለዚህ የደረስነው። ስንት ስቃይና መከራ አብረን አሳልፈናል። እንደ ባልና ሚስት እንኳ አንድ ቀን ተኮራርፈን እንኳ አናቅም።" ፀሀይ ፈገግ አለችና "የሆነ ጊዜ ምን እንዳለኝ ታቂያለሽ? 'ፀሀይዬ ባልና ሚስት ግን ምን ሆነው ነው 'ሚጣሉት? ያውም በገንዘብ? ደሞዙን ታቀዋለች ከልጆቹ ውጭና ከአስፈላጊ ነገር ውጭ ምን ያደርገዋል?'...... ሁሉ ሰው እንደሱ መስሎት....። ስንት ወንድ ሁለት ቤተሰብ እንደሚያስተዳድር አያውቅ።"
" ማታ ማታ ደግሞ በሌሊት ይደውልና ሲያወራይኝ ነው በቃ 'ሚያድረው። አብረውት የሚኖሩ ጓደኞቹ እንደ አፍላ ፍቅረኛ ጀመረው ነበር የሚሉት። ወደ ሌላ ሀገር ለስራ ከተመደቡ ጀምሮ ከ ሁለት ጎደኞቹ ጋር አብረው ነበር የሚኖሩት።" ፀሀይ ሳይታወቃት ፊቷ አበራ። ግን ትንሽም ሳትቆይ እንባዋ መፍሰስ ጀመረ። "ሰብልየ ይህን ባሌን ነው ያጣውት።
ይህን ባሌን........."
ፀሀይ አንድ ትዝታ መቶባት ፈገግ አለች።
"ሰብልዬ ማስተርሱን ዩኒቨርሲቲ ገብቶ እየተማረ እራት ቆንጆ ስጋ ወጥና ጥብስ ተዘጋጅቶላቸው ብቻየን አልበላም ብሎ በላስቲክ ይዞት ማታ ሶስት ሰአት ቤት
👍2
መጣ። እስኪ ይታይሽ አልቸገረን ሁሉ የተሟላ ህይወት ነበር የምንኖረው። ግን የልጆቹ ነገር በስመአብ ቃላት እራሱ የለኝም።"
"የመጀመሪያ ልጃችንን ስወልድ እንደ ሴት; ዘመድ እንደሌለዉ ሰው ሆስፒታል አንድም ቀን ጥሎኝ ሳይወጣ ነው ያስታመመኝ። የተወለደችውን ህፃን ገላዋን አጥቦ ; ጡት እንኳን ሳይቀር በተኛውበት ቀስ አድርጎ አጥብቶ...... ኧረ ስንቱ ሰብልየ ስንቱን ልንገርሽ።"
በቤቱ ውስጥ ዝምታ ሰፈነ።

ከባድና የሚጨንቅ ዝምታ......።

ፀሀይ ካቀረቀረችበት ቀና ብላ እንባዋን እየጠራረገች
"በህይወት መኖር የነበረብኝ ሰው አይደለሁም ግን ለልጆቸ ስል እየኖርኩ ነው። አሁን እነሱ ብቻ ናቸው ተስፍዬ.....የነሱን የወደፌት ህይወት ለማስተካከል; የነሱን ደስታ ለማየት የማይቻለውን ችየዋለሁ። ሁሌም እነሱን የሰጠኸኝ ተመስገን እያልኩ እሱ በፍቃዱ እስኪወስደኝ እጠብቃለሁ።
እኖራለሁ...።

💫አለቀ💫

ላስተያየቶ 👉 @Bruktiaug
👍2
#ማንነት_ቀረጻ

በ'ቅፌ ያደገች ትንሿ ድመቴ
ስብዕናዬን ቀርጻው ሆና ማንነቴ
ምን አንደበት ኖሮኝ ከማንስ አወራለሁ
ፍቅር ሲያቃጥለኝ ጭራዬን እቆላለሁ፡፡

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
#አልቦ_ብሕትውና

ለካስ ብሕትውና ብቻነት አይደለም
የለም ብቻ መኾን ብቸኝነት የለም
ባ'ለም ውስጥ እያለ ወዳጆች ከበቡት
ካ'ለም ተነጠለ መላእክት አጀቡት
ከመላእክት ሲርቅ አጋንት ቀረቡት፡፡

🔘በዉቀቱ ስዩም🔘
#ፍፃሜ_ዓለም

ያ'ዳም ልጆች ክፋት
በዝቶ ሲያስጨንቃት
ልክ እንደ ቅሪላ አብጣ አብጣ ሲበቃት
ፈንድታ ታርፋለች ብለን ስንጠብቃት
ዓለም አለሁ ብላ እኛን አዘናግታ
እንደ አንኳር በረዶ
አሐቀች ቀስ በቀስ
እጃችን ላይ ሟምታ።

🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
#የወርቅ_በርጩማውን_ፍስጋ


#ክፍል_አንድ


#በእንዳለጌታ_ከበደ


(በ1996 የተፃፈ ነው ውድ አንባብያን አንዳንዴ አሁን ላይ ቋጥኝ የሚሆኑብን ነገሮች ቀለል ተደርገው ሲገለፁ ግር እንዳይላችሁ መልካም ንባብ።)
----------=======----------========

የቋንቋ መምህርት ነኝ ...

አንዳንድ ሰው፣ ጥዋት ከእንቅልፉ እንደነቃ 'ምላሱ ላይ የገባ'ን ዘፈን ቀኑን ሙሉ ሲያንጎራጉረው ይውላል፡፡
በእኔ አእምሮ ውስጥ ደግሞ ጥዋት የሰረገ ብሂል አብሮኝ ውሉ ያመሻል፡፡ ዳኛቸው ወርቁ ከፃፈው «አደፍርስ»
ልቦለድ መፅሐፍ ላይ ያገኘሁት አንድ አገላለጽ በውስጤ ታትሞ ቀርቷል፡፡

«... ያቺ በሌላዋ አገር የምትጣደፈው፣
የምትፍለቀለቀው፣ የምትንቦለቦለው ሕይወት እዚህ እፎይ ብላለች። በእርጋታ ፣ በዝግታ ታምማለች በተገማሽረ መስክ ውስጥ እንደሚብሰከሰክ ውሃ ... »

ሰሞኑን ከምንጊዜውም በላይ «ስለሀገር ጉዳይ» ያሳስበኝ ጀምሯል።የብሶቴ ምንጭ ግን ይሄ ብቻ አይደለም። ምን እንደሆነ እኔም አላውቀውም።

ሰራተኛዬ ዘሪቱ ልትሄድብኝ ነው ብዬ ስለሰጋሁ ሳይሆን አይቀርም። ወይም ደግሞ የታናሽ እህቴ የአስቴር እጮኛ 'አሜሪካ ሄድኩ' ይበል እንጂ ደቡብ አፍሪካ ገብቶ ቀበቶ በመሸጥ እንደሚተዳደር ከሚቀርቡት ሰዎች
በመስማቴም ይሆናል ወይም ደግሞ ባለቤቴ ነፍሱን ይማረውና ይሰራበት የነበረው ድርጅት 'ለሟቹ ቤተሰቦች' ብሎ የሠጠኝን ገንዘብ ምናባቴ አድርጌ የረባ
ነገር እንደምፈይድበት ግራ ስለገባኝ ይሆናል። ብቻ የሆነ ነገር ሆኛለሁ፣ ወይም ልሆን ነው።

ዘሪቱ ከሄደችብኝ ቤቴን ማን ቀጥ አድርጎ
ይይዝልኛል? ሁለቱ ልጆቼ ትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ እፈልጋለሁ። የትምህርታቸው ውጤት ዝቅ ቢል የባለቤቴ መንፈስ እንደሚከፋብኝ ስለሚሰማኝ ብቻ አይደለም። አለጊዜያቸው ለምን ከሰውነት ተራ
ይውጡ? እኔ እናታቸው እስካለሁ ድረስ! ... የስምንት ዓመት ወንድና የአምስት ዓመት ሴት ልጆች ያለ አባት
ማሳደግ ይከብድ ይሆን? አላውቅም። . .
ዘሪቱ እኔ ቤት በሰራተኛነት ተቀጥራ መስራት ከጀመረች አራት አመት ሆኗታል፡፡ ያኔ አስቴር ወደ ቤይሩት ለመሄድ ጓዝ ጉዝጓዟን መጠቅለል በጀመረችበት ሰሞን ነው ዘሪቱን ያገኘኋት- ያለተያዥም የቀጠርኩዋት። አመንኩዋት- ታመነችልኝም!

«ባለቤቷን ስለማታምነው ነው ይህቺን መልከ ጥፉ፣ይቺን ከጨለማ በባሰ ሁኔታ የጠቆረች ሴት ለሰራተኝነት
የቀጠረችው! . . .» ተብሎ ተወራ፡፡

ባለቤቴ ሾፌር ነበር፡፡ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ የሥራ አስኪያጁን መኪና ነበር የሚነዳው። ስለ አደጋወም ሆነ ሊሞት ሲል አይቼበት የነበረውን ስቃይ
ላለማስታወስ ለራሴ ቃል ከገባህ: ሁለት ዓመት አልፎኛል።

ጠመዝማዛወና ' እንኩዋንስ ሰወ ዝንጀሮ
አይወጣውም' የተባለለት የአላማጣ መንገድ ለስንቶች ህይወት ማለፍ ተጠያቂ ሆኖ ይሆን?! ... አለማሰብ
ነው የሚሻለው!
*
ከወራት በፊት አንዱን ቀን ፡ የባለቤቴን
የኢንሹራንስ ጉዳይ ዳር ለማድረስ ስሯሯጥ ደካክሞኝ ነበር የዋልኩት። መላ ሰውነቴ ውሃ ውስጥ እንደከረመ
ሳሙና ተልፈስፍሶ ነበር፡፡

« እቴትዬ አለችኝ ዘሪቱ።

« አቤት!»

« አይታዘቡኝና አንድ ነገር ባስቸግርዎትስ?!»

« ምን ሆነሻል?›

«ለእኔ የእርስዎን ያህል ክብር ሰጥቶ የሚያነጋግረኝ የለም! . . ከዚህ ቤት ወጥቼ ሌላ ስራ ባልጀምር ደስ ይለኛል።
ግን የነር ጉዳይ ሆኖ . . ."

«ደሞዝ አነሰኝ ለማለት ነው ይህ ሁሉ ዳርዳርታ?»

ደንገጥ ብላ «ኧረ እቴትዬ ክፍያው አያንሰኝም! ...ግን ታናሽ ወንድሜ ገጠር ከሚሆን እዚህ ሆኖ ቢሰራ ይሻለዋል:: እኔስ እስከመቼ ድረስ የሰራሁትን ሁሉ
ጥቂት ብር ብቻ አስቀርቼ ወደነሱ ልላክ?! . . .)

«ምንድነው የወንድምሽ ስራ?»

«ምንም!››

«እንዴት ምንም?!»

«በአምልኮ ነው ጊዜውን የሚያሳልፈው!»

«በአምልኮ?»

«አዎ! በተወለድኩበት አካባቢ መድረሻውን የማላውቀው አንድ ወንዝ አለ ... 'የዌራ እንደት' ብለው የሚጠሩዋት አምላክ ትኖርበታለች:: ከክፉ ነገር እንድትጠብቃቸው ... ከብቶቻቸውንም በውሃ ሙላት
ከመወሰድ እንድትጠብቅላቸው፣ ከክረምት በቀር ከዓመት እስከ ዓመት
ይገብሩላታል፡፡ ለዌራ እንደት' ክብር
ተብሎ በግ ይታረዳል፡፡ በአዝመራ ጊዜ ነጭ ገብስ በስሟ ይዘራል፡፡ ስብሉ በደረሰ ጊዜ ከሌላ ጥሬ ጋር ሳይደባለቅ
በጥንቃቄ ይቀመጣል፡፡ የግብር ወቅት ሲደርስ 'ለዌራ እንደት' ይወሰድላታል፡፡ ኧረ ብዘ ነገር ነው የሚደረግላት» አለችኝ ዘሪቱ፡፡

«እና ወንድምሽ ምን ለማግኘት ነው ጣዖቷን የሚያመልካት?» አልኩዋት ራሷን ከእምነቱ ተከታዮች ለማራቅ የምታደርገውን ጥረት ከንግግሯ እየተረዳሁ።

«የወርቅ በርጩማ ለማግኘት»

«አልገባኝም»

« ... ወንዙ ውስጥ ግዙፍ የሆነ የወርቅ በርጩማ አለ ይላሉ ወንዙ እምብርት ላይ ሁልጊዜ የሚሽከረከር ነገር አለ፡፡ እሱጋ ነው ያለው ይላሉ:: ውሃው ውስጥ
ገብተው ለማውጣት የሞከሩ ሁሉ ህይወታቸው አልፏል፡፡ዋናተኞችም ቢሆኑ! ... ከልብ 'የዌራ እንደትን ያመለከ
ሰው የወርቅ በርጩማውን ለግሉ ያደርገዋል ተብሎ ይታመናል፡፡»

«አይ አለማወቅ! ይሄማ ከሁዋለኞች ሁሉ ሁዋላ የሚያስቀር አመለካከት አይደል?»

«እንግዲህ፣ እንደዚያ ነው የሚያምኑት - ወንድሜ ደግሞ የሁላችንም ህይወት ሊለወጥ የሚችለው፣
'በርጩማወ' በእጄ ሲገባ ነው ብሎ ያምናል፡፡የወገኖቹን የእጅ ሙያ ወርሶ ልክ እንደናቴ ወንድሞች መንቀሳቀስ ሲገባው! ... በዚያ ላይ በቅርቡ ማግባት
ይፈልጋል»

«እና አሁን ምን አስበሻል? .. .»

«እዚህ ይምጣ፡፡ እንደኔ የማታ ትምህርት ጀምሮ ቁጥርና ፊደል ይለይ! የስራ ሰው ይሁን እስኪደራጅ ድረስ ብዙ ጊዜ ስለሚፈጅበት ልረዳው እፈልጋለሁ፡፡ ለሆዱ የቀን ስራ እየሰራ ለራሱ ይወቅበት!
የአንድ ወር ደሞዝ ቅድሚያ እንዲሰጠኝ ነወ፡ የምለምንዎት....."

ደስ አለችኝ! « ብርቱ ነሽ እኮ የኔ ልጅ! እኔ ደግሞ አንቺን አግዛለሁ» አልኳት።

አቤት! ያን ሰሞን ይሄ «የወርቅ በርጩማ» ነገር እንዴት መዝናኛ ሆኖን ነበር? ለእህቴ ለአስቴር በስልክ
ስነግራት «አትቀልጅ! መጥቼ እድሌን ልሞክር እንዴ? ስትል ቀለደች፡፡ እጮኛዋ ግን ምንም ስሜት አልሰጠውም።

የእህቴን እጮኛ የእህቴን ያህል አውቀዋለሁ።ከወር በፊት፣ እኔ ወደማስተምርበት መለስተኛ
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መጥቶ፣

"ውጭ አገር ልሄድ ነው!» አለኝ «አሜሪካ . . .)ደነገጥኩ፡፡ «እናንተ ልጆች ምን እየሆናችሁ ነው?! አብዳችኋል? አስቴር ቤይሩት ሄደች:: የሄደችው
የሁለታችሁን የተሻለ መኖር የሚያስችላችሁን አቅም ለማጎልበት ነው።ያለን ይበቃናል ፍቅራችን ያኖረናል ማለት ሲገባህ ያንተም ልብ እንደ ጠበል ዕቃ ውጭ ማደር ይጀምር?!...ብዬ ተቆጣሁት።

ጥቁር ድንጋይ ላይ ውሃ የማፍሰስ ያህል ነበር! አስቴርና እጮኛዋ ከተማሪነት ዘመናቸው ጀምሮ አብረው ሲሆኑ መለያየት የሚባል ዕጣ፣ አለመስማማት የሚባል ጣጣ በሁለታቸው መሃከል መንገድ አልዘረጋም...አንድ
ቀን አስቴር 'እቴት፣ ወደ ቤይሩት ልበር ነው።የምነግርሽ እንድታውቂው ነው:: መሄድ እንዳለብኝ ከወሰንኩ በኋላ ጓደኛዬን ለማሳመን ብዙ ሰዓት ፈጅቶብኛል፡፡ ብዙ ቀናት ልበልሽ እንጂ!
እና ላንቺ እያማከርኩሽ ሳይሆን ውሳኔዬን እየነገርኩሽ ስለሆነ አለመሄድ እንደሚሻል በማሳመን እንዳታደክሚኝ አለቺኝ።

'ገንዘብ ከየት ይመጣል አስቴር?!'

'ለመሄጃ?!'

'አዎ!'

'ጓደኛዬ ከወላጆቹ የወረሰውን ቤት በኮንትራት አከራይቶታል፡፡ ከእሱ እወስዳለሁ።የምሄደው ለአንድ
ለሁለት ዓመት ያህል ነው።ሰራርቼ
👍3😁1
እመለሳለሁ...አለችና ሄደች።

አራት ዓመት ሆናት።

አሁን ደግሞ እሱ - በርግጥ ፈገግ ብሎ ነበር የሚያናግረኝ፡፡ ያ ፈገግታ የእሱ እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡የእሱ አይደለም:: የእህቴ ነው። ከአስቴር የኮረጀው ፈገግታ ነው- ፊቱ ላይ እየተነበበኝ ያለው! አ! አ!

የአስቴርም አይደለም. . .ፈገግታውን ፊቱ ላይ ለብዙ ደቂቃ አቆይቶት ነበር፡፡ የተሸነፈ ሰው- ማለት አሸንፋለሁ ብሎ በደጋፊዎቹ ፊት ሲፎክር የቆየ ሰው ከፍተኛ በሆነ የነጥብ ብልጫ ሲሸነፍ ፊቱ ላይ የሚታየው አይነት ፈገግታ ነው ያየሁበት። አስቴር ወደ ቤይሩት ልትሄድ
ስትል ስለ ሀገሯ ስታወራኝ የነበራት አይነት ፈገግታ...ተስፋ የቆረጠ - ሀፍረት የበዛበት ፈገግታ! እንደ ልቡ ለመሆን አቅም ያነሰው!

«እና ልትሄድ ነወ፡ ወሰንክ?!» አልኩት
የሚያወራውን በፅሞና ስሰማ ቆይቼ!

«አዎ! እስኪ ልሂድና ይዤ ልምጣ!»

«ምን?»

«ያንን የዘሪቱ ወንድም ከልብ የሚያመልከውንና የሚፀልይበትን የወርቅ በርጩማ!»

ሀዘን የሞላው ፈገግታ ተለዋወጥን፡፡

ወደ አሜሪካ ሳይሆን ወደ ደቡብ አፍሪካ መሄዱን ከሚያውቁት ሰዎች መረጃ ያገኘሁት ዛሬ ነው! አስቴርንም እንደኔ ዋሽቷት ይሆን?! ማሰላሰል ቀጠልኩ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1