#ያው_እንደኛው_ናቸው
በሰማይ አዋፋት፣ አይዘሩም አያጭዱም
አገር አቆራርጠው፣ ሲራራ አይነግዱም
ግን ከኛ ኑሮ ምን ልዩ አረጋቸው?
ለእፍኝ እድሜ ሲባል፣ የሳር ጎጆ ማልማት
ሞላሁ ለማይል ሆድ፣ እህል በመሻማት
ያው እንደኛው ናቸው።
ያለም ከበርቴዎች
በፈጣን ጀታቸው፤ ሰማዩን ቢገምሱም
ርካታ ካለበት፣ ቀድመውን አይደርሱም
ሻርክ ተፈናጠው፣ ከባህር ቢጠልቁም
መንኰራኩር ጋልበው፣ ከጠፈር ቢመጥቁም
እኛን ከሚያሰጋን፣ አንድ ርምጃ እይርቁም።
የምድሪቱ ጌቶች
ለሰው ዐይን ሞልተው
ትልልቅ ቢመስሉም፣
በኩራት ተነፍተው
ተራራ ቢያከሉም፣
ከተሸከሸኩ፣ አንድ እፍኝ አይሞሉም።
ፍትወትና ፍራት፣ የሚጎትታቸው
ያው እንደኛው ናቸው፣
ባለስትንፋስ ሁላ፣ ቢታይ ተመንዝሮ
በቁመት አይበልጥም፣ ጎልያድ ከስንዝሮ
ለየቅል መሳዩ፣ ያው ነው ዞሮ ዞሮ።
በሰማይ አዋፋት፣ አይዘሩም አያጭዱም
አገር አቆራርጠው፣ ሲራራ አይነግዱም
ግን ከኛ ኑሮ ምን ልዩ አረጋቸው?
ለእፍኝ እድሜ ሲባል፣ የሳር ጎጆ ማልማት
ሞላሁ ለማይል ሆድ፣ እህል በመሻማት
ያው እንደኛው ናቸው።
ያለም ከበርቴዎች
በፈጣን ጀታቸው፤ ሰማዩን ቢገምሱም
ርካታ ካለበት፣ ቀድመውን አይደርሱም
ሻርክ ተፈናጠው፣ ከባህር ቢጠልቁም
መንኰራኩር ጋልበው፣ ከጠፈር ቢመጥቁም
እኛን ከሚያሰጋን፣ አንድ ርምጃ እይርቁም።
የምድሪቱ ጌቶች
ለሰው ዐይን ሞልተው
ትልልቅ ቢመስሉም፣
በኩራት ተነፍተው
ተራራ ቢያከሉም፣
ከተሸከሸኩ፣ አንድ እፍኝ አይሞሉም።
ፍትወትና ፍራት፣ የሚጎትታቸው
ያው እንደኛው ናቸው፣
ባለስትንፋስ ሁላ፣ ቢታይ ተመንዝሮ
በቁመት አይበልጥም፣ ጎልያድ ከስንዝሮ
ለየቅል መሳዩ፣ ያው ነው ዞሮ ዞሮ።