አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
513 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
‹‹አዎ..ሚስቴ ያቺን የመሰለች ቆንጆ ልጅ ያለችበት ግቢ አልገባም ብላ እያስቸገረችኝ ነው… አሁን እሷን ልለምን እየሄድኩ ነው፡፡እሺ ካለቺኝ ጥሩ ..እምቢ ካለችኝ ግን ይሄ የሆነው በአንቺ ምክንያት ስለሆነ ተመልሼ አንቺኑ ነው የማገባው››ብሎኝ እርምጃውን አፈጠነና መኪና ውስጥ ገብቶ ወጥቶ ሄደ…፡፡
ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳች፡፡እኔ በድንዛዜና  በተመስጦ እያዳመጥኳት  ነበርና፤ በመነሳቷ ግራ ተጋባሁ‹‹ምነው…?››
‹‹.ሰላሳ ደቂቃው አለፈ…ወደቤት ልሄድ..ቀጣዩን ደግሞ ሰሞኑን ነግርሀለው››አለችኝ፡፡
‹‹ልክ እሱ አድርጎሽ እንደነበረው አሁንም አንቺ እኔን እያደረግሽ ነው››ስል  አልጎመጎምኩ፡፡
‹‹አይ ዶ/ር..የእሱማ ከምንም አይገጥም ….ጮርቃውን ወጣትነቴን እና የዋህ አፍቃሪነቴን ገና በመጀመሪያው ቀን ተረድቶ ተጫወተብኛል…በል ቸው፡፡››
በዛው ተለያየን፡፡ቀጥታ ወደእማዬ ቤት አመራሁ…..ደግሞ እዛ ምን ይገጥመኝ ይሆን..እርግበ  አሁንም እዛ ትሆን ወይስ ወደዘመዶቾ ሄዳለች?


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
15👍15
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ ሰባት


“እያንዳንዱ ጓደኝነት ውስጥ ትንሽ ትንሽ ጠላትነት አለ!”

ሃይማኖት!

እንደ እኔ መልኳ ብዙም ለማይስብ ሴት፣ ጥሩ አፍቃሪ ማግኜት ከረዥም ዛፍ ላይ በአጭር ቁመት ፍሬ ለማውረድ እንደመሞከር ነው “ሴትነት” ብቻውን በቂ አይደለም፤ ፍሬውን ማውረጃ አንዳች ዘንግ ያስፈልጋል፡፡ ፍሬው ላይ የሚደርስ የትምህርት ፣ የገንዘብ ፣ የጥሩ ምላስ፣ ባለቤት መሆን ያስፈልጋል፤ አልያም ቁመትን የሚያረዝም የጥሩ ቤተሰብ መሰላል ላይ መቆም፡፡ ይኼን ዘንግ በእጄ እስክጨብጥ ስንቱ ያስጎመጄኝ ፍሬ የወፍ ሲሳይ ሆነ፡፡ ተስፋ አስቆራጭ መልክ ነው ያለኝ፡፡ በዚያ ብኩለው በዚህ አስቀያሚነቱ እየባሰበት የሚሄድ፡፡ ምንሽ ነው የሚያስጠላው? ቢሉኝ አላውቅም፤ ግን እንዲሁ መልኬ ቆሜ እያዩኝ እዚያው በቆምኩበት የሚረሳ ዓይነት ነው፡፡ ሰው ካልታወሰ ምኑ ይፈቀራል? የመፈቀር ተቃራኒው መጠላት አይደለም፤ መረሳት ነው፡፡ ማንም የሚያፈቅረውን አይረሳም፤ እኔ ግን ሰዎች አእምሮ ውስጥ በትዝታ መዝገብ እንዳልጻፍ የተረገምኩ ይመስለኛል፡፡ በዚህ እና በሌላ ሌላ ብዙ ምክንያቶች ስለ ራሴ ከማሰብ ይልቅ፣ ስለሌሎች ጉዳይ በማያገባኝ ገብቼ መፈትፈት እወዳለሁ፡፡ ሌሎች ላይ ለመድረስ ሳይሆን ከራሴ ለመሸሽ።

አብሮ አደግ ጓደኛዬ ማኅደረን ጨምሮ የሚቀርቡኝ ሁሉ “ለግጥምና ሥነ-ጽሑፍ ሟች ነሽ' ይሉኛል፣ አይደለሁም። የሚሞትለት ነገር ጠፋ እንዴ? እንዲያውም ግጥም የሚሉትን ነገር አልወድም፤ ምኑም አይጥመኝም፡፡ ግጥም በተለይ ረዥም ግጥም፣ የጅል ለቅሶ ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ ገጣሚዎች በአቀራረባቼው እና ቀለል አድርገው በሚያነሱት ሀሳብ ያስቁኛል፣ ሳቅ ማን ይጠላል? በተለይ እኔ ሳቅ በሁለት ምክንያት እወዳለሁ...የመጀመሪያው ሳቅ ያው ሳቅ ስለሆነ ነው፣ ሁለተኛው ግን ጥርስሽ ያምራል ስለሚሉኝ ስስቅ እኩል ሁለት ደስታዎችን ስለማጣጥም ነው፤ በአንድ የሳቅ ጠጠር፣ ሁለት የደስታ ወፍ እንደማውረድ። የሆነ ሆኖ እንደዚያ ዓይነት ግጥሞችን፣ ፍቅረኛዬ ቶማስ ዝርው፣ተራ፣ ገለባ ናቸው ይላቼዋል፡፡ እሱ ራሱ ዝርው ተራና ገለባ የሆነ ልጅ ነበር፡፡ “ትንሽ ካላሳሰቡሽ ምኑን ግጥም ሆኑ?'' የሚለው ነገር አለ (ግድ ካላሰብኩ ብሎ ነገር!) አስበን የምንደርስበትን እዚያው አስበው ፍሬ ነገሩን ከነገሩን ምን አደከመን? ዘመናችን የጥድፊያ ነው፣ ቁጭ ብሎ ለመቆዘም ፋታ አይሰጥም። ሥራችን ነው ካሉ፣ እዚያው ቆዝመውም ይሁን ተጨንቀው፣ ሊሉን የፈለጉትን በአጭርና በግልጽ ቋንቋ ይንገሩን። ቢሆንም ፍቅረኛዬ ቶማስ የተመረቀው በሥነ-ጽሑፍ ምናምን ነውና በዚህ ጉዳይ ገፍቼ አልከራከረውም፡፡ ለነገሩ በምንም ጉዳይ አልከራከረውም። ቶማስ ውስጡ የተቀበረ ቁጭት አለበት፣ ሰዎች ሲጨበጨብላቼው ይበሳጫል። አንዳንዴ ደግሞ ስም የሌለው ገጣሚ በታዋቂዎቹ መካከል ግጥም ሲያቀርብ እና ከተመልካቹ ቀዝቀዝ ያለ ጭብጨባ ሲቼረው፣ ቶማስ ረዢምና ደማቅ ጭብጨባ ያጨበጭባል፣ ሊቆም የሚያዘግመው ጭብጨባ እንደገና ነፍስ ይዘራል፡፡ ቶማስ ለታዋቂ ገጣሚያን ጥላቻ እንዳለበት እረዳለሁ። ገጣሚያን ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ታዋቂ ሰው ያበሳጨዋል፤ በተለይ ኢትዮጵያዊ፣ ግን ለምን ብዬ አልጠይቀውም ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ ግጥም እንደሚጽፍ ቢነግረኝም፣ በሦስት ዓመት ቆይታችን አንድም _ መስመር ጽፎ ዓይቼ አላውቅም፡፡ _ አይደለምና / ግጥም፣ መደበኛውን መጻፍና ማንበብ መቻሉ እስኪያጠራጥረኝ፣ እጁ ላይ ብዕርም መጽሐፍም ዓይቼ አላውቅም፤ ግድ አይሰጠኝም፡፡

ቶማስ ጋር እንዴት ፍቅረኞች ሆንን? በፍቅሩ ወድቄ ነው? አይደለም፡፡ ፍቅረኛ የሆንበት ብቼኛ ምክንያት ታክሲ ውስጥ ገብቼ ጎኑ ስቀመጥ ገና በወጉ እንኳን ተደላድዬ ሳልቀመጥ “ኦህ! ጥርስሽ እንዴት ያምራል!'' ስላለኝ ብቻ ነው፡፡ ዞር ብዬ አዬሁት፣ ብጉራም ነው እንጂ መልኩ ደህና ነው “አመሰግናለሁ” ብዬ ልዘጋው እቺል ነበር፡፡ ግን በሕይወቴ እንደ ፀሐይ ግርዶሽ በስንት አንድ ጊዜ ያውም ከማያውቀኝ ወንድ የሚሰነዘር አድናቆት እንደ ተራ ነገር ማለፍ የምችል ልጅ አልነበርኩም። አድናቆት ያሳሳኛል፤ የሚያደንቁኝ ሰዎች ጻድቃን ነው የሚመስሉኝ፡፡ ፈገግ ብዬ፣ “ገና ከመግባቴ ...የት አዬኸው ጥርሴን?'' አልኩት፡፡ ይኼ ፈገግታዬ ድፍረት ሰጥቶት ወሬ ጀመርን፡፡ እና ልክ እንደፈላስፎች በቀልድ የሌለውን ፂም እየጎተተ “ታክሲ ውስጥ ከመግባትሽ በፊት ጓደኛሽ ጋር ስትሰነባበች ፈገግ ብለሽ አልነበረምን?'' አለ፡፡ የእውነት አሳቀኝ። እጁን ዘርግቶ “ቶማስ እባላለሁ' አለኝ፡፡ ጨበጥኩት፤ የሴት እጅ እንኳን እንደዚያ አይለሰልስም፡፡ የእጁ ልስላሴ የተለዬ ምቾት ይፈጥራል፡፡ እንዲህ ተዋወቅን፡፡ የዚያን ቀን ስልኬን ሲጠይቀኝ አልከለከልኩትም፤ ግን ይደውላል ብዬ አላስብኩም ነበር፡፡ ላግኝሽ ሲለኝ አልከለከልኩትም፣ግን ቀጥሮኝ ይቀራል ብዬ ፈርቼ ነበር። ልሳምሽ ሲለኝ አልከለከልኩትም፣ ልተኛሽ ሲለኝ አልከለከልኩትም...አብረን የተኛን ቀን አለቀሰ፡፡ እስካሁንም ያ ነገር አንጀቴን ይበላኛል፡፡ እዚህ የጡት ዘር ያልፈጠረበት ባዶ ደረቴ ላይ ተለጥፎ አለቀሰ፡፡ ምንም ነገር ከልክዬው አላውቅም፡፡ እንደማያፈቅረኝ አውቃለሁ፣ እኔም አላፈቅረውም ነበርና ግድ አልነበረኝም። ሥራ አልነበረውም፤ ሳውቀው ጀምሮ ሥራ አልነበረውም። ሥራ ሲፈልግም አይቼው አላውቅም፤ እሱም ያን ያኽል አሳስቦኝ አያውቅም፡፡ እንዲያውም የሻይ እያልኩ በየወሩ የተወሰነ ብር እሰጠው ነበር፡፡ ይኼ ነገር ውለታ ሆኖበት ይሁን ወይም ሌላ መሄጃ ስለሌለው እንጃ እስከ መጨረሻው ከእኔ ጋር ነበር፡፡

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነጽሑፍ ተመርቆ ለሦስት ዓመት ሥራ ሳያገኝ ቆይቷል፡፡ እንዴት እንደሚኖር ለራሴም ይገርመኛል፡፡ግን ጠይቄው አላውቅም፡፡ እየቆዬ ሲገባኝ እሱም ከእኔ በባሰ ሁኔታ የተገፋና በራስ መተማመኑ የተንኮታኮተ ልጅ ነበር፡፡ ልዩነታችን ይኼን መገፋታችንን የተቀበልንበት መንገድ ላይ ነበር፡፡ እኔ ወደ ውስጤ ኖርኩት፤ እሱ በጥላቻ፣ በጠብ፣ በማማረር እና ሌሎችን በማናናቅ ኖረው። መሠረታዊ ችግራችን ግን ያው መገፋት ነበር፡፡ ከጓደኛዬ ማኅደረ ሰላም ፍቅረኛ አብርሃም ውጭ ቶማስን የሚወደው ይቅርና አብሮት ለደቂቃዎች መቀመጥ የሚፈልግ አንድም ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ የሰው ዘር በሙሉ ክንፍ ያለው መልአክ ነው ብላ ልትከራከር የሚቃጣት ጓደኛዬ ማኅደረ እንኳን ቶማስን አትወደውም ነበር፡፡ “አልፈሽ ልትወጂው ብትሞክሪ እንኳን ዙሪያውን በእሾህ አጥር የታጠረ ልጅ ነው፣ በዬት ሽንቁር አልፈሽ እንደወደድሽው እንጃልሽ'' ትለኛለች፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰው ጋር ነው የኖርኩት። “በፍቅር”፡፡ የሆነ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የሥነ-ጽሑፍ ዝግጅት ላይ እንደ ፍቅረኛ ክንዴን ይዞ የወሰደኝ ቶማስ ነበር። ለእኔ ይኼ ማለት ብዙ ነገር ነው፡፡ ለቅሶ ቤት ይውሰደኝ፣ ሰርግ ቤት ጉዳዬ አልነበረም፤ ሳያፍርብኝ እጄን ይዞ ሰው መኻል የሚገኝ ሰው ከጎኔ መኖሩ ብቻውን የሚሰጠኝ ስሜት የተለዬ ነበር። ከዚያ በኋላ ብዙ የሥነ-ጽሑፍና የግጥም ዝግጅቶች ላይ ቶማስ ጋርም ይሁን ብቻዬን እገኝ ነበር። እንዲሁ የግጥም ምሽቶች ላይ መገኜት የሆነ ዘመናዊነት ነገር አለው አይደል?! የሥዕል ኤግዝቢሽን፣ የሥነ-ጽሑፍ ምሽት ምናምን? በተለይ “ምሽት'' የሚለው ደስ ይላል። "Maslow's hierarchy of needs" እንደሚነግረን የሰው ልጅ የዕለት ጉርሱን የዓመት ልብሱን ካገኜ በኋላ ጥጋብና ብርዱን ከመከላከል ባለፈ የመታዬት፣ የመወደድ ፍላጎቱን ለማርካት ይታትራል። ምንም ደሃ አገር ብንኖር
👍418
ያለችንን ለማሳዬት ጥምቀትን መጠበቅ የለብንም። መቼም እንዲህ እንዲህ ያሉት ቦታዎች እንይ ብሎ ለመታዬት የሚሄደው ባይበዛ ነው? ምኔ ነው ተረት ተረት? ምኔ ነው ግጥም? ምኔ ነው ሐሳብ? ጥበብ ቅብርጥስ...እነዚያ በቁማቼው ጫጭተው፣

የተላመጠ የወይራ መፋቂያ ከመሰሉ ገጣሚ ተብዬዎች ምን ጠብ ሊል?...ተጠበ ተጨንቆ ትልቅ ሥራ እንደሠራ ሰው ከመድረክ ወርደው ሲጋራቼውን በላይ በላዩ ሲያቦኑ እና መጠጣቼውን ሲገለብጡ ደሜ ይፈላል፡፡ በእርግጥ ከፍቅረኛዬ ቶማስ ይሻላሉ፤ እሱ እንዲሁ በመቆዘም ብቻ፤ ደክሞ የሚውልና የሚያድር ድብርታም ነበር። ሲጋራና መጠጡም አይቀርበት፡፡ አንድም ቀን ይኼን ሱስህን ቀንስ አልያም አቁም ብዬው ግን አላውቅም፡፡ እንዲያውም የሚያስፈልገውን ገንዘብ እሰጠው ነበር፡፡ ሳንባውና ጉበቱ ከስሎ ቢሞት ግድ አልነበረኝም፡ በእነዚህ ምሽቶች ከብዙ ታዋቂ ደራሲ እና ገጣሚ ሰዓሊ እና ምንትሶች ጋር ተዋውቂያለሁ። የብዙዎቹ መጽሐፎች አሉኝ፡፡ አብሮ ሻይ ቡና ማለቱ ከተራው ሕይወት ትንሽ ከፍ የማለት ስሜት አለው፤ አለ አይደል በቀጥታም ባይሆን “እንትናን አውቀዋለሁኮ!”… “ኧረ ባክሽ? ይኼ እንትን ፊልም የጻፈው? የእንትን መጽሐፍ ደራሲ" ...መባባል የሆነ ስሜት አለው፡፡ በተለይ ለእኔ ብዙ ነው ትርጉሙ፤ ሰው ከማያውቀው ሕመሜ ባይፈውሰኝም እንዳገግም ረድቶኛል፡፡ መልከ ጥፉ ነኝ፣ እራሴን ጠንቅቄ አውቃለሁ። መልኬ ወንዶችን አይስብም። ከእግሮቼና ከጥርሴ በስተቀር ምኔም ምኔም ዕይታ አይስብም፡፡ በእርግጥ ጓደኛዬ ማኅደረ ዓይኖችሽ ያምራሉ ትለኛለች፡፡ ሌላ ሰው ማንም ብሎኝ ስለማያውቅ እርግጠኛ አይደለሁም። ማኅደረ፣ ርግብ ነችና እባብም ቆንጆ ሆኖ የሚታያት ፍጥረት ነች፡፡ ለእሷ የሰው ልጅ በሙሉ ቆንጆ ነው፡፡ የኾነ ሆኖ አላምርምና ዕድሌ ነው ፤ ዓለም የቆንጆዎች ናት ብዬ ቁጭ ልል አልችልም፡፡ እዚሀ አስቀያሚ ሌጣ ደረቴ ውስጥ ያለው ልቤ ሥራው ደም መርጨት ብቻ አይደለምና እንደ ሰው የሚወደኝ የሚያፈቅረኝ ሰው እፈልጋለሁ። ሁልጊዜ ፍቅር እፈልጋለሁ፡፡ ዓይኖቼ ወንዶች ላይ እንደተንከራተቱ ናቸው፡፡ ግን ከ “ሃይስኩል” እስከ ኮሌጅ ፍቅረኛ ኖሮኝ አያውቅም። አደባባይ ላይ ተቁሞ ኡኡ... | የወንድ ያለኽ አይባል ነገር፡፡ ይኼ መገፋት ወደ ትምህርት ገፍቶኝ “ውይ እሷ እንደ

ወጣት አትልከሰከስ ትምህርቷ ላይ ብቻ...'' የሚባልልኝ ጎበዝ ተማሪ ሆንኩ፡፡ (ልልከስከስስ ብል...) ከዚያ በተረፈኝ ጊዜ ቤተክርስቲያን አዘወትራለሁ፡፡ ይኼም የጨዋነት ደረጃዬን ከፍ አደረገልኝ፡፡ የልቤን ናፍቆት ግን ማንም አያውቅም ነበር፡፡ እንዱ ይኼን ወረቀትሽን ወደዚያ ጣይና አግብቼ ልውሰድሽ ቢለኝ፣ ወደዚያ ወርውሬ እከተለው ነበር፡፡ በነጠላ የተሸፈነውም፣ በ'ሚንስከርት' ቡጊ ቡጊ የሚል ልቤ ነበር፡፡ ይገርመኛል ታዲያ፤ ከእህት በላይ የምታውቀኝ ጓደኛዬ ማኅደረን ጨምሮ የሚያውቁኝ ሁሉ የሚያስቡኝ ከዚህ በጣም አርቀው መሆኑ። እንዴት ዓይነት ማስመሰል ብከናነብ ነው? እላለሁ ለራሴ፡፡ ድፍን ወዳጅ ዘመዶቼ በአለፍ ገደም የሚያውቁኝ ሁሉ “ስለ ሃይሚ ጨዋነት በዐሥር ጣታችን እንፈርማለን!" ይላሉ። ከመፈረማችሁ በፊት ... በእርግጥ እንዲህ ስል ወንድ አላውቅም ማለቴ አልነበረም፡፡ አሳፋሪ ቢሆንም ወንድ ጋር መተኛት የጀመርኩት ገና የዐሥረኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነው፡፡ ይኼንን ማንም አያውቅም ማኅደረን ጨምሮ።ምን ተብሎ ይነገራል!? የጎረቤታችን የእትዬ ሆህተ ባለቤት ጋሽ ዓለምነህ ጋር ተኛሁ ተብሎ? ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ የፈጸምኩት እሱ ጋር ነበር፤ ረዥም ቀይ ነው፡፡ ለምን እንደሆነ እንጃ ሳዬው ዶክተር ነበር የሚመስለኝ፣ ኧረ ነጋዴ ነው ተብዬ ሁሉ ዶክተር ነበር የሚመስለኝ፡፡ አብረን እንድንተኛ ሲጠይቀኝ አልተግደረደርኩም(ጠዬቀኝ እንኳን አይባልም) እንዲያውም የሆነ ትልቅ ክብር ነበር የተሰማኝ። እትዬ ሆሀተ “እመብርሃንን የመሰለች" የሚባልላት ቆንጆ ሴት ነበረች፡፡ በፊልም የምናያቸውን የሀንድ ሴት ተዋናያን የመሰለች። በሙያዋ እዚህ ልደታ ፍርድ ቤት ዳኛ ነች፡፡ ሁሉም ሰው እትዬ ይላታል እንጂ፣ ያኔ ዕድሜዋ ከሰላሳ መብለጡን እንጃ፡፡ ታዲያ ባለቤቷ ጋሽ ዓለምነህን (ዓለምዬ ነዉ የምትለው) ከትምህርት ቤታችን ወረድ ብሎ የሕንፃ መሣሪያዎች መሸጫ መደብር ነበረው፣ ነጋዴ ነው፡፡ እኔና ማኅደረ ከትምህርት ቤት ወጥተን ወደ ቤታችን ስናዘግም ድንገት ከተገጣጠምን ያቺን ነጭ

ቶዮታ ኮሮላውን ያቆምና “ኑ! ግቡ'' ይለናል፡፡ እየተሸኮረመምን አንቺ ቅደሚ፣ አንቺ እየተባባልን እንገባለን፣ ይሸኜናል፡፡ ማኅደረን ሜክሲኮ ጫፍ ላይ ካወረዳት በኋላ፣ እኔ ጋር አንድ ሰፈር ስለሆንን እንቀጥላለን፡፡ ብዙ ብዙ የሚያስቅ ነገር እያወራኝ፤ ብዙ ብዙ የሚገባኝንና የማይገባኝን የሥራ ጉዳይ ምናምን እያወራኝ ...ልክ እንደ ጓደኛዉ፣ ውስጤ በጣም ነበር የሚወደው፡፡ እንደዚያም ሆኖ በኋላ መመልከቻ መስተዋቱ ደጋግሞ ዓይኑን ጣል እያደረገ ሲመለከት ብዙ ጊዜ ዓይኖቻችን ቢገጣጠሙም፤ ያው እንደሁሉም ወንድ ማኅደረን ለአጓጉል ነገር የፈለጋት ነበር የመሰለኝ፡፡ ዓይኔ ንቁ ነው። እንዲያውም ማኅደረን በኋላ “ምንድን ነው ባለትዳር አይደል እንዴ? ዐሥር ጊዜ ያፈጥብሻል"አልኳት፡፡ ደንገጥ ብላ “አፈጠጠ እንዴ?...አላዬሁትም'' አለች፡፡ ሁልጊዜ የሷን ወንዶች የማዬው እኔ ነኝ፡፡ እንዲህ ሲሆን ልለምደው ያልቻልኩት ብስጭት ውስጤ ይፈነዳል፡፡ ደንገጡር የሆንኩ ዓይነት። ማኅደረ ጋር የሚያገኙን ወንዶች ሁሉ ከመጀመሪያዋ ሰላምታ በኋላ ከነመፈጠሬ እንደረሱኝ ነው “የት ነው የምትማሩት? ...ስንተኛ ክፍል ናችሁ?...የት እየሄዳችሁ ነው? ..." የሚሉ ጥያቄዎች ሁሉ እኔን ማጀቢያ አድርገው ለማኅደረ የሚቀርቡ ነበሩ፡፡ ጥያቄያቼውን የምመልሰው እንደ አስተርጓሚ እኔ ነበርኩ፡፡ ማኅደረ ሲበዛ ዝምተኛ ናትና የእሷ አንደበት ነበርኩ፡፡ እኔ እየመለስኩ የእሷን ዓይን ለማዬት የሚታገሉት ነገር ያበሳጨኛል፤ምንም ልበል ግድ አልነበራቼውም “ራሴን ላጠፋ እየሄድኩ ነው'' ብላቼው ራሱ ግድ የሚሰጣቼው አይመስለኝም። ታዲያ አንድ ቀን ማኅደረ አባቷ ታመው፣ ከትምህርት ቤት ቀርታ ብቻዬን ታክሲ ስጠብቅ የጋሽ ዓለምነህን መኪና ከሰፈር ስትመጣ አዬኋት፡፡ ብቻዬን ስለሆንኩ እንዳላዬ ያልፈኛል ብዬ እኔም ያላዬሁት ለመምሰል እዚህና እዚያ ዓይኔን ሳቃብዝ፣ ያቺን መኪናውን ፊት ለፊቴ አቆመና መስተዋቱን ዝቅ አድርጎ “ሃይማኖት” ብሎ ጠራኝ፡፡ ታክሲ የሚጠብቀው ሰው ሁሉ ስሙ ሃይማኖት ይመስል ሁሉም ወደ እሱ

ዞረ። በእጁ ምልካት ወደ መኪናው እንድገባ ጠራኝ፣አባቴ ነበር የሚመስለው.. አላንገራገርኩም፣ የኋላውን በር ልከፍት ስታገል...ነይ እዚህ ብሎ ተንጠራርቶ የጋቢናውን በር ከፈተልኝ፡፡ ትንንሽ ነገሮች አሉ ምናልባት ለሌሎች ምንም የሆኑ፡፡ ለእኔ ግን ያች ቅጽበት የንግሥና ዙፋን ላይ የመቀመጥ ያኽል ልዩ የመከበር ስሜት ነበራት፡፡ ሁልጊዜ ይቺን የጋሽ ዓለምነህ ቶዮታ ኮሮላ መኪና ሰፈር ውስጥ በተለይ ማታ ላይ ሳያት፣ ሚስቱ እትዬ ሆህተ በክብር፣ ያኔ እኔ የተቀመጥኩበት ቦታ ላይ ተቀምጣ ነበር የማያት፡፡ ወደ ፊት የሚወደኝን ሰው አግብቼ እያልኩ የምመኜው ምኞት፣ በዚያ መስታወት አልፎ በዓይኔ የተፀነሰ ምቾት ነበር፡፡ በዚያ ላይ መኪናውን የሞላው ሽቶ...
👍375
እስካሁን ያንን ቅጽበት ሳስብ ነፍሴ ሐሴት ታደርጋለች፡፡ የምድር ቆንጆ ሴቶች ሁሉ በእትዬ ሆሀተ ተወክለው የንግሥትነት ዙፋናቼውን የቀማኋቼው መስሎ ነው የሚሰማኝ። ሁልጊዜ ተሸናፊ ነኝ እንጂ፤ ነፍሴ ሽሚያና ውድድር ትወዳለች። ትንሽ እንደሄድን “ዓይናችን እያዬሽ አደግሽኮ ሃይሚ!?” አለኝ፡፡ ሃይሚ!? የምናገረው ጠፍቶኝ ዝም እንዳልኩ “ከማደግሽ፣ ቁንጅናሽ...! ስንተኛ ክፍል ሆንሽ?'' ብሎ እጁን...ያንን ንጹህ እና የሚያምር ቀኝ እጁን፣ ታፋዬ ላይ እንደ ቀልድ ጣል አደረገው፡፡ በድንገተኛው ንክኪ ስቅቅ አለኝ፣ እጁን ለመያዝ የላኩትን እጄን፣ በቀስታ ቀሚሴን ወደ ታች አስተካክዬ መለስኩት፤ግን ለመከላከል አልሞከርኩም። ዓይኖቼ ብቻ እጁ ላይ ተተከሉ፡፡ ትንሽ ዘወርወር _ አለብኝ፤ የመጀመሪያው አስተያዬት ከእጁ ጋር ተዳምሮ ስንተኛ ክፍል እንደሆንኩ ሁሉ እስኪጠፋብኝ ተደነባበርኩ፡፡ እጁ ወደ አጓጉል ቦታ ሲንቀሳቀስ ታፋና ታፋዬን በኃይል ገጥሜ፣ እጁን በእጄ ለማንሳት ያዝኩት “አይዞሽ ፈራሽ እንዴ?'' ብሎ እጁን ራሱ አነሳው፡፡ ከራሴ ክብር ይልቅ ያስቀዬምኩት ነበር የመሰለኝ “ይቅርታ ሰው ነክቶኝ ስለማያውቅ ነው'' አልኩት ፡፡ .“ግዴለም ... ያለ ነገር ነው ዕድሜሽ ነው፤ በዚያ ላይ ቆንጆ ሃሃሃሃሃ ..….እ….ስትወጭ እዚያ ፊት ለፊት ጁስ ቤቱ ጋ እጠብቅሻለሁ፣ አብረን እንሄዳለን" አለኝ፡ እንዳቀረቀርኩ “እሺ!” ብዬ ከመኪናው ወረድኩ። ዝብርቅርቅ እንዳለብኝ ትምሀርት

ቤት ውዬ ስወጣ በጉጉት ወደ ጁስ ቤቱ ተመለከትኩ መኪናዉ ቆማ ነበር።ልቤ እየደለቀች ግራና ቀኝ የሚያውቀኝ ሰው መኖር አለመኖሩን እያማተርኩ (እስኪ ምን አስፈራኝ) ወደ መኪናው ሄድኩ፡፡ በሩን ከውስጥ እየከፈተልኝ “ሃይሚ ቆንጆ ልጅ ...ግቢ ግቢ” አለኝ በፈገግታ ገብቼ ቁጭ አልኩ፡፡ ዐሥር ጊዜ አጭር የትምህርት ቤት ቀሚሴን ወደ ታች እየጎተትኩ እግሬን ለመሸፈን እሞክር ነበር፡፡ “እኔ የምልሽ ትንሽ ቆይተሺ ብትገቢ፣ ስመኝ ትጨነቅ ይሆን እንዴ?'' አለኝ፤ ስመጃ እናቴ ናት። ብዙ ጊዜ ቤተክርስቲያን ጉባኤ ካለ ከትምህርት ቤት ስወጣ በዛው ስለምሄድና አምሽቼ ስለምመለስ ምንም እንደማትል አውቃለሁ፡፡ “እዚያው ቤተስኪያኗ ሄዳ ነው" ከማለት ውጭ እናቴ ሌላ ቦታ ትሄዳለች ብላ ጠርጥራኝ አታውቅም፡፡ ግን ትንሽ መቆዬትን ምን አመጣዉ እያልኩ ምን እንደምመልስ በፍጥነት አስባለሁ ...አይሆንም ብል የሚቀረው ነገር ያጓጓኛል...ክፉኛ ጓጉቼ ነበር። እሺ ብልም ምን ይሆን የሚፈጠረው? የሚል ፍርኃት ያናውዘኛል፣ አፌ ላይ እንደመጣልኝ፣ “እኔ'ንጃ!'' አልኩ፡፡ ልምድ ያለው ሰውነውና ገብቶታል፣ ፈገግ ብሎ መኪናዋን ወደ ጦር ኃይሎች ያግለበልባት ጀመር፡፡ በዝምታ የሚያደርገውን አያለሁ። ጧት የመለሰውን እጁን እንደገና ወደ ታፋዬ ልኮ በቀስታ ቀሚሴን ወደ ላይ እንደመሰብሰብ ሲያደርገው በእጄ ያዝኩት “ሃይማኖት ..አሁን'ኮ ትልቅ፣ ቆንጆ፣ የደረሽ ልጅ ነሽ፤ አትፍሪ ...የከተማ ልጅ አይደለሽ እንዴ? በጣም ነው የወደድኩሽ” አለኝ፡፡ እጄን አላላሁ፤ እጁ ታፋዬ ላይ በቀስታ እየተንቀሳቀሰ የባጥ የቆጡን ያወራኛል፡፡ ምኑንም አልሰማውም፤ ወደ አንድ መኖሪያ ቤት ወደሚመስል ግቢ ገብቶ፣ መኪናውን አቆመና እንውረድ አለኝ፡፡

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍45
ሰው የሚማረው፣

አንድም ከፊደል፣
አንድም ከመከራ ነው፤

አንድ ቃል ከፊደል ጥበብ፣
አንድ ቃል ከመከራ መዝገብ፣
አንድም በሳር "ሀ" ብሎ፣
አንድም በአሣር "ዋ" ብሎ፤

🎴ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን🎴

ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ
300 #Subscriber_Challenge

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍214
#የማይቻል_አንድ ነገር

እዉነት - ቤት ስትሰራ
ዉሸት - ላግዝ ካለች፣
ምስማር ካቀበለች፣
"ቤቱም አልተሰራ
እዉነትም አልኖረች።

     🎴ጌትነት እንየው🎴


ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ
300 #Subscriber_Challenge

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍14👏4
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-14

///
       ሰው ለጥቅሙ ሲል ነው የወደደኝ ብለህ አትማረር፡፡  እኛም እኮ ፀሀይን የምንወዳትና የምናፈቅራት ለሙቀቷ እና ለብርሀኗ ስንል ነው፤ለጥቅማችን ብለን..ከለበለዚያ እሰከመፈጠሯም ትዝ ላትለን ትችል ነበር፡፡ለጥቅም ሲባል መጥላትና መጉደት እንጂ ለጥቅም ሲሉ ማፍቀር ምን ክፍታ አለው፡፡                                                             
በሶስተኛው ቀን እራሴ በጥዋት እቤት ድረስ ሄድኩና በራሴ መኪና ልዕልትን ከነህመምተኛ ባለቤቷ ጭኜ ወደጓደኛዬ ኪኒሊክ ሄድን…ከጓደኛዬ ጋር ቀድሜ ተነጋግሬና ሁሉ ነገር አመቻችቼ ስለነበር ቀጥታ እንደደረስን ያለምንም ውጣ ውረድ በህመምተኛ ተሸክርካሪ አልጋ ላይ ተኝቶ በነርሶች እየተገፋ ማሽኑ ወደሚገኝበት ክፍል ሲወሰድ እኔና ልዕልት በረንዳ ላይ በሚገኝ ወንበር ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠን መጠበቅ ጀመርን፡፡ይሄ ምርመራ ምንም ነገር እንደማይፈይድለትና ..እስከአሁን ስለመስፍን በሽታ ከምናውቀው ዝርዝር መረጃ ተጨማሪ እንደማያሳውቀን በእርግጠኝነት አውቃለሁ፡፡.ግን ይሄንን ምርመራ እንዲያደርግ የፈለኩት ከወንድሟ አቤል ጋር የተነጋርነውን ነገር ለማድረግ ሀሳቡን ለልዕልት ለማቅረብ እንዲያግዘኝና መነሻ ሰበበ ምክንት እንዲሆነኝ ብቻ ስለፈለኩ ነው፡፡በአንድ ሰዓት ሁሉ ነገር ተጠናቀቀና ..ውጤቱን በማግስቱ መጥተን እንድንወስድ ተነገሮን በሽተኛውን ተረከብን፡፡ጭኜ እንዳመጣኋቸው መልሼ ጭኜ ወደቤት ወሰደኳቸውና ጎን ለጎን ተሸክመን መልሰን መደበኛ አልጋው ላይ አስተኛነው..ጎን ለጎን  ሆነን ከመኪናው አውርደን ስንሸከመው አንደኛው እጄና እጇን አንድ ላይ አቆላልፈን በሌለኛው እጃችን ትከሻውን ደግፈን ስለነበረ..ልቤን የሚያቀልጥ ጥልቅ ሙቀት ነበር የለቀቀችብኝ…የእሷን እጅ የጨበጠው እጄ ለዘላለም ባለበት ሆኖ ቢቀጥል ምኞቴ ነበር….የተሸከምነው ባለቤቷ እንኳን የህፃን ልጅ ያህል ስላልከበደኝ ምን አለw መኪናውም ቀርቶ ከሆስፒታል ጀምሮ እንደዚህ እጅ ለእጅ እንዳቆላለፍን ተሸክመነው በመጣን ኖር የሚል የጅል ምኞት  በውስጤ በመብቀሉ ሳልፈልግ  ፈገግ ለማለት ተገድጄ ነበር፡፡
‹‹በይ ልሄድ…ነገ ውጤቱን ተቀብዬ አመጣለሁ፡፡ ››
‹‹እንዴ ዶክተር..የምሳ ሰዓት ደርሷል ..ቁጭ በልና ምሳ በልተህ ትሄዳለህ›› ተላማጠቺኝ፡፡
‹‹አይ ቸኩላለሁ…በፍጥነት ወደሆስፒታል መመለስ አለብኝ..እዛው ቀለል ያለ ነገር እበላለሁ፡፡››
‹‹በጣም አስቸገርኩህ አይደል….ቆያ ጠብቀኝ ብሩን ይዤልህ ልምጣ››
ደነገጥኩ …‹‹የምኑን ብር?››
‹‹ለህክምና የከፈልከውን ነዋ…እርግጥ መጠኑን ስላላወቅኩ አሁን በርሳዬ ውስጥ ያለው ሀያ ሺ ብር ብቻ ነው….የጎደለውን ነገ አሞላላሁ፡፡››
‹‹የሄድንበት ኪኒኒክ የጓደኛዬ ነው ብዬሽ ነበር…. አዲስ ማሽን ስላስገባ እንደማስመረቂያ በነፃ ነው የሰራልኝ፡፡››
‹በፍፅም ዶ/ር..እንዲህ አይት ነገር ልቀበል አልችልም…ጠብቀኝ..››ተንደርድራ ወደ መኝታ ቤቷ ገባች፡፡ተንደርሬ ሳሎኑን ለቅቄ ወጣሁ፡፡ የውጩን በራፍ ከፈትኩና መኪናዬን ውስጥ ገብቼ  ተፈተለኩ… ልትደርስብኝ ስትንደረደር አላቆምኩላትም፡፡ከሰፈር ራቅ እንዳልኩ ያቺ ዘወትር ለልዕልት መስጠት ያቃተኝን አበባ  ሀምሳ ብር እየተቀበለች የምትቀበለኝ እብድ ቦታዋ ላይ ቁጭ ብላ መሬቱን ስትቆረቆር አገኘኋትና እንደወትሮዬ የአስፓቱን ጠርዝ ይዤ…..በዝግታ እየነዳው  ስሮ ስደርስ አቆምኩ፡፡
‹‹እሼ እንዴት ነሽ?››
ቀና ብላ እንኳን ሳታየኝ‹‹50 ብር ካልከፈልከኝ..አበባውን አልቀበልህም፡፡ ››አለችኝ፡፡
ፈገግ አልኩ፡፡ኪሴ ገባሁና 50 ብር በማውጣት ሰጠኋት›ቀና አለችና በቆሻሻ የጠቋቆረ እጇን ዘረጋጀችና 50 ብሩን እየተቀበለቺኝ‹‹ ጎበዝ.. አሁን ደግሞ አበባውን አምጣ..››
‹‹ዛሬ አበባው የለም››
ክው ብላ ደነገጠች…በመደንገጧ እኔም አብሬያት ደነገጥኩ‹‹ምነው ..እሺ ብላ ተቀበለችህ እንዴ?››
‹‹አይ ዛሬ እረስቼው ….ባዶ እጄን ነወ የሄድኩት››
‹‹ወንዶች ድሮውንም ስልቹዎች ናቸሁ…ቶሎ ተስፋ ትቆርጣላችሁ….እሼ ዛሬ አበባውን ለመቀበል ዝግጁ የሆነችበት ቀን ቢሆንስ? ከሰርክ ማለት አይደል…?ለማንኛውም እንካ ››ብላ 50 ብሩን ወደእኔ ዘረጋች፡፡
‹‹ምን ላድርገው..ሰጠውሽ እኮ…ያንቺው ነው››
‹‹አይ..እኔ በነፃ ብር መቀበል አልወድም….በተለይ ከወንዶች የብላሽ ብር መቀበል መዘዙ ብዙ ነው››
ይህቺ ልጅ እብድ ነች ፋላስፋ አልኩና እጃን እንዳንከረፈፈች መኪናውን አስፈንጥሬ ጉዞዬን ቀጠልኩ….፡፡
በማግስቱ ደወልኩና  ትናንት  የተገናኘንበት ቦታ ቀጠርኳት..እያለከለከች መጣች።
ከሰላምታ በኃላ ቀጥታ ወደ ጥያቄ ነው የገባችም።
‹‹ዶ/ር ውጤቱ እንዴት ነው...?የተለየ ነገር አለው?››
‹‹ብዙም አይደል ...ብቻ?››
‹‹ብቻ ምን?››
‹‹ጓደኛዬ ማለት ምርመራውን ያደረግንበት ኪሊኒክ ባለቤት  ከእኔ የተለየ እምነት ነው ያለው?››
‹‹ማለት ?››
‹‹እሱ ውጭ ሄዶ ቢታከም ቢያንስ የመዳን እድሉን አሁን ካለበት  በ10 ፐርሰንት ይጨምራል የሚል ነው።››
‹‹አሪፍ ነዎ...አንተስ ዶ/ር ?በእሱ አስተያየት ላይ ሀሳብህ እንዴት ነው?››በመንሰፍሰፍ ጠየቀችኝ፡፡
‹‹እሱ እንዳለው ትንሽም ቢሆን የመዳን ቻንሱን  በጥቂት ፐርሰንትም ቢሆን ሊጨምር ይችል ይሆናል ..ግን አቅሙ ይኖርሻል ወይ?ከዛ በኃላስ ካልተሳካስ?እሱ ነው የሚያሳስበኝ፡፡››
በአጠቃላይ ወሸት መጥፎና አሳፋሪ ነገር ነው፡፡መሀላ በገቡለት በሞያ ሽፋን መዋሸት ግን የስብእና መቆሸሽን ያሳያል፡፡እራሴን ጠላሁት፡፡ምን እየሰራሁ ነው?
እሷ ቀጠለች"እንዴ ዶ/ር አንድ ፐርሰንት ተጨማሪ እድል የሚያስገኝለት ከሆነ ከመሞከር ወደኃላ አልልም...አቅሙ ላልከው የግድ ነው እንደምንም እሞክራለሁ?ካልሆነ ቤቴን አስይዤ ከባንክ እበደራለሁ ወይም ሙሉ በሙሉ ሸጠውና  አነስ ያለ ማረፊያ ገዝቼ በተቀረው አሳክመዎለሁ..."
‹‹ቁርጠኝነቷን ሳይ ፋዝዝ ብዬ በትኩረት አጤናት ጀመር››
‹‹ይሄውልሽ ልዕልት ..ቀስ ብለሽ ተረጋግተሽ ከዘመድም ከወዳጅም ጋር  ምከሪበት...ከዛ መልሰን እናወራበትና ››
‹‹አይ ወስኜለሁ..በዚህ ጉዳይ ከማንም ጋር መደራደር አልፈልግም…የሚያግዘኝ ከላ ከጎኔ ይሰለፍ…አሻረኝ የሚል ሰው ደግሞ ከመንገዴ ገለል ይበል ››ብላ ተሰናብታኝ ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡የሆነውን ለወንድሞ ደውዬ ነገርኩት፡፡በደስታ ፈነጠዘና ረጅም ምስጋና አዥጎደጎደልኝ፡፡
///

ፍቅር ማለት …ሁለት ልቦች በአንድ ቅኝት አንድ አይነት የልብ-ምት ሲያሰሙ ማለት ነው….፡፡፡ግን እኔና ልእልት እኮ በአንድ አይነት ቅኝት አንድ አይነት የልብ ምት እያስደመጥን አይደለም፡፡የእኔ ልብ ለእሷ ሲንዷዷ…የእሷ ልብ ደግሞ ለመስፍን ይንዷቆዶቃል፡፡የእሱስ ልብ ለማን ይሆን የሚመታው..አሁንም ለብዙ ሴቶች በአንድ ጊዜ ይመታ ይሆን ወይስ ፍቅር የሚባለውን ነገር አለም ረስቶ በህይወት ስለመቆየት ብቻ እያሰበ ይሆን…?
ሚስቶቻችንን እንዳፈቀርናቸው እስከመጨረሻ መዝለቅ አንችልም..ጥቂት አመት አብረን ከኖርን እናቶቻቸን ይሆናሉ።አብዛኛዎቹ የተሳካላቸው ሚስቶች ባለቤቷን እንደመጀመሪያ ልጇ ነው የምታየው... የምትንከባከበውም።ልክ አሁን ልዕልተ መስፍን ለተባለው ባሏ እንደምታደርገው ማለት ነው፡፡
👍487
ምንም ምርጫ አልሰጠችኝም...እድሜ ለወንድሟ ቅርቃር ውስጥ ገብቼያለሁ።አሁን በቃ መሄድ የለበትም እዚሁ እናክመዋለን ብላትም አሻፈረኝ አለች።እሺ ሌላ ሰው ወይም ወንድሙ ይዛት ይሂድ ብትባልም እኔ እያለሁ እንዴት ተደርጎ?አለች። አይኔ እያየ ለእሬሳ የቀረበ ሰው ለማዳን የልጆቾን ማሳደጊያ የወደፊት ጥሪቷን ሰብስባ ለማጥፋት ከመወሰኗም በላይ ልጆቾን ለቤተሠቦቾ ትታ እኔን አውላላ ሜዳ ላይ ጥላኝ በበአድ ሀገር… በአድ የሆነ ፈተና ለመጋፈጥ ልትሄድ ነው?‹‹መጀመሪያ እንግዲያው ለመሄድ በቁርጠኝነት ከወሰንሽ እኔም ልከተልሽ›› ልላት አስቤ ነው።ቆይቼ በመረጋጋት ሳሰላስለው የሚሆን ሆኖ አላገኘሁትም...‹‹ስራዬን እንዴት አደርጋለሁ?ሰውን በተለይ እናቴን ምን ብዬ አሳምናታለሁ...?እሺ እንደምንም ቀባጥሬና ለፍልፌ እናቴን ማሳመን ብችል እንኳን እራሷን ልዕልትን ምን ብዬ ነው ባልሽን ለማስታመም ስራዬን እርግፍ አድርጌ ትቼ አንቺን ተከትዬ ልሂድ ልላት የምችለው?እራስን ሙሉ በሙሉ አጋልጦ ትዝብት ላይ ከመውደቅ በስተቀር እሷን አሳምኖ ይሁንታ ማስገኘት የሚችል ሀሳብ አይደለም...በዚህ የተነሳ አራት ቀን ሌት ያለማቋረጥ ጨጓራዬ እስኪቆስል ድረስ ካሰብኩ በኃላ አንድ አደገኛና አስጠሊታ ውሳኔ ወሰንኩ...አሁን ውሳኔዬን ተግባራዊ ለማድረግ ሙሉ ዝግጅቴን አጠናቅቄ ወደ እነ ልዕልት ቤት እየሄድኩ ነው።

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍324
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ፅዮን እና ታዲዬስ እሁድ ከምሽቱ 12 ሰዓት ሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል ቁጭ ብላው እሷ ለስላሳ እሱ ቢራ አዛው እየተጐነጩ ያዘዙትን መክሰስ በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡የምረቃ በዓሉ ካለፈ በኃላ በሣምንታቸው ዛሬ መገናኘታቸው ነው፡፡‹‹እሺ ፅዮን ለምን ግን ወይን ነገር አትሞክሪም ነበር?››

<<አንደኛ አልኮል የሚባል ነገር ሞክሬ አላውቅም ...ሁለተኛ የማያየው ዓይኔ ሳያንስ ጠጥቼ እምሮዬንም እንዳያይ አድርጌ እንዴት ልሆን ነው?››

‹‹አይ ሳታበዢ ማለቴ እኮ ነው፡፡››

‹‹ያው መጠጣት ከጀመርኩ ቢያንስ አንድ ብርጭቆ መጨረሴ ይቀራል..ያ ማለት ደግሞ እኔን ለማስከር በቂ መጠን ነው…ግድ የለህም ለስላሳው ይብቃኝ፡፡››

‹‹ያው ብትሰክሪም እኮ እኔ አብሬሽ አለሁ ብዬ ነው፡፡››

‹‹አይ እኔ በራሴ ድክመት እራሴን ጥዬ ሰውን ደግፉኝ ማለት አይመቸኝም፡፡››

‹‹ተቀብያለሁ››አለ በጠንካራ መንፈሷ ተደስቶባት፡፡

‹‹ፂ ስለበቀደሙ ጉዳይ እንድናወራ ነው ዛሬ የቀጠርኩሽ››ወደዋናው ቁምነገር ድንገት ገባ።

‹‹ይመቸኛል..እኔም እንደዛ እንደሆነ ተስፋ በማድረግ ነው የመጣሁት..ቀጥል፡፡››

‹‹እንዴት እንደምቀጥል አላውቅም፤ብቻ…..››

‹‹ታዲ ..እኔ የ28 ዓመት ወጣት ነኝ፤በህይወቴ ብዙ ውጣ ውረድ ያየው ሰው ነኝ.. ህይወት ነጩንም ሆነ ጥቁሩን ክፍሎቿን በማፈራረቅ አሳይታኛለች፡፡አንድን ነገር ፈልጌዋለሁና የግድ አገኘዋለሁ ማለት እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡››

‹‹በህይወትማ ምንም ነገር ከልብሽ አገኘዋለሁ ብለሽ ካሰብሽ ታገኚዋለሽ፡፡››

‹‹አውቃለሁ....የሆነ ነገር አገኛለሁ ብለህ ከልብህ ከተመኘህ፤ ምኞትህንም ለማሳካት በሙሉ ጉልበትህ ከተንቀሳቀስክ የማይሳካልህ ነገር እንደሌለ እኔም አምናለሁ፤ይሄ ግን ፍቅር ላይ ሲሆን ከሚሰራበት ጊዜ ይልቅ የማይሰራበት ጊዜ ይበልጣል፡፡››

‹‹እንዴት እንዲህ ልትይ ቻልሽ…?ከፍቅር አምላክ ጋር ትንሽ የተቀያየማችሁ ይመስላል፡፡››

‹‹ትንሽ አልከው...ምን ትንሽ ብቻ ...ለአምስት አመት ተኮራርፈን በደረሰበት ላልደርስ ተማምለን… ሳይደርስብኝ ሳልደርስበት ጥሩ ጊዜ አሳልፈን ነበር ፡፡››

‹‹ታዲያ እንዴት ሆናችሁ?››

‹‹ምን እንዴት ሆናችሁ አለው... አንተን ሳገኝ መሀላዬን አፍርሼ ደጅ እየፀናሁ እያየኸኝ?››

‹‹ደጅ ጽናት አልሽው፤ለማንኛውም እስኪ በምን ተኮራርፋችሁ እንደነበረ ብትነግሪኝ ? ማለት ደስ ካለሽ…..››

ዝም አለች... ጭንቅላቷ ወደታች ተደፋ‹‹…ምን መሰለህ......››ብላ ልትቀጥል ስትል ያዘዙት መክሰስ መጣና ቀረበላቸው፡እየተጎራረሱ በሉ..ከጨረሡ በኃላ አብረው ወደ እጅ መታጠቢያው በመሄድ ታጠቡና ወደመቀመጫቸው ተመለሱ፡፡ታዲዬስ ሁለተኛ ቢራውን አዘዘ..ዛሬ ካለወትሮው ጠጣ ጠጣ አሰኝቶታል፡፡

‹‹ምነው ዝም አልከኝ ...?››አለችው ልትጀምርለት የነበረውን ታሪኳን እንድትቀጥልለት ባለመጠየቁ ቅር ብሏት...

‹‹ኧረ ዝም አላልኩሽም ….ዝም ስላልሽ እኮ ዝምታሽን ላለመረበሽ ብዬ ነው፤እኔ ዝምታዬን ከሚረቡሹኝ ንግግሬን ቢያቋርጡኝ ይሻለኛል፡፡››

‹‹እሱስ እውነትህን ነው….ግን አሁን ዝምታ ውስጥ ስላልሆንኩ አትረብሸኝም

...ይሄውልህ ታዲ እኔ የሻሸመኔ ልጅ ነኝ፡፡ ትውልዴ እስከተወሰነ ጊዜም እድገቴም እዛ ነው፡፡ አባቴን እና እናቴን አላውቃቸውም ማለቴ በአካል አላውቃቸውም...ያሳደገችኝ የአባቴ እናት አያቴ ነች ... እናቴ ገና አንድ አመት ሳይሞላኝ ነው አባቴ ክንድ ላይ ጥላኝ ሀገሩን ጥላ የጠፋችው፡፡ ከአንድ አመት በኃላ አባቴም በተራው ሁኔታዎች ስልችት ሲሉት እኔን ለእናቱ ሰጥቶኝ ውትድርና ተቀጥሮ ለጦርነት ወደ ሰሜን ይሄዳል፡፡

ከዛ በኃላ አያቴ ያለቻትን አንድ ክፍል ቤት በደባልነት አንድ ደደፎ ለሚባል ከገጠር ለትምህርት ለመጣ ልጅ አከራይታ ከእሱ ከምታገኘው ገቢ በተጨማሪም በደካማ አቅሟ ጠላ እየጠመቀች አንዳንዴም አረቄ እያወጣች በመሸጥ እኔን ማሳደግ ትጀምራለች ፡፡ስምንት ዓመት ሲሞላኝ ግን ያልታሰበ ችግር ተፈጠረ..

ዓይኖቼን ይጋርደኝ ጀመር ..በወቅቱ አያቴ እንኳን ለህክምና ለሆዴም መሙያ የሚሆን ሳንቲም ለማግኘት በመከራ ነበር ሚሳካላት…፡፡

ባቅሟ የቻለችውን ፀበሉንም የባህል መድሀኒቱንም ብትሞክርልኝም ከቀን ወደቀን እየባሰብኝ መጥቶ ከአንድ አመት በኃላ ሙሉ በሙሉ ሁለቱም አይኖቼ ታወሩ..ከዛ ትምህርቴንም ከሁለተኛ ክፍል ግማሽ ላይ አቆረጥኩ፡፡አያቴ ግራ ገባት ፡፡በሚመጣው አመት ግን ያ እቤታችን በደባልነት ይኖር የነበር ያልኩህ ተማሪው ልጅ ሚሽኖቹ ጋር ተሯሩጦ በአዳሪነት አስገባኝ፡፡ ይገርምሀል አያቴን ልክ እንደእናቱ ነበር የሚወዳት... እሷም ከእኔ ለይታ አታየውም ነበር እንዲሁ ስሙ ተከራይ ተባለ እንጂ እኛ የምንበላውን ይበላል እሱ የሚበላውን እንበላለን ስናጣ አብረን እንራባለን፡

እኔ ሚሽን በአዳሪነት ከገባሁ በኃላ አያቴ ጋር እኖር ከነበረው ኑሮ በተሻለ ሁኔታ እኖር ጀመር፤ ትምህርቴንም በጥሩ ሁኔታ መከታተል ጀመርኩ፤ድንገት ግን ምን እንደተፈጠረ ታውቃለህ? ብቸኛ ዘመዴ የሆነችው አያቴ ሞተች፡፡በወቅቱ የ5ተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ… ዕድሜዬም ወደ 14 አካባቢ ተጠግቶ ነበር ..በጣም ነው የከበደኝ፡፡ ለመጽናናት በጣም አስቸግሬ ነበር፡፡ይገርምሀል እቤታችንን ተከራይቶ ነበር ያልኩህ ልጅ በወቅቱ አስረኛ ክፍል ደርሶ ነበር፡፡በአያቴን ሞት በጣም ነበር ያዘነው…፡፡

ከዛ እኔን መንከባከብ የእሱ ኃላፊነት እንደሆነ ነበር የሚያስበው፤ በሳምንት ሁለት ቀን እየመጣ ይጠይቀኝ ነበር፤ደግሞ ሲመጣ ባዶ እጁን አይመጣም..ደብተር፣እስኪሪብቶ፣የፀጉር ቅባት፣ማበጠሪያ፣ፓንት ...ብቻ የማይገዛልኝ ነገር አልነበረም፤ካጣ ካጣ የ 25 ሳንቲም ማስቲካም ቢሆን ይዞልኝ ይመጣል..ደግሞ እኮ የሚገርመው እሱም ምንም የሌለው የደሀ ገበሬ ልጅ መሆኑ ነው፡፡ ግማሽ ቀን ይማራል ኑሮውን ለመደጎም ደግሞ ግማሽ ቀን ጋራዥ ይሰራል...ከዛ በሚያገኛት ሽርፍራፊ ገንዘብ ነበር ለእኔ የሚያስፈልገኝን ነገር ይገዛልኝ የነበርው፡፡

በዛ ላይ የቤት ኪራዬን በየወሩ ቀን እንኳን ሳያስተጎጉል አምጥቶ ይሰጠኛል…ተወው ይቅር አያስፈልገኝም ብለውም አይሰማኝም...‹ነገ ብትቸገሪ ለአንድ ነገር ይሆንሻል.. አስቀምጪው >> ይለኛል...እኔ ደግሞ የተለየ ወጪ ስለሌለኝ እጄ ላይ እየተጠራቀመ ሲበዛብኝ አንድ የምወዳት አስተማሪዬ ጋር ማስቀመጥ ጀመርኩ፡፡

እንዲህ እንዲህ እያለ ቀናቶች እየነጐዱ እኔም እያደግኩ በትምህርቴም እየገፋሁ መጣሁ..በነገራችን ላይ ሙዚቃ መሳሪያ መነካካት የጀመርኩት እዛው ሻሸመኔ አይነስውራን ትምህርት ቤት እያለሁ ነበር፡፡

ስምንተኛ ክፍል ስደርስ ደደፎ 12ተኛ ክፍል ጨርሶ ነጥብ ስላልመጣለት መንጃ ፍቃድ አውጥቶ ሹፌር ሆነ፡፡በዚህን ጊዜ በሳምንት ሁለት ቀን መምጣቱን አቁሞ በሳምንት አንዴ
..አንዳንዴም በአስራአምስት ቀን አንዴ ይመጣ
ጀመር፡፡ሲመጣ ታዲያ ይዞልኝ የሚመጣውን
ነገር አትጠይቀኝ ... ምንም የሚቀረው ነገር
አልነበረም፤ለእኔ አይደለም ለጓደኞቼ እራሱ ይተርፍ ነበር፡፡ የጽዮን ወንድም መጣ ከተባለ ጓደኞቼ በሙሉ ጥርስ በጥርስ ነበር
👍738
የሚሆኑት...ታዲያ በዛን ወቅት እሱ ሄዶ መልሶ
እስኪመጣ ድረስ ክፉኛ በናፍቆት እሰቃይ
ጀመር፡፡ ሳይደበዝዝ በውስጤ ተቀርጾ የቀረው
የእሱ ምስል ብቻ ነበር..ከነሙሉ ቁመናው ፤
አቋሙ ፤ መልኩ የማውቀው አንድ ሰው ቢኖር እሱ ብቻ ነበር፡፡ አሁን አሁን ሳስበው
ይገርመኛል...እኔም ልክ ዕዳ እንዳለበት አድርጌ ነበር የማስበው፡፡ከሳምንት አሳልፎ የመጣ ጊዜ
አኮርፈዋለሁ፣እነጫነጭበታለሁ፣የማለቅስበት ጊዜ ሁሉ አለ..ታዲያ ለምኖኝ
ተለማምጦኝ፤በስጦታ ደልሎኝ ይታረቀኛል፡፡

ከዛ ልክ 10ረኛ ክፍል እንደጨረስኩ እሱ የሚሰራበት መስሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ ወደአዲስ አበባ ቀየረው፡፡እዛ ከገባ ደግሞ በወር አንድ ቀን እንኳን መጥቶ ሊጠይቀኝ ይከብደዋል፡፡ጭንቅ ሆነ ፤ሲያማክረኝ አበድኩበት..ሌላ ስራ እዛው ሻሸመኔ ለማግኘት ቢጥርም በፍጥነት ሊሳካለት አልቻለም፡፡ከዛ አብሬህ እሄዳለው አልኩት... ይገርምሀል የተደሰተው መደሰት ልነግርህ አልችልም፡፡ለካ በፊቱንም እሱ እሺ አትለኝም ብሎ ፈርቶ እንጄ ፍላጎቱ እንደዛ ነበር፡፡

ከዛ ተያይዘን ወደ አዲስ አበባ ሄድን፡፡ እንደእድል ሆኖ ደግሞ የሚሰራበት መስሪያ ቤት ሁለት ክፍል መኖሪያ ቤት ከነሙሉ ዕቃው ሰጥቶት ስለነበርን ያለችግር ኑሮን ጀመርን፡፡ የ11ኛ ክፍልም ትምህርቴንም እዛው ቀጠልኩ... ኮንትራት ታክሲ ይዞልኝ ከቤት እየተመላለስኩ ማለት ነው፡፡››

ንግግሯን አቋረጠችና እጇን ሚሪንዳ ወደ ያዘው ብርጭቆ ሰዳ በማንሳት አንዴ ገርገጭ አድርጋ ጉሮሮዋን አራሰችና‹‹ታዲ››ብላ ጠራችው

‹‹አቤት..፡፡››

<<ወሬዬ አልሰለቸህም አይደል...ይቅርታ ይሄን ታሪክ ከጀመርኩ ለማሳጠር ስለሚከብደኝ ነው...፡፡››

‹‹ኧረ ቀጥይ በጣም ተመስጬ ነው እያዳመጥኩሽ ያለሁት... ከፈለግሽ እስከነገም ቢሆን አዳምጥሻለሁ፡፡›› አላትና አንድ ሌላ ቢራ እንድትጨምርለት ለአስተናጋጇ በምልክት ነግሯት ትኩረቱን ወደ ጽዮን መለሰ፡፡

ቀጠለች‹‹....ከዛ በየቀኑ አብሬው እየኖርኩ... አብሬው እያደርኩ ...ትምህርቴን እየተማርኩ አስደሳች ህይወት መኖር ጀመርኩ፡፡ ይገርምሀል እድሜዬ 18 ወይም 19 አካባቢ ደርሶ ትልቅ ልጃገረድ ሆኜ እያለሁ እንኳን እሱ ምኔ እንደሆነ ?በምንስ ሂሳብ አብሬው እንደምኖር ? ለአንድም ቀን አስቤበት እና ተጨንቄበት አላውቅም ነበር፡፡ለምንስ እጨነቃለሁ... ለእኔ እሱ ማለት መላ ነገሬ ነው፤እናት አባቴ አክስት አጐቴ ነው…እሱ ስላለኝ ነው ስለምንም ጉዳይ የማልጨነቀው..

አባቴ ውትድርና ብሎ እንደወጣ ይሙት
አይሙት ሳይታወቅ በዛው ቢቀርም አልፎ አልፎ ባጋጣሚ ከማስታወስ ውጭ እሱን እያሰብኩ በሀዘን ተክዤ አላውቅም፤ ስለእናቴም አንዳንዴ እንኳን
እንደው ባገኘዋት ብዬ ማስበው ያኔ እንደው
በዛ ጮርቃ እድሜዬ ጡት እንኳን በደንብ ጠብቼ ሳልጠግብ ለአባቴ ጥላኝ እብስ ያለችው ምን አጋጥሞት ይሆን . ?.አባቴስ ምን
ያህል ቢበድላት ነው…?በጣም ቢመራት
እንኳን እንዴት ይዛኝ ለመሄድ ሳትሞክር

....?.እነዚህን የመሳሰሉትን የዕድሜ ልክ ጥያቄዎቼን እንድትመልስልኝ ብዬ እንጂ
እናትነቷ አጓጉቶኝ ..
እንክብካቤዋ ናፍቆኝ
አልነበረም፡፡

ደደፎ ሁሉን ነገር ነበር የሚሰጠኝ፤ምንም ያጣሁት ምንም የጎደለብኝ ነገር አልነበረም ፡፡ እንዳልኩት ሆኖ ነው፤ የጠየቅኩትን ሰጥቶኝ ፤የፈለግኩትን ገዝቶልኝ ነው፡፡ሲጠራኝ እንኳን በስሜ አይደለም.. ኪያ ነበር የሚለኝ ..<ኪያ
>ማለት የኦሮሚኛ ቃል ሲሆን ወደ አማርኛ ሲመለስ‹ የእኔ፤ የግሌ›› ማለት ነው ትምህርቴን ስጨርስ በፍላጎቴ ያሬድ ገብቼ ፒያኖ እንዳጠና አመቻቸልኝ፡፡ጀመርኩ፤ሁለት ዓመት ከተማርኩ በኃላ ችግር ተፈጠረ፡፡ትዝ ይለኛል እሁድ ቀን ነው 8 ሰዓት አካባቢ.......

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍6913😁3
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_አርባ_አራት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፅዮን እና ታዲዬስ እሁድ ከምሽቱ 12 ሰዓት ሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል ቁጭ ብላው እሷ ለስላሳ እሱ ቢራ አዛው እየተጐነጩ ያዘዙትን መክሰስ በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡የምረቃ በዓሉ ካለፈ በኃላ በሣምንታቸው ዛሬ መገናኘታቸው ነው፡፡‹‹እሺ ፅዮን ለምን ግን ወይን ነገር አትሞክሪም ነበር?›› <<አንደኛ አልኮል የሚባል ነገር ሞክሬ አላውቅም…»
#ሸሌ_ነኝ


#በሕይወት_እምሻው

"ነይ እዚህ ጋር ! ልብስሽን አውልቀሽ ውስጥ ሳትገቢ...ብርድ ልብሱ ላይ ተኚ" ሲለኝ፣ ልማድ ሆኖብኝ መግደርደር ዳድቶኝ ነበር።

ድሮ፤ ልጃገረድ እንዳለሁ ግዜ መሽኮርመም። ሰው እንጂ ሴት ያልሆኑኩ  መስሎኝ፣ ሥጋ ሸጬ እንጀራ ልገዛ ያልመጣሁ መስሎኝ።

አንገቴን እንደሰበርኩ ወደ አልጋው ሄድኩ    ሲያገኘኝ እሄድ እንደነበረው አይደለም አካሄዴ።ሰበር ሰካ የለውም፣ ዕዩኝ ዕዩኝ የለውም፣ ተገዝቶ ወደ ሚታረድበት ቦታ እንደሚሄድ በግ ነው አካሄዴ።

ገዥዬ የማያውቀኝ፣ ሰው ፊት ልብሴን ሳወልቅ የመጀመርያዬ እንጀሆነ አያውቅም።

ገዥዬ፣ በገንዘብ ተገዝቼ ከወንድ ለመተኛት ስመጣ የመጀመርያዬ እንደሆነ አያውቅም።

ገዥዬ፣ ለዚህ ስራ ድንግል እንደሆንኩ አያውቅም።

ልብሴን ማውለቅ ሳልጀምር እየፈራው፣ "ይቅርታ....መብራቱን ታጠፋው?" አልኩት።

ዞር ብሎ ዐየኝና፣ "ሃሃ...ሃ! ታሾፌያለሽ እንዴ.? ለምንድን ነው የማጠፋው...? አለኝ። ይስቃል።
ፈራሁ ብለው አያምንም። በሰቀቀን ዝም ብዬ ማውለቅ ጀመርኩ። የአልጋው ጫፍ ላይ ኩምትር እንዳልኩ ድንገት እስካሁን መኖሩን ያላወኩት ብርድ አንዘፈዘፈኝ። ሳል ጀመረኝ።

ይሄን ግዜ ሰውየው ዞር ብሎ ዐየኝና ፤ "ምነው.. ብርድ.. ቲቢ.. ምናምን አለብሽ እንዴ?" አለኝ።

"አይ...በርዶኝ ነው...አያመኝም...አሁን በርዶኝ ነው..." ብዬ ብርድ ልብስ ውስጥ ገባሁ።

"ኖኖ!...ከላይ ሁኚ...አትግቢ..." አለኝ ቶሎ ብሎ ፣ ቀጭን ትዛዝ ነበር።

እምቢ ብዬ መሄድ እንደማልችል ማወቁ አስከፋኝ። እሺ ብዬው ስለመጣሁ እምቢ ብዬ ስለማልሄድ እርግጠኛ መሆኑን ሳውቅ ከፋኝ። ከነሳሌ ከብርድ ልብስ ወጣሁ። መጥቶ አጠገቤ ተኛ። ሰውነቴ በፍርሃት ተንዘፈዘፈ። ነውስጥ ሱሪ ብቻ ሲቀረው ዕርቃኑን ነው።

እግዜር በሚያውቀው፣ ከማላውቀው ሰው ቤት ለማደር መምጣት አልፈለግኩም ነበር።

የማላውቀው ሰው እጁቹን ጭኖቼ መሀል  አስገብቶ እንዲፈነጭ አልፈለግኩም ነበር።

የማላውቀው ሰው ጆሮዬን ተጠግቶ እንዲያቃትትብኝ አልፈለግኩም ነበር። ግን ሰውየው አስገድዶ አላመጣኝም። አልደፈረኝም።

ያስገደደኝ ኑሮ ነው።

የደፈረኝ ድህነት ነው።

ሲነጋና ከኔ ጋር ያለውን ጣጣውን ሲጨርስ፣ የሰጠኝን አምስት መቶ አዳዳስ ብሮች እንደያዝኩ በትእዛዝ ያወለኩትን ልብሴን በከፍተኛ ፍጥነት ለበስኩ። ያወለኩት ክብሬ ግን አልጋው ላይ ቀርቷል።

"ቅዳሜ እመጣለሁ....ማን ብዬ ላስጠራሽ ?" አለኝ በተኛበት።

እንድሄድ ፈልጓል። አገልግሎቴ አብቅቷል። አሁን እንደተፋቀ የሞባይል ካርድ ነኝ። አሁን እንደተጫረ የክብሪት ዕንጨት ነኝ። በድጋሚ በጉጉት የሚያየኝ በሚቀጥለው ቅዳሜ መጥቼ እፎይ ማለት ሲያምረው ነው። ስሜን ነግሬው ዞር አልኩና ቦርሳዬን አንጠልጥዬ ለመሄድ ስዞር፣

"ማነሽ...እ...በሩን በደንብ ዝጊው!" አለኝ፣ አልጋው ላይ ተገላብጦ ጀርባውን እየሰጠኝ። ፊት እንኳን የማይገባኝ ሰው መሆኔን ሲነግረኝ ነው በጀርባው የሚያናግረኝ፣ የሚታወስ ሰም እንደሌለኝ ሲነግረኝ ነው ማነሽ ያለኝ።

ይሄን ሳስብ ተዛባሁ፣ ተዛነፍኩ።

ካለ አጥንት እንደተፈጠረ ሰው ሰውነቴ ለመቆምም ለመሄድም እምቢ እያለ ወደ  ታክሲ ተራው ሄድኩ። ተኝቶ የነጋለት ሰው ይተራመሳል።

ታክሲው ውስጥ ገብቼ መስኮቱን ደገፍ አልኩና ያለ እቅድ ስቅስቅ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ። ከዐይኔ ግድብ የሚፈሰው እንባ ጉንጬቼ ላይ የሚያደርቅ ሳይሆን አዋሽ  ወንዝ ለመግባት ያልም ይመስል ይንዠቀዠቃል።

ከክብሬ ጋር አውልቄው የነበረው የአንገት  ልብሴ ላይ ያርፋል።

ከክብሬ ጋር አውልቄው የነበረው ጃኬቴ ላይ ያርፋል።

ከክብሬ ጋር አውልቄው የነበረው ሱሬዬ ላይ ያርፋል።

በለቅሶዬ መሃል፣ "አይዞሽ... ሁሉም ያልፋል" የሚል ድምፅ ሰማሁና ዞርኩ። ከእኔ በእድሜ የምታንስ ልጅ ናት።

"ሁሉም ያልፋል" የሚል የታክሲ ጥቅስ አንብባ የምትደለለው ለዚያ ነው። ትንሽ ልጅ ስለሆነች፣ በቂ ስላልኖረች። አንዳንድ ነገሮች እንደኔ ላለው ሰው እንደማያልፍ የሚያስተምራት የህይወት ልምድ ስለሌላት፣ ቀልደኛ!

ዝም ብዬ አየሇትና በእሽታ ጭንቅላቴን ነቅንቄ ተመልሼ ወደ መስኮቱ ዞርኩ። ሁሉም ቢያልፍ ኖሮ ዛሬ እዚህ ታክሲ ውስጥ እያለቀስኩ ባልተቀመጥኩ፣ ሁሉም ቢያልፍ ኖሮ ለአምስት መቶ ብር አምስት መቶ ቦታ ባልተሰባበርኩ። ሁሉም ቢያልፍ ኖሮ እኔ ትርሲት የአቶ ከለላውና የወይዘሮ ሥምረት ሴት ልጅ፣ የብሌን ታላቅ እህት፣ የዳዊት ታናሽ እህት፣ የዳግም ፍቅረኛ ሀኜ በቀረሁ። አሁን ግን ትርሲት ሸለዋ ነኝ።

ሸሌ ነኝ፣ ሸሌ ብቻ።

ይህንን ሰውየው ዐይን ውስጥ ዐይቼዋለሁ። ይሄንን ሰውየው ትእዛዝ ውስጥ ሰምቼዋለሁ። ይህንን ሰውየው፣ "በሩን በደንብ ዝጊው" ንግግር ውስጥ አድምጭዋለሁ።

ሸሌ ነኝ።

ለማንበብ ደቂቃ የሚፈጅ ሥም በመስጠት የ'ኔን ሥራ ቅዱስ ማድረግ አይቻልምና፣ የለም፣ አንቺ እኮ 'በወሲብ ንግድ የተሰማራች ሴት' ነሽ!" ብላችሁ አታፅናኑኝ።

ከዛሬ ጀምሮ ሸሌ ነኝ።

በረሀብ እያዛጋሁ ቤቴ ገባሁና ከሰል አቀጣጠልኩ። ሳልበላ ውሃ ላፈላ። ሳልበላ በፈላ ውሃ ልታጠብ። ሳልበላ በፈላ ውሃ ገላዬን ልታጠብ። ሸሌነቴን በፈላ ውሃ ሙልጭ አድርጌ ልታጠብ።

ውሃው እስኪፈላ፣ ልብሶቼን አውልቄ ከሌሎቹ ልብሶቼ ጋር እንዳይቀላቀሉ በቤቴ አንዷ መአዘን ላይ ሰብስቤ ጣልኳቸው። ብዙ ልብስ የለኝም፤ ግን እነዚህን ልብሶች መልሼ የምለብሳቸው አይመስለኝም።

'ራቁቴን የሰመጠች አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ ውሃው እስኪፈላ እየጠበቅኩ ቤቴን ዐየሁት። ለሰው የሚነገር ነገር ስለሌለኝ እንትኑ እዚያ ጋር፣ እትኑ ደግሞ እዛ ጋር አለ ብዬ ላወራችሁ አልፈልግም። በዋጋ ከተሰላ፤ አሁን ያለኝ፣ ዋጋ የከፈልኩበት አምስት መቶ ብር ብቻ ነው። አልጋዬ ላይ የተቀመጠው አምስት መቶ ብር።

ምንአልባት ካልገመታችሁ፣ እንዲህ ያለው ዋጋ ያልከፈልኩበት ብር ለማግኘት ሞክሬ ነበር። ማለቴ ዘልዬ ሸሌ አልሆንኩም። አሳጥሬ ልንገራችሁ። ሁሉንም ሥራ ሰርቻለው። ግን እኔንና እኔን የሚጠብቁ ቤተሰቦቼን ሆድ ፀጥ የሚያደርግ፣ አንገት ቀና የሚያደርግ፣ ደረት አስነፍቶ የሚያስኬድ ሥራ አላገኘሁም።

እውነቴን ነው የምላችሁ፣ እንጀራ ፍለጋ ሴት የሆንኩት ሰው ሆኜ ስላልተሳካልኝ ነው።

ልድገመው፣ እንጀራ ፍለጋ ሴት የሆንኩት ሰው ሆኜ ስላልተሳካልኝ ነው።

የሥጋ ለሥጋን ኑሮ የመረጥኩት ሌላ ነገር ሆኜ መኖር ስላልቻልኩ ነው። ለምሳሌ የሆነ ሰሞን የሆነ "ኤን ጂ ኦ" ሸሌ የመሆን አዝማሚያ ያሳየነውንም፣ ገብተው የተንቧቹበትንም ሴቶች ሰበሰበና፣ "ከዚህ አስነዋሪና ቆሻሻ ሥራ ነፃ እናውጣችሁ፣....ያልገባችሁትንም እናድናችሁ" አለን።

"አልጋ አንጣፊ ስለሆነች ከአልጋ ለመውደቅ ቅርብ ነች" ብለው ነው መሰለኝ፣ ፕሮጀክቱ ውስጥ አስገቡኝ። ደስ ብሎኝ ገባሁ። ኤን ጂ ኦው፣ "አማራጭ የገቢ ማግኛ ዘዴዎች" በሚል ለግማሻችን ጥልፍ፣ ለግማሻችን ዳንቴል ስራ አስተምሮ፤ "በሉ እንግዲህ ሂዱና ንፁህ ስራችሁን እየሰራችሁ በብልፅግና ኑሮ" ብሎ አንድ ኮንቴነር ቤት ተከራይቶልን ሄደ።

እኔ ከጥልፎቹ መሀል ነበርኩ። እንደተማርኩት እየጠለፍኩ አዲሱንና ንፁሑን ሥራዬን ነጻ መውጫዬ፣ መልካም እጣ ፈንታዬ፣ የእግዜር ካሳዬ አድርጌ ተቀብዬው ሥራ ጀምሬ ነበር።

ብዙዎቻችሁ፣ " እንዴ ሸሌ የሆነች ወይ ለመሆን ያኮበኮበች ሴት ሁሌም ሸሌ ናት" ብላችሁ እንደምታስቡ አውቃለሁ። "በሚኒ ስከርት መንገድ መቆም የለመደች ሴት፣ በ'እስከ ጉልበት' የሥራ ቀሚስ ቢሮ መቀመጥ አትችልም ብላችሁ እንደምታምኑ ከውቃለሁ።
👍9410😁1
የራሳችሁ ጉዳይ

እኔ ግን በዛ ሰሞን እፎይታ ተሰምቶኝ ነበር።

ሳልጠፋ ስለተገኘሁ ደስ ብሎኝ ነበር።

ሸሌ መሆን የሚያጓጓኝ ሰሞን፣ የከጃጀለኝ ሰሞን አልጋ አንጣፌ ሆኜ የምሰራበት ቡና ቤት ውስጥ ያሉ የሚቀርቡኝ ሸሌዎችን ገድልና እሮሮ በታላቅ ትኩረት፣ በቀን በቀን እሰማ ነበር። ዐይ ነበር።

በመሸ ቁጥር፣ በ'ኮንደም አድርግ አታድርግ" ጭቅጭቅ፣ በጭንቅላቱ ሳይሆን በእንትኑ የሚያስብ ወንድ ጋር እየተጣሉ በፖሊስ መዳኘት አለ፣ በሚሉት የማስፈራራያ ወሬዎች ተሰላችቼ ነበር።

"በጥፊ ካልመታሁሽ ደስ አይለኝም!" እያለ፣ "ከላይም ከታችም ከሚደበድበኝ ወንድ ጋር አድሬ የከፈለኝን ገንዘብ በድብደባ ያበጠ ፊቴን ለመታከም ማዋሉ መረረኝ" በሚሉ ሴቶች ዋይታ ተማርሬ ነበር።

እሺ...ዝርዝሩ ይቅርባችሁ እና እንዲያው በደፈናው፣ በጨለመ ቁጥር ባለተራ ወንድ እላዬ ላይ ስለማይደፋደፍብኝ የእውነት ደስ ብሎኝ ነበር። ከዚህ እጣ ፈንታ ለጥቂት ስላመለጥኩ፣ ደስ ብሎኝ ነበር።

እናም፣ ቀን ቀን እየጋለ አቅልጦ እንደው ውሃ ሊያፈሰኝ በሚዳዳው ሙቀት፣ ሲመሽ ሲመሽ ጥፍር አውጥቶ ሰውነቴን በሚቦጫጭቅ ብርድ ሳልማረር፣ እዛች ኮንቴነር ውስጥ ቁጭ ብዬ ጥልፊን እጠልፍ ነበር።

በየወሩ፤ "አሁንስ በቃኝ...እንኳን ትርፍ ሊያመጣ ለሚያከስር ስራ ደግሞ!" እያሉ ከጥልፉም ከዳንቴሉም ጎራ ወጥተው ሸሌነትን የመረጡ፣ ወይም ወደ ሸሌነት የተመለሱ ጓደኞቼን እያየሁ እንኳን በንፅህና ጎዳና ለመቀጠል ብዙ ለፋሁ።

ብዙ ታተርኩ፣ ብዙ ወጣሁ፣ ብዙ ወረድኩ።

ንጹህ ስራዬ ግን ከሰው በታች አደረገኝ እንጂ ከፍ አላደረገኝም። ሱቄን የሚደጎበኙ ወንዶች ሁሉ፣ ጥልፍ የጠለፍኩበትን አልጋ ልብስ ከመግዛት ይልቅ እኔን ጠልፈው አልጋ ውስጥ ማስገባት ነበር የሚታትሩት። በአምስተኛው ወር የከሸፈውን ፕሮጀክት ተከትሎ የከሸፈውን ህልሜን ኮንቴነሩ ውስጥ ጥዬ ወደ "ሰጥቶ የመቀበል" አለም መጣሁ።

የዛሬው ሰውዬ የመጀመርያዬ ነበር።
"ሀ" ዬ አንደኛ ክፍሌ።

ሳልዋረድ መብላት ብፈልግም፣ ሳልገላመጥ መኖር ብሻም የሞከርኩት ሁሉ አልሳካ ብሎኝ ሸሌ ሆንኩ።ባላያችሁትና ባልኖራችሁት ሕይወቴ ፈርዳችሁብኝ ብትሰድቡና ብትረግሙኝም፣

ዓለም ስትፈጠር ገና ያኔ ከገበሬነት በፊት፣ ከአናጢነት በፊት፣ ከአስተማሪነት በፊት፣ ከምንም አይነት ሥራ በፊት፣ "ሲወርድና ሲዋረድ" እዚህ የደረሰውን ሥራዬ ግን በእርግማንና በስድብ ወጀብ ከምድረ ገፅ እንደማይጠፋ ታውቁታላችሁ

ምክንያቱም፣ በጨለማ ዝቅ ብዬ ያገኘሁት ገንዘብ እጄን የሚጠብቁ ቤተሰቦቼን ከፍ እንደሚያደርግልኝ አውቃለሁ።

ቀን የተጠየፉኝ ሰዎች ማታ እንደሚያመልኩኝ አውቃለሁ።

ቆሻሻው ስራዬ ንጹሕ እንጀራ እንደሚገዛ አውቃለሁ።

ስለዚህ፣ ወንድ ሊሆን የሚመጣን ወንድ ሴት ሆኜ እያስተናገድኩ እንደ ሰው እኖራለሁ። ሸሌ ነኝ።ከዛሬ ጀምሮ ሸሌ ነኝ።

            አለቀ

ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ
300 #Subscriber_Challenge

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍56😢17🔥10👎3👏2😁21
አትሮኖስ pinned «#ሸሌ_ነኝ ፡ ፡ #በሕይወት_እምሻው ፡ "ነይ እዚህ ጋር ! ልብስሽን አውልቀሽ ውስጥ ሳትገቢ...ብርድ ልብሱ ላይ ተኚ" ሲለኝ፣ ልማድ ሆኖብኝ መግደርደር ዳድቶኝ ነበር። ድሮ፤ ልጃገረድ እንዳለሁ ግዜ መሽኮርመም። ሰው እንጂ ሴት ያልሆኑኩ  መስሎኝ፣ ሥጋ ሸጬ እንጀራ ልገዛ ያልመጣሁ መስሎኝ። አንገቴን እንደሰበርኩ ወደ አልጋው ሄድኩ    ሲያገኘኝ እሄድ እንደነበረው አይደለም አካሄዴ።ሰበር ሰካ የለውም፣…»
🍀🍀ኢድ ሙባረክ🍀🍀
በዓለም ላይ ለምትገኙ   ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ 💙💙እንኳን አደረሳችሁ💙💙💙💙💙
👍9
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ ስምንት

አባቶች!

ንጹህና የሚቀዘቅዝ ክፍል ነበር፣ አብረን ከገባን በኋላ፣ አልጋ ላይ ተቀምጦ በእጁ አልጋውን መታ መታ እያደረገ ነይ እዚህ አለኝ፡፡ ቀስ ብዬ ሄጄ ተቀመጥኩ.. ይጣደፋል ክፉኛ ይጣደፋል፡፡ በበኩሌ በአጓጊ _ ሕልም ውስጥ እንዳለሁ ዓይነት ነገሮች ሁሉ ድንገት ባንኜ የሚቋረጡ እየመሰለኝ ነበር፡፡ በዝምታ አድርጊ የሚለኝን ሁሉ አደርጋለሁ፡፡ ጓጉቻለሁ፣ አውቃለሁ ምን እንደሚሆን፣ ጣቴን የምጠባ ሕፃን አይደለሁም፡፡ ከሆነም እዚህ ሰው ጋር መሆኑ የተለዬ ተአምር ነበር- ለእኔ፡፡ እንዲያውም በመኻል “አይ ይቅርብን' ብሎ ተነስቶ እንዳይሄድ እየፈራሁ ነበር፡፡ አጠቃላይ ለነገሩ አዲስ መሆኔና ድንገተኛ ነገር መሆኑ ከፈጠረብኝ መደነባበርና ጭንቀት ውጭ፣ ይኼ ሰው ምንም ቢያደርገኝ ምንም ቅሬታ አልነበረኝም፡፡ይኼ ቆንጆ ሰውዬ፣ ሀብታም ሰውዬ፣ ሳቂታ ሰውዬ፣ ቆንጆ ሚስት ያለችው ሰውዬ፣የሰፈሩ ሰው ሁሉ የሚያከብረው እና የሚወደው ሰውዬ፣ ምንድን ነው እኔ ጋር የሚሠራው “ጫማሽን አውልቂና ከፍ ብለሽ ተቀመጭ፣ አይዞሽ አትፍሪ"...እንዳለኝ አደረግሁ። ጉርድ ቀሚሴ ያጋለጠውን እግሬን እያዬ እና የሸሚዙን ቁልፍ እየፈታ... "ይኼ እግርሽ እንዴት እንደሚያምር ሰዎች አልነገሩሽም...'' አለኝ፡፡ አቀርቅሬ ዝም አልኩ፡፡ ሸሚዙን አውልቆ ወደ ጎን ወርወር አደረገና እጁን የተጋለጠ ጉልበቴ ላይ አሳረፈ ቀስ አድርጎ ወደ ራሱ ሳበኝ ... ደረቱ ላይ ተለጠፍኩ። እጁን ልኮ ከማነሳቼው ብዛት ለመቆንጠጥ እንኳን የሚያስቸግሩ ጡቶቼን ሲነካካኝ፣ ባለ በሌለ ኃይሌ ታፋዬን ገጥሜ ትንፋሼን ዋጥኩ፡፡ ልብሴን ቀስ በቀስ ሲያወልቅልኝ፣ በዝምታ ነበር የተባበርኩት፡፡ ተንጠራርቶ መብራቱን አጠፋው እፎይታ ተሰማኝ፡፡ አንሶላው ደስ የሚል ሽታ አለው፡፡ ከዚያ በኋላ የሆነው ሁሉ ፈጣንና ግራ አጋቢ ሕልም ነበር ሕመም፣ ደስታ፣ የማላውቀው ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነበር የሚሰማኝ፡፡ በዓለም ላይ እንደ እኔ የሚፈቀር ሰው ያለ መስሎ አልተሰማኝም። ወንዶች ይጸዬፉኛል ብዬ አስብ ነበር፣ እንደዚህ ዓይነት ቆንጆ

ሀብታም፣ አገር ያደነቃት ውብ ሚስት ያለችው ሰውዬ ከንፈሬን፣ ጉንጨን፣ አንገቴን ሲስመኝ ዕንባዬ እየፈሰሰ በሁለት እጆቼ እስከቻልኩት ተጠምጥሜበት ሳላስበው? “ጋሽ ዓለምነህ'' አልኩት:: “ወይዬ! የኔ ጣፋጭ” እንዲሁ ነበር ያለኝ “የእኔ ጣፋጭ!"... “እግባኝ!” አልኩት። ጨለማ ነውና መልኩን ባላዬውም ትንታ ከምትመስል አተነፋፈሱ ሳቁ ያመለጠው ይመስለኛል። ዛሬ ላይ ሳስበው የሚያሳፍረኝም የሚያስቀኝም፣ ነገር ነው ይኼ... ቃሉ ራሱ “አግባኝ!'' ጨርሶ ሲነሳ መብራቱን አበራና የአልጋ ልብሱን ገልቦ የሆነ ነገር ተመለከተ፣ ሰውነቴን በእጄ ሸፈንኩ፡፡ “አመመሽ እንዴ?” “አይ! ደህና ነኝ!'” አልኩ እውነታው ግን፣ የሆነ ነገር ውስጤ የቀረ ዓይነት ኃይለኛ የማቃጠልና ታፋና ታፋዬ መገጣጠሚያ ላይ ሕመም እየተሰማኝ ነበር፡፡ “ሃሃሃሃ… የዛሬ ልጆች እሳቶች!'' እያለ ወደ ሻወር ገባ፡፡ ምን ማለት ነው እሳቶች!? ወደ ሻወር እንደገባ በፍጥነት አንሶላውን ገለጥኩና ሲባል የሰማሁትን ብር አምባር ነገር ፈለግሁ፡፡ አንሶላው ላይ ምንም ዓይነት ደም አልነበረም፤ የሆነ የተሳሳተ ነገር አለ? አልኩ ለራሴ፡፡ የሰማሁት እንደዚህ አልነበረም፣ ደም መኖር አለበት፣ ደም! ፊልሙ፣ መጽሐፉ፣ ወሬው ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ነገር ያደረገች ሴት፣ ነጭ አንሶላ ጋር ትፋጠጣለች አላሉኝም፡፡ ከዚያ በፊት ወንድ የሚባል ባላውቅም፣ ምንም ደም አልነበረም፤ ጋሽ ዓለምነህ እንዳላመነኝ ያወቅሁት ቆይቶ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ለወራት ነክቶኝ አያውቅም፡፡ እንዲያውም መንገድም ላይ ሲያዬን አልፎን ነበር የሚሄደው።

የሆነውን ሁሉ በውስጤ አፍኜ እንደገና ላዬው እጓጓ ነበር፡፡ እንዲያውም ይኼን ሁሉ ያደረገ እሱ እያለ ለዓይን ያስጠላችኝ ሚስቱ እትዬ ሆህተ ነበረች፡፡ ሳያት እና ለሁሉ ደግሞ ሁልጊዜ “እንደም? ዋልሽ? ሃይሚዬ” ትለኛለች፡፡ ልክ ባጠገቧ እንደ ዳልሁ። እንደ ማንም ሕፃን ነበር የምታዩኝ፡፡ በየኋት ቁጥር ወደ አእምሮዬ የሚመጠወ ልፍ ዓለምነህ ጋር አጉል ነገር እያደረጉ “የኔ ጠፋጬ!'” ሲላት ነው። ለመሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲተኙ ደም ዓይታ ይሆን? መሆን አለበት፣ እንዲህ እያልኩ አስባለሁ፡፡ እንዳንድ ማታ፣ ባልና ሚስቱ ተያይዘው በሰፈር ሲያልፉ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁለቱም ሰላም ይሉኛል፡፡ ታዲያ እፈራለሁ ድንገት እትዬ ሆሀተ ጠርታኝ “ሃይማኖት! የሚነግረኝ ነገር እውነት ነው ባሌ ጋር ተኝተሻል?'' የምትለኝ፣የምታሳስረኝ፣ ሰፈር ውስጥ የምታዋርደኝ፣ እንደዚያ እንደዚያ ዓይነት ሐሳብ ውስጤ እየገባ እንደ ብርድ ያንዘፈዝፈኛል፡፡

አንዴ ታዲያ ጋሽ ዓለምነህ ከትምህርት ቤት ስንመለስ አገኜንና፣ የተወውን መሸኜት ትዝ ያለው ይመስል ግቡ አለን፣ ገባን፡፡ ስለትምህርት ምናምን እያወራን ማኅደረን ሜክሲኮ አወረዳትና ብቻችንን ስንቀር ያለምንም ዙሪያ ጥምጥም ምን አለኝ ...

“ይች ...ቦይ ፍሬንድ አላት?''

"ማን?"

“ማኅደረ” ያላሰብኩት ጥያቄ:: “ኧረ! እኛ እንደዚህ ዓይነት ነገር አናውቅም'' “ሃሃሃ.. ያንችንማ አዬነው ...አሁን የሷን ንገሪኝ'' እንዳቀረቀርኩ “የላትም'' አልኩ፡፡ “ጥሩ! ነገ ከክላስ ስትወጡ፣ የሆነ ሰበብ ሰጥተሽ ብቻዋን እንድትሄድ አድርጊያት''

“구?” “ወደ ቤቷ ነዋ!'' አለ ቆጣ ብሎ፡፡ “እሺ!'' ነበር መልሴ፡፡ የዐሥረኛ ክፍል ቁጣ! በቀጣዩ ቀን ማኅደረን “ከትምህርት ቤት ስንመለስ ቤተክርስቲያን ፕሮግራም ስላለኝ አልጠብቅሽም” አልኳት፡፡ ቀደም ብዬ ስወጣ፣ ታክሲ መቆሚያው ጋር ከመድረሱ በፊት የጋሽ ዓለምነህ መኪና ቆማ አዬኋት። መንገዱን ተሻግሬ፣ በሩቁ አንድ የቆመ መኪና ኋላ ሰው የምጠብቅ መስዬ ቆምኩ። ማኅደረ ወደ ታክሲ መጠበቂያው አቀርቅራ ስትጣደፍ ጋሽ ዓለምነህ በቀስታ መኪናውን እያሽከረከረ ደረሰባትና ጠራት። የኋለኛውን በር ለመክፈት ሞክራ፣ ጎንበስ ብላ የሆነ ነገር ተናገረችና ወደ ከፈተላት የጋቢና በር ገባች፡፡ ውስጤ የቀረች ተስፋና መፈቀር ዕንባ ሆና ተንጠፈጠፈች፡፡ ወደ ጦር ኃይሎች ብረሪ ብረሪ አለኝ፡፡ ወደ ልደታ ፍርድ ቤት መሮጥ አማረኝ፣ ያቺን ሚስቱን “ባልሽ ማኅደረ ጋር ሊተኛ ይዟት ሄደ” ብሎ ነገር ማቀራቀር አማረኝ፡፡ ከታክሲ እንደወረድኩ እቤቴ አልሄድኩም፣ ልደታ እስኪወጣልኝ ተነፋረቅሁ፤ ቅናት አንገበገበኝ፡፡ ቤተክርስቲያን ገብቼ ወደ ማታ አካባቢ ማኅደረ በብስጭት ብው ብላ እቤት መጠች ፤ የማውቃት ማኅደረ አልነበረችም። “አንቺ! ያ ልክስክስ ሰውዬ ልሸኝሽ ብሎ አስገብቶ ጡቴን አልነካኝም መሰለሽ!'' ብላ ተአምር የነገረቺኝ ያኽል አፈጠጠችብኝ፡፡ “ማነው? አልኩ'' እንዳላወቀ፡፡

“ጋሽ ዓለምነህ ነዋ! ከሱ ብሎ ጋሽ!'' “ምን!? ይኼ ጨምላቃ! ጠርጥሬ ነበር” ብዬ አጋነንኩ እንደማያውቅ:: “አንቺማ ነግረሽኝ ነበር፣ እኔ ነኝ እንጂ ፉዞ፤ አሁኑኑ ሄጄ ለሚስቱ ነው የምነግራት... ነይ እንሂድ!” ብላ መንገድ ጀመረች፡፡ ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ማኅደረ እንደዚያ ተቆጥታ ዓይቻት አላውቅም። “እንዴ! ቆይ የሆነውን ንገሪኝ እንጂ ከዚያ እንወስናለን'' አልኳት፡፡ “...ስወጣ አግኝቶ ልሸኝሽ አለኝ፣ እንዲያውም ሃይሚም የለችም ብቻዬን ከመሄድ ገላገለኝ ብዬ ደስ አለኝ። ከኋላ ልገባ ስል ጋቢና ግቢ አለኝ፣ አገር ሰላም ብዬ ዘው! ትንሽ እንደሄድን 'ዛሬ ብቻችንን ተገናኜኝ የኔ ቆንጆ' ብሎ በዛ ሰፌድ እጁ ጡቴን አላፈሰኝም መሰለሽ...
👍404😢2
“አውርደኝ' ብዬ ስጮኽ ሊሟዘዝ፤ ብጮኽበት ብወራጭ ሊሰማኝ ነው?!...ጭራሽ ከመውረጃዬ ሊያሳልፈኝ...መኪናው ሳይቆም በሩን ልከፍት ስታገል እጄን ያዘኝ፣ በጥፍሬ ያንን ቀይጣላ ፊቱን ተለተልኩለታ! ሳይወድ በግዱ፣ ወደ ዳር ሲወጣ በሥርዓት እንኳን አላቆመም ወርጄ መሮጥ በይው”... “ደግ አደረግሽው የኔ ቆንጆ" ብዬ አቀፍኳት፡፡ እሷ ግን አሁንም በዕልህ እየተንቀጠቀጠችና እያለቀሰች ነበር፡፡ እንደ ሕፃን አባብዬ፣ ለሚስቱ መንገሯን አስተውኳት፡፡ሆ! ሚስቱ ዳኛ፣ ከሥር ከመሠረቱ ላጣራ ብትል፣ ጦሱ ሊተርፈኝ ነው ብዬ ለራሴም ፈርቼ ነው ለነገሩ። ውስጤ ግን በደስታ አብዶ ነበር፡፡ አንዳንዴ ሁሉንም ሰው እንደራሳችን እናይ የለ፣ ማኅደረም እንደ እኔ ተጎትታ ወደ አልጋው ትሄዳለች ብዬ ነበር፡፡ የራሴ መጎተት ያኔም አልቆጨኝም፡፡ የማኅደረ ጋሽ ዓለምነህ ጋር አለመተኛት ግን ልደታን አደራ እንዳላልኩ ሁሉ በውስጤ የማነስ ስሜት ፈጥሮብኛል፤ በጨዋነት የመበለጥ፡፡

ከዚያን ቀን በኋላ የተፈጠረው ነገር አሁን ላይ ያሳዝነኛል፣ ጋሽ ዓለምነህ በስንተኛው ቀን ቅዳሜ ቀን ወደነማኅደረ ቤት ልሄድ ስጣደፍ ለብቻዬ ሰፈር ውስጥ አገኘኝ፡፡ መኪናውን አቁሞ ግቢ አለኝ፣ እንደለመድኩት የጋቢናውን በር ልከፍት ስል፣ “ከኋላ! ከኋላ!'' አለኝ ከኋላ ገብቼ ጉዞ ቀጠልን፡፡ “የት እየሄድሽ ነው?'' “ማኅደረ ጋር” “እዚያች ባለጌ ጋር፣ በጣም ቆሻሻ ናት! የማላውቃት መሰላት ያቺ ሸርሙጣ እናቷ ሹፌር ተከትላ የትም ስትጋደም፣ ከሷ ብሎ ጨዋ! ወትሮም ስድ ያሳደገው ስድ ነው።” አባባሉ ስላስጠላኝ ደፍሬ ማኅደረን መከላከል ባልችልም “አይ! ትንሽ ተቆጥታ ነበር'' አልኩት። “የዐሥረኛ ክፍል ቁጣ! ነገ እንደ እናቷ የትም ቀሚሷን ስትገልብ እናገኛታለን''አለ፡፡ ምን ዓይነት ነው ደግሞ የዐሥረኛ ክፍል ቁጣ? እላለሁ በውስጤ፡፡ ምናልባት የእኔ እሺታ እና መጎተት የስንተኛ ክፍል ይሆን!? እንግዲህ “ብልግና” ያለው፣ ማኅደረ አብረሽኝ ተኚ ሲላት አይሆንም ማለቷን ነው፡፡ በዝምታ እየተጓዝን ዞር ብሎ አዬኝ፡፡ ለምን እንዳዬኝ አልገባኝም፡፡ ፊቱ ላይ ከአፍንጫው ጀምሮ ፂሙ ውስጥ የሚገባ የተተለተለ መስመር ነበር፡፡ የማኅደረ ማስታወሻ፡፡ ምን ሆኜ ነው ብሏት ይሆን ለሚስቱ!? ዝም ብሎ መንዳት ቀጠለ፡፡ የእነ ማኅደረን ሰፈር አልፎ ሲሄድ ምንም አላልኩም፡፡ ወደ ጦር ኃይሎች ማቅናቱን ሳይ ውስጤ በደስታ ቀድሞ መቅለጥ ጀመረ፡፡ ከመጀመሪያው ይልቅ የዚያን ቀን መራመድ እስኪያቅተኝ አመመኝ፣ ነገረ ሥራው ሁሉ የአውሬ ሆኖ ነበር፡፡ የማኅደረን ንዴት እኔ ላይ ተወጣብኝ፡፡ ማታ ሰፈር አምጥቶ ጥሎኝ ሄደ፡፡ ደህና እደሪ እንኳን አላለኝም፡፡ ሁለተኛ አላገኜውም ብዬ ለራሴ ማልኩ፡፡

ግን ከዚያን ቀን ጀምሮ፣ ሲፈልግ እዚያ አልቤርጎ እየወሰደ እንደፈለገ ይዝናናብኝ ጀመር፡፡ አንዳንዴ ከቀጠረኝ ከትምህርት ቤት ሁሉ ዘግቼ ወጥቼ አብሬው እሄድ ነበር፡፡ ምን ተስፋ እንደማደርግ እንጃ፤ ግን ተስፋ አደርግ ነበር። ዐሥራ ሁለተኛ ክፍል ጨርሼ ኮሌጅ እስክንገባ፣ ከሁለት ዓመት በላይ ይኼ ነገር ቀጠለ፤ ማንም አያውቅም _ ነበር። ማኅደረ እንኳን ይኼን አታውቅም ነበር። ተጣብቀው እንደተወለዱ መንትዮች፣ የማትለዬኝ ማኅደረ ያን ሁሉ ጊዜ እንዴት እንደታወረች ሳስብ እስከ ዛሬ እገረማለሁ፡፡አገር _ ምድሩ _ በሚያውቀው፣ መኪናው ድፍን ሜክሲኮና ልደታ የሚያውቀው ነጋዴ፣ አንዲት ፍሬ ልጅ ሲያመላልስ እንዴት ወሬው ሚስቱ ጆሮ እንዳልደረሰ ሳስብ እገረማለሁ፡፡ ዳኛ ናትና ሲነግሯት መረጃ፣ ምስክር፣ ምናምን ካላመጣችሁ አላምንም አለች!? ወይስ ለሞላ ቆንጆ እዚህች ጋር ምንም አያደርግም ብለው ከወሬ አቅም የማልበቃ ሆኜ ንቀው ትተውኝ? የዐሥራ ሁለተኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት መጥቶልኝ ተደስቼ ባለሁበት ሰዓት፣ አስደንጋጭ ነገር ተፈጠረ...አረገዝኩ፡፡ ለጋሽ ዓለምነህ ስነግረው ደነገጠ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ሰው ዓይቶ በሥርዓት ምሳ ጋብዞ፣ ቁጭ አድርጎ አወራኝ፡፡ ፅንሱ መውጣት አለበት ብሎ አሳመነኝ፡፡ ያን ሁሉ ነገር ማውራት አይጠበቅበትም ነበርኮ፣ ዝም ብሎ አስወጭው ቢለኝ መልሴ እሺታ ነበር፡፡ ያኔ ግን በሥርዓት ስላወራኝ ከፅንሱ መውረድ ይልቅ እኔ ጋር በአደባባይ ምሳ መብላቱን ነበር እንደ ትልቅ ክብር ያዬሁት፡፡ አሁን ላይ ነው ፍርኃት መሆኑ የገባኝ፡፡ታዲያ እስከ ዛሬ አስባለሁ... ያን ያኽል ሚስቱ ጋር ሲኖሩ ልጅ አልነበራቼውም፡፡ እምቢ ብሏቼው ነው፣ ያልተሳሉት ታቦት፣ ያልሞከሩት ሕክምና የለም ይባላል፡፡ እዚህ “አስወጭው'' እያለ፣ እዚያ ሲሳል ትንሽ እንኳን ቅር አይለውም? ወይንስ ልጁ በእኔ ወጥቶ መልከ ጥፉ እንዳይሆን ሰግቶ ነበር!? እሺ! ትዳሩ እንዳይፈርስ፣ እንዳይበጠበጥ ይፈለጋል፣ ግን ደግሞ ወጣት ተማሪ እያሳደደ ያወጣል፡፡ ከዚያ ወዲህ ትዳር የሚባለው ነገር ያስፈራኛል፤ ምኑም አይገባኝም፣ ምኑም! ሰርግ እያለ ሕዝቡ ላቡ ጠብ እስኪል የሚጨፍረው፣ ለዚህ የሌባና ፖሊስ ድብብቆሽ ነው!?

የሆነ ሆኖ ጋሽ ዓለምነህ የሚያውቀው ነርስ ይሁን ዶክተር እንጃ፤ እሱ ጋር ልከኝ ፅንሱን አስወጣሁት፡፡እንዳሳመነኝ ቀላል አልነበረም፡፡ ያንን ነገር ካደረግሁ በኋላ ለረዥም ጊዜ የቆዬ የደም መፍሰስ ያስቼግረኝ ነበር፡፡ሆስፒታል ሄዶ ለመታዬት በመፍራቴ፣ ረዥም ጊዜ ጥርሴን ነክሼ ቻልኩት። ቆይቶ መጥፎ ጠረን ያለው ፈሳሽ ከማሕጸኔ እየወጣ ሰው ፊት መቀመጥ እስክሳቀቅ ድረስ ሲረብሸኝ ደፍሬ ታዬሁት:: “ኢንፌክሽን' ነው ብለው መድኃኒት ሰጡኝ፡፡ ሁሉም ነገር ከዚያ በኋላ ቆመልኝ፤ ከመንፈሴ በስተቀር፡፡ ላይመለስ አብሮ የሄደ አንዳች ነገር ውስጤ ነበር፡፡ ቢያንስ ከዚያ በፊት መልከጥፉነቴ ከውጭ እንጂ፣ ውስጤ ውብ ነው የሚል ስሜት ነበረኝ፡፡ ልክ እንደ ልብስ ብገለበጥ በዓለም ተወዳዳሪ የሌላት ቆንጆ ሴት የምትገለጥ ዓይነት፡፡ ከዚያበኋላ ግን ውስጤም ውጨም አስቀያሚ መስሎ ታዬኝ። ወደ ኮሌጅ የገባሁት በእንዲህ ያለ የሥጋም የመንፈስም ስብራት ነበር፡፡ ቢሆንም ጋሽ ዓለምነህ ከውስጤ ሊወጣ አልቻለም፤ ክፉኛ ይናፍቀኝ ነበር። ብዙ ጊዜ ወይ በትምህርት ጉብዝናዬ፣ አልያም በማኅደረ በኩል ከሚቀርቡኝ ወንዶች አንድኛቼውም _ ለፍቅር _ አስበውኝ አለማወቃቼው፣ የሚፈጥርብኝን _ ሕመም የማስታግሰው “ልዕልት የመሰለች ሚስቱን ትቶ እኔ ጋር የተኛ ወንድ ነበር፣ ምድረ ኮሳሳ መጣችሁ ቀራችሁ'' እያልኩ ነበር፡፡ ማኅደረም በሰልፍ ለፍቅር የሚማጸኗትን ወንዶች፣ በእምቢታ እየሸኜች በግቢው “መነኩሴዎቹ'' እስከመባል ደርሰን ነበር፡፡ እስከምመረቅ አንድም ወንድ ጋር ወጥቼ አላውቅም፡፡ በእርግጥ የምቀርባቼው ወንዶች ነበሩ፤ ግን ሁሉም እንደ መጋረጃ እኔን ወደጎን ሰብሰብ አድርገው ወደ ማኅደረ የሚንጠራሩ ነበሩ (ማኅደረ አሁን ያገባችው ባሏን ዮናስን ጨምሮ) የተመደብኩት ንግድ ሥራ ኮሌጅ ስለነበር በየቀኑ ከቤቴ እየተመላለስኩ ስማር፣ አልፎ አልፎ ጋሽ ዓለምነህን ዓዬው ነበር፡፡ ሲያሰኜው የአንገት ሰላምታ ሰጥቶ ያልፈኛል፤ በል ካላለውም ከናካቴው ዘግቶኝ ይሄዳል፡፡ በመጨረሻ እንዴት እንደሆነ እንጃ ሚስቱ ጋር ጠቅልለው አሜሪካ ገቡ አሉ፡፡ ሄጃለሁ ደህና ሁኝ ማንን ገደለ፡፡ ይኼን ስሰማ፣ እስከምሞት ድረስ ወንድ የሚባል የሚቀርበኝ አልመሰለኝም ነበር፡፡
👍371
ከቤት ወደ ሥራ ከሥራ ወደ ቤት መመላለስ የሕይወቴ ዑደት በሆነበት በስንተኛው ዓመት እንደሁ እንጃ ታክሲ ውስጥ አንዱ ብጉራም “ጥርስሽ ያምራል” ብሎ ነጄሰኝ። ተሰብሬ የተገኘሁ እኔ፣ ቶማስ የሚባል መንፈሰ ሰባራ ጋር ለዛ የሌለው ፍቅረኝነት ውስጥ ገባሁ፡፡ ውስጤ ያን ሁሉ ከበደለኝ ጋሽ ዓለምነህ ይልቅ ቶማስ ላይ ያጉረመርማል፡፡ የዚያን ቀን እዚህ ራስ ሆቴል የነበረ የመጽሐፍ ምረቃ ዝግጅት ላይ የሄድኩት፣ ከሳምንት በፊት የገዛሁትን “ሚኒስከርት” የት ልልበሰው? እያልኩ ሳስብ (እንዲሁ ሥራ ቦታ ምናምን የሚለበስ ዓይነት አልነበረም። አንዲት አየር መንገድ የምትሠራ አስተናጋጅ ናት ከፊንላንድ አመጣሁት ያለችኝ፡፡ የሐበሻ ቀሚስ ዓይነት ጥልፍ ያለው የፈረንጅ “ሚኒስከርት'' ገልብጨ ታጉን ሳዬው ሜድ ኢን ቻይና የሚል፣ ከቻይና ፊን ላንድ፣ ከፊን ላድ ኢትዮጵያ የመጣ ከርታታ ስደተኛ ቀሚስ፤ አንቺ እግርሽ ያምራል፤ ሞክሪው ምናምን ብላኝ ብሩን እንኳ ገና አልከፈልኳትም) እና ጓደኛዬ ቶማስ የሥነ-ጽሑፍ ዝግጅት አለ ብሎ ስለጋበዘኝ “ሚኒስከርቴን” ለማሳዬት ነበር የሄድኩት። ታዲያ ማኅደረን ይዣት ሄድኩ። አብርሃም የሚባለውን ጸሐፊ መጽሐፍ አስነብቢያት በአንድ መጽሐፍ እንደመውደድ አድርጓት ነበር መሰል፣ ያን ሰሞን ወሬዋ ሁሉ እሱ ሆኖ ነበር። በምንም ነገር ማኅደረ እንደዚያ ነበረች፡፡ አንድ ነገር ትይዛለች ግራ ቀኝ አትልም! ምንም እንኳን መጽሐፉን ሳውሳት አንብቤ እንደወደድኩት አጋንኜ ቢሆንም፣ እሷ ስታዳንቀው ምን ቢጽፍ ነው? ብዬ ከሷ በኋላ ነበር ያነበብኩት፡፡ ሐዘን አልወድም ያለን መቼ አነሰን?ሳቅስ ከሚፈጥርብኝ ደስታ አልፎ _ ጥርሴን _ የማሳይበት አጋጣሚ ነው- ለእኔ፡፡ በሐዘን ብቆራመት ምን አተርፋለሁ? እዚህ ፊት ላይ እንኳን ሐዘን ተጨምሮበት...! ያ መጽሐፍ ያን ሰሞን የተወራለት የእናት እና ልጅ ታሪክ ነበር ... አንጀት የሚበላ ነገር! አጋምሼ ተውኩት። አንዳንድ ሰው አለ፣ ከአንድ አንድ የተተኮሰው የማይስተው? የዚያን ቀን ማኅደረና አብርሃም ተዋወቁ፤ ትውውቁ ትንሸ አስቂኝ ነገር ነበረው፡፡ ልክ ዝግጅቱ እንዳለቀ፣ ቶማስ አብርሃምን አምጥቶ ሊያስተዋውቁን ወደ ፊት ሄዶ ነበር። የቶማስ ባሕሪ

ይገባኛልና በውስጤ የማይታይ ፈገግታ አለ፡፡ አብርሃም እስኪወጣ ጠብቀን መተዋወቅ እንችል ነበር፤ ግን ማዘዝ እንደሚችል፣ እንደ በግ ማንንም ጎትቶ ማምጣት እንደሚችል፣ ማሳዬት ፈልጓል፡፡ ይቺን ይቺንማ አልስታትም፤ እኔም ውስጥ አለች፡፡ ማኅደረን ሊተዋወቁ ለሚያሰፈስፉ ወንዶች እንደፈለግሁ እንደማዝዛት ለማሳዬት እንደዚያ ያደርገኝ ነበር፡፡ ይኼን እያሰብኩ ዞር ብል ማኅደረ እንደለመደችው ጫማዋ ጠፍቷት ወንበር ሥር ትፈልጋለች። ግራ የሚገባኝ ባሕሪዋ ይኼ ነው፡፡ የትም እንሂድ የት ስትቀመጥ የአንድ እግሯን ጫማ የማውለቅ ዓመል አለባት፡፡ ታዲያ አንዳንዴ ጫማዋ ይጠፋባታል፤ ጫማዬ ጠፋ ትላለች “አትጨማለቂ የአንቺ ጫማ ፈላጊ አይደለሁም!'' ብልም ያው ማፈላለጌ አይቀርም፡፡ ጫማው ሳይገኝ፣ ቶማስ ልክ ግዳይ እንደጣለ አንበሳ አብርሃምን እጁን ይዞ እየጎተተዉ አጠገባችን ደረሰ፡፡ ገና ከመምጣቱ፣ ገና ሳይተዋወቁ “ምን ጠፍቷቸሁ ነው?” አለ፡፡ ማኅደርን እያዬ፣ ድንብርብር ብላ ወደ እግሯ እያሳዬችው “ጫማዬ...!” አለችው፡፡ ባዶ እግሯን እየተመለከተ “እንኳን ጠፋ! ባይጠፋ ይኼን ቆንጆ እግር አናይም ነበር!'' አለ። እስቲ አሁን ይኼን ምን ይሉታል?! ደግሞ የእርሷ መሽኮርመም! ወዲያው ራመድ ብሎ ጫማዋን ከሆነ ቦታ አገኜውና ይዞ መጣ፡፡ ታዲያ ቶማስ በኋላ “ምን እንዲህ ያደናብራታል? ጫማዋ እስኪጠፋ! ድሮም ሴቶች ሲቆላቼው እንዲህ ናቸው፤ ሆነ ብላ እግሯን ለማሳዬትም ይሆናል" አለ፡፡ እሱን ማስረዳት ድካም ስለሆነ ዝም አልኩ፡፡ ሰበብ ፈልጎ ሴቶችን ካልዘለፈ አይሆንለትም፤ በሽተኛ!! ተያይዘን በቅርብ ወደሚገኝ ካፌ ሄድን። አብርሃም ዓይኑን ከማኅደረ ላይ ሊነቅል ነው እንዴ!? ፊታችን አንዴ መልኳን፣ አንዴ ፊቷን ሲያሞግስ ይሉኝታ እንኳን አልያዘውም፡፡ የሆነ ብቻቼውን የተቀመጡ ዓይነት፣ እኔንም ቶማስንም ከሰው አልቆጠረንም፡፡ _ ያቺ ወንድ ለምን አዬኝ ብላ የምትመናቀር _ ማኅደረ እየተሸኮረመመች ዝም! ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ብያለሁ በውስጤ፣ ልክ ከዚያ

በፊት እንደሚተዋወቅ ጓደኛ ነበር አወራራቼው፡፡ በተለይ የማኅደረ ነገር ገርሞኝ ልሞት! ሰውን አውቀዋለሁ ማለት ዘበት ነው፡፡ ከሳምንት በኋላ መሰለኝ እየተፍነከነከች “ደወለልኝ” አለችኝ። ያቺ ደመ ቀዝቃዛ ጓደኛዬ እንደዚያ ስትሆን ዓይቻት አላውቅም። ግንኙነታቼው ፍጥነቱ እስከዛሬም ይገርመኛል፡፡ መኻል ላይ ምን እንዳለፈኝ አለዉቀም፤ ልክ ዓይኔን ከድኜ ስከፍተው በፍቅር እየከነፉ አገኘኋቼው፡፡ ከደወለላት፣ ልብሷን ጥላ መሮጥ፤ ከደወለችለት፣ መድረክ ላይ የሚያነበውን ነገር ትቶ ወደሷ መሮጥ ነው። በተለይ ማኅደረ ልክ ግድቡ የተደረመሰ ውሃ ዓይነት ነበር በፍቅር የጎረፈችው። አልዋሽም ድብን የሚያደርግ ቅናት ተሰምቶኛል፣ የነገሩ ፍጥነት...ስሜቱ፤ በተለይ ስሜቱ። “ተጠንቀቂ እሱ ልጅ ሴት ይወዳል ይባላል!'” አልኳት። እንዲህ የተሳካ ነገር ግን ከዚያ በፊት አእምሮዬ ውስጥ ያልነበረ ዓረፍተ ነገር ከአፌ ተቀናብሮ አመለጠኝ፡፡ “አዎ! ነግሮኛል'' አለችኝ ቀለል አድርጋ እየሳቀች፡፡ እውነቱን ለመናገር ከአንቺ የተሻለ አውቀዋለሁ፣ እኔንም ሞክሮ ነበር ንቄ ትቼው ነው፤ በሚመስል ውስጠ አዋቂ ፈገግታ። እንዲሁ ለማለት ካልሆነ በስተቀር፣ ሴት ይውደድ፣ አልያም መነኩሴ ይሁን፣ ወይም ስልብ የማውቀው ነገር አልነበረም፡፡ በእርግጥ የፍቅረኛዬ ቶማስ ጓደኛ ነበር፡፡ ግን እንኳን ጓደኛውን ራሱ ፍቅረኛዬንስ የት አውቀዋለሁ!? አንዳንዱ ቃል እንደ ትንቢት ይይዝ የለ? ያገኛት ሴት ጋር የሚሄድ በዋል ፈሰስ መሆኑን ቆይቶ ሰማሁ። አሁንም ሰማሁ ነው፤ ትንሽ ቅሬታ ነበረኝና የሰማሁትን ማመን ፈለግሁ፡፡ ስለ እሱ ክፉ የተወራበት ቦታ “እሱ አያደርግም አይባልም'' እያልኩ አልጠፋም፡፡ ቅናት ብቻ አልነበረም... በሆነ የማላውቀው ዓይነት ምሬት ተሞልቼ ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህ፣ ይኼን ይኼን በተለይም ያቺን ለስላሳ ቅናቴን ለማስታገስ፣ የማይገባኝን ሥነ-ጽሑፍ ተንተርሼ በሥራው እየታከክሁ፣ ላገኜሁት ሁሉ የማይረባ ጸሐፊ መሆኑን ማወጅ ጀመርኩ።

ኡኡቴ! በነሀዲስ ዓለማየሁ፣ በነበዓሉ ግርማ፣ አገር... በነጸጋዬ ገብረመድኅን፣ በነስብሀት ገብረእግዚአብሔር አገር... እያልኩ (አንዳቼውንም ከስማቼው በስተቀር ምን ጻፉ ብባል አላውቅም፡፡ ቶማስ እንደመፈላሰፍ ሲያደርገው “የቀደሙትን አጥንት ከመቃብር አውጥተን፣ አሳምረን ስለን ቋሚውን ለመውጋት ማንበብ ምን ያስፈልጋል!? እነሱንስ ከእነሱ በፊት ባሉት አልወጋንም? የአገር ቤቱ አጽም ቢዶለድምብን ከራሽያ በረዶ ሥር ቆፍረን ባመጣነው አጽም፤ ከሙታን አጥንት መርዛማ ፍላጻ በመሥራት ጠቢባን ነን'' ይላል! አንዱ ወጊ እሱ እንዳልሆነ ሁሉ! እናም በአጥንቶቹ ላይ ተረት እመርቅበታለሁ፤ “ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ"? “ሰው ቢታጣ ይመለመላል ጎበጣ”፣ “ሰው ጥሪ ቢሏት ...
👍324
አገር ሲያረጅ ጃርት १८८८!" ማኅደረ ይኼን ሁሉ ስል ስለሌላ ስለማይመለከታት ሰው የማወራ ይመስል በሚያማምሩ የዋህ ዓይኖቿ እያዬችኝ በፈገግታ " ጸሐፊ ይሁን ነብሰ ገዳይ ምናገባኝ? ግን በቃ ውድድ አድርጌዋለሁ" ትለኛለች፡፡ ይኼም ያበሳጨኛል፡፡ ያ ሁሉ ጥቅስ ተረት ማጣጣል ውሃ ሲበላው፤ ያ ሁሉ ፍላጻ ዒላማው ላይ ሳይደርስ ሲመክን ያበሳጨኛል። “አይ በቃ አስደግሞብሽ ነው" እላታለሁ። “ሎጅክ' ሲጠምብን ወደ ተአምር የምንሮጥ ሕዝቦች ነንና የመጨረሻ ጠጠሬን እንዲህ እወረውራለሁ፣ ይኼም ዒላማውን ይስታል፡፡ ምንም እንዳላወራሁ ነገሬን ችላ ብላው «ይልቅ ሃይሚዬ አንድ ነገር ልንገርሽ፣ ወይኔ እቤቱ ያለው ሲዲ “ፕሌየር" አተላለቁ... ድምፁ..." ትልና በሳቅ ፍርስ ትላለች፤ የራሴን ግምት ማመን እጀምራለሁ፡፡ ይኼ ልጅማ አስደግሞባት ነው፣ እስቲ አሁን “ሲዲ ፕሌየር' ምኑ ነው እንዲህ የሚያስለመልመው በእግዚአብሔር!? ቤት ነው መኪና? ጓደኛዬ ማኅደረ ጠይም ናት፣ በጠይሞች አገር ጥይምና ምን ይገርማል? አፍንጫ ነው ጥርስ? ጸጉር ነው ቅርጽ? ብልም የማኅደረ ጥይምና ግን ያያት ሰው ሁሉ

እእምሮ ውስጥ ለዘላለም ታትሞ የሚቀር ዓይነት ነበር፡፡ ሕፃን ሆነን ባርች እያልን ነበር የምንጠራት፤ ስናድግ ግን ጠይምነቷ አብሮ አደገ፡፡ እንደ ቁመት፣ እንደ ጸጉር፣ እንደጥፍር የሚያድግ ጥይምና፤ ዕድገቱ የመጠን አልነበረም ባለበት የመታደስ እንጂ።ጥቁር የነበረችው ልጅ ስታድግ ጠይም ሆነች። ፀሐይ እንደዲን በሚወርድበት _ አገር፣ ፈረንጅ መጥቶ ጠይሞ በሚመስልበት ምድር፣ ጥቁር መጠዬሙ ምን የሚሉት ነገር እንደሆነ እንጃ! በቃ ዓይናችን እያያት ጠየመች፡፡ ተፈጥሮ ወገቧን ታጥቃ የኳለቻት ሴት ማኅደርን አዬሁ፡፡ አንዳንዴ ታዲያ ዝም ብዬ መልኳን ስመለከተው ውስጤን የሆነ ብስጭት ይሞላኛል፡፡ ቁመት፥ጸጉር፥የሰውነት ቅርጽ፣ ዓይን፣ አፍንጫ፣ ክንፈር፣ ጥርስ፣ ጡት፣ እጅ፣ እግር... እንዴት እንዲህ ተስተካክሎ ለአንድ ሰው ይሰጣል? ያቺ ሂያጅ እናቷ ከዬት ከዬት ቀላቅላ ብትወልዳት ነው? እላለሁ፡፡ ከአንድ ወንድ ብቻ የተወለደች እስከማይመስለኝ ድረስ ማኅደረ ቆንጆ ነገር ሁሉ ተለቃቅሞ የተሰጣት ልጅ ነበረች፡፡ እና አሁን ፈጣሪ ፍትሐዊ ነው ማለት እንዴት እችላለሁ?

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍24👎1🥰1👏1
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-15


///
ዛሬም እንደወትሮዬ  የተለመደው  ሱፐርማርኬት ጎራ ብዬ ለልጆቹ ቸኮሌት ለእሷ ደግሞ ትኩስ እንብጥ ፅጌረዳ አበባ ገዝቼ በሚንቀጠቀጥ ሰውነትና በራደ ልብ ጉዞዬን ቀጠልኩ።ሰራተኛዋ የውጩን በራፍ ከፈተችልኝና መኪናዬን ወደውስጥ በማስገባት  እንደተለመደው አበባውን እዛው ባለበት ቦታ ትቼ የልጆቹን  ቸኮሌት ይዤ ወደውስጥ ስገባ ልዕልትን ሳሎን ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ ልጇን ጡት እያጠባች አገኘኋት...ገና ሳሎኑን ከፍቼ ስገባ በአስደንጋጭና ብርሀናዊ ፈገግታ ተቀበለችኝ...እየተንደረደርኩ ወደእሷ ቀረብኩና በተቀመጠችበት ሳላምታ ሰጥቼያት እያጠባች ያለችውን  ልጅ ግንባር ስሜ ከፊት ለፊቷ ተቀመጥኩ።
‹‹ዶ/ር ይሄን ቸኮሌት አቁም ማለት ሰለቸኝ እኮ››
‹‹ከሰለቸሽ  አቁም ማለቱን  አቁሚያ..››
ፈገግ አለች‹‹በጣም እልከኛና የሠው ነገር የማትሰማ ሰው ነህ።››
‹‹ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት አስተያየት ማንም ሰጥቶኝ አያውቅም።››
‹‹እንደአንተ አይነት የተሳካለትን ስፔሻል ዶ/ር ን ማን ነው ደፍሮ ተሳስተሀል የሚለው?..ስትሳሳት ቢያዩህ እራሱ አይ የገዛ አይኔ ነው የተሳሳተው ብለው አይናቸውን ነው የሚጨፍኑት።››ብላ አሳቀችኝ።
‹‹እሺ መስፍን እንዴት ነው?››
‹‹ሰላም ነው...አሁን ሰውነቱን አጣጥቤው  ተኝቷል...ትቸኩላለህ እንዴ?››
‹‹አይ ...አረ አልቸኩልም...ግን ማልቸኩለው ያንን ታሪክሽን ምትነግሪኝ ከሆነ ነው።››
‹‹የቱን?››
‹‹እየሰሰትሽ እና እየቆነጣጠርሽ የምትነግሪኝን የፍቅር ታሪክ ነዋ።››
‹‹እ...እንግዲያው ትንሽ ታገስ መጣሁ›› ብላ ልጆን አንጠልጥላ ከተቀመጠችበት  ተነሳች።ስትነሳ  ልጇ አፍ ውስጥ ተመስጎ የነበረው ጡቷ አፈትልኮ ወጣና  ሙሉ በሙሉ ለእይታ ተጋለጠ...ተንደርድረህ በመሄድ ለቀም አድርገህ ያዝና አፍህ ውስጥ ጨምረው የሚል ስሜት ተናነቀኝ።እንደምንም ስሜቴን ተቆጣጠርኩ....።እሷ ስለእኔ የስሜት መደፍረስ ልብ ሳትል  ጡቷን በግራ እጇ ወደውስጥ መለሰች እና ልጇን  ይዛ ከፊቴ ዞር አለች ...እኔም ተንፈስ አልኩና ስሜቴን ወደነበረበት ለመመለስ ጥረት አደርግ ጀመር።ከ5 ደቂቃ በኃላ ልጇን አስቀምጣ  አንድ ቢራ  ከብርጭቆና ከመክፈቻው ጋር  አመጣችና ከፍታ ከፊት ለፊቴ ቁጭ አለች።
‹‹እሺ ዶ/ር እንዴት ነህ..?››
‹‹ያው እንደምታይኝ ደህና ነኝ...ይልቅ ጊዜ ሳታባክኚ ወደታሪክሽ ግቢ።››
ፈገግ አለችና‹‹እሺ የት ላይ ነበር ያቆምኩት?››
‹‹ቤትሽን ተከራይቶ እቃውን ካስገባ……። ››
‹‹አዎ ..ገባ ።ጥዋት ወደስራ ሲሄድና ማታ ከስራ ሲገባ እየጠበቅኩ እሱን ማየት ጀመርኩ።ባንክ ስለሚሰራ ዘወትር ሙሉ ልብስ ለብሶ ሽክ እንዳለ ነበር...።››
‹‹ቆይ የእውነት..ሚስት አልነበረው? ››
‹‹አረ የምን ሚስት...ገና ሮጦ ያልጠገበ ነበር...ሚስት አልነበረውም...ግን በየሶስት አራት ቀኑ ነበር የተለያዩ ሴቶችን የሚያመላልሰው ።አንዴ የመጣች ሴት ተመልሳ ሌላ ጊዜ አትመጣም።..ያንን ሳይ ይበልጥ እያሳዘነኝ መጣ...?››
‹‹እያሳዘነኝ...?››
‹‹አዎ...እያሳዘነኝ።መቼስ ሰው ወዶ እንደዛ አይሆንም..።አንድ የምትመቸውና የምትረዳው ሴት ቢያገኝ  እንደዚህ ከዚችም ከዛችም ጋር አይንገላታም ነበር ብዬ አሰብኩና እንዴት እንደምረዳው ማሰላሰል ጀመርኩ...።በዚህ መካከል የራሴን ጓደኛ እኔ ጋር ስትመላለስ አያትና ቀጥታ ወደእኔ መጥቶ  ‹‹ጓደኛሽን አጠብሺኝ. ..ወድጄታለሁ።››አለኝ…በጣም ደነገጥኩ...‹‹እሺ ጠይቅልሀለው ..ግን ታገባታለህ?››ስል የሞት ሞቴን ጠየቅኩት።

ፍርጥም ብሎ ‹‹ምን ነካሽ ....እንዴት ታገባታለህ ብለሽ ትጠይቂኛለሽ?››አለኝ።
የውስጤን በውስጤ አፍኜ ‹‹ከወደድካት ብታገባት ምን አለበት..?››አልኩት።
‹‹ቆይ አንቺ ትወጂኝ የለ እንዴ?››ሲል ግራ አጋቢ ጥያቄ ጠየቀኝ።
ደነገጥኩ...ሰውነቴ ሁሉ ሲንቀጠቀጥ ይታወቀኝ ነበር...አንገቴን ደፍቼ‹‹ እሱማ አዎ...እወድሀለው››ስል መለስኩለት።
‹‹እሺ ስንት አመትሽ ነው?››
‹‹17 ››
‹‹በቃ ልክ አስራ ስምንት ሲሞላሽ ሽማግሌ ልካለሁ።››አለኝ።
‹‹የምን ሽማግሌ?››ስል መልሼ ጠየቅኩት።
‹‹ላገባሽ ነዋ...ምነው አንቺ ልታገቢኝ አትፈልጊም?››
‹‹እሱማ ፈልጋለው።››
‹‹በቃ ዕድሜሽ እንደሞላ አገባሻለሁ...እስከዛ ግን ከሌሎች ሴቶች ጋር እደሰታለሁ..አይከፋሽም አይደል?››
‹‹አረ አይሰከፋኝም።››አልኩት የእውነቱን ግን ጥልቅ ድረስ ልቤን በሚሸረካክት መልኩ ነበር የሚከፋኝ ።ግን እሱን ካስደሰተው እኔ ብሰቃይም ችግር የለውም ብዬ ወሰንኩ..፡፡
‹‹እሺ በቃ እንዳልክ...አሁን 17 ዓመት ከሶስት ወሬ ነው።ከዘጠኝ ወር በኃላ ትልካለህ።››አልኩት።
‹‹ተስማምቼለሁ...አሁን ግን እንደአልኩሽ ጓደኛሽን አሳምነሽ አምጪልኝ››አለች።
እንዳለኝም ሳምንት ሙሉ ለምኜና እግሯ ላይ ወድቄ እቤቱ ድረስ አመጣሁለት ...።ከዛ በኃላም እሱ ለሚያመጣቸው ሴቶች ሻይ እያፈላሁ… የሚፈልጉትን ነገር እያቀረብኩ እየተንከባከብኩ ስሸኝ...18 ዓመት እስኪሞላኝ እያንዳንዶን ቀን አልደርስ ብላኝ ስቆጥር  ከረምኩ።..ጓደኞቼ ይሄ ሸርሙጣ ውሸቱን ነው ዞር ብሎ አያይሽም ሲሉኝ ...እኔም እውነት አፍንጫሽን ላሺ ይለኝ ይሆን እንዴ ? ብዬ ስሰጋ አይደርስ  የለ ደረሰ...እሱንም ለማስታወስ እንዲያግዘኝ አያቴን አሳመንኩና የ18 ዓመት ልደቴን ድል አድርጌ ደገስኩ..።.ወንድሞቼ ዘመድ ወዳጅ ፤ጓጀኞቼ አንድ ሰው አልቀረም...መለስተኛ ሰርግ በለው፡፡በእለቱ  ዝግጅቱ ላይ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ቢኖርም ምንም አላለኝም...።እያንዳንድ ሰው የራሱን ስጦታ ሲሰጠኝ ቢውልም እኔ ግን ከእሱ የሆነ  አይነት ስጦታ አዘጋጅቶልኝ ይሆን ብዬ እጅ እጅን ሳይ ነበር የዋልኩት...እሱ እቴ ምንም እንዳለሰበበት ሳውቅ ከፋኝ...ጓደኞቼ ሲያስፈራሩኝ የነበረው እውነት ይሆን እንዴ...?የሚል ስጋት መተንፈስ እንዳልችል ጉሮሮዬን አነቀው። እንዲሁ ስጨነቅ ውዬ ማታ አካባቢ ለሆነ ጉዳይ ወደጓሮ ስሄድ ከየት መጣ ሳልለው አፈፍ አድርጎ ወደቤቱ አስገባኝ...።
በጣም ደነገጥኩ...እዛ ቤት ከገባ አመት ቢያልፈውም አንድ ቀን እንዲህ አድርጎ አያውቅም። በራፋን ቀረቀረና ከግድግዳ ጋር አጣብቆኝ ከንፈሩን ከንፈሬ ላይ አጣበቀው..መተንፈስ አቃተኝ...፡፡በአየር ላይ ሁሉ የምንሳፈፍ ሁሉ መሠለኝ..።ሲረበሽና ሲናወጥ የሠነበተው ውስጤ በደስታ ሲረሰርስ ተሰማኝ...።ምን ያህል ደቂቃ ወይም ሰዓት በመሳሳም እንዳሳለፍን አላውቅም ግን ድንገት ከንፈሩን ከከንፈሬ አላቀቀና በራፉን ከፍቶ..
‹‹የእኔ ፍቅር እንኳንም 18  ዓመት የልደት በአልሽ አደረሰሽ...መልካም ልደት...ይሄ መሳም እንደልደት ስጦታ ተደርጎ ይወሰድልኝ››አለና የመገፍተር ያህል ከደነዘዝኩበት አንቀሳቅሶ ከክፍሉ አስወጣኝና እሱ እዛው ውስጥ ቀርቶ በራፍን ቀረቀረብኝ..።.ድንዛዜዬ በቀላሉ ጥሎኝ ሊሄድ አልቻለም...።ከቤቱ ባያስወጣኝና ለዘለአለምም መሳሙን ባያቋርጥ ደስ ይለኝ ነበር...። እንደምንም በድኔን እየጓተትኩ ወደቤቴ ተመለስኩ..።የእለቱ ዝግጅትም በዛው ተጠናቀቀ።
‹‹እና  ሽማግሌ ላከ?››እኔ ነኝ ጠያቂው።
👍5310🔥1🥰1