አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
512 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ዶ/ር ሶፊያ ግማሽ ልቧን ታዲዬስ ጋር ጥላ እሩብ ልቧን ወደ ትንግርት ልካ በሩብ ልቧ ነው ከሀዋሳ ተመልሳ ቤቷ የደረሰችው፡፡የሳሎኑን በር ከፍታ ስትገባ ፕሮፌሰር ዬሴፍ ሶፋ ላይ ጋደም ብሎ ፊልም እየተመለከተ ነበር፡፡ እንደገባች በፍቅር እና በመፍቀለቅለቅ ተጠመጠመባት ..ከንፈሯን ሳመት…ዝም ብላ ሳትስመው ተሳመችለት፡፡ ሰላምታውን ከጨረሱ በኃላ የፊቷን መገባበጥ ሲመከት በጣም ደነገጠ ‹‹እንዴ ቤቢ.… ምንድነው ይሄ.....? ምን አጋጠመሽ?::<<

‹‹ትንሽ የመኪና ግጭት ነው፡፡››ዋሸችው፡፡

‹‹ታዲያ ተረፍሽ..…?››

‹‹አዎ ቀላል ግጭት እኮ ነው ..ግን አንተ እንዴት መጣህ?››

‹‹አንቺ ጋር ነዋ፡፡››

‹‹እሱማ በስልክ ነገርከኝ ...ማለቴ እንምትመጣ አልገርከኝም ብዬ ነው?››

‹‹ሰርፕራይዝ ላደርግሽ ፈልጌ ነዋ፡፡››

‹‹እብድ እኮ ነህ.....ሰው እንኳን ከአሜሪካ ከደብረዘይት ሲመጣ ይናገራል…፡፡››

‹‹ልጅቷስ የት ሄደች ?››አለችው..ከመጣች ሰራተኛዋን ስላላየቻት ግራ ተጋብታ፡፡

‹‹አለች ..ቢራ እንድትገዛልኝ ልኬያት ነው፡፡››

‹‹ፍሪጅ ውስጥ የለም እንዴ?››

‹‹ጨረስኩታ... ከመጣው እኮ ሶስት ቀን ሆነኝ፡፡››

‹‹እስቲ መጣው በጣም ሞቆኛል... ሰውነቴን ለቅለቅ ልበል››አለችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ወለሉ ላይ አስቀምጣ የነበረውን ሻንጣዋን እየጎተተች ወደ መኝታ ቤት ገባች፡፡

ዬሴፍ ከኃላዋ መላ አቋሟን እና የሚሞናደለውን መቀመጫዋን በአትኩሮት ተመልክቶ‹‹አማላይ ነሽ….›አለና ምራቁን ዋጠ፡፡ በእድለኝነቱም አምላኩን አመሰገነ፡፡ በአንድ ወር ውስጥ ደስ በሚል ሁኔታ ድል ባለ ሰርግ ያገባትና መልሶ ወደአሜሪካ ይዟት ይሄዳል..ወደአሜሪካ የመሄዱን ሀሳብ አልቀበልም ብትለው እንኳን ከእሷ የሚበልጥበት ነገር ስለሌለ እሱ ጓዙን ጠቅልሎ ወደ ሀገር ውስጥ ተመልሶ ከእሷ ጋር ይኖራል ..፡፡አሁን በሱ ህይወት የጎደለችው እሷ ብቻ ነች፡፡የሚፈልገውን አይነት ትምህርት ተምሯል፣የሚፈልገውን ዓይነት ስራ እየሰራ ነው፣የሚፈልገውን ያህል ገንዘብ አጠራቅሟል፣በዚህ ሁሉ ስኬት ላይ ሶፊን ማግባት ከቻለ…እሷ ደግሞ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ልጅ ከወለደችለት ..በቃ በዚህ ምድር ላይ ከእሱ በላይ ዕድለኛ ሰው ከየት ይገኛል?፡፡

ሶፊ መኝታ ቤቷ እንደገባች በቁሟ ነበር አልጋዋ ላይ የተዘረረችው፡፡የሶስት ዓመት
ፍቅረኛዋ በእሷ ትልቅ ተስፋ አድርጎ ውቅያኖስ ተሻግሮ በመምጣት ሳሎኗ ውስጥ ይገኛል፡፡ እሷ ግን በአካል ስታገኘው ውስጧን ደስታ አልተሰማትም…እንደውም በተቃራኒው የቅሬታና የመረበሽ ስሜት ነው በደም ስሯጰየተሰራጨው..በውስጧ የተፈጠረውን ስሜት ልትቆጣጠረው የምትችለው ዓይነት አይደለም፡፡ብቻ ውስጧ በነውጥ እየተናጋ ነው፡፡በልቧ ኃይለኛ ወጀብ ሲደበላለቅ ይሰማታል፡፡ከሚጡ ፣ከሰላም፣ ከሄለን ፣ከሀሊማ እና ከሙሴ ጀርባ የታዲዬስ ምስል በትልቁ ይታያታል፤ፅዬን ደግሞ እሱ ጭንቅላት ላይ ጉብ ብላ ስትደባብሰው.. በውስጧ የተፈጠረው ብስጭት ጭንቅላቷን አቃጠላት፤ከእዛ ሀሳብ ስትሸሽ ደግሞ ትንግርት ተቀበለቻት...ተፈናጥራ ከመኝታዋ ተነሳችና ልብሷን በማወላለቅ ወለሉ ላይ አዝረክርካ ወደ ሻወር አመራች ..የሰውነቷን ሙቀት ብቻ ሳይሆን በአዕምሮዋ የሚተረማመስ ሀሳብ ለማቀዝቀዝ፡፡
ፀጉሯን በላስቲክ ሸፍና ቧንቧውን ከፈተች፤ውሀው ካላይ እየተንፎለፎለ ሰውነቷን ሲያረጥበው ቀስ በቀስ የጋለው ገላዋን አቀዘቀዘላት..ያም ብቻ ሳይሆን የተረበሸ መንፈሷም እየተረጋጋላት መጣ፡፡ በመሀከል ‹‹ቤቢ..ቤብ››የሚለው የፕሮፌሰር ዬሴፍ የጥሪ ድምፅ ከነበረችበት የተመስጦ ድባብ አናጠባት፡፡

‹‹...ቤቢ አልጨረሽም እንዴ?››እያለ መኝታ ቤቱን አልፎ ወደ ሻወር ቤቱ ተጠጋ፡፡

እዛው እንዲጠብቃት በሚፈልግ ስሜት ‹‹ጨርሼያለሁ ...መጣሁ›› አለችው፡፡ እሱ ግን የሻወር ቤቱን መዝጊያ ገፋ አደረገና አንገቱን ወደውስጥ አሰገገ....ዕርቃን ሰውነቷን ሲያይ በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተመለከታት ሁሉ ድንዝዝ በሚያደርግ ስሜት ተውጦ የፈጠጡ ዓይኖቹን እንደተከለባት ለደቂቃዎች ቆመ…፡፡ እሷን ግን ከበዳት፤ ለማታውቀው መንገደኛ ሰው ዕርቃን ሰውነቷን ያሰጣች መሰላት..የተቀሰሩት ጡቶቿን በእጆቿ ሸፈነቻቸው፡፡

‹‹ዬሲ መጣሁ አልኩህ እኮ..!! ሳሎን ጠብቀኝ››ሳታስበው እንደመቆጣት አለች፡፡

‹‹ሶሪ.…››አለና ከደነዘዘበት በመከራ ነቅቶ በራፉን ዘጋላትና በፍቅረኛው ያልተለመደ ሁኔታ ግራ እየተጋባ ወደ ሳሎን ተመለሰ..በፊት ቢሆን ጎትታ ነበር ወደ ውስጥ ምታስገባው.፡፡

.‹‹አይ ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆነች ይሆናል፡፡››ሲል እራሱን አፅናና፡፡

ሁሉን ነገር ጨርሳ ቢጃማዋን ለብሳ ሳሎን ስትመለስ...ሰራተኛዋ ሲኒ ደርድራ ቡና እየቆላች ነበር፡፡ ዬሴፍ ደግሞ እንደበፊቱ ሶፋው ላይ ጋደም ብሎ ቢራውን ይጐነጫል፡፡

‹‹ቤቢ መጣሽ..?›› አለት..ዩሴፍ በፊት

ከኢትጵያ ወደ አሜሪካ ሄዶ ከሶፊያ ጋር በተገናኙ እና ፍቅር በጀመሩበት ጊዜ ‹እናት› ብሎ ነበር የሚጠራት ...እናቴን ትመስያለሽ ለማለት..ከዓመታት በኃላ ግን አገሩን ሲላመድ እና የፈረንጆቹ ባህሪ ሲጋባበት..እናትን እረሳውና በቤቢ ቀየረው…ምሁራዊ የባህል ዕድገት …፡፡

‹‹አዎ ፡፡ >>አለችውና ከእሱ ፈንጠር ብላ ተቀመጠች፡፡

‹‹ቢራ ይከፈትልሽ ቤብ?››

‹‹አይ ይቅርብኝ ..ቡና ነው ያሰኘኝ፡፡››

‹‹እራት ቀርቦ በልተው የተፈላውን ቡና ጠጥተው አጠናቀቁና ተያይዘው ወደ መኝታ ቤት ገቡ፡፡ዮሴፍ ለ7 ወራት ያላገኘው ... በጣም የናፈቀውን ገላ ዳግም የሚያጣጥምበት ሰከንድ መቅረቡን ሲያስብ ውስጡ በደስታ ተጥለቀለቀ….የሰውነቱ ግለትም ለራሱ ተሰማው፡፡ከሁሉም በፊት ግን ያመጣላትን ስጦታ ሊያበረከትላት ፈለገ ፡፡
መኝታ ቤት አስገብቶ ካስቀመጣቸው 3 ሻንጣዎች ውስጥ ግዙፉን ሻንጣ ከፈተ‹‹ቤብ እነዚህ ልብሷች እና ጫማዎች ያንቺ ናቸው..ከግምቴ ትንሽ ወፈር ብለሽ ነው ያገኘሁሽ ስለዚህ አንዳንዶቹ ሊጠቡሽ ይችላሉ››አላት፡፡

ደስ እንዲለው ለቁጥር ከሚያዳግቱ ልብሶች መካከል አንድ ሶስቱን አንሳችና እንደነገሩ ሞከረች..ግን ውስጧን ደስ አላለውም... ‹ከሚያስፈልግሽ በላይ መሰብሰብ ስግብግብነት ነው፤፤››የሚለው የሰላም ንግግር አእምሮዋን ወቀራት፡፡አይደለም ባላት ላይ ተጨምሮ ይቅርና አሁን ፊት ለፊቷ በሻንጣው የታጨቀው ልብስ ብቻ ለሀያ ሴቶች በደንብ ይበቃል‹‹እውነትም ስግብግብነት…፡፡››አለች ..ሳይታወቃት ድምፅ አውጥታ፡፡

‹‹አናገርሽኝ ቤቢ..?››አላት ያናገረችው መስሎት፡፡
‹‹አይ... ያምራል ማለቴ ነው..ለማኛውም ሌሎቹን ነገ ተረጋግቼ እለካቸዋለሁ... አሁን ደክሞኛል፡፡››

‹‹አንደርእስታንድ አረግሻለሁ....ግን ከመተኛታችን በፊት ሌላ አንድ ነገር ላሳይሽ እፈልጋለሁ››

‹‹ምንድነው ዬሴፍ..አሳየኝ ?›አለችው ፡፡

ሁለተኛውን ሻንጣ ከፈተ..ውስጡ ያለውን አወጣ… በጣም ደነገጠች ‹‹..ምንድነው ?››

‹‹ለሰርጋችን ቀን የምትለብሽው ..ከፓሪስ በትዕዛዝ የተሰራ ልዩ ቬሎ..፡፡››

ሰውነቷ ዝልፍልፍ አለባት.. የምትለውን የምትናገረውን አጣች፡፡ዬሴፍም ግራ ገባው..በፊቷ ላይ ያረበበው ድንጋጤ የደስታ ነው ወይስ የቅሬታ? መለየት አልቻለው…፡፡

‹‹ቤብ..ምነው? ፈዘዝሽ እኮ!!!››

‹‹ይሄንን ከማድረግህ በፊት ልታማክረኝ ይገባ ነበር..እኔና አንተ እኮ ስለፍቅር እንጂ ስለጋብቻ አውርተን አናውቅም፡፡››
👍557
‹‹እንዴ!!! ምን ለውጥ አለው ?ከተፈቀርን መገባታችን ይቀራል..?ቤብ አልገባኝም የረጅም ዓመት ፍቅረኛዬ ነሽ.. አፈቅርሻለሁ ታፈቅሪኛለሽ..፡፡ ላገባሽ እደምፈልገው ሁሉ አንቺም ልታገቢኝ ፍላጎት አለሽ የሚል ግምት ነው ያለኝ..የማላውቀው ችግር አለ እንዴ?››

‹‹የችግር መኖርና አለመኖር አይደለም ..እሺ በድንገት መምጣትህን እንደሰርፕራይዝ ልቀበልልህ..በድንገት እንጋባ የምትለውን ግን ይከብደኛል፤ለማንኛውም ተረጋግተን ነገ ከነገወዲያ እንነጋገርበታለን… አሁን ተኛ ደህና እደር ››ብላ ግንባሩን ስማ መኝታ ቤቱን ለቃ ለመውጣት ስትራመድ ግራ እጇን በቀኝ እጁ ጨብጦ‹‹አይሆንም ቤቢ…››አላት በሚቃትት ድምጽ… ፡፡

‹‹ምኑ ነው የማይሆነው?››

‹‹የት እየሄድሽ ነው?››

‹‹ሌላ መኝታ ቤት እኮ አለ..፡፡››

‹‹በጣም እኮ ነው ሚስ ያደረግኩሽ..ለምን እዚሁ አብረን አንተኛም?››

‹‹አያስፈልግም..መልካም አዳር፡፡››ብላው የያዛትን እጇን አስለቅቃው እንደፈዘዘ ጥላው ወጥታ ሄደች፡፡፡

ፕሮፌሰር ዬሴፍ ያልገመተው ሁኔታ ነው ያጋጠመው..እንዲህ የቀዘቀዘ አቀባበል ከእሷ ፈጽሞ አልጠበቀም፡፡ሲያቃት እንዲህ አይነት ሰውን የምትገፋ ሴት አልነበረችም፡፡እርግጥ ባለፉት ሶስት ወራቶች በስልክ ሆነ በስካይፒ በሚያደርጉት ግንኙነት የተወሰኑ የፀባይ ለውጦችን፤አንዳንድ የመነጫነጭና የመቀዝቀዝ ስሜቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ አንብቦባት ነበር..ግን የተረጎመው በእሱ ናፍቆት መነሻነት ብስጭት በልቧ እንደገባ አድርጎ ነበር፤ለዛም ነበር የመምጫ ጊዜውን
በስድስት ወር አሳጥሮ አሁን የመጣው፡፡ይሄ ደግሞ እሷን የሚያስፈነጥዛት አድርጎ ነበር የገመተው..፡፡

አሁን ግን ሁኔታው አላማረውም… በውስጡ ጥቁር ፍራቻ እየተበተነ ነው፡፡ጭራሽ መኝታ መለየት!!!! ተነስቶ እስከ አሁን መምጣቱን እንኳን ወዳልነገራቸው ዘመዶቹ ሊሄድ ፈለገ ፤መልሶ ሀሳቡን ቀየረ....ነገሩን ማክረር ጥሩ አይደለም ፡፡ነገ ተረጋግታ ስታስብበት ፀፅቷት ይቅርታ ትጠይቀኛለች፤እስከዛው መታገስ አለብኝ ብሎ ወሰነ ፡፡ምን አልባት ከመንገድ ስለገባች ተዳክማ ወይም ስራ ላይ የተበላሸ ነገር አጋጥሟት በዛ ተበሳጭታ ይሆናል? ሲል እራሱን ለማፅናናት ሞከረ ፡፡አንሶላውን ገልጦ ገባና መብራቱን አጥፍቶ ከእንቅፍ ጋር ውሰደኝ አልወስድህም ትግል ጀመረ፡፡

ዶ/ር ሶፊያም ወደ ሌለኛው መኝታ ቤት ገብታ ለመተኛት ብትጥርም ግትልትል ሀሳብ በአዕምሮዋ እየተተረማመሰ የእንቅልፍ ስሜቷን ድራሹን አጠፋው፡፡ሲጨንቃት

ሞባይሏን አነሳችና ታዲዬስ ጋር ደወለች፡፡ ይጠራል... ይጠራል አይነሳም፡፡

‹‹ብሽቅ›› አለችና መልዕክት ላከችለት‹‹በሰላም ገብቼያለሁ››፡፡መልዕክቱን ከላከች በኃላ መልሳ ስታስበው ገረማት፡፡‹በሰላም ገብቼያለሁ› ማለት ምን ማለት ነው ?እሱ የእሷ በሰላም መግባት ያለመግባት ቢያሳስበው ደውሎ አይጠይቃትም ነበር…? በግድ ስለእኔ አስብ ብሎ ሰውን ማስጨነቅ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው...?በራሷ ተበሳጨች፤ከብስጭቷ ሳትወጣ በደመነፍስ አንድ ቁጥር ጋር እየደወለች ነው..…. ፍፁም መደወል የማይገባት ቦታ ..ኧረ እየጠራ ነው፤ግራ ገባት ትዝጋው ወይስ ትጠብቅ? ቢነሳ ምንድነው የምትለው?፡፡ክፋቱ ተነሳ

‹‹ሄሎ ማን ልበል?››

ፀጥ አለች..ምን ትበል?

‹‹ሄሎ አይሰማም?››

‹‹ይሰ..ማ.ል››ተንተባተበች፡፡

አሁን ደግሞ ከዛኛው ወገን ረጅም ፀጥታ፡፡

‹‹ምን ፈለግሽ..?ለምንድነው የምትረብሺኝ?››

‹‹ትን..ግርቴ..ልረብሽሽ እኮ ፈ...ልጌ አይደለም፡፡››

‹‹…እና ምን አባሽ ፈልገሽ ነው?››

‹‹በአካል ላገኝሽ እ....ፈልጋለሁ?››

‹‹ምን ለመፍጠር?››

‹‹ምንም ..ብቻ እንዲሁ ማለቴ... ከልቤ ይቅርታ ልጠይቅሽ፡፡››

‹‹ይቅርታ አደረግኩልሽ አልደረግኩልሽ ምን ይጎድልብሻል?››

‹‹እንደዛማ አትበይ ...ይቅርታ በጣም ያስፈልገኛል፡፡››.

‹‹እንግዲያው እዛው ባለሽበት ይቅርታ አድርጌልሻለሁ....ሁለተኛ ግን እንዳትደውይለኝ.. ባለሁበት ሰፈር እንዳትደርሽ …ከህይወቴ ራቂ.. በቃ ጨርሼለሁ.ካለበለዚያ አጥፍቼሽ ጠፋለሁ፡፡››ስልኩን ጠረቀመችባት፡

ዶ/ር ሶፊያ ግን ትንግርት ስልኩን ስለዘጋችባት አልተበሳጨችም ፤እንደውም በተቀራኒው በጣም ነው ደስ ያላት..ቢያንስ አዋርታታለች..ልክ ድምጿን እንደሰማች የምትጠረቅምባት መስሏት ነበር...የሆነች ስንጥቅ ተስፋ ታየቻት ፡፡ከቀን ሙሉ ውሎዋ አሁን ገና ትንሽ ደስ የሚያሰኝ ስሜት ተሰማት፡ አሁን እንቅልፍም ሊወስዳት ይችላል፡፡....

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍6212🥰6🔥1
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ዶ/ር ሶፊያ ቢሮዋ ቁጭ ብላ የእለቱን ስራዋን በመስራት ላይ እያለች ፀሀፊዋ ወደእሷ መጣችና እንግዳ ሊያናግራት እንደሚፈልግ ነገረቻት.. እንድታስገባው ፍቃድ ሰጠቻት፡፡ እንግዳው ሲፈቀድለት ወደ ውስጥ ገባ ..ከመቀመጫዋ ተነስታ በክብር ጨብጣ ተቀበለችውና እንዲቀመጣም ጋዘችው፡፡

ለስራ ጉዳይ የመጣ መስሏት‹‹ምን ልታዘዝ ጌታዬ ..?››አለችው፡፡

‹‹የመጣሁት ለስራ ጉዳይ አይደለም ..ለግል ጉዳይ ነበር፡፡››

ግራ ገባት‹‹ይቅርታ ስለምን እንደሆነ ማወቅ እችላለሁ?›.›

‹‹አዎ በመጀመሪያ ግን እራሴን አላስተዋወቅኩም መሰለኝ ...ሁሴን እባላለሁ..

የትንግርት ባለቤት ነኝ፡፡››

ወንበሯ ላይ ወደኋላዋ በድንጋጤ ተለጠጠችና በረጅሙ ተነፈሰች.....ከዛ እራሷን እንደምንም አረጋጋታ <<ውጭ ሀገር ትምህርት ላይ መስለኸኝ ነበር?››

‹‹ከተመለስኩ 3 ቀን አለፈኝ፡፡››

‹‹ምነው በሰላም…?››

‹‹ምን ሰላም አለ ብለሽ ነው..የአንቺን ወደ ኢትየጵያ መመለስ ከዛም አልፎ ከትንግርት ጋር በአካል መገናኘት ስሰማ ተረጋቼ መማር አልሆነልኝም ..ስለዚህ ትምህርቱን አቋርጬ

‹‹ያን ያህል..?››

‹‹ከዛም በላይ...>>

‹‹እና አሁን ምን ልታዘዝ?››

‹‹እንድንነጋገር እፈልጋለሁ?››

‹‹ምንን በተመለከተ?

‹‹ዶ/ር ሶፊያ እኔ ትንግርትን በጣም አፈቅራታለሁ..በመሀከላችሁ ባለው የቀደመ ግንኙነት የተነሳ በህይወቷ ከበቂ በላይ መስዋዕትት ከፍላለች...ከዛ አዘቅት በከፍተኛ ጥረት ወጥታ በብዙ ትግል ነው ማገገም የቻለችው ፡፡ መልሳ ወደ እዛ ህይወት እንድትገባ በፍፁም አልፈልግም….ከዛ በላይ መሰቃየት አይገባትም፡፡ ለራሴ ብቻ አስቤ አይደለም እኔን ትተወኛለች ብዬ በመስጋት ቀንቼም አይደለም፤አንቺንም ጥፋተኛ ነበርሽ ብዬ ልኮንንሽ ወይም ልፈርድብሽም አይደለም…ግን በምንም አይነት ዳግመኛ ወደአንቺ ተመልሳ  እንድትቀጥሉ ስለማልፈግ ነው፤ እሷን በሙሉ አቅሜ ከሚመጣው ጥፋት የመጠበቅ ኃላፊነት አለብኝ ....››

‹‹እና እኔ ምን ልተባበርህ?››

‹‹አሁን የስራ ቦታ ስለሆነ ሁሉን ነገር በተረጋጋ ሁኔታ ለመነጋገር ምቹ አይደለም ..እኔ እና አንቺ እንደሰለጠነ ሰው ቁጭ ብለን እንድንነጋገር ቦታ ንገሪኝ፡፡›› እፈልጋለሁ፤የሚመችሽን ጊዜና

ዶ/ር ሶፊያ ለደቂቃዎች እንደማሰብ አለችና በዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር ለእሷም የወደፊት ህይወት መረጋጋት እንደሚጠቅማት ስለገመተች በሀሳብ ተስማማችና ቢዝነስ ካርዷን አውጥታ ሰጠችው‹‹ነገ በተመቸህ ሰዓት ደውልልኝና ፕሮግራሜን አመቻችቼ የምንገናኝበትን ጊዜ እና ቦታ እነግርሀለሁ››

ከመቀመጫው ተነሳና ለስንብት እጁን እየዘረጋ‹‹በትህትና ስላስተናገድሺኝ አመሰግናለሁ፤ ይሄንን በመሀከላችን ያለውን ግንኙነት ትንግርት አታውቅም፤ምን አልባት የምትገናኙ ከሆነ ባትነግሪያት ደስ ይለኛል፡፡›› አላት፡፡

‹‹አትስጋ አቶ ሁሴን ..አልነግራትም፡፡›› አለችው ፤አንገናኝም ነበር ለማለት የፈለገችው... ግን እጅ መስጠት ስላልፈለገች አልነግራትም አለችው፡፡ደግሞ ሁሴንን ወዳላታለች... ‹‹ደስ የሚል ወንዳወንድ ቁመና ያለው አማላይ ባል ነው ያገኘችው፡፡››አለች እና የሆነ የመጐምዠት አይነት ስሜት ልቧን ጠቅ ሲያደርጋት ተሰማት….እንዴ ምን አይነት ነገር ነው እያሰብኩ ያለውት..? ብላ ራሷን ለመገሰፅ ሞከረች....ግን የሁሴንን ምስል ከአዕምሮዋ አውጥታ ጥላ ጀምራ የነበረውን ሰራ መቀጠል አልተቻላትም... በዚህም የተነሳ እራሷን ለማረጋጋት ቢሮዋን ለቃ ወጥታ ወደ ቤቷ አመራች፡፡

ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ሰሎሞን እና ሁሴን ካሳንቺስ ከሚገኝ አንዱ ሆቴል ጥግ ይዘው ውስኪያቸውን እየተጐነጩ የናፍቆት ወሬ እያወሩ ናቸው፡፡

‹‹አንተ ደግሞ ቀላህ እኮ !! ከፈረንጅ ሀገር ዕውቀታቸውን ልትኮርጅ ሄደህ የቆዳ ቀለማቸውን ኮርጀህ መጣህ እንዴ?››

‹‹ምን ይደረግ ብለህ ነው...እንደሚታወቀው እኛ ኢትዬጵያውያን ኩረጃ ላይ ቀሺም ነን…..ግን ምን በጣም ናፍቆኝ እንደነበረ ታውቃለህ?››

‹‹አውቃለሁ.. እኔ ነኛ በጣም የናፈቅኩህ፡፡››

‹‹ጉረኛ…አንተ ደግሞ ጭቅጭቅህ ካለሆነ ሌላ ምን የሚናፍቅ ደህና ነገር አለህ ?እነዚህ ጠያይም ወዛና ያላቸው ልዕልት የሀገሬ ሴቶች በዓይኔ ላይ እየሄዱ ፈተና ነበር የሆኑብኝ፡፡››አለው ወደ አስተናጋጆቹ በአገጩ እያመለከተው፡፡

‹‹እንዴ!! እዛስ የፈረንጅ ቆንጆ ሞልቶልህ የለም እንዴ?››

‹‹የሰው ቆንጆ ለእኔ ምን ይሰራል? እኔ ምንም ብትለኝ ምንም እንደሀገሬ ሴት የተለየ ውበት ያላቸው የሉም ባይ ነኝ…የእኛ ሀገር ፉንጋዋ እንኳን የራሷ የሆነ ማግኔታዊ ደም ግባት
ይኖራታል ...ብቻ የትም ብትሄድ የትም የሀገሬ ሴቶች አንደኛ ናቸው፡፡››

‹‹ይሁንልህ... ይሄንን ዲስኩርህን ትንግርት ብቻ እንዳትሰማህ፡፡ >>

‹‹ብትሰማስ ምን አጠፋው ?ያሀገሬን ሴቶች ውበት ነው ያደነቅኩት፡፡››

‹‹አድናቆትህ ወሲባዊ ሆነብኛ፡፡››

‹‹የእኔ አድናቆት ሳይሆን ያንተ ጆሮ አደማመጥ ነው ወሲባዊ ያደረገው... ለማንኛውም ወደ ቁም ነገሩ እንግባ ዳግመኛ ወደ ሆቴልህ ተመለስክ አሉ፡፡››

‹‹አዎ ምን ላድርግ ?ሴቶች እና እኔ ልንገናኝ አልቻልንም፡፡ አገኘኋቸው ስል ይሾልኩብኛል አወቅኳቸው ስል ይጠፉብኛል.... ባክህ እነሱን በተመለከተ ግራ ግብት ብሎኛል፡፡

‹‹አይዞህ ጓዴ ...ይሄ ያንተ ችግር ብቻ አይደለም የአብዛኛው ወንድ ችግር ነው፡፡

ይኖራታል ...ብቻ የትም ብትሄድ የትም የሀገሬ ሴቶች አንደኛ ናቸው፡፡››

‹‹ይሁንልህ... ይሄንን ዲስኩርህን ትንግርት ብቻ እንዳትሰማህ፡፡ >>

‹‹ብትሰማስ ምን አጠፋው ?ያሀገሬን ሴቶች ውበት ነው ያደነቅኩት፡፡››

‹‹አድናቆትህ ወሲባዊ ሆነብኛ፡፡››

‹‹የእኔ አድናቆት ሳይሆን ያንተ ጆሮ አደማመጥ ነው ወሲባዊ ያደረገው... ለማንኛውም ወደ ቁም ነገሩ እንግባ ዳግመኛ ወደ ሆቴልህ ተመለስክ አሉ፡፡››

‹‹አዎ ምን ላድርግ ?ሴቶች እና እኔ ልንገናኝ አልቻልንም፡፡ አገኘኋቸው ስል ይሾልኩብኛል ..አወቅኳቸው ስል ይጠፉብኛል.... ባክህ እነሱን በተመለከተ ግራ ግብት ብሎኛል፡፡

‹‹አይዞህ ጓዴ ...ይሄ ያንተ ችግር ብቻ አይደለም የአብዛኛው ወንድ ችግር ነው፡፡

የአሁኑ ግን የእኔ ጥፋት ነው፡፡››

‹‹አንተ ደግሞ ምን አደረግክ…?››

‹‹እኔ ወደ ሀዋሳ ሂድ ባልልህ ይሄ ችግር አይፈጠርም ነበር፡፡››

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ... እኔ ኖርኩም አልኖርኩም እርግዝናዋ ከመጨንገፍ ይድናል ብለህ ታስባለህ?፡፡››

‹‹እሱ ሊሆን ይችላል ...ምንም ሆነ ምንም ግን አጠገቧ ብትሆን ኖሮ እሷ እንዲህ አታመርም ነበር፤አንተም አኮ ትንሽ አጥፍተሀል››

‹‹ምን አድርጌ አጠፋሁ?››

‹‹ስደውልልህ የእሷን መታመም ብትነግረኝ ሌላ ሰው እልክ ነበር፡፡››

‹‹እሱ ሰበብ ነው.. እናቷ፣አባቷ፣ እህቷ.. ከአስር ሰው በላይ ዙሪያዋን ከቧት ነበር ..ደግሞ በጣም ተሸሏት ወደኖርማል ጤንነቷ
በተመለሰች ጊዜ ነው ተነስቼ የሄድኩት፡፡መልሳ እንደምትታመም እና ይሄ ነገር እንደሚፈጠር ጠንቋይ አልቀልብ በምን ላውቅ እችላለሁ? እንደውም ይሄንን ሰበብ አድርጋ ጋብቻውን ለማፈረስ በምክንያትነት ተጠቀመችበት እንጂ በፊቱኑም ከእኔጋ መኖር የሰለቻት ይመስለኛል፡፡ይሄን ያህል ይቅርታ የማያሰጥ ጥፋት አጥፍቼያለሁ ብዬ አላስብም፤ የጠፋው የእኔም ልጅ ነው፤ ወንድ ልጅ በመሆኑ እንዴት ተደስቼ እንደነበረ…እንዴት በናፍቆት ወደእዚህች ምድር የመምጫውን ቀን እጠብቅ እንደነበረ ከማንም በላይ ጠንቅቃ ታውቃለች፡፡ በተፈጠረው
👍70
ችግር እኔም ተሳቅቄያለሁ ፡፡ግን የእግዚያብሄር ፍቃድ እንደዛ ከሆነ ምን ማድረግ እችላለሁ? አጥፍቼያለሁ ብዬ እግሯ ላይ ወደቅኩ..ሁለት ሶስት ጊዜ የገዛ አባቷን ሳይቀር ሽማግሌ ላኩ.. እርግጠኛ ነኝ አንተም ያናገርካት እና አቋሟን የሰማህ ይመስለኛል ... እንግዲህ ሁሉንም አሻፈረኝ ካለች መንገዱን ጨርቅ ያድርግላት ከማለት ውጭ ምን ማድረግ እችላለሁ?፡፡››

‹‹አይ ጓዴ መልሰህ ወንደላጤ ሆንክ ማለት ነው?››

‹‹አዎ... እንደውም ወንደላጤነትን የመሰለ ነገር የለም... ሙሉ ነጻነትህን አውጀህ ባሰኘህ ሰዓት ገብተህ በሰኛህ ሰዓት ወጥተህ፣ሲያሰኝህ ወጭ አድረህ…ምን አጨናነቀኝ እንደውም ሁለተኛ ትዳር ሚባል ነገር››ተንገሸገሸ፡፡

‹‹እና ልትመለኩስ ነው?››

‹‹ከትዳር ምልኩስና ሳይሻል ይቀራል ብለህ ነው? እንደውም ልጆቼም በነጻነት ሳይሳቀቁ እቤቴ መጥተው የፈለጋቸውን ያህል ቀን አድረው.. እንደፈለጋቸው እንዲሆኑ እፈልጋለሁ፤በቃኝ ዳግመኛ የማንንም ሴት ቀሚስ አልገልብም፤ህርም ይሁንብኝ...››

‹‹አትማል ባክህ ...ያንተ መሀላ ማብቂያ የለውም..እርባን የሌለው መሀላ፡፡››

‹‹አይ መስሎሀል... ታየኝ የለ፡፡››

<<ችግር የለም አይሀለው…አንተ ትናንት ልጆችህ ጋር ሄጄ ነበር እኮ... በጣም ደስተኞች ሆነው ነው የጠበቁኝ ...ሁሉን ነገር ነገረውኛል ምክሬን ስለሰማህ በጣም አመሰግናለሁ፡፡››

‹‹ቀድሞውንም አንተ እስክትወቅሰኝ መጠበቅ አልነበረብኝም፡፡››

‹‹በል 3፡ዐዐ ሆነ እኮ ያንተ ወሬ ማለቂያ የለውም ትንግርት ትጠብቀኛለች፤ አንተም ወደ ሆቴልህ እኔም ወደ ቤቴ፡፡››

ሂሳብ ከፍለው ለነገ ለመገናኘት ተቀጣጥረው በየፊናቸው ተበታተኑ ፡፡ሰሎሞን የሚያድርበት ሆቴል ሰፈር ከደረሰ በኃላ በአቅራቢያው የሚገኘው ግሮሰሪ ጎራ አለ፡፡በደንብ እራሱን እስኪረሳ ካልጠጣ ለሊቱን በሀሳብ ሲገላበጥ ነው የሚያሳልፈው፡፡ስለዚህ የተወሰነ መጠጥ መጨመር አለበት ..በደንብ እስኪሰማ..በደንብ እስኪሰክር…፡፡

5.3ዐ ላይ ሞቅ ብሎት እየተንገዳገደ አንደኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው መኝታ ቤቱ አመራ፤ በመከራ ቁልፉን ከ3 ኪሶቹ ፈልጎ አጣው.. አራተኛው ውስጥ አገኘው.፡፡ በራፉን ሊከፍት ቁልፉን ውስጥ አስገብቶ ሊያዞረው ሲል ከውስጥ ሙዚቃ ተሰማው ፤ግራ ተጋባ፡፡ መክፈቱን አቆመና ‹ተሳስቼያለሁ እንዴ?› ብሎ ወደ በረንዳው ተመልሶ ሄደና ቁልቁል አየ.. አዎ ትክክል ነው ፡፡አንደኛ ፎቅ ላይ ነው ያለው.. የክፍሉን ቁጥርም በአትኩሮት አየ፤ የራሱ ነው ..እዚህ ክፍል ማደር ከጀመረ አስራ አምስት ቀን አልፎታል.. ቤቱ ሆኗል.. እንዴት ሊሳሳት ይችላል?ጆሮውን ቀሰረና ሙዚቃውን አዳመጠ ፤ድሮ የሚያውቀው ምን አልባትም ለአመታት ሰምቶት የማያውቀው የንዋይ ደበበ ዘፈን ነው፡፡

....ሰው አይስማብን ሰው

እኛው እንደጀመርን ...እኛው እንጨርሰው

ግድ የለም /3/

ፍቅር ፍቅር ያለው... የማይሆነው የለም ኧረ እንዴት .. ኧረ እንዴት ልታገስ እንባ ከቅንድቤ... ከጉንጬ ሲታፈስ ፍቅሬ ሆይ ጥፋቴን አላስተባብልም በድንገት መሳሳት አያጨካክንም

‹‹ኤደን ነች ማለት ነው? በስንት ሽማግሌ

ስማፀናት አሻፈረኝ ብላ አሁን ቤቱ ኦና

ሲሆንባት፣አልጋው ሲሰፋባት፣አንሶላው
ሲቀዘቅዛት ተፀፀተች አይደል? የሴት ነገር‹‹አሁን ሶል እራስህን አረጋጋ ..እንደወንዶቹ
ቀብረር በል ... ደግሞ በልጆችህ ጉዳይ ላይ
አሁንም ያላትን አቋም እንድታስተካክል ጠንከር
ያለ አቋም መያዝ አለብህ ፤ ግን ግድ የለም ተወው በዚህ ጊዜ የልጆቹን ጉዳይ ብታነሳ ስሜቷ ስለሚጎዳ ጥሩ አይሆንም….እሱን
ለሌላ ጊዜ ብታስተላልፈው ይሻላል››ከራሱ ጋር ሲመካከር ሙዚቃው አለቀና ከተወሰነ ሰከንድ መቋረጥ በኃላ .. ያው ዘፈን ተደገመ፡፡
ከፈተና በራፉን ገፋ አደረገው.. ሮዝ ቀለም ያለው ሙሉ ቀሚስ ለብሳ ተመሳሳይ ቀለም ያለው ሹርብ ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጋ አልጋው ጐን ያለው የሶፋ መቀመጫ ላይ ቁጭ ብላ በትካዜ ሙዚቃውን እያዳመጠች ነበር፡፡የበረፉን መክፈት ተከትሎ አይኖቿን ወደ ፊት ለፊት ወረወረችና ነቃ ብላ ቁጭ አለች፡፡ ሰሎሞን አይኖቹን አበሰ... ህልምም መሰለው ፣ግራ መጋባቱን አይታ ሙዚቃውን ዘጋችው፡፡

‹‹ምንድነው ?ተሳስቼ ቤትሽ መጣሁ እንዴ ? ይቅርታ ሰክሬ ነው፡፡››

‹‹አይ አልተሳሳትክም... እኔ ነኝ አንተጋር የመጣሁት››

‹‹እንደዛ ነው.... እሱ ከሆነ መልካም የእኔ ጥፋት የለበትም ማለት ነው፡፡›› በማለት በራፉን ዘጋና እየተንገዳገደ ሄዶ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ፡፡

‹‹እሺ የልጆቼ እናት ምነው በለሊት? በሰላም?››

ፀጥ አለችው.. ምን እንደምትለው ለብዙ ቀን ተዘጋጅታበትና ተለማምዳበት የመጣች ቢሆንም አሁን ፊት ለፊቱ ስትሆን ልምምዷ ከሸፈባት ...በተጨማሪም እንዲህ ሰክሮ አገኘዋለሁ ብላ አላሰበችም ነበር፡፡

‹‹ወደ ቤትህ እንድትመለስ ልለምንህ ነበር የመጣሁት?››

‹‹ምን ?ድገሚልኝ እስቲ?››

‹‹ሶል በፈጠረህ ለልጆቻችን ስትል ወደቤትህ ተመለስ ፤አንተም እነሱን ፍለጋ በየሳምንቱ ከምትንከራተት እነሱም እየተሳቀቁ ከሚያገኙህ ወደቤትህ ተመለስ እና አንድ ላይ ኑሩ፤ ደግሞም ስንት ዓመት ለፍተህ የገነባኸው ቤት እያለ ሆቴል ስትኖር ደስ አይልም ...ምን በወጣህ!››

‹‹ቆይ ቆይ አልገባኝም.. እኔ ወደ ቤቴ ተመለስኩ ከልጆቼ ጋር ኖርኩ.. አንቺስ?››

‹‹ከፈቀድክልኝ ሰርቪስ ውስጥም ቢሆን እኖራለሁ፡፡በፈጠረህ በቃ ተቀጥቼያለሁ ... ለልጆቻችን ስትል ይቅር በለኝ?›› ብላ ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ በመነሳት በእንባ እንደታጠበች ጉልበቱ ላይ ተደፋች፡፡

‹‹ኧረ በፈጠረሽ ተነሽ ...አንቺ ብቻ እኮ አይደለሽም እኔም ተቀጥቼያለሁ ...ተነሺና ተቀመጭ እስቲ›› ብሎ አስነሳት.. ተነስታ ፊት ለፊቱ ተቀመጠች ፡፡

‹‹እስቲ ስመጣ ታዳምጪ የነበረውን ሙዚቃ ክፈቺልኝ፡፡››

ሞባይሏን በፍጥነት አነሳችና ከፈተችለት... በተመስጦና በፅሞና ከመጀመሪው እስከ መጨራሻው አንድ ላይ አዳመጡ ...ሲጠናቀቅ ‹‹ልድገመው፡፡››አለችው፡፡

‹‹ለጊዜው ይበቃል ...በቃ ተመለስ ካልሺኝ እመለሳለሁ..››

‹‹እውነት...፡፡››

‹‹አዎ እውነቴን ነው እመለሳለሁ፡፡››

‹‹እሺ የእኔ ጌታ በጣም ነው የማመሰግነው››ተንሰፈሰፈች፡፡

‹‹...ግን ሰርቪስ እንድትኖሪ አልፈልግም፡፡››ደስታዋ በቅፅበት ጭልም አለባት፡፡

‹‹... ይሁን እንዳልክ.. እዛው አካባቢ ቤት ተከራይቼ እወጣለሁ፡፡››

‹‹አይሆንም.. አብረሺኝ እንድትኖሪ ነው የምፈልገው ....ያለፈው አልፏል አንድ ብለን እንደአዲስአዲስ ህይወት እንድንጀምር ነው የምፈልገው.. ለልጆቻችን ስንል ያለፈውን ረስተን ፍፅም ይቅር ተባብለን አንድ ላይ እንድንኖር ነው የምፈልገው፡፡››

የደስታ ሳግ እየተናነቃት ተንደርድራ ከመቀመጫዋ በመስፈንጠር ተጠመጠመችበት…. እሱም አቀፋት፡፡

‹‹አሁን ሰክሬያለሁ ..ድክምክም ብሎኛልም እንተኛ፡፡››

‹‹አይሆንም አሁኑኑ ወደ ቤታችን መሄድ አለብን… አንድ ሰዓት ነበር እኮ የመጣሁት ... የመጣሁበትን ሳልፈጽም አልመለስም ብዬ ነው ስጠብቅህ የቆየሁት.. በል ተነስ፡፡›› እጁን ይዛ ጎተተችው፡፡

‹‹ኧረ ተይ እዚሁ እንተኛ ምን ችግር አለው... ይደፍረኛል ብለሽ ፈራሽ እንዴ?››

‹‹እንደእዛ አላሰብኩም …እንደዛ ታደርጋለህ ብዬ አንተን ፍፁም ልፈራ አልችልም፡፡ ፍቃደኛ ከሆንክ ሁለታችንም ያለፈ ህይወት ስላለን ለሁሉም ተመርምረን ማድረግ ከፈለግን ያኔ እናደርጋለን….አዎ ለልጆቻችን ስንል እንደዛ ማድረግ አለብን ››አለችው፡፡
👍70🤔7👎2
<< አረ ችግር የለም የሴት ቀሚሰ ድጋሚ አልገልብም ብዬ ለጓደኛዬ አሁን ከአንድ ሰዓት በፊት ቃል ገብቼለት ነው የመጣሁት...ለእኔ ወደ ቤቴ መመለስ ብቻ በቂዬ ነው፡፡››

ፈገግ አለችና ‹‹ይሁን እንዳልክ አሁን ግን እሺ በለኝ ወደ ቤታችን እንሂድ... እቃዎችህ እዚሁ ይሁኑ ፤ነገ መጥተን እንወስዳቸዋለን›› ብላ በግድ ይዛው ወጣች ፡፡በእሷ ሹፌርነት እቤታቸው ሲደርሱ ከምሽቱ 6 ሰዓት ዓልፎ ነበር፡፡ ዘበኛው ከወንድ ጋር ሲያያት ‹በስንት ጊዜ እዚህ ቤት ወንድ ገባ፡፡›› ብሎ

እየተደመመ በራፉን ከፈተላቸውና መኪናው ገብቶ ቦታ ይዞ ወንድዬው ሲወርድ የድሮው አባ ወራ ሆኖ ሲያገኘው ማመን አቅቶት በድንጋጤ ጭንቅላቱን ያዘ፡፡


ቤተሰቦች በቅናነት #YouTube #subscribe እያደረጋቹ

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍50🥰63
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_አርባ_ሁለት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ዶ/ር ሶፊያ ቢሮዋ ቁጭ ብላ የእለቱን ስራዋን በመስራት ላይ እያለች ፀሀፊዋ ወደእሷ መጣችና እንግዳ ሊያናግራት እንደሚፈልግ ነገረቻት.. እንድታስገባው ፍቃድ ሰጠቻት፡፡ እንግዳው ሲፈቀድለት ወደ ውስጥ ገባ ..ከመቀመጫዋ ተነስታ በክብር ጨብጣ ተቀበለችውና እንዲቀመጣም ጋዘችው፡፡ ለስራ ጉዳይ የመጣ መስሏት‹‹ምን ልታዘዝ ጌታዬ ..?››አለችው፡፡…»
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስራሁለት


‹መግባት ይቻላል?››ንዴቴን እንደምንም በውስጤ አፍኜ   ጠየቅኳት።

‹‹ግባ..ግባ››በራፉን በደንብ ከፈተችልኝና ዞር ብላ መግቢያውን ለቀቀችልኝ።
ወደውስጥ ገባሁ። ለአመታት የተኖረበት የተደራጀ ቤት ነው የሚመስለው።እርግጥ ወደውጭ ስትሄድ የነበራትን የቤት እቃ ሁሉ እዚሁ እማዬ ጋር አምጥታ አንድ ሰርቤስ ቤት ውስጥ ተቆልሎ እንደተቀመጠላት አውቃለሁ።አሁን እቤቱ ውስጥ ማያቸው እቃዋች ግን እነዛ ብቻ እንዳልሆኑና ከግማሽ በላይ አዲስ የተገዙ እንደሆነ ለመገመት ቀላል ነው።መሀከል ወለል ላይ ቆሜ ግራ ቀኙን እየማተርኩ ጠቅላላ የቤቱን ሁኔታ ስቃኝ‹‹ምነው እቤት ለእንቦሳ አትለኝም እንዴ?››አለቺኝ።
‹‹በጣም አስገርመሺኛል...ምን ለማድረግ እየሞከርሽ እንደሆነም ምንም እየገባኝ አይደለም››አልኳት።

አጠገቧ ያለው ሶፋ ላይ ወጣችና እግሯን አነባብራ በማጠፍ ተቀምጣ ለደቂቃዎች በትዝብት አይሉት በሀዘኔታ አስተያየት ስታየኝ ከቆየች በኃላ።‹‹እስቲ ቁጭ በል››አለችኝ።

እስከአሁን እንደቆምኩ እንኳን ዘንግቼው ነበር።ከፊት ለፊቷ ተቀመጥኩና የምትለኝን ለመስማት  አይን አይኗን በማየት እጠብቅ ጀመር።
‹‹ምን ማወቅ ነው የፈለከው?››

‹‹ሌላው ይቅር ቢያንስ በጓደኝነታችን እንዲህ አስቤለሁ እንዲ ላደርግ ነው አይባልም?››

‹‹ልነግርህ ፈልጌ ነበር...ግን የለህም...ስላልነበርክ ነው።››

ይህቺ ልጅ የፈረንጅ ጂኒ አጠናግሯት ነው እንዴ የመጣችው?‹‹ምን እያወራሽ ነው...?አብረን አይደል እንዴ ያደርነው?››

ፈገግ ብላ ሳቀችብኝ...የትዝብት ሳቅ...የሽርደዳ ሳቅ..
‹‹አልገባኝም?ምን የሚያስቅ ነገር ተናገርኩ?››

‹‹አይ ገርሞኝ ነው...እርግጥ እኔ አብሬህ አድሬለሁ፡፡ አንተ ግን አብረሀኝ አልነበረም ያደርከው፡፡››አለችኝ።

ንግግሯ ቋጠሮ ሊያዝልኝ አልቻለም..ቋጠሮውን ካልያዝኩት ደግሞ እንዴት ብዬ ምኑን ጓትቼ ምስጢሩን ልፈታ እችላለሁ.?፡፡››

‹‹አንቺ ከእኔ ጋር አድረሽ እንዴት ነው እኔ ከአንቺ ጋር ላላድር የምችለው?።››

‹‹አብረን ስናድርም ሆነ እንዲህ አብረን ተቀምጠን ስናወራ መንፈስህ ሙሉ በሙሉ አብሮህ የለም።በድን አካልህ ወይም ግማሽ አንተነትህ ብቻ ነው ያለው..እውነቱን ንገሪኝ ካልከኝ ከመጣው ጀምሮ ገና እንዳላገኘሁህ ነው የሚሠማኝ...አሁንም እንደናፈቅከኝ ነው።መች መቶ በሳምኩት...የት አግኝቼ የልቤን መሻት የውስጤን ምኞት ባወራሁት  እላለሁ።እና ምን አልባት መጥፋትህ ለጊዜው ከሆነ ከሄድክበት ተመልሰህ እራስህን ሰብስበህ እስክትመጣ እዚህ  ከእማዬ ጎን ሆኜ እጠብቅሀለው፡፡መምጣት አቅቶህ እንደወጣህ በዛው ከቀረህም ያው እርሜን አውጥቼ የገዛ ህይወቴን በራሴ መምራት እጀምራለው።››

በንዴት ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ።‹‹የምታወሪው አንድም እየገባኝ አይደለም.. ቅዠት ውስጥ ያለሽ መሰለኝ...››

ልታብራራልኝ አፉን ልትከፋት ስትል በራፉ ተንኳኳ
‹‹ማነው?›› አለች፡፡

የእማዬ ሰራተኛ ነች‹‹እኔ ነኝ …እትዬ ምነው ብናው ቀዘቀዘ እኮ..ቶሎ ኑ ብለዋችኋ››ብላ ተመለሰች። እርግበ ከሶፋው ዘላ ወረደችና ወደመኝታ ቤት ሮጣ በመግባት በደቂቃ ውስጥ ለብሳ በነበረው ልብስ ላይ ቢጃማ ቀሚስ ደርባበት ወደውጭ እየተንደረደረች...‹‹ለማንኛውም ነገ አማኑኤል ሆስፒታል ስራ ጀምራለው…ከዛሬ ወዲህም የምኖረው እዚህ ነው…ተክዘህ ስትጨርስ በራፉን ዝጋውና ና››ብላኝ ጥላኝ ሄደች።

ንፍስ ከበዛባት እየተንበለበለች ለቤቱም ለደጅም ብርሀን እየሠጠች ያለችው ሻማ መጥፋቷ አይቀርም።እርግጥ ያው ስትለኮስ አንድ ቀን መጥፍቷ የታወቀ ነው።አልቋ መጥፍትና ድንገት መጥፍት ይለያያል።እኔም  በሁለቱ መሀከል ስወዛገብ ድንገት በማሀል እንዳልጠፋ ፈራሁ፡፡በጣም ፈራሁ፡፡ሰኞ
በማግስቱ ሰኞ…..
… እያንዳንዱ ቀን የሚያስተዳድሩ ፕላኔቶች አሉ….ሰኞ በጨረቃ ይተዳደራል፡፡በእንግሊዘኛው Monday(moon day)ቀጥታ ይገልጸዋል… እንደሚታወቀው  ሰኞ ሙዲ ቀን ነች …አብዛኛውም ሰው በእለተ ሰኞ  ወይ በጣም ይደበራል ወይ ደስ ይለዋል ፤ተለዋዋጭ ባህሪ ይላበሳል፡፡ይህን ከጨረቃ  የወረሰው ፀባይ  ነው፡፡እኔም በዚህ በአለተ ሰኞ የጨረቃዎ ተፅዕኖ ተጭኖኝ መሰለኝ ጭፍግግ ብሎኝ ነው የዋልኩት፡፡ከስራ እንደወጣው..11፡30 አካባቢ በዛው ስሜት ልዕልትን ላገኝ ፈለኩና ደወልኩላት፡፡ይሄ ማለት ከአቤል ጋር ከተመካከርን ከአንድ ወር በኃላ መሆኑ ነው፡፡
‹‹ሄሎ ልዕልት እንዴት ነሽ?››
‹‹ደህና ነኝ ዶክተር..?አንተስ…?ምነው ድምፅህ አሞሀል እንዴ?››ስትል ጠየቀችኝ፡፡
‹‹ባንቺ ምክንያት ከታመምኩ ቆየሁ እኮ…››በማለት በውስጤ እያብሰለሰልኩ ‹‹አይ ደህና ነኝ..ትንሽ ስራ በዝቶብኝ ስለነበር ደካክሞኝ ነው፡፡››አልኳት
‹‹ነው…ታዲያ ለምን ብቅ አትልምና ጥሩ ብና አላፈላልህም?››ሌላ ቀን ቢሆን ይሄንን አይነት በግብዣ በአንድ አፍ ብዬ ነበር ወደእሷ የምበረው..ዛሬ ግን እዛ ቤት ሄጄ ያን ባሏን ማየት አልፈልግም፡፡ ለዛ የሚሆን አቅም የለኝ፡፡
‹‹አይ እቤት አልመጣም…ግን ከፈለግሽ ወደሰፈራችሁ ቀረብ ልበልና ቢራ ጋብዢኝ..በጣም ነው የጠማኝ፡፡በዛውም ስለመስፍን የማወራሽ ነገር አለ፡፡››
‹‹ወይ ዶ/ር.. ስለመስፍን ምን..?አዲስ ነገር አለ እንዴ?››የድምፆ ቃና ሁሉ በደቂቃዎች ውስጥ ተቀያየረ፡፡
‹‹ኸረ…ምንም አዲስ ነገር የለም…ዝም ብሎ በአእምሮዬ የመጣልኝ ነገር ስላለ…ምን አልባት ብናወራበት ብዬ ነው፡፡የማይመችሽ ከሆነ ግን ችግር የለም ነገ ተነገወዲያ መሆን ይችላል…የሚያስቸኩል ነገር አይደለም፡፡››
‹‹አይ…የመስፍንዬን ስም አንስተህብኝማ ነገ ተነገወዲያ ብሎ ነገር አይሰራም፡፡ይመቸኛል፡፡ከእሱ ጉዳይ ውጭ ሌላ ምን ጉዳይ ኖሮኝ ጊዜ አጣለሁ…በቃ እንደተቃረብክ ደውልና ቦታውን ንገረኝ፡፡ እመጣለሁ፡፡››
‹‹እሺ…እስከዛው ቸው፡፡››ቅዝዝ በለ ስሜት ተሰናበትኳትና ስልኩን ዘጋሁት፡፡ይሄ መስፍኔ የተባለው ሰው ግን የትኛው የልቧ ክፍል ላይ ቢያርፍ ነው እንዲህ ቅልጥልጥ የምትልለት?
ከወትሮ በተሻለ ለብሳ የቀጠርኳት ቦታ መጣች።ስንገናኝ ሰዓቱ 12 ሰዓት ሊሆን 10 ደቂቃ ብቻ ነበር የቀረው።ጉንጭ ለጉንጭ ተሳስመን እንደተቀመጥን ፋታ ሳትሰጠኝ ወደጉዳዮ ገባች‹‹ዶ/ር  ስለመስፍኔ ምን ልትነግረኝ ነው?››
‹‹አረ አትቸኩይ ምንም የረባ ነገር አልነግርሽም...ቢያንስ ቢራዬን ልዘዝና አንድ ጉንጭ ልጎንጭ፡፡››
‹‹ይቅርታ ዶ/ር በጣም እራስወዳድ ሆንኩብህ አይደል?››
‹‹አይ ችግር የለውም...እንደውም ለምን ነግሬሽ አልገላገልም...ለሁለት ነገር ነው የፈለኩሽ? አንደኛው  አንድ ኪሊኒክ ያለው ጓደኛዬ የመስፍኔን በሽታ አሁናዊ ሁኔታ በተሻለ መረዳት የሚያስችለን ተጨማሪ  መረጃዎችን የሚሰጠን አዲስ መሳሪያ አስመጥቶ ስራ ጀምሯል።››
አይኖቾ በሩ  ‹‹እና ዶ/ር ... ?››
‹‹እናማ...ሁኔታውን ባመቻችና ነገ ወይ ተነገ ወዲያ እንዲታይ ብናደርገው  ብዬ አስቤ ነው›› 
በፍጥነት የሆነ ነገር ትለኛለች ብዬ ብጠብቅ ዝም..ቅዝዝ ..ብዝዝዝ አለች።ግራ ገባኝ፡፡ ደነገጥኩም።
‹‹ማለቴ ምንም ሚያስጨንቅ ነገር የለውም..ባይታይም ችግር የለውም..››
ጭራሽ ከነዛ ኮከብ መሳይ ተንከባላይ አይኖቾ እንባዋ ዝርግፍ ዝርግፍ አለ።በድንጋጤ ፊቴ ተከፍቶ የተቀመጠውን ቢራ አነሳሁና በአንድ ትንፍሽ ግማሽ አደረስኩትና ጠርሙሱን አስቀምጬ በቀጣይ የምላት ነገር ስለጠፍኝ።‹‹በጣ...ም ይቅርታ።››አልኳት።
👍404
‹‹…ለምኑ ዶ/ር …በጣም ደስ ብሎኝ እኮ ነው ያለቀስኩት...አንተ በምትረዳኝ መጠን የዕድሜ ልክ ጓደኞቼም አይረድኝም።….አረ ምን ጓደኞቼ የገዛ ወንድሞቼ እራሱ መስፍኔ እንዲድንልኝ የሚፈልጉ አይመስለኝም...አንተ ግን...?››
የስሜቷን መደፍረስ ምክንያት በመረዳቴ እፎይታም  እርካታም ተሠማኝ።እናም በመረጋጋት ማውራት ጀመርኩ።
‹‹እኔማ ስራዬ ነው...››
‹‹ተው እንጂ ህፃን ልጅ አይደለውም ..የትኛው ስራህ የትኛው ደግሞ ከስራህ ውጭ እንደሆነ አውቃለው...ማላውቀው ለምን ይሄን ያህል ሚለውን ነው?።
‹‹እሱን እኔም አላውቅም....ምን አልባት እህት ስለሌለኝ እህቴ እንድትሆኚ ፈልጌ ሊሆን ይችላል፡፡››
‹‹በእውነት እህት የለህም?››
‹‹አዎ ሁለት ወንድሞች ቢኖሩኝም ሴት ልጅ ግን ለቤታችን አልተወለደችልንም. ..እህት ስለሌለኝ ብዙውን ጊዜ ቅር የሚለኝ ቢሆንም አሁን ግን ለልዕልት ስነግራት የድምፄ መሰባበርና የፊቴ መቋጠር በሁኔታው ልቤ የተሠበረ እና ጠለቅ ያለ  ስነልቦናዊ ጉዳት ያለብኝ ነው ያስመሰልኩት...እንዲህ አይነት የመተወን ብቃት እንዳለኝ አስቤው አላውቅም።
‹‹እኛ ቤት ዘጠኝ ነን።ስምንቱ ወንዶች ሲሆኑ እኔ ብቻ ነኝ ሴት።ታዲያ ሲያማርሩ ብታይ....››
‹‹ምን እያሉ ነው የሚያማርሩት?››ገርሞኝ ጠየቅኩ።
‹‹ለምን አንድ እህት ብቻ ኖረን ብለው ነዋ...እንዲህ እንደአንተ ምንም የሌለውም መኖሩን ቢያስተውሉ መልካም ነበር፡፡››
ከወንድሟ በዝርዝር የሠማሁትንና የማውቀውን  ታሪክ ደግማ እየነገረችኝ ቢሆንም እንደአዲስ በአድናቆትና በፈገግታ እየሠማኋት ነው።ለነገሩ እንኳን ሌላ ሰው የነገረኝን ታሪክ ይቅርና እሷ ራሷ ተመሳሳይ አይነት ታሪክ እየደጋገመች በየቀኑ ብተርክልኝ በተመሳሳይ ድምቀት እንደማዳምጣት ጥርጥር የለውም።ምክንያቱም ዋናው የታሪኩ ይዘት ሳይሆን የማን ከንፈር ተነቃንቆ ከማን አንደበት ቃላት ወጥቶ  ተነገረ የሚለው ነው።ጫወታችንን ለማርዘም ሌላ ጥያቄ አስከተልኩ።


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍236
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ ስድስት


ባምንም ባላምንም ተደፍሪያለሁ!

መደፈር ጉልበተኛ እጅ እና እጅን ይዞ፣ በጉልበቱ በፈለቀቃቼው እግሮች መኸራ ገብቶ፣ ኃጢያቱን መድፋት ብቻ አይደለም፡፡ ለምኖ፣ ተለመማምጦ፣ እባክህ ብሎ፣ እግር ሥር ወድቆ መደፈርም አለ፡፡ እንደ እኔ እነደ እኔ አብሮ መተኛት ሳይፈልጉ በፍቅር የመገደድ፣ በክብር በገንዘብ የመገደድ፣ በትዳር የመገደድ (ሚስት ነሽ ታዲያ ምን ትሆኝ? ተብሎ) የመገደድ ዓይነቱ ብዙ ነው። ዕድሜሽ አመለጠሽ ቶሎ ውለጂ ተብሎ፣ ልብ ያልከጀለውን በጀርባ ተንበልብሎ መቀበል፤ ሕግ መደፈር የማይለው ብዙ ነው ዓይነቱ፤ ለዚሀ ዓይነቱ ችሎት አይቆምም፡፡ ሕዝቡም ይላል “ወደሽ ከተደፋሽ፣ ቢረግጡሽ አይክፋሽ” ወደው ከተደፉልን አይዟችሁ ብሎ ማንሳት ጽድቅ፣ መርገጥም መብት ነው ሲሉን፡፡ በወደውናል ሰበብ ስንቶቹን ረገጥን፣ በስንቶቹ ተረገጥን? የእግራችን ዳና ወደውን በጎነበሱልን ልብ ላይ ሕያው ሆኖ ታትሟል “የወደዱትን ቢያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ'' በሚል ብሒል ትተናቼው ስንሄድ ለሌላዋ ባል ሆነው፤ ትተውን ሲሄዱ ለሌላው ሚስት ሆነን፣ ያልታደለ ባል በልባችን ጫካ ማንም ያልሄደበት መንገድ ሊመሠርት ደፋ ቀና ይላል። ሁሉም ልብ ገጣባ፣ እግር የለመደ መንገድ፣ ባል ይሁን ውሽማ፣ “ቦይ ፍሬንድ' ይሁን ምን፣ ያው ተራማጅ ነው የሚሉ የደከማቼው ሚስቶች። ሴት ልጆቻቼውን “ከወንድ ተጠንቀቁ!” እያሉ የሚመክሩ! “ተጠንቀቁ! ወንዶች ቀጣፊ ፍጥረቶች ናቸው" ወንድ ልጆቻቼው ይኼን ቁጭ ብለው ይመዘግባሉ፣ እኩል ከከሬሜላ ጋር መጥምጠውት ያድጋሉ፣ እናም ከፍ ሲሉ.. “ቀጣፊ የሆንኩት ፈልጌ አይደለም፣ ወንድ አድርጎ የፈጠረኝን አምላክ ጠይቁት! ካላመናችሁ እናቴንም ጠይቋት ሁለተኛ ምስክር ናት'' ይላሉ፡፡ አይሄድም ወይ ይኼ ሰው? ባለቤቴ ዮናስ ረፍት ብሎ ከአሜሪካ ከመጠ በኋላ፣ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ እዚሁ ቆዬ፡፡ አትሄድም እንዴ? ብዬ በግልጽ ባልጠይቀውም(ምን አላት ከመሄዴ? እኔን ነው አሜሪካን የወደደችው? እንዳይል ፈርቼ) ውስጤ ግን ይዞኝ ከዚህ አገር

ይሸሻል ብዬ የተደበቅሁበት ሰውዬ፣ በማላውቀው ምክንያት ከአሜሪካ እየሸሸ እኔ ውስጥ መደበቅ መጀመሩ አስገርሞኝም ግራ አጋብቶኝም ነበር “ሲትዝን ስለሆንኩ ችግር የለውም ቆይቼ እሄዳለሁ” ይላል፣ ሰልጠይቀው። እናቱና እህቶቹ በመቶ ት ደስ ብሏቼው እንዲያውም ረፍቱን አራዝሞ እንዲቆይ ይነዘንዙታል፤ እኔስ? እላለሁ በውስጤ እኔስ? በቃ እዚህ ግቢ እየተብሰለሰልኩ ዕድሜዬን ልፍጅ ...12 አንድ ቀን ታዲያ ራት ይዞኝ ወጣና በምሽቱ መርዶ አረዳኝ “ማሬ በቃ እዚሁ አገሬ ላይ ለመኖር ወስኛለሁ።" “ምን ማለት ነው እዚሁ ...?" “እዚሁ ኢትዮጵያ ነዋ!'' “እየቀለድክ ነው?'' “ኖ! ቀልድ አይደለም፣ የምመጣበት አሳማኝ ሰበብ አጥቼ እንጂ፣ ካሰብኩበት ቆይቻለሁ፡፡ አሁን አንቺ አለሽ፣ የአብዬ አለች (ልጃችንን)ምን አደርጋለሁ እዚያ? አእምሮዬ _ እንደ _ አሸን የሚፈላ እንግሊዝኛ ቃል ለመተርጎም ሲታገል መዋል ሰልችቶታል፡፡ ለመኖር መስማት አለብኝ፣ መረዳት አለብኝ፡፡ አገሬ ላይ መላ ሰውነቴ ከእግር ጥፍሬ እስከ ራስ ጸጉሬ ቋንቋዬን ይረዳል... የኔ ነዋ! እዚያ ምን አለኝ? ባሀላቼው፣ ቋንቋቼው፣ ሳቃቼው፣ ለቅሷቼው፣ ሰላምታቼው፣ ፍቅርና ጥላቻቼው፣ ለእኔ የመኖርና ያለመኖር ትግል ነው፡፡ አስቤ እስቃለሁ፣አስቤ አዝናለሁ የምረዳቼው ቋንቋቼው በገባኝ ልክ ብቻ ነው፤ የሚያውቁኝ በምሠራው ሥራና ራሴን መግለጽ በቻልኩበት ልክ ነው፤ ሳንተዋወቅ የምንተዋወቅ መስለን እንኖራለን። ይከፍሉኛል - አገለግላለሁ።ሌላ ሕይወት የለም። ብሞት አያዝኑም፣ሌላ ሰው ይቀጥራሉ። ብደሰት ደስታዬ አያስደስታቼውም። የምለውን ካልኖርሽው አትረጂውም፤ አጉል ፍልስፍና ሊመስልሽ ይችላል።'' በግርምት ዝም ብዬ አዬዋለሁ፤ ፊቱን በአንዴ ያጥለቀለቀው ምሬት ያንን ሁሉ ሳቅና ፈገግታ በምኔው ሸፈነው? እያልኩ እገረማለሁ ...

“…እንዴት እንደማስረዳሽ አላውቅም፣ ጧት የስልክ 'አላርም' እያንባረቀ፣ ሰውነቴን ጨርሶታል። ስንት ቀን ነው እንቅልፍ አስክሮኝ በጉልበቴ እየዳህኩ ወደ መታጠቢያ ቤት የሄድኩት? ሁሉም ነገር ይቅርብኝ አገሬ መጥቼ አንዲት ፍራሽ ብቻ ያለችባት ቤት፣ ማንም ሳይቀሰቅሰኝ እስኪበቃኝ ለመተኛት ተመኝቻለሁ። በእንቅልፍ እጦት የተጥመለመለች ነፍሴ ቀኗን የምትገፋው በቡናና ቀዝቃዛ ውሃ ምርኩዝ ተደግፋ እያነከሰች ነበር:: ከሩቅ በቅዳሴና አዛን ድምፅ እንደ እናት አባብሎ የሚቀሰቅስ አገር ላደገ ሰው፣ የአላርም'ጩኸት ቀውስ የሚያደርግ ነገር ነው፡፡ የጠላት ድምፅ ነው. ምን ትዘፈዘፋለህ? የአባትህ ቤት መሰለህ? ለባርነት ነው ያመጠንህ ተነስ ግርድናህን ጀምር' የሚል የፈረንጅ ድምፅ ነው። ጽዳት ሥራዬ ነው...ዶላር የማገኝበት፣ ቤተሰቦቼን ያንደላቀኩበት ሥራዬ ነው፤ ግን እገረማለሁ የቆሻሻም ዓይነት አለው፡፡ ቆሻሻ ሁሉ ቆሻሻ እንዳይመስልሽ፡፡ የቤት ጥራጊያችንን ተመልከች፣ ቄጤማው፣ የዳቦ ፍርፋሪው፣የጫት ገረባው፣ ሲሞላልን የተራረፈ ምግብ... የፈረንጅ ቆሻሻ ገራገር አይደለም፤ ሽታው እንደ ብረት የጠጠረ ክርፋት ነው፤ ቆሻሻ ሁሉ ቆሻሻ አይደለም። የቆሻሻቼውን ጭካኔ የሚነግርሽ የበሽታቼው ክፋት ነው፤ዳማከሴ የማይፈውሰው መርገምት። ዓለም አሻግሮ በጉጉት የሚያዬው ዘመናዊ ሕክምናቼውና ጥበባቼው የማያድነው መቅሰፍት ነው፡፡ “አሰለቼሁሽ መሰል በምሬት?'' “አይ! እዬሰማሁህ ነው" አልኩ፡፡ እውነቴን ነበር እንደዚያን ጊዜም ሰምቼው አላውቅም። በረዥሙ ተነፈሰና ሩቅ እያዬ በትካዜ ሥራዬ...ቀን ታክሲ እነዳለሁ፣ ማታ Oሥራ ሁለት ፎቅ ያለው ሆስፒታል ውስጥ ከሌሎች መሰሎቸ ጋር ጽዳት እሠራለሁ፡፡ እዚያ ኢራቅና አፍጋኒስታን ሽብርተኛ ተዋጉ _ ለሚሏቼው ወታደሮቻቼው _ ሜዳሊያ ቢሰጡም፣ የአሜሪካ ሕዝብ በዕለት ከዕለት ኑሮው ከሚያመርተው ቫይረስ እና

ጀርም አንገት ላንገት ተናንቆ፣ ከእልቂት የሚጠብቀው ስደተኛው የጽዳት ሠራተኛ ነው- እኔና ወገኖቼ። እንደ ዘይት የረጋ ሺንታቼውን፣ እንደ ወተት ከነጣ የመጸዳጃ ቤት ሰሃኖቻቸው ላይ ማጽዳት ነው ሥራዬ፤ በላስቲክ ጆንያ የሞላ የምግብ ትራፊና አፍ ማበሻ ወረቀታቼውን ማንሳት ነው ሥራዬ፤ የሚቀረና የፕላስቲክ ቡና መጠጫ ኩባያቼውን መሰብሰብ ነው ሥራዬ፤ ቡና እንዴት እንደዚያ ይቀረናል? ቡና ሲባል፣ እጣንና ሉባንጃ የሚያስታውሰው አእምሮዬ ዛሬ ላይ ቡና ሲባል፣ ያንን ክርፋት ነው በምሬት የሚያስታውሰው፡፡ ከዓመት ዓመት ፀሐይ የማይደርስበት ቀዝቃዛ ስሚንቷቼውን በበረኪና ማጠብ ነው ሥራዬ፣ አገሬ ላይ መኖር እፈልጋለሁ፤ ሕዝቡ ደግ-ሆነ ክፉ ግድ የለኝም፡፡ ኑሮው ተወደደ- ረከሰ ግዴለኝም። ከስደት የከፋ መንፈስን ሽባ የሚያደርግ ክፋት የለም፡፡ ድህነት ወለል ላይ ቆሜ ሸቅብ ስመለከት፣ ገንዘብ የሰማይ ጥግ መስሎኝ ነበር፤ እጄ ላይ ሲገባ የሰው መንፈስ እንደህዋ ወሰን የለሸ መሆኑ ገባኝ፤ በገንዘብ የማይሰፈር ረቂቅ ነገር! ይኼን ለሰው ባወራ ጥጋበኛ እባላለሁ አውቃለሁ፤ ድህነት አንዱ የሚነጥቀን ነገር ትክክለኛ ፍርድን ነው። ስንቱ ሥጋው በርሃብ በሚረግፍበት አገር መንፈሴ፣ ነፍሴ ብል መሞላቀቅ ተደርጎ እንደሚታይ አውቃለሁ፡፡ እህቶቼ ተምረው ለወግ ማዕረግ በቅተውልኛል፡፡ ብር ከሆነ እግዚአብሔር ይመስገን የሚበቃኝን ያኽል ይዣለሁ፤ባይበቃም በረከት ከላይ ከሰማይ መሆኑን ካመንኩ ቆይቻለሁ፡፡ ምን አደርጋለሁ እዚያ...? ወደዚህች ምድር የመጣነው በእንግድነት ነው፤ ጭራሽ እንግዳ ሆነን ወደሌሎች ምድር እንሄዳለን፡፡ ስደት
👍416🔥2
ማለት የእንግዳ እንግዳ መሆን ነው፡፡ እንግዳ ሆነን የሄድንባቼው ሰዎች በእንግድነት ሌሎች ሰዎች ቤት ይዘውን ቢሄዱ እንደማለት... እየሰማሽኝ ነው ማሂዬ? ብዥዥ... አለብኝ! ባሌ ይኽን ሲነግረኝ ከልቡ ነበር፡፡ ያ ሳቂታ ልጅ፣ እንዲህ ዓይነት የዘጠና ዓመት አሮጊት እንኳን የማትመረረውን ምሬት ከዬት አመጣው? መሸነፍ ዓይነት አለው... በሕይወት ስሸነፍ መጀመሪያ እጅ ወደ ላይ ስትለኝ፣ አንድ እጄን

አነሳሁ፤ የተነሳ እጄ ላይ ይኼ ባሌ ቀለበት አጠለቀ፤ ማግባቴ መማረክ ነበር። አልተማረኩም ለማለት የአንድ እጅ ምርኮ (መሽኮርመም ለምርኮም ይሠራል) ባለ መሸሻ መደበቂያዬ ስላልኳት አሜሪካ ይኼን ሲለኝ ግን ሁለተኛውንም እጄን ከፍ አድርጌ የተሟላ ምርኮኛ ሆንኩ። እጅሽን ስጭ አለኝ..አንድ እጄን አገሬ ለተወለደ ምሬት፣ ሌላኛውን ለፈረንጅ ምሬት የሰጠሁ ምርኮኛ ነኝ። ሁለት ተኩላ የሚናጠቃት ጠቦት፡፡ ቀሪው ጊዜ ምን ይሆን ብዬ አልሰጋም፤ እንደ ምርኮኛ የሚንከባከብ ባል አለኝ እንደማረከኝ ያላወቀ። የትም ከመውደቅ አይሻልም? ግን ምንድን ነው የትም? ማለቴ ጥሩ ሙያ ያውም ከነሥራ ልምዱ አለኝ፤ እንኳን ለራሴ ለሰው እተርፋለሁ፤ ምንድን ነበር አንቀልቅሎ ትዳር ውስጥ የሞጀረኝ? (መሞጄር የእኔ ቃል _ አይደለም፤ ከዚያ የተረገመ ልጅ የተጣበቀብኝ ቃል ነው...) "ይኼ ውሃ ይኼ ባሕር፣ ርቀቱ አይገባሽም፣ ርቀቱ አይገባኝም፣ ዝም ብለን እንሞጄር፤ እንስጠም ወይ እንንሳፈፍ፣ ከመሞጄር ብቻ አንስነፍ፤'' አብርሽ ጋር ፒዛ እየበላሁ ቡናውን እየጠጣ፣ ድንገት የአፍ መጥረጊያ ናብኪን አንስቶ በጥቁር እስክርቢቶ የጻፈው ግጥም ነው፣ እስካሁን እኔ ጋር አለ፡፡ ይኼው አብረን በተሞጀርንበት ባሕር እኔ ሰመጥኩ እሱ ተንሳፈፈ። የደራሲ ሥራ ሕይወትን መጋፈጥ ነው ወይስ በቃል አሸሞንሙኖ ማለፍ!?

የሆነ ሆኖ እንዴት ነው የምወደው? ቢያገባኝ ምን ይሆን ነበር? ልጅ ካልፈለገ፣ እንወልድም፤ ወሬ ካልፈለገ፣ አላወራም፤ ዘፈን ከጠላ፣ ዘፈን አልከፍትም፤ ..ግን ከሥራ ስመለስ የምወደው ሰው ወዳለበት ቤት ብሄድ ... በቃ ይሀችን ብቻ፤ ወደ እሱ ቤት ስሄድ እንደምደሰተው ወደዬቶም ስሄድ ተደስቼ አላውቅም፣ ሲጀመር ወደየትም ሄጄ አላውቅም፣ ወደሆነ ቦታ ስሸሽ ነው የኖርኩት፡፡ ወደ ሥራ የምሄደው ከቤቴ ለመሸሽ ነበር፣ ወደቤቴ የምሄደውም ከሥራ ለመሸሽ፤ ደስ ብሎኝ የምሄደው ለመሸሽ ሳይሆን ናፍቄው፣ ፈልጌው የምሄደው ወደ እሱ ብቻ ነበር...እሱ ጋር መድረስ፣ በክንዶቹ መኻል መታቀፍ፣ በከንፈሮቹ መሳም ብቻ አልነበረም ደስታዬ፣ መንገዱ ሁሉ ለእኔ ሐሴት ነበር፡፡ ስንት ቀን ታክሲ ላይ መልሴን ረስቼ ወረድኩ? የምናፍቀው ያንን ነው፣ ወደምወደው ቦታ መሄድ፤ አሟሟት ምረጭ ብባል ራሱ ወደምወደው ቦታ ሙዚቃ እየሰማሁ ስሄድ በመኻል ብሞት እላለሁ። “እና ምን አልሽ ማሂዬ ?'' ባለቤቴ ጠዬቀኝ፡፡ “እኔ እንጃ!''ትክ ብዬ አዬሁት፣ ሽበት ጸጉሩን ጀማምሮታል፣ ስንጋባ አልነበረውም፤ ቀለም ተቀብቶ ይሆናል። “ማለቴ እንደፈለክ፣ ለእኔ ችግር የለውም'' አልኩት፡፡ ዘሎ ተጠመጠመብኝና ግንባሬን፣ ጸጉሬን፣ ዓይኔን፣ አፍንጫዬን፣ ጉንጨን፣ ከንፈሬን ትርምስምስ አድርጎ ሳመኝ። ወደ አገሩ መግቢያ “ቪዛ” በእኔ ከንፈር የተመታለት ይመስል። ውስጤ ለባሌ ብሶት አላዘነም፣ ተስፋ ያደረኳት አሜሪካ፣ እያየኋት፣ እንደ አረፋ እጄ ላይ ስትጠፋ በግርምት ፈገግ አልኩ እንጂ፤ ጭራሽ ባል የሚባል ዕዳዋን ጣለችብኝ። ቀልድ የማያልቅባት ዓለም! እናም ባሌ እንዲህ አለ “ከዚህ የጧት ፀሐይ ከሚያስንቅ ፈገግታ እንዴት መራቅ ይቻላል?'' ደግሜ ፈገግ አልኩ፡፡ ገና ቅድም መብላት ያቆምኩትን ምግብ እንደገና ተያያዝኩት፤ ካገባሁ በኋላ ለራሴም እስኪገርመኝ በጣም በላተኛ ሆኜ ነበር፣ ምግብ የቀረበበት ሰሃን የታጠበ እስኪመስል አላቆምም።

“ማሂዬ ጣፍጦሻል መሰል የሆነ ነገር ይጨመርልሽ ...?'' “አዎ!...!'' አልኩ! ሆዳም ናት ብሎ ቢፈታኝ ምናለበት!? የት ሄድኩ እኔ?! እናትነት ርግማን ነው ምርቃት? ልጄን ሳያት ስንት ጊዜ አንጀቴ ተንሰፈሰፈ? ምን የሚያንሰፈስፍ ነገር አለ? አባቷ ከአሜሪካ ሰብስቦ ባመጣላት ድፍን የሰፈሩን ልጅ ማሳደግ በሚችል ልብስ ዘንጣ፣ ጡቴን ከጡጦ እያማረጠች ያማረ ግቢ ውስጥ በሰላምና በደስታ የምትኖር ልጅ፣ እናቷ መንገድ ዳር ጥላት እንደጠፋች አራስ የምታሳዝነኝ ለምንድነው? ትንንሽ እጆቿን አየር _ ላይ _ እያወራጨች ጣቶቿን እየጠባች፣ ከንፈሮቿ ላይ ውብ የማለዳ ጠል የመሰሉ የለሀጭ ጤዛዎች ሲንኳለሉ ስታምር!...ግን ታሳዝነኛለች፤የሆነ ነገር የበደልኳት ይመስለኛል፡፡ ካልራባት አታለቅስም፣ አትስቅም፣ ትንንሽ እጆቿን በባዶው አየር ላይ እያወራጨች ስትደክም የሆነ ቁም ነገር የምትሠራ ነው የምትመስለው፡፡ ዓይኖቼን ከዚህች ትንሽ ፍጥረት ላይ መንቀል አልችልም፡፡ እንዳፈጠጥኩባት ውዬ አድራለሁ፤ ባዬኋት ቁጥር የሆኑ ሰዎች በር አንኳኩተው፣ ልጅቷን አምጭ ብለው የሚወስዱብኝ ነው የሚመስለኝ። ስትተኛ ጠጋ ብዬ ትንፋሻዋን አዳምጣለሁ፤ ወይም በልብሷ ላይ በተነፈሰች ቁጥር ከፍ ዝቀ የሚል የደረቷን እንቅስቃሴ አያለሁ፡፡ “እንዴ! የእኔም ልጅ እኮ ናት ማሂ!'' ይላል አባቷ ሲያቅፋት ነፍሴም ዓይኔም ሲሸበር እያዬ። በእርግጥ የእርሱም ልጅ ናት ግን አስተቃቀፍ አይችልም፤ እንደ ትራስ ነው ድንገት ከአልጋ ላይ አንስቶ የሚያንጠለጥላት። ምንም ጥንቃቄ የሚባል ነገር የለዉም። ወንዶች ግን ምንድን ነው ችግራቼው? ሲያነሱም ሲጥሉም በደመነፍስ ነው? የሆነ ጊዜ ዳይፐር ላመጣ አንዴ ያዛት አልኩት፤ ወዲያው ጭርር ብላ ስታለቅስ ነፍሴን አላውቅም እጄ ላይ የያዝኩትን ሁሉ በታትኜው፣ ከእጁ ላይ ነጥቄ... “ምን አደረካት?" ብዬ ጮኽኩበት፡።

“ደህና ናት! በአጋጣሚ ይኼ ነገር ቧጭሯት ነው!” አለኝ፣ ግራ እጁ ላይ የሚያደርገውን አስቀያሚ ብራዝሌት' እያሳዬኝ፡፡ አንገቷ ላይ ደም የመሰለ ጭረት በረዥሙ ተጋድሞ ነበር። አበድኩበት! “ይኼን ነገር ወደዚያ አውልቅና ጣል!'' ብዬ ጮኽኩበት፡፡ “እኬ! ኦኬ! ማሂ ሶሪ!” ብሎ ወጥቶ ሄደ፡፡ ያ ቡጭሪያ እስከ አሁን ፈዛዛ ሆኖ መስመሩ አንገቷ ላይ አለ፡፡ የሚገርመው ብራዝሌቱምን ከእጁ ላይ አላወለቀውም። ሰው ቢሰማ ምን ይላል እንጂ፣ ይችን ፍጥረት : አባቷ እንደሚጋራኝ ሳስብ እናደዳለሁ፣ ስስት እላለሁ፡፡ማንም ጋር የማልጋራት የብቻዬ እንድትሆን ነው ፍላጎቴ። አባቷ፣ እናቷ፣ አያቷ፣ ምንጅላቷ፣ አክስቷ፣ አጎቷ እኔ ብቻ እንድሆን ነው ምኞቴ፡፡ ይዘሻት ጥፊ ጥፊ ይለኛል፡፡ ወደ ሆነ ሰው ወደማይኖርበት ዓለም፣ ወይም ሰው ወደሚኖርበት አራት ዓመት ስመላለስበት ወደኖርኩት ኮንዶሚኒዬም። ያ "ሲዲ ፕሌየር" ኦህህህ... እኔና አብርሽ ባልና ሚስት ሆነን ብንፋታ፣ ንብረት ክፍፍል ላይ ሁሉንም ነገር ውሰድ ያን “ሲዲ ፕሌየር" ብቻ ስጠኝ፣ እለው ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ለዚያ ሲዲ ፕሌየር የነበረኝን ልዩ ፍቅር በጥልቀት ሳስበዉ እንዲሁ የእኔ ሙዚቃ ወዳድነት ከዚያ ቁስ ጋር የፈጠረው ግጥምጥሞሽ ብቻ እነዳልነበረ ገብቶኛል፡፡ አብረሃም በዚያ ሁሉ ጊዜ አንድም ቀን አፈቅርሻለሁ ብሎኝ አያዉቅም፤ አንድም ቀን! ስንተዋወቅ ስለ እግሬና ስለ ጠይምነቴ ከወረወራት አስተያዬት ውጭ ቆንጆ ነሽ ብሎኝ አያዉቅም፤ ነፍሴ ከምወደው ሰው አድናቆት ትፈልግ ነበር። እቤቱ በሄድኩ ቁጥር በወንድ የተዘፈነ የፍቅር ዘፈን እከፍታለሁ፤ በሲዲ ፕሌየሩ በኩል ከዘፋኙ የሚንቆረቆሩ የፍቅር ውዳሴዎችን ከሚስመኝ፣ ከሚያፈቀረኝ፣ ከሚዳስሰኝ፣ ከሚተኛኝ ከዚያ ሰው ለእኔ እንደሚነገሩ የፍቅር መወድሶች እያሰብኩ
👍331
እራሴን ሳታልል ነው የኖርኩት፡፡ እሱ ጋር ተኝቼ ጆሮዎቼ ዘፈኖቹ ላይ ነበሩ፡፡ የራሴን ምኞት እንደ ፊልም እራሴ እያቀናበርኩ ሕይወቴን ሙሉ አድርጌ በገዛ ራሴ ሐሳብ

ሣልኩ፤ መለያየት ሲዘንብ የሕልም ሥዕሌን አቅፌ ተሰደድኩ፡፡ ያ የሙዚቃ ማጫወቻ ለሚያቅፈኝ አብረሃም የተባለ ሥጋ ነፍስ ነበር፡፡ ሁልጊዜ የማስበው ለእኔና ለልጄ የምትበቃ ትንሽ ቤት እከራያለሁ፣ ጥሩ ሞግዚት ቀጥሬ፣ ሥራዬን እየሠራሁ ብቻዬን እኖራለሁ፡፡ ትንሽ ቤት፣ ሰላምና ሙዚቃ ያለባት፣ እንግዳ የማይመጣባት፣ አክስት፣ አጎት፣ ምናምን የማይንኳተትባት... ባል የሚባል ሰው የሌለባት፣ በአካባቢው ጋራዥ የሚባል የሌለበት፣ ደራሲ የሚባል የማያልፍበት ነጻ ዓለም!! ዝም ብዬ ጡቴን ለዜማ እሰጣታለሁ፣ የጡቶቼ መተለቅ ይገርመኛል፡፡ ከማርገዜ በፊት ከነበራቼው መጠን አምስት እጥፍ ይሆናል ያደጉት፤ ይኼ ነገር ወተት ብቻ ነው? እላለሁ ለራሴ። ከወለድኩ በኋላ ሰውነቴም _ በማይታመን ፍጥነት ግልብጥብጡ ወጣ፡፡ ከውፍረቴ ብዛት ታፋና ታፋዬ ተጣብቆ፣ ስራመድ እየተፋተገ ደስ የማይል የማንጣጣት ስሜት ይፈጥርብኝ ነበር፡፡ ጉንጮቼ ድርፍጭ አሉ፣ የአንገቴ ነገርማ አይወራም፣ እንደ ዔሊ አንገት ተሰብስቦ የተደበቀ ነበር የሚመስለው፤ የአንገቴ መቀበር የማይታመን _ ነበር። _ ከሩቅ _ ለሚያዬኝ ሰው የሆነ የማይታይ ኃይል የለበስኩትን ‘ቲሸርት' ትከሻና ትከሻዬ ላይ በጣቶቹ ቆንጥጦ ወደ ላይ የሳበው ነበር የሚመስለው፡፡በሌ ሳሎን ተጎልቶ በቲቪ የሚያያቼውን የአሜሪካ ፉትቦል ተጨዋቾች መሰልኩ፡፡ እራሴን በመስተዋት እያዬሁ ማኅደረ ሰላም በሥጋ ማዕበል ተመታች እላለሁ። ከበፊት ልብሶቼ አንድ እንኳን ያልጠበበኝ አልነበረም። መጥበብማ የወግ ነው። ልብሶቼን ሳያቼው በዕድሜ እጥፍ የምበልጣት የታናሽ እህቴ ልብሶች ነበር የሚመስሉት፡፡ ስትወልጂ እርግፍ ነው የሚለው ቢሉኝም፣ ሰውነቴ በተለይም ቦርጨ “ቀሪ ልጅ አለ እንዴ?'' እስኪያስብል ከነበረበት ንቅንቅ አላለም፡፡ ከጎንና ጎኔ ተጣጥፎ ቁጭ የሚል ሥጋዬ፣ የለበስኩትን ብለብስ ፈጥጦ ይወጣል፤ በተለይ ስቀመጥ

ለራሴም ይገርመኝ ነበር። ልብስ መምረጥ ባል ከመምረጥ በላይ ሕይወቱን አስጨንቋታል፤ ምንም አያምርብኝም፡፡ አብዝቼ የምለብሰው ሰፋፊ ቲሸርቶችን' ነበር፡፡ “ጅም' ግቢና ስፖርት ጀምሪ አሉኝ በሕይወት ዘመኔ ዐሥር ሜትር ሩጨ የማላውቅ ልጅ፣ ሳስበው ገና ደከመኝ:: ሥጋዬን እንደ ልብስ አውልቀሽ ወደሆነ ቦታ ወርውሪው ይለኛል፡፡ በመስታዎች ራሴን ባዬሁ ቁጥር ብስጭት ውስጤን ይሞላዋል፡፡ ሥጋና ነፍስ እንዲህ ተጣልተው አያውቁም፡፡ ከምንም በላይ አልቅሽ አልቅሽ የሚለኝ ደግሞ ሆዴ ላይ (ከእንብርቴ ትንሽ ዝቅ ብሎ) እንደ ቦርጭ ያበጠውና ቆዳው የተዥጎረጎረው ነገር፡፡ ሁለቱም ታፋዬ ላይ ደግሞ በረዣዥሙ የወጣብኝ ሸንተር ነበር፡፡ ጥይምናዬ ያበሳጨው ምቀኛ ሰይጣን በሚያስጠላ ዥጉርጉር ቀለም በዘፈቀደ ያሰመረው መስመር ነበር የሚመስለው፡፡ መስመርማ የወግ ነው ከሩቅ ቆሞ ቀለም የረጨብኝ ነበር የሚመስለው፡፡ በተለይ ታፋዬ ላይ የወጣው እርከን መስሎ በደረጃ ተሰምሮ ለዓይን ይቀፋል፡፡ ሁሉም ነገር ሲያልፍ ነው መሰል የሚቆጨው፣ ስለጠይምነቴ አጋንነው ሲያወሩ ግዴለሸ ነኝ ብዬ አስብ ነበር፤ አሁን ላይ ግን በሸንተር የደፈረሰ ጠይምነቴ ያንገበግበኛል፡፡ ያልተቀባሁት የአገር ውስጥና የውጭ አገር ቅባት አልነበረም፤ እንዲያውም መስመሩ ደምቆ ወጣ፡፡ አንዳንዴ ታዲያ ምናለ እራቁቴን አንድ እንኳን ፎቶ ኖሮኝ በነበር እላለሁ፡፡ ለአንድ ዓመት የሥጋ ዘር በዞረበት ሳልዞር በምግብ ሞከርኩት፤ ቢተከል ሁለት ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሰላጣ ፈጅቼ- ምንም ለወጥ አላመጣሁም። ባለቤቴ "ውፍረት'ኮ ጸጋ ነው፣ ደግሞ አንቺ ላይ ሲያምር” ይላል፡፡ አስተያዬቱ ግድ አይሰጠኝም፡፡ እንዲህ ሆኜ ያ ደደብ ቢያዬኝ እንደ በፊቱ ለጡቶቸ ይስገበገባል? እንደ በፊቱ ከእግር ጣቴ እስከ ራስ ጸጉሬ ልሳምሽ ይለኛል? እንደ በፊቱ...! በመጨረሻ የድሮ ፎቶዎቼን እያዬሁ “ደህና ሁኚ ማሂ'' ብዬ አለቀስኩ፡፡ አለቃቀሴ

ሙት የመሸኜት ዓይነት የመረረ ነበር፡፡ በአስክሬን ሳጥን ብቻ ሳይሆን በራስ ሥጋ መገነዝም አለ ለካ፡፡ የምወዳቼውን ልብሶች ሁሉ እነዚያን መጠለያዎቼን ለኔ ቢጤዎች እና በቅርብ ለተቀጠረች ሠራተኛዬ ሰጠሁ። አዳዲስ ልብሶቼ ሁሉ በእንግድነት ሄጀ የተጠለልኩባቼው የለቅሶ ቤት ድንኳኖች ይመስሉኛል፡፡ የዚያን ቀን አለቀስኩ፤ በራስ ሰውነት አለማዘዝ መቻል ያሳዝናል። ውፍረት ማለት የትም ሳይሄዱ የራስ ሰውነት ውስጥ መጥፋት ነው። አለ አይደል “የት ሄድኩ እኔ?'' ብሎ ራስን መጠየቅ፤ በቃ እንደዚያ ነው ስሜቱ። እንዲህ የእራሴ ስቃይ ሳያንሰኝ፣ ከአሜሪካ ለመጣ ሰው፣ ለብር ብላ ፍቅረኛዋን ፈነገለችው መባሉን ከጓደኛዬ ከሃይሚ ሰማሁ (የሚፈነግል ይፈንግላቼው) ሃይሚ እንደ በፊቱ ቶሎ ቶሎ አታዬኝም፣ ትናፍቀኝ ነበር፤ ናፍቆቱ ልክ እናቴ ትታን የጠፋት ሰሞን የሚሰማኝን ዓይነት ናፍቆት ነበር። ይሁን እና ሃይሚ _ እንደዚያ ጠፍታ በመጣች ቁጥር የምታወራኝ ወሬ ለቀናት ውስጤን ያንገበግበኛል፡፡ እሷ በየዋኅነት ብታወራቼውም፣ ወሬዎቹ ግን ቅስሜን የሚሰብሩ ነበሩ፡፡ ከሄደች በኋላ ሁልጊዜም አለቅሳለሁ። _ እንዳገባሁ ሰሞን የሚያውቀኝ ሁሉ በረዢም ምላሱ ትኩሱን የከሃዲነቴን ወሬ ለመቅመስ ተጋፋ ... ጨዋ መስላ ተባለ... ድሮስ አንገት ደፊ... ተባለ፣ ጀግና ናት ከዚች አገር በዬትም ብሎ መውጣት ነው ተባለ፡፡ እናንት የአገሬ ልጆች፣ ሕይወቴ የመረረ እኔን ተሰብስባችሁ እንደ አሞሌ ጨው የምትልሱኝ ስለምን ነው!?... ከብት ናችሁን....!? እንደቆዘምኩ ዓመታት ነጎዱ፡፡ ልጄ ዜማ ሁለት ዓመት ሞላት፡፡ አንድ ቀን በረንዳ ላይ ተቀምጨ ሰፊው ግቢ ውስጥ ድክ ድክ እያለች ከአበባ አበባ የሚበሩ ቢራቢሮዎችን የምታባርር ዜማን አያለሁ፡፡ ትልቅ ሥራ እንደሠራ ሰው እያለከለከች መጣች እና ዱባ የሚያካክሉ ጡቶቼን በትንንሽ እጆቿ ለመያዝ መታገል ጀመረች አቅፌ ጡት ሰጠኋት፣ እየጠባች እንቅልፍ ወሰዳት፡፡

የባሌ ቤተሰቦች ለእኔ አዝነው፤ ሁለት ዓመት ከጠባች በቃት እንግዲህ፤ ጸጉርሽም ተነቃቀለ'ኮ ይበቃታል ይሉኛል፡፡ እኔ ግን በጡት ሰበብ ከእቅፌ አለመውጣቷ ዓለሜ ነበር። ሰላም የማገኜው ዜማን አቅፊያት ቁጭ ስል ነበር፡፡ ሐሳቤ ይሰበሰባል፡፡ እንዴ መጥባት ካቆመች ይኼን ያኽል ጊዜ ታቅፋልኝ እንደማትቆይ አውቃለሁ፤ በቃ ከዚያ በኋላ የእኔ ብቻ አትሆንም፡፡ እንዲያውም ከእኔ ይልቅ የባሌ ቤተሰቦች በሚሠሩላት ምግብ፣ በሚያጫውቷት ጨዋታ፣ እየተሳበች ዞራ የምታዬኝ አይመስለኝም፡፡ ሙያ ለሌላት ድብርታም እናት ለማዘን ዕድሜዋ አይደለም። ወደምፈራው ባዶነትና ብቸኝነት መመለስ ያስፈራኛል፡፡ በቀስታ መኝታ ቤቷ ወስጄ አስተኝቻት በሰፊው የሳሎን መስኮት በኩል ቆምኩ፣ ምን እዚያ ወስዶ እንደገተረኝ እንጃ! ምንም አይታይም፤ የግቢው ረዥም የግንብ አጥር፣ ዛፎች እና ንጹህ ሰማይ...የተወለወለ የሚመስል ሰማያዊ! ሰማያዊ ቀለም እወዳለሁ፡፡ በመስኮት አሻግሬ እየተመለከትኩ። መሄድ ያምረኛል፤ መሄጃ የለኝም። ምን ዓይነት የተሳሳተ ሒሳብ ብሠራ ነው ሥራዬን፣ ቤተሰቦቼን፣ ጓደኛዬ ሃይሚን፣ አብርሽን እነዚህን የምወዳቸውን ነገሮች ሁሉ ትቼ ወደዚህ ትዳር ወደሚባል ጋግርታም ዓለም የተሰደድኩት? መሄጃወቼ እነዚህ ነበሩ። ሌላ ምን መሄጃ አለኝ? ድንገት እናቴን አስታወስሁ፣ ማስታወስ ስል ከሥር መሠረቱ፡፡ አእምሯችን እንዲህ ከርሞ ከርሞ ነገርን ከዚያና ከዚህ አሳክቶ የሚደርስበት እውነት የሚመስል ነገር አለ አይደል? እንደዚያ ነበር
👍405
ይኼንኛው ሐሳቤ። እናቴ በመጥፋቷ ውስጤ ለረዠም ዓመታት አዝኖባት ነበር፡፡ ሌላ ወንድ ጋር መሄዷ አባባን የመካድ፣ እኛን ልጆቿን የመጸዬፍ ነገር አድርጌ ወስጄው ነበር፤ አባባ ይወዳታል፣ ያከበራታል። በሥርዓት ይሁን በመልክ፣ በትምህርት ይሁን በሌላው ወላጆች በልጆቻቼው ሊኮሩበት በሚገባ ነገር ሁሉ የምናኮራ ልጆች ነበርናት። ከዚህ በላይ ከሕይወት ምን ፈልጋ ሄደች? ይኼ ነበር የዓመታት ጥያቄዬ፡፡ በዚያች ቅጽበት ግን ጥያቄዬን በሌላ መንገድ እንደገና ጠዬቅሁ...አባባ ጥሩ ሰው ነው- ልክ እንደ ባሌ፡፡ እናቴን ይንከባከባት ነበር፤ ባሌ እኔን እንደሚንከባከበው፡፡ ያፈቅራት ነበር፤ባሌ እኔን እንደሚያፈቅረው፡፡ ግን እናቴ ይኼ ሁሉ ሳይበግራት

ምርጫዋን ተከትላ መንጎዷ ምን ዓይነት ጥንካሬ ቢኖራት ነው!?...ከሌላ ሰው ልጅ ወልዳለች ተብሏል፤ ምናይነት እናት ነው የምትሆነው? አባባን አታፍቅረው እሺ እኔም ባሌን አላፈቅረውም፣ ሌላ የምታፈቅረው ሰው ይኑር እኔም ሌላ ሰው ልቤ ውስጥ አለ ግን ከማላፈቅረው ሰው ብወልዳትም ልጄን ትቼ ከምሄድ ሞቴን እመርጣለሁ! እንዴት ያንን ቻለች? ዕድሜ ልኳን የልጆቿ ናፍቆት ቅጣት እንደሚሆንባት አልጠራጠርም፤ ግን ደግሞ ከማያፈቅሩት ጋር መኖርም ቅጣት ነው። የትኛውም ምቾት የትኛውም ክብርና እንክብካቤ የማይፈውሰው ባርነት፣ መሰሪያ የታጠቀ ወታደር በሩ ላይ ባይቆምም፣ ከፍቅር ውጭ በማንኛውም ሰበብ የተጣመሩበት ትዳር እስር ቤት ነው፤ መስኮት የእስረኛ ነፍስ መነፅር ሳይሆን ይቀራል? በቆምኩበት ቡና ይሼተኛል እናም ያቅለሸልሼኛል አውቀዋለሁ ስሜቱን ሁለተኛ አርግዣለሁ፡፡ ምንም የተለዬ ስሜት አልተሰማኝም፡፡ እንዲሁ ትውልድ የሚባል ነገር በውስጤ የሚያልፍብኝ ባዶ መተላለፊያ ነገር ከመሆን ስሜት ውጭ! ተመልሼ አልጋዬ ጫፍ ላይ ተቀመጥኩና ካለምንም ምክንያት ኮሜዲኖው ላይ የተቀመጡትን ቁልፎች አነሳሁ፡፡ ወደ አምስት የሚሆኑ በቁልፍ መያዣ ዘለበት የተሰኩ ቁልፎች ናቸው፤ የመኪና ቁልፍ የቤት ቁልፍ የካዝና ቁልፍ(እዚያ ካዝና ውስጥ ቁጥር ስፍር የሌላቼው የወርቅ ጌጣጌጦች(የዚህ የባሌ ስጦታ) እና የጋብቻ ዶክሜንቶች አሉ፡፡ ከእኔ በስተቀር ማንም የምን ቁልፍ እንደሆነ የማያውቀው አንድ መካከለኛ ቁልፍ የማንጠለጥላቼው ጥቂት ቁልፎች ጋር ሁሌም አለ። ለዓመታት አንጠልጥዬው ስዞር ማንም(ያው ማንም ባለቤቴ ነው) የምንድን ቁልፍ ነው? ብሎኝ አያውቅም። ጠባሳችን የት ላይ እንዳለ ከራሳችን በስተቀር ማን ያውቃል?! አብርሃም የሰጠኝ የቤቱ ቁልፍ ነበር። ምንም ነገር የለኝም፤ ፎቶው የለኝም፣ ሰጥቶኝ የሚያውቀው ስጦታ የለም፣ ከእርሱ የቀረኝ ብቼኛ ነገር የቤቱ ቁልፍ ነበር፡፡ ይኼ በእጄ ስይዘው እንደ አንዳች ነገር ሰላም የሚሰጠኝ ቁልፍ፤ ስንት ቀን ይኼን ቁልፍ በእጆቼ እያገላበጥኩ እንደ ተአምር አዬሁት? ስንቴ በሃሳብ ነጎድኩ!? ያንን የኮንዶሚኒዬም

የብረት በር ስከፍት ልቤ በደስታ ተመንጥቃ ልትወጣ ትደርስ ነበር። ከቀለበት እኩል የሆነ ቃልኪዳን ነገር ያለበት ቁልፍ ይመስለኛል፡፡ ባወጣ ባወርድ አልገለጥልሽ ያለኝ አንድ ነገር፣ አንዳንዴ ምክንያቱን ለራሳችን እንኳ በማይገባን ምክንያት ለቅርቦቻችን፣ ብዙ ለዋሉልን- ባይውሉልንም፣ ምንም ላልበደሉን ሰዎች ይሁዳ ሆነን አሳልፈን ለሐዘን ስንሰጣቼው፤ ሕይወታችንን ለመሳቀሉ ክፉዎች ግን፣ እንደ ክርስቶስ ካልተሰቀልንላችሁ ስንል የመገኜታችን ነገር ምን ይሆን ሚስጥሩ? ብስጭት ውስጤን ሞላው፤ ቁልፎቹ የተሰኩበትን ዘለበት ፈልቅቄ ያንን ቁልፍ ነጥዬ አወጣሁትና በብስጭት ወደ መፀዳጃ ቤት ገብቼ የሽንት ቤቱ መቀመጫ ውስጥ ወረወርኩት፡፡ ሸክላው ላይ ተቅጨልጭሎ ውሃው ውስጥ በእርጋታ ገብቶ ቁጭ አለ፤ የውሃ መልቀቂያውን ባለ በሌለ ኃይሌ ስጫነው ንጹህ ውሃ እየተዥጎደጎደ ቁልቁል ጎርፎ ሲያልቅ ቁልፉ ከመዓበል በተአምር እንደተረፈ ጀልባ : ቁጭ እንዳለ ነበር። በውሃ አለመወሰዱ አስደሰተኝና ልክ ሳላስበው እንደወደቀብኝ ሁሉ ተስገብግቤ በሁለት ጣቶቼ መልሼ አወጣሁት፡፡ ቁልፉን አጥቤ እጄንም ታጠብኩና ወደ መኝታ ቤቴ ተመልሼ አልጋዬ ጫፍ ላይ ቁጭ አልኩ። የምሠራው ግራ ገብቶኝ ዙሪያውን ስቃኝ ቆዬሁ እና እንደገና ተነስቼ በመስኮት ማዬት ጀመርኩ፡፡ ሳያቋርጥ ያቅለሸልሼኛል!! በራቼው ላይ ቆመው መክፈቻ ቁልፍ የጠፋባቼው ሰዎች ስለምን ያዝናሉ? እኔ መክፈቻ ቁልፍ ይዠ በሩ ከነቤቱ፣ ከነባለቤቱ የጠፋብኝ ሰው ነኝ፡፡ ይኼ ቁልፍ ከእንግዲህ የሚከፍተው የትዝታ በሮችን ብቻ ነው። መልሼ ወደዘለበቱ አስገባሁት እና ኮመዲኖው ላይ ወርውሬው ከልጄ ጎን ተኛሁ፤ የኔ ዜማ የሕይወቴ ቁልፍ፡፡ሰላም የሰፈነበት ድንቡሸ ፊቷን እያዬሁ በሐሳብ ነጎድኩ... ብዙ ብዙ አሰብኩ! ለሰዓታት... እናም ለራሴ ምን አልኩ? አይዞኝ አልኩ!

አይዞኝ! አሁን እናት ነኝ፤ ስለ ልጆቸ ዕጣ ፋንታ ማሰብ አለብኝ። ለሞተ ትላንቴ ሳለቃቅስ መኖር ገና የተጀመረ የልጆቼን ነገ ማበላሸት ነው፡፡ እኔ ምርጫዬን ኖሪያለሁ፤ ለዚሀ ውሳኔ ያበቃኝ አስተዳደግም ይሁን ስሜታዊነት ሁሉም ነገር የራሴ ውሳኔ ነበር። በሕይወት ውስጥ ማንኛውንም የውሳኔ ጠጠር _ ከመወርወራችን በፊት፣ ፊት ለፊታችን የቆመ የነገ መስተዋታችን ላይ ምን ሊፈጥር እንደሚችል ማሰብ የእኛው ኃላፊነት ነው፡፡ ግን ደግሞ ሰውነን እና ብዙ ከማስተዋል ጎዳና የሚያስወጣን ስሜት ይኖራል፡፡ _ የእኔው _ ጠጠር _ መስተዋቴን _ ሰንጥቆት ይሆናል እንጂ ጨርሰ አልተንኮታኮተም፡፡ በሕይወት እስካሉ ጨርሶ መንኮታኮት የሚባል ነገር የለም፡፡ ጥሩ ባል ያላት ባለትዳር፣ የአንዲት ቆንጆ ልጅ እናት እና ሁለተኛ ልጅ ያረገዝኩ ሴት ነኝ።ልጆቼ ያልተረበሸ ነገ ያላቼው፣ ማንንም የማይፈሩ፣ ማንንም የማይለማመጡ፤ ሰውን ከመውደድና ከማክበር ያለፈ ዕዳ የሌለባቼው ልጆች እንዲሆኑ የትኛውንም ዋጋ የመክፈል ግዴታ አለብኝ፡፡ አይዞኝ! ጥሩ ወላጅ ማለት ከጊዜ ጎርፍ ፊት ቆሞ መከራና ስቃይን ወደ ትውልድ እንዳያልፍ አግዶ የሚይዝ ጽኑ ግንብ ነው፡፡ አምላኬ ብርታቱን ይስጠኝ። በእርግጥ ባሌን አላፈቅረውም፤ ግን በዚህ የተልከሰከሰ ዘመን ቢያንስ ማግባት የሚባልን ክብር ያጎናጸፈኝ መልካም ሰው ነው፡፡ የእኔ ትላንት ትዳሩን እንዲረብሸው አልፈቅድም፡፡ ብዙዎች ገና ከቤተሰባቼው ጫንቃ በማይወርዱበት ዕድሜ ከሞት ጋር ተናንቆ ለቤተሰቡ አሸናፊነትን ያሳዬ ሰው ነው። ወጣትነቱን ሰውቶ፣ በስደት ተንከራቶ ያቆመው ሕይወት ነው፡፡ ቢያንስ የባልነት መብቱን ማክበር የልጆቼን ግማሸ ማንነት ማክበር ነው፡፡ ውስጣችን በፍቅር ካልተገዛ ቢያንስ ለሞራል ሕግ እንዲገዛ ማስገደድ አለብን፡፡ ሕመም ቢኖረው እንኳን ላፈቀሩን፣ ባያፈቅሩንም ላከበሩን የሚከፈል ትንሽ ዋጋ ነው፡፡
👍358
ደግሞስ ነገን ማን ያውቃል? ፍቅር ራሳችንን በሰጠነው ቁና ልክ ይሰፈር እንደሆነ ምን ይታወቃል? ዓይነቱ ይለያይ እንደሆን እንጂ ሕይወት እስካለ፣ ማፍቀር ይኖራል፡፡ ልብሳችንን ጥለን _ ከደመና በላይ ባንሳንፈፍም፣ ማንም ሰው በጎጆው ጠሪያ ሥር ትንሽ ፍቅር _ አያጣም፡፡ _ ራስንም _ ቤተሰብንም ጤና ከመንሳት መተሳሰብንና የጋራ ኃላፊነትን ፍቅር ነው ብሎ ማመን ሳይሻል አይቀርም፡፡ ትዳር ከፀሐይ ቢከልለንም በየቤታችን ጭል ጭል በምትል ኩራዝም ቢሆን ከብርሃን ጨርሰን አንቆራረጥም፤ አይዞኝ! ዓይኖቼን ከድኜ እንዲህ ሳስብ፣ የመኝታ ቤቱ በር በቀስታ ሲከፈት ሰማሁ፤ ከአከፋፈቱ ባለቤቴ እንደሆነ አውቂያለሁ። ትንሽ ጸጥታ ሰፈነ፤ አንገቱን ብቅ አድርጎ እኔና ዜማን በርህራሄ እና በፍቅር እያዬን እንደሆነ አውቃለሁ። በቀስታ ተራምዶ የልብስ ማስቀመጫውን ሲከፍት እና
ሲዘጋ እሰማለሁ። ወደ ተኛንበት መጥቶ የምወዳትን ለስላሳ ብርድ ልብስ ደረበልን እና ግንባሬን በስሱ ስሞኝ እንደ አገባቡ በቀስታ ወጥቶ ሲሄድ ዕንባዬ ተዘረገፈ።


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍313
''አስጠላኸኝ'' አለችው
''ለምን'' አላላትም

:

ያውቃታል ጠንቅቆ ምክንያት የላትም።

ካቻምና እንደሆነው :

እርሱ ጋር ስትመጣ
    የበፊት ጌታዋን
''አስጠላኝ'' ብላ ነው።

አንዳንዱ ለመሄድ
ሰበብ ስለሌለው
ፍቅርህን ለመግደል

:

ሲፈልግ ይውላል
ያንተን አንድ በደል!

ለምን ብለኽ አንጀትህን አታላውሰው

:

    አቋቋሙ ያስታውቃል
እንደሚሄድ አንዳንድ ሰው።

🎴ኤልያስ ሽታኹን🎴


ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍386🥰4
#አበጁ!
...
አዳምና ሄዋን፣ ከገነት ባይወጡ፣
ያቺን ዕፀ-በለስ፣ ፍሬዋን ባይውጡ፣
አይጥመኝም ነበር፣ ሕይወት እንዳሁኑ፣
ሳይሠሩ መቀለብ፣ መኖር ሳይቦዝኑ፡፡
እንኳን ተሳሳቱ፣ እኔስ ደስ ብሎኛል፣
ሳይሠራ ‘ሚበላ፣ ወትሮም ያቆስለኛል፡፡🤔

ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ
300 #Subscriber_Challenge

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍15
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሰሎሞን ድቅቅ ካደረገው እንቅልፍ ቢነቃም

ዓይኖቹ አልገለጥ ስላሉት አሻሽቶ ሊያነቃቸው
ፈልጐ ቀኝ እጁን ለማንቀሳቀስ ሲሞክር
አልተቻለውም፤የሆነ እጁ ላይ የተጫነ ነገር አለ፤የሆነ ሰው አቅፎል..‹‹ወይ እዳዬ !!ማታ ተሳሳትኩ መሰለኝ... ሴት ይዤ ገብቼያለሁ ማለት ነው፡፡›› ሲል አሰበ፤ እሱን ተወውና
ግራውን ሞከረ ተመሳሳይ ነው፡፡በዚህን ጊዜ ደነገጠ ..እንዴት ሁለት ሴት ልገዛ እችላለው?›› ድንጋጤው አይኖቹ ተበርግደው እንዲከፈቱ አገዘው ፡፡ወደ ቀኙ ዞረና አየ…..ልጁ ዕፀ-ህይወት ናት ዝርግትግት ብላ ክንዱን
ተንተርሳ በነጻነት ተኝታለች...ወደ ግራው
ዞረ..ሌለኛዋ ልጁ ዕፀ‐ፍቅር በተመሳሳይ ሁኔታ ግራ ክንዱ ላይ ተመቻችታ ተኝታለች፡፡ከእሷ ቀጥሎ ቢጃማ ለባሽ የሆነች ገዘፍ ያለች ሴት ከአንሶላው ሳትወጣ ቁጭ ብላ መፅሀፍ
እያነበበች ነው፡፡

‹‹የፈጣሪ ያለህ!!››አለ የልጆቹ ሲገርመው ከአመታት በፊት የፈታት ሚስቱን ከጎኑ ሲመለከት፡፡ ‹‹ምን ልትሰራ እሱ ቤርጓ ተገኘች?..የቤቱን ዙሪያ ገባ በግርምት ቃኘ... ቤርጎው አይደለም ያለው ፤ የድሮ ቤቱ... የበፊት መኝታው ክፍሉ ውስጥ..የበፊት አልጋው ላይ ከበፊት ሚስቱ ጋር…የሚገርም ጉዳይ ነው፡፡

‹‹እየቃዠው መሆን አለበት?››ድምፅ አውጥቶ ተናገረ፡፡

የውብዳር የተናገረውን በትክክል አጥርታ ባትሰማም የሆነ ነገር እንዳለ ድምፁ ጆሮዋ ጋር ስለደረሰ የምታነበውን መጽሀፍ ቅዱስ በመክደን ያቀረቀረ ግንባሯን ወደ ላይ ቀና አደረገችና << ነቃህ እንዴ….?እንዴት ነው ሰላም አደርክ?››አለችው በፍጹም ትህትና ፡፡

ለእሷ ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ የራሱን ጥያቄ አስቀደመ ‹‹የት ነው ያለሁት?››ጠየቃት፡፡

‹‹ቤትህ ነዋ፡፡››

እንደመበርገግ አለና ልጆቹን ከክንዶቹ ላይ አንሻራቶ እራሱን ነጻ በማድረግ ከእሷ ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ ተቀመጠ፡፡

‹‹ቀስ... ቀስ.. ልጆቸህን ትቀሰቅሳቸዋለህ››አለችው በለሆሳሳ፡፡

‹‹ቆይ ማታ ሰክሬ ነው አይደል የመጣሁት .. ? በጣም እረበሽኳችሁ እንዴ....? ስትረብሽ ልጆችህም አይተውህ ነበር እንዳትይኝ ብቻ… አዝናለሁ፡፡ እንዲህ ለማድረግ ፈልጌ አልነበረም፡፡ ትንሽ ተበሳጭቼ ስለነበር በዛ ላይ መጠጥ አብዝቼ ስወስድበት እራሴን አስቶኝ ነበር ማለት ነው..አንቺም እኮ ትክክል አይደለሽም፤ስመጣ ዝም ብለሽ ታስገቢኛለሽ እንዴ…? ገና ከውጭ በራፍን አልፌ ሳልገባ ዘበኛው እንዲመልሰኝ አታደርጊም ነበር?››

ዝም ብላ በፍዘት ስታዳምጠው ከቆየች በኃላ << ማታ ስለሆነው ሁሉ ምንም ነገር አታስታውስም ማለት ነው?›.አለችው፤ የሆነ ሀይለኛ የሚቀስፍ ስጋት እና የሚቀዘቅዝ ፍርሀት በሰውነቷ እየተሰራጨባት፡፡

‹‹ቆይ ቆይ..ማታ እኔ ቤርጎ አንቺ…››የሆነ እንደህልም አይነት ትዝታ በአዕምሮዎ ብልጭ ድርግም አለበት፡፡

‹‹አዎ መጥቼ ነበር፡፡››

‹‹አዎ እንደ እሱ በይኝ.. እንጂማ ያን ያህል ላብድ አልችልም፡፡ >>

‹‹የምን እብደት አመጣህብኝ?››

‹‹...ቀጥታ ዝም ብዬ እዚህ በመምጣት ካላደርኩ አልልማ ... አንቺን እዛ ሳይ ተከትዬሽ መጥቼ እንጂ..፡››

‹‹እንደዛም አይደለም፡፡››

‹‹ታዲያ እንዴት ነው?››

‹‹እኔ ነኝ ለምኜህ ማለት ይቅርታ ጠይቄህ ይዤህ የመጣሁት...››

‹‹እየቀለድሽ አይደለም አይደል?››

‹‹እውነቴን ነው ሶል... ተነጋግረን ተስማምተን ነበር የመጣሀው፡፡ጥፋት ያጠፋህ መስሎ ከተሰማህ እንኳን ጥፋቱ የእኔ ነው እንጂ ያአንተ አይደለም፡፡ አንተ ምንም አላደረግክም …እኔም ግን ወድጄ አይደለም ፤ እስቲ ልጆቻችንን እያቸው፤ዛሬ ከጎናቸው ብትሆን እንዴት የሰላም እንቅልፍ እንደተኙ.. አቤት ማታ ቀስቅሰህ መጥቼያለሁ ስትላቸው የተደሰቱት መደሰት ልነግርህ አልችልም..ታዲያ ለእነሱ ስትል ይቅር ብትለኝ ምን አለበት..?በቃ ምንም ልበድልህ ... ምንም ላጥፋ ለእነሱ ስትል ልትረሳልኝ አትችልም?››

‹‹ኧረ ቆይ.. አንቺ ባጠፋሽው መጠን እኮ እኔም አጥፍቼያለሁ›..

‹‹ታዲያ በቃ ይቅር እንባባላ..በቃ በስካር
መንፈስም ቢሆን ወደ ቤትህ አንዴ ገብተሀል
..በፈጠረህ በዚህ በምታምንበት መጽሀፍ
ቅዱስ ልለምንህ ፤ ተመልሰህ ከቤትህ
አትውጣ... ከልጆችህ ጋር ኑር...አንተ
ከምትወጣ እኔ ብወጣ ይሻለኛል...ሴት ልጆች
አባታቸውን አብልጠው ይወዳሉ ሲባል አባባል
ብቻ ይመስለኝ ነበር..በራሴ ልጆች ነው እውነት
መሆኑን ያረጋገጥኩት... አንተን አጥተው መኖር
በጣም ነው የሚከብዳቸው... ስለዚህ
ባክህ..ባክህ››በማለት በቃላትም ...በአይኖቿ
እርግብግብታም ተለማመጠችው፡፡እጁን ላካና አቅፎ ወደ ራሱ በመጎተት ደረቱ ላይ ለጥፎት በጆሮዋ ‹‹እኔም የትም አልሄድ ..አንቺ
እንዳልሽው በቃ ያለፈውን እንርሳው... የውሾን
ነገር ያነሳ ውሾ ይሁን››አላት፡፡

‹‹እሺ የእኔ ጌታ አመሰግናለሁ››አለችውና የሚንጠባጠበውን እንባዋን በቀኝ እጇ እያበሰች ከእቅፉ ወጥታ አልጋውን ለቃ ወረደች፡፡በዚህ ጊዜ በመሀከላቸው ያለችው ዕፀ- ህይወት ከእንቅልፏ ባና ዓይኖቿን ከመግለጧ በፊት መጀመሪያ የጠየቀችው ጥያቄ‹‹አባቴስ?›› የሚል ነበር፡፡
‹‹አለሁልሽ የእኔ ቆንጆ >> ብሎ ወደ ራሱ አስጠግቶ አቀፋት... ሙሉ በሙሉ ነቃችና እላዩ ላይ ተንጠልጥላ እያገላበጠች ትስመው ጀመር፡፡ በዚህም አረካችም መንታ እህቷንም ቀሰቀሰቻት ..ሰሎሞን ተይ ትተኛ ቢላትም ልታዳምጠው አልፈለገችም፡፡ ሁለቱም ልጆቹ ለመጀመሪያ ቀን ያዩት ይመስል ትንፋሽ እስኪያጥረው እና ድክም እሲኪለው ተላፉት ፣ሳሙት፣እላዩ ላይ ጨፈሩ፡፡ በመጨረሻ የውብዳር ነበረች በግድ አላቃ ለቁርስ መኝታ ቤቱን ለቀው ወደ ምግብ መመገቢያ ቤት እንዲሄዱ ያስገደቻቸው፡፡

በፊት አብሯቸው ይኖር በነበረበት በመጀመሪያዎቹ የፍቅር ዓመታት በእጇ ትሰራለት የነበረውን እና እሱም በጣም እየወደደውና እሷንም እያመሰገነው ይበላው የነበረውን ምግብ ነበር ሰርታ ለቁርስ ያቀረበችው ፡፡በሳቅ እና በጨወታ ታጅበው
ቁርሳቸውን እየበሉ ግማሽ እንደደረሱ የሳሎኑ በራፍ ተንኳኳ፡፡

‹‹ይግቡ ..ክፍት ነው›› አለች የውብዳር ከመቀመጫዋ ሳትነሳ.፡

በራፉ ተከፈተ..ሁሴን ነበረ የመጣው ፡፡

‹‹እየተጣራጠርኩ ነው የመጣሁት ስልክሽ አይሰ......››ንግግሩን አቋረጠ፡፡እርምጃውንም መሀል ሳሎን ላይ ገታው፡፡የሰሎሞን እዛ ቤት ውስጥ መገኘት ፍጽም ከግምቱ ውጭ የሆነ ክስተት ነበር... የሆነ ውሽማው ቤት ሊሰርቅ የሄደ ሰው ከባልዬው ጋር የመፋጠጥ አጋጣሚ እንዳጋጠመው ሰው ነው አደነጋገጡ፡፡

<< ና እንጂ ....አንተ እንወድሀለን ማለት ነው .. ቁርስ ላይ ደረስክ.…‹ሲበሉ አድርሰኝ ሲጣሉ መልሰኝ› የሚባለው እንደዚህ ነው››አለችው የውብዳር፡፡

ሁሴን ግን የእሷን ወሬ አልሰማም‹‹ይሄ ሰውዬ
እዚህ ምን ይሰራል? ››አላት እንደምንም እግሮቹን አነቃንቆ ወደ እነሱ እየተጠጋ።

‹‹እቤቱ ከልጆቹ እና ከሚስቱ ጋር ቁጭ ብሎ ቁርስ እየበላ ነዋ››

‹‹..ከልጆቹ እና ከሚስቱ ጋር >> ልትል አስባ ነበር ያልተረጋገጠውን የሚስትነት ማዕረጓን መልሳ የዋጠችው›› የምታድርበት ሆቴል እኮ ሁለቴ ነዋ የመጣሁት ስልክህም ዝግ ነው ..ግራ ሲገባኝ ጊዜዬን ከማባክን እነዚህ ልጆች ልይ ብዬ ወደ እዚህ ጎራ ማለቴ እኮ ነበር..እንጂማ.. ››በማለት ለልጆች ይዞላቸው የመጣውን ቸኮሌት አከፋፈሏቸው ወንበር ስቦ ተቀመጠ ፤አመስግነው ተቀበሉት፡፡
👍687
እጁን ታጠበና ማዕዱን አብሯቸው መቋደሰ ጀመረ... የውብዳር ልታጎርሰው ስትል ‹‹ኧረ እዛው የጀመርሽውን አጉርሺ..››አላት፡፡
‹‹ወደ ቤቴ በመመለሴ ተበሳጨህ እንዴ ?››አለው ሰሎሞን እየሳቀ፡፡

‹‹መበሳጨት አይደለም ....ግን ስርዓትና ደንብ ጣሳችሁ ማለቴ ነው ፡፡እንዲሁ ለሞራላችን
እንኳን የውሸት ሽማግሌ አድርጋችሁን <እኛ ነን
እኮ ያስታረቅናቸው> ብለን ትንሽ ብንጎርር ምን
አለበት…?ደግሞ እኮ ቀጠሮ ስላለን ሁለት ሰዓት ነበር ሆቴልህ የደረስኩት በህልም
አይተሀቸው ነጋ አልነጋ ብለህ ነው እንዴ ዶሮ
ሳይጮኽ የመጣኸው?››

‹‹ኧረ ምን ደሮ ሳይጮኸ ..ወገግ ብሎ ሲነጋ አይኖቼን ስገልጥ እዚሁ ቤት የገዛ መኝታ ቤት ከሙሉ ቤተሰቤ ጋር በአንድ አልጋ ላይ ተኝቼ እራሴን አገኘሁት፡፡››

‹‹ኧረ ባክህ በቃ!!! ለሊት ከተኛህበት አፍነው አምጥተውህ ነዋ፡፡››

‹‹መሰለኝ... እስቲ እሷን ጠይቃት፡፡ >>

‹‹ይሄንን ሁለታችሁንም በተናጥል ለየብቻ ነው የምጠይቃችሁ...አሁን ወደ ውጭ ትወጣለህ ወይስ እዚሁ ነው የምትወለው?››
‹‹ኧረ እወጣለሁ... 5 ሰዓት አንድ የምደርስባት ቦታ አለቺኝ›.እጃቸውን ተጣጥበው ተነሱ፡፡

‹‹እንዴ አባ ለምን ትሄዳለህ? አትሂድ፡፡››
‹‹አልሄድም ... ስራ ደርሼ ልመጣ ነው፡፡››

‹‹ዛሬም እኛ ጋር አዚህ ነው የምታድረው ?>>

‹‹አዎ.. ከአሁን ወዲህ ሁል ግዜ እናንተ ጋር ነው የማድረው ..እዚሁ ነው የምኖረው››አረጋገጠላቸው፡
‹‹እንወድሀለን አባ፡፡›› ሁለቱም በአንድ ላይ ወደ ታች አስጎንብሰውት ግራና ቀኝ ጉንጩን ተከፋፍለው ሳሙትና ሸኙት፡፡

የውብዳር ፈራ ተባ እያለች‹‹ለምሳ ብቅ ትላላችሁ እንዴ?›› ስትል ጠየቀች ፡፡

‹‹አዎ የእሱን አላውቅም እኔ ግን እመጣለሁ..ልክ ስድስት ሰዓት ተኩል ላይ ከች እላለሁ..ያቺ ቡናሽን አፍልተሸ የምትጠብቂኝ ከሆነ?

‹‹ግድ የለህም አንተ ብቻ ና..ሁስ አንተስ..?››አለችው ፈዞ ሁኔታቸውን በትኩረት ሲመለከታቸው የነበረውን ጓደኛቸውን፡፡

‹‹ኧረ እኔ ዛሬ ይዝለለኝ፤ይስፋችሁ >>ብሎ ተሰናበታትና ቀድሞት ወደ መኪናው አመራ.. ሰሎሞንም ተከትሎት የገቢናውን በር ከፍቶ ወደ ውስጥ ሊገባ ሲል የውብ ዳር‹‹ ሶል ››ብላ ተጣራች ፡፡

‹‹ሆቴል ብሄድ እቃዎችህን ይሰጡኛል እንዴ?››

‹‹ግድ የለም እኔ ለምሳ ስመጣ ይዤው እመጣለሁ…ደና ዋይልኝ፡፡››

‹‹እሺ ደህና ዋል››አለችው፡፡
ግቢውን ለቀው እንደወጡ‹‹አንተ ጉደኛ ማታ እርም የሴት ቀሚስ ብገልብ እያልክ ስትምል ስትገዘት አልነበረም እንዴ?››

‹‹ታዲያ መች ገለብኩ?››

<<ማለት?>>

‹‹ማለትማ አዲስ ቀሚስ አልገልብም አልኩህ እንጂ ድሮም የእኔ የነበረውን ቀሚስ አልነካም ብዬ አልማልኩም፡፡››

‹‹አይ አንተ መቼስ ማምለጫ አታጣ....ያም ሆነ ይህ ግን በሆነው ነገር በጣም ደስ ብሎኛል፡፡በተለይ ከልጆችህ አንፃር በዚህ ውሳኔህ ብትፀና እኔ ደስተኛ ነኝ..፡፡››

‹‹በቃ አየውት እኮ .. ሁሉንም ፍላጐቶችህን የምታሟላልህ እንከን አልባ ሴት የትም አታገኝም.. እዚህም ቤት ያለው እሳት መልኩን ቀይሮ እዛም ቤት አለ ፡፡ዋናው ተቻችሎ የአንዱን ጉድለት አንዱ ሞልቶ.. አንዱ ሲያጠፋ
አንዱ ይቅር ብሎ. ህይወትን እየተጋገዙ መኖር ነው..፡፡››

‹‹አሪፍ ነው..ይህቺ እንግዲህ ስሜት ያልነካካት ከህይወት ልምድ የተገኘች ጠቃሚ እውቀት ነች››አለና ለሰሎሞን ንግግር ድጋፍ ሰጠው ፡፡በመጀመሪያ የተጓዙት ሰሎሞን አርፎበት ወደነበረው ሆቴል ነው፤ ዕቃውንም እዛ የቆመችውንም መኪናውን ለመውሰድ፡፡ ደርሰው እንደቆሙ ሁሴን ሞባይሉን አነሳና ደወለ..::

‹‹ሄሎ ፍቅር..አንድ አስደማሚ ወሬ ልነግርሽ ነው››ሰሎሞን አንጓጠጠው፡፡

‹‹ጋዜጠኞች ስትባሉ ወሬ ተቀብሎ በአየር ለመበተን ሚቀድማችሁ የለም..ለምን
አንደኛህን በጋዜጣህ አታሳትመውም፡፡››ብሎት ጥሎት የፎቁን ደረጃ መውጣት ጀመረ፤ሁሴንም ችላ ብሎት ከትንግርት ጋር ማውራቱን ቀጠለ፡፡

‹‹ምንድነው.. ?ምን ሰማህ?››

‹‹ሰሎሞን ነዋ፡፡››

‹‹ሰሎሞን ምን ሆነ?

‹‹ታረቀ እኮ፡››

‹‹አንተ እውነትም ደስ የሚል ቦንብ ወሬ ነው የነገርከኝ... ግን እንደዛ ክርር አድርጋው አልነበር እንዴ እንዴት ሀሳቧን ቀየረች..? ይገርምሀል እኔ እራሴ ከሶስት ቀን በፊት እቤቷ ድረስ ሄጄ ለምኛት ነበር....እንዴት መሰለህ ሲያንዘረዝራት የነበረው...ለማንኛውም እንኳን ታረቁ::>>

‹‹ስለማን ነው የምታወሪው…..?ከየውብዳር ጋር እኮ ነው የታረቁት፡፡››

‹‹የውብ ዳር? >>

‹‹አዎ ከውብዳር ጋር፡፡››

‹‹እንዴት ሆኖ?››

‹‹ዝርዝር መረጃው ገና አልደረሰኝም ግን ያው አደገኛ የፍቅር ግርሻ እንደመጋኛ ሁለቱንም አጠናግሯቸዋል፡፡ >>

‹‹በጣም ደስ ይላል ...በቃ በእናትህ ለምን እራት አንጋብዛቸውም፡፡››

‹‹የት.. ?ቤት ?››

‹‹ቤት እማ ትንሽ ይከብዳል ሆቴል››

‹‹አሪፍ ሀሳብ ነው ... ሰባት ሰዓት አካባቢ ተገናኝተን ስለወጪ መጋራቱ እናውራበታለን፡፡››

‹‹ችግር የለውም ይመቸኛል.. ስትፈልገኝ ቢሮ ና ::>>

‹‹እሺ ቻው ፍቅር፡፡››

‹‹ቻው..አፈቅርሀለሁ፡፡››

‹‹እኔም፡፡››

ስልኩን ዘግቶ ሰሎሞን የሚታገዝ ዕቃ ካለው ሊያግዘው ፎቅ ወደ ሚገኘው መኝታ ክፍሉ የሚወስደውን ደረጃ መውጣት እንደጀመረ ሞባይሉ ጮኸ..መጓዙን ሳያቆም አነሳው‹‹ሄሎ ዶክተር፡፡››

‹‹ሁሴን ሰላም ነህ?››

‹‹ሰላም ነኝ አንቺስ እንዴት ነሽ?››

‹‹ይመስገነው ሰሞኑን ትንሽ የስራ ውጥረት ስለነበረ ነው ላገኝህ ያልቻልኩት.. ዛሬ ከአስራአንድ ሰዓት በኃላ ነፃ ነኝ አንተን የሚመችህ ከሆነ…፡፡››

<<ችግር የለም ይመቸኛል..የት እንገናኝ፡፡››

‹‹ግዮን ቢሆን ይመቸኛል፡፡››

‹‹በቃ እዛው በሰዓቱ እደርሳለሁ፡፡››

‹‹እሺ አመሰግናለሁ ሁሴን፡፡››

‹‹እሺ ቻው ዶ/ር ሶፊያ››


ቤተሰቦች በቅናነት #YouTube #subscribe እያደረጋቹ በጣም ቀንሳችኋል 1ደቂቃ አይፈጅም ገብታችሁ #Subscribe አድርጉ አመሰግናለሁ።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍1058🔥1👏1
#ተገላቢጦሽ

ያኔ እኮ አብረሃም
ሲኖሮ በዚህ አለም
ሁሉ ተሟልቶለት
ምንም ሳይጎሎበት
ተናግሮ ነበረ
"ለዚች ትንሽ ጊዜ
ለ ስምንት መቶ አመት
ቤትማ አልቀልስም
ድንኳን መች አነሳት"
ዛሬ የሱ ዘሮች
ለሰማንያ አመት
ህንፃውን ገንብተው
ቤታቸውን ሰርተው
ሰፈሩንም አጥረው
ከድሀው ላይ ነጥቀው
.....ይጠባበቃሉ....
ከደጅ የቆመውን
ከዘጠኙ አንዱን፡፡


🎴ዘውዱ እርቅይሁን🎴


ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ
300 #Subscriber_Challenge

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍377
#ዝምተኛ_ልቦች

አምነው የወደዱ
ወደው የተካዱ
ተክደው የራዱ
ፍርሃት አንሸራቶ ቁልቁል የጣላቸው
የብቸኛ ልቦች የትነው መውደቂያቸው?
የትነው መድረካቸው?
ማነው አጃቢያቸው?
እንዴት ነው ምታቸው
የተካዱ ልቦች አጋር የራቃቸው
የሚያቀነቅኑት ምንድን ነው ዜማቸው?
የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው
ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው
ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበደላቸው
ብቸኝነት ሰርጎ ብቻ ያስቀራቸው
ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው?
ከየት ነው ጥሪያቸው?
በየት ነው ጉዟቸው?
የት ነው መድረሻቸው?
እንደ ሰብአሰገል ጠቅሶ የሚመራቸው
የቃተቱ ልቦች የታል ኮከባቸው?
መቼም ከአምላክ ትንፋሽ ከውሃ ከአፈሩ
ከእምንት እና እውነት ከፍቅር ሲሰሩ
ዝምተኛ ልቦች ጥንቱን ሲፈጥሩ
ተገፍትረው ወድቀው
ደቀው እንዳይቀሩ
በተስፋ ጸንተው ነው ዘላለም ሊኖሩ::

🎴ጌትነት እንየው🎴

ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ
300 #Subscriber_Challenge

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍40👏6🥰3
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-13


‹‹ያልገባኝ ከስምንት ወንዶች መካከል የተወለድሽ ብቸኛ ሴት ሆነሽ ሳለ እንዴት በአያትሽ እጅ አደግሽ...?ወላጆችሽ እንዴት እሺ ብለው ሰጡሽ ...?››ስል ጠየቅኳት
‹‹እሱ የራሱ የሆነ መራር ታሪክ አለው።ከእኔ በፊት ወላጆቼ ሁለት ሴት ልጆችን ወልደው ነበር፡፡ግን በተወለድ በአንድ ወራቸው ሁለቱም ሞቱ።ከዛ እኔ እንደተወለድኩ አያቴ በሶስተኛው ቀን ከእናቴ እቅፍ ነጠቀችና ወሰደችኝ።ከዛ የራሷን ደረቅ ጡት እያጠባች አሳደገቺኝ።በወቅቱ ወላጆቼ እኔን እንደሌሎቹ ትሞትብናለች የሚል  ጥርጣሬ ስለነበራቸው ጨከን ብለው ተይ አትውሰጂያት ማለት አልቻሉም ነበር...በዛ ላይ አያቴ በጣም ተፈሪ ሰው ነበረች።››
‹‹የሚገርም ታሪክ ነው››አልኳት።
እኔ ቢራዬን እየደጋገምኩ እሷ  ኮካዋን በዝግታ እየተጎነጨች ጫወታችንን ቀጠልን።
‹‹ግን እምቢ አልሽ እንጂ ወይን ነገር ብትሞክሪ ደስ ይለኝ ነበር፡፡››
‹‹ውይ ዶ/ር  ግድ የለህም ይቅርብኝ።››
ሲያንቀዠቅዠኝ‹‹ለምንድነው ግን? ስለማትወጂ ነው?››ስል ጠየቅኳት።
‹‹አይ እንደውም በጣም ነው የምወደው..ግን እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ወይን እንድቀምስ ያደረገኝ መስፍኔ ነው...ብዙ ጊዜም እጠጣ የነበረው ከእሱ ጋር ነው።እና አሁን እሱ እዛ አልጋ ላይ ተሰትሮ ለነፍሱ ሲታገል .እኔ  እዚህ ወይን ልጠጣ ብሞክር ከጉሮሮዬ አይወርድልኝም።››ብላ አስገረመችኝ።ከዛ በምን ሞራሌ  ካልጠጣሽ ብዬ ልጫናት እችለው…?የማይሆነውን፡፡.
እኔ በሀሳብ ሰምጬ ስለእሷ እና ባለቤቷ በማሰላሰል ላይ ሳለሁ በመሀል ድምፃን ሰማሁና ከሀሳብ ባነንኩ
‹‹ዶ/ር ለሁለት ነገር ነበር እፈልግሻለሁ ያልከኝ..እንዱን ሰማሁት በጣም ተደስቼያለሁ፡፡ ግን ሁለተኛው ምንድነው?››
ግራ ገባኝ ‹‹የምን ሁለተኛ?››
‹‹እንዴ ዘነጋኸው እንዴ? ለሁለት ነገር ነበር እፈልግሻለሁ ያልከኝ፡፡››
‹‹እ አዎ…ሁለተኛውማ ስለአንቺና መስፍን የፍቅር ታሪክ በቀደም ጀመረሺልኝ ልጆቹ ሲመጡ አቋረጥነው..እና እከዛሬ ሆዴን እንደቆረጠኝ ነው..እባክሽ አሁንእሱን እንድትነግረኝ ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹እንዴ.ዶ/ር አሁን?››
‹‹አዎ..አሁን..››
‹‹ሞባይሏን አነሳችና አየች….ቢበዛ 30 ደቂቃ ብቻ ነው መቆየት የምችለው…መስፍኔ ለረጂም ጊዜ ሲያጣኝ ይሳቀቃል፡››
‹‹ገባኝ…በ30 ደቂቃ የቻልሺውን ያህል ንገሪኝና… ቀሪውን ደግሞ ወደሌላ ቀን እናስተላልፈዋልን፡፡››
‹‹እሺ ካልክ ..ግን ምን ላይ ነበር ያቆምኩልህ…››ለማስተዋስ መጣር ጀመረች፡፡
‹‹ እያበጠርሽ የነበረውን ፀጉርሽን እንዳንጨፈረርሽ የሚከራየውን ቤት ልታሳይው ወደክፍሎቹ እየመራሽ ስትወስጂው ነበር ያቆምሺው፡፡
‹‹አንተ..ጥሩ አድማጭ ነህ፡፡››
‹‹አይ ..ያን ያህል እንኳን አይደለሁም ..››
‹‹እንግዲህ እንዳልኩህ ፊት ለፊት እየመራው ወደክፍሎቹ ይዤው ሄድኩ፡፡ክፍሎቹ አንድ አንድ  ስርቢስ ክፍል ናቸው፡፡ገብቶ ዞር ዞር እያለ አየውና‹‹ቀጣዩም ክፍል ተመሳሳይ ነው?››ሲል ጠየቀኝ፡፡
በራፍ ላይ እንደቆምኩ‹‹አዎ…ከፈለክ ልክፈትልህና እየው፡፡››አልኩት፡፡
‹‹አይ ተመሳሳይ ከሆነ ይቅርብኝ››
ድንግጥ አልኩ‹‹ምነው አልተመቸህም?አልኩት ››
‹‹አይ ተመሳሳይ ከሆነ ያኛውን ማየቱ አስፈላጊ አይደለም እያልኩሽ ነው››
ተንፈስ አልኩና‹‹እ እንደዛ ነው፡፡››
‹‹አዎ..ግን ስታስቢው የሚሆነኝ ይምስልሻል?››
‹‹አዎ በደንብ ይሆንሀል››አልኩት፡፡
ፍጥጥ ብሎ አየኝና ‹‹እንዴ !የምርሽን ነው?››ሲል ጠየቀኝ፡፡
‹‹አዎ እውነቴን ነው....ቀለሙንም ተላልጦል ካልክ ዛሬውኑ አስቀባልሀለው፡፡››
‹‹እሺ ስፋቱስ?››
‹‹ስፋቱ ይበቃሀል..ሰፊ እኮነው…ለአንድ ሰው ይሄ በጣም በቂ ነው፡፡››
‹‹አንድ ሰው ብቻ  እንደሆንኩ በምን አወቅሽ..ሚስት የለኝም ብዬሻለሁ እንዴ?››ብሎ አሳፈረኝም አስደነገጠኝም፡፡
በኩርፊያ መልክ‹‹አይ ሚስት ያለህ ስላልመሰለኝ ነው..ሚስት ካለህ እንኳን ይቅርብህ …ይጠብሀል››አልኩት፡፡
‹‹እሺ ለመሀኑ ኪራዩ ስንት ነው?››
‹‹ሚስት ካለህ ሁለት ሺ ብር..››
ከት ብሎ ሰሳቀና ‹‹እሺ ሚስት ከሌለኝሽ….?››
‹‹ሚስት ከሌለህ ችግር የለውም የፈለከውን መክፈል ትችላለህ፡፡››
‹‹ወደኪሱ ገባና የሆኑ ብሮች አወጣና ቆጠር ቆጠር አድርጎ  ከላዩ ላይ አምስት መቶ ብር አጄ ላይ አስቀመጠና‹‹ይሄ ቀብድ ነው.. በቃ ከዛሬ ጀምሮ ይሄንን ክፍል ተከራይቼዋለው…የዛሬ ሳምንት አካባቢ ገባበታለሁ…አሁን ወደጊቢሽ እንዳስገባሺኝ መልሰሽ አስወጪኝ››አለና ክፍሉን ለቆ በመውጣት እንደአመጣጡ ወደውጭ መራመድ ጀመረ ፡፡እኔም ከኃላው ግራ በመጋባት እከተለው ጀመር…››
‹‹ቆይ ግን ከሚስትህ ጋር ነው የምትገባው?››
‹‹እሱን ማወቅ ምን የደረግልሻል..?ሚስቴን ይዤ ከመጣው 2 ሺ ብር ከፍልሻለሁ…እሷን ፈትቼ ብቻዬን ከገባሁ ግን አንድ ሺ ብር ብቻ ነው የምከፍለው››
‹‹እሺ፡፡››
የውጭ በራፉ ጋር እንደደረስን ወደእኔ ዞሮ ትኩር ብሎ በፈገግታ እያየኝ፡፡‹‹ላንቺ ስል ግን ሚስቴን ይዤ ለመምጣት እሞክራለው፡፡››አለኝ፡፡
አበሳጨኝ‹‹እንዴ ሚስትህ ለእኔ ምን ትሰራልኛለች?››
‹‹ብዙ ነገር..አንደኛ እንዳንቺ በጣም ቆንጆ ስለሆነች ጓደኛ ትሆንሻለች…ሁለተኛ ጥሩ የኪራይ ገንዘብ ታገኚያለሽ፡፡››
‹‹አልፈልግም፡፡››
‹‹ምኑ ነው የማትፈልጊው .?.ከሚስቴ ጋር ጓደኛ መሆኑን ወይስ የኪራዩን ብር..?››
‹‹ሁለቱንም…፡፡››
አይኖቹን ከእኔ አሻግሮ ወደውስጥ ተመለከተና ከኃላችን ሰው እንደሌላ ካረጋገጠ በኃላ
‹‹በይ እስከሳምንት ትናፍቂኛለሽ… ደህና ሁኚ ›› ብሎ ጎንበስ በማለት ጉንጬን ሳመኝና ሌላ ምንም ሳይናገር ፊቱን ዞሮ ሄደ፡፡እኔ ግን እጄን ከንፈሩ ያረፈበትን የጉንጬን አካባቢ በፍቅርና በስስት እየዳበስኩ ድንዝዝ ብዬ ለበርካታ ደቂቃዎች ቆምኩ…ከንፈሩ ጉንጬ ላይ ሲያርፍ ልቤ ላይ ነው የሞቀኝ…አእምሮዬን ነው የነዘረኝ…፡፡.
ከዛ ሳምንቱ እንዴት ይለቅ..?ፍፅም ከዛ በፊት ሆኜ  የማለቀውን አይነት ሰው ነው የሆንኩት…በአየር ላይ ስንሳፈፍ ከረምኩ..ሚስቱን ይዟት ይመጣ ይሆን…?እውነት እንደእኔ ቆንጆ ነች…?ደግሞ እንደአንቺ ቆንጆ ነች ካለ እኮ የእኔን ቆንጆነት ያምንበታል፡፡ግን ሚስት እያለው ለምን ሳመኝ..?ለምንስ ትናፍቂኛለሽ አለኝ….?በሳምንት ውስጥ ሳባት ኪሎ ያህል ሳልቀንስ አልቀርም፡፡ደግሞ ትክክለኛ የሚመጣበትን ቀንና ሰዓት አልነገረኝም ያም ሌላ ስቃይ ነበር የሆነብኝ፡፡በስምንተኛው ቀን በእለተ እሁድ በአንድ ፒካፕ መኪና አልጋ ፍራሽና የተወሰኑ የቤት እቃዎች ጭኖ ከች አለ፡፡ሮጬ ልጠመጠምበትና አገላብጬ ጉንጮችን ልስማቸው ፈልጌ ነበር፡፡ግን እንደዛ ማድረግ አልቻልኩም፡፡እሱም ሰላም እንኳን አላለኝም..በራፍን እንደከፈትኩላቸው መኪናዋ ወደውስጥ ገብታ እንደቆመች ከገቢናው ወርዶ ወደእኔ እየተመለከተ ያለኝ የመጀመሪያ ነገር ቢኖር…‹‹እቤቴ ቁልፍ ነው ወይስ ክፍት?›› ነበር፡፡
ዝም አልኩት..ክፍት ይሆን ቁልፍ ማስታወስ እንኳን ከበደኝ፡፡
እኔን ተወኝና ከላይ የነበረውን ፍራሹን ይዞ ወደጓሮ ሄደ ፡፡እዛው በረንዳ ላይ ደንዝዤ እንደቆምኩ ነው፡፡ ከሹፌሩ ጋር ተጋግዘው ዕቃውን አጓጉዘው ለመጨረስ15 ደቂቃም የፈጀባቸው አይመስለኝም፡፡ከዛ ወደእኔ ጠጋ አለና ‹‹አያትሽ አሉ..ፈልጌቸው ነበር፡፡››አለኝ፡፡
‹‹የለችም..ቤተክርስቲያን ነች፡፡››
‹‹በቃ..ቁልፍ ካለሽ ቤቱን ቆልፊልኝ››ብሎኝ ብቻ ፊቱን አዞረ፡፡
‹‹ልትሄድ ነው?››
👍577🤔2👏1