አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
517 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የካፊያ_ምች

ሳልላክ ተልካ እንሂድ አለቺኝ
ካላጣችው ሰዓት ከቤት አስወጣችኝ
ጥርቅም እቅፍ አድርጋ በካፊያ ሳመቺኝ
የእድሜ ልክ ልክፍቱን ያኔ አስለከፈችኝ

መብረቅ እየጮኸ ዝናብ እያካፋ
የእኔ ልብ በሷ የሷ በእኔ ጠፋ
የሰማዩ ባህር ቁልቁል ተንዶብን
ውሃ ጠማኝ ውሃ እዘነበብን

ጠፍቼ ስመለስ ከእቅፏ ስወጣ
በርዶኝ አተኮሰኝ እቤቴ ስመጣ
እያደር አደረ ከርሞ ከረመብኝ
የዘመን ህመሜን ያን እለት ታመምኩኝ
አሁን አሁን ታዲያ!

ደመናው ሲጠቁር ነጎድጓድ ሲያጓራ
ነፋስ ሲያጉረመርም ክረምቱን ሲጠራ
ግንቦት ማለቂያ ላይ ይነሳል ህመሜ
ሲያቀብጠኝ በዝናብ በካፊያ ተስሜ
ምች ተሳልሜ።

🧿ተፈሪ አለሙ🧿
#የካፊያ_ምች

ሳልላክ ተልካ እንሂድ አለቺኝ ካላጣችው ሰዓት ከቤት አስወጣቺኝ ጥርቅም ዕቅፍ አርጋ በካፊያ ሳመቺኝ
የዕድሜ ልክ ልክፍቴን ያኔ አስለከፈቺኝ፡፡

መብረቅ እየጮኸ ዝናብ እያካፋ
የኔ ልብ በሷ የሷ በኔ ጠፋ
የስማዩ ባህር ቁልቁል ተንዶብን ውሃ ጠማኝ ውሃ እየዘነበብን።

ጠፍቼ ስመለስ ከእቅፏ ስወጣ በርዶኝ አተኮሰኝ እቤቴ ስመጣ እያደር አደረ ከርሞ ከረመብኝ የዘመን ሕመሜን ያን ዕለት ታመምኩኝ፡፡

አሁን አሁን ታዲያ!

ደመናው ሲጠቁር ነጐድጓድ ሲያጓራ ነፋስ ሲያስገመግም ክረምቱን ሊጣራ ግንቦት ማለቂያ ላይ ይነሳል ህመሜ ሲያቀብጠኝ በዝናብ በካፊያ ተስሜ፣ ምች ተሳልሜ፡፡

🎴ተፈሪ ዓለሙ🎴

#Share and #subscribe my #YouTube

አረ ገባ ገባ እያላቹ 500 አስገቡት
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍38🥰17👏4