አትሮኖስ
284K subscribers
113 photos
3 videos
41 files
524 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
የፍቅር ‘ርግቦች
ክፍል አስራ አንድ ፦ ብቸኛ ቅርንጫፍ
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር

በማግስቱ ቅዳሜ በዓል ነበር። ሳሌምና ዳሪክ አልተገናኙም። ሳሌም መጠበቅ ነበረባት። ሰባት ቀናት ፦ እስከሚቀጥለው ቅዳሜ ድረስ። በ‘ነዚህ ሰባት ቀናት በሳሌም ልብ ውስጥ በቅሎ ያደገው ፍቅር ሌላ ፍሬ አፈራ ፦ ናፍቆት። ፍቅር መናፈቅ የሚባል ልጁን ወለደ፦ ሳሌም ልብ ውስጥ። ሳሌም ዳሪክን አብዝታ፣ ከውስጧ ናፈቀችው። ት/ቤት ቀኑን ፍዝዝ ብላ ታሳልፋለች፦ የምታስበው ዳሪክን ነው። ቤት ስትመጣ፣ ሰዎች ሲያወሯት ንጭንጭ ትላለች። የምትፈልገው ዝምታ ነው። በጸጥታው ውስጥ ደሞ የምታስበው አንድ ነገር ነው፦  ዳሪክን።  ሌሊት ጥቂት ሰዐታት ትተኛና ትነቃለች። የመኝታ ቤቷን ኮርኒስ እያየች ማሰቧን ትቀጥላለች፦ ስለ ዳሪክ። ዳሪክ በሳቁ፣ ዳሪክ በጨዋታው፣ ዳሪክ በፍቅርት ጥሪው፣ ዳሪክ በትህትናው፣ ዳሪክ በመልካምነቱ …. በነዚህ ሁሉ የናፍቆት ሃሳቦች መናፈቅን ናፈቃት።

   አይደርስ የለ የሚገናኙበት ቅዳሜ ደረሰ። ሳሌም ማልዳ ተነሳች። የተነሳችው የቤት ስራ ልትሰራ አይደለም። ወይም የምታደርገው አስቸኳይ ነገር አልነበራትም። ሳሌም የተነሳቸው ፍቅሯን ዳሪክ ከልቧ ስለናፈቀችው ነው። ዳሪክን የምታይበትን ሰዐት ጎትታ የምታመጣው ይመስል ነው፦ በጠዋት መነሳቷ። ደቂቃውን ስትቆጥር፣ የምትለብሰውን አንዱን አንስታ አንዱን ስትጥል፣ እንዲሁ ደስ ደስ፣ ዝም ብሎ ሳቅ ሳቅ ሲላት ሰዐቱ ደርሶ ወደ ቸርች ሄደች።

ዳሪክ ጊታር፣ ሳሌም ኪ -ቦርድ የሚለማመዱበት ክፍል ውስጥ ገብታ ተቀመጠች። እርጋታዋ ጠፍቶ፣ ልቧ በፍጥነት ይመታ ጀመር። ጣቶቿ ዝም ብለው በኪ-ቦርዱ ላይ እየሄዱ ቅኝት የሌለው መዝሙር ይጫወታሉ። ሃሳቧ የለም። ልቧ ውጪ ነው። አይኗ በሩ ላይ ነው። ዳሪክን ለማየት እጅግ በጣም ናፍቃለች።  ልታየው ከልክ በላይ ጏጉታለች።

ልቧ አብዝቶ እየናፈቀው አስራ አምስት ደቂቃ አለፈ፦ ዳሪክ አልመጣም።

አይኖቿ በር በሩን እያዩ ግማሽ ሰዐት አለፈ፦ ዳሪክ የለም።

አንድ ሰዐት ፦ ዳሪክን የውሃ ሽታ ሆነ።

ሁለት ሰዐታት፦ ዳሪክ ብቅም አላለ።

ሶስት …አራት… ሰዐታት ዳሪክ ምናልባትም ለመጀመሪያ ጊዜ ያን ቅዳሜ አልመጣም። ዳሪክ ቀረ።

ወደ ቤት ስትሄድ ሳሌም ሌላ ሳሌም ነበረች። ክፍት ብሏታል። ስብር ብላለች። ማልቀስ ፈልጋለች። አዝናለች።

ቤት ደርሳ አልጋዋ ላይ ተዘረጋች። ማሰብ ጀመረች። አእምሮዋ ጦር ሜዳ ሆነ፦የሃሳቦች ‘ርስ ‘በርስ ውጊያ የሚካሄድበት የጦር አውድማ። መጀመሪያ ንዴትና እልህ መጣባት። እንደወደድኩት አውቆ ነው። እንዳፈቀርኩት ገብቶት ነው። አሳየዋለሁ። ልክ አስገባዋለሁ። በእልህ ዛተች።

ሰዐታት ሲያልፉ…ንዴቱ አለፍ ሲልላት ደሞ ረጋ ያለው ልቧ ሃሳቡን ያጫውታት ጀመር። ዳሪክ በፍቅርሽ ላይ የሚተብት ልጅ አይደለም። የፍቅርሽን አንድ የፈተና ጥያቄ (ለምንድን ነው የምትወደኝ?) ብለሽ ስትጠይቂው በከፍተኛ ብቃት ያለፈ ልጅ ነው።እንደወደደሽ፣ እንዳፈቀረሽ በትህትና የነገረሽ ልጅ ነው። '...የምወድሽ...' ብሎ አቆላምጦ የሚጠራሽ ዳሪክ ነው። መውደድሽን እንዴት ያውቃል? እንዳፈቀረሽው በምን ይረዳል? አልነገርሽውም እኮ። እንዳፈቀረሽ እንጂ እንዳፈቀርሽው አያውቅ? እንዴት ብሎ ይተብታል?

ሰክና ስታስበው ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ አልነበራትም።

ታዲያ ለምን ቀረ? ..ቆይታ ደሞ ሌላ ሃሳብ መጣባት። የመጨረሻው ቀን ስለ ተጣላሁት ነው። ስላኮረፍኩት አዝኖ ነው። ሳሌም ራሷን መውቀስ ጀመረች። ምን አደረገኝ?  ምን አይነት መጥፎ ልጅ ነኝ?....እሱ እኔን ለማስደሰት፣ ከክፉ ለመመለስ ጥረት ባደረገና ዋጋ በከፈለ ልናደድበት አይገባኝም ነበር። ሳሌም ከራሷ ጋር እያወራች፣ ያጠፋች መሆኗን ውስጧ እያመነ ሲመጣ ዳሪክን ይቅርታ ለመጠየቅ ከልቧ ፈለገች። እንዴት አግኝቼው ነው ይቅርታ የምጠይቀው ብላ ስታስብ ደግሞ ሌላ ትልቅ ፈተና ሆነ። ሳሌም ዳሪክን ብዙ አታውቀውም።  በአንድ የሴልፎን ክሊክ የምታገኘው፣ የምትደውልለት የት/ቤት ጓደኛዋ አይደለም። ስልክ የለውም። ቤቱ የት እንደሆነ መረጃ የላትም። ሌላው ቢቀር የአባቱን ስም እንኳን አታውቀውም። እስከ ዛሬ ዳሪክን የምታገኘው እሱ ራሱ ስለሚመጣ ነው። እሱ እሷ ያለችበትን ቤትና የምትገኝበትን ቦታ ያውቃል እንጂ እሷ አታውቅም።  ከፈለገ ዳሪክ መጥፋት ይችላል። '...ከዛሬ ጀምሮ አልመጣም፣ሳሌምን ማየት አልፈልግም..' ብሎ ከወሰነ ሳሌም ዳሪክን ለማግኘት የምትችልበት መንገድ አልታይ አላት። ስታስበው ሃሳቡ ራሱ ፍርሃትን ለቀቀባት። በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ልቧን ያሸነፈው ወጣት፣ ያፈቀረችው ልጅ እልም ብሎ ሲጠፋባት ማሰቡ ራሱ በጣም አስፈራት። ….ናፍቆቱ በዚህ በኩል…ዳሪክን የማጣት ፍርሃት በሌላ በኩል…ሁለት ሃሳቦች ሲያንገላቷት፣ ከዚህ ወደ ዚያ ሲቀባበሏት የሌሊቱ አብዛኛው ክፍል አለፈ። በሃሳቦቹ ማዕበል ውስጥ አንድ ሃሳብ ለልቧ ሹክ አላት። ዳሪክ ያለበት ድረስ ሄዳ ማግኘት።

“…ማግኘት አለብኝ!..  ዳሪክን ማየት አለብኝ!...” ለራሷ በራሷ አወራች። ስለ ዳሪክ የምታውቀው አንድ ነገር ሰፈሩን ነው። ነገ ሰፈሩ ድረስ ሄጄ አገኘዋለሁ። አየዋለሁ። ወሰነች። ከወሰነች ቡሃላ ተረጋግታ ተኛች። እንቅልፍ ወሰዳት።

በማግስቱ ከቸርች በፊት ሳሌም እግሯ ወደ መራት፣….ወሎ ሰፈር ከዳሪክ ከሰማችው …የዳሪክ ሰፈር ነው ብላ በምታምንበት መንገድ መጓዝ ጀመረች። ወደ ውስጥ ጥቂት እንደሄደች የማታውቀው ሰፈር ሁኔታው፣ የምታያቸው ልጆች፣ የሚለክፏት መጨመራቸው ትንሽ ቢያስፈራትም ዝም ብላ መሄዷን ቀጠለች…ወደፊት። በአንድ ሱቅ ጋር ሰብስብ ብለው በተሰበሰቡ ወጣቶች አጠገብ ስታልፍ “…ቆንጆ…” አንዱ ጠራት።

ሳሌም ሌላ ለካፊ ነው ብላ ልታልፍ ስትል  “…የአቡቲ ጀለስ፣ ቺኳ…”

ሳሌም የዳሪክን የሰፈር ስም ስትሰማ ቆመችና ዞር ብላ የሚጠራትን ልጅ ስታይ እየሮጠ ወደሷ መጣ።

“…አረፍሽኝ እሙ?...”

“…ምን? ምን አልከኝ?...”

“…አወቅሽኝ ማለቴ ነው?...”

ሳሌም አይታው አታውቅም። ወይም ረስታዋለች። “…ይቅርታ አላወቅኩህም…”

“…ቦዲ ነኝ እኮ… አንድ ቀን ምሽት ላይ…መንገድ ላይ…..”

ሳሌም ትዝ ሲላት በድንጋጤ ወደ ኋላ አፈገፈገች።

“..አይዞሽ ቀሽት አልነካሽም። የአቡቲ ጀለስ ስልሆንሽ እዚ ሰፈር ማንም የሚነካሽ የለም።ያኔም ስላላወቅን ነው። እኛ የሰፈር ልጆች አንነካም። ሌላውንም ቢሆን ሲቸግረን ነው እንጂ የምናስፈራራው.... ግን ማንንም አንጎዳም።…” ቦዲ ልስልስ ብሎ

ሳሌም በጥቂቱ ተረጋግታ ስትሰማው ቦዲ ቀጠለ “…ለማንኛውም ምን ፈለገሽ መሀል ወሎ ሰፈር ከች አልሽ? አቡቲን ፈልገሽው ነው?....”

ሳሌም የጥያቄዋ መልስ ፊት ለፊቷ ሲመጣ ድንጋጤው ለቀቃትና “…አዎ ዳሪክን በጣም ላገኘው ፈልጌ ነው። ቤቱን ታውቀዋለህ?...”

“…ታውቀዋለህ?...” ፈገግ አለ።ቦዲ ፈገግ ሲል ሸራፋ ጥርሱ ወጣ። “…ጎረቤት ነን እኮ  አቡቲ ማለት …”

“…ታሳየኛለህ?.. ሳሌም አቋረጠችው

“…ሰፈራችን እኮ ታች ነው…ትንሽ ይርቃል። ... አሁን እንኳን የጀበና ልል ነበር…”  ቦዲ እየተጠራጠረ

“…በጌታ? ባ'ክህን አሳየኝ?...” ሳሌም በልመና አይን

ቦዲ ሲያመነታ ሳሌም አጥብቃ ልመናዋን ቀጠለች።

ልመናዋ ሲበረታና ሲያዝን...ቦዲ ወደ ጓደኞቹ ዞረ። “…ጠብቁኝ አንዴ አቡቲ ጋር አድርሺያት መጣሁ።…”

“… እሺ እሙዬ እንሂድ …” ቦዲ መሄድ ሲጀምር ሳሌም ተከተለችው።

እየሄዱ ቦዲ ወሬ ጀመረ። ሳሌም ዙሪያዋን እያየች ትሰማለች …በግማሽ ልብ።
👍435
“…አቡቲ ሰፈሩ በሙሉ የሚያከብረው ልጅ ነው።…ሜጋ… ማለቴ ጎበዝ ተማሪ ነው…” በአንድ መስጊድ አጠገብ እያለፉ

“…ከአንድ እስከ አሰረኛ ክፍል አንደኛ እየገጨ እየተሸለመ አስረኛ ፈተናን ሰቅሎ ያለፈ ልጅ ነው…” በቤቶች መሃል በተሰጡ ልብሶች ስር ሲሄዱ።

“…በቃ ምን ልበልሽ የሰፈራችን ተስፋ ነው። ይሰራል፣ ይማራል፣ ልጆችን ሰብስቦ ያስጠናል። የኔ ትንሽ ወንድም ራሱ የመጨረሻ ጎበዝ ተማሪ ሆኗል…አቡቲ እያስጠናው።…” ተጠባብቀው በተሰሩ ትንናሽ ቤቶች ባለ ቀጭን መንገድ ከፊትና ከኋላ እየሄዱ

ጎማ ደርድረው ላዩ ባለ ፕላስቲክ ማጠቢያ ልብስ በሚያጥቡ ሴቶች መሃል፣ ኳስ በሚራገጡ ትናንሽ ህጽናትን ከፍለው፣ ቁልቁለት ሲወረዱ፣  ቦዲ ከሚያወራው ግማሹን እንኳን የሰማችው አትመስልም፦ ሳሌም። ዙሪያውን፣ ሰፈሩን የምታልፍበትን መንገድ፣ ሰውን እያየች ነበር።

“…ሰማሽኝ እሙ?...” ቦዲ እየጠየቃት ነበር

“….ምን አልከኝ?... ይቅርታ አልሰማሁም…”

“….አቡቲን ልትጠይቂው ነው አይደል የመጣሽው? ሰለ ታመመ?...”

“…ምን?....” ሳሌም ባለችበት በድንጋጤ ቆመች “…ዳሪክ ታሟል። መቼ ነው የታመመው? ምን ሆኖ ነው?....”

“…አንድ ሳምንት ነገር ሆኖታል። አሞት ተኝቷል ሲሉ ነው የሰማሁት። እኔ ራሴ አልጠየኩትም። ያወቅሽ መስሎኝ ነው እሙ…”

ሳሌም ድንጋጤዋ አለፍ ሲልላት ጉዟቸውን ቀጠሉ። አሁን ገና ለምን ዳሪክ ትላንት እንደቀረ ገባት።

በዝምታ...መጨረሻ ላይ አንዲት ትንሽ ያዘዘመች የአፈር ቤት ጋር ደርሰው፣ ደገፍ ተደርጎ የተዘጋን የሚንፏቀቅ፣ በጣውላ ተገጣጥሞ የተሰራን በር ከፍተው እስኪገቡ ድረስ አልተነጋገሩም።

ሳሌም እዛ የተጎሳቆለ ቤት ውስጥ ስትገባ አይኗ ያረፈው በቀኝ በኩል ግድግዳው ጥግ መሬት የተነጠፈ ፍራሽ ላይ የተኛው ዳሪክ ነው። አጠገቡ ሄዳ በርከክ አለችና "...ዳሪክ..."ጠራችው

ዳሪክ በሩ መከፈቱን ሲያይ ቀና ብሎ የገባውን ሰው ለማየት እየተጋለ ነው። ፊቱ ጭው ከማለቱ በሙሉ በላብ ተጠምቋል። እንደገናም ሰውነቱ ይንቀጠቀጣል። ለመነሳት ራሱ አቅም አጥቶ፣ መሬቱን ተደግፎ፣ ጥርሱን ነክሶ ሲታገል ቦዲ ደግፈው። ፍርሹ ላይ ሆኖ፣ በግማሽ የፈራረሰውን ግድግዳው ተደግፎ ቁጭ አለና ሳሌምን ያያት ጀመር።

“…የምወድሽ?...” እጁን ዘረጋ።

እጁን ጨበጠችው። ሰውነቱ እሳት ነው። “..አቤት..”

“…ይቅርታ ዛሬ ሰለቀረሁ። ለመምጣት ሞከርኩ ዛ…ሬ….” ዳሪክ ቃላት የጠፉበት ይመስል ዙሪያውን ያይ ጀመር።

ዳሪክ ትላንት ማለቱ ነው። ቀኑ ተምታቶበታል። ትኩሳቱ ከፍ ብሎ በመንቃትና ቅዥት አለም ውስጥ ነው።

ሳሌም ነፍሷ ተንሰፈሰፈ። “….ምን ያህል ጊዜ ሆነው እንዲህ ከታመመ?...” ወደ ቦዲ ዞረች

“…እኔ አላውቅም። ሳምንት ይሆነዋል። የሰፈር ሰዎች ሲያወሩ ነው የሰማሁት።…”ቦዲ ራሱ የዳሪክ ሁኔታ አስደንግጦታል።

እነሱ ሲያወሩ ዳሪክ በሰመመን ቁጭ ባለበት እንደ ማሸለብ አደረገው።ስላልቻለ ፍራሹ ላይ ተመልሶ ተኛ።

….ዳሪክ …ዳሪክ ….ዳሪክ ….” ብትጠራውም አይኑን እየከፈተ መልሶ ከማሸለብ በስተቀር ሊመልስላት አልቻለም።

“…አሞታል። በጣም ታሟል። አሁኑኑ ሃኪም ጋር ልንወስደው ይገባል።….” ሳሌም ነበረች “… ቤተሰቦቹን መጥራት አለብን…”

“…አታርፊም እንዴ? …” ቦዲ ተገርሞ

“…ማለቴ አታውቂም እንዴ?...”ሳሌም ስታፈጥበት ጥያቄውን አስተካከለ።

“…ምኑን?....”

ለሰከንዶች ዝም ብሎ ተመለከታት። “…የአቡቲ ወላጆች ሞተዋል። ቆይተዋል።…”

ሳሌም ሌላ ድንጋጤ ሰውነቷን ወረረው። “…አላወቅኩም …ወንድም?... እህት… የለውም?...” ጠየቀች።

“…የለውም…” ቦዲ በሀዘኔታ “…አንድ ራሱ ብቻውን ነው የሚኖረው…”

ዝም ብሎ የሚስቀው ዳሪክ፣ ሁሌም ደስታ ፊቱ ላይ የሚፈስበት ዳሪክ ብቸኛ ነው። ማንም የለውም። ብቻውን እዚች ትንሽ ቤት ውስጥ ይኖራል።

ሳሌም ወደ ዳሪክ እያየች እንባዋ በአይኗ ሞላ።

እንባ በሞላው አይኗ ቀና ብላ ቦዲን አየችው “…ታክሲ ጥራልኝ…”  ከቦርሳዋ ውስጥ ለማንኛውም ብላ ከምትይዘው ብር አወጣችና ሰጠችው “…ሃኪም ጋር አሁኑኑ እንወስደዋለን።…”

ቦዲ ተስማምቶ ተጣድፎ ወጣ።

  ታክሲው እስኪመጣ ድረስ ሳሌም ዳሪክ ያለበትን ቤት ዙሪያ ማየት ጀምረች። መሬቱ ሙሉ ለሙሉ አፈር ነው። ዳሪክ ከተኛበት በስተቀኝ በኩል ሁለት ወንበሮችና አንድ ጠረጴዛ አለ፦ ሁሉም ያረጁ ናቸው። በጠረጴዛው ላይና ዙሪያውን የተለያዩ የትምህርትና ሌሎች መጻህፍቶች ተደርድረዋል። ግድግዳው ላይ ዳሪክ እየሳቀ ከወላጆቹ ጋር በልጅነቱ የተነሳው ፎቶ ባንድ በኩል አለ። በሌላ በኩል የሁለት መሃከለኛ እድሜ ላይ የሚገኙ ፈረንጆች ተቃቅፈው የተነሱት አነስተኛ ፎቶ ይታያል። የቤቱ አንድ ጥግ በያቅጣጫው በተቦጫጨቀ መጋረጃ ተከልሏል። ከመጋረጃው ጀርባ ያረጀ መሶብ ተቀምጦ ዙሪያውን በተለያዩ የማብሰያ እቃዎች ታጅቧል። የጠቆረው ጣሪያ ደግፎ በያዙት እንጨቶች ላይ የተንጠለጠለ ፍሎረሰንት በኤሌክትሪክ ገመድ ከማብሪያና ማጥፊያው ጋር ተያይዞ ይታያል። በእርጅና የተበሳሳው ግድግዳ በተለያዩ ጋዤጦች ተለጣጥፏል። ይህ የዳሪክ ቤት ነው። ዳሪክ ብቻውን የሚኖርበት ትንሽዬ ክፍል።

  ታክሲው መጥቶ ቦዲና ጓደኞቹ ደግፈው ሲጭኑት ራሱ ዳሪክ ከትኩሳቱ፣ አቅም ከማጣቱ  የተነሳ በድካምና በ’ንቅልፍ መሃል ነበር። በየመሃሉ ብቻ ከንቅልፉ ወጣ እያለና ሳሌም እያየ ‘…የምወድሽ…’ ይላል።

    ሃኪም ቤት ደርሶ ሲታከም ዳሪክ የያዘው ቀላል ኢንፌክሽን ነው። ነገር ግን ህክምና በጊዜ ባለማግኘቱ ብቻ ደሙ ድረስ ተበክሎ ነበር። ጸረ-ባክቴሪያ መድሃኒቶችና በተለምዶ ጉልኮስ የሚባለው ፈሳሽ ሲሰጠው ትኩሳቱ እየቀነሰ ማምሻውን ደህና መሆን ጀመረ።

ዳሪክ ብዙ ድካም ላይ ስለነበረ  እዛውም ማደር ስለነበረበት…ሳሌም አምሽታ ወደ ቤት ሄደች።

በማግስቱ ከት/ቤት መልስ ልታየው ስትሄድ ዳሪክ ተመልሶ ዳሪክን ሆኗል። ሳቅ በሳቅ ሆኖ ጠበቃት። እንደለመደው…እንደ ሁልጊዜው እየቀለደ፣ እያሾፈ ሁለቱም ሲስቁ አመሹ።

ሳሌም ወደ ቤት ልትሄድ አካባቢ አጠገቡ ቁጭ ብላ “..ዲ…”

“…አቤት የምወድሽ…”

“…ብቻህን ነው ግን የምትኖረው? ቤትህ ውስጥ?...”

ዳሪክ ትክ ብሎ አያትና “…አዎ ብቻዬን ነው።…”

"..ወላጆችህ እንደሞቱ ነገሩኝ። ወንድም፣ እህት ዘመድ ምናምን የለህም?...”

ዳሪክ መልስ ሳይመልስ ዝም ብሎ ሲያያት ቆየ። በመቀጠልም ራሱን ግራና ቀኝ አወዛወዘና ወደ ግድግዳው ዞረ። 

ሳሌም ከተቀመጠችበት ተንጠራርታ ስታየው እንባው አይኑ ውስጥ ሞልቷል።

“…ይቅርታ!.. በቃ ሌላ ወሬ እናውራ እሺ…. ይቅርብን ይሄን ነገር ማውራት….” ሳሌም በጸጸት

“…ችግር የለውም የምወድሽ ላንቺ የውስጤን ማውራት እፈልጋለሁ።….” ዳሪክ እንባውን ጠራረገና ማውራት ጀመረ።  

“….የምወድሽ…. አዎ እኔ ብቻዬን ነኝ። ወንድም፣ እህት የለኝም። ወላጆቼ ሞተዋል። የመጡት ከገጠር ነው። የመጡበትን አካባቢውን እንኳን አላውቀውም። ያስተዋወቁኝ አንድ የማውቀው ዘመድ የለም። ካያቴ ስም በላይ አላውቅም። ተከታትለው ሲሞቱም የነገሩኝ ነገር የለም። ከነሱ የቀረልኝ ሁለት ነገር ነው፦ አቡቲና ዳሪክ። አቡት እናቴ የምትጠራኝ ስም ነው። ዳሪክ ደሞ አባቴ። በቃ የቀሩኝ እነዚህ ስሞች ናቸው።ብቻዬን ነኝ። ብቻዬን እኖራለሁ። ብቻዬን ህይወትን እታገላለሁ።….”
👍337👎1
ዳሪክ ጥቂት ዝም አለና ቀጠለ “…አንዳንድ ጊዜ ሳስበው በቤተሰቤ የዘር ግንድ ላይ የቀረሁ የመጨረሻው ቅርንጫፍ የሆንኩ ይመስለኛል። ታውቂያለሽ የሚሰማኝ እንደዛ ነው…ሁሉም ቅርንጫፎች አልቀው እኔ ብቻ የቀረሁ ያህል ነው። ሁሉም ሄደው፣ አልቀው፣ አልፈው …ግንዱ ላይ የቀረሁ አንድ ብቸኛ ቅርንጫፍ ዝም ብዬ ለብቻዬ የምወዛወዝ  ….ያ እኔ ነኝ። …እና ለብቻ ስትሆኚ  ህይወት፣ መኖር አንዳንዴ ያስፈራል። በቃ…” ዳሪክ እንደገና እንባው ሲመጣበት እየታገለ ላለማልቀስ ጥርሱን ነከሰ።

የዳሪክን እንባ የሞሉ አይኖች ስታይ ሳሌም አይን ውስጥም እንባ ሞላ። ከልቧ አዘነችለት። ስፍስፍ አለች።

ሳሌም እጁን ያዘችው “..ዲ…”

“…አቤት የምወድሽ…” ታግሎ እንባውን ዋጠ።

“…ካሁን ቡሃላ  ብቻህን አይደለህም። መቼም ብቻህን አትሆንም።…”

“…አውቃለሁ…”

እንባ በሞሉት አይኖቹ የሷን ተመሳሳይ አይኖች ማየት ጀመረ። ታየዋለች፣ ያያታል።

ሳሌም እንደምትወደው፣ እንደምታፈቅረው ልትነገረው በጣም ፈለገች። ሁሌም ከጎንህ ነኝ፣ እህትህ፣ ምርጥ ጓደኛህ፣ ወንድምህ፣ እናትህ፣ አባትህ፣ ፍቅርህ እንድሆን ….እሻለሁ። ጌታ እኔን ሰጥቶሃል ልትለው ተዘጋጀች፦ ከልቧ።

“…. የምወድሽ…” ዳሪክ ጠራት

“….ወዬ…..” ከሃሳቧ ባነነች።

ዳሪክ ሌላ በልብ ቅርጽ የተጣጠፈ ወረቀት አወጣ “…ዛሬ ዝም ብዬ የጻፍኩልሽ ነው።…”

“…እሺ…”

ሳሌም ተጣድፋ ልትከፍተው ስትል እጇን ያዛት። “….አሁን አይደለም እቤት ስትደርሺ…”

ሳሌም እንደገና  ባይኖቿ ስታየው ዳሪክም መልሶ ያያት ጀመር። ዝም ብለው ….መተያየት… መተያየት። ሳሌም ገብቷታል፦ ይህ ልጅ እንዳፈቀራት። ዳሪክም ተረድቷል፦ ሳሌም እንደወደደችው።

በመተያያት ማውራት፣ በመተያየት መጫወት፣ በመተያየት መግባባት የጀመሩት የዛን ቀን ነው።
*
*
ይቀጥላል
ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍4017
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል አስራ ሁለት፦ ለምለም ህልም
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር

የምወድሽ….
ትላንትና ሌሊት - ባ'ይኖቼ ልቦች- አይንሽን እያሰብኩ
ስሱን ፈገግታሽን - ለነፍሴ ‘የመገብኩ -
እንቅልፌን አሸለብኩ !
ተኝቼም -  የሚያለመልምን -
የፍቅር ህልም አለምኩ!

በህልሜ ….
በእግዜር ዙፋን ፊት የቆምኩ ይመስለኛል
ጌታም “…ምንን ላድርግልህ?
          ምንስ ይሁንልህ ?...  “ ሲል  ይጠይቀኛል

እኔም እንዲህ እመልሳለሁ፦
   “…ጌታ ሆይ ፦ በጄ ያለው ወረቀት- ይቺ ትንሽ ብዕር
ለመግለጽ አልቻለም- ውስጤ ያለን ፍቅር
'ባክህን ፈደላትን ስጠኝ- እውቀትን አወሰኝ- ከጥበብህ ባህር? `

ጌታ ፈገግ ብሎ፦
        “…የፍጥረትን መግዣ- ሰማያዊ በትር
        እንካ ከ‘ኔ ተዋስ - ለአንድ ቀን ተበደር
        የምትፈልገውን - ጻፍ - አትም ስለ ፍቅር..."

እኔም፦
ከእግዜር መንበር ፊት - መጥቼ ወደ ምድር
እንዲህ እጽፋለሁ- እንዲህ እፈጥራለሁ- በተዋስኩት በትር

1……
ስጀምር…
ቀላያት አጠገብ - አሸዋው ዳርቻ - የተዋበ አምባ
‘ንዳንቺ ላለ ልዕልት - ሊሆን የሚገባ
በቅጽበተ -አይን … ያንን ሰርቼልሽ፣
አዎ…ያንን ፈጥሬልሽ
ከ ‘ንቅልፍሽ ሳትነቂ - ኮሽታ ሳትሰሚ - ሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽ
(((((እቅፍ ….እቅፍቅፍፍፍ))))))) 
አድርጌ ባየር ላይ ሳፍፌሽ …  ወስጄሽ ወስጄሽ
ያማረ እልፍኝ ውስጥ - ማረፍን ታርፊያለሽ
   (…በጀርባሽ  ‘ርፍ ብለሽ
      ተካንፈው እጆችሽ
      በስላም ንቅልፍ ውስጥ -ተከድነው አይኖችሽ
      ሳ ….  ይ  … ሽ
      አቤት ስታምሪ !!!!! 
  የተኛችውን ውብ ታስታውሺኛለሽ!!!!…)

2.….
ሲቀጥል….
ከከባዱ ‘ንቅልፍ -ድንገት ብንን በለሽ -አሻግረሽ ስታይ -በልፍኝሽ መስኮት
ኩልል ባለው ሰርክ  - በሲያራ ድምቀት- በከዋክብቶች ውበት
ጠፈር ላይ …ህዋው ላይ …. 
እንዲህ እልሻለሁ 
እንዲህ እጽፍልሻለሁ…
“….የምወድሽ …እኔ አፈቅርሻለሁ…”

3….
ሲሰልስ…
ጨለማው አልፎበቱ-
እንቅልፍን ጨርሰሽ -ስትወጪ ከሌቱ
    (….እንዴ የት ነው ያለሁት ብለሽ??????....)
የተዋቡ እጆችሽ - የአንባሽን መስኮት - በሮቹን ሲከፍቱ
ሰማዩ ላይ…
በቀሰተ ደመና ኅብረ ቀለማት ፦ “…እኔ እወድሻለሁ ውዴ - የምወድሽ…”
የሚል…በፈጣሪ በትር - ከኔ የተጻፈ - መልክት ታያለሽ  
     (….ዋውውውው …ወይኔ ጉዴ!!! ብለሽ…
         ተገርመሽ …ተገርመሽ
         ተከፍተው ባድናቆት…እነዛ አይኖችሽ
           …ሳያልቅ…መደመምሽ…)

4….
ካ’ንባሽ ሰገነት - ሰማያዊውን ውቂያኖስ - ወደ ታች ስታይ
አዎ… ውሃው… ላይ
ያማሩ ደሴቶች - በፊደል ቅርጽ ሆነው -
ተኝተው -  ተንሳፈው
“…ውዴ የምወድሽ ደግሜ ደግሜ እኔ ወድሻለሁ
        እኔ አፈቅርሻለሁ፣ እሳሳልሻለሁ!” ሚል መልዕክት ይዘው
              ………..ትመለከቻለሽ!

5….
ደሞ ቀና ስትይ
አየሩ ላይ
አእዋፍና ርግቦች - ከፍ ብለው - ባንድ ላይ ሲበሩ
ቅርጽ ሲያበጁ - መልዕክትን ሲጽፉ - ቃላት እየሰሩ
እንዲህ እያሉ፦
     “…የምወድሽ ውዴ ወድጄሽ አፍቅሬሽ
           አሁንም ወድጄሽ
              ወደጄሽ ወድጄሽ
                 አይበቃኝ አፍቅሬሽ….”
አዎ ይህን...ፍዝዝ ብለሽ…ቆመሽ….በደስታ ታያለሽ!

የምወድሽ፦
ጠፈር ብራና ሆኖ - “…የምወድሽ…” ብዬ - ሳቀልመው በከዋክብት…
ሰማይ ገጾች ሆኖ - “…የምወድሽ…”ብዬ - ፍቅሬን ሳትምበት…
አየርና ውሃው  - ነጭ ወረቀት ሆኖ - “…ወድጄሽ!... ወድጄሽ!...”  ብዬ ስጽፍበት…
ሌሊቱ ነጋና-  ከ‘ንቅልፌ ባነንኩኝ
ከለምለሙ ህልሜ - በድንገት ወጣሁኝ!

   ይህ ከዳሪክ ለሳሌም የተጻፈው ሁለተኛ የፍቅር ጹህፍ ነው። ሳሌም ይህን ግጥም አነበበችው። ተቀምጣ አነበበችው። አልጋዋ ላይ ጋደም ብላ አነበበችው። ፈገግ ብላ አነበበችው። ኮስተር ብላ አነበበችው። ግጥሙን አስቀምጣ ትንሽ አስባ …እንደገና ደግሞ መልሳ አነበበችው። ጠዋት ተነስታ አነበበችው። ወደ ት/ ቤት ስትሄድ አነበበችው። ት/ቤት ሆና ደብቃ እያወጣች አነበበችው። ከት/ቤት ስትመለስ አነበበችው። የዳሪክ ልቅም ያሉ የ‘ጅ ጹህፍ ፊደላት ቅርጾች ልቧ ውስጥ እስኪሳል ድረስ፣ የፊደላቱ አቀማመጥ አእምሮዋ ውስጥ 'ስኪታተም  ድረስ አነበበችው።

ስታነበው፣ ስታነበው፣ ስታነበው …. ቃላቶቹ፣ መልዕክቱ ..በውስጧ በቅሎ ላደገው የፍቅር ችግኝ ምግብ ሆነ። የፍቅሯ ችግኝ ማደግ ጀመረ። ግንዱ ጠነከረ። የሚያምሩ ለምለም ቅርጫፎች ያሉት ከጥላቻ ሃሩር የሚያሳርፍ ውብ የፍቅር ዛፍ ሆነ። ሳሌም ከዛፉ ስር በጀርባዋ ተኛች። አይኗን ከደነች። በረጅሙ ተነፈሰች…፦ እርፍፍፍፍፍፍፍ …እፎይ …ደስ ሲል። ህይወቷ ሁሉ በፍቅር ምንጭ ዳር ተተክሎ ፣ ከምንጩ እየጠጣ የሚያድግ ለምለም ህያው ህይወት መሰላት። ለምለም ህይወት፦ ህልም የሚመስል ግን ደሞ በእውን አለም የሚኖሩት... ህያው ለምለም ህልም።

… ሳሌም ከት/ቤት መልስ ዳሪክን ስታገኘው ከፊት ለፊት ሄዳ ቁጭ አለችና ዝም ብላ ታየው፣ ትመለከተው ጀመር።

“…የምወድሽ ምነው?....”

ሳሌም በረጅሙ ተነፈስችና ነገረችው።

እንዲህ አለችው “…ለኔም ሊገባኝ በማይችል ሁኔታ፣ እጅግ በሚያስፈራ ሁኔታ ፣  ግን ደሞ እጅግ በጣም በጣም ደስ በሚል ሁኔታ ወድጄሃለሁ። አፍቅሬሃለሁ።…”

ዳሪክ ቀስ ብሎ እጇን ያዘ  “….የምወድሽ…”  አቆመ። ቃላትን የሚፈልግ ይመስል

“…ወዬ …”

ከዛ ቀጠለ" ... እኔም ….በአእምሮ ሊታሰብ በማይችል ሁኔታ በየትኛውም ቀመር ሊፈታና ሊተነተን በማይችል ሁኔታ ግን ደሞ በጣም ደስ ደስ በሚል ሁኔታ  ወድጄሻለሁ።አፍቅሬሻለሁ።….”

ተያዩ፣  ተያዩ   …ያለማቋረጥ!!!  

“….የምወድሽ ትለኝ የለ?...” ሳሌም አይን አይኑን እያየችው

“..አዎ የምወድሽ ሁሌም… ‘የምወድሽ’…. እልሻልሁ። 'ስትንፋሴ 'ስኪቆም ድረስ። መሽቶ ሲነጋ፣ ክረምት በጋ ሲቀያየር፣ ሳምንታት ሲያልፉ፣ በየሰዐቱ፣ በየደቂቃው፣ በቁርጥራጭ ሰከንዶች ሁሉ…ፈቅጄ፣ ከልቤ ሁሌም  'የምወድሽ' እልሻልሁ…”

ሳሌም ፈገግ አለች፦በስሱ “…እኔ ደሞ ከዛሬ ጀምሮ ማን እንደምልህ ታውቃለህ?...”

“…ማን ትይኛለሽ የምወድሽ?...”

ሳሌም ፍዝዝ ብላ እያየችው “…የኔ መልዐክ… ነው የምልህ … የኔ መልዐክ!...”

ዳሪክ የሚለው አጥቶ፣ በመገረም እያያት ሳሌም ቀጠለች “…መጀመሪያ ከተገናኘን ጀምሮ የሆነ በክፉና በኔ መሃል የቆምክ፣ ለኔ በሁሉም ነገር ከፊት የምትወጣልኝ አፍቃሪዬ፣ ስጋ የለበሰ መልዐኬ ነህ ብዬ ነው የማስበው።…የኔ መልዐክ ነህ!...”

ዳሪክ የሳሌምን እጆች ጥብቅ አድርጎ ያዘ። “…እንዳልሽው ፣ እንደጠራሽኝ እንዲሁ እሆንልሻልሁ የምወድሽ። ደስታሽን አበዛዋለሁ፣ ሃዘንሽን ደሞ እቀንሳለሁ ...የምወድሽ። በከፍታሽ እደሰታለሁ፣ ዝቅ ስትይ ደሞ ወደ ላይ ትወጪ ዘንድ አግዝሻልሁ ...የምወድሽ። ሳቅሽን በብዙ ሳቆች መንዝሬ 'መልስልሻልሁ፣ ሲከፋሽ ደሞ '..አይዞሽ የምወድሽ!..'እልሻለሁ የምወድሽ።  ሞት ቢመጣ እንኳን በደስታ ባንቺና በሞት መካከል እቆማለሁ የምወድሽ።….”

ዝም ብለው መተያየታቸውን ቀጠሉ፦ ፍቅራቸው በዚ አለም ቋንቋና ሊገለጽ የሚከብድ በእውነታው አለም የሌለ የሆን ልዕል ተፈጥሮዊ ህልም ይመስል ነበር፦ ለምለም ህልም።
👍275🥰1
….እንዲህ ነው የጀመሩት፦ የፍቅር ርግቦች። ንጹህ ልቦች፣ የዋህ ነፍሶች። በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ሁልጊዜ የሚገናኙበት ጊዜና ቦታ ወሰኑ። ቦሌ መስመር ጫፍ ላይ አንድ ጭር ያለች ትንሽ ካፌ ላይ ሁልጊዜ ከምሽቱ አስራ አንድ ሰዐት ላይ።

እዛች ትንሽ ካፌ አንድ ቀን መጡ። ከዛም ያለ ማቋረጥ በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዐት ደጋግመው መጡ።

….እንግዲህ ዳሪክና ሳሌም መጡ፦ ከምሽቱ አስር ሰዐት አካባቢ። ከየት መጡ?እንዴት መጡ? ማንም አያውቅም። መጥተው በካፌው ውስጥ በአንድ ጥግ ባሉት ወንበሮች ላይ ተቀመጡ።

ሳሌም ሻይ አዘዘች።

ዳሪክ ማኪያቶ።

   የፍቅር ወፎች ናቸው ፦ ዳሪክና ሳሌም። የማይለያዩ… በአየር ላይ፣ ከደመናት በላይ ተንሳፈው ማንም በማይደርስበት አየር ክልል የሚበሩ ወፎች። አሁን በአየር ላይ ያሉት እነሱ ብቻ ናቸው። ዙሪያችውን አያዩም። አካባቢውን አይሰሙም። እሱ እሷን ያያል። እሷ እሱን ታያለች። እሱ እሷን ይሰማል። እሷ እሱን ትሰማለች። ካፌው ውስጥ ተስተናጋጅ ቢጣላ (ቢንጫጫ)፣ ብርጭቆ ቢከሰከስ፣ ወንበር ቢሰባበር፣ ማንኪያ ወድቆ ቢንኳኳ (ኳኳኳኳ…ኳኳ...ኳ.ኳ.ኳ.ኳ…ኳ) እያለ  መሬት ለይ ቢሄድ) እነሱ ግን በራሳቸው አለም ውስጥ ናቸው።

  ደሞ የፍቅር ከዋክብቶች ናቸው፦ ዳሪክና ሳሌም። ሰፊ በሆነው የፍቅር ህዋ ውስጥ ከተለያዩ ‘ጋላክሲዎች’… የተገናኙ በራሪ የመዋደድ ከዋክብቶች። ሁለቱም ሲበሩ አንድ ቀን ተገናኙ።  …ተገናኙ …. ተያዩ … መተያየታቸውንም ሊያቆም የሚችል ነገር ጠፋ። እሷ… እሱን … እሱ…. እሷን ብቻ ለማየት የተፈጠሩ ይመስል ይተያያሉ። አሁን በህዋ ውስጥ ያሉት እነሱ ብቻ ናቸው። ሰው ቢሮጥ፣መኪና ቢበር፣ባቡር በድምጹ ቢያንባርቅ፣ የፖሊስ መኪና ሳይረን (ኡኡኡ…ኡኡኡኡኡ..ኡኡኡ….ኡኡ……) እያለ ቢከንፍ አይሰሙም፣ አያዩም።

…የእነሱ አለም ሶስት ማዕዘን ነው።

አንደኛ ጎን፦ ዳሪክ

ሁለተኛ ጎን ፦ ሳሌም

ሶስተኛ ጎን፦ ትንሽ ካፌ

…ደሞ ሌላ ሶስት ማዕዘን ነው።

ካፌው ፦ የፍቅራቸው መቅደስ

ጥግ ያሉት ወንበሮች፦ የፍቅራቸው ቅድስት

ሻይና ማኪያቶ፦ የፍቅራቸው ቅመም ነው

…ደሞ ሌላ ሶስት ማዕዘን ነው።

የዳሪክ አይኖች፦ ሳሌምን ያያሉ

የሳሌም አይኖች፦ ዳሪክን ያያሉ

በዙሪያቸው ያሉ ሁሉ ፦  ደሞ ሁለቱን ያያሉ

   ካፌው ውስጥ አንዳቸው ቀድመው ደርሰው … ከዛ ሲገናኙ ማየት ነው፦ የፍቅር ዋኖሶችን። ሳይገናኙ በፊት ክረምት ነው፦ በሁለቱም ፊት ላይ። ዶፍ ዝናብ የሚዘንብበት፣ በረዶና ጠል የሚወርድበት፣ ቅዝቃዜው ጆሮን የሚቆርጥበት፦ ድቅድቅ ክረምት። ሳይገናኙ ለሁለቱም ጨለማ ሃምሌ ነው። ሲገናኙ ጸሐይ በፊታቸው ላይ ትወጣለች። የፊታቸው ሰማይ ጭጋጉ ይጠፋል። ይጠራል። ሰማያዊ ይሆናል። ሲተያዩ ጸሐይ ነው፦ ብርሃን፣ ደስ የሚል የፍቅር ብርሃን በሁለቱም ፊት ላይ ያለማቋረጥ ይወርዳል።

   የፍቅር ዋኖሶቹ ፍቅር ሲገላለጹ ንጹህ ናቸው። በዚህ “ፍቅር” የሚለው ቃል ትርጉም ሚዛኑ ተንጋዶ በራስ ወዳድነትና በእኔነት በሚገለጽበት አለም ላይ እንዴት እነሱ በታላቅ ንጽህና መዋደዳቸውን አሳዩ? እኔ አንጃ። እኔ አላውቅም።

አንዳንድ ቀን …

ዳሪክ ያወራታል ሳሌምን። ሳሌም ትስቃለች። አይኗ፣ ፊቷ፣ጥርሷ ይስቃል። በሳቋ የሚያምሩት የእጆቿ ጣቶች አብረው የሚደንሱ፣ እግርቿ የሚያጅቡ ይመስላሉ። እንባዋ እስኪፈስ ትስቃለች። ስትስቅ ጸጥ ያለው ፊቷ የበለጠ ይበራል። ጸጥ ያለ ውቂያኖስ ላይ ጸሐይ በማለዳ ብቅ ስትል የምትሰጠውን ውበት ያህል ፊቷ ይውባል፣ ይበራል።
 
ዳሪክ ፈርዶበት ሳቂታ ነው። ሳሌም ስት ስቅ ደግሞ  የዳሪክ ሳቅ ሞልቶ፣ በዝቶ ይትረፈረፋል። መናገር የፈለገውን ነገር መናገር ስኪያቅተው ድረስ ይስቃል፣…. ይስቃል። ከርግቦቹ ንጹህ ፍቅር የሚፈሰው የደስታ ዝናብ  በሳቆቻቸው ድምጽ ተሳፍሮ ካፈው ውስጥ ላለው ሁሉ ይደርሳል። የነሱ ደስታና ሳቅ በዙሪያቸው ላሉ ነፍሶች ሁሉ ፍስ ሃና ደስታ ይሆናል። ሳያውቀው የሰው ሁሉ ልብ ጮቤ ይርግጣል። ፈገግታዎች ከሁሉም ከናፍርት መሃል ብቅ ይላል ፈገግ… ፈገግ…ፈገግ።

አንዳንድ ቀን…

ዝም ይላሉ። በቃ ዝም ብለው ይተያያሉ። ሰው ዝም ብሎ፣ ቃል ሳያወጣ ይነጋገራል? አዎ። ዳሪክ የሳሌም አይን፣ ሳሌም ደሞ የዳሪክን አይን በስስት ይመለከታሉ። ያያታል፣ ያያታል ደሞ አሁንም ያያታል። አይኗን አልፎ፣ ውስጧን ሰርስሮ፣ በዐጥንቶቿና በጅማቶቿ ላይ ተንሸራቶ፣ በልቧ ትርታዎች ላይ ተሰፈንጠሮ ፦ አዎ ነፍሷ ላይ፣ ነፍሷ ላይ የሚደርስ ‘ስኪመስል ያያታል።

   …ታየዋለች፣ታየዋለች፣ አሁንም ደግማ ታየዋለች። አይኑ ውስጥ የማያቋርጥ ውብ ትዕይንት እንዳለ፣ አይኑ የበጋ ላይ የውቂያኖስ ውብ ውሃ፣የአይኑ ብሌን በውቂያኖሱ ላይ የምትጠልቀውን ቆንጆ ጸሀይ እስኪመስለኝ ድረስ ታየዋለች። ሻይና ማኪያቶ ይረሳል። ይቀዘቅዛል። የፍቅር ዋኖሶች በመተያየት ያወራሉ፣ በመተያየት ይጫወታሉ፣ በመተያየት ይግባባሉ።

አንዳንድ ቀን…

ዳሪክ እጁን ዘርግቶ ሳሌምን ይዳስሳታል፣እጇን ይዞ በዝግታ እየደሳሰ ጣቶቿን በታላቅ ቀስታ ይንካካቸዋል። አደሳሱ፣ አነካኩ አዲስ ሙዝቃን አዲስ በተገኘ ፒያኖ የሚጫወትን ዘማሪ ያህል ነው። በዙሪያቸው ያሉ ሁሉ ደሞ ታዳሚዎች ናቸው።  

….ሳሌም በተመሳሳይ እጁን ትነካካዋለች፦ በዝምታ፣ በስሱ ። ውብ ጣቶቿን በአይበሉባው፣ በቆዳው ላይ በርጋታ ስታስኬድ.. ከአልማዝ፣ ከእንቁና ከሩቢ ውህድ የተሰራ በአለም ያለታየ አዲስ የከበረ ድንጋይ ያህል (…የኔ ብቻ እጅ… የኔ ብቻ…) እያለች የምትነካካው የምታየው ይመስለኛል።

ረጅሙ መንገድ!....

….ለሁለቱ የፍቅር ርግቦች ረጅሙ መንገድ የትኛው ነው? ምን ያህል ነው? ከሃምሳ ሜትር የሚበለጥ አይመስለኝም። ረዥሙ መንገድ ከካፌው እሰክ ታክሲ መያዣው ያለው ነው። ርግቦቹ የአለምን ግማሽ ያህል የሚሄዱ ይመስል ያዘግማሉ። በብዙ ግፊያ ውስጥ የሚሄዱ ይመስል እርምጃቸውን ይቆጥራሉ። በጫማቸው ልክ ይራመዳሉ። እጅ ለእጅ ተያይዘው ይቆማሉ፣ ደሞ ዝግ ብለው (…ኤሊን “…ደሞ ከኔ የባሳም አለ እንዴ?...” ) ብላ በሚያስደምማት አይነት ጉዞ ይጓዛሉ። እንዳይለያዩ እኮ ነው።

አይደረስ የለም ታክሲ መያዣው ጋር ሲደርሱ ደሞ ይቆማሉ።

ታክሲ መጥቶ ይቆማል። ረዳቱ ይጣራል።

…ሁለት ሰው የሞላ ትሄዳላችሁ ቀሸቶች?...”

የሚሄዱ ይመስላሉ። ታክሲው በትእግስት ይጠብቃል።
ደግሞ ይጣራል።

“…ቀዮ ትሄዳላችሁ?”

“…ባክህ እነዚህ ገፈፎች አይሄዱም ንዳው…” ይላል የተበሳጨው ረዳት

ዳሪክና ሳሌም አይሰሙም። ቆመው ያወራሉ። ወይም ዝም ብለው ቆመው ይተያያሉ። አንዳንድ ጊዜ ሳስበው ወሬ የሚመጠላቸው፣ በጥልቅ መተያየት የሚፈልጉት በዚህ በመለያያቸው አስራ አንደኛ ሰአት ላይ ይመስላል።

ደሞ ሌላ ታክሲ ይመጣና ይጣራል።

“…ትሄዳላችሁ ጀለሶች። የሞላ፣ በራሪ ሁለት ሰው ብቻ…”

ሌላ ታክሲ ይመጣል። ይሄዳል። ሌላ ይመጣና ይሄዳል። ደሞ ሌላ ይመጣል።

ሳሌም ወደ ታክሲው መንገድ ትጀምርና ዳሪክ ደሞ ሊያወራት ይጀምራል። ትመለሳለች። ደሞ እንደገና ተያይዘው፣ ቆመው ወሬ ይጀምራሉ። ተለያዩ ሲባል፣ ሲሳሳቡ፣ ሲያወሩ ረዥም ጊዜ አልፎ በመጨረሻ ሳሌም ታክሲ ውስጥ ገብታ ጉዞ ይጀምራል።

ዳሪክ ቆሞ ሳሌም የገባችበትን ታክሲ ያያል። ህጻን ልጇን ላይመለስ እንደተወሰደበት ወላጅ፣ ለመጨረሻ ጊዜ እንደምትታይ መቼም ተመልሳ እንደማትመጣ የጸህይ ጥልቀት ቆሞ ያያል። ታክሲው ከዐይን እስኪሰወር አሻግሮ ይመለከታል። ከዛ በተቃራኒው አቅጣጭ ቀስ እያለ መጓዝ ይጀምራል። ቀኑ መሽቷል። ጸሐይም ጠልቃለች።
👍296🥰3🎉1
ረጅሙ ጊዜ!...

ረጅሙ ጊዜ የትኛው ነው? ፍቅሮቹ ተለያይተው እስከሚገናኙ ድረስ ያለው ነው።
 
  …ሲለያዩ ሰአታት ይቆጠራሉ፣ ደቂቃዎች ይመነዘራሉ፣ ሰኮንዶች ይሸራረፋሉ። የናፍቆት ምጥ ይጀምራል። በሚቀጥለው ቀጠሮ የሚገናኙበትን ጊዜ ዋኖሶቹ መራብ ይጀምራሉ። አሁን ሲለያዩ ሰኔ ነው። እሱ ጸደይ ነው፦ እሷ ደሞ አበባ። ጸደይ አበባን፣ አበባም ጸደይን እንደሚናፍቁ የዋኖሶቹም ናፍቆት እንዲሁ ነው። አሁን ሲለያዩ ጥቅምት ነው። እሱ መስከረም ነው ፦እሷ ደሞ የመስቀል ወፍ። መስከረም የመስቀል ወፍን፣ የመስቀል ወፍም መስከረምን እንዲናፍቁ የእነሱም ናፍቆት እንዲህ ነው።

….ሁላችንንም ያስደመመን፣ ያስደነቀን ሲያትል አምስተኛው ጎዳና ላይ የመጣው ይህ የሁለት ርግቦች ፍቅር የጀመረው እንዲህ ነበር፦ አዲስ አበባ …ወሎ ሰፈር...ደሞ ቦሌ ላይ።
*

ይቀጥላል
ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍286🔥1
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ከትንግርት ጋር ከሀያ ቀናት በኃላ ነው በአካል የተገናኙት፡፡በጣም ናፍቃዋለች፡፡ ምግቡን እየበላ በመሀል ቀና እያለ ሸርፎ ይመለከታታል፡፡‹‹ቤት መዋል ስትጀምሪ ባለሞያ ወጥቶሻል፡፡›› አለ ሁሴን የቀረበለትን ምግብ በልቶ ጨርሶ እጁን እየታጠበ፡፡

የተበላበትን ዕቃ አነሳስታ ከጨረሠች በኋላ ለሁለቱም ተጨማሪ ቢራ ጠረጴዛ ላይ በማስቀመጥ ፊት ለፊቱ እየተቀመጠች፡፡‹‹ባክህ... በእጄ የተሠራውን ምግብ ለመቅመስ እድሉ ስላልገጠመህ እንጂ ድሮም ባለሙያ ነኝ፡፡ >> አለችው

‹‹መጠጥ አሁንም አልተውሽም ማለት ነው?››

‹‹መተው አልተውኩም... ግን በጣም ቀንሻለሁ፤ አንዳንዴ ሲያሠኘኝ ብቻ ነው ቀመስ የማደርገው››

‹‹ይህቺ ቀመስ እራስን መሸወጃ እንዳትሆን?››

‹‹አይመስልህ፤አልፎ አልፎ መጠጣቱ ያን ያህል መጥፎ መስሎ ስላልተሰማኝ ነው እንጂ ለማቆም ከብዶኝ አይደለም፡፡ ጫት፣ ሲጋራና አንተን በአንዴ እርግፍ አድርጌ መተው የቻልኩ ሠው እኮ ነኝ፡፡››

ሁሴን በንግግሯ ፈገግ አለና ንግግሩን ቀጠለ << እኔም ሱስሽ ነበርኩ ማለት ነው?ለዛውም ከጫትና ከሲጋራ እኩል ውስጥሽን የምጎዳ መጥፎ ሱስ? ለማንኛውም እፈልግሃለሁ ብለሽ ያስጠራሸኝ ለምን እንደሆነ ለማወቅ ጓጉቻለሁ ?>>

‹‹ያን ያህል?››

‹‹ከምትገምቺው በላይ፡፡ አንቺን መፍራት ከጀመርኩ ሠነበትኩ እኮ፡፡ ነገረ ስራሽ ሁሉ ተዓምራዊ ነው፡፡ የዛሬው ደግሞ ምን እንደሆነ ልስማዋ!››

ከመቀመጫዋ ተነሳችና ወደ መኝታ ክፍሏ እየተውረገረገች ገባች፡፡ አተኩሮ ተመለከታት… ውበቷ ከቀድሞው በጣም የጨመረ መሰለው፡፡ አንዳንዴ የማያቃት አዲስ ሴት ትሆንበታለች፡፡ እርጋታዋ ያስፈራዋል፣ ብስለቷ ያስደነግጠዋል፡፡ በፊት ተሸፍነው የነበሩ ምርጥ ስብዕናዎቿ ዛሬ ጎልተውና አብበው መታየት ሲጀምሩ የማያውቃት ሴት መስላ ብትታየው ምኑ ይገርማል?፡፡

ተመልሳ መጣችና አንድ አበጥ ያለ እሽግ ካኪ ወረቀት አቀበለችውና ወደ መቀመጫዋ ተመልሳ ተቀመጠች፡፡

‹‹ምንድነው?›› ግራ በመጋባት ጠየቃት፡፡ዝም አለችው

‹‹ልክፈተው?›› መልሶ ጠየቃት፡፡

‹‹ምን አስቸኮለህ መጠጥህን ጨርሰህ ወደ ቤትህ ሄደህ ተረጋግተህ ታየዋለህ፡፡ ያን ያህል ጠቃሚ ጉዳይ አይደለም››አሁኑኑ ቤቱን ለቆ
ወጥቶ እሽጉን ለመክፈትና ውስጡ ያለውን ሚስጢር ምንነት ማወቅ ፈለገ፡፡ ደግሞም ስሜቱን እንደምንም ተቆጣጥሮ ሀሳቡን ቀየረ፡፡ ከእሷ አጠገብ መቀመጥ ከእሷ ጋር ማውራት ፈልጓል፡፡ አሁን ውድ ሆናበታለች፡፡ ሻይ ለመገባበዝ እንኳን እሷ በፈለገችና ባሰኛት ጊዜ እንጂ እሱ ሲፈልግ ሊያገኛት አይችልም፡፡ ስለዚህ ታግሶ ወደ ወሬው ተመለሠ፡፡

‹‹ያንን የጠየኩሽን ነገር ምን ወሠንሽ?›› ቢራውን ከነጠርሙሱ አንስቶ ተጎነጨና ጠየቃት፡፡

<<የቱን??>>

‹‹የሕይወት ታሪክሽን በጋዜጣዬ ላይ በተከታታይ አምድ ማሳተም እፈልጋለሁ ብዬሽ ነበር እኮ፡፡››

‹‹አስታውሳለሁ .. ግን አልወሰንኩም፡፡››

‹‹ብዙ ብር እኮ ነው የሚያስገኝልሽ .. የፈለግሽውን ያህል እከፍልሻለሁ››

የንዴት ፈገግታ ፈገግ አለች፡፡ ‹‹በቃ አንተ ከእኔ የምትፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ በብር ብቻ ነው ለመግዛት የምትጥረው፡፡ ፍቅሬን ወይንም ገላዬን በገንዘብ ስሸጥልህ ኖርኩ፤ዛሬም ታሪኬን በገንዘብ ልሽጥልህ?ያን ያህል አታውቀኝም ማለት ነው?››

ሁሴን ባላሠበው መንገድ ስለመጣችበት ተሸበረ፡፡ ትንግርት የሕይወቷን አቅጣጫ ከተቀየረ በኋላ ያስተዋለባት አንድ ለውጥ ይሄ ነው፡፡ በፊት ሲያውቃት ቻይ፣ሆደ ሠፊ፣ማንኛውን ንግግር የማያስከፋት፣ ቢያስከፋትም መከፋቷን ሳታሳውቅ በሳቅ ማሳለፍ የምትችል ብልህ ነበረች፡፡ አሁን ግን የተለየች ሆናለች::

‹‹እንደዛ ማለቴ አይደለም፡፡ ልዩ ታሪክ እንዳለሽ አምናለሁ፡፡ ይሄ ታሪክ ደግሞ ለተቀረው ማህበረሰብ አስተማሪ ስለሆነ ተዳፍኖ መቅረት የለበትም ብዬ ስለማስብ ነው፡፡ እስቲ እንዲታተም ባትፈቅጂ እንኳን ለራስሽ ፅፈሽ አስቀምጪው::››

‹‹ጽፌዋለሁ... በተለይ ባለፉት አምስት አመታት ያሳለፍኳቸውን በህይወቴ የተከሠቱ አንኳር ድርጊቶች በዲያሪዎቼ ላይ አስፍሬያቸዋለሁ፡፡››

‹‹በቃ እኔ የፈለኩት ይሄን ነው፤አየሽ ያልተጻፈ ነገር እየደበዘዘ ሄዶ ከእለታት አንድ ቀን መረሳቱ አይቀርም፡፡››

‹‹አይዞህ የሚረሳ ነገር አይኖርም፤መታተም አለበት ብዬ ስወስን ወደ አንተ ቢሮ እንደምመጣ ቃሌን እሠጥሀለሁ፡፡››

‹‹አመሠግናለሁ፤ቃልሽንም እንደምትጠብቂ አምናለሁ፡፡… ብቻ አሁን አንድ ነገር ላስቸግርሽ ነው...መጀመሪያ እሺ በይኝ፡፡››

‹‹ምን እንደምትጠይቀኝ ሳላውቅ እንዴት እሽ እላለሁ?»

‹‹በቃ እሽ በይኝ…ማድረግ የማትችይውን ነገር አልጠይቅሽም፡፡››

‹‹ለማድረግ እኮ ማድረግ መቻል ብቻ በቂ አይደለም...ፍላጎትም ያስፈልጋል፡፡››

‹‹ባክሽ ክርክሩን አቁመሽ እሺ በይኝ፡፡››

‹‹ውጪልኝ እንዳትለኝ እንጂ ለሌላው ችግር የለም፡፡››

ትክዝ ብሎ ሀሳብ ውስጥ ገባ፡፡ እራቁት ገላዋ... ቅብጠቷ... የወሲብ ብቃቷ በዓይነ ህሊናው ተመላለሰበት፡፡

ከት ብላ ሳቀችና‹‹ ተነቅቶብሃል፡፡ በፍፁም እሺ አልልህም፡፡የእሱ ጉዳይ ተዘግቶ ፋይሉ ወደ መዝገብ ቤት ተመልሷል፡፡›› አለችው፡፡

‹‹ግምትሽ የተሳሳተ ነው፡፡ እርግጥ ፍላጎቱ የለኝም ብዬ ልዋሽሽ አልፈልግም… በጣም ተርቤሻለሁ፡፡ አሁን ቃል ግቢልኝ ያልኩሽ ግን ለእሱ አይደለም፡፡››

‹‹ለእሱ ካልሆነ ቃሌን ሠጥቼሀለሁ... ጠይቀኝ፡፡››

ጉሮሮውን በመጠኑ ካረጠበ በኋላ ‹‹ከዲያሪሽ ላይ የአንዱን ቀን ውሎሽን እንድታነቢልኝ እፈልጋለሁ፡፡››

<<መቼ>>

<<አሁን ነዋ>>

‹‹አይሆንም .. አይሆንም .. ሌላ ጊዜ፡፡››

‹‹ቃል ገብተሽልናል፡፡››

እንደማሰብ አለችና ‹‹እሺ... ምን ቸገረኝ.. ስለምንድነው መስማት የምትፈልገው? የዩኒቨርስቲ የህይወት ገጠመኜን፣ የቡና ቤት ህይወት ገጠመኜን .. የቱን?››

‹‹ደስ ያለሽን ...ግን…. ስለ ቡና ቤት ቢሆን እመርጣለሁ፡፡››

ወደ መኝታ ቤቷ በመሄድ ስለ ቡና ቤት የሕይወት ገጠመኟ ካሰፈረችባቸው ድያሪዎቿ መካከል አንዱን መዛ ወደ ሣሎን በመመለስ መቀመጫዋ ላይ ተመቻችታ ቁጭ አለች፡፡

‹‹እንግዲህ አዚህ ዲያሪ ላይ ከተፃፈው የአንዱን ቀን ውሎዬን ወይም አዳሬን አነብልሀለሁ፡፡ ግን መርጬ አይደለም፡፡ ዝም ብዬ እከፍተዋለሁ፤አነብልሃለሁ፡፡›ተስተካክላ ተቀመጠችና ዲያሪዋን ከፈተች ወደ መሃከል ገደማ ነው፡፡ ርዕሱን አነበበች ‹‹40 ፐርሰንት›› ይላል ....ይሄንንማ አላነብልህም በጣም ይሰቀጥጣል፡፡

‹‹እድሌ ነው አንብቢልኝ፡፡››

‹‹በናትህ ደባሪ እኮ ነው፡፡››

‹‹ምንም ቢሆን ምንም መስማት እፈልጋለሁ፡፡››

‹‹እሺ ምን ቸገረኝ>> በማለት የገለጠችውን ዲያሪ በዝግታ ማንበብ ..…ሁሴን በጉጉትና በፀጥታ ማዳመጥ ቀጠለ

ሚያዚያ 20/2005

«40 ፐርሰንት››

ቀድሞ ገባ... ተከተልኩት፡፡ የቤርጎው ስፋት መታጠቢያ ክፍሉን ሳይጨምር አራት በሦስት ይሆናል፡፡ የከፈለኝ የጠየኩትን ያህል ብር ነው፡፡ ዝምተኛ፣ ጭምትና የከፋው ቢጤ ነው፡፡ እንዲህ አይነት ወንዶች አንድ የተለየ ነገር አይታጣባቸውም ብዬ ስለማስብ አብሬያቸው ማደር ደስ ይለኛል፡፡

የቤርጎውን በር ከቀረቀርኩ በኋላ ወደ ውስጥ ዘለቅኩ፡፡ ቀድሞኝ አልጋው ላይ ጋደም አለ ከነልብሱ፡፡ እኔም በእጄ ይዤ የነበረውን ኮንዶም ኮሞዲኖው ላይ ጣል አድርጌ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ ሠረቅ አድርጌ ተመለከትኩት አይኑን ጣሪያ ላይ ሠክቶ ይቆዝማል፡፡ ነገር የገባው ፈላስፋ ይመስላል፡፡
👍815👏3👎2😁2🔥1🥰1
‹‹የዚህ አገር ልጅ ነህ?›› የጥያቄውን መልስ ፈልጌ ሳይሆን እንዲያወራኝ ስለፈለኩ ነበር መጠየቄ፡፡

‹ምነው?›› መልሶ በግድየለሽነት ጠየቀኝ፡፡

‹‹እዚህ ሠፈር አይቼህ ስለማላውቅ ነው፡፡››

‹‹ከአሁን በኋላም አታይኝም፡፡›› ደረቅ መልስ መለሰልኝ፡፡

‹‹ኡ. ኡ .ቴ እሱን እንኳን እናያለን፡፡›› አልኩት... አስቤ አልነበረም እንደዛ ያልኩት፤ እንዲሁ ለመቀለድ ስለፈለኩ እንጂ፡፡ ድብርቱን ላላቅቅለት ወስኛለሁ፡፡ ቢያንስ ለዚች ለሊት እንኳን ቢሆን ችግሩን እንዲረሳ .. በደስታ ላንሳፍፈው ቆርጬ ነበር፡፡

‹‹ዝምተኛ ነህ?>>

ታጥቦ እንዳልተተኮሰ ሱፍ ጨርቅ የተጨማደደ ፊቱን እንደቋጠረ‹‹ብንተኛ ምን ይመስልሻል?››አለኝ፤አልከፋኝም፡፡ አይነጥላው
እስኪገለጥለት ነው ስል አሠብኩ፡፡

ከደቂቃዎች በኋላ የሕይወት ታሪኩን እንደሚዘከዝክልኝ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ እንደእሱ አይነት ብዙዎች ገጥመውኛል፡፡

መጨረሻቸውንም በሀዘኔታና በትዝብት ተመልክቼያለሁ ...ቀይ ፒኪኒ ፓንቴ ሲቀር የተቀረውን ልብሴን አንድ ባንድ አወለቅኩ፡፡

አንሶላውን ገልጬ ከውስጥ ገባሁና እሱን መመልከት ጀመርኩ፡፡ ከተጋደመበት ተስፈንጥሮ ተነሳና ማወላለቅ ቀጠለ፡፡ እፍረቱን መሸፈኛ እንኳን አላስቀረም፡፡ መለመላውን ወንበር ስቦ ተቀመጠ፡፡

ከተኛሁበት ሳልንቀሳቀስ አፍጥጬ እየተመለከትኩት ነው፡፡ አወላልቆ ካስቀመጠው የሱሪ ኪስ ሲጋራ አወጣና ለኩሶ ማጬስ ጀመረ፡፡ ገረመኝ፡፡

‹‹በሽተኛ ነው እንዴ?›› ሁሴን አላስችል ብሎት ጣልቃ ገብቶ ጠየቀ፡፡

ከንባቧ ስላደናቀፋት ተበሳጭታ‹‹እያነበብኩልህ እኮ ነው...ሠለቸህ እንዴ?›› አለችው፡፡

‹‹ኧረ በፍፁም…. መጨረሻው አጓጉቶኝ ነው።

ታገስ ካሁን በኋላ ካቋረጥከኝ አላነብልህም›› አለችና ከቢራው አንዴ ተጎንጭታ ከንፈሮቿን በማርጠብ ካቆመችበት ንባቧን ቀጠለች፡፡

‹‹ከሴቶች ጋር ተኝቶ አያውቅም ወይስ ስልብ ነው?›› ስል አሰብኩ፡፡ አጢሶ ሲጨርስ ከኪሱ ሌላ ነገር አወጣና ወደ እኔ አመራ፡፡ ሠፋ ያለ ፕላስተርና የተጠቀለለ ገመድ ነበር የያዘው፡፡ ግምቴን ሳልጨርስ ህገወጥ ሸቀጥ እንደተገኘበት የነጋዴ መጋዘን በሚገርም ፍጥነት አፌን አሸገኝ፡፡ ፋታ ሳይሰጠኝ የለበስኩትን ብርድ ልብስ ከላዬ ላይ ገፎ ወደ  ወለሉ ወረወረውና ከተኛሁበት ጎትቶ አስነሳኝ፡፡ እጆቼን ወደ ኃላ ጠመዘዘና በመንግስት እጅ እንደወደቀ አሸባሪ ወይም ለመንግስት ስልጣን አስጊ እንደሆነ ፖለቲከኛ አንድ ላይ አጣምሮ ጠፈራቸው....መታገል አልቻልኩም፡፡

በፍራቻ ቀስ በቀስ መደንዘዝ ጀምሬለሁ፡፡

ሊገለኝ እንዳሰበ ገመትኩ፡፡ አይኖቹን ተመለከትኳቸው ...የሲኦል እሳት ውስጣቸው
መንቦግቦግ ጀምሯል፡፡ ለበርካታ ደቂቃዎች ፊት ለፊቴ ቆሞ አስተዋለኝ፡፡ እነዛ ደቂቃዎች ለእኔ ከእድሜ ልክ በላይ ነው የረዘሙብኝ፡፡

አንዴ ጡቶቼን ከዛም ጭኔን ጠቅላላ ሠውነቴን በማፈራረቅ እስኪጠግብ ተመለከታቸው፡፡

መመልከቱ ሲበቃው የለበስኩትን ቀይ ፓንት
በእርጋታ አውልቆ ወደ አፍንጫው አስጠጋ፡፡
የፈረንሳይ ሽቶ እንደተነሰነሰበት ውድ መሃረብ በተመስጦ ሽታውን ወደ ውስጥ እየማገ
አጣጣመው፡፡በኋላም በጥንቃቄ አጣጠፈውና
ኮመዲኖው ላይ አስቀመጠው፡፡ ወዲያው
ሃሳቡን ቀየረና ካስቀመጠበት አንስቶ የጃኬት ኪስ ውስጥ ከተተው …ፓንቴን፡፡በዚህ ጊዜ የስነልቦና በሽተኛ መሆኑ በደንብ ገባኝ፡፡ ፍራቻዬ በእጥፍ ጨመረ፡፡ ብዙ የወሲብ በሽተኞች አጋጥመውኝ ያውቃሉ፡፡የዛሬው ግን የተለየ ነው የሆነብኝ፡፡ ነገሩን የከፋ ያደረገው ደግሞ የሆነ ነገር ተናግሬ እንዳላረጋጋው፤ ካልሆነም ያቅሜን ያህል ጮኬ ከውጭ እርዳታ እንዳይመጣልኝ የአፌ መታሸግና የእጄ መታሰር ነው፡፡

ሁለት እግሮቼን ይዞ ወደ አልጋው ጫፍ ሳበኝ፡፡ ወንበሩን አስጠጋና እግሮቼ መሀከል ተቀመጠ፡፡ ልክ ከማህፀን የሚወጣ ህፃን ልጅ እንደምትጠብቅ አዋላጅ ብልቴን አትኩሮ ይመለከት ጀመር፡፡ እንደመባነን አለና ሌላ ሲጋራ መዞ አቀጣጠለ፡፡ በዚህ ጊዜ ይበልጥ

ሠውነቴ መንቀጥቀጥ ጀምሮ ነበር፡፡ ‹ሊያበላሸኝ ነው› ስል ደመደምኩ፡፡ ብልቴን በሲጋራ እሳት ሊተረኩሰው እንደሆነ ገመትኩ፡፡

በዓይኖቼ ተማፀንኩት.... ፍራቻዬ አየለ…. ፊኛዬ ተነፋፋና የሽንት መቆጣጠሪያዬ ተተረተረ፡፡

እሱም በተራው በመገረም አስተዋለኝ፡፡ አዲስ
እንደፈለቀ ምንጭ ከሚንጎለጎለው ሽንቴን
በጣቱ አጥቅሶ ወደ ምላሱ ሠደደው... እናም አጣጣመው፡፡ ልክ የሠራችውን ወጥ እንደምትቀምስ ባለሞያ፡፡ ደግነቱ ምንም የቃጠሎ አደጋ ሳያደርስብኝ ሲጋራውን አጪሶ ጨረሠና ወረወረው፡፡ አወራወሩ የንዴት ይመስላል፡፡

‹‹ከሌላ ፕላኔት የመጣ ፍጡር ይሆን እንዴ?›› ስል አሰብኩ፡፡ መጨረሻዬም አጓጓኝ፡፡ በዚህ ቅፅበት እጁን ወደ ጃኬት ኪሱ ሲሠድ በጨረፍታ ተመለከትኩ፡፡ ብሞት ግድ የሌለኝ መስሎ ይሠማኝ ነበር፡፡ ይህቺን አለም ገና እንዳልጠገብኳት የተረዳሁት ግን በዚህ ክስተት ነው፡፡የሚያብረቀርቅ ጩቤ አወጣ ፤የራሱን እጅ በጭካኔ ሸረከተው፡፡ ደሙ መስመር ሰርቶ መንጠባጠብ ጀመረ፡፡ የተለያዩ ህብረ - ቀለማት አይኖቼ ላይ ተመላለሱብኝ፤ቀስ በቀስ ከማንነቴ እየተነጠልኩ..እየተፋው ሲሄድ ይታወቀኛል፡፡

ወደ ጥልቅ ገደል እየተንሸራተትኩ ምጓዝ

መስሎ ተሠማኝ፡፡.....

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች 
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍9711🥰6😱6👏1😁1
የፍቅር ‘ርግቦች
ክፍል አስራ ሶስት፦ 1.ምን ያህል ትወደኛለህ

  2. ፈሪ አይደለሁም!
  3. የአውሮራ ድልድይ !
  4. የነፍስ ካንሰር

©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር

      አደጋው ደርሶበት ሰመመን ውስጥ እስከሚገባ ድረስ ዳሪክ ለሳሌም እንዲሁ እንደነገራት፣ እንደ ቃሉ ነበር የሆነላት። ዳሪክ ለሳሌም ደስታዋን በብዙ እባዝቶ ሰጣት። ከፍ ስትልለት ሃሴት አደረገ። ሳቋን እልፍ ጊዜ አልፍ አድርጎ መንዝሮ መለሰላት። ሞትም ሲመጣ በደስታና በፈቃዱ ሊያድናት በፍቅሩ ሳሌምና በሞት መካከል ገባ፦ ሳቂታው ዳሪክ!!!

     ዳሪክ በሃኪሞች ተወስኖበት ወደ ማይቀረው ጉዞ ሊሄድ 48 ሰዓታት ያህል ቀርተውት… ሳሌም በስስ ፈገግታዋ ፊቷን አስውባ የዳሪክን ፍቅር፣ ሳቅና ቁምነገር ስትነግረኝ ነፍሴ በደስታ ዳንኪራ እየጨፈረች እሰማትና የምታወራልኝንም እንዲህ በልቤ እጽፈው ነበር።
*
*
  ዳሪክ ያወራታል፦ ሳሌም ትሰማዋለች። ዳሪክ የሚያወራውን ነገር ያለ ማቋረጥ መስማት ለሳሌም ደስታዋ ነው። ብዙ ጊዜ ያስቃታል። ብዙ ጊዜም ቁም ነገር ያወራታል። ዳሪክ ቁም ነገር ሲያወራ የሶስት ነገር ውህደት ነው፦ ጥበብ፣ማስተዋልና መልስ ነው። በጥበብ ይናገራል። በማስተዋል ቃሎቹን ያወጣል። ደስ የሚልና አጥጋቢ መልስ ይሰጣል።

አንድ (1) - ምን ያህል ትወደኛለህ?

ሳሌምና ዳሪክ አብረው እየሄዱ ነው።… አለ አይደል ወክ እየበሉ። ሳሌም ብዙ ጊዜ ልትጠይቀው የፈለገችውን ነገር አለ። ጥቂት አሰበችና

“የኔ መልዐክ?” ጠራችው

“ወይዬ የምወድሽ?”

“ለምን ትወደኛለህ ስልህ ባለሰበኩትና ባልጠበቅኩት መንገድ መልሰልህኛል። አሁን ደሞ ሌላ ጥያቄ ልጠይቅህ ነው?”

ዳሪክ ከፊቷ ቀደመና አይኗን ፊት ለፊት እያየ ቆመ። “ደስ ይለኛል የምወድሽ ጠይቂኝ?”

“ምን ያህል ትወደኛለህ የኔ መልዐክ?”
 
“ምን ያህል?” ፈገግ ብሎ ያልሰማ ይመስል ጥያቄውን ደገመው

“ምን ያህል?” ሳሌም ራሷን በአውንታ ነቀነቀችና ደገመችለች።

ዳሪክ ለሰከንዶች ዝም ብሎ ሲያያት ቆየ “…ሬድ ሺፊት(Red shift) ሲባል ሰምተሽ ታውቂያለሽ የምወድሽ?.”

“ሬድ ም…..…ን?.... ሰምቼ አላውቅም …ምንድነው ደሞ?”

“…የፊዚክስ ተርም ነው የምወድሽ እሱ ይለፍሽና ሌላ ነገር ልንገርሽ። …ይሄ ያለንበት ዩኒቨርስ ከብርሃን በበለጠ ፍጥነት እየሰፋ እንደሚሄድ ታውቂያለሽ….”  ዳሪክ እጆቹን ወደ ጎንና ጎን እያሰፋ ስዕላዊ በሆነ መንገድ ያሳያታል።

“አላውቅም አንተ ከየት ሰማኸው? ከየት አውቅከው?”

“አንስታይን ጀኔራል ሪላቲቪቲ ቲዎሪ” ዳሪክ መለሰ

ከዛም ዳሪክ ቀጠለ “….የምወድሽ ያለንበት ዪኒቨርስ በየደቂቃው፣ በየስከንዱ ከብርሃን በበለጠ ፍጥነት ትሰፋለች። በሌላ አነጋገር የዩኒቨርስ ጫፍ ከመሬት በፍጥነት እየራቀ ያድጋል። ሩቅ ያሉት አለማትና ከዋክብቶች ከመሬት ከብርሃን በበለጠ ፍጥነት እየራቁ ዪኒቨርስ እየሰፋ፣ እያደገ ይሄዳል።ይህ የማያቋርጥ ሂደት ነው። …”

ዳሪክ ትንሽ አሰበና ቀጠለ “…እኔ ላንቺ ያለኝ ፍቅርም እንደዚሁ ነው የሚመስለኝ። እኔ መሬት ነኝ። ያንቺ ፍቅር ደሞ ዩኒቨርስ ነው። መጀመሪያ ያየሁሽ ቀን ፍቅርሽ ቅርቤ ነበር፣ እነካው ነበር። ነገር ግን በየሰከንዱ በሶስት ዳይሜንሽን እየሰፋ፣ እያደገ፣ እየጠለቀ ይሄዳል።…”

ሳሌም በደስታ እየሰማችው ዳሪክ ቀጠለ…

   “…የምወድሽ… አይቼሽ እንደገና ዞር ስል ላንቺ ያለኝ ፍቅር ይሰፋል።…” ወደ ጎን እጆቹን እያሰፋ። 

“…የምወድሽ...ቀኑ መሽቶ ሲነጋ ላንቺ ያለኝ ፍቅር ያድጋል።…” እጆቹን ከጭንቅላቱ በላይ ከፍ አድርጎ። 

“….የምወድሽ… በየደቂቃው፣ በየሰከንዱ ላንቺ ያለኝ ፍቅር ወደ ታች ይጠልቃል።….” እጆቹን ወደ ታች ዝቅ አድርጎ።

“…የምወድሽ…ሬድ ሺፍት የብርሃን ዌቭ ሌንግዝ መለኪያ ነው። ሳይንቲስቶች የዩኒቨርስን ፈጣን እደገትና ከመሬት ያለውን ርቀት ለመለካት ይጠቀሙበታል። ጂኦሜትሪ ነው። የረቀቀ ፎርሙላ አለው።… ምን ያህል ትወደኛለህ? ላልሽው ይህን ያህል ብዬ ልነግርሽ አልችልም…. ምክንያቱም …. ፍቅሬ በየቀኑ እያደገ፣ እየጨመረ የሚሄድ ነው። በሬድ ሺፍት እንኳን አይለካም። የምወድሽ በመሰረቱ እውነተኛ ፍቅር መለኪያ የለውም።…ሰዎች ‘ፍቅሬ ቀነሰ፣’… ‘ፍቅሬን አስጨርሺኝ’… ‘ፍቅሬ አለቀ’…ምናምን ሲሉ ግራ ይገባኛል። የማይለካ ነገር እንዴት ያልቃል? የማይወሰን ነገር እንዴት ይቀንሳል? እንዴት የምወድሽ?...”

ሳሌም ተገርማ፣ተደንቃና ደስ ብሏት ታስባለች “…መታደል ነው። በዚህ ልጅ፣ በነደዚህ አይነት ሁኔታ መወደድ መታደል ነው። ጌታ ሆይ አመሰግንሃለሁ።….”

ትንሽ ቆይታ ደሞ ጠየቀችው። “…የኔ መልዐክ የኔ ቆንጆ?...”

“…ወዬ የምወድሽ?...”

“….ይህን ሁሉ ነገር ከየት ነው የምትሰማው፣…ሬድ ሺፍት .. ጄነራል ሪላቲቪቲ፣… ዩኒቨርስ… ምናምን?...”

“…ከማንበብ የምወድሽ!…. ከማንበብ!…”
*
*
ሁለት (2) - ፈሪ አይደለሁም!

     እንደ ታደጊ ወጣትነቷ ሳሌም ከእድሜ እኩዮቿ የምትሰማው ነገር አለ። ፍቅረኛ ያላችው ልጆች በየቀኑ ያደረጉትን፣ የፈጸሙትን የsex ጀብዱ ሲያወሩ መስማት ባትፈልግም አንዳንዴ የግድ ትሰማለች። ሳሌም በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ አቋም አላት። ከትዳር በፊት ማንም ጫፌን አይነካኝም ብላለች። ግን ደሞ ሳሌም አንዳንዴ ትጨነቃለች። አንድ ቀን ዳሪክ ይህን ነገር እንዳይጠይቃት  አብዝታ የምትሳሳለት ፍቅሯ በማይሆኑ ነገሮች ተሰናካክሎ እንዳይወድቅ ያስፈራታል።

አንድ ቀን ጠየቀችው።

“…የኔ መልዐክ በዚህ ነገር ላይ ያለህ አቋም ምንድን ነው?...”

“…አልገባኝም የምወድሽ…”

“….አየህ የኔ ቆንጆ…የኔ አቋም ከጋብቻ በፊት በንጽሕና መቆየት ነው። በወጣትነቴ የማይገባ ነገር ውስጥ መግባት አልፈልግም።…”

ዳሪክ በፈገግታ አያት። “…የምወድሽ?...”

“…ወዬ… የኔ ቆንጆ…”

“…ፈሪ አይደለሁም የምወድሽ...”

“….ፈሪ አይደለሁም ስትል አልገባኝም ምን ማለትህ ነው?...” ሳሌም የሚለውን ለመስማት ጏጉታ

“….የምወድሽ የትኛው ፈሪ ነው በሆርሞኖች ጩኸት፣ በደቂቃዎች የስሜት ፍትጊያ ልክ የፍቅርን ትርጉም ያስቀመጠው? … ፍቅር እንደዚህ ጠባብ አይደለም። ፍቅር እንደዚህ ታናሽና ደቂቅ ሆኖ አያውቅም። ፍቅር ሰፊና ጥልቅ ነው። የምወድሽ እኔ ፈሪ አይደለሁም። ጌታ እድሜ ቢሰጠኝ ካጠገብሽ ብቻ ሆኜ ሺ አመታት መጠበቅ ፣የጣቶችሽን ውበት ብቻ እያየሁና እያደነቅኩ እልፍ አመታት መቆየት፣ የምወድሽ አይንሽ ብቻ እያየኝ… የአርዲን እድሜ መታገስ እችላለሁ።…”

“…አርዲ ደሞ ማነው የኔ መልዐክ?...”

“….አርዲ ሴት ናት!...” ዳሪክ እየሳቀ “….በአዋሽ ወንዝ አካባቢ በቅርቡ የተገኘች ፎሲል ናት። እድሜዋ ከአራት ሚሊዮን አመታት በላይ ነው ይላሉ….”

“….እና ከአራት ሚሊዮን አመት በላይ ትጠብቃልህ የኔ ቆንጆ?...”

“…አዎን ብችልና ብኖር የምወድሽ ከዛም በላይ ቢሆን…”

   ሳሌም እጁን ጥብቅ አድርጋ ይዛ በእፎይታ ትተነፍሳለች። ከዛም ማሰብ ትጀምራለች። በልቧ መልሳ ትላለች “ ….መታደል ነው። ምን ያህል ብታደል ነው ይህንን አስተዋይና መልካም ልጅ ጌታ የሰጠኝ?...”
*
*

ሶስት(3) - የአውሮራ ድልድይ!
👍433
    ሳሌም ፈሪ አይደለችም። በተቃራኒው ብዙ ነገር ትደፍራለች። ነገር ግን ሰው እንደመሆኗ የምትፈራቸው ሁለት ነገሮች አሉ፦ ከፍታና ውሃ። አባቷ እንደነገራት ውሃ መፍራት የጀመረችው በህጻንነቷ ዋና ወስደዋት ለመስጠም ከቀረበ አደጋ ከተረፈች ቡሃላ ነው። ከፍታ መቼ መፍራት እንደጀመረች አታውቅም። ነገር ግን ከትንሽ የፎቅ ከፍታ ላይ ራሱ ወደ ታች ማየት ይዘገንናታል። ይህንን ፍርሃቷን ዳሪክም ያውቃል።

ሲያትል ከመጡ ቡሃላ አንድ የበጋ ቀን ዳሪክ  “….የምወድሽ ዛሬ የምወስድሽ ምርጥ ቦታ አለ…” አላት

“የት ነው የኔ መልዐክ?.”

“ሰርፕራይዝ ነው የምወድሽ!”

ዳሪክ ቦታውን አልነገራትም። በተለያዩ ባሶች እያቆራረጡ ሄዱ፦ ስርፕራይዝ የተባለው ስፍራ።

ሊደርሱ ትንሽ ሲቀራቸው “አይንሽን መጨፈን አለብሽ የምወድሽ?”

“እሺ!” ሳሌም እንደ ህጻን እየተፍነከነከች

“…መስረቅ፣ ማታለል አይቻልም የምወድሽ  ከጨፍንሽ ቡሃላ አይንሽን እንዳትከፍቺው…”

“እሺ!” ሳሌም አይኗን በደንብ ጨፈነች።

ዳሪክ እየመራ ሳሌም እየተከተለች መሄድ ጀመሩ።

“አልደረሰንም የኔ መልዐክ?.” ትንሽ እንደሄዱ

“እየደረስን ነው የምወድሽ እንዳትከፍች አይንሽን” እንዳትወድቅ ደግፎ እየመራት

“…አሁንስ?...” ሳሌም በጉጉት

“…ደርሰናል …ትንሽ የምወድሽ…”

ለደቂቃዎች ዳሪክ ሲመራ፣ ሳሌም ስትከተል ቆዩና “… አሁን ደርሰናል። የምወድሽ አሁን ተሽክሜሽ ከፍ አድርጌ የሆነ ነገር ላይ አወጣሻለሁ እሺ …እንዳትደነግጪ…”

“…እሺ!...” ሳሌም በሙሉ ልብ ተሰማማች።

ከፍ አድርጎ አወጣትና ሳሌም ወገቧን ግጥም አድርጎ ያዛት።

“የምወድሽ?”

“…ወዬ… የኔ ፍቅር?...”

“….ታምኚኛለሽ አይደል?...”

“…አዎ የኔ መልዐክ ሁልጊዜም…”

“…አይንሽን ከመከፈትሽ በፊት የኔን ድምጽ ብቻ ስሚ እንዳትፈሪ እሺ…”

“…እሺ አልፈራም…”

ዳሪክ ጥብቅ አድርጎ …ግጥም አድርጎ ይዟታል። “…የምወድሽ አሁን አይንሽ ክፈቺ….”

ሳሌም አይኗን ስትከፍት ሰማያዊው የበጋ ሰማይ ጥርት ብሎ ይታያል …. ጎንበስ ስትል ግን “…ጌታ ሆይ!...” በድንጋጤ ጮኸች። ከፍ ያለ ስፍራ ወደ ታች መሬቱ ርቆ ይታያል። ደሞ ከስር መሬት ሳይሆን የተንጣለለ ትልቅ ባህር። ሁለቱ ፍርሃቶቿ ከፍታና ውሃ በአይኖቿ ፊት ቆመዋል። የቆመችው ሲያትል ውስጥ የሚገኘው አውሮራ የሚባለ ድልድይ ጠርዝ ላይ ነው። በድልድዩ ስር የተንጣለለ ግዙፍ ሃይቅ አለ። ድልድዩ ከሃይቁ 51 ሜትር ከፍታ ላይ ነው።  “…ጌታ ሆይ!...  አውርደኝ!...  አውርደኝ!.... በጌታ… አልፈልግም!... አውርደኝ!...” ጮኸች።

“….የምወድሽ…. የምወድሽ…  ተረጋጊና ስሚኝ …ይዤሻልሁ …ልሂድ ብትይ አትሄጂም፣ በዛ ላይ የድልድዩ መከላከያ አጥር ….ከወገብሽ በላይ ነው። የኔን ብቻ ድምጽ ስሚ ተረጋጊ የምወድሽ፣ ተረጋጊና ድምጼን ብቻ ስሚ….”

“ አውርደኝ አልፈልግም “ አሁንም አምርራ ጮኸች።

ዳሪክ አልቀቃትም።“..እመኚኝ የምወድሽ አይንሽ ጨፍነሽ እኔን ብቻ ስሚኝ!”

ሳሌም አማራጭ ስታጣ የፍርሃቷን አይኗን ጨፈነች “….እሺ፣…እሺ…”

“…እመኚኝ የምወድሽ…”

“…እሺ…አምንሃለሁ የኔ መልዐክ…”

“…የምወድሽ እዚህ ያለው ጥርት ያለው ሰማያዊ ሰማይ ውሃው ላይ ሲያንጸባርቅ ውሃው ራሱ ውብ ሰማያዊ ቀለም ፈሶበት ከስር በግርማ ተዘርግቷል። ከዚህ ከፍታ ላይ ሆነሽ ስታየው ደግሞ እንዴት ያምራል መሰለሽ። የምወድሽ ይህን ውብ ትዕይንት ማየት አለብሽ። አትፍሪ እኔ በደንብ ይዤሻለሁ …የምወድሽ….”

ሳሌም ቀስ ብል አይኗን ከፈተች። ማየት ጀመረች። …ሰማያዊ ሰማይ፣ ሰማያዊ ውሃ፣ በሃይቁ ላይ የሚንቀሳቀሱ ውብ ዳክዬዎች፣ ከውዲያ ወዲህ የሚሮጡ ውብ የሚያምሩ ውብ ጀልባዎች፣ ከፊቷ ላይ ከሚፈሰው ደስ የሚል ስስ ነፋስ ጋር  ቀኑ ህይወት ያለው…. ህይወት  ህይወት የሚል ምርጥ የበጋ ቀን ነው። ዳሪክ እውነቱን ነው ሳሌም ቀስ በቀስ ተረጋጋች። ቆይታም ከፍርሃቷ ነጻ ወጣች። ቆማ ማየት ጀመረች “…ሲያምር..” እያለች … ቆይታ ክንዶቿን ዘረጋች እንደሚበር ነጻ እንደወጣ ርግብ፣ ጸጉሯ በንፋሱ ብትን እያለ ወደ ኋላ መርገብገብ ጀመረ  “…ህይወት ያለ ፍርሃት እንዴት ቆንጆ ናት?...”  እያለች ….እዛው  ሆና እጇን ዘርግታ ነፋሱን ማጣጣም፣ ዙርያዋ ያለውን ውብ ትዕይንት ለአይኗ መመገብ ቀጠለች።

ዳሪክም በደስታ “… የምወድሽ…”

“…ወይዬ የኔ መልዐክ?...”

“…አየሽ የምወድሽ አንዳንዴ የምትፈሪያቸው ነገሮች ራሳቸው እጅግ አስደሳች ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ከዚህ ከፍታ ላይ ሆነሽ ውሃውን ስታየው ደስ አይልም የምወድሽ?...”

“…ደስ ይላል… የኔ ቆንጆ…”

በአንድ ቀን የሳሌም ሁለት ፍርሃቶች …ከፍታና ውሃ … ከልቧ ውስጥ ተባረሩ።
*
*

አራት (4) - የነፍስ ካንሰር

ከሶስት አመት በፊት…

ቦሌ ጫፍ ላይ ያለችው ትንሽ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብለዋል፦ ሳሌምና ዳሪክ። ዳሪክ ያወራታል። ሳሌም ትሰማዋለች። እንደ ሁልጊዜውም ዳሪክ በመስማት ሃሴት ታደርጋለች፦ሳሌም።

“…የምወድሽ ዛሬ ሴል ባዮሎጂ ላይ ምን እንዳነበብኩ ታውቂያለሽ?...”

“…ምን አነበበክ የኔ መልዐክ?..”

“…ስለ ካንሰር የምወድሽ…”

“…አስትሮሎጂ ማንበብ ጀመርክ እንዴ የኔ ቆንጆ?...”

“…ኖኖ…ስለ ኮኮብ ቆጣሪው ካንሰር አይደለም የምወድሽ…” ዳሪክ እየሳቀ “…ስለ ካንሰር በሽታ ነው…”

ሳሌም የገመተችው ካንሰር ዳሪክ ከሚለው ካንሰር መራቁን ስታስብ እሷም ፈገግ አለች። “…እሺ ስለ ካንሰር  ምን አነበብክ የኔ መልዐክ እስኪ ንገረኝ?...”

ዳሪክን የሚለውን መስማት ደስ ይላታል። ቁም ነገር አለው። ህይወት ይፈስበታል። “..ንገረኝ  የኔ ቆንጆ?...”

የሳሌም ጆሮዎች ነቅተው ሲያዳምጡት፣ ከልቧ ስትሰማው ዳሪክ ደግሞ በደስታ ያወራላታል።

“…ታውቂያለሽ የምወድሽ ካንሰር በራሱ በሽታ አይደለም።…”

“…አይደለም? እንዴት?...” ሳሌም ተደንቃ

“…አይደለም… ካንሰር የሆነ ባክቴሪያ ወይም ቫይረስ አይደለም የምወድሽ። ካንሰር የራሳችን ሴሎች (ህዋሳት) ከመጠን በላይ ሲባዙ ነው። ሰውነታችን የራሳችን ህዋሳትን ከልክ ባለፈ እንዳይባዙ የሚቆጣጠርበት (ምልክት) አለው፣…ልክ እንደ ትራፊክ መብራት ያለ።…አለ አይደል ትክክለኛው መጠን ላይ ሲደርስ ቀይ አብርቶ አቁም የሚል ምልክት ሰውነታችን አለው።  አንዳንድ ጊዜ የሰውነታችን ህዋሳት ምልክቱን ሳይሰሙ(ወይም ምልክቱ ሲጠፋ) ዝም ብለው ይባዛሉ። ከመጠን በላይ ሲባዙም ካንሰር ይሆናል። የራሳችን ሴሎች ተባዝተው፣ ተባዝተው የራሳችንን ሰውነት ጤና ያስተጓጉላሉ። ሞት ይመጣል።….”

“….ዋው ይገርማል የራሳችን ሴሎች ብዜት?...” ሳሌም እጇን አፏ ላይ ጭና

“…ስለ ሰውነታችን ካንሰር ሳነብ ምን ትዝ አለኝ መሰለሽ የምወድሽ…”ዳሪክ ቀጠለ  “…ትዝ ያለኝ ሌላኛው ካንሰር ነው…”

“የትኛው ሌላ ካንሰር የኔ መልዐክ?”

“ የነፍስ ካንሰር!” ዳሪክ ፊቱን አጨፍግጎ።

“ም…………….ን?” ሳሌም ፊቷን አኮሳትራ “የነፍስ ካንሰር ደሞ ምንድን ነው የኔ መልዐክ?...”

ዳሪክ ፈገግ ብሎ የሳሌም አይኖች ትኩር ብሎ ተመለከተ፦ ነፍሷን የሚያይ ይመስል።
👍37🔥1
“…አየሽ የምወድሽ ሳስበው ሰውነታችን የራሱን ህዋሳት እንዳሉት ሁሉ ነፍሳችንም የራሱ ህዋሳት ያሉት ይመስለኛል። እነዚህ የነፍሳችን ህዋሳት ሃሳቦች ይባላሉ። ልባችንን የሚሞሉት፣ በአእምሮ አችን የሚመላለሱት ሃሳቦች። ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ እምነት፣ ሌሎችን ማገዝ፣ መርዳት የመሳሳሉት መልካም ሃሳቦች(መልካም የነፍስ ህዋሳት) ናቸው። በዛ በተቃራኒ ደሞ ጥላቻ፣ መራርነት፣ ጸብ፣ ቂም፣ ይቅር አለማለት ደሞ ሌሎች ሃሳቦች (ክፉ የነፍስ ህዋሳት) ናቸው።…”

ዳሪክ ላፍታ መናገሩን አቆመና የሳሌምን እጆች ያዛቸው። “…የምወድሽ የኔ ቆንጆ ስሚኝ … ለነፍሳችን ካንሰር የሚሆነው፣ ነፍሳችን የምትታመመው ሌሎችን መጥላት ስንጀምር ነው። የቂም ሃሳብ ካለ መጠን ሲበዛ፣ ይቅር ማለት ሳንችል ስንቀር፣ ልባችን በብዙ የክፋት እሳቤ ሲሞላ…ነፍሳችን ያኔ በነፍስ ካንሰር ተጠቂ ትሆናለች። ነፍሳችን ትታመማለች። የነፍስ ካንሰር የሚሆነው የክፋት ሃሳቦች ሲበዙና ልባችንን በሙልዐት ሲቆጣጥሩት ነው።  የሁሉ ክፋት መሰረት ደግሞ ጥላቻ፣ ቂምና ይቅርታ አለማድረግ ነው።…የምወድሽ ምንም ቢሆን ምንም ሰውን ሁሉ ውደጂ እሺ፣ ካለ ምንም ምክንያት ሳቂ እሺ፣ ዝም ብለሽ ይቅርታ አድርጊ እሺ … ሁሉንም ይቅር በይ የምወድሽ…”
 
ሳሌም የዳሪክን እጆች ጥብቅ አድርጋ ትይዛለች። “…እሺ!... እሺ!... እሺ!... የኔ መልዐክ እንደዛው አደርጋለሁ። የእውነት መልካሙን የምታሳየኝ፣ ጌታ የሰጠኝ መልዐኬ ነህ እኮ…”

ዳሪክን እያየች  ታስባለች ... “…ጥበብ፣ መልካምነትና ማስተዋል እንዴት እዚህ ልጅ ላይ ፈሰዋል። ታድያለሁ እኮ!… ታድዬ!...ታድዬ!...”

የዛን ቀን ሳሌም ሰለ ዳሪክ ፍቅርና ቁምነገር እንዲህ ስትነግረኝ ቆይታ አራተኛው ደርዝ፣የነፍስ ካንሰር ላይ ስትደርስ የሆነ ነገር ትዝ ያላት ይመስል ትክ ብላ በትላልቅ አይኖቿ ታየኝ ጀመር።

“ሴለም ምነው?” ጠይቅኳት

“ምንም ሳዬ.…አንድ ነገር ትዝ ብሎኝ ነው” ወዲያውኑ አይ ፎኗን አውጥታ የሆነ ነገር መፈለግ ጀመረች። አስር ደቂቃም ሳትቶይ ስልኳን በጆሮዋ ላይ አድርጋ “ ሃሎ” እያወራች ከክፍሉ ወጣች።

እዛች ትንሽ ክፍል ውስጥም እኔና በተለያዩ የህክምና ማሽኖች የተከበበውና በዚች ምድር ላይ ሊቆይ ምናልባትም 48 ሰዓታት ያህል የቀረው ሳቂታው፣ቁምነገረኛውና አፍቃሪው ዳሪክ ቀረን።

የተከደኑት የዳሪክ አይኖችን እያየሁ ስለ ዳሪክ ቁም -ነገርና ጥበብ እንደገናም ስለ ሁለቱ 'ርግቦች የማይነጥፍና ጽኑ ፍቅር በልቤ እያሰብኩ እንዳለም....ሳሌም በሩን ከፍታ ገባችና

“ሳዬ ነገ አንድ ቦታ አብረሽኝ ትሄጃለሽ?” አይን አይኔን እያየች በልመና ጠየቀች።
*
*

ይቀጥላል.....

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍489👏1
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ከሌላ ፕላኔት የመጣ ፍጡር ይሆን እንዴ?›› ስል አሰብኩ፡፡ መጨረሻዬም አጓጓኝ፡፡ በዚህ ቅፅበት እጁን ወደ ጃኬት ኪሱ ሲሠድ በጨረፍታ ተመለከትኩ፡፡ ብሞት ግድ የሌለኝ መስሎ ይሠማኝ ነበር፡፡ ይህቺን አለም ገና እንዳልጠገብኳት የተረዳሁት ግን በዚህ ክስተት ነው፡፡የሚያብረቀርቅ ጩቤ አወጣ ፤የራሱን እጅ በጭካኔ ሸረከተው፡፡ ደሙ መስመር ሰርቶ መንጠባጠብ ጀመረ፡፡ የተለያዩ ህብረ - ቀለማት አይኖቼ ላይ ተመላለሱብኝ፤ቀስ በቀስ ከማንነቴ እየተነጠልኩ..እየተፋው ሲሄድ ይታወቀኛል፡፡

ወደ ጥልቅ ገደል እየተንሸራተትኩ ምጓዝ

መስሎ ተሠማኝ፡፡

ለምን ያህል ጊዜ እራሴን ስቼ እንደቆየሁ ትዝ አይለኝም፡፡ አይኖቼን በፍራቻ ስከፍታቸው ባዶ ክፍል ውስጥ ባዶ ሆኜ ብቻዬን ነው ያለሁት፡፡ ዙሪያ ገባውን በጥንቃቄ ቃኘሁ፡፡ የቤቱ ግድግዳ በቀይ ቀለም ተዥጎርጉሯል፡፡ ፅሁፍ ነው፡፡ የሚነበብ ፅሁፍ፡፡ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ ‹‹አፈቅርሻለሁ...አምርሬም እጠላሻለሁ›› የሚል ፅሁፍ አነበብኩ፡፡አይኖቼን ወደ ራቁት ሠውነቴ ስመልስ እንደ ግድግዳው በፅሁፍ ሳይሆን በምልክት ተዥጎርጉሯል፡፡ ሁለቱ ጡቶቼ የራይት ምልክት አለባቸው፣ እንብርቴ አካባቢ የኤክስ ምልክት ይታያል፡፡ግራ ገባኝ እስከዛን ግዜ እጆቼ እንደተጠፈሩ አፌ እንደተለጎመ ነበር፤ የተለየው ነገር የአእምሮዬ በመጠኑ መረጋጋት ነው፡፡ እጁን ሲቆርጥ ያየሁትን ምስል ወደ ኃላ ተመልሼ ሳስታውስ ይሄ ሁሉ ግድግዳው ላይና ሠውነቴ ላይ ያቀለመው በራሱ ደም እንደሆነ ገባኝ፡፡ ሠውነቴ ላይ ያረፉት የራይትና የኤክስ ምልክቶች ፍቺ ግን በቀላሉ ሊገለፅልኝ አልቻለም፡፡እንደ ድንገት ወደ ጎኔ ስዞር በቀኝ  በኩል በሚገኘው ግድግዳ ላይ ሌላ ፅሑፍ አነበብኩ፡፡

‹‹40 ፐርሰንት ብቻ ከእሷ ጋር ትመሳሰላለች፡፡ ስለዚህ አትወክላትም... ያበሳጫል...ይቺን መግደል ትርጉም አይሰጥም፡፡›› ይላል... ዳግመኛ አዞረኝ፡፡ የሚገላትን ሴት በመፈለግ ላይ ያለ ወፈፌ ነው ያጋጠመኝ፡፡ የምልክቶቹም ፍቺ ተገለፀልኝ፡፡ ከሚያውቃት ወይም ካስከፋችው ሴት ጋር እያመሳሰለኝ ነበር፡፡ እየተንፏቀኩ ሄጄ በራፉን በደከመ ጉልበቴ ደበደብኩ፡፡ ዘበኛው ሠምቶ ከፈተልኝና ከእስራቴ ነፃ አደረገኝ፡፡እየተንቀጠቀትኩ ልብሴን በመልበስ ላይ ሳለው ቅድም ያለየሁት ሌላ ምልክት ብልቴ አካባቢ አየሁ፡፡ ጥያቄ ምልክት አስቀምጦበታል፡፡ ኮንትራት ታክሲ አስጠርቼ እቤቴ አደረሠኝ፡፡ እቤቴ ስገባ ልክ ከለሊቱ ስምንት ሠዓት ነበር፡፡ ሠውነቴን ታጠብኩ፡፡ከፍራቻዬ ለመገላገል ለሊቱን ሙሉ ስጠጣ አደርኩ፡፡ እያነበበችለት ያለውን ዲያሪ አጥፋ እያስቀመጠች.....ይሄው ነው አለችው፡፡

በጉንጮቹ ላይ ያለ ፍቃድ የወረደ እንባውን እየጠረገ ‹‹ልብ ወለድ ነው እውነት?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ልብ ወለድ በዲያሪ ይፃፋል እንዴ?››

‹‹በቃ ምንም አላውቅሽም ነበር ማለት ነው….? እራሴን አመመኝ ልሂድ፡፡›› በማለት ከመቀመጫው ተነሳና ግንባሯን በመሳም ተሠናብቷት ወጣ፡፡ እሷም በተቀመጠችበት በስስት በሚንከራተቱ አይኖቿ ሸኘችው፡፡

የሠጠችውን ፖስታ ለመቅደድ እቤቱ እስኪደርስ አላስቻለውም፡፡ ከሠፈሩ ትንሽ ወጣ እንዳለ ነበር ወደ አንድ ሆቴል ጎራ በማለት መኪናውን አቁሞ ከውስጥ ሳይወጣ የከፈተው፡፡ የሚያየው ነገር ግራ ገብቶታል፡፡ አንድ ወረቀት እና መዓት ብሮች! ባለ መቶ፤ሃምሳ እና አስር ብር በየመጠናቸው ለየብቻ በብር ላስቲክ ተጠፍንገው እጁ ላይ ተዘረገፉ፡፡ብሮቹን ትቶ ወረቀቱን አነሳና ማንበብ ጀመረ፡፡

‹‹አንተን ከመጀመሪያ ጀምሬ የቀረብኩህ ሸርሙጣ ስለሆንኩ ሳይሆን ስለማፈቅርህ ነው፡፡ ብር የምቀበልህ ከአንተ ፍቅር እንደያዘኝ በፍፁም እንድታውቅ ስለማልፈልግ ነበር፡፡ ቢሆንም ብሩን ተጠቅሜው ቢሆን ኖሮ ፍቅር ሳይሆን ሽርሙጥና ይሆን ነበር… እና ለሁለት ዓመት ደንበኛዬ ነበርክ፡፡ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ አርባ ዘጠኝ ቀን አብረኸኝ አድረሀል፡፡

ከዚህ ውስጥ አስራ አምስቱን ቀን ብር ስላልነበረህ አልከፈልከኝም፡፡

ለዘጠኝ ቀን -> 5ዐዐ ብር ከፈልከኝ  500×19  9500 ብር ይሆናል

አስራ ሁለት ቀን  4ዐዐ ብር ከፈልከኝ  400×12  4800 ብር ይሆናል

ሦስት ቀን  15ዐ ብር ነው የከፈልከኝ 150x3  45ዐ ብር ይሆናል፡፡ እንግዲህ በድምሩ አስራ አራት ሺ ሰባት መቶ ሃምሳ ብር መሆኑ ነው፡፡ ይሄ ብር እንግዲህ ለመውጫ የምትከፍለውን አርባ.. አርባ ብር አያጠቃልልም፡፡ ቻው፡፡›› ይላል፡፡

አንብቦ ሲጨርስ ወረቀቱን ጨምድዶ አፉ ውስጥ ከተተው፤አኘከው..አደቀቀው  አልተፋውም፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ሠዓቱ ከምሽቱ 2፡30 ሆኗል፡፡ ሠሎሞንና ኤደን ቦሌ በሚገኘው ታዋቂው አቢሲኒያ ሬስቶራንት እራት በአክሱማይት ወይን እያወራረዱ በመመገብ ላይ ናቸው፡፡ የተገናኙት በቀጠሮ አልነበረም፡፡ ሁለቱም በጋራ የሚያውቁት ሠርግ ላይ በመታደማቸው ነበር ድንገት የተገጣጠሙት፡፡ ሠሎሞን እንደ ወትሮው ሙሉ ሱፍ ከሠማያዊ ሸሚዝና ጥቁር መደብ ኖሮት በነጭ መስመር ከተዥጎረጎረ ክራባት ጋር ለብሶ ሙሽራ ባይሆንም ሚዜ መስሏል፡፡

ኤደንም ከሱ ባልተናነሰ ሁኔታ ዘንጣለች፡፡ ጥቁር ቀለም ያለው ከጉልበቷ በላይ የሚቀር ጉርድ ቀሚስ ለብሳለች፣ ከላይ ከሠውነቷ ጋር የተጣበቀ ሮዝ ከለር ያለውና የጡቷን ቅርፅ የሚያጎላና ግማሽ የሚሆን የጀርባዋን ክፍል አጋልጦ የሚያሳይ ‹ፓክ አውት›
ለብሳለች፣ጆሮዋ ላይ ያንጠለጠለችው ጌጥ አርቲፊሻል ቢሆንም ለውበቷ የራሱ የሆነ ድርሻ
ነበረው፣በፊትም ጎላ ጎላ ብለው ሚታዩ አይኖቿን በስሱ ተኩላቸው ይበልጥ ቀልብ ሳቢ ሆነዋል፣የፀጉር አሠራሯም ልዩ ነው፡፡

‹‹ቬሎ ስላለበሽ ነው እንጂ ሙሽራዋ እኮ አንቺ መስለሽኝ ነበር፡፡››

‹‹ኧረ ባክህ! ለእንደዛ አይነት ወግማ መች ታደልን፡፡››

‹‹ምን ማለት ነው?›› አላት ሠሎሞን በግራ እጁ አንገቱ ላይ የተሸመቀቀውን ክራባት እያላላ፡፡

‹‹እብድ አፍቅረን ከእሱ ጋር ስንጃጃል ውዱ ጊዜያችን በከንቱ አልፎ በፈነዳንበትም ወቅት የነበረንን አንፀባራቂ ውበት መጠቀም አቅቶን ዛሬ ከጠወለግን በኃላ ካንቀላፋንበት ስንባንን ረፍዶብን አገኘነው...ምን ማድረግ እንችላለን፤ አረጀን! ማን ይፈልገናል፤ ያው ቆመን መቅረታችን ሳይሆን ይቀራል?›› ትካዜዋን
ከቆነጠረችው ምግብ ጋር ወደ አፏ ልካ አላመጠችው፡፡

ሠሎሞን መናገር ጀመረ ‹‹ለመሆኑ ፊትሽን የምትመለከቺበት መስታወት ቤትሽ የለሽም እንዴ? የአስራ ስድስት አመት ልጃገረድ ነኝ ብትይ እኮ ማንም የሚጠረጥርሽ አይኖርም ፤‹ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ሆኖ ነው እንጂ› መች ላንቺ የሚሆን ባል ጠፋ ብለሽ ነው ... ለማንኛውም ምግቡን ብይ፡፡››

<<ባክህ በቃኝ::>>

‹‹ምነው?መች ተነካና?››

‹‹ግድ የለህም ይብቃኝ.... ባይሆን ወይኑን እደጋግማለሁ፡፡››

‹‹ኧረ ይቻላል! በስንት ወራችን እኮ ነው የተገናኘነው፤ዛሬማ መላቀቅ የለም፡፡››

‹‹ተስማምቼያለሁ፡፡›› አለች ኤደን የወይን ብርጭቆዋን አንስታ እየተጎነጨችለት፡፡
ሠሎሞን የዘወትር ገረሜታው አሁንም እንደገ አገርሸቶበት የኤደንን ውበት በጎሪጥ እየቃኝ በውስጡ ያብሠለሠላል፡፡
👍8810👎3😁3
<<የሠው ፍላጎት እንዴት ነው የተዘበራረቀው? ይህቺን የመሠለች ውብና አፍቃሪ ሴት ገፍቶ እንዴት የማያውቃትን ሴት አፍቅሬያለሁ ብሎ ይሄን ያህል ይሠቃያል?እዚህ አጠገቤ ያለችው ኤደን ምን ይጎላታል? መልክ አላት፣ ፀባይ አላት፣ ብር አላት ... ከዚህ በላይ ምን ማሟላት ይጠበቅባታል?››ከወራት በፊት ስለዚህ ጉዳይ ሁሴንን ጠይቆት የመለሠለት መልስ ትዝ አለውና ፈገግ አለ፡፡

‹‹ወረት ነው አይደል እንዲህ የሚያንቀዠቅዠህ? አጠገብህ በጣም የሚያፈቅሩህ ሴቶች እያሉልህ አንተ ሌላ የማታውቃትን አየር የሆነች ልጅ ፍለጋ ምትሠቃየው?›› የሚል ጥያቄ ነበር ያቀረበለት፡፡

‹‹ትክክለኛ ሄዋኔን ፍለጋ ላይ ነኝ፡፡›› ብሎ መለሠለት፡፡

‹‹ታዲያ እነሱስ ሄዋንህ መሆን አይችሉም?››

‹‹አይመስለኝም፡፡ አየህ የሠው ልጅ አፈጣጠርን መለስ ብለን ስንመለከት

እግዚአብሔር መልኩን ወይም መሠሉን ማየት
ፈለገና ጭቃ አድቦልቡሎ እስትንፋሱን እፍ አለበትና አዳምን ፈጠረው፡፡ ልብ በልልኝ ለአዳም መፈጠር ዋናው ምክንያት እግዚአብሔር በአዳም ውስጥ የራሱን መልክ
ለማየት ስለፈለገ ነበር፡፡በሌላ አነጋገር አዳም
የእግዚያብሄር መስታወት ነው ማለት ትችላለህ፡፡ ቆየት አለና አዳም ደበረው፤ በብቸኝነቱ አጉረመረመ፤
እግዚአብሔርም ሠማው፤ እንቅልፍ ጣለበትና ከግራ ጎኑ አንድ አጥንት መዘዘና ሄዋንን አበረከተለት፡፡ የሄዋን የመፈጠር ምክንያት ደግሞ ምንድነው ?ብትለኝ የአዳም ድብርት ውስጥ መግባት ነው፡፡ አዳም ባይደብረው
እግዚአብሔር ሄዋንን ለመፍጠር ሀሳብ አይመጣለትም ነበር፡፡ወደ ነጥቤ ልመልስህና
በእያንዳንዱ አዳም የግራ ጎን ከእኔ እና ከአንተም ጭምር እግዚአብሔር አንድ አንድ አጥንት ወስዶ አንድ አንድ ሴት ፈጥሮልናል፡፡

ፍቅር የሚባለው ነገር ምን እንደሆነ ታውቃለህ

?ያለ ፍቃድህ ከግራ ጎንህ በእግዚአብሔር የተወሠደብህን የራስህን አጥንት ለማስመለስ
የምታደርገው ውጣ ውረድ ነው፡፡ ታዲያ ብዙውን ጊዜ ፍቅር እንከን የተሞላ የሚሆነው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?ክህደት፣ ውስልትና፣ፍቺ የመሳሰሉት ለምን እንደሚከሰቱስ
ይገባሀል? አንዷን በአጋጣሚ ትቀርባታለህ፤ ይህቺ ከእራሴው አጥንት
የተሠራች ነች ብለህ ትወስናለህ ፡፡አፈቀርኩሽ
ትላታለህ…ታገባታለህ፡፡ አሁን ሙሉ ሠው ነኝ፤
ሙሉ አካልም አለኝ የተወሠደብኝን የግራ ጎኔን
መልሻለሁ ብለህ ትኩራራለህ፡፡ ጥቂት ቆይቶ
ግን ያ አጥንት ካንተ ጎን የተወሠደ ሳይሆን ከሌላ አዳም ጎን የተወሠደ ሆኖ ይገኛል፡፡ ያ ማለት አጥንቱ አንተ ላይ በትክክል ገብቶ
አይገጥምም ማለት ነው፡፡ ወይ ይሠፋል  አሊያም ይጠባል፤ወይ ያጥራል ወይ ደግሞ ይረዝምብሀል፡፡ ያ ደግሞ ምቾትህን ይነሳሀል፡፡ በሽተኛ ያደርግሀል፣ ይቆረቁርሀል፣ይጎረብጥሀል፤ በመጨረሻ ስቃዩ ሲበዛብህ ያ ቦታ እንደድሮ ባዶ ቢሆን ይሻለኛል ብለህ ትወስናለህ፡፡ አውጥተህ አሽቀንጥረህ ትጥለዋለህ ሌላ ያንተኑ ትክክለኛ ግጣምህን ፍለጋ ዳግመኛ አንድ ብለህ መኳተን ትጀምራለህ፡፡….እና
ማጠቃለያዬ ምን መሠለህ ፤የራሴውን አጥንት እንዳገኘሁ እርግጠኛ እስክሆን ድረስ ተረጋግቼ መቀመጥ አልፈልግም፡፡ ካለበለዚያ ያ ያንተ ዕጣ ነው የሚደርሠኝ፡፡›› በማለት ነበር ያስረዳው፡፡ በትውስታው ፈገግ ብሎ ወደ ሌላ ትካዜ ሊሸጋገር ሲል የኤደን ጥያቄ መለሠው፡፡

‹‹ልጆችህ ደህና ናቸው?››

‹‹ደህና ናቸው፤ እግዜር ይመስገን፡፡››

‹‹የውብዳርስ?››

‹‹እኔ እንጃላት፡፡››

‹‹እንዴት እኔ እንጃላት ... ?ወንዶች ስትባሉ በቃ ሁላችሁም አንድ አይነት ናችሁ? ሴትን ልጅ ቀምሳችሁ... ልሳችሁ ጣዕሟን ከጨረሳችሁ በኋላ ተፍታችሁ ከአፈር ስትደባልቁ ጥቂት እንኳን ፀፀት አይሠማችሁም? ግርም የሚለኝ እግኢአብሔር ለምን እናንተን እንደፈጠራችሁ ነው>>

‹‹የፈጠረንማ አንደኛ አቶ ሁሴን እንደሚለው መልኩን በእኛ በኩል ለማየት ነው፤ምክንያቱም እኛ እሱን እንመስላለን፡፡ ሁለተኛው ምድርን እንድናስተዳድርለት ነው፤ሦስተኛው እንድናመሰግነው ይመስለኛል፡፡ እንደ እኔ ሦስተኛው ብዙም የተሳካ አይመስለኝም፡፡ እናንተን ከፈጠረ በኋላ አይናችንን ወደ ፈጣሪ እንዳናነሳ እንቅፋት እንደሆናችሁን ነው የምረዳው፡፡›› ሁለቱም ምግቡን ስላቆሙ አስተናጋጅ መጥቶ መአዱን አነሳና ጠረጴዛውን አፀዳዳው፡፡...

ይቀጥላል

#ድርሰቱ ለምንድን ነው ቶሎ ቶሎ የማይለቀቀው የሚሉ ጥያቄዎች ይመጣሉ ጥሩ ጥያቄ ነው ቶሎ ቶሎ መለቀቅም አለበት ነገር ግን ይሄን ጥያቄ ከምጠይቁት መሀል ምን ያህሎቻቹ   #የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ  አድርጋችኋል ሁሉም ሰው #ሰብስክራይብ ያድርግ አደለም  ነገር ግን ድርሰቱን ከሚያነበው መሀል Post ሲደረግ ቢያንስ አምስት ሰው እንዴት ይጠፋል ከ 100000 ምናምን ሺ ሰው መሀል ማለት ነው እስቲ አሁንም በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #አድርጉ እኛም ሞራል አግኝተን ቶሎ ቶሎ እንልቀቅ
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍11413👎5👏1
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል አስራ አራት:- ጆ ካርሎስ ሬይስ
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር

የሚያምር ብሩህ ቀን ነው። የፀደዩን መምጣት ለማበሰር ጸሐይ አምሮባት፣ ተሞሽራ ብቅ ብላለች። ሙሽራዋ ጸሀይም በሚዜዎቿ ጥርት ባለው ሰማያዊ ሰማይና በስሱ በሚነፍሰው ነፋስ ታጅባለች። ደስ የሚል ውብ ቀ..........ን!

በተሳፈረንበት ትራንዚት ባስ የፊት መስታወት ሳየው መሃሉ በቢጫ መስመር የተከፈለው አስፓልት መንገድ እስከ አድማስ ጥግ የተዘረጋ ይመስላል። ከመንገዱ ግራና ቀኝ ያለው ልምላሜ፣ ከብሩህ የማለዳ ብርሀን ጋር ቀኑን የበለጠ አስውቦታል።

ከሲያትል ከተማ ወጥተን እየተጓዝን ነው ፦ ሳሌምና እኔ። አብረን እንድሄንድ ከመጋበዝ ውጪ፣ የት እንደምንሄድ ምንም የማውቀው ነገር የለም። የዚህ ጉዞ ፕሮግራም የተያዘው ትላንትና በፍጥነት ነው። ሳሌምን ደጋግሜ የጉዞችንን ስፍራና አላማ ብጠይቅም ሳሌም ልትነግረኝ አልፈቀደችም።

"...ሰርፕራይዝ ነው ሳዬ፣ የምሄድበት የራሴ ጉዳይ ስላለኝ ነው… የምሄድበት ስፍራ የምፈጽመው፣ የማደረገው የራሴ ጉዳይ ስላለኝ ነው…አብረሽኝ እንድት ሆኚ ፈልጌ እኮ ነው።…” በቃ ሳሌም ያለችኝ ይህንኑ ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜ ዳሪክን ትታ ስትሄድ '...የት ይሆን?..' ብዬ ማሰቤ ባይቀርም ግን ሳሌምን አምኜ እየሄድን ነው። ስለ እውነትም  ብቸኛ እህቴን የሆንችልኝን ሳሌምን አምናታለሁ። የትም እንሂድ ብትለኝ እከተላለሁ። 

ስለዚህም እየተጓዝን ነው፦ ከከተማ ወጥተን። እየሄድን ነው፦ ላለፉት ሁለት ሰዐታት። እየገሰገስን ነው፦ ወደ ማላውቀው ስፍራ። ወደፊት፦ ሳሌምና እኔ

ጎን ለጎን ቁጭ ብለን፣አንድ የአይፎን …ኤር ፎን ተጋርተን ሁለታችንም ባ’ንድ አንድ ጆሮችን መዝሙሮችን እንሰማለን…

ሀና ተክሌ ፦
ሰው መሆኑን አይደል ፡ ልብሱን ፡ አከበረ
ሰው  በገንዘቡ ልክ ወዳጅ አስቆጠረ (አቤት ፡ አቤት)
ምስኪኑ ሲመጣ አጥቶ የሚቀምሰው
የሚቀርበው ጠፍቶ  ፍቅር እንኳን ከራቀው
አቤት  አቤት አቤቱ ምን አልከው
                      
ደሞ አውታሩ፦  ይቅርታ.. ይቅርታ...የኔ አባት ይቅርታ…

መዝሙሮቹ አንዱ አልቆ ሌላው እየቀጠለ…በጆሮችን እየፈሰሱ… ጉዞችንን ወደ ፊት ቀጠልን።

…ከሶስት ሰዐታት ጉዞ ቡኋላ መንገዶችን አቆራርጠን መጨረሻ ላይ ሳሌም የምትወስደኝ ቦታ ደረስን። ጠዋት በማለዳ በመነሳቴ ወደ ጉዞው መጨረሻው ላይ እንቅልፍ ሸለብ አድርጎኝ ነበር። ስንደርስና ሳሌም ስትቀሰቅሰኝ ተንስቼ አካባቢው ቃኘሁ። ምንም አይታየም።  ከባሱ ስወርድ ያየሁት ምንም በሌለበት ምድረበዳ ላይ የተገነባ መጨረሻው የማይታይ ግዙፍ ግቢ ነው። የግቢው አጥር በረጃጅም የሽቦ አጥሮች ታጥሯል።

በመግቢያው አቅጣጫ የተጻፈውን ሳነብ '...ኮይተን ሪድጅ ኮሬክሻናል ፋሲሊቲ...' ይላል። እስር ቤት ነው።

“…ሴለም እስር ቤት ምን እናደርጋለን?...የታሰረ ዘመድ አለሽ እንዴ?...” ወደ ሳሌም ዞሬ ጠይኩኝ

“…ሳዬ ዝም ብለሽ ተከተይኝ …ሰርፕራይዝ አይደል?...” ወደ መግቢያው ስትሄድ ከኋላዋ ተከተልኩኝ።

በሩ ላይ ስንደረስ በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ ሁለት ወታደሮች ቀረቡን።

“….እንደምን አረፈዳችሁ ወጣት ሴቶች?..” አንደኛው ሰላምታ ሰጠ

ሳሌም ለሰላምታው መልስ ሰጠች።

“…ወደ ሲ አር ሲ ሲ (CRCC) ምን አመጣችሁ?...” ከሰላምታው ቀጥሎ ጠየቀ።

“…የምንጎበኘው ሰው አለ!...” ሳሌም መለሰች።

“…የጉብኝት ወረቀቶቹን ሞልታችኋል?...”

“…አዎ… በሚገባ! " ሳሌም ባግ ፓኳን አውርዳ ሁለት ወረቀቶች ሰጠችው።

“…የመንጃ ፈቃድ ወይም የመታወቂያ ካርድ?...”

“…ሳዬ መታወቂያሽን ስጪው…” ብላ ሳሌም የመታወቂያ ካርዷን አውጥታ ሰጠች።

“…የያዝኩትን ባግ ፓክ አውርጄ ከውስጡ ዋሌቴን አወጣሁ፣ ከዛም መታወቂያዬን።…” እጄ እንደመንቀጥቀጥ ያለ መሰለኝ።

ፖሊሱ ከመታወቂያችን ላይ ያለውን ፎቶ ግራፍ ከመልካችን ጋር ካነጻጸረ ቡሃላ መታወቂያችንን መልሰልንና ደረቱ ላይ ባለው መነጋገሪያ የመግቢያው በር እንዲከፈት መልዕክት አስተላለፈ። ግዙፉ በር እየተንፏቀቀ ተከፈተ። ግቢው ውስጥ ገባን። በሚቀጥሉት ጥቂት ደቂቃዎች ቦርሳችንን ውስጥ ያለው ንብረት አስቆጥረን ማስቀመጫ ሴፍ ውስጥ አስቆለፍን። የእጆቻን አሻሮች በኮንፒውተር ምስላቸው ተነስቶ፣ የጎብኚዎችን የይለፍ ካርድ ባንገታችን ላይ አንጠለጠልንና ወደ መጎብኚያው ክፍለ ካ’ንድ ፖሊስ ጋር መሄድ ጀመርን።

በረጃጅም የሽቦ አጥር በታጠረው የእስር ቤት የግቢ ኮሪደር መሰል መንገድ እየሄድን አብሮን ያለው ፖሊስ ያወራን ጀመር።

“..ጄ..ሲ አርን ለማየት ነው የመጣችሁት…?

“…ይቅርታ ማንን ነው ያልከኝ?...” ሳሌም መልሳ ጠየቀች

“…ማለቴ ጆ ካርሎስ ሬይስ…  እኛ እዚህ ጄ…ሲ..አር ነው የምንለው…”

(….ጆን ካርሎስ ሬይስ ስሙ አዲስ አልሆነብኝም። ማን ነበር?...) ማሰብ ጀመርኩኝ።

ሳሌምና ፖሊሱ ማውራት ቀጠሉ።

“…አዎ እሱን ነው…” ሳሌም መለሰች።

(…..ጆ ካርሎስ ራይስ?... ጆ ካርሎስ ራይስ?...ማን ነበር??....) እኔ አስባለሁ

“…ይገርማል?.. እዚህ ከገባ ጀምሮ ሰው ሲጎበኘው አይቼ አላውቅም። ወዳጆች ናችሁ?...”

“…እህቶቹ ነን…” ሳሌም ባጭሩ

(….ጆ ካርሎስ ራይስ??? …ጆ ካርሎስ …) ስሙንና መልኩን በአእምሮዬ ለማምጣት እየታገልኩ

“…እህቶቹ?...” ፖሊሱ ለማረጋገጥ ጠየቀ

“….ማለቴ በመወለድ ሳይሆን…  የመንፈስ እህቶቹ ነን። ሁላችንም የሰው ልጆች ነን። ቤተሰቦች ነን።….” ሳሌም እያብራራች
  
(…ጆን ካርሎስ ራይስ???....) ድንገት ስሙና መልኩ ሲመጣልኝ…ሲገጣጠሙልኝ

በድንጋጤ ቆምኩኝና ጮህኩኝ። “….አንቺ ሴሌም ጆን ካርሎስ ሬይስ?...”

ዞራ ስታየኝ ሰውየውን እንዳስታወስኩት ገባት። “….ሳዬ ፕሊስ በ’ናትሽ …እመኚኝ ማድረግ ያለብኝን ነው የማደረገው። ዝም ብለሽ ተከተይኝ..."

አፌ ደረቀ። አቅለሸለሸኝ። ደረቴ ላይ የሆነ ነገር መጥቶ ሲወተፍ የማስመልስ መሰለኝ። እንደምንም ተረጋጋሁና አፍጥቼ አያት ጀመር።

ምን ልበላት? ቃላት አጣሁ።  አይኖቼ ‘…ይህንን አላምንም?...’ ብለው በአይን ቋንቋ ሳሌም ላይ አፈጠጡ።

አእምሮዬ ወደ ኋላ ተመለሽ፣ ተመለሽ፣ ሩጪ፣ ከዚህ ስፍራ ውጪ አለኝ።

ጆ ካርሎስ ሬይስ…!  ጆ ካርሎስ ሬይስ… ! ጆ ካርሎስ ሬይስ…! ለምን ሳሌም? ለምን? ለምን?....ብዬ መጮህ አማረኝ።

ግን ቃላት አልወጣ አሉኝ። ተለጎምኩ።

“…ሁሉ ነገር ሰላም ነው?...” የሁለታችንን መፋጠጥ ያየው ፖሊስ ጠየቀ። ያወራነው ባ’ማርኛ ስለሆነ አልገባውም።

“…አዎ ሰላም ነው… እንሂድ …” ሳሌም በቁሜ የደረቅኩትን እኔን ይዛ እየጎተተች ወደፊት ስትሄድ ፖሊሱም ተከተለን።

    ከደቂቃዎች ቡሃላ የመጎብኛው ቡዝ ውስጥ ሆነን፣ በህይወቴ ዘመን ሁሉ ባ’ይኔ አየዋለሁ ብዬ የማላስበውን ፊት… ከፊት ለፊታችን መጥቶ ሲቀመጥ ተመለከትኩ። ጺሙና ጸጉሩ አድጓል። ፊቱ ትንሽ የከሳ ቢመስልም ራሱ ነው። ያየሁት አንድ ቀን ብቻ ነው ፦በቲቪ መስታወት። አንድ ሰሞን መነጋገሪያ ነበር። ከዛ አንድ ቀን ቡሃላ፣ በቲቪ ካየሁት ቡሃላ ...ስለዚህ ሰው የተጻፈውን ወይም የተወራውን ነገር አላየሁም። ማየትም፣ መስማትም አልፈለግኩም። ስሙንም፣ ግብሩንም ጠላሁት። ለዚህም ይሆናል ስሙ ለአፍታ የተዘነጋኝ።

ይህ ጆ ካርሎስ ሬይስ ነው።

ይህ ሰው ከአመት ከምናምን በፊት …አምስተኛው ጎዳና ላይ መጣ። ሳሌምና ዳሪክ ያሉበት ካፌ ውስጥ ገባ። ያለምንም ምክንያት  የማያውቃቸው
👍334
ሰዎች ላይ ሽጉጡን አውጥቶ መተኮስ ጀመረ። …ከዛ ቡኋላ የሆነውን ከተማው ሁሉ ሰምቷል።   

ጆ ካርሎስ ሬይስ ይሄ ነው!
*
*
ሁለት እግሮቹና እጆቹ በሰንሰለት ታስረዋል። የለበሰው ደማቅ ብርቱካናማ  የእስር ቤት ዪኒፎርም፣ የደፈረሰውና የቀላው አይኑ፣ የጸጉሩና የጺሙ ማደግ የበለጠ አስፈሪ አስመስሎታል። በዝግታ፣እየተጎተተ ሲመጣና ከፊት ለፊታችን ሲቀመጥ አየሁት፦ ጆ ካርሎስ ሬይስ።

አራት አይኖች በዚህ በኩል፥ ሁለት አይኖች በዛኛው በኩል። ሳሌምና እኔ በዚህ፥ ጆ ካርሎስ ሬይስ በዛ በኩል። ተፋጠጥን።

ፊት ለፊቷ ሆኖ ስታየው ሳሌም የምትለው የጠፋት ይመስል ለአፍታ ዝም ብላ ተመለከተችው።

ጥቂት ቆይታ ግን በእርጋታ ጠየቀችው። “…ማን እንደሆንኩኝ አውቀኸኛል?...”

ፊቱን አኮሳትሮ፣በደፈረሱ አይኖቹ አፈጠጠባት። “…አላወቅኩሽም። ያለ ዛሬም አላየሁሽም።…”

ሳሌም በስሱ ፈገግ አለች። “…አንተ አታስታውሰኝ ይሆናል። እኔ ግን አስታውስሃለሁ።…አታውቀኝ ይሆናል። እኔ ግን አውቀሃለሁ። በቅጽበተ አይን ህይወቴን ለውጠኸዋል። በሰከንድ ሽራፊ ያላሰብኩት ማጥ ውስጥ ከተኸኛል። አንዳንዴ ስላንተ ብዙ አስባለሁ። ከቀኑ ብዙ ሰዐት ወስጄ ለምን ይህን አደረገ? ለምን ሳያውቀኝ ጠላኝ? እያልኩ ራሴን እጠይቃለሁ። ደሞ ሌላ ጊዜ ከሌሊት ከተኛሁበት በህልሜ ትመጣብኛለህ። ደንግጬ፣በፍርሃት ተውጬ …እየተንቀጠቀጥኩ እነሳለሁ። ስለዚህ አንተ ባታውቀኝም… እኔ ግን አውቅሃለሁ።…”

ጆ ካርሎስ አሁንም ተኮሳትሮ፣ አፍጥጦ እያያት ሳሌም ቆመችና የለበሰችውን ቲ-ሸርት ወደ ላይ ከፍ አደረገች።ጥርት ባለው ቀይ ቆዳዋ ላይ በግራ በኩል ከደረቷ በታች ሁለት ጠበሳዎች ይታያሉ።

“…እነዚህ ጠባሳዎች ይታዩሃል?...” ጠየቀችው።

ጆ ካርሎስ መልስ አልሰጠም።

“…እነዚህ ጠበሳዎች እንዲሁ ሳታውቀኝ፣ ዝም ብለህ ከመሬት ተነስተህ ልትገድለኝ የተኮስክብኝ ጥይቶች ትተውልኝ የሄዱት ጠባሳዎች ናቸው። አታውቀኝም። አላውቅህም። ምንም አላደረግኩህም። ልትገድለኝ ስትመጣ እዛ ስፍራ ላይ ከነፍሴ በላይ ከምወደው ፍቅሬ ጋር ስለ እግር ኳስ እያወራሁ ነበር..."

ሳሌም ንግግሯን ትንሽ ቆም አድርጋ ጆ ካርሎስን ተመለከተችው። 

ምንም ስሜት አይታይበትም። አሁንም አይኑን አፍጥጦ፣ተኮሳትሮ ይመለከተታል።

ቀጠለች “….አምስት ጥይቶችን የተኮስክበት አብሮኝ የነበረው ፍቅሬ፣ መልዐኬ… የት እንዳለ ታውቃለህ? የምታውቅ አይመስለኝም። ስለዚህ ልንገርህ። ፍቅሬ ላለፉት ብዙ ወራት ተኝቷል። ኮማ ውስጥ ነው። ለመጨረሻ ጊዜ አይኖቹን ያየኋቸው አንተ እዛ ካፌ ውስጥ መጥተህ፣ እንዲሁ ዝም ብለህ ልትገድለው የሞክርክ ቀን ነው። አይኖቹን ማየት እንዴት እንደናፈቀኝ? ድምጹን ለሰከንዶች መስማት ምን ያህል እንደጏጏሁ? የቁልምጫ አጠራሩ ከምትነፍሰው አየር በላይ እንደምፈልገው?.....”
 
ሳሌም እዚህ ጋር በደንብ ፈገግ አለች። “…አየህ የአልጋ ቁራኛ ያደረግከው ፍቅሬ ሲጠራኝ ‘የምወድሽ’ ብሎ ነው። ይገርመኛል? የሚገርመኝ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? አንድ ነገር ሊነግረኝ ሲፈልግ፣ ሲያወራኝ ምን ያህል ጊዜ ‘የምወድሽ’ ብሎ እንደሚጠራኝ ነው። ሺ ጊዜ? እልፍ ጊዜ? …አላውቅም። ግን ከሚያወራልኝ ወሬ ይልቅ፣ ከሚነግረኝ ቁምነገር፣ ከሚያስቀኝ ቀልዶቹ በላይ ስንት ጊዜ ‘የምወድሽ’ ብሎ እንደሚል ልነግርህ አልችልም። በዛ ላይ በእያንዳንዱ የምወድሽ አጠራሩ ላይ ያለው ነገር … ‘የምወድሽ’ ሲል …  የፍቅሩ ልቀት፣ ‘የምወድሽ’ ሲል …. የመውደዱ ብዛት፣ ‘የምወድሽ’ ሲል  …አሳቢነቱ፣ ‘የምወድሽ’ ሲል  … የሆነ እንደምጠፋበት፣ እንደምሰበርበት የከበረ ክቡር ነገር ያለው ጥንቃቄ…. ‘የምወድሽ’ ብሎ እኮ አይጠግብም። አይበቃውም። አይሰለቸውም። ከማታውቃት ካ’ንዲት ታዳጊ ወጣት ምን እንደወስድክባት ይታይሃል?....” ሳሌም ፍዝዝ ብላ አይኑን ታየዋለች።

ጆ ካርሎስ አሁን ፊቱ ፈታ ብሏል። ማፈጠጡ ግን እንዳለ ነው።

ሳሌም መናገሯን ቀጠለች በእርጋታ “… ዛሬ ግን የመጣሁት ለአንድ ነገር ነው። አየህ የትኛውም ሰው ሲፈጠር ክፉ ነው ብዬ አላምንም።  አንተም በሆነ ሁኔታ፣ ከሆነ ስፍራ ጥላቻን ተምረኸው ነው እንጂ በተፈጥሮ ክፉ አልነበርክም። ምክንያቱም ጥላቻ፣ ክፋት፣ መለያየት፣ ጸብ፣ አድመኝነት ሌሎችም ብዙ የምንማራቸው ክፉ ሃሳቦች በልባችን ውስጥ እንዲያድጉ፣ እንዲበዙና ወደ ሌሎች ወንድሞችና እህቶችን እንዲተላለፉ የምናደርጋቸው ዘሮች ናቸው። በውስጣችን እንዲያደጉና ወደ ሌሎች ሰዎች እንዲሄዱ የምናደርገው፣ የምንፈቅደው እኛው ነን።ነን። ዛሬ ግን ይሄ የጥላቻ ዘር ይቆማል። ይህ የጥላቻ ዘር  መቆሚያው እኔ ጋር ነው። አያልፋትም። አያድጋትም። አይበዛም።  እኔ ጋር እዚህ ይቆማል። የጥላቻ ዘር በኔ ልብ ውስጥ አያድግም። በኔ አእምሮ ውስጥ ስፍራ አግኝቶ፣ ተባዝቶ ወደ ሌሎች ሰዎች አይተላለፍም። እኔ ለጥላቻ የመጨረሻው መቆሚያ ነኝ። I am a dead end for hate…ስለዚህ ዛሬ የመጣሁት የወሰድክብኝን ልነገርህ፣ የቀማኸኝን አስታውሼ ልሰቅልህ፣ ሃጢያትህን መንዝሬ ገሃነም ትወርዳለህ ልልህ፣ ልሰድብህ ወይም እንቁላል በኪሴ ይዤ ፊትህ ላይ ልፈጠፍጥ አይደለም። ዛሬ የመጣሁት ይቅር ብዬሃለሁ ልልህ ነው። ዛሬ የመጣሁት ጥላቻ መቼም እንደማያሸንፈኝ ልነግርህ ነው። ዛሬ ብዙ ከተሞች አቋርጬ መጥቼ እዚህ የተገኘሁት ከልቤ እወደሃለሁኝ ለማለት ነው። ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር፣ ከጸብ ይልቅ ስምምነት፣ ከመለያየት ይልቅ አንድነትን መርጫለሁ።…”

ሳሌም ተነሳችና ገርሞት፣ ተደንቆ፣ በድንጋጤ አፍጥጦ የሚያያትን ጆ ካርሎስ ተጠጋች።

በተቀመጠበት በጎን በኩል ትከሻውን ጥብቅ አድርጋ አቀፈችና “…ታላቅ ወንድሜ ጆ ካርሎስ ያደረክብኝን አንድም ነገር በልቤ አልይዝብህም፣ ይቅር ብዬሃለሁ፣ ይቅር ማለት ብቻ ሳይሆን ያደረግከውን ሁሉ ለመርሳት ቃል እገባልሃለሁ። ደሞም ከልቤ እወድሃለሁ። ለልብህ የፍቅር ጸሀይ ትወጣ ዘንድ፣ ለነፍስህ የፍቅር ብርሃን እንዲበራም እጸልይልሃለሁ። መልካም ቀን ይሁንልህ።…”

ይህን ካለች ቡሃላ ዝም ብላ ለጥቂት ሰከንዶች አየችው።

ጆ ካርሎስ ቃላት አላወጣም። ምንም አልተናገረም። እንደ ህጻን ልጅ አይኑን እያቁለጨለጨ ያያት ጀመር። አሁን ጆ ካርሎስ ሲያዩት የሆነ ጥፋት አጥፍቶ በወላጆቹ የተያዘ ታዳጊ ነበር የሚመስለው። በግራ መጋባት አይኖቹን እያቁለጨለጨ ብቻ ያያታል፦ ሳሌምን።

ሳሌም ወደ እኔ ዞረች። “…ጨርሻለሁ!... በቃ ሳዬ እንሂድ…”

ሳሌም ወደ በሩ ስትሄድ ከኃላዋ ተከተልኩ።

ከእስር ቤቱ እቃችንን ተረከበን እስክንወጣ ድረስ ሳሌም ያደረገችውን ነገር ባለማመን በውስጤ እያሰብኩኝ ነበር። ምን አይነት ልጅ ናት ይቺ ልጅ?እንዴትስ ልቧ ይህን ያህል መልካም ሊሆን ቻል? እንዴት መልካም መልካሙን ብቻ እየመረጠ ሊያሳድግ ቻለ? 

የህይወት ጉዞ በምርጫ የተሞላ ነው። ሳሌም መልካም፣ መልካሙን ብቻ እየመረጠች በልቧ ውስጥ ሰንቃ ለመያዝ የወሰነች ብልህ ወጣት ምሳሌ ናት።

“…ሳዬ ካስቀየምኩሽ ይቅርታ?...” በሩን አልፈን ስንወጣ ዝም ማለቴ አሳስቧት መሰለኝ

“…ኖ.. ኖ.. ኖ  አልተቀይምኩሽም … ግን ብትነግሪኝ ኖሮ ምን ነበረበት ሴለም?...”

“…እውነቱን ንገሪኝ? ብነግርሽ ትመጪ ነበር ሳዬ?...”

ከባድ ጥያቄ ነው። ጆ ካርሎስ ሬይስን ለማየት ይህን ሁሉ መንገድ ተጉዤ ለመምጣቴ እርግጠኛ አይደለሁም።

መጠራጠሬንና ለመመለስ መቸገሬን ስታይ እየሳቀች “…አየሽ ሳዬ አትመጪም ነበር። ስለዚህ አለመናገሬ ትክክል ነበር ማለት ነው።…”
👍322😢1
“…ይሁንልሽ እሺ ሴለም…” መሸነፌን ሳውቅ  “…ግን በምን አሰብሽው ሴሌም? እንደምን ብለሽ ጆ ካርሎስን ለማየት ወሰንሽ?...”

ሳሌም ፈገግ ብላ አየችኝ። “…የወደዱኝን ብቻ የምወድ ከሆነ ምን ያህል ከንቱ ነኝ? ከጌታስ ምን ተማርኩኝ?...ይህን ሰው ለማየት ብዙ ጊዜ ሳስበው ነበር… የወሰንኩት ግን ትላንት ስለ ነፍስ ካንሰር የኔ መልዐክ የነገረኝን ሳስታውስ ነው። አየሽ ፍቅሬ ባይተኛ አጠገቤ ቢኖር የሚያደርገው እንዲህ ነው። የኔ መልዐክ የሚፈልገው ይህን እንዳደርግ ነው …እንደገናም ጆ ካርሎስን ይቅር ካላልኩት እኔም እሱም ተያይዘን ወደ ጥላቻ ገደል እንደምንገባ ተረዳሁ። እናም ወሰንኩኝ። ይህን ሰው ይቅር በማለት እሱንም…ራሴንም ነጻ ማውጣት እንዳለብኝ አመንኩኝ። ጌታም ረድቶኝ አደረግኩት።…”

ደሞ የሚመልሰን ባስ መጥቶ ስንገባና ስንቀመጥ ሳሌም ፊቷ በደስታ እያበራ እንዲህ አለችኝ “…ታውቂያለሽ ሳዬ ዛሬ ባደረግኩት ነገር የሆነ ክፍተት ሲሞላ በልቤ ተሰማኝ። አለ አይደል እስከዛሬ ጅምሬ ያልጨረስኩት የሆነ የህይወቴ ክብ እንዳለ ነበር የሚሰማኝ። ዛሬ ያ ክብ ተጠናቀቀ። ምሉዕ ሆነ። ሁሉ ነገር ያለቀ ያህል …. ከፍ ያለ፣ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ እረፍት ውስጥ የገባሁ ያህል ነው የሚሰማኝ። ደስ ሲል።….”

ይህን ብላ በተቀመጥንበት መዝመሩን ከፈተችና አይኗን ጨፈነች።

ሳሌም ዝም ብዬ ሳያት የሆነ የማያልቅ ደስታ ውስጥ የምትንሳፈፍ ነው የምትመስለው።

ባሱ ውስጥ ተቀምጠን መዝሙሩን በአንድ አንድ ጆሮችን እየሰማን መጞዝ ጀመርን። ደቂቃም ሳይቆይ ውብ ትላልቅ አይኖቿ ተከድነው ሰላማዊ እንቅልፍ ውስጥ ገባች። ለሚያያት ሳሌም ፍቅሯን በሞት ልትቀማ ያለች ልጅ ፈጽሞ አትመስልም። በእረፍት፣ በሰላም፣ በፍቅርና እምነት እቅፍ ውስጥ እርፍፍፍፍ.....ፍ ያለች ቆንጆ እንጂ።

እንደገናም አስተኛኘቷ ያኔ እዚህ ሃገር ስትመጣ አውሮፕላኑ ውስጥ በሰላምና በእምነት የተኛችበትን ...የነገረችኝንም ያስታውስ ነበር።
*
*
*

የዛን ጊዜ የሆነውም እንዲህ ነበር።

ፍቅር፣ ፍቅር ብለው ፍቅር በጀመሩ… ሃያ ሶስተኛው ወር ላይ ቁጭ ብለው እያወሩ  “….አንድ የምነግርህ ነገር አለኝ የኔ መልዐክ…” ሳሌም ለወራት ያሳሳባትን ነገር መናገር ያለባት ቀን እንድሆነ ገብቷታል።

“….እኔም የምነገርሽ ነገር አለኝ….የምወድሽ….”

“…ደስ የሚል ወይስ የሚደብር?...”

“….በጣም ደስ የሚል  ያንቺስ የምወድሽ። ደስ የሚል ነገር ነው?....”

ሳሌም ጎንበስ አለች።ዝም።

“…የምወድሽ?..." ዳሪክ ካቀረቀረችበት አገጯን ከፍ ሊያደርግ እየሞከረ።

“…ደስ አይልም ‘ባክህ ደባሪ ነገር ነው የኔ መልዐክ…”

“…ምንድን ነው?  ምን ተፈጠረ?....”

ሳሌም ዝም።

“…ንገሪኝ የምወድሽ?...ንገሪኝ?....”

“…አሜሪካ ልሄድ ነው!...” ጥያቄው ሲበዛባት ሳሌም ነገረችው። “….አሜሪካ ልሄድ ነው…”

የዳሪክን አይኖች ማየት የፈራች ይመስል አሻግራ ወደ ወጪ እያየች ቀጠለች።  “…አልሄድም ብልም ከቤተሰቤ የሚሰማኝ አንድ ሰው አጣሁ። …በጣም በጥቂት ወራቶች ነው የቀሩኝ የኔ መልዐክ። ዝም ያልኩህ እንዳላስጨንቅህ ብዬ ነው። ግን ቅሪ በለኝ። አትሂጂ በለኝ።  አሁኑኑ የፕሮሰሱን ወረቀቶች ቀዳድጄ ልጣለው።…”

ሳሌም ዞር ብላ ስታየው ዳሪክ ምንም አልመሰለውም። አልደነገጠም።

ተረጋግቶ እንዲህ አላት “…የምወድሽ አትቀሪም። መሄድ ወዳለበሽ ስፍራ ትሄጃለሽ። ጉዞና፣ ጊዜና ስፍራ…ፍቅራችንን ለመስበር አቅማቸው አናሳ ነው።…”

ከጥቂት ወራት ቡሃላ ሳሌምና ዳሪክ አዲስ አበባ ውስጥ ባንድ ላይ ያሳለፉት የመጨረሻቸው ቀን ነበር።

በጥቂት ቀናት ውስጥም ሳሌም አሜሪካ ሲያትል ውስጥ እንደገና ህይወትን የምትጀምርበት ቀን ነበር።

ሁለት ቀናቶች!... መጨረሻና… መጀመሪያ!... እነዚህን ሁለት ቀናቶች ሳሌም መቼም ቢሆን አትረሳቸውም፦ መቼም።
*

ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍2811
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹዋቤ


የውብዳርስ?››

‹‹እኔ እንጃላት፡፡››

‹‹እንዴት እኔ እንጃላት ... ?ወንዶች ስትባሉ በቃ ሁላችሁም አንድ አይነት ናችሁ? ሴትን ልጅ ቀምሳችሁ... ልሳችሁ ጣዕሟን ከጨረሳችሁ በኋላ ተፍታችሁ ከአፈር ስትደባልቁ ጥቂት እንኳን ፀፀት አይሠማችሁም? ግርም የሚለኝ እግኢአብሔር ለምን እናንተን እንደፈጠራችሁ ነው>>

‹‹የፈጠረንማ አንደኛ አቶ ሁሴን እንደሚለው መልኩን በእኛ በኩል ለማየት ነው፤ምክንያቱም እኛ እሱን እንመስላለን፡፡ ሁለተኛው ምድርን እንድናስተዳድርለት ነው፤ሦስተኛው እንድናመሰግነው ይመስለኛል፡፡ እንደ እኔ ሦስተኛው ብዙም የተሳካ አይመስለኝም፡፡ እናንተን ከፈጠረ በኋላ አይናችንን ወደ ፈጣሪ እንዳናነሳ እንቅፋት እንደሆናችሁን ነው የምረዳው፡፡›› ሁለቱም ምግቡን ስላቆሙ አስተናጋጅ መጥቶ መአዱን አነሳና ጠረጴዛውን አፀዳዳው፡፡...

‹‹ግን እውነት ደህና ነች?›› ጠየቀችው

‹‹እኔም እውነቴን እኮ ነው ..አላውቅም፡፡››

‹‹ምን ማለት ነው?››

‹‹ተፋተናል፡፡››

‹‹ምን?›› በድንጋጤ አፏን በእጇ ሸፍና ከመቀመጫዋ ተነሳችና መልሳ ቁጭ አለች፡፡

‹‹አዋ አራት ወር አለፈን፡፡››

‹‹እንዴት ሳልሰማ? ምን አለበት ደውለህ እንኳ ብትነግረኝ?››

‹‹ምን የሚነገር ነገር አለው? ለሰርጉም ጠርቼሽ ለፍቺውም ጠርቼሽ እችላለሁ... ? ድግስና ጥሪ ለጋብቻ ብቻ ነው ብዬ ነው፡፡››

‹‹ለምን የለውም? የዛሬን አያድርገውና ስንት ጥሩና መጥፎውን ነገር አብረን አሳልፈናል እኮ …ቆይ እናንተን ሀይ የሚላችሁ ሠውም የለ እንዴ? ዳሩ ከእብድ ጋር የሚውል ምን ጤና ይኖረዋል?ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር...> እንደሚባለው ቢጤ እኮ ነው፡፡››

‹‹እንደምታስቢው እኔ ጠልቻት ወይም ሌላ አፍቅሬ እንዳይመስልሽ፡፡››

‹‹እና እንዴት ሆኖ ነው?››

‹‹ሠለቸኋት ... ድብብቆሽ ጨዋታ ውስጥ ገባች...እጅ ከፍንጅ ያዝኳት .. በቃ ይሄው ነው፡፡››

‹‹እኔ አላምንም ... የውብዳር ከሌላ ወንድ ጋር... ምቀኛ በመሀከላችሁ ገብቶ እንዳይሆን?››

‹‹አመንሽም አላመንሽም በወሬ ወይ በጥርጣሬ እንዳይመስልሽ፤እራሷም ባመነችበት አሳማኝ ማስረጃ ነው፡፡››

‹‹ወይ ጉድ!›› አለች ኤደን ግራ ገብቷት፡፡

ሠሎሞን ብርጭቆውን አነሳና ውስጥ ያለውን ጅው አድርጎ በመጨለጥ ጠርሙሱ ውስጥ የነበረውን ለሁለቱም ቀድቶ ሌላ እንዲጨምርላቸው ለአስተናጋጁ በምልክት ትዕዛዝ በማስተላለፍ ንግግሩን ቀጠለ፡፡ ‹‹አየሽ ኤደን ምን አልባት አንቺ ነገሮችን ከራስሽ አንፃር ስትገመግሚያቸው በወንድ በደል ደርሶብኛል ወይም ተገፍቼያለሁ ብለሽ ስለምታስቢ ጠቅላላ ወንዶች ላይ ያለሽ ግንዛቤ አሉታዊ ጎኑ ስለሚያመዝን ወንዶች ሁሉ በዳይ ሴቶች ደግሞ ተበዳይ ሆነው ሊታዩሽ ይችላሉ፡፡ ሀቁ ግን እንደዛ አይደለም ስንት መሠሪና አለሌ ሴቶችም አሉ ፡፡ እና ምን መሠለሽ ...››ንግግሩን የስልኩ መጮህ አቋረጠው፡፡ ከኪሱ አወጣና ደዋዩ ማን እንደሆነ አየው፡፡ ሁሴን ነበር፡፡ አነሳው፡፡

‹‹እሺ ጌታው፡፡››

<አለሁ ባክህ ... ሰርጉ እንዴት ነበር?>>ሁሴን

‹‹አሪፍ ነው፡፡ አሁን ወጥቼያለሁ፡፡ ፍንድቅድቅ ያልክ ትመስላለህ ደግሞ ምን አገኘህ?››

<ደወለች እባክህ::››

<<ማን?>>

ሁሴን ተበሳጨ ‹‹ማን ትላለህ እንዴ? ማን እንድልህ ትፈልጋለህ?››

‹‹ይቅርታ እሺ ደራሲዋ?››

ኤደን ሁሴን እንደደወለ አወቀች፡፡ ሌላ ነገር የምታስብ መስላ ከወይኑ እየተጎነጨች በጽሞና ቃለ ምልልሳቸውን እያዳመጠች ነው፡፡

‹‹ትክክል ነህ፤እሷን ለማግኘት ማድረግ የሚገባኝን ነገረችኝ፡፡››

‹‹አትለኝም ምን አለችህ?››

<<አግባኝ>>

‹‹በተሠቀለው ንጉስ አግባኝ? የምሯን ነው!››

‹‹አዎ ከምሯ ነው፡፡››

‹‹ታዲያ ምን ችግር አለው እሺ በላታ፤ከዛም አግኛትና ካልተመቸችህ ቃልህን ታጥፋለህ፤ቃል ማጠፍ እንደሆነ ላንተ የሚከብድ አይመስለኝም››

የኤደን ስሜት ይበልጥ እየተነቃቃ ውስጧ በቁጣና በቅናት እየነደደ መጣ፡፡ ትቼዋለሁ ወጥቶልኛል ብላ ከሁሴን አጠገብ ከራቀችና እሱን ማግኘት ከተወች ስድስት ወር ቢያልፋትም ውስጧ ግን ዛሬም ይራበዋል፡፡ መሸነፍ ልቧን ያቆስለዋል፡፡

ንግግራቸው ቀጥሏል፡-‹‹ባክህ የዋዛ እንዳትመስልህ የእውነት ከወደድከኝ ቆማጣም ሆንኩ ሸፋፋ የማትተወኝ ከሆነ እና ልታገባኝ ከወሠንክ በመጀመሪያ ሠርግ ደግስ ለምታውቃቸው ሠዎች ሁሉ የሠርግ ጥሪ በትን ከዛ በሠርጉ ቀን ሽማግሌዎችህን ሚዜዎችህንና አጃቢዎችህን አዘጋጅ ልክ
በሠዓቱ እደውልልሀለሁ ያለሁበት ትመጣና ይዘኸኝ ትሄዳለህ፡፡››አለችኝ፡፡

‹‹እንዲህ ነችና ... ልጅቷ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ፊልም እየሠራች ነው እንዴ ...? እኔ ይሄንን ጉዳይ ከዚህ በላይ በስልክ ማውራት አልፈልግም ነገ ጥዋት እቢሮ እመጣለሁ፤ ታወራኛለህ፡፡››

እጠብቅካለው....ለማኝማውም ሚዜ ለመሆን ተዘጋጅ፡፡››

‹‹እሱን እናያለን .. ለማንኛውም አሁን ከኤደን ጋር ነኝ፡፡ሰርግ ቤት ተገናኘን፡፡ ሠላም እያለችህ ነው፡፡››

ኤደን በተቃውሞ ፊቷን አኮሳተረች፡፡

‹‹ተመችቶኃላ .. ላናግራት›› አለ ሁሴን ሠሎሞን ሞባይሉን ዘረጋላት .. ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡ ‹‹በል ቻው፡፡ በአየር ላይ ሠላም ብላሀለች፡፡›› በማለት ስልኩን ዘጋው፡፡

‹‹በቃ አሁንም ስለዛች ደራሲ የቀን ህልም እያለመ ነው?››

‹‹ባክሽ እኔም ግራ ገብቶኛል፡፡››

‹‹እኔ እኮ የሚገርመኝ ቆይ ማን ትሆን እንዲህ የምትጫወትበት?››

‹‹እሱ አይደል እንቆቅልሹ፡፡ አሁን እኮ የሚለኝ ልታየኝ ከፈለክ ድግስ ደግስና አግባኝ አለችኝ ነው >>

‹‹በቃ በቃ እኔ እንዲህ አይነት ቅራቅንቦ መስማት አልፈልግም፡፡ እንደውም መጠጣት ሁሉን መርሳት እፈልጋለሁ፤ ሞቅ ያለ ቤት ውሠደኝ፡፡›› አለችው፡፡

‹‹ኧረ እስማማለሁ፡፡›› በማለት ሂሳቡን ከፍሎ ቀጫጭን የእጆቿን ጣቶች በፈርጣማው ጣቶቹ አቆላልፎ በመያዝ ወደ ጭፈራ ቤት ይዟት ለመሄድ መኪናው ውስጥ ይዟት ገባ፡፡ መኪናውን ከማንቀሳቀሱ በፊት ግን የሞባይል ስልኩን ካስቀመጠበት ኪሱ አውጥቶ የጹሁፍ መልክት ለሁሴን ላከ ‹‹ኤደን ጭፈራ ቤት ውሠደኝ እያለችኝ ነው፡፡ ባንተ የተበሳጨች ይመስለኛል፡፡ ስሰክር ማስተዋሌ እንደሚቀንስ ታውቃለህ፡፡ ምን አልባት አንተን የማያስደስት ነገር በእኔና በእሷ መሀከል ይፈጠር ይሆን? ብዬ ፈራሁ፡፡ ምን ትመክረኛለህ?››መልዕክቱን ላከና የመኪናውን ሞተር አስነስቶ መንዳት ጀመረ፡፡ ወዴት እንደሚሄዱ አያውቅም፡፡ ከሁሴን መልስ እስኪመጣለት ጊዜ ለማግኘት እየጣረ ነው ፡፡ ሠዓቱ 3፡45 ሆኗል፡፡ ከዚህ ሠዓት በኋላ ለብታን ወደ ስካር ለማሸጋገር፤ ለዛውም ከሴት ጋር ጭፈራ ቤት መግባት መጨረሻውን መገመት አዳጋች ነው፡፡ ሞባይሉ ምልክት አሳየው፡፡ መኪናውን ጥግ ይዞ አቆመና የመጣለትን መልስ ከፍቶ ማንበብ ጀመረ፡፡

‹‹ቀሽም አትሁን…ምንም ቅር የሚያሰኝ ነገር የለም፡፡ ግን አደራ በቦርጭህ ሙሉ ተከምረህባት እንዳታፈነዳት፡፡ በል ይመቻችሁ፡፡ በጥዋት ቢሮ ና፡፡ ባይሆን የአልጋ መውረጃ ደህና ቁርስ ጋብዝሀለሁ፡፡››ይላል፡፡አንብቦ ሲጨርስ ፈገግ አለና መኪናውን አስነስቶ ተፈተለከ .....ወደ ጭፈራ ቤት፡፡ እሷ ግን በዝምታዋ ውስጥ እንደሰመጠች ነው፡፡


ይቀጥላል

የዛሬው ዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ የማድረግ እንቅስቃሴ ጥሩ ነው ይልመድባችሁ👍  አሁንም እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12414🥰2😁2
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አምስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹዋቤ የውብዳርስ?›› ‹‹እኔ እንጃላት፡፡›› ‹‹እንዴት እኔ እንጃላት ... ?ወንዶች ስትባሉ በቃ ሁላችሁም አንድ አይነት ናችሁ? ሴትን ልጅ ቀምሳችሁ... ልሳችሁ ጣዕሟን ከጨረሳችሁ በኋላ ተፍታችሁ ከአፈር ስትደባልቁ ጥቂት እንኳን ፀፀት አይሠማችሁም? ግርም የሚለኝ እግኢአብሔር ለምን እናንተን እንደፈጠራችሁ ነው>> ‹‹የፈጠረንማ አንደኛ…»
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹዋቤ

ከለሊቱ ስድስት ሠዓት አልፏል፡፡እንቅልፍ አልወስደው ብሎ አልጋው ላይ ተጋድሞ እየተገላበጠ ሳለ ድንገት ተንቀሳቃሽ ስልኩ ድምፅ አሠማ፡፡ አነሳና ቁጥሩን አየው፡፡ ያልተመዘገበ ቁጥር ነው፡፡ አያውቀውም፡፡ ግራ በመጋባባት አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ ማን ልበል?››

‹‹ይቅርታ ከእንቅልፍ ቀሠቀስኩህ?››

ብድግ ብሎ ቁጭ አለ፡፡ ያልጠበቀው ስልክ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በሞባይል የደወለችለት ሚስጥር!፡፡

‹‹ኧረ አልቀሰቀሽኝም.. እንቅልፍ እና እኔ ከተጣላን እኮ ሰነባበትን

‹‹ኦ! ምን ምቀኛ በመሃላችሁ ገባ እቴ›› በማለት በስሱ ሳቋን ለቀቀች፡፡

‹‹ይሄ ሞባይል ቁጥር ያንቺ ነው?›› ጠየቃት፡፡

‹‹ኧረ ተመስገን ነው፤በፈለኩ ጊዜ ብደውልልሽ አገኝሻለኋ?››

‹‹አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም ሁል ጊዜ አልከፍተውም፤በተለይ ቀን ቀን አይሠራም፤ማታ ከአራት ሠዓት በኋላ ግን ክፍት ነው፡፡››

‹‹ኧረ ይሁን እሱንስ ማን አየበት…፡፡››

‹‹አሁን የደወልኩት ውሳኔህን እንድትነግረኝ ነው፡፡››

<<የቱን ውሳኔ?>>

‹‹በቀደም የተነጋገርነውን ነዋ፤ልታገኝኝ ከፈለክ አግባኝ ያልኩህን ?››

‹‹ግን እኮ በጣም ከባድ ነገር ነው፡፡››

‹‹ከባድ ከሆነማ ልታገኘኝ አትፈልግም ማለት ነው?ስለዚ እንደ ከዚህ ቀደሙ ግንኙነታችንን በስልክ ብቻ እንቀጥላለን፡፡››

‹‹ኖ... እሱማ አይሆንም፤ከባድ ነው እኮ ያልኩት አንቺን ማግባቱ አይደለም፡፡››

‹‹እና ምኑን ነው?››

‹‹ሠርግ ምናምን የሚባለውን ነገር ነዋ፡፡ አየሽ እኔ ለሠርግዐያለኝ አመለካከት በጣም የወረደ ነው:: እንኳንም ሠርግ
መደገስ ሠርግ ስጠራ እንኳን መሄድ አልፈልግም፡፡ በዚህ ፀባዬ ከስንት ወዳጆቼ ተጣልቻለሁ መሠለሽ ... ለምን ዝም ብለን አንጋባም ፤ አሁን በዚህችው ደቂቃ እንኳን ብትፈቅጂልኝ ያለሽበት ድረስ በርሬ መጥቼ አገባሽ ነበር፡፡››

‹‹እና ታዲያ ምን ይሻላል?እኔም እኮ ሠርግ ወድጄ አይደለም፡፡ ግን አንተ አይተኸኝ እንድትተወኝ በፍፁም አልፈልግም፡፡ ካገባኸኝ በኋላ ካልተስማማሁህ ብትፈታኝ ይሻለኛል…በወሩም ቢሆን፡፡ ይሄንኑ ማረጋገጥ ስለምፈልግ ነው ይሄንን ዘዴ የቀየስኩት...፡፡››

‹‹ሚስጥር እኔ በጣም ከምትገምቺው በላይ አፈቅርሻለሁ፡፡ ስለማፈቅርሽም አንቺ እምቢ ብትይኝ እንኳን በህግ ልጠየቅ እንጂ ጠልፌም ቢሆን አደርገዋለሁ፡፡ እኔ የሚያስጠላኝ ቀለበት ሠርግ የሚባለው የድግስ ጋጋታ ነው፡፡ ፍቅሬን ከተጠራጠርሽ ሌላ የምታረጋግጭበት ዘዴ ወይም ፈተና አቅርቢልኝ፡፡››

‹‹ቆይ ላስብበትና ልደውልልህ››

‹‹መቼ ነው የምትደውይልኝ?››

‹‹ዛሬውኑ...ከ3ዐ ደቂቃ በኋላ፡፡››

‹‹እጠብቅሻለሁ፡፡››

ስልኩ ከተዘጋ ገና አስር ደቂቃ ብቻ ያለፈው ቢሆንም የአስር ቀን ያህል ረዘመበት፡፡ ምን አይነት ተቀያሪ ሀሳብ እንደምታቀርብለት መተንበይ አልቻለም፡፡ መንጎራደድ የእሷን የሃሳብ መስመር ሹክ የሚለው ይመስል መኝታ ቤቱን ተሸከረከረ፡፡ ሲደክመው መልሶ አልጋው ጫፍ ላይ በመቀመጥ አንገቱን አቀርቅሮ ወደ ትካዜው ገባ፡፡‹‹እንደምታገባኝ እርግጠኛ የምሆንበት ሌላ ዘዴ ስለሌለኝ መደገስህ የግድ ነው ብትለኝ ምን አደርጋለሁ? እሺ እላታለሁ ወይንስ አይሆንም እላታለሁ?›› ግራ ገባው፡፡ በአሁኑ ሰዓት እርግጠኛ የሆነበት አንድ ነገር ቢኖር እሷን በአካል ማግኘት ካልቻለ ትክክለኛ ሠው ሆኖ ስራውን ማከናወንም ሆነ ህይወቱን መምራት እደሚያስቸግረው ነው፡፡‹‹እና ምን ይሻለኛል?›› እራሱን ጠየቀ አንድ ሀሳብ ብልጭ አለለት፡፡ ማንነቷን ለማወቅ አንድ እድል አለው፡፡ በሞባይል ቁጥሯ በመመራት ከቴሌ አድራሻዋን ማፈላለግ፡፡

‹‹በራሷ ስም ካላወጣችስ?›› አፍራሽ የሆነ ሌላ ጥያቄ ተሠነቀረበት፡፡

‹‹ቢሆንም ቁጥሩን ከቴሌ በስሙ የወሰደውን ሠው ብከታተለው ወደ እሷ ሊመራኝ ይችላል፡፡ >> ይሄን ዕድል ለመሞከር ውሳኔ ላይ እንደደረሰ ስልኩ ጮኸ፡፡ በአንድ ጥሪ ነበር ያነሳው፡፡

‹‹አልተኛህም.. እየጠበቅከኝ ነው?››

‹‹ምኑን ተኛሁ .. ምን ወሰንሽ?››

‹‹ሌላ ተቀያሪ ጨዋታ እንጫወታ፡፡››

‹‹ምን አይነት ጨዋታ?››

‹‹ሌባና ፖሊስ አይነት ነገር፡፡››

‹‹በናትሽ እስቲ ዘርዘር አድርጊልኝ?››

‹‹እንግዲህ አፈቅርሻለሁ ብለኸኛል››

<<በትክክል::>>

‹‹የምታፈቅረኝ ደግሞ ነፍሴን ነው››

‹‹አሁንም ትክክል ነሽ››

‹‹እንግዲህ እንደዛ ከሆነ ነፍስህ ነፍሴን ታውቃታለች ማለት ነው፤ስለዚህ እኔ ማን እንደሆንኩ ለማወቅ ነፍስህ ትረዳሀለች ብዬ አስባለሁ፡፡››

<<እየገባኝ ያለ አይመስለኝም …፡፡››

‹‹በዝግታ ተከታተለኝ እያስረዳሁህ እኮ ነው፡፡››

« .. እሺ ቀጥይ...::>>

‹‹እንግዲያው ከላይ የጠቀስካቸው ሁኔታዎች እውነት ከሆኑ የሦስት ቀን ጨዋታ እንጫወታለን፡፡ ቦታው የትም ሊሆን ይችላል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥም ሆነ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ማንኛውም ከተማ ..ያ ያንተ ምርጫ ነው፡፡ ፈልገህ ካገኘኸኝ በቃ አገኘኸኝ ማለት ነው፡፡››

‹‹እንዴት ነው የምፈልግሽ?››

‹‹በተመቸህ ሳምንት ጨዋታውን እንጀምራለን፡፡ የመጀመሪያው ቀን ግን አርብ ሆኖ ማብቂያው ደግሞ እሁድ ይሆናል፡፡ የትኛው አርብ እንደሚሆን ከወሰንክ በኋላ ትነግረኛለህ፡፡››ሁሴን ይበልጥ እየተገረመና ነገሮች እየተወሳሰቡበት ነው፡፡ በእሷ ላይ ያለው ገረሜታና አድናቆት ይበልጥ በውስጡ እየገዘፈ መጣ፡፡

‹‹እሺ ቀጥይ እየተከታተልኩሽ ነው፡፡››

‹‹በተወሰኑት ቀናቶች ከ1ዐ-12 መሀከል ባሉት ሰዓቶች በተስማማንበት አካበባቢ እገኛለሁ፡፡ በአካባቢህ ካሉት ሴቶች መካከል እኔ የትኛዋ እንደሆንኩ የመለየት ስራው ግን የአንተ ይሆናል፡፡››

‹‹ነገሩን እንዲሁ አወሳሰብሽው እንጂ አንቺን ማግኘት ቀላል ነው፡፡››

‹‹እንዴት ማለት?››

‹‹ያው ትንሽ ፍንጭ ሰጥተሺኝ ነበር እኮ..ረሳሽው እንዴ ?>>

‹‹ኦ .. እሱ ባክህ የመጀመሪያው ጊዜ የቀረበልህ ቀላል ፈተና ነው፤እኔ አይናማ ነኝ፡፡››

‹‹ለመሆኑ ምን ዓይነት ሠው ነሽ ?... ቤተሠቦችሽ እንዴት አድርገው ነው ያሳደጉሽ?››

‹‹እንቆቅልሽ እያስተማሩ፡፡››

‹‹ከለየሁሽ ቀጥታ መጥቼ አነጋግርሻለሁ ማለት ነዋ››

‹‹አይደለም አበባ ትሠጠኛለህ፡፡አበባው ላይ የሚለጠፍ ሦስት ካርድ እንቆቅልሽ የሚል ፅሁፍ ያለበት በፖስታ ቤት ልክልሀለው፡፡ ሦስቱም ላይ ፊርማዬ ያርፍበታል፡፡ አበባው እጄ ሲደርስ ለአሸናፊነትህ ያዘጋጀሁልህ የወርቅ ሀብል ስላለ እሱን አንገትህ ላይ አንጠለጥልልሀለሁ…ሀብሉ ልብ ቅርፅ ነው፡፡››

‹‹በጣም ጥሩ›› አለ ሁሴን ሳይታሠሰበው ድምፅ አውጥቶ፡፡ እሷን የሚለይበት አንድ ምልክት ስለሰጠችው ‹‹በድምፅህ ላይ አንድ ነገር ተረዳው›› አለችው፡፡

<<ምን??>>

‹‹ሀብሉን ከአንገቴ ላይ አውልቄ አይደለም የማጠልቅልህ ፤ከቦርሳዬ ውስጥ አውጥቼ ነው፡፡ ብቻ የልብ ቅርፅ የተሠራና በልብ መሀከል ያንተ ስም የመጀመሪያ ፊደል ያለበት ነው፡፡››

‹‹እሺ ይሁን>> አለ፤ የጭንቀት ትንፋሽ በመተንፈስ፡፡

‹‹እንግዲህ አስታውስ ያሉህ የሦስት ቀናት መጫወቻ ካርታዎች ብቻ ናቸው፡፡ በአንዱ ቀን አንዱን ካርታ ብቻ ነው መጠቀም የምትችለው፡፡ በነገራችን ላይ ጨዋታውን ለምን ቢሾፍቱ አናደርገውም፡፡››

‹‹ቢሾፍቱ .. ደብረዘይት?››

‹‹ምነው? አሪፍ ነው፡፡እንዲያውም ጨዋታችንን ለየት ያደርገዋል፡፡ በዛውም አብዛኞቹን ሀይቆች መጎብኘት እንችላለን፡፡››

‹‹እኔ እኮ በደንብ አላውቃትም››
👍7318