<<የሠው ፍላጎት እንዴት ነው የተዘበራረቀው? ይህቺን የመሠለች ውብና አፍቃሪ ሴት ገፍቶ እንዴት የማያውቃትን ሴት አፍቅሬያለሁ ብሎ ይሄን ያህል ይሠቃያል?እዚህ አጠገቤ ያለችው ኤደን ምን ይጎላታል? መልክ አላት፣ ፀባይ አላት፣ ብር አላት ... ከዚህ በላይ ምን ማሟላት ይጠበቅባታል?››ከወራት በፊት ስለዚህ ጉዳይ ሁሴንን ጠይቆት የመለሠለት መልስ ትዝ አለውና ፈገግ አለ፡፡
‹‹ወረት ነው አይደል እንዲህ የሚያንቀዠቅዠህ? አጠገብህ በጣም የሚያፈቅሩህ ሴቶች እያሉልህ አንተ ሌላ የማታውቃትን አየር የሆነች ልጅ ፍለጋ ምትሠቃየው?›› የሚል ጥያቄ ነበር ያቀረበለት፡፡
‹‹ትክክለኛ ሄዋኔን ፍለጋ ላይ ነኝ፡፡›› ብሎ መለሠለት፡፡
‹‹ታዲያ እነሱስ ሄዋንህ መሆን አይችሉም?››
‹‹አይመስለኝም፡፡ አየህ የሠው ልጅ አፈጣጠርን መለስ ብለን ስንመለከት
እግዚአብሔር መልኩን ወይም መሠሉን ማየት
ፈለገና ጭቃ አድቦልቡሎ እስትንፋሱን እፍ አለበትና አዳምን ፈጠረው፡፡ ልብ በልልኝ ለአዳም መፈጠር ዋናው ምክንያት እግዚአብሔር በአዳም ውስጥ የራሱን መልክ
ለማየት ስለፈለገ ነበር፡፡በሌላ አነጋገር አዳም
የእግዚያብሄር መስታወት ነው ማለት ትችላለህ፡፡ ቆየት አለና አዳም ደበረው፤ በብቸኝነቱ አጉረመረመ፤
እግዚአብሔርም ሠማው፤ እንቅልፍ ጣለበትና ከግራ ጎኑ አንድ አጥንት መዘዘና ሄዋንን አበረከተለት፡፡ የሄዋን የመፈጠር ምክንያት ደግሞ ምንድነው ?ብትለኝ የአዳም ድብርት ውስጥ መግባት ነው፡፡ አዳም ባይደብረው
እግዚአብሔር ሄዋንን ለመፍጠር ሀሳብ አይመጣለትም ነበር፡፡ወደ ነጥቤ ልመልስህና
በእያንዳንዱ አዳም የግራ ጎን ከእኔ እና ከአንተም ጭምር እግዚአብሔር አንድ አንድ አጥንት ወስዶ አንድ አንድ ሴት ፈጥሮልናል፡፡
ፍቅር የሚባለው ነገር ምን እንደሆነ ታውቃለህ
?ያለ ፍቃድህ ከግራ ጎንህ በእግዚአብሔር የተወሠደብህን የራስህን አጥንት ለማስመለስ
የምታደርገው ውጣ ውረድ ነው፡፡ ታዲያ ብዙውን ጊዜ ፍቅር እንከን የተሞላ የሚሆነው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?ክህደት፣ ውስልትና፣ፍቺ የመሳሰሉት ለምን እንደሚከሰቱስ
ይገባሀል? አንዷን በአጋጣሚ ትቀርባታለህ፤ ይህቺ ከእራሴው አጥንት
የተሠራች ነች ብለህ ትወስናለህ ፡፡አፈቀርኩሽ
ትላታለህ…ታገባታለህ፡፡ አሁን ሙሉ ሠው ነኝ፤
ሙሉ አካልም አለኝ የተወሠደብኝን የግራ ጎኔን
መልሻለሁ ብለህ ትኩራራለህ፡፡ ጥቂት ቆይቶ
ግን ያ አጥንት ካንተ ጎን የተወሠደ ሳይሆን ከሌላ አዳም ጎን የተወሠደ ሆኖ ይገኛል፡፡ ያ ማለት አጥንቱ አንተ ላይ በትክክል ገብቶ
አይገጥምም ማለት ነው፡፡ ወይ ይሠፋል አሊያም ይጠባል፤ወይ ያጥራል ወይ ደግሞ ይረዝምብሀል፡፡ ያ ደግሞ ምቾትህን ይነሳሀል፡፡ በሽተኛ ያደርግሀል፣ ይቆረቁርሀል፣ይጎረብጥሀል፤ በመጨረሻ ስቃዩ ሲበዛብህ ያ ቦታ እንደድሮ ባዶ ቢሆን ይሻለኛል ብለህ ትወስናለህ፡፡ አውጥተህ አሽቀንጥረህ ትጥለዋለህ ሌላ ያንተኑ ትክክለኛ ግጣምህን ፍለጋ ዳግመኛ አንድ ብለህ መኳተን ትጀምራለህ፡፡….እና
ማጠቃለያዬ ምን መሠለህ ፤የራሴውን አጥንት እንዳገኘሁ እርግጠኛ እስክሆን ድረስ ተረጋግቼ መቀመጥ አልፈልግም፡፡ ካለበለዚያ ያ ያንተ ዕጣ ነው የሚደርሠኝ፡፡›› በማለት ነበር ያስረዳው፡፡ በትውስታው ፈገግ ብሎ ወደ ሌላ ትካዜ ሊሸጋገር ሲል የኤደን ጥያቄ መለሠው፡፡
‹‹ልጆችህ ደህና ናቸው?››
‹‹ደህና ናቸው፤ እግዜር ይመስገን፡፡››
‹‹የውብዳርስ?››
‹‹እኔ እንጃላት፡፡››
‹‹እንዴት እኔ እንጃላት ... ?ወንዶች ስትባሉ በቃ ሁላችሁም አንድ አይነት ናችሁ? ሴትን ልጅ ቀምሳችሁ... ልሳችሁ ጣዕሟን ከጨረሳችሁ በኋላ ተፍታችሁ ከአፈር ስትደባልቁ ጥቂት እንኳን ፀፀት አይሠማችሁም? ግርም የሚለኝ እግኢአብሔር ለምን እናንተን እንደፈጠራችሁ ነው>>
‹‹የፈጠረንማ አንደኛ አቶ ሁሴን እንደሚለው መልኩን በእኛ በኩል ለማየት ነው፤ምክንያቱም እኛ እሱን እንመስላለን፡፡ ሁለተኛው ምድርን እንድናስተዳድርለት ነው፤ሦስተኛው እንድናመሰግነው ይመስለኛል፡፡ እንደ እኔ ሦስተኛው ብዙም የተሳካ አይመስለኝም፡፡ እናንተን ከፈጠረ በኋላ አይናችንን ወደ ፈጣሪ እንዳናነሳ እንቅፋት እንደሆናችሁን ነው የምረዳው፡፡›› ሁለቱም ምግቡን ስላቆሙ አስተናጋጅ መጥቶ መአዱን አነሳና ጠረጴዛውን አፀዳዳው፡፡...
✨ይቀጥላል✨
#ድርሰቱ ለምንድን ነው ቶሎ ቶሎ የማይለቀቀው የሚሉ ጥያቄዎች ይመጣሉ ጥሩ ጥያቄ ነው ቶሎ ቶሎ መለቀቅም አለበት ነገር ግን ይሄን ጥያቄ ከምጠይቁት መሀል ምን ያህሎቻቹ #የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ አድርጋችኋል ሁሉም ሰው #ሰብስክራይብ ያድርግ አደለም ነገር ግን ድርሰቱን ከሚያነበው መሀል Post ሲደረግ ቢያንስ አምስት ሰው እንዴት ይጠፋል ከ 100000 ምናምን ሺ ሰው መሀል ማለት ነው እስቲ አሁንም በቅንነት እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #አድርጉ እኛም ሞራል አግኝተን ቶሎ ቶሎ እንልቀቅ
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍113❤13👎5👏1