አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሲጨልም

ወደ ሰባዎቹ የሚጠጉ የሚመስሉ አንድ አረጋዊ “ልጄ” አሉት አስተናጋጁን፡፡ “የወሰድኩትን መድኃኒት ይዤብህ መጣሁ፣ እባክህን የሰጠኸኝን ወስደህ . . .”

አላስጨርሳቸውም፡፡ ግርግዳው ላይ ወደተለጠፈው ጽሑፍ አመለከታቸው፡፡‘የተሸጠ መድኃኒት አይመለስም አረጋዊው’ በለሰለሱ ቃላት መማፀን ያዙ፡፡

“ሰውዬ ዞር በል! ስራ ልስራበት! ለእንቶ ፈንቶ ጉዳይ የማባክነው ጊዜ የለኝም. . .” አለ ቁጣው እየተወለደ፡፡

“ዛሬ በዚህ ሰውዬ እንድጨቀጨቅ ተፈርዶብኛል ልበል?”

“እባክህን ልጄ አሳፋሪ ነገር ደርሶብኝ ነው ዘመድና ዕድር የለለኝ በመሆኑ እንጂ . . . ” አሉ ትሁት በሆነች ፈገግታ ሊያባብሉት እየሞከሩ፡፡

“ቅናሽ ዋጋ ብትከፍለኝም . . .”

“ይሄ ሰውዬ ነካ ያረገዋል ልበል?” አለና ሌሎች መድኃኒት ገዥዎችን ያስተናግድ ገባ፡፡ “ከያዙ አይለቁ” 

“ድህነት ቢፈትነኝ ነው ልጄ” አለ¸ያደፈና የነተበ ነጠላቸውን እያሳዩት፡፡ ነጠላው ከሰውነታቸው በከፋ ሁኔታ ያረጀውን ኮታቸውን ደብቆላቸዋል፡፡

“አቅሜ የደከመ ባይሆን ኖሮ . . . ” ጫማ ካገኘ የከረመ እግራቸውን እያዩ፡፡ አንዲት ተስተናጋጅ “አልመልስም ካለ አልመልስም ነው፡፡ ለምንድነው የሚነዘንዙት?” አለች በሚነጫነጭ ድምጽ “ይሄኮ ፋርማሲ እንጂ አዛውንቶች የሚጦሩበት የድኩማን መርጃ ድርጅት አይደለም”

አነጋገሯን ያልወደደው የሚመስል ሌላኛው ጎልማሳ ደግሞ “መድኃኒቱን ሙሉ በሙሉ የገዙት ከዚሁ መደብር ነው?” የሚል ጥያቄ አመጣ፡፡

“አዎ ዶክተሩ ፅፎ በሰጠኝ መሠረት”

“ምን ያሕል ፈጀብዎት?”

“ሰባ ሁለት ብር ከሰማኒያ አምስት ሳንቲም፡፡ መድኃኒቱን ወስደው ግማሹን እንኳን ቢሰጡኝ ምን አለበት?” አሉ በሃዘኔታ፤ “የሁለታችንንም የጋብቻ ቀለበት አስይዤ ነው ከማምነው ሰው የተበደርኩት”

“መድኃኒቱን ለምን መመለስ ፈለጉ?” ዘንቢል ያንጠለጠሉ ያንዲት ምስኪን እናት ጥያቄ፡፡

በዚህ ጊዜ አስተናጋጁ ጣልቃ ገባ፡፡ “ባህላዊ ሕክምና ብትከታተል ኪስ እንደማታራቁት ገብቷቸው ይሆናላ! ወይ ፀበል ሊያጠምቋት! ወይ . . .”

“ኧይ ልጄ! ጉዳዩን ብታውቀው ኖሮ ያፌዝክበት ምላስህን ታፍርበት ነበር . . .” አሉ እንባ እየተናነቃቸው፡፡

“መድኃኒቱን ምን ላድርገው? ልዋጠው ወይስ ሽንት ቤት ልጨምረው?”

“ለባለቤቴ ነው የምገዛላት ብለው አልነበር? በጠና ታማብኛለች የእድሜዬ ጀምበር እየጠለቀ ባበት ሰዓት ለእህል ያላነሱና ለትምህርት ያልደረሱ ሦስት ልጆች በትናብኝ እንዳትሄድ ፀልይልኝ ብለውኝ አልነበር?”

“ማለቱንስ ብዬህ ነበር ልጄ! . . . ብዬ ነበር”

“እና ሩብ ሰዓት ያህል እንኳን ሳይቆዩ ሃሳብዎን አስሰርዞ የገዙትን መድኃኒት የሚያስመልስ ምን ተአምር ተፈጠረ?! ቅድም የማይመለከተኝን ነገር ሲዘላብዱልኝ ነበር እኮ” አረጋዊው አንገታቸውን ደፉ፡፡ “እኮ ምን ቢፈጠር ነው . . . ?”

“ቤቴ ሳልደርስ ነው አንተ ዘንድ የመጣሁት”

“ለምን?” የሌሎቹ ጥያቄ፡፡

“ሰፈርተኞቼ ደጄ ላይ ሲጯጯሁ አየሁ፡፡ ባቤቴን በህይወቷ ልደርስላት አልቻልኩም!” አሉ አረጋዊው ድምጻቸው እየሻከረ፡፡ እንባቸው እየወረደ፡፡ በመድኃኒት ሻጩ ፊት ላይ ፀፀት ድንጋጤ እየታየ ድፍን መቶ ብር አውጥቶ በሻካራ እጆቻቸው ላይ አኖረው፡፡ ሌሎቹም ኪሶቻቸውን ይፈታትሹ ጀምር፡፡

“ይባርካችሁ ልጆቼ! ከፈን መግዣ ስላልነበረኝ እንጂ . . . ” እንባ ተናነቃቸው፡፡

መንሰቅሰቃቸውን እየቀጠሉ ወጡ፡፡

ፀጥታ!😔..😔..😥


YouTube ቻናሉን subscriber እያደረጋቹ ምርጥ ምርጥ ስራዎች

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😢91👍437🤔2
#ውርሰ_ውበት

ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን..

በፈረሶች ፀጉር
ለሚዋቡ ሴቶች
ውርስ ተይላቸው
አብሮሽ አይቀበር
ውበት ይሁናቸው

ብዙ ኩል ቀላቅለው
አሳር ለሚበሉ
ስራ አቅልይላቸው
አይንሽን ይትከሉ

ለቁንጅና ድጋፍ
አፍንጫ ጆሯቸው
ለጌጥ ለሚበሱ
ያንቺን አውርሻቸው
ውብ ጌጥ ነው በራሱ

ሳቃቸው እንዲያምር
ተነቅሰው በመፋቅ
አሳር ለሚበሉት
ጥርስሽን ስጫቸው
ወስደው ያስተክሉት

ሁሉንም አካልሽን
ከአፈር መበስበስ
መቀበር አድኚ
ቆመሽ ብቻ አይደለም
ሞተሽ ውበት ሁኚ

ፀባይሽ ግን ውዴ...

እኔ ያልቻልኩትን
አፈሩ ከቻለው
አደራ አታውርሺ
ፀባይሽ ቢወረስ
ትርፉ መቃጠል ነው

ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...

ውበትን ለሚሹ
ሴቶች አውርሻቸው
እኔም ያንቺ አፍቃሪ

እኔም ያንቺ አፍቃሪ
ውርስሽን ልካፈል
እነሱን ላግባቸዉ

🔘ልዑል ሀይሌ🔘


YouTube ቻናሉን subscriber እያደረጋቹ ምርጥ ምርጥ ስራዎች ታገኙበታላቹ Subscribe አድርጉና ረጅም ልብወለድም እንጀምርበት😘

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍30😁18👏3🤔1
🍄በ'ነሱ ቤት🍄
👁ክፍል አርባ ሁለት👁
👁👁👁
የቤቱ ድባብ ለየት ብሏል ሁሉም በጉጉትና በደስታ ከመሞላታቸው በተጨማሪ ፣ዘፈኑም ሽርጉዱም ደርቷል ፣የጌታነህ እናት ዘመዶቿን ጠርታ የደስታዋ ተካፋይ አድርጋቸዋለች ፣ መሳይ ከልብ ምቷ ጋር ከጉጉታጋር ጥግ ይዛ ተቀምጣ ትቁለጨለጫለች ፣ አሳቧ ሁሉ እዛ የለም ፣በተደጋጋሚ ሰአቷን ታያለች ፣ እነገታነህ እስከ አስር ሰአት ቤት እንደሚደርሱ አሳውቀዋል ፣ እሷም ቶሎ ሰአቱ ቆጥሮ ልጇን ለማየት ጓጉታለች ፣  የጌት ነህ እናት ደሞ በዚ ቀን ለሁሉም ቤተሰቦቿ የልጇን ልጅ ለማስተዋወቅ ቆርጣ የነሱን መድረስ እየተጠባበቀች ነው ፣የአብላካት እናት ይቆይ ብትላትም ፣እሷ ግን ፣መገላገል ፈልጋለች ።
እንግዶቹ የጥሪው ምክንያት በግልፅ ባይገባቸውም ፣የጌታነህ እናት በዛ በተንጣለለ ቬላ ቤቷ ጋብዛ የማይቀር ሆኖባቸው በደስታ ታድመው ፣የቀረበላቸውን እየተቋደሱ ያወካሉ ፣   ሌላ ጥግ ላይ ሰመረ እና አስተናጋጁ ሰሚር ተቀምጠው ፣የነ አብላካትን መድረስ ጓጉተው እየጠበቁ ፣ነው
በተለይ ሰመረ አብላካት ይዛው የሄደችውን ልቡን ይዛለት እስክትመጣ ከራሱጋርም አይመስል ፣
አብላካትን የመጀመሪያ ጊዜ ያገኛትን እለት እያስታወሰ በመገረም በውስጡ ከራሱ ጋር ይነጋገራል ፣ያቺልጅ ትንሽ ልጅ ነበረች ከመቼው ትልቅ ሰው ሆና ተቆጣጠረቺኝ ፣ ይሄማ የፈጣሪ ስራ ነው ፣የኛን የተበላሸ አካሄድ ማስተካከያ የተላከች ናት ፣ኧረ እንደውም በኔ እና በጌት ነህ አማካኝነት ከወላጅ አባቷ እንድትገናኝ አዟዙሮ ያመጣት አስቦ ነው ፣ ሆሆ ነገሩ እኮ የማይታመን ነው ። አብላካት የመስፍን ልጅ ፣ የኔ የልብ ህመም ፣የጌታነህ የወንድም ልጅ ፣ ። በተለይ ደሞ ህመሟ ነው ቤተሰቧን እንድታቅ ያደረጋት ፣ የመስፍን ወላጆች ግን ክፋታቸው ለክፉ አልሰጣቸውም ፣እንዲማሩበት ሁለተኛ እድል ተሰጣቸው ፣እነሱም ተማሩበት ፣ ወይ ጉድ ፣
"ሰመረ "
"አቤት ሰሚር
"አልሰማኽኝም እንዴ
"እም ምን አልከኝ
"እየደረሱነው እያሉ እኮ ነው አልሰማህም እንዴ ፣የጌታነህ አባት ደውሎ ይዣቸው እየመጣው ነው አለ "
"ኧረ ማማነው ያለው "
"መሳይ ናታ አሁን ነግራኝ ስትሄድ አላየሃትም ኧረ ወንድሜን ከራስህ ጋር አልነበርክም ማለት ነው "
"ወይኔ ልብ አላልኳትም "አለ ሰመረ
"ኧረ አትጨነቅ አሁን ሁሉም ነገር አልቋል እኮ ልትደሰት ነው የሚገባው ።ይልቅ ወጣ ብለን እንጠብቃቸው እንዴ"አለው
"አይ እዚው ብንሆን ይሻላል ፣ግርግሩም በዝቷል ፣ይሄ ሁሉ ሰው መጥራት ነበረባቸው ግን ?"አለ ሰመረ አብላካት እንድትጨናነቅ አልፈለገም
"ያው ታውቃለህ በ'ነሱ ቤት ላጠፉት ጥፋት ማካካሻ ነው ፣ "ብሎ ሰሚር ፈገግ አለ
ሰመረ ተከትሎ ፈገግ አለ ፣
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አብላካት በቀጥታ ከመኪናው እንደወረደች ፣እናቷን ነበር የፈለገችው ፣መሳይ አይኗ ሲንከራተት አይታ ሮጣ መጥታ ተጠመጠመችባት ፣ተቃቅፈው አለቀሱ ፣ የጌት ነህ እናት መጥታ እስክታላቅቃቸው ድረስ ፣ሊላቀቁ አልቻሉም ነበር ፣ የጌታነህ እናት አብላካትን ተቀብላ እያገላበጠች ስትስም ፣እንግዶቹ ሁሉ የመሰላቸው ወይ የጌታነህ ወይ የመስፍን እጮኛናት ብለው ነበር ያሰቡት ፣አብላካት የጌታነህን እናት አይኖቿ ውስጥ እያየች ደጋግማ ስትስማት ፣የጌታነህ እናት አንጀቷ ተላወሰ ፣ መስፍን ወደ መሳይ በመሄድ እጁን ዘረጋላት ፣መሳይ ትንሽ ካቅማማች በዋላ አቀፈችው እና "አመሰግናለው ልጄን አተረፍክልኝ አመሰግናለው "ብላ አለቀሰች
"አይ ልጃችን ናት መሳይ እባክሽ ቅሬታሽን አንሺ ልኝ እድሜ ልኬን መክፈል ያለብኝን ዋጋ ላንቺና ለልጄ እከፍላለው ቃሌ ነው "ብሎ ከፊቷ ተንበረከከ
"ኧረ ተነስ እባክህ ተነስ ይቅር ብዬሃለው ፣ፈጣሪ እንዲ እንዲሆን ስለፈለገ ይሆናል ፣ተነስ በቃ"ብላ ጎተተችው ፣
አብላካት የሁለቱን ሁኔታ አየት አድርጋ ወደ ጌታነህ ዞረች ጠቀስ አደረጋት ፈገግ አለች ፣ እናም አይኖቿን ወደሌላ አቅጣጫ አሽከረከረች ፣ የፈለገችውን አገኘች ሰመረ አይኖቹ እሷላይ ሲንከራተቱ ያዘቻቸው....

..
ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
157👍88👏3😁2
#ያሳፈርኩህ_እንዳታፍር_በመፈለጌ_ነው

‹‹ እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ ያምሻል?›› ስል እናቴ ላይ በብስጭት ጮህኩባት ... አንድ ጥግ ላይ ኩርምት ብላ እና አንገቷን ደፍታ በቁጣ የምደነፋባትን ንግግር ሁሉ ስታዳምጠኝ ትልቅ ወንጀል ሰርቶ ዳኛ ፊት የቀረበ ወንጀለኛ እንጅ የሰባት አመት ልጇ የሚጮህባት እናት አትመስልም ነበር !
ብስጭቴ ልክ አልነበረውም እንዲያውም ከንዴቴና ከቁጣየ የተነሳ እናቴ አስጠላችኝ ‹‹አሁኑ ብትሞች ግልግል ነበር›› ስል ጮህኩባት እውነቴን ነበር እንዲህ ከምታሳፍረኝ ብትሞት እና ብገላገል በሰላም እኖር ነበር ! እንዴት እንዳስጠላችኝ እንደቀፈፈችኝ ! ደምስሬ ተገታትሯል እንባየ በአይኖቸ ሞልቶ በእልህና በጥላቻ አስቀያሚዋ እናቴ ፊት እየተንቀጠቀጥኩ ነበር ! አርሷ ግን አንገቷን ደፍታ አሮጌ ጫማወቿን አቀርቅራ እየተመለከተች በዝምታ የምላትን ሁሉ ታደምጥ ነበር !
እናቴ ካለአባት ብቻዋን ነበረ ያሳደገችኝ ….እኔን ለማሳደግ ብቸኛ የገቢ ምንጯ የነበረው በምማርበት ት/ቤት ውስጥ ለመምህራንና ተማሪወች ምግብ በማዘጋጀት የሚከፈላት አነስተኛ ክፍያ ነበር ! እንዲህም ሁኖ የምማርበት ትምህርት ቤት የሃብታም ልጆች መማሪያ ስለነበርና እኔም በልብስም ሆነ በመማሪያ ቁሳቁሶቸ ከማንም ስለማላንስ ስለእናቴ ማንነት ማንም አያዉቅም ነበር እኔም ስለእናቴ ተናግሬ አላውቅም !
በእናቴ የማፍረው ደሃ ስለሆነች ብቻ አልነበረም አንድ አይን ብቻ የነበራት ሴት ስለነበረች እንጅ ! በእውነትም እናቴ አስቀያሚ መልክ ነበራት ! የግራ አይኗ የነበረበት ቦታ ባዶ ጉድጓዱ ብቻ ቀርቶ አንዲት ትንሽ አይኗ ብቻ እየተቁለጨች ድንገት ለተመለከታት ከማስቀየም አልፎ ትቀፍ ነበር ! የብዙ ጓደኞቸ እናቶች አይኖቻቸው በኩል ተከበውና አምረው ስመለከት የእናቴ አንድ አይን ያሳፍረኛል ! ምንም ማድረግ አልችልም ‹‹ምንም ቢሆን እናቴ ናት ›› እያልኩ ነገሩን ለመቀበል ብሞክርም አልቻልኩም ! በእናቴ መልክ በጣም እሳቀቅና አፍር ነበር! በእርግጥም የእናቴ አንድ አይናነት ለእኔ የማልቋቋመው የሃፍረት ምንጭ ነበር !
ቢሆንም እናቴን ማንም ስለማያውቃትና ስለዚህም ጉዳይ ተናግሮኝ የሚያውቅ ተማሪ ስላልነበር እናቴን ሳያት ካልሆነ በስተቀር ትዝ አትለኝም ነበር ! በአንድ የተረገመ ቀን ታዲያ እማርበት ወደነበረው የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተማሪወች ብቻ ወደሚገኙበት አጥር ውስጥ እናቴ ስትመጣ አየኋት ! ራሴን ልስት ምንም አልቀረኝም ... ተማሪወቹ የእናቴን አይን ሲመለከቱ በሳቅ አውካኩ አሾፉባት የእማማ ፊት ላይ ግን ምንም መከፋት ሳይታይ ወደእኔ ትራመድ ነበር …..ድንገት ወደኋላየ ሮጥኩ ‹አላውቃትም እችን ሴት ወዲያ በሉልኝ ›› እያልኩ ሮጥኩ ! ይሁንና ተማሪ ጓደኞቸ መዘባበቻ አደረጉኝ
‹‹አንተ እናትህ አይኗ የት ሂዶ ነው? ››
‹‹እናትህ 'ሆረር' ፊልም የምትሰራ ነው የምትመስለው ››
‹‹እናትህ በአንድ አይኗ ሽንኩርት ስትከትፍ እጇን አብራ አትከትፍም ?ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ›› ተማሪው አሽካካ ተውካካ ለዘላለሙ ልቤን የሚሰብር የእናቴ ድርጊት ሁኖ ተሰማኝ ! ከዛን ቀን በኋላ የትምህርት ቤት ጓደኞቸ የነበሩ ህፃናት የሚስቁት የማሾፍ ሳቅና የሚወረውሩብኝ ቃል የሚያሳፍርና አንገት የሚያስደፋ ነበር ! እድሜ ላሳፈረችኝ እናቴ ! እጠላታለሁ ! እቤቴ ማታ ስመለከታት እንኳ የጓደኞቸ ሳቅ ነው የሚታወሰኝ !
በዚህ ሁኔታ አብሪያት ልኖር ስላልቻልኩ ትንሽ ከፍ ስልና ነብስ ሳውቅ እናቴን ትቻት ወደሌላ ሩቅ አገር ትምህርት ቤቱ ባመቻቸው እድል ተጠቅሜ ተሰደድኩ ! እዛም ማንነቴን በማያውቁ ሰወች መሃል በደስታና በኩራት እኖር ጀመረ ! አድጌ ዩኒቨርስቲ ስገባ ስራ ስይዝ እና ሚስት አግብቸ ልጆች ስወልድ ሁሉ እናቴን አይቻትም ስለእርሷም ወሬ ሰምቸ አላውቅም ነበር ! ትልቅና የሚያምር የግሌ መኖሪያ ቤት ቆንጆ ሚስትና የሚያማምሩና ጎበዝ ልጆች አሉኝ !
ሚስቴም ሆነች ልጆቸ ትክክለኛውን ነገር አያውቁም ነበር ! ስለእናቴ ሲጠይቁኝ እንዲህ እላቸው ነበር ‹‹ እናቴ ውብ ነበረች... በተለይ አይኖቿ ጨረቃን የሚያስንቁ ከውስጣቸው ብርሃን የሚረጩ ውቦች ነበሩ የእናቴን አይን ተመልክቶ በፍቅሯ የማይማረክ የለም ግን ከብዙ አመታት በፊት ሙታለች ›› በቃ!! በዚህም የውሸት ታሪክ ታላቅ ኩራት ሰማኛል !
አንድ ቀን ግን ይህ ውብ ኑሮየን የሚያደፈረስ አሰቃቂ ነገር ተፈጠረ ! የቤቴ በር ተንኳኳ ….ትልቁ ልጀ በጉጉት በሩን ከከፈተው በኋላ በድንጋጤ እየጮኸ ወደቤት ተመለሰ ….ሁላችንም ያስደነገጠውን ነገር ለመመልከት በእኔ መሪነት ክፍቱን ወደተተወው በር ተንጋጋን ይህች አሰቃቂ እናቴ በር ላይ ቁማ ነበር ! ከበፊቱ የበለጠ ተጎሳቁላና የፊቷ አጥንት ቀርቶ የአይኗ ጉድጓድ የባሰ ሰፍቶ ይታያል አንድ አይኗ ሲቁለጨለጭ አንዳች አስፈሪ አውሬ ትመስል ነበር !
ድንጋጠየን ተቋቁሜ ‹‹ምን ልርዳሽ ሴትዮ›› አልኳት አጠያየቄ ግልምጫ የታከለበትና ፍፁም የማላውቃት ሴት መሆኗን የሚያሳይ ነበር
‹‹ የኔ ልጅ ላይህ ጓጉቸ ነበር ….›› ብላ መናገር ከጀመረች በኋላ ወደሚስቴና በድንጋጤ የእናታቸውን ቀሚስ ጨምድደው ወደቆሙት ልጆቸ በዛቹ አንድ አይኗ ተመልክታ እንዲህ አለች ‹‹ ይቅርታ አድራሻ ተሳስቶብኝ ነው ›› ከዛም ተመልሳ መንገድ ጀመረች ጀርባዋ ጎበጥ ብሏል ፀጉሯም ግማሽ በግማሽ ነጭ ሁኗል ! እውነቱን ለመናገር ምንም አላዘንኩም እንደውም በየሄድኩበት እየተከተለች ኑሮየን መበጥበጧ አበሳጨችኝ !!
ከአንድ አመት በኋላ ድሮ እማርበት የነበረው ትምህርት ቤት ያስተማራቸውን ተማሪወች ጠርቶ የምስረታ በአሉን ሲያከብር የክብር እንግዳ አድርጎ ስለጠራኝ ወደጥንት መንደሬ በአሉ ላይ ለመገኘት ሄድኩ ! እናቴ የነበረችበት የጥንት መንደር ምንም ሳይሻሻል ከነ ደሳሳ ቤቶቹ እዛው ነበር !
በአሉን ተሳትፌ ልመለስ ስዘጋጅ አንድ እንደእናቴ የተጎሳቆለ ሰው ወደእኔ እየተጣደፈ መጣና እንዲህ አለኝ
‹‹ እናትህ ሙታለች … !! ›› እውነት እላችኋለሁ ትልቅ እረፍት ተሰማኝ ካሁን በኋላ መሳቀቄ ሃፍረቴ ሁሉ አብሮ ሞተ ! የማፍርበት የኋላ ታሪኬ መቃብር ወረደ ! እፎይይይይይይይይይ! ይሄ መርዶ ሳይሆን ‹‹የምስራች›› ነበር!!
ይሁንና ‹የምስራቹን › ያበሰረኝ ሰው አንድ አሮጌ ፖስታ ከአሮጌ ኮቱ ኪስ አውጥቶ ሰጠኝና ‹‹እናትህ አደራ ስጥልኝ ብላኝ ነው ›› ብሎ ፖስታው ጋር ትቶኝ እየተጣደፈ ሄደ !ፊቱን ሲያዞርና ከእኔ ለመራቅ ሲጣደፍ አንዳች ቆሻሻ ነገር የሚሸሽ ነበር የሚመስለው ! ፖስታውን ከፍቸ ድሮ የማስታውሰው የእናቴ የእጅ ፅሁፍ ጋር ተፋጠጥኩ አጭር እና ግልፅ መልእክት ነበር !
‹‹ የምወድህ ልጀ እድሜ ልክህን ሳሳፍርህ እና ሳሳቅቅህ በመኖሬ ይቅር በለኝ …. ለትልቅ ደረጃ መድረስህን እቤትህ ድረስ መጥቸ በአንድ አይኔ በማየቴ ደስ ብሎኝ ቀሪ እድሜየን ኑሪያለሁ ! ውድ ልጀ ያሳፈርኩህ እንዳታፍር በመፈለጌ ነው ….በልጅነትህ አደጋ ደርሶብህ አንድ አይንህ ጠፍቶ ነበር እድሜ ልክህን በአንድ አይን እንድትኖር የእናት አንጀቴ ስላልቻለ የራሴን አንድ አይን ልለግስህና በቀሪው አንድ አይኔ ደስታህን ልመለከት ስለፈለኩ ይሄንኑ አድርጊያለሁ !! በዚህም እኮራለሁ ልጄ ! ………እናትህ ››
ከውስጥ የማይወጣ ፀፀት ተሰማኝ ያን ፊት እንደገና ማየት ተመኘሁ ግን😢😢
👍87😢456😱3👏2
#የትብብር_ጥያቄ
የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ለማድረግ የሚጠይቀው ውስጣዊ ቅንነትን፣ለሰዎች መልካም ማሰብን፣ደግነትን ብቻ ነው።አሁን በቅንነት የምጠይቃችሁ ነገር ቢኖር ይህንን ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ እንድትተባበሩ ነው።ስለመልካምነታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ።
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
7👍2👏1😁1
#ባራኪ
.
.
አንቺ ዳቦ ሆነሽ
ለበረከት ቀርበሽ፣
እኔ ቄስ ብሆን
የነፍስ አባት ቆራሽ፣
.
.
"ክቡርነትዎ አባ ቄሱ፣
በረከቱ ላይ ይቀድሱ፣
ቀድሰውም ይቁረሱ፣
ቆርሰውም
ለምእመናኑ ያዳርሱ፣"
.
.
ብባል ወስነው ቢፈርዱብኝ፣
መቁረሱ ግዴታ ቢሆንብኝ፣
.
.
በመስቀሉ
ባርኬ ቀድሼሽ፣
ሶስት ቦታ
ከፍዬ ቆርሼሽ፣
እንዲህ ነበር የማከፋፍልሽ ፣
.
.
አንደኛው ለራስ ለቆራሹ፣
ሁለተኛው ለቄስ ለቀዳሹ፣
ሶስተኛው
ለነፍስ አባት
በፀሎቱ ምእመናንን ላስታዋሹ፣
.
.
እልና ሁለመናሽን
እከተዋለሁ ከኪሴ፣
ማንም እጅ አትገቢም
አንቺ ነሽ የራሴ፣
.
.
ባንቺ የመጣ
አልፈራም ኩነኔ፣
ገሀነም ልውረድ
እንጂ
ምንጊዜም ነሽ የኔ!!!

🔘ሀብታሙ ወዳጅ🔘

በቅንነት #Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😁22👍141👎1🥰1
🍄👁በ'ነሱ ቤት👁🍄
👁ክፍል አርባ ሶስት👁
🍄👁🍄👁🍄👁🍄
ሰመረ ፈልጋ ስላየችው ደስ የሚል ልዩ ስሜት ተሰማው ።ከቤተሰቧ ቀጥሎ ለሷ አስፈላጊ ሰው መሆኑን ልቡ ነገረው ።እናም ሂሉንታ ለሚሉት ነገር ቦታ ሳይሰጥ ወደሷ ፈጠነ ፡ አብላካት ልቧ ምቱን ሲቀይር ተሰማት  ፡አስተናጋጁ ሰሚር የሁለቱን ሁኔታ በጉጉት ይመለከት ጀመር ፣ጌታነህ ሰመረ ወደ አብላካት ሲመጣ አይቶ ምን ማድረግ እንዳለበት ለማሰብ ጊዜ ከማግኘቱ በፊት ፣ሰመረ አብላካት አጠገብ ደርሶ ቆመ ፣አብላካት እንደመጣ ያቅፈኛል ብላ ስትጠብቅ አጠገቧ ሲደርስ ፍዝዝ ብሎ ቆሞ ሲያያት ግራ ገባት ለመናገር ፈልጋ ከንፈሮቿ ሲንቀጠቀጡ ዝምታን መረጠች ፣ሰመረ ፍዝዝ ብሎ ሲያያት ቆይቶ " ሚጣ የኔ ውድ ዳግም ተያየን ደስ ሲል"ብሎ እንባ ባዘሉ አይኖቹ አያት
"ሰሙ ዳግም የማገኝህ አልመሰለኝም ነበር "ብላ ተጠጋችው ፣ሰመረ ተጠመጠመባት ። ተቃቅፈው ደስታቸውን ሲገላለፁ የሁሉንም ትኩረት ሳቡ ። መስፍን የልጁን ሁኔታ አይቶ እንዳትጎዳበት አሳብ ገባው ፣ሰመረን ያውቀዋላ ከወንድሙ ጋር በየናይት ክለቡ ሲዞር ለሊቱን ከተለያዩ ሴቶች ጋር ሲያነጉት ሁሉንም ያውቃል ። ሰመረ ለልጁ መገኘት አስተዋፅዖ እንዳለው ቢሰማም ፣ ወንዶች ባሕሪያችን አስቸጋሪ ነው ልጄን ቢጎዳብኝስ ምን ሊፈጠር ነው ብሎ ተጨነቀ ። ጌታነህ በበኩሉ ከሰመረ ጋር ምንም ነገር ለመነጋገር ባልፈለገ ሁኔታ ወደ አስተናጋጁ ሰሚር ሄዶ እንኳን ደስ አለን ብሎ ጨበጠው ። ሰሚር በደስታ ተዋጠ ለአብላካት መትረፍ የሁሉም አስተዋፅዖ ነበረው ።
ሰመረ አብላካትን ለቆ በደስታ አስተዋላት ይበልጥ ቆንጆ ሆናለች ልብ ብሎ ሲያያት የመስፍን የሆኑ ምልክቶች ፊቷላይ መሳሉን አስተዋለ ለራሱ ገረመው አብላካት ከመሳይ እና ከመስፍን አጣምራ የያዘችው ቁንጅና ልዩ ነበር ። ይሄን ውበት ደሞ ይዛ ወደሱ እንደምትመጣ ሲያስብ ልቡ በአሴት ጨቤ እረገጠ ።
  ድንገት ጮክ ብሎ አንድ ድምፅ ሲመጣ ሁሉም በአንድነት ወደ አንድ አቅጣጫ ዞሩ ፣የጌታነህ እናት ነበረች እንግዶቿ እንዲያዳምጧት በትህትና ተናገረች ሁሉም ፀጥ አለ ።የአብላካት እናት በምልክት ለመነቻት ፣ለንግዶቹም ለአብላካትም አዲስ የሆነውን ነገር ልትናገር መሆኑን ገብቷታል ፣አብላካት የመስፍንን አባትነት ስትሰማ እንዳትጎዳባት ፈርታለች ፣የጌታነህ እናት ግን ቆርጣ ተነስታለች ሁሉም በአንድነት እንዲሰሟት ፈልጋለች .....

***

👁በ'ነሱ ቤት👁
🍄ክፍል አርባ አራት🍄
👁🍄👁🍄👁🍄👁
የጌታነህ እናት የሁሉንም ትኩረት መሳቧን ካረጋገጠች በዋላ ፣ጉሮሮዋን አጥርታ ንግግሯን ጀመረች
  "ጥሪዬን አክብራቹ እዚ የደስታዬ ተካፋይ ለመሆን የመጣቹ የምወዳቹ ዘመድ ጓደኞቼ ላመሰግናቹ እወዳለው ፣ ዛሬ ለኔ የተለየ ቀን ነው ፣ ምክንያቱም በጣም ስፈራውና ሲያስጨንቀኝ ከነበረው  የሕይወት መስመር በፈጣሪ ፍቃድ ወጥቼ በትክክለኛው መንገድ ላይ የቆምኩበ ፣ ነው ። ከዚበፊት በልጆቼላይ የነበረኝ አላፊነት ላይ ቸልተኛ በመሆኔ ብዙ ያጠፋውት ነገር ነበር ፣ በዛም ተቀጥቼበታለው ፣ነገር ግን ፈጣሪ ቅጣቱን አላረዘመብኝም ፣ እንደበደሌ ሳይሆን ምህረትን ልኮልኛል ፣ "ብላ እንባዋን ከአይኖቿ ጠረግ አደረገች በዛውም ትንፋሽ ወሰደች ።ጌታነህ ባልተመቸው አይ ነት አስተያየት ያያታል 'ምንድነው ይሄ ሁሉ ይቅርታ እዝቤ ምን እንደምታወራ ሲገባው አይደል ይልቅ ወደገደለው ብትገባስ ማሚ ደሞ 'የላል በውስጡ ፣
የጌታነህ እናት ንግግሯን ቀጥላ "እእ ዛሬ የምነግራቹ ታሪክ ስለ አንዲት ታዳጊ ልጅ ነው ,,,,,,,,,,,,"ብላ ስለ አብላካት የህመም ሁኔታና እንዴት እንዳገኟት በሰፊው ካብራራች በዋላ መልሳ ዝም አለች ፣እንግዶቹ ስለ በጎ አድራጎታቸው መደሰታቸውን በጭብጨባ ገለፁ ፣ የአብላካት እናት ወደልጇ በመሄድ አጠገቧ ቆመች ፣ቀጥሎ በሚነገረው ነገር ችግር ውስጥ እንዳትገባባት ፈርታለች ። መስፍን ወደ አብላካት እያየ ፈገግ ሲል ምላሽ ሰጠች ፣ ሰመረ አብላካትን እጇን ያዝ ሲያደርጋት ወደሱ ዞረች "ሚጣ ገኒ ለምትናገረው ነገር ምንም ይሁን ምንም ተዘጋጂ እሺ ፣የኔ ጠንካራ"ብሎ አንሾካሾከ አብላካት ምን በሚል አስተያየት አየችው  ፣ልቡ አዘነላት እጇን አጥብቆ ያዛት
የጌታነህ እናት ቀጠለች" እና ይህች ልጅ በኛ ትክክል ያልሆነ አስተሳሰብ ምክንያት ያራቅናት  የልጃችን ልጅ ናት !  አአዎ የመስፍን ልልጅ ናት ፣"ብላ አለቀሰች ፣እዛ የታደመው ዘመድ አዝማድ በአንዴ ሃሃ አለ የሚሰሙትን ማመን ነበር ያቃታቸው ፣ሁሉም እርስ በእርስ እየተነጋገሩ ወደ አብላካት ፊታቸውን አዞሩ ፣ መስፍን በደስታ ፊቱ እያበራ ከጌታነህ ጋር ተሳስቆ ተቃቀፈ ፣የአብላካት እናት ልጇ እንዳትወድቅባት የፈራች ይመስል ዞራ አቀፈቻት ፣ሰመረ እጇን አጥብቆ እንደያዛት ነበር ። አስተናጋጁ ሰሚር ጭንቅላቱን በቀኝ እጁ እያሻሸ ወደነ አብላካት እያየ ቀጥሎ ለሚፈጠረው ነገር ተጨንቆሃል ፣  አብላካት በሰማችው ነገር አንዳች ነገር ሳይገርማት እናቷን አቅፋ በመቆሟ ፣ የጌታነህ እናት ግራ በመጋባት ስታይ ቆይታ ፣ከነበረችበት ቦታ በፍጥነት እየተራመደች በመምጣት ጌታነህን እና መስፍንን እጃቸውን ይዛ በማላቀቅ "ምንድነው ?"ብላ ጠየቀች
"ውይ ማሚ ሁሉንም ነገር እዛ እያለን ነገረናታል ለምን ይመስልሻል ልጅሽ የታመመው ፣ አቢ ስለጉዳዩ ስታውቅ እራሷን መቆጣጠር አቅቷት ነበር በዚ የተነሳ ደንግጦ ነበር የታመመው ፣ በዋላ የሱ ሁኔታ ከሷ ሲብስ እሷ ተረጋጋች ፣ ሁሉንም ነገር ለማስተካከል ለለፋው ለትንሹ ልጅሽ አስቢ እድሜ ለሱ በይ !"ብሎ ጌታነህ ደረቱን መታ እያደረገ ጎረረ ። በዚ ጊዜ ትልቅ ነገር በመገላገሏ ጌታነህን አቀፈችው ። ቀጥላ ወደ አብላካት በመሄድ "ሃያትሽን ይቅር ትያታለሽ የኔ ውድ"አለቻት "ይቅር እንድንባባል አስቦ ይህን ሁሉ ነገር ፈጣሪ ካደረገ እኔ ማነኝና ይቅር የማልለው "አለች አብላካት ተረጋግታ "የኔ ውድ የልጅ አዋቂ ነሽ ባንቺ ኮርቻለው ነይ ልቀፍሽ "ብላ አቀፈቻት ።የጌታነህ አባት መጥቶ ተቀላቀላቸው ።አብላካት እስኪደክማት ከዘመድ አዝማዱ ጋር ትውውቅ አደረገች ፣ ሰመረ ብቻዋን ሊያገኛት ቢጥር አልተሳካለትም ያም ያም ይወስዳታል ፣እንኳን እሱ እናቷም ልታወራት አልቻለችም በአብታም ዘመዶች ተከበበች ፣
ጌታነህ ሰመረ አይኖቹ ሲንከራተቱ ሲያይ ትንሽ እራራለት ፣ ወደሱ በመሄድ "እሺ መቼም እኔና አንተ ወደፊት ትንሽ ፋይት ማድረጋችን አይቀርም"አለው
"አሁን ደሞ ለምኑ ነው "አለው ሰመረ
"ያው እህቴን በተመለከተ "አለው
"እእእ ,,"ብሎ ሊቀጥል ሲል
"ኪኪኪኪኪ ኧረ ስቀልድህ ነው ጓደኛዬ ተረጋጋ"ብሎ እጁን ዘረጋለት
"አመሰግናለው እንኳን ደስ አለህ መቼም እንዲ ይሆናል ብለን ባላሰብነው ሁኔታ ነው ሚጣን ያገኘናት"አለው
"አዎ ማን ያቺ ምስኪን ልጅ የኛው መሆኗን ይገምታል ፣"አለ ጌታነህ
"በጣም እኔማ እስካሁን ማመን ተስኖኛል ሚጣ የጌታነህ ቤተሰብ "ብሎ በፈገግታ አፉን ያዘ
"ሚጣ ስትላት ብትሰማ አቢ ትገልሃለች "ብሎ ሳቀ
"ሚጣ አይደለም ስሜ አብላካት ነኝ ነው የምትለው ፣እንደሱ ስትለኝ በጣም ነው ደስ የሚለኝ ኪኪኪ"ብሎ  ሞኛሞኝ የሚያስመስል ሳቅ ሳቀ ።ጌታነህ ሲያየው ቆይቶ"ውይ ጓደኛዬ የሌለ አንግ ይዛሃለች "ብሎ ሳቀበት እና"ብቻ ተጠንቀቅ እጇን የገፋኽው እለት ከኔ ነው ፀብህ ይህን አላፊነት የሰጠውህ ምንም ማድረግ ስለማልችል ነው ፣ምክንያቱም ስላንተ እዛ በነበርንበት ጊዜ ነግራኛለች በጣም ወዳሃለች በፍቅር ጣልቃ መግባት ነገር ማበላሸት ነው ። እና አደራ !"አለው ።ሰመረ አንገቱን ነቅንቆ
👍9217
እሽታውን ገለፀ ። በዚ ጊዜ እንየው መጥቶ ተቀላቀላቸው ፣ ሁለቱንም በመገረም እያያቸው ስለአብላካት ማውራት ጀመረ ከመጀመሪያው ጀምሮ ሲያገኟት የነበረውን እያስታወሰ ፣የሰመረን ሁኔታ ጭምር ።ዛሬላይ የሆነው ሁሉ የሆነው በሰመረ ምክንያት እንደሆነ ተናገረ ፣ ሁሉም በመስማማት ፣አንገታቸውን ነቀነቁ ።ሰመረ አሻግሮ አብላካትና መስፍን ሲያወሩ አየ ፣የአቤል ካት ደስታ ፊቷላይ ይገለፃል ። ውበቷን አደነቀ ከዛ መሃል ድንገት መንጭቀ ይዘሃት ጥፋ ጥፋ የሚል ስሜት ተሰማው የሆነቦታ,,,,ሁለቱ ብቻ የሚሆኑበት ቦታ,,,,ለየት ያለ ቦታ ,,,,,,,,,,,,

ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
85👍28😁1
<<ደሞዝ ወጥቷል>> የሚል፥
ሜሴጅ የገባ ቀን፥ እንዲህ ያደርገኛል
.
.
አዝዤ ልጎርሰው፥
ያጠቀስኩት ሽሮ፥ አፌን ገፍቶ ይርቃል
ማባያ የሰነግኩት፥
አረንጓዴ ቃርያ፥ በቅፅበት ይደርቃል
እንደ በረኅ ምድር፥
እንጀራዬ ከስሎ፥ ይሰነጣጠቃል።
ጆሮዬ ከፒያሳ፥
ቦሌ እሚንቆረቆር፥ ይሰማዋል ድራፍት
አይኔ ካራት ኪሎ፥
ቄራ የሚፈረሽ፥ ይታየዋል ፍትፍት።
.
.
<<ደሞዝ ወጥቷል>> የሚል፥
ሜሴጅ የገባ ቀን፥ እንዲህ ያደርገኛል
.
.
ያበዳሪን ሰፈር፥
በጀግና አረማመድ፥ ሄዳለሁ ሰንጥቄ
የቡቲኩን ጌታ፥
የጃኬቱን ዋጋ፥ አልፋለሁ ጠይቄ
ስቸስት የከዳኝ፥
ወዳጄን ፈልጌ፥ አልሳለሁ ጥፊ
እንዳያዩኝ ብዬ፥
ከተደበቅኋቸው፥
ካ'ከራዬ ጋራ፥ እነሳለሁ ሰልፊ።
.
.
<<ደሞዝ ወጥቷል>> የሚል፥
ሜሴጅ የገባ ቀን፥ እንዲህ ያደርገኛል
.
.
ኤድናሞል ደጃፍ፥ ላይ እንጎራደዳለሁ...
ቮድካ እንኳ ባይገኝ፥
የሜንት ያ'ፕሬቲቭ፥ ቦትል አወርዳለሁ
ባለረዥም ፀጉር፥
ባለ ለስላሳ ድምፅ፥ ባለ አይን ባለ አንገት
እያልኩ የተውኳቸው፥
የቸከሶቼ ስልክ፥ ትዝ ይለኛል ድንገት።
ፀሃይ ሲያዘቀዝቅ፥
እያንገሸገሸኝ፥
እያንቀጠቀጠኝ፥ ፀጥ ያለው ሰፈሬ
ወደ ሃያሁለት፥
ቦሌ መድሃኒያለም፥
ወደ አትላስ ጀርባ፥ይመራኛል እግሬ።
.
.
<<ደሞዝ ወጥቷል>> የሚል፥
ሜሴጅ የገባ ቀን፥ እንዲህ ያደርገኛል

በቅንነት #Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😁39👍19👏73
#ስኳር_መች_ይጣፍጣል?!

በዚህ እጅ ያልነካው ወዳጅ በማይገኝበት ክፉ ዘመን ሰላሳ አራት አመት እስኪሞላት ድረስ የማንም እጅ ሳይነካካት ከወር በፊት የተሞሸረች ልጃገረድ ወዳጅ አለችኝ።

‹‹ያላገባኝ አይነካኝም!›› ብላ….
‹‹ወንድ ልጅ ወተቱን በነፃ ካገኘ ላሚቱን አይገዛም›› ብላ…
ስንቱን የወንድ ፈንጂ በጥንቃቄ እንጣጥ ብላ፣ ስንቱን አማላይና አታላይ አምልጣ፣ እሷም እንደማንም ግጣሟን አገኘችና ጎጆ ወጣች። ተሰበሰበች። አገባች….ተነካች።

በቃል እና በእምነቷ መሰረት፣ ክብር እና ንፅህንናዋን ጠብቃ ኖረ ተዳረች። ከባሏ ተኛች።

በዚህ ዘመን ቀረ ብለን የምንገረምበት ወግ አጥባቂነቷ የአስናቀች ወርቁን ዘፈን ያስታውሰኝ ነበር። አስናቀች ቀኑን ሙሉ ከምታፈቅረው ልጅ ውላ ልክ ሲመሽ ሌላ እንዳያስብ ‹‹ልሂድ›› ስለምትል ወዳጄን የምትመስል ሴት ዘፍናልን ነበር።

‹‹ፍቅርዬ- ፍቅርዬ ደህና ሁን
ሊመሽ ስለሆነ መሄዴ ነው አሁን…..
…እኔ እንደምወድህ – ፍቅሬ ሆይ ውደደኝ
በህጋዊ ስርአት ማልድና ውሰደኝ…
አፍቅረኝ ላፍቅርህ ኑሯችን ባንድ ይሁን
እስከዚያው ድረስ ግን- ፍቅርዬ ደህና ሁን›› እያለች ዘፍናልን ነበር።

እናም…የ34 አመቷ ወዳጄም በህጋዊ ስርአት፣ በአማላጅና በምልጃ የፈለገችውና የፈለገችውን አገኘችና፣ ወሰዳትና አገባች። ተነካች።

ሰርጉ ተከናውኖ…
ጫጉላው አብቦ…
ከስንት ያመለጠው ብር አምባር ተሰብሮ ጥቂት ቀናት ካለፉ በኋላ አሁንስ ይበቃታል ብዬ ደወልኩላት። እንዴት ሆንሽ….አጥሚትና ገንፎ የት ይዘን እንምጣ ልል እና ላጫውታት ደወልኩላት።

ብዙ ሳይጠራ አነሳች።

(በቅቷታል ማለት ነው…)

ሰላምታችን ሲያልቅ ወደ አንገብጋቢውጉዳይ ገባሁና..
‹‹እህስ…ነገሩስ? እንደጠበቅሸው አገኘሽው ወይስ ቅር አለሽ?›› አልኳት።
‹‹ቅር አለሽ ወይ? ወይ ጉድ…አንቺ….ስኳር መች ይጣፍጣል?!›› ብላ መለሰችልኝ።

ከአንጀቴ ሳቅሁ።

እንዲህ ትላለች ብዬ ስላልጠበቅኩም፣ ያ ከአመታት በፊት የሰማሁት ታሪክ ላይ ያለችው ልጅንም አስታወሰችኝና ሳቅሁ።

(ታሪኩ እንዲህ ነው። ልጅቱ ለስኳር ያላት ፍቅር የትዬሌሌ ነው። ‹‹ከስኳር የሚጥም፣ ከስኳር የሚጣፍጥ ነገር በአለም ላይ…አንዳችም ነገር የለም›› የምትል አይነት። እጮኛዋ ‹‹ተይ ተጋብተን ፍቅር ስንሰራ ኋላ ሃሳብሽን ትለውጫለሽ›› ቢላትም እሷ ግን ወይ ፍንክች! በኋላ ጋብቻው ተከናውኖ ባልና ሚስት ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅር እየሰሩ ወደ ማገባደዱ ሲደርሱ የሚስቱን ሁኔታ ያየው ባል በእጁ የጨበጠውን ስኳር በተከፈተ አፏ ውስጥ ሙጅር ያደርጋል። ይሄን ጊዜ የስኳር ነገር የማይሆንላት ሚስቱ ምን አለች? ‹‹ውይ ውዴ…! የምን አፈር ነው አፌ ውስጥ የጨመርከው?!››)

‹‹ወይ አንቺ…እና ታዲያ ይሄን ያህል ጊዜ በመቆየትሽ ትንሽ አልተቆጨሽም ታዲያ?›› አልኳት
ለመመለስ ሰከንድ አልፈጀባትም።
‹‹በጭራሽ! መቆየቴ መቼም አይቆጨኝም….ግን እንዲህ መሆኑን ግን ነገራችሁኝ አታውቁም….››
‹‹ ብንነግርሽስ ኖሮ?››
‹‹እሱስ ምንም ለውጥ አያመጣም ነበር…ያው ምናልባት ትንሽ…ይበልጥ ልጓጓ ግን እችል ነበር……..››

ወሬያችን አልቆ ስልኩን ስዘጋ በዚህ ሁሉም ሰው ሁሉንም ሰው ለመምሰል በሚሮጥበት ጊዜ፣ ለግል አቋምና እምነቷ ባላት ታማኝነት እንዳዲስ ተደነቅኩባት። ቀናሁባት።
ከዚህ ሁሉ በላይ ግን (በእኔ እና በአለም ስሌት) ዘግይታም ቢሆን አዳሜ የአለምን ምሬት የሚያጣፍጠው ፍቅርን በመስራት ስኳር መሆኑን በማወቋ ተደሰትኩላት።

         🔘በሕይወት እምሻው🔘

አረ በቅንነት #Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8215😁6🥰1👏1
#ሀገሬ_ኀምሳ_እግር_ናት

የሀገሬ ወንዝ ዋናው ከነ ገባሩ ሲዘረዘር በንዴት እበግናለሁ።ፉት እንለው፣ ለቅለቅ እንልበት ውሃ ፍለጋ ከከተማ እስከ ገጠር
የምንማስነውን እኛን አስቤ ብግን እላለሁ፡፡

የሀገሬ ቀንድ ከብት ቁጥር፣ ከአፍሪካ አንደኛ” ተብሎ ሲጠራ በንዴት እንተከተካለሁ፡፡ ወተት እየተራጨን በማደግ ፈንታ የላም ወተት የዋልያ ወተት ይመስል ብርቅ የሆነብንን እኛን አስቤ ትክን እላለሁ፡፡

የሀገሬን ስፋት ሳስብ እናደዳለሁ፡፡ የእኔ የምንለው ክብሪት ሣጥን ታክል ቦታ አጥተን በየፊውዳሉ ቤት በጭሰኝነት የልጅነት ሀብታችንን ለምንገብረው እኛ ተቆርቁሬ፣ በንዴት እንገረገባለሁ፡፡

ይሄ ሁሉ እያላት ለእኛ ያልተረፈችው ሀገሬ፣ ሀብት እያላት ድሃ ናት፡፡ ሀገሬ ኀምሳ እግር ናት፡፡

ያ.....    ሁሉ......  እግር እያለው ዘልአለም እንደሚድኸው ቆሞ እንደማያውቀው ኀምሳ እግር፡፡

ከምትድህበት አንስቶ በኀምሳውም እግሯ የሚያቆማት ጎበዝ እስክታገኝ ሀገሬ ኀምሳ እግር ናት፡፡

🔘በሕይወት እምሻው🔘


#Subscribe #Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👏21👍145
👁👁በ'ነሱ ቤት👁👁
የመጨረሻ ክፍል
🍄🌷🍄🌷🍄🌷🍄🌷
ደህነት ክፉ መሆኑን የምታውቀው ሀብታሞች በተሰበሰቡበት ቦታ ስትገኝ ነው ፣ አንተ ለለት ጉርስህ ስንት ቦታ ረግጠህ ጠብ የሚል ነገር አጥተህ ፣ሳትጠግብ ስለነገህ አስቀርተህ ፣ ይሁን እስኪን  ተለማምደህ ስትኖር ። ድንገት በተረፈው ሰው ቤት ተገኝተህ የሚባክነውን  ሁሉ ስታይ  ደህነትህ ይበልጥ ይከፋሃል ውስጥ ያዝናል አንዳች እርግማን እንዳለብህ ይሰማሃል ,,,,,,, አንዳንድ የሞላለት ሰው ይቻላል ሲልህ ውስጥህን ያነቃቃውና የመስራት የማግኘት ጉጉት ያድርብሃል እናም የነጋዴነት ችሎታው ሳይኖርህ ነጋዴ ለመሆን ትፍጨረጨራለህ ፣እንደተባለው ከትንሽ ተነስተህ ነው ትልቅ ቦታ የምትደርሰው እያልክ ለራስህ እየነገርክ መጣር ትጀምራለህ  ትለፋለህ ትደክማለህ ነገርግን በትንሹ እንኳ በጀመርካት ንግድ ላይ ከላይ ታች አባራሪ ያዝብሃል ቀና እንዳትል የሚያደርግህ ቀበሌ ...ወረዳ...ክፍለ ከተማ.....ከስር ከስርህ እየተከተሉ ይገፈትሩሃል ምን ያክል ትቋቋማለህ ?እንጃ ጉሊት ነግደህ ንግድ ፍቃድ አውጣ ትባላለህ ...እሺ ብለህ ስታወጣ የምታገኘው ሌላ ግብሩ ሌላ .....እና ገፍተው ገፍተው ባፍጢምህ ይጥሉሃል ኪኪኪኪ,,,,
,,,,,የአብላካት እናት እዛ የሃብታም ቤት ውስጥ የሚከናወነውን ሁኔታ ሁሉ በትዝብት እያየች የራሷን ችግር እያስታወሰች አምላኳን ትሞግታለች ለለት ጉርሳቸው ሲሉ ከላይ ታች በየመንገዱ ጋሪ እየገፉ ከደንቦች ጋር እየተሯሯጡ ኑሯቸውን የሚገፉትን የስራ ባልደረቦቿን አስታወሰች ፣ የቤትክራይ መክፈል አቅቷቸው ሲጨነቁ ....የአስቤዛው ዋጋ ጣራ ነክቶ አንዱን ስለው አንዱ በሚል ሲወጠሩ .......
እዚ ደሞ ገንዘቤን ምን ላድርገው ባሉ አብታሞች ተከባ በውድ አልባሳት ባሸበረቁ ሴቶች እና ወንዶች መሃል ሆና ምግቡ መጠጡ ሲባክኑ በአይኗ እያየች ነው ፣ሕይወት እንዲ ናት እንግዲ,,,,,,,,,,,,,
፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"ሚጣ እባክሽ ለኔ የሚሆን ጊዜ አለሽ?"አላት ሰመረ አብላካትን ጠጋ ብሎ ።አብላካት ፊቷ በራ ይበልጥ አማረባት ዞር ብላ አይታው
"ሚጣ አይደለሁም ስንቴ ነው የምናገረው አቡሽ አብ ላካት ማለት ያን ያክል ይከብዳል ?"አለችው
"እሺ የኔ ውድ አንዴ ከግር ግሩ እንውጣ "አላት እጇን ያዝ አድርጎ ፣
"እሺ ምን ልታደርገኝ እንደሆን እናያለን "አለችው በፈገግታ ፣ሰመረ እጇን እንደያዘ ሲሄድ ፣አስተናጋጁ ሰሚር አይቶት ፈገግ አለለት ፣ሰመረም አስተናጋጁ ሰሚር ከአንዲ ጠይም ወጣት ጋር ሲያወራ ስለነበር አበጀህ በሚል ጠቀሰው ።
፨፨፨፨፨
አብላካትን ከግርግሩ ካራቃት በዋላ ፣እንዴት እንደሚያወራ ግራ ገብቶት ፈዞ ቀረ ፣አብላካት አይኖቹን በፍቅር አይን እያየችው እንዲያወራ ጠበቀችው ፣ሰመረ ግን አይኖቿን በስስት ማየቱን ቀጠለ ፣ አብላካት የተረዳችው ይመስል
"ሰሙ ይገባኛል ለኔ አሁንም ድረስ የሚሰማህ ስሜት አስፈርቶሃል ነገር ግን መጨናነቅ መፍትሔ አይሆንም በቃ የሚሆነው ነው የሚሆነው ንገረኝ ..."አለችው
"አይ አይ እኔ በቃ ከየት እንደምጀምር ግራ ስለገባኝ ነው ማለት አሁን ላይ አይሆንም ይሆናል በሚል አሳብ እራሴን የምጠምድበት ጊዜ አልፏል ፣ልቤንም በትክክል አዳምጬዋለው በቃ አንቺ የኔ ሰላም ነሽ ካጣውሽ እደክማለው ፣ የፈገግታዬ ምንጭ ሆነሻል ፣የሚጨንቀኝ ስሜቴን ላንቺ የምገልፅበት መንገድ በቂ ይሁን አይሁን  አለማወቄ ነው ፣ምን ያክል ባወራ ውስጤን ላንቺ ያለኝን ፍቅር ይገልፀዋል የሚል ፍራቻ ብቻ ነው........."
"ሰሙ የኔ ፍቅር በጣም በጣም ነው የማፈቅርህ ከቃል በላይ አይኖችህና ድርጊትህ ለኔ ያለህን ፍቅር እና አክብሮት ይገልፅልኛል መቸገር የለብህም"አለችው ሁለቱንም እጆቹን ያዝ አድርጋ ።ሰመረ የተለየ ሙቀት በሰራ አከላቱ ሲዘዋወር ተሰማው ፣እናም የአብላካትን እንጆሪ የመሰለ ከንፈር በስሜት ታጅቦ ተጣበቀባቸው ፣ አብላካት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳመው ከንፈሯ ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍሯ አንዳች መልህክት አስተላለፈባት ከንፈሮቿ ተርበተበቱ .... ውስጧ በደስታ ጮቤ እረገጠ ፣ስለ ዓለም የሚሰማት አስቀያሚ ስሜት ሁሉ ከላይዋ ተገፎ የወረደ መሰላት ዓለም አብራት በስሜት በፍቅር በሰላም በደስታ የተወዘወዘች መሰላት መሰላት በፍቅር የተነሳ በፍቅር የተነሳ,*
*,,,,,,,ተፈፀመ,,,,,,**

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍14639👎10🥰5🤩3
#ትንግርት


#ክፍል_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ሁሴን ዕድሜው ከ 35 ትንሽ ቢዘልም ፈርጣማ የሆነው የስፖርተኛ ተክለ ሰውነቱና ግንባሩ ላይ የተደፋው ጥቁር ሉጫ ፀጉሩ የሃያ አምስት አመት ወጣት ያስመስለዋል፡፡

የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሥነ ጹሁፍ ከአስር ዓመት በፊት ሲቀበል፣ሁለተኛ ዲግሪውን ደግሞ ከፈረንሳይ አገር በፍልስፍና ከሦስት ዓመት በፊት አግኝቷል፡፡ አሁን የሚኖረው እናትና አባቱ ባወረሱት ልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ባለ ሦስት መኝታ ክፍል ቪላ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ወላጆቹ ሞተዋል፡፡እሱ ደግሞ ብቸኛ ልጃቸው ነበር፡፡በአሁኑ ሰዓት አብራው የምትኖረው ፎዚያ ነች፡፡ ሁሴን ፎዚያን እንደእህቱ ቢያያትም ምንም አይነት የስጋ ትስስር ግን የላቸውም ፡፡

ሁሴን ዋና አዘጋጅ ሆኖ በሚሰራበት ፍኖተ ጥበብ በተሠኘ ተነባቢ የግል ጋዜጣ ውስጥ ስልሳ ፐርሰንት የአክሲዬን ድርሻ አለው፡፡
ጋዜጣው ሳምንታዊ ሲሆን፤አንድ መቶ ሺ እትም በየሳምንቱ በመላው አገሪቱ ያሰራጫል፡፡ ጋዜጣው ትርፋማ ነው ብሎ ለመናገር ባያስደፍርም፤ በጣም ተወዳጅና ተነባቢ መሆኑን ግን አስረግጦ መመስከር ይቻላል፡፡

ሁሴን በህይወቱ ብዙ ሴቶች ገብተው ወጥተዋል፡፡ አብዛኞቹ ተስፋ አስቆርጧቸው ትተውት ሄደዋል፡፡ ጋብቻ አይፈልግ፣ ልጅ መውለድ አያጓጓውም፣ ቃል አይገባለቸው ፣ ተስፋ አይሰጣቸው ፤ በቃ... ፍቅርና ወሲብ ብቻ!፡፡ ታዲያ ጫንቃቸው የደህነት ዋስትና የሚሹት ሴቶች ከተወሰነ ርቀት በላይ አይታገሱትም፤ ጥለውት ይሄዳሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ በጭቅጭቅና በንዝንዝ ፋታ ስለሚነሱት ያንገሸግሹታል፡፡ሲያንገሸግሹት ደግሞ ፊቱን ያዞርባቸዋል...ይተዋቸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በህይወቱ ውስጥ ሦስት ሴቶች ቀርተዋል፡፡ አንደኛዋ በንግድ ስራ የምትተዳደረውና አምስት ዓመት በጓደኝነት፤
ስምንት ዓመት በፍቅረኝነት አብራው የዘለቀችው ኤደን ስትሆን፣ ሁለተኛዋ እራሱን ዘና ማድረግ ሲያሠኘው የሚፈልጋት የቡና ቤቷ ትንግርት ነች፡፡ ሦስተኛዋ ደግሞ አዕምሮውን ጠቅላላ ጠፍንጋ የያዘችው፤ በፍቅር ሊቀውስላት ጥቂት የቀረው በአካል የማያውቃት የጋዜጣው አምደኛ ሚስጢር ::

ሁሴን ቀኑን ሙሉ በስራ ተጠምዶ ከዋለበት ቢሮው ለቆ በመውጣት ውጫዊ አካሏ በቀይ ቀለም የተነከረ ቪታራ መኪና ውስጥ ገብቶ ሞተሩን ለማስነሳት ቁልፉን ሲነካካ ተንቀሳቃሽ ስልኩ ተንጣረረች...አነሳው፤ደዋዩ ኢንጅነር ሠሎሞን ነበር፡፡

<<ሄሎ>>

‹‹የት ነህ ወንድም ጋዜጠኛ?››

‹‹ባክህ ገና ከቢሮ እየወጣሁ ነው...ላብድልህ ነው፤ ግራ ተጋብቻለሁ::››

‹‹ደግሞ ምን ገጠመህ?›› ሠሎሞን ነበር ጠያቂው፡፡

‹‹ሌላ ምን ይገጥመኛል ...የዛችው ልጅ ነገር ::››

‹‹ኦ!! የደንበኛህ?››

«አዎ!!>>

‹‹ዛሬም ፖስታዋ ደርሶሀል ማለት ነው?››

‹‹አዎ!! የዛሬው ደግሞ የተለየ ነው፤ልብን ስውር የሚያደርግ ሀሳብ የያዘ ፅሁፍ ነው የላከችልኝ፡፡››

<< ልብህን የሰወረህ ፅሁፍ ነው ወይስ አንተ ለእሷ ያለህ ስውር ፍቅር?››

‹‹ሁለቱም ምክንያት ትክክል ነው፡፡››

‹‹በቃ... አንተ እንደው ስለእሷ ማውራት ከጀመርክ ማብቂያ የለህም አይደል? ልታወራኝ ከፈለክ የመጠጥ ግብዣ እፈልጋለሁ…የተለመደው ቤት ተጎልቼ እየጠበቅኩህ ነው ፡፡››

‹‹እንዴ በቀኑ! ? ገና አስራ አንድ ሠዓት እኮ ነው? >>

ሠሎሞን ተበሳጨ‹‹ባክህ አትጨቅጭቀኝ፤ የምትመጣ ከሆነ ና፡፡››

‹‹እሺ ጌታው ከሃያ ደቂቃ በኃላ ከጎንህ እገኛለሁ፤እስከዛው ቻው፡፡›› ስልኩን ወደ ኪሱ መልሶ ሞተሩን አስነሳና ወደ ሜክሲኮ ከነፈ፡፡ ከሠሎሞን ጋር ከሃያ ዓመት በላይ በጓደኝነት አሳልፈዋል፡፡ በባህሪ፣ በስራ፣ በእምነትና በኑሮ ፍልስፍናቸው በጣም በተለያየ መንገድ የሚጓዙ ቢሆንም ይህ ልዩነታቸው ግን ጓደኝነታቸውን ለመበረዝ ጉልበት አልነበረውም፡፡

ኢንጅነር ሠሎሞን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው፡፡ የሃይማኖቱን ህግና ሥርዓት ለማክበር ዘወትር ከልብ ይጥራል፤ግን አይሣካለትም፡፡
ህግጋቱን ይጥሳል፣ ቀኖናዋቹን ያፈርሳል፣ከዛም በፀፀት ይቃጠላል፡፡ እግዚአብሔርን በማስቀየሙ እራሱን ይቀየማል፡፡ብዙውን ጊዜ ለሥህተት ተጋላጭ እንዲሆን መነሻ ምክንያት የሚሆኑት ሁለት ነገሮች ሚስቱና ስራው ናቸው፡፡ ከየውብዳር ጋር ከተጋቡ አስር ዓመት አልፏቸዋል፡፡ በዚህ የጊዜ ሂደት ውስጥ የተትረፈረፈ ሀብት ባለቤት መሆን ከመቻላቸውም በተጨማሪ ሁለት ሴት ልጆችንም ማፍራት ችለዋል ፡፡ስምምነት ግን አልነበራቸውም፤ ሦስት ቀን በሠላም ቢያሳልፉ ተከታዮቹን ሦስት ቀናት በጥልና በኩርፊያ ጀርባ ተሠጣጥተው ይከርማሉ፡፡ በዚህ ወቅት ታዲያ ሰሎሞን ቤቱ ያስጠላዋል…ጥሎ ይወጣል፤ከወጣም ይጠጣል፤ ብክት እስኪል ይጠጣል፣ሲጠጣ ደግሞ ብዙ ይሳሳታል፣ሠው ያስቀይማል፣ ከሴት ይዳራል፣ብር ይረጫል፤ከዛ በማግስቱ ናላው እስኪዞር
በጥልቀት ይፀፀታል፡፡

ስራውን በተመለከተ ደግሞ ደረጃ ሦስት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (ኮንትራክተር) ነው፡፡ ሥራ ለማግኘት ጉቦ
ይሰጣል፣ሥራው ሲበላሽበት ሥህተቱን ለመሸፈን ጉቦ ይሠጣል፣ ካደረገው በኃላ ግን እንቅልፍ እስኪያጣ
ይበሳጫል፣ይፀፀታል ደግሞ ላለማድረግም ይምላል...ይገዘታል፡፡ ግን መልሶ መላልሶ በተመሳሳይ ስህተት ውስጥ ዘወትር ይዘፈቃል ፡፡ ሠሎሞን ማለት ይሄ ነው፡፡ ጥፋት፣ፀፀት… ጥፋት፣ፀፀት፡፡

ሁሴን ስለ ሠሎሞን እያሠላሠለ ሣይታወቀው የተቃጠሩበት ቦታ ደረሠ፡፡ መኪናውን ተገቢው ቦታ ካቆመ በኃላ ወደ ውስጥ ዘለቀ፡፡ ቡና ቤቱ ጭር ብሏል፡፡ ታዳሚዎቹ በቁጥር ናቸው፡፡ ወንድ አስተናጋጆች እዚና እዛ ተሠባጥረው ቆመው የሚሠጣቸውን ትዕዛዝ እየተቀበሉ ክቡራን ደንበኞቻውን በትጋት ለማስተናገድ ሲታትሩ ይታያሉ፡፡እንደገባ ነበር ሠሎሞንን የለየው፡፡ አጭር ሠላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ፊት ለፊቱ ወንበር ስቦ ተቀመጠ፡፡

‹‹ሙሽሮቻችን አልገቡም እንዴ?›› ሁሴን ነበር ጠያቂው፡፡

‹‹አንተ ደግሞ እነሱን ካለየህ ጉሮሮህ ለመጠጥ አይከፈትም፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ ይንጋጉልሀል፡፡ ንስርህም እንደ ንግስት በጋርዶቾ ታጅባ ከች ማለቷ አይቀርም፡፡››

ሁሴን አስተናጋጁን ጠራና ውስኪ አዘዘ፡፡

‹‹ምነው ውስኪ?›› ጠየቀ ሠሎሞን፡፡

<<እንዴት??>>

‹ለስላሳ የምታዝ መስሎኝ ነበር፤ሃይማኖትህ ይፈቅድልሃል እንዴ?›› ይሄ የሠሎሞን የሁልጊዜ ትችቱ ነው፡፡

‹‹ሃይማኖቴ ምንድነው?››

‹‹መቼም ሁሴን ብሎ ክርስቲያን የለ፡፡››

‹‹ይሄው እንግዲህ የአንተ ችግር እዚህ ላይ ነው፡፡ እርግጥ ማንም እንደሚያውቀው ቤተሰቦቼ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ነበሩ፡፡ በዛ ምክንያት እኔ ስወለድ ምንም ሳይጠረጥሩ
ልጃችን እንደኛው ሙስሊም ስለሚሆን የሙስሊም ስም እንሸልመው ተባባሉና ሁሴን አሉኝ፡፡ እኔ ግን እንደምታውቀው ሙስሊምም፣ክርስቲያንም፣ቡዲስትም መሆን አልቻልኩም፡፡ በዚህም የተነሳ የቤተሠቦቼን ትንቢት አከሸፍኩባቸው ማለት ነው ፡፡ ይሁን እንጂ ለዚህ ስህተታቸው መታሠቢያ ይሆን ዘንድ ሙስሊማዊ ስሜን ይዤ ይሄው እየኖርኩ ነው፡፡››

አስተናጋጁ የታዘዘውን ውስኪ አምጥቶ ፊቱ አቅርቦለት ወደ መቆሚያ ቦታው ተመለሰ ፡፡ ሠሎሞን የተቋረጠ ጫወታቸውን አራዘመው፡፡‹‹ግን ለዚህች ሚስኪን ነፍስህ አንድ ማረፊያ ብታበጅላት ምን አለበት?››

‹‹እንዴት ማለት?››

‹‹ማለት አንድ የራስህ ሃይማኖት ቢኖርህ?››

‹‹እሺ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ሃይማኖቱ ያስፈልገኛል ብዬ ልመን፤ እስቲ ይሄኛው ሃይማኖት ትክክል ነው ብለህ አሳምነኝ እና እሱን ልከተል።.››
👍16410🔥2👏2👎1😁1
‹‹እኔ ይሄኛው ትክክለኛ፤ ያኛው ደግሞ በስህተት የተሞላ ነው ልልህ አልችልም፡፡ ሀይማኖት የምርምር ሳይሆን የእምነት ጉዳይ ነው፡፡ መቼም ማስተርስህን የሠራኸው በፍልስፍና እንደመሆኑ መጠን የአብዛኞቹን ሃይማኖቶች ፍልስፍናዊ ፅንሰ ሀሳባቸውን የመመርመር ዕድሉ እንደነበረህ እገምታለሁ፤ ስለዚህ ከዛ በመነሳት አንዱን መምረጥ የሚያቅትህ አይመስለኝም፡፡››

ሁሴን ፊቱ የተቀመጠውን የውስኪ ብርጭቆ በማንሳት አንዴ ጠቀም አድርጎ ከተጎነጨለት በኃላ መልስ መስጠት ቀጠለ፡፡...

ይቀጥላል

እንደገና ጭቅጭቄን ልጀምር ነው እሱ ምንድነው  #የዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ #አድርጉ #የሚል #ነው ለማድረግ የሚጠይቀው ውስጣዊ ቅንነትን፣ለሰዎች መልካም ማሰብን፣ደግነትን ብቻ ነው።
አሁን #ዩቲዩቡ 119 subscribers አሉት ይሄ ቻናል ከ100,000 በላይ አባላት አሉት ከነዚህ ውስጥ 10 ሰው subscribe ያደርጋል ብዬ እጠብቃለው በጣም ትንሽ ነው ማድረግ ትችላላችሁ በቅድምያ
ስለመልካምነታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ።
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍10415😁6👏1
#ትንግርት


#ክፍል_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

...ሁሴን ፊቱ የተቀመጠውን የውስኪ ብርጭቆ በማንሳት አንዴ ጠቀም አድርጎ ከተጎነጨለት በኃላ መልስ መስጠት ቀጠለ፡፡...

‹‹እርግጥ እኔ በእግዚአብሔር አምናለሁ፡፡ የእኔ እግዚአብሔር ግን በየትኛውም ሀይማኖት ውስጥ እስካሁን አላገኘሁትም፡፡ የእኔ እግዚአብሔር ፍፁም የተለየ ነው፡፡››!

«ለምሳሌ...?>>

‹‹ለምሳሌ ሁሉም ሀይማኖቶች ማለት በሚቻልበት ደረጃ በሲኦልና ገነት ያምናሉ፡፡ ይሄንን ፅንሰ ሀሳብ የእኔ አዕምሮ ደግሞ ፈፅሞ ሊቀበለው አይችልም፡፡እግዚአብሔር ፈጥሮናል ብለን የምናስብ ከሆነ እኛ በዚህች ምድር ላይ ለምንፈፅመው ሥህተት ኃላፊነቱን ብቻችንን መውሰድ ያለብን አይመስለኝም፡፡
የሥህተታችን ዋና ምንጩ አፈጣጠራችን (የተሠራንበት ንጥረ ነገር) ነው ብዬ አምናለሁ....እኛ አሁን የሆነውን የሆነው በእግዚአብሔር ፍቃድና ምርጫ ነው፡፡ ስለዚህ አፈጣጠራችን ለስህተቶች ተጋላጭ እንደሚያደርገን ገና ከመፈጠራችን በፊት ዲዛይኑን የሠራው እግዚአብሔር በደምብ ያውቃል ብዬ አስባለሁ፡፡ ይሄ እውነት ከሆነ ደግሞ የተሳሳተውን ለማጥቃት ሲኦልን መገንባት ለምን አስፈለገ? አለዚያማ እግዚአብሔር የእነ ሂትለር ግልባጭ ነው ማለት ይሆናል፡፡ ሂትለር አይሁዶችን አይሁድ ስለሆኑ ብቻ እየሠበሠበ ጨፈጨፋቸው፣ ቆራረጣቸው፣ አቃጠላቸው፡የሚገርመው ግን እውነታውን ማንም እንደሚገነዘበው አንድም ሰው በፍቃዱ አይሁዳዊ ወይም ጀርመናዊ ሆኖ መወለድ አይችልም፡፡

ሌላው አንድ ምሳሌ ልጨምርልህ ወሲብን ሁሉም ሀይማኖቶች በደቦ ያወግዙታል፤ከጥንት ባህላዊ ሀይማኖቶች በስተቀር ማለቴ ነው፡፡ እስቲ ተመልከት እያንዳንዳችን እኮ የወሲብ ውጤቶች ነን፡፡ አንዲት ሴት አሥር ዓመት ገዳም ሲሞላት ጡቶቿ እንዲያጎጠጉጡላት፣ብልቷ ላይ ፀጉር እንዲበቅልላት፣ የወር አበባዋ ምንጭ እንዲፈልቅላት በየእለቱ በናፍቆትና በጉጉት ታልማለች፡፡ ለምን ይመስልሃል ?በቶሎ ደርሳ እንደ እናቷና እንደ ታላላቅ እህቶቿ አንድ ጎረምሳ አፍቅራ ወሲብ የሚባለውን ተዓምር ለማየት ነው... ወንድዬውም እንደዛው፡፡

የምንበላው ቆንጆ ለመሆን፣ለማደግ፣ብሎም ለመኖር ነው፤የምንማረው በህብረተሠብ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኝት፣ የተሻለ ተመራጭ ሠው ለመሆን ነው፤የዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ የመጨረሻ ግብ ግን በተቃራኒ ፆታ ተመራጭ ሆኖ ፣በወሲብ እርካታ ተደስቶ፣ የዝርያችንን ቀጣይነት አረጋግጦ ፣ በህይወት ውስጥ የድርሻን ለመወጣት ነው... እና ይሄ የህይወት አንኳር ቅመም የሆነው ወሲብ ሀይማኖት መሆን ሲገባው እንዴት ሀጥያት ነው ተብሎ ይፈረጃል?››

‹‹ወዴት..…? ወዴት ...?የትኛውም ሀይማኖት እኮ ወሲብን ስርአት ይበጅለት ይላል እንጂ አያወግዝም፡፡ሚስት አግብተህ ከሚስትህ ጋር እንደፈለክ ወሲብ ማድረግ የሚከለክልህ ሀይማኖት ያለ አይመስለኝም››

‹‹እሱ ነው ማይገባኝ፡፡ድሮ አንድ ወጣት 17 እና 18 ዓመት ሲሞላው አባትዬው ሁለት ጥማድ መሬት ከሁለት በሬ ጋር ይሸልመውና የ13 ወይም የ14 ዓመት እንጭጭ ልጃገረድ ፈልጎ በመዳር ከጣጣው ይገላግለው ነበር፡፡ ወደዚህ ዘመን ነገሩን አምጥተን ስንመለከተው
ግን አንድ ወጣት ሚስት ለማግባት ከማሰቡ በፊት ቀድሞ ኑሮውን በራሱ ተጣጥሮ ማሸነፍ አለበት፡፡ ምክንያቱም አይደለም በከተማ በገጠር እንኳን አባት ከእሱ ተርፎት ለልጁ ቆርሶ የሚሰጠው መሬት ስለማይኖር በቀላሉ ጎጆ መቀለስ የማይታሰብበት ዘመን ላይ ነው ያለነው፡፡ ስለዚህ ለማግባት የግድ ከእሱ አልፎ ለሚስቱ የሚበቃ የገቢ ምንጭ ሊኖረው ያስፈልጋል፡፡ያንን እስኪያሟላ ዕድሜው ቢያንስ በቀላሉ ከ3ዐ በላይ ይሆናል፡፡ይሄ ልጅ እንግዲህ ለአቅመ ወሲብ ከደረሰ ስንት ዓመት አለፈው ብለህ ስታሰላ 14 እና 15 ዓመት ይሆናል ፡፡ ታዲያ ይሄን ሁሉ ዓመት በዘመኑ እንዲህ የተበተኑትን ቆነጃጅት እየተመለከተና እየጎመዠ እስከ ጋብቻ ታቅቦ ለመቆየት የሚያስችል ጥንካሬ በውስጡ የሚኖረው ይመስልሀል? ተፈጥሮስ ትፈቅድለታለች

‹‹እንዴ !!ፍቅረኛ እኮ መያዝ ይችላል፡፡››

‹‹ይችላል... ግን እኮ ብዙዎቹ ሀይማኖቶች ከጋብቻ በፊት ወሲብ ክልክል ነው ይላሉ ፡፡››

‹‹ባክህ አንተ የምትለው አታጣም .. በቃ.. በቃ አሁን ጨዋታ ቀይር፤ሙሽሮቹ እየገቡ ነው፡፡››በማለት የጫወታውን አቅጣጫ ቀየረው፡፡

የሠሎሞንን ንግግር ተከትሎ ሁሴን ፊቱን ወደ
ጓሮ በር አሽከረከረ፡፡ ፀጉረ ረጅም፣ባጭሩ የከረከመች፣ ዊግ የከመረች፣ሱሪ ያረገች፣ቀሚስ የለበሰች፣ ሊፒስቲክ የተለቀለቀች ፣ቅንድቧን የመለጠች፣ ቀጭን፣ወፍራም፤ከየዓይነቱ ለናሙና ተመርጠው የቀረቡ ይመስል በሠልፍ ተንጋግተው ገቡ…ከአስር ይበልጣሉ፤ከመሀከላቸው አንዷ ትንግርት ነች፡፡

የቁመቷ መመዘዝና የመልኳ ቅላት ከሌሎቹ ጎልታ እንድትታይ አድርጓታል፡፡ ትንግርት የሁሴን ቋሚ ደንበኛ ነች፡፡ ከሁለት ዓመት በላይ እውቂያ አላቸው፡፡ ስታሰኘው እቤቱ ይዟት በመሄድ ሲኖረው ይከፍላታል... ከሌለውም ደግሞ ትዘለዋለች፡፡ ትመቸዋለች... ይመቻታል፡፡

‹‹ሥጋዋ ነው እንጂ ነፍሷ ንፁህ ነው፡፡›› ይላል፡፡ ጠንካራ ንግግሯና የአስተሳሰብ ብስለቷ ዘወትር ያስደምመዋል፡፡ በወሲብ ችሎታዋ የዛለ ስጋውንም ሆነ የተጨናነቀች ነፍሱን እኩል ስለምታረግብለት እስከአሁን እንዳይለያት አስሮ ያቆየው ተጨማሪ ሠንሠለት ሆኖበታል... እየተውረገረገች የተቀመጡበት ድረስ መጥታ ሁለቱንም ሠላም አለቻቸው ፡፡

ሠሎሞን በተቀመጠበት አንጋጦ እያየ‹‹ዛሬ ደግሞ ይበልጥ አምሮብሻል፡፡›› ሲል አስተያየቱን ሠነዘረ፡፡

‹‹የእናንተ የባለትዳሮች አስተያየት እኮ ከወንደላጤው በላይ ውስጥ ድረስ ዘልቆ ልብን ይሰረስራል፡፡››

<እንዴት?>>

‹‹እያንዳንዷ ፊት ለፊታችሁ የተከሠተችን ሴት የምታወዳድሩት እቤታችሁ ውስጥ ከምትገኘው ሚስታችሁ ጋር ስለሆነ በጥልቀት ነው የምትመረምሩት፡፡ ወንደላጤው ደግሞ በአእምሮው ውስጥ ከቀበራት ሴት ጋር ነው የሚያወዳድረው፤ በአእምሮው ውስጥ የሳላትን ደግሞ እንደአስፈላጊነቱ ሊያስተካክላት ስለሚችል መመርመሩ ላይ ብዙም ጊዜውን አያባክንም፤ገረፍ ገረፍ አርጎ ውሳኔውን ይወስናል... ወይ ይከተላታል ካልሆነም አልፏት ይጓዛል፤እናንተ ግን ውይ! ..ደም ትመጣላችሁ…ለማንኛውም መጣሁ፡፡›› ብላቸው እንደአመጣጧ እየተውረገረገች ጥላቸው ሄደች፡፡

‹‹ይህቺ ልጅን ግን ደህንነቶች አንተን ለመሠለል እዚህ ያስቀመጧት ሠላይ ትመስለኛለች፡፡››

‹‹ደህንነቶች ለምንድነው እኔን የሚሠልሉት?›› ሁሴን ጠይም ፊቱን ይበልጥ በማጥቆር ሠፊ ግንባሩን አጨማዶ ጠየቀው፡፡

‹‹ምን አውቃለሁ፤እዛ ጋዜጣህ ላይ ፖለቲካ ነገር ፅፈህ ጀርባህን ሊያጠኑህ ይሆናላ፡፡››

‹‹ሠውዬ እኔ የጥበብ አምድ አዘጋጅ እንጂ የፖለቲካ አምድ አዘጋጅ አይደለሁም፡፡››

‹‹እሱን እንኳን ተወው፡፡ ፖለቲካ አምድ ላይ እንደውም ደረቅ ትችትና የሚሻክር ተቃውሞ ነው የሚፃፈው…ማለት ሁሉ ነገር በግልፅ ነው የሚቀመጠው፡፡ ይሄ ደግሞ የደህንነቶችን ሥራ ያቀልላቸዋል፡፡ የፀሀፊው እምነትና አመለካከት ምን እንደሚመስልና የየትኛው ፖለቲካ ድርጅት ደጋፊ ወይም አባል እንደሆን ? ለመለየት ብር ከስክሶ ሠላይ መመደብ አያስፈልጋቸውም፡፡ በቃ አንዱ የፖለቲካ ኤክስፐርታቸው ቢሮው ቁጭ ብሎ ይተነትንላቸዋል፡፡ ያንተ አምድ ግን በቅኔያዊ አሽሙር የተጀቦነ፣በሰምና ወርቅ የሚተነተን ፍቺ ያለው ሚስጥራው መርዝ ነው፡፡በዛች ባንተ ደንበኛ ስም የሚታተሙ አጫጭር ልብ ወለዶችና ግጥሞች እንኳን ብንመለከት ለዚህ ማስረጃ ይሆናል፡፡››

ሁሴን ተንገሸገሸ‹‹ተወኝ ባክህ ስለ እሷ አታንሳብኝ፡፡››
👍11215👏3🔥2🤔2
‹‹ቆይ ግን እስከአሁን ስልኳንም እንኳን ማግኘት አልቻልክም?››

‹‹ምን አገኛለሁ፤አንድ ቀን ሳሪስ አካባቢ ካለ የህዝብ ስልክ ትደውልልኛለች፣ በሌላ ቀን ደግሞ ከካሳንቺስ ይሆናል፣ ሲያሰኛት ደግሞ ከቦሌ ትደውልልኛለች፡፡››

‹‹ግን ለእሷ ያለህ ስሜት ከአድናቆት አልፎ ወደ ፍቅር እንደተመነደገ ነግረሀታል?››

‹‹መቶ ጊዜ ነዋ፡፡››

‹‹እና ምን አለችህ?››

‹‹ብታየኝ ልትጠላኝ ለማፍቀሩ ምን አቅነዘነዘህ ?›› ::

‹አይ ሁሴን! እውነቷን እኮ ነው፡፡ መቼስ አንድ ችግር ሳይኖርባት እራሷን ይሄን ያህል አትደብቅም፤ለዛውም እንዲህ በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያላት ተስፈኛ ደራሲ ሆና...፡፡ እኔም እንደ እሷ የምመክርህ አንድ ነገር ቢኖር እርሳትና የቤት ልጅ ሲያምርህ ኤደንን ፣የቡና ቤት ሲያምርህ ደግሞ ትንግርትህን እየላስክ እንደቀድሞህ ኑሮህን በደስታ ዘና ብለህ ኑር ብዬ ነው፡፡ ሁለቱም ካስጠሉህ ደግሞ መቼም አንተን የማትመኝ የአዲስ አበባ ወጣት የለችም፤ እንኳን ዝና ታክሎበት ቀርቶ እንዲሁም ቁመናና መልክህ የሆሊውድ አክተር አይነት ነው፡፡››

‹‹ኡፍ! ለምን አይገባችሁም፤ እሷን እኮ ነፍሴ ነው ያፈቀራት፡፡በቃ ህልሜ ሆናለች፣ሀይማኖቴ አርጌያታለሁ፣ፈፅሞ ተስፋ አልቆርጥም፣ልረሳትም አልችልም፡፡››

‹‹ቆይ በየጋዜጣው የታተሙላትን ልብወለዶች ሠብስቤ እንድታሳትም አግባባታለሁ ያልከውስ?››

‹‹እባክህ እምቢ አለች፡፡››

‹‹እንዴት .. ? ተው ይህቺ ልጅ መንፈስ ሳትሆን አትቀርም!››

‹‹ይሆናል .. !ማሳተም ከፈለግኩ ግን ሙሉ ውክልና እንደምትልክልኝ ነግራኛለች፡፡››

‹‹ያንተ ያለህ!›› የሠሎሞን መገረም ጨመረ፡፡

‹‹እሺ መፅሐፍ ታተመ እንበል፤የሚገኘው ገቢስ?

‹‹በእኔ ስም ባንክ ቤት እንዳስቀምጠው አሳስባኛለች፡፡››

‹‹በል በል ይሄንን የእብደት ወሬህን አቁምልኝ... ልዝናናበት፤ለራሴ በየውብዳር ጭቅጭቅ አዕምሮዬ ተወጥሮ ነው የመጣሁት፤ሌላ አዕምሮ የሚወጥር ነገር አትጨምርብኝ፤ይልቅ ትንግርትህን ጥራትና ዘና ታርገን፡፡››

ይቀጥላል

ቤተሰቦች #የዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ  ለማድረግ የሚጠይቀው ውስጣዊ ቅንነትን፣ለሰዎች መልካም ማሰብን፣ደግነትን ብቻ ነው።
አሁን #ዩቲዩቡ 128 subscribers አሉት ይሄ ቻናል ከ100,000 በላይ አባላት አሉት ከነዚህ ውስጥ 10 ሰው subscribe ያደርጋል ብዬ እጠብቃለው በጣም ትንሽ ነው ማድረግ ትችላላችሁ በቅድምያ
ስለመልካምነታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ።
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12316😁8
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍84
#ትንግርት


#ክፍል_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


በማግስቱ ሁሴን ገና በጊዜ አንድ ሰዓት ላይ ነበር ወደቤቱ የገባው፡፡ ቀኑን ሙሉ በአንድ ሀሳብ አይምሮው ተጠፍንጎ ስለ ምስጢር ሲያስብ ነው የዋለው፡፡ እንደገባ ያረፈበት ለወትሮው ምቾትን የሚለግሠው የቤቱ ሶፋ ዛሬ ቆረቆረው፡፡ ሞባይሉን ከኪሱ አወጣና መጎርጎር ጀመረ፡፡ ቀን ደውላለት ነበር... ያደረጉትንም የስልክ ልውውጥ ቀድቶታል... ከፈተው፡፡ ደጋግሞ ሲያዳምጠው ይሄ ለ13ተኛ ጊዜ ነው፡፡ እያንዳንዷን ከአንደበቷ የወጡትን ቃላቶች ሸምድዳቸው ተብሎ በፍርድ ቤት ውሳኔ የተላለፈበት ፍርደኛ ይመስላል፡፡ ሞባይሉ ማውራት እሱ ማዳመጥ ጀመረ፡፡

‹‹ከየት ነው ምትደውይው?››

‹‹ከየትስ ቢሆን ምን ይፈይድልሀል?.ይልቅ ለምን ደወልሽ?የሚለው ጥያቄ አይቀልም?››

‹‹እንደዛ ብዬ እንኳን አልጠይቅሽም፤ ዋናው መደወልሽ ነው እንጂ የደወልሽበት ምክንያት ብዙም አያስጨንቀኝም፡፡››

‹‹የውክልናው ወረቀት ደረሠህ?›› ቀጭን ማራኪ ድምፅ፡፡

‹‹አዋ>>

ደርሶኛል...ታደርጊዋለሽ ብዬ ግን አላመንኩም ነበር፡፡››

«ለምን?»

‹‹እኔ እንጃ፤ይሄን ያህል እንዴት ልታምኚን ቻልሽ... ?ግራ የሚገባ ነገር ነው፡፡ በነገራችን ላይ እስከ አሁን በእኛ ጋዜጣ ላይ ከታተሙልሽ ሃያ ሰባት የሚሆኑ አጫጭር ልብወለዶች መካከል አስራ ሁለቱን መርጬ አንብበው አስተያየታቸውን እንዲሠጡኝ ለሁለት ታዋቂ ደራሲያን ሠጥቼያቸው ነበር...፡፡ >>

ጉጉት በማይታይበት የቀዘቀዘ ድምፅ‹‹ጥሩ ነው።>>

‹‹አንደኛው ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ? ‹ይሄ ድርሠት በአማተር ፀሀፊ ተጻፈ ብትለኝ ፍፁም አላምንህም፤ እርግጠኛ ነኝ ፀሀፊው አንተ ራስህ ነህ፤ በስምህ ላለማሳተም መቼም በቂ ምክንያት ይኖርሀል፤ ምስጢር የሚለውን የብዕር ስም ግን ለምን መጠቀም እንደፈለክ ፍፁም አልገባኝም ፡፡ ›ነበር ያለኝ፡፡

‹‹ታዲያ ለምን በራስህ ስም አታሳትመውም?››

‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ?››

‹‹እውነቴን ነው፡፡››

‹‹ቀልዱን አቁሚ... በዚህ ወር መጨረሻ መፅሀፍሽ ይታተማል፤ የምረቃ ፕሮግራም ለማዘጋጀት አስቢያለሁ፤ዝግጅቱ ላይ መቼም ትገኚያለሽ?››

‹‹ኪ...ኪ..ኪ.›› ከት ብላ ሳቀች፡፡ደነገጠ፡፡ ሣቋ ከሆነ ከሚያውቃት ሴት ሳቅ ጋር ተመሳሰለበት፡፡

‹‹ምን ያስቅሻል?››

‹‹አታስብ አልመጣም፡፡››

‹‹ኦ! ....ኧረ በፈጠረሽ ልታቀውሽኝ ነው? ስራዬን በትክክል መስራት እንኳን እየተሳነኝ ነው እኮ፡፡››

‹‹የማይመስል ነገር፤ በአካል እኮ አታውቀኝም::>>

‹‹ምንም ሁኚ ምንም አፈቅርሻለሁ፤ፍፁም ልረሳሽ አልችልም... ነፍስሽን ነው ያፈቀርኳት፤እስቲ በፈጠረሽ ስለ ራስሽ ጥቂት ንገሪኝ...?>>

‹‹ስለ አቋሜ ማለትህ ነው?››

«ይቻላል አዎ::>>

‹‹እንግዲህ እኔ ሦስት አይነት ሰው ነኝ፤እንደ አያቴ፣እንደ ጓደኞቼ እና እንደ አፋቃሪዎቼ...>>

<<ብታብራሪልኝ?>>

‹‹አያቴ ነፍሷን ይማርና የእኔ መላአክ ነበር የምትለኝ፤እሷ ስታደናንቀኝ ክንፍ ሁሉ ያበቀልኩ መስሎ ይሰማኝ ነበር፤ እንደሷ ምልከታ እንከን አልባ አይነት ነኝ፡፡እንደ ጓደኞቼ ደግሞ ቆንጆም ያልሆንኩ ፤ የማላስቀይምም እንደው በድርባቡ አርገው ነው የሚገልፁኝ፡፡ አፍቃሪዎቼ ደግሞ አያቴ እንደምትለው መላአክ ነበርሽ ይሉና፤ ዳሩ ምን ያደርጋልን!! ይጨምሩበታል፡፡››

‹‹ምን ማለት ፈልገው ነው?››

‹‹ቆንጆ መሆኔን አረጋግጠው ...አይነ ስውር በመሆኔ የተሰማቸውን ቅሬታ ለመግለፅ ፈልገው ..››ንግግሩ ተቋረጠ፡፡

<< ትሁን...አይነስውር ትሁን፤ከፈለገች በዊልቸር ትሂድ፤የፈለገችውን ትሁን፤እወዳታለሁ….አፈቅራታለሁ፡፡ከራሱ ጋር ሲያወራ በእጁ ያንከረፈፈው ሞባይሉ ጮኸ፡፡ ኤደን ነበረች፡፡

‹‹ደህና ዋልሽ?››

‹‹ደህና ነኝ..ምነው ጠፋህ?››

‹‹ስራ በዝቶብኝ ነው፡፡››

«የት ነህ?>>

‹‹ቤት ነኝ፡፡››

<<እየመጣሁ ነው፡፡››

<<ወዴት?>>

<<አንተ ጋር ነዋ>>::»

‹‹የተጨናነቀ ስራ ላይ ነኝ፤ብቻዬን መሆን ነር የምፈልገው፡፡››

‹‹ናፍቀኸኛል እኮ!!››

‹‹ከናፈቅኩሽ ነገ እንገናኛለን... ከደበረሽ ደግ ጓደኞችሽ ጋር መሄድ ትችያለሽ፤ እኔን ግን ተይኝ ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ...

ቻው፡፡››ብሎ ስልኩን ጆሮዋ ላይ ጠረቀመባት፡፡ እንዲህ አዕምሮው በተጨናነቀበት ወቅት ከኤደን ጋር መገናኘት ፍፁም አይፈልግም፡፡ በጭቅጭቋ ይበልጥ ታበግነዋለች‹‹ ቅራቅንቦ ጥያቄዎቿን መመለስ ከቀን ስራ በላይ ይከብዳል፡፡›› ይላል፡፡

‹‹ምን ሆነሀል?ምነው ጠቆርክ?...ከማን ተጣለህ?.. ካመመህ ሀኪም ቤት እንሂድ፡፡›› ወዘተ፤ሳይለያዩ ይሄን ሁሉ ዘመን እንዴት አብረው ሊቆዩ እንደቻሉም ግርም ይለዋል፡፡ ስለ አብሮነታቸው ዘውትር እቅድ እንዳወጣች ነው፡፡ አንድም ጊዜ ግን ተሳክቶላት አያውቅም፤ያም ሆኖ ግን ተስፋ አትቆርጥም፡፡ ከተቀመጠበት ተነሳና ሳሎን ውስጥ ተንጎራደደ፡፡ አዕምሮው ፍፁም ሊረጋጋለት አልቻለም፡፡ ወደ ውጭ ሊወጣ ፈለገ፡፡ ሠዓቱን ተመለከተ ፤ሁለት ሠዓት ተኩል ይላል፡፡ ሀሳቡን ቀየረና ስልኩን ደወለ፤ ዘና የሚያረገው ሰው ፈለገ፡፡

‹‹ሄሎ... ትንግርት፡፡››

‹‹እሺ የኔ ፍቅር፡፡››

‹‹አለሁልሽ .. የት ነሽ?››

‹‹ቤተ መንግስት የራት ግብዣ ላይ ነኝ፡፡››

ፈገግ አለ ‹‹ከምሬ ነው፡፡››

‹‹አንድ ደንበኛዬ ጭን ላይ ቁጭ ብዬ እያጋልኩት ነው፡፡››

‹‹መምጣት አትችይም?>>

‹‹ቢዝነስ እኮ ተነጋግሬአለሁ>>

<<ስንት?>>

‹‹የዛሬው ዋጋዬ አራት መቶ ሃምሳ ነው..... ከትላንቱ ትንሽ ረከስ ብያለሁ፡፡››

‹‹ወደ ትላንቱ ዋጋሽ ልመልስሻ ..እኔ ጋር ነይ::>>

‹‹ቀነዘረብህ እንዴ?››

‹‹ብዙም አይደል፤ ብቻ አስፈለግሽኝ... ያቺን ደራሲ ለሠዓታትም ቢሆን እንድታስረሽኝ እፈልጋለሁ፡፡››

<ኦ! ... ምን አይነት እድለኛ ነች ባክህ ... ቀናሁባት፡፡ ለማንኛውም መጣሁ፡፡ የተሻለ ዋጋ ከከፈልከኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቴ በሸርሙጦች መተዳደሪያ ደንብ የተከበረ ነው፡፡››

‹‹በሙሉ ሰርዥው›› አለ ቆጣ ብሎ፡፡ በከፊል ስትል ምን ማለት እንደፈለገች ገብቶታል፡፡ ደንበኛዋ እንዳይቀየማት አንዴ ከውጥረቱ እንዲረግብ ረድታው ለመምጣት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ለሁሴን አይመቸውም፡፡ ቢያንስ እሱ ጋር በምታድርበት ቀን የሌላ ወንድ ጠረን ይዛበት እንድትመጣ አይፈልግም፡፡ተሠነባበቱና ስልኩን ዘግቶ ወደ ሶፋው ተመለሰ፡፡

ሪሞቱን ከጠረጴዛው ላይ አነሳና ቴሌቪዢኑን ከፈተ፡፡ ምን አይነት ፕሮግራም እየተላለፈ እንደሆነ ለማሰብ ሳይጨነቅ ወደ ሀሳቡ
ተመልሶ ተዘፈቀ፡፡ ረዥም ቆንጆ ውብ ወጣት በአየር ላይ እየተንሳፈፈች ወደ እሱ ስትመጣ ይታየዋል፡፡ በግራ እጇ አቅጣጫ መጠቆሚያ ዘንግ ይዛለች፡፡ በቀኝ እጇ ደግሞ አዲስ የፈነዳ እምቡጥ ፅጌሬዳ አበባ ይታየዋል፡፡አይኖቿ አይታዩም፤በጥቁር መነፅር ተሸፍነዋል፡፡ ፈገግ እያለች አበባውን እንዲቀበላት ትማጸነዋለች፡፡ እሱ ደግሞ አበባውን ከመቀበሉ በፊት ከአይኖቿ ላይ የሚያስጠላውን ጭለማ መነፅር አውልቃ እንድትጥለው .. የማያዩትን አይኖቿን ቀጥታ ማየት እንደሚፈልግ እየነገራት ሳለ የሳሎኑ በር ተንኳኳ፡፡ ከጣፋጭ ሀሳቡ ነቅቶ ተነስቶ ከፈተ፡፡
👍11012😁2👎1🔥1😢1
የመጣችለት ሲጠብቃት የነበረችው ትንግርት አልነበረችም.... ኤደን እንጂ፡፡ ወደ ውስጥ ተመልሶ ሶፋው ላይ ተዘረፈጠ፡፡ኤደን ተሽቀርቅራለች፡፡ ከታች ሠማያዊ ጅንስ ሱሪ፣ከላይ በቀይና በጥቁር ቀለም የተዥጎረጎረ ሹራብ ለብሳለች፡፡ ወርቃማ ሉጫ ፀጉሯን ትከሻዋ ላይ ነስንሳዋለች፡፡ በንዴት የመነጨው ላቧ ጠይም ፊቷ ላይ ወዝ ረጭቶ
ተጨማሪ ውበት ለግሷታል፡፡ የለበሰችው ሹራብ ሰውነቷ ላይ ጥብቅ ስላለ ጡቶቿ ወደ ፊት ቀድመው አይን ውስጥ ይመሠጋሉ፡፡ የቁመቷን ማጠር ባደረገችው ባለ ተረከዝ ጫማ አካክሰዋለች፡፡

‹‹ቴሌቪዥን ላይ ለማፍጠጥ ነው አትምጪ ያልከኝ?›› በመውረግረግ ወደ ምትቀመጥበት ቦታ እያመራች የመጀመሪያ ጥያቄዋን ሠነዘረች፡፡

‹‹አይደለም፡፡›› አላት ሪሞቱን ተጠቅሞ ቴሌቪዥኑን እያጠፋ፡፡ አበሳጭታዋለች፡፡ካለ ባህሪዋ እንደ ችኮነቷ የሚያማርረው የለም፡፡ ‹‹ነገሮችን ከራሷ ፍላጎት አንፃር እንጂ ከሌሳ ሠው ፍላጎት አንፃር መዝኖ ማገናዘብ ፍፁም አልፈጠረባትም›› ሲል ሁሌ ይወቅሳታል፡፡››

<<እና?>>>

‹‹ቀጠሮ ስላለብኝ ነው፡፡››

‹‹ቀጠሮ? .... የምን ቀጠሮ? ... ከማን ጋር ?››

‹‹ከትንግርት ጋር፡፡››

‹‹ኧረ! .. ከሸርሙጣዋ ጋር ቀጠሮ!››

‹‹ሁላችንስ ሸርሙጦች አይደለን? እሷ ሸርሙጣ መሆኗን በአዋጅ ያስነገረች የአደባባይ ሸርሙጣ ስትሆን እኔ እና አንቺ ደግሞ ጓሮ ለጓሮ ከሠው ተሸሽገን በሚሥጥ የምንወሰብ ሸርሙጦች ነን፡፡ አሁንም እኮ የመጣሽው እንድንሸረሙጥ ፈልገሽ መሠለኝ >>

ሠውነቷ ተንቀጠቀጠባት፣የጨጓራዋ ቁስለት ሲለበልባት ይሰማታል፡፡ በትንግርት ጉዳይ ብዙ ጊዜ ተጨቃጭቀዋል፡፡ ለቀናቶች በተደጋጋሚ ተኮራርፈውም ያውቃሉ እስከአሁ የተለወጠ ነገር ባይኖርም፡፡ ብዙ ጊዜ እርግፍ አድርጋ ልትተወው ታስብና መሸነፍ ደግሞ ያስጠላታል.... እልህ ትገባለች፡፡‹‹እና ተመልስ እንድሄድልህ ትፈልጋለህ?››

‹‹እንደፈለግሽ፡፡››...

ይቀጥላል


ዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ   አደለም ከ 100,000 በላይ አባላት ውስጥ ቢያንስ ይሄን የምታነቡ እንኳን subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች በቅድምያ
ስለመልካምነታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ።
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍1128🥰7🤔1
Forwarded from Rihrahe Diabetes Healthcare
ርህራሔ የስኳር ጤና ክብካቤ

አገልግሎት ለማግኘት እና ለማንኛውም መረጃ:

Subscribe Our Telegram Channel
> https://xn--r1a.website/Rihrahe

Join Our Telegram group
> https://xn--r1a.website/rihrahe_DM

Visit our Website:  
> http://rihrahe.com

Email:   info@rihrahe.com
Contact us   0995-440344
                       0947-964189

#diabetes #prediabetes
#rihrahe #healthcare

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፣

¤ የስኳር ጤና ራስ አገዝ ስልጠና / ትምህርት
¤ ሀሳብዎን በእኛ ላይ የሚጥሉበት ሁለንተናዊ የመደበኛ ክትትል እና አባልነት አገልግሎት
¤ 24 ሰዓት የማስታመም አገልግሎት
¤ የነርሰ አገልግሎቶች፣
¤ መሰረታዊ የጤና ቅድመ ምርመራ
¤ የላብራቶሪ አገልግሎት
¤ መደበኛ የጥርስ እጥበት
¤ የቤት ለቤት የፊዝዮቴራፒ አገልግሎት
¤ ስኳር መከላከል ኘሮግራም
¤ የስነ ምግብ ስልጠና
¤ ማህበራዊ አገልግሎት
¤ እና ሌሎች ሁለንተናዊ የጤና አገልግሎቶችን ያሉበት ድረስ መጥተን እንሰጣለን።



Office Address Addis Ababa
Jemo, Kafdem Mall, F-306
👍152