አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስር


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርክ አልደር በመጀመሪያ ዳያና ላቭሴይንን ያያት ጊዜ ‹‹የአምላክ ያለህ! እንዳንቺ የምታምር ሴት አይቼ አላውቅም›› አላት፡፡

ያገኛት ሁሉ እንዲህ ይላታል፡፡ ዲያና ያለጥርጥር ውብ ሴት ስትሆን ጥሩ ጥሩ ልብስ መልበስም ትወዳለች፡፡ የዚያን ቀን እጀ ጉርድ ቅልጥሟ ጋ የሚደርስ ቀሚስ ለብሳ ነበር፡፡ እንዳማረባትም አውቃለች።

ማንቼስተር ከተማ ሚድላንድ ሆቴል ውስጥ ራት ግብዣ ተጠርታለች
በግብዣው ላይ ከነበሩት ከባሏ የንግድ ሸሪኮች ጋር በሙሉ ስትደንስ አመሸች ታዲያ ሁሉም አብረዋት የደነሱት ወንዶች ደረታቸው ላይ ይለጥፏታል ወይም እግሯ ላይ ይቆማሉ ሚስቶቻቸው ደግሞ በጥላቻ ዐይን አፈር ድሜ ያስግጧታል፡ ወንዶች ቆንጆ ሴት አይተው ሲቅበጠበጡ
ሚስቶች ለምን ባሎቻቸውን ትተው ሴቷ ላይ በቁጣ እንደሚያፈጡ ሁልጊዜ
ይገርማታል፡፡ እሷ እንደሆነ እነዚህን ጉረኛና በዊስኪ የደነበዙ ባሎቻቸውን
አትፈልግም፡፡

አንድ ጊዜማ የከተማውን ምክትል ከንቲባ በሰው ፊት በማዋረዷ ባሏን አሳፍራው ነበር፡ በኋላም ትንሽ እረፍት አገኝ ብላ ሲጋራ የምትገዛ መስላ ከሆቴሉ ወጥታ ሄደች፡

ኮኛኩን እየተጎነጨ ብቻውን ተቀምጧል። ልክ በክፍሉ ውስጥ የፀሃይ ብርሃን የፈነጠቀች ይመስል ስትገባ ዓይኑን ተከለባት፡ ሰውዬው አጠር ያለና እንደ ህፃን ፍልቅልቅ ያለ ፈገግታ የተላበሰ ሲሆን አሜሪካዊ መሆኑ ሁኔታው ያሳብቅበታል፡፡ ገና እንዳያት አድናቆቱን የገለፀላት ሲሆን ሰውዬው የደስ ደስ ያለው በመሆኑ ፈገግ ብትልለትም አላናገረችውም፡፡ ሲጋራዋን
ገዝታ ቀዝቃዛ ውሃ በጉሮሮዋ ለቀቀችና ወደ ዳንሱ አዳራሽ ተመለሰች፡

ሰውዬው ማን እንደሆነች ከቡና ቤቱ አስተናጋጅ ጠየቀና አድራሻዋን
እንደምንም አግኝቶ የፍቅር ግጥም ፅፎ ላከላት፡፡ ግጥሙን ስታነብ አነባች፡፡
ያስለቀሳት ብዙ ነገር ተመኝታ ሁሉንም ነገር ባለማግኘቷ ነው፡፡ ያለቀሰችው በዚች ደስታ በራቃት ከተማ የዓመት እረፍት መውጣት ከሚጠላ ባሏ ጋር ተጣብቃ በመቅረቷ ነው፡፡ ያለቀሰችው ከአምስት ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ
ጊዜ የፍቅር ግጥም በመስማቷ ነው: ያለቀሰችው ለመርቪን ያላት ፍቅር የተሟጠጠ በመሆኑ ነው፡፡

በነጋታው እሁድ ስለነበር ዳያና ቤቷ ውስጥ መሸገች፡፡ ሰኞ ዕለት ወደ
ከተማው መጽሐፍ ቤት ሄዳ ከዚህ ቀደም የተዋሰችውን መጽሐፍ መለሰችና ፊልም ቤት ገባች፡፡ ከዚያም ለእህቷ ልጆች ስጦታ ስትገዛ ዋለች፡፡ በኋላም
እራት መስሪያ የሚሆኑ ቁሳቁሶች ገዛችና ከከተማ ወጣ ወዳለው መኖሪያዋ
በጊዜ ለመድረስ ባቡር ላይ ተሳፈረች፡፡ ከተማ ውስጥ ስትዟዟርና ቡና ስትጠጣ የአሜሪካዊ አነጋገር ቅላፄ ያለውን ሰው ሳታገኘው በመመለሷ ተከፋች፡፡

ነገር ግን ነገሩን ስታስበው ጅልነት ሆነባት፡፡ ሰውዬውን ያየችው ለአፍታ ጊዜ ሲሆን በወቅቱም አላነጋገረችውም፡፡ ሆኖም ይህ ሰው ለዓመታት ያጣችውን ፍቅር የሚቀሰቅስባት ሆነባት፡ ታዲያ ይህ ሰውዬ ደግማ ብታገኘው ወይ ባለጌ ይሆናል፣ ወይ ወፈፌ ይሆናል፣ ወይ በሽተኛ
ይሆናል፣ ወይ ደግሞ ገላው የሚቀረና ይሆናል ብላ አሰበች

ከባቡሩ ወርዳ የቤቷን መንገድ ይዛ ስትሄድ ባልጠበቀችው ሁኔታ
ሰውዬው ወደ እሷ ሲመጣ በማየቷ ክው ከማለቷም በላይ ተርበተበተች፡፡
ፊቷ ቲማቲም መሰለ፧ልቧም መቶ ሜትር ሸመጠጠ፡፡ እሱም ሲያያት መደንገጡ ባይቀርም ሊያናግራት ቆም አለ፡፡ እሷ ግን እርምጃዋን ቀጠለች።

አልፋው ስትሄድ ‹‹ነገ ጠዋት ማዕከላዊ መጻሕፍት ቤት ጠብቀኝ›› አለችው
መልስ ይሰጠኛል ብላ ባትጠብቅም ሰውዬው ፈጣን አዕምሮ ያለው መሆኑን በኋላ ተረድታለች፡፡ ወዲያው ‹‹የትኛው ክፍል?›› አላት።

አፏ እንዳመጣላት ‹‹ባዮሎጂ ክፍል›› በማለቷ ሳቅ አለ፡፡

ቤቷ የደረሰችው በደስታ ተሞልታ ነው፡

ቤቱ ውስጥ ሰው የለም፡፡ የፅዳት ሰራተኛዋ ስራዋን ጨራርሳ የሄደች ስትሆን
መርቪን ገና አልገባም፡፡

በማግስቱ ቀጠሯቸው ቦታ መጻሕፍት ቤት ከላይ ‹‹ፀጥታ›› የሚል
ፅሁፍ የተንጠለጠለበት ቦታ ተቀምጦ አገኘችውና ‹‹ሰላም›› ስትለው ሌባ ጣቱን ከንፈሩ ላይ አድርጎ ዝም እንድትልና እንድትቀመጥ አመለከታት
ከዚያ ብጣሽ ወረቀት ላይ አንድ ነገር ፅፎ አቀበላት፡፡ ‹‹ኮፍያሽ ያምራል» የሚል ነበር፡፡ ኮፍያዋን በአንድ በኩል ገደድ አድርጋ ራሷ ላይ የደፋች በመሆኗ የግራ አይኗን ከልሎታል፡፡ ይህ ኮፍያ አደራረግ ፋሽን ሲሆን ይህን ፋሽን ለመከተል የሚደፍሩት ወኔ ያላቸው ጥቂት ሴቶች ብቻ ናቸው።

እስክርቢቶ ከቦርሳዋ አወጣችና ‹‹ኮፍያው ላንተ አይሆንም› ብላ ፅፋ
አሳየችው:፡ እሱም ‹‹የግቢዬን አበባ አስቀምጥበታለሁ›› ብሎ ሲፅፍላት በሳቅ ተንከተከተች፡፡ ‹‹ሽሽሽሽ›› አላት ዝም እንድትል፡

ዳያና ይሄ ሰውዬ ወፈፌ ነው አስቂኝ አለች በሆዷ፡፡ ከዚያ
‹‹ግጥሞችህን ወድጃቸዋለሁ›› ብላ ፃፈችለት፡፡

‹‹እኔም አንቺን ወድጄሻለሁ› ብሎ መለሰላት በፅሁፍ፡፡

‹እብድ› ስትል አሰበች፡፡ ሆኖም እምባዋ በዓይኗ ተንቆረዘዘ፡፡

‹‹ስምህን እንኳን አላውቀውም› ብላ ፃፈችለት።

ቢዝነስ ካርድ አወጣና ሰጣት፡፡ ስሙ ማርክ አልደር ሲሆን የሚኖረው ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ነው፡፡
የምሳ ሰዓት ሲደርስ ምሳ ለመብላት ወደ ምግብ ቤት ሄዱ፡ ይህን ሰዓት የመረጠችው ባሏ እንዳያገኛት ነው መቼም በዚህ ሰዓት ባሏ
አይመጣም ብላ፡፡

ከምሳ በኋላ የሙዚቃ ድግስ ለማየት ቴያትር ቤት ገቡ፡፡

ያን ቀን ማርክ የሬዲዮ ኮሜዲ ደራሲ መሆኑን፣ ለታዋቂ ኮሜዲያኖች
እንደሚደርስ፣ እንዲሁም የሬዲዮ ጣቢያ ባለቤት መሆኑን አጫወታት
እንግሊዝ አገር የመጣው ትውልዳቸው ከሊቨርፑል
ውስጥ የሚሳብ የትውልድ ዘር ሐረጎችን ለማፈላለግ መሆኑን ነገራት፡፡

ማርክ አልደር ቁመቱ አጠር ያለ ሲሆን ከዳያና አይበልጥም፧ በእሜም እኩያዋ ነው፡፡ ፊቱ ሁል ጊዜ ፈገግታ አይለየውም፡፡ በአእምሮ የበሰለ አስቂኝና ተጫዋች ሲሆን ባህሪው ልስልስ ያለ በአለባበሱ ሸጋና ፅዱ ነው የሞዛርትን ሙዚቃ የሚወድ ሲሆን ከሁሉም በላይ ግን ዳያናን ወዷታል።
እስካሁን የምታውቃቸው ወንዶች ገላዋን መተሻሸት የሚወዱ፣ ባሏ መርቪን ጀርባውን ማዞሩን አይተው እንተኛ የሚሏት፣ በመጠጥ የደነበዙና ካንቺ ፍቅር ይዞናል እያሉ የሚቀባጥሩ ዓይነት ናቸው፡:

መቼም እሷን ሳይሆን ገላዋን እንደሚፈልጉ ታውቃለች፡፡ ንግግራቸው
የማይጥም ፍሬፈርስኪ ሲሆን እሷ የምትለውን ለመስማት አይፈልጉም፡፡
ስለእሷም ማወቅ ችግራቸው አይደለም:: ማርክ ግን ከነሱ ለየት ያለ ሰው መሆኑን ከቀን ወደ ቀን ማወቅ ችላለች፡፡

መጻሕፍት ቤት በተገናኙ ማግስት መኪና ተከራየና ባህሩ ዳርቻ ወስዶ
አዝናናት፤ ሳንድዊች ጋበዛትና ከለል ያለ ቦታ ፈልገው ተሳሳሙ፡፡

ማርክ ሚድላንድ ሆቴል አልጋ የያዘ ቢሆንም ዳያና እዚያ በጣም ታዋቂ በመሆኗ ከሱ ጋር መግባት አትችልም፡፡ ከምሳ በኋላ እዚያ ከወንድ ጋር ስትገባ ብትታይ በመክሰስ ሰዓት ወሬው በከተማው በሙሉ ይዳረሳል፡በመሆኑም የማርክ ፈጣን አዕምሮ አንድ ነገር ዘየደ፡፡ ሌላ የባህር ዳርቻ ላይ የሚገኝ ከተማ በመኪና ሄደው ሻንጣ አንጠልጥለው ሆቴል ደረሱና አቶ እና ወይዘሮ አልደር ብለው ተመዝግበው አልጋ ያዙ፡፡ ከዚያም ምሳ በሉና አልጋ ላይ ወጡ፡፡

ማርክ በፀጥታ ልብሱን ማወላለቅ ጀመረ፡፡ እሷ ደግሞ እፍረት ስለያዛት
ልብሷን ያወላለቀችው በሳቅ እየተንከተከተች ነው፡፡

ይወደኝ ይሆን ብላ አልተጨነቀችም፡፡ ከመውደድም እንደሚያመልካት
አውቃለች፡፡ እሱም ጥሩ ሰው በመሆኑ አልተረበሸችም
👍16
ከሰዓት በኋላውን በሙሉ አልጋ ውስጥ ገላቸውን ሲያስደስቱ ውለው
ሆቴል ማደር እንደሌለባቸው ሃሳባቸውን የለወጡ መሆኑን በመግለጽ የአዳር ሂሳብ ከፍለው ከሆቴሉ ወጥተው ሄዱ፡ ከዚያም ከቤቷ አንድ ፌርማታ ሲቀራት ከመኪና ወረደችና ባቡር ተሳፍራ በመሄድ ልክ ማንቼስተር የዋለች ይመስል ቀጥ ብላ ቤቷ ገባች፡፡

ማርክ ማንቼስተር በቆየበት ጊዜ ሁሉ በዚህ ሁኔታ አሳለፉ፡፡

መድረስ አይቀርምና የማርክ ወደ አሜሪካ መመለሻ ቀን ደረሰ፡፡
ዳያናና ማርክ ጊዜው ሮጦባቸዋል፡፡ ዳያና ስለወደፊቱ ማሰብ
አስፈርቷታል፡፡ ማርክ አንድ ቀን ጥሏት ይሄዳል፡፡ ሆኖም ነገ እዚህ ነው ያለው ብላ ራሷን አፅናናች፡ አሁን ማሰብ ያለባት ስለዚህ ቀን ብቻ ነው፡፡ልክ እንደ ጦርነት፡፡ ጦርነት አስከፊ መሆኑን ሁሉም ያውቃል፤ መቼ እንደሚጀመር ግን ቅንጣት ታህል አያውቅም፧ እስኪጀምር ግን ሁሉም
የዕለት ተዕለት ስራውን ይሰራል፡፡ ጊዜውንም በደስታ ለማሳለፍ ይሞክራል፡፡

ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ግን አልደር ሊሄድ እንደሆነ ነገራት፡፡

ጡቷን አንገፍጥጣ አልጋ ላይ ተቀምጣለች ማርክ እንደዚህ ስትቀመጥ ደስ ትለዋለች፡ እሱ ጡትሽ ያምራል ቢላትም እሷ ግን ጡቶቼ ትላልቅ ናቸው ብላ ታስባለች፡፡አሁን ስለ ጦርነቱ መወያየት ጀምረዋል፡፡ እንግሊዝ በጀርመን ላይ
ጦርነት አውጃለች በአፍላ ፍቅር ላይ ያሉ ፍቅረኛሞች እንኳን ስለጦርነቱ ማውራት ጀምረዋል።

ዳያና በሁሉም ሰው አዕምሮ ውስጥ የሚጉላላውን ጥያቄ ለማርክ አቀረበችለት።

‹‹ጦርነቱ ምን ሊያስከትል ይችላል?›› ስትል

‹‹ጦርነቱ አስከፊ መሆኑ አይቀርም›› አላት ኮስተር ብሎ፡ ‹‹አውሮፓ
ድምጥማጧ ይጠፋል ብዬ እገምታለሁ ምናልባት እንግሊዝ ከአውሮፓ
በባህር በመለየቷ ብዙ ጉዳት ላይደርስባት ይችላል።››

‹‹ወይ አምላኬ›› አለች ዳያና፣ ፍርሃት እየጨመደዳት

እንግሊዞች እንዲህ አይደሉም፡ ጋዜጣው በሙሉ የሚያትተው
ጦርነት ነው፡፡ መርቪን ጦርነቱን በአዎንታዊነቱ ነው የሚያየው መርቪን ያለው ነገር ትዝ አላት፡ ‹‹አሜሪካ ወደደችም ጠላችም በቅርቡ ጦርነት ውስጥ ትዘፈቃለች፡፡››

ማርክም ‹‹አይመስለኝም: ይሄ የአውሮፓውያን ችግር በመሆኑ እኛን
አይመለከተንም፡ እንግሊዝ በጀርመን ላይ ጦርነት ማወጇ እሺ ነገር ግን
አሜሪካኖች ፖላንድን ለመከላከል ሲሉ የሚሞቱበት ምክንያት አይገባኝም በማለት የተናገረው ዳያናን በእጅጉ አሸማቋታል፡ አነጋገሩ አበሳጭቷታል፡ ሃሳቡ ግን ትክክል ነው ብላ ተቀብላለች፡፡

‹‹እውነት አሜሪካኖች ለፖላንድ ሲሉ አንገታቸውን ለካራ ይዳርጋሉ።
ለአውሮፓስ ቢሆን››

‹‹እኔስ?›› ስትል ድንገተኛ ጥያቄ ሰነዘረች፡፡ ‹‹እስከ ጉልበት የሚደርስ
የተወለወለ ቦት ጫማ በሚያደርጉ ጀርመኖች ብደፈር መቼም አትፈልግም? ትፈልጋለህ?›› አለችው፡

ከዚያም አንድ ኤንቨሎፕ ከሻንጣው አወጣና ሰጣት፡
ከኤንቨሎፑ ውስጥ ትኬት አወጣችና ‹‹ልትሄድ ነው?›› ብላ ጮኸች

የዓለም መጨረሻ የሆነ መሰላት፡ እሱም ፈርጠም ብሎ ‹‹ቲኬቶ ሁለት ናቸው›› አላት፡፡

‹‹ሁለት ቲኬቶች›› አለች ግራ በመጋባት፡፡

አልጋው ላይ ተመቻችቶ ተቀመጠና እጇን ያዝ አደረገ፡፡

ቀጥሎ የሚለውን በመገመቷ በአንድ በኩል ስትደሰት በሌላ በኩል
ፍርሃት ጨመደዳት፡፡

‹‹አገሬ ይዤሽ እሄዳለሁ ዳያና›› አላት ከኔ ጋር ኒውዮርክ በአይሮፕላን እንሄዳለን፡፡ ከዚያ በኋላ ባልሽን ትፈቺና ካሊፎርኒያ ሄደን እንጋባለን፤ እወድሻለሁ››
በአይሮፕላን መሄድ! አትላንቲክ ውቅያኖስን በአየር ማቋረጥ፡፡ እንደዚህ
አይነት ነገር በተረት ነው የምታውቀው፡

ወደ ኒውዮርክ! ኒውዮርክ የታላላቅ ህንፃዎች፣ የምሽት ክበቦች፣ የማፊያ፣ የሚሊየነሮች፣ የፋሽን ንግስቶች እና የምቹ መኪኖች ከተማ፡፡

ፍቺ መፈፀምና ከመርቪን መላቀቅ፡፡

ካሊፎርኒያ እንሄዳለን ፊልሞች የሚሰሩበት፣ ብርቱካን እንደ ልብ
የሚበቅልበትና ከአመት እስከ አመት ፀሃይ የሚፈነጥቅበት አገር፡ ከማርክ ጋር ጋብቻ መፈፀም፣ ማርክን ለዘላለም የራስ ማድረግ፤ ነጋ ጠባ፡፡ መናገር
አቃታት፡

ማርክም ‹‹ልጆች እንወልዳለን›› አላት፡
ሳታውቀው በደስታ ሲቃ ጮኸች

‹‹እንደገና ጠይቀኝ›› አለችው በለሆሳስ፡፡

‹‹እወድሻለሁ፤ የትዳር አጋሬ ትሆኛለሽ? የልጆቼ እናት ትሆኚኛለሽ?››

‹‹አዎ በደስታ›› አለችው ‹‹አዎ፣ አዎ፣ አዎ!!!››
ማታውኑ ለመርቪን መንገር ሊኖርባት ነው፡፡
ቀኑ ሰኞ ነው፡፡ ማክሰኞ እለት ከማርክ ጋር ሳውዝ ሃምፕተን መሄድ አለባት፡ አይሮፕላኑ ሮብ እለት በ8፡00 ሰዓት ይበራል፡፡ ሰኞ እለት ከሰዓት በኋላ እቤቷ እስክትደርስ በደስታ ስትንሳፈፍ ነበር፡፡ እቤቷ ስትደርስ ግን ያ ሁሉ ደስታ ተነነ፡፡

ለባሏ እንዴት ብላ ልትነግረው እንደሆነ ቸገራት፡፡

ቤቷ ጥሩ ነው፡ ትልቅ፣ አዲስ፣ ባለ አራት መኝታ ቤት፡ ሶስቱ ክፍሎች ግን ሰው ተኝቶባቸው አያውቅም፡፡ ቤቱ ዘመናዊ ባኞ ቤት እና ዘመኑ ባመጣቸው ቁሳቁሶች የተሞላ ኩሽና አለው፡፡ አሁን ግን ትታው ልትሄድ በመሆኑ በስስትና በፍቅር እየተዘዋወረች አየችው፡:
ይሄ ቤት ለአምስት አመት ያህል የኖረችበት ቤቷ ነው፡፡
የባሏን እራት ራሷ ነች የሰራችው፡፡ የፅዳት ሰራተኛዋ ቤት ወልውላለች፤ ልብሱንም አጥባለች፡፡ ዳያና ከእራት በስተቀር ሌላ ምንም የምትሰራው
ነገር የለም፡፡ ባሏ ደግሞ ደስ የሚለው ሚስቱ ራቱን ሰራርታ ጠረጴዛ ላይ
አድርጋ ስትጠብቀው ነው፡፡ ባሏ ምንም አይነት ምግብ ቢዘጋጅለትም ምግቡን
መልካም ነው የሚለው፤ ለሱ ምግብ ማለት ሆቴል ሄዶ የሚበላውን ነው፡

ዛሬ መርቪን ራቱ የበሬ ስጋ ሲሆን ሽርጧን አገልድማ ድንች መላጥ ጀመረች፡፡ ጥላው መሄዷን ስትነግረው እንዴት እንደሚቆጣ ስታስበው እጇ
ተንቀጠቀጠና ቢላው ቆረጣት፡፡

የደማውን እጇን በውሃ አጣጥባ በፎጣ አድርቃ በፋሻ አሰረችው:፡
ለምንድነው የፈራሁት? ስትል ራሷን ጠየቀች አይገድለኝ፤ ሊከለክለኝም
አይችልም፤ እድሜዬ ከ21 አመት በላይ ነው! ይህም አገር ነፃ አገር ነው! በማለት ራሷን ለማሳመን ሞከረች፡፡
ይህም ሆኖ ግን ልትረጋጋ አልቻለችም፡፡

ይቀጥላል
👍15👏1
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_አስር ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ ማርክ አልደር በመጀመሪያ ዳያና ላቭሴይንን ያያት ጊዜ ‹‹የአምላክ ያለህ! እንዳንቺ የምታምር ሴት አይቼ አላውቅም›› አላት፡፡ ያገኛት ሁሉ እንዲህ ይላታል፡፡ ዲያና ያለጥርጥር ውብ ሴት ስትሆን ጥሩ ጥሩ ልብስ መልበስም ትወዳለች፡፡ የዚያን ቀን እጀ ጉርድ ቅልጥሟ ጋ የሚደርስ ቀሚስ ለብሳ ነበር፡፡ እንዳማረባትም አውቃለች።…»
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሶስት (3)



ቃል ኪዳናቸውን በደስታ ሳቅ አሳረጉ። ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ማይክል «አሁን ወደቤታችን እንድንመለስ ትፈልጊያለሽ ? » ሲል ጠየቃት። ራሷን በአወንታ ነቀነቀች ። ቀስ እያሉ ብስክሌቶቻቸውን ወዳቆሙበት ቦታ አመሩ። በቀጥታ ወደ ቦስተን ፤‹ወደ ናንሲ መኖሪያ ቤት አመሩ፡፡ እዚያ እንደገቡ ማይክል የደስታ ስሜት ተሰማው ። ለማይክል ሌላው ሁሉ ዝም ብሎ ቤት ነው። ይህቺ የናንሲ መኖሪያ ግን ማረፊያው ነች። የናንሲ መኖሪያ ምቹ በሆኑ የቤት ዕቃዎች የተደራጀች በመሆኗ አይደለም እጅግ ሰፊ ሆና እንደልብ ስታዝናናው በመቻሏም አይደለም። ናንሲ ሰፊ መኖሪያ ቤትም ፤ ምቹ የቤት ዕቃ ሊኖራት አይችልም ። ሆኖም ሰላም በዕቃ ዓይነት ወይም በቤት ስፋት አይገኝም ። ሰላም በዚህ ሁኔታ ቢገኝ ኖሮ እጅግ ሰፊ የሆነው የእናቱ መኖሪያ ይሆን ነበር ለማይክል ሰላምና ዕረፍትን የሚሰጠው ። ያ ያደገበት ቤት ለሱ ምኑም አልነበረም ።

የናንሲ ጠባብ ቤትና በውሶጧ ያሉት ትናንሽ ፅቃዎች ግን ከላይ እንደተገለጠው ሰላምና ዕረፍት ይሰጡታል ። ናንሲ ሰዓሊ ናትና ውበትን የሚያደንቅ ዓይን አላት ። ይህ ስለሆነ ከሰፋፊና ግዙፍ ውድ የእናቱ መኖሪያ ቤት ዕቃዎች ይልቅ የናንሲ የቤት ዕቃዎች ያስደስቱታል ። ግድግዳው የተቀባው ቀለም ፤ የወለሉ ምንጣፎች ለማይክ ደስታ ይሰጡታል ። በዚህ ሁሉ ላይ ናንሲ በሕይወት ተከብባ የምትኖር ፍጡር ናት ። የተጀመሩም ሆኑ ያለቁ ሥዕሎቿ ለሱ ሕያው ናቸው። በመጀመሪያ በኤግዚብሽኑ አዳራሽ ውስጥ ሲያያቸው ያየባቸው ሕያውነት ይበልጥ እውን እየሆነ ሄዶ ነበር ።

በዚህ ሁሉ ላይ በናቱ ግዙፍ አዳራሾችም ውስጥ ሆነ የትም ቦታ የማያገኘው ፤ እንደልቡ ሆኖ እየተዝናና የሚያጣጥመው ያ የቀለም ሽታ ለሱ የሱስ ያህል ነበር። « እዚህ ቤት ስሆን ምን ያህል ደስ እንደሚለኝ ታውቂያለሽ ናንሲ ?» አለ ማይክል ።
« አዎ ... አውቃለሁ » አለችና ዞር ብላ በናፍቆት ተመለከተችው ። ከዚያም ቤቷን በፍቅር እየቃኘች «እኔም እንደዚች ቤት ደስ የሚለኝ ቦታ የለም ። ለመሆኑ ከተጋባን በኋላ እንዴት ነው እምናደርገው !
«ቀላል ነው። እነዚህን ውብ ነገሮች ጥርግ አድርገን እንወስዳለን ። ኒውዮርክ ውስጥ ሽክ ያለ አፓርታማ እንከራያለን ። እቃዎቹ ሲገቡ ቤቱ እንደዚሁ ደስ ይለናል ። አይመስልሽም ?» አለ ።
እንዲህ እያለ በቤቱ ውስጥ ያሉትን ውብ ነገሮች ሲቃኝ ድንገት ዓይኑ አንድ ነገር ሳይ አረፈ፤ « እንዴ ! ያ ምንድን ነው ?» አለ ወደ ሸራ መወጠሪያ አትሮኖሷ እያመለከተ « አዲስ ሥዕል ነው ?» ብድግ ብሎ ወዶ አትሮኑሱ እየሄደ ፤« መቼ ነው የሠራሽው ? የጀመርሽው ? » አለ። ሥዕሉ ገና ጅምር ቢሆንም የመሳብ ምስጢራዊ ኃይሉ እሚከሰትበት ደረጃ ላይ ደርሷል ። ሥዕሉ የገጸ ምድርን ምስል የያዘ ሲሆን የተፈጠረው ገጸ ምስልም ዛፎች የሚገኙበት አንድ ሜዳን ያሳያል ።

ማይክል ወደ ሥዕሉ ተጠጋ ። በዚህ ጊዜ ሌላ ነገር አጋጠመው ። በሥዕሉ ውስጥ ከሚገኙት ዛፎች ባንደኛው ላይ የተደበቀ ልጅ አየ ። የልጁ እግሮች ተንጠልጥለው እሱም ላለመውደቅ ሽምቅቅ ብሎ ታየው። ሥዕሉን በተመስጦ ሲመለከት ከቆየ በኋላ ወደ ልጁ እያመለከተ ፤
« ሥዕሉ ተስሎ ሲያበቃ ልጁ እንዲህ እንዳለ ይታያል ? ማለት የዛፍ ቅጠልም ሆነ ቅርንጫፍ አይሸፍነውም ?» ሲል ጠየቃት ። «እንዲህ እንዳለ ማለት አይቻልም ። ሆኖም' በሆነ መንገድ ልጁ መኖሩ አይቀርም » አለችው ። ቀጥላም « እንዴት ነው? ወደድከው?» ስትል ጠየቀችው።
ጠየቀችው እንጂ እንደወደደው ፣ እንዳደነቀው ከፊቱ ላይ አንብባለች ። ሥዕሎቿን እንደሱ የሚወዳቸው ሰው አጋጥሟት አያውቅም ። ሐሳቧን እንደሱ የሚረዳላት ሰው የለም ። « ወደድከው ወይ?! አፈቀርኩት እንጂ !» አላት። '
«ነው?»
« አትጠራጠሪ »
« እንግዲያስ ይህ ሥዕል የግልህ ነው ። ለሠርግህ ዕለት የማበረክትልህ ስጦታ ነው » አለች ። «ተስማምቻለሁ ። የሠርግ ወሬ ብታነሺ» አለና ሰዓቱን አዬ ፤ «አሁን መሄድ አለብኝ››
«ምንድነው እሱ?ግድ ዛሬ መሔድ አለብህ ማለት ነው?»
«አዎ መሄድ አለብኝ ። ከምሽቱ አንድ ሰዓት ኒውዮርክ ብደርስ ፤ እንደበረራው ትራፊክ ሁኔታ እቤት አንድ ሰዓት ተኩል ብደርስ ፡፤ ማሪዮንን አነጋግሬ የሠርጋችንን ጉዳይ አዘጋጅቼ ከጨረስኩ በኋላ ወደዚህ ለመመለስ ቢያንስ የመጨረሻዋን አውሮፕላን አገኛለሁ። ተመልሼ እዚሁ ነው እማድረው ። ገቢቶ »
«ገቢቶ » አለች ። ሆኖም ለምን እንደሆነ አትወቅ እንጂ የዚያን ዕለት አካሄዱ በምንም መንገድ ደስ አላላትም ። የሆነ ነገር ቅር ይላታል ። ባይሔድ . . . ባይሔድ የሚል ሐሳብ ይሰማታል።
«ሁሉም ነገር እንዲሳካ እመኛለሁ » አለች ።
«አትጠራጠሪ ፤* ይሳካል » አላት። ሆኖም ራሱ የተናገረውን እንደሚይተማመንበት ሁለቱም ያውቃሉ ። ማሪዮንን ያውቋታላ ። ተቃቅፈው ለረጅም ጊዜ ቆዩ ። ከዚያም ተሰናብቷት ሊወጣ ሲዘጋጅ ፤ «እንግዲህ ይቅናህ አለችው›› «ናንሲ በጣም እወድሻለሁ » ሲል መለሰላት ። ሔደ።

ለረጅም ጊዜ ብቻዋን ቁጭ ብላ እባዛሩ ላይ የተነሱትን ፎቶግራፍ ተመለከተች ። ማይክል ሂልያርድና ናንሲ ማክአሊስተር አይደለም ፤ ርሄት በትለርና ስካርለት ኦሀራ… እነዚህ ሁለቱ ዘለአለም በፍቅር ሲነሱ ይኖራሉ ። ማይክና ናንሲ የርሄትንና የስካርለትን ልብስ ለብሰው ሲታዩ የዚያ አለባበስ ዘመኑ አልፏልና ትንሽ ሞኝ አስመስሏቸዋል ። ሆኖም ደስ ብሏቸዋል። ዋናው ደስታ ነው ።

አዎ ፍቅር ደስታ ነው ። ምነው ማሪዮን ሂልያርድ ይህን መገንዘብ ብትችል ! ሞኝነትና ዶስታ እንደሚለያዩ ብታውቅ! የተለያየ ሰው ነው እንጂ ሞኝ እንደሌለ ቢገባት ። ደስታ ግን ደስታ ነው ። ምነው ማሪዮን በሐሳብና በኑሮ መካከል ያለውን ልዩነት ብታውቅ !፣
ናኒስ ብቻዋን በሐሳብ...
👍18
የመመገቢያ ቤቱ ጠረጴዛ እንደ አንድ ፀጥተኛ ሃይቅ ተንጣሏል ፤ ያብረቀርቃል ። ከዳር እስከዳር ያብረቀርቃል እንዳንል ከወደ አንድ ወገን የሆነ ነገር አርፎበታል፡፡ ይለያል ማለት እንጂ ውበቱን ይቀንሳል ማለት አይደለም ። እጅግ ውብ በሆነ የኪነጥበብ ሥራ የተጌጠው የጠረጴዛ ልብስ ፤በሱ ላይ ያረፈው በሰማያዊና በወርቅማ ቀለም ያጌጠ ሳህንና ባጠገቡ የተቀመጠው የቡና ዕቃዎችን የያዘ ሰርቪስ… ሁሉም ውበት ናቸው ። ከነዚህ አጠገብ የመጥሪያ ደወል ይታያል ። ይህም ደወል ከንጹህ ብር የተሠራ ነው::

ማሪዮን ሂልያርድ ብቻዋን ተቀምጣለች ። ሲጋራዋን ለኩሳ ጭሱን ስባ ወደ ውጭ ካስወጣች በኋላ በረጅሙ ተነፈሰች ። በጣም እንደደከማት ይታወቅባታል ። እሁድ ቢባል ሁል ጊዜም ቢሆን ለሷ አድካሚ ቀን ነው ። አንዳንድ ገዜ ከሥራ ቀኖች ይልቅ እሁድ ሥራ ይበዛብኛል ብላ ታስባለች ። እውነት ነው። እሁድ ለሷ ሥራ የበዛበት አድካሚ ቀን ነው። ለሚደርሷቸ ደብዳቤዎች መልስ መስጠት አለባት ። የቤተሰቡን አስተዳደር የምትከታተለውም እራሷ ናት ። ለቅመም ስንት ወጣ? ምን ያህል ሥጋ ተገዛ? የቤት መወልወያ ሰም… ወዘተ… ሁሉን መቆጣጠር አለባት ። ይህን ደግሞ በሌላ ቀን ልታከናውነው አትችልም ። ማሪዮን የኮተር ሂልያርድ ሥራ አስኪያጅ ናት ። ኮተር ሂልያርድ ዶግሞ ከአንድ መንግሥት የሚስተካከል ግዙፍ የኤርክቴክቸር ድርጅት ነው ።

የቤቱን አያያዝ እሁድ እሁድ ነው የምትቆጣጠረው ። ሥራው አሰልቺና አድካሚ ነው ። እንኳን ዛሬ ባለቤቷ ሞቶ የሱን ሥራ ደርባ በምትሠራበት ጊዜ ያኔም ሥራዋ ይኸው የቤት አስተዳደር በነበረበት ጊዜም ቢሆን የቤት ለቤት ሥራ ለማሪዮን አሰልቺ ነበረ። ሆኖም ሥራ ሥራ ነው ። ኃላፊነት ኃላፈነት ነው ። ስለዚህም ማሪዮን ሥራዋን ትሰራለች ። ዛሬም ያኔም። ብቻ ያኔ ማሪዮን አንድ ደስታ ነበራት ። ያኔ ማንም ማን ሳይሻማት ማይክልን ታቅፈው ታጫውተው ነበር ። ማንም ማን ሳይሻማት ማይክልን ይዛ ሽርሽር ትሔድ ነበር…
ከማይክል ጋር ታሳልፍ የነበረውን ጊዜ ስታስታውስ ትዝታ ውስጥ ተነክራ ሳታስበው አይኗን እንቅልፍ እንደያዛት አድርጋ ጨፈነች።ያ ደስ የሚል ጊዜ ነበር። እነዚያ እሁዶች ልዩ ነበሩ። ያለፈ ጊዜ ትመልሶ የማይመጣ ። ዛሬም ማይክልን ትወደዋለች ። ዛሬም ሁሉን ነገር የምታስበው ለማይክል ነው ። የወንዱንም የሴቱንም ሥራ አጣምራ የምትስራው፤ከሰኞ እስከ ሰኞ ያለ እረፍት የምትደክመው ለማይክል ነው ። ደግሞም ልፋቷ ከንቱ አይደለም ። ይኸውና ይህን ግዙፍ ድርጅት እንደሰፋ እንደተንሰራፋ እንዲደርሰው አድርጋለች ። ከዚህ የበለጠ ቅርስ ፤ ከዚህ የላቀ ውርስ ከየት ሊመጣ ይችሳል ?

ድንገት ትዝ አላት ፤ በሁለት አመቱ ድክ ድክ ሲል፤ያ ሪጅም ዘመን ። ማይክል ታያት። ሀፃኑ ማይክል! ውስጧ በትዝታው በራ
«እንዴት ውብ ሆነሻል ፤አምረሻል እማዬ!»
" ይህን ድምፅ ስትሰማ በቅጽበት አይኗን ገለጠች ። ስታስበው የነበረው ማይክል ልጅዋን ፤ ባላሰበችው ጊዜ እፊቷ ቆሞ ስታየው እይኗን ማመን አቃታት ። ሆኖም እውነት ነውና ነገሩ አስደነቃት ። ተነስታ ልክ እንደሀፃንነቱ አቅፋ ልትስመው ፈለገች ፤ ግን አስፈላጊ አይደለም ። የዚያ አይነቱ ስሜታዊ ነገር አጉል ልቡን ያለሰልሰዋል ስትል አሰበች ። ስለዚሀም ስሜቷን አምቃ ቀዝቀዝ ባለ አነጋገር…


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍15
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_አንድ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ከአንድ ዓመት በላይ ዐለፈ።

የጀርመን ያባሕር ዳርቻ መዝናኛዎች በመከሩ ወራት ጀመሪ ላይ በሕዝብ
ተጨናንቀዋል " እነዚህ ቦታዎች በዚሀ ወራት በብዛት እየጉረፉ በሚመጡ እንግሊዞች መሞላታቸው የተለመደ ነው ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደገና ወደ አገራቸው ይመለሳሉ " ስታልከንበርግ በተለይ በዚያ ዓመት በእንግዶች ጢም ብላ ተሞልታለች
ከተማይቱ ስሟን ዝናዋን ሌላም የሷ የሆነ ነገር ሁሉ ያገኘችው ከባላባቱ ከባሮን ቮን እስታልከንበርግ ነው ባርኑ ትክለ ቁመናው ግዙፍና ጠንካራ ጢሙና የራስ ጸጉሩ ሽበት የቀላቀለ ከዕድሜውም ገፋ ያለ በሥን ምግባሩ በአደን
ከሚገድላቸው ከርከሮዎች ያልተሻለ ስድ ነበር በግዝፈት ባባታቸው መጠን የወጡ አራት ወንዶች ልጆች ነበሩት » የመጀመሪያ ልጁ አብዛኛውን ጊዜ ትንሹ ባሮን
ሲባል ሶስቱ ግን የስታልከን በርግ ካውንቶች በሚል የማዕረግ ስም ይጠራሉ » ስለዚህ አንዱን ከሌላው መለየት የሚቻለው በክርስትና ስማቸው ነው ሁለቱ ወታደሮች ሆነው ሔደዋል የመጀመሪያውና የመጨረሻው ልጆች ግን ከአባታቸው ጋር እስታልከን በርግ ግምብ ውስጥ ይኖራሉ ይህ የወላለቀ አሮጌ ግምብ የሚገኘው
ከእስታልከንበርግ ከተማ አንድ ማይል ያህል ወጣ ብሎ ነው " ወጣቱ ባሮን ለማግባት ነፃ ነበር » ሦስቱ ግን ራሷንና ባለቤቷን ማስተዳዶር የሚያስችል ሀብት ያላት ሚስት ካላገኙ በቀር ትዳር ለመያዝ አልፈለጉም ።

እስታልከንበርግ መሰሎቿ ከሆኑት ሌሎች የመዝናኛ ሥፍራዎች የምትለይበት የላትም የሚያምሩ ዛፎች ደስ የሚል ጠቅላላ ትዕይንት የዳንስ የሙዚቃ
ትዕይንት በትእዛዝ የሚዘጋጅ ምግብ ሕዝብ የሚራኮትባቸው የቁማር ጠረጴዛዎች የእግር መንሸራሸሪያ ቦታዎችና የመታጠቢያ ጸበሎች አሏት በተለይ ጸበሎቹ በብዛት ከታጠቡባቸው ማንኛውም ዐይነት በሕሊና የታሰበ በአካል የደረሰ በሽታ ሁሉ ማለት ከሚጥል ሕመም እስከ ፍቅር ትኰሳት ድረስ ይፈውሳሉ እየተባለ በሰፊው ይነገርላቸዋል ይታመንባቸዋል " ለብዙዎቹም እንደ እምነታቸው ተሳክቶላቸዋል

ወጣቱ ባሮን ካባቱ ጋር በማስተያየት ወጣት ተባለ እንጂ ዐርባ አንድ ዓመት
ሞልቶታል በመልኩና በአውሬ አዳኝነቱ ስመ ጥር ሰው ነው " በተለይ የከርከሮና የተኩላ ፀር መሆኑ በስፋት ይነገርለታል ከወንድሙ በዐሥራ አንድ ዓመት ያንስ የነበረው ካውንት ኦቶፎን እስታልክንበርግ ሪዙን በማፍተልተል በመብላትና
በመጠጣት ልማድ ካልሆነ በቀር ሌላ የሚታወቅበት ሙያ የለውም ሽማግሌው
ባሮንም ሆነ ወራሹና የመጀመሪያ ልጁ ወጣቱ ባሮን ስለ መዝናናትና ስለ ቅንጦት ተጨንቀው አያውቁም " የእስታልክንበርግ ግንብ ምግብ እምብዛም
እንደነበር ይነገርለታል ስለዚህ ካውንት ኦቶ ጋባዥ ባገኘ ቁጥር ከሆቴሉ እየሔደ ለመመገብ
ዐይኑን አያሽም ካውንት ኦቶ እስቶልከንበርግ ሙሉ ባለቤትና አስተዳዳሪ በመሆኑ በራሱ ከባድ ማዕረግና ባባቱ ሙሉ ባለሥልጣንነት በመጠቀም በየጊዜው እየተጋበዘ ከሆቴሉ ይመጣል ።

በቦታው የሚገኘው የታወቀው ሆቴል ሉድቢግባድ ይባላል " ሚስተር ክሮ ሰቢ የተባለ ሰው ሚስቱንና ተከታይ የሌላት አንዲት ልጁን የሷን አስተማሪና ሁለት ወይም ሦስት የቤት ሠራተኞችን ይዞ ከዚሁ ሆቴል ዐርፋል
ኢንግላንድ ውስጥ የሰራው
ነገር ወይም የደረሰበት በደል አይታወቅም እሱ ግን ወደ ትውልድ አገሩ ሊመለስ ቀርቶ አስቦት አያውቅም » በውጭ አግር ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረ መኖር ከጀመረ ብዙ ዘመን ሆኖታል

ሚስዝ ክሮስቢይ የደስ ደስ ያላት ተጫዋች ሴት ስትሆን ልጂዋ ሑሌና ክሮስቢም
ደስ የምትል ያሥራ ሰባት ዓመት ቆንጆ ናት ልጂቱ በመልኳም በጠባይዋም ሆነ በአካሏ መዳበር የትልቅ ሰው ሁኔታ ስለሚታይባት ላላወቃት ሰው በዕድሜዋም የበሰለች ትመስላለች » ከዚህም በላይ አንድ አጎቷ ሲሞት ባመት ሠላሳ ሺህ ፓውንድ የሚያስገኝ ውርስ ትቶላታል እናቷ ስትሞት ደግሞ የዐሥር ሺህ ፓውንድ
ያመት ገቢ ውርስ ትጠብቃለች » ካውንት
ኦቶ ፎን እስታልከንበርግ ስለ ሠላላ ሺህ ፓውንድ ውርስ ሲሰማ ፊቱን ወደ ሚስ ሔሌና መለሰ "

“ እንዴ ሠላሳ ሺ ፓውንድና ቆንጆ ልጅ ! ታዲያ እኔስ ከዚህ ሌላ ምን ስጠብቅ ኑሬአለሁ ! አለ ለራሱ "

ስለ ሀብቷ የሰማው ወሬ ትክክለኛ መሆኑን አረጋገጠ " ከዚያ ወዲህ ከክሮስቢ
ቤተሰብ ጋር መቃረብ ጀመረ የዘወትር ጠያቂያቸው ሆነ እሱ ከነሱ ባይለይ ደስ እንደሚለው እነሱም የሱን ቀረቤታ ወደዱት ሌሎች የእስታልከንበርግ እንግዶች ቀኑበት እነሱም ያችን መሳይ ቆንጆ ካለችበት ቤተሰብ ጋር መወዳጀትን ተመኙ " ሚስተር ክሮስቢ ግን ወጣቱን ካውንት ልጁና ሚስቱ ባዩት ዐይን አይቶት
እንደሆነ አይታወቅም " በትሕትና ሲቀርበው እሱም በደስታ ይቀበለዋል "

አንድ ቀን ሽማግሌዉ የእስታልንከንበርግ ባሮን በሠረገላ መጣ " መቸም የሠረገላው ቅርጽና የብር ጌጦች ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ታይቶ አይታወቅም " የአያቶቹ ኩራትና ቅርስ ሆኖ በክብር ተቀምጧል ኑሮ ኑሮ አንዳንድ ጊዜ ካልሆነ በቀር
ከተቀመጠበት አይነቃነቅም በብር ያጌጠ አረንጓዴ ልብስ የለበሱ ምርጥ አሽከሮች አጅበውት ከሎድቪግ ባድ ሆቴል በራፍ ተጠግቶ ቆመ የሆቴሉ ኗሪ በየመስኮቱ
ሆኖ ለማየት ግልብጥ ብሎ አሰፈሰፈ " ሽማግሌዉ መኮንን የመጣው ሚስተር ክሮስቢ ዘንድ ስለሆነ እሱም በታላቅ አክብሮት ተቀብሎ ወደ ሳሎን አስገባው “ ኃያሉ ባሮን ከዚያ ወይም ከዚ Oረፍ ይበሉ ! አለው …

“ ኃያሉ ባሮን የመጣው ክሮስቢን ከሚስቱና ከልጁ ጋር ግብዣ ሊጠራው
ነው " በባሮኑ ቤተ ግምብ ከዚያ በፊት ያልታየ ታላቅ ድግስ ካለፈ ጥቂት ቀኖች
ቆይቶ ካውንት ኦቶፎን እስታልከንበርግ ልጂቱን ሔሌናን ለሚስትነት ለመነ "
ጥያቄውም ተቀባይነት አላጣም ።"

“ ገና ልጅ ናትኮ ” አለ ሚስተር ክሮስቢ በቅሬታ ሁለት ዓመት ብቻ ቢጠብቁ ስለ ጥያቄዎቹ ምንም ተቃውሞ አይኖረኝም ነበር

“ እንዴ እንዴ ! ሁለት ዓመት ይጠብቅ ብለን ሌሎች ይውሰዱብን ብለህ ነው
አይሆንም ተው እነዚህ የእስታልከንበርግ ካውንቶች እኮ አይታመኑም ” አለችው ሚስቱ።

ታድያ ቢሆንሳ ! እሱ በማዕረጉና በሐረጉ ቢመካ ሔሌና ደግሞ በገንዘቧ ትመካለች።

እንግዲያ በደንብ ተመጣጥነዋል ማለት ነው " እኔ ደግሞ እሱን አላሰብኩትም ካውንቴስ ፎን እስታልከንበርግ ሲል ብቻ ለጆሮ ደስ ሲል አዳምጠውማ !

“ ያን ቀፋፊ ሪዙን ወዲያ ቢጥለው ደስ ባለኝ ” አለ ሚስተር ክሮስቢ "

“አንተ ደሞ የማያሳስበው ጥቃቅኑ ነገር ሁሉ ያሳስብሀል ሔሌና እንደ
ሆነች በጣም ወዳለታለች » አሁን የቸገረን ያስተማሪዋ ነገር ነው።

"የሷ ደግሞ ምንድነው ችግሯ ?

እኔ የቀጠርኳት እስከ ገና ስለሆነ ሌላ ስራ ካላገኘሁላት እስከዚያ ድራስ
ደሞዝ መክፈል ሊኖርብኝ ነው "

“እንደ እኔስ ሄሊና አሁን ከምታገባ ከአስተማሪዋ ጋር ብትቆይ ይሻል ነበር"
ሴቶች ልጆች በትንሽነታቸው ሲያገቡ ደስ አይለኝም " አሁን እዚህ ያሉ እንግሊዞች
ምን እንደሚሉ አላውቅም ።

አንተ ካልተናገርክ በቀር ስለ ዕድሜዋ ማንም አያውቅም ዛሬ እሷ ለራሷ ሙሉ ሴት እንጂ ልጅ አትመስልም እንግሊዞችማ እንደዚያ ያለ ዕድል ለነሱ ስላልገጠማቸው በቅናት ከመብሰልሰል በቀር ሌላ ምን ሊሉ ኖረዋል?

ሚስተር ክሮስቢ ተቃውሞው ሁሉ እየከሸፈ ሲያስቸግረው ዝም አለ "
በዚህ መነታረኩ ዋጋ እንደሌለው ዐወቀው "

ሔሌና ክሮስቢ ደሞ በበኩሏ ወደ አስተማሪዋ እየሮጠች ሒዳ ! ማዳም ማዳም ባል ላገባ እኮ ነው ! " አለቻት "

ማዳም ጥውልግ ያለውን ፊቷን ቀና አድርጋ አየቻትና እውነት !” አለቻት
👍152
“ ትምህርቴንም ከዛሬ ጀምሮ ይበቃሻል ብላኛለች እናቴ "

“ ግን ለማግባት ገና ልጅ ነሽ ኮ ሔሌና አለቻት አስተማሪቱ ።

“አንቺም አባባን ይመስል እንዲህ አትበይ «እሱም እየደጋግመ እንደዚህ
ይለኛል "

ካውንት ኦቶን ነው?” አለቻት አስተማሪቱ ምንም እንኳን ሔሌና 'ማዳም ” እያለች ብትጠራትም ሴትየዋ የጠራ የእንግሊዝኛ ድምፅ አወራረድ እንዳላት በግልጽ ይታወቅ ነበር ።
አዎን ካውንት ኦቶን እንጂ ሌላ ላገባ ኖሯል!”

አስተማሪዩቱ ሌላ ሳትሆን ወይዘሮ ሳቤላ ቬን ናት " አይሆኑ ሁና ልውጥውጥ
ብላለች " ብዙ የለዋወጣት የባቡር አደጋ ሲሆን ከሱ የተረፈውን ኀዘንና ጸጸት አስተካክሎታል " ስትራመድ ትንሽ ታነክሳለች « ከትከሻዋ ስግደድ ማለቷም ከቁመቷ ቀንሶባታል " ከላይ አገጯ ጀምሮ የተዘረጋው ጠባሳዋ በታች በኩል የፊቷን ፈጽሞ ሌላ አስመስሏታል "
ጥርሶቿም ጥቂቸቹ ስለ ወለቁ ስትናገር ተኮላተፋለች
የሸበተው ጸጉሯን ጥቅልል አድርጋ ጥብቅ ቆብ ደፍታበታለች እሷም ራሷ የመታወቅ ሥጋትን ለማጥፋት መነጽር ሰክታ አንድ ሰፊ አረንጓዴ ሻሽ እስከ ቅንድቧ ዝቅ አድርጋ ጠምጥማለች " ይኸም መልካም ቅርጿንና መልኳን ለማጥፋት ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል " ወፍራም ዐይነ ርግብ ሳታደርግ ከቤት አትወጣም ሚስዝ ዱሲ እና ሴቶች ልጆቿ እስታልከንበር ውስጥ ሲሰነብቱ በጭራሽ አላወቋትም " ስለዚህ እንጻትታመቅ የነበራት ሥጋት መወገዱን ተገነዘበች በመልከ መልካሟ ወይዘሮ በዱሮይቱ ሳቤላ ቬንና በዛሬይቱ ማዳም ቬን መካከል ምንም ግንኙነት አይታይም " ሚስተር ካርላይል ራሱ እንኳን ቢያያት ሊያውቃት አይችልም " ይሁንና
ይህ ሁሉ ለውጥ ቢደርስባትም መልኳ አሁንም ይስባል እርጋታዋና የደስ ደስ ያለው ግጽታዋም አልጠፋም ሰዎች ያን በመሰለ የወጣት መልክ የሽበት ጸጉር ማየታቸው ይገረሙ ነበር።

በባቡሩ አደጋ ከደረሰባት ጕዳት ካገገመች በኋላ በዚያ አካባቢ ወደ ነበረ አንድ ከተማ ሔደች የክሮስቢ ቤተሰቦች እዚያ ከተማ ውስጥ ይቀመጡ ስለ ነበር የሔለና ተመላላሽ አስተማሪ አድርገው ቀጥረዋት ከነሱ ጋር ሁለት ዓመት ያህል ተቀመጠች።

ለክሮስቢ ቤተስቦች እንግሊዛዊት መሆኗን ፈረንሳዊ ባሏ እንደ ሞተባት ነገረቻቸው ስለ ራሷ የበለጠ እንድታብራራ ብትጠየቅም ብዙ ልትነግራቸው አልፈቀደችም
ሔሌናን እየተመላለሰች ስታስተምር ከፍተኛ ግምት
አሳደረችባቸው ተመላላሽነቷ ቀርቶ ከቤት ጠቅልላ እንድትባ አደረጉ " ስዎቹ እንግሊዞች ወደሚያዘወትሩት የባሕር ዳርቻ መናፈሻ እንደሚሔዱ ብትጠረጥር ኖሮ ቅጥሩንም ለመቀበል ታመነታ ነበር ኋላ ግን ጠቀማት ሚስዝ ዱሲ ሳቤላን እስታል ከንበርግ ላይ ስታገኛት አላወቀቻትም " በዚህ ጊዜ ማንም ድሮ የሚያውቃት ሰው ቢያያት እንደማይለያት ተማመነች"ብዙ መለወጧን አረጋገጠች ተንግዲህ ያለ ምንም ሥጋት የትም መሄድ እንደምትችል ተረዳች።

አሁን አንጀት አንጀቷን እየበላት የመንፈስ ዕረፍት ያስጨነቃት የልጆቿ ናፍቆት ሆነ " እስኪ አንዲት እናት ማንም ትሁን ምን ለትንሽ ጊዜ ከልጆቿ ተለይታ ትዋል ትደርና ናፍቆቱ እንዴት እንደሚያደርጋት እሷው ትናገር የመዝናናት ጉዞ ለማድረግ በመሔድ ለጥቂት ሳምንቶች ብትለያቸው እንኳን
ትንንሽ ፊታቸውን ማየቱ የሚንተባተቡት ምላሶቻቸውን መስማቱ ለስላሳ ጉንጮቻቸውን መሳሙ ! ሌላው ቀርቶ እማማ ደኅና ነሽ ወይ የሚለውን መልእክታቸውን መቀበሎ ምን ያህል
እንደሚያስጨንቅ : ከሁሉ
የበለጠ የሚሰማት ፡ እሷ ናት " ልጆቿን የማየት ፍላጐቷ ከቁጥጥሯ ውጭ ይሆንባታል እነሱ ወዳሉበት በረሽ ሒጂ የሚል ይመጣባታል " የመለየቷ ጊዜ በረዘመ ቁጥር የናፍቆቷ ብሶት ይጠናባታል ታዲያ የዚህ ዐይነቱን ናፍቆት ለብዙ ዓመት በወላድ አንጀቷ እያጠራቀመች ችላው ለኖረችው ለሳቤላ ቬን ምን ያህል ይከብዳት ልጇቿን ስፍስፍ ብላ ትወዳቸው ነበር " ስለ ደኅንነታቸ ስለ አስተዳደጋቸው ከልክ
ያለፈ ትጠበብላቸው ነበር ዛሬ እንዲህ ችላው ልትኖር!ልጆን ከባዕድ እጅ ለመጣል ! ባዕድ ሰው ሥነ ሥርዓት እንዲያስተምራቸው ሐሳብ አልነበራትም "
ይኸን ሁሉ ቁጭ ብላ ታስበውና እጆቿን ዐይኖቿ ላይ ዘርግታ ታቃስታለች "...

ናፍቆቷ እያደር እየጠናባት ሔዶ ትኩሳት ሆነባት አእምሮዋንና ሰውነቷን
ባንድ ጊዜ አጣምሮ የሚለክፍ ትኩሳት የገረጡት ከንፈሮቿ በየጊዜው እየደረቁ
የገዛ ጭንቀቷ በፈጠረው እሳት እየተጠበሱ ከስውነት ወጣች ከሦስት ዓመት
በፊት ሎርድ ማውንት እስቨርን ግሮኖብል ላይ ከጠየቃት ወዲህ ከኤስትሊን ምንም
ነገር ሰምታ አታውቅም " ልጆቿን ለአንድ ቀን ቀርቶ ለአንድ ስዓት እንኳን ቢሆን
አይናቸውን አይታ ከንፈሮቻቸውን ስማ እፎይ ብትል በጣም ትመኝ ነበር "
አሁንም ቢሆን ይህን ካላደረገች ለመኖር የምትችል አልመስላት አለ።

በመጨረሻ እንዲህ ሆነ " ሚስዢ ላቲመር የምትባል የዌስትሊን ነዋሪ የሆነች
ወይዘሮ እንደ ገረድና አነጋጋሪም እንድትሆናት አፊ ሆሊጆንን አስከትላ ወደ
እስታልክንበርግ መጣች አፊ ከመቤቲቱ ጋር አብራ ትቀመጣለች ወይም ትበላለች ማለት ሳይሆን ከብዙ እመቤቶች ደንገጡሮች የተሻለ የመቅረብ ዕድል ነበራት እሷ ደግሞ ይህንን ጫፍ በመያዝ ጓደኛዋ እንደ ሆነች አድርጋ ታወራ ነበር » ሚስዝ ላቲመር ደግ ሰው ነበረች አፊም አባቷ በተገደለበት ጊዜ በነበረው
ሁኔታ የራሷን ታሪክ እያሠማመረች ለመቤቲቱ ታጫውታት ስለ ነበር በጣም ወደደቻት የሚስዝ ላቲመር ክፍል ከሚስዝ ክሮስቢ ቀጥሎ ስለ ነበር ' ሁለቱ ሴቶች ከመተዋወቅ ዐልፈው ባልንጀሮች ሆኑ " የመጀመሪያዋ ሎድዊግ ከገባች ሳምንት ሳይሆናት ምናልባት ሁለቱም ከሌሎች ጋር ብዙ ጊዜ እንዳደረጉት
ለዘለዓለም እትማማችነት ቃል ተጋቡ ".....

💫ይቀጥላል💫
👍83
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


የደማውን እጇን በውሃ አጣጥባ በፎጣ አድርቃ በፋሻ አሰረችው:፡
ለምንድነው የፈራሁት? ስትል ራሷን ጠየቀች አይገድለኝ፤ ሊከለክለኝም
አይችልም፤ እድሜዬ ከ21 አመት በላይ ነው! ይህም አገር ነፃ አገር ነው! በማለት ራሷን ለማሳመን ሞከረች፡፡

ይህም ሆኖ ግን ልትረጋጋ አልቻለችም፡

ጠረጴዛው ላይ የገበታ እቃዎች ደረደረችና ሰላጣ አጠበች፡፡ መርቪን ስራ ወዳድ ቢሆንም እቤቱ የሚመጣው በሰዓቱ ነው፡፡ በሙያው ኢንጂነር ሲሆን ከአይሮፕላን ሞተር መዘውሮች ጀምሮ እስከ ማቀዝቀዣ ሲስተሞችና የመርከብ መፍቻዎች ድረስ ያሉትን ዕቃዎች የሚያመርት ፋብሪካ ባለቤትና ጥሩ የቢዝነስ ሰው ነው፡፡ መርቪን የአይሮፕላን ሞተሮች መስራት ከጀመረ
ጀምሮ ነው ገንዘብ በሻንጣ መቁጠር የጀመረው፡፡ የመዝናኛ አይሮፕላን ማብረር የጊዜ ማሳለፊያው ሲሆን ለዚህም ሲል ትንሽ አይሮፕላን ገዝቷል።
መንግስት አየር ኃይል ሲያቋቁም የአይሮፕላን ሞተር መስራት ከሚችሉት ጥቂት ሰዎች ውስጥ መርቪን አንዱ ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህማ መርቪን ያለ
እረፍት ይሰራል፡፡

ዳያና ሁለተኛ ሚስቱ ስትሆን የመጀመሪያ ሚስቱ ሁለቱን ልጆቹን ይዛ ሌላ ሰው አግብታ ከሄደች ሰባት ዓመት ሆኗታል፡ መርቪንም ፊርማውን ቶሎ ቀደደና ዳያናን ላግባሽ ብሎ ጠየቃት፡፡ መርቪን ፈርጠም ያለና ኪሱ ረብጣ ገንዘብ ያለው ከመሆኑም በላይ ዳያናን ከማፍቀርም አልፎ ያመልካት
ነበር ማለት ይቻላል፡፡ የጋብቻ ስጦታ ብሎ ያበረከተላት የአልማዝ ሀብል ነበር፡፡

የአምስት ዓመት የጋብቻ በዓላቸውን ሲያከብሩ ግን ስጦታ ብሎ
ያበረከተላት የልብስ ስፌት መኪና ነው፡፡ የስፌት መኪናውን ሲሰጣት ትዳሯ እንዳበቃለት ተገነዘበች፡፡ መኪና መንዳት ስለምትችል የራሷ መኪና እንዲኖራት ትመኝ ነበር፤ መርቪን ደግሞ የመግዛት አቅም አለው፡፡ አምስት ዓመት ሙሉ አብረው ሲኖሩ ልብስ ሰፍታ እንደማታውቅ እንኳን
አልተገነዘበም፡፡

ባሏ እንደሚወዳት ብታውቅም እሱ ግን ከሚስትነቷ ውጭ ትኩረት
አይሰጣትም፡፡ እቤት ውስጥ ሚስት የምትባል ሴት እንዳለች፣ ቆንጆ
እንደሆነች፣ በሴትነቷ የሚጠበቅባትን ማህበራዊ ህይወት የማታጓድል፣ምግቡን ሰራርታ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ የምትጠብቅ፣ አልጋም ላይ ፈቃደኛ
የሆነች ሴት አለችው ታዲያ ሚስት ከዚህ በላይ ምን ይጠበቅባታል በእሱ አስተሳሰብ፡፡ ስለምንም ነገር አማክሯት አያውቅም እሷ የቢዝነስ ሰው ወይም ኢንጂነር ባለመሆኗ በሱ ቤት አንጎል የላትም፡፡ ከሷ ይልቅ ፋብሪካው ውስጥ ካሉት ሰዎች ጋር ብዙ ጠቃሚ ሃሳቦችን ይለዋወጣል፡ በሱ አመለካከት መኪና ለወንዶች፣ የስፌት መኪና ደግሞ ለሴቶች ነው፡፡

መርቪን ከልጅነቱም ጮሌ ነበር፡ አባቱ የማሽን ኦፕሬተር ነበሩ¨
መርቪን በማንቼስተር ዩኒቨርስቲ ፊዚክስ ያጠና ሲሆን ለማስተርስ ዲግሪው እንዲያጠና በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ዕድል ቢያገኝም እሱ ግን የትምህርት ሳይሆን የተግባር ሰው በመሆኑ በአንድ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ውስጥ የዲዛይን መምሪያ ውስጥ ተቀጠረ፡፡ በዓለም ላይ በፊዚክስ መስክ የሚደረጉትን
ግስጋሴዎች የሚከታተል ሲሆን ከአባቱ ጋርም ስለነዚህ ነገሮች ይወያይ ነበር፡ ከዳያና ጋር ግን እንደዚህ አይነት ነገር መነጋገር ሲያልፍም አይነካካውም::

እንደ ዕድል ሆኖ ዳያና ፊዚክስ ባለበት ድርሽ ብላ አታውቅም፡፡
አይገባትም፡፡ እሷን የሚጥማት ሙዚቃ፣ ስነጽሑፍ ከፍ ካለም ታሪክ ብቻ ነው:፡ መርቪን ደግሞ ከፊልምና ከዳንስ በስተቀር ሌላው አይጥመውም፡፡ስለዚህ እነሱን የሚያነጋግር ነገር የለም ማለት ነው:

ልጅ ቢኖራቸው ኖሮ ነገሮች ይለዋወጡ ነበር፡፡ መርቪን ከመጀመሪያ ሚስቱ ሁለት ልጅ ስለወለደ ሌላ ልጅ አይፈልግም፡፡ ዕድሉን ቢሰጣት ልጆቹን ማቅረብ ትፈልግ ነበር፤ በየት በኩል? የልጆቹ እናት ከአባታቸው ጋር የነበራት ጋብቻ ያፈረሰው በዳያና ምክንያት መሆኑን በመናገር የልጆቹን
አዕምሮ ስለመረዘች ደመኛ አድርገዋታል፡፡ ታዲያ የእናትነት ፍላጎቷን የምትወጣው ሊቨርፑል ውስጥ በምትኖረው እህቷ መንታ ልጆች ነው፡፡

ክፋቱ አሜሪካ ከሄደች ልጆቹ እንደሚናፍቋት ጥርጥር የለውም፡፡

መርቪን ከከተማው ነጋዴዎችና ባለስልጣናት ጋር ስለመሰረተ በፊት በፊት እቤት በጋበዛቸው ቁጥር እነሱን ማስተናገድ
ያስደስታታል፡ ለጥሩ ልብስ ያላት ፍቅር ከፍተኛ ሲሆን ልብስም
ያምርባታል፡ ነገር ግን ህይወት ማለት ከመልበስም በላይ መሆኑን
ትረዳለች፡

የሚያውቋት ሴቶች መጠጥ የማያበዛ፣ ታማኝ፣ ደግ ባልና ጥሩ
መኖሪያ ቤት ስላላት ዕድለኛ ናት ብለው ያምናሉ፡ ሆኖም እሷ ደስተኛ
አይደለችም፡፡ የማታ የማታ ግን ማርክ የተዘጋ ልቧን ከፈተው፡፡
የመርቪን መኪና ግቢ ሲገባ ሰማች፡፡ የመኪናው ድምጽ የለመደችው ቢሆንም ዛሬ ግን የአውሬ ድምጽ መሰላት፡፡

መጥበሻውን ምድጃው ላይ ስትጥድ እጇ ተንቀጠቀጠ፡፡ መርቪን ወደ ማድ ቤት ገባ፡ ባሏ ነፍስ የሚያስት ቁመና ያለው ሲሆን በጥቁር ፀጉሩ ላይ ጣል ጣል ያደረገበት ሽበቱ የተለየ ግርማ ሞገስ ሰጥቶታል፡፡ ቁመቱ ሎጋ
ሲሆን እንደ ጓደኞቹ ቀፈታም አይደለም፡፡ ኩራተኛም ባይሆን ዳያና በጥሩ ልብስ ሰፊ የተሰፋ ሱፍ ልብስና ውድ ሸሚዞች እንዲለብስ አድርጋዋለች፡፡

ዳያና መጨነቋን ከፊቷ ላይ አንብቦ ምንድን ነው ነገሩ ብሎ
ይጠይቀኛል ብላ ሰግታለች።

መጥቶ ከንፈሯን ሲስማት ሀፍረቷን ውጣ እሷም ሳመችው፡፡ አንዳንድ
ጊዜ እቅፍ አድርጎ በእጁ የቂጧን ፍንካች ሲደባብስ ይሟሟቁና ወደ መኝታ ቤት ሲሮጡ ምድጃው ላይ ያለው ምግብ አርሮ ይጠብቃቸዋል አሁን አሁን ግን እንዲህ አይነት ነገር እምብዛም አያደርጉም፡፡ ዛሬም ከወትሮው የተለየ አይደለም፡፡ እንደ ነገሩ ሳም አደረጋትና ዞር አለ፡፡
ኮቱን፣ ሰደርያውንና ክራቫቱን አውልቆ የሸሚዙን እጀታ ጠቀለለና ፊት መታጠቢያው ላይ ፊቱንና እጁን ታጠበ፡፡ የትከሻው መስፋትና የክንዱ መፈርጠም ለጉድ ነው፡
አሁን አልነግረውም አለች በልቧ፡
ጋዜጣ እያነበበ ስለሆነ ከቁብም አልቆጠራት፡፡

ድንቹ ምድጃው ላይ ሲንጨረጨር ሻይ ጥዳ ዳቦውን ማርጋሪን ቀባች:
የእጇን መንቀጥቀጥ ባሏ እንዳያውቅባት ለመደበቅ እየሞከረች ነው መርቪን
‹‹ስራ ቦታ ውስጥ አንድ በጥባጭ ሲበጠብጠኝ ዋለ›› አላት ሰሃኑን ፊቱ ስታስቀምጥ።

‹እኔ ምን ቸገረኝ ታዲያ አለች በሆዷ እኔ እንደሆነ ከዚህ በኋላ
በቅተኸኛል፡፡› ለምን ሻይህን አፈላውልህ?›

‹‹ደሞዝ እንድጨምርለት ጠየቀኝ፣ እኔ ደግሞ ለመጨመር ዝግጁ
አይደለሁም›› አላት፡፡

ዳያና ፍርሃቷን ዋጥ አድርጋ ‹‹አንድ የምነግርህ ነገር አለ›› አለች:
የተናገረችውን ነገር መልሳ ብትውጥ ወደደች፤ ግን አንዴ አምልጧታል፡

‹‹ጣትሽ ምን ሆነ?›› ሲል ጠየቃት በፋሻ የታሰረውን ጣቷን አይቶ፡

ይህ ጥያቄ ትንሽ ከጭንቀቷ መለስ አደረጋት ‹‹ምንም›› አለች ወንበሩ
ላይ ዘፍ እያለች ‹‹ድንች ስቆርጥ ቢላ ቆረጠኝ›› ብላ ሹካና ማንኪያዋን አነሳች፡:

መርቪን ምግቡን ስልቅጥ አድርጎ በላና ‹‹ከዚህ በኋላ ሰው ስቀጥር
መጠንቀቅ አለብኝ: ችግሩ ጥሩ ባለሙያዎችን ማግኘት በአሁን ጊዜ
አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱ ነው፡››

ስለ ስራው ሲናገር አስተያየት እንድትሰጥ አትጠበቅም፡፡ ሀሳብ የሰጠች እንደሆን ይገላምጣታል፡፡ እሷ እንደሆን ለእሱ ለማዳመጥ ብቻ የተፈጠረች ፍጡር ናት፡፡
👍23🥰1👏1
እሱ ስለአዲሱ ሰራተኛ ሲያነበንብ እሷ የሰርጓ ቀን በሃሳቧ መጣባት።
የተጋቡት ማንቺስተር ውስጥ ሲሆን በሚድላንድ ሆቴል ድል ያለ ድግስ
ተደግሶ ነበር፡ መርቪን የሙሽራ ልብሱን ለብሶ በመላው ኢንግላንድ ካሉ ወንዶች ሁሉ አይን የሚማርክ ሆኖ ነበር የዋለው፡ ዳያና በዛን ጊዜ እንዲህ እንደሆነ ይቀጥላል ብላ ገምታ ነበር፡፡ ጋብቻቸው እንዲህ ባጭሩ ይቀጫል ብላ አስባም አታውቅም፡፡ ይህ ሁሉ በሃሳቧ መጥቶ አልቅሽ አልቅሽ አላት።

መርቪን ጥላው ስትሄድ አእምሮው እንደሚበጠበጥ ታውቋታል”
በአዕምሮዋ ምን እንደሚመላለስ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ የመጀመሪያ ሚስቱ በዚህ ሁኔታ ጥላው ስለሄደች በዳያና መሄድ ኑሮው ምስቅልቅሉ መውጣቱ አይቀርም፡፡

የሥጋ ጥብሱን በቢላ እየቆረጠ በሹካ እየወጋ ከበላ በኋላ ሻይ ደገመ፡፡

‹‹ብዙም አልበላሽ›› አላት፡፡ እውነትም እራቷን አልነካችውም፡:
‹‹ምሳዬን ጥርቅም አድርጌ ስለበላሁ አልራበኝም›› አለች
‹‹የት ሄደሽ ነበር?››

እንደ ቀልድ የጣለው ጥያቄ አስበረገጋት፡፡ ከማርክ ጋር አልጋ ላይ ሆነው ሳንድዊች በልተዋል፡፡ ሊታመን የሚችል ውሸት ብታስብ አልመጣላት አላት፡ ማንቺስተር ውስጥ ያሉት ጥሩ ጥሩ ምግብ ቤቶች በአዕምሮዋ መጡ፤ ነገር ግን አንዳቸውጋ መርቪን ምሳ መብላቱ አይቀርም፡፡ ትንሽ
አስጨናቂ ደቂቃዎች ቆየችና ‹‹ዋልዶርፍ ካፌ›› አለች፡፡ በርካሽ ዋጋ ስጋና ድንች ጥብስ የሚሸጡ ዋልዶርፍ ካፌዎች በከተማዋ ውስጥ እዚህም እዚያም
አሉ፡፡ መርቪን ግን የትኛውጋ እንደበላች አልጠየቃትም፡:

ሰሃኑን ሰብስባ ብድግ ስትል ጉልበቷ ሲብረከረክባት የምትወድቅ መሰላት፡ ሰሃን ማጠቢያው ድረስ እንደ ምንም ሄደችና ‹‹ጣፋጭ ትፈልጋለህ?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎን›› አላት

ወተትና ኬክ አመጣችለት፡ ልትነግረው ትልና ልቧ በፍርሃት ይርዳል፡፡
በኋላ ግን ልትነግረው አቅም ማጣቷ ታወቃት፡፡

መርቪን ማንኪያውን ስኒ ማስቀመጫው ላይ አኖረና ሰዓቱን
ተመለከተ፡ ‹‹አንድ ሰዓት ተኩል ሆኗል፡ እስቲ ሬዲዮ ክፈቺና ዜና
እንስማ›› አላት፡

‹‹አልችልም›› አለች ከሃሳቧ ጋር እየተሟገተች፡፡

‹‹ምን አልሽ?››

‹‹አልችልም›› አለች ሳይታወቃት እንደገና ውጥኗን ልትሰርዘው ነው፡፡
ማርክጋ ሄዳ ሃሳቧን የለወጠች መሆኑን ልትነግረው ነው
እንደማትሄድ ልታረዳው፡፡

ዳያና ባሏ ላይ አፈጠጠችበት፡፡ እውነቱን ፍርጥ ልታደርግለት ዳዳት
ነገር ግን ወኔ አጥታለች፡፡

‹‹መሄድ አለብኝ›› አለችው አንድ የሆነ ማስመሰያ ነገር ወዲያው
አውጠንጥና ‹‹ዶሪስ ዊልያምስ ታማ ሆስፒታል ተኝታለች፤ ሄጄ ልጠይቃት ነው››
‹‹ማናት ዶሪስ ዊልያምስ ለመሆኑ?››

እንደዚህ አይነት ሰው የለም፡፡
‹‹ከዚህ በፊት እኮ ታውቃታለህ, አለች ዳያና አፏ እንዳመጣላት፧
‹‹ኦፕሬሽን ተደርጋለች››

‹‹አላስታውሳትም›› አለ፡፡ ይህን ሲል ግን የጠረጠረው ነገር የለም፡፡
ለነገሩ ብዙም የማያውቀውን ሰው የሚያስታውስ አዕምሮ የለውም፡፡

ዳያናም በድፍረት ‹‹ታደርሰኛለህ?›› ብላ ጠየቀችው:

‹‹ኧረ እኔ አልሄድም›› አላት፡፡

‹‹እንግዲያው ራሴ በመኪና እሄዳለሁ›› አለች፡

‹‹በጨለማ በፍጥነት አትንጂ፡፡›› ከመቀመጫው ተነሳና ሬዲዮ ሊከፍት ሄደ።

ዳያና ከኋላው ባሏን እያየችው ትቼው መሄዴን መቼም ቢሆን
አያውቅም› ስትል በሀዘኔታ አሰበች፡፡

ኮፍያዋን ራሷ ላይ ደፋችና ኮቷን ክንዷ ላይ አድርጋ ወጣች፡ እግዜር
ይስጠውና የመኪናው ሞተር ባንዴ ተረክ ብሎ ተነሳ፡፡ መኪናዋን እየነዳች ከግቢ ወጣችና የማንቺስተርን አቅጣጫ ይዛ ተፈተለከችበጣም ብትቸኩልም የመኪናዋ የፊት መብራት በጦርነቱ ምክንያት ብርሃኑ እንዲቀንስ በመጋረዱ በደንብ ስለማይታያት የኤሊ ጉዞ ለመጓዝ ተገደደች፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እምባዋ እየተንዠቀዠቀ በመሆኑ በከፊል
እይታዋን ጋርዶባታል፡ መንገዱን ባታውቀው ኖሮ መጋጨቷ የማይቀር ነበር፡፡

ከቤቷ እስከምትሄድበት ቦታ ድረስ አስር ኪ.ሜ ያህል ቢሆንም ጉዞው
አንድ ሰዓት ያህል ፈጀባት፡፡
ሚድላንድ ሆቴል ደርሳ ስታቆም ሙሉ በሙሉ ሰውነቷ ዝሎ ነበር፡
ራሷን ለማረጋጋት አንድ ደቂቃ ያህል ቆየችና አልቅሳ የነበረች መሆኗ
እንዳይታወቅባት ፊቷን በፓውደር ደባበሰች።

ማርክ አብራው እንደማትጠፋ ስትነግረው ልቡ እንደሚሰበር ጥርጥር ባይኖርም መቻል አለበት፡፡ የአምስት አመት ጋብቻ ከሚፈርስ መቼም የሚጥም አጭር የፍቅር አለም ቢቋረጥ ይሻላል፡ መቼም የተዋወቁባትን ዓመት ባስታወሱ ቁጥር እሷና ማርክ ከንፈራቸውን መምጠጣቸው አይቀርም፡፡

እንደገና ለቅሶዋን ለቀቀችው:

እዚህ ቁጭ ብሎ ማሰቡ ዋጋ የለውም፤ ቀጥታ ማርክ ያለበት ሆቴል ሄዳ ሁሉም ነገር እንዳበቃለት ትነግረዋለች ፊቷን በሜካፕ አሰማመረችና ከመኪናዋ ወጣች፡፡

የሆቴሉን መተላለፊያ አቋርጣ በቀጥታ ወደ ማርክ ክፍል አመራች፡
የማርክን አልቤርጎ ቁጥር ታውቃለች፡፡ ምንም እንኳን ሴት ልጅ ወንድ ልጅ አልቤርጎ ብቻዋን መሄዷ አሳፋሪ ቢሆንም አይኗን በጨው አጥባ ለመሄድ ወስናለች፡፡ ሌላው አማራጭ ማርክን የሆቴሉ እንግዳ መቀበያ ጋ ወይም ቡና ቤቱ ውስጥ ጠርታ መንገር ነው፡፡ ነገር ግን እንዲህ ያለውን ዱብ ዕዳ ሰው
ፊት ልትነግረው አልፈለገችም፡፡ አካባቢውን ዞራ ባለማየቷ ሰው ይያት አይያት የምታውቀው ነገር የለም፡፡
በሩን ቆረቆረች፡፡ ክፍሉ ውስጥ ባላጣው› ስትል ተመኘች፡፡ ምግብ
ለመብላት ወይም ሲኒማ ለመግባት
ሄዶ ከሆነስ? መልስ ስታጣ እንደገና
በደንብ አንኳኳች፡ እንዴት በዚህ ጊዜ ይሄዳል?

ከአፍታ በኋላ ‹‹ማነው?›› የሚል ድምፅ ሰማች፡፡

‹‹እኔ ነኝ!›› አለች፡፡

ፈጠን ያለ የኮቴ ድምፅ ሰማች፡፡ በሩ ወለል ብሎ ተከፈተና ማርክ
በግርታ አያት፡፡ ከዚያም ፊቱ በደስታ እያበራ ወደ ውስጥ ጎትቶ በሩን ዘጋና እቅፉ ውስጥ ጣላት፡፡

ወዲያው መርቪን ላይ የፈፀመችው የክህደት ዓይነት ስሜት በማርክ
ላይ መፈጸሟ ተሰማት፡፡ በፀፀት ከንፈሩን ስትጨመጭመው የደስታ ሙቀት በደም ስሯ ሲሰራጭ ተሰማት፡፡ ብዙም ሳይቆይ ግን ‹‹ካንተ ጋር አልሄድም›› አለችው፡፡

ማርክ ፊቱ በድንጋጤ አመድ መሰለ፡፡ ‹‹ተይ እንጂ እንዲህ አትበይ›› ክፍሉን እየተዘዋወረች ስትቃኝ ዕቃ እየሸካከፈ መሆኑን አወቀች፡፡ ቁም ሳጥኑና መሳቢያዎቹ በሙሉ ተከፋፍተዋል፡፡ የተከፈቱ ሻንጣዎች ወለሉ ላይ
ይታያሉ፡፡ የታጠፉ ሸሚዞች፣ የውስጥ ሱሪዎችና ካናቴራዎች እንዲሁም ጫማዎች በየቦርሳው ውስጥ ተሸጉጠዋል፡፡ መቼም ጽዳቱን ሲጠብቅ ለጉድ ነው፡፡

‹‹አብሬህ አልሄድም›› አለችው፡፡
እጇን ሳብ አደረገና ወደ መኝታ ክፍሉ ይዟት ገባ፡፡ አልጋው ላይ
አስቀመጣትና ‹‹ከልብሽ ነው?›› ሲል ጠየቃት እየተርበተበተ፡፡

‹‹መርቪን ይወደኛል፡፡ የአምስት ዓመት ባሌ ስለሆነ እንዲህ ያለ ግፍ
በሱ ላይ መፈጸም የለብኝም››

‹‹እኔስ?›› ሲል ጠየቃት

ዳያና ከላይ እስከታች አለባበሱን ስታይ ማርክ አምሮበታል፡፡ ልብ
ይሰርቃል፡፡ ‹‹ሁለታችሁም እንደምትወዱኝ አውቃለሁ›› አለች ‹‹እሱ ግን ባሌ ነው፡፡››
‹‹እሱ ይወድሻል፡፡ እኔ ግን አፈቅርሻለሁ›› አላት ማርክ፡፡
‹‹እሱስ የማያፈቅረኝ ይመስልሃል?››

‹‹ከነመኖርሽ ረስቶሻል፤ አድምጪኝ!
ዕድሜዬ ሰላሳ አምስት ቢሆንም
ካንቺ በፊት ፍቅር አውቃለሁ፡ አንድ ወቅት ላይ እንደውም ስድስት ዓመት የዘለቀ ፍቅር አሳልፌያለሁ፡ ከዚህ በፊት ትዳር መስርቼ ባላውቅም አሁን ወደዚያው እያመራሁ ነው፡፡ አሁን አሁን በእውነት ትዳር ትዳር እያለኝ
ነው፡፡ አንቺ ደግሞ እዚህ ቀረሽ የማትባይ ቆንጆ ነሽ፤ እንደኔም ተጫዋችና ሳቂታ ነሽ፡፡ ስለዚህ አሁኑኑ አልጋ ላይ እንድንወጣ እፈልጋለሁ›› አላት፡፡
👍17👏1
‹‹አይሆንም›› አለች ከልቧ እንዳልሆነ እየታወቃት፡፡

ሳብ ሲያደርጋት እሷም ተሳበችለትና ተማጠጡ፡፡

‹‹አንቺ ለኔ እኔ ላንቺ የተፈጠርን
መሆኑ ይሰማኛል›› ሲል አጉተመተመ:: ‹‹እዚያ ላይብረሪ ውስጥ ሆነን በወረቀት እየተጻጻፍን
የተለዋወጥነውን መልእክት ታስታውሻለሽ? አንቺ እኮ የጨዋታው ህግ ወዲያው ነው የገባሽ፡፡ ሌሎች ሴቶች ቢሆኑ ጨርቁን ጥሏል እንዴ ነበር የሚሉኝ አንቺም በዚህ ሁኔታዬ ነው የወደድሺኝ፡:››

እውነት ነው› አለች በልቧ፡ ፒፓ ብታጨስ ወይም ያለፓንት ቤት
ውስጥ መንጎራደድ ያለ እንግዳ ነገር ብታደርግ ባሏ በንዴት የሚንጨረጨር ሲሆን ማርክ ቢሆን ግን በሳቅ ልቡ ይፈርሳል

ደጸጉሯን ማፍተልተል ጉንጮቿን መደባበስ ጀመረ፡፡ ቀስ በቀስ ፍርሃቷ ለቀቃትና ሰውነቷ መፍታታት ጀመረ፡፡ ራሷን ትከሻው ላይ ደፋችና በከንፈሯ አንገቱን መዳሰሱን ተያያዘችው፡፡ እጁን በቀሚሷ ስር ሰዶ ከስቶኪንጓ በላይ
ያለውን ጭኗን ቀስ እያለ ሲደባብስ የእጁ ሙቀት ተሰማት፡ ይህ ይሆናል ብላ ስላልጠበቀች እግሮቿ ገላዋን መሸከም አቃታቸው፡

አልጋው ላይ ገፍተር አድርጎ ሲጥላት ኮፍያዋ ተሽቀነጠረ

‹‹ተው ይቅርብን›› አለች በደከመ ድምፅ፡፡ በከንፈሩ እያንዳንዱን
ከንፈሯን እየቆነጣጠረ መጠጣቸው፡: ጣቶቹን ከሃር በተሰራው ፓንቷ ውስጥ
ጨምሮ ሲያርመሰምሳቸው በወሲብ ባህር ውስጥ ሰጠመች፡፡

ሁሉን ነገር ጨርሰው ሲተቃቀፉ ሰውነቷ ይንቀጠቀጥ ነበር፡ ከእቅፏ
ውስጥ እንዲወጣ አልፈለገችም::
ጥላው እንደምትሄድ ለባሏ አትነግረውም፡፡ መልሳ መላልሳ የማርክ ፈጣን አዕምሮ ያፈለቀላትን መፍትሄ በአዕምሮዋ እያጠናች ወደ ቤቷ አመራች፡፡

መርቪን ፒጃማውን ለብሶ ሲጋራውን እያቦነነ ሬዲዮ ሲያዳምጥ
አገኘችው፡፡ ‹‹በጣም ቆየሽ›› አለ ብዙም ሳይቆጣ፡፡

ዳያናም ዘና ብላ ‹‹ቀስ እያልኩ ነው የነዳሁት›› አለችና ትንፋሿን ዋጥ
አድርጋ ‹‹ነገ መሄዴ ነው›› አለችው፡፡ ‹‹እህቴንና ልጆቹን ሄጄ አያቸዋለሁ
ናፍቀውኛል፡፡ ባቡር እንደበፊቱ ሁል ጊዜ ስለማይገኝ ይህን እድል አላገኝም፡
የነዳጅ ራሽንም የሚቀጥለው ሳምንት ይጀምራል እየተባለ ነው›› አለችው።

በስምምነት ራሱን ነቀነቀ፡፡ ‹‹ልክ ነሽ ከሄድሽ አሁኑኑ ሂጂ››
‹‹አሁኑኑ ሻንጣዬን ልቀረቅብ ነው፡፡››
‹‹ለኔም ሻንጣዬን አሳስሪልኝ›› አላት፡፡
እንዲህ ሲል ከኔ ጋር ሊሄድ ፈለገ እንዴ?› ስትል አሰበች፡፡ ‹‹ለምን?››
ስትል ጠየቀችው፣ በድንጋጤ፡
‹‹ባዶ ቤት አልተኛም›› አላት ‹‹ክለብ ሄጄ አሳልፋለሁ፤ ረቡዕ መቼም
ትመለሻለሽ፡፡››
‹‹አዎ ረቡዕ እመለሳለሁ›› ስትል ዋሸች፡፡
‹‹ደህና››

ፎቅ ላይ የሚገኘው መኝታ ቤታቸው ሄደችና የውስጥ ሱሪዎቹንና
ካልሲዎቹን ሻንጣ ውስጥ ስትከት ይህን የማደርገው ለመጨረሻ ጊዜ ነው ስትል በልቧ አሰበች፡ የነገረችውን የፈጠራ ታሪክ መቀበሉ እረፍት ሰጣት ነገር ግን የሆነ ነገር የረሳች እየመሰላት መበርገጓ አልቀረም፡፡ እሱን አተካራ
መግጠሙን ብትፈራም ለምን ትታው እንደምትሄድ ልትነግረው ከጅሏታል እድሜ ልኳን ሲጨቁናት መኖሩንና አዕምሮ ቢስ መሆኑን እንዲሁም እንደቀድሞው የማያቀማጥላት
ልትነግረው የማትችል መሆኑን መንገር አሰኝቷት ነበር፡፡ ይህን
አስቆጭቷታል፡፡

ሻንጣዎቹን ዘጋጋችና
የሜክ አፕ እቃዎቿን ቦርሳ ውስጥ
ጨመረቻቸው: የአምስት አመት ጋብቻ በዚህ አይነት ማለቁ አስቂኝ
ሆኖባታል፡

ትንሽ ቆይቶ መርቪን መጣ፡፡ ሻንጣ ማሳሰሩን አጠናቃ መስታወት ፊት
ቁጭ ብላ ሜክ አፕ እየተቀባች ነው፡፡ ከኋላዋ መጣና ጡቶቿን ጨበጥ አደረጋቸው፡:

ተው አይሆንም፧ ዛሬስ ይቅር! አለች በልቧ፡

ምንም እንኳን ሰውነቷ ለወሲብ ቢነሳሳም በማርክ ላይ የሄደች መስሏት ድርጊቱ አሳፈራት፡፡ መርቪን የጡቷን ጫፎች ሲያፍተለትላቸው በወሲብ ደስታ ጫን ጫን መተንፈስ ጀመረች፡፡ እጇን ያዝ አድርጎ ከመቀመጫዋ አስነሳትና ወደ አልጋው ሲወስዳት በእሺታ ተከተለችው፡፡ መብራቱን አጠፋና
በጨለማ ውስጥ እቅፍቅፍ ብለው ተኙ፡፡ ልክ ትታው እንደምትሄድ ያወቀ ይመስል እላይዋ ላይ ወጥቶ በሙሉ ሃይሉ ወሲብ ይፈፅምባት ጀመር፡፡

ሰውነቷም አሳጣትና እፍረቷን ውጣ በወሲብ ደስታ መናጧን ተያያዘችው፡: በሁለት ሰዓት ጊዜ ውስጥ ከሁለት የተለያዩ ስዎች ጋር ወሲብ ፈፅማ የወሲብ እርካታ ላይ መድረሷ አሳፈራትና ስሜቷን ልታምቅ ብትሞክርም
አልሆነላትም፡ የመጨረሻ ወሲባዊ እርካታ ስታገኝ ጮኸች፡፡ መርቪን ግን ይህንም አላስተዋለም፡፡...

ይቀጥላል
👍24
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አንድ ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ የደማውን እጇን በውሃ አጣጥባ በፎጣ አድርቃ በፋሻ አሰረችው:፡ ለምንድነው የፈራሁት? ስትል ራሷን ጠየቀች አይገድለኝ፤ ሊከለክለኝም አይችልም፤ እድሜዬ ከ21 አመት በላይ ነው! ይህም አገር ነፃ አገር ነው! በማለት ራሷን ለማሳመን ሞከረች፡፡ ይህም ሆኖ ግን ልትረጋጋ አልቻለችም፡ ጠረጴዛው ላይ የገበታ እቃዎች…»
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...በመጨረሻ እንዲህ ሆነ " ሚስዢ ላቲመር የምትባል የዌስትሊን ነዋሪ የሆነች
ወይዘሮ እንደ ገረድና አነጋጋሪም እንድትሆናት አፊ ሆሊጆንን አስከትላ ወደ
እስታልክንበርግ መጣች አፊ ከመቤቲቱ ጋር አብራ ትቀመጣለች ወይም ትበላለች ማለት ሳይሆን ከብዙ እመቤቶች ደንገጡሮች የተሻለ የመቅረብ ዕድል ነበራት እሷ ደግሞ ይህንን ጫፍ በመያዝ ጓደኛዋ እንደ ሆነች አድርጋ ታወራ ነበር » ሚስዝ ላቲመር ደግ ሰው ነበረች አፊም አባቷ በተገደለበት ጊዜ በነበረው
ሁኔታ የራሷን ታሪክ እያሠማመረች ለመቤቲቱ ታጫውታት ስለ ነበር በጣም ወደደቻት የሚስዝ ላቲመር ክፍል ከሚስዝ ክሮስቢ ቀጥሎ ስለ ነበር ' ሁለቱ ሴቶች ከመተዋወቅ ዐልፈው ባልንጀሮች ሆኑ " የመጀመሪያዋ ሎድዊግ ከገባች ሳምንት ሳይሆናት ምናልባት ሁለቱም ከሌሎች ጋር ብዙ ጊዜ እንዳደረጉት
ለዘለዓለም እትማማችነት ቃል ተጋቡ

ወይዘሮ ሳቤላ ከአትክልቱ ጓሮ ትገባና ሰው ወደሚያዘወትረው ጥግ ሒዳ መቀመጥ ትወድ ነበር ሔለና ክሮስቢ እንደምታገባ የነገረቻት ጊዜ ጨለማው ለዐይን መያዝ ጀምሯል እንደ ተለመደው እያዘገመች ሔዳ ከአንድ አግዳሚ ወንበር
ተቀመጠች እንዳጋጣሚ ሆኖ አፊ ሆሊጆንም በዚያው መንገድ እየተንጐራደደች መጣች » እሷም በበኩሏ ብቻዋን መሆኗ አስጨንቋታል።

ያቺ ደሞ ማን ናት ? ስትል አሰበች ወደ ወይዘሮ ሳቤላ እየተመለከተች አሃ ! ዐወቅኋት የክሮስቢ ልጅ አስተማሪ ናት በደፋችው ያሮጊት ቆብ ከሩቅ ትለያለች
ሔጄ ከሷ ጋር ላውጋ አለች።

አንዳለችውም ስለ ይሉኝታ ምንም የማትጨነቀው አፊ ሰተት ብላ ሒዳ ከሳቤላ ጐን ቁጭ አለች ደኅና አመሸሽ ማዳም ቬን ? አለቻት "

“ደኅና ፤እንደ ምን አመሸሽ ? አለቻት ሳቤላ በትሕትና ሴትዮዋን የማን እንደሆነች ጨርሳ ዐላወቀቻትም።

ያወቅሽኝ አልመሰለኝም አለቻት የሳቤላን አመለካከት በመገምገም “እኔ እኮ የሚስዝ ላቲመር ጓደኛ ነኝ ዛሬ ከሚስዝ ክሮስቢ ዘንድ ገብታ እዚያው ማምሸቷ ነው " ይኸ እስታልከንበርግ እንዴት ይሰለቻል !

“ እውነት ? እስከዚህ ድረስ ?

"ለኔ አዎን አየሽ ጀርመንኛም ሆነ ፈረንሣይኛ መናገር አልችልም " እዚህ
ያሉት የማናቸውም ቤተስቦች ተከታዮች አብዛኞቹ እንግሊዝኛ አይናገሩም ስለዚህ ዝም ብዬ ድብልቅ እያልኩ እንደ ጒጒት አፈጣለሁ " እዚህ የመጣሁት አሞኝ ነበር ግን የፈለገውን ያድርገኝ እንጂ ወደ ዌስት ሊን ብመለስ ይሻለኛል።”

ሳቤላ ይህችን ሴትዮ እንድታወራት በንግግርም ሆነ በገጽታ አላደፋፈረቻትም ነበር " የመጨረሻውን ዐረፍተ ነገር ስትስማ ግን ልቧ ከውስጧ ዘለለ የናፍቆት ትኩሳት ተነሣባት ።

"ከዌስት ሊን ነው የመጣሽው?"

“አዎን የተረገመ ቦታ ! ከሚስዝ ላቲመር ጋር መኖር እንደ ጀመርኩ ወዲያው መኖሪያዋን ዌስት ሊን አደረገች " ወደዚያ ከመምጣት ወደ አንድ የግዞት ሥፍራ ብትሔድ ኖሮ ይሻል ነበር "

"ግን ለምን ጠላሺው ?

“ ስለማልወደው ነዋ ?”

ኢስት ሊንንሳ ታውቂዋለሽ ?” አለች ሳቤላ ልትጠይቃት የምትፈልጋቸውን ነገሮች ስታስብ ልቧ እየደለቀ ።

ዐውቀዋለሁ እንጂ እኅቴ ሚስ ሆሊጆን የዚያ ቤት የሠራተኞች አለቃ ናት አንቺም ታውቂዋለሽ ማለት ነው ....ሚስዝ ቬን ?”

ከጥቂት ዓመታት በፊት በዚያ አካባቢ ለአጭር ጊዜ ተቀምጬ ነበር » ስለ ካርላይል ቤተሰቦች ደኅንነት ለመስማት ደስ ይለኝ ነበር " ጥሩ ሰዎች ነበሩ ”

አፊ ራሷን ወዝወዝ አደረገች እንደሚመስለኝ አንቺ የምታውቂያቸው የእመቤት ሳቤላ ጊዜ ከሆነ አሁን ብዙ ነገር ተለዋውጧል።

“ እመቤት ሳቤላ?” አለቻት ጥቂት ዝም ብላ ከቆየች በኋላ " አዎን ' ትዝ አለችኝ !የሚስተር ካርላይል ሚስት ነበረች "

እንዴት ያለች ሚስቱ ነበረች መስለሽ ? አለች አፊ በማሾፍ " መቼም ከሰው ተለይተሽ ጫካ ካልኖርሽ በቀር ታሪኳን ሳትሰሚ አትቀሪም ልጆቿን ሁሉ አፍስሳለት ከሌላ ወንድ ጋር ኮበለለች »

" ልጆቹስ በሕይወት አሉ ?

“ አሉ ያልታደሉ ምስኪኖች አንዱን የሳምባ በሽታ እያመነመነው ነው እህቴ ጆይስ ግን እንዲ ብዬ ስናገር በሽታው ይበረታበታል ብላ ትቆጣኛለች "

የትኛው ልጅ ይሆን ? አለች ሳቤላ የወረዛውን ግንባሯን እየጠረገች “ሳቤላ ትሆን

“ ሳቤላ የምትባል ልጅ የለችም " ያለች አንዲት ሴት ናት እሷም ሉሲ ነው የምትባል።

"ዱሮ እኔ ሳውቃቸው አንዲት ሴትና ሁለት ወንዶች ነበሩ እና ሴቲቱ ሳቤላ ስትባል ትዝ ይለኛል።

"ቆይ እስቲ ምን ነበር የሰማሁት አዎን ዊልሰን ሞግዚቲቱ እንደ ነገረችኝ ሚስቲቱ የኮበለለች ሌሊት ሚስተር ካርላይል ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ልጅቷ በሁለተኛ ስሟ ሉሲ ተብላ እንድትጠራ አዘዘ " ይኸንም ማድረጉ አያስገርምም አለች አፊ " እሱም ያንን ስም እየሰማ መኖር አይችልም " ልጂቱም በናቷ ስም ስትጠራ በትዝታዋ እንድትሠቃይ አልፈለገም "

“ እውነት ነው አያስገርምም ለመሆኑ የትኛው ልጅ ነው የታመመው ? አለች ሳቤላ

“ ዊልያም የሚባለው ትልቁ ልጅ ነው " ታመመ እንኳን አይባልም " ግን ሣር መስሎ ቀጥኗል ፊቱ ያለ መጠን ብጭጭ ብሏል ዐይኖቹ እንደ መስታወት ያብረቀርቃሉ " ጆይስ የፊቱ ብጭጭ ማለት የናቱም ከዚያ ይብስ ነበር ትለኛለች እኔ ግን ከሷ የበለጠ ዐውቃለሁ ጤነኞች የዚያን ዐይነት መፍለቅለቅ አይታይባቸውም "

“ እመቤት ሳቤላን አይተሻት ታውቂ ነበር ? ”

“ ኧረ እኔ!” አለቻት አፊ “ እሷን ማየቱንም እንደ ውርደት ነበር የምቆጥረው " አየሽ ማዳም ቬን ... እሷን ከመሰለ ቅሌታም ጋር መግናኘት ምን ያስፈልጋል ?

ሌላ ደግሞ አንድ ትንሽ ልጅ ነበር " ስሙም አርኪባልድ ይመስለኛል እሱስ ?”

“ ያ ረባሽ ጐረምሳ ! እሱ ምንም የለበትም " መቸም ብታይው ቁርጥ አባቱን
ነው " ታዲያ ' ዌስት ሊን ላይ ትንሽ ከቆየሽ የኔንም ስም በመጥፎ ሲያነሱት
ሰምተሽ ይሆናላ ?

“ የሰማሁ ይመስለኛል ግን ዝርዝር ነገሩን አላስታውሰውም "

አባቴ በሰው መገደሉን ሰምተሻል ? ”

“ አዎን አስታውሳለሁ "

“ አንድ ሪቻርድ ሔር የተባለ ሰው ገደለውና ወዲያው ካገር ጠፋ " ቤተሰቦቹን
ታውቂያቸው ይሆናል " እኔም ቦታው አስጠላኝና አባቴን እንዳስቀበርኩ ለቅቄ
ሄድኩ” ለካ ሰዉ ከሪቻርድ ሔር ጋር ኮበለለች ብሎ ያማኝ ኖሯል እንዲህ መባሌን በጊዜ ብሰማ ኖሮ ሁሉንም ልክ ልኩን እነግረው ነበር ” እስቲ እንዴት አድርጌካባቴ ግዳይ ጋር እሔዳለሁ !? ከዌስት ሊን አሉባልተኞች ጥቂቶቹ እንኳን ቢንጠለጠሉ
ለብዙዎቹ ትምህርት ይሆን ነበር ብዬ ለሚስተር ካርላይል ስነግረው ሣቀና' መስቀል አሉባልታን አያስቀርም አለኝ » ከዚያ ሁሉ ሕዝብ ከሪቻርድ ሔር ጋር አለመሔዴን ያመነልኝ እሱ ብቻ ነበር እንዴት ያለ ቀጥኛ ሰው መሰለሽ ?”

" አንቺ ግን በሥራ ላይ ነበርሽ አይደለም ?

“ አዎን ካንድም ሁለት ቦታ ነዋ መጀመሪያ ካንዲት ባልቴት ጋር እንደ ጓደኛ ሁኘ ኖርኩ " በጣም ትወደኝ ስለነበር ስትሞት ደኅና ገንዘብ ተናዘዘችልኝ
ከዚያም ከካውንተስ ማውንት እስቨርን ጋር ሁለት ዓመት ተቀመጥኩ

“ ካውንተስ ማውንት ስቨርን ? እሷማ ከሚስተር ካርላይል ሚስት ጋር በባሏ
በኩል ዝምድና ነበራት » ሎርድ ማውንት እስቨርን ራሱ ዘመድ ነበር "
👍16
“ አዎን አገር አይደል የሚያውቀው እመቤት ሳቤላንስ እንደዚህ ነቅላት የቀረች እሷ አይደለች ሚስጢሩን አውቃለሁ ምነው ራስሽን አመመሽ እንዴ እጅሽ ላይ ያስደገፍሺው ? አለቻትና መልስ ሳትጠብቅ ነገሯን ቀጠለች "እኔ እንኳን
ዌስትሊን ስሜን ካጠፋው በኋላ ልመለስበት አልቸኮልኰም ነበር ግን ሚስዝ ሳቲ መር በጣም ስለ ተስማማችኝ እሷን ተከትዬ መጥቸ ተቀመጥኩበት " ያቺን ቅድስቷን ሚስ ኮርኒሊያን ታውቂያት ነበር ?”

"አይቻታለሁ"

እስከ ዛሬም ስታየኝ ትገላምጠኛለች " እሷ መቸም መልአክንም ብታይ ትገላምጠዋለች

ዛሬም ኢስት ሊን ናት ያለችው ?

“ እንዴት ተደርጎ ! እዚያማ ብትኖር ከሚስዝ ካርላይል ጋር ይተናነቁ ነበር

“ሚስዝ ካርላይል ? አለች ሳቤላ ድርቅ ብላ ደንግጣ ከቆየች በኋላ እንደገና
አንሰራርታ እየተንተባተበች ሚስዝ ካርላይል ደሞ ማናት ?

የሚስተር ካርላይል ሚስት ናታ !ደሞ ማን ልትሆን ኖሯል ?

ሳቤላ ደሟ ተራወጠ " ሰውነቷ ተንቀጠቀጠ "
“ አንደ ገና ማግባቱን አላወቅሁም

ካገባ ዐሥራ አምስተኛ ወሩን ይዟል ሲያገባ ፡ እኔም ለማየት ሔጀ ነበር የነበረው ሕዝብ ለዐይን ያታክት ነበር ሙሽራይቱ እንዴት አምሮባት እንዶ ነበር መግለጽ ያስቸግራል።

ሳቤላ ሲደልቅ የነበረው ልቧን በእጅዋ ድግፍ አድርጋ ያዘች የለበሰችው ኮት ልል ባይሆን ኖሮ ልቧ ሲመታ አፊ በቀላሉ ታይባት ነበር " ቀስ ብላ ድምጿን አደላደለችና “ ባርባራ ሔርን አገባ ” አለቻት "

“ አዎን ምን ይጠረጠራል » ዊልሰን አንደ ነገረችን ከሚስተር ጀስቲስ ሔር ቤት ስለ ነበረች ብዙ ነግር ማወቅ አለባት ግና እመቤት ሳቤላን ለማግባት ከማሰቡ በፈት ፍቅር ነበራቸው ይባላል " ሌላው ደግሞ ብቻ ከዌስት ሊን ወሬ ዐሥሩን እየጣልሽ አንዱን ያዥለት እንጂ ወይዘሮ ሳቤላ ባትሞት ኖሮ አያገባም ነበር ይላል
ሊያገባቸው ነው እየተባሉ የሚታሙ ስድስት ያህል ነበሩ" ሰው ግን ባርባራ ሔርን እንደሚያገባ ማወቅ ነበረበት » አሁን ይኸው ሦስት አራት ወር የሞላው ወንድ ልጅ አድርሰዋል
ሚስዝ ካርላይል ባሏን የፈጣሪን ያህል ነው የምታኩብረው "

ለመጀመሪያዎቹ ልጆችስ ታዝንላቸዋለች ?

“ ከነሱ ጋር እምብዛም የሚያናኛት ነግር ያለ አይመስለኝም " አርኪባልድ
የሚውለው ከልጆች ክፍል ነው ሁለቱ ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ ከአስተማሪያቸው
አይለዩም "

አስተማሪ አለች ማለት ነው ?

“ሚስቱ በጠፍ ጨረቃ ጥላው እንደ ጠፋች በመጀመሪያ ካደረጋቸው ነገሮች አንዱ " ለልጆቹ አስተማሪ መቅጠር ነበር አሁን ግን ጆይስ እንደ ነገረችኝ በቅርቡ ስለምታገባ መልቀቋ ነው " "

“ ወደ ኢስት ሊን ብዙ ጊዜ ትሔጃሽ ?”

“እኔ ከማልወደድበት ቦታ አልሔድም ያቺ ሚስ ካርላይል አትወደኝም"
ወንድሟ ሪቻርድ ሔር እኔን ለማግባት ይፈልግ እንደ ነበር ታውቃለች እሷ ደግሞ
አትፈልግም " ሪቻርድ ይህን ወንጀል ባይፈጽምም የሚረባ ሰው አልነበረም » አቤት እንዲያው በዚህ አለም ስንት ለውጥ ይታያል
ያቺ ሞኝ እመቤት ሳቤላ አብዳ ትታው ባትሔድና ቦታውን ባትለቅላት ኖሮ ሚስ ባርባራ ሚስዝ ካርላይ የመባልን ዕድል አታገኝም ነበር " '

ሳቤላ እርር አለች "

“ዛሬ ስለ እሷ አንድም ክፉ ነገር ለመስማት የማትፈልግ ጆይስ ብቻ ናት ጆይስ
ከዱሮም አመቤት ሳቤላን ልክ ሚስተር ካርይል እንደሚወዳት አድርጋ ነበር
የምትወዳት "

ሚስተር ካርላይል ሚስቱን ይወድ ነበር ? አለች ሳቤላ "

“ የረገጠችውን መሬት እንኳን ያመልከው ነበር እስከ ተለየችበት መጨረሻ
ሰዓት ድረስ በጣም ይወዳት እንደነበር ጆይስ አጫውታኛለች " እሷ ግን የከፈለችው ውለታ ይኸው ሆነ ታዲያ የዓለም ጠባይ ይኸው ነው ሴትም ሆነች ወንድ አንዱ ሌላውን አቅሎ እስኪጠፋ ድረስ ካመለከው ውጤቱ እንደዚሁ ነው "

“ ለመሆኑ የሟቿ መርዶ ሲመጣ ኢስት ሊን ውስጥ እንዴት ነበር ?”

“ ስለሱ ምንም አላወቅሁም " የከተማው አብያተ ክርስቲያናት ደወሎች ዳር
እስከ ዳር ተደወሉ “ ታላቅ ደስታ የተሰማቸው መሰለኝ እኔም ብሆን ኖሮ ደስታውን ባልቻልኩት ደንቆሮና ዲዳ የሆነች እንስሳ እንኳን ግልገሎቿን ትጠብቃለች እሷ ግን ከአንበሳ እንኳን ብሳ ጥላቸው ሔደች " ወደ ቤት ልትገቢ ነው' ማዳም ቬን ?”

“ አዎን መግባት አለብኝ ' ደኅና አምሽ »

እስካሁን ከምትችለው በላይ ችላው ተቀመጠች " የልቧ ሥሮች ክፉኛ ተወጠሩ " አፊ ዓለም ከሚናገረው ግማሹን እንኳን አልነገረቻትም » አሁን ከሰማችው ዘለፋና ውርደት ዐሥር ሺህ ጊዜ መወቀስ መዘለፍ እንደሚገባት ታውቃለች ስለዚህ የምትከላከልበትና ሺፋን የምትሰጠው ምክንያት አልነበራትም "

እንደ ተለመደው ወደ መኝታዋ ሔደች ለመተኛት ሳይሆን በጸጸት ለመቃጠል
በናፍቆት ለመወዝወዝ አፊ የነገረቻት ሁሉ ናፍቆቷን ቀሰቀሰው አቀጣጠለው !
ኢስት ሊን ውስጥ የእንጀራ እናት ገብታ ከልጆቿ አንዱ ወደ ሞት እየተንሽራተተ
ሲወርድ ከፊቷ ተደቀነባት አንድ ጊዜ ብታያቸው አንድ ጊዜ ከመኻላቸው ብትገኝ ይህን ያንድ አፍታ ዕድል ለማግኘት ሕይወቷንም ብትከፍል በወደዶች »

ሰውነቷ በትኩሳት ነደደ » መኝታዋም እንደሷው ጋለ" ብድግ ብላ በክፍሏ ውስጥ ተንጎራደደች የዚህ ዐይነቱ ሁኔታ ከአካላዊ በሽታ ዐልፎ አእምሮዋንም እንዲይነካት ፈራች ሕሊናዋን ብትስት ፡ መለፍለፍ ብትጀምር የደበቀችውን ምስጢር
ሳታውቀው እንዳታጣው ሠጋች እንደገና ካልጋዋ ተጋደችመ ትራሱን
በግንባርዋ አጥብቃ ተጫነችው " የሚስተር ካርይልን ጋብቻ ስትሰማ የብሶቷን ሰሜት በበለጠ በጠበጠው እንድትሞት ባትጸልይም ሞት እንዲመጣላት ግን
ከልቧ ተመኘች።

0ልፎ ዐልፎ አንዳንድ አጋጣሚዎች ይደርሳሉ " በበነጋው ጧት ከቈርስ
በኋላ ሚስዝ ሮስቢ ወደ ማዳም ቬን ክፍል ገባች " ስለ ሔሌና ጋብቻ ስለሷ ኣገልግሎት መቋረጥና ምናልባትም ወደ ኢንግላንድ ለመሔድ የምትፈቅድ ቢሆን ሥራ ልታገኝላት ተስፋ እንዳላት አጫወተቻት ማዳም ቬን ወደ ኢንግላንድ ለመሔድ አንደማትፈልግ ልትነግራት አሰበች መልስ ከመስጠቷ በፊት ሚስዝ ላቲመር መጥታ ብታስረዳት እንደሚሻል ነገረቻትና ሔዳ ጠራቻት "

ትንሽ ቆይታ ሚስዝ ላቲመር መጣች" ሰማሽ ማዳም ከዚህ ቤተሰብ ዘንድ ብትገቢ በጣም ዕድለኛ ነሽ " ጥሩ ሰዎች ናቸው " ወንድየው በማንም ዘንድ
የተከበረና የተወደዶ ሰው ነው ሴትዮዋም ቆንጆና ፈታ ያለች ናት « ቦታው የማይገኝ
ነው ሁሉ ነገር ሁሉ ነገር ዝግጁ ነው አንቺ እንደ እመቤት በከረቤታ ትያዣለሽ አንዴት ሴት ብቻ ናት ተማሪሽ የሷ ተከታይ ለአንድ ሁለት ሰዓት ይገባ ይሆናል
እስከዚህም አይደለም " ደሞዝሽ ባመት ሰባ ሦስት ፓውንድ ተኩል ነው ሚስተርና ሚስዝ ካርላይል ወዳጆቼ ናቸው መኖሪያቸውም ኢስት ሊን የተባለ በጣም ቆንጆ የሆነ ቦታ ነው "

የልጆች አስተማሪ ሆና ኢስት ሊን ከካርላይል ቤተሰብ ዘንድ ልትሔድ ? "
ሳቤላ ትንፋሿ ከዳት "

የነበረቻቸው አስተማሪ ስለምትሔድባቸው” አለች ላቲመር ነገሯን በመቀጠል'“ ሚስዝ ካርላይል ገና እኔ ወደዚህ ስነሣ አንዲት ፈረንሣይኛና ጀርመንኛ
የምትችል የልጆች አስተማሪ እንድፈልግላት ነግራኝ ነበር አሁን ሚስዝ ክሮስቢ
አንደ ነገረችኝ ፈረንሣይኛሽ ልክ እንደ ተወላጆች የጠራ መሆኑን ' ጀርመንኛም
አንደምታነቢና እንደምትጽፊ የሙዚቃ ችሎታሽም የላቀ ነው " ስለዚህ እነሱ
የፈለጉትም ይኸው ነው " ቦታውንም ታገኝዋለሽ " ስለዚህ ምን ይመስልሻል?”
አለቻት "
👍16
“ለኔ እንደ መሰለኝ ” አለች ሚስዝ ክሮስቢ አንቺ እኛ ዘንድ በነበርሽ ጊዜ በሚገባ አገልግለሻል " ይህ አሁን የተገኘው ቦታም ላንቺ የሚገባ ጥሩ ሥራ ነው " ስለዚህ ሊያመልጥሽ አይገባም " በነገሩ ላስብበት እስከ ነገ ጊዜ ይስጡኝ አለቻት።

ያችን እለት ከራሷ ጋር እንደ ተሟተች ዋለች " የመጣውን ሁሉ ችላ ለአንድ ጊዜ
ኖር ለመሔድ ትቆርጥና ፡ ነገሩን ስታስበው እየዘገናት መልሳ ሽምቅቅ ትላለች አንድ ግዜ ልጆቹን ለማየት
ትችል ዘንድ እግዚአብሔር አመቻችቶ የሰጣት ዕድል
አድርጋ በመቁጠር ለመቀበል ትደሰትና በሌላ መልኩ ደግሞ አሳሳችና አደገኛ ወጥመድ ስለሆነ እንዳትቀበል የሚያስፈራራ ስሜት ይደቀንባታል ነገሩን በሌላ መልኩ ስታየው ደግሞ ! ሚስተር ካርላይልን የሌላ ባል ሆኖ እሷም በአንድ ቤት አብራ ተቀምጣ አዲሲቱን ሚስቱን ሲያጫውታት ሲዳብሳት • ምናልባትም ሲስማት ማየቱን እንዴት ትችለዋለች ? መልሳ ታስበውና መጀመሪያ ጸጸቷን ለራሷ ስትናዘዝ የመከራ መስቀሏን በየዕለቱ በትዕግሥት ለመሽከም ቆርጣ ነበር " ይህ ሁሉ ሥራውን ለመቀበል ብላ ልጀቿን ላለማየት ምክንያት ሆኖ ሊያስቀራት እንደማይችል ሆኖ ይታያታል ቀኑ መሸ « እሷ ግን ገና አልቆረጠችም " ገና አንድ የሥቃይ ! የመካራ የእንቅልፍ እጦት ( የልጆች ናፍቆት የጭንቀት ሌሊት አነጋች ይህ ኃይለኛ ናፍቆት
ደግሞ ጠቅላላ የአእምሮዋንና የጉልበቷን ኃይል ሁሉ እንዳለ ዋጠው ፈተናው ሊያስቀሩት የማይቃጣ ሆነባት ዕቅዱ መድረሻው በጉጉት ፊቷ ተደቅኖ የማይበገር ሆነባት " በመጨረሻ" እንዳልሔድ ምን ይከለክለኛል ! የመታወቅ ፍራት ነው ? ታዲያ ቢያውቁኝ አይሰቅሉኝ ! አይገድሉኝ " ግፋ ቢል ልክ አንድ ወታደር
ታምቡር እየተመታበት ከሠራዊቱ እንደሚባረረው ሁሉ እኔንም በደረሰብኝ ውርደትና ባስከተለብኝ ንቀት ላይ ጠለቅ ከበድ ያለ ውርደት በመጨመር ከኢስት ሊን ጎትተው ከማውጣት በቀር ምን ያደርሱብኛል? ሌላውን ሁሉ እንደ ቻልኩት መቻል
አለብኝ " ከእንግዲሀ ለኔ ውርደት ምኔም አይደለም " የመጣው ዐይነት ውርደት
ቢመጣ ልጆቼን በ0ይኔ ማየትና አብሬያቸው ከመሆን ጋር ላወዳድረው አልችልም ፤ልጆቼ ይበልጡብኛል ! ብላ ለመሔድ ቆረጠች ።

ሚስዝ ላቲመር አንዲት በሁሉ ነገር ልትስማማት የምትችል የልጆች አስተማሪ
እንዳገኘችላት ለሚስዝ ካርላይል ስትጽፍላት ሴትዮዋ ማዳም ቬን አንደምትባል ትውልዷ እንግሊዝ ፈረንሳዊ ባሏ የሞተባት ( ሃይማኖቷ ፕሮቴስታንት የቋንቋ
ችሎታዋ የጠራ ) ሙዚቃ የምትችል ሁለት ዓመት የሠራችላት ሚስዝ ክሮስቢ
ከልቧ ያመሰገነቻት እንደ ነበረች በመግለጽ ዘረዘረችላት“ ስለ መልኳ አታስቢ መነጽር ቆብና ያንገት መጠምጠሚያ የምታደርግ ( አገጯና አፋ ላይ ትልቅ ጠባሳ ያለባት ዕድሜዋም ከሠላሳ ዓመት ባይበልጥም ጸጉሯ የሸበተ ' በመጠኑ የምታነክስ ሴት ናት ” ብላ ደመደመችላት።

ይህ ገለጻ ኢስት ሊን ደርሶ ባርባራ ለሚስተር ካርላይል ስታነብለት ተሣሣቁና
"የልጆች አስተማሪዎች በመልካቸው የሚመረጡ ቢሆን ኖሮ ማዳም ቬን ተስፋ አይኖራትም ነበር ” አለ ሚስተር ካርላይል " ከዚያ እንድትቀጠር ተስማምተው የመልስ ደብዳቤ ወደ እስታልከንበርግ ተላh "
ሳቤላ በከባድ ጭንቅ ተዋጠች " ከሱ በፊት የዱሮ ማንነቷን የሚጠቁም አንዳ
ችም ምልክት እንዳይገኝ ዕቃዋን ሁሉ ከጠረጴዛ ኪስ እስከ ልብስ ሣጥን አንድ ሳታስቀር እየበረበረች አራገፈች አብዛኛውን ዕቃዋን ከግሮኖብል ከመነሣቷ በፊት ወደ
ፓሪስ ልካው ስለ ነበር ከመጋዘን እንደገባ ቀርቷል አለባበሷ በማንኛውም ረገድ ከዱሮው እንዳይመሳሰልባት አድርጋ አዘጋጀች " ቆቦቿ ተራና ከግንባሯ ልክክ ያሉ ከመሆናቸው ' በቀር በሌላው ሁኔታቸው ከሚስ ኮርኒሊያ ቆብ ጋር የሚወዳደሩ ነበሩ " የጽሕፈቷን አጣጣል ከተለመደው አጻጻፋ ጋር እንዳይመሳሰልባት ' ሁለት
ዓመት ሙሉ ልምምድ አድርጋ ነበር " ሚስዝ ካርላይል ጽፋላት ለነበረችው ደብዳቤ እጅዋ እየተንቀጠቀጠ መልስ ጻፈችላት " እሷ እመቤት ሳቤላ ለሚስተር ካርላይል ባለቤት ያውም በተወራጅነት ስትጽፍላት ከዚህ የባሰው ደግሞ ጉድፍ
አይንካሽ ተብላ ' ተወዳ ' ተከብራ ' እመቤት ሆና ' በኖረችበት ቤት ለገዛ ጣውንቷ ታዛዥ ሆና የመኖሩ ነገር ሁሉ ሲመጣባት ፡ እንባዋ ክንብል ብሎ ሲወርድ “ባርባራ ካርላይል ከሚለው ፊርማ ላይ አረፈ ነገር ግን ሌላውን ፈተና ሁሉ እንደቻለችው ይኸንንም ከመቻል ሌላ ብልሃት አልነበራትም በመጨረሻ ከሚስዝ ላቲመር ጋር ወደ ኢንግላንድ ወደ ዌስት ሊን የሚነሡበት ቀን ተወሰነ " ቀኑም ሳቤላ እጆቿን አጥፋ በትዕግሥት ስትጠብቀው ደረሰ " ሚስዝ ላቲመር ሳቤላና አፊ ከእስታልከንበርግ ተነሡ "
የምትሔጅላቸው ልጆች ሁኔታ የተነገረሽ ይመስለኛል " አለቻት ሚስዝ ላቲመር “ስለ እናታቸው ምንም ነገር እንዳታነሺባቸው " ጥላቸው ጠፍታለች "

“ እሺ ”

" አዋርዳቸ ስለ ሔደችው ስለ አሳፋሪዋ እናታቸው ለልጆች መንገር ደግ
አይደለም " ሚስተር ካርላይልም ደስ አይለውም " እንዲያውም እናታቸው ሚስዝ ካርላይል ብቻ መሆኗን እንዲያምኑና ያቺን እናታቸው ግን ጨርሰው እንዲረሱዋት አስፈላጊው ጥንቃቄ የተደረገ ይመስሎኛል”

በሕይወት ፈተና የቆሰለው ልቧ ሁሉንም እንዳመጣጡ መቀበል ነበረበት "

እነሱ ዌስት ሊን ሲደርሱ ቀኑ ጉማም ከማምሸቱም በላይ ጨለማው እየተጫነው ድንግዝግዝ ማለት ጀምሮ ነበር ሚስዝ ላቲመር ማዳም ቬን ለኢንግላንድ አዲስ
መስለቻትና ለነጂው የምትወርድበትን ነግራ በሕዝብ ሠረገላ አሳፍራ '' በይ ማዳም መልካም ዕድል ! ደኅና ሁኝ " ብላ ወደ ኢስት ሊን ስደደቻት ።

ዱሮ የምታውቀው ጐዳና እንደ ገና ተመለሰችበት የጀስቲስ ሔርን ቤትና
ከዚያ ጥንታዊና ተወዳጅ ቤት ኢስት ሊን ደረሰች » ሰውነቷ ተረብሾ ልቧ ተጨንቆ በፍርሃት በኀዘን በጸጸት ተወጥራ ቤቱን ቀና ብላ ስታየው ደስታና እርካታ
የሰፈነበት መስሎ ታያት ልቧ በጉጉት በተስፋ ተመላ ሰረገላው እየገሰገሰ መጥቶ ከደረጃዎቹ ጥግ ደርሶ ቆመ ለጊዜው ዐይኖቿም ጭልም አሉባት ወደ ኢስትሊን ለመምጣት በመወሰኗ ተጸጸተች ......

💫ይቀጥላል💫
👍206
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


...መርከቡን የሚሳፈሩበት ሳውዝ ሃምፕተን ከተማ ሆቴል ውስጥ ወደ ወደቡ የሚወስዳቸውን ታክሲ በድል አድራጊነትና ነፃነት እየጠበቁ ነው፡፡

ሆቴሉ ውስጥ ያለው ሁሉ ዓይኑን ከእሷ ላይ አልነቅል ብሏል፡፡ አንድ ከእሷ አስር አመት የሚያንስ ወጣት ዓይኑን ሳይሰብር ያያታል፡ እሷ ግን እንዲህም አይነት ነገር ዘወትር ስለሚያጋጥማት ለምዳዋለች፡፡ ጥሩ የለበሰች
ጊዜ ይኸው ነው የሚያጋጥማት፡፡ ዛሬ ደግሞ አለባበሷ ልብ ይሰቅላል፡፡
የለበሰችው ቀይ ነጠብጣብ ያለው የበጋ ጊዜ ቀሚሷ ሄዶባታል፡፡ ራሷ ላይ
የደፋችው ኮፍያ ደግሞ ውበት ጨምሮላታል፡፡ ከንፈሯን የተቀባችው
ብርቱካናማ ሊፒስቲክና ጥፍር ቀለሟ ቀሚሷ ላይ ከሚታዩት ነጠብጣቦች ጋር ተጣጥመዋል፡፡ ቀይ ጫማ ለመጫማት አስባ ሴተኛ አዳሪ ያስመስለኛል ብላ ትታዋለች፡፡

መቼም ልብሶቿን በሻንጣ ሸካክፋ መጓዝ ትወዳለች: አዳዲስ ሰው እንድትተዋወቅና አዳዲስ ቦታ እንድትታይ ዕድል ይሰጣታል፡፡ በአይሮፕላን
መሄድ ቢያስፈራትም በዚያኛው አትላንቲክ ዳርቻ ያለችው አሜሪካ መሄድ
ግን ከጉዞዎች ሁሉ አስደሳች ጉዞ በመሆኑ ለብቻው ነው፡፡ ስለአሜሪካ ያላት እውቀት ፊልም ቤት ያየችው ብቻ ነው በአይነ ህሊናዋ መስታወት
በመስታወት የሆነ ቤት፣ ዩኒፎርም የለበሰች የቤት አገልጋይ ፀጉራማ ኮት
ስታለብሳት፣ አንድ ጥቁር ሹፌር ወደ ናይት ክለብ ሊወስዳት ሞተሩ የተነሳ
መኪና ይዞ ሲጠብቃት፣ ናይት ክለብ ቁጭ ብላ የጃዝ ባንድ ሙዚቃ እያየች
ደረቅ ማርቲንዋን ስትጨልጥ ታያት፡፡ ይሄ በምናቧ የሚታያትን አኗኗር
አሜሪካ ሄዳ በእውን ለማግኘት ልቧ ቆሟል፡፡ደ

ጦርነቱ የጀመረ ሰሞን ከእንግሊዝ መሰደድና አለመሰደድ መካከል ልቧ
ይዋልል ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ መሰደድ ቦቅቧቃ ቢያስመስልም መሄዱ ግን አጓጊ ነበር፡፡

ዳያና በርካታ ይሁዳውያንን ታውቃለች፡፡ ማንቼስተር ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የይሁዳውያን ማህበረሰብ አለ፡፡ ማንቼስተር ያሉ ይሁዳውያን በአውሮፓ አይሁዳውያን ላይ እየተካሄደ ያለውን ጭፍጨፋ በፍርሃትና
በጭንቀት እየተከታተሉ ነው፡፡ ናዚዎችና ፋሺስቶች ይሁዳውያንን ብቻ
ሳይሆን ጂፕሲዎችን፣ ክልሶችንና ለየት ያለውን ሁሉ ይጠሉታል፡፡

ጦርነት ውስጥ የገባችውን አገሯን በወታደርነት ለመታደግ ብትፈልግም
ዕድሜዋ አይፈቅድም ሆኖም ማንቼስተር ቆይታ የቀይ መስቀል የበጎ
አድራጎት አባል ሆና ቁስለኞችን የማከም አስተዋፅኦ ማበርከት ፈልጋ ነበር።

ይህም ቢሆን በሃሳቧ እንጂ በእውን እንደማይሆን አውቃለች፡፡ ነገር ግን
እሷም የልጆች እናት ልትሆን ነው፡፡ በፓን አሜሪካን አይሮፕላን መሄዷን
ስታስበው በደስታ ተፍነከነከች፡፡

ጋዜጣው ስለዚህ በራሪ ጀልባ የፃፈውን ሁሉ ብታነብም እኔም እበርበታለሁ ብላ አልማ አታውቅም ነበር፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ኒውዮርክ
መድረሱ ተዓምር ሆኖባታል፡፡

ቤቱን ለመጨረሻ ጊዜ ለቃ ስትሄድ ለመርቪን ይህን የሚል ደብዳቤ ጽፋ አስቀምጣለች፡፡

‹‹ዉዱ መርቪን ትቼህ ሄጃለሁ ከቀን ወደ ቀን ግግር በረዶነትህ ይለቅሃል
እያልኩ ብጠብቅም አንተ ግን ያው ነህ:፡ ሌላ ሰው አፍቅሬያለሁ፤ ይህን
ደብዳቤ በምታነብበት ጊዜ እኔ አሜሪካ ነኝ፡፡ ልጎዳህ ፈስጌ ባይሆንም
በከፊል ጥፋቱ ያንተ ነው::

ዳያና››

በመጀመሪያ መልዕክቱን በቀላሉ እንዲያገኘው ወረቀቱን መብል ቤት
ጠረጴዛው ላይ ልታስቀምጥለት ፈልጋ ነበር፡፡ ወዲያው ወደ ክለብ የመሄዱን ሃሳብ ለውጦ ወደ ቤት ከተመለሰ ደብዳቤውን ያገኝና ከማርክ ጋር አገር ለቃ ሳትሄድ ችግር ይፈጥር ይሆናል ብላ በመፍራቷ ደብዳቤውን በመስሪያ ቤቱ አድራሻ በፖስታ ላከችለት፡፡ ባሏ ሰዓት አክባሪ እንድትሆን ስጦታ የሰጣትን የእጅ ሰዓቷን ተመለከተች፡፡ የዘወትር ልማዱን ታውቃለች፡፡ ጧት ጧት ማምረቻ ክፍል ይቆይና እኩለ ቀን አካባቢ ቢሮው ገብቶ ለምሳ ከመውጣቱ
በፊት ደብዳቤዎችን ያነባል፡፡ ደብዳቤው ላይ የግል› የሚል ስለፃፈችበት
ጸሐፊው አትከፍተውም፡፡ ይህን ጊዜ ደብዳቤዋ ጠረጴዛው ላይ ካሉት
ደረሰኞች፣ የስራ ትዕዛዞች፣ ደብዳቤዎችና ማስታወሻዎች መሃከል ይሆናል፡፡የጻፈችለትን ደብዳቤ ስታስብ በባሏ ላይ የፈጸመችው ክህደት ህሊናዋን ቢሸነቁጣትም ከእሱ ከሁለት መቶ ኪ.ሜ በላይ በመራቋ በአንጻሩ እረፍት ተሰምቷታል።

‹‹ታክሲው መጣ፣ እንሂድ›› አላት ማርክ፡፡

ጭንቀቷን ዋጥ አድርጋ፣ የቡና ሲኒዋን አስቀምጣ በፈገግታ ብድግ
አለች ‹‹እሺ›› አለች በደስታ ‹‹መብረራችን ነው›› አለች፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ኤዲ ሴቶች ፊት ሲሆን ያፍራል፡፡

ከአናፖሊስ የባህር ኃይል አካዳሚ ሲመረቅ የሴት ልጅ እጅ እንኳን ጨብጦ አያውቅም፡፡ ከኮሌጅ ተመርቆ በፐርል ሃርበር ስራ ሲጀምር ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር አሸሼ ገዳሜ ማለት ጀመረ። ባህር ኃይል መስሪያ ቤትን ሲለቅ ብቸኝነት ስላጠቃው ጓደኛ ፍለጋ ቡና ቤት መሄድ አዘወተረ፡፡ ካሮል በዚያን ጊዜ ኒውዮርክ በሚገኝ አየር መንገድ ውስጥ በእንግዳ ተቀባይነት
ትሰራ ነበር፡፡ ካሮል ጸጉሯ ቡናማ ሲሆን አይኗ ደግሞ ሰማያዊ ነው፡፡ ኤዲ
እሷን ‹‹ልጋብዝሽ›› ብሎ ለመጠየቅ በፈራ ተባ ብዙ ጊዜ አጠፋ፡፡ አንድ ቀን
አንድ ጓደኛው ቴአትር ቤት መግቢያ ሁለት ቲኬት ሲሰጠው አንዱን ቲኬት
ምን እንደሚያደርገው ሲያስብ ጓደኛው ካሮል አንን አብራው ትገባ እንደሆን
ሲጠይቃት ‹‹እሺ›› አለች፡፡ ኤዲ ባነጋገሯ እንደ እሱው ገጠር አደግ እንደሆነች ተገነዘበ፡፡

ታሪኳን ሲያጠና ብቸኛና ገጠሬ በመሆኗ የከተማ ውጥንቅጥ ስጋት ላይ
የጣላት መሆኑን አወቀ፡፡ ምንም እንኳን በሆዷ ፍላጎት ቢኖርም ወንዶች አፍ አውጥተው እናውጣሽ ብለው ሲጠይቋት በማፈር ታኮርፋለች፡፡ ሰዎች
ይህን እምቢተኛነቷን ስለሚያውቁ አይጠይቋትም፡፡
ኤዲ ይህን ያውቅ ስለነበር ክንዷን ከክንዱ ጋር አቆላልፎ ይንጎራደዳል፡፡
ራት ይጋብዛትና እቤቷ በታክሲ ያደርሳታል፡ ቤቷ ደጃፍ ላይ ቆመው
ስላሳለፉት አስደሳች ምሽት ያመሰግናትና ጉንጮቿን በድፍረት ይስማቸዋል፡፡

እሷም እምባ እየተናነቃት በመላው ኒውዮርክ እንደ እሱ ዓይነት ጨዋ ሰው
እንዳላጋጠማት ትነግረዋለች። እሱ ለሌላ ቀን ቀጠሮ ይጠይቃታል

ቀስ በቀስም ፍቅር ያዘው፡ አንድ ቀን ሊያዝናናት ወደ አንድ ደሴት ይዟት ሄደ፡፡ ከእሱጋ መታየት የሚያኮራት መሆኑን ተገንዝቧል፡፡ የሄዱበት ቦታም አይስክሬም ሲልሱ፣ በሽክርክሪት ሲጫወቱና ፍቅራቸውን ሲለዋወጡ
ዋሉ፡፡ ሽርሽራቸውን ጨርሰው ወደ ቤቷ ሲሸኛት እንደዚህ ቀን ደስ ብሎት
እንደማያውቅ ካንጀቱ ሲነግራት እሷም ‹‹እኔም ደስ ብሎኛል›› አለችው::

ካሮል አን ለፍቶ አዳሪ ደሃ ቤተሰቦቿጋ ወስዳ አስተዋወቀችው፡፡ እነሱን
ሲያይ ቤተሰቦቹ ትዝ አሉት፡፡ ልጃችን እንዴት ቆንጆ ብትሆን ነው ኤዲን የመሰለ መኳንንት የማረከችው! ሲሉ ተደነቁ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ማረፊያ ሆቴሉ ውስጥ ሆኖ በሃሳቡ መጣችበት፡ የሄደ ቀን ተጋጭተው ነበር፡፡ የእሱን ሸሚዝ ለብሳ ከውስጥ ሌላ ነገር ሳትለብስ ሶፋው ላይ ቁጭ
ብላ መጽሐፍ ታነባለች፡፡ ለስላሳው ረጅሙ ጸጉሯ ትከሻዋ ላይ ተዘናፍሏል፡
ጡቶቿ ትንንሽ ቢሆኑም ጉች ጉች ያሉ ናቸው፡፡ በሽሚዟ ስር እጁን ሰደደና
የጡቶቿን ጫፎች አፍተለተላቸው፡፡ እሷ ግን ማንበቧን ቀጥላለች፡
👍221
ራሷን በከንፈሩ ደባበሰው፡፡ ከመጀመሪያውም ሁኔታው ገርሟታል ሁለቱም አፋራሞች ናቸው፡፡ አብረው መኖር ከጀመሩ በኋላ ግን ያ ሁሉ እፍረት ለቋት ስሜቷን እስከመገደቡም አቅቷታል፡፡ አንድ ቀን መብራቱ
እንደበራ ወሲብ መፈፀም እንደምትፈልግ ስትነግረው በእፍረት የሚገባበት
ጠፍቶት ነበር፡፡ በኋላ እየወደደው ቢመጣም እፍረቱ ግን ቶሎ አልለቀቀውም፡፡ ባኞ ቤት ስትገባ በሩን ስለማትዘጋው እሱ ይዘጋል፡፡ አንድ ቀን ገንዳ ውስጥ ሆኖ ገላውን ሲታጠብ ይባስ ብላ
መለመላዋን መጥታ
አብራው ተዳበለች፡፡ እንደዚያ ቀን አፍሮ አያውቅም፡፡ አራት ዓመት ከሞላው ወዲህ ሴት ፊት ራቁቱን ቆሞ አያውቅም፡፡ ካሮል አን ብልቷን ስታጥብ
አይቶ ብልቱ አንዳች አክሎ ነበር፡ ለመደበቅም ብሎ ጨርቅ ሲያስቀምጥበት
አይታ በሳቅ ተንፈረፈረች፡

አጅሪት ቤት ውስጥ ራቁቷን መንጎራደዷን ቀጥላለች፡፡ ኩሽና ሻይ እያፈላ ወይም ጢሙን ሲላጭ ጡቶቿን አንገፍጥጣ በፓንት ብቻ
ትመጣበታለች፡ አልጋው ላይ እንደተኛ ደግሞ ራቁቷን ሆና ቁርሱን በትሪ ይዛ ትመጣለች፡ ቢሆንም ሁኔታዋ ያስደስተዋል፡ ራቁቷን ቤት ውስጥ
የምትንጎራደድ ሚስት ትኖረኛለች ብሎ አልሞም አያውቅም፡ ዕድለኛ ነኝ
ሲል አሰበ፡፡

ዓመት ያህል አብረው ሲኖሩ እሱም እየተለወጠ መጣ፡፡ እሱም ከመኝታ ቤት ወደ ባኞ ቤት እንደ እሷው ራቁቱን መሄዱን ልማድ አድርጓል፡፡ አሁን
አሁንማ ሶፋው ላይ ነው የሚወስባት፡፡

ካሮል አን ከፓን አሜሪካን አየር መንገድ መስሪያ ቤት ለቃ ባንጎር ውስጥ ሱቅ ተቀጠረች፡ ስለ ስራዋ ሊያናግራት ፈልጓል፡

‹‹ምን አልክ?›› አለችው ከምታነበው መጽሐፍ ላይ ቀና ብላ፡፡

‹‹ምንም አላልኩም›› አላት፡፡

‹‹ልትል አይደለም?››

‹‹እንዴት አወቅሽ?››

‹‹የምታስበውን አውቃለሁ›› አለችው፡፡

እጁን ሰደደና በመጠኑ ወጠር ያለውን ሆዷን እየደባበሰ ‹‹ስራውን
እንድትተይው እፈልጋለሁ›› አላት፡፡

‹‹ሆዴ ገና ነው ስራውን አሁን አልተውም››

‹‹ግዴለም ተይው የኔ ደመወዝ ይበቃናል›› አላት፡፡
‹‹አሁን ምንም አላስቸገረኝም ሆዴ ሲገፋ ስራውን እተወዋለሁ
አልኩህ››

‹‹ስራውን ተይው ስልሽ ደስ የሚልሽ መስሎኝ ነበር፡፡ ለምንድነው ስራውን መተው ያልፈለግሽው?››

‹‹ምክንያቱም ገንዘቡ ያስፈልገናል››

‹‹ነገርኩሽ እኮ የኔ ደመወዝ ለሁለታችን ይበቃል››

‹‹እቤት መዋል ይሰለቸኛል››
‹‹ብዙ ሚስቶች እኮ ስራ አይሄዱም››

ይህን ሲላት ‹‹ቤት ውስጥ ታስሬ እንድውል ነው'ንዴ የምትፈልገው?››
አለችው በቁጣ።

‹‹አሁን እንዲህ የሚያስብል ነገር ምን መጣ?›› ሲል እሱም በተራው ቱግ አለ፡፡

‹‹አንተን ለማበሳጨት ብዬ አይደለም፧ እጅ እግሬን ታስሬ ቤት መዋል ስለማልፈልግ ነው››

‹‹የቤት ውስጥ ስራ አትሰሪም››

‹‹ምን?››

‹‹የልጆች ልብስ መስፋት፣ ወጥ መስራት፣ መጋደም››

‹‹አቤት አምላኬ›› አለች ካሮል አን በምሬት፡

‹‹እቤት መዋል ምንድነው ችግሩ?›› አላት፡፡

‹‹ቀኔ ሲደርስ እቤት መዋሌ አይቀርም፧ እስከዚያው ድረስ ግን ነጻ መሆን እፈልጋለሁ››

ኤዲ ብስጭት አለ፤ ከቤት መውጣት ፈልጎ ሰዓቱን ተመለከተና ‹‹ባቡር
ያመልጠኛል መሄድ አለብኝ›› አላት፡፡

ኤዲ በጣም ተናዷል ‹‹ባህሪሽን ማወቅ አቅቶኛል››

‹‹አየህ በአጥር ተከብቤ መዋል አልፈልግም›› አለች፡

‹‹እኔ ላንቺ ጥሩ ያሰብኩ መስሎኝ ነው››

ይህን ሀሳብ በማቅረቡ ጅልነት ተሰምቶታል፤ እሱ ይህን ያለው ለእሷ
ሻንጣውን ከመኝታ ቤት አምጥታ ሰጠችው፡ ኮቱን ለብሶ ሲጨርስ ቀና
አስቦ ቢሆንም እሷ ግን ያየችው እንደ ጭቆና ነው፡
ብላ ስታየው ሳም አደረጋት፡፡
‹‹እንደዚህ ተናደህብኝ አትሂድ እባክህ›› አለችው:

እሱ ግን መልስ ሳይሰጣት ወጥቶ ሄደ፡

አሁን ግን በሰው አገር ሆኖ በዓይነ ህሊናው ታየችው፤ ከዚህ በኋላ ተመልሶ በዓይነ ስጋ ያያት እንደሆን እያሰበ….......

ይቀጥላል
👍19
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አራት (4)



«ስትግባ እንዴት ሳልሰማህ ቆረሁ በል?» ስትል ጠየቆችው ።
«ቁልፍ አለኝ አይደል ፤ በሱ ነው የተጠቀምኩት » አላት።
«ልቀመጥ እችላለሁ?»
«መጠርጠሩሰ !... የሚበላ ነገር ያስፈልግሃል ?»

ማይክል ረጋ ብሎ ሄደና ጠረጴዛው ላይ የተቀመጠውን ሣህን ጎንበስ ብሎ እያዬና እሣህኑ ላይ የቀረውን ምግብ እሚመረምር እየመሰለ ፤ «ኣሃ ... ምንድን ነበር የተበላው ? ቸኮላት ነው?» ሲል እናቱን ጠየቀ። ማሪዮን ይህን ስታይ ደስ አላት ። ሆኖም ደስታዋን መገረም በመሰለ ሳቅ ገታችው። በልቧ ግን አንዳንዴ ልጅ ይመስለኛል ። ደሞም ልጅ ነው። አሁን የጠየቀው የልጅ ጥያቄ ነውኮ ስችል አሰበች ።የበላችውን ምግብ ነገረችውና እንዲመጣለት ይፈልግ እንደሆነ ከጠየቀችው በኋላ ፤ «ከፈለግህ ይምጣልህ ። ማንንም አስቸግራለሁ ብለህ አታስብ ። ማቲስ አሁንም እማድቤት ነው ያለችው » አለች። «ምናልባት የቀረውን እየጎራረሰች ይሆናል» ብሎ ሳቀ ። ይህን እውነት ሊሆን የሚችል ቀልድ ስትሰማ ማሪዮን ሳቅ አለች ። እና የመጥሪያ ደወሏን አንቃጨለች ።

አፍታ ሳትቆይ ማቲስ መጣች ። ጥቁር በወርቃማ ሀር የተዘመዘመ ልብስ ለብሳ ፊቷ በፈገግታ ተበርግዶ ። ማቲስ ሁሌም ስትጠራ እንዲህ ሆና ነው እምትቀርበው ። እድሜ ልኳን ሀብታሞችን ስታገለግል በመኖሯ የሚያስደስታቸውን ነገሮች እሳምራ ታውቃለች ።
«አቤት እመቤቴ» አለች ማቲስ ።
«ማቲስ ለሚስተር ሂልያርድ ቡና አምመጪለት እስኪ» አለችና ወደ ማይክል ዞራ «የሚበላ ነገርስ ምን ይሁንልህ የኔ ውድ ?» ስትል ጠየቀችው ። ራሱን በአሉታ እየነቀነቀ
«ቡና ... ቡና ብቻ ይበቃል» እላት
«እሸ እመቤቴ» አለች ማቲስ ። ማሪዮን ምንም መልስ አልሰጠችም ይህም ለቅፅበት ያህል
በማይክል እእምሮ ውስጥ ጥያቄ አመጣበት ። ይህ ጥያቄ ደግሞ ድንገት የተፈጠረ እልነበረም። ይህን ያህል ጊዜ አብሯት ሲኖር እናቱ እንድም ቀን ለአሽከሮችና ለቤት አገልጋዮች «እሰይ» ወይም «አበጀህ» ወይም ሌላ ይህን የመሰለ የምስጋና ቃል ስትናገር ሰምቷት እያውቅም ። ለምንድነው እንዲህ እማታደርገው? ይላል ። ምናልባት በሷ ቤት አገልጋይ ሁሉ ገና ሲፈጠር እሷን ሊያገለግል እንደተፈጠረ አድርጋ ስለምትቆጥር ይሆን ?! ይህንና ይህን የመሳሰሉ ጥያቄዎች መጡበት ። ከዚያም ፤ ምናልባትም ይልና መልስ ሊሰጥ ይሞክራል ። ስለአሰተዳደጓ የሰማውን ፤ ስለአኗኗሯ ያየውን ማሰብ ይሞክራል ።

ማሪዮን ሂልያርድ የተወለደችው እጅግ ሀብታም ከሆነ ቤተሰብ ነው ። ሰለዚህ ከተወለደችበት ጊዜ ጀምሮ ባካባቢዋ አሽከሮችንና አገልጋዮችን ስታይ ነው ያደገችው ። ምንም እንኳ ገና በሶስት አመቷ እናቷና ታላቅ ወንድሟ በመኪና አደጋ ቢሞቱባትና ብቸኛ ህፃን ሆና ያደገች ቢመስል ማሪዮን ግን ብትወድቅ በሚያነሱ ፤ ብታለቅስ በሚያባብሉ አገልጋዮች ተከባ ነው ያደገችው ። የወንድሟ መሞትም ጎዳት ሊባል እይችልም ። ቢኖር የኮተር የአርኪቴክቸር ድርጅች ወራሽ እሱ ነበር የሚሆነው ።የሱ ሞት ግን የዚህ ግዙፍ ድርጅት ብቸኛ ወራሽ ለመሆን አበቃት፡፡ ዛሬም ቢሆን በፀሀፊዎችና በአማካሪዎች ተከባ ሲያዘጠዝጡላት ነው እምትታየው ። ስለዚህ አንድ ሰው ለፈጸመው ግልጋሎት ምን ብላ በምን መንገድ ጥቅሙን ተገንዝባ ምስጋና ልትሰጥ ትችላለች? ትምህርቱስ ? ኮሌጅ እንዴት ነው?» አለች እናቱ ከሀሳቡ እያናጠበችው ።
«ለአምላክ ምስጋና ይድረሰውና ልንገላገለው ነው ። ሁለት ሳምንት ያህል ። በቃ ! » አለ ማይክል ።
«ይገባኛል ፤ መቼም የምታኮራ ልጅ ነህ ። የዶክትሬት ዲግሪን ማግኘት የሚያስከብር ነገር ነው ። በተለይ በአርኪቴክቸር መሆኑ በጣም ያኮራኛል ። የልብ ልብ ይሰጠኛል» ። ምስጋናውን ሲሰማ ልክ እንደልጅነቱ ደስታና ሀፍረት የተቀላቀለበት ስሜት ተሰማው ። |
« ቤን አቭሪስ ደህና ነው?» .
«ዴህና ነው» አለ ከእፍረቱ ለመውጣት እየሞከረ ።
«ደግ ፤ በዚህ ሳምንት ውስጥ ልናነጋግረው እንሞክራለን… ስለሥራው ጉዳይ ማለት ነው ። ያው እስካሁን አልተነገረውም አይደለም?» አለች ማሪዮን ጉዳዩ ሚስጥር ሆኖ ይቆይ በማለቱ ማይክልን በልቧ ገና ልጅ ነው እንጂ ሥራውን እናቴ ፈቅዳልሀለች ማለት እየቻለ ድንገት መንገሩ ጥቅሙ ምንድነው? ! እንድትለው አድርጓታል ።
«አልሰማም ። ማንም አልነገረውም» አለ ማይክል። '
«አዎ ሳይሰማ መቆየቱ ጥሩ ነው » አለች ። «ደሞም የያዝንለት ቦታምኮ በቀላሉ የሚታይ አይደለም ። ትልቅ ቦታ ነው።»
«ለሱ ችሎታ ያ ቦታ አይበዛበትም
«ያ እንዲሆን ተስፋ አደርጋለሁ ። » ድንገት አየት አድርጋው፤ «አንተስ እንዴት ነው ? ተዘጋጅተሀል በነገራችን ላይ ቢሮህ ተዘጋጅቶ ወደ ማለቁ ነው። ስለ ቢሮው ሲያስብ አይኖቹ በደስታ ሲያንፀባርቁ ይታይ ነበር ። ቢሮውን አይቶታል ፤ ወዶታል ። አሰራሩ ድሮ የአባቱ ቢሮ የነበረውን ሲመስል ፤ የውስጥ ድርጅቱ ፣ መቀመጫው፣ ጠረቤዛውና የመሳሰለው ሁሉ ከለንደን የመጣ ነው ። ራሷ እናትየው ናት ባለፈው ለእረፍት ሄዳ በነበረበት ጊዜ አሰርታ ያመጣችው።

«እኔ ዝግጁ ነኝ ፤ ቢሮው ማለቁ ደግሞ ጥሩ ነው ።ብቻ የውስጡን ዝግጅት በሚመለከት አንዳንድ ነገሮች አሉ ። በመጀመሪያ የግድግዳውን ቀለም ልየው ብዬ ነው» አለ ።«ምንም መጨነቅ አያሻህም ፤ ግድግዳው ላይ ስለሚሰቀሉ ስእሎችና ስለሌላውም እኔው ራሴ አስቤበት አዘጋጅቼልሀለሁ አለች ማሪዮን።

እሱም ይህንኑ አድርጓል ። ናንሲ ንድፎችን መራርጣለት የሚሆኑትን ለይቶ አስቀምጧል ። ናንሲ ትዝ ስትለው ማሪዮን ደግሞ ስለግድግዳው ንድፎች ዝግጅት ስትነግረው ደርሶ ደሙ ልውጥ አለ ። ይህ እንደሆነ እናትዮዋም ወዲያው ገባት ። «እማዬ» አለ አጠጎቧ እየተቀመጠና በረጅሙ የመከፋት ትንፋሽ እየተነፈሰ ። በዚህ ጊዜ ማቲስ ቡናውን ይዛለት ገባች።፡ ቡናውን ስታቀርብለት ፤ «አመሰግናለሁ ፤ ማቲስ » አለ ማይክል ። «ምን አድርጌ ምስጋና ሚስተር ሂልያርድ» አለች ማቲስ በጣም ደስ ተሰኝታ።

ማይክልን ትወደዋለች ። ሁኔታው ሁሉ ሰብዓዊነት የተቀላቀለበት ነው እንጂ እንደጌታ አይደለም። አለችንጂ….
«ሌላ እሚያስፈልግ ነገር አለ ፤ እመይቴ?» አለች ማቲስ በምታውቅበት ትህትና ። «ምንም አያስፈልግም ። እንዲያውም ማይክ ቡናህን ያዝና እቤተ መጻህፍታችን ብንገባ ይሻላል» አለች ማሪዮን። እሺ ብሎ ወደ ቤተ መጺሕፍት ገቡ።

ቤተ መጸሕፍቱ ውስጥ ካራቱ ማእዘን ግድግዳዎች ሁለቱ በመጻሕፍት ግጥም ብለው ሞልተዋል ። ባንድ ወገን ምድጃ ሲኖር አንደኛው ግድግዳ ግን ያባቱን ስዕል ይዟል ። ከሌሎቹ የአባቱ ምስሎች ሁሉ ማይክል ይህን ምስል ይወደዋል ። አባቱን ቅረቡኝ ፤ ቅረቡኝ የሚል ሆኖ የሚያየው እዚህ ምስል ላይ ብቻ ነው። ስለዚህ በልጅነቱ ወደዚህ ክፍል እየገባ አባቱን ሊቀርብና ድምጹን አሰምቶ ሊያነጋግረው ይሞክር ነበር፡፡ አንድ ቀን ይህን ሲያደርግ እናቱ ደረሰችበት ።።« ከምስል ጋር መነጋገር የማይሆን ነገር ነው ። ቂል ያስመስሳል» አለችው። ሆኖም ከጥቂት ጊዜ በኋላ እዚህ ስዕል ስር ተንበርክካ ሽቅብ እየተመለከተችው ስታለቅስ እሱም በተራው አይቷታል ።
👍162🥰1
ምቹ ወንበሯ ላይ ፊቷን ወደ ምድጃው አድርጋ ተቀምጣ በውጋጋኑ ሲያያት ቆንጆ ሆና ታየችው ። እድሜ እየዳመነ ሲሄድ ቁንጅናዋ እየደበዘዘ ሂዷል ። ማሪዮን ሂልያርድ የሞላላት ሴት ወይዘሮ ናት ። እሱ እንኳ ሲያውቃት ምን ያህል ውብ ነበረች ?! እንደበጋ ሰማይ የጠራ ሰማያዊ ቀለም የነበራቸው አይኖችዋ ዛሬ ወደ ግራጫነት እየተለወጡ ነው… ደርሶ ክረምት የገባ ይመስል። አንዴ ልክ የማይክልን ፀጉር ይመስል የነበረው ነጣ ያለ ወርቃማ ፀጉሯ ዛሬ ግራጫ ሆኗል። ዛሬ እድሜና ሥራ ሁሉንም ቀስ በቀስ እየወሰዱባትና እየቀሟት በመሄድ ላይ ናቸው ። የዛሬ ሃያ አምስትና ሃያ ስድስት ዓመት እንዴት ታምር ነበር?! ፎቶ ግራፎችዋን አይቷል ። እሱ የተወለደው የዛሬ ሃያ አራት አመት ነው። ልክ በሰላሳ ሶስት አመቷ።

«ድንገት ስትመጣ አንድ ነገር ልትነግረኝ የመጣህ እንደሆነ የገባኝ መስሎኛል ። ያጋጠመህ ችግር አለ ማይክል ?» አለችና ከሀሳቡ መለሰችው ። እሷም ራሷ ስታስብ ነበር ።ምን ሆኖ ይሆን አንዱዋ አረገዘችበት ይሆን? ወይስ መኪና ተጋጨበት ወይስ በመኪና ሰው ገጭቶ ገደለ? ይህን የመሳሰሉ ጥያቄዎች ።፡ ርግጥ ችግር የለውም … እሱ ደህና ይሁን እንጂ ሁሉም ነገር መፍትሄ ያገኛል ። እሷ እያለች ችግር ሊያስጨንቀው አይችልም ።
« ችግር . . . ችግርስ አላጋጠመኝም ግን አንድ ልንመካከርበት የምፈልገው ነገር አለ ። »
‹‹ልንመካከርበት» ማለቱ ደስ አላለውም « ልንገርሽ» ማለት ነበረበት ። ተሳሳትኩ አለ በሀሳቡ ።
«ካሰብኩበት በኋላ » አለ «እንግዲህ ሁለታችንም የልባችንን መነጋገር ይኖርብናል ።
«እንዳባባልህኮ አብዛኛውን ጊዜ ከልብ የማንነጋገር ነው ያስመሰልከው ።፡ »
«ነው ። አሁንም ቢሆን አሉ እንዳንድ ነገሮች ፤እኔም የልቤን የማልነግርሽ ፤ አንቺም የልብሽን እማትነግሪኝ ። ስለናንሲ የየልባችንን በልባችን እንጂ የልባችንን አውጥተን ተነጋግረን አናውቅም ፤ አይደለም እማዬ ? »

«ናንሲ ? ናንሲ አልከኝ?» አለች ድምጽዋ ባዶ ነበር ። ንቀቷን ግን ሰምቶታል ። ብድግ ብለህ በጥፊ አልሳት የሚል ስሜት ተናነቀው ። ‹‹አዎ ናንሲ። ናንሲ ማክአሊስተር ። ጓደኛዬ››
«አ... ትዝ አለችኝ» አለችና ስኒና ማንኪያ ኢያጫወተች ትንሽ ዝም ካለች በኋላ « ታዲያ ስለናንሲ የልባችንን ያልተነጋግርነው መቼ ነው ?» ስትል ጠየቀች ። «ምን ጊዜም ። አንድም ቀን የልባችንን ተነጋግረን አናውቅም ። አንች ሁልጊዜ ናንሲ እንደሌለች ፤ እንዳልተፈጠረች ለማድረግ ስትሞክሪ አይሻለሁ። እኔ ደግሞ ስለናንሲ እንዳልነግርሽ ድንገት እንዳትበሳጪ እያልኩ እሰጋለሁ ። ስለዚህ ተነጋግረን አናውቅም ፤ አሁን ግን ግድ መነጋገር አለብን ። ናንሲን ለማግባት ወስኛለሁ ። በዚህ በአስራ አምስት ቀን ውስጥ ጋብቻችንን እንፈጽማለን» አለና በኃይል ተነፈሰ ። ወዶ ኋላው ተለጠ
ጠና ተቀመጠ ።

«ነገሩ እንዲያ ነው? አለች ማሪዮን ቀዝቀዝ ብላ ።፡ ‹ገባኝ፣ ግን ምነው ተጣደፋችሁ ? ምን ተፈጠረ? አረገዘች ወይስ»
«እርግዝና? አላረገዘችም»
«እድለኛ ነን አትለኝም ። ግን እንዲያ ካልሆነ ለምንድነው እምትጋቡት? ማለት ለምንድነው ጋብቻው በድንገት በዚህ ባሥራ አምስት ቀን ውስጥ መፈጸም አለበት ብላችሁ የወሰናችሁት?»
« ምክንያቱም ያኔ ትምህርቴን እጨርሳለሁ ። ምክንያቱም ያኔ ወደኒውዮርክ መመለሴና እዚህ መኖሬ ስለሆነ መጋባታችን አስፈሳጊ ስለሆነ...»
« አስፈላጊ ስትል ለማን ? » አለች ማሪዮን እንደበረዶ በሚቀዘቅዝ ድምፅ ። ያ ድምፅዋ ማንንም ሰው ተስፋ ሊያስቆርጥ ይችላል ።
«‹ ለኛ ... ለኛ ስለሚያስፈልግ ፤ ለሁላችን »
« ለኔ ግን አስፈላጊ አይደለም ፡፡ ጋብቻችሁ አያስፈልገኝም ፡፡ » አለች ።ትንሽ ለስለስ ያለች በመምሰል እንዲሀ ስትል ቀጠለች …

‹‹በነገራችን ላይ ከዚህ በፊት የፎርድን ማዕከል ስንሰራ ድርጅታችን ምን ያህል ትርፍ እንዳገኘ ታውቃለህ ። ያንን ማዕከል ያሰሩት ሰዎች በሽፋንም ቢሆን የሚሳተፉበት አንድ የህክምና ማዕከል ሳንፍራንሲስኮ ውስጥ ለማሰራት ኮንትራቱን ወስደን ጨርሰናል ። ለዚያ ሥራ ሌላ ሰው የለኝም ። እምነቴን ሁሉ የጣልኩት ባንተ ላይ ነው ስለዚህ አትችልም ። ለሚስት ጊዜ ያለህ አይመስለኝም ። ሚስት በኋላ ሰርተህ ጠንከር ካልክ በኋላ ታገባለህ ። እውነቱን ለመናገር ማንም ትሁን ማን፤ እንዲህ ተቻኩለህ እንድታገባ አልፈልግም ፡። እንድትቆይ እፈልጋለሁ »

« ግንኮ እማዬ፤ ናንሲ ሥራ እምትከለክለኝ ሳትሆን እምትረዳኝ ልጅ ናት… ለሁላችንም ትልቅ ስጦታ ናት እኮ »
‹‹ትሆን ይሆናል ። ምናልባትም ደህና ስጦታ !... ለመሆኑ ግን የሚፈጠረውን አጉል ወሬ አስበህበታል»
« የምን አጉል ወሬ?»
« ማንነቷን አውቀሃል? ስለአስተዳደጓስ ነግራሃለች ? »
« ማን እንደሆነች ስትይ ምን ማለትሽ ነው ?»
« ታገሰኝና ሁሉን ነገር ግልፅ አደርግልሃለሁ ።» ይህን ብላ የቡና ሲኒዋን አስቀምጣ ተነሳችና ከጽሕፈት ጠረጴዛዋ ኪስ አንድ ፋይል አውጥታ ሰጠችው ።*
«ምንድነው ይሄ ደሞ?»

«ሪፖርት ነው ፤ አንብበው።ማንነቷን ፤ ማለት የሰአሊዋን ጓደኛህን ማንነት አጥንቶ የሚነግረኝ ሰው በግል ቀጥሬ ያገኘሁት ሪፖርት ነው ። ይህን አይቼ ካወቅኳት በኋላ ነገሩ ሁሉ የማይሆን መሆኑ ገባኝ። ቁጭ በል እባክህ ። እና አንብበህ ራስህ ተረዳ » አልተቀመጠም እንደቆመ ማንበብ ቀጠለ። ሪፖርቱ ስለናንሲ ማክአሊስተር ወላጆች ይናገራል ።

የናንሲ አባት የሞተው ናንሲ ገና ሕፃን እያለች ሲሆን ያረፈበት ቦታም በእስር ቤት ውስጥ እንደሆነ ይናገራል ። የናንሲ እናት አባትየው በሞተ በሁለተኛው ዓመት ላይ እንዳረፈች ሪፖርቱ ይገልፃል ። አባትዬው እስር ቤት የገባበት ምክንያት መሳሪያ ታጥቆ ዝርፊያ በመፈጸሙ እንደነበረ በሪፖርቱ ላይ ተገልጺል ። እንዲሁም እናቱ የሞተችው መጠጥ ታበዛ ስለነበረ በዚሁ ጠንቅ እንደሆነ ተዘግቧል ። ወዘተ…
👍16
ማይክል ከዚህ በላይ ሊያነብ አልቻለም።በዚያ ላይ ደግሞ፣ «እንዴት ዓይነት ጥሩ ሰው እንደመረጥክ ታየህ የኔ ልጅ » የሟለው የማሪዮን ድምፅ በጣም አናደደው። ማሪዮን ይህን ስትል ፋይሉን አሽቀንጥሮ ጣለና
«እንዲህ ዓይነት ትርኪ ምርኪ አላነብም !» አለ።
«ሚስትህ ስትሆን ግን አይቀፍህም » አለች ማሪዮን ።
«እሷ እንዲህ አይደለችም ። ወላጆችዋ ምንም ይሁኑ ምን እሷ አይደለችም ! አባቷ ቀማኛ ቢሆኑ ፤ እናቷ ሰካራም ብትሆን የናንሲ ጥፋት እምኑ ላይ ነው ?»
«ጥፋት አልከኝ ? ጥፋት የለባትም ግን ከነዚህ ሰዎች ስለተ ወለደች አልታደለችም ። አልተባረከችም ። አንተም እሷን ስታገባ ያው ነው ልጄ !ምን ነካህ ? እደግ እንጂ። ይህ ሀብትኮ በቀላሉ አልተገኘም።ስንት ጥረት ተደርጐበታል ። እና በአጉል ወሬ ለአጉል ሴት ስንል ይፈታ ነው እምትል እንዴ። ዛሬ ትልቅ ሰው ነህኮ፡፤ ለኑሮ አስብ ። በኔ በኩል ነገሩን መርሳት አለብህ ከሚለው የተለየ ምንም አማራጭ አይታየኝም» አለች ማሪዮን ።
«ርሳው ? ይረሳዋል ብለሽ አስቢ !» ድንገት ነበር እንደብራቅ የጮኸው ። «ዘላለም አለሜን ያንችን ግንባር ሳይና ያንችን ፈቃድ ስፈጽም መኖር እንደማልችል አታውቂም እንዴ እናት አለም ! የለም አልችልም ! እንደፈረስ ገርተሽ ፤ ሰንገሽ ድርጅት የምትይውን ጋሪ የሚጐትት እንሰሳ ልታደርጊኝ ነው እንዴ እምትፈልጊው ? ቢፈልግ ውርስ የምትይው ነገር እንጦርጦስ ይውረድ ። እኔ ምፈልገው ስራ ነው። እድርጅት ውስጥ ተቀጥሬ እሰራለሁ። ከዚያ በላይ ምንም አልፈልግም። ከዚያ በላይ ምንም አትፈልጊብኝ። ተቀጣሪሽ ስሆን ስራዬን እንጂ ሕይወቴን በሙሉ ያንቺ ልታደርጊው አትችይም ። ስለዚህ በሌላ በኩል ያሻኝን የማድረግ መብት እለኝ ። የወደድኳትን የማግባት መብት አለኝ። »
‹‹ማይክል!››
በዚህ ጊዜ ጆርጅ ኮሎዌይ ገባና አቋረጣቸው፡፡ ኮሎዌይ የማረዮን ሂልያርድ ቀኝ እጅ ነው ። የማይክል አባት ሲሞትና ማሪዮን ሂልያርድ ስራ እስኪያጅነቱን ስትረክብ ስሙ የሷ ይሁን እንጂ የኮተር ሂልያርድ ስራ አስኪያጅ ጆርጅ ነበር ። ጆርጅ እድሜው በሃምሳና በስድሳ መካከል የሚገኝ ግርማ ሞገስ ያለው ሰው ነው። በነገሩ ዝግተኛ ሲሆን ፍርዱና ውሣኔውም ማመዛዘን የተሞላ ነው ። ጆርጅ ኮሎዊይ የማሪዮን ሂልያርድ የቅርብ አማካሪና የሚስጢሯም ተካፋይ ነው ። ጆርጅ የማያውቀው ነገር የለም ። ለዚህ ነው ሲገባ የፊቷን መገርጣትና ጠቅላላ ሁኔታዋን ሲያይ ጮክ ብሎ «ማይክል !» ያለው ። ግን በኋላ ለስለስ ብሎ፤
«ማሪዮን ደህና ነሽ ?» አለ ። ይህን የጠየቀው በከንቱ አልነበረም ። ማሪዮን ሂልያርድ እከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የደም ግፊት ከያዛት ቆይቷል። ይህን ግን ሐኪሟና ጆርጅ ኮሎዌይ ካልሆነ ሌላ ማንም ሰው አያውቀውም ። በተጨማሪ የልብ ድካምም አለባት።
«ደህና ነሽ ወይስ ?»
«ደህና ነኝ ። አዎ ደህና ነኝ» አለች «ደህና አመሸህ ጆርጅ
«ደህና ደህና. .. ጥሩ ጊዜ አይደለም የደረስኩት መሰለኝ? ንግግራችሁን ሳትጨርሱ ።»
«አይ ደህና... እንዲያውም ጥሩ ጊዜ ነው የደረስከው ። እኔ መውጣቴ ነበር» አለ ማይክል ። «ደህና እደሪ›› ብሎ ወጣ።
«ማይክል ነገ ስልክ ደውዬ እነግርሃለሁ ሁሉንም በስልክ እንጨርሳለን›› አንድ አንጀት የሚቆርጥ ነገር ሊናገራት ፈለገና ተወው። ምን ጥቅም አለው ብሎ።
«ማይክል….››
መልስ አልሰጣትም ። ዝም ብሎ ጆርጅን ጨብጦ ወጣ። ዞር ብሎም አላየ። ዞር ብሎ ቢያይ ኖሮ በጆርጅ ፊት ላይ የሚታየው መጨነቅና የእናቱን ድክምክም ማለት ማየት ይችል ነበር ።

"ምን ተፈጠረ ? » አለ ጆርጅ
«የሆነ እብደት ይዞታል ፤ የእብድ ስራ ካልሰራሁ እያለ ነው»
‹‹አደርጋለሁ ስላለ ብቻ ላያደርገው ይችላል።ሁላችንም ይህን አደርጋለሁ ፤ያን እያልን አንዳንዴ መፎከራችን ያለ ነው »
«ድሮ እዎ። በኛ ጊዜ መፎከር ነበር ፤የዛሬ ልጆች ግን ማድረግ ነው » አለች ማሪዮን ።» በጣም ደክማለች።
«መድሐኒት ወስደሻል ዛሬ?»አንገቷን በአሉታ ነቀነቀች ።
‹‹የት ነው ያሰው?»
‹‹እቦርሳዬ ውስጥ»

መድሐኒቱን መርጦ ሰጣት። ቀስ እያለ ስልብ አድርጓት ኖሮ ውሀውን አስጠግቶ ሲያስውጣት አይኗ ተገለጠ ። «ጀርጅ ፤ አንተ ባትኖር ምን ይውጠኝ ነበር ? » አለች ፈገግ ብላ።
«እኔስ ያላንቺ ምን ይውጠኝ ነበር ማሪዮን። ሳስበው እንኳ እጨነቃልለሁ ። አሁን ልሂድ ትንሽ አረፍ ትይ ?
«ብቻዬን ከሆንኩ ስስማይክል እያሰብኩ ብስጭት ብቻ ነው እማተርፈው »
‹‹ምንድነው ? ለድርጅቱ አልስራም አላለም አይዶል ? ነው ወይስ...!»
«አላለም ፤ ነገሩ ሴላ ነው››
ያ ከሆነ ስለልጅቱ ጉዳይ መሆን አለበት ፣ አለ ጆርጅ ኮሎዌይ በሃሳቡ ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍15👏1
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_ሦስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


የአዳራሹ በሮች ወለል ብለው ተከፈቱ ወርቅማው ብርሃን ደረጃዎቹን አጥለቀለቃቸው » ሁለት የወንድ አሽሮች ከበሩ ቆሙ አንዱ ከነበረበት ሲቆም
ሌላው ወደ ሰረገላው ተጠጋና ሳቤላን ደግፎ ሲያወርዳት ፒተር መሆኑን 0ወቀችው » ምን ያደርጋል ፒተር እንደምነህ ? " የማትው ነገር ! ለጊዜው የምትናገረውም ጠፋት ድንግርግር አላት ድምጿም ድክምክም አለ "

“ ሚስዝ ካርላይል ከቤት አሉ ?” አለች "

“ አዎን አሉ "

ወዲያው ጆይስ ልትቀበላት ወደፊት ቀረበችና “ማዳም ቬን ይመስሉኛል ? አለቻት " " በዚህ በኩል ይምጡ ” አለቻት በአክብሮት።

ሳቤላ ግን ዕቃዋን ያወረደው አሽከር በትክክል መግባታቸውን የምትመለከት መስላ ከኮሪደሩ ቆም ብላ ጠበቀች " ዋናው ሐሳቧ ግን ጆይስ ወደ ሚስተር ካርላይልና ሚስዝ ካርላይል ዘንድ የምታስገባት ስለ መሰላት ጥቂት 0ረፍ ለማለት ነው » ጆይስ ግን እሳት ይነድበት ከነበረው ሳሎን አስገብታ ሳሎንዋ እሱ መሆኑን ነግራ “ መኝታዎን እስካሳይዎ ድረስ ምን ልዘዝልዎ ? አለቻት

“አንድ ስኒ ሻይ” አለች ሳቤላ " ጆይስ ሻይ እንዲዘጋጅ አዘዘችላትና ሔዶች" ሳቤላም ልቧ እየመታ ዱሮ የራሷ ከነበረው ክፍል ዐልፋ ወደ ፎቅ ወጡ " የበፊቱ
መኝታ ቤቷና መልበሻ ክፍሏ ተከፍተው ስለ ነበር በናፍቆት አየቻቸው " ወደ ሌላ ባለቤት ከመዞራቸው በቀር ውበታቸውና ያማረ ዝግጅታቸውን ሁሉ አልቀነሱም "የነበሩት ጌጦቻቸው አልተነኩም ። ከሶፋው ላይ አንድ መጽሐፍ እና አንድ ያንገት መደረቢያ » አልጋው ላይ ተቀይሮ የተጣለ የመስለ አንድ የሐር ቀሚስ ይታያሉ " ቀጠለችና ዱሮ ሳቤላ ሙሽራ ሁና ወደ ኢስት ሊን በመጣች ጊዜ ' ሚስ ኮርኒሊያ በኋላ ለቃው ወደ ምድር ቤት እስክትወርድ ድረስ ይዛው ወደ ነበረው ክፍል ጆይስ ፊት ፊት አየመራች ሳቤላ እየተከተለች ገቡ " ዕቃውን ከጋሪው ያወረደውና አንድ ረዳቴ ሆነው አስገቡት " ጆይስ የሚያስቀምጥበትን አሳየችው " ሰውየው ጓዟን አደራጅቶ የታሰሩትን ሳጥኖች ፈትቶ ወጣ " ሳቤላ እንደ ሐውልት ድርቅ ብላ ቁማ ቀረች " ልብሷን ለመቀየር እንኳን አልሞከረችም "

“ ሌላ ምን የማደርግልሽ ነገር አለ ?” አለቻት ጆይስ »


ከመድረሷ ጀምሮ እንዳትታወቅ መሥጋት የጀመረችው በተለይም የጆይስን ንቁ ዐይን በጣም ስለ ፈራች ነበርና ቶሎ አንድትወጣላት ብላ ምንም እንደማትፈልግ ነገረቻት

“ የምትፈልጊው ነገር ቢኖር ደውይ ሐና የምትፈልጊውን ትታዘዛለች " ብላት ወጥታ ሔደች " በሩ እንደገና ሲከፈት ወይዘሮ ሳቤላ ቬን ቆቧን አውልቃው ነበር » ቶሎ አለችና አንሥታ እንደገና ከራሷ ላይ ደፋችው በሩን የከፈተችው ጆይስ ነበረች "

“ ብቻሽን ወደታች ለመውረድ መንገዱ ይጠፋሽ ይሆን ማዳም ? አለቻት።

“አይጠፋኝም" አለች ሳቤላ "ወይ ጉድ ሳቤላ ኢስት ሊን ገብታ መውጫና መግቢያ ሊጠፋት !

ወይዘሮ ሳቤላ ቀስ ብላ ልብሷን ቀየረች ምንም ቢሆን የባለቤቶቹን ዐይን
ማየቱ ላይቀርላት ጊዜ መውሰድ ጥቅም እንደሌለው ተሰማት " በተፈጥሮም ሆነ በጥበብ ኃይል ፍጹም ተለውጣ ሌላ ስለ መሰለች የመታወቅ ሥጋቷ እንኳን ይህን ያህል አልነበረም ይሁንና እንባዋ አንድ ጊዜ ከፈነዳ ጨርሳ ከራሷ ቁጥጥር ውጭ
እንደምትሆንና ነገሩ ሁሉ እንደሚበላሽ አሰበች " ገንፍሎ የመጣባትን የትዝታና የሆድ ብሶት ስሜት በብዙ ትንንቅ ገታችው " በርግጥ ዓለሟን አይታ ወደ አደገችበት የትዳርን ክብር የባልን ፍቅር ወደ አጣጣመችበት ቤቷ ወደ ኢስት ሊን እንዲሁ ሁና መመለስ መራር ፈተና ነው አስጨናቂ የመንፈስ ሽብር ነው " አሁን ግን
ከመቻል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም ስለዚህ ራሷን ተቆጣጥራ የተደቀነባትን ፈተና
ተቀብላ ለመቻል ትዕግሥትንና ብርታትን ለማግኘት ከአልጋዋ ጎን ተንበርክካ ጸለየች።

ከዚህ በላይ ለመቆየት
ምክንያት አልነበራትም
ስለዚህ ጧፍ እያበራች ደረጃውን ወርዳ ወደ ሳሎኑ አመራች ስትገባ ሁሉ ነገር ተዘጋጅቷል " የሻይ ማቅረቢያው ከጠረጴዛው ተቀምጦ የሻዩ ጀበና ይንሿሿል ።

ሻይዋን አሰናድታ የራቧን ያል በላች የተለያዩ ሐሳቦች በአእምሮዋ ይመላለሱባት ጀመር ።ልጆቹ ከየትኛው ክፍል ይሆኑ ? ሚስተርና ሚስዝ ካርላይል ራት
እየበሉ ይሆን ? ደወሎች አሁንም አሁንም ሲደወሉ አሽከሮች ወዲያ ወዲህ ሲሉ ትሰማለች " እሷም በልታ አበቃችና ደወለች።

አንዲት አለባበሷ የጸዳ ነቃ ያለች ግንባረ ፍት ልጅ መጣችና ዕቃውን
አነሣች ጆይስ እንዳለችው የሳሎኑ ሠራተኛ ያስተማሪቱ ተላላኪ የተባለችው ሐና ነበረች " ሳቤላ ብቻዋን እንደተቀመጠች አንድ ድምፅ ሰማች ከመደንገጧ
የተነሣ ልቧ ደረቷን ሰንጥቆ የሚወጣ መስሎ ዘለለ ኤሌክትሪክ የነዘራት ይመስል ከተቀመጠችበት ወንበር ብድግ አለች ።

ነገሩ ማንንም የሚያስደነግጥ አልነበረም የሰማችው ድምፅ የልጆች ንግግር ነበር የልጆቿ!ምናልባት ልጆቹን ወደ እሷ ዘንድ እያመጧቸው ይሆን ? ከጭንቀቷ የተነሣ እንደ ወናፍ ከፍ ዝቅ የሚለው ደረቷን በእጀዋ ድግፍ አድርጋ ያዘችው"

እሱስ ከክፍል ክፍል ሲተላለፉ ኖሯል የስማቻቸው ድምፆቹ ቀስ በቀስ ጠፉ።ምናልባትም ራት በልተው ወደ መኝታቸው እየሔዱ ይሆናል አዲሱን ሰዓቷን አየች"
አንድ ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር የዱሮውን በዚህኛው ለውጣዋለች ከድሮዎቹ ጥቃቅን ጌጦች ሁለት ብቻ አስቀርታ ሌሎቹን ወደ ኢስት ሊን ካመጣቻቸው እንዳይታወቁባት ፈርታ በመሸጥ ወይም በመለወጥ ጨርሳቸዋለች " ያስቀረቻቸው ሁለት
ጌጦችም አንድ በትንሹ የተሠራ የናቷ ምስል ነው "
ሌላው እሷና ፍራንሲዝ ሌቪሰን መጀመሪያ ሲገናኙ በድንገት የተሰበረው ትንሽ የወርቅ መስቀል ነው እንደ
ሚታወሰው ይህ ባለ ሰባት አረንጓዴ ዕንቁ ቀለበት የናቷ ስጦታ ነበር ሁለቱን ነገሮች ከሷ ልትለያቸው አልፈለገችም ስለዚህ በጥንቃቄ አሽጋ ማንም በቀላሉ አንዳያያቸው ከልብስ ሳጥኗ ውስጥ በሥር አስቀመጠቻቸው » አሁን ሰዓቷን እንዳየች ወዲያው ፒተር ገባ።

ወደ ላሎን መሔድ ትችያለሽ ?” አላት
ምናልባት አልደከመሽ እንደሆነ እሜቴ ሊያነጋግሩሽ ይፈልጋሉ አላት። ዐይኗ ጭጋግ ለበሰ ያ መራራ ስዓት ደረሰ ሚስተር ካርይልን ፊት ለፊት
ልትግናኘው ነው " ፒተር ከፍቶ በያዘው መዝጊያ ዐልፋ ሔደች » ፊቷና ከንፈሮቿ 0መድ እንደ ለበሱ ተሰማት ፊቷን ከሰውየው ፊት ዘወር አደረገችው "

ሚስዝ ካርላይል ብቻቸውን ናቸው ? አለችው ዋናው ጥያቄዋ ግን የሚስተር ካርላይልን መኖር ለማወቅ ነበር።

" ብቻቸውን ናቸው " ጌታዬ ዛሬ ከውጭ ራት አለባቸው ባልሳሳት አንቹ ማዳም ቫይን መሰልሺኝ ?አላት በእንግሊዝኛው አባባል መምጣቷን ሊነግር የሳሎኑን የመዝጊያ እጀታ እንደ ጨበጠ »

አሷም በፈረንሣዊኛው አጠራር “ ማዳም ቬን ” ብላ አረመችው።

“ ማዳም ቬን መጥተዋል
አለ ፒተር እንግዳይቱን ወደ
ውስጥ እንድትገባ በእጁ አመለከታት ባርባራ በቀንዲሉ ብርሃን ፊት ለፊት ተቀምጣለች አንድ ጊዜ ሳቤላ ከባሏ ጋር ሁና ከቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ባርባራን አይታት ነበር “ ማን መሆንዋን ሚስተር ካርላይልን ጠይቃው ባርባራ ሔር ናት ያላት ጊዜ ከነበረችበት ሁኔታ የጨመረች አትመስልም በዚያን ጊዜ ባርባራ ሔር
ነበረች «ዛሬ ባርባራ ካርላይል ሆናለች " ያን ጊዜ ሳቤላ ካርላይል የነበረችው ደግሞ ዛሬ ያ ሁሉ ተገላብጦ ሳቤላ ቬን ሆናለች "
👍11