አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ሳቤላ ባርባራ ሔርን እንደዚህ ምሽት አምሮባት አይታት የምታውቅ አልመ
ሰላትም። ባርባራ ከሁሉ የምትወደውንና ለሷም የሚስማማትን ሰማያዊ የማታ ልብስ ባንገቷ የወርቅ ሐብል በክንዶቿ የወርቅ አምባሮች አጥልቃለች » የሚያምረው ፊቷ እንደ ወትሮው ይስባል " ጉንጮቿ የጽጌረዳ አበባ መስለው ያሳሳሉ " ዐይኖቿ
ይንቦግቦጋሉ ላመል ቀላ ያለው ጸጉሯ ብዛቱ ከፊት ለፊቷ ከተቀመጠችው ምጥጥ ካለችው ሴትዮ ጸጉር ጋር ሲነጻጸር ልዩነቱ የሰማይና የምድር ያህላል ።

ባርባራ ተነሥታ የጅ ሰላምታ ሰጥታ ተቀበለቻት መንገድ እንደ ዋልሽ ነሽ ጉዞው በጣም እንዳላደከመሽ ተስፋ አደርጋለሁ "

ሳቤላ እምብዛም ያልተሰማ ነገር አጉመተመችና የቀረበላትን ወንበር ጨለም
ወዳለው ጥግ ገፋ አደረገችው "

“ አመመሽ እንዴ ? አለቻት ባርባራ ፊቷ ያለመጠን ሲገረጣ ተመልክታ "

“ አላመመኝም ” አለች ዝቅ ባለው ድምጿ „ “ትንሽ ስለ ደከመኝ ነው ”
“እንግዲያው ሔደሽ ብትተኝና ነገ ጧት ባነጋግርሽ ይሻላል ?”

ሳቤላ ግን ባይሆን የመጀመሪያው ንግግር በፀሐይ ብርሃን ከሚሆን ይልቅ በሻማ ብርሃን እንዲሆንላት ፈለገች
“ ፊትሽ እኮ ባንድ ጊዜ ተለዋወጠብኝ እኔማ አሞሽ እንደሆነ ፈርቸ ነው ”

“ ብዙውን ጊዜ መልኬ እንደዚሁ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ግርጣቱ ይጨምራል"
ጤናዬ ግን ደኅና ነው "

“ በደንብ እንደምትስማሚን ሚስዝ ላቲመር ጽፋልኛለች " ለመጣሽበት ሥራም ለኑሮሽም እንደሚስማማሽ ተስፋ አደርጋለሁ " ኢንግላንድ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተቀምጠሻል ? ”

“ ዱሮ በልጅነቴ ”

ሚስዝ ላቲመር እንደ ፃፈችልኝ ባልሳሳት ባልሽም ልጆቶሽም ሙተውብሻል።

" ሁሉም አልቀውብኛል " አለቻት አሁንም ዛል ባለ ድምጿ"

አቤት ! አቤት የልጆችን ሞትስ አያምጣው እኔ ምንም ብሆን ከልጄ
መለየት አይሆንልኝም "

“ አዎን መራርና ሊችሉት የሚያስጨንቅ መከራ ነው " አለች ሳቤላ በልቧ
ታውጠነጥን ነበር " ሚስዝ ካርላይል እንግዳይቱ ስለምታስተምራቸው ልጆች ማስረዳት ጀመረች።

"ልጆቹ ሚስተር ካርላይል ከመጀመርያ ሚስቱ የወለዳቸው እንጂ የኔ አለመሆናቸውን ሚስስ ላቲመር ሳትነግርሽ አልቀረችም እናቲቱ ጥላቸው ስለ ኮበለለች
በተለይ ሴቱቱ ልጅ ደስተኛ አይደለችም " መቸም ነገሩ ሲያስቡት ያንቀጠቅጣል ።

ግን ሙታለች ሲሉ የሰማሁ መሰለኝ ” አለች ሳቤላ ርዕስ ለማስለወጥ በመፈለግ ሚስዝ ካርላይል ግን ያልሰማች ይመስል ነገርዋን ቀጠለች "

“ ሚስተር ካርላይል የሟቹ የሎርድ ማውንት እስቨርንን ልጅ እመቤት ሳቤላ
ቬንን አገባ " መቸም በጣም ቆንጆ ነበረች " ግን ለባሏ እስከዚሀም ደንታ የነበራት
አልመሰለኝም " ያም ሆነ ይህ ጥላው እልም አለች "

'' አቤት ! እንዴት ያለ አሳዛኝ ነገር ነው ? አለች ሳቤላ ታዛቢ ብቻ ሳትሆን
መናገር ስለ ነበረባት "

“ ማሳዘን ብቻ ? ያረመኔ የወራዳ ሥራ ነው እንጂ " በሕይወት ካሉት ወንዶችና
ባሎች ሁሉ ከሚስተር ካርላይል ጋር የሚስተካከል የለም " እሱ እንደዚህ ያለ ውለታ የሚከፈለው ሰው አልነበረም እሷ ግን በባሏ ላይ ሌላ መውደዷን ማንም አልጠረጠራትም ካርላይል ይህን ሁሉ ሳያስበው ከቤቱ በእንግድነት አስጠግቶት ከነበረው ከፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር ተመሳጥራ አብራው ኮበለለች ዛሬ ሰር ፍራንሲዝ ተብሏል " ለምን እንደዚህ እንዳደረገች አሁንም ወደ ፊትም ለሚስተር ካርላይልም
ሆነ ለሌሎቹ ሁሉ ምስጢር እንደ ሆነ ይኖራል ።

ማዳም ቬን መነጽሯን አስተካከለች "

በርግጥ ውርደቱ ከልጆቹ ጋር ይቀራል እናታቸው

“ሙታ የለ? ” አለቻት ሳቤላ ነግሯን ሳትጨርስ "

ሙታለች ግን ሰው ጣንቱን በልጆቹ በተለይ በሴቲቱ ላይ መቀሰሩን አያስቀረውም አሁንም አሁንም እናታቸውን ያነሣሉ ትለኛለች ዊልሰን አንቺ ግን
አደራሽን ለዚህ ነገር መንግድ አትስጫቸው ቢረሷት ይሻላል " ሚስተር ካርላይል ቢሆን እናታቸው ስለሆች ሊረሱለት ስለ አልቻሉ ነው እንጂ የሷን ትዝታ ከልባቸው ጨርሶ ፍቆ ቢያጤፋው ይወድ ነበር " ልጅቱም የናቷ ዕድል እንዳያገኛት ደኅና አድርገሽ እንደምታስተምሪያት አምናለሁ

“እሞክራለሁ ” አለች ሳቤላ ውስጥ ውስጧ ካነጋገሯ የበለጠ ግለት እየፈጃት
ልጆቹስ ከእርስዎ ጋር ተላምደዋል ?

"አይ ! እኔ ከልጆች ጋር መዳረቅ መቸ እወድና " የኔዎቹም ሲያድጉ ከሕፃናት መጫወቻቸውና ከትምህርት ቤታቸው እንዲውሉ እንጂ አላስቀርባቸውም "
በሞግዚት ሊሰሩ የሚችሉት ነገሮች ሁሉ በሞዚቲቱ ይፈጸሙ ሞግዚቲቱ ግን እምነት የሚጣልባት መሆኑን ማረጋግጥ ያስፈልጋል " የልጆቹን ጩኸት ጫጫታ ረብሻ ሁሉ እሷ ትቻለው ቦታዋ ከልጆች ጋር ከልጆቼ መዋያ ነው » ስለልጆቹ ለሌላ አሳልፌ የማልሰጠው ጉዳይ የሥነ ሥርዓት ሥልጠናቸውን ነው በየቀኑ
በተወሰነ ሰዓት ልጆቹን በዙሪያዬ ሰብስቤ መልካም ሥርዓት እንዲማሩ የሕይወት
ግዴታዎችን እንዲያወቁ ማድረግ አለብኝ " ይህ የናት ተግባር ነው » ሌላውን ሞግዚት ትሥራ » አንድ ልጅ የሚያግባባና ልብን የሚማርክ የእርጋታ ምክር ካልሆነ በቀር ሌላ ነገር ከናቱ መስማት የለበትም » እናቲቱ ደግሞ ሁልጊዜ ከልጆች
ጋር ከዋለች ሁልጊዜ መልካም ነገር ብቻ መናገር አትችልም "

ሳቤላ በሚስዝ ካርይል ሐሳብ ተስማማች "

እኔ መጀመሪያ ወደ ኢስት ሊን ስገባ የሚስተር ካርላይልን ልጆች አሁን
በምልሽ ሥልጠና ረገድ ሚስ ማኒንግ በደንብ ይዛቸው ነበር ትንሹን እንኳን ሳትተው ጧት ጧት ለአጭር ጊዜ ከእሷ ጋር ትይዛቸዋለች እኔም ይዞታዋ ጥሩ መሆኑን አይቼ ጣልቃ አልግባሁም እሷ ከሔዶች በኋላ ይኸው አንድ ወር መሆኑ ነው እኔ ራሴ ያዝኳቸው እሷ በጣም ተስማምታቸው ነበር አንቺም በሴቲቱ ልጅ ሙሉ ኃፊነት ይኖርሻል በትምህርት ሰዓትና ከዚያ ውጭም ካንቺ አትለይም
ጓደኛሽ ትሆናለች "

“ ኃላፊነቱን ለመቀበል ዝግጁ ነኝ " ለመሆኑ ልጆቼ ደኅና ናቸው ? ጤንነታቸው ጥሩ ነው ?

“ ደኅና ናቸው " ባለፈው ጊዜ ኩፍኝ ይዟቸው ነበር " አሁን ሲለቃቸው በትልቁ ልጅ ሳል ተከለበት " ሚስተር ዌይንራይት እያደገ ሲሔድ ይለቀዋል ይለናል "

“ እስካሁንም ያስለዋል ማለት ነው ?

“ አዎን ! ማታና ጧት ሲሆን ያስለዋል " ባለፈው ሳምንት ሚስ ካርላይል ዘንድ ሔደው ጥቂት አምሽተው መጡ ። ቀኑም ጨፍኖ ውሎ ነበር ከመጣ በኋላ
ልቡ ውልቅ እስኪል አሳለው እንደዚያን ዕለት ሆኖ ሲስል ሰምተነው አናውቅም" ሚስተር ካርላይል ሁኔታው በጣም አሳሰበውና ምግቡን አቋርጦ ወደ ልጆቹ ቤት በመሔድ ልጁ ይህን ሳሉን እስካልተወው ድረስ ማታ ጭራሽ እንዳይወጣ ብሎ ለጆይስ አጥብቆ ነገራት ።

“የሳንባ በሽታ ይሆን ? አለች ሳቤላ።

“ አይመስለኝም !ይዞታው የማይድን አይነት አይደለም » ሳሉም ቀስ በቀስ ይለቀዋል ነው የሚለን ሐኪሙ ዌይንራይትም " ልጆቹም ቢሆኑ ባባታቸው በኩል
በዘራቸው የወረደ በሽታ የለባቸውም " በናታቸውም በኩል የምጠረጥርበት ምክንያት የለኝም • በርግጥ እናታቸው ገና በልጅነቷ ብትቀጭም በአደጋ እንጂ "
በበሽታ አልሞተችም " ስንት ልጆች ነበሩሽ ማዳም ቬን አለቻት ድንገት ርዕሷን ለውጣ።

ሦስትና አንድ ባራስነቱ የሞተ ሕፃን

“አቤት አቤት ! አራት ልጅ ማጣት!በምን ሞቱ?” አለች ባርባራ እያዘነች
ሁሉም በየራሳቸው በሽታ አለቁ ”
አለች እንደ ልብ በማይሰማ ድምፅ
“ከባልሽ በፊት ነበር የሞቱት ? ካልሆነ መቸም ኀዘኑ አይቻልም " "
“ ሕፃኑ በኋላ ነው የሞተ " አለች በግንባሯ የተንቆረዘዘውን የላብ ጤዛ እየጠረገች ሰውነቷ እንደ ታወከ መንፈሷ እንደ ተረበሸ ያስተዋለችው ባርባራ ስለ
ልጆቿ ስለ አነሣችባት ሀዘኑን የቀሰቀችባት መሰላት።
👍9🔥1
“ ዝርዝር ነገር በመጠየቄ እንደትቀየሚኝ አምናለሁ ሚስዝ ላቲመር የጨዋ ልጅ እንደ ነበርሽ በጨዋ ደንብ እንዳደግሽ ጽፋልኛለች

“ አዎ ውልደቴም አስተዳደጌም ከጨዋ ቤተሰብና በጨዋ ደንብ ነበር።

“ አዎን የጨዋ Aጅ ያስታውቅ የለ ድኅነት እንዲህ ድንገት ግልብጥ ብሎ ሲወድቅብን ያሳዝናል መቸም እንዳሁኑ በአስተማሪነት እቀጠራለሁ ብለሽ ያላሰብሺው ነገር መሆኑን አልጠራጠርም ”

ፈገግታ ብጤ በሳቤላ ከንፈሮች ዘረር አለ ።

" የለም በጭራሽ አስቤው አላውቅም ነበር ” አለቻት "

“ ባለቤትሽ የተወልሽ ሀብት አልነበረም ?

“ እሱ ሲሞት ሁሉ ነገር አብሮ ሞተ " ባዶ እጄን ቀረሁ " አለቻትና ሚስዝ
ካርይል በአነጋገሯና በገጽታዋ አዝና ስትተክዝ አንዲት ሠራተኛ ገባች "

“ልጁ ልብሱ ወልቆለት እርስዎን ይጠብቃል ትላለች ሞግዚቲቱ ... እሜቴ"
አለች ሠራተኛዋ "

ሚስዝ ካርላይል ተነሣችና መንገድ ከጀመረች በኋላ አመነታች "

ለዛሬ እዚህ ይምጣ መጐናጸፊያ ደርባ ወዲህ እንድታመጣው ለሞግዚቲቱ
ንገሪያት አሁን የልጄ የራቱ ሰዓት ነው '' አለች ፈገግ አለች ወደ ሳቤላ ዞር ብላ"
" አሁን ሚስተር ካርላይል ስለሌለ ሕፃኑንም ለአንድ ጊዜ ወደዚህ ላስመጣው
እችላለሁ " አንዳንድ ጊዜ እኔም ስወጣ ሞግዚቲቱም ብትሆን ልትመግበው ትችላለች » "

በልጁ ምክንያት ከቤት አይቆዩም ማለት ነው ?”

" በጭራሽ እኔና ሚስተር ካርላይል ውጭ ማምሸት ካለብን ልጁን ሞግዚቲቱ ትንከባከበዋለች " ምንም ቢሆን የባሌን ፍሳጎት በልጁ ምክንያት አላሰናክለውም " ባሌን በጣም እወደዋለሁ "

ሞግዚቲቱ ዊልሰን መጎናጸፊያውን ገለጥ አድርጋ ሕፃኑን ከሚስዝ ካርላይል ጭን ላይ አኖረችው " የደስ ደስ ያለው የስድስት ወሩ ሕፃን ቆንጅዬ ነበር " የሚያምሩ ዐይኖቹን አፍጥጦ " ራሱን ቀና አድርጎ የቀንዲሉን ብርሃን እየተመለከተ ክንዶንቹን ያማታ ጀመር ንጹሕ ንፁህ ነጭ ልብሱን ለብሶ የሌሊት ቆቡን ደፍቶ ከናቱ ጋር
ሲያዩት ደስ የሚል ነበር እሷም በዘመኗ አሁን ሚስዝ ካርላይል ከተቀመጠችበት
ወንበር ተቀምጣ ያሁኑን ሕፃን የመሰለ ቆንጆ በጉልበቷ አስቀምጣ ታይታበታለች ምን ይሆናል ያ ሁሉ ዐለፈ " በትኩሳት የሚያቃጥለው ራሷን ከእጅዋ ላይ አስደግፋ እርር ትክን እያለች በቅናት መንገብገብ ጀመረች

ዊልሰን ሁኔታዋንና አለባበሷን ሁሉ ከእግር እስከ ራሷ ካስተዋለቻት በኋሳ የማስተማር ሥራዋ ከመልኳ የማይሻል ከሆነ ሉሲ ቄስ ትምህርት ቤት መሔድ አንደ ሚሻላት ራሷ ለራሷ ገምግማ ስታበቃ “ ልቆይ እሜቴ ” አለች -

ሒጂ ሲያስፈልግ
እደውልልሻለሁ “

ልጁ ራቱን በልቶ መተኛቱ ቀረና ጨዋታ ጀመረ አጆቹን ወደ መብራቱ ዘርግቶ እየተወራጨ ጮኽቱን ቀጠለ እናቱም አስተካክላ ይዛ ትክ ብላ ታየውና
እቅፍ አድርጋ እየመላለሰች ጨመጨመችው » ከዚያ ደሞ አቅፍ አድርጋ ካነሳችው በኋላ ቀጥ አድርጋ አስቀመጠችውና ወደ ማዳም ቬን ዞር ብላ እንዲህ የሚያምር ልጅ አይተሽ ታውቂያለሽ ? አለቻት "

በጣም የሚያምር ልጅ ነው ግን እርስምን አይመስልም " አለቻት በስንት መከራ ተጨንቃ "

"በአካል ውዱን ባሌን ነው የሚመስል » ሚስተር ካርላይልን ስታይው …"
አለችና ባርባራ የምታዳምጥ መስላ ጆሮዋን ዘንበል አደረገች

« ሚስተር ካርላይል መልከ መልካም ናቸው መሰል ? አለች ምስኪኗ ሳቤላ ·
ባርባራ ንግግሯን አቋርጣ ዝም ስትል ጊዜ ለሷ ፋታ ለመስጠት አሰባ
ያደረገችው መስሏት "

መልከ ቀና ነው ዋናው የሚማርከኝ ግን መልኩ አይዶለም መሳይ የሌለው የአውነት ሰው በማንም ዘንድ የተከበረ የታፈረና የተወደደ ሰው ነው
እሱን የማታደንቅ ያቺ የፊት ሚስቱ ብቻ ነበረች " ሚስተር ካርላይልን ባል ብላ
ኪያዘች በኋላ እንዴት በሱ ላይ ሌላ ልትፈልግ እንደ ቻለች እንዴት ጥላው እንደ
ጠፋች የእሱን ማንነት ለሚያውቁ ሰዎች ሁሉ አስግራሚ ምስጢር እንደሆነ ነው ስትላት ነገሩ መረራት አንጀቷን አፍተለተላት እንዲያውም ደርሶ ጮኺ እሪ በይ የሚል ንዴት መጣባት ልትለቀው ስትል ለጥቂት መለሰችው

ከደጅ የሚስተር ካርላይል ሠረገላ ድምፅ ተሰማ

ሳቤላ እንዴት እንደ ተቀመጠች የሰውነቷን መራድ እንዴት እንደ ደበቀች
ምንም አልታወቃትም " ባርባራ ልጅዋን ታቅፋ ወደ ሳሎን በር እንደ ተጠጋች
ወዲያው ገባ ሳቤላ ቬን እንደገና ከድሮ ባሏ ፊት ከአንድ ክፍል አብራ ቆመች

እሱ ደግሞ ሌላ ሰው መኖሩን አላስተዋለም ጎንበስ ብሎ ሚስቱን እንቅ
አድርጐ በፍቅር ስሜት ሲስማት የቅናት ዐይኖቿን ወደነሱ አዞረች ባርባራም
በበኩሏ ጭምጭም አድርጋ ስትስመው በጆሮው “ የኔ ፍቅር ” ብላ ስታንሾካሹከ አየቻት ከሚስቱ ቀጥሎ አበባ የመሰሉትን የሕፃኑን ከንፈሮች ሳመ ሳቤላ
ፊቷን በእጆቿ ጋረደች ይኸን ጉድ ለማየት ኖሯል የመጣችው ? ችላ ልትሸከመው ለራሷ ቃል ከገባችበት ፈተና አንዱ ክፍል ይኸው ስለሆነ መቻል ግድ ሆነባት

ሚስተር ካርላይል ወደ መኻል ሲገባ አያትና ደነገጠ " ወዲያው ሚስቱ አስተዋቀቻቸው እሱም ቀረብ ብሉ በከበሬታ እጁን ሲዘረጋላት የሚንቀጠቀጠው
እጅዋን ሰዳ ጨበጠችው ሚስተር ካርሳይል የጨበጠው እጅ ካስል ማርሊንግ ቤተ ክርስቲያን ቃል የገባለት ሺ ጊዜ እቅፍ አድርጎ ይጨብጠው የነበረው እጅ መሆኑን አልጠረጠረም።

እያንዳንዷ የደም ጠብታ ከሰውነቷ ተንጠፍጥፋ የወጣች መሰላት » መቆም
ሲሳናት ከወንበሯ ተቀመጠች " ሚስተር ካርላይል አንዳንድ ጥያቄዎች አቀረበላትና ቀና ብላ ማየት ስለ አልደፈረች እንዳቀረቀረች መለሰችለት "

“ በጊዜ መጣህሳ አርኪባልድ ዳኞች ዓመታዊ የራት ግብዣ በጣም ያስመሽ እንደ ነበር ስለማውቅ በጊዜ ትመጣለህ ብዬ አላሰብኩም '' አለችው

“ ዛሬም ያው ነው የትምባሆ መጠዎቻቸውን ሲያቀርቡ እኔ ቀስ ብዬ ወጣሁ " ሲያጡኝ ዴል አብሯቸው ስላለ እሱ አቃንቶ ይነግራቸዋል "

እስኪ ስማኝ አርኪባልድ አባባ ከስኳየር ስፒነር ጋር ለሦስት ቀን ለሥራ ወደ ለንደን እንደሚሔድ ስምቻለሁ "
“እነሱ ደግሞ ሦስት ቀን ይጨምራሉ " እነዚህ ሽማግሌ መኮንኖች በተለይ
ደግሞ የገጠር ዳኞች ለንደን ግብተወ መቸ እንዲህ በቀላሉ ይወጣሉ ? እና የሔዱ እንደሆነስ ባርባራ?

“እኔማ አባባ ውጭ በሚቆይባቸው ቀኖች ውስጥ እማማን እንደ ምንም አግባብተን ከዚህ እንድትሰነብት እሺ ብናሰኛት ብዬ ነበር " ለሷ ትንሽ ለውጥ ማድረግ ይጠቅማታል።

“ ኧረ ከሆነስ ጥሩ ነበር » አንቺ ከተውሻቸው ወዲህ ኑሮአቸው በጣም የሚሰለች ነው እሳቸው ግን ሁሉን ነገር በልባቸው እየያዙ ችግራቸውን መናገር አይፈልጉም " እና ጥሩ ሐሳብ ነው ባርባራ ሞክሪ የሚስዝ ካርላይል እናት በሽተኛና ብቸኛ ናቸው » አሁን ከቤት ምንም ልጅ የላቸም ” አላት በትሕትና ወደ ማዳም ቬን ፊቱን መልሶ።

ማዳም ቬን የቃል መልስ ለመስጠት ራሷን ስላላመነች ዝም እንዳለች ራሷን ነቀነቀች " እሱም ቀዝቀዝ ስትልበት ጊዜ መለስ ብሎ ልጁን በሁለት እጆቹ አቅፎ እያደረገ የተሰቀለውን መብራት እያስነካ ያጫውተው ጀመር ከዚያ እየቦረቀ እየሣቀ የሚደሰተውን ልጅ ስሞ ሲያበቃ “ንደዚህ ያሉት የሕፃናት አስቸጋሪነት
ትወጃለሽ ማዳም ቬን ይህ ሕፃን ቆንጆ ነው ይላሉ ሰዎች ምን ይመስልሻል?.

“ በጣም ደስ የሚል ልጅ
ማን ተባለ ?

“ አርተር ” አላት "

“አርተር አርኪባልድ ” አለች ባርባራ ለማዳም ቬን'“ እኔ እንኳን አርኪባልድ እንዲባል ነበር ፍላጎቴ ፤ከሱ በፊት ሌላ ተሰይሞበታል . . . አንቺ ነሽ እንዴ :ዊልሰን ? ወስደሽ ምን እንደምታደርጊው አላውቅም እሱ እንደሆነ እስከ እኵፈኩለ ሌሊትም የሚተኛ አይመስልፈለኝም "
👍7
ዊልሰን ማዳም ቬንን እንደገና እስኪበቃት ካየቻት በኋላ ሕፃኑን ከሜስተር
ካርላይል ተቀብላ ይዛው ወጣች

ማዳም ቬንም ተነሣችና ተሰናብታ ወደ መኝታዋ ሔደች።

ስታያት አታስገርምህም ? " አለች እሷና ባሏ ብቻቸውን ሲቀሩ ይህን ሰማያዊ መነጽር ለምን እንደምታደርገው አልገባኝም " መልክን ለማጥፋት ካልሆነ
ዐይንን ለማገዝ ፈ አይመስለኝም " አለችው "

“ እኔስ ” አለ ሚስተር ካርላይል ከሕልሙ የነቃ መስሎ“ ፊቷን ሳየው ..”

ፊቷ ደሞ ምኑ ይታያል ?” አለችውና ሚስቱ''ለመሆኑ ስለማን አሳሰበህ?”

“እኔ እንጃ እገሌ ነው ብዬ በተለይ መጥቀስ አልችልም ..ሻያችንን እንጠጣ ባርባራ...

💫ይቀጥላል💫
👍121👎1
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

..ናንሲ ሌኔሃን የሰውነቷ ክብደት መጨመሩ ታወቃት፡፡ ያለችው
ሊቨርፑል ከተማ አዴልፊ ሆቴል ውስጥ ነው፡፡ ናንሲ አስጠሊታም ቆንጆም
አይደለችም፧ አፍንጫዋ ሰልካካና ጸጉሯ የተዘናፈለ በመሆኑ የደስ ደስ
አላት፡ ደህና ልብስ ስትለብስ ዓይን ትስባለች፡፡ ይሄ ደግሞ የሁልጊዜ
ገጽታዋ ነው፡፡ ኮቷ ስለጠበባት ቁልፎቹ ሲቆለፉ ቀፈት ቢጤ ይወጣባታል:
ይህ የሆነው ሰሞኑን ለአንድ ወር ያህል በፓሪስ ምግብ ቤቶች እየዞረች ምግብ መሰልቀጥ ስላበዛች ነው፡፡ አትላንቲክን በመርከብ ስታቋርጥ ግን ስባት
ያለበት ምግብ ላለመብላት ወስናለች፡፡ ኒውዮርክ ስትደርስ የቀድሞው
ሽንቅጥናዋ ይመለሳል።

ከዚህ በፊት ውፍረት ችግሯ አልነበረም፡፡ ጥሩ ምግብ ብትወድም ብዙ አታግበሰብስም፡፡ አሁን አሁን ውፍረት የእርጅና ምልክት ነው ብላ መፍራት
ጀምራለች፡

ዛሬ አርባኛ አመቷን ደፍናለች፡፡

ሁልጊዜም ሸንቃጣ ነበረች፡፡ ውድ ልብስ ገዝቶ ወይም አሰፍቶ መልበስ ጫማ መግዛት ትወዳለች፡፡ በፋሽን እቃዎች ንግድ ላይ በመሰማራቷ ጥሩ
ነገር መልበስ እንዳለባት ታውቃለች፡፡

ናንሊ የተወለደችው በ1899 ዓ.ም ሲሆን ይህ ወቅት አባቷ የጫማ ፋብሪካ ከፍተው ንግዱን የጀመሩበት ጊዜ ነው፡፡ ከእንግሊዝ አገር ጥራት ያላቸውን ጫማዎች አስመጥተው አስመስሎ በመስራት በርካሽ ዋጋ ይሸጣሉ፡፡ ሃያ ዘጠኝ ዶላር የሚያወጣውን የለንደን ጫማ አስር ዶላር
ከሚያወጣው የራሳቸው ጫማ ጋር ጎን ለጎን እያስቀመጡ ‹‹እነዚህ
ጫማዎች ልዩነታቸው ምንድን ነው?›› እያሉ ማስታወቂያ ያስነግራሉ፡ ጥሩ ጥሩ ጫማ በማምረት እውቅና እያገኙ ሲመጡ የአንደኛው የዓለም ጦርነት
ሲቀሰቀስ የወታደር ጫማ አቅርቦት ትእዛዝ ጨረታ አሸናፊ ሆኑ።

በ1920 ዓ.ም አሜሪካ ኒው ኢንግላንድ ስቴት ውስጥ በርካታ ሱቆች በመክፈት ራሳቸው የሚያመርቱትን ጫማ ብቻ መሸጡን ተያያዙት፡፡ በ1930 ዓ.ም በተከሰተው የኢኮኖሚ
ድቀት ምክንያት ገበያው
ስለቀዘቀዘ የሚፈበረኩትን የስታይል ዓይነቶች መቀነስ ተገደዱ፡፡ ኢኮኖሚው እያንሰራራ ሲመጣ ለተለያዩ ስታይል ጫማዎች አንድ ዓይነት ዋጋ በመቁረጥ ገበያውን ተቆጣጠሩት፡፡ በዚህ ብልጠታቸው በመጠቀም ሌሎች ነጋዴዎችን ከገበያ
በማስወጣት በትርፍ ላይ ትርፍ ማጋበሱን ቀጠሉ።

የናንሲ አባት ‹‹መጥፎ ጫማ ለመስራት የሚወጣው ወጪ ጥሩ ጫማ ለማምረት ከሚወጣው ወጪ አይተናነስም›› ይሉ ነበር፡፡
ለናንሲ ጥሩ ጫማ ማምረት ጥሩ ቤት ውስጥ መኖር፣ ጥሩ መልበስና ማጌጥ፣ ጥሩ ጥሩ መኪና መንዳትና በየጊዜው መደገስ ማለት ነው፡፡ወንድሟ ሰላሳ ስምንት ዓመቱ ነው፡፡ አባታቸው ለሁለቱ ልጆቻቸው
ለእያንዳንዳቸው 40 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ አውርሰዋቸው ከሞቱ አምስት ዓመት ሞላቸው፡፡ የአባታቸው እህት አክስታቸው 10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ ሲወርሱ ቀሪው 10 በመቶ ደግሞ በታማኝነት ላገለገሏቸው አዛውንት ጠበቃ ደርሷቸዋል፡፡

ናንሲ አባታቸው ሲሞቱ የኩባንያውን ኃላፊነት ቦታ ለእሷ እንደሚሰጡ
ትገምት ነበር፡ ሴት የኩባንያ ኃላፊነት ቦታ መያዟ ባይለመድም አባቷ
ከፒተር ይልቅ ቢዝነሱን እንድትመራ እሷን ይመርጡ ነበር።

አባቷ ናት ሪጅዌይ የሚባል እሳት የላሰ ምክትል ነበራቸው፡፡ እሱ በበኩሉ የብላክ ቡትስ ጫማ ፋብሪካ ዋና ኃላፊ መሆን ይመኛል።

ፒተርም የኃላፊነቱን ቦታ መከጀሉ አልቀረም፡፡ እሱ ደግሞ የቤተሰቡ ወንድ ልጅ ነው ናንሲ አባቷ ከፒተር ይልቅ ስለሚያቀርቧት ሁልጊዜ ትሸማቀቅ ነበር፡ ፒተር በአባቱ እግር ካልተተካ በጣም እንደሚያዝን ጥርጥር የለውም፡፡ ናንሲም እሱ ከሚያዝን በማለት ኃላፊነቱን እንዲወስድ
ቦታውን ለቀቀችለት፡፡ እሷና ወንድሟ በድምሩ 80 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ
ይዘዋል፡፡

ናት ሪጅዌይ በዚህ ተቀይሞ ኒውዮርክ የሚገኘው ጄኔራል ቴክስታይልስ
የተባለ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ተቀጠረ፡፡ የእሱ ኩባንያውን ለቆ መሄድ
ክስረቱ ለብላክ ቡትስ ብቻ ሳይሆን ለናንሲ ጭምር ነበር፤ አባቷ ሊሞቱ
አካባቢ ከናንሲ ጋር ወዳጅነት ጀምሮ ነበር፡፡
ናንሲ ባሏ ከሞተ ወዲህ ከማንም ወንድ ጋር ወዳጅነት አልመሰረተችም
ነበር፡፡ ናት ፤ደግሞ "በትክክለኛው ጊዜ ነው የደረሰላት ባሏ ከሞተ አምስት ዓመት በኋላ ህይወቷ ሁሉ ስራ ብቻ በሆነበትና የወንድ ፍቅርና የገላ ጠረን እየናፈቃት በመጣበት ዘመን፡፡ በወቅቱ የተወሰኑ ቀናት ራት ጋብዟታል ቴአትር ቤትም ወስዷታል አንድ ቀን ቤቷ ሲሸኛት ምጥጥ አድርጋ
ስማዋለች፡፡ ነገር ግን ይህ ግንኙነት ብዙም ሳይዘልቅ ናት ሪጅዌይ ጥሏት
እብስ አለ፡፡ መሸወዷን ስታውቅ ክፉኛ በሸቀች፡

ከዚያ በኋላ ናት ረጂዌይ
በጄኔራል ቴክስታይልስ ኩባንያ ታዋቂነትን አትርፎ የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ለመሆን በቃ፡፡ከዚያ በኋላ ከናንሲ አስር ዓመት የምታንስ ቆንጆ ሴት አገባና ናንሲን አሳፈራት፡፡

ፒተር የኃላፊነቱን ቦታ መወጣት አልቻለም፡፡ የኩባንያው ስራ
አስኪያጅነት ቦታ በእጁ በሆነበት አምስት ዓመት ጊዜ የኩባንያው ገቢ
ቁልቁል ወረደ ሱቆቹ በሙሉ ዋናቸውን ከማስመለስ በስተቀር ትርፍ ማግኘት አቃታቸው ኒውዮርክ ውስጥ የሴቶች ጫማ መሸጫ
ቢከፍትም ይህም ሱቅ ከኪሳራ አልዳነም፡፡

ናንሲ የምትመራው ፋብሪካ ብቻ ነው አትራፊ የነበረው:: አገሪቱ የኢኮኖሚ አዘቅት እየወጣች ባለችበት በአስራ ዘጠኝ ሰላሳዎቹ አጋማሽ
ዓመታት ክፍት የሴቶች ሰንደል ጫማ ማምረት ጀመረችና በአንድ ጊዜ
ተወዳጅ ሆነላት፤ ወደፊት የሴቶች ጫማ ገበያ የደራ እንደሚሆን ተገነዘበች
የማምረት አቅሙ ቢኖራት አሁን ከምትሸጠው የጫማ ቁጥር እጥፍ ትሸጥ ነበር፡፡ ነገር ግን እሷ ያመጣችው ትርፍ በፒተር ኪሳራ ስለሚዋጥ ፋብሪካውን ማስፋፋት አልቻለችም፡፡
ናንሲ የጫማ ንግዱን ከኪሳራ ለማዳን አንድ ነገር መደረግ እንዳለበት
ተገነዘበች፡፡

የማስፋፊያ ካፒታል ለመፍጠር የጫማ መደብሮቹ ለኃላፊዎቹ መሸጥ አለባቸው፡፡ ከመደብሮቹ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ፋብሪካውን ለማዘመንና ለማስፋፋት ስራ ላይ ይውላል ፒተር ደግሞ የስራ አስኪያጅነቱን ቦታ
ለእሷ ይለቅና የወጪ ገደብ ጣሪያ ተሰጥቶት የኒውዮርኩን መደብር ብቻ
ያንቀሳቅሳል፡፡

ፒተር የኩባንያውን ሊቀመንበርነት ከነሙሉ ክብሩና ጥቅሙ ይዞ
እንዲቆይ፣ የፒተርን መደብ ከእሷ ኩባንያ ከሚገኘው ትርፍ በገደብ ልትደጉም ሆኖም እውነተኛ ስልጣኑን እንዲለቅ ልታደርገው ፈልጋለች፡

እነዚህን እቅዶቿን ለሌሎች ሳታሳውቅ ለፒተር ለብቻው አቀረበችለት እሱም አስቦበት መልስ እንደሚሰጣት ቃል ገባ፡፡ የኩባንያው ገቢ መቀነስ
በዚሁ ሁኔታ መቀጠል እንደማይገባው በዚህ እቅድ የማይስማማ ከሆነ እሱን
አልፋ ለቦርድ በማቅረብ እሱን አስነስታ ቦታውን እንደምትይዝ በእርጋታ
አስጠነቀቀችው፡፡ ይህን ሳይቀበል ቀርቶ አምባጓሮ ማንሳት ከመረጠ አሳፋሪ
ሽንፈት እንደሚገጥመውና ምናልባትም ከእህቱ ጋር ተቆራርጦ እንደሚቀር
ጥርጥር የለውም
እስካሁንም ምንም ጥቃት አልከፈተም::የተረጋጋ ተቆርቋሪና ተጫዋች መሰለ፡ ፓሪስ ላይ ፒተር ለመደብሮቹ የወቅቱን ፋሽን የተከተሉ ጫማዎች ሲሸምት እሷ ደግሞ ለራሷ ጫማዎች ስትገዛ የፒተርን ወጪ በጥንቃቄ አጠናች፡

ሁሉም እንደሚያደርገው ወንድምና እህት ወደ አሜሪካ መመለስ
እንዳለባቸው ወሰኑ

ቦታው ሁሉ ስለተያዘ በአይሮፕላን ለመሄድ ደግሞ አልተቻለም፡፡
በመጨረሻ ከሊቨርፑል የሚነሳ ውርከብ ቲኬት ገዛች፡፡ ከፓሪስ በባቡር ረጅም ጉዞ ከተጓዙ በኋላ በጀልባ ወደ ለንደን አመሩ፡

ዛሬ በአየር በራሪው ጀልባ ሊበሩ ነው፡፡
👍231
ናንሲ እንግሊዝ ለጦርነቱ እያደረገች ያለችውን ዝግጅት ስታይ ነርቭ
አደረጋት፡ ትናንት ከሰዓት በኋላ የሆቴሉ ሰራተኛ መኝታ ክፍሏ ገባና
መስኮቶቹን ብርሃን በማያስገባ መጋረጃ ጋረዳቸው፡ በማታ ከሰማይ ወደ ምድር ከተማዋ እንዳትታይ መስኮቶቹን በሙሉ ጥቁር መጋረጃ እንዲሸፈኑ መንግስት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ከተማዋ በቦምብ ስትደበደብ መስታወት እንዳይ ፈነጣጠር መስታወቶቹ በ X ቅርፅ የወረቀት ማጣበቂያ ፕላስተር ተለጥፎባቸዋል፡ በሆቴሉ መግቢያ አካባቢ በአሸዋ የተሞሉ ጆንያዎች የተደረደሩ ሲሆን ከጀርባ ደግሞ ከአየር ጥቃት መደበቂያ መጠለያ ተቆፍሯል፡

እሷን ስጋት የገባት አሜሪካ ጦርነት ውስጥ ከገባች ሁለቱ ወንድ ልጆቿ መዝመታቸው የማይቀር መሆኑ ነው፡ ‹ሂትለር ስልጣን ሲይዝ ጀርመን በኮሚኒስት አገዛዝ ስር እንዳትወድቅ ይከላከላል› ይሉ ነበር አባቷ፡ ስለ ሂትለር መጨነቅ የተወችው ያኔ ነበር፡፡ ስለ አውሮፓ የሚያስጨንቃት
ነገር አልነበረም
እንደ ዓለም አቀፍ ፖለቲካ፣ በኃያላን ሀገሮች መሐል ያለ የሃይል ሚዛን ወይም የፋሺዝም መነሳት ያሉ ምናባዊ አስተሳሰቦች ከልጆቿ ህይወት ጋር ሲወዳደሩ ለእሷ ምንም አይደሉም፡፡ፖላንዶች፣ ኦስትሪያዎች፣ ይሁዳውያንና ክልሶች መቀመቅ ቢወርዱ እሷ ምን ተዳዋ፡፡ የእሷ ስራ
ልጆቿን ሊያምንና ሂዩን ክፉ እንዳይነካቸው መጸለይ ነው፡፡

ልጆቿ የእሷን ጥበቃ የሚፈልጉበት ዕድሜ ላይ አይደሉም ያሉት፡ናንሲ በልጅነቷ አግብታ ነው ልጆቿን ዱብ ዱብ ያደረገቻቸው፡ ልጆቹ
አሁን ትልልቆች ሆነዋል፡ ሊያም ትዳር ይዞ ሂውስተን ውስጥ ይኖራል፤
ሂዩ ደግሞ ዩኒቨርሲቲ መጨረሻ አመት ላይ ደርሷል፡፡ ሂዩ በትምህርቱ
እምብዛም ሲሆን የስፖርት መኪና ገዝቶ አሸሼ ገዳሜ እያለ መሆኑን ሰምታለች፡ ነገር ግን አሁን የእናቱን ምክር የሚሰማበት ዕድሜ ላይ አይደለም፡፡ እሷም ብሔራዊ ውትድርና እንዳይወስዷቸው ማድረግ የማትችል መሆኑን አውቃለች፡፡

ናንሲ በጦርነት ጊዜ ቢዝነስ እንደሚጧጧፍ ታውቃለች፡፡ የኢኮኖሚ እድገት ሲኖር በርካታ ሰዎች ጫማ መግዛታቸው የተለመደ ነው፡፡ አሜሪካ ጦርነት ውስጥ ገባች አልገባች ጦሩ ይስፋፋል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ መንግስት
ተጨማሪ የጫማ ትዕዛዝ ይሰጣል ማለት ነው፡ በዚህ ምክንያት በሚቀጥሉት ሁለትና ሶስት ዓመታት የጫማ ሽያጭ እጥፍ ወይም ሶስት እጥፍ
ይሆናል ብላ ገምታለች፤ ፋብሪካውን ለማስፋፋት ሌላ ምክንያት ይሆናል፡

ሆኖም ይህ ሁሉ ልጆቿ ዘምተው እና በፅኑ ቆስለው ጦር ሜዳ ቢሞቱ
ከሚያሳድርባት የመንፈስ ስብራት ጋር ሲወዳደር እዚህ ግባ የሚባል
አይሆንም።

ሻንጣዎችን ሊወስድ የመጣው ኩሊ ከሃሳቧ አናጠባት፡፡ ፒተር
ሻንጣዎቹን አዘገጃጅቶ እንደሆነ ጠየቀችው፡፡ ሰውየውም ሻንጣዎቹን ትናንት ማታ ወደ መርከቡ እንደላከ ነገራት፡፡ ፒተር ለጉዞ የተዘጋጀ መሆኑን
ለማየት ወደ ክፍሉ አመራች፡፡ በሩን ስታንኳኳ የከፈተችላት አልጋ አንጣፊ
ትናንት መሄዱን ነገረቻት፡
ናንሲ የፒተር ነገር እንቆቅልሽ ሆነባት፡፡ ትናንት ማታ ሆቴሉ የገቡት
አብረው ነበር፡፡ እሷ እራቷን
ክፍሏ ድረስ አስመጥታ እንደምትበላና በጊዜ
እንደምትተኛ ስትናገር ፒተርም እንደዚሁ እንደሚያደርግ ነግሯት ነበር፡ ሃሳቡን የቀየረ ከሆነ የት ሄደ? የት አደረ? አሁንስ የት ነው?›

ስልክ ለመደወል የሆቴሉ እንግዳ ተቀባይጋ ሄደች፤ ነገር ግን ማንጋ
እንደምትደውል አታውቅም፡፡ እንግሊዝ ውስጥ እሷም ሆነች ፒተር ማንንም አያውቁም፡፡ ሊቨርፑል ከባህሩ ባሻገር ከሚገኘው የአየርላንድ ዋና ከተማ
ደብሊን ብዙም አይርቅም፡፡ ‹ታዲያ ፒተር የቅድመ አያቶቹን አገር ለማየት እዚያ ሄዶ ይሆን?› ስትል አሰበች፡፡ ነገር ግን መርከብ መሳፈሪያቸው ጊዜው ስለደረሰ ለዚህ ጊዜ እንደሌለው ያውቃል፡፡

ከዚያም ስልከኛው ከአክስቷ ቲሊ ጋር እንዲያገናኛት ስልክ ቁጥሩን
ሰጠችው: ከአውሮፓ ወደ አሜሪካ ስልክ ሲደወል መስመር የሚገኘው
በዕድል ነው፤ በቂ መስመር ስለሌለ፤ አንዳንድ ጊዜ ረጅም ጊዜ መጠበቅ የግድ የሚልበት ጊዜ አለ፡፡እድለኛ ከሆኑ አንዳንድ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ መስመር ሊገኝ ይችላል፤ ከተገኘ ደግሞ
የድምፅ ጥራት ስለማይኖረው ለመነጋገር በጣም መጮህ ያስፈልጋል፡፡

ቦስተን ውስጥ አሁን ከጧቱ አንድ ሰዓት በመሆኑ ይሄን ጊዜ አክስቷ
ከእንቅልፍ ተነስተዋል እንደ ብዙዎቹ ባልቴቶች እንቅልፍ ብዙም
አይተኙም የሚነሱትም በጧት ነው፡፡

አሜሪካ ውስጥ በዚህ ጊዜ ብዙዎቹ ሰራተኞች ቢሮ ስለማይገቡ የስልክ
መስመሩ አይጨናነቅም፡፡ አምስት ደቂቃ ቆይቶ ስልኩ ጮኸ፧ ናንሲ
መናገሪያውን አንስታ ጆሮዋ ላይ አደረገች ፤

‹‹ሄሎ?›› አሉ አክስት፡፡
‹‹አክስቴ፣ ናንሲ ነኝ››
‹‹ወይ አምላኬ ደህና ነሽ?››
‹‹እኔ ደህና ነኝ፤ ጦርነቱ ቢጀመርም ገና አልተጋጋለም ልጆቹ ደህና
ናቸው?››
‹‹ሁለቱም ደህና ናቸው ሊያም ካለበት ፖስት ካርድ ልኮልኛል፤
ጃኩሊን ባህር ዳርቻ ጸሃይ ላይ ስትንቃቃ ስለምትውል የገላዋ መጥቆር ውበት ጨምሮላታል፡ ሂዩ አዲስ በገዛት መኪና ሊፍት ሰጥቶኛል፡፡ መኪናዋ
ታምራለች፡››

‹‹በፍጥነት ነው የሚነዳው?›› ጠየቀች ናንሲ፡፡

‹‹እኔ ፊት ጠንቃቃ ነው፡ ሰዎች መኪና የሚነዱ ከሆነ መጠጣት
የለባቸውም በሚል መጠጥ አልጠጣም ብሏል፡››
‹‹ጥሩ››
‹‹መልካም ልደት የኔ ማር፤ እንግሊዝ አገር ምን ትሰሪያለሽ? አሉ
አዛውንቷ፡
‹‹አሁን ወደ ኒውዮርክ የሚሄደው መርከብ ላይ ለመሳፈር ሊቨርፑል
ነው ያለሁት፡፡ ፒተር ጠፍቶብኛል፡ ስልክ ደውሎልሽ ነበር?››
‹‹አዎ ደውሎልኛል፡፡ ከነገ ወዲያ ጠዋት የቦርድ ስብሰባ እንደሚኖር
ነግሮኛል፡››
ናንሲ ሚስጥሩ አልገባት አለ፡፡ ‹‹ዓርብ ጠዋት ማለትሽ ነው?›› ስትል ጠየቀች፡፡
‹‹አዎ የኔ ማር፡፡ ከነገ ወዲያ ዓርብ›› አሉ ቲሊ፡፡

ናንሲ አሁንም እንቆቅልሹ አልተፈታላትም፡፡ ፒተርና እሷ እንግሊዝ እያሉ ለዓርብ ጠዋት የቦርድ ስብሰባ መጥራት ምን ይፈይዳል? ሌሎቹ የቦርድ ዳይሬክተሮች ቲሊና ዳኒ ሪሌይ ናቸው፧ እነሱ ደግሞ ብቻቸውን
መወሰን አይችሉም፡፡ ነገር ግን ይሄ ነገር የሆነ ሴራ መሆን አለበት። ፒተር የሆነ ነገር እየጠነሰሰ ይሆን?› ስትል አሰበች፡፡

‹‹አክስቴ አጀንዳው ምንድን ነው?››

‹‹አጀንዳውን አሁን እያየሁት ነው፡፡ በሊቀመንበሩ በተደረገ ስምምነት
መሰረት የብላክ ጫማ ኩባንያን ለጄኔራል ቴክስታይልስ ኩባንያ መሸጥን ማፅደቅ››

‹‹ወይ አምላኬ!›› ናንሲ ይሄን ስትሰማ ራሷን ልትስት ምንም
አልቀራትም፡፡

ፒተር እሷ ሳታውቅ ኩባንያውን ሊሽጥ! አይደረግም! ለተወሰነ ጊዜ መናገር አቅቷት ዝም አለች፡፡ ከዚያም እንደምንም ብላ
በሻከረ ድምፅ ‹‹አክስቴ እስቲ እንደገና አንብቢልኝ›› አለች፡፡
አክስቷ ደገሙላት፡
ናንሲ ብርድ ብርድ አላት፡፡ ፒተር አፍንጫዋ ስር ሆኖ እንዴት እንዲህ
ሊያደርግ ቻለ? መቼ ነው ድርድር ያደረገው? ያንን የሚስጥር
ስምምነታቸውን ከነገረችው ጊዜ ጀምሮ ነው ይህን ሲጠነስስ የከረመው ማለት ነው፡፡ ያቀረበችለትን ሀሳብ እሺ አስብበታለሁ› እያለ ለካ እሱ ሴራ
ሲጠነስስ ከርሞል።

ፒተር ደካማ መሆኑን ብታውቅም እንደዚህ አይነት ተንኮል መስራቱ
አስገርሟታል፡

‹‹ናንሲ አለሽ?›› ሲሉ አክስቷ ጠየቁ፡

ናንሲ የተናነቃትን ሳግ ዋጥ አደረገችና ‹‹አለሁ አክስቴ፤ ገርሞኝ እኮ ነው፡፡ ፒተር ለኔ የነገረኝ ነገር የለም››

‹‹በእውነት ይህማ ደግ አይደለም›› አሉ አክስት፡

‹‹እኔ በሌለሁበት ውሳኔ ማሳለፍ ፈልጓል። ነገር ግን እሱም ስብሰባው ላይ መገኘት አይችልም፡፡ መርከብ ላይ የምንሳፈረው ዛሬ ነው፡ አሜሪካ ለመድረስ አምስት ቀን ይፈጃል፡››
👍10
ፒት አሁን የት እንዳለ አይታወቅም› አለች በሆዷ፡

‹‹አሁን ከእንግሊዝ የሚነሳ አይሮፕላን የለም?›› ሲሉ ጠየቁ አክስቷ
‹‹በአየር በራሪው ጀልባ››
‹‹አዎ›› አሉ አክስቷ ‹‹ዳኒም ፒተር በዚህ አይሮፕላን እንደሚመጣና
ለቦርድ ስብሰባው እንደሚደርስ ነግሮኛል፡፡››

ናንሲ አስታወሰች፡ በየጋዜጣው ሁሉ የተፃፈው ስለሱ ነው፡፡ በአንድ ቀን አትላንቲክን አቋርጠሽ መምጣት ትቺያለሽ፡፡ ፒተር እንደዚያ ሊያደርግ ነው እንዴ? አለች ናንሲ በሆዷ፡፡ እናም ወንድሟ የዋሻት መሆኑን መቀበል አዳገታት፡፡ እስከ ሊቨርፑል ድረስ አብሯት ወደ አሜሪካ በመርከብ.እንደሚሄድ አድርጋ እንድትገምት አድርጓት ነበር፡ ሆቴል ገብተው ወደየ ክፍላቸው ከሄዱ በኋላ እሱ ወዲያው ተመልሶ ወጥቶ ሌሊቱን በሙሉ ተጉዞ ሳውዝ ሃምፕተን ገብቷል፤ በጊዜ አይሮፕላኑ ላይ ለመድረስ፡፡ ይህን ሁሉ ሴራ በሆዱ እያውጠነጠነ እንዴት ከእሷ ጋር ያን ያህል ሰዓት ማውራትና አብሯት መብላት ቻለ?›

‹‹ለምን አንቺስ በበራሪ ጀልባው አትመጪም?›› አሏት አክስቷ፡

ጥሏት መጥፋቱን ስታውቅ እሱን ፍለጋ እንደምትጀምርና ልትደርስበትም እንደማትችል ገምቷል፡ ነገር ግን የፒተር ችግር ሰዓት ላይ መሆኑን ደግሞ
አሳምራ ታውቃለች፡፡

‹‹እሞክራለሁ›› አለች ናንሲ ለአክስቷ፤ ‹‹ደህና ሁኚ አክስቴ›› ብላ.ስልኩን ዘጋች፡ ስለቀጣይ እቅዷ ማሰብ ጀመረች፡ ፒተር ትናንት ሌሊት ተነስቶ ሌሊቱን ተጉዟል፡፡ በራሪ ጀልባው ከሳውዝ ሃምፕተን ዛሬ ተነስቶ ኒውዮርክ ነገ ይደርስና ፒተር የዓርቡ ስብሰባ ላይ ይገኛል ታዲያ በራሪ ጀልባው በስንት ሰዓት ይነሳል? ናንሲ ከመነሳቱ በፊት ትደርስ ይሆን?

ልቧ እንደተንጠለጠለ እንግዳ ተቀባዩጋ ሄዳ የፓን አሜሪካኑ አየር መንገድ የአየር በራሪ ጀልባ ከሳውዝ ሃምፕተን በስንት ሰዓት እንደሚነሳ ጠየቀችው፡

‹‹አምልጦዎታል የኔ እመቤት›› አላት፡፡

‹‹እስቲ ሰዓቱን አጣራልኝ እባክህ›› አለች ትዕግስት ማጣቷ ከድምጿ እንዳይታወቅባት እየጣረች፡፡

የበረራ መርሃ ግብሩን አውጥቶ ተመለከተ ‹‹ስምንት ሰዓት›› አለች፡
ሰዓቷን ስታይ ስድስት ሰዓት ይላል፡፡

እንግዳ ተቀባዩም ‹‹የግል አይሮፕላን ቆሞ የሚጠብቆት እንኳን ቢሆን
ከዚህ በኋላ ሳውዝ ሃምፕተን አይደርሱም›› አላት፡
‹‹የግል አይሮፕላኖች አሉ?›› ስትል ጠየቀች

ሰውዬው በዚች የውጭ አገር ሰው ጅልነት መገረሙን
ፊቱ ያሳብቅበታል፡ ‹‹ከዚህ አስር ኪ.ሜ ያህል ርቆ የሚገኝ አየር ማረፊያ አለ
ጥሩ ዋጋ ከከፈሉ የትም ሊወስዶት የሚችል ፓይለት አያጡም፡፡ ታዲያ አየር ማረፊያው ጋ መድረስ፣
ፓይለቱን ማግኘት፣
መጓዝ፣ ሳውዝ ሃምፕተን አጠገብ ማረፍ እና ከዚያም ወደ ወደቡ በመኪና መሄድ
ይኖርቦታል፡ ነገር ግን ከመድከምዎ በፊት ይህ ሁሉ በሁለት ሰዓት ውስጥ
እንደማይሆንልዎት ላረጋግጥሎት እወዳለሁ የኔ እመቤት።››

በተስፋ መቁረጥ ከሰውዬው ፊት ገለል አለች ናንሲ፡

በቢዝነስ ዓለም ውስጥ ያለ ሰው በሌላ ሰው መናደድ ገንዘቡ አይደለም፡፡
ይህን ከረጅም ጊዜ በፊት ተምራለች፡፡ ‹‹ቦስተን በጊዜው አልደርስም፧ ነገር
ግን የኩባንያውን ሽያጭ እዚህ ሆኜ ማስቆም እችላለሁ›› ስትል አሰበች፡፡
ወደ ስልኩ ዞረችና አሁን ቦስተን ውስጥ አንድ ሰዓት ነው፡፡ ጠበቃዋ ፓትሪክ ማክ ብራይድ ይሄኔ ቤቱ ነው የሚሆነው፡ ለስልከኛው የጠበቃዋን ስልክ ሰጠች...

ይቀጥላል
👍11
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሦስት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ ..ናንሲ ሌኔሃን የሰውነቷ ክብደት መጨመሩ ታወቃት፡፡ ያለችው ሊቨርፑል ከተማ አዴልፊ ሆቴል ውስጥ ነው፡፡ ናንሲ አስጠሊታም ቆንጆም አይደለችም፧ አፍንጫዋ ሰልካካና ጸጉሯ የተዘናፈለ በመሆኑ የደስ ደስ አላት፡ ደህና ልብስ ስትለብስ ዓይን ትስባለች፡፡ ይሄ ደግሞ የሁልጊዜ ገጽታዋ ነው፡፡ ኮቷ ስለጠበባት ቁልፎቹ ሲቆለፉ…»
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አምስት (5)

ማይክ ከኒውዮርክ ከመነሳቱ በፊት ወደ ናንሲ ስልክ ደውሎ በዘጠኝ ደቂቃ ውስጥ እንደሚደርስና ተዘጋጅታ እንድትጠብቀው ነገራት ። ከጥቂት ምልልሶች በኋላ የምትዘጋጀው በሰርግ ሊጋቡ እንደሆነ ሲገልፅላት ፤
«ለምን ዛሬ ማታ? ለምን ?» አለችው
«ደመነፍሴ የሆነ ነገር ነገረኝ ። ብቻ ነገሩ የተገባ ነው» አላት ። በቃ ልታገባ ነው ። ትዳር ልትመሰርት! ማይክልና እሷ የሕግ ባልና ሚስት ሊሆኑ ! በፈገግታ ተመላች።
«መጣሁ ፣ ዘጠኝ ደቂቃ ብቻ. . . እና ደሞ ናንሲ!»
«እ ?»
«በጣም እወድሻለሁ !» ይህን ብሎ ስልኩን ዘጋውና እየሮጠ አውሮፕላኑ ላይ ተሳፈረ።

ግው! ግው !ግው !
እየደጋገመ በሩን ይጠልዘው ገባ ። ይህን በር ሲደበድብ ሶስት ደቂቃ ያህል አልፏል። ግን ተስፋ ቆርጦ ሊሄድ አልፈለገም። የቤን አቭሪን ጠባይ ያውቃል ። እቤት ውስጥ እንዳለም በደንብ ይገባዋል ።
‹‹ቤን ! ስማ ፤ ቤን !»
ግው!ግው ! ግው!
« ቤን ! በስላሴ ስማኝ ! ትሰማኛለህ ሰውዬው !...»
ግው! ግው? ግው! ..ግው ግው! ግው!.....
«ቤን ..›..»
ግው! ግው! ግው!..
በመጨረሻ ኮቴ ተሰማው ፤ የተደናበረ ኮቴ ። ቀጥሎ አንድ ነገር መታና ተንኳኳ ። የመደነቃቀፍ ድምፅ ተሰማው ። በሩ ሲከፈት እንቅልፍ ያናወዘው ቤን አቭሪ ብቅ አለ ፤ ግራ ተጋብቶ ፤ በከነቴራና ሙታንታ ብቻ ።
«ገና በአምስት ሰዓት የተኛኸው ምን ነካኝ ብለህ ነው ፣ በክርስቶስ ?» አለ ማይክል ። ቤን ግን አልመለሰለትም ። ማይክ ፊቱን ሲመለከት ነገሩ ሁሉ ገባው።
«አረ በስላሴ ! ቤን ፤ ጥምብዝ ብለህ ሰክረሃልና ?»
«ከራስ ፀጉሬ እስከ እግር ጥፍሬ » አለ ቤን ቁልቁል እግሩን እየተመለከተ ፤ የስካር ፈገግታ ፈገግ ብሎ። እግሩ ሲብረከረክ ይታይ ነበር ።
«ስካርህን በቶሎ ማብረድ አለብኝ። ለብርቱ ጉዳይ እፈልግሀለሁ
«ተባለ እንዴ ስድስት ቢፍ- ኢተር ጂን ቶኒክ ውሀ ሲበላው ታየኝ ኮ!ያን ሁሉ ስጠጣ ያመሸሁት ፤ባንተ መምጣት ብቻ ላበላሸው ነዋ፤ ቡልሽት››
«ስድቡም ይቆይ፣ ስካሩም ቢበላሽ አይጐዳ ፤ ይልቅስ ቶሎ ነቃ በልና ልብስህን ለባብስ»
«የለበስኩት በቃኝ!» ቤን ይህን ሲል ማይክል አልፎት ገብቶ ነበረና መብራቱን አበራው ። ቤን አቭሪ ግን አይኑን ሊገልጥ ተቸግሮ ማጨናበስ ጀመረ ። «ሄይ ! ... ምን ማድረግህ ነው›› አለ ቤን ። መብራቱን አብርቶ ወደ ኩሽና መንገዱን ቀጠለ ። ‹‹ምን እያደረክ ነው?» አለ ቤን ።
«አንተ ብትሆን እኩሽና ውስጥ ምንድነው እምታደርገው !! የቦምብ ከምሱር ትነቅላለህ ?» አለ ማይክል። «አትጠራጠር ። እነቅልና እወረውር …
‹‹ይልቅ ወሬውን ተውና አንድ ትልቅ ፌሽታ ለማድረግ ዝግጁ ሁን» አለ ማይክ ፈገግ ብሎ። ቤን ነቃ አለ " እፊቱም ላይ አንድ ነገር ለማግኝት ተስፋ የማድረግ ስሜት ታየበት፡፡ «ፌሽታው ምንድነው? ልንጠጣ ያስችለናል ? ››
‹‹የፈለግነዉን ማድረግ እንችላለን ግን አሁን አይደለም፡፡ ሁሉም በኋላ ያደርሰናል»
‹‹ባዶ ተስፋ ጅልህን ብላ›› አለና እወንበሩ ላይ ሄዶ ተወዘፈ
«ጉዳዩ ምን እንደሆነ አውቀሃል ?» አለ ማይክ ።
«እሚያስጠጣ ጉዳይ ካልሆነ ላውቀውም አልፈልግ ፤ ልትነግረኝም አልሻ ። አኔ ጌታዬ ፤ ዶክትሬቴን ልቀበል ነው ። ሌላ ባጣ እሱን እያሰብኩ መጠጣት እችላለሁ ።
« እኔ ደግሞ ዛሬ እሱኑ አሳብቤ ሚስት ላገባ ነው »
«እሱም አይክፋም » አለ ቤን። እና ድንገት ቀና ፣ ነቃ ብሎ « ምናልክ ? ምን መሆኔ ነው አልክ ?» አለ ።
«ሰምተኽኛል ፤ ምን ትጠይቀኛለህ ናንሲ እና እኔ ልንጋባ ነው አልኩህ » ማይክል ይህን ሲናገር በኩራትና ያለው ነገር እንደሚፈፀም በተማመነ ድምፅ ነበር።
«የቀለበት ማሰሪያ ፌስታ መሆኑ ነዋ!» አለ ቤን በጣም ነቃ ብሎ።« ይኸ ከሆነማ ብዙ ቢፍ - ኢተር ጂን ሊያስጨምር ይችላል ።። ቢያንስ ሌላ ስድስት ወይም ሰባት ስምንትም ያስጨምራል አትለኝም !››
«ቀለበት አይደለም ፤ ሰርግ ። ሰርግ አልኩህ « ሰርግ ታወቃለሀ፣ ቤን»
«ዛሬ? ሰርግ ?» አለ ቤን ግራ ተጋብቶ «ለምን ዛሬ "ለምን ?»
«ምክንያቱም ዛሬውኑ እንዲሆን ፈለግና ። ዛሬ መጋባት ደስ አለና !» አለ ማይክል ። «ያም ሆነ ይህ እንዲህ ደንዝዘህ ቢነግሩህም ስለማይገባህ ይቅር ። ግን ሚዜ አንደኛ ሚዜው አንተ ነህ ብልህ ያን ያሀል ሰምተህ መረዳት ትችላለህ››
«በደንብ ነዋ!-የውሻ ልጅ።ደሞ ይኸን ልጣ ግን እውነት ዛሬ ልትጋቡ ነው” እንደ እዞ ብድግ ብሎ ከወንበሩ ላይ ዘሎ ሲወርድ አደናቀፈውና ጀበናውን በእግሩ መታው ። «የተረገመ እንቅፋት»
«እየው። እንዲህ ከሆንክ ራስሀን ታጠፋለህ ። ስለዚህ ቀስ ብለህ ሂድና የሆነ ልብስ...» አለ ማይክል። .
«ልክ ብለሃል...»
እያጉተመተመ ወደ መኝታ ቤቱ ገባ ። ሲመለስ ትንሽ ስውነቱን ሰብሰብ ለማድረግ ሞክሮ ነበር ። ትንሽ ነቃ ብሎ ልብሱንም ለብሶ ነበር። አንዲያውም ሰማያዊና ነጭ ነጠብጣብ ባለው ቲሸርት ላይ ክራሻት አስሮ ነበር ። ማይክል ሁኔታውን ካዬ በኋላ ፈገግ ብሎና ራሱን ነቅንቆ ፤ «ምናለበት ባይሆን ቆለሙ ወደ ቲሸርቱ የሚጠጋ ክራቫት ብታስር ! መቼም ቲሸርቱ ይሁን እንበል» አለ ። ክራቫቱ ጥቁር ሲሆን አልፎ አልፎ ቤዥ ጣልጣል ያለበት ነበር። «ለመሆኑ ክራሻች ያስፈልገኛል እንዴ ?» አለ ቤን ። «ለዚህ ቲሸርት የሚሆን ቀለም ያለው የማገኝ አይመስለኝም» ሲል ጨመረ እየተጨነቀ ።
«ተወው አትጨነቅ ፤ ይቅር ። ግን ለጊዜው ሱሪህን ቆልፍ። ከዚያ አለቀ። እንሄዳለን ። ደሞ ጫማ ያደረግከው ባንድ እግርህ ነው? ያኛው እግርሀም ጫማ ሳያስፈልገው አይቀርምና በል አንደኛውን ጫማ ፈልገው» ቤን እግሩን አየና ባንድ እግሩ ብቻ ጫማ እንዳደረገ ሲገነዘብ ሳቁን ለቀቀው ።
👍21😁1
«እሺ ፤እሺ ። በቃ ዞሮብኛል ። ምንም ማድረግ አልችልም ። ወይ አስቀድመህ ዛሬ ማታ እፈልግሃለሁ ብትለኝ ደግ ። ዛሬ ጧት ተገናኝተን ነበር ፤አይደለም ?ያኔ ልትነግረኝ ትችል ነበር ቢያንስ» አለ ቤን አቭሪ ፤እየሳቀ ጀምሮ ወደ መጨረሻው ግን ከምር በሆነ አነጋገር።
«ጧት አላሰብኩትማ፤ይህ እንደሚሆን እላወቅኩም ነበርኮ»
«አላወቅኩም ነበር›› ቤን ይህን ጥያቄ የጠየቀው ስካር የሚባል ነገር በማይሰማበት ድምፅና በቁም ነገር ነበር ።
«በፍጹም ስልህ!›
«እውነትህን ነው? ወይስ ታሾፋለህ?››
«ምንም አላሾፍኩም ። አሁን በቃ ። እንዴት አላወክም ፤ ጭቅጭቅ ፤ ስብከት አልፈልግም ። አሁን ካንተ የምፈልገው የረሳኸውን ሁሉ አስተካክለህ እንድንሄድ ነው ። ናንሲ ትጠብቀናለች ማይክል ይህን ሲል ቤን እቭሪ ግራ በመጋባት ይመለከትው ነበር። ይኸኔ ማይክል ፣ «ስካሩ ትንሽ ለቀቅ እንዲያደርግህ ይሀን ጠጣበት» ብሎ ቡና ሰጠው። ቤን ቡናውን ትቀብሎ ፉ…ት እድርጎ ከጠጣለት በኋላ ፊቱን አኮፋተረና በመፀፀት ድምጽ…
«ያን የመሰለ ጂን እንዲህ ብላሽ ሆኖ ይቅር» አለ ።
«ግዴለህም ፤ ከሰርጉ ፍጥምጥም በኋላ ትተካበታለህ»
«በነገራችን ላይ የት ነው ፍጥምጥሙን የምታደርጉት?»-
«ልታየው እይደለም ? አይዞሀ ምንም ችግር የለም ። ሁል ጊዜም የማትረሳኝ አንዲት ትንሽ ከተማ አለች ። ከዚህ የአንድ ሰዓት መንገድ ያህል ብትሆን ነው ። በልጅነቴ እንድ ጊዜ ለእረፍት ወስደውኝ አይቻት እንደ ወደድኳት ቀረሁ ። ለሰርግ የምትስማማ ናት»
«እንዴት ነው ፤ የጋብቻ ፈቃድስ ?» አለ ቤን ። (ያገባ ሰው በጋብቻ ላይ ጋብቻ እንዳይፈጽም በማሰብ ማንም ሰው እገሌ የተባለው ሰው ያላገባ ወይም ወዘተ ስለሆነ ሊያገባ ይችላል የሟል ፈቃድ ያስፈልገዋል ።)
«አያስፈልገኝም ። ከተማዋ ከዚህ አይነቱ ጣጣ ነፃ ናት። የፈለግከውን በፈለግከው ሰዓት ብታደርግ ማንም አይጠይቅህም ። ገለፃው ይበቃ መሰለኝ ። አሁን ዝግጁ ከሆንክ እንሂድ» ቤን ቡናውን ጨለጠና «አዎ መሄዱ ይሻላል። እረ በእግዚአብሔር ፤ ሁሉ ነገር እንግዳ ሆነብኝ አይደለም እንዴ ?፣ ተደነጋገርኩኩ ፤ ፍርሃት ፤ፍርሃት አይልህም ? »
«ቅንጣት ታህል!» |
‹‹ የምናልባት ነገሩን ደህና አርገህ ባታላምጠው ይሆናል ። እኔ እንጃ ... ሠርግ ፤ ጋብቻ ሲሉኝ… ህእ!» ቤን ይህን ተናግሮ ራሱን በአግራሞት እየነቀነቀ እንደገና ባንድ እግሩ ጫማ እንዳላደረገ እየ ።ጫማውን ሊፈልግ እየተነሳ «ምንም እንኳ ናንሲ ግሩም ልጅ ብቅሆን!» አለ ስለ ጋብቻ እንደማይገባው የተናገረውን በመቀጠል ።

«ከግሩምም በላይ ናት» አለ ማይክል። ቤን ይነሳ እንጂ ጫማውን ለመፈለግ አልሄደም ነበረና ማይክል ፈልጎ አመጣለት ። ከዚያም በአክብሮት ጎንበስ ብሎ በሁለት እጁ ጫማውን ለቤን አቀረበለት፡፡
«ተባረክ» አለ ቤንም ቀልዱን በመቀበል ። ደርሰው ለመሂድ እቆበቆቡ ። ከዚህ ዓይነቱ ጭቅጭቅ ሲወጡ የሚችሉት ቤቱን ሲለቁ መሆኑን የተገነዘቡ ይመስሉ ነበር… ከዚህ የቁም ነገር ምልልስ ለመላቀቅ ፤ ለመፈንጠዝ ፤ በደስታ ቴሞልቶ ለመሳቅ ።

“እንዴት ነው አሁን? ምንም የሚያሳፍር ነገር የለም ?» አለ ቤን ጫማውን ካደረገ በኋላ እሱሪው ኪስ እየገባ ። «የምን ማሳፈር፣ዝንጥ ብለሀልንጂ !»
«እሱን ተወው ! ያ የተረገመ ቁልፍ መያዣዬን ደሞ የት ጣልኩት ይባላል !» ማይክል እያየው ሲስቅ ግራ ተጋብቶ የተቀመጠበትን ቦታ እና አካባቢውን መቃኘት ጀመረ። ቁልፍ መያዣው እሱሪው የጎን የቀበቶ ማስገቢያ ጥብጣብ ላይ ተንጠልጥሎ ነበር ። «ያውልህ ቁልፉ ፤ ቶሎ በል። በቃ እንሂድ»

ከዚያም ክንድ ለክንድ ተያይዘው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የመጠጥ ቤት ዘፈን እየዘፈኑ ወጡ ። እየዘፈኑ ጉዟቸውን ቀጠሉ። ማንም ሰው ወጥቶ አትረብሹን አላላቸውም። ያ አካባቢ በጠቅላላ የሀርቫርድ ተመላላሽ ተማሪዎች ተከራይተው የሚኖሩበት አካባቢ ስለሆነ በተለይ እንዲህ ትምህርት ቤት ለእረፍት ሊዘጋ አካባቢ ፤ ማለትም ከፈተና በኋላ ሁሉም የሚያደርገው በመሆኑ ማንም ማንን ረበሽከኝ ሲል አይችልም ። ወቅቱ የነፃነትና የመቦረቅ ነበር ።

እናንሲ ቤት አጠገብ ሲደርሱ መኪናቸውን አቆሙ ። ከዚያም ማይክል ጥሩምባውን አንዴ አምባረቀው። ናንሲ ዝግጁ ሆና ስትጠብቅ ዓመታት ያለፉ ሲመስላት ነበርና ጥሩንባውን ሲያንባርቀው ተንደርድራ ወጥታ በአፍታ አጠገባቸው ገጭ አለች ። ናንሲን ሲያዩ ሁለቱ ወንዶች መብረቅ የመታቸውን ያህል
ደነገጡ። ፀጥ አሉ። «የስላሴ ያለህ ናንሲ። እንዴት ነው እንደዚህ ቁንጅት ያልሽው በይ!-..ደሞ ይኽን ቀሚስ ከየት አመጣሽው?» አለ ማይክል ፀጥታውን እየገሰሰ። «ነበረኝ!» አለች ናንሲ ። ሁለቱም የፍቅርና የመነፋፋቅ ፈገግታን ተላበሱ ። በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ስሜቷ ሲራወጥ ተሰማት ። ድንገት ሁለንተናዋ የሙሽራ የሆነ መሰላት ። ለሱም ። ክእግር እስከራሷ ሙሽራ ሆና ታየችው።

አንገትጌው በሐር ጥልፍ የተጌጠ ነጭ ረጂም ቀሚስ ለብሳ ፤ ጥቁር ሐር ምስጋን ይንሳው በሚያሰኘው ፀጉሯ ላይ ሰማያዊ የሐር ኮፍያ አድርጋለች ። ነጭ ሰንደል ተጫምታ ፥ በእጇም ጥንታዊነት ያለው የሚመስል እጅግ የሚያምር የተጠለፈ መሀረብ ይዛለች። ቃላት ሊገልጹት በማይደፍሩት መጠን ተውባ ፤ ቆንጅታ ነበረና ለተወሰነ ጊዜ ማይክል ምንም ቃል ትንፍሽ ሊል አልቻለም። ቤን አቭሪ እንኳ እንዲያ ሆና ሲያያት ስካሩ ፈፅሞ ጥሎት የበረረ ይመስል ነበር ።

«ታያላችሁ ይህንን ? በጣም ውብ ፤ በጣም ጥንታዊ ነው» አለች መሀረቡን እያሳየቻቸው ፤«ከሴት አያቴ ያገኘሁት የውርስ እቃ ነው»
«ልእልት መስለሻል ኮ ናንሲ» አለ ቤን አቭሪ።
«እግዜር ይስጥልኝ ቤን»
«እንዴ!.›. ቆይ ...ስሚ ናንሲ። በውሰት የወሰድሽው አንድ እቃ ይዘሽ የል! »
«ምን ማለትህ ነው ቤን?»
«ውብ... ጥንታዊ የሆነ መሀረብ ይዘሻል፤ አይደለም? ጥሩ… አሁን ደግሞ አዲስ የሆነ ውብ እቃ መዋስ ያስፈልግሻል» አለ ቤን ፤ « ያ እቃ አለሽ?» ፣
«የለኝም» አለች እየሳቀች ።
«ደግ» አለና ካንገቱ አንድ ነገር ለማውለቅ መታገል ጀመረ ቆንጆ የወርቅ ሀብል አወለቀና፤ «ያዥ ። ይኸ ግን ስጦታ አይደለም ። ውሰት ነው። ለምረቃ በአል የደስ ደስ እህቴ የላከችልኝ ስጦታ ነው፡፡ ችኩል አይደለሁ! ከምረቃው በፊት አደረግሁት ። ስለዚህ ለሰርግሽ እለት ላውስሽ እችላለሁ» አለና ከመኪናው ወጥቶ እንገቷ ላይ አጠለቀላት ።

የወርቁ ሃብል ከአብረቅራቂው የቀሚስ ጥልፍ ጋር በጣም አደመቃት። «አሁን ሁሉ ነገር ድንቅ ሆነ» አለች ወርቁን እያየች ። «አንችም ድንቅ ልጅ ነሽ» አለ ማይክ እየወጣና የመኪናውን በር እየከፈተ ። «በል ቤን ወደ ኋላ እለፍ›› የኔ እመቤት ፤አንች ጋቢና ግቢ »
«ለምንድነው ኋላ እምሄደው? ለምን ? እጭኔ ላይ መቀመጥ አትችልም?» አለ ቤን እንደ ሀፃን ልጅ እየተነጫነጨ። ማይክል በቁጣ አፈጠጠበት ። በዚህ ጊዜ ቤን ወደኋላ ወንበር እየተሸጋገረ ፤
«እሺ ፤ በቃ አትቆጣ ! እኔ ደሞ አንደኛ ሚዜ ስለሆንኩ ምንም አይደል ...»
«ይህን ጠባይህን በጊዜ ካላረምክና ካልተጠነቀቅክ ...ዋ! ለነፍስህ ብታዝናላት ይሻልሀል »
👍15
እንዲህ እየተቀላለዱ ቦታ ቦታቸውን ያዙ። ናንሲ ማይክልን በጉጉት አየት አደረገችው። ወዲያው ማሪዮን ምን ብላው ይሆን ? የሚል ጥያቄ መጣባት ።ግን በሀሳቧ አልገፋችበትም ። አሁን ስለሷና ስለማይክል ብቻ ማሰብ ያለባት ጊዜ ነው። «ምን አይነቱ ሌሊት ነው? ምስቅልቅሉ የወጣ ፤ ጅል የሚያደርግ ! ግን ደስ ይላል» አለች። ከዚያም እየቀለዱ ፤ እየተበሻሸቁ ፤ የውሸት እየተጣሉ ጉዟቸውን ቀጠሉ። ከጊዜ በኋላ ድንገት ጸጥ አሉ። ሁሉም በየግል ሐሳባቸው ውስጥ ሰመጡ። ማይክል ከእናቱ ጋር ስለተለዋወጣቸው ንግግሮች ሲያሰላስል ፤ ናንሲ ደግሞ ይህች ዕለት በሕይወቷ ውስጥ ተመዝግባ ለዘለዓለም የምትኖር ልዩ ሌሊት እንደሆነች ታስብ ነበር ። በዚህ ሁኔታ ብዙ ተጓዙ ።

« ገና ብዙ መንገድ ቀረን ፤ ማይክ ፣ » እለች ናንሲ ።ደርሶ ጭንቅ ፣ ጭንቅ ይላት ጀምሮ ነበር ። መሐረቧም መጨማደድ ጀምሯል። «ይደርሰናል ። አምስት ማይል ያህል ቢቅረን ነው» አለ ማይክል አንድ እጁን ሰደድ አድርጐ የናንሲን እጅ ጭብጥ እያደረገ ። እጅዋን እንደያዘ ፣ « በቃ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሕግ ባልና ሚስት ነን። ሚስ ማክአሊስትር ሚስዝ ሂልያርድ ትሆናለች » አለ ።
« እንደሱ ካልክ ታዲያ ምን ትንቆራዘዛለህ ። ቤንዚን ስጠዋ ለመኪናው። እኔ 'ኮ እዚሀ ብቻየን ተቆራምጄ ብርድ ወደ በረዶነት ሊቀይረኝ ምንም ያህል አልቀረኝ አለ ቤንጃሚን አቭሪ ከኋላ ወንበር በቀልድ የእሮሮ ድምፅ ። በዚሀ ጊዜ ሦስቱም አንዴ ሳቁ፡፤ እወኩ ። እየሳቁ ሲጠመዝዝ መኪናው ተወንጭፎ ሲዞር ሳቁ ባንዴ ቀጥ አለ … ወደ ፍርሃት ትንፋሽ ተቀይሮ አንድ የጭነት መኪና መንገዱን ግጥም አድርጎ ያላንዳች ማመንታት ወደነሱ ሲምዘገዘግ ያየው ማይክል በሆነ መንገድ ሾልኮ ለማምለጥ ከመሪው ጋር በብዙ ታገለ ። ሆኖም የመጣባቸው ካምዮን ፍጥነት ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ፍሬኑ የተበጠሰ ይመስል ነበር። ወይም ነጂው እንቅልፍ ተጭኖት ሊሆን ይችላል አይታወቅም ። ሁሉ ነገር ባዶ ሆነ ። በዚያች ቅፅበት ኖንሲ የሰማችው ድምፅ ቢኖር «አህ ! እምላኬ »- የሚለውን የቤን እቭሪን ድምፅና የራሷን ጭርር… ያለ ጩኸት ነበር «ከዚያ ቀጠለ ፤የመስታወት መሰበር ድምፅ… ከሽ…..ጥርቁስ...ከሽ…ቃቃ.. ከሽ…ከሽ... ብረት ቋ ድቅቅ. . . ጥርምስ. ጥርምስምስምስ የሞተር ማጓራት ፤ ድርርር ጥዝርር . . እጅ ሲወናጨፍ ፣፤ እግር ሽቅብ ሲነሳ ፤ የመቀመጫው ሶፋ ቆዳ ሲሰረጠጥ . . ፕላስቲክ ሲቀረደድ ታያት ። ቀጥሎም ሁሉ ነገር የመስታወት አቧራ ሆኖ ታያት። በመጨረሻ ሁሉም ነገር ፀጥ፤ቀጥ አለ። ፡ አለም ባዶ.ሆነች ። ጨለማ ሆነች ።

ቤን አቭሪ ነፍሱ መለስ ስትልና ሲነቃ አያሌ ዓመታት ያለፉ መሰለው ። ራሱን እንደ ታምቡር ይወቅጠዋል ፤ ሁሉ ነገር ጨለማ መሰለው ። አፉ ውስጥ እፍኝ አሸዋ የተጠቀጠቀ መስሎ ተሰማው ። ካያሌ ዓመታት በኋላ ዓይኑን የገለጠው ደግሞ ከበርካታ ሰዓቶች በኋላ ሆኖ ተሰማው ። በዚህ ረጂም ጊዜ ውስጥ ዓይኑን በመግለጥ ያደረገው ትግል ከማድከም አልፎ' የሕመም ስሜት አሳደረበት ። ዓይኑን እንደገለጠ ያየውን ነገር ምንነት ለመ ገንዘብ አልቻለም ። እየቆየ የሚያየው ነገር ዓይን መሆኑን ተገነዘበ። ቆይቶ ማይክል መሆኑን አወቀ ። በመጀመሪያ ያየው የማይክልን ቀኝ ዓይን ነበር ። ይሀን ሲያይ ጋቢና ውስጥ መሆኑንና ከማይክል ጎን መውደቁን ትረዳ ። ቀስ እያለ የማይክልን ሙሉ ፊት ሳይሆን በስተጎን እንደሚያየው ሲረዳና ከማይክል ከቅንጡ ወይም ከጆሮ ግንዱ አካባቢ ደም ኮለለለለ… እያለ በእንገቱ ላይ ሲወርድ ተመለከት ። ምንም እንኳ ደም ከጓደኛው ላይ ሲወርድ ዝም ብሎ በመደነቅ መመልከት የሌለ እንገዳ ነገር ቢሆን በዚያች ቅፅበት ቤን አቭሪ የፈጾመው ግን ይሀንኑ ነበር። ቆይቶ ተመለከተ…. ማይክልዋ ነው |...» ደሙ እየፈሰሰ ቱ ነው ! የየሱስ ክርስቶስ ያለህ ! ማይክ እየደማ...ደማ።.... ቢያንስ የማይክል ደም እየፈሰሰ መሆኑ ትውር አለለት። ምን? አደጋ ፤?... አደጋ ደርሶ ነበር… ትዝታ በቀስታ ። ማይክ ነበር መኪናውን ይነዳ የነበረው ። ቀና ብሎ ሁኔታውን ለመመርመር ሲሞክር የሆነ ነገር ቀወረው እንደመዶሻ ። ወደነበረበት ተመለሰ ። ዓይኑም ተከደነ ። ደቂቃዎች አለፉ ። እንደገና ዓይኑን ገለጠ ። ማይክል አሁንም አለ። አሁንም ደሙ እየፈሰሰ ነው። ማይክል ቅድም እንዳየው ፀጥ ብሎ ወድቋል ። በደንብ ተመለከተው ። ሲተነፍስ ታየው። አልሞተም፣ ሕይወቱ አላለፈችም ። እንደገና ሊነሳ ሞከረ አሁን ራሱን ምንም ነገር አልመታውም ። እንደ ምንም ብሎ ቀና አለ ፡፡

ከማይክል ጐን የገጫቸው ካሚዮን ተገልብጦ ጎማዎቹ ተንጠልጥለው አየ ። ያኔ ያላየው ነገር ቢኖር የካሚዮኑን ሾፌር ነበር ። ያ ሾፌር እጋቢናው ሥር ወድቆ መኪናው ተጭኖ ገድሎት ነበር ። ምናልባትም ያን ሰው ማንም ሳያየው በርካታ ሰዓቶች ሊያልፉ ይችሉ ይሆናል ። አካባቢውን ቀስ እያለ ሲመለከት ወደ ውጭ የሚያየው በክፍት ቦታ አሳልፎ መሆኑን ተገነዘበ የአቶሞቢሏ መስትዋት እንዳለ የለም። ረግፏል ። አቧራ ሆኖ አልብሷቸዋል አፉ ውስጥ አሸዋ የመሰለው የደቀቀ መስታወት ኖሯል። በማይክል በኩል ያለው በር ተገንጥሏል ። ይህን ጊዜ አንድ ነገር ትዝ እለው። ምን? ምን ? አዎ አንድ ሰው አብሯቸው ነበር። አዎ ነበረ ።ማን?.... ናንሲ!... ናንሲ አብራን ነበረች !.... የት ነበር የሚሄዱት? የት . ?ሊያስታውስ አልቻለም ። ከባድ ራስ ምታት ይወቅረዋል ። ናንሲ ! ተገላበጠ ። ጠቅ አደረገው ራሱን ። ተንቀሳቀሰ ። እንደጦር የሚወጋ የሕመም ስሜት በአካሉ ዳር እስከ ዳር የተሰመጠጠ መሰለው። ያ ሕመም ሽቅብ ወገቡ ድረስ ዘልቆ ተገላበጠ። ከሕመሙ ለመሸሽ ተንቀሳቀለ ። ያኔ አያት ናንሲን ። የሆነ ነጭና ቀይ ቀለም ያለው ዝንጉርጉር ቀሚስ ለብሳ ፤ የፊት መስታወት በነበረበት በኩል ዘልቃ ፣፤ እኮፈኑ ላይ በፊቷ ተደፍታ ። ናንሲ ! ሞታለች ማለት ነው ! አሁን ስለ ሕመሙ አልተጨነቀም ። እግሩ እንደጦር ቢወጋውም አልተሰማውም ። ወዳለችበት እንደምንም ተገላብጦ እየተጎተተ ሄደና ወጣ። አዎ መሄድ አለበት... እንደምንም ብሎ መገልበጥ አለበት
ናንሲ… ወይኔ ናንሲ ! . . ሲጠጋ ፀጉሯ ላይ የተበተነው የደቀቀ መስታወት ታየው ። ለብሳዋለች። የፊት መስታወቱን በጠቅላላ በአካሏ ለብሳዋለች ። ደቃቅ ዱቄት ሆኖ ልብስ ሆኗታል ። ፀጉሯ፤ ልብሷ ፤ ጠቅላላ አካላቷ - - አምላኬ ምነው!.. ምነው! .. ያለውን ኃይል አጠራቅሞ ቀስ ብሎ ገለበጣት ። ከዚህ በኋላ በሚያሳዝን ሁኔታ በጨለማ ብቻውን እንደተዉትና እንደፈራ ልጅ ያምቧቅስ ጀመረ ።
«ምነው አምላኬ !..ምነው!»

ፊቷ!.. ወይኔ ናንሲ ?. . . ፊቷ ፈፅሞ ጠፍቶ ነበረ። ሞታ ይሆን ! ? ርግጠኛ መሆን አልቻለም ። ሆኖም ላንዲት አስፈሪ ቅፅበትም ቢሆን ብትሞት ሲል ተመኘ ። ጭካኔ አልነበረም ይህን ያስመኘው ። ተርፋም ሰው እንደማትሆን ስለተገነዘበ ነበር ። ድንገት ስለገባው ነበር ። ውብ ፊቷ ምንም ቅሬታ ሳይተው ሞቷል ። ሌላ የተተፈተፈ ፤ የተጠቀጠቀ ፤ የተተለተለ ፊት ሆኗል። ናንሲ አልነበረችም ናንሲ የለችም። ይህን ሲያስብ መንፈሱ እጅግ ተጨነቀ ። ከዚያም ምህረት ወረደለት ። በሷ ደምና በሱ እምባ እንደራሰ ተዝለፈለፈና አሸለበ ።


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍21👎4
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_አራት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


በቢዝነስ ዓለም ውስጥ ያለ ሰው በሌላ ሰው መናደድ ገንዘቡ አይደለም፡፡
ይህን ከረጅም ጊዜ በፊት ተምራለች፡፡ ‹‹ቦስተን በጊዜው አልደርስም፧ ነገር
ግን የኩባንያውን ሽያጭ እዚህ ሆኜ ማስቆም እችላለሁ›› ስትል አሰበች፡፡
ወደ ስልኩ ዞረችና አሁን ቦስተን ውስጥ አንድ ሰዓት ነው፡፡ ጠበቃዋ ፓትሪክ ማክ ብራይድ ይሄኔ ቤቱ ነው የሚሆነው፡ ለስልከኛው የጠበቃዋን ስልክ ሰጠች.

ማክ የወንድም ያህል ነው ለእሷ ባሏ የሞተ ጊዜ ሁሉን ነገር አድርጎላታል፤ ቀብሩን ማስፈፀም፣ የባሏን ኑዛዜ እና የግል ገንዘቧን
መቆጣጠርና መከታተል፣ ልጆቿንም ወደ መጫወቻ ቦታ በመውሰድ በትምህርት ቤት የተወኑትን ድራማ በማየት፣ ኮሌጅ ሲገቡ የሚመርጡትን
ትምህርትና ኮሌጅ ካጠናቀቁም በኋላ የሚይዙትን የስራ አይነት በማማከር በኩል የአባት ያህል ሚና ተጫውቷል፡፡ ስለወሲብ ማወቅ የሚገባቸውን ነገር
እንኳን አልደበቃቸውም፡፡ የፒተርና የናንሲ አባት የሞተ ጊዜ ፒተር የኩባንያው ሊቀ መንበር እንዳይሆን የተቻላትን ማድረግ እንዳለባት መክሯት
ነበር፡፡ እሷ ግን የነገራትን በወቅቱ አልተቀበለችውም፡ አሁን የደረሰው ነገር ታዲያ ማክ በዚያ ጊዜ ያለው ትክክል መሆኑን አሳይቷታል ማክ እንደሚወዳትም ታውቃለች፡፡ ማክ አጥባቂ ካቶሊክ ሲሆን ለሚስቱ ታማኝ አይደለም ለፈስፈስ ያለና ራሰ በራ ነው፡፡ እሷ የምትፈልገው ቆፍጣናና
ፀጉረ ሙሉ ወንዶችን ነው ልክ እንደ ናት ሪጅ ዌይ ያሉ፡፡

የስልክ ግንኙነት እስከሚገኝ ድረስ ያለችበትን ሁኔታ ማውጠንጠን ጀመረች፡፡ ከፒተር ጋር አብሮ ሴራ የሚያውጠነጥነው የአባቷ ምክትልና የአንድ ወቅት ፍቅረኛዋ የነበረው ናት ሪጅ ዌይ ነው፡፡ ናት የኩባንያውን ዋና ኃላፊነት ቦታ ሲያጣ ኩባንያውንና ናንሲን እርግፍ አድርጎ እብስ አለ፡ አሁን ደግሞ የጄኔራል ቴክስታይልስ ኩባንያ ፕሬዚዳንት በመሆኑ የብላክ ጫማ ኩባንያን ለራሱ ለማድረግ ይመኛል፡፡

ናት የጫማ ሳምፕሎች ሊሰበስብ ፓሪስ መምጣቱን ታውቃለች፧ ምንም እንኳን ባታገኘውም፡፡ ፒተር ከእሱ ጋር ተገናኝቶ ስምምነት እንዳደረጉ ገምታለች፡፡ ናንሲ ደግሞ ይህን አልጠረጠረችም ምን ያህል በቀላሉ እንደተታለለች ስታውቅ በፒተርም በናትም በጣም ተናደደች በይበልጥ ግን በራሷ።

ስልኩ ጮኸና አነሳችው፡፡ ዛሬ የስልክ እድሏ ሰምሮላታል፡
ማክ አፉን በምግብ ሞልቶ ሃሎ አላት፡፡
‹‹ማክ ናንሲ ነኝ››
የጎረሰውን ዋጥ አደረገና ‹‹ይመስገነው መደወልሽ፡፡ አውሮፓ ውስጥ አንቺን በስልክ ያልፈለኩበት ቦታ የለም፡፡ ፒተር. አለ፡፡

‹‹አውቄያለሁ አሁን ሰማሁ›› ስትል አቋረጠችው ‹‹ምንድን ነው
ስምምነታቸው?››

‹‹ለብላክ ጫማ አምስት አክሲዮኖች ከጄኔራል ቴክስታይልስ አንድ አክሲዮን ከ27 ሳንቲም ጋር››

‹‹በኢየሱስ ይሄማ በነፃ መስጠት ነው!››

‹‹አሁን ከምታገኙት ትርፍ አንፃር ፒተር ያቀረበው ዋጋ ትንሽ አይደለም፡፡››

‹‹ታዲያ የእኛ የቋሚ ንብረት ዋጋ እኮ ከፍተኛ ነው›› አለች ናንሲ ጮሃ።

‹‹እንዴ ከእኔ ጋር እኮ አይደለም ጠብሽ›› አላት ለስለስ ብሎ

‹‹ይቅርታ ማክዬ ተናድጄ ነው››

‹‹ይገባኛል፡፡››

በስልኩ ውስጥ ልጆቹ ሲንጫጩ ይሰማታል፡፡ አምስት ልጆች አሉት ሁሉም ሴቶች ናቸው፡፡ ሬዲዮና ጀበና ሲያፏጭ ይሰማታል፡፡
‹‹ፒተር ያቀረበው ዋጋ ዝቅተኛ እንደሆነ አሁን ገብቶኛል፡ ብላክ ጫማዎች ኩባንያው የሚገኘውን ትርፍ እንዲህ ያለውን ቋሚ ንብረትና የወደፊት እምቅ ሃይል ግምት ውስጥ አላስገባም›› አለ ‹‹ሌላም ነገር አለ››

‹‹ምንድን ነው?››

‹‹ጄኔራል ቴክስታይልስ የእናንተን ኩባንያ ከተረከበ በኋላ አምስት አመት ድረስ ፒተር እንደሚያስተዳድረውና አንቺም ቦታ እንደሌለሽ
ተስማምተዋል፡››

ናንሲ ዓይኗን ጨፈነች፡፡ እንደዚህ አይነት ጥቃት ደርሶባት አያውቅም፡፡
ህመም ተሰማት፡፡እስከዛሬም ወንድሟ ደካማነቱ እንዳይታወቅ በኃላፊነት እንዲቆይ ስትረዳውና ኩባንያውም ከስሮ ከገበያ እንዳይወጣ ስትለፋ ኖራ እሷ ከስራ ትባረር! ‹‹እንዴት ይሄንን ደባ በእኔ ላይ ይፈፅማል?›› አለች፡፡

‹‹ወንድሜ አይደለም?››
‹‹ናን በደረሰብሽ ዱብ ዕዳ አዝናለሁ››
‹‹አመሰግናለሁ ማክ›› አለች፡፡
‹‹እኔ መቼም ከድሮም ፒተርን አላምነውም ነበር››
‹‹አባታችን ይህን ቢዝነስ ለዓመታት ሲገነባ ኖረ›› ስትል አለቀሰች፡:
‹‹ፒተር ይህን ኩባንያ ማጥፋት የለበትም››
‹‹ምን ላድርግልሽ እኔ ታዲያ?›› አለ ማክ
‹‹ይህን ደባ ማስቆም እንችላለን?››
‹‹የቦርድ ስብሰባው ላይ ብትደርሺ የአክስትሽና የዳኒ ሪሌይን ሃሳብ ማስለወጥ የምትችይ ይመስልሻል?››
‹‹በሰዓቱ መድረስ አልችልም ችግሬ ይሄ ነው፡፡ አንተ ልታሳምናቸው አትችልም?››
‹‹እችል ይሆናል ነገር ግን ምን ሊፈይድ፡፡ ፒተር ባለው የአክሲዮን ድርሻ የአክስቱን ሃሳብ ውድቅ ማድረግ ይችላል፡ የአክስቱና የዳኒ አክሲዮን ቢደመር 20 በመቶ የእሱ ደግሞ 40 በመቶ ነው፡፡››

‹‹አንተ እኔን ወክለህ ድምፅ መስጠት አትችልም?›

‹‹የአንቺ ውክልና የለኝም››
‹‹በስልክ ድምፅ መስጠት እችላለሁ?››

‹‹ይሄ ሃሳብ ምናልባት ያስኬድ ይሆናል፡፡ የቦርዱ ውሳኔ ነው፡፡ ነገር ግን አሁን ፒተር ባለው ሃይል ሃሳቡን ውድቅ ማድረግ ይችላል፡››

ሁለቱም አዕምሮዋቸው በሃሳብ ሲርመሰመስ ለጥቂት ጊዜ ፀጥታ ሰፈነ፤
በዚህ ጊዜ ይሉኝታ ማጣቷ ታወሳትና ‹‹ቤተሰብ እንዴት ነው?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ልጆቹ ደህና ናቸው፤ ቤቲም አርግዛለች››

‹‹አሁንም?›› ልጅ መውለድ ያቆሙ መስሏት ነበር፡ ‹‹የመጨረሻው ልጅ ገና አምስት አመቱ አይደለም እንዴ?›› ስትል ጠየቀችው:

‹‹የችግሩን መፍትሄ አሁን ገና ነው ያገኘሁት›› አለ፡፡
ናንሲ ሳቀች ‹‹እንኳን ደስ አለህ!››
‹‹አመሰግናለሁ፡ ቤቲ ደስታም ሀዘንም ተሰምቷታል››
‹‹ደመወዝህ ግን ቤተሰብ ለማስተዳደር ይበቃሃል?››
‹‹ይበቃኛል፡፡ አይሮፕላን እንደማታገኚ ግን አረጋግጠሻል?››

ናንሲ ጫን ጫን ተነፈሰችና ‹‹አሁን ያለሁት ሊቨርፑል ነው፡ ሳውዝ ሃምፕተን ከሊቨርፑል 200 ኪ.ሜ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ እናም አይሮፕላኑ ሊነሳ የቀረው ሰዓት ከ2 ሰዓት አይበልጥም፡፡ አይቻልም››

‹‹ሊቨርፑል ከአየርላንድ እኮ ብዙ አይርቅም››
‹‹እባክህ ተወኝ ጂኦግራፊውን›› አለች፡፡
‹‹በራሪ ጀልባው አየርላንድ ያርፍ የለም እንዴ?››
የናንሲ ልብ ዘለለ ‹‹እርግጠኛ ነህ?››
‹‹ጋዜጣ ላይ አንብቤያለሁ››
ማክ የሰጣት አስተያየት ልቧን አነሳሳው፡ ተስፋዋም ለመለመ፡፡ ‹‹የት ነው የሚያርፈው ደብሊን ነው?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹አይደለም፡፡ በምዕራብ የባህር ዳርቻ የሆነ ቦታ፧ ስሙን ረሳሁት ያም
ሆነ ይህ ትደርሻለሽ›› አላት
‹‹አረጋግጬ እደውልልሃለሁ ባይ ባይ››
‹‹ናንሲ››
‹‹ምንድን ነው?››
‹‹መልካም ልደት››
ናንሲ ፈገግ አለች ‹‹አንተ የምትገርም ነህ፤ መቼም አትረሳም፡፡››
‹‹መልካም ዕድል››

‹‹ደህና ሁን›› አለችና ስልኩን ዘጋች፡ ወደ እንግዳ ተቀባዩም ሄደች ሰውዬውን ልክ ልኩን ልትነግረው ፈልጋ ነበር፤ ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት እርዳታውን ስለምትፈልግ የባሰ እንዳይተበትባት ማድረግ ነው ያለባት፡
‹‹በራሪ ጀልባው አየርላንድ ውስጥ ያርፋል አይደል?›› አለች ተለሳልሳ፡፡
‹ልክ ነው የኔ እመቤት፡፡ ፎየንስ የሚባል ቦታ፡››
‹ለምንድን ነው ታዲያ ቅድም ይህን ያልነገርከኝ አንተ ጉረኛ› ልትለው ፈልጋ ነበር ነገር ግን ፈገግ ብላ በስንት ሰዓት?› ስትል ጠየቀች፡
👍16
የበረራ ፕሮግራሙን አየና ‹‹ከቀኑ በ9፡30 ያርፍና 10:30 ላይ ይነሳል››
‹‹ታዲያ በሰዓቱ የምደርስ ይመስልሃል?›› ስትል ጠየቀች፡፡
‹‹ትንሽ አይሮፕላን የሁለት ሰዓት መንገድ ነው ፓይለት የሚያገኙ ከሆነ የሚሆንልዎት ይመስለኛል፡››

የልብ ምቷ ጨመረ፡፡ የሚቻል ነገር ይመስላል፤ ‹‹ወደ አየር ማረፊያው
የሚወስደኝ ታክሲ ጥራልኝ፡፡›› ጣቱን ፈትሎ በማስጮህ ተላላኪ ጠራና
‹‹ለእሜቴ ታክሲ ጥራላቸው›› አለው፡፡
‹‹ሻንጣዎችዎስ?አይሮፕላኗ ትንሽ በመሆኗ ይህን ሁሉ ሻንጣ አትችልም››
‹‹በመርከብ ላክልኝ፡፡ ደግሞ የሆቴሉን ክፍያ ተቀበለኝና ደረሰኝ ቶሎ
አምጣልኝ›› አለች፡፡

‹‹መልካም›› አለ እንግዳ ተቀባዩ

ናንሲ ወደ አልቤርጎዋ ተመልሳ በትንሽ ሻንጣ ውስጥ በጣም አስፈላጊ
የሆኑ እቃዎችን ብቻ ጠቀጠቀች፡፡ በእጇ ለብርድ የሚሆን ሹራብ ያዘች፡፡
‹‹እሜቴ ይሄውሎት ደረሰኙ›› አለ ስትመለስ፡፡
ያለባትን ወጪ ለመክፈል ቼክ ፃፈችና ከቲፕ ጋር ሰጠችው
‹‹አመሰግናለሁ እሜቴ፤ ታክሲ እየጠበቆት ነው››
ከሆቴሉ በጥድፊያ ወጣችና ታክሲ ውስጥ ጥልቅ አለች፡፡ እንግዳ ተቀባዩ ሻንጣውን ታክሲው ውስጥ አስገባና ታክሲ ነጂው ሴትዮዋን
የሚወስድበትን ቦታ ነገረው፡፡

‹‹በተቻለህ መጠን ፍጠንልኝ›› አለችው ናንሲ፡፡
መኪናው በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት መፈትለክ አልቻለም፡፡
ጫማዋን በብሽቀት ትጠበጥባለች፡፡ የትራፊክ እንቅስቃሴው የተጎተተው
የመንገዱ መሐል በቀለም እየተሰመረ ስለሆነ ነው፡፡ ይህም የሚደረገው ማታ
ማታ መብራት ስለሚጠፋ ለባለመኪኖች ምልክት እንዲሆናቸው መሆኑ
ገብቷታል፡፡

ታክሲው ከከተማ እንደወጣ መፍጠን ጀመረ፡፡ ይህ ቦታ ገጠር በመሆኑ የጦርነት ዝግጅት አይታይበትም፡፡ ጀርመኖችም በአጋጣሚ ካልሆነ የእርሻ ቦታዎችን በቦንብ አይደበድቡም፡፡ ሰዓቷን አሁንም አሁንም ታያለች፡ስድስት ሰዓት ከሰላሳ ሆኗል፡ የግል አይሮፕላንና ፓይለት አግኝታ ዋጋ ከተስማማች በሰባት ሰዓት ላይ ትበራለች፡፡ የእንግዳ ተቀባዩ በረራው ሁለት ሰዓት ይፈጃል ስላላት በዘጠኝ ሰዓት ትደርሳለች፡፡ ከዚያ በኋላ ከአየር ማረፊያው ወደ ፎየንስ (አየርላንድ) ትበራለች፡፡ ፎየንስ ርቀቱ ብዙም
ስላልሆነ እድል ከቀናት በጊዜ ትደርሳለች፡፡ እዚያ ከደረሰች በኋላ እስከ ባህር
ዳርቻው የሚደርስ መኪና ታገኝ ይሆን? ራሷን አረጋጋች፡፡

ወደ ኒውዮርክ የሚበረው የአየር በራሪ ጀልባ ቦታ በሙሉ ቢያዝስ አለች በሆዷ

የመርከቦች ቦታ በሙሉ ተይዟል፡
ይህን ሀሳብ ከአዕምሮዋ አወጣች፡፡
ለመድረስ ምን ያህል እንደቀረ ባለታክሲውን ልትጠይቅ ስትል ታክሲው
ወደ አየር ሜዳው በር ሲጠመዘዝ ‹‹እፎይ›› አለች፡፡ ታክሲው ግቢው ውስጥ ሲገባ በርካታ ትንንሽ አይሮፕላኖች ስታይ ልቧ በደስታ ዘለለ፡
የአይሮፕላኖቹ ቁጥር ቢያረካትም ፓይለት ማግኘት የግድ ይላታል፡በአካባቢው ደግሞ የፓይለት ዘር አይታይም፡፡
እዚህ መጉላላት አትፈልግም፡፡

ማረፊያው ላይ ሶስት አይሮፕላኖች ቢኖሩም ፓይለት ግን የለም መቼም የሆነ ፓይለት በአካባቢው መኖር አለበት አለበለዚያ በር ይዘጋ ነበር ወደ አይሮፕላኖቹ መጠለያ ጀርባ ስትሄድ ሶስት ሰዎች አንድ ትንሽ አይሮፕላን አጠገብ ቆመዋል፡፡

አይሮፕላኗ ከላይና ከታች በእንጨት ምሰሶ የተደገፉ ሁለት ክንፎች ያሏት ሲሆን አፍንጫዋ ላይ አንድ ሞተር ተሰክቷል፡፡

አይሮፕላኗ ነዳጅ እየሞላች ነው፡፡ በዘይትና በግራሶ የታጀለ ቱታ የለበሰ
አንድ ሰው አይሮፕላኗ መሰላል ላይ ቆሞ የነዳጅ ጋኑ ውስጥ ነዳጅ ይሞላል፡፡ መሬት ላይ በናንሲ ዕድሜ የሆነ አንድ መልከ መልካም ረጅም ሰው ራሱ ላይ የብረት ቆብ ደፍቶ ቆሟል፡፡ እሱም ከሌላ ሶስተኛ ሰው ጋር ወሬ ይዟል፡፡

ናንሲ ወደ ሰዎቹ ጠጋ ብላ ‹‹ይቅርታ ወንድሞቼ›› አለቻቸው፡፡ሁለቱ ሰዎች ድምጿን ሲሰሙ ዞር ብለው አይዋትና ፊታቸውን
መልሰው ወሬያቸውን ቀጠሉ፡፡

‹‹ወሬያችሁን ስላቋረጥኩ ይቅርታ፤ አይሮፕላን መከራየት ፈልጌ ነበር
አለች ናንሲ፡፡

ረጅሙ ሰው ወሬውን አቋረጠና ‹የለንም›› አላት፡፡

‹‹እባካችሁ አስቸኳይ ጉዳይ ገጥሞኝ ነው›› አለች ናንሲ፡
‹‹እኔ ታክሲ ነጂ አይደለሁም›› አለና መልሶ ፊቱን አዙሮ ወሬውን ቀጠለ፡፡

ናንሲም በጣም ተናደደችና ‹‹ሰውዬ ምን እንዲህ ያደርግሃል? አለችው።

ሰውየው ወደ ናንሲ ፊቱን አዞረና በዓይኑ ገረመማት፡፡ ጥቋቁር ቅንድቦቹ ያምራሉ፡፡ ‹‹ለዛ ብዬ ሳይሆን አይሮፕላኔ አትከራይም፡፡ እኔም ተከፍሎኝ የምነዳ ፓይለት አይደለሁም›› አላት፡፡
ተስፋዋ ሊሟጠጥ ትንሽ ቀርቶታል ‹‹እንደ ስድብ ካልቆጠርክብኝ ገንዘብ ከሆነ ያልከውን ዋጋ እከፍልሃለሁ. .

ሰውዬው ይህን ሲሰማ በንዴት ፊቱን ወደ ናንሲ አዞረ፡፡

ሰውዬው ነጭ መስመሮች ያሉት ጠቆር ያለ ሱፍ ልብስ የለበሰ ሲሆን ውድ ጫማ ተጫምቷል፡ ለመዝናናት ሲል የራሱን አይሮፕላን የሚያበር ሀብታም ሰው ለመሆኑ ሁኔታው ያሳያል፡

‹‹ሌላ ፓይለት አገኝ ይሆን?›› ስትል ጠየቀች።

መሰላሉ ላይ ቆሞ ነዳጅ የሚሞላው መካኒክ ‹‹ዛሬ ማንም የለም›› አለ፡
ናንሲ በተስፋ መቁረጥ ልታለቅስ ምንም አልቀራት፡፡ እዚህ ጥሩ አይሮፕላንና ፓይለት እያለ ደህና ገንዘብ እንኳን ብትከፍል የሚወስዳት የለም፡

‹‹ፎየንስ ልሄድ ፈልጌ ነበር›› አለች በደከመ ድምፅ፡ አይኖቿ እምባ አቆርዝዘዋል፡
ረጅሙ ሰው ፊቱን ወደ እሷ አዞረና ‹‹ፎየንስ ነው ያልሽኝ?›› ሲል ጠየቃት
‹‹አዎ››
‹‹ለምንድነው እዚያ የምትሄጂው?››
ሰውዬው አሁን ጆሮ እየሰጣት ነው፡፡ ‹‹የፓን አሜሪካን የአየር በራሪ
ጀልባ ላይ ለመሳፈር››
‹‹የሚገርም ነው›› አለ ‹‹እኔም ወደዚያው እየሮጥኩ ነው››
ተስፋዋ እንደገና አቆጠቆጠ ‹‹ወይ አምላኬ!ወደ ፎየንስ ነው የምትሄደው?››

‹‹አዎ›› አለ ፊቱን ቅጭም አድርጎ ‹‹ሚስቴን እያሳደድኩ ነው›› አላት፡
አባባሉ አስገረማት፡ አንድ ሰው ስለእንደዚህ አይነት ነገር ለሌላ ሰው ከተናዘዘ ወይ ደካማ ነው ወይ ደግሞ በራሱ በጣም ይተማመናል፡
አይሮፕላኗ ከፊትና ከኋላ ሁለት መቀመጫዎች አሏት፡
‹‹ሁለት መቀመጫዎች አሏት አይሮፕላንህ›› አለች በጉጉት ሰውዬው ገልመጥ አደረጋትና ‹‹አዎ ሁለት መቀመጫ አላት›› አለ፡፡
‹‹እባህክ ካንተ ጋር ልሂድ›› አለችው በሚያሳዝን ሁኔታ:
ለአፍታ ከራሱ ጋር መከረና ‹‹ምናለ እንሂድ›› አላት ትከሻውን ነቅንቆ፡፡
በደስታ ራሷን ልትስት ምንም አልቀራት ‹‹እግዚአብሔር ይስጥህ የኔ ወንድም›› አለች በእፎይታ፡፡
‹‹ምንም አይደል›› አለና አንዳች የሚያክል እጁን ለትውውቅ ዘረጋ
‹‹መርቪን ላቭሴይ እባላለሁ››
እጁን ጨበጠችና ‹‹ናንሲ ሌኔሃን›› ብላ መለሰች፡፡...

ይቀጥላል
👍16😱21👎1
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አራት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ በቢዝነስ ዓለም ውስጥ ያለ ሰው በሌላ ሰው መናደድ ገንዘቡ አይደለም፡፡ ይህን ከረጅም ጊዜ በፊት ተምራለች፡፡ ‹‹ቦስተን በጊዜው አልደርስም፧ ነገር ግን የኩባንያውን ሽያጭ እዚህ ሆኜ ማስቆም እችላለሁ›› ስትል አሰበች፡፡ ወደ ስልኩ ዞረችና አሁን ቦስተን ውስጥ አንድ ሰዓት ነው፡፡ ጠበቃዋ ፓትሪክ ማክ ብራይድ…»
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ስድስት (6)

እንዲያ ደሙ ምጥጥ ብሎ እሆስፒታል አልጋ ላይ ስታየው የእናት ልቧ በሐዘን ፍላፃ ተወጋ ። ሆስፒታሉ የደረሰችው ከሌሊቱ አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ነበር ። አደጋው መድረሱን እንደሰማች ባለው መንገድ በርራ ደረሰች ። መጓጓዣ ቢጠፋ በእግሯም ቢሆን መንገድ መቀጠሏ አይቀርም ነበር ። ግን ደግሞ ችግር አልነበረም ፤ ቢሆን ለማለት እንጂ ። በዚች ዓለም ያለሱ ማን አላት ። ያለሱና ያለ ድርጅቱ ኑሮ ለሷ ምኗም አይደለም ። ድርጅቱን የምትንከባከበው ይበልጥ እንዲደረጅ ፣ እንዲበለፅግ ያላንዳች ዕረፍት የምትደክመው ደግሞ ለሱ ለማውረስ ነው። እንድ ያላት እሱ ነው ። ለሱ ደግሞ ተራ ነገር ልትሰጠው ፤ ተራ ነገር ልታበረክትለት አትፈልግም ። ያዘጋጀችለት በረከት ኮተር ሂልያርድን ያህል ግዙፍ ድርጅት ነው ። ይሆን ስጦታዋን ታዲያ እንደቀላል ነገር ወርውሮላት ሊሄድ! ሊሞት!... የክርስቶስ ያለህ ! ዘገነናት ።. . . ያች መናጢ ናት ይኸን ሁሉ ችግር ያመጣችው. .. ያቺ ርጉም ሴት ናት እሷ መሆን አለባት ይህን ሁሉ እንዲያደርግ የገፋፋችው ።

አየችው-። ትናንት ሌሊት ላይ አደጋው ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ነፍሱን አያውቅም ። አንዴም ቀና አላለም ማሪዮን ሂልያርድ ክፍሉን ቃኘችው-። ያን ክፍል በደንብ ታውቀዋለች ። ከዚሀ በፊትም እዚህ ቦታ ተቀምጣ እንዲህ ሆኖ አይታዋለች ። ሐሳቧ ጠለፋት። የለም እሱ አይደለም ። ያኔ የታመመው ማይክል እልነበረም ። ሪቻርድ ነበር ። ሪቻርድ ሂልያርድ ፣ ሟች ባለቤቷ የማይክል አባት ትዝ አላት፡፡ ሆስፒታሉ ይህ አልነበረም ። ግን ያው ነው ፤ተመሳሳይ ነው አለች በሐሳቧ ።

ሪቻርድ ሂልያርድ በደም ሥሩ ውስጥ የረጋ ዶም አጣድፎ ሲገድለው-… ዕንባ አነቃት ። እንደምንም ታግላ መለሰችው ። ግን... ግን ማይክል አልሞተም ። አይሞትም ።እንዲሞት አልፈቅድለትም። እኔ እያለሁ አይሞትም ። ለማይክል የተመደበችው ነርስ ስትመለከታት አየች ። በነርሷ ፊት ላይ ምንም ዓይነት የተለየ ስሜት አይታይባትም ነበር። ከተቀመጠችበት ተነስታ ማይክል ወደተኛበት ሄደች ። ዓይኑን ገልጣ ተመለከተች ። ይህን ስታይ ማሪዮን ሐሳቧን አቋርጣ ወደ አልጋው ቀረበች ። ነርሷ ቀና ብላ አየቻትና
«ያው ነው ምንም ለውጥ አያሳይም » አለቻት ። ቀኑን ሙሉ እንዲህ ስትላት ነው የዋለችው… ምንም የተለየ ሁኔታ የለም ! ነርሷ ይህን ብላ ማሪዮንን በሥጋት አየቻት። ከማይክ ይልቅ ለማሪዮን ያዘነች ትመስላለች ።
« ዶክተር ዊክፊልድ አሥራ አንድ ሰዓት ሲሆን ዕረፍት እንድታደርግ ንገሪያት ብሎኝ ነበር » አለችና ሰዓቷን አየች ።
«አሁን አሥራ አንድ ከሩብ ሆኗል » አለች በጊዜው መልዕክቷን ባለማድረሷ እያፈረች ።
« ስላሰባችሁልኝ አመሰግናለሁ ። ትንሽ ዘወር ዘወር ብዬ እመጣለሁ ። እስከማረፊያ ክፍል ድረስ ብሄድ ይበቃል ? » አለች ማሪዮን ።

ከመጣች ጊዜ ጀምሮ ካጠገቡ አልተለየችም ። ሙሉ አሥራ ሁለት ሰዓት አልተለየችውም ። ይህን ያህል ጊዜ ስትቆይ ነፍስ ከሥጋዋ ጋር እንድትቆይ ለማድረግ ብቻ ሁለት ሲኒ ሻይ ጠጣች እንጂ ሌላ አልቀመሰችም ። አሁንም ልትለየው አትፈልግም ። አጠገቡ ሆና ትጠብቀዋለች ። እሷ አጠገቡ ካለች ኦይሞትም ፤ ምንም አይደርስበትም ። ሂጂ ሂጂ ፣እረፊ እረፊ ብለዋት ስትወጣ ነበር ሪቻርድም የሞተው ። ያን ያህል ሰዓት አጠገቡ ስትቀመጥ አልሞተም ። እንደወጣች ሞተ ብለው ነገሯት ። ማይክልን ግን ትጠብቀዋለች ። ካጠገቡ ንቅንቅ አትልም ።
« ሚስዝ ሂልያርድ » አለች ነርሷ የማረዮንን ክንድ በለዘብታ ነካ እያደረገች ። « ትንሽ ማረፍ አለብሽኮ ። ዶክተር ዊክፊፈልድ የምታርፊበት ክፍል እንዲዘጋጅ አድርጓል »
« የለም አልደከመኝም » አለች ማሪዮን ፈገግ ለማለት እየሞከረች ። «ሆኖም» አለችና ተነስታ ወደ ማረፊያ ክፍሉ ሄዳ ራቅ ብላ አንድ ማዕዘን ይዛ ተቀመጠች ። አሁንም ፤ አሁንም የምትለኩሰውን ሲጋራ እንኳ ለረጂም ሰዓት ረስታው ኖሯል ። አንድ ሲጋራ አውጥታ ለኮሰች ። በመስኮት ትንሺን የዩኒቨርስቲ ከተማ ስትመለከት የሆነ ነገር ተሰማት ። ክበር ተመስገን ጌታዬ፤ ይች ከተማ እንደትንሽነቷ ደህና ሆስፒታል ባይኖራትና ለቦስተን በጣም ቅርብ ባትሆን ምን ይውጠኝ ነበር ? ተመስገን ፤ ለቦስተን በመቅረቧ ታዋቂ ዶክተሮችን ማስመጣት ቻልን አለች በሐሳቧ።

በማሪዮን ሂልያርድ አስተሳሰብ ከማንኛቸውም ፤ ማለት ከሶስቱም ይበልጥ በአደጋው የተጎዳው ማይክል ነበር። ምንም እንኳ የጎላ የሚታይ ቁስል ባይኖር አብዛኛው ውስጣዊ ሊሆን ይችላል ። ያ ይበልጥ አደገኛ ነው ። ስለሁለቱ ማሰብ ቀጠለች ። ቤን ምንም እንኳ ሰውነቱ ብዙ ቅጥቅጣት ቢደርስበት ምንም አይልም። ግን ሁኔታው ሁሉ ደህና ነው ። ነፍሱን ሊስት ቀርቶ ዓይኑን እንኳ ገርበብ አላደረገም ነበር ። እሷ ከደረሰች በኋላ ነበር አባትዬው መጥቶ ባምቡላንስ ወደ ቦስተን እንዲዛወር ያደረገው ፤ ከቀትር በኋላ ላይ ።
እጁ ሳይሰበር አልቀረም ። እንዲሁም ቅልጥሙና ጭኑም ተሰብሯል ። ትከሻው ላይም ቢሆንም ወጣት ነው ። ባንዴ ይጠገናል

ልጅቱ ምንም ቢደርስባት በጥፋቷ ነው ። ያለምንም ምክንያት እንደዚያ ዓይነት ነገር… ማሪዮን ይህን ሐሳብ አንጠልጥላ ሲጋራዋን ጣለችና በእግሯ በኃይል ረገጠችው ። ምንም ቢሆን አትሞትም ። ያው መኖሯ አይቀርም ።ምን ሆነች ? ፈቷ ብቻ ነው ከጥቅም ውጭ የሆነው ። እንዲያ መሆኑ ደግሞ ማለፊያ ነው። ይህን ስታስብ ትንሽ እረፍት ተሰማት ። ለትንሽ ጊዜ ደግሞ ከስሜቷ ጋር ተጣላች ። በናንሲ ላይ ያላትን ቅሬታ ለውጣ ትንሽ ልታዝንላት ፈለገች ። ሰውን ውደድ ፤ የተቸገሩትን መፅውት የሚለውን በማሰብ ርህራሄና ሐዘኔታ ስለተሰማት ልትመጸውታት ፈለገች ። ልጅዋን ይገድልና ይበቀላት ይሆን ? ይህን በማለት ለናንሲ ሐዘኔታ ልትመጸውት ከጀለች። ግን አልቻለችም ። ማሪዮን ለናንሲ ያላት ጥላቻ እነፍሷ ውስጥ ዘልቆ የገባና ሥር የሰደደ ነበር ። ልጅዋን ፤ አንድ ያላትን ልትቀማት ልታሳጣት !
👍7
« ዕረፍት እንድታደርጊ እንዲነግሩሽ ትዕዛዝ አስተላልፌ የሄድኩ መስሎኝ ነበር » ይሀን ድምፅ ስትሰማ ድንግጥ አለች ። ድምፁ ወደ መጣበት አካባቢ ብትት ብላ ዞር አለች ።። ዶክተር ዊክፊልድ ነበር ። በሚገባ ይተዋወቃሉ ። እንዲያውም በማቆላመጥ ዊስ ብላ ነው እምትጠራው ።
« ማሪዮን እንዲያው አንድ ቀን እንኳ ሳት ብሎሽ ሰው ያለሽን አትሰሚም ማለት ነው?» አለ ዶክተሩ ።
«ችግሩ ለኔ ካልተሰማኝ ሰው መስማት የለብኝም እንዴት ነው የማይክል ሁኔታ ?››
«ደህና ነው።ወዳንቺ የመጣሁት የሱን ሁኔታ ገብቼ ካየሁ በኋላ ነው ። ምንም መጨነቅ አያስፈልግም አሁን ይሻለዋል አደጋው ሲደርስ ድንጋጤ አንጎሉን ክፉኛ ነክቶታል
« እኔንም እንደዚያው » አለች ። ምን ይደረግ በሚል የማስተዛዘን ሁኔታ አንገቱን ነቀነቀ ።
«ለወደፊቱ በጤናው ላይ ጠንቅ ጥሎ የሚያልፍ ነገር ይኖር ይሆን ?» አለችና በፊቷ ላይ ጭንቀት ውልብ ሲል ታዬ። ቀጥሎም « የአንጐል መጎዳት ጠንቅ? » ስትል እየፈራች ተናገረች ። ዊክፊልድ ትከሻዋን መታ መታ አድርጐ በማረጋጋት ሁኔታ አጠገቧ እየተቀመጠ ፣
« ነገርኩሽ እኮ ማሪዮን ፤ በሚቻለኝ መጠን የማውቀውን ነገርኩሽ ። አሁን ባለበት ሁኔታ በጣም ረጅም ጊዜ ካልቆየ በስተቀር ምንም አይሆንም ። ይህ ደግሞ ይቆይበት አይመስለኝም ። ማለቴ ይቆይበታል ብሎ ልቤ አልፈራም አለ።
«የኔ ልብ ግን ፈርቷል » አለች ። ይህን ስትል ቀና ብሎ አያት ። ገረመው። ለካ እሷም ትፈራለች !አለ ። አንዳንድ ማንም ሰው የማያውቃቸው የማሪዮን የሆኑ የግል ባህርዮች አሉ ። እንዲህ ድንገት ካልሆነ በስተቀር ማንም አያውቃቸውም ።
« እሷስ እንዴት ናት ?» አለች ማሪዮን ። ይቺ ሁሌ እማውቃት ማሪዮን ናት ? አለ ዶክተር ዊክፊልድ ስለልጅቷ ስትጠይቀውና ስለናንሲ ሲያስብ ልቡ በሐዘን ስብር ብሎ ። « እሷ ያው ናት ፤ እንዳገኘናት ናት። ምንም ያህል ዕርዳታ ልናደርግላት አልቻልንም ። በርግጥ ነፍሷን ታውቃለች ። ከትናንት ጀምሮ ስትናገርም ፤ ምን ስትልም ደህና ናት ። ሚዛኗን የመሳት አዝማሚያ አይታይባትም ። በሕክምናው ረገድ ከሄድን ግን ምንም ዓይነት ነገር ልናደርግላት አልቻልንም ። አንደኛ ፤፡ ባሁኑ ደረጃ ላይ ዕርዳታ ሊደረግላት የሚያስችል አይደለም የደረሰባት አደጋ' ። ሁለተኛ ጊዜው ሲመጣም ያንን ዓይነት ርዳታ ሊያደርግላት የሚችል ባለሙያ ከመሐከላችን የለም ። የዚያ ዓይነቱን ሙሉ በሙሉ የፈረሰ ኣካል እንዳለ ለመመለስ የሚችሉ በመላው የዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው ። ፊቷ ኮ ፈፅሞ የለም። አጥንቷ ተለብሯል ። የፊቷ ነርቮች ተበጣጥሰዋል ። ቆዳዋ ፈፅሞ የለም ። ባጠቃላይ በፊቷ ላይ ከሚገኙ አካላት በሚገርም ሁኔታ ምንም ጉዳት ያልደረሰባቸው ሁለቱ ዓይኖቿ ናቸው» አለ ዶክተር ዊክፈልድ ሐዘን በተመላ ድምፅ ።

« የተበላሸ ፊቷን ለማየት ይጠቅማታል ዓይኗ » አለች ማሪዮን ። ዊክፊልድ ይህን ሲሰማ በጣም ደነገጠ ። በተለይ ማሪዮን ይህን የተናገረችበት የድምፅ ቃና ነፍሱን አናወጣት ።
« ማሪዮን ምን ማለትሽ ነው ? መኪናውን ሲነዳ የነበረው ማይክል ነው እሷ ምናጠፋች...?» አለ መናገር ሲችል። ማሪዮን ግን መልስ አልሰጠችውም ። እውነትህን ነው ለማለት በሚመስል ሁኔታ አንገቷን ነቀነቀች ። ልጅቷ ጥፋተኛ መሆኗን ታውቃለች ። ወስናለች ። ለዚህ ሰው ግን ያንን ጥፋቷን ማሳየት እትችልም ። ስለዚህ ክርክር ውስጥ ልትገባ አልፈቀደችም ።

« እንዲህ ዓይነት አደጋ የደረሰበት ሰው ምንም ሕክምና ባይደረግለት ምን ይሆናል ? በሕይወት ሊኖር ይችላል ?» አለች ማሪዮን ።
« አለመታደል ሆኖ ለሞት አያበቃም » አለ ሐኪሙ
« ግን እንዲህ ሆኖ መኖር ምን ኑሮ ሊሆን ይችላል? የሃያ ሁለት ዓመት ጉብል ገፅታዋን ተገፍፋ ፤ ማስፈራሪያ ሆና ፤ አእምሮዋ እንዴት ሊስተካከል ይችላል? እንዴት ነው ፤ ለመሆነ መልከመልካም ነበረች ?»
« ይመስለኛል ።. አንተዋወቅም ። አይቻት አላውቅም " አለች ድምጺ በጭካኔ የጠጠረ ነበረ።
« እንዲያ ነው? ያም ሆነ ይህ ለሷ እንግዲህ ሕይወት ፈተና መሆኗ ነው።ትንሽ ቁስሉ መጠጥ ሲል የቻሉትን ያህል ርዳታ ያደርጉላታል ። ግን ዋጋ የለውም። ከዚያ በኋላ . .. ለመሆኑ ገንዘብ አላት ? »
«ምንም የላትም ? » አለች ምርር ብላ ።
« እንግዲያስ ያለቀለት ጉዳይ ነው ። የዚህ ዓይነቱን የፕላስፒክ ቀዶ ጥገና ሥራ የሚችሉ ባለሙያዎች ለነፍስ ብለው ሰው የሚረዱ ዓይነት አይደሉም ። ዋጋ የሌለው ልፋት ነው »
« ይህን ማድረግ የሚችል የምታውቀው ሰው አለ ?»
« አዎ ።ስማቸውን የማውቃቸው ሁለት ሐኪሞች አሉ። ከሁለቱ አንደኛው በሙያው እጅግ የተራቀቀ ነው ። ሳንፍራንሲስኮ ነው መኖሪያው » አለ ዶክተር ዊክፊልድ ። ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ልቡ ላይ ፍንጥቅ ስትል ታየው ። ማሪዮን ሂልያርድ የተረፋት ቱጃር ናት ። ልቧ ቢራራ ! « ስሙ ፒተር ግሬግሰን ይባላል ። ከብዙ ዓመታት በፊት ተገናኝተን ተዋውቀን ነበር ።መቼም የችሎታው ነገር የሚደንቅ ነው » አለ ተስፋው ስለገፋፋው ።
👍3👏2😁2
« እንዲህ እንደሷ ከጥቅም ውጭ የሆነውን አካል በሚገባ ሊጠግን ይችል ይመስልሃል ?» ይህን ስትል ተስፋው እጅግ ገነነ ። ምን ዓይነት ደግ ሰው ናት ! ሲል በልቡ ማሪዮንን አደነቃት ። ቀጥሎም ፣
«የሚቻል ከሆነ የሚችለው እሱ ብቻ ነው።እንዴት ነው? ማለት ልሞክር ? ማለት እንዳነጋግረው ትፈልጊያለሽ ? » አለ እየፈራ ። ተናግሮ ሲጨርስ ቀና ብላ አየችው ። የምትመዝነው መስሎ ተሰማው። ምን ይሆን እምታስበው አለ በሀሳቡ ።
« ሐሳቤን እነግርሃለሁ » አለች ።
« ደግ » አለ ። እና አከታትሎ « አሁን ትንሽ ማረፍ አለብሽ ይበቃል ትጐጃለሽ ። ይህን የምልሽ ደግሞ ከልቤ ነው ።»
«አውቃለሁ » አለችና ፈገግ አለች ፤ ለደግነቱ ፈገግ እንደመመፅወት ። ቀጥላም « ሆኖም አላደርገውም። ይህ ደግሞ በሚገባ ይገባሀል ። ማይክልን ትቼ የትም ልሄድ አልችልም ላርፍም ወይም ሌላ ነገር ልሠራ»
«ሞትም አለኮ !. . ልትሞችም ትችያለሽ ኮ»
« የለም ፡ የለም አልሞትም ። በጣም ክፉ ሰው ስለሆንኩ አልሞትም ። በዚያም ላይ ከመሞቴ በፊት የማከናውነው ብዙ ብዙ ሥራ አለ… እና አትስጋ ዊክ »
‹‹እሺ እንዳልሽው ይሁን ። ሆኖም አንድ ሰዓት ብቻ ነው እምሰጥሽ «ከዚያ በኋላ አላርፍም ካልሽ መጥቼ በግድም ቢሆን የእንቅልፍ መርፌ ወግቼ እየጎተትኩ ወስጄ አስተኛሻለሁ ። ቀልዴን አይደለም ። በዚህ ተስማማን ? »
« ተስማምተናል » አለች ። ደጋግማ ከለኮሰቻቸው ሲጋራዎች በዚያ ሰዓት በእጅዋ ላይ የነበረውን ረግጣ ጉን ጩን ቆንጠጥ አደረገችው እና በተጨማሪ ዊክ አለችና ቀና ብላ አየችው። ለዚያች ቅፅበት ውብና ርህሩህ ሆና ታየችው ።በጥያቄ ዓይን ሲያያት «ለዚህ ሁሉ ነገር አመሰግንሀለሁ» አለች። ጎንበስ ብሎ ጉንጭን በለሆሳስ ሳም አደረጋት ። ክንዷን ጨበጥ አድርጎ አይዞሽ በሚል መንፈስ ለቀቅ አደረጋትና ትንሽ ፈንጠር ብሎ ቆመ።
« አይዞሽ ማሪዮን ። ምንም አትስጊ ። አሁን ይሻለዋል »አለ ። ከዚያ በኋላ ናንሲ በሀሳቡ ብትመጣም በፊቷ ሊያነሳት ድፍረት አላገኘም ። ሊቆይ ይችላል ። ሰዓቱ የዚያ ሲሆን ራሱ ይነሳ የለም ? ምን ያስጨንቃል ? በፈገግታ ብቻ ተሰናብቷት ሄደ ። የለም ያሰጋታል ። ቅድም ደዉሎ ጆርጅ ኮሎዎይን መጥራቱ ጥሩ ዘዴ ነው ። በዚህ ሁኔታ ባቻዋን አትችልም። የልቧን በመጠኑም ቢሆን የምትነግረው ያስፈልጋታል። ማሪዮን ዶክተሩ እስኪሰወር በአይኗ ከተከተለችው በኋላ ሁለቱ እየተጫወቱ ሳለ የመጣላትን ሀሳብ ትንሽ አሰብ አደረገችና የምታደርገውን ወሰነች ።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ናንሲ እተኛችበት አካባቢ ደረሰች። በጠና የታመሙና በጥብቅ የሚጠበቁ በሽተኞች የሚተኙበት አካባቢ ስለሆነ ጸጥ ያለ ነበር። የለቅሶ ማንተግ አይነት ድምፅ ተሰማት ። ድምጹ በመጣበት አቅጣጫ ስትመለከት የክፍሉን ቁጥር አየች ። የናንሲ ክፍል ነበር። ቀስ ብላ ተጠጋች ። ለቅሶው አሁን በደንብ ተሰማት ። እበሩ ላይ ቆማ ለረጂም ጊዜ ፍዝዝ ብላ ቆየች ። ልግባና. . . ላድርገው? ... ግራ ገባት ። ለማይክል ነው። ለማይክል ስል ነው። ማይክልን ነፃ ማውጣት አለብኝ አለች ራሷን ለማበረታታት ። ቀስ እያለች እግሮቿን እየጐተተች ወደ ክፍሉ ውስጥ ገባች።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍7👏1
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ትናንት ማታውን ሚስተር ካርላይል ትክ ብሎ ሲያስተውላት ነበርና አሁን
እንዳያውቃት ሰጋች " በበነጋው ጧት ሳቤላ ወደ ሳሎኑ የሚወስደውን መንገድ ከሚስተር ካርላይል ነጻ መሆኑን ለማረጋገጥ ከመኝታ ቤቷ በር ቁማ ታዳምጥ ጀመር
ሚስተር ካርላይልን ከምንጊዜም የበለጠ ወደደችው » እሱ ደግሞ የሌላይቱ ባል ስለሆነ ተንግዲህ እሱን አጥብቆ ማየቱ ከነውር የሚቆጠር መሆኑን በማሰብ ጭምር
ነበር እንዳታየው የፈራችው

እሷ በዚህ ሁኔታ ቁማ ሳለች መደ አምስት ዓመት የሚገመት አንድ ቆንጆ ልጅ
መጣ" የማድ ቤት መጥረጊያ በሁለቱ ጭኖቹ መኻል አድርጎ እንደ ፈረስ እየጋለበ በኮሪዶሩ በኩል ደረሰ ልጅዋ አርኪባልድ ለመሆኑ አስተዋዋቂ አላስፈለጋትም ሚስተር ካርላይልን ቁርጥ ነው መልኩ ልትቋቋመው ባልቻለችው የስሜት ግፊት
ተደፋፍራ እንዲያ ሶምሶማ እየረግጠ ዐልፋት ሊሔድ ሲል ከነመጥረጊያው እቅፍ
አድርጋ ወደ ክፍሏ ወሰደችው።

“ከአንተ ጋር እንድተዋወቅ ያስፈልጋል” አለችው እንደ ማባበል አድርጋ ትንንሽ ልጆችን እወዳለሁ።

ከአንድ ትንሽ ወንበር ላይ ተቀመጠች » ልጁን ጭኗ ላይ አስቀምጣ መላልሳ
ሳመችው " እንባዋ እንደ ምንጭ ውሃ መውረድ ጀመረ " በምንም መንገድ ልትገታው አልቻለችም መሳሙንም መተው አልሆነላትም ቀና ብላ ስታይ ዊልሰንን አየቻት " ስትገባ አልሰማቻትም » ሳቤላ ልክ ራሷን እንዳጋለጠች ሆኖ ተሰማት አሁን እንግዲህ አንድ የሆነ ምክንያት መስጠት ነበረባት

ልጆቼን አስታውሶኝ እኮ ነው አለቻት ለዊልሰን ይተናነቃት የነበረውን የስሜት ፍላት ለመዋጥ እየታገለች በተቻላት መጠን እንባዋን ለመደበቅ ተጣጣረች » ነገሩ የገረመው አርኪባልድ ጣቱን እየጠባ ዐይኖቹን አፍጥጦ ትልቁን ሰማያዊ መነጽሯ ይመለከት ጀመር።

“የወለድናቸውን ስናጣ ካጠገባችን የምናያቸውን ለመውደድ እንገደዳለን”
አለች ሳቤላ "

ዊልሰን ይህች አዲሲቱ የልጆች አስተማሪ ድንገተኛ ዕብደት ያልደረሰባት
መሆኑን ለማረጋገጥ ብላ አስተዋለቻት ከዚያ ወደ አርኪባልድ መለስ ብላ አንተ
ባለጌ እንዴት አባክ ብትደፍር ነው የሳራን መጥረጊያ ይዘህ የምትሮጠው ? የለም
የለም ዕብደቱን እያበዛኸው መጥተሃል ቆይ ለእእማማ ባልናገርልህ ” አለችና ጭምድድ አድርጋ ይዛ ደጋግማ ናጠችው " ሳቤላ እጆቿን ሽቅብ አንሥታ እያራገበች “ተይ ተይ እባክሽ አትምቺው ! ሲመታ ላየው አልችልም !” ብላ በሚያሳዝንና ልብ
በሚነካ ድምፅ ቁማ ለመነቻት "

"ሲመታ !” ብላ ጮኽች ዊልሰን በደንብ ቢገረፍማ ይሻለው ነበር" እስከ ዛሬ ትንሽ ቸብ ቸብ ከማድረግ ወይም ከመወዝወዝ በቀር ገርፌው አላውቅም እሱ ደሞ ይህን አምንም አልቆጠረውም አልጠቀመውም ብልግናውና አስቸጋሪነቱን ብነግርሽ አታምኚም " ሌሎቹ የሱን ያህል አያስቸግሩኝም"
አሁን ወዲህ ና አንተ ከይሲ ! ከልጆች ክፍል አስግብቸ ነው የምዘጋብህ" አሁን ብዘጋበትም እኮ በጉበኑ ተንጠልሎ ወጥቶ ለመክፈት ከመሞከር አያርፍም ” አለቻት " ልጁን እየገፈተረች ከገባበት ክፍል አስወጥታ በኮሪደሩ እያዳፋች ወደ ልጆቹ ክፍል ወሰደችው ፤ሳቤላ መንፈሷ እየተፋጨ ፡ ልቧ ታጥቦ እንደሚሰጣ ጨርቅ እየተጠመቀ ቁጭ አለች የገዛ ልጅዋን ሠራተኛይቱ ስታንገላታው ዐይኗ እያየ ልትከለክላት አልቻለችም "

ወደ ግራውጫው ሳሎን ወረደች "
ቁርስ ቀርቦ ሁለቱ ትልልቅ ልጆች ተቀምጠው ሲጠብቋት ገባች እሷ ስትገባ አብራቸው የነበረችው ጆይስ ወጣች

አንዲት የስምንት ዓመት ደርባባ ሴት ልጅና ከሷ አንድ ዓመት የሚያንስ
አንድ ስልል ያለ ደካማ ወንድ ልጅ ነበሩ ። ሁለቱም ልጆች የዱሮው የናታቸውን ቅርጽ ስልክክ ያለ መልክና ትልልቅ ለስላሳ ዐይኖችን በሚገባ ወርሰዋል እንደ እናትነቷና እንደ ናፍቆቷ ስሜቷን ለመግለጽ ብትችል ኖሮ ብዙ ማየትና መስማት ይቻል ነበር ። ሆኖም ብሶቷን በግድ እምቅ አድርጋ ይዛ ጐንበስ ብላ ሁለቱንም ሳመቻቸው ሉሊ ምንጊዜም የረጋችና ዝምተኛ ነበረች ዊልያም ግን ለፍላፊ ብጤ ስለ ነበር ወሬ ጀመረ ።

“አንቺ አዲሷ አስተማሪያችን ነሽ ? ” አላት
“ አዎን ፤ ጥሩ ወዳጆች መሆን አለብን ።

“ እንሆናለን አለ ልጁ ከሚስ ማኒንግ ጋርም ጥሩ ወዳጆች ነበርን አሁን ያለብኝ ሳል በቅርቡ እንደ ለቀቀኝ ላቲን መማር እጀምራለሁ አንች ላቲን
ታውቂያለሽ ?”

“የለም ለመምሀርነት የሚያስችል ዕውቀት የለኝም "

“አባባም እንደማታውቂ ነግሮኛል " ሴቶች እምብዛም ላቲን አያውቁም ። ስለዚህ ሚስተር ኬን እየመጣ ላቲን እንደሚያስተምረኝ ተነግሮኛል ”

ሚስተር ኬን ? ”አለች ሳቤላ ያ ስም ትዝ አላትና “ ሚስተር ኬን የሙዚቃ አስተማሪው ? ”

የሙዚቃ አስተማሪ መሆኑን በምን ዐወቅሽ ? ” አላት ብልሁ ልጅ ።እመቤት ሳቤላ ሳታስበው ስለ አመለጣት ነገር በመደንገጧ ፊቷ ፍም መሰለ የምትለው ጠፍቷት ጥቂት ግራ ከተጋባች በኋላ ከሚስዝ ላቲመር መስማቷን ነገረችው "

“ አዎን የሙዚቃ መምህር ነው ። ግን ብዙ ገንዘብ አያገኝበትም " ሚስ ማኒንግ ከሔደች ወዲህ እየመጣ ሙዚቃ ያስተምረናል " እማማም ተጠንቅቀን አንድንማር ትነግረናለች

“ ሁልጊዜ በቁርስ የምትመገቡት ዳቦና ወተት ነው ? አለች የቀረበላቸውን አይታ።

አንዳንድ ጌዜ ሲሰለቸን ወተትና ውሃ ዳቦና ቅቤ ወይም ማር ይሰጠናል
ከዚያ እንደገና ወደ ዳቦና ወተት እንመለሳለን አክስት ኮርኒሊያ ናት አባታችሁም
በልጅነቱ ሌላ ቁርስ አግኝቶ አያውቅም እያለች ዳቦና ወተት እንዲቀርብልን የም
ትናገር ።

ሉሲ ቀና ብላ አየቻትና ቁርሴን ከአባባ ጋር ስበላ በነበረ ጊዜ አንድ አንድ
ዕንቁላል ይሰጠኝ ነበር " አክስት ኮርኒሲያ ዕንቁላል ለኔ ጥሩ አይደለም ብትለውም ዝም ብሎ ዕንቈላሉን ይሰጠኝ ነበር ሁልጊዜ ከሱ ጋር ነበር ቁርሴን የምበላው ”

ታዲያ ዛሬስ ለምን አብረሺው አትበይም ?
እንጃ እማማ ከመጣች ወዲህ ቀርቤ አላውቅም "

የንጀራ ናት የሚለው ቃል ትውስ ሲላት ሳቤላ ልቧ ተንደፋደፈባት ሚስዝ ካርላይል ልጆቹን ካባታቸው እየለየቻቸው መሆኑን ተገነዘበች

ቀርስ ተበልቶ አቐቃና ስለ ትምህርታቸው ስለ መዝናኛ ስአታቸው ስለ ዕለት ከዕለት ኑሮዋቸው ስትጠይቃቸው ይኸ ኮ መማሪያ ክፍል አይደለም ” አላት
ዊልያም መማሪችን እላይ ነው እፎቅ ይህ ምግብ ቤታችን ማታ ማታ ደግሞ • ያንቼ ማፊያ ገው "

ከደጅ የሚስተር ካርይል ድምፅ ተሰማ ሉሲ ድምፅ ወደ ሰማችበት ልትንደረደር
ብድግ አለች » ሳቤላም ልጂቱን በበራፉ ስትዘልቅ ካየ እንዳይገባ ፈራችና
እጅዋን ለቀም አድርጋ አቆመቻት "

“ እዚህ ቆይ ሳቤላ
“ ሉሲ እኮ ነው ስሟ ” አለ ዊልያም ቶሎ ቀና ብሎ እያያት '“ ለምን ሳቤላ
ትያታለሽ?”

እኔማ - እኔማ ሳቤላ ብለው ሲጠሯት የሰማሁ መስሎኝ ነበር ” ብላ ተንተባተበች "

“ስሜ ሳቤላ ሎሲ ነው ” አለቻት ልጂቱ“ ግን ሳቤላ ተብዬ ስለማልጠራ ማን እንደ ነገረሽ ገርሞኛል
እ... እ..ልንገርሽ ? . . . እማማ ጥላን ከሔደች
ወዲህ ተጠርቸበት አላውቅም " ዱሮ የነበረችው እማማ ማለት እኮ ነው »"

“ ሔደች ? አለቻት ሳቤላ በስሜት ፍላት ስለ መልሱ ሳታስብ
"ተጠለፈች ” አለቻት በሹክሹክታ
“ ተጠለፈች ?” አለቻት አሁንም በመገረም "
“ አዎን ባትጠለፍማ መች ትሔድ ነበር አንድ ክፉ ሰው የአባባ እንግዳ ሆኖ መጥቶ ሰረቃት እማማ ስሟ ሳቤላ ነበር ከያኔ ጀምሮ ሳቤላ ተብዬ እንዳልጠራ አባባ ከለከለ "

“ ግን አባባ መከልከሉን በምን ዐወቅሽ ? አለቻት "
👍15🔥1
“ እኔ ሰማሁት እሱ ለጆይስ ነገራት ጆይስ ደግሞ ለሠራተኞቹ በመሉ ነገረቻቸው" ከደብተሬ ላይ ሳቤላ ሉሲ ብዬ ጽፈ አባባ አይቶ ሳቤላ” በሚለው ላይ
በእርሳስ አሠመረበትና ለሚስ ማኒንግ እንዳሳያት ነገረኝ ከዚያ ሚስ ማኒንግ “ሉሲ እያልኩ እንድጽፍ ነገረችኝ" ለምን እንደሆነ ብጠይቃት ' ሉሊ የሚለውን ስም አባባ ስለ ወደደው ነው ብላ ሌላ ጥያቄ እንዳልጠይቃት ከለከለችኝ

እያንዳንዱ ቃል ልቧን እየቦረቦረው ልጂቱን ግን ዝም በይ ልትላት አልቻለ
ችም "

“እመቤት ሳቤላ ነበረች የኛ የእውነት እናት ይህች እማማ ግን አይደለችም
“ ይህችን እናታችሁን እንደዚያችኛይቱ ትወዷታላችሁ ?

"አዬ ! እማማን በጣም በጣም ነበር የምወዳት ግን ሁሉ ዐለፈ » ዊልሰንና
አክስት ኮርኒሊያ እንግዲህ እንዳትወዷት ይሉናል " ዊልሰንማ በተለይ ብትወዳችሁ ኖሮ ጥላችሁ አትሔድም ነበር ትለናለች » ከኛ መለየት ባትፈልግ ኖሮ ሰው ሲጠልፋት ዝም አትልም ነበር ብላ ነግራናለች አኔማ የሞተችውም እሱ መቷት
ይመስለኛል ሌሊት እንኳን ተኝቼ ምኑ ገደለሽ ? ያ ክፉ ሰውዬ መትቶሽ ይሆን '
እያልኩ አስባለሁ እሷ ከሞተች በኋላ አዲሷ እማማ መጣች አባባም በወይወሮ ሳቤላ ምትክ የመጣች እናታችን ስለሆነች እንድንወዳት ነገረን "

ትወጃታለሽ ? አለች ሳቤላ ሲቃ እየተናነቃት "
" የማማን ያህል አልወዳትም ” አለች ሉሲ ራሷን ነቀችና

ጆይስ የመማሪያ ክፍሉን ለእንግዳይቱ አስተማሪ ልታሳያት ገባች" ልጆቹም
ጭምር ተክትለዋት ወደ ፎቅ ወጡ " ወይዘሮ ሳቤላ ከመስኮቱ እንደ ቆመች ሚስተርካርላይልን በሠረገላ ሳይሆን በእግር ወደ ቢሮው ሲሔድ አየችው ባርባራም ከውጨኛው በር ድረስ ልትሸኘው ክንዱን በክንዷ ጠምጥማ ይዛ አብራው ታዝግም ነበር።

ባርባራ ልጆቹ የሚሠሩባቸውንና የሚጫወቱባቸውን ሰዓቶች ለአስተማሪቱ ለማስረዳት ጧቱን ወደ መማሪያው ክፍል ገባች ንግግርዋ ትሕትና ቢኖረውም ለቤቱና ለልጆቹ †ቀናቃኝ የሌላት አዛዥ ሆኗ በቃሏ አነዛዘር ይታወቃል ሳቤላ ያለችበት ደረጃ ከምን ላይ እንደሆነ ከልብ ተሰማት ። አንጀቷ እርር መንፈሷ ኩምትር አለ " ነገር ግን የተሰጣትን ትእዛዝ በአክብሮት እጅ ነሥታ ተቀበለች በዚያን ቀን ልጆቿን ከደረቷ እቅፍ አድርጋ ለመያዝ እያማራት ብዙ ጊዜ እየቃጣች መልሳ ስሜቷን እየገታች እንዲሁ እንደ ተጨነቀች ዋለች »

ከሻይ ሰዓት ቀዶም ብላ፡ፀሐይዋ ወደ ምዕራብ አድማስ ማቆልቆል ስትጀማምር ሁለቱን ልጆች ይዛ ወጣች » ከአውራው መንገድ የቁጥቋጦ አጥር ብቻ በሚለየው የእርሻ ላይ ቀጭን መንድ ተከትለው ሔዱ ። ፍራንሲዝ ሌቪሰን የሚስተር ካርላይል
አንቅስቃሴ እየተሹለከለከ ይከታተልበት የነበረው በዚሁ መንገድ ነበር "
ያለፈውን ታሪክ ከቦታው ጋር በማገናዘብ እያስታወሰች ወደፊት ስትሔድ ሚስተር ካርላይልና ባለቤቲቱ ክንድ ለክንድ ተያይዘው
ከዌስት ሊን ወደ ቤታቸው ሲመጡ አገኘቻቸው " ሳቤላ ሰላምታ ስትለዋወጥ ድንግርግር አላት " ከዚያ ባልና ሚስቱ ፊት ፊት እየመሩ ፡ እሷና ልጆቹ ኋላ ኋላ እየተከተሉ ወደ ቤት አመሩ።

ከነሱ ራቅ ለማለት እርምጃዋን ቀነሰች ግን እንዳሰበችው አልሆነላትም
ከአንድ የአጥር በር ላይ ደረሱ ። ባርባራን ደግፎ ካሳለፋት በኋላ ልጆቹ ያለ ምንም እርዳታ ሹልክ ሹልክ ብለው ሲያልፉ እሷን ስለ ትሕትና ሊረዳት ቁሞ ጠበቃት
“አመሰግናለሁ : እርዳታ አያስፈልገኝም ” አለችው .

እሱ ግን ቢሰማትም ዝም ብሎ ስለ ጠበቃት በዚያ አስቸጋሪ መወጣጫ መውጣት ግድ ሆነባት " የበሩን አስቸጋሪነት የሷ መርበትበት አባባሰው ከፊቷ ሚስተር ካርላይል እጁን ዘረጋላት እሷ የተጨነቀች የጣቷን ጫፎች አስጨበጠችው በዚህ ጊዜ ስትርበተበት በገዛ ልብሷ እግሮቿን ተጠለፈች " ተተብትቦ ከያዛት ጨርቅ ለመላቀቅ ልትዘል ስትሞክር ሚስተር ካርላይል በክንዶ ተቀብሎ ባያድናት በግንባሯ ትደፋ ነበር ።

“ አልጐዳሽም አይደለም ?” አላት እያዘነ "

"ይቅርታ ጌታዬ ልብሴ ኮ ጠልፎኝ ነው ደኅና ነኝ " ከዚያ ያንን ካለፉ በኋላ እሱ ቀድሟት ሔደና ስትጠብቀው የነበረችውን ሚስቱን አቅፎ መንገድ
ቀጠሉ ። ሳቤላ ይርበደበድ የነበረውን ልቧን ለማረጋጋት ወደ ኋላ ቀረት አለች "

ከቤት ደርሰው እሷና ሁለቱ ልጆች ከግራጫው ሳሎን ገብተው ሻይ ሲጠጡ
ዊልያም ሳሉ ተቀሰቀሰበት " ረጅምና ኃይለኛ ሳል ነበር " ሳቤላ ከተቀመጠችበት
ተነሣች ልጁን ወደሷ አስጠጋችው ። አንገቷን በሱ ላይ ደፍታ እቅፍ አድርጋ እንደያዘችው ድንገት ቀና ብላ ስትመለከት ዐይኖቿ ሚስተር ካርላይል ላይ ዐረፉ ሚስተር ካርላይል ልብስ ቀይሮ ከፎቅ ሲወርድ የልጁን ሳል ሰምቶ ሊያየው ገባ ሳቤላ አባትየውን ድንገት ስታየው ደነገጠችና ልጁን መልሳ ጣል አደረገችው።

እንደማይሽ በተፈጥሮሽ የልጆች ፍቅር ያለሽ ትመስይኛለሽ ” አላት የደስ
ደስ ባለው ፈግግታው እሷን እሷን እያየ .

ምን እንደ መለሰችለትም አላወቀችውም ምናቸውም የማይሰሙ ቃላት አልጎመመችና ጨለም ወዳለው ጥግ አፈገፈገች

ምንድነው ? አለች ሚስዝ ካርላይል ወደ ውከጥ እየተመሰከተች " እሷም የራት ልብስ ለብሳ ከፎቅ ስትወርድ ነበር " እሷ ስትደርስ ሚስተር ካርላይል ልጁን
ከጐልበቱ አስቀምጦ አቅፎ ይዞት ነበር

የዊልያም ሳል አሳሳቢ እየሆን ነው እኔ ደስ አላለኝም .... ባርባራ •
ዌይንራይትን እንደገና እንዲመጣ ማረግ አለብኝ "

“ምንም አይደለም " አለች ባርባራ ሻይ ሲጠጣ ስለነበር ትን ብሎት ይሆናል ራት ኮ ቀርቧል ... አርኪባልድ "

ሚስተር ካርይል ልጁን ከእቅፉ አውርዶ አስቀመጠውና ሊሔድ እንደ ቆመ ልጁን ለአንድ ደቂቃ ያህል ትኩር ብሎ አየው ሳሉ ጋብ ሲልት ፊቱ 0መድ መስለ " ደማቅ የነበረው የፊቱ ቀለም ጠፋ " ሰውነቱ ዛለ ።ድክምክም ! ዝልፍልፍ
አለ « አፊ እንዳለችው የፊቱ ወዝ ሙልት አለ ሚስዝ ካርላይል ክንዷን በባሏ ክንድ ጠምጥማ ሲሔዱ ፊቷን ወደ ኋላ በመመለስ'' ማዳም ቬን .... በዪ አንቺም ..በኋላ ከሉሲ
ጋር ወደ ሳሎን እንድትመጪ " ፒያኖ ስትመች ልንሰማሽ እንፈልጋለን " ብላት ሔደች።

በትእዛዝ መልክ ነው የተነገራት ምን ይደረግ ባርባራ ሚስዝ ካርላይል
ሆኖለች " ሳቤላ የመጀመሪያው ወንድ ልጅዋን እንደገና ወደሷ ሳብ አድርጋ አስጠጋችው " በራስ ምታት የሚሠቃየው ግንባሯን ከላዩ ላይ ደፋች

“ ሌሊት ያስልሃል እንዴ አንተ የኔ ዓለም ?”

“ ብዙም አያስለኝም " ጆይስ ከመኝታዬ ጐን የፍሬ ማር ታኖርልኛለች ሲነሣብኝ ከሱ እበላለሁ ከጥቁር ዘቢብ የተሠራ ማር ነው "

“ ከክፍልህ የሚተኛ ሰው አለ ?

“ የለም እኔ ለብቻዬ አንድ ክፍል አለኝ "

ከሷ መኝታ ቤት ለሱ የምትሆን አንዲት ትንሽ አልጋ ለማስግባት ይፈቀድላት እንደሆነ ለመጠየቅ መድፈር መቻል አለመቻሏን ስታውጠነጥን ሐሳብ ይዟት
ጭልጥ አለ " የሷን ያህል ማን ያየዋል ? ማን ይከውነዋል ? ከዊልያም ጋር ስትነጋገር በአንድ ቀን እንደ ተረዳችው ልጁ ከዕድሜው ልቆ የሚያስብና ይኸም ብዙ ጊዜ የሰውነት ድካምን እንዳስከተለበት ተገንዝባው ነበር ካነጋግሩ ' ካመላለሱ የስባት መሆኑ ቀርቶ ያሥራ አራት ዓመት ልጅ መስሎ ታያት አንድ ልጅ ከሚጠበቀው በላይ በጣም ልቆ ያሰበ እንደሆነ ለልጁ ደግ አይዶለም ዕድሜ አይኖረውም የሚል የባልቴቶች አባባል አለ "

“ ከኔ ክፍል ለመተኛት ደስ ይልሃል ” አለችው ሳቤላ "
👍13🔥2👏1
“ እኔ እንጃ ! ለምድነው ካንቺ ክፍል የምተኛው ?”
“ እጠብቅሃለሁ ሳልህ ሲነሣብህ የፍሬ ማርህን ወይም ሌላ የሚያስፈልግን
ነገር አቀርብልሃለሁ እናትህ ልታደርግልህ ትችል የነበረን ያህል እንከባከብሃለሁ እወድሃለሁ

“ እማማ እኮ አትወደንም ነበር”አላት “ ብትወደን ኖሮ ጥላን አትሔድም ነበር


· እንዴት አትወደንም ትላለህ ትወደን ነበር እንጂ ” አለች ሉሲ ቆጣ ብላ“
“ጆይስም ትወዳችሁ ነበር ብላናለች እኔም ትዝ ይለኛል ብትጠለፍም የሷ ጥፋት
አልነበረም "

ዝም በይ ሉሲ ሴቶች ልጆች ምንም አያውቁም " እማማ

“ልጄ ሰማህ ልጄ " አለች ሳቤላ ነግሩን አቋርጣ እንደ
ንፍር ውሃ የሚጠባበስ
እንባ ከዐይኖቿ እየወረደ " እናታችሁ ትወዳችሁ ነበር " በጣም ተጨንቃ ነበር
የምትወዳችሁ እንደናንተ የምትወደው አልነበራትም "

“ስለሷ መናግር አትችይም ማዳም ቬን ”አላት ዊልያም ድርቅ ብሎ „'' አንቺ
አማማን አታውቂያትም " ከዚህ አልነበርሽም "

' ትወዳችሁ እንደ ነበር በርግጥ እተማመናለሁ " እኔ ከዚህ የቆየሁት አንድ
ቀን ብቻ ነው ግን ባንድ ጊዜ ለመድኳችሁ " አሁን በጣም እወዳችኋለሁ ” አለችና
በትኩሳት የሚቃጠሉት ጐንጮቹን ሳመችው ይህ ሲሆን 0መፀኛው እንባዋን
ልትገታው ስለ አልቻለች እሱም እንዳሻው እየወረደ ከልጁ ጉንጭ ላይ ያርፍ ጀመር ።....

💫ይቀጥላል💫
👍12🥰76
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰባት (7)


በሩ ላይ ቆማ ለረጂም ጊዜ ፍዝዝ ብላ ቆየች ። ልግባና. . . ላድርገው? ... ግራ ገባት ። ለማይክል ነው። ለማይክል ስል ነው። ማይክልን ነፃ ማውጣት አለብኝ አለች ራሷን ለማበረታታት ። ቀስ እያለች እግሮቿን እየጐተተች ወደ ክፍሉ ውስጥ ገባች።

ክፍሉ ጨለማ ነበር። ምንም ብርሃን እንዳይገባ የተከለከለ ይመስላል። መብራቱም አልበራም ። ሻተሮቹም ተዘግተዋል ። አሁንም የለቅሶው የማንተግ ድምፅ ይሰማታል ። ቀስ ብላ ተጠጋች። አልጋው እንደ ጥላ ሆኖ ይታያል ። የልቅሶው ድምፅ ጐላ እያለ ይሰማ ጀመር። «ሰውነው... ማነው? » አለች ናንሲ ። ማሪዮን ተጠጋች። የናንሲ ራሷ ፊቷ በጠቅላላ በፋሻ ተጠቅልሏል ። ድምጺም የታፈነና እንግዳ ነገር ሆኖ ተሰማት ለናንሲ ለራሷ።
«ማነው... ሰው አለ?» አለች ናንሲ ። እና ታለቅስ ጀመር ። «አይኔ አያይም ... ሰው አለ?... አይኔ ፈፅሞ አያይም» አለችና ሳግ አከታትሎ ይነትጋት ጀመረ ። « አይንሽ ምንም አልሆነም ። ሁለቱም አይኖችሽ ደህና ናቸው፤ እንዳታይ የሚከላከልሽ የተሸፈንሽበት ፋሻ ነው» አለች ማሪዮን፡፡ ናንሲ ይህን ብትሰማም ለቅሶዋ ጨመረ ።
«ለምንድን ነው እንቅልፍ ያልወሰደሽ?» አለች ማሪዮን ድርቅ ባለና ስሜቱ በተሟጠጠ ድምፅ «የሚያስተኛ መድሀኒት አልሰጡሽም ?» ማሪዮን ራሷ በህልሟ የምትነጋገር መስሎ ተሰማት። .... መርፌ ወግተውኝ ነበር። ግን መድሀኒቱ ሊሰራ አልቻለም። እንቅልፍ ባይኔ አልዞር አለ» አለች ናንሲ። «ይጠዘጥዝሻል...ወይም ውጋት የመሳሰለ ህመም አለው «ምንም አይሰማኝም ። አካሌ በጠቅላላ ደንዝዟል ። ማን... አንቺ ማን ነሽ?» ስሟን ልትነግራት አልደፈረችም ። በዚያ ፋንታ አልጋው አጠገብ ወንበር ስላየች ሂዳ እዚያ ላይ ቁጭ እለች ። የልጅቷን እጅ አየች። ሁለቱም እጆቿ እንዲሁ በፋሻ ተጠቅልለዋል አይንቀሳቀሱም ። ትዝ አላት ዶክተር ዊክፊልድ የነገራት ። ፊቷ እንዳይጐዳ በእጅዋ መከላከሏ ያለ ነው ። ስለዚህ ሁለቱም እጆቿ በጣም ተጐድተዋል። ለወደፊቱ በሰዓሊነት ሀይወቷን ለመቀጠል ተስፋ የላትም ስትል አሰበች ።

‹‹ናንሲ» አለች ማሪዮን ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን ስም እየጠራች። ግድ የለም ይሁን ለማይክል ስል... ‹‹ናንሲ ....» ድምጺ ለስለስ ያለ ነበር ። «ፊትሽ ምን ያህል እንደተጐዳ ሀኪሞቹ ነገሩሽ » .. በክፍሉ ፀጥታ ነገሰ። ዘለአለም አለም ያህል ጊዜ ሁለቱም ጸጥ ብለው ቆዩ። ድንገት የለቅሶ ሳግ ፀጥታውን አደፈረሰው «በፊትሽ ላይ የደረሰው አደጋ መጠን ከምን እስከምን እንደሆን ነገሩሽ ? አሰቃቂ እንደሆነ አውቀሽዋል ?» አለች ማሪዮን አሰቃቂ የሚለውን ቃል ስትናገር ልቧ ሊከዳት ምንም አልቀራትም። ሁሉ ነገር አስጠላት ። ሆዷ ተገላበጠ ። አንጀቷ ተላወሰ ወዲያው የለም፣ መዳከም አያስፈልግም አለች ማይክልን እያሰበች። «ናንሰ. ፤ የቀድሞ መልክሽን መመለስ ይትርና ትንሽ እንኳ ለማስተካክል በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ እንደተበላሸሽ ነግረውሻል?» አለች ማሪዮን ። የናንሲ ለቅሶ ቁጣ የተቀላቀለበትና ስቃይ የተሞላበት ሆነ።
«አልነገሩኝም ዋሽተውኛል እነሱ ያሉኝ...»
«ናንሲ ፤፡ ሀክምናውን ሊያደርግልሽ የሚችል በሀገሪቱ ውስጥ ያለ አንድ ሃኪም ብቻ ነው ። እሱን ለማግኘትም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዶላሮች ያስፈልጋሉ ። ይህን ያህል ገንዘብም አንች የለሽም ማይክልም አያገኝም »
«ቢኖረውም ያን ያህል ገንዘብ ከፍሎ እንዲያሳክመኝ አልፈቅድም «» የሚያነጋግራት ድምፅም ኑሮና እድልዋም አናደደዷት፤ «አልፈቅ. .. ቅድለትም » አለች ሳግ ኢያቋረጣት ።
«ያሰብሽው ነገር አለ?» አለች ማሪዮን ።
«ምንም ያሰብኩት ነገር የለም!»
«ይህን መስለሽ የማይክልን ፊት ማየት ትደፍሪያለሽ ? እሱስ የሚችል ይመስልሻል ? ርግጥ መቼም በይሉኝታ ትንሽ ሊሞክር ይችላል ። ታማኝ ለመሆን መሞከሩ አይቶርም ። ግን ያን ሁሉ የሚያደርገው ወዶሽ ሳይሆን አዝኖልሽ እንደሆነ እያወቅሽ ደስታ ልታገኝ የምትችይ ይመስልሻል !? » ከዚያ በኋላ ማሪዮን እነገሩ ውስጥ ዝፍቅ ብላ ገባችበት ።
«ናንሲ … ሃኪሞቹን አነጋግሬ ነበር ከድሮው ገፅታሽ አንድም ያልተለወጠ ነገር የለም ። ፊትሽ ፈፅሞ ሌላ ሆኗል ። ስለዚህም የነበረሽ ነገር ሁሉ የለሽም ። ካሁን በኋላ ... ከዚህ በፊት ከኖርሽው ነገር ላንቺ የሚሆን እንደሌለ መገንዘብ አለብሽ ለተወሰነ ጊዜ ሁለቱም ፀጥ አእሉ። ማሪዮን ቀጠለች ። «ከማይክል ጋር ለመኖር ብትሞክሪ ከላይ እንደነገርኩሽ ላንቺም ለሱም ስቃይ እንጂ ሌላ ትርፍ የለውም ። ስለዚህ ቁረጪ ናንሲ። ተለያይታችኋል በቃ ።ማለት ከወደድሽው ይ…ገባሻል። ለሚወዱት ሰው ስቃይ መሆን ደስ አይልም ። አንቺም:..አንቺም ቢሆን መሰቃየት የለብሽም ። አንቺም አዲስ ህይወት ሀ ብለሽ ልትመሰርቺ የምትችይበት መንገድ አለ ናንሲ » ማሪዮን ናንሲ ትናገር እንደሆነ ጠበቀች ናንሲን ግን ሳግ ሲነትጋት ይሰማ እንጂ ምንም ቃል አልተነፈሰችም ። «ይህ ቢሆን አዲስ ህይወት ፤ አዲስ አለም ልታገኝ የምትችይበት መንገድ ይኖራል » አለች ማሪዮን ። አሁንም መልስ የለም ። «አዲስ ፊት ፤ አዲስ ገፅታ ፣ አዲስ ኑሮ!» አለች ማሪዮን ሳጉ ቆመ ።
«ከየት ? እንዴት ›› አለች ናንሲ ።
«እኔ እማውቀው ሰው አለ ። ሳንፍራንሲስኮ ውስጥ የሚኖር። ይህ ሰው እንደገና ቆንጆ ሴት ሊያደርግሽ ይችላል ። ይህ ሰው የስእል ስራሽን እንድትቀጥይ ሊያደርግ ይችላል ። ይህን ለማድረግ በርግጥ ረጂም ጊዜና በርካታ ገንዘብም ይወስዳል ። ሆኖም ገንዘብም ቢጠፋ ፤ ጊዜም ቢወስድ ከሚገኘው ጥቅም ጋር ሲነፃፀር ኢምንት ይሆናል ። አይመስልሽም ናንሲ?›› አሁን ማሪዮን በነገሩ ገባችበት ። ውል መዋዋል ነው የንግድ ውል ። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚተረፍበት ውል። ያ ደግሞ ሥራዋ ነው።

«ታዲያ ያን ያህል ገንዘብ እኛ ከየት እናመጣለን!›› አለች ናንሲ። «እኛ» የሚለውን ቃል ስትሰማ ማሪዮን ሂልያርድ ሽምቅቅ አለች ። « እኛ›› ያለችው እሷን ከማይክል ጋር ደብላ መሆኑ ነው ስትል አሰበች። ተናደደች። ቢሆንም ለጊዜው መቻል አለባት። ይህን የጀመረችውን ነገር በትእግስት ከዳር ማድረስ አለባት፡፡
«ልክ ነሽ ናንሲ ። በቀላሉ የሚቻል አይደለም ። ግን እችላለሁ ። ማን እንደሆንኩ እስካሁን ሳታውቂ አልቀረሽም፤ አይደለም ?››
« አውቄአለሁ»
«እንዳልኩሽ ማይክል ከእንግዲህ ያንች ሊሆን እንደማይችል ገብቶሻል ፤ አይደለም ? በተለይ እንዲህ ሆነሽ ቢያይሽ እሱንም ፀፀቱ ሊገለው እንደሚችል ይገባሻል ፤ አይደለም
«ይገባኛል »
«ስለዚህ ታማኝነትህን አሳየኝ ማለት ያውም ቢተርፍ ማለቴ ነው፤ መፈታተን ፤ በጣም ከፍተኛ የሆነ ክፋት እንደሆነ ትረጃለሽ፤ አይደለም ናንሲ ? ይህን አእትረጂም ?›»
«እረዳለሁ » አለች ድክም ባለ ድምፅ ።
«ስለዚህ የቀረ ነገር ቀርቷል ።። የጠፋ ነገር ጠፍቷል ፤ አይደለም?»
«አዎ»
«ናንሲ ፤፡ አንድ ሃሳብ ላቀርብልሽ እፈልጋለሁ ። ድርድር ነው፡።፡ እንደምንስማማ ተስፋ እለኝ፡፡
👍15