አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
በህይወት መንገድ ላይ
(ታጋቾቹ)

ምእራፍ 5

ዘሪሁን ገመቹ

"""
-ምንበላው ብስኩትና ኩኪስ የመሠሉ ደረቅ ምግቦች ቢሆኑም አልተራብንም፤ውሀም በተመሳሳይ ቢያንስ ሁለት ደርዘን የሚሆን አለን፤አሁን ያጣነው ትዕግስት ነው። በ6 ሰዓት ውስጥ እናወጣችሆለን ብለው እኛጋ ለመድረስ የላኩትን ቱቦ መልሰው በመሳብ የተገኘውን ቀዳዳ ሙሉ በሙሉ የደፈኑት ሰዎች እንሆ ከ20 ሰዓት በላይ ሆኖቸዋል። ምንም የሙከራ ምልክት ሆነ ከላይ የሚረግፍ አፈር የለም።እንግዲህ እዚ ወጥመድ ውስጥ ከተያዝን ሁለተኛ ቀናችንን አጠናቀን ሶስተኛውን ልንይዝ ነው።
"ሰዎች ይሄ ነገር እያስፈራኝ ነው"አለ ጋሽ አህመድ።
"ጋሽ አህመድ አንተስ ሁለት ልጅ ወልደህ ዘርህን ተክተሀል፤እኔ አለው እንጂ ያን ሁሉ ዘመን አርሼ አርሼ ባዶዬን ልመርሽ ነው። እስኪ ልጅስ ይቅር ለማስለቃሻ የሚሆን ደህና ፎቶ እንኳን ተነስቼ ለእናቴ ብሰጣት አትሉም...የማረባ ነኝ"
"ትቀልዳለህ አይደል፤ይልቅ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ?"አይዳ ነች
"ቀጥይ"
"ትናንትና በሬዲዬ ሲያናግሩን ወደውስጥ የተቀበርነው ወይም አሁን የምንገኝበት ወደ 30 ሜትር ጥልቀት እርቀን ነው።እንደምናየው ያለንበት ክፍል ድፍን ነገር ነው ....ታዲያ አየር ከየት እያገኘን እስከአሁን ቆየን?እንዴት ሳንታፈን?"
"በጣም ነው የተገረምኩባት "you are a gunies " እንዴት እስከአሁን ታፍነን ሳንሞት?"ጥያቄዎን መልሼ ጠየቅኩ..ሁሉም መልስ ለማግኘት ጭንቅላቱን ማሠራት ጀመረ
"ስንጥቁ" ?"
"የምን ስንጥቅ?"ጠየቅኩ
"የእኔ ስንጥቅ አልልህ መቼስ....የማወራው የደፈነው..ዘንዶው የመጣበት"ይሄንን የምትናገረው ወደዛው እየተንቀሳቀሰች ነው...ሠላምን ጨምሮ ሌሎቻችንም ተከተልነው።
"ይሄን እኮ ደፍነነዋል...መድፈን ይቅርና በሙቀት ጊዜ እቤታችንን መስኮት እንኳን ስንዘጋ እንዴት ነው?
"አዎ እውነትህን ነው....ግን ስለዚህ ቦታ ብዙም የምናውቀው ነገር የለም"
"እሺ ምን እናርግ?""
"እኔ ይሄንን የደፈነውን ስንጥቅ መልሰን እንክፈተው..ከቻልን ሰፋ እናድርግና እስከየት እንደሚወስድ እንወቅ"፤ንግግሬን ሳልጨርስ በሪሁን ወደኃላ ተመልሶ ብረት በማምጣት መቆፈር ጀመረ።
"ቀስ ይሄ የተነደለ ጭንቅላትህ ሳይድን ሌላ አደጋ እንዳያጋጥምህ ?"ሰላም ነች ያስጠነቀቀችው
"መበርቀሱ ቀላል ነው ይልቅ ያ ዘንዶ መጥቶ እንዳይውጠኝ ፀልይልኝ፤ቆይ እንደውም"አለና መቆፈሩን አቋርጦ ትናንት ከተላከልን ዕቃዎችን ማተረማመስ ጀመረ
"ምን ፈልገህ ነው?"ጠየቀችው ሰላም
"ትናንት ቢላዋዎች ተልከውልን ነበር አይደል፤አዎ አገኘሁት ይሄው አለና ከሶስቱ ቢላዎ መካከል ተለቅ ያለውን አነሳና ሽፍኑን ገልጦ ወገብ ላይ ሸጉጦ ወደቁፋሮ ተመለሠ
"በቢላዎ ብቻ ልትቆፍር እንዳይሆን?"
"አይ አይደለም ቅድመ ጥንቃቄ ነው...ዘንዶ ከዎጠኝ ሆድን በዚህ ቀድጄ ነፃ ወጣለው"
ጋሽ አህመድና በሪሁን ተጋግዘው ሲቆፍሩ ቆዩና ከ30 ደቂቃ ብኃላ አንገት የሚያሾልክ አይነት ቀዳዳ ተገኘ...ሁላችንም በየተራ አንገታችንን አስግገን በማስገባት አሻግረን ለማየት ሞከርን፤ጭለማ ነው ምንም የሚታይ ነገር የለም ግን ልኬቱን መገመት በሚያስቸግር እሩቅ ቦታ ላይ ምንነቱን መለየት የማይቻል አነንፀባራቂ ነገር ይታያል።
"ሠማይ ነው እንዴ ሚታየው?"እኔ ነኝ ግራ ገብቶኝ የጠየቅኩት
"ምን አልባት ውሀም ሊሆን ይችላል...ማለት የቢሾፍቱ ሀይቅ ውሀ"አይዳ
ውሀ ከሆነ እኮ የሀይቁ ወለል ነው ሚሆነው ሰባና ሰማኒያ ሜትር ዎኝተን ነው የላይኛውን ወለል የምናገኘው?"
አልኩኝ ሀሳብ ይዞኝ
"ታዲያ ምን ችግር አለው...እዛ ለመድረስ ያብቃንጂ"
"ሁለችሁም ዋና ትችላላችሁ እንዴ?"
"እኔ አልችልም" አለ ጋሽ አህመድ
"አንተስ ኢንጂነር ?" ጠየቀችች ሠላም ችላለው የሚል መልስ እንድመልስ በመመኘት
"አረ እኔ በፍፅም አልችልም"
"እኔ ጋሽ አህመድን አዝዬ ዋኛለው..ሠላምና አይዳ ደግሞ ኢንጂነሩን..ግን ቅድሚያ መስማማት አለብን የአመት ደሞዛችሁን ለእኛ ትለቃላችሁ"
"የአመት ደሞዜን ለቅቄ ዲቃላዎቼን ምን ላበላልህ ነው?"
"በህይወት ስትተርፋ አይደል የምታበላቸው ተወው እንደውም በአመት ደሞዝ አያዎጣኝም..እናንተስ ያዋጣችሆል..?አለ ወደ ሴቶቹ ዞሮ
"ባክህ ቀልድን ተውና ምን እናድርግ የሚለውን ብንመካከር ነው ሚሻለው"
አንቺ ደግሞ ዛሬም ከሞት ጋር ፊት ለፊት ተፋጠን ቁምነገር ብቻ እንዳወራ ትጠብቂያለሽ..እንደውም ደክሞኛል የሚበላ ነገር ስጪን ..ብሎ ባለበት ቁጭ አለ ..ጋሽ አህመድም ተከትሎት ተቀመጠ፤እኔና ሰላም ተጋግዘን እቃችን ያለበትን ጋወን ወደእነሡ አስጠጋነው
👍24
ሰላም ያደለችንን ብስኩት በውሀ እየማግን በመብላት ላይ ሳለን ..የሆነ ጋጋ..ጋ የሚል ድንገተኛ ድምፅ ሰማን ።ሁላችንንም እያላመጥን ያለነውን እንኳን ሳንውጥ በድንጋጤና በተስፋ ፈጠን ቀረን።
"በጌታ ስም ደረሱልን መሠለኝ"ሠላም ነች
"አዎ ሰዎች...'"ንግግሬን ነጓድጓዳዊ ናዳ አቋረጠኝ ..አይናችን እያየ ከላይ እየተንደረደረ በሚመጣ አለትና አፈር ያ ሁሉ ክፍት ቦታ ተጠቅጥቆ መሙላት ጀመረ...ወዲህና ወዲያ እየተንፎቀቅን እራሳችንን ለማትረፍ በእውር ድንብር መዳከር ጀመርን...ግን በቃ አልቆልናል..እርስ በርስ ተፋፍገንና ተጣብቀን ብንቆምም በናዳው የመጣው ቁልል አፈር እኛንሞ እየዋጠን ነው።ጉልበታችን ጋር ደርሷል
"ወይኔ ሙሙዬን ሊደፍናት ነው...ምን አለ ከምሰስት እዚህ ላላችሁት እንኳን አንዳንዴ አቅምሼያችሁ ቢሆን"አይዳ ነች።
"አረ እንቺ በእግዜር እጅ ተይዘሽ እንኳን ለዚህ ባለጌ አፍሽ ዚፕ ማበጀት አትችይም?"
"በእግዜር እጅ እንሁን በቆሪጥ እጅ በምን አወቅክ?እንደውም ታያለህ በቆሪጥ እጅ ከሆነ ያለነው ከእሱ ጋር ስንገናኝ ሀለቃችሁ የምሆነው እኔ ነኝ...ታዲያ በዛን ጊዜ ጋሼ ኢንጂነር አንተን አያድርገኝ..."
"እኔ እንደውም ሳስበው ይሄ ሁሉ መቅሰፍት የመጣብን ባንቺ ሀጥያት ምክንያት ነው"ትበሳጫለች ብዬ ነበር እንደዛ ያልኳት እሷ እቴ
"እኔም ስጠረጥር እንደዛ ይመስለኛል"
"ጭቅጭቁን አቁሙና አሁን ምን እናድርግ?"ጋሽ አህመድ የጭንቅ ጥያቄ ጠየቀ።በሪሁን እንደምንም ከጎኑ የነበረችውን ሰላም ወገብ በሁለት እጆቹ ያዘ
"ምን እያደረክ ነው?"አለች ግራ በመጋባት
"እንደምንም እግርሽን ለማላቀቅ ሞክሪ ..ጋሽ አህመድ አንተም ወደላይ ጎትታት..ሁለቱ ተረዳድና ከአፈሩ ነፃ አድርገው በአየር ላይ አንጠለጠሏት
"አሁን ልክ እንደልጅነትሽ ትከሻዬ ላይ ውጪ"እንደምንም ቧጣና ተፍጨርጭራ ያላትን አደረገች።
"እሺ እንዳልከው ወጣው ከዛስ..?."
"እኔስ ማንኛችሁ ላይ ልውጣ"አይዳ ነች ከጎኔ እየተቁነጠነጠች የጠየቀችው"እስኪ ባልጠፋ ጊዜና ቦታ በዚህ ቀውጢ ጊዜ ከእኔ ጎን እንዴት ልትሆን ቻለች?"
"ባለሽበት አርፈሽ ቁሚ"አልኳት በንዴት
እኔን ተከትሎ በሪሁን ማውራት ጀመረ.."ከዛማ አንቺ ከሁላችንም የተሻልሽ አማኝ ስለሆንሽ ..በሆነ ታምር ከተቻለ ሁላችንም ካለበለዚያ ቢያንስ እኔና አንቺ እንዲያተርፈን ፀልይ"አላት
"እውነትም ጊዜ ሳታጠፋ ለፀሎት አይኖቾን ከደነች..አፈሩ ወገባችን ጋር ደርሷል..ምን አለ እኔሞ በዚህ ሰዓት እንኳን መፀለይ ብችል?ህይወት ግን እንዴት ሸርሙጣ ነች።አሁን ባለፈው ወር ታናሽ እህቴ ቸገረኝ 10ሺ ብር አበድረኝ ስትለኝ የለኝም በሚቀጥለው ወር አልኳት..እያለኝ እኮ ነው...ለካ በሚቀጥለው የሚባል ነገር ሁሌ የለም ...ሁሉን ነገር ለመከወን ትክክለኛው ሰዓት አሁን ብቻ ነው።
"እናንተ "የሚል የበሪሁን የማንቂያ ድምፅ ነው ከገባውበት የፀፀት ድባቴ ያወጣኝ..
"ቆሟል...ፀሎትሽ ደርሷል "
አዎ እውነቱን ነው የሚናደው ነገር ተንዶ አልቆ ሁሉ ነገር ረጋግቷል..የነበርንበት ዋሻ ግን 95 ፐርሰንት የሚሆነው ክፍት ቦታ አሁን አጥተነዋል...ከላይ ቆፍረው ይደርሱልናል የሚለው ተስፋችንም ለዜሮ የቀረበ ሆኗል...ታዲያ ለጊዜው ብቻ በመትረፋችን ሙኑ ነው ያስደሰተን..?ከአንድ ሰዓት ግፋ ቢል ከአንድ ቀን ብኃላ ያበቃልናል።እና ጣራችንን ከማስረዘም በዘለለ ትርፋችን ምንድነው?"
"የመውረድ ሀሳብ የለሽም?"አላት
"ወይ ይቅርታ "ብላ እንደምንም ተንሸራታ ከትከሻዋ ለይ ወረደችና አፈሩ ላይ አረፈች..
"በይ እንደአለብሽ ውለታ መጀመሪያ እኔ እግሮቼን ነፃ እንዳወጣ አግዢኝ" አላት"
ተንበረከከችና አፈሩን ከእግሩ አካባቢ ማንሳት ጀመረች እኛም እራሳችንን ነፃ ለማውጣት መሞከር ጀመርን ።እኔ ግን ለራሴም ባልገባ ሁኔታ የራሴን ትቼ አይዳን ነፃ ለማውጣት መታተር ጀምሬ ነበር
"በለስላሳ እጆችህ እኮ ጭኔ ን አርመሰመስከኝ ..ወደ እሙሙዬ እንደዛ መጠጋትህ ካልቀረ ፊንገር ለምን አትሞክርም"አለችኝ...እንደዛ ስትለኝ ከነበርኩበት ጥልቅ ከሆነ መመሰጥ በከፍተኛ ንዴት ነቃው...እዛው ባጎነበስኩበት ጭኖን በጥሮሶቼ ብሞዠልቀው ደስታዬ ወደር አልነበረውም...
"አንቺ ምን አይነት ክብር የማይወድልሽ ብሽቅ ሰው ነሽ?"
"ምን አበሳጨህ እዚህ ሀገር ድሮም እውነቱን ፊት ለፊት የሚናገር ሰው አይወደድም"
በእፍረት ተሽማቅቄ እሷን ማገዙን ትቼ እራሴን ነፃ ለማውጣት መጣር ጀመርኩ ።ከሀያ ደቂቃ ብኃላ ሁላችንም ነፃ መሆን ብንችልም ግን በከፍተኛ መተፋፈግ እርስ በርስ ተጠጋግተን ነው ያለነው ።

ይቀጥላል....


ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
❤️
👍23
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

አንድ ዝናባማ ከሰዓት

ሰማዩ ከብዶ ዝናቡ በጣም እየወረደ ነው: ክፍላችን ውስጥ ያሉ መብራቶች
ሁሉ በርተዋል፡ ቲቪውም እንደተለመደው ተከፍቷል። ክሪስ የመስኮቱን ከባባድ መጋረጃዎች በሁለት እጆቹ ከፈት አድርጎ ይዞ በመቆም ከሩቅ ትንሽ የአሻንጉሊት ባቡር መስሎ ሁልጊዜ አስር ሠዓት ገደማ አሳዛኝ ፊሽካውን እያሰማ የሚያልፈውን ባቡር ለማየት እየጠበቀ ነው:

በራሱ ዓለም ውስጥ ነው፧ እኔም በራሴ አለም ውስጥ እግሮቼን አጣምሬ እኔና
ኬሪ የምንጋራው አልጋ ላይ በመቀመጥ እናታችን ለመጨረሻ የመጣች ጊዜ
ካመጣችው መፅሄት ላይ ምስሎች እየመረጥኩ በውስጡ ያሉትን ፎቶግራፎች በጥንቃቄ እየቆረጥኩ የማልመውን አይነት በደስታ የምኖርበት ቤት፣ ሺ ሴቶችን በጎኑ የሚደርግ ሳይሆን እኔን ብቻ የሚወደኝ የምምኘውን አይነት ረጅም፣ ጠንካራ፣ ጥቁር ፀጉር ያለው ባል በማድረግ የቆራረጥኳቸውን የምስል ቁራጮች ሌላ መፅሀፍ ላይ እየለጠፍኩ ህይወቴን እየሳልኩ ነው።

ዳንሰኛ መሆን ሳቆም ባልና ልጆች ይኖሩኛል የማልመው አይነት ቤት ሲኖረኝ ደግሞ ከውድ ድንጋይ የተሰራ የመታጠቢያ ገንዳ ይኖረኛል ከዚያ ለውበት የሚሆኑ ዘይቶች አደርግበትና ማንም በሩን እያንኳኳ ፈጠን በይ
ሳይለኝ ከፈለግኩ ቀኑን ሙሉ ተዘፍዝፌ እውላለሁ። ከዚያ ቆዳዬ በጣም
ለስላሳና ምንም እንከን የሌለበት ጥርት ያለ ይሆንና ደስ የሚል ሽታ ያለው
የሽቶ ጠረን ይኖረኛል። ይሄ የበሰበሰ አሮጌ ደረቅ እንጨት ሽታና ጣሪያው
ስር ያለው ክፍል አቧራ ከነችግሮቹና አሮጌ እቃዎቹ ጋር እኛን ወጣቶቹን ልክ እንደዚህ አሮጌ ቤት ያለ ጠረን እንዲኖረን አድርጎናል

ክሪስ” አልኩት ጀርባው ላይ እያፈጠጥኩ። “አሁን ጠንካሮች ነን፤ ታዲያ
ለምንድነው እናታችን ተመልሳ እስክትመጣና ሽማግሌው እስኪሞት መጠበቅ ያለብን? ለምንድነው የማምለጫ መንገድ የማንፈልገው?” ቃል አልተነፈሰም። ግን እጆቹ የመጋረጃውን ጨርቅ ጨምድደው ሲይዙ ተመለከትኩ::

“ክሪስ...”

“ስለሱ ማውራት አልፈልግም” አለ በንዴት
“ስለመሄድ እያሰብክ ካልሆነ ታዲያ ለምንድነው እዚያ ቆመህ ባቡሩ እስኪያልፍ የምትጠብቀው?”

“ባቡሩን እየጠበቅኩ አይደለም! በቃ ዝም ብዬ ወደ ውጪ እየተመለከትኩ
ነው:”

በግንባሩ የመስኮቱን መስታወት ተደግፏል። ቅርብ ያለ ጎረቤት እንዲያየው የደፈረ ይመስላል

“ክሪስ ከመስኮቱ ዞር በል የሆነ ሰው ሊያይህ ይችላል”

“ማንም ቢያየኝ ግድ የለኝም!”

የመጀመሪያ ስሜቴ ወደሱ ሮጬ በክንዶቼ አቅፌ ከእናታችን ያጣቸውን
እነዚያን መሳሞች ለማካስ ፊቱን በሙሉ በሚሊየን በሚቆጠሩ መሳሞች
ማዳረስ ነበር እሷ እንደምታደርገው ጭንቅላቱን ደረቴ ላይ አስደግፌ ፀጉሩን እያሻሸሁ በፊት ወደነበረበት አይነት ደስተኛ፣ የሚናደድበት ቀን የሌለው፣ መልካም ነገር ብቻ የሚመለከት ሰው ወደመሆኑ ልመልሰው ፈለግኩ። ነገር ግን በፊት እናታችን ታደርግለት የነበረውን ነገር ሁሉ ባደርግለትም ተመሳሳይ
እንደማይሆን አውቅ ነበር፡ እሷን ነው የሚፈልገው: ተስፋዎቹ፣ ህልሞቹና
እምነቱ በሙሉ በአንዲት ሴት ውስጥ ታሽጓል በእናታችን፡፡

አሁን ከመጣች ሁለት ወር አልፏታል! እዚህ ቤት የምናሳልፈው አንድ ቀን በትክክለኛው ህይወት ሲለካ ከወር በላይ እንደሚረዝም አልገባትም
ስለኛ አትጨነቅም? እንዴት እንደምንኖር አታስብም? ያለምንም ማብራሪያ፣
ምክንያት ወይም ሰበብ ስትተወን እያየ ክሪስ ሁልጊዜ የሷ ቀንደኛ ደጋፊ
እንደሚሆን ታምናለች? ፍቅር በጥርጣሬና በፍርሀት በአንድ ጊዜ ሊፈርስ
እንደሚችልና በፍፁም ዳግመኛ ሊገነባ እንደማይችል አታውቅም?

"ካቲ” አለ ክሪስ ድንገት “የሆነ ቦታ የመሄድ ምርጫ ቢኖርሽ የት ትሄጃለሽ?

“ደቡብ” አልኩ “የሚሞቅና ፀሀያማ የባህር ዳርቻ ወዳለው… ሞገዶች ለስላሳ
ወደሆኑበትና ሀይለኛ ነፋስ ወደማይነፍስበት መሄድ እፈልጋለሁ በነጭ አሸዋ ላይ ጋደም ብዬ የፀሀይ ብርሃኔን እየጠጣሁ ለስለስ ያለ ንፋስ ፀጉሬ ውስጥና ጉንጮቼ ላይ ሲንሸራሸር መስማት ነው የምፈልገው”

“ልክ ነው…” ተስማማ፡ “የገለፅሽበት መንገድ አሪፍ ይመስላል እኔ ግን ልክ
እንደ በረዶ ሸርተቴ ሁሉ በሀይለኛ ሞገድ ውስጥ መንሳፈፍም እወዳለሁ።”

ምስሎቹን እየቆራረጥኩ የነበርኩበትን መቀስና መፅሄቱን አስቀምጬ ሙሉ
በሙሉ ክሪስ ላይ ትኩረት አደረግኩ፡ ክሪስ የሚወዳቸውን ብዙ ስፖርቶች አጥቶ፣ በአንድ ክፍል ውስጥ ታሽጎ፣ ከእድሜው በላይ አርጅቶና አዝኖ ስመለከተው ላፅናናው ብፈልግም እንዴት እንደማፅናናው ግን አላወቅኩም።

ክሪስ እባክህ ከመስኮቱ ጋ ተመለስ?” አልኩት።

“ተይኝ! ይሄ ቦታ እጅግ ሰልችቶኛል ይህንን አታድርግ፣ ያንን አታድርግ፣
ካላናገሩህ እንዳትናገር መባል፤ በየቀኑ እነዚህን በደንብ በደንብ የማይሰሩ ጣዕም አልባ ምግቦች መብላት ታክቶኛል
በምግብም እንኳን እንዳንደሰት ሆነ ብላ ነው እንደዛ የምታደርገው: ስለዛ
ሁሉ ገንዘብ ሳስብ ደግሞ ግማሹ የእናታችንና የእኛ በመሆኑ እንደሚገባን
አስባለሁ። ያ ሽማግሌ መቼም ለዘላለም መኖር አይችልም:"

“በዓለም ላይ ያለ ገንዘብ ሁሉ ቢደመር ያጣናቸውን የመኖሪያ ቀኖች ያህል
ዋጋ የለውም!” በቁጣ መለስኩለት ወደኔ ዞር አለ፤ ፊቱ ቀልቷል። “ምናልባት
አንቺ በተሰጥኦሽ ገንዘብ ታገኚ ይሆናል እኔ ግን ከፊት ለፊቴ የብዙ አመታት
ትምህርት ይጠብቀኛል፡ አባታችን ዶክተር እንድሆን ይጠብቅ እንደነበረ ታውቂያለሽ፡ እንደምንም ብዬ ያንን ማሳካት አለብኝ፡፡ ከዚህ ከኮበለልን ግን
መቼም ዶክተር መሆን አልችልም: አንቺንና መንትዮቹን እንዲሁም ራሴን
ማኖር ይኖርብኛል። እስቲ እኛን ለማኖር ልሰራ የምችላቸውን ስራዎች
ንገሪኝ… ፍጠኚ! ሳህን አጣቢ ወይም ፍራፍሬ ለቃሚ ሌላ ምን መሆን
እችላለሁ? እነዚህ ስራዎችስ የህክምና ትምህርት ቤት ያስገቡኛል?”

የነደደ ቁጣ ሞላኝ፡ እኔ ላደርገው ስለምችለው አስተዋፅኦ ትንሽ እንኳን
ዋጋ አልሰጠውም: “እኔም መስራት እችላለሁ!” አልኩት። “ሁለታችን
ሆነን ማስተዳደር እንችላለን፡ ክሪስ የተራብን ጊዜ አራት የሞቱ አይጦች
ስታመጣልኝ፣ እግዚአብሔር በትልቅ መከራ ጊዜ ለሰዎች ተጨማሪ ጥንካሬና
ችሎታ ይሰጣል ብለኸኝ ነበር፡ እኔም እንደሚሰጥ አምናለሁ: ከዚህ ወጥተን በራሳችን መኖር ስንጀምር በአንድም በሌላም በኩል መንገዳችንን እናስተካክላለን፡ እናም ዶክተር ትሆናለህ! ያንን ዶክተር የሚለውን ማዕረግ
ከስምህ በፊት ለማየት የትኛውንም ነገር አደርጋለሁ፡”

“ምን መስራት ትችያለሽ?" በጥላቻና በመመረር አይነት ጠየቀኝ፡ መልስ መስጠት ከመቻሌ በፊት ከጀርባችን ያለው በር ተhፍቶ አያትየው በሩ ላይ ቆመችና ወደ ክፍሉ ሳትገባ ክሪስ ላይ አፈጠጠች: እሱ ደግሞ እንደበፊቱ ለመታዘዝ ፈቃደኛ ባለመሆን ግትርና እምቢተኛ ሆነና ከመስኮቱ ጋር ሳይንቀሳቀስ ፊቱን መልሶ እንደገና ዝናቡ ላይ ማፍጠጥ ቀጠለ።

“ልጅ!” ተጣራች። “ከመስኮቱ ጋር ዞር በል አሁኑኑ!

“ስሜ ልጅ አይደለም፧ ስሜ ክሪስቶፈር ነው በተሰጠኝ ስም ልትጠሪኝ ትችያለሽ ወይም ጭራሽ አለመጥራት ትችያለሽ ... ግን እንደገና ልጅ ብለሽ እንዳትጠሪኝ፡”
👍38😁2
ጀርባው ላይ ተፋችበት፡ “በተለይ ያንን ስም የአባትህ ስለሆነ እጠላዋለሁ!
አባትህን እናቱ ስትሞትና የሚኖርበት ቤት ሲያጣ ከልቤ ደግነት የተነሳ እዚህ
አመጣሁት ባለቤቴ እዚህ እንዲኖር አልፈለገም ነበር። እኔ ግን ወላጆቹን ላጣና መኖሪያ ላልነበረው ትንሽ ልጅ አዘንኩ። ስለዚህ ባለቤቴን ታናሽ ወንድሙ እኛ ጣራ ስር እንዲኖር እንዲፈቅድለት ጨቀጨቅኩት ከዚያ
አባትህ መጣ: ምርጥ የሚባል ትምህርት ቤት አስገባነው: ከሁሉም ነገሮች
ምርጦቹን ሰጠነው እሱ ግን ጎበዝና ቆንጆ መሆኑን ተጠቅሞ ደግነታችንን
መጠቀሚያ አደረገው: የወንድሙን ልጅ፣ ልጃችንን ሰረቀን ያለችን እሷ ብቻ ነበረች እሷ ብቻ! እናም በምሽት ይዟት ኮበለለ፡ ከሁለት ሳምንት በኋላ በደስታ እየሳቁ መጡና ፍቅር ላይ በመውደቃቸው ይቅር እንድንላቸው ጠየቁን፡ በዚያ ምሽት ባለቤቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የልብ በሽታ ያዘው እሷና ያ
ሰው ለአባቷ የልብ ህመም መንስኤ መሆናቸውን እናታችሁ ነግራችኋለች?
ባለቤቴ ቤቱን ለቅቃ እንድትወጣና ተመልሳ ወደዚህ ቤት እንዳትመጣ ነግሯት ወለሉ ላይ ወደቀ" አለችና አየር ለመሳብ ንግግሯን ቆም አድርጋ ጠንካራና በአልማዝ ቀለበቶች ያሸበረቀውን እጇን ጉሮሮዋ ላይ አደረገች

ክሪስ በመስኮት ከሚያይበት ፊቱን መልሶ ልክ እኔ እንዳደረግኩት አፈጠጠባት።ይሄ እዚህ ቤት ልንኖር ከመጣን ጀምሮ ካወራችው ነገሮች ሁሉ የበዛው ነበር።

“ወላጆቻችን በሰሩት ጥፋት እኛ መወቀስ የለብንም" አለ ክሪስ በግዴለሽነት

“አንተና እህትህ ለሰራችሁት ነገር ነው የምትወቀሱት”

“ምን ኃጢአት የሆነ ነገር አድርገናል?” ሲል ጠየቃት፡ “ከአመት አመት አንድ ክፍል ውስጥ እየኖርን ልንተያይ እንደማንችል ታስቢያለሽ? እዚህ እንድንቀመጥ በማድረግ ረዳሽን፣ ግን ደግሞ ሠራተኞቹ እንዳይገቡ በሚል ምክንያት ይህኛውን የህንፃ ክፍል ትቆልፊዋለሽ፡ አንቺ ክፉ ነው ብለሽ የምትቆጥሪውን ነገር ስንሰራ ልትይዥንና ለእኔና ለካቲ ስለእናታችን ጋብቻ ያለሽ የተሳሳተ አመለካከት ትክክል እንደሆነ ልታሳምኚን ትፈልጊያለሽ…ራስሽን ተመልከቺው፤ ብረት የመሰለ ግራጫ ቀሚስሽን ለብሰሽ ህፃናት ልጆችን እያስራብሽ ለራስሽ ግን ኃይማኖተኛና ፃድቅ እንደሆንሽ ይሰማሻል?”

በአያትየው ፊት ላይ ያየሁት ነገር ስላስፈራኝ “አቁም ክሪስ! ምንም ነገር አትበል!" ስል ጮህኩበት፡ ይሁን እንጂ አስቀድሞ ብዙ ብሏል በሩን በሀይል ዘግታ ስትወጣ ልቤ ጉሮሮዬ ውስጥ የተወተፈች መሰለኝ፡ “ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል እንሂድ።” አለ ክሪስ በእርጋታ። “ይህቺ ቦቅቧቃ ደረጃውን መውጣት ትፈራለች፡ እዚያ ደህና እንሆናለን፣ የምታስርበን ከሆነ ደግሞ አንሶላ ቀደን በሰራነው መሰላል ወደ መሬት እንወርዳለን፡"

እንደገና በሩ ተከፈተና አያትየው በእጇ አረንጓዴ መግረፊያ ይዛ አይኗ ላይ
አሰቃቂ ቁርጠኝነት እየተነበበ ገባች: መግረፊያውን ቅርብ ቦታ ሳትደብቀው አልቀረችም ምክንያቱም ያመጣችው በጣም በፍጥነት ነበር። “ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ሄዳችሁ ብትደበቁ አንዳችሁም ለሌላ ሳምንት ምግብ የሚባል አትቀምሷትም!” አለችና ፈጠን ብላ የክሪስን ክንድ ያዘችው ከዚያ “ልትታገለኝ ብትሞክር አንተን ብቻ ሳይሆን እህትህንና መንትዮቹን ጭምር
እገርፋቸዋለሁ።” አለች:

ወሩ ጥቅምት ነበር በህዳር ክሪስ አስራሰባት አመት ይሆነዋል። ግን ከእሷ
ግዙፍ ሰውነት ጋር ሲነፃፀር አሁንም በጣም ልጅ ነው፡ ሊታገላት ካሰበ በኋላ
ወደ እኔና እርስ በርሳቸው ተጣብቀው ወደቆሙት መንትዮች ተመለከተ።
ከዚያ ያቺ አሮጊት ወደ መታጠቢያ ቤት እየገፋች እንድትወስደው ፈቀደ
መታጠቢያ ቤቱን ዘግታ በሩን ቆለፈችና ልብሱን አውልቆ የመታጠቢያ
ገንዳውን እንዲመረኮዝ አዘዘችው፡

መንትዮቹ ወደ እኔ ሮጡና ፊታቸውን ጭኔ ውስጥ ቀብረው “አስቁሚያት
ክሪስን እንዳትመታው አድርጊ” እያለች ኬሪ ለመነችኝ:

አለንጋው እርቃን ቆዳው ላይ ሲያርፍበት ምንም ድምፅ አላሰማም: ባለፈው
አመት ውስጥ እኔና ክሪስ እንደ አንድ ሆነናል እሱ ልክ እንደ ሌላው ጎኔ በመሆኑ አለንጋው ስጋውን ሲገሸልጠው እያንዳንዱ ህመም ይሰማኝ ነበር።
አልጋው ላይ ተቀምጬ መንትዮቹን በክንዶቼ አቅፌያለሁ በጣም ጠላኋት።ጥላቻዬ በውስጤ እጅግ እያደገ እንደመጣ ስለተሰማኝና ያንንም ከመጮሀ በስተቀር በሌላ በምን ላስወጣው እንደምችል ስላላወቅኩ በጩኸት አወጣሁት።
እግዚአብሔር እንደሚሰማ ተስፋ አደርጋለሁ፡ ሠራተኞቹ እንዲሰሙ ተስፋ አለኝ ያ እየሞተ ያለው ወንድ አያቴም እንደሚሰማ ተስፋ አደርጋለሁ:

መግረፊያውን በእጇ እንደያዘች ከመታጠቢያ ቤቱ ወጣች: ከኋላዋ ክሪስ ወገቡ ላይ ፎጣ አስሮ ተከተላት አመድ መስሏል መጮኼን ማቆም አልቻልኩም::

“ዝጊ!” አለንጋውን አይኔ ፊት እያወዛወዘች አዘዘችኝ: “አንቺም መመታት
ካልፈለግሽ አሁኑኑ ፀጥ በይ!” ሊከላከሉልኝ የሞከሩትን መንትዮች ወደ ጎን ገፍትራ ጥላ ከአልጋው ላይ ጎትታ ስታስወርደኝም መጮህ አላቆምኩም: ኮሪ እግሯን ሊነክሳት ሲሞክር
በአንድ እርግጫ አሽቀነጠረችው ከዚያ እኔም ወደ መታጠቢያ ቤት ተወስጄ ልብሴን እንዳወልቅ ታዘዝኩ።

“አውልቂ አለዚያ ላይሽ ላይ እንዳለ እቦጫጭቀዋለሁ”

ማውለቅ ጀመርኩ… ቀስ እያልኩ የሹራቤን ቁልፎች ፈታሁ። ጡት መያዣ
አልለበስኩም: ጡቶቼንና ልጥፍ ያለ ሆዴን ስትመለከት አየኋት። በንዴት
አይነት አይኖቿን አሸሸች: “አንድ ቀን ይመጣል አንቺ አሮጊት!” አልኳት።
“አንቺም አቅም የለሽ የምትሆኚበት ቀን ይመጣል፡ የዚያን ጊዜ እኔም በእጄ አለንጋ እይዛለሁ። በፍፁም የማትበይው ምግብ ወጥ ቤት ውስጥ ይኖራል:
ምክንያቱም ራስሽ ሁልጊዜ እንደምትይው እግዚአብሔር ሁሉንም ያያል። እና ፍትህ የሚሰጥበት የራሱ መንገድ አለው… በእሱ መንገድ ለአይን አይን ነው አያቴ!”

“ሁለተኛ እንዳታነጋግሪኝ!” አለች: ከዚያ እኔ የእሷን እጣ ፈንታ የምቆጣጠርበት
ጊዜ እንደማይመጣ በመተማመን ፈገግ አለች: በሞኝነት በመጥፎ ሰዓት
ተናገርኩ፤ እሷም አቀመሰችኝ አለንጋው ስጋዬ ላይ ሲያርፍ መንትዮቹ
መኝታ ክፍሉ ውስጥ ሆነው “ክሪስ… አስቁማት! ካቲ እንድትጎዳ አትፍቀድ!
እያሉ ጮኹ።

መታጠቢያው አጠገብ በጉልበቴ ተንበርክኬ ፊቴንና ጡቶቼን ለመከላከል
እጥፍጥፍ አልኩ፡ ከቁጥጥር ውጯ እንደሆነች አውሬ ሴት የአለንጋው መያዣ እስኪወልቅ ድረስ ገረፈችኝ። ህመሙ እንደ እሳት ነበር አለንጋው ሊበጠስ የደረሰ መስሎኝ ነበር፡ ግን ረጅም መያዣ ያለው መጥረጊያ አነሳችና ጭንቅላቴንና ትከሻዬን መታችኝ፡ እንደ ክሪስ ጀግና ሆኜ ላለመጮህ ብሞክርም
እንዲወጣልኝ ግድ ነበር፡ ጩኸቴን ለቀቅኩት: “አንቺ ሴት አይደለሽም! አንቺ
ጭራቅ… ጭራቅ ነሽ የሆንሽ ኢሰብአዊና የሰው ፍጥረት ያልሆንሽ!” አልኩ።
ለዚህ ሽልማቴ በቀኝ በኩል ጭንቅላቴን በሀይል መመታት ነበር ከዚያ
ሁሉም ነገር ጨለመ:

ወደ እውነታው ስመለስ ሰውነቴ ሁሉ ታሟል። ጭንቅላቴ በህመም ተከፍሏል።አይኖቼን ስከፍት ክሪስ አጎንብሶ ቁስሎቼን መድኃኒት እየቀባና ፕላስተር
እየለጠፈ ነበር አይኖቹን የሞላው እምባ ሰውነቴ ላይ እየተንጠባጠበ ነበር።
መንትዮቹን እንዲጫወቱ ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ላካቸውና ባገኛቸው
የህክምና መገልገያዎች በመጠቀም የሚችለውን አደረገልኝ እኔም የእሱን
በደም የተጨማለቀ ጀርባ አከምኩ ልብስ መልበስ ቁስሉ እንዲባባስ
ስለሚያደርግ ሁለታችንም ልብስ አልለበስንም: በመጥረጊያው እንጨት
በጭካኔ የተመታሁበት በጣም በልዟል፡ ጭንቅላቴ ላይ ጥቁር እብጠት ነበር።
ክሪስ የአእምሮ መናጋት ሊያመጣ እንደሚችል ፈርቶ ነበር።
👍32😢2
ህክምናችን ሲያበቃ አንሶላው ውስጥ በጎናችን ተኝተን አይን ለአይን እየተያየን ነበር: በፍቅርና በቀስታ ጉንጬን ዳሰሰኝ፡ “የእኔ ጥፋት መሆኑን አውቄያለሁ መስኮቱ ጋ መቆም አልነበረብኝም፡ አንቺንም ልትጎዳሽ አይገባም ነበር” አለ
“ምንም አይደል፤ ፈጠነም ዘገየም ማድረጓ አይቀርም ነበር። ከመጀመሪያው
ቀን ጀምሮ በሆነ ምክንያት ልትቀጣን እቅድ ነበራት ያንን አለንጋ ሳትጠቀም
ይህንን ያህል ጊዜ መቆየቷም ተአምር ነው”

“እኔን እየመታችኝ ሳለ አንቺ ስትጮሂ ስለሰማሁ እኔ አልጮህኩም የጮህሽልኝ ለእኔ ነበር ካቲ… ጩኸትሽ ረዳኝ፡፡ እየተሰማኝ የነበረው የአንቺ ህመም እንጂ የእኔ አልነበረም::”

እርስ በርሳችን በጥንቃቄ ተያያዝን፡፡ እርቃን ሰውነታችን ተነካክቷል። ጡቶቼ ደረቱ ላይ ጥብቅ ብለዋል ከዚያ ስሜን በሹክሹክታ እየጠራ የፀጉር መያዣዬን ፈታ: ከዚያ ጭንቅላቴን በእጆቹ ይዞ ቀስ ብሎ ወደ ከንፈሩ አስጠጋው እርቃኔን ክንዶቹ ላይ ሆኜ ሲስመኝ እየተሰማኝ የነበረው ትክክል ያልሆነ እንግዳ ነገር ነበር። ወንድነቱ እየጠነከረ ሲመጣ እየተሰማኝ ስለነበር “ተው!
ይህንን ነው ያደረግን የሚመስላት:” ስል በፍርሀት አንሾካሾኩ ራቅ ከማለቱ በፊት በምሬት እየሳቀ ምንም ነገር እንደማላውቅ ነገረኝ፡ “ፍቅር መስራት ከመሳሳም የበለጠ ነገር አለው: እና እኛ ደግሞ መቼም ቢሆን ከመሳሳም የበለጠ ነገር አድርገን አናውቅም"

“ወደፊትም አናደርግም” አልኩ ድክም ባለ ድምፅ

በዚያ ምሽት አለንጋውንና የመጥረጊያ እንጨቱን ሳይሆን መሳሙን እያሰብኩ
ተኛሁ: በሁለታችንም ውስጥ ባለው የሚሽከረከር የስሜት ትኩሳት የተነሳ
በውስጤ የተኛ የሆነ ነገር ሲንቀሳቀስና ሲፈጥን ተሰማኝ።

ሁሉም ተረቶች በመሳም፣ በሰላምና በደስታ እንደሚፈፀሙትና ተረት ላይ
ያለችው ልዕልትም ልዑሉ መጥቶ እስኪስማት ድረስ እንደተኛችው አይነት
እኔንም ወደ ደስታ ፍፃሜ የሚያመጣኝ ክሪስ ሳይሆን አንድ ሌላ ልዑል መኖር አለበት.....

ይቀጥላል
👏19👍15👎1
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሰባት ፡ ፡ #ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ አንድ ዝናባማ ከሰዓት ሰማዩ ከብዶ ዝናቡ በጣም እየወረደ ነው: ክፍላችን ውስጥ ያሉ መብራቶች ሁሉ በርተዋል፡ ቲቪውም እንደተለመደው ተከፍቷል። ክሪስ የመስኮቱን ከባባድ መጋረጃዎች በሁለት እጆቹ ከፈት አድርጎ ይዞ በመቆም ከሩቅ ትንሽ የአሻንጉሊት ባቡር መስሎ ሁልጊዜ አስር ሠዓት ገደማ አሳዛኝ ፊሽካውን እያሰማ የሚያልፈውን…»
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...“የገዛ ልጁን ለሞት አሳልፎ ለመስጠት አገር ላገር የሚያሳድደው ከሆነ አረመኔ ነው የምለው " አለች እንባዋ በሽፋሽፍቷ እየተንቆረዘዘ " ከዚያ ዐይኗን ተጠንቅቃ አደራረቀችና ወደ ቁርስ ቤት ገባች።

የሔር ቤተሰብ እንግዳ በማይኖራቸው ጊዜ ራት የሚበሉት በዐሥር ሰዓት
ነበር " የራት ሰዓት ደረስና ሁሉም ከበታው ተቀመጡ ሚስዝ ሔርም ተሽሏት
ነበር ብራው ቀንና የውሎው ሽርጉድ የሕልሙን ሐሳብ አውርደውላት ልቧ ዕርፍ
ብሎላት ዋለ " ሚስተር
ሔር የጆይስን ወድቃ መሰበር ነገራቸው
ጠያቂም ሳይመጣ እነሱም ሳይወጡ ስለ ዋሎ አልሰሙም ነበር " ጆይስ ሁሉም ይወዳት ስለ ነበር ሚስዝ ሔር አዘነች።

የጠረጴዛው ልብስ ተነሥቶ ሚስተር ሔር ወይኑን እስኪጨርስ ጥቂት ተቀመጠና ተነሣ !ምክንያቱም የሥራ ጓደኛው ከነበረው ከጀስቲስ ሔርበርት ጋር ከራት
በኋላ ትምባሆ ለማጤስ ቀጠሮ ነበረው ።

“ ለሻይ ትመለሳለህ አባባ ? ” አለችው ባርባራ

“ አንቺ ደግሞ ብመጣ ባልመጣ ምን ጥልቅ አደረገሽ የኛ እመቤት ?

“አይ ምናልባት የምትመጣ ከሆነ እንድንጠብቅህ ብዬ ነው የጠየቅሁሀ እንጂ ነገሩስ ምንም አያገባኝም

“ ከሚስተር ሔርበርት ጋር አመሻለሁ ያልክ መስሎኝ ነበር ? ” አለች ሚስዝ
ሔር።

“ አዎን አመሻለሁና ! ብቻ ባርባራ የገዛ ምላሷ ሲንቀለቀል መስማት ደስ ይላታል ” አለ አባቷ
የጆይስ ነገር አሳዘነኝ" ወደ ኢስት ሊን በግሬ ተሻግሬ ልጠይቃት እፈልጋለሁ " " የባርባራ ልብ ቶሎ ቶሎ መታ መቸም እሷ ጊዜና ለውጥ የማይሽረው
እውነተኛና የማይጠፋ ፍቅር ይዟታል " ምናልባትም ከውስጧ ተቀብሮና ተዳፍኖ
ስለ ተቀመጠ ይሆናል ኃይልና ጥልቀት እየጨመረባት ሔደ።

“ በእግሬ ሔጄ አልሽ እማማ ? ” አለች ባርባራ "
“ አዎን አሁን አሁን ብዙ የእግር ጉዞ ልምምድ ስለ አደረግሁ የምችል ይመስለኛል » ደግሞም ዛሬ ምንም አልወጣንም " ግን በስንት ሰዓት እንሒድ ?”

"በአንድ ሰዓት ብንደርስ ራት በልተው የምናገኛቸው ይመስለኛል

"አዎን!” አለች ሁልጊዜ ሌላ ሰው ሲወስንላት ደስ የሚላት ሚስዝ ሔር !
ግን ከመነሣታችን በፊት ሻይ ባገኝ ደስ ይለኛል ”

ባርባራ እናቷን ሻይ አጠጥታ ስታበቃ ወደ ኢስት ሊን ጉዞ ጀመሩ ደስ የሚል ሞቃት ምሽት ነበር በራሪ ነፍሳት እየተቅበዘበዙ ሲያነበንቡ በመዋገድ ላይ የነበረውን በጋና ሞቃት አየሩን የሚሻሙ ይመስላል " ሚስዝ ሔር በመጀመሪያ
በጣም ደስ አላት ወደ መጨረሻው ስትቃረብ ግን ከአቅሟ በላይ መጓዟ ታወቃት" ከኢስት ሊን መኖፈሻ በር ስትደርስ የመዝጊያውን ብረት ይዛ ቀጥ አለች ".

በመምጣቴ ተሳስቼ ኑሯል ' ባርባራ ?”

ግድ የለም እማማ
በጣም ሙቀት ስለሆነ ጭምር ነው የደከመሽ ።
አሁን ከመናፈሻው አግዳሚ ወንበሮች ስንደርስ ትቀመጭና ከመግባታችን በፊት ዐረፍ ትያለሽ ።

ከጥላማ ዛፎች ሥር ከነበሩት መቀመጫዎች ደረሱና ሚስዝ ሔር ተቀመጠች።ሚስተር ካርላይል ሚስቱና እኅቱ ከእንግዳቸው ከፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር ሆነው ራት
እንደበሉ በመናፈሻው አበቦች መኻል ሲንሸራሸሩ ከሩቅ ለዩዋቸውና ወዲያው
ሒደው ከበቡቸው ልጆቹም ከመጠረሻሙ በቀር አብረው ነበሩ እመቤት ሳቤላ ሚስዝ ሔርን በደስታ ተቀበለቻት » ከዚያች ረቂቅና ሥቃይተኛ ሴትዮ ጋር በጣም ከፍተኛ መፈቃቀር ነበሪት "

ይኽውልህ አርኪባልድ እኔው በሽተኛ ሁኜ በሽተኛ ልጠይቅ ስመጣ ደከምኩና ከመንገድ ቆምኩ " የጆይስን ነገር ስምቸ በጣም አሳዘነችኝና መጣሁ
አለችው ሚስዝ ሔር "

አሁን ከመጡ እንግዲህ እዚህ 0ረፍ ብለው ያመሻሉ ሻይ ሲጠጡ ደግሞ
ያበረታዎታል ” አለች እመቤት ሳቤላ ።

ተባረኪ ልጄ ሻይ እንኳን ጠትተናል ”

ታዲያ ሁለተኛ የማትጠጡበት ምክንያት አለ ? እንዲያውም በጣም ስለደከሙ ለሁለት ሰዓት ያህል እኛ ዘንድ እስረኛ ሆነው መቆየትዎ አይቀርም ” አለች ሳቤላ

"እሱንስ እኔም እንዳልሺው ፈርቻለሁ "

“እነማን ናቸው ? ሲል ካፒቴን ሌቪሰን አሰበ ለራሱ እንግዶቹን ገና ከሩቅ
ሲያያቸው ። “ እንዴት የምታምር ልጅ ናት ! እስኪ ቀርቤ ልያቸው " '

ቀረበና ትውውቅ ተደረገ ካፒቴን ሌቪሰን ሚስዝ ሔርና ሚስ ሔር ትንሽ ከተነጋገሩ በኋላ ካፒቴን ሌቪሰን ከትንሹ ዊልያም ካርላይል ጋር አየተሯሯጠ
ይጫወት ጀመር ።

“ እናትሽ በጣም የታመሙ ይመስላሉ " አለ ሚስተር ካርላይል ለባርባራ ሁለቱም ከወይዘሮ ሳቤላና ከሚስዝ ኮርኒሊያ ካርላይል ጋር ስትነጋገር ከነበረችው
ከሚስዝ ሔር ጆሮ ርቀው ነበር '' በቅርቡ በጎ መሆን ጀምረው ነበር።"

“አየህ ሚስተር ካርላይል
እሷ ብዙውን ጊዜ በሽተኛ የምትመስለው እነዚያ አስጨናቂ ሕልሞች ሲታይዋት መሆኑን ታስታውሳለህ ” ዛሬ ጠዋትም በመጀመሪያ የነገረችኝ እነዚያን ሕልሞች ማየቷን ነበር ።

ሚስተር ካርላይል፡ ስለሕልሙ ምንም ሳይናገር “እንዲያው የሪቻርድ ወሬ
መጥፋት አይገርምሽም ?”

“ በጣም አሳስቦኛል " እናቴም በነገሩ ተጨንቃበታለች ዛሬ ጧትም ስለሱ ስትናገር ስትለፈልፍ ነበር ። እኔ ለራሴ በሕልምም አላምንም ። እናቴ መላልሳ ስላአየቻቸው ሕልሞች ግን ልዩ ስሜት እንዳሳደረብኝ ለመካድ አልችልም በተለይ ደግሞ ትናንት ሌሊት ያየችውን ሕልም በቀላሉ ላየው አልችልም ሚስተር
ካርላይል

"የትናንቱ ምን ነበር ? አለ ሚስተር ካርላይል "

እውነተኛዉ ወንጀለኛ ዌስት ሊን መጥቶ ታያት በሕልሟ ሰውየው ከኛ ቤት የገባ ይመሰላታል " እሷ እንደምትለው አንድ እንግዳ በጧት ከኛ ቤት ይመጣና
እኔና እሷ ሆነን ስለ ግድያው ስናነጋግረው እሱ ያልፈጸመ መሆኑን ክዶ በሪቻርድ
ሊያላክክበት ፈለገ " ወዲያው ደግሞ እሱ ተቀምጦበት ከነበረው ወንበር በስተኋላ ቁም ለነበረው ለኦትዌ ቤቴል አንድ ነር በጆሮው ሹክ አለ ይኸ ደግሞ ሌላ እንግዳ ነገር ነው አለችው ባርባራ ዐይኖቿን ወደ ሚስተር ካርላይል ፊት ቀና አድርጋ”

“በእንቆቅልሽ ነው የምትናገሪው ... ባርባራ ምኑ ነው እንግዳ ነገር ?

“ኦትዌይ ቤተል፡ሁልጊዜ በሕልሟ መታየቱ ራሱ አይገርምህም ? ሪቻርድ
በመጣ ጊዜ እስኪነግረን ድረስ ቤተል በግድያው አካባቢ መኖሩንም አናቅም
ነበር እሷ ግን ከዚያ በፊትም ታየው ነበር በእርግጥ ሪቻርድ ቤተል በነገሩ እንዳልነበረ ባት ተናግሯል እማማ ግን ይህ ሰው ከወንጀሉ ጋር አንዳች ግንኙነት እንዳለው ታምናለች "

ግን እናትሽ ገዳዩ ማነው ይላሉ ?

“ልታስታውሰው አልቻለችም ብቻ አየህ ... እኛ ስለ ካፒቴን ቶርን ያነሣንላት ነገር የለም ሰውየው በሁኔታው የትልቅ ስው ልጅ ይመስላል ትላለች "

“አንቺም ራስሽ በሕልም እያመንሽ መሰለኝ ከልብሽ ተከታትለሽዋል አላት

“ እኔን የሚያሳስበኝ የሕልሙ ጉዳይ ሳይሆን የወንድሜ ነገር ነው " ይኽን
ምስጢር መግለጥ ቢቻለኝ ድካምንና መከራን ሳልፈራ በባዶ እግሬ እስከ ዓለም
ዳርቻ በተጓዝኩ ቶርንን ወደ ዌስት ሊን ተመልሶ ለመምጣት ቢያበቃው እንደ
ባለፈው በዋዛ አልለቀውም እስከ መጨረሻ እተናነቀዋለሁ " አለችው "

“ ቶርን እንኳን ዳግመኛ ወደ ዌስት ሊን ለመምጣት የሚጓጓ አይመስልም"
ምንያቱም ባርባራ ክንዱን ቶሎ ያዝ አድርጋ ምልክት ስትሰጠው ዝም አለ ሁለቱ ስለዚህ ጉዳይ እየተነጋገሩ መናፈሻውን አቋርጠው በልዩ ልዩ ቅርጽ ወደ ተጌጠው አካባቢ ሲሔዱ ዙሪያውን በትልልቅ ቋጥኞች ከተከበበ ጠባብ የእግር መንገድ ደረሱ
ልክ ሚስተር ካርላይልና ባርባራ ከቆሙበት ቦታ ላይ ከነበረው ትልቅ ድንጋይ ላይ
ፍራንሲዝ ሌቪሰን ጀርባውን ለነሱ ሰጥቶ ተቀምጦ ነበር
👍19🥰2
ሲመጡ ዳናቸውን ይስማም አይስማም አይታወቅም። እሱ ግን ዞር ብሎ አላያቸውም » እነሱም አረማመዳቸውን ጨመር በማድረግ ሴቶቹ ወደ ነበሩበት ተመለሱ።

“ስንናገረው የነበረውን ሰምቶን ይሆን ? አለች ባርባራ ቀስ ብላ "

“ሐሳቡ በሌላ ነገር ካልተጠመደ በቀር ሳይሰማ የሚቀር አይመስለኝም
ግን ልብ ብሎ ወደኛ ላያዳምጥ ይችላል ደግሞ ቢሰማም ምንም አይደለም

“ እኔ ገዳዩ ካፒቴን ቆርን መሆኑን ስናገር ነበር ።

“ ቢሆንም እኮ ስለ ሪቻርድ ወይም ስለ እንቅስቃሴዎች አልተናገርሽም ሌቪሳን ለዚህ አካባቢ እንግዳ ሰው ስለሆነ ስለ ጉዳዬ የሚያውቀው ነገር የለም
ቶርን የሚለውስ ስም ሲነሣ ቢሰማ ወይም የምንነጋገርበት ጕዳይ ስለምን እንደሆነ ቢያውቀውም እንኳን ለሱ ምንም ስሜት ስለማያሳድርበት በአንድ ጆሮው ሰምቶ በሌላው ያፈሰዋል አታስቢ
ባርባራ "

ይኸን ነገር በሚነግራት ጊዜ ልስልስ ልዝብ ብሎ ተመለከታት » ደግሞ ከነሳቤላ ሊጨመሩ ሊቀላቀሉ ትንሽ ስለ ቀራቸው ሳቤላ አመለካከቱን ልብ ብላ አየችው " መጠርጠርና መቅናት እንደማይኖርባት ባሏ ከዚ ቀደም ቢያረጋግጥላትም
ገና ከነሱ ተነጥለው ሲሔዱ ጀምራ በይኗ ተከተለቻቸው " ከዐይኗ የጠፉት ላጭር
ጊዜ ቢሆንም ወደ ሰዋራ ቦታ ዞር በማለት ተሰርቀው ለመጫወት ስለ ፈለጉ ነው ብላ ደመደመች " ደግሞ እንደ አጋጣሚ ያንለት ማታ ባርባራ በጣም የሚያምር ልብስ ለብሳ ከደማቅ ዐይኖቿ የደስ ደስ ካለው የፊቷ ቅርጽና የቀለሟ ማማር ጋር ለተመለከታት የምታጓጓ ሆና አምሮባት ነበር እሷና ሚስተር ካርላይል እየተነጋገሩ ሲመጡ በጣም የሚያምሩት የጸጉሯን ማፈኛ ሲባጐዎች ፈትታቸው ይንዘላዘሉ ስለ ነበር ይበልጥ ሐሳብ ውስጥ የገባች መስላ ረጋ ብላ ጫፎቻቸውን ይዛ በትካዜ
እያፍተለተለች ትጫወት ነበር።

ባርባራ..."ዛሬ እንዴት ሆነን ነው ከቤታችን የምንደርሰው ? አለቻት ሚስስ ሔር።በእግሬ መድረሴን እጠራጠራለሁ "ወይ ምነውያን ቤንጃሚንን
ሰረገላውን እንዲያመጣልን ነግሬው በሆኖ ኖሮ።

“ እኔ ልልክበት እችላለሁ አለ ሚስተር ካርላይል "

ግን እናንተን ከነ አሽከሮቻችሁ በማስቸገሬ አዝናለሁ " አለችው "

“ እንዴ ! እንዴ ! በጣም ነው ያስቸገሩኝ ... ሚስዝ ሔር ” አለ ሚስተር ካርላይል እየቀለደ። “አዩ ሚስዝ ሔር .... እርስዎ ሁልጊዜም የራስዎን ትተው ለሰው እንዳዘኑ ነው'

ሚስተር ካርላይል .... አንማ መቸም ማንንም ሳታስቀይም የሁሉን ችግር እንደ ፈታህ ነው ኑሮህ ሰማሽ እመቤት ሳቤላ ... ልጅነት ቢኖረኝ ኖሮ በደጉ ባልሽ እቀናብሽ ነበር እንደሱ ያሉ ባሎች በቁጥር ናቸው ብዙ የሉም።

ሳቤላም በልቧ ልጅነት ያላት ሌላይቱ ልትቀናባት እንደምትችል እያሰበች
ፊቷ ልውጥ አለ ቀላ ሚስተር ካርላይል እጁን ወደ ሚስዝ ሔር ዘርግቶ “እስካሁን ከዚህ ተቀምጠው ያረፉት በቂ ስለሆነ ይነሡና ቀስ ብለው ወደ ቤት ይግቡ ከሶፋው ላይ ዐረፍ ሲሉ ይመችዎታል ይነሡ እኔ እደግፍዎታለሁ " አላት "

ተያይዘው ወደ ቤት ሲያመሩ ሚስዝ ሔር አንድ መኮንን ባውራው መንገድ ሲያልፍ አየችና ወደ ልጅዋ ምልስ ብላ “ ባርባራ . . . ነይማ ሩጭ ያውልሽ ቶም
ሔርበርት ወደኛ ቤት አቅጣጫ እየሔደ ነው” ስለዚህ በደጅ ሲያልፍ ጠርቶ ሠረገላ እንዲያመጡልን እንዲነግራቸው ንገሪው " ቶሎ በይ በግማሽ ደቂቃ ትደርሽበታለሽ "

ሚስር ካርላይል አሽከር ይላካል ብሎ ከመሔድ ሊያስቀራት ከመቻሉ በፊት
በአንድ ጊዜ ከበሩ ደረሰች " ሔርበርትም ስትሮጥ ከሩቅ አያትና ቁሞ ጠበቃት “

“በኛ ቤት በኩል ነው የምታልፍ ? አለችው ባርባራ እንደደረሰች እሷ ቶም ሔርበርትን ስታነጋግር ኦትዌይ ቤቴል ዶግሞ ጥቂት ራቅ ብሎ ከመንገዱ ትይዩ ፈንጠር ብሎ ቆሞ አየችው "

"አዎን ምነው ? አላት " ቶም ሔርበርት በተፈጥሮው ነገረ ግልጽ ቢሆንም በልማዱ ችኩል ስለ ነበር በጠባዩ አምብዛም በደግ አይነሣም ነበር "

እናቴ እዚህ መጥታለች አሁን በእግሯ መመለስ ስለማይሆንላት በኛ በር
ስታልፍ ቤንጃሚንን ጠርተህ ሠረገላ ይዞ እንዲመጣ እንድትነግርልን እናቴ ንገሪው ብላኝ ነው " አለችው "

“ ደግ እሺ ጠርቸ እነግረዋለሁ በስንት ሰዓት ይምጣ ?

አባባ ቤት ሳይገባ እንድንደርስ ባርባራ ስለ ሰዓቱ አልተነገራትም ነበርና ዝም ብላ በአራት ስዓት በለው አለችው "

ለዚያስ ትደርሳችሁ " አላት ቶም ሔርበርት " አባትሽ ኣባቴና ሌሎችም ሁለት ሦስት ስዎች ሆነው ጢሱን እንደደመና ሲያትጐለጉሉት ለመተያየት እንኳን ያቅታል " ደግሞ ራት ከበሉ በኋላ እንደሚመለሱበት እርግጠኛ ነኝ " እኔ
የምልሽ ግን ባርባራ
ልጃገረዶቻችን የዛሬ ሳምንት ወይም ሁለት ሳምንት ሽርሽር ለመሔድ ያስባሎ ወንድሜ ጃክም መጥቶ ከቤት ነው ሰምተሽ የለ?እና አንቺስ ሽርሽር ለመሔድ ትፈልጊለሽ ?

“ ኧረ ... መጣ ? አለች ባርባራ ድንግጥ ብላ "

ይኸውልሽ ትናንት ደብዳቤው ደርሶን እሱ ዛሬ ገባ " አሁን ልጃገረዶች የሽርሽሩ ለት በደንብ ካልተጫወቱ በዕረፍት ጊዜ ሁለተኛ እዚህ እንደማይመጣ ይናገራል " ስለዚህ እንደ ምንም ብለሽ የሆነ ጫወታ ይዘሽ እንድትመጭ ደኅና እደሪ ”
አላት "

ከነሱ ተሰነባብታ ስትሔድ ሌላ የእግር ኮቴ ሰማችና ዙራ ብታይ ሁለት መኮንኖች ክንድ ለክንድ ተያይዘው አጠገቧ ደርሰው አየቻቸው አንደኛው ሻለቃ ሔርበርት የሚባለው ጃክ መሆኑን ለየችው "

“ ከተለያየን ጥቂት ዓመታት ዐለፉ ቢሆንም ያን ጊዜ የትንሽ ልጃገረድ ወዘና የነበራትንና ዛሬ ደግሞ ደርባባ ወጣት እመቤት የሆነችውን የባርባራን ፊት
አልረሳሁትም ” አላት ።

“ መምጣትህን አሁን ወንድምህ ሲነግረኝ ነበር » እንዲያውም በመጪው
ሳምንት ይመችሽ እንደሆነ ሽርሽር '' ብላ ስትጀምር አንድ ከዚህ ቀደም ያየችው ቢሆንም ማን መሆኑን ግን የረሳችው ፊት አየችና ድርቅ አለች መልኳ ተለዋወጠ " ሻለቃ ሔርበርት እየተናገረ እሷ ፈዛ ትመለከተው ጀመር እሱን ቸል ያለችው ከአዲሱ ሰውዬ ጋር መተዋወቅ ፈልጋ መሰለውና፡ “ ካፒቴን ቶርን ይባላል ሚስ ሔር ” አላት » ባርባራ ነፍሷ ምልስ አለ እኔ እኮ የት እንደማውቀው ቸግሮኝ ነበር
ብላ ተንተባተበች "

“ አዎን አንድ ጊዜ ለአምስት ቀን ያህል ዌስት ሊን መጥቼ ነበር “ አላት ካፒቴን ቶርን "

“ አሁንስ ብዙ ትቆያለህ ?”

“ በርግጥ የብዙ ሳምንት ፈቃድ አለኝ " ምን ያህል እንደምቆይ ግን አሁን
ለመናገር አልችልም "

ከዚያ በኋላ ከነሱ ተለየችና ተመልሳ እናቷ ሚስ ካርይልና ሚስተር ካርላይል ቁመው ከነበሩበት ሒዳ ተቀላቀለች ሳቤላን አላየቻትም እናቷ ጆይስን
ልታይ ስትገባ እሷ ሚስተር ካርላይልን ይዛው ገለል አለችና : “ አርኪባልድ
ለብቻህ ላነጋግርህ እፈልጋለሁ '' አለችው ሳቤላ እንዳጋጣሚ ወዲያው መጣችና ክንዱን ይዛ ስትወስደው ስታነጋግረውና ፊቷ ደም ሲመስል ጭምር ተመልክታ
ነበር " በአንዱ የሳሎን መስኮት ዘልቃ በጓሮው ሲጓዙ ትንሿ ሳቤላንም ወደ ቤት እንድትገባ ሲመልሳላት ሁሉ አየች እመቤት ሳቤላ ካገባችበት ጊዜ ጀምሮ እንደ
ዚያች ዕለት ምሽት እርር ብላ ቀንታ አታውቅም።

“ እንደዚህ አጣድፌ ወደዚህ ስላመጣሁህ አትቀየመኝ " "
ምን የምትገልጪው ምስጢር አለሽ ? አላት ሚስተር ካርላይል ስለ እማማ ሕልም ስንነጋገር ትክክለኛው ገዳይ ዌስት ሊን አለ የሚል እምነት እንዳደረባት አልነገርኩህም ? ነገሩ የማይስል ቢሆንም ከዚህ
እምነቷ ፍንክች ለማለት አልቻለችም እምልህ . .ልክ አሁን

እንዴ ባርባራ ምንድነው ነገሩ ? አላት ሚስተር ካርላይል ሲቃ ይዟት
ስትቃትት አይቷት።

“ አሁን አየሁት"
👍54
አየሁት ? አላት ሚስተር ካርላይል በጤናዋ መሆኗን እየተጠራጠረ።

“ ያ ቶርን ወደ ዌስት ሊን ይመለስ እንጂ እሱን ለማጋለጥ የማላደርገው
ጥረት አይኖረኝም ብዬህ ነበር " ይኸውልሀ አሁን ከቶም ሔርበርት ከሻለቃ ሔር በርትና ከቤተል ጋር አገኘሁት ታዲያ አሁን በውኔ ይሁን በሕልሜ ማወቅ ቢሳነኝ ምኑ ያስደንቃል ? . . . የጥቂት ሳምንቶች ዕረፍት ስላላቸው ነው የመጡት"

“ ይኸ በውነቱ ልዩ የሆነ አጋጣሚ ነው ” አለ ሚስተር ካርላይል።

"ወንጀለኛው ቶርን መሆኑን የሚያሳምነኝ የእማማ ሕልም ነው" እሷ የሆሊጆን
ገዳይ ዌስት ሊን ገብቷል” ማለቷና የሱ መምጣት ገጠመ "

በዛፎች ጥላ ሥር በሚወስደው መንድ እያወሩ ሲሔዱ አንድ መጠምዘዣ
ላይ ደረሱና ፍራንሲዝ ሌቪሰንን አገኙት አሁንም ባርባራ ይነጋገሩት የነበረውን ሰምቶ እንደሆነ በማለት ሐሳብ ያዛት " ከዚያ ወዲህ ሰውዬውን ከልቧ ትጠላው ጀመር ወደነሱ ቀረበና አብሯቸው ሊመለስ ሲያስብ እለፍ መጣሁ ካፒቴን ሌቨሰን ” አለው ሚስተር ካርላይ።

" ይህን ካፒቴን ሌቪሰን ትወደዋለህ ? ” አለችው ባርባራ ከማይስማበት
ርቀት መድረሱን አይታ።

“እወደዋለሁ ለማለት አልችልም ግን በመተዋቅም የማይሻሻል ሰው ነው''

"እኔ ደግሞ የምንለውን ለመስማት የሚከታተለን ይመስለኛል " "

አዬ ለዚህ ብሎ ይደለም .... ባርባራ " ምን ይጠቅመዋል ?

ባርባራ በዚህ ጉዳይ አልተከራከረችም " ከልቧ አንዱን ማዕዘን ይዞት ወደነበረው ጉዳይ ተመለሰችና " አሁን የቶርንን ነገር ምን እናድርግ ? '' አለችው።

"አስቸጋሪ ነገር እኮ ነው አሁን ቀጥታ ሒዶ የሆሊጆን ገዳይ ነወ ብሎ መክሰስ አይቻልም ሪቻርድ ያለው ሰውዬ ለመሆኑ እንኳን እርግጠኞች አይደለንም"

“ እርኪባልድ ... የሱ ዛሬ ከዚህ ቦታ መገኘት ከእማማ ሕልም ጋር ሊስማማ
እያየህ እንዴት ትጠራጠራለህ ከዚህ የበለጠ ማረጋጫ ምን ፈልገህ ነው ?

“እንደሱ አይደለም ” አላት ሚስተር ካርላይል ፈገግ ብሎ እሁን ማድረግ ያለብን ሰውየው እሱ መሆኑን በጥንቃቄ ለማረጋገጥ መሞከር ነው።

"ይኸንስ ቢሆን ካንተ ሌላ ማን ሊያደርገው ይችላል ? ያ ሁሉ ፉከራዬ ከንቱ ቀረ ማለት ነው? ወደ ዌስት ሊን ተመልሶ ለመምጣት ቢበቃልኝ አልለቀውም እያልኩ ስፎክርበት እንዳልነበር ሁሉ አሁን ሲመጣ ግን ምንም ማድረግ አልቻልኩም
ማለት ነዉ ?”

በጕዳዩ ከዚህ በላይ የሚነጋግሩበት ስለ አልነበራቸው ወደ ቤት ማምራት ጀመሩ ካፒቴን ሌቪሰን ከነሱ ቀደም ብሎ ገባና ሳቤላን በመስኮት ቁማ አግኛት ተጨባጭ ባልሆነው በደሏ እየተከዘች ወደ ውጭ ትመከት ነበር "

"ይህች ሚስ ሔር ማናት ? ” ብሎ ጠየቃት “ በሁለቱ መኻል ከፍተኛ መግባባት ያላቸው ይመስላል ዛሬ ከመሸ እንኳን በምስጢር ሲነጋገሩ ሁለት ጊዜ አየኋቸው።

" ወደኔ ነው የምትናገረው . ጌታዬ ? ” አለችው ቆጣ ብላ "

እሷ ለነገሩ ብትጠይቀውም የተናገረውን በትክክል እንደ ሰማችው ስለ ዐወቀ
እኔ አንቺን ለማስከፋት አይደለም ስለ ሚስተር ካርይልና ሚስ ሔር ግንኙነት ምን እንደሆነ ለማወቅ ነው የተናገርኩት ” አላት.....

💫ይቀጥላል💫
👍20
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


በመጨሻ እኖታችን

እኔና ክሪስ በግርፋቱ ቀን በመሀከላችን ስለተፈጠረው ነገር በፍፁም አላወራንም
በአብዛኛው አተኩሮ ሲመለከተኝ እይዘዋለሁ፧ ግን አይኖቼ አይኖቹን ሲመለከቱ አይኖቹን ያሸሻል እኔም ሳየው ከያዘኝ አይኖቼን ወዲያው እመልሳለሁ።

እኔም እሱም በየቀ እያደግን ነው፡ ጡቶቼ ሙሉ ሆነዋል። ዳሌዬ ሰፋ ብሎ ወገቤ ቀጠን ብሏል ግንባሬ አካባቢ የተቆረጠው ፀጉሬ አድጎ ደስ በሚል አይነት ተጠቅልሏል። ክሪስ ደግሞ ትከሻው ሰፍቷል። ደረቱና ክንዶቹ የበለጠ ወንዳወንድ ሆነዋል አንድ ጊዜ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ
ሆኖ የተገረመ በሚመስል አይነት ወንድነቱን ወደታች ሲመለከትና ሲለካው
ይዤዋለሁ። ርዝመቱ ምን ጥቅም እንዳለው ለማወቅ ስለጓጓሁ “ለምን?” ብዬ
ስጠይቀው አንድ ጊዜ አባታችንን እርቃኑን ሆኖ እንዳየውና አሁን ያየው
ነገር መጠኑ በቂ እንደማይመስል ነገረኝና ፊቱን አዞረ። ልክ እኔ እናታችን የምትለብሰው የጡት መያዣ መጠን ስንት እንደሆነ ማወቅ እንደምፈልገው ማለት ነበር። “እንደገና እንደዚያ እንዳታደርግ።" አልኩት። ኮሪ ያለው የወንድ አካል ትንሽ ስለሆነ ክሪስን ተመልክቶ ልክ እንደ ክሪስ መጠኑ ትንሽ ነው
የሚል ስሜት ቢሰማውስ?

ድንገት የመማሪያ ክፍሉን ወንበሮች ማፅዳቴን አቁሜ ወደ ኬሪና ኮሪ ተመለከትኩ፡ አምላኬ! በጣም መቀራረብ እንዴት እይታን እንደሚያደበዝዝ!
ሁለት አመት ከአራት ወር የተቆለፈብን ቢሆንም መንትዮቹ እዚህ የመጣን
ጊዜ ከነበሩት አልተለወጡም ጭንቅላታቸው ተለቅ ብሎ ስለሚታይ የአይኖቻቸው መጠን ያነሰ ይመስላል፡ ሰውነታቸው ጭንቅላታቸውን መሸከም
የሚችል አይመስልም ፍዝዝ ብለው ወደ መስኮቱ ያስጠጋነው አሮጌ ፍራሽ
ላይ ተቀምጠዋል እስኪተኙ ጠበቅኩና ቀስ ብዬ ለክሪስ “ተመልከታቸው ምንም አላደጉም: ጭንቅላታቸው ብቻ ነው ትልቅ የሆነው:” አልኩት።

በከባዱ ተነፈሰ፤ ከዚያ አይኖቹን አጥብቦ ወደ መንትዮቹ ቀረበና የገረጣውን ቆዳቸውን ለመንካት ዝቅ አለ፡ “ውጪ ጣሪያው ላይ ከእኛ ጋር ወጥተው ፀሀይና ንፁህ አየር ቢነካቸው ጥሩ ይሆን ነበር ካቲ፤ ምንም ያህል ቢጮሁና ቢንፈራገጡ ወደ ውጪ እንዲወጡ ማስገደድ አለብን” አለኝ።

እንቅልፍ ላይ እንዳሉ ተሸክመን ወደ ጣሪያው ብንወስዳቸውና ፀሀይ ላይ ሆነው እኛ እንዳቀፍናቸው ቢነቁ ደህንነት ይሰማቸዋል ብለን አሰብንና ክሪ ኮሪን በጥንቃቄ ሲያነሳ፣ እኔም ኬሪን ብድግ አደረግኳት ወደ ተከፈተው የጣሪያው ስር ክፍል መስኮት ቀረብን፡ የጣሪያውን የኋላ ክፍል መጠቀም የተሻለ ነው: ቀኑ ሀሙስ ስለሆነና ሰራተኞቹ ቀኑን ሙሉ ከተማ ስለሚውሉ ጣሪያው ላይ ወጥተን የምንዝናናበት ብቸኛው ቀን ነው።

ክሪስ ቀስ ብሎ ኮሪን እንደያዘ መስኮቱን አልፎ ሲወጣ የበጋ ፀሀይ ኮሪን
ከእንቅልፉ አነቃው ዙሪያውን ሲመለከት እኔም ኬሪን ተሸክሜ ጣሪያው ላይ
ልወጣ መሆኑን ሲመለከት ጮኸ! ኬሪ ከእንቅልፏ ባነነች። ክሪስ ኮሪን ይዞ
ጣሪያው ጫፍ ላይ ሆኖ እኔ ደግሞ የት እየወሰድኳት እንደሆነ ስትመለከት
ጩኸቷን አቀለጠችው።

ክሪስ ጣሪያው ጫፍ ላይ እንዳለ “አምጫት! ለራሳቸው ነው ይህንን ማድረግ አለብን:” አለኝ፡ መጮህ ብቻ አይደለም እየተራገጡና እየመቱን ነበር።ኬሪ ክንዴ ላይ ስትነክሰኝ እኔም ጮህኩ። በጣም ትንንሾች ቢሆኑም አደጋ ላይ እንደሆኑ በማሰባቸው በጣም በጥንካሬ እየታገሉን ነበር። ፊቴን አዙሬ ወደ መማሪያ ክፍሉ መስኮት አቀናሁና እየተንቀጠቀጥኩ ኬሪን በእግሮቿ አቆምኳት እኔም አየር አጥሮኝ እያለከለክኩ ወንበሩን ተደግፌ በሰላም ወደ ውስጥ እንድመልሳት ስላደረገኝ እግዚአብሔርን አመሰገንኩ። ክሪስም ኮሪን
እህቱ አጠገብ መለሰው፡ ሙከራችን ጥቅም አልነበረውም እነሱን ጣሪያው ላይ እንዲወጡ ማስገደድ የአራታችንንም ህይወት አደጋ ላይ መጣል ነው።

በጣም ስለተናደዱብን በመጀመሪያ ቀን ወደዚህ ክፍል ስንመጣ ቁመታቸውን
ወደ ለካንበት ግድግዳ ምልክት ስንወስዳቸው ሁሉ እየታገሉን ነበር ክሪስ
ሁለቱንም ቦታው ላይ አድርጎ ሲይዝልኝ እኔ ምን ያህል እንዳደጉ ለማንበብ
ሞከርኩ፡

ሊሆን መቻሉን ባለማመን በድንጋጤ አፈጠጥኩ: በዚህ ሁሉ ጊዜ የጨመሩት
ሁለት ኢንች ብቻ ነው? ሁለት ኢንች! እኔና ክሪስ ከአምስት እስከ ሰባት
አመት እድሜያችን መሀከል ብዙ በጣም ብዙ ነበር ያደግነው ሲወለዱም
ክብደታቸው ትንሽ የነበረ ቢሆንም የተሻለ ማደግ ነበረባቸው።

የደነገጠና የፈራ ገፅታዬን ማየት እንዳይችሉ በእጆቼ ፊቴን መሸፈን ነበረብኝ፡፡
ከዚያ ሳግ ጉሮሮዬን ሲይዘኝ ጀርባዬን ሰጥቻቸው ፊቴን አዞርኩ።

“አሁን እንዲሄዱ መልቀቅ ትችላለህ” አልኩት ዞር ብዬ ሳያቸው ልክ እንደ ሁለት አይጦች በደረጃው እየተንደረደሩ ወደ ተወዳጁ ቴሌቪዥን ሮጡ።

ክሪስ hጀርባዬ ቆሞ እየጠበቀ ነው: “ምን ያህል ቁመት ጨምረዋል?” አለኝ:

ፈጠን ብዬ እምባዬን በእጄ ጠራርጌ ወደ እሱ ዞርኩ ከዚያ አይኖቹን እየተመለከትኩ ሁለት ኢንች እንደሆነ ነገርኩት᎓ አይኖቼ ውስጥ ህመም ነበር።
እሱም ያየው ያንን ነበር:

ጠደ እኔ ተጠግቶ አቀፈኝና ጭንቅላቴን ወደ ደረቱ አስጠጋኝ፡ አለቀስኩ በጣም
አለቀስኩ ይህንን በማድረጓ እናታችንን ጠላኋት የእውነት ጠላኋት! ልጆች እንደ አትክልት እንደሆኑና ለማደግ የፀሀይ ብርሃን እንደሚያስፈልጋቸው
ታውቃለች በወንድሜ እቅፍ ውስጥ እንዳለሁ ተንቀጠቀጥኩ። ነፃ ስንሆን
እንደገና ቆንጆ እንደሚሆኑ ራሴን ለማሳመን እየሞከርኩ ነበር። ቆንጆ ይሆናሉ፤ ያጡትን አመታት ያካክሳሉ፡ ልክ የፀሀይ ብርሃን ማግኘት ሲጀምሩ እንደ አትክልት ያድጋሉ። አዎ ያድጋሉ፤ ጎንጮቻቸው በጣም የጎደጎዱት፣አይኖቻቸው ወደ ውስጥ የገቡት ረጅም ጊዜ ቤት ውስጥ ስለሚቀመጡ ነው እና ያ ሁሉ ሊስተካከል ይችላል፤ አይችልም?

ከዚያ በሻካራ ድምፅ “ገንዘብ ነው አለምን የሚያሽከረክራት ወይስ ፍቅር? ለመንትዮቹ በቂ ፍቅር ሰጥተናቸዋል እናም ስድስት፣ ሰባት፣ ምናልባትም ስምንት ኢንች ቁመት መጨመር ነበረባቸው: ሁለት ብቻ አልነበረም" አልኩ፡

እኔና ክሪስ ወደዛ ወደ ደብዛዛው እስር ቤታችን ተመለስንና እንደ ሁልጊዜው
እጆቻቸውን እንዲታጠቡ ላክናቸው የምግብ ጠረጴዛችን ጋ በፀጥታ ተቀምጠን ሳንድዊቻችንን እየበላንና ወተት እየጠጣን ቲቪ ስንመለከት የክፍላችን በር ተከፈተ: መዞር አልፈለኩም ነበር። ግን ዞርኩ:

እናታችን እየሳቀች ወደ ክፍሉ ገባች የሚያምር ልብስ ለብሳለች የለበሰችው
ጃኬት አንገቱና እጆቹ ላይ ፀጉር አለው: “ውዶቼ!” አለች በመጓጓት አይነት
ሰላምታ: ከዚያ አንዳችንም ሰላም ልንላት ባለመነሳታችን እያመነታችና እርግጠኛ ባልሆነ ስሜት “መጥቻለሁ! ስታዩኝ ደስ አላላችሁም? ስላየኋችሁ እንዴት ደስ እንዳለኝ አታውቁም በጣም ስናፍቃችሁ፣ ስለናንተ ሳስብና ሳልም ነበር፡ እና በጣም በጥንቃቄ የመረጥኳቸው የሚያምሩ ስጦታዎች አምጥቼላችኋለሁ: እስክታዩዋቸው ጠብቁ፡፡ ረጅም ጊዜ የጠፋሁበትን ማካካስ እፈልጋለሁ፡ ለምን እንደምሄድ ልነግራችሁ ፈልጌ ነበር፣ እውነቴን ነው፣
ግን በጣም የተወሳሰበ ነው: ለምን ያህል ጊዜ እንደምቆይ አላወቅኩም
ነበር። ናፍቃችሁኛል! በደንብ ተይዛችኋል አይደል? አልተሰቃያችሁም
ተሰቃይታችኋል እንዴ?”

ተሰቃይታችኋል? ናፍቃችሁኛል? እሷ ማናት? አፍጥጬ እያየኋትና አራት
የተደበቁ ልጆች የሌሎችን ህይወት እንዴት አስቸጋሪ እንደሚያደርጉ እየሰማሁ
መጥፎ ሀሳቦች መጡብኝ፡ ሁለተኛ በጭራሽ እንዳትጠጋኝ ላደርጋት ፈለግኩ።ከዚያ አቅማማሁ በተስፋ ተሞልቼ እንደገና ልወዳትና ላምናትም ፈለግኩ
👍42👎2
መጀመሪያ ክሪስ ተነሳና “በመምጣትሽ ደስ ብሎናል! አዎ ናፍቀሽናል ግን ምንም አይነት የተወሳሰቡ ምክንያቶች ቢኖሩሽ፣ ሄደሽ ይህንን ያህል መቆየትሽ
ስህተት ነው" አለ፡

“ክሪስቶፈር” አለች አይኖቿ በመገረም ፈጠጡ። “አንተ አትመስልም” አይኖቿ
ከእሱ ወደ እኔ ከዚያ ወደ መንትዮቹ ተመላለሱ። ደስታዋ ቀዝቀዝ አለ፡
“ክሪስቶፈር የተበላሸ ነገር አለ?”

“የተበላሸ?” ሲል ደግሞ ተናገረ፡ “እማዬ አንድ ክፍል ውስጥ ስለመኖር
ምን ትክክል ነገር አለ? ራስህን አትመስልም አልሽ ... በደንብ ተመልከችኝ።አሁንም ትንሽ ልጅ መስዬ ነው የምታይሽ? ካቲንም ተመልከቻት እሷስ ትንሽ ልጅ ትመስልሻለች? መንትዮቹን ተመልከቻቸው ምን ያህል እንደረዘሙ
በደንብ አስተውይ፡ ከዚያ አይኖችሽን እንደገና ወደ እኔ መልሺና እኔና ካቲ
አሁንም ትንንሽ ልጆች እንደሆንና የትልልቅ ሰዎች ጉዳይ እንደማይገባን
ንገሪን፡ አንቺ ሄደሽ ጥሩ ጊዜያት ስታሳልፊ እኛም ዝም ብለን እጃችንን አጣጥፈን አልተቀመጥንም: እኔና ካቲ መፃህፍቶችን በማንበብ በቢሊየን
የሚቆጠሩ ህይወቶች ኖረናል ... ህያውነት እንዲሰማን የሞከርንበት አንዱ ዘዴ ያ ነው::"

እናታችን ልታቋርጠው ፈለገች። ክሪስ ግን ትንሹን ድምፅዋን በድምፁ ዝም
አሰኘና ያመጣቻቸውን ስጦታዎች አየት አደረጋቸው: “እና ሁልጊዜ ስህተት እንደሰራሽ ሲገባሽ እንደምታደርጊው የሰላም መስዋዕት ይዘሽ መጣሽ? እንዴት አሁንም እነዚህ የማይረቡ ስጦታዎችሽ ያጣነውንና ያለማቋረጥ እያጣነው ያለነውን ነገሮች ሁሉ ሊያካክስ ይችላል ብለሽ ታስቢያለሽ? እውነት ነው በአንድ ወቅት በታሰርንበት ክፍል ውስጥ በምታመጭልን መጫወቻዎች፣
አሻንጉሊቶችና ልብሶች እንደሰት ነበር፡ አሁን ግን አድገናል ስጦታ ብቻ
አይበቃም:"

“ክሪስቶፈር እባክህ…” ለመነችው፡ ከዚያ በማይመች አይነት ወደ መንትዮቹ አየት አድርጋ ወዲያው አይኖቿን መለሰች፡ “እባክህ ልክ እኔን መውደድ እንዳቆምክ አይነት አድርገህ አትናገር፡ ያንን መቋቋም አልችልም”

“እወድሻለሁ፧ አንቺን መውደዴን እንድቀጥል ራሴን አስገድደዋለሁ: ምንም ነገር ብታደርጊ ልወድሽ ይገባል: ሁላችንም ልንወድሽ ግድ ነው፧ እናም
እናምንብሻለን…ፍላጎታችንን ለማሟላት እየሞከርሽ መሆኑን እናስባለን፡ ግን
እስቲ ተመልከቺን፣ በደንብ ተመልከቺን፡ ካቲም እኔም እያደረግሽብን ያለውን
ነገር ላለማየት አይኖችሽን እንደጨፈንሽ ይሰማናል፡ እየሳቅሽ ትመጫለሽ፣
ጆሯችንን በወደፊቱ ብሩህ ተስፋ ትሞያለሽ፤ ግን አንድም ጠብ ያለ ነገር
የለም: ከረጅም ጊዜ በፊት በመጀመሪያ ስለዚህ ቤትና ስለ ወላጆችሽ ስትነግሪን
እዚህ ክፍል ውስጥ የሚዘጋብን ለአንድ ምሽት ብቻ ነው ብለሽ ነበር። ከዚያ
ወደ ጥቂት ቀናት ለወጥሽው ከዚያ ደግሞ ሌላ የተወሰኑ ሳምንታት…..

“hዚያ ሌሎች ጥቂት ወራት. ሽማግሌው እስኪሞት ስንጠብቅ ከሁለት አመት በላይ አለፈ ዶክተሮች ከመቃብር አፋፍ እሱን የሚመልሱበት መንገድ ስላላቸው ላይሞትም ይችላል። እዚህ ክፍል መኖር ጤናችንን እያሻሻለው አይደለም ይህንን ማየት አልቻልሽም?” እየጮኸ ነበር። ራሱን የመቆጣጠሩ
ነገር ጫፍ ላይ በመድረሱ ፊቱ ደም መስሏል፡ እናታችንን፣ ተወዳጇን እናቱን
እንደዚህ የሚያናግርበት ቀን ላይ ይደርሳል ብዬ አስቤ አላውቅም።

በጣም ጮክ እንዳለ ተሰምቶት መሰለኝ፣ ድምፁን ዝቅ አድርጎ በእርጋታ
መናገር ቀጠለ፡ ቃላቶቹ ግን የጥይት ያህል ውጤት ነበራቸው “እማዬ፣
የአባትሽን ብዙ ንብረት ወረሰሽም አልወረስሽም ከዚህ ክፍል መውጣት
እንፈልጋለን! በሚቀጥለው ሳምንት ወይም ነገ አይደለም፣ ዛሬውኑ! አሁን!
በዚች ደቂቃ! ያንን ቁልፍ ለእኔ ስጭኝና ርቀን እንሄዳለን፤ በጣም ርቀን፡
ከፈለግሽ ገንዘብ ትልኪልናለሽ ካልፈለግሽም አትላኪ ችግርሽን የሚያቃልልሽ
ከመሰለሽና ምርጫሽ ከሆነም ዳግመኛ እኛን ማየት አያስፈልግሽም: ከህይወትሽ እንወጣለን፡ አባትሽም እስከ መፈጠራችን አያውቅም አንቺም የሚተውልሽን
ሁሉ ልትወስጂ ትችያለሽ፡ ሁሉንም ለራስሽ ውሰጂ”

እናታችን በድንጋጤ ገረጣች::

እኔም ምሳዬ ግማሹ እንደተበላ ወንበር ላይ ቁጭ ብዬ ነበር አሳዘነችኝ።
ሀዘኔታዬ ሊከዳኝ ነበር ግን የተራብንባቸውን እነዚያን ሁለት ሳምንታት…አራት ቀን ብስኩቶችና ቺዝ… ሶስት ቀን ካለምንም ምግብ ውሀ ብቻ እየጠጣን
ያሳለፍናቸውን ጊዜያት… ከዚያ ግርፋቶቹ ፀጉሬ ላይ የተደረገብኝ ሬንጅ…
hሁሉም በላይ ደግሞ ክሪስ መንትዮቹን ለመመገብ ደም ስሩን መቁረጡ… ያንን ሁሉ ሳስብ እንዳላዝንላት ጠነከርኩ

እና ክሪስ ያላት ነገር በሙሉና የተናገረበት ቁርጠኝነት በአብዛኛው የእኔ ስራ ነበር።

ያንን የገመተች ይመስለኛል ምክንያቱም በሚወጋ አስተያየት ገላመጠችኝና
በማዘን አይነት “ከዚህ በላይ እንዳትናገረኝ ክሪስቶፈር፣ ራስህን እንዳልሆንክ ማየት ግልፅ ነው” አለች።

ከተቀመጥኩበት ተነስቼ አጠገቡ ቆምኩ፡ “ተመልከቺን እማዬ፣ ልክ እንዳንቺ የሚያንፀባርቅ የነበረውን ጤናማ ገጽታችንን አስተውይ በተለይ ሁለቱን ትንንሽ ልጆችሽን በደንብ ተመልከቻቸው ደካማ አይመስሉም፣ ይመስላሉ
እንዴ? ጉንጮቻቸው የከሱ አይመስሉም፣ ይመስላሉ እንዴ? አይኖቻቸው
አልጠቆሩም፣አልጎደጎዱም፣ ጎርጉደዋል እንዴ? ስታያቸው ምን ያህል
እንዳደጉ፣ እንዴት ጤናማ እንደሆኑ አየሽ? ለእኔና ለክሪስቶፈር ማዘን
ካልቻልሽ፣ ለእነሱ እዘኝላቸው” አልኳት።

“አቁሚ!” ስትል ከተቀመጠችበት አልጋ ላይ ዘላ እየወረደች ጮኸች: እኛን ላለማየት ፊቷን አዞረች ድምፅዋ ውስጥ ሳግ እንደተናነቃት ይሰማል።
“እናታችሁን በእንደዚህ አይነት ለማናገር ምንም መብት የላችሁም: እኔ
ሁላችሁም መንገድ ላይ ከምትራቡ ብዬ ነው” ድምፅዋ ተቆራረጠ፡ በጎን
ሆነችና ክሪስን አየት አደረገችው: “የቻልኩትን ነገር አላደረግኩላችሁም?
የቱ ጋ ነው የተሳሳትኩት? ምን አጣችሁ? አያታችሁ እስከሚሞት በዚ ሁኔታ እንደሚቀጥል ታውቃላችሁ እስኪሞት እዚህ ትኖራላችሁ ከሁሉም ነገር ምርጥ የተባሉትን እያመጣሁላችሁ ነው: መፃህፍት፣ መጫወቻዎች
አሻንጉሊቶች፣ ገንዘብ ሊገዛው የሚችለውን ጥሩ ልብሶች የምትበሉት ጥሩ
ምግብ አላችሁ፣ ቲቪ አላችሁ:” አሁን ፊት ለፊት እያየችን ነው: እጆቿን ዘርግታ በጉልበቷ ልትወድቅ የተዘጋጀች መስላ የሚለምኑ አይኖቿን እኔ ላይ አደረገች: “አዳምጪኝ! አያትሽ በጣም ታሟል አሁን ሙሉ ጊዜውን የሚያሳልፈው አልጋ ላይ ነው የሚገፋ ወንበሩ ላይ እንዳይቀመጥ እንኳን ተከልክሏል። ዶክተሮቹ ሊቆይ የሚችለው ለጥቂት ቀናት ወይም ቢበዛ ጥቂት
ሳምንታት ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል። ልክ የሞተ ቀን እኔ ራሴ መጥቼ በሩን ከፍቼላችሁ ይዣችሁ እወርዳለሁ። ከዚያ ሁላችሁንም ኮሌጅ ለመላክ በቂ
ገንዘብ ይኖረኛል። ክሪስ የህክምና ትምህርት ቤት ይገባል፡ አንቺም የዳንስ ልምምድሽን ትቀጥያለሽ፡ ለኮሪ ምርጥ የሙዚቃ አስተማሪ አገኝለታለሁ ለኬሪ ደግሞ የምትፈልገውን አድርጋለሁ፡ የተሰቃያችሁባቸውን አመታት
ልክ ግባችሁን ልትመቱ ጥቂት ሲቀራችሁ አለምንም ሽልማት ልትወረውሩት የምታወሩትን ነው? ብዙ ገንዘብ ሲኖራችሁ በምን በምን እንደምታጠፉት እየሳቃችሁ የምታወሩትን አስታውሱ: ያቀድናቸውን እቅዶች አስታውሱ... ሁላችንም እንደገና አብረን ስለምንኖርበት ቤት አስቡ ልክ ልታሸንፉ ስትሉ ትዕግስት
በማጣት ሁሉንም ነገር አትወርውሩት። እናንተ ስትሰቃዩ ደስ ይለኛል? እና በዚያ እስማማለሁ? ንገሩኝ፡ ያንን ሁሉ በአስር እጥፍ እመልሳለሁ።”
👍38
እንደተነካሁ አምናለሁ እና ካለማመን መራቅ ፈልጌያለሁ: አጠገቧ አንዣበብኩ፣ እንደገና ላምናት ፈለግኩ፤ ግን ትዋሻለች የሚለው ፍርሀት ጥንካሬ አንቀጠቀጠኝ፡ ገና ከመጀመሪያው ጀምሮ የመጨረሻ ትንፋሹን
እየተነፈሰ ነው ብላን አልነበረ? ከአመት እስከ አመት የሚተነፍሰው ሁሉ የመጨረሻ ትንፋሹን ይሆን? እማዬ፣ ከአሁን በኋላ አናምንሽም ብዬ ልጩህ? ልክ እኛ በእምባዎቻችን፣ በመገለላችንና በብቸኝነታችን እንደቆሰልነው ላቆስላት ፈልጌያለሁ። ስለ ቅጣቱ ምንም አልነገርናትም።

ግን ክሪስ በመከልከል አይነት ሲመለከተኝ... ችላ ብዬው አፌን ልክፈትና አያታችን ያለምንም ምክንያት እንደቀጣችን ጮኬ ልናገር ፈልጌ ነበር ግን
እንግዳ በሆነ ምክንያት ዝም አልኩ። ምናልባት መንትዮቹ ብዙ እንዳያውቁ ለመከላከል ይሆን ይሆናል። ምናልባት ክሪስ በመጀመሪያ እንዲነግራት
እየጠበቅኩ ይሆናል።

ቆሞ በሀዘኔታ እየተመለከታት ነው፡ ፀጉሬ ላይ የተደፋብኝ ሬንጅና ያለ ምግብ ያሳለፍናቸውን ሳምንታት፣ እንዲሁም በጨውና በበርበሬ ያጣፈጣቸውን የሞቱ አይጦችና ግርፋቱን ሁሉ ረስቶታል አጠገቤ ቆሞ ባለመወሰን ግራ እየተጋባ ነው፡ እናታችን ማልቀስ መጀመሯን ሲመለከት ደግሞ አይኖቹ
በተስፋና ተስፋ በመቁረጥ እይታዎች ተሰቃዩ: እናታችን አጠገቧ ያለው አልጋ ላይ ተደፍታ እየተንሰቀሰቀች ልክ እንደ ልጅ ትራሱን እየደበደበች ነበር።

“እናንተ ክፉና ምስጋና ቢስ ልጆች ናችሁ በአለም ላይ ካሉ ሰዎች ሁሉ
የምወዳችሁን እኔን እናታችሁን እንዲህ ታደርጉኛላችሁ?! የማስብላችሁ እኔ ብቻ ነኝ፡ ወደ እናንተ የመጣሁት ደስ ብሎኝ፣ መልካም ዜና ልነግራችሁና
ከእኔ ጋር ደስ እንዲላችሁ ላደርግ ነበር፡ እናንተስ ታዲያ ምን አደረጋችሁ? ያለምንም ሀዘኔታና ፍትህ አጠቃችሁኝ! የቻልኩትን ያህል ጥሩ ነገሮች አድርጌላችሁ እናንተ ግን አታምኑም። ጥፋተኝነትና እፍረት እንዲሰማኝ
አደረጋችሁኝ!"

ድንገት ሳናስበው እኔና ክሪስ በሀዘኔታ ተመታን፡ ያለችው ነገር ሁሉ እውነት ነበር። የምትወደን፣ የምታስብልን ብቸኛ ሰው እሷ ብቻ ናት። በእሷ ውስጥ መዳናችን፣ ህይወታችን፣ ወደፊታችንና ህልሞቻችን አሉ። ወደ እሷ ሮጥን።
እኔና ክሪስ ክንዶቻችንን አንገቷ ላይ ጠምጥመን በቻልነው ሁሉ ይቅርታዋን ለመንን፡፡ መንትዮቹ ከማየት በስተቀር ምንም አላሉም።

“እማዬ፣ እባክሽ ማልቀስ አቁሚ! ስሜትሽን ለመጉዳት ብለን አይደለም ይቅርታ በጣም ይቅርታ! እንቆያለን፡ እናምንሻለን፡ ወንድ አያታችን ሊሞት ነው የሆነ ቀን ይሞታል አይደል?”

በጣም በጣም አለቀሰችı ማፅናናት አልቻልንም።

“አናግሪን እማዬ፣ እባክሽ መልካሙን ዜና ንገሪን፡ ማወቅ እንፈልጋለን ከአንቺ ጋር መደሰት እንፈልጋለን፡፡ ያንን ሁሉ ነገር ያልንሽ ለምን እንደሆነ ሳትነግሪን በመሄድሽ ስለተጎዳን ነው፡ እማዬ፣ እባክሽ እባክሽ እማዬ"

ልመናችን፣ እምባችን፣ ሀዘናችን በመጨረሻ እሷ ጋ ደረሰ። ከዚያ መቀመጥና ካ የሚል ፊደል በተፃፈበት መሀረብ አይኖቿን መጠራረግ ጀመረች።

እኔንና ክሪስን ወደጎን ተወት አድርጋን ልክ የሚያቃጥሉ ይመስል እጆቻችንን አራገፈችና ቆመች: የሚለምኗትና የሚማፀኗትን አይኖቻችንን እየሸሸች ነበር።

“በጥንቃቄ የመረጥኳቸውን ስጦታዎቻችሁን ክፈቱና እንደማላስባችሁና
እንደማልወዳችሁ፣ ስለፍላጎቶቻችሁና ስለሚያስፈልጋችሁ ምርጥ ነገሮች
እንደማላስብ፤ ራስ ወዳድና ግድ የለሽ እንደሆንኩ ገገሩኝ፡" አለች ሳግ ባነቀው ቀዝቃዛ ድምፅ፡

ልታገኝ ስለምትፈልገው ነገር ስትል ድራማ የምትሰራ አድርጌ የማስባት
ለምንድነው? እኔን ችላ ብላ ክሪስን ተመለከተች።.....


ይቀጥላል
18👍16
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስምንት ፡ ፡ #ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ በመጨሻ እኖታችን እኔና ክሪስ በግርፋቱ ቀን በመሀከላችን ስለተፈጠረው ነገር በፍፁም አላወራንም በአብዛኛው አተኩሮ ሲመለከተኝ እይዘዋለሁ፧ ግን አይኖቼ አይኖቹን ሲመለከቱ አይኖቹን ያሸሻል እኔም ሳየው ከያዘኝ አይኖቼን ወዲያው እመልሳለሁ። እኔም እሱም በየቀ እያደግን ነው፡ ጡቶቼ ሙሉ ሆነዋል። ዳሌዬ ሰፋ ብሎ ወገቤ…»
በህይወት መንገድ ላይ....
(ታጋቾቹ)
ምዕራፍ-6
(በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)
////
አስቤዛችን ሆነ ውሀችን በናዳው ተቀብሯል።
"በትክክል ምን ይሻላል የሚለው ጥያቄ መጠየቅ ያለበት አሁን ነው?"አልኩ ከልቤ አዝኜ እና ደንግጬ…..
በሪሁን "ማን ሊመልሰው?"አለ ከፊቱ ላይ አባረውን እያራገፈ፡፡
"እንኳንም እሙሙዬ ሳትደፈን ተረፈች እንጂ ጥያቄውን እንደፈረደብኝ እኔ እመልሳለሁ … እራሳችንን እንደምንም ነፃ እንዳደረግን ሁሉ በተመሳሳይ ቢያንስ ግማሽ እቃችን ማለቴ ምግባችን፤ ውሀችንና መቆፈሪያ ብረታችንን ነፃ ማውጣት አለብን
"
ከዛስ?
"ከዛ ቀጥሎ ያለውን እናስብበታለን"
እኔ ስከራከር በሪሁንና ጋሽ አህመድ በሀሳቧ ተስማምቶ ስራ ጀምረዎል…..አረ ሰላምም እያገዘቻቸው ነው?
"ኢንጂነር ያንተ እጅ ለወርማፕ እንጂ አፈር ለመግፈት አይሆንም አይደል?"በአሽሙር
በሪሁን"ምነው የእኛ ለወርማፕ አይሆንም እያልሽ ነው?"አላት …ለእኔ የወረወረችው አሽሙር እሱን እንደነካው በሚያሳብቅ ቅላፄ
"ያው ለጫወታው ድምቀት ብዬ እንጂ እሱማ አሁን ለምሳሌ እኔን ብትጠይቁኝ ....ደልደል፤ ጠንከር ፤ሻከር ያለ መዳፍ በሰውነቴ ላይ አርፎ ሲዳብሰኝ... ሲጨምቀኝ... ሲሸረክተኝ... ሲያቆስለኝ ..ሲያደማኝ...ዋው ተው ባክህ አሁን አሁን መስሎኝ በጉጉት ሙሙዬ ረጠበች"

እሷ ብቻ አይደለችም ጋሽ አህመድን ጨምሮ ሶስታችንም ወንዶች አፍችንን ከፍተን ነበር እያዳመጥናት የነበረው...ሰላም ብቻ ነች በማይነበብ ስሜቷ አንደበቷን ቆልፋ አንገቷን አቀርቅራ ስራዎን በመስራት ላይ ያለችው....ለማንኛውም ከአንድ ሰዓት በላይ በፈጀ የጋራ ትግል መቆፈሪያና ቢላዎቻችንን ጨምሮ ግማሽ ራሽናችንን በእጃችን አስገባን
"so what now?"
"ዌል እንግዲ...አሁን ሬሽናችን እንደየአስተዋፅኦችን ይታደለንና እናገግም"
‹‹ከዛ ቡኃላስ?››
‹‹ሲደርስ እንነጋገርበታለን››
" ወደሰላም ሬሽኑ ቀረበ..እሷም በአይነትም ሆነ በመጠን ሳታዛንፍ ለሁላችንም የምንቀምሰውን አደለችን"
"አንቺ ሶሻሊስት የሆንሽ ልጅ...እንዴትና በምን ስሌት ነው በርዬና ኢንጂነሩ እኩል ድርሻ የሚደርሳቸው?"
ሰላም ፈገግ ብላ ዝም አለች...እኔም ከእሷ ጋር እንካ ሰላምታ ስላላሰኘኝ አርፌ በዝምታ የተሠጠችኝን ብስኩት በውሀ እያወራረድኩ መኮርሸሜን ቀጠልኩ....ዞር ዞር ብዬ ስመለከት ሁሉም ምግብን ጨርሷል ።ከጀርባዬ ወዳለችው አይዳ ዞሬ ..."እሺ..ከሁንስ..?››ስል እሷ የለችም።ልክ ሳባና ቢች ዳር እንዳለች ሰላማዊ ኮረዳ ለሽ ያለ እንቅልፍ ወስዷታል።
"ታድለሽ "አልኩና እኔም ባለውበት ወደኃላ ልክ እንደእሷ ጋደም አልኩ...በጣም ደክሞኝ ስለነበር ወዲያው ነው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰደኝ።
ከእንቅልፌ ስባንን ከሰላም በስተቀር ሁሉም በየቦታው ፍግም ብሎ ተኝተዋል።ሠላም ግን እደተለመደው ልክ እንደብድሀ መለኩሴ እግሮቾን አንድ ላይ አቆላልፋ ና አጣጣጥፋ እጇቾን አንድ ላይ አድርጋ ወደ ግንባሯ አድርጋ በተመስጦ ጠፍታለች።
"ነቀነቅኩና አይዳን አስነሳዎት...በዝግታ አይኖቾን ገለጠችና"ምነው ነጋ እንዴ?"አለችኝ
"ቀልደኛ ነሽ ምን መምሸትና መንጋት አለ?"
"ውይ እቤቴ ያለው መስሎኝ"
"አንቺ እቤትሽ ብትሆኚ እኔ ከጎንሽ ምን እሰራለው?"
"እኔም የገረመኝ እኮ እሱ ነው....አሁን አይኖቼን አጨንቁሬ ከፍቼ አንተን ሳይህ ከአልጋዬ ፊት ለፊት ቆመህ ሽታው የሚያውድ ምርጥ እንቁላል ፍርፍር ቁርስ ሰርተህ..‹ውዴ ተነሽ ቁርስ ደርሷል..በገዛ እጇቼ በፍቅር ያበሰልኩት ስለሆነ ልዩና ጣፋጭ ነው..እባክሽ ተነሽ ላጉርስሽ › በማለት እየለመንከኝ መስሎኝ ምን ሰይጣን አሳስቶኝ ይሄን ሰው አገባው ብዬ ስበሳጭ ነበር"
ምናወራው ሠላምን እንዳንረብሻት በለሆሳሳ ነው
"ጥሩ ታልሚያለሽ ባክሽ!!!ጭራሽ እኔን ማግባት ሲያስቆጭሽ...?በይ አሁን ንቂና ወዳለሽበት አሳዛኝና ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ቀልብሽን መልሰሽ ወንዷቹን ቀስቅሺያቸውና አንድ ነገር እናድርግ"
ከ10 ደቂቃ ብኃላ ሠላምም ፀሎቷን ጨርሳ እነበሪሁንም ከእንቅልፋቸው ተነስተው ሁላችንም ተፋፍገን ለውይይት ተቀመጥን።
"ምንድነው የምናደርገው...አሁን ከላይ ቆፍረው ያወጡናል የሚለው ተስፋችን ሞቷል....ብንተርፍም ብናልቅም በራሳችን ጥረት ነው የሚሆነው።"እኔነኝ የመወያያ ርዕስ ያቀረብኩት።
"ይሄንን ቆፍሩት"ሠላም ነች ተናጋሪዎ
"ምን? "የንግግሯ እርግጠኝነት እኔን ግራ አጋባኝ
"አዎ መውጫ መንገዳችን በዚህ እንደሆነ ጠንካራ ስሜት ተሠምቶኛል....ግዴላችሁሞ እንቆፍር"
"እንደምንተርፍ ታምኚያለሽ ማለት ነው?"
"ሁላችንም ላይሳካልን ይችላል ግን ከአምስታችን አንዳችን እንኳን ተርፈን ህይወት ሌለ እድል የምትሰጠን ከሆነ ሊሳካልን የሚችለው በዚህ መንገድ ስንጓዝ ነው።"
"በእውነት ድንቅ የሆነ ተስፋ አስቋራጭ ንግግር ነው ያደረግሽው...አሁን ሁላችንም በውስጣችን ተራፊው አንድ ሰው ከሆነ ያ ሰው እኔመሆን አለብኝ እያልን ከራስ ወዳድነታችን ጋር እንድንፋለም እያደረግሽን ነው"
"እኔ ደግሞ ተራፊው አንድ ሰው ከሆነ ያ ሰው እራሷ ነች እያልኩ በውስጤ እያሰብኩ ነበር?››አልኩ በእውነት ያሰብኩትን ነው የነገርኳቸው
"ለምን እንደዛ ልታስብ ቻልክ?"አለቺኘ ሰላም
"ያው የታወቀ ነው ከእኛ በተሻለ ከእግዜያብሄር ጋር ቀረቤታው ስላለሽ..."
"እና በዛ የተነሳ ለእኔ የተለየ ፌቨር እንደሚያደርግ ገመትክ.."
"በርግጥም እንደዛ ነው ያሠብኩት"
"ይገርመኛል.. ብዙ ሰዎች እግዚያብሄርን የሚያስብት በሰው ሚዛን ነው?እነሱ ቢሆኑ የሚያደርጉትን እሱም የሚያደርግ ይመስላቸዋል...ለማንኛውም እኔ አንድ ሰው ብቻ ይተርፋል አላልኩም...ስንት ሰው እንደሚተርፍ እርግጠኛ አይደለሁም"እርግጠኛ የሆንኩበት ሁለት ጉዳይ ግን ንገሪን ካላችሁ ልንገራችሁ››
"ንገሪን..ንገሪን"
"አንደኛ ሁላችንም ከዚህ ዋሻ በህይወት አንወጣም....ሌላው ከማይወጡት ውስጥ ደግሞ እኔ አንዷ እንደሆንኩ በእርግጠኝነት አውቃለው ።››
"ምን እያልሽ ነው? ታዲያ እንደምትሞቺ እያወቅሽ...ምን አስለፋሽ?››አይዳ ነች የእኛንም ጥያቄ የጠየቀቻት
"ከእዚህ እንደማልወጣ እርግጠኛ ነኝ አልኩ እንጂ በመሞቴ እርግጠኛ ነኝ አላልኩም።ሌላው ደግሞ በዚህ ወጥመድ ውስጥ ከመውደቃችን በፊትም እኮ ሁላችንም አንድ ቀን ሞቾች እንደሆን እያወቅን ግን ተስፋ ሳንቆርጥ የእየእለት መከራችንን ለማቃለል ከመጣር ወደ ብለን አናውቅም፡፡ስለዚህ አሁን ክርክሩን እና ጭቅጭቁን አቁመን መቆፈረ ብንጀምር የሻላል

"አምንሻለው"አለና መቆፈሪያውን በማንሳት ስንጥቁን ለመስፋት መቆፈር ጀመረ "የተከራከረ ሰው አልነበረም..ላባችን ጠብ እስኪል ድረስ ለሁለት ሰዓት ለፍን ..ከዛ ቀጠን ያለ ሠው ታኮ ማሾለክ የሚያስችል ክፍተት አገኘን...ማን ቀድሞ ይሹለክ?ከሾለክን ብኃላ ምንድነው የሚያጋጥመን...? እርግጠኛ ነኝ በሁላችንም አእምሮ እየተመላለሠ የሚያስጨንቀን ጥያቄ ነበር"
"ያው መቼስ ጉድጓድ በእኔ ልክ የቆፈራችሁት ቀድሜ እኔ እንዳልፍ ነው... ያ ዘንዶ አፍን ከፍቶ የሚጠብቀኝም ከሆነ ከወዲሁ ሰላም ሁኑ"አይዳ ነች
👍221
"አረ ተይ ስለትሽንማ ሳታደርሺ በዘንዶ መበላት የለብሽም"አላት በሪሁን
ቀሚሶን ወደላይ ሰብሰብ እንደማድረግ ብላ"እሺ ና ግባ ትንሽ ሰጥቼህ ልሂድ"አለች..ከእኔ በስተቀር ሁሉም በንግግሯ ፈገግ አሉ
"ምትሄጂ ከሆነ ጊዜ አታባክኚ ይሄው ባትሪ ሂጂና ያለውን ነገር ንገሪን"እኔ ነኝ ብስጭትጭት ብዬ የተናገርኩት
ምንጭቅ አድርጋ ባትሪውን ተቀበለችኝ..."ምን አለ ሰጥቼው ብሞት …?ቅናት ነው አይደል.? አንተ ልጅ ጭኔን ከደባበስክ ብኃላ ስለእኔ ያለህ ፍላጎት እየተቀየረ ነው...ነግሬሀላው ብኃላ ፍቅር ይዞህ እንዳትሰቃይ.. ለማንኛውም ቢላዎንም ስጡኝ "
ጋሼ አህመድ ፈጠን ብሎ አቀበላት..ሠላም ተንደርድራ አቅፋት ጉንጮን ሳመቻትና….አምላክ ካንቺ ጋር ነው እንዳትፈሪ"አለቻት
አይዳ ለመሹለክ አንገቷን ወደቆፈርነው ጉድጓድ አሰገገች... ደስ አላለኝም.."እሷ ሳትሆን ሌላ ሰው ነው ቅድሚያ መግባት ያለበት?ካልሆነ ካልሆነ እኔም ብቀድም ይሻል ነበር..አደጋ ቢያጋጥማትስ?..".በውስጤ የተርመሰመሰ የስጋት ሀሳብ ነው"ምን እየሆንኩ ነው ..?.እጠላት የለ እንዴ? ነው ወይስ እሱ ከምድር በላይ የነበረ ያለፈ ታሪክ ይሆን?እናም እሷ እንዳለችው በእሷ እየተሳብኩ ይሆን?መቼስ ከእሷ ፍቅር ከያዘኝ በራሴ አመት ነው የምስቀው…. (አምላክ የምስቅበት ተጨማሪ ጊዜ ከሰጠኝ ማለቴ ነው።) ሀሳቤን ሳልጨርስ እሷ ሾልካ ከእኛ ተለይታለች..
"እ ምን ይታይሻል..?"
"ቆይ እስኪ ትንፋሽ ልሰብስብ"አለችን...ጊዜ ልንሰጣት ሞከርን እያንዳንዷን ሰከንድ መጠበቅ ግን ጣር ነበር
"ሰዎች"
"አቤት አይዳ ሰላም ነሽ..ምንም አልገጠመሽም?"እኔ ነኝ ተስገብግቤ የጠየኳት
"ዘንዶው ውጦኝ ስላልተገላገልከኝ አዝናለው...ስለይህ እንደነበረው ሰላም ነኝ"አለች
"እሺ ምን አየሽ"
ማለቂያው የማይታወቅ ዋሻ...ወደ 50 ሜትር ሄጄ በዛው እንዳልጠፋ ፈርቼ ነው የተመለስኩት... ያለን ምርጫ እናንተም ወደእዚህ እኔ ወዳለሁበት መምጣት ነው...ባይሆን ከዛ ብኃላ አብረን እንጠፋለን።"
"እሺ መጣን...እኔ ቀድሜ ወደአንቺ እመጣለሁ እንዳትፈሪ"
"ኪ..ኪ..ኪ"ከአንድ የዋሻው ግድግዳ ወደሌላው እየተማታ የፈጠረው የገደል ማሚቱ ሳቆን አደመቀው
"ምን ያስገለፍጥሻል?"
"አትበሳጭ የእኔ ጀግና...ብቻ ፈጥነህ ናልኝ"አለቺኝ በሚያበሽቅ የደምፅ ቅላፄ
ከማፈሬ የተነሳ ላቤ ከግንባሬ ተንጠባጠበ...አጠገቤ ብትሆን በጥፊ ላቃጥላት እችል ነበር...ለማንኛውም ከሁሉም ቀድሜ እሷ ወዳለችበት የዋሻ ክፍል ለመሹለክ ዝግጅ ሆንኩ...

ይቀጥላል....


ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
❤️❤️❤️
👍9
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ሳቤላ በባሏና በባርባራ ሔር ግንኙነት የነበራት ቅናት ፍራንሲዝ ሌቪሰን
ኢስት ሊን ከገባ ወዲህ ከምን ጊዜም የበለጠ ጨምሮ ታደሰባት ባርባራ በበኩሏ ሪቻርድ ባረጋገጠው መሠረት ወንጀሉን የፈጸመው ፍሬድሪክ ቶርን መሆኑን በማመን፡ የተሰወረው ምስጢር ገሃድ ሆኖ ወንድሟ ከወደቀበት ከባድ መከራ በፍርድ ነጻ ተለቆ ለማየት ከመጓጓቷ የተነሣ ልቧን ከመሳት አፋፍ ደርሳ ነበር ።በነገሩ ብታምንበትም ምንም ለማድረግ ኃይል አልነበራትም ከእንቅልፍ ይልቅ ቅዠት የበዛበት ሌሊት ዐልፎ በነጋ ቁጥር ' ' ምነው ዛሬ አንዳች የማረጋገጫ ነጥብ ባገኘሁ! ተጠርታም
ከሔርበርት ቤት ብዙ ጊዜ ተመላልሳለች የሚስተር ሔርበርት ሴት ልጆችም ባልንጀሮቿ ስለ ነበሩ ፡ ለዕረፍት ለመጣው ወንድማቸው ልዩ ዝግጅት አድር?ው ሲጠሯት ካፒቴን ቶርንን ብዙ ጊዜ አይታዋለች
እንዶዚህ በመስሉ አጋጣሚዎች ስለ ዐለፈው ታሪኩ አንዳንድ ነር ትለቃቅምና ያገኘችውን ይዛ ወደ ሚስተር ካርላይል ትሮጣለች ከቢሮው ስትሔድ ቶርን ያያት
እንደሆነ እንዳይነቃ በመፍራት ወዶ ኢስት ሊን ሔዳ አለበለዚያ ደሞ ወደ ቢሮ ሲሔድ ወይም ከቢሮ ሲመለስ ከመንገድ ጠብቃ ነበር የምታገኘው "ነገር ግን ! ይኸን ያህል የሚጠቅም ነገር ይዛ መጥታ አታውቅም » አንድ ቀን ማታ ቶርን ዱሮ
ዌስት ሊን እንደ ነበረ ልትነግረው መጣች " በሌላ ቀን ደግሞ ለይምሰል እመቤት ሳቤላን ለመጠየቅ መጣችና ሚስተር ካርይልን ለብቻው ልታነጋግረው እንደምትፈልግ ነገረችው " ተመራርተው ወጡና ኢያወሩ እስከ መናፈሻው በር አብሯት ሲሔድ ሁሉ የሳቤላ ቀናተኛ ዐይኖች ያዩዋቸዋል " ስለ ቶርን ትነግረው " የነበሩት ነጥቦች ሁሉ ጠንካራ አይደሉም እነሱንም ሚስተር ካርላይልም ቀደም ብሎ
ያውቃቸዋል " እሱ ግን መስማቱን ሳይገልጽላት በጉጉትና በስሜት ያዳምጣታል "

ሳቤላ ባሏና ባርባራ ሲገናኙ በዐይኗ አይታ ተናደደች ቁጠዋ ተቀስቅሶ የአእምሮዋ ሰላም ደፍርሶ ትትከነከናለች " ፍራንሊዝ ሌቪሰን ደግሞ እሷ ያላየቻችውን ግንኙነቶች እየተከታተለ ይነግራት ጀመር " ሚስተር ካርላይል ለጤና ይበጃል እያለ ይበልጡን ጊዜ ከቢሮ ወደ ቤት በእግሩ ይመላለስ ነበር " በሚስተር ሔር ቤት ሲያልፍ ባርባራ እየጠበቀችም ሆነ ባጋጣሚ ስታገኘው የቶርንን ነገር በምታነጋግረው ጊዜ ካፒቴን ሌቪሰን ቁጥቋጦ ለቁጥቋጦ እንደ እባብ እየተምለገለገ ሔዶ
ይመላከታቸውና እየጨማመረና እያጋነነ ለሳቤላ ይነግራት ጀመር "

ባርባራ ግን ስለ ሳቤላ ቅናት ምንም ነገር አታውቅም እሱም ሚስቱን እንደሚወድና ለሷም አንዲት የፍቅር ፊት አሳይቷት ስለማያውቅ ሳቤላ በሷ መቅናቷን ሰው ቢነግራት እንኳን በነጋሪዋ ከመሣቅ በቀር አታምንም ነበር
ዱሮ በፍቅር ትነድለት የነበረው ሁሉ ከሁኔታው ተረድታ ትታው' አሁን ካርላይል ዘንድ የሚያመላልሳት
የወንድሟ ጉዳይ ብቻ ሆኖ ነበር "

ኣንድ ቀን ጠዋት ሚስተር ካርላይል ከልዩ ቢሮው ገብቶ ሲሠራ ዋና ጸሐፊው
ሚስተር ዲል ገብቶ ባለጉዳይ ሊያነጋግረው እንደሚፈልግ ነገረው "

አሁን ሥራ ይዣለሁ : ማንንም ማነጋገር አልችልም
" ምነው እያወቅህ ..
ዲል ? አለው።

“ እንደዚያ ብነግረው : እጠብቃለሁ " አለኝ » ያ ካፒቴን ቶርን የሚባለው
ከጆን ሔርበርት ቤት ያረፈው እኮ ነው .

ሚስተር ካርላይል ቀና ብሎ ከዲል ጋር ተያዩና እሱንስ አነጋግረዋለሁ አስገባው አለው ።

የካፒቴን ጕዳይ ቀላል ነበር በየጊዜው ብዙ መኮንኖች እንደሚያደርጉት በዱቤ ዕዳ ምክንያት ክርክር ስለ ተነሣበት የሚስተር ካርላይልን የሕግ ምክር ለመጠየቅ ነበር "

ምክሩን ልሰጥህ እችላለሁ ነገር ግን የማንንም ጉዳይ ከማጥናቴ በፊት
ማንነት በደንብ ማወቅ አለብኝ " አባቴም አንድን ጉዳይ ከመቀበሉ
በፊት የባለ ጉዳዩን ትክክለኛ ሰው መሆንና የጉዳዩንም ሐቀኛ አነሣሥ ያጠና ነበር እኔም ከሱ ወርሼ በዚህ ዐይነት ነው የምሠራው "

“ ቤተሰቦቼም የታወቁ ናቸው " አለው ካፒቴን ቶርን

“ የኔ ጥያቄ የቤተሰብ ጥያቄ አይደለም » እኔ የቀን የጉልበት ሠራተኛም ሆነ
ለምኖ አዳሪ ቢመጣ ሐቀኛ ሰው መሆኑን በትክክል ካወቅሁ አነጋግረዋለሁ " ስለዚህ አሁንም ካንተ የምፈልገው ስለ ራስህና ስለ ጠባይህ ለማወቅ ነው
ታዲያ እኔ ጥሩ ሰው መሆኔን በምን ላሳምንሀ እችላለሁ ? አለው ካፒቴኑ
የጠበቃው ጥያቄ እንግዳ ቢሆንበትም በትሕትናውና በአቀራረቡ ተደፋፍሮ " አገሬን ማገልገል የጀመርኩት ካሥራ ስድስት ዓመቴ ጀምሬ ሲሆን የሥራ ጓደኞቼ በኔ ጠባይ ምንም የቅሬታ ነጥብ አግኝተውብኝ አያውቁም ከዚህ በተረፈ ጆን ሔርበርትን መጠየቅ ይቻላል ”

“ እስቲ በል ባለብኝ የሥራ ብዛት ምክንያት ጥብቅና ልቆምልህ አስቀድሜ
ቃል ልገባልህ ባልችልም ' ለጊዜው ማድረግ የምትችለውን ልነግርሀ እችላለሁ ” ካፒቴን ቶርን ችግሩን ገለጸለትና አስፈላጊውን ምክር ከሰጦው በኋላ ሌላ
ጨዋታ ያዙ " የዛሬ ዐሥር ዐመት ኢስት ሊን አልነበርክም ? አንድ ጊዜ እባቴ መጥተው ክደህ ነበር በኋላ ግን ከዚህ እንደ ነበርክ ደረስኩበት ” አለው

በርግጥ እንዲዛመት የማልፈልገው የግሌ ምክንያት ስለ ነበረኝ ነው እንጂ እሱስ ነበርኩ " አሁንም ካንተ አይለፍ እንጂ ብነግርህ ግድ የለኝም በዌስት ሊን ኣካባቢ ነበርኩ ያን ጊዜ የልጅነት ጠባይ ይዞኝ በሴት የተነሣ አንድ ነገር ተፈጠረ
ዛሬም በዚህ አካባቢ መኖሬ እንዲወራ ኣልፈልግም "

“ ገባኝ ” አለ ሚስተር ካርላይል የልቡ አመታት እየጨመረ “ ልጅቱ አፊ
ሆሊጆን የምትባል ነበረች "
“ አፊ ሆሊጆን ? እኔ እንደዚህ ያለ ስም በሕይወቴ ሰምቸ አላውቅም " "

በዚያን ዘመን አንድ አሳዛኝ ነገር መፈጸሙን አላወቅህም ? አልሰማህም ?
አሃ ! ቆይ እስቲ ያቺ አባቷ እንደ ተገደለ መጥፋቷን ቶም ሔርበርት የነገረኝ
እንደሆነች ?
“ አዎን ከገዛ ቤቱ ከልጁ ፊት የተገደለው ያባቴ ጸሐፊ ነበር ” አለው ሚስተር ካርላይል

“የገደለው ደግሞ የጀስቲስ ሔር ልጅ የዛያች ቆንጆይቱ የባርባራ ወንድም ትንሹ ሪቻርድ ሔር ነበር ይህን ነገር ብታነሳ አንድ ጊዜ ሰዎች የነገሩኝ ትዝ አለኝ
መጀመርያ ሔርበርት ቤት የመጣሁ ዕለት ማታ ጀስቲስ ሔርና ሌሎችም ትምባሆ ለማጤስ እዚያ መጥተው ነበር ያን ጊዜ ደግሞ ባባራን ካንተ ግቢ በር አይቻት ነበርና ቶም ሔርበርት ስለ ግድያው አጫወተኝ የሔርን ቤተሱብ ከባድ መከራ ነው
ያገኛቸው " ሚስ ሔርም በቂ ሀብትና ጥሩ መልክ እያላት ባል አግብታ ስሟን መለወጥ ሲገባት እስከ ዛሬ ባርባራ ሔር መባሏ በዚህ ምክንያት ይመስለኛል "

ምክንያቱ እንኳን እሱ አይደለም " ወንድሟ ነፍስ አጥፍቷል ቢባልም እሷን
ለማግባት የጠየቄ ብዙ ሰዎች እንዳሉ ዐውቃለሁ ስለዚህ ስሟን አታጉድፈው
ይኸን አባባልህን ዐርም ።

“እኔስ በዚህ አልንቃትም እንዲያውም ልጅቱ በጣም ደስ ትለኛለች " አለና ካፕቴን ቶርን ጫወታውን ቀጠለ “ እና ያቺ አፊ ከዚያ ወዲህ ወሬዋ ተሰምቶ አያውቅም ?

“ በጭራሽ ” አለ ሚስተር ካርላይል "ደህና አድርገህ ታውቃት ነበር አለው ሆነ ብሎ ።

“ እኔ ቶም ሔርበርት ስለሷ ሳይነግረኝ በፊት ስሟንም ሰምቸው አላውቅ ግን ለምንድነው የማውቃት መስዬ የታየሁህ ?

ሚስተር ካርላይል ' ሰውየው የሚናገረው እውነት ይሁን ውሸት ለማረጋገጥ በጣም ጓጓ "
👍15😁2
“ አየህ አፊ ፈገግታዋ ፡ ጨዋታዋ ግልጽነቷ ውበቷ ግድ የለሽነቷና ሽቅርቅር ባይነቷ ብዙ ወዳጆች ስበውላት ነበር የሷን የፍቅር ጮራ የመሞቅ ዕድል ከገጠማቸው ውስጥ አንዱ ካፒቴን ቶርን የተባለ መኮንን ነበር " ያ ሰው አንተ አይደለህም ?”

“ እኔስ በሷ የመወደድ ዕድል አላጋጠመኝም "

“ እንግዲያ ከዚህ አካባቢ አንድ ትልቅ ምክንያት የሆነችህ ቆንጆ እሷ አይደለችም ? አለው ሚስተር ካርላይል "
.
አይደለችም በርግጥ ያችም ሁኔታዋ ሁሉ ልክ አሁን አፊን እንደ ገለጽክልኝ ብጤ ሆኖ ባለ ትዳር ነበረች » ከጊዜ በኋላ ግን ነገሩ እየበረደ መጣና እሷም
ምንም የማያውቅ ባላገር ከነበረው ባሏ ጋር ታረቀች እኔ ግን ከዚያን ነገሩ ያሳፍረኝ ጀመር በተለይ እየበሰልኩ ኢያደግሁ ስሔድ ስፈጽመው የነበርኩት ዕብደቴን ሁሉ ሳስበው እኔ መሆኔን እንድታውቅ አልፈልግም ።

ካፒቴን ቶርን ቶሎ ወጣ ሚስተር ካርይል ሰውየውን እሱ ይሁን አይሁን ለማወቅ በጥርጣሬ እንደ ተወጠረ ተቀምጦ ቀረ " ከሱ ቀጥሎ ሚስተር ዲል ገባ።

“ ሚስተር አርኪባልድ ይህ ሰው ከአፊ ጋር ለመዳራት ከስዌንሶን በፈረስ እየጋለበ ይመጣ እንደ ነበረ አንድ ጊዜ የነገርከኝ መቶ አለቃ መሆኑን ትዝ አለህ ?

“እሱስ በደንብ ትዝ ብሎኛል” አለው ሚስተር ካርላይል 'አሁንም ቢሆን
ይህ ሰውዬ እሱ ለመሆኑ ለሚያረጋግጥልኝ አምስት መቶ ፓውንድ ከኪሴ እከፍል ነበር።

ከሔርበርት ዘንድ ከመጣ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አይቸዋለሁ ”አለ ዲል

እኔም የምንፈልገው ሰው እሱ ሳይሆን እንደማይቀር የነበረኝ ጥርጣሬ እየጠነከሪብኝ መጣ " ትናንት ዶክተር በዛንት ከስዊንሰን መጥቶ ስለነበር አብረን ስንሔድ
ካፒቴን ቶርንን አገኘውና ከሱ ጋር ሰላም ተባባሉ የት እንዳወቀው ሚስተር ፍረደሪክ እንደሚባል ነገረኝ " እኔም ቀበል አድርጌ ከፍረዶሪክ ሌላ ተጨሪ ስም አለው? ” አልኩት

“ስሙ ቶርን መሆኑን ዐቃለሁ አለኝ " ነገር ግን ከጥቂት ዓመት በፊት
ስዌንስን ሳለ 'ቶርን የሚለውን ስም ተወውና ከተማው ሁሉ ሚስተር ፍረዴሪክ ብሎ ይጠራው ነበር። እዚያ ምን ይሠራ ነበር?” ብለው ራሱን ማስደስት አንዳንድ ጊዜም
ከባድ ነገር ባይሆንም በሱ ዕድሜ ያሉት እንደሚያደርጉት ሁሉ ጠብ ማንሣት ችግር መፍጠር አለኝ ስለ ፈረሰኝነቱ ጠይቄው ከልክ ያለፈ ፈረሰኛ መሆኑን ሁልጊዜ
ብዙ እርቀት መጋለቡንም ነገረኝ ። ጊዜዉ እንዳሰብኩት ደግሞ' ያ አሳዛኝ ግድያ
በተፈጸመበት ዘመን ነበር ታዲያ ምን ይመስልሃል ሚስተር ካርላይል ?”

“እኔማ ሰውየው እሱ መሆኑን አምኘበታለሁ ” አለና ከወንበሩ ተደግፎ ከፊቱ ተዘርግቶ የነበረውን ብራና ተወት አድርጎ ሐሳብ ይዞት ጭልጥ አለ ።.....

💫ይቀጥላል💫
👍17🥰1😁1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ትርጉሜ_ሀኒም_ኤልያስ

...ልታገኝ ስለምትፈልገው ነገር ስትል ድራማ የምትሰራ አድርጌ የማስባት ለምንድነው? እኔን ችላ ብላ ክሪስን ተመለከተች።

ለሚቀጥለው ልደትህ ኢንሳይክሎፒድያ አዝዤልሀለው። ማተምያው ድረስ ራሴ ሄጄ ነው ያዘዝኩት ስምህንና ቀኑን ሰጥቺያቸዋለሁ ግን ወደዚህ በቀጥታ መላክ አይችሉም:: የሆነ ሰው ሊቀበላቸው ይገባል ልክ ሁልጊዜ ራስህን ለማስተማር ምርጡን ልሰጥህ እንደምፈልግ ሁሉ የሚያስደስትህን ስጦታ ሳስብ ሳስብ ቆይቼ ነው ያዘዝኩልህ”

ክሪስ የሚናገረውን አጣ ፊቱ ላይ የሚታየው ድብልቅልቅ ስሜት ነበር፤አይኖቹ ግራ የተጋቡና የፈዘዙ መሰሉ። አምላኬ! ካደረገችው ነገር በኋላ እንኳን ይወዳታል ማለት ነው::

ስሜቶቹ ቀጥታ ናቸው:: በቁጣ ነደድኩ እንደዚህ አይነት መፅሀፍት ከአንድ
ሺ ዶላር በላይ ይፈጃል: ምናልባትም ሁለት ወይም ሶስት ሺም ሊፈጅ ይችላል። ይህንን ገንዘብ ለምን የማምለጫ ገንዘባችን ውስጥ አትጨምረውም?
ልክ ኬሪ ስትቃወም እንደምታደርገው ልጮህ ስል ክሪስ አይኖች ላይ ያየሁት ነገር አፌን እንድዘጋ አደረገኝ፡ ሁልጊዜ እነዚያ መፃህፍት እንዲኖሩት ይፈልግ ነበር፡ በዚያ ላይ አንድ ጊዜ ታዟል: አሁን ለሷ ገንዘብ ምኗም አይደለም፧
ምናልባት እንዲያው ምናልባት አያታችን ዛሬ ወይም ነገ ሊሞት ስለሚችል አፓርታማ መከራየትም ሆነ ቤት መግዛት አያስፈልጋት ይሆናል፡

ጥርጣሬዬ ተሰምቷታል።

እናታችን ጭንቅላቷን ቀና አደረገችና ወደ በሩ ተራመደች። ስጦታዎቻችንን
ገና አልከፈትንም፤ ስንከፍት የሚኖረንን ስሜት ለመመልከትም አልቆየችም።
እየጠላኋት ለምንድነው በውስጤ የማለቅሰው? አሁን አልወዳትም አልወዳትም።

በሩጋ ደርሳ እየከፈተች “ዛሬ ስለፈጠራችሁብኝ ህመም ስታስቡና እንደገና
በፍቅርና በአክብሮት ልታስተናግዱኝ ስትችሉ ተመልሼ እመጣለሁ ከዚያ
በፊት ግን አይሆንም::” አለች።

መጣች።

ሄደች።

መጥታ ስትመለስ
ኬሪና ኮሪን አልነካቻቸውም አልሳመቻቸውም አላናገረቻቸውም ለምን እንደሆነ አውቄያለሁ፤ ሀብት ማግኘት መንትዮቹን ምን ያህል ዋጋ እንዳስከፈላቸው ማየት መቋቋም ባለመቻሏ ነበር።

ከጠረጴዛው አጠገብ ተነስተው እየሮጡ ወደ እኔ መጡና ቀሚሴን እየጎተቱ
ፊቴ ላይ አፈጠጡ ትንንሽ ፊቶቻቸው ጭንቀትና ፍርሀት አጥልቶባቸዋል።
እነሱም ደስታ እንዲሰማቸው መደሰቴን ለማየት ፊቴን እያጠኑ ነው:
ተንበርክኬ እሷ የጎዳቻቸውን በመሳምና በማቀፍ አጥለቀለቅኳቸው።
መልካችን ያስጠላል?" ጠየቀች ኬሪ በመጨነቅ፤ ትንንሽ እጆቿ እጄን
ይዘውኛል

“አይ በጭራሽ! አንቺና ኮሪ ቤት ውስጥ ብዙ በመቆየታችሁ ትንሽ የገረጣችሁ ትመስላላችሁ”

“በደንብ አድገናል?”

“አዎ፣ አዎ አድጋችኋል” እየዋሸሁ እንኳን ፈገግ ብያለሁ: በዚያ የማስመሰል
ደስታና የውሸት ፈገግታ ወለሉ ላይ ከክሪስና ከመንትዮቹ ጋር ተቀምጠን
አራታችንም ልክ እንደ ገና ቀን ስጦታዎቻችንን መክፈት ጀመርን። ሁሉም
በውድ የስጦታ ወረቀቶች በሚያምር ሁኔታ የታሸጉ ናቸው።

ወረቀቱን ቀደድን ሪቫኑን ጥለን የታሸጉበትን ካርቶኖች ገነጣጥለን ውስጡ ያለውን አወጣን... በውስጡ ለእያንዳንዳችን የሚያማምሩ ልብሶች ነበሩ:
አዳዲስ መፃህፍት፣ መጫወቻዎች፣ አንድ አይነት ቅጠል የሚስል ቅርፅ ያላቸው በትልቅ ካርቶን ውስጥ የታሸጉ የስኳር ከረሜላዎች።

እንደምታስብልን ማሳያው ይኸው! ሁላችንንም በደንብ ታውቀናለች።ከመጠኖቹ በስተቀር ፍላጎታችንን፣ ማድረግ የምንፈልገውን ሁሉ ታውቃለች።
በፈቃደኝነት ሞተን ስንቀበር ማየት ደስ በሚላት ጠንቋይ አያታችን ጥበቃ ስር የተተውንባቸውን እነዚያን ባዶና ረጃጅም ወራት በስጦታዎቹ ከፈለችን።

በዚያ ላይ እናቷ ምን አይነት እናት እንደሆነች እያወቀች... የምትሰራው ሁሉ በልቧ ትክክል እንዳልሆነ እያወቀች በመጫወቻዎቹና በአሻንጉሊቶቹ
ልትደልለንና ይቅርታ ልትጠይቀን ፈለገች
በጣፋጭ የስኳር ከረሜላ መራራውን ብቸኝነታችንን ከአፋችን፣ ከልባችንና
ከአእምሯችን ልትወስድ ተስፋ አደረገች ምንም እንኳን ክሪስ መላጨት
የሚያስፈልገው እኔም ጡት መያዣ መልበስ የሚገባን እድሜ ላይ የደረስን
ቢሆንም በእሷ አስተሳሰብ አሁንም ልጆች ነን ልክ በምታመጣው መፃህፍት
ርዕስ ትንሽ አድርጋ ለዘለዓለም ልታስቀምጠን ትፈልጋለች፡

ኬሪን አዲስ ቀይ ቀሚስ ሳለብሳትና ሀምራዊ ሪቫን ሳደርግላት ፈገግ እንዳልኩ
ነበር አሁን ሁልጊዜ እንደምትፈልገው አይነት ለብሳለች የምትወዳቸውን
ቀለማት እግሮቿ ላይ ሀምራዊ ካልሲ ከነጭ አዲስ ስኒhር ጋር አለበስኳት “በጣም ታምሪያለሽ ኬሪ” እሷም ብሩህ ቀለም ያለው ልብስ በመልበሷ ተደስታለች።

ቀጥሎ ኮሪን ቀይ አጭር ሱሪና ኪሱ ቀይ የሆነ ነጭ ካኒቴራ አለበስኩት፡

ከዚያ “አንተንም ላልብስህ ክሪስቶፈር?” ስል ቀለድኩ

“ልብሽ ከፈቀደ ቆዳዬን ገልብጠሸ ማልበስ ትችያለሽ”

“ጋጠ ወጥ አትሁን!”

ኮሪ ሌላ የሙዚቃ መሳሪያ መጣለት፡ እሱ የሙዚቃ መሳሪያውን እየነካካ ኬሪ
ትዘፍንለታለች።

ሁሉም ነገር ላይ ያለኝን ደስታ የሚወስዱብኝ እግዚአብሔር የሰጠኝ ክፉ
ሀላቦች ነበሩኝ: ማንም የማያያቸው ከሆነ ቆንጆ ልብሶች ምን ይጠቅማሉ?
እኔ የምፈልገው በሚያምሩ ወረቀቶች ያልተጠቀለሉ፣ በሪቫን ያልታሰሩ፣ ሱቆች ውስጥ በካርቶን ያልተቀመጡ ነገሮችን ነው፧ የምፈልገው ገንዘብ
ሊገዛቸው የማይችላቸውን ነገሮች ነው: ጸጉሬ ከፊቴ በአጭሩ መቆረጡን
አስተውላለች? እንዴት እንደሳሳ አይታለች?የገረጣና የሳሳው ቆዳችንን እያየች
ጤነኛ እንደሆንን ታስባለች?

ለእኔ የተባሉትን ቆንጆ ቆንጆ ልብሶች ተመለከትኩ፡ ሰማያዊ ቬልቬት ቀሚስ፣ ለግብዣ የሚለበስ ሮዝና ሰማያዊ የምሽት ጋዋን አብሮት ከሚሄድ ጫማ ጋር፧ እዚያ ተቀምጬ ከረሜላውን እየበላሁ የሆነ ነገር ትዝ አለኝ፡፡
“ኢንሳክሎፒዲያ!” ለዘለዓለም እዚህ ልንኖር ይሆን?

የስኳር ከረሜላ በጣም ከምወዳቸው ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ይህንን የከረሜላ
ካርቶን ያመጣችው ለኔ ነበር ለኔ፡ እኔ ግን መብላት የቻልኩት አንድ ብቻ
ነበር። ያንንም በጣም በችግር።

የከረሜላው ካርቶን መሀል ላይ ተቀምጦ ክሪስ ኮሪና ኬሪ ከበውት ተቀምጠው
በጣም በመደሰት ከረሜላዎቹን እያጣጣሙ ነበር፡ “ከረሜላዎቹን ሁሉ
መጨረስ አለባችሁ ለረጅም በጣም ለረጅም ጊዜ የማታዩት የመጨረሻ
ከረሜላችሁ ነው፡” አልኳቸው በመረረ ጥላቻ

ክሪስ አየት አደረገኝ ሰማያዊ አይኖቹ ደስተኛና የሚያበሩ ሆነዋል።
እምነቶቹና መተማመኑ ሁሉ እናታችን ለአጭር ጊዜ ባደረገችው ጉብኝት
እንደተመለሱለት ለማየት ቀላል ነበር፡ ስጦታዎቹ እሷ ከዚህ በኋላ ለእኛ ግድ የሌላት የመሆኑን ሀቅ የመደበቂያ መንገድ እንደሆነ ለምን ማየት አልቻለም? ከዚህ በፊት እንደነበርነው አሁን ለእሷ እውነት እንዳልሆንን እኔ
እንዳወቅኩት እንዴት አያውቅም? እኛ ልክ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ እንዳሉት አይጦች፣ ሰዎች ሊነጋገሩባቸው ከማይፈልጓቸው ደስ የማይሉ ርዕሶች ውስጥ ነን፡

“እዚያ ቁጭ ብለሽ የማይናገር ምሰይ” አለ፡ ክሪስ ደስታውን እኔ ላይ እያንፀባረቀ: “እኛ ሶስታችን አይጦቹ መጥተው ከመብላታቸው በፊት አምሮታችንን ስንወጣ አንቺ ከረሜላውን እምቢ በይ: አንቺ ቁጭ ብለሽ ስታለቅሺ፣ ለራስሽ
ስታዝኚና ራስን መስዋዕት በማድረግ ሁኔታችንን መለወጥ እንደምትችይ ስታስመስይ ኮሪ፣ ኬሪና እኔ በልተን ጨርሰን ጥርሶቻችንን እናፀዳለን፡ ቀጥይ
ካቲ አልቅሺ! ሰማዕት ሁኚ! ተሰቃይ! ጭንቅላትሽን ከግድግዳ አላትሚ! ጩኺ እኛ እንደሆነ ወንድ አያታችን እስኪሞት እዚህ መሆናችን የማይቀር ነው::በዚያ ላይ ከረሜላዎቹ ሁሉ ያልቃሉ! ያልቃሉ! ያልቃሉ”
👍423
እየቀለደብኝ በመሆኑ ጠላሁት! ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ራቅ ያለው ጥግ ላይ ሄድኩና ጀርባዬን ሰጥቻቸው አዳዲስ ልብሶቼን መለካት ጀመርኩ። ሶስት
የሚያማምሩ ቀሚሶች ናቸው: አንድ በአንድ ለካኋቸው እስከወገቤ ድረስ
በቀላሉ ይዘጋሉ። ነገር ግን ቀሚሱ ደረቴ ላይ ሲደርስ ከኋላ ያለው ዚፕ
አይዘጋም፡ “ለመዝጋት ስሞክር አንደኛውን ቀሚስ ቀደድኩት። የገዛችልኝ ቀሚሶች ሁሉ አላየችሽም እያሉ የሚጮሁ የልጅ ቀሚሶች ነበሩ። ሶስቱንም
ቀሚሶች ወለሉ ላይ ጥዬ ወደ ሱቅ እንዳይመለሱ አድርጌ በእግሮቼ
ረጋገጥኳቸው፡

ክሪስ ከመንትዮቹ ጋር ወለሉ ላይ ተቀምጦ እየሳቀብኝ ነው “የሚገዛልሽን ነገር
በዝርዝር ፃፊ” ሲል ቀለደብኝ፡ “የጡት መያዣ መልበሻ ጊዜሽ ነው: በባዶ ወዲህ ወዲያ አትበይ የወገብሽንም ቁጥር ፃፊ”
ደስተኛ ፊቱን በጥፊ ማጮል በቻልኩ! “ዝጋ!” ጮህኩበት። “ለምንድነው ዝርዝር ፅፌ እናታችንን ምንም ነገር የምጠይቀው? ብታየኝ ኖሮ ምን ልብስ እንዳለኝና ምን መልበስ እንደሚገባኝ ታውቅ ነበር፡ የማዘውን የጡት መያዣ
መጠን እንዴት አውቃለሁ? መቀነትም አልፈልግም! አንተ የሚያስፈልግህ ሀፍረትህን የምትሸፍንበትና ቁራጭ ጨርቅና በጭንቅላትህ ውስጥ ከመፅሀፍ
የማይገኝ ትንሽ ስሜት ነው!” የደነገጠ ገፁን ስመለከት ደስ አለኝ።

“ክሪስቶፈር” አልኩ እየጮህኩ፤ ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም አንዳንድ ጊዜ እናቴን እጠላታለሁ! ያ ብቻ አይደለም አንዳንዴ አንተንም እጠላሀለሁ አንዳንዴ ሁሉንም ሰው በተለይ ራሴን እጠላዋለሁ! አንዳንዴ በሞትኩ ብዬ
እመኛለሁ: ምክንያቱም እዚህ ቦታ በቁም ከመቀበር መሞት ይሻላል! እኛ የበሰበሰ፣ የሚራመድ፣ የሚያወራ አትክልቶች ነን!...

ይቀጥላል
17👍6
በህይወት መንገድ ላይ…
ምዕራፍ-7
(በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)
///
የሠው ልጅ ከሌላው እንስሳ የሚለይበት አንድና አበይቱ ነገር ተስፋ በማድረግ ችሎታው ነው። የሠው ልጅ ህይወት ከተስፋ ጋር ጥብቅ የሆነ ሚስጥራዊ ቁርኝት አለው።አንድ በሬ ፊት ለፊቱ የሚፈሰው ወንዝ ጋር ደርሶ ውሀ በመጠጣት ከጥሙ እንደሚረካ ደመነፋሳዊ ተስፋ የማድረግ ችሎታ ሊኖረው ይችላል።የሠው ልጅ ተስፋ የማድረግ ችሎታው ግን በይዘትም በመጠንም እጅግ ውስብስብ በምናባዊ ትዕይንት የተገመደ ነው...ህይወት በአብዛኛው ኢተገማቾች ሲሆኑ..የሰው ልጅ ተስፋ የሚያደርገው የእለት ጉርሱንና የአመት ልብሱን ወይንም ምቾቱንና ድሎቱን በተመለከተ ብቻ አይደለም ከሞት ብኃላ ስላለው መንፈሳዊም ህይወት ጭምር የማለምና ተስፋ የማድረግ ልዩ ችሎታ አለው።እኛም ይሄው ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ሆነን እራሱ ተስፋ ማድረጋችንን ቀጥለናል፡፡
በመጀመሪያ የቀረንን ሬሽንና ውሀ ከዋሻው ወዲያማዶ ላለችው ኤደን እናቀብላት በሚለው ተስማማንና አንድ በአንድ በማቀባል አጠናቀቅን ፤አሁን ተራ በተራ እኛም ወደ እሷ ለመሸጋገር ዝግጁ ሆን፡፡
‹ሰላም አንቺ ቅደሚ››
‹‹ምነው እኔ ልቅደም ስትል አልነበረም እንዴ?››
‹‹አዎ ብዬ ነበር አሁን ግን ሀሳቤን ቀየርኩ.ለደቂቃም ቢሆን ከዚህች ሴይጣን ጋር ብቻዬን እዛ መሆን እፈራለሁ፡፡››
‹‹እና እኔ ልቅደም?››
‹‹አዎ ቅደሚ››
አዎ እሷን ገፍተን አሻገርናት…በመቀጠል እኔ ተሸገርኩ.፤ቀጥሎ ትንሽ ቢያስቸግርም በሪሁን ተሸገረ..አሁን ጋሽ አህመድ ብቻ ቀረ..ጭንቅለቱን ቀድሞ ወደእኛ አሾለከ ግዙፍ ትከሻው ግን አንቆ ያዘው ፡፡ ብንጎትተውም እሱም እራሱን ለመርዳት ቢፋተግም ንቅንቅ የሚል ነገር ጠፋ‹‹ …ምን ይሻላል?›አይዳ ጠየቀች
‹ጋሽ አህመድ ወደኃላ ተመለስና መሽሎኪያውን ትንሽ ሰፋ እናድርገው››ሀሳብ አመጣው፡፡
‹‹አዎ ወደኃላ ተመለስ›በሪሁንም በሀሳቤ ተስመማማ….አይዳ በጭንቀት እጇቾን እያፋታገች ነው...ሰላም ፀጥ ብላለች. በፊቷ ላይ .ምንም አይነት የተለየ ስሜት አይነብባትም…ዝም ብላ ብቻ ከእኛ ፈንጠር ብላ እጆቾን አጣምራ አንጋቷን ወደመሬት ቀብራ ቆማለች
ጋሽ አህመድ ምክራችንን ሰምቶ ወደኃላው ተመለሰ...ቀድመን ወደ እኛ ያሻገርነውን ብረት እኔና በሪሁን አንድ አንድ ያዝንን…እና በተቻለን አቅም በጥንቃቄ መቆፈር ጀመርን…
ግን ከጨለማው ሲኦል የተላከ መአት ሲወርድብን ሁለት ደቂቃ አልሞላም….መለከት ሳይነፋ፤፤ከበሮ ሳይመታ ድንገት ነጓድጓድ የመሰለ ደምፅ…ምፅአት የመሰለ መደርመስ ተከሰተ..ሁለችንም በደመነፍስ ወደኃላችን ተስፈንጥረን በመሸሽ ከናዳው ለማምለጥ ሞከርን….እኛ ቢሳካልንም ጋሽ አህመድ ግን ሙሉ በሙሉ አፈር ለብሷል…
‹‹ወይ ጋሽ አህመድ…ወይኔ ሞተ ወይኔ ወንድሜን…. ››አይዳ በማያቆርጥ ጩኸት ዋሻውን አናጋችው፡፡በሪሁን ወደኃላ ከሸሸበት በመመለስ አፍሩን በእጁም በብረቱም ወደኃላው መበተን ጀመረ...ስራው በማሰብ ሳይሆን በድንጋጤ ነበር የሚከውነው…ጋሽ አህመድን ለማትረፍ ከጊዜ ጋር ግብ ግብ መግጠም….እኔም እሱ እንደሚያደርገው ማድረግ ጀምርኩ...አይዳም ከጩኸትና ከለቅሶ እራሷን ሳትገታ አፈሩን በመናድ ታግዘን ጀመረ….ሰላም ግን ከቆመችበት አልተንቀሳቀሰችም….በቁሟ ተኝታ የተፈጠረውን ነገር አላወቅችም ይሆን እንዴ…?ስል አሰብኩ….ቢሆን ዋናው አጣዳፊ ነገር ስለእሷ ማሰብ ሳይሆን ጋሽ አህመድን ለማዳን የመጨራሻውን ጥረት ማደረግ ነው..
አስር ከሚሆኑ ደቂቃዎች ቡኃላ ‹‹እጁን ያዝኩት.እጁን››በማለት ጮኸች ..አይዳ...እኔና በሪሁን ወደጠቆመችኝ ቦታ ተስፈነጠርንና እጅን ይዘን ለመጎተት ሞከርን፡፡
‹‹ኸረ ይጎዳል ትገነጥሉታላችሁ››
‹ተገንጥሎም ቢሆን መትረፍ ከቻለ እድለኞች ነን ››አልኳት
ግን አሁን በህይወት ማውጣት ችለን እግሮቹ ድቅቅ ቢሉስ እንዴት ነው ከዚህ መታገት በእግሩ ቆሞ መራመድ የማይችል ሰው ይዞ መጎዝና ከዚህ ወጥምድ እራስን ማዳን የሚቻለው…?.የሚል ሀሳብ በአእምሮዬ መጣና ጭንቅ ውስጥ ከተተኝ፡፡
ጋሽ አህመድን ብዙ ጥረት ከአፈሩ አላቀን ማውጣት ቻልን .ግን በድኑን ነው ያገኘነው...ይሄ በህይወቴ ሙሉ በሰው ሞተ ምክንያት ያጋጠመኝ እጅግ መራሩ ሀዘን ነው፡አባቴ ሲሞት እንኳን ምን አልባት ልጅነት ዕድሜዬ ላይ ስለነበርኩ እንደሆነ አላውቅም እንዲህ ልቤ አንቅሽቅሽ እስኪል አላዘንኩም ነበር፡፡ልጆቹ ፊቴ ላይ መጥተው ድቅን አሉ…ከአንድ ወር በፊት እኮ ነው ሶስት ክፍል ሰርቢስ ቤት ሰርቶ የቤት ምርቃት ጠርቶኝ እቤቱ ሄጄ ልጆቹንና ሚስቱን የተዋወቅኩት….እንዴት እንደሚወዳትና እላዩ ላይ ይንጠለጠሉበት እንደነበረ ትዝ ሲለኝ አጥወለወለኝና ባለውበት ቁጭ አልኩ፡፡..እኔ ራሴ በየትኛው ደቂቃ እንደሚያልቅልኝ እርግጠኛ ባልሆንም ውስጤን ግን የጥፋተኝነት ስሜተ እየቦጫጨቀኝ ነው፡፡ጉድጓዱን ስቆፍር ከልምድ ማጣት ያልሆነ አቆፋፈር ቆፍሬ እንዲናድ ያደረኩት እኔ ልሆን እችላለሁ.?በፀፀት እሳት እየተለበለብኩ ነው፡፡
.በሪሁን ሬሳውን እያገላበጠና እያንገላታ ፍርፍር ብሎ እያለቀሰ ነው….ከእሱ ጋር እንደታላቅ ወንድምም እንደጓደኛም ስሚቀራረቡ ከሁላችንም በላይ ማዘኑ የሚጠበቅ ነው፡፡
አይዳ አሁን ዝም ብላላች…ግን ፊቷ ጥውልግልግ ብሏል…የለበሰችው ልብስ ሁሉ አቧራ ከመልበሱ በላይ ቲሸርቷ መሀል ላይ ተቦጭቆ ቀኝ ጡቷ አፈትልኮ ወጥቶ ሙሉ በሙሉ ለእይታ ተጋልጧል….እሷ ግን በሀዘን ከመደንዘዞ የተነሳ ነገሬም ያለችው አይመስለኝም.. በአጠቃላይ ያቺ ሽቅርቅሯ ልጅ ጭቃ አቡኪ መስላለች…ከተዘረፈጥኩበት እንደምንም ተነሳውና የለበስኩትን ጃኬት አውልቄ ወደእሷ ሄጄ ትከሻዋ ላይ አለበስኮት…ቀና ብላ አየችኝና መልሳ አይኗን ሰበረች…በሌላ ጊዜ ቢሆን ይሄኔ ምገባበት እስኪጠፋኝ በተረብ አጥረግርጋኝ ነበር….ወደቦታዬ ተመለሰኩና ቁጭ አልኩ..፡፡
ጃኬቱን አስተካክላ ለበሰችና ዚፑን በመቆለፍ ጡቶቾን ወደእስራታቸው መለሰቻቸውና ቀጥታ ወደሰላም ተራመደች …ተጠጋቻት‹‹ታውቂ ነበር አይይል?››አለቻት፡፡
‹‹ምኑ ነው የምተውቀው?››ግራ ገብቶኝ ጣልቃ ገባው፡፡
‹የሆነ አደጋ እንደሚከሰት ታውቅ ነበር?.››
‹‹እውነቷን ነው እንዴ?››በሪሁን አፈጠጠባት
‹አዎ.. .ወደኃላ ተመለስ ብላችሁት ሲመለስ ከዛ በህይወት መውጣት እንዳማይችል ተሰምቶኝ ነበር››
‹‹ታዲያ ለምን አላስጠነቀቅሺም?››
‹ማስጠንቂያው ለውጥ ላያመጣ ለምን ነግራችሆለው..?ቢያንስ የምትወዱትን ሰው ለማትረፍ መጣራችሁ እራሱ አንድ ነገር ነወ››
በሪሁን ከተቀመጠበት ተነሳና ‹‹.ተቀልጂያለሽ እንዴ…?ቢያንስ ወደኃላ ተመለስ አንለውም ነበር...ቀስ ብለን እየጎተትን ስበን እናወጣው ነበር››
‹‹ነገርኮችሁ እኮ….ወደፊትም ወደኃላም ቢመለስ አይተርፍም ነበር..ዛሬ የተቆረጠለት የመጨረሻ ቀኑ ነበር››
‹‹ቆይ ይሄ ትከሻዬ ነገረኝ የምትይው ነገር ምንድ ነው?›
‹‹የእምነት ጉዳይ ነው..ብነግራችሁም ወይ አትረዱኝም አልያም አታምኑኝም፡፡
‹‹ሞክሪን….ማመን ያለማመኑን ለእኛ ተይልን››
‹‹እንግዲያው ትከሻዬ የምላችሁ ጠባቂ መላኬን ማለቴ ነው፡፡እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ጠባቂ መልዐክ አለው.. ግን ሁላችንም በሚባል መልኩ ትኩረት አንሰጠውም...እንዳሉንም የምናወቅ ጥቂቶቻቸን ነን..እኔ ግን ያው እንደምታውቁት መንፈሳዊ ልምምድ ስላለኝ ያው ››
👍15👏2