“ሁሉም ጊዜው ሲደርስ ቢገለጽም አልመረጥኩም አልልሽም ባርባራ
ባርባራ ያንገት ልብሷን የምታስተካክል መስላ ይዞት የነበረውን እጅዋን አስለቀቀች የልቧ ምት ጨመረ ሰውነቷ ከእግር እስከ ራሷ የተረበሸች መሆኗን እንዲያው ቅባትም አልፈለገችም ከሷ ሌላ ያገባ ይሆናል የሚል ግምት አልነበራትም "
“ ፊትሽ ተለወጠብኝሳ... ባርባራ ? ፈጠንኩብሽ መሰለኝ ? ” አላት "
ያልሰማችው መስላ ክንዱን ከክንዷ አጠላለፈችና ሲሔዱ ሚስተር ካርላይል የድንበሩን ቅጠሉንም ሣሩንም በያዘው ጥላ ያለ ልቡ መጨፍጨፉን እየጨመረ ሔደ " ብዙ አልቆየም የጥላው እጀታ ለሁለት እንክት አለ
“ እኔ እንደምትሰብረው ዐዉቄ ነበር '' አለችው ባርባራ ' ያዘነ መስሎ ሰባራውን ሲመለከት አየችውና ግድ የለም ሌላ አመጣልሻለሁ ” አለና ዐይነቱን በማስታወሻ አሰፈረ "
'' ለምንህ ነው ? " አለችው "
የጻፈውን በዐይኗ አንድታይ አስጠጋላት “ ቡና ዐይነት ጃንጥላ እንዳልረሳው ብዬ ነው . . . ባርባራ
ባርባራ የጻፈውን ስትመለከት ፒያኖ ' ሣህን ከዝርዝሩ ተጽፈው አየች “አየሽ ለንደን ስሔድ ማምጣት ያለብኝን ነገሮች እንዳልረሳ ለመጠንቀቅ ነው
“ለንደን ? እኔኮ ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ወደ ካሰል ማርሊንግ የምትሔድ መስሎኝ ነበር -
“ ሚስተር ካርላይል ' ' ለንደን ' የሚለው ቃል ሳያስበው አምልጦት የወጣ ስለ ነበር ' ምናልባት ካስል ማርሊንግም ለንደንም እደርስ ይሆናል ጨረቃይቱ እንዴት ደምቃለች ! አየሽ ... ባርባራ ? ” አላት
“ በጣም በድምቀቷና በሰማዩ ጥራት ምስጢርህን ማንበብ ቻልኩ " ፒያኖ የምግብ ገበታ ዕቃ ግን ምን ሊያደርግልህ ነው ?”
“ለኢስት ሊን ! ”
“ ነው ? ቤቱን ለሚከራዬት ? '' ኣለችና ስለ እቃዎቹ የነበራት ጥርጣሬ እዚህ ላይ አበቃ "
እንዲህ እያሉ ደረሱና ሚስተር ካርይል በሩን ከፍቶ ያዘላት እናቷንም ኣይቷት እንዲሔድ ከቤት እንዲገባ ብትጠይቀው መቸኮሉን ነግሯት በሩን በስተኋላው ሳብ አድርጎ ዘግቶ ሊሔድ ሲል ከሱ የመለየት ነር ጨነቃት
“ ሳምንት ትቆያiህ ? ''
“ እቆይ ይሆናል " አየሽ የዣንጥላውን ስባሪ ይዠብሽ ልሔድ ነበር በይ እንቺ
ሰባራውን ሳልሰርቅ አዲስ እገዛልሻለሁ ”
“ አርኪባልድ . . . አንድ ነገር ልጠይቅህ ከተመኘሁ ብዙጊዜዬ ነበር '' አለችው የጥላውን ስባሪዎች ተቀብላ በዐጸዱ በኩል ወደ ነበረው ቀጭን መንገድ ወረ
ወረችና ጭንቀቷን ለማመቅ እየተጣጣረች “ እንዲያው አትታዘበኝና አምና የወርቅ ሐብልና ከሐብሉ ጋር የሚታሰር የማስታወሻ መያዣ የወርቅ ሙዳይ እንደሰጠኸኝ ታስታውሳለህ ? "
“ አዎን " እና ምን ሆነ ? ”
ከዚች ሙዳይ ውስጥ የአና የሪቻርድን ጸጉሮች አኑሬበታለሁ " አሁንም እንደ ምታየው ቦታ አለው " አለችና እንዳሰረችው ከፍታ አሳየችው "ስለዚህ እኔ የምርጥ ወዳጆቼን መታሰቢያ ይዤ ሁልጊዜ ላስታውስበት ስለ ፈለግሁ ያንተንም አንዲት ጸጉር ብትሰጠኝ
" ጸጉሬን !”አላት ጭንቅላቱን ቆርጦ እንዲሰጣት የጠየቀችው ይመስል ድንግጥ ብሎ "
“ ምን ይጠቅምሻል ? ''
እ. . . . . እኔ የምወዳቸውን ሰዎች ማስታሻ ለመያዝ ስለፈለግሁ ብቻ ከዚህ ሌላ ለምንም አልፈልገውም
እሱ የመንፈሷን መጨነቅ ለዚህ ጥያቄ ያበቃትን የውስጧን ስሜት ልብ ብሎ አለተገነዘበም ስለዚህ ጥያቄዋን ሰምቶ አዩ ጉድ ምን
ምን ነው ትናንት ጸጉሬን ሳልስተካከል ነግረሽኝ ቢሆን ኖሮ የተቆረጠውን አፍሼ እልክልሽ
አልነበረም በይ ልጄ ....ፊርማዬንና ጸጉሬን በመጠየቅ ወደ ወሊንግተን ከፍ ከፍ አታዳርጊኝ
ብሎ ተንኮል በሌለበት ፡ በቅን ልቡና ቀልድ መለሰላትና !በይ ከዚህ በላይ መቆየት አልችልም ደህና እደሪ '' ብሏት ሔደ ....
💫ይቀጥላል💫

👍28
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
...ለመሄድ እየተነሳች "አሁን መሄዴ ነው"ስትል መንትዮቹ ተላቀሱ
“እማዬ አትሂጂ! አትተይን! ሁለቱም በትናንሽ ክንዶቻቸው እግሮቿ ላይ ተጠመጠሙ: ወደ እኔ እየተመለከተች “የምችለውን እንደማደርግ ቃል እገባለሁ እናንተ መውጣት የምትፈልጉትን ያህል እኔም ከዚህ ቤት እንድትወጡ እፈልጋለሁ:"
በሩ ጋ ስትደርስ የቆሰለ ጀርባዋን ማየታችን ምን ያህል አያታችን ጨካኝ እንደሆነች እንድናውቅ ስለሚያደርገን ጥሩ መሆኑን ነገረችን፡ “ስለእግዚአብሔር
ህጎቿን ጠብቁ: መታጠቢያ ቤት ስትጠቀሙ ስርአት ይኑራችሁ። ክፉ የምትሆነው ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእኔ ለሆኑት ሁሉ እንደሆነ አስታውሱ”አለች ከዚያ ለሁላችንም ክንዶቿን ዘረጋችልንና ሁላችንም ወደ እሷ ሮጥንና
አቀፍናት። “ሁላችሁንም በጣም እወዳችኋለሁ:” ስትል ተንሰቀሰቀች። “ይሄንን ልብ በሉ… እምላለሁ ከዚህ በፊት ከነበረው በበለጠ ሁኔታ ምን ያህል እንደምወዳችሁ አሳያችኋለሁ፡ እኔም ልክ እናንተ የሆናችሁትን ያህል እስረኛ ነኝ። ልክ እናንተ በሁኔታዎች እንደተጠመዳችሁት እኔም እንደዚያው ነኝ። ዛሬ ማታ ደስ የሚል ሀሳብ እያሰባችሁ ወደ መኝታችሁ ሂዱ። ምንም ያህል መጥፎ ቢመስልም እንኳን ሁሉም ነገር ያን ያህል መጥፎ አይደለም።
ተወዳጅ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። አንድ ወቅት ላይ አባቴ እጅግ በጣም ይወደኝ ነበር፡ ያ እንደገና እኔን የመውደዱን ነገር ቀላል ያደርግለታል ብዬ አስባለሁ፤ አይደል እንዴ?” አለችን።
አዎ አዎ ያደርግላታል።
“እኔ ነገ እዚያ ትምህርት ቤት ከገባሁ በኋላ እዚህ ክፍል ውስጥ ለሰዓታት ስትቀመጡ እንዳይሰለቻችሁና ደስተኞች እንድትሆኑ ወደ ሱቅ እሄድና አዳዲስ አሻንጉሊቶችና መጫወቻዎች ገዝቼላችሁ እንደምመጣ አስታውሱ፡ አባቴ
እንደገና እንዲወደኝና ስለሁሉም ነገር ይቅርታ እንዲያደርግልኝ ለማድረግ ብዙ ጊዜ አይወስድብኝም:”
“እማዬ… ግን ለእኛ መጫወቻ ለመግዛት የሚሆን በቂ ገንዘብ አለሽ?” አልኳት
“አዎ” አለች በፍጥነት። “በቂ ገንዘብ አለኝ፡ አባቴና እናቴ ኩሩ ሰዎች ናቸው በጓደኞቻቸውና በጎረቤቶቻቸው ፊት አንሼም ሆነ የቆሸሸ ለብሼ እንድታይ
አይፈልጉም፡ ስለዚህ ገንዘብ ይሰጡኛል፡ እኔ ደግሞ ለእናንተ መጫወቻ እገዛላችኋለሁ: የሚተርፈኝን እያንዳንዱን ደቂቃና ያልተጠቀምኩበትን እያንዳንዱን ብር አስቀምጠውና በፊት እንደነበርነው የራሳችን ቤት ሲኖረንና እንደገና አንድ ቤተሰብ ስንሆን እንድንጠቀምበት እቅድ አወጣለሁ።አለች
እነዚህ ከመውጣቷ በፊት የነገረችን ቃላቶች ነበሩ: ከዚያ በሩን ዘጋችና ቆለፈችው: ከተቆለፈ በር ጀርባ ሁለተኛ ምሽታችን ነበር።
አሁን ብዙ ነገር አውቀናል ... ምናልባትም በጣም ብዙ።
እናታችን ከሄደች በኋላ እኔና ክሪስ ሁለታችንም አልጋዎቻችን ውስጥ ገባን::ክሪስ አይኖቹ በእንቅልፍ እንደተዳከሙ ወደ እኔ ዞሮ አይኖቹን እየጨፈነ “ደህና እደሪ ካቲ ቁንጮቹ እንዳይበሉሽ አድርጊ: ብሎ አጉረመረመ።
ክሪስቶፈር ከተኛ በኋላ እኔም የኬሪን ትንሽዬና ሞቃት ሰውነት እቅፍ አድርጌና ፊቴን ወደ ለስላሳው ፀጉሯ ዝቅ አድርጌ ተኛሁ።
እንቅልፍ ሊወስደኝ ስላልቻለ ወዲያው በጀርባዬ ተኛሁና ወደ ላይ አፈጠጥኩ::እዚህ ግዙፍ ቤት ውስጥ ያለው ፀጥታ ተሰማኝ በግዙፉ ቤት ውስጥ ከሩቅ
የሚሰማ የስልክ ጥሪ ወይም ደግሞ የወጥ ቤት ዕቃዎች መንኳኳት ድምፅም ሆነ ምንም አይነት እንቅስቃሴም የለም ከውጪ ውሻ እንኳን ሲጮህ ወይም መኪና ሲያልፍ ድንገት ብልጭ የሚያረገው መብራት እንኳን በትልልቆቹ መጋረጃዎች አልፎ አይታይም።
የማንፈለግ፣ የተቆለፈብን.. ከሰይጣን የተፈለፈልን መሆናችንን የሚነግረኝ መጥፎ ሀሳብ መጣብኝ፡ ሀሳቦቹ በጭንቅላቴ እየተመላለሱ አበሳጩኝ።
ከጭንቅላቴ ለማስወጣት የሆነ
መንገድ መፈለግ አለብኝ፡ እናታችን ትወደናለች…ትፈልገናለች ጥሩ ፀሀፊ ለመሆን እየሞከረች ነው: አያቶቻችን ከእኛ ሊያርቋት የሚፈልጉበትን መንገድ እንደምትቋቋም አምናለሁ።
“እባክህ እግዚአብሔር እማዬ ፈጥና እንድትማር እርዳት” ብዬ ፀለይኩ ክፍሉ በጣም የሚሞቅና የሚያስጨንቅ ነው: ውጪ ንፋሱ ቅጠሎችን ሲያንቀሳቅስ ይሰማኛል ግን እዚህ ገብቶ እኛን ለማቀዝቀዝ አልቻለም የንፋሱ ድምፅ ውጪው ቀዝቃዛ እንደሆነ እና እኛም መስኮቶቹን መክፈት ብንችል ወደ ውስጥ መግባት እንደሚችል እየነገረን ነው: ንፁህ አየር በመናፈቅና በመመኘት
ተነፈስኩ። ተራራማ ቦታ በበጋም ጭምር ሁልጊዜ ቀዝቃዛ እንደሆነ እናታችን ነግራን አልነበረም? አሁን እኮ በጋ ነው ግን መስኮቶቹ ሁሉ ስለተዘጋጉ አይቀዘቅዝም:
በደብዛዛው ብርሃን ክሪስ በሹክሹክታ ጠራኝና “ምን እያሰብሽ ነው?” አለኝ።
“ስለ ንፋሱ” አልኩት
“እንደዚያ አይነት ሀሳብ እንደምታስቢ አውቃለሁ"
“ሌላም ሀሳብ አለኝ የሚያንሾካሹኩት ነፍሳት እንደሞቱ ሰዎች ነፍሶች የሆነ ነገር ሊነግሩን እየሞከሩ ነው:"
ተናደደ “አሁን አድምጪኝ ካተሪን ዶል (አንድ ቀን እንደምጠቀምበት
ያቀድኩት ስም ነው፡) ተኝተሽ አስፈሪ አሳቦችን ከማሰብ፣ እያንዳንዱን ሰዓት እንዳመጣጡ እንውሰደውና የሚቀጥለውን ለማሰብ ቆም እንበል። ይህንን ዘዴ
መጠቀም በቀናትና በሳምንታት ከማሰብ እጅግ የሚቀል ነው ስለ ሙዚቃ፣ስለ ዳንስና ስለ መዝፈን አስቢ ሙዚቃ አእምሮሽ ውስጥ ሲደንስ ሀዘን እንደማይሰማሽ ስትናገሪ ሰምቼ የለ?”
“አንተስ ስለምን ታስባለህ?”
“እንቅልፌ በደንብ ካልመጣ ብዙ አይነት ሀሳቦችን አስባለሁ ግን አሁን እንደምታይኝ መልስ ለመስጠት ደክሞኛል። ለማንኛውም አላማዬን ታውቂዋለሽ ከአሁን ጀምሮ ለመጫወት ጊዜ ስለምናገኝለት ጨዋታ አስባለሁ” አፋሽኮ
ከተንጠራራና ወደ እኔ እያየ ፈገግ ካለ በኋላ “አጎቶች የወንድሞቻቸውን ልጆች አግብተው ስለሚወልዷቸው ሸኮና፣ ጅራትና ቀንዶች ስላሏቸው ልጆች ምን ታስቢያለሽ?”
“እንዴ! ሁሉንም እውቀቶች ፈላጊና የወደፊት ሀኪም አይደለህ እንዴ…
በህክምና ሳይንስ የሚሆን ይመስልሀል?”
“በፍፁም!” መለሰልኝ፡ ልክ በዚያ ርዕስ በደንብ የተማረ ይመስል ነበር። “እንደዚያ ቢሆን ኖሮ አለም ዲያቢሎስን በሚመስሉ ፍጥረታት የተሞላች ትሆን ነበር፡ እና እውነቱን ለመናገር ዲያቢሎስን አንድ ጊዜ ላየው እፈልጋለሁ”
“እኔ ሁልጊዜ በህልሜ አየዋለሁ።”
“አሀ! አንቺና ያበዱ ህልሞችሽ! ግን መንትዮቹ አልገረሙሽም? ያቺን ግድንግድ አያታችንን እንዴት በድፍረት እንደተጋፈጧት… እኔማ በጣም ኮርቼባቸዋለሁ፡ እንደ ንዴቷ. የሆነ የከፋ ነገር ታደርጋለች ብዬ ፈርቼ ነበር።”
“ያደረገችው ነገር የከፋ አይደለም እንዴ? ኬሪን እኮ ፀጉሯን ይዛ ነው
ያንጠለጠለቻት። እንዴት እንደሚያም ባወቅክ… ኮሪን ደግሞ በጥፊ መትታ ጣለችው። ያም ያሳምማል ከዚህ የበለጠ ምን ትፈልጋለች?"
“የከፋ ነገር ማድረግ ትችል ነበር"
“ራሷም እብድ ሳትሆን አትቀርም”
“ልክ ነሽ” እያንቀላፋ ነው፡
“መንትዮቹ ህፃናት ናቸው ኮሪ ኬሪን እየተከላከለ ብቻ ነበር። ታውቃለህ እሱ ስለሷ፣ እሷ ስለሱ እንዴት እንደሚሆኑ?” አመነታሁ። “ክሪስ እናታችንና አባታችን በፍቅር በመውደቃቸው ልክ የሰሩ ይመስልሀል? ለማስቆም የሆነ
ነገር ማደረግ አይችሉም ነበር?”
“አላውቅም: የማይመች ስሜት ስለሚያሳድርብኝ ስለዚያ አናውራ”
“ለዚያ ነው ለካ ሁላችንም ሰማያዊ አይኖችና ወርቃማ ፀጉር የኖረን”
“አዎ” አፋሸከ “የድሬስደን አሻንጉሊቶች እኛ ነን፡”
“ልክ ነህ። ሁልጊዜም ቀኑን ሙሉ መጫወት እፈልግ ነበር። እና አሁን
እናታችን ያንን አዲሱን መጫወቻ ስታመጣልን ቢያንስ ጨዋታውን ለመጨረስ በቂ ጊዜ ይኖረናል።”

👍33🥰5❤2👏1😁1
“እና መንትዮቹ ባንከኞች እንዲሆኑ እናስተምራቸዋለን”
“መጀመሪያ መቁጠር ልናስተምራቸው ግድ ነው''
“አዲስ ነገር አይሆንባቸውም: ምክንያቱም ፎክስወርዞች ስለ ገንዘብ ያውቃሉ።”
“እኛ ፎክስወርዞች አይደለንም:"
“ታዲያ ማን ነን?”
“ዶላንጋንገሮች ነን!
“እሺ… እንደፈለግሽ!” አለኝና “ደህና እደሪ” ብሎኝ ተኛ።
እንደገና አልጋው ጎን ተንበረከኩና ለመፀለይ እጄን አገጬ ስር አድርጌ በፀጥታ መጸለይ ጀመርኩ፡ ለመተኛት ስጋደም ነፍሴን እንዲጠብቃት ለጌታ
ፀለይኩ. ግን ከመንቃቴ በፊት ብሞትስ? ነፍሴን ስለመውሰድ ምንም ማለት አልቻልኩም: ከዚያ ክሪስንና መንትዮቹን እንዲባርካቸው፣ አባቴንም ባለበት
በመንግስተ ሰማያት ውስጥ እንዲባርhው ፀለይኩ ከዚያ እንደገና ወደ አልጋዬ ውስጥ ስመለስ አያትየው ትናንት ማታ ጥሩ ልጆች ከሆንን ስለምታመጣልን ኬክ ወይም ኩኪስና አይስክሬም በከፊል ቃል
ስለመግባቷ ማሰብ ጀመርኩ።
እና ጥሩ ልጆች ነበርን᎓
ቢያንስ ኬሪ መረበሽ እስክትጀምር ድረስም ቢሆን አያትየው ወደ ክፍሉ ጣፋጭ ይዛ አልመጣችም ነበር በኋላ ላይ ጣፋጭ የማይገባን እንደምንሆን
እንዴት ልታውቅ ቻለች?
“አሁንስ ምንድነው የምታስቢው?” ሲል ክሪስ እንቅልፍ በያዘው ድምፅ ጠየቀኝ፡ የተኛ መስሎኝ ነበር ለካ እሱ እያየኝ ነው:
“ምንም አይደል አያትየው ጥሩ ልጆች ከሆንን እንደምታመጣልን ስለነገረችን አይስክሬም፣ ኬክና ኩኪስ እያሰብኩ ነበር።” አልኩት።
“ነገም ሌላ ቀን ነው፡ ተስፋ አትቁረጪ ምናልባት መንትዮቹ ነገ ውጪ የመውጣቱን ነገር ይረሱት ይሆናል᎓ አንድን ነገር ረጅም ጊዜ አያስታውሱም:"
“እውነትህን ነው። አባታችን የሞተው ገና ያለፈው ሚያዚያ ላይ ቢሆንም እነሱ ረስተውታል። ኮሪና ኬሪ እንደዚያ የሚወዳቸውን አባታቸውን እንዴት በቀላሉ
እንደረሱት ይገርማል። እኔ ልረሳው አልችልም ረስቼውም አላውቅም፧
አሁን በግልፅ ባላየውም ... መኖሩ ግን ይሰማኛል።....
✨ይቀጥላል✨

👍20❤17
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
....እሱ የመንፈሷን መጨነቅ ለዚህ ጥያቄ ያበቃትን የውስጧን ስሜት ልብ ብሎ አለተገነዘበም ስለዚህ ጥያቄዋን ሰምቶ አዩ ጉድ ምን
ምን ነው ትናንት ጸጉሬን ሳልስተካከል ነግረሽኝ ቢሆን ኖሮ የተቆረጠውን አፍሼ እልክልሽ
አልነበረም በይ ልጄ ....ፊርማዬንና ጸጉሬን በመጠየቅ ወደ ወሊንግተን ከፍ ከፍ አታዳርጊኝ
ብሎ ተንኮል በሌለበት ፡ በቅን ልቡና ቀልድ መለሰላትና !በይ ከዚህ በላይ መቆየት አልችልም ደህና እደሪ '' ብሏት ሔደ ....
« ቶሎ ቶሎ እየተራመዶ ሔደ ባርባራ ፊቷን በሁሉ አጆቿ ሸፍኖ ቀረች።
"እንዴ ! ምን አደረሁ !ምን አጠፋሁ ?” አለች ለራሷ ድምጿን ከፍ አድርጋ እንደዚህ የግድ የለሽነት ጠባይ ማሳየት የተፈጥሮው ነው ስሜት የለውም
ግን ይደርሳል ዛሬ ማታ እንዴት ያለ ደስታ ሰማሁ ሚስት መምረጡን ቀልድ አስመስሎ የነገረኝ ከልቡ ነው ይኸን ምስጢር ከኔ በቀር ለማንም አልነግረወም እኔን የሚርበኝን ያህል ለኔ የሚያስብልኝን ለማንም አላደረገውም ስለዚ ማንን
እንደመረጠ ለመገመት ብዙ ምርምር አይጠይቅም ግልጽ ነገር ነው " አዬ አርኪባልድ ሚስትህ ከሆንኩ በኋላ ነው ምን ያህል እንደምወድህ የምታውቀው እስከዚያ ድረስ ግን ልታውቅ አትችልም "
የሚያምረውን ፊቷን ቀና አድርጋ ወደ ደማቁ ጨረቃ በተመስጦ ከተመለከተች በኋላ በአትክልቱ በኩል የሚያልፈውን የእግር መንገድ ተከትላ ወደ ውስጥ አመራች ያን ያህል ብቻዋን ስታወራ አንድ ሰው ካጠገቧ ከዱሩ ውስጥ ሆኖ ያያትና ያዳምጣት እንደነበረ አልጠረጠረችም ብትጠረጥር ደግሞ ያን ያህል አትለፈልፍም ነበር ።
ሚስተር ካርላይል ወደ ካስል ማርሊንግ በሔዶ በአምስተኛው ቀን ሚስተር ዲል ለሚስ ካርይል አንድ ደብዳቤ አምጥቶ'“ ፖስተኛው ከኛዎቹ ደብዳቤዎች ጋር አደባልቆ አምጥቶ ነው” ብሎ ሰጣት "
" ምን የሚያስጽፍ ነገር አገኘ ? መቸ እመጣለሁ ይላል ? '' አለችው "።
ብታነቢው ይሻላል .. ሚስ ኮርነሊያ ለኔ በጻፈልኝ ውስጥ ስለ መምጣቱ አላነሳምፀ።
ደብዳቤውን ከፍታና ገልጣ እንዳየችው አጠግቧ ከነበረው ወንበር ዘፍ ብላ ተቀመጠች በሕወይቷ ሙሉ እንደዚያን ጊዜ ደንግጣና ፈዛ አታውቅም "
ካስል ማርሊንግ ግንቦት 1 ቀን
“ ለምወድሽ እህቴ ለኮርኒሊ ከእመቤት ሳቤሳ ቬን ጋር ዛሬ ጠዋት ተጋባን ነገሩን እንድታውቂው ብዬ ባጭሩ በችኮላ ነው የጻፍኩልሽ " ነገ ወይ ከነ ወድያ ከዚህ ሰፋ አድርጌ እጽፍልሻለሁ " ምንጊዜም ውድ ወንድምሽ
አርኪባልድ ካርላይል "
መላ ነው ” አለች ሕሊናዋ ተመልሶ አንደበቷ መናገር ሲችል ሚስተር ዲል የድንጋይ ቅርጽ መስሎ ዝም ብሎ ቆመ "
“ ውሸት ነው ብያለሁ ! "አለችና ደነፋች “ ባንድ እግሩ የቆመ የዝይ
አውራ አስመስሎ የገተረህ ምንድን ነው ? " አለችና በዚያ ክፋት የለሽ ሰወዬ ላይ ዞረችበት "
“ውሸት ነው አይደለም ? "
“ እኔም በጣም ገርሞኛል ... ሚስ ኮርነሊያ ነገሩ ውሸት አይደለም " ለኔም ጽፎልኛል
“ እውነት ሊሆን አይችልም ከአምስት ቀን በፊት ከዚሀ ሲሒድ የማግባት ሐሳብ አልነበረውም "
“ እኛ እንዴት ልናውቅ እንችላለን ... ሚስ ኮርኒ ? ” የሔደው ሊያገባ እንደ ሆነስ ማን ያውቃል እኔ ይመስለኛል " "
“ ሊያገባ መሔድ አያደርገውም መቸ አበደና?ያቺን የሕፃን ወይዘሮ! የለም? የለም አያረገውም "
“ይኸውልሽ በጋዜጣ እንዲወጣ ይኸን ልኮልኛል " ብሎ አንድ ወረቀት ሰጣት መጋባታቸውስ እርግጠኛ ነው ” አላት "
ሚስ ካርላይል ተቀበለችና ዘርግታ ስትመለከተው እጇ በረዶ ሆነ " ልክ የሰነፈ ይመስል ተንቀጠቀጠ
“ ተጋቡ - የኢስትሊኑ አርኪባልድ ካርላይልና የሟቹ ማውንት እስቨርን ኧርል ዊልያም ቬን ብቸኛ ልጅ የሆነችው ወይዘሮ ሳቤላ ሜሪ ቬን በዚህ ወር የመጀመሪ
ያው ቀን ካስል ማርሊንግ ላይ የማውንት እስቨርን ኧርል ነፍስ አባት በተገኙበት ተጋብተዋል ።
ሚስ ካርላይል ወረቀቱን ብጥስጥስ አድርጋ ቀዳ በተነችው " ከዚያ በኋላ ሚስተር ዲል በቃሉ አስታውሶ ጻፈና ወደ ጋዜጣ እንዲወጣ ሰደደው - ይህ በዚህ አበቃ "
“ እሱንም ሆነ እሷን ይቅር አልላቸውም ! አንኗኗራትም " ይህ ልበ ውልቅ ደንቆሮ !ሔደና ገንዘብ የማይጠቅማትን የማውንት እስቨርን ኧርል ልጅ አገባልኛ !
ባለላባ ባርኔጣ ከቁመቷ በላይ ሦስት ሜትር ተርፎ የሚጐተት ቀሚስ አጥልቃ ቤተ መንግሥት የምትመላለስ ቅምጥል !
“ ደንቆሮ እንኳን አይደለም ... ሚስ ኮርነሊያ ” አላት ዲል። "
“እረ ይበሳል ክፉ ሰው ነው” አላችና በእንባና በንዴት መኻል ያዘች ለዚህ ብሎ ሲሔድ አብዶ መሆን አለበት » ትንሽ ጫፍ ሰምቸ ብሆን ኖሮ የዕብደት ወረቀት አስወጥቸ አስይዘው አልነበር " ለመሆኑ የት ሊቀመጡ ነው ? ”
“ ኢስትሊን ይሆናል እንጂ " "
“ ምን ! ” ብላ ጮኸች “ ከካሪው ቤተሰብ ጋር ኢስት ሊን ሊቀመጡ ነው ! አንተም ማበድህ ነው መሰለኝ "
ከካሪው ጋር የነበረው ንግግር ተሽሯል ... ሚስ ኮርነሊያ » ሚስተር አርኪባልድ በፋሲካ ከካስል ማርሊንግ እንደ ተመለሰ የውል መሻሪያ ደብዳቤ የጻፈላቸው መሆኑን ከቀሪው መዝገብ አይቸዋለሁ " ያን ጊዜ ኢስትሊንን ራሱ ሊገባበት የወሰነው ከመይዘሮ ሳቤላ ጋር ጨርሶ ስለመጣ መስለኝ አላት "
ሚስ ካርላይል ይኸን ስትሰማ አፏን ከፍታ ድርቅ ብላ ቆየች » ትንሽ ለቀቅ አድርጓት ሕሊናዋን በከፊል ስታውቅ ገርሞት ወደ ቆመው ሰውዬ ከበስተኋላሙ ጠጋ
አለችና የኮቱን አንገትያ በሁለት እጆቿ ጭምድድ አድርጋ ይዛ ለብዙ ዶቂቃዎች ንጣ ' ንጣ ' ንጣ ለቀቀችው " ያ ምስኪኑና ቀትረ ቀላሉ ሚስተር ዲል እንደዚያ
አድርጋ በዚያ ቁመቷና ኃይሏ ያን ያህል ስታወዛውዘው የትንፋሹ ነገር እስከ መጨረሻ ያከተመለት መስሎት ነበር "
“ባንተ ጭምር ነበር የዕብድ መያዣ ደብዳቤ የማወጣብሀ ... አንተ ሸረኛ ! አንተም አብረህ ዶልተህ በል በል ስትለውና ስትረዳው ነበር "ነገሩን የሱን ያህል
አውቀኸው ነበር "
“ ኧረ እኔ ምንም አላወቅሁም ” አለ ሚስተር ዲል ትንፋሹ ተስተካክሎ መናገር ሲችል „ “ እኔ በዚህ ነገር የለሁበትም ደብዳቤ ደርኝ ሳየው ከመደንገጤ የተነሣ በላባ ብትመችኝ እወድቅ ነበር ”
“ እኮ ለምን እንደዚህ ካለ ጣጣ ገባ ? ገንዘብ የማይጠቅማት ቤሳ የሌላት ሴት አንተስ ብትሆን ኢስትሊንን እንዲያከራይ የመከርከው ምንድነው? አንተ ባታ
ደፋፍረው ኢስትሊን እኖራለሁ ብሎ አያስበውም ነበር
“እኔ ንግግሩን ከመሻሩ በፊት ያወቅሁት ነገር አልነበረም ደሞ ባውቅም እኔ የሚስተር ካርላይል ትእዛዝ ፈጻሚ እንጂ አዛዥ ወይም መካሪ አይደለሁም ኢስት ሊንን ለራሱ መኖሪያ ባያስበው ኖሮ ስሙን • “አርኪባልድ ካርላይል የኢስትሊኑ ተብሎ አያውጅም ነበር " ደሞኮ . . ሚስ ኮርኒ ቢገባበት አቅሙም ይፈቅድለታል
ወለዷ አቻው አትሁን እንጂ የደስ ደስ ያላት ቆንጆና የምትወደድ ልጅ ናት ” አላት"
ደግ ነው " የዕብደቱን ዋጋ ከጐኑ ያገኘዋል "
“ በይ ሚስ ኮርኒ ! ወደ ቢሮ ቶሎ መመለስ አለብኝ ” አለ ሚስተር ዴል ሩን ሲደመድም ። “ በኔ ላይ ይኸን ያህል በመቆጣትሽ ግን በጣም ነው የተናደድኩት "
“ አሁንም እየመጣህ ከፌቴ ብትደቀንብኝ እደግምሃለሁ "

👍18😁1
ብቻዋን ስትቀር ተቀመጠች ፊቷ ድርቅ ምጥጥ አለ እጆቿን ጉልበቷ ላይ ስታደርግ የሚስተር ካርላይል ደብዳቤ ወደቀ " ትንሽ ቆይቶ ፊቷ መለዋወጥ ጀመረ ራሷን በአዎንታ ነቀነቀች አንድ ጊዜ አንድ እጅዋን ቆይታ ሌላውን እያፈራረቀች ስታነሣ በአእምሮዋ ውስጥ በተለያዩ ነጥቦች ክርክር ገጥማ ነበር " ከዚያ ተነሣችና ለባብሳ ስታበቃ ወዶ ጆስቲስ ሔር ቤት አመራች " ጀንበር ሳትጠልቅ በመላ ዌስትሊን የሚደርሰው የጋብቻ ወሬ እንደ ውርደት ሆኖ ተሰማት " በጣም ተወዳጁ
ወንድሟ የበለጠ የምትቀርበውንና የሚወዳትን ለማምጣት ሲል ከዳት " ይኸን ደግሞ ሳይነግራት ከሷ ደብቆ ነበር የፈጸመው ስለዚህ ወሬውን በአራቱ ማዕዘን ለማሠራጨት የመጀመሪያይቱ ለመሆን ፈለገች ሚስ ኮርኒ ከዐጸዱ ስትገባ ባርባራ ከተለመደው ሳሎን ከመስኮት አጠገብ ተቀምጣ ነበር " ኮርኒሊያ የንዴት ሰሜቷ ገና ባይለቃትም ባርባራ ወሬውን ስትሰማ
የምትሆነውን እያሰበች በደረቁ ፈገግ አለች " ባርባራ ለሚስተር ካርላይል የነበራት ፍቅርና የመጋባት ተስፋ ኮርነሊያ ጠለቅ ብላ ታውቀዋለች "
“ ኮርነሊያ ወደዚህ የሚያስመጣ ምን ነገር አገኘች ? ” ብላ አሰበች» አየሩ ያለወትሮው ደስ የሚል ሞቃት ስለነበር ባርባራ የበጋ ልብስ ለብሳ በጣም አምሮባታል - “ እንደምነሽ ? ” አለቻት በመስኮት ተደግፋ " “ የዛሬው አየር እማንም አጓጓት አባባ በሰረገላ ወደ ሊንብራ ወሰዳት ግቢ በሩ እኮ ክፍት ነው
ሚስ ካርላይልምንም ሳትመልስላት ዝም ብላ ገባችና አንድ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለነገር መነሻ ያህል እንደ ማቃሰት ብላ ተነፈሰች።
“ ምነው ምን ነገር አገኘሽ ? አመመሽ እንዴ ? ምን ሆንሽ?” አለቻት ባርባራ።
ኧረ እኔ ምን የማልሆነው ነገር አለኝ ! ስሜቴም ልቤም የውስጡ ወደላይ ተገልብጧል " ከባድ መከራ አግኝቶኛል . . .ባርባራ „ ”
“ አርኪባልድ ደኅና አይደለም እንዴ ? የባቡር አደጋ ደረሰበት ? ”
“ ምነው ባደረገለት • ኧረ ከዚያ የባሰ መዓት ነው ”
“ የካሪው ቤተሰብ ኢስትሊን ሊገባ የነበረውን ሐሳባቸውን ቀየሩ ? ”
“ እነሱ ኢስትሊንን አይገቡበትም ። ሌላ ሊገባበት ስለሆነ ብልሁ ወንድሜ አርኪባልድ ሔዶ ራሱን አጃጅሏል . . . ባርባራ ( እና አሁን ደግሞ ኢስትሊንን መኖሪያው አድርጎ ለመቀመጥ ሊመጣ ነው "
ምንም እንኳን ነገሩ በደንብ ባይገባትም ከፊቷ ይታወቅ ነበር ።
''ውስጣዊ ደስታና እርካታ እንደተሰማት ወሬውን ሽማግሌው ዲል ነው ዛሬ ጧት ድንገት ያመጣልኝ " መብረቅ እንደመታኝ ነው የቆጠርኩት " እኔም ዲልን የኮቱን አንገት ይዠ ክንዴን እስኪያ
መኝ ድረስ ወዝውዤ ወዝውዤ ለቀቅሁት አየሽ . . .አርኪባልድን የተንኮል ሥራ ሲያደፋፍረው ኑሯል " ለኔ ሊነግረኝ ሲገባው ከሱ ጋር ተመሳጥሮ ሸሸገኝ ኮርነሊያ ምን ልትናገር እንዶ ፈለገች አልገባት ብሎ ባርባራ ገርሟት ብዝምታ
ተቀመጠች
"ያቺን ልጅ ታስታውሻት የለ ? ያቺ የማውንት እስቨርን ልጅ ? አሁንም ነጭ በነጭ ለብሳ ' በፈርጦች አጊጣ ' ጸጉሯ እስከ ታች ወርዶ • ልክ በተረት ዓለም ያለች ልዕልት መስላ ከሙዚቃ አዳራሽ ስትገባ በሐሳቤ መጣችብኝ ያሁሉ እንደዚያ ማጌጥ ለራሷ ጥሩ ሊሆን ይችላል " ለኛ ግን አይደለም "
“ እና እሷ ምን ሆነች ? አለች ባርባራ "
“ አርኪባልድ አገባት "
ነገሩ ከልክ በላይ እንዳስደነገጣት የፊቷ መለዋወጥ በግልጽ ቢያሳይባትም እሷም እንደ ሚስ ኮርነሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠራጠረች "
“ ውሸት ነው ... ኮርነሊያ „ ”
“ ስነግርሽ ትናንት የማውንት እስቨን ነፍስ አባት ካስል ማርሊንግ ላይ አጋቧቸው " አስቀድሜ ዐውቄ በሆነና እዚያ ለመሔድ ብችል ኖሮ አለያያቸው ነበር "ዳሩ ግን ምን ይሆናል ትናንት ዛሬ አይሆን !
“ አንድ ጊዜ ይቅርታ አድርጊልኝ እማማ ለሠራተኞቹ እንድ ነገር የሰጠችኝን ትአዛዝ እስካሁን ረሰቸው ስለነበር እንዳፍታ አስረድቸ ልምጣ " አለች ባርባራ '
ለሠራተኞች የሚነገር ትእዛዝ ወዲያው ሔደችና ከፎቅ ወጥታ ከመኝታ ቤቷ ገብታ ወለሉ ላይ ተዘረረች እስካሁን የነበረው ሁኔታ ጭጋጉ ለቀቀውና ጥርት ብሎ
ታየ ከፊቷ ቁመው ይታይዋት የነበሩት የተስፋ መሰላሎች ወደቁ " ልቧ እስኪ ጠፋ ትወደው የነበረችው አርኪባልድ ለሷ ግድ አንዳልነበረው ገባት " ባርባራ እጆቿን ወደላይ አነሣችና ዐይኖቿን ጨፈነች ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ሕይወቷ የፀሐይ ብርሃን እንደ ጠለቀባት ዐወቀችው "ካሰበችው በላይ ጨኻ ተንሰቀሰቀች » በበሩ አጠገብ የነበረች አንዲት ሠራተኛ
ከፈት አድርጋ ስትመለስ ተዘርግታ ስትራዥ አየቻት ነገሩ አካላዊ በሽታ ሳይሆን የእምሮ ጭንቀት መሆኑን የገመተችው ሠራተኛ ጣልቃ መግባቱ ደ ስላልመሰላት በሩን እንዳከፋፈቷ ዝግ አድርጋ ዘግታው ተመለሰች።
ባርባራ የመዝጊያው መያዣ ቀጭ ሲል ሰማችና ድንግጥ ብላ ተነሣች » አንድ ብርጭቆ ውሃ ጠጣች ጸጉሯን በወግ በወጉ አደረገችና ስሜቷንም ለማረጋጋት
በመሞከር እንደ ምንም ብላ የውሸት ፈገግታ እያሳየች ወደ ኮርነሊያ ተመለስች ኮርነሊያ ግን ገና ስላልወጣላት አሁንም ቅሬታዋን መዘክዘክ ጀመረች »
“ሰተት ብሎ እንደዚህ ከመሰለ መዘዝ ከሚዘፈቅ ለአንድ ሁለት ዓመት ከአምሮ ሕሙማን መጠበቂያ ቤት ቢዘጋበት ይሻል ነበር " በፊት ባውቅ ኖሮ ደግሞ
ለዚሁ ወረቀት አስወጣለት ነበር »
ያገባል ብዬ በጭራሽ አላሰብኩትም ደግሞ ብዙ ጊዜ መhሬው ነበር ”
የአቻዎች ጋብቻም አይደለም
“የነሱ ጋብቻ ” አለች ኮርነሊያ “ልክ በተረት እንደሰማነው ቆንጆይቱና አውሬው እንደሚለው ታሪክ ዐይነት ነው እሷ " ትውልዱ እዚያ ላይ' ለራሷ ከልብስ ልብስ ካልማዝ አልማዝ ከግብዣ ግብዣ ስትል ያደገች ያልቃልን ይጐድላልን
የታውቅ እሱልክ እንደ ተረቱ አውሬ ከጭራው በቀር ይኸን ሁሉጣጣ የማያውቅ ከብት
ባርባራ የራሷም ብሶት ባይኖራት ኖሮ በኮርነሊያ አነጋገር ስቃ አታበቃም ነበር
“ ደኅና ' አሁን ከራሴ ውሳኔ ደርሻለሁ ” ነገ ወደ ኢስትሊን ሔጄ እነዚያን የቀጠራቸውን አምስት አሽከሮች አሰናብቼ ዕቃዬንና አሽከሮቼን ይዠ እገባለሁ” እንኳን እሷ ታክላበት ወትሮም ቢሆን በሁለት በኩል ወጭ አይቻልም ፊትስ ቢሆን ኢስትሊንን ይከራዩታል ለተባሉት ለካሪው ቤተሰብ የተቀጠሩ መሰለኝ እንጂ 'ለራሱ የቀጠራቸው መሆናቸውን አስቀድሜ ባውቅ መቸ እንዲህ ይሆን ነበር ።
“ ግን ያንቺ አብረሽ መኖር ደስ ይላታል ? ”
“ዴስ ባይላት የራሷ ጉዳይ ! በይ አሁን እንግዲህ ወሬውን ከነገርኩሽ ልመለስ። እሱ ግን በሞተ ይሻለው ነበር "
ግን እንዳልቀናሽ እርግጠኛ ነኝ ”
“ ሊሆን ይችላል ” አለቻት ሚስ ካርላይል ፊቷን ኮስተር አድርጋ “ አንቺም ብትሆኝ አርኪባልድን እኔ እንዳሳደግሁት አንድ ልጅ አሳድሽ ቢሆን ኖሮና በሕይወትሽ ከሱ በቀር የምትወጂው ምንም ነገር ባይኖርሽ ' እሱ ደግሞ አንቺን በግድ የለሽነት ጣል አድርጎ የበለጠ የምትቀርበውንና የምትበልጥበትን ቆንጆ ሚስት ቢያግባ መቅናትሽ አይቀርም" ....

👍18❤4
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
ሰዓታት የሚመስሉ ደቂቃዎት
ሁሉም ቀኖች በአንድ ዓይነት አለፉ
ጊዜን ተትረፍርፎ ስታገኙት ምን ትሰሩበታላችሁ? ሁሉንም ነገሮች አይታችሁ ከጨረሳችሁ አይኖቻችሁን ምን ላይ ታሳርፋላችሁ? የቀን ህልሞች ወደ ባሰ ችግር ሊመሯችሁ የሚችሉ ከሆነ፣ ሀሳቦቻችሁ የትኛውን አቅጣጫ ሊይዙ ይገባል? ውጪ ስሮጥ፣ ጫካ ውስጥ ለመጫወት ነፃ ስሆን፣ የደረቁ ቅጠሎች
እግሬ ስር ሲንኮሻኮሹ አስባለሁ በአቅራቢያ ባለው ሀይቅ ውስጥ መዋኘትን አልማለሁ፤ ወይም በቀዝቃዛ የተራራ ምንጭ ውስጥ ስለ መንቦራጨቅ አሰላስላለሁ። ነገር ግን የቀን ህልሞች ወደ እውነታው በተመለሱ ጊዜ ልክ
እንደሸረሪት ድር በቀላሉ የሚቀደዱ ናቸው። ደስታዬ የት ነው? ትናንትናዎች ውስጥ? ነገዎች ውስጥ? በዚህ ሰዓት፣ በዚህ ደቂቃና በዚህ ሰኮንድ አይደለም? የደስታ ፍንጣቂ የሚሰጠን አንድ ነገር አለ፣ አንድ ነገር ብቻ እሱም ተስፋ ነው።
ክሪስ ጊዜ ማባከን ከባድ ወንጀል ነው ይላል ጊዜ ዋጋ አለው ማንም በቂ ጊዜ የለውም ወይም በበቂ ሁኔታ ለመማር በቂ ጊዜ አይኖርም ዓለም ወደ እሳት እየሄች እንዳለች ሁሉ “ፍጠኑ! ፍጠኑ!” የሚል ጩኸት ሞልቷል።
እኛ ግን የምናባክነው ጊዜ፣ የማንሞላው ሰዓት፣ የምናነባቸው በሚሊየን የሚቆጠሩ መፃህፍት፣ ሀሳቦቻችንን ክንፍ የሚያስወጣ ጊዜ አለን፡ መፍጠር የሚችል አዋቂ ሰው የሚጀምረው ዝም ብሎ ከመቀመጥ ቅፅበት ነው
የማይቻለውን በማለም ከዚያ እውነት እንዲሆን ያደርገዋል።
እናታችን ቃል እንደገባችው ልታየን መጣች ሰዓታችንን የሚይዙልን
አዳዲስ መጫዎቻዎችና አሻንጉሊቶች ተሸክማ ነበር። ለመንትዮቹ ግን ህግ
ያለበት ጨዋታ ለመጫወት እድሜያቸው ስላልደረሰ ከባድ ነበር፡ ምንም ነገር ፍላጎታቸውን ይዞ አይቆይም እናታችን ካመጣቻቸው ብዙ ትንንሽ
መጫዎቻዎች ውስጥ በአልጋዎቹ ስርና በልብስ ማስቀመጫው ላይ የሚሄዱ የኤሌክትሪክ ባቡሮችና ገልባጭ መኪናዎችም ነበሩበት የሆነ ብንለውጠውም እንኳን መንትዮቹ ጣሪያው ስር ያለውን ክፍል ሁሉ ነገሩን ጠልተውት ስለነበር ይህንን በማግኘታቸው አስደሳች ሆነላቸው።
ጮሆ የሚቀሰቅስ ሰዓት የለንም: ያለን የእጅ ሰዓት ብቻ ነው፡ ቢሆንም ግን በየቀኑ በጠዋት እንነሳለን፡ እኔማ ብፈልግም እንኳን በሰውነቴ ውስጥ ያለው
አውቶማቲክ የጊዜ መቁጠሪያ አርፍጄ እንድተኛ አይፈቅድልኝም
ከአልጋችን ስንነሳ ሁሌም ወንዶቹ ቀድመው መታጠቢያ ክፍሉን ይጠቀማሉ። ቀጥሎ ኬሪና እኔ እንገባለን አያትየው ከመግባቷ በፊት ልብሳችንን ለብሰን መጨረስ አለብን፡ ከዚያ... አያትየው ወደ አስቀያሚው ደብዛዛ ክፍል ትገባና የያዘችውን የሽርሽር ቅርጫት አስቀምጣ እስክትሄድ ድረስ በተጠንቀቅ እንጠብቃለን አልፎ አልፎ ታናግረናለች። የምታናግረንም ምግብ ከመብላታችንና ከመተኛታችን በፊት መፀለያችንንና ትናንት ከመፅሀፍ ቅዱስ
አንድ ገፅ ማንበባችንን ለመጠየቅ ብቻ ነው:
“አይ” አለ ክሪስ አንድ ማለዳ፤ “ያነበብነው አንድ ገፅ ሳይሆን ብዙ ምዕራፎችን ነው " አለ። መፅሀፍ ቅዱስን የምታነቡት በቅጣት መልክ ከሆነ፣ ብትተውት
ይሻላል እኛ አስደናቂ ምንባብ ሆኖ ነው ያገኘነው: ካየናቸው ፊልሞች በላይ ስለደምና ስለ ወሲባዊ ነገር የሚናገር መፅሀፍ ነው: ካነበብናቸው ሌሎች መፅሀፍት በላይ አብዝቶ ስለ ኃጢአት የሚናገር መፅሀፍ ነው
“ዝጋ አንተ ልጅ!” ጮኸችበት: “የጠየቅኩት እህትህን እንጂ አንተን አይደለም"
ቀጥሎ ከመፅሀፍ ቅዱስ ያጠናሁትን አንድ ጥቅስ እንድነግራት ጠየቀችኝ።
አብዛኛውን ጊዜ በዚህ መንገድ በእሷ ኪሳራ ቀልዶች እንፈጥራለን᎓ ምክንያቱም በደንብ ካያችሁትና ረጅም ጊዜ ከፈለጋችሁ፣ ከመፅሀፍ ውስጥ የትኛውንም
ሁኔታ የሚመጥኑ ቃላት ታገኛላችሁ በዚህ ማለዳ መልስ ስሰጥ “በመልካሙ ፋንታ ለምን ክፉን መለሳችሁ?” ዘፍ 444 አልኳት።
ፊቷን አጨፈገገችና ዞራ ሄደች። ክሪስ ላይ ከመጮኋ በፊት ሌሎች ጥቂት ቀናት አለፉ፡ መንገዱን ሳታይና ጀርባዋን እንዳዞረች “ከኢዮብ መፅሀፍ ውስጥ
ያጠናኸውን ጥቅስ ንገረኝ፡ መፅሀፍ ቅዱስ ሳታነብ
እንዳነበብክ አድርገህ
ልታሳምነኝና ልታሞኘኝ እንዳትሞክር” አለችው:
ክሪስ በደንብ የተዘጋጀና በራሱ የሚተማመን ይመስላል፡ ኢዮብ 2812 ነገር ግን ጥበብ የምትገኘው ወዴት ነው? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው
ኢዮብ 2828 “እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል ነው" ኢዮብ 31፡35 “የሚያዳምጠኝ ምነው በኖረልኝ እነሆ የእጅ ምልክት ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፡” ኢዮብ 32፡1 “በዕድሜ ያረጁ
ጠቢባን አይደሉም: ያለማቋረጥ እየቀጠለ ነበር። ነገር ግን የአያትየው ፊት በቁጣ ቀለሙን ቀየረ ከዚያ በኋላ ክሪስን ከመፅሀፍ ቅዱስ ያነበበውን ጥቅስ እንዲነግራት ጠይቃው አታውቅም: በመጨረሻ እኔንም መጠየቅ አቆመች::
ምክንያቱም እኔም ሁልጊዜ የምነግራት የሚያናድዷትን ጥቅሶች ነበር:
ሁልጊዜ ምሽት አስራ ሁለት ሰዓት ገደማ እናታችን እያለከለከች በችኮላ ትመጣለች: ስጦታዎች፣ የምንሰራቸው አዳዲስ ነገሮች ፣ የምናነባቸው አዳዲስ መፃህፍት፣ የምንጫወታቸውን አዳዲስ ጨዋታዎች ተሽክማ ትመጣለች: ከዚያ ሰውነቷን ለመታጠብና ምድር ቤት ለሚዘጋጀው የራት
ግብዣ የሚመጥን ልብስ ለመልበስ ፈጥና ትመለሳለች ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ እያለ እንደምትነግረን ከሆነ አሽከሮችና ገረዶች በጠረጴዛው አጠገብ
ቆመው በሚጠብቁበት ግብዣ ላይ፣ አብዛኛውን ጊዜ እንግዶች አብረዋቸው ይመገባሉ፡ “ትልልቅ የስራ ስምምነቶች የሚከናወኑት በምሳ ውስጥ ወይም በእራት ጠረጴዛ ላይ ነው'' ተብሎ ተነግሮናል።
ከጥቂት ደቂቃዎች የበለጠ ጊዜ አብራን የምታሳልፈው ቅዳሜና እሁድ ብቻ ነው ትንሽዋ ጠረጴዛችን ላይ ለምሳ አብራን ትቀመጣለች። ሆዷን መታ መታ እያደረገች “ከአባቴ ጋር ምሳ ከበላሁ በኋላ እንደገና ከልጆቼ ጋር ለመብላት ስል መተኛት እፈልጋለሁ ብዬ ነው ወደዚህ የምመጣው: እንዴት
እንደወፈርኩ ተመልከቱ” ትለናለች።
ከእናታችን ጋር መመገብ ከአባታችን ጋር የነበረውን የድሮውን ጊዜ ስለሚያስታውሰኝ ደስ የሚል ነበር። አንድ ቅዳሜ እናታችን ገና ውጪ ሆና
ሽታው የሚጣራ የቫኒላ አይስክሬምና የቸኮሌት ኬክ ይዛ መጣች: አይስክሬሙ ቀልጦ ሾርባ መስሏል ግን በላነው ምሽቱን አብራን እንድትቆይና በኬሪና
በእኔ መካከል ተኝታ ጠዋት ስንነቃ አጠገባችን መሆኗን ማየት እንድንችል ለመንናት: ምስቅልቅል ያለውን መኝታ ቤት ዙሪያውን ተመለከተችና ጭንቅላቷ ነቀነቀች “አዝናለሁ አልችልም በፍፁም አልችልም: ሠራተኞቹ አልጋዬ ለምን እንዳልተተኛበት ይጠራጠራሉ ይሄኛው አልጋ ደግሞ ይጠብባል አለችን።
“እማዬ፣ ለምን ያህል ጊዜ ነው? ሁለት ሳምንት ሆኖናል ግን ልክ ሁለት አመት ያህል ነው የሚመስለው: አያታችን አባቴን በማግባትሽ አሁንም ይቅር አላለሽም? አሁንም ስለኛ አልነገርሽውም?” ብዬ ጠየቅኳት
የማይጨበጥ አድርጌ በቆጠርኩት አነጋገር “አባቴ አንደኛውን መኪናውን
እንድነዳው ሰጥቶኛል፡ ይቅርታ እንደሚያደርግልኝ አምናለሁ ባይሆን ኖሮ መኪናውን እንድጠቀም ወይም አብሬው እንድኖር ወይም የእሱን ምግብ

👍39❤5
እንድበላ አይፈቅድልኝም ነበር፡ ግን የደበቅኳቸው አራት ልጆች እንዳሉኝ ለመንገር ገና ድፍረት አላገኘሁም:: ይህንን ለማድረግ ጊዜውን በጥንቃቄ መምረጥ ስላለብኝ ትዕግስት ሊኖራችሁ ይገባል:"“ስለኛ ቢያውቅ ምን ያደርጋል?” ተኮሳትሮ የሚመለከተኝን ክሪስን ችላ ብዬ ጠየቅኳት። “ብዙ ጥያቄዎች መጠየቅ ከቀጠልኩ፣ እናታችን በየቀኑ ልታየን
መምጣቷን ታቆማለች ከዚያ ምን እናደርጋለን?” ሲል ብዙ ጊዜ ጠይቆኛል።
“ምን እንደሚያደርግ እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው” በፍርሀት አንሾካሾከች።
ካቲ፣ ሠራተኞቹ እንዲሰሙ ለማድረግ እንደማትሞክሪ ቃል ግቢልኝ! ጨካኝ፣ ክፉና ትልቅ ኃይል ያለው ሰው ነው፡ ለመስማት ዝግጁ የሚሆንበትን ሰዓት
በጥንቃቄ ልምረጥ:”
አንድ ሰዓት አካባቢ ልክ እንደተኛን ሄደች። በጊዜ እንድንነሳ የምንተኛው በጊዜ ነው: ረጅም ከተኛን ቀኑ አጭር ይሆንልናል: ልክ አራት ሰዓት እንዳለፈ
መንትዮቻችንን ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ይዘን እንሄዳለን፡ ያንን ክፍል በመመርመር ጊዜያችንን ከሚይዙልን ምርጥ መንገዶች አንዱ ነው: ሁለት
ፒያኖዎች አሉ: ኮሪ ወደ ላይና ወደ ታች የሚለው ክቡ ወንበር ላይ ይወጣና ይሽከረከራል፡ ከዚያ ቢጫዎቹን የፒያኖ ቁልፎች እየነካካ በጥንቃቄ ያዳምጣል።
ከቅኝት ውጪ ነው፡ እናም የሚያወጣው ድምፅ ራስ የሚያሳምም ይሆናል።
“ድምፁ ትክክል አይደለም፤ ለምንድነው ድምፁ ትክክል ያልሆነው?” አለ
“መቃኘት ይፈልጋል” አለ ክሪስ እና ለመቃኘት ሲሞክር ብረቱ ተሰበረ ያ በሁለቱ አሮጌ ፒያኖዎች ሙዚቃ የመስራት ሙከራችን መጨረሻ ሆነ።
ብዙ የሙዚቃ ቅጂዎች አገኘን፡ በደንብ እንኳ አልተቀመጡም ወለሉ ላይ ተዝረክርከው ነበር። በግማሽ ልብ ተቀምጠን ማዳመጥ ጀመርን:: የአንደኛው ዘፋኝ ድምጽ በጣም ቀጭን ከመሆኑ የተነሳ የውሸት ይመስል ስለነበር እኔና ክሪስ አሪፍ ነው የተባለው ለምን እንደሆነ ገርሞን ነበር። ግን በሆነ ምክንያት
ኮሪ ወደደው አንዳችን
ከዚያ ቀስ በቀስ ማጫወቻው ድምፁን እየጎተተው ሲመጣ
መያዣውን ጠበቅ አድርገን ስንይዘው ድምፁ በሚያስደንቅ ሁታ ፈጣን እየሆነ መንትዮቹን ያስቃቸው ነበር።
ኮሪ ቀኖቹን ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ሙዚቃዎችን ሲያዳምጥ ያሳልፋል ኬሪ ግን ደስተኛ አልነበረችም: በተሻለ ሁኔታ የምትስራው ነገር
ፈላጊ ነበረች።
“ይህንን ትልቅ መጥፎ ቦታ አልወደድኩትም! ለሚሊየንኛ ጊዜ ተናገረች ከዚህ መ.. ጥፎ ቦታ አውጡኝ! አሁኑኑ አውጡኝ! በዚህ ደቂቃ አውጡኝ አለበለዚያ ግድግዳዎቹን በእርግጫ እደበድባለሁ! እችላለሁ!”
ወደ ግድግዳዎቹ እሮጠችና በትናንሽ እግሮቿና ቡጢዎች እጇ በልዞ እስክታቆም ድረስ ግድግዳውን መምታት ቀጠለች ለእሷና ለኮሪ አዘንኩላቸው፡ ሁላችንም ግድግዳዎቹን በእርግጫ አፍርሰን ማምለጥ እንፈልጋለን፡ ኬሪ ግድግዳው ልክ
እንደ ኢያሪኮ ግምብ በሀይለኛው የድምፅዋ ጩኸት እንዲወድቅ ትፈልጋለች:
በእርግጥ ኬሪ በደረጃዎቹ ታች ወዳለው መኝታ ቤት ወርዳ ከአሻንጉሊቶቿ ከሻይ ስኒዎቿና ከትንሽዋ ምድጃዋ እንዲሁም ከትንሽዋ የልብስ መተኮሻዋና
ከማትግለው ትንሽዋ ካውያ ጋር መጫወት መቻሏ እፎይታ ነበር።
ለመጀመሪያ ጊዜ ኮሪና ኬሪ እርስ በእርስ ተለያየተው ጥቂት ሰዓታትን አሳለፉ ክሪስ ጥሩ ነገር እንደሆነ ተናገረ፡ ላይ ጣሪያው ስር የኮሪን ቀልብ የሳበ ሙዚቃ አለ፡ ኬሪ ደግሞ ከ“ዕቃዎቿ” ጋር እየተጫወተች ነው።
ብዙ ጊዜ መታጠብም ጊዜን የማሳለፊያ አንዱ መንገዳችን ነበር። ፀጉርን መታጠብ ደግሞ የበለጠ ጊዜ የሚፈጅ ነበር። በህይወት ካሉ ልጆች ሁሉ
ንፁህ ነበርን፡፡ ከምሳ በኋላ ደግሞ ትንሽ ሸለብ እናደርጋለን፡፡ እንደፈለግን እናረዝመዋለን፡ ክሪስና እኔ ልጣጩ ሳይቆረጥ ረጅም ሆኖ እንዲወጣ የማድረግ አፕል የመላጥ ውድድር እናደርጋለን የቺዝ ብስኩቶች ያሉበት ትንንሽ ካርቶኖች እየቆረጥን ለአራት እኩል እኩል እናካፍላለን።
በጣም አደገኛ ግን አስደሳች ጨዋታችን አያትየው የምታደርገውን መኮረጅ
ነው: ግራጫ ልብሷን ለማስመሰል ከጣሪያው ስር ያገኘነውን ቆሻሻ ግራጫ አንሶላ እንጠቀማለን፡ ድንገት ብትይዘን እጅግ አስፈሪ ነው ክሪስና እኔ እዚህ ላይ ማንም አይችለንም ነበር መንትዮቹ ግን እሷ ክፍል ውስጥ ካለች
አይናቸውን ለማንቀሳቀስ እንኳን ይፈሯት ነበር።
ክሪስ በሩ ላይ ሆኖ የማይታይ የሽርሽር ቅርጫት ይይዝና “ልጆች ጨዋ፣የተከበራችሁና ስርዓት ያላችሁ ሆናችኋል? ይህ ክፍል የተዘበራረቀ ይመስላል አንቺ እዚያ ጋ ያለሽው አይኖቼን በማፍጠጥ ጭንቅላትሽን ከመፈጥፈጤ
በፊት ያንን የጎበጠ ትራስ አስተካክይ!” ይላል፡
እኔ ደግሞ ወለሉ ላይ በጉልበቴ እንበረከክና እጆቼን አገጬ ስር አጥፌ “ይቅርታ አያቴ ጣሪያው ስር ያለውን ክፍል ግድግዳ ሳፀዳ ስለቆየሁ ደክሞኝ ነው: ማረፍ አለብኝ" እያልኩ አለቅሳለሁ
“ማረፍ!” አያትየው በሩ ጋ ሆና ትቆጣለች። ቀሚሷ ሊወድቅ ደርሷል። ለክፉዎች፣ ለሸረኞች፣ ለረከሱ ሰዎችና ለዋጋ ቢስ ሰዎች ዕረፍት የለም።እስኪሞቱ ድረስ ያለው ስራ ብቻ ነው: ገሀነም ውስጥ ባለው ዘለአለማዊ
እሳት ውስጥ ትሰቃያላችሁ!" ከዚያ መንትዮቹን በፍርሀት በሚያስጮህ አይነት እጆቹን በአንሶላው ስር ያንቀሳቅሳል
የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ራሳችንን ለማዝናናት ሁሉን ነገር ብናደርግና አብዝተን ፀጥ ለማለት ብንችልም ሰከንዶቹ ወደ ሰዓታት የተቀየሩ ይመስል ነበር። ጥርጣሬዎችና ፍርሀቶች፣ ተስፋዎችና ይሆናል ብለን መጠበቃችን ልባችን እንደተንጠለጠለ አቆዩት ነገር ግን ምንም ያህል አብዝተን ብንጠብቅ
ከዚህ ወጥተን ምድር ቤት ወደ መወሰድ ገና አልተጠጋንም:
መንትዮቹ ትንንሽ ቁስሎቻቸውንና የበለዘ ሰውነታቸውን እንዲሁም ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ የሚገኝ የበሰበሰ እንጨት ተሰብሮ ስንጥር የተሰካባቸውን እጃቸውን ሊያሳዩኝ ወደኔ ሮጡ። እኔም በጥንቃቄ በወረንጦ አወጣሁላቸው ክሪስ ደግሞ መድኃኒት ቀብቶ ፕላስተር ሲለጥፍላቸው እጅግ
ተደሰቱ የቆሰለች ትንሽዬ ጣታቸው የሚፈልጉትን የልጅ ነገር ለመጠየቅ፣እሹሩሩ ተብለው አልጋ ላይ ለመተኛት፣ ጉንጮቻቸውን ለመሳምና እንዲስቁ ለማድረግ በቂ ምክንያት ነው: ትንንሽ ክንዶቻቸው አንገቴን ጥብቅ አድርገው አቅፈውኛል፡ በጣም በጣም እወደዳለሁ እና እፈለጋለሁ፡
መንትዮቹ አወራራቸው ሳይሆን፣ የሆነ ነገር ሲhለከሉ በትንንሽ እጆቻቸው አይኖቻቸውን የሚያሹበትና ለንቦጫቸውን የሚጥሉበት መንገድ፣ እንዲሁም
የሚፈልጉትን ነገር እንዲሰጣቸው ለማስገደድ ፍም እስኪመስሉ ድረስ ትንፋሻቸውን መያዛቸው፤ ከአምስት አመት ይልቅ የሶስት ዓመት እድሜ ያላቸው ይመስሉ ነበር። ከክሪስ ይልቅ ለእንደዚህ አይነት ነገር የምደነግጠው
እኔ ነበርኩ ክሪስ ማንም ሰው ራሱን በዚህ መንገድ ማፈን እንደማይችል ለማሳመን ይሞክራል: ግን አሁንም እንደዚያ ሲሆኑ ማየት ያስፈራኛል::
“በሚቀጥለው ጊዜ እንደዚህ ሲያደርጉ ችላ እንድትያቸው እፈልጋለሁ ካላስቻለሽ ወደ መታጠቢያ ቤት ግቢና በሩን ቆልፊ: እመኚኝ አይሞቱም:
አለኝ ክሪስ በሚስጥር:
ኮሪ፣ ክሪስ እንደሚለብሰው አይነት ቁምጣ ስለሚለብስ በጣም ኩራት ይሰማኛል::.

👍31❤1
ዳይፐር ማድረግ ካቆመ ብዙ ጊዜ ስላልሆነው ሽንቱ ቶሎ ቶሎ ይመጣታል: ኬሪ ደግሞ ትንሽ ፍራፍሬ ከበላች ወደታች ይላታል፡ ኬሪ ፍራፍሬ ስለምትወድ ፍራፍሬዎች የሚመጡልንን ጊዜያት በጣም ነው የምጠላቸው:: :የሆነ ፍራፍሬ ወደቤት ሲመጣ በጣም ነው የሚከፋኝ: ምክንያቱም ልክ እኛ
መብረቅ ካልፈጠንኩና ጊዜው ሳያልፍ ኬሪን አንጠልጥዬ ወደ መታጠቢያ ቤት ካልወሰድኩ የተበላሸውን ፓንት ማጠብ ግድ ይለኛል። በሰዓቱ ካልደረስኩ
ክሪስ በሁኔታው ይስቃል ኬሪ ከቀደመችኝም እንደዚያው:ኮሪ መታጠቢያ ቤት መግባት ፈልጎ ድንገት መታጠቢያ ቤቱ ተይዞና በሩ ተቆልፎ ከሆነ ክሪስ ያንን ሰማያዊ የአበባ ማስቀመጫ ይጠቀማል። ድንገት ግን ኮሪ የውስጥ ሱሪውን ካረጠበ ስለሚያፍር ፊቱን ጭኔ ውስጥ ይደብቃል:ኬሪ ግን አታፍርም፡ እኔ ቀርፋፋ በመሆኔ ጥፋቱ የእኔ እንደሆነ አድርጋ ነው የምታስበው።
“ካቲ፣ መቼ ነው ወደ ውጪ የምንወጣው?” አለ ኮሪ
“እናታችን እንደምንችል ስትነግረን” “እናታችን ለምንድነው ትችላላችሁ ያላለችው?”
“እኛ እዚህ መሆናችንን የማያውቅ አንድ ሽማግሌ ምድር ቤት አለ፡ እና እናታችንን እንደገና እስኪወዳትና እኛንም እስኪቀበለን መጠበቅ አለብን፡
“ሽማግሌ ማነው?"
“አያታችን”
“እንደ ሴት አያታችን አይነት ነው?”
“አዎ ይመስለኛል”
“ለምንድነው የማይወደን?”
“የማይወደን... ምክንያቱም… ምክንያቱም ጭንቅላቱንና ልቡን ስላመመው ይመስለኛል”
“እናታችን አሁንም ትወደናለች?”
ማታ ሳልተኛ የማያሳድረኝ ጥያቄ ይሄ ነው እናታችን ቀን ላይ ከመጣች እሁድ ሲመጣ ሳምንቱ አለፈ ከትምህርት ቤት የእረፍት ቀን እንዳላትና እዚህ ቤት ውስጥ የሆነ ቦታ እንዳለች ስለምናውቅ
አብራን አለመሆኗ ይጎዳናል። ወለሉ ቀዝቀዝ ስለሚል በሆዴ ተኝቼ መፅሀፍ አነባለሁ: ክሪስ ደግሞ ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል አዲስ የሚነበብ ነገር
ለመፈለግ ሄዷል። መንትዮቹ ደግሞ ትንንሽ የመጫወቻ መኪናቸውን እየገፉ
ይጫወታሉ።
ቀኑ ወደ ምሽት ሲቀየር በመጨረሻ እናታችን የቴኒስ ጫማ፣ ነጭ ቁምጣና ነጭ ካኒቴራ ለብሳ ወደ ክፍላችን ገባች: ደጅ እየተጫወተች እንደነበረ
ያስታውቃል። በጣም ጤነኛና በማይታመን አይነት ደስተኛ ትመስላለች። እኛ ግን እዚህ ክፍል ባለው ከባድ ሙቀት ምክንያት ጠውልገናል በቅሬታ አተኩሬ እያየኋት ቆዳዬ ፀሀይ እንዲነካውና እግሮቼ እንደሷ እግሮች
ጤናማ ቀለም እንዲኖራቸው ተመኘሁ። ፀጉሯን ንፋስ በታትኖት ትልቅናወደ አርባ አመት የተጠጋች ቢያስመስላትም አስር እጥፍ ቆንጆና አማላይ አስመስሏታል።
በግልፅ እንደሚታየው ይህ ከሰዓት በኋላ አባታችን ከሞተ በኋላ ካሉት ቀኖች ሁሉ የበለጠ ደስታ ሰጥቷታል አስራ አንድ ሰዓት አካባቢ ሆኗል። ምድር ቤት ውስጥ አንድ ሰዓት ላይ ራት ይቀርባል። ያ ማለት ከእኛ ጋር ለማሳለፍ ያላት ሰዓት ጥቂት ነው ማለት ነው ምክንያቱም ወደ ክፍሏ ሄዳ መታጠብና ለእራት የሚመች ልብስ መቀየር አለባት።
መፅሀፌን አስቀመጥኩና ተነስቼ ቁጭ አልኩ። ስለተጎዳሁ ልጎዳት
ፈልጌያለሁ፡ “የት ነበርሽ?” ብዬ በአስቀያሚ ድምፀት ጠየቅኳት፡ እኛ ተቆልፎብን ተቀምጠንና ልጆች ማድረግ ያለባቸውን መብታቸው የሆኑትን ነገሮች ከማድረግ ተከልክለን እሷ ራሷን የምታስደስትበት ምን መብት አላት?አስራ ሁለት አመት ሲሆነኝ በጋውን አላየውም፤ ክሪስም አስራ አራተኛውን በጋ አይደሰትበትም፤ መንትዮቹም አምስተኛቸውን በጋ ሳያዩት ያልፋል።
አስቀያሚው የድምፄ ከሳሽ ድምፀት የሚያበራ ፊቷን አደበዘዘው: ገረጣች ከንፈሮቿ ተንቀጠቀጡ፡ ምናልባትም ቅዳሜ ወይም እሁድ መቼ እንደሆነ
ማወቅ የሚያስችለንን ትልቅ የግድግዳ ላይ ቀን መቁጠሪያ ስላመጣችልን እየፀፀታት ይሆናል የቀን መቁጠሪያው በትክክል በቀይ የኤክስ ምልክቶች ተሞልቷል። የታሰርንባቸው ቀናት፣ ሙቀቱ፣ ብቸኝነቱ፣ የልብ መሰቀሉ
የተጎዳንባቸው ቀናት ላይ በሙሉ ምልክት አድርገንባቸዋል:.....

👍31
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
ሎርድ ማውንት እስቨርን ስለ ጋብቻው ያወቀው ከጋዜጣ አንብቦ ነበር “እሱም ቢሆን እንደ ሚስ ኮርኒ አይሁን እንጂ በመብረቅ የተመታ ያህል ደንግጧል " በንዴት
እየጤሰና እየተከነ ዕለቱን ወደ ኢንግላንድ ሲመለስ' ሚስቱ ስለ ጉዳዩ ከጻፈችለት ደብዳቤ ጋር በመንግድ ተላለፉ ሚስተር ካርላይልንና ወይዘሮ ሳቤላን ለንደን ውስጥ ዊስት ኤንድ ከሚባለው አካባቢ ሆቴል ይዘው ስለ ነበር አገኛቸው ሙሹሮቹ አንድ ሁለት ቀን ለንደን ካደሩ በኋላ ዐልፈው ለመሔድ ዕቅድ ነበራቸው ሚስተር ካርይል ወጣ ብሎ ስለነበር ሳቤላን ለጊዜው ብቻዋን አገኛት "
“ ይሀ ነገር ምን ማለት ነው?” ብሎ ጀመረ ያለ ምንም የሰላምታ ቃል “አገባሽ ? ”
“አዎን ከጥቂት ቀኖች በፊት አገባሁ"
“ ጠቢቃው ካርላይልን ? እንዴት ሊሆን ቻለ ? ”
ሳቤላ በቂ የሆነ ግልጽ መልስ ለመስጠት እንዴት ሊሆን እንደ ቻለ ታሰላስል ጀመር “በፋሲካ ወደ ካስልማርሊንግ መጥቶ ሳለ ቢጠይቀኝ ለጊዜው ደነገጥኩ
ሆኖም አስቤ ጥያቄውን ተቀበልኩት።
ኧርሉ ትክ ብሎ አያትና : “ ታድያ ለኔ ለምን ተሸሸገኝ .... ሳቤላ ? ”
“አለማወቅህን አላውቅም » ሚስተር ካርላይልም ወይዘሮ ማውንት እስቨርንም
በየበኩላቸው ጽፈውልህ ነበር”
“ለኔ እንደ መሰለኝ ሰውየው ባባትሽ ፈቃድ ኢስት ሊን እየተመላለሰ ይጠይቃችሁና ይጫወት በነበረ ጊዜ hአንቺ ጋር ተዋወቃችሁ ከዚያ ፍቅር ያዘሽ ”
“ በእውነት አይደለም እኔ የሚስተር ካርላይል ፍቅር ይይዘኛል ብዬ አስቤም አላውቅ”
"ከሱ ጋር ፍቅር አልያዘሽም ?
"የለም ! ” አለችው እየፈራች ቀስ ብላ " “ ለኔ ሲበዛ ደግ ሰው ነው እኔም በደግነቱ በጣም ነው የምወደው” “
ታዲያ ከሚስተር ካርላይል ጋር ፍቅር ካልያዘሽ በፍቅር በመጠመድና በሌላ ቁም ነገሩ በመውድድ መካከል ያለውን ልዩነት በምን ዐወቅሽው? ከሌላ ጋር ፍቅር ይዞሻል እንዴ ? ” አላት"
ጥያቄው ልብራሷን ነካት ፊቷ ባንድ ጊዜ ቀላ “እኔ ባሌን ነው የምወድ” አለችው አንገቷን ደፍታ ያለ ልቧ ከሰዓት ማሰሪያዋ ጋር እየተጫወተች
“ አዬ ልጄ ! ” አለ ኧርሉ እሱም ሳያስበው " የአንድ ነገር ጫፍ ከያዘ እስከ መጨረሻው መከታተል ይወድ ነበር “ እኔ ከሔድኩ ወዲህ ከካስል ማርሊንግ መጥቶ
የሰነበተ ሰው ነበር ? አላት "
“ሚስዝ ሌቪሰን መጥተው ነበር ”
“ኧረ ወንዶች ልጅ እግር ወንዶች ማለቴ ነው ”
"ፍራንሲዝ ሌቪሰን ብቻ መጥቶ ነበር "
ፍራንሲዝ ሌቪሰን ? መቸም ካላበድሽ በቀር የሱ ፍቅር አይዝሽም " "
ሳቤላ ድንግርግር አላት " ልትደብቀው አልቻለችም ። ኧርሎም ሁኔታዋን አየና
ነገሩ በትክክል ስለገባው ' ከዚያ በላይ መጠየቅ አላስፈለገውም ። መሬት መሬት የሚያዩት ዐይኖቾን እያየ በጣም አዘነ "
"ሳቤላ” ብሎ ጀመረ “ ካፒቴን ሌቪሰን ጥሩ ሰው አይደለምና ጥሩ ሰው ነው የሚል አስተሳሰብ ካለሽ ካሁኑ ከአእምሮሽ አውጥተሽ ጣይው " ከሱ ጋር ያለሽን ዕውቂያ አቁሚ ካጠገብሽ እንዳታስደርሺው ፡ ጭራሽ ፊት አትስጭው "
“ እኔ እንኳን ትቸዋለሁ ዳግመኛም ከሱ ጋር የሚያገናኘን ምክንያት የለም።ግን ወይዘሮ ማውንት እስቨርን ከቤቷ ተቀብላ የምታስትናግደው ጥሩሰው ሆኖ ስለ አገኘችው መሰለኝ።
“እሷም ብትሆን ስለሱ ጥሩ አስተሳሰብ የላትም። ፍራንሲዝ ሌቪሰን ጥሩ ሰው ነው
የሚልሽ አንድም ሰው አታገኝም » እሱ ያክስቴ ልጅ ነው እሷ ከምትሰበስባቸው አለባበስ አሳማሪዎች ቀፎራስ አውደልዳይ ቦዘኔዎች አንዱ እሱ ነው ሳቤላ
እኔ ነገርኩሽ ከሷ የተሻልሽ ሁኝ - ነገር ግን ካርላይልን የማግባትሽን እንቆቅልሽ አይፈታውም " እንዲያውም የበለጠ ውስብስብነቱን ያሳያል " ምናልባትም አባብሎና አግባብቶ እሽ ያሰኘሽ እሱ ሳይሆን አይቀሮም ”
ሳቤላ መልስ ከመስጠቷ በፊት ሚስተር ካርላይል ገባ እጁን ለኧርሉ ሲዘረጋለት ኧርሉ ያላየው መስሎ ዝም አለ "
“ሳቤላ ...” አለ ኧርሉ : “ ያላችሁ ሳሎን ይኸ ብቻ መሰለኝ » ስለዚህ ሚስተር ካርላይልን ለብቻው ትንሽ ላነጋግረው ስለምፈልግ አንቺን ውጭ ልናቆይሽ ነው ትታቸው ወጣች " ኧርሉም ወንበሩን ወደ ሚስተር ካርላይል ዞር አደረገና
“ እስቲ ንገረኝ ጌታው ... ይህችን ልጅ እንዴት ልታገባት ቻልክ ? እኔ ባገር የማልገኝበትን የተመቸ አጋጣሚ ጠብቀህ ' በቤተሰቤ ሰተት ብለህ እመቤት ሳቤላ ቬንን አታልለህ ፡ በድብቅ ስታገባት ትንሽ ኃፍሪት አይሰማህም?”
“ ጌታዬ . . . የሚናገሩት አንዱም አልገባኝም ” አለው
“ የምናገረው እኮ ግልጽ ነገር ነው። የቤቶሰቡ ኃላፊ የልጂቱ ያደራ አባት ያለመኖሩን ጠብቆ ' አንዲት ልጃገረድ አታልሎ ከደረጃዋ በታች የሆነ ጋብቻ እንድትፈጽም ማድረግ ስውር ተንኮል እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል ? ”
“ እኔ በመቤት ሳቤላ ላይ ምንም ዐይነት ስውር ተንኮል አልፈጸምኩም ”
“ ለሳቤላ ቬን ያለኋት ቁርጠኛ ወገን እኔ ብቻ መሆኔ እየታወቀ ለምን አልተነገረኝም ? እንዴት እንደ ማንም ባዳ በጋዜጣ ልስማው ?
“እመቤት ሳቤላን ለጋብቻ በጠየቅኋት ጊዜ . . .”
“ የዛሬ ወር እኮ ነው ያውም ” አለና በቁጣ አቋረጠው
“አዎን ' የዛሬ ወር ነው ” አለው ካርላይል ረጋ ብሎ !“ሳቤላ ጥያቄውን እንደቸቀበለችኝ
የመጀመሪያው ተግባሬ ለእርስዎ መጻፍ ነበር " አሁን ግን መጀመሪያ
በበኩሌ አንድም መልስ ስለ አልጻፉልኝ በእርስዎ በኩል የመልካም ሥነ ምግባር
ጉድለት ነው ብዬ ቅር ብሎኝ ነበር።
ምን ብለህ ጽፈህ ነበር?”
“ዋሆነውን ነገር ገልጬ ስለ ስምምነታችንና ሳቤላና እኔ ጋብቻው በቶሎ እንዲፈጸም መፈለጋችንን ሁሉ ዘርዝሬ ጽፌለዎት ነበር ”
ደብዳቤውን በምን አድራሻ ላክኸው ?
“ ወይወሮ ማውንት እስቨርን አድራሻውን ሊሰጡኝ ስለ አልቻሉ • እሳቸው እንደሚልኩት ነገሩኝና ሰጠኋቸው እሳቸውም ከዚያ በኋላ እርስዎ መፍቀድዎንና መልስ ግን ያለመጻፍዎን በሳቤላ ደብዳቤ በኩል ላኩብኝ በአመለካከትም የፈለገውን ጥፋት
ቢያዩብኝም እኔ እውነተኛ ሰው ነኝ ስለ ጋብቻው ጉዳይ አለማወቅዎን ግን ግና አሁን መስማቴ ነው”
“እንዲህ ከሆነ ይቅርህን ካርላይል” ግን በፋሲካ ጠይቀኻት ሳቤላእንደምትነግረኝ
ከሦስት 0ምንት በኋላ ተጋባችሁ እንደዚህ ያጣደፈህ ምንድነው?”
“እኔ ይህን ሁሉ ያደረግሁት ለሷ ምቾትና ደስታ ስል ነው" ስለዚህ የማይሆን ሆኖብኝ ነው እንጂ እንደኔስ ቢሆን ኖሮ የእሽታ ቃልዋን የሰጠችኝ ዕለት አግብቼ እወስዳት ነበር ' አለው ሚስተር ካርላይል "
“ እውነት ? እንደዚህ ያጣደፉህን ምክንያቶች ልታስጨብጠኝ ትችላለህ ?
ምክንያቶቹ ለእርስዎ ደስ አያሰኙምና መስማቱ ቢቀርብዎ "
“ ግድ የለም ዳኝነቱን ለኔ ተውልኝ።"
“ዓርብ የስቅለት ዕለት የሥራ ጉዳይ ወደ ካሰል ማርሊንግ ወስደኝ እርስዎና ሳቤላ አድርጋችሁልኝ በነበረው ጥሪ መሠረት ወደ ቤትዎ ሔድኩ? - ካሰል ማርሊንግ ድረስ መጥቸ እርስዎ ዘንድ ሳልመጣ ብመለስ ቅር እንዳላስኝዎ ብዬ ነበር አመጣጤ " ስደርስ ጊዜ ሳቤላ ከደስታ ተለይታ ከእርስዎ ቤት ተዋርዳና ተንገላታ አገኘኋት
ምን አልከኝ ? ተዋርዳና ተንገላታ ?” አለ ኧርሉ የካርላይልን ንግር በማቋረጥ ተርዳና ተንገላታ አገኘሁዋት!?”
አዎን ጌታዬ ተዋርዳ ተደብድባ”
ኧርሉ በሚስተር ካርላይል ላይ እንዳፈጠጠ በድን ሆኖ ቁሞ ዝም አለ ሚስተር ካርላይል ንግግሩን ቀጠለ።

👍9
“ይኸንንም ለማወቅ የቻልኩት ትንሹ ልጅዎ ሲናገር ስምቸ ነው እንጃ እሷ ብትሆን ኖሮ ከነጭራሹም አታነሣልኝም ነበር ልጁ ከተናገረ በኋላ ግን እሷም አልሸሸገችም ኑሮ መሯት የምትሆነው ጠፍቷት መንፈሷ በኀዘን ስብር ብሎ መድረሻና ታዳጊ በምትፈልግበት ሰዓት ስለ ነበር ለመካድ አልፈለገችም እኔም ሁኔታውን ሁሉ ስሰማ በንዴት ተቃጠልኩ " ከዚህ የሥቃይ ኑሮ አላቅቀህ ፍቅርና ደስታ ወደምታገኝበት ውሰዳት' የሚል ስሜት መጣብኝ " ይህን ለማድረግ ደግሞ አንድ መንገድ ብቻ ነበረኝ ይህም ሚስቴ ሁና ወደ ቤቷ ወዶ ኢስት ሊን እንድትመለስ መጠየቅ ነበር!
በመገረም በድን ሆኖ የነበረው ኧርል ቀስ በቀስ ነፍሱ ተመለሰ እንግዲያውስ አሁን ካባባልህ እንደምረዳው ' የዚያን ለት ከቤቴ ስትመጣ ሳቤላን ለማግባት
የመጠየቅ ሐሳብ አልነበረህም ማለት ነው ? ”
ኧረ በጭራሽ አላሰብኩትም እኔ ስደርስ የነበረችበትን ሁኔታ ካየሁ በኋላ ነው ያስብኩት ኧርሉ አሁንም ግራ እንደ ገባውና መንፈሱ እንደ ተሸበረ በክፍሉ ውስጥ ጎርድድ ጎርድድ ሲል ቆየና “ እንዲያው አንድ ነገር ብጠይቅሀስ? ለመሆኑ ትወዳታለህ? ”
ሚስተር ካርላይል መልስ ከመስጠቱ በፌት ትንሽ ዝም ብሎ ሲቆይ ፊቱ ደም መሰለ " " እነዚህን ስሜቶች ሰዎች ብዙም አይገላጽዋቸውም ቢሆንም ለእርስዎ አልደብቆዎትም ከልቤ እወዳታለሁ » ግና ኢስትሊን ሳለች ነበር ከልቤ የገባችው ነገር ግን ያ ያልታሰበ የካሰል ማርሊንግ ግቡኝቴ ባይኖር ኖሮ መሙደዴን እስከ ሕይቴ መጨረሻ በውስጤ አፍኜ አስቀረው ነበር " ምንም ቢሆን ለማንም አልገልጸውም ነበር " እሷን የማግባቱን ነገር ያላሰብኩትም በሌላ ምክንያት ሳይሆን በማዕረግ እንደምትበልጠኝ በማሰብ ነበር ”
“ አዎን ነበረችና ” አለ ኧርሱ "
ከዚህ በፊትም የመኳንንት ልጆችን ያገቡ የገጠር ጠበቆች ነበሩ " አለ
ሚስተር ካርላይል እኔም አሁን የነሱን ቁጥር በአንድ ብቻ ያሳደግኩት።
“ግንኮ እንደ ትልቅ ሰው ልጅ አድርገህ የምትይዛት የምትችል አይመስለኝም"”
“ ኢስትሊን ቤቷ ይሆናል «ባባቷ ግዜ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በርግጥ አነስተኛ ነው " ጸጥ ያለ ነው " ወይዛዝርት መኳንንት አይንጋጉበትም » ከመጠን ያለፉ ገረዶች ሌሎቹም አይተራመሱበትም ይኸንንም ለሳቤላ ዘርዝሬ አስረድቻታለሁ
ብትፈልግ የገባችውን ቃል ማፍረስ ትችል ነበር " ይኸንኑ ለባለቤትዎም ገልጬላቸው
ነበር" ልጆች ከወለድን ኢስት ሊን እንደደንቡ ለትልቁ ወንድ ልጃችን ይሆናል ሙያዬ ጥቅም የሚያስገኝ ነው ገቢዬ ጥሩ ነው። እኔ ብሞት ሳቤላ ኢስት ሊንን
ወርሳ በዓመት ሦስት ሺፓውንድ ይኖራታል አስተማማኝ ኑሮ ልትኖር ትችላለች"የዚህ ሁሉ ዝርዝር ሳይደርስዎ በቀረው ደብዳቤ ተንትኘው ነበር " አሁን ይህን ሁኔታ ሲረዱ እኔ በእመቤት ሳቤላ ቬን ላይ አንድም ሥውር ተንኮል እንዳላቀድኩ ሊግነዘቡ
ይችላሉ „”
ሎርድ ማውንት እስቨርን እጁን ዘረጋ ቅድም ስትመጣ ... ሚስተር ካርላይል እንዳየኸው እጄን ነፍጌህ ነበር " ምንም እንኳን እኔ እጅሀን ለመጨበጥ ክብር
የሚሰማኝ ቢሆንም ' አንተም አሁን በተራህ ልትነፍገኝ ትችላለህ እኔ ስሳሳትና ወዲያው ስታርም ትክክለኛውን ነገር ለመቀበል አላመነታም " ራሴን ከሐቅ በላይ
አድርጌ አልመለከትም አድራጎትህ ርኅራኄና ክብር የተመላ ነው "
ሚስተር ካርላይል ሣቅ አለና እጁን ዘርግቶ ኧርሉን ጨበጠ " ኧርሉም የጨጠውን እጅ ያዘና ድምፁን ዝቅ አድርጎ'' በርግጥ ስለ ሳቤላ መንገላታት ስትናገር ስለ ሚስቴ መናገርህን ግብቶኛል " ግን ' ይኸ ወሬ ከናን† ዐልፎ ወጥቷል?”
እኔም ሆንኩ ሳቤላ ይኸንን ነገር ለማንም አልተነፈስንም » እኛም ከአእምሮአችን እናወጣዋለን። ነገሩ ዐልፍልና እርስዎም ምንም ነገር እንዳልሰሙ ይርሱት''
“ሳቤላ” አለ ኧርሉ ለመሔድ ሲነሣ “ ዛሬ ስገሠግሥ የመጣሁት ቢያስፈልግ ባልሺን ለመደብደብ ነበር " አሁን ግን እንዳሱበኩት ሳይሆን አክብሬው መመለሴ ነው መታመንና መከበር የሚገባው ትልቅ ሰው ስለሆነ አንቺም ታማኝና ጥሩ ሚስት ሁኝለት።"
"በርግጥ እንደምትለኝ እሆናለሁ ” አለችው ሳቤላ "
ሎርድ ማውንት እስቨርን ወደ ካስል ማርሊንግ ተመልሶ ከሚስቱ ጋር አሽከሮቹ እስኪ ሰሙ ድረስ የጦፈ ጭቅጭቅ ፈጠረ ከዚያም እንዶ ተበሳጨ ዕለቱኑ ወደ ማውንት እስቨርን ሔዶ ።
አይ ... ለንደን ላይ ከመገናኘታችን በፊት ከቁጣው ለመብረድ በቂ ጊዜ ያገኛል አለች ሚስቲቴ ለራሷ

👍14
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
....ምናልባትም ቅዳሜ ወይም እሁድ መቼ እንደሆነ እየፀፀታት ይሆናል የቀን መቁጠሪያው በትክክል በቀይ የኤክስ ምልክቶች ተሞልቷል የታሰርንባቸው ቀናት፣ ሙቀቱ፣ ብቸኝነቱ፣ የልብ መሰቀሉ
የተጎዳንባቸው ቀናት ላይ በሙሉ ምልክት አድርገንባቸዋል.
ወንበር ላይ ተቀምጣ የሚያምሩ እግሮቿን አነባበረችና ራሷን ለማቀዝቀዝ ልታራግብበት መፅሄት አንሳች ደስ የሚል የፍቅር ፈገግታ ወደኔ አቅጣጫ እያሳየች “ስላስጠበቅኳችሁ ይቅርታ። ጠዋት መጥቼ ላያችሁ ነበር። ግን
አባቴ ሙሉ ትኩረቴን ፈልጎ ስለነበር ከሰዓት ልጎበኛችሁ እቅድ አወጣሁ:: ከዚያ የሄድኩበትን ጉዳይ አሳጥሬ ከእራት በፊት ከልጆቼ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ
እንድችል ብዬ ስሮጥ መጣሁ” አለች: “ሀይቁ ላይ እየቀዘፍኩ ነበር።ወንድሞቼ የዘጠኝ አመት ልጅ ሳለሁ እንዴት እንደምቀዝፍ አስተምረውኝ ነበር ከዚያ አባታችሁ እዚህ ሊኖር ሲመጣ እንዴት መቅዘፍ እንዳለበት
አስተማርኩት ሀይቁ ላይ ብዙ ጊዜ እናሳልፍ ነበር፡ መቅዘፍ ልክ እንደ
መብረር ነው... አስደናቂ ደስታ ይሰጣል” የእሷ ደስታ የእኛን ደስታ እንደሰረቀ አስተውላ መናገሯን አቆመች።
“መቅዘፍ?” ጮህኩ። “ለምን ምድር ቤት ሄደሽ ለወንድ አያትየው ስለኛ አልነገርሽውም? እዚህ ውስጥ ቆልፈሽ የምታስቀምጪን እስከ መቼ ነው?
ለዘለዓለም?”
ሰማያዊ አይኖቿ ክፍሉ ውስጥ ተንከራተቱ ከወንበሩ ላይ ልትነሳ ከጀለች:ክሪስ ጣሪያው ስር ካለው ክፍል መፅሀፍቶች ተሸክሞ መጣ።
“ካቲ እናትሽ ላይ አትጩሂባት!” አለኝ፡ “ሰላም እማዬ፣ በጣም አምሮብሻል፡'የያዛቸውን መፃህፍት ጠረጴዛ ላይ አደረገና አቀፋት በእናቴ ብቻ ሳይሆን በወንድሜም እንደተጎዳሁ ተሰማኝ፡ ምንም ሳናደርግ በጋው ሊያልቅ ነው።
ሽርሽር ወይም ዋና ቦታ አልሄድንም ወይም ጫካ ውስጥ አልተንሽራሸርንም ጀልባ አላየንም ወይም የዋና ልብስ ለብሰን ጓሮ ያለው የመዋኛ ገንዳ ውስጥ
እንኳን አልተንቦራጨቅንም
“እማዬ!” ጮህኩ፡ በእግሮቼ ቆሜ ለነፃነታችን ለመታገል እየተዘጋጀሁ
“ለአባትሽ ስለኛ ለመንገር ጊዜው ደርሷል ብዬ አስባለሁ! እዚህ ክፍል ውስጥ መኖርና ጣሪያው ስር ያለው ቦታ ላይ መጫወት ሰልችቶኛል! መንትዮቹ |
ንፁህ አየርና የፀሀይ ብርሀን እንዲያገኙ እፈልጋለሁ። እኔም መውጣት እፈልጋለሁ ወንድ አያታችን አባታችንን በማግባትሽ ይቅር ካለሽ ለምን እኛን ሊቀበለን አይችልም? እኛን የስጋ ዘመዶቹ እንደሆንን የማይቆጥረንና
የሚያፍርብን ያን ያህል አስቀያሚ አስቸጋሪ ወይም ደደብ ነን እንዴ?"
ክሪስን ገፋ አድርጋ የተነሳችበት ወንበር ላይ አንገቷን አቀርቅራ ፊቷን በእጆቿ ቀብራ ተቀመጠች: በደመነፍስ ከዚህ በፊት ደብቃን የነበረን የሆነ እውነት ልታወጣው እንደሆነ ገመትኩ። ኮሪና ኬሪን ጠርቼ ጎንና ጎኔ አስቀመጥኳቸው:
ክንዶቼን እያንዳንዳቸው ላይ አደረግኩ፡ ክሪስ ከእናታችን ጎን ይሆናል ብዬ ሳስብ ወደኛ መጥቶ አልጋው ላይ ከኮሪ አጠገብ ተቀመጠ፡ እንደገና እንደ በፊቱ ከባድ ንፋስ ሊወስደን ያለ፣ በልብስ ማስጫ ገመድ ላይ የተቀመጥን ትናንሽ ወፎች መስለን ነበር።
"ካቲ፣ ክሪስቶፈር…” ስትል ጀመረች:: አሁንም አንገቷን እንዳቀረቀረች ነው:
“ለእናንተ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ አልነበርኩም” አለች ልክ ይህን እንዳልገመትኩ ሁሉ፡-
“ዛሬ ለእራት ከእኛ ጋር አትቆይም?” ስል ጠየቅኳት በሆነ ምክንያት ሁሉንም እውነቶች አለማንሳት ፈልጌያለሁ።
“ስለጠየቅሽኝ አመሰግናለሁ መቆየት እፈልግ ነበር ግን ለዚህ ምሽት ሌሎች እቅዶች አሉኝ" ይህ የእኛ ቀን ነው እስኪጨልም ከሷ ጋር የምንሆንበት ጊዜ ትናንትና ከእኛ ጋር የቆየችው ለግማሽ ሰዓት ብቻ ነበር።
“ደብዳቤው” አጉረመረመችና አንገቷን ቀና አደረገች: “ግላድስተን እያለን እናቴ
የፃፈችው ደብዳቤ ላይ እዚህ እንድንኖር ጋብዞናል ግን ደብዳቤው መጨረሻ ላይ አባቴ አጭር ማስታወሻ ፅፎ እንደነበር አልነገርኳችሁም:"
“አዎ” እኔም ገፋፋኋት፡ “መንገር ያለብሽን ንገሪን እንቀበለዋለን” አልኳት።
እናታችን ራሷን የምትቆጣጠር ሴት ናት᎓ ነገር ግን መቆጣጠር የማትችለው አንድ ነገር አለ እሱም እጆቿን ነው: ሁልጊዜም እጆቿ ስሜቶቿን ይከዳሉ።እጆቿ ረፍት የለሽና ልክ እንደሚታጠብ ሰው ይንቀሳቀሳሉ።
“ሴት አያታችሁ ደብዳቤውን ፅፋ ፈረመችው፣ መጨረሻው ላይ ደግሞ አባቴ የራሱን ማስታወሻ ጨመረበት…" አመነታች: አይኖቿን ለአንድ ወይም ለሁለት ሰከንድ ጨፈነች: ከዚያ ከፈተቻቸውና እንደገና አየች። “ወንድ
አያታችሁ ሲፅፍ አባታችሁ በመሞቱ ደስ እንዳለውና ክፉ ሰዎች ሁልጊዜም የሚገባቸውን እንደሚያገኙ፣ ከእኔ ጋብቻ ብቸኛው መልካም ነገር የሰይጣን
ዘሮች አለመፈጠራቸው እንደሆነ ተናግሮ ነበር፡
በፊት ቢሆን “ምንድነው?” ብዬ እጠይቅ ነበር፡ አሁን ግን አውቃለሁ የሰይጣን ዘሮች ማለት ከሰይጣን የተፈለፈሉ ከሚለው ጋር አንድ ነው የሆነ ክፉ፣ የተበላሸ፣ መጥፎ ሆኖ የተወለደ።
ክንዶቼን መንትዮቹ ላይ እንዳደረግኩ አልጋው ላይ ተቀምጬ ወደ ክሪስ
ተመለስኩ፡ ክሪስ ቁርጥ አባታችንን ይመስላል: አባታችን ነጭ የቴኒስ ልብስ የሚለብስ፣ ረጅም፣ ኩሩ፣ ባለ ወርቃማ ፀጉርና ነሀስ የመሰለ ቆዳ ያለው ነበር:
ክፉ የሚባለው ደግሞ ጥቁር፣ ጠማማ፣ ያደፈጠና ትንሽ እንጂ ዋሽተው የማያውቁ ንፁህ ሰማይ የመሰሉ ሰማያዊ አይኖች ያሉትና የሚያምር ፈገግታ ያለው ረጅም ሰው አይደለም።
“እናቴ እናንተን ስለመደበቅ ያላትን እቅድ አባቴ ባላነበበው ደብዳቤ ላይ አሰፈረች" አለችና አጠቃለለች ፊቷ ቀልቶ ነበር።
“አባታችን የወንድሙን ልጅ በማግባቱ ምክንያት ብቻ ነው እንደ ክፉና ምግባረ ብልሹ የተቆጠረው?” ክሪስ ጠየቀ፡ “የሰራው ስህተት ያ ብቻ ነው?
“አዎ!” ብላ ጮኸች የምትወደው ልጇ ስለተረዳት ደስ ብሏታል። “አባታችሁ ህይወቱን ሙሉ አንድ ይቅር የማይባል ኃጢአት ሰርቷል እሱም ከእኔ ጋር በፍቅር መውደቁ ነው ህጉ በአጎትና በወንድም ልጅ መካከል ያለ ጋብቻን
ይከለክላል፤ ዝምድናቸው በግማሽ ቢሆንም እንኳን። እባካችሁ አትርገሙን
እንዴት እንደነበረ ነግሬያችኋለሁ ከሁላችንም አባታችሁ በጣም ምርጥ ነበር” ልታለቅስ ደረሰች በአይኖቿ እየለመነችን ነበር ቀጥሎ የሚመጣውን
አውቄያለሁ:
“ክፋት ምንድነው? ምግባረ ብልሹነት ምንድነው? ሁሉም ያለው በተመልካች አይን ውስጥ ነው:” በእሷ መንገድ እንድናየው በጥድፊያ ቀጠለች። “ወንድ
አያታችሁ መልአክ ላይ ሳይቀር ስህተት ያገኛል። እሱ በሁሉም የቤተሰቡ አባላት ላይ ፍፁምነት የሚጠብቅ አይነት ሰው ነው እሱ ግን ከፍፁምነት እጅግ የራቀ ነው: ነገር ግን ያንን ልትነግረው ብትሞክር በጥፊ ያጮልሀል
ክሪስቶፈር፣ የሆነ ጊዜ ስላንተ ልነግረው እችላለሁ ብዬ አስባለሁ። እንዴት ጎበዝ ተማሪ እንደሆንክና ሁልጊዜ ትልቅ ማርክ የምታገኝ እንደሆንክ ካቲን ሲያይና ትልቅ የዳንስ ተሰጥኦዋን ሲያውቅ… እነዚህ ሁለት ነገሮች
ብቻ ገና መንትዮቹን ሳያይ እንዲለዝብ ያደርጉታል። እንደማስበውና ተስፋ
እንደማደርገው በቀላሉ ይሸነፍልንና ጋብቻችን ትክክል እንዳልሆነ ማመኑ ስህተት እንደነበረ ይረዳል”

👍31❤4
“እማዬ” አልኳት በደከመ ድምፅ ላለቅስ ደርሻለሁ። “ስትናገሪ ጭራሽ እንደማትነግሪው ይመስላል: መንትዮቹ ምንም ያህል ቆንጆ ቢሆኑም፣ ክሪስ
ምንም ያህል ጎበዝ ቢሆንም፣ እኔ ምንም ያህል ጥሩ ዳንሰኛ ብሆንም እንኳን በፍፁም አይወደንም: የትኛውም ነገር ለእሱ ልዩነት አያመጣም: አሁንም
ይጠላናል: የሚያስበን የሰይጣን ዘሮች አድርጎ ነው አይደል?”
ተነስታ ወደ እኛ መጣች: እንደገና በጉልበቷ ተንበርክካ ሁላችንንም ልታቅፈን ሞከረች: “ከዚህ በፊት ረጅም ጊዜ በህይወት እንደማይቆይ አልነገርኳችሁም?
ቶሎ ካልሞተ ስለ እናንተ የምነግርበት መንገድ እፈልጋለሁ እምልላችኋለሁ።እነግረዋለሁ። ብቻ ታገሱ ተረዱኝ አሁን ያጣችሁትን ደስታ በሙሉ በኋላ
ሺ እጥፍ አድርጌ እክሳችኋለሁ" አለች:
እምባ ያቀረሩት አይኖቿ እየለመኑን ነው፡ “እባካችሁ. ስለምትወዱኝና
ስለምወዳችሁ ለኔ ብላችሁ ትዕግስት ይኑራችሁ፡ ረጅም አይሆንም፣ ረጅም ሊሆን አይችልም:: ህይወታችሁ አስደሳች እንዲሆን የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለሁ አንድ ቀን በቅርቡ የሚኖረንን ሀብት አስቡ፡ “ችግር የለም እናቴ” አለ ክሪስ ልክ አባታችን ያደርግ እንደነበረው እያቀፋት። “ብዙ ትርፍ
ነገር የምናገኝበት ባይሆንም እንኳን የጠየቅሽን ብዙ አይደለም::''
“አዎ” አለች እናታችን በጉጉት። “የጥቂት ጊዜ መስዋዕትነትና ትንሽ ተጨማሪ ትዕግስት… ከዚያ በህይወት ውስጥ ያሉ መልካምና ጣፋጭ ነገሮች ሁሉ
የእናንተ ይሆናሉ” ለመናገር የቀረኝ ነገር ምናለ? እንዴት መቃወም እችላለሁ? አሁንም ከሶስት
ሳምንት በላይ መስዋዕት አድርገናል ተጨማሪ ቀናት ወይም ሳምንታት ወይም ሌላ ወር ቢሆንስ? ግድ የለም፣ ከቀስተደመናው መጨረሻ የወርቅ ማሰሮ እየጠበቀን ነው:
ቀስተደመና በጣም ቀጭንና በቀላሉ ከሚሰበር ድር የተሰራ ሲሆን፣ ወርቅ ደግሞ ብዙ ይመዝናል፡ እና ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ሁሉንም ነገር የመስራት
ምክንያት ወርቅ አይደል?

❤14👍10
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
አንድ ጊዜ ከተናገረች የማትመለሰው ሚስ ካርላይል ፥ ቤቷን ለቃ ሚስተር
ካርላይል የቀጠራቸውን ሠራተኞች አሰናብታ ፒተርንና ሁለት ሠራተኞቿን ይዛ
ጓዟን ሁሉ ጠቅልላ ኢስት ሊን ገባች " ሚስተር ዲል አድራጎቷ የማይባ መሆኑን
ሊያስረዳት ቢሞክርም አልተቀበለችውም
ሚስተር ካርላይልና ሚስቱ በተጋቡ በአንድ ወራቸው ዓርብ ቀን ማታ ወደ
ቤታቸው ተመለሱ " መምጣታቸው አስቀድሞ ታውቆ ስለ ነበር ሚስ ካርላይል ከበረንዳው ቁማ ስትጠብቅ አንድ የሚያምር ሠረገላ በአራት ፈረሶች እየተሳበ ዘለቀ።
ሚስ ካርላይል የሠረገላውን ማማርና ትልቅነት ዐይታ በንዴት ከንፈሯን መጠጠች " ጠቆር ያለ ደስ የሚል የሐር ቀሚስ ለብሳ አዲስ ባርኔጣ ደፍታ ነበር » በአንድ ወር ውስጥ ቁጣዋ በረዶላታል የሚሻለው የሚቻላትን ሁሉ አድርጋ ሙሽሮቹን በደስታ መቀበል መሆኑን አስባና አምና ተዘጋጅታ ጠበቀቻቸው ሚስተር ካርላይል ከሳቤላ ጋር ሆኖ ደረጃዎቹን ወጣ "
“ መጥተሻል እንዴ ኮርነሊያ ? እሰይ ጎሽ ! እንደ ምን ሰነበትሽ ሳቤላ .. እኅቴ ናት ” ብሎ አስተዋወቃት
ሳቤላ እጅዋን ስትዘረጋላት ኮርነሊያ መልካም ፈዷ ሆኖ የጣቶቿን ጫፍ ነካ አደረገችላትና
“ደኅና ነሽ እመቤት ? '' አለቻት በሚቆረቁር ድምፅ
ሚስተር ካርላይል አንድ ላይ ተዋቸውና ከሠረገላው ዕቃ እንዳይቀር ለመቆጣጠር ወጣ ሚስ ካርላይል ወደ ሳሎን ገብታ ሳቤላን '' በይ እንግዲህ እመቤት. .ከፎቅ ወጥተሽ ከራት በፊት የመንገድ ልብስሽን ብትቀይሪው አይሻልም? አለቻት"
ኣመሰግናለሁ፤ ወዶ ክፍሌ እሔዳለሁ ራት ግን አያስፈልገኝም " እመንገድ በልተናል ”
ታዲያ ምን ብትቀምሺ ይሻልሻል ? ” አለች ሚስ ካርላይል
“ ሻይ ባገኝ ከሆነማ » በጣም አምሮኛል "
“ ሻይ ? ” አለች ካርላይል በመገረም “ ሻይ አሁን ! የፈላ ውሀ መኖሩንም አላውቅም ከሌሊቱ አምስት ሰዓት ላይ ሻይ ከጠጣሽ የአንዲት ቅፅበት እንኳን ዕንቅልፍ ሳታገኝ ይነጋል ”
" አዬ .. እንግዲያውስ ግድ የለም ይቅርብኝ » አስፈላጊነቱም እስከዚህ አይደለምና ባላስቸግር ይሻላል " ” ከመተላለፊያው ላይ ከማርቨል ጋር ፊት ለፊት ተጋጠሙ " ምንም ቃል ሳይለዋወጡ ተፋጠጡ " ማርቨል አለባበስ ዐዋቂ ነበረች አሁንም ባለ አምስት ደረጃ ቀሚስ አጥልቃ ዐይነርግቧን አድርጋ ዣንጥላዋን ይዛ ሽክ ብላ አምሮባት ነበር " ይህ ሲሆን ሳቤላ ቬን ከተቀመጠችበት እየተንሰቀሰቀች ዕንባዋን ታወርደው ጀመር ሆድ ባሳት ወደ ቤቷ ወደ ኢስት ሊን የተመለሰች አልመስላት አለ " ሚስተር ካርላይል ገባና ሁኔታዋን ተመለከተ "
“ ሳቤላ !” አላት ነግሩ ገርሞት ወደ እሷ አየተጠጋ “የኔ ፍቅር"
ምን ነካሽ?”
“ ደከመኝ መሰለኝ ” አለችው ዝግ ብላ ወደዚህ ቤት ተመልሶ መምጣቱ አባባን አስታወሰኝ የትኛው እንዶፈደሆነ አላውቀውም አሁንስ ወደ መኝታዬ ብሔድ ደስ ይለኝ ነበር።
ሚስተር ካርላይልም አላወቀውም ሚስ ካርላይል መጣችና እዚያ
ከቤተ መጻሕፍቱ ጐን ያሉት ምርጥ ክፍሎች ናቸው" እኔ ልውስዳት ? ” አለች "
ሚስተር ካርላይል ግን ራሱ መሔድን መረጠና ለሳቤላ እጁን ዘረጋላት " እሷም በሚስ ካርላይል ፊት ስታልፍ ፊቷን በዐይነ ርግቧ ጋረደች
ሲገቡ ቀንዲሎች አልተለኮሱም ክፍሉ ይቀፋል ይቀዘቅዛል
“ነገሩ ሁሉ እንዶ ተዘበራረቀ ነውሳ? የተደረገ ዝግጅት የለም አለ ሚስተር ካርላይል “ አሽከሮቼ የጻፍኩላቸው ደብዳቤ በደንብ ስለ አልገባቸው ነገ ማታ የምንመጣ መስሏቸው ነው " "
“ አርኪባልድ ” አለች ሳቤላ የራስ መሸፈኛዋን ያወለቀች በጣም ድክም ብሎኛል ደግሞ ምንም ደስ አላለኝም እንግዲህ ወደ ሳሎን ባልወርድና ልብሴን አወላልቄ ብተኛስ ? ”
ቀና ብሎ አያትና ፈግ አለ ባልወርድሳ አልሽ? ከገዛ ቤትሽ መመለስሺን ረሳሺው ? እንዳፈቀደሽ እንጂ የደስታ ቤት እንደሚሆንልሽ አምናለሁ ..የኔ
ፍቅር እንዲሆንልሽም የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ ” አላት ።
ከሱ ላይ ድግፍ ብላ ጩኻ ስትንሰቀለቅ ብስጭቷን ብትክትክ ማለቷን በትዕግሥት ችሎ እያባበለ ፡ ቀና ብሎ የሚያየው ፊቷን እየሳመ ያረጋጋትና ያጽናናት
ጀመር የሱ ፍላጐት ይች ከእጅ የባችውን ውብ አበባ ተንከባክቦ ለመያዝ ነበር ነገር ግን ራሱን ከእኅቱ የበላይነት ማላቀቅ ካልቻለ ዓላማው ግቡን እንዳይስት ሊያ
ሠጋው ይችላል ሳቤላ ባልዋን እንደምታፈቅረው በደንብ ብታውቅም በደግነቱና ባለውለታዋ በመሆኑ ለማፍቀር እንድትበቃም ትመኝ ነበር ።
“ ምን ትቀምሽ ... ሳቤላ ? ” አላት ሚስተር ካርላይል “ ሻይ ይምጣልሽ ?
“ተወው ... አመስግናለሁ ” አለችው የሚስ ካርላይልን መልስ በማስታወስ"
“ የለም አንድ ነገር መቅመስ አለብሽ » ከሠረገላው ውስጥ ሳለን የምጠጣው ነገር ባገኘሁ ስትይ ነበር "
“ውሃ ይበቃኛል ይሻለኛል ማለቴ ነው እሱንም ማርቨል ትሰጠኛለች''
ሚስተር ካርላይል ወጥቶ ሲሔድ የሳቤላ ደንገጡር አንጀቷ እርር ብሎ ተናዳ ለምቦጯን ጥላ ምላሷ እየተንቀጠቀጠ የእመቤቷን ልብስ አወለቀችላት "
የጋብቻዉ ዕለት የሚንከባከብ ከፍተኛ ማዕረግ ያለው የወንድ ሎሌ ባለመኖሩ ከዚያ ቀን ጀምሮ ንዴቷ ሲጠራቀም ሰንብቷል " ያለፈው ቅሬታ እንዳይበቃት
ከቤት ብትመጣ ደግሞ እሷ እንደምታውቀው እንደ ታላላቅ መኳንንት ቤት የሠለጠኑ
የልፍኝ አሽከሮች የቤት አዛዥና የምግብ አሳላፊዎች አለመኖራቸውን ስታውቅ የባሰውን ተናደዶች " በተጨማሪ ከሚስ ካርላይል ጋር ተጋጨች » ማርቨል የእመቤቷን ልብስ የያዘ አንድ አነስተኛ ጥቅል ተሸክሞ የሚያስገባ አሽከር ቀብረር እያለች ስትጣራ ሚስ ካርላይል አገኘቻትና ራሷ ተሸክማ እንድታስባው ነገረቻት "ማርቭል የባሰውን እሳት ሆነች ሴትዬዋ ማን መሆንዋን አስቀድማ በማወቋ ተወቻት እንጂ
ማርቨል ዕቃውን አንሥታ ራሷ ላይ ልትወረውረው ቃጥቷት ነበር "
ሌላስ ምን ቀረ እሜቴ ? - አለች ማርቨል ዕቃውን አስገባችና "
ምንም አለች ሳቤላ “ልትሔጂ ትችያለሽ "
ሳቤላ የቤት ውስጥ የሙቀት ልብሷን ደራርባ የሙቀት ጫማ አድርጋ መጽሐፍ ይዛ ተቀመጠች ማርቨል እጅ ነሥታ ወደ መኝታዋ ሔደች » ሚስተር ካርላይል
ከሳቤላ ዘንድ ወጥቶ እኅቱን ፍለጋ ሔዶ። ራት የምትበላ እሷው ብቻ መሆኗን ስታውቅ በተለይ የዛንለት ቀደም ብላ መብላት አሰኛት " ሚስተር ካርላይል ሲገባ አንድ
የዶሮ ክንፍ ይዛ ስትግተግት ሚስ ካርላይልን አገኛት።
“ኮርነሊያ ”አላት " “ እኔ ነገሩ ሁሉ አልገባኝም " የኔን አሽከሮች አላየኋቸውም " ያንቺን ግን አያቸዋለሁ " የኔዎቹ የት ነው ያሉት ? ''
"ሔዱ ! ”
ሔዱ ? ለምን ? በጣም ጥሩ አሽhሮች መስለውኝ ነበር ።"
“ እንዴታ ! ለጥረታቸውስ ወግ አለው ! እንዴ በውድ ልብሶች የሚሽቀረቀሩ ስለቤት አያያዝ ምንም ግድ የሌላቸው ደንታ ቢሶች ኦሽከር ብሎ ዝም ነበሩ”
ትላለህ ? ዳሩ አንተ ምኑን ታውቀዋለህ? እኔስ ትርፍ ስለሆኑ አሰናበትኳቸው ወደ ፊትም ቢሆን አርኪባልድ . . . በቤት ውስጥ ጣጣ እንዳትገባ " በል አሁን ከሱ ምላስ ሥጋ ቁረጥልኝ አለችው "
“ ግን ምን አጠፉ ? ” አላት ያዘዘችውን ሥጋ እየቆረጠላት "

👍15
“ አርኪባልድ ካርላይል . . እንዲያው እንዲህ ከንቱ ሆነህ ትቀር ? ለማግባት ብትፌልግስ አቻዎችህ የሆኑ ብዙ ቆንጃጂት ሞልተውልህ አልነበረም ?
"ተይ ቆይ ” አላት ንግግርዋን ሳትጨርስ አቋርጦ …“ ስለ ጋብቻዬምኮ ማወቅ የሚገባሽን ሁሉ አንድ ባንድ ዝርዝር አድርጌ ጽፌልሽ ነበር አሁን ስለሱ ለመhራከር አልፈልግም " እንዲህ በማለቴ ይቅርታ አድርጊልኝ » ይልቅስ ወደ አሽከሮቹ ነገር እንመለስ " የት ናቸው ? ''
“ ትርፍ ስለሆኑ አሰናበትኳቸው አልኰህ ከቤት አራት አሉን እመቤቲቱም አንዲት ጥሩ ገረድ አምጥታለች 1 አምስት በል « እኔ ደግሞ እዚህ የመጣሁት ለመቀመጥ ነው "
ሚስተር ካርላይል ጥቃት ተሰማው ሁልጊዜ ከእኅቱ ፈቃድ ወጥቶ አያውቅም " ግን ' ' እኔና ሚስቴ ብቻችንን ብንሆን ይሻለናል ' የሚል ሐሳብ መጣበት "
የራስሽ ቤትሳ ? ” አላት "
“ዕቃውን አሟልቸ አከራየሁት " ተከራዮቼ ዛሬ ገቡበት " እንግዲህ ከኢስት ሊን አውጥተህ ከመንገድ አትጥለኝ " ሁለት ቤት ባንይዝም ወጪያችን ብዙ ነው ባንተ
ደረጃ የሆኑ ብዙ ሰዎች በኔ አብሮ መኖር በጣም ደስ ባላቸው ነበር " ሚስትህ እመቤት ሁና ተከብራ ትቀመጣለች » ክብሯን አልነካባትም ስለ ቤት አያያዝ ማንኛውንም ሥራ እኔ እቈጣጠርላታለሁ እሷም በሕይወቷ የቤት ሠራተኞች አዝዛ የምታውቅ ስለማትመስልና ልምድም ስለሌላት እኔ ካለሁላት ደስታውን አትችለውም ”
ነገሩን በዚሀ መልኩ አቀነባብራና አሳምራ ስታቀርብለት፡ እውነትም ጥሩ ሐሳብ ሳይሆን አይቀርም ብሎ አመነታ " ለእኅቱ አስተሳሰብ ታላቅ አክብሮት ነበረው " መቸም በሁላችንም ቢሆን የልማድ ኃይል ይበረታብናል "
“ በርግጥ ኮርነሊያ ... በኢስት ሊን ላንቺ የሚሆን ቦታ አለ "
ከመጠን በይ ነዋ ያውም እኛ ሁላችን ግማሹን ከያዝን በኋላ ለእመቤቲቱ የሚቢቃትን ያህል ሊተርፍላት ይችላል " አለችው።
"ኢስት ሊን ኮ የኔ ነው ” አላት "
"ዕብደትህም ጭምር የራስህ ነው "
" ስለ አሽከርቼ እንደሆን " አላት ንግግርዋን ቸል ብሎ አሳልፎ "አስፈላጊ
የመሰሉኝን ያህል ማሳደር እችላለሁ እኔ ሚስቴን በሽልማትና በጌጥ ላንቆጠቁጣት ባልችልም ፡በተቻለኝ ሁሉ እንዲመቻት አደርጋለሁ ሠረገላውንና ፈረሶቹን የሚንከባክብ እንኳን አንድ ሰ ው
ኮርነሊያ የሠራ አካላቷ ዛለ “ “አረ በፈጠረሀ ምንድነው የምታወራው ?
“ከሎንደን አንድ ቆንጆ ግልጽ ሠረገላና ጥንድ ድንክ ፈረሶች ገዝቻለሁ
አሁን የመጣንበት ሠረገላ የሎርድ ማውንት እስቨርን ስጦታ ነው "
"አርኪባልድ ! የምትሠራው ወንጀል ! ”
"ወንጀል ? ”
“ አሳብ የለሽ አባካኝነት ' የሚያሳስብ ችግርን ያመጣል " ይህን በልጅነትህ
አስተምሬሃለሁ መቆጠብ ደግ ነው ገንዘብ መበተን ኃጢአት ነው ''
“ ያለ ዐቅም ማውጣት ኃጢአት ሊሆን ይችላል ዐቅምን አይቶ ጥቅምን ገምቶ
የሚደረግ ወጭ ግን ማባከን አይባልም » ኃጢአት አይደለም ከዐቅሙ ቀላይ ያወጣል ብለሽ አትሥጊ።
“ባዶ ኪስ ከሙሉ ኪስ ይሻላል በላ ! አለችው በቁጣ ይህ አሁን የደረሰን ፒያኖ ፡ ገዝተኸው ነው ? ”
“ ለሳቤላ የገዛሁት ስጦታ ነው "
“ ምን ያህል ፈጀ ? ”
“ዋጋውስ ትንሽ ነው አሮጌው ፒያኖ ስለ ተበላሸ ነውየተሻለ የገዛሁት "
“ ምን ያህል ፈጀ ነው ያልኩህ ”
“ አንድ መቶ ኻያ ስድስት ፓውንድ = "
ሚስ ኮርነሊያ በገንዘቡ ብዛት ደንግጣ እጅዋን ወደ ሰማይ አነሣች አሽከሩ
የወይን ጠጅ አመጣላቸው " ሚስተር ካርላይል አንድ ብርጭቆ ጠጣና ውሃና
ወይን ይዞ ወደ ሳቤላ ክፍል ሔደ አንገቷን የክንድ ማስደገፊያ ካለው ወንበርላይ
በከፊል ቀብራ ፊቷን ሸፍና ተቀምጣ አገኛት " የእግር ዳና ሰምታ ቀና ስትል ፊቷ
ልውጥውጥ ብሎ ' ዐይኖ ተበርዘው ሰውነቷ ሲንቀጠቀጥ ተመለከታት "
“ ምን ነካሽ ? ” አላት ድንግጥ ችኩል ብሎ
“ማርቨል ከወጣች በኋላ ፍራት ፍራት
አለኝ " ደወሉ ያለበት ሲጠፋኝ ጊዜ
በተስፋ ስጠባበቅ ደረስክልኝ "
“ እኔ ኮርነሊያን ሳነጋግራት ነበር " ግን ምንድነው የሚያንቀጠቅጥሽ ”
ብዙ አስፌሪ ነገሮች በሐሳቤ ይመጡብኛል አርኪባልድ. አትቆጣኝ እንጂ አባባ የሞተው እዚሀ ክፍል ነበር ። ስለ ሌሊት ወፎቹ የሰማሁት ታሪክ ይመጣብኛል" ልክ አባቴ የሞተ ጊዜ እንዳደረጉት ከመስኮቱ የሠፈሩ ይመስሉኛል "
“ በይ አይዞሽ ! ክፍሎችሽ ነገ ይለወጣሉ።
አይ ተወው እዚሁ እንቆይ አባቴ የነበረባቸው ክፍሎች መሆናቸውን እያሰብኩ እዚሁ እንቆይ " ከእንግዲህስ አልደነግጥም "
እንደዚያ እየተናገረች እንኳን የመልኳ መለዋወ ንግርን ሲያስተባብልባት ይታይ ነበር" ሚስተርካርላይል ወደ በሩ ሲያመራ ሮጣ ሔዳ አየችውኖ :
“አርኪባልድ' በጣም ትቆያለህ እንዴ ? " አለች
“ አይ ከአንድ ስዓት የበለጠ አልቆይም ” ብሏት መልሶ በክንዶቹ እቅፍ
አድርጐ ያዛት " ወዲያውም ደወለና ማርቨል መጣች...

👍21
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
አሁን ሙሉውን እውነት አውቀናል
ወንድ አያታችን እስኪሞት ድረስ እዚህ ክፍል መቆየታችን የማይቀር ነው::አንዳንዴ ሲከፋኝና ቅር ሲለኝ ምናልባት ገና ከመጀመሪያው እናታችን አባቷ ማንንም በምንም ጉዳይ ይቅር የሚል ሰው አለመሆኑን ታውቅ ይሆናል ብዬ
አስባለሁ፡
“ግን…” አለ ደስተኛውና በጎ አሳቢው ወንድሜ: “በሆነ ቀን ሊሞት ይችላል።የልብ በሽታ እንደዚህ ነው: የደም ስሩ ተበጥሶ ደሙ ወደ ልቡ ወይም ወደ
ሳምባው ይፈስና ልክ እንደ ሻማ ያጠፋዋል” አለ።
እኔና ክሪስ በመካከላችን ክፉና ተገቢ ያልሆነ ነገር እንባባልና በልባችን ግን እንታመማለን፡ እየደማ ላለው የራሳችን ክብር የሚሰማንን ህመም ሌላኛችንን
ባለማክበር እንዲሻለን መሞከራችን ቢሆንም ስህተት ነበር።
“አሁን ረዘም ላለ ጊዜ እዚህ መቆየታችን ካልቀረ፣መንትዮቹንም ሆነ ራሳችንን ዘና ለማድረግ ብዙ የሚያዝናኑ ነገሮችን ለማድረግ መወሰን ያስፈልጋል።ለዚያ ደግሞ የሆኑ አስደሳችና አሪፍ ነገሮችን ማለም እንችላለን” አለ፡
“እንደሚታየው ይህ ክፍል አስቀያሚና ቆሻሻ ነው፡ ግን ለምን እኛ በሆነ መንገድ የፈጠራ ተሰጥኦዎቻችንን ተጠቅመን ከአስቀያሚ አባጨጓሬነት
ወደሚያምር ቢራቢሮነት አንለውጠውም?” አለና ለእኔና ለመንትዮቹ በማራኪና
በሚያሳምን መንገድ ፈገግ አለልን፡ ይህንን የሚያስጠላ ቦታ ለማሳመር መጣርና መንትዮቹ ውበት እያደነቁ ዥዋዥዌ የሚጫወቱበት በቀለማት
ያሸበረቀ የውሸት የአትክልት ቦታ ማዘጋጀት ደስ የሚል ሃሳብ ነው እርግጥ ነው በማንኛውም ቀን አያታችን ሊሞትና ይህንን ቦታ ዳግመኛ ላንመለስበት
ለቀን ስለምንሄድ ሙሉውን ክፍል አስጊጦ ለመጨረስ አንችልም።
የዚያን ቀን ምሽት እናታችን እስክትመጣ መጠበቅ አልቻልንም: ልክ እንደገባች እኔና ክሪስ የጣሪያውን ስር ክፍል የማሳመር እቅዳችንን በጉጉት
ነገርናትና መንትዮቹ የማይፈሩት የሚያምር የአትክልት ስፍራ ልናደርገው እንደሆነ አስረዳናት ለቅፅበት አይኖቿ ላይ እንግዳ የሆነ እይታ ተንፀባረቀ
“ቦታውን የሚያምር ለማድረግ፣ መጀመሪያ ንፁህ ማድረግ አለባችሁ: እኔም ምን እንደምረዳችሁ አስብበታለሁ” አለች።
ከዚያ እናታችን መጥረጊያዎች፣ መሬት መፈግፈጊያ ቡርሾችና የዱቄት ሳሙና አመጣችና በጉልበቷ ተንበርክካ የጣሪያውን ስር ክፍል ጥጋጥጎች፣ ጠርዞቹንና
በትልልቆቹ ዕቃዎች ስር ያሉትን ቦታዎች አፀዳች: እናታችን እንዴት
እንደሚፀዳና እንደሚወለወል በደንብ ታውቃለች: ግላድስተን ውስጥ ስንኖር የእናታችንን እጅ የሚያቀላና ጥፍሮቿን የሚሰብርባትን ከባባድ ስራዎች ሁሉ የምታግዛት በሳምንት ሁለት ቀን የምትመጣ ሠራተኛ ነበረችን።
አሁን ግን እሷ ራሷ አሮጌ ስማያዊ ጂንስና አሮጌ ሸሚዝ ለብሳና በጉልበቷ ተንበርክካ ፀጉሯን ወደ ላይ ሰብስባ እያፀዳች ነው: አደነቅኳት። ከባድ፣ አድካሚና አሰልቺ ስራ ነው:: እሷ ግን አንድ ጊዜ እንኳን አላማረረችም:: ደስ
የሚል ነገር እንደሆነ ሁሉ እየሳቀችና እየተደሰተች ነበር።
ከአንድ ሳምንት ከባድ ስራ በኋላ አብዛኛውን ቦታ በተቻለ መጠን አፀዳነው።ከዚያ የነፍሳት ማጥፊያ አምጥታ ስናፀዳ ልናገኛቸው ያልቻልናቸው ነፍሳት የተደበቁበት ቦታዎች ላይ ሁሉ ረጨች᎓ የሞቱ ሸረሪቶችና ሌሎች ነፍሳትን
በባልዲ ውስጥ ሞልተን በጀርባ ባለው መስኮት በኩል ስንደፋው ታችኛው የጣሪያው ክፍል ላይ አረፈ፡ በኋላ ዝናቡ አጥቦ በአሸንዳው በኩል ወደታች
አወረዳቸው:: ከዚያ አራታችንም መስኮቱ ጠርዝ ላይ ተቀምጠን ወፎች ሲበሏቸው ተመለከትን፡፡
አሁን ቦታው ስለተፀዳ እናታችን አረንጓዴ ተክሎችንና በገና ወቅት የሚያብብ አበባ አመጣችልን: እዚህ እንደምንሆን ስትናገር ስሰማት ተኮሳተርኩ።
ጉንጬን እየነካካች “በመኮሳተር ያልተደሰትሽ አትምሰይ፤ ስንሄድ ይዘነው እንሄዳለን፡ ሁሉንም አትክልቶች ይዘናቸው እንሄዳለን፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ፀሀይን የሚወድ የትኛውንም ነገር ትተን መሄድ አንችልም:" አለች:
አትክልቶቹን በሙሉ ወደ ምስራቅ የዞረ መስኮት ባለው የመማሪያ ክፍል ውስጥ አስቀመጥናቸውና በጣም በመደሰት ሁላችንም በጠባቧ ደረጃ እየሮጥን
ወረድን: እናታችን ታጠበችና ድካም ስለተሰማት ወንበሯ ላይ አረፍ አለች።እኔ ለምሳ ጠረጴዛውን ሳዘገጃጅ መንትዮቹ ጭኗ ላይ ወጥተው ተቀመጡ፡ እስከ እራት ሰዓት አብራን ስለቆየች ደስ የሚል ቀን ሆኖልን ነበር፡ ከዚያ በረጅሙ ተነፈሰችና መሄድ እንዳለባትና አባቷ ስለእሷ እንደሚጠይቅ ሁልጊዜ ቅዳሜ ቅዳሜ የት እንደምትሄድና ለምን እንደምትቆይ ማወቅ እንደሚፈልግ ነገረችን
“ከመኝታ ሰዓት በፊት ተደብቀሽ መጥተሸ ልታይን ትችያለሽ?'' ክሪስ ጠየቃት።
“ዛሬ ማታ ወደ ሲኒማ እሄዳለሁ፤ ከመሄዴ በፊት ግን ላያችሁ ብቅ እላለሁ በምግብ ሰአቶቻችሁ መካከል የምትበሏቸው የካርቶን ዘቢቦች ገዝቼላችሁ ነበር። ሳላመጣ እረሳሁት" አለች።
መንትዮቹ በዘቢቡ እጅግ ደስ ሲላችው እኔም ለእነርሱ ደስ አለኝ። “ወደ ሲኒማ የምትሄጂው ብቻሽን ነው?” ስል ጠየቅኳት
“አይ አብራኝ ያደገች ልጅ አለች: የልብ ጓደኛዬ ነበረች: አሁን አግብታ እዚሁ አካባቢ ትኖራለች ወደ ሲኒማ የምሄደው ከእነሱ ጋር ነው:” ተነስታ ወደ መስኮቱ ስትሄድ ክሪስ መብራቱን አጠፋው: ከዚያ መጋረጃውን ገለጥ አድርጋ
የልብ ጓደኛዋ የምትኖርበትን ቤት አቅጣጫ አመለከተችን፡ “ኤሌና ሁለት ያላገቡ ወንድሞች አሏትı አንደኛው ጠበቃ ለመሆን እያጠና ነው ሀርቫርድ የህግ ትምህርት ቤት ገብቷል: ሌላኛው ደግሞ የቴኒስ ተጫዋች ነው:"
እማዬ ከነዚያ ወንድማማቾች ከአንዱ ጋር ቀጠሮ ኖሮሽ ነው?” ስል ጮህኩ።እየሳቀች መጋረጃውን ሸፈነችና “ክሪስ መብራቱን አብራው" አለችው: ከዚያ ካቲ እኔ ማንንም አልቀጠርኩም ኤሌና መውጣት አለብሽ ብላ ችክ አለች እንጂ፤ እውነቱን ለመናገር በጣም ደክሞኛል ቀጥታ ወደ አልጋ መሄድ ወይም ከልጆቼ ጋር መቆየት ይሻለኝ ነበር። ግን መውጣት አለመፈለጌን
ስነግራት ለምን እንደሆነ ከመጠየቅ አላቋርጥ አለች አልፎ አልፎ ወደ ሲኒማና ወደ መርከብ ሽርሽር የምሄደው ሰዎች ሁልጊዜ በሳምንቱ መጨረሻ ለምን ቤት እንደምቀመጥ እንዲጠረጥሩ ስለማልፈልግ ነው:”
ከጣሪያው በታች ያለውን ክፍል ማሳመርና በቀስተደመና ያጌጠ ቆንጆ የአትክልት ስፍራ ለማድረግ የማይታሰብ ይመስል ነበር: እጅግ በጣም ከባድ ስራና የፈጠራ ችሎታ የሚጠይቅ ነበር፡ ወንድሜ ግን ማድረግ እንደምንችል
አምኖ ስለነበር እናታችን በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት ስትሄድ ቆራርጠን የምንለጥፋቸው አበቦች የተሳሉበት መፅሀፎችና የስዕል ዕቃዎች ይዛ እንድትመጣ ሀሳብ አቀረበ፡ የውሀ ቀለሞች፣ በርካታ ብሩሾች፣ ሳጥን ሙሉ እርሳሶች፣ ብዙ የስዕል ወረቀቶች፣ ማጣበቂያዎችና አራት ጥንድ መቀሶች አመጣችልን።
“ለመንትዮቹ ከለር መቀባትና አበቦችን መቁረጥ አስተምሯቸው” ስትል አዘች፡ እና በምትሰሯቸው ነገሮች ሁሉ እንዲሳተፉ አድርጓቸው: የመዋዕለ
ህፃናት አስተማሪዎቻቸው እንድትሆኑ ሾሜያችኋለሁ:"
በሚቀጥለው ቀን የአንድ ሰዓት የባቡር መንገድ ርቀት ላይ ወደሚገኘው ከተማ ሄዳ መጣች: ጥሩ ጤንነት ላይ ነበረች ቆዳዋ ከውጪው አየር የተነሳ ትኩስ

👍35👎1
የፅጌረዳ ቀለም ያለው ሆኗል ልብሶቿ ከማማራቸው የተነሳ ትንፋሽ አጠረኝ። የተለያዩ ቀለማት ያላቸው ጫማዎችና “የማይረቡ” ብላ የምትጠራቸውን ጌጣጌጦች ጥቂት በጥቂት ማከማቸት ጀምራለች: አሁን ያደረገቻቸው ጌጦች የማንፀባረቃቸውን ሁኔታ ስመለከት አልማዝ ሊሆኑ እንደሚችሉ አሰብኩ።በጣም ደክሟት ግን እጅግ ተደስታ ወንበሯ ላይ አረፍ አለችና ስለቀን ውሎዋ ነገረችን “እነዚያ የፅህፈት መኪና ላይ ያሉት ቁልፎች ላያቸው ላይ ፊደል ስላልተፃፈባቸው ከአንድ መደዳ በላይ ለማስታወስ በየጊዜው ግድግዳ ላይ
የተፃፉትን ማየት አለብኝ ያ ደግሞ ፍጥነቴን ይቀንሰዋል፡ እና ከታች
መደዳ የተፃፉትን ማስታወስ ላይም ብዙም ጎበዝ አይደለሁም ፍጥነቴም በጣም ቀርፋፋ ነው: በዚያ ላይ ብዙ ስህተቶች እሰራለሁ፡ ግን ተነፈሰች: “… ግን በመጨረሻ በደንብ የምችላቸው ይመስለኛል። ሌሎች ሰዎች ከቻሉ እኔም እችላለሁ”
እማዬ አስተማሪዎችሽን ወደሻቸዋል?” ሲል ክሪስ ጠየቀ
መልስ ከመስጠቷ በፊት እንደ ልጃገረድ ተሸኮረመመች: “በመጀመሪያ የመኪና
ፅህፈት ስለምታስተምረን አስተማሪ ልንገራችሁ: ስሟ ወ/ሮ ሄሌና ብራዲ ይባላል ቅርፅዋ ልክ የአያታችሁን ይመስላል። ግዙፍ ነች። ጡቶቿ በጣም ትልልቅ ናቸው! እንደሷ አይነት ትልልቅ ጡቶች አይቼ አላውቅም የጡት
መያዣዋ ገመድ ወደ ትከሻዋ ስለሚወርድባት ወደ ቦታው ለመመለስ ሁልጊዜ
በቀሚሷ አንገት በኩል ስለምትጎትተው ክፍሉ ውስጥ ያሉ ወንዶች እያዩ ይስቁባታል”
በጣም ስለገረመኝ “የፅህፈት መማሪያ ትምህርት ቤት ውስጥ ወንዶችም ይማራሉ እንዴ?” ብዬ ጠየቅኩ “አዎ፣ ጥቂት ወጣት ወንዶች አሉ አንዳንዶቹ ጋዜጠኞች፣ ደራሲዎች፣
ወይም ደግሞ የፅህፈት መሳሪያ በመጠቀም የተለያዩ ሥራዎች የሚሰሩ ሰዎች ይማራሉ። ወ/ሮ ብራዲ ከባሏ የተፋታች ሴት ናት እና አንዱ ወጣት ላይ አይኗን ጥላለች: ቢያንስ ከእሱ በአስር አመት ያህል ትበልጣለች እሱ
ችላ ሲላት እሷ ግን ትሽኮረመማለች፡ እሱ ደግሞ የሚመለከተው እኔን ነው:
ነግሬሻለሁ ምንም አይነት ሀሳብ ውስጥሽ እንዳይገባ ካቲ፡ በጣም አጭር ከመሆኑ የተነሳ እኔ ልሸከመው የምችለው አይነት ሰው ነው፡ እኔ ደግሞ በር
ላይ ተሸክሞ ሊያስገባኝ የሚችል ሰው ካልሆነ ማግባት አልፈልግም”
ሁላችንም ሳቅን‥ ምክንያቱም አባታችን ረጅምና እናታችንን በቀላሉ ሊሸከማት
የሚችል ሰው ነበር። በተለይ ወደቤት በሚመለስበት አርብ ምሽት ብዙ ጊዜ
እንደዚያ ሲያደርግ እናየው ነበር
“እማዬ እንደገና ስለማግባት እያሰብሽ አይደለም፣ ነው እንዴ?” ሲል ክሪስ ጠበቅ
አድርጎ ጠየቃት። “አይ ውዴ በጭራሽ! አባታችሁን በጣም ነው የምወደው።
የእሱን ጫማ ለመሙላት እጅግ በጣም ልዩ የሆነ ሰው ያስፈልጋል እስካሁን
ካልሲው ጋ የሚደርስ እንኳ አላገኘሁም::” አለችና አቀፈችው::
አራት ሰዓት ላይ ቁርሳችን በልተን ከጨረስን በኋላ የበላንበትን ሳvን አጥበንና
የተረፈውን ምግብም የክፍሉ ቀዝቃዛ ቦታ ላይ አስቀምጠን፣ ሠራተኞቹ
ከሁለተኛው ፎቅ ወጥተው ሲሄዱ እኔና ክሪስ የመንትዮቹን እጆች ይዘን
ጣሪያው ስር ወዳለው የመማሪያ ክፍል ሄድን፡ እዚያ ቁጭ ብለን አበቦች
ስንስል፣ ስንቆራርጥና ቀለም ስንቀባ ቆየን፡ ክሪስና እኔ ምርጥ የሚባሉ
አበቦች ሰራን
የሠራናቸውን ትላልቅ አበቦች በግድግዳው ለጣጠፍን፡ ክሪስ አሮጌው መሰላል
ላይ ቆሞ ከዳር እስከዳር ገመድ ዘረጋና ያለማቋረጥ የሚንቀሳቀሱ ባለቀለም
የአበባ ስዕሎችን ሰቀልን፡
እናታችን ጥረታችንን ለማየት መጥታ የደስታ ፈገግታ ሰጠችን: “አዎ
የሚያስደንቅ ስራ ተሰርቷል። ቆንጆ አድርጋችሁታል። እና ልክ የሆነ ነገር
ልታመጣልን እንደምትችል በማሰብ አይነት ወደ አበቦቹ ተጠግታ አየችና
በሚቀጥለው ቀን በትልቅ ጠፍጣፋ ሳጥን ባለቀለም የመስተዋት ዶቃዎች
ይዛልን መጣች:: ስለዚህ የአትክልት ስፍራችን እንዲያንፀባርቅ ውበት
ልንጨምርበት ቻልን፡፡
መንትዮቹ ቦታውን ለማሳመር ያለንን ትጋት ሲመለከቱ፣ ከጣሪያው ስር

ወይም ደግሞ የፅህፈት መሳሪያ በመጠቀም የተለያዩ ሥራዎች የሚሰሩ ሰዎች ይማራሉ። ወ/ሮ ብራዲ ከባሏ የተፋታች ሴት ናት እና አንዱ ወጣት ላይ አይኗን ጥላለች ቢያንስ ከእሱ በአስር አመት ያህል ትበልጣለች እሱ
ችላ ሲላት እሷ ግን ትሽኮረመማለች እሱ ደግሞ የሚመለከተው እኔን ነው
ነግሬሻለሁ ምንም አይነት ሀሳብ ውስጥሽ እንዳይገባ ካቲ በጣም አጭር ከመሆኑ የተነሳ እኔ ልሸከመው የምችለው አይነት ሰው ነው እኔ ደግሞ በር

ሁላችንም ሳቅን ምክንያቱም አባታችን ረጅምና እናታችንን በቀላሉ ሊሸከማት የሚችል ሰው ነበር። በተለይ ወደቤት በሚመለስበት አርብ ምሽት ብዙ ጊዜ እንደዚያ ሲያደርግ እናየው ነበር።
“እማዬ እንደገና ስለማግባት እያሰብሽ አይደለም፣ ነው እንዴ?” ሲል ክሪስ ጠበቅ አድርጎ ጠየቃት። “አይ ውዴ በጭራሽ! አባታችሁን በጣም ነው የምወደው።የእሱን ጫማ ለመሙላት እጅግ በጣም ልዩ የሆነ ሰው ያስፈልጋል እስካሁን
ካልሲው ጋ የሚደርስ እንኳ አላገኘሁም::” አለችና አቀፈችው::
አራት ሰዓት ላይ ቁርሳችን በልተን ከጨረስን በኋላ የበላንበትን ሳህን አጥበንና የተረፈውን ምግብም የክፍሉ ቀዝቃዛ ቦታ ላይ አስቀምጠን፣ ሠራተኞቹ
ከሁለተኛው ፎቅ ወጥተው ሲሄዱ እኔና ክሪስ የመንትዮቹን እጆች ይዘን ጣሪያው ስር ወዳለው የመማሪያ ክፍል ሄድን፡ እዚያ ቁጭ ብለን አበቦች ስንስል፣ ስንቆራርጥና ቀለም ስንቀባ ቆየን፡
ክሪስና እኔ ምርጥ የሚባሉ
አበቦች ሰራን።
የሠራናቸውን ትላልቅ አበቦች በግድግዳው ለጣጠፍን፡ ክሪስ አሮጌው መሰላል ላይ ቆሞ ከዳር እስከዳር ገመድ ዘረጋና ያለማቋረጥ የሚንቀሳቀሱ ባለቀለም የአበባ ስዕሎችን ሰቀልን።
እናታችን ጥረታችንን ለማየት መጥታ የደስታ ፈገግታ ሰጠችን: “አዎ የሚያስደንቅ ስራ ተሰርቷል። ቆንጆ አድርጋችሁታል። እና ልክ የሆነ ነገር ልታመጣልን እንደምትችል በማሰብ አይነት ወደ አበቦቹ ተጠግታ አየችና
በሚቀጥለው ቀን በትልቅ ጠፍጣፋ ሳጥን ባለቀለም የመስተዋት ዶቃዎች ይዛልን መጣች:: ስለዚህ የአትክልት ስፍራችን እንዲያንፀባርቅ ውበት
ልንጨምርበት ቻልን፡፡
መንትዮቹ ቦታውን ለማሳመር ያለንን ትጋት ሲመለከቱ፣ ከጣሪያው ስር ያለውን ክፍል ስም ስናነሳ መነጫነጭና መናከሳቸውን አቆሙ ምክንያቱም
ክፍሉ ቀስ በቀስ ግን ደግሞ በእርግጠኝነት ደስ ወደሚል የአትክልት ቦታ እየተቀየረ ነበር እየተቀየረ በመጣ ቁጥር እኛም የቀሩትን የግድግዳ ክፍሎች
ለመሸፈን የበለጠ ቆራጥ ሆንን!
በእያንዳንዱ ቀን እናታችን ከዚያ የፅህፈት ሥራ ትምህርት ቤት ወደኛ ስትመጣ የየቀኑ ስራችንን ማየት ነበረባት። “እማዬ” አለች ኬሪ ትንፋሽ ባጠረው የወፍ ድምፅዋ “ቀኑን ሙሉ አበባ ስንሰራ ብቻ ነው የዋልነው፣ ካቲ አንዳንድ ጊዜ ታች ወርደን ምሳ እንድንበላ አትፈልግም::” አለች:
ካቲ ምግብ መብላታችሁን እስክትረሺ ድረስ ያንን ክፍል በማሳመር ስራ መወጠር የለብሽም:”
“ግን እማዬ ወደዚያ ሲሄዱ እንዳይፈሩ ለእነሱ ስንል እኮ ነው የምንሰራው፡”
ሳቀችና አቀፈችኝ፡፡ ካቲዬ አንቺና ወንድምሽ ሁለታችሁም ፅኑ አቋም ያላችሁ ናችሁ: ከአባታችሁ የወረሳችሁት መሆን አለበት እንጂ መቼም ከእኔ አይደለም እኔ በቀላሉ ተስፋ የምቆርጥ ነኝ፡"
“እማዬ አሁንም ትምህርት ቤት እየሄድሽ ነው? አሁን መፃፍ ላይ የተሻልሽ እየሆንሽ ነው አይደል?” ስል ጮህኩ ደስ አላላትም፡
“አዎ” እንደገና ፈገግ አለችና ተመልሳ ወንበሯ ላይ ተቀመጠች። እጇን ከፍ አድርጋ ስትታይ ያደረገችውን አምባር እያደነቀች ትመስል ነበር። ትምህርት
ቤት ለመሄድ ለምን ይሄ ሁሉ ጌጣጌጥ እንደሚያስፈልጋት መጠየቅ ስጀምር ሌላ ነገር መናገር ጀመረች: “አሁን የአትክልት ቦታችሁ ውስጥ
የሚያስፈልጋችሁ እንስሳት መስራት ብቻ ነው" አለች
“ግን እማዬ፣ ፅጌረዳ አበባ ለመሳል እንደዚህ ካስቸገረን እንዴት እንስሳት መሳል እንችላለን?” መራራ ፈገግታ እያሳየችኝ በጣቷ ጫፍ አፍንጫዬን ነካ አደረገችኝና ካቲ እንዴት እኮ ተጠራጣሪ እንደሆንሽ! ሁሉን ነገር ትጠይቂያለሽ ሁሉን ትጠራጠሪያለሽ አንድን ነገር በጣም ከፈለግሽው
የምትፈልጊውን መስራት እንደምትችይ ማወቅ ይገባሽ ነበር በዚህ አለም ላይ ስኖር ያወቅኩትን ሚስጥር እነግርሻለሁ። ሁሉ ነገር ሲወሳሰብ፣ ሁሉንም ነገር እንዴት በቀላሉ ማድረግ እንደሚቻል የሚያስተምር መፅሀፍ ደግሞ
አለ፡”
አዎ ማወቅ ያለብኝ ያንን ነው፡
እናታችን በደርዘን የሚቆጠሩ የአርት መማሪያ መፅሐፎች አመጣች: ከዚያ አመናችሁም አላመናችሁም መሠረታዊ ዘዴውን ብቻ በመጠቀም ጥንቸሎች፣
ወፎችና ትናንሽ ፍጥረታትን በእጆቻችን መስራት ቻልን
እውነትም ለየት ያሉ ሆኑ፤ በጣም ደስ የሚሉ ያደረጋቸው ለየት ማለታቸው እንደሆነ አሰብኩ ክሪስ የሰራቸውን ሁሉንም እንስሳት ትክክለኛ ቀለማቸውን የሚመስል ቀባቸው እኔም የራሴን የምፈልገውን ቀባኋቸው: እናታችን
የልብስ ስፌት እቃዎች የሚገኙበት ሱቅ ገብታ የተለያዩ ቀለማት ያላቸው ክሮች፣ ቁልፎችና ሌሎች የማስጌጫ ቁሳቁሶች ገዝታልን መጥታ እጄ ላይ ስታስቀምጥልኝ አይኖቼ ለእሷ ያለኝን ፍቅር በሙሉ እንዳሳዩዋት አውቃለሁ።
ይህ ሌላ አለም ውስጥ ስትሆንም ስለኛ እንደምታስብ ማረጋገጫዬ ነበር።የተገደበውን ኑሯችንን በተቻለ መጠን አስደሳች ለማድረግ እየሞከረች እንጂ
ለራሷ አዳዲስ ልብሶች፣ አዳዲስ ጌጣጌጦችና ኮስሜቲክስ ለመግዛት እያሰበች አልነበረም:
አንድ ቀን ኮሪ ቀኑን ሙሉ ለመስራት ሲደክም የዋለውን ብርቱካናማ የወረቀት
ቀንዳውጣ ይዞ እየሮጠ ወደ እኔ መጣ፡ ወደ ስራ ሊመለስ ቸኩሎ ምሳውን እንኳ የበላው በጥቂቱ ነበር።
ትንንሽ እግሮቹን አንፈራጦ ፊቴ ላይ የሚታየውን ስሜት ለማንበብ በኩራት ቆሟል፡ የሰራው ነገር የተጣመመ ኳስ የሚመስል ነገር ነበር።

👍24👏2
“ጥሩ ቀንዳውጣ ይመስልሻል?” ብሎ ጠየቀ: የምናገረው ቃል ማግኘት ባለመቻሌ ተኮሳትሮና ተጨንቆ ነበር።
“አዎ” አልኩ በፍጥነት “በጣም አስገራሚና ቆንጆ ቀንዳውጣ ነው” ብርቱካን እንደሚመስል አድርገህ አልሰራኸውም አይደል?”
“አይ ብርቱካን እንደዚህ ቀንዳውጣ የተጥመለመለ አይደለም ወይም የተጣመመ
መዳሰሻ የለውም” ኬሪ መቀስ በመጠቀም የሆነ ሀምራዊ ቀለም ያለው ነገር ሰራችና ትል ብላ
ጠራችው ስሙ “ቻርሊ ነው” አለችና ባለ አራት እግሩን “ትል” ሰጠችኝ፡፡
በወረቀት አበባዎች በሰራነው የአትክልት ስፍራችን ውስጥ በአንደኛው ግድግዳ ላይ ቀንዳውጣውን ለጠፍነው: ክሪስ ተቀመጠና በቀይ ቀለም እንስሳት፣
ከመሬት ትል ተጠንቀቁ!!!´ የሚል ምልክት ፃፈ እኔም የኮሪ ቀንዳ አውጣ ችግር ላይ እንደሆነ ስለተሰማኝ የራሴን ማስጠንቀቂያ
ፃፍኩ “እዚህ ቤት ዶክተር አለ?” ኮሪ ቀንዳ አውጣውን “ሲንዲ ሉ” ብሎ ጠራት እናታችን የዛሬውን ቀን ስራችንን እየሳቀች ተመለከተች: ምክንያቱም
ደስ ተሰኝተንበት ነበርና
“አዎ እዚህ ቤት ዶክተር አለ” አለችና የክሪስን ጉንጭ ለመሳም ሳብ አለች:የኔ ልጅ ሁልጊዜም ለታመሙ እንስሳት ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል።ኮሪ አንተ ደግሞ ቀንዳውጣህን ወድጃታለሁ ግን በጣም... በቀላሉ የምትጎዳ
ትመስላለች” አለች።
ኬሪም በመጓጓት “የኔንስ ቻርሊ ወደድሽው?” ስትል ጠየቀች᎓ “ጥሩ አድርጌ ነው የሰራሁት ቆንጆ እንዲሆንልኝ ሀምራዊውን ቀለም ሁሉንም ነው የተጠቀምኩት። አሁን ምንም ሀምራዊ ቀለም የለንም”
“በጣም ቆንጆ ትል ነው: በእውነት በጣም ያምራል::” አለች እናታችን
መንትዮቹን ጭኗ ላይ አስቀምጣ አንዳንዴ እየረሳችው የምትሄደውን ማቀፍና መሳም እየሰጠቻቸው ነው: “በተለይ ከቀዩ አይን ዙሪያ ያደረግሽውን ጥቁር መስመሮች ወድጄዋለሁ በጣም ውጤታማ ነው:” ደስ የሚል የቤት ትዕይንት
ነበር። ሶስቱ እናቴ ወንበር ላይ ተቀምጠዋል ክሪስ በክንዱ የወንበሩን መደገፊያው ተመርኩዞ ፊቱ የእናቱ ፊት ጋር ተጠግቶ ቆሟል። እኔ ደግሞ ሄጄ ትዕይንቱን በጥያቄ ላበላሸው ግድ ነው
“አሁን በደቂቃ ስንት ቃላት መፃፍ ቻልሽ እማዬ?”
“እያሻሻልኩ ነው።”
“ምን ያህል አሻሻልሽ?”
የምችለውን እያደረግኩ ነው ካቲ ቁልፎቹ ፊደል እንዳልተፃፈላቸው
ነግሬሻለሁ እኮ ካቲ፡ እየሞከርኩ ስለሆነ ትዕግስት ሊኖርሽ ይገባል፡ መቼም እንደዚህ አይነት ነገሮችን በአንድ ምሽት አትማሪም
ትዕግስት ትዕግስትን ግራጫ ቀብቼ ከጥቁሩ ደመና ጋር ሰቀልኩት ተስፋን ጠዋት ለጥቂት ሰዓታት እንደምናያት ፀሀይ ቢጫ ቀባሁት ፀሀዩዋ በፍጥነት
ሰማዩ ላይ ከፍ ብላ ትወጣና እኛን ለሀዘን ጥላን ፈጥና ከእይታ ትሰወራለች።
ስታድጉና ትልልቆች ሊሰሩት የሚገባ ብዙ ነገሮች ሲኖራችሁ፣ አንድ ቀን ለልጅ ምን ያህል ረጅም እንደሆነ ትረሱታላችሁ: በሰባት ሳምንታት ኮርስ ለአራት አመታት እየኖርን ይመስለኛል በሌሊት ተነስተን እንዳበደ ሰው ከመኝታ ወደ መታጠቢያ ቤት እየተሯሯጥን
መፈጠራችንን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን የምናጠፋበት አርብ መጣ፡ አንሶላውን ከአልጋው ላይ ገፍፌ እንደ ኳስ በማድቦልቦል የትራስ ጨርቁ ውስጥ ከተትኩት
ብርድ ልብሱንም እንደዚያው አደረግኩ፡ ከዚያ አያትየው እንዳዘዘችኝ የአልጋ
ልብሱን ፍራሹ ላይ አነጠፍኩት፡ ትናንት ማታ ነበር ክፍሉ ምንም ነገር እንዳይኖረው አድርገን ያፀዳነው- መታጠቢያ ቤቱን ጭምር፡ ከዚያ አያትየው
መጣችና ያመጣችውን የሽርሽር ቅርጫት ከጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ወስደን ቁርሳችንን እዚያ እንድንበላ አዘዘችን፡፡ ቤት ውስጥ ያሉት ቁሳቁሶች
ሁሉ እስኪያንፀባርቁ ድረስ አሻራችንን ሁሉ ጠረግን፡፡ አያትየው ይህንን ስትመለከት በከባዱ ተኮሳተረችና ከአቧራው ማንሻ ውስጥ ያለውን አቧራ
በመጠቀም ዕቃዎቹን በሙሉ አቧራ እንዲለብሱ አደረገች።
አንድ ሰዓት ላይ ጣሪያው ስር ያለው መማሪያ ክፍል ውስጥ የቀዘቀዘ ቁርሳችንን እየበላን ነበር ታች ሠራተኞቹ ክፍላችን ውስጥ ወዲያ ወዲህ ሲሉ በጣም በትንሹ ይሰማናል በጣቶቻችን እየተራመድን ደረጃው ጫፍ ላይ
ቆምንና ታች የሚከናወነውን ለመስማት ሞከርን፤ ይሁንና በእያንዳንዷ ደቂቃ
እንታያለን ብለን እየሰጋን ነበር።
አያትየው የልብስ ማስቀመጫው አጠገብ ቆማ መስታወቱን እንዲያፀዱ ስትነግራቸው ሠራተኞቹ ሲስቁና ሲቀላለዱ ይሰማኛል እንግዳ የሆነ ስሜት
ተሰማኝ እነዚያ ሠራተኞች እንዴት አንድ የተለየ ነገር አያስተውሉም?
ብዙ ጊዜ ኮሪ አልጋ ላይ ይሸናል'ኮ እና እንዴት ምንም አይነት ሽታ
አልሸተታቸውም? ልክ እንዳልተፈጠርን፣ በህይወት እንደሌለን፣ እንዴት ጠረናችን እንኳን ሳይቀር የማይታወቅ ሀሳባዊ የሆነ ፍጥረታት ሆንን?!
በመከፋት እርስ በርስ ጥብቅ አድርገን ተቃቀፍን፤ ጥብቅ አድርገን ሠራተኞቹ ወደ ልብስ ማስቀመጫው አልገቡም: ረጅሙን ጠባብ በርም
አልከፈቱም: እኛንም አላዩንም:: አልሰሙንም ቧንቧውን ሲፈትጉ፣
መታጠቢያውን ሲያፀዱ፣ መሬቱን ሲፈገፍጉ አያትየው ለሰከንድ እንኳን ክፍሉን አለመልቀቋ እንግዳ ነገር መሆኑ አልተሰማቸውም: ያ አርብ ሁላችንንም እንግዳ ነገር ፈጠረብን፡ ስለራሳችን ባለን ግምት እንደጠወለግን አመንን፡ ምክንያቱም ከዚያ በኋላ መናገር የምንችለው ቃል አላገኘንም።
ጨዋታችንን ወይም መፃህፍቶቻችንን አልተደሰትንባቸውም፡ አበባዎችን
በፀጥታ እየቆራረጥን እናታችን እንደገና ተስፋ ይዛ እስክትመጣ መጠበቅ ቀጠልን አሁንም ልጆች ነን፤ ተስፋ ደግሞ በልጆች ውስጥ እስከ እግር ጥፍራቸው
ድረስ የሚደርስ ጠንካራ ስር አለው ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ስንሄድና እያማረ ያለውን የአትክልት ስፍራችንን ስንመለከት፣ መሳቅና ማስመሰል እንችላለን:...

👍49
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...ሚስተር ካርላይል ወደ በሩ ሲያመራ ሮጣ ሔዳ አየችውና:
“አርኪባልድ በጣም ትቆያለህ እንዴ ? " አለችው።
“አይ ከአንድ ሰዓት የበለጠ አልቆይም ” ብሏት መልሶ በክንዶቹ እቅፍ አድርጎ ያዛት " ወዲያውም ደወለና ማርቨል መጣች።
ትጠብቀው ለነበረችው ለኮርነሊያ የማይመጣ መሆኑን እንድትነግራት ልኮ በሩን ዘጋና ሚስቱን ትክ ብሎ ሲያያት በጣም ነው የሚጨነቅልኝ ለካ ብላ አስበች " በበነጋው ጧት በቁርስ ጊዜ ኮርነሊያ አስቀድማ ቦታዋን ያዘች ቀጥለው ባልና ሚስቱ መጡ "
“ እንዴት አደርሽ...እመቤቲቱ ደኅና ተመችቶሽ አደርሽ ? ” እለቻት "
“ ደኅና ነኝ አመሰግናለሁ ” አለችና ከሚስ ካርላይል ፊት ለፊት ልትቀመጥ ስትል ያንቺ ቦታ ያ ነው...እሜቴ ” ብላ በእጅዋ ወደ ገበታው ራስጌ አመለከተቻት
ቡናውንም ፈቃድሽ ቢሆን እኔ ልቅዳልሽና ከመቅዳቱ ችግር ላድንሽ ” አለቻት።
“ ከሆነ በጣም ደስ ይለኛል ” አለች ሳቤላ።
ቁርስ ተበልቶ ሊያበቃ ሲል የሥጋ ደንበኛቸው ምን ምን ሥጋ እንደሚ
ቀርብ ለመጠየቅ መምጣቱን ፒተር ገብቶ ተናገረ መልሱ የሚጠበቀሙ ከሳቤላ ነበር።
እሷ ለራሷየዚህ ልምድ አልነበራትም " ምን እንደምትል ግራ ገብቷት ዝም አለች "
ነገረኛይቱ ኮርነሊያ ከአጠገቧ ባትኖር ኖሮ ) ከባልዋ ጋርም ቢሆን ትመካከርበት ነበር
አሁን አልቻለችም " እኅቲቱም ዝም ብላ ጠበቀቻት " ፒተርም መልስ ይዞ ለመሔድ እንደ ቆመ ቀረ
“ ጥቂት ለቅቅልና ለጥብስ የሚሆን ነገር እንዲያመጣ ብትነግረው ” አለች ሳቤላ ፈራ ተባ እያለች "
ቀስ ብላ ነበር የተናገረችው ሚስተር ካርላይልም ስለ ቤት አያያዝ ከሷ የተሻለ ስለማያውቅ የሷን ቃል ደገመው "
“ አዎን ለቅቅልና ለጥብስ የሚሆን ነገር እንዲያመጣ ለሰውየው ንግረው ፒተር አለ "
ሚስ ኮርነሊያ ብድግ አለች እንደዚህ ያለውን ትእዛዝ እየሰማች ዝም ልትል አልቻለችም " “ ለመሆኑ እንደዚህ የመሰለ ትአዛዝ ሥጋ ሻጩን ግራ እንደሚያጋባው ዐውቀሻል... እመቤት ? የሚያስፈልገውን ትእዛዝ ለዛሬ እኔ ልስጥልሽ ዓሳ ሻጩም አሁን ይመጣል ”
ከሆነስ እሺ!” ሳቤላ ከጭንቀቱ በመገላገሏ ደስ እያላት ፡ “ እኔ የዚህ ልምድ የለኝም " ወደፊት ግን የግድ መማር አለብኝ ስለ ቤት አያያዝ ምንም ነገር የማውቅ
አይመስለኝም
ሚስ ኮርኒ ምንም ሳትመልስላት ነጠቅ ነጠቅ ያለች ወታ ሔደች ሳቤላም ተይዛ እንደ ተለቀቀች ወፍ ከወንበሯ ብድግ አለችና ከባሏ ጎን ቆመቾ አበቃህ
አርኪባልድ ?
“ ማብቃቴ ነው የኔ ፍቅር ! ቡኖዬ ለካ ይኸው ይኸውና በቃ ጨረስኩ
እስኪ በግቢው ትንሽ ዘወር ዘወር እንበል ” አለችሙ እሱም ከተቀመጠበት ተነሣ ቀጭን ሽንጧን በእጁ አየዳበስ አስተውሎ አያት አሁን ሦስት ሰአት ዐልፏል እንደምታቂው ደግሞ አንድ ወር ሙሉ ቢሮ አልገባሁም"
እንባዋ ባይኗ ምላ ከኔ ጋር ብትቆይ ደስ ይለኝ ነበር " እኔስ ሁልጊዜ አብረከኝ መሆንክን እመኛለሁ » ኢስት ሊን ያላንተ ኢስት ሊን አይሆንም።
በተቻለ መጠን ካንቺ አልለይም
ፍቅሬ " አላት በጆሮዋ“ አሁን ነይና
በግቢው መኖፈሻ አብረን እንሸራሽር "
ወደ ክፍሏ ገብታ ለባበሰችና ተያይዘው ወጡ ካርላይል ስለ እህቷ ለማንሳት ምቹ አጋጣሚ ሆነለት "
እሷ ከእኛ ጋር ለመቀመጥ ትፈልጋለች ምዓ እንደምወስን አላወቅሁም በአንድ በኩል ቤቱን በማስተዳዶር ብዙ ልትጠቀምሽ ትችል ይሆናል " በሌላ በኩል
ደግሞ እኔና አንቺ ብቻችንን ብንሆን እንደ ልባችን ሆነን ደስ ብሎን የምንኖር ይመስልሻል?
ሳቤላ የተቋጠረ ፊቷ የማይፈታው ሚስ ኮርነሊያ ቋሚ ጠባቂ መሆኗን ስታስበው ልቧ ፍስስ አለ ግን ተጨናቂ ይሎኝተኛ ለሌሎች ስሜት አጥብቃ የምታስብ ረቂቅ ሰው ስለ ነበረች ምንም የቅሬታ ቃል አልተነፈሰችም “ ላንተና
ለሚስ ካርላይል ደስ የሚላችሁ ከሆነ ይሁን ” አለችው ላቤላ "
“ ሳቤላ .. ” አላት ኰስተር ብሎ።“እኔ የምፈልገው ላንቺ ደስ የሚልሽ እንዲሆን ነው " ማንኛውም ነገር እንደሚያስደስትሽ ሆኖ እንዲደራጅ እፈልጋለሁ
እኔ አሁን በሕይወቴ ዋናው ዓላማዬ ያንቺ ደስታ ነው ”
አባባሉ ከልቡ መሆኑን ሳቤላ ተረዳችው እሱን የመሰለ እውነተኛ ፍቅረኛና ጠባቂ ከጐኗ ካለ ሚስ ካርላይል የኑሮን ሰላም እንደማታበላሽባት ተሰማትና
ተዋት ትቀመጥ ፡ አርኪባልድ ... ምንም አታስቸግረንም ” አለችው "
“ እስቲ ለሁሉም ለአንድ ሁለት ወር ያህል ሁኔታውን እንየው ” አላት " እንዲህ እየተወያዩ ከመናፈሻው በር ደረሱና ሊለያት ሲል፡“ እኔስ ብቻዬን ወደ ቤት ከምመለስ አብሬህ ወደ ቢሮህ ሔጄ ጸሐፊህ በሆንኩ ደስ ይለኝ ነበር ' አለችው
እሱም በአነጋገሯ ሳቀና ተሰናብቷት ሔደ »
ሳቤላ ክፍሎቹን ሁሉ እየዞረች አየች » ሁሉም ጸጥ ብለዋል " ባባቷ ዘመን የነበራቸው ድምቀትና ሙቀት ጠፍቷል “ ከመልበሻ ክፍሏ ስትገባ ማርቨልን
ተንበርክካ የተጠፈረ ዕቃ ስትፈታ አየኘቻት " ሳቤላ ስትገባ ከእምብርክኳ ተነሣች
“ አንድ ጊዜ ላነጋግርዎ እሜቴ ? "
"ምንድነው?"
ማርቨል ከዚያ ሞቅ ሞቅ የማይል ትንሽና ቀዝቃዛ ግቢ መኖር ስለማይስማማት የእመቤቷ ፈቃድ ቢሆን ዕለቱን ለመሰናበት መፈለጓንና ይኸንኑም ተስፋ በማድረግ ዕቃዋን እንደ መጣ ያለ መፍታቷን ነገረቻት "
“ስለ አሽከሮቹ ጉዳይ አንድ የተፈጸመ ስሕተት ስለ አለ ነው " በተቻለ ፍጥነት ይታረማል " በተረፈ የሚስተር ካርላይል ቤት ምጥን ያለና ውሱን መሆኑን
ገና ከማግባቴ በፊት ነግሬሽ ነበር።
“ እመቤቴ እሱን ሁሉ እችለው ይሆናል ከሚስ ካርላይል ጋር ግን አንኳንም እንዲያውም ሁለት ግልፍተኞች ስንገናኝ አፍ እንዳንካፈትና ከዚያም አልፈን እጅ እንዳንሰናዘር እፈራለሁ እኔ በዚህ ዐይነት ሥፍር ቁጥር የሌለው ወርቅ ቢሰጡኝም አልቀመጥም " የዚህ ያሁኑ ሩብ ዓመት ደሞዜም ቢይዙብኝም ለመቅረት
አልፈልግም " ስለዚህ የተጠፈረውን ዕቃ ካደራጀሁልዎ በኋላ እንዲያሰናብቱኝ ብቻ
ነው የምለምነዎ "
ሳቤላ ፡ ማርቭል እንዳትሔድባት ለመለመን ክብሯ ባይፈቅድላትም ያለ ደንገጡር ምን እንደሚበጃት ሐሳብ ያዛት" ቢሆንም እርሳስና ወረቀት ይዛ የምትሰጣትን ዶሞዝ
አስልታ የብርና የወርቅ ገንዘቦች ከጠረጴዛው ላይ ካደረገችላት በኋላ ማርቨል . . ማግኘት ከሚገባሽ በላይ ነው " አስጠንቅቀሽና በቂ ጊዜ ሰጥተሽኝ መሔድ ነበረብሽ ” አለቻትና ትታት ወጣች " ማርቨልም እንዳለችው ትናንትናውን የገባውን ዕቃ አደራጅታ ስታበቃ ጆይስ እየሰደበቻትና እያዘነችባት ወጥታ ሔደች "
ሳቤላ ለምሣ ልብሷን ልትለብስ ወደ ክፍሏ ስትሔድ ጆይስ ተከትላት ገባች "
“ እኔ ለራሴ ስለ ወይዛዝርት ደንገጡርነት ልምድ የለኝም ነገር ግን ቢፋቅዱልኝ የምችለውን እንድረዳዎ ሚስ ካርላይል ልከውኝ ነው የመጣሁት አለቻት
ሳቤላ የሚስ ካርላይልን ደግነት በልቧ አመሰገነች "
“ የእቃዎችዎን ቁልፎች አምነው ከሰጡኝ እያሰብኩ አሰናዳልዎታልሁ ”
“እኔ ስለ ቁልፎች ምንም አላውቅም" ይዠም አላውቅ " አለቻት ሳቤላ ።ጆይስ የሚቻላትን ሁሉ ካደረገች በኋላ ' ሳቤላ ወደ ምግብ ቤት ወረዶች » ጊዜው
ወደ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ተቃርቦ ነበር ፤የራት ሰዓት ማለት ነው። ሳቤላ ሚስተር ካርላይልን ሲመጣ ለማግኘት ወደ መናፈሻው በር እያዘገመች ሔደች "
ከበሩ ዐልፋ ጥቂት ራመድ ካለች በኋላ በመንገዱ ዘቅዝቃ ብትመለከት አጣችው " ስለዚህ ተመልሳ ገብታ ከመንገዱ ትይዩ ፈንጠር ብላ ከአንድ ጥላማ ዛፍ
ሥር ተቀመጠች ወራቱ የግንቦት መገባደጃ በመሆኑ በጣም ይሞቅ ነበር ።

👍19👎1