አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ግማሽ ሰዓት ያሀል እንደ ቆየች ሚስተር ካርላይል እየገሠገሠ የመንገዱን አቀበት ወጥቶ በሩን አልፎ ከሣሩ ላይ ሲደርስ ሚስቱን አያት " ራሷን ከዛፉ ግንድ አስደግፋ እንቅልፍ ወስዷታል " የራሷ መሸፈኛና ጃንጥላዋ ከግሯ ሥር ወድቀዋል " ያንገቷ ሻሽ ሾልኮ መሬት ወርዷል ከንፈሮቿ ገርበብ ብለው ጉንጮቿ ቲማቲም መስለው ጸጉሯ በሁሉም ዙሪያ ተዘናፍሎ እስካንገቷ ወርዶ የሚያስደስት ሕፃን መስላለች።
ካርላይል ያ ሁሉ ውበት የሱ ገንዘብ መሆኑን አያሰበ የልቡ ምት ጨመረ " እሷን አያየ እንደ ቆመ ዐይኖቿን ገለጠችና ዙሪያዋን ስትመለከት የት እንደ ነበረችም ለጊጊዜው ማስታወስ አቃታት "

“ አርኪባልድ ! .. ተኝቸ ነበር እንዴ ? " አለችው

“ አዎን ' ልትሠረቂብኝም ትችይ ነበር ''

“ እንቅልፍ እንዴት እንደ ወሰደኝም አላውቅም " እኔ እዚችው ተደግፌ ያንተን መምጣት ሳዳምጥ ነበር።

“ቀኑን ሙሉ ምን ስትሠሪ ዋልሽ ?

” አላት ክንዷን ሳብ አድርጎ እጅ ለጅ ተያይዘው እየሐዱ ።

“ ኧረ ምኑን ዐውቄው ? አዲሱን ፒያኖ ስሞክር ስዓቱ ቶሎ ቶሎ ሔዶልኝ መምጫህ እንዲደርስ እየተመኘሁ አሁንም አሁንም ሰዓቴን ሳይ ፈረሶቹና ሠረገላውኮ ደረሱ ... አርኪባልድ "

“ አዎን ዐውቄአለሁ ፡ የኔ ፍቅር ከቤት ውጥተሽ ብዙ ቆየሽ ? L

አልመጣሁም አንተ እስክትመጣ ስጠብቅ ነበር ” ከዚያ ስለ ማርቭል ነገረችው " በጣም ተበሳጨ ባስቸኳይ ሌላ እንድትተካ ነገራት ሳቤላ ካስል ማርሊግ በነበረች ግዜ የሎርድ ማውንት እስቨርን ቤት ሥራ ስለ ከበዳት እመቤት ማውንት እስቨርን ትታ የወጣች አንዲት ልጅ እግር ሴት እንደምታውቅ ነገረችው

“ጻፊላትና ትምጣ ” አለ ሚስተር ካርይል "

ባልና ሚስቱ ሲገቡ ሚስ ኮርኒሊያ ከኮሪዶሩ አገኘቻቸው "

“ ምሣ ተሰናድቶ ሲጠበቅ ከግማሽ ሰዓት በላይ ሆነ "
አለችው ወንድሟን እየጮህች

አንቺ ደሞ የጠፋሽ መስሎኝ ነበር ... እሜቴ " አለቻት ፊቷን ወደ ሳቤላ መለስ አድርጋ

ቢእያንዳንዱ ዐረፍተ ነር እሜቴ የሚለውንል መጨመሯ ሳቤላን አልገባትም በተለይ ከኮርነሊያና ከሳቤላ ዕድሜ አንጻር ሲታይ ጨርሶ አለቦታው የገባ ቃል
"ነው ሚስተር ካርላይል በሰማው ቁጥር ግንባሩን ይቛጥራል " ጆይስ ግን ሚስ ካርላይል ይሆን ቃል የምትናገረው ስትቆጣ መሆኑን ደኅና አድርጋ ታውቃለች ከዚያ በፊት ከቢሮ ሊወጣ ባለመቻሉ መቆየቱን ነገራትና ወደ መልበሻ ክፍሉ አቀና ሳቤላም የካርላይልን መውጣት አይታ ኮርነሊያ የብስጭቷን ያህል እንዳትናራት ስለ ፈራች ሳይሆን አይቀርም እየሮጠች ተከተለችው ነገር ግን እሷ ሳትደርስ በሩ ተዘጋ " የእንግድነቷ ስሜት ገና ስላልለቀት
ከፍታ መግባቱ ደስ አላላትም
በሩን ከፍቶ ብቅ ብቅ ሲል ከመቃኑ ተደግፋ ቁማ አገኛት።

“ እንዴ ሳቤላ ! .... መጥተሻል እንዴ ? ”
“ አየጠበቅሁህ ነው አበቃህ ? '

“ማብቃቴ ነው ” ከዚያ እጅዋን ይዞ ወደ ውስጥ አስገብቶ ከይረቱ ልጥፍ አጀረጋት " በበነጋው ሌላ ጉድ ፈላ “ ሚስተር ካርላይል አዲስ ያመጣውን የድንክ ፈረሶች ሠረገላ ለቤተ ክርስቲያን መሔጃ እንዲዘጋጅ አዘዘ እኅቱ ቡራ ከረዩ አለች"

አርኪባልድ ! ምን እያልክ ነው ? እኔ መቸ እፈቅድና ? ”

“ ምንድነው የምትፈቅጅው ?

“ ፌረሶቹ በሰንበት ቀን እንዳይወጡ ነዋ ! እኔ አዕማዶ ምስጢርን በሚገባ የተማርኩ ሃይማኖተኛ ሴት ስለሆንኩ የሰንበት ቀንን የሠረግላ ጉዞ አልፈቅድም "እመቤት ” አለች ወደ ሳቤላ ዞር ብላ "

“ አርኪባልድ . . . ምናልባት ቀስ እያልን በእግራችን ብንሔድ ምንም ላይዳን ይችላል ” አለችው "
ሚስተር ካርላይል ሣቅ ብሎ ራሱን በአዎንታ ነቀነቀና | “ ዝም ብለሽ ለአራት ሰዓት ተኩል ተዘጋጂ ” አላት ።

እናስ በእግሯ ልትሔድ ነው ?” አለች ሚስ ኮርኒሊያ ሳቤላ ወጣ ስትል"

“ የለም በዚህ ሙቀት በግሯ መሔድ አትችልም እንድትሞክርም አልፈቅድላትም ስለዚህ ሳይጀመር ቀደም ብለን ስለምንሔድ ጆን ሠረገላውን ያዘጋጅልናል።

ከሱካር ነው እንዴ የተሠራችው ? የምትሟሟ ናት ? " አለችው "

- የኔ ጥበቃና እንክብካቤ የሚያስፈልጋት ገና ያልጠናች ለጋ ተክል ናት “

ካርላይል ልክ እንደሷ አነጋገር ቁርጥ ፍርጥ አድርጎ ነግሯት ወጣ ኮርኒሊያ እጅዋን አንሥታ አንድ ሕመም የተሰማት ይመስል ቅንጥና ቅንጧን ጥብቅ አድርጋ
ያዘችው "

ሠረገላው ቀረበ ሚስተር ካርላይልና ሳቤላ ተሳፍረው ቀስ እያሉ ሲሔዱ ሚስ ካርላይል ደግሞ በእግር መሔድ እንደማያሟሟት በግብር ለማሳየት የፈለገች ይመስል ስልድባብ የሚያህል ትልቅ ዣንጥላዋን ዘርግታ በአጠግቧ ያልፍ የነበረውን ሰረገላ እንኳን ቀና ብላ ሳታየው በረጅሙ እየተራመዶች ትግሠግ ጀመር "

ቤተክርስቲያኑ ዘድሮም እንዳለፈው ዓመት ትልቅ ነገር ለማየት አሰፍሶ ይጠብቃል " የሎርድ ዊልያም ቬን ልጅ በከበረና ባማረ የሙሽራ ጌጥና ልብስ ተንቈጥቁጣ ስትዘልቅ ለማየት ጓጉቷል - ነገር ግን አሁንም እንደ ታሰበው አልሆነም ።
ሳቤላ አዲስ ሙሽራ ሆና ወዳባቷ ቤት ' ወዳባቷ ደብር ብትመጣም የሙሽራ ልብስ አልለበሰችም " የኀዘን ልብሷን አልቀየረችም » ነጩ የራስ መሸፈኛዋ ሳይቀር ዐልፎ ዐልፎ በውስጡና በውጭ ባለ ጥቋቁር አበቦች ነበር ሚስተር ካርላይል ከቤተ ክርስቲያኑ እንደ ደረሰ በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ምስኪኑ ሎርድ ቬን ይቀመጥበት ከነበረው ከኢስት ሊን መንበር ተቀመጠ" ኮርነሊያ ካርላይል ግን ከራሷ ቦታ ቁጭ አለች።

ባርባራ ሔር ፡ ከወላጆቿ ጋር ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥታ ስለነበር በቅናት ዐይን ትመለከታቸው ጀመር " የዚያን ዕለት ወደ እዚያ በመምጣቷ ሀዘንን እንጂ
ደስታን አላገኘችም "

ኋላ የሎርድ ቬን መቃብር ወደ ነበረበት ወደ ቅጥሩ ምዕራባዊ ክፍል አመሩ " ሳቤላ ፊቷ በይነ ርግብ እንደ ተሸፈነ የመቃብሩን ሐውልት ጽሑፍ አየችው ።

ሳቤላ ቀስ ብላ ስትንሰቀሰቅ “ ቆይ እንጅ ፍቅሬ'ዛሬ ከዚህ ቦታ አይለቀስም” አላት " ክንዷን ወዶ ጐን ሳብ በማድረግ በጆሮዋ ሹክ ብሎ“ እንደ ምንም ብለሽ ለመቻል ሞክሪ” አባቴ አብሮኝ ከዚህ ቤተ ክርስቲያን የነበረበት ጊዜ ከትናንት ወዲያ ነው የሚመስለኝ " አሁን ደግሞ ይኸው . . . እዚህ ! ” አለችና ወደ ሐውልቱ እያመለከተች
“ በመቃብሩ ዙሪያ ጥቂት ማገሮች ያስፈልጉት ነበር ” አለች እንደ ምንም ብላ እንባዋን ገትታ ድምጿን መቈጣጠር ከቻለች በኋላ

“ አዎን እኔም ለሎርድ ማውንት እስቨርን ብነግራቸው አስተሳሰባቸ ተለየብኝ ! ግን ምንም አይደለም ! እኔ አሳጥረዋለ።

“ ወጪውን በጣም አበዛሁብህ እንጂ " "

“ እንደዚህ ያለውን ወጪ ስላወጣው ብቀር ነው የሚያሳዝነኝ "

“ በል እስቲ እኔ ያንተን ውለታ በምን እመልሰዋለሁ ” አለችና በረጅሙ ተነፈሰች " ያለመጠን ደስ አለውና ትክ ብሎ ፊቷን ሲያያት እሷም ያይኑን አገለጥ አይታ ፈገግ አለች “ ጆን ይኸውና ከሠረገላው ዘንድ እንሒድ አርኪባልድ” አለችው "

ከበሩ ውጭ ቆመው ከደብሩ አለቃ ቤተሰብ ጋር ሲያወጉ ከነበሩት ብዙ ሴቶች ውስጥ አንዷ ባርባራ ሔር ነበረች ሚስተር ካርላይል ሚስቱን ደግፎ ከሠረገላ ሲያስግባትና ተያይዘው ሲሔዱ ከንፈሮቿ ዐመድ መሰሉ "
አብረዋት የነበሩት የመልኳን ድንገተኛ መገርጣት ሲያዩባት ጊዜ አቤት ሙቀቱም መዓት ሆነ።
አለቻቸው "

ሚስተርና ሚስዝ ሔር ሲለምኑሽ አብረሽ መሔድ ነበረብሽ

« እሱስ በእግሬ መሔድ ፈልጌ ነው » አቻቸው ውስጥ ውስጡን እየተንገበገበች።

« እንዴት ያለች የታምር ልጅ ናት» አለች ወይዘሮ ሳቤላ ባሏን " "
ማን ትባላለች ? »

"ባርባራ ሔር "

💫ይቀጥላል💫
👍255
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


... ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ስንሄድና እያማረ ያለውን የአትክልት ስፍራችንን ስንመለከት፣ መሳቅና ማስመሰል እንችላለን።

አያትየው ምን እንደምንሰራ ለማየት አንድ ጊዜ እንኳን ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል አልመጣችም አብዛኛውን ጊዜ የመኝታ ቤቱን በር በቻለችው መጠን ድምጽ ሳታሰማ ስትከፍትና ስትቆልፍ እንደማንሰማት ተስፋ ታደርጋለች
የሆነ ክፉ ነገር ወይም ኃጢአት ስንሰራ ለመያዝ በቀዳዳ ታጮልቃለች።

ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ እግዚአብሔር ጅራፉን እስኪገምድ ድረስ ካለምንም መከልከል የምንፈልገውን ለማድረግ ነፃ ነን፡፡ አያትየው አንድ ቀን እንኳን እሷ ባታየን እግዚአብሔር እንደሚያየን ሳትነግረን ክፍሉን ለቃ ወጥታ አታውቅም ነገር ግን አንድ ቀን እንኳን ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል የሚያስወጣውን ደረጃ ለመመልከት ሞክራ ባለማወቋ ምክንያቱን የማወቅ ጉጉቴ ከፍ አለ፡፡ ስለዚህ እናታችን ስትመጣ ጠየቅኳት።

“አያትየው ራሷ ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል መጥታ ለምን ምን እንደምንሰራ አትመለከትም?”

እናታችን ደክሟትና ተስፋ የቆረጠች መስላ ልዩ ወንበሯ ላይ ተቀምጣለች አዲሱ አረንጓዴ የሱፍ ልብሷ በጣም ውድ ይመስላል፡ ፀጉር ሰሪ ጋ ሄዳ
የፀጉሯን ስታይል ቀይራለች: ምንም ማሰብ ሳያስፈልጋት መልስ ሰጠችኝ ከዚህ በፊት አልነገርኩሽም እንዴ? አያታችሁ ክላስትሮፎቢያ አለባት፡ ይህ ማለት በተጨናነቀ ጠባብ ቦታ ውስጥ መተንፈስ ያስቸግራታል ማለት ነው አየሽ በልጅነቷ ወላጆቿ ለቅጣት የልብስ ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ ይቆልፉባት ነበር”

ዋው! አንዲት ትልቅ አሮጊት ሴት በአንድ ወቅት የምትቀጣ ትንሽ ልጅ የነበረች መሆኗን ማሰብ እንዴት ይከብዳል፡ ይህ ዜና ለእኔና ለክሪስ የጠባቧን
መተላለፊያ የዘጉ ግድግዳዎችን በምስጋና ለመሳም በቂ ምክንያት ነበር።አብዛኛውን ጊዜ እኔና ክሪስ ሁሉም ቁሳቁሶች ጣሪያው ስር ካለው ክፍል ውስጥ ቢወሰዱ ብለን እናስባለን፡፡ ግን አንድ እግር ብቻ የሚያሳልፍ ስፋት
ባላት ደረጃ በትንሽዋ የልብስ ማስቀመጫ በኩል ማሳለፍ ስለማይሞከር ከጣሪያው በታች ወዳለው ክፍል የሚወስድ ሌላ ሰፋ ያለ በር ለማግኘት
ብዙ ብንሞክርም አልተሳካልንም አንዱ ምናልባት በእኛ አቅም
ልናንቀሳቅሳቸው የማንችላቸው ቁምሳጥኖች ጀርባ ሊሆን ይችላል: ክሪስ እንደሚያስበው ክፍሉ ውስጥ ያሉት ትልልቅ ዕቃዎች እዚያ ውስጥ የገቡት
በአንደኛው ሰፊ መስኮት ውስጥ አልፈው ነው።

ያቺ ጠንቋይ አያታችን በየቀኑ በባልጩት አይኖቿ ልትወጋን፣ በስስ ጠማማ ከንፈሮቿ ልትጮህብን ወደ ክፍላችን ትመጣለች ስትመጣም ሁልጊዜ
ተመሳሳይ ጥያቄ ትጠይቃለች።

“ምን እያረጋችሁ ነው? ከጣሪያው ስር ባለው ክፍል ውስጥ ምን
ስትሰሩ ነበር? ዛሬ ከመብላታችሁ በፊት አመሰግናችኋል? ትናንት ማታ ተንበርክካችሁ ወላጆቻችሁ ለሰሩት ኃጢአት እግዚአብሔር ይቅር እንዲላቸው ፀልያችኋል? ለሁለቱ ትንንሽ ልጆች የእግዚአብሔርን ቃል አስተምራችል?ወንድና ሴት አንድ ላይ መታጠቢያ ቤት ተጠቅማችኋል? ሁልጊዜ ጨዋ
ናችሁ? የሰውነታችሁን ክፍሎች ከሌሎች አይን ጠብቃችኋል? ማፅዳት በማያስፈልግበት ወቅት ሰውነታችሁን ነካክታችኋል?”

አምላኬ! የሰውን አካል እንዴት ነው እንደዚህ ቆሻሻ የምታስመስለው? ከሄደች በኋላ ክሪስ እየሳቀ “ከውስጥ ልብሷ ጋር ተጣብቃለች መሰለኝ” ሲል ቀለደ።

“አይ በሚስማር መትታው ነው!” ስል ጨመርኩበት

“ግራጫ ቀለም ምን ያህል እንደምትወድ አስተውለሻል?”

“አስተውለሻል? ማንስ አያስተውልም? ሁልጊዜ ግራጫ ነው: አረንጓዴ ግራጫ ቀለም ከሌላ ቀለም ጋር ተሰርቶ ሲለበስ ያምራል፡ የእሷ ግን ሁልጊዜ
አይነቱም ሆነ ቀለሙ አንድ አይነት ነው፡ እናታችን ስትነግረን እንደዚህ
አይነት ልብሶች የምትሰራ ባሏ የሞተባት ሴት አለች᎓ ይይህችን ሴት የአያታችን ጓደኛ ናት፡ ወንድ አያታችሁ ጆርጂያ ውስጥ በጣም ጥሩ ጨርቅ የሚያመርት
ፋብሪካ አለው፤ ሴት አያታችሁ ግን አዘውትራ ግራጫ ቀለም ያለውን ልብሷን የምትለብሰው ርካሽ ስለሆነ ነው” ብላናለች

አምላክ ሆይ ሀብታሞችም ስስታሞች ናቸው::

አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ፣ መታጠቢያ ቤት ለመድረስ ጣሪያው ስር ካለው ክፍል እየተንደረደርኩ ደረጃውን ስወርድ ከአያትየው ጋር ተጋጨሁ᎓ ትከሻዬን ጨምድዳ ይዛ ፊቴ ላይ አፈጠጠች: “የምትሄጅበትን አስተውይ! ለምንድነው
የቸኮልሽው?” ስትል ጮኸች:
በለበስኩት ስስ ሰማያዊ ሹራብ ውስጥም የያዙኝ ጣቶቿ ልክ እንደ ብረት ነበሩ። ትንፋሼ ቁርጥ ቁርጥ እያለ “ክሪስ በጣም የሚያምር ስዕል እየሰራ ነው እና ቀለሙ ከመድረቁ በፊት ንፁህ ውሀ ይዤ መመለስ አለብኝ” ስል አብራራሁ:
ውሀውን ለምን ራሱ አያመጣም? ለምን ታቀብይዋለሽ?”

እየሳለ ስለነበር ውሀ ላቀብለው እችል እንደሆነ ጠየቀኝ፣ ከማየት በስተቀር ምንም እየሰራሁ ስላልነበረ ላመጣለት ተስማማሁ መንትዮቹ እንዲያመጡ
ቢደረጉ ደግሞ ውሀውን ይደፉታል።"

ጅል! ለወንድ አትታዘዢ፤ ራሱን እንዲያስተናግድ አድርጊ፡ አሁን እውነቱን አውጪ እዛ ላይ ምንድነው የምትሰሩት?”

እውነቱን ነው የተናገርኩት። መንትዮቹ እዚያ ሲሆኑ እንዳይፈሩ ክፍሉን ማሳመር ጠንክረን እየሰራን ነው ክሪስ ደግሞ ጎበዝ አርቲስት ነው"

“በምን አወቅሽ?” ስትል በንቀት ጠየቀች

“የአርት ተሰጥኦ አለው አያቴ፣ አስተማሪዎቹ ሁሉ እንደዚያ ብለዋል”

“እርቃንሽን ሆነሽ ፊቱ እንድትቆሚ ጠይቆሻል?”

ደነገጥኩ “ኧረ በጭራሽ!”

“ታዲያ ለምን ደነገጥሽ?”

“እኔ ... እኔ ስለምፈራሽ ነው” ተንተባተብኩ፡ “ሁልጊዜ ስትመጪ የምትጠይቂን ምን ኃጢአት ወይም ያልተቀደሰ ነገር እየሰራን እንደሆነ ነው… እና በእውነት
ምን ይሰራሉ ብለሽ እንደምታስቢ አላውቅም በግልፅ ካልነገርሽንና መጥፎ መሆኑን ካላወቅን እንዴት መጥፎ ከመስራት መቆጠብ እንችላለን?”

ዙሪያዬን፣ ከዚያ ወደታች ባዶ እግሬን ተመለከተችና በሽሙጥ ፈገግ አለች
“ታላቅ ወንድምሽን ጠይቂው ምን ማለቴ እንደሆነ ያውቃል። ወንዶች ክፉ የሆነውን ነገር ሁሉ ከመወለዳቸው ጀምሮ የሚያውቁ ዘሮች ናቸው”

ወንዶች! አይኖቼን አርገበገብኩ ክሪስ አስቸጋሪ የሚሆንበት ጊዜ አለ እንጂ ክፉ ወይም መጥፎ አይደለም: በጭራሽ ክፉ አይደለም: ይህንን ልነግራት
ሞከርኩ እሷ ግን ልትሰማ አልፈለገችም:: የዚያን ቀን በኋላ ላይ ቢጫ አበባ የተተከለበት የሸክላ ማስሮ ይዛ ወደ ክፍላችን መጣች: ከዚያ በቀጥታ ወደኔ
ቀረበችና ማሰሮውን እጆቼ ላይ አስቀመጠች: “ለውሸት የአትክልት ስፍራሽ እውነተኛ አበባ ይኸውልሽ” አለችኝ፡፡ ድምፅዋ ውስጥ ደስታ አልነበረም:: እሷ
የምታደርገው ነገር ነው ብዬ ባለማሰቤ እጅግ ተደነቅኩ ልትለወጥና በተለየ ሁኔታ ልትመለከተን ነው? እኛን መውደድ እየቻለች ነው? ስለ አበቦቹ እጅግ
አመሰገንኳት ምናልባትም አብዝቼ ሳላመስግናት አልቀረሁም ምክንያቱም ልክ እንዳፈረ ሰው አጎንብሳ ክፍሉ ውስጥ እየተንጎራደደች ነበር።

ኬሪ እየሮጠች መጥታ ፊቷን ብሩህ የሆኑት ቢጫ ቅጠሎች ላይ አደረገች:: “ካቲ በጣም ያምራሉ… ልወስዳቸው እችላለሁ?” አለች: “አዎ ትችያለሽ:: ያ ማሰሮ የመማሪያ ክፍሉ ውስጥ ወደ ምስራቅ ወደዞረው መስኮት አጠገብ በጥንቃቄ ይቀመጣል፡ ከሩቅ ከሚታዩ ተራሮችና ኮረብቶች እንዲሁም በመካከላቸው ካሉ ዛፎች ውጪ ምንም አይታይም ከሁሉም ነገሮች በላይ ደግሞ ሰማያዊ ጭጋግ አለ፡፡ እውነተኞቹ አበቦች ሌሊቱን ከእኛ ጋር
👍29🥰1
ይሆናሉ። ስለዚህ መንትዮቹ ጠዋት ሲነቁ የሆነ ቆንጆ ህይወት ያለው ነገር አጠገባቸው አድጎ ይመለከታሉ። ልጅ ስለመሆን ባሰብኩ ቁጥር፣ እነዚያን
በሰማያዊ ጭጋግ የተሸፈኑ ተራሮችና ኮረብቶች እንዲሁም ዳገቱ ላይና ታች ላይ ተሰልፈው ጥቅጥቅ ብለው የቆሙትን ዛፎች እያየሁ የእኛ የነበረውንና
በየቀኑ እተነፍሰው የነበረውን አየር እንደገና አሽታለሁ። አእምሮዬ ውስጥ ካሉት ጥላዎች ጋር የተደባለቀውን ጣሪያው ስር ያለውን ክፍል ጥላ እንደገና
አያለሁ እናም እንደገና ያልተመለሱትን ለምን? መቼ? ለምን ያህል ጊዜ? የሚሉትን ጥያቄዎች አዳምጣለሁ።

ፍቅር ብዙ እምነት አድርጌበታለሁ፡

እውነት ... ሁልጊዜም በጣም
ከምትወዷቸውና ከምታምኗቸው ሰዎች ከንፈር የሚወጣ እንደሆነ ማመን ቀጥያለሁ።

እምነት. ከፍቅርና ከማመን ጋር የተሳሰረ ነው አንደኛው አልቆ ሌላኛው የሚጀምረው የት ላይ ነው? እና ከሁሉም በላይ ፍቅር እውር መሆኑን እንዴት ታውቃለህ?

ከሁለት ወር በላይ አለፈ አያታችን አሁንም በህይወት አለ።

ቆምን፣ ተቀመጥን፣ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ባሉት ወደ ውጪ በሚያሳዩት መስኮቶች ላይ ተንጠለጠልን: የዛፎች ጫፍ የሚታዩበት ክፍል ውስጥ እንዳለን የዛፎቹ የበጋ ጥቁር አረንጓዴ ቀለም ወደ በልግ ብርቱካንማ፣
ወርቃማና ቡናማነት ሲለወጥ ተመለከትን: ቅር አሰኘኝ፤ ሁላችንንም ቅር አሰኝቶናል ብዬ አስባለሁ መንትዮቹንም እንኳን በጋው ሄዶ በልግ ሊመጣ
እኛ ግን ያሰብነው እንጂ ያላለፍንበት በመሆኑ ተከፋን፡
ከዚህ እስር ቤት ለማምለጥ ንፋሱ ፀጉሬን ሲበትነውና ቆዳዬ ላይ ሲያርፍ ለመስማትና እንደገና በህይወት መኖሬ እንዲሰማኝ በመፈለግ ሀሳቤ በረረ፡ እኔ ሳደርገው እንደነበረው ውጪ በነፃነት በሳሩ ላይ በሚሮጡና በእግራቸው ደረቁን ቅጠል እያንኮሻኮሹ በሚራመዱ ልጆች ቀናሁ።

እንደፈለግኩ በነፃነት በምሮጥባቸው ጊዜያት እየተደሰትኩ መሆኑን ለምን
አላስተዋልኩም? የዚያን ጊዜ ደስታ የሚገኘው ገና ወደፊት ትልቅ ሰው ስሆን፣ የራሴን ውሳኔ ሳሳልፍ፣ በራሴ መንገድ ስሄድና የራሴ ሰው ስሆን ነው ብዬ ለምን አሰብኩ? ልጅ መሆን ብቻ በቂ ያልመሰለኝ ለምንድነው? መደሰት
ራሱን ሙሉ በሙሉ በመጠን ላደጉ ሰዎች አስቀምጧል ብዬ ለምን አሰብኩ?

“ያዘንሽ ትመስያለሽ” አለ ክሪስ ወደኔ እየተጠጋ ኬሪ በሌላ ጎኑ አለች ኮሪ ደግሞ በእኔ ጎን በኩል ነው አሁን አሁን ኬሪ ትንሽዋ ጥላዬ ሆናለች በምሄድበት ሁሉ ትከተለኛለች፡ የምሰራውን ተከትላ ታደርጋለች። ክሪስም የራሱ ትንሽ ጥላ አለው ኮሪ: እኛ እንደምንቀራረበው የሚቀራረቡ እህትና ወንድሞች ካሉ እነሱ አንድ ላይ የተወለዱ አራት መንትያዎች መሆን አለባቸው።

“መልስ አትሰጪኝም?” ክሪስ ጠየቀ፡ “ለምንድነው ያዘንሽ የመሰልሽው? ዛፎቹ በጣም ውብ ናቸው: አይደሉም እንዴ? በጋ ሲመጣ፣ በጋን በጣም
እወደዋለሁ። በልግ ሲመጣ ደግሞ በልግን የበለጠ እወደዋለሁ። ክረምት
ሲመጣም የምወደው ወቅት ክረምት ይሆናል። ከዚያ ደግሞ ፀደይ ሲመጣ ፀደይን የበለጠ እወደዋለሁ።” የኔ ክሪስቶፈር እንግዲህ እንደዚህ ነው:
ሁልጊዜም እዚህና አሁን ነው የሚኖረው፤ ስለሆነም ሁኔታው ምንም ይሁን ምን ሁልጊዜ ጥሩ ያስባል።

“ታሪክን እጅግ ደባሪ ሰዎቹንም እውነት ያልሆኑ አድርጋ ታስተምረን
ስለነበረችው ስለ ወ/ሮ ቤትራምና ስለ አሰልቺ ንግግሯ እያሰብኩ ነበር አሁን ግን እንደገና እንደዚያ እንዲሰለቸኝ ተመኘሁ።"

“አዎ” ሲል ተስማማ ክሪስቶፈር “ምን ማለትሽ እንደሆነ አውቃለሁ።ትምህርት ቤት አሰልቺ እንደሆነ ታሪክም በተለይም የአሜሪካ ታሪክ ደባሪ እንደነበር አስብ ነበር ነገር ግን ትምሀርት ቤት ሳለን ቢያንስ በእኛ እድሜ
ያሉ ልጆች የሚያደርጓቸውን ነገሮች እናደርግ ነበር፡ አሁን ግን ምንም ሳንሰራ ጊዜያችንን እያባከንን ነው ካቲ እባክሽ አንድ ደቂቃ እንኳን አናባክን! ራሳችንን ከዚህ ቤት ለምናወጣበት ቀን እናዘጋጅ በአእምሮሽ ውስጥ ጠንካራ ግብ ካላስቀመጥሽና ልትደርሽበት ካልጣርሽ ምንም አትሰሪም እኔ ዶክተር መሆን ካልቻልኩ ገንዘብ ሊገዛው ከሚችለው ነገር በላይ ምንም እንደማልፈልግ ራሴን አሳምኜዋለሁ" አለ።

ይህንን የተናገረው በጋለ ስሜት ነበር የባሌት ዳንሰኛ መሆን እፈልጋለሁ ሆኖም ሌላም ነገር ልሆን እችላለሁ፡ ክሪስ የማስበውን ያነበበ ይመስል፣ሰማያዊ አይኖቹን ወደኔ መልሶ እዚህ ከመጣን ጀምሮ አንድ ጊዜ እንኳን
ተለማምጄ ባለማወቄ አሾፈብኝ ካቲ ነገ አሳምረን የጨረስነውን ቦታ
አዘጋጅልሽና ልክ ትምህርት ቤት ውስጥ እንደሆንሽ አስበሽ በቀን አምስት ወይም ስድስት ሰዓት ትለማመጃለሽ" አለኝ።

“አልለማመድም! ማንም ምንም ነገር እንዳደርግ አይነግረኝም! በዚያ ላይ ለዳንስ የሚሆን ልብስ ካልለበስክ በደንብ ልትለማመደው አትችልም” አልኩት።

“ምን አይነት የሞኝ ነገር ነው የምታወሪው?”

“ሞኝ ስለሆንኩ ነዋ! አንተ. አንተ ብቻ ነህ ማሰብ የምትችለው!” ይህንን እየተናገርኩ እምባ ቀደመኝና ጣሪያው ስር ካለው ክፍል እየሮጥኩ ወጣሁና
ደረጃው ጋ ደረስኩ። እጣ ፈንታ እንድወድቅ እንዲያደርገኝ፣ እግሬን ወይም አንገቴን እንዲሰብረውና ገድሎ የሬሳ ሳጥን ውስጥ እንዲከተኝ በመፈተን በጠባቡ የእንጨት ደረጃ ወደ ታች ተንደረደርኩ ስሞት ሁሉም ምን አይነት ዳንሰኛ ይወጣኝ እንደነበር አስቦ ያዝናል።

አልጋዬ ላይ ራሴን ወረወርኩና ትራሱ ላይ ተደፍቼ ተንሰቀሰቅኩ። እዚህ ምንም የለም: ህልምም ሆነ ተስፋ… ምንም የተጨበጠ ነገር የለም: እንደገና ሌሎች ሰዎችን ሳላይ አሮጊትና አስቀያሚ እሆናለሁ እነዚያ ሁሉ ዶክተሮች
ለዘለዓለም እንዲኖር ለማድረግ እየጣሩ ስለሆነ፣ ምድር ቤት ያለው ያ ሽማግሌ መቶ አስር አመት ሊኖር ይችላል፡ ለራሴ አዘንኩ የሆነ ሰው ለዚህ ሁሉ ስራው መክፈል… መክፈል… መክፈል አለበት የሆነ ሰው. የሆነ ሰው!

ሁለቱ ወንድሞቼና ትንሽዋ እህቴ የቆሸሹ ነጫጭ ስኒከሮቻቸውን አድርገው፣ካላቸው ነገር ውስጥ ሊያፅናኑኝ ስጦታ ይዘውልኝ መጡ፡ ኬሪ ቀይና ሀምራዊ
ከለር፣ ኮሪ ደግሞ የጴጥሮስ ጥንቸሉን የታሪክ መፅሀፉን ነበር ይዘው የመጡት። ክሪስ ግን ዝም ብሎ ተቀምጦ ይመለከተኝ ነበር።

አንድ ምሽት እናታችን ዘግይታ መጣችና የያዘችውን ትልቅ ካርቶን እንድከፍተው እጆቼ ላይ አስቀመጠችልኝ፡ በነጭ ስስ ወረቀት የተጠቀለሉ የዳንስ ልብሶች ነበሩ: አንደኛው ደማቅ ሮዝ ቀለም ያለው ሌላኛው ደግሞ አብሮት የሚለበስ ሰማያዊ ጫማ ያለው ነበር ካርቶኑ ውስጥ ያለው ትንሽ ካርድ ላይ “ከክሪስ”
የሚል ተፅፎበታል ለዳንስ የሚሆኑ ሙዚቃዎች የተቀዱባቸው ካሴቶችም ነበሩ፡ እጆቼን ዘርግቼ ወደ እናቴ ከዚያ ወደ ወንድሜ ስሄድ እያለቀስኩ
ነበር፡ አሁን ግን ተስፋ የመቁረጥና የመከፋት እምባዎች አልነበሩም- የደስታ እምባዎች ናቸው አሁን ልሰራ የምችለው ነገር አለኝ።

እናታችን እንዳቀፈችኝ “ከሁሉም በላይ ልገዛልሽ ያሰብኩት ከላይ የሚታጠፉ ነጫጭ ላባዎች ያሉበት ኮፍያ ያለው ነጭ ልብስ ነበር እሱንም አዝዤልሻለሁ
ካቲ: አንቺን ለማበረታታት ሶስት የዳንስ ልብሶች ይበቁሻል፡ አይበቁሽም?" አለችኝ

ክሪስ ከጣሪያው ስር ባለው ክፍል ውስጥ ባዘጋጀልኝ ቦታ ሙዚቃውን ከፍቼ ለሰአታት መለማመድ ጀመርኩ፡ እዚህ እማርበት እንደነበረበት ቦታ ትልቅ መስታወት ባይኖርም፣ ጭንቅላቴ ውስጥ ስዬ ነበር፡ ራሴን አስር ሺህ ሰዎች
በተሰበሰቡበት አዳራሽ ውስጥ እየደነስኩ ተመለከትኩት፡፡ ከእያንዳንዱ አንዳንድ ፅጌረዳ አበባ እየተሰጠኝ በደርዘን የሚቆጠር እቅፍ አበባ ስቀበል ይታየኛል።
👍30🥰85👏2
በሚያምር ሙዚቃ መደነስ ከራሴ ያወጣኝና ለጊዜውም ቢሆን ህይወት እያለፈን የመሆኑን ነገር ያስረሳኛል፡ የምደንስ ከሆነ ምን አለ? ከባዶቹን የዳንስ አይነቶች ስሰራ የሚደግፈኝና አብሮኝ የሚደንስ እንዳለ አድርጌ አስባለሁ ስወድቅ እየተነሳሁ ትንፋሽ እስኪያጥረኝ፣ ጡንቻዎቼ እስከሚታመሙ፣ልብሴ በላብ ሰውነቴ ላይ እስኪጣበቅና ፀጉሬ እስኪረጥብ ድረስ መደነሴን
እቀጥላለሁ።

አንድ ጊዜ የማጠቃለያ እንቅስቃሴዬን ስሰራ፣ ክሪስ እንግዳ ስሜት ፊቱ ላይ እየተነበበ ሲመለከተኝ አየሁ: በቅርቡ አስራ አምስት አመት ልደቱን ያከብራል፡ እንዴት ይሆናል? ትልቅ ሰው እንጂ በጭራሽ ልጅ አይመስልም
ከልጅነት በፍጥነት እየወጣ እንደሆነ የሚናገሩት እነዚያ አይኖቹ ናቸው?ከዚያ ወደ ክሪስ ሄድኩና እጆቼን ወደ እሱ ዘርግቼ “ክሪስ ና ከእኔ ጋር እንደንስ፧ እንዴት እንደሆነ ላስተምርህ?” አልኩት።......

ይቀጥላል
25👍10😱4
#ሳቤላ


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ለሚስተርና ለሚስዝ ካርላይል ጋብቻ ደስታቸውን ለመግለጽ የአካባቢው ታላላቅ ሰዎች እንደየአቅማቸውና እንደ ደረጃቸው በተለያዩ ሠረገዎች እየሆኑ በልዩ
ልዩ የክብር ልብሶች አጊጠው ጌጠኛ ልብስ በለበሱ አሽከሮች እየታጀቡ ኢስትሊን መግባት ጀመሩ ።

ሚስተር ካርይል መኖሪያውን ኢስት ሊን ቢያደርግም እመቤት ሳቤላ ቬንን ባያገባ ኖሮ እነዚያ ሁሉ መኳንንትና ወይዛዝርት ይኸን ያሀል ክብር ሰጥተው እሱን ጥየቃ ብለው እንደዚህ በብዛት አይንጋጉለትም ነበር "

ደስታቸውን ለመግለጽ ከመጡት ታላላቅ ሰዎች መካከል ጀስቲስ” ሔር'ሚስቱና ልጁ ባርባራ ሔር ነበሩ " በነዚያ ጭራቸው መሬት በሚነካ ኣካላተ ሙሉና ጸጉረ ለስላሳ ፈረሶች ይሳብ የነበረው ጥንታዊ ሠረገላ የሚንቀሳቀሰው እንደ ዛሬው በመሳሰሉ አጋጣሚዎችና ከፍተኛ የበዓል ቀኖች ብቻ ነበር "

እንግዶቹ ኢስት ሊን በደረሱበት ሰዓት ሳቤላ ከመልበሻ ክፍሏ ሆና ጆይስ ከሷ ጋር ስለምትጠቃለልበት መንግድ ትነጋገር ነበር » ጆይስም የደንገጡርነቱን ሥራ ደኅና እየተለማመደችው ስለ ነበርና ሚስ ካርላይልም ያለምምንም ቅሬታ እንደ ምትፈቅድላት ስለምታውቅ ወይዘሮ ሳቤላ ከፈቀደች ደስ እያላት ከሷ ጋር ለመሆን እንደምትፈልግ ስትነግራት ነበር " በዚህ መኻል በር ተንኳኳ " ጆይስ በሩን ስትከፍተው አንዲት የዌስት ሊን ተወላጅ የሆነች አዲስ የተቀጠረች ሠራተኛ ሆና አገኘቻት " ሳቤላ ሁለቱ ሴቶች የሚባባሉትን ትስማ ነበር ።

« እሜቴ አሉ ? »

« አሉ »

« እንግዶች መጥተዋል " ፒተር ንገሪ ብሎ ልኮኝ ነው ። እነማን መሰሉሽ ? ሚስተር “ጀስቲስ” ሔር ከነቤተሰባቸው እሷም አብራ አለች " መቸም ያለባበስ ነገር አታንሺው የራስ መሸፈኛዋ በውስጡ ሰማያዊ ጥሩንባ ቅርጽ አበቦች አሉት " በስተውጪ መጥረጊያ የሚያክል ነጭ ላባ ሰክታበታለች ከሠረገላ ስትወርድ ልብ ብዬ አየኋት " »

« ማናት እሷ ? » አለች ጆይስ ፊቷን ኮስተር አድርጋ

« ሚስ ባርባራ ናታ እስኪ ተመልከች አሁን እሷም ልጠይቅ ብላ መምጣቷ ምን ይባላል ? ይልቅ እሜቴን መርዝ እንዳታጠጣቸው ቢጠነቀቁ ይሻላል »

ጆይስ ሠራተኛይቱን በዛው ሸኝታ ' በሩን ዘጋችና ወደ እመቤቷ ተመለሰች "በሹክሹክታ የተመላለሱትን ነገር ሳቤላ መስማቷን አላወቀችም "

« ሱዛን ናት " እንግዶች መምጣታቸውን ልትነግር ነው የመጣችው • ሚስተር ጀስቲስ ሔር ' ሚስዝ ሔርና ሚስ ባርባራ ከሳሎን ገብተው ተቀምጠዋል ትላለች »

ሳቤላ ሱዛን ስለ ተናረችው ምስጢራዊ ነገር ኢያሰበች እንግዶች ወዶ ዐረፉበት ክፍል ወረደች "

ዳኛው አዲስ ሰው ሠራሽ ጸጉር ያጠለቀ ጉረኛና የተናገረውን ቃል ማያጥፍ ችክ ያለ ሰው ይመስላል ሚስዝ ሔር ልስልስ ግርጥት ያለች ወይዘሮ ስትሆን ባርባራ ደግሞ የምታምር ቆንጆ ናት " ሳቤላ ስትገባ እንዳየቻቸው ያሳደሩባት ስሜት ይህን ይመስል ነበር "

ብዙ ሲጫወቱ ቆዩ " ሳቤላ ያቺን መከረኛና ረቂቅ ወይዘሮ ሚስዝ ሔርን ስታያት በጣም ወደደቻት ሚስ ካርይል ስትግባ እንግዶቹ ለመሔድ ተነሱ" ሚስ ካርላይል ግን ለባርባራ የምታሳያት ነገር ስለ ነበራት እንዲቆዩ ብትሞክርም
በዐሥራ አንድ ሰዓት ከቤቱ እንግዳ ስለጠራና አሁን ግማሽ ሰዓት ብቻ ስለ ቀረው ባርባራ ብትፈልግ ልትቆይ መቻሏን ነግሮ ከሚስቱ ጋር ተያይዘው ሔዱ "

ባርባራ ፊቷ ደም መሰለ ሆኖም ሚስ ኮርኒሊያ ካርላይል ያቀረበችላት የራት ሰዓት ደረሰ ሳቤላ የራት ልብስ ለመልበስ ከፎቅ ወደሚገኘው ክፍል
ወጣች " ጆይስ እዛው ስትጠብቃት አገኘቻት " ወዲያው ከሷ ጋር ስለምትሆንባት
ጉዳይ መነጋግር ጀመሩ

« እሜቴ » አለች ጆይስ « ሚስ ካርላይልን አነጋግሬአቸዋለሁ " ወደ እርስዎ ብዛወር ፈቃደኛ ናቸው " ነገር ግን በታሪኬ አንድ ደስ የማይል ነገር ስለ አለበት
አስቀድሜ መግለጽ እንዳለብኝ ነግረውኛል እኔም ራሴ አስቤበት ነበር " ሚስ ካርላይል ጠባያቸው ደስ አይልም ግን እውነተኛና ቀጥተኛ ሰው ናቸው "

« ምንድን ነው ደስ የማይለው ታሪክሽ ? »

« አባቴ የሚስተር ካርላይል አባት ጸሐፊ ነበር " እናቴ በስምንት ዓመቴ ሞተችና አባቴ የሚስተር ኬን ዋርሳ የምትሆን ሴት አግብቶ አፌ የምትባለዋን እኅቴን ወለዶችለት እሷም አፊ ገና ያመት ልጅ ሳለች ሞተች " ሕፃኗም የናቷ
አክስት ልታሳድጋት ወሰደቻት እኔ ግን ከአባቴ ጋር ሁኘ በልጅነቴ ትምሀርት ቤት እመላለስ ነበር ካደግሁ በኋላ ባርኔጣ ሥራና ልብስ ሰፌት ተማርኩ አባቴ የራሱ
የሆነ ቤት ከጫካው ዳር ነበረው " የቤት ሥራ የምትረዳ የቀን ሠራተኛ ነበረች እሷም በየቀኑ ከኛ ጋር የምትቆየው ለጥቂት ሰአት ብቻ ነበር አባቴን እንዳይከፋው እየተንከባከብኩ ጊዜ ሲኖረኝ ብቻ ከአንዳንድ ወይዛዝርት ቤት እየሔድኩ እሠራ ነበር "

« በዚህ ዐይነት ብዙ ዓመት ከኖርን በኋላ አፊ ተመልሳ መጣችና ከኛ ጋር ተቀመጠች አክስቲቱም ሞተች " ገንዘቧም አብሮ ሞተና ምንም እንኳን አፊን በደንብ ብታሳድጋትም ስትሞት አንድም ነገር ልትተውላት አልቻለችም " እኛም አፊ ፈራናት " አለባበሷና ልዩ ፍሳጐቷ ሰማይ ነበር ደስተኛ መልከኛና የተቅበጠበጠች ነበረች" ከዌስት ሊን የሕዝብ ንባብ ቤት እየተዋሰች የምታመጣቸውን መጻሕፍት ከማንበብ በቀር አንድም ነገር አትሠራም ነበር አባቴ ደግሞ ይኸን ጠባይዋን
አልወደደውም እኛ ለራሳችን ለፍቶ አዳሪዎች ስንሆን እሷ ደግሞ አክስቷ ቤት እንደ ለመደችው ትዘባነንብን ጀመች እንዲህ ስትል ስትል ከሪቻርድ ሔር ተዋወቀች "

ወይዘሮ ሳቤላ ' ቶሎ ቀና ብላ አየቻት

« የሚስተር ጀስቲስ ሔር ብቸኛ ወንድ ልጅና ! የሚስ ባርባራ ወንድም ነው አፊ ፊት ስትሰጠው ጊዜ ፍቅር ያዘው ከዚያም ቀስ በቀስ ሌሎችንም መሳብ ጀመረች አባታችን በሥራ ምክንያት ከቤት በማይኖርበት ጊዜ አጫፋሪዎቿ
የፈለገችውን እየያዘች ከቤት ታመሻለች።
« ከብዙ ወዳጆቿ አንዱና ዋናው ሪቻርድ ሔር ነበር ሌላ ደግሞ ራቅ ካለ ቦታ በፈረስ እየመጣ የሚጠይቃት ወዳጅ ነበራት " እሱ ግን አስከዚህም የነበረ አይመስለኝም " ከሚስተር ሪቻርድ ሔር ጋር የነበራት ግንኙነት ግን አባቴን እስከ ገደለበት ድረስ ቀጠለ "

« ማን ? » አለች ሳቤላ ድንግጥ ብላ ።

« ሪቻርድ ሔር ነዋ . . .እሜቴ » አባቴ እነዚህ የትልቅ ሰዎች ልጆች ድሆች ሴቶች ልጆችን የሚከታተሏቸው ለጋብቻ እያሰቧቸው እንዳልነበር ያውቅ ነበር በርግጥ በሚስተር ሪቻርድ ቀና አመለካከት ባይኖረውና በአፊጉዳት ያደርሳል ብሎ
ቢጠረጥረው ኖሮ ጠበቅ ያለ ገደብ ይፈጥር ነበር " አንድ ቀን ዌስት ሊን ላይ ስዎች የሷን ስም ከሪቻርድ ጋር አዳብለው በክፉ ሰያነሡት ሰማ ማታ ሲጠጣ እኔ ባለሁበት ከሪቻርድ ጋር ያላት ግንኙነት እንዳይቀጥል እሷም ፊት እንዳትሰጠ ለአፊ ነገራት " ይገርምዎታል በበነጋው ማታ ሪቻርድ ሔር አባቴን በጥይት ገደለው » አለቻት።

« አቤት እንዴት ያሳዝናል ልጀ ! »

« ታዲያ ይህ ነገር ሆነ ተብሎ የተፈጸመ ይሁን ወይም ካለመጠንቀቅ ጠበንጃው ጋር ሲታገል ይባርቅበት አልታወቀም ሕዝቡ በማን አለብኝነት የተፈጸመ
👍17
የግፍ ግድያ ነው ብሎ ነበር የሚያስበው " በዚያ ዘመን እኔ ከሚስተር ጀስቴስ ሔር ቤት ነበር የምሠራው ያን ዕለት ማታ ከሥራዬ ውዬ ስመጣ የደረሰብን ሁኔታ ምን ጊዜም አልረሳውም አባቴ ከወለሉ ተዘርሯል ሕይወቱ ዐልፋለች ቤቱ በሕዝብ ግጥም ብሎ ሞልቷል " አፊ የነገሩን ምንነት በደንብ ማስረዳት አልቻለችም በድርጊቱ ጊዜ እሷም ወደ ዱሩ ሔዳ ስለ ነበር ያየችውና የሰማችው ነገር አልነበረም ብቻ
ወደ ቤት ተመልሳ ስትመጣ አባቷ ወድቆ ሚስተር ሎክስሌይ በላዩ ላይ አጐንብሶ አየችው " እሱ ለአፊ እንደ ነገራት ተኩስ ሰምቶ ሲመጣ ሪቻርድ ሔርን ጠበንጃው
ወርውሮ ከቤት ወጥቶ ሲሸሽ ጫማው ደም ነክቶ እንደ ነበር አይቶታል " »

« ወይ ጐድ እና ሪቻርድ ሔር ምን ሆነ ? »

« አመለጠ " የዚያኑ ሌሊት ወጥቶ እንደ ጠፋ እስከ ዛሬ የት እንደ ግባ የሚያውቅ የለም በነፍሰ ገዳይነት ተፈርዶበታል " የገዛ አባቱም ያገኙት እንዶሆነ ወዲያውኑ
ለፍርድ እንደሚያቀርቡት ተናግረዋል " በዚህ የተከበረ ከባድ ቤት የደረሰ መከራ
በጣም የሚያሳዝን ነው ከዚህ የተነሳ ሚስዝ ሔር የልጃቸው ነገር ቀስ በቀስ ወደ ሕይወታቸው ፍጻሜ እያቀረባቸው ነው »

« አፊ አልሻት ? ምን ማለት ነው . . . ጆይስ ? »

«የክርስትና ስሟ አፍሮዳይት ነበርና እኔና አባቴ አፊ ብለን ነበር የምንጠራት" ከሁሉ የሚያሳዝነው ሥራዋ ግን ምርመራው እንዳበቃ ሪቻርድ ሔርን ተከትላ መጥፋቷ ነበር በአውነት እልዎታለሁ እሜቴ አለች ጆይስ አሳዛኙ ትዝታ ያቀላው
ፊቷንና በእንባ የራሰው ሽፋሽፍቷን እመቤቷ እንዳታይባት ዞር ብላ
« ይኸው አሁን ሁለቱም በዚህ ታዩ ' በዚያ ተሰሙ አይባሉም " አሜሪካ ይግቡ • አውስትራሊያ የሚያውቅ የለም " በአባቴ ሞት ድንጋጤና እኀቴ አሳፋሪ ድርጊት ለብዙ ጊዜ ታመምኩ " ከዚያ ሚስ ካርላይል ከቤታቸው አስገብተው ከነገረዶቻቸው አስታምመው አዳኑኝ " ሚስ ካርላይል አፋቸው ሰውን ያስቀይማል ራሳቸውን
ከማንም አብልጠው ይመለከታሉ እንጂ ልባቸው ርኅሩኅ ነው " ከዚያ በሽታ በኋላ የገረዶቹ የበላይ ሁኘ ከእሳቸው ጋር ተቀመጥኩ »

« ወይ ጉድ ! ይህ ከተፈጸመ ስንት ዓመት ሆነው ? »

« የሚመጣው መስከረም አራት ዓመት ይሆነዋል እሜቴ » ያባቴ ቤትም ግድያ የተፈጸመበት ነው እየተባለ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ደፍሮ የሚገባበት ጠፍቶ ባዶን ቀርቷል እንዳልሸጠው ደግሞ አፊም የኔን ያህል መብት ስለ አላት አልቻልኩም አንዳድ ጊዜ እሔድኩ በሮቹንና መስኮቶቹን ከፍቸ አናፍስዋለሁ . .ይኸውለዎ እኔ እርስዎን እንዳገለግል ከመምረጥዎ በፊት ልገልጽልዎ የፈለግሁት ታሪኬ ይሽ ነው " ብዙ ወይዛዝርት (እህቷ ባሳፋሪ ሁኔታ ላይ የምትገኝ ሴትን መቅጠር ደስ አይላቸውም " »

ሳቤላ ልዩነቱ አልታያትም ከወንበሯ እንዶ ተቀጠች ወዶ ኋላዋ ደገፍ ብላ ታስብ ጀመር "

« ጆይስ ! ቅድም አንቺና ሱዛን ከመዝጊያው ተጠግታችሁ ስትንሾካሾኩ የሰማሁዋቸው ምን ነበር?» አለች ወይዘሮ ሳቤላ ድንገት ሚስ ሔር ለኔ አንድ
ጣባ መርዝ እንደምትሰጠኝ ስትነጋገሩ ነበር?እንዶዚያ ጮኻ ማንቮካሾኳን እንድትተው ለሱዛን ንገሪያት »

ጆይስ ብትደነግጥም ሣቅ አለች « ኧረ ዝም ብሎ ፍሬ የሌለው ነገር ነው እሜቱ ሰዉ ከሚስ ባርባራ ጋር ፍቅር ይዟታል በየጊዜው ይገናኛሉ እንዲያው ሁለቱ ይጋባሉ" እያለ ያወራል « እኔ ግን የፈለጋትን ያህል ብትወዳቸውም የምትመቻቸው ዐይነት አትመስለኝም »

ሳቤላ ፊቷ ልውጥውጥ አለ የቅናት ስሜት ከልቧ ገባ " ምንጊዜም ባሏ ከሌላ ሴት ጋር መግጠሙን የምትወድ ሴት የለችም " ምንም ቢሆን ጥርጣሪ ማሳደሯ አይቀርም " ሳቤላ እጅጌውና ግርጌው በነጭ ዳንቴል የተዘመዘመ በጣም ውድና የሚያምር ጥቁር ዳንቴል ሥራ ቀሚስ ለብሳ ወረዶችና ወደ እንግዶቹ ክፍል ገባች » ከመጠን በላይ አምሮባት ነበር ባርባራ ውበቷን ልብሷን የኧርል ልጅነቷን የሚያስይ ለስላሳውና ቆንጆው መሐረቧን አይታ ቅናት ተሰማትና ፊቷን አዞረችባት " እሷም
በበኩሏ ቀላል ሰማያዊ ቀሚስ ለብሳ ሚስተር ካርላይል የስጣትን ያንገት ሐብል አድርጋ ጥሩ ሁና አጊጣና አምራ ነበር "

ሁለቱም በመስኮት ቁመው ወዶ ውጭ ሲመለከቱ'ሚስተር ካርሳይልን ሲመጣ አዩት " እሱም አያቸውና ባንገቱ ሰላም አላቸው " ሳቤላ የባርባራ ጉንጭ ወደቀይነት ሲለዋወጥ አየችው "

« ባርባራ እንደምነሽ ? ልታይን መጣሽ ከጠፋሽ እኮ ብዙ ጊዜ ሆነሽ " ፍቅሬ አንቺስ ደኅና ነሽ ? » አለ ወደ ሳቤላ ዞር ብሎ በለሆሳስ " ከሰው ፊት ያደርገዋል ብላ ባትጠብቀውም ሁልጊዜ ከሰላምታ ጋር ያስለመዳት መሳም ስለ ቀረባት ቅሬታ ተሰማት "

ራት ተበላ » ኮርኒሊያ ባርባራን ይዛት ወጣችና ጎመኑን ሰላጣውን
አስፖራጐሱን ያስተከለችባቸውን መደቦች ታሳያት ጀመር ባርባራ ግን ግድ እምቢ የማይባል ሆኖባት ነው እንጂ ኮርኒሊን ተከትላ ከመውጣት ምንም እንኳን የሌላ ባል ቢሆንም ከፊቱ ባትለይ ነበር የምትፈልግ " ሳቤላ ከቤት ውስጥ ቀረች

« ለመሆኑ እንዴት ሁና አኘሻት ? » አለች ባርባራ ኮርኒሊያን ስለ ሳቤላ ስትጠይቃት "

« እንደ ፈራኋት አይደለችም " ኩራት ' መመጻደቅ • የጌታ ልጅነቷን ለማሳየት መሞከር የመሳሰሉት ጠባዮች የሉባትም " አርኪባልድ ቢለያት አትወድም ድመት አይጥን እንደምትጠብቅ ወደ ቤት ሲመለስ ትጠብቀዋለች እሱ ከሌለ ሰዓቱ ፈቀቅ አይልላትም " ሁሉ ነገር ያስጠላታል "

« ጊዜዋን ምን እየሠራች ታሳልፈዋለች ? »

« ምንም ነገር ባለመሥራት » አለች ኮርነሊያ ነጠቅ አድርጋ » « ትንሽ ትዘምራለች ፒያኖ ትመታለች ጥቂት ታነባለች እንግዶች ሲመጡ ትቀበላለች " እንዲህ ስትልፈሰፈስ ቀኑ ይመሻል ከቁርስ በኋላ ደግሞ አርኪባልድን ስታሽበለብለው ስታወዳድሰው የሥራ ሰአቱን ታሳላልፍበታለች " ይሀም አይበቃትም እስከ አጥሩ በር ስትሸኘው ከወጣ በኋላ ከግቢው ቶሎ ለመድረስ እጥፍ ጊዜ እንዲወስድ ታደርገዋለች " ዝናብ እንደ መዓት እየወረደ እንኳን አትቀርም " ልብሷን ዝናቡ ቢያበሰበብሰውም ግድ የላትም - ስትነግሪያትም አትሰማም " ማታ ደግሞ ሔዳ ከመንገድ ትቀበለዋለች « ዛሬም እናንተ ባትኖሩ ኖሮ ትሔድ ነበር እሱም
የሥራውን ነገር የሚያስበው ከሷ በኋላ ነው »

« ይኸ መቸም በሁሉም ዘንድ ያለ ነገር መሰለኝ » አለች ባርባራ "

« እኔ ደግሞ መነኋለል ይመስለኛል » አለች ሚስ ካርላይል « ይገርምሻልኮ በተለይማ ማታ እኔ ይህን ያህልም ከጨዋታቸው አልግባም » ክንድ ለክንድ ተያይዘው ግቢውን ይዞራሉ ወይም ፒያኖ እየመታች ትዘምራለች ቀልጦ ወዶ ገንዘብ
ከተለወጠው ከማንኛውም ወርቅ ከተባለ ሁሉ አብልጦ ያያታል" ትናንት ያየሁትን ልንገርሽ " ሰው ጥየቃ ብለው በሠረግላ ተሳፍረው ሔዱልሽና እልም ብለው ጠፍተው ለራት ሲያስጠብቁኝ አመሹ " አርኪባልድ እንዲህ እየሰነበተ የሚነሳበት ራስ ምታት ተቀሰቀበትና ራት ከበላን በኋላ ከሚቀጥለው ክፍል ሔዶ ሶፋ
ላይ ተጋደመ ። ከዚያ አንድ ስኒ ሻይ ይዛለት ሔደች » አስቀድታ ከጠሬጴዛ ላይ የተወች የራሷ ሻይ ውሃ ሆኖ እስኪበርድ ድረስ ገብታ ቀረች " የሻዩን መብረድ ልነግራት በሩን ገፋ ባዶርገው የመቤቲቱ ነጭ መሐረብ በአዶኮሎኝ ተነክሮ ግንባሩ ላይ ተደርጓል እሷ ደግሞ ከፊቱ ተንበርhካ ዐይን ዐይኑን ታየዋለች " እሱም በክንዱ ጥምጥም አድርጐ ይዟታል " እስኪ ባርባራ ...
👍91
አንቺስ ስታስቢሙ ከወንድ ጋር እደዚህ መቃበጥ ምን ያስፈልግ ነበር ? አየሽ ፊት ሳያገባ ግን ራስ ምታቱ ሲነሣበት ጨውና ምናምኑን አደባልቄ አፍልቼ እሰጠውና ቶሎ እንዲተኛ ሳዶርገው በእንቅልፍ ያልፍለት ነበር ።»

ባርባራ ምንም መልስ ሳትሰጣት ፊቷን ከሚስ ካርላይል ምልስ አደረገች "

ከዚያ ወደ አትክልተኛው መጡና ሚስ ካርላይል ስለ አትክልቱ አያያዝና አተካከል ልዩ ልዩ ትእዛዝ ሰጠችው » እሱ ደግሞ ከሚስተር ካርላይል የተሰጠውን ትእዛዝ እሷ እንደምትለው እንዳልሆነ ሲያስረዳ ረጅም ንትርክ ሆነ ባርባራ ሰልችት ሲላት ወደ ቤት ገባች"

ሳቤላና ሚስተር ካርላይል ከፒያኖው ክፍል ነበሩ ባርባራ ያንን ጥሩ ድምፅ ለመስማት ዕድል አጋጠማት ባርባራ ሚስ ካርላይል አደረግሁ ብላ የነገረቻትን ይዛ በሩን ከፈት አድርጋ ወደ ውስጥ ተመለከተች " ሰዓቱ መሽቶ ድንግዝግዝ ብሎ ለዐይን መያዝ ጀምሮ ነበር !ቢሆንም ሳቤላ ከፒያኖው ተቀምጣ ሚስተር ካርላይል በስተኋላዋ ቁሞ ታያት ነበር ። “ የቦሄሚያ ቆንጆ ' ከሚለው የኦፔራ ዘፈኖች አንዱን ሌሎች ከንፈሮች የሚለውን ስትጫወትለት ነበር ።

« ይህን ዘፈን ለምን ነው ይህን ያህል የወደድከ . . . አርኪባልድ? አለችው ስትጨርስ።

« ኧረ እንጃ " ካንቺ እስክሰማው ድረስ እኮ ይሆን ያህል አልወደውም ነበር »
« ሰዎቼ ገብተው ይሆን ? ወደ ሳሎን ብንሔድ አይሻልም ? »

« መጀመሪያ ይህን ብቻ አንድ ጊዜ ተጫወችልኝ የሚሰማኝን ሁሎ ብነግርሽ ዝርዝሩ ይቅር ምን ያደርጋል ከንቱ ነው ነገሩ፤ የሚለውን የጀርመንኛ ትርጉም
ተጫወችልኝ " ሙዚቃው በጣም ደስ ይላል »

«እውነትክን ነው የሙዚቃ ፍቅርህ ልክ የአባባ ዐይነት መሆኑን ታውቃለህ ... አርኪባልድ ? ለስላሳ የትካዜ ዘፈኖችን ይወድ ነበር አንም ያው ነህ እኔም ደስ ይለኛል » አለችና ልብን በሚሠውር ዜማና ምት አንቆረቆረችለት "

« ያውልህ አርኪባልድ ! ቢያንስ ዐሥር ዘፈኖች ተጫወትኩልህ » አለችውና ራሷን የኋሊት ከሱ ላይ አስደግፋ አንጋጣ ዐይን ዐይኑን እያየች « ለዚህ መክፈል አለብህ» አለችው "

ያንን የሚወደውን ፊት ያዘና ደህና አድርጐ ሳማት " ባርባራ ወደ መስኮቱ ዞር ብላ ግንባርዋን ከመስኮቱ አስጠግታ ስትመለከት ቀስ ብላ አቃሰተች ሳቤላ
ከባሏ ጋር ክንድ ለክንድ ተያይዛ ወደ ተከታዩ ክፍል ስትገባ ባርባራን አገኙዋት "

«ብቻሽን ነሽ እንዴ ሚስ ሔር ? በእውነት ይቅርታ አድርጊልኝ እኔኮ ከሚስ ካርላይል ጋር ያለሽ መሰለኝ» አለቻት

«ኮርኒሊያስ ... ባርባራ ? » አላት ሚስተር ካርላይል "

«ገና መግባቴ ነው እሷም እየተከተለችኝ መሰላኝ »

እውነትም ደርሳ ኖሮ ወዲያው ድምጿን በቁጣ ከፍ አድርጋ ነገር ጀመረች "

« አርኪባልድ ... ስለ አበባው መደብ ለብሌር ምንድነው የነገርከው አራቱም ማዕዘን እኩል እንዲሆን ተነጋግረን ነበር " ለምን ሞላላ አድርግ አልከው ? »

« ሳቤላ ሞለል ያለ ቅርጽ ቢኖረው ደስ ይላታል »

« የለም አራቱም ጎኑ እኩል ሲሆን ነው የሚሻለው » አለች ኮርነሊያ "

« ተይው ዝም በይ ... ኮርኒሊያ ብሌር በሰጠሁት ትእዛዝ መሠረት ይሰራዋል ”

« ብሌር ብሎ ነገር ! እሱስ መቸ ይረባና ቢነግሩት የማይሰማ ችኮ ነው »

« ኮርኒሊያ ... በእውነት ለኔ ደሞ ጥሩ ሠራተኛ ነው የሚመስለኝ »

« አንተማ የሰው ጥፋት አይታይህ ምንም የማይገባህ መና ነህኮ ! »

ሚስተር ካርላይል የእኅቱን ጠባይ ከልጅነት እስከ ዕውቀት የሚያውቀው ስለ ሆነ ምንም ቅር ሳይለው ሣቅ ብሎ ዝም አለ " ሳቤላ ግን ከባሏ ጋር የነበራት ግንኙነት እያደር እየጠነከረ ስለ ሔደ ኮርኒሊያ በሚስተር ካርላይል ላይ ትሰነዝረው የነበረውን ዘለፋ ከልቧ ትጠላው ነበር "

«ደግነቱ የማንም ሰው አስተሳሰብ እንዳንቺ አይደለም » አላት ወዶ ሳቤላና ወደ ባርባራ እየተመለከተ " ሁሉም የሻዩን ጠረፔዛ ከበው እንደ ተቀመጡ ነበር
ጊዜው መሸ አራት ሰዓት ተደወለ " ባርባራ ከወንበሯ ብድግ አለችና «አቤት ! እኔ እኮ እንዶዚህ የመሸ አልመሰለኝም አሁንስ ሰዎቼም ፍለጋ ሳይመጡ አልቀ ሩም » አለች

« እስኪ ልጠይቅ » አለች ሳቤላ " ሚስተር ካርላይል መጥሪያውን ደወለ ማንም እንዳልመጣላት ተረዱ "

« እንግዲህ ፒተርን እንዲሸኘኝ ማስቸገሬ ነው እማማ ስለ ደከማት ተኝታ ይሆናል " አባባም ረስቶኝ ነው ። ቤቱ ከተዘጋብኝ ደግሞ እቸግራለሁ » አለች ባርባራ
እየተፍነከነከች "

« ከዚህ በፊት አንድ ቀን ማታ ዘግተውብሽ እንደ ነበረው » አላት ሚስተር ካርላይል አንድ ቀን ማታ ከዚያ ካልታደለው ወንድሟ ጋር ከግቢያቸው ዐጸድ ሳለች አባቷ ዐልፎ ገብቶ ቤቱን ሊቆልፍ ሲል የደረሰችበትን ጊዜ ማስታወሱ ነበር ወሬውን የነገረችው እሷ ነበረች » አሁን ግን ትዝታው እንደ ውጋት ተሰማት ፊቷም ልውጥ ሲል ታየ ።

«ተው አርኪባልድ ... ተው እሱን አታንሣው»አለችው » ሳቤላ ደግሞ፡ ምን ነገር ቢሆን ነው አታንሣው የምትለው ? ' ብላ ሐሳብ ያዛት
« ፒተር ሊሸኘኝ ይችላል ? » አለች ባርባራ ንግግሯን በመቀጠል
« አሁን መሽቷልና እኔ ባደርስሽ ይሻላል » አላት ሚስተር ካርላይል "ባርባራ ይኸን ስትሰማ ልቧ በጣም ይመታ ጀመር ልብሷን ስትደርብ ሳቤላንና ኮርኒሊያን ፡ « ደኅና እደሩ» ስትል፡ ከዚያም ወጥታ ስትሔድና፡ ክንዱን ስትይዘው ሁሉ ልቧ ይመታ ነበር።አሁን እሱ የሌላ ባል ከመሆኑ በቀር ሲቃዋና ስሜቷ ሁሉ ከበፊቱ አልተለወጠም የጨረቃ ብርሃን አልነበረም ነገር ግን በበነጋው ጥሩ ሰማይ
የደመቀ ደስ የሚል ሞቃት የሰኔ ምሽት ነበር ባርባራና ሚስተር ካርላይል በመናፈሻው አልፈው ወርደው፡መንዱን ተሻግረው ከአጥሩ መውጫ ደረጃ ደርሰው በዳኛው ሔር ቤት ጀርባ በኩል ከሚወስደው መንገድ መገንጠያ ሲደርሱ ባርባራ ቆም አለች

« በእርሻው በኩል ብንሔድ ይሻላል ... ባርባራ ? ሣሩ እርጥበት አለው ይኸኛው መንገድ ረጅም ነው " »

«ግን ከመንገዱ አቧራ እንድናለን»

«ጥሩ አንቺ ከመረጥሺ እሺ " የሦስት ደቂቃ እንኳን ልዩነት አይኖረውም»

“ አሁን ኮ ወዶሷ ለመመለስ ቸኩሎ ነው እኔ ዘልዬ ላንቀው ነው!አለበለዚያ ልቤ መፍሰሱ ነው ' አለች በሐሳቧ "

ሚስተር ካርላይል የበሩን ደረጃ አልፎ ባርባራንም ደግፎ አሳለፋትና እንደ ገና ክንዱን ሰጣት " ከዚህ ቀድሞም እንዲሁ የሸኛት ጊዜ'ጃንጥላዋን ተቀብሏት እንደነበረው ሁሉ አሁንም ተቀብሎ ይዞላት ነበር " ዛሬ ግን ከቅጠሎ ከሣሩ ጋር አላማታውም " የዚያን ጊዜ የሺኝታ ጉዞ ትዝታ ከነቃላቱ ' ከነመደለያ ተስፋዎቹ ከመራራው ፍጻሜው ጋር መጥቶ ድቅን አለባት።

ሚስተር ካርላይል ካገባበት ጊዜ ጀምሮ ፍቅርና ቅናት ሁልጊዜ የሚያኝኳት መቆሚያ የሌለው የልብ ሥር ውጋት እሱን ለማግባት የነበራት ምኞትና ተስፋ
ከንቱ ሆኖ መቅረትና በዚህም ምክንያት የተሰማት ኃፍረት ሁሉ • በአንድነት ተደራርበው ብጥብጥ አደረጓት " የዚያን ቀን ለሚስቱ ሲገልጽላት የነበረው የፍቅር
ጭውውትና፡ የነበራቸውንም ደስታ አብራ በማምሸት በዐይኗ ስለ ተመለከተች ልቧን ሰወራት " ሕይወትን †ወዳጅ ሊያደርግ ከሚችል ነገር ሁሉ እንደ ተገለለች ሆኖ ተሰማት.....

💫ይቀጥላል💫
👍2311😁2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

....አንድ ጊዜ የማጠቃለያ እንቅስቃሴዬን ስሰራ፣ ክሪስ እንግዳ ስሜት ፊቱ ላይ እየተነበበ ሲመለከተኝ አየሁ: በቅርቡ አስራ አምስት አመት ልደቱን ያከብራል፡ እንዴት ይሆናል? ትልቅ ሰው እንጂ በጭራሽ ልጅ አይመስልም
ከልጅነት በፍጥነት እየወጣ እንደሆነ የሚናገሩት እነዚያ አይኖቹ ናቸው?ከዚያ ወደ ክሪስ ሄድኩና እጆቼን ወደ እሱ ዘርግቼ “ክሪስ ና ከእኔ ጋር እንደንስ፧ እንዴት እንደሆነ ላስተምርህ?” አልኩት።በመገረም ፈገግ አለና ጭንቅላቱን በመነቅነቅ እንደማይችል ነገረኝ፡ “ባሌት ዳንስ ለእኔ አይሆንም ቫልስ ግን መማር እፈልጋለሁ” አለ፡ አሳቀኝ በዚያን ወቅት የነበረን ብቸኛው የቫልስ ሙዚቃ አሮጌ ነበር፡ ወደ ማጫወቻው እየፈጠንኩ ሄጄ እየተጫወተ የነበረውን አወጣሁና የቫልሱን ከተትኩት ክሪስ ገልጃጃ ሆኖ ነበር የያዘኝ በሚያስቅ አይነት አያያዝ ነበር። በዚያ ላይ ያፈረ ይመስላል ደጋግሞ እየተደነቃቀፈ ሮዝ ቀለም ያለው ሹል ጫማዬ ላይ ይቆማል። ቀላል የሆኑትን እንቅስቃሴዎች ላለመሳሳት ጠንክሮ መሞከሩ ልብ የሚነካ ነበር ተሰጥኦው አእምሮው ውስጥና በጥበበኛ እጆቹ ክህሎት
ላይ እንጂ አንዳቸውም ወደ ቅልጥሞቹና ወደ እግሮቹ እንዳልወረዱ ልነግረው
አልቻልኩም::

በመጨረሻ እናታችን የሚያምሩ ላባዎች ያሉበት ጠባብ ኮፍያ፣ ነጭ ጫማና ቀሚስ ያለበት የዳንስ ልብስ ይዛ በበሩ ስትገባ በከባዱ ተነፈስኩ ፍቅር፣ ተስፋና ደስታ በአንድ ሀምራዊ ሪባን በታሰረበት ትልቅ ካርቶን በኩል
በጣም በሚያስብልኝ አንድ ሰውና ሀሳቡን ውስጧ በከተተው በሌላ ሰው አማካይነት ወደ ፎቁ የመጣ ይመስል ነበር በመጨረሻ ክሪስን ሌሎች ዳንሶችን ላስተምረው ስል ተቃወመኝ፡፡ “እንዳንቺ ሁሉንም የዳንስ አይነቶች መማር አያስፈልገኝም: ምክንያቱም እኔ መድረክ ላይ አልደንስም የምፈልገው ከሴት ጋር የመደነስ አጋጣሚ ቢመጣ መቀለጃ
እንዳልሆን ብቻ ነው:" አለኝ፡

“ክሪስ፣ አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር አለ በየአመቱ የዳንስ አይነቶች ልክ እንደ ልብስ ፋሽን ይለዋወጣሉ፡ ስለዚህ ከጊዜው ጋር መሄድ አለብህ አለበለዚያ
ማንም ሴት አታፈቅርህም::”

“ልታፈቅረኝ የምትችል ሴት አትኖርም:”

እንደዚያ አይነት ሰው ፋሽን ያለፈበት ቢሆንም እሱ ግን ማንም ሰው ለራሱ ያለውን ምስል እንዲለውጥ እንዲያስገድደው አይፈቅድም የራሱ ሰው
በመሆኑ እወደዋለሁ የኔ ሰር ክሪስቶፈር

ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ እንደሆንን ወቅቶች ለወጥን፡ የለጠፍናቸውን አበቦች አውርደን በበልግ ቅጠሎች ተካናቸው ክረምት ሲመጣም እዚህ
የምንሆን ከሆነ በረዶ መጣል ሲጀምር የቆራረጥናቸውን ነጫጭ ንድፎች እንሰቅላቸዋለን፡፡
ክሪስ መፅሀፍ በማያነብበት ጊዜ ስዕሎችን በውሀ ቀለም ይስላል በበረዶ የተሸፈኑ ኮረብታዎች፣ የበረዶ ሸርታቴ የሚጫወቱ ሰዎች የሚያቋርጧቸውን ሀይቆች፣ በረዶ ውስጥ የተቀበሩ ቢጫና ሮዝ ትንንሽ ቤቶችና ከጭስ መውጫው ውስጥ የተጥመለመለ ጭስ ሲወጣ የሚያሳይ ይሰራል። ሲጨርስ የመስኮቱን ጥቁር ፍሬም ቀለም ይቀባና ስዕሉን ግድግዳው ላይ ሲለጥፈው ደስ የሚል እይታ ያለው ክፍል ይሆንልናል

አንድ ጊዜ እኔና ክሪስ አሮጌው ፍራሽ ላይ ጎን ለጎን ተጋድመን እያወራን ነበር ነፃና ሀብታም ስንሆን ስለምንኖረው ኑሮ እቅድ ስናወጣ “በዓለም ዙሪያ እንጓዛለን፤ በጣም ቆንጆ፣ አስተዋይና የምትስብ ሴት አገኝና ፍቅር ይይዘኛል። ልጅቷ ታማኝ፣ ቤት አያያዝ ላይ ጎበዝ የሆነች፣ የማትጨቃጨቅ፣የማታማርር፣ የማትጮህ... ትሆናለች” ብሎ ሲናገር የበታችነት እንዲሰማኝ
አደረገኝ የወደፊት ትዳር ጠያቂዎቼን የምመዝንበት ደረጃ እያወጣልኝ እንደሆነ አውቄያለሁ: ታዲያ እንደ ክሪስ ያለ ወንድን ፍላጎት ማሟላት የምችለው እንዴት ነው?

ክሪስ… ይቺ ጎበዝ፣ ማራኪ፣ እውቀት ያላትና ቆንጆ ሴት ያልካት አንድ ትንሽ ጉድለት እንኳን የላትም?”

“ለምን ጉድለት ይኖራታል?”

“ለምሳሌ እናታችንን ውሰድ። ምናልባት ጎበዝ ከሚለው በስተቀር በሁሉም ነገር የምታስባት አይነት ሴት ናት።”

“እናታችን ደደብ አይደለችም!” ተከላከለላት᎓ “በተሳሳተ አይነት አካባቢ ስላደገች ብቻ ነው! በልጅነቷ ዝቅ ተደርጋ ትታይ ነበር። ሴት በመሆኗ ዝቅተኝነት
እንዲሰማት አድርገዋታል"

በበኩሌ ለተወሰኑ አመታት ታዋቂ ዳንሰኛ ከሆንኩኝ በኋላ ለማግባት
ስፈልግ ክሪስ ጋ ወይም አባቴ ጋ ካልደረሰ ምን እንደማደርግ አላውቅም።መልከመልካም እንደሚሆን አውቃለሁ- ምክንያቱም ልጆቼ ቆንጆዎች
እንዲሆኑ እፈልጋለሁና። ጎበዝ እንዲሆን እፈልጋለሁ አለበለዚያ ላላከብረው እችላለሁ የመተጫጫ የአልማዝ ቀለበቱን ከመቀበሌ በፊት ቁጭ እንዲል
አደርግና ጨዋታ እንጫወታለን፡ ደጋግሜ ካሸነፍኩት ፈገግ እልና ጭንቅላቴን ነቅንቄ ቀለበቱን ወስዶ የገዛበት ሱቅ እንዲመልሰው እነግረዋለሁ

ማሰሮ ውስጥ የተተከሉት አበቦቻችን ጠወለጉ ለአትክልቶቻችን የፍቅር
እንክብካቤ እናደርግላቸዋለን እናወራቸዋለን፣መምሰል አቁሙ እንላቸዋለን አንገቶቻቸውን ቀጥ እናደርግላቸዋለን ከሁሉም በላይ በጣም ጤናማ የሆነውን የምስራቅ የጠዋት ፀሀይ ያገኙ ነበር።ቅጠሎቹ ግን እየሞቱ ነበር‥. ቢጫ፡ እየሆኑ ይሄዱ ጀመር ።

እያደር ኮሪና ኬሪ ውጪ ለመውጣት መጠየቃቸውን አቆሙ፡ ኬሪ በትንንሽ
እጆቿ ቡጢ ጨብጣ በሩን መደብደቧን ተወች:: ኮሪ በእግሮቹ መሬቱን መደብደብ አቁሞ ትንንሽ የእግሮቹን ጣቶች የማያጣብቃቸውን ለስላሳ
ጫማዎች ማድረግ ጀመረ

አሁን የሚያገኙት ብቸኛው “ውጪ” ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ የሚገኘው የአትክልት ስፍራ ብቻ መሆኑን ተቀበሉ። ምስኪን መንትዮቹ...ከጊዜ በኋላ በሚያሳዝን ሁኔታ ከዚህ ከተቆለፍንበት ክፍል ውጪ ሌላ አለም ከነመኖሩም ይረሳሉ
ልጆች ለማደግ የፀሀይ ብርሀን ያስፈልጋቸዋል እኛ ማድረግ ያለብን እየሞቁ ያሉትን ተክሎች መመልከትና የጣሪያው ስር ክፍል ውስጥ የአትክልት ቦታችን ላይ ያደረግነውን ነገር መታዘብ ብቻ ነው: ፀሀይዋ እኛ ክፍል
ውስጥ ስለማትገባ ፀሀይ ለማግኘት ፍራሾችን መስኮቱ ስር እንከምርና ላዩ ላይ እንሆናለን

በአጭር ጊዜ ውስጥ ፀሀዩዋ መስኮታችን ጋ ስትደርስ ምንም ሳናፍር ልብሶቻችንን ሁሉ አወላልቀን ፀሀይ እንሞቃለን፡፡ የእያንዳንዳችንን ልዩነት
አየንና ስለነገሩ ብዙም ሳናስብ ያደረግነውን በግልፅ ለእናታችን ነገርናት ምክንያቱም የፀሀይ ብርሀን በማጣት መሞት የለብንምና፡ እናታችን እይታዋን
ከክሪስ ወደ እኔ እያደረገች ደካማ ፈገግታ አሳየችን፡ “ምንም አይደለም ግን አደራ አያታችሁ እንዳትሰማ! ሁላችሁም እንደምታውቁት እሷ በዚህ ደስ
አይላትም” አለች።

መጀመሪያ ክሪስን ከዚያ እኔን እያፈራረቀች ትመለከተን የነበረው ንፁሁነታችንን የሚያሳይ ወይም ስለ ፆታዊ ግንኙነቶች መንቃታችንን የሚያመለክት ምልክት ለመፈለግ መሆኑን አውቄያለሁ መንትዮቹ እርቃናቸውን ሆነው እንደ ህፃናት መጫወት ይወዳሉ አንድ
ቀን ኬሪ “ለምን ክሪስ…?” ብላ ጠየቀች᎓ እሱና ኮሪ ያላቸውና እሷ የሌላትን የሰውነት ክፍል እየጠቆመች። ክሪስ ትክክለኛና እውነተኛ የሆነውን መልስ
ለመመለስ በመሞከር “ሁሉም ወንድ ፍጥረታት የመራቢያ አካላቸው የሚገኘው
ከውጪ ነው: የሴቶች ደግሞ ከውስጥ ስለሆነ ነው። ወላጆቻችን እርቃን ሰውነታችንን ልክ እንደ አይኖቻችንና ፀጉራችን ተቀብለውታል ስለዚህ ባለን
መደሰት አለብን” አላት

“ወንድ ወፎች ደግሞ ልክ እንደ ሴቶች የመራቢያ አካላቸው ያለው ከውስጥ በኩል ነው: አለች ኬሪ

ተገርሜ “እንዴት አወቅሽ?" ብዬ ጠየቅኳት᎓

“በቃ አወቅኩ፡”

“መፅሀፍ ላይ አንብበሽ ነው?”
👍26👏2👎1🥰1😁1
“እና? ታዲያ ወፉን ይዤ
ተመራምሬ ነው?”

“መቼም አያልፍሽም”

“ቢያንስ የማነበው አእምሮዬን ለማሻሻል ነው። ለመዝናናት አይደለም”አንዳንድ ቀናት ፀሀይ ለመሞቅ በጣም ብርዳማ ናቸው: የሚሞቁ ልብሶች ለብሰን እንኳን ካልሮጥን በስተቀር ያንቀጠቅጠናል፡ ወዲያው የጠዋቷ ፀሀይ hምስራቅ ስትሸሽ በደቡብ በኩል መስኮት ቢኖር ብለን እንመኛለን፡ መስኮቶቹ
ግን ተቆልፈዋል

“ምንም አይደል በጣም ጤናማው የጠዋት ፀሀይ ነው” አለች እናታችን፡ ያላስደሰተን ንግግር ነው ምክንያቱም ጤናማው ፀሀይ ውስጥ እየኖሩም አትክልቶቻችን አንድ በአንድ እየሞቱ ነበር።

ህዳር ሲጀምር ጣሪያው ስር ያለው ክፍል እጅግ መቀዝቀዝ ጀመረ። ጥርሶቻችን
ተንቀጫቀጩ፤ አፍንጫዎቻችን ረጠቡ፡ ማስነጠሱ ሲበረታብን ለእናታችን የጭስ ማውጫ ያለው ምድጃ እንደሚያስፈልገን ነገርናት። ምክንያቱም
በመማሪያ ክፍሉ ውስጥ ያሉት ሁለቱም ምድጃዎች ተበላሽተው ነበር።የኤሌክትሪክ ወይም የጋዝ ማሞቂያ እንደምታመጣልን ነግራን ነበር። ነገር ግን የኤሌክትሪክ ምድጃው ከሌሎች ገመዶች ጋር ከተገናኘ እሳት ሊያስነሳ
ይችላል ብላ ፈራች: የጋዝ ምድጃ ደግሞ የጭስ ማውጫ ያስፈልገዋል።
ስለዚህ ወፍራም ልብሶች አመጣችልንና እነዚያን ልብሶች ለብሰን በነፃነት ልንሮጥበትና ከአያትየው አይኖች ልንሸሽበት ወደ ምንችልበት ጣሪያው ስር
ወዳለው ክፍል በየቀኑ መምጣት ቀጠልን አንድ ቀን ድብብቆሽ እየተጫወትን እያለ ኮሪ የተደበቀበትን አጣነው
በአብዛኛው ለመደበቅ የሚመርጠው ክሪስ ተደብቆበት የነበረውን የመጨረሻ
ቦታ ስለነበር እሱን ማግኘት ቀላል ነው: ስለዚህ ቀጥታ ወደ ሶስተኛውና ትልቁ የልብስ ማስቀመጫ ሳጥን ስንሄድ ኮሪ ወለሉ ላይ ኩርምት ብሎና አሮጌዎቹ ልብስ ስር ተደብቆ እናገኘዋለን ብለን አምነን ነበር- ግን አላገኘነውም፡

“የሚደበቅበት አዲስ ቦታ አግኝቷል ማለት ነው" አለ ክሪስ፡ እውነትም አዲስ መደበቂያ ፈልጎ ከሆነ፣ በዚህ ጣራ ስር ያለ ክፍል ውስጥ ብዙ ጥሩ ጥሩ
መደበቂያ ቦታዎች አሉ

“ኮሪ!” ብዬ ጮህኩ፡ ካለህበት ቦታ ውጣ፣ ምሳ ሰዓት ደርሷል!” አሁን ይሄ ያመጣዋል። በምሳ ቀልድ የለም።

ይሁንና አሁንም መልስ አልሰጠም፡ ክሪስን በቁጣ ተመለከትኩት::"የምትወደው አይነት ምግብ ነው" አልኩኝ ሮጦ እንዲመጣ ሊያደርገው ይገባ ነበር አሁንም ድምፅም፣ ለቅሶም፣ ምንም የለም:

ድንገት ፈራሁ። ኮሪ በዚህ ሰፊ ክፍል ውስጥ ፍርሀቱን አሸንፎ ጨዋታውን በቁምነገር ይወስደዋል ብዬ ማመን አልቻልኩም ምናልባት ደግሞ ክሪስን ወይም እኔን ለመኮረጅ ይሞክር ይሆን? አምላኬ! “ክሪስ! ኮሪን ማግኘት አለብን በፍጥነት” ስል ጮህኩ ድንጋጤዬ ተጋባበትና የኮሪን ስም እየጠራ እንዲወጣና መደበቁን እንዲያቆም እያዘዘ ሮጠ፡ ሁለታችም ኮሪን ደጋግመን እየተጣራን እየሮጥን መፈለግ
ቀጠልን የድብብቆሹ ሰዓት አልቆ አሁን የምሳ ሰዓት ነው! መልስ ግን
የለም ያንን ሁሉ ልብስ ለብሼም በረዶ ሆኛለሁ: እጆቼ ሳይቀሩ ሰማያዊ መስለዋል

“ወይኔ አምላኬ!” ሲል ክሪስ አጉረመረመ: “ምናልባት አንደኛው ሻንጣ ውስጥ ሲደበቅ ድንገት ክዳኑ ተዘግቶበት ይሆን?”

ኮሪ ሊታፈን ይችላል ሊሞት ይችላል!

እንዳበደ ሰው እየሮጥን የእያንዳንዱን ሻንጣ ክዳን እየበረገድን መክፈት ጀመርን፡ ሻንጣዎቹ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሁሉ እየበታተንን ፍለጋችንን
ቀጠልን እየሮጥኩና እየፈለግኩ “አምላኬ ሆይ እባክህ ኮሪ እንዲሞት አታድርግ” እያልኩ ደጋግሜ እየፀለይኩ ነበር

ካቲ አገኘሁት!” ሲል ክሪስ ጮኸ፡ ክሪስ ወዳለበት ስዞር ክዳኑ ተዘግቶ ከነበረ ሻንጣ ውስጥ የኮሪን የማይንቀሳቀስ ትንሽ አካል ሲያነሳ አየሁት በእፎይታ
ወደ እነሱ ተጠጋሁና ኦክስጂን በማጣት የቆዳው ቀለም የተቀየረውን የኮሪን ትንሽዬ የገረጣ ፊት ሳምኩ፡ የደከሙት አይኖቹ እያዩ አልነበረም: ራሱን ወደ መሳት ቀርቧል “እማዬ…” አለ በሹክሹክታ “እናቴን እፈልጋለሁ:”

እናታችን ግን ሩቅ ናት የታይፕ
ፅህፈት እየተማረች ነው። ያለችው ሀዘኔታዐያልፈጠረባት አያት ብቻ ናት: እሷንም ድንገተኛ አደጋ ሲያጋጥመን እንዴት እንደምናገኛት አናውቅም ክሪስ “በፍጥነት ሩጪና የመታጠቢያ ገንዳውን በሙቅ ውሀ ሙይው” አለ፡ ግን “በጣም እንዳይሞቅ!” ብሎኝ ኮሪን በክንዶቹ አቅፎ ወደ ደረጃው ተንደረደረ
ቀድሜው ወደ መኝታ ክፍሉ ደረስኩና ወደ መታጠቢያ ቤቱ ፈጠንኩ።ወደኋላ ስመለከት ክሪስ ኮሪን አልጋው ላይ ሲያጋድመው ተመለከትኩ፡፡ ከዚያ ጎንበስ ብሎ የኮሪን የአፍንጫ ቀዳዳ አፍኖ ያዘና ጭንቅላቱን ዝቅ አድርጎ
እንዲተነፍስ ለመርዳት አፉን ኮሪ አፍ ላይ ገጥሞ አየር ሊሰጠው ሲሞክር ልቤ ዘለለች! ሞቷል? መተንፈስ አቁሟል?

ኬሪ ምን እየሆነ እንደሆነ አየች
ስትመለከት መጮህ ጀመረች:
በመታጠቢያ ክፍሉ ውስጥ
ሁለቱንም ቧንቧዎች እስከመጨረሻው ከፈትኳቸው፡ ኮሪ ሊሞት ነው፡ ሁልጊዜ ስለ ሞት ሳልም. ብዙ ጊዜ ህልሜ
እውን ይሆናል፡፡ እና እንደ ሁልጊዜው እግዚአብሔር እንደተወንና ጀርባውን
እንደሰጠን ሳስብ፣ እምነቴን ለመያዝ እዞራለሁ፤ ኮሪ እንዲሞት እንዳይፈቅድ እየጠየቅኩ መፀለይ ጀመርኩ. እባክህ እግዚአብሔር እባክህ እባክህ ...

ልክ ክሪስ እያደረገለት እንዳለው አርቲፊሻል የመተንፈሻ ዘዴ የእኔም የተስፋ መቁረጥ ፀሎት ኮሪን ወደ ህይወት ይመልሰው ይሆናል

“እንደገና መተንፈስ ጀመረ” አለ ክሪስ ፊቱ ገርጥቶ እየተንቀጠቀጠ፡ ኮሪን
ተሸክሞ ወደ መታጠቢያው እየወሰደው “አሁን ማድረግ ያለብን እንዲሞቀው
ማድረግ ብቻ ነው” ወዲያውኑ የኮሪን ልብስ አውልቀን በሙቅ ውሀ የተሞላው ገንዳ ውስጥ ከተትነው ኮሪ ሲነቃ “እማዬ… እማዬን እፈልጋለሁ” አለ
እየደጋገመ በሹክሹክታ እንደዚያ ሲል፣ እጆቼን ጨበጥኩና ግድግዳውን መታሁት: ፍትሀዊ አይደለም! ምን ማድረግ እንዳለባት የማታውቅና
የምታስመስል እናት ሳይሆን ራሷን እናቱን ማግኘት ነበረበት በቃ! ጎዳና ላይ መለመን ቢኖርብኝም እንኳን ከዚህ መውጣት እፈልጋለሁ።

ነገር ግን ክሪስ ቀና ብሎ ተመልክቶኝ በማረጋገጥ ፈገግ እንዲልልኝ በሚያደርግ
ሁኔታ በእርጋታ ተናገርኩ፡ “እኔ እናትህ እንደሆንኩ ለምን አታስመስልም? እሷ የምታደርግልህን ነገሮች ሁሉ አደርግልሀለሁ: ጭኔ ላይ አድርጌ
አቅፍሀለሁ፣ ትንሽ ምሳ ከበላህና ጥቂት ወተት ከጠጣህ እሹሩሩ እያልኩ አስተኛሀለሁ " አልኩት ይህንን ስናገር እኔና ክሪስ ተንበርክከን ነበር እኔ ቀዝቃዛ እጆቹን ለማሞቅ ሳሻሽለት ክሪስ ደግሞ የኮሪን ትናንሽ እግሮች
እያሸለት ነበር፡ የሰውነቱ ቀለም ወደ ነበረበት ሲመለስ ሰውነቱን አድርቆለት የሚሞቅ ፒጃማ ካለበሰው በኋላ በብርድ ልብስ ጠቀለለውና ጣሪያው ስር ካለው ክፍል ውስጥ ያመጣው የሚወዛወዝ ወንበር ላይ ተቀምጬ ጭኔ ላይ
አስቀመጥኩት። ከዚያ ፊቱን ሁሉ እየሳምኩና ደስ የሚሉ ነገሮች በጆሮው እያንሾካሾኩ እንዲስቅ አደረግኩት።

መሳቅ ከቻለ ደግሞ መብላት ይችላል፡ በትንንሹ እየቆረስኩ ሳንድዊች አጎረስኩት። ለብ ያለ ሾርባና ወተት እንዲጠጣ አደረግኩ። ይህንን ሳደርግ
በአስር ደቂቃ ውስጥ አስር አመት ያህል ያደግኩ መሰለኝ ክሪስ ምሳውን ለመብላት ሲቀመጥ አየት አደረግኩት እሱም ተለውጧል፡ አሁን የፀሀይ ብርሀንና ንፁህ አየር ከማጣት ባሻገር በዚያ ጣራ ስር ያለ ክፍል ውስጥ አደጋ መኖሩን አወቅን፡ እያንዳንዳቸውን አይጦችና ሸረሪቶች የገደልናቸው ቢሆንም እንኳን ሁላችንም ለመኖር ችክ ካሉት ከእነሱ የበለጡ እጅግ የከፉ ነገሮችን ተጋፍጠናል፡
👍343
ክሪስ ብቻውን ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ለመሄድ ወደ ደረጃዎቹ ሲያመራ ኮሪንና ኬሪን ሁለቱንም ጭኖቹ ላይ አስቀምጬ መዝሙር እየዘመርኩላቸው
ወደፊትና ወደኋላ እየተወዛወዝኩ ነበር። ድንገት ሠራተኞቹ ሊሰሙት
የሚችሉት በመዶሻ የሚመታ አይነት ሀይለኛ ድምፅ ከላይ ሲመጣ ሰማን፡

ኬሪ እንቅልፍ እያዳፋት ሳለ ኮሪ “ካቲ እናታችን እዚህ አለመኖሯ ከዚህ በኋላ ደስ አይለኝም” አለ ቀስ ባለ ድምፅ

“አይዞህ እማዬን ታገኛታለህ፤ እኔም ደግሞ አለሁልህ"

“አንቺ እንደ እውነተኛዋ እናቴ ጥሩ ነሽ?”

“አዎ ነኝ ብዬ አስባለሁ፡ በዚያ ላይ በጣም እወድሀለሁ ኮሪ፤ እውነተኛ
እናት የምታደርገው ደግሞ ያንን ነው:: ኮሪ በትልልቅ ሰማያዊ አይኖቹ አተኩሮ ተመለከተኝ፡ የምሬን መሆኑን ወይም ዝም ብዬ ለማባበል ስል የተናገርኩት መሆኑን ለመለየት የፈለገ ይመስላል። ከዚያ ትናንሽ ክንዶቹ
አንገቴ ላይ ተጠመጠሙና ጭንቅላቱን ትከሻዬ ላይ አሳረፈ: “እንቅልፌ መጥቷል እማዬ፣ ግን መዘመርሽን እንዳታቆሚ፡” አለኝ
ክሪስ ፊቱ ላይ እርካታ እየተነበበበት ተመልሶ ሲመጣ እኔ አሁንም በቀስታ እየዘመርኩ ልጆቹን እንዳቀፍኩ ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየተወዛወዝኩ ነበር።

“ሻንጣዎቹ ከዚህ በኋላ ድንገት እንደገና አይዘጉም: ምክንያቱም እያንዳንዱን ቁልፎችና መዝጊያዎች ሁሉ ሰባብሬያቸዋለሁ” አለ፡
በመስማማት ጭንቅላቴን ወዘወዝኩ።.....

ይቀጥላል
👍3212🥰1
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሰባት ፡ ፡ #ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ ....አንድ ጊዜ የማጠቃለያ እንቅስቃሴዬን ስሰራ፣ ክሪስ እንግዳ ስሜት ፊቱ ላይ እየተነበበ ሲመለከተኝ አየሁ: በቅርቡ አስራ አምስት አመት ልደቱን ያከብራል፡ እንዴት ይሆናል? ትልቅ ሰው እንጂ በጭራሽ ልጅ አይመስልም ከልጅነት በፍጥነት እየወጣ እንደሆነ የሚናገሩት እነዚያ አይኖቹ ናቸው?ከዚያ ወደ ክሪስ ሄድኩና እጆቼን…»
#ሳቤላ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


....ሚስተር ካርላይል ካገባበት ጊዜ ጀምሮ ፍቅርና ቅናት ሁልጊዜ የሚያኝኳት መቆሚያ የሌለው የልብ ሥር ውጋት እሱን ለማግባት የነበራት ምኞትና ተስፋ ከንቱ ሆኖ መቅረትና በዚህም ምክንያት የተሰማት ኃፍረት ሁሉ በአንድነት ተደራርበው ብጥብጥ አደረጓት " የዚያን ቀን ለሚስቱ ሲገልጽላት የነበረው የፍቅር ጭውውትና የነበራቸውንም ደስታ አብራ በማምሸት በዐይኗ ስለ ተመለከተች ልቧን ሰወራት " ሕይወትን ተወዳጅ ሊያደርግ ከሚችል ነገር ሁሉ እንደ ተገለለች ሆኖ ተሰማት የባርባራና የሚስተር ካርላይል ይህን ያል መቀራረብ በእርሷ ላይ ፎቅር ሲያሳድርባት በሱ በኩል ግን እንደ እህቱ እንጂ እንደ ፍቅረኛ አድርጎ አስቧት
አያውቅም እሷ በሐሳብ ማዕበል ስትንገላታና ስትበጠበጥ የዚያ ሁሎ ሁከቷ ምክንያት እሱ መሆኑን ሊገነዘብ ቀርቶ ችግር እንደ ነበረባት ንኳን አላወቀላትም » ስለዚህ እሷ ሲቃ ይዟት ተጨንቃና ተወጥራ እያለ ብሷቷን ባለመረዳት ያልተጨነቀችበትንና ያላሰበችበትን ርዕስ ጣልቃ በማስባት ፡ « አባትሽ ድርቆሹን መች ያስከምሩታል ...ባርባራ?» አላት።

ዝም አለችው " ስሜቷን ለማዳፈን ከራሷ ጋር ስትተናነቅ ሚስተር ካርላይል መልሶ ጠየቃት ባርባራ . . . አባትሽ ድርቆሹን መች እንደሚያስከምሩት ጠይቄሽ ነበር»

አሁንም አልመለሰችለትም መልሶ መናገር አቃታት ጉሮሮዋ ተላወሰ
የአፏ ጡንቻዎች ተኮማተሩ ሰውነቷ ተንሰፈሰፈ ቀጠለችና ጮኻ መንሰቅሰቅ ጀመረች "

« ባርባራ ...አመመሽ እንዴ ? ምንድነው ? » አላት

ፍቅር ንዴት በደልና ጭንቀት አንድነት ተደባልቀው ይፈሉባት ጀመር ብርክ ያዛት እምታደርገውን ማወቅ ተሳናት " ሚስተር ካርላይል በከፊል ተሸክሞ በከፊል እየሳበ ከአጥሩ መወጣጫ ሁለተኛው ደረጃ በክንዱ ደግፎ ይዞ አሳረፋት " በዚያ ጸጥ ባለው የለሊት ሰዓት ረብሻ መፈጠሩ ለምን እንደሆነ የገረማቸው
አንዲት አሮጊት ላምና ሁለት ጥጆች ወደ ስዎቹ በመቅረብ ትክ ብለው ይመለከቷቸው ጀመር ።

ባርባራ ከስሜቷ ግፊት ጋር ባላት አቅም ተናነቀች እንባዋ ተገታ መብረክረኳና የአቅል መሳት ምልክቶቿ ለቀቅ አደረጓት " ደግፎ የያዛትን ክንዱን ወዲያ ገፍታ አጥሩ ላይ በጀርባዋ ተደግፋ ቆመች " ሚስተር ካርላይል ወደ ኩሬው ሮጦ ውሃ ለማምጣት ቃጣው " ነገር ግን ውሃ የሚያመጣበት ከባርኔጣው በቀር ምንም ነገር አልነበረውም ።

« ተሻለሽ ... ባርባራ ? ምን ነክቶሽ ነው? » አላት "

«ምን ነክቶሽ ነው? » ብላ ጮኸችበት « እንዲህ ብለህ ልትጠይቀኝ ትችላለህ ? »

« ነገሩ አልገባኝም " እኔ
የበደልኩሽ ካለ በውነቱ በጣም አዝናለሁ »

«እንዴታ ! አይጠረጠርም ታዝናለህ እንጂ !ለመሆኑ እኔ ነገ ካፈር ብገባ» አለችው መሬቱን በእግሯ እየደበደበች « አንተ ምን ቸገረህ ? እኔ ምንድነኝና አንተ አንደ ሆንክ ሚስትህ አለችልህ ? የኔ መከራ የኔ ሥቃይ ለአንተ ምንህ ሆነና? ስማህ አርኪባልድ ካርላይል ... እኔ የአሁኑን ኑሮዬን ታግሸ ችየው ለመግፋት ከመድከም ሙቸ ብቀበር ይሻለኛል " ያለሁበት ጭንቅ ከምችለው በላይ ነው»

«ነገርሽ ያልገባኝ ለመምሰል አልፈልግም » አላት ብስጭት ብሎ « ግን ባርባራ እኔ ላንቺ ከማስብልሽና ከማከብርሽ የበለጠ እንድታስቢ ያደረግሁት ነገር የሰጠሁሽ ፍንጭ የለም»

«ምክንያት የሚሆነኝ ፍንጭ አልሰጠኸኝም ! .. እንዶ ጥላ እየተከተልhኝ ከቤታችን ስትመላለስ ይኸን አምጥተህ ስትሸልመኝ » ካባዋን ጣል አድርጋ የወርቅ ጌጥ መያዣዋን እያሳየችው « ከወንድም የበለጠ ስትቀርበኝ !
«አይ ባርባራ ቁም ነገሩን አሁን ገና አመጣሽው እኔ ላንቺ
ከወንድምነት በቀር ሌላ ነገር በሐሳቤ መጥቶብኝ አያውቅም » አላት በተለመደው ቀጥተኛ አነጋገሩ።

«እንደ ወንድም ብቻ ሌላ ምንም» አለች ድምጿ በስሜት እየናረ " ልትቆጣጠረው የቻለች አትመስልም « አንተ ስለኔ ስሜት ምን ቸገረህ ? የኔን ፍቅር
ለማግኘት ለምን ብለህ ትቸገራለህ ? »

« ባሮባራ . . ረጋ በዪ እስኪ ትንሽ አስተውዬ በርግጥ ላንቺ ንጹሕ የሆነ ጥልቅ ስሜትና አክብሮት አለኝ " እኔ ያላሰብኩት ስሜት ሊያድርብሽ የቻለውም በዚህ የተነሣ ሊሆን ይችላል " ስለዚህ ለኔ ሳይታወቀኝ በሐሳቤ የሌለ ስሜት ላንቺ እንዲታወቅሽ እንዲሰማሽ በማድረጌ በጣም አዝናለሁ »

ጥቂት በረድ አለላት " እየለቀቃት ሔደ " ሁኔታዎችን አመዛዘነች ፊቷን ወደ ሚስተር ካርላይል ቀና አድርጋ ተመለከተች "

« እሷ ከመኻላች ባትገባ ኖሮ ትወደኝ ኖሮዋል ? »

« እንጃ እንዴት ማወቅ እችላለሁ? እኔ አንቺን እንደ እኅቴ እንደ ንጹሕ ባልንጀራዬ ነበር የማይሽ ስለዚህ ግንኙነታችን ከዚህ ሌላ ምን ሊመስል ይችል እንደ ነበር ለማወቅ አልችልም »

« እኔ ኮ ላንተ እንዳልታወቀህ ሁሉ ለሌላውም ባይታወቀው ኖሮ በቻልኩት ነበር • • •አርኪባልድ »

« በውነቱ በጣም አዝናለሁ - አሁንም ሁሉን ነገር እንደምትረሺው ተስፋ አደርጋለሁ " የዛሬ ማታው ንግግራችንም ከአእምሮሽ ይጥፋ " አሁንም ንጹሕ ባልንጀሮች እኅትና ወንድም እንደሆን እንቀጥላለን " ደግሞ አንቺ የተሰማሽን ግልጽልጽ
አድርግሽ በመናገርሽ ባንቺ ላይ ያለኝን ግምት ምንም አልቀነሰውም »

በግርግሩ አጥር ዘሎ ለመሔድ ያሰበ ይመስል ሊንቀሳቀስ ባርባራ ግን ንቅንቅ አላለችም " እንባዋም ዝም ብሎ ይወርድ ጀመር " በዚህ ጊዜ አንድ ነገር ሰሙ "

« አንቺ ነሽ ሚስ ባርባራ ? »

ባርባራ በጥይት የተመታች ያህል ድርቅ አለች " ከአጥሩ በስተውስጥ የቤታቸው የገረዶች አለቃ የነበረችውን ዊልሶንን አዩዋት ሚስዝ ሔር ጃስፐርን ወደ
ባርባራ ከላከችው በኋላ እሱ እስኪመለስ ድረስ መጠበቅ ስለ አልቻለች እንደገና እሷን ስለላከቻት መምጣቷን ነገረቻቸው " ከዚያ ቦታ ምን ያህል ቆይታ ምን ያህል
ምስጢር እንደ ሰማች አይታወቅም ሚስተር ካርላይል ለራሱ ዐለፈና ባርባራንም
እጅዋን ይዞ አሳለፋት "
« ከዚህ በላይስ መሔድ አያስፈልግህም ይብቃህ ተመለስ» አለችው ቀስ ብላ "

« የለም ከቤት አስገባሻለሁ » ብሎ ክንዱን ሰጣትና ተያይዘው በጸጥታ አዘገሙ " ወደ ማድቤት ከሚያስገባው ከዐጸዱ ጀርባ ካለው በር ሲደርሱ ዊልሰን ቀድማቸው ገባች " ሚስተር ካርላይል ባርባራን እጆቿን ይዞ ደኅና እደሪ ባርባራ » አላት "

ባርባራ ትንሽ አሰበች " ያ ሁሉ ስሜታዊ ንዴት በረደላት የፈጸመችው ነገር ከዕብደት የሚቆጠር አሳፋሪ መሆኑ ታወቃት ሚስተር ካርላይልም ምን
ያህል እንደ ተሰማትገባው

« ይህን ሁሉ ነገር ስናገርህ እውነት አብጀ ነበር መሰለኝ እንጂ በደኅናዬ የነበርኩ አይመስለኝም" አንተ ግን እንዳልተፈጸመ እንዳልተነገረ አድርገሀ ቁጠረው

«ስለዚህ ግድየለሽም ሐሳብ አይግባሽ »
ለሚስትህ አትነግርብኝም ? » አለችው እየቃተተች
«እንዴ ባርባራ ! »
«አመሰግንሃለሁ ደኅና እደር »

እሱ ግን እጁን ይዞ ዝም አለ
«ሰማሽ ባርባራ ፍቅርሽን ከኔ በበለጠ ለመቀበል የታደለ በቅርቡ እንደምታገኝ አምናለሁ።»

«በጭራሽ አልቃጣውም እኔ እኮ በቀላሉ አላፈቅርም ፤ በቀላሎም አልረሳም ከእንግዲህ እስከ ዕድሜ ልኬ ባርባራ ሔር እንደ ተባልኩ እኖራታለሁ እንጂ ባል አግብቼ ሚስዝ እገሌ አልባልም

ሚስተር ካርላይል ስለ ደረሰው ሁኔታ እያሰበ ወደ ቤቱ ገሠገሠ እሷ ባሰበችው መንገድ እሱ ሚስቱን በሚያፈቅራት ዐይነት አይሁን እንጂ ባርበራን ይወዳትና
ያከብራት ነበር " ስለዚህ በባርባራ አነጋገር ኀዘን ተሰማው "
👍19
ባርባራ ሔር ሁና ተወልዳ ስሟን ሳትለውጥ መሞት እንኳን ወጣት ሴቶች ሲበሳጩ የሚናገሩትና ወዲያው የሚረሱት ነገር ነው " ይልቁን ለልቧ ደስ የሚላትን ሰው አግኝታ እኔን እንድትረሳኝ እመኝላታለሁ አለ ለብቻው "

« አርኪባልድ ! »

ከመናፈሻው የመጨረሻውና ከሌሎቹ ሁሉ ለቤቱ ቅርብ ከሆነው ዛፍ ሲደርስ ብቻውን ሲያወጣ ሲያወርድ ከነበረው ሐሳብ ያቋረጠው ድምፅ ከዛፉ ሥር ቁሞ ከነበረው ጥቁር ቅርጽ የወጣ ነበር "

« አንቺ ነሽ እንዴ ፍቅሬ ? »
« ልቀበልህ እኮ ወጥቸ ነው ግን በጣም አልቆየህም ?»

«መሰለኝ ያውም እኮ ገረዲቱን ከመንገድ አግኝተናት ነበር " ግን ዝም ብዬ ቤት ድረስ ሔድኩ »

« ከጀስቲስ ሔር ቤተሰብ ጋር የቅርብ ግንኙነት አላችሁ ? »

« አዎን ኮርኒሊያ እኮ ትዛመዳቸዋለች »
« ባርባራ ቆንጆ ትመስልሃለች ? »
« በጣም ! »
« ታዲያ እንዶዚህ ቅርብ ግንኙነት ካለህ ከሷ ጋር ፍቅር ይዞህ አያውቅም?
ሚስተር ካርላይል ከባርባራ ጋር ሲነጋገሩት የነበረው ትዝ አለውና ሣቀ
«ምን ! ምን አልሺኝ ሳቤላ ? »
« ከባርባራ ሔር ጋር ፍቅር ይዞህ አያውቅም ወይ ? »

« ፍቅር ! ምን ሐሳብ ነው በጭንቅላትሽ የገባው ... ሳቤላ ? እኔ ከአንዲት ሴት በቀር ወድጄ አላቅም ያችንም ሴት ሚስቴ አድርጌያታለሁ»
፡ ፡ ፡ ፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡
ሳቤላና ሚስተር ካርላይል ከተጋቡ ሁለተኛ ዓመታቸውን ያዙ " ሚስ ካርላይልን ባይጥልባት ኖሮ ሳቤላ ደስተኛ ትሆን ነበር " ሌትዮይቱ እስካሁንም ኢስትሊን ላይ ተደላድላ ቁጭ አለችና ጠቅላላ ቤቱን ጤና ነሳችው " ለስሙ የቤቱን ኃላፊነትና ባለቤትነት ለሳቤላ ሰጠች " የእውነቲቱ የቤቱ ባለቤትና አዛዥ ግን ራሷ ሚስ ኮርኒሊያ ካርላይል ሆነች" ሳቤላን ከዕቃ ይህን ያህልም አብልጣ አታያትም ምስኪኗ ሳቤላ በጠራው ጠባይዋና በዐይነ አፋርነቷ ሞገደኛይቷን ሴትዮ
መቋቋም ስለ አልቻለች ከዛ ቤቷ ተጨቁናና ተዋርዳ ተቀመጠች "

ሚስተር ካርላይል ከቤቱ እንደዚህ የመስለ ችግር አለ ብሎ ጠርጥሮ አያውቅም ከቤት የሚገኘው ጧትና ማታ ብቻ ነው ይኸንም ከሥራ ውጭ ሰዓት አብዛኛውን ማንም ሰው ሳይጨምሩ እሱና ሚስቱ አብረው ሲያሳልፉትም እሷ እንዲህ ሆንኩ "ብላ አትነግረውም
በተረፈ የሥራው ብዛት ከጊዜ ወደጊዜ እየበዛበትና እየተጫነው በመሔዱ ከቤት ውስጥ አለመጣጣም መኖሩ አልታየውም

አንድ ቀን ሁለቱ ሴቶች ተጋጩና ነገር ተፈጠረ " በመጨረሻ ሚስ ካርላይል ትእዛዟን ስለአነሣች ሊፈታ ቢቻልም ዐመሏ ከመቸውም የበለጠ ከፋ ሳቤላ አንድ ቀን ለብቻቸው ቢቀመጡ የበለጠ የደስታ ኑሮ እንደሚኖሩ ለባሏ አነሣችለት " ለዚሁም ሚስ ካርላይልን የበደለችና ያስቀየመች መስሏት ከመጨነቋ የተነሣ ልቧ
ይመታ ጀመር " ፊቷ ደም መሰለ ተሣቀቀች እሱም ነገርን መደበቅና ማለባበስ ስለማይችል ለእኅቱ ፍርጥ አድርጎ አስረዳት " እሷ ደሞ በበኩሏ ዘለለች " ጉብ ቂጥ
አለች » በመጨረሻም ምን እንዳስቀየመች ለብዙ የሚበቃ ትልቅ ቤት ይዘው ለምን አንድ ጥግ ሊነፍጓት እንደ ፈለጉ ሳቤላን ጠየቀቻት » ሳቤላም ጠላቷን እንኳን ለማስቀየም ስለማትወድ ወዲያው መልሳ ይቅርታ ጠየቀች » ባሏንም የነገረችውን ሁሉ እንዲረሳው ለመነችው " እሱም ከዚያ ወዲህ ነገሩን አስቦት አያውቅም " ውስጠ ነገር እንደ ነበረባትም አልጠረጠረም። ከእውነተኛው ሁኔታ ትንሽ
ጫፍ ቢይዝ ኖሮ ግን ' ሚስቱን ከሚስ ካርላይል አምባገነን ጭቆና ለማላቀቅ አፍታ
እንኳን አይቆይም ነበር "

አንድ ቀን መታገሥ እንኳን ወግ ነበር “ የሚስተር ካርላይል ጋብቻ ከባድ ድህነት ላይ የሚጥል ወጭ የሚያስከትል እንደሚሆን ሳቤላን በየአጋጣሚው ትጨቀጭቃት ጀመር " ይህም ንግግር ከልክ ያለፈ ልቧን አስጨነቀው በተለይ በወጭ ረገድ እውነትም የሚስተር ካርላይል አጥፊው እንደ ሆነች በአእምሮዋ ተቀረጸ " አንድ ቀን የገና ጊዜ ማውንት እስቨርን ከልጁ ጋር ሆኖ ሊጠይቃቸው መጣ " ሳቤላ በርግጥ ሚስተር ካርላይል ሲያገባት ሌላ ቢያገባ ኖሮ ላይፈጽመው ይችል የነበረ
ውን ነገር አድርጐላት እንደሆነና ይኸን በማድረጉም ያልተጠበቀ ወጭ አስወጥቶት እንደሆነ አስተያየቱን ጠየቀችው » በርግጥ የፈራችው ነገር የደረሰባት መሆኑንና አሁንም ቢሆን የቸርነቱን ወለታ መዘንጋት እንደማይገባት ነገራት " እሷም የተነገራትን በማመን ምክሩን ተቀበለች » ከሚስ ካርላይል ጋርም ምልልስ አቆመች "የባሏን ውለታ ለመመለስ ለሚስ ካርላይል ፈቃድና ፍላጐት ተገዛች ኢስት
ሊን ሲታደስና ዕቃው ሲሟላ ለሚስ ካርላይል ብዙ ገንዘብ አውጥታ ነበር ከነሱ ዘንድ የተደረበችውም ለራሷ ገንዘብ ለማጠራቀም አልነበረም " ገንዘቧን ያወጣችው
ለኢስት ሊንም ሆነ ለሌላ ዙሮ ዙሮ በመጨረሻ ገቢነቱ ለሚስተር ካርላይል ነበር ስለዚህ ሳቤላ ስትገባ ያስወጣችው አንሶ አሁንም ደሞ ኮርንሊያን በማወስወጣት ብዙ ገቢ ልታስቀርበት ደስ አላላትም።

ማንም ሊያስበው ወይም ሊያምነው ከሚችለው በላይ የተፈጥሮዋ ሥጉና ድንጉጥ
የሆነችው ሳቤላ ከቢጤዎቿ የመኳንንት ልጆች የተለየ ከሰዎች ተገልላ የሕይወትን ውጣ ውረድ ልምድ ሳታይ ያደች ስለነበረች ከዓለም ጋር ለመታግል በተለይም ከሚስ ካርላይል ጋር ለመቋቋም የምትችል አልነበረችም " ከአይቷ ጋር አለመቻቻሏን ብቻ ሳይሆን ውለታ የሚለው ነገርም ያለ መጠን ከበዳት አባቷም ያለ
ምንም ቤሳ ጥሏት የሞተ ከካስል ማርሊንግ በቀር ምንም የምትጠጋበት ቤት አጥታ ሰማይ ተደፍቶባት መሬት ጨልሞባት በነበረበት ሰዓት ነበር ካርላይል
ስታየው ሸሽጎ የተወላት አንድ መቶ ፓውንድ ሳይቀር እየተቆላለፉ በአእምሮዋ ተቀርጸው ትዝ እያሏት አፏን አሳርፋ ጻጥ ብላ እንድትቀመጥ ግድ ሆነባት "

የሚስተር ካርላይልን በጎ አድራጊነት ማመስገን እንዳለባት ከልቧ ተስማት

በሷ ምክንያት ከሚችለው በላይ ብዙ ገንዘብ ማውጣቱን • እሷ የሀብቱ ጠንቅ መሆንዋን በየቀኑ መስማቱ ግን ከማትችለው የሕይወት ምሬት ከተታት ጀፈድፍረት ቢኖራት ኖሮ ከባሏ ጋር በግልጽ ተነጋግራ ' የገንዘብና የሌላም ያለፈ እርዳታ ባለውለታነት የሚባለው የዛች አስተሳሰበ ጠባብ እኅቱ አስተያየት እንጂ የሱ ..አለመሆኑን እሷንም ያገባት | አሁንም የያት ስለሚያፈቅራት ብቻ መሆኑን በአንድ ቃል ሊያረጋግጥላት ይችል ነበር "

እሷ ግን፥ከዚህ ሁሉ ሳትደርስ ሚስ ካርላይል የሚጕተመተም ዐመሏ ሲነሳባት ወይ ዝም ብላ ታዳምጣለች " አለበለዚያ ደግሞ በራስ ምታት የሚሠቃየውን
ራሷን በሁለት እጆቿ መኻል ደፍታ ምንም ሳትመልስ ውስጥ ውስጧን እያረረ በሆዷ መቻል እንጂ ለባሏ ስለ ብሶቷ ገልጻለት አታውቅም።.....

💫ይቀጥላል💫
👍267🤔2
ደመና ☁️ ጥሩ ነው
ዝናብም ደስ ይላል
ደም መና ሲሆን ግን
በጣም ያሳዝናል።
👍69😢21🔥119
የከፋው ሰው ሲሞት
የደላው መች ቀረ
ሁሉም ተከታይ ነው
አስጠላም አማረ።
55👍32👏9👎4
#ሳቤላ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


....እሷ ግን፥ከዚህ ሁሉ ሳትደርስ ሚስ ካርላይል የሚጕተመተም ዐመሏ ሲነሳባት ወይ ዝም ብላ ታዳምጣለች " አለበለዚያ ደግሞ በራስ ምታት የሚሠቃየውን
ራሷን በሁለት እጆቿ መኻል ደፍታ ምንም ሳትመልስ ውስጥ ውስጧን እያረረ በሆዷ መቻል እንጂ ለባሏ ስለ ብሶቷ ገልጻለት አታውቅም።

አንድ ቀን በየካቲት ወር ውስጥ አሽከሮች አንድ ስሕተት ሠሩ " ኮርኒሊያ ቀጥታ ሳቤላን ሳይሆን አሽከሮችን ስትሳደብ ስትጮህ ቆየችና ዝም አለች ሁሉም ጸጥ አለ " መንፈሷ ተጨንቆ ተስፋ የቆረጠች መስላ ፍዝዝ ብላ ተቀምጣ የነበረችው ሳቤላ ለራሷ የምትናገር መስላ ሚስ ካርላይል ግን እየሰማቻት « አዬ ! ምነው አሁንስ ቶሎ በመሸ » አለች "

« ለምን ቶሎ እንዲመሽ ፈለግሽ ?» አለቻት"

« አርኪባልድ ወደ ቤቱ እንዲመጣ ብዬ»

ሚስ ካርላይል ደስ የማይል ጉርምርምታ አሰምታ «የደከመሽ ትመስያለሽ .ፈእመቤት ሳቤላ» አለቻት "

« በጣም ደክሞኛል»

« አያስደንቅም " እኔ እንዳንቺ ቀኑን ሙሉ ምንም ሳልሠራ ብውል ለሞት የሚያደርስ ድካም ይይዘኝ ነበር " ሳስበው በሕይወቴ የምቆይ አይመስለኝም " "

« የሚሠራ ነገር እኮ የለም » አለቻት ሳቤላ "

«መሥራት ለሚፈልጉ ምን ጊዜም የሚሠራ ነገር አይታጣም " ለምሳሌ ዝም ብለሽ ከመቀመጥ እነዚህን የገበታ መሐረቦች ስቀመቅም ልትሪጅኝ ትችይ ነበር » አለች ኮርኒሊያ ካርላይል "

« እኔ መሐረብ ልቀመቅም ? » አለች ሳቤላ በመገረም "
« ከዚህ የባሰ ትሠሪ ይሆናል . . እሜቴ » አለች ኮርኒሊያ ካፏ ነጠቅ አድርጋ
« እኔ የዚህ ዐይነት ሥራ አይገባኝም » አለች ሳቤላ ረጋ ብላ
« ሌላውም ቢሆን ካልሞከረው በቀር አይገባወም በበኩሌ እጆቼን አጣጥፌ ከመቀመጥ ጫማ ብሠፋና ባድስ ይሻለኛል " ጊዜ ማባከን ወንጀል ነው "
« ዛሬ እንኳን ጤንነት አልተሰማኝም » አለች ሳቤላ »
« አድካሚ ሥራ መሥራት አልችልም»

« እንደሱ ከሆነ ደግሞ እኔ ብሆን በሠረገላ ወጣ ብዬ አየር እቀበል ነበር ሙሉ ቀን ከቤት ውስጥ ሲጠማረሩ መዋል ለስንኩላንም አይበጃቸውም »

«ግን ባለፈው ሳምንት ፈረሶቹ በርግግው ስለ አስነገጡኝ አርኪባልድ ራሱ ካልነዳ በቀር እንድወጣ አይፈቅድልኝም »

« ጆንም ቢሆን ያንቺን ባል ያህል የመንዳት ልምድ አለው " ፈረሶቹ አንድ ቀን የበረገጉ እንደሆነ ሁለተኛ ይበረግጋሉ ማለት አይደለም በይ አሁንም ጆን
ሠረገላውን እንዲያቀርብልሽ ደውይ " የኔ ምክር ይኸው ነው»

ሳቤላ ራሷን ነቀነቀችና «አይሆንም! በዝጉ ሠረገላ ካልሆነ በቀር ያለሱ እንዳል
ወጣ አርኪባልድ ነግሮኛል " እሱ ስለኔ ብዙ ያስባል " ስለዚህ ፈረሶቹ ቢዶፈደነብሩ እንኳን እሱ አብሮኝ ካለ እንደማልደነግጥ ያውቃል»

« አሁንስ በጣም ሆዶ ባሻ እየሆንሽ ሔድሽ መሰለኝ » አለቻት ኮርኒሊያ "

«ለኔም እየመሰለኝ ነው » ብላ መለሰችላት ሳቤላ « ከወለድኩ በኋላ ደኅና እሆናለሁ እንዳሁን አይጨንቀኝም " ብዙ የሚሠራ ነገር ይኖረኛል »

« ለሌሎቻችንም ብዙ ሥራ ይተርፈናል ብዬ አስባለሁ» ብላ አጕረመረመች ቀና ብላ አዬች
«እንዴ ! ምን ሆኖ ይሆን ? አርኪባልድ መጣ በዚህ ሰዓት ምን
አግኝቶት ይመጣል ? »

« አርኪባልድ ! » አለችና ሳቤላም ሒዳ ጥምጥም አለችበት « አንተን ሳይ ፀሐይ የወጣች ነው የመሰለኝ ፍቅሬ ግን ለምን መጣህ ? »

« በሠረገላ ሽርሽር ልወስድሽ » አላት ደወሎን እየደወለ "

« ጧት አልነገርከኝም »

« ምክንያቱም ለመምጣት መቻሌን አላረጋገጥኩም ነበር . . .ፒተር ! የድንክ
ፈረሶቹን ሠረገላ አምጣልኝ " ፈጠን በል እሱን ነው የምጠብቀው »

« ለምንድነው ? ሠረገላውን ለምን ፈለግኸው ? » አለችው ሚስ ካርላይል ሳቤላ ልብሷን ለመቀየር ስትወጣ።

« ለሽርሽር ትንሽ ወጣ ብለን አየር ተቀብለን ለመምጣት »

« ሽርሽር ? »

« አዎን እስቲ ሳቤላን ተመልከቻት እንደዚህ ሁና እያየሁ አምኜ ያለኔ አላስወጣትም »

«እንደዚህ እየተሆነ ነው ሥራ የሚሠራ በቀን እኩሌታ ሥራ እየጣሎ መውጣት»
አለችው ኮርነሊያ "

« በአሁን ጊዜ ከሥራ የሳቤላ ጤንነት የበለጠ ያሳስባል“ ደግሞ ዲልና ሌሎቹ ጸሐፊዎቼ እኔን ተክተው መሥራት እንደሚችሉ ታውቂያለሽ»

« ጆን ካንተ የተሻለ ሠረገላውን ይነዳ የለ ? »
« እሱም ጥሩ ነጂ ነው" ቁም ነግሩ ግን የሱ መቻል ወይም አለመቻል አደለም» ሳቤላ ለባብሳ ጭንቀቷ ሁሉ ለቋት እየተፍለቀለቀች መጣች " ሚስተር
ካርይል ደግፎ ካሳፈራት በኋላ ' ራሱ እየነዳ ሲሔድ ሚስ ካርላይል ቆማ ፊቷን ጭፍግግ አድርጋ ቁማ ትመለከታቸው ጀመር።

ሳቤላን የማያስዶስታት ይኸን የመሳሰሉ ብዙ ሁኔታዎች ነበሩ ነገር ግን ከሚስተር ካርላይል ፊት ክፉ ተናግራት አታውቅም » እሱን ሁልጊዜ ብትወርፈውም የለመደው ነገር ነበር » ሳቤላ ግን ከዚያ ንዝንዝ ውስጥ ድርሻዋን የምትቀበል አይመስለውም ነበር "

ወሩ ሚያዝያ ሰዓቱ ማለዳ ነው " ጆይስ ከእመቤት ሳቤላ ካርላይል መልበሻ ውስጥ እጆቿን በጭንቀት እያፋተገች ዕንባዋን በጉንጮቿ እያወረደች ተቀምጣለች በጣም ፈርታ ነበር
የመታመምን ምንነት ደጋግማ ያየች ይሁን እንጂ እንደ ዛሬው የመሰለ ሕመም ግን አጋጥሟት አያውቅም " ጆይስ ተቀምጣ ትጨነቅበት ከነበረው ክፍል ቀጥሎ ሚስዝ ሳቤላ ካርላይል በሕይወትና በሞት መኻል ሆና
ትስቃያለች "

በመተላለፊያው በኩል የሚያስገባው በር ቀስ ብሎ ተከፈተና ሚስ ካርላይል ገባች " በሕይወቷ ዘመን እንደዚያ ተጠንቅቃ በቀስታ ተራምዳ ታውቃለች ለማለት አያስደፍርም » ተደራርቦ በተጠቀጠቀ መደረቢያ ራሷንና ጆሮዋን ሸፍናለች"
ኩምሽሽ ብላ አንድ ወንበር ላይ ተቀመጠች ጆይስ ቀና ብላ ስታያት ፊቷ ልክ ንጋት ጢስ መስሏል"

« ጆይስ » አለቻት በሹhሹhታ
«ያሠጋል? »

« ኧረ የለም ... እሜቴ አይመስለኝም : ማየቱ እንዲህ ከባድ የሆነ ለደረሰበትማ በጣም አስጨናቂ መሆን አለበት »

« እሱ መቸም የጋራችን እርግማን ነው ጆይስ " አንቺና እኔ ግን ከዚህ ዕጣ ጋር የሚያገናኘን መንገድ ባለ መምረጣችን ዕድለኞች ነን » አለችና ትንሽ ዝምአለች »
«አደራውን ከክፉ ይሰውራት እኔ እሷ እንድትሞት ልፈልግም»

ሚስ ካርላይል በጣም ተጨንቃ ቀስ ብላ ነበር የምትናገር ምናልባት ይች ወጣት አዪቷ የሞተች እንደሆነ ጸጸቱ የዕድሜ ልክ የሕሊና ሸክም ሆኖባት እንዳይቀር ፈርታ ይሆናል " እሷ ብትፈልግ ኖሮ አጭሩ የጋብቻ ዘመኗን የደስታና የእፎይታ ጊዜ ልታደርግላት ትችል እንደ ነበር ከባድና የማይወርድ ሸክም ሹክ ይላት እንደሆነ አይታወቅም : በጣም የፈራችና የተጨነቀች ትመስላለች "

« ጆይስ ... እንዲያው የሚያሠጋ ይመስልሻል ? »
«ለምንድነው ስለ ሥጋት የሚያስቡት? ሌሎች እንዴዚህ ታመው አያውቁም እንዴ”

« አይመስለኝም ... ጆይስ የሷ ለየት ያለ መሰለኝ " ለምንድነው
ዶክተር ማርቲን ቶሎ እንዲደርስ
ቴሌግራም ወደ ሊንበራ የተላከ ?»

ጆይስ ከው ብላ ደነገጠች
«ዶክተር ማርቲን ቶሎ እንዲደርስ ? ማን ላክ
«መቸ ተላከበት ? »

« እኔ የማውቀው መልእክት መተላለፉን ብቻ ነው " ሚስተር ዌይንራይት ከጌታሽ ዘንድ ገብቶ ከወጣ በኋላ ጆንን ወደ ዌስት ሊን የቴሌግራም ቢሮ ጋልቦ እንዲሔድ አዘዘው -ፈረሱ ሲጋልብ ኮቴው እንደዚያ ሲጮህ ጆሮህ የት ነበር ? . .

ሲጋልብ ሰምቸ ለምን እንደሆነ ገባኝ " ስለዚህ ፍራት ፍራት አለኝ ሚስተር ካርላይል ዘንድ ሔጄ ብጠይቀው ደግሞ እሱ ምንም እንደማያውቅ ነገረኝና በሩን እፊቴ
ዘጋብኝ "
👍18
ጆይስ ምንም አልመለሰችላትም " ከመደንገጧ የተነሣ ሰውነቷ ዛለ » ከሚቀጥለው ክፍል ዐልፎ ዐልፎ ይሰማ ከነበረው ድምፅ በቀር ሁሎም ነገር ጸጥ ብሏል“
ሚስ ካርላይል ከተቀመጠችበት ተነሣች " ደኅና አድርጐ ላስተዋላት የምትንቀጠቀጥ ትመስል ነበር "

« እኔ ይህን ሥቃይ መስማት አይሆንልኝም " ጭንቅ ጭንቅ ይለኛል ስለዚህ መሔዴ ነው
ጆይስ ቡና ወይም ሌላ ነገር ቢፈልጉ ጠይቂኝ እልካለሁ »
ብላ ወጣች "

« እሺ እጠይቃለሁ » አለች ጆይስ የሠራ አካላቷ እየተንቀጠቀጠ "

« ሊገቡ ነው እንዴ ...እሜቴ ?» አለቻት ጆይስ በአግሯ ጣት እየተራመዶች በቀስታ ወደ ውስጠኛው በር ስታመራ አየቻትና ሳቤላም የታየቻት እንደሆነ ደስ
እንደማይላት ገመተች

« እኔን ግን በክፍሉ ሌላ ሰው አያስፈልግም ብለው አስወጡኝ » አለቻት "

«ኧረ እኔ አልገባም ገብቶ የማይረዳ ሰው ከነጭራሹ ባይገባ ይሻላል እኔም የምረዳው ነገር የለም » አለች ኮርነሊያ

« ሚስተር ዌይንራይትም ሲያስወጡኝ ይኸንኑ ነው የነገሩኝ» አለች ጆይስ
ኮርነሊያ ወደ ኮሪደሩ አለፈችና ወጥታ ሔደች "

ጆይስ ተቀመጠች " ጊዜው ማብቂ ያለው አልመስላትም አለ " ትንሽ ቆይቶ ዶክተር ማርቲን ሲገባ ሰማችው " ከዚያ ሚስተር ዌይንራይት ጆይስ ወደ ነበረችበት ክፍል መጣ " ገና ስታየው ምላሷ ከትናጋዋ ተጣጋና · « የሚያሠጋ ይመስልሃል?” የሚለውን ሐረግ ከመተንፈሷ በፊት አልፏት ሔደ"

ሚስተር ዌይንራይት ሚስተር ካርላይልን አገኘዋለሁ ብሎ ወዳሰበቀት ክፍል ገባ " ሚስተር ካርላይል ከዚያ ክፍል ሌሊቱን ሙሎ ሲንጎራደድበት አድሮ ነበር "
ሐኪሙ ሲገባ የገረጣው ፊቱ ቀላ

« ዌይንራይት ... ዶክተር ማርቲን ከገባ ኻያ ደቂቃ ሆነ " ምን ይላል ? »

« እኔ ከተናገርኩት የተለየ ነገር አላገኘም " ምልክቶቹ በጣም አሳሳቢ ናቸው !ቢሆንም ምንም እንደማትሆን ተስፋ አለው » ግን በትዕግሥት ከመጠበቅ በቀር
የሚደረግ ነገር የለም " አሁን እንኳን የመጣሁት ሚስተር ካርላይል ... ቄስ ሊትልን ብታስጠራቸው ብዬ ነው :

ቄስ ሊትል የቤተ ክርስቲያኑ አለቃ ናቸው ሚስተር ካርላይል ቄስ የሚያስጠራ ምን ነገር ተገኘ ብሎ በድንጋጤ ጮኸ "

« እንዴ ለሚስትህ አይደለምኮ » አለ ሐኪም ዌይንራይት ፈጠን ብሎ «ለሚወለደው ሕፃን ነው " ምናልባት በሕይወት ካልቆየ ላንተም ለሚስዝ ካርላይልም
መጠመቁን ስታውቁ ደስ ይላችኋል »

« አይ ደኅና ተባረክ እሺ ይላክበታል » አለው ሚስተር ካርይል "

« አንተ በቃ የቄስ ነገር ሲነሣ የሚስትህ ነፍስ የበረረች መሰለና ደነገጥህ ? ኧረ ፈጣሪ አደራውን ይህ ባያድግ እንኳን ሌሎች ልጆች እንድትተካልህ ዕድሜ ይስጥልህ»

« እስቲ እግዚአብሔር ይስማህ»

ጊዜው ዕኩለ ቀን ነበር » ቄስ ሊትል ሚስተር ካርይልና ሚስ ካርላይል አንድ ትልቅ ባለጌጥ የሸክላ ገበታ መጥመቂያ ውሃ እንደያዘ ከመኻሉ ከተቀመጠበት
ጠረጴዛ ዙሪያ ከበው እንደ ቆሙ ጆይስ አንድ የተጠቀለለ ጨርቅ መሳይ ይዛ ቀረበች "ሚስተር ካርላይል ለሚስቱ ከነበረው ጭንቀት ጋር ሲነጻጸር ለዚህ ጥቅል ጨርቅ አምብዛም አልተጨነቀበትም

« ጆይስ . . እስካሁን ሁሉ ነገር ደህና ነው ? » አለ ሚስተር ካርላይል ሥርዓተ ጸሎቱ ተጀመረ « ይመስለኛል..ጌታዬ » ካህኑ ሕፃኑን ትቀበለ » « ስሙን ማን ትሉታላችሁ ? »

ሚስተር ካርላይል ስለ ስሙ እምብዛም አላሰበበትም ነበር ቢሆንም ምንም ሳያመነታ
«ዊልያም » ብሎ መለሰ

ምክንያቱም ይሀ ስም ሳቤላ የምትወደውና የምታከብረው መሆኑን ያውቅ ነበር።

ካህኑ ጣቶቹን ከውሃው ነከረ ጆይስ ነገሩ ግራ ገብቷት ወደ ጌታዋ እየተመለከተች « ኧረ ሴት ነች እኔ እኮ ቅድም ተናግሬ ነበር » አለችው

ሁሉም ጥቂት ዝም አሉ » ከዚያ
ለልጅቱ ስም አውጣላት » አለ ቄሱ

« ሳቤላ ሉሲ » አለ ሚስተር ካርይል ኮርነሊያ ሥያሜው አስከፋትና አፍንጫዋን ነፋች " ምናልባት በሷ ስም ብትጠራላት ፈልጋ ኖራ ይሆናል " እሱ ግን
አንድ ጊዜ በሚስቱና በናቱ ስም ሠይሞ አበቃ።

ሚስተር ካርላይል ለማየት እስከ ማታ ሳይፈቀድለት ዋለ አሁን ገብቶ ሲያያት ዐይኖቹ አንጸባረቁ " እሷም ስሜቱን ተረዳችና ከትንሽ ፈገግታ በኋላ ከንፈሯን ገርበብ አደረጀቻቸው "

« ጭንቄን መቻል አቃተኝ መሰለኝ... አርኪባልድ ? ቢሆንም በማለፉ አምላካችንን ማመስገን ይገባናል " የሥቃይን መጠን በራስ ደርሶ ካልቀመሱት በቀር
ማንም ሊያውቀው አለመቻሉም ትልቅ መታደል ነው»

« እኔ ደግሞ ማወቅ የሚችሉ ይመስለኛል » አለ ሚስተር ካርላይል "
« እኔ የምስጋናን ምንነት እስከ ዛሬ ቀን ድረስ አላውቀውም ነበር »

« በሕፃኒቱ መትረፍ ነው ? » አለችው ሳቤላ "

« ባንቺ መትረፍ አንጂ . . . ሳቤላ ' ለኔ ተረፍሽልኝ · ዳንሽልኝ እስከ ዛሬ እውነተኛ ጸሎት በጭንቅ የተያዘ ልብ የሚያደርገው ጸሎት አይገባኝም ነበር "

« ሕፃኗን ለምን በኔ ስም ሠየምካት ? »

« ከዚህ ያማረ ስም መስጠት እችል ይመስልሻል ? አልችልም »

« ምነው ወንበር አስመጥተህ ባጠገቤ ብትቀመጥ ? »

ሳቅ አለና ራሱን ግራ ቀኝ ነቀነቀ » « ቢቻለኝ ኖሮ ደስ ይለኝ ነበር ነገር ግን ሐኪሞቹ ካንቺ ጋር እንድቆይ የፈቀዱልኝ ለአራት ደቂቃ ብቻ ነው " ዌይንራይት
ሰዓቱን እያየ ከመዝጊያው ጥግ ቁሞ እየጠበቀኝ ነው "

እውነትም የሁለቱ ጭውውት ከመጀመሩ ሰዓቱ ደረሰ "...

💫ይቀጥላል💫
👍34👎1
#ሰቆቃው_ይሁዳ

እጣ ያልደገፈኝ ፤ አለም ያላፅናናኝ
ከሰው ሁሉ በላይ ፣ መውደቅ የሚቀናኝ
እድለ ጠማማ ፣ መሆኔን ያወኩት
ሰዎች የካዱት ለት ፣ እኔ ስሜን ሸጥኩት።

🔘ሄኖክ🔘
👍418😢8🤔2
ሰውን በመፍጠሩ እግዜር የሚጠቀመው
ሰውም በመፈጠር ከእግዜር የሚያገኘው
አንዳች እውነት ባይኖር አንዳች ድብቅ ነገር
ምድሪቱን ለመሙላት ከብት ይበቃ ነበር።

🔘ኤፍሬም ስዩም🔘
👍4427👏26🥰4🔥3🤔3
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


...የምስጋና ቀንና ገና እንደቀረበ ሊያስታውሰን ህያው የቀን መቁጠሪያችን የሆነው የረጅሙ አትክልት አገዳ ትንሽ እምቡጥ ያዘ፡ ያልደረቀው ብቸኛ አትክልታችን እሱ ብቻ ስለነበር በጣም የምንወደው ንብረታችን ነበር᎓ ጣሪያው ስር ካለው ክፍል አንስተን አንድ ሞቃት ምሽት ከእኛ ጋር እንዲያሳልፍ ወደ መኝታ ክፍላችን ወሰድነው: በየማለዳው ገና ሲነጋ ኮሪ ያቺ እምቡጥ ምሽቱን በደህና ማሳለፏን ለማረጋገጥ ሮጦ ሄዶ ይመለከታታል ኬሪም ተከትላው ሄዳ አጠገቡ ትቆምና ሌሎች ሲደርቁ ብቻዋን በመቆየቷ ያቺን ድል አድራጊ ጠንካራ ተክል ታደንቃለች አፈሩ ውሀ የሚፈልግ መሆኑ መንትዮቹ ቢሰማቸውም፣
ግድግዳው ላይ የተሰቀለውን ቀን መቁጠሪያ እየተመለከቱ ቀኑ አረንጓዴ ተሰምሮበት፣ አትክልቱ ውሀ የሚፈልግበትን ቀን እንዲያመለክት ይጠብቃሉ።
ያ ስለማይሆንና በራሳቸው ለማድረግም እርግጠኛ ስለማይሆኑ ወደ እኔ ይመጡና “አትክልቱን ውሀ እናጠጣው? ውሀ የጠማው፦ ይመስልሻል?” ሲሉ ይጠይቁኛል።

ስም የምንሰጠውና የኛ የምንለው ግዑዝም ሆነ ህያው ነገር የለንም
አትክልታችን ብቻ ከኛ ጋር ለመኖር ቆርጧል ኬሪም ሆነች ኮሪ ከባዱን ማሰሮ ይዘው በቅርብ የፀሀይ ብርሃን ወደሚኖርበት ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ለመውሰድ ጥንካሬ አልነበራቸውም፡ ስለዚህ እኔ አትክልቱን እንድይዘው ተፈቀደልኝ ሲመሽ ደግሞ ክሪስ ወደታች ይመልሰዋል በእያንዳንዱ ምሽት ተራ በተራ ቀኖቹን በቀይ ቀለም ምልክት እናደርጋለን፡ እስካሁን መቶ ቀኖች
ላይ ምልክት አድርገናል።

ክረምቱ በመግባቱ ዝናብ መጣ፡፡ ሀይለኛ ንፋስ እየነፈሰ ነው፤ አንዳንድ ጊዜ ከባድ ጭጋግ የጠዋቷን የፀሀይ ብርሀን ይከልላታል ምሽት ላይ ደግሞ
ነፋሱ የደረቁትን የዛፍ ቅርንጫፎችን ከቤቱ ጋር ሲያስታክካቸው ከእንቅልፌ
ያባንነኝና የሆነ አስፈሪ ነገር መጥቶ የሚበላኝ እየመሰለኝ ትንፋሽ ያጥረኛል በኋላ ላይ ወደ በረዶ ሊለወጥ የሚችል ዝናብ እየወረደ ባለበት ቀን እናታችን
ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ እያለ የምስጋና ቀን በዓል እንዲመስልልን ጠረጴዛችንን
የምናስጌጥባቸው የሚያማምሩ የግብዣ ጌጣጌጦች ይዛ ወደ መኝታ ክፍላችን ገባች በተጨማሪም ብሩህ ቢጫ ቀለም ያለው የጠረጴዛ ልብስና ጥልፍ
ያለበት ብርቱካናማ የአፍ መጥረጊያ መሀረቦች ይዛ ነበር።

የያዘችውን ዕቃ በሩ አጠገብ ያለው አልጋ ላይ እያስቀመጠችና ለመውጣት ፊቷን እያዞረች: “ነገ እራት ላይ እንግዶች አሉብን” ስትል አብራራች: “እና አንደኛው ለእኛ ሌላኛው ደግሞ ለሰራተኞቹ የሚሆን ሁለት ዶሮዎች
ይጠበሳሉ፡ ነገር ግን አያታችሁ የሽርሽር ቅርጫት ይዛ በምትመጣበት ወቅት አይደለም ግን አትጨነቁ፣ ልጆቼ በምስጋና ቀን ለቀኑ የሚመጥን ምግብ
ሳይኖራቸው በዓልን አያሳልፉም እንደምንም ብዬ እኛ ከምንበላው ምግብዐለእናንተ የማመጣበትን መንገድ እፈልጋለሁ ለአባቴ ራሴ እንዳቀርብለት እፈልጋለሁ ብዬ ብዙ አዘጋጅና ለእሱ የማቀርበውን ሳሰናዳ በሌላ ትሪ ደግሞ
ለእናንተ ላስቀምጥላችሁ እችላለሁ ነገ ሰባት ሰዓት አካባቢ ጠብቁኝ” አለች።

በትልቅ ሳህን የሚቀርብ ትኩስ የምስጋና ቀን ምግብ ለመብላት በመጠበቅ ደስታ ውስጥ ጥላን ልክ በበሩ በኩል እንደሚገባው ነፋስ ገብታ ወጣች።

“የምስጋና ቀን ምንድነው? አለች ኬሪ።

“ከምግብ በፊት ከማመስገን ጋር አንድ ነው” ሲል ኮሪ መለሰላት በአንድ በኩል ልክ ነው ብዬ አስባለሁ።

ሰባት ሰዓት መጣ፣ ሄደ። ኬሪ ጮክ ብላ አጉረመረመች “አሁን ምሳችንን እንብላ፣ ካቲ!”

“ታገሺ እናታችን ልዩ ትኩስ ምግብ፣ ዶሮና ማባያዎቹ ሁሉ ያሉበት ትሪ ይዛ ትመጣለች ይኼኛው ለእራታችን ነው ምሳ አይደለም” አልኳት: የእኔ የቤት እመቤትነት ስራ ለጊዜው አለቀና በደስታ አልጋው ላይ ጥቅልል ብዬ
ማንበብ ጀመርኩ።

ካቲ ሆዴ ትዕግስት የለውም” አለ ኮሪ፤ ክሪስ በሸርሎክ ሆልምስ ታሪክ ተመስጧል፡ መንትዮቹ ሆዳቸውን ፀጥ እንዲል አድርገው እንደ እኔና እንደ ክሪስ ቢያነቡ ጥሩ አልነበር?

“የተወሰኑ ዘቢቦች ብላ ኮሪ”

“ምንም የተረፈ የለም”

“ለውዝ ብላ”

“ለውዙም ሁሉም አልቋል”

“እሺ ብስኩት ብላ”

“የመጨረሻውን ብስኩት ኬሪ በልታዋለች”

“ኬሪ ብስኩቶቹን ለምን ለወንድምሽ አላካፈልሽውም?”

“የዚያን ጊዜ አልፈልግም ብሎኝ ነው”

ስምንት ሰዓት ሆነ አሁን ሁላችንም እርቦናል። ሁልጊዜም ልክ ስድስት
ሰዓት ላይ ነው የምንበላው፡ እናታችንን ምን አዘገያት? በመጀመሪያ ራሷ ልትበላና ከዚያ ልታመጣልን ነው? ግን'ኮ እንደዚያ አላለችንም ነበር።

ዘጠኝ ሰዓት አለፍ እንዳለ እናታችን በችኮላ ገባች ከላይ በሳህኖች የተሸፈነ ትልቅ ብራማ ቀለም ያለው ትሪ ይዛለች። ሰማያዊ የሱፍ ቀሚስ ለብሳለች። ፀጉሯ ደግሞ ከፊቷ ላይ ተሰብስቦ ኮሌታዋ አካባቢ ዝቅ ብሎ በፀጉር መያዣ
ተይዟል፡ እንዴት ታምራለች! “እንደራባችሁ አውቄያለሁ።" ወዲያውኑ ይቅርታ መጠየቅ ጀመረች: “በመጨረሻዋ ደቂቃ ላይ አባቴ ሀሳቡን ቀይሮ
ተሽከርካሪ ወንበሩን በመጠቀም ከእኛ ጋር ለመብላት ወሰነ።” በመጠኑ ፈገግ አለችልን። “ካቲ ጠረጴዛውን ቆንጆ አድርገሽ አዘጋጅተሽዋል። ሁሉንም ነገር
በትክክል ነው ያደረግሽው: እኔ ግን አበቦቹን ስለረሳሁ ይቅርታ: መርሳት አልነበረብኝም: ዘጠኝ እንግዶች ነበሩብኝ ሁሉም እያዋሩኝና ለብዙ ጊዜ የት
እንደነበርኩ ሺ ጥያቄዎችን እየጠየቁኝ ነበር እና ጆኒ ሳያየኝ የአስተናጋጆቹ ጓዳ ውስጥ መግባት እንዴት ችግር እንደሆነ አታውቁም ያ ሰው ከኋላው
ሳይቀር አይን ያለው ነው የሚመስለው ማንም ሰው እንደኔ ከምግብ ላይ አስር ጊዜ ቁጭ ብድግ ሲል አይታችሁ አታውቁም

“እንግዶቹ ጨዋ እንዳልሆንኩ፣ ወይም ሞኝ እንደሆንኩ ሳያስቡ አይቀርም ግን ያም ሆኖ ሳህኖቻችሁን መሙላትና መደበቅ ችዬ ነበር ከዚያ ወደ መመገቢያው ጠረጴዛ መመለስ፣ ፈገግ ማለትና ሌላ ክፍል ገብቼ አፍንጫዬን
ከማፅዳቴ በፊት ደግሞ አንዴ መጉረስ ነበረብኝ፡፡ መኝታ ክፍሌ ውስጥ ባለው የግል መስመር የተደወሉልኝን ስልኮች መመለስና ማንም እንዳይገምት ድምፄን
መቀነስ ሁሉ ነበረብኝ የዱባ ኬክ ላመጣላችሁ ፈልጌ፣ ጆን ቆራርጦ ሳህኖች ላይ አድርጓቸው ነበር። ምን ማድረግ እችላለሁ? አራት ኬኮች ቢጠፉበት ማወቁ አይቀርም:"በአየር ላይ ሳመችን ደስ የሚል ግን የችኮላ ፈገግታ ሰጠችንና ከበሩ ወጥታ ተሰወረች: አምላኬ ሆይ! እውነትም ህይወቷን አወሳስበንባታል! ለመብላት ወደ ጠረጴዛው ተጣደፍን፡ ክሪስ አንገቱን ዝቅ አድርጎ ጆሮዎች ልብ የሚነካ ምስጋና በሚሰሙበት በዚህ ቀን እግዚአብሔርን ብዙም የማያስደስት የችኮላ ምስጋና አቀረበ፡ “ጌታ ሆይ፣ ስለዚህ ስለዘገየ የምስጋና ቀን ምግብ
እናመሰግንሀለን፡፡ አሜን!”

በክሪስ ቀጥታ ወደ ጉዳዩ የመግባት ባህርይ እየሳቅኩ፣ አስተናጋጃችን እርሱ በመሆኑ ሳህን አቀበልኩትና አንድ በአንድ ምግባችንን ሳህኖቻችን ላይ አደረገልን ምግቦቹ እየቀዘቀዙ ነበር: “ቀዝቃዛ ምግብ አንወድም!” አለች ኬሪ ሳህኗ ላይ የተደረጉላትን ምግብ እየተመለከተች።

የእውነቴን ለእናቴ አዘንኩላት ለእኛ ትኩስ ምግብ ለማምጣት ስትሞክር የራሷን ምግብ በስርዓት ሳትበላ በእንግዶቹ ፊት እንደሞኝ ተቆጥራ፣ አሁን ደግሞ እነዚህ ሁለቱ ሶስት ሰዓት ሙሉ ራበን እያሉ ሲነጫነጩ እንዳልቆዩ
ስለቀዘቀዘ አንበላም ይላሉ… አይ ልጆች!

ክሪስ በየጠዋቱ በሽርሽር ቅርጫት መጥቶ ከሚወረወርልን የችኮላ ምግብ በተለየ በሚጥም ሁኔታ የተሰራውን ምግብ በመብላት በደስታ አይኖቹን ጨፈነ። እውነት ለመናገር አያታችን አንድም ቀን ረስታን አታውቅም።
👍316🥰1