አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
479 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እንትንሽ #እንዴት #ነው😳

እንትንሽ እንዴት ነው?እዩኝ እዩኝ የሚለው
ሲየዩት ግን የሚያመው
መጠን ያላገኘው የሚፎካከረው
እንዴት ነው እንትንሽ ማለቴ አይኖችሽ
አሁንም ያያሉ እንደ ጥንቱ ናቸው
እንደ ጥንቱ ናቸው ቀልብን ይገዛሉ
ከንፈርሽስ ውዴ ሳሙኝ ሳሙኝ የሚለው
ስስመው የሚጣፍት ጣፋጩ የማያልቀው
ዛሪም ለስላሳ ነው ወይስ ፀሀይ አ ደረቀው
አረ በፈጣሪ እንትንሽ እንዴት ነው
እንዴት ነው እንትሽ ማለቴ ጥርሶችሽ
እንደድሮ ያምራል
ስትስቂ ያየሽ ሰው በፍቅር ይወድቃል
ፀጉርሽ እንዴት ነው ሀረግ የሚያስንቀው
አሁን አጥሮብሻል ወይ ስ እረጅም ነው
አረ ተናገሪ እንትንሽ እንዴት ነው
አፍንጫሽስ ውዴ ዛሪም እንደ አክሱም ነው
ጎብኝው በጣም በዛ ወይስ አናሳ ነው
አንገትሽስ እንዴት ነው ቀጥኖ የረዘመው
ምን ይሆን ምክንያቱ እንዲ ያሳመረው
ጡትሽ ግን እንዴት ነው ተወጥሮ የቆመው
ወይስ አስተኛሽው እንቅልፍ አሸለበው
ወገብሽ እንዴት ነው ሞዴል የሚያ ስብልሽ
መጠን ተገኘለት ይሚፎካከረው
ውይ እረስ ቼው እንዴት ነው እንትንሽ
ሀገር ጉድ የሚያ ስብለው ያኛው ትልቅ ዳሌሽ
ሁሉም ደና ናቸው
ከቶ አልተቀየሩም ምንም አልነካቸው
ምንድን ነው ያልጠቀሰው
ምንድን ነው ያልዘረዘረው
አልቃሻው ብእሬ
እስቲ ተናገሪ ስሞትልሽ ፍቅሬ
ብቻ ያልገለ ፅኳት አልች አንድ ነገር
ላወጣት አልቻልኩም አቃተኝ መናገር
እንትን እንትን ብዬ ከዘረዘርኳቸው
ያልጠቀስኩት አለ ሁሉን የሚበልጣቸው
በቃ ልናገረው እስቲ ልተንፍሰው
ምን አጨናነቀኝ ቃሉ ሶስት ፊደል ነው
.
.
.
.
.
.
#ፍቅር ነው ፊደሉ #ፍቅር ነው ቃላቱ
#ፍቅር ነው የሱ ስም ጤነኛ የሚያሳብድ
እብዶችን የሚያክም
#ፍቅር ነው ፊደሉ #ፍቅር ነው የሱ ስም
ሌላ ምንም አይደል #ፍቅር ማለት እንትን
እንትን ማለት #ፍቅር ምንም ነገር የለም እሱን የሚፎካከር እናልሽ አለሜ
እናልሽ አለሜ እንትንሽ ደህና ይሁን
ደህና ሁኚ ፍቅሬ
ደህና ሁኚ
ደህና ሁኚ

በጆጆ አሌክስ
👍2
#እንዴት_ነህ_አቦወለድ
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ከቶ እንደምን አለህ
ኑሮ እንዴት ይዞሃል
አሁንም ልጅ ነህ ወይ
ወይስ ጎርምስሃል
መጎርመሱንማ ጎርምሰን ነበረ
የቀመስነው ሁሉ ኮምጣጤ ሆኖብን ከሬት የመረረ
እንዳንተ ሚጣፍጥ የልጅነት ጊዜ ናፍቆን እንደቀረ
ቀልድ ሁሉ ጠፍቶብን የፊታችን ጅማት በመናደድ ብዛት እንደተገተረ
መጎርመሱንማ ጎርምሰን ነበረ
....እንዴት ነህ አቦ'ለድ .......!
የልደታችን ቀን
ከሻማችን ጀርባ
ከእስታር ብጥብጥ ጣገብ ከፈንዲሻው በላይ የምትቀመጠው
ሁለት ብር ለሌለን
እሽግህን ፈጠህ በችርቻሮ ዋጋ በስሙኒ ሂሳብ ሱቅ የምትሸጠው
ጠጠር ከረሜላን
ጋሌጣ ብስኩትን
የፉትቦል ማስቲካን በዋጋ ምትበልጠው
እንዴት ነህ አቡወለድ እንዴት ነህ ሳቂታው
የኛን አትጠይቀኝ የኛ እዳ ገብስ ነው
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
አቡወለድ
በኢቶጲስ ዘመን ልጆች የማይታወቅ የማይወደድ
👍2
#እንዴት_ይሄን_አታውቂም!?

የሰው ልጅ ታሪክ ሲመረመር
እኩይና ጥሩ ሰው ነበር፡፡
እኩዮች አፈር ለብሰዋል
ጥሩዎች ሞት ድል ነስተዋል::
እንዴት ይሄን አታውቂም!?

በቅርቡ እንኳን በቅርቡ - የታየ የተነገረ
በጎረቤታችን ምድር የሰው ደም ጎርፎ ነበረ፡፡
ወንድም በወንድሙ ላይ - ስለምን ሞት አነገሰ?
ለምን የንፁሃን ደም - በየጎዳናው ፈሰሰ?
እንዴት ይሄን አታውቂም!?

የባቢሎን ስልጣኔ - ባለመግባባት ፈራርሷል
ኢያሪኮን የመሰለ ግንብ - በጩኸት ተደረማምሷል
ብቻውን የቆመ አንበሳ - በጅቦች መንጋ ተበልቷል
የተባበሩ ጉንዳኖች - የመሬትን ሆድ ቀደዋል፡፡
እንዴት ይሄን አታውቂም!?

ቂም በቀል ያረገዘች ልብ - ሰላምን ልታቅፍ አትችልም
ሰላምን ያላገኜች ነብስ - ፍቅርን አታስተምርም:
ፍቅር የራቃት ህይወት - የምትሰራው ቤት ጥላቻ
በጥላቻ የተሞላች ቤት - አማራጫ መፍረስ ብቻ::
እንዴት ይሄን አታውቂም!?

እንዴት ይሄን አታውቂም!?
ካወቅሽስ ምነው ችላ አልሽው?
ማፍረሱን ነው የናፈቅሽው?
መፍረሱን ነው የፈለግሽው?
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
እ.ን.ዴ.ት ይ.ዴ.ን ኢታ.ው.ቂ.ም!?
እንዴት!!???

🔘በሙሉቀን🔘
#እንዴት?

የአለሜን ስፋት
የህልሜን ፍቺ ወሰን
የብርሀኔን ልክ
አንቺን በልቤ የዤ፤
ከጎጆዬ
ከሰማዬ . . .ጣራ፣
የብቸኝነት
ግት
በበረዶ እንገሩ ያቀዘቅዘኛል?
ለእምነቱ የቀረበ
ለእውነቱ የቆረበ
ሞጋች
ወትዋች . . . ልቤ
ስለ ፍቅርሽ ሲሆን፣ እሽሩሩ ይለኛል?

የትኛው ነው እውነት?
የትኛው ነው እምነት?
ከባዶው ሶፋ ላይ ያንቀላፋች ድመት!
የቀረበው ስኒ፣ ቡና ያልተቀዳበት!
የካፌው በረንዳ፣ አንቺ የሌለሽበት!
የማለዳው ጸሀይ፣ አንቺ ያልደመቅሽበት!
. . . . . . . ............የማየው የሚያየኝ?
ወይስ . . .
ትዝታሽ
ጠረንሽ
የሽንቁሬ ውታፍ፣ አሳጥሮ ያሰረኝ?
.........................አትዋጋ ሚለኝ?

ዳሩ በዚህ ቅዠት፣
ዳሩ በዚህ መንፈስ፣
ጨርቁን በጣለ አለም፤
ቋሚ ስፍር የለም
ገፍፈው የሚጥሉት፣
ስልባቦት ነው እምነት፤
ብጣሪ ነው እውነት፡፡

🔘በድሉ ዋቅጅራ)🔘
👍121