አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ማሪየስ ካደገ በኋላም እንደ ልጅነቱ ቤተክርስቲያን መሄዱን
አላቋረጠም:: በልጅነቱ ከአክስቱና ከአያቱ ጋር ዘወትር ነበር የሚሄዱት፡፡
የሚሄዱት ደግሞ ቀደም ሲል ከተነጋገርንበት ከደግናል ጸሎት ቤት ነበር፡፡

አንድን ቀን እሑድ እንደለመደው ቤተክርስቲያን ሄዶ ከጀርባው
«መሴይ ማብዩፍ ቸርች ዎርደን» ተብሎ ከተጻፈበትና በወይን ጠጅ ቀለም ከተለበደ ወንበር ላይ ይቀመጣል፡፡ ጥቂት እንደቆየ አንድ ሽማግሌ ይመጠና
«ወንድም ይቅርታ፧ ይህ ቦታ ለእኔ የተመደበ ነው» ይሉታል፡፡ ማሪየስ
በአሳብ ጭልጥ ብሎ ሄዶ ነበር፡፡ ከአሳቡ ሲነቃ ማሪየስ ወንበሩን ለሽማግሌው ይለቅላቸውና ሽማግሌው ይቀመጣሉ፡፡

ቅዳሴ ካለቀ በኋላ እንኳን ማሪየስ ከሐሳቡ አልወጣም፡፡ ለሽማግሌው ወንበሩን ይልቀቅላቸው እንጂ ከሥፍራው ርቆ አልሄደም:: ሽማግሌው
የማሪየስ ከሐሳብ ባህር መዘፈቅ አይተው ከቅዳሴ በኋላ አናገሩት፡፡
«ይቅርታህን ልጄ፧ ቅድም አስቀየምኩህ መሰለኝ:: ምናልባት ምን ዓይነት ደፋር ሰው ነው' ብለህ ታዝበኸኝ እንደሆነ ላስረዳህ፡፡»

«ጌታዬ» አለ ማሪየስ፤ «ምንም አያስፈልግም፡፡»

«የለም» ሲሉ ሽማግሌው ቀጠሉ፤ «ተቀይመኸኝ እንድትሄድ
አልፈልግም፡፡ ስለዚያች ቦታ ብዙ የማስታውሰው ነገር ኣለኝ:: ለዚህች ቦታ የተለየ ስሜት አለኝ፡፡ እንደዚያ ያልኩትም ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ታሪኩን ላጫውትህ፡፡

«አንድ ብርቱ፡ ሰው ነበረ፡፡ ይህ ሰው እጅግ በጣም የሚወደው ልጅ ነበረው:: ሰውዬው በኣንድ ውርስ ምክንያት ከልጁ ጋር ይለያያል፡፡ ከተለያየም
በኋላ ልጁን ተመልሶ እንዳያይ ይደረጋል፡፡ አባት ልጁን ይወድ ስለነበር በየሁለት ወይም ሦስት ወር ከዚህች ሥፍራ እየመጣ ካስነሳሁህ ቦታ አጠገብ ካለው ምሰሶ ተደብቆ ልጁን አይቶ ይሄዳል:: አሥር ዓመት ሙሉ
ሌላ ሥራ ሳይኖረው ከዚህ እየመጣ ልጁን አይቶና እንባውን አፍስሶ ይሄዳል፡፡ ልጁ አባቱን ስለማያውቅ የሰውዬው መመላለስ ልብም አይልም::
ከሰውዬው ጋር ከጊዜ በኋላ ተዋውቀን ነው ታሪኩን ያጫወተኝ፡፡ ሰውየው
አንድ ሀብታም አማች ነበረው:: አባት ልጁን መጥቶ ቢያይ የአያቱንና የአክስቱን ሀብት ሊወርስ አይችልም ብሎ ማን እንዳስፈራራው ትዝ አይለኝም:: ብቻ አባት ልጁ አንድ ቀን ያንን ሀብት ወርሶ ደስ ብሎት
ይኖራል በሚል እምነት የራሱን ደስታና ፍቅር መስዋዕት አደረገ፡፡ የልጁ አባትና አያት ደግሞ በዘመነ ባለው የፖለቲካ ሽኩቻ የተነሣ
እንደማይስማሙም አጫውቶኛል፡፡ ስለፖለቲካ ጉዳይ መወያየቱ መልካም ነው:: ግን አንዳንድ ሰዎች የፖለቲካ ወሬ ከጀመሩ ማባሪያ የላቸውም::
ከዚህም በላይ የአንዱን ወገን ይዘው ጭልጥ ብለው ወደ አንድ አቅጣጫ ይሄዳሉ፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው አንዱን ወገን ተከትሎ ዋተርሉ ላይ ስለተዋጋ ብቻ መጥፎ ሰው ነው ለማለት ያዳግታል:: አባትንና ልጅን በዚህ የተነሣ ማለያየት ደግሞ ተገቢ አይሆንም:: አሁን የምልህ ሰው ከቦናፓርቴ ጦር ውስጥ ኩለኔል ነበር፡፡ ዛሬ እንኳን ሰውዬው የሞተ ይመስለኛል፤ ቬርኖን
ከተባለ ከተማ ይኖር ነበር፡፡ ወንድሜ ቄስ ሲሆን የሚኖረው ከዚያ ከተማ ውስጥ ነው:: የሰውዬው ስም ፓንትመርሲ ይባላል፡፡»

ልጁ «ፓንትመርሲ!» ብሎ ስሙን ደግሞ ከተናገረ በኋላ ፊቱ
ኃይል ይለዋወጣል፡፡

«አዎን ፓንትመርሲ፧»

ታውቀዋለህ?»

«አባቴን» አለ ማሪየስ፧ «የሚሉት ሰው አባቴ ነበር፡፡»

ሽማግሌው እጁን በእጁ መታ:: «ያ ልጅ ማለት አንተ ነህ! ልክ
ነው፤ ልጁ የአንተን እድሜ ሊይዝ ይችላል:: እንግዲያውስ ልጁን በጣም የሚወድ አባት ነበረኝ ብለህ ልትኩራራ ይገባሃል፡፡»

ሽማግሌውና ማሪየስ ብዙ ተጫወቱ:: በመጨረሻ እጅ ለእጅ
ተያይዘው ወደ ሽማግሌው ቤት ሄዱ፡፡ በሚቀጥለው ቀን ማሪየስ አያቱን ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡

«ከጥቂት ጓደኞቼ ጋር አደን ለመሄድ ተነጋግረን ነበር፡፡ ለሦስት
ቀን ከእነርሱ ጋር ብሄድ ትፈቅድልኛለህ? »

«ለአራት ቀንም መሄድ ትችላለህ፡፡ ሂድና ራስህን አስደስት» አሉት..
ሽማግሌው ወደ ሴት ልጃቸው ዞር ብለው ከጠቀስዋት በኋላ «የፍቅር
ጉዳይ ይሆናል!» አሉዋት በሹክሹክታ፡ ሽማግሌው ያሰቡት ዓይነት ፍቅር ሳይሆን የአባት ፍቅር ነበር፡፡

ማሪየስ ወደ ቬርኖን ሄዶ ከአባቱ መቃብር አጠገብ ብዙ ጊዜ
አጠፋ:: ከቬርኖን ሲመለስ በቀጥታ ወደ ሕግ ትምህርት ቤት ቤተ መጻሕፍት ሄደ:: የቆዩ ጋዜጦችን ጠየቀ::ስለሪፑብሊኩና ስለንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ታሪክና ስለሴንት ሄለና የተጻፉትን ብዙ አነበበ፡፡ ጋዜጣን፧ መጽሔትንና መጻሕፍትን አገላበጠ::ስለታላቁ ጦር ሠራዊት ባነበበ ጊዜ የአባቱ ስም ከዚያ ተጠቅሶ አየ:: አባቱ
ጆርጅ ፓንትመርሲ ከየትኛው ጄኔራል ጦር ስር እንደነበረ ሲፈልግ ከጄኔራል ማብዩፍ ቸርችዎርደን ጦር ስር እንደነበር ደረሰበት:: ጄኔራሉ ቤተክርስቲያን
ውስጥ ያገኛቸው ሽማግሌ እንደሆነ አወቀ:: እየተመላለሰ ጠየቃቸው፡፡ጄኔራሉ ስለአባቱ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፤ስለሚሸጠው አበባ፤ ስለብቸኝነቱ ብዙ ነገሩት:: ማሪየስም ስለዚህ ተንኖ ስለጠፋውና ስለተረሳው ጀግና አባቱ ብዙ ተማረ::

በጀመረው ምርምር ብዙ ስለተዋጠ እነመሴይ ጊልኖርማንድን ረሳቸው:: ብዙ ጊዜ አይገናኙም:: የሚተያዩት በገበታ ጊዜ ብቻ ሆነ፡፡ሲፈልጉት አያገኙትም፤ «አሁን ወጣ» ይባላል፡፡ አክስትየው ማጉረምረም ጀመረች:: አያት ፈገግ እያሉ «እባክሽ ተይው፧ ከሚያቅበጠብጥ እድሜ ላይ
ስለሆነ ነው» ይላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን «ይኼ ሰይጣን! ሙያ ያለው ነገር የሚሠራ መስሎኝ ነበር፤ ለካስ ለስሜቱ ነው ተገዥ የሆነው» ብለው ይናገራሉ፡፡

እውነትም የስሜት ተገዥ! ማሪየስ ስሜቱ አስገድዶት የአባቱ
ተገዥ ሆነ፡፡ በአጓዳኝ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የአመለካከት ለውጥ አደረበት። ቀስ እያለ በፊት የነበረው አሳብ በሌላ ተቀየረ:: የአስተሳሰብ አድማሱ
እየሰፋና እየተለወጠ መሄዱ ታወቀው:: ይኸው ነው፣ ብዙ ነገር ባጋጠመን ቁጥር የአስተሳሰብ ይዞታችንን ደረጃ በደረጃ መልኩን እየቀየረ ይሄዳል፡፡

የሚያነበው ታሪክ አስገረመው:: በመጀመሪያ ነገሩ ሁሉ ተምታቶበት ነበር፡፡ ሪፐብሊክ ወይም የንጉሠ ነገሥት ግዛት ማለት ለእርሱ ዝም ብሎ
በይበልጥ ይገረማል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ያለበት ይጠፋዋል፡፡ ቀስ በቀስ የመደነቁና ቃላት መስለውት ነበር፡፡ ስለሁለቱ የአስተዳደር ዘይቤዎች ባነበበ ቁጥር
የመገረሙ ነገር እየጠፉ ነገሮችን በግልጽ ወደማየትና ወደማመኑ አዘነበለ፡፡አርእስተ-ጉዳዮችን ያለ ስህተት መተንተን ቻለ:: አብዮትና የንጉሠ አገዛዝ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ቁልጭ ብሎ ታየው:: ሰዎች ራሳቸውን እንዴት እንደሚከፋፍሉ ታወቀው። እውነተኛ ሪፑብሊክ የሰዎች መብት ማስከበሪያና የንጉሠ ነገሥት አገዛዝ ማክተሚያ መሆኑን ተረዳ፡፡ «ይዂማ ጥሩ ነው» ሲል አሰበ

በጣም ተጸጸተ፡፡ ራሱንም ወቀሰ፡፡ አባቱ በሕይወት ቢኖርና ሊያገኘው
ቢችል ወይም በአንድ ዓይነት ተአምር ከተቀበረበት ነፍስ ዘርቶ ቢነሣ እንዴት አድርጎ ወደ እርሱ በርሮና ሮጦ ሄዶ በማልቀስ «አባዬ፣ መጣሁልህ!
እኔ ልጅህ ነኝ! የእኔ ልብ እንዳንተው ልብ ነው!» ቢለው ምንኛ ደስ ባለው::ይህ ቢሆን ያቅፈዋል፤ ይስመዋል፤ ፀጉሩን በእንባ ያርስለታል፤ ከፊቱ ላይ
የነበረውን ጠባሳ ያሻሽለታል፤ እጆቹን ጥብቅ አድርጎ ይይዛል፤ ልብሱን ይነካካል፤ ጫማውን ይስማል::
👍21
ለምን አባቱ ያለ እድሜ ይሞታል? ትክክለኛውን ፍርድ ሳይቀበል
በልጅ ፍቅር ሳይረካ ለምን ቶሎ ሞተ? ማሪየስ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፡፡እውቀቱ እየጎለበተና እምነቱ እየጠና ሄደ፡፡ ለአባቱና ለአገሩ ያለው ፍቅር ሰውነቱ ውስጥ ሠርጾ ገብቶ አንገበገበው:: በየደቂቃው እውነት እየጎላ መጥቶ የአስተሳሰቡን አድማስ አሰፋለት:: በመንፈስ ያደገ መሰለው::

አንድ ቀን ማታ ሻማ አብርቶ መጽሐፍ እያነበበ ከክፍሉ ውስጥ
ብቻውን ቁጭ ይላል:: የነበረበት ክፍል መስኮት ተከፍቶአል። ብዙ ዓይነት ነገር ከጭንቅላቱ ውስጥ ገብቶ አሳቡን አመሰቃቀለበት:: ሌሊት ሌሊት እኮ ስንት ነገር ይታያል! የሚርመሰመስ ድምፅ ይሰማል፤ ከየት እንደሚመጣ
ግን አይታወቅም:: ካለንበት ምድር አንድ ሺህ ሁለት መቶ ጊዜ የምትተልቀው ጁፒተር እንደ ቁርበተ-አሊም እያበራች ማታ ማታ ነው የምትታየው::ማታ ማታ ከዋክብት ይብለጨለጫሉ፤ ሌሊት ደግሞ የፍርሃት መስፈሪያ ነው....

💫ይቀጥላል💫
👍103
#ጌታችን_ተነስቷል…!

በቃሉ መሠረት፤ ጌታ ከድንግል ተወለደ፣
ከሠማየ ሠማያት መጣ፤ እኛን ስለወደደ፡፡

ሠውን ሊያድን መጣ፣
ከሐጢዓት አረንቋ፤
………….ሃርነት ሊያወጣ፣
ሞትን በሞቱ ሊደመስስ፤
…………ሠይጣንን ሊቀጣ፡፡

እንትፍ ብሎ ምራቁን፤ እውሩን አበራ፣
የዓለም ብርሃንነቱ፤ በምድር ላይ በራ፡፡

የሚያዩም …. እንዲታወሩ፣
…… በሐጢዓታቸው እንዲታሰሩ፡፡
ጌታ ለፍርድ መጣ፣
ምኩራቡን ሊገለብጥ ስህተትን ሊያወጣ፡፡

የማያዩ …. እንዲያዩ ፣
……….. ጌታን እንዲለዩ፡፡
መስዋዕት ሆኖ መጣ፣
ዓለምን ነፃ ሊያወጣ፡፡

አይሁድ ሊወግሩት፤ ድንጋይን ቢያነሱ፣
ቀኑ ስላልሆነ፤ እምቢ አለ መንፈሱ፡፡

የኔ ጌታ…..

አልዓዛርን ከተኛበት፤ በድምፁ ቀሰቀሰ፣
ድውያውንን ሁሉ፤ አንድ በአንድ ፈወሰ፡፡
የአላዛር ወላጆች፤ አይሁድን ስለፈሩ፣
ድንቅ ታምራቱን፤ ሳይናገሩ ቀሩ፡፡
እሱ ሙሉ ሠው ነው፤ ጠይቁት ቢሉም፣
ፈሪሳውያኑ፤ ሊያምኑ ግን አልቻሉም፡፡

የእግዚአብሔርን ስራ፤ በብዙ ገለጠ፣
እልፍ ታዓምር ሠራ፣ ክፋትን ለወጠ፡፡
በዓለም እያለ፤ የዓለም ብርሃን ሆነ፣
የተኛውን ሁሉ፤ በፍቅሩ አባነነ፡፡

የካህናት አለቆች፤ ሸንጎ ተቀመጡ፣
ፈሪሳውያኑ፤ መያዣ አወጡ፡፡
መከሩ.. ዘከሩ፤ እቅዳቸውን ነደፉ፣
የቀያፋን ምክር፤ በድምፅ አሳለፉ፡፡
ከራሱ አይደለም፤ ቀያፋ የተናገረ፣
ስለህዝቡ ይሞት ዘንድ፤ ቃል ስለነበረ፡፡
ትዕንቢቱ ሊፈፀም፤ የግድ ስለሆነ፣
የቀያፋ ምክር፤ ተፈፃሚ ሆነ፡፡

የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉ፣
መጡ ህዝቡ ሁሉ፣
ሆሳዕና በአርያም እያሉ፡፡

ትዕንቢቱ እንዲፈፀም፤ ኢየሩሳሌም ተመረጠ፣
በአህያ ውርንጫ፤ ጌታ ተቀመጠ፡፡
የሠው ልጅ ሊከብር፤ ሠዓቱ ደረሰ፣
ነፍሴ ታውካለች፤ ብሎ እየመለሰ፡፡

በዓሉ ቢደርስም የአይሁዶች ፋሲካ፣
የእኛ ፋሲካችን፤ በፍቅር ተተካ፡፡
እኔ ቁራሽ አጥቅሼ፤ ለሱ የምሠጠው፣
እሱ ነው እኔን፤ በገንዘብ የሚሸጠው፤
………………………ብሎ ተናገረ፣
………………………ቀድሞ መሠከረ፡፡

ዲያቢሎስ ይሁዳን በሃሳቡ ደለለ፣
የአስቆሮቱ ይሁዳ፤ ለመሸጥ ቸኮለ፣
ጌታን አሳልፎ ሊሠጥ፤ ልቦናው ታለለ፡፡

ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሄር እመኑ፣
ቀኔ ደርሷልና፤ ምንም አትዘኑ፡፡
አላቸው ኢየሱስ፤ ለደቀመዛሙርቱ፣
ስፍራ ሊያዘጋጅላቸው፤ ሊፈፀም ትእንቢቱ፡፡

የካህናት አለቆች፤ ወደ ጌታ መጡ፣
በይሁዳ መሪነት፤ ኢየሱስን ሊይዙ፤
……………………. አምላክን ሊቀጡ፡፡

ማንን ትፈልጋላችሁ? ብሎ ቢጠይቃቸው፣
‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስን›› ሲሉ፤
……………………‹‹እኔ ነኝ›› አላቸው፡፡

ስምዖን ጴጥሮስም፤ መዘዘ ሠይፉን፣
የማልኮስን ጆሮ ቆረጠ፤
…………………………… ሊዘጋ አፉን፡፡

ኢየሱስም አለ፤
………. ‹‹ሠይፍህን ወደ ሠገባው ክተት››፣
አብ የሠጠኝን ፅዋ፤ ልጠጣት በድፍረት፡፡

ለእኔ ብሎ ጌታ፤ ሕመሜን ታመመ ፣
ለሠው ፍቅር ብሎ፤ መስቀል ተሸከመ፡፡
ጌታችን ታሠረ፤ ምንም ሳያጠፋ፣
ቃሉ ሊፈፀም፤ ምክሩ የቀያፋ፡፡
ክርስቶስ ኢየሱስን፤ ጲላጦስ ገረፈው፣
የእሾህ አክሊል ጎንጉኖ፤
…………….. ከአናቱ አሳረፈው፡፡
ተሳለቁበት ጌታን፣ በጥፊ መቱት፣
በውጪ አውጥተው፤ ለህዝቡ ሠጡት፡፡

ለእኔ ብሎ ጌታ፤ ሕመሜን ታመመ ፣
ለሠው ፍቅር ብሎ፤ መስቀል ተሸከመ፡፡
መስቀሉን አሸክመው፤ ወሰዱት ጎልጎታ፣
ለሠው ፍቅር ብሎ፤ ነፍሱን ሊሠጥ ጌታ፡፡

ከሌቦቹ መሃል፤ ጌታዬን ሠቀሉት፣
ባልዋለበት ሃጢያት፤ አውለው አኖሩት፡፡

ጲላጦስም ፃፈ፣ የአይሁድ ንጉስ ብሎ፤
ከጭፍራዎቹ አንዱ፤ ጎኑ ላይ ጦሩን ተክሎ፡፡
ደምና ውሃ ወጣ፤ ከተወጋው ጎኑ፣
ስለኛ ሲሠዋ፤ ጌታ ማሳዘኑ፡፡

ለእኔ ብሎ ጌታ፤ ሕመሜን ታመመ ፣
ለሠው ፍቅር ብሎ፤ መስቀል ተሸከመ፡፡
ጌታ ነፍሱን ሠጠ፤ ዓለምን ፈወሰ፣
ሠውን ለማዳን ብሎ፤ ደሙን አፈሰሰ፡፡

የአርማትያሱ ዮሴፍ፤ ስጋውን ለመነ፣
ገንዞ ሊቀብር፤ ፍፁም እያዘነ፡፡

እንደአይሁድ ልማድ፤ ገንዘው ቀበሩት፣
በአትክልቱ ስፍራ፤ ጌታዬን አኖሩት፡፡

መግደላዊት ማርያም መጣች በማለዳ፣
ቢፈለግ ባዶ ነው፤ የመቃብሩ ጓዳ፡፡
ደቀመዛሙርቱ ሁሉ፤ ወደ መቃብር ሄዱ፣
የመፅሐፉን ቃል፤ ከቶ ሳይረዱ፡፡

እልል በሉ ሠዎች፤ ጌታችን ተነስቷል፣
የፋሲካው ንጉስ፤ ሞትን ድል አድርጓል፡፡


መልካም የፋሲካ በዓል…!

🔘እሸቱ ብሩ ይትባረክ🔘
👍16
#የመደርደሪያው_ጫፍ


#በአሌክስ_አብርሃም

“አብርሃም !"

“አቤት”

“ስምህ ማነው ?” አለኝ ፊቴ የተቀመጠው ደግ ፖሊስ፡፡ ፊቱን ሳየው ማፏጨት ጀምሮ መሐል
ላይ ሲደርስ ሊያፏጭ የፈለገው ዜማ የጠፋበት ጎረምሳ ይመስላል፡፡ ስሜን ጠርቶ ስምህ
ማነው? ሲለኝ ቢጎርመኝም በትህትና ተናገርኩ፡፡

“አብረሃም”

“አ.ብ.ር.ሃ.ም”ፊደል የቆጠረ ፃፈ፡፡

የአባትህ ስም" ነገርኩት ጻፈ፡፡
“አብረሃም ! ለምንድነው የሰው ባል ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በሚዛን ስሀን የፈነከትከው”
አለኝ፡፡ አጠያየቁ 'ባትመልስልኝም ግድ የለም” የሚመስል ሰሜት ነበረበት፡፡

ኧረ ስላበሳጨኝ ነው እንጂ እኔ ሰው ጋር ተሰዳድቤ እንኳን አላውቅም፤ እንኳን በጭካኔ..
ዓረፍተ ነገሬ እየተወለጋገደ መለስኩ፡፡

“እሱማ ታስታውቃለህ፡፡ ጨዋ ልጅ ነህ፡፡ ጨዋ ባትሆን ኖሮ ሰሀኑ ላይ የተቀመጠውን አንድ ኪሎ መመዘኛ ብረት ትተህ በሰሃኑ ብቻ ኣትፈነከተውም ነበር፡፡ ጎበዝ ራስህን መግዛትህ ትልቅ ነገር ነው:: ራሱን የሚገዛ አገር ከሚገዛ ይበልጣል ይባላል፡፡ ቢሆንም ግን አብረሃም ዋስ ትጠራለሁ፡፡

“እሺ አልኩና ትዝ ሲለኝ የሚዋስ ሰው የለኝም፡፡

እንካ ደውልና ጥራ !" ብሎ ቅድም ወደ ማረፊያ ቤት ስገባ የተቀብለኝን ስልኬን ወደ ፊቴ
ገፋልኝ፡፡

ወደ አእምሮዬ የመጣችው ሂሉ ነበረች፡፡ ግን ሀሳቡ በራሱ ሳቁን አመጣብኝና ተውኩት፡፡ ባሏን
ፈንክቼ ሚስቱን ዋስ ሁነኝ ማለት በእርግጥ ያስቃል፡፡ ዝም ብዬ ዋስ የሚሆነኝ ሰው ሳወጣና ሳወርድ ቆየሁና "ዋስ የለኝም !" አልኩት ለደጉ ፖሊስ፡፡

እንዴት ዋስ አይኖርህም? ከሰው አልተወለድክም ? ጓደኛ የለህም? ወይም ጎረቤት ” አለ ፖሊሱ፡፡ እንዲህ ሲለኝ ዘመድም ጓደኛም የምለው ሰው እንደሌለኝ ትዝ አለኝና እንባዬ በዐይኔ
ግጥም አለ፡፡

“ደህና እስቲ የአንድ ሰው ስም ንገረኝ አለ ለመፃፍ እየተመቻቸ፡፡

“የአንድ ሰው ማለት?

"በቃ ዝም ብለህ የአንድ ሰው ስም ንገረኝ” አለ፡፡

"እበራ " ማረፊያ ቤቷ ውስጥ አበራ አንበሳው ! የሚል ስም በተወለጋገደ የእጅ ጽሁፍ አይቼ
ሰለነበር አፌ ላይ ድንገት መጣልኝ፡፡

“የአባቱ ስም ማነው ?"

"እኔ ንጃ ተገርሞ አየኝና ፈገግ ብሎ አጉተመተመ፡፡

“በቃ አበራ ቀለጠ ብዬዋለሁ - ዋስሀ ነው:: አብረሃም አምንሃለሁ፤ ጥሩ ልጅ ነህ፤ ይሄ መቼም
የዕለት ግጭት ነው:: ከአሁን በኋላ እዛ ሱቅ አካባቢ ብትደርስ ግን ዋስህን እቀፈድደዋለሁ፤

' ነግሬያለሁ” አለ እየሳቀ፡፡
እዚች ምድር ላይ ይኑር አይኑር በማይታወቅ ዋስ ከእስር የወጣሁ ሚስኪን ሰው፣ ቀበቶዬን
ተቀብዬ ከታጠቅኩ በኋላ ወደ ቤቴ አዘገምኩ፡፡ ፖሊሱ ያሳየኝ እምነት በጣም ነው የገረመኝ፡፡
ለምን እንደሆነ ባላውቅም ሰው ከመሬት ተነስቶ ያምነኛል፡፡ ሌባ ብሆን መቼም ባንዴ ሃብታም
ነበር የምሆነው፤ ሰዎች እንዲያምኑህ እና እንዲዘናጉ ማድረግ ትልቁ የሌብነት ጥበብ ነውና፡፡
ሰፈሬ ስደርስ ወደ ህሊና ሱቅ መንገድ ጀመርኩና ትዝ ሲሰኝ ደንግጬ መንገዴን ቀየርኩት፡፡ ሱቅ አካባቢ እንዳልደርስ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶኛል፡፡ ወይኔ ከሁሉም ከሁሉም ህሌናን ሳላይ መዋል እንዴት ያስጠላል?! ህሊናን እንዳላይ በህግ ተከልክያለሁ፡፡ ያ ፖሊስ በሕግ አላስፈራራኝም
ሕጉን ነው አእምሮዬ ውስጥ ተክሎ በፍቅር ያጠረው፡፡

ሂሉ እስካሁኝ በዱቄት የተበከለ ጋውኗን ስብሳ ፊቷ በሚነድ ሻማ የሆነ ነገር እያደረጋች ይሆናል፤
ወይም የለስላሳ ሳጥን ላይ ቆማ እንደ ነብር ሽንጧ ተመዞ የላይኞቹ መደርደሪያዎት ላይ ሳሙና
እየደረደረች ይሆናል፡፡ ስትንጠራራ እኮ ስታምር! ሰማይ ላይ በተቀመጠ ገብታ በሚያማምሩ
ጣቶቿ እግዜር ጋር ቼዝ የምትጫወት ነው የሚመስለኝ፡፡
ሂሉ የኔ ውብ ! የኔ ቆንጆ! የግርማ
ሚስት ፤ ሰው እንዴት ግርማን ያገባል በእግዚኣብሔር

ብቸኛ ነኝ ! ሁሉም ነገር የሰለቸኝ የሃያ ሰባት ዓመት ወጣት፡፡ ቤቴ እገባለሁ፤ እወጣለሁ ሶስት ዓመት ሙሉ እዚህ ሰፈር ስኖር የማውቃት ህሌናን ብቻ ነው፡፡ መንገዴ ላይ ሱቅ አላት፣ድምቅ ያለ ሱቅ፡፡ የሱቁ ድምቀት ህሊና ራሷ ሳትሆን አትቀርም፡፡

ህሊና ጨዋ ሴት ነበረች። እኔም ጨዋ ልጅ ነበርኩኝ፡፡ የህሊና ባል ግን ጨዋ ስላልነበረ ሊያሳሰተኝ
ሞከረ፡፡ ይሄ አሳሳች ደስ ይበለው፤ ተሳክቶለት ተሳሳትን፡፡ በእርግጥ ስሀተታችን ጣፋጭ ነበር፡፡

ለሚስቱ ሱቅ ከፍቶ ወንድ ደንበኛ በመጣ ቁጥር 0ይኑን ማጉረጥረጥ ተገቢ ነው? ገበያተኛ በመጣ ቁጥር የሚስቱን ፈገግታ መለካት እና ማታ ማታ በልክ ፈገግ በይ እያለ መነትረክ
እግዚር ይወደዋል? እሽ ይሄ ይሁን ግዴለም…ግን አብረሃም የሚባል ልጅ እዚህ ሱቅ ለምን ይመጣል ለሞላ ሱቅ?!” ብሎ መጠየቅ ከአንድ ባለ ሱቅ ይጠበቃል? ... መንግስት ሳያዳላ ሕዝብ
እንዲያገለግልበት በሰጠው ንግድ ፈቃድ እከሌ ይምጣ እከሌ ይሂድ ብሎ ሰው ይመርጣል?
እሺ (ሂሂሂሂ…ኧረ ይሄስ ያሳፍራል) ግን ሚስቱ ጋር፤ ቆንጅዬ ሚስቱ ጋር እቅፍቅፍ ብሎ ከመተቃቀፍም አልፎ መርፌና ክር ሆነው ሌላ ዓለም ውስጥ ሲዋኙ ድንገት የማይቋረጥ ነገር
አቋርጦ፣ “ለምንድን ነው አብረሃም ቲማቲም የሚገዛው? ማን ሊያበስልለት?” ብሎ ሚስቱን
ይጠይቃል፥ እንዲህ ይደረጋል ?

ሂሉዬ ብስጭት ብላ “ራሱ ይሰራላ” ስትለው፣ ራሱ እንደሚሰራ በምን አወቅሽ ?” ይባላል ?ለጥያቄና መልስ ይሄ ቦታው ነው ? ሰዓቱስ ነው ?

ባሏ ቀልቡ አይወደኝም፥ እቀፈዋለሁ፡፡ እኔ ሱቁ በር ላይ ስቆም ዐይኔን ላለማየት የማያየው ነገር የለም፡፡ የተደረደረውን ሳሙና፣ የተሰቀለውን ሙዝ፣ የተለጠፈውን "ዱቤ ክልክል" ነው የሚል ማስታወቂያ...ብቻ ማየት የቻለውን ሁሉ ፌቱን እጨፍግጎ ይቃኛል፡፡ አናቴን ሊፈነከተኝ ፈልጎ
ደህና መፈንከቻ ያጣ ነው የሚመስለው:: በዛ ላይ ሆነ ብሎ ህሊናን በወሬ ያጨናንቃታል፡፡
እንዳናወራ መከላከሉ እኮ ነው፡፡

እጃክስ አለቀ እንዴ?” ይላታል፤

ኧረ አለ!"

"ለስላሳ ዛሬ አላወረድሽም ?"

“ገና ትላንት እኮ ነው ያወረድኩት !”

በቃ የማይቀባጥረው ነገር የለም፡፡

እንግዲህ ስገባና ስወጣ ሰላም የምላት ብቸኛ ሴት ባለ ሱቋ ህሊና ነች፡፡ ሱቋ መንገዴ ላይ
ስለሆነች አስቤዛዬን የምሸምተው ከሷው ነው፡፡ ታዲያ ህሊና ጥሩ ልጅ ስለሆነች ነው መሰል
ከደንበኝነት ከፍ ያለ ቅርርብ ነው ያለን፡፡

ዛሬም ልክ ደመወዝ እንደተቀበልኩ ሄድኩ፤ ባሏ የለም፡፡ ሁለታችንም ደስ አለን፡፡

አንተ?" ትለኛለች፡

በቃ ስሜን ጠርታኝ አታውቅም፡፡ አንተ ነው የምትለኝ፡፡ እውነቱን ለመናገር ህሊና 'አንተ'
ስትለኝ ስሜን ያቀናጣችው ነው የሚመስለኝ፡፡ አብርሃም ሲቀናጣ 'አንተ ! በእኔ ጆሮ ብትሰሙት
በጣም ይገጣጠማል !!

ሰላም 'ሂሉ' ባሏ ከሌለ ሂሉ ነው የምላት፤ በእርግጥ አንዳንዴ እሱም እያለ ያመልጠኛል፡፡

“ምን ሆነህ ነው ዐይንህ የቦዘዘው” ትላለች በትልልቅ ዐይኗ እያየችኝ፡፡ ዐይኖቿ ዐይኔን
ይስሙኛል፡፡

“ዱቤ ልከፍል ስለሆነ ይሆናላ !”

በዚህ ሁኔታ መቀለድ መቻሌ ግዴላችሁም ብርቱ ሰው ብሆን ነው!

ሂሂሂሂሂሂሂሂ….ውይ አታስቀኝ ከምሬ ነው!” ትላለች፣ ስቃ ከወጣላት በኋላ እኮ ነው፡፡ ከዛም
የወሩ እዳዩን እንተሳሰባለን፡፡
"ዱቤ ክልክል ነው" ከሚለው ጽሑፍ ስር ያስቀመጠችውን የዱቤ መጻፊያ ደብተር ታወጣና
ቁልቁል በእስክርቢቶዋ እየጠቆመች “ካርድ የ 100 ብር ግን መቶ ብር ካርድ ምን ያደርግልሃል?
ወሬ እንኳን አታበዛ” ትላለች፤

ዳቦ

ዳቦ

ዳቦ ሰነፍ ስለሆንክ እኮ ነው ዳቦ የምትበላው ! ብቻ አንጀትህ እንዳይደርቅ ፤ ምናለ እንደ
ወንዶቹ እንቁላል እንኳን ብትጠብስ …" ትቀጥላለች፡፡

“…የተፈጨ ቡና…!
👍23👏1😁1
ሻይ ቅጠል…!

ኮካ !

አምቦ ውሃ ሂሂሂሂሂሂሂሂ እስኪ ሰው ዳቦ እየበላ አምቦ ውሃ ሆሆ ስትስቅ ደሰ ስለምትለኝ
ዝም ብዬ አያታለሁ፥ ስታምር!

እ.እ.እና አንድ ሊትሯን ውሃ በድምሩ…መቶ ሰላሳ ሁለት ብር”
ሀምሳ ብሩን ረስተሻል ! እላታለሁ፡፡
“የምን ሃምሳ ብር?" ትለኛለች፡፡
“አንድ ቀን ተበድሬሽ ለታክሲ እንኳ."
“አላስታውስም
እኔ አስታውሳለሁ” እላትና ሁለት መቶ ብር እዘረጋላታለሁ፡፡ አንዱን ብቻ አንስታ አንዱን
እጄ ላይ ትተወዋለች፡፡

“ብር አለህ ግን?" ትለኛለች፣ደግሞ ከልቧ መሆኑን ዐይኗ ያስታውቃል።

ዛሬማ ሃብታም ነኝ

“ያንተ ሀብታምነት እንደሁ እድሜው ሦስት ቀን ነው” ታየኛለች፤ በዕይኗ የነካችኝ ነው
የሚመስለኝ፡፡

አእምሮዬ ባለትዳር መሆኗን እንዳያምን ጣቷን ላለማየት እጥራለሁ፡፡ የሆነች ለስላሳ ነገር ነች፣አንገቷን በዐይኔ ስነካው ይለሰልሶኛል፡፡ ባሏ ግርማ ሲያቅፉት የሚኮሰኩሳት ነው የሚመስለኝ፣ የሆነ ሰውነቷ የሚንደበደብ።

ሂሉን ሱቅ ውስጥ ቆማ ሳያት መደርደሪያው ሁሉ የተሞላው በፍቅር ይመስለኛል። “ማነሽ
ሁሉንም በጅምላ ገዝቼዋለሁ፤ ከነመደርደሪያው፣ ከነሚዛኑ፣ ከነመዛኟ !!

በትልቅ ጥቁር ፌስታል ቋጥሮ እኔንም እዛው ውስጥ መጨመር፧ ወደ ውጭ ማየት የለ፣ ወደ
ውስጥ የሚመለከት የለ፤ እርፍ !

ኤጭጭ! ከኋላዬ ጥላው ሲከብደኝ ታወቀኝ…ግርማ መጣ፤ ባሏ መጣ የተደገፍኩትን መደርደሪያ ከፍቶ ሲገባ ወድቄ ነበር፡፡

ይቅርታ ልገባ ነው አይባልም ? ሂሉ በባሏ ብልግና ስትሳቀቅ ይታወቀኛል፡፡ ይሄ ውሻ የሆነ ሰው
በቃ የሂሉም ፊት ኮስትር የእኔም ፊት ኮስተር !! መደርደሪያው ይንኳተትብኛል፡፡ ማካሮኒ፣
ፖስታ፣ ሳሙና፣ ምንትስ…ያ ሁሉ ፍቅር እልም ! ይሄ ሰሐራ ባሏ ሲገባ ፍቅር ይተናል፡፡

ሰላፈው ከስራ ወጥቼ ወደ ቤቴ አዘግማለሁ፡፡ ድክም ብሎኝ ስለነበር ሂሉን ረስቻት ነበር፡፡
ልክ በሱቋ ሳልፍ “እንተ ብላ ጮኸች፡፡ የሂሉን ድምፅ ሲሰሙ ድካም፣ ድንዛዜ ሁሉ ጠጠር
እንደተወረወረበት የወፍ መንጋ እኔ ከምባል ዛፋቸው ላይ ግርር ብለው ሲበሩ ታውቀኝ፡፡ከንፈሬ ሳላዘው ግራና ቀኝ ሸሽ፤ ፈገግ አልኩ፡፡ እናም ወደ ሱቋ ሄደኩ፤ ከድካሜ ብዛት ደረጃውን
ስወጣ ገድገድ ብዬ ነበር፡፡

"እኔን!" አለች ሂሉ፤

ሱቁ ላይ ስደርስ ግርማ ተቀምጧል፡፡ ድካሞቼ ሁሉ ተጠራርተው ድብርትን ጨምረው
ስፈሩብኝ፤“ሰላም ዋላችሁ! አልኩ፤
እግዚያብሄር ይመስገን!” አለች ሂሉ፣ እግዜር ቀኑን የሰጠው ለሷ ብቻ ይመስል፡፡ ያ ጋግርታም
ባሏ ዘጋኝ! ይዝጋው ! ምን እንደማወራ ጠፍቶብኝ አንዴ መደርደሪያው ላይ ያሉትን እቃዎች፣ አንዴ ሂሉን ስቃኝ
ቆየሁና…“ሳሙና ስጭኝ!" አልኩ፡፡ ሂሉ ሳቋ መጥቷል፤ ድንገት አንደዘባረቅኩ አውቃለች፡፡
ቢሆንም ከመጨረሻው መደርደሪያ ላይ ልታወርድ የላስላሳ ሳጥኑን አስጠጋችና ጫማዋን አውልቃ
ኩርሲዋ ላይ ቆመች። እግሯ እንዴት ነው የሚያምረው ! ተረከዟ ነጣ ብሏል፤ ተንጠራራች፤
ተመዘዘ ሽንጧ …! ሽንጧ የሚመስለው…የምንትስ ሃረግ.” እያልኩ በሃሳቤ ስዘፍን እና ምራቄን ስውጥ ቆይቼ ዞር
ስል ግርማ ዐይኑ ቀልቶ እኔ ላይ አፍጥሏል፡፡ “ነብር አየኝ በል!” አይነት ዛቻ ቀመስ ዕይታ…!
የሚጮህ ዐይን ያየሁት ግርማ ላይ ነው፡፡ ዐይኔን ከዚህ ፈጣጣ ላይ ነቅዬ በጥግ በኲል ስልክ
የኮንዶም ካርቶኑ ላይ አረፈ፡፡ የግርማም ዐይን ዐይኔን ተከትሎ ይሁን ወይም የዐይኑ እግር
ጥሎት እዛው ላይ አረፈ! ወይም ያረፈ መሰለኝ፡፡

ሂሎ የቆመችበት ኩርሲ ነቅነቅ ሲል “እኔን ብዬ በድንጋጤ ጮህኩ፤ አደነጋገጤ ለራሴም
ገርሞኛል። ውሃ ጠገብ ባሏ ምንም ያልመሰለውን እኔን ምን ቆርጦኝ ነው የደነገጥኩት? ምን
አስበረገገኝ? “የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ" አሉ! እንደውም የግርማ አስተያየት ምነው በፈረጥሽ! የሚል ያስመስልበታል፡፡

ሳሙናዬን ተቀብዬ ወደ ቤቴ አዘገምኩ፡፡ በቀጣዩ ቀን ቅዳሜ ሂሉ እንባዋ ጠብ እስኪል እየሳቀች ሳሙናውን ገዝቼ ከሄድኩ በኋላ ከግርማ ጋር የተባባሉትን እንዲህ ስትል ነገረችኝ፡፡....

ነገ ያልቃል
👍188😁2
#ምንዱባን


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

...ማሪየስ በመጨረሻ ስለናፖሊዮን ጦር ሠራዊት ነበር ከሚያነብበው::መፅሀፍ አልፎ አልፎ የአባቱ ስም ያያል የንጉሱ ስም ግን በየምራፍ ይጠቀሳል
አገሪትዋ በሙሉ ለንጉሱ እንደተሰራች ተደርጎ ነበር ፅሁፉ የቀረቡት እንደ መአበል ከውስጥ አካሉ አንድ ነገር ሲያብጥ ተሰማው:: አባቱ በአጠገቡ አልፎ በሹክሹክታ ያነጋገረው መሰለው::
ተደርጎ ነበር ጸሐፉ የቀረበው:: እንደ ማዕበል ከውስጥ አካለ አንድ ነገር ሲያብጥ ተሰማው
አባቱ በአጠገቡ አልፎ በሽኩክታ ያነጋገረው መሰለው የከበሮ፤ የመድፍ፤ የመለከት፤ በሩቁ የሚሰማ የሠራዊትና የፈረስ ኮቴ
ከፊቱ ድቅን አለ፡፡ ማንበቡን ትቶ በመስኮት ወደ ሰማይ ተመለከተ::
የሚያብለጨልጭ ነገር ከሰማይ ተወርውሮ የሚያነብበው መጽሐፍ ውስጥ የወደቀ መሰለው፡፡ ፍርሃት፣ ፍርሃት አለው፡፡ የሚተነፍሰው በግድ ሆነ::
ሰውነቱ ራደ:: ማን እንዳዘዘውና ምን እንዳስገደደው ሳይታወቀው
ከተቀመጠበት ብድግ አለ፡፡ ወደ መስኮቱ ሄዶ እጆቹን ወደ ውጭ ዘረጋ::

በጨለማ ሰማዩንና ምድሩን በዓይኑ ማተረ፡፡ ዓለም ጸጥ ረጭ ብላለች::በድንገት «እድሜ ለንገሠ ነገሥቱ» ሲል ጮኸ፤ በማፌዝ፡፡

ከዚያን እለት ጀምሮ ማሪየስ ጨርሶ ተለወጠ፡፡ ለአባቱ ንጉሠ ነገሥቱ እንደ ተወዳጅ ካፕቴን እንደነበሩ ተገነዘበ፡፡ ተወዳጁን ካፕቴን ያደንቅና ለእርሱም ሕይወቱን አሳልፎ እንደሰጠ ታወቀው:: ለማሪየስ ናፖሊዮን ማለት ግን ከዚህ የበለጠ ነበር፡፡ የወደፊት ተስፋ ፧ የድምበር
መከታና የፈረንሳይ አለኝታ ከናፖሊዮን ቦናፓርቴ ላይ አየ:: ናፖሊዮን ጨካኝ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን እርሱ መታየት ያለበት ከሪፑብሊክ ምስረታ፧
ከለውጥ፤ ከአብዮት ጋር ነው:: ናፖሊዮን የሕዝብ ሰው እንደሆነ አመነ፡፡አባቱ ጦር ሜዳ የተዋጋውና ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠው ለሰዎች እኩልነትና "
ለሪፑብሊኩ ምሥረታ እንደሆነ በፍጹም ልቡ ተቀበለ፡፡ የዚህ ተቃዋሚ የሆነውን የቡርዣን አገዛዝ ጠላ፡፡

አያቱ መሴይ ጊልኖርማንድ የሚደግፉት እርሱ የጠላውን ነበር፡፡ በዚህ የተነሣ በአያትና በልጅ ልጅ መካከል አለመግባባት ተፈጠረ:: ከነአካቴው አያቱ ከአባቱ ጋር ያለያዩት በዚህ መሠረታዊ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት እንደሆነ በተገነዘበ ጊዜ አያቱን በጣም ጠላቸው:: በዚህ በግል ጥቅም በታወሩ ሰው ምክንያት ርህራሄ በተለየው ጭካኔ ልጅ ሊያፈቅረው ከሚችል አባቱ፧ አባት ከሚወደው ልጁ መለያየታቸው እጅግ በጣም አሳዘነው። ማሪየስ ከአባቱ ጋር የተለያየው በዚህ ምክንያት መሆኑን ባወቀ ጊዜ ለአባቱ
ያለው ፍቅር ሲገነፍል ለአያቱ የነበረው ጥላቻ ግን ከደሙ ጋር ተዋሃደ። አባቱ ማለት ለሰዎች ደኅንነት፤ ለሰዎች እኩልነትና ለትክክለኛ ፍርድ የቆመ ታላቅ ሰው ማለት ሲሆን፧ መሴይ ጊልኖርማንድ ማለት ደግሞ
በግል ጥቅም የታወሩ፤ ለጥቂት ሰዎች ደኅንነት ጥብቅና የቆመና እንደ መዥገር በሰዎች ደም የሰቡ ሰው ናቸው።ስለዚህ ቅራኔያቸው የሚታረቅ አልሆነም፡፡ ይህም የአያቱን ዓይን ላለማየት አስወሰነው:: ሰበብ አስባብ
እየፈጠረ ከቤት ይጠፋ ጀመር፡፡ አክስቱ ድንገት አግኝተው የት እንደነበር ሲጠይቁት «ጥናት በዝቶብኝ ከጓደኞቼ ጋር ሳጠና፧ ፈተና ስለነበረብን ከአንድ ጓደኛዬ ቤት ውስጥ ተዘግተን ስናጠና፧ ፍርድ ቤት ሄደን ስለፍርድ
አሰጣጥ ትምህርት ስንቀስም፤ አሁን ትምህርቴን ወደማጠናቀቁ ስለሆነ የመመረቂያ ጽሑፍ መጻፍ ስለጀመርሁ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ስለምውል»እያለ ሌላም፤ ሌላም መልስ ይሰጣቸዋል::
አያቱ ግን «ማሪየስ ፍቅር ይዞት ፍቅረኛው እያንከራተተችው ነው»
በሚል መደምደሚያ ላይ ስለደረሰና እርሳቸውም በዚህ ዓይነት ገጠመኝ ያለፉ ስለሆነ ብዙም አልተጨነቁበትም:: ሆኖም ማሪየስ እንኳን ቀን ሊገባ አድሮም የሚመጣበት ጊዜ በረከተ።

አንድ ቀን ‹‹የት ሊሄድ ይችላል?» ሲሉ አክስቱ ጠየቁ::

ማሪየስ አባቱ በጻፈለት ማስታወሻ መሠረት ተናድዬን ለመጠየቅ
ሞንትፌርሜ ሄዶአል፡፡ ከዚያም የቀድሞውን የዋተርሉ ሃምሣ አለቃ ፧የዛሬው የሆቴል ቤት ጌታ ሚስተር ቴናድዬ ከስሮ ሆቴል ቤቱ ስለተዘጋ ፍለጋው አራት ቀን ወሰደበት።

በእርግጥ ፈሩን እየለቀቀ ነው» አሉ አያቱ እንደዚያ ሲቆይ፡፡

በጥቁር ጨርቅ የተንጠለጠለ አንድ ነገር ከሸሚዞ ስር ከአንገቱ ላይ ማሰሩን አባትና ልጅ ቀደም ሲል ማየታቸውን አንስተው ተወያዩ::

ማሪየስ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፓሪስ ከተማ ሲጠፋ የሄደው ወደ ቬርኖን ነበር። ቬርኖን ከተማ ሄዶ በጠፋ ቁጥር አያቱ «ተኝቶ ነው» ይላሉ፡፡
አንድ ቀን ጠዋት ማሪየስ ከቬርኖን ተመልሶ ከቤት ሲገባ አያቱ
ይሰሙታል፡፡ ከሁለት ቀን የአሳብ ጭንቀትና መንገድ በኋላ ስለነበረ
የተመለሰው በጣም ደክሞታል:: ብዙ እንቅልፍ ስላላገኘ ቶሎ ብሎ ለአንድ ሰአት እንኳን ቢሆን ለመተኛት ይፈልጋል፡፡ ኮቱንና አንገቱ ላይ ያጠለቀውን
አውልቆ አልጋው ላይ ወረወረ፡፡ እንዳይረበሽ ከመዋኛ ሥፍራ አጠገብ በሚገኝ ክፍል ውስጥ ለመተኛት ፈልጎ ወደዚያው ሄደ:: ጤነኛ የሆነ ሽማግሌዎች በጠዋት መንቃታቸው የተለመደ ስለሆነ መሴይ ጊልኖርማንድ በዚያን እለት በጠዋት በመንቃታቸው ማርየስ ከውጭ ሲገባ ሰሙት ካልጋቸው ተነስተው በሽማግሌ እግር ቶሉ ቶሉ በመራመድ የማሪየስ የመኝታ ቤት ወደነበረበት ክፍል ወደ ፎቅ ወጡ:: የወጡት ሊያቅፉና
ሊስሙት፧ በዚያውም ከየት እንደሚመጣ ሊጠይቁት ነበር፡፡ ግን ከክፍሉ ሲደርሱ ማሪየስ አልነበረም:: አልጋው እንደተነጠፈ ነው:: ኮቱና አንገቱ ላይ የሚያንጠለጥለው በጥቁር ሪሪበ የታሠረው ነገር ከአልጋው ላይ
ተቀምጠዋል፡፡

«ይህቺ ጥሩ ናት» አሉ መሴይ ጊልኖርማንድ::

ልጃቸው ወደ ነበሩበት ወደ ምድር ቤት ሳሉን ወረዱ:: እህትየው
ተነስተው ኖሮ ከሳሉን ቤት ቁጭ ብለው ጥልፍ ይጠልፋሉ፡፡ መሴይ
ጊልኖርማንድ በአንድ እጃቸው የማሪየስን ኮት በሌላ እጃቸው አንገቱ ላይ የሚያንጠለጥለውን ነገር ይዘዋል::

«ድል ይሉሻል ይኼ ነው ፤ ምስጢሩን ሳንደርስበት አንቀርም::
መጨረሻውን እንደርስበታለን፤ ይኸውልሽ ጉዳ» ሲሉ ጮሁ ፤ ልጃቸው ከነበሩበት ክፍል እንደገቡ፡፡

በሪበን የተንጠለጠለው ነገር የሳጥን ቅርጽ ያለውና የሚከፈት ነው ሽማግሌው ሳይከፍቱት አተኩረው ተመለከቱት::

‹‹አባባ ፧ ክፈተውና እንየው» አለች ልጃቸው::

ሳጥኑን ጫን ሲሉት ይከፈታል፡፡ በውስጠ ያገኙት ከብጣሽ ወረቀት
በስተቀር ሌላ ነገር አልነበረም::
«ከአንድዋ ፍቅረኛው ወደ ሌላዋ» አለ መሴይ ጊልኖርማንድ በኃይል
እየሳቀ:: «ምን እንደሆነ አውቀዋለሁ ፤ የፍቅር ደብዳቤ!››
‹‹ይሆናል፧ ይነበባ!» አለች የማሪየስ አክስት::

መነጽርዋን አደረገች፡፡ ወረቀቱን ዘረጋጋችና አነበበችው::

«ለምወድህ ልጄ ፣ ዋተርሉ ጦር ሜዳ ላይ በተደረገው ጦርነት
ስለፈጸምኩት ጀብዱ የባሮንነት ማዕረግ ተሰጥቶኝ ነበር፡፡ ማዕረጉን በደሜ የዋጀሁት ስለሆነ ለልጄ ማውረስ እችላለሁ:: እኔ አሁን ማዕረጉ ይገባዋል ወይም አይገባውም ብዬ መናገር የለብኝም:: ››

የአባትና የልጅ ፊት እንዴት እንደተለዋወጠና ስሜታቸው ምን እንደነበር መግለጽ ያዳግታል:: የሞት ጥላ እንደተጋረደበት ሰው በብሽቀት ደነዘዙ፤ እብድ ሆኑ:: በንዴት ሰከኑ:: ዝም ዝም ተባባሉ፡፡ በመጨረሻ መሴይ ጊልኖርማንድ እርስ በራሱ እንደሚናገር ሰው እጅግ ዝቅ ባለ ድምፅ ተናገሩ::

‹‹የዚያ ጦረኛ የእጅ ጽሑፍ ነው::»
👍22
«አክስቱ ጽሑፉን አገላብጣ መረመረችው:: አገላብጣ ካየችው በኋላ ከሳጥኑ ውስጥ መልሳ ከተተችው:: እርስዋ ወረቀቱን ስትጨምር ለአላውቅ
ሰማያዊ ቀለም ያለው ወረቀት ከማሪየስ ኮት ኪስ ወደቀ:: ብድግ አደረገችው አንድ መቶ የግል ካርዶች ነበሩ፡፡ እንዱን ለመሴይ ጊልኖርማንድ ሰጠቻቸው
ከካርዶቹ ጀርባ ባሮን ማሪየስ ፓንትመርሲ የሚል ጽሑፍ ተጽፎበታል፡፡ ፍሉም

ሽማግሌው ደወል ደወሉ:: አሽከር ገባ:: ሪበኑንና ሳጥን መሳዩን ነገር!
እንዲሁም የማሪየስን ኮት ከመሬት ከወረወርዋቸው በኋላ «ከዚህ አጥፋልኝ ! ሲሉ ተናገሩ፡፡

አንድ ሰዓት ሙሉ በዝምታ አለፈ:: ኣባትና ልጅ ጀርባ ተሰጣጥተው
ዝም ተባብለው ተቀመጡ:: ምናልባት ስለተመሳሳይ ነገር ሳያስቡ አልቀሩም ፡
ከአንድ ሰዓት በኋላ የማሪየስ አክስት «ይሁና፤ ደህና ነዋ!» ስትል ተናገረች::

ወዲያው ማሪየስ ሰዎቹ ከነበሩበት ክፍል ገባ፡፡ ከሳሎኑ እንደገባ
ካሳተመው ካርድ አንዱን አያቱ ይዘውት ተመለከተ:: የማሪየስ ወደ ሳሎን መግባት ሽማግሌው ባዩ ጊዜ ‹‹ቁም! ቁም! ቁም! አሁን እኮ አንተ ባሮን ነህ::
እንኳን ደስ ያለህ እልሃለሁ:: እስቲ ይህ ምን ማለት እንደሆነ አስረዳን?» ሲሉ ተናገሩ::

ማሪየስ ጥቂት ደንገጥ ቢልም ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ ሰጠ፡፡
«ትርጉሙማ እኔ የአባቴ ልጅ ነኝ ማለት ነው» አለ፡፡
«አባትህ! አባትህማ እኔ ነኝ» አሉ መሴይ ጊልኖርማንድ
«አባቴ» አለ ማሪየስ በመደንገጥ የመሴይ ጊልኖርማንድን ዓይን፥
ኮስተር ብሎ እያየ፤ «አባቴ ሪፑብሊኩንና ፈረንሳይን ያገለገለ ጀግና ሰው ነበር፡፡ ስሙ ከጀግኖች ታሪክ ማኅደር ውስጥ ተጽፎ ይገኛል፡፡ የአገሩን ድምበር ላለማስደፈር ለሃያ አምስት ዓመታት የቀን ፀሐይ፣ የማታ ቁር
ሳይበግረው ቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ ኖሮአል:: የአገሩን ክብር ለማስጠበቅ ሲዋጋ ከሃያ ቦታ ላይ ቆስሉአል:: ሆኖም ለአገሩ የሰጠው አገልግሎት ተረስቶ እንዳልሆነ ሆኖ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ:: አባቴ የፈጸመው ስህተት ቢኖር ሁለት ነው:: እነርሱም አገሩንና እኔን ከመጠን በላይ መውደዱ ናቸው::

ይህ አነጋገር የመሴይ ጊልኖርማንድ ሕሊና ሊቀበለውና ሊያደምጠው የሚችል አልነበረም:: ገና ሪፑብሊክ የሚል ቃል ሲሰሙ ከመቀመጫቸው
ብድግ አሉ:: ራሳቸው የንጉሠ ነገሥቱ ወገን ነኝ» ብለው ስለሚያምኑ ማሪየስ አፍ የወጣው እያንዳንዱ ቃል እንደ ጦር እየወጋ ፊታቸውን አከሰመው::

«ማሪየስ» ሲሉ ጮሁ:: አንተ ትፋታም! አባትህ ምን እንደነበር
- ባውቅም፤ ለማወቅም አልፈልግም ስለእርሱ የማውቀው ነገር የለኝም:: እሱነቱንም አላውቅም:: የማውቀው ነገር ቢኖር በአንድ ወቅት ርባነቢስ
የሆኑ ጥቂት ሰዎች እንደነበሩ ነው እነሱም ቢሆኑ ለማኞች ነፍሰገዳዮች የሚሊቴር ፖሊሶች ሌቦች ነበሩ፡፡ ሁሉም ሁሉም ነው
የምለው:: ከዚህ የተለዩ አልነበሩም:: ከዚህ የተለየ እኔ ማንንም አላውቅም::ሁሉንም ነው የምለው:: ማሪየስ ፤ ሰማህ? አንተ ብሎ ባሮን እነዚያ ሽፍቶች ፤ ቀማኞች ፧ አታላዮች ፤ አታላዮች ፤ አታላዮች እውነተኛውን ንጉስ
ከድተው ቦናገርቴን የተከተሉ ፈሪዎች ፧ የፈሪ ፈሪዎች ናቸው:: ዋተርሉ ላይ ጠላቶችን ፈርተው የሸሹ ወርቦለች! ይኽ ነው እኔ የማውቀው::አባትህ ከነዚህ ዉስጥ ከሆነ አዝናለሁ አላውቀውም ብል ይሻላል::....

💫ይቀጥላል💫
👍213
#የመደርደሪያው_ጫፍ

፡(የመጨረሻ ክፍል)
#በአሌክስ_አብርሃም


....ሳሙናዬን ተቀብዬ ወደ ቤቴ አዘገምኩ፡፡ በቀጣዩ ቀን ቅዳሜ ሂሉ እንባዋ ጠብ እስኪል እየሳቀች ሳሙናውን ገዝቼ ከሄድኩ በኋላ ከግርማ ጋር የተባባሉትን እንዲህ ስትል ነገረችኝ፡፡.አወራሯ
ድራማ ነው የሚመስለኝ። ሂሉ ሲበዛ ነፃ ነች፡፡

እንተ ” በሳቅ ፍርስርስ አለች፤

“ምን ያስቅሻል?”

"እይውልህማ…ብታይ…ትላንት ሳሙና ስጭኝ ስትለኝ ሰጥቼህ (ረዥም ሳቅ )..ሰጥቼህ ከሄድክ
በኋላ ግርምሽ ብስጭት ብሎ ሲነዘንዘኝ አላመሽ መሰለህ! ሆሆ!”

“ምን አነዛነዘው ?”

ነገረችኝ፤ ልከ እኔ እንደወጣሁ ግርማ ሂሉን ጠየቃት፣

".…እኔ የምልሽ! አብረሃም 'ሳሙና ስጭኝ' ነው ያለሽ አይደለም እንዴ?”

“እዎ እና እኔስ ሌላ ምን ሰጠሁት?”

“ምን እንደሰጠሽውማ አንችው ታውቂያለሽ”

“እንዴ! ግርምሽ ምን ማለትህ ነው?”

“የሳሙናውን ዓይነት አልተናገረም፡፡ እንዴት ዘለሽ እዛ ትንጠላጠያለሽ? እዚህ የገላ ሳሙና አለ፥ እዛጋ አጃክስ አለ፤ ላርጎ ፈሳሽ ሳሙና አለ፤ ምን እንደፈለገ በምን አወቅሽ ?”

ሂሉ ደነገጠች፡፡ ቢሆንም ኮስተር ብላ መለሰችለት፡፡

“ሁልጊዜ የሚወስደው ይሄንን ነዋ!"

“እስኪ እሱን የዱቤ ደብተር አቀብይኝ አለ፤ አቀበለችው፡፡ የወሰድኩትን ዝርዝር አየና የታለ
ሳሙና ወስዶ የሚያውቀው?” አላት በብስጭት፡፡

“እየከፈለ ነው የሚወስደው"

“ያሁኑን መቼ ከፈለ ?

“ኤጭ እንግዲህ አትጨቅጭቀኝ ! ወይ 'ሱቁን ዝጊና ቤት ተቀመጭ! በለኝ አለች ብስጨት ብላ፤

በዱቤ ደብተሩ ወርውሮ ሳታት፡፡ ከፀያፍ ስድብ ጋር “ሸርሙጣ!"

ይህን ሰትነግረኝ ሁለታችንም ከልባችን ሳቅን፡፡ ስቃ ስቃ ሲወጣላት “እንተ ምናለብህ ሳቅ ገብተህ በሰላም ለጥ ትላለህ፤ የሰው ትዳር እየበጠበጥክ ልክ ስለሌላ ሰው ትዳር የምታወራ ነበር የምትመስለው።

ባሏ ግርማ ከሌለ ወሬያችን መቆሚያ የለውም፡፡ እንደማልወደው ታውቃለች፡፡ እሱም እንደማይወደኝ ታውቃለች። ይሄ ነገር ሳያስቃት አይቀርም፡፡ ሰው ከመሬት ተነስቶ ይጠማመዳል?ሆሆሆ ትላላች። ከዛም ልክ የመጀመሪያው ወሬ አካል እስኪመስለኝ ሌላ ርዕስ ውስጥ ትገባለች፡፡

"አንተ እቺ ሸሚዝ አሁንም አለች?” አለችኝ ድንገት የለሰስኳትን ሸሚዝ በግርምት እየተመለከተች፡፡

"አዎ የት ትሄዳለች ?”

የመጀመሪያ ቀን እዚህ ሱቅ ስትመጣ እችን ነበር የለበስከው..ፀጉርህ ጨብረር ብሎ እዚች ጋ ቆመህ.ወረፉ ነበር፣ ሰው ሁሉ እያለፈህ ገዝቶ ሲሄድ እንተ ዝም ብለህ ቆመህ ..ሂሂሂሂ
ሌባ መስለከኝ፣ ስልኬን አንስቼ መሳሲያዩ ውስጥ አስቀመጥኩት ሃሃሃሃ…ከዛ በአንድ ዐይኔ አንተን
እያየሁ፡ በአንድ ዐይኔ ደንበኞቼን ሳስተናግድ ነበር፡፡…ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ !” አወራሯ ያስቃል፡፡ ሌባ ትመስላለህ እያለች እንኳን ታስቃኛለች።.ደግሞ የሚገርመኝ አሳሳቋ ሳቁ
እንሳቅ ዓይነት ግብዣ ነው በቃ !

ግርምሽም ሌባ ነበር የምትመስለው አሁንም ሐሳቡን የቀየረ አይመስለኝም፡፡
ሃሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂ…” ሁለተኛዋን አረፍተ ነገር ስራዬ ብላ እኔን ለማብሸቅ የጨመረቻት
ብትሆንም እያውቅኩም ተበሳጨሁ፡፡

"እናትክን በይው እሺ!”

"ሃሃሃሃ አንተ ባለጌ ስድ ባሌ እኮ ነው! ሂሂሂሂሂሂሂ…»

"እኮ ባልሸን እናትክን በይው!.…ማታ እቅፍ አድርገሽ ጉንጩን እየሳምሽ : መቼም ይሄ ማቀፍም
መሳምም አይገባው…'የኔ ቆንጆ አብርሃም እናትክን ብሎሃል እሽ ! በይው"

ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃም የሚያልፈው ሰው እየዞረ እስኪመለከት ሳቋን ለቀቀችው፤
እየሳቀች እንባዋ ሲፈስ ገርሞኝ ነበር፡፡ በቀጥታ እየሳቀች ማልቀስ መጀመሯን ያወቅኩት ወዲያው
ነበር፡፡

እንዴት እንደመረረኝ!” አለችኝ፡፡ ደነገጥኩ፡፡ ብሶቷን ዘረገፈችው፡፡

የሐረር ልጅ ናት፡፡ ዘጠነኛ ክፍል እያለች ይሄ ያሁኑ ባሏ ግርማ ወታደር ሆኖ ሰፈራቸው የነበረ
ካምፕ ውስጥ ይኖር ነበር፡፡ ያኔ ተጫዋች፣ ወንዳወንድ፣ በቃ የሚፈቀር ሰው ነበር፡፡ ለጓደኝነት
ሲጠይቃት አላንገራገረችም፡፡ “
ይዤሽ ልጥፋ!” ሲላት አምናዋለች፡፡ ካለ እናት ያሳደጋትን አንድ አባቷን ጣጥላ ይሄን መዶሻ ራስ ተከትላ እዲስ አበባ ገባች፡፡ እናቱ፣ እህቶቹ፣ ወንድሞቹ
ሳይቀሩ አተካኗት፡፡ ለጎብረት ያገቧት ይመስል በትዳሯ እየገቡ መፈትፈት ጀመሩ፡፡ ነፃ ሆኗን
አለሌነት፣ ሳቋን የሽርሙጥና ደውል አድርገው ዐይንሽን ላፈር አሏት፤ እንደ አዲሳባ ሰው በሯንም
ጥርሷም በልኩ መከፈት ያላደገባትን፡፡ ሚስኪን ! ልለማመድህ ብትለውም አልሆነላትም፡፡

" ኤጭጭ አቦ እንደፈለጉ ይሁኑ!" ብላ ሳቋንም ነፃነቷንም ተያያዘችው፡፡ ይባስ ብሎ ሳቋ ማርኮት እንዳልወደዳት “ሳቅሽን አቁሚ!“ አላትና አረፈው!! ብዙ ባሎች የባል ድንበሩ የት ድረስ እንደሆነ አያውቁም፡፡ ትንሽ ባሎች ደግሞ ድንበራቸው ላይ ሳይደርሱ ይቆማሉ፡፡

አባቷ እሷን ፍለጋ ተከራትቶ ተንከራትቶ ሲሞት አፈር አላለበሰችውም፡፡ የሐረር ሰው ውሎ ይግባ አልቅሶ ቀበረው፡፡ በምድር ላይ የነበራት አንድ መሸሻ ዋሻ ተደፈነ፡፡አሁን ግርማ መድረሻ
የሌላት ከንፏ የተሰበረ ወፍ አደረጋት። “በየመንገዱ ስታገጭ ነው ያገኘሁሽ" አላት ፣ እንደ
ሚስት ሳይሆን እንደ ሰራተኛ ከፍ ዝቅ አድርጎ ያዝዛት ጀመረ፡፡ ያኔ ካስቀመጠባት መንበር ጎትቱ
አወረዳዳት፡፡ ለሴት ልጅ ትልቁ ከብሯ ቤተሰቧ መሆኑን አመነች፡፡ ለምን አፈር ጠርጎ የሚተኛ
ደሃ አይሆንም ቤተሰብ አለኝታ ነው ! ፍቅር ይወጣል፣ ይጠልቃል፡፡ እቃ ! የሰው ፍቅር እንደ ፀሐይ ምስራቅና ምዕራብ አለው:: እየጣፈጠ ወጥቶ፣ እያቃጠለ ይጠልቃል! ቤተሰብ ግን ሰማይ ነው:: የሕይወት ፀሐይና ጨረቃ ሰፈራረቅ የማይቀያየር፣ የማይጠልቅ፣ የማይጠቀለል ቦታውንም
የማይቀይር ሰፊ ሰማይ ማለት ቤተስብ ነው፡፡ ሂሉ ቤተሰብ የላትም፡፡ ሰማይ የለም፡፡ ቀጥ ስትል ኦና ነው ባዶ ነው ! ኮከብ የለም፣ ጨረቃ የለችም፣ ፀሐይም የለችም፡፡ ሰማይ በሌለበት
ምንም የለም፡፡ እግዜር የት ይሆን መቀመጫው ? የት ሆኖ ይሆን ይህን ጉድ የሚመለከተው?!

የአዲስ አበባ ኑሮ አንሸገሻት። ለምሬቷ ጣዕም ኮሶ የጨመረው ባሏ ነው:: “ታምናለህ…. ከሳመኝ
ስንት ጊዜው ? አለችኝ፡፡ ግን እወደዋለሁ ! ስድቡ፣ ማቃለሉ እያቃጠለኝ እንኳን እወደዋለሁ !

ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ አንተ እስለፈለፍከኝ :" አለችና ሳቋን ለቀቀችው:: የኔ ሚስኪን !!
ባለፈው ሐሙስ ደግሞ ሂሉ ወደኔ ጠጋ ብላ ፊት ለፊቴ ቆመች::መሐላችን ላይ ሚዛኑ አለ፡፡ ፊቷ ልክ አልነበረም፡፡ ቶሎ እንድሄድባት መፈለጓ በግልፅ ያስታውቃል፡፡

አንድ ትንሽ ልጅ መጥቶ "ሳሙና ስጭኝ ! ቢጫውን አላት፤
“የለም " አለች፣ ግን ፊት ለፊት ተደርድሮ ነበር፡፡
ሌላ ሴት መጣችና “ስኳር ስጭኝ ሕሊና ኣለቻት፡፡
“የለም !" ፈት ለፊት ኩንታል ስኳር ተቀምጧል፡፡ ገርሞኝ ጠየቅኳት፡፡
“ሂሂሂ.አንተ ካልሄድhልኝ በስተቀር ምንም ነገር አልሸጥም ዛሬ እየቀለደች መስሎኝ ነበር።
“ማሪያምን !" ስትለኝ የላፕቶፕ ቦርሳዬን እንስቼ፣ “በይ ቻው !” አልኳት፡፡
“ቻው አብርሽ !" አለችኝ በቅሬታ ፈገግታ፡፡ “አብርሽ ብላኝ አታውቅም፤ ግራ ገባኝ፡፡
በቀጣዩ ቀን ሂሉ የለችም ነበር፤ ባሏ ተገትሯል፡፡

"ሰላም ዓርማ"
“ምን ልስጥህ?” አለኝ ኮስተር ብሎ፣
"ኮካ"
"የለም"
"እሺ ቀዝቃዛ ሰፕራይት አድርገው"
"የለም"
👍32👎2
“ትንሿን ውሃ ስጠኝ እሺ ! ውሃውን ሊሰጠኝ ዘወር ሲል ፊት ለፊት ሰማያዊ መደብ ላይ በነጭ የተጻፈ ማስታወቂያ መለጠፉን ተመለከትኩ፡፡ “የኔ ብጤና ዱሴ ፈላጊ እግዘር ይስጥል ይላል።" የብልግና ጥግ ! ሂሉዩ ይሄን ለመጋረድ ነበር ትላንት ፊቴ እንደ ጨው አምድ ተገትራ
የነበረው፡፡

ይሄን ብትገነጥይ እገነጥልሻለሁ” ብሎ ፎከረባት፡፡ ግርማ እንደለጠፈው ቆይቶ ሰማሁ፡፡ እኔን
ለማኝ! ለማለት ፒያሳ ሂዶ ማስታወቂያ ያጽፋል !?…ጓጉንቸር!!

ህሊና ከሰዓት እፏን በስካርቭ ሸፍና ቆማ አገኘኋት፡፡

"ምነው ሂሉ?"

ትንሽ ጥርሴን አሞኝ ! ፊቷ ሞቶ ነበር፡፡ ዐይኖቿ ባዶ ቀፎ፤ አንድ የሕይወት ምዕራፍ በሆነ
ምክንያት የተዘጋ አይነት። ህሊና የትላንቷ አልነበረችም፡፡ ባላወቅኩት ምከንያት ተቆጣሁ፡፡
እስቲ ስካርቭዥን አንሺው” አልኳት፡፡

" ሂድ በቃ አብርሽ !" ብላ እንባዋ ተዘረገፈ፡፡ ከዛ በኋላ ህሊናን ለአንድ ሳምንት አላየኋትም፡፡
ለሁለት ለሦስት…ለስድስት ወር !!
ከአንድ ሳምንታ በኋላ ወደ ሱቁ ስሄድ ግርማ ከአንዲት የማልወዳት ሴት ጋር ቆሞ እያወራ
ነበር፡፡ ቀንቀት እያየኝ፡ “ አሁን ደግሞ ምን ቀረህ? ከሚስቴ ጋር አጣላኸን !” አለኝ፡፡ ዞር ብዬ
ሌላ ሰው መኖሩን ተመለከትኩ፤ እኔን አልመሰለኝም ነበር፡፡

አንተን ነው ባክህ ምን ታስመስላለህ አለኝ እያመናጨቀ። አንዲት የህሊናን እግር መውጣት
ተከትላ ግርማን እንደ ጭልፊት ለመንጠቅ ያሰበች የምትመስል ማዲያታም ሴት “ሆሆ..የልብን
ሰርቶ እንደገና ዐይንን በጨው አጥቦ መምጣት አለ እንዴ?” አለች፡፡ ይህቺ ሴት ካሁንም በፊት እኔና ህሊናን ስትመለከት ዐይኗ ደም የሚለብስ በተሳሳቅን ቁጥር በርሷ እየመሰላት የምትመናቀር

ለግርማም ነገር የምታመላልስ ነገረኛ ነበረች፡፡

“በሰላም ነው አልኩት።

“ወደዛ ሂድ ባክህ ' ሁለተኛ ሱቄ በር እንዳትደርስ፡፡ እዚህ አካባቢ ባይህ ጥርስህን ነው የማራግፈው!” አለ እያመናጨቀኝ፡፡ አሁን ዩኒፎርሙ ብቻ ሲቀር ወታደርነቱ ተመለሰበት፡፡ አብራው ያለችው ሴት “ግርምዬ በመቤቴ ተረጋጋ! የማይረባ ሰው ጋር አትጋጭ ፡ እጅህ ላይ አንድ ነገር ይሆንብሃል ? አለች፡፡

እንዲህ ስትለው ጭራሽ ለያዥ ለገናዥ አስቸግር ቁጭ አለ፡፡ እውነቱን ለመናገር ግርማንም ሆነ
ሴትዮዋን ከቁም ነገር አልፃፍኳቸውም፡፡ እንደው ነገሩ ገረመኝ እንጂ !

“አንተ ልክስክስ የሸርሙጣ ልጅ " ብሎኝ ቁጭ ! ቀኝ እጄኝ ጌታ ይባርከው !! ከቁጥጥሬ
ውጭ ተወንጭፍ ግርማ ጉንጭ ላይ በብርሃን ፍጥነት ሲያርፍ በመደርደሪያው ስር ተንገዳግዶ
ወደቀና ወዲያው አፈፍ ብሎ ተነሳ፡፡ ፊት ለፊቴ የነበረውን የሚዛን ሰሀን አነሳሁት፡፡ በአንድ
በኩል አንድ ኪሎ ግራም ብረት ነበር፡፡ እኔ ግን ሰሀኑን አንስቼ በቀጥታ ግርማ ግንባር ላይ
በጠርዙ በኩል አሳረፍኩት፡፡ ባባቴ ወንድ ነኝ፡፡

እልወጣልኝም፡፡ እሪታዋን የምታቀልጠውን አቃጣሪ በጥፊ አቃጠልኳት! ከዛ አገር ምድሩ
ተሰብስቦ ገላጋይ ሆነ። ግርማ ደሙን እያዘራ ይፎክራል፡፡ ወደፊት “ደሜን አፍስሼ ባቆምኩት
ሱቅ” እያለ ታሪክ ያዛባ ይሆናል፤ ይሄ የማይረባ ! ታሰርኩ፡፡ እናም ደግ ፖሊስ ገጥሞኝ ተፈታሁ፤ “ሂሉ ጋ እንዳትደርስም ብባልም ከዛ በኋላ እሷም ራሷ እንደጠፋች ሰማሁ፡፡ ስልክ እንኳን አልነበራትም ሂሉ፡፡ ከዛ ሰፈር ቤት የቀየርኩበት ምክንያት ያንን የመቃብር ቦታ የመሰለ ሱቅ ላለማየት ነበር፡፡

አንድ ምሽት ከስድስት ወር ይሁን ሰባት ወር በኋላ ስልኬ ሲጮህ አነሳሁት፡፡

“እንተ!"

ዝም.. ደንግጬ ነበር፡፡

“እብርሽ !"

ሄሉ !”

"ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ…ተኝተህ ነው ? እንቅልፋም !" ልክ ትላንት የተገናኘን ነበር የሚመስለው
አነጋገሯ፡፡ ልታገኘኝ ቀጠረችኝ፡፡ ነገ ቅዳሚ ነው፤ እንኳን የሂሉ ቀጠሮ ተጨምሮቀት

ሂሉዬ አምሮባታል፤ አወራን፡፡

የዚያን ግዜ ግርማ የሚያስጠላ ማስታወቂያ ለጥፎ እንዳትገነጥይ አለኝ፤ እኔ ግን በብስጭት ገንጥዬ
ስጥለው በቦብስ ጥርሴን መታኝ፡፡ ሰማይ ምድሩ ነበር የዞረብኝ፡፡ ሴት በቦክስ ይመታል…ያውም እኔን ግልምጫ የሚበቃኝ ሂሂሂሂ" አለች፡፡ በጣቷ ነጭ ጥርሶቿ መሐል በግራ በኩል የተተካች
ሰው ሰራሽ ጥርስ እያሳየችኝ፡፡ አነጋገሯ ልብ ይሰብር ነበር፤ አጋዥ የሌለው አቅመቢስ ሰው
ዓይነት። በቃ ስካርፍ አድርጌ ያየኸኝ ቀን ማታ በሚኒባስ ተሳፍሬ ወደ ሐረር…ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ

ትንሽ እንደ መተከዝ አለች፡፡

አባቴ ሲሞት ሐረርም የሞተች መስሎኝ ነበር፡፡ ጓዋደኞቼ፣ የአባቴ ጓደኞች፣ ጎረቤቱ እንደ አዲስ ልቅሶ ተቀምጦ የአባቴን ሞት አዲስ አደረገው፡፡ አይዞሽ! አለኝ፡፡ ሰው ሁሉ የአባቴን ሞት ያፅናኑ መስሏቸው እኔን ከሞት ቀሰቀሱኝ፡፡ ሐረር ፍቅር ናት ሰው ሰው ይሸታሉ ሰዎቹ እንባዋና የደስታ ፈገግታዋ ተቀላቀለ፡፡ ሰው በሰው ሲረካ እንደዛን ቀን ተመልክቼ አላውቅም፡፡

ሂሉ አቤትትትትት እንዴት ስወድሽ እንደነበር እኮ !" አልኳት።

"አንተ አንድ ጥርስ አለብህ ላንተ የከፈልኩት ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ

እየተንጠራራን ነበር ከሕይወት መደርደሪያ ላይ አስከፊ ትላንታችንን የምናጥብበት ሳሙና
ልናወርድ !

ሂሉ ባልሽን በሚዛን ፈነከትኩት እኮ…" አልኳት፡፡ አነጋገሬ “ተበቀልኩልሽ” ይሁን፣ አልያም
ጀግና ነኝ” ማለት ለራሴም አልገባኝ !

"ሃሃሃሃሃሃሃ ሰማሁ እኮ… አቦ ጌታ ይባርከህ! ሃሃሃሃሃሃ ባለጌ ነህ ግን.…ገና ሰማኒያችን
አልተቀደድም እኮ ! አሁን የመጣሁት ለዛ ነው...”

እየተንጠራራን ነበር፡፡ ከአዲስ አበባ ሐረር፣ ከሐረር አዲስ አበባ መደርደሪያው ቢርቅም ያቆምንበት የማፈላለግ ኩርሲ እንደምንም እያደራረሰን፡፡ ሂሉዪ አዲስ ኣበባ ዘመድ የላትም፡፡ እኔም ሐረር የማውቀው ሰው የለም፡፡ ግን እኔንም ሐረር ፣ ሂሉንም አዲስ አበባ ደጋግሞ ያስረገጠን ጉዳይ ምንድን ነው ? “ከምር ግን ምንድን ነው ? የሚሉ ጠያቂዎች ቢከሰቱ መልሳችን አንድ ነው፡፡

አቦ አትነዝንዙና !"

አለቀ
👍52
#አለሁላት…!


#በአሌክስ_አብርሃም


እናቴ ሁልጊዜ ሁለት እጆቿን ወደ ሰማይ ዘርግታ እግዜርን እንዲህ ትለዋለች፣
“አብርሽዬ የሚያገባትን ሴት ሳታሳየኝ እንዳትገለኝ፡፡


አገባሁ !
እናቴ እለት እጆቿን ወደ ሰማይ ዘርግታ እግዜርን እንዲህ አለችው፣

“ምነው ይሄንንስ ከሚያሳየኝ በገደለኝ

ሀና ምንተስኖት ትባላለች የምኮራባት ሚስቴ፡፡ እወዳታለሁ፣ አፈቅራታለሁ፡፡ ክፉ ነገር በሰፈሯ
እንዲያልፍ አልፈልግም፡፡ ሀኒዬ የእኔ ጥሩ ሱስ፣ ካላየኋት ያዛጋኛል' ስል ሰዎች አያምኑኝም፤ ሀኒ
የእኔ ልብ፣ የጠላችው ጠላቴ ነው:: ይሄ አባማ የሚባል ሰውዬ በቴሌቪዥን ያደረገው ንግግር
አስጠላኝ ብትለኝ፣ ሲ አይ ኤን ሳልፈራ፣ ኤፍ.ቢ.አይን ከቁብም ሳልቆጥረው ኦሳማ ላይ የግድያ
ሙከራ ባደርግ ደስታዬ ነው:: እንቅ አድርጌ አይኑን አፍጥጦ፣ “ኧረ አብርሽ በእናትህ የዛሬን
ማረኝ..ሁለተኛ በየትኛውም ሚዲያ ከመቅረቤ በፊት ንግግሬን ለሀና ምንተስኖት ኣሳውቃታለሁ..
ካልፈቀደችልኝ ኣላደርጎውም” ቢለኝ አልምረውም፡፡ እማምላክን አልምረውም !!

ሀናዬ የነብሴ ፍራሽ…ላያት ድሎቴ ናት። ሀና ካዘዘችኝ…አቤት ፍጥነቴ ገና ልትናገር ስትጀምር እኔ ሮጫለሁ፡፡ አልጋ ላይ ጋደም ብላ ቴሌቪዥን እያየች እኔ ቆንጆ ቡና እያፈላሁላት…የሆነ ነገር ብትፈልግል ልትናገር ስትጀምረው ነገሩን አምጥቼዋለሁ ፡፡ ለምን ትጨርሰዋለች.…ቃሏ ፍቅር
ነው..ፊደሎቾ እንደ ረሀብ ቀን እህል ያሳሱኛል፡፡

“አብርሽ " ስትለኝ በቦታህ!' እንዳሉት ሯጭ እዘጋጃለሁ፡፡ ወደ መሻቷ ተፈትልኮ በምድር
ላይ ያሉ ወንዶች ሁሉ የሚሰቶቻቸውን ፍላጎት ካሟሉበት ሰዓት የተሻለውን ለማስመዝገብ፡፡
"ድ." ብላ ስትጀምር ፈትለክ ብዬ ድስት…ድራፍት…ድንች ድልህ...ድፍድፍ (ከእማማ ፈጠኑ ቤት ድመት...ድንጋይ..ድራማ (ሲዲ) ይዤላት እያለከለኩ ከተፍ ስል፣ "ውይ አብርሽዬ…በቲቪ ድብ አይቼ ድቡን እየው ልልህ ነበር እኮ" ትለኛለች በፍቅር ዐይን እያየችኝ...!! አይከፋኝም ለምን እከፋለሁ፡፡ እንደገና ድብ ባየችና “ድ ብላ ስትጀምር፣ አሁን ባመጣኋቸው ነገሮች ላይ
ድብ ጨምሬ ባመጣሁላት..የእኔ ሀኒ መክሊት ብያታለሁ፡፡ እሷ ናት ቀኝም ግራም ጎኔ፡፡

ሀኒዬን እናቴ አትወዳትም፡፡ “አንዳች አስነክታው ነው ልጄን እቺ የሰው ጉድ” ትላታለች፡፡
አባቴ ገና ሲያያት የእናቱ፣ የአባቱ፣ የሁለት እህቶቹ ገዳይ ነው የምትመስለው አቤት ሲጠላት፡፡ በወሬ ወሬ “መንገድ ላይ አብረሃም እና... ሲሉት፣ "በቃ " ብሎ ይጮሀል።አብርሃም ካላችሁ አይበቃም….እናን ምን አመጣው?” ይላል፡፡ ያውቃል ማንም ጋር እንደማልታይ፤
ሀኒ ጋር ነኝ ቤት ውስጥ የምትበላውን እየሰራሁላት፡፡ ሀኒ ጋር ነኝ መንገድ ላይ ቦርሳዋን ይዤላት፤….ዣንጥላዋን ይዤላት ዕቃ ከገዛን አስቤዛም ቢሆን እኔ ይዣላት ሀኒ ጋር ነኝ የትም!!

ሀኒን እህቴ አትወዳትም፡፡ ከዘመናዊ ጓደኞቿ ጋር ሆና ከሩቅ ካየችኝ በሬ እንዳሯሯጠው ሰው መንገድ አሳብራ የጓደኞቿን እጅ እየጎተተች ትሸሻለች፡፡ “ወንድሜ በሬ አገባ” እያለች ነው የምታወራው አሉ!

ወንድሜ ሀናን አይወዳትም፡፡
"ለስንት ስንጠብቅህ እዚሂች አዚፋ ጋር ትወዘፋለህ” ይለኛል፡
&አዚፋ' ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ግዴለም ሀኒዬ 'አዚፋ ከሆነች፣ አዚፉ ይባረክ ! ስድብ ሰውን ካረከሰው፡ ሰው ስድቡን ስለምን አያከብረውም? ሀኒዬ አዚፉን አከበረች… እወዳታለሁ፡፡

ሀኒ ቆንጆ አይደለችም፡፡ የኔ ቆንጆ፣ ቆንጆ አይደለችም፡፡ "ኪንኪ ፀጉሯ ጠዋት ስትነሳ ያስፈራል”
ይላሉ፣ አዎ እውነት ነው፡፡ “አፍንጫዋ በአይኗና ቀላይኛው ከንፈሯ መካከል ያለ ሁለት የሽንቁር ነጥብ ነው እያሉ ያሟታል…እውነት ነው !!

ከንፈሯ ወጣ ወጣ ባሉ ጥርሶቿ (ገጣጣ ነው እነሱ የሚሉት) ከርስቱ ተገፍቷል፡፡ በዛ ላይ
ብትስቅ ዞሮ ማጅራቷ ላይ ይዘያየራል ይላሉ፡፡ አዎ እውነት ነው !!

የጣቶቿ መዶልዶም ከዘጠኝ ዓመቷ እስከ አስራ ዘጠኝ ዓመቷ 10000000000000000000
ኩንታል ገብስ ሳታቋርጥ የወቀጠች ያስመስላታል" ቢሉም (ተጋነነ እንጂ) እውነት ነው !!

“እግሯ ከየትኛውም ጫማ እንዲጣላ ተደርጎ ነው የተፈጠረው” ያሉትም አልዋሹም፡፡

lዚህ ሁሉ መናቅ፣ በዚህ ሁሉ መገፋት ተገፍታ እኔ የምባል ጥግ ላይ ደረሰች የሀኒ ዓለም
መጨረሻ፡፡የት ትሂድላቸው? አለሁላት ወንድሟ ነኝ:: ፍቅረኛዋ ነኝ፡፡ባሏም ነኝ!! አላፍርባትም፡፡
ኮራባታለሁ !! ሀኒዬ የኔ ናት:: ማነው እኔን አልፎ የሚዘልፉት ወንድ ?' የኤሌክትሪክ አጥሯ
ጠባቂ ውሻዋ ነኝ፡፡ ከእግሯ ስር የማልጠፋ::ባለቤቱ ያላከበረው አሞሌ፡ ወላ መልኩ ወላ
ዘመናዊነቱ አያስከብረውም፡፡ አንዱ የወረወራቸው አይደሉ ሌላኛው መኪና ላይ የሚኮፈሱት!
የተናቁ አሞሌዎች !! ሀኒዬን አከብራታለሁ !! እግዜር ያውቃል ልቤን !!

“ጥርስሽ አያምርም ቢሏት ከሳቅ ተጣላችላቸው፡፡ ሰው ፊት አትስቅም ሀኒ፡፡ የመጻፍ መብታችን፣የመሰለፍ መብታችን ተነካ የሚሉ የአገሬ ልጆች፣ የህኒዩን የመሳቅ መብት በአደባባይ ነጠነቁ፡፡እስካሁን ሻይ ቡና ለማላት ካፍቴሪያ መግባት ያስፈራታል፡፡ ራሷ ቤት ውስጥ ስትቀመጥ እንኳን እግሮቿን ሶፋ ስር ልትደብቅ ይከጅላታል፡፡ በመንገድ ዳር ዘለፋ መሳቀቅን ሸልመዋታል፡፡ ሰው ለሰላምታ ስትጨብጥ ትሳቀቃለች፡፡ የመዳፏን ሻካራነት በየጭብጡ የሚጮኸ አዋጅ አድርገው
ልቧ ውስጥ ተክለውባት፡፡

ሆኒዩን ቆንጆ ካልሆንሽ ሰው ከመሆን መንበር ተንኮታኩተሻል” ብለዋታልና ቆንጆዎች አምላክ
ይመስሏታል፡፡ የሴት ልጅ የክብር ጥጉ በየሆቴሉ ወንበር ተጎትቶላት መቀመጧ ነውን ? በአደባባይ
መታቀፍስ የፍቅር ኦሜጋ ሆኖ የታወጀው መቼ ነው ? እየተውረገረጉ የወንድ ጭብጨባ
ያደነቆራቸው ሀኒዬን ቃል ሳያወጡ በድርጊት ቀበሯት፡፡

አነሆ ለአንዲት ደሀ.ለአንዲት መልከ ጥፉ ደሀ ተልኬ የምታስተናግድበት ተራ ሻይ ቤት ተከሰትኩ፡ ያውም 'አዩኝ' ብሎ የሚቆሽሽ ነጭ ሸሚዝ ባማረ ጂንስ ሱሪ ለብሼ፣ ጥቁር መነፅሬን ሰክቼ እየተቆነንኩ በረንዳው ላይ ካሉት ወንበሮች በአንዱ ላይ ሰፈርኩ፡፡

“ምን ልታዘዝ!” አለች ሀኒዬ እየተሸቆጠቆጠች፡፡ ሳያት ላማትብ ቃጥቶኝ ነበር፡፡ እግዜር ሰውን
የት ድረስ ውብ እንደሚያደርግ አውቃለሁ፡፡ የት ድረስ መልከ ጥፉ አድርጎ እንደሚፈጥር እነሆ
የእጁን ውጤት ፊቴ አቁሞ አሳየኝ፡፡ “አቤት ችሎታው ምን ይሳነዋል!” አልኩ ::

ስራዬ በዛው ግድም ነበርና ደጋግሜ ሳያት ከቀን ወደቀን እየባሰ የሚሄድ ይሄ ጎደለው የማይባል ፍፁም የሆነ አስቀያሚነት እንዳሸከማት እየተገረምኩ ታዘብኩ፡፡ ግና የገረመኝ፣ “አቤት ስታስጠላ
እያልኩ ላያት መፈለጌ ደንበኛ ሆንኩ፡፡

“ምን ልታዘዝ?"

"ቡና"

"ምን ላምጣልህ?"

“ቡና”

“ሰላም! ምን ላምጣልህ?”

“ቡና”

“ቡና ነው ዛሬም” (ፈገግ ለማለት እየሞከረች)

"አዎ" (በፈገግታ)

ከዛ ሳላዛት ቡና አመጣችልኝ…ቡና..ቡና….ቡና.…ሰላምታ ሀና ነው ስሟ፣ አንድ ቀን ጠየቅኳት…
ነገረችኝ፡፡ ስራ ከሌላት አጠገቤ ትመጣለች እናወራለን…እንዴት ደስ እንደምትል፡፡ ትልልቅ ጡቶቿን አልፎ ልቧ ይታያል ንጹህ ነው !

አንድ ቀን ከጎኔ የተቀመጡ ተስተናጋጆች "የሰው ጅብ” ሲሏት ጆሮዬ ጥልቅ አለ ያዘዝነው ዘገየብን ብለው !! በመሰደቧ ሳይሆን እኔ ፊት በመሰደቧ
በመሰደቧ የቅስሟ መስተዋት
ክፍት አፍ በወረወረው የዘለፉ ጠጠር ሲንኮታኮት ፊቷ ላይ እንዴት አንጀት የሚበላ መሳቀቅ አየሁ፡፡ ተሳዳቢዎቹ ጋር
የነበረች አንዲት ሴትም ላንቃዋ እስኪላቀቅ ሳቀች፡፡ አዘንኩ፡፡ ለምን አዘንኩ እኔንጃ !!
👍30😁4
የውበት ጥርሳቸውን ስለው ወንዱን ሊከረትፉት ከተማውን በቀን የወረሩት ሴቶች ያውም የጉም ጅቦት ላይ አፋቸውን ለአድናቆት ሲበረግዱ የሚውሉ ዘመናዊ ተብዬ ቅርፊት የከተማ ወንዶች፣አንዲት ደሀ ሚስኪን “የሰው ጅብ!” ብለው ተሳሳቁ፡፡ሰርታ በኖረች በጅብ አፋቸው ጅብ አሏት፡፡

በቀጣዩ ቀን አንገቷን ደፍታ፣ ምን ልታዘዝ?” አለችኝ በመከራ አንገቷን ብቅ ካደረገችበት
ግንኙነት በዘለፋ ኩርኩም ወደ ትንሽነት መልሰዋት ከ ሀ እስጀመሯት፡፡

"ስልክ እለሽ? አልኳት፣

"ቡና” የምል መስሏት ልትመለስ ካለች በኋላ ያልኩትን ባለማመን፣

"እ" አለችኝ

"ስልክ ቁጥርሽን ስጭኝ!"

“የድርጅቱኝ ነው?” ስትል ጠየቀችኝ፤

"ያችን የራስሽን!"

ዝም አለች:: ቆይታ…ቆይታ

"ዐ9…" አለች

"09 አልኳት ስልኬ ላይ እየፃፍኩ
"እ 09…" ፈራች፡፡ ማመን ከበዳት ፤ የኔ ሚስኪን! ጀግናው ወገኗ፣ ዘላፊ ወገኗ፣ ሃይማኖተኛ
ህዝቧ የገደላት…ሙት መቃብሯን ለመፈንቀል ሁሉም በየአፉ የወረወረባትን ድንጋይ፣ በአሽሙር
አካፋው በለበጣ መጋፊያው የመለሰባትን የቀብር አፈር መፈንቀል ከበዳት፡፡

“በዚህ ምልክት አድርጊልኝ እጠብቅሻለሁ' ብዬ ቁጥሬን ያመጣችው ደረሰኝ ላይ ፅፌ ሰጠኋት…

የሴት ክብር መሳም ነው ? መታቀፍ ነው ? ተስመው የተወረወሩ፣ ታቅፈው የተሸቀነጠሩ
ይናገሩ፣ ሴት ልጅ ያመነችው ወንድ፣ ጣላት፣ ተዋት! ከሚል አሽሙር ሲታደጋት፣ ያኔ ነው
ክብር ቦታዋ ላይ የምትቀመጠው: ሴት ልጅ ስታፈቅር እድሜዋን ነው ሸርፋ የምትሰጠው::
ሸራርፈው ሸራርፈው ሴቶቹን ከእድሜያቸውም ከውበታቸውም አጤልተው ገሸሽ ያሉ ወንዶች
ይስሙ! እኔ ሽቅርቅሩ ሀናን ወደድኳት፣ ወረተኛ አይደለሁም፡፡ ምንም ቢመጣ አልተዋትም፡፡
አዝኜ አይደለም፡፡ ሰማኋት፣ አይኔን ሳልወድ በግድ አስጨፈነችኝ፡፡

መንገድ ላይ ሀኒዬን በኩራት ሳቅፋት፣ የሚታቀፍ ጠፍቶ ይላሉ ሊታቀፉ ከየቤታቸው የወጡ እቅፍ ናፋቂዎች ሁሉ

ስስማት የሚያቅለሸልሻቸው አይናቸውን አዞሩ፡፡ ሀኒዩን አበድኩላት " ሆና ሴት ናት !! እግዜር
“ሴትነትን መደበቂያ ቢያጣ ባልረባ ስጋ ጠቅልሎ ያኖረባት የክብር መዝገብ፡፡ ወንዶች እግር
ላይ ሴትነትን ሲፈልጉ፡፡ ያማረ አፍንጫና ጥርስ ላይ ሴትነትን ሊያጠምዱ መንጠቆ ሲወረውሩ
እግዜር እንቁውን የት እንዳስቀመጠው ተመልከቱ፡፡

አገባታለሁ ሀናን “አገባታለሁ ያልኩ ቀን ሙሾ ባይነት ባይነት ወረደ፡፡ ሀና ራሷ ደነገጠች፡፡ከዛ በፊት እንዲሁ ከምቀር ፍቅር የሚባለውን ነገር ልሞከረው ቢያንስ ከትዝታው ጋር እኖራለው ብላ እንጂ፡ ያገባኛል ብላ በምን ጠርጥራ(በኋላ እንደነገረችኝ)፡፡

ተወራ በመንደሩ፣ አብርሀም ቡጡቃ ሻይ ቤት ያለችውን “ሆረር ሊያገባ ነው"

“እትቀልድ ባክ"

“ማርያምን?"

“ክርስቶስ ምስከሬ"

“ወላሂ”

“አበደ እንዴ?”መካሪ የለውም?

ተቀባበሉ ወሬውን

ለከብሩ…ለወጉ ለመዓረጉ፡ “ሀኒን ላገባት ነው ! ዳሩኝ!” አልኩ ቤተሰቦቼን፣

“አያገባም !!” አሉ፡፡

የራሳችሁ ጉዳይ! ብያቸው ከሀኒ ጋር አብረን መኖር ጀመርን፡፡ ወላ ቤተሰብ፣ ወላ ጓደኛ ድራሹ ጠፋ፡፡ ሀኒዬን ወደድኳት፡፡ ከዚህ ሁሉ አሰቃቂ መልከ ጥፉነት መሀል የተረፉት ጡቶቿ መስውሰውኝ በስሜት እንዳይሆን የወደድኳት ብዬ ጀማው ሲንጫጫ ፈራሁ…ኧረ ሀቂቃው ፍቅር ነው !!

አራት ዓመት አሳት በሆነ ፍቅር ኖሮን፣ ባሰብኝ ወደድኳት፡፡ ይሄው እርጉዝ ናት፤ ያውም የስምንት ወር፡፡ ሀኒ እኔ ጋር ትስቃለች፡፡ እኔ ጋር እግሯን አትደብቅም፡፡ በነበረው ግዝፈት ላይ እርግዝናና ያሳበጠው አስቀያሚ እግሯን ጉልበቴ ላይ አስቀምጬ ሳሽላት እንዴት ደስ እንደሚለኝ..

"አብርሽዬ"

"ያ እላታለሁ"

"እንትን ፈልጌ ነበር"

"ምን.." በቦታህ አብርሽ! ተዘጋጅ!

"ሰ" ሂድ ዲዲዲዲዲዲ ስጋ ስዕል (ከሰዓሊ ጓደኛዬ).ስስ ፒጃማ ስንግ ስራስር ነገር(ድንች፣
ቀይ ስር፣ ካሮት) ስእለት (ለማሪያም ሀኒ በሰላም ትገላገል ብዬ) እያለከለኩ ስመለስ፣ ውይ
አብርሽዬ……ስልኬን አቀብለኝ ለማለት ነበርኮ፧ ሮጥክብኝ…ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ…እኔ ፊት ስትስቅ
አትሳቀቅም ሀኒዬ !!

አለቀ
👍47👏181
#ምንዱባን


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


.....ማሪየስ ፤ ሰማህ? አንተ ብሎ ባሮን እነዚያ ሽፍቶች ፤ ቀማኞች ፧ አታላዮች ፤ አታላዮች ፤ አታላዮች እውነተኛውን ንጉስ
ከድተው ቦናገርቴን የተከተሉ ፈሪዎች ፧ የፈሪ ፈሪዎች ናቸው:: ዋተርሉ ላይ ጠላቶችን ፈርተው የሸሹ ወርቦለች! ይኽ ነው እኔ የማውቀው::አባትህ ከነዚህ ዉስጥ ከሆነ አዝናለሁ አላውቀውም ብል ይሻላል

መሴይ ጊልኖርማንድ በቃላት ወናፍ ሲያራግቡት ማሪየስ በተራው ጨሰ፣ ተናደደ ፤ ቁጣው ገነፈለ፡፡ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡፡ የሚያደርገውን አጣ፤ የሚናገረውም ጠፋው፡፡ የአባቱ ስም ከፊቱ ተረገጠ፤ ተናቀ፡፡ በማን
በአያቱ፡፡ ታዲያ እንዴት ይበቀል? አያቱን መልሶ እንዳይሰድብ ያስነውራል::ዝም እንዳይልም አሳቡ ዘገነነው፡፡ በአንድ በኩል የአባቱ መቃብር በሌላ በኩል የአያቱ ሽበት ታየው፡፡ ነገሩ ሁሉ ስለተምታታበት ፈዝዞ ቀረ ።
ጥቂት ቆይቶ ቀና በማለት አያቱን አፍጥጦ አያቸው::

«በርበኖችና ትልቁ አሳማ ልዊ 18ኛ ይውደሙ» ሲል በታላቅ ቁጣና ጩኸት ተናገረ::

ንጉሡ ልዊ 18ኛ ከሞቱ አራት ዓመት አልፎአል:: ግን ለማሪየስ
ለውጥ አላመጣም::

ሽማግሌው በድንገት ፊታቸው በንዴት ብዛት ከፀጉራቸው ጀምሮ
ጠቆረ፡፡ ከዚያም ቃል ሳይናገሩ አንዴ ወደ መስኮት፧ አንዴ ወደ በሩ
በዝግታ ተራመዱ፡፡ ቀጥሉም እንዳረጀ በግ ድምብርብራቸው ወደ ወጣው ሴት ልጃቸው ዞር ብለው ፈገግ በማለት የሚቀጥለውን ተናገሩ፡:

«እንደ መሴይ ያለ ባሮን እንደ እኔ ያለ ቡርጓዥዋ ከአንድ ጣራ ስር
ለማኖር ያዳግታል፡፡» ሰውነታቸው እየተንቀጠቀጠና ቁጣቸው እንደነበልባል ከፊታቸው
ላይ እየሰራ ቀጥ ብለው ቆሙ:: እጃቸውን ወደ ማሪየስ ዘርግተው «ከዚህ ቤት ውጣልኝ» ሲሉ ጮሁ:: ማሪየስ ከቤቱ ወጣ፡፡
በሚቀጥለው ቀን ለሴት ልጃቸው ሲናገሩ «ለዚህ ደም መጣጭ
በየስድስት ወር ስልሣ ፒስትልስ ትልኪለታለሽ፤ ለእኔ ግን ሁለተኛ ምንም ነገር እንዳታነሺ» ሲሉ አዘዙ፡፡

ነገሩ በጣም ስላሳዘናቸውና ስላናደዳቸው በሚቀጥሉት ሦስት ወራት የሚይዙትንና የሚጨብጡትን አሳጣቸው:: ሴት ልጃቸውን ሲያነጋግሩ እንኳን እጅግ ቀዝቀዝ ብለው ነበር፡፡

ማሪየስ ከቤቱ የወጣው ወደዚያ ቦታ ነው የምሄደው ሳይል ነበር
እነርሱም የት እንደሚሄድ አልጠየቁትም:: ጋሪ ተከራይቶ ዘልሉ ከገባ በኋሳ ጋሪው ወደ መራው ሄደ፡፡

ማሪየስ ምን ሊያደርግ ነው?

የእህቤሴ ጓደኞች

ማሪየስ ከቤቱ በወጣበት ጊዜ የለውጥ አየር ይነፍስ ነበር፡፡ ሰው ሁሉ ሳይታወቀው ንቅናቄ ውስጥ እየገባ አብዮተኛ ሆኖኣል፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ አንድ እርምጃ ወደፊት ተራመደ፡፡ ንጉሣውያን ቤተሰብ እንኳን ሳይቀሩ በነገሩ ገቡ።ሰዎች ከጊዜ በኋላ ናፖሊዮንንና ነፃነትን እንደ አምላክ የማምለክ ስሜት አደረባቸው:: ሌሎች ደግሞ ዓለም ፍጹም እንድትሆን ተመኙ::
የዛሬው ምኞት ነገ ሥጋና ደም ለብሶ እሙን እንደሚሆን አመኑ፡፡

የአህቤሴ ጓደኞች እነማን ናቸው? አህቤሴ የተረገጡ፤ የተከፉና
የተረሱ ጭቁኖች ሲሆኑ እነዚህ ሰዎች በፖለቲካው እንቅስቃሴ ሳቢያ ብዙ ወዳጆች ያፈሩ ናቸው:: ጓደኞቻቸወም ከወደቁበት እንዲነሱ ከልብ ተመኙ:: ሰዎቹ ብዙ አልነበሩም:: ፓሪስ ከተማ ውስጥ ሃሌስና ኮርኒት ከተባሉ ሥፍራዎች በየጊዜው ከአንዲት አነስተኛ ቡና ቤት ውስጥ
ይሰበሰባሉ: ሥፍራው ወዛደሮች የሚኖሩበት አካባቢ ነው:: በዚያ አካባቢ ተማሪዎችም በብዛት ይገኛሉ፡፡ የአህቤሴ ጓደኞች የሚሰበሰቡበት ቡና ቤት
«ካፌ ሙሴን» ይባላል፡፡ ቡና ቤቱ ሰፊ ጓዳ ስለነበረው የአህቤቴ ጓደኞች ከዚያ ክፍል ውስጥ ይሰበሰባሉ:: ክፍሉ ከዋናው መጠጫ ክፍል ትንሽ ራቅ
ያለ ነበር፡፡ በጓሮ በኩል ወደ ውጭ የሚያስወጣ በር አለው::

ጓደኛሞቹ ከዚያች ክፍል ውስጥ ይጠጣሉ፤ ሲጃራ ያጨሳሉ:፧
ይጫወታሉ፤ የፖለቲካ ወሬ ያወራሉ:: የማያነሱት ነጥብ የለም፡ከክፍለ ግድግዳ ላይ የበፊቱን የፈረንሳይ ሪፑብሊክ ካርታ ሰቅለዋል።

የዚህ ቡድን አባሎች አብዛኞቹ ተማሪዎች ሲሆኑ ጥቂት ወዛደሮችም ነበሩበት፡፡ ጥቂት ቀንደኛ መሪዎች አሉዋቸው:: ከመሪዎቹ መካከል ኔንጀልራስ የተባለው የሀብታም ልጅ ቀንደኛ መሪ ሲሆን ደስ የሚልና
መልከ መልካም ወጣት ነው:: ደግሞም በጣም አዋቂ ከመሆኑም በላይ ወኔው ለጉድ ነው:: ከቀንደኛው መሪ ከኢንጆልራስ ጎን የተሰለፉ ሌሎችም ረዳት መሪዎች አሉ::
አንዳንዶቹ በፖለቲካው ሌሎቹ ደግሞ በሰው ልጅ ፍቅር የሰከሩ ናቸው:: አንዳንዶቹ ‹‹ጭቁኖችን ነፃ እናወጣለን ብለው የተነሱ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ «አገራችን ውስጥ አድልዎ የተለየው ትክክለኛ ፍርድ እንዲሰፍን ጽኑ እምነታችን ነው» የሚሉ ናቸው::

ሆኖም በመካከላቸው አንድ ተጠራጣሪ ሰው ነበር፡፡ ታዲያ የሕዝቦችና የግለሰብ መብት፧ የፈረንሳይ አብዮት ፧ ሪፑብሊክ ፧ ዲሞክራሲ ፧ ለሰው ሥልጣኔ፤ ሃይማኖት፧ መሻሻልና የመሳሰሉት ቃላት ለእርሱ ትርጉም የላቸውም:: እነዚህን ቃላት በሰማ ቁጥር ይስቃል:: ታዲያ ከነዚህ የተለየ ዓላማ ካላቸው ሰዎች መካከል ይህ ሰው እንዴት ሊደባለቅ ቻለ?

ይህ ሰው ተጠራጣሪ ቢሆንም የራሰ እምነት ነበረው:: እምነቱ
በኢንጂልራስ ላይ ነው:: ኢንጂልራስን ይወደዋል፣ ያደንቀዋል፣ ያምንበታል::
ለዚህ ነው በዓላማ አንድ ከነበሩና እንደ ቤተሰብ ከሚተያዩ ሰዎች መካከል ሊገባ የቻለው:: ኢንጆልራስ ይህን ተጠራጣሪ በፍልስፍና ወይም በነበረው
የተለየ አሳብ ሳይሆን በጠባዩ ነው የገዛው፡፡

አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ፤ ሕይወት በአጋጣሚ የተሞላች ናትና፧
አንድ ነገር በአጋጣሚ ይሆናል፡፡ ከፈረንሳይ አብዮት ጠንሳሾች መካከል አንዱ ከካፌ ሙሴን በራፍ ግድግዳ ተደግፎ ቆሞአል:: እርሱ ከዚያ እንደቆመ ጋሪ በዚያ በኩል ያልፋል፡፡ ይህ ሌግል የተባለ ወጣት ጋሪውን ሲመለከተው
በጣም ዝግ ብሎ ስለሚሄድ አንድ ነገር እንደሚፈልግ ጠረጠረ:: አነስተኛ ሻንጣ የያዘ ሰው ጋሪው ላይ ከነጂው ጎን ቁጭ ብሎአል፡፡ ሻንጣው ላይ ማሪየስ ፓንትመርሲ የሚል ጽሑፍ በጉልህ ተጽፎበት ስለነበር ሌግል ጽሑፉን ያነባል::

ማሪየስ ፓንትመርሲ የሚለው ስም በጣም ማረከው:: ጋሪው ከአጠገቡ ሲደርስ «መሴይ ማሪየስ ፓንትመርሲ» ሲል ተጣራ:: ጋሪው ቆመ:: ጋሪው
ላይ የነበረውና በአሳብ መጥቆ ሄዶ የነበረው ወጣት ቀና አለ፡፡
«ምን ነበር?» ሲል ጠየቀ፡፡
«መሴይ ማሪየስ ፓንትመርሲ ማለት አንተ ነህ?»
«ነኝ፡፡»
«ስፈልግህ ነበር፡፡»
«እንዴት ሊሆን ይችላል? አታውቀኝ፤ አላውቅህ» ሲል ማሪየስ ጠየቀው
«ትናንት ትምህርት ቤት አልመጣህም፡፡»
«ላልመጣ እችላለሁ::»
««በርግጥ አልመጣህም::
‹‹ተማሪ ነህ አንተም?»
«አዎን፧ እንዳንተው ተማሪ ነኝ:: ከትናንት ወዲያ ልክ ወደ ክፍል
ልገባ ስል፧ አለ አይደል አንዳንዴ አስተማሪዎች ሦስት ጊዜ ስምህን ሲጠሩ አቤት ካላልክ ይሠርዙሃል፡፡ ስልሣ ፍራንክ ቀለጠች ማለት ነው::»
ማሪየስ ዝም ብሎ ይሰማል:: ሌግል ንግግሩን ቀጠለ፡፡

«ብሎንዳው የሚባለው አስተማሪ ነበር ስም የሚጠራው፡፡ አስተማሪውን ታውቀዋለህ አይደል? ያ እንኳን ቀፋፊና ግትር አፍንጫ ያለው! የቀረ ተማሪ
👍18
የመዘገበ እንደሆነ ደስታው አይጣል ነው:: ስም ሲጠራ ሁሉም አቤት ስላለ በጣም ተከፋ:: ብሉንዳው ዛሬ የሚቀጡት ሰው ስላላገኙ አዘኑ የኔ ፍቅር አልኩ በልቤ፡፡ በድንገት ወዲያው ማሪየስ ፓንትመርሲ ሲል ይጣራል፡፡ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንደገና ማሪየስ ፓንትመርሲ ሲል
ተጣራ፡ ብዕሩን አነሳ፡፡ ተቅማጥ ያዘኝ:: ስሙ ጎበዝ፤ ይህን ተማሪ እናድነው፧ ሞት ለብሉንዳው አልኩኝ በልቤ፡፡ ብዕሩን እንዳነሣ ለሦስተኛ ጊዜ ማሪየስ
ፓትመርሲ ሲል ተጣራ:: እኔ እንዳቀረቀርኩ 'አቤት' ስል መለስኩለት:: ስምህ ከመሰረዙ ዳነ፡፡›

" ጌታው..!» አላ ማሪየስ::
«ጌታማ ነበርኩ» ሲል ሌግል መለሰ::
«አልገባኝም» አለ ማሪየስ፡፡
ሌግል ወሬውን ቀጠለ፡፡
ስሜ ሌግል ይባላል፡፡»
«ሌግል፧ ደስ የሚል ስም ነው» አለ ማሪየስ፡፡
«አቤት ብዬ ስመልስ አስተማሪው ነብር መስሉ ቀና ብሎ ያየኛል፡፡
አንተ ፓንትመርሲ ከሆንክ እንግዲያው ሌግል አይደለህም' ሲል ስሜን ከዝርዝሩ ውስጥ ፋቀው፡፡»
«በጣም አዝናለሁ» ሲል ማሪየስ ጣልቃ ገባ፡፡ ሌግል ከት ብሎ ሳቀ::

«እኔ እንደሆነ ደስ ነው ያለኝ:: አንተ ከገባህበት የሕግ ትምህርት ልገባ
ገና ትምህርቱን ልጀምረው ስል ይህ አጋጣሚ አዳነኝ:: ስለዚህ በዚህ ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ አንተን ላመሰግን እንጂ! ለመሆኑ የት ነው የምትኖረው?»

“ከጋሪው ላይ» አለ ማሪየስ እንደማፌዝ ብሎ::

የቱጃርነት ምልክት ነዋ!» ሲል ሌግል መለሰ:: «እንኳን ደስ ያለህ::
በአመት ወደ ዘጠኝ ሺህ ፍራንክ ነው ለባለጋሪው የምትከፍለው?»

ልክ ሌግል ይህን ሲናገር ጓደኛው ኩርፌይራ፡ ከቡና ቤቱ ብቅ አለ::
ማርያስ የመገረም ፈገግታ አሳዬ

ካጋሪው ሳልወርድ ለሁለት ሰዓት ያህል ተንቀዋልያለሁ:: አሁን
ግን ቢበቃኝ ይሻላል:: የት እንደምሄድ ግን አላውቅም ብል ለወጣቶች አዲስ ነገር አይሆንም::»

«አይዞህ» አለ ኩርፌይራክ፣ «ከእኔ ቤት ልንሄድ እንችላለን::
ያን እለት ወደ ማታ ኩርፌይራክ ከሚያርፍበት ሆቴል ማሪየስ |
አብሮ ሄደ፡፡

በጥቂት ቀናት ውስጥ ማሪየስና ኩርፌይራክ በጣም ተቀራረቡ::
በወጣትነት ዘመን ወዳጅ ማፍራት ቀላል ነው:: ማሪየስ ጓደኛው ኩርፌይራክ እስካለ ድረስ ደስ እያለው በነፃነት ይኖራል:: እንደፈለገው ነፃ ሆኖ መኖር ና?
ለእርሱ አዲስ ነገር ነበር፡፡ ኩርፌይራክ ጥያቄ በማብዛት አይነተርከውም፡ እነርሱ በደረሱበት የወጣትነት እድሜ ንትርክ እንደሚጠላ ኩርፌይራክ
ጠንቅቆ ያውቃል፡፡

ኩርፌይራክ ማሪየስን ወደ ካፌ ሙሴን ይዞት ሄደ:: ከዚያም ፈገግ
እያለ ወደ ጆሮው ጠጋ ብሎ «የንቅናቄው አባል እንድትሆን የመግቢያ ፈቃድ እሰጥሃለሁ» ሲል አንሾካሾከለት:: የእህቤሴ ጓደኞች ከሚሰበሰቡበት ክፍል ወሰደው:: ከሌሉች አባሎች ጋር «ተማሪ ነው»ሲል አስተዋወቀው።
ለምን ተማሪ ነው ብሎ እንዳስተዋወቀው ማሪየስ አልገባውም::

የማሪየስ አስተዳደግ የብቸኝነት ሲሆን እንዲህ ዓይነቱን ግርግር
አልለመደውም:: ወጣቶች በብዛት ተሰባስበው እርስ በእርስ ሲፋጩና በአንድ ላይ ሲወያዩ ለእርሱ አዲስ ነገር ነው:: አንዳንድ ተስፈንጣሪዎች በነገር
ስለሚነካኩ በመጠኑም ቢሆን ይደናገረዋል:: እነዚያ ወጣቶች ሁሉ በነፃነት እንደዚያ ሲወያዩ ገረመው:: አንዳንዴም ከመገረም አልፎ ይደነቃል፡፡ እነዚያ ወጣቶች በአስተሳሰብ በተለይም በፖለቲካ ጉዳይ መጥቀው ሄደዋል።
ወጣቶቹ ስለፍልስፍናና፧ ስለሥነጽሑፍ፤ ስለታሪክ፤ ስለሃይማኖት፧ ስለሥነ ጥበብና ስለመሳሰሉት ነገሮች ሲወያዩ አልፎ ኣልፎ መከታተል ይሳነዋል።
የአያቱን አስተሳሰብ ጥሎ የአባቱን በተከተለ ጊዜ ሁለተኛ የአሳብ ግጭት የሚደርስበት አልመሰለውም ነበር፡፡ ግን ባይናገረውም እንደዚያ አልሆነም፡፡ ቀደም ሲል የነበረው ማንኛውም አመለካከት ቀስ እያለ ይለወጥ ጀመረ፡፡
አንዳንዴም አሳብ እርስ በእርስ እየተጋጨበት ከግራ ወደ ቀኝ ያወዛውዘዋል፡፡ይህም እስከ መሰቃየት አደረሰው::

ወጣቶቹ የሚፈሩት ወይም በነፃነት የማይወያዩበት ነገር አልነበረም፡፡
እነርሱ የሚወያዩበት ነገር እርሱን በጣም ያስፈራዋል:: ስለንጉሱና
ስለናፖሊዎን እያነሱ በነፃ ይወያያሉ።

ማሪየስ ከዉይይቱ፡ ወስጥ ገብቶ አሳብ የሰጠ እንደሆነ ራሱ
ይገርመዋል:: አንድ ቀን ማታ የእህቤሴ ጓደኞች በሙሉ መጥተው ስብሰባ ይካሄዳል፡፡ ትልቁ መብራት ስለበራ ክፍሉ ወለል ብሏል፡፡ አርእስት እየቀያየሩ
ይወያያሉ፡፡ ውይይቱ ሲካሄድ ብዙ አይንጫጩም:: ስለዋተርሉ ጦርነትና ስለ ለናፖልዮን ወሬ ሲነሣ ማሪየስ ሳያስበው በድንገት ብድግ ብሎ ንግግር ይጀምራል

«እኔ አዲስ መጤ ነኝ፣ ሆኖም እስካሁን በሰማሁት በጣም ነው
የገረማችሁኝ:: የት ነው የምናመራው? እኛ ማን ነን? እናንተ ለመሆኑ እነማን ናችሁ? ወጣቶች መስላችሁኝ ነበር፡፡ ታዲያ ወኔያችሁን ምን ሰለበው?
ናፖሊዮንን ካላደነቃችዉ ማንን ልታደንቁ ነው? ከእርሱስ ይበልጥ መሪ ማንን ነው የምትፈልጉት? ያንን ትልቅ ሰው ካልወደዳችሁ ከእርሱ የተሻለ ማንን ልታመጡ ነው? ጓደኞቼ ስለእውነት ተናገሩ፡፡ ከእርሱ ይበልጥ ለሕዝብ የቆመ መሪ ከየት ሊመጣ ነው! ትልቅ መንግሥትና ታላቅ ጦር መፍጠር፤ እንደ ኣእዋፍ ሠራዊቱን በየተራራው ለማስራጨት፤ ከባድ
ክፍለ ጦር ለማሠማራት፤ ለማጥቃት፧ ለማርበድበድ ፤ አውሮጳ ውስጥ ተከብሮ ለመኖር፧ በታሪክ አምድ ከፍተኛ ሥፍራ ለማግኘት፤ ዓለምን አንዴ ሳይሆን ሁለቴ ለማሸነፍ ከእርሱ ይበልጥ ታላቅ ሰው ማን አለ? ከዚህስ ይበልጥ የከበረ ነገር ምን ይገኛል?»

«ነፃ መሆን» አለ ከስብሰባው ተሳታፊ አንዱ፡፡ ማሪየስን ለጥ ብሎ እጅ ነሳው። «ነፃ መሆን» በማለት የተጠቀሱት ቃላት አጥንቱን ሰርስረው ነው የገቡት ቀና ቢል መልስ የሰጠው ሰው ከነበረበት የለም:: አንድ ሰው ቶሎ
ቶሎ እያለ ሲዘፍን ተሰማ:: ዘፈኑ ስለጁለየስ ቄሣር የተዘፈነ ነበር:: ማሪየስ ውድ እናቴ» እያለ አዜመ:: ኤንጀልራስ ከኋላ መጥቶ ትከሻውን መታ መታ አደረገው።

«ወንድም፤ ውድ እናት ማለት እኮ ሪፑብሊክ ናት» አለው::

ማሪየስ ከሁለት እምነት መካከል ይወጠራል:: የጥንቱን ጨርሶ
ከሕሊናው አላስወጣም፤ አዲሱም ከልቡ ውስጥ ሥር አልሰደደም:: የትኛውን ያጠንክር? ከሁለት አንድ መምረጥ ቀላል አይደለም:: ለመወሰን ትክክለኛውን መንገድ የሚያሳይ መብራት ያሻል፡፡

ማሪየስ ለመቀጠል፤ ወደፊት ለመራመድ፤ ለማሰብ፤ ለመመራመር ሁኔታው ያስገድደዋል:: ወደፊት በሄደ ቁጥር አባቱን የቀረበ ይመስለዋል:
ከአባቱ እምነት ለመራቅ ደግሞ አይፈልግም:: ከአያቱም ሆነ ከጓደኞቹ ጋር በአሳብ ተራርቋል፡፡ ወደ ካፌ ሙሴን መሄዱን አቆመ::

በሕይወት፧ ለማሰላሰል የማይፈልጉትን ነገር ከጭንቅላት አውጥቶ ለመጣል ያዳግታል፡፡ ይህም በመሆኑ ሁለት ተቃራኒ አሳቦች ከሕሊናው ሊወጡ አልቻሉም:: አንድ ቀን ጠዋት የሚኖርበት ሆቴል ጠባቂ ከክፍሉ . ይገባሉ::

«መሴይ ከርፌይራክ ለአንተም ኃላፊ ነው?»
«አዎን»
«ግን ገንዘብ ያስፈልገኝ ነበር!»
«ኩርፌይራክ እንዲያነጋግረኝ ይንገሩት» አለ ማሪየስ፡፡

ኩርፌይራክ መጣ፧ የሆቴሉ ጠባቂ ከክፍሉ ወጣ፡፡ ማሪየስ በዓለም
ላይ የእኔ ነው የሚለው ዘመድ ወዳጅ እንደሌለው ለኩርፌይራክ ቀደም ብሎ ለመንገር ፈልጎ እንደነበር ገለጸለት::

«ታዲያ ምን ይሻልሃል?» ሲል ከርፌይራክ ጠየቀ::
👍131
«እኔ እንጃ!» ሲል ማሪየስ መለሰ፡፡
የማሪየስ አክስት የልብ ክፋት ስለሌላት ማሪየስ እንዴት ሆኖ ይኖር ይሆን ብላ በማጠያየቅ የት እንዳረፈ ትደርስበታለች፡፡ አንድ ቀን ማሪየስ ከትምህርት ቤት ሲመለስ አክስቱ የጻፈችለትን ደብዳቤ ያገኛል፡፡ ከደብዳቤው ጋር ስድስት መቶ ፍራንክ በፖስታ ታሽጎ ተሰጠው:: ማሪየስ ገንዘቡን
መልሶ ለአክስቱ ላከላት:: ከገንዘቡ ጋር ለመተዳደሪያ የሚሆን ገንዘብ ራሱ ለማፍራት መቻሉን በመግለጽ ትህትና የተሞላበት ደብዳቤ ጻፈላት፡፡ በዚያን ጊዜ ኪሱ ውስጥ የነበረው ገንዘብ ግን ሦስት ፍራንክ ብቻ ነበር፡፡

ገንዘቡን ለመመለሱ አክስቱ ለአያቱ አልነገረቻቸውም፡፡ አያቱ ቀደም ሲል ስለእርሱ ሁለተኛ እንዳታነሳብኝ ስላለ የማሪየስን ወሬ ማንሳት አልፈለገችም:: ማሪየስ እዳው ስለበዛበት ሆቴል ቤቱን ለቅቆ ወጣ፡፡....

💫ይቀጥላል💫
👍15🥰1
#ዶክተር_አሸብር


#አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም


ቦምብ እንዲኖረኝ እፈልግ ነበር!! እንደ እጅ ስልኬ በፈለግኩበት ሰዓት ቁልፎቹን የምጫነው…
የራሴ፣ የግሌ ቦምብ፡፡ ቦምብ ሲባል ግን ይሄ ሰባት ሰው አቁስሎ፣ ሁለት ሰው ገደለ መስተዋት ሰባበረ ግድግዳ ደረመስ የሚባለው ዓይነት ቦንብ ሳይሆን በጅምላ ፊቱን ያጠቆረብንን፣ በጅምላ
የበደለንን፣ በጅምላ የገፋንን ሕዝብ በጅምላ ድራሹን የሚያጠፉ ኒውክሌር ቦምብ።

ቡምምምምምምምምምም ሰፈራችንን የዶግ አመድ አዲሳባን ከነስሟ ድራሿን የሚያጠፋ..

ወይ አዲስ አበበ አወይ ሸገር ሆይ

ከተማ እንደጤዛ እልም ይላል ወይ

እየተባለ እስኪዘፈን ወላ ሙሾ እስኪወርድ ድረስ በቃ አዲስ አበባን ባዶ የሚያደርግ .እንጦጦን
ሳይቀር ከስሩ ነቅሎ ህንድ ውቅያኖስ የሚጥል አዲሳባ የምትባል ከተማ እዚህ ነበረች፡፡ ምክንያቱ ባልታወቀ ፍንዳታ ጠፋች” እንዲሉ ባለታሪኮች፤ ምከንያት ነጋሪ ባለታሪክ አይተርፍማ፡፡

ኒውክሌር ቦምብ እንዲኖረኝ እፈልግ ነበር፡፡ ሰዎች 'የግል ቤትና መኪና ቢኖረን ብለው
እንደሚመኙት ቦምብ ቢኖረኝ እያልኩ እመኝ ነበር፡፡ እዚሀ መሐል አዲስ አበባ ሲፈነዳ ንዝረቱ የሩሲያን የበረዶ ግግር የሚሰነጣጥቅ ካናዳ ሊታጨድ የደረሰውን የስንዴ አዝመራ
የሚያረግፍ ኒውክሌር ቦምብ፡፡
ይሄ የተመኘሁት ቦምብ ቢኖረኝ ለመጥፎ ነገር አልጠቀምበትም፡፡ እንደ ቤት ዕቃ እንደ ፍሪጅ
ቁምሳጥን በቀጥታ ወስጄ አቶ ቀሰመ ወርቅ ቤት ውስጥ መሐሉ ላይ አስቀምጠውና እንዲፈነዳ
ቁልፉን እጫነዋለሁ፡፡ ቡምምምምምምምምም ከእኛ ሰፈር ጀምሮ አፈር ነሽ ድንጋይ፣ ዛፍ ነሽ ተራራ ነሽ እየጠራረገ...ወደታች ወደ ሜክሲኮ ሕንፃውን ሁሉ አመድ እያደረገ መንገዱን ሁሉ
እየገለባበጠ ይወርድና ወደ ጦር ኃይሎች (አቶ ቀለመወርቅ እዛ ወንድም አላቸው ..ከዛ ወደ
አየር ጤና፣ ዓለም ባንክ (አዲስ ቤት እያስገነቡ ነው ተበሏል ዓለም ባንክ አካሳቢ)

በዚህ በኩል ደግሞ ከመስቀል አደባባይ አድርጎ ካዛንችስ ነሽ ሀያ ሁለት፣ መገናኛ፣ መሪ ሲኤምሲ እየጠራረገ በኮተቤ በኩል ሲቪል ሰርቪስ (እዛ የአቶ ቀለመወርቅ ትልቁ ልጃቸው ይማራል ይሄ ደነዝ ተምሮ ላይገባው የመንግሥት እህል ይፈጃል ! ፍንዳታው ወደ ቦሌ፣ ኢምፔርያል ገርጅም መሄድ አለበት በቃ !! ማነው የሚከለክለኝ የፈለግኩትን ማሰብ መብቴ ነው ማንም ሰው በሀሳሱ ቀአንድ ጀምበር ዓለምን ማጥፋት ይችላል እንኳን ይህቺን ቢጢቃ
ካላቅሟ የምትንጠራራ በውራጅ የምትንደላቀቅ አዲስ አበባን ቀርቶ፡፡

አዲስ አበባ አቅፋ ደብቃ ጠጅ እያጠጣች ጮማ አያስቆረጠች አንቱ ብላ ባኖረችው፣ ቀለመወርቅ
በሚባል ሰው በላ ጭራቅ ሽማግሌ ምክንያት አሸብር የሚባል ቂሙን የማይረሳ ጠላት አፍርታለች፡፡

እኔ ነኝ አሸብር፡፡ አዲስ አበባ አዲስነቷን ሳትወድ ተነጥቃ
'አዲስ ፍራሽ' ትሆናታለች የታባቷ !!

መብቴ ነው በሀሳቤ ሕንፃዎቿን የፍርስራሽ ክምር ማድረግ ታሪክ ማድረግ፡፡ “እዚህ ላይ እኮ
ቀልበት መንገድ ነበር” እያለ ድሮ የሚያውቃት እስኪያዝንላት(ለወሬ ነጋሪ የሚተርፍ ካለ) አመድ ማድረግ ይህቺን አመዳም፣ የሰው ፊት እያየች የምታዳላን ወረተኛ ከተማ ንፋስ ያየው ዱቄት ማድረግ፡፡ ደግሞ ከሷም ብሶ አዱ ገነት…ኡኡቴ!!

እንዲህ እያልኩ ሳስብ ነፍሴ ትረካለች ውስጤ ይረጋጋል፡፡ አዲስ አበባን የተበቀልኳት
ይመስለኛል….ደስ ይለኛለ:: በቁጣ የጋላ ሰውነቴ ይቀዘቅዛል። አዕምሮዬም ተረጋግቶ ወደ
ማሰቡ ይመለሳል፤ አበቦች አበባ ሊመስሉኝ ይጀምራሉ፡፡ አይኔም በጎ በጎውን ማየት ይጀምራል፣
ውርውር የሚለውን ሰው እና መኪና ቆንጆዎቹን ሴቶች፣ ባጠቃላይ ሕዝቡን ማየት እጀምራለሁ…ግን ሁሉንም እጠላቸዋለሁ፣ አልወዳቸውም፡፡

ጥላቻ የዘወትር ጸሎቴ ነው፡፡ የጥፋት ምኞት አባታችን ሆይ የዕለት ድጋሜ !! ምነው “በደፈናው ጥላቻ የሚል የእርጎ ዝንብ ሲንጋጋም አዲስ አበባን ከነሕዝቧ አልወዳትም፡፡ ደግሞ “አዲስ አዱዬ…እዱ ገነት” እያሉ ይመፃደቁላታል፡፡ ኡኡቴ አዱ ሲኦል !! የአፍሪካ ዋና ጀሀነም፣ የሰይጣን ንብረት መሰብሰቢያቸውን !!

አልወዳትም አዲሰ አበባን፡፡ አልወደውም ሕዝቡን፡፡ እንዲህ ነበር የማስበው ሁልጊዜም፡፡ ጧት
የአዲስ አበባ ቅዳሴ ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ሲናኝ መስጊዶቿ በአዛን የማለዳ አየሯን ሲሞሉት፣
እናንተ ከፉ ሕዝቦች ደግሞ ነጋላችሁ፡ ለክፉት ተነሱ' የሚሉ ይመስለኝ ነበር፡፡ ማታ ሕዝቡ
በየበረንዳው ተኮልኩሎ ድራፍቱን ሲገለብጥ፣ ቢራውን ሲያጋባ ውስጡ የተከለውን ክፋት
እንዳይደርቅበት ውኃ የሚያጠጣ ይመስለኝ ነበር፡፡ ሕዝቡ ራሱ ስለራሱ ደግነት፣ ስለራሱ ቸርነት፣
ስለራሱ እንግዳ ተቀባይነትና አማኝነት ለራሱ ሲያወራ ይገርመኛል፡፡ ለእኔ የአዲስ አበባ ህዝብ ብዙ አይደለም፤ አንድ አምሳል አንድ አካል ያለው ቀለመወርቅ' የሚባል አንድ ሰው ነው !!


አሸብር ነው ስሜ ዶክተር አሽብር በአምላክ 'በአምላክ' አባቴ አይደለም፣ አያቴም አይደለም
ማን እንደሆነ አላውቅም...እናቴም አታውቅም፡፡ ልክ ለእኔ አሸብር የሚል ሰም እንደወጣልኝ

“አባት' ለሚለውም ቃል በአምላክ የሚል ስም ወጣለት፡፡ የእኔን ስም ያወጣችው ብዙ ላሞች ያሏት ክፋትን እንደ ላም የምታረባ እና ባወራች ቁጥር ከንፈሯን በአውራ ጣቷና በአመልካች ጣቷ በቄንጥ የምትጠርግ ክፉ ባልቴት ነበረች፡፡የአባቴን ስም ያወጣችልኝ ግን እናቴ ናት፡፡ እናቴ አፀደ ! አቲዬ ነው የምላት (በዚህች ምድር ላይ ስሟ ላይ ዩ፥ ጨምሬ እቆላምጬ የምጠራት ብቸኛ ሰው እኔ ልጇ አሸብር ብቻ ነበርኩ፡፡)ደ

አንደኛ ከፍል እስከመዘገብ የአባት ስም አልነበረኝም፡፡ ልክ ትምህርት ቤት አቲዬ ወስዳኝ ስመዝነብ
ጉጉት የመሰለው መዝጋቢ እናቴን እያጣደፈ ጠየቃት፡፡ ድሪቶ ቀሚሷ በዓይኑ ቀፎት እያመናጨቀ
የእኔን ስም ጠየቃት፡፡ የንቀት አስተያየቱን፣ እናቴን ዝቅ የሚያደርግ የፊቱን ገፅታ አይቼዋለሁ በዚያው ድሪቶ ቀሚስ ስር በፍርሃት ተከልዬ.አይቼዋለሁ ቅንድብና ቅንድቡ እስኪነካኩ ሲጠጋጉ እናቴ ላይ ሲኮሳተር፡፡ ለራሷ ኑሮ የገላመጣት እናቴን ሲገላምጣት አይቼዋለሁ፡፡

አቲዩ አስመዝግባኝ ከፊቱ ዞር ስትል ፊቱን ጨፍግጎ መጥፎ ጠረን እንደሚያባርር ሰው ግራ እጁ አየሩን እያራገበ ሲያባርር አይቼዋለሁ፡፡ በእርግጥ አቲዩ እማማ የብርጓል ቤት እንኩሮ እያነኮረች ነበር፡፡ “ምዝገባው ዛሬ ነው የሚያልቀው“ ሲሏት ነው ብድግ ብላ ሳትለቃለቅ የመጣችው፡፡ ቢሆንስ ልክ ቆሻሻ እንደሸተተው ሰው ፊት እንዲያየው አድርጎ እጁን ያራግባል ? የእማማ የብርጓል ቁጥር አንድ የጠላ ደንበኛ እንዳልሆነ ሁሉ፣ አሻሮ ሸተተኝ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል ? ነብር አየው !! እንኳን ይህቺን አይቼ እንዲሁም ጥላቻ ጥላቻ ይለኛል፡፡ ያንን የውሻ ልጅ አስተማሪ እንደ ጠመድኩት
ጡረታ ወጣ !! ደግሞኮ አያፍርም መንገድ ላይ ሲያገኘኝ “የእኔ ተማሪ ነው!" እያለ በኩራት ያወራል።

“ስም ” አላት አቲዬን።

“የእኔን ነው ” አለች እየፈራች። ፈሪ ነበረች እናቴ፡፡ ፈሪው የአዲስ አበባ ሕዝብ እንደያቅሙ ደሀ ማስፈራራትን ተክኖበታል፡፡ በትእቢት ማከላፈቱ፣ በክፋት፣ በስድብና ዘለፋው እናቴን ፈሪ
በርጋጊ እድርጓታል፡፡
👍36👏1
"አንቺ ነሽ አንደኛ ክፍል የምትመዘገቢው ?” አላት፡፡ አጠገባችን ያሉት ሁሉ ሳቁለት፡፡ አቲዬ ተሳቀቀች፡፡ ሰውነቷ ሽምቅቅ ሊል ቍሚሷን አንቄ ተሰምቶኛል፤ የመሸማቀቋ ንዝረት እንደ ታላቅ
የመሬት ርዕደት ለእኔ ለልጇ ተሰምቶኛል። የሰዎቹ ሳቅ በፍርሀት ሲያንቀጠቅጣት ተሰምቶኛል፡
የአንድን ታዳጊ የፍቅር ሕንፃ የሚያፈርስ የመሬት መንቀጥቀጥ እናት የምትባል ሚስኪን ምድር
ላይ ሲነሳ በሳቅ የሚያጅቡ ጅሎች ዙሪያችንን እያሳዘኑ ነበር ፡፡

"የልጅሽን ስም ንገሪኝ ሴትዮ!” አላት ከከበበው ሰው የተበረከተለትን ሳቅ ካጣጣመ በኋላ፡፡
የእሱ….አ..ሸብር….አሸብር ነው ስሙ" አለች ራሴን እያሻሸት፡፡

"የአባት ስም ?”

"ያባት” ብላ ዝም አለች፡፡ አባቴን መንደርተኛው ሁሉ ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ ወኔ ቢኖረው ሁሉም በኀብረት እንደ መፈክር በአንድ ላይ የአባቴን ስም ሊጠራው ይችል ነበር፡፡ ግን እንደማያውቅ ሁሉ የአቲዩን አፍ በጉጉት ይመለከት ጀመረ፡፡

"የአባቱ ስም ማነው”

“ቀ" መጨረስ አልቻለችም ቀለመወርቅ!” ልትል ፈልጋ እንደነበር የገባኝ ካደግኩ በኋላ ነው፤ የዛሬዋ ደግሞ የጉድ ናት የልጇም አባት የሚጠፋት...” ብሎ እንደገና እንዲስቁለት ሰዎቹን
አየ፡፡ ያልደመቀ ሳቅ ሳቁለት፡፡ “በይ ወደዛ ሁኝ ስታስታውሺ ትመለሻለሽ ተረኛ ቀጥል!” አለ
እስክሪብቶውን እያወናጨፈ፡፡ እናቴ ከእንቅልፉ እንደባነነ ሰው፣ 'በአምላክ…በአምላክ ነው ያባቱ ስም አለች፡፡ ጎረቤቱ እርስ በእርሱ ትያያ፣ እንሾካሾከ፡፡ መዝጋቢው ራሱን ግራና ቀኝ በብስጨት እያወዛወዘ መዘገበኝ፡፡ ራስ የሚያስወዘውዝ ስንት ጉዳይ እያለ፣ አቲዬ የእኔንኔ አባት
ስም እፈአሰበች ብሎ ይሄን በአድሉዎ የተሞላ ራሱን ይንጣል፡፡ ብዙ ሰዎች አንድን ነገር በቀላሉ
ስለሚያግኙት ማንም ሰው በቀላሉ የሚያገኘው ይመስላቸዋል፤ ለምሳሌ አባት !

ከምዝገባ ስንመለስ አቲዬን ጠየቅኳት፣ "አባቴ ማነው?”፡፡ ደንግጣ አየችኝና አጥብቃ በያዘችኝ እጇ ወደ መንገዱ ዳር ሳብ አደረገችኝ፡፡ ከሩቅ የሚመጣ እኛ ካለንበት ነገም የሚደርስ የማይመስል የጭነት መኪና እንዳይገጨኝ፡፡ አቲዬ መኪና መንገድ ላይ ስሄድ መኪናው በእካል ባይደርስ እንኳን ድምፁ የሚገጨኝ ነው የሚመስላት፡፡ ትሳሳልኛለች

!!አባትህማ በአምላክ ነው….አምላክ” አለችኝ፡፡ አነጋገሯ የገጠር ተፅእኖ ይጫነዋል፡፡ በአምላከ የሚለው ስም ለራሷም ሳይገርማት አልቀረም ::

“የት ነው ያለው?"

"ሁሉም ቦታ"

የታለ ? ብዬ ዞር ዞር አልኩ፡፡

አይታይም ..እሉ ግን እኔና አንተን ያየናል፡ ችግር ካጋጠመን ከየት መጣ ሳይባል ከተፍ ይላል”

"ከተፍ"

"አዎ ከተፍ ድንገት” አለችኝ አቲዬ እልህ በተሞላበት ድምፅ:: እንዲህ ስትለኝ አባቴ ፖሊስ መሰለኝ፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ሲያወሩ "ፖሊስ ከትፍ ብሎ” ሊሉ እሰማ ነበር፡፡....
”አቲዬ!”
“ወይዩ!”
"አባቴ ልክ እንደ እግዚያቢር ነው?
“አዎ ቁርጥ እንደ እግዚያብሄር፡፡" በአባቴ ዝና ትንሽ ልቤ ይሞላል፡፡
“አቲዩ!"
“ወይ” ትንሽ ያሰላቸኋት ትመስላለች፡፡
“ከእግዚያብሔርና ከአባቴ ማን ይበልጣል ?”
እኩኩል ናቸው እኩል ትለኛለች።..

አላለቀም
👍37😁9
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

...ሕይወት ለማሪየስ እየከበደች ሄደች:: ልብሶቹን ሽጦ እስከመብላት የሚያደርስ ችግር ገጠመው:: ችግሩ በጣም የጠናውና ጦም ውሎ ማደር
የመጣው የሚሸጠው ንብረት ሲያልቅበት ነበር፡፡ ደረቅ ዳቦ ጠፍቶ በባዶ ሆዱ ሲተኛ፧ ጠኔ እንቅልፍ አላስወስድ ብሎ ቁልጭ ብለው ሲያነጉ፤ መብራት ጠፍቶ በጨለማ ሲተራመሱ፧ ማንደጃ ላይ እንጨት ወይም ከሰል ጠፍቶ ብርድ ሲያንቀጠቅጥ፤ ያለሥራ ሌት ተቀን ሲቀመጡ፧ የወደፊት
ተስፋ ሲጨልም፧ ሱሪ ከቂጥ ላይ ሲቀደድ፧ በጭቅቅት የደለበና ቀዳዳ ያለበት ቆብ ሲያጠልቁ፤ የቤት ኪራይ ስላልከፈሉ በር ከውጭ ሲዘጋ፣ በዚሁ ሳቢያ ጎረቤት ሲሳለቅ፤ ሀፍረት አንገት ሲያስደፋ፤ ሰው ሁሉ እንደለማኝ ሲቆጥር፤ የሚያዝን ቢገኝ 'ምስኪን' እያለ ሲጠራ፤ ምሬት፧
ብስጭትና ንዴት ራስ ሲያዞር ነው የኑሮ ጉድ ፧ የኑሮ መከራ የሚታየውና እነ ምንዱባን መጡ የሚባለው::

ማሪየስ ይህ ዓይነት ሁኔታ ሲገጥም ምን እንደሚኮን ከደረሰበት አጋጣሚ ትምህርት ቀሰመ:: አንገት ከመድፋት በስተቀር ሌላ ምርጫ
እንደሌለው አወቀ፡፡ ሆኖም የሚያሳዝነው የዚህ ዓይነት ሁኔታ ሲገጥም ሰው በተፈጥሮው የሚመኛቸው እንደክብርና ፍቅር የመሳሰሉትን ነገሮች ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን በስውር ሕሊናው ልብሱ ስለተቀዳደደና ስላደፈ ሰዎች
የሚያሾፉበት፤ ድሃ በመሆኑ ሰዎች የሚሳለቁበት ይመስለዋል፡፡ ማሪየስ በወጣትነት ዘመኑ ከዚህ ዓይነት ፈተና ውስጥ በመውደቁ ያደረገው ቦት ጫማ ማለቅና መቆሸሽ ዓይኑን ዘቅዘቅ አድርጎ ያያል፡፡ በአጠቃላይ ያለበትን
ሁናቴ ያጤናል:: ፈተናው ደካሞች ስማቸው የሚጠፋበት ፤ ብርቱዎች በህፍረት ማቅ ተንነው የሚጠፉበት መሆኑን ይገነዘባል፡፡

በፈተና ጊዜ ከፈተናው ለመውጣት በሚደረገው ጥረት ሳይታወቅ ብዙ ጠቃሚ ነገር ይሠራል:: ጉልህ ሆኖ የማይታይ ጉብዝና ይከሰታል፡፡
ሕይወት፤ መጥፎ አጋጣሚ ብቸኝነት መረሳት ድህነትና ሌሎችም የኑሮ ጦር ሜዳዎች ሲሆኑ እያንዳንዳቸው የተሰወሩ ጀግናዎች ናቸው::አንዳንዴም ከእውነተኛው የጦር ሜዳ ጀግና የላቁ ይሆናሉ::

በችግር አለንጋ ተፈትነው የሚወጡ ጀግኖች ጥቂቶች ናቸው::ሆኖም ለጀግንነታቸው ድንበር የለውም:: መከፋት ግላዊ ክብርን እንደሚንከባከብ ሁሉ መጥፎ አጋጣሚም ጡት አጥብቶ ያሳድገዋል፡፡ ‹‹ችግር ብልሃትን ይፈጥራል» ይባል የለ፡፡

ማሪየስ ያሳለፈው ሕይወት ከዚህ የራቀ አልነበረም፡፡ ቤቱን ራሱ ነበር የሚወለውለው:: ቀለቡን በብር ሳይሆን በሳንቲም ነበር የሚገዛው::ቀለቡን ለመግዛት ሴቶች እንጂ ወንዶች ከማይሄዱበት ሲሄድ ሰውነቱ
እየተሸማቀቀ ነበር:: ጨለማን ተገን በማድረግ ነበር ብዙውን ሥራ የሚሠራው:: በሣንቲም የገዛውን አነስተኛ ቀለብ ራሱ እየቀቀለ ለሦስትና ለአራት ቀን ነበር ቆጥቦ የሚበላው::

አያቱ ባዘዙት መሠረት አክስቱ በየወሩ ብር ብትልክለትም
ገንዘቡን ሳያመነታ ይመልስላታል፡፡ ሲመልስላት አልቸገረኝም እያለ ነበር የሚጽፍላት::

ማሪየስ የአባቱን ሀዘን አልጨረሰም:: አሁንም ቢሆን በአንድ ወቅት ትቶት የነበረውን ጥቁር ጨርቅ ልብሱ ላይ አድርጎአል፡፡ ግን የነበረው ልብስ ሁሉ እያለቀ በመሄዱ ጥቁር ጨርቅ የሚለጥፍበትም ኮት አለቀ:: የሚቀይረው ሌላ ኮት የለውም:: ሱሪዎቹም ተቀዳደዱ:: ጓደኛው ኩርፌይሪክ እስካሁን የዋለለት ውለታ አንሶ ጨርሶ መራቆቱን ስላየ አሮጌ
ኮቱን ሰጠው::

ማሪየስ ትምህርቱን ጨርሶ የሕግ ባለሙያ በሆነ ጊዜ ለአያቱ ይህን
በመግለጽ ደብዳቤ ጻፈላቸው:: አያቱ እጃቸው እየተንቀጠቀጠ ደብዳቤውን አነበቡት፡፡ ከዚያም ቀዳድደው ከመሬት ጣሉት፡፡ ከሁለት ወይም ከሦስት ወር
ቀን በኋላ አያቱ ክፍላቸው ውስጥ ብቻቸውን ሲነጋገሩ አክስቱ ይሰማሉ:: ሽማግሌው ነገር ሲገባቸው የሚያደርጉት ልምድ ነው:: «ቂል ሰው ባትሆን ኖሮ አንድ ሰው ባንድ ጊዜ ባሮንና የሕግ ባለሙያ ሊሆን እንደማይችል ታውቅ ነበር» ብለው ሲናገሩ ነው የሰማቻቸው::

ችግር እንደ ማንኛውም የመጥፎ ነገር ውጤት በዝግታ አንድ ዓይነት
ቅርፅ አውጥቶ ይለምዱታል:: ከዚያም ቁሞ ለመሄድ የሚያስችል የኑሮ ፈር ይቀድዳል:: ለዚህ ነው ብዙ ችግረኞች ኑሮን ኖርን የሚሉት፧ ቆሞ መሄድ መኖር ከሆነ:: በዚህ ዓይነት ነበር የማሪየስ ፓንትመርሲም ኑሮ
የተመሠረተው::

ማሪየስ ለመኖር ባደረገው ጥረት ከጨለማ ወደ ጭላንጭል ለመሸጋገር ችሎ በዓመት ወደ ሰባት መቶ ፍራንክ ማግኘት ቻለ፡፡

የጀርመንኛና እንግሊዘኛ ቋንቋን አጠና፡፡ ኩርፌይራክ ከመጽሐፍ አሳታሚ ድርጅቶች ጋር ስላስተዋውቀውና ቀን ከሌሊት ሳይል የትርጉም ሥራ ስለሠራ ነበር ያንን ሰባት መቶ ፍራንክ ለማግኘት የቻለው፡፡ ይህ ገንዘብ ቆሞ ለመሄድ የሚያስችል ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ከዚያ የተሻለ ነኑሮ
የሚያኖር ነበር።

በዓመት ለቤት ኪራይ ሰላሣ ፍራንክ፣ በየወሩ ሦስት ፍራንክ ክፍሉን ለሚያጸዱለት ሴት ይከፍላል፡፡ ከዚህችም ገንዘብ እንደነገሩ ቁርስ ይሠሩለታል፡፡ በዓመት ወደ ሦስት መቶ ስልሣ አምስት ፍራንክ ለአንዲት )
እራት ለሚያዘጋጁለት ሴት ይሰጣል፡፡ ለልብሱና ለሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች ወደ ሁለት መቶ ሃምሣ ፍራንክ ገደማ ያወጣል:: በዚህ ዓይነት ማንኛውንም ወጪ ችሎ በዓመት ወደ ሃምሣ ፍራንክ ይተርፈዋል:: ይህም ሀብታም የሚያሰኝ ነበር፡፡ እስከናካቴው እስከ አስር ፍራንክ የሚደርስ ገንዘብ ለጓደኞቹ ያበድራል:: አንድ ሰሞን ጓደኛው ኩርፌይራክ ስልሣ ፍራንክ ተበድሮታል።


ማሪየስ ሁለት ዓይነት ልብሶች ነበሩት፤ አንድ የዘወትር ሌላው
የክት፡፡ ሁለቱም ልብሶች ቀለማቸው ጥቁር ነበር፡፡ ሦስት ሸሚዞች ነበሩት:: አንዱን ሲለብሰው ሌላውን ለመቀየሪያ መሳቢያ ውስጥ ያስቀምጠዋል፡፡
ሶስተኛውን ለአጣቢ ይሰጣል፡፡ ቶሎ ያለቀው በአዲስ ይተካዋል፡፡
ሆኖም ብዙውን ጊዜ ሸሚዞቹ ቀዳዳ ስለማያጡ ያንን ለመደበቅ ኮቱን እስከ አንገቱ ነበር የሚቆልፈው::

ማሪየስ ለዚህ ማዕረግ የበቃው ከብዙ ዓመታት ስቃይና መከራ በኋላ ነበር በስንት ትግል፤ በስንት መከራና ስቃይ የታለፉ ዘመናት ፤ ከድንጋይ የከበዱ ዓመታት! ማሪየስ ግን ለአንድ ቀን እንኳን በዚህ ችግር አልተፈታም፤
ተጋተረው እንጂ እጁን አልሰጠም፤ ከዚህ ችግር ለመላቀቅ ብድር ከመበደር በስተቀር ያልፈጸመው ተግባር፧ ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም፡፡ የሰው
እዳ አምስት ሣንቲም አልነበረበትም፡፡ ቢያሻው ጦሙን ውሎ ጦሙን ያድራል እንጂ ሰው አያስቸግርም፤ ብድር አይጠይቅም:: ብድር የባርነት
መጀመሪያ መሆኑን ያውቃል፡፡ ባርነት እኮ በገንዘብ መሸጥ ብቻ አይደለም::አበዳሪ ከጌታ የከፋ መሆኑን ያምናል፡፡

ጌታ አንተነትህን ነው የሚገዛው:: አበዳሪ ግን አንተን ብቻ ሳይሆን
የሚገዛው ክብርህንም ጭምር ስለሆነ ከሰው ፊት ያስጨንቅሃል፤ ነፍስህንም ያሳድዳታል፡፡ ለዚህ ነበር ማሪየስ እዳ ከመግባት ለብዙ ቀናት በተከታታይ
ጦም ማደሩን የመረጠው:: ካልተጠነቀቅን፤ የሕይወትን አስቸጋሪ ዘመን ካላሳለፍን ሥጋችን ብቻ ሳይሆን ነፍሳችንም ጭምር የባለሀብቶች ባርያ ትሆናለች፡፡ ለዚህ ነበር ማሪየስ ክብሩን በቅናት ዓይን እያየ የጠበቃት::ለዚህ ነበር በዓይነ ህሊና ወደኋላ ተመልሶ ሲያዩት የሚያጸጽት ሥራ ለመስራት ያልደፈረው።

ከደረሰበት የኑሮ ፈተና አዲስ ኃይል ፤ አዲስ ጉልበት ለማግኘት
ተጣጣረ እንጂ አልተማረረም:: የዚህ ዓይነት እምነት ካለን ነፍሳችን ሥጋችንን ትገፋፋለች:: ወፍ እኮ የራስዋን ጎጆ ቀይሳና ተንከባክባ ነው የምትኖረው።
👍18
ማሪየስ ሃያ ዓመት ሞላው:: የአያቱን ቤት ለቅቆ ከወጣ ሶስት
ዓመት አለፈ፡፡ ሁለቱም ወገን እጃቸውን ሳይሰጡ በእምነታቸው
ጸንተውና ለእርቅ ሳያጎበድዱ ነበር ዓመታቱ ያለፉት፡፡ አልተፈላለጉም፤ ለመጣላት ምን አፈላለጋቸው

እንደ እውነቱ ከህን ፧ ማሪየስ ስለአያቱ በነበረው አመለካከት ተሳስቷል በእርሱ አመለካክት አያቱ፡ መሳይ ጊልኖርማንድ ጨርሰው አይወዱትም
«ይህ ጠናዛ ሽማግሌ፣ አንዳንዴ እኔን ሲያይ ፊቱን ፈካ የሚያደርገው እወድሃለሁ ብሎ የሚምለውና የሚገዘተው በውሸት ነው» ይላል:: አዝህ ላይ እጅግ ተሳስቷል፡፡ ልጁን የማይወድ አባት ሊኖር ይችላል፡፡ የልጅ ልጁን የማያደንትቅና የማይወድ አያት ግን የለም:: መሴይ ጊልኖርማን
ማሪየስን እንደ አምላክ ነበር የሚያመልኩት:: ልባቸው በእርሱ ፍቅር ተሞልቷል፡፡ ማሪየስ ከቤት ወጥቶ በሄደ ጊዜ ቤቱ ወና፤ ልባቸው ባዶ ቀፎ ሆኖ ቀርቷል፡፡ ከቤታቸው ወጥቶ እንደሄደ ማንም ሰው ስለዚህ ልጅ
እንዳያነሳብኝ» ብለው የሰጡት ትእዛዝ መከበር አስቆጫቸው:: በመጀመሪ ይህ የቦናፖርቴ ተከታይ፤ ይህ ሽብር ፈጣሪ፤ ይህ ረባሽ ሲቸግረው ተመልሶ
ይመጣል» የሚል እምነት ነበራቸው:: ግን ሣምንታት፤ ወራት፧ ዓመታት እያለፉ ሲሄዱ «ደም መጣጩ ልጅ» ባለመመለሱ መሴይ ጊልኖርማን ተስፋ ቆረጡ፡፡ «ከማባረር ሌላ እርምጃ በወሰድሁ» ሲሉ ተጸጸቱ። ያ ውሳኔ እንደገና የሚፈጸም ቢሆን አሁን አደርገው ነበር?» ሲሉ ራሳቸውን
ጠየቁ፡፡ ክብራቸው «አዎን» ብሎ ሲመልስ የሽማግሌ ጭንቅላታቸው ግን «የለም» በማለት ከወዲያ ወዲህ ተነቃነቀ፡፡
ልጁን በጣም ናፈቁት::

ሽማግሌዎች ፀሐይ ብርሃንን እንደሚሹ ሁላ! የልጆቻቸውንም ፍቅር ይፈልጋሉ፡፡ ፍቅራቸው ያሞቃቸዋል፡፡ መሴይ
ጊልኖርማንድ ብርቱ ሰው ቢሆኑም የማሪየስ ከቤታቸው መጥፋት አንድ ዓያነት ድክመት አሳደረባቸው:: ሆኖም ይህን ወሮበላ» ለመፈለግ አንድ
እርምጃ እንኳን ወደ ፊት አልተራመዱም:: ነገር ግን በጣም ተሰቃዩ ያስቡታል ግን አይፈልጉተም፡፡ ይመኙታል ግን ሊያዩት አይፈልጉም፡፡ ያ ሳቁ፤ ፈገግታው፧ ጨዋታው ፧ ትህትና ከፊታቸው ድቅን ይላል:: «ወይ ጉድ! አሁንስ በመጣና የፈለገውን ባደረግሁት» ይላሉ በልባቸው:: ሳይመጣ ሲቀር ሰውነታቸው ይዝላል።

አክስቱስ! እርስዋማ ለፍቅር ብዙም የማትጨነቅ ሴት ነበረች፡፡
ለእርስዋ ማሪየስ ማለት በጭላንጭል የሚታይ ብርሃን ነው:: እርሱን አሰላስለ በመጨነቅ ከድመት ጋር መጫወት ትመርጣለችካ.ጋትን ትመርጣለች:: የአያቱ የጊልኖርማድል የምሥጢር ስቃይ ያባባሰው ስለማሪየስ ሁለተኛ እንዳታነሣ የስጥዋት ትእዛዝ ነበር፡፡ ድንገት ከውጭ የመጣ ሰው ከማሪየስ አክስት ፊት «ያ ልጅዎ ምን በላው? የት ነው ያለው? ምን ይሠራል?» ተብላ የተጠየቀች እንደሆነ የኛ ባሮንማ የነገር ቀዳዳ ሲያገኝ የሕግ ሰው ነውና
እርሱን እየጠቀመ ነዋ ያለው» ስትል ትመልሳለች::

ሽማግሌው በጸጸት ሲነዱ ማሪየስ ግን የሕሊና እረፍት አግኝቶ ደስ
ብሎት ነበር የሚኖረው:: ያሳለፈው የመከራና የፈተና ዘመን የወደፊት
ህይወቱን ሞረደለት፡፡ ብረት በእሳት ይፈተናል እንዲሉ ማሪየስም በችግር ተፈትኖ ፈተናውን አለፈ፡፡ በልጅነት የሚደርስ ችግርና ድኅነት የወደፊት ኑሮን የማሻሻልና ታግሎ የመወጣት ዝንባሌን አሳድሮ በሕይወት ዘመን የልብ አሸናፊነትን ያጎናጽፋል። ድኅነት ያልጨበጡትን ለመጨበጥ ጉጉት ይፈጠርና ሐሞተ ቆራጥ ያደርጋል፡፡ ይህም ከጥሩ ደረጃ ያደርሳል፡፡

የሀብታም ልጅ አእምሮ ተደስቶ ለመኖር ይፈልግና በልጅነት ዘመኑ
ባዶ አእምሮው በፈረስ ግልቢያ፧ በአደን፣ ሲጃራ በማብነን፧ በዳንኪራ፤ ግብር በማግባት ፣ በፍቶተ ሥጋና በመሳሰሉት ይጠመዳል:: ሌላ የሚመኘው
ነገር አይኖርም:: የድሃ ልጅ ግን የእለት እንጀራውን ለማግኘት መሥራት አለበት:: የእለት እንጀራውን ካገኘ ያቺን ይበላል:: በዚህም ይደሰታል፡፡ ዓመታት ከተፈጥሮ ጋር የቅርብ ግንኙነት ስላለው ያንን ያደንቃል:: በሰዎች መካከል ስለሚሰቃይ የሰዎች ስቃይ ያስጨንቀዋል:: በላቡና በወዙ የሚበላውን ዳቦ በማፍራቱ ታግሎ መውጣትና የትልቅነት ስሜት ያድርበታል:: የስቃይ ብዛት ከሚፈጥረው ራስን የመቻል ፍላጐት ከመጨነቅ ወደ ማሰብ፣ ከማሰብ ችግሩ ደግሞ ራስን የመውደድ ስሜት ስለሚያሳድርበትና ለራሱም
ወደ መፈላሰፍ ስለሚያሸጋግረው የማወቅና የመማር ስሜት ይቀረጽበታል፡፡
ችግሩ ደሞ ራስን የመውደድ ስሜት ስለሚያሳድርበት
ለራሱም ስለሚያዝን የበለጠ ነገር ለማግኘት ይጥራል:: ይህም ችግር ከጫንቃው ሲወርድለት ራሱን እየረሳ ለተቸገረ ሁሉ ማዘን ይጀምራል፡፡ መንፈሳቸውን
ላቀነና ሕይወትን በፀጋ ለተቀበሉ ተፈጥሮ ደስታ እንደሚለግሳቸው
ለተደፈኑ ነፍሳትም ደስታ ይነሳቸዋል:: የአሳብና የእውቀት ሀብታም የሆኑት ለ።ጥሬ ገንዘብ ሀብታሞች ያዝናሉ:: የአሳብ ባለፀጋ ጥላቻን ከልቡ ሲፍቅ
የተስፋ ብርሃን ሕሊናውን ሰንጥቆ ይገባል:: ታዲያ ይህን ጊዜ ይከፋዋል ወይስ አይከፋውም?

የወጣትነት ስቃይ እውነተኛ ስቃይ አይባልም:: አንድ ወጣት የገንዘብ
ድሃ ሊሆን ይችላል፤ ግን ጤናው ፤ ጉልበቱ ፣ ፈጣን እርምጃው፣ የሚያበሩ ዓይኖቹ፤ የሚያሞቀው ደሙ፧ ወለላ ከንፈሩ፤ ከወተት የነጡ ጥርሶቹ ፤ ንጹህ ትንፋሹ ሁሉ የሚያስቀኑ በመሆናቸው የጨረጨሰ ንጉሥ ይቀናበታል::
ይህም በመሆነ ነው ማሪየስ በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ሳይታክተው የእለት እንጀራውን ፍለጋ የወጣው:: በእጆቹና በአእምሮው ተጠቅሞ ለእለት እንጀራው ሲሠራ ጀርባው እየበረታና እየጠነከረ አእምሮው በአሳብ እየተሞላ
ሄደ:: ሥራውን ሲጨርስ መመራመሩን ቀጥሎ እግሩ ለእንቅፋት፤ ለእሾህ አንዳንዴም ለጭቃ መጋለጡንና አእምሮው ግን በብርሃን መከበቡን አመነ።
መንፈሰ-ቆራጥ፧ ረጋ ያለ ጭምት ወጣት ከመሆኑም በላይ በጣም ጨዋ፧ሀብታሞች የሌላቸውንና ነፃነት ያጎናጸፈውን ጤነኛ ጉልበትንና ጨዋነትን ያስገኘለት ምርምርን ስለሰጠው ጠዋት ማታ ፈጣሪውን አመሰገነ።

ማሪየስ ሁለት ጓደኞች ነበሩት፡: እነርሱም ወጣቱ ኩርፌይራክና
ሽማግሌው ማብዩፍ ናቸው።
ሽማግሌውን በይበልጥ ያቀርቡታል፡፡ ለዚህም ምክንያት ነበረው:: ማብዩፍ የማሪየስን አባት የሚያውቁና የሚወዱ ሰው
ናቸው:: በአጋጣሚ ነው አባቱ ስለቆመለት ዓላማና እርሱም ማን እንደነበር መሴይ ማብዩፍ ያጫወቱት::

መሴይ ማብዩፍ ፖለቲካ ብዘም አይወዱም:: የእርሳቸው ፖለቲካ ስለተክልና ስለመጻሕፍት ያላቸው ፍቅር ነው:: በዓለም ላይ ብዙ በሚደነቁ እንደ ዛፎች ማደግ፤ እንደ ኣበባ መፈንዳት እንደ ሳር መለምለምና እንደ ጽጌረዳ ማማር በመሳሰሉ ነገሮች ላይ ጊዜ እንደማጥፋት ሰዎች ስለሕዝባዊ ወይም ስለንጉሣዊ አገዛዝ፤ ስለሪፑብሊክ፤ ስለሕጋዊ አልጋ ወራሽና ስለመሳሰሉት ነገሮች በመጨቃጨቅ ጊዜ ማጥፋታቸው ይገርማቸዋል።እኚህ ሰው ሰዎችን ሲያፈቅሩ ሁካታቸውን ይጠላሉ:: ሰዎች ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለማይነጫጩና ከዚያ ሥፍራ የመንፈስ እረፍት ስለሚገኝ ወደዚያ አካባቢ መሄድን ያዘወትራሉ:: ራሳቸውን የሚያስተዳድሩት ከአንዲት ከደረሱት መጽሐፍ ሽያጭ በሚገኝ ገቢ ሲሆን በዓመት እስከ ሁለት ሺህ ፍራንክ ያገኛሉ:: በጣም የሚያቀርቡት ወዳጅ መጽሐፍ ሲሆን መሴይ ማብዩፍ ምርጥ
ምርጥ መጻሕፍትን መሰብሰብ ይወዳሉ፡፡

እኚህ ሰው ከእርሳቸው በየዋህነት የማይተናነሱ የሴት ሠራተኛ
ነበርዋቸው:: ሴትዮዋ በየሳምንቱ እሑድ ከቤተክርስቲያን መልስ ጊዜያቸውን የሚያጠፉት በየጊዜው እየገዙ ያጠራቀሙትን ልብስ በመቀጠርና በማገላበጥ
ነበር:: እኚህ ሴት ማንበብ ስለሚችሉ አልፎ አልፎ የመሴይ ማብዩፍን መጻሕፍት ያነብባሉ፡፡
👍12🥰1
በ1830 ዓ.ም. ገደማ የመሴይ ማብዩፍ ወንድም ይሞታለ፡፡ ወዲያው አከታትሉ መሴይ ማብዩፍ ላይ ሌላ መጥፎ አጋጣሚ ይደርሳል። በወንድማቸውና በራሳቸው ስም በአደራ የተቀመጠወ አሥር ሺህ ፍራንክ በእሳቸው ሳይሆን በሌላ ስው ስህተት የተነሣ ይጠፋል:: ስለአበቦች የጻፉትም መጽሐፍ ገበያ ያሽቆለቁላል:: በሐምሌ ወር በተጀመረው ንቅናቄ ምክንያት
ነበር የመጽሐፍ ገበያ ያሽቆለቆለው:: መሴይ ማብዩና አንድ መጽሐፍ እንኳን ሳይሸጡ ሳምንታት አለፉ፡፡ በመጨረሻም ከጻፉት መጽሐፍ የተወስነውን በቅናሽ ዋጋ ሸጠው ቀደም ሲል ይሠሩት የነበረውን ሥራ ትተው ከግቢው ወጡ:: ከተማ ውስጥ እጅግ አነስተኛ በሆነ ገንዘብ ትንሽ
ቤት ተከራይተው ሲኖሩ ከቤታቸው እንዲመጡ የተፈቀደላቸው ማሪየስና አንዲት የመጽሐፍ ቤት ባለቤት ብቻ ነበሩ:: ሠራተኛቸውን ይዘው ነው የሄዱት፡፡

ማሪየስ በእግር መንሸራሸር በጣም ይወዳል:: አንዳንድ ቀን አበቦች ካሉብት አንዳንድ ቀን ደግሞ ዝም ብላ ከአውራ ጎዳናው ላይ ከወዲህ ወዲያ ይላል በመንገድ የሚያልፉ ተጓዦች አተኩረው ያዩታል፡፡ አንዳንዶቹ
አዘውትረው ስለሚያዩት ‹‹ምነው ገና በለጋነቱ አሳብ አበዛ» እያለ
ያዝኑለታል::

ማሪየስ ብዙ ጊዜ ያስብ የነበረው ስለኑሮው ነበር እንጂ ለንቅናቄው
የነበረው ስሜት ስለቀዛቅዞ ብዙም አያስጨንቀውም፡፡ ለኑሮ የነበረውን
ፍልስፍና አልለወጡም፡፡ ሆኖም ፍልስፍናው ወደ ሀዘኔታ እየተለወጠበት ነበር። እምነቱ ሁሉ ያተኮረው ስለሰዎች ደኅንነት ሆነ:: ይህም እምነቱ ሀገሩን በይበልጥ አስወደደው:: አገሩን ወደደ ስንል ደግሞ ለሕዝቡ በጣም ተቆረቆረ ማለታችን ነው:: በተለይ ደግሞ ለሴቶች በጣም ያዝናል፡፡

አንድ ቀን ሠራተኛው ‹‹ጎረቤቶቻችን እኮ ከቤታቸው ሊባረሩ ነው» ትለዋለች:: እርሱ አብዛኛው ጊዜውን የሚያጠፋው ከቤት ውጭ ስለነበር በአካባቢው ማን እንዳለ አያውቅም:: እነማን እንደሆነ ባያውቅም በምን ምክንያት» ብሎ ይጠይቃል፡፡

«የቤት ኪራይ መክፈል ስለአቃታቸው!» ስንት ይሆን ያለባቸው?»

«ሃያ ፍራንክ»
"
ማሪየስ ለመጠባበቂያ እንዲሆን ከቤት ያስቀመጠው ሰላሣ ፍራንክ
ነበረው።

«ይኸው ሃያ አምስት ፍራንክ፡፡ ሃያውን ለቤት ኪራይ ክፈይላቸው::
አምስቱንም ደግሞ ኣንዳንድ ቀዳዳ ቢደፍንላቸወ ስጫቸው:: እኔ እንደሰጠኋቸው ግን አትንገሪያቸው::....

💫ይቀጥላል💫
👍17
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#ሁለት


....አሸብር ብላ ስም ያወጣችልኝ ከቤታችን በላይ ብዙ ላም የምታረባ ቅሌታም ባልቴት ናት፡፡ ሰው ከእኔ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ከአቲዬም ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡ እኔ ልወለድ አቲዬ ምጥ የተያዘች ቀን የዚህች አቃጣሪ ባልቴት የአሜሪካ ላም ያልታወቀ ነገር በልታ ሆዷ
ተቆንዝሮና አረፋ ደፍቃ እየጓጎረች ነበር አሉ።

የመንደሩ ሰው ከእኔ እናት ምጥ ይልቅ የዚህች የመንደራችን ሀብታም ላም ነፍስ አስጨንቆት
አዋላጇ አልማዝ ሳትቀር ወደዛው ሂደው ነበርና አቲዩ ብቻዋን እኔን ተገላገለች፡፡ ወለደችኝ!!
የቀን ሥራ ያጠነከራት ብርቱ ሴት ባትሆን ኖሮ ሟች ነበረች፡፡ ብቻዋን ወለደችኝ !!"

አንድ የእንስሳት ሀኪም ተጠርቶ የአቃጣሪዋን ዘርፈ ላም ሆድ እስክሪብቶ በሚመስል ነገር
ወግቶ ሲያስተነፍስላትና ላሟ መጓጎሯን ስታቆም መንደርተኛው እልልታውን አቀለጠው!
እልልልልልልልልልል… አቲዬ እልልታውን ከሩቅ ሰምታለች፡፡ በዚህ መሀል አዋላጇ፡ “በሞትኩት ያቺ ሚስኪን ምን ደርሳ ይሆን?” ብላ ወደ ቤታችን ተጣደፈች። አቲዬን የተፈለቀ ወርቅ የመሰለ ወንድ ልጅ አቅፋ አገኘቻት፡፡ ያ የተፈለቀቀ ወርቅ እኔ ነበርኩ ያውም ገና በእሳት ሊፈተን የተዘጋጀ ወርቅ፡፡

ዘርፌ የሚሏት ሀብታም ባለላም የላሟን ደኅንነት ሊጠይቃት ቤቷ ሲጎርፍ የዋለውን ቅቤ አንጓች
ሁሉ ስታስተናግድ ውላ ወደ ማታ አስር እንጀራና ክክ ወጥ ይዛ ቤታችን መጣችና መንደርተኛው
በእኔ ላም በተሸበረበት ቀን ተወልዷልና አሸብር ብዬዋለሁ” አለች፡፡ አሸብር ሆኜ ቀረሁ!! ነገ አድጌ ብረብሽ! ስምን መልዓክ ያወጣዋል የሚል ሒሳብ 'መልዓክ ነኝ ልትል፡፡ እች…ስድብ የማይገልፃት…!ለ 'አንቱታ' የደረሰች ሴትዮ ናት፣ 'አንች የምላት ባትስማኝም ስንቃት ደስ ስለሚለኝ ነው፡፡
እንግዲህ አሸብር የተባልኩት አንዲት ተራ አጋሰስ..የአሜሪካ ላም ባጋበሰችው ፈስታል ታምማ
መንደርተኛውን ባሸበረችበት ቀን በመወለዴ ነው በቃ ! ደግሞ ምኔም የማያሸብር እንደወም
ቅጠል ሲንኮሻኮሽ እቲዬ አሮጌ ቀሚስ ስር የምደበቅ ፈሪ ነበርኩ ስሜን ያወጣው መልዓክ
አይደለም ዘርፌ የምትባል ቀንዳም ሰይጣን ናት!!

እኔኮ ሚያበሳጨኝ.…የዛን ጊዜ ዘመኑ ስላልሰለጠነ ነው ብዪ ውስጤ ከተመረዘበት ጥላቻ
እንዳይሽር፣ ዛሬም ድረስ ጎረቤቶቻችን ስለዛ ጊዜ ሲያወሩ ፊታቸው የተቀመጠችውን አቲዬን….ብቻዋን መውለዷን ከቁምነገር ሳይቆጥሩት ማለፋቸው ሳይበቃ፣ ከሞተች የቆየችውን የአሜሪካ ላም ደግነት፣ ባልዲ ሙሉ መታለብ ፌስታል በልታ ስታቃስት አንጀታቸው መንሰፍሰፉን
እየተቀባበሉ ማውራታቸው ነው፡፡ ደግሞ የሚንሰፈሰፍ አንጀት እንዳለው ሰው፡፡ጎማ አንጀት ሁሉ!!

አቤት ስጠላቸው! ልቤ ተሸንቁሮ የቋጠረው ፍቅር ፈሶ ያለቀበት ይመስል የተረፈኝ አፅናፍ
የለሽ ጥላቻ ብቻ ነው፡፡ ማንንም አልወድም ሁሉንም እጠላለሁ ! ዘርፌ መልዓክ ብትሆን ጥሩ ነበር
ስሜን እንድሆን፤ ይሄን ከመሬት ተነስቶ የሚሸበርና የሚያሸብር አውራና ምንዝር ጎረቤት ሁሉ እንዳሸብረው !! ወይ ነዶ ለሞላ ቦንብ ምናለ አንዲት ኒውክሌር ቦምብ ብትኖረኝ !! ለክፉ ነገር አልጠቀምባትም፣ ቀለመወርቅ ግቢ እወስድና …

አቲዩ ከገጠር ወደ አዲስ አበባ ስትገባ ገና 14 ዓመት እንኳን አሳምሮ አልሞላትም ነበር፡፡ ገጠር
የሚኖሩ ቤተሰቦቿ ምናምኒት የሌላቸው ያጡ የነጡ ድሆች ስለነበሩ በልጅነቷ ነው ልፋት
ዕጣ ፋንታዋ የሆነው ገጠር ስልችት አላት፡፡ ባል አልነበረም የስደቷ መነሻ፡፡ ያላቻ ጋብቻ
ምንትስ ብላ አልነሳረም ወደ ከተማ መኮብለሏ፡፡ የከተማ ሰው ከድህነት የሚያላቅቅ ዓመድሽን
የሚያራግፍ ደግ ነው ብለዋት እንጂ ባል ሽሽት አልነበረም፡፡

ከተሜው ያላቻ ጋብቻ እያለ የሚወተተው ሲያስመስል እኮ ነው፡፡ ለሀብት፥ በዘር፣ በእምነት
አቻ በማሳደድ ሱስ ስለተለከፈ፣ የመከፋፈልና የማግለል ንቅዘቱ ነው የሚያስለፈልፈው፡፡ ተራራ
ተሻግሮ የሚጮኸው ከተሜ ስንት የነቀዘ ባህል፣ የገማ ዓመል ጉያ ውስጥ ሸጕጧል። አሱን ብሎ የመብት ተከራካሪ፣ እሱን ብሎ ታዳጊ፡፡ ምን በወጣሽ ካለ እድሜሽ ማግባት እያለ
የገጠሯን ሴት በአዞ እንባ ሙሾ የሚያስወርድ ከተሜ በየጓዳው ከከፉ ባል ይከፋል፡፡

የልጅነት እግሮቿ ወደ አዲስ አበባ መሯት። ዘርፌ የምትባል ባለ ብዙ ላም ሴት የደሀ መንደር ከእኔ ወዲያ ሀብታም ላሳር' የምትል ክብረ ቢስ ባልቴት ላይ ሰዎች አምጥተው ጣሏት፡፡ ሴትዮዋ
ብዙ የአሜሪካ ላሞች ስለነበሯት አቲዬን በሰራተኝነት ቀጠረቻት፡፡
ገጠር ትታው የመጣችው አዛባ መዛቅና ላም ማላብ እዚህም መሀል አዲሳባ ጠበቃት፡፡ ሰው
እየመሰለው ይሮጣል እንጂ እጣ ፋንታውን በመሽሽ አያመልጠውም፡፡ እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል ብሂል ጋር ስንተላለፍ እጣ ፉንታችንም አብሮን እያለፈ ከፊታችን ይጠብቁናል፡፡ እንዲያ ነው አቲዩን የገጠማት፣ ከእርሻ ላም ወደ አሜሪካ ላም!! አዲሳባ ራሷ የአሜሪካ ላም ናት፡፡ ብዙ
ላበላት ብዙ የምትታለብ፡፡ አላቢም ታላቢም ግፍ የሞላባት፣ ውጪዋ አብረቅራቂ ቀለም የተቀባ ሰፊ በረት !!

አንዳንድ የአሜሪካ ላሞች ከሰው ልጆች የበለጠ ክብር ይሰጣቸዋል፡፡ የአሜሪካ ላም ስለሆኑ ወይም፣ ላም ብቻ ስለሆኑ አይደለም ወትት ስለሚታለቡ፡፡ ስጋቸው ስለሚበላና ሌላ የምትታለብ ላም የሚታረድ በሬ ስለሚወልዱ፡፡ ይሄ የዓለማችን የደነዘ የምጣኔ ሀብት ቀመር ነው
የበለጠ የሚታለበውን የበለጠ ተንከባከበው !! ይልኻል በአደባባይ በከራቫት በታነቀ ተወካዩ፡፡ በተወካዩ መሪነት የስግብግብነትና የከፋት ኪራላይሶ የሚደግም አህዛብ ከተሜ ይባላል፡፡

አገር ይሁን ሰው ምንም ከሌለው ምናምቴ ነው፡፡ ይገፋል ይረገጣል፡፡ ለጠብታ ነዳጅ አንድ
አገር ሰው ቢፈጅ ዓለም ጭጭ የሚለው ለፅድቅ የሚሆንን መንገድ በግፍ ለመቀየስ ነው ካለወጉ !!ሰብዓዊነት ገደል ይግባ! ብለው ሰው መሆንህን ሊክዱ የሚዳዳቸው ሁሉ፣ በዕድልም ይሁን በችሎታህ አምልጠህ ሰው ስትሆንባቸው ገደል ያስገቧትን ሰብዓዊነት ጎትተው የሚያወጡባትን
ገመድ እንድትሰጣቸው ፊትህ ቁመው ጅራታቸውን ይቆላሉ፡፡ ደግነቱ ጭራቅ ለጭራቅ እስኪበላላ አይጨካከንም የጭራቅ ሕግ አለ፣ የጭራቅ መሀላ በየወንዙ የሚማማሉት ዓይነት፡፡ እንደ አተዬ አይነት ሚስኪን ልፋት የፈጠራት እንደ አህያ ያሻቸውን የሚጭኑባት ፍጥረት የሚማማሉበት ወንዝ ዳር ከተገኘች፣ አደፈረሽብን ከማለት አይመለሱም

እንደሰው ባልቆጠሯት እናቴ ጉልበት ሰው የሆኑ ብዙዎች ሰው ብቻ እንዳልሆኑ፣ ይልቅ በጣም
ሰው እንደሆኑ ሲሰማቸው (ከጣት ጣት ይበላለጣል የሚል ተረት ሁሉ አላቸው፡፡) የአትዬ ወጣት ሰውነት ላይ አይናቸውን ያቁለጨልጩ ጀመረ፡፡ ቀለመወርቅ የሚባል ካፖርትና ክብ ኮፍያ የማይለየው ባለ ትልቅ ቤትና ባለ መኪና ሰው ነበር። እሱስ አሁንም አለ፣ እኔ ውስጥ ከሞተ ቆየ እንጂ ! በውስጤ ሚሊየን ጊዜ ገድየው፣ ሚሊየን ጊዜ ተነስቷል የክፉ ሰው ነፍስ ጣር ይበዛበታል፡፡

ሁሉም ሰው ጋሽ ቀለሙ ነው የሚለው እና ይሄ ካፖርታም ቤታም እና መኪናም አጋሰስ
👍273