#ጌታችን_ተነስቷል…!
በቃሉ መሠረት፤ ጌታ ከድንግል ተወለደ፣
ከሠማየ ሠማያት መጣ፤ እኛን ስለወደደ፡፡
ሠውን ሊያድን መጣ፣
ከሐጢዓት አረንቋ፤
………….ሃርነት ሊያወጣ፣
ሞትን በሞቱ ሊደመስስ፤
…………ሠይጣንን ሊቀጣ፡፡
እንትፍ ብሎ ምራቁን፤ እውሩን አበራ፣
የዓለም ብርሃንነቱ፤ በምድር ላይ በራ፡፡
የሚያዩም …. እንዲታወሩ፣
…… በሐጢዓታቸው እንዲታሰሩ፡፡
ጌታ ለፍርድ መጣ፣
ምኩራቡን ሊገለብጥ ስህተትን ሊያወጣ፡፡
የማያዩ …. እንዲያዩ ፣
……….. ጌታን እንዲለዩ፡፡
መስዋዕት ሆኖ መጣ፣
ዓለምን ነፃ ሊያወጣ፡፡
አይሁድ ሊወግሩት፤ ድንጋይን ቢያነሱ፣
ቀኑ ስላልሆነ፤ እምቢ አለ መንፈሱ፡፡
የኔ ጌታ…..
አልዓዛርን ከተኛበት፤ በድምፁ ቀሰቀሰ፣
ድውያውንን ሁሉ፤ አንድ በአንድ ፈወሰ፡፡
የአላዛር ወላጆች፤ አይሁድን ስለፈሩ፣
ድንቅ ታምራቱን፤ ሳይናገሩ ቀሩ፡፡
እሱ ሙሉ ሠው ነው፤ ጠይቁት ቢሉም፣
ፈሪሳውያኑ፤ ሊያምኑ ግን አልቻሉም፡፡
የእግዚአብሔርን ስራ፤ በብዙ ገለጠ፣
እልፍ ታዓምር ሠራ፣ ክፋትን ለወጠ፡፡
በዓለም እያለ፤ የዓለም ብርሃን ሆነ፣
የተኛውን ሁሉ፤ በፍቅሩ አባነነ፡፡
የካህናት አለቆች፤ ሸንጎ ተቀመጡ፣
ፈሪሳውያኑ፤ መያዣ አወጡ፡፡
መከሩ.. ዘከሩ፤ እቅዳቸውን ነደፉ፣
የቀያፋን ምክር፤ በድምፅ አሳለፉ፡፡
ከራሱ አይደለም፤ ቀያፋ የተናገረ፣
ስለህዝቡ ይሞት ዘንድ፤ ቃል ስለነበረ፡፡
ትዕንቢቱ ሊፈፀም፤ የግድ ስለሆነ፣
የቀያፋ ምክር፤ ተፈፃሚ ሆነ፡፡
የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉ፣
መጡ ህዝቡ ሁሉ፣
ሆሳዕና በአርያም እያሉ፡፡
ትዕንቢቱ እንዲፈፀም፤ ኢየሩሳሌም ተመረጠ፣
በአህያ ውርንጫ፤ ጌታ ተቀመጠ፡፡
የሠው ልጅ ሊከብር፤ ሠዓቱ ደረሰ፣
ነፍሴ ታውካለች፤ ብሎ እየመለሰ፡፡
በዓሉ ቢደርስም የአይሁዶች ፋሲካ፣
የእኛ ፋሲካችን፤ በፍቅር ተተካ፡፡
እኔ ቁራሽ አጥቅሼ፤ ለሱ የምሠጠው፣
እሱ ነው እኔን፤ በገንዘብ የሚሸጠው፤
………………………ብሎ ተናገረ፣
………………………ቀድሞ መሠከረ፡፡
ዲያቢሎስ ይሁዳን በሃሳቡ ደለለ፣
የአስቆሮቱ ይሁዳ፤ ለመሸጥ ቸኮለ፣
ጌታን አሳልፎ ሊሠጥ፤ ልቦናው ታለለ፡፡
ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሄር እመኑ፣
ቀኔ ደርሷልና፤ ምንም አትዘኑ፡፡
አላቸው ኢየሱስ፤ ለደቀመዛሙርቱ፣
ስፍራ ሊያዘጋጅላቸው፤ ሊፈፀም ትእንቢቱ፡፡
የካህናት አለቆች፤ ወደ ጌታ መጡ፣
በይሁዳ መሪነት፤ ኢየሱስን ሊይዙ፤
……………………. አምላክን ሊቀጡ፡፡
ማንን ትፈልጋላችሁ? ብሎ ቢጠይቃቸው፣
‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስን›› ሲሉ፤
……………………‹‹እኔ ነኝ›› አላቸው፡፡
ስምዖን ጴጥሮስም፤ መዘዘ ሠይፉን፣
የማልኮስን ጆሮ ቆረጠ፤
…………………………… ሊዘጋ አፉን፡፡
ኢየሱስም አለ፤
………. ‹‹ሠይፍህን ወደ ሠገባው ክተት››፣
አብ የሠጠኝን ፅዋ፤ ልጠጣት በድፍረት፡፡
ለእኔ ብሎ ጌታ፤ ሕመሜን ታመመ ፣
ለሠው ፍቅር ብሎ፤ መስቀል ተሸከመ፡፡
ጌታችን ታሠረ፤ ምንም ሳያጠፋ፣
ቃሉ ሊፈፀም፤ ምክሩ የቀያፋ፡፡
ክርስቶስ ኢየሱስን፤ ጲላጦስ ገረፈው፣
የእሾህ አክሊል ጎንጉኖ፤
…………….. ከአናቱ አሳረፈው፡፡
ተሳለቁበት ጌታን፣ በጥፊ መቱት፣
በውጪ አውጥተው፤ ለህዝቡ ሠጡት፡፡
ለእኔ ብሎ ጌታ፤ ሕመሜን ታመመ ፣
ለሠው ፍቅር ብሎ፤ መስቀል ተሸከመ፡፡
መስቀሉን አሸክመው፤ ወሰዱት ጎልጎታ፣
ለሠው ፍቅር ብሎ፤ ነፍሱን ሊሠጥ ጌታ፡፡
ከሌቦቹ መሃል፤ ጌታዬን ሠቀሉት፣
ባልዋለበት ሃጢያት፤ አውለው አኖሩት፡፡
ጲላጦስም ፃፈ፣ የአይሁድ ንጉስ ብሎ፤
ከጭፍራዎቹ አንዱ፤ ጎኑ ላይ ጦሩን ተክሎ፡፡
ደምና ውሃ ወጣ፤ ከተወጋው ጎኑ፣
ስለኛ ሲሠዋ፤ ጌታ ማሳዘኑ፡፡
ለእኔ ብሎ ጌታ፤ ሕመሜን ታመመ ፣
ለሠው ፍቅር ብሎ፤ መስቀል ተሸከመ፡፡
ጌታ ነፍሱን ሠጠ፤ ዓለምን ፈወሰ፣
ሠውን ለማዳን ብሎ፤ ደሙን አፈሰሰ፡፡
የአርማትያሱ ዮሴፍ፤ ስጋውን ለመነ፣
ገንዞ ሊቀብር፤ ፍፁም እያዘነ፡፡
እንደአይሁድ ልማድ፤ ገንዘው ቀበሩት፣
በአትክልቱ ስፍራ፤ ጌታዬን አኖሩት፡፡
መግደላዊት ማርያም መጣች በማለዳ፣
ቢፈለግ ባዶ ነው፤ የመቃብሩ ጓዳ፡፡
ደቀመዛሙርቱ ሁሉ፤ ወደ መቃብር ሄዱ፣
የመፅሐፉን ቃል፤ ከቶ ሳይረዱ፡፡
እልል በሉ ሠዎች፤ ጌታችን ተነስቷል፣
የፋሲካው ንጉስ፤ ሞትን ድል አድርጓል፡፡
መልካም የፋሲካ በዓል…!
🔘እሸቱ ብሩ ይትባረክ🔘
በቃሉ መሠረት፤ ጌታ ከድንግል ተወለደ፣
ከሠማየ ሠማያት መጣ፤ እኛን ስለወደደ፡፡
ሠውን ሊያድን መጣ፣
ከሐጢዓት አረንቋ፤
………….ሃርነት ሊያወጣ፣
ሞትን በሞቱ ሊደመስስ፤
…………ሠይጣንን ሊቀጣ፡፡
እንትፍ ብሎ ምራቁን፤ እውሩን አበራ፣
የዓለም ብርሃንነቱ፤ በምድር ላይ በራ፡፡
የሚያዩም …. እንዲታወሩ፣
…… በሐጢዓታቸው እንዲታሰሩ፡፡
ጌታ ለፍርድ መጣ፣
ምኩራቡን ሊገለብጥ ስህተትን ሊያወጣ፡፡
የማያዩ …. እንዲያዩ ፣
……….. ጌታን እንዲለዩ፡፡
መስዋዕት ሆኖ መጣ፣
ዓለምን ነፃ ሊያወጣ፡፡
አይሁድ ሊወግሩት፤ ድንጋይን ቢያነሱ፣
ቀኑ ስላልሆነ፤ እምቢ አለ መንፈሱ፡፡
የኔ ጌታ…..
አልዓዛርን ከተኛበት፤ በድምፁ ቀሰቀሰ፣
ድውያውንን ሁሉ፤ አንድ በአንድ ፈወሰ፡፡
የአላዛር ወላጆች፤ አይሁድን ስለፈሩ፣
ድንቅ ታምራቱን፤ ሳይናገሩ ቀሩ፡፡
እሱ ሙሉ ሠው ነው፤ ጠይቁት ቢሉም፣
ፈሪሳውያኑ፤ ሊያምኑ ግን አልቻሉም፡፡
የእግዚአብሔርን ስራ፤ በብዙ ገለጠ፣
እልፍ ታዓምር ሠራ፣ ክፋትን ለወጠ፡፡
በዓለም እያለ፤ የዓለም ብርሃን ሆነ፣
የተኛውን ሁሉ፤ በፍቅሩ አባነነ፡፡
የካህናት አለቆች፤ ሸንጎ ተቀመጡ፣
ፈሪሳውያኑ፤ መያዣ አወጡ፡፡
መከሩ.. ዘከሩ፤ እቅዳቸውን ነደፉ፣
የቀያፋን ምክር፤ በድምፅ አሳለፉ፡፡
ከራሱ አይደለም፤ ቀያፋ የተናገረ፣
ስለህዝቡ ይሞት ዘንድ፤ ቃል ስለነበረ፡፡
ትዕንቢቱ ሊፈፀም፤ የግድ ስለሆነ፣
የቀያፋ ምክር፤ ተፈፃሚ ሆነ፡፡
የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉ፣
መጡ ህዝቡ ሁሉ፣
ሆሳዕና በአርያም እያሉ፡፡
ትዕንቢቱ እንዲፈፀም፤ ኢየሩሳሌም ተመረጠ፣
በአህያ ውርንጫ፤ ጌታ ተቀመጠ፡፡
የሠው ልጅ ሊከብር፤ ሠዓቱ ደረሰ፣
ነፍሴ ታውካለች፤ ብሎ እየመለሰ፡፡
በዓሉ ቢደርስም የአይሁዶች ፋሲካ፣
የእኛ ፋሲካችን፤ በፍቅር ተተካ፡፡
እኔ ቁራሽ አጥቅሼ፤ ለሱ የምሠጠው፣
እሱ ነው እኔን፤ በገንዘብ የሚሸጠው፤
………………………ብሎ ተናገረ፣
………………………ቀድሞ መሠከረ፡፡
ዲያቢሎስ ይሁዳን በሃሳቡ ደለለ፣
የአስቆሮቱ ይሁዳ፤ ለመሸጥ ቸኮለ፣
ጌታን አሳልፎ ሊሠጥ፤ ልቦናው ታለለ፡፡
ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሄር እመኑ፣
ቀኔ ደርሷልና፤ ምንም አትዘኑ፡፡
አላቸው ኢየሱስ፤ ለደቀመዛሙርቱ፣
ስፍራ ሊያዘጋጅላቸው፤ ሊፈፀም ትእንቢቱ፡፡
የካህናት አለቆች፤ ወደ ጌታ መጡ፣
በይሁዳ መሪነት፤ ኢየሱስን ሊይዙ፤
……………………. አምላክን ሊቀጡ፡፡
ማንን ትፈልጋላችሁ? ብሎ ቢጠይቃቸው፣
‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስን›› ሲሉ፤
……………………‹‹እኔ ነኝ›› አላቸው፡፡
ስምዖን ጴጥሮስም፤ መዘዘ ሠይፉን፣
የማልኮስን ጆሮ ቆረጠ፤
…………………………… ሊዘጋ አፉን፡፡
ኢየሱስም አለ፤
………. ‹‹ሠይፍህን ወደ ሠገባው ክተት››፣
አብ የሠጠኝን ፅዋ፤ ልጠጣት በድፍረት፡፡
ለእኔ ብሎ ጌታ፤ ሕመሜን ታመመ ፣
ለሠው ፍቅር ብሎ፤ መስቀል ተሸከመ፡፡
ጌታችን ታሠረ፤ ምንም ሳያጠፋ፣
ቃሉ ሊፈፀም፤ ምክሩ የቀያፋ፡፡
ክርስቶስ ኢየሱስን፤ ጲላጦስ ገረፈው፣
የእሾህ አክሊል ጎንጉኖ፤
…………….. ከአናቱ አሳረፈው፡፡
ተሳለቁበት ጌታን፣ በጥፊ መቱት፣
በውጪ አውጥተው፤ ለህዝቡ ሠጡት፡፡
ለእኔ ብሎ ጌታ፤ ሕመሜን ታመመ ፣
ለሠው ፍቅር ብሎ፤ መስቀል ተሸከመ፡፡
መስቀሉን አሸክመው፤ ወሰዱት ጎልጎታ፣
ለሠው ፍቅር ብሎ፤ ነፍሱን ሊሠጥ ጌታ፡፡
ከሌቦቹ መሃል፤ ጌታዬን ሠቀሉት፣
ባልዋለበት ሃጢያት፤ አውለው አኖሩት፡፡
ጲላጦስም ፃፈ፣ የአይሁድ ንጉስ ብሎ፤
ከጭፍራዎቹ አንዱ፤ ጎኑ ላይ ጦሩን ተክሎ፡፡
ደምና ውሃ ወጣ፤ ከተወጋው ጎኑ፣
ስለኛ ሲሠዋ፤ ጌታ ማሳዘኑ፡፡
ለእኔ ብሎ ጌታ፤ ሕመሜን ታመመ ፣
ለሠው ፍቅር ብሎ፤ መስቀል ተሸከመ፡፡
ጌታ ነፍሱን ሠጠ፤ ዓለምን ፈወሰ፣
ሠውን ለማዳን ብሎ፤ ደሙን አፈሰሰ፡፡
የአርማትያሱ ዮሴፍ፤ ስጋውን ለመነ፣
ገንዞ ሊቀብር፤ ፍፁም እያዘነ፡፡
እንደአይሁድ ልማድ፤ ገንዘው ቀበሩት፣
በአትክልቱ ስፍራ፤ ጌታዬን አኖሩት፡፡
መግደላዊት ማርያም መጣች በማለዳ፣
ቢፈለግ ባዶ ነው፤ የመቃብሩ ጓዳ፡፡
ደቀመዛሙርቱ ሁሉ፤ ወደ መቃብር ሄዱ፣
የመፅሐፉን ቃል፤ ከቶ ሳይረዱ፡፡
እልል በሉ ሠዎች፤ ጌታችን ተነስቷል፣
የፋሲካው ንጉስ፤ ሞትን ድል አድርጓል፡፡
መልካም የፋሲካ በዓል…!
🔘እሸቱ ብሩ ይትባረክ🔘
👍16