አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
በእናቴ ቁንጅናና ወጣትነት ቋመጠ፡፡ ትልልቅ ልጆች አሉት፡፡ ሚስቱ ጋር ተፋትቷል (ባይፋታ
ነበር የሚገርመው)፡፡ ይሄ የአምሳ ምናምን ዓመት ሰው አንዲት ፍሬ ልጅ ሊያጠምድ ዘርፌ የምትባል አቃጣሪ ያረጀች አሮጌ መረብ ሰፈሩ ላይ ወረወረ፡፡ “ዘርፍዬ እንዴት ያለችውን ልጅ አመጣሻት ደሞ! » ሲል ይታየኛል በዓይነ ህሊናዬ፡፡
አቲዬ የምትባል ሚስኪን አሳ የህይወትን ዋና ልትለማመድ ስትፍገመገም መረቡ ውስጥ ገባች፤ዘርፌ የምትባል ቁራጭ የአሳማ ስጋ የከፋት መንጠቆ ላይ ተሰክታ አቲዬን አታለለቻት፡፡

"አፀደ!”

"እመት እትዬ"

"ኤዲያ እንደ ባላገር እመት!' አትበይ፣ አቤት! ነው የሚባል፡፡ ነይ እስቲ ለጋሽ ቀለሙ ወተት
አድርሽለት!” አለች ዘርፌ፡፡

"እሽ!” ብላ የወተት ጠርሙሱን እንስታ ልትሄድ መንገድ ጀመረች - የእኔ ታዛዥ አቲዬ፡፡ ባልቴቷ ተቆጣች::

ነይ ወዲህ የምን መንካተት ነው እቴ..ማንም መደዴ ቤት የምትሄድ መሰላት እንዴ…እንዲህ ተንኳተሽ ትልቅ ሰው ቤት ...ምኗ ገልቱ ነሽ አንችዬ..በይ ፊትሽን ታጠቢ እግርሽንም እዛ ድንጋይ ላይ ፈትገሽ ታጠቢው።

አቲዬ ሰውነቷ ነክቶት የማያውቀውን ልብስ፣ እግሯ ተጫምቶት የማያውቀውን ጫማ ከእመቤቷ ተቸራት፡፡ በደስታ ሰከረች፡፡ ስለከተሜ ሰዎች ቸርነት የሰማችው ቃል ስጋ ለብሶ ፊቷ ሲገተር አየችው:: አበባ መሰለች፡፡ ድሮም አበባ ነበርች !! እንኳን ያኔ አሁንም ውብ ናት የእኔ እናት !!

በዚህ ዓይነት ቀለሙ ለሚባለው ውሻ ወተት አደረሰች፡፡ደጋገመችው፡፡ ስትመላለስ ቆየች፡፡

የቀለመወርቅ ቤት ቤተመቅደስ መሰላት፣ ካልታጠቡ የማይረግጡት፡፡ አንድ ሌላ ቀን ዘርፌ አቲዬን ጠራቻት፡፡

"አፀደ”

"እመ...አቤት እትዩ!” (እመት አትበይ የባላገር ነው' ተብላለቻ፡፡)
ጋሽ ቀለሙ አመም አድርጎታል፡፡ ቤት ሰውም የለ፣ ሂጂ እስቲ እህል ውሃ ስሪለት፡፡ እኛ እያለን
በረሀብ አይሞት መቸስ ጡር ነው፡፡”

"ምን አገኛቸው?!” አለች አቲዬ የኔ የዋህ በእባቦች ጨዋታ መሃል ንፁህ ልቧን በአደራ እያስቀመጠች፣

"ምን እንደነካው እሱኑ ጠይቂው፣ እኔ መች ሞልቶልኝ እየሁት ብለሽ” አለች ዘርፌ፡፡

አቲዬ ወደ አቶ ቀለሙ ሄደች፣ ዋለች፣ አደረች፡፡ ልታስታምም ሄዳ እድሜ ልኳን ህሊናዋ ውስጥ የሚመረቅዝ በሽታ ይዛ ተመለሰች: አቲዬ ከዛን ቀን ጀምሮ ቅስሟ ተሰበረ፡ ፈገግታዋ ጠፋ፡
አንገቷን ደፋች፡፡ ቀለመወርቅ ይሉት መዥገር ግን ወጣትነቷን የመጠጠው ይመስል አማረበት
አረማመዱ ሳይቀር እንደወጣት ሆነ፡፡ ግዴላችሁም እድሜም እንደገንዘብ ይነጠቃል፡፡ ይሄ
ሰው የእናቴን እድሜ በግፍ ነጥቋታል፡፡

አቲዬ በዚህ ልክ የሌለው መከፋት፥ መግለጫ አልባ በሆነ ቅስም መሰበር ውስጥ እንዳለች :
“አፀደ!” አለች አሰሪዋ ዘርፌ፡፡
አቲዩ "አቤት!" አላለችም፣ ዝም ብላ አቃጣሪዋ ፊት ሄዳ ቆመች፡፡ እመትን በስልጣኔ ስም "አቤትን'
ከክብሯ ጋር ቀምተዋት ምኑን አቤት ትበል…፡፡ ዘርፌ ትእዛዟን እንዲህ ስትል ጀመረች፣

“ጋሸ ቀለሙ ሴት ሂጃና…"

“አልሄድም !" አለች እንባ ተናንቋት፡፡

“ምናልሽ እንች እከከከከከ ጭቅቅትሽን ሳላቅቅልሽ እንዲህ አፍሽን ሞልተሽ ትሰድቢኝ " ባልቴቷ በያዘችው የኒኬል ሰሀን አቲዬን ፊቷ ላይ ደረገመቻትና፣ እች ደነዝ እጄን አሳመመችኝ አለች
ሰሀኑ የስሚንቶው ወለል ላይ ወድቆ ተቅጨለጨለ፡፡ አቲዩ በቀኝ እጇ ሰሀኑ ያረፈበትን ፊቷን
ሸፍና፣ አግሯ እንደመራት ወደ መኪና መንገዱ በረረች፡፡ ትንሽ እንደሄደች እዚሁ አሁን ትልቁ ዳቦ
ቤት የተሰራበት ቦታ ላይ አንዲት ኪዮስክ ነበረች፣ አንዳንዴ እቲዬ እየተላከች እቃ የምትገዛባት
ባለቤቷ የአቲዬን ወጣትነት ስታይ ሁሌ ምራቋን የምትውጥ (ለሰራተኝነት)…ጠራቻት፡፡

"አፀደ.አንችን እኮ ነው!”

ዝም፡፡

“ምን ሆነሻል ?

ዝም…እርምጃዋን ቀንሳ እየቆመች፡፡

“አንችን እኮ ነው!”

ዝም፡፡

“እንዴ ደግሞ ፊትሽ ምን ጉድ ነው? እረ ጉዴ፣ ምንድነው ይሄ ሁሉ ደም?"

አቲዬ ደነገጠች፡፡ እጇን ከፊቷ ላይ እንስታ ተመለከተችው፣ በደም ተሸፍኖ ነበር፡፡

አሁን ያፈነችው እንባ ፈነዳ፡፡ ከልጅነቷ ጀምሮ ውስጧ የተጠራቀመው ጩኸት እና እዬዬ፣
መንደሩን የሚያሸብር ዋይታ ሆነ፡፡ መንደርተኛው ተሰበሰቡ፡፡

ምንድን ነው?

እንዴ እትዩ ዘርፈ ሰራተኛ አይደለችም እንዴ ምን አገኛት?”
ማናባቱ ነው የዘርፍዬን ልጅ እንዲህ ያደረጋት? ..ዘርፌ ዘርፍዬ…ወይዘሮ ዘርፌ እሜቴ ዘርፌ የዘርፌ ሰራተኛ
ሰው በመሆኗ ሳይሆን፣ በዘርፌ ንብረትነቷ መንደሩ ዘራፍ አለ፡፡

አኮ ማናባቱ ነው የነካት?

ተናገሪ ማነው የመታሽ?”

ዘርፌ ራሷ !

ዝም ሰፈሩ !! ዝምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምም!!

ምን ኣጥፍተሽ ነው" አሏት አቲዩን፡፡
እሷም ዝም !

ታስታውቃለች ተንኮለኛ፡፡ ዝም ያለችው ጥፋቷ ቢሆን ነው።"

አንዲች ዘርፌ.የሴት ወንድ መች መጨማለቅ ትወድና..አንድ ነገር ስታደርጊ አግኝታሽ ነው::”

መንደርተኛው ዘባረቅ፡፡ ይሄ ዘባራቂ ሁሉ…፡፡ ይሄ ጉዳይ ከሆነ ስንትና ስንት ዓመቱ ሰፈሩ ግን አሁንም ዘባራቂ ነው !! ባለ ኪዮስኳ ብቻ ለአቲዬ አገዘች፡፡ “የሚመታ ይምታት፣ ምንስ
ብታደርግ እንዲህ ደም በደም እስከትሆን ትመታታለች፡፡ እች ጥጋበኛ ባልቴት፣ ምነው እች
ሴትዮ በመቁረቢያ እድሜዋ እግሯን አንስታ ፏለለች” አለች በብስጭት፡፡

ባለ ኪዮስኳና ዘርፌ ፀበኞች ነበሩ፡፡ ሁለቱም በመንደሩ ውስጥ የተሰሚነት የክብር ጉዳይ
ያጋጫቸዋል፡፡ አቲዬ ባለኪዮስኳ ጋር ሰራተኛ ሆና ቀረች፡፡ እጣ ፋንታን በመሸሽ አያመልጡትም ::

ይህች ሴት የምትደገፈው ሁሉ እሾህ፡ የምትረግጠው ሁሉ አረንቋ ይሆንባት ዘንድ ድፍን አዲስ አበባን ማነው በአሜኬላ የሞላባት? የእኔ ከርታታ ኩንታል ሙሉ የምስር ክክ፡ ሱቅ ሙሉ
ባልትና ማዘጋጀት፣ የሚሸጥ እንጀራ መጠፍጠፍ ነበር የጠበቃት፡፡ ልብሷ ሰውነቷ ላይ ተበጣጥቆ ፀጉሯ ላይዋ ላይ ጀልቶ ብልጣ ብልጧ ባለኪዮስክ ጉልበቷን እንደ ምስጥ መጠጠቻት፡፡

ደም መጣጭ የደሀ ክብር መጣጭ ! መንደር ሙሉ መዥገር ! እቺ ሚሊየን አዲስአበቤ፣

አምራና ተውባ በየመንገዱ ሰበር ሰካ የምትል ወይዛዝርት፣ የሚንጎማለል ሸበላ ሁሉ፣ 'የሰው
ላብ ገንዘቤ ውስጥ የለም ብለህ ማል ቢባል እግሬ አውጭኝ በሚል ሯጭ መንገዱ በተሞላ

ታላቁ የሽሽት ሩጫ !!


አላለቀም
👍31👏4
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

የሁለት ከዋክብት መቀራረብ

አሁን እንግዲህ ማሪየስ አድጎ የሚያስቀና መልከ መልካም ወጣት ሆኖአል፡፡ አፍንጫው ስልክክ ብሉ ከቁመቱ ዘለግ ያለና በሩቁ የሴቶች ዓይን የሚስብ ጎረምሳ ነው፡፡ ረጋ ብሎ ሲራመድ የዋህነቱ ከፊቱ ይነበባል፡፡ ጭምትና አሳቢ ከመሆኑም በላይ ለአዋቂነቱ ወደር የለውም
ማሪየስ አንደበቱ የሚጣፍጥ፣ ከንፈሩ ወለላ፣ ጥርሱ ከወተት የነጣ ፈገግታው ውሃ የሚያደርግ ስለሆነ አሟልቶ የሰጠው ወጣት ነው::

ድኅነት አኮማትሮት የተቀዳደደ ልብስ ይለብስ በነበረበት ጊዜ እንኳ ልጃገረዶች በአጠገቡ ሲያልፉ ሰርቀው እንደሚያዩት ያውቃል፡፡ እርሱ ግን አቀርቅሮ በመሄድ ይሸሻቸዋል፡፡ የለበሰው ልብስ እያዩ የሚሳለቁበት እንጂ
በውበቱ ተስበው እንደሆነ አይገነዘብም ነበር፡፡ እውነታው ግን በውበቱ በቁመናው ተማርከው ነበር የሚያፈጥጡበት::

ከሚያፈጥጡበት ሴቶች መካከል ሁለቱን ግን አይሸሽም፡፡ እነርሱ
ባለጢማምዋ አሮጊት ሠራተኛውና አንዲት መንገድ የሚያያት ልጅ ናቸው ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሮ ዘወትር ለሽርሽር በወጣ ቁጥር የሚያያት
አንዲት ልጅ ነበረች፡፡ በየቀኑ በአንድ በተወሰነ መንገድ ሲያልፍ አንድ ጠና ያለ ስልሣ ዓመት ገደማ የሚሆነው ሽማግሌና አንዲት ልጅ ዘወትር ከአንድ ቦታ ጎን ለጎን ቁጭ ብለው ያያቸዋል፡፡ ሰውዬው ኮስተር ያለና ጡረታ የወጣ ወታደር ይመስላል:: ሀዘን ከፊቱ ላይ ይነበባል:: እርሱን ደፍሮ
ለማናገር ያስፈራል::

አብራው የምትቀመጠዋን ልጅ ማሪየስ በመጀመሪያ ያያት እለት
አሥራ ሦስት ወይም አሥራ አራት ዓመት ቢሆናት ነው ብሎ ገምቷል
በመጀመሪያ ሲያያት ይህን ያህል መልክዋ የሚስብ አልመሰለውም ነበር በኋላ ስታድግ ግን በጣም ቆንጆ ሆነችበት:: ልብስዋ የገዳም ተማሪ ዩኒፎርም ነው። ሽማግሌውና ልጅትዋ ጎን ለጎን ቁጭ ብለው ለተመለከተ አባትና ልጅ ለመሆናቸው አያጠራጥርም።

ማሪየስ በአጠገባቸው ሲያልፍ ሁለትና ሦስት ቀን ድረስ እነዚ ሰዎች ምንድን ናቸው ብሎ ራሱን ከመጠየቅ ሌላ ብዙ አልተጨነቀበትም እነርሱ ግን እንዲያውም ያዩት አይመስልም:: ሁለቱ ሲገናኙ የራሳቸው
ጨዋታ ይጫወታሉ እንጂ ለአለፈና ለአገደመ ደንታ አልነበራቸውም ልጅትዋ እየሳቀች ሳታቋርጥ ለረጅም ጊዜ ታወራላች:: ሽማግሌው
በመጠኑ ነው የሚያወራው አስተያየቱ አባት ለልጁ ያለውን ፍቅር ያመለክታል፡:

በዚያ መንገድ በየቀኑ መጓዝ እንደልምድ አድርጎ ወስዶታል፡፡ በየቀኑ በዚያ ሲያልፍ ደግሞ እነዚያን አባትና ልጅ ከተወሰነ ቦታ ተቀምጠው ያያቸዋል፡፡ ማሪየስ በመንገዱ አንድ ጊዜ ብቻ ማለፍ ሳይሆን በቀን አምስት ወይም ስድስት ጊዜም የሚያልፍበት ቀን አለ፡፡ እንግዲህ ሰዎቹን በየቀኑ
አምስት ወይም ስድስት ጊዜ ያያቸዋል ማለት ነው:: ግን ሁለቱም ወገን ሰላምታ አይለዋወጡም፡፡ እርግጥ ነው ሁለቱ ሰዎች በየቀኑ በተወሰነ
ሰዓት ከዚያች ከተወሰነች ሥፍራ ስለሚቀመጡ የማሪየስን ብቻ ሳይሆን የሌሎችም ከዚያ ሥፍራ አየር ለመቀበል የሚወጡ ተማሪዎች ዓይን መማረካቸው አልቀረም፡፡ ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል ኩርፌይራክም ይገኛል:: ማሪየስ በልጅትዋ ስለተሳበና ዘወትር የምትለብሰው ልብስ ጥቁር ስለነበር «ወት/ጥቁር»፣ አባትየው ደግሞ ብዙውን ጊዜ ነጭ ልብስ ስለሚለብስ
«ክቡር ነጭ» የሚል ስም አወጣላቸው:: ስሞቹ እየተለመዱ ስለሄዱ ተማሪዎች በዚያ ባለፉ ቁጥር «ክቡር ነጭና ወት/ ጥቁር ሥፍራ ሥፍራቸውን ይዘዋል» እያሉ ይፎትቷቸዋል፡፡

እኛም ለአገላለጽ ስለሚያመች ስለታሪካቸው ስንናገር በዚሁ ስም
እንጠራቸዋለን፡፡ ማሪየስ በየቀኑ ለአንድ ዓመት ሙሉ ሲያያቸው ክቡር ነጭን ይወዳል:: ወ/ት ጥቁርን ግን እስከዚህም አላፈቀራትም፤ ግን አይጠላትም::

በሁለተኛው ዓመት ማሪየስ ለራሱ እንኳን ግልጽ ባልሆነ ምክንያት
በዚያ መንገድ ለስድስት ወር መንሸራሸሩን ያቆማል፡፡ ከስድስት ወር በኋላ አንድ ቀን በዚያ ያልፋል:: አየሩ ጥሩ ስለነበር ማሪየስ ደስ ብሎት ነበር
የሚራመደው:: ከዚያች ከተወሰነች ሥፍራ ሲደርስ አባትና ልጅ አሁንም ከዚያች ከተወሰነች ሥፍራ ተቀምጠው ይጫወታሉ፡፡

ሲቀርባቸው በሰውዬው ላይ ምንም ለውጥ አላየም:: ልጅትዋ ግን በጣም ተለውጣለች:: በጣም ቆንጆ ሆና ታየችው:: በአጠገባቸው ሲያልፍ
አቀርቅራ ስለነበር ዓይኖችዋን ለማየት አልቻለም::

በመጀመሪያ የልጅትዋ ታላቅ እህት እንጂ እርስዋ አልመሰለችውም::
ግን እየተመላለሰ ሲያያት ራስዋ መሆንዋን አረጋገጠ፡፡ በስድስት ወር ጊዜ እጅግ ውስጥ ትልቅ ሴት መሰለች:: የደረሰችበት እድሜ እንደ አበባ የምትፈነዳበትና
አምራና ደምቃ የምትታይበት ነበር፡፡ በድንገት የጽጌረዳ አበባ መሰለች::የትናንትናዋ የዋህ ሕፃን የዛሬዋ አደገኛ ሴት ሆነች::

ቁመትዋ ብቻ አልነበረም ያደገው መልኳም ጭምር ነበር የተለወጠው:: በዝናብ ወራት ዛፎች ብዙ ቅርንጫፎችን እ
አብቅለው በመስከረምና በጥቅምት ወራት በአበቦች ቅርንጫፎቻቸውን እንደሚያጌጡ
ሁሉ ልጅትዋም በአለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በመልክ አበባ አጌጠች፥ ተዋበች::

ጥቁር ልብስዋን አውልቃ ከቀለምዋ ጋር የሚሄድ ያሸበረቀ ልብ ለበሰች:: በአጠገብዋ ሲያልፉ የምትቀባው ሽቶ ያውዳል፤ የልጅነት ጠረንዋ ልብ ይሰነጥቃል::

በሁለተኛው ቀን ማሪየስ በአጠገብዋ ሲያልፍ ቀና ብላ አየችው::የተለየ ስሜት አልሰጣትም:: ማሪየስ ሌላ ነገር እያሰበ መንገዱን ቀጠለ። አራት ወይም አምስት ጊዜ እየተመላለሰ በልጅትዋ አጠገብ አለፈ።
እንደለመደው ለመንሸራሸር ነበር እንጂ ዞር ብሎ እንኳን አላያትም፡፡

በሚቀጥሉት ቀናት የሽርሽር ሰዓቱን ጠብቆ በዚያ አለፈ፡፡ ግን ወደ እነዚያ ሁለት ሰዎች ብዙም አልዞረም:: ልጅትዋ መለዋወጥዋንና ቆንጆ
መሆንዋን ካረጋገጠ በኋላ ከወጥመድዋ እንዳይገባ ቸለል ማለቱን መረጠ።የሚያልፈው ግን እርስዋ ከምትቀመጥበት መቀመጫ በጣም ቀርቦ ነበር፡፡

በጣም ደስ የሚል ቀን ነው:: ማሪየስ ልቡን ገልጦ የተፈጥሮ ውበት ራሱን አበርክቷል፡፡ የተፈጥሮ ውበት መላ ሕሊናውን ስለያዘበት ሌላ ነገር
ከጭንቅላቱ ውስጥ ሊገባ አልቻለም:: የተፈጥሮን ውበት እያሰላሰለ በተለመደው ሥፍራ ሲያልፍ የልጅትዋና የእርሱ ዓይን ግጥም አሉ፡፡ዓይንዋ ውስጥ ምን አለ? ማሪየስ እንዲነግረን ብንጠይቀው እንኳን ሊነግረን
አይችልም:: ልብን የሚሰልብ ነገር አለው:: ግን ዓይንነቱ ያው ዓይን ነው።
ሆኖም አንድ አይነት እንግዳ የሆነ ብልጭታ አለው።

ዓይንዋን መለስ አደረገችው:: እርሱም መንገዱን ቀጠለ፡፡

ዓይንዋን ሲያየው ያ የምናውቀው ገራገሩ የልጅ ዓይን አልነበረም፡፡
ምሥጢራዊ ጥልቀት ነበረው:: ገለጥ አድርጋ ወዲያው ነው የመለሰችው፡፡

እያንዳንድዋ ወጣት ልጃገረድ የዚህ የተለየ አስተያየት የምታይበት ጊዜ አላት:: በዚያች ሰዓት ከዓይንዋ ለሚገባ ወዮለት!

ገና ምንነትዋን የማታውቅ ነፍስ የመጀመሪያ እይታ ከጎሕ መቅደድ
ጋር ይመሳሰላል፡፡ ጎሕ ሲቀድ አንድ የማይታወቅና የሚያበራ ነገር ከእንቅልፉ ሚነቃበት ሰዓት ነው:: ጎሕ ሲቀድ ያልታሰበ ውበት፧ ያልታሰበ ድምቀት ያልተጠበቀ ነገር ያሳያል፡፡ እንዲሁም የፈነዳች አበባ የምትመስል ልጃገረድ እይታ ምንም ሳይታወቅ ካልታሰበ ወጥመድ ውስጥ ልብን አጥምዶና ያልታሰበ ጭንቀት ውስጥ ወዝፎ ካልተጠበቀ መንከራተት ያደርሳል:: ይህ
👍13😁2
ምትሃታዊ ኃይል ያለው ሳይወዱ በግድ ልብን ፈንቅሎ በመግባት እንደ ሽቶ ከሩቅ የሚጠራውና እንደ መርዝ ከቅርብ የሚያብሰለስለው ሕቅ ሕቅ፧ ያዝ
ለቀቅ፤ ሰፋ ጠበብ የሚያደርገውና ሳይታሰብ በድንገት አንቆ የሚይዘው ነገር ሰዎች ፍቅር ብለው ይጠሩታል፡፡ ይህ ፍቅር የሚሉት ነገር ማሪየስን
ጠለፈው::

ያን እለት ማታ ማሪየስ ወደ ቤት በተመለሰ ጊዜ የለበሰውን ልብስ
ወደ መስታወት ተመለከተው:: ግርማ ሞገስ የሌለውና በሰዎች ዘንድ ክብር ሊያጎናጽፍ የማይችል ልብስ መሆነን ለመጀመሪያ ጊዜ ተገነዘበ፡፡ ይህም ሞኝነት እንደሆነ አወቀ:: በሥራ ልብስ ሽርሽር መውጣት ስህተት መሆኑን
ደረሰበት:: ዘወትር የሚለብሰው የሥራ ልብስ የቀን ሠራተኛ እንዳስመሰለው አሁን ገና ገባው::

በሚቀጥለው ቀን ሽርሽር ከመሄዱ በፊት የክት ልብሱን ከቁም ሣጥን
አወጣ፡፡ አስተካክሎ ከለበሰና ፀጉሩን ጥሩ አድርጎ ካበጠረ በኋላ ወደ ሽርሽሩ ቦታ ሄደ:: ከሥፍራው እንደደረሰ ክቡር ነጭ እና ልጅትዋ ተቀምጠዋል፡፡
ኮቱን ቁልፍ ቆለፈ:: የተጨማደደ ካለ ቀጥ ብሎ እንዲዘረጋ ኮቱን ሳብ፤ሳብ፤ አሸት፧ አሸት አደረገው:: አባትና ልጅ ተቀምጠውበት ከነበረው ሥፍራ ደረሰ፡፡ ከሥፍራው እየተጠጋ ሲሄድ ከእርምጃው ዝግ እለ::
ለእርሱ እንኳን ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ሰዎቹ ከነበሩበት ሲደርስ ቀጥ ብሉ በመቆም ወደ አባትና ልጅ ፊቱን አዞረ:: በሌላ ቀን መንገዱን በመቀጠል
አልፎአቸው ነበር የሚሄደው:: የልጅትዋን ዓይን በመሳብ ትየው ወይም አትየው አይታወቅም:: ሆኖም ቀረም እርሱ ከአጠገብዋ ቀጥ ብሉ ራሱን ለትርኢት አቀረበ፡፡ ወደፊት ለመጓዝ ፈልጎ የስሜቱ ኃይል ጉልበቱን ስላፈሰሰበት መራመድ ተሳነው:: ልጅትዋ ሠርቃ ማየትዋን ተመለከተ::
በእርስዋ በኩል አፍጥጦ ማየቱን አልደፈረም:: ግን ሠረቅ አድርጎ
እንደተመለከተው ባለፈው ቀን የለበሰችውን ልብስ ለብሳ ከሽማግሌው ጋር ትጫወታለች፡፡ ወደፊት ጥቂት ተራምዶ ወደኋላ ተመለሰ፡፡ እንደገና በቆንጆይቱ ልጅ አጠገብ አለፈ:: ልቡ በኃይል ይመታል:: ዞር ብሎ ሳያያትም
እርስዋ እንደምታየው አልተጠራጠረም:: አፍጥጣ የምታየው መሆኑን በእሳብ ሲያሰላስል የሆነ ነገር አደናቀፈው::

ሰዎቹ ከነበሩበት ጥቂት እልፍ እንዳለ ከድንጋይ ላይ ቁጭ አለ፡፡
ከዚያ በፊት አልፎ ይሄዳል እንጂ ተቀምጦ አያውቅም:: ከሩብ ሰዓት በኋላ ተነስቶ እንደገና ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ሰውዬውም ሳያየኝ አይቀርም የሚል እምነት ስላደረበት እንደማፈር አለና ወደ መሬት አቀርቅሮ ነው መንገዱን
የቀጠለው:: ወደ ቤቱ ሄደ::

ያን እለት ማታ እራት መብላቱን ረስቶ ከክፍሉ ውስጥ እንደተጋደመ ሁለት ሰዓት ሆነ፡፡ ከዚያ በኋላ ሆቴል ቤት ፍለጋ ከመውጣት ደረቅ ዳቦ
መብላቱን ስለመረጠ ደረቅ ዳቦ ቆርጥሞ ልብሱን አውልቆ ከመስቀያ ላይ ከሰቀለ በኋላ ተኛ::
በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንት በየቀኑ ከሽርሽሩ ቦታ እየሄደ አባትና ልጅ ከሚቀመጡበት አካባቢ እየሄደ ምክንያቱን ሳያውቅ ከዚያ ይቀመጣል::ልጅትዋን ባያት ቁጥር በየቀኑ በይበልጥ የቆነጀች ይመስለዋል::

በሁለተኛው ሳምንት መጨረሻ ገደማ ያልተጠበቀ ነገር ይሆናል:: "ማሪየስ ከተለመደው ቦታ ቁጭ ብሎ መጽሐፍ ያነባል፡፡ ግን መጽሐፉን ይያዘው እንጂ እንደ እውነቱ ከሆነ አያነበውም ነበር፡፡ ለሁለት ሰዓት ቁጭ ብሎ ከመጽሐፉ ላይ ያፍጥጥ እንጂ አንድ ቅጠል እንኳን አልጨረሰም፡፡
ድንገት ቀና ሲል አንድ ነገር በማየቱ መላ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡፡ ልጅትዋ
የአባትዋን ክርን ይዛ ወደ እርሱ ስትመጣ ተመለከተ:: ማሪየስ ገልጦት የነበረውን መጽሐፍ አጠፈ፡፡ መልሶ ገለጠው:: ለማንበብ ሞከረ፣ መላ ሰውነቱ ተቅበጠበጠ፡፡ በቀጥታ ወደ እርሱ ነው የሚመጡት:: «ወይኔ ኮተት
ጉዴ» ሲል አሰበ፡፡ «ምን ሊሉኝ ነው::አባትና ልጅ ቀስ ብለው ነው የሚራመዱት:: ሺህ ዓመት መሰለው:: ግን ለጥቂት ሰኮንድ ነው የተጓዙት፡፡
«በአጠገቤ ሊያልፉ ነው? ወይስ ሊያናግሩኝ ነው? ካለፈችም እኮ ከቅርብ ሆና ታየኛለች» ሲል ማሪየስ ተጨነቀ:: መጽሐፉ ላይ እንዳተኮረ ኮቴ ስለሰማ መቃረባቸውን አወቀ፡፡ ሽማግሌው በቁጣ የሚያየው መሰለው።
እንዳቀረቀረ ጥቂት ቆየ:: ቀና ቢል ከአጠገቡ ናቸው:: ወጣትዋ በአጠገቡ አለፈች፡፡ ስታልፍ ትኩር ብላ አየችው:: ስታየው ተኮሳትራ ስለነበረ ልቡ እንደ ከበሮ መታ::

አንጎሎ በእሳት የተያያዘ መሰለው:: «በአጠገቤ አለፈች እኮ! ደግሞ እንዴት ብላ ነው የምታየኝ!» እርሱ ካሰባት ይበልጥ ቆንጆ መሰለችው። አይ ቁንጅና፧ ዘፋኞችን አፍ የሚያስከፍት፤ ደራሲያንን ብዕር የሚያስጨብጥ
ቁንጅና! የሰውን ብቻ ሳይሆን የመልአክትን ውበት ያጣመረ ቁንጅና! በቅዠት ዓለም የሚዋኝ እንጂ በእውን ሰው ሆኖ ሰው የሚያይ አልመሰለውም፡፡ ጫማው ላይ ትንሽ አዋራ ስላየና እርስዋም ከነአዋራው ስላየችው ተናደደ፡፡
በዓይኑ ተከተላት:: ከዓይኑ በተሰወረች ጊዜ ብድግ ብሉ ተነስቶ እንደ እብድ ከወዲያ ወዲህ ይቅበጠበጥ ጀመር፡: እንደወፈፌም ብቻውን ሳቀ፣
ጮክ እያለ ተናገረ:: በፍቅር መያዙን በአካባቢው የነበረ ሁሉ አወቀበት::

ከዚያችሥፍራ በየቀኑ ሲመላለስ አንድ ወር ሙሉ አለፈ፡፡ የመሄጃው
ሰአት ከደረሰ ወደዚያ ከመሄድ የሚያስቀረው ነገር ጠፋ፡፡ «አገልግሎት ማበርከት ሄደ» እያለ ኩርፌይራክ ይሸረድደው ጀመር፡፡ በሄደ ቁጥር ልጅትዋ ታየዋለች።

ቀስ በቀስ እየደፈረ በመምጣቱ አባትና ልጅ ከሚቀመጡበት እየተጠጋ መጣ፡፡ አባትየው እንዳያውቅበት የተቻለውን ሁሉ አደረገ፡፡ መቀመጫውን
ጀርባ እንዲሆን መረጠ፡፡ ከዛፎች ወይም ከዚያ ከሚገኝ ሐውልት
ጀርባ ሆኖ ለልጅትዋ በግልጽ እንዲታይና ከአባትዋ ግን እንዲሰወር የሚያስችል
ስፍራ መርጦ ነበር የሚቀመጠው፡፡ አንዳንድ ጊዜ መጽሐፍ በእጁ ይዞ ዛፍ በመደገፍ ከግማሽ ሰዓት በላይ እየቆመ ያያታል፤ እርስዋም እየሰረቀች
ታየዋለች:፡ አመለካከቱ የጤና አለመሆኑን ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ገብቷታል፡፡ የእርስዋም የዓይን ምላሽ ነገር እንዳለበት አውቋል፡፡

ማሪየስ እንደዚያ ሲመላለስ አባባ ሸበቶም ሳይገባው አልቀረም::
አሁን ክቡር ነጭ በማለት ፋንታ አባባ ሸበቶ እያለ ነው የሚጠራው::ማርየስ ይከተላቸው እንደሆነ ለማየት ዘወትር ከሚቀመጡበት ተነስተው
መላ ስፍራ ይቀይሩ ጀመር፡፡ ማሪየስ ፈተና የተሰጠው መሆኑን ባለመጠርጠር ስተት ይሠራል፡፡ አባባ ሸበቶ ሰዓት እየቀያየረ ይመጣ ጀመር፡፡ አንዳንድ
ልጅትዋን ይዞ አይመጣም:: ልጅትዋ አብራ ካልመጣች ማሪየስ ቶሎ ይሄዳል፡፡ ሌላው ስህተት!

ሦስተኛ ከባድ ስህተት ልጅትዋ የት እንደምትኖር ለማወቅ መፈለጉ
፡፡ አንድ ቀን ተከትሉአቸው ሄደ:: መኖሪያቸውን አየ፡፡ መኖሪያቸውን
ካየ ጀምሮ ከሽርሽሩ ቦታ እስኪሄዱ ድረስ ጠብቆ ኋላ ኋላቸው እየተከተለ ይሸኛቸው ጀመር፡፡ አንድ ቀን ማታ አንደ ልማዱ ከቤታቸው ድረስ ተከትሎ
የድፍረቱ ብዛት ዘበኛውን አነጋገረው::

«አሁን የገቡት ሽማግሌ የሚኖሩት አንደኛ ፎቅ ላይ ነው ፧ አይደል?»
“አይ ሦስተኛ ፎቅ ላይ ነው የሚኖሩት፡፡»

በሚቀጥለው ቀን አባባ ሸበቶና ልጅትዋ ከሽርሽሩ ቦታ ቶሎ ሄዱ።
👍17
እንደ ልማዱ ማሪየስ ተከተላቸው:: ከቤታቸው ከመግባታቸው በፊት አባባ ሸበቶ መለስ በማለት ማሪየስን አፍጥጦ አየው:: በሚቀጥለው ቀን ከሽርሽሩ
ቀሩ:: ማሪየስ እስኪጨልም ጠበቃቸው:: በጣም ሲመሽ ተነስቶ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሄደ:: ሦስተኛ ፎቅ ላይ መብራት አየ:: መብራቱ ሲጠፋ ከወዲያ ወዲህ ተንሸራሸረ:: መብራቱ ሲጠፋ ተነስቶ ወደ ቤቱ ሄደ በዚያ ዓይነት ድርጊት አንድ ሳምንት ሙሉ አሳለፈ::
በስምንተኛው ቀን ወደ ልጅትዋ ቤት ሲሄድ መብራት አልበራም::
«ለምን!» አለ ለራሱ፡፡ «እስካሁን መብራት አላበሩም ማለት ነው? ወይስ !
ምንድነው ነገሩ? ጊዜው ጨልሞአል፡፡» እስከ እኩለ ለሊት ጠበቀ፡፡ በመስኮት !
የሚታይ መብራት አልነበረም፡፡ በጣም አዝኖ ወደ ቤቱ ሄደ ::
በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ከሰዎቹ ቤት ሄዶ በማንኳኳት ዘበኛውን
ኣፈአነጋገረው::
«ሦስተኛው ፎቅ ላይ የነበሩት ሰውዬስ?»
«ለቅቀዋል፡፡»
«ከመቼ ጀምሮ?» አለ ማሪየስ በዱላ እንደተመታ ሰው እየተንገዳገደ:
«ከትናንት::»
«የት ነው የገቡት ኣሁን?»
«እኔ እንጃ፡፡»
«አድራሻቸውን አልተዉማ?»
«አልተዉም::»

💫ይቀጥላል💫
👍164
#ዶክተር_አሸብር


#ሶስት


#በአሌክስ_አብርሃም


...አቲዩ ለስድስት ወር ከሰውነት ተራ እስከትወጣ ለባለኪዮስኳ ስትሰራ ከከረመች በኋላ ክረምት ገባ፡፡ ባላኪዮስካ አቲዬን በንስር ዓይን ስትከታተላት ነበር፡፡ ከእያንዳንዱ ቀን ጋር
እየተሽቀጓደመች ነበር፡፡ አንድ ማለዳ የአቲዬን ድሪቶ ልብሶች በፌስታል ቋጥራ ከድፍን ሃምሳ
ብር ጋር ሰጠቻትና፣ “በይ እግዜር ይከትልሽ!” ብላ ከቤቷ አስወጥታ ወረረቻት፡፡ የአቲዬ ሆድ ገፍቶ ነበር፡፡ የቀለመወርቅ ፅንስ ከውስጥ፣ የመንደሩ ሰው ከውጭ እየገፋ ሰው በሞላው አገር
እናቴን ምድረ በዳ ላይ አቆሟት፡፡

አቲዪ ስትፈጭ እና ስታነፍስ የዋለችው የምስር ክክ ብናኝ ፊቷና ፀጉሯ ላይ ተነስንሶ ነበር፡፡ ከስድስት ወር በፊት የነበረችው ልጅ እግር ቆንጆ ልጃገረድ ናት ቢባል ቀለሙ ራሱ አያምንም፡፡ መንገድ ዳር ቆመች፡፡ የክረምት ዝናብ ያካፋል፡፡ አንድ የመኪና ዕቃ መለዋወጫ ሱቅ በር ላይ ፍዝዝ ብላ ቆመች::ምንም እያየች ምንም ሰው፣ ምንም መኪና ምንም ቤት፡፡ ህይወት ዝም የምትልበት፣ አዕምሮ ዝም
የሚልበት፣ የሰው ልጅ ለሆነች ቅፅበት በቁሙ የሚሞትበት ቅፅበት አለ አይደል፡፡ አቲዬ በቁሟ ሞተች፡፡

አላዛርን ከሞት ያስነሳ ራሱም ከሞት የተነሳ ክርስቶስ አቲዬ! ብሎ ልክ እኔ እንደምጠራት
ጠራት፡፡ ዞር አለች ወደ ኋላዋ፡፡ ክርስቶስ ሳይሆን እንዲት ምቾት መድረሻ ያሳጣት ቆንጆ
ወጣት ነበረች … “ወደ ውስጥ ግቢ! ዝናብ መታሽ እኮ” አለቻት አቲዬን፡፡ ገና ሲያጉረመርም
እግሬ አውጭኝ ብሎ ሰው የሚሸሸው ዝናብ እንኳን፣ እንዳሻው ሰው ሳይ ይጨፍር ዘንድ ሰው በቁሙ የሚጠፋበት ቀን አለ፡፡ አቲዬ ጠፍታ ነበር፡፡

ወጣቷ ከፍ ያለ ወንበር ላይ ተቀምጣ እንፋሎቱ ወደ ላይ የሚመዘዝ ትኩስ ሻይ እየጠጣች ነበር፡፡

እቲዬ ወደ ውስተ ገባችና ኩርምት ብላ አንዱ ጥግ ቆመች፡፡ እንደ ቆመች ዝናቡ አባራ፡፡ ሰዉ
በያቅጣጫው ሩጫውን ጀመረ፡፡ አቲዪ ግን አልተንቀሳቀሰችም፡፡ የእርሷ ዝናብ አላባራም፣
መጠጊያ ላጣ ሰው የሕይወት ዶፍ አባርቶ አያውቅም፡፡ ሰው የፍቅር ዣንጥላ፣ የዝምድና ዣንጥላ፤
የጓደኝነት ዣንጥላ፣ የትዳር ዣንጥላ፣ የእውቀት ዣንጥላ፣ የስራ ዣንተላ፣ የተስፋ ዣንጥላ፣
የእምነት ዣንጥላ ይዞ ስለሚኖር እንጂ ከሕይወት ሰማይ ላይ ነፍስን የሚያበሰብስ መንፈስን
እንደ ወረቀት የሚያላሽቅ የብቸኝነት እና የተስፋ መቁረጥ ዝናብ አባርቶ አያውቅም፡፡

የአቲዬ ዝናብ አላባራም፡፡ ይሄን ሁኑ የነፍስ ዣንጥላ ጨካኝ ንፋስ ከእጇ ነጥቋታል፡፡ ንፋሱ
ቀሚሷን በግድ ገልቦ ውስጧ ቅዝቃዜ አስቀምጧል፡፡ ንፋሱ የሕይወት አቧራ አንስቶ ፊቷና
ፀጉሯን አልብሷል።ንፋሱ የተስፋ ጎጆዋን አፈራርሶ እዚህ አቁሟታል፡፡ አቲዬ የእኔ እናት
መሄጃ የላትም።

ቁልፎች ታንኳኩ፡፡ ቆንጆዋ ልጅ ጃኬቷን ደረበች፡፡ ውጭ የተደረደሩ እቃዎችን አስገባች፤ እናም ቁልፏን በሚያማምሩ ጣቶቿ እንዳንጠለጠሰች አቲዩን ግራ በመጋባት አየቻት፣ “
ውጪ!' ማለት ብልግና ነው፡፡ ቀድሞ ወጥቶ፣ ውጪ ጋር መቆም ግን ያው ውጪ ማለት ነው፡፡

አትዬ ዝናብ እስከያባራ ከተጠለለችበት ሱቅ በቀስታ እርምጃ ወጣችና በረንዳው ላይ ቆመች፤ባለሱቋ ቆንጆ ሴት ሱቋን ቆላለፈች፡፡ የአቲዩ ነገር ሳያሳዝናት አልቀረም፣ እ..ምን ሆነሽ ነው
እናትዬ?አለቻት፡፡ እቲዬ ዝም፡፡ ዓይኗ እንባ አቅርሮ ዝም…ወደ ሞቀ ቤቷ አልያም ወደ ቀጠራት ፍቅረኛዋ ልትሄድ ያኮበኮበች ወጣት የአቲዬን የአርባ ቀን ዕጣ ከየት ጀምሮ ቢነገራት ይገባታል? አቲዪ ዝም አለች፡፡ አልለመደባትም እንዲህ ሆንኩ ብሎ ማውራት፣ አልለመደባትም ምሬት መዘብዘብ ልማዷ አይደለም።

ወጣቷ ጥቂት ብሮች ከቦርሳዋ አውጥታ ለአቲዬ ዘረጋችላትና “አይዞሽ! ይሄን ያዥ በቃ” አለቻት።
አተዬ ግን አማትባ ከተዘረጋው የወጣቷ እጅ በድንጋጤ አፈገፈገች፡፡ ልክ ጩቢ እንደተሳነዘረበት ሰው ነበር የበረገገችው፡፡ ለማኝ ልሆን?” ብላ በውስጧ አሰበች፡፡ እንባዋን እያዘራች ሽቅብ እግሯን ተከትላ ትጓዝ ጀመር፡፡

የትም የማያደርሱ የሚመስሉ እርምጃዎች አንዳንዴ አዕምሮ አስቦ ከሚደርስበት የተሻለ መፍትሄ ላይ ይደርሳሉ። ሰዎች የፈጣሪ መንገድ ይሏቸዋል፡፡ አቲዬ ዝም ብላ ብዙ ርቀት ተጓዘች። መታጠፊያ ስታገኝ እየታጠፈች፣ መንገድ ስታገኝ እየተሻገረች ዝም ብላ ወደፊት፡፡ ከዕጣ ፋንታዋ ትሸሽ ይመስል መንገዱ ባያልቅ ብላ ተመኘች፡፡ በቃ እስካዓለም ጥግ ዝም ብሎ ቀሪ እድሜዋን መጓዝ ::

ቀጥ ብላ ተመለከተች። ፀጥ ያለ ቤተከርስቲያን ከነታላቅ ጉልላቱ ፊት ፊቷ መንገዱን ተሻግሮ
ይታያል፡፡ የልብስ ፌስታሏን አንጠልጥላ አሮጌ ሃምሳ ብሯን በእጇ እንደጨበጠች፣ ዓለምን
መዳፉ የጨበጠ እግዚአብሔር ጋር የተፋጠጠች መሰላት፡፡
በዚህ ሁሉ በደል የዚህ ሁሉ ግፍና ስቃይ ጠንሳሽ እግዚኣብሔርን ፊትለፊት ያገኘችው መሰላት፡፡
እግዚአብሔር አይቷት ሳያፈገፍግ፣ የበደላት ሁሉ አሳፍሮት ሳይሸሽ በፊት ልትደርስበት መንገዱን
አቋርጣ ወደ ቤተክርስቲያኑ ገሰገሰች፡፡

እግዜር ፈርቷት እግሬ አውጭኝ የሚል መሰላት አቲዬ፡፡ መኪናዎች አምባረቁ፣ ሹፌሮች መኪናቸው መስኮት ብቅ ብለው ፀያፍ ስድብ ወረወሩባት። አንበሳ ጋር ልትፋለም ታላቁን ፈጣሪ 'በላ ልበልሃ' ልትለው በድፍረት የምትገሰግስ ጀግና በውሻዎች ጩኸት የምትበረግግ መስሏቸው።
አቲዬ ቤተክርስቲያኑ በር ላይ ደረሰች፡፡ እግዜር ያኔ ለያት፡፡ ከሰማየ ሰማያት ዙፋኑ ላይ
እንደተቀመጠ ድምፅ ከወደ ምድር ሰማ፡፡ ቅዱስ ቅዱስ” እያሉ በታላቅ ድምፅ የሚሰግዱና
የሚያሸበሽቡ እልፍ አእላፍ መላክትን “ዝም በሉ አንድ ለየት ያለ ድምፅ ከምድር ሰምቻለሁ” አለ፡፡
“ጌታ ሆይ ሞልቃቆች በስሱ እያማተቡ መኪናቸው ውስጥ ሆነው ሽው የሚሉት አይነት ድምፅ ይሆናል" አሉት መላዕክቱ፡፡

“አይደለም” አለ እግዚአብሔር፡፡

"የኮተታሞች የኮተት ጥያቄ ይሆናል" አሉት በምድራዊ ትርኪምርኪ የስጋ ጥያቄ የተማረሩት መላዕክት፡፡

"አይደለም አልኩ እኮ” አለ እግዚአብሔር በታላቅ ድምፅ፡፡

“ጌታ ሆይ! ምናልባት የሀብታሞች ከስኳር፣ ከደም ግፊት ከፈወስከኝ መጋረጃ ዣንጥላ የሚሉት
አይነት የተለመደው ስእለት ይሆን” ጠየቁ መላዕክቱ፡፡

ዝም አለ እግዚአብሐር !! ዝምታው አንዳች አስፈሪ ነገር አለው፡፡ በዝምታው ውስጥ ፅንፍ
የለሽ ሀዘንና ፍቅር ነበር።

ከልጅ ስጠኝ ንዝንዝ፣ ከስራ ስጠኝ ንትርክም የተለየ ድምፅ ነበር፡፡ ድምፄ ካማረልኝ ብላ
የምትዘምር ሴትም አልነበረችም፡፡ ከታላቅ ግርማ ሞገስ በእሳት ሰረገላ ደርሰህ ጠላቴን አፈር
ድሜ የምታስበላ የነገስታት ንጉስ፡፡ ከፀሐይ አስራ ዘጠኝ እጅ የምታበራ እያለች በተጠና
መንፈሳዊ ፉከራ መንፈሳዊ ዘራፍ የምታደነቁር ሴትም አልነበረችም፡፡ ከታሰበረ ልቧ በወጣ ማቃተት ዙፋኑን የነቃነቀችው እዚህ ግቢ የማትባል ሴት ናት፡፡ አንዲት ሴት በሩ ላይ ስትቆም፣
“ማነው የልብሴን ጫፍ በዕምነት የነካው” ብሏል እግዚአብሔር!

አቲዩ የእኔ ጀግና ማንንም ደጅ አልጠናቸም፡፡ በልብሷ መቆሸሽ ይናቋት እንጂ የእኔ እናት
ከአዲስ አበባ የሕዝብ ጎርፍ ቁራሽ አልለመነችም፡፡ ለማን ስሞታ እንደምትናገር አውቃለች፡፡
አጥሩን በድንጋይ ቢያጥር፣ ባማረ መኪና ቢንፈላሰሰ፣ ሴቱ በወርቅ ሽቆጠቆጥ..የአዲስ አበባ
ሰውና አቲዬ ልብ ለልብ ተነቃቅተዋል፡፡

አይታዋለች ሕዝቡን የህሊናውን ዓይን ጨፍና ጎዳና የፈሰሱትን የራሱን ጉዶች እንቁልልጭ እያለ
በየስጋ ቤቱ በረንዳ ላይ ጥሬ ስጋውን ሲያጋብስ፣ ቢራና ውስኪውን ሲገለብጥ አይታዋለች፡፡
👍271👏1
በረሀብ የተቆራመቱ፣ ልብሳቸው ላያቸው ላይ ያላቀ ሚስኪን ሕፃናት በምቾት ብዛት ገና በሕፃንነታቸው የስጋ ክምር ከተሸከሙ ብጤዎቻቸው የሚሆኑ ሕፃናት የተረፋቸውን እንዲሰጧቸው
እጃቸውን በልመና ሲዘረጉ - አይታለች፡፡ የደህ ልጆች የሀብታም ልጆችን መኪና እየተከተሉ
ሲለምኑ አይታለች፡፡ የተረፈውን ሳንቲም በምፅዋት ስም ሲወረውር ደግ ይመሰላል ሕዝቡ
የደግነት ከበሮ እየደለቀ ደግነት ባህሌ ነው የሚለው ህዝብ !!

የልብስ ፌስታሏን ከጓኗ አስቀምጣ በግንባሯ ተደፍታ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡ ቃል አልተነፈስችም፤
ከስሩ ተነስታ ቀጥ ብላ ወደ ምፅዋት ማስቀመጫ ሳጥኑ ሂደችና ቀእጇ የጨበጠችውን ድፍን ሃምሳ ብር አጣጥፋ በጠባቧ የምጽዋት ሽቁር እስገብታ ፈቷን አዙራ እርምጃዋን ቀጠለች ባዶዋን !

እግዚአብሔር በምድር ላይ ከባዱን ብድር ጥላበት የሄደችውን ሴት እንዲህ አላት፡፡

ልጅሽ እልፍ እጥፍ ብድርሽን እከፍልሻለሁ፡፡ አቲዬ ምሀፀን ውስጥ በፅንሰቴ ከተገላበጥኩ፡
በቃ በዚህ ቀን መሆን አለበት እስከዛሬ ድረስ ትልቅና ውብ ቤተክርስቲያኖችን ሳይ በአትዬ ሃምሳ ብር የተገነቡ ነው የሚመስለኝ።

ቀና ስትል ፊት ለፊቷ ማንን እገኘች? አባ እስጢፋኖስን !! በተዓምር ማመን የዳዳኝ አቲዬ
ይህንን ስትነግረኝ ነው፡፡ አባ እስጢፋኖስ አቲዩን እያዩ፣ “አንቺ ዘርፌ ቤት የነበርሽው ልጅ
አይደለሽም እንዴ ?” አሉና ጠየቋት መነፅራችውን እያስተካከሉ፡፡ አባ እንኳን በዚህ ድንግዝግዝ አመሻሽ ቀርቶ በጠራራ ፀሐይ የቤተክርስቲያኑን ዋና በር የሚስቱ ፅኑ የዐይታ ችግር ያለባቸው አባት ነበሩ። አቲዬን ግን ተመለከቷት በመነፅራቸው ሳይሆን በእግዚፈር ዓይኖች !!

ያን ቀን አባ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ውስጥ አንዲት እናት መነኩሲት የሚኖሩባት የመቃብር ቤት አትዬን ወስደው አኖሯት፡፡ ሆዷ ውስጥ ወደዚች ምድር ሊቀላቀል የተዘጋጀ ፅንስ ከረገጠችው የቤቱ ወለል ስር ይህቺን ዓለም ጥግብ እስኪል ኖሮባት የተሰናበታት ሀብታም ሽማግሌ አፅም..
አትዬ መሐል ላይ፡፡....

አላለቀም
👍202
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


አደገኛው

የበጋው ወራት አልፎ ክረምት ገባ:: ግን አባባ ሸበቶም ሆነ ልጅቷ ድሮ ይመላለሱበት ከነበረው የሽርሽር ቦታ ብቅ አላሉም:: ማሪየስን ያስጨነቀውና ያጓጓው ያቸን ወለላ ፤ ያንን በውበት ያጌጠን ፊት ለማየት
ነበር፡፡ በቃኝ፤ ሰለቸኝ፧ ደከመኝ፤ ሳይል ጠዋት ማታ ፈለጋት:: ወጣ፧
ወረደ፤ ተንከራተተ፤ ግን አላገኛትም:: በዚህም የተነሳ ወትሮ ቆራጥ፧ ደፋር፧ ብልህ፣ አርቆ አስተዋይና የወደፊት ሕይወቱን በኩራትና በተስፉ ይመራ የነበረው ወጣት ከቤት እንደተባረረ ውሻ ዓላማቢስና ተንከራታች ሆነ፡፡ በአሳብ ባህር ሰጠመ:: የእርሱ ነገር በቃ ፤ አከተመ:: ሥራ አስጠላው፡ ቆሞ መሄድ ሰለቸው ፤ ብቸኝነት ሰውነቱን ወረረው:: ከፊቱ፡ ድቅን ብለው ይታዩ የነበሩት ብሩኅ ተስፋ፣ የኑሮ ግብና እውቀት እንደ ጭስ ተነኑበት፡ ዓለም የጨለመችና የተደፋችበት መሰለው:: አሁን የሚኖረው ቀደም ሲል ይኖርበት ከነበረው ቤት ውስጥ ነው::በዚያ አካባቢ ለነበረ ለማንም ደንታ አልነበረውም:: አንድ ጊዜ ተቸግረው የቤት ኪራይ የከፈለላቸው ጎረቤቱ፡ አሁንም አሉ:: ሌሎች ጎረቤቶቹ ግን
ቤት ለቅቀው ወደ ሌላ ሰፈር ሄደዋል፡፡ አንዳንዶቹም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል:: አንዳንዶቹም የቤት ኪራይ ለመክፈል ባለመቻላቸወ
ተባርረዋል::

እንድ ቀን በጠዋት ተነስቶ ቁርሱን በልቶ እንደጨረስ የነበረበት
ክፍል በር በዝግታ ይንኳኳል፡፡ የሚሰረቅ ንብረት ስላልነበረው ብዙውን ጊዜ የቤቱን በር አይቆልፍም፡፡ በሩን የሚቆልፈው ከበድ ያለ ሥራ ሲይዝ ብቻ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወደ ውጭ ሲሄድ እንኳን በሩን ክፍት ትቶ ነበር
የሚሄደው::

በሩ እንደገና በዝግታ ተንኳኳ፡፡
«ይግቡ» አለ ማሪየስ፡፡
በሩ ተከፈተ::
«ይቅርታ ያድርጉልኝ፤ ጌታዬ!»
የሚያቃስትና የደከመ ድምፅ ነበር፡፡ በመጠጥ ኃይል ተዳክሞ በቅጡ መናገር የተሳነው የሽማግሌ ድምፅ ይመስላል፡፡ ማሪየስ ዞር ብሎ ሲያይ
አንዲት ወጣት ልጅ ከበሩ ቆማለች::

ወጣትዋ ገና ልጅ ናት:: የለበሰችው ልብስ የተቀዳደደ ቡትቶ ስለነበር ስውነትዋ በብርድ ይንቀጠቀጣል፡፡ ሰውነትዋ ከመገርጣቱም በላይ አመድ
የለበሰች ይመስል ነጫጭባ ሆኖአል፡፡ ትንሽም አካልዋ የተሽፈነው ከወገብዋ
በታች ነው እንጂ ራቁትዋን ናት ማለት ይቻላል፡፡ በቀበቶ ፈንታ ቀሚስዋን የታጠቀችው በገመድ ነው:: ፀጉርዋንም ያሰረችው በቃጫ ገመድ ነው፡፡እጆችዋ በጭቃ ላቁጠዋል:: አንዳንድ ጥርሶችዋ የሉም:: ዓይኖችዋ ከመቦዘዝ አልፈው ፈዝዘዋል:: የአሥራ አምስት ዓመትዋ ወጣት የሃምሣ ዓመት አሮጊት መስላለች:: ታስጠላለች፤ ታሳዝናለች:: ማሪየስ ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ በመገረም አያት:: በቅዠት ዓለም የምትታይ እንጂ በእውን ያለች አልመሰለውም።

የሚያሳዝነው አፈጣጠርዋ አስቀያሚ አልነበረም:: ተፈጥሮ የውበት ፀጋ አስታቅፎአታል:: በሕፃንነትዋ በጣም የምታምር፤ በጣም የተዋበች ልጅ እንደነበረች ታስታውቃለች:: የችግር ብዛት ውበትዋን ጨርሶ ሊያጠፋውና ሊያበላሸው አልቻለም:: ደመና በሰፈነበት እለት የፀሐይ ጨረር ለመታየት እንደሚታገልና ብልጭ ድርግም እንደሚል ሁሉ ውበትዋ
በማጣት ጨለማ ቢዋጥም መታየቱ አልቀረም::
«ምን ነበር፤ የእኔ እህት?» ሲል ማሪየስ ጠየቃት::
ልጅትዋ እንደሰከረ ሰው እየተንገዳገደች ተናገረች::
«ይህን ማስታወሻ ስጭ ነው የተባልኩት መሴይ ማሪየስ::
ማሪየስ ብላ ነው በስሙ የጠራችው:: እንደምታውቀው ተገነዘበ፡፡
ግን ማን ናት ይህቺ ልጅ? የማሪየስን ስም እንዴት አወቀች?

«ግቢ» ብሎ ሳይጋብዛት ወደ ውስጥ ገባች፡፡ ያልተነጠፈውን አልጋና ከወለሉ ላይ የተበታተነውን ወረቀት አየች፡፡ ጫማ አላደረገችም ባዶ እግርዋን ናት፡፡ ጭንዋ አካባቢ ልብስዋ ስለተቀደደ ገላዋ ይታያል፡፡ ከጉልበትዋ ጀምሮ ልብስዋ በመቦጫጨቁና ፀጉርዋ በመቆሙ በጣም እንደበረዳት በጉልህ ይታያል፡፡

ደብዳቤውን ሰጠችው:: ማሪየስ ደብዳቤውን ከፍቶ አነበበው::

«ውድ ጎረቤትና የተወደድክ ወጣት..

በጣም እንደምታዝንልኝ ሰምቻለሁ፡፡ ባለፈው ጊዜ የስድስት ወር የቤት ኪራይ እንደከፈልክልኝ ደርሼበታለሁ:: የእኔ ልጅ እግዚአብሔር
ይባርክህ፡፡ ላለፉት ሁለት ቀናት እህል የሚባል ነገር በአፋችን እንዳልገባ ትልቅዋ ልጄ ትነግርሃለች:: ባለቤቴም ታምማለች፡፡ ከአሁን ቀደም ልብህ
እንደራራልኝ ሁሉ አሁንም እንደማትጨክንብኝ እተማመናለሁ፡፡ ስለዚህ
የተቻለህን እርዳን:: ልጄም የፈለገኸውን ሁሉ ትታዘዛለች፡፡»
ማሪየስ ተገርሞ የደብዳቤውን መልዕክት ሲያሳያት ልጅትዋ በድፍረት ክፍሉ ውስጥ ከወዲህ ወዲያ ትላላች:: ራቁትዋን መሆንዋን ብታውቅም
ስሜት አልሰጣትም:: ወንበሮችን አስተካክላ የወዳደቁትን ወረቀቶች አንስታ ከጠረጴዛ ላይ አኖረች::

«እህ መስታወትም አለህ!» አለች::

እንደ ማንጐራጉር ብላ ትዘፍን ጀመር:: ሆኖም በውስጥዋ የተዳፈነ ጭንቀትና ፍርሃት እንዳለባት እንጉርጉሮው ሳያሳጣት አልቀረም፡፡ ካላበዱ
በቀር ከሰው ቤት ገብቶ ባለቤት መሆን እንደሚያሳፍር የታወቀ ነው፡፡

ማሪየስ «ዝም ልበላት ወይስ ልናገራት» እያለ አሰላሰለ፡፡ ወደ መጽሐፍ መደርደሪያው ሄደች::

«እንዴ! ብዙ መጽሐፍ ነው ያለህ» አለች፡፡

ፊትዋ በራ ፧ ኩራት ኩራት አላት:: ማንኛውም ሰው አንድ የሚኩራራበት ነገር ካገኘ መንፈሱ ይረካል፤ ሞራሉ ይገነባል፡፡

«ማንበብ እችላለሁ ፤ እውነቴን ነው እችላለሁ» ስትል ተናገረች::
ቶሎ ብላ ተገልጦ የነበረውን መጽሐፍ አንስታ ማንበብ ጀመረች::ወዲያው ማንበቡን በመተው መጽሐፉን አስቀመጠች:: መንጎል አነሳች::
«መጻፍም እኮ እችላለሁ::»
ከቀለም ብልቃጥ አጠቀሰች:: ወደ ማሪየስ በመዞር «ለማየት
ትፈልጋለህ? መጻፍ እንደምችል ላሳይህ?» ስትል ጠየቀችው::

መልስ እንዲሰጣት ሳትጠብቅ ከጠረጴዛው ላይ ከነበረው ባዶ ወረቀት ላይ ጻፈች፡፡ ከዚያም ቀና ብላ ማሪየስን አየችው::

«በጣም ቆንጆ ልጅ እንደሆንክ ታውቃለህ?» ስትል ጠየቀችው::
እርስዋ ለምን ፈገግታ እንዳሳየችው እርሱ ደግሞ ለምን ፊቱ በቶሎ እንደቀላ በመገረም ሁለቱም በየበኩላቸው ያሰላስሉ ጀመር፡፡

ወደ ማሪየስ ተጠግታ እጅዋን ከትከሻው ላይ አሳረፈች:: ምነው
ሁልጊዜም ትዘጋኛለህ፡፡ እኔ እንደሆነ በደምብ አውቅሃለሁ፡፡ ደረጃ ላይ ዘወትር እንገናኛለን፡፡ እኔ አይሃለሁ ፤ አንተ ግን አታየኝም:: ፀጉርህ እንዲህ ተንጨባሮ ሳየው ደስ ይለኛል፡፡»

ስትናገር አንደበትዋን አለስልሳ ነው፡፡ ድምፅዋን ዝቅ አድርጋ በመናገርዋ ወይም በሌላ ምክንያት ይሁን አይታወቅም ከተናገረቻቸው ቃላት አንዳንዶቹ
ማሪየስ ጆሮ ውስጥ አልገቡም:: ማሪየስ ቀስ ብሎ ወደኋላ አፈገፈገ።በዚህ ጊዜ ወደ አንድ ሌላ ሰው እንድታደርስ የተጻፈውን ሌላ ማስታወሻ ገልጣ አሳየችው::

“ይኸው» አለች ፤ «ይህን ማስታወሻ መንገዱን አቋርጦ ከሚገኘው ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚገኙ መነከሴ የምሰጠው ነው:: ምናልባት ከራሩልን ለቁርሳችን የሚሆን ምግብ ይሰጡናል::»

ይህን እንደተናገረች መሳቅ ጀመረች:: (ማሽላ እያረረ ይስቃል» ይባል የለ፡፡ ንግግርዋን ቀጠለች::

ዛሬ ቁርስ ብናገኝ ምን እንደሚባል ታውቃለህ? ከሁለት ቀን በኋላ
ቁርስ ቀመስን ይባላል:: ቁርስ ከተገኘ እንግዲህ ከትናንት ወዲያ ጀምሮ መብላት የነበረብንን ቁርስ፣ ምሳና እራት በላን ማለት ነው:: ከተገኘማ እሱንም በአንዴ መጠቅጠቅ ነው!»

ይህን ስትናገር ልጅትዋ ለምን እንደመጣች ታወሰው::
👍13
ሰደርያው ኪስ ውስጥ ገባ፤ ምንም አልነበረም:: ልጅትዋ ግን ንግግርዋን ቀጠለች:: ስትናገር ማሪየስ ከአጠገብዋ መኖሩን ጨርሳ የረሳች ትመስላለች፡፡

አንዳንድ ቀን ማታ ማታ ወደ ውጭ እወጣለሁ:: አልፎ አልፎ በዚዬው እንደወጣሁ እቀራለሁ:: ባለፈው ዓመት አሁን ካለንበት ቤት
ከመግባታችን በፊት ከድልድይ ስር ነበር የምናድረው:: መቼም ብርዱ አይጣል ነው:: ትንሽዋ እህቴ እንዴት ይበርዳል ፤ አልበሱኝ እያለች ስትጮህ ነበር የምታድረው:: ታዲያ አንዳንድ ቀን በጣም ሰልቸት ሲለኝ ዝም ብዬ
በባዶ ሆዴ እዞር ነበር፡፡ ሁሉም ነገር ይምታታብኛል ፤ ይዞርብኛል::
የሚሆነውን ሁሉ አላውቅም:: ድምፅ ብቻ እሰማለሁ፡፡ አለ አይደል፧ ሆድ ባዶ ሲሆን የሚያደርገው ዓይነት::»

በመጨረሻ ዓይንዋ እየተንከራተተ አተኩራ አየችው::

ማሪየስ ኪሱን ሁሉ ሲበረብር አምስት ፍራንክና አሥራ ስድስት ሱስ አገኘ፡፡ የነበረው ገንዘብ ይኸው ነው:: «ለምሣ ይሆነኝ ነበር» ሲል አሰበ::
«ግን እኮ ነገ የሚሆነው አይታወቅም::ገንዘቡን አነሳና ለልጅትዋ ሰጣት.. ቶሎ ብላ ቆጠረችው::
«ተመስገን፧ ፀሐይዋ በራች» ስትል ተናገረች:: ከዚያም በማመስገን
ለጥ ብላ እጅ ነሳችው:: «እግዚአብሔር ይስጥልኝ» ብላ ወደ በሩ አመራች::
ከበሩ አጠገብ የሻገተ ዳቦ ወድቆ አየች:: ቶሎ ብላ አንስታ ቆረጠመችው::
«ጥሩ ነው፤ ግን እንደ ድንጋይ ደርቋል:: የተረፉት ጥርሶቼን ብቻ
እንዳያወልቅብኝ» እያለች ከክፍሉ ወጥታ ሄደች::

ለአምስት ዓመታት ማሪየስ በድኅነት፤ በብቸኝነትና በመከፋት ነው የኖረው:: እውነተኛ ችግር ማለት የቱ እንደሆነ ያወቀው ግን በዚህ ጊዜ ነበር፡፡ የወንድ ልጅ ስቃይ ያየ ሁሉ ስቃይና ችግር ማለት ምን እንደሆነ አውቃለሁ ብሎ ቢናገር ተሳስቷል፡፡ እውነተኛ ስቃይ፤ እውነተኛ መከራና
እውነተኛ ችግር የሚታየው በልጅነት ዘመን ደርሶ ሲታይ ስለሆነ እውነተኛ ችግር፣ ስቃይና መከራ ምን እንደሚመስል ያቺ መከረኛ ልጅ ለማሪዮስ
አሳየችው::

ማሪየስ ጎረቤቶቹ እንዴት እንደሚኖሩ እስከዚያን ጊዜ ድረስ ባለማየቱ ራሱን ወቀሰ፡፡ በአንድ ወቅት የቤት ኪራይ የከፈለላቸው ቅጽበታዊ ስሜት ገፋፍቶት ነበር፡፡ ለሰው የሚያዝን ሁሉ የሚያደርገው ነው:: ግን ማሪየስ
ከዚህ ልቆ መገኘት ነበረበት፡፡ ለምን ቢሉ እነዚህ ሰዎች ጋር የሚለያየው በአንድ ግድግዳ ስለሆነ ነው:: ከእርሱ ክፍል ቀጥሎ ያሉት ሰዎች ጦማቸውን
ውለው ጦማቸውን ያድራሉ፡፡ የቅርብ ጎረቤታቸው እርሱ ነው:: ሲተነፍስ እንኳን ይሰማቸዋል:: ሆኖም መኖር አለመኖራቸው እንኳን አልተገነዘበም::
በየእለቱ ድምፃቸውንና ኮቴያቸውን ቢያደምጥም እየሰማ አልሰማቸውም፤ እያሉ መኖራቸውን አላጤነም:: ቆሞ መሄድና መኖር ለየቅል ናቸው::
እርሱ በሌላ አሳብ ነበር የተያIlው:: የእርሱ ዓለም ከጎረቤቱ በጣም የተራራቀ ነው:: እርሱ በቅዠት ዓለም ሲንገዋለልና በፍቅር ዓለም ሲንሳፈፍ ጎረቤቱ በስቃይና በመከራ ዓለም መስመጣቸውን ልብ አላለም:: ከእነርሱ ቀጥሎ
ያለው ክፍል ምናልባት ለሰው የሚያዝን ሀብታም ቢገባበት ኖሮ ሰዎቹ ይረዱበት ነበር፡፡ ታዲያ ምን ይሆናል እርሱ መንገዱን ስለዘጋው ተስፋቸው በመነመነበት ፡፡ በርግጥ ሰዎቹ እድለቢስ፤ የአሳብ፤ የመንፈስና የገንዘብ ድሆች፤ክፉዎችና በሰዎች ዘንድ የተጠለ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ነው ምንዱባን ማለት የምድር ጎስቋላዎች ብለን የምንጠራቸው:: የማነው ጥፋቱ? የማይመለስ ጥያቄ! የተቸገረ በገጠመ ቁጥር የያዙትን ሁሉ መርጨት ይቻላል? አሁንም የማይመለስ ጥያቂ!

ማሪየስ ልጅትዋን ባየ ጊዜ ራሱን ከሚገባው በላይ ወቀሰ፡፡ ሁለቱን
ሰዎች የለየው ስስ ግድግዳ አተኩሮ ተመለከተው፤ መረመረው፡፡ ኮርኒሱ አጠገብ የሦስት ማዕዘን ቅርፅ ያለው ቀዳዳ አለ:: ጣራ ላይ ቢወጣ በዚያ
ቀዳዳ የጎረቤቱን ቤት ለማየት ይችላል፡፡ እስቲ ሰዎቹ ምን እንደሚመስሉ ባያቸውስ» ሲል አሰበ:: ወደ ቀዳዳው ተጠግቶ የጎረቤቶቹን ኑሮ በዓይኑ
ተመለከተ፡፡

ማሪየስ ራሱ ድሃ በመሆኑ የቤቱ እቃ እስከዚህም አልነበረም:: ቢሆንም ክፍሉ ንጹህ ነው:: ግን በቀዳዳ ያየው ዋሻ የከብት በረት እንጂ ሰው የሚኖርበት አይመስልም:: የመቆሸሹ፤ የወናነቱ፤ የመዝረክረኩና የማስጠላቱ መጠን እንዲህ ነው ብሎ ለመግለጽ ያዳግታል፡፡ የተሰባበሩ ሁለት የቀርከ
ወንበሮች፤ ቆሻሻ ያለበትና አንድ እግሩ የተሰበረ ጠረጴዛና የተሸራረፉ ሁለት ወይም ሦስት ሳህኖች ከክፍሉ ውስጥ ነበሩ:: ጥቀርሻ የመሰለ የሻይ
ማፍያ ጀበናና መጥበሻም ነበራቸው:: በመስኮትና በቀዳዳ ከሚገባ ብርሃን በስተቀር ሌላ መብራት የላቸውም:: መጋረጃቸው የሸረሪት ድር ነው:: እብድ እንደቦጫጨቀው ልብስ ወይም ድመት እንደቧጠጠው ፊት የቤቱ
ግድግዳዎች ተሰነጣጥቀዋል:: የማሪየስ ክፍል ወለል ሸክላ የተነጠፈ ሲሆን የእነዚህ ሰዎች ወለል ግን አዋራ የለበሰ ነው:: ከምድጃ ጭስ መውጣቱ ይታያል።

ከጠረጴዛው አጠገብ እንደ አሞራ አንገቱ የሳሳና እንደግመል ወገቡ
የጎበጠ ሽማግሌ ከወለል ላይ ተቀምጧል:: ሰውዬው የተቀዳደደ የሴት ሽሚዝ ለብሶ የተጣጣፈ ሱሪ ታጥቋል:: የእግሩ ጣቶች ካደረገው አሮጌ ቦት ጫማ ሾልከው በመውጣታቸው ከሩቅ ይታያሉ፡፡ ፒፓ ካፉ ላይ ሰክቶ
ይታያል፡፡

ያጨሳል፡፡ ከቤት ውስጥ ዳቦ ይጥፋ እንጂ ትምባሆ ኣ
ከልጠፋም:: ሰውዬው
እየጮኸ ሲናገር ማሪየስ ሰማው::
«ከሞትን በኋላ እንኳን ሁላችንም እኩል ነን ብሎ ማሰብ ሞኝነት
ነው:: ትልቅ ሰው ሲሞት የሚታጀበው በሠረገላ ነው:: ድሃ ሲሞት ቀባሪ እንኳን የሚያገኘው በግድ ነው:: የመቃብር ቦታም ቢሆን በምርጫ ነው የሚወሰነው:: ድሃ ከወንዙ ተረተር ወይም ከረግረጉ ላይ ሲቀበር ሀብታሙ ከአፋፉ ከደረቁ ቦታ ላይ ነው የሚቀበረው::»

አንዲት አርባ ወይም መቶ ዓመት ይሁናት የማታስታውቅ ሴት
ምራቅዋን ከእሳት ማንደጃው ላይ ደጋግማ ትተፋለች፡፡ እንደ ሰውዬው ! እርስዋም የተቀዳደደ ሸሚዝና የተጣጣፈ ጉርድ ቀሚስ ለብሳለች፡፡ ጉልበትዋን
አጣጥፋና ወገብዋን ሰብራ ብትቀመጥም ረጅም መሆንዋን ታስታውቃለች::አጠገብዋ አንዲት ቀጠን ያለች ልጅ ተቀምጣለች፡፡ ልጅትዋ ማጋነን ባይሆን
ራቁትዋን ናት ማለት ይቻላል፡፡ ይህቺ ልጅ ከቤቱ ውስጥ የነበሩት ሰዎች የሚያወሩትን ማዳመጥ ቀርቶ የምትሰማ ወይም ከነአካቴው በዚህ ዓለም
የመኖር ጉጉት ያላት አትመስልም:: ልጅትዋ ከማሪየስ ቤት የመጣችው ልጅ ታናሽ እህት መሆን አለባት:: አሥራ አንድ ወይም አሥራ ሁለት ዓመት ቢሆናት ነው::

ልጅቱ ሳትፈልግ በግድ የተወለደች ትመስላለች:: የልጅነትም ሆነ
የወጣትነት ዘመን ምን እንደሆነ አታውቅም:: በአሥራ አምስት ዓመትዋ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ፤ በአሥራ ስድስት ዓመትዋ የሃያ ዓመት ሴት ሳትመስል አትቀርም:: የዛሬዋ ትንሽ ልጅ የነገዋ አሮጊት ናት::

ማሪየስ ከዚያ ተንጠልጥሉ ለጥቂት ጊዜ ያንን ወና ቤት ቃኘው። ቅል የለው ማሰሮ፤ ወና ባዶ ቤት! ከመቃብር ቤት ይበልጥ ያስፈራል። ሰውዬው ዝም ብሎአል፡፡ ሴትዮዋም ቃል አትተነፍስም፡፡ ልጅትዋ መናገር
ቀርቶ የምትተነፍስ እንኳን አትመስልም፡፡

ሰውዬው ቆይቶ ቆይቶ «ተልካሻ፤ ሁሉም ነገር ተልካሻ ነው» ሲል
አጉረመረመ፡፡
👍15
ማሪየስ ባየው ነገር በጣም ተሳቅቆ ከነበረበት ሊወርደው ሲል ድምፅ በመስማቱ ከዚያው እንዲቆይ ይገደዳል፡፡ ሰዎቹ የነበሩበት ክፍል በር በችኮላ ይከፈታል፡፡ ትልቅዋ ልጅ ብቅ አለች:: በጭቃ የተለወሰ የወንድ 1
ጫማ አጥልቃለች:: ከአንድ ሰዓት በፊት ከማሪየስ ቤት ስትመጣ
ያልለበሰችውን የሌሊት ልብስ መሳይ ነገር ደርባለች:: ምናልባት ከማሪየስ ቤት ስትመጣ ለማሳዘን ብላ የደረበችውን ልብስ ከአጥር ውጭ አስቀመጣው ስትመለስ ለብሳው ይሆናል፡፡ በሩን በኃይል በርግዳ ከገባች በኋላ በኃይል
ወርውራ ዘጋችው:: ትንፋሽዋን ለመሰብሰብ ቆም አለች:: ከክፍሉ ውስጥ ስትገባ ትንፋሽ አጥሮአት በኃይል ነበር የምትተነፍሰው፡፡ ከዚያም የደስታ የእፎይታ አይታወቅም «እየመጣ ነው» ስትል ጮኸች፡፡

አባትየው ቀና ብሎ ተመለከታት፡፡ እናትየዋ ፊትዋን አዞረች፡፡ ትንሽዋ
ልጅ ነቅነቅ አላለችም::

«ማነው እሱ?» ኣባትየው ጠየቀ::
«ሰውዬው!»
«ለነፍሱ ያደረው?»
«አዎን»
«ደጉ ሰውዬ ነው?»
«አዎን»
«እውነትዋን ነው እንዴ? እየመጣ ነው?»
«በጋሪ እየመጡ ነው፡፡»
አባትየው ተነሳ፡፡
«እርግጠኛ ነሽ፤ እየመጣ ነው? ብቻ ይህቺን ወስላታ ማን ያምናል
ይህን ጊዜ ኣድራሻው ጠፍቶባት ይሆናል፡፡»
አባትየው ይህን ሲናገር በራቸው በዝግታ ተንኳኳ፡፡ ሰውዬው ሮጦ
ሄዶ በሩን ከፈተ፡፡ እየደጋገመ በማጎንበስ እጅ ነሳ፡፡
«ይግቡ ጌታዬ፤ ይግቡ:: እመቤት ገባ በይ እንጂ፤ ቤት ለእንግዳ፤
ግቡ! ግቡ» ሲል ቀባጠረ፡፡
አንድ ጠና ያለ ሰውና አንዲት ወጣት ከክፍሉ ውስጥ ገቡ:: ማሪየስ ከነበረበት እያየ ነው:: ምን ዓይነት ስሜት እንደተሰማው ለመግለጽ ያዳግታል፡፡

«እስዋው ናት፡፡»

ከፍቅር ወጥመድ ገብቶ የወጣ ብቻ ነው «እስዋው ናት» ማለት ምን ዓይነት ስሜት እንደሚያሳድር ሊገባው የሚችለው::

በእርግጥ እስዋው ነበረች:: በድንገት ዓይኑን የጋረደው ደመና መሰል ስድስት ወር መላ የጠፋችበት የጨለማ ኮከብ፤ በድንገት ብቅ አለች:: ያ ነገር ስላጨለመው በግልጽ ሊያያት አልቻለም:: ያቺ የዓይኑ ተስፋ ፤ ያቺ
እረፍት የነሳው ዓይን፤ ቅንድብ፤ አፍ፤ ከዓይኑ የተሰወረ ውበት ከፊቱ ድቅን ሲል ሕልም እንጂ እውን አልመሰለውም:: ያቺ ቆንጆ የመጣችው ያንን በረት የመሰለ ቤት ልታይ ነው።

የማሪየስ ሰውነት ተንሰፈሰፈ:: ምን! አሁን እርስዋ ናት ማለት ነው!
የልቡ ዓመታት እይታውን ጋረደበት:: ስቅስቅ ብሉ ሊያለቅስ ፈለገ፡፡ እንዴት? ከብዙ ቀን ፍለጋ በኋላ በድንገት እንደገና ስላገኛት! ወይስ ጠፍቶ የነበረውን ነፍሱ እንደገና ስላገኘ! የምን ማልቀስ አይገባም::

ብዙም አልተለወጠችም:: ትንሽ ግን ገርጥታለች:: ፊትዋ ባደረገችው ሰፊ ቆብ፤ የሰውነትዋ ቅርፅ በለበሰችው ካፖርት በመጠኑ ተሸፍኖአል፡፡
አብሮአት ያለው ሰው «አባባ ሸበቶ» ነው::

ወደ ውስጥ ራመድ በማለት በእጅዋ ይዛው የነበረወን አንድ
የተጠቀለለ ነገር ከጠረጴዛው ላይ አስቀመጠች::

ትልቅዋ ልጅ ወደ ኋላ ሸሸት ካለች በኋላ ኮዜት ያጠለቀችውን ሰፊ
ባርኔጣ፤ የሐር ቀሚስና የደስ ደስ ያለው ፊት በቅናት ዓይን ተመለከተች::

አባባ ሸበቶ በሩህሩህ ዓይን እያየ ሰውዬውን አነጋገረው::

«ከዚህ ከተጠቀለለው ፓኮ ውስጥ ጥቂት አዳዲስ ልብሶችና
ብርድልብሶች ስላሉ ተጠቀሙበት::»

«ምስጋናችን በጣም የላቀ ነው:: ውለታዎ በጣም ከባድ ነው» አለች
ትልቅዋ ልጅ ለጥ ብላ እጅ እየነሳች:: ልጅትዋ ይህን ስትናገር አባትዋ ወደ ልጅቱ ጆሮ ጠጋ ብሎ በሹክሹክታ «አላልኩሽም? እቃ ብቻ! ገንዘብ የለም፡፡ ሁሉም ያው ናቸው» አላት:: አባባ ሸበቶና ኮዜት የቤቱ ሁኔታ አስገርሞአቸው
ጣራና ግድግዳውን ሲያዩ ሰውዬው ምንድነው የሚለው ብለው ስላልተጨነቁ፤ አልሰሙትም:::

ልጅትዋ ሁለቱን እንግዶች በአድናቆት ማየትዋን ቀጠለች:: እየተናገረች እንኳን ሰውዬውንና ልጅትዋን ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር እየቃኘት ነበር፡፡ ባልተቤቱ በድንገት ከመሬቱ ላይ ተጋድማ ወደነበረችው ወደ ሚስቱ
ፈጠን ብሎ ሄደ:: ድምፁን ዝቅ አድርጎ «ይህን ሰው ተመልከቺው» ሲል ተናገረ፡፡ ከዚያም ወደ አባባ ሸበቶ ሄዶ የሚከተለውን ተናገረ፡፡

«አዬ ጌታዬ! እንደሚመለከቱት ገላዬን የሸፈንኩት በባለቤቴ ሸሚዝ ! ነው:: እርሱም ቢሆን የተቀዳደደ ነው:: ሸሚዝ ባይኖር የታጠቁት ሱሪ ገመናዬን ባልሸፈነ ነበር፡፡ ጊዜው ደግሞ ክረምት ነው:: በልብስ እጦት ምክንያት ብርዱ ስለሚያስፈራ ከቤት አልወጣም:: ጌታዬ ፤ ነገ ምን እንደሚሆን ያውቃሉ? ነገ የካቲት 4 ቀን ነው:: (በአውሮጳ
ወርሃ የካቲት ክረምት ነው)፡፡ ቤቱ ያከራዩኝ ሰው እስከዚህ ቀን ዋዜማ ድረስ የቤቱን ኪራይ ;
ልከፍል ከዚህ ቤት እንደሚያስወጣኝ የመጨረሻ ቃሉን ሰጥቶኛል፡፡ ዛሬ ማታ መሆኑ ነው መሰለኝ! እንግዲህ ነገ ጠዋት ገመምተኛዋ ባለቤቴ ፧ሁለቱ
ልጆቼና እኔው ራሴ ከዚህ ቤት እንባረራለን ማለት ነው:: ከበረንዳ
በስተቀር ሌላ መጠጊያ የለንም:: በዚህ ብርድ ፧ በዚህ ቅዝቃዜ ያለልብስ በረንዳ ማደር ማለት ምን እንደሆነ ጌታዬ የሚያውቁት ነው:: ዝናብ ይዘንባል ፧ ወጨፎ አለ፡፡ አይጣል ነው ብቻ! ጌታዬ የስድስት ወር የቤት ኪራይ አለብኝ:: የተጠራቀመብኝ ውዝፍ ስልሣ ፍራንክ ነው::»

ግን ሰውዬው ውሸቱን ነበር፡፡ ማሪየስ የሁለት ወር የቤት ኪራይ
ስለከፈለለት ያለበት ውዝፍ ኪራይ የስድስት ወር አይሞላም:: አባባ ሸበቶ ከኪሱ አምስት ፍራንክ አውጥቶ ጠረጴዛው ላይ በተናቸው::

ዦንድሬ ማለት ሰውዬው ወደ ትልቅዋ ልጅ ዞር ብሉ «ይኼ
በሽቲያም! አምስት ፍራንክ ምን እንዳደርገው ነው የሚጥልልኝ?» ሲል በሹክሹክታ ተናገረ::

ወዲያው አባባ ሸበቶ ካፖርቱን አውልቆ ካጣጠፈው በኋላ ከወንበር ድጋፍ ላይ አስቀመጠው::

«በአሥራ ሁለት ሰዓት እመለሳለሁ» ካለ በኋላ «ያኔ ስመለስ ስልሣውን ፍራንክ አመጣልሃለሁ» ሲል ተናገረ::
«ባለውለታዎ ነኝ፤ በጣም ደግ ሰው ነዎት» ሲል ዦንድሬ እየጮኸ
መለሰ፡፡

የትልቅዋ ልጅ ዓይን ከካፖርቱ ላይ አረፈ፡፡

«ጌታዬ፤ ካፖርትዎን ረስተዋል!» ስትል አስታወሰች፡፡
ሚስተር ዣንድሬ ልጅትዋን ክፉኛ በዓይኑ ገሰፃት፡፡
አባባ ሸበቶ ወደ ልጅትዋ ዞር በማለት በፈገግታ መለሰላት፡፡
«ረስቼ አይደለም፤ ሆን ብዬ ነው ያስቀመጥኩት::»
“ጌታዬ» አለ ዦንድሬ ፤ በጣም ለተቸገረ ያዝናሉ ማለት ነው ፤
ከማመስገን በስተቀር ውለታዎን መክፈል አይቻልም:: እስከበሩ እንድሸኝዎት ቢፈቀድልኝ፡፡»

«ከወጣህ» አለ አባባ ሸበቶ፣ ‹‹ካፖርቱን ልበሰው በጣም ይበርዳል::»

ሚስተር ዣንድሬ በድጋሚ እስኪነገረው አልጠበቀም ፧ ቶሉ ብሎ ካፖርቱን ለበሰው:: ሁለቱ እንግዶችና ሚስተር ዦንድሬ ተያይዘው ወጡ፡፡
ሚስተር ዦንድሬ ቀደም ቀደም አለ፡፡.....

💫ይቀጥላል💫
👍27
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አራት


እትዬ ያረፈችባቸው መነኩሲት “የኔ ልጅ አይዞሽ የበላነውን እየበላሽ ልብሽ እስከፈቀደው ጊዜ መቆየት
ችያለሽ የእግዜር ቤት ነው ቤትሽ ነው” አሉና ድርብ የሰሌን ምንጣፍ ብዙ ቦታ ላይ ብዙ ዓይነት ክርና መጣፈያ ከተጠቀመ ብርድ ልብስ ሰጧትና አንዷ ጥግ ላይ ራሳቸው አነጣጠፉላት፡፡

አለም ላይ ጭካኔ ሲፈነጭ ማን አለብኝነት በሀሴት ዋንጫ ልቅለቃውን ሲያስነካው፡ ሰብዓዊነት መቃብር ቤት ውስጥ በፍፁም ፀጥታ ከአትዬ ጋር ተገናኘ፡፡ አትዬ ከደጓ መነኩሴት ጋር በመቃብር ቤት ውስጥ ተቀመጠች፡፡ ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል ቢባልም ቅሉ ኑሮው አልሞቃትም፡፡አጥንቷ ድረስ ዘልቆ የሚያንዘፈዝፍ የፍርሀት ብርድ ሰላም ነሳት፡፡ መሄጃ የለኝም ከሚል ስጋት ለጊዜውም ቢሆን አርፋለች፡፡ ግን መቃብር ቤቱ ውሰጥ የነበራት ቆይታ የስቃይና ዮፍርሀት ነበር፡፡ሰው የተቀበረበት ቤት ውስጥ መተኛቷ ፍርሃት ለቀቀባት፡፡ ከተኛችበት ሰሌን ስር በስብሶ አፅሙ የቀረ ሬሳ ታኝቷል፡፡ በአፈ ታሪክ እንደሰማችው (አሁንም ድረስ እንደምታምነው ደግሞ ሙታን አካላቸው ቢጋደምም መንፈሳቸው አርፎ አይቀመጥም፡፡ መነኩሲቷ ወጣ ካሉ ተከትላ ደጅ ትቆማለች፡፡ እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርጋት አንድ ስጋው ሁሉ ረግፎ ጭራሮ የመሰሉ ጣቶቹ ብቻ የቀሩ አጥንታም እጅ የተኛችበትን መሬት ፈነቃቅሎ አንገቷን ሲያንቃት ይታያትና ኡኡታዋን ታቅልጠዋለች…ቅዠት! መነኩሲቷ አቲዬን ማረጋጋት ለአቲዬ መፀለይ ብቻ ሆነ ስራቸው::

በፍርሀት ሁለት ቀንና ሌሊት እንቅልፍ ስላልወሰዳት በሦስተኛው ቀን ምሽት እንቅልፍ እሰካራትና ሰሌኗ ላይ ኩርምት ብላ ተኛች ዓለም ገፍቶ ገፍቶ የመገነዣ ሰሌኗ ላይ የጣላት ሚስኪን ሴት፧ መነኩሲቷ በሀዘን ግንባሯን እንደ ትንሽ ልጅ እያሻሹና አተነፋፈሷ የተስተካከለ መሆኑን እያዳመጡ እንደ መልካም ወላጅ ቀስ ብለው ድራቡን አልብሰዋት ወደ ፀሎታቸው ተመለሱ::

ብዙ ሳይቆይ ትንሸዋ የመቃብር ቤት በአስደንጋጭ ጩኸት ተሞላች፡፡ እቲዬ ልጄን..ልጄን
እያለች አንደ እብድ ከመኝታዋ በርግጋ በመነሳት ራሷን ይዛ መጮህ ጀመረች፡፡ አቅመ ደካማዋ መነኩሲት አቲዬን ሊያስቆሟት አልቻሉም፡፡ የሷ ባልሆነ ጉልበት ገፈታትራቸው በሚገርም ፍጥነት ሰሌኑን ጠቅልላ የቤቱን ወለል በጥፍሯ ትቧጥጥ ጀመረች፣ "ልጄ.....ልጄን ወሰዱብኝ” እያላች በመረጋጥ ብዛት የደደረውን አፈር ትመነጭር ጀመረ፡፡

እንባዋ በጉንጮቿ ሳይ ለጉድ እየፈሰሰ፣ በላብ ተነክራ እየቃተተች ከትንንሾቹ መቃብር ቤቶች
ጩኸቷን ሰምተው የወጡ መነኮሳት ወደ እማሆይ ቤት መጥተው ተረባርበው እስኪያስቆሟት ድረስ አቲዬ በአስሩም ጥፍሯ መሬቱን እየቧጠጠችና እየቆፈረች ኡኡታዋን ማቅለጥ አላቆመችም
ነበር፡፡

ክፉ ቅዠት የዘወትር ቅዠቷ የሆነው ጭራሮ እጅ ዛሬም ከፈነቀለው መቃብር ውስጥ እጁን
ብቻ ሳይሆን ከትከሻው በላይ ነበር ተመዝዞ የወጣው አፈር እንደለበሰ…!! ከዛም በአስፈሪ
ዓይኖቹ እቲዩ ላይ አፈጠጠባት፤ አየችው ቀለመወርቅ ነበር፡፡ ያውም አፈር ከነሰነሰ ባርኔጣና
ካፖርታው !! "ልጄን አምጪ” ብሎ አጥንታም እጁን ወደ ሆዷ ላከና በቅፅበት አንድ ቀይ የሚያምር ሕፃን ይዞ ተመለሰ፡፡ ሆዷ ባዶ ሲሆን ታያት፤ ቀለላት፡፡ ልጇን በደስታ ትመለከተውና ወደ ውስጥ ወደ መሬት ይዞት ሰረገ፡፡ ልክ ጫጩት ነጥቆ ወደ ጉድጓዱ እንደሚገባ ሸለምጥማጥ'
መሬቱን ከፍቶ ሲገባ፣ መጋረጃ ገልጦ የገባ ነበር የሚመስለው፡፡

በቀጣዩ ቀን አባ እስጢፋኖስ ሁኔታው ሲነገራቸው ድሮም ለአቲዬ ቋሚ መኖሪያ ሲያፈላልጉ ነበርና ፍለጋውን አፋጥነው ከሁለት ቀን በኋላ በፊት ትኖርበት ወደ ነበረው መንደር ወስደው አንዲት ከዋናው የቀበሌ አጥር ጋር ተያይዛ የተሰራች የቆርቆሮ ቤት ውስጥ አስገቧት፡፡ የመንደሩ እድር እቃ ማስቀመጫ ነበረች፡፡ የእቃ ማስቀመጫዋ ቤት ጣራና ግድግዳዋ በድንብ ስላልገጠመ፣ ሌሊት ብርዱ ቀን ፀሐዩ በክፍተቱ ውስጥ እያለፈ ይገባ ነበር፡፡ አባ እስጢፋኖስ ከንሰሀ ልጆቻቸው ለምነውም ተለማምጠውም ያገኟቸውን አሮጌ ፍራሽ፣ ብርድ ልብስና የውሀ መያዣ ጎማ ለእቲዬ እያሳዩ እንደምታውቂው ቤሳ ቤስቲን የሌላኝ የእግዚሃር አገልጋይ ነኝ፡፡ ከዚህ የተሻለ ባይሆን ጎንሽን ማሳረፊያ ካገኘሽ ሌላው ሌላው በፈጣሪ ፈቃድ ቀስ እያለ ይሟላል እኔም እየመጣሁ አይሻለሁ።" ብለዋት ሄዱ።

የእድሩ ድንኳን፡ እንጨቶች፣ ወንበሮችና ስጋጃ ምንጣፎች በአንድ በኩል ተሰድረው ገባ ብሎ ወደ ውስጥ ካለችው ትርፍ ቦታ ላይ ደግሞ የአቲዬ ፍራሽ ተዘርግታለች፡፡ ብዙ ጊዜ ሞት ወይም መርዶ ሰለሚኖር የእድሩ እቃ አይኖርም፡፡ ስለዚህ ሰፋ ትላለች ቤቷ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ
እድርተኛው እቃውን ሲመልስ በግዴለሽነት ወንበሩን፣ እንጨቱን ከባባዶቹን ምንጣፎች አቲዩ
መኝታ ላይ ጥለውት ይሄዱ ስለነበር ያንን ሁሉ ጓዝ ጎትቶ ቦታ ማስያዙ ለአንዲቷ ነፍሰ ጡር ሴት ፈተና ነበር።

አትዬ ግን ታደርገዋለች፣ እንዲህ አታድርጉ” አትል ነገር ሆሆ ወደዛ ውጪ ቢሏትስ፡፡

አባ እስጢፋኖስ ብዙ ቤት ሊያስቀጥሯት ደክመው ነበር፡፡ ይሁንና ቀጣሪዎቹ ነፍሰ ጡር
መሆኗን ሲሰሙ ሁሉም አቲዬን ቤታቸው ማስገባት አልፈለጉም፡፡ አባ ቢጨንቃቸው የአቲዬ ነገር
ሰላም ቢነሳቸው አቲዩን ለዚህ ሁሉ መከራ የዳረገቻት ዘርፈ ቤት ሳይቀር ሄዱና፣ እችን ደሀ ይቅር በያት ባክሽ ብለው ታማፀኑ፡፡

አይይይይ አባ ምነው እያወቁት… እንደ ልጆቼ አንከብካቤ በያዘኩ አይደለም እንዴ ጥጋብ ፈንቅሏት ለመንደሩ ሁሉ ስሜን አጥፍታው የሄደች” አለች አቃጣሪዋ፡፡ አባን በአፍ መሸንገል
እግዜርን መሸንገል ይመስል የአቲዬን በደለኝነት ስትዘረዝር ደስ እያላት ነበር፡፡

ልጅ አይደለችም እንደ ወለተማሪያም ደግሞስ አንች ቤት ከመቼ ወዲህ ነው ይቅርታ የነጠፈው ተይ እንጂ” አሉ አባ፡፡

በዛብኛ አባ በዛብኝ ...ምን በደልኩ እናት በሆንኳት…የበላሁትን ባበላሁ የለበስኩትን ባለበስኩ ሰው ሁኝ፣ ሰልጥኝ!' ባልኩ ይሄ ይገባኝ ነበር እንባ እየተናነቃት አባ ፊት በደሏን ዘረዘረች እች አስመሳይ!!

ይሄው የትም ስትንዘላዘል ዲቃላዋን ይዛ አረፈችው” አለች ዘርፌ፡፡ ከእኔ የተጣላ እጣ ፋንታው
ውድቀት ነው" ልትል እየዳዳት…፡፡

አባ እንደሆኑ የአቲዬን ነፍስ መታደግ ይቅደም ብለው እንጂ የቀለመወርቅንና የዘርፌን ሴራ ውስጣቸው ያውቀዋል፡፡ አንዳንዴ የእግዜር አገልጋይ ከመሆን ሽፍታ በሆንኩ፡ ነፍስ ገዳይ በሆንኩ የሚያስብሉ እንደ ዘርፌ ዓይነት ገርፈው የሚጮኹ ጅራፎች ሲያጋጥሙ የንስሀ አባቶች
ልብ ምን ያህል ይሰበር ይሆን? ቢቻል ጥምጣምና መስቀልን ላንዴ አስቀምጦ ምንሽር መታጠቅና እንዲህ አይነቶቹን እድሜ ጠገብ እባቦች ግንባር ግንባራቸውን ማለት ነበር፡፡

ዘርፈ hዚህ ሀሉ ፉከራና ማስመሰል በኋላ እቲዬን ቤቷ እንደማትመልሳትና ከፈለገች ተመላልሳ ላሞቹን የመንከባከብ ልብስ የማጠብ ስራ እንድትሰራ በወር 10 ብር ልትከፍላት ለአባ ቃል ገባች፡፡

“ያው ለነፍሴ ብዬ እንጂ የደረሰች እርጉዝ ምኗ እለቻቸው ሰእባ፡፡

“ግዴለም ወለተማሪያም መቼስ ሰው እንዳረገዘ አይኖር ሁሉ ነገር ሲወለድ ጊዜ አለው፡፡ ደግሜ ይሁን ክፉ ተረግዞ አይቀርም፣ ነገን ነው ማየት” አሉ አባ፡፡ የቄስ ምንሽሩ ቅኔ ነው ተኮሱባት
አባ!

የቅኔ ጥይት ከተኳሹ እስከ ኢላማው ለመድረስ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ለዛ ነው ዘርፈ አባ እግር ስር ድፍት ያላለችው ይድፋትና!! አባ እውነት ነበራቸው፣ እንደ ተረገዘ የሚኖር በደል የለም ይወለዳል አንድ ቀን፡፡
👍23🥰1
አቲዬ በዙሪያ ገጠም እጣፋንታዋ ዙራ ዘርፌ ቤት ገባች (ዞሮ ዞሮ መዝጊያው ጭራሮ እያለ
መንደሩ… እውር ቢሽፍት ጓር ድረስ ነው እያለ እሽሟጥጬ.) እንደገና ወተት ማለብ፣ እንደገና
አዛባ መዛቅ፣ እንደገና ጉልበቷን መገፍገፍ ሊያውም ቀጥ ብላ እመቤቷን በማታይበት የሞራል.
መዳሸቅ ተተብትቦ የበደሏትን ይቅርታ ጠይቃ፡፡ የዘርፌ ደግነት ግን በመንደሩ ተወራ::
"መልሳ ተቀበለቻት እኮ ዘርፌ ሆዷ ቂም አይቋጥር…” እየተባል፡፡

አቲዬ አባባ ያገኙላት የቆርቆሮ ቤት ውስጥ እየኖረች፣ ለመንደሩ ሰው ሁሉ የቀን ሥራ እየሰራች
ኑሮዋን ጀመረች፡፡ ዘርፌን በድላ በመመለሷ እንደተማረከ ባሪያ ጉልበቷን ትገፈገፍ ጀመረ፡፡
የመንደሩ ሰው ሁሉ ዳኛ ወንጀለኛው ሁሉ ፈራጅ ሆነ እናቴ ላይ!! የማያሰሯት ነገር አልነበረም።

እነዚህ ባሎቻቸው ከየመሸታ ቤቱ እያነሱ፣ በየመንገዱ እየለቃቀሙ፣ ከየገጠሩ እያመጡ ሰው
ያደረጓቸው…ጊዜ ያነሳቸው ቅሎች ለፍቶ በመኖር፤ አምላክን በማመን በእጆቿ ንፁህ ፍሬ የምትኖር እናቴን ብረት መንፈስ ሰበሩ፡፡

ጊዜ ያነሳው ቅል እንኳን ድንጋይ ብረት ይሰብራል!!

እጠላቸዋለሁ…!!

በባሎቻቸው ገንዘብ እድሜያቸውን የሚገፉ፣ ሰማኒያ ሚባል ህጋዊ ፈቃድ የባሎቻቸውን
ዳረጎት እየተቀበሉ የሚዘባነኑ የስማኒያ ለማኞች፡፡ ሰማኒያ የሚሉት፣ ፍቅር ሲያልፍ ያልነካው
የልመና ንግድ ፈቃዳቸው ሲቀደድ ከአቲ የባሰ አዘቅት ውስጥ የሚወድቁ ሁሉ ሚስኪን እናቴ
ላይ ተዘባነኑባት፡፡

ምነው ይሄ ምንጣፍ እንዳልረባ ነገር እዚህ ተጣለ?” ይላል አንዱ ጎረቤት ወደ አንዱ ጥግ
የዘመን ቆሻሻውን ተሸክሞ ወደ ተጣለ አሮጌ ምንጣፍ እያሳየ፡፡

አየ..አፈር ተሸክም በስብሶ ማን እሱን ይታገላል? ትላለች ባለቤት ተብዬዋ…ትላንት የከሰል ጆንያ ሳይቀር የምታጥብ የነበረች …ከሰራተኝነት ወደ ሚስትነት በአንድ ሌሊት የአልጋ ወለምታ
የተሸጋገረች መሆኗን አገር እያወቀ፡፡

“ግዴለሽም አፀደ ግማሽ ቀን ብትውልበት አባባ ይመስሳል ይላል መካሪው፡፡

አቲዬን ይጠሩና ያዟታል፡፡ ግማሽ ቀን ጭቃ ታጥባለች፡፡ እንዳሉትም አበባ ይመስላል ምንጣፉ፤
አቤት ቤት አያያዝ ! የምንጣፏ ንጣት ብቻ ለመርገጥ ያሳዝናል እኮ እከሊት ! የእሷ ባል
ሚስት አገባሁ ይበል…” ይባልላታል። ተወዝፋ አቲዬን ቁራሽ በማይገዛ ብር መንደር የሚያለብስ ምንጣፍ ያሳጠበች እከሊትን፣ በእናቴ ጉልበት የምስጋና ካባ ይደርቡላታል።

አፀደ በይ እችን ያዥ” ትልና ሶስት ብር ትሰጣታለች፡፡ አቲዬ ተቀብላ ወደ ማደሪያዋ ትመለሳለች
.አትከራከርም፡፡ ይሄንንም እንደብልጠት ይወስዱታል፡፡ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የደሀን
ጉልበት በነፃ በሚጠጋጋ ክፍያ መበዝበዝን እንደብልጠት ያዩታል፡፡

ቀናቸው የተዳረሰ እርጉዝ አሰሪዎች ስላሳ ትራስ ደልድለው በረንዳቸው ላይ ይቀመጡና ቀኗ
የደረሰ እናቴን፣ “በደንብ እሺው እንጂ" እያሉ ልብስ ያሳጥቧታል፡፡ ለዘመናት በስንፍናቸው
ቤታቸው የከመሩትን ቆሻሻ ሲያስፀዷት ይውላሉ፡፡ 'እንኳን ማሪያም ማረችሽ!' የሚል ጠያቂ
ቤታቸውን እንዳይታዘብ…የበከተ ቤታቸውን…ከቅዱስ ዮሐንስ እስከ ቅዱስ ዮሐንስ ውሀ ነክቶት
የማያውቅ መጋረጃቸውን ያሳጥቧታል !! ወይስ ከእርጉዝ እርጉዝ ይለያል፡፡ የደሀ እርግዝና
ቢጨነግፍም እዳው ገብስ ነው ዓይነት ፍዳዋን ያበሏት ነበር እናቴን፡፡

ለምን ላፋች አይደለም የምለው ! ግን የለፋችበትን የላቧን ዋጋ ከልከለዋታል። አፈር ያብላቸውና
የደም ገንዘብ የበሉ ናቸው:: ዳሌያቸውን እያገማሸሩ ወንድ የሚያሳድዱ ሴት ልጆቻቸው አቲዬ
ከእርግዝና ህመም ጋር እየታገለች ያጠበችውን ልብስ የለበሱ እርኩሳን ናቸው…፡፡ ሕፃናት
ልጆቻቸው በየሜዳው ሲንከባለሱ እናቶች በሳምንቱ መጨረሻ ስለሚደክመው የአቲዬ ጉልበት
ሳይሆን ስለሳሙናቸው ነበር የሚጨነቁት፣ 'አንተ ልጅ አረ የሳሙና ጡር አለው' እያሉ፡፡ አቲዬ
ቃል ሳትተነፍስ ማንንም ሳታማርር እስከ ወለደችበት ቀን ድረስ ስትሰራ ነበር፡፡....

አላለቀም
👍3014👎1
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


....ማሪየስ የሆነውን ሁሉ ከጣራ ላይ ተንጠልጥሎ አንድም ነገር ሳይቀረው ተመለከተ፡፡ ሆኖም ልቡ ያረፈው ክፍለ ውስጥ ከተፈፀመው ድርጊት ላይ
ሳይሆን ከወጣትዋ ላይ ነበር፡፡ ነፍስና ሥጋው ከልጅትዋ ላይ ነበር የተፈናጠጠው:: ከክፍሉ ስትወጣ የነበረው አሳብ አንድ ነበር፡፡ ይኸውም ከሄደችበት መከተልና አድራሻዋን ማየት ነው:: እንዲህ በድንገት በአጋጣሚ
አግኝቶአት ሁለተኛ እንድታመልጠው አልፈለገም:: ከነበረበት ቶሎ ብሎ ወርዶ ቆቡን አነሳ፡፡ በሩን ከፍቶ ሊወጣ ሲል አንድ ነገር ትዝ ብሎት ቆም
አለ፡፡ ሚስተር ዦንድሬ ለፍላፊ እንደመሆኑ ምናልባት በወሬ ይዟቸው ቶሎ ከዋናው መንገድ አይደርሱ ይሆናል ሲል አሰበ፡፡ ቀድመውት ሳይወጡ
ቀርተው ድንገት ቢተያዩ ጥሩ እንደማይሆን ገመተ:: ካዩት ምናልባት እንዳለፈው ጊዜ ዘዴ ፈጥረው እንዳይጠፉብት ልቡ ጠረጠረ፡፡ ታዲያ ምን ማድረግ ይሻላል? ትንሽ ከቤት ውስጥ መቆየት! ቢያመልጡኝስ! ማሪየስ
ግራ ገባው:: በመጨረሻ የሆነ ይሁን ብሎ በድፍረት ከክፍሉ ወጣ::

መንገድ ላይ ሰው አልነበረም፡፡ ወደ ውጭ እየሮጠ ወጣ፡፡ ወደ
ዋናው መንገድ እንደደረሰ አንድ ጋሪ ከኩርባው ላይ እጥፍ ሲል በሩቁ ተመለከተ፡፡

ማሪየስ ተመልሶ ከክፍሉ ውስጥ ገባ፡፡ በሩን ወደኋላ ወረወረው::
ሆኖም ገርበብ አለ እንጂ አልተቀረቀረም፡፡ በሩ ተዘግቶ እንደሆነ ለማየት ዞር ሲል የበሩ እጄታ ሲንቀሳቀስ ተመለከተ፡፡ በሩ በዝግታ ከውጭ ተገፋ፡፡
«ማነህ? ምንድነው የምትፈልጉት?» ሲል ጠየቀ፡፡
የሚስተር ዦንድሬ ልጅ ነበረች::
«አንቺ ነሽ እንዴ! ምነው እንደገና መጣሽ? አሁን ደግሞ ምን
ትፈልጊያለሽ?» በማለት ግሳፄ በተሞላበት አንደበት ጠየቃት፡፡
ልጅትዋ በመሽማቀቅ አቀረቀረች:: ጠዋት አሳይቶአት የነበረው
መልካም አቀባበል አሁን በመንፈጉ ግራ ተጋባች:: ከክፍሉ ውስጥ | እንደመግባት የበሩን እጀታ ይዛ እዚያው ከበራፍ ቀረች፡፡ በሩ በግማሽ ገርበብ ብሎአል፡፡

«ግቢያ ታዲያ! ምነው አሁን ተዘጋሽ? ከእኔ የምትፈልጊው ምንድነው?» ሲል በድጋሚ ጠየቃት::

አሳዛኝ ዓይንዋንና አንገትዋን ቀና አደረገቻቸው:: በተኮናፈዘ አንደበት
«መሴይ ማሪየስ፤ አሳብ የገባህና የአዘንህ ትመስላለህ፤ ክፉ ነገር አጋጠመህ እንዴ?» ስትል እየፈራች ጠየቀችው::

«እኔን ነው የምትዪው?»
«አዎን አንተን ነው::»
«ምንም አላጋጠመኝም፤ ምንም አልሆንኩም::»
«እውነትህን ነው?»
«አዎን፧ ምንም ነገር የለም::»
«አላምንህም፤ አንድ ነገር አለ፡፡»
ዝም ብል ይሻላል መሰለኝ::
ማሪየስ በሩን ሊዘጋባት ሞከረ፡፡ ግን እርስዋ አጥብቃ ይዛ ኣላዘጋም አለችው።

«ቆይ እስቲ አትቸኩል።» አለች «ዛሬ ጠዋት ደህና ነበርክ፡፡ በሀዘኔታ ነበር ያነጋገርከኝ፡፡ አሁን ግን ተለወጥክብኝ፡፡ እንደጠዋቱ ብትሆን ደስ ይለኛል የምረዳህ ነገር አለ? አንተን የመርዳት አቅም ካለኝ ያንን ከመፈጸም
ወደ ኋላ አልልም፡፡ ብቻ ምሥጢርህን ሁሉ አካፍለኝ ማለቴ አይደለም፡፡ሆኖም የምረዳው ነገር ካለ ንገረኝ፡፡ እቤት ውስጥ የምሠራው ወይም የምትልከኝ ነገር ቢኖር እዘዘኝ፤ እፈጽማለሁ፡፡»

ልጅትዋ ይህን ስትናገር ማሪየስ ጥሩ አሳብ መጣለት:: ሰው ሲሰምጥ ያገኘውን ሁሉ ለመጨበጥ እንደሚሞክር ሁሉ በመጣለት አሳብ ለመጠቀም
አላመነታም:: ወደ ልጅትዋ ጠጋ አለ፡፡
«ስሚ» ኣላት ጥቂት ፈገግ ብሎ፡፡
በጣም ደስ ብሉአት ጣልቃ ገብታ አሳቡን አቋረጠች፡፡
ምን «አዎን እንደዚህ ፈገግ እያልክ አናግረኝ፡፡ እንዲህ ስትሆን ደስ ይለኛል

«እሺ» ሲል ቀጠለ፡፡ «ከእናንተ ቤት መጥቶ የነበረውን ሽማግሌ ከነልጁ እየመራሽ ያመጣሻቸው አንቺ ነሽ? አይደል?»
«አዎን፤ እኔ ነኝ፡፡»
«ቤታቸውን ታውቂዋለሽ?»
«አላውቀውም፡፡»
«ማወቅ ትችያለሽ?»
«እሱን ነው የምትፈልገው?» በማለት እየተከዘች ጠየቀችው::
«አዎን እሱን ነው የምፈልገው» ሲል መለሰላት:: «ሰዎቹን
ታውቂያቸዋለሽ?»
«አላውቃቸውም፡፡»
«ማለቴ» አለ በችኮላ፤ «ልጅትዋን አታውቂያትም? ግን ከፈለግሽ
ለመተዋወቅ ትችያለሽ፤ አይደል?»
«እነርሱን» በማለት ፈንታ «እርስዋን» በማለቱ አንጀትዋ ተኮማተረ::
«ብረዳህ ምን ታደርግልኛለህ?»
«የፈለግሽውን!»
«የፈለግሁትን?»
«አዎን፤ የፈለግሽውን፡፡›
«ቤታቸውን አገኝልሃለሁ፡፡»
በመተከዝ ወደ መሬት አቀረቀረች፡፡ ወዲያው በሩን ዘግታ ሄደች::
ማሪየስ ብቻውን ሆነ፡፡ ወንበር ላይ ቁጭ እንዳለ ፊቱን በእጅ ሸፍኖ
ክርኑን ከአልጋው ላይ አስደገፈ:: በአሳብ ተውጦ ከዚያው ቀረ:: ቆይቶ ቆይቶ በድንገት ከአሳቡ ባነነ፡፡ የሚስተር ዦንድሬ ጎርናና ድምፅ ቀሰቀሰው::
«እርግጠኛ ነኝ አላልኳችሁም፧ አውቀዋለሁ ብዬ አልተናገርኩም?»
ሚስተር ዦንድሬ ስለማነው የሚያወራው? ማንን ነው ያወቀው?
አባባ ሸበቶን? ቀደም ሲል ያውቀዋል ማለት ነው? ያቺ ልቡን የሰለበችው ልጅና አባትዋ የታወቁ ሰዎች ናቸው ማለት ይሆን? እነማን እንደሆኑ
ድንገት ይፋ አውጥቶ ይነግረኝ ይሆን? እያለ ማሪየስ ተጨነቀ፡፡
ቀደም ሲል ከነበረበትና የእነሚስተር ዦንድሬን ክፍል ወደሚያሳየው ክፍት ቦታ አመራ:: ከላይ ሆኖ የሚስተር ዣንድሬን ቤተሰብ በድጋሚ ያስተውል ጀመር፡፡

የሚስተር ዣንድሬ ቤተሰብ የመጣላቸውን ስጦታ ሲከፍቱ ልብስ በማግኘታቸው እናትና ልጆች አዳዲስ ልብስ ለብሰዋል:: የሚያማምሩ የአልጋ ልብሶች ከወለሉ ላይ ተዘርግተው ተቀምጠዋል፡፡

ሚስተር ዦንድሬ ከውጭ ገባ፡፡ ሁለቱ ልጆች ከእሳት ማንደጃው
አጠገብ መሬት ላይ ቁጭ ብለዋል:: እናትየው መደብ ላይ ጋደም ብላለች።
ሚስተር ዦንድሬ እንደገባ መቀመጡን ትቶ ከወዲህ ወዲያ ተንቆራጠጠ፡፡ፊቱ ላይ የተለየ ገጽታ ይታያል፡፡ ባለቤቱ የሆነው ነገር እውነት ስላልመሰላት
በአንዴ ይህ እውነት ነው? እርግጠኛ ነህ?» ስትል ጠየቀችው::
«እርግጠኛ ነኝ! ከስምንት ዓመት በፊት ነው ያየሁት፧ መልኩ
አልጠፋኝም፤ ገና ሳየው ነው ያወቅሁት:: አንቺ ግን አልመሰለሽም?
«አልመሰለኝም::»
እኔ እኮ በሚገባ እንድታጤኒው ነግሬሽ ነበር፡፡ ቁመቱ መልኩ፧
እድሜው አንድ ነው፡፡ አንዳንድ ቶሎ የማያረጁ ሰዎች አሉ፡፡ ሰው እንዴት ላያረጅ እንደሚችል አይገባኝም፡፡ ድምፁ እንኳን አልተቀየረም፡፡ አለባበሱ
ግን በጣም ተሻሽሎአል፡፡ ሌላ ለውጥ የለውም፡፡ ይህ የጃጀ ርኩስ ሰይጣን፣አውቄበታለሁ!»

ገልመጥ ሲል ሁለቱን ልጆቹ ስላያቸው «ምን ታፈጣላችሁ፤ ውጡ ከዚህ! ዓይናችሁን ያውጣው» ሲል ጮኸባቸው::

ሁለቱ ልጆች ወጥተው ሊሄዱ ሲሉ የትልቅዋን ልጅ እጅ ይዞ «ልክ
በአሥራ አንድ ሰዓት እንድትመለሱ፤ ሁለታችሁንም እፈልጋችኋለሁ» በማለት አስጠነቀቃቸው::

ማሪየስ ኮስተር ብሉ ማጤኑን ቀጠለ፡፡ ሚስተር ዣንድሬና ባለቤቱ ብቻቸውን ቀሩ፡፡ ሚስተር ዣንድሬ ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ መንቆራጠጥ ጀመረ፡፡ የተቀዳደደ ሸሚዙንና
ትሪውን አስተካክሎ ወደ ሚስቱ ዞር አለ፡፡

«ስለኮረዳዋ አንድ ነገር ላጫውትሽ?» ሲል ጠየቃት፡፡
«ኮረዳዋ አልክ! እስቲ ምን ይሆን ልስማዋ!» ስትል መለሰችለት።
የሚነጋገሩት ስለኮዜት እንደሆነ ማሪየስ አልተጠራጠረም:: በጉጉት ጆሮውን አቀና፡፡

ሚስተር ዦንድሬ ወደ ሚስቱ ጠጋ ብሉ በሹክሹክታ ለሚስቱ አንድ
ነገር ነገራት፡፡ ምን እንዳላት ማሪየስ አልሰማም፡፡ በመጨረሻ ግን ሰውነቱን ቀና አድርጎ «ይኸውልሽ እርስዋ ናት» ሲል ጎላ ባለድምፅ ተናገረ፡፡
👍25
“ያቺ ልጅ?» ስትል ሚስቱ ጠየቀች፡፡
“ያቺ ልጅ!» ሲል መለሰላት፡፡
ይህን ቃል ስትሰማ የሴትየዋ ፊት ተለዋወጠ፡፡ ቁጣዋ ገነፈለ፡፡
ጥላቻና ቁጣ ተመሰቃቀሉባት:: በጣም ተገረመች::

«ሊሆን አይችልም!» ስትል ጮኸች:: «የእኔ ልጆች የእግራቸው
መጫሚያ ሳይኖራቸው በባዶ እግር ራቁታቸውን እየሄዱ! እንዴት ተደርጎ የሀር ካባ፣ ባለወርቀ ዘቦ ቆብ፣ የአዞ ቆዳ ቡት ጫማ! እስከ ሁለት መቶ ፍራንክ የሚያወጣ ልብስ ለብሳ ልትሄድ! ያቺ ልጅ! ኧረ ተሳስተሃል፡እርስዋ ልትሆን አትችልም:: ይህቺ እንደሆነ ሲያይዋት ጨዋ የጨዋ ልጅ
ትመስላለች:: ምንዋም ዱርዬ አይመስል:: የለም፣ የለም ተሳስተሃል፡፡»

«መስሎሻል፤ ራስዋ ናት፤ ደግሞም ታያለሽ፡፡»

ባልዋ አረጋግጦ ሲነግራት ከተጋደመችበት ብድግ አለች፡፡ :
ያ ድቡልቡልና ግዙፍ አካልዋ የተቆጣች ነብር አመለካከት ያላት አሳማ አስመሰላት፡፡

«ምን!» በማለት ቀጠለች፡፡ «ይህቺ ልጆቼን ሀዘን በተሞላበት ዓይን እያየች ያነጋገረችው ቆንጆ ልጅ ያቺ ዱርዬ ልትሆን! የት አባትዋ፧ አንዴ በጥፊ ብላት ምንኛ አንጀቴ በራሰ!» በማለት ሰውነትዋ በንዴት እየተንቀጠቀጠ ተናገረች፡፡ ልጅትዋ ከአጠገብዋ ያለች ይመስል ልትመታት እጅዋን ዘረጋች፡፡ ሰውዬው ሚስቱ የምትለውን ብዙም ሳይሰማ ከወዲህ ወደ ወዲያ መንቆራጠጡን ቀጠለ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች ዝምታ በኋላ ግን ተናገረ።

«ከፈለግሽ አሁንም አንድ ነገር ልነግርሽ እችላለሁ፡፡»

«ምን?» ስትል ጠየቀችው፡፡
ቶሎ ብሉ ዝግ ባለድምፅ ጨዋታውን ቀጠለ፡፡

«የእድላችን በር ተከፈተ፡፡»
ሴትዮዋ አፍጥጣ አየችው:: «ይኼ ሰውዬ አበደ እንዴ» ስትል
አሰበች፡፡ እርሱ ግን ንግግሩን ቀጠለ፡፡

«በደምብ አድምጪኝ፡፡ ይህን ተመጻዳቂ፣ ይህን ቱጃር ያዝኩት፡፡
ጥሩ ነው ጉዳዩ አልቆአል፡፡ ሁሉም ነገር በሚገባ ተስተካክሎ ታቅዷል፡፡ ሰዎች እንደሆነ አነጋግሬያቸዋለሁ:: ጀምበር ልትጠለቅ ስትል በአሥራ ሁለት
ሰዓት ገደማ ይመጣሉ፡፡ ይህ ወሮበላ! ስልሣውን ፍራንክ ይዞ ይመጣ የለ አየሽ ነገሩን እንዴት እንዴት አድርጌ እንዳቀናጀሁት? ስልሣ ፍራንካ የቤቱ ጌታ፣ የካቲት 4 የምን ስድስት ወር፣ ሦስት ወር እንኳን አይሞላም:: ብልህ ነኝ አይደል? አየሽ ሰውዬው በአሥራ ሁለት ሰዓት ይመጣል፡፡ በዚያ ሰዓት ጎረቤታችን እራቱን ፍለጋ ይወጣል፡፡ የቤት ጠባቂዎች
እንደሆነ በዚህ ሰዓት ሥራዋን ልትሠራ ወደ ከተማ ትወጣለች፡፡ ግቢያችን ውስጥ ከእኛ በስተቀር ማንም አይኖርም ማለት ነው:: ጎረቤታችን እንደሆነ ከአምስት ሰዓት በፊት ከቤቱ አይገባ! ልጆቻችን ከበር ላይ ቁመው ሰው
መምጣት አለመምጣቱን ይጠባበቃሉ፡፡ አንቺ ደግሞ ትረጂኛለሽ፡፡ ሰውዬው ግን በራሱ ይፈርዳል።»

«በራሱ ላይ ባይፈረድስ?» ስትል ምሽቲቱ ጠየቀች፡፡
ዦንድሬ በንቀት ዓይን እያየ መለሰላት::
«እኛ እንፈርድበታለን፡፡»
ይህን እንደመለሰ ከት ከት ብሎ ሳቀ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲስቅ ማሪየስ አየው፡፡ የፌዝ ሳቅ ስለነበር ማሪየስን አስፈራው::

ዦንድሬ ሳጥኑን ከፍቶ አንድ ያረጀ ቆብ ካወጣ በኋላ በለበሰው ልብስ እጅጌ ጠራረገው፡፡ ጠራርጎ ሲጨርስ አጠለቀው፡፡

«አሁን» አለ፤ «ወደ ውጭ መውጣቴ ነው:: የማነጋግራቸው ሰዎች ይቀሩኛል፡፡ ጥሩ ወዳጆች! ውጥኔ እንዴት እንደሚሠራ ታያለሽ፡ በተቻለ ፍጥነት ቶሎ እመለሳለሁ፤ ቤቱን ጠብቂ፡፡ የዛሬዋ ቀን ሌላ ናት፡፡»

ደረጃውን እያንኳኳ ቶሎ ቶሎ ሲሄድ ማሪየስ ኮቴውን ሰማ። በዚህም ወደ ውጭ መውጣቱን አረጋገጠ፡፡ ወዲያው በአካባቢው የሚገኝ ቤተክርስቲያን የስዓት ደወል ደውሎ ሰባት ሰዓት መሆኑን አበሰረ::.......


💫ይቀጥላል💫
👍181🥰1
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አምስት


...እኔ የተወለድኩ ቀን ጠዋት አቲዬ አቃጣሪዋ ዘርፌ ቤት ወተት ስታልብ ነበር፡፡ ረፋዱ ላይ
የአንዲት ጎረቤት በርበሬ ስትቀነጥስ ዋለች፡፡ ውጋት ሲጀምራትና ምጡ ሲጫናት ከበርበሬ ቅንጠሳው በኋላ ልብስ ወደምታጥብበት ቤት ለመሄድ እየተዘጋጀች ነበር፡፡ ህመሙ ሲጀምራት ግን መንገዷን ቀይራ ወደ መንደር አዋላጅ አልማዝ ቤት ሄዳ እየፈራች፣ “እትዬ አልማዝ
እያመመኝ ነው፡: ምጥ ነው መሰለኝ…" አለቻት፡፡

“ውይ በሞትኩት መጣሁ ሂጂና ቤትሽ አረፍ በይ…" አለቻት፡፡

አቲዬ እንደታዘዘችው አደረገች፡፡ እዛች እሮጌ ፍራሽ ላይ ተኝታ ምጥ እየናጣት በር በሩን ማየት
ጀመረች፡፡ አልማዝ ግን ወደ አቲዬ አልሄደችላትም፡፡ ምክንያቱም እቲቲዬ ምጥ የተያዘች ቀን፣
ዘርፌ የምትባለዋ አቃጣሪ ባልቴት የአሜሪካ ላሟ ያልታወቀ ነገር በልታ ሆዷ ተቆዝሮና አረፋ
ደፍቃ እየጓጎረች ስለነበር፣ መንደርተኛው ሁሉ ወደዚያው ሄዶ ነበር፡፡ አዋላጇ ኣልማዝም
ቅድሚያ ለወርፌ ላም ሰጥታ ነበር፡፡

አንድ ግብርና የሚሰራ የእንስሳት ህክምና ባለሙያ ተጠርቶ እስከሪብቶ በሚመስል ነገር የላሟን ሆድ ወግቶ ካስተነፈሳት በኋላ ላሟ ነፍሷ መለስ በማለቱ የመንደሩ ሰው ደስታውን በእልልታ
ገለፀ፡፡

በዚህ መሐል እዋላጇ አልማዝ፣ “በሞትኩት ያች ሚስኪን ምን ደርሳ ይሆን?” ብላ ወደ ቤታችን
ተጣድፋ ብትደርስ አቲዩ እኔን አቅፋ አገኘቻት፡፡ የወርቅ ፍልቃቂ የመሰልኩ እኔ፣ በእሳት የተፈትንኩና የጥላቻ እሳት የምትፋ እኔ፣ አላፊ አግዳሚውን የምራገም እኔ በእናቴ እቅፍ ላይ ታሪክ ይወቀኝም አይወቀኝም፣ እናት የተባለች ታላቅ ሀገር ከስግብግብ፣ ከአስመሳይ፣ ከራስ
ወዳድ፣ ከአሽቃባጭ፣ ደሀ ከማይወድ፣ እምነት ከሌለው፣ ሆድ አምላኩ ከሆነ አመንዝራ እና
ጨካኝ ጎረቤት ቅኝ ግዛት የወጣሁ ጀግና እኔ ተወለድኩ !! አገሬ እናቴ አፀደ ናት ! ባንዲራዬም
የእናቴ ቀለም አልባ አሮጌ ቀሚስ !! ድምጿ መዝሙሬ ነው፣ ትዕዛዟ ሕገ መንግስቴ !! እናቴ
አፀደ ወይንም ሞት!! አቲዬ ትቅደም !! አቲዬ ለዘላለም ትኑር!

መዝመሬ፣

ተንቀሽ የኖርሽው ድሮ ከዚህ ቀደም፧
እናቴ አፀደ የደፈረሽ ይውደም !!

በሰሜን ስግብግብ የደሀ ደም መጣጭ ጎረቤቶች፣ በደቡብ ራስ ወዳድ በድሀ እምባ የሚዋኙ
እጋሰሶች፣ በምስራቅ የእናቴን ፀሐይ እንዳትወጣ የሚጋርዱ አስመሳይና ሆዳሞች፤ በምዕራብ
ሚስኪን ሴት ደፋሪዎች እና ትውልድ የሚነዱ ካፖርታሞች…፡፡ ከታች በባዶ እግሯ የምትረግጠው
ምድር፣ ከላይ እግዚአብሔር (የባህር በሯን የሚያዋስናት ሀገር አፀደ ትባላለች - የእኔ አገር እሷ
ናት !!

አፀደ ከሰማይ ዱብ እንዳለ ጉድ ዘመድ የላትም፡፡ እናት፣ አባት፣ አክስት፣ አጎት የላትም፡፡
አልተማረችም ገንዘብም የላትም፡፡ ግን ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ ለሆነ ባለፅጋ አግዚያብሔር እንብና ድፍን የኢትዮጲያ ሃምሳ ብር ያበደረች ልበ ሙሉ ሴት ናት፡፡ እግዚያብሔርም የማንም
ብድር በእጁ ይቆይ ዘንድ አይወድምና ብድሩን ይከፍል ዘንድ እኔን መንገድ አደረገ፡፡ በድፍን ሀያ አምስት ዓመታትም አነፀኝ ደለደለኝ።

እግዚኣብሔር ፈጠነም ዘገየም ወደ እያንዳንዱ ሰው ሕይወት ውስጥ ይመጣል፡፡ ሲመጣ የእግዜርን እርምጃ የእግሩንም ዳና የሚቋቋም መንገድ የሚሰራው መከራ በሚባል ኮንክሪት ነው :: ዙሪያህን የከበበህን ችግርና እልህ አስጨራሽ የሕይወት ፈተና ስታልፍ፣ የእግዜር የመጀመሪያ
እርምጃ ትጀምራለች፡፡ ያኔ ታዲያ ርሀብን ብቻ ሳይሆን ጥጋብንም የምትችል አድርጎ እንዳነፀህ ይገበሀል።

አሰራሩ እንደዛ ነው፤ ሳይሆንም እኔ እንደዛ ነው እላለሁ፡፡ አንተን ከድህነት ማውጣት ብቻ ሳይሆን መጭውን የጥጋብ ዘመንም የሚሸከም ትከሻ እንዲኖርህ አድርጎ ይሰራሀል ካለመንክ
እንደ የዕምነትህ መጽሀፍህን ግለጥ፣ አዱኒያን እንደ ምናምንቴ ንቀው ፈጣሪን ያመኑ፣ የተከተሉ
ሁሉ ሰፈርህ ሕንፃ አቁሞ እንደሚሸልለው እብሪተኛ ሃብታም ባንዴ ሰማይ ጥግ አልደረሱም፡፡

ፈጣሪ ሲሰራህ ቀስ ብሎ ነው፣ ግን መቼም እንዳትፈርስ አድርጎ፡፡ ያኔ ደስ ይልሃል ወደህ ነው ጎንበስ ብለህ ታመሰግናለህ በግድህ አንተ ላለማመስገን ብትጥር እንኳን ስጋህ ያማረ ፍራሸ ላይ ለሽ ሲል፣ በርሀብ የተንሰፈሰፈ አንጀትሀ ውስጥ የጣመ ምግብ ሲጎዘጎዝ፣ በላዩ ላይ ጥሩ ቡና ስትጨምርበት፣ ከምንም በላይ ደግሞ ራስህን ስትገዛና ልብህ በሰላም ሲሞላ፣ እግሲያብሔር ይመስገን ይልሀል አፍህ ከአንተ ትዕዛዝ ውጭ!!

አቲዬ እኔን ከወለደች በኋላ ትንሽ ተስፋ ልቧ ውስጥ አደረ፡፡ አባቱ በልጁ አይጨክንም መቼም
ብላ፡፡ ግን አባት በልጁ ጨከነ፡፡ ቀለመ ወርቅ አባት የመሆን ሞራሉም ብቃቱም የሌለው
ሴሰኛ ሽማግሌ መሆኑን የአቲዬ ልብ ያወቀው ብዙ ቆይቶ ነበር፡፡ ወንዶች ለአገር ዳር ድንበር
እየፎከሩና እየሸለሉ የመዝመታቸውን ያህል አባትነትን ለመቀበል፣ ትዳርንም አሜን! ብሎ
ለመኖር፣ ከነፍሳቸው ጋር የሚገጥሙት ጦርነት ቀላል አይደለም፡፡ ለመውለድ ወንድ መሆን በቂ ነው፡አባት መሆን ግን ታላቅ ጀግንነትን ይጠይቃል፡፡ ቀለመወርቅ ደግሞ ጀግና አልነበረም፡፡ስለዚህ እኔን ልጁን ዶሮ ሳይጮህ ሦስቴ ካደኝ፡፡

አቲዬ የእኔ ብርቱ ግን በሰባት ቀኗ ከአራስ ቤቷ ተነስታ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ስራዋን
ጀመረች፡፡ “ኧረ ወገብሽ ይጥና” ያላት አልነበረም፡፡ የበሰበሰ ድሪቷቸውን ከምረው ጠበቋት
እንጂ ! 'የምትገርሚ ጠንካራ ልጅ እያሉ ፡፡ እርሳ ቐን ሙሉ አርባ ቀን ሙሉ ተዘፍዝፈው ሊጣቸውን ሲያሻምዱ ኑረው ሲወጡ እንኳን አራስነት ምን ያህል ከባድ መሆኑን እንደማያውቁ ሁሉ፥ አቲዩን በሥራ
ሲያጣድፏት ምንም አልከበዳቸው፡፡

ልጅ ይዛ ሥራ መሥራት ከባድ ነበር ለአቲዬ:: በየቤቱ በረንዳ ላይ እያስተኛች ሳለቅስባት እያጠባችኝ(ምናባቴ እንደሚያስለቅሰኝ እንጃ !)፡፡ አቲዬ እናቴ ብርቱ ሰው ከህይወት ጋር ትግሏን ቀጠለች.…አንድ.. ሁለት..ሦስት...አራት ወር ለአቃጣሪዋ ዘርፌ አቲዬ እየፈራች እንዲህ አለቻት፡

“አትዬ እኔ እንግዲህ እስካሁን ለልጁ አንድ ነገር ያደርጋሉ ብዩ ጠበቅኳቸው እሳቸው ግን
“ማናቸው ልጄ አለች ዘርፈ አካሄዱ አላምር ብሏት ፊቷን አጨፍግጋ፡፡

“ጋሽ ቀለመወርቅ" አለች አቲዬ፡፡

"እህ…ደም እሱ ምን ቤት ነው ባንች ልጅ”

"እትዬ ፈርቼ አልነገርኮትም እንጂ፣ እኔ ሌላም ወንድ ነክቶኝ አያውቅ ተሳቸው ነው :"

“ወዲያ ዝም በይ…ምን ትላለች
እቺ..የተከበረ ሰው አናት ዘሎ ፊጥ ማለት ምን ይሉት ብልግና
ነው?! ሁላተኛ እንዲህ ያለ ነውር ስትተነፍሽ ብሰማ ውርድ ከራሴ፡፡ ሂጂ አሁን ወዲያ ያው
ደሞዝሽ!"

ብላ አስር ብር ወረወረችላት፡፡ ስራዋ አስደንግጧት እንጂ ሳምንት ነው ገና ደሞዝ ለእቲ ከከፈለቻት፡፡

ቀለመወርቅ ይህችን ጭምጭምታ ሲሰማ ተንኮሉን ጀመረው:: አቲዬን ከመንደሩ ሊነቅል እንቅልፍ አጣ፡፡ አቲዬ ለአባ እስጢፋኖስ ሽምግልና ላከችበት፡፡

“ቀለመወርቅ መቼስ ዘር አይጣላም፡፡ ነገ የት እንደሚደርስ አንድ ፈጣሪ ነው የሚያውቀው፡፡
ሌላው ቢቀር የወተት መግዣ እንኳን ስጣት መቼስ እሷ ጋር እንዲህ ሠራህ፣ እንዲህ አደረግክ
ለማለት ባልደፍርም ልጁ ቆርጠው የጣሉት አንትን ነው…”
👍311
“ምን ማለተዎ ነው አባ.…እኔን በእንዲህ ያለው ቅሌት እንዴት ይገምቱኛል?” ብሎ በአባ ከፉኛ
ተቆጣ፡፡ ቀለመወርቅ ሽምጥጥ አድርጎ ካደ !! መቸም ቁርጥ አድርገው የጣሉት ሰይጣን ነው፤
ይባስ ብሎ ከዘርፌ ጀምሮ መንደርተኛው ሁሉ አቲዬን ሥራ ማሠራቱን እንዲያቆም ተንኮል
ይሸርብ ጀመረ ተሳካለት፡፡ አንድ መንደር ሕዝብ አንዲት ደሀ ላይ እመፀ፡፡ ቀለመወርቅ እና
ዘርፌ ነበሩ የተንኮል ድሩ ፈታዮች፡፡

“ነገ ባልሸን ስሙን ብታጠፋውስ.. ሰው እንደሆነ አንች ቤት ልብስ ማጠቧን፣ ገባ ወጣ ማለቷን
ነው የሚያየው” ይሏታል ለአንዷ አሰሪ፡፡

አውነትዎትን ነው እትዬ ዘርፈ ለኣቶ ቀለምወርቅ ያልተመለሰች እች…" ትላለች፡፡ በቃ አቲዬን
በሰበብ አስባብ ታባርራታለች፣ “ውይ ትላንት ልጆቹ አጠቡት ልብሱን” በቃ !

አታዩ ግራ ገባት። እኔን አዝላ ስትንከራተት ትውልና የሚሠራ ሥራ አጥታ ማታ ቤት ትመሰላለች፡፡ቤት ውስጥ የነበረችው ርጋፊ በሶ ብቻ ነበረች፡፡ ወደ ማታውቀው መንደር እየሄደች፣ የሚታጠብ ልብስ አላችሁም ትላለች፡፡
"የለንም"

"ወፍጮ የሚሄድ እህል በርበሬ ካለ.”

“የለም…የለም” ይላሉ ያዘለችውን ልጅ እያዩ፡፡

እቲዬ ተንከራተተች፡፡ በመጨረሻም ያላት አማራጭ ልጇ በርሀብ ከሚሞት ቀለመወርቅ እግር
ላይ ወድቃ ይማሩኝ!” ማለት ነው፡፡ ቀለመወርቅ - ቀጣፊው ነብይ እሱ በመንደሩ “ይታሰር"
ያለውን ሥራ ሰይጣን በድፍን አዲስ አበባ ያስረዋል፡፡ አቲዬ ይቅር ይበሉኝ ልጁ የእርስዎ
አይደለም ሲቸግረኝ ነው ክፉ የተናገርኩት” ልትል ወደ ቀለመወርቅ ቤት ገሰገሰች፡፡

ለከፋቱ ደግሞ ዓይን የለ አፍንጫ፣ ፀጉር የለ ጆሮ እኔ ቁርጥ ቀለመወርቅን ነበር የምመሰሰው፡፡
ለክህደት የማልመች ጉድ፡፡ ቀለመወርቅ ብቻውን የወለደኝ ይመስል አቲዪን የሚመስል አንዲት ነገር የለኝም፡፡ የቀለመወርቅን የልጅነት ፎቶ ቁጭ!! ቢሆንም "ይቅር በለኝ ልጅህ አይደለሁም ስል በእናቴ ጀርባ ላይ ወደ ኣባቴ እየሄድኩ ነው -አባት ያሳጣውና፡፡ ይሄ የውሻ ልጅ !

ቀለመወርቅ የእድር ዳኛው ጋር ተነጋግሮ አቲዩን ከማደሪያዋ ሊያፈናቅላት ሲዶልት እንዳመሸ
የዘርፌ ሠራተኛ ለአቲዩ ሹክ ብላት ነበር፡፡ ለይቅርታ የባስ ያሮጣት አንዱ ጉዳይም ይሄ ነው፡፡
ጀግነት ጥግ እንደሌለው ሁሉ ከፋትም መጨረሻ የለውም፡፡ ይሄ ከፉ አቲዬን ማሳደዱን በትጋት
ተያይዞት ነበር፡፡ እናም አቲዬ ይቅርታ ልትጠይቅ፤ “ማረኝ ጌታዬ ልትለው ወደ ቤቱ ሄደች።
ወዳጄ እግዜር ይቅርታ ይወዳል ማለት 'ማንም ጥጋበኛ እግር ስር እየሄድክ እንድትደፋ ይሻል
ማለት አይደለም፡፡ አቲዬ የእኔን የልጄን ነፍስ ለማትረፍ ራሱን በፈጣሪ ቦታ አስቀምጦ ይቅርታ
ሲጠየቅ የታዘጋጀው ካፖርታሙ ቀለመወርቅ ቤት ልክ በሩ ላይ ስትደርስ እና የግቢውን በር
ልታንኳኳ እጇን ስታነሳ፣ እግዜር “ተመለሽ” አላት፡፡ ያው እንግዲህ እግዜር ሲናገር በሰው
አይደል…፡፡
የእድር ለፋፊው ጉልማው እሳት ጎርሶ እሳት ለብሶ አቲዬን ከኋላዋ በቁጣ ጠራት፡፡ በስሟ
አይደለም፣ "አንች..አንችን እኮ ነው፡፡ ምን ያለችው ናት ጃል” እያለ፡፡ አቲ እየተጣደፈ ወደ
እርሷ የሚመጣውን ለፋፊ ቁማ ጠበቀችው፡፡ እጠገቧ ሲደርስ፣ "ምን መሆንሽ ነው እንች ሴትዮ
የአዙሪት ቅጠል ረግጠሻል እንዴ?” አለ፡፡

“ምነው?” አለች ግራ ገብቷት፡፡

“ምነው ትለኛለች እንዴ በይ ነይ አሁን፡ እቃ ማስቀመወጫ ቤቱን ክፈችላቸው፡፡ ሰው ሞቶ ድንኳን ልናወጣ ብንል ቁልፍ ይዘሽ ጠፋሽ፡፡ አገር ተረፈ እንዴ፣ ያልኳተንኩበት የለም አንችን
ፍለጋ” አለ በማማረር፡፡ አቲዬ ቁልፍ ልትሰጠው አስባ አንድ እቃ ቢጠፋስ ብላ ሰለፈራች
የሰውየውን የማያቋርጥ ድንፋታ እየሰማች ይቅርታው ይቆየኝ ብላ ወደ እድሩ እቃ ማስቀመጫ
ቤት ተመለሱ፤ ሰፋፊው መንገዱን ሙሉ እየነተረካት ነበር አቲዬን፡፡

“እግር ተረፈኝ እንዴ ዘርፌ ቤት፣ ከዘርፌ ቤት ጀሚላ ቤት፣ ጀሚላ 'ወደ ላይ ሄደች ብትለኝ
ዝናሽ ቤት፣ ዝናሽ. አንዳንዱ ሰው አያባራም፡፡ ከእሱ ያነሰ ሰው ያገኘ ሲመስለው ሌሎች ያሉትን ሁሉ ይዘረግፋል፡፡ ሌሎች በናቁት ልክ ሊንቅ ይፍገመሞማል፡፡

እቃ ቤቱ ሲደርሱ ብዙ ሰዎች ተሰብስበው ነበር፡፡ ነጭ የእቃ መጫኛ መኪናም ቆማለች::
መኪናዋ ጎን ነጠላዋን ያዘቀዘቀች ሴት፣ ጀርባዋ ላይ ፎጣ ጣል ያደረጎች ፀጉሯን በሻሽ አስራ
ከቀሚሷ ስር ቱታ ሱሪ፣ የቱታውን ጫፍ ካልሲዋ ውስጥ ጠቅጥቃ ነጭ ሸራ ጫማ የተጫማች
ደልደል ያለች ቀይ ወይዘሮ ቆማለች፡፡ (የአዲስ አበባ ሴቶች ሀዘን ማካበድ ይችሉበታል።
ትጥቃቸው ሲታይ ዘመቻ የሚሄዱ እኮ ነው የሚመስሉት፣ የሟችን ነፍስ ሊያስመልሱ ያሰቡ
የከተማ አርበኞች)

እች ከራስ ሻሽዋ እስከ እግር ካልሲዎ የነገርኳችሁ ወይዘሮ እጥፍ ወርቅ ትባላለች፡፡ ዋናው
መንገድ ላይ ወደ ግራ ታጥፎ ከሹልቃ ክትፎ ቤት አጠገብ ያለው ባለ ሁለት ፎቅ ሆቴል የእርሶ
ነበር፡፡ ጋሪ መቆሚያው አጠገብ ነዳጅ ማደያው ኋላ ያለው ሰፊ ግቢ መኖሪያ ቤቷ ነው፡፡ እና
እች ሀብታም ሴት፣ አቲዬ ተጠርታ ከመድረሷ በፊት በወሬ ወሬ፣

“ዘበኛው ነው የጠፋው ?” ተላለች፡፡

“አይ እዚህ የምትኖረው ልጅ ናት” አላት የእድሩ ሊቀመንበር፡፡

“እዚህ መጋዘን ውስጥ ሰው ይኖራል ያውም ሴት ልጅ” እለች ከልቧ ደንግጣ፡፡

በቆርቆሮ ቤቱ ዙሪያ የሽንት መሽኝያ፡ ቆሻሻ መድፊያ ቦታ ሲሆን፣ እዛ አካባቢ ለደቂቃ መቆም እንኳን ከርፋቱ አይጣል ነበር፡፡ በቤቱ ጥግጥግ ሳርና ቅጠላቅጠል አብቅሎበት መቃብር ቤት አስመስሎታል፡፡ ጣሪያውም ላይ ሀረግ ተጎዝጉዟል፡፡ በቀንም የሚያስፈራ ቤት ነበር እንኳን በሌሊት፡፡

አቲዬ ስትደርስ የሴትዬዋ ድንጋጤ እና ሀዘን ጨመረ፡፡ ከጎኗ ለቆመው ሰው፣ “ጭራሽ ሕፃን ልጅም ይዛ ነው እዚህ የምትኖረው?" አለችው::
እዚሁ ነው እኮ የወለደችው¨ አላት የእድሩ ሊቀመንስሩ፡፡ ሴትዩዋ አንጀቷ ተንሰፈሰፈ፡፡ ቤቱ
ሲከፈት እች ሴት ጉዱን ልየው ብላ ወደ ውስጥ ተራመደች፡፡
አትዩ አጥናፍ ወርቅ አረ አቧራ ነው ጉንፋን ያስይዝሻል እያሉ ተንጫጩ ያእድሩ ሰዎች፡፡ አፍንጫ ያላት
ፍጥረት እቺ ሴት ብቻ ይመስል። ወይዘሮ እጥፍ ወርቅ ግን ወደ ውስጥ ገብታ የአትዬንና የእኔን መኝታ ተመለከተች። የተበሳሳውን የቤቱን ግድግግዳና ጣርያ በታላቅ ሀዘን ቃኘች በራሷ ዓይን ሳይሆን በእግዜር ዓይን፡፡ እናም ሁለት ጊዜ እስነጠሰችና አቲዩን እንዲህ አለቻት

አሁኑኑ የምትፈልጊውን እቃሸን መኪና ላይ ጫኝ፡፡ እኔ ቤት ትኖሪያለሽ፡ ማነህ ና አግዛት
አለችው የሕድሩን ሀላፊ፡፡ ዕቃችን የቆመችው መኪና ላይ ተጫነ፡፡ (ወጉ አይቀር ዕቃ ልበል
እንጂ) የእድር ለፋፊው ማውራቱን አላቋረጠም፣ ያንች ዕጣ ፋንታ እንደ መብራት ሊበራ እኔ
ካላምስት ሳንቲም እንዲህ መኳተን…ነገ ሰው ብትሆኝ አንድ ዋንጫ ጠላ አትይኝም፡፡ አውቀዋለሁ እጄ አመድ አፋሽ ነው፡፡ አገር ቀረኝ እንዴ፣ ዘርፌ ቤት የለችም ሲሉኝ. እንደ አዲስ ጀመረ፡፡...

አላለቀም
17👍15
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


....ደረጃውን እያንኳኳ ቶሎ ቶሎ ሲሄድ ማሪየስ ኮቴውን ሰማ። በዚህም ወደ ውጭ መውጣቱን አረጋገጠ፡፡ ወዲያው በአካባቢው የሚገኝ ቤተክርስቲያን የስዓት ደወል ደውሎ ሰባት ሰዓት መሆኑን አበሰረ::

ማሪየስ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ተረኛ መኰንን እንዳለ ጠየቀ
መኮንኑ አለመግባታቸው ተገለጸለት:: ሆኖም አስቸኳይ ከሆነ ዋናውን አዛዥ ማነጋገር እንደሚችል ተነገረው፡፡

«አስቸኳይ ነው» አለ ማሪየስ፡፡

የቀኑ ዘበኛ ወደ ዋናው አዛዥ ቢሮ አመላከተው፡፡ ዋናው ኃላፊ
ከቁመቱ ዘለግ ያለ ጢማምና ቁጡ ሰው ነው: ሲያዩት ከሞት
ይበልጥ ያስፈራል ወፍራምና ረጅም ካፖርት ለብሷል ፊቱ ክብ ሆኖ ሪዙ ላይ ሽበት ጣል ጣል አድርጎበታል አፍጥጦ ሲያይ ወደ ውስጥ የገባውን ኪስ የሚገለብጥ ይመስላል:: ጠቅላላ ሁኔታው ከዦንድሬ የተለየ አልነበረም ሆኖም የሕግ ስው በመሆኑ ብቻ ከተኩላ ውሻን ማየት እንደሚሻል ዓይነት ትርኢት ነበር ለማሪየስ፡፡
«ጉዳይህ ምንድነው?» ሲል አክብሮት በተለየው አነጋገር ጠየቀው:
«እኔ እንኳን የፈለገሁት የእለቱን ተረኛ መኰንን ነበር፡፡»
«አልመጣም እሱ ፤በእርሱ ምትክ ጉዳይህን እኔ ልፈጽምልህ
እችላለሁ፡፡»
«ጌታዬ ትልቅ ምሥጢር ነው፡፡
«ተናገራ ታዲያ፡፡»
«እና ደግሞ በጣም አስቸኳይ ነው፡፡»
«ይሁና አሳብህን ቶሉ ልስማው፡፡»
ዋናው አዛዥ ይህን ተናግሮ ዝም አለ፡፡ ከጥቂት ጊዜ ጨዋታ በኋላ
ከማሪየስ ሳይሆን ከአሰረው ከረባት ጋር ይነጋገር ይመስል አዛዡ እንዳቀረቀ
«መቼስ መጠንቀቅ ያስፈልጋል» ብሎ ከተናገረ በኋላ መልሶ ዝም አለ:
«ቁጥር 50 52 ፤ ሰፈሩን አውቀዋለሁ፡፡»
‹‹ምን ማድረግ ይቻላል?» ሲል ማሪየስ ጠየቀ፡፡
«ያልካቸው ሰዎች ትልቁን በር የሚከፍቱበት ቁልፍ አላቸው! አንተስ አለህ?»
«እነሱም አላቸው፤ እኔም አለኝ፡:››
‹‹ቁልፉን አሁን ይዘኸዋል?»
«ይዤዋለሁ:፡»
«ስጠኝ» አለ ዋናው አዛዥ::
ማሪየስ ቁልፉን ከኪሱ አውጥቶ ሰጠው፡፡
«የነገርክዎት ነገር ካመኑበት ኃይል ይዘው ቢመጡ መልካም ነው፡፡
ዋናው አዛዥ እንደ መናደድ፧ እንደ መብሸቅ ብሎ ማሪየስን ቀና ብሎ
አየው፡፡ ‹‹ልጅ ለእናትዋ ምጥ አስተማረች» ዓይነት ሆነበት፡፡ ቢሆንም ነገሩ?
ናቅ አድርጎ በመተው ከካፖርቱ ግራና ቀኝ ኪስ ሁለት ሽጉጥ አወጣ:
ሁለቱንም በችኮላ ለማሪየስ ሰጠው።

«ያዛቸውና ወደ ቤትህ ተመለስ፡፡ ክፍልህ ውስጥ ተደበቅ፡፡ ስትገባ
ባያዩህ ጥሩ ነው ወደ ወጭ ወጥቷል ብለው እንዲያስቡ ድምፅህን አታሰማ፡፡ ሽጉጦቹ ጥይት አለባቸው:፡ እንደነከረከኝ ከሆነ የሁለታችሁን ክፍል የሚያገናኘው ግድግዳ ቀዳዳ አለው፡፡ ሰዎቹ መጥተው ከክፍሉ
ውስጥ ከገቡና ነገሩ አንተ ባልከው ዓይነት ሲጀመር አንድ ጊዜ ተኩስ ግን እንዳትፈጥን ወይም እንዳትዘገይ:: ጥሩ ሰዓት ነው በምትልበት ጊዜ ነው
የምትተኩሰው:: ከዚያ በኋላ የእኔ ጉዳይ ይሆናል፡፡»

ማሪየስ ሽጉጦቹን ይዞ ለመውጣት እጁን ከበሩ እጄታ ላይ እንዳሳረፈ ዋናው አዛዥ ያናግረዋል፡፡

«በነገራችን ላይ፣ ከአሁን ጀምሮ እስከ ማታ ብትፈልገኝ እኔ ከዚሁ
ስለምሆን ራስህ ልትመጣ ወይም ሰው ልትልክብኝ ትችላለህ፡፡ ከመጣህ ዣቬር ብለህ ጠይቅ::»

ማሪየስ እጅ ነስቶ ወጣ፡፡

የማይደርስ የለም ፤ ሰዓቱ ደረሰ፡፡ ደመና ስለነበረ ገና በአሥራ ሁለት
ለዓይን ያዝ ማድረግ ጀምሮአል፡፡ ማሪየስ ወደ 50 52 ተመለሰ፡፡ ትልቁ በር ክፍት ነበር፡፡ ቀስ ብሎ ድምፅ ሳያሰማና ማንም ሳያየው ከክፍሉ ገባ፡፡ካልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠ፡፡ ልቡ በኃይል ይመታ ጀመር፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ምን ሊሆን እንደሚችል ታወሰው፡፡ በአንድ በኩል የወንጀል
ሙከራ ሲደረግ በሌላ በኩል ፍትሕ ሲሰፍን ታየው:: ልቡ አልፈራም፡፡ የሕይወት አጋጣሚን መጋፈጥ ደስ እንደሚለው እንደማንኛውም ሰው እርሱም ደስ አለው:: የተወጠነው ነገር ሕልም እንጂ እውነት አልመሰለውም::

ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ፡፡ ማሪየስ በር ሲከፈት ሰማ፡፡ ሁለት ልጆች
በር ከፍተው ሲገቡና አባታቸው ሲጮህባቸው አዳመጠ፡፡ ቀጥሎ የብዙ ሰዎች ድምፅ በሩቁ ተሰማ፡፡
«ስሙ ልጆች፤ አንዳችሁ በላይኛው አንዳችሁ በታችኛው በር በኩል ሆናችሁ የሚመጣ ሰው ካለ ተጠባበቁ፡፡»

«በዚህ ብርድ በባዶ እግራችን ከውጭ ልንቆም» በማለት ትልቅዋ
ልጅ አጉረመረመች::

«ነገ ምን የመሰለ ጫማ ትገዢያለሽ» ሲል አባትዋ መለሰላት፡፡

ማሪየስ ከለመደበት ሥፍራ ወጥቶ መጠባበቅ እንዳለበት ገመተ፡፡

ቀዳዳው ከነበረበት አካባቢ ወጥቶ ቁጭ አለ፡፡ ወደ እነሚስተር ዦንድሬ ክፍል ተመለከተ፡፡

ከክፍሉ ውስጥ ከሰል ተቀጣጠለ እንጂ ሌላ ብርሃን አልነበረም:: ከበሩ አጠገብ ረጅም ገመድና ሁለት ወፍራም የብረት ዱላዎች ተቀምጠዋል፡፡በኋላ ሻማ አያያዙ፡፡

ሚስተር ዦንድሬ ፒፓውን አያይዞ ከወንበር ላይ ቁጭ አለ፡፡ ባለቤቱ ዝግ ባለ ድምፅ ታናግረዋለች:: በድንገት ዦንድሬ ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ::

«በነገራችን ላይ በዚህ ብርድ ሰዎቹ በጋሪ እንጂ በእግራቸው
አይመጡም፡፡ ታዲያ አንቺ ምን ማድረግ ያለብሽ ይመስልሻል? ወዲያው የፈረስ ኮቴ እንደሰማሽ ቶሎ ብለሽ ትወጪና ለሰዎቹ ሰላምታ ሰጥተን በፍጥነት እቤት ይዘሻቸው ትመጫለሽ፡፡ ከዚያም «ቤት ለእንግዳ» በማለት
ካስገባሻቸው በኋላ ቶሎ ብለሽ ወደ ጋሪው በመመለስ ሂሣቡን ከፍለሽ ታሰናብቺዋለሽ:: እሺ?»
«የሚከፈለው ገንዘብ የት አለ?» ስትል ሴትዮዋ ጠየቀችው::
ዠንድሬ ኪሱን ዳበስ ፤ ዳበስ በማድረግ አምስት ፍራንክ ሰጣት::
«ምንድነው እርሱ?» ስትል ጠየቀች፡፡
ዛሬ ጠዋት ጎረቤታችን የሰጠን ገንዘብ ነዋ! አሁን እንግዲህ ቶሎ
ብለሽ ወደ በሩ ሄደሽ ብትጠባበቂ ይሻላል፡፡ የለም፤ አሁኑኑ ቶሎ ሂጂ፡፡»
ትእዛዙን ተቀብላ ቶሎ ወጥታ ሄደች:: ዦንድሬ ብቻውን ቀረ፡፡
የእሳት ማንደጃው፤ ጠረጴዛውና የቤቱ ሁለት ወንበሮች ማሪየስ
ከሚያይበት ቀዳዳ ትይዩ ነበሩ፡፡ አካባቢው በጣም ጭር ስላለ ማንኛውም ድምፅ በቀላሉ ከሩቅ ይሰማል፡፡

ዦንድሬ በአሳብ በመዋጡ ፒፓውን መማግ እንዳለበት ረስቶ እሳቱ ይጠፋል፡፡ እጁን ዘርግቶ የጠረጴዛውን ኪስ ሳበ፡፡ ከኪሱ ውስጥ የነበረውን ጩቤ አነሳ፡፡ ስለት እንዳለው በአውራጣቱ ሞከረው:: በኋላ መልሶ ከጠረጴዛው ኪስ ውስጥ አስቀመጠውና መሳቢያውን መልሶ ዘጋው::

ማሪየስ ደግሞ ከቀኝ ኪሱ ውስጥ የነበረውን ሽጉጥ አውጥቶ ቃታውን ስቦ ያዘው:: ቃታውን ሲስብ ሽጉጡ ድምፅ አሰማ፡፡
ዦንድሬ ደንግጦ ከተቀመጠበት ብድግ አለ፡፡

‹‹ማነህ?» ሲል ጮኸ፡፡

ማሪየስ ትንፋሹን ያዝ አደረገ፡፡ ዦንድሬ ጆሮውን አቅንቶ አዳመጠ፡፡ ከዚያም ብቻውን ይስቅ ጀመር፡፡
«ምን ጅል ነኝ! የኮርኒሱ እንጨት ድምፅ መሆኑን ማወቅ እንዴት
ተሳነኝ!» ሲል ዦንድሬ ራሱን ነቀፈ::

ማሪየስ ሽጉጡን እንደያዘ ቀረ

ልክ አሥራ ሁለት ሰዓት ስለሆነ በአካባቢው የሚገኘው ቤተክርስቲያን ደወል ተደወለ፡፡ ሚስተር ዦንድሬ የሚጠብቃቸው ሰዎች ከመጡ ብሎ የቤቱን በርና መስኮቶች ዘጋጋ፡፡ ይበራ የነበረውን ሻማ እየተመለከተ ከቤት ውስጥ ይንቆራጠጥ ጀመር፡፡ መንቆራጠጥ ሰልችቶት ከወንበር ላይ ቁጭ አለ፡፡ ወንበር ላይ እንደተቀመጠ የቤቱ በር ተከፈቱ:: የመጣችው ባለቤቱ
👍161👏1
«ልግባ» ስትል ጠየቀችው::
«ምን ማለትሽ ነው? ግቢ እንጂ» ሲል መለሰላት::
አባባ ሸበቶ ተከትሉአት ገባ፡፡ አራት ልዋ ከጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ፡፡
ዦንድራ ከጠየቀው ገንዘብ በጣም የላቀ ነበር::
«ይህን ገንዘብ ላልከው የቤት ኪራይና ለአንዳንድ ጉዳይ ይሆናችኋል፡፡
ወደፊትም ለሚሆነው ነገር እንረዳዳለን::»
«የሰማዩ ጌታ ዋጋዎን ይክፈልዎ፧ ባለውለታዎ ነን፡፡ ያልታሰበ
እንጀራ ይስጥዎት» አለ ሚስተር ዦንድሬ ሚስቱን በዓይኑ እየገሰጸ::
ቀደም ሲል የተነጋገሩትን እንድትፈጽም በዓይኑ እየገሰጻት ነበር፡፡
የተነጋገሩት ተገቢውን ሂሣብ ከፍላ ባለጋሪውን እንድትሽኝ ስለነበር ይህንኑ ለማድረግ ከክፍሉ ወጣች:: ብዙ አልቆየችም ቶሎ ተመለሰች::
ወደ ባለቤትዋ ጆሮ ጠጋ ብላ በሹክሹክታ ተሸኝቶአል» አለችው::
ኃይለኛ ዝናብ ይዘንብ ስለነበር ጋሪው ሊሄድ አልተሰማም::
እርስዋ ወጥታ ሳለ ዦንድሬ ለአባባ ሸበቶ ወንበር አቀረበለት ፤
እርሱም ከእንግዳው ትይዩ ተቀመጠ፡፡

በዝናቡ የተነሣ አካባቢው በጣም ጭር ብሎአል፤ ጊዜውም ጨልሞአል። አልፎ አልፎ ኃይለኛ መብረቅ ስለነበር በጣም ያስፈራል:: ሁለቱ ወንዶች
ገጽ ለገጽ እየተያዩ ተቀምጠዋል:: ሴትዮዋ ጥግ ይዛ ቆማለች : ሁለቱ
ሴቶች ልጆች ከውጭ ጥቂት ራቅ ብለው ጥግ ይዘው የሚመጣ ሰው ይጠባበቃሉ:: አባባ ሸበቶ በሥራው በጎ ተግባር ደስ ስላለው ፊቱን ፈካ ሲያደርግ ሚስተር ዦንድሬ ደግሞ ከአንገት በላይ ፈገግታ ተውቧአል፡ ማሪየስ ከመወጣጫ ላይ ወጥቶ በቀዳዳ ወደታች ያያቸዋል:: ሽጉጡን በእጁ
ይዞ ቃል ሳይተነፍስና ድምፅ ሳያሰማ ነው የተቀመጠው::

ተንኮል ቢያስቡ ወዲያው ጣልቃ በመግባት ይህን ደግ ሰው
አድነዋለሁ» የሚል እምነት ስላደረበት ደስ ብሎትና ጣቱን ከሽጉጥ ቃታ ላይ አሳርፎ ነው ያለው፡፡ የፖሊስ ኃይል በአካባቢው አድፍጦ እንደሚጠባበቅ
ያውቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለረጅም ጊዜ ሲያስጨንቀውና አንጀቱን ሲበላው የቆየው የኮዜት ጉዳይ በዚህ አጋጣሚ መልስ እንደሚያገኝ ይተማመናል::

ሚስተር ዦንድሬ አባባ ሸበቶን ሲያዋራ ቀደም ሲል ያላየው አንድ
ሰው ከወደ ጓዳ ውልብ ብሎ ሲያልፍ ማሪየስ ይመለከታል፡፡ ሰውዬው የሚራመደው ድምፅ እንዳያሰማ ፈርቶ በጥንቃቄ ነው:: ይህ ሰው እንደ ሚስተር ዦንድሬ ያረጀና የተቀዳደደ ልብስ ለብሷል:: ለእግሩ መጫሚያ አላደረገም፡፡ ክንዱ ላይ ንቅሳት አለው:: ፊቱን ከሰል ቀብቶ ሸለምጥማጥ
መስሎአል፡፡ ጓዳ ውስጥ ከነበረው በርጩማ መሳይ ነገር ላይ ሲቀመጥ ጨለማ በመሆኑ በግልጽ አይታይም:: ይህ ሰው የነበረው ልክ ከአባባ ሸበቶ
ጀርባ ነው::

አባባ ሸበቶ ጀርባውን ስለከበደው ልክ ማሪየስ ሰውዬውን ሲያይ
እርሱም ዞር ብሉ አየ::
«ማነው እርሱ?» ሲል ጠየቀ::
«እሱማ ጎረቤቴ ነው» ሲል ዦንድሬ መለሰለት::

በዚያ ሰፈር ንጥረ ነገሮችን ሠርተው የሚያወጡ ፋብሪካዎች ስለነበሩና ፋብሪካዎቹ ውስጥ የሚሠሩ ሰዎች ከዚያ ሲወጡ ፊታቸው ጥቀርሻ ለብሶ
መጥቆሩ የተለመደ ነገር ስለነበር የሰውዬው ፊት መጥቆር ኣባባ ሸበቶን አላስደነገጠውም:: ስለዚህ ወደ ጨዋታቸው በመመለስ «ይቅርታ ምን ነበር እያ
ያልከው?» ሲል ዦንድሬን ጠየቀው::

«እለውማ የነበረው ጌታዬ፧ ኣንድ ልሸጠው የምፈልግ ስእል አለ
እያልኩ ነበር የማጫውትዎት» ሲል ፈገግታ በተሞላበት ዓይን እያየ መለሰለት::

በር መከፈቱን የሚገልጽ ድምፅ ከወደ በሩ ተሰማ:: ሁለተኛው ሰው
ከቤቱ ውስጥ ገባ፡፡ ከሚስተር ዣንድሬ ባለቤት አጠገብ ከነበረው አልጋ ጫፍ ላይ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ ይህም ሰው ፊቱን ጥላሸት ቀብቷል፡፡

ሰውዬው በጣም ዝግ ብሎ ድምፅ ሳያሰማ ቢገባም አባባ ሸበቶ
አይቶታል፡፡

«ከቁጥር አያስገቧቸው፤ እንደሌሉ ቆጥረዋቸው፤ እኛ እንጫወት፡፡
ዝም በሏቸው:: ይኸውልዎ ያንን ስእል ለመሽጥ ፈልጌ በማለት በጣቱ እያመለከተ እንግዳውን ለማዘናጋት» ሲል ዦንድሬ ብዙ ለፈለፈ፡፡

ዦንድሬ ብድግ ብሎ ተነስቶ ወደ ግድግዳው ሄደ:: አንድ ስእል
መሳይ ነገር ተሸፍኖ ነበረና ገለጠው:: የበራው ሻማ ብርሃን ደካማ ስለነበር አባባ ሽበቶ ስእሉን በጉልህ ለማየት አልቻለም:: ሰውዬው ምን ለማድረግ
እንደፈለገ ማሪየስ ሊገባው ስላልቻለ ግራ ተጋባ፡፡

«ታዲያ ይኼ ምንድነው?» ሲል አባባ ሸበቶ ጠየቀው:

«አገራችን ውስጥ ዝናው የገነነ ሰአሊ የሳለው ስእል ነዋ! ጌታዬ ልክ እንደ ልጆቼ ነው የማየውና የምወደው:: ብዙ ነገር ያስታውሰኛል፡፡ ሆኖም ችግር ስለጠናብኝ ከቤቴ ላኖረው አልችልም:: እንደነገርኮት ልሸጠው
እፈልጋለሁ» ሲል ዦንድሬ ጮክ እያለ በሀዘኔታ ተናገረ፡፡

በአጋጣሚ ይሁን በጥርጣሬ አባባ ሸበቶ ስእሉን እያየ ወደኋላ ቢመለከት አራት ሰዎች ጓዳ ውስጥ አሉ፡፡ ሦስቱ አልጋ ጫፍ ላይ ተቀምጠዋል፤
አንደኛው ቆሞአል፡፡ አራቱም ፊታቸውን ጥላሸት ቀብተዋል፡፡ አልጋ ጫፍ ላይ ከተቀመጡት መካከል አንደኛው ግድግዳ ተደግፎ ያሸለበው ይመስል
ዐይኑን ጨፍኖአል፡፡ ይህ ሰው በእድሜ ጠና ያለ ነው:: ፀጉሩ ሽብቶ ሳለ ፊቱን ጥላሸት ሲቀባ ጊዜ በጣም ያስፈራል፡፡ የተቀሩት ሁለቱ ልጅ እግሮች ሲሆኑ አንደኛው ጢሙን፣ ሌላው ፀጉሩን አሳድገዋል:: ማንኛቸውም
ቢሆኑ ጫማ አላደረጉም::

የአባባ ሸበቶ ዓይን ከእነዚህ ሰዎች ላይ መተከሉን ዠንድሬ ተገነዘበ፡፡

«ጓደኞቼ ከመሆናቸውም በላይ ጎረቤቴ ናቸው» አለ። «ፊታቸው
የጠቆረው ከሰል ማምረቻ ውስጥ ስለሚሠሩ ነው:: የእነርሱ ከዚህ መገኘት አያስጨንቅዎት:: ስእሉን ቢገዙኝ በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ባይፈልጉት እንኳን ለእኔ ብለው ይግዙኝ:: እኔ ደግሞ እርስዎን ብዙ ገንዘብ አልጠይቅም::
ስንት የሚያወጣ ይመስልዎታል?»

«ነገር ግን» አለ አባባ ሸበቶ የዦንድሬን ዓይን እየጠበቀ፤ «መኝታ ቤት የሚሰቀል ዓይነት ስእል በመሆኑ ሦስት ፍራንክ ቢያወጣ ነው:: »

ዦንድሬ ረጋ ባለመንፈስ መልስ ሰጠ፡፡

«ገንዘብ ከያዙ አንድ ሺህ ክራውን ይበቃኛል::»

አባባ ሸበቶ ራመድ በማለት ጀርባውን ለግድግዳ ሰጠ፡፡ በግራው በኩል ዦንድሬ ቆሞአል:: የዦንድሬ ባለቤትና አራቱ ሰዎች በስተቀኙ ናቸው አሁንም ሰዎቹ ከነበሩበት አልተነቃነቁም:: እንዲያውም ከነአካቴው እርሱን አያዩትም:: ዦንድሬ መለፍለፉን ቀጠለ፡፡ በዚህ ጊዜ አባባ ሸበቶ
ይህ ሰው ችግር ያሳበደው ነው» ሲል አሰበ::

«የእኔ ጌታ፧ ስእሉን ካልገዙኝ» አለ ዦንድሬ፧ ‹‹ሌላ የገቢ ምንጭ
ስለሌለኝና ብዙ ችግር ስለገጠመኝ ወንዝ ውስጥ ገብቼ ራሴን አጠፋለሁ::»
ዦንድሬ ይህን የተናገረው አባባ ሸበቶን እያየ አልነበረም፡፡ የአባባ
ሸበቶ ዓይን ግን ከዦንድሬ ላይ ነው፡፡ ማሪየስ ከበላያቸው ሆኖ ተራ በተራ ዓይኑን ከሰዎቹ ላይ አሳረፈ፡፡ «ይህ ሰው አሁን በእውነት ሞኝ፤ ቂላቂል
ሰው ነው?» ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡ ዠንድሬ «ራሴን ማጥፋት አለብኝ» ሲል ደጋግሞ ተናገረ::

የዦንድሬ ሰውነት በድንገት ተለዋወጠ፡፡ ፊቱ በደስታ ፈካ፡፡ ወደ
አባባ ሸበቶ ጠጋ ብሎ «አሁን ችግሩና ጥያቄው ይህ አይደለም! ለመሆኑ ታውቀኛለህ?» ሲል ጮኸ፡፡

የክፍሉ በር በድንገት ወለል ብሎ ተከፈተ፡፡ ፊታቸውን በምናምን
የሽፈኑ ሦስት ሰዎች ዘልለው ገቡ፡፡ አንደኛው ወፍራም የብረት ዱላ
ይዞአል፡፡ ሁለተኛው ትልቅ ቢላዋ፤ ሦስተኛው መጥረቢያና ትላልቅ ቁልፎችን ይዞኣል፡፡

ለካስ ዦንድሬ እነዚህን ሰዎች ነበር የሚጠባበቀው፡፡ ዦንድሬ የብረት
ዱላ ከያዘው ሰው ጋር ንግግር ቀጠለ፡፡
👍20
«ሁሉም ነገር ዝግጁ ነው?» ሲል ዦንድሬን ጠየቀው፡ ፡
«አዎን» ሲል መለሰለት፡፡
«ታዲያ ሞንትፐርናሴ የት አለ?»
«ከልጅህ ጋር ውጭ ቆሞ ያወራል፡፡»
«ከየትኛዋ ጋር?»
«ከትልቅዋ፡፡»
«መንገድ ላይ የቆመ ጋሪ አለ?»
«አዎን፡፡»
«ሰረገላ ተዘጋጅቷል?»
«ተዘጋጅቷል፡፡‟
«ፈረሶቹስ፤ ብርቱዎች ናቸው?»
«በጣም፡፡»
«ሰረገላው እኔ እንዲቆም ካዘዝኩት ሥፍራ ነው የቆመው?»
«አዎን፡፡»
«በጣም ጥሩ» አለ ዦንድሬ::
አባባ ሸበቶ ቀልቡ ተገፈፈ:: ወጥመድ እንደገባች አይጥ ዓይኑ
ተቅበዘበዘ፡፡ የፍርሃት ምልክት ሳይታይበት ከነበረበት በዝግታ መነቃነቅ ጀመረ: ከጥቂት ደቂቃ በፊት ወገቡ የጎበጠ ሽማግሌ ይመስል የነበረው በድንገት ግስላ ሆነ::

ፊታቸውን ጥላሸት ከቀቡ ሰዎች መካከል ሦስቱ የብረት ቆመጥ
ይዘው ከበሩ ላይ ቆሙ፡፡ እንቅልፍ የወሰደው ሽማግሌ ግን አሁንም
አልጋው ላይ ነው፡፡ ግን ዓይኑን ገልጧል፡፡ የዦንድሬ ባለቤት አጠገቡ ተቀምጣለች።

ማሪየስ አሁን ጣልቃ መግባት አለብኝ በማለት እጁን ወደ ጣራ
አነሳ ሽጉጡን ለመተኰስ ተዘጋጀ:

ዦንድሬ የብረት ዱላ ከያዘው ሰውዬ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ አባባ ሸበቶ ዞር አለ፡፡ ፊቱን አኮማትሮ የፌዝ ሳቅ እየሳቀ አናገረው፡

«አላወቅኸኝም?»

አባባ ሸበቶ ፊቱን አተኩሮ እየተመለከተ ‹የለም» ሲል መለሰለት፡፡

በዚህ ጊዜ ዦንድሬ ወደ ጠረጴዛው ጠጋ አለ፡፡ ግንባሩን ወደ አባባ ሸበቶ አስጠግቶ ልክ አውሬ ጠላቱን ነክሶ ለማጥቃት እንደሚያጓራ ሁሉ እሱም አጓራ፡፡

«የእኔ ስም ዦንድሬ አይደለም:፡ ስሜ ቴናድዬ ነው፡፡ እኔ እኮ
ሞንትፌርሜ ላይ ሆቴል የነበረኝ ሰው ነኝ፤ ገባህ? ቴናድዬ! አሁን አወቅኸኝ አይደል?››

በቃላት ሊገለጽ የማይቻል ቁጣ ከአባባ ሸበቶ ፊት ላይ ታየ፡፡
የመርበተበትና የመረበሽ ስሜት ሳያሳይ ቁጣውን ዋጥ አድርጎ ረጋ ብሎ ተናገረ፡፡

«ብዙም አልተለወጥህም፡፡»

ማሪየስ መልሱን አልሰማም በሰማው ነገር ክው ነው ያለው፡
ዦንድሬ ስሜ ቴናድዬ ነው» ብሎ ሲናገር ጉልበቱ ከድቶት የሚወድቅ መሰለው ግድግዳውን ተደገፈ ልቡ በጦር የተወጋ መሰለው ከዋተርሉ ጦር ሜዳ ላይ የአባቱን ሕይወት ማትረፉንና አባቱም ሲሞት ‹‹የዚህን ሰው
ነገር አደራ» ብሎ የተናዘዘው ትዝ አለው:: ሽጉጥ ለመተኰስ ወደ ጣራው አቅንቶት የነበረው ቀኝ እጁ በመዝለፍለፍ ፀሐይ እንደመታው ቅጠል አጎነበሰ

ገባህህ፧ «ቴናድዬ» ሲል ዦንድሬ በድጋሚ ተናገረ: ሽጉጡ ከማሪየስ እጅ ሊወድቅ ምንም ያህል አልቀረው.....

💫ይቀጥላል💫
👍17
Forwarded from Yared😊 buttons

📌 በሀዘን😔
በደስታ😀
💻 በስራ ቦታ
💺 የእረፍት ጊዜ ለይ

የሚደመጡ ዝማሬዎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇
👍7
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#ስድስት


አቲዬ ለመርገጥ የሚያስፈራው የወይዘሮ እጥፍወርቅ ግቢ ውስጥ አንዲት ቆንጆ ሠርቪስ ቤት
ተሰጠቻት፡፡ ያውም ከነሙሉ ዕቃው፡፡

“ማነው ስምሽ እናቱ?” አለቻት አቲዩን ወይዘሮ እጥፍወርቅ፡፡

“አፀደ"

"ውይ የኔ ድንቡሽቡሽ! ስንት ወሩ ነው” አለች እኔን እያያች፡፡

“አሁን የፊታችን ገብሬል መንፈቅ ይሞላዋል" እጇን ወደኔ ዘረጋች። ፈገግ ብዬ እጇን ለቀም፡፡ ሕፃናትን
መለይካው ይመራቸዋል የሚባለው እውነት ሳይሆን አይቀርም። ወይም ሴትዬዋ እጅ ላይ የተገጠገጠው የወርቅ ቀለበትና ጌጣጌጥ መጫወቻ መስሎኝ:: ወይዘሮ እጥፍወርቅ አቲዬን እንዲህ አለቻት፤

“ላንችና ለልጅሽ ሆድ አታስቢ.! እዚህ ተርፎ ለሚደፉ እህል የበላነውን ትበያለሽ፡፡ ብትወጅ እኛ ጋር እየሰራሽ፣ ከፈለግሽም የፈለክሽውን እየሰራሽ እዚሁ ኑሪ ቤትሽ ነው::

ኑሪ ኑረ ኑሪ ኑሪ…ኑሪ…በሕይወት ኑሪ፡፡ ሌሊት ኮሽ ባለ ቁጥር ሳትሰጊ ኑሪ፡፡ ልጅሸን
እንደፈለግሽ የምታጥቢበት፣ የሽንት ጨርቅ የምታጥቢበት ውሀ ሳያሳስብሽ ኑሪ፡፡ ልጅሽ የሚበላው
ነገር ሳይቸግረው ኑሬኑሪ.: እግዚርም ሲናገር ልክ እንዲህ ነበር፡ ያውላችሁ ምድር ኑሩበት፤
ውሀው ያው ምግቡ ያው፣ መኖሪያው ያው ይሄው ወይዘሮ እጥፍወርቅ ግቢ ዘፍጥረት
ራሱን ሲደግም፡፡
“በመጀመሪያ ምድር ባዶ ነበረ፡፡ ባዶው ላይ አንዲት የጨለመባት ሚስኪን ሴት ልጅ አዝላ ቆማ ነበረ፡፡ እግዜር ብርሃን ይሁን አለ፡፡ ቦግ !” ከእግዜር ብርሃን ጋር ሲወዳደር ቀለመወርቅ አብሪ ትል ማለት ነው፡፡ ዘርፌ ሀይሏን የጨረሰች የእጅ ባትሪ፡፡ ወይዘሮ እጥፍወርቅ ጨረቃ የእግዜርን ብርሃን የምታንፀባርቅ፡፡ እግዜር ግን ፀሐይ ከአድማስ እስከ አድማስ በብርሃን የሚያጥለቀልቅ እናም የሚምቅ !

አቲዩ በተሰጣት ምርጫ መሠረት እዛው ቤት ልትሰራ ወሰነች፡፡ በዕርግጥም የተሻለ ምርጫ
ነበረ፡፡ የማንንም ፊት ከማየት በእጅጉ የተሻለ፡፡ ለእኔ በተለይ ግቢው መቦረቂያዬ፣ የወይዘሮ
እጥፍወርቅ ፈገግታ ምቾቴ ሆነልኝ፡፡ በዛ ሰፊ ግቢ ውስጥ ወይዘሮ እጥፍወርቅ፣ ወጣት ተማሪ ልጃቸውና እኛ ብቻ ነበርን የምንኖረው፡፡ የወይዘሮ እጥፍወርቅ አምስት ልጆች ኑሯቸው ቀውጭ ሀገር ነበር፡፡

ወይዘሮ እጥፍወረቅ አስገራሚ ሴት ነበረች፡፡ እንኳን አቲዬ የድሮ እመቤቷ ዘርፌ ራሷ
የማታልመውን ከውጭ ሀገር የመጣ አንድ ሻንጣ ልብስ ለአቲዬ ሰጠቻት፡፡ ለእኔም ቆንጆ
ቆንጆ ልብስ ገዛችልኝ ዘነጥን !! እኔና እቲዬ ቂቅ ብለን ዘነጥን ደግሞ ስናምር!!

አቲዩ ከወይዘሮ እጥፍወርቅ የተሰጣትን ልብስ ለበሳ አበባ መስላ ብቅ ስትል ዘርፌ ዓይኗ ደም ለበሰ፣ ቀለመወርቅ ደም ግፊቱ ከፍ አለ፡፡ ክፉ አሳቢዎች ምን ሀብት ቢተርፋቸው የያዙት ነገር አያስደስታቸውም፡፡ ይልቅ የሚያጠሉት ሰው ጥቃቅን ለውጥ ያንገበግባቸዋል፡፡ ዘርፌና ቀለመወርቅ የምቀኛ ግንባር ፈጥረው ተንገበገቡ፡፡ የግንባሩ ጸሐፊ ሰይጣን!! እናም ሰይጣን ከቀለመወርቅ እና ዘርፌ ኋላ እግዜርም ከአቲዬ ፊት ቆመው ጦርነቱ ተጀመረ !! አሁን በኑሮ ማስፈራራት በክብር መንጠባረር የለም፡፡ ማንም ሆዱ ከሞላ ጀግና ነው፡፡ ማንም ቢመታ የሚወድቅበት፣ ሲቆስል የሚታከምበት ካለው ጀግና ነው፡፡ ማንም የሚያከብረው ሰው ከጎኑ ካለ ለሌሎች ንቀት ሞራሉ እንደደረቅ እንጨት አይሰበርም፡፡ ዋናው ስንቅና ትጥቅ ግን ማንም እግዚያብሄር ከኋላው እንዳለ ካመነ ልበ ሙሉ ነው !!

እቲዬ ይሄን ሁሉ ሆና ነው ወደ ጦርነቱ የገባችው !! እናም ጦርነቱ በታሪክ ወርቃማው ጦርነት በመባል ይታወቃል በእኔ በነፍሴ ዘገባ !! ወደፊት ልጆቼ “ለምን ወርቃማው ጦርነት ተባለ ?” ብለው ሲጠይቁኝ መልሴ አንድ እና አንድ ነው፤ “በቀለመወርቅ እና በእጥፍወርቅ መካከል በተደረገ ሰብዓዊ ጦርነት በእሳት የተፈተኑ ወርቆች ወደ ምቾት አገር ስለተሰደዱ” እላቸዋለሁ፡፡

የባርነት አስከፊ ገፅታ ያለው በባርነት መግዛቱ ላይ ሳይሆን በባርነት የተገዙበት መንገድ ላይ
ነው፡፡ በፍላጎት ለሌሎች ባሪያ መሆን ለራስ ህሊና የጌትነት ማዕረግ ሰለሚያጎናፅፍ፣ ለነፃነት
ትግል ሳይሆን ምስጋና ራስህን እንድታዘጋጅ ነው የሚያደርግህ:: እሰይ! እንኳንም ባሪያ ሆንኩ የሚባልለት ባርነት አለኮ፡፡ ሰዎች በፍቅር ለሀገራቸው ባሪያ ይሆናሉ፡፡ ለፈጣሪያቸው ይገዛሉ፡፡ ለሚወዷቸው ያገለግላሉ፡፡ ግን ደስተኞች ናቸው፡፡ ለምን ? መንገዱ ፍቅር ነዋ !

አቲዬ ዙሪያውን በረዥም የግንብ አጥር ወደተከበበው ግቢ ገብታ ብትከትምም ዕጣፋንታዋን ግን አላመለጠችውም፡፡ ዕጣፋንታ እኮ ጥላ ነው:: በዙሪያህ ያለውን ችግርና መከራ ፍንትው
አድርጎ የሚያሳይ ብርሃን ሲጠፋ፣ አብሮ የጠፋ ይመስለሃል እንጂ፣ ቀን የሚሉት ፀሐይ ወጋገኑን
ሲቀድ ከትላንቱ በላይ ደምቆ ካንተ በላይ ገዝፎ ከፊትህ ይመራሀል ከኋላህም ይከተልሀል፡፡

አትዬም ዕጣ ፋንታዋን ስንዝር አላመለጠችውም፡፡ ከባርነት ወደ ፍቅር ባርነት ተቀይሮ በትልቁ
ነፍስ ዘራችበት፡፡ ሰፊውን ግቢ ከጧት እስከ ማታ አፅድታ ትልቁን ቤት ውብት ትደፋበታለች፤
ግቢ ውስጥ ጠበቃት እንጂ፡፡ሰው አጥቶ፣ ውርማ ውጦት የነበረውን የወይዘሮ እጥፍወርቅ ግቢ
የወይዘሮ እጥፍወርቅን ሆቴልም ቀጥ አድርጋ የያዘችው አቲዬ ራሷ ነበረች፡፡

የሆቴሉን እንጀራ ሙሉ በሙሉ ትጋግራለች፡፡ የአልቤረጎዎቹን አንሶላዎች ታጥባለች፡፡ እንደዛም
ሆኖ በጣም ደስተኛ ነበረች፡፡ ወይዘሮ እጥፍወርቅ ደግ ሴት ነበረችና ምንም በደረግላት ይገባታል፤የአቲዬ ባርነት ጣፋጭ ነበር፡፡ መሀተመ ጋንዲ ወደ ወይዘሮ እጥፍወርቅ ግቢ ጎራ ቢሉ ኖሮ፣ "ነመስቴ…እኛም የታገልነው ለዚህች አይነቷ ባርነት ነበር በርቱ!” ብለው የሚሄዱ ይመስለኛል!

በእርግጥ ወይዘሮ እጥፍወርቅ አቲዬን እንጀራ ጋግሪ አላለቻትም፡፡ ራሷ አቲዬ ለሆቴሉ እንጀራ
ግዥ እየተባለ በቅን የሚወጣውን ብር ስትመለከት፣ “ምጣድ ግዙልኝ ሪሴ እጋግራለሁ" አለች እንጂ፡፡ የሆቴሉን አንሶላ፣ “እጠቢ ያላት ማንም አልነበረም፡፡ አጣቢዋ ስትጨማለቅ ስታያት አቲዬ የኔ የልብ ሰው፣ “ምነው እቴ ሰው የሚታኛበት እይደለም እንዴ” አለችና አጇን ሰቅስቃ
ገባችበት፡፡“አቦ የእጥፍወርቅ ቤርጎ እንሶላው ብትል ፎጣው እንዴት ይጸዳል” እስኪባል፡፡ የወይዘሮ እጥፍወርቅ ልብ አቲን በልጅነት መንበር ላይ ወስዶ አስቀመጣት፤ እኔንም የልጅ ልጅነት !!

ግቢው የእኔ ነበር፡፡ እንዳሻኝ የምሆንበት ግዛቴ፡፡ የሳሎኑ ዕቃ የእኔ ነበር፡፡ ጆሮ ጭው የሚያደርግ ዋጋ የተከሰከሰበት ሶፋ ላይ ሸንቼበታለሁ፣ ወተት ደፍቼበታለሁ፡ አቀርሽቼበታለሁ፡፡ ለዓይን የሚያሳሳውን የቡፌ ዕቃ እንኮታኩቼዋለሁ፡፡ የወደዘሮ አጥፍወርቅን ባለ አልማዝ ፈርጥ የአንገት ሀብል ከእንገቷ ላይ በጣጥሼዋለሁ፡፡ (የዚህ ሀገር ወርቅ አንጥረኛ አይሰራውም ተብሎ ተቀምጦ ቀረ…) የፋናዬን (እህቴ ማለት ናት - የወይዘሮ እጥፍወርቅ ልጅ) ቀይና ውብ ፊት ቦጫጭረዋለሁ፣ ፋኒዬን እንደ ህፃን ልጅ ነበር የማስለቅሳት፡፡
አትዬ ስትነግረኝ ፋናዬ ከትምህርት ቤት ስትመጣ ቦርሳዋን እንዳዘለች እኔ ላይ ትጠመጠምና ድበድብ ነው፡፡ ሱቅ የተሰቀለ አሻንጉሊት ካየች፣ የሕግን ልብስና መጫወቻ ዓይኗ ውስጥ ከገባ፡ ለእኔ ለመግዛት ከእናቷ ጋር ብር ስጭኝ አልሰጥም” ጦርነት ነው::
የእናቴ ንፁህ ልብ እንደስፖንጅ ፍራሽ በሕይወቴ መንገድ ላይ ተነጥፎ የዛች ቅፅበት የነበረ
👍245