#አለሁላት…!
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
እናቴ ሁልጊዜ ሁለት እጆቿን ወደ ሰማይ ዘርግታ እግዜርን እንዲህ ትለዋለች፣
“አብርሽዬ የሚያገባትን ሴት ሳታሳየኝ እንዳትገለኝ፡፡
አገባሁ !
እናቴ እለት እጆቿን ወደ ሰማይ ዘርግታ እግዜርን እንዲህ አለችው፣
“ምነው ይሄንንስ ከሚያሳየኝ በገደለኝ
ሀና ምንተስኖት ትባላለች የምኮራባት ሚስቴ፡፡ እወዳታለሁ፣ አፈቅራታለሁ፡፡ ክፉ ነገር በሰፈሯ
እንዲያልፍ አልፈልግም፡፡ ሀኒዬ የእኔ ጥሩ ሱስ፣ ካላየኋት ያዛጋኛል' ስል ሰዎች አያምኑኝም፤ ሀኒ
የእኔ ልብ፣ የጠላችው ጠላቴ ነው:: ይሄ አባማ የሚባል ሰውዬ በቴሌቪዥን ያደረገው ንግግር
አስጠላኝ ብትለኝ፣ ሲ አይ ኤን ሳልፈራ፣ ኤፍ.ቢ.አይን ከቁብም ሳልቆጥረው ኦሳማ ላይ የግድያ
ሙከራ ባደርግ ደስታዬ ነው:: እንቅ አድርጌ አይኑን አፍጥጦ፣ “ኧረ አብርሽ በእናትህ የዛሬን
ማረኝ..ሁለተኛ በየትኛውም ሚዲያ ከመቅረቤ በፊት ንግግሬን ለሀና ምንተስኖት ኣሳውቃታለሁ..
ካልፈቀደችልኝ ኣላደርጎውም” ቢለኝ አልምረውም፡፡ እማምላክን አልምረውም !!
ሀናዬ የነብሴ ፍራሽ…ላያት ድሎቴ ናት። ሀና ካዘዘችኝ…አቤት ፍጥነቴ ገና ልትናገር ስትጀምር እኔ ሮጫለሁ፡፡ አልጋ ላይ ጋደም ብላ ቴሌቪዥን እያየች እኔ ቆንጆ ቡና እያፈላሁላት…የሆነ ነገር ብትፈልግል ልትናገር ስትጀምረው ነገሩን አምጥቼዋለሁ ፡፡ ለምን ትጨርሰዋለች.…ቃሏ ፍቅር
ነው..ፊደሎቾ እንደ ረሀብ ቀን እህል ያሳሱኛል፡፡
“አብርሽ " ስትለኝ በቦታህ!' እንዳሉት ሯጭ እዘጋጃለሁ፡፡ ወደ መሻቷ ተፈትልኮ በምድር
ላይ ያሉ ወንዶች ሁሉ የሚሰቶቻቸውን ፍላጎት ካሟሉበት ሰዓት የተሻለውን ለማስመዝገብ፡፡
"ድ." ብላ ስትጀምር ፈትለክ ብዬ ድስት…ድራፍት…ድንች ድልህ...ድፍድፍ (ከእማማ ፈጠኑ ቤት ድመት...ድንጋይ..ድራማ (ሲዲ) ይዤላት እያለከለኩ ከተፍ ስል፣ "ውይ አብርሽዬ…በቲቪ ድብ አይቼ ድቡን እየው ልልህ ነበር እኮ" ትለኛለች በፍቅር ዐይን እያየችኝ...!! አይከፋኝም ለምን እከፋለሁ፡፡ እንደገና ድብ ባየችና “ድ ብላ ስትጀምር፣ አሁን ባመጣኋቸው ነገሮች ላይ
ድብ ጨምሬ ባመጣሁላት..የእኔ ሀኒ መክሊት ብያታለሁ፡፡ እሷ ናት ቀኝም ግራም ጎኔ፡፡
ሀኒዬን እናቴ አትወዳትም፡፡ “አንዳች አስነክታው ነው ልጄን እቺ የሰው ጉድ” ትላታለች፡፡
አባቴ ገና ሲያያት የእናቱ፣ የአባቱ፣ የሁለት እህቶቹ ገዳይ ነው የምትመስለው አቤት ሲጠላት፡፡ በወሬ ወሬ “መንገድ ላይ አብረሃም እና... ሲሉት፣ "በቃ " ብሎ ይጮሀል።አብርሃም ካላችሁ አይበቃም….እናን ምን አመጣው?” ይላል፡፡ ያውቃል ማንም ጋር እንደማልታይ፤
ሀኒ ጋር ነኝ ቤት ውስጥ የምትበላውን እየሰራሁላት፡፡ ሀኒ ጋር ነኝ መንገድ ላይ ቦርሳዋን ይዤላት፤….ዣንጥላዋን ይዤላት ዕቃ ከገዛን አስቤዛም ቢሆን እኔ ይዣላት ሀኒ ጋር ነኝ የትም!!
ሀኒን እህቴ አትወዳትም፡፡ ከዘመናዊ ጓደኞቿ ጋር ሆና ከሩቅ ካየችኝ በሬ እንዳሯሯጠው ሰው መንገድ አሳብራ የጓደኞቿን እጅ እየጎተተች ትሸሻለች፡፡ “ወንድሜ በሬ አገባ” እያለች ነው የምታወራው አሉ!
ወንድሜ ሀናን አይወዳትም፡፡
"ለስንት ስንጠብቅህ እዚሂች አዚፋ ጋር ትወዘፋለህ” ይለኛል፡
&አዚፋ' ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ግዴለም ሀኒዬ 'አዚፋ ከሆነች፣ አዚፉ ይባረክ ! ስድብ ሰውን ካረከሰው፡ ሰው ስድቡን ስለምን አያከብረውም? ሀኒዬ አዚፉን አከበረች… እወዳታለሁ፡፡
ሀኒ ቆንጆ አይደለችም፡፡ የኔ ቆንጆ፣ ቆንጆ አይደለችም፡፡ "ኪንኪ ፀጉሯ ጠዋት ስትነሳ ያስፈራል”
ይላሉ፣ አዎ እውነት ነው፡፡ “አፍንጫዋ በአይኗና ቀላይኛው ከንፈሯ መካከል ያለ ሁለት የሽንቁር ነጥብ ነው እያሉ ያሟታል…እውነት ነው !!
ከንፈሯ ወጣ ወጣ ባሉ ጥርሶቿ (ገጣጣ ነው እነሱ የሚሉት) ከርስቱ ተገፍቷል፡፡ በዛ ላይ
ብትስቅ ዞሮ ማጅራቷ ላይ ይዘያየራል ይላሉ፡፡ አዎ እውነት ነው !!
የጣቶቿ መዶልዶም ከዘጠኝ ዓመቷ እስከ አስራ ዘጠኝ ዓመቷ 10000000000000000000
ኩንታል ገብስ ሳታቋርጥ የወቀጠች ያስመስላታል" ቢሉም (ተጋነነ እንጂ) እውነት ነው !!
“እግሯ ከየትኛውም ጫማ እንዲጣላ ተደርጎ ነው የተፈጠረው” ያሉትም አልዋሹም፡፡
lዚህ ሁሉ መናቅ፣ በዚህ ሁሉ መገፋት ተገፍታ እኔ የምባል ጥግ ላይ ደረሰች የሀኒ ዓለም
መጨረሻ፡፡የት ትሂድላቸው? አለሁላት ወንድሟ ነኝ:: ፍቅረኛዋ ነኝ፡፡ባሏም ነኝ!! አላፍርባትም፡፡
ኮራባታለሁ !! ሀኒዬ የኔ ናት:: ማነው እኔን አልፎ የሚዘልፉት ወንድ ?' የኤሌክትሪክ አጥሯ
ጠባቂ ውሻዋ ነኝ፡፡ ከእግሯ ስር የማልጠፋ::ባለቤቱ ያላከበረው አሞሌ፡ ወላ መልኩ ወላ
ዘመናዊነቱ አያስከብረውም፡፡ አንዱ የወረወራቸው አይደሉ ሌላኛው መኪና ላይ የሚኮፈሱት!
የተናቁ አሞሌዎች !! ሀኒዬን አከብራታለሁ !! እግዜር ያውቃል ልቤን !!
“ጥርስሽ አያምርም ቢሏት ከሳቅ ተጣላችላቸው፡፡ ሰው ፊት አትስቅም ሀኒ፡፡ የመጻፍ መብታችን፣የመሰለፍ መብታችን ተነካ የሚሉ የአገሬ ልጆች፣ የህኒዩን የመሳቅ መብት በአደባባይ ነጠነቁ፡፡እስካሁን ሻይ ቡና ለማላት ካፍቴሪያ መግባት ያስፈራታል፡፡ ራሷ ቤት ውስጥ ስትቀመጥ እንኳን እግሮቿን ሶፋ ስር ልትደብቅ ይከጅላታል፡፡ በመንገድ ዳር ዘለፋ መሳቀቅን ሸልመዋታል፡፡ ሰው ለሰላምታ ስትጨብጥ ትሳቀቃለች፡፡ የመዳፏን ሻካራነት በየጭብጡ የሚጮኸ አዋጅ አድርገው
ልቧ ውስጥ ተክለውባት፡፡
ሆኒዩን ቆንጆ ካልሆንሽ ሰው ከመሆን መንበር ተንኮታኩተሻል” ብለዋታልና ቆንጆዎች አምላክ
ይመስሏታል፡፡ የሴት ልጅ የክብር ጥጉ በየሆቴሉ ወንበር ተጎትቶላት መቀመጧ ነውን ? በአደባባይ
መታቀፍስ የፍቅር ኦሜጋ ሆኖ የታወጀው መቼ ነው ? እየተውረገረጉ የወንድ ጭብጨባ
ያደነቆራቸው ሀኒዬን ቃል ሳያወጡ በድርጊት ቀበሯት፡፡
አነሆ ለአንዲት ደሀ.ለአንዲት መልከ ጥፉ ደሀ ተልኬ የምታስተናግድበት ተራ ሻይ ቤት ተከሰትኩ፡ ያውም 'አዩኝ' ብሎ የሚቆሽሽ ነጭ ሸሚዝ ባማረ ጂንስ ሱሪ ለብሼ፣ ጥቁር መነፅሬን ሰክቼ እየተቆነንኩ በረንዳው ላይ ካሉት ወንበሮች በአንዱ ላይ ሰፈርኩ፡፡
“ምን ልታዘዝ!” አለች ሀኒዬ እየተሸቆጠቆጠች፡፡ ሳያት ላማትብ ቃጥቶኝ ነበር፡፡ እግዜር ሰውን
የት ድረስ ውብ እንደሚያደርግ አውቃለሁ፡፡ የት ድረስ መልከ ጥፉ አድርጎ እንደሚፈጥር እነሆ
የእጁን ውጤት ፊቴ አቁሞ አሳየኝ፡፡ “አቤት ችሎታው ምን ይሳነዋል!” አልኩ ::
ስራዬ በዛው ግድም ነበርና ደጋግሜ ሳያት ከቀን ወደቀን እየባሰ የሚሄድ ይሄ ጎደለው የማይባል ፍፁም የሆነ አስቀያሚነት እንዳሸከማት እየተገረምኩ ታዘብኩ፡፡ ግና የገረመኝ፣ “አቤት ስታስጠላ
እያልኩ ላያት መፈለጌ ደንበኛ ሆንኩ፡፡
“ምን ልታዘዝ?"
"ቡና"
"ምን ላምጣልህ?"
“ቡና”
“ሰላም! ምን ላምጣልህ?”
“ቡና”
“ቡና ነው ዛሬም” (ፈገግ ለማለት እየሞከረች)
"አዎ" (በፈገግታ)
ከዛ ሳላዛት ቡና አመጣችልኝ…ቡና..ቡና….ቡና.…ሰላምታ ሀና ነው ስሟ፣ አንድ ቀን ጠየቅኳት…
ነገረችኝ፡፡ ስራ ከሌላት አጠገቤ ትመጣለች እናወራለን…እንዴት ደስ እንደምትል፡፡ ትልልቅ ጡቶቿን አልፎ ልቧ ይታያል ንጹህ ነው !
አንድ ቀን ከጎኔ የተቀመጡ ተስተናጋጆች "የሰው ጅብ” ሲሏት ጆሮዬ ጥልቅ አለ ያዘዝነው ዘገየብን ብለው !! በመሰደቧ ሳይሆን እኔ ፊት በመሰደቧ
በመሰደቧ የቅስሟ መስተዋት
ክፍት አፍ በወረወረው የዘለፉ ጠጠር ሲንኮታኮት ፊቷ ላይ እንዴት አንጀት የሚበላ መሳቀቅ አየሁ፡፡ ተሳዳቢዎቹ ጋር
የነበረች አንዲት ሴትም ላንቃዋ እስኪላቀቅ ሳቀች፡፡ አዘንኩ፡፡ ለምን አዘንኩ እኔንጃ !!

👍30😁4