#ዝግመተ_ለውጥ
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
ረዥም ነገር አልወድም፡፡ ረዥም ቁመት እንደ ሰብለ፤ ረዥም መንገድ በእኔና በእነሰብለ ቤት
መካከል እንዳለው፣ ረዥም ወሬ ስብለ እኔን አሰቀምጣ ስልክ እንደምታወራው፣ ረዥም ዕድሜ
እንደሰብለ አያት እና ረዥም ቀን እንደዛሬው. ዛሬ እሁድ ነው !
እሁድ ከመርዘሙ የተነሳ የሚመሸው ከነገ ወዲያ ይመስለኛል። እሁድ ለእኔ መጀመሪያና መጨረሻ ያለው ዘላለም ነው፡፡ “ለምን?” እንዳትሉኝ፣ ታሪኩ ረዥም ነው፡፡ ረዥም ታሪክ አልወድም፣ እንደ እኔና እንደሰብለ የፍቅር ታሪክ፡፡
ሰብለ ፍቅረኛዬ ነበረች፡፡ ሰብለ የሚለው ስም በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ይመስለኛል፡፡ ሰላቢ
ሰለበ..ሰብሱ አያለ የተሻሻለ ዓይነት፡፡ እሁድም ከ24 ሰዓት ተነስቶ ዘላለም የሆነ....
ዛሬ እሁድ ነው፣ ይሄ ጋግርታም ሕፃን እሁድ፣ አርጅቶ መካነ ሰኞ ውስጥ እሰኪከተት ምናባቴ
እየሰራሁ..የት አባቴ ሄጄ ላሳልፈው ይሆን?' እያልኩ አስባለሁ፡፡ አንድ ሀሳብ መጣልኝ፡፡ ቤቴ በር ላይ ተቀምጬ ፀሐይ እየሞቅኩ የሆነ ነገር ማንበብ ..በቃ!!
ኩርሲ ነገር አወጣሁና ተመልሼ ከጠረጴዛዬ ላይ የሚነበብ ነገር ልፈልግ አንድ ጋዜጣ አገኘሁ
መልሼ አስቀመጥኩት ረዥም ጋዜጣ ነው ! የሰብለ አባት ይሄን ጋዜጣ ይወዱት ነበር ነብሳቸው
ይማረውና እሳቸው የሞቱ ቀን የቀብር ሥነ ሥርዓቱ አረዛዘም መቼም አይረሳኝ…፡፡ ከሰው
የተለየ ኃጢያት የተበተባቸው ይመሰል ፍትሀቱ ረዥም ነበር፡፡ ለነገሩ አራጣ አበዳሪ ነበሩ::
ሀሳቤን ቀየርኩና ጋዜጣውን ይዤ መጣሁ፤ ፀሐዩ ሲጠነከር አናቴ ላይ ጣል አደርገዋለሁ።
በር ላይ ቁጭ ብዬ አላፊ አግዳሚውን መመልከት ጀመርኩ፡፡ እማማ ትሁኔ የሽሮ እህል ያሰጣጣሉ፥ የሚገርሙ ሴትዮ ሁልጊዜ የሚያሰጡት ነገር አያጡም፡፡ የሚሰጣ ነገር ቢጠፋ
የማስጫውን ሰማያዊ ፕላስቲክ ብቻውን ያሰጡታል፡፡ ታዲያ ያሰጡትን ቢያሰጡ፤ ስጡ ላይ
አንድ ሁለት ከሰል ጣል ማድረጋቸው አይቀርም፡፡ አንድ ቀን ጠየቅኳቸው፡፡
"እማማ ትሁኔ!"
“ወዬ አብርሽ"
"ይሄ ከሰሉ ምንድን ነው?"
"የቱ ?"
“ይሄ ስጡ ላይ ያለው"
"አረ.ይሄን እስከዛሬ አታውቅም? ሆሆ…” ካሉ በኋላ ባለማወቄ ተገርመው አጭር ማብራሪያ
ሰጡኝ::
“ይሄ እንግዲህ..ስጥ ስታሰጣ አንድ ሁለት ከሰል ጣል ካደረግክስት ሰላቢ አጠገቡ አይደርስም፤ መዳኒት ነው” አሉ ወደ አልማዝ ቤት እያዩ ፀበኛ ናቸው፡፡
“ሰላቢ ምንድን ነው ?"
“የሚሰልብ ነዋ…እንተ ይንበርስቲ በጥስህ ሰላቢ ይጠፋሃል...ሰላቢ ባይኑ የሚሰልብ ነው ያየውን
ነገር ሁሉ ላየ የሚያደርግ፡፡ እህል አይል፣ ዘይት አይል፣ ሊጥ አይል.የተጋገረ እንጀራ አይል በቃ አየት ሲያደርጉት ሽው ነውር …ወደቤቱ ያጋባታል ..." አሉ አልማዝ እንድትሰማ ጮክ ብለው፡፡
ከሰል ከሰላቢ ሲያድን እኔ ኩንታል ከሰል ተሸክሜ ስብለን ስከተላት በዋልኩ ነበር፡፡ አንድ ሰላቢ ባለጋራጅ ነው የሰለበኝ፡፡ ለነገሩ ሰብለ ኣንኳን ከሰል ጣል ማድረግ፣ ከሰል ጉድጓድ ውስጥ ቢያስሯትም መስለቧ አይቀርም፡፡ ሲፈጥራት ሰላቢ ነገር ነበረች፡፡ ከፍቅር የበለጠ ምን ከሰል አለ? ሲያቀጣጥሉት የሚንቀለቀል እሳት፡፡ የከህደት አመድ ሲያለብሱት፣ የተዳፈነ ረመጥ፤
ሲያጠፉት ጥቁር ታሪክ ! ከፍቅር የባሰ ምን ከሰል አለ
አንድ ባለጋራጅ ነው ከእጄ ነጥቆ ሰብለን የወሰዳት፡፡ ምን ይወስዳታል፣ ሄደች እንጂ። አንዳንዴ ከሥራ ስወጣ፣ በምታምር ቀይ መኪና ሲሸኛት እንገጣጠማለን፡፡ ጋቢና ተቀምጣ በኩራት ታየኛለች፣ አየህ ያለሁበትን ዓይነት መኮፈስ፡፡ ሰው ከሰው ልብ ላይ ወርዶ፣ ቆርቆሮ ውስጥ ስለተቀመጠ ይሄን ያህል መኮፈስ ነበረበት?
በሬ ፥ላይ ተቀምጬ አላፊ አግዳሚውን መመልከቴን ቀጠልኩ:: ኤጭጭ…መምሬ
ታምሩ ሳር ቅጠሉን ሰላም እያሉና እያሳለሙ መጠብኝ!! ምክራቸው ረዥም ስለሆነ ሳያቸው ገና ይደክመኛል፡፡ እንግዲህ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም” ሊሉኝ ነው፤ ታዲያ ለእሳቸው ስል ከማን አባቴ ጋር ልሁን? የእናቴ ንሰሀ አባት ነበሩ፣
እሳቸው ግን ራሳቸውን የእኔም ንሰሀ አባት እድርገው ቁጭ አሉ፣ ንስሀ አያቴ፡፡
እጠገቤ ሲደርሱ፣ “አብረሃም እንደምን አደርክ?
"ደህና እደሩ አባ”
“አይ የአንተ ነገር፡፡ ሰው ሲያነብ መነጥሩን ነው የሚወለውለው:: አንተ ሁልጊዜም ስታነብ
ጥርስህን ትፍቓለህ፣ በጥርስህ ታነብ ይመስል አሉኝ፤ አሁን ይሄ ከንሰሃ አባት የሚጠበቅ ንግግር
ነው ? በዕርግጥ የወይራ መፋቂያ በእጄ ይዤ ነበር፡፡ በከብሮት ቆምኩና ሁለት እጆቼን እንስራ
እንደተሸከመች ሴት ከኋላዬ አነባብሬ ግንባሬን ወደ እሳቸው እሰገግኩ፡፡
ወደ ሰማይ ዓይናቸውን ተክለው ጋቢና ካርታቸውን በቀኝ እጃቸውእየሰረሰሩ ከኮታቸው የውስጥ ኪስ መስቀላቸውን ሊያወጡ ሲታገሉ በትዕግስት ጠበቅኳቸው፡፡ ሁልጊዜም እንዲህ ሲያደርጉ መስቀላቸው ከውስጥ ኪሳቸው ሳይሆን ከልባቸው ውስጥ የሚያወጡ ነው የሚመስለኝ፡፡ አሳለሙኝ፡፡ እዚህ
ሁሉ ልብስ ውስጥ ተቀምጣ መስቀላቸው ግንባሬን ስትነካኝ ለምን እንደምትቀዘቅዘኝ ይገርመኛል !
“አብረሃም!" አሉኝ ድምፃቸውን አለስልሰው፡፡ እንግዲህ ሊጀምሩ ነው)
“አቤት አባ"
“እንደው ቢመክሩህ አልሰማ አልክ.…ኧረ ተው..ተው አብረሃም ተው:: እኔ ወድጄ አይደለም
የምነዘንዝህ የናትህ አደራ ከብዶኝ ነው፡፡ ምናለ አንዷ ን ጥሩ ከርስቲያን አግብተህ ብታርፍ፡፡ ለነገሩ የት ታገኛታለህ፤ ቤተስኪያን መምጣቱንም ትተኸዋል...!! እስቲ ምን ጎደለህ? የጠገበ ደመወዝ
ትበላለህ፣ ምን የመሰለ ሰፊ አልጋ አለህ…” አሉ በአገጫቸው ወደ ቤቴ ውስጥ እያመለከቱ፡፡
እንዴ አባ..አልጋና ትዳር ምን ያገናኘዋል፡ ያላገባሁት አልጋ ይጠበኛል ብዬ መሰላቸው እንዴ
ወይስ በትዳር ወጥመድ ውስጥ እንድገባ አልጋዬ ላይ ቁራጭ ስጋ እየጣሉልኝ ነው::
“ሁልጊዜ ልጅነት የለም...እየው… አሱና ምስጢር እንደሚያወራ ሰው ጠጋ አሉኝና ጋቢያቸውን
ወደ ላይ ወደ ትካሻቸው አሰተካከሉ፡፡ ከዛም ድምፃቸውን ቀነስ አድርገኑ፣ ..እንደውም አንዲት ትሁት እግዜር የባረካት ልጅ አቃለሁ፣ ከዚህ.…ማነው..ይሄ ሴቶቹ ከሚሄዱበት አገር “ማነው…” አረብ አገር" አልኩ ቶሎ እንዲላቀቁኝ፡፡ አረብ አገር የሚሄዱት ሴቶች ብቻ ናቸው የተባለ ይመስል
“እእእ ተባረክ አረብ አገር….እና እዛ ሄዳ ትንሽ አመም አድርጓት ነው የመጣችው .ጨዋ ድምፅ
ሲወጣት የማትሰማ፣ ከቤቷ ቤተስኪያን ከቤተስኪያን እቤቷ ነው እርግት ያለች የጨዋ ልጅ
ላንተ የምትሆን ናት ግዴለህም እያት ! ሳምንት እኔው ራሴ አስተዋወቅሃለሁ፡፡ አንተማ ዞሮብሃል እንኳን የትዳር አጋር ልትፈልግ ራስህም ጠፍቶሃል.ምን ታረግ ቤትህ ጠበል አይረጭበት፡
ዳዊት እንኳን አትደግም” ልቃወም አፌን ከፍቼ ተውኩት፡፡
አይደለማ አይደለም…” ብለው እንደገና ሴላ ረዥም ምክር እንዳይጀምሩ ፈርቼ ዝም አልኩ፡፡
ብቻቸውን በግዕዝ እያነበነቡ ወደታች ወረዱ፡፡
እንዲሁ ስለመምሬ እና ለትዳር ስላሰቡልኝ ልጅ እያሰብኩ የያዝኩትን ጋዜጣ መቃኘት ጀመርኩ፡፡.....
✨ነገ ያልቃል✨

👍37❤6🔥1
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
...የሦስቱ፡ ልጆች ዕድሜ ቢደመር ሃያ አራት ዓመት አይሞላም:: እነዚህ ልጆች የኅብረተሰቡን ገጽታ የሚጠቁሙ ሲሆኑ በአንድ በኩል ቅናትን በሌላ በኩል ደግሞ ሐሜትንና ንቀትን ያመለክትል
ገባ ወጣ እያለች ከወዲያ ወዲህ ትል የነበረችው ሚስስ ቴናድዬ
ድንገት ዞር ስትል ኮዜት ከሥራዋ ተዘግናታ በሁለቱ ልጆች ጨዋታ
መማረክዋን ተገነዘበች፡፡
«አይሻለሁ ፤ አንቺ እርጉም»ስትል ጮኸችባት፡፡ «ሥራ እንዲህ ነው
የሚሠራው! ያቺ የምታውቂያትን ሰበቅ ካልቀመስሽ ልብሽ ሥራሽ ላይ ላይውል ነው!»
እንግዳው ከተቀመጠበት ሳይነሳ ወደ ሚስስ ቴናድዬ ፊቱን አዞረ::
«እሜቴ» አለ ፈገግ ብሎ፤ «ይፍቀዱላትና ከልጆቹ ጋር ትጫወት::
ብዙ መጠጥ በመጠጣትና ምግብ በመብላት ብዙ ወጪ በማውጣት ብዙ ገቢ ያስገኘ ደምበኛ ቢሆን ታከብረው ነበር፡፡ ይህ የእራት መብያ እንኳን
የሚሆን ገንዘብ የሌለውና የተጎሳቆለው መንገደኛ ኣሳብ መስጠቱ አስቆጣት፡፡
«ስለምትበላ መሥራት አለባት፡፡
ሥራ እንድትሠራ እንጂ ቁጭ ብላ እንድትጦር አይደለም የምንረዳት፡፡»
«ምንድነው አሁን የምትሠራው? በማለት በጣም በረጋና በለሰለሰ
አንደበት ሲጠይቅ ጠቅላላ ሁኔታው ከለበሰው ልብስ ጋር አልሄድ አላት፡፡
«የእግር ሹራብ ነው:: ልጆቼ የእግር ሹራብ አልቆባቸዋል፡፡ በባዶ እግራቸው ከመሄዳቸው በፊት ትሥራላቸው ብዬ ነው፡፡»
ሰውዬው የኮዜትን ባዶ እግር ተመለከተ፡፡
«የጀመረችውን ሹራብ ለመጨረስ ስንት ቀን ይወስድባታል?»
«ምን የተረገመች ፤ ቶሎ ቶሎ- አትሠራ ሦስት ወይም አራት ቀን )
ይወስድባታል፡፡»
«ስትጨርሰው በገንዘብ ቢተመን ምን ያህል ያወጣል?»
ሚስስ ቴናድዬ በንቀት ዓይን አየችው::
«ቢያንስ ሰላሳ ሱስ፡፡»
«በአምስት ፍራንክ ይሸጡታል?» ሲል ጠየቀ፡፡
«በአምስት ፍራንክ! ይሸጡታል ?" ሲል ጠየቀ
«እንዴ!» አለ እየሳቀ ወሬያቸውን ያዳምጥ የነበረ ሌላ እንግዳ፡፡
ይህቺ ጉራ ናት:: ደግሞ አምስት ጥይት!»
ሚስተር ቴናድዬ «አሁን ነው መልስ መስጠት» ሲል አሰበ፡፡
አዎን፡ ከፈለጉ አምስት ፍራንክ ከፍለው ሽራቡን ሊወስዱ ይችላሉ::እንግዳችንን ማስቀየም እንፈልግም'::
"ታዲያ ገንዘቡን አሁኑኑ እጅ በእጅ ነው» አለች ሚስስ ቲናድዩ::
"የእግር ሹራቡን ገዝቼዋለሁ” አለ ሰውዬው:: ወዲያው ከኪሱ
አምስት ፍራንክ፡ አወጥቶ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ::
ከዚያም ወደ ኮዜት ዞር ብሎ ..ጉልበትሽን ስለገዛሁ አሁን መጫወት ትችያለሽ አላት።
ሌላው እንግዳ ጆሮሮውን ስላላመነ ተነስቶ ከጠረጴዛው ላይ የተቀመጠውን አምስት ፍራንክ ሄዶ ተመለከተ::
እውነት ነው፣ ቃል የገባበትን ገንዘብ ሳያጓድል ነው የከፈለው»
ሲል ጮኸ፡፡ «የከፈለው ደግሞ የውሸት ሳይሆን እውነተኛ ገንዘብ ነው::»
ሚስተር ቴናድዬ ገንዘቡን አንስቶ ከኪሱ አደረገ፡፡ ሚስስ ቴናድዬ
በቁጭት ከንፈርዋን ከመንከስና ፊትዋን በጥላቻ ከማኮሳተር ሌላ ምንም መናገር ስላልቻለች ዝም ብላ ቁጭ አለች::
ኮዜት በፍርሃት ተንቀጠቀጠች፡፡ ስትፈራ ስትቸር «እሜቴ፣ እውነት
ነው? መጫወት እችላለሁ?» ስትል ጠየቀች፡፡
«ተጫወች!» አለች እጅግ በሚያስፈራና በብሽቀት አነጋገር፡፡
«እሺ እመቤቴ» አለች ኮዜት መንገደኛውን ከልብ እያመሰገነች::
ሚስተር ቴናድዬ ወደ መጠጡ ተመለሰ፡፡ ሚስቱ ወደ ጆርው ተወግታ የሆነ ነገር ኣለችው::
«ይሄ ሰውዬ ምንድነው?»
«በሚሊዮን የሚቆጠር ሀብት እያላቸወ እንደዚህ ሰውዬ ጎስቆል
ብለው መታየትን የሚመርጡ ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ» ሲል በጎረነነ ድምፅ መለሰላት::
ኮዜት የሹራብ ሥራዋን ታቁም እንጂ ከነበረችበት አልተንቀሳቀሰችም።ብዙ ጊዜ ከአንድ ቦታ ቁጭ ካለች እጅግ አትቅለበለብም:: ኩርምት ብላ
ሳትንቀሳቀስ ነው የምትቀመጠው:: አጠገብዋ ከነበረው ትንሽ ሳጥን ውስጥ
ቁርጥራጭ ጨርቆችና ኣንድ ከቆርቆር የተሰራ አነስተኛ ቢላዋ አወጣች::
ኢፓኒንና አዜልማ የሚሆነውን ሁሉ አላጤኑም:: ኣሻንጉሊቶቻቸውን እየወረወሩ ከድመት ጋር ይጫወታሉ:: ኢፓኒን ታላቅ ስትሆን የእጅ ጓንት
ለማስገባት ትታገላለች፡፡
ጠጪዎች የስካር መንፈስ ይዟቸው ያንጎራጉራሉ::: አንዱ
ሲያንጎራጉር ሌላው እስከ ጣራ ስለሚስቅ ቤቱ ታውኳል፡፡ ሚስተር ቱናድዬ አብሮ ያስካካል፡፡
ወፎች ከሚረባውና ከማይረባው ጎጆአቸውን እንደሚቀልሱ ሁሉ
ልጆችም በአገኙት ነገር መጫወቻ ይሠራሉ፡፡ ኢፓኒንንና አዜልማ ድመቲቱን ልብስ ለማልበስ ሲጥሩ ኮዜት ከእጅዋ የገባውን ቡትቶ ጨርቅ ከቆርቆሮ የተሠራውን ቢላዋ ለማልበስ ትታገላለች፡፡
ጨርቅ ካለበሰችው በኋላ ጭንዋ
ላይ አስቀምጣ እንዲተኛ እሽሩሩ በማለት አባበላች::
ሚስስ ቴናድዬ ወደ መንገደኛው ጠጋ አለች::
«የኢፓኒን አባት ልክ ነው:: ምናልባት ይህ ሰው መሴይ ላፈት
ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ሀብታሞች እጅግ በጣም እንግዳ የሆነ ነገር ይፈጽማሉ» ስትል አሰበች፡፡
ሰውዬው ተቀምጦበት ከነበረው ወንበር አጠገብ ከተቀመጠው ጠረጴዛ ላይ ክርንዋን አስደገፈች፡፡
«ጌታዬ…» አለች፡፡
ጌታዬ ብላ ስትጠራው ተገርሞ ወደ እርስዋ ዞር አለ፡፡ ቀደም ሲል
ደጋግማ «ጎበዝ» እያለች ነበር የጠራችው::
«ልጅትዋ እንድትጫወት ስፈቅድላት አዩ ጌታዬ!» አለች ፊትዋን በፈገግታ አስውባ፡፡ ፈገግታዋ ይበልጥ እንዲጠላት አደረገው እንጂ ወደ እርሱ አላስቀረባትም:: ደግ ሰው ስለሆኑ ለእርስዎ ስል ነው የፈቀድኩላት፡፡
ልጅትዋ መናጢ ስለሆነች ሥራ መሥራት ነበረባት፡፡
«ልጅዎ አይደለችማ?» ሲል ጠየቃት።
«ምነው ጌታዬ! ምጽዋተኛ ናት እንጂ ልጄ አይደለችም፡፡ ረዳት
ስለሌላት አስጠግተናት ነው፡ ቢያይዋት የተረገመች ደደብ ልጅ ናት ጭንቅላትዋ ውስጥ ያለው ንፍጥ ብቻ መሆን አለበት:: እንደሚያዩት ; ጭንቅላትዋ ትልቅ ነው፡፡ እኛ ግን ሀብታሞች ባንሆንም መደረግ ያለበትን
ሁሉ እናደርግላታለን፡፡ ገንዘብ እንዲልኩላት ወዳጅ ዘመዶችዋ ብዙ ጊዜ ደብዳቤ ብንጽፍም መልስ አልመጣም:: አሁን ከጻፉልን ስድስት ወር
አልፎታል። ምናልባት እናትዋ ሳትሞት አልቀረችም::»
«ይገርማል!» ብሎ ወንበሩን ለመደገፍ ወደኋላ ሸሽት አለ፡፡
«እናትዋ እስከዚህም የምትረባ ሴት አልነበረችም» አለች ሚስስ
ቴናድዬ፡፡ «መጥፎ፣ የገዛ ልጅዋን የምትከዳ!»
ኮዜት ስለእናትዋ እንደሚነጋገሩ ስሜትዋ ስላነገራት ዓይንዋን
ከሴትዮዋ ላይ አላነሳችም፡፡ የሚናገሩትን አስተውላ ትሰማለች፡፡ ሆኖም ራቅ ብላ ስለነበር የተቀመጠችው አንዳንዱን እንጂ ሁሉንም አልሰማችም፡፡
ሁለቱ ሲወያዩ አብዛኞቹ ጠጪዎች ስለሰከሩ ጫጫታው ደግሞ
እየተጋጋለ ሄዶ ነበር፡፡ ሚስስ ቴናድዬ ወደ ጠጪዎች ሄደች:: ኮዜት ያንን በብትቶ የተጠቀለለ የቆርቆሮ ቢላ እንደ አሻንጉሊት ይዛ «እሽሩሩ» በማለት
ታዜማለች፡፡ ደጋግማ የምታዜመውም «እሹሩሩ እናቴ እኮ... ሞታለች፣
እሹሩሩ እናቴ እኮ ሞታለች» እያለች ነበር::
ሚስስ ቴናድዬ ስለጨቀጨቀችው እራት እንዲቀርብለት መንደገኛው
ተስማማ፡፡
«ጌታዬ ምን ይምጣልዎት?»
«ዳቦና ሻይ ካለ ይበቃል» አለ ሰውዬው::

👍9🥰1😁1
«እውነትም ይህ ሰው ለማኝ መሆን አለበት» ስትል አሰበች፡፡
ኮዜት ዜማዋን በድንገት አቆመች፡፡ ፊትዋን ስታዞር የእነአዜልማን
አሻንጉሊት ድመት ስትጫወትበት ተመለከተች:: ግራና ቀኝ አየች:: ባልና ሚስት ራቅ ብለው ስለሆነ ነገር ይጨቃጨቃሉ፡፡ ሁለቱ ልጆችም የሞቀ ጨዋታ ይዘው አቀርቅረዋል:: ድመትዋ ትጫወትበት የነበረው አሻንጉሊት
ከእርስዋ ሩቅ አይደለም:: ማንም እንደማያያት ካረጋገጠች በኋላ ቀስ ብላ አሻንጉሊቱን አምጥታ ትጫወትበት ጀመር፡፡ በእውነተኛ አሻንጉሊት ተጫውታ ስለማታውቅ አሁን በማግኘትዋ በጣም ደስ አላት::
ይህን ትርኢት መንገደኛው ሰውዬ እንጂ ማንም አላየም:: ኮዜት
ማንም ሳያያት በአሻንጉሊቱ መጫወትዋን ቀጠለች:: ከሩብ ሰዓት በኋላ ግን በጥንቃቄ የያዘችው አሻንጉሊት ታየባት፡፡ የአሻንጉሊቱ እግር ከአቀፈችበት
ቡትቶ ውጭ ስለነበርና የሚነድደው እሳት ውጋጋን ስላረፈበት ከሩቁ ታየ፡፡ በመጀመሪያ ያየችው አዜልማ ነበረች፡፡
«አየሽ፧ አየሽ!» አለቻት ለትልቅ እህትዋ፡፡
ሁለቱ ልጆች ጨዋታቸውን አቆሙ:: ኮዜት ደፍራ አሻንጉሊታቸውን
በመውሰድዋ እጅግ በጣም ተገርመው እርስ በእርስ ተፋጠጡ:: ኢፓኒን የያዘችውን ድመት እንደታቀፈች ወደ እናትዋ ሄዳ የእናትዋን ቀሚስ ሳብ አደረገች፡፡
«ምነወ ብትታዪኝ! » አለች እናትዋ:: ልጅትዋ ግን አለቀቀቻትም::
"ምንድነው የምትፈልጊው?"
«እማዬ» አለች ልጅትዋ! «እስቲ ወደዚያ ተመልከቺ!» ካለች በኋላ
ወደ ኮዜት አመለከተቻት፡፡
ኮዜት ባቀፈችው አሻንጉሊት በጣም ተመስጣ ስለነበር ስለሚዶለትባት ነገር አልሰማችም፤ አላየችም፡፡ የሚስስ ቴናድዬ ፊት በቁጣ ገነፈሉ።
ከመቅጽበት ተለዋወጠ፡፡
«ኮዜት!» ስትል ጆሮ በሚያደነቁር ድምፅ ጮኸችባት::
ኮዜት መሬት ተከፍቶ የዋጣት መሰላት፡፡ በፍርሃት ተርበደበደች::
ፊትዋን አዞረች እንጂ መልስ አልሰጠችም::
«ኮዜት» ስትል እንደገና ጮኸችባት::
አሻንጉሊቱን ከነበረበት ወስዳ በዝግታ አስቀመጠችው:: ፊትዋ ላይ የተስፋ መቁረጥ ምልክት ታየ፡፡ ከልብዋ አዘነች:: ማምሻውን ውሃ ለመቅዳት በሄደችበት ጊዜ ያየችው ጨለማና የባልዲው ክብደት እንደ ሚስስ ቴናድዬ
ቁጣ አላሳዘናትም:: እንባ ከጉንጮችዋ ላይ ኮለል ብሎ ይወርድ ጀመር፡፡አለቀሰች፤ ተንሰቀሰቀች፡፡
መንገደኛው እንግዳ ብድግ አለ፡፡
«ምን ነካዎት!» ሲል ሚስስ ቴናዲዬን ተናገራት::
«አያዩም ጌታዬ!» አለች ሚስስ ቴናድዬ ወደ ኣሻንጉሊቱ እየጠነቆለች::
«ታዲያ፧ ምንድነው እርሱ!» ሲል መለሰ፡፡
«ይህቺ ለማኝ፤ ዛሬ ደግሞ ብላ ብላ በልጆቼ መጫወቻ ትጫወት
እንዴ!»
«ይኼ ሁላ በጩኸት ለእርሱ ነው? ብትጫወትበት ምን ይሆናል?» ሲል ጠየቀ፡፡
«በቆሻሻ እጆችዋ ነው እኮ የነካችው! በእነዚያ አስቀያሚ ጣቶችዋ እኮ ነው የምታፍተለትለው!»
ኮዜት በይበልጥ ከፍ ባለ ድምፅ ተንሰቀሰቀች::
«ዝም በይ ዛሬ ይሻልሻል» ስትል ፎጮኸችባት::
ሰውዬው በቀጥታ ወደ በሩ አምርቶ በሩን ከፍቶ ወጣ፡፡ እንግዳው ስለወጣላት ደስ ብሎአት ወደ ኮዜት ሮጣ ሄዳ አንዴ በርግጫ ፤ አንዴ በጥፊ ከካቻት፡፡ ኮዜት እንደሚሟሟ ጨውና እሳት ወስጥ እንደገባ ጅማት ጭርምት ኩርምት አለች::
በሩ እንደገና ተከፈተ:: ከአሁን በፊት የተነጋገርንበትንና የሰፈሩ
ልጆች ሁሉ የሚያደንቁትንና የሚመኙትን ትልቁን አሻንጉሊት ይዞ እንግዳው ተመልሶ ገባ፡፡ ከኮዜት ፊት አስቀመጠው::
«ያውልሽ፤ የአንቺ ነው ፤ ተጫወችበት» አላት::
ኮዜት ቀደም ሲል እንዳቀረቀረች ኮቴ ሰምታ ቀና ብላ ስትመለከት
ያቺን አሻንጉሊት በማየትዋ ፀሐይ ከሰማይ ወርዶ ወደ እርስዋ የሚመጣ መሰላት፡፡ «የአንቸ ነው» የሚል ቃል በሰማች ጊዜማ አንዴ ሰውዬውን አንዴ ደግሞ አሻንጉሊቱን አየች፡፡ ከዚያም ወደ ኋላ አፈግፍጋ ላለመታየት
ከጠረጴዛው ስር ተወሸቀች::
ልቅሶዋን ከማቆም አልፋ መተንፈስዋ እስኪያጠራጥር ድረስ ዝም አለች፡፡ ሚስስ ቴናድዩና ሁለቱ ልጆችዋ እንደ ሐውልት ተገትረው ቀሩ፡፡ ጠጪዎችም ጫጫታቸውን አቁመው ፀጥ አሉ:: ቤቱ በአጠቃላይ ከመቅጽበት እርጭ አለ፡፡
ሚስስ ቴናድዬ ስለሰውዬው ማንነት ለማወቅ የነበራት ጉጉት
አገረሸባት፡፡ «ይኸ ሽማግሌ ማነው? ዱር አዳሪ ወሮበላ ይሆን? ወይስ የብዙ ሺህ ብር ጌታ?» ብላ ራስዋን ከጠየቀች በኋላ «ምናልባት ሁለቱም
ይሆናል ፧ በስርቆት ተግባር የተሰማራ ባለሀብት ሊሆን ይችላል» ስትል ደመደመች፡:
ሚስተር ቴናድዬም ከተቀመጠበት አንድ ጊዜ እንግዳውን ቀጥሉ
አሻንጉሊቱን እያየ ስለሰውዬው ያሰላስል ጀመር፡፡ «አሻንጉሊቱን ስንት ገዘቶት ይሆን» እያለ አሰበ፡፡ ወደ ሚስቱ ጠጋ ብሎ በጆሮዋ «ይኸ አሻንጉሊት እኮ ቢያንስ ሰላሣ ፍራንክ ያወጣል:: ምን ትሞኛለሽ፤ ሰውዬውን እስቲ
ጠጋ፧ ጠጋ እያልሽ አጫውቺው እንጂ» አላት፡፡
«በይ እንጂ ኮዜት» አለች በለሰለሰ ግን ማር በተለወሰ የክፉ ሴት
የጭካኔ አንደበት:: «አሻንጉሊትሽን እጅ ነስተሽ ተቀበያ!»
ኮዜት ከተወሸቀችበት ለመውጣት ሞከረች፡
«ኮዜትዬ» አለ ሚስተር ቴናድዬ በማሞካሸት እየተናገረ፡፡ «ክቡርነቱ አሻንጉሊቱን ገዛልሽ፤ ተቀበዪው:: አሻንጉሊቱ የአንቺ ነው።»
ኮዜት ኣሻንጉሊቱን በፍርሃት አየችው:: አሁንም ቢሆን ዓይንዋ እንባ እንዳቀረረ ነው:: ከደስታዋ ብዛት እንባዋ ሊፈስ ሆነ:: አሻንጉሊቱን የነካችው
እንደሆነ እንደ መብረቅ የሚጮህ መሰላት፡፡
አልተሳሳተችም፤ አሻንጉሊቱን ብትወስድ ምናልባት ሚስስ ቴናድዬ ትቆጣት ወይም ትደበድባት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ውበቱ ስለማረካት ተሸነፈች::
በመጨረሻ ስትፈራ ስትቸር ወደ ሚስስ ቴናድዬ ፊትዋን አዙራ በጣም ዝግ ባለድምፅ ተናገረች::
«እሜቴ መውሰድ እችላለሁ?»
«ኧረ ወዲያ» አለች ሚስስ ቴናድዬ፣ «የአንቺ እኮ ነው፤ እርሳቸው ናቸው ለአንቺ የሰጡሽ፡፡»
«እውነት ነው ጌቶች? ለእኔ ነው የገዙት?» ብላ ከጠየቀች በኋላ
««በእርግጥ አሻንጉሊትዋ የኔ ናት!» ስትል ተናገረች::
የእንግዳው ዓይን እንባ አቀረረ፡፡ ቃል የተነፈሰ እንደሆነ እንባው ዱብ የሚል ስለመሰለው አቀርቅሮ ቀረ::
ኮዜት የአሻንጉሊቱን እጅ ያዘች:: ግን ኣሻንጉሊቱ እሳት በውስጡ
ያለበት ይመስል ቶሎ ብላ እጅዋን አንስታ ወደ መሬት አቀረቀረች::
ወዲያው ደግሞ ሳታውቀው በድንገት ምላስዋን ጉልጉላ ወደ ውጭ አወጣች::
ወዲያው ደግሞ ቀና በማለት አሻንጉሊቱን አፍጥጣ ካየችው በኋላ በቅጽበት አፈፍ አደረገችው፡፡
«ስምዋ ካተሪን ይሆናል»::
ልስልስ ያለው የአሻንጉሊቱ ልብስ የኮዜትን ቡትቶና ገላ ሲነካ ጊዜ
ኮዜት እንግዳ የሆነ ስሜት ተሰማት::
«እሜቴ፤ አሻንጉሊቴን ወንበር ላይ ላስቀምጣት?» ስትል ጠየቀች፡፡
«አስቀምጫት የእኔ ልጅ» ስትል ሚስስ ቴናድዬ መለሰች፡፡
ኮዜትን በቅናት ዓይን የማየት ተራ የኢፓኒንና የአዜልማ ሆነ፡፡
ኮዜት ካተሪንን ወንበር ላይ አስቀመጠቻት:: እሷ ግን ከወንበሩ
አጠገብ ወለሉ ላይ ቁጭ አለች:: ነቅነቅ ሳትል አሳብ እንደገባው ሰው ቃል ሳትናገር ለረጅም ጊዜ ተቀመጠች፡፡
«ኮዜት፧ ለምን አትጫወችም?» ሲል እንግዳው ጠየቃት፡፡
«እጫወታለሁ» ስትል መለሰችለት::

👍14
ይህ አድራሻውና ከየት እንደመጣ የማይታወቀውን እንግዳ ለኮዚት
ከፈጣሪ የተላከ በመሆኑ እጅግ ስታፈቅረው ለሚስስ ቴናድዬ ግን በዓለም ላይ ካለ ፍጡር ሁሉ የሚጠላ ነው:: ሴትዮዋ ስሜትዋን አምቃ ከመያዝ በስተቀር ሌላ ምርጫ አልነበራትም:: ጥላቻዋ ግን ለመሸከምና ለመዋጥ
ከምትችለው በላይ ነበር፡፡ ልጆችዋ እንዲተኙ አዘዘቻቸው:: ኮዜትም እንድትተኛ የእንግዳውን ፈቃድ ጠየቀች::
«ዛሬ በጣም ስትደክም ስለዋለች ብትተኛ ይሻላል» አለች በእናትነት
አንደበት፡፡ ኮዜት ካተሪንን ታቅፋ ወደ መኝታዋ ሄደች::
ከዚያ በኋላ ሰዓቱ ነጉደ ! እኩለ ሌሊት አለፈ፡፡ ጠጪዎች ወደ
የቤታቸው ለመሄድ ከሆቴሉ ወጡ፡፡ በሩ ተዘጋ። ቤቱ እርጭ አለ፡፡
የምድጃው እሳት ጠፋ፡፡ እንግዳው ግን ከመቀመጫው አልተነሳም:: ኩርምት ብሎ እንደተቀመጠ ቀረ፡፡ አገጩን የሚያስደግፍበት ክርኑን እየቆየ ፡ እየቆየ ይቀያይራል፡፡ በተለይ ኮዜት ከሄደች ጀምሮ እንድ ቃል ከአፉ አልወጣም::
ሚስተር ቴናድዩ በኃይል ከሳለ በኋላ አክታውን ተፋ፡፡ መሐረሱን
አውጥቶ ንፍጡን ተናፈጠ፡፡ ሊነቃነቅ የተቀመጠበት ወንበር ተንቋቋ፡፡
እንግዳው ሰው ግን ድምፅ ሰማሁ ብሉ አንገቱን ኣላቀናም ወይም ፊቱን አላዞረም፡፡ «ይህ ሰው እንደተቀመጠ እንቅልፍ ይዞት ሄደ እንዴ!» ሲል ሚስተር ቴናድዬ አሰበ፡፡ ዞር ብሉ ሲያየው እንቅልፍ አልወሰደውም::
ጭልጥ አድርጎ ከወሰደው አሳብ የሚመልሰው ነገር አልተገኘም:: በመጨረሻ ሚስተር ቴናድዬ ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ ወደ እንግዳው አመራ፡፡
«ጌታው አልደከመህም ! አትተኛም?» ሲል ጠየቀው::
«አቤት! ልክ ነህ! ብተኛ ይሻላል፤ የምተኛበት ሥፍራ ወዴት
ነው?» ሲል ጠየቀ፡፡
«እኔ አሳይሃለሁ» አለ ሚስተር ቴናድዬ::
እንግዳው እቃውን ይዞ ተከተለው:: ወደ አንድ ክፍል ወሰደው::
ጥሩ ኣልጋ ወዳለበትና እጅግ ወደ አማረ ክፍል ነበር የወሰደው::
«ምንድነው ይኼ?» ሲል እንግዳው ጠየቀ፡፡
«ታላላቅ ሰዎች ሲመጡ የሚያርፉበትና ካሉን ክፍሎች ሁሉ የላቀ ክፍል ነው:: እኔና ባለቤቴ የምናድርበት ክፍል ብቻ ነው ይህን የሚስተካክል፡፡
ክፍሉ በዓመት ሦስት ወይም አራት ሌሊት ቢከራይ ነው» አለ ሚስተር ቴናድዬ::
«ከዚህ ያነሰ ክፍል ቀርቶ በረት እንኳን ብተኛ ደንታ አልነበረኝም?»
ሲል እንግዳው በድፍረት ተናገረ፡፡
ሚስተር ቴናድዬ ባገኘው መልስ ተገርሞ ምንም ነገር እንዳልሰማ
ሰው ዝም አለ፡፡ ሁለት ሻማዎችን አበራ:: ክፍሉ ውስጥ የእሳት ማንደጃ ስለነበር ክብሪት ለኩሶ ከምድጃው ላይ የነበረውን እንጨት አያያዝለት::
እንግዳው ይህ ሁሉ ሲሆን ፊቱን ወደ መስኮት አዞሮ ስለነበር ምንም
አላየም: በመጨረሻ ፊቱን ቢያዞር ሰውዬው ሄዷል:: «ደህና እደር ማለቱ እንኳን መዳፈር ይሆንብኛል ብሎ አስቦ ነው ዝም ብለ ወጥቶ የሄደው
ጠዋት ግን በተቻለ እንግዳውን ለመቦጥቦጥ አቅዷል፡፡....
💫ይቀጥላል💫

👍22❤2😁2
#አንቺዬ... ...
ይዤሽ በወጣሁኝ ፣ በዚህ ድቅድቅ ምሽት
"ባሕር ያሞራል”፣ አትበይ ከኔ ልብ ሽሽት።
የባሕር ዳር ውበት ፣ በስሜትሽ ዐይተሽ
ጨረር አታድንቂ ፤ ጨረቃን ረስተሽ፤
ዕዪው... ልብ ብለሽ!
ባሕር ለጨረቃ ፣ ደረቱን ገልብጦ፤
የጨረቃ ጨረር፣ በባሕር ተውጦ፤
ሲግባቡ እያየሽ፣
አንቺ ግን ሔዋኔ
ብርሃን ፍላጋ ፣ጨለማ ላይ ቆየሽ።
ባሕር ምን ቢሰፋ ፣ጨረቃ ሞላችው
ጨረቃስ ብትሞቅ ፣ አላደረቀችው።
የመዋዋስ ፍቅር፣ከልባቸው ጠፍቶ
ሲሞላሉ ዐየሽ ፣ኀይሏቸው ሰፍቶ።
ተቃርኖ ተመልከች!
ጨረቃ ወላድ ናት፣ እናት ብርሃን፤
ባሕር ጨለማ ነው፤ የብልጭታ መሀን።
ተቃርኖ ተመልከች!
ባሕር ሕይወት አለው፤ ከሰው የረቀቀ፤
ጨረቃ ግን በድን ፣ ከሕይወት የራቀ።
የዋጡትን ዐየሽ...
የሌላትን ሕይወት በብርሃን ቀዘፋ
ጨረቃን ተመልከች ፣ ከባሕሩ ገዝፋ።
የዋጡትን ዐየሽ...
ሕይወትን ቢቀዝፍ ፤ ጨለማን ተዋርሶ፣
ዕድሜ ለጨረቃ...
ባሕሩን ተመልከች ፣ እስከሰማይ ደርሶ፡፡
ያዋጡትን ዐየሽ
ሕይወት ከጨለማ ፣ ጨለማ ከሕይወት፣
በድን ከብርሃን ፣ ብርሃን ከበደን
ሲሰጣጡ ጊዜ
ትንሿ ጨረቃ ፣ ባሕር ስትከድን።
ይዤሽ የወጣሁት ፣ በዚህ ድቅድቅ ሞሽት
ባሕር ያምራል አትበይ ፤ከኔ ልብ ሽሽት።
ጨረቃና ባሕር ፣ሲግባቡ ያስቃል፤
ያአዳሜ ና ሔዋን ፣ፍቅሩ በቃል ያልቃል።
ያዋጡትን ዐየሽ!
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
ይዤሽ በወጣሁኝ ፣ በዚህ ድቅድቅ ምሽት
"ባሕር ያሞራል”፣ አትበይ ከኔ ልብ ሽሽት።
የባሕር ዳር ውበት ፣ በስሜትሽ ዐይተሽ
ጨረር አታድንቂ ፤ ጨረቃን ረስተሽ፤
ዕዪው... ልብ ብለሽ!
ባሕር ለጨረቃ ፣ ደረቱን ገልብጦ፤
የጨረቃ ጨረር፣ በባሕር ተውጦ፤
ሲግባቡ እያየሽ፣
አንቺ ግን ሔዋኔ
ብርሃን ፍላጋ ፣ጨለማ ላይ ቆየሽ።
ባሕር ምን ቢሰፋ ፣ጨረቃ ሞላችው
ጨረቃስ ብትሞቅ ፣ አላደረቀችው።
የመዋዋስ ፍቅር፣ከልባቸው ጠፍቶ
ሲሞላሉ ዐየሽ ፣ኀይሏቸው ሰፍቶ።
ተቃርኖ ተመልከች!
ጨረቃ ወላድ ናት፣ እናት ብርሃን፤
ባሕር ጨለማ ነው፤ የብልጭታ መሀን።
ተቃርኖ ተመልከች!
ባሕር ሕይወት አለው፤ ከሰው የረቀቀ፤
ጨረቃ ግን በድን ፣ ከሕይወት የራቀ።
የዋጡትን ዐየሽ...
የሌላትን ሕይወት በብርሃን ቀዘፋ
ጨረቃን ተመልከች ፣ ከባሕሩ ገዝፋ።
የዋጡትን ዐየሽ...
ሕይወትን ቢቀዝፍ ፤ ጨለማን ተዋርሶ፣
ዕድሜ ለጨረቃ...
ባሕሩን ተመልከች ፣ እስከሰማይ ደርሶ፡፡
ያዋጡትን ዐየሽ
ሕይወት ከጨለማ ፣ ጨለማ ከሕይወት፣
በድን ከብርሃን ፣ ብርሃን ከበደን
ሲሰጣጡ ጊዜ
ትንሿ ጨረቃ ፣ ባሕር ስትከድን።
ይዤሽ የወጣሁት ፣ በዚህ ድቅድቅ ሞሽት
ባሕር ያምራል አትበይ ፤ከኔ ልብ ሽሽት።
ጨረቃና ባሕር ፣ሲግባቡ ያስቃል፤
ያአዳሜ ና ሔዋን ፣ፍቅሩ በቃል ያልቃል።
ያዋጡትን ዐየሽ!
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍16❤6
#ዝግመተ_ለውጥ
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
...እንዲሁ ስለመምሬ እና ለትዳር ስላሰቡልኝ ልጅ እያሰብኩ የያዝኩትን ጋዜጣ መቃኘት ጀመርኩ፡፡.
በደማቅ ጥቁር ቀለም፣ “በማኅበር ተደራጅተው ጫት የሚያመርቱ አርሶ አደሮች ኑሯችን
ተለውጧል አሉ...” ይላል፡፡
ወረድ ብሎ፣ “አንዳንድ የማኅበሩ አባላት “ጫት በመሸጥ አይሱዙ መኪና ገዝተናል፣ ልጆቻችንንም
ከተማ ልከን እያስተማርን ነው ሲሉ ገልፀዋል” ከጽሑፉ ስር አይሱዙ መኪና ተደግፈው ፎቶ
የተነሱ አርሶ እደር ምስል ይታያል፡፡
ወረድ ብሎ ሌላ አርዕስት፣
አንድ አይሱዙ መኪና ሃያ ሜትር ጥልቀት ያለው ገደል ውስጥ ገብቶ ከላይ ጭኗቸው የነበሩ
ሰባት ሰዎች ሞቱ፡፡ ከሟቾቹ አራቱ ከገጠር ከተማ እየተመላለሱ የሚማሩ ተማሪዎች ሲሆኑ
ፖሊስ የአደጋው መንስዔ ሹፌሩ ጫት እየቃመ ማሽከርከሩ ነው ብሏል !"
ጋዜጣውን እጥፌ ሰፈራችንን ማየት ጀመርኩ፡፡ ቅድስት ቀይ የእራት ልብስ ለብሳ እቃ ታጥባለች፧እያንጎራጎረች፣ “በሰባራ ፎሌ ውሀ አያጠለቅም" አይ ቅድስት ! እንደኛ ሰፈር ሴት የባከነበት መንደር ያለ አይመስለኝም፡፡ ቆንጆ ናት 'ሞዴል' የመሆን ፅኑ ፍላጎት ነበራት፡፡ እንደውም የሰፈር ልጆች ሲፎግሯት፣ “ውበት ውጪያዊና ውስጣዊ ነው' ሲሉ ሰምታ ውስጣዊ ውበቷን ለማየት
እልትራሳውንድ ተነሳች” ይሏታል፡፡ ሰታንጎራጉር እየሰማኋት የድምጿ ማማር ተገረምኩ፤
“ወይ ይህቺ አገር ዘፋኞቿ በየማጀቱ እቃ እያጠቡ እቃ አጣቢዎቿ በየአደባባዩ እንዝፈን እያሉ ያደነቁሩናል" አልኩ ለራሴ፡፡ የቄሳርን ለእግዜር፡ የእግዜርን ለእግዚሃር፡፡
የመንደራችን የአንድ እሁድ ውሎ ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው ነው:: ከጧቱ 12፡00 ሰዓት
አልማዝ የምትባለው ጎረቤታችን በሯ ላይ ስለተጣለው ድግምት ታማርራለች፣ ትራገማለች፡
ጠበል ታርከፈክፋለች፡፡ ድግምት በመጣል የሚጠረጠሩ ጎረቤቶቿን ታሸሙራለች፣ “እችኑ ኑሮ
ብለዋት...” እያለች፣ ብዙ ጊዜ የሞተ እይጥ ነው በሯ ላይ ተጥሎ የሚገኘው:
ከ 12፡30 እስከ ጧቱ 2፡00 ሰዓት እማማ ዘብይደሩ ጭንቅሎ የተባለውን የልጅ ልጃቸውን
ይረግማሉ፣ ይሳደባሉ፣ ይውገራሉ፡፡ አንዳንዴ ወገራው ሲበዛ ገላጋዮች ይገባሉ፡፡ “ባጭር ቅር….ይሉትና ሲታመም ሆስፒታል ለሆስፒታል አዝለውት ይዞራሉ፡፡
ከሁለት ሰዓት እስከ አራት ሰዓት የመንደሩ ልጆች እኔ ቤት ፊት ለፊት ያለች (ሰርቪስ ቤት እንኳን
የማታቆም) ቢጢቃ ሜዳ ላይ ኳስ ይራገጣሉ፡፡ የሚያስነሱት አቧራ ልጆቹን ስለሚሸፍናቸው
እንደ ህልም ነው ብዥ ብለው የሚታዩት፡፡
ከሚጫወቱት ልጆች መሃል ጭንቅሎ (የእማማ ዘብይደሩ የልጅ ልጅ)፤ ሃይለሚካኤል 'አረቡ'
(የእማማ የውብዳር የልጅ ልጅ)፣ ሙስጠፋ (የእማማ ዘሃራ የልጅ ልጅ)፣ ሲቲና ወንዳወንድ ሰለሆነች 'ከቤ' ይሏታል (የነማማ ትርሃስ የልጅ ልጅ ናት)፤ ከላይ ከተዘረዘረው የዘር ሃረግ
እንደሚታየው መንደራችን አንድ እናት' የሚባል ትውልድ ገድፏል፣ አባት የሚባል ሃረግ ዘሏል
ሕፃናቱ ከአያቶቻቸው ጋር ነው ያደጉት፡፡ ያውም አቅም ከሌላቸው ደሃና እቅመ ደካሚ ባልቴት
አያቶቻቸው ጋር! እናቶቻቸው የት ሄዱ? አባቶቻቸውን ምን በላቸው?' ቢባል መልሱ ከሁለት
ጉዳዮች አያልፍም፡፡ እንድም ወልደው ለእናቶቻቸው እየሰጡ አረብ እገር ሄደዋል፡ አልያን
በኤችአይቪ አልቀዋል፡፡ የመንደራችን እውነታ ነው ይሄ !! ደግሞ ሕፃናቱ የተመካከሩ ይመስል በየምክንያቱ ሲጣሱና ሲነታረኩ የሁሉም መሃላ አንድ ዓይነት፣ እናቴ ትሙት !” የሚል ነው፡፡
ልክ ከአራት ሰዓት እስከ አምስት ሰዓት፣ ሁላቱ የመንደራችን እንጀራ ሻጮች ሙሉና ዝናሽ. ዱላ ቀረሽ ስድድብ ይጀምራሉ፡፡ በደንበኛ መቀማማት ነው የሚጣሱት፣
“ለማያውቅሽ ታጠኚ..ደግሞ ሙያ እንዳለው ሰው:: ማየት የተሳነው እንጀራ እየጠፈጠፍሽ.
እኩል ታወሪያለሽ…"
“ኤጅ እባከሽ…እኔ ሙሉ በወፍጮ ቤት ጥራጊ አይደለም ደንበኞቼን የማስተናግደው፣ ጥርት
ባለ ጤፍ ጥር…ት”
“ሂሂሂሂሂ መጣፈጡ ቀርቶ እጄን በሰቀቀኝ አሉ እትዬ አሰለፍ፣ ጥራቱ ቀርቶብሽ ቡሃቃሽን
በወር እንዴ እንኳን ባጠብሽው:: ሰዉን ሁሉ በሆድ ቁርጠት ጨረሽው” ትላለች ዝናሽ። የሙሉ
ደንበኛ ስለሆንኩ በዚህ ኣባባሏ ሆዴ ይጮሃል፣ ..ኡ... ወር ሙሉ የማይታጠብ ቡሃቓ እቺ
ስድድብ ደንበኛን ለማስከዳት ወሳኝ የቃላት ጦርነታቸው ናት፡፡
ልክ አምስት ሰዓት ሲሆን እማማ መጣፈጥና ስንቅነሽ ቡና ይጠራራሉ፡፡ ወደ ስድስት ሰዓት
ጀሚላ የቅንድቧን ኩል ጆሮና ጆሯዋ ጥግ ድረስ ተኩሳ በስልኳ እያወራች ወደላይ ትጣደፋለት፡
ሃቢቢ መጣሁ ወጥቻለሁ” እያለች፡፡ ኣፍንጫ የሚሰነፍጥ ሽቶዋ መንደሩን ያውደዋል፡፡ ጀሚላ ስታልፍ ጥርኝ ያለፈች ነው የሚመስለው:: የታከከችው ነገር ሁሉ ሽቶ ሽቶ፣ መቼም ሃቢቢዩ
የአፍንጫ መሸፈኛ ማስካ ያደረገ ሰው መሆን አለበት፡፡
ይሄን ሁሉ ሳይ ይከፋኛል። ብቸኝነት ይጫጫነኛል፡፡ ከወንዙ ተገንጥሎ ኩሬ ውስጥ እንደተኳታሪ ውሃ እዛው የምሻግት አልያም የተቀመጥኩበት በትነት የማልቅ ነገር መስሎ ነው የሚሰማኝ
ይሄን…የተረገመ እሁድ ወደዛ አልቆ ሥራዩ በገባሁ ! ለነገሩ ከእሁድ ይሻላል ብዬ እንጂ ሥራዬም ሠልችቶኛል፡፡ የባንክ ሠራተኛ ነኝ፡፡ ብዙ ሰዎች የባንክ ሠራተኛ መሆኔን እንደትልቅ እና አስደሳች ሥራ እድርገው ሲያወሩ ይገርመኛል፡፡ ለእኔ የባንክ ሥራ በምድር ላይ ካሉ አስከፊ ሥራዎች
ሁሉ አስከፊው ይመስለኛል፡፡ እንደውም ለሰው ሳይሆን ለሮቦቶች የሚስማማ ሥራ ቢኖር የባንክ ሥራ ነው እያልኩ አስባለሁ፡፡
አንድ አይነት ቅርፅ ያላቸው ብር ዮሚባሉ መርገምቶችን መቁጠር፡፡ አራት ዓመት ሙሉ
ቆጠርኳቸው..ኤጭ ድፍን አገር የሚራኮትለት ብር ለእኔ አንዳች ቆሻሻ ነገር መስሎ ነው
የሚታየኝ፡፡ ብር ይሸታል፡፡ ካላመናችሁ ወደ ኣፍንጫችሁ አስጠጉና ሞክሩት፡፡ እንደ ብር
መጥፎ ሽታ ያለው ነገር ምን አለ ? ለነገሩ የዘንድሮ ብር ላሸትተውም ብትሉ አፍንጫችሁ ላይ
ላይደርሰ ያልቃል ሰላቢ ነገር ነው::
ምስላቸው ብር ኖት ላይ ያሉት ሰዎች ከመኖር ብዛት የቢሮ ባልደረባ መስለውኛል፡፡ ደግሞ
አልወዳቸውም፡፡ ለምሳሌ አንድ ብር ኖት ላይ ምስሉ ያላውን ሰው መንገድ ላይ ባገኘው ገላምምጬው የማልፍ ይመስለኛል፡፡ አስር ብር ላይ ያለችው ሴትማ ስታበሳጨኝ፤
የሆነች ነገረኛ ነገር፡፡ በደንብ አይታችኋታል? ስፌት የምትሰፋ ትመስላለት እንጂ ጆሮዋን አቁማ
ነገር የምትሰማ እኮ ነው የምትመስለው፡፡ ደግሞ ፊቷ ላይ የአሽሙር ፈገግታ አለ፡፡ ከሁሉም
ከሁሉም የሚያበሳጨኝ ነገር ደግሞ ከንፈሯ ! የከንፈሯ ማማር የሰብለን ከንፈር እኮ ነው
የሚመስለው !! ከነስፌቷ እጎኗ ላለው አንበሳ ነበር መስጠት !!
ባንክ ቤት ስትሰሩ ስጋችሁ በሱፍ ተጀቡኖ ወሩ መጨረሻ ላይ የሱፍ ቆሎ መግዣ እንኳን የማይተርፋችሁ መናጢ ደሃ መሆናችሁን ብዙ ሰው አይረዳም፡፡ ቁጥርና ስጋት ባንድ ላይ
የሚኖሩት ባንክ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ብር ስትቆጥሩ በስጋት ነው:: አንዱን የብር ኖት ሌላ የተደራረበ እየመሰላችሁ በፍትጊያ ፍዳውን ታበሱታላችሁ፡፡ በዛ ላይ ሰው ለብር ያለውን ሟችነት፣ ስግብግብነት፣ ደግነትም ጭምር ትታዘባላችሁ፡፡

👍32❤1👎1👏1🎉1
ሃሃሃ የሆነ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ አንድ ቀን እንጂ እኔ ወዳለሁበት መስኮት ጠጋ አለችና ትልልቅና
የተራቆቱ ጡቶቿን መስታወቱ ጋር ጨፍልቃቸው በሸንቁሩ ታናግረኝ ጀመረ፡፡ ደረትና ጡቷን የወረራት ብጉር መሰል ነጠብጣብ ያስቅቃል፣ መቶ ሺ ቁጫራጮች የሚርመሰመሱበት ደረት ነው
የሚመስለው፡፡ እንደው አንዳንድ ሴቶች ምን “ማሳየት እና ምን መደበቅ እንዳለባቸው አያውቁም፡፡
እኔ ደግሞ ከኋላዋ ተራ የሚጠብቁ ደንበኞች ወደሷ ሲያፈጡ፣ “እቺ ሴት ታዋቂ ትሆን?” ብዬ አሰብኩ፡፡ ለካስ ወደኔ ስታጎነብስ በጣም አጭር ጉርድ ቍሚሷ ከኋላዋ ታፋዋ ድረስ በመራቆቱ ነበር ያ ሁሉ ዕይታ፣
“ምን ልታዘዝ የኔ እመቤት" አልኳት፡፡ በሚያበሳጭ መሞላቀቅ ቻፕስቲክ አውጥታ ደዘደዝ
ከንፈሯን ቀባችና ቍጭ አድርጋ ዘግታ ወደ ቦርሳዋ መለሰች፡፡ በትዕግስት ጠበቅኳት።
“ዶላር ተልኮልኝ ነበር"
"ክየት ነው?"
"ከዲሲ ..ሜሪካ"
“የላኪው ስም?”
"ዳኒዬ” አለች በፈገግታ፡፡
“ዳንኤል ነው?”
“ያ"
"ስንት ነው የላከልሽ?"
“ሰሪ ኦር ፎር ሃንድረድ ዶላር ስታወራ አንገቷን ትሰብቀዋለች፡፡
ዳንኤል የላከላት ግን አንድ መቶ ዶላር ሊያውም መላኪያው ከዛው ላይ የሚቆረጥ ነበር፡፡ይሄንኑ
ስነግራት ደዘደዟ ምልቃቃዋ እና ቁጫጫሟ ሞልቃቃ - ፊቷ ተቀያየረ፡፡ ስልኳን አውጥታ
ደወለችና ጥርት ባለ አማርኛ፣ "አንች ያ ችጋራም መቶ ዶላር ብቻ ነው የላከልኝ ዳንኤል እርገጤ ነዋ ብላ እርፍ፡፡ ወዲያው አንድ ቁሽሸ ያለ ቱታ የለበሰ ጎልማሳ ሰው መጣና፣
“ይቅርታ ይቺን ብር ትራንስፈር ታደርግልኝ” አለኝ እየተጣደፈ በልጅቱ ትከሻ ላይ የባንክ
ደብተሩን እያቀበለኝ:: ልጅቱ የቱታው መቆሸሽ ደብሯት ፊቷን እጨፈገገች።
“ወደየት ነው?” አልኩት፡፡
“ወደ ጅማ”
“አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን፡፡ ሞልቃቃዋ ሰውየውን ቀጥ ብላ አየችውና ፈገግ ብላ በአከብሮት
ቦታውን ለቀቀችለት:: ወዲያው የሚያደርጋትን አሳጣት፣ "ወደዚህ ጠጋ ብለህ አናግረው፣ ሶሪ
ቦታ ያዝኩብህ አለችው በፈገግታ፡፡ ዞሮ እንኳን አላያትም፡፡ (የውሸት አከብሮቷና ፈገግታዋ ከሰረ፡፡ ሰውዬው እናትዬ ስራ ልቡን ያወለቀው ላብ አደር ነገር ነው እሷን ለማየት ጊዜውም የለው…! “ሚስኪን ዳኒዬ!” አልኩ በሆዴ፡፡
በቃ ይሄ ነው ስራዬ ብር መቁጠር መስጠት፡፡ ብር ማስገባት፣ ማስወጣት..ኤጭጭ ! ቢሆንም
ከእሁድ ይሻላል፡፡
እማማ መጣፈጥ ስንቅነሽን ቡና ሲጣሩ ሰማሁ ገና አምስት ሰዓት ወይ እዳ!
ቅድስት አሁንም እያንጎራጎረች ነው፤ “የቤቱ ወለሉ ጣራ እና ግድግዳው…" የቤታቸውን ግድግዳና ጣራ ከውጭ በኩል በረዥም መጥረጊያ እያፀዳች ነበር፡፡ ቆንጆ ናት፣ ጠይም ቆዳዋ ጥረት ያለ፧ በታለይ እንዲህ ከኋላዋ ሁና ስትንጠራራ ላያት የአቦሸማኔ ሽንጥ፡፡ ቅድስት ቆንጆ ናት፡፡ እንደው ተፈራርተን እንጂ እኔና ቅድስት ሳንከጃጀልም አልቀረን፡፡ ባየኋት ቁጠር አቅፈህ ሳማት ሳማት ይለኛል። ...እሷም በሰበብ አስባቡ እቤቴ ጎራ ማለት ታበዛለች ግን - እንፈራራለን፡፡
ቅድስት፡ አርሴማ፣ ሃያት፤ ጀሚላ፣ ሜሮን፣ ሂሩት እና ሄለን አረብ አገር ለስራ ሄደው የትመለሱ የመንደራችን ሴቶች ናቸው፡፡ ያልተመለሱትንማ አረብ አገር እዛው ይቁጠራቸው፡፡
መጀመሪያ አረብ አገር የሄደችው አርሴማ ነበረች፤ እንዳሁኑ ባልተለመደበት ጊዜ። ታዲያ
አርሴማ ብዙ አልቆየችም ባልታወቀ ምክንያት በሶስት ወሯ ተመለሰች፡፡ ዘጠኝ ወር ሲሞላት
ግን ምከንያቱ ታወቀ፤ ወንድ ልጅ ተገላገለች ! የመንደሩ ሰው እርጉዝ መሆኗን ካወቀበት ቀን ጀምሮ ፥ የሚወለደው ልጅ አረብ ይመስሳል…. አይመስልም” እያለ ሲነታረክ፣ ሲወራረድና ብር
ሲያሲዝ ከረመ፡፡ አርሴማ የሚያምር ከልስ ልጅ ወለደች፡፡ ገና ከአራስ ቤት ሳትወጣ ደግሞ
መነሻው ያልታወቀ ወሬ ይናፈስ ጀመረ::
አርሴማ የወለደችው ትሰራበት የነበረ ቤት ተቀጥሮ ከሚሰራ ፓኪስታናዊ ዘበኛ ነው" ይሄ
ወሬ ለጉድ ተናፈሰ፡፡
“ቱ! ለሞላ ወንድ” ተባለ፡፡ “አንገት ደፊ እገር እጥፊ" ተባለ፡፡
ይሄ ወሬ እድሜው ከሳምንት አላለፈም፡፡ የመልስ ምት በሚመስል ሌላ ወሬ ተተካ፡፡
“አርሴማ ያረገዘችው ከኪዌቱ አሚር ሁለተኛ ልጅ አብደል ናስር ነስረዲን ነው...እነሱ ቤት
ነበር የምትሰራው” ይሄንኛው ወሬ ከመጀመሪያው የበለጠ ገነነ፡፡ እንደውም በቅርቡ መጥቶ
ሰፈራችንን በሊዝ ሊገዛውና በአርሴማ በኢትዮጵያ አንደኛ የሆነ ሕንፃ ሊገነባላት እንደሚችል
ሁሉ ተወራ፡፡
ሲወዳት መቸስ ለብቻው ነው፣ እሷን ሲያይ ጥምጣሙ እስኪበር ነው በደስታ የሚምነሸነሸው”
እየተባለ ወሬው ደመቀ፡፡ ጥምጣሙ እስኪበር የሚያፈቅር የአሚር ልጅ እዚህ ጭርንቁስ
መንደራችን ውስጥ መጥቶ ለማየት እኔ ራሱ ጓጓሁ፣ የፍቅርን ኃያልነት ለመታዘብ አሰፈሰፍኩ፡፡
ሕፃኑን ልጅ አያቱ ኃይለሚካኤል” አሉት፤ ኃይለሚካኤል ኣብደል ናስር ነስረዲን በዚህ ሁኔታ
የመንደራችን ኣባል ሆነ፡፡ (አረቡ ይሉታል በቅፅል ስም፣ በኢትዮጵያና ኩዌት መካከል ወደፊት ለሚኖረው ወዳጅነት ይህ ታሪካዊ እንቦቀቅላ ታላቅ ሚና ሳይኖረው አይቀርም.… ሂሂሂ)፡፡ አድጎ አስር ዓመት እስኪሆነው ግን አባቱ ነኝ ያለ የአሚር ልጅ አልታየም፡፡ አንድ ቀን ታዲያ አያቱ፣
ዓሚሩ ቀርቶበት ዘበኛውም በመጠና የአባትን ጣዕም ባውቀው” አሉ በቁጭት፡፡
ከአርሴማ በኋላ ሜሮንና ጀሚላ አረብ አገር በመሄድ ሁለት ዓመት ቆይተው ተመለሱ፡፡ እነጀሚላ
ቤት አዲስ ምንጣፍ ስለተነጠፈ ጫማ ሳያወልቁ መግባት ተከልከሉ ነበር፡፡ በአንድ እግሩ
ምንጣፉን የረገጠ እንግዳ በጀሚላ ጩኸት ሁለተኛ እግሩን በአየር ላይ እንዳንጠለጠለ ደርቆ
ይቆማል፡፡ እማማ ሐዋ (የጀሚላ እናት) ታዲያ “ይሄን ምንጣፍ ወዲያ ኣንሽልኝ ላታመም ጠያቂ፡
ሲቸግረኝ ደራሽ ጎረቤቶቼን አራቀብኝ አሉ፡፡ ሲቆይ ግን ምንጣፉም ቆሸሸ መዓቀቡም ተነሳ፣ መጀሪያ ቤተሰቡ ከዛም ሁላችንም መንደርተኞች ከነጫማችን መግባት ጀመርን፡፡
ሜሮን እንደመጣች እካባቢ ደግሞ የተረፈ ምግብ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ እየደፋች አሰቸግራ
ነበር፡፡ ኧረ ለልጆቹ መክሰስ ይሆናል እህሉን እትድፊ ጡር ነው” ብትባል፣ “ላላ ላላ” እያለች
መገልበጥ ሆነ፡፡ ከወራት በኋላ እንኳን ሊተርፍ ዋናውም እያነሰ ቤተሰሱ መነጫነጭ ስለጀመረ
እህል መድፋቱ በዛው ቆመ፡፡
አረብ አገር የሄዱት ሁሉ ኮንትራታቸውን ጨርሰው ባንዴ ወደ መንደራችን በመጡበት ወቅት
የሚገርም የባህል፣ የኢኮኖሚ፣ የቋንቋ መቀየጥ ተከሰተ፡፡ ፓስፖርት፣ ቪዛ፣ ኮንትራት፣ በርሜል፣ ካርጎ፣ ጉምሩክ፣ ሃቢቢ..ሃቢብቲ የሚሉ ቃላት ተዘወትሩ፡፡ በመንደራችን ሻይ አብዝቶ መጠጣትና ሩዙን ከእንጀራ እኩል ገብታ ላይ ማቅረብም ተለመደ፡፡ በሳተላይት ዲሽ የእረብኛ ፊልሞ ተከታታይ ድራማዎችን ማየትም አንዱ ለውጥ ነበር፡፡
እርስ በእርስ መንደርተኞች ሲጣሉ አረብኛ ስድቦችን መቀላቀል ሁሉ ተጀመረ፡፡ እንደውም አንድ አረብኛ ስድብ ለእኔም ደርሶኛል፡፡ ቅድስት የአስቴርን ሲዲ ልትዋስ ቤቴ ሰትመጣ በቃሌ የሸመደድኩትን ግጥም ብቻዬን ሳነሰንብ ደረሰችና “መጅኑን!" አለችኝ፡፡ በኋላ ሜሮን
እንደተረጎመችልኝ ከሆነ “ወፈፌ" ማለት ነው አሉ፡፡
በዚህ ወቅት ሂሩት አረብ አገር እሄዳለሁ ብላ ተነሳች፡፡ “እንዴ ደግሞ አንቺ ምን አጣሽ ኑሯችሁ
ጥሩ፤ ትምህርትሽን እየተማርሽ ነው” ብትባል

👍24❤1
“እንዴት ነው ምን አጣሽ ተውኝ..ተውኝ እባካችሁ ሆድ አታስብሱኝ፡፡ ያጣሁትን እኔ ነኝ
የማውቀው፡፡ የመንደሩ ሴት ሁሉ በአረብኛ ሲሰዳደብ እኔ እስከመቼ በአማርኛ ስሳደብ እኖራለሁ
ማን ከማን ያንሳል?!" አለች እንባ እየተናነቃት፡፡ ሄደችና ሁለት ዓመት ቆይታ ብዙ አረብኛ ስድቦችና አንድ በርሜል ልብስ ይዛ ተመለሰች፡፡
አስገራሚ በሆነ ሁኔታ በርሜሉ ውስጥ ሙሉ የቤይሩት መቶ አለቃ ዩኒፎርም ተገኘ፡፡ የሂሩት
እባት ያንን ግጥም ኣድርገው ለብሰው እንዳንድ ቤይሩት ኖረው የመጡ ሴት እህቶቻችንን
በሰላም አገር ሲያስደነግጡ ከረሙ:: ሂሩትም ሃሜት አልቀረላትም፣ “ፖሊስ ቤት ተቀጥራ ነበር የምትሰራው ልብሱን ሰርቃ አምጥታ ነው" አሏት፡፡
ሂሩት ግን አንድ ቀን ቁጭ ብለን ስናወራ ስለ ዩኒፎርሙ ይሄን ታሪከ ነገረችኝ፡፡ አንድ መቶ
አለቃ ሂሩትን ድንገት አያትና በፍቅሯ ተነደፈ፡፡ መጀመሪያ በሃር የተጠለፈ መሃረቡን ላከላት፤
(የፍቅር መግለጫ መሆኑ ነው) ዝም ስትለው አሃ አንሶብሽ ነው! ሰማዎት የፖሊስ ኮቱን
ከነ መአረጉ ላከላት፡ መጨረሻ መልስ ሲያጣ ሱሪውን ላከላት በሱሪው ተጠቅሎሎ ደግሞ ክላሽንኮቭ ጠመንጃው አብሮ ነበር፡፡ እንግዲህ ወንድ ልጅ ሱሪና ጠመንጃውን ከሰጠ ምን ቀረው ? ይሄ ምስኪን አፍቃሪ ፖሊስ እስካሁን በፓክ አውትና በግልገል ሱሪ በቤይሩት ጎዳናዎች ላይ ግዳጁን እየተወጣ ይገኛል፡፡ (አያድርስ ነው…አይሳቅም፡ እኔስ አለሁ አይደል ለዛች ሰላቢ ሰብለ ነፍሴን ሰጥቼ እርቃኔን የቀረሁ፡፡)
ሄሩት ዮኒፎርሙንም ክላሽንኮቭ ጠመንጃውንም ይዛ ወደ ኢትዮጵያ ስትገባ ኤርፖርት ፍተሻ ላይ ተያዘች።
“መሳሪያው አያልፉም ይወረሳል፣ ዩኒፎርሙን ችግር የለም ማስገባት ትችያለሽ” አሏት ፈታሾቹ፡፡
አረ የሰው ስጦታ ነው በናታችሁ!” ብትላቸው፣
ሕግ ነው” ብለው ግግም አሉባት፡፡ ወደ ሀላፊው ቢሮ ገብታ ጉዳዩን ነገረችው፡፡ ገና ክላሸ ስትለው፣ “አያልፍም አላት በቁጣ፡፡
ምናለበት ባታካብዱ ባንድ ጠመንጃ መንግሥት እይገለበጥ!” አለችው ግልፍ ብሏት፡፡
“ዋይ ተይ ባክሽ እኛም ደርግን ስንገለብጠው ባንድ ክላሽንኮቭ ነው የጀመርነው ብሎ ሸኛት፡፡
ሂሩትና ጀሚላ “ዩኒፎርም ስርቃለች” በሚለው ሐሜት አቧራ ያስነሳ ፀብ ገጠሙ፡፡ በአረብኛ እና
በአማርኛ ነበረ ስድድቡ፡፡ ቅድስት መሀል ገብታ እየገላገለች እግረ መንገዷን አረብኛ ስድቦችን
ለእኛ ለመንደርተኞች ትተረጉምልን ነበር፡፡
"ከልብ” አለች ሂሩት ጀሚላን፡፡ ቅድስት፣ ኧረ እንዲህ አይባልም እግዜር አይወደውም ሂሩት"
በማለት ነገሩ ለማብረድ እየሞከረች ወደ እኛ ዞር ብላ
“ከልብ ማለት ውሻ ማለት ነው:: ትለና ወደ ላ ማግላገሏ ትመለሳለች፡፡
እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል እሁድ መሽ ! ድንገት ቅድስት ዝንጥ ብላ እቤቴ
መጣች፣ ከሰዓት ሰርግ ነበራት፡፡ ኡፍፍፍ የለበሰችው ረዥም ቀሚስ እንዴት እንዳማረባት፡፡ ስናወራ ቆየንና "ለምን ቡና እናፈላም” ብላ ስታስፈቅደኝ ማቀራረብ ጀመረች፡፡ ባንዴ ቤቱን ነፍስ ዘራችለት፡፡ እጣኑ ተጫጭሶ ሙዚቃው ተከፍቶ ቅድስት ፊት ለፊቴ የሚያምር ጠይም እግሯ በቀሚሷ ቅድ እየታየ እንደተቀመጠች ደስታ መላ ሰውነቴን አጥለቀለቀኝ፡፡ እውነቱን
ልንገራችሁ አይደል፤ ማግባት ሁሉ አማረኝ፡፡
በድፍረት “ዛሬ ለምን እዚህ አታድሪም?” አልኳት፡፡
“ባለጌ ስትለኝ ለመስማት ጆሮዬን ይዤ ነበር፡፡
“እና ካሁን በኋላ ልሄድልህ ነው?” ስትለኝ ማመን አልቻልኩም፡፡ ዞር ብዪ እልጋዩን አየሁት።
እስከዛሬ እዚህ ባህር ላይ ብቻዬን የምንሳፈፍ ሚስኪን ጀልባ መሆኔ ተሰማኝ። ዘልዩ አቀፍኳትና
ግጥም አድርጌ ከንፈሯን ሳምኳት፡፡
"ሂድ መጅኑንም አለችኝ፡፡ እንደዚህ ቃል አሪፍ የፍቅር ቃል ሰምቼ አላውቅም፡፡ ራሴ ስተረጉመው
"በፍቅር የወፈፈ” ማለት ሳይሆን አይቀርም !! “ሰው ብቻውን ሆን ዘንድ መልካም አይደለም
እደግመዋለሁ.አባ ልክ ናቸው፡፡
የአሁድ ሌሊት እንዴት አጭር ነው ለዚህ ጊዜማ ይጣደፋል !
✨አለቀ✨

👍28❤5
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
....ጠዋት ግን በተቻለ እንግዳውን ለመቦጥቦጥ አቅዷል፡፡.
ሚስተር ቴናድዬ ገና ጎሕ ሳይቀድ ከመኝታው ተነስቶ ወደ እንግዳ
መቀበያ ሥፍራ ሄደ፡፡ ሻማ አብርቶ የእንግዳውን ሂሳብ ያሰላል፡፡ ሚስቱ ከአጠገቡ አጎንብሳ ቆማለች:: ሂሣቡን ሲያሰላና ቁጥሮችን ሲጽፍ በዓይንዋ
ትከተለዋለች፡፡ ግን አሳብ አይለዋወጡም፡፡ ከቤት ውስጥ ድምፅ ተሰማ አንድ ሰው ክፍሎችን ይጠርጋል፡፡
ከአንድ ሩብ ሰዓት በኋላ ሚስተር ቴናድዬ ሂሣቡን አስልቶ ጨረሰ::
ከዚያም ክፍሉን ለቅቆ ወጣ፡፡ እርሱ ልክ ሲወጣ እንግዳው እርሱ ከነበረበት ክፍል ገባ። ሚስተር ቴናድዬ ብዙ አልራቀም፥ ሚስቱ ክፍሉ ውስጥ ሆና ታየዋለች:: እንግዳው እቃውን በእጁ ይዞ ነው ከክፍሉ የገባው::
«ምነው ቶሎ ተነሱ!» አለች ሚስስ ቴናድዬ፤ «ገና ሳይነጋ ሊሄዱ
ነው እንዴ?»
እንግዳው አሳብ የገባው መሰለ፡፡ መልስ ቶሎ አልሰጠም:: ቆይቶ
ግን «አዎን እሜቴ፤ መሄድ አለብኝ» አለ፡፡ወደ ሌላ «አገር ማለፍዎ ነው? ሞንትፌርሜ ውስጥ ሥራ የለዎትም
ማለት ነው?» ስትል ጠየቀች::
«የለም፧ ስለመሸብኝ ነው ያደርኩት እንጂ እዚህ የተለየ ጉዳይ
የለኝም» ካለ በኋላ ሂሣቡ ስንት እንደሆነ ጠየቀ፡፡
ሚስስ ቴናድዬ የቃል መልስ ሳትሰጠው ባልተቤትዋ ያዘጋጀውን
ሂሣብ ኣንስታ ሰጠችው::
መንገደኛው ወረቀቱን በማገላበጥ ሂሣቡን ተመለከተ፤ ግን ወረቀቱ
ላይ ያፍጥጥ እንጂ አሳቡ ሌላ ቦታ ነበር::
«እሜቴ» አለ፧ «ሞንትፌርሜ ውስጥ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ
እንዴት ነው?» ሲል ጠየቃት::
«ምንም አይደል» ብላ መለሰችለት በመገረም::፡ እርስዋ የጠበቀችው ሌላ ጥያቄ ነበር፡፡ «ክቡርነትዎ እንደሚያውቀው መቼም ጊዜው እስከዚህም የሚያስደስት አይደለም:: ከተማዋ ውስጥ ብዙ ብር ያላቸው ሰዎች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው:: ከተማዋም እንደሚያዩዋት በጣም አነስተኛ ከተማ ናት፡፡ እንደ እርስዎ ያለ ሀብታም እንግዳ የሚያጋጥመን አልፎ አልፎ ነው፡፡
ወጪያችን ግን በጣም ብዙ ነው:: ያቺ ትንሽ ልጅ እንኳን ብዙ ታስወጣናለች»
በማለት ችግርዋን ደረደረች::
«ከእርስዋ ብትገላገሉስ?» አለ ነገሩን በማናናቅና በማንቋሸሽ፡፡
«ከማን? ከኮዜት?»
«አዎን፡፡»
የሴትዮዋ ፊት እንደማታ ጨረቃ ወገግ አለ፡፡
«አይ ጌታዬ! ውሰዷት፤ የትም አድርሷት፤ ቢፈልጉ እንደ ምግብ
ብሏት፤ እንደ ውሃ ጠጧት ብቻ ውሰዷት እንጂ እንደፈለጉ ያድርጓት፡፡እምዬ ማርያም ከእርስዋ ብትገላግለኝ ሻማ አበራታለሁ:»
«ተስማምቻለሁ፡፡»
«ይቀልዳሉ መሰለኝ፣ አሁን እውነት ከልብዎ ነው? ይዘዋት ይሄዳሉ?»
«አሁኑኑ እወስዳታሁ፤ ልጅትዋን ይጥሯት፡፡»
«ኮዜት!» ስትል ሚስስ ቴናድዬ ተጣራች::
«ልጅትዋ እስክትመጣ ሂሣቡን ላጠናቅቅ ስንት ነበር?»
ሂሣቡን ከወረቀቱ ላይ አየ:: ግን የመገረም ምልክት አላሳየም::
«ሃያ ሦስት ፍራንክ?»
በዚህ ጊዜ ሚስተር ቴናድዬ ከክፍሉ ውስጥ ገባ፡፡
«የለም ጌታው፤ ያለብህ ሃያ ስድስት ሱስ ብቻ ነው» አለ፡፡
«ሃያ ስድስት ሱስ» ስትል ሴትዮዋ ጮኸች::
«የክፍሉ ኪራይ ሃያ ሰስ ሲሆን የእራት ሂሣብ ስድስት ሱስ ነው::
ስለልጅትዋ ግን እኔና አንተ እንነጋገራለን፡፡ አንቺ ደግሞ ጉዳዩን ለእኛ ብትተይው ይሻላል፡፡»
ሚስስ ቴናድዬ በባልዋ ሁኔታ ተገርማ መልስ ሳትሰጥ ከክፍሉ
ወጥታ ሄደች::
ባለቤቱ እንደወጣች «ምነው ቆምክ? እስቲ አንዴ ቁጭ በል» በማለት ወንበር አቀረበለት:: መንገደኛው ቁጭ አለ፡፡ ሚስተር ቴናድዬ ግን አልተቀመጠም፡፡
«ጌታው» አለ ሚስተር ቴናድዬ ፤ «መቼም ይህቺ ልጅ በጣም
የማደንቃትና የምወዳት ናት፡፡»
እንግዳው ሰውዬ አተኩሮ በማፍጠጥ ተመለከተው::
«የምን ልጅ?»
ሚስተር ቴናድዬ ቀጠለ፡፡
«የእርስዋ ነገር አይሆንልኝም፤ ይህቺን ልጅ በጣም ነው የማደንቃት!»
«የትኛዋን ልጅ ነው የምትለው?» ሲል እንግዳው ጠየቀ፡፡
«ውይ አልገባህም እንዴ! ይህቺ የኛይቱ ትንሽዋ ኮዜት ናታ! እና
አሁን አንተ ልትወስድብን ትፈልጋለህ! እኔ መቼም በዚህ አልስማማም::ከሄደች እጅግ በጣም ትናፍቀኛለች፡፡ ከሕፃንነትዋ ጀምሮ ኣብራን ስለኖረች
የእርስዋ ነገር አይሆንልንም እርግጥ ነው ብዙ ታስወጣናለች፤ ብዙ ጥፋትም ታጠፋለች:፡ እኛ ደግሞ የተትረፈረፈ ሀብት የለንም፡፡ ሆኖም አንድ ጊዜ
ታማ አራት መቶ ፍራንክ ለመድኃኒት አስወጥታኛለች፡፡ ለሰማዩ ጌታ ስል ይህን ያህል ወጪ በማውጣታችን አልተማረርንም፡፡ እናትም አባት
የላትም፡፡ እኔ ግን እንደ አባትም እንደ እናትም ሁኜ አሳደግኋት:: አሁን ቢሆን ለእኔና ለእርስዋ የሚሆን የእለት እንጀራ ኣላጣም፡፡ ስለዚህ ይህቺ ልጅ እንድትሄድብኝ አልፈልግም:: መቼም የምለው ነገር ይገባሃል፡፡ ልጅትዋን
እንወዳታለን፡፡ ባለቤቴ አንዳንዴ ችኩል ናት:: ነገር ግን እርስዋም ብትሆን ልጅትዋን ትወዳታለች፡፡ እንደ ራሳችን ልጅ ነው የምናያት፡፡»
ሚስተር ቴናድዬ ይህን ሁሉ ሲለፈልፍ እንግዳው መንገደኛ ዓይኑን ከተናጋሪው ዓይን አላነሳም:: ሰውዬው ንግግሩን ቀጠለ፡፡
«ይቅርታ አድርግልኝና ማንም ሰው ቢሆን ልጁን ለማያውቀው ሰው
አንስቶ አይሰጥም፡፡ ልክ አይደለሁም? መቼም አንተ እንዲሁ ሲያዩህ የጨዋ
ልጅ እንደሆንክ ታስታውቃለህ፡፡ ሀብትም የተረፈህ ትመስላለህ፡፡ ልጅትዋን ልውሰዳት ስትል ስለልጅትዋ ብለህ እንደሆነ ማወቅ ይኖርብኛል፡፡ ገባህ
አይደለም? ለእርስዋ ስል ስሜቴን ልግታ፤ ጥቅሜን መስዋዕት ላድርግ ብል እንኳን የት እንደምትወስዳት ማወቅ አለብኝ:: ሌላው ቢቀር የወደፊት
አድራሻዋ የት እንደሚሆንና ከማን ጋር እንደምትኖር ባውቅ እየተመላለስኩ እጠይቃታለሁ፡፡ አሁን ለምሳሌ ስምህን እንኳን አላውቅምና ልጅትዋን ማን
ወሰዳት ተብዬ ብጠየቅ ምን እላለሁ? ነገር ግን ልጅትዋን ልውሰዳት የምትለው ለሕፃንዋ ብለህ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ሌላው ቢቀር ፓስፖርትህን
ወይም የመታወቂያ ወረቀትህን እንኳን ማየት አለብኝ፡፡»
መንገደኛው አሁንም ዓይኑን ከዓይኑ ሳያነሳ የሚቀጥለውን መለሰ፡፡
ሚስተር ቴናድዬ፤ ሰዎች ከፓሪስ ከተማ ወጣ ባሉ ቁጥር የመታወቂያ ወረቀት አይዙም
ኮዜትን ከወሰድኳት እወስዳታለሁ፤ በቃ:: ሌላ አጀብ አያስፈልገውም፡ ለዚህ ማን እንደሆንክ፤ የት እንደምኖር፤ ልጅትዋ ወደፊት የት እንደምትኖር ማወቅ አያስፈልግህም፡፡ እንዲያውም እግርዋ ከዚህ ቤት ከወጣ ዳግም እንድታይዋት አልፈልግም፡፡ በዚህ ትስማማለህ? እሺ ወይም
ሰውየው ከባድ ሰው እንደሆነ ሕሊናው ጠረጠረ፡፡ ማታ ከጠጪዎች ጋር ቢጠጣ፤ ቢስቅና ቢያሽካካም ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ሰውየውን
አጢኖታል፡፡ ማምሻውን ዓይኑ ከኮዜት ዓይን ላይ እንዳላነሳ ልብ ብሉአል፡፡ለምን ወደዳት? ይህ ሰው ማነው? ይኸ ሁሉ ብር ተሸክሞ ሳለ ምነው አዳፋ ልብስ ለበሰ? እነዚህንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች አንስቶ መልስ
ለማግኘት ባለመቻሉ ተበሳጭቶ ነው ያመሽው:: አያትዋ ነው? ታዲያ ለምን ራሱን አያስተዋውቅም? አባትዋ ሊሆን አይችልም! መቼም ማንም
በሆን መብቱን አይሸሽግም፡፡ ታዲያ ይህ ሰው ማነው? ነገር ግን ሰውየው ትልቅ ሰው እንደሆነና ለመታወቅ የማይፈልገው ደግሞ በአንድ ምከንያት መሆኑን አልተጠራጠረም፡፡ ከእንግዳው ጋር ጨዋታ ሲጀምር የተደበቀ
ምስጢር መኖሩን ልቦናው አውቋል፡፡ ስለዚህ የሰውዬው ቆራጥ መልስ አላብረከረከውም፡፡ ነገር ቶሎ የሚገባው ሰው ስለሆነ ያልጠበቀው መልስ ቢመጣም አልተረበሸም፡፡ እንዲያውም እድሌ አሁን ነው ሲል አሰበ። ወዲያው ፍርጥም ብሉ ቴናድዬ ተናገረ::

👍21❤1👏1
«ጌታው!» አላ«አንድ ሺህ አምስት መቶ ፍራንክ ይከፈለኝ»::
እንግዳው ከኪሱ የቆዳ ቦርሳውን አውጥቶ ከፈተው፡፡ ገንዘቡን
ከጠረጴዛው ላይ ካስቀመጠ በኋላ ጣቶቹን ከገንዘቡ ላይ አሳረፈ:: «ኮዜትን ሂደህ አምጣ» ሲል የቡና ቤቱን ጌታ አዘዘው፡፡
ወዲያው ከመቅጽበት ኮዜት ሰዎቹ ከነበሩበት ክፍል ገባች፡፡
መንገደኛው ጠቅልሎ ይዞት የነበረውን እቃ ፈታ፡፡ የሚያምሩ
የሰባት ዓመት ልጅ ልብሶች ነበሩ:: ጫማና እስካርፍ እንኳን አልቀረም።
ልብሶቹ ጥቁር ናቸው::
«ልጄ» አለ ሰውዬው፤ «ልብሶቹን ወስደሽ ቶሎ ለብሰሽ ተመለሺ።»
ኣንዲት የሀዘን ልብስ የለበሰች ትንሽ ልጅ አስከትሎ ከከተማው ወጥቶ ገና ሲነጋ ከቤቱ የወጣ የከተማው ነዋሪ ባይተዋር የሆነ ሰው መሄዱን አየ፡፡ ኮዜትም አዲሱን አሻንጉሊትዋን ይዛ ወደ ፓሪስ በሚያመራው መንገድ ባይተዋሩን ተከትላ ሄደች::
ሰውዬው ማን እንደሆነ ማንም አላወቀም:: ኮዜትም አዳዲስና እጅግ የሚያምሩ ልብሶች በመልበስዋ ብዙም ሰው አልለያትም::
ኮዜት መሄዱንስ ትሂድ፤ ግን ከማን ጋር ነው የሄደችው? በየዋህነት
እንደ በግ እየተነዳች ሄደች፡፡ የት እንደምትሄድ ታውቃለች? አታውቅም:. ነገር ግን የምታውቀው ነገር ቢኖር የእነዚያን ጨካኝ ሰዎች ሆቴል ቤት
ለቅቃ መውጣትዋን ነው፡፡ ከቤት ስትወጣ «ደህና ሁኝ» ያላት ሰው
አልነበረም፡፡ እርስዋም «ደህና ሁኑ» ብላ የተሰናበተችው ሰው የለም፡፡ ከዚያ ቤት ተጠልታና ጠልታ ነው የወጣችው::
ኮዜት ሰማይ ሰማዩን እያየች ሰውዬውን ተከትላ ሄደች፤ ነጐደች::አልፎ አልፎ ደጉን ሰውዬ ቀና ብላ ታየዋለች፡፡ የእግዜር መልእክተኛ መሰላት::
መሸት ሲል ዣን ቫልዣ ልጅትዋን ይዞ ከፓሪስ ከተማ ደረሰ፡፡ ከተማ
እንደገቡ በጋሪ ተሳፍረው ከከተማው ክልል ወጡ እርሱ ከፈለገበት ቦታ ሲደርሱ ለባለጋሪው ሂሣባቸውን ከፍለው ወረዱ፡፡ ዣን ቫልዣ የልጅትዋን ትንሽ እጅ ይዞ ጥቂት ከተጓዙ በኋላ ከአንድ አልቤርጎ ገቡ፡፡ እራታቸውን በሉ::ብዙ ስለተጓዙ ደክሞአቸዋል፡፡ ኮዜት እንደደከማት ስለተገነዘበ አቀፋት፧
እሷም አሻንጉሊትዋን ታቀፈች:: ወዲያው ከዣን ቫልዣ እጅ ላይ እንቅልፍ ይዞአት ሄደ፡፡....

👍12❤3
#ፈንዲሻ_ሲቆሎት_ድምፅ #ሲሰሉት_ድምፅ
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት አድርገን እንደተቀመጥን፤ ፕሮግራሙ ቶሎ እንዲያበቃ ሌላ የህሊና ጸሎት ጀመርኩ፡፡ ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን ለማከበር የክፍለ ከተማው የሴቶች ሊግ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ተገኝቻለሁ፡፡
ሊጉ በመሥሪያ ቤታችን በኩል ግዳጅ የተቀላቀለበት ጥሪ አቅርቦልን አለቃዬ ሂድ !" ስላለኝ
የቀበሌው አዳራሽ ውስጥ ተገኝቻለሁ። ያውም ቅዳሜን በሚያክል ቀን ከሰዓት!! ሰኔና ሰኞ
ገጥሞብኝ፡፡
አሁን ደግሞ የከፍለ ከተማችን የሕፃናትና ሴቶች ፑል ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ደርባቤ በላቸው
እንስራውን ሰብሮ ወሰዳት ልጅቱን የሚል ምርጥ ግጥም ያቀርቡልናል…" አለ ጉጉት የመሰለው መድረክ አስተዋዋቂ፡፡ አፉ ላይ የደቀነውን ማይክሮፎን ድምፅ ማጉላቱን የተጠራጠረ ይመስል በጣም እየጮኸ ነው የሚናገረው::
ቀጠለ "ወ/ሮ ደርባቤ ለክፍለ ከተማችን፣ ብሎም ለከተማችን፣ ብሎም ለኢትዮጵያ ሴቶች፣
ብሎም ለአፍሪካ ሴቶች ታላቅ ምሳሌ የሚሆኑ የዘርፈ ብዙ ሙያዎች፣ ተሰጥኦዎች፣ ትምህርቶች፣ስልጣኖች ባለቤት ናቸው” አለና፣ “…እስቲ ወ/ሮ ደርባቢን ወደ መድረክ…”
...ቿ..ቿ...ቿ..
ጥልፍ ቀሚስ የለበሱትና አንዳንድ ልማታዊ ዝግጅቶች ላይ ልማታዊ ግጥም በማቅረብ የሚታወቁት
ወ/ሮ ደርባቤ መድረክ ላይ ቆመው በፈገግታ ለሕዝቡ ጎንበስ ቀና እያሉ ምስጋና ይሁን ሰላምታ
ያለየለት ግማሽ ስግደት አቀረቡ፡፡ ግጥሙን ሊያቀርቡ ነው ብለን ፀጥ ስንል አስተዋዋቂው
ማዋደዱን ቀጠለ፣ “….ብታምኑም ባታምኑም ወ/ሮ ደርባቤ ይሄን ዝግጅት አስመልከቶ ግጥም
እንድትፅፍልን የነገርናት (አንች አላት) ትላንት ዘጠኝ ሰዓት ነው፡፡ ይገርማችኋል ሌሊቱን ስትፅፍ
አድራ ጧት ስደውልላት በስልክ ግጥሙን አነበበችልኝ…'ወይ መባረክ' ነው ያልኩት።( በሕዝብ
ስልክ ስምንት ገፅ ግጥም እያነበቡ አላየንም ባርኮት)፡፡
“...የግጥሙን ጥልቀት እና ውበት ራሳችሁ ታዘቡት እስቲ ለዚህች ብርቱ ሴት ሞቅ ያላ ጭብጨባ…" ብሎ ጭብጨባውን ራሱ ጀመረው፡፡ ማይኩን በሌላኛው እጁ ሲጠፈጥፈው አዳራሹ ጓጓጓ.. በሚል ልጆሮ የሚቀፍ እስቅያሚ ድምፅ ተሞላ፡፡ ከታዳሚው የተንቦጫረቀ ደካማ ጭብጨባ ጋር ተዳምሮ ጓጓታው በቀላል የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች የታጀበ የከባድ መሳሪያ ድምፅ ነበር የሚመስለው፡፡
ብዙው ታዳሚ በየእጁ ፈንዲሻ እና ለስላሳ ይዞ ስለነበረ ማጨብጨብ አልቻለም እንጂ በጭብጨባማ የእኛን ኮፍለ ከተማ ሴቶች ሊግ ጽሕፈት ቤት ሰራተኞች ማን ብሏቸው::በተለይ እጃቸው ባዶ ሲሆን የሚያጨበጭቡት ጭብጨባ ቢሾፍቱ ይሰማል፡፡ እጃቸው ባዶ ሲሆን ለዜና ያጨበጭባሉ፣ ለሪፖርት ያጨበጭባሉ፣ የቀበሌው ሊቀመንበር ሲያስነጥሱ ሁሉ
ያጨበጭባሉ፣ እጃቸው ሞላ ካለች ግን ጠቅላይ ሚንስትራችን ቢዘፍኑም አያጨበጭቡም
እንዳንዴ ታዲያ ጭብጨባዎች ሲቀንሱ ኢኮኖሚያችን ያደገ ይመስለኛል፡፡
ቀጠለ አስተዋዋቂው (ወ..ይ ዛሬ) "ወ/ሮ ደርባቤ.ገጣሚ ብቻ አይደሉም፤ የታሪክ ተመራማሪም
ናቸው፡፡ (ወ/ሮ ደርባቤ ቆመው በቁማቸው ገድላቸው ሲለፈፍ በፈገግታ ያዳምጣሉ )..ከፍተኛ
አድናቆት ያተረፈውንና የከፍላ ከተማችን የእድገት ማራቶን ሩጫ ከዘመነ ደርግ ውድቀት ቀኋላ' የሚለውን መጽሐፍ ጨምሮ አራት የግጥም መጻሕፍትን አሳትመዋል፤ ይሄን ያህል
ካልኩ እንዳላሰለቻችሁ ወደ ወ/ሮ ደርሳቤ ልምራችሁ...” ብሎ ማይኩን በአክብሮት ለሴትዬዋ
አቀበላት፡፡ (እፎይ! አንድ አዛ ለቀቅ ይላሱ እማማ ሩቅያ ሲተርቱ)
..ማይኩን ተቀብላ ጓ...ጓ አደረገችና (የፈረደበት ማይክ ተጠፍጥፎም፣ ያወሩትን ሁሉ ተቀብሎ አጉልቶም እሳዘነኝ)፡፡ እ..እኔ እንኳን የተባለውን ያህል ነኝ ብዬ አላምንም.፣ ምከንያቱም እንደ እኔ ዕድሉን ቢያገኙ እንኳን ኢትዮጵያን ዓለምን ጉድ የሚያስብሉ ሴቶች ከእናንተ መሀል አሉ ብዬ ስለማምን ነው…" አለች ወይዘሮ ደርባቤ፡፡
ጭብጨባ…! ቿቿቿቿቿቿቿቿቿ (ፈንዲሻው አለቀ ባአንዴ ጭብጨባው ደመቀኮ)
ከጎኔ የተቀመጠች ሴት “እውነት ነው" ብላ ጮኸት፡፡ (ዓለምን 'ጉድ' ከሚያስብሉት ሴቶች
መሐል እንዷ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ዞር ብዬ ሳያት በግራ እጇ ሞባይል ስልኳን፣ በቀኟ፣ መዳፏ
እስኪወጣጠር የዘገነችውን ፈንዲሻ ይዛ በስሜት ወደ መድረኩ እያየች ቁጭ ብድግ ትላለች፡፡
..ከፈንዲሻው ኮርሽም አደረገችለት፡፡)
ሴትዮዋ ግጥሟን ከማቅረቧ በፊት ሰላሳ ደቂቓ አወራች፡፡…እንዴት የወንዶችን ተፅዕኖ ተቋቁማ ታላቅ ገጣሚ' ለመሆን እንደበቃች፣ ሴቶች የርሷን ፈለግ ይዘው እንዲከተሏት፣(ብትወዱስ እኔን ምስሉ ዳርዳርታ)ይሄን ሁሉ አወራችና “እንዳላሰለቻትሁ” በማለት ወደ ግጥሟ ተሸጋገረች
(ገና ድሮ የሰለቸንውን !?)
ወደ መድረክ ስትወጣ መነፅሯኝ ቦታዋ ላይ ረስታው ስለነበር፣ " አቀብሉኝ”ስትሳቸው የእጅ ቦርሳዋን አራት ሰዎች ግራና ቀኝ ይዘው (ማሸርገዳቸው ስላበሳጨኝ የጨመርኩት ነው) አቀበሏት፡፡ቦርሳዋ ውስጥ አስር ደቂቃ ፈልጋ መነፅሯን ቤቷ መርሳቷን አረጋገጠች፡፡..እናም ወደ ብርሃኑ ቀርባ ግጥሟን ማንበብ ጀመረች፡፡
እንስራውን ሰብሮ ወሰዳት ልጅቱን(ርዕስ)
አረ አያ ደገፋው አንተ ትልቀ ሰው፣
አንዲት ፍሬዋን ልጅ ማስቸገርህን ተው!
ውሃ ልትቀዳ ወንዝ ስትሄድ፡
ቁመሽ አውሪኝ አልካት በግድ፣
ይሄ እልበቃ ብሎህ ሰው ጭር ሲልልህ
ሕፃኗን ደፈርካት እግዜር ይይልህ (ውይ ወንዶች አለች ከጎኔ ያለችዋ ባለ ፈንዲሻ)
ደሟን እያዘራች እቤቷ ስትደርስ፣
እንስራ ሰበርሽ ብለው ጎረፉት አያድርስ.
ደሞ በሌላ ቀን እንደገና አድብተህ..፣
አሁንም ደፈርካት አንተ ምን ዓይነት ሰው ነህ። ('በስማም ጭካኔ.ሌላዋ ሴት)
አዳራሹ ፀጥ ብሎ 'ግጥሙን' እያዳመጥን ድንገት ጎኔ ያለችው ሴት ጎርደምደምደም…ከሻሸሽ…
ስታደርግ ደንግጬ ዞሬ ተመለከትኳት፡፡ ተመስገን ፈንዲሻ እየበላች ነው፡፡…እኔማ በግጥሙ
ተመስጣ በስህተት ስልኳን ቆረጣጠመቻት ብዬ ነበር፡፡
ግጥሙ ለድፍን ሀያ ሰባት ደቂቃ ተነበበ፡፡ የግጥሙ የመጨረሻ ስንኞች
ፊስቱላ ተይዛ ስትንከራተት፣
ጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኛ አግኝታታ!
እዲሳባ በመኪና አመጣቻት.
መንግሥታችን በሠራው ዘመናዊ አስፓልት…?
አመሰግናለሁ !!
ቿቿቿቿቿቿቿቿቿ….(ታዳሚው ፈንዲሻውን ጨርሶ ነበር)
ለመውጣት ሳቆበቁብ አስተዋዋቂው እንዲህ አለ….
“ለሴቶች ቀን ያልሆነ ግጥም ለመቼ ይሆናል' በማለት ወይዘሪት ዘቢደር የወጣቶች ሊግ አትተባባሪ
ለግንቦት ሃያ አንብባው የተደነቀላትን 'ታታሪዋ ሥራ ፈጣሪ' የሚለውን ግጥምን ላቅርብ
ብላለችና እስቲ ወደ መድረክ…”
ተነስቼ ወጣሁ፡፡ ወደ ቤቴ ስሄድ ከኋላዬ የአስተዋዋቂው ድምፅ ይሰማኛል፡፡
"ወጣት ዘቢደር የእንስቷ ጣጣ የሚል በቅርቡ በታተመ የግጥም መድብሏ ከፍተኛ እውቅና
ያተረፈች ብርቱ ሴት ስትሆን...” እያለ ቀጠለ፡፡
ይሄ ቀበሌ ነዋሪው ሳይሰማ ማተሚያ ቤት ከፈተ እንዴ?.. እንዴት ነው ይሄ መድብል ማሳተም እንዲህ የቀሰለው ጎበዝ? ?!

👍24😁12👎1
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
አሮጌው ቤት
ከአርባ ዓመት በፊት እጅግ ጭር ያለ ሰፈር የነበረው ዛሬ ብዙ
ሕዝብ ይተራመስበታል፡፡ ገጠር መሆኑ ቀርቶ ወደ ከተማነት ተለውጧል፡፡ አካባቢው ዣን ቫልዣ ሲያውቀው ከፓሪስ ከተማ ወጣ ያለ ባላገር ነበር፡፡ዛሬ የከተማው አካል ሆኖአል፡፡ ብዙ ቤቶች ተሠርተዋል፤ መንገድም
ወጥቶለታል፡፡ ቢሆንም ግን የገጠርነት ስሜት አሁንም ይታይበታል፡፡ከመንገዱ ግራና ቀኝ ሳር በቅሎአል:: ቤቶቹም ቢሆኑ እስከዚህም የጸዱ አይደሉም፡፡ የፈረስ ገበያ ከዚያ አካባቢ ስለነበር የስፍራው ጽዳት ይህን
ያህል አያስደስትም::
ከዋናው መንገድ ትንሽ ራቅ ብሎ የሚታይ ባለአንድ ፎቅ አሮጌ ቤት
አለ፡፡ በሮቹ በምስጥ ስለተበሉ አልፎ አልፎ ቀዳዳ ይታይባቸዋል:: የቤቱ መስኮቶች በጣም ሰፋፊ ናቸው:: የመስኮቶቹ መስታወት አንዳንዶቹ ስለተሰበሩ
በካርቶን መሳይ ወረቀቶች ተሸፍነዋል :: መጋረጃዎቹም ቢሆነ
ከመበለዛቸውም በላይ ጫፍ ጫፋቸው ተቀዳደዋል:: ወደ ፎቅ በሚያስወጣው መሰላል ሲራመዱ ደረጃው እንደ መዚቃ መሣሪያ ያፍጮሃል:: በረት የመሰለ
ትልቅ ክፍል ከሩቁ ይታያል፡፡ የዚህ ክፍል ሀለቱም መስኮቶች ሰፋፊ ሲሆኑ በዚያ በኩል ወደ ውጭ በማየት በመንገድ የሚያልፈውን ማየት ይቻላል::የቤቱ ቁጥሩ 5052 ነው
ዣን ቫልዣ ከዚህ አሮጌ ቤት አጠገብ ሲደርስ ቆም ብሎ ቤቱን
አየው:: ጭልፊት የሚያሳድዳት ጫጩት የተሰወረ ከለላ እንደምትፈልግ ሁሉ እርሱም ከነዣቬር ለመሰወር ከለላ ይፈልጋል:: የዚህ ቤት አቀማመጥ
ደግሞ በጣም የተሰወረ ስለነበር የሚፈልገውን ያገኘ መሰለው፡፡ ከኪሱ ውስጥ ቁልፍ አውጥቶ በሩን ከፈተው:: ከገባ በኋላ መልሶ ዘጋው:: ኮዜትን ታቅፎ በደረጃው ወደ ፎቅ ወጣ፡፡ ደረጃውን ወጥቶ ሲጨርስ ሌላ ቁልፍ ከኪሱ አወጣ፡፡ የተቆለፈውን በር ከፍቶ ወደ አንድ ክፍል ገባ፡፡
ስፋ ካለ ክፍል ወለል ላይ ትልቅ ፍራሽ ተዘርግቷል፡፡ ጥቂት
ቦታ ወንበሮችና ጠረጴዛም አለ፡፡ የእሳት ማንደጃ ከአንድ ጥግ ይታያል:: አንድ ትንሽ የልጅ አልጋም አለ፡፡ ዣን ቫልዣ ቀስ ብሎ ኮዜት ሳትነቃ ከትንሹ አልጋ ላይ አስተኛት::
በሩን መልሶ ከዘጋ በኋላ ሻማ አበራ:: የመንገዱ መብራት ክፍሉን
ያሳይ ስለነበር ሻማ እስካበራ ድረስ በጨለማ አልተንገዳገደም:: በአለፈው ቀን እንዳደረገው ሁሉ ኮዜት ተኝታ ሳለ ዐይኑን ከዐይንዋ አላነሳም:: ለረጅም ጊዜ ኣፍጥጦ ተመለከታት:: ኮዜት ከማን ጋርና የት እንደተኛች ሳታውቅ ለብዙ ሰዓት እንቅልፍዋን ለጠጠች::
ዣን ቫልዣ ጎንበስ ብሎ እጅዋን ሳማት:: ከዘጠኝ ወር በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ እንቅልፍ ወስዶአት ሳለ የእናትዋን እጅ ስሞ ነበር፡፡
ተመሳሳይ የሆነ የሀዘኔታና የጭንቀት ስሜት ተሰማው:: ኮዜት ከተኛችበት አልጋ አጠገብ ተንበረከከ፡፡
ወገግ ብሎ ነግቷል:: ግን ልጅትዋ አሁንም እንቅልፍ እንደወሰዳት
ናት። ከባድ እቃ የጫነ ጋሪ በዚያ ሲያልፍ ያንን አሮጌ ፎቅ ቤት አነቃነቀው፡፡ ኳኳታው በኃይል ስለነበር እንኳን የትኛን የሞተን ይቀሰቅሳል ማለቱ የድምፁን ብርታት መግለጽ እንጂ ማጋነን አይሆንም::
«እመት እመቤቴ» አለች ኮዜት ፈንጠር ብላ ከአልጋው እየተነሳች::
ቀጠለችና ደግሞ መጣሁ መጣሁ» ስትል ጮኸች:: ዓይንዋን ሳትገልጥ ካልጋው ዘላ ወረደች።
እየተንጠራራች ወደ ግድግዳው ሄደች።
«ወይ ጣጣ፤ መጥረጊያው የት አለ!» አለች::
ኣሁን ዓይንዋን ገልጣለች:: በፈገግታ ያጌጠ የዣን ቫልዣን ፊት
ተመለከተች::
«እህ! ለካስ…» አለች ልጅትዋ ፧ «እንደምን አደሩ ጌታዬ::»
ቶሉ ብሎ አካባቢውን መላመድና ባለው መደሰት የልጆች ባህርይ
ነው:: ተደሳች ሁነው ሰው ያስደስታሉ፡፡
ኮዜት ካተሪንን ከአልጋዋ ስር አየቻት፡፡ ወዲያው ብድግ አድርጋ
አቀፈቻት፡፡ ከአሻንጉሊቱ ጋር እየተጫወተች ዣን ቫልዣን የመዓት ጥያቄ ጠየቀችው:: የት ነበረች? ፓሪስ ትልቅ ከተማ ነው? አሁን መዳም ቴናድዬ ከዚህ አይመጡም? ከዚህ የሚስስ ቴናድዬ ቤት ምን ያህል ይርቃል?
ሌላም፧ ሌላም፡፡ በመስኮቱ ወደ ውጭ አይታ «እንዴት ያምራል፤ እንዴት ደስ ይላል» ስትል ተናገረች::
የነበረችበት ሁኔታ በመጠኑም ቢሆን ያስፈራ ነበር፡፡ ነገር ግን
እርስዋ ነፃ የወጣች መሰላት::
«ቤቱን ልጥረግ?» ስትል ጠየቀች::
«የለም፧ ተጫወች» ሲል ዣን ቫልዣ መለሰላት::
ስትጫወት ቀኑ አለፈ:: ስላለችበት ሥፍራም ሆነ ሁኔታ ለማወቅ
ራስዋን ሳታስጨንቅ ከአሻንጉሊትዋ ጋርና ከጓደኛዋ ጋር እየተጫወተች ደስ ብሎአት ነበር የዋለችው::
በሚቀጥለው ቀን ጎሕ ሲቀድ እንዳለፈው ቀን ኮዜት ስትነቃ ለማየት ዣን ቫልዣ ከአልጋው አጠገብ ሲቀመጥ አዲስ ስሜት ተሰማው፡፡ ዣን ቫልዣ ከዚያ በፊት ምንም ነገር አፍቅሮ አያውቅም፡፡ ትዳር ሳይዝ፣ ልጅ ሳይወልድ ፤ ሴት ሳያፈቅርና የልብ ጓደኛ ሳያበጅ ለሃያ አምስት ዓመት ብቻውን ነው የኖረው:: እስር ቤት ሆኖ ኑሮው የጨለማና የስቃይ ነበር፡፡
ዣን ቫልዣ እስር ቤት ከመግባቱ አስቀድሞ ከቤቱ ሲወጣ ልቡ በተስፋ የደነደነ፤ ሐሞተ ሙሉ ሰው ነበር:: እህቱና ልጆችዋ ከሕሊናው ጨርሰው
ባይፋቱም በአሳብ የሚታዩት እጅግ ተንነው ሲሆን እነርሱን ለማግኘት ብዙ ጥረት አደረገ፡፡ ግን አላገኛቸውም:: ጊዜ እንደሚሽረው እንደማንኛውም ነገር ከጊዜ በኋላ ግን ረሳቸው:: ሌሎችም በወጣትነት ዘመኑ የሚያውቃቸው
ነገሮች ሁሉ እንደዚሁ ከሕሊናው ውስጥ መንምነው ጠፍተዋል፡፡
ኮዜትን አግኝቶ ከዚያ የስቃይና የመከራ ኑሮ ሲያወጣትና ይዞአት
ሲሄድ ስሜቱ እጅግ ይነካል፡፡ ይህም ለሰው ልጅ የነበረውን ፍቅር ቀሰቀሰበት። የፍቅሩ ጽናት ከዚህች ልጅ ዙሪያ ተሰባሰበ፡፡ ወደ ኮዜት አልጋ ጠጋ ብሎ ሲመለከታት ልቡ በደስታ ፈካ:: እናት ለልጅዋ ፍቅር እንደምትብረከረክ ሁሉ እሱም በዚህች ልጅ ፍቅር መዋጡ ገረመው፡፡
የፍቅሩ ግለትና የሀዘኔታው ብዛት ሊገባውና በቃላት ሊገልጸው ከሚችለው እርሱ ሃምሣ አምስት ዓመቱ ሲሆን እርስዋ ስምንት ዓመትዋ ነው:: ስለዚህ ፍቅሩ ግሪኮች አጋፔ ብለው የሚጠሩት እናት ለልጅዋ ያላት ፍቅር
ዓይነት እንጂ የሌላ አልነበረም፡፡
በሕይወት ዘመኑ ለሁለተኛ ጊዜ የሕይወት ተመስጦአዊና አስጨናቂ ትርኢት አየ፡፡ ከእስር ቤት ሲወጣ ያገኛቸው ጳጳስ የሕይወቱን አድማስ
ያሰፉለትና የሕይወት ጣዕም ሕያቀደዱለት የመጀመሪያው ፍጡር ናቸው፡፡
ኮዚት ደግሞ ተጨማሪ የፍቅር ጎሕ ከፈተችለት፡፡ ይህንኑ እያሰላሰለ ጥቂት ቀናት አለፉ::
አሳዛኝዋና ምስኪንዋ ኮዜትም ቢሆን ሳይታወቃት እየተለወጠች
ነበረ፡፡ እናትዋ ጥላት ስትሄድ ጨቅላ ልጅ ነበረች፡፡ በዚያን ጊዜ ምን ትመስል እንደነበር ለማስታወስ አትችልም፡፡ ልጆች እንደ ሐረግ ካገኙት ላይ እንደሚጠመጠሙ ሁሉ እርስዋም ከሰዎች ላይ ተጠምጥማ ለማፍቀር ብትሞክርም ሰዎች የማፍቀር እድል አልሰጥዋትም ነበር፡፡ እነሚስተር ቴናድዬ ፤ ልጆቻቸውና ሌሉችም ቢሆኑ ፍቅር አላሳይዋትም: ከቤታቸው
የነበረውን ውሻ ትወደው ነበር፡፡ ግን እሱም ሞተ፡፡ ውሻው ከሞተ ጀምሮ እንኳን ሰው የቤት እንሰሳም ቢሆን አላቀረባትም:: ስለዚህ ጥፋቱ የእርስዋ ባይሆንም ገና በስምንት ዓመትዋ ለሰው ፍቅር አልነበራትም:: ቢወድዋት

👍12
ግን ትወድ ነበር፤ ምክንያቱም የማፍቀር ኃይል ስለነበራት ነው፡፡ ያንን ደግ ሽማግሌ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ነው ያፈቀረችው:: ፍቅሯ በየእለቱ
እየዳበረ ሄደ፡፡ ከዚያ በፊት የማታውቀው ስሜት ተጠናወታት፡፡ ለእርስዋ ደጉ ጓደኛዋ አንድ ምስኪን ሽማግሌ ሳይሆን እጅግ የተዋበና ዕፁብ፣ ድንቅ
የሆነ ዣን ቫልዣ የተባለ ሰው ነው::
በዣን ቫልዣና በኮዜት መካከል ያለው የእድሜ ልዩነት በሞላ ጉደል ሃምሣ ዓመት ቢሆንም በሕይወት ዘመናቸው የደረሰባቸው ስቃይና መከራ ፤ምንም እንኳን ርዝማኔው ቢለያይም፧ አሳዛኝነቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህም
አንድ እንዲሆነና እንዲቀራረቡ ምክንያት ሆናቸው:: የኮዜት ውስጣዊ ስሜት የሚመኩበት አባት ሲፈልግ የዣን ቫልዣ ፍላጎትና ምኞት ደግሞ
የደረሰበትን የሚያቃልልለት ልጅ ማግኘት ነበር፡፡ ስለዚህ የሁለቱ መገናኘት ማለት የፍላጎትና የስሜት መርካት ማለት ስለነበር ነፍሶቻቸው እርስ በእርስ የሚፈላለጉ መሆናቸውን አወቁ፡፡ ስሜታቸውን ለማርካት ተቃቀፉ፡፡
በቃላት ኃይል ሁኔታውን አጥርቶ መግለጽ ኣይቻልም እንጂ ዣን
ቫልዣ ማለት ሞተ ተብሉ የተለቀሰለት አባትዋ ሲሆን ኮዜት ማለት ደግሞ የሙት ልጅ ናት፡፡ ስለዚህ ነው ዣን ቫልዣ የኮዜት እውነተኛ አባት ባይሆንም የመንፈስ አባትዋ ሊሆን የቻለው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ኮዜት
በጨለማ ውሃ ለመቅዳት በሄደችበትና በሞትና በሽረት መካከል በነበረችበት ሰዓት ሊረዳትና ባልዲውን ከእጅዋ ወስዶ ሲሸከምላት ከየት መጣ ሳይባል በድንገት ብቅ ያለው ፍጡር መለኮታዊ ኃይል የሰጣት አባትዋ ነው::
ዣን ቫልዣ ለመደበቂያ ብሎ የመረጠው ቤት ተስማሚ ነበር::
ከዚያ ሥፍራ ማንም ያገኘኛል ብሎ የሚጠራጠሩት ወይም ያጋልጠኛል ብለው የሚፈሩት አልነበረም፡፡ ዣን ቫልዣ ቤቱን እንዳለ አልተከራየውም::
ምድር ቤቱን ነጋዴዎች እቃ ጭነው የመጡባቸውን ከብቶች ያሳድሩበታል::ፎቁ ላይ ብዙ ክፍሎች ያሉት አፓርትመንት ቢሆንም ከእነርሱና ከአንዲት
አሮጊት በስተቀር ሌላ ሰው አልነበረበትም፡፡ አርጊትዋም ብትሆን የዣን ቫልዣ ሠራተኛ ነበረች፡፡ የተቀሩት ክፍሎች ባዶ ናቸው:: አሮጊትዋ የቤቱም ጠባቂ ሁና ትሠራ ስለነበር የነበሩበትን ክፍል ያከራየቻቸው ይህቺ ሴት ናት፡፡ እንደ አጋጣሚ ቤቱን የተከራዩት የገና እለት ነበር፡፡ ዣን ቫልዣ ራሱን ሲያስተዋውቅ ከሩቅ አገር የመጣ፤ ክስረት
የደረሰበት ነጋዴና የሚኖረውም ከልጅ ልጁ ጋር እንደሆነ አድርጎ ነው::የስድስት ወር የቤት ኪራይ በቅድሚያ ከፈለ፡፡ ቀኑ አልፎ ሳምንት፧ሳምንት አልፎ ወራት ተተኩ፡፡ ኮዜትና ዣን ቫልዣ ከዚያ አስቀያሚ ቤት ደስ እያላቸው ኖሩ፡፡
በጠዋት ተነስቶ እንደሚያዜም ወፍ ኦክትም በጠዋት እየተነሳች
ትጫወታለች፤ ትስቃለች፤ ትዘፍናለች:: ኣንዳንዴ ዣን ቫልዣ እጅዋን እየያዘ ያንሸራሽራታል፡፡
ሕይወትዋን ሙሉ በግሣዔና በድብደባ ያሳለፈች ልጅ አሁን ኑሮ በድንገት ስለተለወጠላት እንዳንዴ ግር እያላት እንደማፈር
ትላለች::
ኮዜት እንደ ድሮው የተቦጫጨቀ በትቶ አትለብስም:: እንደ ሀዘነተኛ
ጥቁር ነው የምትለብሰው:: ጥቁር ይሁን እንጂ ማራኪ ልብስ ስለሆነ
አምሮባታል፡፡ ከድህነት ወጥታ የኑሮን ምንነት እየቀመሰች ነው፡፡
ዣን ቫልዣ ፊደል ያስቆጥራት ጀመር:: ራሱ ፊደል የቆጠረው እስር ቤት ሆኖ ነው:: ኮዜትን ማስተማርና መጠበቅ የዣን ቫልዣ የእለት ተእለት ተግባር ሆነ፡፡ አንዳንዴ ቁጭ ብለው ሲጫወቱ ስለእናትዋ ያወጋታል፡፡ በጸሎትዋ እንድታስባት ያስተምራታል:: እሷም «አባባ» እያለች ነው የምትጠራው፡፡ ይህ እንግዲህ የራስዋ ግምት እንጂ የነገራት አልነበረም።
ዣን ቫልዣ ኮዜትን አግኝቶ ባፈቀራትና በራራላት ጊዜ የነበረበትን ሁኔታ መግለጽ ተገቢ ይሆናል፡፡ ኮዜትን ያገኛት የሰውን ልጅ ክፉነት፧ የህብረተሰብን ጭካኔና ችግር፤ እንዲሁም የዓለምን አንዱን ገጽታ ብቻ
ባየበት ወቅት ነበር፡፡ የሴቶችን ችግር በፋንቲን መከራና ስቃይ ተጠልለና ተጠቃሎና
የባለሥልጣንን ኃይል በዣቬር ተመስሎ በቀረበበት፣ ለሰው ደግ እሠራለሁ በማለቱ እንደገና እስር ቤት እንዲገባ በተወሰነበትና በዚህም የተነሳ እጅግ በተማረረበት ወቅት ነበር
ኮዜትን ያገኛት ምንአልባትም እኛያ ህይወቱን የለወጡት ጳጳስ ትዝታ በመነመነበትና «እንደገና ተመልሰህ ወደ ተንኮል ፧ ክፋትና ምቀኝነት ኑሮ ተመለስ» የሚል ስሜት ሕሊናው ውስጥ በተቀረጸበት ሰሞን ሊሆን ይችላል ኮዜትን ያገኛት፡፡ በዚህ ወቅት ነው ፍቅር በድንገት ብቅ ብሎ ሕይወቱን እንደገና የለወጠውና የመንፈስ ኃይል የተጎናጸፈው::
ከኮዜት ይበልጥ ጉልበትና አቅም ስለነበረው ኮዜትን ጠበቃት፤ ተንከባከባት:: እርስዋም የበለጠ ብርታት ኣጎናጸፈችው፡፡ ምስጋና ለዣን ቫልዣ ይሁንና
እርስዋም ቀጥ ብላ መራመድ ቻለች፡፡ ምስጋና ለእርስዋም ይሁንና ሕይወቱን ከቀና ጎዳና እንዲያስገባ አደረገችው፡፡ እርሱ እንደደገፋትና እንደረዳት ሁሉ
እርስዋም ደገፈችው፧ ረዳችው..

👍19❤6
#የጉድ_ሀገር ...
ከረሞናታ ልቤ
ወደድኩኝ በል ብቻ ፣ዳግሞ ተካልቤ፤
ከረምናታ ስሜ
ናፈቀችኝ በላ ፤ተጠገነ ቅስሜ።
ያቺን የቀድሞዋን
ከመቼው ወደሀት፣
ከመቼው አጣሀት፤
እስቲ ሰከን በል፤
ሰው ማፍቀር አይቀድምም ፣ልብን ከማባበል።
እባክህን ልቤ ፣ራስህን ቆንጥጥ፤
የትም አትዳረስ ፣እነደተረሳ ጥጥ።
የሄድክ የነጎድከው ፣ አዲስ ገላ ወደህ
እኔን ለማን ክደህ።
አልኖርሞ ያለሷ ያልከኝ
እኔን የት አረከኝ።
እስቲ ሰከን በል ፤ በባለፈው ቆዝም፤
ያልተረጋጋ ግንድ ፣ሥር አፈር አይዝም።
በማጣትህ እዘን፤
ነገን አያቆምም ፣ ዛሬ ሳይመዘን።
የትናንትን ፍቅር ፣ ሳታስታምም ቀርተህ
ከሴት ተኛኹ አትበል ፤ከሐዘን ተኝተህ።
የመለየት ጥጉን
ሐዘን ሳትቀመጥ ፣የትሞ አትሰደድ፤
ማስተዛዘኛ እንጂ
ፍቅር አይባልሞ ፣ ከሕመሞ ቀጥሎ ፣ የተገኘ መውደድ።
ከረምናታ ልቤ!
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
ከረሞናታ ልቤ
ወደድኩኝ በል ብቻ ፣ዳግሞ ተካልቤ፤
ከረምናታ ስሜ
ናፈቀችኝ በላ ፤ተጠገነ ቅስሜ።
ያቺን የቀድሞዋን
ከመቼው ወደሀት፣
ከመቼው አጣሀት፤
እስቲ ሰከን በል፤
ሰው ማፍቀር አይቀድምም ፣ልብን ከማባበል።
እባክህን ልቤ ፣ራስህን ቆንጥጥ፤
የትም አትዳረስ ፣እነደተረሳ ጥጥ።
የሄድክ የነጎድከው ፣ አዲስ ገላ ወደህ
እኔን ለማን ክደህ።
አልኖርሞ ያለሷ ያልከኝ
እኔን የት አረከኝ።
እስቲ ሰከን በል ፤ በባለፈው ቆዝም፤
ያልተረጋጋ ግንድ ፣ሥር አፈር አይዝም።
በማጣትህ እዘን፤
ነገን አያቆምም ፣ ዛሬ ሳይመዘን።
የትናንትን ፍቅር ፣ ሳታስታምም ቀርተህ
ከሴት ተኛኹ አትበል ፤ከሐዘን ተኝተህ።
የመለየት ጥጉን
ሐዘን ሳትቀመጥ ፣የትሞ አትሰደድ፤
ማስተዛዘኛ እንጂ
ፍቅር አይባልሞ ፣ ከሕመሞ ቀጥሎ ፣ የተገኘ መውደድ።
ከረምናታ ልቤ!
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍11❤8
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሦስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
...እነዣን ቫልዣ ከነበሩበት አካባቢ ከቤተክርስቲያን ደጃፍ የማይጠፋ
አንድ ለማኝ ነበር:: ዣን ቫልዣ በዚያ ባለፈ ቁጥር ሣንቲም ይጥልለታል፡፡ለማኙን የሚመቀኙ የመንደሩ ሰዎች ሰላይ ነው እያሉ ያወሩበታል፡፡ አልፎ አልፎ ዣን ቫልዣ ቆም እያለ ያዋራዋል፡፡ ግን ሲያዋራው ለማኙ ቀና አይልም::
አንድ ቀን ማታ ዣን ቫልዣ በዚያ ሲያልፍ ለማኙ ዘወትር
ከሚቀመጥበት ቁጭ ብሎ ያየዋል:: ያን እለት ኮዜት አብራው አልነበረችም::ሰውዬው ከተቀመጠበት አጠገብ የመንገድ መብራት በርቶ ስለነበር በጉልህ
( ይታያል:: ዣን ቫልዣ እንደተለመደው ወደ እርሱ ሄዶ ሣንቲም ሰጠው::ለማኙ ቀና ብሎ በማየት አፈጠጠበት:: ወዲያው ወደ መሬት አቀረቀረ፡፡
ፊቱን ሲያየው ያ ዘወትር ጎብጦ እና የሰባ ዓመት ሽማግሌ መስሉ
የሰውዬው አመለካከት ቅጽበታዊ ስለነበር ገዣን ቫልዣን አስደነገጠው:: ይቀመጥ የነበረው ሰው ቀደም ሲል የሚያውቀውና የሚከታተለ ክፉ ሰው እንደሆነ ጠረጠረ፡፡ በዚህ ጊዜ ጥቅጥቅ ካለ ጫካ ነብር ያየ መሰለው::
መናገር ወይም መሮጥ ወይም መቆም ተሳነው:: ለማኙን አተኩር ከማየት ግን አልቦዘነም::
«ወይ ጉድ!» አለ ዣን ቫልዣ እርስ በራሱ ሲነጋገር፡፡ «አበድኩ፤
በሕልሜ መሆን አለበት! ሊሆን አይችልም!» አለ እየተጨነቀና እየተከዘ ወደ ቤቱ ተመልሶ ሄደ፡፡ ያየው ለማኝ ዣቬር እንደሆነ ራሱም ማመን አቃተው:: በ ቅዠት እንጂ እውነት አይሆንም ሲል ደመደመ፡፡
ያን እለት ማታ ያየው ሰው ዣቬር እንደሆነ ለማወቅ እንዲችል
ስላላናገረው በጣም ቆጨው:: በሚቀጥለው ቀን ለዓይን ያዝ ሲያደርግ ወደዚያ ሥፍራ ሄደ፡፡ ለማኙ ከተለመደው ሥፍራ ጸሎት የሚያደርስ መስሎ ቁጭ ብሎአል። እንደተለመደው ሣንቲም እየጣለለት «ታዲያስ
ደህና አመሸህ» ሲል ሰላምታ ሰጠው። ለማኙ «እግዚአብሔር ይስጥልኝ ያስንብትልኝ» ብሎ መልስ ከሰጠ በኋላ መፅዋቾቹን ለማየት አሁንም ቀና አለ፡፡ እውነትም ጠዋሪ ያጣ የሽማግሌ ለማኝ እንጂ ዣቬር እንዳልነበረ
አረጋገጠ፡፡
«እኔስ ምን ማለቴ ነው? አሁን ዣቬር ከየት መጣ ብዬ አሰብኩ? ወይ ጉድ! ዓይኔ እየደከመ ነው?» በማለት ካሰላሰለ በኋላ ነገሩን ረሳው::
ከጥቂት ቀናት በኋላ፤ ከምሽቱ ወደ ሁለት ሰዓት ገደማ ይሆናል፤
ከክፍሉ ውስጥ ኮዜትን የእጅ ጽሑፍ እያለማመደ ሳለ የቤቱ ዋና መግቢያ ያለወትሮው ተከፍቶ ሲዘጋ ሰማ:: እንግዳ ነገር ሆነበት:: ከቤቱ ውስጥ የሚኖሩት እሱ ራሱ፤ ኮዜትና አሮጊትዋ ናቸው:: አሮጊትዋ እንደሆነ ሻማ ለመቆጠብ ስትል ገና ሳይጨልም ነው የምትተኛው:: ኮዜት ዝም እንድትል ምልክት ሰጣት:: በደረጃው ሰው ለመውጣቱ ኮቴ ሰማ፡፡ ምናልባት አሮጊትዋ
ትሆናለች ሲል አሰበ፡፡ አሁንም አዳመጠ፡፡ ከበድ ያላ ኮቴ ስለነበረ የወንድ ኮቴ መሰለው:: ግን አሮጊትዋ የምትጠቀምበት መጫሚያ እኮ በጣም ከባድ
ነው። ሆነም ቀረም ዣን ቫልዣ ሻማውን አጠፋ፡፡
ኮዜት እንድትተኛ ዝቅ ባለ ድምፅ ከነገራት በኋላ ግምባርዋን ሳማት፡
የኮቴው ድምፅ ፀጥ አለ። ዣን ቫልዣ ከነበረበት ሳይነቃነቅ ዝም ብሎ ከቆየ በኋላ ፊቱን ወደ በር ኣዞረ፡፡ አካባቢው ፀጥ እንዳለ ጥቂት ጊዜ አለፈ፡፡ በበሩ
የቁልፍ ቀዳዳ የሻማ መብራት ጭላንጭል አየ:: በዚህም ከበሩ አካባቢ በውጭ በኩል አንድ ሰው ሻማ ይዞ እንደቆመ አረጋገጠ፡፡
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በቁልፉ ቀዳዳ ይታይ የነበረው ጭላንጭል ጠፋ፡ ግን ኮቴ አልተስማም:: ዣን ቫልዣ ልብሱን ሳያወልቅ ከአልጋው ላይ
ተጋደመ፡፡ ሆኖም ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ አልወሰደው፡፡
ሊነጋጋ ሲል ትንሽ እንዳሸለበው በር ተከፍቶ ኖሮ በሩ ሲንጣጣ ስ
ቀስቀሰው:: ሌሊት የሰማው ዓይነት ኮቴተ ተንቀሳቀሰ:: የኮቴው ድምፅ በመቃረቡ እየጉላ ሄደ፡፡ ብድግ ብሎ ወደ በር በመሄድ በበሩ ቁልፍ ቀዳዳ ወደ ውጭ ተመለከተ፡፡ ሰፊ ቀዳዳ ስለነበር በደምብ ያሳያል፡፡ አንድ ሰው
በዣን ቫልዣ ክፍል በራፍ አለፈ፡፡ በሩ አጠገብ ሲደርስ አልቆመም፡ ብዙ ብርሃን ስላልነበረ የሰውዬውን ማንነት ለመለየት አልቻለም። የሰውዬው ሙሉ ቁመና ከጀርባው ባየ ጊዜ በጣም ረጅም ሰው መሆኑን ተገነዘበ፡፡
ቅርጹንና የለበሰውን ልብስ ከዣቬር ጋር ሲያስተያየው ተመሳስሉበት፡፡
የመስኮቱን መጋረጃ በመግለጥ በመስኮት ሰውየውን ለመየት ለመመለስ ድፍረት ስላነሰው ተወው፡፡ ይህ ሰው በሩን በቁልፍ ከፍቶ እንደገባ አልተጠራጠረም:: ታዲያ የበሩን ቁልፍ ማን ሰጠው? ምንድነው ነገሩ?
ከጠዋቱ በአንድ ሰዓት መቶ ፍራንክ ከቦርሳው አውጥቶ ካጣጠፈው በኋላ ኪሱ ውስጥ ጨመረው፡፡ እጁን ከኪሱ ሲያወጣ ሣንቲሞች ከኪሱ ሾልከው መሬት በመውደቃቸው አስደነገጡት፡፡ ወደ ምድር ቤት ወርዶ
በድብቅ ውጭውን ተመለከተ፡፡ ጭር ብሏል፤ ማንም በዚያ አካባቢ አይታይም፡፡ ሆኖም በአካባቢው ብዙ ዛፎች ስለነበሩ ማን እንደትደበቀ ለማየት አይቻልም:: ወደ ክፍሉ ተመለሰ፡፡ «ኮዜት ተነሽ» አለ። እጅዋን
ይዞ ተያይዘው ከቤታቸው ወጡ፡፡
በጨለማ የሚሸፍት ድምፅ
የለሽ ውሻ
ዣን ቫልዣ ዋናውን መንገድ ትቶ በመንደር ውስጥ ተጓዘ፡ መንደር
ቆየ ውስጥ የሚታጠፍ መንገድ ካጋጠመው ቀጥታውን ትቶ ይታጠፋል፡፡
ገበሩ ይህንንም ያደረገው ምናልባት የሚከተለው ሰው ካለ ዱካውን ለማጥፋት
ነበር፡፡
ጨረቃዋ ሙሉ ነበረች:: ይህም በመሆኑ ዣን ቫልዣ ደስ አለው።
የጨረቃው ብርሃን ሁሉንም ያሳይ ስለነበረ በተለይ ራቅ ብሎ ሲሄድ ሰው እንዳልተከተለው አረጋገጠ፡፡ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ገደማ በ14ተኛ ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ አለፈ:: ከጣቢያው ጥቂት እንደራቀ ማጅራቱን ከበደው፡፡
ፊቱን ወደኋላ አዙሮ ተመለከተ፡፡ የጣቢው መብራት ወገግ ብሉ ይበራ ስለነበር ሦስት ሰዎች እንደሚከተሉት ተገነዘበ፡፡
«ትንሽ ፈጠን በይ ልጄ» አላት ኮዜትን፡፡ ከዚያ አካባቢ ቶሎ ለመጥፋት ፈጠን ኣለ:: ጥቂት እንደተጓዙ ከአደባባይ ደረሱ:: ጨረቃዋ ከፍ በማለትዋ የአደባባዩ አካባቢ ወለል ብሎአል፡፡ እነዚያ ሦስት ሰዎች እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ዣን ቫልዣ ጨለምለም ካለ ከአንድ በር አጠገብ ተሸጉጠ፡፡
ብርሃን ስለነበር ሰዎቹ በኤደባባዩ ሲያልፉ ሊያያቸው ይችላል:: ሰዎቹ ጊዜ አልወሰዱም፤ ወዲያው ከአደባባዩ ደረሰ፡፡ አሁን አንድ ሰው ተጨምሮ አራት ሆኑ፡፡ አራቱም ዱላ ይዘዋል፡፡ ሁሉም ግዙፍ ሰውነት ስለነበራቸው በጣም ያስፈራሉ፡፡
ከአደባባዩ ሲደርሱ ቆም ብለው ይወያዩ ጀመር፡፡ ከመካከላቸው
አንዱ መሪያቸው ሳይሆን አልቀረም፤ ዣን ቫልዣ ወደሔደበት አቅጣጫ አመለከተ፡፡ ሌላው ደግሞ ወደ ሌላው አቅጣጫ በጣቱ በመጠንቆር አሳየ::
የቡድኑ መሪ ወደ አመለከተበት አቅጣጫ ፊቱን ሲያዞር የጨረቃ ብርሃን ከፊቱ ላይ በማረፉ በግልጽ ታየ:: መሪው ዣቬር እንደነበር ዣን ቫልዣ አወቀው::
«ወዴት ይሄድ ይሆን» ሲል ዣን ቫልገ አሰበ፡፡ ሰዎቹ ቆመው
ሲከራከሩ እርሱ ለማምለጥ ፈልጎ ከተደበቀበት ወጥቶ ሳይታይ በአቋራጭ መንገዱን ቀጠለ፡፡ መንገዱ ላይ ሰው አልነበረም:: ፈጠን ፈጠን አለ፡፡ወደኋላ ዞር ብሎ ተመለከተ:: ማንም የለም::
ድልድይ ካለበት ደረሰ፡፡ አንድ ትልቅ እቃ የተጫነ ጋሪ ድልድዩን
ቀስ ብሉ ሲያቋርጥ እየ:: ጋሪው እርሱ ወደሚሄድበት አቅጣጫ ነበር የሚሄደው:: ጋሪውን ከለላ በማድረግ መንገዱን ቀጠለ፡፡ ጥቂት ከተጓዘ በኋላ ፊቱን አዙሮ ወደኋላ ተመለከተ:: ከሩቁ የአራት ሰዎች ጥላ አየ፡፡ ሰዎቹ ግን በአካል አልታዩትም::

👍17😢4👏2
አዳኝ እንደደረሰባት ድኩላ ሰውነቱ ተረበሸ፧ ተስፋው መነመነ:: ብዙ
ዛፍ ከነበረበት ሜዳ ከደረሰና መንገዱን ካሳበረ እንደሚያመልጣቸው ያውቃል።
ከአንድ ቀጭን መንገድ ስለደረሰ በዚያ ታጥፎ ሩጫውን ቀጠለ፡፡ ጥቂት እንደተጓዘ ከመንታ መንገድ ደረሰ:: ወደቀኝ ይታጠፍ ወይስ ወደ ግራ፣ አላወላወለም፧ ወደ ቀኝ ታጠፈ፡፡ ለምን?
ምክንያቱም ወደ ግራ የሚታጠፈው መንገድ ነዋሪ ወደሌለበት ወደ ገጠር ነበር የሚወስደው::አልፎ ኣልፎ ወደኋላ እየዞረ ያያል፡፡ ሁልጊዜም የሚጓዘlው ብዙ ብርሃን የሌለበትንና ጨለምለም ያለውን መርጦ ነው:: ከኋላ ትቶት የመጣው መንገድ ቀጥ ያለ ነበር:: ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ ወደኋላ ዞር ሲያይ ማንም አልተከተለውም:: ምድሪቱ አሁንም ጸጥ እንዳለች ናት:: ትንሽ
ተንፈስ አለ፤ ጉዞውን ግን አላቆመም:: ጥቂት እንደተጓዘ አሁንም ፊቱን ቢያዞር በሩቁ የሚነቃነቅ ነገር ያየ መሰለው::
ፈብን፧ ፈጠን ብሎ በመሄድ የሚታጠፍ መንገድ ፈለገ::
የሚከተሉትን ሰዎች ለማሳሳት ነበር፡፡ አንድ ትልቅ ግንብ ካለበት ደረሰ: የተጓዘበት ጠባብ መንገድ ግንብ ከነበረበት ሲደርስ አለቀ:: የግንቡን ጥግ ይዞ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ማለፍ ይቻላል:: አሁንም ዣን ቫልዣ መወሰን ነበረበት፤ ወደ ቀኝ ወይስ ወደ ግራ? ወደ ቀኝ ተመለከተ፡፡ በሩቁ ጠበብ ያለ ጉዳና ታየው:: ከመንገዱ ባሻገር ከነበሩ ፎቅ ቤቶች አጠገብ ያሉት ዛፎች መሸሸጊያ ሊሆኑ ይችላሉ።
ከዚያ ቢደርስ ራሱን ለመደበቅ የሚችል መሰለው::
ከቀጭኑ መንገድ ሲደርስ አሁንም መንገዱ ለሁለት ተከፈለ:: ወደግራ
ሲመለከት አንድ ትልቅ ነጭ ቀለም የተቀባ የግንብ አጥር አየ:: ግንቡ ወደ ሁለት መቶ እርምጃ ቢርቅ ነው፡፡ ግራው መንገድ የሚሻል መሰለው::ወደ ግራ ለመታጠፍ እንደወሰነ አንድ ሀውልት ወይም ሰው መሆነ
የሚያጠራጥር ነገር በሩቁ አየ:: እርሱን ለመከታተል ትእዛዝ ደርሶት
የሚጠባበቅ ሰው መሰለው:: ዣን ቫልዣ ደነገጠ፡፡ መንገዱን ዘግቶ ሰው እንደሚጠብቀው ተረዳ::
ምን ይሻላል?
ወደ ኋላ ለመመለስ ጊዜ የለም:: ዣቬር ከነሠራዊቱ ቶሎ ደርሶ
እንደሚይዘው ጠረጠረ:: ምናልባትም ተቃርበዋል:: እስካሁንም ያጓተተው
የመንገዱ ጠመዝማዛነትና መከፋፈል ሊሆን ይችላል፡፡ ፖሊስ እንደመሆኑ መጠን መግቢያ መውጫውን በሚገባ ያውቀዋል፡፡ በየማለፊያው ሰው አስቀምጦ ይሆናል:: ወደ ሰማይ የተበተነ አዋራ ወደየአቅጣጫው እንደሚተን ሁሉ የዣን ቫልዣም አሳብ እንዲሁ ተበተነ፡፡ ወደፊት መራመድ ማለት ቆሞ ከሚጠብቀው ሰው እጅ መውደቅ ማለት ሆነ:: ወደኋላ መመለስ
ማለት ደግሞ ከዣቬር እጅ መግባት ነው:: ዣን ቫልዣ ቀስ በቀስ በሚጠመጠም ሰንሰለት የተጠፈረ መሰለው:: ተስፋ በመቁረጥ ወደ ሰማይ
አንጋጠጠ፡፡...

👍19😢12
#ከፍሪጅ_የተጫረ_እሳት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
አዲሳባ ውስጥ ከሚኖሩ ሃምሳ ዱርዬ ሴቶች መካከል የሰላሳ ዘጠኙ ስም ሜሮን ይመስለኝ
ነበር፡ አምስቱ ሄለን አምስቱ ሃያት፣ አንዷ ግን አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ስም እየቀያየረች
የምታጭበረብርና ስሟ የማይታወቅ፤ ቦሌ ቢባል ካዛንችስ፣ ፒያሳ ቢባል አራት ኪሎ፣ ነርስ ብትሆን ሱቅ ጠባቂ፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ብትሆን ሴተኛ አዳሪ…ብቻ ስሟን የምትቀያይር ሴት ነበረች የምትመስለኝ፡፡
አዎ ስሟን እየቀያየረች በአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ስም የምትዶርር (ዱርዬ የምትሆን) ትዕግስት፣ ሳባ፣ ገነት፣ ማርታ፣ መቅደስ፣ ትርሃስ፣ ሐረገወይን፣ ወላንሳ፣ ዙሪያሽ፣ ፍሬ፤ቃልኪዳን፣ ቲቲ፣ መዓዛ፣ ራሄል፣ ሚሚ፣ ሙና፣ አስናቁ፣ ዘሪቱ፣ መንበረ፣ አለምነሽ፣ ያኔት፤ሊና፣ ላራ፣ ሃና አንድ ነጥብ አምስተኛው ላይ ሜሮን ትሆናለች፡፡ እች እስስት !!
እስስት ብያለሁ አዎ !! ስም እኮ ቀለም ነው፤ ሰው ስሙን ሲቀያይር ቀለሙን ለመቀየር መሞከሩ ነው፡፡ እና ጥሩወርቅ ጎጃምኛ ቀለሟን ቀይራ ሊያ ነኝ ስትል ምን እየሆነች ነው? አካባቢዋን እየመሰለች፤ አዲሳስባን እየመሰለች፡፡ እስስትስ ከዚህ የተለየ ምን አደረገች ? ያው አካባቢዋን ለመምሰል ቀለሟን ነው የቀየረችው፡፡ አነጋገርን ለመቀየር የሚደረግ ድካም ምንን ለመቀየር ነውጥ ? ቀለምን ! እናም ሰውና እንስሳት ከሚመሳሰሉስት ባህሪ ዋናው የተጠጉትን መምሰላቸው ይመስለኛል፡፡
ስምንተኛ ክፍል እንደነበርኩ ፍቅር ያዘኝ፡፡ ሜሮን ከምትባል፣ ሁልጊዜ በብዙ ሴት ጓደኞቿ ከምትከበብ ልጅ ደግሞ ስትስቅ ታምራለች ስትኮሳተር ግን ታምራለች፣ አነጋገሬ ተምታታ አይደል ? እንዲህ ነበር የተምታታብኝ !! ቀይ ናት፣ ከቢጫነት ጋር የሚዋሰን ቅላት፡፡ አፏ ሰፋ ያለ ከንፈሯ ቀይና ወደታች ወረድ ብሎ የሆነ “ከምታፈጥ መጥተህ አትስመኝም” ብሎ የሚጣራ ነገረኛ ከንፈር፤ ሕፃን ሆነን አባ ገመቹ አጥር ላይ ተንጠልጥሎ የሚያስጎመዥንን ፕሪም የመሰለ፡፡
የላይ እና የታች ከንፈሮቿ በአንድ ላይ ሲታዩ የሆነ ልብ የሚሰውሩ የልብ ቅርፅ፡፡ ሜሮንን በአይኔ
ሳይሆን በልቤ ነበር የማያት፡፡ ሳያት የልቤ ሽፋሽፍት ይርገበገባል ! በስንት መከራ ያውም ወደ ዘጠነኛ ክፍል ስናልፍ “ሳይሽ የልቤ ሽፋሽፍት ይርገበገባል..” ብዬ ደብዳቤ ፃፍኩላት፡፡ ሄለን እና ሃያት የሚባሉት ጋጠወጥ ጓደኞቿ ጋር በመሆን በዚች ዓረፍተ ነገር ምክንያት ዓመቱን
ሙሉ መሳቂያ መሳለቂያ አደረጉኝ:: መሪያቸው አንዲት ስሟን የማላውቃት አይጠ መጎጥ የመሰለች ልጅ ነበረች፡፡ልክ እኔ ሳልፍ ደረታቸውን በእጆቻቸው እያራገቡ በሳቅ ያውካካሉ፡፡
እይጠ መጎጧ በአካፋ ዓይኗ አሸዋ ወንድ ስትግፍ የምትውል ከንቱ !! ስሟን አላውቀውም፤
ስሟን አስር ጊዜ ትቀያይራለች ስሟ ብዙ ነው፡፡ ሁሉንም ስሞቿን የኢትዮጵያ ቄሶች ሁሉ እየተጋገዙ ይጥሩት !!
የእርሷ ሳቅ ሳቄን ገድሎታል፡፡ የእርሷ የፌዝ ዕይታ ሩቅ እንዳላይ አንገቴን አስደፍቶኛል:: የልብ ሽፋሽፍት የሚል ግጥም ፅፋ ለፀረ ምንትስ ከበብ ዓመታዊ ዝግጅት ሰልፍ ሜዳ ላይ አንብባ 843 ተማሪ ሲባዛ 32 ጥርስ = 26 976 ጥርስ ይርገፍና !! ቆይ የአስተማሪዎቹን ረስቼው ነበር፡፡ ሲደመር 23 ሲባዛ 32 = 736 ሲቀነስ 32 (ቲቸር አንድም ጊዜ አልሳቁም)፡፡
የፍቅር አፒታይቴን” ምድረ ጥርሳም በሳቃቸው ቆልፈውት አስራ ሁለተኛ ክፍል ጨርሼ ዩኒቨርስቲ እስከምገባ ድረስ ሴት የምትባል ፍጥረት አጠገብ ድርሽ ብዬ አላውቅም፡፡ እና ምን ተባልኩ ?ጨዋ !! እንኳንም ያልቀረብኩ !! ምናቸው ይቀራል? ያች አይጠ መጎጥ፣ አስቀያሚ፣ ጥርሳም፣ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊየን ስማም ! ዛሬ የራሷ አንድ ስም እንኳን ጠፍቶ ማንም አንቺ
የሚላት የካፍቴሪያ አስተናጋጅ ሆናለች፡፡ ሻይ አዞ ስሙኒ ጉርሻ ለተወላት ሰብለ፤ ቡና ጠጥቶ ለገለፈጠላት ናኒ እየሆነች እስስቷ የስሟን ቀለም እየቀያየረች አለች፡፡ ብር ዛፍ ቁርስ ቤት ሳልፍ ሳገድም ከነቀይ ሽርጧ አያታለሁ
ዩኒቨርስቲ የተመደብኩት እዚሁ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ነበር፡፡ ደስ አላለኝም፡፡ ምክንያቱም ከአዲስ አበባ ውጭ ከወላጅ ራቅ ብዬ የመኖር የቆየ ፍላጎቴ ተሰናክሏልና፡፡ አስከፊው ነገር
ደግሞ ዩኒቨርስቲው “የአዲስ አበባ ልጆች እየተመላለሳችሁ ተማሩ በቂ መኝታ የለኝም አለ ይሄ ደግሞ ዩኒቨርስቲና ሃይ ስኩል የሚለያዩበትን አንድ ድንበር አፈራረሰው፡፡ ዩኒቨርስቲ
ውስጥ የገባሁ አልመስልህ አለኝ፡፡ ወደ አስራ ሶስተኛ ክፍል ያለፍኩና እዛው የነበርኩበት ትምህርት ቤት የቀጠልኩ አይነት ስሜት ነበር የተሰማኝ፡፡ ያ ሁሉ የተወራለት፣ በፊልም እና በሰመመን መጽሐፍ ብዙ የተባለለት የዩኒቨርስቲ ሕይወት፣ ላየው የጓጓሁለት “የግቢ ላይፍ ውሃ በላው !! ወይ ነዶ! አንድ አራት ወር እየተመላለስኩ እንደተማርኩ እዛው ዩኒቨርስቲው አካባቢ ቤት ተከራይቼ ለመማር ወሰንኩ፡፡ ምንም አስቤ ሳይሆን የአዲስ አበባ ታክሲ ጊዜዬን እየበላብኝ ስለተቸገርኩ ነበር፡፡ ማንም አልተከራከረኝም፤ ዩኒቨርስቲው ከሚወረውርልኝ ሳንቲም ላይ ቤተሰብ በየወሩ ድጎማ እየመረቀበት ቤት ተከራየሁ፡፡ድከም ያለች ቤት አንድ ሰፈር ውስጥ፡፡ እንግዲህ የእኔ
ቤትና ከጎኔ ያሉት ጭርንቁስ ቤቶች በመደዳ የተሰለፉ ነበሩ ፊት ለፊት ደግሞ ፊታቸውን
ወደ እኔ ቤት ያዞሩ ስስሪትም፣ በመጠንም ከእኔ ቤት ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ሌላ መደዳ ቤቶች አሉ፡፡ መስኮቴን ስከፍት ፊት ለፊት ያለው ቤት መስኮት ጋር እፋጠጣለሁ፡፡ በሬን ስከፍት ፊት
ለፊት ካለ በር ጋር ! በሁለቱ መደዳ ቤቶች መካከል ቀጭን የእግር መንገድ አለች፡፡ የእኔ ቤትና ፊት ለፊቴ ያለው ቤት ጣራቸው ሊገጣጠም ምንም ያህል ስለማይቀረው በመካከላችን በቀጭኗ የእግር መንገድ የሚያልፍ ሰው ረዥም ኮሪደር ውስጥ የሚያልፍ ሊመስለው ይችላል፡፡ ከበሬ ላይ አንድ ጠቀም ያለ ርምጃ ወደፊት ብራመድ ፊት ለፊት ያለው ቤት በር ላይ አርፋለሁ፡፡ ይሄ ነው የተከራየሁት ቤት::
ሜሮንን ትሻግሮ ሜሮን አለች ወይ…
በአንድ ርምጃ ርቀት ጣራዬ፣ ከጣራው የሚነካካው ቤት ውስጥ ፊት ለፊቴ 'ሜሮን' የምትባል
ልጅ መኖሯን ያወቅኩት ቤቱን በተከራየሁ በሁለተኛው ቀን ነበር፡፡ በጊዜና ቦታ ርቀት ትቼ የመጣሁት “ሜሮን” የሚባል እንደ ጥላ የሚከተል ስም እዚህም መጣ፡፡ ሜሮን ሜሪ ሜሪቾ ሜሪዬ…ይላታል የመንደሩ ሰው፡፡ ጥቁር ትሁን ቀይ አይቻት አላውቅም ነበር፡፡ ለሰባት ወራት
ያህል ጧት እየወጣሁ፣ ማታ እየገባሁ በሰላም ኖርኩ፡፡
በአንድ ጠራራ የግንቦት ቀን ከክላስ ወደ ቤቴ እየገባሁ ነበር፡፡ የፀሐዩ ቃጠሎ ከንፈሬን ሁሉ
አድርቆታል፤ ሰውነቴ ሁሉ የተነነ ነው የመሰለኝ፡፡ ድርቅ የመታኝ !! ቀዝቃዛ ውሃ ለመግዛት ጫፍ ላይ ወዳለች ኪዮስክ ሄድኩና “ቀዝቃዛ ውሃ ስጭኝ እስቲ” ብዬ አስር ብር ባለሰሃኑ
ሚዛን ላይ ጣል አደረግኩላት፡፡ አስር ብሩ ሚዛኑ ላይ ሲያርፍ ሚዛኑን ዝቅ አላደረገው ከፍ…
“ቀዝቃዛ የለም !” አለች እስር ብሩን በእጇ ይዛ፣
"እሽ ቀዝቃዛ ኮካ”
“ቀዝቃዛ ኮካም የለም ከውጭ ልስጥህ ?” አለች፣
ቀዝቃዛ ነገር ምንድን ነው ያለሽ ?”
“ፍሪጅ የለኝም ከውጭ ነው ሁሉም !”
“ተይው በቃ !” ብዬ ብሬን ልቀበል እጄን ዘረጋሁ፡፡ ቅር እያላት ብሬን መለሰችልኝ፡፡ ፊቴን ኮሰኮስኩ በጣም ነበር የተበሳጨሁት፡፡ ኤጭ!!

👍33