#ከፍሪጅ_የተጫረ_እሳት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
አዲሳባ ውስጥ ከሚኖሩ ሃምሳ ዱርዬ ሴቶች መካከል የሰላሳ ዘጠኙ ስም ሜሮን ይመስለኝ
ነበር፡ አምስቱ ሄለን አምስቱ ሃያት፣ አንዷ ግን አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ስም እየቀያየረች
የምታጭበረብርና ስሟ የማይታወቅ፤ ቦሌ ቢባል ካዛንችስ፣ ፒያሳ ቢባል አራት ኪሎ፣ ነርስ ብትሆን ሱቅ ጠባቂ፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ብትሆን ሴተኛ አዳሪ…ብቻ ስሟን የምትቀያይር ሴት ነበረች የምትመስለኝ፡፡
አዎ ስሟን እየቀያየረች በአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ስም የምትዶርር (ዱርዬ የምትሆን) ትዕግስት፣ ሳባ፣ ገነት፣ ማርታ፣ መቅደስ፣ ትርሃስ፣ ሐረገወይን፣ ወላንሳ፣ ዙሪያሽ፣ ፍሬ፤ቃልኪዳን፣ ቲቲ፣ መዓዛ፣ ራሄል፣ ሚሚ፣ ሙና፣ አስናቁ፣ ዘሪቱ፣ መንበረ፣ አለምነሽ፣ ያኔት፤ሊና፣ ላራ፣ ሃና አንድ ነጥብ አምስተኛው ላይ ሜሮን ትሆናለች፡፡ እች እስስት !!
እስስት ብያለሁ አዎ !! ስም እኮ ቀለም ነው፤ ሰው ስሙን ሲቀያይር ቀለሙን ለመቀየር መሞከሩ ነው፡፡ እና ጥሩወርቅ ጎጃምኛ ቀለሟን ቀይራ ሊያ ነኝ ስትል ምን እየሆነች ነው? አካባቢዋን እየመሰለች፤ አዲሳስባን እየመሰለች፡፡ እስስትስ ከዚህ የተለየ ምን አደረገች ? ያው አካባቢዋን ለመምሰል ቀለሟን ነው የቀየረችው፡፡ አነጋገርን ለመቀየር የሚደረግ ድካም ምንን ለመቀየር ነውጥ ? ቀለምን ! እናም ሰውና እንስሳት ከሚመሳሰሉስት ባህሪ ዋናው የተጠጉትን መምሰላቸው ይመስለኛል፡፡
ስምንተኛ ክፍል እንደነበርኩ ፍቅር ያዘኝ፡፡ ሜሮን ከምትባል፣ ሁልጊዜ በብዙ ሴት ጓደኞቿ ከምትከበብ ልጅ ደግሞ ስትስቅ ታምራለች ስትኮሳተር ግን ታምራለች፣ አነጋገሬ ተምታታ አይደል ? እንዲህ ነበር የተምታታብኝ !! ቀይ ናት፣ ከቢጫነት ጋር የሚዋሰን ቅላት፡፡ አፏ ሰፋ ያለ ከንፈሯ ቀይና ወደታች ወረድ ብሎ የሆነ “ከምታፈጥ መጥተህ አትስመኝም” ብሎ የሚጣራ ነገረኛ ከንፈር፤ ሕፃን ሆነን አባ ገመቹ አጥር ላይ ተንጠልጥሎ የሚያስጎመዥንን ፕሪም የመሰለ፡፡
የላይ እና የታች ከንፈሮቿ በአንድ ላይ ሲታዩ የሆነ ልብ የሚሰውሩ የልብ ቅርፅ፡፡ ሜሮንን በአይኔ
ሳይሆን በልቤ ነበር የማያት፡፡ ሳያት የልቤ ሽፋሽፍት ይርገበገባል ! በስንት መከራ ያውም ወደ ዘጠነኛ ክፍል ስናልፍ “ሳይሽ የልቤ ሽፋሽፍት ይርገበገባል..” ብዬ ደብዳቤ ፃፍኩላት፡፡ ሄለን እና ሃያት የሚባሉት ጋጠወጥ ጓደኞቿ ጋር በመሆን በዚች ዓረፍተ ነገር ምክንያት ዓመቱን
ሙሉ መሳቂያ መሳለቂያ አደረጉኝ:: መሪያቸው አንዲት ስሟን የማላውቃት አይጠ መጎጥ የመሰለች ልጅ ነበረች፡፡ልክ እኔ ሳልፍ ደረታቸውን በእጆቻቸው እያራገቡ በሳቅ ያውካካሉ፡፡
እይጠ መጎጧ በአካፋ ዓይኗ አሸዋ ወንድ ስትግፍ የምትውል ከንቱ !! ስሟን አላውቀውም፤
ስሟን አስር ጊዜ ትቀያይራለች ስሟ ብዙ ነው፡፡ ሁሉንም ስሞቿን የኢትዮጵያ ቄሶች ሁሉ እየተጋገዙ ይጥሩት !!
የእርሷ ሳቅ ሳቄን ገድሎታል፡፡ የእርሷ የፌዝ ዕይታ ሩቅ እንዳላይ አንገቴን አስደፍቶኛል:: የልብ ሽፋሽፍት የሚል ግጥም ፅፋ ለፀረ ምንትስ ከበብ ዓመታዊ ዝግጅት ሰልፍ ሜዳ ላይ አንብባ 843 ተማሪ ሲባዛ 32 ጥርስ = 26 976 ጥርስ ይርገፍና !! ቆይ የአስተማሪዎቹን ረስቼው ነበር፡፡ ሲደመር 23 ሲባዛ 32 = 736 ሲቀነስ 32 (ቲቸር አንድም ጊዜ አልሳቁም)፡፡
የፍቅር አፒታይቴን” ምድረ ጥርሳም በሳቃቸው ቆልፈውት አስራ ሁለተኛ ክፍል ጨርሼ ዩኒቨርስቲ እስከምገባ ድረስ ሴት የምትባል ፍጥረት አጠገብ ድርሽ ብዬ አላውቅም፡፡ እና ምን ተባልኩ ?ጨዋ !! እንኳንም ያልቀረብኩ !! ምናቸው ይቀራል? ያች አይጠ መጎጥ፣ አስቀያሚ፣ ጥርሳም፣ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊየን ስማም ! ዛሬ የራሷ አንድ ስም እንኳን ጠፍቶ ማንም አንቺ
የሚላት የካፍቴሪያ አስተናጋጅ ሆናለች፡፡ ሻይ አዞ ስሙኒ ጉርሻ ለተወላት ሰብለ፤ ቡና ጠጥቶ ለገለፈጠላት ናኒ እየሆነች እስስቷ የስሟን ቀለም እየቀያየረች አለች፡፡ ብር ዛፍ ቁርስ ቤት ሳልፍ ሳገድም ከነቀይ ሽርጧ አያታለሁ
ዩኒቨርስቲ የተመደብኩት እዚሁ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ነበር፡፡ ደስ አላለኝም፡፡ ምክንያቱም ከአዲስ አበባ ውጭ ከወላጅ ራቅ ብዬ የመኖር የቆየ ፍላጎቴ ተሰናክሏልና፡፡ አስከፊው ነገር
ደግሞ ዩኒቨርስቲው “የአዲስ አበባ ልጆች እየተመላለሳችሁ ተማሩ በቂ መኝታ የለኝም አለ ይሄ ደግሞ ዩኒቨርስቲና ሃይ ስኩል የሚለያዩበትን አንድ ድንበር አፈራረሰው፡፡ ዩኒቨርስቲ
ውስጥ የገባሁ አልመስልህ አለኝ፡፡ ወደ አስራ ሶስተኛ ክፍል ያለፍኩና እዛው የነበርኩበት ትምህርት ቤት የቀጠልኩ አይነት ስሜት ነበር የተሰማኝ፡፡ ያ ሁሉ የተወራለት፣ በፊልም እና በሰመመን መጽሐፍ ብዙ የተባለለት የዩኒቨርስቲ ሕይወት፣ ላየው የጓጓሁለት “የግቢ ላይፍ ውሃ በላው !! ወይ ነዶ! አንድ አራት ወር እየተመላለስኩ እንደተማርኩ እዛው ዩኒቨርስቲው አካባቢ ቤት ተከራይቼ ለመማር ወሰንኩ፡፡ ምንም አስቤ ሳይሆን የአዲስ አበባ ታክሲ ጊዜዬን እየበላብኝ ስለተቸገርኩ ነበር፡፡ ማንም አልተከራከረኝም፤ ዩኒቨርስቲው ከሚወረውርልኝ ሳንቲም ላይ ቤተሰብ በየወሩ ድጎማ እየመረቀበት ቤት ተከራየሁ፡፡ድከም ያለች ቤት አንድ ሰፈር ውስጥ፡፡ እንግዲህ የእኔ
ቤትና ከጎኔ ያሉት ጭርንቁስ ቤቶች በመደዳ የተሰለፉ ነበሩ ፊት ለፊት ደግሞ ፊታቸውን
ወደ እኔ ቤት ያዞሩ ስስሪትም፣ በመጠንም ከእኔ ቤት ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ሌላ መደዳ ቤቶች አሉ፡፡ መስኮቴን ስከፍት ፊት ለፊት ያለው ቤት መስኮት ጋር እፋጠጣለሁ፡፡ በሬን ስከፍት ፊት
ለፊት ካለ በር ጋር ! በሁለቱ መደዳ ቤቶች መካከል ቀጭን የእግር መንገድ አለች፡፡ የእኔ ቤትና ፊት ለፊቴ ያለው ቤት ጣራቸው ሊገጣጠም ምንም ያህል ስለማይቀረው በመካከላችን በቀጭኗ የእግር መንገድ የሚያልፍ ሰው ረዥም ኮሪደር ውስጥ የሚያልፍ ሊመስለው ይችላል፡፡ ከበሬ ላይ አንድ ጠቀም ያለ ርምጃ ወደፊት ብራመድ ፊት ለፊት ያለው ቤት በር ላይ አርፋለሁ፡፡ ይሄ ነው የተከራየሁት ቤት::
ሜሮንን ትሻግሮ ሜሮን አለች ወይ…
በአንድ ርምጃ ርቀት ጣራዬ፣ ከጣራው የሚነካካው ቤት ውስጥ ፊት ለፊቴ 'ሜሮን' የምትባል
ልጅ መኖሯን ያወቅኩት ቤቱን በተከራየሁ በሁለተኛው ቀን ነበር፡፡ በጊዜና ቦታ ርቀት ትቼ የመጣሁት “ሜሮን” የሚባል እንደ ጥላ የሚከተል ስም እዚህም መጣ፡፡ ሜሮን ሜሪ ሜሪቾ ሜሪዬ…ይላታል የመንደሩ ሰው፡፡ ጥቁር ትሁን ቀይ አይቻት አላውቅም ነበር፡፡ ለሰባት ወራት
ያህል ጧት እየወጣሁ፣ ማታ እየገባሁ በሰላም ኖርኩ፡፡
በአንድ ጠራራ የግንቦት ቀን ከክላስ ወደ ቤቴ እየገባሁ ነበር፡፡ የፀሐዩ ቃጠሎ ከንፈሬን ሁሉ
አድርቆታል፤ ሰውነቴ ሁሉ የተነነ ነው የመሰለኝ፡፡ ድርቅ የመታኝ !! ቀዝቃዛ ውሃ ለመግዛት ጫፍ ላይ ወዳለች ኪዮስክ ሄድኩና “ቀዝቃዛ ውሃ ስጭኝ እስቲ” ብዬ አስር ብር ባለሰሃኑ
ሚዛን ላይ ጣል አደረግኩላት፡፡ አስር ብሩ ሚዛኑ ላይ ሲያርፍ ሚዛኑን ዝቅ አላደረገው ከፍ…
“ቀዝቃዛ የለም !” አለች እስር ብሩን በእጇ ይዛ፣
"እሽ ቀዝቃዛ ኮካ”
“ቀዝቃዛ ኮካም የለም ከውጭ ልስጥህ ?” አለች፣
ቀዝቃዛ ነገር ምንድን ነው ያለሽ ?”
“ፍሪጅ የለኝም ከውጭ ነው ሁሉም !”
“ተይው በቃ !” ብዬ ብሬን ልቀበል እጄን ዘረጋሁ፡፡ ቅር እያላት ብሬን መለሰችልኝ፡፡ ፊቴን ኮሰኮስኩ በጣም ነበር የተበሳጨሁት፡፡ ኤጭ!!

👍33
#ከፍሪጅ_የተጫረ_እሳት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
...በቃሌ መሰረት ልደቷን ልናከብር ተቀጣጠርን፡፡ ከሰፈር አብረን መውጣቱ ለጎረቤት ሃሜት
ስለሚዳርግ የሆነ እሷ የመረጠችው ሬስቶራንት ስምንት ሰዓት ላይ እንገናኝ ተባባልን፡፡....
እኔ በበኩሌ የዚህ ዓይነት ሴት አይቼ አላውቅም፤ ቀድሚያት ነበር የደረስኩት፡፡ ቀይ የለበሱት
ጠረጴዛዎች የአገር ሹካና ማንኪያ፣ ቢላዋና የጨው የምናምን እቃ ዙሪያቸውን ተደርድሮባቸው፣ፈዘዝ ያለ ብርሃን ያለበት አዳራሽ ውስጥ በሰፊው ተንጣለዋል፡፡
ምቾት አይመቸኝም፤ ቅንጦት አያቀናጣኝም፤ ጨነቀኝ !
ሜሮን ስትደርስ ልቤ በድንጋጤ ልትቆም ምንም አልቀራትም፡፡ የሚያምር አጭር ጉልበቷ ላይ
የቆመ ቡና ዓይነት ቀሚስ ለብሳለች፡፡ ውብ እግሮቿን ለማሳየት ሆን ተብሎ የተሰራ የሚመስል ረዥም ተረከዝ ያለው ጫማ፣ ጥልፍልፉ ፍርጥም ያለ ባቷ ላይ እንደሃረግ እየተጠመጠሙ ወጥቶ ጉልበቷ ላይ የደረሰ፣ ጡቶቿ ደረቷ ላይ ክፍት በሆነው ቀሚሷ ታቅፈውና ተሳስመው የሲኦል ሸለቆ እንደሰሩ፣ ፀጉሯ ወደ አንድ በኩል ተሰብስቦ በማስያዣ ተይዟል፤ ዓይኗ በኩል ተከቧል፣ ኦህህህህህህ ስታምር! የአዲስ አበባ እናቶች እድሜ አቆጣጠር አይችሉም ይሆናል እንጂ ይህቺ ልጅ አስራ ስድስት ዓመቷ ብቻ አይመስለኝም፡፡ በዚህ እድሜ ቀጠሮን የመከሸን ሳይንስ እንዴት ነው መካን የሚቻለው? እኔ እኮ በዚህ እድሜም አልችልበትም፡፡
ቆሜ ተቀበልኳት፤ ጉንጫችንን አነካካነው፤ መሳሳም መሆኑ ነው፡፡ አቤት ሽቶዋ! ..ፊቴ ዝም
ብላ ቆመች ! ..ቆምኩ …አሃ ለካ ወንበር ይሳባል ! ሳብኩላት፤
“ቴንኪው !” ብላ ተቀመጠች፤
“በጣም ቆንጆ ሆነሻል”
“እመሰግናለሁ” የተጠና ምልልስ መሰለብኝ እንጂ ከልቤ ነበር የተናገርኩት፡፡ በዚህ ቀን ከሜሮን
ጋር ከዘፍጥረት እስከ ራእይ አወራን፡፡ ሜሮን ካለ እድሜዋ የበሰለች ጉድ ነበረች፤ እናም
እንዲህ አልኩ፣
“ 'አዲስ አበባ ውስጥ ከሚኖሩ ሃምሳ ዱርዬ ሴቶች ውስጥ ሰላሳ ዘጠኙ ስማቸው ሜሮን
ይመስለኛል ግን ማናባቱ ነው ይሄን ቆጠራ ያካሄደው ደደብ!”ሜሮን ጋር ተዋድደን
ነበር በቃ ! እኔ ጋር በመሆኗ ነፍሷን እስክትስት ተደስታ ነበር፡፡እኔማ ነፍሴን ከሳትኩ ሰንብቻለሁ፡፡ ልዩ ሰው አድርጋ እንደምታስበኝ ነገረችኝ፤ ሰፈር ውስጥ ዝምታዬ መስጧታል።
ደግሞ ወሬው ሁሉ ከየት መጣልኝ ? የሰው ሰው በሳቅ ልገድል !! እግዜር ሲያስወድድህ ብዙ ሳቅ የወደደህ ሰው ልብ ውስጥ ያስቀምጣል፤ ከዛም የውድህ ሳቅ መውጫ በር፣ መተንፈሻ መስኮት ያደርግሃል፡፡ አንተ በፈለግከው መንገድ አፍህን ክፈት፣ ቃላትን አውጣ፤ ሜሪዬ የኔ ውብ አቤት ሳቋ ሲያምር ! እዛ ዩኒቨርስቲ “ሄይይ ምን አዲስ ነገር አለ ” እያሉ ሳቅ ፍለጋ እንደሚባዝኑ ሕይወታቸውን በጊዜ ያሟጠጡ ደነዝ ሴቶች አይደለችም፡፡ ቻፕስቲካም ከንፈራቸውን እስከጆር
ግንዳቸው ለቀው በ 'ዊትኒ ሆስተንኖ ለመሳቅ ቆርቆሮ ድምፃቸውን እንደሚያንኳኩ ኳኳታሞች አይደለችም፤ ሜሪ ራሷ ሳቅ ነበረች፤ ፍንትው ስትል ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ፀጉሯ በሳቅ
የምትጥለቀለቅ ! እንደእኔ አይነቱ ሰው ተሳቀልኝ ቢል ያምርበታል፤
ልብ ነበራት፤ የፍቅር የሰላም ያልተነካካ፡፡ 'ውይ ወንዶች? እያሉ ያለፈ እንኩሮ ሕይወታቸውን
አዲስ የፍቅረኛ ምጣድ ላይ በትዝታ ስም እንደሚጠፈጥፉ ሴቶች አልነበረችም፡፡ ብታውቀውም ባታውቀውም ነገ ይናፍቃታል፡፡ ማንንም አልጎዳች፣ ማንም አልጎዳትም፡፡ ተረት የላትም ! ተረት አይደለችም፡፡ እነእከሌ ተፋቀሩ” ስትባል አትቀናም፡፡ “ተለያዩ" ሲባል አትፈርድም፤ ከተማውን የሞላው ፈራጅኮ ግማሽ ፍርዱ በቀል ነው፡፡ የደረሰበትን ሊስቀል፣ ያደረሰውን
ሊያስተባብል! ሜሪ ግን ብቻዋን ናት፡፡ ብቻዋን ወደ ሕይወቴ መጣች፤ አልከበደችኝም፡፡
ከዛን ቀን ጀምሮ ሁልጊዜ ማታ ማታ በር ላይ እንቆምና ስናወራ እናመሻለን፡፡ ውሃ ልትደፋ
ወጥታ ሊሆን ይችላል፡፡ “ቻው በቃ መሸ !” ትለኝና ቆም ትላለች፡፡ ከቻው በኋላ አንድ የሆነ
ነገር የማድረግ ፍላጎት ሁለታችንም ልብ ውስጥ አለ፡፡ ግን ማን ይድፈር ? ከቻው በኋላ
አንድ ሰዓት እናወራለን፡፡ “ምን አወራችሁ ?” ቢባል እንጃ !! ብዙ ጊዜ ቤቴ እንዳትገባ ሆነ
ብዬ እከላከላለሁ፤ ፈተናው ይከብደኛል፤ ስለዚህ በር ላይ ቆመን እናወራለን፡፡ ወሬኛ ነኝ፡፡
የማላወራላት ነገር የለም !! ባወራሁበት የምከፈለው ደመወዝ ሳቋ ነው፡፡ የጠገበ ደመወዝ፡፡
እግዜርዬ የፍቅር ዩኒቨርስቲ አስመርቆ የሰጠኝ ምርጥ ስራ - ሃሌ ሉያ !” አስመርቆ 'ስራ ፍጠር
ቢለኝ ምን ይውጠኝ ነበር ? ሳቋ ደመወዜ ነው፡፡….ስቃታለሁ፤ የማወራላት ምንም የማይጠቅም
ነገር ቢሆንም የሳቅ ደመወዜን አስቀርታብኝ አታውቅም፡፡
ታዲያ አንዳንዴ ማታ ቆመን ስናወራ ከሩቅ የጅብ ድምፅ ይሰማል፡፡ አውውውው…! ወደ እኔ
ጠጋ ትላለች፤ ሜሪዬ የመጨረሻ ፈሪ ናት፡፡ ጠረኗ ይጠርነኛል፡፡ ከምሽቱ አየር ጋር ወደ ሳንባዬ
ተስገብግቤ እስበዋለሁ፤ ጠረኗን !! እሷን ራሷን እንደአየር ስቤ ውስጤ ያስገባኋት እስኪመስለኝ፤ ጅቡን እድሜውን ያርዝምልኝና በጣም ትጠጋኛለች፡፡
ስለጅብ አወራላታለሁ፡፡ “የጅብ ጥፍር አንገትሽ ላይ ካሰርሽ በቃ የሄድሽበት ሁሉ ሲበሉ ነው
የሚያደርስሽ”
“ውሸትህን ነው ! ሂሂሂሂሂሂሂ…”
“ለምን እዋሽሻለሁ በሳይንስ የተረጋገጠ ነው”
“አላምንህም ! ሃሃሃሃሃሃ…”
እይውልሽ የአሜሪካ ሳይንቲስቶች ናቸው እኮ ያጠኑት”
“ውይ ውሸት አላምንልህም ! እንዴት አድርገው ያጠኑታል ? ... ታየኝ እኮ ስንት ስራ ትተው
አንገታቸው ላይ የጅብ ጥፍር አስረው ሲዞሩ ! ሂሂሂሂሂሂሂሂሂ…” ፍልቅልቅ ትላለች፡፡
ቀላል ነው፤ አንድ ጊዜ ይህን ጥናት እናጥና ብለው አለቃቸውን ሊያስፈቅዱት የጅብ ጥፍር አንገታቸው ላይ ልክ እንደዚህ እንደማተብ (እንገቷ ላይ ያሰረችውን ማተብ እየነካካሁ) አስረው ሳይንቲስቶቹ
ወደ ኃላፊያቸው ክፍል ሊገቡ ኃላፊው ምን እያደረገ አገኙት መሰለሽ…? በርገሩን እየገመጠ፡፡
ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ…ውሸት ! ውሸት ”
“..ከዛ ጥናቱ ተፈቀደላቸውና ወደ አፍሪካ መጡ፤ የሆነ ሰው የማይኖርበት ጫካ እካባቢ
አውሮፕላናቸው ተከለከሰ”
ኦ ማይ ጋድ! እውነትህን ነው ?” አለች ደንገጥ ብላ፡፡
ያ! ግን ማንም አልሞተም፡፡በተዓምር ተረፉ፡፡ ሁሉም አንገታቸው ላይ የጅብ ጥፍር አስረዋል፤ ከዛ የሆነ
ነገር ሸትቷቸው ዞር ሲሉ ጫካው ውስጥ የሚኖሩ አዳኞች ምን የመሰለች ጥንቸል ለምሳቸው እየጠበሱ:
“ወይኔ ውሸትህ ሂሂሂሂሂ…አልሰማህም !”
“እስኪ ጥናቱን የበለጠ ለማረጋገጥ ወደ ሌላ ዓለም እንውሰደው አሉና ናሳ ጋር ተነጋግረው ወደ ጨረቃ የሚጓዙ ጠፈርተኞች አንገት ላይ የጅቡን ጥፍር አሰሩላቸው፡”
“አሁንስ አበዛኸው ሕፃን ልጅ መሰልኩህ እንዴ ?” ብላ የውሸት ተቆጣች፡፡ ሜሪ ከዚህ »
ቀጥሎ የሚፈነዳውን ሳቅ ስለማውቅ ውሸቴን ቀጠልኩበት፡፡
“ልክ ጠፈርተኞቹ ጨረቃ ላይ ሲያርፉ ከእነሱ ቀድመው ጨረቃ ላይ ያረፉ የሩሲያ ጠፈርተኞት
ራት ሊበሉ ሲዘገጃጁ ደረሱ እልሻለሁ”
ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ሁለተኛ አላዋራህም እሺ ! ስታስጠላ ! እኔ ቁም ነገር የምታወራ መስሎኝ ! ሂሂሂሂ…” ሳቋ መቆሚያ የለውም፡፡ እኔም በሳቋ ልቤ ሃሴት ያደርጋል፡፡

👍31👏1