#ዝግመተ_ለውጥ
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
ረዥም ነገር አልወድም፡፡ ረዥም ቁመት እንደ ሰብለ፤ ረዥም መንገድ በእኔና በእነሰብለ ቤት
መካከል እንዳለው፣ ረዥም ወሬ ስብለ እኔን አሰቀምጣ ስልክ እንደምታወራው፣ ረዥም ዕድሜ
እንደሰብለ አያት እና ረዥም ቀን እንደዛሬው. ዛሬ እሁድ ነው !
እሁድ ከመርዘሙ የተነሳ የሚመሸው ከነገ ወዲያ ይመስለኛል። እሁድ ለእኔ መጀመሪያና መጨረሻ ያለው ዘላለም ነው፡፡ “ለምን?” እንዳትሉኝ፣ ታሪኩ ረዥም ነው፡፡ ረዥም ታሪክ አልወድም፣ እንደ እኔና እንደሰብለ የፍቅር ታሪክ፡፡
ሰብለ ፍቅረኛዬ ነበረች፡፡ ሰብለ የሚለው ስም በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ይመስለኛል፡፡ ሰላቢ
ሰለበ..ሰብሱ አያለ የተሻሻለ ዓይነት፡፡ እሁድም ከ24 ሰዓት ተነስቶ ዘላለም የሆነ....
ዛሬ እሁድ ነው፣ ይሄ ጋግርታም ሕፃን እሁድ፣ አርጅቶ መካነ ሰኞ ውስጥ እሰኪከተት ምናባቴ
እየሰራሁ..የት አባቴ ሄጄ ላሳልፈው ይሆን?' እያልኩ አስባለሁ፡፡ አንድ ሀሳብ መጣልኝ፡፡ ቤቴ በር ላይ ተቀምጬ ፀሐይ እየሞቅኩ የሆነ ነገር ማንበብ ..በቃ!!
ኩርሲ ነገር አወጣሁና ተመልሼ ከጠረጴዛዬ ላይ የሚነበብ ነገር ልፈልግ አንድ ጋዜጣ አገኘሁ
መልሼ አስቀመጥኩት ረዥም ጋዜጣ ነው ! የሰብለ አባት ይሄን ጋዜጣ ይወዱት ነበር ነብሳቸው
ይማረውና እሳቸው የሞቱ ቀን የቀብር ሥነ ሥርዓቱ አረዛዘም መቼም አይረሳኝ…፡፡ ከሰው
የተለየ ኃጢያት የተበተባቸው ይመሰል ፍትሀቱ ረዥም ነበር፡፡ ለነገሩ አራጣ አበዳሪ ነበሩ::
ሀሳቤን ቀየርኩና ጋዜጣውን ይዤ መጣሁ፤ ፀሐዩ ሲጠነከር አናቴ ላይ ጣል አደርገዋለሁ።
በር ላይ ቁጭ ብዬ አላፊ አግዳሚውን መመልከት ጀመርኩ፡፡ እማማ ትሁኔ የሽሮ እህል ያሰጣጣሉ፥ የሚገርሙ ሴትዮ ሁልጊዜ የሚያሰጡት ነገር አያጡም፡፡ የሚሰጣ ነገር ቢጠፋ
የማስጫውን ሰማያዊ ፕላስቲክ ብቻውን ያሰጡታል፡፡ ታዲያ ያሰጡትን ቢያሰጡ፤ ስጡ ላይ
አንድ ሁለት ከሰል ጣል ማድረጋቸው አይቀርም፡፡ አንድ ቀን ጠየቅኳቸው፡፡
"እማማ ትሁኔ!"
“ወዬ አብርሽ"
"ይሄ ከሰሉ ምንድን ነው?"
"የቱ ?"
“ይሄ ስጡ ላይ ያለው"
"አረ.ይሄን እስከዛሬ አታውቅም? ሆሆ…” ካሉ በኋላ ባለማወቄ ተገርመው አጭር ማብራሪያ
ሰጡኝ::
“ይሄ እንግዲህ..ስጥ ስታሰጣ አንድ ሁለት ከሰል ጣል ካደረግክስት ሰላቢ አጠገቡ አይደርስም፤ መዳኒት ነው” አሉ ወደ አልማዝ ቤት እያዩ ፀበኛ ናቸው፡፡
“ሰላቢ ምንድን ነው ?"
“የሚሰልብ ነዋ…እንተ ይንበርስቲ በጥስህ ሰላቢ ይጠፋሃል...ሰላቢ ባይኑ የሚሰልብ ነው ያየውን
ነገር ሁሉ ላየ የሚያደርግ፡፡ እህል አይል፣ ዘይት አይል፣ ሊጥ አይል.የተጋገረ እንጀራ አይል በቃ አየት ሲያደርጉት ሽው ነውር …ወደቤቱ ያጋባታል ..." አሉ አልማዝ እንድትሰማ ጮክ ብለው፡፡
ከሰል ከሰላቢ ሲያድን እኔ ኩንታል ከሰል ተሸክሜ ስብለን ስከተላት በዋልኩ ነበር፡፡ አንድ ሰላቢ ባለጋራጅ ነው የሰለበኝ፡፡ ለነገሩ ሰብለ ኣንኳን ከሰል ጣል ማድረግ፣ ከሰል ጉድጓድ ውስጥ ቢያስሯትም መስለቧ አይቀርም፡፡ ሲፈጥራት ሰላቢ ነገር ነበረች፡፡ ከፍቅር የበለጠ ምን ከሰል አለ? ሲያቀጣጥሉት የሚንቀለቀል እሳት፡፡ የከህደት አመድ ሲያለብሱት፣ የተዳፈነ ረመጥ፤
ሲያጠፉት ጥቁር ታሪክ ! ከፍቅር የባሰ ምን ከሰል አለ
አንድ ባለጋራጅ ነው ከእጄ ነጥቆ ሰብለን የወሰዳት፡፡ ምን ይወስዳታል፣ ሄደች እንጂ። አንዳንዴ ከሥራ ስወጣ፣ በምታምር ቀይ መኪና ሲሸኛት እንገጣጠማለን፡፡ ጋቢና ተቀምጣ በኩራት ታየኛለች፣ አየህ ያለሁበትን ዓይነት መኮፈስ፡፡ ሰው ከሰው ልብ ላይ ወርዶ፣ ቆርቆሮ ውስጥ ስለተቀመጠ ይሄን ያህል መኮፈስ ነበረበት?
በሬ ፥ላይ ተቀምጬ አላፊ አግዳሚውን መመልከቴን ቀጠልኩ:: ኤጭጭ…መምሬ
ታምሩ ሳር ቅጠሉን ሰላም እያሉና እያሳለሙ መጠብኝ!! ምክራቸው ረዥም ስለሆነ ሳያቸው ገና ይደክመኛል፡፡ እንግዲህ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም” ሊሉኝ ነው፤ ታዲያ ለእሳቸው ስል ከማን አባቴ ጋር ልሁን? የእናቴ ንሰሀ አባት ነበሩ፣
እሳቸው ግን ራሳቸውን የእኔም ንሰሀ አባት እድርገው ቁጭ አሉ፣ ንስሀ አያቴ፡፡
እጠገቤ ሲደርሱ፣ “አብረሃም እንደምን አደርክ?
"ደህና እደሩ አባ”
“አይ የአንተ ነገር፡፡ ሰው ሲያነብ መነጥሩን ነው የሚወለውለው:: አንተ ሁልጊዜም ስታነብ
ጥርስህን ትፍቓለህ፣ በጥርስህ ታነብ ይመስል አሉኝ፤ አሁን ይሄ ከንሰሃ አባት የሚጠበቅ ንግግር
ነው ? በዕርግጥ የወይራ መፋቂያ በእጄ ይዤ ነበር፡፡ በከብሮት ቆምኩና ሁለት እጆቼን እንስራ
እንደተሸከመች ሴት ከኋላዬ አነባብሬ ግንባሬን ወደ እሳቸው እሰገግኩ፡፡
ወደ ሰማይ ዓይናቸውን ተክለው ጋቢና ካርታቸውን በቀኝ እጃቸውእየሰረሰሩ ከኮታቸው የውስጥ ኪስ መስቀላቸውን ሊያወጡ ሲታገሉ በትዕግስት ጠበቅኳቸው፡፡ ሁልጊዜም እንዲህ ሲያደርጉ መስቀላቸው ከውስጥ ኪሳቸው ሳይሆን ከልባቸው ውስጥ የሚያወጡ ነው የሚመስለኝ፡፡ አሳለሙኝ፡፡ እዚህ
ሁሉ ልብስ ውስጥ ተቀምጣ መስቀላቸው ግንባሬን ስትነካኝ ለምን እንደምትቀዘቅዘኝ ይገርመኛል !
“አብረሃም!" አሉኝ ድምፃቸውን አለስልሰው፡፡ እንግዲህ ሊጀምሩ ነው)
“አቤት አባ"
“እንደው ቢመክሩህ አልሰማ አልክ.…ኧረ ተው..ተው አብረሃም ተው:: እኔ ወድጄ አይደለም
የምነዘንዝህ የናትህ አደራ ከብዶኝ ነው፡፡ ምናለ አንዷ ን ጥሩ ከርስቲያን አግብተህ ብታርፍ፡፡ ለነገሩ የት ታገኛታለህ፤ ቤተስኪያን መምጣቱንም ትተኸዋል...!! እስቲ ምን ጎደለህ? የጠገበ ደመወዝ
ትበላለህ፣ ምን የመሰለ ሰፊ አልጋ አለህ…” አሉ በአገጫቸው ወደ ቤቴ ውስጥ እያመለከቱ፡፡
እንዴ አባ..አልጋና ትዳር ምን ያገናኘዋል፡ ያላገባሁት አልጋ ይጠበኛል ብዬ መሰላቸው እንዴ
ወይስ በትዳር ወጥመድ ውስጥ እንድገባ አልጋዬ ላይ ቁራጭ ስጋ እየጣሉልኝ ነው::
“ሁልጊዜ ልጅነት የለም...እየው… አሱና ምስጢር እንደሚያወራ ሰው ጠጋ አሉኝና ጋቢያቸውን
ወደ ላይ ወደ ትካሻቸው አሰተካከሉ፡፡ ከዛም ድምፃቸውን ቀነስ አድርገኑ፣ ..እንደውም አንዲት ትሁት እግዜር የባረካት ልጅ አቃለሁ፣ ከዚህ.…ማነው..ይሄ ሴቶቹ ከሚሄዱበት አገር “ማነው…” አረብ አገር" አልኩ ቶሎ እንዲላቀቁኝ፡፡ አረብ አገር የሚሄዱት ሴቶች ብቻ ናቸው የተባለ ይመስል
“እእእ ተባረክ አረብ አገር….እና እዛ ሄዳ ትንሽ አመም አድርጓት ነው የመጣችው .ጨዋ ድምፅ
ሲወጣት የማትሰማ፣ ከቤቷ ቤተስኪያን ከቤተስኪያን እቤቷ ነው እርግት ያለች የጨዋ ልጅ
ላንተ የምትሆን ናት ግዴለህም እያት ! ሳምንት እኔው ራሴ አስተዋወቅሃለሁ፡፡ አንተማ ዞሮብሃል እንኳን የትዳር አጋር ልትፈልግ ራስህም ጠፍቶሃል.ምን ታረግ ቤትህ ጠበል አይረጭበት፡
ዳዊት እንኳን አትደግም” ልቃወም አፌን ከፍቼ ተውኩት፡፡
አይደለማ አይደለም…” ብለው እንደገና ሴላ ረዥም ምክር እንዳይጀምሩ ፈርቼ ዝም አልኩ፡፡
ብቻቸውን በግዕዝ እያነበነቡ ወደታች ወረዱ፡፡
እንዲሁ ስለመምሬ እና ለትዳር ስላሰቡልኝ ልጅ እያሰብኩ የያዝኩትን ጋዜጣ መቃኘት ጀመርኩ፡፡.....
✨ነገ ያልቃል✨

👍37❤6🔥1
#ዝግመተ_ለውጥ
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
...እንዲሁ ስለመምሬ እና ለትዳር ስላሰቡልኝ ልጅ እያሰብኩ የያዝኩትን ጋዜጣ መቃኘት ጀመርኩ፡፡.
በደማቅ ጥቁር ቀለም፣ “በማኅበር ተደራጅተው ጫት የሚያመርቱ አርሶ አደሮች ኑሯችን
ተለውጧል አሉ...” ይላል፡፡
ወረድ ብሎ፣ “አንዳንድ የማኅበሩ አባላት “ጫት በመሸጥ አይሱዙ መኪና ገዝተናል፣ ልጆቻችንንም
ከተማ ልከን እያስተማርን ነው ሲሉ ገልፀዋል” ከጽሑፉ ስር አይሱዙ መኪና ተደግፈው ፎቶ
የተነሱ አርሶ እደር ምስል ይታያል፡፡
ወረድ ብሎ ሌላ አርዕስት፣
አንድ አይሱዙ መኪና ሃያ ሜትር ጥልቀት ያለው ገደል ውስጥ ገብቶ ከላይ ጭኗቸው የነበሩ
ሰባት ሰዎች ሞቱ፡፡ ከሟቾቹ አራቱ ከገጠር ከተማ እየተመላለሱ የሚማሩ ተማሪዎች ሲሆኑ
ፖሊስ የአደጋው መንስዔ ሹፌሩ ጫት እየቃመ ማሽከርከሩ ነው ብሏል !"
ጋዜጣውን እጥፌ ሰፈራችንን ማየት ጀመርኩ፡፡ ቅድስት ቀይ የእራት ልብስ ለብሳ እቃ ታጥባለች፧እያንጎራጎረች፣ “በሰባራ ፎሌ ውሀ አያጠለቅም" አይ ቅድስት ! እንደኛ ሰፈር ሴት የባከነበት መንደር ያለ አይመስለኝም፡፡ ቆንጆ ናት 'ሞዴል' የመሆን ፅኑ ፍላጎት ነበራት፡፡ እንደውም የሰፈር ልጆች ሲፎግሯት፣ “ውበት ውጪያዊና ውስጣዊ ነው' ሲሉ ሰምታ ውስጣዊ ውበቷን ለማየት
እልትራሳውንድ ተነሳች” ይሏታል፡፡ ሰታንጎራጉር እየሰማኋት የድምጿ ማማር ተገረምኩ፤
“ወይ ይህቺ አገር ዘፋኞቿ በየማጀቱ እቃ እያጠቡ እቃ አጣቢዎቿ በየአደባባዩ እንዝፈን እያሉ ያደነቁሩናል" አልኩ ለራሴ፡፡ የቄሳርን ለእግዜር፡ የእግዜርን ለእግዚሃር፡፡
የመንደራችን የአንድ እሁድ ውሎ ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው ነው:: ከጧቱ 12፡00 ሰዓት
አልማዝ የምትባለው ጎረቤታችን በሯ ላይ ስለተጣለው ድግምት ታማርራለች፣ ትራገማለች፡
ጠበል ታርከፈክፋለች፡፡ ድግምት በመጣል የሚጠረጠሩ ጎረቤቶቿን ታሸሙራለች፣ “እችኑ ኑሮ
ብለዋት...” እያለች፣ ብዙ ጊዜ የሞተ እይጥ ነው በሯ ላይ ተጥሎ የሚገኘው:
ከ 12፡30 እስከ ጧቱ 2፡00 ሰዓት እማማ ዘብይደሩ ጭንቅሎ የተባለውን የልጅ ልጃቸውን
ይረግማሉ፣ ይሳደባሉ፣ ይውገራሉ፡፡ አንዳንዴ ወገራው ሲበዛ ገላጋዮች ይገባሉ፡፡ “ባጭር ቅር….ይሉትና ሲታመም ሆስፒታል ለሆስፒታል አዝለውት ይዞራሉ፡፡
ከሁለት ሰዓት እስከ አራት ሰዓት የመንደሩ ልጆች እኔ ቤት ፊት ለፊት ያለች (ሰርቪስ ቤት እንኳን
የማታቆም) ቢጢቃ ሜዳ ላይ ኳስ ይራገጣሉ፡፡ የሚያስነሱት አቧራ ልጆቹን ስለሚሸፍናቸው
እንደ ህልም ነው ብዥ ብለው የሚታዩት፡፡
ከሚጫወቱት ልጆች መሃል ጭንቅሎ (የእማማ ዘብይደሩ የልጅ ልጅ)፤ ሃይለሚካኤል 'አረቡ'
(የእማማ የውብዳር የልጅ ልጅ)፣ ሙስጠፋ (የእማማ ዘሃራ የልጅ ልጅ)፣ ሲቲና ወንዳወንድ ሰለሆነች 'ከቤ' ይሏታል (የነማማ ትርሃስ የልጅ ልጅ ናት)፤ ከላይ ከተዘረዘረው የዘር ሃረግ
እንደሚታየው መንደራችን አንድ እናት' የሚባል ትውልድ ገድፏል፣ አባት የሚባል ሃረግ ዘሏል
ሕፃናቱ ከአያቶቻቸው ጋር ነው ያደጉት፡፡ ያውም አቅም ከሌላቸው ደሃና እቅመ ደካሚ ባልቴት
አያቶቻቸው ጋር! እናቶቻቸው የት ሄዱ? አባቶቻቸውን ምን በላቸው?' ቢባል መልሱ ከሁለት
ጉዳዮች አያልፍም፡፡ እንድም ወልደው ለእናቶቻቸው እየሰጡ አረብ እገር ሄደዋል፡ አልያን
በኤችአይቪ አልቀዋል፡፡ የመንደራችን እውነታ ነው ይሄ !! ደግሞ ሕፃናቱ የተመካከሩ ይመስል በየምክንያቱ ሲጣሱና ሲነታረኩ የሁሉም መሃላ አንድ ዓይነት፣ እናቴ ትሙት !” የሚል ነው፡፡
ልክ ከአራት ሰዓት እስከ አምስት ሰዓት፣ ሁላቱ የመንደራችን እንጀራ ሻጮች ሙሉና ዝናሽ. ዱላ ቀረሽ ስድድብ ይጀምራሉ፡፡ በደንበኛ መቀማማት ነው የሚጣሱት፣
“ለማያውቅሽ ታጠኚ..ደግሞ ሙያ እንዳለው ሰው:: ማየት የተሳነው እንጀራ እየጠፈጠፍሽ.
እኩል ታወሪያለሽ…"
“ኤጅ እባከሽ…እኔ ሙሉ በወፍጮ ቤት ጥራጊ አይደለም ደንበኞቼን የማስተናግደው፣ ጥርት
ባለ ጤፍ ጥር…ት”
“ሂሂሂሂሂ መጣፈጡ ቀርቶ እጄን በሰቀቀኝ አሉ እትዬ አሰለፍ፣ ጥራቱ ቀርቶብሽ ቡሃቃሽን
በወር እንዴ እንኳን ባጠብሽው:: ሰዉን ሁሉ በሆድ ቁርጠት ጨረሽው” ትላለች ዝናሽ። የሙሉ
ደንበኛ ስለሆንኩ በዚህ ኣባባሏ ሆዴ ይጮሃል፣ ..ኡ... ወር ሙሉ የማይታጠብ ቡሃቓ እቺ
ስድድብ ደንበኛን ለማስከዳት ወሳኝ የቃላት ጦርነታቸው ናት፡፡
ልክ አምስት ሰዓት ሲሆን እማማ መጣፈጥና ስንቅነሽ ቡና ይጠራራሉ፡፡ ወደ ስድስት ሰዓት
ጀሚላ የቅንድቧን ኩል ጆሮና ጆሯዋ ጥግ ድረስ ተኩሳ በስልኳ እያወራች ወደላይ ትጣደፋለት፡
ሃቢቢ መጣሁ ወጥቻለሁ” እያለች፡፡ ኣፍንጫ የሚሰነፍጥ ሽቶዋ መንደሩን ያውደዋል፡፡ ጀሚላ ስታልፍ ጥርኝ ያለፈች ነው የሚመስለው:: የታከከችው ነገር ሁሉ ሽቶ ሽቶ፣ መቼም ሃቢቢዩ
የአፍንጫ መሸፈኛ ማስካ ያደረገ ሰው መሆን አለበት፡፡
ይሄን ሁሉ ሳይ ይከፋኛል። ብቸኝነት ይጫጫነኛል፡፡ ከወንዙ ተገንጥሎ ኩሬ ውስጥ እንደተኳታሪ ውሃ እዛው የምሻግት አልያም የተቀመጥኩበት በትነት የማልቅ ነገር መስሎ ነው የሚሰማኝ
ይሄን…የተረገመ እሁድ ወደዛ አልቆ ሥራዩ በገባሁ ! ለነገሩ ከእሁድ ይሻላል ብዬ እንጂ ሥራዬም ሠልችቶኛል፡፡ የባንክ ሠራተኛ ነኝ፡፡ ብዙ ሰዎች የባንክ ሠራተኛ መሆኔን እንደትልቅ እና አስደሳች ሥራ እድርገው ሲያወሩ ይገርመኛል፡፡ ለእኔ የባንክ ሥራ በምድር ላይ ካሉ አስከፊ ሥራዎች
ሁሉ አስከፊው ይመስለኛል፡፡ እንደውም ለሰው ሳይሆን ለሮቦቶች የሚስማማ ሥራ ቢኖር የባንክ ሥራ ነው እያልኩ አስባለሁ፡፡
አንድ አይነት ቅርፅ ያላቸው ብር ዮሚባሉ መርገምቶችን መቁጠር፡፡ አራት ዓመት ሙሉ
ቆጠርኳቸው..ኤጭ ድፍን አገር የሚራኮትለት ብር ለእኔ አንዳች ቆሻሻ ነገር መስሎ ነው
የሚታየኝ፡፡ ብር ይሸታል፡፡ ካላመናችሁ ወደ ኣፍንጫችሁ አስጠጉና ሞክሩት፡፡ እንደ ብር
መጥፎ ሽታ ያለው ነገር ምን አለ ? ለነገሩ የዘንድሮ ብር ላሸትተውም ብትሉ አፍንጫችሁ ላይ
ላይደርሰ ያልቃል ሰላቢ ነገር ነው::
ምስላቸው ብር ኖት ላይ ያሉት ሰዎች ከመኖር ብዛት የቢሮ ባልደረባ መስለውኛል፡፡ ደግሞ
አልወዳቸውም፡፡ ለምሳሌ አንድ ብር ኖት ላይ ምስሉ ያላውን ሰው መንገድ ላይ ባገኘው ገላምምጬው የማልፍ ይመስለኛል፡፡ አስር ብር ላይ ያለችው ሴትማ ስታበሳጨኝ፤
የሆነች ነገረኛ ነገር፡፡ በደንብ አይታችኋታል? ስፌት የምትሰፋ ትመስላለት እንጂ ጆሮዋን አቁማ
ነገር የምትሰማ እኮ ነው የምትመስለው፡፡ ደግሞ ፊቷ ላይ የአሽሙር ፈገግታ አለ፡፡ ከሁሉም
ከሁሉም የሚያበሳጨኝ ነገር ደግሞ ከንፈሯ ! የከንፈሯ ማማር የሰብለን ከንፈር እኮ ነው
የሚመስለው !! ከነስፌቷ እጎኗ ላለው አንበሳ ነበር መስጠት !!
ባንክ ቤት ስትሰሩ ስጋችሁ በሱፍ ተጀቡኖ ወሩ መጨረሻ ላይ የሱፍ ቆሎ መግዣ እንኳን የማይተርፋችሁ መናጢ ደሃ መሆናችሁን ብዙ ሰው አይረዳም፡፡ ቁጥርና ስጋት ባንድ ላይ
የሚኖሩት ባንክ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ብር ስትቆጥሩ በስጋት ነው:: አንዱን የብር ኖት ሌላ የተደራረበ እየመሰላችሁ በፍትጊያ ፍዳውን ታበሱታላችሁ፡፡ በዛ ላይ ሰው ለብር ያለውን ሟችነት፣ ስግብግብነት፣ ደግነትም ጭምር ትታዘባላችሁ፡፡

👍32❤1👎1👏1🎉1