ቤቴ ገብቼ ቱታ ቀየርኩና ፍራሹ ላይ በጀርባዬ ተንጋልዬ በእፎይታ ተነፈስኩ፡፡ ወዲያው በር
ሲንኳኳ በግርምት ወደበሩ ተመለከትኩ፡፡ ጆሮዬን አቁሜ ብጠብቅም ምንም ድመፅ አልነበረም መልሼ ጋደም ልል ስል በድጋሜ ተንኳኳ፤ በቀስታ ! ላለፉት ሰባት ወራት አንድም ጊዜ በሬ ተንኳኩቶ ስለማያውቅ ተገረምኩ፡፡ “ማነው?” አላልኩም፡፡ በቀጥታ ሄጄ ከፈትኩት፡፡ አንዲት
ስለሚታይ ቅዝቃዜው ያስጎመዣል፡፡ ምራቄን ዋጥኩ እና ልጅቱን አየኋት፡፡ እሷም ታስጎመዥለች፣ሬራ
እሷን እንደመድኃኒት ውጦ በያዘችው ውሃ ማወራረድ ነበር!
እየፈራች “ሱቅ ውሃ ጠይቀህ ስላጣህ ከቤት አምጥቼልህ ነው"አለችኝና ውሃውን ዘረጋችልኝ፡፡
ሳላንገራግር ተቀበልኳት፡፡ 'ቴንኪው የለ ! ምን የለ !
ቆንጆ ነች !በጣም ቆንጆ ነች !በተለይ ዓይኗ፣ በተለይ ጥቁር የሚያብረቀርቅ ፀጉሯ ከቁጥርጥሩ ገና የተፈታ እንደሆነ ያስታውቃል፡፡ በተለይ ደግሞ ጡቷ ! የለበሰችውን ስስ ቦዲ ስሸካክቶ ሊተኮስ የተሰናዳ የሆነ ተተኳሽ ነገር !! በተለይ ደግሞ ሁሉም ነገሯ፡፡
የተጋለጠ ደረቷ ማር የተንጣለለበት ሜዳ ይመስላል፡፡ ቆንጆ ነበረች፣ ግን ልጅ ነበረች፤ ቢበዛ አስራ ስድስት ቢሆናት ነው፡፡ ዞር ስትል መቀመጫዋንም አይቻለሁ...(ለምን ይደበቃል?)፡፡
ለአስራ ስድስት ዓመት ልጅ ይበዛል፤ ግን ቆንጆ ቆንጆ እና ልጅ፣ ቆንጆ ልጅ !! እንትፍ ትፍ
ትፍ እደጊ ! መቼም አዲሳባ ቆንጆ እያጣመመ ነው የሚያሳድገው !! ለማንኛውም እደጊ !!
ከእኔ በር ወደ ራሷ ቤት ስትሄድ እኔም ውብ ሰውነቷን ቆሜ ስገመግም አንድ መንገደኛ
ሜሪ !” አላት፤ እርፍ !! ሜሮን ናት ለካ !! በፍቅር ውሃ ጥም ለዓመታት ያደረቀችኝ ሜሮን የምትባል ደረቅ ወንዝ ተሻግሬ በቀዝቃዛ ውሃ ጥሜን የምታስታግስ ሜሮን የምትባል ጅረት ላይ ደረስኩ፡፡
ሜሮንን ተሻግሮ ሜሮን እለች ወይ
ሞትና ውሃ ጥም አንድ አይደለም ወይ፡፡
እየጠጣህ አብርሽ ! ብዬ ራሴን ጋበዝኩት፡፡ ቀዝቃዛውን ላንደቀድቀው ነበር፤ ግን ገና አንዴ
ስጎነጭለት ጥርሶቼ ሁሉ ጠፉኝ፤ ቦታቸው ላይ ደነዘዙ፤ ምን እዳ ነው ! ልብም ጥርስም ደንዝዞ
የት ይደረሳል !? ጥርስ የሌለው ልበ ቢስ አንበሳ የሆንኩ መሰለኝ፣ ቢሆንም አንድ የተለኮስ
ነገር ነበር፡፡
ፍሪጅ እና ቦኖ ውሃ በምን ይለያያል !?
ሜሮን ትላንት ያመጣችልኝን ጆግ ልትወስድ ስትመጣ ፈገግ ብዬ ተቀበልኳት፡፡ ባዶዋን አልነበረችም፡፡ ሌላ ጆግ ሙሉ ቀዝቃዛ ውሃ ሰጥታኝ ባዶ ጆግ ወሰደች፡፡ .…ጆግ ውሃ .ጆግ
ውሃ ፤ ከብዙ የጆግና ውሃ ምልልስ በኋላ ተቀራረብን፡፡
“የት ነው የምትማሪው ?
“ሚኒሊክ…” ጆግ ውሃ …ጆግ ውሃ…
"አሳይመንት ተሰጥቶኝ ነበር ጊዜ ካለህ ትሰራልኛለህ ?”
አምጭው ኧረ !” ብጥርጥር አድርጌ ሰራሁላት፣ አስረዳኋት፤…አንዴዴዴዴ! እንዲህ አይነት
አደገኛ አስተማሪ ነበርኩ እንዴ ለካ !
ጆግ.ውሃ ጆግ..ዉሃ እና አንድ ቀን ለስላሳ ቀዝቅዝ ያለ ሚሪንዳ !!
“የምን ለስላሳ ነው ሜሮን ?”
“ታዘብኩህ ዛሬ ልደቴ ነበር፣ 16 አመቴ፤ ሃፒ በርዝደይ! ሳትለኝ” ፈገግ ብላ፡፡
“በቃ ቅዳሜ ራሴ አከብርልሻለሁ”
“ፕሮሚስ ?!” ብላ የሚያምር መዳፏን በጉጉት ዘረጋችልኝ፤ ፊቷ በፈገግታ ተጥለቅልቆ ነበር፡፡
“ፕሮሚስ !” ብዬ መዳፌን መዳፏ ላይ አስቀመጥኩ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ መነካካታችን ነበር !!
እጄን አልሰበሰሰችም፤ እኔም እጄን አላነሳሁም፡፡ እግዜር መሃላውን እስካፀድቀው እጃችሁን
እንዳለ ሳይለያይ አቆዩት!” ያለን ነበር የምንመስለው፡፡ ዓይኗ ውስጥ ፀሐይ አየሁ፤ ሁለት ፀሐይ!አማረችኝ፡፡ የሆነ የሚያምር መናፈሻ መሰለችኝ፡፡ ውስጧ እረፍት የተዘራ፡፡ ሲደከም ለኖረ
አንድ እኔ ሰፊ አልጋና እረፍት ያለባት አገር፡፡
ጆግ ውሃ ጆግ ውሃ ቅዳሜ ሆነ !!
ከማክሰኞ እለከ አርብ ያላሰብኩትን ቅዳሜ ጧት ተጨነቅኩ፡፡ የእስራ ስድስት ዓመት ልጅ ይዤ የት አባቴ ነው የምጋብዛት ? ..ቤተሰቦቿስ ምን ይላሉ? (ለነገሩ ሴት አያቷ እና እሷ ብቻ ናቸው የሚኖሩት) .. ቢሆንም ጎረቤቱስ ምን ይላል?…ወይ ጉድ !
ሜሮን በጧት መጣች፤ ተኝታም ያደረች አልመሰለኝም፡፡
“አንተ እስካሁን ተኝተሃል !?” አለችኝና የተኛሁበት ፍራሹ ጫፍ ላይ ተቀመጠች፡፡ ቤቴ መግባት
ፍራሽም ላይ መቀመጥ ጀምራለች፡፡ ጧት ስትመጣ ደስ አይለኝም፤ ስስ ፒጃማ ቁምጣና
ባለማንገቻ ጉርድ ቦዲ ስለምትለብስ እፈተናለሁ፡፡ በዛ ላይ በጣም ተጠጋግተን ስለምንቀመጥ ጠረኗ አፍንጫዬን ይዞ ወደ ጡቶቿ መሃል ይጎትተኛል፡፡ ፈተና ነው በቃ !…እርሷ ደግሞ በፍፁም "ንጹህ ልብ እንደፈለገች ትሆናለች፡፡
በቃሌ መሰረት ልደቷን ልናከብር ተቀጣጠርን፡፡ ከሰፈር አብረን መውጣቱ ለጎረቤት ሃሜት
ስለሚዳርግ የሆነ እሷ የመረጠችው ሬስቶራንት ስምንት ሰዓት ላይ እንገናኝ ተባባልን፡፡....
✨ነገ ያልቃል✨

👍31❤2
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አራት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
...ጫጫታ ከሩቅ ተሰማ:: ዣን ቫልዣ አንዱን ቤት ተጠግቶ ለመደበቅ ፈለገ፡፡ ከሩቅ የሚንቀሳቀስ ጥላ ተመለከተ:: ሰዎች ወደ እርሱ ማምራታቸውን
ተገነዘበ፡፡ ተንጠላጥሎ ድምፅ ወደሚሰማበት አቅጣጫ ተመለከተ፡፡ የዣቬርን ግዙፍ ሰውነት መለየት አላዳገተውም፡፡ በፖሊስ ጥንቃቄ ግራና ቀኝ እያዩ
መራመዳቸውን ተመለከተ፡፡ ቆም እያሉ፣ አካባቢውን እየሰለሉ ነው
የሚሄዱት፡፡ የመደበቂያ ሥፍራ እንዳለ ኣጥርተው እንደሚፈትሹ
ያስታውቃል፡፡ ሰፈሩ ማምለጫ መንገድ የለውም::
በዚያ አካሄዳቸው ሥፍራውን እየፈተሹ ሲመጡ ዣን ቫልዣ
ከነበረበት ለመድረስ ምናልባት ሩብ ሰዓት ቢወስድባቸው ነው:: እጅግ በጣም የሚያስጨንቅ ሰዓት ነበር፡፡ በሕይወቱ ዘመን ለሦስተኛ ጊዜ ከአስፈሪ
ሕይወት ጫፍ ላይ የደረሰ መሰለው፡፡ አሁን ያስጨነቀው የእስር ቤት ኑሮ ብቻ ሳይሆን የኮዜት ከእርሱ መለየት ጭምር ነበር፡፡ ሁለት አማራጭ ነበረው፤ የመለኮት ኃይል አውጣኝ ብሎ መማጠን ወይም ባለው ጉልበት
ተጠቅሞ ሰዎቹን መጋፈጥ፡፡
እስር ቤት ባገኘው ልምድ ዣን ቫልዣ ቀጥ ካለ ግንብ፧ ቁመቱ እንደ ፈለገው ቢረዝም እንኳን፤ በቀላሉ የመውጣት ችሎታ አለው:: ከፊት ለፊቱ የነበረውን ግንብ ርዝማኔ በዓይኑ መተረው:: ወደ አምስት ሜትር ገደማ ይሆናል፡፡ በተጠረበ ድንጋይ የተሠራ ግንብ ነበር፡፡
አሁን የምታስቸግረው ኮዜት ስትሆን ኮዜት ከግንብ ላይ መውጣት አታውቅበትም:: ታዲያ ይተዋት? አሳቡ አንገሸገሸው:: እርስዋን ተሸክሞ መውጣት ደግሞ የማይቻል ነው፡፡
መፍትሔው ትልቅ ገመድ እንደሆነ ተገነዘበ፡፡ ግን ዣን ቫልዣ
ገመድ አልነበረውም:: ታዲያ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ገመድ ከየት ሊያመጣ ይችላል? በዚያች ሰዓት ዣን ቫልዣ አገረ ገዢ ቢሆን ግዛቱን በአንድ ወፍራምና ረጅም ገመድ ይለውጥ ነበር፡፡
የሚደንቀው አንዳንድ ጊዜ በጭንቀት ሰዓት የሚያስገርም ወይም ዐለማመን የሚያስቸግር ነገር ይሆናል:: ቫንቫልዣ ግራና ቀኙን ሲቃኝ መብራት የተንጠለጠለበት ገመድ አየ:: በዚያን ብርሃን ባልነበረበት ዘመን በጋዝ የሚሠሩ መብራቶች ከፍ አድርገውና የሚሰቅሉትና የሚያወርዱት በወፍራምና በረጅም ገመድ ነበር፡፡
ዣን ቫልዣ ገመዱ ወደ ተንጠለጠለበት ሮጦ በያዘው ቢላዋ ቆረጠው።ቀደም ሲል እንደተገለጸው በተለይ ያን ምሽት ጨረቃዋ ሙለ ስለነበረች
የመንገድ መብራቶች አልተለኩሰም:: ስለዚህ ዣን ቫልዣ ገመዱን ሲቆርጥ ምናልባት መብራቱ ቢሰበር ልብ የሚለው አልነበረም:: ኣካባቢውም ጭር
ያለ ነበር፡፡ዣን ቫልዣ ከወዲህ ወዲያ ሲሮጥ፤ ዓይኑ ሲቅበዘበዝ አሳብ ሲያስጨንቀው በማየትዋ ኮዜት ደነገጠች:: እርስዋ በመሆንዋ እንጂ ሌላ
ልጅ ብትሆንማ ልቅሶዋን ነበር የምትለቅቀው፡፡ የኮቱን ጭራ አጥብቃ ይዛ ዝም ብላ ነበር የምትከተለው፡፡ በአካባቢው የሚሰማው ድምፅ እየጎላ መጣ።
«አባባ» አለች ኮዜት በጣም ዝቅ ባለ ድምፅ፤ «ፈራሁ፤ ማነው
የመጣው?
«ዝም በይ፤ ዝም በይ» አለ የተከፋው ሰው፤ «ሚስስ ቴናድዬ
ናት፡፡»
የኮዜት ሰውነት በፍርሃት ተንቀጠቀጠ! ሰውዬው ንግግሩን ቀጠለ፡፡
«አይዞሽ እኔ አለሁልሽ፤ ግን ዝም ነው፤ ካለቀስሽ ወይም ድምፅ ካለማሽ ሚስስ ቴናድዬ ትሰማሻለች፡፡ አንቺን ፍለጋ ነው የመጣችው::»
ዣቬርና ሌሎች ፖሊሶች እነርሱ ከነበሩበት ደርሰው ሊይዟቸው
ስለሚችሉ ጊዜ ማባከኑ ይበልጥ የሚያጋልጥ መሆኑን ተገነዘበ፡፡ ከረባቱን አውልቆ በከረባቱ የኮዜትን ወገብ አሰረ:: ጫማውንና ካልሲውን አውልቆ ከግንቡ ላይ ወረወረ፡፡ የገመዱን አንዱን ጫፍ ከቋጠረ በኋላ ከኮዜት ወገብ
ላይ ከታሠረው ከረባት ጋር አሰረው:: ከዚያ በኋላ የገመዱን አንድ ጫፍ በእጁ ይዞ ከግንቡ ላይ መውጣት ጀመረ:: ኮዜት ከመሬት ሆና ዝም ብላ ታየዋለች:: የሚስስ ቴናድዬ ስም በመጠቀሱ በጣም ስለደነገጠች ለመናገር
ብትፈልግ እንኳን መናገር አትችልም::
ብዙ አልቆየም ወዲያው እጅግ ዝቅ ባለ ድምፅ ዣን ቫልዣ ሲጠራት ሰማች::
«ጀርባሽን ለግድግዳ ስጪ፡፡»
እንዳዘዛት አደረገች::
«እንዳትናገሪ፧ እንዳትፈሪ» አለ ዣን ቫልዣ ቀጠለና፡፡
ከግንቡ ጫፍ ደረሰች:: ወዲያው ዣን ቫልዣ እቅፍ አደረገና በጀርባው መሬት ለቅቃ ስትንጠለጠል ታወቃት፡፡ የት እንዳለች ሳታውቅ አዘላት:: እጆችዋን በግራ እጁ ያዘ፡፡ እንደገመተው ከግንቡ ኋላ ቤቶች
ነበሩ። በውስጥ በኩል የግንቡ ርቀት እስከዚህም ሩቅ አልነበረም:: ርቀቱን በዓይኑ መተረው፡፡
ልጅትዋን እንዳዘለ በቀላሉ ከአንድ ቤት ጣራ ላይ ለማረፍ ቻለ::
ከላይ ሆኖ ከአጥሩ ውጭ የዣቬርን ድምፅ ሰማ፡፡
«በየመንገዱ ፣ በየሥርቻው ቶሎ ብላችሁ ፈልጉት፡፡ በየቤቱ
እየገባችሁ ፈልጉ፡፡ ስለሚደርሰው ነገር እኔ አልፋለሁ» አለ ዣቬር እየጮኸ
ዣን ቫልዣ ከጣራው ላይ ቁጭ አለ፡፡ ኮዜትን በገመዱ አንጠልጥሉ የዛፍ ግንድ ይዛ በመውረድ መሬት እስክትደርስ ጠበቃት፡፡ ኮዜት ጎብዛም
ይሁን ፈርታ ቃል አልተነፈሰችም:: እጅዋን ሲጨብጣት ግን በጣም አልቦአት ነበር፡፡
ዣን ቫልዣ ከጣራ ወርዶ ሲጓዝ ከአንድ የአትክልት ቦታ ደረሰ
አካባቢው በጣም ጭር ያለ ነበር፡፡ በመጀመሪያ ጫማውንና ካልሲው
መፈለግ ነበረበት፡፡ ጫማውን ፈልጎ ካጠለቀ በኋላ ከኮዜት ጋር ከዛፍ ስር ተቀመጡ፡፡ ምንጊዜም ቢሆን የሚሸሽ ሰው ያመለጠ ስለማይመስለው ሁልጊዜም እንደ ደነገጠ ነው፡፡ ኮዜት ስለፈራች ከጎኑ ተሸጉጠች:: እነዣቬር ከሁንም ሲጠራሩ አሁንም ይሰማል፡፡ ግን ከሩብ ሰዓት በኋላ ድምፁ እየደከመ ሄደ
ቢሆንም የዣን ቫልዣ ልብ አሁንም አልረጋም፡፡ ኮዜትም ዝምታዋን ቀጠለች ከዚህ መጣ የማይባል ድምዕ በድንገት ተሰማ:: የደናግል ዝማሪ ነበር፡፡ ደናግል ተሰባስበው የሚዘምሩት አትክልት ውስጥ ነበር፡፡ ድምጻቸው ጥርት ብሎ ነው የሚሰማው:: ዣን ቫልዣ ይህን ድምፅ ሲሰማ የድምፁ።
አቅጣጫ ፍለጋ ዞር አለ፡፡
ፊቱን ሲያዞር ከአትክልቱ ውስጥ ሰው መኖሩን አየ:: አንድ ሰው
ጎንበስ ቀና ይላል፡፡ ሰውዬው ሥራ ይዞ መሆን አለበት፧ እቃ ከአንድ
ሥፍራ አንስቶ ወደ ሌላ ቦታ እንደሚወስድ ሰው ጎንበስ ይልና ቀና ብሎ ጥቂት ይራመዳል፡፡ ተመልሶ መጥቶ ጎንበስ ይልና ቀና ብሉ ይሄዳል።
ዣን ቫልዣ ደነገጠ፡፡ ምናልባት ዣቬርና ተከታዮቹ እዚህም ጠባቂ
ያስቀመጡ መሰለው:: ይህ ሰው የእነርሱ አባል ከሆነ «ሌባ፤ ሌባ» እያለ ቢያሲዘኝስ ሲል አሰበ፡፡ የተኛችውን ኮዜት ቀስ ብሎ አንስቶ ግቢው ውስጥ ከነበረው አሮጌ አግዳሚ መቀመጫ ላይ አሳረፋት:: ኮዜት አልነቃችም፡፡
ከኮዜት አጠገብ ተቀምጦ የሰውዬውን እንቅስቃሴ ተከታተለ፡
የቃጭል ድምፅ ይሰማል፡፡ ሰውዬው አንድ ነገር ለማንሳት ጎንበስ ሲል ቃጭሉ ሲቃጨል እኩል ስለመጣ ዣን ቫልዣ ይህ አጋጣሚ ይቀጥል!እንደሆነ ጠበቀ፡፡ አሁንም እኩል መጣ፤ ጨርሶ አልተዛባም:: ሰውዬው
ሲንቀሳቀስ ቃሉ ድምፅ ያሰማል፡፡ ሲቆም ዝም ይላል፡፡ የሚደንቀው!
ደግሞ ሰውዬው ሥራውን ጨርሶ ሲያርፍ ደወሉም ፀጥ ይላል፡፡ የደወሉ ገመድ ከሰውዬው ወገብ ላይ ታስሮ ይሆን?» ሲል አሰበ፡፡
ይህን እያሰላሰለ የኮዜትን እጅ አሻሽ፡፡ እንደበረዶ ቀዝቅዟል፡፡

👍19🔥2🥰1
“ምን ይሻላል?» ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡
«ኮዜት» ሲል በለሰለሰ ድምዕ ጠራት::
ዓይንዋን አልገለጠችም፡፡ ቀስ ብሎ ወገብዋን ይዞ ነቅነቅ አደረጋት፡፡
«እንዴ፤ ይህቺ ልጅ ሕይወትዋ ከሥጋዋ ተለየ እንዴ?» ሲል
በድንጋጤ ከተቀመጠበት ብድግ አለ::
አልጋ ላይ እንደተኛ ሰው እግርዋን ዘርራ ነው የተኛችው:: ትንፋሽዋን
አዳመጠ፤ ትተነፍሳለች፡፡ ሕይወቱ መለስ አለች፡፡ ብርዱ ሊጎዳት እንደሚችል ያውቃል፡፡ «ምን ላልብሳት? በምን ላማሙቃት? በብርድ ልትሞት ነው»
ሲል አሰላሰለ፡፡ ከነበረበት ጥቂት ተራምዶ ከሥፍራው ፈቀቅ አለ:: የብርድ ልብስ ያገኝ ይመስል ዓይኑ ተቅበዘበዘ፡፡ በቶሎ ኮዜት ከቤት ውስጥ ገብታ ቢቻል እሳት መሞቅ እንዳለባት አስተዋለ፡፡
በቀጥታ ሲንቀሳቀስ ወዳየው ሰውዬ ሄደ፡፡ ከሰደርያው ኪስ ውስጥ ጠቅልሎ ያስቀመጠውን ገንዘብ አወጣ፡፡ ሰውዬው አጎንብሶ ይሠራ ስለነበር ወደ እርሱ የሚመጣውን ዣን ቫልዣን አላየውም:: ዣን ቫልዣ ሰውዬው
ከነበረበት ደረሰ፡፡
ዣን ቫልዣ ጠጋ ብሉ «መቶ ፍራንክ› ሲል ተናገረ:: ሰውዬው
ደንግጦ ቀና አለ፡፡
«ካሳደርከኝ መቶ ፍራንክ እከፍላለሁ» አለ ዣን ቫልዣ፡፡
ከዣን ቫልዣ ፊት ላይ የጨረቃ ብርሃን አርፎ ነበር፡፡
«እንዴ፤ አባታችን ማንደላይን፤ ከእዚህ ምን ትሠራለህ?» ሲል
ሰውዬው ጠየቀው፡፡
በዚያ ጨለማ፤ በዚህ ባልታወቀ ቦታ፤ በዚህ በማይታወቅ ሰው ይህ
ስም ሲጠራ በመስማቱ ዣን ቫልዣ ወደኋላ ሸሽት አለ፡፡
ሰውዬው ያጠለቀውን ቆብ ብድግ አደርጎ እጅ ነሳው።
“ቁጭ በል! ቁጭ በል! ቤት ለእንግዳ:: ግን አባታችን እዚህ እንዴት መጣህ? እንዴ፤ ደግሞ ከዚህ ግቢ ውስጥ እንዴት ልትገባ ቻልክ? ከሰማይ ነው የወረድከው ወይስ ከምድር ነው የፈለቅከው?» ሲል በጥያቄ አጣደፈው::
ማን ነዎት እርስዎ? ቤቱስ የማነው? » ሲል ዣን ቫልዣ ሰውዬውን ጠየቃቸው::
«በጣም ነው ደስ ያለኝ» አሉ ሽማግሌው:: «አንተ እኮ ነህ ከዚህ ያስገባኸኝ:: ይህን ቤት ደግሞ አንተ ነህ ያሰጠኸኝ፡፡ እንዴ! እንዴት ይሆናል፧
አታስታውሰኝም?»
«ይቅርታ፧ አላስታወስኩም ኣላ ዣን ቫልዣ :: «የት ነው !
የምንተዋወቀው?»
«ሕይወቴን እኮ አድነሃታል» አለ ሰውዬው::
ዣን ቫልዣ አሁን ትዝ አለው፡፡ የሽማግሌውን ፊት አስተዋለ::
እኚያ የጭነት ጋሪ ተጭኖዋቸው ሊሞቱ ሲሉ ከጋሪው እግር ፈልቅቆ
ያወጣቸው ሰው መሆናቸውን አወቀ፡፡
«ለካ እርስዎ ነዎት!» አለ ዣን ቫልዣ ፤ «አሁን አስታወስኩ ሚስተር ፎሽለማ ነዎት፤ አይደለም?»
«ጥሩ አጋጣሚ ነው» አሉ ሽማግሌው::
«እርስዎስ ከዚህ ምን ይሠራሉ?» ሲል ዣን ቫልዣ ጠየቀ፡፡
«ከዚህ ሥራ እየሠራሁ ነው፤ አንተስ ምን ትሠራለህ?» አሉ ቀጠሉና።
ዣን ቫልዣ በቀድሞ ስሙ እየጠራ የሚያናግረውና የሚያውቀው
ሰው በማግኘቱ ጥቂት ተዝናና፡፡ የእንግዳ ዓይን አውጣ እንደ መጠየቅ እርሱ ጥያቄ ያበዛል፡፡
«ጉልበትዎ ላይ ያሰሩት ደወል ምንድነው?»
«እሱማ» አሉ ሽማግሌው፧ «መምጣቴን አውቀው ከእኔ እንዲሸሹ ድምፅ የማሰማበት መሣሪያ ነው፡፡»
«ከእኔ እንዲሸሹ?»
አዎንታቸውን ለመግለጽ ሽማግሌው ግንባራቸውን ወደ ላይ ሳብ አደረጉ፡፡
«ከዚህ ግቢ ውስጥ ያለው ከእኔ በስተቀር ሁሉም ሴት ነው:: ወጣት
ልጃገረዶች በብዛት አሉ፡፡ ከእኔ ጋር መገናኘቱ አደገኛ ነው መሰለኝ፤ ደወለ ለመምጣቴ ማስጠንቀቂያ ነው:: እኔ ስደርስ ይሸሽጋሉ፡፡»
«ቤቱ የኔ ነው?»
«ምነው፧ ታውቀው የለም እንዴ?»
«የለም፤ አላውቀውም፡፡»
«ምነው፧ አንተ አይደለህም እንዴ በአትክልተኝነት ተቀጥሬ እንድሠራ
ያደረግኸው:: »
«ለምጠይቀው ጥያቄ ምንም አያውቅም ብለው በመገመት መልስ ይስጡኝ።»
«አንተ ካልክ እሺ፡፡ ይህ ገዳም እኮ በዚያን ጊዜ የፐቲ ፔክፐስ ገዳም ነበር የሚባለው፡፡»
ዣን ቫልዣ አስታወሰ፡፡ በአጋጣሚ ከሚያውቀው ገዳም መግባቱን
ተገነዘበ፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት ሽማግሌው የእቃ መጫኛ ጋሪ ወድቆባቸው እያለ የአካል ጉዳት ስለደረሰባቸው በአትክልተኝነት ገዳሙ እንዲቀጥራቸው
የድጋፍ ደብዳቤ ጽፎላቸው ነበር፡፡ የድጋፉ ደብዳቤ ነው እንዲቀጠሩ
የረዳቸው፡፡
«የፐቲ ፔክፐስ ገዳም» አለ ዣን ቫልዣ እርስ በራሱ ይነጋገር
ይመስል፡፡
«እንዴት ኣድርገህ ከዚህ ልትገባ እንደቻልክ ንገረኝ እንጂ ፤ ሰው
ስለሆንክ መልአክ ለመሆን አትችልም፡፡ በምንም መንገድ ደግሞ ወንድ ከዚህ ገዳም እንዲገባ አይፈቀድም፡፡»
«ይኸው እርስዎ ከዚህ ይኖሩ የለ!»
«ያለ እኔ እኮ ሌላ ወንድ የለም::»
«ግን» ኣለ ዣን ቫልዣ ከዚህ መኖር አለብኝ፡፡»
«ያንተ አለህ!» ሲሉ ሚስተር ፎሽለማ በመደነቅ ዓይነት ተናገሩ፡፡
ዣን ቫልዣ ወደ ሽማግሌው ጠጋ ብሉ ዝቅ ባለ ድምፅ «ምነው
ሕይወትዎን ማዳኔን ረሱት?» አላቸው::
«መዘንጋት አልነበረብኝም» አሉ ሚስተር ፎሽለማ፡፡
«እንግዲያውማ እኔ ለእርስዎ ያደረግሁትን ዛሬ እርስዎ ለእኔ ማድረግ ይኖርብዎታል፡፡›
ፎሽለማ በተጨማደደ እጃቸው የሚንቀጠቀጠውን የዣን ቫልዣን
እጅ ያዙ፡፡ ለጥቂት ሰኮንድ እጁን እንደያዘ ዝም ብለው ቆሙ:: በመጨረሻ፡-
«እኔ ለአንተ አንድ ነገር ማድረግ ከቻልኩ እግዚአብሔር ባረከኝ፣
ቀደሰኝ ማለት ነው:: የአንተ ውለታ እኮ ተከፍሎ የሚያልቅ አይደለም::
ሕይወትህን አድንልሃለሁ! ክቡር ከንቲባ ፤ ሽማግሌው በአንተ ቁጥጥር ሥር ነው:: ››
ሽማግሌወ ይህን ሲናገሩ በጣም ደስ እያላቸው ነበር:: ለዚህ
በመብቃታቸው መንፈሳቸው ረካ፡፡ ለመደሰታቸው ፊታቸው መሰከረ።
ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?» አሉ ቀጥለው::
«ግድ የለም አስረዳዎታለሁ፡፡ አንድ ክፍል አለዎት?
«ከዚያ ጥግ አንዲት የማትረባ ክፍል አለች፡፡ ግን ሰው የሚኖርባትም አትመስል፡፡ እኔ ያለሁበት ቤት ባለ ሦስት ክፍል ነው::
እውነትም የሰውዬው ቤት የማይረባ ዝቅተኛ ቤት ነበር፡
አቀማመጡም ሆን ብሎ ሰው ለመደበቂያ የተሠራ ይመስል ከአሳቻ ሥፍራ ነበር፡፡ ዣን ቫልዣ ከግቢው ውስጥ ሲገባ ያልታየው በዚህ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
«ጥሩ ነው» አለ ዣን ቫልዣ ፤ «አሁን ሁለት ነገር ነው የምጠይቅዎት
«ምንና ምን ናቸው ክቡር ከንቲባ፡፡ ብቻ እርስዎ' እያልክ ባትጠራኝ
«እሺ! አንደኛ፤ አሁን ስለራሴ የምነግርህን ለማንም እንዳታወራ፧
ሁለተኛ እኔ ከምነግርህ ውጭ ስለእኔ ለማወቅ እንዳትሞክር፡፡»
«አንተን ደስ እንዳለህ፡፡ አሳፋሪ ነገር የማትሠራና የእግዚአብሔር ሰው እንደሆንክ አውቃለሁ:: ከዚህም በላይ ከዚህ እንድትገባ የረዳኸኝ አንተ ስለሆንክ ቤትህ ነው:: እኔም ያንተ ነኝ፡፡».
«በጣም ጥሩ፧ ና አሁን ተከተለኝ፤ ልጅትዋን እናምጣት::»
«እንዴ» አሉ ፎሽለማ በመገረም:: «ልጅም አለች!»
ውሻ ጌታዋን ተከትላ እንደምትሄድ፤ ሰውዬው ሌላ ቃል ሳይናገሩ ዣን ቫልዣን ተከትለው ወጡ።
ከግማሽ ሰዓት በኋላ እሳት ተቀጣጥሎ ኮዜት እሳት ትሞቅ ጀመር።
ሽማግሌው ኮዜትን አልጋ ላይ አስተኝዋት:: ዣን ቫልዣ ወደ ግቢ
ወርውሮአቸው የነበሩትን እቃዎቹን አግኝቶ ተመለሰ፡፡ ሽማግሌው
ከጉልበታቸው ላይ ያሠሩትን ቃጭል ፈትተው አስቀመጡ:: ሁለቱ! ሽማግሌዎች እራት እየበሉ ጨዋታ ቀጠሉ፡፡
የሚገርም ነው ክቡር ከንቲባ፡፡ በመጀመሪያ አላወቅኸኝም፤ ሰዎች ሕይወታቸውን ካዳንክላቸው በኋላ ትረሳቸዋለህ? ይኸ ደግ አይደለም። እነርሱ ግን አይረሱህም:: የምትረሳ ሰው አይደለህም፡፡»
💫ይቀጥላል💫

👍27❤5
Forwarded from ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ (፲፬)
መዝሙር_በሰሙነ_ሕማማት_የሚደመጥ
በ''ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ''
SUBSCRIBE 👇
https://youtube.com/watch?v=T1GfR3zJnoM&feature=share

👍2
#ዓለሞን_ትቻለሁ
ሁሉንም ንቄያለሁ
አንተን ናፍቄያለሁ
ጌታዬ ደፋ ቀና ያልኩት
የእሳትን ቅጣት ፣ ስለምፈራ ነው ፣አንተን ያመለኩት፤
ግና መስገዴ ለጥቅሜ
እሳትን ጫረብኝ ፣ የብልጥነት አቅሜ።
ገነትን እየሻትኩ
የልጅ ጠረን ሳይኾን ፣ እጣን እያሸተትኩ፤
ለመኖር ማለሜ ፣ በሐሳብ መንኜ
ገነትን አሳጣኝ ፣ ምኞት ሲዖል ሆኜ፤
ጌታዬ ፈለግሁ
ጌታዬ አጣሁህ ...
እሰማይ ላይ ባስስ ፣ብፈልግ ላመልክህ
ከምድርም አለ ፣ የዘላለሞ መልክህ፤
አንድዬ
ዓለምን አልተዉኩሞ፤
ሁሉንም አልናቅኩሞ፤
ምን በሰው ብቆስል፣ ምን ጣሬ ቢበዛ
ጣሬን አልጠላውሞ፤ ሰውን አልጥለውም ፣ አንተ አለህ በዚያ፧
ሁሉንም ንቄያለሁ
አንተን ናፍቄያለሁ
ጌታዬ ደፋ ቀና ያልኩት
የእሳትን ቅጣት ፣ ስለምፈራ ነው ፣አንተን ያመለኩት፤
ግና መስገዴ ለጥቅሜ
እሳትን ጫረብኝ ፣ የብልጥነት አቅሜ።
ገነትን እየሻትኩ
የልጅ ጠረን ሳይኾን ፣ እጣን እያሸተትኩ፤
ለመኖር ማለሜ ፣ በሐሳብ መንኜ
ገነትን አሳጣኝ ፣ ምኞት ሲዖል ሆኜ፤
ጌታዬ ፈለግሁ
ጌታዬ አጣሁህ ...
እሰማይ ላይ ባስስ ፣ብፈልግ ላመልክህ
ከምድርም አለ ፣ የዘላለሞ መልክህ፤
አንድዬ
ዓለምን አልተዉኩሞ፤
ሁሉንም አልናቅኩሞ፤
ምን በሰው ብቆስል፣ ምን ጣሬ ቢበዛ
ጣሬን አልጠላውሞ፤ ሰውን አልጥለውም ፣ አንተ አለህ በዚያ፧
❤9👍8🥰1
#ከፍሪጅ_የተጫረ_እሳት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
...በቃሌ መሰረት ልደቷን ልናከብር ተቀጣጠርን፡፡ ከሰፈር አብረን መውጣቱ ለጎረቤት ሃሜት
ስለሚዳርግ የሆነ እሷ የመረጠችው ሬስቶራንት ስምንት ሰዓት ላይ እንገናኝ ተባባልን፡፡....
እኔ በበኩሌ የዚህ ዓይነት ሴት አይቼ አላውቅም፤ ቀድሚያት ነበር የደረስኩት፡፡ ቀይ የለበሱት
ጠረጴዛዎች የአገር ሹካና ማንኪያ፣ ቢላዋና የጨው የምናምን እቃ ዙሪያቸውን ተደርድሮባቸው፣ፈዘዝ ያለ ብርሃን ያለበት አዳራሽ ውስጥ በሰፊው ተንጣለዋል፡፡
ምቾት አይመቸኝም፤ ቅንጦት አያቀናጣኝም፤ ጨነቀኝ !
ሜሮን ስትደርስ ልቤ በድንጋጤ ልትቆም ምንም አልቀራትም፡፡ የሚያምር አጭር ጉልበቷ ላይ
የቆመ ቡና ዓይነት ቀሚስ ለብሳለች፡፡ ውብ እግሮቿን ለማሳየት ሆን ተብሎ የተሰራ የሚመስል ረዥም ተረከዝ ያለው ጫማ፣ ጥልፍልፉ ፍርጥም ያለ ባቷ ላይ እንደሃረግ እየተጠመጠሙ ወጥቶ ጉልበቷ ላይ የደረሰ፣ ጡቶቿ ደረቷ ላይ ክፍት በሆነው ቀሚሷ ታቅፈውና ተሳስመው የሲኦል ሸለቆ እንደሰሩ፣ ፀጉሯ ወደ አንድ በኩል ተሰብስቦ በማስያዣ ተይዟል፤ ዓይኗ በኩል ተከቧል፣ ኦህህህህህህ ስታምር! የአዲስ አበባ እናቶች እድሜ አቆጣጠር አይችሉም ይሆናል እንጂ ይህቺ ልጅ አስራ ስድስት ዓመቷ ብቻ አይመስለኝም፡፡ በዚህ እድሜ ቀጠሮን የመከሸን ሳይንስ እንዴት ነው መካን የሚቻለው? እኔ እኮ በዚህ እድሜም አልችልበትም፡፡
ቆሜ ተቀበልኳት፤ ጉንጫችንን አነካካነው፤ መሳሳም መሆኑ ነው፡፡ አቤት ሽቶዋ! ..ፊቴ ዝም
ብላ ቆመች ! ..ቆምኩ …አሃ ለካ ወንበር ይሳባል ! ሳብኩላት፤
“ቴንኪው !” ብላ ተቀመጠች፤
“በጣም ቆንጆ ሆነሻል”
“እመሰግናለሁ” የተጠና ምልልስ መሰለብኝ እንጂ ከልቤ ነበር የተናገርኩት፡፡ በዚህ ቀን ከሜሮን
ጋር ከዘፍጥረት እስከ ራእይ አወራን፡፡ ሜሮን ካለ እድሜዋ የበሰለች ጉድ ነበረች፤ እናም
እንዲህ አልኩ፣
“ 'አዲስ አበባ ውስጥ ከሚኖሩ ሃምሳ ዱርዬ ሴቶች ውስጥ ሰላሳ ዘጠኙ ስማቸው ሜሮን
ይመስለኛል ግን ማናባቱ ነው ይሄን ቆጠራ ያካሄደው ደደብ!”ሜሮን ጋር ተዋድደን
ነበር በቃ ! እኔ ጋር በመሆኗ ነፍሷን እስክትስት ተደስታ ነበር፡፡እኔማ ነፍሴን ከሳትኩ ሰንብቻለሁ፡፡ ልዩ ሰው አድርጋ እንደምታስበኝ ነገረችኝ፤ ሰፈር ውስጥ ዝምታዬ መስጧታል።
ደግሞ ወሬው ሁሉ ከየት መጣልኝ ? የሰው ሰው በሳቅ ልገድል !! እግዜር ሲያስወድድህ ብዙ ሳቅ የወደደህ ሰው ልብ ውስጥ ያስቀምጣል፤ ከዛም የውድህ ሳቅ መውጫ በር፣ መተንፈሻ መስኮት ያደርግሃል፡፡ አንተ በፈለግከው መንገድ አፍህን ክፈት፣ ቃላትን አውጣ፤ ሜሪዬ የኔ ውብ አቤት ሳቋ ሲያምር ! እዛ ዩኒቨርስቲ “ሄይይ ምን አዲስ ነገር አለ ” እያሉ ሳቅ ፍለጋ እንደሚባዝኑ ሕይወታቸውን በጊዜ ያሟጠጡ ደነዝ ሴቶች አይደለችም፡፡ ቻፕስቲካም ከንፈራቸውን እስከጆር
ግንዳቸው ለቀው በ 'ዊትኒ ሆስተንኖ ለመሳቅ ቆርቆሮ ድምፃቸውን እንደሚያንኳኩ ኳኳታሞች አይደለችም፤ ሜሪ ራሷ ሳቅ ነበረች፤ ፍንትው ስትል ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ፀጉሯ በሳቅ
የምትጥለቀለቅ ! እንደእኔ አይነቱ ሰው ተሳቀልኝ ቢል ያምርበታል፤
ልብ ነበራት፤ የፍቅር የሰላም ያልተነካካ፡፡ 'ውይ ወንዶች? እያሉ ያለፈ እንኩሮ ሕይወታቸውን
አዲስ የፍቅረኛ ምጣድ ላይ በትዝታ ስም እንደሚጠፈጥፉ ሴቶች አልነበረችም፡፡ ብታውቀውም ባታውቀውም ነገ ይናፍቃታል፡፡ ማንንም አልጎዳች፣ ማንም አልጎዳትም፡፡ ተረት የላትም ! ተረት አይደለችም፡፡ እነእከሌ ተፋቀሩ” ስትባል አትቀናም፡፡ “ተለያዩ" ሲባል አትፈርድም፤ ከተማውን የሞላው ፈራጅኮ ግማሽ ፍርዱ በቀል ነው፡፡ የደረሰበትን ሊስቀል፣ ያደረሰውን
ሊያስተባብል! ሜሪ ግን ብቻዋን ናት፡፡ ብቻዋን ወደ ሕይወቴ መጣች፤ አልከበደችኝም፡፡
ከዛን ቀን ጀምሮ ሁልጊዜ ማታ ማታ በር ላይ እንቆምና ስናወራ እናመሻለን፡፡ ውሃ ልትደፋ
ወጥታ ሊሆን ይችላል፡፡ “ቻው በቃ መሸ !” ትለኝና ቆም ትላለች፡፡ ከቻው በኋላ አንድ የሆነ
ነገር የማድረግ ፍላጎት ሁለታችንም ልብ ውስጥ አለ፡፡ ግን ማን ይድፈር ? ከቻው በኋላ
አንድ ሰዓት እናወራለን፡፡ “ምን አወራችሁ ?” ቢባል እንጃ !! ብዙ ጊዜ ቤቴ እንዳትገባ ሆነ
ብዬ እከላከላለሁ፤ ፈተናው ይከብደኛል፤ ስለዚህ በር ላይ ቆመን እናወራለን፡፡ ወሬኛ ነኝ፡፡
የማላወራላት ነገር የለም !! ባወራሁበት የምከፈለው ደመወዝ ሳቋ ነው፡፡ የጠገበ ደመወዝ፡፡
እግዜርዬ የፍቅር ዩኒቨርስቲ አስመርቆ የሰጠኝ ምርጥ ስራ - ሃሌ ሉያ !” አስመርቆ 'ስራ ፍጠር
ቢለኝ ምን ይውጠኝ ነበር ? ሳቋ ደመወዜ ነው፡፡….ስቃታለሁ፤ የማወራላት ምንም የማይጠቅም
ነገር ቢሆንም የሳቅ ደመወዜን አስቀርታብኝ አታውቅም፡፡
ታዲያ አንዳንዴ ማታ ቆመን ስናወራ ከሩቅ የጅብ ድምፅ ይሰማል፡፡ አውውውው…! ወደ እኔ
ጠጋ ትላለች፤ ሜሪዬ የመጨረሻ ፈሪ ናት፡፡ ጠረኗ ይጠርነኛል፡፡ ከምሽቱ አየር ጋር ወደ ሳንባዬ
ተስገብግቤ እስበዋለሁ፤ ጠረኗን !! እሷን ራሷን እንደአየር ስቤ ውስጤ ያስገባኋት እስኪመስለኝ፤ ጅቡን እድሜውን ያርዝምልኝና በጣም ትጠጋኛለች፡፡
ስለጅብ አወራላታለሁ፡፡ “የጅብ ጥፍር አንገትሽ ላይ ካሰርሽ በቃ የሄድሽበት ሁሉ ሲበሉ ነው
የሚያደርስሽ”
“ውሸትህን ነው ! ሂሂሂሂሂሂሂ…”
“ለምን እዋሽሻለሁ በሳይንስ የተረጋገጠ ነው”
“አላምንህም ! ሃሃሃሃሃሃ…”
እይውልሽ የአሜሪካ ሳይንቲስቶች ናቸው እኮ ያጠኑት”
“ውይ ውሸት አላምንልህም ! እንዴት አድርገው ያጠኑታል ? ... ታየኝ እኮ ስንት ስራ ትተው
አንገታቸው ላይ የጅብ ጥፍር አስረው ሲዞሩ ! ሂሂሂሂሂሂሂሂሂ…” ፍልቅልቅ ትላለች፡፡
ቀላል ነው፤ አንድ ጊዜ ይህን ጥናት እናጥና ብለው አለቃቸውን ሊያስፈቅዱት የጅብ ጥፍር አንገታቸው ላይ ልክ እንደዚህ እንደማተብ (እንገቷ ላይ ያሰረችውን ማተብ እየነካካሁ) አስረው ሳይንቲስቶቹ
ወደ ኃላፊያቸው ክፍል ሊገቡ ኃላፊው ምን እያደረገ አገኙት መሰለሽ…? በርገሩን እየገመጠ፡፡
ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ…ውሸት ! ውሸት ”
“..ከዛ ጥናቱ ተፈቀደላቸውና ወደ አፍሪካ መጡ፤ የሆነ ሰው የማይኖርበት ጫካ እካባቢ
አውሮፕላናቸው ተከለከሰ”
ኦ ማይ ጋድ! እውነትህን ነው ?” አለች ደንገጥ ብላ፡፡
ያ! ግን ማንም አልሞተም፡፡በተዓምር ተረፉ፡፡ ሁሉም አንገታቸው ላይ የጅብ ጥፍር አስረዋል፤ ከዛ የሆነ
ነገር ሸትቷቸው ዞር ሲሉ ጫካው ውስጥ የሚኖሩ አዳኞች ምን የመሰለች ጥንቸል ለምሳቸው እየጠበሱ:
“ወይኔ ውሸትህ ሂሂሂሂሂ…አልሰማህም !”
“እስኪ ጥናቱን የበለጠ ለማረጋገጥ ወደ ሌላ ዓለም እንውሰደው አሉና ናሳ ጋር ተነጋግረው ወደ ጨረቃ የሚጓዙ ጠፈርተኞች አንገት ላይ የጅቡን ጥፍር አሰሩላቸው፡”
“አሁንስ አበዛኸው ሕፃን ልጅ መሰልኩህ እንዴ ?” ብላ የውሸት ተቆጣች፡፡ ሜሪ ከዚህ »
ቀጥሎ የሚፈነዳውን ሳቅ ስለማውቅ ውሸቴን ቀጠልኩበት፡፡
“ልክ ጠፈርተኞቹ ጨረቃ ላይ ሲያርፉ ከእነሱ ቀድመው ጨረቃ ላይ ያረፉ የሩሲያ ጠፈርተኞት
ራት ሊበሉ ሲዘገጃጁ ደረሱ እልሻለሁ”
ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ሁለተኛ አላዋራህም እሺ ! ስታስጠላ ! እኔ ቁም ነገር የምታወራ መስሎኝ ! ሂሂሂሂ…” ሳቋ መቆሚያ የለውም፡፡ እኔም በሳቋ ልቤ ሃሴት ያደርጋል፡፡

👍31👏1
እስካሁን ስሚያት አላውቅም፡፡ ሳማት ሳማት…ከንፈሯን ጉረሰው ጉረሰው ይለኛል፤ ጨለማ
የሆነ ሰይጣን ነገር ሳይኖረው አይቀርም ! ቀን እዚሁ ቦታ ላይ ቆመን በጭራሽ የማይሰማኝ
ስሜት ማታ የሚገፋፋ አንዳች ነገር አለው፡፡ ወደ ደረቴ ስትጠጋኝ የጡቱቿ ጫፎች ደረቴን
ሸንቁረው በጀርባዬ በኩል ብቅ ያሉ ይመስለኛል፡፡ ..ፈተና ነው !
ጅብ ሲጮህ ስለጅብ አወራታለሁ፡፡ ድመት ከጮኸ ስለድመት፤ አባባ ካለች ስለአበባ…፡፡ ስናወራ
ስናወራ ሰካራሙ ጎረቤታችን ጉግሳ እየተወላገደ፣ እየዘፈነ ይመጣል፡፡
“አንተ ጉግሳ መጣ አራት ሰዓት…” ትላለች ሜሪ፡፡ ጉግሳ አራት ሰዓት ላይ እንደሚመጣ የታወቀ
ነው፤ የመንደሩ ሰዓት ነው ጉግሳ፡፡ ወሬ ሲወራ ሁሉ ልክ ጉግሳ ሲመጣ ይባላል፡፡ ልክ
አራት ሰዓት እንደማለት፡፡ እየዘፈነ፣ እየገጠመ (እያዝናና እና እያስተማረ ይሉታል ሲፎግሩ)
ከተፍ ይላል፤ ጉግሳ፡፡
ለእግሩ ጫማ የለው ለራሱ ባርኔጣ፡
የቅጣቸው አባት አሁን ገና መጣ፡፡
ይላል ጉግሳ (ቅጣቸው ልጁ ነው)፡፡ ወተር ወተር እያለ በጨለማው ውስጥ ሲራመድ የእማማ ትሩፋት ቡችላ ትጮህበታለች፡፡ ው ው ው ው ው ው ው…!!
ጉግሳ ቆም ብሎ ቡችላዋ ወዳለችበት ግቢ በንቀት እየተመለከት፤
•ቡችላ! ወንድ ከሆንሽ…የእመቤትሽ ውሽሞች አጥር ሲዘሉ አትጮሂም ? በአገልግል ዶሮው ተቋጥሮ በጓሮ በር ለውሽሞች ሲላክ አትጮሂም ? .…ውሻ ..የውሻ ልጅ !! ..ይቅርታ ! ደግ እናትሽን አሰደብሽኝ..! ነፍሷን ይማርና እናትሽ ጥሩሩሩሩሩሩ ውሻ ነበረች፡፡ ቤቴ ድረስ ሸኝታኝ
ነበር ቤቷ የምትገባው፡፡ ..የልጅ ዘመድ የለውም አንች…”
አይጨርሰውም፡፡
ጉግሳ እኔና ሜሪን ያየናል፡፡ ከእርሱ በፊት ቀድሞ አጠገባችን የሚደርሰው የአረቄና ጠጅ ሽታው
ነው፡፡ ቆም ብሎ ንፋስ እንደገፋው ዛፍ እየተወዛወዘ ኮፍያውን ያወልቅና በአክብሮት ጎንበስ ብሎ
(በግንባሩ እንዳይደፋ እሰጋለሁ) “ወጣቶች ልጆቻችን…የነገ አገር ተረካቢ እንደምን አመሻችሁ…!
ሃሃሃሃሃ…!! እኛንም እንዲህ ነበር ድሮሮሮሮሮ የሚሉን፤ ኪኪኪኪ…፡፡ የአገር ርክክቡ ሲዘገይ
እየጠጣን እንጠብቀው ብለን ሰካራም ሆንን ! ሃሃሃ…" ይላል በስካር ድምፅ፡፡
“ደህና አመሹ ጋሽ ጉግሳ!” እንለዋለን፡፡
ትከ ብሎ ያየንና፣ “መፋቀር ጥሩ ነው፤ እጅግ በጣም በጣም ጥሩ ነው ! ይሄ ቡዳ ሰፈር! በቡዳ
እንዳይበላችሁ ቤት ግቡ!” ይለናል፡፡ ሜሪ ሳቋን አፍና ዝም ትላለች፡፡
“መጽሐፉጋብቻ ቅዱስ ነው ይላል፤ ደግሞ ፍቅር ከሌለ ቆርቆሮ ቁራሌ ቆረቆንዳ ነህ ይላል፤ እኔ አሁን አምሳልን አፈቅራታለሁ፡፡ አስራ ሶስት ዓመት ስንኖር ተጣልተን አናውቅም፡፡ ለምን
?…ፍቅር ይሻላላ ! መጽሐፉ ተፋቀሩ ይላል !.…ጎበዞች ! አይዟችሁ ደህና እደሩ !” ይልና
እየተወላገደ ያልፋል፡፡ ሜሪ ደረቴ ላይ ድፍት ብላ ስሳቅ ፍርስስስስ ትላለች፡፡
ጉግሳ ትንሽ አለፍ እንዳለ፣ “እያንዳንድሽ ወየውልሽ ! ..በየጥጋጥጉ እየቆምሽ የምትባልጊ ሁሉ!
..ወየውልሽ !” ይላል እጁን ወደ ሰማይ ዘርግቶ፤ አመልኮች ጣቱን እየነቀነቀ፡፡ “መጽሐፉ በጨለማ የሰራሽውን ሁሉ በፀሐይ እገልፀዋለሁ፤ ስራሽን እንደ በርበሬ ዛላ፣ እንደታጠበ ልብስ፣
ለወፍጮ እንደተዘጋጀ የሽሮ ክክ ፀሐይ ላይ አሰጣዋለሁ ይላል መጽሐፉ!…ወዮልሽ! አርፈሽ
አትማሪና ኮከብ ስትቆጥሪ አምሺ…” ካለ በኋላ በዜማ ይቀጥላል፤
እንኳን ቤትና የለኝም እግር፣
እደጅ ድራለሁ ኮከብ ስቆጥር
“ኮከብ ቆጣሪ አስማተኛ ሁሉ...” ሌላ ርዕስ ውስጥ ይገባል፤ ጉግሳ እንዲህ ነው::
ሜሪ ጋር አንዳንዴ 'ወክ' እናደርጋለን፡፡ ንፁህና ፀጥ ያለ ኤምባሲ አለ፡፡ በሱ በኩል ማታ ክንዴን ደገፍ ብላኝ በጣም ተነካክተን ብርዱ ለስላሳ ቆዳችን ላይ የፈጠራቸው እንድብድቦችና የሜሪ እንድብድቦች እየተነካኩ፣ ሽቶዋ እየተቀላቀለብኝ ደስ ብሎን እንዝናናለን፡፡ስንሄድም ሆነ ስንመለስ አገር ሲያየን ግድ አልነበረንም፡፡ አሁን አውርተናል፡፡ 'ውስጤ ውስጥ ነሽ ብያታለሁ፤ 'ወድጄሻለሁ! ብያታለሁ፤ ምንም አላለችኝም፤ ግን እንባዋ መጥቶ ነበር።
አንድ ቀን ከ'ወክ' ስንመለስ እኔ ቤት ገባን፡፡ ፍራሽ ላይ እግሯን አነባብራ ዘርግታ ተቀመጠች፡፡ ቀሚሷ ስላጠራት ትንሽ ተጨናንቃ ነበር፡፡ እጠገቧ ተቀመጥኩ፡፡ ሁለታችንም የሆነ ነገር በጣም በጣም ፈልገናል፤ ግን…፤እዮኋት ቀሚሷ ላይ ባለች ቁልፍ ትጫወታለች፡፡ ፈራሁ! … አዕምሮዬ በሀሳብተራወጠ፤
1 የኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንዲት ሴት አስራ ስምንት ዓመት ሳይሞላት ወዳና
ፈቅዳም ሆነ ሳትወድና ሳትፈቅድ ወሲብ ብትፈፅም፣ ወሲብ የፈፀመባትን ሰው ዘብጥያ ..ከርቸሌን
ወላ ጀሜ አስገባው ይላል!!
2. ሕገ እግዜር ወዳ ፈቅዳ ሴት ወንድ ምናምን አይልም፤ “አታመንዝር!” በቃ !! ከፈለግክ
የከጀልካትን ሴት አግብተህ እንዳሻህ ሁን፡፡ አለበለዚያ አምሮትህን 'ሲያምርህ ይቅር!' ብለህ ገስፀው፡፡ ከዚህ በተረፈ ሲኦል ወላ ጀሀነም ትወረወራታለህ ! ይላል፡፡
3 የእኔ ይዞ ሟች ልብ የሜሪን የሚያምር ባት፣ የፈረጠመ ዳሌና ጫፋቸው የሚጣራ ጠይም
ጡቶች እያየ ከምድራዊውም ከሰማያዊውም ሕግ ሊያጋጨኝ በደም ፍላት ደም ይረጫል፡፡ ልቤ
ሲደልቅ ግግም ግግምግም ሲል አንድ ታዋቂ ትግረኛ ዘፋኝ ከነከበሮ ደላቂው በልቤ አዳራሽ
የሙዚቃ ስራውን የሚያቀርብ ይመስለኛል፡፡
የልቤ ምከር፣ “አብርሽ ሜሪ ትወድሃለች፡፡ ያደረጋችሁትን ለማንም አትናገርም፡፡ ደግሞ እያት
ከንፈሯ እንዴት እንደሚንቀጠቀጥ…ስትንከረፈፍ አንዱ እንዳይልፍህ !…እጆችህን ጡቶቿ ላይ አሳርፋቸው - አይዞህ ጠጋ ስላት፡፡ ኤጭጭጭ የምን መጨናነቅ ነው…የወንጀል ሕጉ አንጀባ ነው ባክህ !እግዜር ደግሞ እንኳን አንተን ስንቱን ይቅር ብሎ የለ !? ..ኧረ ሳይመሽ ፍጠን !
ነገ በዚህ ስሜት አታገኛትም፡፡ እንደውም ያልፈለካት መስሏት በዛው ነው የምትቀረው…...”
ብሎ ደም ይተፋል ልቤ፤
እነሆ በህገ እግዜር፣ በወንጀለኛ መቅጫ ህግና በግልፍተኛ ልብ መሃል ሚስኪኑ አብረሃም
ሜሪ አንድ እግሯን ሰብሰብ ስታደርገው ከጠይምነቷ የቀላ ለስላሳ ታፋዋ ተጋለጠ፡፡ ቀሚሷን
ሳብ አደረገችው፤ ግን አልሸፈናትም፡፡ ቀጥ ብላ አየችኝ፡፡ አይኗ ቡዝዝ ብሎ ነበር፡፡ ትከሻዬ
ላይ ራሷን ደገፍ አደረገችው፡፡ …ኡኡኡኡኡኡኡ ኡኡኡኡኡ ጠረኗ አመንዝር ይለኛል፡፡ውበቷ አመንዝር ይለኛል፡፡ ልቤ አመንዝር ይለኛል፡፡ ቤቱ አመንዝር ይለኛል፡፡ ሁኔታው አመንዝር ይለኛል፡፡ፍራሹ “ኑ እንጂ እየጠበቅኳችሁ አይደለም እንዴ! የምን መጎለት ነው! ይለኛል፡፡ እርግጠኛ ነኝ ሰይጣንም እንደአምፊ ቲያትር ከነጅሪው ተሰብስቦ እያየን ነው፡፡
ሜሪ በቀኝ እጄ ጣቶች እየተጫወተች ነበር፡፡ አቤት እጇ አለሳለሱ !! ደግሞ ይሞቃል ! ….ቆይ ምናባቴ ነው የማደርገው ? ... ሕግ ይሄን ያያል ? አያይም ! ?
ሕግ የሜሪ ጡቶች ማማራቸውን እንደቅጣት ማቅለያ ያያል…?
እናቴ አበባ ይዛ ምርቃቴ ላይ ለመገኘት ካሁኑ ስታወራ ምን ያህል በደስታ እንደምትምነሸነሽ
እያወቅኩ ምርቃት በቴሌቪዥን ባየች ቁጥር “አሁን የኔ ልጅ…” እያለች በደስታ እና በተስፋ ፊቷ

👍20
ላይ የምትለኩሰውን ብርሃን እፍ ብዬ ላጥፋው ? “ልጅሽስ ?” ስትባል (ኧረ ባትባልም፡፡) በኩራት
“ዩኒበርስቲ ገባኮ” እያለች በሳቅ የምትምነሸነሽ እናቴን በሐዘን አንገቷን ደፍታ እስር ቤት ሰሃን ይዛ
እድሜ ልኳን እንድትመላለስ ልፍረድ ? ከሁሉም በላይ እግዚያብሄር ይቅር ባይ ነው፤ ልክ
ነው ! የንስሃ ቀብድ ግን አይቀበልም፡፡ “ላጥፋ እንዴ፣ ይቅር ትለኝ እንደሆን ?” እንደማለት !!
የሜሪን እጅ ከእጄ ላይ አነሳሁ፡፡ ከፍራሹ ላይ ተነስቼ ቆምኩ፤ ከዛም “መሸ አይደል ?!”
አልኳት፤ “ውጪ” ነበር የሚመስለው አነጋገሬ ገብቷታል፡፡ ተነስታ ልብሷን አስተካከለችና
“አንተ ፍሪጅ አያስፈልግህም፤ ራስህ ማቀዝቀዣ ነገር ነህ” አለችኝ፡፡ “ደህና እደር!” ሳትለኝ
ወጣች፤ አልተመለሰችም!! የፍሪጅ ውሃውም በዛው ቆመ !
እግዚያብሔር ታዲያ እንዲህ ሲል በታላቅ ድምፅ ያወጀ መሰለኝ፣
“ልጄ አብረሃም ሆይ ! ህግጋቴን ላከበሩ፣ በፈተና ሰዓትም የቃሌን ጭላንጭል ሊመለከቱ
ለተፍገመገሙ ሁሉ፣ አንድ ጆግ ቀዝቃዛ ውሃ ሲከለከሉ እንኳን ስለነሱ ዓለምን በቀዝቃዛ ውሃ
አረሰርሳታለሁ !!!”
ክረምት ገባ !!
..
ዝናብ፣ ውሽንፍሩ፣ ደመናው
አዲስ አበባ ቀዝቀዝ አለች !! ክረምቱ የእኔ ክረምት መሰለኝ፡፡
አዲሳባ ውስጥ ፍሪጅ ካላቸው ሃምሳ ሴቶች መካከል ሃምሳውም ስማቸው ሜሮን ይመስለኛል፤
የፍሪጆቹ ዓይነትና ስም ቢለያይም ባህሪያቸው አንድ ነው፣ "አመድ በዱቄት መለወጥ” በሰጣት
ጠብታ ውሃ ጎርፍ ማንነትን በውለታ መልክ መቀበል ያምረዋል ፍሪጁ !! ፍሪጁን ከነስጦታው
የሚሹ ይሄ ታላቅ ክረምት የእነርሱ አይደለም !!
ፍራሼን ተመለከትኩት፤ ሰፊና ንፁህ ነው:: ብቸኝነት ሰላም፣ ፍራሹም ሰፊ ነው፡፡
✨አለቀ✨

👍26👏7
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
....ዣን ቫልዣ ለመተኛት ዓይኑን ከመጨፈኑ በፊት «ከዛሬ ጀምሮ
ከዚህ እኖራለሁ» ሲል ተናገረ:: እነዚህ ቃላት የሚስተር ፎሽለማን ጭንቅላት ሲበጠብጡ አደሩ:: ሁለቱም እንቅልፍ ሳይወስዳቸው ነው ያደሩት:: ዣቬር ፍለጋውን እንደሚያጧጥፍ ዣን ቫልዣ ያውቃል፡፡ ኮዜትና ዣን ቫልዣ
ወደ ከተማ የተመለሱ እንደሆነ ይያዛል፡፡ ስለዚህ ከገዳሙ ውስጥ መቆየት እንደሚሻል ዣን ቫልዣ አመነ፡፡ ሆኖም ለመደበቅ የሚያመች ስፍራ ቢሆንም ወንድ ከዚያ ስለማይገባ አደገኛ ነው፡፡ ከገዳሙ ውስጥ መኖሩ
ከታወቀ በወንጀል ተከስሶ ይታሰራል::
ሚስተር ፎሽለማ ደግሞ ስለነገሩ ግራ ገብቷቸው ስለተጨነቁ እንቅልፍ አልወሰዳቸውም፡፡ «እንዴት ከንቲባው ከዚያ ሊገባ ቻለ? ጋዳሙ ዙሪያውን በግንብ አጥር በመታጠሩ ሰው ከዚያ ሊገባ አይችልም:: ልጅትዋን ከየት አመጣት? ማንም ቢሆን ልጅ አዝሎ ከግንብ ላይ ሊወጣ አይችልም:: ልጅትዋስ የማን ልጅ ናት? ከየት ነው የመጡት? ምናልባት ገንዘብ አጉድሎ
እየሽሽ ይሆን? ወይስ በፖለቲካ ጉዳይ እየተፈለገ ነው?» ሲሉ ሽማግሌው ራሳቸውን ጠየቁ፡፡ «ምናልባት ገዳሙን የመረጠው ጥሩ የመደበቂያ ሥፍራ
ስለሆነ ይሆን?» ሲለም አሰበ::
«መሴይ ማንደላይን ከሞት ያዳነኝ ሰው ስለሆነ አሁን የእኔ ተራ
ነው» በማለት ዣን ቫልዣን ለመርዳት ወሰኑ፡፡
«ለሕይወቱ ሳይሳሳ ያንን የሚያህል ጭነት ከጫነው ጋሪ ስር ገብቶ ነው ሕይወቴን ያዳናት! ግን እርሱን ከዚህ ማኖር ወንጀል ነው:: ብያዝ ምን እመልሳለሁ ሲሉ
ተጨነቁ
ሽማግሌው እስከዚህም ለሰው የሚጨነቁና ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰው አልነበሩም:: አሁን ግን በእድሜም እያረጁ ስለሄዱ ፣በስተእርጅና ሰው ላይ ምን አስጨከነኝ፣ የሚል ስሜት ተሰማቸው:: የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ገዳም ውስጥ ለሁለት ዓመት ስለኖሩ ስለሕይወት የነበራቸው አመለካከት
ሳይለወጥ አልቀረም:: በመጨረሻ ሕይወታቸውን ለመሴይ ማንደላይን ለመሰዋት ወሰኑ።
ሚስተር ፎሽለማ ቀስ ብለው በር ሲያንኳኩ «ይግቡ» የሚል መልስ
አገኙ:: የገዳሙ ኃላፊዎች ቢሮ ነበር፡፡ ከቢሮው እንደጎቡ ለጥ ብለው እጅ
«እርስዎ ነዎት እንዴ አባታችን፡፡›
እንደገና ለጥ ብለው እጅ ነሱ፡፡
«እኔ ነኝ ያስጠራሁዎት፡፡»
«በጥሪው መሠረት መጥቻለሁ::»
«ለምን ነበር እኔን ለማነጋገር የፈለጉት?»
«ጉዳይ ነበረኝ፡፡»
«የምን ጉዳይ?»
ሚስተር ፎሽለማ ለሁለት ዓመት ገዳሙ ውስጥ ሲኖሩ ከተማው
ውስጥ የሚነገረውን ሁሉ ይሰማሉ፡፡ ግን የሰሙትን ሁሉ የመደበቅ ችሎታ ነበራቸው:: የገዳሙ ነዋሪ እንደቂል ነበር የሚያያቸው:: ሴሮች ግን
በጣም ያከብሯቸዋል። ሽማግሌው ስለሥራቸው ስፋት ለሴሮች ኃላፊ ብዙ አወሩ። ቀኑ አልበቃ ብሏቸው ሌሊቱን ሁሉ በጨረቃ ብርሃን እንደሚሠሩም «ብዙ ለኃላፊዋ ከገለጹ በኋላ አንድ ወንድም እንዳላቸውና
እርሱም ከእርሳቸው
በእድሜ ይነስ እንጂ ልጅ አለመሆኑን አስረዱ፡፡ ወንድማቸው ከእርሳቸው ጋር እንዲኖር ቢፈቀድላቸው በሥራ ብዙ ሊረዳቸው እንደሚችል ሲናገሩ
የኃላፊዋ ሰውነት ተሸማቀቀ፡፡
ሽማግሌው ንግግራቸውን በመቀጠል ወንድማቸው ጎበዝ አትክልተኛ መሆኑን እርሱ ካልረዳቸው በእድሜ ምክንያት ሥራው ስለሚከብዳቸው
ምናልባት ሥራውን ለመልቀቅ እንደሚገደዱ ተናገሩ፡፡ በተጨማሪም ወንድማቸው ትንሽ ሴት ልጅ እንዳለውና ከእርሳቸው ጋር እንዲኖር ከተፈቀደላቸው ልጅትዋ በሃይማኖት ተኮትኩታ ልታድግ እንደምትችልገለጹ:: ምናልባት አንድ ቀን ይህቺ ልጅ መንኩሳ ቤተክርስቲያንን ልታገለግል እንደምትችልም አስረዱ፡፡
ሽማግሌው እንደጨረሱ ኃላፊዋ መነኩሲት ሥራ እንዲሠሩ
አዘዝዋቸው፡፡
«እስከ ነገ ማታ አንድ ወፍራም ብረት ሊገዙልኝ ይችላሉ?»
«ለምን ሥራ?»
«ለአንድ ሥራ!»
«ምን ገድዶኝ፣ እችላለሁ እንጂ!» ሲሉ መለሱ ሽማግሌው፡፡
ኃላፊዋ መነኩሲት ይህን ተናግረው ወጥተው ሄዱ:: ፎሽለማ ብቻቸውን ቀሩ
አንድ ሩብ ሰዓት አለፈ፡፡ ኃላፊዋ ሴር ተመልሰው ከመቀመጫቸው
ተቀመጡ፡፡ ሁለቱም አሳብ የያዛቸው መሰሉ፡፡
«አባታችን?»
«እማሆይ!»
«የጸሎት ቤቱን ያውቁታል?»
«ለቅዳሴ አልፎ አልፎ ወደዚያ ስለምሄድ አውቀዋለሁ፡፡»
«ከዚያ ይሄዳሉዋ?»
«ከአንዴም ሁለቴ፤ ከሁለቴም ሦስቴ ሄጃለሁ፡፡»
«ከዚያ የሚፈነቀል ትልቅ ድንጋይ አለ፡፡
«ከባድ ነው?»
«የሚፈነቀለው ድንጋይ ያለው ከቤተመቅደሱ አጠገብ ነው::»
«ብዙ ቦታ ከሆነ አንድ ሰው ብቻውን መፈንቀል አይችልም:: ሁለት ወንዶች ያስፈልጋሉ፡፡»
«ከመነኮሳቱ መካከል አራቱ ይረዱዎታል፡፡»
«ይኸው ነው ሥራው?»
«ዛሬ ጠዋት አንዲት ሴር እንደሞቱ ያውቃሉ?»
«የለም፤ አላወቅሁም::»
«ለሙታን የሚደረገውን ሁሉ ማድረግ አለብን፡፡ ሟችዋ ሴር ቆመው ይጸልዩበት ከነበረው መሬት ስር አጽማቸው ያለሳጥን ማረፍ አለበት፡፡
ነፍሳቸው ከሥጋቸው ከመለየቱ አስቀድሞ የጠየቁት ጥያቄ ነው:: መጠየቅ ሳይሆን ያዘዙት ነገር ስለሆነ መፈጸም ይኖርበታል፡፡
«ከዚያ ጸሎት ቤት ሰው መቅበር እኮ የተከለከለ መሆኑን ያውቁ
የለ፡፡»
«ወንዶች ናቸው የከለከሉት? ፤ እግዚአብሔር ግን ይፈቅዳል፡፡
«ወሬ ቢሰማስ?»
«በእርስዎ ላይ እምነት አለኝ፡፡»
«ግን እማሆይ፤ የጤና ጥበቃ ተወካይ..»
«የሃይማኖት መሪዎች ስለቀብር የደነገጉት ሕግ አለ፡፡»
«ሆኖም የፖሊስ አዛዥ ...
«የጥንት ነገሥታት ፈቅደዋል፡፡»
«አስተዳዳሪው...»
«በእግዚአብሔር ፊት እርሱም ከቁጥር አይገባም::»
«አሁን እማሆይ?» አሉ ሽማግሌው::
«እምነት እንጣልብዎ?»
«እታዘዛለሁ::»
«በዚሁ ይለቅ፡፡»
«እማሆይ ለጠቀሱት ሥራ ሁለት ሜትር የሚሆን ወፍራም ብረት
ያስፈልገኛል፡፡»
«የት ታገኛለህ?»
«እዚሁ ግቢ ውስጥ እቃ ከምናስቀምጥበት ሥፍራ ብረት ያለ ይመስለኛል፡፡»
«ይኸው ነው እማሆይ? አሁን ስላሉት በሰዓቱ እገኛለሁ::»
««የለም፤ ሌላም ነገር አለ፡፡»
«ምን አለ?»
«የተገዛው የሬሣ ሣጥን ጉዳይ::»
ሁለቱም መልስ ሳይሰጡ ተፋጥጠው ለጥቂት ሰኮንድ ቆዩ::
«የሬሣ ሣጥኑን ምን እናደርገዋለን?» ሲሉ ኃላፊዋ ጠየቁ፡፡
«ይቀበራላ!»
«ባዶውን?»
«እማሆይ፤ እኔ ባፈር እሞላዋለሁ:: አፈር ቢሞላበት ሰው ያለው
ይመስላል፡፡»
«ልክ ነዎት፡፡ ሰውም ቢሆን እኮ ከአፈር ነው የተሠራው:: እንግዲህ
ባዶውን ሣጥን እርስዎ ያዘጋጁታል?»
«በሚገባ!» ብለው ከመለሱ በኋላ ለመሄድ ወደ በር አመሩ፡፡
«በመልዕክት አቀባበልዎ ደስ ነው ያለኝ:: ወንድምዎን ነገ ከእኔ
ዘንድ ያምጡት፡፡ ልጁንም ይዞ ይምጣ፡፡
ያን እለት ማታ ዣን ቫልዣ ኮዜትን ይዞ ወደ ኃላፊዋ ሴር ሄደ፡፡
ሴርዋ ዣን ቫልዣን ከእግር እስከ ራስ አዩት:: ኮዜትንም እንደዚሁ ከአዩዋት በኋላ
«ይህ ቤት ሳያስማማት አያቀርም» ሲሉ ተናገሩ::
ኃላፊዋ ሴር አብረዋቸው ከነበሩት ከሌሎች ሁለት ሴሮች ጋር
ጥቂት ተወያዩ:: ከዚያም ኃላፊዋ ሚስተር ፍሽለማን እያዩ፡- «አባታችን፤ ሌላ ጉልበት ላይ የሚታሰር ቃጭል ይሰጥዎታል፡፡ አሁን እንግዲህ ሁለት ወንዶች ስለምትሆኑ ሁለት ቃጭል ነው የሚያስፈልጋችሁ» አሉ፡፡
በሚቀጥሉት ቀኖች የሁለት ቃጭል ድምፅ ከአትክልቱ ውስጥ ተሰማ፡፡
ሴሮች በዚያ ባለፉ ቁጥር ሁለት አትክልተኞች ጎን ለጎን ሁነው አበባውን ሲኮተኩቱ ተመለከቱ፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ሴሮች በብዛት በዚያ አለፉ፡፡ሁለቱ አትክልተኞች ድምፅ ሳያሰሙ ይኮተኩታሉ፡፡ ፀጥታው ድንገት ደፈረሰ፡፡
«አብሮ የሚኮተኩተው ረዳት አትክልተኛ ነው» ካለ በኋላ የአባታችን የሚስተር ፎሽለማ ወንድም ነው» ሲሉ ተናገሩ፡፡

👍19👎2
ዣን ቫልዣ አዲሱ ስሙ ኽልቲመስ ፎሽለማ ሆነ፡፡ ኃላፊዋ ሴት እንደተነበዩት ኮዜት ግቢው ተስማምቷት በአጭር ጊዜ
ብዙ ጓደኛ ኣፈራች:: አንድዋ ጓደኛዋ ኃላፊዋ ሴር ነበሩ፡፡ ከልጃገረዶች ትምህርት ቤት ውስጥ የነፃ ትምህርት እድል ተሰጥቷት ትምህርትዋን
ቀጠለች፡፡
ኮዜት ገዳሙ ውስጥ ከሴቶች ትምህርት ቤት ገብታ ዩኒፎርም
ለበሰች፡፡ ከእነ ሚስስ ቴናድዬ ቤት ስትወጣ የለበሰችውን ጥቁር ልብስ ዣን ቫልዣ ጥሩ አድርጎ ካጣጠፈው በኋላ ሳጥን ውስጥ አስቀመጠችው:: ከዚያ
ወዲህ እርስዋ አዳሪ ትምህርት ቤት ገብታ ስትማር እርሱ የአትክልተኛነት ሥራውን ቀጠለ፡፡ ሥራውን በትጋት ስለሠራ ግቢው ውስጥ ለውጥ ታየ፡፡
ኮዜት በየቀኑ እየመጣች ለአንድ ሰዓት ያህል ከእርሱ ጋር እንድትጫወት ተፈቅዶላታል፡፡ ሴሮች ብዙውን ጊዜ ዝም ስለሚልዋትና እርሱ ዘንድ በመጣች ቁጥር ብዙ ስለሚያሳስቃት ዣን ቫልዣን ዘወትር ከሴሮች ጋር እያነፃፀረች እርሱን እንደ አምላክ ታመልከዋለች:: ሁለቱ ወንዶች የሚኖሩበት ቤት እርስዋ ስትመጣ በጣም ይደምቃል:: በእረፍት
ሰዓት ወጥተው ሲጫወቱ ዣን ቫልዣ ዘወትር በሩቁ ሆኖ ያያታል፡፡
ሳቅዋ የተለየ ስለነበር ድምፆን በሩቁ ይለየዋል ኮዜትም ያ ዝምታ ቀርቶ አሁን ሳቂታ ልጅ ሆናለች::
ከጊዜ በኋላ ኮዜት በጣም እየተለወጠች ሄደች:: ያ ኮሶ ፊትዋ
በፈገግታ ተለወጠ፡፡ ሳቅ ብርሃን ስለሆነ ጨፍግጎት የነበረው ፊትዋ ብርሃን ፈነጠቀበት::
የእረፍቱ ሰዓት አልቆ ወደ ክፍልዋ ስትገባ ዣን ቫልዣ የክፍልዋን
መስኮት በሩቁ ይመለከታል፡፡ ከዚያ ክፍል ውስጥ እንዴት ሁና እንደተቀመጠች ያሰላስላል፡፡
ገዳሙ በአጋጣሚ ሲገባበትም ለእርሱ ሁለተኛው እስር ቤት ነበር:: መጀመሪያ ታስሮበት የነበረው እስር ቤትና ገዳሙ በኣንዳንድ ነገር
ይመሳሰላሉ፡፡ ነገር ግን የመጀመሪያው እጅግ የመረረ ሲሆን የሁለተኛው እንደ መጀመሪያው የከፋ አልነበረም:: ሆኖም ሁለቱም በከባድ አጥር
የተካለሉና በራቸው በብረት መቀርቀሪያ የሚቀረቀር ነበር፡፡ አንዱ በወታደር
አጥር ሲከበብ ሌላው በብርሃን መቅረዝ የተሞላ ነው፡፡ የመጀመሪያው ቅጣት የሚቀበሉበት ሥፍራ ሲሆን ሁለተኛው በጸሎት የሚማቅቁበትና ደግነት፧ ትህትናና ሩህሩህነት የሚታሰብበት ቦታ ነው:: ከመጀመሪያው
ይበልጥ ሁለተኛው ዝምታ ይበዛበታል፡፡
ዣን ቫልዣ ሁለቱን በይበልጥ ባነፃጸረ ቁጥር ቅስሙ በይበልጥ
እየተሰበረና የኑሮ ፍላጎቱም በይበልጥ እየደከመ ሄደ፡፡ ያለፈውን ሕይወቱን ወደኋላ እያየ ለራሱ ያዝናል፡፡ አንዳንዴ እስከ ማልቀስም ይደርሳል፡፡ በዚህ
ዓይነት ከእስር ቤት ሲወጣ ያገኛቸው ጳጳስ በደግነታቸው፤ ኮዜት በፍቅርዋና ገዳሙ በተገራ ኃይል የቀረጹበትን ውስጣዊ ስሜቱን እያመቀ ስድስት ወር
ከገዳሙ ውስጥ ተቀመጠ፡፡
የአትክልቱ ቦታ ፀጥታ፤ የአበቦች መዓዛ፤ የልጆች ጫጫታ የደናግሉ
ዝማሬና ትህትና ቀስ በቀስ ሳይታወቀው ሕይወቱን ለወጡት፡፡ ልቡ በብቸኝነትና በዝምታ ኑሮ ስለተዋጠ ከመንፈሳዊ ኑሮ በስተቀር የሚያስበው
ነገር ጠፍቶት እየኖረ ብዙ ዘመናት አለፉ፡፡ኮዜትም እያደገች ሄደች፡፡....

👍20❤6
#ሸረኛ_እና_ደህና_በአንድ_ላይ #ሲሄዱ_በሸረኛው_በኩል_ተናደ #መንገዱ
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
#ሸረኛ
የዶክተር ደበጫ እርገጤ መዝገበ ቃላት ሸረኛ የሚለውን ቃል ሲያብራራው እንዲህ ይላል፡
ሸረኛ ስም፣ እንዳገባቡ 'ተውላጠ ስም፣ አንዳወጣጡ ግስ'፣ ሳይገባም ሳይወጣም ራሱን ችሎ
ዓረፍተ ነገር !
ትርጉሙ፡- (በተንኮል የሰው ማንነት፣ መልካም ስም፣ መልካም ሥራ፡ መልካም ግንኙነት
የሚሸረሸር፣ የሚሰረስር፣ የሚቦረቡር፣ የሚደረምስ፣ የሚያጠለሽ... ይለዋል። መዝገበ ቃላቱ ይሄን ሁሉ ነገር ከሚያንዛዛ በቀላሉ መግለፅ ይችል ነበር ልክ እንደዚህ፣
ሸረኛ፡- ሰው አቶ እጅጉ ! በቃ! አጭር ግልፅና ወቅታዊ ፍቺ !!
ምሳሌ፣ አቶ እጅጉ ሸረኛ ነው። ትክከል !! ይሄ ምሳሌ አይደለም፣ እጅጉ (እጅ እግሩን አስሮ
ሲኦል ይወርውረውና) 'ሸረኛ' ነው፡፡ ሸረኛ ብቻ አይደለም፣ ምቀኛም ነው፡፡ የሚቀናበት ነገር
ሲያጣ እኩል በተሰጠን 24 ስዓት ይቀናል፡፡ (“እንደው በየትኛው ጊዜ ብትማሩት ነው ይሄን ሁሉ ነገር ያወቃችሁት?” ይላል የማያውቀውን ነገር አውቀን ካገኘን፡፡ ለነገሩ እሱ ምንም
አያውቅም፡፡) ምን ይሄ ብቻ! እግዜር በፈጠረው አየር ሳይቀር ይቀናል፤ የቢሯችን መስኮት
ተከፍቶ እንደልብ አየር ሲገባ ብቅ ይልና፤ ይሄን አየር በነፃ ትሉታላችሁ” ይላል፡፡ እንከፈል?
ሸረኛም ምቀኛም ብቻ አይደለም መሰሪ ተንኮለኛም ነው:: አሟልቶ አይሰጥም' ይባላል አንጂ
ይሄው የተሟላ ክፉ ሰው፡፡
እንግዲህ ሸረኛ፣ ምቀኛ፣ መሰሪ ሆኖ ደግሞ አለቃዬም ነው፡፡ ጥሎበት አይወደኝም፡፡ እኔም
ሰለማልወደው ተመስገን ቢወደኝ ምን ይውጠኝ ነበር?' እላለሁ ሁልጊዜ፤ ለምወደው ሰው
ነው የምጨነቀው፡፡ አሁን በዚች ቅፅበት በሆነ አጋጣሚ ነገር ሎተሪ ምናምን ኣይነት እድል
ገጥሞኝ በድንገት የብዙ ኢ ቢሆን የመጀመሪያ ሥሪዬ ሁለት እጆቼን ኪስና ኪሴ ከትቼ በቀዳዳ ኪሴ ውስጥ በሾለኩ ጣቶቼ ራቁት ታፋዩን በማፏጨው ሙዚቃ 'ሪትም' እየተመተምኩ ጀነን ብዪ ወደ አለቃዬ ቢሮ ሄድና አንኳኳለሁ፣ ኖ..ኖ.አላንኳኳም፤ በሩን በእግሬ ገፋ አድርጌው እገባለሁ፡፡ (ካፈቀሩ ከነፍስ፣ ከጠሉም ከነፍስ ነው የምን ማስመሰል) ፊት ለፊት፣ ጉማሬ ፊቱ አለቃዬ ሁልጊዜ በሚደፈርሱ አስቀያሚ ደመኛ አይኖቹ ያፈጥብኛል። ቀጥሎ ኪሶቼ ውስጥ የወሸቅኳቸውን እጆቼን በቁጣ ያያል፤ (ደንግጨ
ከኪሲ እንዳወጣቸው እንድርበተቡት፡፡) ፀጥ ብዪ በትዕቢት ሳየው የኢትዮጵያን ሲጋራ ሁሉ ብቻውን ያጨሰ ከሚያስመስሉት አስቀያሚና ገጣባ ከንፈሮቹ ቃላት ደፈለፈላሉ፤ ሰው ሰው የማይሸቱ እብሪተኛ ቃላት፡፡
ምናልባትም፣ “ብላችሁ ብላችሁ ማንኳኳቱንም ተዋችሁት." ይል ይሆናል፡፡ (እግዜርና ሰይጣን
ለዚህች ቅፅበት እርቅ አውርደው ይሄን ድንጋይ ራስ ኣለቃዬን በመዶሻ ያንኳኩትና።) ወይም
“ኪስህ የወሸቅከውን እጅህን አውጣ!" ሊልም ይችላል፣ አላወጣም !(ኪሴ ቀዳዳ ሲሆን
ቀዳዳውን ተሻግሮ ያለም ወንድነት የራሴ ርስት ነው . ዘራፍ ! በቀዳዳ እኛነታችን ውስጥ እያለፈ ወንድነታችንን ያኮላሹን ክፉዎች ሁሉ ከዛሬ ጀምሮ አድርጉ ያሉትን አናደርግም፡፡
ኮራ ብዬ "እእእእ አቶ እጅጉ” እለዋለሁ፡፡ (“አቶ" በማሾፍ ሲጠራ እንዴት ያለ አሪፍ ስድብ ነው፡፡) ለምሳሌ፣ እኔ "አቶ” ከሚለው ቅፅል ይልቅ ከስሜ በፊት ሰሃራን የሚያህል ባዶ ምድረ በዳ ቢዘረጋ ይሻለኛል፡፡ በተለይ አለቃዬ "አቶ" ከሚለኝ ። ...አዎ ! እሱ "አቶ"
ሲለኝ በውስጡ “መቼም ለአቶነት አትበቃም በቸርነቴ 'ከቶ'ነት ልስጥህ እሰቲ” የሚል ይመስልበታል፡፡ አቷም።
እና አቶ እጅጉ ከዛሬ ጀምሮ ሥራ ለቅቄያለሁ” እለዋለሁ በኩራት፡፡ 'እእእእ' የምትለዋን ዘገምተኛ ቃል ማስቀደም አልረሳም፡፡ አራት ዓመት ሙሉ የሱን አስቀያሚ እእእ' ችዬ ኖሬ የለ ስለዚህ የምለው እንደዚህ ነው:: “እእእእ.አቶ እጅጉ ከዛሬ ጀምር...እእእእ ሥራ ለቅቄያለሁ !”
ይደነግጣል፣ አያምንም፡፡ እኔ ስፈጋ የዋልኩበትን ሥራ ሁሉ ለአለቆቹ እንዲህ ሠርቼው እንዲህ
አድርጌው እያለ በስልክ መወሽከቱ ሊቆም ሲሆነ ይደነግጣል እሰይ ! ወሽካቶች መደንገጥ አለባቸው።
ወዲያው የበሰበሰ የማኔጅመንት 'ሲስተሙን' እኔ ላይ ሊሞክራት ይፍገመገማል፣ “አትደነግጥ
የበታች ሠራተኛህ ፊት አዋቂ፣ ልብ ሙሉ ምንትስ ሆነህ ቅረብ፣ ባትሆንም ሁን…” የምትለዋን
ያስብና ጉሮሮውን ጠራርጎ፣ “እእእ….እዚህ መሥራቱ ራስህን ለማሳደግም ሆነ ቤተሰብህን ለመርዳት አይሻልህም? ይላል፡፡ ሥራ ብለቅ ቤተሰቦቼ በረሃብ ዛሬውኑ የሚያልቁ በሚያስመስል ሁኔታ 'ቤተሰብ የምትለዋ ቃል ላይ አፅንኦት ሰጥቶ፡፡
ከፉዎች መሳሪያ ልጅህ ላይ ባይደግኑም፡ እናትና አባትህን አፍነው ባይወስዱም፣ የነገን ጨለማነት እየነገሩ ያግቱUል፡፡ ስንቱ መሰለህ ቁራጭ ዳቦ እንዳይነሱት ፈርቶ ለማንም አጋሰስ ጉልበቱን የሚገፈግፈው፤ ስንቱስ ነው ' ከሥራ መባረር የሚባል የታንክ አፈ ሙዝ ልቡ ላይ ተደግኖበት ዘመናዊ ባርያ የሆነው !! ስንቷን ሚስኪን በፀሃፊነት ስም የጭን ገረዱ ያደረጋት ጋንጩር አለ ቢሮ ይቁጠረው !
ሀላፊ ሲባል አርቲስት ነው፡፡ ወንበሩን መድረክ ያደረገ ተዋናይ፡፡ ያውም ድብን ያለ ትራጀዲ
የሚተውን፡፡ እና እኔ ምን እለዋለሁ ሃሳቤ ደስ ብሎኝ ሳምሰላስል፣ ዙፋን ዘው ብላ ወደ ቢሮዬ
ገባች፡፡ ጥሎባት ማንኳኳት አትወድም፡፡ 'እንኳኪ!' ብሏት የሚያውቅም የለም፡፡
"ብርሽዩ” ትለኛለች፡፡ (ስሟን ከነአያቷ ቄስ ይጥራትና) ! ሁልጊዜ ስትጠራኝ እንዲሁ ነው፡፡ ታዲያ አጠራርዋ ከማማሩ ብዛት እኔን ለጠራችኝ ሌሎቹ 'ወይዬ' ሊሏት ይዳዳቸዋል፡፡
እንዲህ በሀሳብ ጭልጥ ያልከው ወዴት ሄደህብኝ ነው?” ወዴትስ ብሄድ ምን አገባት፡፡ ጭራሽ
የምሄደውስ የምቀረውስ ለሷ ነው እንዴ? (ሄደህብኝ !! ጥርግ ብል እንትናዬ እያለች አንዱ ቢሮ ልትንኳተት፡፡
"እ..ምነው ጠፋሽ?” አልኩ እንደመጣልኝ፡፡ የምለው አጥቼ እንጂ ዙፋን ደግሞ መቼ ጠፍታ
ታወቅና፡፡ በአንድ ጊዜ ሰባት ቢሮ ውስጥ የምትገኘውን ዙፋንን ጠፋሽ ማለት መሬትን “ምነው
በዚህ ሳምንት መዞርሽን አቆምሽ?” ብሎ ከመጠየቅ አይተናነስም፡፡
ሆሆ ከየት ተገኘሽ፣ አሁን እንኳን ስመጣ አራተኛዬ ነው” አለችና ከጠረጴዛዬ ፊት ለፊት ወንበር
ስባ ተቀመጠች፡፡ ወንበሩ ተንጫጫ፡፡ ጉርድ ቀሚሷ ቀይ ታፋዋን ወለል አድርጎ ያሳያል…..
ኤጭጭጭጭጭ!!
“ቆንጆ ናት” ይባላል፡፡ “ትሁት ናትም” ይሏታል። “የሰለጠነች፣ ሰው አከባሪ" የሚሏትም ብዙ
ናቸው፤ እንደው ባጠቃላይ እዚህ ቢሮ ዙፋንን ለማናገር፣ ለማቅረብ፣ ሲመቸው ወደ ኣልጋው
ጎትቶ አብሯት ለመጋደም የማይመኝ ያለ አይመስለኝም፡፡
ዙፋን እኛ ቢሮ ሥራ ስትጀምር ከሥራ ልምዷ ጋር ከእግዜር የተላከ “ከዛሬ ጀምሮ ያየ አመነዘረ፤ የሚለው ጥቅስ ተሰርዟል” የሚል ደብዳቤ ይዛ የመጣች ይመስል፣ እዛ ፋይናንስ ከሚሠራው ዲያቆን ወልዱ ጀምሮ ሰው ሰላም ሲል እገጩ መሬት እስኪነካ የሚያጎነብሰው ጴንጤው ምክትል ኃላፊያችን የዙፋንን እግርና መቀመጫ አይተን እንሙት አሉ፡፡ ዙፋንም ታዲያ የዕለት እንጀራዋ የሰው አይን ይመስል ነገረ ሥራዋ ሁሉ የታይታ ነው፡፡ አቤት መታየት ስትወድ፡፡ ሰው ከኋላዋ እንደሚያያት ከጠረጠረች ለከፉ ቀን ያስቀመጠችውን መቆናጠር ሁሉ ትጠቀምበታለች፡፡

👍26🔥1
ጥሎብኝ አልወዳትም፣ እሷም ታውቀዋለች፤ ምንም ትልበስ፣ እንዴትም ትራመድ እንደገለባ
ትቀልብኛለች፡፡ ብትሞት ቢሮዬን ሳትረገጥ አትውልም ዛሬስ እንዴት ነኝ? ኣይነት፡፡ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ፀሃፊ ናት፡፡ ቅርብ ጊዜ ነው የተቀጠረችው ሃሃሃሃ ወይ መቀጠር፣ ቅጥር ነፍሰ ገዳይ።
የአለቃዩ አለቃ ፀሃፊ ናት፡፡ የተመቻት የሃብታም ልጅ፤ ቤት ከመዋል ብላ ፀሃፊ የሆነች። እሷ "ፀሃፊ” ሲሷት አትወድም፣ ሴክሬታሪ ነኝ ነው የምትለው፡፡ ውድ ልብሶችን የምትለብስ፣
በተረከዘ ረጅም ጫማ ከቢሮ ቢሮ ስታውደለድል የምትውል ቆንጆ እንዴት ፀሃፊ ትባላለች? የሚያማልሉ ቀያይ እግሮች ያሏት፣ የከረመና የታጀለ የወረቀት ጠረን የሞላውን ቢሮ በሽቶዋ የምትፈውስ ዙፋን እንዴት 'ፀሃፊ' ትባላለች? ገና ሳያት እንደረዥምና እንደማያልቅ መንገድ ትደከመኛለች፤ እንደ ረዥም
ለዛ ቢስ ወሬ ትሰለቸኛለች፡፡ ከልቤ ትሰለቸኛለች፡፡ ባትመጣብኝ ደስታዬ ነው፡፡ ይሄንን ነገር
ማመን አልቻለችም፡፡ በሕይወት ዘመኗ እንደኔ ፊት ነስቷት የሚያውቅ ወንድ ያለም አይሰለኝም፡፡
…ትለዋለች በተዘዋዋሪ፣ -..እከሌ እኮ ጨዋ ነው፤ የኔ ጌታ እሱን ያገባች የታደለች፡፡ቢሮው ስሄድ
ከወንበሩ ብድግ ብሎ ሥራውን እርግፍ አድርጎ ትቶ እኮ ነው የሚያዋራኝ ." እንኳን ተነሳላት
ለምን ከመነሳት አልፎ ዘሎ ኮርኒሱ ጋር አይጋጭም፡፡ እንኳን ለደቂቃ ሥራ ማቆም፣ ለምን
የሥራ መልቀቂያ አያስገባላትም፡፡ አዝግ፣ ታዝገኛለች፡፡ ኮተታም ከብር አሳዳጅ፡፡
የጠላሁባት ምክንያት እንደ አንዳንድ ወንዶች ከራሳቸው ጋር ፈተና ሲገቡ መሻታቸውን ሲሸሹ ሴት እንደሚያንቋሽሹት አይነት አይደለም፡፡ ቁልጭ ያለ አገር ያወቀው ፀሐዪ ያገረረው፣ በአምባገነን እግሯ ምንም በሆነ ሴትነቷ፣ ፍትህ ትረግጣለች፣ ያማረችው በሚስኪኖች እንባ ታጥባ ነው:: ንፅህናዋ ንፁህ ነፍሳትን ትቢያ አድርጋ ነው፡፡ ያውም ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሚስኪኖችን፡፡ ሸረኛ ናት፡፡ ዙፋን ሸረኛ ናት፡፡ አለቃዬ
ሸረኛ ነው፡፡ እዚህ የተሰበሰሱ ወተፈናም ኃላፊ ተብዬዎች ሁሉ ሸረኞች ናቸው:: እና፣
መዝገበ ቃላቱ፣ እና የምትለዋን ቃል አያያዥ፣ ብቻዋን የማትቆም ቁንፅል ይላታል፡፡ በአጭር
ምስሌ "እና እኔ ነኝ፡፡ በሸረኞቹ እና በደህነኞቹ መሀል ያለውኑ ወይ አልሸርር ወይ አልደህንን
“እና” እኔ ነኝ፡፡ ምንም ታሪክ፣ ምንም ትርጉም የለኝም፡፡ሥራዬም ባህሪዬም የሆኑ ነገሮች መሐል
መደበቅ ይበዛበታል “እና” ነኝ !! እና ምን ይጠበሰ፡፡
ደህና፣ እማማ መለኮት መዝገበ ቃላቱ ሳይሆን መዝገበ እግዚሃር “ደህና” ብሎ የሚላቸው
አይነት ናቸው፡፡ እማማ መለኮት እድሜያቸው ሃምሳ ሁለት ወይም ሃምሳ ሰባት (እራሳቸው
እንደሚሉት)፣ ትሁት፣ በዚህ እድሜያቸው ለሁሉም ሰው ታዛዥ እና የሁላችንም መካሪ፡፡
እማማ መለኮትን የማይወድ ማንም የለም. መስፈሪያው ቢለያይም፡፡ ምንም ይሰፈር በምን፡ እንደኔ የሚወዳቸው ግን የለም፡፡
የዛሬ ዓመት አካባቢ እማማ መለኮት ቢሮዬ መጥተው ከጠረጴዛዬ አንድ ሁለት እርምጃ ራቅ ብለው ቆሙና ከወገባቸው ጎንበስ በማለት ሰላምታ አቀረቡ፡፡ ያረጁ ይመስላሉ፡፡ ፊታቸው
በሀዘን አኮፍኩፎ በእድሜ እናቴን ይበልጣሉ፡፡ ከወንበሬ ተነስቼ ለሰላምታ እጄን ዘረጋሁላቸው፡
በሁለት እጆቻቸው አሁንም ጎንበስ ብለው ሰላም አሉኝ፣ እጃቸው ይሻክራል፡ ልክ እንደ እናቴ....
✨ነገ ይለቅ✨

👍26
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
ማሪየስ
ጋርቡለስ
ዣን ቫልዣና ኮዜት ገዳም ከገቡ ከስምንት ወይም ከዘጠኝ ዓመት
በኋላ አንድ ያልተጠበቀ ነገር ይሆናል፡፡ የአሥራ አንድ ወይም የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ የተቀዳደደ የትልቅ ሰው ጫማና ልብስ አድርጎ ዋና ጎዳና ላይ ይንቀዋለላል፡፡ ይህ ልጅ ልብሱን ያገኘው ከአባቱ ወይም ከእናቱ
ሳይሆን ለነፍሴ ብሎ ካደረ መንገደኛ ነው፡፡ እናትና አባቱ ግን በሕይወት አሉ፡፡ አባቱ ስለልጁ ደንታ የለውም ፤ እናቱም ብትሆን እስከዚህም አትወደውም:: ይህ ልጅ እናትና አባት እያላቸው ቤተሰቦቻቸው የትም
እንደሚጥልዋቸው እንደማናቸውም ልጆች የሚታዘንለት ልጅ ነበር::
ልጁ መንገድ ለመንገድ በሚዞርበት ጊዜ በጣም ደስ ይለዋል።መንገድ ላይ የተነጠፈው ድንጋይ እንደ እናቱ ልብ ደንድኖና ጠጥሮ አይቆረቁረውም:: እናትና አባቱ ከቤት አስወጥተው የትም ጥለውታል።
ልጁ በጣም ንቁ፤ ቀልጣፋና ጮካ ልጅ ቢሆንም ታሞ የዳነ ይመስል ሰውነቱ ከመገርጣት አልፎ ክስት ብሏል፡፡ ይሮጣል፤ ይዘላል፤ ይጫወታል፧ ይዘፍናል ፧ የማያደርገው ነገር የለም:: ሲያመቸው ይሠርቃል፧ ሳያመቸው
ይለምናል:: አለዚያም ይቆምራል፡፡ ከጮሌነቱ ብዛት «ልጅ» እያሉ ሲጠሩት ከመቅጽበት ከተፍ ይላል፡፡ የሚለብሰው ልብስ፤ የሚበላው ምግብና
የሚጠለልበት ማደሪያ ወይም ደግሞ የሚወደውና የሚያፈቅረው ሰው የለውም:: ነገር ግን ነፃ ሆኖ በመኖሩ ደስተኛ ነው::
ከእንደነዚህ ያሉ ሰዎች ላይ ኅብረተሰቡ ይጨክናል፡፡ ከጭካኔው ብዛት አድቅቆ ይፈጫቸዋል፡፡ ግን ልጆች ከዚህ አይነቱ ጭካኔ አልፎ አልፎ
ያመልጣሉ:: ትንንሽ ልጆች በመሆናቸው በመጠኑም ቢሆን ህብረተሰቡ ስለሚያዝንላቸው ያልፋቸዋል:: ልጆቹም ማምለጫ ቀዳዳ አያጡም፡፡
ሆነም ቀረም፤ ይህ ብቸኛ ልጅ በየሁለት ወይም ሦስት ወር «አሁንስ እናቴ ጋ እሄዳለሁ» እያለ በየጊዜው ለራሱ ቃል ይገባል:: ወደዚያው ለመሄድ መንገድ ጀምሮ ከተወሰነ ሥፍራ ሲደርስ ‹‹
አሁንስ ወዴት ነው የምሄደው?» በማለት ራሱን በመጠየቅ ይቆማል፡፡ ቆም ብሎ ራሱን የጠየቀው ከአሁን ቀደም ከጠቀስነው ቁጥሩ 50-52 ከሆነ ቤት በራፍ ነበር፡፡
በተጠቀሰው ጊዜ ቤቱ ላይ «የሚከራዩ ክፍሎች» የሚል ጽሑፍ ከበሩ ላይ ተንጠልጥሎአል፡፡ ዣን ቫልዣ ከዚያ ሥፍራ ክፍል በተከራየበት
ጊዜ የነበረችው የቤቱ ጠባቂ ሞታለች:: ልክ እርስዋን የምትመስል ሴት ተተክታ ትሠራለች:: ስምዋ ማዳም ቡርዧ ይባላል::
ከዚያ ቤት ውስጥ ክፍል ከተከራዩት ሰዎች መካከል አንዱ አራት ቤተሰብ ያለው መናጢ ድሃ ይገኝበታል:: እነዚህ እናት፣ አባትና ለአቅመ ሔዋን የደረሱ ሁለት ሴቶች ልጆች የሚኖሩት ከአንድ ክፍል ውስጥ ነው::መንገድ ለመንገድ የሚንከራተተውም ልጅ የዚህ ቤተሰብ ልጅ ነበር፡፡ ልጁ
ከዚያ ቤት ሲደርስ የቆመው ልግባ ወይስ አልግባ በሚል የሕሊና ሙግት ምክንያት ነበር።
ቢገባ ያው ኩርፊያና ዱላ ነው የሚጠብቀው፡፡ የመጀመሪያው ጥያቄ ደግሞ «ከየት መጣህ?» የሚል ይሆናል፡፡ መልሱም ‹‹ከበረንዳ» ይሆናል፡፡ተመልሶ ሲወጣ ደግሞ «የት ነው የምትሄደው?» ብለው ይጠይቁታል፡፡መልሱም «ወደ በረንዳ» ነው የሚሆነው፡፡ እናቱ፡ ይህን ጊዜ «ታዲያ አሁን
ለምን መጣህ?» ብላ ትጠይቀዋለች::
እውነተኛ የአባት ወይም የእናት ፍቅር ለምን እንደሆነ ስለማያውቅ ልጁ በዚ ቅር አይሰኝም። እናቱ የልጁን እህቶች በጣም ትወዳቸዋለች::ልጁ የሚጠራው በእውነተኛው አባቱ ስም ሳይሆን በሌላ ነው:: ምነው ቢሉ የዚህ ዓይነት የተበላሸና የተመሰቃቀለ ኑሮ የሚኖሩ ሰዎች ዘራቸውን መቁጠር አይፈልጉምና ነው::
እነዚህ ቤተሰቦች የሚኖሩበት ክፍል የሚገኘው ከአንድ ጥግ ሲሆን በሌላ አቅጣጫ ከጥግ ያለውን ክፍል የተከራየው ሰው ደግሞ ማሪየስ የሚባል ወጣት ነበር፡፡
ይህ ማሪየስ የተባለው ወጣት ማነው?
የታወቁ ቡርዥዋ
ፓሪስ ከተማ ውስጥ ለብዙ ዓመታት ከኖሩ ሰዎች መካከል አንዱ መሴይ ጊልኖርማንድ የሚባሉ አንድ ሽማግሌ ነበሩ:: በ183 1 ዓ ም «ለረጅም
ዘመን ኖረዋል» ተብለው ከሚጠቀሱት ሰዎች መካከል አንዱ እኚህ ሰው ናቸው፡፡ ሰውዬው እድሜያቸው በጣም በመግፋቱ «ትውልድ የተላለፈበት»የሚል የቅጽል ስም ይታወቃሉ፡፡ እኚህ ሰው በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን
ጥሩ የእውነተኛ ቡርዣዎች ርዝራዥ በመሆናቸው ብዙ ሀብት አላቸው::
ድሜያቸው ወደ ዘጠና ዓመት ይሆናል፡፡ ብዙ ጊዜ ቶሎ የመቆጣት ስሜት ይጠናወታቸዋል
ሲናገሩ ይጮሃሉ፡፡ በዚህ እድሜያቸው ብዙ ይጠጣሉ፤ ቀጥ ብለው ይራመዳሉ፡፡ ከሰላሳ ሁለት ጥርሶቻቸው መካከል አንዱ እንኳን ኣልወለቀም:: ዓይኖቻቸው አልደከሙም፧ ሲያነቡ ብቻ ነው መነጽር የሚያደርጉት:: ገቢያቸው ከፍተኛ ቢሆንም ድሃ እንጂ
ሀብታም ነኝ አይሉም:: አሽከሮቻቸውን መደብደብና ማንቋሸሽ ይወዳሉ::
ሃምሣ ዓመት ያለፋት ያላገባች ሴት ልጅ አለቻቸው፡፡ ሲከፋቸው ሴትዮዋን ከመቆጣት አልፈው ይገርፏታል፡፡ በእርሳቸው ዓይን ልጅቱ የሃምሣ ሳይሆን
የስምንት ዓመት ልጅ ናት::
ሰውዬው የሚኖሩት በራሳቸው ቤት ሲሆን ቤታቸው ባለ ብዙ ፎቅ
ነው:: ግቢው እጅግ በጣም ሰፊ ሲሆን በአሸበረቁ አበቦችና ዛፎች ተሸፍኖአል።ሽማግሌው በወጣትነት ዘመናቸው ብዙ ሴቶች አታልለዋቸዋል፡፡ ሆኖም
አሁንም ቢሆን በዘጠና ዓመታቸው ራሳቸውን ወጣት አድርገው ነው
የሚገምቱት:: አለባበሳቸውም እንደወጣት ነው፡፡ ነገር ግን በወጣቶች የሚመራውን የፈረንሳይ አብዮትን እጅግ በጣም ይነቅፋሉ:: እርሳቸው እየሰሙ አንድ ሰው የነገሥታትን አገዛዝ ነቅፎ ሪፐብሊክ የሚመሠረትበትን
ሁኔታ ቢናገር ፊታቸው ከመቅጽበት ደም ይለብሳል:: ይህን ሲሰሙ በጣም ስለሚቆጡ ራሳቸውን እስከ መሳት የሚደርሱበት ጊዜ ነበር፡፡
የወንድና የሴት አሽከሮች በብዛት አሉዋቸው:: ሠራተኞቹን በጎሣቸው
እንጂ በራሳቸው ስም አይጠሯቸውም:: ለምሳሌ አንድ ቀን አዲስ የወጥ ቤት ሠራተኛ ለመቅጠር ፈልገው ሰዎችን ያነጋግራሉ፡፡
«ደመወዝ ስንት ትጠይቂአለሽ?»
«ሰላሣ ፍራንክ›
«ስምሽ ማነው?»
«ኦሎምፒ»
«ሃምሣ ፍራንክ እንከፍልሻለን፤ ስምሽ ግን ኒኮሌት ይሆናል፡፡» (ኒኮሌት የአንድ ጎሣ ስም መሆኑ ነው፡፡)
ሁለት ሚስቶች ነበሩዋቸው:: ከሁለቱም አንዳንድ ሴት ልጅ ሲወለዱ አንደኛዋ ልጅ በሰላሣ ዓመትዋ ነው የሞተችው:: ባል አግብታ ነበር ባልዋን ያገባችው አፍቅራና ተፈቅራ ወይም በአጋጣሚ ይሁን አይታወቅም
ወታደር ነበር፡፡ በትልቅ እህትዋና በእርስዋ መካከል የአሥር ዐመት የዕድሜ ልዩነት ነበር:: ትንሽዋ ስታገባ ትልቅዋ ቆማ ትቀራለች:: ምናልባት በዚህ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም፧ ትልቅዋ ልጅ ዘወትር ትተክዛለች፡፡የምትተክዝበትን ትክክለኛ ምክንያት ግን ከራስዋ በስተቀር የሚያውቀው የለም:: ሕይወትዋ በድን ለመሆኑ ፊትዋ ይመሰክራል፡፡
ከአባትዋ ጋር ነው የምትኖረው:: በታሪኩ መጀመሪያ ያየናቸው!
ጳጳስ ከእህታቸው ጋር እንዲኖሩ ሁሉ እኚህ ከበርቴ ደግሞ ከልጃቸው ጋር ነው የሚኖሩት፡፡ አንደኛው የሌላው ደጋፊ ነው::
ከቤቱ ውስጥ ከአባትና ልጅ ሌላ አንድ ልጅ ነበር፡፡ ይህ ልጅ
ተሽቆጥቁጦና ተንቀጥቅጦ ነው ያደገው፡፡ ሚስተር ጊልኖርማንድ ልጁን በቁጣ እንጂ በለዘበ አንደበት አናግረውት አያውቁም፡፡
«ና በል! ወሮበላ፤ ጥፋ፧ ሰማህ፤ ዱርዬ፤ መልስ እንጂ፤ አህያ»
( በእንደነዚህ ዓይነት ስሞች በቁጣ ሲጠሩት በእጃቸው ሰበቅ ይዘው ነው፡፡

👍20🥰1
ልጁ ዘወትር የሚሰማቸው ቃሎች ናቸው:: ሚስተር ጊልኖርማንድ ልጁን ልጁ ግን ሰውዬውን እንደ አምላክ ነው የሚያያቸው:: ልጁ የሽማግሌው የልጅ ልጅ ሲሆን ስለልጁ ወደፊት ብዙ እንሰማለን፡፡
አያትና የልጅ ልጅ
ቬርኖን ከተባለች ትንሽ ከተማ ያለፈ ሁሉ አንድ ወደ ሃምሣ ዓመት እድሜ ያለው ከእድሜው በላይ ያረጀ ፤ የተጨማደደ ቆብ ያጠለቀ፣ የተቦጫጨቀ ልብስ የለበሰ፤ ፊቱ በፀሐይ ብዛት የጠቆረ፤ ፀጉሩ የሸበተ፧
ፊቱ ላይ ትልቅ ጠባሳ ያለበት፧ ወገቡ የጎበጠ፤ ዘወትር አካፋና የአትክልት መከርከሚያ ይዞ የሚራመድ፤ ከሴን ወንዝ ድልድይ አካባቢ የማይጠፋ ሰው ሳያይ አያልፍም:: የተጠቀሰው ሰው በ1817 ዓ.ም. እጅግ በጣም
አነስተኛ ከሆነ ቤት ውስጥ ይኖር ነበር፡፡ ይህ ሰው በድኀነት እየማቀቀ ካንዲት አሮጊት አይልዋት ልጅ ፤ ቆንጆ አይልዋት ፉንጋ፧ ከበርቴ አይልዋት ድሃ፧ ከተሜ አይልዋት ገጠሬ ሴት ጋር ይኖራል፡፡ ሰውዬው ጠዋት ማታ
ከሚንከባከበው የአበባ ሥፍራ
ተለይቶ አያውቅም:: ኑሮውን የሚገፋው አበባ እየሸጠ ነው፡፡
ይህ ሰው በአፍላው ዘመን ጦር ሜዳ ትልቅ ጀብዱ የፈጸመ ሲሆን
ስሙ ጆርጅ ፓንትመርሲ ይባላል፡፡ በልጅነቱ በወታደርነት ተቀጥሮ ዋተርሉ ከተባለ ጦር ሜዳ ሠራዊት እየመራ ዘምቷል:: ጦር ሜዳ ላይ የጠላት መሣሪያ ማርኮና በደም ተበክሉ ከንጉሡ ፊት በቀረበ ጊዜ «አይ ጀግና
የጀግና ዘር ተብሎ ከተሞገሱ በኋላ የኰሎኔልነት ማዕረግና የጀግና ሜዳሊያ ሽልማት ይፈቀድለታል:: ማዕረጉና ሽልማቱ እንደተፈቀደለት
«ግርማዊ ሆይ! በባል አልባ ባለቤቴ ስም አመሰግናለሁ» ብሎ ይናገራል፡፡ይህንን ከተናገረ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሕሊናውን ስቶ ከመሬት ይዘረራል፡፡ ይህ
ጀግና ወታደር ነው ዛሬ የአበባ ሻጭ ሆኖ በችግር የሚማቅቀው::
ጆርጅ ፓንትመርሲ በጦርነቱ ስለተጎዳ እጅግ አነስተኛ የሆነ የጡረታ እበል ተፈቅዶለት ቬርኖን ከተማ እንዲመለስ ተደረገ፡፡ የሚያሳዝነው ንጉሡ
ቃላቸውን ረስተው ለሰውዬው ምንም እንኳን ሹመቱና ሜዳሊያው ቢሰጠውም እነዚህ ነገሮች ያስገኙት የነበረውን ጥቅም ሳያገኝ ቀረ፡፡ ሆኖም
ከቤቱ በወጣ ቁጥር የጀግንነት ሜዳልያውን ሳያደርግ አይወጣም::
የጡረታው ገንዘብ በጣም ትንሽ ስለነበር በጣም ዝቅተኛ የሆነ ቤት
ተከራየ:: በዚህ ጊዜ ነበር የከበርቴው መሴይ ጊልኖርማንድን ልጅ ያገባው::
የከበርቴው ልጅ ይህን ድሃ በማፍቀርዋ አባትዋ ከማዘን አልፈው በጣም ይናደዳሉ፡፡ ነገር ግን እርስዋ ከፈለገች መቼስ ምን ይደረጋል በሚል በጋብቻው
ተስማሙ:: የሚያሳዝነው ግን ሴትዮዋ ምንም እንኳን እጅግ ተናፋቂና ተወዳጅ ሴት ብትሆንም ብዙ አልኖረችም፡፡ በ1815 ዓ.ም ሕፃን ልጅ ከኋላዋ ትታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች:: ልጁ የኰሎኔሉን የብቸኝነት ኑር
ለመለወጥ የደስታ ምንጭ መሆን ይገባው ነበር፡፡ ግን ሊሆን አልቻለም ፤ምክንያቱም አያቱ «ልጁ ለእኔ ካልተሰጠኝ ሀብቴን አላወርሰውም» ስላሉ ልጁ ከአባቱ ተነጠለ፡፡ አባት ጥያቄውን የተቀበለው ለልጁ ሲል ነበር፡፡
የወለደውን ልጅ ለማግኘት ባለመቻሉ የልጁን ፍቅር በአበባ ፍቅር ለወጠው::
መሴይ ጊልኖርማንድ ከሴት ልጃቸው ባለቤት ጋር የቀረበ ግንኙነት አልነበራቸውም:: ለእርሳቸው ከሎኔሉ «ሽፍታ» ነው:: ኮሎኔሉም ሽማግሌውን ነገር እንደማይገባቸው «ደደብ» ሰው ነበር የሚያያቸው፡፡
መሴይ ጊልኖርማንድ ሁናቴ ካላስገደዳቸው ወይም ለመፎተት ካልሆነ በስተቀር ስለኰሎኔሉ ማንሳት አይፈልጉም:: አባት «ልጄን ካላየሁ ወይም
ካላነጋገርኩ» እያለ ቢያስቸግር ልጁ የአያቱን ሀብት ሊወርስ እንደማይችል ለኵሎኔሉ በቅድሚያ ተገልጾለታል፡፡ ኰሎኔሉ በዚህ መስማማቱ ምናልባት
ጥፋተኛ ሳይሆን አልቀረም፡፡ ግን ይህን ግዳጅ የተቀበለው ለልጁ በማሰብና የራሱን ደስታ በመሰዋት ሊሆን የወሰደው እርምጃ ትክክል መሆኑን ስላመነ ነው::
ልጁ በቀጥታ ከአያቱ ሊወርሰው የሚችለው ሀብት እስከዚህም ብዙ አልነበረም፡፡ ከእናቱ ታላቅ እህት ማለት ከከክስቱ ሊወርሰው የሚችለው ሀብት ግን እጅግ ብዙ ነበር፡፡ እክስቱ በእናትዋ በኩል የወረሰችው ብዙ ሀብት ነበራት:: የእህትዋ ልጅ ደግሞ ቀጥተኛ ወራሽ ነው:: የልጁ ስም ማሪየስ ይባላል:: ማሪየስ አባት እንዳለው ያውቃል:: ከዚያ ወዲያ ስለአባቷ
የሚያውቀው ነገር የለም:: እንዲያውም ከነአካቴው በአካባቢው የሚወራውን ወሬ ስለሰማ በአባቱ ያፍራል።.....

👍23❤4🔥2
#ሸረኛ_እና_ደህና_በአንድ_ላይ
#ሲሄዱ_በሸረኛው_በኩል_ተናደ
#መንገዱ
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
...ፊታቸው በሀዘን አኮፍኩፎ በእድሜ እናቴን ይበልጣሉ፡፡ ከወንበሬ ተነስቼ ለሰላምታ እጄን ዘረጋሁላቸው፡
በሁለት እጆቻቸው አሁንም ጎንበስ ብለው ሰላም አሉኝ፣ እጃቸው ይሻክራል፡ ልክ እንደ እናቴ.
እነዚህ ሞረድ እጆች የስንቶቻችንን ባለ ለስላሳ እጆች ሆይወት እንደሞረዱ ፈጣሪ ይወቅ!
እንዲቀመጡ ወዳመለከትኳቸው ወንበር ቀስ ብለው ተቀመጡና የመጡበትን ጉዳይ ቀስ ብለው
እንደምታውቀው እዚህ ቤት ነገረ ሥራቸው ሁሉ ውስጥ ለውስጥ ነው:: ደከመኝ፣ ሰለቸኝ
አስረዱን፣ አቶ አብረሃም (አቤት አቶ በእሳቸው አንደበት እንዴት ክብር እንዳለው ) ያው እንደምታውቀው እዚህ ቤት ነገረ ስራቸው ሁሉ ውስጥ ለውስጥ ነው ደከመኝ ሰለችኝ ሳልል በሰራህ ለትንሽ ትልቁ 'እሺ' ብዬ ባደርኩ ድንገት ከሥራዬ ነቀሉኝ፡፡" አሉና እንባቸው ተዘረገፈ፡ እድሜ በሸነተረው የቆዳቸው እጥፋት ሽብሽብ ውስጥ እንባቸው ጎረፈ፡፡ በነጠላቸው ጫፍ እይናቸውን ጠረጉ፡፡ (እዚህች ባልቴት ውስጥ ይሄ ሁሉ እንባ እንዴት ሊኖር ቻለ? እድሜ ልካቸውን ያጠራቀሙት ይሆን?) እማማ መለኮት ከፅዳት የሥራ ገደብ ተነስተው በሀያ ዓመት የሰርክራሲ ባቡር ተጉዘው ፅሃፈ ለመሆን የበቁ ፅኑ ሴት ናቸው፡፡ ከልምድ እንዳየሁት ብዙ
ታላላቅ ድርጅቶች ሱፍ ለብሰው በሚኮፈሱት አለቆቻቸው ሳይሆን በሚስኪኖች ትከሻ ላይ
ተጭነው ነው የቆሙት፡፡ እማማ መለኮት የድርጅታችን ዋልታ ይሄው ተባረሩ፡፡
ከዛ በፊት፡ ከመባረራቸው በፊት፤ አሽሙር የሚመስል ስብሰባ ተደረገ፡፡ አንዲት ረዳት የሌላቸው
ሚስኪን ባልቴት ለማባረር ቱባ ቱባ ባለስልጣን፣ ከቱባው የተተረተሩ ክር አቃጣሪዎች እና እኛዎች" ውሃ ቡና ቀርቦ ስብሰባ ተደረገ፡፡የስብሰባው መሪ፣ "ሸረኛው" እጅጉ፣ ፀሃፊው “ሽረኛው"
አለሙ፣ ተላላኪው፣ ወሬ አቀባዩ (እንደ ሰው አልባ አውሮፕላን እያንዣበባ ሰላሉት አለቆቹ ወሬ ይቃርማል፡፡ “መታዘዝ ፅድቅ ነው” ሲባል የመታዘዝ ፅድቅነትን የማያመዛዝን አዕምሮ ተሸክሞ የሌሎች ባሪያ መሆን ማለት አይደለም፡፡ ሰብዓዊ ትዕዛዝ፣ ሰው መሆን ይቅርብሆ ተብለህ ሳይሆን፣ ለእኔ ማለት ይቆየኝ፣ ቅድሚያ ለሌሎች ከሚል በጎነት መነሳት ነው:: በጎነት በትዕዛዝ አይመጣም፡፡)
ስብሰባው ተጀመረ፡፡ ለአንዲት ባልቴት ተሰበሰቡ እንዳይባል የማይረባ አርሲ ኩርሲ አጀንዳ
ጋር ተደምሮ የእማማ መለኮት መባረር መቀነስ” የሚል የዳቦ ስም ተሰጥቶት አጀንዳ ሆነ፡፡
“ባንድ ላይ ሲሄዱ” መዝገብ ቃላቱ በአንድ ላይ መሄድን በአንድ ላይ ከመታየት ነጥሎ አለማየቱ ትልቅ ጉድለት ነው::
የሸረኛ፣ “እና” ና “ደህና” ስብሰባው ላይ በአንድ ላይ ተገናኘን፣ በማንኛችን በኩል መንገዱ እንደሚናድ ልናይ - ቀድሞ የተናደውን፡፡
“ተናደ"
ስብሰባውን የጀመረው አለቃችን አቶ እጅጉ ነበር፡፡ ኩፍስ ብሎ የኮቱ አጥፋት ሸብዳዳ ትከሻው ላይ ተከምሮ (ከኮቱ ውስጥ ትንሽ የሶፋ ትራስ ያስቀመጠ ይመስለኛል)፡፡ ጨዋ ለመምሰል በሚዳዳው ድምፅ ስብሰባው መጀመሩን አረዳ (አበሰረ የሚሉም አሉ “ከሸረኞች ወገን ናቸው)
እ...ያው እንደምታውቁት…" አለ (ምንም በማናውቀው ነገር) ...መሥሪያ ቤታችን ያለውን
መልካም ሰምና ዝና ለማስቀጠል (ሂሂሂሂ ጉድ ፈላ በቀን የሚመጣው ባለጉዳይ ሁሉ እዩዬ እያለ ተራግሞ የሚሄድበት መሥሪያ ቤት መልካም ስምና ዝና ይሁና) ዘመናዊ የአሠራር ሲሰተም
ዘመን አፈራሽ መሳሪያዎች እንደሚያስፈልጉ በማመን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ወስደን
እየተንቀሳቀሰን 'ያለበት ሁኔታ ነው ያለው….
እነዚህ ዘመናዊ መሳሪያዎች ደግሞ ብቻቸውን ጠብ የሚል ለውጥ እንደማያመጡ እሙን
ነው፣ ስለዚህ ቢሯችንን 'በአመለካከት በእውቀት እና በተግባር ከመሳሪያዎቹ ጋር አብሮ
በሚሄድ ወጣት የሰው ኃይል ማደራጀቱ ለነገ የማይባል አንገብጋቢ ተግባር ነውሸ
(እማማ መለኮት በኩል መንገዱ ተናደ:: ጨዋነትን የጫነው መኪና ገደል ገባ፡፡ ትህትና ተሽቀነጠረ፡፡ መንገድ ስለሌለ ወደኋላ ተመለስን፡፡ መንገድ አፍራሽ ሸረኞች ራእይ እንደ ህልም
ያያሉ፡፡ ከመድረስም ተጣልተዋል፡፡ መንገድ የለማ ...! ከአባይ ወዲያ ማዶ ያለ ዘመድ ሆነ የእማማ መለኮት ሥራ፣ እንባቸው በአይናቸው የሞላ እለት ዋይ ብለው ቀሩ፡፡
እንዲት በእድሜ የገፉ ሚስኪን አባሮ በየቢሮው እየዞረች ምስጋና የምትቀላውጥ ገልቱ
ለመቅጠር ምድረ ጉማሬ ሚስኪኑን ላብ አደር ሰብስቦ አላዘነ፡፡ ደግሞ ስላዘመናዊነት
ያወራሉ፣ እግዚኦ አለቆቻችን ስለዘመናዊነት አወሩ፡፡ስልካቸው ባትሪ ሲጨርስ ተበላሸ
ብለው ሠሪ ቤት የሚሮጡ አለቆቻችን ዘመናዊነትን ሰበኩ፡፡ ከፕሪንተር የሚወጣ ወረቀት ደመና ሰንጥቆ እንደሚወጣ መልአክ በግርምት የሚመለከቱ፡፡ (አይ ፈረንጅ ነፍስ መፍጠር እኮ ነው የቀረው!' እየተባባሉ፡፡) እለቆቻችን ዘመናዊ እንሁን አሉ፡፡
እማማ መለኮት በጡረታ ስም ተባረሩ፡፡ (ተቀነሱ በል አቶ አብረሃም ተብያለሁ፡፡) ዙፋን
ተቀጠረች አሁን ድርጅቱ ዘመናዊ ሆነ፡፡ “እንደምን ዋላችሁ…”፣ “ሃይ ጋይስ” በሚል ሰላምታ .
በመተካቱ እልልል ቢሯችን ዘመናዊ ሆነ፡፡
ዙፋን የዘመናዊነት ፋና ወጊ፣ አንድ ገፅ ደብዳቤ ስትፅፍ አንድ ከግማሽ ገፅ ስህተት የምትዘራ
ጉድ፡፡ ወሬ ብቻ መሽኮርመም ብቻ፣ በየሰሙ ላይ “ዬ" መጨመር ብቻ (አብርሽዬ..ቶማስዬ.
ጋሽ ሰይድዬ ተፈራዬ... ሐጎስዬ.. ገኒዬ..እግዚያብሄርዬ..ጂሰስዬ_) እንደ ዬ ፈደል ትልቅ አፍ ብቻ
ያላት መርገምት፡፡ደህና ነገር ሲናገር ከንፈሩ እንደደረቀ ሰው በየደቂቃው ቻፕስቲክ እየተለቀለቀች በየቢሮው ማውራት !! (ውይ ጥርስ አታስከድንም፤ ተጫዋች ምናምን ይሏታል የሸረኛው መንጋ፡፡
ቆንጆ ብቻ መሆን እንዴት ይቃፋል፡፡ ሴት ብቻ በመሆን ከወንድ የሚቻር ወሲባዊ ክብር ምንኛ ውድቀት ነው?! ዕድሜ ከፍ ባለ ቁጥር የሚናድ የእንቧይ ካብ፡፡ እንዴት ሰውን ያህል ፍጥረት
ያውም እናትነትን ያሀል አደራ ትቀበል ዘንድ ተፈጥሮ የወከለቻት ሴት ስለጥፍር አንድ ሰዓት ሙሉ ታወራለች? ስለፀጉር ሁለት ሰአት፣ ስለጥፍር ቀለም ሙሉ ሸን፣ስለ ልብስ...
የመታየት ልክፍት (ኤግዝቢሽኒያም ይለዋል በሬቻ)፡፡ በፋሽን ስም ነጋቸው ላይ ውበት ሊዘሩለት ሚችሉትን ዛሬ አርሲ ኩርሲ የውበት ኮተት እያወሩ ይፈጁታል፡፡ ይሄ የሴት ውበት ነው የሴት ብክነት፡፡ ስለውበት የሚደሰኩር ሚዲያ ላይ አፍጥጣ የምትውል ዙፋን፣ ቆዳዋን በምናምን አደንድና ፍቅር እንዳይስርአት ራሷን ሳታዋድድ ትኖራለች። ሴት ከምልክ የተሻለ መወዳደሪያ በሌላት ውድድሩ ውስጥም የምትኖረው ቢበዛ ለጥቂት ዓመታት ነው፡፡ ባካና ! ዙፋን ባካና ናት፤ ስሟ ራሱ እሷ ላይ ሲደርስ 'ዙፋን' የሆነ፣ የመወዘፍ አይነት ደውል ነው፡፡ (ውዝፍ ከሚለው ስረወ ቃል የመጣ)
ከአለቃዬ ጋር በአይኗ ስትዳራ ስንት ጊዜ ታዘብኩ፡፡ እማማ መለኮትን ነቅላ ላትፀድቅ ነገር
ራሷን የተከለችበትን ቆሻሻ መንገዷን አይቻለሁ፡፡ ለፀሃፊነት ሥራ ውድድር መሰለፍ የማይችል
ባልጩት ጨንቅላቷ ላይ ሰው ሰራሽ ፀር ጎዝጉዛ ክቡር ሴትነቷን በየቢሮው ስትጎዘጉዝ ሳናይ
አላወራንም፤ “ጭስ ካለ እሳት አለ” ብለንም እይደለም፡፡ ቆይቶ የተደረገ ግምገማ ላይ የተገደደች
አስመስላ ቀባጠረችው እንጂ፡፡ (የሸረኞች መንገድ የተናደች" እለት)

👍19❤2
ባለቤት የለሽ ስጥ ማንም አላፊ አግዳሚ የሚዘግናት፡፡ ወንዶች በምናምናቸው እየተመሩ
የሚደርሱባት ጥግ፡፡ የሴትነት ባንዲራ ዝቅ ብሎ የሚውለበለብባት ፀያፍ ምሶሶ፡፡ ለወረደ የሴትነት ባንዲራ ሴሰኛ ወንዶች ሲዘምሩ ምሰሶው እንዴት ቴንኪው' እያለ ይሽኮረመማል?
የእድሜ ጉዳይ ነው፡ ያች የሴትነት ባንዲራ ትወርዳለች፡፡ ያኔ ዘማሪ ሲጠፋ ሴትነት የተነጠለው
“ሰው መሆን ብቻውን” ሲቆም ይሄ ከተማውን የሞላው አላፊ አግዳሚውን በቅናት ግልምጫ
የሚጎነትል፣ “ምከሩ ላይ ስቆ የመከራ ዱላ መድረሻ ያሳጣው፣ ፍቅር እልባ የሴት ፊት ሁሉ”
ዙፋን ተባለች መሀበርትኛ ይመረቅለታል፡፡
አቀባበል ይደረግላት ተባለ ዙፋን፡፡ ሰው እንዴት ምንም ይቀበላል? በግ ታርዶ፣ ቢራ ቀርቦ
“አንዲት ፀሃፊ ለመቀበል ይሄ ሁሉ ድግስ” እንዳይባል፣ ለአቀባበሉ ህዝባዊ ስም ወጣለት
“የሩብ ዓመቱ የግምገማ ማጠቃለያ'፡፡ ሲበላ፣ ሲጠጣ ሸረኞች የሸረኛ ልዕልታቸውን ከብበው እያውካኩ ጥሬ ከብስል ሲሰለቅጡ እማማ መለኮች ናፈቁኝ፡፡ እንዲህ ዝግጅት ሲኖር እሳቸው ሌሊት ሁሉ እያደሩ ወጥ ይሰሩ ነበር አምስት ሳይከፈላቸው፡፡ ነጭ ልብሳቸውን ለብሰው፣ምድረ ሆዳም ሲያስተናግዱ ይውሉ ነበር፡፡
መንገዱ
ግብዣው ሹልክ ብየ ወጣሁና፤ አጠያይቄ እማማ መለኮት ቤት ሄድኩ፡፡ በራቸው ላይ ቁጭ ብለው
ምስር እየለቀሙ ነበር፡፡ ሲያዩኝ በድንጋጤና በግርምት ተርበተበቱ፡፡ የምስር ክክ የያዘውን
ትሪ ወደቀኛቸው ካለች መደብ ነገር ላይ ሲያስቀምጡ የተለቀመው ካልተለቀመው ተቀላቀለ፡፡
ኣንደእኛ ቢሮ፣ እንደእኛ ሃሳብ፣ እንደእኛ ፖለቲካ፣እንደእኛ እኛነት ተመልሶ መልቀም፡፡ አዲስ እንግዳ
ሃሳብ፣ እንግዳ አሰራር፡ እንግዳ ርዕዮተ ዓለም ሊመጣ ያከበርን መስሎን የሰራነውን ማፍረስ፡፡
ከመቀመጫቸው ተብድግ ብሰው በእከብሮት ቆሙ፡ "ውይ በሞትኩት እዚህ ድረስ ምን አለፋህ
አቶ አብረሃም - እጄ ቆሻሻ ነው ቆይ” ብለው ቀሚሳቸው ጋር ጠራረጉና በተስፋ እያዩኝ
ጨበጥኳቸው፣ ምናልባት ወደሥራ ልመልሳቸው የሄድኩ ይመስላቸው ይሆን? ግባ አሉኝ፤ ገባሁ
ንፁህና ጠባብ ናት ክፍላቸው፡፡ ወደጓዳ መግቢያ ላይ ባለጥልፍ ነጭ መጋረጃ፡፡ ባለመደገፈያ
የቀርከሃ ሶፋ:: ግድግዳ ላይ አንድ ጥቁርና ነጭ የትልቅ ሰው ፎቶ አለ (ባላቸው ይሆኑ?)፡፡
ከጎኑ ባለድግሪ ወጣት ባለቀለም ፎቶ፡፡ እማማ መለኮት መጋረጃዋን ገለጥ አድርገው ወደ ጓዳ ገቡ፡፡
ቡና እንደምወድ ያውቃሉ፡፡ ላፍላልህ ሳይሱ ቡናውን አቀራረቡ፡፡ አወሩኝ ስለነበረው፡
“ግራ ገብቶኛል፣ እንቅልፍም አልወስድሽ ብሎኝ ነው ያደርኩት፡፡ እንግዲህ በዚህ ዕድሜ ሰው
ቤት ልብስ ላጥብ ነው ? እንጀራ ልጋግር ? እኔኮ ሌላው አይደለም ያሳዘነኝ፣ ይሄን ያህል ዓመት
ያገለገልኩበት ቤት ነው፡፡ ምናላ ለወጉ ጠርተው እንግዲህ በቃሽ ቢሉኝ፡፡ አቶ እጅጉ መጥቶ
ሰሜን እንኳን አልጠራኝም፡ ይሄን ኮምፒተር አፀዳጅው፤ እንግዲህ ጡረታ መውጫሽም እየደረሰ
ነው፤ በቃ እንዲህ ነው ያለኝ፡፡ የዛሬን ቀን አያምሽልኝ፣ እንዲሁ አለኝ..ይባላል ? አቶ ኣብርሃም
እስቲ ፍረድ፣ ፍርድ ለራስ ነው መቸም…"
አለቀሱ እማማ መለኮት:: የማደርገው ነገር ጠፋብኝ፡፡ “ብዙ ያየሁ ሰው ነኝ፣ ይከፋኛል፣
ማግኘትም ማጣትም ማጀቴን የጎበኘው ሰው ነኝ፡፡ባሌ የሞተብኝ ሴት ነኝ አርጅቻለሁ፡፡ ልጄ
ምጥ ይግባ ስምጥ የጠፋብኝ ብሶተኛ ነኝ፡፡ ለትንሽ ትልቁ ደፋ ቀና የምለው ቀባሪ የለኝም፣
'የአገሬ ሰው ነው ቀባሪዩ” ብዬ ነው:: እንዴት እንዲህ ያመንኩት ህዝብ ይተፋኛል? እንዴት
ባዕድ እሆናለሁ? አይዞሽ ማንን ገደለ? ፀሃፊነቱን ይተዉት እናትነት ይወረወራል ? አንድ ሰው
በሬ ዝር አይልም ? በሃዘን በደስታው ከሥራዬ አልፎ ተርፎ ለድግሳቸው ጉልበቴን ገብሬ
ቤታቸውን አላቀናሁም ? ፍረድ አቶ አብረሃም - ፍርድ እንደራስ ነው” ስኳር ወደ ስኒዎቹ ጨመሩ፡፡ በዝምታችን ውስጥ ቡናው ሲቀዳ ደስ የሚል ድምፁ ጠባቧን ቤት ሞላት፡፡ አንዲት ክስት ያላች ጥቁር ድመት ገብታ ረከቦቱ አጠገብ ቆመች፡፡ ለቡና ቁርስ ከተቆራረሰው ዳቦ ቆንጥረው ሰጧት፡፡
"እማማ መለኮት!” አልኩ ቀስ ብዬ፣
“ወይዩ!” አሉ ቡናውን እያቀበሉኝ፡፡
“ልጄ ጠፋ ነው ያሉኝ?” ወይ ወሬ መውደድ አሁን የሰው ብሶት ከመቀስቀስ ውጭ ምንም
ላልፈይድ ምን አጠያየቀኝ…::
“አዎ.ይሄ ፎቶ የሱ ነው” አሉ ወደ ባለድግሪው ወጣት እየጠቆሙኝ፡፡ ጭራሽ ተነስተው ፎቶውን
ከተሰቀለበት አወረዱና ሰጡኝ፡፡ መልከ መልካም ወጣት ነው፣ ሳቂታ፡፡
ልጄ ነው አንድ ልጄ፡፡ ስድስት ኪሎ በድግሪ ተመርቆ ወር ሳደቆይ 'ወደ ውጭ አገር ልሂድ ብሎ ተነሳ፡፡
ኬኒያ የሚባል አገር ደረስኩ ብሎ ደወለልኝ፡፡ ይሄውልህ ከዛ በኋላ ይኑርም ይሙትም ወሬው የለም ብለው እንባቸውን ዘረገፉት፡፡
“ከሄደ ቆየ ?..." በሃሳቢ ኬኒያ ያሉ ጓደኞቼን 'ይሄን ልጅ ካላገኛችሁ ወዮላችሁ! ልል ተዘጋጅቼ፡፡
እንግዲህ ወደ አስራ አምስት ዓመት አይሆነውም ብለህ ነው” ፎቶው ላይ አፍጥጬ ቀረሁ፡፡
“ቡናው ቀዘቀዘብህ፣ የኔ ነገር" ብለው ፎቶውን ከእጄ ተቀበሉና ቦታው መለሱት፡፡
ስናወራ ቆይተን እንደምጠይቃቸው ነግሬያቸው ስወጣ፣ "አቶ አብረሃም፣ ካላስቸገርኩህ በቅደም
ተጣድፌ እኔ መሳቢያ ውስጥ መሃረቤን ረስቸው መጣሁ፡፡
እንደው ላቶ ሽብሩ
ብትሰጥልኝ በዚሁ ሲያልፍ ያቀብለኛል" አሉ፡፡ አቶ ሽብሩ የመስሪያ ቤታችን ሹፌር ነው፡፡
የችን ተዓምረኛ መሃረብ የቢሮው ሰው ያውቃታል፡፡ እማማ መለኮት ፀበል ቤት ይሄዱና ወይም
ቤታቸው ዝክር ብጤ ትኖራቸውና በምንቀርባቸው ባልደረቦቻቸው የፀበል ቤት ዳቦ በመሃረባቸው
ጠቅልለው ያመጡልናል - በቀይ ክር የሀረግ ጥልፍ ዙሪያውን የተጠለፈበት መሃረብ::
፡
በቀጣዩ ቀን ቢሮ ስገባ አቶ እጅጉ ደረጃው ላይ አገኘኝና፣ ”አቶ አብረሃም፣ ምነው ድግስ ረግጠህ
ወጣህ?” አለኝ፡፡ “አጋሰስ” አላልኩትም፡፡
የእማማ መለኮትን መሃረብ ለማምጣት ወደ ዙፋን ቢሮ ሄድኩ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር እማማ መለኮት ከለቀቁ በኋላ ወደዚህ ቢሮ የመጣሁት፡፡ ዙፋን እፏን ከፈተችው፣ "አ..ንተ በመጨረሻ መጣህ፡፡ ዝም ብለህ ትንቀባረራለህ መምጣትህ ላይቀር" አለች ፊቷ አንበሳ ገዳይ አይነት ፉከራ ሰፍሮበት - ደነዝ!! አጎንብሳ እግሯን የሆነ ነገር እያደረገች ነበር የምታወራኝ - ጠረጴዛሁ እግሯን ጋርዶኛል፡፡
“ምን እዚህ ይሄ መንገዳችሁ አቧራ ብቻ ነው ኤጭ":: ተሽከርካሪ ወንበሯን ወደእኔ ስታዞረው የተራቆተ ቀኝ ታፋዋ ስለተቀመጠች በጣም ገዝፎ ታየኝ፡፡ አይኔን ወደታች ስልከ ባለተረከዝ ጫማዋን እየወለወለች እንደነበር ገባኝ፡፡ ቀእጂ፣ በቀይ ክር ሃረግ የተጠለፈበት የእማማ መለኮት መሃረብ በከፊል አቧራ ለብሶ...

👍22
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
...የማሪየስ አባት በየሁለትና ሃ'ስት ወር ፓሪስ ከተማ እየመጣ ልጁ
ከአያቱ ጋር ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄድ ያየዋል:: የገባውን ቃል አፍርሶ ስለሆነ የሚያየው ሰው እንዳያየው ተጠንቅቆ ከአሳቻ ሥፍራ በመደበቅ ነበር ልጁን የሚያየው።
ማሪየስ እንደማንኛውም ልጅ ትምህርት ቤት ገብቶ ይማራል። የታወቀ ጎበዝ አስተማሪ ከቤት ተቀጥርለት ትምህርቱን በሚገባ ይከታተላል: ኮሌጅ ከጨረሰ በኋላ የሕግ ትምህርት ለመከታተል ከሕግ ትምህርት ቤት ገባ፡፡
ለአያቱ ብዙም ፍቅር የለውም:: የአያቱ፡ አሽሙርና ንቀት ልቡን አቁስሎታል፡፡የወላጅ አባቱ ጉዳይ ግን ዘወትር ያሳስበዋል:: ልጁ በተፈጥሮው ጨዋ ረጋ ያለ ፤ በራሱ የሚተማመን ኩሩ ልጅ ነበር፡፡ ከዚህም በላይ ፈሪሃ
እግዚአብሔር ያደረበት ነው፡፡ በ1827 ዓ.ም ማሪየስ የአሥራ ስምንት ዓመት ወጣት ነው:: አንድ ቀን ማታ አያቱ ከነበሩበት ክፍል ሲገባ ደብዳቤ በእጃቸው ይዘው ደረሰ፡፡
«ማሪየስ» አሉ መሴይ ጊልኖርማንድ ነገ ጠዋት ወደ ቬርኖን ትሄዳለህ፡፡»
«ለምን?» ሲል ማሪየስ ጠየቀ::
«አባትህን ለማየት::»
ማሪየስ ደነገጠ፡፡ አንድ ቀን ከአባቴ ጋር እገናኛለሁ የሚል ሀሳብ
በእውኑም ሆነ በሕልሙ አስቦት አያውቅም:: ምንም ነገር ከዚህ ይበልጥ አስደንጋጭና ያልተጠበቀ ሊሆንበት አይችልም ነበር፡፡
በሀገሪቱ ውስጥ ስለነበረው የፖለቲካ አቋም የተቃውሞ አሳብ
ሊኖረውም እያቱ እንደሚሉት አባቱ የቡርዥዋን አገዛዝ የሚቃወም
የማይረባ ወታደር» ነው:: በዚህ የተነሣ ለአባቱ የነበረው ፍቅር ይህን ያህል አልነበረም:: ከዚህም በላይ ወላጅ አባቱ እርሱን ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠቱ ጭካኔ ስለመሰለው ጠላው:: «አባቴ አይወደኝም» ሲል አምነ።
ይዞ በዚህ እንዳለ በዚያች ቅጽበት ያልጠበቀው ጥያቄ ከአያቱ ስለመጣዐበመደንገጡ የአዎንታም ሆነ የእምቢታ መልስ ለመስጠት አልቻልንም። አያቱ ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡
«አባትህ ታሟል መሰለኝ፤ ሊያይህ ይፈልጋል::
በሚቀጥለው ቀን ጀምበር ልትጠልቅ ስትል ማሪየስ ክሼርኖን ከተማ ደረሰ በመጀመሪያ ያገኘውን ሰው «የመሴይ ፓንት መርሲ ቤት የት እንደሆነ ያውቃሉ?ሲል ይጠይቃል::
ተጠያቂው ቤቱን ያውቅ ኖሮ አመላከተው:: ከቤቱ ሲደርስ በሩን
በመደብደብ አንኳኳ፡፡ አንዲት ሴት በሩን ከፈተችለት::
«መሴይ ፓንትመርሲ አሉ?» ሲል ማሪየስ ጠየቀ::
ሴትዮዋ ደንግጣ መልስ ሳትሰጠው ዝም ብላ ቆመች::
«አሉ እንዴ?» ሲል እንደገና ጠየቀ፡፡
ለመኖሩ ግምባርዋን ወደ ላይ በመግፋት አረጋገጠችለት::
«ላነጋግራቸው እችላለሁ?»
እንደማይቻል ጭንቅላትዋን በመነቅነቅ ገለጸችለት::
«እኔኮ ልጃቸው ነኝ» አለ ማሪየስ፡፡ «እንደምመጣ ደግሞ ስለሚያወቁ
ይጠብቁኛል፡፡»
«ከእንግዲህ ወዲያ አይጠብቅህም» አለች ሴትዮዋ፡፡
በዚህ ጊዜ አተኩሮ ሲመለከታት ቀደም ሲል ታለቅስ እንደነበር አወቀ።
ወደ አንድ ክፍል ባመለከተችው ጊዜ ወደ ክፍሉ ገባ፡፡ ክፍሉ
ውስጥ ሦስት ሰዎች ነበሩ፡፡ አንዱ ቆሞአል፤ ሌላው ተንበርክኮአል፡፡ ሦስተኛ ከመሬት ላይ ተንጋልሎ ተኝቷል፡፡ ተጋልሎ የተኛው አባቱ ነው::ከሁለቱ ሰዎች አንደኛው ሐኪም ሲሆን ሌላው ጸሉት የሚያደርሱ ቄስ ነበሩ፡፡
ኵሎኔሉ በጠና ከታመመ ሦስት ቀን ሆኖታል። ወዲያው ሕመሙ
እንደጀመረው ነበር ልጁ እንዲመጣለት በመልክተኛ ደብዳቤ ለመሴይ ጊልኖርማንድ የላከው:: ደብዳቤውን እንደላከ ሕመሙ እየጠናበት ሄደ።
ማሪየስ ቬርኖን በደረሰበት እለት ልጁ ከመድረሱ በፊት «ልጄ አልመጣም?
እሱ ካልመጣ እኔ ሄጄ እገናኘዋለሁ» እያለ ካልጋው ዘሎ ይወርዳል፡፡
ሠራተኞች ሊይዙት ቢሞክሩም ሊይዘት ባለመቻላቸው ከክፍሉ ወጥቶ ከበረዳ ሲደርስ ይወድቃል፡፡ እዚያው እንደወደቀ ሕይወቱ አለፈች፡፡
ሕይወቱ ከማለፉ በፊት ሐኪም እንዲመጣ ሰዎች ተራራጡ፡፡
ነገር ግን ሐኪሙ ከመድረሳቸው በፊት ኰሎኔሉ ሞተ:: ቄሱም ቢሆኑ ነፍሱ ከወጣ በኋላ እንጂ አስቀድመው አልደረሱም:: ልጁ ግን የደረሰው ዘግይቶ ነው::
ክፍሉ ውስጥ የነበረው መብራት ደብዛዛ ቢሆንም ከኩሎኔሉ ጉንጭ
ላይ ከመሞቱ በፊት እምባ መውረዱ ያስታውቃል፡፡ እንዲያውም እምባው
ጨርሶ አልደረቀም:፡ ያለቀሰው ልጁ በጊዜው ስላልደረሰለት ነበር፡፡
ማሪየስ ሰውዬውን አፍጥጦ ተመለከተው:: ለመጀመሪያና
ለመጨረሻ ጊዜ ነበር አባቱን ያየው:: የአባቱ ዓይኖች ሲገለጡም እርሱ ያያቸዋል እንጂ እነርሱ አያዩትም:: የአባቱ እጅ ተገልጦ ስለነበረ የጦር
ሜዳ ቁስሎቹ ጠባሳ በብዛት ይታያሉ፡፡ ከፊቱም ላይ ትልቅ ጠባሳ አለ፡፡
አባቱ እንደሆነና ሕይወቱ እንዳለፈች ማሪየስ አወቀ፡፡ በድንጋጤ ክው ስላለ
ከነበረበት አልተነቃነቀም:: ያዘነው ሀዘን ወደር አልነበረውም፡፡ እንኳን
የወለደው አባቱ ማንም ሰው ቢሆን እንደዚያ ተዘርሮና ሞቶ ቢያይ በጣም ማዘኑ አይቀርም።
ሀዘን፤ መሪር ሀዘን ከዚያች ክፍል ውስጥ ሰፍኖአል፡፡ ሠራተኛዋ
ከጥግ ቆማ ታነባዋለች፡፡ ቄሱ ይጸልያሉ፤ ግን እየጸለዩ ሲንሰቀሰቁ ይሰማል፡፡
ሐኪሙ ወዲያው፧ ወዲያው ዓይናቸውን በመሐረብ ይጠርጋሉ፡፡ ሬሳውም
ቢሆን የሚያለቅስ ይመስላል::
ሐኪሙ፤ ቄሱ፤ ሴትዬዋ ቃል ሳይተነፍሱ ማሪየስን አዩት:: ከውጭ የመጣ እንግዳ እሱ ብቻ ነው:: ማሪየስ ከነበረበት ትንሽ ነቅነቅ አለ። በጣም እፍረት ተሰማው፡፡ ያደረገውን ቆብ አውልቆ በእጅ ይዞት ስለነበር
ሳይታወቀው ከእጁ አምልጦ ከመሬት ወደቀ፡፡ ነገር ግን በጣም ከማዘኑ የተነሣ ቆቡን እንኳን ለመያዝ አቅም እንደሌለው ለማሳየት እንጂ እውነትም
አምልጦት አልነበረም::
ስለአባቱ የነበረውን አመለካከትና ግምት አስታውሶ ተጸጸተ::
መጸጸት ብቻ ሳይሆን ራሱን በጣም ነቀፈ:: ግን ጥፋቱ የእርሱ ነው? ኰሎኔሉ ወደኋላ የተወው ሀብት አልነበረም:: ከቤቱ ውስጥ የነበሩት እቃዎች ተሽጠው ለቀብሩ የወጣውን ወጪ እንኳን ለመሸፈን አልቻሉም፡፡ሠራተኛዋ አንዲት ወረቀት አግኝታ ለማሪየስ ሰጠችው:: ኩሎኔሉ ከመሞቱ
በፊት የጻፈው ማስታወሻ ሲሆን ቃሉም የሚከተለው ነው፡፡
«ለምወድህ ልጄ ፤ ዋተርሉ ጦር ሜዳ ላይ በተደረገው ጦርነት
ስለፈጸምኩት ጀብዱ የባሮንነት ማዕረግ ተሰጥቶኝ ነበር፡፡ ማዕረጉን በደሜ የዋጀሁት ስለሆነ ለልጄ ማውረስ እችላለሁ፡፡ እኔ አሁን ማዕረጉ ይገባዋል
ወይም አይገባውም ብዬ መናገር የለብኝም:: ከወረቀቱ ጀርባ ላይ ኲሉኔሉ የጻፈው ማስታወሻ ደግሞ ‹‹በዚሁ በዋተርሉ ጦርነት አንድ የሃምሣ አለቃ ሕይወቴን አድኖአል:: ስሙ ቴናድዬ ይባላል:: ከፓሪስ ከተማ ወጣ ብሎ
ሞንትፌርሜ ከተባለ ሥፍራ አንዲት አነስተኛ ሆቴል እንደነበረው አውቃለሁ:: ድንገት ካገኘኸው በተቻለህ እርሱን እርዳልኝ» የሚል ነበር፡፡
የአባቱ ፍቅር አስገድዶት ሳይሆን «የሞተን አክብር.» ብሎ በሚገፋፋን ውስጣዊ ኃይል ተመስጦ ማሪየስ ወረቀቱን በኃይል ጨመደደው::
ስለኩሎኔሉ ከዚያ በኋላ የታወቀ ነገር የለም:: ዩኒፎርሙንና
ጉራዴውን መሴይ ጊልኖርማንድ ለውራጅ እቃ ሸማች ሸጡት፡፡ ኰሎኔሉ የተከላቸውን አበቦች ጎረቤቱ ቀጥፈውና አትክልቱን አበላሽተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ድራሹን አጠፉት::
ማሪየስ ለሁለት ቀን እዚያው ቬርኖን ቆይቶ ከቀብሩ ሥነሥርዓት
በኋላ ወደ ፓሪስ ተመለሰ፡፡ ከዚያም የአባቱ መሞት ብዙም ሳይረብሸው ትምህርቱን ቀጠለ፡፡ ኵሎኔሉ በሞተ በሁለተኛው ቀን ተቀበረ፤ በሦስተኛ ቀን ተረሳ፡፡
ማሪየስ ለጥቂት ቀናት ከኮቱ ኮሌታ ላይ ጥቁር ጨርቅ አደረገ፡፡
የሀዘን ምልክት መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ ሌላ የተደረገ ነገር አልነበረም::

👍12