አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
479 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ፈንዲሻ_ሲቆሎት_ድምፅ #ሲሰሉት_ድምፅ


#በአሌክስ_አብርሃም


የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት አድርገን እንደተቀመጥን፤ ፕሮግራሙ ቶሎ እንዲያበቃ ሌላ የህሊና ጸሎት ጀመርኩ፡፡ ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን ለማከበር የክፍለ ከተማው የሴቶች ሊግ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ተገኝቻለሁ፡፡

ሊጉ በመሥሪያ ቤታችን በኩል ግዳጅ የተቀላቀለበት ጥሪ አቅርቦልን አለቃዬ ሂድ !" ስላለኝ
የቀበሌው አዳራሽ ውስጥ ተገኝቻለሁ። ያውም ቅዳሜን በሚያክል ቀን ከሰዓት!! ሰኔና ሰኞ
ገጥሞብኝ፡፡

አሁን ደግሞ የከፍለ ከተማችን የሕፃናትና ሴቶች ፑል ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ደርባቤ በላቸው
እንስራውን ሰብሮ ወሰዳት ልጅቱን የሚል ምርጥ ግጥም ያቀርቡልናል…" አለ ጉጉት የመሰለው መድረክ አስተዋዋቂ፡፡ አፉ ላይ የደቀነውን ማይክሮፎን ድምፅ ማጉላቱን የተጠራጠረ ይመስል በጣም እየጮኸ ነው የሚናገረው::

ቀጠለ "ወ/ሮ ደርባቤ ለክፍለ ከተማችን፣ ብሎም ለከተማችን፣ ብሎም ለኢትዮጵያ ሴቶች፣
ብሎም ለአፍሪካ ሴቶች ታላቅ ምሳሌ የሚሆኑ የዘርፈ ብዙ ሙያዎች፣ ተሰጥኦዎች፣ ትምህርቶች፣ስልጣኖች ባለቤት ናቸው” አለና፣ “…እስቲ ወ/ሮ ደርባቢን ወደ መድረክ…”

...ቿ..ቿ...ቿ..

ጥልፍ ቀሚስ የለበሱትና አንዳንድ ልማታዊ ዝግጅቶች ላይ ልማታዊ ግጥም በማቅረብ የሚታወቁት
ወ/ሮ ደርባቤ መድረክ ላይ ቆመው በፈገግታ ለሕዝቡ ጎንበስ ቀና እያሉ ምስጋና ይሁን ሰላምታ
ያለየለት ግማሽ ስግደት አቀረቡ፡፡ ግጥሙን ሊያቀርቡ ነው ብለን ፀጥ ስንል አስተዋዋቂው
ማዋደዱን ቀጠለ፣ “….ብታምኑም ባታምኑም ወ/ሮ ደርባቤ ይሄን ዝግጅት አስመልከቶ ግጥም
እንድትፅፍልን የነገርናት (አንች አላት) ትላንት ዘጠኝ ሰዓት ነው፡፡ ይገርማችኋል ሌሊቱን ስትፅፍ
አድራ ጧት ስደውልላት በስልክ ግጥሙን አነበበችልኝ…'ወይ መባረክ' ነው ያልኩት።( በሕዝብ
ስልክ ስምንት ገፅ ግጥም እያነበቡ አላየንም ባርኮት)፡፡

“...የግጥሙን ጥልቀት እና ውበት ራሳችሁ ታዘቡት እስቲ ለዚህች ብርቱ ሴት ሞቅ ያላ ጭብጨባ…" ብሎ ጭብጨባውን ራሱ ጀመረው፡፡ ማይኩን በሌላኛው እጁ ሲጠፈጥፈው አዳራሹ ጓጓጓ.. በሚል ልጆሮ የሚቀፍ እስቅያሚ ድምፅ ተሞላ፡፡ ከታዳሚው የተንቦጫረቀ ደካማ ጭብጨባ ጋር ተዳምሮ ጓጓታው በቀላል የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች የታጀበ የከባድ መሳሪያ ድምፅ ነበር የሚመስለው፡፡

ብዙው ታዳሚ በየእጁ ፈንዲሻ እና ለስላሳ ይዞ ስለነበረ ማጨብጨብ አልቻለም እንጂ በጭብጨባማ የእኛን ኮፍለ ከተማ ሴቶች ሊግ ጽሕፈት ቤት ሰራተኞች ማን ብሏቸው::በተለይ እጃቸው ባዶ ሲሆን የሚያጨበጭቡት ጭብጨባ ቢሾፍቱ ይሰማል፡፡ እጃቸው ባዶ ሲሆን ለዜና ያጨበጭባሉ፣ ለሪፖርት ያጨበጭባሉ፣ የቀበሌው ሊቀመንበር ሲያስነጥሱ ሁሉ
ያጨበጭባሉ፣ እጃቸው ሞላ ካለች ግን ጠቅላይ ሚንስትራችን ቢዘፍኑም አያጨበጭቡም
እንዳንዴ ታዲያ ጭብጨባዎች ሲቀንሱ ኢኮኖሚያችን ያደገ ይመስለኛል፡፡

ቀጠለ አስተዋዋቂው (ወ..ይ ዛሬ) "ወ/ሮ ደርባቤ.ገጣሚ ብቻ አይደሉም፤ የታሪክ ተመራማሪም
ናቸው፡፡ (ወ/ሮ ደርባቤ ቆመው በቁማቸው ገድላቸው ሲለፈፍ በፈገግታ ያዳምጣሉ )..ከፍተኛ
አድናቆት ያተረፈውንና የከፍላ ከተማችን የእድገት ማራቶን ሩጫ ከዘመነ ደርግ ውድቀት ቀኋላ' የሚለውን መጽሐፍ ጨምሮ አራት የግጥም መጻሕፍትን አሳትመዋል፤ ይሄን ያህል
ካልኩ እንዳላሰለቻችሁ ወደ ወ/ሮ ደርሳቤ ልምራችሁ...” ብሎ ማይኩን በአክብሮት ለሴትዬዋ
አቀበላት፡፡ (እፎይ! አንድ አዛ ለቀቅ ይላሱ እማማ ሩቅያ ሲተርቱ)

..ማይኩን ተቀብላ ጓ...ጓ አደረገችና (የፈረደበት ማይክ ተጠፍጥፎም፣ ያወሩትን ሁሉ ተቀብሎ አጉልቶም እሳዘነኝ)፡፡ እ..እኔ እንኳን የተባለውን ያህል ነኝ ብዬ አላምንም.፣ ምከንያቱም እንደ እኔ ዕድሉን ቢያገኙ እንኳን ኢትዮጵያን ዓለምን ጉድ የሚያስብሉ ሴቶች ከእናንተ መሀል አሉ ብዬ ስለማምን ነው…" አለች ወይዘሮ ደርባቤ፡፡

ጭብጨባ…! ቿቿቿቿቿቿቿቿቿ (ፈንዲሻው አለቀ ባአንዴ ጭብጨባው ደመቀኮ)
ከጎኔ የተቀመጠች ሴት “እውነት ነው" ብላ ጮኸት፡፡ (ዓለምን 'ጉድ' ከሚያስብሉት ሴቶች
መሐል እንዷ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ዞር ብዬ ሳያት በግራ እጇ ሞባይል ስልኳን፣ በቀኟ፣ መዳፏ
እስኪወጣጠር የዘገነችውን ፈንዲሻ ይዛ በስሜት ወደ መድረኩ እያየች ቁጭ ብድግ ትላለች፡፡
..ከፈንዲሻው ኮርሽም አደረገችለት፡፡)

ሴትዮዋ ግጥሟን ከማቅረቧ በፊት ሰላሳ ደቂቓ አወራች፡፡…እንዴት የወንዶችን ተፅዕኖ ተቋቁማ ታላቅ ገጣሚ' ለመሆን እንደበቃች፣ ሴቶች የርሷን ፈለግ ይዘው እንዲከተሏት፣(ብትወዱስ እኔን ምስሉ ዳርዳርታ)ይሄን ሁሉ አወራችና “እንዳላሰለቻትሁ” በማለት ወደ ግጥሟ ተሸጋገረች
(ገና ድሮ የሰለቸንውን !?)

ወደ መድረክ ስትወጣ መነፅሯኝ ቦታዋ ላይ ረስታው ስለነበር፣ " አቀብሉኝ”ስትሳቸው የእጅ ቦርሳዋን አራት ሰዎች ግራና ቀኝ ይዘው (ማሸርገዳቸው ስላበሳጨኝ የጨመርኩት ነው) አቀበሏት፡፡ቦርሳዋ ውስጥ አስር ደቂቃ ፈልጋ መነፅሯን ቤቷ መርሳቷን አረጋገጠች፡፡..እናም ወደ ብርሃኑ ቀርባ ግጥሟን ማንበብ ጀመረች፡፡

እንስራውን ሰብሮ ወሰዳት ልጅቱን(ርዕስ)
አረ አያ ደገፋው አንተ ትልቀ ሰው፣
አንዲት ፍሬዋን ልጅ ማስቸገርህን ተው!
ውሃ ልትቀዳ ወንዝ ስትሄድ፡
ቁመሽ አውሪኝ አልካት በግድ፣
ይሄ እልበቃ ብሎህ ሰው ጭር ሲልልህ
ሕፃኗን ደፈርካት እግዜር ይይልህ (ውይ ወንዶች አለች ከጎኔ ያለችዋ ባለ ፈንዲሻ)
ደሟን እያዘራች እቤቷ ስትደርስ፣
እንስራ ሰበርሽ ብለው ጎረፉት አያድርስ.
ደሞ በሌላ ቀን እንደገና አድብተህ..፣
አሁንም ደፈርካት አንተ ምን ዓይነት ሰው ነህ። ('በስማም ጭካኔ.ሌላዋ ሴት)

አዳራሹ ፀጥ ብሎ 'ግጥሙን' እያዳመጥን ድንገት ጎኔ ያለችው ሴት ጎርደምደምደም…ከሻሸሽ…
ስታደርግ ደንግጬ ዞሬ ተመለከትኳት፡፡ ተመስገን ፈንዲሻ እየበላች ነው፡፡…እኔማ በግጥሙ
ተመስጣ በስህተት ስልኳን ቆረጣጠመቻት ብዬ ነበር፡፡
ግጥሙ ለድፍን ሀያ ሰባት ደቂቃ ተነበበ፡፡ የግጥሙ የመጨረሻ ስንኞች

ፊስቱላ ተይዛ ስትንከራተት፣
ጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኛ አግኝታታ!
እዲሳባ በመኪና አመጣቻት.
መንግሥታችን በሠራው ዘመናዊ አስፓልት…?

አመሰግናለሁ !!

ቿቿቿቿቿቿቿቿቿ….(ታዳሚው ፈንዲሻውን ጨርሶ ነበር)

ለመውጣት ሳቆበቁብ አስተዋዋቂው እንዲህ አለ….

“ለሴቶች ቀን ያልሆነ ግጥም ለመቼ ይሆናል' በማለት ወይዘሪት ዘቢደር የወጣቶች ሊግ አትተባባሪ
ለግንቦት ሃያ አንብባው የተደነቀላትን 'ታታሪዋ ሥራ ፈጣሪ' የሚለውን ግጥምን ላቅርብ
ብላለችና እስቲ ወደ መድረክ…”

ተነስቼ ወጣሁ፡፡ ወደ ቤቴ ስሄድ ከኋላዬ የአስተዋዋቂው ድምፅ ይሰማኛል፡፡

"ወጣት ዘቢደር የእንስቷ ጣጣ የሚል በቅርቡ በታተመ የግጥም መድብሏ ከፍተኛ እውቅና
ያተረፈች ብርቱ ሴት ስትሆን...” እያለ ቀጠለ፡፡

ይሄ ቀበሌ ነዋሪው ሳይሰማ ማተሚያ ቤት ከፈተ እንዴ?.. እንዴት ነው ይሄ መድብል ማሳተም እንዲህ የቀሰለው ጎበዝ? ?!

አለቀ
👍24😁12👎1