አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
በሣቅሽልኝ ቁጥር ፣ ወደደችኝ ያልከት፣
ሣቅሽን በፍቅር ፣ እየተረጎምኩት፣
የምወቃቀሰው፣
የምቀዋውሰው፣
እስኪታዘበኝ ሰው።
ጅል አይደለሁ? መቼም
በሣቅሽልኝ ቁጥር ፣ ልቤን ስታሞኒ
ወንድ አይደለሁ? መቼም
ቀልዴን ጨረስኩብሽ ፣ ቤቴ ሳትኾኚ፤
ቀልዱን ለጨረሰ ፣ በወደድሽኝ ተስፋ
በእንባ ላይበተን ፣ከሳቅ የተሰፋ
ቆይ ምን ምን ሆኜ ጃል
በሴት ሣቅ ሞጃጃል?
የጥርስሽ ዘብ ሆኜ ፣ ሞቴ ተወጠነ፤
ቀልዴን መጨረሴሞ ፣ ራሱ ቀልድ ሆነ፤
ቀልድ የጠፋው አዳም፣
ቀልድ ያለቀበት ወንድ፣
ከታዘብሽ ከሰማሽ ፣ ወርደትን ሸክፎ
አትፍረጅ ግድ የለም
ለሴት ጨርሶት ነው ፣ በጥርሷ ተለክፎ፤


🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍19🥰9👏41
#የፍርምባ_ጦርነት


#በአሌክስ_አብርሃም


በንቃት ድንበር እየጠበቅኩ ነው ፤ ጠላት ፊት ለፊቴ አፍጥጧል፡፡ በማንኛውም ሰዓት ወደ እኔ
ሊንደረደር ይችላል፡፡ በመጠኑ ያደፈች ጅንስ ቁምጣዬን ከጉርድ ቀይ ካኒቴራ ጋር ለብሼ ነጠላ
ጫማዬ ከእግሬ ላይ ትበር ይመስል በእግሮቼ ጣቶች በመንከስ ከቤታችን በር ላይ ነው ያለሁት በእጄ ከአቅሜ በላይ የሆነ ብትር ይዣለሁ…የአያቴ የተሰበረ መቋሚያ ነው…መቋሚያውም
የተሰበረው እዚሁ በዓይነ ቁራኛ የምጠብቀው ጠላት ጀርባ ላይ ነበር :: አባቶቻችን ያወረሱንን
ጠላት አያቶቻችን ባወረሱን ሰባራ መቋሚያ እየተከላከልሁ ነው፡፡
ነገ በዓል ነው፡፡ ቤታችን ትንሽ ጠቦት ታርዶ ቤቱ ስጋ ስጋ ይሸታል፡፡ እናቴ ቤቱን እና ስጋውን
እንድጠብቅ ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥታኝ ገበያ ሄዳለች፡፡ በዋናነት የተሰጠኝ ተልዕኮ፣

1. ዶሮዎች የተሰጣውን የሽሮ ክክ እንዳይበትኑ

2. ሌባ ወደቤታችን እንዳይገባ

3ኛው እና ዋናው…“ገንባው እዚህች ግድም ድርሽ እንዳይል…” ነው፡፡ (እዚህች ግድም ድርሽ
እንዳይል ? ማን ? ገንባው !!)

ዶሮዎች ስጡ አካባቢ መለቃቀም ይችላሉ፡፡ ስጡን መብላትም ሆነ መበተን ግን የለባቸውም፣…
ሌባ በአጥራችን ጥግ መሄድ ይችላል፣ “ደህና አደራችሁ” ብሎም ማለፍ አይከለከልም፡፡ ሰላምታ የእግዜር ነው ትላለች እናቴ….ዕርግጥ ሲደጋግሙባት ሦስት ጊዜ እንዴት አደራችሁ አንዱ ለነገር ነው ትልና የእግዜር ሰላምታ መደጋገም ባለቤትነቱ የሰይጣን ሊሆን እንደሚችል በተዘዋዋሪ
ትናገራለች፡፡ እና ሌባው እስካልደጋገመ ድረስ ሰላም ብሎ ማለፍ ይችላል፡፡ ገንባው ግን
እዚህች ግድም ድርሽ ማለት የለበትም :: መላ ሰላም ማለት ሁሉ አይችልም፡፡ ሰላምታውን
ደገመም አልደገመም ፤ በቃ የበላይ ትዕዛዝ ነው !!
ገንባው በመንደራችን የሚኖር ባለቤት የሌለው ትልቅ ድመት ነው :: የበግ ግልገል የሚያክል
ዥጉርጕር ድመት ! እኔ ከተቀመጥኩበት አንድ አስራ አምስት ሜትር ራቅ ብሎ ከኋላው ሸብረክ በማለት ሁለት የፊት እግሮቹን ቀጥ አድርጎና ደረቱን ነፍቶ ጉርድ ፎቶ ሊነሳ ፎቶ አንሽ ፊት የተቀጠ ጎረምሳ መስሎ ቁሟል ፡፡

ተራ ድመት እንዳይመስላችሁ.. በሰፈራችን ውስጥ ያልገለበጠው ድስት፣ ያልከፈተው መሶብ፣
የመንጠቅ ሙከራ ያላደረገበት የስጋ ዘር የለም፡፡ መንደራችን ውስጥ ዶሮም ይሁን በግ ሲታረድ
ገንባውን ጠባቂ ቃፊር ማቆም ቸል የማይባል ጉዳይ ነው፡፡ “ገንባው ሲመቸው ቆሞ ከሚሄድ
በግ ሳንባ ይመነትፋል” ይሉታል..ሞኝ ሰፈርተኞች!! ታሪክ የሚተነፍሱበትን፣ የተዓማኝነት
ሳንባቸውን በቁማቸው እንደመነተፉቸው ማን በነገራቸው::

ገንባው ግዙፍ ቢሆንም የተጎሳቆለና በእድሜ የገፋ ድመት ነው:: ትንሽ ያነክሳል፡፡ በዛ ላይ
ዓንድ አይን የለውም፡፡ ጅራቱም ቆራጣ ነው፡፡ ሲጮኸ ድምፁ ያስፈራራል፡፡ እማማ ብርዘገን
ለፋሲካ የገነጣጠሏትን ዶሮ ላጥ አድርጎባቸው ሲሮጥ ጉሮሮውን በቢለዋ ወግተውት ነው ድምፁ
ተበላሽቶ የቀረው፡፡ የዛሬን አያድርገውና "ሚያውውውው" ሲል የአይጥ ሰራዊትን የሚያርድ፣
ሴት ድመቶችን የሚያማልል ድምፀ መረዋ ድመት ነበር ::

ድሮ የጋሽ ታምሩ ድመት ነበረ፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ፍርምባ የሚባል ነገር ሰረቀ ብለው አባ ታምሩ በአንካሴ ወጉት፡፡ ከዛ በኋላ እሳቸው ቤት መኖር አቆመ፡፡ ጨካኝ ናቸው:: ፍርምባ
ለምታክል ስጋ ብለው…ተወልዶ ካደገበት ቤት አባረሩት ፣ ያውም በአንካሴ ወግተው፡፡ እሳቸው
ግን፣ “ድመቱን ለፍርምባ ብዬ አልወጋሁትም” ብለው ዋሹ፡፡ ትልቅ ሰው ይዋሻል ? ደግሞ
እኮ ያኔ የሆነውን ሁሉ በዓይኔ በብረቱ አይቻለሁ…ማሪያምን አይቻለሁ !

ድመቱ ፍርምባውን በአፉ እንጠልጥሎ መሬት ለመሬት እየጎተተ እኛ ቤት ፊት ለፊት ወዳለው የውሃ መውረጃ ቱቦ ሲሮጥ አባ ታምሩ ልክ እንደኦሎምፒክ ተወዳዳሪ ግራ እጃቸውን ወደፊት ቀስረውና ጦር የጨበጠ ቀኝ እጃቸውን እስከቻሉት ድረስ ወደኋላ ለጥጠው በሰፋፊ ርምጃዎች
ተንደረደሩ 1..…2..3..ጦሩን ዥው ...አደረጉት፡፡ ድመቱ ሲሮጥ ጦሩ ሲከተለው፣ ጦሩ ህይወት ያለው ይመስል ነበር፡፡ ልክ ቱቦው ጫፍ ላይ ሲደርስ የድመቱ የኋላ እግር ታፋ ላይ ጦሩ ተቀበቀበ…አቤት ገንባው እንዴት አሰቃቂ ጩኽት እንደጮኸ ..እንዳንቡላንስ
ነው የጮኸው ሚያያያያያያያያያያያያያ…! ሲጮህ በአፉ የያዘው ፍርምሳ ወደቀ፡፡ አንድ ነጭ ያልቆሰለም ያልተወጋም ድመት ቀልቦት ወደቱቦው ውስጥ ጥልቅ አለ…!!

ጎረቤቱ ሁሉ፣ “አቤት አጨካከን እናትዬ የእግዜር ፍጡር ነው…ምን በደለ ?” እያለ ሲያጉረመርም
አባ ታምሩ ታሪክ ፈጠሩ፡፡ “የልጅ ልጄን ዓይኗን ሊያወጣት ነበር እኮ፣ ግዴላችሁም ይሄ ድመት
አውሬ ሆኗል...” በማለት የፍርምባውን ፀብ ትውልድ ለማዳን የተደረገ ጦርነት አስመሰሉት፡፡

የሚገርመኝ ታዲያ የመንደሩ ሰው ነው፡፡ በወሬ ወሬ “ ይሄ ድመት ምን ሆኖ ነው የሚያነክሰው?
ሲባል ፤ ..."ይሄ አውሬ ነው ጋሽ ታምሩን የልጅ ልጅ ዓይኗን ሊያወጣ ሲል አያቷ ሃይሌ
በአንካሴ ወጉት” ይላል :: ጭራሽ አይጦቻቸውን እያሳደደ እንዳልፈጀላቸው አውሬ የሚል
ስም ሰጡት ለዚህ ሚስኪን ገንባው !!

ትልልቆቹ ሰዎች ሁሉ፣ ፀጉራቸው የሸበተው አስተማሪው ሰውዬ (ትልቁ ግቢ ቤት ውስጥ የሚኖሩት
ሳይቀሩ ይሄን የፈጠራ ታሪክ ያወራሉ፡፡ታዲያ ስለ አገር ታሪክ እናውራ ሊሉ አላምናቸውም
ትላንት አፍንጫቸው ስር ያውም በጠራራ ፀሐይ የተፈፀመ የድመት ታሪክ ወጊው በፈለጉበት መንገድ
የተረኩ ሁሉ ስለአገሬ ታሪክ
እናውራህ ሲሉኝ እንዴት ልመናቸው? በመደራቸው
የድመት ታሪክ ያልታመኑ ሁሉ ስለአገራቸው አንበሶች ጀብዱ ሲደሰኩሩ እንዴት ልቤ እሺ ብሎ
ይቀበል ?ታሪክ ማውራት ታሪክ ከመስራት እኩል ጀግንነት እንደሚጠይቅ የገባኝ ያኔ ነው

ከዛን ቀን ጀምሮ ጦርነቶች ሁሉ የአደባባይ ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን ከኋላቸው ፍርምባ
የሚባል ስጋ ያለ ይመስለኛል፡፡ ገንባው አውሬ አይደለም፡፡ ገንባው የከለከሉትን የዕለት እንጀራ ነጥቆ “ተመስገን” የሚል ሚስኪን ድመት ነው፡፡ የዕለት እንጀራውን ቢነጥቃቸው የዘላለም
ስሙን ነጠቁት፡፡ “ያኔ ባንካሴ ሳንወጋው ኖሮ ትውልዱ ሁሉ እውር በሆነ እያሉ ከድመት
ጥፍር በባሰ የውሸት ጥፍራም ታሪከ ጭፍን ትውልድ ይፈጥራሉ፡፡

በሀሳብ ካቀረቀርኩበት ቀና ስል ገንባው የለም፡፡ “በስማም የት ሄደ ሰባራ መቋሚያዬን ወድሬ ወደ ጓዳ ሮጥኩ፡፡ መስኮቱ ገርበብ ብሏል፡፡ የጠቦቱ ታፋም ተሰቅሎ በነበረበት ቦታ የለም፡፡ .…ወይኔ ጉዴ ዛሬ እናቴ ገደለችኝ በቃ::

ሮጬ ወደ ውጭ ስወጣ ገንባው ታፋውን እየጎተተ ወደ ቱቦው ጥልቅ ሲል አየሁት፡፡

“ወይኔ አንካሴ ኖሮኝ በነበር..ይሄን አውሬ አልለቀውም ነበር" አልኩ ለራሴ፡፡


አለቀ
👍32👏4
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

....ካንድ አመት ተኩል በፊት፣ በክረምት፣ ቤቱ ማሞቂያ
ስላልነበረውና የክረምቱ ብርድ ስለበረታበት፣ ካፌ «ሴንትራ» ያድር
ነበር፡፡ አሁን ደሞ የኒኮል እምባ እያባረረው ካፈ «ሴንትራ»
ያድራል። ሲጋራ እያጨሰ ሲተክዝ ያድራል፡፡ ስለ ኢራን ሲያሰላስል
ያድራል። ከንቱ ሀሳብ ሲያወጣ ከንቱ ሀሳብ ሲያወርድ ከንቱ
ሌሊቶችን ያነጋል

ያን ሰሞን የሲልቪ መፅህፍ ለሶስተኛ ጊዜ እምቢ አለ።
ለሶስተኛ ጊዜ አባረረችኝ። እኔም መፃፍ አቃተኝ፡፡ እንዴትስ ላያቅተኝ ይችላል? ሲልቪ በጉልህ ሰማያዊ አይኖቿ ብርሀን ካላየችኝ፡
በውብ ሰፊ አፏ ሙቀት ካልሳመችኝ፣ ሰለስላሳ ገላዋ ካላቀፈችኝ እንዴት ልስራ እችላለሁ? መስራቱን ተውኩት
ዩኒቨርሲቲው አጠገብ ያለው መናፈሻ ውስጥ የኤክስ አዛውንት
በስጋው አቧራ ውስጥ “boule” ሲጫወቱ፡ በኮሚክ የደቡብ
ፈረንሳይኛቸው እየፎከሩ አንዷን የብረት ኳስ በሌላ እያነጣጠሩ
ወርውረው እየገጩ እየተሳደቡ ወይም እየተሳሳቁ ሲንጫጩ አያለሁ
ከዚያ ወደ ኩር ሚራቦ ሄጄ Monoprix የተባለው ትልቅ ሱቅ
ፊት ለፊት ከአንዱ ሽማግሌ ወይም ከአንዷ አሮጊት አጠገብ
አግድም ወምበር ላይ እቀመጥና፣ የኤክስ ሚስቶችና እናቶች
ከመንገዱ ወደ ሱቁ እየገቡ፣ ከውስጥ “Monoprix የሚል
የታተመባቸው የሞሉ ቡኒ የወረቀት ከረጢቶች ይዘው ወደ መንገዱ ሲጎርፉ አያለሁ፡፡ አስተያየታቸውም ሆነ አለባበሳቸው ወይም
አረማመዳቸው የጎረምሳ አይን አይስብም፡፡ ድሮ የጎረምሳ አይን
ስበው፣ ፍቅረኛ ይዘው፣ አግብተው ወልደው በቅቷቸዋል። አሁን
ወይም አርጅተዋል፣ ወይም ወፍረዋል ወይም ተዝረክርከዋል
ኮረዳዎቹ ጡታቸውን አሹለው! ዳሌያቸውን አሳብጠው፤
አይናቸውን ተኩለው፣ ፀጉራቸውን ተሰርተው ሽቶ አርከፍክፈው
እጅጌ የሌለው የበጋ ልብስ እየለበሱ፣ የብብታቸውን የተለያየ ከለር ፀጉር እያሳዩ፣ በጎረምሳ ታጅበው እየሳቁ እያወሩ በኩር ሚራቦ ይመላለሳሉ፡፡ ወይም ካፌዎቹ በር አጠገብ መንገዱ ላይ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው ግማሽ ጭናቸውን እያሳዩ ልዩ ልዩ ቀዝቃዛ
እየጠጡ ያወራሉ

አሮጊቶቹና ሽማግሌዎቹ አግድም ወምበር ላይ ፈዘው ቁጭ
ብለው ፀሀይ ይሞቃሉ። እኔም ቁጭ ብዬ ስለሲልቪ ስለባህራም፣ስለኒኮል፣ ስለሉልሰገድ፣ ስለአማንዳ እያሰብኩ አላፊ አግዳሚውን
እመለከታለህ
ሲልቪ መቼ መጥታ ወደ እቅፏ ትጠራኝ ይሆን? ጊዜው አላልፍልህ ይለኛል። ወደ ዘጠኝ ሰአት ላይ ሲኒማ " እገባለሁ።
ከሲኒማ ወጥቼ አንዱ ካፌ እሄድና ኣንድ ቢራ ጠጣለሁ

አንድ ቀን ወደ አስራ ሁለት ሰአት ላይ ነበር። ሰማዩ ቀልቶ፣
ፀሀይዋ እንደ ቀይ ብርቱካን ከምእራባዊው አድማስ በላይ
ተንጠልጥላለች፡ ግን ገና አትጠልቅም፡ እስከ ሁለት ሰአት ተንጠልጥላ ኤክስን ታስውባታለች
አየሩ የሚለሰልስበት ጊዜ፣ ብቸኝነት የሚፈለግበት ሰአት ነው፡
የትዝታ የትካዜ ሰአት
ካፈ ኒኮል ሄድኩና በረንዳው ላይ ፊቴን ወደ ፀሀይዋ አድርጌ ቁጭ ብዬ ቡና አይነቱን ቢራ አዘዝኩ፡፡ አሮጊቷ ቢራውን እያቀረቡልኝ
"Ça fait longtemps qu'on vous a pas vu monsieur" አሉኝ ብዙ ጊዜ ሆነን ካየኖዎት)
Oui, madame." አልኳቸው
ጓደኛዎትስ ደህና ናቸው?»
ደህና ነው። አገሩ ገብቷል
ትምህርታቸውን ጨረሱ?»
"Il était tres gentil, votre ami“ (በጣም ጥሩ ሰው ነበር ጓደኞት")
"Oui, madame"
አሮጊቷ ሄዱ፡፡ ብቻየን ቀረሁ፡፡ ከቀይዋ ፀሀይ ጋር፣ ከቡናማው
ቢራ ጋር። ከሉልሰገድ ትዝታ ጋር መንግስተ ሰማያት ማለት
ሴት በየዛፉ ስር፣ በየግድግዳው ጥግ የሚበቅልበት ማለት ነው
አየህ፣ የኒኮል ጡት እንደ ነጭ ውብ ሰማይ ነው፡፡ ሰማዩ መሀል ላይ በሮዝ ቀለም የተከበበች ወይን ጠጅ ጨረቃ አለች እኔ 'ምልህ! ከኒኮል ጋር አልጋ ላይ የወጣህ ጊዜ' በቅዱስ ብልግናዋ ትባርክሀለች
አይ አንተ ባላገር መባዳት ቁላን እምስ ውስጥ መክተት ይመስልሀል። ስንት ሳይንስና ስንት አርት እንዳለው ባወቅክ! ኒኮልን
በቀመስክ!.....
ፀሀይዋን ከለለኝ፡ ከሉልሰገድ ነጠለኝ፡፡ ቀና ብዬ አየሁት፡፡
ባህራም። አጠገቡ አንድ ቀጭን ባለመነፅር ሰውዬ ቆሟል። ቁመቱ
ከባህራም ትንሽ ይበልጣል። ያገሩ ልጅ ይመስላል ብድግ አልኩ፡፡ ሰውዬው ፈገግ አለ። ፈገግታው ደስ ይላል። የልጅ ፈገግታ ይመስላል። እጁን እየዘረጋ፣ በጣም ወፍራም በሆነ
ድምፅ በእንግሊዝኛ ከለንደን መምጣቴ ነው አለኝ
ጨበጥኩት፡፡ አጨባበጡ ልዩ ሆኖ ተሰማኝ። እጁ አይመችም።
በኋላ ሳየው መሀል ጣቱ ወደ አንድ በኩል ተጣሟል አይታጠፍም።ሌሎቹ ጣቶቼ ረዣዥም ቀጭን ቆንጆ ናቸው
እንኳን ደህና መጣህ!» አልኩት። ቁጭ አልን፡፡ባህራም ግን አልተቀመጠም። እኔን «ይሄ ማኑ ነው።የፈለግከውን ልትነግረው ትችላለህ» አለኝና ወደ ካፌው ውስጥ ገባ የማኑ ግምባር በጣም ጠባብ ነው: ወደኋላ የተበጠረው ፀጉሩ ከቅንድቦቹ ጋር ሊገናኝ ምን ያህል አይቀረው
ሳቅ አለ፡፡ የላይኛ የፊት ጥርሱ ሁለቱ የራሱ አለመሆኑን አስተዋልኩ ሰው ሰራሽ የአጥንት ጥርስ ነው። ጥያቄው አመለጠኝና

ጥርሶችህ የት ሄዱ?» አልኩት። የልጅ ሳቁን እየሳቀ ሰባራ
መሀል ጣቱን በግራ እጁ እያሻሸ
“አገሬ ትቻቸው መጣሁ:: እስር ቤት ውስጥ ኣለኝ፡፡ ወፍራም
ድምፁ ውስጥ መመረር አያሰማም፡፡ ሲስቅ ከመነፅሩ ኋላ አይኖቹ ጥፍት ይላሉ

«አህ! » አልኩት፡፡ ምን ማለቴ እንደሆነ እንጃ

«አሁን ጥርሶቼን ፍለጋ አገሬ መመለስ አለብኝ፡፡ ባህራም
ቢያፋልገኝ ቶሉ አገኛቸው ነበር። እሱ ግን ኣላግዝህም አለኝ»

«የጥርስ ኣዳኝ መሆን አልፈልግም አለ? »

“እህስ! ያውም የኔን የጓደኛውን ጥርሶች! አይገርምህም?»
በጣም እንጂ» ይሄ ምን አይነት ንግግር ነው? የሚል ሀሳብ
ጨረፈኝ

“ካንተ ጋር ብተዋወቅና በሰፊው ባወራ ደስ ይለኝ ነበር። ግን
እቸገራለሁ። ጥርሶቼ ናፍቀውኛል» አለ። ይስቃል
«ይገባኛል» አልኩት እየሳቅኩ
ባሀራም እንደሚያስፈልገኝስ ይገባሀል?»
“አዎን"
ሳቁ ከፊቱ ጠፋ፡፡ ጉንጮቹ ወደ ውስጥ የጎደጎዱ ናቸው፡፡ በብዙ
የሚመገብ አይመስልም። ቆንጆ ጣቶቹን አየሁዋቸው፤ ንፁህ ናቸው፤ የሲጋራ ልማድ አልተለጠፈባቸውም

አሮጊቷ ሲመጡ ማኑ ቀዝቃዛ ወተት አዘዘ፡፡ አንዲት ኮረዳ
ባጠገባችን ስታልፍ ሽቶዋ አንድ ጊዜ አወደን፡፡ ነጭ ሸሚዝና
ሰማያዊ ቁምጣ የለበሰው ቅርፅዋ አይን ይማርካል፡ የሚወዛወዝ ዳሌዋ ያስጎመጃል፡፡ ማኑ አይኑን ጣል አረገባት፡ ያኔውኑ ረሳት፡ ወደ
ካፌው ውስጥ እስክትገባ በአይኑ አልተከተላትም። ለምግብም፤
ለሲጋራም፣ ለመጠጥም፡ ለሴትም ጊዜ ያለው አይመስልም። ጊዜውን
በሙሉ ለሬቮሉሽኑ መድቧል? ስራውም፤ ጨዋታውም፣ እረፍቱም
ያው ሬቮሉሽን ይሆን?
እንዲህ አይነቶቹ ታጥቀው ሲነሱ፤ በሁለት አመት ውስጥ ሞስኮ፤ ፒኪንግ፣ ቡዳፔስት ወዘተርፈ እየዞሩ ሶስት ሚልዮን
ፓውንድና አስራ አምስት ሺ መትረየስ የሚያከማቹ ጎልማሶች
ታጥቀው ሲነሱ፡ እስር ቤት ውስጥ ጣታቸው ተሰብሮ ጥርሳቸው
የተሽረፈ ሰዎች ታጥቀው ሲነሱ፣ ለሴትም ለመጠጥም ጊዜ የሌላቸው ጎረምሶች ታጥቀው ሲነሱ፡ የኢራን ሻህ ለምን ያህል ጊዜ ዙፋኑ ላይ ሊቆይ ይችል ይሆን?

ማኑ እንዲህ አለኝ
👍311
«ባህራም እዚህ አገር ውስጥ ደምበኛ ስራ ለመያዝ የሚያበቃ
ትምህርት ወይም የሙያ ችሎታ የለውም፡፡ ግፋ ቢል አንድ ፋብሪካ
ውስጥ ይቀጠራል፡፡ ሲሰራ ውሉ ማታ ሲጠጣ ያመሻል። እኔ
ወደምሄድበት አብሮኝ ለመምጣት አለመቻሉ እየቆጨው ይሄዳል።
ከሁለት አመት በኋላ ዋና ሰካራም ይወጣዋል' ራሱን አይጠብቅም'
ማንንም አይጠቅም፡፡ ልጅቱም . ኒኮል ነው ስሟ? እሷም
ሲበላሽ እያየች ትንቀዋለች፡፡ አበላሸሁት ብላ ፀፀት ውስጥ መኖር ትጀምራለች። ትንሽ ቆይታ ፍታኝ ትለዋለች። ኑሮው በሙሉ ፈሩን ሳተ ማለት ነው

«ከኔ ጋር የመጣ እንደሆነ ግን »

«ይህን ሁሉ አውቃለሁ'ኮ» አልኩት

«እንግዲያው አግዘኛ! እሱንም እግዘው። በዚያውም በሀያ
ሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ታግዛለህ»
ላግዝህ መቻሌን እንዴት ታውቃለህ?» አልኩት
«ማወቁንማ አላውቅም፡፡ ምናልባት ብትችል ብዬ ነው " እንጂ።
አየህ! ባህራም ያስፈልገናል። በጣም ያስፈልገናል። ለሱም የኛ
አይነት ኑሮ ያስፈልገዋል»

«ላግዝህ የምችል አይመስለኝም። ግን አንድ እኔ የማውቀው
ነገር አለ። ምናልባት ሊረዳህ ይችል ይሆናል»
«ንገረኝ»
ግን እኔ ማወቄን ባህራም እንዳያውቅ»

«ግድ የለህም»

ስለኒኮል ስለሉልሰገድና ስለጀምሺድ የማውቀውን
አጫወትኩት። ጭንቅላቱን አስር ጊዜ ወደ ላይ ወደ ታች እየነቀነቀ
በፀጥታ አዳምጠኝ፡፡ ነግሬው ስጨርስ፡
“ገባኝ። እንኳን አንተን እገኘሁህ!> አለኝና ተነሳ። እኔም ተነሳሁ፡፡ ባህራም ከካፈው ውስጥ መጣ። ማኑ እየጨበጠኝ
(የተጣመመች ጣቱ እየቆረቆረችኝ
ልታግዘኝ ባለመቻልህ አዝናለሁ። ደህና ሁን አለኝ
ከባህራም ጋር ጎን ለጎን እየተራመዱ ከኔ ራቁ። ማኑ ትንሽ
ትንሽ ያነከሳል። ከበላያቸው ሰማዩ ደም ለብሷል ቅድም ወደ ካፌው የገባችው ባለቁምጣ ልጅ ወጣች።
ስትራመድ የውብ ቂጧን ከፍ ዝቅ በአይኔ ተከተልኩ። አይቼው
የማላውቀው የኒኮል ቂጥ ትዝ አለኝ። አየህ የኒኮል ቂጥ
እንድያው ለመቀመጫ የተፈጠረ ቂጥ እይደለም፡ የውበት ክምር
ነው። አንዳንዴ አልጋው ላይ በሆዷ እስተኛትና ያንን ቂጧን
አየዋለሁ' አየዋለሁ' አየዋለሁ! አይቼ አልጠግበውም፡፡ እያየሁት
በእጀ እንዲህ፣ እንዲህ' እያደረግኩ እዳብሰዋለሁ፡፡ ጎምበስ ብዬ
እንደ ቤተ ክርስትያን እስመዋለሁ። አይተህልኛል የኒኮልን
አይኖች? አረንጓዴ የውበት ሀይቆች የሀዘን ሀይቆች። አቤት
አይኖቿ ውስጥ ያለው ሀዘን ሲያምር. , ,

የኒኮል ውበት ለባህራምም እንዲህ ጎልቶ ይታየው ይሆን?
እግዲህ ከኒኮልና ከማኑ ማን ያሸንፍ ይሆን?

ለመሆኑ የዚህ የማኑ አለም ውስጡ እንዴት ያለ ይሆን?
የመጠጥ ሙቀትና የኮረዳ ትኩሳት የሌለበት አለም አይቀዘቅዝም?
ወይስ ቀዩ የሬቮሉሽን ኮከብ ዘለአለማዊው የሳጥናኤል ኮከብ ንፁህ ሙቀትና ውብ ትኩሳት ይሰጠው ይሆን? እነካስትሮ እነሆቺሚን እነማኦ በወጣትነታቸው እንደማኑ ነበሩ? ወይስ እንደ ባህራም ነበሩ?
፣ እንደ ባህራም ቢሆኑ ኖሮ እንደ ኒኮል ያለች ውብ ኮረዳ
ግማሽ መንገድ ላይ አታስቀራቸውም ነበር? ወይስ ግርማዊው
የሳጥናኤል ኮከብ በቀይ ብርሀኑ ከሩቅ ሲጠራህ፣ ከለስላሳ የሴት ልጅ ጭን ሙቀት ወጥተህም ቢሆን ጥሪውን ማክበርህ አይቀርም ይሆን? እስቲ እናያለን

ቀዩ ሰማይ እየጠቆረ ሄደ፡፡ ካፌው ውስጥ መብራት በራ። ሌላ
ቢራ ኣዘዝኩ፡፡ ስለኒኮል ማሰብ ጀመርኩ፡፡ በጭለማው ኣልጋ ውስጥ ተቃቅፈን፣ እጄን ሙታንቲዋ ጠርዝ ላይ ሳሳርፍ ትዝ አለኝ።የፍትወት ትኩሳት ጀመረኝ። ያን ሰሞን እርግዝናዋ አፋፍቷት፣
ከመቸም የበለጠ ታምራለች። በበጋው ሙቀት በዝግታ ስትራመድ የግብረ ስጋ እመቤት ትመስላለች፡፡ ባየኋት ቁጥር ፍትወት ያቁነጠንጠኛል። ለመሆኑ፣ ማኑን ስለነሉልሰገድ ያጫወትኩት ለምን ኖሯል? ባህራም ሄዶ የሚወደውን ሬቮሉሽን እንዲቆሰቁስ ነበር?
ወይስ ባህራም ሄዶልኝ እኔ ኒኮልን እንድቆሰቁስ ነበር? ወይስ
ሁለቱም ነበር?
ማታ አምስት ተኩል ላይ ከሲኒማ ስወጣ፣ ሲልቪን በሩ ላይ
አገኘሁዋት። ሳያት ከመጠን በላይ ደስ አለኝ፡፡ ፈራሁ። እቺን ልጅ
እንዴት አድርጌ ልለያት እችላለሁ? ፈገግታዋ ልቤን አሞቀው።
የተዘረጋ ቀኝ እጂን በግራ እጄ ተቀብዬ እያሻሽ እንዴት ታምሪያለሽ!» አልኳት
«ዛሬ ከኔ ጋር ማደር ትፈልጋለህ?»
«በጣም! ታድያ ግን እንቅልፍ አልፈልግም»
«ካልክስ እኔም አልፈልግም
መኪናዋ ጋራዥ ገብታ ስለነበረ፣ ወደ ቤቷ ስንራመድ፣
ትከሻዋን እያቀፍኩ
«እንዴት አገኘሽኝ?» አልኳት
እየሳቀች ሲቲ ሄጄ ኣጣሁህ፡፡ ስለዚህ ሲኒማ ቤት ሳይሆን
አይቀርም አልኩ፡፡ የኢጣልያ ፊልም የሚታይበት መሆን አለበት
አልኩ፡፡»
“A la Sherlock Holmes, quoi!” አልኳት (በሸርሎክ ሆምዝ ዘዴ ነዋ)
እየተራመድን፣ ዳሌዋ በአንዱ እርምጃ እየተጠጋኝ በሌላው
እየራቀኝ፡ እየራቀኝ እየተጠጋኝ እየራቀኝ፣ የጫማዋ ኳኳ
እየተሰማኝ
«ደስ ይለኛል» አለችኝ «እየሄድን እጅህን ራሴ ላይ ስታሳርፈው
በሀይል ደስ ይለኛል። እጅህ ከክፉ የሚከልለኝ ይመስለኛል፡
የሚባርከኝ ይመስለኛል፡፡ ካንተ ጋር ባልሆንኩ ጊዜ ሳስብህ፣
መጀመሪያ ትዝ የሚለኝ እጅህ ራሴ ላይ ሲያርፍ ነው»
እየተራመድን እጇን ሳምኩት
«አሁን የሳምከው የተራ ሰው እጅ እንዳይመስልህ» አለችኝ፣
ደራሲ እጅ ነው»
የውብ ደራሲ እጅ ነዋ ያውም!» አልኳት
«እውነቴን'ኮ ነው። ዛሬ ከኤዲስዮን ግራሴ (Editions Grasset) ደብዳቤ ደረሰኝ። አስራ ሶስቱ አንተ የመረጥካቸው አጫጭር ልቦለዶቼ Treize de Sylvie ተብለው ሊታተሙ ነው።»
«ውሽትሽን ነው!»
«መፅሀፉ ለሚመጣው ፀደይ ይወጣል»
«ማርሰይ እንሂድ?» አልኳት
«ለምን?»
«ይህን ግሩም ቀን ማክበር አለብን። ይገባሻል? እንግዲህ'ኮ
ስምሽ ከነፍራንስዋዝ ሳጋን፣ ከነኮሌት ጋር ሊጠራ ነው:: ቀስ ብሎ ከነፍሉብር፣ ከነፕሩስት፣ ከነማልሮ ጋር ይጠራል»
«ይመስልሀል?»
«እርግጠኛ ነኝ»
«እንዴት ጥሩ ነው!»
«ብቻ እንዳልኩሽ ነው:: የመሰለሽን ሁሉ ሳትፈሪ ፃፊ»
«አልፈራም። በጭራሽ አልፈራም»
«እንደሱ ነው! አሁን ማርሰይ እንሂድ?»
«የለም። ቤት እንሂድና በሩን ቆልፈን ራቁታችንን ወጥተን
እንዳንድ ቀኑ እንሰሳዎች እንሁን። በሀይል ናፍቀኸኛል።
«እኔም በሀይል ናፍቀሽኛል»
"Parole d'honneur?"
“Parole d'honneur! እጅሽን አምጪ እስቲ። አይታወቅሽም?»
«ይታወቀኛል። ለኔ ነው እንዲህ እሚዘለው?»
«ላንቺ አይደለም፡፡ ለእንትንሽ ነው»
ሳቀች፡ ቅንዝረኛ የጉሮሮ ሳቋን ሳቀች
ከኤክስ ወጣ እንዳልን
«ባህራም ሰውየውን የገደለው እዚችጋ ነበር» አለች። ትንሽ ሄድ
ካልን በኋላ «እኔ እዚችጋ ነበርኩ»
«ከዚያ ቤትሽ ወሰድሽው»
እየተጠጋችኝ «አዎን» አለች
«ከዚያስ?»
«ከዚያማ የሆነውን ነግሬህ የለ?»
«የነገርሽኝ በሙሉ እውነት ነበር?»
«አዎን»
«ባህራም ግን እኔ ነኝ በብዙ ተለማምጭ እሺ ያሰኘኋት እንጂ
እሷስ እምቢ ብላኝ ነበር» አለኝ
«ውሸቱን ነው»
«ለምን ይዋሻል?» አልኳት
«እንዳያጣላን ፈርቶ፡፡
«አንቺ አለመዋሸትሽን በምን አውቃለሁ?»
«እኔ ለምን እዋሻለሁ? ታውቀኝ የለ? ስንትና ስንት ጉድ
አውጥቼ ነግሬህ፣ እዚች ላይ ውሸት እነግርሀለሁ? ይመስልሀል?»
👍23
«ከዚያ በኋላ ተገናኝታችሁ ታውቃላችሁ?»
«የለም»
“ምነው? እምቢ አልሽው ወይስ እምቢ አለሽ?»
ሁለታችንም ተውነው»
«ለምን?»
«እሱ ላንተ ሲል ይመስለኛል»
«አንቺስ?»
“እኔም ላንተ ስል ይመስለኛል። ግን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡»
«እንዴት?»
«ተለውጫለሁ መሰለኝ። ለምሳሌ ከፓሪስ ከተመለስን ካንተ ሌላ
ማንም ወንድ አልሄድኩም፡፡ በፈት ግን ካንተ ሌላ በሳምንት ቢያንስ
አንድ ወንድ ካልቀመስኩ አይሆንልኝም ነበር። ፓሪስ ሆነን ሌሎቹ ጋ እየሳክከኝ የራስህ የብቻህ አደረግከኝ መሰለኝ
«ሌሉቹ ጋ እየሳክኩሽ የብቻዬ አደረግኩሽ?»
«አትሳቅ፡፡ እኔ የምሬን ነው:: በፊት፣ ሌላ ወንድ እያሰብኩ
እንዳቅፍህ ስለፈቀድክልኝ እንደ ልቤ አደረግኩትና ጠገብኩት።
አሁን ማንንም ሳቅፍ ሌላ ሰው ማሰብ የለብኝም፡፡ ድኛለሁ። ሙሉ
ነፃነት ስለሰጠኸኝ ነገሩን ጠገብኩትና ወጣልኝ፡፡ አሁንም እንደሱ አርገህል መሰለኝ።»
«እንዴት ማለት?»
«ፓሪስ ሆነን እንደ ልቤ ወንድ እንዳሳድድ ፈቀድክልኝ፡፡ ወንድ
እያቀያየርኩ እስኪደክሙኝ ተደስቼ ስመለስ፣ በሙሉ ልብህ
ተቀበልከኝ። ስትቀበለኝ ጊዚ ወንድ መለዋወጡ ክልክል መሆኑ ቀረ።
ስለዚህ ሰለቸኝ፣ ጠገብኩት፡፡ ተውኩት ይመስለኛል።»

«እርግጠኛ ነሽ?»

“እርግጠኛ ለመሆንማ ጊዜ ያስፈልገኛል። ግን የሚገርም ነገር
ነው። ሙሉ ነፃነት ስለሰጠኸኝ ታሰርኩ፡፡ አይታይህም?»
«መታሰርሽን ገና አላወቅነውም» አልኳት ለመቀለድ እየሞከርኩ
«እኔ አውቄዋለሁ፡፡ ለምሳሌ፡ ከዚህ በፊት መፅሀፌ " እምቢ
ሲለኝ፣ አንተን አባርሬ ምን ነበር የማረገው መሰለህ?»....

💫ይቀጥላል💫
👍221
#ተሸከመናታል !!


#በአሌክስ_አብርሃም


እናቴ ሁልጊዜ እንድናጠና ስትመክረን እንዲህ ትላለች፡-

እናንተ ልጆች አጥኑ፣ ተማሩ እባካችሁ ! ..እኔ ባለሙማሬ ነው ጉዴን ተሸክሜ የዋልኩት፤”
ማንበብም መፃፍም ስለማትችል ንግግሯ በቁጭት ነበር፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ይሄ ተሸክማ የዋለችው ጉድ ምን እንደሆነ ለማወቅ ጓጉቼ ጠየቅኳት፣
“ማሚ የምን ጉድ ነው ተሽከመሽ የዋልሽው ?”
አወራችኝ…


በደርግ ጊዜ መስከረም ሁለት ቀን ሕዝቡ በግድም ሆነ በውድ የድጋፍ ሰልፍ ይወጣ ነበር፡፡
መስከረም ሁለት ደርግ ንጉሱን ገልብጦ ሥልጣን የያዘበት ቀን ነው፡፡ በአጭር አገላለፅ መስከረም ሁለት የደርግ ግንቦት ሃያ ነበር፡፡ ያሁኑ እንኳን መቼ እንደሆነ እኔንጃ ካወቃቹ ንገሩኝ ታዲያ እናቴ በወቅቱ የነበረውን የግዳጅ ውትድርና በመፍራት
የመጀመሪያ ልጇን ወታደር ቤት እንዳይወስዱባት ከከተማው ወጣ ያለ አክስታችን ቤት ደብቃ፣
ሁለተኛ ልጇንም ገጠር እናቷ ጋር ልካ፣ ሦስተኛውን ልጇን አልጋ ስር አስቀምጣ፣ አባቴንም
“ታምሜያለሁ በል!' ብላው፣ እሷ ግን ነጭ ልብስ ለብሳ ሰልፍ ወጣች፡፡ ግዴታ ነዋ!

ቀበሌ ስትደርስ ሴት ወንዱ ያለውን ለብሶ ተሽቀርቅሮ፣ ቀበሌውም በተለያዩ መፈክሮችና በባለ ቀለም
መብራቶች አጊጦ ጠበቃት፡፡ የቀበሌው የኢሴማ ኃላፊ የነበረች ሴት በባለእጀታ የጣውላ ሰሌዳ ላይ ተፅፈው የተዘጋጁ በመቶ የሚቆጠሩ መፈክሮችን ለእናቴ እያሳየቻት፣“ምረጭና አንዱን ያዥ” አለቻት፡፡

እናቴ ቀለል ያለችና በደማቅ ቀይ ቀለም የተሽሞነሞነች መፈከር መርጣ አነሳችና ወደ ሰልፉ
ተቀላቀለች፡፡ ከለበሰችው የሚያምር የአበሻ ቀሚስ እና ከራሷም ቁንጅና ጋር ተዳምሮ የኦሎምፒክ መከፈቻ ላይ ኢትዮጵያ የሚል ምልክት ይዛ ሰልፉን የምትመራ ቆንጆ የአበሻ ሴት ትመስል ነበር፡፡

በዕለቱ መስቀል አደባባይ ላይ እናቴን በርካታ ሰዎች በግርምትና በአድናቆት ሲመለከቷት ዋሉ፡፡
ታዲያ በዚያ ሰሞን ማታ በቴሌቪዥን ደጋግመው እናቴን ከነመፈክሯ ያሳይዋት ጀመረ፡፡ ምን ይሄ ብቻ፣ ዓመቱን ሙሉ ፎከረውም እናቴን ማሳየት፣ ኢህአፓ ብለውም እናቴን፣ መኢሶን ብለውም እናቴን፣ ቀይ ሽብር ብለውም እናቴን፣ ጓድ ሊቀመንበር ተናግረው ሲያበቁም እናቴን ማሳየት፡፡

ጭራሽ ብሔራዊ ውትድርና ተብሎ ምድረ ወጣት ሲጋፈ ፣ የብሔራዊ ውትድርና አገር አቀፍ ዓርማ የእናቴ ፎቶ ሆኖ በየቦታው ተለጠፈ፡፡ በነጭ ልብስ ተውባ መፈክር ይዛ የቆመች እናቴ የብሔራዊ ውትድርና አገር አቅፍ አርማ ሆነች፡፡አንድ ጋዜጣ ላይ የእናቴ ፎቶ ስር እንዲህ የሚል ጽሑፍ ሰፍሮ ነበር፤

“አብዮታዊት ሶሻሊስት ኢትዮጵያ ነጭ ቀሚስ ለብሳ”

እናቴ ታዲያ መጀመሪያ አካባቢ በቴሌቪዥን በታየች ቁጥር በቁንጅናዋ የተመረጠች መስሏት
አባቴ ላይ በኩራት ትነሰነስበት ነበር፣ “ጓዳ ለጓዳ ስውል ቀላል ሰው አድርገኸኝ፣ እግሬ ወጣ ካለ አገር ነው የሚሰግድልኝ!” ትለዋለች ኮራ ብላ፡፡ አባቴ አፉን ሸርመም አድርጎ፣ “እዩኝ እዩኝ ማለት ደብቁኝ ደብቁኝ ያመጣል ” ይላታል::

“የቅናት ወሬ ነው ይሄ” ትልና ሆነ ብላ ለማበሳጨት በቴሌቪዥን ደጋግሞ የሚታየውን
ምስሏን አተኩራ እየተመለከተች፣
“አንዲት ፍሬ ልጅ እኮ ነኝ” ትላለች፡፡ አባባ ታዲያ “ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ…” ብሎ በረዥሙ ይሰቅና “ሰልፍ ላይማ መንግስትም አንድ ፍሬ ነኝ ነው የሚለው” ይላል፡፡
“ኤዲያ እንግዲህ ቦለቲካህን ልትጀምር ነው…” ብላ ወደ ጓዳዋ ትገባለች፡፡
ይሁንና እናቴ እየቆየች በቴሌቪዥን መታየቱ እና ስለ እርሷ መወራቱም ሲደጋገምባት ፈራች፡፡
በተለይም ጓድ መንግስቱ ኃይለማሪያም መስቀል አደባባይ በትልቁ የተሰቀለውን የእናቴን ፎቶ
ለተሰበሰበው ሕዝብ እያሳዩ በደም ፍላት፣
“እንደነዚህ ዓይነት ጀግና እናቶች ያሉባት አገር በማንም ወመኔ ከሃዲ ስትወረር እንዴት
ወንዶቿ አልጋ ስር ይደበቃሉ? እነዚህን ቦቅቧቃ ወንዳገረዶች ቂጣቸውን በሳንጃ…” እያሉ
ንግግር ካደረጉ በኋላ እናቴ ስጋቷ ከፍ አለ፡፡

ስጋቷን ለማስታገስ፣ “ኧረ ይሄ መፈክር ምንድን ነው የሚለው?” ብላ የተማረ ሰው ጠየቀች፡፡
መስከረም ሁለት ሰልፍ ላይ ይዛ ስለወጣችው መፈክር ተሸክማው ስለነበረው ጽሑፍ ሚያዚያ
ላይ “ምንድን ነው?” ብላ ጠየቀች፡፡ ሲነበብላት አመዷ ቡን አለ ፤ ብርክ ያዛት፡፡ መፈከሩ እንዲህ ነበር የሚለው

“የአብዮት ጠላቶችን ለማደባየት እኛ እናቶች ልጆቻችንን፣ ካስፈለገም ባሎቻችንን በደስታ እናዘምታለን!”

አለቀ
👍36😁189👏2
አትሮኖስ pinned «#ተሸከመናታል !! ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም እናቴ ሁልጊዜ እንድናጠና ስትመክረን እንዲህ ትላለች፡- እናንተ ልጆች አጥኑ፣ ተማሩ እባካችሁ ! ..እኔ ባለሙማሬ ነው ጉዴን ተሸክሜ የዋልኩት፤” ማንበብም መፃፍም ስለማትችል ንግግሯ በቁጭት ነበር፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ይሄ ተሸክማ የዋለችው ጉድ ምን እንደሆነ ለማወቅ ጓጉቼ ጠየቅኳት፣ “ማሚ የምን ጉድ ነው ተሽከመሽ የዋልሽው ?” አወራችኝ… በደርግ ጊዜ…»
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


....ከዚህ በፊት መፅሀፌ " እምቢ
ሲለኝ፣ አንተን አባርሬ ምን ነበር የማረገው መሰለህ?»

«ከመፅሀፍሽ ጋር የምትታገዪ ነበር የሚመስለኝ»

ተሳስተሀል። በየቀኑ ከምሳ በኋላ ማርሰይ እወርድና፡ ከሰአት
በኋላውን፣ ማታውን፣ አንድ አራት አምስት ወንድ ተኝቶኝ፣ ወደ
እኩለ ሌሊት ላይ ድክም ብሎኝ ወደ ኤክስ እመለሳለሁ:: በቀን
በቀኑ ይህን አረጋለሁ። አንድ ቀን ልሄድ ስዘጋጅ ፃፊ ፃፊ ይለኛል፡፡
መፃፍ እጀምራለሁ፡፡ ወንዶቹ በቁኝ ማለት ነው። በፊት እንዲህ ነበር
የማረገው

«አሁንስ?»

“አሁንም ላደርገው ተነሳሁ። ማርሰይ ወረድኩ። ግን ምንም
ሳላረግ ተመለስኩ።
«ወንዶችሽ እምቢ አሉሽ?»
በጉሮሮዋ ውስጥ ቅንዝረኛ ሳቋን እየሳቀች
“ትቀልዳለህ?» አለችኝ ተለውጬ ነው እንጂ። ወንድ መሄድ
ሱስ መሆኑ ቀረ»
«ሱስ መሆኑ ቀረ እንጂ መደረጉ ግን አልቀረም፣ እ?»
«መደረጉማ ለምን ይቀራል? የስሜት ደስታ አይደለም እንዴ?»
ይህን ጊዜ ቤቷ ልንደርስ አንድ መቶ ሜትር ያህል ቀርቶናል፡፡
ታሻሽው የነበረውን እጄን ለቀቀችና
ማን ይቅደም?» ብላ ትታኝ ሮጠች፡፡ እንዳልቀድማት ብዬ
ጫማዬን በሀይል እያስጮህኩ ተከተልኳት። እሷ እየጮኸች፣ እኔ
እየሳቅኩ ቤቷ ጋ ስንደርስ፣ በሩን ቀድማኝ በእጇ ነካችው
ቀደምኩህ!» አለችና በሩን ተደግፋ ቁና ቁና ስትተነፍስ፣
ጉንጮቿን በእጆቼ ይዤ ግምባሯን ሳምኳት እንደዚህ ለዋውጠኸኝ፣ በኋላ ያላንተ እንዳት ልሆን ነው?»
አለችኝ፡፡ በሀይል አሳዘነችኝ፡፡ ሆዴ ሽምቅቅ አለ፡፡ ወደኔ አስጠግቼ
ራሷን እየደባበስኩ ውይ የኔ ቆንጆ! እንድተውሽ አትፈልጊም እንዴ?» አልኳት
«አልፈልግም አልፈልግም አልፈልግም!» እያለች በጣም
ተጠጋችኝ፡ ራሷን አንገቴ ውስጥ ሸሸገች፡፡ እምባዋ አንገቴን ነካኝ
«እኔም ልተውሽ አልፈልግም፣ የኔ ቆንጆ፣ አልተውሽም፡፡
እስከመቼም አልተውሽም፡፡ ምንም ቢመጣ አልተውሽም» አልኳት
«እፈራለሁ፡፡ ካንት መለየቱን ሳስበው እፈራለሁ፡፡ አንተ አገርህ
ትሄድና፣ ከዚያ በኋላ አንገናኝም። እስከመቸም አላይህም፡፡ በቃ
ለዘለአለም?! ውይ! እቀፈኝ! እቀፈኝ!. . . መኖር እንዴት አስቸጋሪ
ነው!»
«አይዞሽ አንለያይም፣ የኔ ሲልቪ»
«አንለያይም?»
«አንለያይም። አይዞሽ አታስቢ። አሁን እንግባ»
አልጋ ውስጥ ላዬ ላይ አደረግኳትና፣ ጀርባዋንና አንገቷን
ጭንቅላቷን እየደባበስኩ ብዙ ጊዜ ከቆየን በኋላ፤
«አሁን ተለያይተን በወድያኛው ህይወት የምንገናኝ እንኳ
ቢሆን፣ ምናልባት እችለው ነበር» አለችኝ ግን መለያየቱ ለዘለአለም
ቢሆን፡ አንድ ጊዜ አይህና ከዚያ በኋላ ለዘለአለም ለዘለአለም
እስከመቸም የማንተያይ ስንሆን፣ በጣም ያስፈራኛል!» ብላ ተጠመጠመችብኝ

«አይዞሽ እንለያይም»
«አንለያይም?»
በሩ ተንኳኳ። ድንግጥ አለች
«አይዞሽ አይዞሽ»
በሩ እንደገና ተንኳኳ
«ማነው በይ» አልኳት
«ማነው?» አለች ጮክ ብላ
«ባህራም!»
ድንጋጤዋ ወደ ብሽቀት ተለወጠ። እየተነጫነጨች ተነስታ የሌሊት ካፖርቷን ራቁት ገላዋ ላይ ጣል አርጋመቀነቱን እየታጠ
ቀች ሄዳ በሩን ከፈተች
ባህራም «ይቅርታ በዚህ ሰአት ስላስቸገርኩ» እያለ ገባ። ጥቁር
ሙሉ ሱፍ ልብስ፣ ውሀ ሰማያዊ ሸሚዝ፣ ደማቅ ሰማያዊ ክራቫት::
ፂሙን ተላጭቶ፣ ፀጉሩን ወደ ኋላ አበጥሯል፡፡ ከጎንና ከጎን የበቀለው
ሽበት' የእርጅና ምልክት መሆኑ ቀርቶ ልዩ ጌጥ መስሏል፡፡ የድል
አድራጊነት ፈገግታ የሚጨፍርበት ፊቱ ወጣትነት ተላብሷል መጥቶ የተጋደምኩበት አልጋ አጠገብ ወምበር ላይ ሲቀመጥ
«እንዲህ ዘንጠህ የት ልትሄድ ነው? » አልኩት
ሲልቪ መጥታ ከጎኔ አልጋው ውስጥ ገባች
«እገሬ መግባቴ ነው» ከለ
“ልሰናበታችሁ ነው የመጣሁት»
«መሄድህ ነው በቃ?» አለችው ሲልቪ
“አዎን"
«ቆይ ዊስኪ ላምጣልህ» ብላ፣ ከአልጋው ወጥታ ወደ ወጥ ቤት
ሄደች፡፡ ቶሎ ከኪሱ አንድ ወረቀት አውጥቶ፣ ወምበር ላይ
የተሰቀለው ኮቴ ኪስ ውስጥ ከተተና፣ በሹክሹክታ
«ለብቻህ አንብበህ ቅደደው » አለኝ
"ላንተም ላምጣልህ? » አለች ከወጥ ቤቱ
«ለኔም ላንቺም አምጪ» አልኳት
ይዛ መጣች። ከልጋ ውስጥ ገባች። ዊስኪውን አነሳሁና ባሀራምን
«መልካም ጉዞ!» አልኩት
ፉት አልን
«ከመሄዴ በፊት ጥቂት ልነግርህ የሚገባኝ ነገር አለ» አለኝ።
ሲልቪ ትታን ልትሄድ ስትል «ካንቺ የሚደበቅ ያለበት አይደለም»
አላት
«እሺ» አልኩት
ብዙ ልነግርሀ በፈቀድኩ። ግን አብዛኛው የኢራን ኮሙኒስት
ፓርቲ ምስጢር ነው፡፡ አንተን አምንሀለሁ፡፡ ግን ፓርቲው
እንድነግርህ አይፈቅድልኝም»
«ይገባኛል፡፡ ምንም መናገር የለብህም»
«አውቃለሁ፡፡ ሁለት ነገር ብቻ በጠቅላላ ባጭሩ ልንገርህን
«ሁለት አመት ሙሉ በይሩት ነበርኩ፡፡ ግን ዩኒቨርሲቲው
ውስጥ የህክምና ትምህርት አልተማርኩም፡፡ ሌላ ስራ ነበረኝ። በቅርብ ምስራቅ ውስጥ ያሉትን የኢራን ኮሙኒስቶች ሳደራጅ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደሞ ከሻህ ሰላዮችና ከሲ.አይ.ኤ ጋር ረዥም ጦርነት ስናካሂድ ነበር። ሲ.አይ.ኤ ሊገድለኝ ሲሆን ጊዜ፣ ቱዴህ (የኢራን ኮሙኒስት ፓርቲ) እንድሸሽ አዘዘኝ። ወደ ኤክስ መጣሁ። እውነተኛ ስሜን
ልነግርህ አልችልም፡ ግን ባህራም አይደለም። ባሀራም ከፍሻር
በይሩት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ህክምና ይማር ነበር። በሱ ስም የውሽት ፓስፖርት አውጥቼ ነው፡፡

«ቤቶችህ ይህን ያውቃሉ?»
«ታላቅ ወንድሜ ያውቃል። ስም በቀየርኩ ቁጥር አዲስ ስሜን
በደብዳቤ ነግረዋለሁ፣ ከቤት ገንዘብ ሲመጣልኝ እሱ በአዲሱ ስሜ እየላከው ነው፡፡ እዚህ ላይ አንድ ነገር አለኝ የምነግርህ»
ምን?»
«ደጋግመህ መልክህ የኢራንን ሻህ ይመስላል ብለኸኛል።
እውነትክን ነው:: ሻህ የስጋ ዘመዴ ነው»
አጭር ዝምታ
«ላሳየኸኝ ጓደኝነትና ለዋልክልኝ ውለታ ላመሰግንህ አልችልም፡፡
ስለዚህ ሳላመሰግንህ መሄዴ ነው» አለኝና ተነሳ፡፡ በቁሙ ዊስኪውን ጨልጦ፣ ብርጭቆውን ኮሞዲኖ ላይ አኖረው:: ልሸኘው ካልጋ ልነሳ ስል
«አትነሳ። ማኑ እዚህ ውጭ ይጠብቀኛል። አብረኸኝ ብትመጣ
ያለቅስብኛል፡፡ እሱ ሁልጊዜ እንደተጠነቀቀ ነው። ወዴት በኩል
እንደምንሄድ አንተ'ንኳ እንድታውቅ አይፈልግም» ይስቃል፡፡ ማኑን
ስለሚወደው ይስቅበታል። ከማኑ ጋር ለመሆን በመቻሉ እጅግ ደስ
ብሉታል፡፡ ወጣትነቱን እንደገና አግኝቷል። እጄን ዘረጋሁ:: ጨበጠኝ። በኔ በኩል ተንጠራርቶ ሲልቪን ሳማት። ሊሄድ ወደ በሩ በኩል ከዞረ በኋላ
«ለመሆኑ አልኩት ዞረ። ፊቱ ላይ ፈገግታ የለም፡፡ የኢራንን ሻሀ ይመስላል።አፍንጫው ትልቅ ነው
«ለመጀመሪያ ጊዜ
ሳገኝህ ሶስት አሜሪካኖች
ይዘውህ ሊደበድቡህ መጀመራቸው ነበር» አልኩት
“A bas les Yankecs!” አለኝ እየሳቀ
“A bas!" አልኩት
ሰአቱን አየ፡፡ ቸኩሏል
“ሊደበድቡህ ይዘውህ ሳለ፣ ማኑ ያስተማረሀን የመከላከል ዘዴ
ለምን አልተጠቀምክበትምን» አልኩት
«ተማሪዎች ይሁኑ ወይ የሲ.አይ.ኤ ሰዎች ይሁኑ እርግጠኛ አልነበርኩም። ምናልባት እኔን ፍለጋ የመጡ የሲ.አይ.ኤ ሰዎች ቢሆኑስ? ያን አይነት ያምባጓሮ ዘዴ ማወቄን ካወቁ ባህራም አለመሆኔን ይጠረጥራሉ። ለዚህ ነው:: በሎ ደህና ሁኑ። ማኑ ይጠብቀኛል»
👍30🥰1👏1😁1
ደህና ሁን! አልነው ሁለታችንም
“Vive Etoile Rouge!” አለኝ (ቀዩ ኮከብ ለዘላለም ይኑር!) (Et
vive l'amitie!" (ጓደኝነትም ለዘላለም ይኑር)
“Vive!" አልኩት
ቀፈጣን እርምጃው በሩጋ ደረሰ። መለስ አለ። አሁንም የድል
አድራጊነት ፈገግታ ወጣት ፊቱ ላይ እየተጫወተ
«ሳልነግራችሁ ረስቼ» አለን ያን ጊዜ ሊገድለኝ ተገዝቶ
የመጣውን ማን እንዳስመጣው ታውቃላችሁ? ማንም
ቢያስመጣው የኔ ሞት በፋሺስቶቹ ላይ መላከኩ አይቀርም ነበር።
ይልቁንም አስመጪው ቀስ ብሎ ኮሙኒስቶቹ ተማሪዎች መካከል
ይህን ወሬ የነዛ እንደሆነ። ገባችሁ? በውነቱ ግን ነብሰ ገዳዩን ገዝቶ ያስመጣው አንድ የሻህ ሰላይ ነበር። ማን ይመስላችኋል?»

ማን?» አልነው ሁለታችንም
ደስ የሚል ወጣት ሳቁን ሳቀ
«ጀምሺድ ጓደኛችን የሻህ ሰላይ ነበር

እንዲህ ተቃቅፋችሁ ደስ ስትሉ! እንግዲህ ባሰብኳችሁ ቁጥር፣
እንዲህ ሆናችሁ ነው የምትታዩኝ፡፡ እንዴት ቆንጆ ነው! መቼም
እንደማትለያዩ ተስፋ አለኝ፡፡ አቤት እናንተ የምትወልዱት ልጅ!
ይታየኛል፡፡ እንደ ካስትሮ ያለ ጀግና ነው የሚሆነው»
እጁን አወዛወዘልን። ወደኛ እያየ በሩን ከፈተ። ወጣ፡፡ በሩን
ዘጋ። ከህይወታችን ወጣ። ሁለታችንም እንወደው ነበር። ግን ሲለየን በጣም አላዘንም። ብቻውን እንዳልሆነ እናውቃለን፣ ውጪ ጨለማው ውስጥ ጓደኛው እንደሚጠብቀው እናውቃለን። ሁለቱንም ሀያ ሚሊዮን ህዝብ እንደሚጠብቃቸው እናውቃለን። ይሂዱ፡፡መንገዳቸውን የሳጥናኤል ኮከብ ያብራላቸው!

እኔና ሲልቪ ባሀራም የወጣበትን በር በፀጥታ ስንመለከት ብዙ
ጊዜ ቆየን። ካጠገቤ ብድግ አለች፡፡ ከበላዬ ቆማ የሌሊት ካፖርቷን አውልቃ ጣለችው:: ራቁቷን ቆመች። እግሯን፣ ጉልበቷን፣ ጭኗን መሳም ጀመርኩ
ቆይ አለችና፣ ከአልጋው ወርዳ፣ ሀር ፀጉሯንና ውብ ወጣት
ዳሌዋን እያወዛወዘች ወደ በሩ ሄዳ ቆለፈችው:: ወደኔ ስትራመድ
የተገተሩት ወጣት ጡቶቿ ይንቀጠቀጣሉ። አንሶላውን ወደዚያ ገፋሁት። መጥታ ላዬ ላይ ወጣች። አበባ መሳይ ጡቷን አጎረሰችኝ፡፡

እጄን ወፍራም ዳሌዋ ላይ አኖርኩት። ሌሊቱ ተጀመረ ...

💫ይቀጥላል💫
👍23
#የአባዬ_ስልክ_እና_ባዮሎጂ


#በአሌክስ_አብርሃም


እንዲህ እንደዛሬው በየሰዉ ኪስ ሳይልከሰከስ በፊት ስልክ ተዓምራዊ የሀብት መለኪያ ነበር፡፡
አቤት ስልክ እንዴት እንደሚከበር ! እንደሚፈራ.! ያኔ ኔትወርክ እንጂ ስልክ አልነበረም፡፡ዛሬ ግን ስልክ እንጂ ኔትወርክ የለም።

እንግዲህ በሰፈራችን አንድ የቤት ስልክ ብቻ ነበረ ያለው፤ ስሙ ደግሞ “የአባዬ ስልክ”፤ ብዙው የሰፈር ሰው የእኔን እናት ጨምሮ በዚህ ስልክ ነበር የሚጠቀመው፤ ደግሞ ድምፁ የትናየት እንደሚሰማ…ኪሊሊሊሊሊሊሊሊ ሲል የመንደሩ ሰው ሁሉ ሥራ ያቆማል፡፡ ወጣቶች ፍቅረኞቻቸው የደወሉ መስሏቸው የያዙትን ሥራ እርግፍ አድርገው ጆሮና ልባቸውን ያቆማሉ፣እናቶች ሊጥም እያቦኩ ከሆነ ነጭ የቦክስ ጓንት ያጠለቁ መስለው ብቅ ይላሉ፡፡ የአባዬ የስልክ ድምጽ መቼም አይረሳኝም፡፡ አሁን የመጡ ስልኮች ቢዘፍኑ ሲንቀጠቀጡ የአባዬን ስልክ ድምፅ
ከአዕምሮዬ ሊፍቁት አልቻሉም፡፡

ስልኩ ሲጮኸ ልጆቻቸው አረብ አገር ያሉ እናቶች ልባቸው ይሰቀላል…፤ እናቴ ራሷ “ አቡቹ !
እስቲ እሱን ቆርቆሮ ቀንሰው” ትላለች፤ ቴፑን ማለቷ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄ ሁሉ ሰው እንዳቆበቆበ የአባዩ ልጅ ቡጡጡ በራቸው ላይ ትቆምና “እማማ ፋጤ ስልክ ! ከውጭ ነው ቶሎ በሉ!” ብላ ትጮሀለች፡፡ እማማ ፋጤ ወደ አባዬ ቤት ሲሮጡ ሌላው ጎረቤት ወደየስራው ይመለሳል፤ስልኩ በተደጋጋሚ የሚጮኸው ለበዓል አካባቢ ነው፤ በተለይ ለአዲስ ዓመት!

ቀላል ስልክ እንዳይመስላችሁ፤ በዚህ ስልክ ስንቱ ከውዱ ጋር አውግቷል፤ ስንቱ የውዱን
መርዶ ተረድቶ በድንጋጤ ስልኩ የተቀመጠበት ጠረንጴዛ ስር ተጠቅልሏል፤ ስንቱ ከጠፋ
ዘመዱ ተገናኝቷል፤ ስንቱስ ብር እንደተላከለት ሰምቶ ፈንጥዟል! ኧረ ስንቱ! ወደ አባዬ ቤት
ሲንደረደር እንቅፋት አንግሎት ባፍጢሙም የተተከለ፣ ጥፍሩ የተነቀለ…አለ፡፡

ለምሳሌ የአረጋሽ ጥፍር ተጣምሞ የቀረው ወደ አባዬ ቤት ስትሮጥ እንቅፋት አንግሏት ነው፡፡ አረጋሽ
ህመሙን ቻል አድርጋው ስልኳን እናገረችና ልክ ስልኩን ስትዘጋው፣ “ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ ብላ ጮኸች፡፡ መርዶ የሰማች ነበር የምትመስለው፡ በኋላ ሲጣራ ከስልኩ በፊት ለመታት
እንቅፋት ነው ያለቀሰችው፡፡ ጥፍሯ ግን ተጣምሞ ቀረ፡፡

ይሄ ስልክ ስልክ ብቻ አይደለም፣ ጩኸቱ የምስራች ነው! ጩኸቱ መርዶ ነው፡፡ ከመንደሩ
በላይ ያለው የጊዮርጊስ ቤተከርስቲያን ደውል ድምፅ የአባዬን ስልክ ጩኸት ያህል ግርማ ሞገስ የለውም
ለመንደርተኛው:: የኛን መንደር ሰዎች ወፍራም እንጀራ፣ ደንዳና ናፍቆትና ፍቅር በቀጭን የስልከ ሽቦ ውስጥ ተጉዞ የሚያርፍበት ኬላ የት ነው ሲሉን “የአባዩ ቤት እንል ነበር ።

ይህን ስልከ በጉጉት ከሚጠብቁ ቤተሰቦች መሃል የእኛ ቤተሰብ አንዱ ነበር፡፡ አባቴ ለሥራ ከእኛ
ርቆ ይኖር ስለነበር እኛ ልጆቹን የሚመከረው ለሚስቱም የሆድ የሆዱን የሚናገረው በአባዬ
ስልክ ነበር፡፡ እንደውም ግንባር ቀደሙ የእባዬ ስልክ ተጠቃሚ ቤተሰብ የእኛ ቤተሰብ ነበር
ማለት ይቻላል። ታዲያ አባቴ ለበዓል ሲመጣ ለበአል የሆነ ነገር ይዞ ስለሚመጣ ስልከ ስንጠራ
ቤተሰባዊ ቃና ባለው መንገድ ነው፡፡ “ስልክ” ብቻ አንባልም፤ “እንዳይቆጥርበት ፍጠኑ ጋሼ
ነው ? የሚል ማስጠንቀቂያም ይጨመርበታል፡፡

ለምሳሌ አባቴ ሲደውል እናቴ ከፊት፣ እህቴ ከኋላ፣ ወንድሜ ቀጥሎ፣ እኔ፣ ትንሽዋ እህቴ
ተግተልትለን እንሄዳለን፡፡ መጀመሪያ እናቴ ናት የምታናግረው፤ ድምጿን ቀንሳ ፊቷ በሃፍረት በናፍቆትና በፍቅር ተጥለቅልቆ ብዙ “አዎ” እና “አይይ!” የበዛበት ንግግር ታደርጋለች፡፡

አዎ!
አዎ!
አዎ!

አይይይይይ!

የአባዬ ስልክ ደግሞ ለክፋቱ ይጮሃል፤ በአሁኖቹ የእጅ ስልኮች ቋንቋ ላውድ ስፒከር ላይ
ያደረጉት ይመስላል፡፡
“እንደምነሽ ! …ምነው ድምፅሽ ጎረነነ ? አመመሽ እንዴ የኔ እናት ?” ይላል አባባ፤
“አይይይይ! ደህና ነኝ! " ትለለች እናቴ፤ አንዳንድ የፍቅር ነገርም ለለሚናገር ቶሎ መሰናበት
ትፈልጋለች፡፡

ቀጣይ ተረኛ ትልቅ እህቴ ናት፡፡

“ምን ልላከልሽ"

"ስኒከር ጫማ"

"እሺ"

"ነጭ"

"እሺ የኔ ማር" ድምፁ ውስጥ ናፍቆት አለ፡

"እንደባለፈው ሰፊ እንዳታመጣ ባባ"

"እሺ የኔ ቆንጆ"

ወንድሜ ይቀጥላል...

"ታኬታ ጫማ ባለ ብሉኑን"

“ባለ ቡሎን ጫማ አለ እንዴ ?" ይላል አባቴ በግርምት፡

"እንክት!"

እሽ እፈልጋለሁ ! አንተ ብቻ እናትህን እንዳታስቸግር፡ በደንብ ተማር!"

እኔ አባትህን አናግር ስባል አላናግርም፡ አብሬ ሮጬ አባዪ ቤት ድረስ ሄጄ ግን ብሞት አላናግርምፀ እናቴ ትበሳጫለች፡፡

“እሺ ምን ላምጣልህ ይልሃል" ትላለች በብስጭት፡

"ምንም!” እንባዬ ይመጣብኛል፡ አባቴን እወደዋለሁ፡ ግን በስልኮ አላናግረውም፡፡ ለምን ቢባል መልስ የለኝም፡፡ የተባለው ነገር ሁሉ ሲመጣ ግን እህቴ ያንን ሁሉ ማብራሪያ ሰጥታ ጫማዋ ይሰፋል ወይ ይጠባታል፡፡ ወንድሜ ባለብሎን ታኬታ አያመጣለትም፡ ኧረ እንዲያ የሚባል ጫማ የለም!" ይለዋል አባባ፡፡ እኔ ግን ምንም ሳልናገር ምርጥ ነገር ያመጣልኛል፡ አባቴ እኔን ራሴን እስኪመስለኝ ምርጫው ልክ ነው፡፡

እኛ ሰፈር እንዲት ሴት ጎረመሰች የምትባለው በአባዩ ስልክ ቤተሰብ ወይም ዘመድ ያልሆነ ወንድ ከደወለላት ነው፡፡ ሁሉም ሴቶች ለፍቅረኞቻቸው የአባዬን ስልክ ነው የሚሰጡት። ወንዶችም አልፎ አልፎ ይሰጣሉ ፡፡ ታዲያ አባዬ ቤት የተወራችው ነገር ስልኩ እንደ ሜጋፎን እየጮኸ ምስጢሩን ስለሚዘራው ጎረቤቱ ጋር ወዲያው ይደርሳል፡፡

“ሮማን የያዘችው ልጅ ሹፌር ነው መሰል ሁልጊዜ ከተለያየ እገር ነው የሚደውለው?

“አትይኝም!"

"ሙች!...አንዴ ከጅቡቲ፣ አንዴ ከሞያሌ፤ ቢጡ ሲያወራ ሰምታ ነው የነገረችኝ፡፡ ሲሉ የአባዬ
ልጅ ናት፡ ማን ከማን ጋር ምን አወራ የሚለውን ለመንደሩ የምታዳርሰው እሷ ናት፡፡

እንዲህ እየተባለ በቃ የተወራው የተደረገው ሁሉ ሰፈሩ ውስጥ ይናኛል፡፡ አንዲት ሴት ወይም
ወንድ በከባዬ ስልክ ካልተደወለለት ጉርምስናው እውቅና አያገኝም፡፡

አንዲት ሴት ስልክ ማናገር እና አለማናገሯ የፀባይ መለኪያ ሆኖ በመንደርተኛው ያስወቅሳታል፡፡
አልያም ያስመሰግናታል፡፡ “ውይ እሷ አንገቷን የደፋች፣ አባዩ ቤት አንድ ቀን ረግጣ አታውቅ
"ይባላል፡፡ ወይም “እች ልጅ የአባዩን ቤት አዘወተረች፤ መዘዟን እንዳትመዝ” ይባላል፡፡ ታዲያ
የአባዬን ቤት ከማይረግጡ 'ጨዋ ጎረምሶች መሃል አንዱ እኔ ነበርኩ፡፡ ስምንተኛ ክፍል ስደርስ
ግን ጨዋነቴ ተገሰሰ፡፡

የስምንተኛ ከፍል የባዮሎጂ አስተማሪያችን እትዬ መክሊት በጣም አይናፋር ሴት ነበረች፡፡
ምእራፍ ዘጠኝ የስነተዋልዶ አካላት የሚል ርእስ ላይ ስንደርስ ፊቷ ቀልቶ እያፈረች ስታስተምረን
ትዝ ይለኛል፡፡

“የስነ ተዋልዶ አካላት እንግዲህ..ያው…ወንድ እና ሴት ...ያው…” ጭንቅ ይላታል እትዬ መክሊት፣ እኛ ደግሞ ጆሮ ብቻ እንሆናለን፡፡ ስልሳ የምንሆን የእንድ ከፍል አጉል እድሜ ላይ ለምንገኝ ተማሪዎች ይሄ ጉዳይ የነፍስ ጉዳይ ነበር የምንጓጓላት፣ ለመስማት የምንሰስትለት፤ የስነተዋልዶ አካል ነገር ልባችንን ሰቅሎት፣ ትንፋሻችንን ውጠን እንቁለጨለጫለን፡፡ በክፍለ ጊዜው መርፈ ቢወድቅ ይሰማል ፀጥታው፡፡

“ውይ…ምነው ሁልጊዜ እንዲህ በትኩረት በተከታተላችሁ…! አያችሁ መማር ለራስ ነው፤ ትምህርት አገርን ይቀይራል፡፡ ያደጉት አገሮች ዝም ብለው አላደጉም፡፡ …ትምህርት…" ኤጭጭ እኛ ስለ ስነተዋልዶ አካላት ለመስማት ጓጉተን እትዬ ምክር…መክራ፣ መክራ ምከሯ ሲያልቅባት
👍35👏1
“ወንድ ልጅ ሲጎረምስ ፂም ማውጣት የተለያየ የሰውነት ክፍሉ ላይ ፀጉር ማብቀል.…እና ድምፁ
መጎርነን ይጀምራል ገባችሁ ?"
ስምረት እጇን ታወጣለች፣ “ፀጉር የሚወጣባቸው የተለያዩ አካላት የትኞቹ ናቸው ቲቸር?"

“ውይ አንች ደግሞ ፈተና ላይ የማይመጣ ነገር ምን አጠያየቀሽ ? ትልና ታፍራለች እትዬ፤ ሁላችንም እንስቃለን፡፡

መስፍን እጁን ያወጣል በተራው፣ የመስፍን ማውጣት ይገርመናል፤ በገመድ አስረውም
ቢጎትቱት እጁ የማይዘረጋ ልጅ ዛሬ እጁን ሲያወጣ ይገርመናል፡፡ ሽባ የተተረተረ ያህል በግርምት
እንመለከተዋለን፡፡

"ሴት ስትጎረምስስ ምን ምልክት ይታይባታል ?” ብሎ ይጠይቃል፤ ክፍሉ በሳቅና በጩኸት
ይደበላለቃል፡፡ እትዬ ታፍራለች፡፡
“ዝም በሉ ልክ ነው ጥያቄው የምን መገልፈጥ ነው፡፡ እስቲ ከእናንተ ይህን ጥያቄ የሚመልስ”
ትልና እኛኑ ታጋፍጠናለች፡፡ ቶማስ እጁን ያወጣል “ሴት ስትጎረምስ ያው…አለ አይደል..” ብሎ
ደረቱ ላይ እጆቹን ያሳርፍና እንደ ጡት ያጎብጣቸዋል፡፡ የከፍሉ ተማሪ በሳቅ ያውካካል፡፡

እትዬ በሃፍረት መግቢያው ይጠፋባታል፤ ድንገት አንድኛችንን ትጣራለች፡፡

"አብርሃም !

"አቤት!” እላለሁ በድንጋጤ፤"

“የሴት ልጅ ጉርምስና ምልክቶች ምን ምን ናቸው?”

በፍርሃት ላብ ላብ እያለኝ እየፈራሁ ሞከርኩ “ስ…..ልክ”

“ምን ”

“ስልክ ማለት የአባዬ ስልክ” ከፍሉ በሳቅ ተንጫጫ፤

“ጥያቄው አልገባህም." ብላ እንድቀመጥ ምልክት አሳየችኝ፡፡ “መልሱ ስላልገባት ጥያቄው
አልገባህም ትላለች እንዴ!”ብዬ አኮረፍኩ፡፡

አጎጠጎጤ፣ የድምፅ መስረቅረቅ፣ የዳሌ መስፋት እና የወር አበባ ማየት የሴት ልጅ ጉርምስና
ምልክቶች መሆናቸውን ባዮሎጂው ነገረን፡፡


ትዕግስት የምትባል የክላስ ልጅ የወደድኩት በዛው ሰሞን ነበር፡፡ ትዕግስት ቆንጆ፣ በነፃነት
ያደገች የሃብታም ልጅ ናት፡፡ ቤታቸው ስልክ አላቸው ፡፡ ብቸኛ ችግሯ አውርታ የማትጠግብ፣
ሳታቋርጥ ሙሉ ቀን የምታወራ ወሬኛ መሆኗ ነበር፡፡ ስታወራ በጣም ትጮሃለች፡፡ በቃ ቀስ
ብሎ ማውራት አትችልም ፡፡
ሁሉን ነገር ለመሞከር የቸኮለች ከመሆኗ ብዛት ጓደኛ እንሁን ብዬ በጠየቅኳት በቀጣዩ ቀን

ከክፍላችን ኋላ ተቀምጠን ጉንጬን ስማኝ አስነዘረችኝ፡፡ ከምር ነዘረኝ፡፡በቀጣዩ ሳምንት ከንፈሬን ስማ ንዝረቱን ከፍ አደረገችው በጣም ስለወደድኳት ከትምህርት ቤት ውጭ ላወራት ፈልጌ እኔም የአባዬን ስልክ ቁጥር ሰጠኋት።


አንድ ቀን ከወደ አባዬ ቤት ስሜ ተጠራ፣

"አብርሽ ስልክ"

“አቤት መጣሁ " አለቸ እናቴ!

"ጋሼ አይደለም አብርሽን የሚፈልግ ሌላ ሰው ነው አለች ሚጣ፡፡ ልላ ሰው የታወቀ ነው የታወቀ ነው ትርጉሙ

አባዬ ቤት ስደርስ የገጠመኝ ነገር አስደንጋጭ ነበር፡፡ ቀኑ የኪዳነምህረት ቀን ነበር፤ አባዬ ቤት ዝክር ተደርጎ ፀበል ጸዲቀ ስለነበር ከሩቅም ከቅርብም የተሰበሰበው ጎረቤትና ዘመድ አዝማድ ግጥም ብሎ ያውካካል፡፡ መራመጃ እንኳን አልነበረም፡፡ ግጥም ብሎ በሰው ተሞልቷል ቤቱ ደግሞ ለክፋቱ ስልኩ ስር ያለች ኩርሲ ላይ እማማ በላይነሽ የሚባሉት የሰፈራችን ነገረኛ ባልቴት ተቀምጠዋል) ገና ከመግባቴ ለከፉኝ፡፡

“አብቹ አንተም መጣህ ና እለፍ በዚህ!” አሉኝ፡

የደወለችው ትዕግስት ነበረች፡፡ በሆነ ነገር ተደባብረን ስለነበር አትደውልም ብዬ ነበር፡፡ ትዕግስት
በባህሪዋ ጫሂ ናት፡፡ እንክዋን የሚጮህ ስልከ ጋር ተዳምራ! የስልክ ንግግር ሳይሆን ለዛ ሁሉ
ስው አዋጅ የምታወጅ ነበር የምትመስለው፡፡

“አብርሽዬ?"

“አቤት" አልኩ ኮስተር ብዬ፡፡ ፀበል ቀማሹ ሁሉ ወሬ ቅመስ ተብሎ የተጠራ ይመስል ጭጭ ብሎ ጆሮውን ቀሰረ፡፡

“አብርሽ ምነው ጨዋ ሆንክ?” አለችኝ ትዕግስት፡፡ ልክ እንደ ራዲዮ ድራማ ፀበልተኛው ይሰማል፡፡

"እ"

“አብርሽ ችግር አለ..? ትላንት ከንፈርህን ስለሳምኩህ ደበርኩህ?”

እግዚኦኦኦኦኦኦኦኦ! ስልኩ አጠገብ የኪዳነ ምህረት ስዕል ተቀምጧል፤
ኪዳነምህረት የዚችን ልጅ አፍ ወይም የፀበልተኛውን ጆሮ ከዘጋሽልኝ የዛሬ ወር አንድ ፓኮ
ሻማ ብዩ ተሳልኩ፡፡ ስልኩን በጆሮዬ ለማፈን ወደ ጆሮዬ ጥብቅ እድርጌ አስጠጋሁት፡፡
ትዕግስት ትቀባጥራለች፡፡

አብርሽ እኔኮ ሴክስ እናድርግ ስትለኝ እንቢ ያልኩህ ፈርቼ ነው፤ በናትህ አብርሽ…እሽ በቃ
አርብ እክስቴ ቤት አድሬያለሁ ልበልና አንተም አመቻችተህ…”

እማማ በላይነሽ ወሬ እያዳመጡ ፉት ያሉት ጠላ ሰርናቸው ውስጥ ገብቶ ትን አላቸው፡፡ከኩርሲያቸው ላይ እስኪፈነገሉ ተንፈራፈሩ፡፡ “…ውሃ ውሃ ስጧቸው ! ጀርባቸውን ምቷቸው!” ይል ጀመረ ፀበልተኛው፡፡ እኔም የአባዬን ስልከ ዘግቼ ቀስ ብዬ ወጥቼ ተፈተለኩ፤ ወደ ቤቴ፡፡

"ወዲያው ሰፈሩ ውስጥ ዝናዬ በመወራቱ እናቴ አበደች"

“እንዴት ታዋርደኛለህ! እንዲህ ላገር መሳቂያ ታደርገኛለህ፣ አብረሃም?! ... አባቱ ሳይኖር ሴት
ቢያሳድገው ልታስብለኝ ....” እያለች እንባ እየተናነቃት ስትገስፀኝ በመሐሉ ቢጣ ተጣራች፡፡

“ሶስና…ሶሲ ..ስልክ ጋሼ አይደለም ! ሌላ ሰው ነው !፡፡ እናቴ በድንጋጤ ውሃ ሆነች፤ ሶስና
ትንሿ እህቴ ናት፡፡ የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ፤ ሶሲ ጎረመሰች ፤ በእህቴ መጎርመስ እኔ እና እናቴ
መደፈር ተሰማን፡፡ አናግራ ስትመለስ ልንወርድባት ተዘጋጀን!

አለቀ
👍36😁18🔥3
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

....ጧት ተነስቼ ቁርስ ከበላሁ በኋላ ከሲልቪ ቤት ወጥቼ ወደ
ሲቴ አመራሁ፡፡ ትላንት “ማታ ባህራም ኪሴ ውስጥ ያስቀመጠውን ወረቀት መንገድ ላይ አነበብኩት፡፡ ኒኮል የፃፈችለት ደብዳቤ ነው
«ውድ ባህራም
«እንዴት ልጀምር? አስቸጋሪ ነው። እወድሀለሁ፣ ከልቤ እወድሀለሁ። አሁን የምነግርህ ነገር የማልወድህ ሊያስመስለኝ
ይችላል። ግን እወድሀለሁ፤ ከልቤ አፈቅርሀለሁ
«ያለሬቮሉሽን መኖር አትችልም። ከኔ ጋር መኖር አትችልም። ስለዚህ እኔን ትተኸኝ መሄድ አለብህ
«እኔ ስለሪቮሉሽን በጭራሽ ሊገባኝ የማይችል ብዙ ብዙ ነገር
አለ። ለምሳሌ ደም ማፍሰስ። ብዙ ተከራክረንበታል፣ ታስታውሳለሁ::
ደጋግመህ አይገባሽም! ስለሪቮሉሽን በጭራሽ አይገቤሽም ብለኸኛል። እውነትክን ነው:: አይገባኝም። ግን በደምብ የገባኝ አንድ ነገር አለ። አንተ ያለ ሬቮሉሽንህ መኖር አትችልም። ስለዚህ መለያየት አለብን።

“ከዚህ ቀጥሎ የምነግርሀ ሊገባህ አይችልም። ስለዚህ እንዲገባህ ለማድረግ አትሞክር። ዝም ብለህ እመነው። ይኸው የማፈቅረው አንተን ነው። የተረገዘው ልጅ ግን ያንተ አይደለም። የሉልሰገድ ነው። ልነግርህ ሞክሬ ነበር። ብዙ ጊዜ ሞከርኩ፣ አቃተኝ፡፡ አሁንም
ቢሆን መነፅራሙ ጓደኛህ ባያግዘኝ ኖሮ አልችልም ነበር

አዝናለሁ:: ስላደረስኩብህ ሁሉ ችግር በጣም አዝናለሁ።
ብትችል በልብህ ይቅር በለኝ። ባትችል ጥላኝ፡፡ ብቻ ሂድና
ሬቮሉሽንህ ውስጥ ኑር። ደስታ ሊስጥህ የሚችል እሱ ብቻ ነው።
በሄድክበት ይቅናህ፡፡ ደህና ሁን።
ያንተ ኒኮል።
P S ልታገኘኝ አትሞክር። አታገኘኝም። ልሰናበትህ ባለመቻሌ አዝናለሁ። ግን ፊትህ ላይ ቂም ማየት እፈራለሁ። ደህና ሁን። ይህን ደብዳቢ ሶስት ጊዜ ደጋግሜ አነበብኩት፡፡ ኒኮል ለምን
ፃፈችው ይህን? ቀዳደድኩት። ቁርጥራጮቹን በተንኳቸው:: ሲቲ ሄጄ ገላዬን ታጥቤ፣ ልብሴን ቀይሬ ወደ ኒኮል ቤት ሄድኩ አልጋዋ ላይ ተጋድማ ሲጋራ እያጨሰች ሙዚቃ ትሰማለች ታቹን ነጭ ክሮሽ እንደ ሸማኔ ጥለት የከበበው ቡና አይነት ቀሚስ ለብሳለች። ስገባ ፈገግ እያለች
«እንኳን መጣህ! ጭር ብሎኝ ነበር» አለችኝ
ደህና ነሽ?
«ደህና ነኝ፡፡ በጣም ደህና ነኝ። ግን ሌላ ሰው ማየት
አልፈልግም። እባክህን በሩን ቆልፈው።
ቆልፌው ስመጣ፣ የተጋደመችበት አልጋ ላይ እንድቀሙጥ በእጇ አመለከተችኝ። ጥፍሮቿ ሀምራዊ ተቀብተው ያብለጨልጫሉ።
ተቀመጥኩ፣ አየሁዋት። በጣም የተለወጠች መሰለኝ፡፡ ከንፈሮቿ እንደ ጥፍርቿ ሀምራዊ መሳይ ቀለም ተቀብተዋል፡ ቅንድቦቿን ወደ ሰማያዊ የሚወስድ ጥቁር ቀለም አድምቋቸዋል፣ ከግምባሯ ንጣት ጋር ሲታዩ በጣም ያምራሉ። የአይኖቿ ቆዳ ልክ የአይኖቿን
የሚመስል ውሀ እረንጓዴ ኩል ተቀብቶ፣ አይኖቿ ውስጥ ተነክሮ
የወጣ ይመስላል። ከመጠን በላይ አምሮባታል። ከጥንታዊት
ግብፃዊት ጋር ያለሁ መሰለኝ። ፀጉሯ እንደ ድሮው አመዳም
አይደለም፡ ንፁህ ቡናማ ቀለም ተነክሯል
«ምን ነካሽ?» አልኳት
«ምነው?»
«እንደዚህ የምታምሪ አይመስለኝም ነበር»
"Merci
«እውነት ግን ምንድነው?» አልኳት
«እንደዚህ ነኝ፡፡ ሳዝን ሰው እንዲያውቅብኝ አልፈልግም። አሁን
ያዘንኩ እመስላለሁ?»
በጭራሽ
«ለዚህ ነው አይኔንም የተኳልኩት፣ ፀጉሬንም የተነከርኩት»
«አዝነሻል?»
«እንደ ዛሬም አዝኜ አላውቅ፡፡ ሲሄድ ደህና ዋል አለህ?»
«አዎን»
የፃፍኩለትን አሳየህ?»
«አዎን፡፡ ለምን ፃፍሽው?»
«እንዴት እንደፃፍኩት ልንገርህ?»
«ንገሪኝ»
«ከትላንት ወድያ ማታ፣ እንደዚህ ተጋድሜ ሙዚቃ ስሰማ፣
አንድ ሰው መጣ፡ መልኩ ሰው ይመስላል እንጂ እንደኔና እንዳንተ
ህዋሳቱ ውስጥ ደም እንደሚፈስ ልምልልህ አልችልም። ምናልባት
ከነሀስ የተሰራ ሰው ሊሆንም ይችላል። ረዥም ቀጭን ነው፡ መነፅር ያረጋል። ግምባር የለውም፡ ከአይኑ ቀጥሎ አናቱ ይመጣል፡፡ ድምፁ ወፍራም ከመሆኑ የተነሳ ከሆዱ እንጂ ከጉሮሮው የሚወጣ
አይመስልም»
«ጠልተሽዋል እ?»
«መጥላት አይደለም፡፡ ፈራሁት። ቀፈፈኝ፡፡ አየህ፣ ገባና
በወፍራም ድምፁ
ኮል ማለት እርስዎ ነዎት?» አለኝ
ነኝ» አልኩት
“ጥሩ። እኔ ከኢራን ኮሙኒስት ፓርቲ ተልኬ የመጣሁ ነኝ
«ታድያ እኔ ከኢራን ኮሙኒስት ፓርቲ ምን አለኝ?
«እርስዎ አይናገሩ፡፡ ጊዜ የለኝም» አለኝ፡፡ ድምፁ በጭራሽ
አይለዋወጥም፡፡ ምንም ነገር ሲናገር በዚያው በወፍራም ድምፅ ነው
“የኢራን ኮሙኒስት ፓርቲ ባህራምን ይፈልገዋል፡፡ በጣም
ይፈልገዋል። እኔን ፓርቲው ልኮኛል። ከትእዛዝ ጋር፡፡ ወያም
ባህራምን ይዘኸው ና፣ ወይም ገድለኸው ተመለስ ተብያለህ
ግደለው? ለምን?» አልኩት
ቀላል ምክንያት፡፡ የኛን ምስጢር ያውቃል፡፡ ምስጢራችንን
በሙሉ ያውቃል፡፡ ስለዚህ፣ ወይም ከኔ ጋር ይምጣል፡ ወይም
ይሞታል። ሌላ ምርጫ የለም፡፡ ግን አንድ ነገር አለ» አለኝ
ምን?»
ባህራም አልመጣም የሚለው በእርስዎ ምክንያት ነው:: እርስዎ
ባይኖሩ ይመጣል፡፡ ስለዚህ እርስዎ እንዳይኖሩ ማድረግ፡፡»
ሆዱ እየፈራ፤ «እንዴት?» አልኩት
«መግደል» አለኝና፣ ከኪሱ አንድ የታጠፈ ጩቤ አወጣ፡፡ ጫን
ሲለው ጩቤው እንደ ብልጭታ ክፍት አለ ሻህን ልግደለው!' አለኝና፤ ያንን የኢራን
ስእል አመለከተኝ፡፡ ባህራም ነው እዚያ የለጠፈው፡፡ ልተኛ ስልና ልነሳ ስል፣ ሻህ እንዲታየኝ እፈልጋለሁ ብሎ ሰቀለው::»
ግድግዳው ላይ የኢራን ሻህ የጦር ጠቅላይ አዛዥ የማእረግ
ልብሱን ለብሶ ቆሞ በከለር የተነሳው ትልቅ ፎቶ አለ
"ለምሳሌ ሻህ እርስዎ ነዎት። ጉሮሮውን ይመልከተቱ" አለና
ጩቤዋን ወረወራት። የሻህ ጉሮሮ ላይ ስክት አለች። ሰውየው ወደ
ስእሉ ሄዶ ጩቤውን ነቀለና አጥፎ ኪሱ ከተተ መንገድ ላይ እርስዎ ሲራመዱ ወይም ሲሮጡ እኔ በፈጣን መኪና እየሄድኩ ጩቤ ብወረውር፣ ጉሮሮዎትን እልስተውም፡፡ ገባዎት?» አለኝ። በድምፁ ሊያስፈራራኝ በጭራሽ አልሞከረም፡ ልክ የጂኦሜትሪ ፕሮብሌም እንደሚያስረዳኝ ያህል ነበር ገባኝ» አልኩት። እንደዚያን ጊዜ ፈርቼ አላውቅም
«ለባህራም ይንገሩት»
«ምን ብዩ?»
«ያረገዝኩት ካንተ አይደለም፣ ይበሉት
«ታድያ ከማን ነው ልበለው?»
« እንደፈለጉ። ለምሳሌ እጀምሺድ ወይም ከሉልሰገድ ነው
ሊሉት ይችላሉ፡፡ እነሱን ሊጠይቃቸው አይችልም»
«እሺ» አልኩና ደብዳቤውን ፃፈኩ። አጣጥፎ ኪሱ ሲከተው
«ባሀራም ይህንን ካነበበ በኋላም ከርስዎ ጋር መሄድ ባይፈቅድስ?»
አልኩት
«እምቢ አይልም»
«ቢልስ?»
«እገድለዋለሁ። ደህና እደሩ» አለኝና ወጣ። እንደሱ ያለ
ከሰውነት የራቀ ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም
ኒኮል ዝም አለች፡፡ ዝም ብዬ እየኋት። በጣም ታምራለች።
ውሀ እረንጓዴ ኩሏና ሀምራዊ የከንፈር ቀለሟ የፈርኦን ዘመን
ግብፃዊት አስመስሏታል። ሳቅ አለች
«ምነው ትኩር ብለህ ታየኛለህ?»
«አማርሽኝ» አልኳት። ውስጡን ደነገጥኩ። እንደዚህ ለማለት
አላሰብኩም ነበር። ውሀ አረንጓዴ ቆዳ ሽፍን ግልጥ በሚያደርጋቸው
ውህ እረንጓዴ እይኖቿ አየችኝ፡፡ ሀምራዊ ከናፍሯ በፈገግታ
ተላቀቁ። እጄን ጉልበቷ ላይ አሳረፍኩ፣ አልከለከለችኝም
«ጫማዬን ላወልቅ ነው» አልኳት
👍285
ኮቴንም ኣውልቄ አጠገቧ ተጋደምኩና እጄን አንተራስኳት
“ደራሲ መሆን እንደምፈልግ ታውቂ የለ?» አልኳት
«አውቃለሁ፡፡ ልትጠይቀኝ " ምትፈልገው ጉዳይ እንዳለም
አውቃለሁ»
“ታውቂያለሽ?
«አዎን፡፡ ለምሳሌ፣ ልጄ ምን ይሆናል? አይደለም አንዱ
ጥያቄህ?»
«ካልፈለግሽ አትመልሺ»
“ብነግርህ ግድ የለኝም። መሀን ለሆኑ ሰዎች አራስ ልጆችን
የሚሰጥ ድርጅት አለ። ወልጄ ልጄን ለድርጅቱ አስረክባለሁ፡፡»
«ለምን አላስወረድሽውም?
«ለምን ገድለዋለሁ? ቢኖር እይሻለውም? እኔኮ በህይወት
አምናለሁ፡፡ አንተስ አታምንም?»
«አምናለሁ፡፡ በህይወትም በውበትም አምናለሁ» አልኩና
ጉንጫን ሳምኳት። ራሴን በለስላሳው ወደዚያ እየገፋች
«ቆይ» አለችኝ
«ምነው?»
«ሌላ ነገር እያሰቡ ሲስሙኝ አይመቸኝም፡፡ መጀመሪያ ጥያቄህን
ሁሉ ልመልስልህ»
«እሺ»
«የሚቀጥለው ጥያቄሀ፣ ልጁ የማን ነው? ነው:: እርግጠኛ
አይደለሁም። የጀምሺድ ወይም የባህራም ሊሆን ይችላል። ግን
የሉልሰገድ አይመስለኝም፡፡ የመጨረሻ ጥያቄ፣ ባህራምን እወደዋለሁ
ወይ? አዎን 'ወደዋለሁ። ከልቤ 'ወደዋለሁ፣ አፈቅረዋለሁ። እንግዲያው ለምን ጀምሺድንና ሉልሰገድን ጠቀለልኳቸው? አላውቅም። ግን
አይቆጨኝም፡፡ የተጋደሉት በኔ ምክንያት ይመስለኛል። አሳዘኑኝ።
በወጣትነታቸው በመቀጨታቸው አዘንኩላቸው:: ግን እዚህ ውስጥ
እኔ ጥፋተኛ ነኝ ብዬ አንድ ጊዜ እንኳ አምኜ አላውቅም፡፡ ገና ለገና
ሁለቱ ተኝተውኛል ተብሎ፣ ከዚህ በኋላ፣ እኔን ነፃነትና ምርጫ
እንዳላት ሴት ሳይሆን፣ እንደ ንብረት ቆጥረው ተጣሉብኝ፡፡ ስለዚህ የራሳቸው ጉዳይ ነው»
አየኋት። ስለምንም ግድ የሌላት፣ በጣም ጠንካራ፣ በጣም ቆንጆ
ሴት ናት። በሀይል ደስ አለችኝ።
“Tuten fouts, eh?” አልኳት ደንታ የለሽም፣ እ?»)
“Epédument?” (ብጭራሽ» አለችና፣ እንደተጋደምኩ ብድግ
ብላ፣ በክርኗ ትራሱ ላይ ተደግፋ ወደታች እየችኝ። ጎምበስ ብላ
አይኖቼን ተራ በተራ ሳመቻቸው። ፈገግ እያለች
«ስላንተም ቢሆን ደንታ የለኝም፡፡ ስለኔ ምንም ብታስብ የራስህ
ጉዳይ ነው:: ብቻ ደስ ትለኛለህ፡፡ በሀይል ደስ ትለኛለህ፡፡ እንዴት
ቆንጆ ነህ!» አለችና ጎምበስ ብላ ታምራዊ ኣፏን ኣፌ ላይ ደቀነች፡፡
አቀፍኳት። ውብ ብልግና ተጀመረ
ያቺ ልጅ መንግስተ ሰማያትን እጣጥፋ ጠቅላ በጭኖቿ
ውስጥ ደብቃ ነው " ምትዞረው ልልህ እችላለሁ . . . እኔ ምለው፡
እንደ ኒኮል ያለች ሴት እየተኙ ሁለት አመት ኖረው ቢሞቱ
ምናለበት? ቢሰነብቱ ትርፉ ማርጀት አይደለም? እርጅና መጥቶ፣ አጥንቶቼን አኮራምቶ፣ ጅማቶቼን ሽምቅቆ፣ ቆዳዬን አጨማዶ፣ አይኔን አጨናብሶ፣ ጠረኔን ሰርቆ በቁሜ በኤክስ አሮጊቶችና ሽማግሌዎች ሽታ ከሚገንዘኝ፣ ኒኮልዬ ጭኖች መሀል ገብቼ ሙቀቱ ውስጥ ቀልጬ፣ ርጥበቱ ውስጥ ሟሙቼ ጥፍት ብል እመርጣለሁ።
የሰው ልጅ መጨረሻውን መምረጥ ቢችል' መጨረሻዬ ኒኮል ውስጥ ቢሆንልኝ እመርጣለሁ. . .»

💫አለቀ💫

ውድ አንባብያን ሆይ
ይህን በነፃነት ተኑሮ፣በነፃነት ተፅፎ፣በነፃነት የታተመውን ልብ ወለድ እየተዝናናችሁ አልፎ አልፎም እየሳቃችሁ እንዳነበባችሁት በመተማመን እጆቼን(ሁለቱንም) በቡራኬ እየዘረጋሁ
"ኑሩ በሰላም "

ስብሐት ለአብ
👍25🥰1
አትሮኖስ pinned «#የአባዬ_ስልክ_እና_ባዮሎጂ ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም እንዲህ እንደዛሬው በየሰዉ ኪስ ሳይልከሰከስ በፊት ስልክ ተዓምራዊ የሀብት መለኪያ ነበር፡፡ አቤት ስልክ እንዴት እንደሚከበር ! እንደሚፈራ.! ያኔ ኔትወርክ እንጂ ስልክ አልነበረም፡፡ዛሬ ግን ስልክ እንጂ ኔትወርክ የለም። እንግዲህ በሰፈራችን አንድ የቤት ስልክ ብቻ ነበረ ያለው፤ ስሙ ደግሞ “የአባዬ ስልክ”፤ ብዙው የሰፈር ሰው የእኔን እናት…»
#ትንሽ_ወደግራ_ዘምበል...
:
:
#በአሌክስ_አብርሃም

አባቴ ሲራመድ ትንሽ አንከስ ይላል፡፡ ያን ያህል እንኳን አይደለም፡፡ ወታደር ስለነበር ታፋው አካባቢ ጥይት ጨረፍ አድርጋው ነው፡፡ (ለጡረታ ሰበብ ትሆን ዘንድ ከእግዜር የተተኮሰች
ጥይት ይላታል አባቴ ራሱ) !! አንድ አራት እርምጃዎቹ ኖርማል ይሆኑና አምስተኛዋ ላይ
ትንሽ ወደግራ ዘምበል ይላል እንደ እኛ ታሪክ !! የራሳችን ፊደል፣ የራሳችን ቋንቋ፣ አድዋ፣መቅድላ፣ ድርቅ አንከስ ወደ ግራ !! ይሄው ነው !

ታዲያ አባቴን ጥምድ አድርጎ የያዘው የግራ እግሩን በፈንጅ ያጣ ወታደር ጎረቤት አለን ፣ “ለዚች
በየአምስት እርምጃው ለምትከሰት እንከሻው የአካል ጉዳተኛ ተብሎ ጡረታ ይበላል፡፡ ይሄ ለጳግሜ ከመስከረም እኩል ደመወዝ ከመክፈል አይተናነስም አይ እች አገር ! አይ ታሪክ " እያለ ያሸሙረዋል በክራንቹ መሬት እየቆረቆረ…!!

የአባቴን እግር የጨረፈችው ጥይት ለአባቴ ግንባር የተተኮሰች መሆኗን ዘንግቶ፡፡ የተጫረ እግር
ከተቆረጠ እግር እያወዳደረ በጉድለት ቁና የታሪክ ገለባውን ሊሰፍር ይዳዳዋል ፡፡ ጡረታን
የጉዳት ዳረጎት አድርጎ የሚያስብ ከንቱ !! ሰው አንገቱን ተቆርጦ ጡረታ እየተቀበለ መኖር
ቢችል ኖሮ፣ “ለአገራቸው ክብር” አንገታቸውን የተቆረጡቱ “ግራ እግር ምን አላት” ብለው
በተቆረጠው ግራ እግሩ በሳቁበት ነበር ፤ “አንዱ ባንዱ ሲስቅ ጀምሰሯ ጥልቅ” (በጨለማ መሳቅ
የለመደ ህዝብ ስለጀምበር መጥለቅ ምን ገዶት፡፡ ለምን እንጦሮጦስ አትወርድም፡፡ ኮኮቦችን ወላ ጨረቃዋን አስከትላ፡፡)

ቀን ቀን ትሁት፣ የተከበረ፣ የተጣላ የሚያስታርቅ የመንደሩ ዋልታ ነው አባቴ ፡፡ ማታ…. አቤት ቀንና ማታ በአባቴ ባህሪ ሲለኩ ያላቸው ልዩነት፡፡ ጧት የነበረው አባቴ ሌላ ክፍለ ዘመን፣ ማታ የሚከሰተው ደግሞ ሌላ ላይ የተፈጠረ ፤ ሁለት አባት ያለኝ እስኪመስለኝ !! አባቴ
ማታ ማታ ከራሱና ከእነዛ ሁለት ሥዕሎች ጋር ይጣላል ።
ጠጭ ነው:: በየቀኑ ይጠጣል፡፡ ሲጠጣ ቤተሰብ አይረብሽም፡፡ እናቴን አይናገርም፡፡ ቤታችን
ግድግዳ ላይ የተለጠፉት ሁለት ሥዕሎች ጋር ነው ዱላ ቀረሽ ግብ ግብ የሚፈጥረው በቃል !!

አባትህ ስራው ምንድን ነው ?” ብባል፣ “አባቴ ስራው ምን እንደሆነ አላውቅም” ነው መልሴ፡፡
ማሪያምን አላውቅም ! ትምህርት ቤትም እንደዚሁ ብዬ መልሼ ሁሉም ሳቁብኝ፡፡ እኔ ግን ለምን
እንደሳቁ አልገባኝም !! የተማሪዎቹ እሺ ይሁን ምድረ ኩታራ፡፡ ቲቸር ምን አሳቀው ? (ከሳቁ በፊት አንቱ ነበር የምለው፡፡) የቲቸር ሳቅ ስላበሳጨኝ ሆነ ብዬ እንዲህ ስል ሳቁን ተረጎምኩት፣
“አባትህ ቢያጣ ቢያጣ መምህር መሆን ያቅተዋል ?” ማለቱ ነው፡፡” ባይሰማኝም አንጀቴ ራስ፡፡
ይሄን አስቀያሚ መላጣ፣ ኮቱ የተዛነፈ ሂሳብ አስተማሪ ተውትና ስላባቴ ልንገራችሁ..(ሲጀመር
ሂሳብ እስተማሪ ስለአባቴ ሥራ ምን አገባው ደሞ ይስቃል እንዴ!)

ስለአባቴ ሥራ እንዴት ልበላችሁ? አባቴ አሁን ሹፌር ነው ተብሎ አንድ ፌርማታ ሳያልፍ ራፖርት ጸሐፊ ይሆናል፣ እሳቸው የሚጽፉት ማመልከቻ መሬት ጠብ አይልም" ተብሎ ባለጉዳይ
ቤታችን ሲመጣ፣ አባቴ መጋዝና ሜርቴሎውን ይዞ ገና ድሮ አናፂ ሆኗል፡፡ እንግዲህ በክረምት
ጣራችሁ አፍስሶ ወይ የእንጨት አጥራችሁ ወድቆ ትላንት ግንቦት ላይ አናፂ የነበረ አባቴን ሰኔ
አንድ "ጠግንልን” ብላችሁ ብትመጡ አባቴ ከተከመረ የከሰል ጆንያ ኋላ ቆሞ የከሰል ነጋዴ
ሆኖ ታገኙታላችሁ (“ዱቤ ክልክል ነው” ከሚል ፅሁፍ ጋር)..እና አባቴ ሥራው ምንድን ነው ልበል ? ብዙ ሥራ ያለውና ምንም ብር የሌለው አባት !

ብር ከአንዱ ይበደራል፣ የተበደረውን ከሌላ ሰው ተበድሮ ይከፍላል፡፡ ለሌላው ሰው ደግሞ
ከሌላ ሌላ ሰው ተበድሮ ይከፍላል፡፡ ሕፃን እንደነበርኩ ታዲያ ይሄ የአባቴ የመበደርና ብድር የመክፈል ሳይክል መጨረሻ ያለው ስለማይመስለኝ አባቴ እስከዘላለሙ በብድር የሚከሰስ፣ የሚታሰር አይመስለኝም ነበር፡፡ ብድር ይከፍላል፡፡ እጁ ላይ ምንም ብር አይኖረውም፡፡ ብር ለምን ይጠቅማል ቢሉኝ፣ ብድር ለመከፈል፡፡ 'ደመወዝ ለምን ይጠቅማል?' ብባል ብድር
ለመክፈል፤ ታዲያ ለምንድነው ሰዎች 'በባንክ ብድር ቤታቸው ተሸጠ የሚባለው? - እንደኔ
አባት ብልህ ስላልሆኑ ነዋ !!

ሥዕሎቹ፣
1. አባቴ በመጠኑ ሲሰከር (ሞቅ ብቻ ሲለው) ፊት ለፊቱ ቆሞ “ሳተናው ደህና አመሸህ!” የሚላቸው የአፄ ቴዎድሮስ ሥዕል የሽጉጣቸውን አፈሙዝ አፋቸው ውስጥ አስገብተው መቅደላ ጫፍ ላይ ሬሳና ቁስለኛ ከስራቸው ተለሽልሾ የሚታይበት ሥዕል፣ በቀኝ በኩል ከዕቃ መደርደሪያዋ በላይ ግድግዳው ላይ ተለጥፎ ይገኛል፡፡ (አባቴ ከዚህኛው ስዕል ጋር የመረረ ጥል የለውም፣ አልፎ
አልፎ ካልሆነ፡፡)

2. አባቴ ስካሩ ከመደበኛው ስካር ከፍ ሲልና፣ ቀን ከገጠመው የሕይወት ስንክሳር ጌሾ ጋር
ሲቀየጥ ደግሞ ከማይጋጩት ባላጋራ ጋር ይጋጫል፣ “.የጌታ እየሱስ ከርስቶስ” ምሥል ጋር!!

እየሱስ ቀይ መጎናፀፊያ ለብሶ፣ ረዥም ምርኩዙን በብብቱ ስር ይዞ፣ በር እያንኳኳ.. በግራ
በኩል!! አባቴ ከዚህ ሥዕል ጋር ይጣላል (ድፍረቱ ኢይገርምም ?)

አባቴ ገና በር ሲያንኳኳ እናቴ ስካሩ አንደኛ ደረጃው ይሁን ወይም ሁለተኛው ደረጃ ታውቀዋለች ፣ እንዴት ታውቃለች ? እግዜር ይወቅ !! እነዚህ እናቶች በየድራፍት ቤቱ ስለማይደሰኩሩ እንጂ በየሬዲዮና በየቴሌቪዥኑ ስለማይቀባጥሩ እንጂ ስንት ጉድ ተዓምር አለ በውስጣቸው:: ስንት
ጉድ፣ መላ.. :: እንኳን ባላቸው በር ሲያንኳኳ ቀርቶ ዙፋን ላይ ቂብ ሊል ያቆበቆበ ባለተራ ዓይነ ውሀውን አንብበው ክፉ ይሁን ደግ ያውቃሉ ዘመን ምስክር ነው !

ሁለተኛው ዓይነት ስካር ከሆነ እናቴ ተንደርድራ ከክርስቶስ ሥዕል ፊት ትሄዳለች - በፈጣን
አነጋገር፣ “ጌታ ሆይ እባክህ የተናገረውን ሲናገር አትቁጠርበት ይቅር በለው" ብላ የንሰሃ ቀብድ
ታስይዛለች ! (ሙሉውን አባቴ ራሱ ስካሩ ሲበርድለት ያወራርዳል !! ) ከዛ በሩን ትከፍትለታለች!
ፊቱ ወዝቶ አይኑ በአስፈሪ ሁኔታ ጉሽርጥ መስሎ ይገባል:: “ሰላም አመሻችሁ!” የለ ምን የላ!
“የአባትህ ገዳይ እዛ ቤት ተደብቋል፣ በግራ በኩል ከአልጋው በላይ ታገኘዋለህ” ብለው የላኩት ይመስል ዝም ብሎ ይገባና በቀጥታ ወደግራ ታጥፎ ከእልጋው በላይ የተሰቀለው የከርስቶስ ስዕል ፊት ይቆማል ፡፡
ፂሙን እያሻሸ ለረዥም ደቂቃዎች በዝምታ ሥዕሉ ጋር አፍጥጦ ይቆይና ድንገት፣ “አንከፍትም”
ብሎ ይጮሃል፡፡ እናቴ ሽምቅቅ ትላለች፡፡
“ለስንቱ እንከፈት፣ ሲያንኳኩ ስንከፍት ገብተው እኛን ሲያስወጡን፡፡ በጣታቸው ሲያንኳኩ 'ቤት ለእንግዳ' ብለን ስንከፍት በክንዳቸው ሲደቁሱን ከመክፈት ጋር ተጣልተናል ፤ አንከፍትም….”

እናቴ ወደ ጣራው ዓይኗን ልኮ በለሆሳስ ታነበንባለች፡፡ ለከርስቶስ “ቅድም ያልኩህን እንዳትረሳው
አደራ!” የምትል ይመስለኛል፡፡ አባቴ ይንጎማለላል፡፡ ረዥም ነው ቁመቱ፡፡ ብን ተደርጎ የተበጠረ
ጥቁር ከርዳዳ ፀጉሩ ላይ ወደፊት አካባቢ ትንሽ ሽበት ጣል ያደረገበት ፡፡ የጨርቅ ሱሪው የተኩስ መስመር ቀጥ ማለት፣ “ሱሪውን ከለበሰው ጀምሮ ተቀምጦ አያውቅም እንዴ” የሚያስብል በሚገባ የተወለወለ አሮጌ የወታደር ቦት ጫማ ፡፡ ይንጎማለላል ..
👍312
“አንከፍትም ! እድሜ ልኬን በርህን ሳንኳኳ የከረቸምክብኝ፣ እንዴት ነው የኔን ልብ ዛሬ የምከፍትልህ፡፡ የገቡትንም ማስወጪያ አጥተናል እንኳን አዲስ ለሚያንኳኳ ልንከፍት አንከፍትም''
ይንጎራደዳል፡፡ አንዳንዴ ፊቱ ላይ የሚንቀለቀለውን ቁጣ ላይ፣ “በቃ ገንጥሎ ጣለው ክርስቶስዬ
ጉዱ ፈላ” እላለሁ፡፡ ይሄ ሥዕል ከድሮ ጀምሮ ግድግዳችን ላይ ስለተለጠፈ ነው መሰለኝ ክርስቶስ
ከእኛ ቤት ሌላ መሄጃ ያለው አይመስለኝም ነበር፡፡ እናቴና ክርስቶስ የአባቴን ባህሪ ችለው
የኖሩት ሌላ መሄጃ ስለሌላቸው ይመስለኝ ነበር፡፡እኔ፣ ክርስቶስና እናቴ የአባቴን ባህሪ ችለን
የተቀመጥነው ሌላ መሄጃ ስለሌለን ይመስለኝ ነበር.

"አንከፍትልህም ይህቺ ሚስኪን (ወደናቴ እየጠቆመ) ለስንቱ ሃብታም፣ ለስንቱ ጀግና፣ ለስንቱ ባለ ሥልጣን የከረቸመችውን ልቧን ለኔ ከፈተች፡፡ ምን ተጠቀመች ? ምንም !! እድሜ ልኳን ጡረታ የወጣ ወታደር ባሏ ሰከሮ ሲመጣ በር ከፋች ሆና ቀረች .." (ስለሌላ ባል እንጂ ስለራሱ የሚያወራ አይመስልም፡፡) “እሷን ተዋት..እቺ አገር ራሷ..እቺ እጇን ወደአንተ ትዘረጋለች የተባለችው... ሃሃሃ ..እቺ ኢትዮጵያ .…ጓደኞቼን ዋጥ ስልቅጥ ያደረገችው አገር ራሷ...ለንጉሥ ልቧን ስትከፍት፣
ለወታደር ልቧን ስትከፍት፣ ለወንበዴ ልቧን ስትከፍት፣ ለሶሻሊዝም፣ ለምናምኒዝም ልቧን
ስትከፍት ይሄው መከፈት መዘጋት የሰለቸው በሯ ተገንጥሎ ክፍቷን ቀረች፡፡እናስ ? ምናችን
ጅል ነው የምንከፍትልህ ?..አንከፍትም !! አንከፍትም !! በከፈትን ቁጥር እየገባ የታጨቀብንን
ጣጣ ባስወጣህልን ይልቅ !.ላንተም አይመችህ .ውስጣችን ነድዷል፣ ከሰሏል የተቃጠለ ቤት
ውስጥ ለመኖር ይሄን ያህል ስታንኳኳ መኖር..ኤዲያ" እናቴ እንባዋ ጠብ ሲል ይታየኛል፡፡

ልቤ ይታፈናል፡፡ ልብ ድካም የሚባለው ይሄ ይሆን ? ቤታችን ይታፈናል፡፡ በጣም ብዙ
መላዕክት ቤታችን ውስጥ ታጭቀው፣ “ኧረ ጌታ ሆይ ይሄ ሰውዬ አበዛው፣ ፍቀድልንና ወደዛ
ቦጫጭቀን ሲኦል እንወርውረው…” እያሉ እየሱስን የሚያስፈቅዱ ይመስለኛል፡፡
“እስቲ ተዉት…እሱ ያለፈውን መከራ ማን አለፈ ? ..የዚህን ሚስኪን ልጄን ቀንበር ማን ተሸከመ?
እስከመጨረሻው እለምነዋለሁ!” የሚላቸው ይመስለኛል በሩን ማንኳኳቱን ሳያቋርጥ፤ ክርስቶስ
የኔ ልብ አዋቂ ! አባቴ እያነሰ ክርስቶስ እየገዘፈ ይሄድብኛል አሁን ደግሞ ለአባቴ እሰጋለሁ፡፡

ጎምለል ጎምለል...“እንከፍትም !!
አናውቅም እንዴ…ወላ መስኮት ወላ በሩ በተዘጋ ቤት ሰተት
ብለህ ገብተህ ሰላም ለእናንተ ስትል? አሁን ምን ያዘህ?.ግባ… ይሄው በግድግዳው ግባ፡፡
መቼም ዓይናችን እያየ አንከፍትልህም…” እያጉተመተመ ልብሱን ያወላልቃል፡፡ መጀመሪያ
ኮቱን ገበሩ ተቀዳዷል፡፡ እያጣጠፈ ያጉተመትማል - “ወይ መክፈት… " ሱሪውን በሥርዓት
አልጋው ላይ ዘርግቶ በእጁ እየተኮሰ ያጣጥፋል፡፡ ቢሰክርም ባይሰክርም ልብሱን በመስመሩ
ማጠፍና በሥርዓት ማስቀመጥ አይረሳም፡፡ ሊተኛ ሲል ያየኛል፡፡ ልክ የአልጋ ልብሱን ገለብ
ሲያደርግ ኩርምት ብዬ እናቴ ስር፡፡ “አይዞህ አንበሳዬ…ምነው ከኔ ከምትፈጠር በቀረብህ...
የማይረባ አባት ለአንድ ልጁ እንኳን የማይሆን ወይ አባት አላየንም አባት እንደለማዳ
ውሻ ስምህን ተከትሎ ከሚጮህ ስሜ ሌላ ምን አወርስሃለሁ ቤሳቤስቲን..” እየተናገረ አልጋ
ልብሱ ውስጥ ገብቷል፡፡ በብርድ ልብሱ የታፈነ እንቅልፍ የተጫጫነው ድምፁ ያጉተመትማል፣ከንቱ…ለራሴ ከንቱ ሆኜ የሰው ሰው ከንቱ አድርጌያት ቀረሁግራ ገብቶኝ ግራ ረዥም
ዝምታ፣ የተኛ እስኪመስለን :: ድንገት፣ “አለሜ..እራት በልታችኋል” ይላታል እናቴን፡፡

“ጠዎ ወይም “አልበላንም” አትልም፡፡ ሁልጊዜ መልሷ ይገርመኛል፣
“ቆንጆ ወጥ ሰርቻለሁ ፡ ትንሽ ልስጥህ እስቲ.." ትለዋለች፡፡ ገና ቅድም ተነስታ ጓዳው በር
ላይ ደርሳለች፣

“አ..ይ.. ይላል ስልል ባለ ድምፅ፡፡ አንዳንዴ “አይ” ብሏትም ታቀርብለታለች፣ ተነስቶ
ይበላል፡ አንዳንዴ "አይ…" ካለ ትመለሳለች፡፡ በሁለቱ 'አይ'ዎች መሃል ያለውን ልዩነት ብዙ ጊዜ
ለማጥናት ሞከርኩ፡፡ በድምፅ ርዝመት፣ በቅላፄ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ እናቴ ግን በሁለቱ 'አይ'ዎች መሃል የአባቴን መሻት በቀላሉ ታውቃለች፣ አለመሻቱንም፡፡ (አለመሻቱ እንኳን አይ ካለ አይ ነው :: ግን እንዴት አይ ያለ ሰው አይ ያለበትን ጉዳይ እንደፈለገው ማወቅ ቻለች ??????)

አማርኛ አስተማሪያችን “ልጆች ቋንቋን ከቤተሰብ ከማኅበረሰብ ይማራሉ” አሉኝ እንጂ ቋንቋን
የምንማረው ከሕይወት፣ ለዛውም መተሳሰብ፣ መከባበረ እና መፈቃቀር ካለበት የሕይወት
ልምዳችን ብቻ ነው:: አማርኛ አስተማሪያችን ራሳቸው፣ አባባ “አይ” ሲል እራት “አቅርቢልኝ”
ማለት መሆኑን በጭራሽ አያውቁም፡፡ ከማህበረሰቡ ይሄን አልተማሩማ !! ስሜትና ስዋሰው
ለየቅል ናቸው !!
ጧት ከእንቅልፌ ስነቃ ታዲያ ብቻዬን ነኝ፡፡ እናትና አባቴ ቤተ ክርስቲያን ሄደዋል፡፡ የክርስቶስ
ሥዕል ግን አሁንም አለ፡፡ ቆይ አባቴ ከሌለ ማን እንዲከፍትለት ነው የሚያንኳኳው ? በብርድ
ልብሴ ተጠቅልዬ ሥዕሉን እያየሁ አስባለሁ፣ “አባታችሁን ታዘዙ፣ ቤተሰቦቻችሁ የማይወዱትን
በመሥራት አታሳዝኗቸው” ይሉን የለ የሰንበት አስተማሪያችን ? ስለዚህ...

“አልከፍትም !!” እላለሁ ቀስ ብዬ

አለቀ
👍17😁4👏2
#ምንዱባን


#ክፍል_አንድ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

ቀና ሰው

በ1815 መሴ ቻርለስ ብየንቬኑ መሪል የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ነበሩ፡፡ እድሜያቸው 75 ሲሆን የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ሁነው የተሾሙት በ1806 ዓ.ም ነበር፡፡ ጳጳሱ ወደ ሀገረ
ስብከታቸው ሲመጡ እህታቸው ወ/ት ባፕቲስታን አብረዋቸው ነበር
የመጡት:: እህትዬዋ ምንም እንኳን ትዳር ባይዙም እድሜ የጠገቡ ሲሆኑ ወንድማቸውን በአሥር ዓመት ይበልጧቸዋል፡፡

ከጳጳሱ ቤት ውስጥ ሌላም ሴት ነበሩ፡፡ እኝህ ሴት የወ/ት ባፕቲስታን እኩያ ናቸው:: ሴትዬዋ ወ/ሮ ማግልዋር ይባላሉ:: ሴትዮዋ ቀደም ሲል የሌላ ሰው አገልጋይ ሆነው ሠርተዋል፡፡ አሁን ደግሞ የወ/ት ባፕቲስታንና
የጳጳሱ ቤት ጠባቂ ሁነው ተቀጥረው ይሠራሉ፡፡

ጳጳሱ ከሀገረ ስብከታቸው እንደደረሱ በሀገሩ ደምብ መሠረት ከፊልድ ማርሻል ቀጥሎ ያለውን ሹመት ይሰጣቸዋል፡፡ የክፍለ ሀገሩ መሪና የማዘጋጃ ቤቱ ሹም ከቤታቸው ሄደው «እንኳን ደህና መጡ» በማለት እጅ ይነስዋቸዋል፡፡ አቡኑም በተራቸው ከዚያ ለተገኙ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ቡራኬ ይሰጣሉ፡፡ የከተማው ሕዝብ በአጠቃላይ አዲስ የተሾሙለትን ጳጳስ
ለማየት በጉጉት ሲጠባበቅ ነበር፡፡

የጳጳሱ ቤት ከአንድ ሆስፒታል አጠገብ ሲሆን ቤቱ እጅግ በጣም
ሰፊና ያማረ ነው:: ሆስፒታሉ ይገኝ የነበረው ከረባዳ ሥፍራ ላይ ሲሆን ግቢው እንደ ጳጳሱ ቤት አይሰፋም:: ጳጳሱ ወደዚያ ሲሄዱ በሦስተኛው ቀን ሆስፒታሉን ይጎበኛሉ:: ከጉብኝቱ በኋላ የሆስፒታሉ አስተዳዳሪ ከቤታቸው
ድረስ መጥቶ እንዲያነጋግራቸው ይጋብዙታል:: አስተዳዳሪው ከጳጳሱ ቤት ይሄዳል::

በሆስፒታሉ ውስጥ «ስንት በሽተኞች አሉ? » ሲሉ አስተዳዳሪው ጠየቁ::

«ሃያ ስድስት» ሲል መለሰላቸው::

«ልክ እኔ እንደቆጠርኳቸው ናቸው አልተሳሳትክም» አሉ ጳጳሱ::
ጳጳሱ የቤታቸውን አዳራሽ በዓያናቸው ቃኙ:: አመለካከታቸው
አዳራሹን በዓይነ ሕሊናቸው የሚለኩና የሚያከፋፍሉ ይመስሉ ነበር ።

«ይህ ክፍል ብቻ ሀያ አልጋ ይይዛል» አሉ እርስ በራሳቸው? ሲነጋገሩ።
ከዚያም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚቀጥለውን ተናገሩ::

«ወዳጄ የምለውን አጢነህ ስማኝ፡፡ እዚህ ቦታ አንድ ስህተት የተፈጸመ ይመስላል፡፡ እናንተ አምስት ወይም ስድስት ጠባብ ክፍሎች ናቸው ያሏችሁ::
ከዚያ ውስጥ ሃያ ስድስት ሰዎች ይተኛሉ፡፡ እኛ እዚህ ሦስት ሰዎች ብቻ ነን፡፡ ያለው ቦታ ግን ለስልሣ ሰው የሚበቃ ነው:: ታዲያ ይህ የአደላደል ስህተት አይመስልህም? የእኔን ቤት አንተ ብትወስድ ፤ የአንተን ደግሞ እኔ
ብወስድ ይሻላል፡፡›

በሚቀጥለው ቀን ሃያ ስድስቱ በሽተኞች ወደ ጳጳሱ ቤት ተዛወሩ፡፡
ጳጳሱም ሆስፒታሉን ተረከቡ:: ወሬው በከተማው ተነዛ፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ የጳጳሱን በጎ ምግባር በመከተል ለበጎ ተግባር የሚውል እርዳታ ይጎርፍ ጀመር፡፡ በየቀኑ ከጳጳሱ ቤት በር የሚያንኳኳ ሰው ቁጥር እየበዛ
ሄደ፡፡ ሆኖም የሚመጣው ሰው ሁሉ እርዳታ ለማድረግ ብቻ ሳይሆን ምፅዋት ለመቀበልም ነበር፡፡ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ጳጳሱ የብዙ ችግረኞች ቀላቢ፣ ምፅዋት ሰጪና ገንዘብ ሰብሳቢ ሆነ፡፡ ብዙ ገንዘብም ከጳጳሱ እጅ እየገባ ለድሃ ይሰጥ ጀመር:: የሚገኘው ገቢ ግን ልክ ከደረቀ
አፈር ላይ እንደሚፈስ ውሃ ገና ከመገኘቱ ወጪ ሆኖ በቶሎ ያልቃል፡፡ጳጳሱ ገንዘብ ቢያገኙም ከተገኘው ገቢ ጥቂቱን እንኳን ለራሳቸው ወደኋላ አላሉም፡፡ እንዲያውም ከነአካቴው የራሳቸውንም ይዞ ይሄድ ጀመር፡፡
ጳጳሳትን ከስማቸው አስቀድሞ ንጽህናቸውን ለማረጋገጥ ብፁዕ ወቅዱስ እያሉ መጥራት የተለመደ ቢሆንም በዚያ አካባቢ ይገኙ የነበሩት ነዳያን ፍቅራቸውንና ቅርበታቸውን ለመግለጽና የጳጳሱን ደግነት ለማውሳት ብፁዕ ወቅዱስ በማለት ፈንታ «አባ ደጉ» እያሉ ይጠርዋቸዋል፡፡

እኚህ ደግ ሰው በ1815 ዓ.ም ምንም እንኳን 75 ዓመት ቢሞላቸወም ከስልሣ ዓመት በላይ የሆናቸው አይመስሉም ነበር:: ቁመታቸው እጅግም ረጅም ሳይሆን መጠነኛ ሆኖ ሰውነታቸው ደልዳላ ነው:: ክብደታቸውን
ለመቆጣጠር በእግር መሄድ ያዘወትራሉ:: ሲራመዱ መሬት በኃይል እየረገጠ ከወገባቸው ትንሽ ጎበጥ ይላሉ::

የልጅ ፈገግታ በተጎናጸፈ አንደበት ሲናገሩ ከግርማ ሞገሳቸው ብዛት
የሰማቸው ሁሉ የመንፈስ እርካታን ያገኛል:: ከመላ ሰውነታቸው ደስታ
የሚንፀባረቅ ይመስላል፡፡ ደግነት የተቆራኘው አካላቸውና ወተት የመሰለው ጥርሳቸው ፈገግ ሲል እኚያ «ጨዋ ሰው ፤ እድሜ የተቸረ ሽማግሌ፤ ደግ ሰው» በማለት ለደጋግ ሰዎች የምንሰጠው ቅጻል ሁሉ በእኚህ ሰው ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ላያቸው እንኳን ስለብቃታቸውና
ስለደግነታቸው አይጠራጠርም:: ነገር ግን አንድ ሰው ለጥቂት ሰዓት ከጳጳሱ ጋር ቢቆይና በአሳብ ባህር ተወጠው ቢያያቸወ ቀስ በቀስ
መለወጣቸውን ይገነዘባል፡: ግርማ ሞገሳቸው በቃላት ለመግለጽ በማይቻል ሁኔታ ያስፈራል፡፡ ሰፊውና ኮስታራው ፊታቸው እንዲሁም ሻሽ የመሰለው
ፀጉራቸው ክብር የተጎናጸፈ ለመሆነ በግልጽ ይታያል:: ግርማ ሞገስ ከውስጣቸው እየፈለቀ ሲወጣ የሚያልቅ ቢመስልም የእንዐባራቂነት ኃያል
እንዳለው አያጠራጥርም:: እንዲያውም አንድ ሰው ሁኔታቸውን በጥሞና ሲመለከት «አንድ መልአክ በፈገግታ አጊጦ ያየኛል» የሚል ስሜት
ያድርበታል፡፡ እኚህ ሰው የሚያሰላስሉት ስለ ክቡር ጉዳይ እንጂ ስለርካሽ ነገር ላለመሆኑ ጥርጣሬ አይገባውም::

ጸሎት ማድረስ፤ ምፅዋት መስጠት፧ የመንፈስ ስቃይ የደረሰበትን ማጸናናት፤ ወንድማማችነትን መስበክ፤ ራስን ለሌሎች መስዋዕት ማድረግ፤
በእምነት ራስን መግራት የጳጳሱ የእለት ተዕለት ኑሮ ሲሆን ይህም ኑር በበጎ አሳብ፤ በምርጥ ቃላትና በበጎ ተግባር የተሞላ ነበር፡፡

ክረምት ይሁን በጋ ሁለቱ ሴቶች ሲተኙ ብፁዕነታቸው ወደ ጓሮ
ሄደው አትክልት ውስጥ ለአንድ ወይም ለሁለት ሰዓት ፈጣሪያቸውን በማሰብ ከዚያ ካልቆዩ ኑሮአቸው የተሟላ አይመስላቸውም:: አሳባቸውን
ሰብስበውና የመንፈስ እርጋታን አግኝተው የምሽቱን ሰላምና ፀጥታ ከሰዎች የመንፈስ እርካታ ጋር እያነፃፀሩ የከዋክብትን ብዛት በመመልከት ከአትክልቱ
ውስጥ ይንሸራሸራሉ፡፡

በዚያች ሰዓት አበቦች ያለመስገበገብ የሚለግሱትን መልካም መዓዛ እየማጉ ጥቅጥቅ ካለ ጨለማ ውስጥ እንደበራ ሻማ ብቻቸውን በፍጥረታት
መካከል በደስታ የተዋበው ነፍሳቸውን ዘርግተው ይቆማሉ:: አእምሮአቸው ውስጥ ምን እንዳለ ራሳቸውን ቢጠይቁ መልሱን አያውቁትም:: ሆኖም ከሰውነታቸው ውስጥ አንድ ነገር ወጥቶ እንደሚሄድና አንድ ነገር ደግሞ ከሰውነታቸው ላይ እንደሚያርፍ ይሰማቸዋል ፤ አንድ ዓይነት ምሥጢር መከናወኑን ይገነዘባሉ::

እኚህ እድሜ የጠገበና ፈጣሪያቸውን የቀረበ ሰው የእረፍት ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ቀን ቀን አትክልት በመኮትኮት ሲሆን ማታ ማታ ደግሞ ፈጣሪያቸውን በጸሎት በማመስገን ስለሆነ ሌላ የሚፈልጉት
ነገር አልነበረም:: ምድሩ በአበባ ፤ ሰማዩ ከከዋክብት በማጌጡ የመንፈስ እርካታ ይሰጣቸዋል::

ውድቀት

ጊዜው 1815 ዓ.ም ወሩ ጥቅምት ነው:: ፀሐይዋ ልትጠልቅ አንድ ሰዓት ያህል ሲቀራት አንድ በእግሩ የሚጓገዝ ሰው ወደ ሞንቴስ ሱር ሞንቴስ
👍47😁3👏2👎1🔥1
ትንሺቱ ከተማ ይገባል፡፡ በየመስኮቶቻቸውና በየቢሮዎቻቸው አጠገብ የቆሙ
ጥቂት ሰዎች ይህን መንገደኛ ይጠራጠሩታል፡፡ ሆኖም ከእርሱም ይበልጥ የተሰቃየ ሌላ ሰው ለማግኘት እንደማይቻል ፊቱ ይመሰክራል፡፡ ቁመቱ መካከለኛና አጥንተ-ወፍራም ሲሆን የሰውነቱ አፈጣጠር ግዙፍ ነው::
በእድሜው ሙሉ ሰው ይመስላል፡፡ ምናልባት አርባ ስድስት ወይም አርባ
ሰባት ዓመት ሳይሆነው አይቀርም:: የፀሐይ ጨረር፣ ነፋስና ከሰውነቱ የወጣው ላብ ያጠቆረውና ያንገላታው ቆብ ግማሽ ፊቱን ሸፍኖበታል::

ቀደም ሲል የፈሰሰው ላቡ ከፊቱ ላይ ደርቆ አዲሰ ደግሞ ከፊቱ ላይ
ሲወርድ ድካሙን በግልጽ ያሳያል:: የለበሰው ሸካራና ቢጫ ሸሚዝ ከብዙ ቦታ ላይ በመቦጫጨቁ የደረቱን አጥንት ለፀሐይ ዳርጎታል:: ሸሚዙ በነፋስ
ኃይል እንዳይሄድ ሳይሆን አይቀርም ከረባትና አሮጌ መስቀል በተንጠለጠለበት
ገመድ አሲዞታል፡፡ የተቀዳደደ ሰማያዊ ሱሪ ታጥቋል:: ሱሪው አንደኛው ጉልበቱ ላይ ሳስቶ ሲነጣ ሌላው ላይ ተቀዳድዶአል፡፡ ከአንድ ጎኑ ላይ አረንጓዴ ጨርቅ የተጣፈበትና ግራጫ መልክ ያለው አሮጌ ሰደርያ ደግሞ
ደርቦአል:: በምናምን የተሞላ አዲስ አቆማዳ በዱላ በማያያዝ በጀርባው አንጠልጥሎአል፡፡ በእጁ ደግሞ ሌላ ባለትልቅ ቋር ዱላ ይዟል:: የተንሻፈፈና
ከጎኑ የተቀደደ አሮጌ ጫማ ያለካልሲ አጥልቆአል:: ፀጉሩን ተላጭቶት የበቀለ ሲሆን ጢሙ ግን በኃይል አድጓል:: ላቡና የሰውነቱ መዛል በእግር ብዙ መጓዙን ያረጋግጣል:: ከላዩ ላይ የሰፈረው አዋራ ለሰውዬው መጎሳቆል ሌላው ማስረጃ ነው::

ይህ ሰው ወደ ከተማው እንደገባ ወደ ግራ ታጥፎ ወደ ማዘጋጃ ቤት
ያመራል:: ከዚያም ከማዘጋጃ ቤት ሹም ቢሮ ገብቶ ከሩብ ሰዓት በኋላ ከቢሮው ይወጣል፡፡
በከተማው ውስጥ ጥሩ ማረፊያ ቤት ነበር፡፡ መንገደኛው ወደዚያች
ማረፊያ ቤት ሄደ፡፡ ማረፊያ ቤቱ በከተማው የታወቀና ምርጥ የተባለ ነበር፡፡ በቀጥታ ወደ ወጥ ቤት ሄደ:: የወጥ ቤቱ የጓሮ በር ወደ ዋናው ጉዳና የሚያስወጣ ሲሆን መንገደኛው የገባው በዚህ በኩል ነበር፡፡ ወጥ ቤቱ ወስጥ ከአብዛኞቹ ምድጃዎች ላይ እንጨት በኃይል ተያይዞ እሳቱ
ይንቦገቦጋል፡፡ የወጥ ቤቱ ኃላፊ እሳቱ ከሚነድበት በችኮላ እየተራመደ ሄዶ የምግቡን ሁኔታ ይቃኛል:: የምግቡን መዳረስ የሚጠብቁ ለሎች መንገደኞች
ቀጥሎ ከነበረው ክፍል ውስጥ ሲስቁና ሲንጫጩ ይሰማል:: የሚዘጋጀው ምግብ መልካም ቃና፧ እንኳን ለሚቀምሰውና ለሚያሸትተው ይቅርና
መንገደኛውን ከሩቅ የሚጠራ ዓይነት ስለነበር እንግዶቹ፣ ምን ዓይነት ሰዎች እንደነበሩ ለመገመት አያዳግትም::

የወጥ ቤቱ ኃላፊ በር ሲከፈት ሰምቶ እንግዳ መግባቱን ስለተገነዘበ አንገቱን ቀና ሳያደርግ «ጌታዬ ምን ይፈልጋሉ?» ሲል ይጠይቃል፡፡
‹‹የሚላስ፧ የሚቀመስና ማደሪያ ነው የምፈልገው» ይላል እንግዳው::
«ከዚህ የቀለለ ምን ነገር አለ!» ብሎ ኃላፊው ከተናገረ በኋላ አንገቱን ቀና አድርጎ ባይተዋሩን በመመልከት ‹‹ግን ይከፈላል» ይለዋል:: ሰውዬው
ከኪሱ ወስጥ ትልቅ ቦርሳ አውጥቶ ገንዘብ አለኝ» ሲል መለሰለት::
«እንግዲያውስ» አለ አስተናጋጁ ፧ «ምን ልታዘዝ?»
ሰውዬው ቦርሳውን መልሶ ከኪሱ ውስጥ ከተተ:: ስልቻውን ከጫንቃው ላይ አውርዶ ከመሬት ላይ ወረወረው:: ዱላውን እንደያዘ እሳቱ አጠገብ
ከነበረው ወንበር ላይ ቁጭ አለ፡፡ ከተማው የተሠራው ከተራራ ጫፍ ላይ በመሆኑና ወሩም ጥቅምት ስለነበር የአካባቢው አየር በጣም ቀዝቃዛ ነበር፡፡
የቤቱ ባለቤት ወዲህና ወዲያ ባለ ቁጥር መንገደኛውን አተኩሮ
ይመለከተዋል::
«ምግብ ደርሷል?» ሲል መንገደኛው ጠየቀ፡፡
«ተቃርቧል» አለ ኃላፊው::
እንግዳው ጀርባውን ለእሳት ሰጥቶ ሲሞቅ የሆቴሉ ባለቤት ቁራጭ
እርሳስ ከኪሱ ካወጣ በኋላ ከመስኮት አጠገብ ከነበረው አነስተኛ ጠረጴዛ ላይ
ተቀምጦ ከነበረው የማስታወሻ ደብተር አንዲት ቅጠል ቀደደ:: ምናምን ጻጽፎ ወረቀቱን በአቅራቢያው ለነበረውና እንደ ተላላኪም፧ እንደ ቤት
ጠራጊም ይሠራ ለነበረው ልጅ ሰጠው:: የሆነ ነገር በጆሮው ለልጁ ሹክ ካለው በኋላ ልጁ ወደ ማዘጋጃ ቤት ሹም ቢሮ አቅጣጫ ይሮጣል:: ይህ ሲሆን ግን መንገደኛው አላየም::

«እራት ደርሷል?» ሲል ለሁለተኛ ጊዜ ጠየቀ::

«አዎን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ማቅረብ እንጀምራለን» አለ የቤቱ
ጌታ::

ልጁ ወረቀቱን በእጁ እንደያዘ ተመለሰ፡፡ የሆቴሉ ባለቤት ቸኩሉ
አስቸኳይ መልስ ለመስማት እንደሚጓጓ ሰው ሁሉ የተጣጠፈውን ወረቀት ከፈተ፡፡ በጥሞና ማንበብ ጀመረ:: ከዚያም በአንድ እጁ አገጩን ይዞ እንደማሰብ አለ:: በአሳብ ባህር የተዋጠ ወደሚመስለው መንገደኛ ተጠጋ::

«ጌታዬ» አለ፤ «ልረዳዎት ባለመቻሌ አዝናለሁ:: ያልተያዘ ክፍል ያለ መስሎኝ ነበር፤ ግን የለም፡፡»

«ታዲያ» አለ መንገደኛው «አልጋ እንኳን ባይኖር የትም ቢሆን ሳር:
ተጎዝጉዞልኝ ልተኛ ለማንኛውም ከእራት በኋላ እንወያይበታለን::

«እራትም ልሰጥዎት አልችልም፡፡»

መንገደኛው ይህን ሲሰማ «ይህስ ለነገር ነው» ይላል፡፡ከተቀመጠበት
ብድግ አለ፡፡

«እህ.... እህህ፤ ታዲያ እኔ እኮ በጣም ስለራበኝ ጠኔ ይዞኛል::»

«ምንም የለኝም» አለ የሆቴሉ ጌታ::

ሰውዬው ሳቁን ለቀቀው:: ወደ እሳት ማንደጃው ዞር ብሎ የተጣደውን ምግብ ሁሉ ተመለከተ፡፡

«ምንም የለኝም! ያ ሁለ ምግብ እያለ!»

«ያ ሁሉ ምግብ ለሌላ ሰው ነው የተዘጋጀው::

ሰውዬው እንደገና ቁጭ አለ፡፡ ድምፁን ዝቅ አድርጎ ‹‹ሆቴል ቤት
ውስጥ ነው ያለሁት፤ ተርቤአለሁ፤ እኔ ደግሞ እዚሁ ነው የማድረው»
አለ፡፡

የሆቴሉ ባለቤት አንገቱን ዝቅ አድርጎ ንዴት እየተናነቀው «ሰውዬ
ውጣ» ይላል፡፡

መንገደኛው ወደሚነደው እሳት ጠጋ ብሎ ትርኳሽ እንጨቶችን
በያዘው ዱላ ወደ እሳቱ ረመጥ እያስጠጋ ሳለ «ውጣ» የሚል ቃል ሲሰማ መልስ ለመስጠት ፊቱን ያዞራል፡፡ የሆቴሉ ጌታ አፍጥጦ እያየው ለመናገር እድል ሳይሰጠው «ቢበቃን ይሻላል ፤ በመጀመሪያ ማንንም ቢሆን በትህትና ማናገር ልማዴ ነው ፤ ሰውዬ ያለ ጭቅጭቅ መንገድህን ብትቀጥል ይሻልሃል»ይለዋል::

ሰውየውን እጅ ከነሳ በኋላ ስልቻውን ተሸክሞ ከቤቱ ወጥቶ ሄደ፡፡

አውራ ጎዳናውን ይዞ ወዴት እንደሚሄድ ሳያውቅ የሀፍረት ሽማውን ተከናንቦ እንደ አዘነተኛና እንደተዋረደ ሰው እየታሸማቀቀ ጉዞውን ቀጠለ፡፡

ያስጠጉኝ እንደሆነ በማለት የየቤቱን በር አንኳኳ፡፡ ግባ የሚለው ቢያጣ ፊቱን ሳይመልስ ቀጥ ብሎ ወደፊት ተጓዘ፡፡ ከሆቴል ቤቱ ቢመለስ ኖሮ
የሆቴሉ ባለቤት እዚያ ቤት ውስጥ ከነበሩት እንግዶችና ከተላላፊ መንገደኞች ጋር ቆሞ በጣቱ እየጠቆመ ስለእርሱ በጉጉት ሲያወራቸው ያይ ነበር፡፡
ቢያያቸው ኖሮ ደግሞ የእርሱ ወደዚያ መምጣት የከተማው ወሬ እንደሚሆን ከሁናቴያቸውና ከአመለካከታቸው ሊገምት ይችል ነበር፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን ግን መንገደኛው አላየም:: ከችግር ማጥ ውስጥ
የሚዋትቱ ሰዎች ወደኋላ መለስ ብለው አይመለከቱም፤ ሰንኳላ እድል እንደሚከተላቸው ያውቃሉና:: ከአውራ ጎዳናው ሳይወጣ ለጥቂት ጊዜ
እንደተጓዘ ከማያውቀው ሰፈር ደረሰ፡፡ በሀዘን የተዋጠና የተከፋ ሰው ድካም እንደማይሰማው ሁሉ ድካሙ አልተሰማውም:: ግን በድንገት ረሃብ ሞረሞረው:: ሐሞቱ ሲንሰፈሰፍ ተሰማው:: ምሽት ተቃርቧል።
👍345
ከተባረረበት ሆቴል ቤት ጀምሮ ከወደኋላው ይከተሉት የነበሩት
ሕፃናት ድንጋይ ወረወሩበት:: በቁጣ ወደ እነርሱ ዞሮ በያዘው ዱላ ሲያስፈራራቸው እንደ ወፍ መንጋ ተበተኑ፡፡ የእስር ቤት በራፍ እንዳለፈ ከደወል ጋር ተያይዞ ከበር ላይ የተንጠለጠለ የብረት ሰንሰለት አየ:: መለስ ብሎ ደወሉን ደወለው:: በሩ ተከፈተ::
«ቤቶች» አለ ቆቡን አውልቆ በትህትና እጅ እየነሳ ፤ ለዛሬ ብቻ ከዚህ ያሳድሩኛል?»

«እስር ቤት ሆቴል ቤት አይደለም ፤ ወንጀል ሠርተህ ከመጣ በሩን
እንከፍትልሃለን» አለ አንድ ድምፁ ከሩቅ:: በሩ ተመልሶ ተዘጋበት:: የዘበኞች ኃላፊ ነበር የተናገረው:

ጊዜው እየመሸ ነው:: ቀዝቃዛ አየር ከተራራው ወደ ነበረበት ሰፈር
ይነፍሳል:: እግሩ እየከበደው ቢሄድም መራመዱን ቀጠለ፡፡ ከከተማው ትንሽ ወጣ ሲል ለማደሪያ የሚሆነው የትልቅ ዛፍ ከለላ ወይም የተከመረ
ድርቆሽ እንደሚያገኝ ተስፋ አደረገ፡፡ አንገቱን አቀርቅሮ ጉዞውን ተያያዘው::ሰው ከሚኖርበት አካባቢ የወጣ ስለመስለው አንገቱን ቀና አድርጎ አካባቢውን
በዓይኑ ቃኘ፡፡ ከእርሻ ሜዳ ደርሷል:: ከፊት ለፊቱ ከሚገኘው ጉብታ ላይ የነበረው እህል ታጭዶ የሚታየው ቀሪው ገለባ ብቻ ነው:: አካባቢው በአጠቃላይ የተላጨ ፀጉር መስሉአል:: ሰማዩ ጨልሞ ደመና ዞሮበታል፡፡ የደመናው ብዛት በአካባቢው የሚገኙት ኮረብታ ላይ ያረፈ አስመስሎታል፡፡
ሆኖም ከአንዳንድ ሥፍራ የሚታዩት ዋክብት ነፋስ ይዞት እንደሚሄድ ኩራዝ ደፋ ቀና ይላሉ:: ጨረቃውም ሳሳ ካለው ደመና ላይ ነጭ መስመር የዘረጋች ይመስል ብልጭ ድርግም ትላለች:. አልፎ አልፎ መስመሩን
የሚዘረጋው ጨረቃና ደፋ ቀና የሚሉት ከዋክብተ አካባቢው ጨርሶ ጨለማ እንዳይሆን ረድተዋል :: ስለዚህ የመሬቱን የሰማዩን ያህል አልጨለመም:: ሆኖም አካባቢው በጣም ያስፈራል፡፡.....

💫ይቀጥላል💫
👍20
አትሮኖስ pinned «#ምንዱባን ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ ቀና ሰው በ1815 መሴ ቻርለስ ብየንቬኑ መሪል የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ነበሩ፡፡ እድሜያቸው 75 ሲሆን የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ሁነው የተሾሙት በ1806 ዓ.ም ነበር፡፡ ጳጳሱ ወደ ሀገረ ስብከታቸው ሲመጡ እህታቸው ወ/ት ባፕቲስታን አብረዋቸው ነበር የመጡት:: እህትዬዋ ምንም እንኳን ትዳር ባይዙም እድሜ…»