አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የአባዬ_ስልክ_እና_ባዮሎጂ


#በአሌክስ_አብርሃም


እንዲህ እንደዛሬው በየሰዉ ኪስ ሳይልከሰከስ በፊት ስልክ ተዓምራዊ የሀብት መለኪያ ነበር፡፡
አቤት ስልክ እንዴት እንደሚከበር ! እንደሚፈራ.! ያኔ ኔትወርክ እንጂ ስልክ አልነበረም፡፡ዛሬ ግን ስልክ እንጂ ኔትወርክ የለም።

እንግዲህ በሰፈራችን አንድ የቤት ስልክ ብቻ ነበረ ያለው፤ ስሙ ደግሞ “የአባዬ ስልክ”፤ ብዙው የሰፈር ሰው የእኔን እናት ጨምሮ በዚህ ስልክ ነበር የሚጠቀመው፤ ደግሞ ድምፁ የትናየት እንደሚሰማ…ኪሊሊሊሊሊሊሊሊ ሲል የመንደሩ ሰው ሁሉ ሥራ ያቆማል፡፡ ወጣቶች ፍቅረኞቻቸው የደወሉ መስሏቸው የያዙትን ሥራ እርግፍ አድርገው ጆሮና ልባቸውን ያቆማሉ፣እናቶች ሊጥም እያቦኩ ከሆነ ነጭ የቦክስ ጓንት ያጠለቁ መስለው ብቅ ይላሉ፡፡ የአባዬ የስልክ ድምጽ መቼም አይረሳኝም፡፡ አሁን የመጡ ስልኮች ቢዘፍኑ ሲንቀጠቀጡ የአባዬን ስልክ ድምፅ
ከአዕምሮዬ ሊፍቁት አልቻሉም፡፡

ስልኩ ሲጮኸ ልጆቻቸው አረብ አገር ያሉ እናቶች ልባቸው ይሰቀላል…፤ እናቴ ራሷ “ አቡቹ !
እስቲ እሱን ቆርቆሮ ቀንሰው” ትላለች፤ ቴፑን ማለቷ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄ ሁሉ ሰው እንዳቆበቆበ የአባዩ ልጅ ቡጡጡ በራቸው ላይ ትቆምና “እማማ ፋጤ ስልክ ! ከውጭ ነው ቶሎ በሉ!” ብላ ትጮሀለች፡፡ እማማ ፋጤ ወደ አባዬ ቤት ሲሮጡ ሌላው ጎረቤት ወደየስራው ይመለሳል፤ስልኩ በተደጋጋሚ የሚጮኸው ለበዓል አካባቢ ነው፤ በተለይ ለአዲስ ዓመት!

ቀላል ስልክ እንዳይመስላችሁ፤ በዚህ ስልክ ስንቱ ከውዱ ጋር አውግቷል፤ ስንቱ የውዱን
መርዶ ተረድቶ በድንጋጤ ስልኩ የተቀመጠበት ጠረንጴዛ ስር ተጠቅልሏል፤ ስንቱ ከጠፋ
ዘመዱ ተገናኝቷል፤ ስንቱስ ብር እንደተላከለት ሰምቶ ፈንጥዟል! ኧረ ስንቱ! ወደ አባዬ ቤት
ሲንደረደር እንቅፋት አንግሎት ባፍጢሙም የተተከለ፣ ጥፍሩ የተነቀለ…አለ፡፡

ለምሳሌ የአረጋሽ ጥፍር ተጣምሞ የቀረው ወደ አባዬ ቤት ስትሮጥ እንቅፋት አንግሏት ነው፡፡ አረጋሽ
ህመሙን ቻል አድርጋው ስልኳን እናገረችና ልክ ስልኩን ስትዘጋው፣ “ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ ብላ ጮኸች፡፡ መርዶ የሰማች ነበር የምትመስለው፡ በኋላ ሲጣራ ከስልኩ በፊት ለመታት
እንቅፋት ነው ያለቀሰችው፡፡ ጥፍሯ ግን ተጣምሞ ቀረ፡፡

ይሄ ስልክ ስልክ ብቻ አይደለም፣ ጩኸቱ የምስራች ነው! ጩኸቱ መርዶ ነው፡፡ ከመንደሩ
በላይ ያለው የጊዮርጊስ ቤተከርስቲያን ደውል ድምፅ የአባዬን ስልክ ጩኸት ያህል ግርማ ሞገስ የለውም
ለመንደርተኛው:: የኛን መንደር ሰዎች ወፍራም እንጀራ፣ ደንዳና ናፍቆትና ፍቅር በቀጭን የስልከ ሽቦ ውስጥ ተጉዞ የሚያርፍበት ኬላ የት ነው ሲሉን “የአባዩ ቤት እንል ነበር ።

ይህን ስልከ በጉጉት ከሚጠብቁ ቤተሰቦች መሃል የእኛ ቤተሰብ አንዱ ነበር፡፡ አባቴ ለሥራ ከእኛ
ርቆ ይኖር ስለነበር እኛ ልጆቹን የሚመከረው ለሚስቱም የሆድ የሆዱን የሚናገረው በአባዬ
ስልክ ነበር፡፡ እንደውም ግንባር ቀደሙ የእባዬ ስልክ ተጠቃሚ ቤተሰብ የእኛ ቤተሰብ ነበር
ማለት ይቻላል። ታዲያ አባቴ ለበዓል ሲመጣ ለበአል የሆነ ነገር ይዞ ስለሚመጣ ስልከ ስንጠራ
ቤተሰባዊ ቃና ባለው መንገድ ነው፡፡ “ስልክ” ብቻ አንባልም፤ “እንዳይቆጥርበት ፍጠኑ ጋሼ
ነው ? የሚል ማስጠንቀቂያም ይጨመርበታል፡፡

ለምሳሌ አባቴ ሲደውል እናቴ ከፊት፣ እህቴ ከኋላ፣ ወንድሜ ቀጥሎ፣ እኔ፣ ትንሽዋ እህቴ
ተግተልትለን እንሄዳለን፡፡ መጀመሪያ እናቴ ናት የምታናግረው፤ ድምጿን ቀንሳ ፊቷ በሃፍረት በናፍቆትና በፍቅር ተጥለቅልቆ ብዙ “አዎ” እና “አይይ!” የበዛበት ንግግር ታደርጋለች፡፡

አዎ!
አዎ!
አዎ!

አይይይይይ!

የአባዬ ስልክ ደግሞ ለክፋቱ ይጮሃል፤ በአሁኖቹ የእጅ ስልኮች ቋንቋ ላውድ ስፒከር ላይ
ያደረጉት ይመስላል፡፡
“እንደምነሽ ! …ምነው ድምፅሽ ጎረነነ ? አመመሽ እንዴ የኔ እናት ?” ይላል አባባ፤
“አይይይይ! ደህና ነኝ! " ትለለች እናቴ፤ አንዳንድ የፍቅር ነገርም ለለሚናገር ቶሎ መሰናበት
ትፈልጋለች፡፡

ቀጣይ ተረኛ ትልቅ እህቴ ናት፡፡

“ምን ልላከልሽ"

"ስኒከር ጫማ"

"እሺ"

"ነጭ"

"እሺ የኔ ማር" ድምፁ ውስጥ ናፍቆት አለ፡

"እንደባለፈው ሰፊ እንዳታመጣ ባባ"

"እሺ የኔ ቆንጆ"

ወንድሜ ይቀጥላል...

"ታኬታ ጫማ ባለ ብሉኑን"

“ባለ ቡሎን ጫማ አለ እንዴ ?" ይላል አባቴ በግርምት፡

"እንክት!"

እሽ እፈልጋለሁ ! አንተ ብቻ እናትህን እንዳታስቸግር፡ በደንብ ተማር!"

እኔ አባትህን አናግር ስባል አላናግርም፡ አብሬ ሮጬ አባዪ ቤት ድረስ ሄጄ ግን ብሞት አላናግርምፀ እናቴ ትበሳጫለች፡፡

“እሺ ምን ላምጣልህ ይልሃል" ትላለች በብስጭት፡

"ምንም!” እንባዬ ይመጣብኛል፡ አባቴን እወደዋለሁ፡ ግን በስልኮ አላናግረውም፡፡ ለምን ቢባል መልስ የለኝም፡፡ የተባለው ነገር ሁሉ ሲመጣ ግን እህቴ ያንን ሁሉ ማብራሪያ ሰጥታ ጫማዋ ይሰፋል ወይ ይጠባታል፡፡ ወንድሜ ባለብሎን ታኬታ አያመጣለትም፡ ኧረ እንዲያ የሚባል ጫማ የለም!" ይለዋል አባባ፡፡ እኔ ግን ምንም ሳልናገር ምርጥ ነገር ያመጣልኛል፡ አባቴ እኔን ራሴን እስኪመስለኝ ምርጫው ልክ ነው፡፡

እኛ ሰፈር እንዲት ሴት ጎረመሰች የምትባለው በአባዩ ስልክ ቤተሰብ ወይም ዘመድ ያልሆነ ወንድ ከደወለላት ነው፡፡ ሁሉም ሴቶች ለፍቅረኞቻቸው የአባዬን ስልክ ነው የሚሰጡት። ወንዶችም አልፎ አልፎ ይሰጣሉ ፡፡ ታዲያ አባዬ ቤት የተወራችው ነገር ስልኩ እንደ ሜጋፎን እየጮኸ ምስጢሩን ስለሚዘራው ጎረቤቱ ጋር ወዲያው ይደርሳል፡፡

“ሮማን የያዘችው ልጅ ሹፌር ነው መሰል ሁልጊዜ ከተለያየ እገር ነው የሚደውለው?

“አትይኝም!"

"ሙች!...አንዴ ከጅቡቲ፣ አንዴ ከሞያሌ፤ ቢጡ ሲያወራ ሰምታ ነው የነገረችኝ፡፡ ሲሉ የአባዬ
ልጅ ናት፡ ማን ከማን ጋር ምን አወራ የሚለውን ለመንደሩ የምታዳርሰው እሷ ናት፡፡

እንዲህ እየተባለ በቃ የተወራው የተደረገው ሁሉ ሰፈሩ ውስጥ ይናኛል፡፡ አንዲት ሴት ወይም
ወንድ በከባዬ ስልክ ካልተደወለለት ጉርምስናው እውቅና አያገኝም፡፡

አንዲት ሴት ስልክ ማናገር እና አለማናገሯ የፀባይ መለኪያ ሆኖ በመንደርተኛው ያስወቅሳታል፡፡
አልያም ያስመሰግናታል፡፡ “ውይ እሷ አንገቷን የደፋች፣ አባዩ ቤት አንድ ቀን ረግጣ አታውቅ
"ይባላል፡፡ ወይም “እች ልጅ የአባዩን ቤት አዘወተረች፤ መዘዟን እንዳትመዝ” ይባላል፡፡ ታዲያ
የአባዬን ቤት ከማይረግጡ 'ጨዋ ጎረምሶች መሃል አንዱ እኔ ነበርኩ፡፡ ስምንተኛ ክፍል ስደርስ
ግን ጨዋነቴ ተገሰሰ፡፡

የስምንተኛ ከፍል የባዮሎጂ አስተማሪያችን እትዬ መክሊት በጣም አይናፋር ሴት ነበረች፡፡
ምእራፍ ዘጠኝ የስነተዋልዶ አካላት የሚል ርእስ ላይ ስንደርስ ፊቷ ቀልቶ እያፈረች ስታስተምረን
ትዝ ይለኛል፡፡

“የስነ ተዋልዶ አካላት እንግዲህ..ያው…ወንድ እና ሴት ...ያው…” ጭንቅ ይላታል እትዬ መክሊት፣ እኛ ደግሞ ጆሮ ብቻ እንሆናለን፡፡ ስልሳ የምንሆን የእንድ ከፍል አጉል እድሜ ላይ ለምንገኝ ተማሪዎች ይሄ ጉዳይ የነፍስ ጉዳይ ነበር የምንጓጓላት፣ ለመስማት የምንሰስትለት፤ የስነተዋልዶ አካል ነገር ልባችንን ሰቅሎት፣ ትንፋሻችንን ውጠን እንቁለጨለጫለን፡፡ በክፍለ ጊዜው መርፈ ቢወድቅ ይሰማል ፀጥታው፡፡

“ውይ…ምነው ሁልጊዜ እንዲህ በትኩረት በተከታተላችሁ…! አያችሁ መማር ለራስ ነው፤ ትምህርት አገርን ይቀይራል፡፡ ያደጉት አገሮች ዝም ብለው አላደጉም፡፡ …ትምህርት…" ኤጭጭ እኛ ስለ ስነተዋልዶ አካላት ለመስማት ጓጉተን እትዬ ምክር…መክራ፣ መክራ ምከሯ ሲያልቅባት
👍35👏1