#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
በሰፊ ውብ አፏ እየሳቀችብኝ፡ እየወደደችኝ ድንገት ሳቁን እየተወች አንድ ነገር ልነግርህ እፈልግ ነበር» አለችኝ ንገሪኝ
እንዳትቆጣ፡፡ ወንድ ሆነህ አትስማኝ፡ ደራሲ ሆነህ አዳምጠኝ እንጂ
«እሺ»
"Parole d'honneur?"
"Parole d'honneur!"
«አንተን እወድሀለሁ። ከልቤ አፈቅርሀለሁ፡፡ ግን ፖልን ልረሳው
አልችልም። የመጀመሪያዬ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን፣ ሳልጠግበው
ስለሄደብኝ ጭምር ይመስለኛል። «ይገባሀል?»
«ይገባኛል»
«እና አንድንድ ጊዜ ይናፍቀኛል፡፡ ይመስለኛል፣ በውስጤ
የልጃገረድነቴ ጊዜያት ከሱ ጋር ተዋህዷል፡፡ እና ያ ጊዜያት
ሲናፍቀኝ፣ ፖል ይናፍቀኛል። ከልቤ ላወጣው ልረሳው እሞክራለሁ።
ግን የምችል አይመስለኝም፡፡ የምልህ ይገባሀል?»
«ይመስለኛል»
«ስለዚህ ፖልን የሚመስል ሰው ሁሉ ደስ ይለኛል፤ ይስበኛል።
... እና ስለ ባህራም ልነግርህ እፈልጋለሁ፡፡»
ይናገራል ብላ ዝም አለች። መናገሩ እየከበዳት ሄዷል። ዝም
ብዬ ሳያት ቀጠለች
«አንተ ነህ ባህራምን እንድወደው ያረግከኝ፡፡ ስለሱ ብዙ ብዙ
አወራህልኝ። አራት ወር ሙሉ አወራህልኝ፡፡ ከወሬህ እንዳየሁት፣
በጣም በጣም ታከብረዋለህ። ግን እንደማውቅህ አንተ ማንንም
አታከብርም፡፡ ስለዚህ፣ ይሄ ባህራም እንዴት ያለ ሰው ቢሆን ነው? አልኩ። አንዲት ሴት እንዲህ ካለች ደሞ መመለሻ የላትም። ይህን ያባሰው ምንድነው? ከወሬህ እንደተገነዘብኩት ባህራም እንደ ፖል ያለ ሰው ነው። እንደሌላው ሰው ከተራ ጭቃ ተጠፍጥፎ አልተሰራም፡፡ ጀግናዎቹ ከሚሰሩበት ከልዩ ጭቃ ተቀርፆ፣ በልዩ ንፁህ እሳት ውስጥ ነው የተጠበሰው። ባህራምን እንደዚህ አድርገህ
ነው ያሳየኸኝ
«አንተ ያንን ያህል እያከበርከው፣ ከፖል ጋር ያንን ያህል
እየተመሳሰለ፣ እንዴት ላይለኝ ይችላል? እኔ ደሞ
እንደምታውቀኝ ነኝ:: እንዴት ላልመኘው እችላለሁ?»
«ፍቅር ይዞሻል?»
ራሷን በሀይል
እየነቀነቀች፡ ከኋላዋ ጥቁር ሀር ፀጉሯ እየተወዛወዘ፣ የደስታ ሳይሆን የመሰቃየትና የመደናገር ፈገግታ ውብ አፏን እየሸመቀቀው
እኔ እንጂ! እኔ እንጃ! እኔ እንጃ!» አለችና ራሷን ጠረጴዛው ላይ
ደፋች
ረዥም ፀጥታ
እጄን ሰድጄ ራሷ ላይ አሳረፍኩት። ቀና ብላ አየችኝ፡፡ እምባዋ
ይወርዳል
«ሶስት ፍቅር አንድ ላይ ሊይዝ ይችላል?» አለችኝ
“ሴትዮዋ ተራ ከሆነች አይችልም» አልኳት
ጠረጴዛው ላይ የነበረ እጄን ወስዳ ከጎንጯ ጋር እያተሻሸት፣
በእምባዋ እጄን እያረጠበች፡ በተጨነቀ ድምፅ
«ብዙ ጎዳሁህ፣ የኔ ቢራቢሮ?» አለችኝ
ግድ የለሽም አልኳት
«አለኝ እንጂ። ላንተ ብዙ ግድ አለኝ፡፡ ለዚህ እኮ ነው
የምነግርህ፡፡»
«አውቃለሁ»
ለኔ እንዴት ጥሩ ነህ! አሁን ምን ይሻለኛል?»
ቆንጆ ነሽ። ተወዳጅ ነሽ፡፡ ለምን አትወጂውም?»
በመሀረቤ እምባዋን እየጠረገች
«አንተስ? አትቀየምም?»
ሌሎች ጋ ትሂጂ የለ? ስለዚህ ለኔ ያው ነው»
ውይ! እንዴት ደግ ነህ!?»
«ለምን?»
ውሸትክን ነዋ» ተናፈጠች
እኔ እንድደሰት ብለህ
ትሰቃያለህ፡፡»
«የምን ስቃይ?»
መሀረቤን አጥፋ እየመለሰችልኝ
«እንግዲህ አትዋሽ። ይበቃሀል። አውቅሀለሁ'ኮ። ከምትገምተው
በላይ አውቅሀለሁ፡፡ ፊትህ ላይና አይኖችህ ውስጥ ስንትና ስንት ነገር ይታየኛል መስለህ።»
«ምን ይታይሻል?»
«ስለባህራም ስነግርህ በብዙ ነው ያዘንከው::
«ላንቺ ነዋ ያዘንኩልሽ፡፡
«እሱም ታይቶኛል። ግን ለራስህም በሀይል በመሰቃየት ላይ ነህ፡፡ እና በጣም አዝናለሁ፡፡ እንዲህ በመሆኔ በጣም አዝናለሁ፡፡»
«በማዘን የትም አይደረስም፡፡»
አውቃለሁ የኔ ቆንጆ:: ግን ማዘን አይቀርም፡፡»
ዝም ዝም ሆነ
«በኔ ብቻ ሳይሆን በባህራምም ጭምር ነው ያዘንከው። ልክ
ዝም አልኳት
«እንግዲህ ልንገርህ፡፡ እውነቱን ብታውቅ ይሻላል። ልንገርህ?»
«እሺ፡፡»
«ያን እለት ማታ ያ ሰውዬ ባህራምን ሊገድለው አልመጣም?
እና አንተ ኒኮልን ይዘህ ማርዕይ አልሄድክም? ከኒኮል ጋር
ምንም አልሰራችሁም? እውነት ተናገር፡፡»
«ምንም አልሰራንም፡፡ ይልቅ ቀጥዪ።»
«እና ሰውየውን ሲገድለው አላየሁም? እሱን ነግሬሀለሁ። እና
ከዚያ ወደ ቤት ሄድን፡፡ ባህራም ልክ ምንም እንዳልስራ በእርጋታ
ሶፋ ላይ ተቀመጠ። እኔ መጠጥ ሰጠሁትና ሶፋው ላይ አልጋ ብጤ
አነጠፍኩለት፡፡ አንጥፌ ስጨርስ 'እንግዲህ እዚህ ውስጥ ይተኛል።
ነብስ ገድሏል፤ ግን እዚህ ውስጥ ይተኛል። ከጀግና ጋር ነው'ኮ
ያለሁት። ከነብሰ ገዳይ ጋር ነው ያለሁት ብዬ አሰብኩ፡፡ ዘወር ብዬ
አየሁት። አንተ እንደ ነገርከኝ ነው። ዝም ሲል የኢራንን ሻህ
ይመስላል። ግን ማን ያውቃል? ጀግና ስለሆነ አንድ ቀን የኢራንን
ሻህ ይገድለው ይሆናል'ኮ!' ብዬ አሰብኩ
«እና በሀይል ተመኘሁት፡፡ ፍትወት ያንን ያህል አንቆ ይዞኝ
አያውቅም፡፡ ራሴን 'ተይ እንደሱ አታርጊ! - ተይ!'
እያልኩ
ከተቀመጠበት ሄድኩና እግሩ አጠገብ ተምበርክኬ ወደላይ አየሁት።
እንደ ቄስ እጁን ራሴ ላይ አሳረፈና
«ምን ሆነሻል?» አለኝ
ቀስ ብዬ ተነሳሁና አፉ ላይ ሳምኩት
አሁንም «ምን ሆነሻል?» አለኝ። ግን ገብቶታል
«ፈልጌሀለሁ» አልኩት
«እኔ አልፈልግሽም» አለ
«አውቃለሁ ትፈልገኛለህ፡፡ ትፈልገኝ የለ?»
«አዎን፡፡ ካየሁሽ ጀምሮ እንደፈለግኩሽ ነው::»
«ይኸዋ፡፡ አለሁልህ!»
«አይሆንም!»
«ለምን አይሆንም?»
«ምክንያቱን መቼ አጣሽው» አንተን ማለቱ ነው
«እሱ ንደሆነ ግድ የለውም» ኣልኩት
«እኔ ግድ አለኝ!»
«ለምን?»
«ጓደኛዬ ነው:: እፈልግሻለሁ፡፡ ግን እሺ አልልሽም። ስለዚህ
እርሺው!»
«አልረሳውም፡፡ ልረሳው አልችልም፡፡ ልረሳው አልፈልግም።
ሌሊት እመጣለሁ!» አልኩትና ሄጄ አልጋዬ ውስጥ ገባሁ፡፡ ልተወው
ቆረጥኩ። ምናልባት አንድ ሰአት ያህል ቆየሁ። ከዚያ በላይ ግን
ልቆይ አልቻልኩም፡፡ እንደዚህ አላስችል ያለኝ እሱ ስለሆነ ብቻ
ነበር፣ ወይስ ሰው ሲገድል ስላየሁት ነበር? አላውቅም፡፡ የሆነ ሆኖ፣ እሱ እዚያ ተጋድሞ እኔ እዚህ ሆኜ ልታገስ አልቻልኩም
ራቁቴን ወጣሁ፡፡ ሽቶ ተቀባሁ፡፡ ከመኝታዬ ወጣሁ፡፡ የንግዳ
ቤቱን መብራት አበራሁ። እንቅልፍ አልወሰደውም ነበር። በቀጥታ
ሄድኩና ከበላዩ ቆምኩ፡፡ ወደላይ አየኝ፡፡ ሲያየኝ ብዙ ጊዜ ቆየ፡፡
እጁን ሰደደ። ጭኔን ይዞ ወደታች ጎተተኝ
ካሸነፈኩት በኋላ ወደ አልጋዬ ሄድን፡፡»
ዝም አለች፡፡ ያችን ሌሊት እንደምታስታውስ ያስታውቃል፡፡
እንዴት ያለች ሌሊት ነበረች ይሆን? ብጠይቃት እንደማትነግረኝ
እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ስለሌሎቹ ወንዶች በሰፊው ትንገረኝ እንጂ፣
ስለነሱ ጥቃቅኑን ስጋዊ ተግባር ሳይቀር ትዘርዝርልኝ እንጂ፣
ስለፖልና ስለ ባሀራም አትነግረኝም፡፡ እኔም ስለነሱ መጠየቅ ልክ አልመሰለኝም፡፡ ዝም አልኩ። ቀጠለች
«ስለሌሊቱ ልንገርህ እንዴ?» አለችኝ
«ልትነግሪኝ ትፈልጊያለሽ?»
«አልፈልግም። ከፈለግክ ግን እነግርሀለሁ።»
ይህን ያለችኝ «ሳትፈልጊ ብትነግሪኝ ደስ አይለኝም»
እንደምላት አውቃ ነው እንጂ፡ ንገሪኝ ብላትም እንደማትነግረኝ
አውቃለሁ
«ሳትፈልጊ ብትነግሪኝ ደስ አይለኝም» አልኳት

👍16🤔3
ዝም አለች። እኔም ዝም አልኩ
«እንግዲያው ከአልጋ ውጪ የሆነውን ልንገርህ፡፡»
«ባሀራም ጧት ተነስቶ ገላውን ታጥቦ ቁርስ ከበላን በኋላ
«አንድ ነገር ላስረዳሽ እፈልጋለሁ። ፍቀጂልኝ አለኝ
ምንድነው?» አልኩት
«በጣም ቆንጆ ሴትዮ ነሽ፡፡ ማንንም ወንድ ማዘዝ ትችያለሽ፡፡
ባንቺ መገዛት በጣም እፈልግ ነበር። ግን ትላንት ሌሊት
የመጨረሻችን ሌሊት መሆኑን እወቂ» አለኝ
«ለምን?» ብለው
«እያወቅሽ አትጠይቂኝ። የሱን ስም እዚህ ባላነሳ ፈቃዴ ነው።
ትላንትም ነግሬሽ ነበር። ትላንት ልታሸንፊኝ ቻልሽ። ከንግዲህ
ወዲያ ግን በጭራሽ እንዳትጠጊኝ። አደራሽን። ስለሌሊቱ በጣም አመሰግንሻለሁ፡፡ ግን በጣም በጣም ይቆጨኛል!» አለኝ
«እኔ ነኝ ሊቆጨኝ የሚገባው:: ግን ፈፅሞ አልቆጭም አልኩት
«አውቃለሁ፡፡ የተለያየን አይነት ሰዎች ነን። አየሽ፣ እኔ በሰው
ልጆች ብዙ እምነት ኣለኝ። ለምሳሌ፣ እሱ ኒኮልን ቢፈልጋትም ለኔ ብሎ እንደሚተዋት እርግጠኛ ነኝ፡፡ ስለዚህ፤ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ታውቂ የለ?»
«አላውቅም አረ፡፡ ምን ማድረግ አለብህ?»
የበደልኩትን ጓደኛዬን ሂጄ ይቅርታ መለመን አለብኝ»
«ምን?»
«ሄጄ ይቅርታ እለምነዋለሁ። ትላንት ማታ የሰራሁትን
እነግረዋለሁ»
“ይቅርታ ባያረግልህስ?»
«ያረግልኛል»
ባያረግልህስ?»
«እሱ እንግዲህ የራሱ ፋንታ ነው»
«ጓደኝነታችሁ አበቃ ማለት አይደለም?»
«ጓደኝነታችን በውሽት ተደግፎ ከሚቀጥል ቢያበቃ ይሻላል።»
«ይህን ስትነግረው እሱ ይጎዳ የለም?»
«ጠንካራ ነው። ምንም ነገር ሊጎዳው አይችልም። ወንድ ነው»
አለኝ፡፡ አየህ፤ እኔ ብቻ አይደለሁም የብረት ሰው ሆነህ የምትታየኝ»
«ቀጥይ» አልኳት
« እና የኔንስ ነገር እንዴት ታረጋለህ? ብትነግረው ይተወኛል።
እኔ ደሞ እወደዋለሁ። ታድያ፣ ተደስተህብኝ ስታበቃ፣ ለጓደኝነትህ
ንፅህና ስትል የኔን ፍቅር ታፈርስብኛለህ?' አልኩት፡፡»
« ያምነኛል' አለኝ “አንቺ አማርሽኝና በጉልበት ተኛሁሽ
ብል፣ ማንም ወንድ ያምነኛል
ሊሄድ ሲል « አአንድ ነገር ልለምንህ 'ባክህን' አልኩት»
ምን?»
«እኔ ራሴ እንድነግረው ፍቀድልኝ»
«እኔ ብነግረው ይሻልሻል» አለኝ
«ግድ የለህም አልኩት
«እሺ» አለኝ
«ግን እውነቷን ነው የምነግረው» አልኩት
«ለምን?» አለኝ
«ጓደኝነት ብቻ ነው በእውነት ውስጥ መኖር ያለበት? ፍቅርስ
እውነት ኣይወድለትም?» አልኩት
ሳቅ አለ። «ይቅርታ አርጊልኝ፡፡ እንዲህ አይነት ፍቅር
አልመሰለኝም ነበር። እንግዲያው አንቺ ብትነግሪው ይሻላል» አለኝ
«እና እንዲህ ሲለኝ የባሰውን ወደድኩት። ምን ይሻለኛል?»
አለችና፣ እንደገና ራሷን ጠረጴዛው ላይ ደፋች ዝም አልኳት። እንደዚህ ሆነን ረዥም ጊዜ ቆየን። እንደተደፋች
ቦዩ መጥቶ ከኋላዋ ቆመና ይገላምጠኝ ጀመር፡፡ ባለ ፀጉራም እጅ ጎረምሳ ነው። ምናልባት ሊደበድበኝ የሞከረ እንደሆነ ለመከላከል
ያህል ቢራ የሞላ ብርጭቆዬን ጨበጥኩ። በልቤ «አብሾዋም
ፈረንሳይ!» አልኩ
ሲልቪ ቀና አለች። አሁንም እምባዋ ይወርዳል። መሀረቤን
ሰጠኋት፡፡ እምባዋን ስትጠርግ ቦዩ እሷ ልታየው ወደምትችልበት
ቦታ (ወደኔ አጠገብ) ራመድ አለና፣ እኔን ቀሚቆጣ፣ ግን እሷን
በሚያባብል ድምፅ
“Mademoiselle a besoin de u፡elue chose?” አለ («ማድሟዜል
የሚያስፈልጋቸው ነገር አለ?»)
ወደሱ ተመለከተች። የተጨበጠ ፀጉራም እጁ ታያት። ገባት።
“Merci, monsieur , je suis avec un ami” («እግዜር ይስጥልኝ መስዬ፣ ከጓደኛዬ ጋር ነኝ») አለችና፣ በብሩህ ፈገግታ እጇን ሰዳ እጄን እየያዘች “un tr cher ami” አለች። («በጣም ውድ የሆነ ጓደኛ»)
ቦዩ በለዘበ ድምፅ “Pardon momsieur” አለኝና ሄደ፡፡ አንዳንዶቹ ፈረንሳዮች ግሩም የሆነ ጠባይና አስተዳደግ አላቸው
ሲልቪ ፈገግታዋ እየጠፋ
«ምን ይሻለኝ ይመስልሀል?» አለችኝ
«በሱ በኩል ተስፋ የለሽም፡፡ ተይው» አልኳት
«ከዚህ ውሰደኝና ውድድ አርገኝ 'እስቲ። ትችላለህ?»
«ለምን አልችልም?»
«ይህን ሁሉ ከነገርኩህ በኋላ?»
«አሁንም እወድሻለሁ፡፡»
«አውቃለሁ፡፡ እኔም እወድሀለሁ፡፡»
ከፍለን ስንወጣ የቦዩ ፈገግታ ሸንን ፍቅራችንን ወዶልናል...
💫ይቀጥላል💫

👍22👎3
#ሚስቴን_አከሸፏት
፡
፡
#ሶስት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
...ከዚህ ሁሉ የሚከፋው ግን ወሬዋ ..! ወይኔ ወሬዋ ! ሰው እንዴት በቅሌቱ አንቱ ለመባል ይጥራል በእግዚአብሔር። እኔ ጥሎብኝ ዋው! እሷ እኮ ተጫዋች ምናምን.. ለመባል ብሎ የሚቀባጥር ሰው ያስመርረኛል።
“ዋው እንትናዬ ! እንዴት አባቱ የሚጥም ተጨዋች መሰለሽ ...! ሙድ ያለው ጨዋታው ብትይ፣
የሚወስደኝ ቦታ ብትይ፣ በዛ ላይ አልጋ ላይ ሂሂሂሂሂሂሂሂሂ” አፏን እስከመጨረሻው ከፍታ
ታሽካካለት…። ይህቺን ሴትዮ ሳስባት ከእናትና ከአባት ሳይሆን እንደሙጃ ሕይወት ይሉት ዝናብ
ዘንቦባት ድንገት ሜዳ ላይ ቱግ ብላ የበቀለች አረም ነው የምትመስለኝ የሰው አራሙቻ !
ከፌቨን ጋር የተዋወቁት በአንድ የግል ድርጅት ሲሠሩ ነበር።
“ኦ ማሜ ማለትኮ እናት ማለት
ትላታለች ሚስቴ ይህቺን ሴት ስታደንቃት .. !ይታያችሁ እናት !ለነገሩ እናት” ናት።
"ፌቪዬ የኔ ማር…! ይሄን ሽንኩርት የሚባል ነገር እየከተፍሽ ቆንጅዬ እጅሽን ልታበላሽው ነው…።”
ትላታለች። ፌቨን ልታስተናግዳት ጉድ ጉድ ስትል እኮ ነው፤ ምክሯ ሁሉ ግራ ነው የሚያጋባው።
አንዳንዴ ደግሞ እኔና ፌቨንን እየተመለከተች፣ “እንዴ እናንተ ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ፤ የምን እንጀራ መጠፍጠፍ ነው .. የቀን ሠራተኛ ቅጠሪና ወጥ ምናምን ሠርታ ፍሪጅ ውስጥ ማስቀመጥ፣ እንጀራ ከሱቅ ገዛ አድርገሽ መጠቀም፤ እንደው አበሻ ጓዳ ገብቶ ፍዳውን ካልበላ ካላቦካ፣ ካልተጨማለቀ እሳት ላይ ካልተጠበሰ የበላ አይመስለውም፤ ... አይደል እንዴ አብርሽ? ሂሂሂሂሂሂ …ይህቺን የመሰለች ማር የሆነች ልጅማ ሽንኩርት አታስከትፋት…።”
ፌቨን ምሳ ሠርታ ይህቺ መካሪ በደንብ እያጣጣመች ከበላች በኋላ መልሳ እንዲህ ትላለች፣
“ላለለት ሰውማ ማን እንደ ቤት ምግብ እናቴ ትሙት (እናቴ ትሙት ብሎ መሐላ አይቀፍም?) ... ውይ
እንዴት ርቦኝ ነበር። ጥሞኝ በላሁ። ፌቪዬ ከአልጫዋ ትንሽ ጨምሪልኝ ትላለች። እውነቱን ለመናገር
እንደዚህ ስትል ታሳዝነኛለች። ሴት ራበኝ ስትል አልወድም። በዛላይ አንዲት ሴት ያውም ኢትዮጵያዊት
ሴት የፈለገ የሞራል ውድቀት ውስጥ ብትገባ የዚህ ዓይነት አኗኗር የምትመርጥ አይመስለኝም። አንድ
ከሕይወቷ መጽሐፍ የተገነጠለ የኑሮ ገጽ ይኖራል፣ ወይም አንዱ ደደብ የሕያውነት አንቀጿን በክፋት
ሰርዞታል። ወዶ አይደለም ወሬዋ የሚምታታው..
በጣም ቆንጆ ናት። ያውም ውብ የሚባል ዓይነት። ላግባ ብትል እግሯ ላይ ወድቆ የሚያገባት ሺ
ከሚሊየን ነው (በዚህ ዕድሜዋ እንኳን ላግባ ብትል የሚሻማባት ጎረምሳ ብዙ ይመስለኛል…) ግን
ከርታታ ናት። በቃ እዛ ስታድር፣ እዚህ ስትውል፣ ሽሽቷን ልታዘምነው አንዴ ትልልቅ ሆቴሎች፣ ሌላ ጊዜ ሌላ የመዝናኛ ቦታዎች ብትንከራተትም ዓይኗ ላይ እንደሩቅ አገር እሳት ቢል ቢል ሲል የሚታየው አምሮት … እፎይ ማያ ጎጆ መናፈቋ ነው!!
እናም ፌቨንን ፊቴ እንዲህ አለቻት፣ ፌቪ ማር…!ይሄ እንቁላል ቅርፅ ያለው ፊትሽ በዚህ ፀጉርሽ
ባይሸፈን ኖሮ መልክሽ የሚያሳብድ ይሆን ነበር። ብዙ ሳይሆን ትንሽ አጠር …፤ ምን አሁን እኮ ፀጉር ጀርባ ላይ ለቅቆ አንበሳ መምሰል ትንሽ ጊዜው አልፎበታል። ዳሩ አንቺ ወጣ ብለሽ አታይ፤ እዚህ ባልሽ ጋር ታፍነሽ እየዋልሽ ሂሂሂሂሂሂ። ቀልድ አልብሳ መርዟን ረጨችው።
ማታ እንደተኛን ፌቨን ድንገት ከጎኔ ቀጥ ብላ ደረቴ ላይ አገጯን አስደገፈች። ጥቁር ፀጉሯ ፊቴ ላይ
ተነሰነሰ።ዓይኖቼን ጨፍኜ የፀጉሯን ዝናብ ተጠመቅኩት በደስታ … እንደ ሩፋኤል ፀበል።
“አብርሽዬ…”
“እ!”
“ዓይንህን ግለጣ” አለች፤ ገለጥኩ። ከጥቁር ደመና ውስጥ ብቅ ያለች ጠይም ፀሐይ ከበላዬ።
“ማሜ ያለችው ነገር ግን አልገረመህም፤ እንዴት እስከዛሬ አላሰብኩትም…?”
“ምኑን?” አሁን እኔም ነቃ አልኩ።
“ፀጉሬን ባሳጥረው እንደሚያምርብኝ ፀጉር የምትሠራኝ ልጅም ደጋግማ ነግራኛለች” ፊቷ ላይ ያለው
ስሜት የመጠየቅ ሳይሆን ፀጉሯን የምትቆርጥበት መቀስ እንዳቀብላት የመጠየቅ ዓይነት ያበቃለት መርዶ ነበር። ሁሉም ነገር ቅድሚያ የሚቆረጠውም የሚቀጠለውም ልብ ላይ ነው።
“ፀጉርሽን እንድትቆረጭ አልፈልግም። እንኳን መቆረጥ ፀጉርሽን ስታበጥሪ ማበጠሪያው ላይየሚቀሩት የፀጉር ዘለላዎችሽ ያሳዝኑኛል። እና ለእኔ የምታምሪኝ እንደዚህ ስትሆኝ ነው። ፀጉርሽን ከዓይኖችሽ፣ ከአፍንጫሽ እና ከእነዚህ ውብ እጅና እግሮችሽ እኩል እወደዋለሁ፤ እንደ አንድ የሰውነትሽ ክፍል ነው
የማየው” አልኳት ጣቶቼን ፀጉሯ ውስጥ እያርመሰመስኩ።
“እንደዚህ አንበሳ ስመስል ነው የምትወደኝ?” ብላ በማሾፍ ከተናገረች በኋላ ፀጉሯን በጣቷ
መነጨረችውና ከንፈሬን ስማኝ ደረቴ ላይ ልጥፍ ብላ ተኛች። (ይሄ መሳም ቃሌን መስማት ይሁን
ወይስ ስሞ መሸጥ ዓይነት ይሁዳዊ መሳም አልገባኝም)። አተኛኘቷን ሳየው የልብ ምቴን የምታደምጥ ነበር የምትመስለው እንቅልፍ ወሰዳት።ስንተኛ ፀጉሯን ስለማታስይዘው እንዲሁ ነው የምትተኛው።በእንቅልፍ ልቧ በተንቀሳቀሰች ቁጥር የፀጉር መዓበል ትራሱ ላይ ሲነሳ ከትራሱ ላይ እየተንሸራተተ ፍራሹ ላይ ሲርመሰመስ ነፍሴ ሐሴት ታደርጋለች።
ፀጉር እኮ መንፈስ ነው። በተለይ የሴት ልጅ ፀጉር። የቅዱሳን ሥዕልላይ ከራሳቸው በላይ እንደሚታየው የብርሃን አምድ …. የሴት ልጅ ፀጉርም ባፈቀራት ወንድ ብቻ የመንፈስ ዓይን የሚታይ የውበት አምድ
ነው ! የሴት ልጅ ሰውነት በማይታይ የክብር ብርሃን የተከበበ ሕያው ቅድስና ነው። ትልቁ ችግር የብዙ ሴቶች ፍላጎት ለብዙኃኑ ቆንጆ ሆኖ የመታየት መሆኑ ነው። ብዙኃኑ አድናቂ ነው። ብዙኃኑ ጤዛ የሆነ አብሮነቱ ከዓይን ሲርቁ አብሮ ይከስማል። ብዙኃኑን የኔ ከምንለው ሰው ጋር በአንድ ሚዛን ልናስቀምጠው አይገባም። ለብዙኃኑ ብዙ ሆኖ መገኘት በመፈለጋቸው አንዱንም ሳይዙት ምንም ሆነው እንዲቀሩ ያደረጋቸው ብዙ ናቸው።
ፌቨን ተኛች። ስትተኛ የተመጠነ አተነፋፈስና ሰላም ያለው እረፍት ፊቷ ላይ ይረብባታል። የፌቨን
እንቅልፍ ሰላም ባለው ሰፊ ባሕር ላይ ያለ ምንም እንቅስቃሴ በጀልባ እንደመንሳፈፍ ይመስለኛል።ተኝታ ሳያት ታሳሳኛለች። እና ቀስቅሳት ቀስቅሳት ይለኛል። ለብቻዬ ትታኝ ወደሆነ ሰላም ወዳለው ዓለም የሄደች ይመስለኛል፤ እኔ ግን በሐሳብ ነጎድኩ። ወደኋላ … ፌቨንን ዓይቻት ፍቅር የጀማመረኝ
ሰሞን ከሩቅ ስመለከታት የሚገርመኝ ፀጉሯ ነበር። ድብን ያለ ጥቁርና ጠንካራ ፀጉር። ከርዝመቱ ብዛቱ። ከተዋወቅንና ከተቀራረብን በኋላ ደግሞ ፀጉሯ መሐል ጣቶቼ ጠፉ ማለት ዘበት ነው። አንገቷን ወደግራ ዘንበል ስታደርግ ፀጉሯ ወደ ግራ ይናድና በግራ ትከሻዋ አልፎ እየተርመሰመሰ የግራ ጡቷን
ይሸፍነዋል።
ፀጉር ቤት ቆይታ ስትመለስ የሆነ የተቃጠለ ፀጉር ሽታ አፍንጫዬን ያውደዋል። ያንን ሽታ እወደዋለሁ።
እንደውም በሴቶች ፀጉር ቤት ሳልፍ ይሄ የተቃጠለ የፀጉር ሽታ ሲሸተኝ ፀጉር ቤቱ ውስጥ ፌቨን ያለች ይመስለኛል። ፀጉር መተኮስ ማለት እኮ ለውበት አምላክ የሚቃጠል የፀጉር መስዋዕት እንደማቅረብ ነው። (የመረረ የፋሽን ጥላቻ ኖሮብኝ ሳይሆን ውበት ዋጋ እንደሚያስከፍል ለመግለፅ)
ጠዋት ከእንቅልፌ የቀሰቀሰችኝ ፌቨን ናት ቁርስ ሰርታ ሁልጊዜም እንዲሁ ነች። ቁርስ እየበላን
ድንገት ፍርፍሩ ውስጥ አልያም እንቁላል ጥብሱ ውስጥ የፀጉር ዘለላ ማግኘቴ አይቀርም። ዛሬም
ይሄው አንድ ቢመዘዝ የማያልቅ የፌቪን ፀጉር አገኘሁ።
ተሳሳቅን።
የግራ እጄን ጣቶች ወደ ዓይኗ አስጠግታ እየተመለከተች እንዲህ አለች፣ “ይሄ ሽንኩርት እጄን
"አሻከረው”።
ዝም አልኩ።
ዝም ተባባልን።

👍37
የዛች ዋጋ ቢስ ፍጥረት መንፈስ ቃል በቃል በመካከላችን ሥራውን እየሠራ ነው።
ማታ ከሥራ ስመለስ ፌቨን ፊቷ በሳቅ ተጥለቅልቆ ሶፋ ላይ ተቀምጣለች። ቤቱ በእጣን ታፍኖ ቡና ቀራርቧል። ፀጉሯን ተቆርጣ ወደ ቢጫ የሚያደላ ወርቃማ ቀለም ተቀብታዋለች። ዙሪያውን ጆሮዋ አካባቢ ተቀልብሶ ሲታይ ወርቃማ ኮፍያ ያጠለቀች ነበር የሚመስለው። ፈፅሞ አላማረባትም። የሆነ ነገሯ ተገፍፎ እርቃን ነገር ሆናለች። አንገቷ ወደ ላይ የተመዘዘ ይመስል ረዝሟል (የዚህች ልጅ አንገት እንዲህ የመሞቻዋን ቀን እንዳወቀች ወፍ የሰለለ ነበር እንዴ?)። ትከሻዋ የሆነ የተራቆተ ተራራ መስሏል። ትላንት ገና ዛፉ የተቆረጠ …። ፌቨን ነፍስ ይማር! ዘጋኝ። ማየት ዘጋኝ፤ መሳቅ ዘጋኝ፤ መኖር
ራሱ ዘጋኝ !
ጉዳዩ የፀጉር አይደለም..
“እሺ አሁንስ እንደሚያምርብኝ አመንክ…?” አለችኝ ድንገት ቆማ ወገቧን በመያዝ አንዴ ወደፊት አንዴ ወደኋላ እየዞረች በመውረግረግ ... ውበቷን ለማሳየት። እጄን ልኬ ፀጉሯን ነካሁት፤ ማረጋገጥ ፈልጌ
ነበር። እንደው የሆነ ተዓምር ነገር ሆኖ ጥቁር ፀጉሯ ከወርቃማው ኮፍያ ውስጥ ቁልቁል እንዲዘንብ
በልቤ እየፀለይኩ። የፌቨን ፀጉር በቦታው የለም። በቃ የለም። ፀጉሯ ናፈቀኝ። ፌቨን ናፈቀችኝ። የኔ
ፌቨን ከነጥቁር የፀጉር መጋረጃዋ በእጇ ወደ ኋላዋ መለስ የምታደርገው ጥቁር ዘንፋላ ፀጉሯ ጠፋ ...ተገለጠች ! ተገላለጠች። እናም ልዩነቷን አስቆርጣ ጥላ መንገድ ለመንገድ ትርፍርፍ ያሉትን ሁሉንም ሴቶች ሆነች ! ሁሉንም ለመሆን ወደ መንጋው ለመቀላቀል ነበር ይሄ ሁሉ ሩጫ ! እኔና ሁሉም ባለቀለም ፀጉሮች አንድ ቤት ያለን መሰለኝ። ቢሮ … ሱፐር ማርኬት … ካፌ ውስጥ ... ታክሲ ውስጥ .. ቡና ቤት ውስጥ ..የዘፈን ክሊፖች ውስጥ ስልችት ያሉኝ ሴቶች ቤቴም !! ቤቴ አደባባይ የሆነ መሰለኝ!
አካባጅ ሆኜ ነው ?… አይደለም !
“ተቆረጥሽው!” አልኳት፤ጥያቄ አልነበረም።
“አብርሽዬ ፀጉር ቤት የሚሰሩኝ ልጆች እንዴት እንደተገረሙ። ይሄን ያህል የሚያምርብሽ አልመሰለንም ነበር አሉ…።” አሉ አሉ አሉ አሉ አሉ … የፀጉር ቤት ሰራተኞች ብዙዎቹ ለሚሠሯቸው ሴቶች የሚሉት ተመሳሳይ ነገር፣ “ከምሠራቸው ሴቶች ፀጉር ያንቺ ይለያል ለተፈለገው ስታይል የሚሆን ምርጥ ፀጉር
… ምናምን” ሴቶቹ ደግሞ ያምናሉ። ይገርመኛል። እናም ፌቨንን ዝም ብዬ ስመለከታት ድንግልናዋን ሆነ ሌላ ሰው የገሰሰው ዓይነት ስሜት ተሰማኝ። ድንግልና ማለት የእኔ የግሌ ብለን የምናምንበት ጉዳይ እንደሆነ የገባኝ አሁን ነው።
ድንግልና የሥጋ ጉዳይ አይደለም። ማንም ሴት እድሜ ልኳን የምታስቀምጠው የቃል ድንግልና አለ።ለባሏ ብቻ፣ የኔ ላለችው ሰው ብቻ የምትናገረው። ደግሞም የውበት ድንግልና አለ። ፋሽንም ዘመንም የማይገስሰው። የኔ ለምንለው ሰው ብቻ ርካታ የተፈጠረ። ያንን ድንግልና ነው አስረክባ የመጣችው።
አካባጅ አይደለሁም። ፌቨን ራሷ ምስክር ናት። ስንቱን ጉድ፣ ወሳኝ የሕይወት ስንክሳር በቸልታ
ሳልፈው ታውቀኛለች። ይሄ ግን… ከዛ ቀን ጀምሮ ዘጋኝ ! ሁሉም ነገር ዘጋኝ።
“አዝናለሁ” አልኳት። የፊቴ መቀያየር አስደንግጧታል። ድንጋጤዋ ደደብ መስላ እንድትታየኝ አደረገኝ። ሚስቴ ደደብ ከመሰለችኝ ቃሉን በማሰቤ ራሱ ወይ እኔ በቁሜ ሞቻለሁ፣ አልያም የሚስቴ ሕልውና በውስጤ አክትሟል። የሆነ ዓለም ግማሽ ጎኗ የተሸረፈ መሰለኝ። ክብር ራሱ ግማሹ ተሸርፎ
በንቀትና በጥላቻ ምድር ላይ የተከሰከስ
“አብርሽ አልወደድከውም?” አለችኝ ግራ ገብቷት እንደቆመች። እንዴት ነው አንገቷ ተመዝዞ የሆነ
ቆቅ ነገር የመሰለችው፣ በእግዚአብሔር። ወደሷ ማየት ቀፈፈኝ። መኝታ ቤቴ ገብቼ ተኛሁ። ልክ እንደብርሃን በሆነ ቀዳዳ ገብታ ፊቴ የምትቆም ይመስል ጥቅልል ብዬ ዓየር እንኳን እንዳይገባ ታፍኜ ተኛሁ። ግን ምን ያደርጋል በጨለማው ውስጥ ወርቃማ ፀጉሯ እያብረቀረቀ አእምሮዬን ሞላው!
እንዴ ራት አንበላም እንዴ?” አለች፤ እንባ እየተናነቃት ነበር ድምፅዋ ያሳብቃል። አብረን በትዳር
በቆየንባቸው ጊዜያት ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር እንዲህ መጥፎ ፊት ያሳየኋት። በቀጥታ መጥታ
የለበስኩትን የአልጋ ልብስ ገፍፋ ወደዛ ጣለችው። አራስ ነበር ሆና ነበር። “አንተ ራስህን በምን ሒሳብ
ነው የምታስበው፣ ማንኛዋም ሴት የምታደርገው ተራ ነገር ነው ይሄ፣ ለምን ታሳቅቀኛለህ…”
ይሄው “ማንኛዋም ሴት ሆነች ሚስቴ !
ያልወደድከው ነገር ካለ መናገር ትችላለህ። ምን ተፈጥሮ ነው እንዲህ የሚቀያይርህ?”በእልህ ዓይኗን ጎልጉላ ነበር የምትናገረው። እንዲህ ጮኻ ስትናገር ሰምቻት አላውቅም።ግን ምን ዋጋ አለው፤ ጩኸትም ቁጣም የሚያስደነግጠው ለካ ለተቆጪው ባለን ክብርና ፍቅር ልክ ነው። ይሄ ባንዴ ከውስጤ የተነነው የፌቨን ነገር ግርማ ሞገሷንም ድራሹን አጥፍቶት ይሄን ሁሉ ጩኸቷ በሰፈራችን
እያለፈ “ቁራሌ” ከሚል ሰው ጩኸት እንኳን ለይቼ አላየሁትም።
ድንገት ውስጤን ፈንቅሎ በወጣ ጩኸት፣ “አስቀያሚ” አልኳት። በድንጋጤ ሽምቅቅ አለች። አቤት
ብልግና። ከየት አባቴ ነው እንዲህ መዥረጥ አድርጌ ያወጣሁት! ለካ ጨዋ የምንሆነው በትርፍ
ጊዜያችን ነው። ወደ ዋናው እኛነታችን በቁጣ አልያም በደስታ ስንዘፈቅ ብልግናችን እንዲህ እርቃኑን ይቆማል። ፌቨን የጨው አምድ ሆና ቀረች። የአልጋ ልብሱን ገፍፌ እየጎተትኩ ወደ ሳሎን ሄድኩና ሶፋ ላይ ተኛሁ። አልተከተለችኝም። እንኳን ያልተከተለችኝ። ተቀያይሬ ነበር። የሆነ ነገር ባደርጋት ደስታዬ
ነበር። ከሆነ ረዥም ሕንፃ ላይ ብገፈትራት ነገር (ጭካኔ ይመስላል አይደል … ግን ቦታው ላይ ካልሆኑ ስሜቱ አይገባም … ለካ ሰው ሚስቱን በገጀራ አንገቷን አላት ምናምን የሚባለው በእንዲህ ዓይነቱ አጋጣሚ ነው .… ትህትና፣ ዘመናዊነት፣ ሴትን ማክበር ቅብርጥስ የሚባሉት ጣጣዎች ለካ አልገቡንም
.. ገና አልዘመንንም ለካ !)
ከዛ በኋላ ፌቨን ትኑር ትሙት አላውቅም። ሶፋ ላይ አድሬ ጠዋት ወደ ሥራ እሄዳለሁ።ማታ ጓደኞቼ ጋር አምሽቼ እኩለ ሌሊት አካባቢ ወደ ቤት እመለሳለሁ። አልጠጣም፤ ግን ፌቨንን ላለማየት ያለኝ አማራጭ እጅግ በጣም የምጠላቸው መጠጥ ቤቶች ለስላሳ ይዤ መጎለትና ለዛ ቢሱን የሰካራሞች መለፋደድ ማዳመጥ ነበር። እኔ ሚስቴ አበሳጨችኝ ብዬ መጠጥ የምጋት ሰው አይደለሁም። ስወድም
በራሴ አዕምሮ፣ ስጠላም በንፁህ አዕምሮዬ መጥላት እፈልጋለሁ። ከሚስቴ ጋር ተጣላሁ፣ ፍቅረኛዬ
ካደችኝ፣ ቅብርጥስ በሚል ሰበብ የጠርሙስ አንገት አንቀው የሚጨማለቁ ሰዎች በራሳቸው ሕይወት ላይ ድራማ የሚሰሩ ይመስለኛል።
አንድ ቀን የፌቨን እናት ደወሉና በጥብቅ እንደሚፈልጉኝ ነገሩኝ። አከብራቸዋለሁ ግን በቀጠሩኝ ሰዓት ሳልሄድ ቀረሁ። በቀጣዩ ቀን አምሽቼ ቤት ስገባ የፌቨንን እናት ቤት መጥተው አገኘኋቸው። ፌቨን
ጎናቸው ተቀምጣለች። ፀጉሯን በጥቁር ሻሽ አስራዋለች። እንዲህ ግራ ከመጋባት … አስቀያሚ !
“አብርሽ ምንስ ቢሆን እናትህ አልነበርኩም” ብለው ወቀሱኝ እናቷ። ከልቤ አዘንኩ። ግን ስለፌቨን ማውራት አልፈለግኩም። “የሆነውን ሁሉ ሰምቻለሁ፣ ልጅ ናት ሴቶቹ የሚያደርጉት ነገር ያምራታል።
በዕርግጥ ተይ ስትላት መስማት መመካከር ደግ ነበር፤ ግን አንዴውኑ ሆነ። ሁለተኛ እንዳይደገም መመካከር እንጂ እዚህም የሚያደርስ አልነበረም”ብለው ነገሩን ቀለል ሊያደርጉት ሞከሩ። አልገባቸውም
ማዘር። ማንም የእኔ ጉዳት አይገባውም። ማንም የእኔ ጥልቅ ስሜትና ሐዘን አልገባውም።
“ማዘር በጣም የማከብርዎት ሰው ነዎት። ልጅዎትንም አክብረው ሰጥተውኛል። እኔም አንድ ነገር
አስቀይሜያት አላውቅም”

👍24
"አውቃለሁ አብርሽ” አሉ ፊታቸው ላይ ሐዘን ነበር።
“አሁን ግን ከፌቨን ጋር አብሬ መኖር አልፈልግም። ዓይኗን ማየት አልፈልግም። መፋታት ነው
የምፈልገው” አልኳቸው። ፌቨን ያቃሰተች መሰለኝ። እናቷ በድንጋጤ ወደ ፌቨን ዞረው አፈጠጡባት።
አስተያየታቸው፣ “አንቺ ሌላ ያደረግሽው ነገር አለ እንዴ” የሚሉ ይመስላል። እውነቴን ነው ፌቨንን
መፍታት ብቻ ነው የምፈልገው። ለሞተው ትላንታችን ፍቺ የቀብር ስነስርዓቱ ነው ለእኔ! ምን ያደርጋል የበከተ የፍቅር ሬሳ ተሸክሞ ማንዘፋዘፍ። ወደዛ ቀብሮ እርም ማውጣት ነው እንጂ። እርሜን ማውጣት
እፈልጋለሁ። አካባጅ እባላለሁ አውቀዋለሁ። ግትር እንደምባል አውቀዋለሁ። በዘመነው ዘመን ኋላ ቀር እንደምባል አውቃለሁ። ዘመናዊ ለመባል ግን ስሜቴን ማፈን አልፈልግም .…. ፍቺ ፍቺ ፍቺ !!
እዚህ ምድር ላይ መናቅ፣ መገፋት የበዛብን እኛ ቢያንስ ቤተሰባችን ያልነው ካልሰማን፣ ተንቆ ከመኖር፣
ፍላጎታችንን ሲቆርጡ ሲገነጥሉ፣ እኛነታችንን ማንነታችንን ያልሆነ ቀለም ቀብተው አሳመርንላችሁ”
ሲሉን “ገደል ግቡ አንፈልግም” እንል ዘንድ ቢያንስ በትዳራችን ላይ ሥልጣን ሊኖረን ይገባል !! ገደል
ትግባ ፌቨን የምትባል ደነዝ ! እሷን ብሎ ሚስት። የትዳር አጋር ክቡር ቃል ነው። ቃሌ ከመንደርተኛ ቃል ካልተሻለ፣ እኔ ተራ ጎረቤቷ እንጂ ባሏ አይደለሁም። ገደል ትግባ ! ገደል ትግባ … ገደል ትግባ ! ባዶ አድርጋኛለች። አንዲት ሚስት የባሏን ስሜት መረዳት ካቃታት፣ ያውም ሺ ጊዜ የነገራትን … ወጥ
መወጥወጥና ቀለበት ሰክቶ መንከርፈፍ ትዳር ነው ያለው ማነው ... የማትረባ !! እኔ ቁጡ ነበርኩ ? አልነበርኩም !! እና ሳቄን ማን አከሰመው፣ በውስጤ ማን ቁጣ ዘራ ....…. ራሷ ፌቨን።
✨ይቀጥላል✨

👍9❤4
#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
የሞት ጥሪ
አማንዳ
ወደ ኤክስ ልንመለስ ሶስት ቀን ሲቀረን ሲልቪ ቤቶቿን ለመሰናበት ሄደች። ጊዜው ንፁህ ብርህንና ለስላሳ ሙቀት በዝግተኛው ነፋስ የሚንሳፈፉበት ውብ የፀደይ ቀን ነበር። የፓሪስ ሴቶች ወደ ሰፊው ስመ ጥሩ ጎዳና ወደ ሻንዜሊዜ እንደሚጎርፉ ታወቀኝ፡፡ በሜትሮ ወደዚያው ሄድኩ ሱቆቹ የፀደይ ሞድ ልብሶቻቸውን መስኮቶቻቸው ላይ ዘርግተዋል፤ ካፌዎቹ ጠረጴዛ ወምበሮቻቸውን ወደ መንገዱ
አውጥተው ከአብዛኛዎቹ ጠረጴዛዎች በላይ በልዩ ልዩ ቀለማት ያጌጡ ሰፋፊ ጃንጥላዎችን ዘርግተዋል። ሰዉ ይንጋጋል፤ ትራፊኩ ይፈሳል። አንዱ ካፈ ውጪ ሰዉ የሚተላለፍበት ቦታ አንዲት ትንሽ ጠረጴዛ አጠገብ ተቀመጥኩ
በፀደይ ቀን ሻንዚሊዜ ጎዳናው ዳር ቁጭ ብሎ ቢራ እየጠጡ
አላፊ አግዳሚዋን ፈረንሳዊት እና የስንትና ስንት ሌላ አገር ሴት
መቃኘት። ከዚህ የበለጠ ምን ደስታ ይገኛል? ሴቶቹ የፀደዩን
ብርሀንና ነፋስ ለመቀበል የፈነዱ አበባዎች ይመስላሉ፡፡ የወፍ ቋንቋ
መሳይ ፈረንሳይኛቸውን በልዝብ ድምፃቸው እንደዘፈን እየተቀባበሉ፣የተነጠፈውን ድንጋይ በረዥም ተረከዛቸው ኳ! ኳ! እያረጉ፤ ውብ ዳሌያቸውን እያወዛወዙ ወደላይና ወደታች ይተላለፋሉ፡፡ አይኔ
አብሯቸው ይመላለሳል
ቀስ እያለ አይኔ ሰከረ፡፡ ውበት በዛበት። የአንዷን ኩሩ አረማመድ ሳደንቅ ትንሽ እንደ ተራመደችልኝ፡ ህዝቡ መሀል ገብታ ትጠፋለች፡፡ የሌላዋ ግሩም ቅርፅ አይኔን ይስባል፡ ከዳሌዋና ከባት ከተረከዟ የቱን እንደምመርጥ ገና ሳልወስን ህዝቡ ይውጣታል። ደሞ
የአንዷ ፀጉርና አንገት ልቤን ይወስደዋል። የምትቀጥለዋ ወጣት ነጭ ጥብቅ ያለ ሱሪ ለብሳ ስታልፍ አይኔ በዳሌዋ እንቅስቃሴ ላይ ይተከላል። እሷንም ሚንጋጋው ህዝብ ይውጣታል። ሌላ ወበት ሌላ ሴት ላይ ተጭኖ ሲሄድ አይኔን ይስባል። እንደዚህ ሰል አይኔ ሰከረ
የቢራዩን ሂሳብ ከፍዬ ወደ ፕላስ ደ ሌትዋል በኩል ስራመድ
የአንዷ ፀጉር አይኔን ማረካው:: ሴትዮዋ ከኋላ ሲያዩዋት ምንም
አትል አረ ሻንለዚ ስላየሁዋት ነው እንጂ ሌላ ቦታ ባያት በጣም ደስ ትላለች። አጠር ያለች ወጣት ናት። ቀይ ቦርሳ አንጠልጥላለች። ገላዋን እቀፍ አርጎ የሚሸፍን፣ ነጭ ባለ ሽንሽን የፀደይ
ቀሚስ ለብሳለች። ወገቧን ሰፊ ቀይ ቀበቶ አቅፎታል። ቀይ
ባለረዥም ተረከዝ ጫማ የረገጡት እግሮቿ ወፈር ብለው፣ ቀለማቸው ወደ ቡናማ የሚያደላ ነው። ወፍራም ዳሌዋ ከነጭ ልብሷ
ስር ሲመዛዝ ያስታውቃል፣ ምኞት ይቀሰቅሳል። ግን ዋናው ውበቷ
ፀጉሯ ነው:: ይሄ ንፁህ ነጭ ፀጉሯ ወደኋላዋ ትከሻዋ ድረስ ተለቆ፣
ፀሀዩ ውስጥ ይብለጨለጫል። የረጋ የጨረቃ ብርህን የሚመስል
ንፁህ ፀጉር ከዚህ በፊት የት ነው ያየሁት? የት? መቼ? የት?
ሴትዮዋ ወደ ቀኝ በኩል ተጠምዛ ከሻንዜሊዜ ወጥታ፣ አንድ
ሌላ መንገድ ይዛ ወደሳይ በኩል መራመድ ጀመረች። ለምን
ተከተልኳት? አላውቅም
መንገዱ ዳር ብዙ መኪናዎች ቆመው ነበር፡ እሷ አንድ ጥቁር
ጃጉዋር ስፖርት መኪና ውስጥ ገባች። አልፌያት ወደ ላይ በኩል
መንገዴን ስቀጥል፣
“Hi there!” አለችኝ። ባለሁበት ቆምኩ፡፡ የአማንዳ፥ ድምፅ!
ጆሮዬን ማመን አልቻልኩም፡፡ ግን ፀጉሩ የሷ ነው። አሁንም
አስታወስኩ። ወደሷ ዞርኩ፡፡ ከመኪናዋ ወጥታ እየሮጠች መጣችና ተጠመጠመችብኝ። ሽቶዋ በጣም ደስ ይላል።
“አማንዳ ነሽ እውነት?
«እዎን»
«ታድያ ያ ሁሉ ጮማ የት ሄደ?»
«ሸጥኩት» አለችና ትንሽ ከኔ ራቅ ብላ አንድ ሁለት ጊዜ
እየተሽከረከረች ምን ይመስልሀል?» አለችኝ
«ተአምር ነው፡፡ በአይኔ ባላይሽ ኖሮ አላምንም ነበር»
"Thank you"
«እውነቴን ነው:: አሁንኮ ማን እንደሆንሽ ሳላውቅ ከኋላሽ
በኩል ሳይሽ የማናት ቆንጆ ፈረንሳይ? እያልኩ ስከተልሽ ነበር»
«አንዲት ሴት ምን መስማት እንደምትወድ ብጥር አርገህ
ታውቃለህ መቸስ፡»
«እውነቴን ነው ኧረ!»
«ደስ ካልኩህ አብረኸኝ ምሳ ብላ እስቲ»
«ጥሩ»
ወደ ቆንጆ ጥቁር መኪናዋ ገባን፡፡ አማንዳ ድሮ ቁምቡርስ
ነበረች፣ አሁን ግን ቢራቢሮ ሆናለች። ትርፍ እገጯ ጠፍቷል፣
አንገቷ ዙርያ ተጠፍጥፎ የነበረው ጯማ ረግፏል። ፊቷ ሙሉ ነው፡
ግን ደስ ይላል፡፡ ከንፈሮቿ ሮዝ ብጤ ቀለም ተቀብተው፣ ሰማያዊ
አይኖቿ በጥንቃቄ ተኩለው፣ ቀይ ጉትቻዋ ከነጭ ፀጉሯ አጠገብ
ሲታይ በረዶ አጠገብ የተንጠለጠለ እንጆሪ ይመስላል።
ከአስቀያሚዎቹ ሴቶች ማህበር ወጥታ፣ ቆንጆዎቹ ማህበር
ገብታለች፡፡ ድምፅዋ ሳይቀር ተለውጧል። ድሮ አልቃሻ ብጤ ነበር፤አሁን ግን ልስልስ ያለ ቆንጆ ድምፅ ነው
«ንገሪኝ እስቲ፡ ምን እንደዚህ ለወጠሽ?» አልኳት
«አንድ ሰካራም አለችኝ
«ምን?»
«ሉን ተሰናብቼ ወደ አገሬ ስሄድ፡ ኤሮፕላኑ ውስጥ አንድ
ሰውዬ አጠገብ ተቀመጥኩ፡፡ ሰውየው ሰክሮ ነበር። ሉ ትዝ እያለኝ ለብቻዬ ሳለቅስ
« ምን ያስለቅስሻል? የወደድሽው ሰውዬ እምቢ አለሽ? ደግ አረገ! በዚህ እድሜሽ ምን እንዲህ አወፈረሽ? አለኝና ያኔውኑ
ረሳኝ፣ እንቅልፍ ወሰደው
«እኔ ግን ቃላቱን እስከ መቼም አልረሳቸውም። ለመጀመርያ
ጊዜ አንድ እውነት ተገለፀልኝ። ይኸውም፣ ጅል ሆኜ ነው እንጂ፣
ውፍረቴን እንደ ጭነት ተሸክሜ መዞር የለብኝም፡፡ ጭነቱን አውርጄ ልጥለው እችላለሁ። ልጥለው ቆረጥኩ። ሳን ፍራንሲስኮ ሄጄ ሙያቸው ክብደት መቀነስ ከሆነ ሰዎች ጋር አራት ወር ሙሉ ሰራሁ። ውጤቱን አንተም አመሰገንክልኝ አለች። ሳቋ ውስጥ ወጣትነትና የህይወት ድል አድራጊነት ይጨፍራል!
ባለ አራት ኮከብ (ማለት ከሁሉ ይበልጥ ምቾት ያለበት) ሆቴሏ
ወሰደችኝ። ክፍሏ ሆነን በቴሌፎን ሁለት ምሳ አዘዘች። አሁንም
አስደነቀችኝ። ኤክስ ሳውቃት ፈረንሳይኛውን በአስቀያሚ የአሜሪካን ቅላፄ ነበር የምታዜመው፣ አሁን ግን የፓሪስ ፈረንሳይኛ ሊሆን ምንም አልቀረው:: እያየችኝ ስትስቅ
“እንደዚህ የሚያስደስት ለውጥ አይቼ አላውቅም።
"Thank you, you re really sweet" አለችኝ
ከምሳ በኋላ «ፓሪስ ምን ትሰራለህ?» አለችኝ፡፡ ነገርኳት፡፡
«አንቺስ?» አልኳት።
«ከኒው ዮርክ የዛሬ ሳምንት መጣሁ፡፡ ይሄ ጃጉዋር ከኢንግላንድ እስኪመጣልኝ ነበር " ምጠብቀው። ነገ ወይም ተነገ ወድያ ወደ ኤክስ መሄዴ ነው:: . . ሉን ማግኘት አለብኝ፡፡ ደህና ነው? አሁንስ የሚፈልገኝ ይመስልሀል? ለጊዜው ሴት አልያዘ እንደሆነ ጥርጥር የለውም። ይዞ እንደሆነ፣ ነጥቄ መውሰድ ይኖርብኛል።»
«ምን?»
«ነጥቄ እወስደዋለሁ። ምነው ገረመህ? የድሮዋ አማንዳ
መስዬህለሁ እንዴ? ተለውጫለሁኮ:: ተዘጋጅቼ ነው የመጣሁት፡፡ ቢያንስ አርባ የሳይኮሎጂ መፅሀፍ አንብቤያለሁ። ደሞ ሉን
አውቀዋለሁ፡፡ ግብረ ስጋ በጣም ይወዳል። ለሱም ተዘጋጅቻለሁ፡፡»
«እንዴት?»
«ለሌላ ሰው ቢሆን ይህን አልነግረውም። አንተ ግን
ትወደኛለህ። ወፍራም ሳለሁም ትወደኝ ነበር፡፡ ለኔ ግድ ነበረህ፡፡
የተሻልኩ ሰው ሆኜ ስላየኸኝ ደሞ በጣም ደስ ብሎሀል። ይሄ ለኔ
ትልቅ ስጦታ ነው። በጣም ተወዳጅ ነህ፡፡ እና ለምን እንደሆነ
ሳላውቅ በጣም አምንሀለሁ፡፡ ለምንድነው እማምንህ?»

👍14🤔2
«ምክንያት የለውም፡ ምክንያት አያስፈልገውም።»
«እውነትክን ነው፡፡ ብልህ ነህ፡፡ እውነቴን ነው፣ ብልህ ነህ፡፡
አገሬ ሆኜ ብዙ ሳስብህ ነበር። ኤክስ ሆነህም እወድህ ነበር፤ ግን ያኔ ስሜቴን ለመናገር እፈራ ነበር። ድፍረት መስሎ ይታየኝ ነበር።
አሁን ግን ሳልፈራ ስሜቴን ልናገር እችላለሁ። ተለውጫለሁ፡፡ ጤነኛ
ሆኛለሁ። ስለዚህ ልንገርህ። በጣም ነው የምወድህ፡፡ ፂምህን ስትላጭ በጣም ታምራለህ፡፡ ቆንጆ ስለሆንክና ስለምወድህ ልስምህ እፈልጋለሁ፡፡ ትፈቅድልኛለህ?» አለችና ፈት ለፊቴ ከተቀመጠችበት
ሶፋ ተነስታ በዝግታ እፌ ላይ ስማኝ ተመልሳ ቁጭ አለች፡፡
እያየችኝ ሳቀች
ግራ ስለገባኝ አሁን አታረሳሺኝ፡፡ ለግብረ ስጋ ተዘጋጅቻለሁ
ስትዪ ምን ማለትሽ ነው?» አልኳት
ቀላል ነው፡፡ ሳላስበው ከአንድ የሰላሳ ሰባት አመት ህንድ ጋር
ገጠምኩ፡፡ ፒ-ኤች-ዲ ያለው ሊቅ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ጎብኚ
መምህር ነው:: እሱ ስለ ግብረ ስጋ ያስተማረኝን ብነግርህ ልታምነኝ አትችልም፡፡ ልነግርህም አልችልም። ቃላቱን አላውቀውም፡፡ ግን ስራውን በሀይል እችልበታለሁ፡፡ ፕሮፌሰሩ ገና ገና ቀሽም ነሽ ይለኛል፡፡ እውነቱን ነው፣ ከህንዶቹ ጋር ስተያይ ቀሽም ነኝ። ግን ሉን ሄጄ አንድ ሌሊት ከኔ ጋር ሳሳድረው እብድ እንደሚሆንልኝ
እርግጠኛ ነኝ፡፡»
«ከዚያስ?»
«ከዚያ እንጃ፡፡ ሉ ከፈለገ አሜሪካ እንሄዳለን። ካልፈለገም ኤክስ
እንቀራለን፡፡ ወይ ፓሪስ እንመጣለን። ካንድ ሶስት አመት በኋላ፣ ሀሳቤን ያልለወጥኩ እንደሆነ፣ እንጋባለን፡፡»
«እምቢ አላገባሽም ያለሽ እንደሆነስ?»
«እሱንም አስቤበታለሁ። ተዘጋጅቻለሁ።»
አየሁዋት። ትችላለች። የፈለገችውን ለማግኘት ትችላለች
በሶስተኛው ቀን አማንዳ፣ ሲልቪ፡ እኔ በአማንዳ ጃጉዋር ወደ
ማርሰይ አመራን። ኤክስ ስንደርስ አርብ ማታ ነበር። ሉልሰገድ
ከጀምሺድ ጋር ሞንቴ ካርሉ ሄዷል። እንግዲህ አማንዳ እስከ ሰኞ ጧት መታገስ ይኖርባታል።
እኔ ፓሪስ ሄጀ ቅናት ውስጥ ስንፈላሰስ ኤክስ ውስጥ ምን ምን
ተደረገ? ከባህራም፣ ከተካና ከኒኮል የሰማሁትን ሳገጣጥመው እንደ እሚከተለው ሆነ፡-...

👍16❤7
#ሚስቴን_አከሸፏት
፡
፡
#አራት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
....የፌቨን እናት ተቀየሙኝ። ሊያስታርቁን መጥተው፣ “ልጅዎትን ከዚህ በኋላ ማየት አልፈልግም ስላልኳቸው ተቀየሙ። ማንም ወላጅ ቢሆን ይሰማዋል። በደካማ አቅማቸው ከየትና የት ድረስ መጥተው ለማስታረቅ ሲሞክሩ እንቢ አይለኝም ብለው ነበር ያሰቡት። የእኔ ፌቨንን መጥላት ...
ርሳቸውን መናቅ መሰላቸው “አንዲት ሴት ፀጉሯን መቆረጧ ትዳር እስከማፍረስ ካደረሰ ከፍቺው ኋላ ፀጉር ብቻ ሳይሆን ሌላ ምክንያት አለ ማለት ነው” ብለው እንዲያስቡ አድርጓቸዋል። እውነት ነው
ከፌቨን ፀጉር ኋላ ሚሊየን ምክንያቶች ነበሩ፤ ሁሉም ምክንያቶች ግን መነሻቸው ፍቅር ነበር።
“ፍቅር ይታገሳል” ይሉኛል ጉዳዩን የሰሙ ሁሉ፣
ሰው በሰላሙ ቀን እግዜሩንም መጽሐፉንም አሽቀንጥሮ አሸሼ ሲል ይከርምና የቁርጥ ቀን ሲመጣ በየሥርቻው የጣለውን የሕይወት መጽሐፍ አቧራውን አራግፎ እያነሳ ሁሉም ሰባኪ፣ ሁሉም ቃል አጣቃሽ ካልሆንኩ ይላል።
“ፍቅር ይታገሳል”ይለኛል መካሪ። እንዲህ ሲሉኝ ተናገር ተናገር ጩህ ጩህ ይለኛል። “እስቲ እንዲህ
ለነፍስህ ያደርክ ከሆንክ ቃሉ እንደሚለው አታመንዝር ! አዎ አንተ ራስህ ይሄን የምትመክረኝ …
እስቲ በየስርቻው ራሳቸውን ነጥቀህ በቀለም የምታዥጎረጉራቸውን የወሲብ እቃዎችህን እንደሰው ቁጠር ! እዚህች አገር እንደ ሴት መጫወቻ የሆነ ፍጥረት አለ ... ? የማንም ወጠጤ መጥቶ የብልግና
ብሩሹን አንከርፍፎ መንገድ ላይ እንደተሰጣ ሸራ ሴቶችህ ላይ ብልግናውን ሲስል የት ነበርክ…” ማለት ያምረኛል።
አዎ ውስጤ በቁጣ ይሞላል፣ “ላንት 'መብታቸው ነው እያልክ በየመጠጥና ጫት ቤቱ እንደ ጥራጊ ማንም ሲረግጣቸው የነበሩ ሴቶችህን ስታልፍ .… ዛሬ ሴተኛ አዳሪነት፣ወሲብን አቃልሎ ማየት፣ በፋሽን ሥም ሴትነትን መንገድ ዳር አቅርቦ መቸብቸብ ሰተት ብሎ ጓዳህ ገባ! ሴቶች በጓዳ አይቅሩ አደባባይ
ይውጡ ከሚለው የሚበዛው ለሴቶች መጨቆን ያዘነ እንዳይመስልህ። በአደባባይ እንደ ፋሲካ በግ ዳሌና ሽንጥ በዓይኑ እየመተረ ለመምረጥ ነው! ምነው የሚመች ጓዳ፣ ክብር ያለው ጎጆ አግኝተው ሴቶች ጓዳቸው ውስጥ አርፈው በተቀመጡ። ግን ባትለውም ኑሮ ራሱ እየመዘዘ አደባባይ ያሰጣቸዋል።
ያውም የኛ ኑሮ…” ብዬ በአደባባይ ድፍን የአበሻ ወንድ ላይ መጮህ መደንፋት ያምረኛል።
“ለመሆኑ የሴቶችን ልብስና ጫማዎች ታዝበሃል ? ለተረት የሚመች አይደለም ሁሉም። ሴት ልጅ ከቤቷ ወጥታ ወደ መኪናዋ ከመኪና ወደ ሥራ ረጋ ያለ ሕይወት እና እንቅስቃሴ እድትኖር ታስበው የተሰሩ ናቸው። እንዳንተ ስኒከር፣ ሸራ ጫማ፣ ከስክስ አይደለም የሴቶች ጫማ ! ሴቶችህ ራሳቸው ለአደባባይ ማንነት “መብት” የሚል ሽፋን ይሰጡታል እንጂ በብዙሃኑ የከተማ ሴት አዕምሮ ውስጥ
ያለው እውነት ጥሩ ሥራ አግኝቶ ወይም አንዱን ኃብታም አግብቶ “
እርፍ” የሚል ሕልም ነው !
(ይሄ አንዳንዶችን ያበሳጫል ግን ምን ይደረግ እውነት ነው። ከተማውን ከሰኞ እስከ አርብ የዘነጠ ሽቅርቅር ትውልድ ሲሞላው ሥራ አጥነት ጣራ እንደነካ አስተውል። የታደሉ ዜጎች የቆሸሸ እጅ፣የሥራ ቱታ የለበሱ ሰውነቶች የታደሉ ናቸው። ከሰኞ እስከ አርብ መዘነጥ ከሰኞ እስከ አርብ አዕምሮም ሰውነትም ሥራ መፍታቱን የሚያሳይ የውድቀት ባንዲራ ነው !” እንዲህ ብዬ የሚሞግተኝን ሁሉ መሞገት ያሻኛል። ምክራቸው መከራ ከመጨመር ውጪ ወንዝ የማያሻግር እንቶፈንቶ ይሆንብኛልና ሁሉም መጽሐፉ እንደሚለው “የሚያደክሙ አፅናኞች” ናቸው።
በሚስቴ ሰርጥ አልፌ ወደ ሰፊው የሴትነት ባሕር ስመለከት ሴቶች ባሕሉ ብቻ ሳይሆን ልብስና
ጫማቸው ሳይቀር ካቴና ሆኖባቸው ይታየኛል።ፋሽን ነፃነታቸውን ነጥቆ፣ ምቾታቸውን ቀምቶ፣ ወንዱ ፊት የእይታ አምሮት እንዲያሳረፍ ይደረድራቸዋል። እነሱም ፍልቅልቅ እያሉ በካቴናቸው ይኮራሉ ..
ፋሽን ነዋ። እንደውም ትክክለኛው ዘመቻ መሆን ያለበት ሴቶች አደባባይ ይውጡ ሳይሆን ወደ ጓዳ ይመለሱ ነው ! ጓዳቸው ምቹ ይሁን ነው !! እግሯ እስኪቀጥን ከተማውን የምታካልል ቆንጆ የሆነ
ቀን እፎይ ዙረት ሰለቸኝ” ስትል ትሰማታለህ ..ዙረት የሴት ልጅ ተፈጥሮ አይደለማ ! በተሰጣቸው
የተፈጥሮ ፀጋ ልጆችን ሊያሳድጉ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው። ልጅን ለማሳደግ እግርን ሰብስቦ ቤት
ውስጥ መቀመጥ፣ ደስታን አሳልፎ መስጠት ይጠይቃል። ልጅ ጭፈራ ቤት ውስጥ አያድግም። ይሄ የዘመናችን አጉል ዘመናዊነት እንዲህ ተጣምሞ ካደገ፣ ልጆቻቸውን በጋሪ እየገፉ በደረቅ ሌሊት ጭፈራ
ቤት የሚሰየሙ እናቶችን መፍጠሩ አይቀሬ ነው።
ደግሞ እንደ ደንቃራ በመብት ስም ስለእንዝላልነት ልትሞግተኝ ፊቴ የምትደቀን እንስት ብስጭቴን
ጣራ ታስነካዋለች። “አንቺ ራስሽ እስቲ ራስሽን ተመልከች፣ ለምንድነው ፀጉርሽን ቀለም የተቀባሽው ከፊትሽ ከለር ጋር እንደሚሄድ' ባለሞያዎቹ ነግረውሽ …. ወይስ እንዲሁ ሲያደርጉ አይተሽ …. ሞኝ ነገር ነሽ … ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት አጠቃላይ የፀጉር ሞያተኞች ስንት ይሆኑ በሙያው ጥልቅ እውቀት
ያላቸው። ጥቂቶች በጣም ጥቂቶች። ሌላው የተከበረ ፊትና ፀጉርሽን ቤተ ሙከራ የሚያደርግ
የልምድ አዋላጅ' ነው ! እንግዲህ ይሄ መደዴ ፀጉር ተኳሽ ነው የፊትሽ ቅርፅ፣ የቆዳሽ ልስላሴ፣ ይሄን ቀለም ተቀቢ፣ ያንኛውን ሜካፕ ተለቅላቂ እያለ ቅዠቱን የሚመክርሽ !
እየውልሽ የፀጉር ፍሸናው አንቺን አጥፍቶ የሆነች ሌላ ሴት ማስመሰል እንጂ፣ ያለሽን ውበት ማጉላት አለመሆኑ የሚገባሽ የፍሸናውን ስም ስትሰሚ ነው፣
ቢዮንሴ ሹርባ፣
ሪሃና ቁርጥ፣
ዊትኒ ስታይል..
አንቺ ግን ስምሽ አረጋሽ ነው፣ ወላ ነጃት፣ ወላ ነፊሳ፣ ሄለን፣ ሲቲ፣ ቲቲ ሁኝ ብትፈልጊ…። ካናትሽ
ላይ ቆሞ ፀጉርሽን የሚሰራ የሚመስልሽ የፀጉር ባለሞያ በካውያው ፀጉርሽን እየተኮሰ በማያባራ ለፋፊ አንደበቱ ግን አዕምሮሽን ነው በጋለ የውበት እና ፋሽን ካውያው የሚተኩስሽ ! አንቺነትሽን ሊያተን ነው። ከዛ ምንም ከሌሎቹ ሴቶች የተለየ ውበት አይጨምርልሽም። መጨረሻ ላይ እንደሌሎች
ሴቶች ትሆኛለሽ። በቃ ይሄው ነው። ደግሞ ወንዱ ባንቺ ውበት ይደነቃል ብለሽ አትድከሚ። ወንዱ
በሚጎረጉረው ስልኩ መለዓክ የመሰሉ ሴቶች ፎቶ ላይ አፍጥጦ ነው የሚውለው፤ ምንም ብትሆኝ
አይደንቀውም፡፡ ጉዳዩ ከሰውነትሽ ነው። ከስልኩ ወዲያ አምሮት የቀሰቀሰበትን ገላ ሲያጣ አጠገቡ
ያለሽውን አንቺን እንደማስታገሻ ከማይረባ የፍቅር ዲስኩር ጋር ይወስድሻል ! የአንቺን ሥጋ አቅፎ
መንፈሱ በተመለከተው ገላ ላይ ነው የሚቃዠው…” ብቻዬን ተቀምጬ እንዲህ ነው የማስበው።ሴት ወንዱ በሽተኛ የሆነ ይመስለኛል። ለክርክር የሚያሞጠሙጠው አፉ ለምን ራሱን ለመጠየቅ
እንደማይጠቀመው ግራ ይገባኛል።
“እንደ ኳስ መካሪው ወደ ፋሽን …. ፋሽኑ ወደ ወንድ፣ ወንዱ ወደ አልጋ፣ አልጋው ወደ ተዘባረቀ ሕይወት እየተቀባበለ በሴት ልጅ ሕይወት ጨዋታውን ያሞቀ ዘመን እንደዚህ ዘመን ከቶ አልተከሰተም።ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ነውና ዘመኑ ራሱን 'የሰለጠነ የሚል ስም አከናንቦታል ከክንብንቡ ስር … በስልጣኔ መዳፍ አፋቸውን የታፈኑ 'ስልጡን የፋሽን ባሮች ዓየር አጥሯቸው ይወራጫሉ። ለዚህ መፍትሄው ራስን መሆን ነው። በዚህ ዘመን በትክክል የሚያስፈልገው “ራስሽን ሁኚ” የሚል መካሪ ነው። ልድገመው ራስሽን ሁኚ ! የነፈሰው ንፋስ ጋር ልንፈስ ካልሽ እብድ የበላው በሶ ሆነሽ ትቀሪያለሽ... የኔን ሚስት አታያትም … ይቺን አስቀያሚ ! በክብር ካኖርኩባት ዙፋን ላይ ፀቁልቁል በአናቷ ወርዳ

👍29❤1🔥1😁1
ስትፈጠፈጥ።” የሚል ሆድ የባሰው መካሪ… ባይሰማም ኡኡ ብሎ የሚጮህ… ቃል አንድ ቀን ሥጋ መልበሱ አይቀር። ክፉ ስጋ ለብሶ ፍልጥ ከማንሳቱ በፊት በዘመነ ፈሊጥ ቃሉን የማያቀሉ ብፁዓን ናቸው።
በዕርግጥ ይሄንን ስል ሊመክረኝ የሞከረ ትሁት ወዳጅ ነበረኝ። ምን አልኩት ? ሂድ እባክህ ..
አንተን ብሎ መካሪ ! አንተ ስለሚስቴ ፀጉር የምታውቀው አንድ ነገር የለህም ! እንደውም ራስህ በየጓዳህ የምታለቅስበትን እውነት ነው እዚህ በአደባባይ ፋራ ላለመባል የምትቃወመው! እኔ ለሚስቴ ታማኝ ነኝ ! በዚህም እኮራለሁ ! ለፌቨን ታማኝ ነኝ። እንኳን ከትዳሬ ውጭ ሌላ ሴት ልነካ፣ ለሚስቴ የምጠቀመውን የአድናቆት ቃል ብሞት ለሌላ ሴት አልጠቀምም። ስለማያምረኝ አልነበረም። አምናኝ እኔጋ የሆነች ሚስቴን ማክበር ራሴን ማክበር መሆኑን ስለማውቅ ነው። ደግሞም ደስተኛ ነበርኩ።
ፍፁም ደስተኛ።”
እያንዳንዷ ቃሌ በሚስቴ ፊት ሞገስ እንዲኖራት እፈልጋለሁ። በትዳር ውስጥ በጋራ ጉዳይ ላይ የግል አመለካከት የሚባል ነገር የለም። በሚስቴ ሰውነት ላይ ስለምትደረግ እያንዳንዷ ነገር ያገባኛል። ምክንያቱም “አንድ አካል አንድ አምሳል ሆናችኋል” ብለው ያጋቡንን ቄስ ተላልፌ ሲመቸን አንድ ላይ ሳይመቸን በየግላችን እንድንዳክር አልፈቅድም። በምንም ነገር 'ስለኔ አይመለከትህም የምትል ሴት ወይ በሽተኛ አልያም የትዳር ኃላፊነት ያልገባት መደዴ ሴት ናት። መከባበር በሌለበት ውበት
ገደል ይግባ። የስጋ ክምራ ስላማለለህ ዘለህ አልጋ ላይ ትወድቃለህ፣ ከአልጋህ ስትወርድ ምድርህ እሳት ለብሶ ይጠብቅሃል። ፍቺ በማሕበረሰብህ ጸያፍ ነገር ነውና እያስመሰልክ ትኖራለህ። ማስመሰል ደግሞ ያንገሸግሻል። ራስህን በእሳት ልምጭ መግረፍ በለው። በዚህ ዓይነቱ ኑሮ እንኳን ሚስት ተብዬዋ ያጠለቀችልህ ቀለበት፣ ቀለበት የተጠለቀበት ጣትህም ይቀፍሃል።”
“ሚስቱ ስለእርሱ ሕይወት የት ድረስ እንደሚያገባትና የት ድረስ የእርሱ ጉዳይ እንደማይመለከታት
መስመር የሚያሰምር ወንድም ድድብና ከነጓዙ የሰፈረበት ደነዝ ይመስለኛል።ይህን የምለው ወንድ
በመገሰፅ ሚዛናዊ ለመሆን አይደለም፤ የነፍስ ሐቄ፣ የኖርኩበትም መንገድ ስለነበር እንጂ። ይጠየቅ ጎረቤት። ይጠየቅ ቤተሰቤ። ኧረ ራሷ ፌቨን ትጠየቅ። ምርር ቢልም ተገደን መዋጥ ያለብን እውነት ይሄ ነው። ባልም ለሚስቱ፣ ሚስትም ለባሏ ተገዥ ናቸው። ውልፍት የለም። አንዱ ካለአንዱ ፍላጎት ስንዝር ሊራመዱ አይገባም። ሚስቴ እኔ ላይ በዚህ ምድር ካለ ማንኛውም ሰው በላይ ኃላፊ ነች። እኔ የርሷ ነኝ፣ ርሷም የእኔ ናት። ፋሽንም በለው ዘመን አመጣሽ ቅራቅንቦ በጎጆዬ ውስጥ የጥፍር ቁራጭ የሚያክል ቦታ እንዲኖራቸው አልፈልግም። ለምን መሰለህ ..ከሦስቱ ጉልቻ አንዱም ከውጭ አይመጣም፤ አንተ፣ ሚስትህና ፍቅር ብቻ ናችሁኮ ጉልቾቹ…” መካሪዬን በደም ፍላት ደንፍቼበት አመንኩበት ባልኩት ሐቅ አከላፍቼው አጠገቤ ድርሽ እንዳይል አባረርኩት።
ምን ላድርግ …. ሳሎን የተቀመጠ ስልኩ ሲጠራ ሚስቱ እንዳታነሳበት በአፉ እስኪደፋ ከሻወር ወደ ሳሎን የሚሮጥ ወንድ ልምከርህ ሲለኝ ምን ላድርግ ታዲያ። መተዋወቃችንኮ ነው ችግሩ። ሐቅ መቼስ ለራስ ነው ሰላም የሚሰጠው። እኔ እንዳይሆን የምፈልገውን ነገርም ሚስቴ ከእኔ ፍላጎት ውጭ
ልታደርግ አንዳች ስልጣን የላትም። የራሴ የምትለው ሰውነት የላትም። የዘመናችን በሽተኛ ሴታዊ አምባገነንነት፣ በሽተኛው ፌሚኒዝም' እሳቤ ውስጥ ገብተው የተነከሩ ለፋፊዎችን በአማርኛ መስማት ከትርጉሙ ሳይሆን ከመንፈሱ አቀባበል የማይነቀል ደዌ ሴቶቻችን ልብ ውስጥ ዘራ። እነሱም ያሰቡትን ( ነፃነት ላያገኙ እኛም ካንዷ ወደ ሌላዋ ያደግንበትን የወንድነት ክብር ፍለጋ ስንዘል ዘመን ጣጥሎን
እብስ ! የሴት ልጅ ክብር በፍቅር እንጂ በትጥቅ ትግልም በአደባባይ ጩኸትም አይመጣም !! በቤቱ ሚስቱ የገፋችው፣ ፍቅረኛው ያቀለለችው ወንድ ሺ ሕግ ፣ሚሊየን መመሪያ ቢወጣ ሴትን ያከብራል ማለት ዘበት ነው።
አባትና እናቱ ሲደባደቡና ባለመከባበር አፍ ሲከፈቱ እያየ ያደገ ሕፃን ባባቱ ሲወጣ እያዩ፣ ልጅ የፍቅር ገመድ ነው ይሉናል። በጥላቻና በመናናቅ ትዳር ውስጥ የበቀለ ሕፃን የፍቅር ሳይሆን የማሕበረሰቡን ሕግና ባሕል ማነቂያ ገመድ ነው ! ብዙዎቹን 'ዘመናዊነት' ፍዳቸውን የሚያበላቸውን ሴቶች ታዘብ
እስቲ ፤ መነሻቸው ፍቅሩን አሟጥጦ እየተቋሰለ የኖረ ግድ የለሽ ቤተሰብ ነው። ካልተፋቀርን ምን አወላለደን! ልጅ አሻንጉሊት አይደለም !! ቃላችንን ማፅናት ሲያቅተን፣ ሥጋ ለበስ ሐውልት ቤታችን ውስጥ ተክለንልና መልክ ይዳዳናል! “ልጅ ወለድን” ብለን አንመፃደቅ። በልጆቻችን እናት ካልተደሰትን የልጆቻችንን ግማሽ ክፍል አንወደውም ማለት ነው። እናቶቹም ቢሆኑ፣ “ለልጄ ስል እንዲህ ሆንኩ፣ ለልጄ ስል ተፈለጥኩ ተቆረጥኩ…”፤ እስቲ መጀመሪያ ለእኛ ለባሎቻቸው ሲሉ ይፈለጡ ይቆረጡ።የልጅሽ ግማሽ አካል እኛ ባሎች አይደለንም እንዴ ?! እነዚህ ኮተታም ዘፈኖችና ፊልሞች በቀጥታም በተዘዋዋሪም የወንድን ልክስክስነት ለሴቶቻችን ሲሰብኩ፣ “ታዲያ ለማን ብለሽ ነው የምትታመኝው”
እያሉ ለመደዴነት ሚስታችንን፣ እህታችንን እያዘጋጇት መሆኑን ዘግይቶ ነው የሚገባን።
እና ሚስቴ ካለፍቃዴ ፀጉሯን ተቆረጠች ስል፣ 'መብቷ ነው ቅብርጥስ' የሚለኝ መብዛቱ መልሶ እኔኑ ይገርመኛል። ትዳርም ይሁን ፍቅር ለወደዱት ሁሉን ነገር መስጠት ነው። ግማሽ መሰጠት የሚባል ነገር የለም። እዚህ አዲስ አበባ ብልጣብልጥ ነፍሶች ፍቅርን እንደሚሸቅጡት ዓይነት ማለቴ ነው።እንዳሻኝ እዘልላለሁ ማለት የፈለገ ጓዙን ጠቅልሎ እዛው ተራ ዝላዩ ላይ !! ሲጀመርም ጭብጨባው አምሮት እንጂ እንዲህ ዓይነቱ አጋር የትዳር ወኔው የለውም !! ልክ በመንፈሳዊው ዓለም፣ “አንድም
ከእግዜር አንድም ከሰይጣን” እንደሚባለው በትዳርም አንድ እግርን ትዳር ውስጥ ሌላኛውን አጉል ምኞት ውስጥ ማቆም የለም!! ጥቅልል ብሎ መሰጠት ካልሆነ ጓዝን ጠቅልሎ ወደ መሄጃው !! ከተልካሻ
አብሮነት ከጠነዛና ከደነዘዘ የሁለትዮሽ ስብሰባ ብቸኝነት በስንት ጣዕሙ።
በዚህ ሆድ በባሰው ለዛ ቢስ ጊዜ ጋብቻን የልጅ ማሽን አድርገው የሚመለከቱ ወላጆች ክፉኛ
ተበራክተዋል። ይሄ ነገር ይቆጨኛል (ሆድ እንደባሰኝ ላውራው)። የፍቅር ሰንሰለት ያላቆራኘው ልባቸውን በመውለድ ሊያጣምሩ የሚደክሙ ! ቃል ነው ማሰሪያው ልጅ አይደለም ! ቃል ነው ስጋ ለብሶ ልጅ የሚሆነው! አብርሽ ውለዱ ልጅ ቢኖር እንዲህ በትንሽበ ትልቁ አትጋጩም ይሉኛል ... !! እንኳን ካለፍቃዴ ፀጉሯን ተቆርጣ ... የአንዲት በየቤቱ መዞርን ትዳር ያደረገች ሴት ምክር ሰምታ ይቅርና … ሳስነጥስ ይማርህ አላለችኝም ብዬ መፍታት እችላለሁ !! ልጅም ምንም አያግደኝም !
“ዋናው ያልበጀ ቅራሪው ሰው ፈጀ”
ሚስቴ ካለፍቃዴ ፀጉሯን ስለተቆረጠች እፈታታለሁ ...
እንኳን ፀጉሯን መቆረጥ እኔ በማልወደው “ስታይል” ማበጠርም እንደሌለባት የጉልበት ሕግ ሳይሆን የአብሮነትና የመተሳሰብ መርህ ሊያስገድዳት ይገባል ! ይህ ካልገባት ሚስቴ ደንዝዛለች፣ የሆነ የማስተዋል ችሎታዋ ተወስዷል !መተሳሰብን እና ፍቅርን ችላ ከማለት ሕግን ችላ ብትል ይሻልሃል! 'መብቴ ነው' ይሉት ጥራዝ ነጠቅ እንቧ ከረዩ ሕጋዊ ቢሆንም ከሰብዓዊ ጥላቻ ግን አያድንም። ህግ ኑሮህን ከእንከን ይከላከላል እንጅ ራሱ ኑሮ አይሆን ። የአንድ ፍቅረኛ ትልቁ ብቃት መርታት ሳይሆን
ያፈቀረውን ሰው በፍቅር መርታት መቻሉ ላይ ነው።...
✨ይቀጥላል ✨

👍28👏3👎1
#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አራት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
....እኔ ፓሪስ ሄጀ ቅናት ውስጥ ስንፈላሰስ ኤክስ ውስጥ ምን ምን
ተደረገ? ከባህራም፣ ከተካና ከኒኮል የሰማሁትን ሳገጣጥመው እንደ እሚከተለው ሆነ፡-.
አንድ ማክሰኞ ከሰኣት በኋላ (ኒኮል ከፋሺስቶቹ ተደብቃ
ሰንብታ ከተመለሰች በኋላ) ባህራም የሚሰራበት ትምህርት ቤት ዲሬክተር ቢሮው አስገባውና ከስራዎ ላሰናብትዎ ነው» አለው።
ባህራም «ምነው?» ቢለው “በስራዎ በጣም ተደስቼ ነበር፤ ግን የጋርደን ከተማ የፖሊስ ሹም እንዳሰናብትዎ አዘዘኝ» አለው
«እዚህ ውስጥ የፖሊስ ሹም ምን አገባው?» አለ ባህራም
«አዩ፣ እርስዎ የውጭ አገር ዜጋ እንደመሆንዎ መጠን፣ እዚህ
አገር ስራ ለመያዝ ልዩ ፈቃድ ያስፈልግዎታል። እስካሁን ያለ
ፈቃድ ወረቀት ስለስሩ እርስዎም እኔም ልንቀጣ እንችል ነበር፡፡ ግን
የፖሊስ ሹሙ ጓደኛዬ ነው፡፡
የስራ ፈቃድ እንደሌለኝ እንዴት አወቀ?» አለ ባህራም
ሰው ነገረው:: ይመስለኛል፣ ኤክስ ውስጥ ጠላቶች አሉዎት።»
ባህራም ገባው። ፋሽስቶቹ መሆን አለባቸው
«እሺ ደመወዜን ይስጡኝ አለ። የሁለት ወር ከሶስት ሳምንት
ደመወዝ አለው። ዲሬክተሩ ገንዘቡን ከቢሮው ጠረጴዛ ኪስ አውጥቶ አቀበለው። ባህራም ገንዘቡን ቆጠረ። የተዋዋሉት ገንዘብ ሲሶ ነው።
«ሌላውስ?» አለ ባህራም
ዲሬክተሩ ከጠረጴዛው ኋላ እንደተቀመጠ፣ ቅዝቅዝ ባለ ክፉ
ድምፅ
«የምን ሌላ?» አለው
«ይሄ ሙሉ ደመወዜ አይደለም፡፡ አንድ ሶስተኛው ነው::
«ማን ነው ያለው? ደመወዝህን ሰጥቼሀለሁ፡፡ ከፈለግክ ውሰደው፣
ካልፈለግክ ተወው:: ድሮ አልጄርያ ሳለሁ አረቦቹን ከዚህ ባነሰ
ደመወዝ ነበር የምናሰራችሁ»
ባህራም ረጋ ባለ ድምፅ አረቦቹን ቅኝ ግዛት ስላደረጋችኋቸው
በካልቾ ብለው ካገራቸው አስወጧችሁ፡፡ የሆነ ሆኖ፣ እኔ አረብ አይደለሁም፡፡ የኢራን ሰው ነኝ፡፡ የኢራን ሰው ሰውን አይነካም። ግን ማንም ሰው የኢራንን ሰው አይበድልም፡፡ ስለዚህ አለና ድንገት
በጠረጴዛው ተንጠራርቶ ሰውዬውን አነቀው፡፡ ሰውየው ራሱን ለማስጣል አልሞከረም፡፡ ባህራም ሲያፈጥበት፣ በደነገጠ ድምፅ
«አይነቁኝ፡፡ አስም በሽታ አለብኝ» አለው ባህራም ለቀቀው፡፡ ሰውዬው ከጠረጴዛው ኪስ ሌላ ገንዘብ አውጥቶ ባህራም ፊት ቆጠረው። ባህራም ገንዘቡን አንስቶ ኪሱ ከተት። ሰውየውን አየው፡፡ ወምበሩ ላይ ተቀምጦ ወደ ላይ ይመለከተዋል። ባህራም አፉ ውስጥ ብዙ ምራቅ ሰበሰበ፡፡ ሰውዬው ፊት ላይ ተፋው፡፡ ሰውዬው መሀረብ ሊያወጣ እጁን ወደ ኪሱ ሲከት ባህራም ትቶት ወጣ
ከዚያ እየጨሰ ወደ ኤክስ የሚወስደውን አቶቡስ ተሳፈረ
ያን ቀን ተካን ባያገኘው ጥሩ ነበር
ተካ በበኩሉ ከአንድ ወር በላይ ሲበሳጭ ሰንብቷል። ጀርመንዋ
ልጅ እየባሰባት ሄደ። በፊት እንኳ ከዚያ ካገሯ ልጅ ጋር የምትወጣው አልፎ አልፎ ነበር፡፡ አሁን ግን ቢያንስ በሳምንት አራት ማታ ከሱ ጋር ነች። ተካ እንግዲህ ቢበዛ በሳምንት ሁለት ማታ ቢያገኛት ነው። ለዚያውም ሁለቱም ማታ የንትርክ ማታ ነው።
ሁልጊዜ ስለጀርመኑ ይጨቃጨቃሉ
«ከሱ ጋር ምን ትሰሪያለሽ?»
በራሴ ህይወት ምን አገባህ?»
አብራችሁ ትተኛላችሁ?»
«ምን አገባህ?»
በጥፊ እየመታት «ንገሪኝ! ይተኛል?» ይላታል
በንዴት «አዎን ይተኛኛል! በል ምን ትሆን!?» ትለዋለች
እንደገና አንድ ሁለት ጥፊ ያቀምሳትና፣ በግድ ታግሎ
ይተኛታል
አንድ ማታ ግን፣ ዝግ ባለ ድምፅ
«ልሰናበትህ ነው የመጣሁት» አለችው
ልቡ እየፈራ «ምነው? የት ልትሄጂ ነው?» አላት
«የትም አልሄድም፡፡ እስቲ
ዛሬ እንኳ ሳንጣላ እንደር፡፡
የመጨረሻችን ሌሊት ነው፡፡ ሄርማን ሊያገባኝ ቆርጧል፡፡ እኔም እሺ ብየዋለሁ።»
በሰላም አደሩ፡፡ ከዚያ በኋላ አነጋግራው አታውቅም
ጀርመንዋ ያስለመደችው ሲቀርበት ጊዜ ያንገበግበው ጀመር፡፡በቶሎ ሴት ማግኘት እንዳለበት ገባው:: ቢመለከት፣ ኒኮል አለች::መልኳ እጅግም ነው፡ ወንድ በብዙ ልትስብ አትችልም፡፡ ለዚህ አይደል ባህራምን በገንዘቧ 'ምታኖረው? ግን አሁን ባህራም
አብዛኛውን ጊዜ ከኤክስ ውጪ ነው:: ስለዚህ ሌላ ወንድ መፈለጓ
አይቀርም። እንድያውም ይህን ጊዜ እሱ (ተካ) ሴት ያስፈለገውን
ያህል እሷም ወንድ መፈለጓ አይቀርም፡፡ ሌላ ሴት እስኪያገኝ ማቆያ ትሆነዋለች። እሷም በበኩሏ ባህራም እስኪመጣላት ማቆያ ይሆናታል፡፡ የጋራ ጥቅም!
ማክሰኞ ከምሳ በኋላ ቤቷ ሄደ
ቡና አፈላችለትና «ዛሬስ ምን ሰማህና ልትጎበኘኝ መጣህ?»
አለችው
«እንድ ነገር አስቤ ነው» አላት
«ምን?»
«እኔንና አንቺን የሚጠቅም ሀሳብ ነው»
«ንገረኛ»
«ደስ ትዪኛለሽ፡፡ ስለዚህ ባህራም በሌለበት ጊዜ እዚህ ብመጣ
ጥሩ ይመስለኛል»
«መጥተህስ?»
«እናወራለን፤ እንጫወታለን» እያለ እጁን እጇ ላይ አስቀመጠ
እጇን እያሸሸች «ለኔ የሚሆን ጨዋታ ያለህ አይመስለኝም»
አለችው
«አለኝ»
«የለህም»
«ከባህራም በምን አንሳለሁ?»
በሁሉም ነገር»
«ሞኝ ነሽ። ይልቅ አንድ አቃጣሪ አረብ እየከፈልሽው
ከሚተኛሽ፣ እኔ ያለ ገንዘብ ብተኛሽ አይሻልሽም?» አላት
ፊቷ በቁጣ እሳት መሰለ፣ ግን ድምፅዋ አልተለወጠም
«ወንድ ከሆንክ ሂድና ባሀራምን አቃጣሪ አረብ ነህ በለው። እኔ
ወንድ ስላልሆንኩ የሚገባህን ቅጣት ልሰጥህ አልችልም። ግን ቆሻሻ ነህ፡፡ አንጎልህም ቆሻሻ ነው፣ ሰውነትህም ቆሻሻ ነው። እግርህ ይገማል፣ አፍህ ከሬሳ እኩል ይቆንሳል። አሁን ቤቴ ሳይገማ ተነስና ሂድልኝ አለችው
ተነሳ። ቁጭ እንዳለች ሳታስበው በጥፊ መታት። ከወምበሯ
ተከነበለች። ከወለሉ ላይ በፀጉሯ ጎትቶ እነሳትና እንገቷን ሳማት።
ስትፍጨረጨር እጁን ጠምዞ ወደ አልጋዋ ወሰዳት። አልጋው ላይ
ጣላትና አንድ ጡቷን ጭብጥ አርጎ ያዘ፡፡ መፍጨርጨሯን ተወች
በኣፏ ብቻ
ተወኝ! ብትተወኝ ይሻልሀል!» እያለች ትፎክራለች እጁን ሰደደና ሙታንቲዋን ሊያወልቅ ሲል እንደገና መፍጨርጨር ጀመረች፡፡ ጡቷን የባሰውን በሀይል ዉበጠው:: ፀጥ አለች፡፡ ሙታንቲዋን አወለቀው። እምባዎ ይወርድ ጀመር፡፡ ቁጣዋ
ወደ ልመና ተለወጠ
እባክህ ተወኝ፡፡ ምን አረግኩህ?»
ልመናዋን ከምንም አልቆጠረውም። ጡቷን ጨብጦ እንደያዘ የሱሪውን ቀበቶ ፈታ
አሁንም እምባዋ እየወረዳ «እባክህን ተወኝ፡፡ እርጉዝ ነኝ፡፡
የሁለት ወር ነብሰ ጡር ነኝ» አለችው
የሱሪውን ቁልፍ ይፈታ የነበረው እጁ ባለበት ደረቀ። ጡቷን ይዞ የነበረው እጁ ለቀቃት፡፡ ሱሪውን መልሶ ቆለፈ፡፡ ትቷት ወጣ
አልጋዋ ላይ ተደፍታ ስታለቅስ ባህራም ደረሰ፡፡ ከጋርደን
እያበሽቀ መምጣቱ ነበር። በጥፊ ተመትቶ የቀላውን ፊቷን አየ፡፡
እያለቀሰች የሆነውን ሁሉ ነገረችው
ተናዶ ተካን ፍለጋ ወጣ፡፡ ኒኮል ተከተለችው። ምናልባት
ኣደገኛ ነገር እንዳይስራ ፈርታለች። እሱ በረዥሙ ሲራመድ እሷ
አልደርስበት ብላ ከኋላው ከሩቅ ሱክ ሱክ ስትል፤ ኤክስን አቋርጠው ሲቴ አጠገብ ሲደርሱ ባህራም ተካን አየው፡፡ ጠራው፡፡ ተካ ቆመ፡፡አንድ ትልቅ ዛፍ ስር ነበር። ባህራም ደረሰና ቃል ሳይናገር በጥፊ መታው። ተካ ቡጢ ሰነዘረበት። ባህራም ጎምበስ ብሎ አመለጠና፡
በፍጥነት የተካን እጅ ይዞ ጠምዞ በሀይል ወረወረው: ከዛፉ ጋር
አጋጨው። ከዚያ በኋላ ተካ ሊካላከል አልቻለም፤ አንጎሉ ዞሮበታል፡ ባህራም እጅ ውስጥ እንደ ህፃን ሆነ። ባህራም ጭንቅላቱን ይዞ ፊቱን
ከዛፉ ጋር ደጋግሞ ደጋግሞ አጋጨው። የተካ ፊት በደም ተበከለ።ኒኮል ደርሳ ባታስጥለው ኖሮ ምናልባት ይገድለው ነበር

👍21❤1
ተካ አልሞተም፡፡ ብቻ ሳየው ግራ እጁ በፋሻ ተጠምጥሞ፣ ደረቱ ላይ ታጥፎ፣ ከአንገቱ በፋሻ ተንጠልጥሏል። ፈገግ ሲል አንዱ
የላይኛ የፊት ጥርሱ ወልቋል
ከሁለት ሳምንት በኋላ ወርቅ ጥርስ አስተከለ ባህራምን «እውነት ኒኮል አርግዛለች?» አልኩት
«አዎን አለኝ «እንግዲህ ታሰርኩ ማለት ነው፡፡
ዝም አልኩ፡፡ ምን ልበል?
ያ ሁሉ የሬቮሉሽን ወሬ ከንቱ ቀረ። ኒኮል ካረገዘች ሁለት
ወር አለፈ። ታሰርኩ፡፡»
«ለምን አላስወረዳችሁትም?»
«እንዴት እርገን ልጃችንን እንገድላለን?» አለኝ
ለዚህ መልስ አልነበረኝም፡፡ ዝም አልኩ፡፡ ማን ያውቃል?
ምናልባት የተረገዘው ልጅ የባህራም አማንዳ ወሬውን ስትሰማ አብሬያት ነበርኩ። ሆቴል ክፍሏ ውስጥ ቁጭ ብለን ስናወራ ስንስቅ በሩ ተንኳኳ
“Corne in... I mean Entrez!” አለች እየሳቀች
ተካ እጁን እንደጠመጠመ ገባ፡፡ አየነው
«ሰምተሀል?» አለኝ በአማርኛ። ሸራፋው ክፍት ክድን ይላል
«ምን?» አልኩት
“ሞንቴ ካርሎ ሆቴል ውስጥ ጀምሺድና ያገራችን ልጅ ሞተው ተገኙ።»
“What is it? What is it?” አለች አማንዳ
«እርግጠኛ ነህ?» አልኩት
“What is it?”
«እርግጠኛ ነኝ። ፖሊሶቹ እንደሚሉት፣ ጀምሺድ መጀመርያ
የኛን ልጅ በሽጉጥ ግምባሩን ብሉ ገደለውና -»
"What is it?"
ቀጥሉ የራሱን አንጎል ብትንትን አደረገ፡፡ አሁን
ሬሳዎቻው ወደየአገራቸው ሊላኩ ነው::»
አማንዳ ተነሳችና (እኔ ለካ ሳይታወቀኝ ተነስቻለሁ) ትከሻዬን
እየነቀነቀች፡ በእንግሊዝኛ
«እባክህን ንገረኝ። ምንድነው?» አለችኝ
«አዝናለሁ» አልኳት
«ሉ ነው?» አለች። በሀይል ፈርታለች «ንገረኝ፣ ሉ ነው?»
በጭንቅላቴ አዎን አልኳት
ምን ሆነ? ምን ሆነ? ንገረኝ!» አለችኝ
«ልታገኚው ባትሞክሪ ይሻላል። ወደ ፓሪስ ተመለሺ፡፡»
«ለምን? ለምን? ምን ሆኗል?»
«ልታገኚው አትችይም»
በሀይል እየነቀነቀችኝ፤ በጠንካራ ድምፅ
«ንገረኝ!» አለችኝ
“ከንግዲህ ማንም ሊያገኘው አይችልም» አልኳት
በሹክሹክታ መሳይ ድምፅ፤ «ሞቷል?» አለችኝ
ዝም አልኳት፡፡ ወደ ተካ ዞረችና፣ በተዘረጋ እጇ በሩን እያመለከተች
«Get Out!" ብላ ጮኸችበት
ባማርኛ «ቂንጥራም!» ብሏት ወጣ፡፡ በሩን ዘጋ፡፡
ረጋ ባለ ሁኔታ ቦርሳዋን ከሶፋው ላይ አነሳች፣ ወደ በሩ
መራመድ ጀመረች። ዘልዬ ቀደምኳትና በሩጋ ቆምኩ፡፡
አሳልፈኝ» አለችኝ፡፡ አታለቅስም፡፡ ያዘነችም አትመስልም፡፡
አይኖቿ ፍዝዝ ብለው፣ በህልም ውስጥ ያለች ትመስላለች
«የት ትሂጂ?» አልኳት
«ሄጄ ሉን አየዋለሁ።
ሁለት እጄን ትከሻዋ ላይ ጫንኩና
«እንድታዪው አይፈልግም፡፡ እንደድሮው ሲስቅ ሲጫወት
እንድታስታውሺው ነው የሚፈልገው» አልኳት
«ሲስቅ ሲጫወት! ሲስቅ ሲጫወት!» አለችና ስቅስቅ ብላ
ማልቀስ ጀመረች። ትከሻዋ ላይ፧ ባሉት እጆቼ ወደኔ ሳብ
አደረግኳት። ራሷን ደረቴ ላይ አንተራሰችና ለቅሶዋን ቀጠለች
አልቅሳ ስትጨርስ ሀኪም ጠራሁላት፡፡ የሚያስተኛ መርፌ
ወጋትና ሄደ
«አጠገብሽ ብሆን እወድ ነበር» አልኳት
ክፍሉ ውስጥ አንድ ትንሽ አልጋ አስነጠፈችልኝ፡፡ ተኛች።
ሲመሽ ወጣ ብዬ እራት በልቼ ተመለስኩ፡፡ ተኝታለች። ልብወለድ
መፅሀፍ ሳነብ አምሽቼ ተኛሁ።
ጧት ተነሳች። ገላዋን ታጠበች። ረዥም ስስ ሀምራዊ የሌሊት
ልብሷ ላይ ከፎጣ የተሰራ ወይን ጠጅ የቤት ካፖርት ደርባለች።
ብርሀን መሳይ ፀጉሯ በሚያስደስት አኳኋን ተሞነጫጭሯል። አብረን
ቁርስ በላን። ሉልስገድን እንዳናነሳ ፈርተን ስለሆሊውድ ማውራት
ጀመርን ቁርስ በልተን ስናበቃ፣ እኔ ሶፋው ላይ ቁጭ እንዳልኩ
ተነሳችና ከፊቴ ቆመች። በዝግታ የፎጣ ካፖርቷን መቀነት ፈታች።
ካፖርቱን አውልቃ ለቀቀችው። ምንጠፉ ላይ እግሮቿ ዙርያ ተጠቀለለ፡፡ ሀምራዊ ስስ የሌሊት ልብሷ ድምብሼ ገላዋን እንደ ደመና ከቦታል እንጂ አልሸፈነውም፡፡ጡት
መያዣና ሙታንቲ አላደረገችም፡፡ አቤት ወርቃማ ጭገሯ ማማሩ! እጇን ዘርግታ ፊቴን ዳሰሰች። ትርጉሙ የማይታወቅ ፈገግታ
ፊቷ ላይ ሰፍሯል።
ከተቀመጥኩበት ወደፊት ጎንበስ በማለት ምንጣፉ ላይ ተምበረከክሁ።
ፊቴን ለስላሳ ሆዷ ላይ አሳረፍኩ፡ እጆቼን ወፍራም ዳሌዋ ዙርያ
ጠመጠምኩ፡፡ ራሴን እቅፍ አደረገችኝ። እንደዚህ ሆነን ረዥም ጊዜ ቆየን። ምን እንደፈለገች ስላልገባኝ፡ ምንም ባላደርግ ይሻላል በማለት ባለሁበት ረጋሁ። በኋላ፤ ከተምበረከክሁበት አስነሳችኝ። ወደ አልጋዋ ወሰደችኝ። መኖሩን ሰምቼው የማላውቅ አዲስ የግብረ ስጋ
አገር አሳየችኝ ይሄ ሁሉ ሲሆን፣ ያ ትርጉሙ የማይታወቅ ፈገግታ ፊቷ ላይ ብቅ ጥፍት ይል ነበር። ምሳ ከበላን በኋላ ሻንጣዋን መኪናዋ ኋላ ወምበር ላይ አስቀመጥኩት። አብሬያት ከኤክስ ወጣሁ። ወደ
አቪኞን የሚወስደውን መንገድ እንደያዘች መኪናዋን አቆመች።
አየችኝ። ሰማያዊ አይኖቿ እምባ አቀረሩ። አንገቴን ስባ አፈ ላይ
ሳመችኝ። መሀረቤን እያቀበልኳት
«አሁን የት ነው የምትሄጂው?» አልኳት
«እኔ እንጃ። ብቻ ከ'ንግዲህ ኤከስን ማየት አልፈልግም» አለች
እንባዋን እየጠረገች ከአጭር ዝምታ በኋላ «አንድ ነገር ልጠይቅሽ እፈልግ ነበር»
አልኳት። ግን አመነታሁ፡፡
«ገብቶኛል» አለችኝ «ጧት ለምን እንደዚያ እንደሆንኩ ልትጠ
ይቀኝ ነው የምትፈልገው?»
«አዎን»
ሳቅ እያለች «አንተስ ለምን እሺ አልከኝ?» አለችኝ
«እኔማ ሻንዜሊዚ ካየሁሽና ሌላ ሴት እየመሰልሽኝ ከተዋወቅን
ጀምሮ "አምረሽኝ ነበር።»
«እንደሱ ቢሆን ኖሮ ፓሪስ የተገናኘን ጊዜ በጣም ይመች
አልነበረም? ይልቅ እውነቱን ንገረኝ፡፡»
«እኔ ለራሴ በጣም ደስ እንዳለኝ አውቃለሁ እንጂ፣ ምኑም
አልገባኝም፡፡ አንቺ ንገሪኝ እስቲ»
ያ ምስጢራዊ ፈገግታ ፊቷ ላይ ብቅ አለ
«እውነቱን ለመናገር የሚበቃ ቃላት የለኝም» አለችኝ ግን
እንዲህ ልበልህ፡፡ ሞት መጥቶ በግድ ካልወሰደኝ በስተቀር፣ እውስጤ ገብቶ ስፍራ እንዲይዝ አልፈቅድለትም፡፡ መቸም ቢሆን፥ ጥልቅ ሀዘን ውስጥም ብሆን፡ ህይወት ሞትን ድል እንዲነሳው እፈልጋለሁ፡፡ ጧት ሳይታወቅህ፣ እውስጤ ገብተህ ሞትን እንዳባርረው አግዘኸኛል።
ምነው በመገረም ታየኛለህ? ተለውጫለሁ አላልኩህም እንዴ?»
«አሁንማ ገባኝ፡፡ ውስጥሽ ከፀጉርሽ ይበልጥ ውብ ሆኗል»
አይኖቿ እንደገና እምባ ሞሉ። እንደገና በአንገቴ ስባ በረዥሙ
ሳመችኝ
«ተጠንቅቀሽ 'ንጂ፡ እሺ?» አልኳት
ሳቅ አለች «አትስጋ። አገርህ ከመሄድህ በፊት ፓሪስ ብቅ ብለህ
ታየኝ የለ?»
«እመጣለሁ፡፡ እስከዚያ አድራሻሽን ላኪልኝ፡፡»
«ትፅፍልኛለህ?»
«በሳምንት በሳምንት፡፡»
«ጥሩ ልጅ ነህ፡፡ በጣም ጥሩ ልጅ ነህ፡፡»
«ላንቺ ብዬ አይደለም፡፡ ለራሴ ብዬ ነው። እንዳንቺ ያለች
ብርቱ ውብ ሴት ካየሁ አያስችለኝም፡፡»
እንደገና በአንገቴ ስባ አፌ ላይ በሀይል ሳመችኝ። ከመኪናዋ
ወረድኩ፡፡ ሞተሩን ቀሰቀሰች። ጭልጥ አለች። እስክትጠመዘዝ
በአይኔ ተከተልኳት። ጥልቅ ሀዘን ተሰማኝ። የሄደችበትን መንገድ
ሳይ የቆየሁበት አይኔ ብዥ አለብኝ። አይኔን በሀይል ጨፈንኩ።እምባው ጉንጩ ላይ መውረድ ጀመረ። እጄን ኪሴ ከተትኩ።
መሀረቤ የለም፡፡ እማንዳ ይዛው ሄዳለች
ፊቴን ወደ ከተማው መለስኩ፡፡ ኤክስ ራቅ ብላ ትታየኛለች።
ከበላይዋ ንፁህ ሰማይ ተዘርግቷል። የአማንዳን አይኖች ይመስላል....
💫ይቀጥላል 💫

👍20
#ተነሳና_ተነስ
ቀልደኛ ገበሬ ሳይቀልድ
በሰኔ ወር እየሞተ
ሰኔና ሰኞ ገጥሞበት
ሀገሬው እያቃሰተ
እያየህ በየጎዳናው
እያየህ ባደባባይ ላይ
ከምድር አረንቋ በዝቶ
ከሰማይ ተከፍቶ ቀላይ
ባትፈረጅ ምን አለበት
ባትባልስ ክፉ ብቃይ
አትነስ እንዳነሱቱ
ለፍቶ አዳሪውን አታብግን
በተንኮል ከዘሩት ማሳ
ከሰዎች ጭዳ ሳትዘግን
ከራስህ ትንሽ ቀንሰህ
ላገርህ በብዙ ወግን
ልጅ እያለህ በጨቅላነትህ
ከመላእክት ስታወጋ
ፈገግ ብለህ ባደክበት
በእናት ባባትህ አልጋ
በእስተርጅና ጭንቀት ሳይሆን
ምሽታቸዉ እንዲነጋ
አትቅበዝበዝ ሰከን በል
ከቀልብህ ሁን ትንሽ እርጋ
ግድ የለህም እንኳን ለሞት
ለእርጅና እንኳን ይጠብቋል
” እደግ" ብሎ ” እንትፍ” ያለም
ለነፍስ ይማር ይመርቋል
የጭብጨባ ጎርፍ አይዋጥህ
ላልባሌ ጆሮህን ድፈን
ብቻህን ብትሆን ቢበርድህ
ቢያቆራምድህ የኑሮ ቆፈን
በማሕበር አትመራ
ዙርያህን እያየህ መርምር
” የማይሆን” ቢሆንስ? ብለህ
አንዳንዴ በልብህ ጠርጥር
የሰጡህ ጭምብል አይሆንም
ፊትህ ላይ እንዳታጠልቀው
እምነትህን በታማኝነት
ደግመህ ደጋግመህ አጥብቀው
ላብህ ነው ጥሪት የሚሆን
ሳትጠረጥር እወቀው
ያርባ ቀን እጣህን ይዘህ
የሌሎችን ግን ልቀቀው
ሞትን እየሞትክ ሳይሆን
በሕይወት ሆነህ ጠብቀው
🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
ቀልደኛ ገበሬ ሳይቀልድ
በሰኔ ወር እየሞተ
ሰኔና ሰኞ ገጥሞበት
ሀገሬው እያቃሰተ
እያየህ በየጎዳናው
እያየህ ባደባባይ ላይ
ከምድር አረንቋ በዝቶ
ከሰማይ ተከፍቶ ቀላይ
ባትፈረጅ ምን አለበት
ባትባልስ ክፉ ብቃይ
አትነስ እንዳነሱቱ
ለፍቶ አዳሪውን አታብግን
በተንኮል ከዘሩት ማሳ
ከሰዎች ጭዳ ሳትዘግን
ከራስህ ትንሽ ቀንሰህ
ላገርህ በብዙ ወግን
ልጅ እያለህ በጨቅላነትህ
ከመላእክት ስታወጋ
ፈገግ ብለህ ባደክበት
በእናት ባባትህ አልጋ
በእስተርጅና ጭንቀት ሳይሆን
ምሽታቸዉ እንዲነጋ
አትቅበዝበዝ ሰከን በል
ከቀልብህ ሁን ትንሽ እርጋ
ግድ የለህም እንኳን ለሞት
ለእርጅና እንኳን ይጠብቋል
” እደግ" ብሎ ” እንትፍ” ያለም
ለነፍስ ይማር ይመርቋል
የጭብጨባ ጎርፍ አይዋጥህ
ላልባሌ ጆሮህን ድፈን
ብቻህን ብትሆን ቢበርድህ
ቢያቆራምድህ የኑሮ ቆፈን
በማሕበር አትመራ
ዙርያህን እያየህ መርምር
” የማይሆን” ቢሆንስ? ብለህ
አንዳንዴ በልብህ ጠርጥር
የሰጡህ ጭምብል አይሆንም
ፊትህ ላይ እንዳታጠልቀው
እምነትህን በታማኝነት
ደግመህ ደጋግመህ አጥብቀው
ላብህ ነው ጥሪት የሚሆን
ሳትጠረጥር እወቀው
ያርባ ቀን እጣህን ይዘህ
የሌሎችን ግን ልቀቀው
ሞትን እየሞትክ ሳይሆን
በሕይወት ሆነህ ጠብቀው
🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍6❤3
#ሚስቴን_አከሸፏት
፡
፡
#አምስት (መጨረሻው)
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
...ፌቨን ከዛ ቀን በኋለ የፀጉሩ ነገር እንዳበቃለት ሲገባት ያማልለኛል ያለችውን ነገር ሁሉ እያሳየች የተንኮታኮተ ፍቅሬን ልትመልሰው ተፍገመገመች። አንዴ አጭር ቀሚስ ለብሳ እግሯን እስከታፋዋ ታሳየኛለች፤ (እግርሽ ያምራል እላት ነበር ድሮ እንደዛሬው እያንቀዠቀዠ አልባሌ ቦታ ሳይወስዳት በፊት) የእጇን ጣቶች ብታወናጭፍ፣ ዓይኗን ብታፈጥ፣ከንፈሯን ብታሞጠሙጥ... ውሉን ቆርጣ ጥላ ትርፍራፊ ውበቷን ብታግተለትል ወይ ፍንክች። እንደውም የባሰ አስጠላችኝ። አይናገረውም እንጂ ሁሉም አፍቃሪ ለዘላለሙ የሚያመልከው የሚያፈቅረው ሰው ላይ በየቀኑ ዓይኑ የሚፈልገው የውበት አማካይ ቦታ አለው። ሌላው ሁሉ ካለዚህ ነጥብ ባዶ ነው። ለእኔ የፌቨን አማካይ የውበት ቦታ ፀጉሯ ነበር። ፌቨንን እንደከተማ ብመለከታት መሐል አደባባይዋ ፈርሷል። አንጋፋ ፍቅር አዲስ ከተማ ላይ መኖር ያንገሸግሸዋል።
የዘመናዊው ፋሽን ትልቅ ችግር የሴቶችን ፀጉር የሚያደንቅ ተፈጥሯችንን በግድ ጠምዝዞ ሴቶች ዳሌ ላይ ለማሳረፍ መጣሩ ነው። ሴቶች እግር ላይ ሴቶች ጡት ላይ ዓይናችንን በግድ ማስተከል። እንቢ ማየት
አንፈልግም ስንል ውበት የማይገባን ገገማዎች መሆናችንን በማሳመን ስልጡን አይደላችሁም ይለናል ሞላ ያለች ሴት እይታችንን ትስበው ይሆናል። ፋሽን ተብዬው ግን የትከሻዋ አጥንት ካልተሰረጎደ
ሴት ምኑን ሴት ሆነች ብሎ ሊያሳምነን ይጥራል። ፋሽን ጉልበተኛ ነው። በተለይ ሴቶች ላይ ክንዱ ይበረታል። ዛሬ ፋሽን ለመከተል ፀጉሯን የቆረጠች ሴት ነገ የላይኛውን የፊት ጥርስ አስነቅሎ በባዶ ድድ መገልፈጥ ያምርብሻል ብትባል ጥርሷን ከማራገፍ አትመለስም፡፡ የተጋነነ ይመስላል እንጂ ባለፉት
አስር ዓመታት በአገራችን አይሆኑም ያልናቸው ጉዳዮች ዛሬ ላይ ለትውልዱ ተራ ጉዳዮች ሆነዋል።ደግሞ ፍጥነታችን
የፌቨንን ፀጉር መቆረጥ ከሴት ልጅ ግርዛት ለይቼ አላየውም። ልዩነቱ የሴት ልጅ ግርዛት በሴቷ ስሚት ላይ መቀለድ ሲሆን ይሄንኛው በእኔ ፍላጎትና ስሜት ላይ መጫወት መሆኑ ነው። እናም ፌቨንን እፈታታለሁ !! እሷን ብሎ ሚስት። የፍርድ ቤት ቀጠሮዬ ነገ ነው። ፌቨን እናቷ ጋር ከሄደች ሃያ ቀናቶች አልፈዋል፡፡ አልናፈቀችኝም። እንደውም የተሰማኝ ሰላም ልክ አልነበረውም። ትንሽ የተሰማኝ ፌቨንንም ሆነ እናቷን በገንዘብ የምረዳቸው እኔ ነበርኩ በዚህኛው ወር ግን ምንም አልሰጠኋቸውም። ከፌሽን
ጋር ስለተጣላሁ ሳይሆን ብሩን ብልክላቸው ፌቨንን የመፈለግ ስሜት ያደረብኝ እንዳይመስላቸው
በማሰብ ብቻ ነው….
ከፌቨን ጋር ከተለያየን በኋላ ብዙዎች እንዳሰቡት ስትናፍቀኝ “ማሪኝ” ብዬ ቤቷም አልሄድኩ።
ስልክም አልደወልኩም። እንደውም አንዳንዶች፣ “ሚስቴ ቤቱን ጥላልኝ ስትሄድ ቤቱ ሊበላኝ ደረሰ፣ ጭር አለ ኦና ሆነ” ምናምን የሚሉት ነገር ለምን እንደሚባል ገረመኝ። በጣም ነው ቤቱ የተስማማኝ ገነት ነው የሆነብኝ ! ምግብ ራሴ አበስላለሁ፣ ቤቴን በደንብ አፀዳለሁ፣ አነባለሁ፣ ፊልም አያለሁ
(እንደውም ከዚያ ፌቨን ከምትከፍተው አሰልቺ የቴሌቪዥን ድራማ ተገላገልኩ) እና ደግሞ ሰላም ሆንኩ!! እንደውም ባልና ሚስት የፈለገ ቢፋቀሩ፣ ትንሽ መለያየት፣ ራሳቸውን የሚያደምጡባት
“ሱባዔ” መሰል ብቸኝነት ታስፈልጋቸዋለች ብዬ አሰብኩ።
ፌቨንን ለራሴ እንኳን ስሟን በውስጤ መጥራት ይቀፈኛል። በቃ በተፈጥሮዬ ወግ አጥባቂ ነገር ነኝ ማለት ነው ብዬ አሰብኩ። እና እንዴት ይሄን ሁሉ ዓመት አብራኝ የኖረች ሴት ያውም በፍቅር ተነስታ ስትሄድ ምንም ሳይመስለኝ ቀረ። ለደቂቃ መኝታ ቤታችን ውስጥ ስትበር የነበረች ትንኝ
እንኳ በሆነ ሽንቁር ስትወጣ የሚናፍቅ ነገር አላት። አይ ጤነኛ አይደለሁም ማለት ነው። ወይስ የሆነ ውስጣችን ሳያውቀው የሚሰለቸው አብሮነት አለ ... ምክንያት ፈልጎ የሚፈነዳ ... ፌቨንን ሳላስበው ውስጤ ሰልችቷት ይሆን ? ዓይቷት የማይቋምጥ ወንድ የለም … ቁንጅናዋ እንግዳ ነገር ነው ..
መኝታ ቤት ገብታ ወደ ሳሎን ስትመለስ እንኳ አዲስ ቆንጆ ሴት እንዳየ ጎረምሳ ልቤ ይደነግጥላት
ነበር ... እና እንዴት ነው ነገሩ ... እንዲህ ልክ የሌለው ግዴለሽነት የሞላኝ ወይስ እየቆየ እንደተዳፈነ
እሳት ሊያንገበግበኝ ይሆን ...
ለነገሩ ቆንጆ ሴቶች ቶሎ ነው የሚሰለቹት ይባላል። በጥናት ባይረጋገጥም የሆነ እውነት እንዳለው በብዙ ቆንጆ ፍቅረኛ ባላቸው ጓደኞቼ ታዝቤያለሁ። በተለይ ከተጋቡ በኋላ ቆንጆ ሚስቶች ለውጭ ተመልካች እንጂ ለባሎቻቸው ያን ያህል አስገራሚም አስደሳችም ነገር የላቸውም እየተባለ ከፉኛ
ይታማል ሚስቶቹም ራሳቸው ይሄ ነገር ግራ ይገባቸዋል አንድ ጓደኛዬ እንዳለኝ ከሆነ እንደውም
ቃል በቃል፣ ለዛ ቢስ ናቸው !!” ነበር ያለው እንግዲህ ከሰፊ የብሶት ምክሩ የተወሰነውን ሳስታውስ (ያኔ እንኳ ችላ ብዬው ነበር) ቁንጅናቸው ይስብሃል፣ ቁንጅናቸውን ትፈልጋለህ፣ ታገኘዋለህ፣ ቁንጅናቸው መጋረጃ ሆኖ ስለሚጋርድህ ከማግኘት ቀጥሎ ያለውን ሕይወት አታስበውም። መጋረጃውን ስታልፍ ግን ጭው ያለ በረሃ ይጠብቀሃል.. ሰሐራ ! ምንም አይኖርም ወላ ሃንቲ !! ሁሉም ነገራቸው ወዲያው ነው
የሚሰለችህ... እንደውም እነሱን ለማግኘት የደከምከው ድካም ከንቱ ሆኖ ስለሚታይህ ነጭናጫ
ትሆናለህ ድሮ ይቺን ሚስትህን አፍቅረህ ስትንከራተት ፊት የነሳሃት በፍቅር ዓይን ስትስለመለምልህ
የነበረች ጎራዳ ሽቦ ፀጉር ልጅ ሁሉ ትናፍቅሃለች ! ለዛ ነው ብዙውን ጊዜ “ልዕልት የመሰለች ሚስት
አስቀምጦ ሰራተኛው ጋር…” ምናምን ሲባል የምትሰማው እንጅማ ሚስትህ ልዕልት ባትመስልም ሌላ ሴት ጋር ሂድ የሚል ፍርድ የለም መቼስ።” የጓደኛዬ ምክር ይከሰትልኝ ይጀምራል። የበላኝን
እንደሚያክልኝ ሁሉ ንግግሩን የራሱ ልምድና አመለካከት አድርጌ ከማድመጥ በላይ ዓለምአቀፍ
የሴቶች ባህሪ አድርጌ ልቀበለው ይዳዳኛል። ማንም ሰው በጋራ ብሶት ውስጥ ሲኖር በአዕምሮው ልክ ሳይሆን በብሶቱ ልክ ያስባልና።
“ሴትን ልጅ ለማየት ይሄ ደካማ ሥጋዊ ዓይን በቂ አይደለም ድፍን የስሜት ሕዋሳቶችህ፣ በአካባቢህ ያለው እውነታ፣ ታሪክ፣ ፍልስፍና፣ ኃይማኖት፣ አስተዳደግህ፣ የትምሕርት ደረጃህ ሁሉ “ተቀናጅቶ” መሥራት ይኖርበታል። በደመ ነፍስ ዘለህ ከገባህ በደም ግፊት ዘለህ መቃብር ጉድጓድህ ውስጥ ነው
የምትገባው ያውም በጭንቅላትህ። ፍቅር ላይ ያለህ ነገር ከተበላሸ በምድር ላይ ያለህ ማንኛውም ነገር እንደተበላሸ ቁጠረው። ሌላው ቢቀር እየቆየ የሚያገረሽ የተበላሸ ትዝታ ይኖርሃል። ልብህን ለፍቅር
ስትሰጥ ወሲብ ያዞረው ናላህን አሽቀንጥረህ መጣል አለብህ። እሱ ነው እንደጋሪ ፈረስ ሸብቦ አንድ ነገር ብቻ እንድታይ የሚነዳህ። ለምን እቅጩን አልነግርህም ያኔ አንድ ቤት የሁለትዮሽ ስብሰባ ላይ ስትገናኝ
ተረከዝ አይመስጥህ፣ ዳሌ አያማልልህ፣ ከንፈር አያስጎመዥህ፣ ስርቅርቅ ድምፅ ቀልብ አያሳጣህ፣ ጉችም ይበል
ዝርግፍም ይበል ጡት ከመጤፍ አይቆጠር ሃቂቃዋ የፍቅር ዘርልብህ ውስጥ ከሌለች
አለቀልህ !”

👍45❤3👏3👎1
“የተንዛዛ እና የሚያዛጋ የሕይወት ድራማ ውስጥ ራስህን ታገኘዋለህ አቤት ሲያስጠላ። አንድ
የማይመሽና የማይነጋ ረዥም ቀን ላይ ያለህ ነው የሚመስልህ። ሁልጊዜ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት የሚመስል የሆነ ጠራራ ሕይወት ! በቲቪ፣ በመጽሔት ምናምን ታዋቂ ሰዎች፣ “ሚስቴን እወዳታለሁ፣ ባሌን እወደዋለሁ” ሲሉ ሰምተህ ታውቃለህ አይደል ? እስቲ ዝም ብለህ አስበው ሚስቱን ካልወደደ
ማንን ሊወድ ነበር ታዲያ። እሷስ “ባሌን እወደዋለሁ” … ፓ ተናግራ ሞታለች እና ምን ይጠበስ::
ባልን መውደድ የተለየ ብቃት የሚያስፈልገው ጉዳይ ሲያስመስሉ ይገርመኛል። መዋደድ ያንተም የሚስትህም ብቃት አይደለም። (ሰምተኃል) ፍቅር ለሁለታችሁም ያደላችሁ ፀጋ ብቻ ነው ! ፍቅር የተጠራ ሞተበት የውሻሸት አብሮነት የተሸከመ ጎጆ ሁለት ያልተመቻቸው ሬሳዎች ያቀፈ የአስክሬን ሳጥን ነው !! ለስንቱ በነጭ ቬሎ ስር ጥቁር የውስጥ ልብስ ለለበሰ ትዳር ሃይሎጋ ብለናል !”
“እና በዚች ምድር በጥልቀት ማሰብ ያለብህ ነገር ፍቅርህን ማን ላይ እንደምትጥል ነው። መጽሐፉ
የከበረውን እንቁ አሳሞች እግር ስር አትጣሉ ሲልህ ቀልድ መስሎህ ችላ እንዳትል። ይሄ ለሴትም ይሰራል። ስንቷ መሰለችህ ያላትን ማንነት አራግፋ ለአንዱ አሳማ አፍቃሪ ሰጥታ አፍንጫሽን ላሽ ስትባል እድሜ ልኳን ከራማዋ እንደተገፈፈ የውሻሸት ኖራ ያለፈች ! ካላመንክ እዚሁ አዲስ አበባ አንዷን ኑሮ
የተመቻት የምትመስል ቆንጆ ጠጋ በልና “እህ” ብለህ አድምጣት። ከእድሜዋ በላይ ብሶት ትዘረግፍልሃለች። ብሶት የሌላት ለአቅመ ሔዋን የደረሰች ሴት ካገኘህ ወይ እድሜዋ ለአቅመ
ብሶት አልደረሰም አልያም ከባቄላ ፍላት ያመለጠች ጥሬ ባቄላ አጋጥሞሃልና ፈጣሪህን አመስግን። ሆድ ይፍጀው ብሎ እየተሽቀረቀረ ነው እንጂ ከተማው ሁሉ በፍቅር ቁስለኛ የተሞላ ማገገሚያ ሆስፒታል እኮ ነው። ሁሉም አንድ ቀን ባንድ ላይ የብሶቱን ያህል ስቅስቅ ብሎ እስኪወጣለት ቢያለቅስ አዲስ
አበባ ላይ ብቻ ትልልቁን ሕንፃ ሁሉ እንደጀልባ የሚያንሳፍፍ የእንባ ባሕር ይፈጠር ነበር !”
ደግሞ አንተ ቀለል አድርገህ የምታየው ነገር ለሴቶች እንዴት ትልቅ ታሪክ መሰለህ አድዋ ነው!
እውነቴን ነው። በቅርቡ የተዋወቅካትን ፍቅረኛህን ያለፈ ሕይወት ብትጠይቅ (ባትጠይቅም ትነግርሃለች …ችግሩ የምትነግርህ መናገር ያለባትን ሳይሆን የርሷን ታማኝነት፣ ታጋሽነት፣አፍቃሪነት፣የካዳትን ፍቅረኛዋን ርኩስነት፣ አርዮስነት ያሳያል ብላ ያሰበችውን ተረት ብቻ ነው) ለምሳሌ እያወራችሁ እያለ ትክዝ ብላ እንዲህ ልትልህ ትችላለች፤
“ዘነበ የሚባል ፍቅረኛ ነበረኝ። ስምን መልዓክ ያወጣዋል። በያገኘበት የሚዘንብ። እና አንድ ቀን እዚህ ቶታሉጋ አበራሽ ሥጋ ቤት ከራሴ ጓደኛ ጋር ... ማንትስ ድርጅት ሴክሬቴሪዋ ...ከእሷ ጋር እየተጎራረሱ ቅቅል ሲበሉ በዓይኔ በብረቱ አየኋቸው .. ድሮም ወንድ ማመን” ብላ እንባዋ በዓይኗ ግጥም። አንተ ታዲያ፣ቅቅል መብላት ምን ይገርማል.. ብለህ ካሰብክ አለቀልህ። ቅቅል' ቅኔም ሊሆን ይችላል፤ አንተ ጠበስኳት ስትል እሷ ትልቅ የተረት ብረት ድስት ውስጥ እየቀቀለችህ !”
ወይኔ ጉዴ ብቻዬን ባዶ ቤት ተቀምጩ በሐሳብ ስባዝን ማበዴ ነው መሰል። ፌቨን እያለችኮ ማሰብ አልችልም ነበር። ትንሽ ዝም ካልኩ፡ ምን ሆንክ የኔ ማር ... መሥሪያ ቤት ተጋጨህ አመመህ
ራስህ…” በቃ ንዝንዝ ነው። አሁን እስከ ነገ ወዲያ ባስብ ማን ከልካይ አለብኝ ሃሌ ሉያ !!
እና ከሚስቴ ፌቨን ጋር ልፋታ የመጨረሻው የፍርድ ቤት ቀጠሮዬ እንደነገ ሆኖ እንደዛሬ ማታ አንድ ጥግ ላይ ኩርምት ብዬ እንዲህ የባጥ የቆጡን ሳስብ ሌሊቱ ተጋመሰ። “አብርሽ እስካሁን አልተኛህም”የሚል ድምጽ ሰምቼ ቀጥ ብል ማንም በቤቱ የለም … ግን የሆነ አናቱ ላይ እሳት የመሰለ ወርቃማ ፀጉር
የሚንቀለቀልበት ፍጡር ውልብ ሲል ያየሁ መስሎኝ ነበር። በስመዓብ (የማርያምን ብቅል ፈጭቻለሁ አንቺ። በራሴ አባባል በደረቅ ሌሊት ከት ብዬ ሳቅኩ። እስቲ አሁን ምን አሳቀኝ። አይይይይይ ያ እኛ ሰፈር የነበረው ጃንቦ የሚባለው ሰውዬ ልክ የዛሬ ሃያ አመት መወፈፍ ሲጀምር ከሌሊቱ ስምንት ስዓት እንዲህ እንደኔ ከትከት ብሎ ስቆ ነበር አሉ። ማበዱንስ ልበድ …. ግን እንዴት ፋሽኑ ያለፈበት አስተባለድ አብዳለሁ…
ለነገሩ የሳቅኩት ነገ ዳኛዋ ስታፋታን ምን እንደምንል አስቤ ነው። ቆይ ሰው ሲጋባ በሐዘን ቢሆን በደስታ፣ በጤና ቢሆን በሕመም አብሬያት ... አብሬው ልሆን ምናምን ተብሎ ቃል ይገባል። ባልና ሚስት ሲፋቱ ምን ይሆን የሚሉት። ሰው ሲፋታ አይቼ ስለማላውቅ ግራ ገብቶኛል ...
በመንገድ ቢሆን በሥራ ቦታ፣ በፒያሳ ቢሆን በመርካቶ፣ የደረሰችበት ላልደርስ …. ሃሃሃሃ
እኔና ፌቨን ስንጋባ ያጋቡን የእናቴ ንስሃ አባት መምሬ አምሳሉ ነበሩ። እሳቸው የሚሉትን እየተከተልኩ
እንድል አዝዘውኝ ነበር። በነገራችን ላይ መምሬ እኔን ስለማያምኑኝ ቶሎ ቃልገብቼ በቀለበት ስታሰር
ለማየት ቸኩለው ነበር። እናቴንም ብለዋታል፣አዬ አብርሃም ላገባ ነው ሲልሽ አምነሽ በሬ አስገዛሽ፣ እንጀራ ጋገርሽ፣ ዳስ አስጣልሽ…”
እና ሲያጋቡኝ መስተዋቱ በተሰነጠቀ መነፅራቸው አናት በጥርጣሬ እያዩኝ ነበር ቃል ያስገቡኝ፣
“በጥጋብ ቢሆን በርሃብ ከጎኗ ልሆን ቃል እገባለሁ!” አሉ።
“ብጠግብም ባልጠግብም ቃል እገባለሁ!” አልኩ ተቀብዬ፤ እኔ አሳጠርኩ ብዬ ነው።
አብርሃም … ተው በሰርግህ ቀን እንኳን ያላዘዙህን አታውራ” በማለት ሰርገኛው ሳይሰማ ወደእኔ ጠጋ ብለው አንሾካሾኩ። ፌቨን በሳቅ ፍርስስስስ !ፌቨን ያሳቃት ገብቶኛል። ብዙ ጊዜ ትለኛለች፣ “አብርሽ አንተኮ አንዳንዴ ወሬ ስትጀምር ከጉዳዩ ጋር የማይያያዘውንም፣ የሚያያዘውንም ትቀላቅለዋለህ” አባ ስለደገሙላት ነው የሳቀችው። መምሬ ግን በፌቨንም ሳቅ ተቆጡ፣
“ኤዲያ አንቺ ደሞ እስቲ ለሰርግሽ ቀን እንኳ በልኩ ሳቂ…” ብለው የሆነ ነገር በግዕዝ ተናገሩና በአማርኛ ተረጎሙት፣ “ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳሉ።” መምሬ የሚሉትን እኔና ፌቨን ተከትለን ቃል ገባን። ምነው የዛን ጊዜ፣ “ባሌ ሳይፈቅድ ቅንጣት ፀጉር ላልቆረጥ” የሚል ቃል ጨምረውልኝ በነበረ
ፍርድ ቤት ስደርስ ግቢው ውስጥ የፌቨን እናት፣ ወንድሟ፣ ፌቨንና ያች ማሜ የምትባል ተደርድረው
ተቀምጠዋል። በቀጥታ ሄጄ ማዘርን ሰላም አልኳቸው። “
አብርዬ” ብለው በሁለት እጃቸው ሰላም አሉኝ። ልክ እንደሆነ ባለሥልጣን ነበር ያከበሩኝ። ውስጤ የሆነ ሕመም ተሰማው። የባሰ ያዘንኩት ደግሞ ወንድሟ በስርዓት ሰላም ሲለኝ …. ኮሌታው ንትብ ያለ ሸሚዝ ለብሷል። አያለሁ፣ አያለሁ ዓይኔ
እየተስገበገበ እያንዳንዷን ነገር ያያል። እየቀፈፈኝ ማሜ የምትባለውን የፌቨንን ጓደኛ ሰላም አልኳት። በስርዓት ሰላም አለችኝ። ዛሬ ሰዉን ሁሉ ምን ነካው ብዬ ተገረምኩ። ችሎቱ እስከሚጀመር አብረን ተቀመጥን። ፌቨን በፍርሃት አልፎ አልፎ ቀጥ እያለች ታየኛለች። ፀጉሯን በጥቁር ሻሽ አስራዋለች።
ዳኛዋ አንዴ አየት አድርጋኝ ገባች ..
“እና ሐሳብህን አልቀየርክም አብርሃም” ንግግሯ ተለሳልሷል።

👍20❤1
“አልቀየርኩም። ዳኛዋ እንደማሰብ አለች እናም ያለምንም ውጣ ውረድ ከሰዓት ቀጠረችን።
ልታፋታን። ከችሎቱ ስወጣ ፌቨን እንደ ጆቢራ ድንገት ፊቴ ተገተረች። ሁሉም ነገር ስልችት እንዳላት ታስታውቃለች። እናም አየችኝ፣ በጣም አየችኝ። ዓይኖቿ በእንባ ተሞሉ። ከንፈሯ ይንቀጠቀጣል፤ ልታብድ መስሎኝ ነበር።
“አትረባም አብርሽ አትረባም” ብላኝ ልትሄድ መንገድ ከጀመረች በኋላ ተመልሳ እጇን ስትዘረጋ
በጥፊ አጮለችኝ ብዬ ዓይኔን አጨናበስኩ። ፌቨን ግን ምን እንዳደረገች ታውቃላችሁ። ፀጉሬ ላይ ያየችውን የሆነ ነቁጥ ነገር አንስታልኝ ቀስ እያለች በርቀት ወደሚጠብቋት ቤተሰቦቿ አዘገመች። ምን ማለት ነው። ማንም ይሄ ምን ማለት እንደሆነ መግለፅ አይችልም። ደግሞ ልታስመስል አልነበረም
አውቃታለሁ ፌቨንን።
ፈዝዤ አንዱ ጥግ እንደቆምኩ ማሜ የምትባለው ደንቃራ ሴትዮ ፊት ለፊቴ እየተውረገረገች መጣች። የለበሰችው አጭር ቀሚስ ለመራመድ አስቸግሯታል። ያደረገችው ጫማ ረዥም ቁመቷን የባሰ ብቅል አውራጅ አድርጎታል። ሁሉም ሰው እየተገላመጠ ያያታል። ቅላቷ የሚያንቦገቦግ ነገር ነው።አጠገቤ ስትደርስ የዙሪያዬ ዓየር በሽቶ ጠረን ተሞላ የሚያፍን ነገር።እንደወትሮው አላሽካካችም፣ አልጮኸችም፣ በታፈነ ግን በሚያስፈራ ጠንካራ ድምፅ እንዲህ አለችኝ፣
አብርሃም እንደማትወደኝ አውቃለሁ። የራስህ ጉዳይ ነው፤ ወደድክ አልወደድክ ምን ልትቀንስብኝ። ደግሞም ማንም እንዲወደኝ አልፈልግም ለየትኛው እድሜ” አለችኝ። አነጋገሯ በታሪክ ከሷ ይወጣል ብዬ አስቤው አላውቅም። ኧረ መኮሳተር !ቀጠለች፣ ፌቨን ላንተ ብላ ሥራ እንዳቋረጠች እያወቅከ፣
ከነቤተሰቧ በርሃብ እየቀጣሃት ነው። ብትጠላኝም እኔ አከብርሃለሁ። እንዲህ ዓይነት ተራ ሥራ ትሰራለህ ብዬ አላስብም። ፌቨን እየተራበች ነው ..ይገባሃል አብርሽ”። በቃ ይሄን ተናግራ ተመልሳ ሄደች መርዝ ! በሰከንድ አዕምሮዬን ገለባበጠችው። ርሃብ አልወድም። በተለይ የሴት ልጅን ርሃብ አልወድም። ካፌ ገብቼ እንኳን ሴት ልጅ ቶሎ ቶሎ ስትበላ ካየሁ ታሳዝነኛለች። ርሃብ አልወድም። ርሃብ ማለት ምግብ አለመብላት ብቻ አይደለም። በምድር ላይ በጣም ትንሹን ነገር የዕለት ጉርስን የሚሰጠን ሰው ማጣት ማለት ነው ለኔ ... ርሃብ አልወድም !
ፌቨን ራበኝ ካለችኝ ምንም ልሥራ ምን እርግፍ አድርጌ ትቼ ወደ ምግብ !!ፌቨን እኮ ስትራብ ስታሳዝን በእግዚአብሔር ! እነዛ የሚያማምሩ ጣቶቿ ሳይቀሩ እቃ ማንሳት አይችሉም። በቃ በተፈጥሮዋ ረሃብ አትችልም። ቆይ ግን ስንት ቀን ተርባ ይሆን ..የኔ ተራ ኩርፊያ ስንት ቀን አንድን ቤተሰብ አስርቦ ይሆን
እግዚኦ እንዴት ዓይነት ድድብና ውስጥ ነኝ ! የፌቨን እናት ማለትኮ አገር ያወቃቸው የተራበ ሁሉ
ቤታቸው ገብቶ ጠግቦ የሚወጣ ደግ እናት ነበሩ። ዛሬ ጊዜ ጥሏቸው የአንድ ጭንጋፍ እጅ ጠባቂ ሆነው እኔም ወጉ ደርሶኝ አንድ ቤተሰብ አስርባለሁ። ትላንት የበላሁት ፒዛ ግማሹን ነካክቼ የመለስኩት፣ ዛሬ ጠዋት የበላሁት ቋንጣ ፍርፍር ትዝ አለኝ ሆዳም ነኝ ! ደደብ !!
ምሳ መብላት አልቻልኩም። ቀጠሮው እስኪደርስ ውኃ አዝዤ እዛው አካባቢ ያለ ካፌ ቁጭ አልኩ።
ከሰዓት ፍርድ ቤቱ ስደርስ ወደነ ፌቨን ሄድኩ።
"ፌቨፕ” አልኳት፡፡ ቀጥ ብላ አየችኝ እና መጣች ወደኔ።
“ላናግርሽ ነበር…”
በጓሮ በኩል ወዳለ ቦታ ሄድን። እኔ ከመናገሬ በፊት የፌቨን እንባ ተዘረገፈ። በእንባዋ ውስጥ እያየችኝ እንዲህ አለች፣
“አብርሽ ይቅርታ፣ ሁሉም ነገር ይቅር በማርያም አትለየኝ እወድሃለሁ” አሁን እኔ እንዲህ የሚለመን ምን ነገር አለኝ፤ ምንም። ራሴ አስጠላኝ ከምር። ቀስ እያልን ወደ ዋናው በር አዘገምን። ማለት ፌቨን
አንድም ቃል ባትናገር ደስታዬ ... የእሳት አለንጋ ... ነገሮች ሁሉ አንዳንዴ ይገለባበጣሉ። ዝም ብለን ወደ ውጭ፤ ከኋላዬ ምን ሰማሁ፣
“አቶ አብረሃም ዓለምሰገድ እና ወ/ሮ ፌቨን…” የችሎት ተራችን ደርሶ ሥማችን እየተጠራ ነበር።
(እንዳልሰማ ከግቢው ውልቅ፣ ሁሉንም እዛው ጥለናቸው) አንድ የምንወደው ሬስቶራንት ነበር እኔና
ፌቨን የምንሄድበት። እዛ ተገኘን። ፊት ለፊቴ ተቀምጣ ፌቨን ታየኛለች። እናም በሚንቀጠቀጡ እጆቿ እጄን ያዘችኝ።
“ተሳስቻለሁ”። ስትገርም፤ ይሄን ሁሉ የምታደርገው አንድ ተራ ወንድ መለማመጥ ፈልጋ እንዳልሆነ አውቃለሁ። ፌቨን ምንጊዜም ከሴትነቷ ሰው መሆኗ የሚቀድምባት ልጅ ስለሆነች እንጂ።እና ሳላስበው
መለፍለፍ ጀመርኩ ያውም ሳላባራ። ፌቨን ዓይን ዓይኔን እያየች እንዲወጣልኝ ታዳምጠኛለች።
“አራት ኪሎ ፈርሶ ውብ ሕንፃ ተገነባበት። ትዝታው አብሮ ፈረሰ። ኧረ ትዝታችን ሲባል ፀረ
ልማት ተባልን። ከዛ ጭርንቁስ የጭቃ ቤት ይሄንኛው ውብ ሕንፃ መሻሉን ሳናውቅ ቀርተን ነው ?
አይደለም ፌቪ ... ሰው ከስጋና ከደም ብቻ አይደለም የሚሰራው። ማንነቱን ደግፎ የያዘው የትዝታ
አፅም የመላመድ አጥንት በውስጡ አለ ! እሱን ነው ያፈራረሱት ! መቼም የማይለማ ማንነታችንን ነው ያወደሙት። አሁንም ፀጉርሽ ትዝታችን ነበር . ትዝታችን ሲፈራርስ ….ፋራ የሴቶች እኩልነት ያልገባው ምናምን ይሉኛል ፌቪ . ያኔ በፍቅረኝነት ዘመናችን የቀጠርሽኝ ቦታ ስትመጪ እዛ ማነው
ስሙ ኪዎስክ ጋር ስትደርሽ ፀጉርሽን ንፋስ ሲበትነው … ከሩቅ ጥቁር ፀጉርሽ ንፋስ ሲያራውጠው
በእጅሽ መለስ እያደረግሽው ወደ እኔ ስትመጪ … ፀጉርሽ የፍቅር ባንዲራ ነበር የሚመስለኝ -
ባንዲራዬን ነው የቆረጡብኝ ፌቪ” ፌቨን እጆቼን እያሻሸች ዝም ብላ ታየኛለች። አውራ ጣቴን ይዛ
የምታስለፈልፈኝ ነበር የሚመስለው
“ለሚታየው እና ለሚዳሰሰው ማንነታችን ስንት የማይታዩ ጥቃቅን ማንነቶች አሉ
እነዚያን እየቀፈቀፍን ባዶ ግንዱ የቀረ እንጨት በመብት ስም እንድናቅፍ ለምን ይገፋፉናል አልፈልግም
! ባንዲራዬን መሬት ጥላ ቆሻሻ አድርጋዋለች ብዬ አዝኜብሻለሁ። ከጥራጊ ጋር ያን ውብ ፀጉሯን ወደ
ገንዳ እንዲወረውሩ ፈቀደችላቸው ብዬ አዝኜብሻለሁ ፌቪ … አራት ኪሎን ሲያፈርሱት ቦታው የኛ
ስላልሆነ ዝም ብለናል ... ሚስቴ ግን የኔ ነች … የጋራችንን ትዝታ ስታፈራርስ እንደ መንገደኛ መቼስ
ምን ይደረግ ብዬ ዝም አልልም። የእጇ ልስላሴ፣ የከንፈሯ ጣዕም፣ ፈገግታዋ ሁሉ ሕዝብን ነው
የሚወከለው በፀጉሯ ባንዲራ ... ይሄን ፀጉር መቁረጥ ድንበር ከመገንጠል ለይቼ አላየውም ብዬ
በቻዬን ተማርሬብሻለሁ ፌቪ” ፌቨን እንባዋ ጉንጫ ላይ እየፈሰሰ ዝም ብላ ታየኛለች..
ፌቪ አስጠልተሽኛል፣ አበሳጭተሽኛል፣ የናቅሽኝ የገፋሽኝ መስሎ ተሰምቶኛል። እኔን ከሕይወትሽ ገፍትረሽ ሌላ ሰው ከሰውም ሰው ማሜ የምትባል ሴትዮ የኔን ቦታ የሰጠሻት መስሎኛል። እና
አፈቅርሻለሁ !”
ፌቨን ትንፋሽ እስኪያጥረኝ ከንፈሬን
ቅድም ሊያፋታን የነበረው ሕግ በአደባባይ ከንፈር ለከንፈር መሳሳም ወንጀል ነው ይላል አሉ! ይበላ
የፌቨን እንባ ይፋጃል !!
✨አለቀ✨

❤22👍13👏2
#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
የቀይ ኮከብ ጥሪ
ባህራም
ባህራም እየተለወጠ ሄደ፡፡ እነ ማኦ ትዜ ቱንግ የደረሱዋቸውን
መፃህፍት ማንበብ ተወ:: ስለኮሙኒዝም ማውራት ተወ፡፡ ክፍል መግባት ተወ:: እኔንም ይሽሸኝ ጀመር። እንደቀስተ ደመና ውብ የነበረውን የሬቮሉሽን ተስፋውን በብዙ የእሳት ቃላት ይነግረኝ ስለነበረ' አሁን ቀስተ ደመናው ተሰባብሮ ወድቆ ከበሰበሰ በኋላ፣ እንደገና
ሊያነጋግረኝ አልፈቀደም፡፡ ኒኮልም ፊት ነሳችኝ፡፡የባህራምን ክንፍ እንደሰበረችው ስላወቅኩ ፊት ነሳችኝ
የኤክስን ሰማይ የሉልሰገድና የጀምሺድ መቀሰፍ አላስደነገጠውም፡ የአማንዳ ጉብዝና አላስደነቀውም፡ የኒኮል ማርገዝ አላናደደውም፡ የባህራም መታሰር አላሳዘነውም፡፡ የኤክስ ሰማይ ለዚህ ሁሉ ደንታ የለውም
የኤክስ ሰማይ አብዛኛውን ጊዜ እንደ አማንዳ አይን ብሩህ
ሰማያዊ ነው፡ አንዳንድ ጊዜ እንደ ኒኮል አይን ውሀ አረንጓዴ
ይሆናል፡ ወደ ማታ ጊዜ እንደ ሲልቪ ጉንጭ ይቀላል
የኤክስ ሰማይ ደመና አይለብስም፤ ሁልጊዜ ራቁቱን ነው! ሁልጊዜ ውብ ነው፡ ሁልጊዜ ሰላማዊ ነው። ሌሊት የአልማዝ
ከዋክብትና የሰላም ፀጥታ ለብሶ ያድራል
የኤክስ የፀደይ ፀሀይ እየበረታች ሄደች። ንፁህ ብርሀኗ ቀስ
እያለ ወደ ብጫ ሀሩር ተለወጠ፡ ለስላሳውን የፀደይ ንፋስ
አደከመው፡ የሚወብቅ የአየር ባህር አደረገው፡፡ በጋ መጥቶ ኤክስ ውስጥ እንደ ሰፊ ድካም ተንሳፈፈ። አሮጊቶቹና ሽማግሌዎቹ ጥላ ውስጥ ቁጭ ብለው በዝግታ እያለከለኩ፣ የሞትን ምህረት የሚጠብቁ
ይመስሉ ጀመር
እንዳንድ ጊዚ ባህራምንና ኒኮልን ምግብ ቤቱ ሲገቡ ወይም
ሰወጡ አያቸዋለሁ። ባህራም ከስቷል፡ አይስቅም፣ በፍጥነት
አይራመድም። ሽበቱም የበዛ መሰለኝ፡፡ ኒኮል ግን ወፈር ብላ፣
እርግዝናዋ በጣም አምሮባታል፡ በዝግታ ስትራመድ ታስጎመጃለች
ቀስ በቀስ ምግብ ቤት መምጣቱን ተዉት ተካ የኒኮልን ማርገዝ ለመሸሸግ ያሉት ነው» አለኝ፡፡ ሌላ
ነገር ነገረኝ ባህራም ማታ ማታ ኒኮልን ቤቷ ትቷት ይወጣና
ሲኒማ ይገባል ከሲኒማ ወጥቶ ካፌ 'ሰንትራ' ይሄዳል፡ እዚያው
ያድራል፤ ሲነጋ ወደ ኒኮል ቤት ይኳትናል፡ ተኝቶ ይውላል
አንድ ማታ ወደ ስድስት ሰአት ላይ ከሲኒማ ወጥቼ ወደ ቤቴ
በኩል ስራመድ፡ ከኋላዬ እንደ ፈጣን እርምጃ ሲከተለኝ ተሰማኝ።
እንዳልሰሙ መንገዴን ቀጠልኩ። ደረሰብኝ፡፡ ባህራም፡፡ ወደ ካፌ
ሰንትራ ሄደን ቢራ ካዘዝን በኋላ
ቁጭ ብለን ካወራን ብዙ ጊዜ ሆነን አለኝ፡፡ አይኖቹ እንደ
መድከም ብሏቸዋል፡ ፊቱ ላይ የአምስት አመት ያህል እድሜ
ተጨምሯል
"አንተ አትገኝም አልኩት"
በገዛ ራሴ ጥፋት በታሰርኩ' አንተ ጋ መጥቼ ባለቅስብህ ተገቢ
ማስሉ አልተሰማኝም
ጥሩ እድል አጋጥሞህ ቢሆን ኖሮ ግን መጥተህ ታጫውተኝ
ነብር፡ ደስታህን ታካፍለኝ ነበር»
አዎን። ይኸውልህ፡ ልክ ከፓሪስ እንደተመለስክ እንድንጋገርበት አቅጄ ነበር፡፡ ግን ገና ሳትመለስ ጣጣ ውስጥ ገባሁ። ስትመጣ ታድያ፤ መንፈሴ ተሸንፎ ስለነበረ ያቀድኩትን ችላ አልኩት፡፡ አሁን ፈቃደኛ ከሆንክ ብንነጋገርበት ጥሩ ይመስለኛል።»
"ጥሩ"
መጀመር አስቸገረው። ሲጋራ አቀጣጠለ።
ስለሰልቪ ጉዳይ ነው። ነግርሀለች?»
«አዎን፡፡
«ምን አለችህ?»
የነገረችኝን ባጭሩ አጫወትኩት። ዝም ብሎ ሰማኝ። ስጨርስ
«ውሸቷን ነው» አለኝ
«እንዴት?
«እኔ ነኝ የለመንኳት፡፡ እሷ እምቢ ብላኝ ነበር። ለብዙ
ተለማመጥኳት። 'አሁን አሁን ከሞት ጋር ስታገል ነበር፡ ውስጤ
በፍርሀት ተሞልቷል፡ ብቻየን ነኝ፡ የሰው ሙቀት ያስፈልገኛል፣
በጣም ያስፈልገኛል አልኳት። እሺ አለችኝ። ግን እሺ ያለችኝ ብዙ
ከተለማመጥኳት በኋላ ነው»
«ማንኛችሁን ልመን?»
«እኔን
«ለምን?»
«ውሸት አልነግርህማ»
«እሷስ ለምን ውሽት ትነግረኛለች?»
«እንዳንጣላ ብላ»
ዝም አልኩ። ንዴቱ ውስጤ ሲጠራቀም ይሰማኛል
«ከፈለግክም አገጣጥመን» አለኝ፡፡ ቁጣዬን ለመግታት ስል
መዋሽት ጀመርኩ
«ግድ የለም ይቅር። አሁን ስላንተ ንገረኝ አልኩት። ድምፁ
እንደተለወጠ ተሰማኝ
«ይቅርታ አርገህልኛል ማለት ነው?» አለኝ
«እንርሳው» አልኩት
«እፍረት ይሰማኛል። አይንህ ውስጥ ንቀት ይታየኛል»
«ንቀት አይደለም» አልኩት
«ታድያ ምንድነው?»
«ስሜቴን ልግለፅልህ?»
«አዎን»
እኔ ሳላውቀው የተጨበጠ ቀኝ እጄ በፍጥነት ሄዶ አገጩን
መታው:: ከነወምበሩ ወደኋላ ተገለበጠ። እጆቼን እንደ ጨበጥኩ ከበላዩ ቆምኩ፡፡ የተገለበጠው ወምበር አጠገብ እንደተጋደመ ወደ ላይ ያየኛል። ማንኛችንም አልተንቀሳቀስንም። ወደ ላይ እያየኝ ቀስ ብሎ መሀረቡን ከኪሱ አወጣ፡፡ መሀረቡ ውስጥ ተፋ። ደም፡ ቀና
ብሉ ቀይ ፈገግታ ሰጠኝ፡፡ እጁን ዘረጋልኝ። ጨበጥኩት፣ ወደ ላይ
ሳብኩት። በየቦታችን ተመልሰን ተቀመጥን
ካፌው ውስጥ ሌሎች ሰዎች እንዳሉና እንደሚያዩን ገና አሁን
ታወቀኝ። አፈርኩ፡፡ ግምባሬን አላበኝ፡፡ መሀረቤን አውጥቼ
ጠረግኩት። ባህራም እንደገና መሀረቡ ውስጥ ተፋ፡፡ ሳቅ እያለ
«እንደሱ እንኳ ይሻላል» አለኝ
አንድ ነገር አስታወስኩ፡፡ ባህራም ቢፈልግ ነብሴ እስኪመጣ
ሊደበድበኝ ይችል ነበር! እንደገና አላበኝ። በመሀረቤ ጠረግኩት
ከዚህ በኋላ ከባህራም ጋር እንደ ድሮው ማውራት ጀመርን።
የደረሰበትን እጫወተኝ። ኒኮል ማርገዟን ስታውቅ መበሳጨት
ጀመረች፡፡ ባህራም ከስራ ሲወጣ ብስጭቷ እየባሰባት ሄደ።
ሉልሰገድና ጀምሺድ ከሞቱ በኋላ፣ ብስጭቱ ወደ እምባ ተለወጠ፡፡
ማታ ማታ ታለቅሳለች። ባህራም ያባብላት፣ በስጋ ይገናኛትና
ያስተኛታል እሷ ስትተኛ እሱ ሲጋራ አቀጣጥሎ በጨለማው ስለ ኢራን
ያስባል። ከንቱ! ያ ሁሉ ዝግጅት ከንቱ ቀረ፡፡ ያ ሁሉ አመታት
በከንቱ አለፈ፡፡ ማኑ ያ ኢራን ሳሉ የ«ፍሬ አለቃው የነበረ
ስለአምባጓሮ ያስተማረው ውድ ጓደኛው ማኑ በሱ ቦታ ቢሆን
አሁን ምን ባደረገ ነበር? ለመሆኑ፣ ማኑ የት ይሆን? እዚያው
እንግሊዝ አገር ይሆን?
«ይገርምሀል” አለ ባህራም ሲነግረኝ አንድ አስር ቀን ያህል
በተርታ፣ ማታ ማታ ስለማኑ ብዙ ብዙ አሰብኩ። እና አንድ ቀን
ከሱ ደብዳቤ መጣልኝ። አይገርምህም? አድራሻዬን እንዴት እንዳገኘ
«ደብዳቤው ምን ይላል?» አልኩት፡፡
ከኪሱ ሁለት በአረብ ፊደላት የተፃፉ ደብዳቤዎች አውጥቶ
አንዱን ተረጎመልኝ
«ብዙ ብዙ የምነግርህ አለኝ፡፡ ግን በደብዳቤ አይሆንም።ስንገናኝ ነው። እዚህ ለንደን ውስጥ ሶስት ሚልዮን ፓውንድና ኣንድ
ዘመናዊ ማተሚያ ቤት አለን፡፡ ገንዘቡ ከቻይና፣ ከሶቭየት ህብረትና ከሌሎች ወዳጆች የተሰጠን ነው፡፡ ብዙ ሌላ እርዳታም ተሰጥቶናል፡፡
አስራ አምስት ሺ ካላሽኒኮቭ ጭምር! እንግዲህ ጊዜው ደረሰ፡፡
ፎቶግራፍህን ላክልኝና ፓስፖርት ይዤልህ እመጣለሁ። እኔና አንተ
አገራችን እንገባለን፡፡ እዚያ ብዙ ብዙ ስራ ይጠብቀናል። ዝግጁ ነህ?እንዲያው ነው የምጠይቅህ እንጂ ዝግጁ እንደሆንክ እርግጠኛ ነኝ፡፡ይህን ሁለት አመት የት የት ነበርኩ መሰለህ? ፒኪንግ፣ ሞስኮ፣ፕራግ፣ ቡዳፔስት ብቻ ስንገናኝ እነግርሀለሁ። ቶሎ ፎቶህን ላክልኝ»
ባህራም ደብዳቤውን እጥፎ ኪሱ ከተተ። ረዥም ዝምታ ሰዎቹ ካፌው ውስጥ ያወራሉ። አንዷ ኮረዳ ከሽንት ቤት ወጥታ

👍18❤1
ሶስት ጎረምሶች መካከል ተቀመጠች።
«ፎቶህን ላክለት?»
«የለም»
«ምነው?»
«ከሱ ጋር ልሄድ አልችልማ»
«ለደብዳቤው መልስ ፃፍክለት?»
«አዎን። 'ካንተ ጋር ልመጣ አልችልም፡፡ ሀሳቤን ለውጫለሁ'
አልኩት
«መቼ ነበር ይሄ የሆነው?»
«ከአስራ አምስት ቀን በፊት። ዛሬ ሌላ ደብዳቤ ደረሰኝ።
'ሀሳቤን ለውጫለሁ ብትለኝ አላምንህም። ይልቅ ምን እንደሆንክ
ንገረኝ ይላል።»
«ትነግረዋለህ?» አልኩት
«እኔ እንጃ
ዝም ብለን ብዙ ጊዜ ቆየን
ደብዳቤው ከደረሰህ በኋላ ነው እዚህ 'ሰንትራ' ማደር
የጀመርከውን
«እዎን።»
ከኒኮል ጋር ማደር አልቻልኩም፡፡ ለቅሶዋ ሊያሳብደኝ ነው።»
አሁንማ ስትዘጋጅበት፣ ስትጓጓለት የነበረው ስኬት ሲመጣልህ
እኔ ከለከልኩህ፡ ገደልኩህ፣ እኔ አንተን ገደልኩህ!» እያለች ነው
የምታለቅሰው፡፡ አልቻልኩትም፡፡ ባንድ በኩል ቁጭት፣ ባንድ በኩል
የሷ ለቅሶ፡፡ በዛብኝ፡፡»
ካንድ አመት ተኩል በፊት፣ በክረምት፣ ቤቱ ማሞቂያ
ስላልነበረውና የክረምቱ ብርድ ስለበረታበት፣ ካፌ «ሴንትራ» ያድር
ነበር፡፡ አሁን ደሞ የኒኮል እምባ እያባረረው ካፈ ሰንትራ» ያድራል። ሲጋራ እያጨሰ ሲተክዝ ያድራል፡፡ ስለ ኢራን ሲያሰላስል ያድራል። ከንቱ ሀሳብ ሲያወጣ ከንቱ ሀሳብ ሲያወርድ ከንቱ ሌሊቶችን ያነጋል...

👍9❤2