አትሮኖስ
286K subscribers
123 photos
3 videos
41 files
585 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አመሻሽ_ላይ

እንፋሎት ይመስል
ዕድሜው ሽቅብ ሄደ
አቅሙ ጅረት ኾነ
ወደ ታች ወረደ
የጥርሶቹ ንጣት
ሸሽ ወደ ፀጉሩ
በፀጉሮቹ ምትክ
ጥርሶቹ ጠቆሩ
እሱና ፈገግታ ተቆራርጠው ቀሩ፡፡
ዕድሜ ራሱ አርጅቶ
ተዝለፍልፎ ዘምሞ
ተመርኮዘበት
ወገቡን ቆልምሞ
ሣቅልን አትበሉት
ሣቅ አያውቅም ጥርሱ
ሰው ካረጀ ወዲያ
በገና ናት ነፍሱ
ለሚነካካው ጣት
ወዮታ ነው መልሱ፡፡
#ባለ_ዕፀ_መስውር

ዕፀ መሰውርን፣ ከደብተራ አግኝቶ
ከሰው እንዲሰወር፣ ገላውን ቀብቶ
እንደ እግዜር ሳይታይ
በሚታይ ጎዳና
ወደ ባንክ ሄደና፣
በንቁ ዘበኛ በሚጠበቀው በር
አልፎ ገንዘብ ሲዘርፍ አይታይም ነበር፡፡
በዚህ ተደስቶ
ከዘላለም ቀንበር፤ ካ'ይን ነጻ ወጥቶ
ግና፣ ግና፣ ግና
ተመልካች ባይኖረው
ሆድ ነበረውና
እህል ወዳለበት በፍጥነት አቀና
ምግብ ቤት ሲገባ፣ ማንም አልታዘዘው ፣
አይታይምና፡፡

🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_ስድስት


#በአሌክስ_አብርሃም

ሳሌም፣ እኔና መሐሪን ገና ከሩቅ ስታየን፣ በሚቅጨለጨል ሳቋ ታጅባ ወደኛ ትሮጣለች፡፡ እናቷ ቀስ!.…ቀስ!” እያለች በዓይኗ ትከተላታለች፡፡ በየተራ እንስማታለኝ፡፡ መሃላችን ገብታ በማይገባን ቋንቋ ትኮላተፋለች፡፡ እጅና እጇን ይዘን ኦፕ! ኦፕ! እያለች ወደ እናቷ እንወስዳታለን፡፡ እንዳንዴ ትተናት ወደቤታችን ስንሄድ፣ ካልወሰዳችሁኝ ብላ መንገዱ ላይ በደረቷ ተኝታ ታለቅስ ነበር::

እኔና መሐሪ ለውዝ አሰፍረን በየኪሳችን እንይዝና፣ ለሳሌም እናካፍላታለን፡፡ ለለውዙ አንከፍልም፡፡ ለጋሽ ዝናቡ እንዳትናገር አስጠንቅቀን በዱቤ እንወስዳለን፤ ያው ቅዳሜ ልብስ ለማጠብ እነ መሐሪ ቤት ስትመጣ ማሚ “ምን ይሻላቸዋል? እነዚህ አንበጣ የሆኑ
ልጆች እያለች ትከፍላለች፡፡ ሳሌምን የዱቤ ለውዝ አስለምደናት፣ ገና ሲሰፈር መሬት
ላይ በቂጧ ዝርፍጥ ትልና ቀሚሷን ዘርግታ ታመቻቻለች፡፡ ለውዙን እንደ ዶሮ ጥሬ ቀሚሷ ላይ እንስትንላታለን፡፡ በትንንሽ እጆቿ እየለቀመች ትቆረጥማለች አንዳንዴ አንዲት የለውዝ ፍሬ ታመልጣትና፣ ያችን ለመያዝ ስትነሳ፣ የቀሚሷ ላይ በሙሉ መንገዱ
ላይ ይበታተናል፡፡ ብዙ ጊዜ ለውዟን ከያዘች ቻው ስንላት እንኳን ቀና ብላ አታየንም፤ ሐሳቧ ለውዙ ላይ ነው… “አንቺ! ቻው በያቸው እንጂ?” ትላለች እናትየዋ በሐፍረት፤ ሚስኪን የገጠር ሴት ናት፡፡

እየተሳሳቅንና ለውዛችንን እየቆረጠምን፣ ወደ ቤታችን እናዘግማለን፡፡ ለውዝ አበላላችን በራሱ ትንሽ ትርኢት ይመረቅበት ነበር፡፡ ገለባውን አራግፈን ወደላይ እንወረውርና፣ አፋችንን ከፍተን እንጠብቀዋለን…ብዙውን ጊዜ ብንካንበትም አልፎ አልፎ ግን
ከጥርሳችን ጋር እየተጋጨ አልያም አፋችን ስቶ መሬት ላይ ይወድቃል፡፡ አንስተን መብላታችን አይቀርም፡፡ ብዙ ጊዜ የሚስተው መሐሪ ነበር፡፡ ጥርሳም ስለሆንከ ነው እለዋለሁ፡፡ መላፋት እንጀምራለን፡፡ እንዲህ ነበር ደርሶ መልሳችን!

አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ስንመለስ፣ የኢየሩስ ጉሊት ባዶ ሆኖ አገኘነው፡፡
የምትቀመጥበት ድንጋይ ብቻ ነበር ያለው፡፡ የት ሄደው ነው? ተባብለን አለፍን፡፡ በቀጣዩም ቀን ባዶ ነበር፡፡ በሦስተኛው ቀን መሐፊ እቤቷ ሄደን እንያት አለኝ፡፡ ደብተሬን አስቀምጨ ተመለስኩና፣ መሐሪን ስጠራው “ማሚ ነገ ቅዳሜ እንያትና፣ ካልመጣች ትሄዳላችሁ” ብላለች” እለኝ፡፡ ረቡዕ፣ ሐሙስና ዓርብ መሆን አለባቸው ቀናቱ
ምክንያቱም በቀጣዩ ቀን ማሚ እንዳለችው ጥድቄ እነመሐሪ ቤት መጥታ ነበር፡፡ ገና በጧቱ መሐሪ እቤታችን መጣና፣ ሁልጊዜ ሲጨነቅ እንደሚያደርገው እጁን እያፍተለተለ
“ባሏ ደብድቧት ነው የጠፋችው?” አለኝ፡፡

“ማን?

“ጥድቄ”

“መጣች እንዴ?” አልኩት …

"ጧት መጣች፤ ልብስ ልታጥብ፡፡ ማሚ ግን እንዲህ ሁነሽማ እታጥቢም! ምናምን ብላት ቁጭ ብለው እያውሩ ነው፡፡ እንዳለ ፊቷ በሞላ እባብጧል፡፡ በቢለዋ ሊያርዳት ነበር፤ አምልጣ ጎረቤት ቤት ተደበቀች

አረ!?”

ራሷ ናት ለማሚ እያለቀሰች የነገረቻት፡፡ ፊቷ ሁሉ እንዳለ አባብጧል…ጥርሴ ተነቃንቋል ብላለች!” መሐሪ ሊያወራ በፍጥነት ነበር፡፡ ልክ እሱ ራሱ ሲደበደብ አምልጦ በሩጫ የመጣ ዓይነት፡፡ ሁልጊዜም ሲጨነቅ ወይ ሲፈራ፣ እንደዚህ ነው አወራሩ፡፡ ተያይዘን
ወደቤታቸው ሄድን:: ገና በሩ ላይ ስንደርስ ሳሌም ኦፕ! ኦፕ! እያለች ወደኛ ሮጠች!
ጥድቄ ዓይኗ ሁሉ አባብጦ ከንፈሯ ደም አርግዞ ከልብስ ማጠቢያው አጠገብ ባለ
አግዳሚ የድንጋይ ወንበር ላይ፣ ከማሚ ጋር ጎን ለጎን ተቀምጠው ነበር፡፡

ማሚ በጣም ከመበሳጨቷ የተነሳ፣ ከመሐሪ ጋር ተከታትለን ስንገባ፣ እንደወትሮው ስላም እንኳን አላለችኝም፡፡ በየመሀሉ እየደጋገመች “ወይ ጥጋብ! ወይ ጥጋብ! ወይ ጥጋብ!” እያለች ከድምፅዋ እኩል ቸብ ቸብ እያደረገች ታጨበጭባለች፡፡ እንዲህ
እንደተቀመጡ ጋሽ ዝናቡ ነጭና ጥቁር መስመር ያለበት በልኩ የተስፋ የሜዳ አህያ ቆዳ በሚመስል ዥጉርጉር የሌሊት ልብሱ ላይ፣ ከጥጥ የተሠራ ነጭ ጸጉራም ካፖርት ደርቦ እየተንጠራራ ከቤት ወጣና በረንዳው ላይ ቆሞ አዛጋ፡፡ ሲያዛጋ ድምፁ በሌሊት ከሩቅ የሚስማ የጫካ እንሰሳ ዓይነት ድምፅ ይመስል ነበር፤አዋአዋዋአዋአዋአዋአዋአዋእዋእዋ!
“ጎሽ! ተነስቷል” አለች ማሚ ! እሱን እየጠበቁ ነበር
ማሚ ወደ በረንዳው መጣች፡፡ እኔና መሐሪ ደረጃው ላይ ተቀምጠን ከህጻኗ ጋር እየተጫወትን ስለነበር፣ እንድታልፍ ጠጋ አልንላት፡፡ እዚያው ደረጃው ሥር እንደቆመች ጋሽ ዝናቡን ሽቅብ እያየች፣

“ይኼ ባለጌ የሠራውን አየህ?” አለች።

“ማነው” አሉ ኮስተር ብሎ፡፡

ወደ ጥድቄ እየጠቆመች ባል ተብየው ነዋ!” አለች፡፡ጋሽ ዝናቡ ጥድቄን ገና ያኔ ያያት ይመስል ደህና አደርሽ?” አላት::

ከተቀመጠችበት ተነስታ ጎንበስ ቀና እያለች እግዚሃር ይመስገን! ጋሽ ደህና አደሩ” አለች።

እንዲህ ሕግ ባለበት አገር፣ እንደ እባብ ቀጥቅጦ ቀጥቅጦ፣ ጎረቤትኮ ነው ነብሷን ያተረፈው:: ነይ ወደዚህ አሳይው!” አለች፤ ማሚ፡፡ እንደዚህ ቀን ስትበሳጭ አይቻት አላውቅም፡፡ ጥድቄ ቀረብ አለች፤ ስትራመድ ታነከስ ነበር…

“አንድ ነገርማ አድርግ ዝናቡ እንዲህ ዓይነቱን ጥጋበኛማ “ሀይ!” ካላሉት፣ ነገ ተነስቶ ሰው ይገድላል፣ የምታረገውን አርግ በቃ!” ጋሽ ዝናቡ፣ ማሚ ተማምናበት የሆነ ውለታ ስለጠየቀችው ይሁን ወይም በጕዳዩ አዝኖ፣ ብቻ ፊቱ ላይ የሆነ ኩራትና ወንድነት
እንዣበበት፡፡

ፊቷን በትኩረት ከተመለከተና ምን ልሁን ብሎ ነው እንዲህ ያደረገሽ?” አለ፡፡

“ጥጋብ ነው ጋሸ

“ምንድነው ጥጋብ? በደንብ ንገሪኝ አለ ጋሼ ችሎት ላይ እንደተሰየመ ዳኛ ነበር
አነጋገሩ፡፡
ለኔ የነገርሽኝ እንድ ባንድ ንገሪው አትፍሪ እሱ መላ አያጣም” አለች ማሚ፡፡ ብስጭት ብላ ነበር ።

ንገሪኝ አትፍሪ! አለ ጋሼ ጋሽ ዝናቡና ማሚ በአንድ ጉዳይ ላይ እንዲህ
ተስማምተው ሲያወሩ ሳያቸው፣ የመጀመሪያዬ ነበር፡፡

እኔ ሰይጣን ይላካቸው ጠላት፣ ምናባቴ አውቄ.. እዚህ ፈረንጆቹ ቤት ውስጥ ያሉ
ሁለት ፈረንጆች፤ምን ፈረንጅ ናቸው አማረኛውን ሲያቀላጥፉት ያዩ እንደሆነ፣ ለጉድ ነው ጋሽ፣ እኔም እንደነሱ አይፍታታልኝ:: መጡና ባል አለሽ ወይ? አሉኝ፡፡ አዎ! ስላቸው ጊዚ
ባለቤትሽ ቤት በሚኖርበት ቀን ሁለታችሁንም እናነጋግራለን፣ እቤትሽ ውሰጅን አሉ:: እኔ ደሞ መቼም ደሀ ጉጉ ነው፣ እርዳታ ይሰጣሉ ሲባል ሰምቼ፣ አዝነውልኝ ሊሰጡኝ ይሆናል ብያለሁ፣ በኋላ ማክሰኞ አመሻሹ ላይ ተቃጥረን ሦስት ሁነው እቤቴ መጡ፡፡
መጡና 'ይችን ልጃችሁን ፈረንጅ አገር ልከን እናስተምራት፣ ለሷም ለእናተም ጥሩ ነው:: አሉ”

“አሃ …ማደጎ” አለ፤ ጋሽ ::

“ማደጎ ይሁን? ምን ይሁን? ምናባቴ አውቄ ብለው፡፡ ከመሬት ተነስተው ከፈቀዳችሁ እንውሰዳት፤ እዚህ መንገድ ለመንገድ ከምትበላሽ አሉ እንጅ! …ኋላ እንደው እንዲህ ሲሉ ነጥቀው የወሰዱብኝ መሰለኝ አንዘፈዘፈኝ፤ ጋሽ! አንዘፈዘፈኝ !ሌላ ምን ተስፋ አለኝ
ምን የዓይን ማረፊያ አለኝ … ልጄን አቅፌ ውጡልኝ ከዚህ ቤት ብዬ ኡኡ! አልኩ፡፡
አስቡበት ብለው ወጥተው ሄዱ …
እሽ! " አለ፣ ጋሽ ብዙም የገረመው አይመስልም፡፡
“ፈረንጆቹ ወጣ እንዳሉ፣ ባለቤቴም ከተል ብሎ ወጥቶ ሄደ፡፡ ካለወትሮው እስከ እኩለ ሌሊት አምሽቶ፣ ስክር ብሎ መጣ፣ መጣና የልጄን ዕድል ልታበላሽ ደህና እግዜር ያያትን፤ ትሄዳለች፤ እኔ አባቷ ፈቅጃለሁ፤ ፈረንጅ አገር በአውሮፕላን ሽው! …እዚህ ማስክ የለም! ጭርንቁስ.…እከካም! ትሄዳለች” አለኝ፡፡ ልጄን ሊነጥቁኝ ሲማከሩብኝ ያመሹ
መሰለኝ ጋሸ፡፡ ሰካራም ነው፡፡ አንድ
👍1
መለኪያ አረቄ ከሰጡት ይደለላል” ብላ ማልቀስ ጀመረች፡፡

ማሚ ወዲያ አታልቅሽ! አሁን ነጥብ ነጥቡን ንገሪው!” አለችና ትከሻዋን በስሱ ቸብ እያረገቻት፡፡

ልጄን እንዲች ብለህ እንዳታይብኝ፣ ከፈለክ አንተኑ ፈረንጅ አገር ይውስዱህ ብዬ ልጄን አቅፌ ቁጭ እንዳልኩ፡፡ ድንገት እንደ መብረቅ ተወርውሮ ፀጉሬን ጨመደደና፣ እዚች አንድ ፍሬ ልጅ ፊት፣ አይሠሩ ሥራ ሰራኝ፡፡ ደም ባፍና ባፍንጫዬ እስኪደፍቀኝ፡፡የአባትም ገዳይ እንዲህ አይደረግ፡፡ ጭራሽ ተንደርድሮ ቢላ አነሳ፣ እንደው የሞት ሞቴን
ልጄን አንጠልጥዬ ብር ብዬ ወደ ጎረቤት አመለጥኩ፡፡ ይኼው ሦስት ቀን ጎረቤት ቤት ተጠግቼ አስታመሙኝ፡፡ እግዜር ይስጣቸው፡፡ አሁንም ልጄን ካላመጣሽ፣ ካልወሰዷት እያለ ጧት ማታ እየዛተብኝ ነው፡፡ ሦስት ቀን ባይኔም እንቅልፍ አልዞረ። ያስጠጉኝን ሰዎች ሳይቀር ያስፈራራቸው ይዟል ጋሻ!…አድኑኝ! ልጄን ተነጥቄ ስውም አልሆን፤ አድኑኝ ለነፍስ እሆነወታለሁ ጋሸ”፡፡ ጋሽ ዝናቡ እግር ሥር ተደፍታ እዬዬ አለች፡፡
ላሌም እጄን ከእጃችን ነጥቃን የእናቷን ቀሚስ እየጎተተች ኡኡ ብላ አለቀሰች
ማሚም አብራቸው አለቀሰች፡፡

ተነሺ…ተነሽ ቀላል ነው” አለ፤ ጋሽ ዝናቡ፡፡

“እውነትዎትን ነው ጋሸ”

ነገርኩሽ፤ ተነሸ ቀላል ነው …አንችው ካልፈለግሽ በስተቀር እኛ እያለን ልጅሽን ማንም አይወስዳትም !”

ኧረ! እኔ አልፈልግም! ልጄን ከሚወስዱብኝ ነፍሴን ጋሼ ነፍሴን ይውሰዷት” አመልካች ጣቷን እንደሊላ ቀስራ፣ የእራሷን አንገት እንደምታርድ ዓይነት ከረከረችው፡፡

ማሚና ኢየሩስ ተያይዘው ወደውስጥ ከገቡ በኋላ፣ ጋሽ ዝናቡ በረንዳው ላይ ባለው ተወዛዋዥ ወንበር ላይ ተቀምጦ በዝምታ ወደ ፊትና ወደ ኋላ ሲወዛወዝ ቆየና፣ ረጋ ባለ ድምፅ፣

“መሐሪ ቦርሳዬን አቀብለኝ” አለ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ግርዶሽ

ተነሻል እንደውሀ፥ ዳምነሻሌ እንደጉም
አንጋጥጬ አያለሁ፥ መዝነብሽን አላውቅም
ጋራ ተከልለሽ፥ውቅያኖስ ከፍሎሽ
እንደ ምሽት ጀንበር፥ እንደጮራ ደምቀሽ
በስስት እያየሁ፥እንዴት ትጠልቂያለሽ

🔘በተስፋ አማረ🔘
#እኔም_ናፍቄአለሁ

ናፍቀሻል ነገሩኝ ፥ እኔም ናፍቄለሁ
አይኖቼን ሳልከድ ፥ እጠብቅሻለሁ

🔘በተስፋ አማረ🔘
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_ሰባት


#በአሌክስ_አብርሃም

...ማሚና ኢየሩስ ተያይዘው ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ፣ ጋሽ ዝናቡ በረንዳው ላይ ባለው ተወዛዋዥ ወንበር ላይ ተቀምጦ በዝምታ ወደ ፊትና ወደ ኋላ ሲወዛወዝ ቆየና፣ ረጋ ባለ ድምፅ፣

“መሐሪ ቦርሳዬን ኣቀብለኝ” አለ፡፡

ሁል ጊዜ ሥራሲሄድ የሚያንጠጥለሰውን ቡናማ የቆዳ ቦርሳ ከፍቶ ወረቀቶች፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መድሐፍና እና ጥቁር ብድር አወጣ፡፡

ልጅቱን ጥራት አለው መሐሪን በአገጩ ወደገባችበት እየጠቆመ ፡፡ ማሚና ትድቄ
ተያይዘው መጡ።

"የባለቤትሽ ስም ማነው?"

ጋንጩር ነው እንጂ ምን ስም አለው ብላ በብስጭት ከተናገረች በኋላ፣ ማሚ በከንዷ ግሸም ስታደርጋት ተረፈ! ተረፈ መርጊያ ምን ይተርፋል ይኼ ጦሱ ነው የተረፈን አለች

“ከዚህ በፊት ደብድቦሽ አልያም ሰድቦሽና እስፈራርቶሽ ያውቃል …”

ስድብና ማስፈራርያማ ስንቁ ነው…ምሳና ራቴ … ድንገት ያሰረችውን ሻሽ ከራሷ ላይ መንጭቃ ፈታችና የተጎሳቆለ ጸጉሯን ከጆሮዋ በላይ ገለጥ ገለጥ አድርጋ …"ይኼው የዛሬ ዓመት በቡና ስኒ ወርውሮ የፈነከተኝ፡ ሐኪም ዘንድ ሄጄ ተሰፍቼ ነው!እስካሁንም ቅዝቃዜ
ሲሆን ያመኛል ፡ ያዞረኛል” አለች፡፡ ማሚ አዲስ የሰማችው ነገር ስለሆነ ተንጠራርታ ጠባሳውን አየችና ወይ ጥጋብ!" ብላ በብስጭት ተነፈሰች፡፡

ጋሽ ዝናቡ ጥድቄን የተለያየ ነገር እየጠየቀ፡ አንድ ገጽ ከግማሽ የሚሆን የክስ ማመልከቻ ፅፎ ጨረሰና ጉሮሮውን ጠርጎ በጎርናና ድምፁ አነበበላት፡፡ “በተደጋጋሚ በሚያደርስብኝ
አካላዊ ጥቃት የእኔም ሆ የልጄ ሕይዎት አደጋ ላይ በመውደቁ እያለ፣ እንብቦ ሲጨርስ ጥድቄ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡ ወረቀቱ ግርጌ ላይ በጣቷ አስፈርሟት፡፡
መፅሀፍቱን ወደ ቦርሳው ጨማመረና፡ ለራሱ በሚመስል ድምፅ “በቃ! ሰኞ ክስ እንመሰርታለን አለ።

ማሚ ወደኋላ ቀረት አለችና ጋሽ ዝናቡን

“ቡና ላፍላ እንዴ? አለችው።

"እሽ" አለ ሁለቱም ንግግራቸው ለስለስብሎ ነበር
በስንተኛው ቀን እንደሆነ እንጃ፣ የጥድቄ ባል ታሰረ ብሎ መሐሪ ነገረኝ፡፡ ለሁኔ ግን መልኩን እንኳን ከማላውቀው ሰውዬ እስር በላይ፣ እስካሁን ውስጤ የቀረው ማሚ
ከጥድቄ ጋር ፍርድ ቤት ሂዳ ያየችውን ስታወራ ጣል ያደረገችው ነገር ነበር፡፡ ባልየው ችሎት ገብቶ ዳኛው ፊት ሲቆም፣ መርፌ ቢወድቅ በማያሰማው የችሎቱ ጸጥታ ውሰጥ አባባ ባቦ የሚል ድምፅ ተሰማ፡፡ ሳሌም ነበረች

ዐመሉ ውሻ ነው እንጂ፤ ማታ ሲገባ ለልጁ በኪሱ ዳቦ ሳይዝ አይገባም ነበር አለች ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጥድቄና ሳሌም እነ መሐሪ ሴት እቃ ቤት” የምንላት፡ በዋናው ቤት ኋላ ባለች ሰርቪስ ቤት ውስጥ መኖር ጀመሩ፡፡ ይኼንንም ሐሳብ ያመጣው መሐሪ ይሁን እንጂ ሙግቱ ላይ ነበርኩበት፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ እኔና መሐሪ አገር ምድሩ ያውቃው ዳኛ፡
ጋሽ ዝናቡ ፊት በድፍረት ቁመን የራሱን ቤት ለአንዲት ደሀ ያካፍል ዘንድ የሞገትንበት፣ ሞግተንም ያሸንፍንበት ፋይላችን ነበር፡፡ ዝም ብሎ ሲሰማን ቆየና

“ጥሩ ጠበቃ ወጥቷችሁ የለም እንዴ ጃል” ብሎ ፈቀደ፡፡ ያኔ ሳሌም ዕድሜዋ ከሁለት ዓመት አለፍ ቢል ነበር፡፡ ሲበዛ ሁለት ዓመት ከአምስት ወር!

አባቴ ጎበዝ አናጺ ነበር፣ ከአናጺነት የካኪ ቱታው ውጭ የክት ልብስ ሲለብስ ይጨንቀዋል፡፡ በተለይ ጋቢ ሲለብስ አንዴ ከትከሻው እየጠንሸራተት፣ ሌላ ጊዜ መሬት ለመሬት እየተጎተተ ያስመርረው ነበር፡፡ የፈለገ ቢዘንጥና ቢታጠብ፡ ልብሱ ላይ የተለጠፈ፣ አልያም ጸጉሩ ላይ የተሰካ አንዳች የእንጨት ፍቃፋቂ አይጠፉም፡፡ ብዙ ማውራትና ብዙ መቀመጥ አይሆንለትም፡፡ በሕይወቱ ዘለግ ያለ ነገር አወራ ከተባለ፣ ወይ
ስለዕቁብ ነው፣ ካልሆነም ስለ እንጨት እና ሚስማር መወደድ ነው:: ዘወርወር ያለ ዉሬ በቀላሉ የሚረዳ ሰው አልነበረም። ነገሩ ሁሉ አጭርና ቀጥ ያለ ነው። ይኼንን ነገሩን እኔ ብወድለትም፣ እናቴ ግን ሁልጊዜ ምን ቢያደርጉት ይሻላል ይኼ ሰው ነገር መዘንኮር እያለች ትበሳጫለች፡፡
ታዲያ እንደ ሁልጊዜው በእናቴ እስገዳጅነት ጧት ተነስቶ ቤተክርስቲያን ደረስ ብሎ መመለሱ ነበር፡፡ በር ላይ ቁሜ እጁን እያስታጠብኩት ነው፣

ከሰብከቱ ሁሉ የማይዋጥልኝ፣ ይኼ ክርስቶስ አናጢ ነበር የሚሉት ነገር ነው ..
ታዲያ ቢሆን እና ምንህ ተነካ ሥራህን ተሻማህ!?…ሆ” አለች እናቴ፡፡

እኔ ምኔ ይነካል እንደው የመምሬ አፈወርቅ ነገር ቢገርመኝ ነው እንጅ!”
እሳቸው አልጻፉት መጽሐፉን ነው የሰበኩት!” አባቴ ዝም ብሎ ቆየና ድንገት
ክርስቶስ መምህር ነበር ሲሉን አይደለም እንዴ፤ ይኼው ቄስና መምህሩን ሁሉ
የምንፈራና የምናከብር

እና አለች እናቴ ሐሳቡ ኤልያያዝ ብሏት፡፡

“አናጢ ነበር ካሉ፣ ለምን አናጢ አያከብሩም ታዲያ? መምሬ አፈወርቅ ራሳቸው የሚያከራዩትን ሁለት ክፍል ቤት የሠራሁበትን የላቤን ዋጋ እስካሁን መች ከፈሉኝ? እንግዲህ በክርስቶስ አምሳል መዶሻ ያነሳውን የመንደርሽን አናጢ ካላከበርሽ፣ ክርስቶስንስ መች ታከብሪያለሽ! መስቀል ላይ ስላልቸነከሩኝ ነው እንዴ? ይሄው የዕቁብ ከፍይ ጎደለብኝ

እናቴ ዝም አለች፡፡ ይኼኛው ዝምታዋ የኩርፊያ ነው፡፡ በዝምታዋና በዝምታዋ መካከል ያለውን ልዩነት፣ ፊቷን እንኳን ባላይ መለየት እችላለሁ፡፡ እንዴት እንደሆን እንጃ፤ ወሬ ለማስቀየር ይሁን፣ አልያም በአባቴ ብስጭት ንዴቷን እኔ ላይ ለመወጣት፣ “ምናለ እንዲያው እሁድ እንኳን ቤተክርስቲያን ብትስም፣ ይኼው መሐሪን እንኳ ስሞ ሲመለስ
አገኘነው የተባረከ ልጅ አለች፡፡ መሐሪ ለምን ቤተክርስቲያን እንደሚሄድ ስለማውቅ፣ሳቄን አፍኜ ዝም አልኩ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ሰበብ ወጥተው ከሮሐ ጋር እሁድ እሁድ ጧት ይገናኛሉ፡፡ ዛሬም አብረው ነው ያገኟቸው…

አባቴ ድንገት “አብራው የነበረችው ልጅ የግርማ ልጅ አይደለችም እንዴ?” ብሎ ጠየቀ።

ብትሆንሳ ታዲያ? አብረው ነው የሚማሩት?” እናቴ ስለተበሳጨች ንጭንጭ ብላለች፡፡

እሱማ ..እንዲያው ግን፣ የግርማ ልጅና የዝናቡ ልጅ አብረው ሳይ

ነሽ እቴ …የማያሳስበው ያሳስብሃል”

“ግርማ ጥሩ ሰው ነበር …ሆቴሉን በጠገንኩ ቁጥር አክብሮ ክፍያውስ ቢሆን፡ ከጥሩ ሰው ልጅ ጋር መግጠም ጥሩ ነው” አለ አባቴ፡፡ የሮሐ አባት ጋሽ ግርማ ከተማው ውስጥ የታወቀ ሀብታም ነው::ወደኋላ ክብልስ የሚል ጸጉር ያለው፣ የህንድ የፊልም አክተሮች የመሰለ፣ ፈገግታ ከፊቱ የማይጠፋ ሰውዬ፡፡ የነዳጅ ማደያ እና ትልቅ ሆቴል አለው::
ከሁለት ዓመት በፊት በሆነ ጉዳይ ተከሶ ፍርድ ቤት ይቀርባል ፡፡ጉዳዩ በትክክል ምን እንደሆን እንጃ፤ ከመንግሥት ጨረታ ጋር የተያያዘ ነገር ነው ሲሉ ነው የሰማሁት

ዳኛው ጋሽ ዝናቡ ነበር፡፡ እንግዲህ እንደሚወራው፤ ጋሽ ግርማ ነገሩ አላምር ሲለው፤ ከክሱ ነፃ ለመውጣት ሲል ለጋሽ ዝናቡ ጠቀም ያለ ብር ጉቦ ለመስጠት አማላጅ ይልካል፡፡ ጋሽ ዝናቡ አማላጁንም ጋሽ ግርማንም ጠራርጎ እስር ቤት አስወረወራቸው።ጭራሽ የሮሐን አባት፣ በተከሰሰበትም ጒዳይ የሁለት ዓመት እስር አከናንቦት፣ ፍርዱ ወደ ገንዘብ ተቀይሮለት ነው የተፈታው ይባላል። ሮሐና መሐሪ ታዲያ የአባቶቻቸውን ታሪክ
ለአባቶቻቸው ትተው የጦፈ ፍቅር ውስጥ አሸሼ ይላሉ!

ሮሐ አባቷ ለመሐሪ ቤተሰቦች ያለውን ጥላቻ ስትገልጽ ታዲያ፣ እየሳቀች እንዲህ ትላለች
“መሐሪ እኛ ቤት ሽማግሌ ቢልክ፣ ዳዲ ገና ሊያገባኝ የጠየቀው የጋሽ ዝናቡ ልጅ መሆኑን ሲያውቅ፣ ሁሉንም ነው የሚረሽናቸው ሂሂሂሂ፡፡ እኛም እንዲህ ነበር የምናስበው:: ጋሽ ዝናቡ መሐሪ ሴት ማፍቀር ብቻ ሳይሆን የጋሽ ግርማን ልጅ ማፍቀሩን ቢሰማማ

ለዚያም ነበር ያንን ሁሉ ጊዜ
👍1
መሐሪና ሮሐን በመከላከል ያልተቀጠርኩ እጃቢ ሆኜ መከረሜ፡፡ይገርመኛል፣ ሁለት ሰዎች በቀን አራት ጊዜ የሚገናኙባት ጠባብ ከተማ ውስጥ መሐሪና ሮሐ በፍቅር ናውዘው ከተማውን ሲያካልሉ፣ ፈጣሪ የደመና ዓምዱን አውርዶ ጋርዷቸው ይሁን፣ አልያም የመገናኛ ሰዓታቸውን የማለፊያ መንገዳቸውን ሳይቀር፣
ስንዝር በስንዝር፣ ሰከንድ በከንድ አጥንቼ ቀዚህ ሂዱ በዚያ ተመለሱ የምል እኔ፣
“ፎርሙላዬ” ሠርቶ .. ብቻ ሁለት ዓመት አካባቢ ለሚሆን ጊዜ፣ ከሁለቱም ቤተሰቦች ዓይን ተሰውረው ነበር።(እንደዛ ነበር የማስበው)፡፡ ይኼ ፍቅር የሚባል ነገርማ የሆነ ዙርያውን የሚያደነግዝ ነገር ሳይኖረው አይቀርም። የመሀሪ እሺ ይሁን ሮሐ እንደ ሰንደቅ ዓላማ ከየትና የት ማንም የሚለያት ልጅ፣ (ወይ የጋሽ ግርማ ቆንጆ የሚሏት)
እንዴት ከወሬኛ ዓይን ተሠወረች …እያልኩ አስብ ነበር፡፡

ወደ አስራ ሁለተኛ ክፍል አልፈን ለማትሪክ የምንዘጋጅበትን መጽሐፍና፣ ያለፉ ዓመታት ተፈታኞችን የፈተና ወረቀቶች ሰብስበን እንሙት ባልንበት ክረምት ታዲያ፣ ይሆናል ብለን ያላሰብነው፣ የልብ ምታችንን ቀጥ አድርጎ ሊያቆም የሚችል፣ ድንገተኛ ነገር ተፈጠረ (የሰው ልብ አቻቻሉ )

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ፍኖተ_አርነት

ክቡር መንፈሴ ሆይ!
አንተው ሕግ አርቃቂ
አንተው ፍርድ አጽዳቂ
የወኅኒው ባለቤት
የወኅኒው ጠባቂ
ደካማው ሰለባህ
በኀይልህ ሥር ታስሮ
ያመልጥ ይኾን ሰብሮ
ይበቀለኝ ዞር
ምን ያስብ ምን ያቅድ
ምን ይክብ ምን ይንድ?
ብለህ በማውጠንጠን ዕረፍት ከምታጣ
ምርኮኛኽን ፈተሕ አንተው ነጻ ወጣ፡፡

🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_ስምንት


#በአሌክስ_አብርሃም

ወደ አስራ ሁለተኛ ክፍል አልፈን ለማትሪክ የምንዘጋጅበትን መጽሐፍና፣ያለፉ ዓመታት
ተፈታኞችን የፈተና ወረቀቶች ሰብስበን እንሙት ባልንበት ክረምት ታዲያ፣ ይሆናል
ብለን ያላሰብነው፣ የልብ ምታችንን ቀጥ አድርጎ ሊያቆም የሚችል፣ ድንገተኛ ነገር
ተፈጠረ (የሰው ልብ አቻቻሉ )

ትምህርት ቤት ለክረምት ከተዘጋ በኋላ፣ በተለይ ቅዳሜ ቅዳሜ ሄኖክ የሚባል አብሮን የሚማርና ሮሐን ክፉኛ ይከጅል የነበረ ልጅ፣ ተስፋ ቆርጦ ይሁን አልያም እሷን ባላገኛትም እንኳን፣ ጠረኗ ቤቴን ይሙላው ብሎ …ብቻ ለጥናት በሚል ሰበብ፣ የተከራያትን አንዲት ክፍል ቤት ለመሐሪና ሮሐ ይለቅላቸውና ዓለማቸውን ሲቀጩ ይውላሉ፡፡ የዓለም ቀጨታው ከመሳሳም አያልፍም” ቢልም ወዳጄ መሐሪ … ነፍሴ እሺ ብላ አታምንም ነበር፡፡ እንዲያው ይሁንልህ በሚል ቸልተኛ መሸነፍ አምኘለት እናልፈዋለን፡፡

ታዲያ ሲመሻሽ ሄኖክን ለቤቱ አመስግነን ሮሐን በአሳቻ መንገዶች እያቆራረጥን
እስከቤቷ አቅራቢያ ሸኝተን (የት ዋልሽ ስትባል የት እንደምትል እንጃ ወደ ቤታችን
እናዘግማለን፡፡ መሐሪና ሮሐ ሁልጊዜ ከዚህ ቤት ሲወጡ ዝምተኛና አንገታቸውን የደፉ የሚሆኑበት ነገር አለ፥ ምን ሆናችሁ አልልም፡፡ በሌለሁበት ጉዳይ መተፋፈሩ እኔም ላይ ተጋብቶ አፌን ይዘጋኛል፡፡ ወደ ቤት ስንመለስ በመንገዳችን፣ መሐሪ ዓይኔ ቀላ እንዴ? ከንፈሬ አበጠ እንዴ? - ጸጉሬ እንዴት ነው? የሚሉ አንዳንድ ወላጅ ሊያውቃቸው የማይገቡ ነገሮችን ማድረጉን ሊጠቁሙ የሚችሉ ምልክቶችን ተባብረን አሻራ እናጠፋለን፡፡ እቤት የሚጠብቀው ሣር ቅጠሉን የሚጠራጠር የዳኛ ዓይን ነው!

የዚያን ቀን ቅዳሜ ማታ መሐሪ፣ “ግባና ሰላም ብለሃቸው ትሄዳለህ ብሎ ገፋፍቶኝ
(ሁልጊዜ ራሳቸው ቤት ውስጥ ብቻውን መግባት ለምን እንደሚፈራ አይገባኝም) …ወደ ቤታቸው ተያይዘን ገባን፡፡ ጋሽ ዝናቡ በረንዳው ላይ ተቀምጦ መጽሐፍ ያነብባል፡፡
መጽሐፉን አጠፍ አድርጎ ጎረምሶች ከየት ነው” አለ።

እግራችንን እናፍታታ ብለን .” አልኩ (ተከላካይ ጠበቃ ይመስል የምፈጥነው ነገር አለ)

"ሙሉ ከሰዓት እግር ስታፍታቱ …መልካም ዝም ተባባልን፡፡

እንግዲህ ወደ መጨረሻው መጀመሪያ እየቀረባችሁ ነው፣ ዝግጅት እንዴት ነው?
“ያው …" መሐሪ ተንተባተስ ድንገት ጋሽ ዝናቡ ሂዱ እስቲ ወንበር ይዛችሁ ኑ!” አለ፡፡ የየራሳችንን ወንበር ይዘን መጠንና፣ ፊት ለፊቱ ተቀመጥን፡፡ ተጨንቀናል። ጋሽ ዝናቡ ቁጭ በሉ አለ ማለት፣ ልክ አሰተማሪ ውጣ ተንበርከክ እንደሚለው ዓይነት፣ የቅጣት ስሜት ያለው ነገር ነው፡፡

እና እግር ማፍታታቱ የት የት ወሰዳችሁ?” አለን ድንገት፡፡ እኔና መሐሪ ተያየን
አብርሃም” አለኝ (የማሪያምን ብቅል ፈጭቻለሁ ብል ደስታዬ)

"አቤት ጋሸ”

“መሐሪ ወንድምህ ማለት ነው፤ እናንተ አሁን ጓደኛ አትባሉም፣ ለኛም ቢሆን ከመሐሪ ለይተን የማናይህ ልጃችን ማለት ነህ፣ የመሐሪ ነገር የእኔን ያህል የእናቱን ያህል ሊያሳስብህ ይገባል፡፡ እፈለጋችሁበት ስትሄዱ፣ የት ወጣህ? የት ገባህ? የማንለው ለምን ይመስልሃል? ስላደገ ችላ ብለን ነው? አይደለም! አንተን ስለምናምንህ፣ ጥሩ ልጅ ስለሆንክና፣ መጥፎ ቦታ ሲውል ዝም ብለህ እንደማትመለከተው ስለምናምን ነው፡፡
ይገባኛል ጓደኝነታችሁ፣ እርስ በርስ ነገሮችን የምትሸፋፍኑት ነገር፥ ግን ደግሞ
ከሪያሊቲው ብዙ መራቅ የለባችሁም፡፡” ብሎ ተራ በተራ አዬንና

ስለ ሮሐ ሁሉንም ነገር አውቃለሁ፡፡” አለን:: የመሐሪ ጉሮሮ ገርገጭ ሲል ሰማሁት፡፡ ምራቁን ሳይሆን ሰላሳ ሁለት ጥርሱን ባንዴ የዋጠው ነበር የሚመስለው፡፡
“ሮሐ ኧረ ሮሐን አናውቃትም …ማናት? …” ብዬ ወደ መሐሪ ስዞር፣ አንገቱን ደፍቶ
መሬት መሬቱን ይመለከታል ፡፡

“መሐሪ እናተ ቤት ነኝ እያለ፣ የት ያመሽ እንደነበር አውቃለሁ፡፡ ከመጀመሪያው
አውቃለሁ ኢትስ ኦኬ” አሁን ልወቅሳችሁ አልያም ልከሳችሁ አይደለም ዕድሜያችሁ ነው፡፡ ሰው እናትና አባቱን ይተዋል…” ይላል መጽሐፉም አይደለም እንዴ መሐሪ እሁድ ጧት ቤተክርስቲያን ስትሄድ እንደዛ ሲሉ አልሰማህም?…” እለና ሃሃሃሃ ብሎ ሳቀ፡፡አሳሳቁ የመሐሪን የእሁድ ጧት ጉዳይ እንዳወቀ የሚያሳብቅ ዓይነት ነበር፡፡ “ሕፃን አይደላችሁም፤ በመደባበቅ ጫካ ለጫካ በመሄድ፣ የጥናት ጊዚያችሁን ማባከን የለባችሁም ያውም ባለቀ ሰዓት ትምህርት ዋናው ጉዳይ ነው፡፡ ትምህርት!
ትምህርት! ባለማመን ቀስ ብዬ የጋሽ ዝናቡን ፊት ስመለከተው ዓይን ለዓይን
ተገጣጠምን፡፡ መልሼ አቀረቀርኩ ፡፡

“መሐሪ”

“እቤት ጋሽ”

“ስሚመቻት ቀን አምጣትና ከእኔም ከእናትህም ጋር እስተዋውቀን፡፡ ከዚህ በኋላ ጢሻ ለጢሻ እየዞራችሁ ጊዚያችሁን ስማይረባ ድብብቆሽ እንዳታሳልፉ፡፡መገናኘት ሲኖርባችሁ እዚሁ ትምጣ

“ማን መሐሪ ተንተባተበ፡፡

“ከዚህ ሳምንት እንዳያልፍ! አሁን ሂዱ” ማሚን እንኳን ገብቼ ሰላም ሳልላት በቀጥታ ከበረንዳው ወደ ቤቴ ሮጥኩ፡፡

መንገድ ላይ ለራሴ እንዲህ እያልኩ ነበር፡፡ “ከስብከቱ ሁሉ የማይዋጥልኝ ይኼ ሰው እናትና አባቱን ይተዋል የሚሉት ነገር …አሁን ጋሽ ዝናቡ ልተውህስ ቢሉት የሚተው ሰው ነው ?
👍1
እነዚያ ለማትሪክ የተዘጋጀንባቸው ወራት አለፉ፡፡ ፈታኝ ስድስት ወራት፣ በወረቀት
ዋሻዎች ውስጥ የመነንባቸው፣ የዓለምን ዕውቀት ሁሉ ከወረቀት ማሕፀን ልናዋልድ
ማሪያም ማሪያም ያልንባቸው የምጥ ወራት፡፡ እንደ ሰዓት ቦምብ እያንዳንዷን ደቂቃ በጭንቀት የቆጠርንባቸው፤ ግን ደግሞ ልክ እንደ ምጥ ከአእምሯችን አብራክ የሚወለደውን ነገ፣ በሚያጓጓ ተስፋ የጠበቅንባቸው በጣት የሚቆጠሩ ወራት፡፡ ሌላ ዓለም አልነበረንም፣ ሌላ ሕልም አልነበረንም፡፡ ገነት የት ነው ቢሉን? ዩኒቨርስቲ መግቢያው በዬት ነው? ቢሉን፣ በዚህ በቆለልነው ወረቀት በኩል ባዮች ነበርን፤ዕውቀት አልነበረም ዓይኖቻችን ሲቃርሙ የነበሩት፣ በኬሚስትሪና ፊዚክስ፣ በሂሳብና
እንግሊዝኛ ተመስጥሮ የተዘጋ የገነትን ቁልፍ መክፈቻ ተአምር እንጂ፡፡ ይኼም ቆይቶ ገባኝ፡፡ ዘግይቶ አይባልም መቼም፡፡

የሚበዛውን ጊዜ የምናድረው እነ መሐሪ ቤት ነበር፡፡ ያቺ በመስኮቷ የግቢውን አበቦች ስትጋብዘን፣ ችላ ብለን ወረቀት ላይ ያቀረቀርንባት የመሐሪ መኝታ ቤት፣ ከአራት ግኡዝ ግድግዳ የተሠራች ክፍል ሳትሆን፤ እኛን ልትወልድ በበኩሏ በምጥ የምትናጥ የብሎኬት ማሕፀን ነበረች፡፡ ማሚ ሌሊቱን ሙሉ፣ አንዴ ቡና፣ አንዴ ሻይ እያፈላች፣ ወዳለንባት ክፍል ብቅ ትልና፣ እንደደከመው ሰው አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ ብላ፣ “ ትንሽ አረፍ
እያላችሁ …ችክ አትበሉበት ትለናለች፡፡ በኋላ ስንቀልድ “ማትሪክን አብረሽን ተፈተንሽ!” እንላት ነበር፡፡ እጄን…ያንን የሚቅጨለጨል ወርቃማ ማሰሪያ ያለው የማይሠራ ሰዓት የምታስርበትን ግራ እጇን ወደላይ ቀስራ እናሸንፋለን!”
ትለናለች፡፡

“ማሚ ስዓትሽ ለምን እይሠራም?”

“ማሰሪያውን አታዩትም፣ እያረጀ ነው …እንዲህ ያለው ሰዓት ዓመትን እንጂ ደቂቃና ሰዓት አይቆጥርም፡፡” ትልና ቅሬታ ያረበበት ፈገግታዋን አሳይታን ተነስታ ትሄዳለች፡፡ ምን ማለቷ ነው አላልንም፡፡ የሚያሳስበን ብዙ ጉዳይ ነበር፡፡

ጋሽ ዝናቡ በነዚህ ወራቶች ባሕሪው ተለሳልሶ አልፎ አልፎ ቀልድ የሚያወራ አባት ሆኖ ነበር፡፡ ጋሽ ዝናቡ ቀልድ ጣል ሲያደርግ፣ ደም ሥራችን እሲኪወጣጠር ጣር የሚመስል ሳቅ የምንሰቀው፣ ከቀልዱ ይልቅ ስምንተኛው ሺ የቀረበ እየመሰለን ሳይሆን አይቀርም፡፡ እንዲሁ ጋሽ ዝናቡ መቀለዱ አያስቅም? አንድ ቀን ማሚን እንዴ ጋሼ መቀለድ ሁሉ
ጀመረኮ” ስንላት “ይኼ ስራው ኮስታራ አደረገው እንጂ፣ ድሮማ ጥርስ አያስከድንም ነበር አለን፡፡ መሐሪ ታዲያ ከዚያ በኋላ በሆነ ነገር ሲጨናነቅ “ሳቃቸውን ድሮ ጨርሰው እኛ ያጨናንቀናል” ይላል፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_ዘጠኝ


#በአሌክስ_አብርሃም

ጋሼ መቀለድ ሁሉ
ጀመረኮ” ስንላት “ይኼ ስራው ኮስታራ አደረገው እንጂ፣ ድሮማ ጥርስ አያስከድንም ነበር አለን፡፡ መሐሪ ታዲያ ከዚያ በኋላ በሆነ ነገር ሲጨናነቅ “ሳቃቸውን ድሮ ጨርሰው እኛ ያጨናንቀናል” ይላል፡፡

ጋሽ ዝናቡ ለምሳ ወደቤት ካልተመለሰ፣ በቀን አንዴ እየደወለ እሺ! ጥናት እንዴት
ነው?” እያለ ይሰልለናል፡፡ ያን ሰሞን ሥራ ይበዛበት ስለነበር (ተዘዋዋሪ ችሎት የሚባል ነገር) ብዙ ባያገኘንም አምሽቶ ሲመጣ፣ በቀጥታ ወደ ከፍላችን ብቅ ይልና በሩን ያንኳኳል፡፡ እንደማሚ በርግዶ አይገባም፣ እንዲያውም ወደ ውስጥ አይገባም እንዴት እየሄደ ነው?” ይለናል፡፡ አፋችን እየተንተባተበና ቃላት አፋችን ላይ እየተጋጩ “ጥሩ ነው! ምንም አይል፡፡” እንላለን፡፡ “አይዞን!” ብሎ ተመልሶ ይሄዳል፡፡ ዓርብ ዓርብ ታዲያ
እዚያዉ በር ላይ እንደቆመ ዋሌቱን ከኋላ ኪሱ ያወጣና፣ ድፍን አምሳ ብር መዞ በሩ ሥር የቆመች የመጽሐፍ መደርደሪያ ጫፍ ላይ አስቀምጦልን ይሄዳል፡፡ ብዙ ጊዜ ሮሐንን እንጋብዝዎታለን፡፡ በተረፈው ለሳሌም እና ለማሚ ኬክ እንገዛላቸዋለን፡፡ ሁለቱም ኬክ ይወዱ ነበር፡፡ ማሚ ኬክ በኛ ጊዜ ቀረ …እያለች፣ ሳሌም ነገም ኬክ እንበላለን እያለች ትዝታና ተስፋን ዛሬ ላይ እንጋብዛለን፡፡

ሮሐ ቅዳሜ ቅዳሜ እነ መሐሪ ቤት መምጣት ከጀመረች ሰነባብታ ነበር፡፡ ጋሽ ዝናቡ ወታደራዊ ትዕዛዝ መሠረት በስንት ክርከርና ፍርሃት (መሐሪ አይሆንም ብሎ በኔው ውትወታ) አምጥተን ካስተዋወቅናት በኋላ፤ ከእኛም በላይ ቤተኛ ሆና ቁጭ አለች፡፡
“በምን ቀን ነው ያስተዋወቅናትም እስከምንል፡፡ በተለይ ማሚ ልክ እንደ ልጇ ሚስት ነበር አቀባበሏ፡፡ ታዲያ መሐሪን ለብቻው እንደዚህ ስለው ሚስት ናትና ይለኛል፡፡ማሚም ፊት ይሁን ጋሽ ዝናቡ ፊት፣ ሮሐ በመጣች ቁጥር ግን ሁልጊዜ ያፍራል። ፍቅረኛው እቤቱ መምጣቷ ብዙ ምቾት የሰጠው አይመስለኝም ፡፡ እውነቱን ለመናገር
እኔም የሮሐ ነገር ምቾት ነስቶኝ ነበር፡፡

እስተዳደጓ ይሁን አልያም ተፈጥሮዋ፣ ሮሐ ፍርሃት የሚባል ነገር ያልፈጠረባት ልጅ ነበረች፡፡ ከልክ ያለፈ ነጻነቷም በመሸማቀቅ ጭብጦ ላከልነው ለእኔና መሐሪ በቀላሉ የሚለመድ ነገር አልሆን ብሎ ተቸግረን ነበር፡፡ መሐሪ ወላጆቹ ባሉበት ሮሐን ፈጽሞ አጠገቡ እንድትቀመጥ አይፈልግም፡፡ ሮሐ ደግሞ ጎኑ ከመቀመጥ አልፋ ክንዱን ትከሻው
ላይ ጣል ታደርጋለች፡፡ ጋሽ ዝናቡ ፊት ጭምር እንደዚያ ታደርጋለች፡፡ መሐሪ ታዲያ ክንዷ ባረፈበት ቁጥር፣ ዝንብ እንዳረፈበት ፈረስ ሰውነቱን እያነዘረ ክንዷን ሊያባርረው ይታገላል፡፡ አቤት ያ ትዕይንት እንዴት እንደሚያዝናናኝ፡፡

አንድ ቀን ማትሪክ ወስደን ዕረፍት ላይ በነበርንበት ሰሞን፣ ሮሐ እነመሐሪ ቤት መጥታ ሰብሰብ ብለን እናወራለን፡፡ ልክ እንደ ጓደኛዋ ነበር ጋሽ ዝናቡን የምታወራው፡ስትጠራው ሁሉ “አንተ” እያለች ነው፡፡ ድንገት “ጋሺ ማሚ ጋር እንዴት ተገናኛችሁ ግን አለችው፡፡ እንዲሁ አለችው፡፡ እኔና መሐሪ ተሳቀን ልንሞት፡፡ መሐሪ በቀስታ አመልካች ጣቱን ከጆሮው በላይ ራሱ ላይ ሰክቶ እንደቡለን መፍቻ እያዞረ አሳየኝ፣ የማታል እንዴ?” ማለቱ ነበር: ትከሻዬን ሽቅብ ሰበቅኩና ሳቄን አፍኜ ዝም አልኩ፡፡ ተነሽና ከዚህ ቤት ውጭ ቢላትስ እያልኩ ሳስብም ነበር: ጋሽ ዝናቡ ግን፣ ከት ከት ብሎ ስቆ ራሷ ትንገርሽ እኔ እርጅናው ነው መሰል ነገር እየረሳሁ ነው? አላት

በእነዚያ ወራት ያ በጋሽ ዝናቡ የቁጣ መንፈስ የተሞላ ሰፊ ግቢ፣ የጥሩ ቤተሰብ ድባብ አርብቦበት ነበር፡፡ የተቋጠረው የጋሸ ፊት እነመሐሪ ግቢ እንደልጅ ተንቀባራ ባደገችው
ሳሌም የልጅነት ቡረቃ ተፈቶ ዘና ሲል አይቸዋለሁ በሮሐ ግዴለሽ ወሬ ሳይወድ በግዱ የተለጎመ አፉ ተፈቶ ሲያወራ ታዝቢያለሁ! “ጋሼ ይኼኮ በቃ የሥራ ጐዳይ ነው አጋጣሚ ነው …ለምን ከአባባ ጋር አትታረቁም ትለዋለች፡፡ ጋሽ ዝናቡ እየሳቀ አባትሽ ከሕግ ጋር እንጂ መች ከእኔ ጋር ተጣላ” ይላታል።

“ዋትኤቨር ብትታረቁ ይሻላችኋል …እዚች ጠባብ ከተማ ውስጥ በተገናኛቹ ቁጥር
ከምትገለማመጡ፡፡ ጋሽ እያያት ይስቃል፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ጋሽ ለእኔና መሐሪ ሮሐ
ጥሩ ልብ ያላት ልጅ ናት፤እንዳታስቀይሟት ብሎን አረፈው፡፡ መሐሪስ እሽ፣ እኔ ምን
ቤት ነኝ እያልኩ ተገረምኩ፡፡ አድናቆቱ ወደማሚም ተጋብቶባት ነበር ሮሐዬ ድንጋይ የምታናግር ተጨዋች አሉ እንጅ የኛ ዝጎት፣ ማልጎምጎም ብቻ፤ ወይ ፈታ ብለው አያወሩ " አለች ወደኔና መሐሬ እያየች፡፡ ሮሐ ታዲያ ኧረ ጋሽ እንደምታካብዱት አይደለም፣ ደስ የሚል ፈታ ያለ ሰው ነው ትለናለች! እኔና መሐሪ በአንድ አፍ ያልተያዘ … ብለን እንሳሳቃለን:: የዚያ ሰሞን የአስራ ሁለተኛ ክፍል የአማርኛ። ላይ የነበረ ጥያቄን እያስታወስን፡

ጥያቄ ቁጥር 7. ያልተያዘ.........
ሀ መያዝ አለበት

ሊ ግልግል ያውቃል

ሔ መያዙ አይቀርም

መ. ሁሉም መልስ ነው፡፡ ይች 'ለ' የሆነች ልጅ ጋሽ ዝናቡን “ዘና ያለ ሰው ነው” አለችን።

የዚያ አዚማም ግቢ ሌላዋ ድምቀት ሳሌም ነበረች፡፡ ማሚና ጋሽ ዝናቡ አንድ መሐሪን ብቻ ወልደው የረሱትን የልጅ ሳቅ እንደገና እያስታወስች፣ በትዝታ የምታነጉዳቸው ውብ ፍጥረት። ግቢው ውስጥ ቢራቢሮዎችን ተከትላ ስትቦርቅ ጋሽ ዝናቡ የሚወዛወዝ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ በፈገግታ ይመለከታታል ማሚ ብቅ እያለች ቀስ እንዳትወድቂ
ቃቢዳ ትላታለች፡፡ ቃቢዳ ነበር የምትላት፡፡ ሳሌም የምትበላው ከመሐሪ ፣
የምትቀመጠው ከመሐሪ ጋር፣ የመሐሪ ነገር ሞቷ ነበር፡፡ እኔና መሐሪ የአሥራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ስንወስድ ፈረንጆቹ ቤት” በተቋቋመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ሆና ነበር…ሰማያዊ አጭር ባለማንገቻ ቀሚስ፣ ጉልበቷ ድረስ የሚደርሰ ነጭ ካልሲ ለብሳ፣ ገና በዚያ ዕድሜዋ ወገቧ ላይ የደረሰ ጥቁር
ጸጉሯ ቁጥርጥር ተሠርቶና ጫፉ ላይ በቀይ ቢራቢሮ ቅርፅ ባላት የፀረር ማስያዣ ተይዞላት(ማሚ ነበረች ብዙ ጊዜ የምትስሠራት) ቀተራመደች ቁጥር እንደ ጅራት እየተወዛወዘ፣ ስትሄድና ስትመጣ እስካሁን ዓይኔ ላይ አለች፡፡

እስከ ዛሬ እንደ ሳሌም ዓይነት ቆንጆ ሕፃን አይቼ አላውቅም፤ ስለምወዳትም እንደሆን እንጃ፡፡ በዚያ ላይ አፏ ዝም የማይል ፈጣንና ወሬኛ ነበረች፡፡ ስታድግ ምኞቷ ዶክተር መሆንና መሐሪን ማግባት እንደሆነ ለማሚ ነግራታለች፡፡ ካቶሊኮች ትምህር ቤት ከገባች በኋላ ግን፣ ምኞቶቿ ወደ ሦስት ከፍ ብለው ነበር ዶክተር መሆን ፣መሐሪን ማግባትና የካቶሊክ መነኩሌ መሆን፡፡ ሮሐ ይኼን ስትሰማ እየሳቀች “ይች ካሁኑ ቁልት ያደረጋት
ልጅ መሐሪን ማሚ እንኳን እንደሷ የት ወጣህ? የት ገባህ? አትለውምኮ እኔን ስታይ እንዴት ፊቷ እንሚቀያየር ትላለች፡፡

አረ ሕጻን አይደለችም እንዴ! ምን ታውቃለች? ይላል መሐሪ።
አንዳንዴ ሮሐና ሳሌም ይከራከራሉ …ሮሐ ድምፅዋን ቀንሳ (ማሚ እንዳትሰማት)
ሳሌም፣ መሐሪ የኔ ባል ነው፣ ይዤው እሄዳለሁ እሺ?” ትላታለች።

ኧረ ባክሽ! የኔ ባል ነው …ብትፈልጊ ሌላ ሰው አግቢ”

ሌላ ሰው የለም

“ይኼው አብርሽን አግቢ” ትልና ወደ እኔ ትጠቁማታለች በሐፍረት ዓይኔን የማሳርፈበት ይጠፋኛል፡፡ ሮሐ እንደ ቀልድ በጀመረችው ክርክር እንደ ትልቅ ሰው በሳሌም ትበሳጫለች፡፡

አንቺ ሕፃን ነሽ …ባል ምን ያደርግልሻል?” ትላታለች ፍጥጥ ብላ፡፡

ያስጠናኛል፣ የቤት ሥራ ይሠራልኛል፣ኬክ ይገዛልኛል .…አንችስ ባል ምን ያደርግልሻል?” ይች ሕፃን አይደለችም ትላለች ሮሒ

"ቅድም ሕፃን ነሽ አላልሽም? …ሂሂሂ”
👍1
እናቷ ጥድቄ እዚያው ካቶሊኮች ትምህርት ቤት በጽዳት ሠራተኝነት ተቀጥራ ጧት ወጥታ ማታ ነበር የምትመለሰው፡፡ እንዲህ ነበር ግቢው እንዲህ ነበር ያ ከሰፈሩ በትልቅነቱ፣ በረዥም የግንብ አጥሩ፣ እንደደብር የሚፈራው የጓደኛዬ መሐሪ አባት የዳኛ
ዝናቡ አውላቸው ቤት! ግቢው ውስጥ የነበሩ ዕድሜ ጠገብ ግዙፍ ዛፎች ላይ ወፎች ጎጇቸውን ሠርተው ይሰፍሩበት…ቢራቢሮዎችም ግቢውን በሞሉት አበቦች ላይ ያንጃብቡ ነበር፡፡ ግዙፍ የብረት በሩ የሚያስፈራ፣ዳኛ ሳይሆን ሕግ ራሱ ነፍስ ዘርቶ የሚኖርበት የሚመስል ግቢ፣ እዚያ ነው ያደግነው፡፡ አናፂው አባቴ በገዛ እጆቹ ካቆማት ባለሁለት ክፍል የጭቃ ቤታችን በላይ ይሰብሰብ ሲባል ከልጅነት እግሮቼ ዳና እስከ ጉርምስና መዳፌ አሻራ መገኛው እዚህ ግቢ ውስጥ ነበር፡፡ ከቤታችን እስከዚህ ግቢ በተዘረጋችው
አቧራማ መንገድ ላይ የታተሙት የጫማዬ ዳናዎች ቢቀጣጠሉ ሰው አልረገጣቸውም ብለው ካስተማሩን ፕላኔቶች አንዱን ነክተው በተመለሱ፤ ግን ከመንገዱ ይልቅ ልቤ ላይ ነበር እያንዳንዱ እርምጃዬ በጋለ ብረት ማኅተሙን የተወው፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
አትሮኖስ pinned «#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን ፡ ፡ #ክፍል_ዘጠኝ ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ጋሼ መቀለድ ሁሉ ጀመረኮ” ስንላት “ይኼ ስራው ኮስታራ አደረገው እንጂ፣ ድሮማ ጥርስ አያስከድንም ነበር አለን፡፡ መሐሪ ታዲያ ከዚያ በኋላ በሆነ ነገር ሲጨናነቅ “ሳቃቸውን ድሮ ጨርሰው እኛ ያጨናንቀናል” ይላል፡፡ ጋሽ ዝናቡ ለምሳ ወደቤት ካልተመለሰ፣ በቀን አንዴ እየደወለ እሺ! ጥናት እንዴት ነው?” እያለ ይሰልለናል፡፡ ያን ሰሞን…»
#የመገፋት_ደርዙ

ጭላንጭል ብርሐን ከውስጥህ ሳይጠፋ
መጭውንም ናፍቀህ ተሞልተህ በተስፋ
ያለአንዳች መታከት ቀን ከሌሊት ልፋ፡፡
ብሒል ነው የነበር
“በእግሩ ይራመዳል ዕንቁላል ቀስ በቀስ”
የቻልከውን ያህል
እንደንፋስ ንፈስ ብረር ተንቀሳቀስ፡፡
ተረጋግተህ እንዳቀር በሰው ስትገፋ
ተገፋ ሁኝ ብለህ ጭራሽ አትከፋ፡፡
ግዑዙ ቅቤ እንኳ ክብርን ያላጣው ፤
ስለተገፋ ነው አናት ላይ የወጣው።

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
👍1
#ግራ

የምሬን አፍቅሬሽ
ወይ አልኖርኩ አብሬሽ።
የእውነት ጠልቼሽ
ወይ አልሔድኩ ሸሽቼሽ፡፡
ሰው የማያውቀውን ካለእግዜር በስተቀር
ምስጢሬን ልንገርሽ ተመሥጥሮ እንዳይቀር፡፡
ይኸውልሽማ
ውስጣዊ ስሜቴ መላቅጡ ጠፍቶ
መላው ሕዋሳቴ ሥርዓቱ ተናግቶ
ግራ እሚያገባ ቢሆን የኔ ነገር
አቅቶኛል መጥላት፤ ተስኖኛል ማፍቀር፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ አደሬ🔘
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_አስር


#በአሌክስ_አብርሃም

ከቤታችን እስከዚህ ግቢ በተዘረጋችው
አቧራማ መንገድ ላይ የታተሙት የጫማዬ ዳናዎች ቢቀጣጠሉ ሰው አልረገጣቸውም ብለው ካስተማሩን ፕላኔቶች አንዱን ነክተው በተመለሱ፤ ግን ከመንገዱ ይልቅ ልቤ ላይ ነበር እያንዳንዱ እርምጃዬ በጋለ ብረት ማኅተሙን የተወው፡፡

ጋሽ ዝናቡ በደስታ ሁለት እጆቹን በሰፊው ዘርግቶ እፊቱ ያገኛትን ማሚን ቢያቅፋት (አፈሳት ቢባል ይሻላል) በቁሟ እጥፍጥፍ ብላ እንደ ከረባት በሰፊው ደረቱ ላይ ተቀመጠች፡፡በዚያ ሰዓት እፊቱ የኤሌክትሪክ ምሰሶም ቢያገኝ የሚያቅፈው ይመስለኛል።
መሐሪን አቅፎ ግንባሩን ጸጉሩን ሳመው::መሐሪን እንዳቀፈው እኔንም ጎትቶ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምታሳድር ዶሮ ግራና ቀኝ አቅፎ ሰፊ ደረቱ ላይ ለጠፈን፡፡ በረዥሙ ተንፍሶ ለቀቀንና ትክ ብሎ እያየን፣ ልክ ሴቶች እንደሚያለቅሱ ጠይም ፊቱ ላይ እንባው
ድንገት እየፈሰስ ችፍርግ ባለዉ ፂሙ መሃል ሰረገ፡፡ መሐረሙን አውጥቶ ዓይኑን
ጢረገና፣ ሶሪ ብሉን ወደ ውስጥ ገባ፡፡ ማሚ እንደ ፎካሪ ሳሎኑ ውስጥ እየተንራደደች ደጋግማ በየተራ ጉንጫችንን አገላብጣ እየሳመች “የኔ አንበሶች እንዲህ ነዋ! እንደ ዛሬም
ኮርቼ አላውቅ ትላለች፡፡

ጋሽ ዝናቡ ፊቱ በደስታ እንደተጥለቀለቀ ተመልሶ መጣና “ሮሐ እንዴት ሆነች?” አለ ስሪ ፖይት ቱ አለ መሐሪ፡፡

እጅግ በጣም ጥሩ ውጤት …ዋናው ያችን በር አልፎ ሙግባቱ ነው

የማትሪክ ውጤት ተነግሮ ነበር፡፡ እኔም መሐሪም አራት ነጥብ አምጥተን ዩኒቨርስቲ እንኳን የረገጠ ተማሪ በሌለበት ሰፈር ታሪክ ተባለልን፡፡ ገድላችን ከላይ እስከታች ተወራ፡፡ ጠባብ ከተማችን ሐውልት አታቆምልን ነገር ቸገራት እንጂ ስማችን አየሩን ሞላው እነዚያ መንትያ የሚመስሉት ልጆች ነቀነቁት” ተባለ፡፡ ይኼ የዳኛው የዝናቡ ልጅ እና በቀደም ቆርቆሮ ሲጠግን ከጣራ ላይ የወደቀው አናጢ ልጅ፣ ሁለቱም አራት ነጥብ
(እባቴ ከአስራ አምስት ቀን በፊት ከመሰላል ላይ ወድቆ እግሩን ወለም ብሎት እቤት ውሎ ነበር፡፡ ይኼም ወሬ ሁኖ ምልክት ሆነ)
መሐሪ ጋር ተያይዘን ወደ እኛ ቤት ሄድን፡፡ እቤት ስንደርስ፣ እናቴ ደስ ብሏት በእልልታ
ተቀበለችን፡፡ ቀድማ ሰምታ ነበር፡፡ ወሬው ቀድሞን ነበር፡፡ አገላብጣ ስማን ስታበቃ
ወደኔ ዞር ብላ ታዲያ አሁን ዩንበርስቲ ሌላ አገር ልትሄድ ነው? ብላ ጠየቀችኝ፡፡
ድምፅዋ ውስጥ እንባ የሚያቀባብል ሊተኮስ የተዘጋጀ ለቅሶ ነበር፡፡ አባቴ ጋደም ባለበት ና ሳመኝ ና የኔ ግስላ! …” ብሎ ሳመኝ፡፡(መሐሪ ከዚያች ቀን በኋላ ለሳምንት ግስላው እያለ ያበሽቀኝ ነበር፡፡ አባባ ታዲያ እየሳመኝ እዚያው ላይ እቁቡን ተቀብሎ ስለሚገዛልኝ ምን የመሰለ ልብስ” ነገረኝ፡፡ እናም በዚያው የዕቁብ ወሬ ሊጀምር ዳር ዳር ሲል፣ እናቴ
ገስጻ ወደ እኔ ውጤት መለሰችው፡፡ አይ አባባ! በጣም እኮ ነው የምወደው እንደው ዩኒቨርስቲ ስለ ዕቁብ የሚያጠና ራሱን የቻለ የትምህርት ክፍል በኖረና፤ አጥንቼ በከተማችን ትልቁን እቁብ በመሠረትኩለት እስከምል፣ በጣም ነው የምወደው አባባን፡፡ በምድር ላይ ተስፋ የሚያደርገው ብቸኛ ነገር ቢኖር ዕቁብ ነው! ልጀ ተምሮ ይጦረኛል የሚል ተስፋ እንኳን ያለው አይመስለኝም!! አሁን ራሱ ልጅህ አራት ነጥብ አመጣ ከሚለው ዜና ይልቅ፤ ልጅህ ዕቁብ ደረስው ቢሳል፣ የእግሩን ወለምታ ረስቶ ዘሎ ሳይቆም
ይቀራል? …እባባና ዕቁብ !

ውጤታችንን ስለማን ልክ በአስራ አምስተኛ ቀኑ፣ ማሚና ጋሽ ዝናቡ ድል ያለ ድግስ ደግሰው፣ ከመንደሩ ሰው እስከ ትምህርት ቤት አስተማሪዎቻችን ጓደኞቻችን ድረስ ጠሩ፡፡ ከተማው ውስጥ ያለ ጠበቃና ዳኛም አልቀረም፡፡ እንዲያውም ጋሽ ዝናቡ ሮሐን
እንዲህ አላት እሽ ካለና ከመጣ ለአባትሽ ይኼን መጥሪያ ስጭው' ብሎ የሮሐ አባት እንዲገኝ ጥሪ ላከለት፡፡ “ቢመጣም ባይመጣም እኛ እንቀውጠዋለን አለች ሮሐ፡ ጋሸ ታዲያ ፈገግ ብሎ “ እብድ የሆንሽ ልጅ፤ ወይ መጥሪያውን መሰጠት እንዳትረሸ

እሰጠዋለሁ፣ ብቻ የፍርድ ቤት መጥሪያ መስሎት አባቴን ካገር እንዳታስጠፋው ጋሽ?”

“ሀሀሀሀሀሀሀሀ” ብሎ ሳቀ ጋሼ፡፡ ከዚያ በፊትም ከዚያ በኋላም እንደዚያ ሲስቅ
አላየሁትም፡፡

የድግሱ ቀን፣ ነጫጭ የፕላስቲክ ወንበሮች ግቢውን በመደዳ ሞልተው ሲታይ፣ የግቢው ጥርሶች ይመስሉ ነበር፡፡ ያ ፈዛዛ ግቢ የሚስቅ ዓይነት፡፡ በቤቱ በረንዳ ላይ ትልልቅ ድምፅ ማጉሊያዎች ግራና ቀኝ ቆመው ግቢው ላይ የሰፈረውን የዝምታ አጋንንት ሊያባርሩ ከባሕላዊ እስከ ዘመናዊ ዘፈን ይረጫሉ ከበረንዳው ሥር ተቀጣጥለው የተቀመጡና ነጭ ጨርቅ የለበሱ ረዣዥም ጠረጴዛዎች ላይ የተደረደረው ምግብ፣ እንኳን ቢበሉት እያነሱ ቢደፉት የሚያልቅ አይመስልም፡፡ ከጠረጴዛዎቹ እለፍ ብሎ በቀይ የፕላስቲክ ሳጥን በብዙ መደዳ ቢራ ተከምሯል ..

ጋሽ ዝናቡ እዲስ ጥቁር ሙሉ ልብስ ለብሶና፣ ጥቁር የቴክሳስ ባርኔጣውን አናቱ ላይ ደፍቶ፤ በእንግዶቹ መሀል እየዞረ፣ ብሉልኝ ጠቱልኝ ይላል፡፡ ማሚ በበኩሏ እንደዛን ቀን አምራ አይቻት አላውቅም ከወትሮው ረዘም ያለ ሹል ተረከዝ ያለው ደማቅ ቀይ ጫማ
ለረዥም ቅዱ ጉልበቷ ድረስ የሚዘልቅ ቀይ ቀሚስ ለብሳ በተጋባዥ መካከል
ትውረገረጋለች፡፡ ሰርግ ነበር የሚመስለው::ሳሌም ከኋላዋ ማሰሪያ ያላት ነጭ ቀሚስ ለብሳ እንደ ትንሽ ነጭ ቢራቢሮ በሰው መሀል እየተሸሎከለከች መሐሪ በሄደበት ትከተለዋለች፡፡ ማረፊያዋም መነሻዋም መሐሪ ነው፡፡ ሮሐ ታዲያ ዛሬ እንኳን ብትፋታው ምናለበት” ትላለች፡፡

ከሳምንት በፊት መሐሪ ማሚን “ይኼ ነገር ግን አልሰፋም” ብሏት ነበር፡፡ ለድግሱ ስትሯሯጥ፤ “ዝም በል ወደዛ! ይኼን የፈዘዘ ግቢ ምን ምክንያት አግኝቼ ባጫጫስኩበት ስል ነው የኖርኩት፣ ገና ስትዳሩ " ብላ የሁለታችንንም ትከሻ ቸብ አደረገችና ሂሂሂ እያለች ወደ ሥራዋ ተመለሰች፡፡ እንዳለችውም ከማጫጫስ አልፎ በምግብና በመጠጥ፣በዘፈንና በዳንስ ግቢው አበደ፡፡ በዚያ ምሽት የእኔና መሐሪ ስም እየተነሳ ጀብዷችን ሲወሳ አመሸ፡፡ ዕድሜ ከተጫጫናቸው የፊደል አስተማሪያችን ከመምሬ
ምስሉ ጀምሮ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል መምህራኖቻችን ድረስ “የቀለም ብልቃጥነታችንና ያነገይቱ ኢትዮጵያ በተስፋ የምትጠብቀን ወጣቶች መሆናችንን መሰከሩ፡፡ እንኳን እኛ
አጉል ወጣቶች፣ ዓለም ለምኔ ብሎ ለነፍሱ ያደረ ሰው እንኳን ቢሆን፣ በእንደዚህ ዓይነት አጋጣሚ ህዝብ ፊት ሲሞካሽና ሲደነቅ ሁለት ጭልፋ ኩራት፣ አንድ የሾርባ ማንኪያ መታበይና፣ ግማሽ የሻይ ማንኪያ ትዕቢት የተቀላቀለበት ፅንስ ልቡ ውስጥ መፈጠሩ አይቀርም፡፡ ደረቴ ሲነፋፋ ይሰማኝ ነበር፡፡ እንዲያው ድንገት ትን ብሎኝ ብሞት፣ አገሪቱ
አብራኝ ድፍት ብላ የምትቀር፣ ከኔ ሌላ ሰው የሌላት መሰለኝ፡፡
ይባስ ብሎ በዚህ ስሜት ላይ ጋሽ ዝናቡ ሁለት የቢራ ጠርሙዞች ይዞ ወደኔና መሐሪ መጣና ደሽ ደሽ እያደረገ ከፍቶ ለዛሬ ብቻ ዋ!” ብሎ ከማስጠንቀቂያ ጋር ሰጥቶን እየሳቀ ሄደ፡፡ እኔም መሐሪም ከዚያ በፊት አልኮል ቀምሰን አናውቅም፡፡ የመጀመሪያችን ነበር፡፡
ሮሐ ጋሽ ዝናቡ ገና ከመሄዱ እንደመደነስ እያደረጋት መጣችና ሄይ ዐይኔ ነው ወይስ ጋሽ ዝናቡ ቢራ ሰጣችሁ” አለችን፡፡ ሁለታችንም ጠርሙዛችንን ከፍ አድርገን ችርስ አልናት፡፡ ፍልቅልቅ እያለች ጠብቁኝ አለችና፣ በሰው መካከል እየተሽለኮለከች ሂዳ ወዲያው ተመለሰች፡፡ ከላይ የምትደርበውን ጃኬት በእጇ ይዛ ነበር፡፡ አጠገባችን ደርሳ ለልጥ ስታደርገው ግን፣ አንድ ጠርሙዝ ውስኪ ነበር “ጋሼ እንዳያየን ደብቄውኮ ነው፣ እንቀምቅመው በቃ” ብላ ሳቀች

“ኖ” አለ መሐሪ
እታካብድ ባክህ …” ብላ ዞር እያለች ጋሽ ዝናቡን እየተመለከተች ጠርሙሱን አፏ ላይ ለግታ ትንሽ ተጎነጨችና ለመሐሪ አቀበለችው፡፡ ዞር ብሎ ተመለከተኝ፡፡ ፈገግ አልኩ፡፡ ተቀበላትና ቀመስ አድርጎ ፊቱን አጨፈገገ፡፡ እኔም ወጉ አይቅርብኝ ብዬ ከቢራው ልጠጣ ብሞክርም፣ ሽታውና ምሬቱ አንዳች የማቅለሽለሽ ስሜት ስለፈጠረብኝ፣ ቀስ አድርጌ
ጠረጴዛው ሥር ጣልኩትና፣ ውስኪውን እንዴ ተጎነጨሁለት፡፡ ልክ እንደ እሳት ነበር
ጉሮሮየን እያንገበገበኝ የወረደው፡፡

ሮሐ ቀስ እያላችሁ ጠጡ ልጆች፤ እኔ ልደንስ ነው” ብላን ጠርሙዙን ትታልን ግርግሩ ውስጥ ገባች፡፡ እኔ ውስኪውም ስራውም ይቅርብኝ ብዬ ግርግሩን ስመለከት አመሸሁ፡፡
መሐሪ ግን ምሸቱን በሙሉ ጋሽ ዝናቡን በዓይኑ እየተከታተለ ዞር ሲልለት፣ ከጠረጴዛው ስር የደበቀውን ውስኪ፣ ሲፈልግ ቢራውን እያነሳ ሲለጋው አመሸ፡፡ ብዙ ሳይቆይ አፉን ያዝ ያደርገው እና ሳቅ ሳቅ ይለው ጀመረ፡፡ በመጨረሻ ተደብቆ ሲጠጣ የነበረው ልጅ፣ የውስኪ ጠርሙዙን ከፍ አድርጎ ይዞ እየተንገዳገደ እንደ መደነስም፣ እንደ መዝፈንም ይቃጣው ጀመር፡፡ ልቀማው ስሞክር
ገፈተረኝና “ሥርዓት” ብሎ አስጠነቀቀኝ፡፡ ልክ ዕድሜ ልኩን ሲጠጣ የኖረ ሰካራም ነበር የሚመስለው፡፡ መጀመሪያ እስቆኝ ነበር፡፡ በኋላ ግን በራሱ ድግስ ቀጥ ብሎ ሄዶ ሄኖክ የሚባል በዚያ ክፉ ዘመን ሮሐ ጋር እንዲዝናኑ የኪራይ ቤቱን ቁልፍ ሲሰጠው የኖረውን
የክፉ ጊዜ ወዳጃችንን ካልደበደብኩ ብሎ ሲጋበዝ፣ ነገሩ መምረሩ ገባኝ፡፡ ምክንያቱ
ደግሞ፣ ሮሐ ጋር ለምን ደነሱ? ብሎ ነበር:: ሮሐ ፊቷ ተቀያየረ መሐሪን ጎትታ ወስዳ ጠርሙሱን ቀማችና ባለጌ ነህ!” አለችው፡፡

“ባለጌ? ኦ የኛ ጨዋ ! ብትፈልጊ አብረሽው ሂጅ የሀብታም ልጅ እና የሀብታም ልጅ በቆይታቸው ሲጀመር እንደዚህ ለብሰሽ የመጣሽው እሱን አትራክት ለማድረግ ነው? አይ
ኖ በራሴ ቤት እፊቴ ግን ኔቨር…” መሐሪ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሌላ ሰውነት ተቀየረ ፡፡ ወደማላውቀው መሐሪ፡፡ ሮሐ በለበሰችው አጭር ቀሚስ ረዣዥም ውብ እግሮቿ እንደ ብርሃን ዓምድ ሲያበሩ ነው ያመሹት፡፡ ከኋላ በግማሽ ክፍት የሆነ ቀሚሷ ጥርት ያለ ሰውነቷንና የቀኝ ትከሻዋን አጋልጦ ብርሃን ባረፈባት ቁጥር፣ ቀይ ሰውነቷ ያንፀባርቅ ነበር ፡፡ እንኳን የሩቁ ሰው እኔ ራሴ ዓይኔን ከሷ ላይ መንቀል እስኪከብደኝ አምሮባት ነበር፡፡

ገና ስትገባ እኛ ሞዴል አልጠራንም” ብዬ አዳንቂያት ነበር!

ልክ መድረክ ላይ እንደቆመች፣ ሞዴል ወገቧን ይዛ ዞር ዞር እያለች ልብሷን እያሳየችኝ “ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ …ሂሂሂ" ማሚና ሮሐ የምሽቱ ድምቀቶች ነበሩ፡፡ ታዳሚው ዓይን ያውጣችሁ" እስከሚል፡፡ መሐሪ ድርጊቱ ስላስደነገጠኝ፣ ይዥው ልገባ ስሞክር እጄን ነጥቆኝ በንቀት ከእግር እስከራሴ እየተመለከተኝ “ምንድነህ አንተ የእኔ ሞግዚት ነህ ወይስ የሷ ደላላ?…”

“ይኼ ብልግና ነው ሥርዓት ያዝ!”

“ምንድነው ብልግና ብልግና የምትሉት? ቆይ ቆይ! አንተ እኔን ባለጌ የምትለኝ አንተ ማን ሁነህ ነው? ያ ሙስኛ አባቷ ስንት ከፈለህ? ከእኔ ለያት ብሎ … እ? እንዲያውም ስንት ዓመት ስደበቅ የኖርኩት ምን ስለሆነ ነው?…ሂድ ንገረው! ደግሞ ተጠርቶ ያልመጣው ማን አባቱ ስለሆነ ነው ?…የሱ አሮጌ ሆቴል እና አሮጌ ነዳጅ ማደያና …አሮጌ መኪናና
አሮጌ ምናምን የሚገርመኝ መሰለው እንዴ? መሐሪ ነኝ መሐሪ ዝናቡ አውላቸው .. ሐሳቡን ሳይጨርስ ወደ ሮሐ ዞሮ…

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
#እንዳትገረሚ

ሊሆኑ ማይችሉ ፥ ግን ደሞ የሆኑ
ለማመን ሚከብዱ ፥ ግን የሚታመኑ
ታሪኮች አሉና
“አፈቀርኩሽ ስልሽ ፥ እንዳትገረሚ
ታአምር የሚመስል ፥ ታሪክ ላውጋሽ፣ ስሚ።

የቀደሙ እናቶች ፥ በስራ ተጠምደው
በምድር ያለን ጥጥ ፥ ጠቅላላ አገባደው
ሰማይ ባዶ እስኪቀር ፥ ደመናን ሲፈትሉ
የሚዘንብ ጠፍቶ
በጋራ ደረቀ ፥ ሳር ቅጠል እህሉ።
እናም በዚህ ጊዜ
አንድ የተራበ አባት
ለሚስቱ እንዲህ ሲል ፥ ቅኔ ተቀኘ አሉ።
“ምትበዪው ሳይኖርሽ ፥ አምሮሽ መከናነብ
ደመናን ፈትለሽው
ከለበሽው ኋላ ፥ ዝናብ ከየት ይዝነብ?!
ሆዴስ እንዴት ይጥገብ
ልብሽና ልቤስ ፥ በምን ይቀራረብ?
ሆዴ እየተራበ ፥ ልቤ እንዴት ይሙላ
ለብሶም አያጌጥም
ሆድ እየበረደው ፥ አይሞቀውም ገላ።”
ይህንን ስትሰሚ..
ከቆየች ሚስቱ ፥ ቅኔ ተፈጠረ
እንዲህ ትል ጀመረ
“ሁሉን ቢናገሩት ፥ ሆድ ባዶ ይቀራል
ደመና ቢጠፋ
ጠቢብ ሰው ከ'ሳት ጢስ ፥ ደመናን ይፈጥራል።
ልብህን ከልቤ
ለፈተለው ጠቢብ ፥ አይገኝም ወደር
ለሆድ ልብ አልሰጥም
እንጀራ ይሆናል ፥ ልብስ ሽጦ ማደር።
ፍቅርን የለበሰ
ሆዱን አይበርደውም ፥ ረቂቅ ነው ማፍቀር።”
••••
ሊሆኑ ማይችሉ ፥ ግን ደሞ የሆኑ
ለማመን ሚከብዱ ፥ ግን የሚታመኑ
ታሪኮች አሉና
“አፈቀርኩሽ” ስልሽ ፥ ፈፅሞ እንዳይደንቅሽ
ይልቅ ልብ ስጪኝ
በልብሽ አድምጪኝ
ታ'ምር የሚመስል ፥ ታሪክ ላሳውቅሽ ።
የዛሬ ብዙ ዓመት
አንድ ታላቅ ነብይ
እናትም ድንግልም
ስለምትሆን ሴት ፥ ሲናገር ትንቢቱን
ህዝቡ ባለማመን
አዞሮበት ልቡን ፥ ፊት ነስተውት ፊቱን
“ከመች ጀምሮ ነው
እናት የሆነች ሴት ፥ ድንግል የምትሆነው
እንዲህ ያለን ነገር
ስሙኝ ብሎ መጮህ ፥ ምን ይሉት ንቀት ነው?
እያሉ ሲንቁት !
ለናቁት ልቦች ልብስ ፥ ክብርን ሸመነ
ቀድሞ ያውቃል ነብይ
አለማመን ራሱ ፥ ማመን እንደሆነ።

ለማመን ሚከብዱ ፥ግን የሚታመኑ
ሊሆኑ ማይችሉ ፥ ግን ደግሞ የሆኑ
ክስተቶች አሉና
እንዳትገረሚ !
ተአምር የሚመስል ፥ ታሪኬን ስነግርሽ
በቃ እወድሻለሁ ፥ ለጉድ ነው ሳፈቅር!!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም

....ደግሞ ተጠርቶ ያልመጣው ማን አባቱ ስለሆነ ነው ?…የሱ አሮጌ ሆቴል እና አሮጌ ነዳጅ ማደያና …አሮጌ መኪናና
አሮጌ ምናምን የሚገርመኝ መሰለው እንዴ? መሐሪ ነኝ መሐሪ ዝናቡ አውላቸው .. ሐሳቡን ሳይጨርስ ወደ ሮሐ ዞሮ…
እንዲህ ለብሰሽ…ምን ለብሰሽ ተራቁተሸ የመጣሽው ሳይጨርሰው ጋሽ ዝናቡ ከየት እንደመጣ ሳላየው ድንገት ደርሶ የመሐሪን ክንድ አፈፍ እደረገውና ግማሽ መግፋት በተቀላቀለበት ማባበል ወደ ቤት ሊወስደው ሲሞክር ጭራሽ ወደ ጋሽ ዝናቡም ዙሮ፣

ጋሼ ቆይ አትግፉኝ፡ አሁን ሕፃን ልጅ አይደለሁም፤ የዚችን አባት ጠርተኸዋል አይደል? ማንን መናቁ ነው ያልመጣው እኛ የታሰረው በራሱ ጥፋት እንጅ ጋሼ መሐሪን እየገፋ ወደ ቤት ወሰደው፡፡ ሳሌም ተጨንቃ ከኋላ ከኋላቸው የመሐሪን ቲሸርት ይዛ ተከትላቸው ገባች ፡

ሮሐ ግራ በመጋባት ትንሽ ቆማ ሲገቡ አየቻቸውና ድንገት ፊቷን አዙራ ወደ ግቢው በር በቁጣ አመራች፡፡ የውስኪውን ጠርሙስ ግቢው ጥግ ችፍርግ ብለው ወደበቀሉት አበቦች ወርውራ፣ ከሩጫ በማይተናነስ እርምጃ ወደ ውጭ ስትገሰግስ ተከትያት ሮጥኩ፡፡
“ሮሐ! ትንሽ ጠጥቷል የሚናገረውን አያውቅም”

“እም ፋይን!” ዝም ብዬ ከጎኗ መራመድ ቀጤልኩ፡፡ ከግቢው እንደወጣን ኮረኮንቹ
አላራምዳት ስላለ፣ ጫማዋን አውልቃ በእጇ አንጠለጠለችውና በባዶ እግሯ መንገድ ጀመረች፡፡ ስትራመድ ትንሽ ትንገዳገድ ነበር፡፡ ብዙ ጠጥታለች፡፡ የተቀባችው ሽቶና ከሰውነቷ ላይ የሚተነው የአልኮል ሽታ ያፍናል፡፡ ምን እንደምላት ግራ እንደገባኝ ከንዷን
ያዝ አድርጌ አስቆምኳት፡፡ እንባዋ ተዘረገፈ !

“ስቱፒድ ነገር ነው!”

እሺ! ነገ ሁሉንም ነገር እንነጋገራለን፣ መንገዱ በጠርሙዝ ስብርባሪና በምናምን የተሞላ ነው፣ አሁን ከቤት የሆነ ጫማ ላምጣልሽ ፕሊስ”
አሁን ገና ያየችው ይመስል ወደ ባዶ
እግሯ አቀርቅራ ተመለከተች፣ የእግሮቿን ጣቶች አንቀሳቀሰቻቸው፡፡ አቧራማው ኮረኮንች ላይ አርፈው ግቢው አጥር ላይ በተተከለው ቀይ መብራት የደመቁት ውብ እግሮቿ፣ ደማቅ ቀይ የጥፍር ቀለም ከተቀቡ ረዥም ጣቶቿ ጋር፣ በብዙ ጭንቀት የተነሳ የሆነ የጥፍር ቀለም ማስታውቂያ ውብ ፎቶ እንጂ
ሕያው እግር አይመስሉም ነበር፡፡
ሳሎን ሶፋው ሥር ፍላት ጫማ አስቀምጨረ ነበር፡፡ ካላስቸገርኩህ አቀብለኝ?” አለችኝ፡፡
የቆመችበት ትቻት ወደ ግቢ ሮጥኩና ጫማውን ይዠ ስመለስ፣ ልክ የተተከለች ይመስል ሳትንቀሳቀስ እዛው ጋ ቁማ አገኘኋት፡፡ ጫማውን ለማድረግ አንድ እግሯን ስታነሳ፣ ክፉኛ ተንገዳገደች፡፡ በርከክ ብዬ በእጄ ትከሻዬን ተደግፋ የአንድ እግር ጫማዋን እንዳጠለኵላት፣ ሳቅ ስምቼ ዞርኩ፡፡ መሐሪ ነበር ከኋላው ሳሌም ተከትለዋለች፡፡

በማላጋጥ አጨበጨበ እና፣ ወገቡን በሁለት እጁ ይዞ ቁሞ፣ ባለጌ ጓደኛህ በደንብ ብልግናው እንዲጎላ እስከ መንበርከከ የሚደርስ ጨዋነት እያሳየህ ነው ….? ጥሩ ነው ምድረ ኢዲየት!' ሂድ እቤቷ አዝለህ አድርሳት! አባቷ ለሚድራት ሀብታም አዝለህ አድርስለት… አቃጣሪ” ብሎኝ ጀርባውን አዙሮ ወደግቢው ተመለሰ፡፡ ሳሌም ተከትላው ከሥር ከሥሩ ትሮጣለች፡፡

ለምን እንደሆነ ባይገባኝም፣ እስካሁን ያልተነቀለ ቅሬታ በዚያች ቅጽበት ልቤን ወግቶኝ ቀረ፡፡ ስካር ቀድሞ ውስጣችን የሌለ ነገር ይፈጥራል ወይ? ወይንስ ያለውን ነው የሚያጎላው? እያልኩ እብሰለሰላለሁ፡፡ ስካሩም ሳይሆን ይኼ የሴትና የወንድ ጉዳይም ሳይሆን፣ መሐሪ ድምፅ ውስጥ የሰማሁት ንቀት አመመኝ፡፡ ጨለማ ውስጥ አጭር ቀሚስ
የለበሰች ፍቅረኛው እግር ሥር ተንበርክኬ ጫማ ማጥለቄ በሄኖክ እንደቀናው
አላስቀናውም፡፡ (አውቀዋለሁ ሙሉ ዘመናችንን ጓደኞች ነን) እንደወንድ አይደለም ያየኝ እንደ አሽከር ነው እንደ አሽከር አይደለም… እንደ አቃጣሪና በመሃላቸው ክፍተት ለመፍጠር እንደምሞክር እኩይ ገፀባህሪ ዓይነት ነው ያየኝ፡፡ ለሆነ ሰው ሮሐን አዝዬ
አድራሽ፤ ድምፁ ውስጥ አንዳች ቦታዬን ደረጃዬን የሚጠቁም ትዕቢተኛ ቃና ነበር
ጓደኛ አልነበርንም!! ለሚያነክስ ሰው ምርኩዝ አብሮት ዘላለም ቢቆይ ጓደኛው ሆነ ማለት አይደለም፡፡ በመሐሪ የተጎዳ ሥነ ልቦናውን እደግፍ ዘንድ፣ ምርኩዙ ሆኜ የኖርኩ ሰው ነበርኩ፡፡ ፍቅረኛው ግኡዝ ምርኩዙን ነው ተደግፋ ያገኛት፤ ሰክሮ ነው ብዬ ማድበስበስ እልቻልኩም፡፡

ሁለቱም አስጠሉኝ፡፡ ሮሐም መሐሪም መሀል መንገድ ላይ ጥያት መመለስ ግን
አልፈለኩም፡፡ ሁልጊዜ የምንሸኝባት ቦታ ግዙፉ ባለ ሁለት ፎቅ ቤታቸው ፊት ለፊት
ያለች አሳቻ ጨለማ ድረስ ሸኝቻት ልመለስ ስል፣ ክንዴን ይዛ ወደ ራሷ
ሳበችኝና፣ አቅፋ ጉንጨን ሳመችኝ! አሳሳሟ ድምፅ፣ ሙቀትና ኃይል ያለው ነበር፡፡ ልክ ማኅተም ወረቀት ላይ እንደሚመታው ዓይነት ነበር ከንፈሮቿ ከጉንጬ ጋር የተጋጩት፡፡ ምናልባት
ስለሰከረች ሚዛኗን መጠበቅ አቅቷትም እንደሆን እንጃ፡፡ ስመለስ ወደነመሐሪ ቤት
አልገባሁም …ጭፈራና ጩኸት ከውስጥ ይሰማል፡፡ እንደዋልኩበት ቤት ሳይሆን ልክ እንደማላውቀው ምንድነው እዚህ ግቢ ውስጥ ዛሬ ያለው? ብሎ እንደሚያልፍ መንገደኛ አልፌ ወደ ቤቴ ሄድኩ፡፡ ገና ትላንት መሐሪ እዚሁ ነው የምታድረው፣ እቤት ንገራቸው ብሎኝ ስለነበር እንደማድር ለእናቴ ነግሪያት ነበር፡፡

በነገራችን ላይ ስደርስ፣ ቆሜ ወደ ሰማይ አንጋጠጥኩ፡፡ ሰማዩ የዘመናት ጥላሸት ተሸክሞ እንደ ረገበ አሮጌ የማዳበሪያ ኮርኒስ የተቆዘረ ዥንጉርጉር ሆዱን አንጠልጥሎታል! አልፎ አልፎ ከሚያስተጋባው ጉርምርምታ ጋር ተዳምሮ አንዳች እንግዳ ፍጡር ሊወልድ
የሚያምጥ ነፍሰጡር ፍጥረት ይመስል ነበር! “አህያ የማይችለው ዝናብ መጣ ይላሉ በመንገዱ ከሚያልፉ ሰዎች መሃል አንዲት አሮጊት፣ ጨለማው ከባድ ስለነበር
ከቆምኩበት ሁኜ ሰዎቹ የለበሱት ነጠላ በድንግዝግዙ ሲንቀሳቀስ እንጂ መልካቸውን ማየት አልችልም ነበር፡፡ እንደገና ወደ ሰማይ ፊቴን አንጋጠጥኩ፡፡ ደመናው በሆነ ሹል ነገር ወጋ ቢያደርጉት፣ ውሃ ሳይሆን ጥላሸት የሚያዘንብ ነበር የሚመስለው !
ወደ ቤት ገባሁ፡፡ እናቴ ለአባባ ስለ ድግሱ ድምቀት እያወራችለት ነበር፡፡ እግሩን ክፉኛ ስለታመመ አልሄደም፡፡ ከፊቱ ማሚ ቋጥራ የላከችለት የድግስ ምግብ ከትልቅ ጎድጓዳ ሰሃን ላይ ተቀንሶ ቀርቦለት አልጋው ላይ ደገፍ እንዳለ ይበላል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ድህነት የሚባለው ነገር እንደሳትራት በቤታችን ፈዛዛ አምፖል ዙሪያ ሲበርና ትርኪምርኪው የቤት
እቃ ላይ ሲያርፍ ታየኝ፡፡ ልክ ያጠለቁበትን ጥቁር ጭንብል የማያውቀው ቦታ ወስደው ድንገትም እንዳነሱለት ሰው ነበር የቤታችንን ዙሪያ የቃኘሁት፡፡ እንዳላደግሁለት፣ ዛሬ ገና እንዳየሁት ዓይነት፡፡ እናቴ ታዲያ እንዲህ አለችኝ፣
“ውይ መጣህ እንዴ የምታድር መስሎኝ ደሞ ጉንጭህ ላይ የምን ቀለም ነው?” በመዳፌ ጠረኩት …የሮሐ ሊፕስቲክ ነበር፡፡ ወደ መኝታዬ አልፌ ከነልብሴ አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ዘፍ አልኩና፣ ተንጋልዬ ተኛሁ፡፡ ከሁለቱ ክፍሎች የውስጠኛዋ ላይ የተዘረጋች የሽቦ
አልጋ ናት መኝታዬ፡፡ በሁለቱ ክፍሎች መግቢያ በር ላይ አንዲት ያደፈች የጨርቅ
መጋረጃ ተሰቅላለች፡፡ ዙሪያ ግርግዳው ላይ መጥበሻው፣ ድስቱ፣ የበረት ምጣዱ፣
ሰፌዱ፣ ወደ አንድ ጥግ የተቀመጠ የእንጀራ ሞሰብ፣ ግድግዳው ጋር ተጣብቆ በተሰራው የጣውላ መደርደሪያ ላይ ስኒዎት፣ ጀበና፣ ብርጭቆ ተደርድሯል፡፡ እዚያ ፊት ለፊት
ደግሞ የአባቴ የአናጺነት እቃዎች የታጨቁበት ትልቅ የቆዳ ከረጢት፡፡ እና እዚህ ሁሉ መሀል እኔ …! እኔ ውስጥ አልቅስ አልቅስ የሚል፣ እንደቀመስኩት ቢራ የሚጎመዝዝ ስሜት!!
👍1