አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
586 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እንዳትገረሚ

ሊሆኑ ማይችሉ ፥ ግን ደሞ የሆኑ
ለማመን ሚከብዱ ፥ ግን የሚታመኑ
ታሪኮች አሉና
“አፈቀርኩሽ ስልሽ ፥ እንዳትገረሚ
ታአምር የሚመስል ፥ ታሪክ ላውጋሽ፣ ስሚ።

የቀደሙ እናቶች ፥ በስራ ተጠምደው
በምድር ያለን ጥጥ ፥ ጠቅላላ አገባደው
ሰማይ ባዶ እስኪቀር ፥ ደመናን ሲፈትሉ
የሚዘንብ ጠፍቶ
በጋራ ደረቀ ፥ ሳር ቅጠል እህሉ።
እናም በዚህ ጊዜ
አንድ የተራበ አባት
ለሚስቱ እንዲህ ሲል ፥ ቅኔ ተቀኘ አሉ።
“ምትበዪው ሳይኖርሽ ፥ አምሮሽ መከናነብ
ደመናን ፈትለሽው
ከለበሽው ኋላ ፥ ዝናብ ከየት ይዝነብ?!
ሆዴስ እንዴት ይጥገብ
ልብሽና ልቤስ ፥ በምን ይቀራረብ?
ሆዴ እየተራበ ፥ ልቤ እንዴት ይሙላ
ለብሶም አያጌጥም
ሆድ እየበረደው ፥ አይሞቀውም ገላ።”
ይህንን ስትሰሚ..
ከቆየች ሚስቱ ፥ ቅኔ ተፈጠረ
እንዲህ ትል ጀመረ
“ሁሉን ቢናገሩት ፥ ሆድ ባዶ ይቀራል
ደመና ቢጠፋ
ጠቢብ ሰው ከ'ሳት ጢስ ፥ ደመናን ይፈጥራል።
ልብህን ከልቤ
ለፈተለው ጠቢብ ፥ አይገኝም ወደር
ለሆድ ልብ አልሰጥም
እንጀራ ይሆናል ፥ ልብስ ሽጦ ማደር።
ፍቅርን የለበሰ
ሆዱን አይበርደውም ፥ ረቂቅ ነው ማፍቀር።”
••••
ሊሆኑ ማይችሉ ፥ ግን ደሞ የሆኑ
ለማመን ሚከብዱ ፥ ግን የሚታመኑ
ታሪኮች አሉና
“አፈቀርኩሽ” ስልሽ ፥ ፈፅሞ እንዳይደንቅሽ
ይልቅ ልብ ስጪኝ
በልብሽ አድምጪኝ
ታ'ምር የሚመስል ፥ ታሪክ ላሳውቅሽ ።
የዛሬ ብዙ ዓመት
አንድ ታላቅ ነብይ
እናትም ድንግልም
ስለምትሆን ሴት ፥ ሲናገር ትንቢቱን
ህዝቡ ባለማመን
አዞሮበት ልቡን ፥ ፊት ነስተውት ፊቱን
“ከመች ጀምሮ ነው
እናት የሆነች ሴት ፥ ድንግል የምትሆነው
እንዲህ ያለን ነገር
ስሙኝ ብሎ መጮህ ፥ ምን ይሉት ንቀት ነው?
እያሉ ሲንቁት !
ለናቁት ልቦች ልብስ ፥ ክብርን ሸመነ
ቀድሞ ያውቃል ነብይ
አለማመን ራሱ ፥ ማመን እንደሆነ።

ለማመን ሚከብዱ ፥ግን የሚታመኑ
ሊሆኑ ማይችሉ ፥ ግን ደግሞ የሆኑ
ክስተቶች አሉና
እንዳትገረሚ !
ተአምር የሚመስል ፥ ታሪኬን ስነግርሽ
በቃ እወድሻለሁ ፥ ለጉድ ነው ሳፈቅር!!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘