ብሽቅ! መሐሪ ብሽቅ ነው!!
ከሰውነቴ ላይ የሽቶ፣ የመጠጥና የድግስ ወጥ ጠረን እየተነነ ራሴን ያፍነኛል፡፡ ስቀላውጥ የዋልኩ መሰለኝ፡፡ ወጡ የሰው መጠጡ የሰው ሽቶው የሰው ከጠረን አቅም የራሴ ጠረን እንኳን አልነበረኝም … ይኼ እንግዳ ጠረን የብርድልብሴን የዘወትር ሽታ ሳይቀር፣ገፍቶ ተንሰራፍቶ አብሮኝ ተኝቷል፡፡ ቀስ በቀስ የወጡና የመጠጡ ጠረን እየቀነሰ የሽቶው
ጠረን እየገነነ መጣ፡፡ የሮሐ ሽቶ በእንቅልፍ ከመውደቁ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ እንደሰመመን የታየኝ የሮሃ ውብ እግሮች ነበሩ፡፡ ከነደማቅ ቀይ ጥፍር ቀለማቸው አቧራ መንገድ ላይ እያበሩ፡፡ አንዳንዱ እግር ክንፍ ይመስላል ሲራመድ ሳይሆን ሲበር የኖረ ንጹሕና ለስላሳ፡፡
፡፡፡
ከሩቅ የሚመጣ የአንዲት ሴት እሪታ ነበር ከእንቅልፌ ያነቃኝ፡፡ እንደ ሰመመን ከሩቅ
በተደጋጋሚ ብሰማውም፣ ችላ ብዬ ለመተኛት ሞከርኩ፡፡ እንደሁልጊዜው ዋናው መንገድ ላይ ካሉ መሸታ ቤቶች የመጣ ድምፅ ነበር የመሰለኝ፡፡ በተለይ ቅዳሜ ቅዳሜ ከእነዚያ በሚቀፉ ቀያይ መብራቶች የተጥለቀለቁ ቡና ቤቶች የሰፈራችንን ጨለማ እየሰነጠቀ የሚመጣ የሰካራምና የሴተኛ አዳሪዎች የጨኸትና እሪታ ድምፅ የተለመደ ነበር ፡፡
እሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪረረ…” የዛሬዋ ግን እሪታዋ ማቆሚያ አልነበረውም፡፡ ድምፁ ከፍ ብሎ ይጀምርና፣ እየቀነሰ እየቀነሰ ሂዶ ይጠፋል፡፡ በመሀል ትንሽ ዝም ትልና፣
ከመጀመሪያውም በጠነከረ ድምፅ ትቀጥላለች፡፡ እሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪ …” እንዲያውም ቀስ በቀስ የሌሎች ሴቶች እሪታና በበራችን የሚሮጥ የብዙ ሰው ኮቴ ድምፅ ተከተለ።
የኮቲያቸው ብዛትና ጥንካሬ ፈረስ እየጋለቡ የሚያልፉ ነበር የሚመስሉት፡፡ የሚሮጡት ሰዎች ሩጫ ለሚያርገበግበው ድምፅ እላይ ሰፈር ነው እያሉ ይንጫጫሉ፡፡ ጩኸቱ እየተባባስ እና እየጨመረ ሲመጣ፣ ብርድ ልብሴን ከላዬ ላይ ገፍፌ ተነሳሁ፡፡ ለመቆም
ስምክር ስለዞረብኝ፣ ትንሽ እሰክረጋጋ አልጋ ጫፍ ላይ ተቀምጨ ጩኸቱን ማዳመጥ ቀጠልኩ...
እሳት ይሆን እንዴ ትላለች እናቴ፡፡ ተነስቼ ከጓዳዬ ስወጣ እናቴ በቁጣ፣ አርፈህ
ተቀመጥ! ምን እንደሆነ ሳታውቅ ዘለህ መውጣት ምን ይሉታል! “ ብላ አንባረቀችብኝ፡፡ በዚሁ ቅጽበት የበራችን በር ተንኳኩቶ አንድ የሰፈር ልጅ ጥድፍ ባለ ድምፅ፣ አብርሽ እነ መሐሪ ቤት ነው የሚጮኸው? ብሎኝ ተፈተለከ፡፡ በሩን ከፍቼ በጨለማ እየተደነቃቀፍኩ ሽቅብ ሮጥኩ፡፡ እየሮጥኩ አእምሮዬ ውስጥ ቁጥር ስፍር የሌለው መላምት እየቀያየርኩ አስባለሁ፡፡
ቀን ለድግስ ተለኩሶ የተረሳ እሳት ሴቱን አነደደው፡፡
ጋሽ ዝናቡ ማሚን አንድ ነገር አደረጋት?
መሐሪ ጠጥቶ የማያውቀውን መጠጥ ጠትቶ ታመመ ?
ግቢ ውስጥ የተተወ ዕቃ ሊሰርቅ ዘሉ የገባ ሌባ እጅ ከፍንጅ ተያዘ?
በድካም እያለከለኩ ስደርስ፣ የግቢው በር በሰው ጎርፍ ተጥለቅልቋል ሁሉም በየአፉ
ያወራል፡ እንዳንዱ እየጮኸ ይራገማል ማንን እንደሚረግም አልገባኝም፡፡ እናቶች
ደረታቸውን እየደቁ ያለቅሳሉ፡፡ በሩ ላይ ዩኒፎርም የለበሱና መሣሪያ የታጠቁ ሦስት ፖሊሶች ከምኔው እንደ ደረሱ እንጃ፡ ወሬ ሊመለከት የከበበውን ሕዝብ ወደ ኋላ እንዲመለስ በጩኸት ያዝዛሉ “ወደ ኋላ ተመለሱ ወደ ኋላ ብያለሁ" ወደ ግቢው ልገባ ስንደረደር አንዱ ፖሊስ ክንዴን አፈፍ አድርጎ ይዞ ገፈተረኝ ተመለስ ማለት አማርኛ አይደለም፤? ብሎ አምባረቀብኝ፡፡ ወደ ኋላዬ ስገዳገድ የሆነ ሰው ደግፎ ከመውደቅ አተረፈኝ ዞር ብዬ አየሁት ጋሽ አዳሙ የሚባል ታዋቂ የሰፈራችን ሰካራም ነው፡፡ ሁልጊዜ እየጮኸ ወደታች ሲፈር የሚያልፍ፡፡ ከዚያ ሁሉ ሰው እሱ ነው እንግዲህ ደግፎ ያቆመኝ፡፡ ቀን ሲጥል፡፡
ከግቢው ውስጥ የጥድቄ ለቅሶ የቀላቀለ ጩኸት ይሰማል፡፡ የሆኑ ወንዶች የጎረነነና
የተጣደፈ ድምፅም ይሰማል፤ የሚያወሩት ግን አይሰማም ነበር፡፡ ወዲያው አንዲት....
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ

👍1
#ነፃነት? ወይስ #ባርነት?
በልበቅንነት በጉ ዓላማ ይዞ
በፍኖተ እውነት በዕውቀት ታግዞ
በልዩነት አምኖ በአንድነት ታንጾ
በሥልጡን አመራር የሰውልጅ አምጾ
መስዋትነት ከፍሎ ካልቆመ ለአርነት
ይበልጥ ይጋለጣል ለከፋ ባርነት
ለአደጋ ይዳረጋል የማሰብ ነፃነት፡፡
የመፃፍ ነፃነት። የመኖር ነፃነት።
ለሰው ልጀ ተጠቃሽ የሚሆን አብነት
ኧረ ለመሆኑ ምንድ ነው ነፃነት?
ማሳያ መስታውት ባላንጣን አቅሎ
ጭቆናን ተጋፍጦ ባርነትን ታግሎ
የገዛ ሕይወተን መስዋትነት ከፍሎ
ነፃነት መሞት ነው ለነፃነት ብሎ።
ክፋትን ማሳያ ለሰው ልጅ አብነት
አረ ለመሆኑ ምንድ ነው ባርነትን
በሕግ ማይፈቀድ ሚያስቀጣ ወንጀል
በሐይማኖት መንገድ ኃጢአት ወይም በደል
ሕሊናን ወርውሮ
ስርቻ ውስጥ መጣል ሆድ ለሚባል ገደል
ንፁህ ደምን ማፍሰስ ባርነት ነው መግደል።
ባርነት? ወይስ ነፃነት?
ባርነት
ፍፁም የማይቻል ሥቃዩና ሕመሙ
ከነፃነት ይልት ግዙፍ ነው ሸክሙ?
በተስፋ መቁረጥ ውስጥ
ተስፋ ማሳጣት ነው ባርነት ትርጉሙ ።
ባርነተ? ወይስ ነፃነት?
በልበቅንነት በጉ ዓላማ ይዞ
በፍኖተ እውነት በዕውቀት ታግዞ
በልዩነት አምኖ በአንድነት ታንጾ
በሥልጡን አመራር የሰውልጅ አምጾ
መስዋትነት ከፍሎ ካልቆመ ለአርነት
ይበልጥ ይጋለጣል ለከፋ ባርነት
ለአደጋ ይዳረጋል የማሰብ ነፃነት፡፡
የመፃፍ ነፃነት። የመኖር ነፃነት።
ለሰው ልጀ ተጠቃሽ የሚሆን አብነት
ኧረ ለመሆኑ ምንድ ነው ነፃነት?
ማሳያ መስታውት ባላንጣን አቅሎ
ጭቆናን ተጋፍጦ ባርነትን ታግሎ
የገዛ ሕይወተን መስዋትነት ከፍሎ
ነፃነት መሞት ነው ለነፃነት ብሎ።
ክፋትን ማሳያ ለሰው ልጅ አብነት
አረ ለመሆኑ ምንድ ነው ባርነትን
በሕግ ማይፈቀድ ሚያስቀጣ ወንጀል
በሐይማኖት መንገድ ኃጢአት ወይም በደል
ሕሊናን ወርውሮ
ስርቻ ውስጥ መጣል ሆድ ለሚባል ገደል
ንፁህ ደምን ማፍሰስ ባርነት ነው መግደል።
ባርነት? ወይስ ነፃነት?
ባርነት
ፍፁም የማይቻል ሥቃዩና ሕመሙ
ከነፃነት ይልት ግዙፍ ነው ሸክሙ?
በተስፋ መቁረጥ ውስጥ
ተስፋ ማሳጣት ነው ባርነት ትርጉሙ ።
ባርነተ? ወይስ ነፃነት?
#ቆሞ_ቀር
ከሀገሩ ወግ ልማድ ከሥርዓቱ ወጥታ
ከሴቶች መካከል በሐሳብ ተለይታ
ከሥጋዋ እርቃ ከነፍሷ ተስማምታ
ባለአልቦ ሆናለች ፤ መንፈሷንም ገዝታ::
ዛዲያ
እንደ እኩዮቿ አግብታ ባትፈታ
ወዶገብም ባትሆን እንደአብሮ አደጓ
“ባል” የሚባል ጌታም አለመፈለጓ
መች ሆኖባ ለሷ?? ክብርና ማዕረጓ፡፡
የፆታ አጋሮቿ እንደምትኖር ቆጥረው ፈላጊ ባል አጥታ
“ቆሞ ቀር!” ይሏታል ያብጠለጥሏታል ብለው “ጋለሞታ”::
ያሻቸውን ቢሉ እንዳትሸነፊ
እንደፀናሽ ፅኚ አንገትሽን አትድፊ፡፡
ስማሽ ወይ?! እህቴ
አንገትን ከመድፋት ይልቅ ከማቀርቀር
እውነቱን መተንፈስ ይሻላል መናገር፡፡
“ቆሞ ቀር” ለሚሉሽ ለሚሸነቁጥሽ ሁልጊዜ በነገር
እንደዚ በያቸው አብሮ ይስማሽ ሀገር፡፡
“ጐብኚዎቹን ሁሉ አፍዞ የሚያስቀር ፤
ስለሆነ እኮ ነው አክሱምም ቆሞ ቀር፡፡”
ከሀገሩ ወግ ልማድ ከሥርዓቱ ወጥታ
ከሴቶች መካከል በሐሳብ ተለይታ
ከሥጋዋ እርቃ ከነፍሷ ተስማምታ
ባለአልቦ ሆናለች ፤ መንፈሷንም ገዝታ::
ዛዲያ
እንደ እኩዮቿ አግብታ ባትፈታ
ወዶገብም ባትሆን እንደአብሮ አደጓ
“ባል” የሚባል ጌታም አለመፈለጓ
መች ሆኖባ ለሷ?? ክብርና ማዕረጓ፡፡
የፆታ አጋሮቿ እንደምትኖር ቆጥረው ፈላጊ ባል አጥታ
“ቆሞ ቀር!” ይሏታል ያብጠለጥሏታል ብለው “ጋለሞታ”::
ያሻቸውን ቢሉ እንዳትሸነፊ
እንደፀናሽ ፅኚ አንገትሽን አትድፊ፡፡
ስማሽ ወይ?! እህቴ
አንገትን ከመድፋት ይልቅ ከማቀርቀር
እውነቱን መተንፈስ ይሻላል መናገር፡፡
“ቆሞ ቀር” ለሚሉሽ ለሚሸነቁጥሽ ሁልጊዜ በነገር
እንደዚ በያቸው አብሮ ይስማሽ ሀገር፡፡
“ጐብኚዎቹን ሁሉ አፍዞ የሚያስቀር ፤
ስለሆነ እኮ ነው አክሱምም ቆሞ ቀር፡፡”
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
ከግቢው ውስጥ የጥድቄ ለቅሶ የቀላቀለ ጩኸት ይሰማል፡፡ የሆኑ ወንዶች የጎረነነና
የተጣደፈ ድምፅም ይሰማል፤ የሚያወሩት ግን አይሰማም ነበር፡፡ ወዲያው አንዲት አምቡላንስ ሳይነሯን እያሸች መጥታ ልክ ማታ እኔና ሮሐ ቆመንበት በነበረው ቦታ ላይ ስትደርስ ቆመች፣ ሁለት ሠራተኞች ከኋላ ቃሬዛ አውጥተው ወደግቢው በር
ተጠግተው ቆሙ:: ቃሬዛውን ሳይ እንደሐሞት የመረረ ፈሳሽ በአፍና በአፍንጫየ ሊወጣ ሲተናነቀኝ ይሰማኝ ነበር፡፡ አምቡላንሱ መኪና አናት ላይ የሚሽከረከረው ደማቅ ቀይ መብራት፡ ከነጭ ሰሀን ላይ እየጨለፈ አካባቢው ላይ ደም የሚረጭ አንዳች ነገር
ይመስል ነበር፡፡ የመኪናው የፊት መብራት የፈጠረው ረዣዥም የሰዎች ጥላ ወዳቦ
ወዲህ ሲንቀሳቀስ አስፈሪ ሕልም ይመስላል፡፡ ጋሽ ዝናቡ ማሚን አንድ ነገር እንዳደረጋት አልተጠራጠርኩም፡፡
እንዱ ፖሊስ የግቢውን በር እንጓጉቶ አምቡላንስ መጥቷል” ብሎ ጮኸ፡፡ ወዲያው በሩ ተከፍቶ፣ አንድ የሰፈራችን ልጅ በወጠምሻ ከንዶቹ ጋቢ የለበሰ ሰው አንከብክቦ አቅፎ መጣ፡፡ ገና ከላይ ከደረቡላት ጋቢ ወጥቶ የተንጠለጠለ ጸጉሯን ሳይ ብርክ ያዘኝ፡፡ ሳሌም
ነበረች፡፡ ከአንገቷ ጀምሮ በጋቢ ተሸፍናለች፡፡ እየጮኸች እና እጁን እያወራጨት ታለቅሳለች::ቃሬዛ ላይ አስተኝተውና የሚወራጭ እጅና እግሯን ይዘው፣ ወደአምቡላንሱ ይዘዋት ሮጡ፡፡ ወዲያው ጥድቄ ተከትላ ወጣች፡፡ ግቢው በር ላይ ድፍት ብላ በቁሟ ወድቃ ፌቷን እየነጨች ኡኡ ትል ጀመር፡፡
አገር ፍረደኝ: አንዲት ፍሬ ልጅ ጉድ ሠሩኝ ኡኡኡኡ " በጩኸት ብዛት ድምፅዋ
ጎርንኖ በየመሀሉ ሹክሹክታ ይሆናል፡፡ “
ጉድ ሠሩኝ ጉድ ሰሩኝ ይኼ ምን ዕድል
ነው ምን ጭካኔ ነው? ተሰምቶ ያቃል ወይ? በሰው ደርሶ ያውቃል ወይ? ፊቷን
በሁለቱም በኩል ከዓይኖቿ በታች ክፉኛ ተልትላው ይደማል፡፡ የደም እምባ የሚፈስስት ነብር የሚመስለው፡፡ የሰፈሩ ሴቶች አብረዋት ኡኡ ሲሉ፣ ትኩስ ሬሳ የወጣበት ቤት መሰለ፡፡ሰዎች ክንዷን ይዘው ከወደቀችበት ሊያነሷት ሲሞከሩ፣መሬቱ ላይ ተንከባለለች፡፡
ቀሚሷ ተገላልቦ ሰውነቷ ሲጋላጥ፣ እንዲት ሴትዮ ነጠላቸውን ከራሳቸው ትከሻ ላይ ገፈው ሊሸፍኗት ሞከሩ፣ ግን እልሆነላቸውም፡፡ በዛ ያሉ ሰዎች አፋፍሰው እዚያው አምቡላንሱ ውስጥ አስገቧት፡፡ የአምቡላንሱ በር ከመዘጋቱ በፊት ጥድቄ እንዲህ እያለች ትጮህ ነበር
“በሳሌም? በሳሌም?… በሳሌም? በእህትህ መሐሪ በላሌም? እኮ በሳሌም? በእህትህ ጨክነህ መሐሪ ….በሳሌም? በሳሌ.. በሩ ጓ ብሎ ሲዘጋ ድምጿ ቆመ፡፡ ፍዝዝ ብዬ እንደቆምኩ የግቢው በር እንደገና ተከፍቶ ሁለት ፖሊሶች መሐሪን መሃላቸው አድርገው ይዘውት ወጡ፡፡ እጁ በካቴና ወደፊት ታስሮ ነበር፡፡ ክንድና ክንዱን ይዘው እንዳተኝ ሳብ አደረጉት፡፡ እንዳቀረቀረ ፍጥነቱን ጨምሮ፣ ቶሎ ቶሎ ተራመደ፡፡ ማሚ ቀን ለብሳው በዋለችው ቀሚስ ላይ ነጠላ እንደደረበች ተከትላው ከኋላ ከኋላ ትሮጣለች፡፡
ፖሊሶቹ እንደከበቡት ወደ ዋናው መንገድ በሚወስደው ጨለም ያለ ኮረኮች በኩል፣
እያጣደፉ ይዘውት ሄዱ፡፡ ሕዝቡ ግር ብሎ ተከትሎ ወደፖሊስ ጣቢያ ተመመ
በቆምኩበት ከእግሬ ጀምሮ ወደላይ ሰውነቴ እየደነዘዘ ሲሄድ ይታወቀኝ ነበር።
የተሰበሰበው ሰው ይሳደባል፣ ይራገማል፣ ግማሹ ቀን ድግሱ ላይ ሲመርቅ ሲያመሰግን የዋለ ነው፡፡
ግራ ግብት እንዳለኝ፣ አንድ ድምፁ እንደ ጣውላ መሰንጠቂያ ማሽን የሚጮህ ሰው “ይኼም ጓደኛው ነው!” ብሎ ከኋላ ጀርባዬን በከዘራው ጫፍ ወጋ አደረገኝ፡፡
የሚጠዘጥዝ መጠርቆስ ነበር፤ ዞር አልኩና ባለ በሌለ ኃይሌ የከዘራውን ጫፍ ይዠ ወደኔ ሳብኩት፣ እየተንገዳገደ ሲጠጋኝ በጥፊ አቃጠልኩት፡ትልቅ ሰው ነበር፤ ግድ አልሰጠኝም፡፡ የተሰበስቡት ሰዎች እግር ሥር እንደ ትል ጥቅልል ብሎ ወድቆ በህግ አምላክ” እያለ ሲጮህ እዚያው ልረጋግጠው ፈልጌ ነበር፡፡ ከየት እንደመጣች እንጂ፣ እናቴ ክንዴን ይዛ ስትጎትተኝ ወደኋላዬ ተመለስኩ፡፡ እየጎተተችኝ ወደ ቤት ስትገሰግስ
ልክ እንደለማዳ በግ በዝምታ ተከተልኳት፡፡ እቤት ስንደርስ፣ እናቴ ተንጠራርታ ጥብቅ
አድርጋ አቀፈችኝና፣ አለቀሰች፡፡ እኔም እየተነፋረቅሁ መሆኑ የገባኝ፣ እንባዬን
ስትጠርግልኝ ነበር!
“ምንድነው” ይላል አባቴ የእግሩ ወለምታ ስላላስኬደው እዚያው እተኛበት ሆኖ
የሆነውን ለመስማት ጓጉቷል፡፡ “ምንድነው? አትናገሩም እንዴ?”
“ምንም አይደል አንተ ደግሞ ዝም ብለህ ተኛ
ምን እተኛለሁ ...ን ከፍተሸብኝ ሂደሽ፣ ንፋስ ገባ መሰለኝ ይኼው ደህና የተሻለኝን እግሬን እየጠዘጠዘኝ ነው!”
ቆም ብዬ አባቴን እየሁትና “እና ቢጠዘጥዝህ ትሞታለህ”አልኩት
እ...አለ ደንግጦ፡፡
ወደ ውስጥ ገብቼ አልጋ ላይ በፊቴ ተደፍቼ ተኛሁ፡፡ ምንም ነገር አልገባኝም፣ ምንም ነገር አላሰብኩም፡፡ አንድ ነገር ብቻ፣ እግዚአብሔርን መሆነ ሰዓቶቹን ወደኋላ መመለስ! ብዙ አይደለም፣ በቃ
እንድ አምስት ሰዓቶች ብቻ ወደኋላ መመለስ:: እግዚአብሔር ይችን ቢያደርግ ምን ይጎዳል? ምናልባት የሆነ ነገር ከአምስት ሰዓት በፊት ሎተሪ የደረሰው ደሃ፣ መልሶ ወደ ለመደው ድህነት ቢመለስ ነው! ድህነት ወንጀል
አይደል፣ ቢበዛ በድስትና በሰሃን በተከበበች ምኝታ ቤት ቢተኛ ነው …ምናለበት … ይችን ብቻ ይችን ብቻ!! ድንገት ቀን ስበላው የዋልኩት በቅመም ያበደ ቀይ ወጥና አልጫ ሆዴ ውስጥ እንደ ማዕበል ተገለባብጦ፤ ወደ ጉሮሮዬ ሊወነጨፍ፣ ከአልጋዬ። ዘልዬ ተነሳሁ፡፡ ዘግይቼ ነበር፤ ከአልጋዬ ሥር ባለው ላስቲክ በተነጠፈበት ወለል ላይ
ትውከቴን ለቀኩት !
“ልጄን! ልጄን እያለች እናቴ ወደ እኔ ስትሮጥ ይሰማኛል …ቀለል አለኝ !

#አዳሪ
ስሚ አንቺዬ!… ይሄን ሁሉ ውበት ይሄን ሁሉ ሲሳይ
አልፈነው ብንሄድ እንዴት ይቻለናል?
ለይቶ ያማረንን ለይተን ብንወድ ለኛስ ምን ይለናል?
~
“ምኔን ነው?” ስላቸው
ውበትሽን ይሉኛል
ሽንጥሽን ዳሌሽን
ደረትና ጡትሽ ይምጣብን ይሉኛል።
ሴትነቴን ወደው
እኔነቴን ንቀው
በፍቅሬ ተማርከው
ገላዬ ስር ወድቀው
እንደር ይሉኛል በስሜት ታውረው
እነሱ ቀድመውኝ በወንድነት አድረው።
~
በሴትነት ባድር
ባውንድ እንድቆጥር
ጦም ውዬ እንዳላድር
አዳሪ ይሉኛል ባስተዳደርኳቸው
ሴትነቴን እንጂ ስሜንና ክብሬን ከቶ ሳልሸጣቸው
ስሜን ነጠቁና ጠሩኝ በሥማቸው።
~
የነሱን ስም ይዤ አዳሪ ተብዬ
ወንደኛ አዳሪዎችን ሳስተዳድር ውዬ
መቼም ሆድ ነውና እንጀራ ነው ብዬ
በሸፍጥ የሰጡኝን ሥሜን ተቀብዬ
በግድ እኖራለሁ አዳሪ ተብዬ።
~
አለሁበት መጥተው “ወደድን!” ይሉኛል
እኔ ብቀር እንኳ አትቀሪም ብዬ ነው
ሰርክ የለፋሁትን ሰርክ የምገብረው
ምን አስነክተሽኝ በምን ዳብሰሽኝ ነው
ደጀ ሰላምሽን ስስም የምገኘው?
“እኔን ነው?” ብላቸው
እሙዬ ሙች!
ብርሃንሽን ያጥቢያ ኮከብሽን!
“ዓይንሽን!” ይሉኛል
ደረትሽን ዳሌሽን ይምጣብን ይሉኛል።
~
ደሃ አካሌን ገዝተው
በሴትነቴ ላይ በወንድነት አድረው
በድህነቴ ላይ በሽታ ጨምረው
ከጊዜያዊ ውጥረት ለጊዜው ተንፍሰው
ያው እስካሁን አለሁ ስኖር እንደዋዛ
ሴትነት እየሸጥኩ በሽታን ስገዛ።
~
ህይወት ጨካኝ ሆና ጨክኜ እምኖረው
ተስፋ ኖሮኝ ሳይሆን ሆድ ስላለብኝ ነው፤
ይሄ ነው እንግዲህ ዘወትር የኔ ዕጣ
የበረደው ሲሄድ የጋለው ሲመጣ
የበረደው ሲሄድ የጋለው ሲመጣ…
🔘አበባው መላኩ🔘
ስሚ አንቺዬ!… ይሄን ሁሉ ውበት ይሄን ሁሉ ሲሳይ
አልፈነው ብንሄድ እንዴት ይቻለናል?
ለይቶ ያማረንን ለይተን ብንወድ ለኛስ ምን ይለናል?
~
“ምኔን ነው?” ስላቸው
ውበትሽን ይሉኛል
ሽንጥሽን ዳሌሽን
ደረትና ጡትሽ ይምጣብን ይሉኛል።
ሴትነቴን ወደው
እኔነቴን ንቀው
በፍቅሬ ተማርከው
ገላዬ ስር ወድቀው
እንደር ይሉኛል በስሜት ታውረው
እነሱ ቀድመውኝ በወንድነት አድረው።
~
በሴትነት ባድር
ባውንድ እንድቆጥር
ጦም ውዬ እንዳላድር
አዳሪ ይሉኛል ባስተዳደርኳቸው
ሴትነቴን እንጂ ስሜንና ክብሬን ከቶ ሳልሸጣቸው
ስሜን ነጠቁና ጠሩኝ በሥማቸው።
~
የነሱን ስም ይዤ አዳሪ ተብዬ
ወንደኛ አዳሪዎችን ሳስተዳድር ውዬ
መቼም ሆድ ነውና እንጀራ ነው ብዬ
በሸፍጥ የሰጡኝን ሥሜን ተቀብዬ
በግድ እኖራለሁ አዳሪ ተብዬ።
~
አለሁበት መጥተው “ወደድን!” ይሉኛል
እኔ ብቀር እንኳ አትቀሪም ብዬ ነው
ሰርክ የለፋሁትን ሰርክ የምገብረው
ምን አስነክተሽኝ በምን ዳብሰሽኝ ነው
ደጀ ሰላምሽን ስስም የምገኘው?
“እኔን ነው?” ብላቸው
እሙዬ ሙች!
ብርሃንሽን ያጥቢያ ኮከብሽን!
“ዓይንሽን!” ይሉኛል
ደረትሽን ዳሌሽን ይምጣብን ይሉኛል።
~
ደሃ አካሌን ገዝተው
በሴትነቴ ላይ በወንድነት አድረው
በድህነቴ ላይ በሽታ ጨምረው
ከጊዜያዊ ውጥረት ለጊዜው ተንፍሰው
ያው እስካሁን አለሁ ስኖር እንደዋዛ
ሴትነት እየሸጥኩ በሽታን ስገዛ።
~
ህይወት ጨካኝ ሆና ጨክኜ እምኖረው
ተስፋ ኖሮኝ ሳይሆን ሆድ ስላለብኝ ነው፤
ይሄ ነው እንግዲህ ዘወትር የኔ ዕጣ
የበረደው ሲሄድ የጋለው ሲመጣ
የበረደው ሲሄድ የጋለው ሲመጣ…
🔘አበባው መላኩ🔘
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
"ልጄን! ልጄን እያለች እናቴ ወደ እኔ
ስትሮጥ ይሰማኛል …ቀለል አለኝ !
።።።።
ለድፍን አንድ ሳምንት ከቤቴ ሳልወጣ አሳለፍኩ፤ ከእሁድ እስከ እሁድ፡፡ ምን እኔ ብቻ፣ ከዚያች ምሽት ጀምሮ እናቴ እንቅልፍ አልነበራትም፣ ለወትሮው ጧት ጧት ሳታዛንፍ የምትስመውን ቤተክርስቲያን ርግፍ አድርጋ ትታ፣ የእኔው ጠባቂ ሆና አብራኝ ታሰረች፡፡ እንኳን ከቤት ርቄ ልሄድ፣ ለሽንት እንኳን ከቤታችን ኋላ ወዳለው መፀዳጃ ቤት ደረስ ብዬ ለመመለስ አታምነኝም፡፡ ተከትላኝ ወጥታ በር ላይ ትቆማለች፡፡ ተጨንቃ ነበር፡፡
እውነት ነበራት ደግሞ፤ ድፍን ከተማው ሌላ ወሬ አልነበረውም፡፡ “የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛው የአቶ ዝናቡ ልጅ እቤታቸው ያስጠጓትን ምስኪን ሕፃን ልጅ ደፈረ…”
እግዚኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦ! ስምንተኛው ሺ!”
ጎረቤቱ ከላይ እስከታች በአንድ ጊዜ የነመሐሪን ቤተሰቦች ረጋሚ እና ዘላፊ ሆኖ ነበር፡፡
ይኼ ዘለፋ ታዲያ ባለፍ ገደም ወደኔም እንጥፍጣፊው መድረሱ አልቀረም፡፡ ያስገረመኝ የዚህ የጥላቻ ዘመቻ ዋና አራጋቢዎች ሰፈር ውስጥ ትምህርት እምቢ ያላቸው ልጆች መሆናቸው! እነሱም ብሎ ጎበዝ ተማሪም ይላሉ፡፡ መቼም መሐሪ ሲነሳ “እነሱ” ከተባለ
ያው አንዱ እኔው ነኝ፡፡ እስቲ አሁን ጉብዝናችን ላይ ምን ወስዶ አንጠላጠላቸው? በዚህ ሰበብ ጉብዝናችንን ካዱትም አልካዱትም ትምህርት ሚኒስተር መጽዋች ስለሆነ አይደለም አራት ነጥብ የሰጠን፡፡ ምን ያገናኘዋል? ሲያጨበጭቡልን እየተበሳጩ ነበር እንዴ ሰፈራችንን አስጠራችሁት ያሉት፣ ሰበብ አግኝተው እንደ ኦሪት መስዋዕት ከሰፈር አውጥተው ሊያቃጥሉን ነበር እንዴ? ግን ከተፈጠረው ነገር ይልቅ፣ የተበለጡትን መከረኛ ትምህርት እያነሱ፣ መሐሪንም እኔንም ሲያንቋሽሹ ነበር ውለው የሚያድሩት፡፡
አብሯቸው የኖረ የበታችነት እና የመብለጥ ስሜት፣ ሳሌም የምትባል መርፌ ስትወጋው እንደባሉን እየተነፈሰ ነበር ፡፡
አባባ እንደ ማንኛውም ቀን ፣ምንም እንዳልተፈጠረ፣ በነጠላ እራፊ የተጠመጠመ እግሩን በተደራረበ ትራስ ላይ አሳርፎ፣ (አስር ጊዜ ትራሱን አስተካክልልኝ እያለ)ስለእቁብ
ሲያወራ ይውላል፡፡ ይኼ ነገሩ ትንሽ ቢያሳዝነኝም፣ ከእናቴ ጭንቀት ይልቅ የእርሱ ግድ የለሽነት የተሻለ ያረጋጋኝ ስለነበር፣ ብዙውን ጊዜ የማሳልፈው ከአባባ ጋ በማውራት ነበር፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን የሆነ ነገር እንዲለኝ ፈልጌ ነበር፡፡ ቢያንስ አይዞህ እንዲለኝ፡፡
አይዞህ ብቻ፡፡ ምንም ቢያወራ ነገሬ ብዬ ከማልሰማው አባባ፣ አንድ ቃል ናፈቀኝ፡፡
አባትነት ልጅ በመውለድ ብቻ የሚመጣ ነገር እንዳልሆነ የገባኝ ያኔ ነው እየወደድኩት ውስጤ ያዝን ነበር፡፡ ነፍሱ ውስጥ እኔ የለሁም እላለሁ፡፡ ሩቅ
ሐገር ተፈጽሞ በዜና ቢሰማ እንኳን ስሜትን የሚረብሽ ነገር እዚህ አፍንጫው ሥር፣ ያውም ከወንድምም በሚቀርብ የልጁ ጓደኛ ተፈጽሞ ፣ ጎረቤቱ ሁሉ እየዛተና እየፎከረ - “ድሮውንም አንገት
ደፊ” በሚል ገደምዳሞሽ አሽሙር፣ በሌለሁበት እኔንም ጨምሮ እየቀጣኝ ምንም ስሜት ያልሰጠው አባት፣ እንዴት ዓይነት ተፈጥሮ ቢኖረው ነው!? እያልኩ እገረማለሁ፡፡
ለእኔ ብቻ ሳይሆን፣ የእናቴን ጭንቀት ትንሽ እንኳ ቢካፈላት፣ ሌት ተቀን ልጇን ሊነጥቋት እንደከበቧት አራስ ነብር፣ ቁጣና ስጋት ከቧት ስትንቆራጠጥ፡ ኮሽ ባለ ቁጥር ብርክ ሲይዛትና፣ በበር ሽንቁር ወደውጭ እያጨነቆረች ስትመለከት፣ እይዞሽ ቢላት ምናለበት፣ እያልኩ አስባለሁ፡፡ ተኚ እኔ አለሁ ለምን አይላትም? እልናገረውም ግን
አስባለሁ፡፡ ምንም ይሁን አባት፣ ፈርጣማ ክንድ ባይኖረው እንኳ፣ ተስፋና ማጽናናት
እንዴት ይነጥፍበታል፡፡ “እንድ ሰው የልጄን ስም ያነሳና፣ ውርድ ከራሴ፣ እሱ ምን
ያርጋችሁ? እዚህ እንደ እንሽላሊት በየጥጋጥጉ እየሄዳችሁ የምታሽሟጥጡት” ቢል ምን
ይሆናል አንድ ቤት የምንኖር ሳይሆን፣ ታክሲ ፌርማታ ላይ ድንገት ተገናኝተን፣ ታክሲ እስከሚመጣ የምንጠብቅ መንገደኞች የሆንን እስኪመስለኝ ምንም የምንጋራው ስሜት አልነበረም፡፡ ቸልተኛ ነበር፤ እሽ ይሁን፡ ቸልተኝነቱን ትንሽ ወደ ምክር ቢለውጠው እና አይደል፤ አትስማቸው '' ችላ ብሎ ማለፍ ነው" ቢል፡፡
ገና እቤት መዋል በጀመርኩ በሦስተኛው ቀን፡ እናቴን እንዲህ እላት፡፡ “በመንደሩ ያለው ሰው የዝናቡ ልጅ ብቻ ነው እንዴ?…ይውጣና ኮመንደሩ ልጆች ጋር ንፋስ ተቀብሎ ይምጣ፤ እንግዲህ አንዴ የሆነው ሁኗል፡ የፈሰሰ ውሃ እይታፈስ!”፡፡ እንዴ የሆነው ሁኗል ማለት ምን ማለት ነው? እንዳትደግመው እንጂ የሆነው ሆኗል ነበር የሚመስለው አነጋገሩ፡፡ ከዚያ በፊት ችላ ብየው፣ አልያም ሳላስተውለው ቆይቼ የገረመኝ ነገር ደግሞ፣አባቴ መሐሪን በስሙ ጠርቶትም ሆነ ጓደኛህ” ብሎ አያቅም፡፡ “የዝናቡ ልጅ” ነው የሚለው፡፡ ለነገሩ አባባ፣ መሐሪን ብቻ ሳይሆን፣ ሕፃንም ይሁን ወጣት በስም
አይጠራም፡፡ የእከሌ ልጅ ነው የሚለው፡፡ ሴቶችን ሳይቀር “ይች የእከሌ ሚስት” ነው የሚለው፡፡
ይኼው አሁንም “የዝናቡ ልጅ ብቻ ነው ወይ በመንደሩ ያለው? ይለኛል፡፡እና በመንደሩ ማን አለ? …ከመሐሪ ሌላ ማን አለ? …መሐሪ ከሰፈር ልጆች እንዱ አልነበረምኮ መሐሪ ጓደኛ ብቻ አልነበረምኮ ከመኖር ብዛት የራሳችንን ቋንቋ የፈጠርን፣ ሁለት ሰዎች ውስጥ የተቀመጠች አንዲት ውብ ነፍስ የተጋራን ፍጥረቶች ነበርን፡፡ ቃል ሳንተነፍስ
ልባችን ውስጥ ያለውን ሐሳብ በአንድ የዓይን ጥቅሻ የምንካፈል፡፡ ትንሽ ዓለሜ
የቆመችው፣ ሁለት ምሰሶዎች ላይ ነበር፡፡ አንዱ እኔ ራሴ፣ አንዱ መሐሪ! ግማሽ እኔ እስር ቤት ውስጥ ነኝ ሚዛኗን ስታ እየተንገዳገደች ያለች ሚጢጢ ዓለሜን፣ ወደፊት መራመዱ ቢቀር፣ ቀጥ ብላ እንድትቆም እየታገልኩ ነበር፡፡ ለድጋፍ እጁን የሚሰጥ ሰው እንጂ፣ ግዴለም በአንድ እግርህ ውጣና፣ ሌላ እግር ፈልግ የሚል ሰው አልነበረም ፍላጎቴ! “ከሰፈር ልጆች ጋር ነፋስ ተቀበል” ይለኛል፡፡ እንኳን አብሬው ነፋስ የምቀበለው የሰፈር ልጅ፣ በመንደሩ ውስጥ ነፋስ አለ ወይ?… መንደሩስ ራሱ አለወይ … እቤቴ ቁጭ
ያልኩት (ምን ቁጭ ያልኩት የተደበኩት) እንደ ሕፃን ልጅ የራሴን ዓይን ስጨፍን
ከዓለም ሁሉ የተደበቅሁ መስሎ እየተሰማኝ፣ ለአፍታም ቢሆን እፎይታ ስለሚሰማኝ ነበር፡፡ በሆነው ሁሉ ከማፈሬ ብዛት የሰው ዓይን ፈርቼ ነበር፡፡
መሐሪ ሁለት ቀን ፖሊስ ጣቢያ ቆይቶ በሦስተኛው ቀን ፍርድ ቤት ቀረበ ተባለ፡፡ የዚያኑ ቀን ከሰዓት በኋላ፣ ወደ ትልቁ ማረሚያ ቤት እንደተወሰደ ሰማሁ፡፡ ይኼን ሲነግሩኝ፣ ያ አሮጌ የብረት በር እየተንሳጠጠ ከኋለው ሲከረቸምበት ታየኝ፡፡ ውስጤ ሂድ ሂድ ይለኛል፡፡ከስንት ዓመታት በፊት ያየሁት ማረሚያ ቤት ሲታወሰኝ፣ዘገነነኝ፡፡ የማቅለሽለሽ
ስሜትም ተሰማኝ፡፡ ለምን እንደሆነ እንጃ፣ ዝም ብሎ የማቅለሽለሽ ስሜት ቶሎ ቶሎ
ይሰማኛል፡፡ሳምንቱን ሙሉ እንደ ነፍሰጡር ምግብ ሲሸተኝ፣ ጧት ስነሳ ያቅለሸልሽኝ ነበር፡፡
ግንኮ እስከ ዛሬ ብዙ ነገር ይስተካከል ይሆናል” ብዬ እራሴን ለማጽናናት ሞከርኩ፡፡ለምሳሌ ማረሚያ ቤቱ ውስጥ ዘመናዊ የመዋኛ ገንዳ ተሠርቶ ሊሆን ይችላል (መሐሪ ዋኝቶ አያውቅም እንጂ ዋና ይወዳል፡፡ ስናድግ እቤቱ የመዋኛ ገንዳ ሊያስገባ ሐሳብ ነበረው) ምናልባት ምሳቸው በባልዲ የተቀዳ ወጥ ሳይሆን፣ ነጫጭ ልብስ በለበሱ ጠረጴዛዎች ላይ፣ በቆንጆ አስተናጋጆች በሸክላ ሰሀን የሚቀርብ ብዙ ዓይነት ምግብ ሊሆን ይችላል፡፡ በቅመም ያበደ ሻይም ከምሳ በኋላ ይቀርብላቸው ይሆናል። (መሐሪ
ከምሳ በኋላ እንደዚያ ዓይነት ሻይ ይወዳል) ከዚህ ሁሉ

ሐሳብ መሃል ድንገት ምንጥቅ ብዬ ወጥቼ ወደማረሚያ ቤቱ ሩጥ ሩጥ ይለኛል፡፡ ግን ከእናቴም ጭንቀት በላይ እፈራለሁ፡፡ ከቤት ብወጣ መንገደኛው ሁሉ ጓደኛው ነው ብሎ በድንጋይ ወግሮ የሚገድላኝ ይመስለኛል፡፡ እሱም አለበት የሚል እብድ ሰፈሩን የሞላው መሰለኝ፡፡
አልፎ ሲያስቡት ቀላል የሚመስል፣ ግን እንደመርግ የሚጫን ፍርሀት ተጭኖኝ ነበር፡፡ እንደዚያም ሁኖ መሐሪን በክፉ ቀን የካድኩት መስሎም ይሰማኝ ነበር፡፡
ጎረቤቱ ሲያልፍ ሲያገድም ጎራ እያለ፣ እናቴ ጋር ያወራል፡፡ አወራራቸው ራሱ
የሚጨንቅና በሹክሹክታ የተሞላ ነበር፡፡ (ማን እንዳይሰማቸው ነው) ታዲያ ያወሩትን አውርተው ሊሄዱ ሲሉ፣ ማሳረጊያቸው እኔ ነበርኩ፡፡ እስቲ እስኪረጋጋ ይኼ ልጅ ወጣ ወጣ አይበል” ይላሉ፡፡ ውስጤ በሐዘን ግራ መጋባት እየተናወጠ፣ እንደሩቅ ሰው ስለ
መሐሪ፣ ስለ ማሚ፣ ስለ ጋሽ ዝናቡ፣ ስለ ሳሌም ጥድቄ ውሎና አዳር፣ ከጎረቤት አፍ መስማት ጀመርኩ፡፡ በአንድ አዳር የሩቅ ሰው ሆንኩ፡፡ ሩቅ!
በዚያ ሰሞን ሌሊት ሌሊት የነመሐሪን ቤት ሰዎች በድንጋይ እየወገሩባቸው ተቸግረው
ከረሙ፡፡ ሲበዛባቸው ማሚ ፖሊያ ጣብያ ማመልከቷንና፣ ፖሊሶች ሰፈር ውስጥ ሲዞሩ እንደሚያድሩ፡፡ ነገሩን ግቢው በር ላይ በከሰልና በጠመኔ ጸያፍ ስድብና ዛቻ
ይጽፉባቸዋል፡፡ማሚ ጧት እየተነሳች በውሃና በጨርቅ ትወለውላለች“ልጅሽ ይሰቀላል የሚል ጽሑፍን እንባዋን እያዘራች ለማጥፋት ትታገላለች፡፡ የሞት ፍርድን በውሃና በጨርቅ ልታነሳ፡፡ አሳቻ ሰዓት ጠብቀው መልሰው ጽፈው ይሄዳሉ፡፡ “ሞት ለደፋሪ!!
ወንጀል ባህሪ አልያም ቅፅበታዊ የሆነ ድርጊት እንጂ ማንነት አይደለም! ወንጀል የቱንም ያህል ትልቅ ይሁን፣ የወንጀለኛውን የሰውነት ክብር ሊነጥቅ አይችልም ሕጉም ቢሆን
“ወንጀል የሠራህ ሰው ነህ” እንጂ “ወንጀል ስለሠራህ ሰው አይደለህም” አይልም፤ እንዴት ነው ሰዎች አእምሮ ውስጥ እንድ ሰው ላሳየው የወንጀለኝነት ባሕሪም ይሁን ድርጊት ሰውነቱን መንጠቅ ፍትሕ የሚመስላቸው?
የሚያሳዝነው፣ ጎረቤቱ እየሆነ ያለውን ነገር የሚያወራው፣ በማዘን ስሜት ሳይሆን፣ “ደግ አደረጓቸው በሚልና አድራጊዎቹን በሚያዳንቅ ድምፅ ነበር፡፡ ድምጻቸው… ቢመቻቸው እነሱም ጨለማ ለብሰው ቤቱን ለመውገር እንደማይመለሱ ያሳብቅ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም “ገና ለገና ሀብታም ሆኑና ደሀ ላይ እንዲህ ያለ ግፍ …” ይሉ ነበር፡፡ “ባለጌ ከመውለድ ይሻላል ማስወረድ!”ብለው ይተርታሉ፡፡ የሆነው ነገር ግራ አጋብቶኝ ለፍርድ ብቸገርም፣ መሐሪ ባለጌ እንዳልሆነ፣ ቤተሰቦቹም “ሀብታም ሆንን” ብለው ደሀ ላይ ግፍ
የሚውሉ እንዳልሆኑ አውቃለሁ፡፡ ሲጀመርስ፣ ሀብታም ነበሩ ወይ? …እንዴት ነው የይሉኝታ ወንዝ በአንድ ሌሊት ደርቆ፣ እንዲህ ስንት ዘመን ለክፉም ይሁን በደጉ
የተረዳዳ ጎረቤት፣ የመከባበርን ድንበር በእግሩ የተሻገራት?
በዚህ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ታዲያ፣ ሁልጊዜ ማታ ማታ በበራችን አልፎ ወደታች ሰፈር የሚሄድ ጋሽ አዳሙ የሚባል ሰካራም ይገርመኝ ነበር፡፡ ስክር ብሎ፣ ሲፈልግ በዜማ፣ ሲፈልግ በንግግር፣
“ወረተኛ ሁሉ! ያሳደግሽውን ልጅ እንደድመት ልትበይ አሰፍስፈሻል ና ውርርርር ድመት ሁሉ እያለ ይጮኻል፡፡ ጮኸ ብሎ ይጣራል አብርሃም …አይዞህ! እናስፈታዋለን! ድመት ሁሉ! ውርርርርር …የነገ ዶክተር ….የነገ ኢንጅነር …የነገ ጠቅላይ ሚንስትር ልትበይ አሰፍስፈሻል! …ውርርርርርር …ልጆቻችን ናቸው! …ውርርር! ደፋሪም ተደፋሪም ልጆቻችን ናቸው! ለሁለቱም ማልቀስ ነበር የሚበጀን ሁልጊዜ ማታ ጋሽ አዳሙን እጠብቅ ነበር፡፡ የተመሰከረለት ሰካራም ቢሆንም ቅሉ፣ በእውነት፣ እንደ ደግ አባት
የጨለማ ንግግሩ ይናፍቀኝ ነበር፡፡

👍2
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
“ወረተኛ ሁሉ! ያሳደግሽውን ልጅ እንደ ድመት ልትበይ አሰፍስፈሻል ና ውርርርር ድመት ሁሉ እያለ ይጮኻል፡፡ ጮኸ ብሎ ይጣራል አብርሃም …አይዞህ! እናስፈታዋለን! ድመት ሁሉ! ውርርርርር …የነገ ዶክተር ….የነገ ኢንጅነር …የነገ ጠቅላይ ሚንስትር ልትበይ አሰፍስፈሻል! …ውርርርርርር …ልጆቻችን ናቸው! …ውርርር! ደፋሪም ተደፋሪም ልጆቻችን ናቸው! ለሁለቱም ማልቀስ ነበር የሚበጀን ሁልጊዜ ማታ ጋሽ አዳሙን እጠብቅ ነበር፡፡ የተመሰከረለት ሰካራም ቢሆንም ቅሉ፣ በእውነት፣ እንደ ደግ አባት
የጨለማ ንግግሩ ይናፍቀኝ ነበር፡፡
ቤት ውስጥ በተቀመጥኩ ልክ በሳምንቱ፣ እሁድ ቀን እዚያ ታች ሰፈር የሚኖሩ ሁልጊዜ ከእናቴ ጋር ቤተክርስቲያን የሚገናኙ ሴትዮ፣ አንድም እናቴን ቤተክርስቲያ ስላላገኟት ለመጠየቅ፣ እግረመንገዳቸውንም አባባን ተሻለህ ወይ ለማለት፣ ከቤተክርስቲያን ሲመለሱ
እቤታችን ጎራ አሉ፡፡ ገና እንደገቡ እኔን ሲያዩ አንተ አብርሃም እንዲያው ምን
ይሻላችኋል” ብለው አለፍ አሉና ተቀመጡ፡፡ ቡና ተፈልቶ ስለነበር (አቦል ረግጠውማ አይሄዱም) ተብለው ቁጭ አሉ፡፡ቡና እየጠጡ ያው የዚያን ሰሞኑን ወሬ ሲያወሩ ድንገት እናቱን ያየ ሰው ያች ቆንጆ ናት ወይ ያስብላል፣ ባንዴ አመዱን ነስንሶባታል አሉ፡፡ ጆሮዬ ቆመ፤ ስለመሐሪ እናት ስለማሚ ነበር የሚያውሩት፡፡
“ምን ታርግ፣ ይኼ መዓት እንኳን እሷን …" እናቴ ሳትጨርስ ተወችው፡፡
ትላንት ለልጁ ስንቅ ልታደርስ ወደ እስር ቤት ስትሄድ፣ እዚህ ኮረኮቹ ላይ ወደ
ፈረንጆቹ ቤት መገንጣያዋ ጋ፣ የተደበቁ ልጆች ድንጋይ ወርውረው መቷት አሉ፡፡
“ውይ ውይ ውይ የሚመታ ይምታቸው እቴ፣ ሰይጣኖች! እሷ ምናረገች፡፡ ሰው ቀና ብላ የማታይ ሴት፣ ምናረገች ይላሉ እሰቲ አሁን፣ ተጎዳች… ምኗን መቷት?” አለች እናቴ፡፡እንባ ተናንቋት ደረቷን እየደቃች ነበር፡፡
እንጃ ምኗን እንዳገኟት ምን እንደገፋኝ እንጃ ከተቀመጥኩበት ጥግ ተነስቼ በእናቴና በሴትዮዋ መሀል የተዘረጋውን ረከቦት ዘልዬ ወደነመሐሪ ቤት ከነፍኩ፡፡ የቆምኩት የግቢያቸው በር ላይ ስደርስ ነበር፡፡ በሩን ሳንኳካ ፊት ለፊት መንገዱን ተሻግሮ ያለ ግቢ በር ገርበብ ብሎ ተከፈተና፣ መዓዛ የምትባለው የጎረቤት ልጅ ብቅ ብላ አይታኝ፣ መገዱን ተሻግሮ እስኪሰማኝ ኤጭ!” ብላ በሩን ወርውራ ዘጋችው! መዓዛ እኔን አይታ
ኤጭ አለች፡ህ! …እኔና መሐሪን ባየች ቁጥር፣ ቀሚሷን እንደ ሰላም ባንዲራ
እያውለበለበች በዓይኗ ከሁለት አንዳችሁ ተኙኝ እያለች ስትማጸን የኖረች ከንቱ ናት!
ከንቱ ብቻ አልነበረችም፣ ደደብም ጭምር ነበረች፡፡ እኔ የሠራሁላት የቤት ሥራና
አሳይሜት ብቻ ቢቆጠር፣ ከሷ የበለጠ የሷን ትምህርት ተማርኩላት ያስብል ነበር፡፡ደደብ ብቻም አልነበረችም፡፡ ዓይናውጣ። ነገርም ነበረች፡፡ መሐሪን የቤት ሥራ ሥራልኝ ብላ እቤታቸው ሄዳ ልትስመው ሞክራ፡ ገፈታትሮ አስወጥቷት፡ እየሮጠ እኔ ጋ መጥቶ ነግሮኝነበር፡፡አሯሯጡ ራሱ ነፍሱን የሚያድ እንጅ ከንፈር የተቃጣባትን አይመስልም ነበር
ሁሉም የተናቀውን ያህል ሰበብ ፈልጎ ሊንቅ ሲያደባ የኖረ ነበር እንዴ? ውስጤ ተቆጣ ይኼ ሕዝብ ወንጀል አይጸየፍም እንዲያውም የጠላቸውን እና ቀን
የሚጠብቅላቸውን ሰዎች ማጥቂያ በረከት አድርጎ ነው የሚመለከተው።
“ማነው?” አለች ማሚ፡፡ ለዘመናት ሲጸልይ ቆይቶ፣ ፈጣሪ ከሰማይ ድምፁን እንዳሰማው አማኝ፡ ድምጿ ተአምር ነበር የሆነብኝ፡፡
"እኔ ነኝ ማሚ"
በሩን በፍጥነት ከፍታ፣ ሁለት እጆቿን እንደ ከንፍ እንደዘረጋች ተንደርድራ አቀፈችኝና፡
ደረቷ ላይ ለጥፋኝ ማልቀስ ጀመረች ጥብቅ አድርጋ አቀፈችኝ፡፡ ከማጥበቋ ብዛት የተነሳ ደረቷ ላይ ያለችው የወርቅ ሐብል ማጫወቻ ጉንጨን የበሳችው እስኪመስለኝ እየወጋችኝ ነበር፡፡ የማደርገው ነገር ግራ ገብቶኝ፣ ደረቷ ላይ ተለጥፌ ዝም አልኩ፡፡ ወጥ ወጥ
ትሽታለች:: ትንሽ አቅፋኝ እንደቆየች፣
“የኔ ነገር፣ ና ግባ ና አለችና መልሼ እንዳልሄድ የፈራች ይመስል በአንድ እጇ
እንባዋን እየጠረገች፣ በሌላኛው እጇ እጄን ይዛ እየጎተተች ወደ ውስጥ መራችኝ፡፡
“ግቢው፣ ቤቱ አዲስ ሆነብኝ፡፡ብዙ ዓመት ቆይቼ የመጣሁ ያህል አዲስ ሆነብኝ፡፡ ዛፎቹን እንደ ሰው እያቀፍኩ ብስማቸው ብዬ ተመኘሁ፡፡ በረንዳ ላይ የተቀመጠውን የጋሽ ዝናቡን ተወዛዋዥ ወንበር፣ እንደ ሰው ስላም ልለው ዳዳኝ፡፡ ከዚህ ግቢ ለአንድ ሳምንት የቀረሁበትን ጊዜ አላስታውስም፡፡ ጭር ብሏል፡፡
የመጠየቂያው ስዓት እንዳይረፍድብኝ ብዬ ወጥ እየሠራሁ ስሯሯጥ ቤቱንም
እላዘጋጀሁት እለች፡፡ እስረኛ መጠየቂያው ስዓት ማለት አልፈለገችም፡፡ ሳሎን ባለው
ሶፋ ላይ፣ በርከት ያሉ የመሐሪ ልብሶች እዚያና እዚህ ተዝረክርከዋል፡፡ የተወሰኑት
በሥርዓት ታጥፈው በአንድ ጎን ተቀምጠዋል፡፡ ቅያሬ ልብስ ልትወስድ አዘጋጅታቸው ነበር፡፡
ድንጋይ እንደወረወሩብሽ ሰምቼ ነው የመጣሁት አልኩ፡፡ ድንገት ነው ያመለጠኝ፡፡
“ዝምብለው ነው ባክህ ልጆች
ጎዱሽ …
አረ ጠጠር ነው፡፡ እግሬን ጫር አድርጎኝ አለፈ፡፡ ታውቀው የለ፣ የዚህ ሰፈር ውሪዎች ጨዋታቸው ለዛ ቢስ ነው፡፡ እናተም ያው ነበራችሁ፡፡ በየቀኑ ስሞታ ነበር ብላ ለመሳቅ ሞከረች ፡፡ ዓይኔን ወደ እግሯ ላከሁት ነጭ ካልሲ አድርጋለች፡፡ ማሚ በጭራሽ ካልሲ አድርጋ አይቻት አላውቅም! ወደ ማድቤት አብሪያት ሄድኩና፣ ግድግዳውን ተደግፌ
ቆምኩ፡፡ የኤሌክትሪክ ምድጃ ላይ ሁለት ብረት ድስት ጥዳ ወጥ እየሠራች ነበር፡፡
አንዱ ድንች በሥጋ የመሐሪ ቁጥር አንድ ምግብ (ሚስቴ አሪፍ ድንች በሥጋ መሥራት ከቻለች ለምን እንፋታለን ብሎኝ ነበር ..ድሮ ስለ ሚስት ይሁን ስለ ፍች ስናወራ )
ከማሚ ጋር ሳንነጋገር ዘለግ ያሉ
ደቂቃዎች ቆየን፡፡ ወዲያ ወዲህ ስትል በዝምታ እመለከታታለሁ፡፡ማንኪያ ታነሳለች፣ ታስቀምጣለች፣ ማማሰያ ታነሳለች እንዲሁ ወጡን ነካክታ ትመልሰዋለች፡፡ ጸጉሯ በሻሽ ጥፍንግ ብሎ ስለታሰረ ነው መሰል፣ ግንባሯ ወጣ
ብሏል፡፡ውስጤ እንደገና እቀፋት እቀፋት ይለኛል፡፡ፊቷን ኮስተር አድርጋ እንዳቀረቀረች በፍጥነት ነበር ወዲያ ወዲህ የምትለው፡፡ አውቃለሁ ማሚ እንዲህ የምትሆነው፣ እንባ
እየተናነቃት ላለማልቀስ ነው፡፡
ድንገት ከሩቅ በመጣ በሚመስል ድምፅ
“እየተዘጋጀህ ነው?” አለች፡፡
“ለምኑ? አልኩ፡፡
“ዩኒቨርስቲ መሄጃችሁ እየደረሰኮ ነው…ልብውልቅ”
ዝም ተባብለን ቆየንና፣ “መሐሪም እዚያ እተረገመ እስር ቤት የሚቆይ አይመስለኝም፤
አብራችሁ ዩንቨርስቲ መሄዳችሁ አይቀርም፡፡ አላደርስ አለኝ እንጂ ዳቦ ቆሎም በሶም አዘጋጅላችኋለሁ፡፡ ግዴለም ትንሽ ቀን አለ” ብላ ወገቧ ላይ ያሰረችውን ሽርጥ ወደ ላይ ስባ እንባዋን ጠረገች፡፡ ምን እንደምል ጨንቆኝ ዝም ብየ እንደቆምኩ፣ ድንገት የግቢው
በር ተንኳኳ፡፡
አንተ እዚሁ ቆይ" ብላኝ ሄደች፡፡ ተከተልኳት፡፡ እናቴ ነበረች፤ ነጠላዋን እንኳን በወጉ ሳትለብስ አንጠልጥላ ስትከንፍ የደረሰችው። ገና ስታየኝ፣ እጇን ልቧ ላይ አድሮ እንባዋን ዘረገፈችው፡፡
“ምንም ኤልሆነልኝም ዘንድሮ፣ በስንቱ ተጨንቄ ልሙት እኔ፣ ምን አደረኩ ምን
በደልኩ እያለች ማልቀስ ስትጀምር፣ ማሚ አቅፋ አጽናናቻት፡፡ ድንገት ዋናው ጉዳይ
ትዝ ያላቸው ይመስል፣ እኔን ትተውኝ ተቃቅፈው ይኼን ለቅሶ እስኪወጣላቸው
አስነኩት፡፡ መሐሪ ከታሰረ በኋላ የተገናኙት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ አልቅሰው ሲወጣላቸው እንግዲህ እግዜር አመጣው፣ ተይው፣ ተይው” ተባብለው ተያይዘው ወደ ቤት ገቡ፡፡
እናቴ በለቅሶ ድምፅ ዘንድሮ መቼም እንዳትታዘቢኝ” ከማለቷ

ማሚ ካፏ ተቀብላት
“አይ አንች፣ የምን መታዘብ አመጣሽብኝ፣ ሰፈሩ ባለጌ ነው እናቴ! አፋቸው አያርፍም፣ ይኼንንም አንዱ ተናግሮት በእልህ ተጋጭቶ ሌላ ጣጣ ውስጥ ሳይጨመረን፣ እንኳን እዛው ያሽልኝ፣ የዚህኛው ይበቃናል” የዚያን ቀን እናቴ ማሚን፣ “እስቲ አረፍ በይ" ብላ
የጀመረችውን ወጥ ጨራረሰችላት፡፡እያወሩ ነበር፡፡ ማሚ ረጋ ባለ ድምፅ ሳታቋርጥ ታወራለች፡፡ በተፈጥሮዋ ብዙ የማታወራ ሴት ብትሆንም፣ የዚያን ቀን ግን፣ ስለሆነው ነገር ሁሉ ሳታቋርጥ ለእናቴ አወራቻት …
“…ባልወልዳትም እናት ነኝ ብዬ በነጋታው ሳሌምን ልጠይቅ ሆስፒታል ብሄድ፣ ጥድቄ እንደውሻ አከላፍታ መለሰችኝ፡፡ ያች ምስኪን ናት ወይ ትያለሽ፡፡ ሰው ጉድ እስኪል፣ ምን ቀርቶሽ መጣሽ ብላ ኡኡ አለች፡፡ ውሻ አረገችኝ …ውሻ፡፡ ቀና ብዬ የሰው ዓይን ማየት እስከፈራ አቀርቅሬ ወጣሁ፡፡ ይሁን እናት ናት፣ አላዘንኩም፡፡ በኋላ ስሰማ ሳሌምንም ጥድቄንም ፈረንጆቹ እዚያው ግቢ ወስደው አስጠጓቸው አሉ” እንባዋን ጠራረገችና ቀጠለች፡፡

#አለሽ_ስል
አለሽ ስል፣
ድምጽሽ የነብሴ ጸናጽል ፣
.. በእቅፍሽ ውስጥ አስተኝቶኛል !
ሲያባንንሽ ነቅቻለሁ ፣ ሲያቃዠኝ ቀስቅሰሽኛል!
ማለዳ ከርቤ መአዛሽ፣ ከወፍ፡ ቀድሞ አንቅቶኛል።
ባትኖሪም!
አለሽ ስል
አመሻሽ ለንፋስ ወጥተን ፣
ጀምበርን ለአዳር ሽኝተን ፤
ጀማው አብረን አይቶናል፤
ነሀሴ በካፊያ እረጥበን፣ ጥቅምት አደይ ቀጥፈናል፡፡
ውበት፣
የተፈጥሮ ወረት ፤
ፍቅር፣
አይበጠስ ድር ፤
መሆኑን ለአድባር ነግረናል፡፡
ባትኖሪም፡፡
ምነው ታዲያ?
‹‹የለሁም” ስትይ በቃልሽ፣ ባቢሎን ሆነ እምነቴ እንደ ፋሲል ግንብ አረጀ፣ ሽንቁሩ በዛ ህይወቴ፡፡
ምነው!
🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘

#የእኔ_እግዚአብሔር
ሃጥያቴን ተቀባይ
የሁልግዜ ይቅር ባይ
ልክ አንደ እግዚአብሔሬ
አይደለችም ውዴ አይደለችም ፍቅሬ
ለእኔ እግዚሐብሔሬ
በልቤ ያኖርኩትን በልቤ መስጥሬ
ጠንቅቆ ያውቀዋል
እንኳንስ ዘርዝሬ እንኳንስ ተናግሬ
በሁሉም ቻይነቱ
በምህረቱ እኮ ነው ምስጥሩ የመኖሬ
ስማኝ እግዚአብሔሬ
የውስጤን ታውቅ የለ? ልዘዝህ ይሁንልኝ
ቅድሚያ ለድፍረቱ ይቅርታ አድርግልኝ
ባክህ እግዚአብሔራ
የመጨረሻዬ አላስቸግርህም
ይህችን ፈፅምልኝ ፣
አፍቅራ ልብ ውስጥ
አንተን ፍጠርልን
ባክህ ፈጣሪዬ።
ሃጥያቴን ተቀባይ
የሁልግዜ ይቅር ባይ
ልክ አንደ እግዚአብሔሬ
አይደለችም ውዴ አይደለችም ፍቅሬ
ለእኔ እግዚሐብሔሬ
በልቤ ያኖርኩትን በልቤ መስጥሬ
ጠንቅቆ ያውቀዋል
እንኳንስ ዘርዝሬ እንኳንስ ተናግሬ
በሁሉም ቻይነቱ
በምህረቱ እኮ ነው ምስጥሩ የመኖሬ
ስማኝ እግዚአብሔሬ
የውስጤን ታውቅ የለ? ልዘዝህ ይሁንልኝ
ቅድሚያ ለድፍረቱ ይቅርታ አድርግልኝ
ባክህ እግዚአብሔራ
የመጨረሻዬ አላስቸግርህም
ይህችን ፈፅምልኝ ፣
አፍቅራ ልብ ውስጥ
አንተን ፍጠርልን
ባክህ ፈጣሪዬ።
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
“…ባልወልዳትም እናት ነኝ ብዬ በነጋታው ሳሌምን ልጠይቅ ሆስፒታል ብሄድ፣ ጥድቄ እንደውሻ አከላፍታ መለሰችኝ፡፡ ያች ምስኪን ናት ወይ ትያለሽ፡፡ ሰው ጉድ እስኪል፣ ምን ቀርቶሽ መጣሽ ብላ ኡኡ አለች፡፡ ውሻ አረገችኝ …ውሻ፡፡ ቀና ብዬ የሰው ዓይን ማየት እስከፈራ አቀርቅሬ ወጣሁ፡፡ ይሁን እናት ናት፣ አላዘንኩም፡፡ በኋላ ስሰማ ሳሌምንም ጥድቄንም ፈረንጆቹ እዚያው ግቢ ወስደው አስጠጓቸው አሉ” እንባዋን ጠራረገችና ቀጠለች፡፡
ዝናቡም ይኼው ሳምንቱን ሙሉ ቃል ሳይተነፍስ፣ ከቤትም ሳይወጣ ጧት እዚች
በረንዳ ላይ እንደተቀመጠ ማታ ገብቶ ይተኛል፡፡ ላናግረውም ብል አይተነፍስም፡፡
መሐሪም በሄድኩ ቁጥር አባባ ደህና ነው ወይ ካጠገቡ አትለዬ እንዳለኝ ነው፡፡
እንደሸማኔ መወርወሪያ ከዚያ ከዚህ ስል እውላለሁ… እንደ እብድ ብቻዬን ማውራት
ሁኗል ሥራዬ …የምያዝ ምጨብጠውን አጥቻለሁ”
ዛሬ ጋሽ ዝናቡ የት ሂዶ ነው ታዲያ?”
“ካለወትሮው ጧት ተነስቶ፣ እስቲ ነጠላ ስጭኝ ቤተከርስቲያን ልሂድ አለኝ
እሰይ እንኳን ሄደ፡፡ እሱ መድኃኒያለም ይስማው አለች እናቴ፡፡ እኔ ግን ገረመኝ፡፡
ጋሼን ሳውቀው ጀምሮ ቤተክርስቲያን ረግጦ የሚያውቀው፣ ሰው ሲሞት ለቀብር ብቻ ነበር፡፡ ማሚ ልብሱንም ምግቡንም በሁለት ፌስታሎች ቆጣጥራ አብረን ወጣን፡፡
አብሬሽ ልሂድ ማሚ” አልኳት፡፡ እናቴ ይሉኝታ ይዟት ዓይኗን ማሳረፊያ አጥታ
ስታንከራትት፣ ማሚ የእናቴ ነገር ገብቷት ይሁን አልያም እውነቷን እንጃ፣ ሌላ ቀን! ዛሬ ቤተሰብ ብቻ ነው …አንድ ሰው ብቻ ነው የሚያስገቡት” ብላ ወደ እናቴ ገፋ አደረገችኝና እየተጣደፈች ሄደች፡፡ ገብቶኛል፣ እንባዋ መጥቷል፡፡ እሷ ወደግራ እኛ ወደቀኝ ስንለያይ ዞር ብዬ ከኋላ ተመለከትኳት፡፡ ያች በተረከዘ ረጅም ጫማና ባጭር ቀሚስ መንሳፈፍ በሚመስል መውረግረግ መንገዱ ላይ የምትነግሥ ሴት፣ አላፊ አግዳሚው ጎንበስ ቀና እያለ ወገቡ እስኪቀነጠስ ለሰላምታ የሚያሸረግድላት ሴት፣ ነጠላዋን ተከናንባና ባለማስሪያ ሸራ ጫማ አድርጋ ከኋላዋ የሚያሳድዳት አንዳች ነገር እንዳለ ሁሉ፣ ከሶምሶማ ባልተናነሰ ርምጃ ትገሰግሳለች፡፡ ብቻዋን፡፡ አንድ ልጇን፣ ጓደኛዋን፣ ሁሉ ነገሯን
ወደታሰረበት ማረሚያ ቤት፡፡
እንዴት ነው አሁን መሐሪን የሚያርሙት? ሁለተኛ ሴት እንዳትደፍር ሊሉት ነው?…ሁለተኛ ይችን ምስኪን እናትህን ትተህ የትም እንዳትሄድ ሊሉት ነው ? ጓደኛህ
ሁሉም ነገር የተደበላለቀበት በአንተ ምክንያት ነው፤ ከአሁን በኋላ ሴት ከመድፈርህ በፊት አማክረው ሊሉት ነው ምን ብለው ነው የሚያርሙት ?ምናለ እግዚአብሔር እኔን ለአንድ ጊዜ እግዚሐርነቱን በከፊል ሊያውሰኝ እና፣ ነገሮችን በአንድ ሳምንት
ወደ ኋላ ብመልሳቸው .እግዚሐርነቴን እውር ላብራበት፣ አልያም ሽባ ልተርትርበት አልልም፣ የሞተም በሰላም ይረፍ፣ እሱን አስነስቼ አላንዘፋዝፍም፡፡ አንዲት ነገር ብቻ ትንሽ ተአምር … ሮሐ ያመጣችውን ውስኪ በተአምር ወደ ውሃ፣ ቢራውንም ወደ አምቦ ውሃ ለመቀየር፡፡ ገድልም ይጻፍልኝ አልል፡፡ እንደው በምስጢር ይችን ተአምር ለማድረግ ብቻ!
።።።።
መሐሪን ሳልጠይቀው ሠላሳ ቀናት ነጎዱ፡፡ ድፍን አንድ ወር፡፡ ሰውን ፈርቼ አልነበረም፡፡ሰው ስለመሐሪ እስኪበቃው አውርቶ ወጥቶለት፣ ችላ ወደማለቱ ነበር፡፡ መሐሪን ራሱን ማየት ፈራሁ፡፡ ፊቱን ማየት ፈራሁ፡፡ የመሐሪን ፊት ማየት ፈራሁ፡፡ በቃ አንድ ቀን በጨመረ ቁጥር ፍርሃቴ በዚያው ልክ እያደገ ዓይኑን ማየት ፈራሁ፡፡ መሐሪን አለመጠየቄ ከቤተሰቦቹም አራቀኝ፡፡ ለምን አልጠየቅኸውም ቢሉኝ ምን እላለሁ? የሚል ፍርሃት፡፡ እናቴ እንኳን ከእኔ ተሽላ “አሁን ተረጋግቷል ሂደን ጠይቀነው እንመለስ” ስትለኝ፣ “አንች
ሂጂ ብያት ቀረሁ፡፡ ደርሳ እክትመለስ በጉጉት ስጠብቃት ቆየሁና፣ ከመጣች በኋላ ስለ መሐሪ ልታወራኝ እስረኛው ብዛቱ ብላ ስትጀምር፣ ትቻት ወደ ውጭ ወጣሁ፡፡
የሆነ ዝግንን የሚል ስሜት ሰውነቴን ወረረኝ፡፡ ማንም ሕመሙን ሊረዳው አይችልም፡፡ እንቁላል እራሱ ላይ
አስቀምጦ በቀጭን ገመድ ላይ እንደሚራመድ ሰው ነበር፣ ትላንቴ
ወድቆ እንዳይንኮታኮት የምታገለው፡፡ በቃ የመሐሪ ነገር “ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን” ሆነ፡፡በዚህ ዝምታ ውስጥ እያለሁ ነበር የተመደብንበት ዩኒቨርስቲ ዝርዝር በጋዜጣ የወጣው፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተመደብኩ፡፡ ውስጤ የዓመታት ምኞቱ እንደተሳካለት ሰው አልፈነደቀም፡፡ እናቴ ምናለች?
እልልልልልልል … የትም ይሁን፤ ብቻ ከዚህ የተረገመ ሰፈር ሂድልኝ እንዲህ እያለች ታዲያ አቅፋኝ ታለቅሳለች፡፡
ዓይኔ ጋዜጣው ላይ ይንከራተታል፡፡ መሐሪ ጎንደር ዩኒቨርስቲ፣ አፄ ቴዎድሮስ
ከነሠራዊታቸው መጥተው እኔ መናገሻ ላይ የተመደበውን መሐሪን ፍቱ ብለው እስር ቤቱን ሰባብረው ነፃ ቢያስወጡት በቁሜ ቃዠሁ፡፡ (ያበድኩ እስኪመስለኝ) ሮሐ መቀሌ ተመደበች ሁሉም የመቀሌ ወንድ ዙሪያዋን ከብቦ ከበሮ እየደለቀ ምድራችን ላይ
ምናይነት ቆንጆ መጣችብ(ል)ን እያለ ሲጨፍር ታየኝ፡፡ አንድ ክፍሎም የሚባል የቀድሞ ታጋይ፣ የአሁን ባለስልጣን አግብታ አስራ አንድ ቆንጆ ልጆች ትወልዳለች፡፡ ብርክቲ፣ጸጋ፣ አብረኸት፣ ረዳኢ፣ ሐየሎም፣ወልደሰንበት፣ ገብረእግዚ፣ ጎይሌ፣ አጽብሃ ወላ መለስ
እና አርከበ ትላቸዋለች፡፡ ምንም አይለውጥም፣ የባለሥልጣን ሚስት ብትሆን ጊዜን ወደ ኋላ መመለስ አትችልም፡፡ እቃዣለሁ፡፡
ዝም ብዬ ተቀምጨ፣ የስንት ሺህ ተማሪ ስም ዝርዝር፣ አንድ በአንድ አንብቤ ጨረስኩ፡፡ ስጨርስ፣ ቆንጆ ልብ ወለድ እንዳነበበ ሰው እንደገና ከላይ ጀምሬ ማንበብ ጀመርኩና ድንገት፣ ከዚህ ሁሉ ሺህ ተማሪ እንዴት መሐሪ ተለይቶ እስር ቤት ገባ?” ብዬ አሰብኩ፡፡
ዓይኖቼን ከድኘ አንዱ ስም ላይ ጣቴን አሳርፌ ዓይኔን ስገልጥ፣ “ገረመው ታደሰ አለበል”ይላል፡፡ እሽ ገረመው ታደሰ አለበል ለምን አንዲት ሕፃን ኤልደፈረም? ምናልባት ገረመው የመሽኛ ዝግጅት አልተደረገልትም ይሆናል፣ ምናልባት ገረመው መጠጥ አልጠጣም ይሆናል፣ ወይም የዚያን ቀን የገረመው ጓደኛ፣ ከገረመው ጋር አድሮ ከዚህ መዓት
ታድጎት ይሆናል፡፡ ወይም ገረመው ገና ውጤት ተቀብሎ ወደ ቤት ሲሮጥ፣ መኪና
ገጭቶት ሞቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ለሞተ ሰው ምደባ አይመጣም ያለው ማነው? ይኼው ለታሰረስ ሰው እየመጣ አይደል እንዴ …?! እቃዣለሁ፡፡
እንዲህ እያልኩ ሳስብ ነበር፣ አንድ ሕፃን በራችንን አንኳኩቶ ሰው እንደሚፈልገኝ
የነገረኝ፡፡ ሮሐ ነበረች፡፡ መንገድ ዳር ላይ ቁማለች፡፡ መሐሪን ያየሁ ያህል ውስጤ በፍርሃት እየተሸማቀቀ ወደሷ ሄድኩ፡፡ ፈገግ ብላ አቀፈችኝ፡፡ እኔም አቀፍኳት “እንች… “አንተ” ስንባባል ቆይተን ስለ ምደባ ወሬ ጀመርን፡፡
እንኳን ደስ ያለሽ” አልኳት፡፡“እንኳን ደስ ያለህ አንተም ዝም ተባብለን ቆየንና አቀርቅራ መሬት መሬት እያየች…
አብርሽ …መሐሪን መጠየቅ ፈልጌ ነበር… እታካሂደኝም?” አለችኝ፡፡ ውስጤ በደስታ
ሲናወጥ ተሰማኝ፡፡ ለምንም አልነበረም፤ ለመሐሪ በዚህ ሰዓት ከማንም በላይ ሮሐ
ታስፈልገዋለች፡፡ እኔ ራሴ መሐሪን የማየት ድንገተኛ ፍላጎት ውስጤን ሞላው፡፡ በቀጣዩ ቀን ልንሄድ ተቀጣጥረን ተለያየን፡፡
ብዙ እስረኛ ጠያቂዎች እስረኞች፣ ፊት ለፊት እየተያዩ በመደዳ የተቀመጡበት ከእንጨት ርብራብ የተሠራ የማይመች አግዳሚ ላይ፣ እኔና ሮሐ ተቀምጠን ግርግሩን ስንመለከት፣
እሰረኞች ሮሐን ፍጥጥ ብለው ሲያዩዋት ጨነቀኝ፡፡ ዓይናቸውን አይነቅሉም ነበር::
ከጠያቂዎቻቸው ጋር እያዎሩ፣ ዐይናቸው ሮሐ ላይ ነው፡፡ ያኔ ስለ ጉዳዩ የሰሙና፣

ይቺ ነች ፍቅረኛው የሚሉ ነበር የመሰለኝ፡፡ ቆይቶ ነው የሮሐ ቁንጅና እንኳን እስረኛ ነፃውንም ሰው በምኞት የሚያሰክር መሆኑ ትዝ ያለኝ፡፡
መሐሪ ከእሩቅ ሲመጣ አየሁት፡፡ እዚያ ከነበሩት፣ ከሁሉም ወጣቱ እስረኛ እሱ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሮሐ ድንገት እጄን ጥብቅ አድርጋ ይዛ ለቀቀችኝና “መጣ” አለች፡፡ አዲስ ሰማያዊ ጅንስ፣ በነጭ ስኒከር ጫማ፣ ከላይ ደረቱ ላይ የ ቪ ፊደል ያለው ጥቁር ቲሸርት ለብሶ አምሮበት ነበር፡፡ ቀጥ ብሎ ወደእኛ መጣና ሲያየን ፈገግ አለ፡፡ሁለታችንም
ተነስተን ቆምን፡፡ገረመኝ ፈገግታው ገረመኝ፡፡ ሲያየን ኡኡ! ብሎ የሚያለቅስ ነበር የመሰለኝ፡፡ ከሮሐ ጋር ተቃቅፈው ተሳሳሙ፡፡ ከእኔም ጋር ተቃቀፍን ጀርባዬን መታ መታ እደረገኝ፡፡
ፊት ለፊታችን ባለው አግዳሚ ላይ ተቀምጦ፣ ተራ በተራ በፈገግታ አየንና እሽ፡ አለን፡፡ መረጋጋቱና ፈገግታው፣ እኛ ታስረን የሚጠይቀን እንጂ፣ እሱን ልንጠይቅ የሄድን አይመስልም ነበር፡፡ ጭራሽ የእሱ መረጋጋት እኛን አሸማቀቀን፡፡ መቼም እስረኛ ጠያቂ፣
“አይዞህ አትዘን …እንዲህማ አትተከዝ፣ መታሰር በአንተ አልተጀመረ፣ ምናምን” ለማለት ነው የሚሄደው፡፡ እንዲህ ቡና ለመጠጣት እንደተቀጣጠረ ጓደኛ፣ ፈገግና ዘና ብሎ እሽ!”ለሚል ሰው ምን እንበል? እረ ፈገግታህን ቀንሰውና እናፅናናህ አይባል ነገር፡፡
ድንገት ሮሐ ወደ ፊት ሰገግ ብላ ሹከሹክታ በሚመስል ድምፅ “ለምን መሐሪ …ለምን?” አለችው፡፡ ፊቷ ተቀያይሮ እንደ ቲማቲም ቀልቷል፡፡
“ለምን ምን አላት ምንም ሳይመስለው ፈገግ እንዳለ፡፡
ለምን ሳሌምን.....

#ከራስ_ወድያ
እንዳትገረሚ እንድትደነቂ
ለማየት ጓጉቼ ከልብ እንድትስቂ
ያኮራሻል ብዬ
ቀዘመድ አዝማድ ፊት ትታያለሽ ብዬ የምርም ደስ ብሎሽ
አልማዝና እንቁ ላኩልሽ ለጥሎሽ፤
ፍቅሬ አልተገኘሽም ባህልና ልማድ የሠርግ ወግ ከልሎሽ።
እንያ ሚዚዎችሽ ምንኛ ይገርማሉ!
"ያንሳታል ጥሎሽ" ብለውኛል አሉ።
ለምትሰጠኝ ፍቅር
በሐዘን በደስታ ለመሆን ከእኔ ጋር
ቆርጣ ለወሰነች ለዕድሜ ልኬ አጋር
ከአልማዝ የላቀ ከዕንቁ የከበረ
ምን ነገር ይገኛል?!..ከምን ነገር ይሰጣል?!
የጥሎሾች ጥሎሽ ከወዴት ይመጣል?!
ሕይወትን ከመስጠት ከራስ ወድያ መጣል።
🔘በፋሲል ተካልኝ🔘
እንዳትገረሚ እንድትደነቂ
ለማየት ጓጉቼ ከልብ እንድትስቂ
ያኮራሻል ብዬ
ቀዘመድ አዝማድ ፊት ትታያለሽ ብዬ የምርም ደስ ብሎሽ
አልማዝና እንቁ ላኩልሽ ለጥሎሽ፤
ፍቅሬ አልተገኘሽም ባህልና ልማድ የሠርግ ወግ ከልሎሽ።
እንያ ሚዚዎችሽ ምንኛ ይገርማሉ!
"ያንሳታል ጥሎሽ" ብለውኛል አሉ።
ለምትሰጠኝ ፍቅር
በሐዘን በደስታ ለመሆን ከእኔ ጋር
ቆርጣ ለወሰነች ለዕድሜ ልኬ አጋር
ከአልማዝ የላቀ ከዕንቁ የከበረ
ምን ነገር ይገኛል?!..ከምን ነገር ይሰጣል?!
የጥሎሾች ጥሎሽ ከወዴት ይመጣል?!
ሕይወትን ከመስጠት ከራስ ወድያ መጣል።
🔘በፋሲል ተካልኝ🔘
#መጉደልን_ወረስኩት
አንቺን እየፈለግከ፣ . . .
ስንት እዳሪ አለማሁ፣ ስንት ችግኝ ተከልኩ ፤
ስንት ጥቅምት አብቤ፣ ማፈራት እንዳማረኝ፤
የናፍቆትሽ ግንቦት፣ አክስሞ አረገፈኝ፡፡
በናፍቆት ሰማይ ላይ፣ በምናብ ጨረቃ ፤
አልሜሽ ሳልነቃ፣
አንግሼሽ ሳበቃ ፤
እውኔ ላደርግሽ፣ መኖርሽን ናፍቄ ፤
ከያበባው ዱቄት፣ ውብ ቀለም ጠምቄ፣
ስንት ግጥም ጻፍኩኝ፣ ስንት ዜማ ደረስኩ!
አንቺን እየጠበቅኩ፡፡
ደግሞ ተመልሼ፣ . .
ምኞቴ ሸራ ላይ፣ በተስፋ ብሩሼ ፣
እምቡጥ ሳፈነዳ፤
ቅጠል ሳለመልም ፧
ኩሬ እየቆፈርኩ፣ በረሀ ሳጠጣ ፤
አንኳን እጽዋቱ፡፤ አጽም ስጋ ለብሶ፣ አለት ስር አወጣ፡፡
ምን ያደርጋል ግና . . .
ያለ ፍሬ የቀረው፣ የተከልኩት ችግኝ፤
ውዳሴ ያደረግከት፣ የቋጠርኩት ስንኝ ፤
አብሮኝ አረጀና . . .
አብሮኝ አረጀና
የናፍቆትሽ ችግኝ ፤
የናፍቆትሽ ስንኝ ፤
የናፍቆትሽ ስእል፤
መጉደልን ለመድከት፣ ሆነኝ የራስ ምስል፡፡
🔘በደሉ ዋቅጅራ🔘
ጥቅምት፣ 2012፣ አዲስ አበባ
አንቺን እየፈለግከ፣ . . .
ስንት እዳሪ አለማሁ፣ ስንት ችግኝ ተከልኩ ፤
ስንት ጥቅምት አብቤ፣ ማፈራት እንዳማረኝ፤
የናፍቆትሽ ግንቦት፣ አክስሞ አረገፈኝ፡፡
በናፍቆት ሰማይ ላይ፣ በምናብ ጨረቃ ፤
አልሜሽ ሳልነቃ፣
አንግሼሽ ሳበቃ ፤
እውኔ ላደርግሽ፣ መኖርሽን ናፍቄ ፤
ከያበባው ዱቄት፣ ውብ ቀለም ጠምቄ፣
ስንት ግጥም ጻፍኩኝ፣ ስንት ዜማ ደረስኩ!
አንቺን እየጠበቅኩ፡፡
ደግሞ ተመልሼ፣ . .
ምኞቴ ሸራ ላይ፣ በተስፋ ብሩሼ ፣
እምቡጥ ሳፈነዳ፤
ቅጠል ሳለመልም ፧
ኩሬ እየቆፈርኩ፣ በረሀ ሳጠጣ ፤
አንኳን እጽዋቱ፡፤ አጽም ስጋ ለብሶ፣ አለት ስር አወጣ፡፡
ምን ያደርጋል ግና . . .
ያለ ፍሬ የቀረው፣ የተከልኩት ችግኝ፤
ውዳሴ ያደረግከት፣ የቋጠርኩት ስንኝ ፤
አብሮኝ አረጀና . . .
አብሮኝ አረጀና
የናፍቆትሽ ችግኝ ፤
የናፍቆትሽ ስንኝ ፤
የናፍቆትሽ ስእል፤
መጉደልን ለመድከት፣ ሆነኝ የራስ ምስል፡፡
🔘በደሉ ዋቅጅራ🔘
ጥቅምት፣ 2012፣ አዲስ አበባ