አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
576 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ብዙ_ተባዙ

ሰውን በመፍጠሩ እግዜር ሚጠቀመው
ሰውም በመፈጠር ከእግዜር የሚያገኘው
አንዳች እውነት ባይኖር አንዳች ድብቅ ነገር
ምድሪቱን ለመሙላት ከብት ይበቃ ነበር።

🔘ኤፍሬም ስዩም🔘
#የሟች_ሃገር_እውነት

#ልጄ
"ሀገር ማለት ሰው ነው” ያሉህን ተቀበል፣
ሰው በሞተ ቁጥር ሀገሬ ሞተች” በል ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ለተመልካች_ሰማይ_ቅርቡ_ነው

ትውልድ ተበላሽ በሱስ ተጠመደ
ተስፋውን ለቀቅ ሄዶ ተሰደደ
ማንነቱን አጣ ህልውናወ ተናደ
የታመቀ ኃይሉ ትኩስ ማንነቱ በነነ ተነነ
እንደማይሆን ሆነ
ከንቱ የማይረባ ሲባል ሽክም ዜጋ
በተስፋ መቁረጠ በር አዕምሮውን ዘጋ
እንኳንስ ግዴታው ጠፋበት መብቱ
ፈሶ ወኔ አሞቱ
አስረካቢም ጠፋ እንኳን ተረካቢ
ከራሱ ያስፈ ለወገን አሳቢ
ግን ቢሆንም አይገርምም ይኼ ሁሉ ነገር
ከዛ ከዚህ ሆኖ ላይ ታች ብሎ
ቃሉን ተቀብሎ
እሱን ቤተሰቡን ህገሩን አስቦ
ሕልሙን አሰናድቶ አላማ ሰንቆ
ወደፊት ነጉደ አልሸነፍ ብሎ
ተማረ በረረ የልቡ ምኞቱ
ምርቃት ፍጻሜው ደስ አለው ሰዓቱ
እሱ መቼ ገባው በሀሳብስ መች መጣ
የእንዲህ ያለው ወጉ
ከመመረቅ ይልቅ ሕልም የሚያጨልመው
ሥራ መፈለጉ፡፡

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#እማማ_ዣ


#ክፍል_አምስት(የመጨረሻ ክፍል)


#በአሌክስ_አብርሃም

እቡቹ ቆንጆ እዲስ ባለሰሊጥ ዳቦ መጥቷልእንካ በነፃ ልጋብዝህ" ብላ በገዛሁት ዳቦ ላይ ልትመርቅልኝ በብረት መቆንጠጫ ትንቦክ የሚል ዳቦ አነሳች፡

አይ እልፈልግም” ብዬ የገዛሁትን ብቻ አንስቼ ሮጥኩ! ከኋላ ሳቋ ይሰማኛል… የዚህ ልጅ ኩራቱ … ካካካ !

#በፖሊስ
እማማ ዣ፣ ድሮ ድሮ ለግንቦት ልደታ በግ አሳርደውና ነጭ ልብስ ለብሰው ሰፈሩን ሁሉ ስለሚጋብዙት፣ ግንቦት ልደታ ራሳቸው እማማ ያንዣቡ ይመስሉኝ ነበር:: ለምን እንደሆነ እንጃ፣ ከሆነ ዓመት በኋላ ግን መደገሱን እርግፍ አድርገው ተውት:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እንደበፊቱ መልበስና መዘነጡንም ተውት፤ አልፎ አልፎ ወጣ ሲሉም ቀለል ያለ የፈረንጅ ቀሚስ እንጂ እንደበፊቱ የሐበሻ ቀሚስ አይለብሱም ነበር! ጎረቤቱ ይኼንንም
አፈ-ታሪክ ከሚመስል ታሪካቸው ጋር አገናኘው። … ወሬው ብዙ ዓይነት ነው!

ታዲያ አንድ ቀን እቤታቸው ገብስ ሊወቅጥ ከመጣ ወዛደር ጋር እያወሩ(ወዛደሩን ጠርቼው ያመጣሁት እኔው ነኝ ሻይ እና ዳቦዬን ይዤ በረንዳው ላይ ተቀምጫለሁ፡፡
ወዛደሩ ገብሱን እንጨት ሙቀጫ ውስጥ እያስገባ በሚገርም ኃይል ይወቅጠዋል፡፡
የሙቀጫው ንዝረት በረንዳው ድረስ ዘልቆ፣ ስሚንቶው ወለል ላይ ያስቀመጥኩት ብርጭቆ ውስጥ የነበረውን ሻይ በቀስታ ያንቀሳቅሰው ነበር! ….ክንዱ ላይ ከጠቀለለው
ካኪ ሸሚዙ ሥር ብቅ ያለው ፈርጣማ ከንዱ የሚሰነዝረው ምት፣ የእማማ ዣን ዘመን ያስቆጠረ የቤት ምሰሶ ይነቀንቀዋል … እማማ ዣ በረንዳቸው ላይ ወገባቸውን ይዘው ቆመው፣ “እሰይ! እንዲህ ነው እንጂ የሥራ ስው እያሉ ያደንቁታል! በመኻል እናቴ ጠርታኝ እቤት ደርሼ ስመለስ፣ እማማ ዣ ለወዛደሩ ሻይ በዳቦ አቅርበውለት፣ ሞቅ ያለ ወሬ ይዘው አገኘኋቸው። የሙቍጫው ዘነዘና በከፊል የተፈተገ ገብስ የሞላውን ሙቀጫ ደገፍ ብሎ ቁሟል፡፡ እማማ ዣ በወሬ ተጠምደው መግባቴንም ያዩ አልመሰለኝም፡፡ አልያም ቢያዩኝም ወሬው በልጦባቸው ችላ ብለውኛል፡፡ በሁለት ነገሮች በጣም ተገረምኩ፡፡የመጀመሪያው ያስገረመኝ ነገር፣ የእማማ ዣ አቀማመጥ ነበር፡፡ በረንዳቸው ላይ ያለው ከፍ ያለ የቀርቀሃ ወንበር ላይ እንኳን ደጋግመው በጨርቅ ካላራገፉና “ይቀዘቅዘኛል” እያሉ ትራስ ቢጤ ጣል ካላደረጉ በቀር የማይቀመጡት ሴትዮ፣ እግር ሲረመርመው በሚውለው የበረንዳው ደረጃ ላይ፣ ያውም ምንም ነገር ሳያነጠፉ ወርደው ተቀምጠዋል:: ወዛደሩ ከሳቸው ዝቅ ብሎ ለአበባ መደብ መከለያ በተደረደረው ቀያይ ጡብ ላይ ነበር አረፍ ያለው፡፡ ታፋና ታፋው በቁምጣው ሙልት ብሎ ደህና ስፖርተኛ ይመስላል::
ሁለተኛው ግርምት፣ ለወዛደሩ ስለ ባላቸው እያወሩት ነበር፡፡ እዚህኛው ላይ ከመገረምም አልፌ ትንሽ ተበሳጨሁ፡፡ ከመጀመሪያው መስማት ባለመቻሌ፤ ወሬያቸው መኻል ላይ ደርሶ ነበር::

“…እኔ ልጅት አንዴ ከሰነዘርኩ
እንኳን ሰው ሰይጣንም አይመክተኝ ...ያንን ባል ተብዬ
ወተፋንም (የድሮ ባላቸውን ነው) “ አቤት ቁመና… አቤት መልክ .…” እያለች ምድረ
ኮማሪ ስታቀብጠው ጊዜ፣ እኔ ያንዣቡ ላይ ሊንቀባረር ከጄለዋ! አንድ ቀን ለባብሶ መቼም አለባበስ ከሱ ወዲያ ላሳር ነው…ደረቱን፣ ይኼን ትከሻና ትከሻውን ያየህ እንደሆነ፣ እንዲህ እንዳንተ ሳንቃ ነው…” ብለው ለወዛደሩ ዳቦ ከተከመረበት ሰሃን ላይ አንድ ዳቦ አንስተው ጨመሩለት፡፡
ወጋቸውን ቀጠሉ “አንድ ቀን እዚህ ነኝ እዛ ነኝ ሳይል፣ በዋለበት አድሮ አረፋፍዶ
ወደምሳ ሰዓት መጣ፡፡ ጭራሽ ይኼ ሲገርመኝ ..እልፍ ብሎ ገብቶ ተኝቶ ዋለና ...ወደ አመሻሹ ላይ ተነስቶ፣ ካሁን አሁን የት እንዳደረ ሊያወራኝ ነው ብዬ ስጠብቅ፣ ሙሉ ልብሱን ግጥም አርጎ ለባበሰና ሚኒስቴር መስሎ ..ደህና ዋይ እንኳን ሳይለኝ ውልቅ ብሎ ሊሄድ ...

“ምን ሁነሃል!? …ወዴት እየሄድክ ነው ከመሸ …?” አልኩት… እንዲህ ወደ ማጀት አንዲት ደዘደዝ ሠራተኛ ስታጨማልቀው ምኗም አላምረኝ ብሎ ወዲያ ገፍቼ ራሴ ሊጥ እያቦካሁ እጄ ሁሉ ሊጥ ሁኗል ያመልጠኛል ብዬ ለቅለቅ እንኳን አላልኩትም፣ የትስ ብሄድ አንችን ማን ቦሊስ አረገሽ? ..አርፈሽ ጓዳሽ ግቢና ሊጥሽን አቡኪያ” ብሎኝ ጎምለል ጎምለል እያለ ውልቅ፡፡ እኔ ያንዣቡ እንኳን እንዲህ ከፍ ዝቅ ሊያረገኝ ቀርቶ፣ አፍንጫው መሬት እስኪነካ አሥራ ሁለተዜ ሰግዶ ነው ያገኘኝ.አሁን እጁ አስገባኝና፣ ቀን ከሌት የልቡን አድርሶ መናቁ ነዋ! ….ብልጭ አለብኝ! እንዲያው አንዳች ነገር ዓይኔ ጋረደኝ ..ሰማይ ልሁን መሬት አላውቀውም ንቀቱ ማጣጣሉ አይደለም፤ በዓኑ ያቀለለኝ ነገር ... አስተያየቱ አመመኝ! እዚህ ደጅ የተከመረ የቤት ጥራጊ እንኳን እንዲ አይታይም. እንደ ገረድ ጓዳ ለጓዳ ስንፏቀቅ፣ እውነትም ባሪያ መስዬው እንደሁ እንጃ
ደሞ አለ ... “ማን ቦሊስ አረገሽ?…ይኼ አንኮላ! ሴት ልጅ ለክብሯ ማንም ባይሾማትም ቦሊስ መሆኗ መች ገባው የማቦካና የምጠፈጥፈው ለሱ አልነበረም እንዴ? ... ሰው ካለ ነገሩ የት ትሄዳለህ ብሎ አይጠይቅምኮ፣ የኔ ብዬ ባከብረው ነበር፡፡ ማደሩ አንገብግቦኛል፣ ጭራሽ ይኼ ሲጨመር ደሜ ፈላ፣ ደርደር ብዬ ወጥቼ እዚህ ታዛው ላይ አዲስ ተፈልጦ ከተከመረው ፍልጥ አንዱን ላጥ አድርጌ አንድ ጊዜ ጀርባውን ባቦንነው የናቴ ልጅ .…የሰው ገላ እንደ ነጋሪት ሲኖጋ የዛን ቀን አየሁ!

“አላተረፍሽውም!” አለና፣ ወዛደሩ በግርምት ዳቦውን መብላቱን አቁሞ አፉን ከፈተ፡፡

“…ፍልጡ ሲያርፍበት እንደ ወንድ እንኳ ዘራፍ አላለም፡፡ ከዚህ ከኔ በር የበረረ፣ እዚህ ።አሁን ዘመናይ ሱቅ የተባለውጋ ቆመ፡፡ ልምረው ነው …ተከተልኩት ...ሰው አዬኝ . አላዬኝ ብሎ ዞር ዞር አለና፣ የሸሚዙን ኮሌታ አስተካክሎ “እብድ!” ብሎኝ እርፍ! .
አታምጣው ስለው አምጥቶ ቆለለው ኣሉ ካልክማ ብዬ አበድኳ! … አይሮጥ፣ ሰዎች አሉ፣ ኀፍረት ያዘው፣ ….አይቆም፣ ፍልጡን ፈራ፤ እንዲሁ ሲደናገር ደርደር ብዬ የበላሁ የጠጣሁትን አንቆራጠጥኩት! ሲብስብት እንደሴት እሪሪሪ ብሎ ሲጮህ ያየኸው እንደሆነ፣ ያ ጎምላላ፣ ያ ወንዳወንድ ነው ወይ ያስብላል ...

የአንድ እግሩን ጫማ አረጋሽ የምትባል እዚህ ታች አለች .እሷ በር ጥሎ እግሬ አውጭኝ ሊያመልጠኝ መሰለህ ... እንዳራስ ነብር ተወርውሬ ከረባቱን ጨመደድኩና (መቸስ አዙሮ አያይም እንጂ አንገቱ ለከረባት የሰጠ ነበር) እንደ በግ እየጎተትኩ አንጄቴ የጤሰውን ያህል፣ እስኪበቃኝ አበራየሁት! የሞት ሞቱን እየተውገረገረ ተነስቶ በረረ..ይኼው ስንት ዓመቱ ከዚያን ቀን ጀምሮ ይኑር ይሙት እንጃ፣ ጠፋ ጠፋ! አንዷ ኮማሪ
ጋር ጠቅልሎ ገብቶ የቢራ ብርጭቆ እያጠበ ይሆናል! ምናሻኝ ለምን እግር አያጥብም!
ያንዣቡ ምን እዳየ ..ከዛ ወዲያ አንድ ወንድ ንክች ሳያደርገኝ ይኼው ቅብርር ብዬ አለሁ” አሉ፣ ፉከራ በሚመስል ድምፅ ...አንገታቸውን በኩራት እየሰበቁ።
ኧረ አንችስ እሳት ነሽ የናቴ ልጅ!” አለ ወዛደሩ በስሜት ተውጦ! እንዴዴዴዴ...ቅድም ገብስ የሚወቅጥበትን ዋጋ ሲነጋገሩ …” አንቱ!” እያለ አልነበር ሲያናግራቸው የነበረው?
…ከምኔው “አንቺ!” አለ? ብዬ ገረመኝ!
እየገረመኝ ይኼን ሰምቼው የማላውቅ አዲስ ታሪካቸውን እያብሰለሰልኩ ማታ ሁሉ እንቅልፍ አልወስድ ብሎኝ አመሸ ።

#ዘጭ
በቀጣዩ ቀን፣ እማማ ያንዣቡ ሲጀምሩና ሲያቋርጡ የኖሩቱን የጃንሆይ ታሪክ፣ ድንገት አውሩልኝ ብዬ ሳልጠይቃቸው፣ ከመሬት ተነስተው ያወሩልኝ ጀመ፡ር …

አንድ ቀን አገር ሰላም ብዬ እዚህ እታች ባንኩ ቤት ደርሼ ስመለስ ብለው ሲጀምሩ ሌላ ወሬ መስሎኝ ነበር።
👍2
አንድ ዘባተሎ ድሪቶውን መንገድ ለመንገድ የሚጎትት እብድ ይሁን ለማኝ እንጃለት
… አንች! …ብሎ ጠራኝ …ሰው አንች ሲለኝ አልወድም።

'ምን ሆንከ? አልኩት፣ ለእብድ ፊት መስጠት ጥሩ አይደለም፡፡

“ጃንሆይ፣ ከዙፋኑ ዘጭ አለ!” ብሎ ከራማዬን ገፈፈው፡፡

ሂድ ወዲያ ዘላን ዘጭ የሚያደርግ ዘጭ ያርግህ እቴ!” ብዬ ተቆጣሁ፡፡ አባባ ጃንሆይን ሲናገሩብኝ አልወድም:: እርምጃዬን ፈጠን ፈጠን ባደርግ፣ ያ ዘባተሎ ሊተወኝ መሰለህ ከነተሸከመው ድሪቶ ከኋላዬ ጀፍ ጀፍ እያለ

ህህህህህ …ጃንሆይ ዘጭ! …ሽማግሌው! ..ዘጭ! …ጆሮውን ይዘው ዘጭ አደረጉት!
.ህህህህ ጭብጦ በምታህል መኪና እንደ ጤፍ ጭነው ወሰዱት ህህህህህ…”

ድሮውንም እብድና ውሻ ዘሎ ሰው እንዳዋረደ ነው ብዬ ወደ ቤቴ ገባሁ! ..…ለካስ ያ ወፈፌ እውነቱን ኖሯል ራዲዮ
ነሺ… ቴሌቢጅን ነሽ፣ ጃንሆይ ተዙፋናቸው ወረዱ እያለ ከበሮ ይደልቃል፡፡ ይኼውልህ እኒያ ተሰማይ ተምድር የገዘፉ ንጉሥ በምድረ ኩታራ ከዙፋናቸው ወርደው አረፉት! ጊዜ ዝቅ ሲያደርግ መርዶህን እንኳን ደህና ሰው አያረዳልህም፡፡ እንዲህ ቤተ መንግሥትህን ማንም ይረግጠዋል ..ዙፋንህ ላይ ማነው
ቂጡን ያልጠረገ ግስንግስ ይወዘፍበታል ነገር ዓለሙ ዘጭ አለ! አገር ምድሩ ዘጭ
ለእግራችን የተጠየፍነውን በቂጣችን ተደላድለን ዘጭ አልንበት! አንድ ተፈሪን ያወረዱ መስሏቸው፣ እችን ልቃቂት አገር እራሷን ይዘው ሲጎትቱ ተዘክዝካ ውሏ ጠፋ በዚ ቢመዙ…. በዚህ ቢመዙ እንደ ፀጉር ተንጨፍርሮ ሁሉም ውል ነኝ አለ ..ቢጎትቱት ላይፍታታ፤ የጃንሆይ ነገር እንዲህ ሁኖ ቀረ እልሃለሁ… አቡቹ!” አሉና ተከዙ…. ትክ ብዬ አየኋቸው፡፡ ፀጉራቸው ገብስማ ሆኗል! ዓይናቸው ዙሪያውን ኩል ተኩሎ ነበር ከዚህ በፊት ተኩለው አይቻቸው አላውቅም።

“አቡቹ”

"እ"

ሂድ ዳቦ ገዝተህ ና” ብለው ድፍን አዲስ አሥር ብር ሰጡኝ፡፡ ቦርሳቸው
አልጠፋቸውም፤ በትክክል ሂደው ከተቀመጠበት ነበር ያነሱት፡፡ እየበረርኩ ሄጀ አፍታ " ሳልቆይ ባዶ እጄን ተመለስኩ

“ምነው ባዶህን መጣህ?” አሉ፣ አንዴ እኔን አንዴ መልሼ የዘረጋሁላቸውን ብር
እየተመለከቱ፡፡

“የዘመናይ ሱቅ ታሽጓል”

“ምነዋ?”

“ስሩ ላይ 'ግብርዎትን በወቅቱ ስላልከፈሉ ታሽጓል የሚል ወረቀት ተለጥፎበታል” አልኩ፡፡

“በል ብሩን ይዘህ ሂድና ከወደድከው ቦታ ብስኩትም ቢሆን ገዝተህ እቤትህ ቁጭ በልና ብላ…መልሱንም ስክርቢቶ ግዛበት” አሉኝ፡፡ ባለማመን አየኋቸው ..ከዛ በፊት በሕይዎት ዘመኔ ድፍን አሥር ብር ኖሮኝ አያውቅም፡፡የድፍን አዲስ አሥር ብር ጌታ! እቤቴ እስክደርስ ሦስት አራት ጊዜ ባለማመን ብሯን እያየሁ ተፈተለኩ፡፡

የዚያኑ ቀን ማታ ወደ ምሽቱ አንድ ሰዓት ይሆናል ...ሁልጊዜ እንደማደርገው ቤታችን በር ላይ ተቀምጬ እግሬን እታጠባለሁ፡፡ ታጥቤ እንኳን ጨርሻለዉ የታጠበ እግሬን ቆሻሻ እንዳይነካው አንፈራጥጬ ተቀምጬ እስኪደርቅ ቁጭ ብዬ ጥቁሩ ሰማይ ላይ የተዘሩትን ከዋክብት አያለሁ፡፡ ድንገት አንድ ሰው በጨለማው ውስጥ ከወደታች
መጥቶ፣ ወደ ማማ ዣ ቤት ሲጣደፍ ተመለከትኩ! በዓይኖቼ ጨለማውን እየሰረሰርኩ ማንነቱን ለመለየት ስታገል… ከአንድ ቤት መስኮት በመሹለክ የጨለማው ወሽመጥ መስላ መንገዱ ላይ የተጋደመች ብርሃን በእርምጃ ሲሻገር ባንዴ ለየሁት! ወዛደሩ ነበር!…ገብስ ወቃጩ ወዛደር! ...

በዚህ ምሽት ምን አመጣው…የእማማ ዣን የግቢ በር ከፍቶ ሲገባ፣ ባለቤት ነበር
የሚመስለው፡፡ እርምጃው ከሐሳቤ ይፈጥን ስለነበር፣ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ተጋብቼ ረዘም ላሉ ደቂቃዎች በገባበት በር ላይ ዓይኔን ተከዬ ቆየሁ፡፡ ድንገት “ሰውዬው ሌባ ሲሆንስ!?” የሚል ሐሳብ ወደ አእምሮዬ መጣ፡፡እንደውም ሰተት ብሎ የገባው ሌባ ቢሆን ነው፤ ሌባ መቼም አንኳኩቶ አይገባ!! ትላንት ሲሰልላቸው ውሎ በጨለማ ሊዘርፋቸው ተመልሶ ቢሆንስ? ከሐሳቤ እኩል ሰውነቴም ከተቀመጠበት
ተስፈንጥሮ ተነሳ።

ግራ-ቀኝ ሰው መኖር አለመኖሩን እየተመለከትኩ ወደ ግቢው በር ሮጥኩ፡፡ መኻል መንገድ ላይ ስደርስ፣ ግቢው ከውስጥ ቊጭ ብሎ ሲቆለፍ ሰማሁ… ቆም አልኩ .. ትንሽ ጆሮዬን ቀስሬ አዳመጥኩና ወደ ግቢው በር ሄጄ ልከፍተው ብሞክር፣ በሩ በቁልፍ
ተዘግቷል. ይኼ በር በዚህ ሰዓት በጭራሽ ተዘግቶ አያውቅም ነበር፡፡ ቁልፉ እማማ ዣ አንገት ላይ ይንጠለጠልና ቁልቁል ወደ ጡቶቻቸው መሀል ይጠፋል! ማን ሌባ አስገብቶ በሩን ከውስጥ ይቆልፋል? ...ምናልባት ዓይኔ ይሆናል እንጂ የገባም ሰው ላይኖር ይችላል፡፡ ጆሮዬን በሩ ላይ ለጥፌ ሳዳምጥ፣ እማማ ዣ ለስለስ ባለ ድምፅ “ጠፋብህ እንዴ ቤቱ!” ሲሉ ሰማኋቸው! በቀስታ ዞሬ ወደ ቤቴ ተመለስኩ .. የታጠበ ርጥብ እግሬ
አፈር ቅሞ መቆሸሹ ትዝ ያለኝ፣ እቤት ስገባ ነበር፡፡ በባዶ እግሬ ነበር የሮጥኩት!

አንዱን የሰፈር ማቲ ጠርቼ እኪሴ በተቀመጠችው ድፍን አሥር ብር “ኦሞ ገዝተህ ና” ማለት አማረኝ ..ለእግሬ!!!

💫አለቀ💫
አትሮኖስ pinned «#እማማ_ዣ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት(የመጨረሻ ክፍል) ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም እቡቹ ቆንጆ እዲስ ባለሰሊጥ ዳቦ መጥቷልእንካ በነፃ ልጋብዝህ" ብላ በገዛሁት ዳቦ ላይ ልትመርቅልኝ በብረት መቆንጠጫ ትንቦክ የሚል ዳቦ አነሳች፡ አይ እልፈልግም” ብዬ የገዛሁትን ብቻ አንስቼ ሮጥኩ! ከኋላ ሳቋ ይሰማኛል… የዚህ ልጅ ኩራቱ … ካካካ ! #በፖሊስ… እማማ ዣ፣ ድሮ ድሮ ለግንቦት ልደታ በግ አሳርደውና ነጭ…»
#ፍራቻ

አብሬህ እያለሁ እምነት ካልጣልክብኝ
ያንተው ነኝ እያልኩህ ከተጠራጠርከኝ
እውነቴን እያየህ እፈራለሁ ካልከኝ
ፍሬ ቢስ ድርጊትህ ከልክ ከወጣ
እኔም ልፍራ መሰል ፍራቻህ ቅጥ አጣ።
#ያለ_እኔ

ዐይን ዐይኔን እያየ ቅልስልስ እያለ
በውብ ቃላቶቹ በዐይኑ እያባበለ
ሕይወቴ ባዶ ነው ያላንቺ አልኖር ቢለኝ
ያለ እኔ እማይኖሩት ብዛታቸው ገርሞኝ
አትኩሬ አስተዋልኩት
ላሁኑ ካለኔ ከማይኖር ከዛኛው ነኝ አልኩት።

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#ስጦታ


#በእየሩስአሌም_ነጋ

ልጆቿን በግራና በቀኝ ክንዶቿ ላይ አቅፋ እንደተኛች የሰከረውን ባሏን ከአንገቷ ቀና ብላ አየችው፡፡ ባሏ በከፈተው በር
ሰተት ብሎ የገባው፥ ነፋስ ፊቷን ሲገርፋት፣

“ኧረ ልጆቼን ብርድ እንዳታስመታቸው?” ብላ ውርጩን በእጁ ትከላከል ይመስል ክንዷን መከተች።
“ምናለበት ልጆች ናቸው። ልጅና ፊት አይበርደውም ሲባል አልሰማሽም ድንበሬ?” አለ እንደ ሰንበሌጥ እየተወዛወዘ፡፡
“እላያችን ላይ እንዳትወድቅ!”
“ይልቅ ድ..ድንበርዬ ህእ... እራቴን ህእ ብ.ብትሰጭኝ...”
አላት ስርቅታ የሚቆራርጠውን ትንፋሹን እየታገለ፡፡
“የምን እራት?”
“እራት ነዋ! ህእ.የሚበላ ትንሽ... ትንሽ ቂ…ቂጣም ቢጤ
ሊሆን ይችላል
“ይቀጥቅጥህ አንዳች! እሱንስ የምታገኘው ሲኖር አይደል።ወገኛ”
“ህእ...በናትሽ አት...አትቀልጂ?” ፈገግ ለማለት ሞክሮ አልተሳካለትም፡፡
“ምነው ያገሬ ጅብ በበላህና በተገላገልኩ” እሱን ፊት ለፊት ላለማየት ጥረት አደረገች፡፡
ደረቱን በእጁ እየደቃ፣ ጭንቅላቱን በየአቅጣጫው እያወዛወዘ፣
“ምነው የኔ ሸጋ አጋርሽን! መ..መከታሽን!” አላት፡፡
“እ..ጉድ እቴ! እንዲህም አድርጎ አጋር የለ! አጋር ሳትሆን ችጋር ነህ አንተ?”

“እኔ ችጋር?.…እኔ?” ዐይኑን እያጉረጠረጠ
ግድግዳውን ደቃው፡፡
“ስነ-ስርአት! ይህን ያጎነበስ ግርግዳ እንዳትጥልብን!”
“ወድቆ ህእ... ባረፈና በተገላገልኩ፡፡ እንኳን እሱ እኔም እኔም ወ..ወድቄያለሁ”
“እሱ ቢወድቅ አገልግሎ ነው። አንተ ምን ስርተሃል?”
“ኧከከከከ! እንዴት ንቀሽኛል ባክሽ?”
“ኤድያ! እርባና ቢስ!” ቀስ ብላ ክንዶቿን ከልጇቿ ስር አነሳችና እዚያው ቁጭ አለች፡፡
“ገደልከኝ በቁሜ ቀበርከኝ” አለች በንቀት እያስተዋለችዉ።
“አሁን ስለቀብር የሚ..የሚወራበት ጊዜ ነው?"
“ጉድጓድ ያስገባህ ያባቴ አምላክ! የተረገምክ!” ከተቀመጠችበት
ተፈናጥራ ስትነሳ የረገበው ሽቦ አልጋ ሁለቱን ልጆች ወደ መካከል
አደባልቆ አስተኛቸው፡፡
ብቻ እንዳትመችኝ?” አለና እጁን እያወናጨፈና እየተንገዳገደ፣ በቤቱ ውስጥ ወዳለችው ብቸኛ ወንበር አመራ።
“አሁን ቁጭ ማለት` አያስፈልግም ፤ ተነስና ተኛ!” አለችው
ወዳልጋው እያመለከተች።
“አልተኛም! አልተኛም! እስቲ ምን ምን ይዋጥሽ?”
“ተገትረህ እደር! ግን ከአሁን በኋላ
አንድ ልፍለፋ እንዳልሰማ!”
“እሰይ! ይኸው ነው የቀረሽ አንደኛሽን አትትለጉሚኝም? እ...”
ወንበሩ ላይ ሲቀመጥ መቀመጫው ወደታች ወርዶ እሱን ወንበሩ
ውስጥ ቀረቀረው።
የተንጨፈረሩ እጆቹንና እግሮቹን በመጸየፍ እያየች፣

“ወንበሬን ታነክተው? አንድ ስው ማሳረፊያ ቢኖረኝ! አይ እንደው ፈጣሪዬ በምኑ በተረገመው ቀን ነው ከአንተ ጋር
የተገናኘሁት? አይይ...ይ!” እያማረረች ተፈቶ የተንዘላዘለውን ሻሿን ማሰር ጀመረች፡፡
ገስጥ ከተወተፈበት ወንበር ውስጥ ለመውጣት ተፍጨርጭሮ፣
የወንበሩን ማያያዣ እንጨቶች የእንቁላል ቅርፊት ሰብራ እንደምትወጣ ጫጩት ሰባብሮ ወለሉ ላይ ተንደባለለ።

ድንበሬ ዕይኗ እያየ ወንበሯ ሲበተን በንዴት የምትይዘውንና የምትጨብጠውን አጣች።
ስሚ! የሚበላ ብያለሁ የሚበላ! በኋላ ነገር እንዳ...እንዳትፈልጊኝ!”
“አየህ አይደል የሠራኸውን ብልግና? መስከሩንስ የራስህ ጉዳይ
ነው፣ አቅተኸኛል። የዚህን ቤት እቃ በሰከርክ ቁጥር ማውደምህ
ነው የሚያንገበግበኝ! እሺ ምን ቀረህ ንገረኝ? ምን ቀረህ?”
“አንቺ! አንቺ ብቻ ነሽ የቀረሽኝ፡፡”
“ወቸ ጉድ! አንተን በዱላ ወቅቶ ወቅቶ መጣል ነበር!”
ሂጅና ያባትሽን ጤፍ ውቂ! አላ..ላበዛችውም?” በፍርሃት
ድምጹን ቀነስ አድርጎ ተናገራት፡፡
“አቤት ንቀትህ? አቤት! ንግግርህ እንኳ ለከት የለው...”
“እንዴት አይነቷ ሞኝ ነሽ ባክሽ? ህእ ...ሰክሬ ለከት እንዲኖረኝ ትፈልጊያለሽ?”
“ድጋሚ እንኳን እንዳይሰራ አድርገህ እኮ ነው የለያየኸው።
ነፍስና ስጋህን እንደዚህ ይለያየው!” የተበታተኑትን እንጨቶች እያነሳች ተመለከተችና አንዱን የወንበር እግር አንስታ “በዚህ ነበር ወገብህን ማለት!” አለችው።
ገስጥ በንዴት ያፈጠጠችውን ሚስቱን በልምምጥ ዐይን ዐይኗን እየተመለከተ “አንቺ .....አንቺ አታረጊውም አይባልም፡፡ ሰክሬ በመጣሁ ቁጥር ያንቺ ዱላ ነው ያማረረኝ ደግሞስ እራሽው
በሰጠሽኝ ብር ነው የሰ...የሰከርኩት” አላት።

“ጨምረህ ጠጥተህ እንጂ እኔ የሰጠሁህ ብር ይህን ያህል የሚያሰክር አልነበረም፡፡ ደግሞ ለኔ ማዘን የጀመርክ መስሎኝ እንጂ እንደተጫወትክብኝ መች ገባኘ ነበር!” አለች የያዘችውን የወንበር
ስባሪ በቁጭት እያያች።

“በይ አሁን እሱን አስቀምጭና...”
“ያስቀምጥህ ያባቴ አምላክ!”
“ሲያስቀምጠኝም ጥሩ መቀመጫ ፈልጎ ነው፡፡ እንዳንቺ ወንበር ሲቀመጡበት የሚንቃቃ ....።”
“ተቅማጥ ያስቀምጥህ ነው ያልኩት ደግሞ ላንተ መቀመጫ ልመኝ እርጉም የተረገምክ !”
“እርግማኑ እንኳን አይጎዳኝም።”
“ታዲያ ወንበሬን አንክተህ የምለቅህ መስሎኻል?”
“እንደው በፈጣሪ ይዤሻለሁ! እሱ ወንበር ያንቺ ብቻ ነው?
ይልቅ አሁን ልጆች ከ...ከሚረበሹ...”
“ድንቄም! ለልጆችህ ትቆርቁረህ?”
“የኔ ቆ...ቆንጆ!” አለና ትንሽ ፈገግታ ብልጭ አደረገላት።
“ምን? የኔ ቆንጆ!? የኔ ቆንጆ!” እያሽሟጠጠች አየችው።
“ምነው? የኔ ቆንጆ ማለት በኔ አልተጀመረ...”
ገርሟት ከልቧ ሆዷን ደግፋ ሳቀች፡፡
“የኔ ቆንጆ መባል እንዲህ የሚያፍነከንክሽ መሆኑን ባውቅ ኖሮ
ያለእረፍት የኔ ሸጋ፣ የኔ ጠንበለል፣ የኔ ዛጎል ዐይን እልሽ ነበር፡፡”
“ግን ማነው አሰልጥኖ የላከህ? አሁን በስተርጅና ይሄ የሽንገላ
ቃል ያስደስታታል ብለህ ነው? የሰደብከኝ እንጂ ያሞገስከኝ እንዳይመስልህ።” የግንባሯ ላይ ደምስሮች ተገታተሩ።
“ወይ ጉድ! ድሮስ ሲያሞግሱሽ መች ትወጃለሽ?”
“ያንተን ሙገሳ ከስድብ እንጂ...”
የምትናገረውን ሳትጨርስ
“ያንችን ጭቅጭቅ ለማምለጥ ውጭ ወጥቼ ንፋስ መቀበል ይሻለኛል።" ብሏት ተመልሶ ወጣ፡፡ ድንበሬ ያዛሬው መስከሩ
ምክንያት እስዋው እንደሆነች ስታስበው በራሷ ተናደደች፡፡

ትላንትና ምሽት ሳይሰክር ገብቶ አስደስቷት ነበር።እንደዛሬው አልሰከረም፡፡ ገና እንደገባ፣

ይህንን ልብስ ለኪው።” አላት፡፡
“ምን?” የተናገረውን ቃል ማመን አቅቷታል፡፡
“ለኪው!” የያዘውን ፌስታል አቀብሏት አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ አለ፡፡
“ከየት አመጣኸው?” አለች ፌስታሉን ከዐይኗ ስር ራቅ አድርጋ እያየችው።

“ከየትም ይምጣ! ብቻ ለኪው።”
ከዚህ በፊት ልብስ ገዝቶላት ስለማያውቅ እየገረማት የተቋጠረውን ላስቲክ ለመፍታት መታገል ጀመረች። የፌስታሉ
ቋጠሮ አልፈታ ሲላት ቀዳ አወጣችው። አንድ ሙሉ ቀሚስና ሹራብ ነበር፡፡ በጣም ገርሟት ገስጥን አየችው፤ በሙሉ ፈገግታ እያያት በኩራት ተኮፍሷል፡፡
“እስቲ ንገረኝ በባትህ ሞት? እውነት ለኔ ገዝተኸው ነው?”
“አንቺ ደግሞ ብር ባይኖረኝ እንጂ... ላንቺ ሳላስብልሽ ቀርቼ ነው?”
ልብሱን አገላብጣ አየችው።
ሹራቡንም ልበሽው” አላት።
ለበሰችውና እንባ ባቆረ ዐይኗ አጨንቁራ አየችው፡፡ የደስታ እንባ በዐይኗ መሙላቱን ሲመለከት እሱም በደስታ ፈካ፡፡
“ስንጋባ አንድ ልብስ ብቻ ነበር የጣልክልኝ አሁን በስንት
ዓመትህ ጸደክብኝ?” አለችው፡፡
“እስይ የኔ ቆንጆ! አሁን ደስታው ይቆየን እርቦኛል፡፡” ሲላት ከልጆቿ የተረፈ ነገር ጠራርጋ ሰጠችውና ለሊቱን ደስ ብሏቸው
አደሩ፡፡

በነጋታው ስራ ለመሄድ ሲወጣ ከደስታዋ የተነሳ እጇ ላይ ያለውን ብር አንስታ አንድ ሁለት ብርሌ ጠጅ ጠጣበት ብላ
ሰጠችውና በቀራት ብር ለልጆቿ የሚበሉት ነገር ለመግዛት አዲስ ልብሷን ከእግር እስከ
👍21
ደረቷ ደጋግማ እያየች ወጣች፡፡ ከሱቁ አጠገብ
ልትደርስ አራት እርምጃ ሲቀራት የልብስ መደብር ውስጥ የምትሰራ
የምታውቃት ሴት ከመደብሯ ውስጥ እንዳለች አንገቷን ብቅ አድርጋ
ሰላምታ አቀረበችላት። ድንበር በፊት ትለግሳት ከነበረው ሰላምታ
ለየት ያለ የሞቀ ሰላምታ ሰጠቻት።
አሁን ከሰው እኩል የመሆን ስሜት ተሰማኝ፡፡ ፈገግታዬ እንኳን እንዴት እንደጨመረ! አለች ለራሷ የሰላምታዋን አጸፋ እንኳን በውል ሳትጨርስ፡፡
“ልብሱ እላይሽ ላይ እንዴት ግጥም ብሏል! እንደው ተለክቶ የተሰፋ ነው የሚመስል!” አለቻት ወደርሷ እየመጣች፡፡
“ተለክቶ አለመሰፋቱን ማን ነገረሽ?” አለች ድንበር፡፡
“አይ አልሰሜን ግባ በሉት አሉ! ባልሽ አልነገረሽም እንዴ?
ይልቁንስ እዳ አለብሽ፡፡ የሹራቡን ግማሽ ብቻ ነው የከፈለው እራሷ
ትከፍላለች ብሏል።” ድንበር ሰማይና ምድር ዞረባት፡፡
ቀኑን ሙሉ ስትናደድ ውላ እስከ ምሽት ጠብቃው እንቅልፍ
ሲያንጎላጃት ልጆቿን አስተኝታ እሷም ሲያሸልባት ነበር ባሏ በስካር
አቅም ያነሰው ሰውነቱን ተሸክሞ የመጣው። ሁሉም ነገር ትዝ
ሲላትና የጠዋቱ ንዴቷ ደግሞ ሲቀሰቀሰባት የወንበሩን ስባሪ ይዛ
ወደ ውጭ ተፈተለከች።

💫አለቀ💫
አትሮኖስ pinned «#ስጦታ ፡ ፡ #በእየሩስአሌም_ነጋ ልጆቿን በግራና በቀኝ ክንዶቿ ላይ አቅፋ እንደተኛች የሰከረውን ባሏን ከአንገቷ ቀና ብላ አየችው፡፡ ባሏ በከፈተው በር ሰተት ብሎ የገባው፥ ነፋስ ፊቷን ሲገርፋት፣ “ኧረ ልጆቼን ብርድ እንዳታስመታቸው?” ብላ ውርጩን በእጁ ትከላከል ይመስል ክንዷን መከተች። “ምናለበት ልጆች ናቸው። ልጅና ፊት አይበርደውም ሲባል አልሰማሽም ድንበሬ?” አለ እንደ ሰንበሌጥ እየተወዛወዘ፡፡…»
#በቃ_ዝም

ዝምታ ወጌ ነው ዝምታ ልማዴ
የሆዴን በሆዴ
ብዬ ዝም እላለሁ
አንዳንዴ እፈራለሁ
እኔ ምን አውቃለሁ
ያለ ሰሚ ጩኸት ያሉ አዳማጭ ወሬ
ከሆነ ነገሬ
ብዬም እሰጋለሁ ከዛ ዝም እላለሁ
ውስጤ ነገር ከብዶት ሚዛኔን ሲያስተኝ
ከወዲህ ከወዲያ ወስዶ ሲያላትመኝ
ላራግፈው ብዬ ደግሞ እተወዋለሁ
በቃ ዝም እላለሁ
ሳቅና ደስታዬ ብሶት እሮሮዬ እየተጣሉብኝ
በፍርሀት ሲያስጮሁኝ
በአንድ ሲመጡብኝ በእጅጉ እፈራለሁ
ደግሞ እንዲህ እላለህ
የዝምታዬን ጨኸት ውስጤ ያለውን ነገር
ምንስ ባልናገር
ያውቁት ይሆን እንዴ ያለውን በሆዴ
እልና እሰጋለሁ
ግን ያው ዝም እላለሁ
ውስጣዊ ስሜቴን የኔን ፍላጐቴን
የሚረዳኝ ካጣሁ ሰሚ ካላገኘሁ
ለምን አወራለሁ በቃ ዝም እላለሁ
ያሆነ ይህ ሆነ
መፍትሔ አልባ ከሆነ
ማውራት ምን ያደርጋል ኬላ ካልዘለለ
ችግርን የሚቀርፍ አዳማጭ ከሌለ
እያልኩ ብነግረው ውስጤን ባስጨንቀው
ይባስ ግራ አጋባኝ
ከዝምታ ጩኸት ይሻላል እያለኝ፡፡
#ሐኑን


#ክፍል_አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም

የዚያን ቀን በሰላም ወደ ቤቴ የተመለስኩት ፈጣሪ ጠባቂ መላእክቱን ልኮ ጋርዶኝ መሆን አለበት፡፡ እንጅማ ያንን ተራራ የሚያህል ዱሩዬ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ አድርጌ አበሻቅጨው እንኳን በሰላም መመለሴ በሕይዎት መመለሴም ተዓምር ነበር፤ ግን ሆነ፡፡
ልክ የማደንዘዣ መርፌ እንደወጉት ሰው እኮ ነው ፍዝዝ ብሎ ሲመለከተኝ የነበረው፡፡እንኳን እኔ፡ በዚያ ጋን ጋን በሚሸት ትንፋሹ እፍ ቢለኝ ሱሉልታ የምገኝ ላንጌሳ ቀርቶ፣መሣሪያ ለታጠቀ ፖሊስም የማይመለስ ጉድ ነው፡፡ የዛሬ ዓመት የፍርድ ቤት መጥሪያ
ሊሰጠው የሄደውን ፖሊስ እይደለም እንዴ ጆሮ ግንዱን በጥፊ እንድዶት፣ ከነመሣሪያው ካፈር የቀላቀለው?! ቆቡ አንድ ቦታ፣ የክላሽንኮቩ የጥይት መጋዘን ሌላ ቦታ ተበታትኖ፣ ለቃቅመው ነበር በቃሬዛ የወሰዱት፡፡ ማዕረጉ ሳይቀር ከትከሻው ላይ ተነቅሎ በርሮ ቱቦ
ውስጥ ነው የተገኘው፡፡ ምን እሱ ብቻ፤ጋሽ አለበልንስ ቢሆን እንዲህ ሁለት የፊት ጥርሱን በቡጢ አርግፍ፣ አፉን የጋራዥ በር አስመስሎ የቀረው ማን ነው? …ይኼው ወጠምሻ ዱርዩ ነው !!

የጋሽ አለበልን ጥርስ ለማውለቅ (ማውለቅማ ወግ ነው፤ አረገፈው እንጂ ምን እንዳነሳሳው ሲጠየቅ “በቀን አሥር ጊዜ ሰላም እያለ አስመርሮኝ ነው አለ አሉ: እስቲ ለግዜር ሰላምታ ቡጢ መመለስ ምን የሚሉት እብደት ነው? …ጋሽ አለበል፣ ሚስኪን የሦስት ልጆች አባት ነው፡፡ ጎረቤቱ ሁሉ “ሰላምታ ይብቃ ይከተት በጋሽ አለበል!” የሚልለት ሰላምተኛ … ታዲያ አንድ ቀን ለምሳ ወደቤቱ እየገባ፣ ይኼን ወመኔ መሃል
መንገድ ላይ ቁሞ ያገኘዋል። ባርኔጣውን ከራሱ ላይ አንስቶ ፣በአክብሮት ጎንበስ
በማላት፣ “ሰላም ዋልክ ብሎ አለፈ፤ ሰው መስሎት፡ አለፍ ከማለቱ ዱርየው እንደ
አንዳች ነገር ተወርውሮ፣ ከኋላው ኮሌታውን ጨምድዶ ከያዘ በኋላ፣ በዚያ የግንድ ጐማጅ በሚያከል እጁ በቡጢ ከመሬት ደባለቀው፡፡ ሚስኪኑ አለበል ጥቅልል ብሎ ወደቀና እንደ ትል እጥፍ ዘርጋ እያለ አፈር ላይ ተንፈራገጠ፡፡ በኋላ ነው ጥርሱም መርገፉን ያወቀው፡፡ ደግሞ አያፍሩም ሰው አግኝተው ሙተው ይኼን ዱርየ ስሙን ኢዮብ አሉት፡፡ ስም አይገዛ! “ስምን መላእክት ያወጡታል” ቢባልም ቅሉ፣ የአንዳንዱ ሰው ስም ሲወጣ፤ መላእከት በአካባቢው ዝር እንደማይሉ የገባኝ በዚህ ሰው ነው ፡፡

ሌላ ጊዜ ደግሞ ኢዮብ ጌታን ተቀብያለሁ፤ ከአሁን በኋላ ወንጌል ሰባኪ ነኝ!" አለና መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ እዚያቹ ሁልጊዜ የሚቀመጥባት ድንጋይ ላይ ተቀምጦ፣ አላፊ አግዳሚውን እያስቆመ፣ስብከት አይሉት ማስፈራሪያ ጀመረ፡፡(ሰው ነፍሱ ሲቀየር እንዴት
ወንበሩ አይቀየርምስ) ትተውት እይሄዱ ነገር ኢዮብ ሆነባቸው፡፡ ከሰማዩ እሳት በፊት የኢዮብ ቡጢ ትዝ እያላቸው ደግሞም ጋሽ አለበልን ያየ፣ ኢዮብን ከኋላው አድርጎ እንዴት በሰላም ይራመዳል ብለው ቁመው ይሰሙት ጀመረ፡፡ መቼስ ክርስቶስ ከተሰቀለ
ወዲህ፣ ወንጌልን እንዲህ አድርጎ የሰበከ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም! ድንገት አንዱ መንገደኛ ፊት መንገዱን ዘግቶ፣ እንደ ጅብራ ይገተርና የደፈረሰ ዓይኑን አፍጥጦ ኢየሱስ ጌታ ነው!" ሲል ማነው ወንዱ የሚቃወም?! ጋሽ ሐምዛ እንኳን ሳይቀሩ ለጁሙዓ ሶላት ወደ መስጅድ እየተጣደፉ ሲሄዱ መንገድ ላይ አስቆማቸውና…

“ጋሽ ሐምዛ!” አላቸው፡፡

ለብይካ !"

“ኢየሱስ ጌታ ነው!” ሲላቸው፣

እንግዲህ ከአንተ ጋር ስነዛነዝ ሶላት ከሚያመልጠኝ፣ ይሁና ኢዮብ ብለው ወደ
መስጅዳቸው!! ወዲያው አንድ ወር እንኳን ሳይቆይ፣ ይኼ ወጠምሻ ፓስተር ደብድቦ
ታስረ፡፡ “ለምን ፓስተር ደበደብከ?” ሲባል “ከፉ መንፈስ አለብህ ብሎኝ ነው!” አለ፡፡
ከእስር ሲፈታ መጽሓፍ ቅዱሱን ጣጥሎ ወደ መጠጥ ቤቱ ተመለሰ፡፡እንዳገረሽ ዱርየንት አደገኛ ነገር የለም፤ባሰበት! ዓምደ ሚካኤል የሚባለው የሰንበት ትምርት ቤት ኃላፊ ሳይቀር፣ “ከዚህስ ያንኑ የመናፍቅ ስብከት ቢሰብከን ይሻል ነበር!” እሰኪል ድረስ፡፡ ይሄው ሲጠግብና ሲሰከር አላፊ አግዳሚውን እየደበደበ፣ እጁ ላይ ሳንቲም ሲያጣ እየነጠቀ፤ቦዝኖ ተመችቶት ይኖራል፡፡ ይኼን ጉድ ነው እንግዲህ እንዳይሞት እንዳይሽር
አድርጌ በስድብ እጥረግርጌው በሰላም ወደቤቴ የተመለስኩት፡፡ ያውም እቤቱ ሂጄ እፈልግሃለሁ ና ውጣ " ብዬ፡፡ ምን አገናኛቸው?” የሚል አይጠፉ መቸስ ጎደሎ ቀን ነዋ።

ኢዮብ የባለቤቴ ታላቅ ወንድም ነው የመጀመሪያ ልጃችንን የወለድን ጊዜ እንደወጉ ቁርጥ አባቱን ከሚለው አራስ ጠያቂው ይልቅ “ኢዮቤ አጎት ሆነ!"ባዩ ይበዛ ነበር፡፡
ሰው የመናገር ነፃነትን የሚነፍገው አምባገነን መንግሥት ብቻ ይመስለዋል፤ በየመንደሩ ስንት ጥቃቅን አፋኝ አለ! አንድ ቀን ታዲያ ይኼ አፄ በጉልበቱ የማይታለፍ መስመር አለፈ- እንኳን እንድ የመንደር ዱርየ፣ ሞት ራሱ መጥቶ እፊቴ ቢቆም፣ የማልደራደርበትን ጉዳይ ደፈረ አበድኩ እግሮቼ እንደ እግር ሳይሆን እንደ ክንፍ አብርረው ወደቤቱ ወሰዱኝ፣ ያውም ከሥራ እንደወጣሁ ሙሉ ልብሴን ከነከረቫቴ ግጥም አድርጌ ለብሼ፡፡

ሰው አገሩ ሲነካበት አሮጌ ጠመንጃ አንስቶ ከሰማይ ከምድር ከገዘፈ ጠላት ጋር የሚፋመው፣ ከጀግንነት ይልቅ በፍቅር ተገፍቶ መሆኑን ያወቅሁት በዚያች ቀን ነው፡፡
ኢዮብን እየተንጠራራሁ እንባረኩበት…ማነኝ ነው የምትለው!? አልኩት …መንደር
ለመንደር እየዞርክ ማንንም ስላስፈራራህ የምፈራህ መሰለህ ወይ? አልኩት… ወይ እኔ፣ ወይ እንተ እንሞታለን እንጂ ፍርሃት የሚባል ነገር የለም አልኩት፡፡ ኢዮብ ቢጨንቀው ቡጢውንም፣ ጡጫውንም ረስቶ…የተወው ሃይማኖተኝነት አስታውሰና፣ “ኧረ ጌታ ይገፅስህ አለኝ :።በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜም አንድ እርምጃ ወደኋላ አፈገፈገ፡፡
እኔም ቀሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጠብና ድብድብ እንድ ርምጃ ወደፊት ተራመድኩ፡፡ከዚህ ሁሉ ጩህቴ በኋላ ግን የምለውም የምናገረውም አልቆብኝ፣ በእልህ እየተንቀጠቀጥኩ ማለት የቻልኩት “ምን አደረገቻችሁ ብቻ ነበር፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት መደረግ የማይገባውን ነገር አደረግሁ፡፡ ጉዳዩን የሰማ ሰው ሁሉ “ተሳስተሃል? ይለኛል፡፡ መሳሳቴን ገና ድሮ ነው ያወቅሁት፡፡ ምክር ፈልጌ ስሄድ፣ ፍርድ አሸክመውኝ እመለሳለሁ፡፡ ከመምከር ይልቅ መፍረድ ቀላል ሳይሆን አይቀርም፡፡አገር ምድሩ እኔ ላይ ለመፍረድ የተሠየመ ችሎት እስኪመስል፣ እስትንፋስ ያለው ሁሉ
እኔ ላይ ፈረደ፡፡ እግዜር የፈጠረው ሳር ቅጠል ሁሉ ጠበቃና ዳኛ ሆነ፡፡ ነገሩ የጀመረው ከቤቴ ነው፣ ሚስቴ ሔራን ገና ከጅምሩ እኔ ላይ ፈረደች፡፡ “ምን ታድርግ፤እውነት አላት ብዬ ዝም አልኩ፡፡ቤተሰቦቼ እኔ ላይ ፈረዱ፡፡ያው መቼስ ለልጅ የሚወረወር ድንጋይ፣የወላጅን ልብ መውገሩ አይቀርምና፣ የወላጅ ፍቅራቸው ነው ያበሳጫቸው ብዬ ቻልኩ፡፡ እንዲያውም አባቴ ቁጣው ገንፍሎ እንዲህ አለኝ

ስማ ይኼን ነገር ወዲያ እልባት አበጅተህ ካላረፍከ፣ እደጄ እንዳትረግጥ፤ አባቴ
ብለህም እንዳትጠራኝ፣አልበዛም እንዴ? ከዛሬ ነገ ልጅነትህ ሲያልፍ ልብ ትገዛለህ
ብለን ዝም አልን፡፡ አንተ ጭራሽ እሰይ! የተባልክ ይመስል አድሮ ቃሪያ፣ ከርሞ ጥጃ ትሆናለህ፣ በዘራችን የሌለ መልከስከስ ከየት አመጣኸው!? ሌላው ይቅር፣ በሥራህ ቦታ ያለህበት ደረጃ ቀላል ነው እንዴ? እንዴት ለራስህ አክብሮት አይኖርህም!? በቃ ውስጤ
በአባቴ ተቀየመ … ከወላጆቼ ቤት ቀረሁ ፡

ጓደኞቼ እኔ ላይ ፈረዱ:: ሲጀመር ተው!" ብለው ሲመክሩኝ አልሰማኋቸውምና፣ ፍርድና ግፃፄያቸውን የሚገፋ ወኔ አልነበረኝም:: እንዲያውም የቅርብ የምላቸው ጓደኞቼ ቀስ እያሉ ከእኔ ራቁ፡፡ የሚስቴ ስሞታ ሰልችቷቸው መሆን
👍3
አለበት፡፡ ጉዳዩን የሰሙት ሁሉ
እኔ ላይ ፈረዱ፡፡ ገና የሚሰሙትም ሁሉ፡ እኔ ላይ ይፈርዳሉ፤ አውቃለሁ፡፡ እኔ ራሴ
በየቀኑ፣ በየሰዓቱ፣ ከምተነፍሰው አየር እኩል ጸጸት ከቦኝ እውላለሁ፣ አድራለሁ፡፡ አዎ! እኔ ራሴ ራሴን እወቅሳለሁ፡፡ በዚህ ሁሉ ወቃሽ ስዋከብ ያልውቀሰችኝ፣ እንደውም የምታፅናናኝ አንዲት ሴት ብቻ ነበረች፡ …ሐኑን !!

“ሐኑን ማለት ምን ማለት ነው?” አልኳት የተዋወቅን ሰሞን፡፡

ሁለት ቋንቋ ሁለት ትርጉም ያለው ስም ነው ይላሉ" ብላ አብራራችልኝ - በሱማሌኛና በአረብኛ … ደግሞ የሚገርመው የትርጉሙ መራራቅ፡፡ሲላላ ህመም፣ ጠበቅ ተደርጎ ሲነበብ 'ጣፋጭ ማለት ነው አሉ፡፡ እኔ ከራሴ ውጣ ውረድ ተነሰቼ ሁለቱንም ትርጉም አቀላቀልኩት ጣፋጭ ሕመም ሐኑን ጣፋጭ ሕመሜ ነበረች፡፡ልክ ሐኪም በእጅህ እንዳትነካኩ ያለንን ብጉር በእጅ መንካት እያመመ ደስ እንደሚለን ዓይነት፤የሆነ ቀን ከብጉሩ ውጭ ሌላ ሰውነት የሌለ እስኪመስለን ድረስ እጃችን አሥር ጊዜ ወደዚያው
እንደሚሮጠው ዓይነት፡፡ የነፍስ እጆቼ ወደ ሐኑን እንደተንጠራሩ ነበር፡፡
የበደልኳት እሷን ነው፤ እሷን ብቻ፡፡አንድም ቀን በደሌን አንስታ ወቅሳኝ የማታውቀውም እሷ ብቻ ናት፡፡እንደው በሰራሁት ሥራ ልክ "ይወገርም ይሰቀልም” ተብሎ ቢፈረድብኝ፡
እንደኛ መውግሪያ ድንጋይ እንስታ ከወጋሪው ሰልፍ ፊት መገኘት የነበረባት፣ እሷ አልነበረችም እንዴ?? የማሰቀያ ገመዴን ሸምቀቆ አንገቴ ላይ ማጥለቅ፣ የሷ ሐቅ አልነበረም እንዴ ?? ግን ባየቺኝ ቁጥር፣ ትልልቅ ዓይኖቿ ሰማይ ከፍቶ ብቅ እንዳለ መልአክ በክብርና በጉጉት እያዩኝ፡ ንጹህና ደግ ፈገግታ ከፊቷ ሳይነጥፍ የምትቀበለኝ እሷ ነበረች፡ እሷ ብቻ ይኼ ቻይነቷ ሕመሙ አይጣል ነው። ሳስባት ያመኛል፡፡ በአካል ሳገኛትም ያመኛል፡፡ ከዚህ ሕመም የምፈወስበት አንዳች መድኃኒት ባገኝ፣ ሕይወቴን እከፍላለሁ፡፡ ግን ምን ያደርጋል፣ዙሪያዩን የከበበኝ ሁሉ ስንጥሩን ይዞ ወደ ቁስሌ የሚልክ፣ የሚያደክም አጽናኝ ብቻ ሆነ፡፡

እግዚሐብሄር በሚያውቀው! ከ ባለቤቴ የደበቅኋት አንድም ነገር አልነበረም፡፡ሐኑን
ከእርሷ በፊት የነበረች ፍቅረኛዬ ነበረች:፡ ከ ሀ እስከ ፐ ታሪካችንን፣ለምን እንደተለያየንም ጭምር ታውቃለች፡፡ አሁን ምንም ዓይነት የፍቅር ግንኙነት የለንም፡፡ ግን የእኔ እርዳታ ስለሚያስፈልጋት ልርቃት አልችልም፡፡ መደገፍ ስላለብኝ እደግፋታለሁ፡፡ ድጋፌ ብር ያውልሽ እያሉ መወርወር ብቻ አይደለም፡ እንደሰው ከጎኗ መቆም እንጂ፡፡ይኼንንም ባለበቴ ጠንቅቃ ታውቃለች፡፡ ቅንነት ከጎደለው ዕውቀት፡ አለማውቅ ይሻላል፡፡ ይህን
የነገርኳት መጀመሪያዉኑ ገና ሳንጋባ በፊት ነበር፡፡ የመለሰችልኝ መልስ እስካሁን ጆሮዬ ላይ ያቃጭላል።

ምን ነካህ?? ይኼ እኮ ምንም ማለት አይደለም፤ ማንኛችንም ችግር ሊያጋጥመን ይችላል፡፡ ደግሞ አምንሃለሁ፤ አትጨናነቅ፡ እንዲያውም ዕድሉን ከሰጠኸኝ፡ እኔም ፈረዳት እችላለሁ ቃል ለቃል እንዲሁ ነበር ያለችኝ፡፡ ንግግሯ ከሴቶች ሁሉ ከፍ ያለች፣
አስተዋይና ደግ አድርጌ እንድመለከታት አድርጎኛል፡፡ከተጋባን በኋላ ግን ነገሮች
በሚያስደነግጥ ፍጥነት ተቀያየሩ፡፡ ስለ ሐኑን ከእኔና ከሔራን ቤተሰቦች አልፎ ጓደኞቼ ሁሉ ሰሙ፡፡ ሰላም የሚባል ነገር ከቤታችን ውስጥ ጠፉ፡፡ በተለይ ከወለደች በኋላ፡፡
አንድ ቀን “ሐኑንን ሰላም ብያት ልምጣ፤ በዚያውም የቤት ኪራዩን ብር ላቀብላት” ብዬ ለመሄድ ስነሳ፣

ፍቅር አለችኝ፡፡ ስትጠራኝ እንዲህ ነው፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share
👍1
አትሮኖስ pinned «#ሐኑን ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም የዚያን ቀን በሰላም ወደ ቤቴ የተመለስኩት ፈጣሪ ጠባቂ መላእክቱን ልኮ ጋርዶኝ መሆን አለበት፡፡ እንጅማ ያንን ተራራ የሚያህል ዱሩዬ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ አድርጌ አበሻቅጨው እንኳን በሰላም መመለሴ በሕይዎት መመለሴም ተዓምር ነበር፤ ግን ሆነ፡፡ ልክ የማደንዘዣ መርፌ እንደወጉት ሰው እኮ ነው ፍዝዝ ብሎ ሲመለከተኝ የነበረው፡፡እንኳን እኔ፡ በዚያ…»
#ማስታወስን_መርሳት

ከሁሉም ከሁሉም
እሱን በማምለኬ ፥ እኔን የሚቆጨኝ
የሰናፍጭ ቅንጣት
ታህል እምነት ሰጥቶኝ ፥ ተራራ ሚያጋጨኝ
ቃሌን ሳለሰልስ ! የሚያነጫንጨኝ
እንባዬ ጨው ሆኖት...
ደጁ እየጠራ ፥ እንባ የሚያስረጨኝ
አለ የሆነ አምላክ!
በሴቶች ልብ ላይ ፥ ጀምሮ ማይቋጨኝ፡፡

ጀመረ ልማዱን !
ካቻምና ካንዷ ጋር ፥ በፍቅር ዘረረኝ
እሷን እሷን እያልኩ
እሱን ስለረሳሁ ፥ አጣልቶ መከረኝ፡፡
ስጣላት ደጁ ሔድኩ
አልቅሼ ልማፀን ፦ "አታሳጣኝ” ብዬ
ባይሰማኝም ሰማኝ ፥ ደረሰው እንባዬ
"አንድ አለችኝ" ምላት.
ልቤ ላይ ከሰመች ፥ አስረሳኝ አንድዬ፡

ጀመረ ላይቋጨኝ !
አምናም ከአንዷ ጋር ፥ በፍቅር ተሰዋሁ
እሷን እሷን” እያልኩ ፥ የሡን መኖር ረሳሁ፡፡
ስረሳው ትዝ አልኩት ፥ እንባዬ ናፈቀው
ልቤን ከልቧላይ ፥ በደማቁ ፋቀው።
ስፋቅ ደጁ ሔድኩኝ..
እንደለመደብኝ ; እሱን አስታውሼ
እሷን ረሳኋት
ወጣች ከልቤ ላይ ሸኘኋት አልቅሼ ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ሐኑን


#ክፍል_ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም

ፍቅር አለችኝ። ስጠራኝ እንዲህ ነው።

“ወይዬ" አልኩ፡፡ ያው የተለመደውን ተጠንቅቀህ ንዳ፡እና እንዳታመሽ” ምክር ነበር የጠበቅሁት፡፡

እስከ መቼ ነው ይችን ልጅ የምንረዳው? ምንድነው መጨረሻው? አትማርም፣
አትሠራም እሺ ይሁን መርዳት ካለብህ እርዳት፣ ለምን የሚያስፈልጋትን ነገር
አትልክላትም? በአካል መገናኘቱ ለምን አስፈለገ?” አለችኝ፡፡ ሐኑንን ከዛ በፊት “ይቺ ልጅ!” ብላ ጠርታት አታውቅም ነበር፡፡ ልለብስ ያዘጋጀሁትን ኮት እንዳንጠለጠልኩ በግርምት ዙሬ ተመለከትኳት፡፡ ፊቷ አይቼው የማላውቀው ምሬት ተጥለቅልቆ፣
ዓይኖቿን ከእኔ ላይ ዘወር አደረገች።

እንዴ! …ከምርሽ ነው?” ብየ ጠቅኋት ተገርሜ፡፡

ከምርሽ ነው ማለት ምን ማለት ነው? የግድ አፍ አውጥቼ መናገር ነበረብኝ?
“እንደ ሌሎች ሚስቶች መጨቃጨቅ ነበረብኝ”

እንደዚያ ማለቴ ሳይሆን " እና እንዴት ማለትህ ነው?…ምን ማለት ነው ከምርሽ ነው ወይ' ማለት ?…ልክ ተአምር ነገር እንደተናገርኩ፣ የምትገረመው ለምንድነው? ከዚህ በኋላ ባታገኛት ደስ ይለኛል፣በቃ! ሁሉም ነገር ልክ አለው፡፡ ሥራ መሥራት ካለባት ትስራ ! ማግባት ካለባትም አንዱን ታግባ!" ንግግሯ ምሬት የተቀላቀለስት፣ ከጥያቄ ይልቅ ወደ ትእዛዝ ያዘነበለ ነበር፡፡ ያነሳሁትን ኮት ሶፋው መደገፊያ ላይ ጣል አድርጌ፤ ከተቀመጠችበት ሶፋ ፊት ለፊ ያለ
ክብ የመስተዋት ጠረጴዛ ጫፍ ላይ፤ ፊት ለፊቷ ተቀመጥኩ፡፡ ጉልበታችን ሲነካካ፣
እግሯን ወደኋላ ሰብሰብ አደረገች! በውስጤ፣ “በእርግዝናና በወሊድ ወቅት የሴቶች ሆርሞን መጠነኛ የባሕሪ ለውጥ እንደሚያስከትል” ያነበብኩትን እያሰብኩ ላረጋጋት ሐሳብ ሳሰባስብ፣ ልክ ያሰብኩትን ቀድማ ያወቀችዉ ይመስል(አውቀችው እንጂ)

“ምን እንደምታስብ ይገባኛል፤ሆርሞን ምናምን ብለህ ልታጽናናኝ እንዳትሞከረ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ እዚያው ስለ ወንድነትህ ሆርሞንህ እስብ:: በየትኛውም ሎጅክ ቢሆን እያደረከው ያለው ነገር ልክ አይደለም፡፡በቃ! ቤተሰብ ቀልድ አይደለም! ትዳር ነው ይኼን!” ግራ ገባኝ ፤ሐኑን በራሷ በባለቤቴ ጥሪ፣ በሰርጋችን ዕለት አብራን ነበረች ቤታችን ውስጥ ዝግጅት ሲኖር፡ ባለቤቴ እየጠራቻት ስትመጣና በደስታውም በሐዘኑም አብራን ስታሳልፍ ቆይታለች፡፡በእርግጥ ሐኑን ከባለቤቴ ጋር ባትገናኝ ደስ ይለኝ ነበር:ምክንያቱም ለሳር ቅጠሉ ትሁትና የሚመች ፀባይ ያላት ባለቤቴ ሔራን፣ ሐኑን ላይ ሲሆን ትንሽ የሚጫን ባሕሪ አላት። ለእኔ ብቻ የሚገባ ሲበዛ ውስብስብ የሆነ ባህሪ ነው፡፡ ግን አንዴ
ከተዋወቁ በኋላ ባለቤቴ ራሷ እየደወለች፣ በአካልም እያገኘቻት፡ ልክ እንደጓደኛ
ስለተቀራረቡ ምንም ማድረግ አልቻልኩም ፡፡ብናገርም ሌላ ጥርጣሬ መፍጠር ነው ብየ
ዝም አልኩ፡፡ ቢሆም ግን፣ የባለቤቴና የሐኑን ጓደኝነት መቼም ቢሆን ተውጦልኝ
አያውቅም እሳትና ጭድ፡፡

ቆይ! እስከዛሬ እምነሽበት የተቀበልሽውን ነገር ዛሬ…”

አምነሽበት? ምኑን ነው
የማምንበት? እንዴት ነው የምታስበው? በዚህ በሠለጠነ ክፍለ ዘመን ባሌ
እንደድሮ ሰው በትዳሩ ላይ ቅምጥ ማስቀመጡን ነው የማምንበት? ይኼን ነው የማምንበት? በቃ ከዚህ በኋላ ይኼ ነገር መቀጠል የለበትም፡፡ የባንክ አካውንት ከፍተህም ቢሆን የምትፈልገውን ብር አስገባላት፡፡ እያወጣች ትጠቀም፣ጤነኛ ናት፤
እየሄድክ ሰማንያ አታርሳትም:: እንደውም እንደሴቶቹ ሂዳ ትስራ አረብ አገር
የሚልኩ ሰዎኝ ጋር ላገናኛት እችላለሁ! ከዚህ በኋላ በምንም መንገድ ከእሷ ጋር
እንድትገናኝ ከልፈልግም :: ሁሉም ነገር ልክ አለው በቃ”

ጩህቷ እና ቃል አባይነቷ ግልፍ አደረገኝ እናም ሶሬ አልችልም!" አልኳት፡፡

ምን ማለት ነው አልችልም? ይሄኮ ጥያቄ ወይም አስተያየት አይደለም፡ ሕጋዊ ባለቤትህ። ነኝ! ሳንጋባ በፊት ስለነበረው ነገር እይመለከተኝም፣ ከተጋባን በኋላ ግን አያገባሽም እያልክ ብቻህን መወሰን ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው የበፊት ፍቅረኛህን አዲስ አበባ ድረስ አምጥተህ ቤት ተከራይተህ ማኖርህን እሽ ይሁን ብዬ ተቀበልኩ፣ በየወሩ ገንዘብ ተቆራጭ ማድረግህንም ይሁን ብዬ ፈቀድኩ፤ ይሄን ሁሉ የተቀበልኩት መብትህ ስለነበረ
እይደለም. ከራስሀ እንዲመጣ ስለፈለኩ እንጅ! ጭራሽ በየጊዜው እቤቷ እየሄድክ
መዋልና ማምሸትሆን አቁም ስላልኩህ፣ እፍህን ሞልተህ አልችልም ትለኛለህ እንዴ? እኔን ብትንቅ እንኳን፣ ለልጅህ ስትል ትዳርህን አታከብርም!? ብላ፣ ቤቱ እስኪናወጥ ጮኸት፡፡ ገና የሁለት ወር ልጅ ምነው ተወልዶ ሰበብ ላደረኩት ብላ በጉጉት የጠበቀችው ነው የሚመስለው፡፡ “ልጅህ” ስትል፣ አቅፋ ጡት የምታጠባውን ልጅ ስለናጠችው፣ መጥባቱን አቁሞ ጭርር ብሎ አለቀሰ: ለማጥባት ሳይሆን አፉን ለማዘጋት
በሚመስል ሁኔታ የጡቷን ጫፍ አፉ ውስጥ በእልህ ወተፈችበት ሲያለቅስ ወደውስጥ የሳበውን አየር እንኳን ሳያወጣው አጉረምርሞ ዝም አለ፡፡ አፍና የገደለችው ነበር የመሰለኝ፡፡ ማመን አልቻልኩም፡፡ ይኼን የተናገረችው ባለቤቴ ሔራን ናት ብዬ መቀበል ተሳነኝ።

ዝም ብዬ አየኋት! ዙሪያዋን የተዝረከረከውን ማቀፊያ ልብስ፣ጡጦ እና ምናምን ሁሉ በቁጣ በታትናው ልጃችንን አቅፋ እያለቀሰች ወደ መኝታ ቤት ገባችና የቤቱ መሠረት እስኪነቃነቅ ቀሩን በእግሯ ወደኋላዋ ወርውራ ዘጋችው፡፡ጓ...ሳሎን መሃል ተገትሬ
ቤቱን ቃኘሁት፡ችግር ችግር ሸተተኝ፡፡ አደጋ አደጋ፡፡ ቤታችን ከግድግዳ ሳይሆን ከአራት ቋሚ ችግሮች የተሠራ የመብረቅ ጣሪያ ከላይ የተደፋበት መሰለኝ፡፡ የዘራሁት ኃጢያት ማቆጥቆጥ እንደጀመረ ገባኝ፡፡ ለመሆኑ ሐኑን ብር በባንክ ብልክላትና ሁለተኛ አልመጣም ብላት (አልላትም እንጂ ) ምን ይሰማት ይሆን? ሐኑን…. ሐኑን ሐኑን ሐኑን …የቀጠፍኳት አበባ መዓዛዎ አስክሮኝ ውበቷ አስክሮኝ ጨብጫት ኖሬ ወደቀልቤ
ስመለስ እና የጨበጥኩበትን መዳፌን ስዘረጋ፣ እፍኝ ሙሉ እሾህ ተሰከስኮባት፣ ያውም የሚያንገበግብ እና የሚመረቅዝ ቁስል ፈጥሮ አገኘሁት፡፡ አላርፍ ያለ መዳፍ ፡፡

ከስድስት ዓመት በፊት የምሠራበት ባንክ ወደ ድሬደዋ መድቦ ሲልከኝ፡ግማሽ ልቤ አዲስ በተሰጠኝ እድገት እና ደመወዝ ሲደሰት፣ ግማሽ ልቤ ደግሞ ከአዲስ አበባ በመራቄ ደብቶት ነበር፡፡ ባየሁት ቁጥር የዓለም መጨረሻ የደረሰ የሚመስለኝ ችኩል ሥራ አሰኪያጅ ወደ ቢሮው ጠራኝና እንዲህ ሲል መርዶ ይሁን የምሥራች ግራ ያጋባኝን ዱብ ዕዳ አፈረጠው፡፡

እ..ያው እንደሚታወቀው፣ አዲስ አበባና ወደዚህ ወደ ሰሜኑ ያሉ ቅርንጫፎቻትን
ሥራችንን ካሰብነው በላይ እያስኬዱልን ነው፡፡ ይሁንና፣ ድሬዳዋ የከፈትነው ቅርንጫፍ በየዓመቱ ችግር ብቻ ነው የሚያተርፈው፤ ሰውየውም ከሠራተኞቹ ጋር መግባባት አልቻለም፣ እና ማኔጅመንቱ ትላንት በነበረው ስብሰባ፣ ጉዳዩ ላይ በስፋት ተነጋግሮበት አንድ ውሳኔ አሳልፏል” ካለ በኋላ የስልኩን እጀታ አንስቶ ወደ እኔ እየተመለከተ፣

“ምን ይምጣልህ?” አለኝ :

“ምንም እልፈልግም” አልኩ በአክብሮት፡፡ እኔ እንደሆንኩ ለወሬው ነበር የቸኮልኩት

ኃላፊየ ግን ያልኩትን ወደጎን ትቶ፣ “ሁለት ቡና አምጡልን!” ብሎ አዘዘና ወደጉዳዩ ገባ፡፡በረዥሙ ስለሁኔታው ሲያብራራ ቆይቶ

እና እንደነገርኩህ ማኔጅመንቱ ድሬደዋ ላለው ቅርንጫፍ ቢሮ መፍትሔ ብሎ ያሰለው፤እዛ ያለውን ሰው በማንሳት፣ ጠንካራና ኮሚትድ የሆነ ሥራ አስኪያጅ መመደብ ነው::ለቦታው የሚመጥን ሰው ስናነሳና ስንጥል ቆይተን ….በመጨረሻ…”

ቡና እንድታመጣ የታዘዘችው ልጅ ድንገት በሩን ከፍታ ገባችና ቡናውን በየፊታችን
አቅርባልን ወጣች፡፡ ምንም አልፈልግም ያልኩት ሰውዬ
1👍1
ኃላፊዩ በግድ ያዘዘልኝን
ጥቁር ቡና፡ ገና ከመቅረቡ አንስቼ ፉት አልኩና እያጣጣምኩ ወሬውን እስከሚቀጥል በጉጉት ጠበቅሁ። ጆሮዬ በዚያች ሰዓት፣ ሞያሌ ድንበር ላይ መርፌ ብትወድቅ ይሰማ ነበር፡፡

•እ -ምንም እንኳ ለቦታው አንዳንድ የማታሟላቸው ነገሮች ቢኖሩም፣ ቀስ በቀስ እንደምታሟላ በማስብ፣በመጨረሻ አንተን እዚያ ብራች ላይ ሥራ አስኪያጅ አድርገን እንድንመድብህ ወስነናል፡፡ በዚህ አስራ አምስት ቀን ውስጥ ወደቦታው ስለምትንቀሳቀስ፣ አንዳንድ ነገሮችን አመቻች፡፡ ቤት እና ትራንስፖርት እዚያው ያሉ ሰዎች ያመቻቹልሃል፡፡ አንተ በዋናነት ቢቻል በዚህ ስድስት ወር፣ ቢበዛ በቀጣዩ እንድ ዓመት በቢሮው ላይ የሚታይ ለውጥ በማምጣት ላይ ብቻ አተኩር፡፡መልካም ሥራ!" ብሎ እሱው የጀመረውን እራሱ ጨረሰና፤ የሥጋ ድልዳል ያደለበውን ሰፊ መዳፉን ለሰላምታ
ዘረጋልኝ ፈቃዴን መጠየቅ የለ፣ ምን የምትለው ነገር አለ ብሎ አስተያየት እንድሰጥ ዕድል መስጠት የለ፤ በቃ ወታደራዊ ትእዛዝ፣ “ተነስና ሂድ !!" መቼስ ወፍራም እንጀራ ጣት ከነሚያስቆረጥም ወጡ፤ ያውም ከአራትና ከአምስት ዓመት በኋላ እንኳን ከማልደርስበት እድገት ጋር ጭነው፣ ቼ ሊሉኝ ሽምጥ ጋልቦ ድሬዳዋ ላይ ከማረፍ ሌላ፣ ምን አማራጭ ነበረኝ? ወደ ኋላ የሚጎትት፣ ሚስት የለኝ ድስት .. ደግ ዘመን!

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share
#ሐኑን


#ክፍል_ሶስት


#በአሌክስ_አብርሃም

ድሬዳዋ ግሪክ ሰፈር የሚባል ሰፊ የሀብታም ግቢ ውስጥ፣ የራሱ ገላ መታጠቢያ ከፍልና፣ መጸዳጃ ቤት ያለው ባለ ሁለት ክፍል ቤት ከነዕቃው ተዘጋጅቶልኝ ነበር፡፡ ቤቱ የአንድ ባለሀብት ቤት ሲሆን፡ የምሠራበት ባንክ የተከራየው ሕንፃ ጭምር የሰውዬው ነበር፡፡ እንዲሁ ስጠረጥር ባለሀብቱ ቤታቸውን ያከራዩት፣የኪራይ ብር አስጨንቋቸው
ሳይሆን፤ሕንፃቸውን ተከራይቶ በየዓመቱ ጠቀም ያለ ብር የሚከፍላቸውን ባንክ ሥራ አስኪያጅ፣ ቤተኛ ለማድረግ ይመስለኛል፡፡ “ባለቤቱ ይኼ ናቸው” ቢሉኝ ገረመኝ፡፡
ሽርጥ ያገለደሙ ተራ ሰንደል ጫማ ያጠለቁ፣ ከጉያቸው ሥር ምንጊዜም በላስቲክ የተጠቀለለ ጫት የማይጠፉ፣ ጺማቸው በርስሬ መስሎ የቀላ ሽማግሌ፤ የዚያ ሁሉ ሀብት ባለቤት አልመስል ብለውኝ ነበር፡፡ ሰውዬው ለምንም ነገር ግድ የላቸውም፡፡ ሁልጊዜ ከሰዓት በኋላ ጫታቸውን ይዘው በረንዳቸው ላይ ይፈርሹና፤ ጓደኞቻቸው ከመጡ
ከጓደኞቻቸው ጋር፣ ከሌሉም ብቻቸውን ቁጭ ብለው፣የምታምር ልጃቸው አንዴ ቡና አንዴ ሻይ እያቀረበችላቸው፣ ሱዳንኛ ዘፈን ከፍተው ጫታቸውን እየቃሙ ይውላሉ፡፡ያንን በሚያክል ግቢ ውስጥ፣ ከአንዲት ቆንጆ ሴት ልጃቸው ጋር ብቻቸውን ነው የሚኖሩት፡፡ መጀመሪያ አካባቢ አብሪያቸው ጫት እንድቅም በተደጋጋሚ ይጋብዙኝ ነበር፡፡

ልጅ …ጫት አትቅምም ?” ይሉኛል፡፡

“ኤልቅምም አባባ!” “ምነው? በሰላም!?”

ሳቄ ይቀድመኛል፡፡በኋላ እንደማልቅም ገብቷቸው፣ማጨናነቁን ትተው፣እቤት ከዋልኩ ኮካ-ኮላና ለውዝ ይልካልኛል፡፡ ቡናና ሻይ ሲፈላ ደግሞ ልጃቸውን፣ “ሐኑን ነይ ለዚህ ልጅ ውሰጅለት” ይሏታል፡፡
ልጃቸው ሐኑን ከፀጉሯ ላይ እየተንሸራተተ የሚያስቸግራትን መሸፈኛ አሥር ጊዜ
ወደፊት፣ወደግንባሯ ሳብ እያደረገች፣ ቡና አልያም ሻይ በሚያምር ሰርቪስ ትሪ ይዛልኝ ትመጣለች፡፡ ቢነኳት የምትፈርጥ የምትመስል ቆንጆ ልጅ ነች፡፡ ገና በር ላይ በአክብሮት ጫማዋን አውልቃ ስትገባ፣ ውብ እግሮቿ ላይ ዓይኔ እያረፈ ኧረ ጫማሽን አታውልቂ እላታለሁ፡፡ ምንግዜም ግን ሳታወልቅ አትገባም፡፡ በእርግጥ በዕድሜ ከእኔ ታንሳለች::
በስምን ወይም በዘጠኝ ዓመት ሳልበልጣት አልቀርም፡፡ ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ ካየኋት ቀን ጀምሮ ባየኋት ቁጥር፣ ለመቀራረብ የሚገፋኝን ፍላጎቴን መቋቋም አልቻልኩም፡ ቀስ በቀስ ማውራት ስንጀምር፣ የበለጠ ቀረብኳት፡፡ ብዙ አታወራም ፈገግ ብላ ትልልቅ ዓይኖቿን እያንከባለለች ዝም ትላለች፡፡ ምንም ቃል ሳይወጣት ብዙ
ያወራን የሚመስለኝ ነገር ነበር፡፡

ሐኑን፣ ከሌላ ሴት የወለዷት የሰውዬው ዘጠነኛ ልጅ ናት፡፡ ስምንት የወለደችላቸውን ሚሰታቸውን አስቀምጠው፣ያውም እቤታቸው ሠራተኛ ሆና ከተቀጠረች ሴት ነበር ሐኑንን የወለዱት፡፡ ይኼ ነገር በልጆቻቸውም ሆነ በሚስታቸው በቀላሉ የሚታለፍ ነገር
አልሆነም፡፡ ትዳራቸውን ሊበትነው ደረሰ፡፡ በመጨረሻ ሠራተኛዋን ከነልጇ ቤት
ተከራይተው በድብቅ እስቀመጡ፡፡ ወሬው ግን የሚደበቅ አልሆነም፡፡ ባልና ሚስት
ከዝያ በኋላ በሰበብ አስባቡ መጋጨት ሆነ ሥራቸው :: በተለይ ሚስት ከልጆቻቸው ጋር አብረው ሰውዬውን መቆሚያ መቀመጫ አሳጧቸው፡፡ሰውየው ደግሞ ንዝንዝ አይወዱም፡፡ ለአንድ ሰዓት ሰላም በልዋጩ ያላቸውን ሀብት ቢከፍሉ የማይቆጫቸው
ዓይነት ሰው ናቸው፡፡

በስልክ እንኳን እያውሩ ትንሽ ንዝንዝ ቢጤ ከሆነባቸው “አቦ! ልቃምበት እንግዲህ አትነጅሱኝ ብለው ጥርቅም ያደርጉና ስልካቸውን ወዳያ ይወረውሩታል፡፡ሐኑን አንስታ
እለመሰበሩን ካረጋገጠች በኋላ እቤት ታስቀምጥላቸዋለች፡፡

አንድ ቀን ታዲያ ሚስታቸውን ቁጭ አደረጉና፣ እንግዲህ አጠፋሁ፤ የተተፋ ምራቅ መልሶ አይዋጥም፣ አንቺም ጧት ማታ እያነሳሽ በሰበቡ ከምትነዘንዥኝ፣ ከልጆቼም ጋር ከፉ ደግ ከምነጋገር የወደድሽውን ንብረት ያዥና ከልጆችሽ ጋር ኑሪ፣ በቃ ፈትቼሻለሁ ብለው ቤቱን ለሚስታቸውና ለልጆቻቸው ትተው ወጡ፡፡ ከቤት ሲወጡ የያዙት ነገር ቢኖር፥ የጀመሯት በላስቲክ የተጠቀለለች ጫት ብቻ ነበር፡፡በሽማግሌ ወደ ቤታቸው
እንዲመለሱ ቢለመኑ ቢደረጉ እምቢ አሉ፡፡ብዙም አልቆዩም ሐኑን እናት ጋ ጠቅልለው ገቡ ፡፡ የልጆቻቸው እናት ይሄን ሲስሙ፣ ድሮም ጤና አልነበራቸዉም ውሎና አዳራቸው ሆስፒታል ሆነ፡፡በመጨረሻም እንዲቹ እንደተብሰለሰሉ አረፉ፡፡ ልጆቻቸው የእናታቸው
ገዳይ የሐኑን እናት እንደሆነች ነው የሚያምኑት፡፡ ጦሱ ምንም ለማታውቀው ሐኑንም ተርፎ ልክ የሌለው ኃይለኛ ጥላቻ ነበር ያለባቸው፤ለዓይናቸው ሊያዩዋት
አይፈልጉም፡፡ቃል በቃል የገረድ ልጅ እናታችንን ያስገደለች ይሏታል፡፡

የእርሷም እናት እኔ እዚያ ቤት ከመግባቴ ከአምስት ዓመት በፊት ነበር የሞተችው፡፡
ለዚያም ይሆናል ሁሉጊዜም በቆንጆ ፊቷ ላይ እንደ ስስ ደመና የሐዘን ስሜት
የማያንዣብብ የሚመስለኝ፡፡አስረኛ ክፍል ላይ የትምህርት ነገር በቃኝ ብላ፣ ቤት ውስጥ ነበር የምትውለው፡፡ አባቷም ከቤት እንድትወጣ አይፈልጉም ፡፡ አላህ እንዲህ ያለልክ አሳምሮ ኸልቆብኝ በገባች በወጣች ቁጥር ይሄ ባለጌ ወንድ ሁሉ እየተከተለ አስቸገራት፡ አቦ ከዚህ ሁሉ ብትተወውስ ብየ፣ ይኼው እቤት ነው ውሎዋ_አላህ ደጉን ኢማን ያለውን ሰው እስኪወፍቃት” ምከንያታቸው ይኼ ብቻ አልነበረም፡፡ የራሳቸው ልጆች
አንድ ነገር ያደርጓታል ብለው ይፈራሉ፡፡ እኔም በኋላ ሳውቃቸው ልጆቹ አያደርጉም የሚባሉ ዓይነት አልነበሩም፡፡

ሐኑን ጋር ቀስ በቀስ ተላመድን፡፡ እንዲያውም ቡና ከማመላለስ ባለፈ፣ አንዳንዴ ኣባቷ ሳይኖሩ እኔ ቤት ትመጣና ስንጫወት ቆይተን ትሄዳለች፡፡ ረጋ ያለ አነጋገሯ አንዳች ጊዜን የማቆም ኃይል ያለው ይመስለኛል፡፡ በተፈጥሮዬ ተኝቼ እንኳን ሐሳቤ የማያርፍ እዚያና እዚህ የምዛብር ሰው ነኝ፡፡ ፊልም እንኳን ከፍቼ አንድ ቀን መጨረሻውን አይቼ አላውቅም የሚያንቀዠቅዥኝ ነገር አለ፡፡ ሐኑን ጋር ስሆን ግን አንዳች የመረጋጋት ስሜት ይሰፍንብኛል፡፡ ጥልቅ ዕረፍት ውስጥ ነፍሴ ትዋኛለች ፡፡ይኼንንም ፍቅር ነው
ብየ ነበር::

እሷም ብትሆን እንደወደደችኝ ገብቶኝ ነበር፡፡ በእፍረቷ፣ አንዳንዴ ደግሞ እያመለጣት በምትናገራቸው ቃላት፡፡ ስንቆይ፣ አንዱን የቤቴን ቁልፍ ወስዳ፣ በሌለሁበት ቤቴን አዘጋጅታልኝ ትሄዳለች፡፡ ሁልጊዜ አልጋየ የሚያሰክር ሽቶ ተረጭበት ሳገኘው፣ ነፍሴ ሐሤት ታደርጋለት በድሬዳዋ ቆይታዬ ሐሳቤ ሁሉ ሁለት ነገሮች አይዘልም ሐኑንና ስራዬን፡ክፉኛ እየወደድኳት ነበር፡፡ ከሥራ ስወጣ ወደ ገነት የምሄድ እስኪመስለኝ ድረስ
ልቤ በደስታ ትዘላለች፡፡ ቁልቁለት ላይ እንደሚሮጥ ሰው፣ ራሴን ልቆጣጠርና ልቆም ስታገል፣ ግን ግፊቱ ሲያንደረድረኝ ይሰማኛል ፡፡

አንድ ቀን ልነግራት ወሰንኩ፡፡ ግን በብዙ ሐሳቦች ዙሪያውን ተወጣጥሬ ቃል መተንፈስ አቃተኝ፡፡ በሁለት ምክንያቶች እንደምወዳት ለመናገር ፈራሁ። አባቷ እንደ ልጃቸው ስለቀረቡኝ፣ ድንገት ይኼ ጉዳይ ጆሯቸው ቢገባና፣ አዲስ አበባ ላሉት አለቆች
“የላካችሁት ጎረምሳ ልጄን እያማገጠ ነው? ብለው ቢናገሩ፣ የሚለው ሐሳብ
አስጨነቀኝ፡፡ ለብዙ ነገር ግዴለሽ ናቸው የሚባሉ ሰዎች፣ በማይወላውል ለሰላሳ ማንነት እንደተራራ ረጋ ብለው ቢቀመጡም፤ ድንገት እንደ እሳተገሞራ በውስጣቸው ያለው እሳት ወጥቶ፣ አካባቢያቸውን የሚያቃጥልበት ሽንቁርም አይጠፋቸውም::እኒህም ሰው
ለሀብታቸውም ሆነ በዙሪያቸው ላለ ነገር ግዴለሽ ይመስላሉ ማለት፤ ለልጃቸው ግዴለሽ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ዓይናቸው ናት ሐኑን፡፡ዋጋ የከፈሉባት፡፡ ብትመነዘር የስምንት ልጅ ዋጋ ያላት፡፡

ሌላው ጭንቀቴ ሐኑን ራሷ ነበረች፡፡ ገና ለፍቅር ሳስባት
👍21
የሚጨንቀኝ ነገር አለ፡፡
ዓይኖቿን ስመለከት፣ እርጋታዋን ስታዘብ ፣ተረጋግቶ ሰፊ ቦታ ላይ የተኛ ንጹህ የሐይቅ ውሀ ትመስለኛለች፡፡ወደ ሕይወቷ በፍቅር ሰበብ ብገባ፣ የምትደፈራርስ የምትናወጥ ይመስለኛል፡፡ተፈጥሮን የምረብሽ የማዛባ ዓይነት፡፡እራሴን አላምነውም አንዳንዴ ውሳኔዬ
ድንገተኛና እራሴንም የሚያስደነግጥ ነው፡፡ይኼ ድንገተኛና ደፋር ዉሳኔዬ ከዕድል ጋር ተዳምሮ በሕይወቴ ውስጥ ብዙ ቢጠቅመኝም፣ ሁልጊዜ ፋሲካ የለም ይለኛል ውስጤ፡፡ ይህ ፍቅር የመሰለኝ ስሜት፡ ውሎ አድሮ ተራ ፍላጎት ሆኖ ቢገኝስ? እላለሁ ለራሴ፡፡ ስልቹ ነኝ፡፡ተንሰፍስፌ የገዛሁት ልብስ ሳምንት ሳይሞላው ሊሰለቸኝ ገና ተማሪ
እያለሁ የወደድኳቸው፣ በፍቅራቸው የምይዝ የምጨብጠውን አጣሁ ያልኩላቸው ሴቶች፡በቀረብኳቸው የወራት ዕድሜ ዓይናቸውን ማየት ሲያስጠላኝ ራሴን ታዝቤዋለሁ፡፡ ምርጫዬን አላምነውም ብቻዬን ብወድቅ ብነሳ የራሴ ጉዳይ ነው ሐኑንን ፣ይችን ንጹህ
ነፍስ፣ ምንም የማታውቅ የዋህ ልጅ ይዣት የሕይወት ማዕበል ውስጥ መግባት እፈራለሁ፡፡ ግን እልቻልኩም፡፡ መዓበሉ ራሱ ወደ እሷ ገፋኝ፡፡

አንድ ቀን ታዲያ፣ ሐኑን እቤቴ መጣችና፣ እያወራን ድንገት(አምልጦኝ መሆን አለበት )

“ሐኑን ላገባሽ እፈልጋለሁም"አልኳት፡፡ እወድሻለሁ አላልኳትም፡፡ አፈቅርሻለሁ አይደለም ያልኳት፡፡ ላገባሽ እፈልጋለሁ አንድም ነገር ሳትናገር ፀጉሯ ላይ ጣል ያደረገችው ክንብንቧ ጫፍ ላይ የተንጠለጠሉ ክሮችን እያፍተለተለች ቆየች፡፡ ጣቶቿን አያቸዋለሁ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share