#እማማ_ዣ
፡
፡
#ክፍል_አምስት(የመጨረሻ ክፍል)
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
እቡቹ ቆንጆ እዲስ ባለሰሊጥ ዳቦ መጥቷልእንካ በነፃ ልጋብዝህ" ብላ በገዛሁት ዳቦ ላይ ልትመርቅልኝ በብረት መቆንጠጫ ትንቦክ የሚል ዳቦ አነሳች፡
አይ እልፈልግም” ብዬ የገዛሁትን ብቻ አንስቼ ሮጥኩ! ከኋላ ሳቋ ይሰማኛል… የዚህ ልጅ ኩራቱ … ካካካ !
#በፖሊስ…
እማማ ዣ፣ ድሮ ድሮ ለግንቦት ልደታ በግ አሳርደውና ነጭ ልብስ ለብሰው ሰፈሩን ሁሉ ስለሚጋብዙት፣ ግንቦት ልደታ ራሳቸው እማማ ያንዣቡ ይመስሉኝ ነበር:: ለምን እንደሆነ እንጃ፣ ከሆነ ዓመት በኋላ ግን መደገሱን እርግፍ አድርገው ተውት:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እንደበፊቱ መልበስና መዘነጡንም ተውት፤ አልፎ አልፎ ወጣ ሲሉም ቀለል ያለ የፈረንጅ ቀሚስ እንጂ እንደበፊቱ የሐበሻ ቀሚስ አይለብሱም ነበር! ጎረቤቱ ይኼንንም
አፈ-ታሪክ ከሚመስል ታሪካቸው ጋር አገናኘው። … ወሬው ብዙ ዓይነት ነው!
ታዲያ አንድ ቀን እቤታቸው ገብስ ሊወቅጥ ከመጣ ወዛደር ጋር እያወሩ(ወዛደሩን ጠርቼው ያመጣሁት እኔው ነኝ ሻይ እና ዳቦዬን ይዤ በረንዳው ላይ ተቀምጫለሁ፡፡
ወዛደሩ ገብሱን እንጨት ሙቀጫ ውስጥ እያስገባ በሚገርም ኃይል ይወቅጠዋል፡፡
የሙቀጫው ንዝረት በረንዳው ድረስ ዘልቆ፣ ስሚንቶው ወለል ላይ ያስቀመጥኩት ብርጭቆ ውስጥ የነበረውን ሻይ በቀስታ ያንቀሳቅሰው ነበር! ….ክንዱ ላይ ከጠቀለለው
ካኪ ሸሚዙ ሥር ብቅ ያለው ፈርጣማ ከንዱ የሚሰነዝረው ምት፣ የእማማ ዣን ዘመን ያስቆጠረ የቤት ምሰሶ ይነቀንቀዋል … እማማ ዣ በረንዳቸው ላይ ወገባቸውን ይዘው ቆመው፣ “እሰይ! እንዲህ ነው እንጂ የሥራ ስው እያሉ ያደንቁታል! በመኻል እናቴ ጠርታኝ እቤት ደርሼ ስመለስ፣ እማማ ዣ ለወዛደሩ ሻይ በዳቦ አቅርበውለት፣ ሞቅ ያለ ወሬ ይዘው አገኘኋቸው። የሙቍጫው ዘነዘና በከፊል የተፈተገ ገብስ የሞላውን ሙቀጫ ደገፍ ብሎ ቁሟል፡፡ እማማ ዣ በወሬ ተጠምደው መግባቴንም ያዩ አልመሰለኝም፡፡ አልያም ቢያዩኝም ወሬው በልጦባቸው ችላ ብለውኛል፡፡ በሁለት ነገሮች በጣም ተገረምኩ፡፡የመጀመሪያው ያስገረመኝ ነገር፣ የእማማ ዣ አቀማመጥ ነበር፡፡ በረንዳቸው ላይ ያለው ከፍ ያለ የቀርቀሃ ወንበር ላይ እንኳን ደጋግመው በጨርቅ ካላራገፉና “ይቀዘቅዘኛል” እያሉ ትራስ ቢጤ ጣል ካላደረጉ በቀር የማይቀመጡት ሴትዮ፣ እግር ሲረመርመው በሚውለው የበረንዳው ደረጃ ላይ፣ ያውም ምንም ነገር ሳያነጠፉ ወርደው ተቀምጠዋል:: ወዛደሩ ከሳቸው ዝቅ ብሎ ለአበባ መደብ መከለያ በተደረደረው ቀያይ ጡብ ላይ ነበር አረፍ ያለው፡፡ ታፋና ታፋው በቁምጣው ሙልት ብሎ ደህና ስፖርተኛ ይመስላል::
ሁለተኛው ግርምት፣ ለወዛደሩ ስለ ባላቸው እያወሩት ነበር፡፡ እዚህኛው ላይ ከመገረምም አልፌ ትንሽ ተበሳጨሁ፡፡ ከመጀመሪያው መስማት ባለመቻሌ፤ ወሬያቸው መኻል ላይ ደርሶ ነበር::
“…እኔ ልጅት አንዴ ከሰነዘርኩ
እንኳን ሰው ሰይጣንም አይመክተኝ ...ያንን ባል ተብዬ
ወተፋንም (የድሮ ባላቸውን ነው) “ አቤት ቁመና… አቤት መልክ .…” እያለች ምድረ
ኮማሪ ስታቀብጠው ጊዜ፣ እኔ ያንዣቡ ላይ ሊንቀባረር ከጄለዋ! አንድ ቀን ለባብሶ መቼም አለባበስ ከሱ ወዲያ ላሳር ነው…ደረቱን፣ ይኼን ትከሻና ትከሻውን ያየህ እንደሆነ፣ እንዲህ እንዳንተ ሳንቃ ነው…” ብለው ለወዛደሩ ዳቦ ከተከመረበት ሰሃን ላይ አንድ ዳቦ አንስተው ጨመሩለት፡፡
ወጋቸውን ቀጠሉ “አንድ ቀን እዚህ ነኝ እዛ ነኝ ሳይል፣ በዋለበት አድሮ አረፋፍዶ
ወደምሳ ሰዓት መጣ፡፡ ጭራሽ ይኼ ሲገርመኝ ..እልፍ ብሎ ገብቶ ተኝቶ ዋለና ...ወደ አመሻሹ ላይ ተነስቶ፣ ካሁን አሁን የት እንዳደረ ሊያወራኝ ነው ብዬ ስጠብቅ፣ ሙሉ ልብሱን ግጥም አርጎ ለባበሰና ሚኒስቴር መስሎ ..ደህና ዋይ እንኳን ሳይለኝ ውልቅ ብሎ ሊሄድ ...
“ምን ሁነሃል!? …ወዴት እየሄድክ ነው ከመሸ …?” አልኩት… እንዲህ ወደ ማጀት አንዲት ደዘደዝ ሠራተኛ ስታጨማልቀው ምኗም አላምረኝ ብሎ ወዲያ ገፍቼ ራሴ ሊጥ እያቦካሁ እጄ ሁሉ ሊጥ ሁኗል ያመልጠኛል ብዬ ለቅለቅ እንኳን አላልኩትም፣ የትስ ብሄድ አንችን ማን ቦሊስ አረገሽ? ..አርፈሽ ጓዳሽ ግቢና ሊጥሽን አቡኪያ” ብሎኝ ጎምለል ጎምለል እያለ ውልቅ፡፡ እኔ ያንዣቡ እንኳን እንዲህ ከፍ ዝቅ ሊያረገኝ ቀርቶ፣ አፍንጫው መሬት እስኪነካ አሥራ ሁለተዜ ሰግዶ ነው ያገኘኝ.አሁን እጁ አስገባኝና፣ ቀን ከሌት የልቡን አድርሶ መናቁ ነዋ! ….ብልጭ አለብኝ! እንዲያው አንዳች ነገር ዓይኔ ጋረደኝ ..ሰማይ ልሁን መሬት አላውቀውም ንቀቱ ማጣጣሉ አይደለም፤ በዓኑ ያቀለለኝ ነገር ... አስተያየቱ አመመኝ! እዚህ ደጅ የተከመረ የቤት ጥራጊ እንኳን እንዲ አይታይም. እንደ ገረድ ጓዳ ለጓዳ ስንፏቀቅ፣ እውነትም ባሪያ መስዬው እንደሁ እንጃ
ደሞ አለ ... “ማን ቦሊስ አረገሽ?…ይኼ አንኮላ! ሴት ልጅ ለክብሯ ማንም ባይሾማትም ቦሊስ መሆኗ መች ገባው የማቦካና የምጠፈጥፈው ለሱ አልነበረም እንዴ? ... ሰው ካለ ነገሩ የት ትሄዳለህ ብሎ አይጠይቅምኮ፣ የኔ ብዬ ባከብረው ነበር፡፡ ማደሩ አንገብግቦኛል፣ ጭራሽ ይኼ ሲጨመር ደሜ ፈላ፣ ደርደር ብዬ ወጥቼ እዚህ ታዛው ላይ አዲስ ተፈልጦ ከተከመረው ፍልጥ አንዱን ላጥ አድርጌ አንድ ጊዜ ጀርባውን ባቦንነው የናቴ ልጅ .…የሰው ገላ እንደ ነጋሪት ሲኖጋ የዛን ቀን አየሁ!
“አላተረፍሽውም!” አለና፣ ወዛደሩ በግርምት ዳቦውን መብላቱን አቁሞ አፉን ከፈተ፡፡
“…ፍልጡ ሲያርፍበት እንደ ወንድ እንኳ ዘራፍ አላለም፡፡ ከዚህ ከኔ በር የበረረ፣ እዚህ ።አሁን ዘመናይ ሱቅ የተባለውጋ ቆመ፡፡ ልምረው ነው …ተከተልኩት ...ሰው አዬኝ . አላዬኝ ብሎ ዞር ዞር አለና፣ የሸሚዙን ኮሌታ አስተካክሎ “እብድ!” ብሎኝ እርፍ! .
አታምጣው ስለው አምጥቶ ቆለለው ኣሉ ካልክማ ብዬ አበድኳ! … አይሮጥ፣ ሰዎች አሉ፣ ኀፍረት ያዘው፣ ….አይቆም፣ ፍልጡን ፈራ፤ እንዲሁ ሲደናገር ደርደር ብዬ የበላሁ የጠጣሁትን አንቆራጠጥኩት! ሲብስብት እንደሴት እሪሪሪ ብሎ ሲጮህ ያየኸው እንደሆነ፣ ያ ጎምላላ፣ ያ ወንዳወንድ ነው ወይ ያስብላል ...
የአንድ እግሩን ጫማ አረጋሽ የምትባል እዚህ ታች አለች .እሷ በር ጥሎ እግሬ አውጭኝ ሊያመልጠኝ መሰለህ ... እንዳራስ ነብር ተወርውሬ ከረባቱን ጨመደድኩና (መቸስ አዙሮ አያይም እንጂ አንገቱ ለከረባት የሰጠ ነበር) እንደ በግ እየጎተትኩ አንጄቴ የጤሰውን ያህል፣ እስኪበቃኝ አበራየሁት! የሞት ሞቱን እየተውገረገረ ተነስቶ በረረ..ይኼው ስንት ዓመቱ ከዚያን ቀን ጀምሮ ይኑር ይሙት እንጃ፣ ጠፋ ጠፋ! አንዷ ኮማሪ
ጋር ጠቅልሎ ገብቶ የቢራ ብርጭቆ እያጠበ ይሆናል! ምናሻኝ ለምን እግር አያጥብም!
ያንዣቡ ምን እዳየ ..ከዛ ወዲያ አንድ ወንድ ንክች ሳያደርገኝ ይኼው ቅብርር ብዬ አለሁ” አሉ፣ ፉከራ በሚመስል ድምፅ ...አንገታቸውን በኩራት እየሰበቁ።
ኧረ አንችስ እሳት ነሽ የናቴ ልጅ!” አለ ወዛደሩ በስሜት ተውጦ! እንዴዴዴዴ...ቅድም ገብስ የሚወቅጥበትን ዋጋ ሲነጋገሩ …” አንቱ!” እያለ አልነበር ሲያናግራቸው የነበረው?
…ከምኔው “አንቺ!” አለ? ብዬ ገረመኝ!
እየገረመኝ ይኼን ሰምቼው የማላውቅ አዲስ ታሪካቸውን እያብሰለሰልኩ ማታ ሁሉ እንቅልፍ አልወስድ ብሎኝ አመሸ ።
#ዘጭ
በቀጣዩ ቀን፣ እማማ ያንዣቡ ሲጀምሩና ሲያቋርጡ የኖሩቱን የጃንሆይ ታሪክ፣ ድንገት አውሩልኝ ብዬ ሳልጠይቃቸው፣ ከመሬት ተነስተው ያወሩልኝ ጀመ፡ር …
አንድ ቀን አገር ሰላም ብዬ እዚህ እታች ባንኩ ቤት ደርሼ ስመለስ ብለው ሲጀምሩ ሌላ ወሬ መስሎኝ ነበር።

👍2