#ፍካሬ_እውነት
“ሰማዩ!
እንዲህ እንደዛሬ ርቆ ሳይወረወር
ሁሉ 'ንዳሻው የሚቆርሰው
ሁሉ 'ንዳሻው የሚጎርሰው
ግዙፍ እንጀራ ነበር»
ብለሽ የነገርሽኝን እውነት ነው ተቀብያለኹ
ምክንያቱም ወድሻለኹ
“አያቴ!
ሦስት መቶ ዓመታት ኖሩ
የመቶ ዓመት ሰው እያሉ
ብርቱ ጽኑ ነበሩ
ዝሆን በጥፊ ጣሉ
አንድ ጥይት ተኩሰው ሦስት ነብሮች ገደሉ”
ብለሽ የነገርሽኝን እውነት ነው ተቀብያለኹ
ምክንያቱም ወድሻለኹ
“አባቴ!
ከሰዎች ሁሉ ይለያል
ባ'ይኖቹ ብቻ ባይኾን በማጅራቱም ያያል
ብለሽ የነገርሽኝን እውነት ነው ተቀብያለኹ
ምክንያቱም 'ወድሻለኹ
ግና ጅል እንዳልመስልሽ አይደለሁም ተላላ በርግጥ በጄ ብላሻለች ነፍሴ ሁሉን ተቀብላ
እውነት ማለት ከሚወዱት መስማማት'ንጂ
አይደለምና ሌላ፡፡
🔘በዕውቀቱ ሰዩም🔘

#ሐኑን
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
ክንብንቧ ጫፍ ላይ የተንጠለጠሉ ክሮችን እያፍተለተለች ቆየች ጣቶቿን አያቸዋለሁ።ጫፎቻቸው እንደቲማቲም የቀሉ፣ ስትዘቀዝቃቸው የሚንጠባጠቡ የደም ጤዛዎች ይመሳስላሉ ውብ ጣቶች አስቀይሚያት ይሆን ብዬ ስለፈራሁ፤ ቀረብ አልኳትና በሁለት እጆቼ ጉንጮቿን ይዤ ቀና አደረኳት፡፡ እንባዋ በንጹህ ቀይ ቆዳዋ ላይ ኮለል ብሎ ፈሰሰ።ቃል አልተነፈሰችም አልተነፈሰችም፡፡ በለስላሳ እጇ ጉንጫ ላይ ያረፈ እጄን ያዘችኝ፡፡ትኩስና ለስላሳ መዳፏ ልክ እንደ ከንፈር የልቧን ሐሳብ የሚያወራ ይመስል ነበር፡፡ጥብቅ አድርጋ ያዘችኝ፤ እናም አንድ ነገር ብቻ ተናገረች
እውነትህን ነው? እኔን ታገባኛለህ?”
እዎ”
መልሳ አቀረቀረች፡፡ እጇ ግን እጄን እንደያዘ ነበር፡፡ይኼ ቃሌ እስካሁንም እንደ እሳት ጅራፍ ራሴን ይገርፈኛል፡፡ወንዳዊ ማንነቴ በደመነፍስ የፈጠረው ክፉ ማጭበርበር ነበር። ልምዱ ኑሮኝ አልነበረም፡፡ እንዲያው እንዲህና እንዲያ ልበላት ብዬ ቃል ቀምሬም አልነበረም፡፡ከየት እንደመጣ ባላውቀውም እእምሮዬ አጠቃላይ ሁኔታወችን በፍጥነት ደምሮና ቀንሶ ሐኑን ምን እንደምትፈልግ ገብቶት ነበር: አፍቅራ እዚህ መኖር አልነበረም
ፍላጎቷ፡፡ ከዚህ በጠቆረ ትዝታ ከጠቆረ ግቢ ብን ብላ መውጣት ነበር መሻቷ ልክ በውሃ በተከበበ ደሴት ላይ ተከባ መውጫ ላጣች ነፍስ፣ራሴን ከዚህ መውጫ ጀልባ ነኝ ብዬ አቀረብኩላት፤ ማቄን ጨርቄን ሳትል ጀልባዋ ላይ ወጣች!!
እጇ ትንሽ የተንቀጠቀጠ መሰለኝ ወይስ የእኔ ነው!? ከዚህ ቀን በኋላ ሐኑን እኔ
በፍቅር ከነፍን፡፡ ግን ፍቅር ነው ወይ እላለሁ፣ ራሴን አላምነውም፡፡ የአባቷ እግር ከቤት ከወጣ የሐኑን እግር እኔ በር ላይ ነው፡፡ ፍቅር እንደ እሳተ ገሞራ ነው- የተረጋጋውን ምድር፣በሰላም ለዘመናት ተኮፍሶ የኖረን የአለት ተራራ ሽቅብ ፈነቃቅሎት ሲወጣ፣ ብናኝና ጭሱ አካባቢውን ይሸፍነዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ገሞራ የፈነዳበት ምድር ወደነበረበት
ተፈጥሮው አይመለስም:: እዚያ ግቢ የዚያን ጊዜ የሆነው እንደዚያ ነበር፡፡ የፍቅር ገሞራው ሲፈነዳ፣ ብናኙ የሐኑንን ፊት ሸፈነው፡፡ረጋ ያለችው ልጅ፣ የምትይዝ
የምትጨብጠውን አጣች፡፡ ብናኙ ፈገግታ ሆኖ ፊቷን ሸፈነው…ብናኙ የመሻት ነበልባሉን ወደቤቴ ልኮ አለት ብቸኝነቴን አቀለጠው፡፡ የሐዘን ደመና ከውብ ፊቷ ላይ ተገፎ እንደጥዋት ፀሐይ ውብ ፈገግታ ሲረጭ ግቢውን እሳት ሞላው፣ደግሞ ግቢውን ውሃ ሞላው ግቢው በረሃ ሆነ ደግሞም ግቢዉ የኤደን ገነት ሆነ፣ በአንድ ጊዜ ሁሉም ነገር ሆነ፡፡ በዚህ ፍንዳታ ውስጥ ተረጋግተው ጫታቸውን የሚቅሙት አባቷ
ልጅ ትንሽ አትሞክርም? ይሉኛል ጫታቸውን እያሳዩኝ፡፡ “በዚህ ላይ ጫት
ተጨምሮበት” እላለሁ በውስጤ፡፡ አለመታመንኮ ነው ሰው ግቢ ገብቶ የሰው ሴት ልጅ - ያውም ያመኑት የአንድን ትልቅ ተቋም ሥራ አስኪያጅ ነው፣ ራሱን የገዛ ሰው ነው ያሉትን ሰው … ግን ደግሞ ቦታና ጊዜ፣ ሥራና ደረጃ፣ ፍቅር ፊት ምን ጉልበት አላቸው? ዋናው ጥያቄ ይኼ እብደት ፍቅር ነው ወይ ነው? ራሴን አላምነውም!
ሐኑን ጋር ዓይኖቻችን ተንሰፍስፈው ይፈላለጋሉ፡፡ ግድቡን እንደጣሰ ጎርፍ ራሷን መቆጣጠር አቅቷት ነበር፡፡ አንዳንዴ አባቷ እቤት እያሉ ጭምር ድንገት እቤቴ
ትመጣለች ፡፡
ኧረ አባባ እላለሁ በጭንቀት ድምፄን ቀንሸ፡፡
እየሰገደ ነው ትለኛለች፡፡ ከዛ እቅፌ ውስጥ ናት፡፡
ኧረ አባባ እላለሁ፣
ውጭ ስልክ እያወራ ነው ትላለች፡፡ ይሉኝ ነካክቼ እንደ አልኮል ያስከራትን ፍቅር
በምን ላረጋጋው? ዓይኗንም ልቧንም የሠወረው ፍቅር፣ሁለታችንንም አባቷ ዓይን ላይ ሊጥለን እያዳፋ የሚነዳ ደራሽ ጎርፍ ሆነብኝ፡፡ ፈጣን ነበር_ሁሉም ነገር በጣም ፈጣን እየተጨነቅሁ እሰማታለሁ፡፡ እያሰብኩ በደመነፍስ እጓዛለሁ፡፡ አንዳንዴ ሌሊት ትደውልልኛለች፡፡ ፍቅር ከጊዜ ሥርዓት ያፈነገጠ ስሜት መሆኑ የገባኝ ያን ጊዜ ነበር፡፡ ብዙ ከዛ በፊት ያልገባኝ ነገር የገባኝ ያኔ ነበር፤ ብዙ ከዛ በፊት ገብቶኛል ያልኩት ነገር የጠፋብኝም ያኔ ነበር፡፡ የመኝታ ቤቷ መስኮት እና የሳሎኔ መስኮት ትይዩ ስለሆነ መጋረጃችንን ሰብስበን ዝም ብለን እንተያያለን እስር ቤት ያሉ ነፍሶች ነበር የምንመስለው፡፡
እነዚያ ሌሊቶች መቼም የሚረሱኝ አይደሉም አንድ ምሽት ደረቅና ሞቃታማዋ ድሬዳዋ፣በድንገተኛ ዶፍ ዝናብ ተጥለቀለቀች፡፡ የድሬደዋ ሰማይ ግፏን አፍና እንደኖረች ሴት፣ ድንገት ነው አስፈሪ ዶፉን እንደ እንባ የሚዘረግፈው፡፡ ዝናቡ ከሰማይ ብቻ ሳይሆን፤ከምድርም ይፈልቅ ይመስል፣ ከምኔው ምድሩ በጎርፍ እንደሚጥለቀለቅ ይገርመኛል፡፡ የዚያን ቀን ዝናቡ ሌሊቱን ሙሉ አላቋረጠም፡፡ በየመኻሉ ሰማዩን ሰንጥቆ
አካባቢውን በብርሃን የሚያጥለቀልቅ የመብረቅ ብልጭታ የመስኮቴን መጋረጃ እያለፈ ቤቴን በብርሃን ይሞለዋል፡፡ በተደጋጋሚ ወገግ ይላል፡፡ ምን እንደገፋኝ እንጃ ፣ተነስቼ የመስኮት መጋረጃዬን ሰበሰብኩት፡፡ ሐኑን ልከ የተቀጣጠርን ይመስል መጋረጃዋን ስብስባ ውብ ጉርድ ፎቶ ግራፍ መስላ መስኮቱ ጋ ቆማ ነበር …በእያንዳንዱ ብልጭታ፣ የሐኑንን ውብ ፊት አእምሮየ እንደፎቶ እያተመ ያስቀምጣል፡፡ በግራ ትከሻዋ በኩል
አልፎ ጡቷ ላይ የሚርመሰመሰዉ ጸጉሯ ግማሽ ፊቷን የከበበ ጥቁር ፍሬም መሰሏል፡፡ እስከ ዛሬ ሐኑንን ሳስብ፣ ያ መልኳ ነው ቀድሞ የሚታወሰኝ፡፡ እንደ ቲማቲም የቀሉ ከንፈሮች ከመቅላቱ ብዛት በወርቃማ ቆዳ የተለበጠ የሚመስል ደረት…ሥዕል፡፡
በየመስኮት መስታዎቶቻችን ላይ የሚንኳለለው የዝናብ ውሃ፣ ነጋችንን አውቆ እርሙን የማያወጣ የዘመን እንባ ይመስል ነበር፡፡ ጡቶቿ ቢጫ የሚበዛበትን ባለብዙ አበባ ሥዕል፣ ስስ የሌሊት ልብሷን ወጥረው፣ ከተደገፈችዉ መስተዋት ጋር ጫፋቸው ተነካክቷል፡፡ ወደ መስተዋቱ ስትጠጋ፣ አፍንጫዋ በመስተዋቱ እየተደፈጠጠ ያስቀኛል፡፡
እኔን በፈገግታ እያየች መስተዋቱን ስትስመው፣ቀያይ ውብ ከንፈሮቿ መስተዋቱ ላይ በክቡ ተለጥፈው፣ ትንፋሽዋ መስተዋቱ ላይ ጭጋግ ይፈጥራል፡፡ በትንፋሽዋ ጉም
በተሸፈነው መስተዋት ላይ፣በጣቷ የልብ ቅርጽ ትሥልበታለች ፡፡ትንፋሽዋ መስተዋቱ ላይ በሚፈጥረው ላቦት ምስሏ መደብዘዝ ሲጀምር፣ መስተዋቱን በመዳፏ ትወለውለዋለች፡፡ በዚህ ጊዜ የደበዘዘዉ ምስሏ ቦግ ብሎ ይወጣል፡፡ በቃ እንተያያለን፣ ያለድምፅ ዝም ብለን
መተያየት…በምልከት ልተኛ ነው ስላት በእጇ ትንሽ እንድቆይ ትለምነኛለች፡፡ያ ሌሊት በተደጋጋሚ ሕልሜ ይመጣል፡፡
መስተዋት ተደግፌ አድሬ፣ ሊነጋጋ ሲል ድብን ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡ ጧት የቤቴ በር ሲከፈት እንኳን አልሰማሁም፡፡ በጧት እንደ እሳት የሚፋጅ ላሰላሳ ገላዋ፣ የሞቀ አልጋዬ ውስጥ ገብቶ ስትለጠፍብኝ ነበር የነቃሁት፡፡ በእንቅልፍ በሰከረ አእምሮዬ ላይ በሽቶ ባበደ ጠረኗ የታጀበ ሰውነቷ ሲያቅፈኝ፡ ነገሩ ሕልም ይሁን እውነት በወጉ እንኳን ሳይገባኝ፣ የሐኑን የሚንቀጠቀጡ ትኩስና ለስላሳ ከንፈሮት፣ ከንፈሬ ላይ አርፈው ነበር፡፡
ሰውነቴ ከእእምሮዩ ቀድሞ ነቃ፤ ረዥም በሰመመን የተሞሉ ደቂቃዎች ይሁኑ ሰዓታት ከሥሬ ሆና በለስላሳ ቀይ ፊቷ ቆዳ ላይ እንባዋ ኮለል ብሎ ወደ ጆሮዋ ሲወርድና በሕመም ስትቃትት፡ ሥጋዊ ወንድነቴ ከሚሰማው አብሮነት ይልቅ፡ አንዳች የነፍሴ ክፍል ላይ ነፍሷ ለዘላለም ሲነቀስ ይሰማኝ ነበር፡፡ አእምሮዬ በአንድ ጊዜ ሁለት ተቃራኒ ሐሳቦችን እያሰበ ነበር፡፡ እየተሳሳትኩ ነው” እና “ልክ ነኝ” የሚሉ ሐሳቦች፡፡ እንደዚያ ነበር የማስበው፡፡ አእምሮየ ምንም ያስብ ምን፡ ገና ከጅምሩ ሰውነቴ ለአእምሮዬ መታዘዙን ትቶት ነበር፡፡ ብዙ ሰው የሆንኩ እስኪመስለኝ ድረስ

👍1🔥1
ተከፋፍዬ፣ ተሰነጣጥሬ፣ ሁሉም ስንጣሪ ውስጥ ስጋትና ደስታ እኩል ተሰትኖ ነበር፡፡
የዚያ ቀን፣ አባቷ ከሚያከራዩት ሱቅ፡ አንደኛዉ ዉስጥ ጎርፍ ገባበት ተብለው በጧት የሄዱ፣ ወደምሳ ሰዓት ነበር የተመለሱት፡፡ገና የግቢውን በር እግራቸው እንዳለፈ “ሐኑን አዘጋጅልኝማ!ብለው፡ ገላቸውን ሊታጠቡ ከቤቱ ኋላ ወዳለው መታጠቢያ ቤት ሲገቡ፣
አላስችለኝ ብሎ ወጣሁና “ደህና ነሽ” አልኳት ዕፍረት ባረበበት ፊት “ደህና ነኝ"
አለች፡፡ቀና ብላ አላየችኝም፡አባቷ ጫታቸውን አቅርበው በረንዳቸው ላይ ቁጭ እንዳሉ፣ አላስችለኝ ብሉ እንደገና ብቅ እልኩ፡፡
“ልጅ ሥራም አልሄድክ እንዴ?” አሉኝ፡፡ ስላዩኝ ደስ ብሏቸው ነበር::
“ዛሬ እልገባሁም፣ እቤት ሆኜ የምጨርሰው ነገር ነበር… "
እንኳን ያልሄድክ፣አገር ምድሩ ጎርፍ ሁኗል፡፡ ማረፍ ጥሩ ነው…ዱኒያ እንደሁ
እትሞላ! ታዲያ ይችን ነገር ትንሽ ኤልሞክርም አልክ?ብለው የያዙትን ጫት እጃቸው ላይ መታ መታ እያደረጉ ጋበዙኝ፡፡ የጫት ቅጠሎቹ ጫፋቸው ወደቀይ የሚያደላ ቡና አይነት ነበሩ ልክ እንደ አባባ ፂም ብዙ ጊዜ እንደማደርገው የበረንዳውን ብረት ተደግፌ ፈታቸው ቆምኩና ስለጎርፉ አወራን፡፡ በመሃል፣
“ሐኑን ወንበር አምጭለት የኔ ነገር" አሉ፡፡
“ቆይ ራሴ አመጣለሁ” ብዬ ወደቤት ገባሁ፡፡ ሐኑን ውሃ በፕላስቲክ ጆግ ይዛ ስትወጣ፣ ልክ እንደማይተዋወቅ ሰው በሩ ላይ ተሳለፍን፡፡ ስንተላለፍ እስከ ዛሬ ከአእምሮየ ያልጠፋዉ ጠረኗ አውዶኛል፡፡ ልብሷ እንደ መንፈስ በስሱ ዳስሶኝ አልፏል፡፡ የዛን ቀን፣ ከወትሮው ረዘም ላለ ሰዓት ከአባቷ ጋር ተቀምጨ ስናወራ ቆየን በየመሀሉ ሐኑንን በጠሯት ቁጥር እሳቀቅ ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወንድ ጋር የተኛች ሴት፣ እንዲህ ቁጭ ብድግ ስትል፣ ምን የተለየ ነገር ይሰማት ይሆን? የሚል ምርመራዬን በዓይኔ እየተከታተልኩ፡አባቷ ጋር የባጥ የቆጡን እናወራለን፡፡
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share

#ክፍል_አምስት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
ለመጀመሪያ ጊዜ ከወንድ ጋር የተኛች ሴት፣ እንዲህ ቁጭ ብድግ ስትል፣ ምን የተለየ ነገር ይሰማት ይሆን? የሚል ምርመራዬን በዓይኔ እየተከታተልኩ፡አባቷ ጋር የባጥ የቆጡን እናወራለን፡፡ የሚበዛው ወሬ ሱቃቸው ዉስጥ
ስለገባው ጎርፍ ነበር፡፡ ሐኑን ማረፍ ባለመቻሏ፣ የሆነ ደስ የማይል ነገር ቢፈጥርብኝም፣ አጠገቧ መሆኔ ግን ምቾት ሰጥቶኝ ነበር፡፡እርሷም ገብቷታል፡፡ አባባ ጎን ተቀምጣ፣ ሳወራ ታየኛለች፡፡ አስተያየቷ ሥጋን ዘልቆ ነፍሴ ድረስ የሚሰማ ሐዘን ይለቅብኝ ነበር፡፡ ዓይኖቻችን ሲጋጩ ዓይኖቿ ማረፊያ ያጣሉ፡፡
ከዚያን ቀን ጀምሮ፣ ሐኑን የምታደርገው ነገር ሁሉ ያስደነግጠኝ ነበር:: አንድ ቀን ድንገት የሥራ ቦታዬ መጣች፤ ደስታም ድንጋጤም ተቀላቀለብኝ፡፡ሰዎች እንዳይሰሙ ድምፅዋን ቀንሳ ናፈከኝ!” አለችኝ፤ እንዲያዉ የአባቷ ነገር እያስጨነቀኝ እንጂ፣ እኔም የምይዝ
የምጨብጠውን ነገር አላውቅም ነበር፡፡ እንደትኩስ ፍቅር ምን አደገኛ ነገር
አለ?…ፍቅራችን በጭንቀትና በጥንቃቄ የተሞላ ደስታ ነበር፡፡ ልክ የተከሰከሰ ጠርሙስ የተዘራበት ወለል ላይ በባዶ እግር እንደሚራመድ ሰው፣ እጅግ በጥንቃቄ፣ ግን ደግሞ ትንፋሽ የሚያሳጣ፣ አብረው ሆነው የሚያነፋፍቅ አንዳች ነገር፡፡ አንዳንዴ ከሐኑን ጋር
አንድ ግቢ ውስጥ ከመኖራችን እና ብዙውን ጊዜ አብረን ከማሳለፋችን የተነሳ፣ ግንኙነታቸን ከፍቅረኝነት ይልቅ ትዳር የሚመስል ቅርፅ ይይዝ ነበር፡፡ ልብሶቼን ላውንደሪ ወስዳ ትሰጥልኛለች፣ ምግብ አባባም ቢኖሩ ባይኖሩም ውጭ በልቼ ካልገባሁ እነሱ ጋር ነበር የምበላው፡
አንዳንድ ቀን አባባን ነግረናቸው ፣አብረን ወደ ገበያ እንሄዳለን፡፡ አባባ ሐኑንን ብቻዋን ከቤት አያስወጧትም፤ ወይ አብረዋት ይወጣሉ፣ አልያም አትወጣም፡፡ እኔ ጋር ግን ስትወጣ “ልጅ መንገድ ላይ እንዳትጠፋፉ እጇን ይዘህ አደራ! ከማለት ውጭ ምንም ቅሬታ ፊታቸው ላይ አይታይም ነበር፡፡ እንደውም አንዳንዴ 'አንች ልጅ ሰው ጋር
እንዳታጋጭው” ብለው ለእኔ ያስባሉ፡፡ ከግቢው እንደወጣን ሐኑን “
እጇን ያዛት ተብለሃልኮ ትልና ክንዴን ይዛ በሳቅ እየተፍለቀለቀች፣ በጋሪ ተሳፍረን ቀፊራ ወደሚባለው ገበያ እንሄዳለን፡፡ ንፋሱ ክንብንቧን ሊገፉት ሲታገል፣ ክንዴን ይዛ አንገቴ ስር ትሸጎጣለች፡፡ አብረን እስከሆንን ድረስ ጋሪው የትም ቢወስደን ግድ አልነበረንም፡፡ ቀፊራ ወርደን ከቴምር እስከጭሳጭስ፣ ከዶሮ እስከ ብርቱካን እንገዛለን፤ የሚበዛውን ጊዜ ግን እንዲሁ በመዞር ነበር የምናሳልፈው፡፡ እየተነሳ ፊት ላይ በሚሞጀረው አቧራ ውስጥ፣
በጫጫታውና ግርግሩ ውስጥ፣ በእነዛ ጎሊቶች መሃል ሐኑን ቀይ ሽቲ በቀይ ሻርፕ
ለብሳ(ብዙ ጊዜ ስትወጣ እንደዛ ነበር የምትለብሰው) ተያይዘን ስንዞር ውለን
የሸመትነውን ጭነን፣ በጋሪ ወደ ቤት ስንመለስ በደመና ሰረገላ ላይ ተጭነን ወደ ሰማየ ሰማያት የምንመጥቅ እስኪመስለኝ፣ደስታዬ ወደር አልነበረውም፡፡
ሁሉም ነገር የተረጋጋ፣ ደሰ የሚልና ሰላም የሰፈነበት፣ ሕልም የሚመስል ሕይወት ነበር፡፡የሐኑን አባት እልፎ አልፎ አልጋ ላይ ከሚጥላቸው ሕመም በስተቀር፣ሁሉ ሰላም ነበረ:: የሰላም ትክክለኛ ትርጉም ረብሻ አለመኖር እይደለም፣ መነሻው ፍቅር የሆነ ረብሻ በነፍስ ውስጥ እንደመዓበል መተራመሱ ነው፡፡ ፍቅር የሌለው ሰላም ውሃው እንደደረቀ ወንዝ
ነው፡፡ በሰላም ውስጥ ወንዝ መፍሰስ አለበት ፣ወንዙን ሊሻገሩ የሚታገሉ ነፍሶት መኖር አለባቸው፤ በውሃው ውስጥ የሚጋጩ የሚሳሳሙ ድንጋዮች መኖር አለባቸው፣አሳዎች መኖር አለባቸው፡፡ ሰላም ነበረን እኔና ሐኑን፡፡
አባቷ ህመማቸው ቶሎ ቶሎ ባይነሳባቸውም ሲያማቸው ግን የሚያስደነግጥ ነበር፡፡ ደግሞ ለከፉቱ ቀድሞ አፋቸውን ነው የሚይዛቸው፡፡ እኔ እዛ ቤት ከተከራየሁ እንኳን ይኸው ሕመም ሁለት ጊዜ ሲያማቸው አጋጥሞኝ ነበር፡፡ ከስኳር ሕመም ጋር የተያያዘ
መሆኑን ነግረውኛል፡፡ደግነቱ ብዙ አይቆይባቸውም ነበር፡፡ ሐኑን የአባቷ ነገር
እይሆንላትም፡፡ በምድር ላይ ያሏት ብቸኛ ዘመድ እሳቸው ናቸው ፡፡ አባቷ ከወንድሞቿና ከእህቶቿ ጋር እንድትቀራብ ያላደረጉት ጥረት የለም፡፡ ይሄንኑ ነገር አንድ ጊዜ፣ በጣም ከተቀራፈብን በኋላ በሐዘን ነግረውኛል
“መቼስ! ሰው ይሳሳታል፤ አንዴ እጠፋሁ፣አባት ላይ ይጨከናል? እሷስ እህታቸው እይደለችም? ቤቱ እንደሆነ እንኳን ለነሱ ለባዳውም ይበቃል፡፡ እንዴት እህታቸውን ካለዘመድ ያስቀሯታል? ዕድሜዬም ገፍቷል፡ በሽታውም እየበረታብኝ ነው፡፡ድንገት
አላሀ በቃህ ካለኝ እች ልጅ ብቻዋን እንዳትቀር ብየ፣ እኔ ቁልቁል ወደ ልጆቼ ታረቁኝ ብዬ ሽማግሌ ብልክክ አከላፍተው መለሷቸው፡፡ መቼስ በእኔ አይጨከኑም ብዬ ራሴዉ ብሄድ፡ የተቀመጥኩበት እየጣሉኝ ወጡ፡፡ ልቤ አዘነ፤ ግን ኤልረገምኳቸውም፣ሥጋ
ናቸዋ አባት ቢያጠፋስ ይኼ ተገቢ ነው? ድፍን ድሬዳዋ ይጠየቅ፣ አንቀባርሬ ነው
ያሳደኳቸው፡፡ አሜሪካ ሲሉ፤ አውሮፓ … እንሂድ ሲሉ ልኬ፣ ካለወጉ ከድሬደዋ አሜሪካ ብር እየላኩ ያስተማርኳቸው እኔ ነኝ፡፡ እኔስ እሺ፡ በድያቸው ይሆናል፣ እዚች አንድ ፍሬ ልጅ ላይ ይጨከናል? እንኳን ሥጋው ሁና፣ ይችን ልጅ አያቶ የሚጨከን መገደኛ አለ አነጋገራቸው ያሸብራል ሽማግሌ ፊታቸው ላይ የሚያንዣብበው ሐዘን…ማረፊያ አጥተው ዙሪያ ገባው ላይ የሚንከራተቱት ዓይኖቻቸው፣ አንጀት ይበሉ ነበር፡፡
ከአራት ዓመታት የድሬዳዋ ቆይታ በኋላ፣ ዋናው መሥሪያ ቤት ድንገት ወደ አዲስ አበባ ሲጠራኝ ትንሿ ገነታችን ጨለማ አጠላባት፡፡ ከሐኑን ጋር መለያየት ገደል ቢሆንብኝም፣ ወደ አዲስ አበባ መመለስ የረዥም ጊዜ ምኞቴ ነበርና ማቄን ጨርቄን አላልኩም፡፡
ሐኑንም እንደምሄድ ካወቀችበት ቀን ጀምሮ ከቤቴ ቀረች፡፡ ድንገት ግቢ ውስጥ ስንገናኝ እንኳን፣ ድንብርብሬ ወጥቶ ትሸሸኛለች፡፡ አንድ ቀን ታዲያ አባባ ወጣ ሲሉ ጠብቄ ወደ ትልቁ ቤት ሄድኩ፡፡ ስገባ የተንጣለለው ሳሎን ውስጥ፣ አልጋ የሚያክለው ሰፊ ሶፋ ላይ ኩርምት ብላ ተቀምጣ አገኘኋት፡፡ ምንም እየሰራች አልነበረም፡፡እንደ ወትሮው
ቴሌቪዥን አልተከፈተም፤ በቃ ቁጭ ብላ ባዶው ላይ አፍጥጣለች፡፡ እጇ ላይ
የምታምር፣ እንደሷ ፊት ብርሃን የሚረጩ ጠጠሮች የተሰከሰኩባት መቁጠሪያ ይዛ
ነበር፡፡ ድንገት ስገባ የምታደርገው ግራ ገብቷት፣ ተነስታ ቆመችና ዝም ብላ ስታየኝ ቆይታ በቆመችበት እንባዋ መውረድ ጀመረ፡፡ አቀፍኳት! ለረዥም ደቂቃ አቅፈያት ቆምኩ፡፡ ደረቴ ላይ ሸሚዜን አልፎ የትኩስ እንባዋ እርጥበት ይሰማኝ ነበር፡፡
ሐኑን አዲስ አበባ እንደደረስኩ ቤት እከራያለሁ፣ ነገሮችን አመቻችቶ በአንድ ወር ውስጥ እመለሳለሁ”
“ለምን?”
“ምን ማለት ነው ለምን አባባን እንነግራቸዋለን እንጋባለን!
በቁጣ ከእቅፌ ወጥታ ራቅ አለችና፣ በትልልቅ ዓይኖቿ አፍጥጣብኝ "አትዋሸኝ እኔ እዚህ ባዶ ግቢ ውስጥ ሌላ ተስፋ የለኝም፣ የምጠብቀው አንተን ነበር የማትመለስ ከሆነ እኔን ለማጽናናት ብለህ አትዋሽ”
እልዋሽሽም እዚህ ሁልጊዜ በስጋት ከመኖር፣ አዲስ አበባ እወስድሽና ተጋብተን በሰላም እንኖራላን፣ እመለሳለሁ፡ ቶሎ እመለሳለሁ፣በጣም ቢበዛ ሁለት ወር፣ ለአንቺ ስል አይደለም፣ ለራሴ ነው፤ አፈቅርሻለሁ! ያላንቺ መኖር አልችልም፡፡አንቺ ጋር ስሆን ደስተኛ ነኝ ሐኑን ከልቤ ነበር፡፡ ያልኳትን ሁሉ ያልኳት ከልቤ ነበር፡፡
“ታዲያ ካፈቀርከኝ ለምን ትሄዳለህ? ደስተኞች ነን፣ ጥሩ ስራ አለህ አባባን ንገረውና
“መማር አለብኝ፡ መለወጥ አለብኝ፣ ከተጠራሁ ደግሞ መሄድ ግዴታዩም ነው”
“ለምንድነው ከተጠራሁ የምትለው?እነሱ ብዙ ሠራተኛ

👍1
አላቸው
፣ እኔ ግን ያለኸኝ አንተ ብቻ ነህ በአላህ አትሂድ ቢያባርሩሀም አባባ የሆነ ነገር ይከፍትልናል፡፡ ትንሽም ሱቅ ብትሆን ደግሞ ይወድሃል.» በረዥሙ ተንፍሼ ዝም ብየ እየኋት፡፡እንደወሰንኩ ስለገባት
ድንገት እጆቼን በእጆቿ አጥብቃ ያዘችኝና እንባ እየተናነቃት እሽ! እውነቱን ንገረኝ
ትመለሳለህ? የምትለው ሁሉ ከልብህ ነው? በአላህ አትዋሸኝ"
አልዋሽሽም ሐኑን እሺ ምን ልበል? ልማልልሽ” ትክ ብላ አይታኝ ፈገግ አለች! ልክ በደመና እንደተከበበች ፀሐይ ቅሬታ የተጫነው ውብ ፊቷ ላይ፣ ለስላሳ ፈገግታ ፊቷ ያሳሳ ነበር፡፡ከንፈሯን ሳምኳት፡፡እጆቿን በወገቤ ዙሪያ አጥብቃ ጠመጠመቻቸውና ደረቴ
ላይ ተለጥፉ፣
የእውነት ልታገባኝ ትፈልጋለህ?”
አችን ማግባት ብቻ ነው የማስበው ማግባት ማግባት!"
ቤተሰቦችህ የሚወዱኝ ይመስልሃል? አለች።
“ምናገባቸው ? ግን በጣም ነው
የሚወዱሽ እርግጠኛ ሁኚ … ሰይጣን ራሱ አንቺን መጥላት አይችልም
“ያልተማረች ሥራ የሌላት ሴት ስታገባ
እናቴ እስካሁን በጣቷ ነው የምትፈርመው፡፡ ላለፉት አርባ ዓመታት የቤት እመቤት ነበረች ከት ከት ብላ ሳቀች፡፡
በእርግጥ አባቴን ፍሪ፡ መሠረተ ትምህርት እስከ ሦስተኛ ከፍል ተምሯል ውብ ሳቋ ቤቱን ሞላው፡፡

#የማያልፍ_የትአለ
ስምን ያተረፈ ያበቀለ ዝና
ሳይለፋ ያገኘ ማንም የለምና
ክብርና ዝናን አንቱታንጰተላብሶ
ተወልዶ ያየሁት የለምና ነግሶ
የድርሻዬን መጠን የልፋት ድካሜን
መች እቀመጣለሁ ሳላሳካው ህልሜን
ችግር ፈተናውን እየተወጣሁት
በብርቱ ጥረቴ ሁሉን ካሳለፍኩት
ደግሞ የነገውን ከፊቴ ያለውን
ካይኔ ተሰውሮ ባላውቀው መጪውን
ከሕይወት ጥለት ላይ እስኪቋጭ አለሜ
ሩጫዬ አይቆምም እውን ሳይሆን ህልሜ።
🔘ሰላም ዘውዴ🔘
ስምን ያተረፈ ያበቀለ ዝና
ሳይለፋ ያገኘ ማንም የለምና
ክብርና ዝናን አንቱታንጰተላብሶ
ተወልዶ ያየሁት የለምና ነግሶ
የድርሻዬን መጠን የልፋት ድካሜን
መች እቀመጣለሁ ሳላሳካው ህልሜን
ችግር ፈተናውን እየተወጣሁት
በብርቱ ጥረቴ ሁሉን ካሳለፍኩት
ደግሞ የነገውን ከፊቴ ያለውን
ካይኔ ተሰውሮ ባላውቀው መጪውን
ከሕይወት ጥለት ላይ እስኪቋጭ አለሜ
ሩጫዬ አይቆምም እውን ሳይሆን ህልሜ።
🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#ሐኑን
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
በእርግጥ አባቴን ፍሪ መሠረተ ትምህርት እስከ ሦስተኛ ከፍል ተምሯል ውብ ሳቋ
ቤቱን ሞላው፡፡
''ቡና ላፍላልህ ?” አብሪያት ብዙ እንድቆይ ስትፈልግ መደለያዋ ቡና ነበር፡፡ ቡና ሲፈላ ተረጋግቼ ቁጭ እላለሁ፡፡ ታውቃለች።
አባባ ሲመጡ አፍልተሸ ከጠራሽኝ - እመጣለሁ
ልጅ ዛሬ የሰንብት አትቅምም…” ብላ ቀለደች
እንኳን ጫት ጨምሬበት ልጅዎን ሳያት እየመረቀንኩ ተቸግሬያለሁ' አልኩ፣ በአባባ ድምፅ፡፡ከንፈሯን እንደገና ስሚያት ወጥቼ ወደ ቤቴ ገባሁ፡፡ በቀጣዩ ቀን ከእንቅልፌ ስነሳ ሐኑን አልጋየ አጠገብ ወንበር ላይ ተቀምጣ ትክ ብላ እያየችኝ ነበር፡፡
ትተኸኝ አትሂድ!”
ድፍን ሦስት ዓመታት ከድሬዳዋ ሰማይ ሥር፣ አንዲት እንደ ላባ የለሰለሰች ነፍስ፣
እንዲህ በፍቅር አውሎ ንፋስ እየተንሳፈፈች ነበር፡፡ በሰላም በምትኖርበት ግቢ እንደነፋስ
በሽንቁር ገብቼ ነፍሷን በአየር ላይ እንዳንሳፈፍኳት፣ በዚያው በተስቀለችበት የኋሊት ትቻት፣ ወደ አዲስ አበባ ተመለስኩ፡፡የሚወስደኝ መኪና በር ላይ
መጥቶ ሲቆም፣ አንድ ሽማግሌ ከቆንጆ ልጃቸው ጋር፣ ትልቁ የግቢ በር ላይ ቁመው እጃቸውን ለስንብት
ሲያውለበልቡልኝ ከእንባዬ ጋር እየታገልኩ ነበር፡፡ “ምን ፈልጌ ነው የምሄደው? ምን? እያልኩ ለራሴ፡፡ ድሬዳዋን ለቅቄ ስወጣ እንደ ጥይት ከምትወነጨፈው መኪና ግራና
ቀኝ ወደ ኋላ የሚሮጡ የሚመስሉት ቁጥቋጦና ድንጋዮች፣ አንዲት ሚስኪን አፍቃሪ ባዶ ግቢ ዉስጥ ትቼ መሄዴን ሰምተው ሊያፅናኗት ወደ እሷ የሚሮጡ ይመስሉ ነበር፡፡ ከሩቅ አፍቃሪ የቅርብ ድንጋይና ቁጥቋጦ ይሻላል የሚሉ ዓይነት፡፡
አዲስ አበባ የጠበቀኝ ገና አዲስ ተከፍቶ ውጥንቅጡ የወጣ ቅርንጫፍ ነበር፡፡ ሙሉ ቀን የማያባራ ችግር የደንበኞች ንጭንጭ የማይለየው ባንክ፡፡ ለዚሁ ቅርንጫፍ ነው እንግዲህ እድግት ብለው ያመጡኝ፡፡ ገና ከመድረሴ በሥጋም በነፍስም ሥራየ ላይ ተጠመድኩ፡፡ ሠራተኞቹ በሙሉ አዲስ ነበሩ፡፡ ሚስኪን የኒቨርስቲ ተመራቂዎች። ሁሉም ነገር ላይ የተሳሳቱ የሚመስላቸው፤ ሁሉም ደንበኛ ብር ሊያወጣና ሊያስገባ
ሳይሆን ሊያጭበረብርና ሊዘርፍ የመጣ የሚመስላቸው ስጉ ነፍሳት፡፡ እእምሯቸው ቁጥር ስፍር በሌለው ሕግ ማስጠንቀቂያ ተሞልቶ በፍርሀት የተሸበበ፡፡ የማይጠይቁኝ ጥያቄ አልነበረም፡፡ እንዳንዴማ ከረባት አስተሳሰር ሁሉ ይጠይቁኝ ነበር።
በተደጋጋሚ ዋናው መሥሪያ ቤት የሚያግዘኝ ሰው እንዲልኩልኝ ብወተውትም፣ ለአንድ ወር ብቻየን ፍዳዩን አበሉኝ፡፡ሲሳካልህ ለማጨብጨብ ከወደቅህም ትችታቸውን
እንደለይፍ ለመምዘዝ ጥጋቸውን ይዘው እንደሚመለከቱ ሥራ አሥኪያጆች የሚያስጠላኝ ፍጥረት የለም፡፡ የኔዎቹ እንደዛ ነበሩ፤ ስልክ እየደወሉ “በአንተ እንተማመናለን ይሉኛል አድናቆት እንደሙዳ ስጋ እየወረወሩ የቢዝነስ አጥራቸውን ሲያስጠብቁኝ ሊያድሩ
ይዳዳቸዋል፡፡ እያመሸሁ ከመሥራት አልፎ ቅዳሜ ሳይቀር እየገባሁ ለመሰራት ተገድጄ ነበር፡፡ በእነዚህ ጊዚያት እንኳንስ ለሐኑን ቃል እንደገባሁት ቤት ልከራይ ቀርቶ፣ ቀልቤን ሰብስቤ ጓደኞቼን እንኳን ማግኘት አልቻልኩም ነበር፡፡ መጨረሻ ላይ ሲብስብኝ፡ ወደ ሥራ እስኪያጁ ቢሮ በአካል ሄጀ ከዚህ በኋላ ሰው ካልመደባችሁ ምንም ማድረግ አልችልም አልኩት፡፡
በቀጣዩ ሳምት በወረቀት ተከብቤ ባቀረቀርኩስት፣ በመስተዋት የተከለለች በር አልባ ቢሮዬን አልፋ አንዲት ሴት እፊቴ ተገተረች፡፡ መጀመሪያ ያየሁት፣ ከጉልበቷ በላይ በቀረ ጉርድ ጥቁር የቢሮ ቀሚሷ ምክንያት የተጋለጡትን ጠይምና ውብ እግሮቿን ነበር፡፡ ቀና ብዬ ፈገግ ለማለት ሞከርኩ፡፡ ፈገግ ብላ በስሜ ጠራችኝ፡፡ ግር እያለኝ “አቤት! ምን ልታዘዝ? እልኳት፡፡ እየተፍለቀለቀች
"እራስህ ምን ልታዘዝ ከሰላም ቢሮ አፈናቅልህ ያስመጣሃኝ አንተኮ ነሆ" ተሳሳቅን፡፡
ከዋናው መሥሪያ ቤት አዲስ የተላከች ልጅ ነበረች፡፡ ቀደም ብዬ አንዲት ሴት
እንደምትመጣ ብሰማም እንዲህ ወጣት ትሆናለች ብዬ አልጠበኩም ነበር፡፡ ምክንያቱም ስለሷ ጉብዝና አጋነው ነበር የነገሩኝ፡፡ “ሔራን እባላለሁ ቦስ! ትርፍ ወንበር ነገር የላችሁም” ብላ ዙሪያውን ተመለከተችና፣ ጥግ ላይ ከተቀመጡት ተሽከርካሪ ወንበሮች አንዱን ራሷ እየገፋች መጥታ፣ ፊት ለፊቴ ተቀመጠች፡፡ እንደ ደም የቀላ ትልቅ የቆዳ ቦርሳዋን ከስሯ አሰቀመጠችና እሺ እንዴት እየሄደ ነው? ብላ ፈገግ አለች፡፡ ጠይም ቆዳዋ ጥራቱ የሚገርም ነው፡፡ጠይም ነበልባል፡፡ ደስ የሚል ወርቃማ ቀለም የተቀባዉ
ረዥም ጸጉሯ፡ መጀመሪያ ላይ የራሷ አልመሰለኝም ነበር …ስትስቅ እስከ ጆሮ ግንዷ ደርሰው የሚመለሱ ትልልቅ እና የሚያምሩ ከንፈሮቿ ከውብ ጥርሶቿ ጋር ተዳምረው ፈገግታዋ የልብ ያደርሳል” የሚባልላት ዓይነት አድርገዋታል፡፡ ቁመቷ ዘለግ ያለ ነው፡፡ በዝያ ላይ ውብ ቅርጽ፤ ስትናገርም ስትንቀሳቀስም ፈጣን፡፡ እንዲህ ነበር የመጀመሪያዉ ትውውቃችን፡
ሔራን ባንከ ውስጥ ተወልዳ ያደገች እስኪመስለኝ፣ እያንዳንዱ ሥራ በደም ሥሯ ውስጥ የሚፈስ ነበር የሚመስለው፡ በዛ ላይ ላለሁበት ቦታ የነበራት አክብሮትና ስርዓት እስገራሚ ነበር፡፡ በአጭር ቃል ብቻዬን ከመራወጥ አሳረፈችኝ፡፡ ተመድባ በመጣትች
በአስራ አምስት ቀኗ፣ አስር ጊዜ እየተቆራረጠ ካስመረረኝ የኮምፒውተር ሲስተም እስከ ፋይል ዝግጅት፣ ነገሮችን በሚገርም ፍጥነትና ብቃት ቦታ ቦታቸዉን አስያዘችልኝ፡፡ በተለይ እነዚያን ውሃ ቀጠነ ብለው የሚጨቃጨቁ ደንበኞች፣ በዛ ውብ ፈገግታዋ ውሃ ቸልሳባቸው፣ አረጋግታ ስታባርራቸው ተገርሜ እመለከት ነበር፡፡ ሲጀመር ከእሷ ጋር
ሲያወሩ፣ ከሌሎቹ ጋር እንደሚያወሩት አይቆጡም ኃላፊዎቻችንም ሴት ሳይወዱ
አይቀሩም መሰለኝ፤ እኔ ለሳምንት ተነዛንዤ ምላሽ የሚሰጡበትን ጉዳይ፣ ሔራን ደውላ ምን እንደምትላቸው እንጃ፡ ጠዋት ደውላ ከሰዓት በኋላ ይጨርሱታል ስንት ጊዜ ስነዛነዝ ቸል ያሉኝ የኮምፒውተር ባለሙያዎች ተንጋግተው መጥተው ሲስተሙን
አስተካክለውልን የሄዱት በአንድ ስልከ ጥሪ ነበር፡፡ በእርግጥ እኔ በኃላፊነት
በተቀመጥኩበት ቦታ አንዲት የበታች ሰራተኛ የበለጠ መሰማቷ የፈጠረብኝ ለስላሳ ቅሬታ ነበር፡፡ ምናልባት ከአንዱ ኃላፊ ጋር ነገር ይኖራት ይሆናል” ብዬ እስክጠረጥር፡፡ በኋላ በደንብ ሳውቃት ነው ልጅቱ ለማሳመን የተፈጠረች መሆኗን ያመንኩት፡፡
ከሐኑን ጋር በየቀኑ እናወራ ነበር፡፡ ባለኝ ክፍት ሰዓት ሁሉ እደውልላታለሁ፣ ያለውን
ነገር እነግራታለሁ፡፡ ይግባት አይግባት ባላውቅም፣ ዝም ብላ ትሰማኛለች፡፡ ምንጊዜም ከወሪያችን በኋላ ጥያቄዋ የታወቀ ነበር፡፡ ግን ትመጣለህ አይደል?” እውነት ነበራት::
በአንድ ወር ውስጥ ቤት ተከራይቼ እመለሳለሁ ያልኩት ልጅ፣ ቤተሰቦቼ ቤት እየኖርኩ ሦስት ወራት አለፉ፡፡ በመጨሻ እሷ ሰው አታጣም ብዬ ቤት መከራየት እንደምፈልግ ለሔራን ነገርኳት፡፡ አብረን ምሳ መብላት ጀምረን፣ ተቀራርበን ነበር፡፡
በቀጣዩ ቀን እየተፍለቀለቀች መጥታ እንኳን ደስ ያለህ ቦስ… ቤት ተገኝቶልሃል፡፡ አሪፍ ባለ አንድ መኝታ፣ አንደኛ ፎቅ ላይ ከሥራ እንደወጣን ወሰደችኝ፡፡ቤቱን ወደድኩት፡፡ በቀጣዩ ቀን የሶስት ወር የቤት ኪራይ ከፍዬ ተገላገልኩ፡፡ ቤት መከራየቴን ለቤተሰቦቼ ስነግራቸው እዚህ ምን አጥተህ ነው በኪራይ የምትገፈገፈው ?” ብለው ትንሽ
አጉረመረሙ፡፡ ግን ብዙ አልተጫኑኝም “
ለሥራውም ለምኑም ብቻውን መሆን
ካስፈለገው አለች እናቴ “ለምኑም” ስትል ድምፅዋ ውስጥ ትንሽ አሽሙር ነበረች
“ይሁና ብሉ ዝም አለ! አባቴ፡፡
ሔራን እና እቃህን መቸ ልታስገባ ነው?” አለችኝ፤እቃ መግዛቱንም ረስቼው ነበር፡፡

"ለካ እሱም አለ”
“ለካ እሱም አለ!? - ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ድፍን የባንኩ ሠራተኛ ዙሮ እስኪያየን ሳቋን
አቀለጠችው::ሳቋ ያምራል፡፡ሁሉም ሠራተኛ ላይ የሚጋባ ዓይነት ሳቅ ነው ያላት፡፡አንዳንዴ እዚያ ሩቅ ሆና ስትስቅ እኔ እዚህ ፈገግ እላለሁ፡፡
ባክሽ ምንም ዕቃ የለኝም፣ ገና ልገዛ ነው ስል እንደገና እየሳቀች…
“ምን ይሻላችኋል ወንዶች?' ብላ፣ ትክ ብላ አየችኝና…
ፈርኒቸር ቤት ያላት ጓደኛ አለችኝ፣ ብር ካጠረህ ዋስ እሆናለሁ፡፡መቼም አታዋርደኝም”
አይ! ለጊዜው የብር ችግር የለብኝም፣ ግን ካላስቸገርኩሽ፣ የቤት እቃ ገዝቼ
ስለማላውቅም
ችግር የለውም! መቸ ይመችሀል? ሄደን ትመርጣለህ: ራሳቸው ቤት ድረስ ወስደው ይገጣጥሙልሃል”
እንዳለችውም ከአልጋ እስከ ሶፋ፣ ምንም ሳልደከም አመራረጠችኝ፡፡ምርጫዋ የሚገርም ነበር፡፡ የተከራየሁት ቤት ድረስ ወስደው ገጣጠሙልኝ። አንድ እዳ ቀለለ። ለሐኑን ስነግራት በደስታ አበደች፡፡ እና መቼ ልትመጣ ነው?”
ፍቃድ ጠይቄ በዚህ ወር መጨረሻ አካባቢ” አልኳት፡፡ ግን ፈርቼ ነበር።
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ

👍2
#ሐኑን
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
ለሐኑን ስነግራት በደስታ አበደች፡፡ እና መቼ ልትመጣ ነው?”
ፍቃድ ጠይቄ በዚህ ወር መጨረሻ አካባቢ” አልኳት፡፡ ግን ፈርቼ ነበር፡፡ ምን እንደሆነ ያልገባኝ ነገር፣ ውስጤን ያስጨንቀው ነበር፡፡ መጨረሻ ላይ አውርጄና አውጥቼ ጉዳዩን ለታላቅ እህቴ ልነግራት ወሰንኩ አንድ ቅዳሜ ቀን “ምሳ ልጋብዝሽ” ስላት
ዛሬ ምን መልአክ ተጠጋህ ባክህ!?” እያለች የተቀጣጠርንበት ቦታ መጣች፡፡ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ስለ ሐኑን ነገርኳትና፣ ፎቶዋን አሳየኋት። “ውይይይይ!! የኔ ቆንጆ! እንዴት
ታምራለች!? ብላ አዳነቀችና “ምንም የሚካበድ ነገር የለውምኮ፤ ከወደድካት፣ እርግጠኛ ከሆንክና ከተግባባችሁ…በቃ እቤት እንነግራቸዋለን፤ አለቀ! እንደውም እኔ እነግራቸዋለሁ” ብላ ድንገት ከት ከት ብላ ሳቀችና
“ግን ልጅ ምናምን ወልደህ፣ አልደበክም አይደል …? እኔኮ እዚያ ሂደህ ድምፅህ ሲጠፋ
ባክሽ ምንም ነገር አልጀመርንም " ትክ ብላ በማሾፍ አየችኝና፣
“ይችን የመሰለች ልጅ ጋር አንድ ግቢ እየኖራችሁ ምንም ካልጀመራችሁ መልአክ ወንድም አለኝ እያልኩ ማውራት እጀምራለሁ" ተሳስቀን ተለያየን፡፡ በቀጣዩ ቀን እቤት ስገባ፣ የሁሉም ፊት ሳቅ አፍኖት ጠበቀኝ፡፡ በመጨረሻ አባቴ አላስችለው ብሎት እስቲ ና አንተ! … እዚህ ቁጭ በል! የምን የዙሪያ መሄድ ነው?” እናቴ ለወሬ ቸኩላ፣ ልታጥብ ያዘጋጀችውን እንቁላል የተጠበሰበት መጥበሻ እንዳንከረፈች ከውስጥ ወጥታ ፊት ለፊቴ ተቀመጠች፡፡
ፎቶዋ ታለህ ወዲህ በል እንያት አለኝና ፎቶዋን እየተቀባበሉ አይተው፣
ቆንጆ ልጅ ቆንጆ ልቅም ያለች ቆንጆ እያሉ አዳነቁ፡፡ ማነው ስሟ?
ሐኑን
“ምንኛ ነው ደሞ የዛሬ ልጆች ስማቸው
አረብኛ
እረብኛ ? እስላም ናት እንዴ? አለ አባቴ ፊቱን ኮስተር አድርጎ
እዎ” ሁሉም ተያይተው ዝም አሉ፡፡
“ምነው? ችግር አለው”
አይ! ከወደድክ ምናሻን፤ግን እንደው እምነት አንድ ዓይነት ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ ነገ ልጆች ይወለዳሉ፣ ብዙ ነገር አለ፤ፍቅር እንደሆነ ሁልጊዜ እንዳጀማመሩ አይሆንም …”
አይ! እንግዲህ አታሟርቱበት” ብላ እህቴ ጣልቃ ገባች፤ ቤታችን ውስጥ የምትፈራ
ዓይነት ናት፡፡ አባቴ ፊቱ ላይ ቅሬታው እንዳረበበ ይሁን፣ ዋናው መፈቃቀዱ ነው
ብሎ ተነስቶ ወደመኝታ ቤቱ ገባ፡፡ ግን ደስተኛ እንዳልነበረ ፊቱ ላይ ያስታውቅበት
ነበር፡፡
ሁሉንም ነገር ጨራርሼ ወደ ድሬዳዋ ለመመለስ ተዘጋጀሁ፡፡ ዋና ሐሳቤ ድሬዳዋ እንደደረስኩ እዚያዉ ካፈራኋቸው ጓደኞቼና የሥራ ባልደረቦቼ መካከል ቀድሜ በስልክ ያዋራኋቸውን፣ ለሽምግልና ወደሐኑን አባት መላከ ነበር፡፡ሐኑን ድምፅዋ ውስጥ የምሰማው የደስታ ሲቃ፣ የእኔንም ጉጉት ጨምሮት፣ ቀኑን በጉጉት ነበር የጠበቅሁት፡፡
እንደነብሰ ጡር ቀን እየቆጠርን ቆይተን ቀኑ ሲደርስ ወደ ድሬደዋ በረርኩ፡፡ ድሬደዋ ራቀችብኝ፡፡ በመነሻና መድረሻ መካከል መንገድ የሚባል እንቅፋት አለ፡፡ ጉዞ ማለት አብሮ ለመሆን ለሚፈላለጉ ነፍሶች መሃል የተዘረጋን መንገድ የሚባል መጋረጃ ቀዶ መጣል ነው ፡፡ ርቀትም በመነሻና በመድረሻ መሃል ያለ የመንገድ ዕድሜ፡፡ የመንገድን ዕድሜ የሚያሳጥረው ጥሩ እርግማን፣ መጓዝ ብቻ ነው፡፡ ተጓዝኩ፡፡
የድሬዳዋ ሙቀት የሐኑን እቅፍ ይመስለኛል፡፡ለስለስ ያለ እና ምቾት ያለው፡፡ እንደደረስኩ ወደያዝኩት ሆቴል ገብቼ ሰውነቴን ተለቃለኩና ለባብሼ ወደማታ አካባቢ ለሽምግልና ከመረጥኳቸው ጓደኞቼ ጋ ወደተቀጣጠርንበት አቀናሁ፡፡ እንደሙሽራ
ተንካባክበው ራት ጋበዙኝ ፡፡እኔ ለማገባው ፣ የእነሱ ደስታ ወደር አልነበረውም፡፡ ባንክ
ውስጥ አለቃቸው ሆኜ ለአራት ዓመታት ሠርተናል፡፡ በእነዚያ አራት ዓመታት ዉስጥ ለሥራ ጉዳይ ተነዛንዘናል፣ ተጣልተናል፣ ባስ ሲልም እስከ ጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የሰጠኋቸው ነበሩ፡፡ ዛሬ ላይ እንዱም ነገር በልባቸው ውስጥ የለም፡፡ የእውነት ተደስተው ነበር፡፡ ከጥንት ጀምሮ በሽምግልና ታሪከ ውስጥ ያጋጠሙ ታሪኮችና ገጠመኞት፣ ሲነሱ ሲጣሉ አመሹ፡፡ ብዙ ሳቅ እንዲች ብለህ እንዳትጨነቅ፣ እንቢ ካሉ፣ አንድ ገጣባ የጋሪ ፈረስ አዘጋጅተንልሃል፤ ጠልፍሃት እየጋለብ መሄድ ነው ሃሃሃሃሃሃሃ
በማግስቱ ሽማግሌዎቼ ወደነሐኑን ቤት ሄዱ፡፡ ቀድመው አባባን ቀጥረዋቸው
ስለነበር፣ነገሩ ሽምግልና መሆኑን አውቀዋል፡፡ ልጃቸውን ጠያቂው ማን መሆኑን ብቻ ነበር ያላወቁት፡፡ ሆቴሌ ውስጥ እየተቀመጥኩ እየተነሳሁ ስንቆራጠጥ ዋልኩ፡፡ከብዙ
እንዲህ ተብለው ይሆናልና እንደዛ ተብለው ይሆናል” ከሚል መላ ምት ጋር፡፡
የላክኋቸዉ ሽማግሌዎች ካሰብኩት በላይ አምሽተው፣ ወደያዝኩት ከፍል መጡ፡፡
በጉጉት አፍ አፋቸውን ስመለከት፣ አንተ ተናገር አንተ በሚል እየተያዩ ግራ አጋቡኝ፡፡ ሲሄዱ የነበራቸው ፈገግታና ሞራል ፊታቸው ላይ አልነበረም፡፡
አልተሳካም!” አለ አንዱ፣
“ምን ማለት ነው አልተሳካም”
እባቷ አልተስማሙም፡፡ ልናሳምናቸው የቻልነውን ሁሉ ሞከርን፣ ግን አልሆነም?”
ሁሉም እንደ ሐዘን ቤት ፊታቸውን አጨፍግገው እንዳቀረቀሩ ዝም አሉ፡፡ እየቀለዱ መስሎኝ ነበር፡ትንሽ ቆይተው በሳቅ እየተፍለቀለቁ፣ እንኳን ደስ ያለህ እንዲሉኝ ጠበቅሁ፤ ግን የጠበቀኝ የመርዶው ዝርዝር ነበር፡፡ፈጽሞ ያልታሰበ
ነገር፡፡ ሽማግሌምቹ እንደደረሱ፣ አባባ አክብረው ነበር የተቀበሏቸው፡፡ የሄዱበትን ጉዳይ ሲነግሯቸውም ደስ ነው ያላቸው፤ ችግሩ የመጣው የእኔን ማንነት ሲሰሙ ነበር፡፡
“አይይይይይይይ…" ብለው ተከዙ፡፡ “ምንም የማይወጣለት ጥሩ ልጅ ነው፣ ሰውንም ሥራውንም የሚያከብር፣ ብታመም አስታማሚ፣ ቢከፋኝ እህ ብሎ የሚሰማ፣እንደ ልጅ የማየው ልጅ፡ ግን አይሆንም! እሱ ክርሰቲያን፣ እኛ ሙስሊሞች፣ እንዴት ይሆናል አይ
ግዴለም ይቅር አስተዋይ ልጅ አልነበር፣ ምን ነካው…?
“አባባ ይኼኮ ችግር የለውም፣ ከተዋደዱ ተቻችሎ መኖር…"
አባባ በቁጣ ገነፈሉ፡፡ “ይኼኮ ቦለቲካ አይደለም፣ ምን ነካችሁ ልጆች? …የነፍስ ጉዳይ ነው፡፡እንዴት እንዴት ነው የምትናገሩት? የአላህን ትዛዝ እኔ አልሽረው፤ ዓይኔ እያየ ልጀ ገሃነም እሳት ስትገባ፣ እንዴት ነው እሽ የምለው!? ሃይማኖታችን አይፈቅድም፣ በቃ!
ይሄን ሁሉ ዓመት አብረን እንደ አባትና ልጅ ስንኖር፣ አንድ ቀን ሐይማኖቱን ጠይቄው አውቃለሁ?አላውቅም መቻቻል እሱ ነው! አብረን ስንበላ፣ አብረን ስንጠጣ፣ ሐይማኖታችን ከልክሎናል? አልከለከለንም! መቻቻል እሱ ነው! እቤቴ ሲኖር ከዚች ከልጄ ነጥዬ አላየሁትም፤ መቻቻል ይኼ ነው። ጋብቻ ግን የማይሆን የማይታሰብ ነው!! ጀሀነብ ቀልድ እንዳይመስላችሁ ልጆቼ እንኳን እንዲህ እንዳሻን ኑረን፣ በጥፍራቸው ቁመው ተንቀጥቅጠው…ትዛዙን አክብረው ለኖሩትም አስፈሪ ናት ያች ቀን፡፡ ጥሩ ልጅ
ነው ወላሂ ጥሩ ልጅ ነው በዚህ ዘመን እንደሱ ያለ ሰው አይገኝም፤ የተማረ
አስተዋይ፣መጠጥ በአፉ አይዞር፣ጫት እንኳ እይቀምስም ግን በኋላ ይች ነፍስ ለጥያቄ መቅረቧ አይቀር! ጥሩ ልጅ ነው ሲባል፣ ወድጄ ነው ሲባል የአላህ ቃልና ትዛዝ አይሰረዝ አይከለስ ግዴላችሁም እንዳማረብን ቀጉርብትናችን እንቀጥል”
ቢጨንቀው አንዱ ሽማግሌ፣ “አባባ፣ በቃ
ከወደዳት ይሰልማላ አቦ!” ይላቸዋል
አባባ ከመጀመሪያውም ኮስተር ብለው፣” የአላህን መንገድ ነፍስያችን ወዷትና ፈቅደን እንጂ ሴት ተከትለን የምንሄድባት አይደለችም ካስቀየምኩት አፉ በሉኝ፣ ከኔ አቅም በላይ ሲሆንብኝ ነው ልጆቼ፣ በዚህ አትምጡብኝ እንደው ብታርዱኝ እሽ አልልም ወላሂ ብለው ተነስተው ቆሙ ሽማግሌዎቹም ተሰናብተው ከመውጣት ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም

አንዳንዴ ሲሳቅልን፣ አንዳንዴ የተወደድን ሲመስለን፣ የልዩነት መስመር ደብዝዞ
አይታየንም አይደል በመንገዴ ላይ ለዓይን የማትታይ ቀጭን ክር መዘርጋቷን አላየሁም ነበር፡፡ያች ክር ናት ጠልፋ የጣለችኝ፡፡ ውድቀቴን ያከፋው ክሩ አይደለም፤የተንደረደርኩበት ፍጥነት እንጂ፡፡
ሽማግሌዎቹን አመስግኜ ራት በልተን ከሸኘኋቻዉ ስኋላ፣ ብቻዬን ቁጭ ብዬ ሳስብ ቆየሁና፣ ለሐኑን ምልክት አደረኩላት ፤ምናልባት አባቷ ጋር ከሆኑ መልሳ እንድትደውል።ወዲያው ደወለች ፡፡ ሁለታችንም ከምን እንደምንጀምረው ግራ ገብቶን ዝም ብለን ቆየንና ፣« አባባ አይሆንም አሉ!» አልኳት ፡፡ ስታለቅስ ትንፋሸዋ ይሰማኝ ነበር፡፡
“ሐኑን
''አዎ”
“አብረሽኝ መኖር ትፈልጊያለሽ ወይስ አባባ እንዳሉት ?…”
ከአንተ ጋር መኖር ነው የምፈልገው… የትም ቢሆን አንተ ጋር መሆን ነው የምፈልገው
ሌላ ምን አለኝ”
“በቃ ተዘጋጂ አብረን አዲስ አበባ እንሄዳለን…”
አባባን ትቼ መሄድ አልችልም! በብስጭት ይሞትብኛል፤ ዕድሜ ልኬን ጸጸቱም
አይለቀኝ
እና ምንድነው ሐሳብሽ !?”

#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
"እና ምንድን ነው ሐሳብሽ!?"
እወድሃለሁ!.. እኔ በቃ እኔ ዕድሌ ይኼ ነው፣ ሂድ እርሳኝ ሂድ አትደውል፣ እኔን አታስብ፡ እርሳኝ፣ አባባን ባዶ ቤት ትቼው ብሄድ ርግማኑ ለአንተም ይተርፋል፡፡ ቁም ነረኛ ነህ፣የቻልከውን አድርገሃል፣ በአንተ የማዝንበት ምንም ነገር የለም፡፡ በቃ ሂድ፡ ሂድ ወደ አገርህ፣ ከወደድካት ጋር በሰላም ኑር"
"በቃ"
“አትዘንብኝ"
ስልኩን ዘጋችው ቀልድ መሰለኝ፡የሆነ ጨዋታ ነገር፡፡ የሆቴሉን መጋረጃ ከፍቼ ቁልቁል በሰፊው የድሬደዋ ከተማ ጨለማ ላይ፡ ኮከብ መስለው የተዘሩት አምፑሎች
ሲብለጨለጩ እየተመለከትኩ በሐሳብ ነጎድኩ: ነገሮች ሁሉ እንደሳሙና አረፋ እጄ ላይ ሲሟሙ ታወቀኝ፡፡ ለትንሽ ለትንሽ… በቃ ለትንሽ! ጥሩ ቀን እንደንጥላ ከበላዩ ሲታጠፍና፣ የብቸኝነት፣ የመለየት የባዶነት ዶፍ ሲወርድብኝ፣ ነፍሴ ስትኮራመት ተሰማኝ ፍቅር ከሽፎ እንኳን ሰው ያድናል፡፡ ሞቶ ራሱ ሕይወት ይሰጣል፡፡ የእኔና የሐኑን ፍቅር እጣው የወደቀው እዛው ላይ ነበር፡፡አንድ ሚስኪን ሽማግሌ በሰላምና በጤና ይኖሩ ዘንድ፣ የእኔና የሐኑን ፍቅር መሞት እና መሰዋት አለበት። አንድ ሽማግሌ አይደሉም ደግሞ አባት ናቸው ትዳራቸውንና ልጆቻቸውን በትነው፣ አንድ እሷን ብቻ
መርጠው ያሳደጉ ደግ አባት፤ እውነት አላት፣ያለችው ሁሉ እውነት ነው፡፡ ሌላም አንድ እወነት ደግሞ እለ፡ እኔ ሐኑንን ማፍቀሬ!
ውስጤ ቅጥል አለ፣ተንገበገብኩ፡፡ “ይሄ ነገር ፍቅር ነው ወይ? እያለች የኖረች ነፍሴ፣በዚያች ምሽት ለራሷ እንዲህ አለች “እዎ ፍቅር ነበር” ፍቅር ማለት በዚህ
በምትመለከተው ጨለማ ውስጥ ከሚብለጨለጩት ቁጥር ስፍር የሌላቸው እምፑሎች መሀል፣ ነፍስ አንዷን መርጣ ብርሃኗ ስትደምቅ ነው፡፡ ብርሃን ሁሉ የነፍስን ጨለማ አይገፍም ሲበዛ የራስህን ብርሃን ትፈልግ ዘንድ ያግዝህ ይሆናል፡፡ራሳችንን፣ አካባቢያቸንን፣ ዓለምን፣ መላውን የሰው ልጅ ሁሉ እንድናይ የሚረዳን ብርሃን ተመርጦ
በልባችን ጓዳ ይበራል ሰው የቱንም ያህል በደማቅ ብርሃን ቢከበብ፣ እውነተኛውን
የራሱን ብርሃን እስካላገኘ ድረስ ነፍሱ ጨለማ ውስጥ ናት
ሐኑን ሀሳቧን ብትቀይር ብዩ ሆቴሌ ውስጥ ሁለት ቀን በዝምታ ጠበኩ፡፡ ምንም አልነበረም፡፡ እንደዚያ ደረቴን ነፍቼ እንደ አንበሳ ገዳይ እየፎከርኩ የሄድኩት ሰውዬ እንደተነፈሰ ትልቅ ፊኛ መንፈሴ ተጨማትሮ ወደ አዲስ አበባ እየተጎተትኩ ተመለስኩ፡፡ ያውም እመለሳለሁ ካልኩበት ቀን አንድ ሳምንት ቀድሜ፡፡ በቀጥታ ወደ ቤቴ ሄጀ ተኛሁ ሳምንቱን ሙሉ ለማንም ሳልደውል፣ ስልኬን ዘግቼ እቤቴ ተቀመጥኩ፡፡ ቅዳሜ
ማታ ስልኬን ስከፍት፣ በርካታ የጽሑፍ መልእክትና የከሸፉ ጥሪዎች ስልኬን ሞልተውት ነበር ዓይኔ ተስገብግቦ የሐኑንን ስም ፈለገ፡፡ ይቅርታዋን ፈለግሁ፡፡ ሐሳቤን ቀይሬያለሁ የሚል ቃሏን ናፈቅሁ፡፡ምንም የለም አልቅስ አልቅስ የሚል ስሜት ተናነቀኝ አልቻልኩም ደወልኩላት፤ስልኳ አይጠራም፣ ዝግ ነበር፡፡ እስከ እኩለ ሌሊት ደጋግሜ
ስሞከር አመሸሁ፤ ዝግ ነበር፡፡ ስልኬን እንደያዝኩ እንቅልፍ ገላገለኝ! ጧት ስነሳ በጉጉት ስልኬን ተመለከትኩ፣ ምንም! ደጋግሜ ደወልኩ፣ ድካም ነበር ትርፉ!
እራሴን እንደምንም አነቃቅቼ ሻወር ወሰድኩና፣ ልብስ ቀያይሬ ወጣሁ፡፡ አዲስ አበባ የተለመደ ሕይወቷን ቀጥላለች፡፡ ሕዝቡ ሁሉ፣መንገደኛው ሁሉ፣ በሬዲዮና በቴሌቪዥን የሆንኩት ነገር በአዋጅ ተነግሮት የራሱ ጉዳይ!” ብሎ ችላ ያለኝ መሰለኝ፡፡ አንድ ካፌ ገብቼ ቁርስ አዘዝኩ! ቡና ጠጣሁ፡፡ እናም እንደገና ስልኬን መቀጥቀጥ ጀመርኩ! ሊሰለቸኝ እና ድከም ሲለኝ ለሔራን ደወልኩ፡፡ በአንድ ጊዜ አንስታ፣
አንተ! ምን ሆነህ ነው እንዲህ የጠፋኸው ባክህ ? ሰው ይሰጋልም አይባልም?
“ደህና ነኝ!
“ምን ሆነሃል ደግሞ፣ ድምፅህ የሰካራም ድምፅ መስሏል የምትናገርበት ፍጥነትና
አእምሮዬ የሚረዳበት ፍጥነት አልመጣጠን አለኝ
“ትንሽ አሞኛል፣ ነገ አልገባም
“ምነው? የት ነው ያለኸው?
"እቤት ነኝ"
“ወደዚያው የምመጣበት ጉዳይ አለኝ፣ በዛው ብቅ ብዬ ልይህ ?”
“አይ አትቸገሪያ"
ትግር የለውም! ብቅ እላለሁ፤ እንደጨረስኩ እመጣለሁ ቻው ሳትለኝ ስልኩን ዘጋችው እንዳለችው ወደ አሥራ አንድ ሰዓት አካባቢ እቤት መጣች፤ ቤቱ ተተረማምሶ፣ ሻንጣዬ ሳይከፈት በሩ ሥር ቁሞ ስታይ፣
እና የሆነ የተሳሳተ ነገርማ አለ፣ልትጠፋ ነበር እንዴ?ሂሂሂ” እያለች ገብታ ተቀመጠች አንድም ነገር ተንፍሽ የማላውቀውን የሐኑንን ጉዳይ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ
ሳትጠይቀኝ ዝርግፍ አድርጌ ነገርኳት፡፡ በግርምት ስታዳምጠኝ ቆየችና፣ እንደ ሕፃን ልጅ ተነስታ መጥታ ጥብቅ አድርጋ አቀፈችኝ፤ ታቀፍኩላት። የዚያን ቀን ስታወራኝ እና ስታጽናናኝ አመሽች፡፡ ችግር የለውም፣ አሞኛል ብለህ ሳምንቱን እረፍ
ብላኝ ተስናብታኝ ሄደች እንዲያውም ልደር ብላኝ ነበር፡፡ ጧት ሥራ ገቢ ነሽ ሂጂ ብዬ ሸኘኋት፤ እውነቱን ለመናገር፣ ብታድር ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ብቸኝነቴን እንደጉድ ነበር
የፈራሁት።
ጧት አንድ ሰዓት ላይ የቤቴ በር ሲንኳኳ፡ ተነስቼ ከፈትኩ ሔራን ነበረች፡፡ ቁርስ
ይዛልኝ መጥታ፡
ከሥራ እንደወጣሁ፣እመጣለሁ ውጣና ምሳ ብላ፣ እደውልልሃለሁ” ብላኝ
እየተጣደፈች ሄደች ከሥራ መልስ ለትልቅ የፕላስቲክ ዘንቢል የታሸገ አዲስ ብርድ
ልብስና፣ ሌላ ትልቅ ቦርሳ ይዛ መጣች፡፡ቤት የቀየረች ነበር የምትመስለው፡፡ ያንን ሁሉ ተሸክማ ደረጃ በመውጣቷ፣ በድካም ቁና ቁና እየተነፈሰች እበር ላይ ቁማ ሳያት
አሳዘነችኝ፡፡ ራት አምጥታልኝ ነበር፡፡ የዚያን ቀን ስታወራኝ አምሽታ፣ ያመጣችውን
ብርድ ልብስ ለብሳ ሶፋ ላይ አደረች፡፡ ቦታ
እንድንቀያየር ብለምናት እምቢ አለች፡፡
ሳምንቱን ሙሉ እኔጋ ነበር ያደረችው እዚያች ሶፋ ላይ ኩርምት ብላ፡፡ የእውነትም አጽናናችኝ፡፡ በቀጣዩ ሳምንት ምንም እንዳልተፈጠረ ሥራዋ ላይ ተገኘሁ፡፡ ሕይወት ጠባሳችን ዕድሜ ልክ አብሮን እንዲኖር እንጂ ዕድሜ ልክ ስናለቅስበት እንድንኖር አትፈቅድልንም፡፡ ካለቀስንም እየኖርን እንድናለቅስ ነው የምታደርገን፡፡
በተከታታይ ለአንድ ወር አካባቢ ለሐኑን ብደውልም፣ ስልኳ ዝግ ነበር፡፡ እንዲያውም በመሀል ተነስና ሂድ ሂድ ይለኛል፡፡ የመለያየት ቀፋፊ ገጹ ድምፃችንን ለመስማት ለሚንሰፈሰፉ ውዶቻቶን፣ ግድ ስሙን ብለን ደጅ መጥናታችን ላይ ነው ፡፡ ግን ምን
አደረኳት?” እላለሁ በየቀኑ በተቃራኒው ከሔራን ጋር ቅርበታችን ከፍ እያለ፣ ሥራ ቦታ አብሮ ምሳ ከመብላት አልፎ፣አብረን ለእራት መውጣት ጀመርን፡፡ እራሴን ክፍትፍት አድርጌው ነበር፡፡ለወትሮው ቁጥብ የሆነው ባሕሪየ ዝርክርክ ያለ እስኪመስለኝ ድረስ እያንዳንዷን ዝርዝርና በአእምሮየ ውስጥ የሚመላለሰዉን ሐሳብ ሁሉ፣ ሳትጠይቀኝ ለሔራን እናዘዝ ነበር፡፡ ሔራን ጥሩ ልጅ ነበረች፤ ከሐኑን ጋር እንደገና እንድንገናኝ የቻለችውን ሁሉ ብታደርግም፣ አልተሳካም፡፡ አይደለምና ብሶቴን ፣ሥራዬን ሳይቀር እሷ እየሠራች ለፊርማ ብቻ ታመጣልኝ ነበር፡፡ ፈጣሪ ጠብቆኝ እንጂ፤ ባቀረበችልኝ ጊዜ ሁሉ ሳላይ የፈረምኩበት የብር መዓት አገር ይገዛል፡፡
ድሬደዋ ጓደኞቼን “ሐኑን እንዴት ናት?” ብዬ ደውዬ ስጠይቃቸው፣ ደህና እንደሆነችና አልፎ አልፎ መንገድ ላይ አባቷ ጋር ሲሔዱ እንደሚያገኟቸው ይነግሩኛል፡፡ ብቸኛ ምክንያቷ ከእኔ መራቅ ከሆነ፣ እንደፈለገች ትሁን ብዬ እኔም መሞከሬን ርግፍ አድርጌ ተውኩት። በተቃራኒው ከሔራን ጋር ከቀን ወደ ቀን ቅርበታችን ከፍ እያለ፣ በየቀኑ በሚባል ሁኔታ እቤቴ መምጣት ጀመረች ከሥራ እንደወጣን አብረን

❤1👍1
የሆነ ቦታ ራት እንበላና፣ ወደቤት ሄደን ስናወራ ወይም ፊልም ስናይ እናመሻለን፡፡ አንዳንዴ ታድራለች፤ ወይም አምሽታ ትሄዳለች፡፡
ቀናት እና ወራት አለፉ፡፡ ከሐኑን ጋር ከተለያየን ከስምንት ወራት በኋላ፣ለለውጥ ያህል ቅዳሜና እሁድን ለማሳለፍ ከሔራን ጋር ሃዋሳ ሄድን። ሔራን ነበረች እንሂድ ብላ የወሰደችኝ፡፡ ደስ የሚል ጊዜ ነበር ያሳለፍነው፡፡ ከተማዋን ስናስስ ውለን ማታ
ወዳረፍንበት ሆቴል ስንመለስ፣ እራት ጋበዝኳት፡፡ አልተነጋገርንም ምሽታትን ዝምታ ይበዛው ነበር፡፡“ተጫወት” “ተጫወት ዓይነት፣ በዝምታ ገፆቻቸን መሃል እንደ እልባት የሚገቡ ቃላት ከመወርወር ባለፈ ብዙም አላወራንም፡፡ ወደሆነ ነገር ለማለፍ የፈራንና
ማን ይጀምረው በሚል ጥበቃ ላይ ያለን ነበር የምንመስለው፡፡ ወደያዝነው ክፍል