አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ዜሮን_ፅፌ_አንድ_አለኝ

ሁለት ነው ልቤ!
አንድም ሞኝ ሲሆን ፤ አንድም ነው ወረቀት
አንድ የሚያደርጋቸው ፤ አለ አንድ ተረት
አለ አንዳች እውነት።

የያዙትን ነገር ፤ አይለቁም ሁለቱም
ዜሮን እየፃፉ
"አንድ አለኝ ይላሉ ፤ ሞኙም ወረቀቱም።

እኔ ካንቺ በፊት ፤ የማውቃቸው ሴቶች
ዛሬ ዜሮ ናቸው
ተፅፈው የቀሩ ፥ የሌሉ ስሌቶች።
ሔደዋል ብዙዎቹ ፤ በኔ እየተገፉ
አልፈዋል ብዙዎቹ ፤ እኔን እየገፉ
ዛሬ አንቺ ስትመጪ
በሞኝ ልቤ ላይ ፤ አኖርኩሽ አቅፌ
ለወረቀት ልቤ
"አንድ አለችኝ" አልኩት ፤ ዜሮዎቼን ፅፌ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ቅበላ


#ክፍል_ሦስት


#ከአዶኒስ

...ውቃቢ እስኪርቀው የቁጣ መዓት ካወረደችበት በኋላ ዳግም
“እንዲህ ዓይነት ነገር” ሲያደርግ የሷና የሱ “መጨረሻ” እንደሚሆን አስጠንቅቃው ነበር ጭራውን ቆልፎ ወደ
ትምህርት ቤት የሄደው፡፡ ያም ሆኖ ማሙሸት ቢያንስ የአቅሚቲውን ያህል ለእናቱ ፍትህን ለመስጠት እንደሚያስችለው አጥብቆ ያመነበትን ይህን ነገር በቀላሉ ወደጎን ሊለው አልቻለም። ለእናቱ ማሳወቁን ብቻ
ይተውና ድርጊቱን ይቀጥላል፡፡ አጋጣሚው አመቺ መስሎ በታየው ጊዜ ሁሉ የእንግዶቹን ኪሶች መፈተሽና
እንደየሁኔታው አምስትም አሥርም እየመዘዘ በሚስጥር ማጠራቀም ይጀምራል፡፡

ማመሽት የእናቱን እንግዳዎች ኪስ ዘና ብሎ ለመፈተሽ የሚያስችለውን አስተማማኝ ስዓት ከልምድ አውቆታል፡፡ የዕለቱ እንግዳ የሆነው ሰው የመጣበትን
ጉዳይ ሊጨርስ አፍታዎች ሲቀሩትና አቅሉን ሙሉ በሙሉ ሊስት የሚያደርገውን ልጓም አልባ እንቅስቃሴና
የሚያወጣውን ያልተለመደ ዓይነት ድምጽ እንደሰማ ማሙሸት እጁን መሰስ አድርጎ በመላክ የሰውዬውን ኪሶች አንድ በአንድ ያብጠረጥርና የሚወስደውን ያህል ወስዶ የልብሶቹ አቀማመጥ ልክ እንደነበረው መሆነን ያረጋግጣል።

ታዲያ እናቱ በባሰባት በባሰባት ጊዜ ከአንድ የሃብታም ልጅ ከሆነና በየጊዜው
ከሚረዳው ጓደኛው አመጣሁ እያለ በዕለቱ ያስፈለጋትን ያህል ገንዘብ
ይሰጣታል።ለትምህርት ቤቱ የሚያስፈልገውን ወጪም ራሱ መሸፈን ከጀመረ ከራርሟል፡፡ የኋላ የኋላ ግን ፀዳል ሚስጥሩን ትደርስበታለች፡፡ ይሁን እንጂ ደጋግሞ ከጉድ ያወጣትንና አንድም እንግዳ ገንዘብ ጠፋኝ ብሎ አማርሮ የማያውቅበትን ይህን ረቂቅ የገንዘብ ምንጭ አጉል ነካክታ
ማድረቅ ርባናው አልታይ ይላታል፡፡ እንደውም ውሎ አድሮ ነገርየው እየጣማት ሲመጣ እንግዶቿ ልብሳቸውን
አውልቀው የሚያስቀምጡበትን ወንበር እንደዘበት ለማሙሽት በሚያመቸው ሁኔታ ወደ አልጋው ጠጋ ማድረግ ጀመረች ይህ ሁሉ ሲሆን እናትና ልጅ
ይህ ሁሉ ሲሆን እናትና ልጅ “ውሾን
ያነሳ ውሾ ይሁን” ዓይነት ስለጉዳዩ በይፋ ለመነጋገር ደፍረው አያውቁም:: ፀዳል ነገሩ እንደገባት ማሙሽት ያውቃል - እንደሚያውቅ እሷም ታውቃለች፡፡ ታዲያ
በሚቻላት ሁሉ ማሙሸት ራሱ አስቦ እስኪሰጣት ትጠብቃለች እንጂ አፍ አውጥታ አትጠይቀውም። አልፎ
አልፎ ሁሉ ነገር ጭልምልም ሲልባት ብቻ ምሬቷን ማጉተምተምና በትንሽ በትልቁ መነጫነጭ ትጀምራለች::
ይሄኔ የሁለታቸውን ብቸኛ ቋንቋ እያወራች እንዳለች የሚገባው ማሙሸት ወደ “ጓደኛው ይሄድና ገንዘብ ይዞላት ይመጣል።

ሰዓቱ ወደ እኩለ ሌሊቱ እየገፋ ሲሄድና የዕለቱ ተስፋዋ በእጅጉ እየተመናመነ ሳለ ነበር አንድ እንግዳ ድንገት ከጥቁሩ ሰማይ ዱብ እንዳለ መና ከበራፉ ገጭ ያለላት፡፡ እሷና ማመሽት ወጡ እንኳን ቢቀርባቸውቢያንስ ጥብስ ጠበስ አድርገው ጦማቸውን ለመያዝ በቂ ጊዜ እንዳላቸው ገመተችና በሆዷ ተመስገን አለች፡፡ሰውየው ከዚህ በፊት አንድ ሶስቴ ያስተናገደችው ሰው ነበረና ሞቅ ባለ ፈገግታ ተቀበለችው። በራፏ ላይ
እንደተቀመጠች አልፏት ወደ ውስጥ የዘለቀው ይህ እንግዳዋ ከአልጋዋ ጎን ካለው ብቸኛ ወንበር ላይ አረፍ አለ፡፡ ሞቅ ያለው ይመስላል:: ፀዳል ወዲያው ብድግ ብላ በሯን ቀረቀረችና ፀጉሯን በጣቶቿ እያፍተለተለች ዝግ ባለ አረማመድ ወደ እንግዳዋ በመቅረብ አልጋዋ ጫፍ ላይ ተቀመጠች::
"""
“ምነው ጠፋህ? አለችው ፈዘዝ ካለ ፈገግታ ጋር፡፡ ወደሷ ሲመጡ የመጀመሪያቸው ላልሆነ እንግዶች
ሁሉ እንደ ንግግር መክፈቻ የምትጠቀመው የተለመደ ጥያቄዋ ነው።
“እንዴት አልጠፋ ከዚህ ያልጠፋሁ ከየት
ልጥፋ?” አላት የጃኬቱን ቁልፍ እየፈታ እምብዛም የጨዋታ ቃና በሌለው አንደበት።
“እንዴ ምነው? - አጥፍቼም ከሆነ ካሺኝ
ይባላል እንጂ እንደው ዝም ብሎ ይጠፋል እንዴ?”አለች ለዛዋን በጥንቃቄ እየመከነች::
“እሱማ ትክሺኛለሽ - ወደሽ ነው የምትክሺኝ?”
አለ የጫማዎቹን ክሮች ተራ በተራ እየፈታና ባቀረቀረበት ከራሱ ጋር የሚያወሪ ዓይነት።

“ሃሃሃ! - ወድጄማ ነው።

ነ..... ው?” አላት ጫማዎቹን እያወለቀ፡፡
“አዎና..ሃሃሃ! - ሳይወዱ ካሳ አለ እንዴ?”
“ሴትዮ ለወሬ አይደለም የመጣሁት
ይልቅ ተዘጋጂ ብድግ ብሎ ሱሪውን ካወለቀና ካጣጠፈ በኋላ ወንበሩ ላይ አስቀመጠው:: ጃኬትና ሸሚዙንም እዚያው ላይ ከደረበ በኋላ ወንበሩን ብድግ በማድረግ ከአልጋው አርቆ ትይዩ ካለው ግድግዳ ጥግ አስቀመጠና ወደ
አልጋው ተመለሰ፡፡ ሰውዬው ጨዋታ ጨዋታ እንዳላለው የተረዳችው ፀዳል ያለ ምንም ተጨማሪ ቃላት ልብሶቿን አወላልቃ ጣለችና አልጋዋ ላይ ወጣች።

በአገልግሎት ብዛት የተዳከመው የፀዳል አልጋ የተለመደውን ዓይነት የማቃሰት ድምፅ ማሰማት ሲጀምር የማሙሸት ጆሮዎች ሙሉ በሙሉ በመንቃት ለክትትል ተዘጋጁ:: የእናቱን እንግዶች በድምፃቸው ብቻ የመለየት ችሎታው ከእለት ወደ እለት እየሰላ ለመጣው ለማሙሸት የሰውየው ድምፅ አዲስ አልሆነበትም:: ጥቂት እንዳሰላሰለ
በትክክል አስታወሰው:: ከጥቂት ሳምንታት በፊት እንዲህ እንደዛሬው አምሽቶ መጥቶ ነበር።ታዲያ ያን ዕለት
ከዚህ ሰው ኪስ ሃያ ብር ቀንጭቦ እንደነበር ማሙሸት ትዝ አለው።ዛሬም የዚያኑ ያህል ምናልባት ዕድል ከቀናችውም የተሻለ - እንደሚያገኝ ተስፋ አደረገ፡፡ ሙሉ ቀልቡን ከበላዩ እያቃሰተ ወዳለው አልጋ አድርጎ ማዳመጥና መጠባበቅ ጀመረ።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ያቺ ማሙሸት
የሚጠብቃት አመቺ ቅፅበት ደረሰችለት:: ወዲያውኑ በዝግታ እጁን መሰስ አድርጎ በማውጣት መደባበስ ጀመረ:: እንኳንስ የሰውዬው ልብሶች ወንበሩ ራሱ በቦታው
ያለመኖሩን ሲረዳ ግራ ተጋባ፡፡ የአልጋው ላይ ሁካታ ይብሱን እየደመቀ መጣ፡፡ ማሙሸት በዝግታ በደረቱ፡ እየተሳበ ወደ አልጋው ጠርዝ ተጠጋና ወለሉ ድረስ
የተንዠረገገውን የአልጋ ምንጣፍ፡ በጥቂቱ፡ ገለጥ አድርጎ ተመለከተ። የሰውዬው ልብሶች የተቀመጠበት ወንበር የአድማስ ያህል ርቆ ታየው:: እንደገና የኋሊት እየተሳበ ወደነበረበት ተመለሰና በደረቱ ለጥ እንዳለ የዕለት
ዕድሉን ክፉኛ ረገመ።ሰውዬውን እንደ አባቱ ገዳይ ጠላው:: አሁን ቀረ የሚባል ተስፋ ካለ ያቺው ሰውዬው ለእናቱ የሚወረውርላት አምስት ብር ናት:: ምኗን
ከምኗ አድርጋ ቅበላዋን እንደምትወጣው ስለ እናቱ እየተጨነቀላት ሳለ ከበላዩ ይካሄድ የነበረው ግርግር ጋብ አለ።

ቀድሟት ከአልጋ ወርዶ መለባበስ የጀመረው የፀዳል እንግዳ ጫማውን እያጠለቀ ነው:: እሷ ግን ገና ዱሮ ጥንቅቅ ብላ አልጋዋ ጫፍ ላይ ቁጢጥ
ብላለች:: እጆቿን ደረቷ ላይ እንዳጣመረች ነገረ ነገሩ ሁሉ ያላማራትን የዚህን ሰው እንቅስቃሴ አንድ በአንድ ትከታተላለች።

ጫማዎቹን አሥሮ እንዳበቃ ካቀረቀረበት ቀና አለና ከኋላ ኪሱ ቦርሳ አወጣ:: ግልፅ ከሆነ የምፀት ፈገግታ ጋር ቦርሳውን እየከፈተ ካየ በኋላ መልሶ ከዚያው ከኋላ ኪሱ ከተተውና ወደ ፀዳል ቀና አለ፡፡

“እ ...ሺ የኛ አራዳ - " አላት ወደፊት ዘመም ብሎና ክንዶቹን ጉልበቶቹ ላይ አንተርሶ ጣቶቹን እያፍተለተለ፡፡ “ዛሬ ሰራሁልሽ አይደል? - አየሽ እንዲህ
እንዲህ ነኝ እኔ የአራዳው ቆንጨራ!”

“ማለት? አለችው አይኖቹን አትኩራ እየመረመረች:: አልገባኝም::”

ኧረ.....? አልገባሽ.....ም? ታድያ ምን ችግር አለ ሲገባሽ ትነግሪኛለሻ!”

ምኑን?” ይብሱን ግራ የተጋባች ትመስላለች:: “ምኑን ነው ሲገባኝ የምነግርህ?”

“ስሚ - እንኳን እንዳንቺ ያለችው ደደብ ሸርሙጣ ሌላ አይበላኝም እኔ ቆንጨራው!”

“ምንድነው የምታወራው?”

“ምን እንደማወራማ እናትሽን ጠይቂያት! ለዚያውስ እናት ሲኖርሽ አይደል
👍3
- ዘረቢስ ሸርሙጣ!”

“ ኦኦ - እሺ ለማንኛውም ሂሣቤን ስጠኝና ስድቡን እንዳሻህ::”

“ “ሂሳቤ ...ን ? አፈር ደቼ ነው ሂሣብ! - ገና ሂሣብም ያምርሻል?”

“እንዴት? - ለምድነው የማያምረኝ?”

“እንግዲያው - እንዳማረሽ ይቀራል!”

“ሰውዬው ጤና የለህም ልበል?”

“እናትሽ ናት ጤና የሌላት! ትርፍ ቃል እንዳትናገሪኝ እሺ!

"እኔ ትርፍ ቃል አልወጣኝም ሂሳቤን ስጠኝ ማለት ትርፍ ቃል ነው እንዴ?

"የምናባሽ ሂሳብ ገና የሶስት አለብሽ" አላት ጥርሱን እየነከሰና እያጉረጠረጠባት..

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#መናገር_መብቴ_ነው

ካለመናገሬ
እንደቀረብኝ ሳውቅ ፤ ደጃዝማችነቱ
"ዝምታ ወርቅ ነው" ፤ ብለው የሚተርቱ
ምነው "ዝም" ብለው ፤ ወረቅ ቤት ቢከፍቱ?!!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ንፃሮት

ህይወት ሽንቁሯ ብዙ ነው ፤ ከበደኝ ስትል ይቀላል
ሙሉ ነው ካልነው ነገር ላይ ፤ ጎዶሎ መሆን ይጎድላል።
ፍፁምነት ፍፁም የለም!
ካንዱ እርኩሰት አንፃር ነው ፤ አንደኛው ባንዱ የሚፀድቀው
እከክን ያወቅነው ቀን ነው ፤ የጥፍርን ጥቅም ምናውቀው።
#ቅበላ


#ክፍል_አራት


#ከአዶኒስ

"እኔ ትርፍ ቃል አልወጣኝም ሂሳቤን ስጠኝ ማለት ትርፍ ቃል ነው እንዴ?"

“የምናባሽ ሂሳብ? ገና የሶስት አለብሽ!” አላት ጥርሱን እየነከሰና እያጉረጠረጣባት።

“ገባሽ የኛ አራዳ? የዛሬው ሲቀነስ ገና የሶስት ቀን ይቀርብሻል!"

“ የሶስት ቀን?? - የምን ሶስት ቀን ነው እሱ? . ምንድነው የምታወራው?”

“ባክሽ ሂጂና የምታጃጅይውን አጃጅይ! - የመቼዋ ነሽ በናትሽ?”

“ ኦ ....! የባሰበት መጣ አሉ - እሺ ለማንኛውም ሂሣቤን ስጠኝ::”

“እንዴታ! በጣም ነው እንጂ የምሰጥሽ - በ ...ጣም!”

“ሰውዬ - ምን አለ ነገር ባታመጣ?”

“ኧረ ....? ማስፈራራትሽ ነው?”

“እኔ አላስፈሪራሁህም - ሂሣቤን ስጠኝ፡፡”

“አንቺም ሃያ ብሬን ቁ .....ጭ! - ከዛ በኋላ ሂሣብሽን መጠየቅ ትችያለሽ።"

“ ሃያ ብሬን? ” ግንባሯን አጨመታተረች:: “የምን ሃያ ብር

“ኧረ? አላወቅሺውማ ?”

“የምን ሃያ ብር ሰጥተኸኛል?”

“ ምናባሽ እሰጥሻለሁ - በሆነ ተዓምር ከኪሴ ሞጨለፍሺኝ እንጂ ! ”

· “ከኪሴ?”

አዎ! እንዴትአባሽ አርገሽ እንደሆን ባለፈው ከቦርሳዬ ነጥለሽ ላፍ ያረግሺኝን
ሃያ ብር ቁጭ አርጊያት!”

“እኮ እኔ ካንተ ቦርሳ?”

“አይ የለ ሰይጣን ወሰደው በይኛ! እዚህ መታጠፊያው ላይ ያለችው ሱቅ ዘርዝሬ
ከአንዴም ሁለቴ ቆጥሬ -ቦርሳዬ ውስጥ አስተካክዬ ከትቼ - በቀጥታ ወዳንቺ የገባሁ ሰውዬ - ከዚህ ወጥቼም ወዲህ ወዲያ ሳልል በቀጥታ ወደ ቤት የገባው ሰውዬ ከቦርሳዬ ሃያ ብር ሲጎድል
የት ገባ እንድል ትፈልጊያለሽ? ሟሟ በይኛ ! - እ ? -ተነነ በይኛ!”

“ሰውዬው አብደህ ከሆነ አማኑኤል መሄድ ትችላለህ አሁን ግን ሂሳቤን።"

“ዛሬ ግን ሰራሁልሽ! ልብሴን ከአጠገብሽ ራቅ አድርጌ አስቀመጥኩ! - እንዴት አባሽ ትደርሺበት? አየሽ እንዲ ነኝ እኔ!"

“አሁን ሂሣቤን ትሰጠኛለህ አትሰጠኝም?"

“አልሰጥሽም! - ምናባሽ እንደምታመጪ አያለሁ::

“እኔ ምንም አመጣለሁ አላልኩም - ሂሣቤን ስጠኝ።

“ኧረ ....? ሰጠሁሽ እንዴ? - ገና አሥራ አምስት ብር ይቀርብሻል እኮ ነው ምልሽ! ገና ሶስቴ እመጣልሻለሁ ደስ ባለኝ ቀንና ሰዓት! ”

“ሰውዬ በጉልበትህ አምላክ - ሂሣቤን`

“ ገንዘብ የሌለኝ መስለሽ እንዳይሆን ቦርሳውን እያሳያት “ይኸውልሽ ተመልከች በርሳዬ ውስጥ ያለውን
ብር ግን ሰባራ ሳንቲም አልሰጥሽም! - ሞሽላቃ ሌባ!”
ፀዳል ከላይ እስከ ታች እንደ ማንቀጥቀጥ አደረጋት:: ሥሮቿ መገታተር ጀመሩ:: አገጯ ጥግ ያሉ የመንጋጋ አጥንቶች የትርታ ዓይነት ሁለት ሶስቴ ገባ
ወጣ አሉ፡፡ አተነፋፈሷ ፍጥነት ጨመረ::

ዠሂሣቤን - ስጠኝ::” አለችው ጥርሶቿን ግጥም አድርጋ እንደነከሰች ከንፈሮቿን ብቻ በማንቀሳቀስ::

“ሂጂና የምታስፈራሪውን አስፈራሪ እሺ? - እንኳን አንዲት ኪስ አውላቂ ሌባ ሌላም አያስፈራራኝ! ለመውጣት ዓይነት ብድግ አለ::

“ሂ - ሣ - ቤን! - በንጥቀት ተነስታ በሁለት እጆቿ ጃክቱን ጨመደደችው::

“ሴትዮ ልቀቂኝ! - ሂሣብ ያለብሽ አንቺ ነሽ ማለት አማርኛ አይደለም?” እጆቿን መንጭቆ ጃኬቱን ካስለቀቀ በኋላ ባለ በሌለ ኃይሉ አሽቀንጥሮ አልጋዋ ላይ
ጣላት። “ካሁን ወዲያ ብትጠንጊኝ በእጄ ስበብ እንደምትሆኚ እወቂ!

ፀዳል ከወደቀችበት በግማሽ ቀና አለችና እሳት የምትተነፍስ ዓይነት እያለከለከች እዚያው በዚያው ደም በለበሱ ዐይኖቿ ሰውዬውን አምርራ አየችው:: ወዲያው
ተስፈንጥራ ተነሳችና አስር ጣቶቿን እንዳንጨፈረረች ዘልላ ፊቱ ላይ ተከመረችበት ባልጠበቀው እርምጃዋ
የተደናገጠው ሰው የሸሚዙ ቁልፎች ተበጣጥሰው እስኪወድቁና ፊቱና ደረቱ በቡጥጫዋ እስኪዥጎርጎር ድረስ ታግሎ እንደምንም ከተላቀቃት በኋላ በሰነዘረው
ቡጢ መንጋጭላዋን ሲላት እንደገና እዚያው አልጋዋ ላይ በጀርባዋ ፍንችር ኣለች:: ለመነሳት እየተንገታገተች
ሳለ ሰውዬው ተንደርድሮ ሰውየው ጉብ ይልባትና በሁለት እጆቹ

አንገቷን አንቆ ወደዚያው ደፈቃት:: ፀዳል እጆቹን በእጆቿ ግጥም አድርጋ ይዛ ለማስለቀቅ እየታገለች እግሮቿን አወራጨች፡፡ ለመጮህ ስትሞክር ከታነቀው ጉሮሮዋ ድምፅ አልወጣ አላት:: ጣዕራ ጨመረ።

ማሙሸት ጭንቀት ገባው:: እናቱ በእንግዳዋ ስትበሻቀጥ ስትሰደብም ሆነ ስትደበደብ የመጀመሪያዋ አይደለም:: የተለያዩ ደንበኞቿ በተለያዩ ጊዜያት ይህን
ያደርጋሉ:: ታዲያ እናቱ ምንም ዓይነት ፀብ ውስጥ ብትገባ ራሷ እንደምትወጣውና እሱ በምንም ዓይነት
ከቦታው ንቅንቅ እንዳይል ጥንቱኑ ስላስጠነቀቀችው ለጥ ብሎ ከማዳመጥና ሕመሟን ከመታመም ሌላ ጣልቃ ለመግባት ሞክሮ አያውቅም:: በኋላ በኋላማ ከነገሩ ተደጋጋሚነት የተነሣ እየለመደው ሲመጣ ከበላዩ በሚያዳምጠው ግርግር መሃል ሌሎች ሌሎች ዕለታዊ ፍሬከርሲኪዎችን ማሰላሰል እስከመቻል ደርሷል::
የዛሬው ግን ለየት ያለ ሆነበት:: እናም ክፉኛ ተፈታተነው:: በደረቱ እንደተኛ አንደኛውን ጆሮውን ወደአልጋው ቀስሮ
ማዳመጥና መቁነጥነጥ ጀመረ።

ማሙሽት እየሰማው ካለው ግርግር ብቻ ሰውዬው ፀዳልን በጣም እየጎዳት መሆኑን አልተሳነውም፡፡ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለበት ትንሿ ደመነፍሱ ክፉኛ ጨቀጨቀችው:: ይሁን እንጂ የእናቱን ሕግ መጣሰም የዚያኑ ያህል ስለከበደው እንደምንም ጥርሱን ነከሰ፡፡
የሰውዩው ሁለት እጆች አሁንም በፀዳል ቀጭን አንገት ዙርያ እንደተቆላለፈ ነው።
የሰውየውን እጆች ጭምድድ አድርገው እንደያዙ ጥፍሮቿ ቆዳውን ዘልቀው ገብተዋል።እግሮቿን እያወናጨፈች
የሰውየውን እጆች ከአንገቷ ለማላቀቅና ድምዕ ለማውጣት ጣረች:: ውጪ ድረስ ሊሰማላት የሚችል ድምፅ ማውጣት ግን አሁንም አልሆነላትም ሰውዬው ያምጣል ያለከልካል ከስሩ የሞት የሽረቷን የምትወራጨው ሴት የግምቱን ያህል ቀላል ሆና ያገኛት አይመስልም....

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ነገ እንጨርሰዋለን መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#ብቸኝነት

እልፍኝህ እንዳ'ብርሃም ቤት ፤
አደባባይህ እንደጥምቀት ፤
የሰው አሸን ቢወረው ፣ጠጠር መጣያ ቢገድም፤
ለመሀላህ ካስማ ሚሆን ፣ሲያነቅፍህ የምጠራው ስም፤
ከልቦናህ ሲነጥፍ፣ አንደበትህን ሲያንቀው፤
ብቻህን ነህ ያኔ እወቀው።

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘

መጋቢት 11 2012
#የጀግና_ሀገር_አይመሽም

"መሽቶብኛል" ብለህ፣ መተኛት አትውደድ
ጀግና ተጓዥ እንጂ ፤ የለም ጀግና መንገድ።
ራሱ ጀግንነት ነው!
ብርሃን እስኪገኝ ፣ በጨለማ መሔድ!!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ቅበላ


#ክፍል_አምስት(የመጨረሻ ክፍል)


#ከአዶኒስ

ውድ ተከታታዮቼ እንዴት ናችሁ ካቅም በላይ በሆነ ችግር በቃሌ አልተገኘሁም የጀመርኩትን መጨረስ አልቻልኩም ለዚህም ይቅርታዬ ባያላችሁበት ይድረስልኝ🙏

....የሰውዬው ሁለት እጆች አሁንም በፀዳል ቀጭን አንገት ዙሪያ እንደተቆላለፉ ነው:: የሷም
የሰውየውን እጆች ጭምድድ አድርገው እንደያዙ ጥፍሮቿ ቆዳውን ዘልቀው ገብተዋል:: እግሮቿን እያወናጨፈች
የሰወዬወን እጆች ከአንገቷ ለማላቀቅና ድምፅ ለማውጣት ጣረች።ውጪ ድረስ ሊሰማላት የሚችል ድምፅ ማውጣት ግን አሁንም አልሆነላትም።ሰውዬው
ያምጣል ያለከልካል ።ከሥሩ የሞት የሽረቷንየምትወራጨውን ሴት የግምቱን ያህል ቀላል ሆና ያገኛት አይመስልም:: ድንገት ያለ የሌለ ኃይሉን አሰባሰበና
ጫናውን ጨመረ:: ፀዳል እየታረደ እንዳለ ዶሮ እግሮቿን አወነጨፈቻቸው:: አናቷን ግራ ቀኝ እያወራልጨች ከአልጋው ጋር ታላጋው ጀመር፡፡

ማሙሸት መቋቋም ተሳነው። በሰራ አካላቱ ያሉ ጅማቶች መወጣጠር ጀመሩ:: የልብ ትርታው አየለ::
የእናቱ ሕግ ከዚህ በላይ አስሮ ሊያቆየው አልቻለም፡፡ኮሽ እንዳይልበት እየተጠነቀቀ በደረቱ፡ ዳግም ወደ አልጋው ጠርዝ በመሳብ የተንዠረገገውን የአልጋ ምንጣፍ ገለጥ አደረገና ዐይኖቹን በጠባቧ ክፍል ከወዲያ ወዲህ አማተረ፡፡
ቅድም ፀዳል ሽንኩርት የከተፈችበት ቢላ እዚያው መክተፊያው ላይ እንደተወችው ነበር፡: ማሙሸት አንዲት ቅፅበት አላጠፋም፡፡ በደረቱ እየተሳበ ከአልጋው ሥር ወጣ፡፡ ቢላውን ለቀም አድርጎ አነሳና እጀታውን በእጆቹ መሃል እያመቻቸ እናቱ ላይ እንደ ጥንብ አንሳ እያጆፈጆፈባት ወዳለው ሰው ተንደረደረ፡፡ እንደደረሰም
በሁለት እጆቹ አጥብቆ የያዘውን ቢላ ከአናቱ በላይ አንስቶከቁልቁል በሰውዬው ማጅራት መሃል ሰካው።

ከየት መጣ ሳይለዉ ማጅራቱ ወስጥ
በተሰነቀረበት ቀዝቃዛ ባዕድ ነገር ለጊዜው ግራ የተጋባው ሰው እዚያው ባቀረቀረበት ዐይኖቹ ፈጠጡ፡፡ ቀስ በቀስም በፀዳል አንገት ዙሪያ ያቆላለፋቸው ጣቶቹ እየላሉ መጡ::
ማሙሸት ወደ በሩ አፈገፈገና ቁና ቁና እየተነፈስ ሁኔታውን መከታተል ጀመረ:: ሰውዬው በዝግታ ከፀዳል ላይ ቀና አለ፡፡ ከማጅራቱ የሚፈሰው ደም ቁልቁል
በጀርባው መውረድ ጀምራል፡፡ ዝግ ባለ እንቅስቃሴ እጆቹን ወደ ማጅራቱ ላከና እጀታው ሲቀር ስለቱ ሙሉ በሙሉ
የገባበትን ቢላ ደባበሰው:: ፀዳል የግንባሯ ሥራሥሮች እንደተገታተሩ በአንድ እጇ ማንቁርቷን እያሻሸችና በሀይል እያሳለች በሌላኛወ እጇ አልጋውን ተደግፋ ከተንጋለለችበት በከፊል ቀና አለች:: ሰውዬው ቢላውን ለመንቀል ይታገላል:: ማሙሸት በሩ ላይ በጀርባው
እንደተለጠፈ አንዴ ሰውዬውን አንዴ እናቱን እያየ ያለከልካል፡፡ የታችኛው ከንፈሩ ይንቀጠቀጣል። ፀዳል
ሳሏ ጋብ እንዳለላት ቆባቸው የተንጠለጠለ ዐይኖቿን እንደምንም ገልጣ ከፊት ለፊቷ ጣረ-ፍዳውን እያየ ያለውን ሰውና በሩጋ ቆሞ የሚብረከረከውን ልጇን በነጎድጓድ
ብልጭታ ፍጥነት እያፈራረቀች ተመለከተቻቸው፡፡

“በል ቶሉ ውጣ ቶሎ ውጣ አላችው ሁለመናውን ጆሮ አድርጎ አፍ አፏን እያየ ለሚጠብቃት ልጇ፡፡ “ቶሎ ውጣና ከዚህ ሰፈር ጥፋ! ማንም ቢጠይቅህ
ትሰማኛለህ?ምንም የሰማኸው ማንም ቢጠይቅህ - ምንም ያየኸው -ምንም የምታውቀው ነገር የለም!
ጨርሶ እዚህ አካባቢ አልነበርክም ማለት ነው! - እሺ?”

ማሙሸት ራሱን በመነቅነቅ እሺታውን ገለፀላት:: “እኮ በል ውጣ! - ውጣ!` አካለበችው - ከትንፋሿ ጋር ቁርጥ
ቁርጥ በሚሉ ቃላት:: ማሙሸት በሚርበተበቱ እጆቹ በሩን ከፈተና ፈትለክ ብሎ በመውጣት ከድቅድቁ ጭለማ
እቅፍ ገባ፡፡

ሰውዬው ድንገት አጓራ።በግራ እጁ ከማጅራቱ በላይ ያለውን አናቱን ደግፎ ይዞ በቀኝ እጁ ቢላውን ለመንቀል እየታገለ የሞት ሞቱን ማሙሸት በከፈተውበርግጥ ወጣ፡፡ መራመድ የተሳነው ዓይነት እዚያው ደጃፉ
ላይ ቆም አለና ማጓራቱን ቀጠለ፡፡

ወዲያው ጩኸቱን በሰሙ ተላላፊዎችና
ከየጉራንጉሩ እየተሯሯጡ በመጡ የመንደሩ ሰዎች የፀዳል ደጃፍ ተጥለቀለቀ:: ወደሚያጓራው ሰው
ለመቅረብ የሞከረ አንድም ሰው የለም። በጥቂት ክንዶች ርቀት ከብበው ጣዕር ላይ ያለውን ሰው በተሻለ ለማየት
ይጋፋሉ፡፡

የሰውዬው ድምፅ እየደከመ መጣ፡፡ ቢላውን ለመንቀል ያደርግ የነበረውን ጥረት ትቶታል:: ደሙ ቁልቁል በሰውነቱ ሙሉ ወርዶ ከመንገዱ የድንጋይ
ንጣፍ ላይ ተንጠባጠበ፡፡ ተጨፍነው የቆዩ አይኖቹን እንደምንም በግማሽ ገለጠና ወደፊት እንደመንቀሳቀስ
ሲል ከፊትለፊቱ የነበሩት ተመልካቾች በሽሽት እየተጋፉ ወደግራና ወደ ቀኝ ተበተኑ። አንድ ሁለቴ እንደተራመደ
በሙሉ ቁመቱ እንደ ደመራ ግንድስ ብሎ ወደቀ፡፡ ሰዎቹ እንደገና የወደቀውን ሰው በቅርበት ለማየት መጋፋት
ግርግሩ ደመቀ፡፡ ተጨማሪ ሰዎች ወደ ሥፍራው መጉረፍ ጀመሩ፡፡ የወደቀው ሰው ምንም እንቅስቃሴ .አይታይበትም:: አሁንም ወደ ሰውዬው በቅጡ ለመቅረብ
የደፈረ የለም:: እያንዳንዱ ሰው በየቆመበት የየራሱን አስተያየት ይወረውራል፡፡

“ሳይሞት አይቀርም! - የታል የሚተነፍሰው? ምናለ በሉኝ ሞቷል!”

“መሞትስ አልሞተም! - ይልቅ ቢላው ይነቀልለት!"

“አአ - ቢላው ከተነቀለማ አለቀለት! - ደሙ ፈስሶ ያልቅ የለ እንዴ? - ይልቅስ እንዲሁ እንዳለ ሆስፒታል ማድረስ ነው!”

“በጭራሽ! . አባዲና ሳይመጣ አንድ ሰው
እንዳይነካው! - ኋላ ጣጣ ውስጥ እንዳትገቡ!”

“አዎ - አሻራ ሳይነሳማ መንካት አይገባም

“ይልቅ ፖሊስ ይጠራ!”

“ፖሊስ ምን ይረዳዋል? - አምቡላንስ ነው
መጥራት

ከወዲህም ከወዲያም አስተያየቶች ተዥጎደጎዱ፡፡

በዚህ መሃል ፀዳል በአንድ እጇ ወገቧን እንደያዘች በሌላኛው እጄ ያንኑ ጉርርዋን እያሻሸች በዝግታ ወደ በሯ ብቅ አለች፡፡ ወዲያውኑ የሁላቸውም ትኩረት ሃውልት መስላ በሯ ላይ ወደተገተረችው ሴት ዞረ
ምንም ዓይነት የመደናገጥ ምልክት አይታይባትም፡፡ይልቁንም - ተጋጣሚውን በዝረራ እንዳሸነፈ ሻምፒወን ሰውየውን ቁልቁል እያየች የሚሆነውን የምትጠባበቅ መሰለች፡፡ ከተመልካቾቹ መሃል ወደእሷም ለመቅረብ የደፈረ የለም:: በቅርብ የሚያውቋት ሴት ጎረቤቶቿ ብቻ ከግራም ከቀኝም በጥያቄ አጣደፏት፡፡ ዐይኖቿን ለአፍታ እንኳን ከወደቀው ሰው ላይ ያልነቀለችው ፀዳል የሰዎቹን ጥያቄዎች መመለስ ይቅርና ቀድሞ ነገር የምትሰማቸው
አትመስልም::

ብዙም ሳይቆይ ጥቂት ፖሊሶች እየተጣደፉ ከቦታው ደረሱ። የከበበው ሰው ገለል ገለል አለላቸውና ሰውየውን በቅርበት እያጤኑት ሳለ በሯ ላይ ቆማ
የነበረችው ፀዳል እንደገና ወደ ውስጥ ገባች፡፡ ሰውዬውን አልብሶት የቆየው ጥላዋም እንደ ጥቁር ቬሉ ከኋላዋ
እየተጎተተ ተከትሏት ገባ። ይሄኔ መንገዱ ላይ የተንጋለለው ሰው ከላዩ ጣል ተደርጎበት የነበረ ስስ ከፈን የተነሳለት ዓይነት እንደገና በግልፅ መታየት ጀመረ፡፡

የፀዳልን ወደ ውስጥ መዝለቅ ልብ ያሉት ፖሊሶች እርስበርስ ተጠቋቆሙ። ወዲያው ከመሃከላቸው ሁለቱ ወደ በሯ እንደማምራት ሲቃጣቸው ፀዳል ነጠላ ቢጤ ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጋ እንደገና ብቅ አለች::

ሁለቱ ፖሊሶች ከተቀሩቱ ጋር በፖሊስኛ
ከተንሾካሾኩ በኋላ ወደ ፀዳል አቅጣጫ መንቀሳቀስ እንደጀመሩ እሷው ራሷ በሯን መለስ አደረገችና ወደ እነሱ በማምራት በመሃላቸው አልፋ ከፊት ከፊታቸው
እየመራች የዋናውን መንገድ አቅጣጫ ያዘች።

ሰዉ ወደየመጣበት ተበታተነ።ማሙሸት ብቻ ታጅባ እየተወሰደች ያለችውን እናቱን በርቀት ሲከተላት ቆየ።
በስፋት የተንጣለለው ግራጫ የአስፓልት ጎዳና ፀጥ ረጭ ብሏል:: ቀስ በቀስ በማሙሸትና በእነፀዳል መሃል
ያለው ርቀት እየሰፋ እየሰፋ ሄደ::
👍1
የፖርላማው ሰዓት ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት መሆነን በተለመደው ደወል አሰማ። ማሙሸት ከአንድ መስቀለኛ መንገድ ሲደርስ ቆም አለ፡፡ ድንገት ብንን የማለት ዓይነት ለመጀመሪያ ጊዜ ሁሉም ነገር እውን መሆኑ ታወቀው:: ግራና ቀኝ
ባጀቧት ፖሊሶች መሃል አንገቷን ቀና አድርጋ በሙሉ እርጋታ እየተራመደች ከርቀት የምትታየው እናቱ ይብሱን የኮከብ ያህል ርቃ ግን ደግሞ የዚያኑ ያህል
ከመቼውም በላይ ገዝፋ ታየችው:: ትንሿ ልቡ እዚያው በዚያው ሽብር ሽብር ማለት ጀመረች:: ዐይኖቹ እርጥበት አጋቱ:: ትከሻዋ ላይ ጣል ካደረገችው ነጭ ነጠላዋ ጋር ዕብነበረድ መስላ ከርቀት ትታየው የነበረችው እናቱ ነፋስ ባወከው የተኛ ውኃ ላይ ተንፀባርቆ እንደሚታይ
ምስል ብዥዥዥዥ .....አለችበት።

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2
#ዘበት_ሊሆን_ነው_ወይ

ዘበት ሊሆን ነው ወይ፤
..................ታሞ ጠበል መሄድ፤
.................................ተሰብሮ ወጌሻ፤
አልጋ የሚይዝ ጠፋ፣
.....................እርሳስ እንደኪኒን፣
................................እየዋጠ አበሻ።

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘

ጥቅምት 2010
°°°°እማሆይ ፍልስፍና

ከዳተኛው ልቤ - መካድ የለመደ
'እግዜር የለም' አለ አንቱን በወደደ
🔘©ሲራክ 🔘

--------//////_________
#ከዓለም_ ታሪክ_የተዘለለ_አንድ_አንቀጽ

በ1994 ጫማዬ ተሸነቆረ
ለቀጣይ አራት ዓመታት
እንደ ተሸነቆረ ቀረ ፤
ጫማ የተፋው አውራ ጣቴ፣ ውጋት ይሰማው ነበረ

ክሥተትን ሁሉ ጋረደ፣ ያ'ውራ ጣቴ ትንሽ ሕመም
የጫማዬን ሽንቁር ያኽል፣ ጎድላ ታየችኝ ዓለም
ከእኔና ከእግር አምላኬ በቀር፣ ማንም ይህን አላስተዋለም

ሊቃውንት የዓለምን ክሥተት ሲጽፉ
የምድር ወገብ መስመር በሳሎኔ ባለማለፉ
መኖሬን ገደፉ፣

ሁሉም እንደ ፈቃዱ ቢመርጥ የታሪክ ርእስ
አንዱ በፈረንሳይ አብዮት ቀለም ቢጨርስ
አንዱ በግሪክ ቢጀምር
የዓለም ታሪክ አይሟላም የጫማዬን ሽንቁር ሳይጨምር፡፡

🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘
#ማዕዶት


#ክፍል_አንድ


#በየዝና_ወርቁ

“ወይኔ !... ዘንድሮ እንዴት ጉድ ሆንኩ!? አለች ማዕዶት ለራሷ ብቻ በሚሰማ ድምፅ - ራሷን በቁጭት እየነቀነቀችና ገና ሁለት ወር እንኳ ያልሞላው ፅንስ በእጇ ይታወቃት ይመስል ከእምብርቷ በታች ያለ
ሰውነቷን እየዳሰሰች :: ሰሞኑን ሁሉ እንዲህ እየተቆጨችና እየተበሳጨች ነበር የሰነበተችው:ፈ።

ዛሬም የሰነበተባት ጭንቀት እያናወዛት
የምርመራ ውጤቷን ለመስማት በክሊኒኩ የእንግዶች ማረፊያ አግዳሚ ወንበሮች በአንዱ ላይ ተቀምጣለች።ወረፋ አስከባሪዋ ተረኛ ለመጥራት ብቅ ስትል ትደነግጣለች፡፡ ሌላ ሰው ጠርታ ስትመለስ ደግሞ ትጨነቃለች፡፡ ሁለቱ ቀያይ ጉንጮቿ ፍም መስለዋል፡፡
ለወትሮው እንደህፃናት ዐይኖች ጥርት ብለው የሚጉሎት ዐይኖቿ ደፍርሰው ቀጫጭን የደም ስሮች ቅርንጫፎቻቸውን ዘርግተውበታል፡፡ ሳምንቱን ሙሉ
ማበጠሪያ ያልገባበት ፀጉሯ በተከናነበችው ጥቁር ሻርፕ
ቢሸፈንም በግንባሯ ዳርዳር ክርችፍ ብሉ ይታያል፡፡ጭንቀት ያጋለው ሰውነቷ ላብ ማመንጨት ሲጀምር ራሷን ያሳክካት ጀመር፡፡
እንደ እሷ የምርመራ ውጤታቸውን የሚጠብቁ ሰዎች በወረፋ ቁጥራቸው እየተጠሩ ውጤት ወደሚሰማበት ክፍል እየገቡ ይወጣሉ፡፡ ማዕዶትውጤታቸወን ለመገመት ፊታቸወን አተካራ
ታስተወላለች፡፡ አንዳንዶቹ የግንባራቸወን ላብይጠርጋሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ መልዕክት አድርሱ የተባሉ
ይመስል እየተጣደፉ ከግቢ ይወጣሉ፡፡

አንዳንዶቹ ምንም ስሜት አይነበብባቸውም።እንዲህ ፊታቸውን እያነበበች ሁኔታቸውን እያስተዋለች ውጤታቸውን ለመገመት ስትሞክር ትቆይና ሳትወድ ወደ ምትሸሸው ወደ ራሷ ትመለሳለች፡፡ በሃሳቧ የተሰራ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭ የሚል ወረቀት ፊቷ ላይ
ሲደቀን ይዘገንናታል፡፡ እንደመባነን ዐይነት ራሷን በኃይል ትነቀንቃለች:: በሰራ አካላቷ የጭንቀት እሳት ይቀጣጠላል።

“ወይኔ ምን አሳበደኝ? ደግሞ ትክክለኛ ስሜንና አድራሻዬን እንዴት እሰጣለሁ? ምን አደነዘዘኝ? ትላለች።

ደም ከመስጠቷ በፊት የምክር አገልግሎት የሰጠቻት ነርስ የምርመራ ውጤትሽ በምስጢር የሚያዝ
ነው:: መዝገብ ላይ የምናሰፍረው ለስታትስቲክስ እንዲሆን በኮድ ቁጥር ነው:: ካንቺ ፈቃድ ውጭ ለማንም አይነገርም

ብላታለች፡፡ መጀመሪያ አምናት ነበር፡፡ ደም ከሰጠች በኋላ ግን የማይታመን ነገር ሆነባት፡፡ በዚያም ላይ ምንም እንኳ ለመመርመር የፈለገችበትን ትክክለኛ
ምክንያት ባትነግራትም ከነርሷ ጋር ረዘም ላለ ጊዜ አውርተዋል፡፡ ከአሁን በኋላ የትም ቦታ ብታገኛት እንደምታውቃት አሰበች፡፡ እና ነርሷ በከተማው ሙሉ
ተባዝታ ታየቻት፡፡ ታክሲ ውስጥ ፣ ገበያ መሀል ፣መዝናኛ ቦታዎች... ምናልባትም እኮ የሚያውቃት ሰው ዘመድም ጓደኛም ጉረቤትም ልትሆን ትችላለች! እንዲህ
ባሰበችው ቁጥር - በአደባባይ መሀል እርቃኗን የቆመች እየመሰላት ሄደ፡፡ እና “እንዲያውም ምስጢር ባይባል
ኖሮ ስራዬ ተብሎ ይወራ ይችል ነበር!» አለች:: እጆቿ በጭንቀት ይንቀጠቀጣሉ፡፡

ወረፋ አስከባሪዋ ግን ብቅ ትልና በተረጋጋ
መንፈስ በቁጥራቸው እየጠራች ትመለሳለች:: ማዕዶት ከከአሁን አሁን ተጠራሁ እያለች በ ጭንቀት
ታስተውላታለች፡፡ የወረፋ ቁጥራቸው ደግሞ ቅደምተከተልና የጠበቀ አይደለም፡፡ እና የሷን ቁጥር እያለፈች
ሌላ ስትጠራ ትባትታለች፡፡

“በቃ ነኝ ፣ ነኝ...” ትላለች፡፡ “
ፖዘቲቭ የሆንነውን ነው ወደኋላ ያቆዩን፡፡ ረዥም ምክር ሊሰጡን፣ እንዳንሸበር
በቂ ጊዜ ሰጥተው ሊያረጋጉን ፣ ለሌሎች እንዳናስተላልፍ ሊያስተምሩን! ... አቤት ፈጣሪዬ! ... ምን አሳበደኝ?
... ምነው እንደሸሸሁት ሳልመረመር ብቀር?...»
“ማዕዶት መጀመሪያ ፍቅረኛዋ ከአያልነህ ጋር በጥል የተለያዩ ወዲህ ለበርካታ

ዓመታት በጥርጣሬና


በ ጥ ንተት እየታመሰች ከወንዶች ርቃ ኖራለች።ተመርምራ ሁኔታዋን ለማወቅ እየፈራችም ብዙ የትዳር አጋጣሚዎቿን ሽሽታ አሳልፋቸዋለች:፡ እምነታችንን
በፈጣሪ አድርገን ሳንመረመር እንጋባ የሚሏትን ወንዶች ትጠራጠራቸዋለች | ትፈራቸውና እርግፍ አድርጋ ትተዋቸዋለች፡፡ “ተመርምረን ነው መጋባት ያለብን የሚለ ሲያጋጥሟት ደግሞ ራሷን ትጠራጠርና መመርመሩን ትፈራና ትጨነቃለች፡፡ ድንገት ቫይረሱ
በደሟውስጥ ቢገኝስ? ከዚያ ወዲያ ህይወትም ዓለምሌላት ሆኖ ይታሰባታል:: እና አያልነህን ትረግምና ሳታገባም ሳትወልድም እንዲሁ መኖርን ትመርጣለች፡፡

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እንዲሁ ሳታገባ ሳትወልድ ህይወቷ የማለፉ ነገር ያስጨንቃታል፡፡ እናት የመሆን
ፍላጐት ፣ ባለትዳር የመሆን ምኞት ተጠናውቶ ይወተወታታል።ታዲያ ውትወታው እረፍት ሲነሳት ፣ ቀስፎ ሲያስጨንቃት ፣ ዕድሜዋን ታሰላና
«ገና ብዙ ጊዜ አለኝ:: እስከዚያ መድኃኒቱ ይገኝ ይሆናል» ትልና ራሷን ትደልላለች::

በርካታ ወዳጅ ዘመዶቿ ቀጠን ረዘም ያለውንና በአለባበስ አዋቂነቷ ታግዞ የሚዋበውን ተክለ ሰውነቷን፣አጠር ካለው አፍንጫዋ በላይ እንደከዋክብት የሚያበሩትን ዐይኖቿን ፣ ከፊቷ ጋር በሚስማማ ቅርፅ እየተቆረጠች
በካውያ አለስልሳ በምታበጥረው ፀጉሯ የሚፈካውን የደም ገምቦ ገፅታዋን እያስተዋሉ ሳታገባ ጊዜዋ መንጎዱ
ይከነክናቸዋል።
በአንዳንድ አጋጣሚዎች ተደፋፍረው
እንድታገባ ሲመክሯት ግን ምክንያት እየደረደረች ስትከራከር ሃያዎቹን ጨርሳ ወደ ሰላሳዎቹ ተሻግራለች::

ወዳጅ ዘመዶቿን እንዲህ ግራ ይግባቸው እንጂ እሷማ ከአስር ዓመት በፊት በወጣትነት እድሜዋ አግብታ
ጉልበቷ ሳይደክም በሞቀ ፍቅርና ትዳር ልጆቿን የማሳደግ ዕቅድ ነበራት:: ከንግድ ስራ ኮሌጅ በቢሮ ማኔጅመንት በዲኘሎማ ተመርቃ አሁን ከምትሰራበት መስሪያ ቤት እንደተቀጠረች ሰሞን የሠራተኞች ጉዳይ
ኤክስፐርት ከነበረው ከአያልነህ ጋር ተግባቡ:: በፍቅር ተስማምተው ለመጋባት ወሰኑ:: ያንጊዜ የሃያ ሶስት ዓመት ወጣት ነበረች:: እሱም ወደ ሃያዎቹ መገባደጃ
ደርሷል፡፡

በዚያን ዘመን ከኤች.አይ.ቪ ራስን ለመጠበቅ የሚታሰበው ተጋብቶ አንድ ላንድ ተወስኖ በመኖር እንጂ ከጋብቻ በፊት ተመርምሮ ራስን ማወቅ ትኩረት
የሚሰጠው ጉዳይ አልነበረም:: በዚያም ላይ በአብዛኛው ሰው እምነት ኤች.አይ.ቪ የጠጪ ወንዶችና የሴተኛ አዳሪዎች መቅሰፍት ነበር፡፡

የአያልነህ ተግባቢና ቀበጥባጣ ባህሪ ከማዕዶት ጭምትነት ጋር ሲዋሀድ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንኳን
ለነሱ ላያቸውም ወደድኳቸው የሚያሰኝ ህብር ፈጥሮ ነበር፡፡
ተጋብተው ጎጆ ለመውጣት ከሁለቱም ደሞ እየቀነሱ ሲያጠራቅሙ፣ ስለሰርጋቸው ድግስ ፣ ስለዚቤት ዕቃ... እያሰሉ ሲብተከተኩ ሁለት ዓመት አሳለፉ

በመሀከሉ አያልነህ በእድገት የሠራተኛ ማስተዳደሪያ ክፍል ኃላፊ ሆኖ ወደ ናዝሬት ተዛወረ:: ማዕዶት ያገኘው የሁለት መቶ ብር ጭማሪ ቀርቶበት ባይለያዩ ነበር
የፈለገችው:: ለአያልነህ ግን የሞኝ ሀሳብ ሆነበት፤

“እድገት እንዴት እምቢ ይባላል፡፡ እንኳን
ይኼንን ያህል የደሞዝ ልዩነት እያለው አላት::
“ፍቅራችን በመካከላችን እስካለ ድረስ እንኳን ዘጠና ዘጠኝ ኪሎ ሜትር አንድ ሺም ቢሆን ችግር የለውም
ብሎ አግባባት::

የመጀመሪያዎቹን ስድስት ወራት በየሳምንቱ መጨረሻ ያለማቋረጥ እየተገናኙ ጥሩ ጊዜ አሳለፉ፡፡
አያልነህ ሲያስበው ግን ከደመወዛቸው ከወጪ ቀሪ ሆኖ የሚጠራቀመው ገንዘብ እንዲያወም እድገት ሳያገኝ ከነበረው ያንስበት ጀመር:: በዚህ ከቀጠሉ ትዳር
የመመስረታቸው ነገር የህልም እንጀራ ሆኖ ታየው። እና በአስራአምስት ቀን አንድ ጊዜ ቢገናኙ እንደሚሻል በጨዋታ መሀል አነሳባት:: ጠረጠረችውና ተቆጣች።
እንዲያውም ለነገር የማይመች ሆኖባት ነው እንጂ በሱ ተግባቢ ባህርይ ተለያይተዉ መኖራቸወ የበለጠ
እያሳሰባት
👍3
ሄዷል፡፡ እንዲህ ሆነው የመጀመሪያው ዓመት አለቀ::
ኢያልነህና ናዝሬት ተዋሀዱ:: የሚያውቀውና የሚወደው ሰው ብዛት ተወልዶ ያደገባት ከተማ አስመሰላት:: በተለይ እንደ ሴት ጓደኛቸው የግል
ችግራቸውን የሚያዋዩት ሴት ባልደረቦቹ መበራከት ማዕዶትን ቅር ያሰኛት ጀመር፡፡ በአንድ የግል ፋብሪካ ውስጥም ተቀላጥፎ የትርፍ ጊዜ ስራ አገኘ፡፡ የወር ገቢው ጨመረ፡፡ ማዕዶትም ትምህርቷን በስራ አመራር ወደ ዲግሪ ከፍ ለማድረግ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማታው
ክፍለ ጊዜ ጀመረች:: እና ሳያስቡት የሚገናኙበት ጊዜ እያነሰ ሄደ::

መራራቃቸው እየሰፋ ሲሄድ አለመግባባት
ይከሰት ጀመር፡፡ ማዕዶት ችላ አልከኝ ትለዋለች:: ድሮ እንቅስቃሴወን ከወር ገቢ አንፃር እያሰላች የተቆጣጠረችው ይመስላት ነበር፡፡ አሁን ግን ባለትርፍ
ገቢ ሆኗል:: የኤች.አይ.ቪ ወሬም ተስፋፋ:: ናዝሬት ድሬደዋና ባህርዳር ትኩረት እየሳቡ ሄዱ:: ስጋትና ጥርጣሬ
ያነጫንጫት ጀመር:: አያልነህም በበኩሉ እስኪያገኛት ይጓጓ የነበረውን ያህል ንጭንጫን መሳቀቅ ጀመረ::

በዚህ ሁኔታ እያሉ ለፈተና እረፍት ወስዳ
በነበረበት አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ ድንገት ናዝሬት ትሄዳለች:: ያሰበችው ከቢሮው ሳይወጣ ደርሳበት አብረው ሲዝናኑ እንዲያመሹ ነበር፡፡ ሆኖም ከአውቶቡስ ተራ ወርዳ በታክሲ ወደ መስሪያ ቤቱ ስትሄድ በእግሩ እየተጣደፈ ቁልቁል ሲወርድ አየችው:: አሁን አሁን
ስታስበው ምነው በጠራሁት ኖሮ!» እያለች ትቆጫለች፡፡ ያን ጊዜ ግን የቅናት ዛር በላይዋ ላይ ሰፍሮ መላቅጧን
ያሳጣት ስለነበር እያመነታች ዝም ብላ ትንሽ ከሄደች በኋላ ድንገት ታክሲውን አስቁማ ወረደች::

ከዚያ በኋላ በርቀት ተከተለችው፡፡ ሄዶ ሄዶ
በቀለ ሞላ ሆቴል ገባ፡፡ ወደኋላ ቀረት ለማለት ሞከረች።አመነታች:: የያዛት የቅናት ዛር ግን ቀላል አልነበረም።
እየገፈተረ ወደ ውስጥ አስገባት:: መናፈሻው በረንዳ ላይ ከምትጠብቀዉ ሴት ጋር ተገናኘ:: ብድግ ብላ
ተቀበለችው:: ሞቅ ባለ ሁኔታ ተጨባብጠው፤ ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙና ስሜት በተሞላበት ሁኔታ የሆነ ነገር ተነጋግረው ተቀመጠ፡፡ ምናልባት ስለዘገየ ይቅርታ እየጠየቃት ሊሆን ይችላል፡፡ ማዕዶት ላይ ተሳፍሮ
ለከረመው የቅናት ዛር ግን እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ምሱ ነበርና ወረደ:: እያስጋለባት ሄደችባቸው።

ሴትዮዋ የመስሪያ ቤቱ ባልደረባ ናት:: ማዕዶትን መጀመሪያ በርቀት ስታያት ከአያልነህ ጋር የመጣች ስለመሰላት ፈገግ አለች:: ቀረብ ስትል ግን ሁኔታዋ
አስደነገጣት:: አያልነህ ድንጋጤና ንዴት ተቀላቅለው ፊቱን ደም አስመሰሉት:: ሆኖም በዚያ ቦታ ላይ ሊደርስበት
የሚችለውን ውርደት ፈርቶ በር ጋታ ተቀበላት፡፡አከታትለም ሴትየዋ ከአለቃዋ ጋር ባለመግባባቷ ምክንያት እየደረሰባት ያለውን ችግር ልትነግረው መሆኑን
ሊተርክላት ሞከረ:: ማ ዕ ዶት ግን መብረ ድም መረጋጋትም አልቻለችም:: ቅናት እያተነነው የሄደው የድሮው ጭምትነቷ ጭራሽ ጠፍቶ የማያውቃት ሴት
ሆናለች::
በዚህ ሁኔታ ላለመቆየት ሴትየዋን አሰናብቶ እሷን ይዟት ወደቤቱ ሄደ:: እንደተጣሉ አመሹ፡፡ ሌሊት ላይ.....

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
1👍1
#እንዲሁ_ሲወደድ

እኔ አንቺን ስወድሽ...
አይንሽን ጥርስሽን፤አይደለም አይቼ
በጡት ወይ በዳሌሽ፤አይደለም ጓጉቼ
አይደለም በፀባይ፤ወይም በቁመናሽ
እንዲሁ ወደድኩሽ!
ፈተና አይደለሽም ፤ እኔ አንቺን ማጠናሽ።
መውደዴን ስነግርሽ....
"ምን አይተህ?" አትበይ ፤ ፍቅሬን ለማጓደል
ሳላይ ነው ምወድሽ ፥ ፍቅረሸ እውረሸ አይደል?!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#መቅለጥ_መገፋት

"ቅቤ ተገፍቶ ነው
አናት ላይ የወጣው"
የሚል ቢሂል ይዞ ፤ የሚገፋን በዛ
ከፍታ ነው ካሉን
ካናት ቀልጠን ስንወርድ ፣ ገፊ በኛ ወዛ።
አንዳንዱ እንደዚህ
ራሱን ሊያወዛ ፥ ራሱን ሊኳኩል
አንድ ተረት መዞ ፣ ከአንድ እውነትህ በኩል
ታች ሆኖ ለመውዛት ፣ ይስቅልሃል ከላይ
ተገፍቶ መውጣት ደግ ፣ ቀልጦ መውረድ ስቃይ።
#ማዕዶት


#ክፍል_ሁለት


#በየዝና_ወርቁ

ያመሸበትን ብስጭት ቻል አድርጎ ነገር ሊያበረድ አሰበና ሊያቅፋት እጁን ዘረጋ፣

በዚህ ሁኔታህ በዚ መጥፎ ጊዜ እንዴት ላምንህ እችላለሁ አለች ፤እንዳያቅፉት እጁን እየገፋች።ያመረረች ስላልመሰለው

እንደጠረጠርሺኝ ከሆንኩማ ለአንቺም ከተረፈሽ ቆይቷል ማለት ነው አለ እየሳቀ ከዚያ ሊያቅፋት እንደገና እጁን ዘረጋ ማዕዶት የባሰ እየተናደደች

'አጉል ቀልድ' አለችና ተስፈንጥራ ተነስታ የአልጋውን ልብስና አንዱን ትራስ አንጠልጥላ ሄዳ ሶፈው ላይ ተኛች።የምሯን አልመሰለውም ነበር። የምትመለስ ስለመሰለው ሲጠብቃት እንደቆየ እንቅልፍ ወሰደው ወፍ ሲንጫጫ ተነስታ በበራሪ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰች።

አያልነህ የወደፊቱ ህይወታቸው እንዴት እንደሚቀጥል በጣም አሳሰበው።በዚህ ዓይነት ቢጋቡ ህይወቱ ሰላም እንደሚያጣ ታየው። እና በጋብቻ ከመተሳሰራቸው በፊት ግኑኝነታቸው ቢቋረጥ እንደሚሻል ወሰነ።መአዶት ግን ለመታረቅ ፍቃደኛ አለመሆኗ እርግጠኛ ባትሆንም አያልነህ ሳይደውልላት የሚቀር አልመሰላትምነ ነበር። አለመደወሉ የጠረጠረችው ሁሉ አረጋገጠላት
ምነው ከሱ እንደተለየሁ ወዲያውኑ ጨክኜ በተመረመርኩ፡፡ ቁርጤን አውቄ ህይወቴን አስተካክል ነበር አለች- እንደመባነን እያደረጋት:: ሳታስበው ሃያው
ደቂቃ ነጉዷል:: በእንግዳ ማረፊያው አግዳሚ ወንበሮች ላይ ተኮልኩለው ከነበሩት ብዙ ሰው ሄዷል። እንደገና
ሰዓቱ ሳይታወቃት እንዳያልፍ ሐሳቧን ወረፋ ወደሚጠብቋት ሰዎች መልሳ ፊታቸውን ማጥናት ጀመረች።ብዙዎቹ በአስማት የተያዙ ይመስል ድንዝዝ
ብለው ለየብቻቸው ተቀምጠዋል።

የውጤት መቀበያው ክፍል ተከፈተና ወጣት ወንድና ሴት ፊታቸው በደሰታ በርቶ ወጡ። ደረጃውን እንደወረዱ ሁለቱም ድንገት ተቃቀፉና በደስታ ስሜት
ከንፈር ለከንፈር ተሳሳሙ። እንደገና ተላቀው ዐይን ለዓይን ተያዩና ተቃቀፉ። ከተቀመጡት ሰዎች ከፊሎቹ ነቃ እንደማለት ብለው ደስታቸውን ተጋሩ። አንዳንዶቹም የባሰ ተሳቀቁ። ማዕዶትም ለመጋባት የተመረመሩ መሆናቸውን ገመተችና ራሷን እየወቀሰች ጭብጥ ብላ
ተቀምጣ አስተዋለቻቸው።

ተከትሎ አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ እንዳለባት ይሰማት ጀመር።

በዚሁ የተነሳ ባለፈው አመት ከወንዶች እንደምትርቅ አስተውሎ ከቀረባት ሰው ጋር ፍቅር ጀምራ ነበር፡፡ ባህርያቸውን ተጠናንተው ለትዳር እስኪወስኑ
አልፎ አልፎ የገቡበትን ስሜትም ኮንዶምን ተከልለው አሳልፈዋል፡፡ በኋላ ግን ለጋብቻ መተሳሰባቸውን ተከትሉ
በዚህ የተነሳ ባለፈው ዓመት ከወንዶች
ያነሳባትን የእንመርመር ውትወታ መቋቋም ስላቃታት ራቀችው፡፡ እሱም ተመርምሮ በመጋባት አጥብቆ ያምን
ስለነበር ብዙ ጊዜ ሊያሳምናት ሊያደፋፍራት ጣረ።በመጨረሻ እየሸሸችው መሆኗን ሲረዳ ግን የሷን ያህል የተማረ፤ ዘመናዊ ሰው ተመርምሮ ራሱን ለማወቅ የማይደፍርበት ምክንያት ሊገባው አልቻለም።ሰለዚህ ቀደም ብላ ተመርምራ ብታውቅ ነው ብሎ ጠረጠረና
ፈራት። ከዚያም ተዋት።

ብቸኝነት እንደገና ! ዓመት አለፈ...

ማዕዶት ሳይታወቃት ለረዥም ጊዜ ጭብጥ ብላ ተቀምጣ ስለቆየች ሳይሆን አይቀርም ሆዷ ላይ ህመም ተሰማትና ቀና አለች።ከዚያ የተሰማትን ህመም
ለማስታገስ ወደኋላዋ ጋለል ብላ ሆዷን እየዳሰሰች ፍዝዝ ብላ እንደቆየች ሃሳብ ነጥቆ ለማርገዟ ምክንያት ወደሆናትና ማስታወስ ወደማትፈልገው ከሳምሶን ጋር
ወዳሳለፈችው ጊዜ ጭልጥ አርጎ ወሰዳት ...
ከሳምሶን ጋር የተዋወቁት ከሶስት ወራት በፊት ለስብሰባ በአውሮኘላን ወደ ድሬዳዋ ስትሄድ ነበር፡፡ የለበሰው
ሰማያዊ ጅንስ ጃኬትና ሱሪ ሰውነቱ ላይ ልክክ ብሎ ወንዳወንድ ቁመናውን አጉልቶ አውጥቶታል።ቀላል ጓዝ የያዘ የመንገድ ሻንጣውን በትከሻው ላይ አንጠልጥሉ
አነስ ያለ የእንግሊዘኛ መፅሐፍ በእጁ ይዟል፡፡ ንጥረ ንጥር የሚለው አረማመዱ ነጭ እስኒከር ጫማው ውስጥ ስኘሪንግ የተቀበረ አስመስሎታል።ያለ ጉዳይ በሰፊው የመንገደኞች መቆያ ወለል ላይ እየተንሸራሽረ ዐይኖቿን ከሳበው በኋላ በዐይኖቹ ያጫውታት ጀመር፡፡ በመጀመሪያ ላይ “ዐይናውጣ በሚል ተሳዳቢ አስተያየት ገላምጣዋለች::
ዐይኖቿንም ልትነፍገው ሞክራ ነበር፡፡ በኋላ ግን ከዓመት በላይ የወንድ ገላ ነፍጋው የቆየችው ሰውነቷ የመልካም
ቁመናውን ጥሪ የሚቋቋም አልሆነም:: እና የመነሻ ሰዓታቸው ደርሶ ወደ አውሮኘላኑ ሲጓዙ እንደተከተላት
እያወቀች አልራቀችውም:: ተከታትለው ስለገቡ አንድ ላይ ለመቀመጥ አልተቸገሩም:: ገና እንደተቀመጠ
የደህንነት ቀበቶውን እያጠበቀ፣

“ጥሩ ቀን ይመስላል፣ አየሩ ብሩህ ነው” አላት፡ በአዎንታ አረጋገጠችለት:: ከዚያ መፅሃፉን ገለጠና ወደኋላው ለጠጥ ብሎ ማንበብ ጀመረ።
ፀጥ ብሎ ማንበቡን ሲቀጥል ማዕዶት ባልጠበቀችው ድርጊቱ ግራ ተጋብታ የግራ እጁን የቀለበት ጣት መልካት
አደረገች፡፡ ለጌጥ የተደረገ የወርቅ ቀለበት ነው፡፡ የጋብቻ አለመሆኑን አረጋገጠችና ዘና ብላ ተቀመጠች፡፡ በብልጠት
የበለጠችው መሰላት እንጂ እሱም ጣቶቿ ላይ የጋብቻ ቀለበት አለመኖሩን ገና እንግዶች ማረፊያ ወስጥ እያሉ
ነው ያረጋገጠው።

ለአስር ደቂቃ ያህል ከኣሁን አሁን እንደገና
ያናግረኛል ብላ ጠበቀችው መፅሀፉ ላይ አተኩሮ ጭራሽ መኖራንም የረሳ መሰለ፡፡ ተናደደችና ራሷን ከወንበሯ የኋላ መደገፊያ ላይ ጣል አድርጋ ፊቷን በትንሹ ወደሱ አቅጣጫ መለስ አደረገች:: ከዚያ እንቅልፍ እንደያዘው ሰው ዐይኖቿን ጨፈነቻቸው:: ሳምሶን ሁኔታዋ ገባውና
ዘወር ብሎ እያያት፤

ደበርኩሽ አይደል?” አለ፡ ልክ ረዘም ያለ ጊዜ ትውውቅ እንዳላቸው ሁሉ ፈገግ ብሎ:: ጥርሶቹ በንፅህና የተያዙ ናቸው:: ጠቆር ካለው የፊቱ ቆዳና ደፍጠጥ
ብሉ ቀዳዳዎቹ ሰፋ ካሉት አፍንጫው ስር እጅብ ካለው ጢሙ ጋር ህብር ፈጥረዋል:: አነስ ያሉት ዐይኖቹ ንቁ
ናቸው።

ግድየለም አንብብ » አለችው፣ እንቅልፍ
እንደያዘው ሰው ድክምክም ብላ፡፡

“ጥሩ የመንገድ ጓደኛ አይደለህም እያልሽኝ ነው አይደል? አላት መፅሐፍ ባልያዘበት ግራ እጁ ትከሻዋን
መታ አድርጎ እየሳቀ:: ነቃ ብላ እንደ መሳቅ እያለች አየችውና የየሰው ተሰጥኦ ገረማት።የሚያግባባ የሚያላምድ ፊትና ሁኔታ አለው::

"ኖ! ኖ! አንብብ እኔ እተኛለሁ አለችው።
"በአጭር የአውረፕላን ጉዞ ውስጥ ይኄ እንዳልኩት እንዳልኩት ደባሪ እያልሽኝ ነው! »

እንዲህ በክርክር ቢጤ ወሬ ጀመሩና በዚያ ቀጠሉ፡፡ ወደ ድሬዳዋ ለምን እንደምትሄድ ጠየቃት ከፍተኛ ኤክስፐርት መሆኗንና ለስብሰባ እንደምትሄደ
ነግራው የሱን ጠየቀችው:: በመንግስት መስሪያ ቤት ደህና ቦታ ላይ ይሰራ እንደነበርና አሁን ግን የግል ስራ
ለመጀመር ድሬዳዋ ሁኔታዎችን ለማጥናት እየሄደ መሆነን ነገራት፡፡

አውሮኘላኑ ያሬዳዋ አውሮኘላን ማረፊያ ደርሶ ሲለያዩ ፤ አዲስ አበባ ሲመለስ ሊጠያየቁ፡ ተስማምተው በየሞባይል ስልክ ቁጥሮቻቸውን ተለዋወጡ፡፡ በማግስቱ ስብሰባውን ተካፍላ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰች፡፡

ከዚያ በኋላ ማዕዶት ሳምሶን ይደወላል ብላ ስትጠብቅ ሰነበተች።ሳምንት አለፈው፤ አልደወለም፡አስረኛው ቀን ቆጠረች ድምጹን አላሰማትም፡፡
ልትደውልለት ፈለገች:: ጥሩ አልመሰላትም፡፡ ተወችው፡፡በዚህ ሂደት ግን ብዙ አሰበችው:: ባሰበችው ቁጥር ደግሞ አእምሮዋ ውስጥ እየጎላ እየጎላ ቦታ እየያዘ ሄደ::በሶስተኛው ሳምንት ላይ ሳምሶን ደወለ። ጉዳዩ አላልቅ ብሎት ሁለት ጊዜ ድሬዳዋ ደርሶ መመለሱን
ነገራት እያይዞም ራት እስረው እንዲበለ ጋበዛት፡፡

ከስራ በአስራ አንድ ሰዓት ተኩል ስትወጣ መኪና ይዞ በር ላይ ጠበቃት የበዙ ጊዜ ትውውቅ ያላቸው ያህል እየተሳሳቁ ተሳሳሙ፡፡ ደህንነታቸውን በመጠያየቅ
👍3
የጀመሩት ወሬ እንደተነፈሰ የውሃ ግድብ ወለል እያለ ወረደ:: ሰፊና ጨለም ያለ ግቢ ወዳለው ሆቴል ወሰዳት፡፡
መኪናቸው ውስጥ እንደሆኑ ራት አዘዙ:: የሚጠጣ ነገር ጥያቄ ሲቀርብ ፤

ስኘራይት ይሻለኛል አለችው:: ሳቅ አለና፣
ለበላነው ማወራረጃ አምቦ ውሃ እንጠጣ:: ከዚያ በኋላ ግን የፍቅረኞች መጠጥ ማርቲኒ ነው" አላት::
በጣም ዘመናዊ ሰው ነው ብላ አሰበች::

ራታቸውን እያጎረሳት በሉ:: ማርቲኒውን
እየተሳሳሙ መጠጣት ቀጠሉ:: አንድ ከራሷ አንድ ጊዜ ከራሱ ብርጭቆ እያቀናጣ ሲያስጎነጫት ሳታውቀው ብዙ
ጠጣች:: የወንድ ገላ የናፈቀው ገላዋ መጠጡ በፈጠረባት ሞቅታ ታግዞ ለመጋል ጊዜ አልፈጀበትም::

የሚወጡና የሚገቡ መኪናዎች እላያቸው ላይ መብራት እያበሩ ሲያስቸግራቸው ክፍል ውስጥ ገብተው እንደልባቸው ቢሆነ እንደሚሻል ጠየቃት፡፡ ድንገት
ጠረጠረችው።ፈራች። እና

“እኔ ኮ ራሴን አላቀውም ሳሚ” አለችው መሚለማመጥ ቅላፄና በጨዋ ቋንቋ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
#ምን_አለኝ_ሃገሬ ?

ወፊቷ ካልጮኸች
በወንዜ ዝማሬ
ፊቴን ውርጭ ካስመታው
ከውጪ ማደሬ
ምን አለኝ ...ምን አለኝ
ምን አለኝ ሃገሬ ?

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘