#ከዓለም_ ታሪክ_የተዘለለ_አንድ_አንቀጽ
በ1994 ጫማዬ ተሸነቆረ
ለቀጣይ አራት ዓመታት
እንደ ተሸነቆረ ቀረ ፤
ጫማ የተፋው አውራ ጣቴ፣ ውጋት ይሰማው ነበረ
ክሥተትን ሁሉ ጋረደ፣ ያ'ውራ ጣቴ ትንሽ ሕመም
የጫማዬን ሽንቁር ያኽል፣ ጎድላ ታየችኝ ዓለም
ከእኔና ከእግር አምላኬ በቀር፣ ማንም ይህን አላስተዋለም
ሊቃውንት የዓለምን ክሥተት ሲጽፉ
የምድር ወገብ መስመር በሳሎኔ ባለማለፉ
መኖሬን ገደፉ፣
ሁሉም እንደ ፈቃዱ ቢመርጥ የታሪክ ርእስ
አንዱ በፈረንሳይ አብዮት ቀለም ቢጨርስ
አንዱ በግሪክ ቢጀምር
የዓለም ታሪክ አይሟላም የጫማዬን ሽንቁር ሳይጨምር፡፡
🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘
በ1994 ጫማዬ ተሸነቆረ
ለቀጣይ አራት ዓመታት
እንደ ተሸነቆረ ቀረ ፤
ጫማ የተፋው አውራ ጣቴ፣ ውጋት ይሰማው ነበረ
ክሥተትን ሁሉ ጋረደ፣ ያ'ውራ ጣቴ ትንሽ ሕመም
የጫማዬን ሽንቁር ያኽል፣ ጎድላ ታየችኝ ዓለም
ከእኔና ከእግር አምላኬ በቀር፣ ማንም ይህን አላስተዋለም
ሊቃውንት የዓለምን ክሥተት ሲጽፉ
የምድር ወገብ መስመር በሳሎኔ ባለማለፉ
መኖሬን ገደፉ፣
ሁሉም እንደ ፈቃዱ ቢመርጥ የታሪክ ርእስ
አንዱ በፈረንሳይ አብዮት ቀለም ቢጨርስ
አንዱ በግሪክ ቢጀምር
የዓለም ታሪክ አይሟላም የጫማዬን ሽንቁር ሳይጨምር፡፡
🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘