YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Update: #የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫ፣ ዛሬ በአዲስ አበባ የተደረገው የራያ ተወላጆች ሰልፍ የትግራይ ሕዝብን አንድነትን ለማዳከም በሚፈልጉ ሀይሎች የተጠነሰሰ ነው በማለት ተቀባይነት እንደሌለው ገልጿል።

➡️ https://t.co/tdym50EL71

ከላይ ባለሁ ሊንክ ሙሉውን ማንበብ ይችላሉ።
©Tigray C.A.Bureau
@YeneTube @Fikerassefa
#የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳደር ዶ/ር #ደብረፅዮን ገብረሚካኤል #በኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያሥ አፈወርቂ በተደረገላቸው የጥሪ ግብዣን መሰረት በማድረግ በሚቀጥሉት ሳምንት ወደ አስመራ ይጓዛሉ።

ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በአስመራ ጉዞአቸው በኤርትራ እና በትግራይ ህዝብ መሀል ያለውን ወንድማዊ ትስስሩን የበለጠ ለማጠናከር ከኢሳያስ ኣፈወርቂ ጋር በሰፊው ይመካከራሉ።

📌ሼር ያድርጉ!!
©ዋልታ ቴሌቨዠን
@YeneTube @Fikerassefa
#በኤርትራ ለዓመታት የትጥቅ ትግል ለመድረግ ሲንቀሳቀስ የነበረው #የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ሁለት ሺህ ያህል ታጣቂዎች ወደ ሀገር ቤት ተመለሱ።

ወታደሮቹ በጉዞ ላይ እንዳሉ በደረሰ የመኪና አደጋ ቢያንስ ሶስት ወታደሮች ሲሞቱ በርከት ያሉ ቆስለዋል።

ወደ ዛለምበሳ የሚያመራ ወታደሮቹ የተሳፈሩበት የጭነት መኪና በመገልበጡ አደጋው መድረሱን እማኞች ተናግረዋል። ትህዴን በኤርትራ ከፍተኛ ቁጥር ካላቸው ታጣቂ ቡድኖች #አንዱ ነው።

ድርጅቱ ወደ ሀገር ቤት የተመለሰው ከመንግስት ጋር ባደረገው ድርድር በሰላማዊ ትግል ለመሳተፍ በመወሰኑ ነው።
ቀሪ ወታደሮችም በቀጣዮቹ ቀናት #ይመለሳሉ
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27
#የትግራይ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዘመን 13 መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው #ዕለት ይጀምራል።

የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ በ12ኛ መደበኛ ጉባዔ የነበረውን ቃለ ጉባዔ ያፅድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የክልሉን የፈፃሚ እቅድ እንደሚመለከት ነው የተገለፀው።
እንዲሁም ምክር ቤቱ የከፍተኛ ፍርድ ቤትና ዋና ኦዲተር አመታዊ እቅድ በአጀንዳነት መያዙ ተጠቁሟል።

በዚህ ጉባዔ የቀበሌ ገጠር መሬት ዳኝነት፣ስልጣንና ተግባር እና የጠበቃ ምዝገባ፣ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር እንዲሁም ሌሎች አዋጆችና ደንቦችን ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሏል።
ምንጭ ፦ FBC
@yenetube @mycase27
#የትግራይ_ክልል_መንግስት_ለጌዲኦ_ተፈናቃዮች_የ5_ሚሊዮን_ብር ድጋፍ አደረገ።

የትግራይ ክልል መንግስት ለደቡብ ክልል ጌዲኦ ዞን ተፈናቃዮች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡ ክልሉ 25 የጤና ባለሞያዎችን ወደ ስፍራው ለመላክ መወሰኑንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡

የክልሉ ህዝብ እና መንግሥት ድጋፉን ያደረገው ካለው የተጣበበ በጀት ላይ መሆኑን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ድጋፉን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ 15 ዶክተሮች እና 10 ነርሶች በድምሩ 25 የህክምና ባለሞያዎች ቡድን ወደ ስፍራው በመላክ የህክምና ድጋፍ እንዲያደረጉ የክልሉ መንግሥት ውሳኔ ማስተላለፉ ወ/ሮ
ሊያ ካሳ አስታውቀዋል።

ምንጭ፡EBC
@YeneTube @Fikerassefa
#የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ውዝፍ ብድር መኖሩን አስታወቀ።

ውዝፍ ብድሩ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የሚገኝ ሲሆን፥ ይህም ሃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣትና የአጋር ድርጅቶች #ትኩረት_ማነስ ምክንያት ያጋጠመ መሆኑን የክልሉ የእርሻና የገጠር ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አትንኩት መዝገበ ተናግረዋል።

ችግሩን ለመቅረፍም ወጥ የሆነ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት በነፍስ ወከፍ ተበዳሪዎች ዘንድ ተጠያቂነትን ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት 15 ወራት የፖለቲካ እስረኛ የሆኑ #የትግራይ_ተወላጆችን ከእስር ለማስለቀቅ የተቋቋመው ዐለም ዐቀፍ ኮሚቴ የታሳሪዎቹ ጉዳይ በገለልተኛ አካል ይጣራ ሲል ጠይቋል፡፡ #በአዲስ_አበባ ብቻ 300 እስረኞች፤ በቤንሻንጉል ክልልም በሚስጢራዊ ማጎሪያ ቤቶች በርካታ ታሳሪዎች አሉ ማለቱንም አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ በሕገ ወጥ መንገድ የታሰሩና ለፍርድ የቀረቡ የብሄሩ ተወላጆች ሁሉ ባስቸኳይ ይለቀቁ፤ ለጥፋቱም ተጠያቂ አካል ይኑር ሲል አሳስቧል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የቻይናዋ ሃንዥ ግዛት ልዑካን ቡድን ወደ #መቀሌ እንዳይጎዝ መከልከሉን #የትግራይ_መገናኛ_ብዙኻን_ዘግቧል፡፡

ቡድኑ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የተመለሰው በመንግሥት ትዕዛዝ ነው ተብሏል፡፡ የክልሉ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ አብርሃም ተከስተ ወደ አዲስ አበባ ሂደው ከቡድኑ ጋር የማዕድን፣ ቱሪዝምና ግብርና የትብብር ስምምነቶችን ፈርመዋል፡፡

የትኛው የመንግስት አካል እንደከለከለ ግን ገና አለመታወቁን ሃላፊው ተናግረዋል- ብሏል ዘገባው፡፡

Via:- wazema
@Yenetube @Fikerassefa
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 1,600 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል ::

የክልሉ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠርና ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ በልዩ ሁኔታ 1,548 ወንድና 53 ሴት በድምሩ 1,601 ታራሚዎች እንዲፈቱ ወስኗል።

ምንጭ ~ #የትግራይ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
@Yenetube @Fikerassef