YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በኤርትራ ለዓመታት የትጥቅ ትግል ለመድረግ ሲንቀሳቀስ የነበረው #የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ሁለት ሺህ ያህል ታጣቂዎች ወደ ሀገር ቤት ተመለሱ።

ወታደሮቹ በጉዞ ላይ እንዳሉ በደረሰ የመኪና አደጋ ቢያንስ ሶስት ወታደሮች ሲሞቱ በርከት ያሉ ቆስለዋል።

ወደ ዛለምበሳ የሚያመራ ወታደሮቹ የተሳፈሩበት የጭነት መኪና በመገልበጡ አደጋው መድረሱን እማኞች ተናግረዋል። ትህዴን በኤርትራ ከፍተኛ ቁጥር ካላቸው ታጣቂ ቡድኖች #አንዱ ነው።

ድርጅቱ ወደ ሀገር ቤት የተመለሰው ከመንግስት ጋር ባደረገው ድርድር በሰላማዊ ትግል ለመሳተፍ በመወሰኑ ነው።
ቀሪ ወታደሮችም በቀጣዮቹ ቀናት #ይመለሳሉ
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27