YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ ተይዘው የተገኙ የቀበሌ ቤቶች ተለይተው ለችግረኞች ሊተላለፉ ነው

በህገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶች ተለይተው ለችግረኞች እንደሚተላለፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ እንደገለፁት በህገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶችን በሁሉም ክፍለ ከተማ የማጥራት ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናገረዋል፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብቻ በአንድ ሳምንት 150 ቤቶች በህገወጥ መንገድ ተይዘው መገኘታቸውንና ወደከተማ አስተዳደሩ ገቢ መደረጋቸውን ገልፀዋል።

ቤቶቹም በዚህ ሳምንት ለተቸገሩ እና አንገት ማስገቢያ ላጡ ነዋሪዎች እንደሚተላለፉ ም/ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።
ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት
@yenetube @mycase27
⬆️⬆️የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራራች አዲስ አበባ ገቡ

የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ፕሮፌሰር #ብርሃኑ ነጋና አቶ #አንዳርጋቸው ፅጌ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ከእነርሱ በተጨማሪ #ከ250 በላይ የድርጅቱ አባላት ከደቂቃዎች በኋላ አዲስ አበባ #እንደሚገቡ ነው የተገለፀው።

#በአዲስ አበባ ስታዲየምም ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ተገልጿል።
@yenetube @mycase27
#በአዲስ አበባ ፒያሳ፣ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ ፊትለፊት የሚገኘውን #የዳግማዊ ምኒልክ ሐውልት #ለማፍረስ ሞክረዋል የተባሉ ወጣቶች በጸጥታ አስከባሪዎች ተበተኑ፡፡

ከትናንት ጀምሮ ሐውልቱን የማፍረስ ፉከራ ሲያሰሙ ነበሩ የተባሉ የኦነግ ደጋፊዎች ዛሬ ከቀትር በኋላ በቡድን ሆነው ሐውልቱ ወዳለበት ሥፍራ ሲያመሩ በፖሊስና መከላከያ ሠራዊት በአስለቃሽ ጋዝ እንዲበተኑ ተደርገዋል፡፡

#በንብረትም ሆነ በሰው ላይ ጉዳት መድረስ አለመድረሱ የታወቀ ነገር የለም፡፡

📌ወደ ማዘጋጃ ቤቱ የሚያመሩ መንገዶች በሁሉም አቅጣጫ በጸጥታ ኃይሎች በመዘጋታቸው ጋዜጠኞች ወደ አካባቢው ገብተው ሁኔታውን መቃኘት አልቻሉም ።
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27
#በአዲስ አበባ ለዛሬ የተጠራ ምንም ዓይነት ሰልፍ አለመኖሩን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

ኮሚሽኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው፥ ህብረተሰቡ በመዲናዋ ምንም ዓይነት የተጠራ ሰልፍ አለመኖሩን አውቆ መደበኛ የእለት ተእለት እንቅስቃሴውን እንዲያከናውን አሳስቧል።

መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ለረቡዕ በአዲስ አበባ የተጠራ ሰልፍ አለ በሚል ያወጡት መረጃ ሙሉ በሙሉ የተሳሳተም ነው ብሏል።
©fbc
@yenetube @mycase27
Update #ብራዩ⬆️

#በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በተፈጠረ ግጭት ተፈናቅለው በጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ከነበሩ 15 ሺህ 86 ያህል ዜጎች መካከል 1 ሺህ 786 ያህል ወደመጡበት የመኖሪያ ቀያቸው መመለሳቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

📌የከተማ አስተዳደሩ እንዳስታወቀው፣ በመጭው ሰኞ ተፈናቃዮች የተጠለሉባቸው 9 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን መቀበል ስለሚጀምሩ፣ በትምህርት ቤቶች ተጠልለው የሚገኙ 9,000 ዜጎችን ወደ ሌላ ቦታ በማዘዋወር ላይ ይገኛል።

📌አስተዳደሩ ለተፈናቃዮቹ እስካሆን ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጉንም አስታውቋል።

@YeneTube @Fikerassefa
#በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ዘጠኝ አባላትን ያቀፈ #የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ተሰይሟል።

በዚህም መሰረት
1, ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከአ/አ ዩኒቨርሲቲ
2, ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ከአ/አ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ
3, ዶ/ር ኢ/ር ብርሀኑ አሰፋ ከአ/አ ዩኒቨርሲቲ
4, ዶ/ር ታቦር ገ/መድህን ከአ/አ ትምህርት ቢሮ
5, ዶ/ር ፍሬህይወት ገ/ህይወት ከ አ/አ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ
6, ዶ/ር ቶላ በሪሶ ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ
7, ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ ከአ/አ ጤና ቢሮ
8, ወ/ሮ መስከረም ታምሩ ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር
9, አቶ ዮሀንስ ምትኩ ከአ/አ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ሆነዋል።
ዶ/ር ፍሬህይወት ገ/ህይወት የቦርዱ ሰብሳቢ እና ዶ/ር ኢ/ር ብርሀኑ አሰፋ ም/ ሰብሳቢ ሆነው ተሰይመዋል።

ምንጭ ፦የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ ቤት
@yenetube @mycase27
#በአዲስ አበባ ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውለው በጦላይ ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ 1 ሺህ 174 ወጣቶች ዛሬ ከእስር #ተለቀዋል

ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩት 1 ሺህ 174 ወጣቶች ዛሬ ረፋድ ላይ ከእስር መለቀቃቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው፥ ዛሬ ማለዳ ላይ የጋራ ውይይት ከተደረገ በኋላ ተጠርጠጣሪዎቹን ወደ አዲስ አበባ የሚመልሱ ተሽከርካሪዎችን በማቀረብ እንዲለቀቁ ተደርጓል ብለዋል።

ወጣቶቹ ከመስከረም 2 እስከ መስከረም 8 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆኑ፥ በቆይታቸውም የተለያዩዩ ስልጠናዎችን ሲወስዱ መቆየታቸው ተመልክቷል።

በዚህም መሰረት ወጣቶቹ በጦላይ ለአንድ ወር እራስን ከወንጀል ስለማራቅ እና ተያያዠ ስልጠናዎችን ለመስጠት የተያዘውን የጊዜ ሰሌዳ በማጠናቀቃቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ የማጓጓዝ ስራ ተጀምሯል ብለዋል።
©fbc
@yenetube @mycase27
እንዲሁም ትላንት - #በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ #አቃቂ_ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 9፣ በኮዬ ፈጬ አደባባይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ መከፋፈላቸውን በመቃወም ሰልፍ ተደረገ። ሰልፈኞች የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከመሬታቸው ለተፈናቀሉ #አርሶ_አደሮች ይሰጡ ሲሉ ጠይቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
⬆️"እኛ #በአዲስ_አበባ የምንገኝ የግል #የህክምና ተማሪ እና #ዶክተሮች ነን በአሁን ሰአት #የስራም ሆነ የኢንተርንሺፕ እድል ባለማግኘታችን ፋና አካባቢ #ድምፃችንን እያሰማን እንገኛለን!"

ፎቶ: R-Yenetube
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት 15 ወራት የፖለቲካ እስረኛ የሆኑ #የትግራይ_ተወላጆችን ከእስር ለማስለቀቅ የተቋቋመው ዐለም ዐቀፍ ኮሚቴ የታሳሪዎቹ ጉዳይ በገለልተኛ አካል ይጣራ ሲል ጠይቋል፡፡ #በአዲስ_አበባ ብቻ 300 እስረኞች፤ በቤንሻንጉል ክልልም በሚስጢራዊ ማጎሪያ ቤቶች በርካታ ታሳሪዎች አሉ ማለቱንም አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ በሕገ ወጥ መንገድ የታሰሩና ለፍርድ የቀረቡ የብሄሩ ተወላጆች ሁሉ ባስቸኳይ ይለቀቁ፤ ለጥፋቱም ተጠያቂ አካል ይኑር ሲል አሳስቧል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa