YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳደር ዶ/ር #ደብረፅዮን ገብረሚካኤል #በኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያሥ አፈወርቂ በተደረገላቸው የጥሪ ግብዣን መሰረት በማድረግ በሚቀጥሉት ሳምንት ወደ አስመራ ይጓዛሉ።

ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በአስመራ ጉዞአቸው በኤርትራ እና በትግራይ ህዝብ መሀል ያለውን ወንድማዊ ትስስሩን የበለጠ ለማጠናከር ከኢሳያስ ኣፈወርቂ ጋር በሰፊው ይመካከራሉ።

📌ሼር ያድርጉ!!
©ዋልታ ቴሌቨዠን
@YeneTube @Fikerassefa
⬆️⬆️በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የመማር ማስተማሩ ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳር ዶክተር #ደብረፅዮን_ገብረሚካኤል አስታወቁ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች መማር ማስተማሩን ሰለማዊ ለማድረግ የተደረገውን ዝግጅት በተመለከተ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ትምህርት የእውቀት፣ ቴክኖሎጂ፣ ሳይንስ እንዲሁም የሀገሪቱ ኢኮኖሚና ፓለቲካ መሪዎች የሚፈልቁበት በመሆኑ የመማር ማስተማሩ ሂደት ሰላማዊና የተረጋጋ እንዲሆን ይጠበቃል ብለዋል በመግለጫቸው።

የተረጋጋ ሁኔታ ከሌለ ተማሪዎች በአግባቡ መማር እንደማይችሉ የገለፁት ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ፥ ለዚህም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩንቨርስቲዎችና በክልሉ መንግስት ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። ከዚህ በፊት ባሉት ዓመታት በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የመማር ማስተማሩን የሚያውኩ ሁኔታዎች ብዙም አለመስተዋላቸውን ተናግረዋል።

ሆኖም ችግሮች አይከሰቱም ተብሎ ስለማይታለፍ እንደ መንግስት ተቋማቱ ሰላማዊ እንዲሆኑ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎል ሲሉ አስታውቀዋል። ተማሪዎችም ችግሮች ካሉ ተወያይተውና ተነጋግረው እንደሚፈቱ እምነቴ ነው በማለት ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።

ምንጭ: FBC
@Yenetube @Fikerassefa
የትግራይ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር #ደብረፅዮን በአላማጣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር እየተወያዩ ነው::
በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች የተገኙበት ውይይት #በአላማጣ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
@yenetube @mycase27