YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በቀጣዩ ሳምንት የጣልያን ጠቅላይ ሚንስትር #ጁሴፒ ኮንቴ ኢትዮጵያና ኤርትራን ይጎበኛሉ።

የጉብኝቱ አላማ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተደረሰውን የሰላም #ስምምነት ለመደገፍ ነው ተብሏል።
©wazema
@yenetube @mycase27
የተጠናከረ የአቶ ዳውድ ኢብሳ ለዋልታ ቲቪ የተናገሩት ቅንጫቢ⤵️

📌"ኦነግ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ከኢትዮዽያ መንግስት ጋር ትጥቁን #ፈቶ #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ነው ተብሎ የሚነገረው መሰረተ ቢስ ወሬ ነው"

📌"እኛ ትጥቅ እንድንፈታ የተስማማንበት #ስምምነት_የለም። የታጠቀው ኣአካል ትጥቅ ይዞ እያለ እኛ ትጥቅ የምንፈታበት ምክን ያት የለም።"

📌"ትጥቅ መፍታት የሚባል #sensitivity ጥያቄ ነው። ትጥቅ ፈቱ መባልም አንፈልግም። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣው አንዱ ትጥቅ የሚፈታ አንዱ ትጥቅ የሚያስፈታ ይመስላል። የሀገሪቱ ሰላም እንዲጠበቅ ኦነግ ያለው ሚና ምን እንደሚሆን ነው የተስማማነው።"

📌አቶ ዳውድ #ሰኔ_16 በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ በተደረገው የግድያ ሙከራ ድርጅታቸው እንዳልተሳተፈ ገልፀዋል። #በቡራዩና_በአዲስ አበባ በተፈጠሩ ግጭቶችም ኦነግ #አለመሳተፉን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

📌#በቤኒሻንጉል#በወለጋና #በከፋ በተፈጠሩ ግጭቶች #ኦነግ መሳተፉንና አለመሳተፉን ለማረጋገጥ ማጣራት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

📌አቶ ዳውድ በበደኖና በአርባ ጉጉ #በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ #በገለልተኛ አካል እንዲጣራ የኦነግ ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል።
@YeneTube @Fikerassefa
#update የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (#ኦብነግ) ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ስለተደረሰው #ስምምነት የሰጠው አስተያየት የስምምነቱን መንፈስ የሚያንፀባርቅ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ መንግስት #አስታወቀ

ድርድሩን በቅርበት የሚያውቁና ስማቸውን ይፋዊ መግለጫ እስኪሰጥ የሸሸጉ የመንግስት ተወካይ #ለዋዜማ እንደተናገሩት ስምምነቱ ኦብነግ ወደሰላማዊ ትግል እንዲመለስና ጥያቄዎቹን በጋራ በሚቋቋም ኮሚቴ እያቀረበ እንዲፈታ ከሚል ውጪ ትርጉም ያለው አልነበረም።

በኦብነግ በኩል የሚሰጠው አስተያየት ለፕሮፓጋንዳ #ፍጆታ ካልሆነ በስተቀር የውይይቱን መንፈስ አያሳይም ብለዋል ባለስልጣኑ።

ኦብነግ መንግስት የእስከ መገንጠል መብታችንን በህዝበ ውሳኔ እንድናረጋግጥ ተስማምቷል ሲል ለቢቢሲ መግለጫ ሰጥቶ #ነበረ

ቢቢሲ ዘግይቶ ባወጣው #ማረሚያ " ቀደም ሲል በወጣው ዘገባ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ጋር ካደረገው ተከታታይ ውይይት በኋላ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ተስማምቷል ተብሎ የተፃፈው #ስህተት ነው" ብሏል::
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት #ሳህለወርቅ ዘውዴ ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ ተጓዙ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ወደ ደቡብ ሱዳን ያቀኑት ባለፈው መስከረም በአዲስ አበባ የተፈረመውን የደቡብ ሱዳን የሰላም #ስምምነት ለማብሰር በተዘጋጀው ስነስርዓት ላይ ለመሳተፍ ነው።
@yenetube @mycase27