YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በቤንሻንጉል ክልል በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ70 ሺህ በላይ መድረሱን #የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።

ችግሩ ተባብሶ ይቀጥላል የሚል ስጋት እንዳለው የገለፀው ድርጅቱ አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

አምነስቲ ከ40 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ሲናገር ነዋሪዎች ግን የሟቾች ቁጥር ከአንድ መቶ በላይ ነው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶችም ተቃጥለዋል ብለዋል።

ኦነግ በግጭቱ ውስጥ እንዳለበት በርካታ መረጃዎች እየወጡ ነው። ድርጅቱ ግን የግጭቱ ተሳታፊ አለመሆኑን ተናግሯል። ግጭቱ የተጀመረው አራት የቤንሻንጉል ክልል ባለስልጣናት #አጎራባች ኦሮሚያ ውስጥ ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸው ነው።

በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው ኦሮምኛና አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን "#መጤ" ተብለው የጥቃት ዒላማ ተደርገዋል።
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27
#በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ በደረሱ ጥቃቶች #44 ሰዎች መገደላቸውን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት #አስታወቀ

የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችልም ገልጿል።

በሁለቱ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች በአካባቢው አሁንም ጥቃት አለመቆሙን እና ቤቶች እየተቃጠሉ እንዳሉ ለDW እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ኃላፊ አቶ ዘላለም ጃለታ ለ«DW» እንደተናገሩት በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ላይ በደረሰ ጥቃት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ 16 ሰዎች ከኦሮሚያ ደግሞ 28 ሰዎች መገደላቸውን #ተናግረዋል

ባለፈው ረቡዕ መስከረም 16 አራት የካማሺ ዞን አመራሮች መገደላቸውን ተከትሎ በአካባቢው በተቀሰቀሰ ግጭት ምክንያት በክልላቸው ብቻ 20 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልል ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በሰሞኑ ግጭት 70 ሺህ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

ይህንን መረጃ መመልከታቸውን የተናገሩት አቶ ዘላለም ሰዎቹ የተፈናቀሉት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል #ብቻ ሳይሆን በወሰን አካባቢ ካሉ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ጭምር ነው ብለዋል።

በሰሞኑ ግጭት ቀያቸውን ለቅቀው “ወደ በረሃ መሸሻቸውን” የሚናገሩ አንድ ተፈናቃይ በአካባቢያቸው አሁንም ግጭቱ መቀጠሉን ለDW ተናግረዋል።

ከነቀምት ከተማ 42 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለች አንገር በተሰኘች አነስተኛ መንደር ነዋሪ እንደሆኑ የተናገሩት አቶ ኤርሚያስ አበራ ከአምስት ቀን በፊት የተኩስ #ድምጽ ሲሰሙ እና ቤቶች መቃጠል ሲጀምሩ ህይወታቸውን ለማትረፍ መሸሻቸውን ገልጸዋል። በአካባቢያቸው ከስምንት እስከ 10 ሰው እንደሞተ መስማታቸውን እና ደብዛቸው እስካሁን ያልታወቀ እንዳለም ጠቁመዋል።

በመኖሪያ መንደራቸው ያለው ሁኔታ መሻሻሉን ለማየት ዛሬ ወደ ስፍራው የሄዱት አቶ አበራ ቤቶች ሲቃጠሉ እንደተመለከቱ የዓይን እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። ። በአካባቢው የመከላከያ ሰራዊት ቢሰማራም ጥቃቱ አለመቆሙንም አስረድተዋል።

በአንገር እና አካባቢው ያለው ጥቃት አሁንም መቀጠሉን ያረጋገጡት አቶ ዘላለም ጉዳዩ ከክልሉ አቅም በላይ በመሆኑ ተጨማሪ የመከላከያ ኃይል ወደ ስፍራው እንዲገባ መጠየቁን #ገልጸዋል
ምንጭ ፦ DW
@yenetube @mycase27
#Benishagul #በቤንሻንጉል ጎሙዝ ክልልና በኦሮምያ አጎራባች አካባቢዎች የተፈጠረው ግጭት አሁንም #አልቆመም

የተፈናቃዮች ቁጥር #ከዕለት ወደ ዕለት #እየጨመረ መሆኑንና አሁን ከ85 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የረድዔት ሰራተኞች እየተናገሩ ነው።

መንግስት ጣልቃ ገብቶ ለማረጋጋት እየሞከረ ቢሆንም በገጠራማና ሰሞኑን ሰላም ከነበሩ አካባቢዎች ነዋሪዎች እየተፈናቀሉ ነው።

ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@Yenetube @Mycase27
#በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ሰሞኑን በተፈጸመ ጥቃት 74 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ90 ሺህ በላይ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) ዛሬ አስታወቀ። ከሟቾቹ ውስጥ አስራ ዘጠኙ ፖሊሶች ናቸው ብሏል
©DW
@YeneTube @Fikerassefa