YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት #ግርማ ወልደጊዮርጊስ ስም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ቤት በቡታ ጅራ ከተማ ሊገነባ መሆኑን የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች #ገልጸዋል

95 በመቶ የሚሆኑትን ተማሪዎች በነፃ ተቀብሎ ያስተምራል።

ትናንት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ስም ሊገነባ መሆኑን ይፋ ካደረጉት አስተባባሪዎች መካከል የገቢ ማሰባሰብ ስራውን የሚመራው አቶ ብሩክ ዳንኤል እንደገለፀው፤ ግንባታው በጎ ፍቃደኛ በሆኑት ባለሀብት አቶ አህመድ ሁሴን ሃሳብ ጠንሳሽነት የሚጀመር ነው።

ትምህርት ቤቱን ለመገንባት 10 ሚሊዮን ብር የመነሻ ካፒታል በባለሀብቱ የተመደበ ሲሆን ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ 120 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ጠቁሟል።

የፕሮጀክቱ ጠንሳሽ እና ባለቤት የሆኑት አቶ አህመድ ሁሴን ትምህርት ቤቱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ እውቀትን ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ከማስጨበጡ ባሻገር ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ አኩሪ ባህል፣ ሰላም እና አንድነት ሁሉንም ዜጎች ያለምንም ልዩነት ያስተምራል። የትምህርት ቤቱ ዋና ዓላማም ኢትዮጵያዊነትን በአዲሱ ትውልድ ማስረፅ መሆኑን ተናግረዋል።

የተቀደሰ ዓላማ ባለው ፕሮጀክት ላይ ኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች በቀናነት እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን ያቀረቡት አቶ አህመድ፤ ትምህርት ቤቱን ገንብቶ ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ወጪ ለማሟላት በአገር ውስጥ እና በውጪ አገራት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።

ትምህርት ቤቱ በ10 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን መማሪያ ክፍሎች፣ ዲጂታል ቤተመፃህፍት፣ በዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ የጥናት ማዕከል ይኖረዋል።

📌በተጨማሪ አረጋዊያንን የሚረዳ ማዕከል እንደሚካተትበት ለመረዳት ችለናል።

ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ፕሬሥ ድርጅት
@yenetube @mycase27
#በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ በደረሱ ጥቃቶች #44 ሰዎች መገደላቸውን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት #አስታወቀ

የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችልም ገልጿል።

በሁለቱ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች በአካባቢው አሁንም ጥቃት አለመቆሙን እና ቤቶች እየተቃጠሉ እንዳሉ ለDW እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ኃላፊ አቶ ዘላለም ጃለታ ለ«DW» እንደተናገሩት በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ላይ በደረሰ ጥቃት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ 16 ሰዎች ከኦሮሚያ ደግሞ 28 ሰዎች መገደላቸውን #ተናግረዋል

ባለፈው ረቡዕ መስከረም 16 አራት የካማሺ ዞን አመራሮች መገደላቸውን ተከትሎ በአካባቢው በተቀሰቀሰ ግጭት ምክንያት በክልላቸው ብቻ 20 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልል ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በሰሞኑ ግጭት 70 ሺህ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

ይህንን መረጃ መመልከታቸውን የተናገሩት አቶ ዘላለም ሰዎቹ የተፈናቀሉት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል #ብቻ ሳይሆን በወሰን አካባቢ ካሉ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ጭምር ነው ብለዋል።

በሰሞኑ ግጭት ቀያቸውን ለቅቀው “ወደ በረሃ መሸሻቸውን” የሚናገሩ አንድ ተፈናቃይ በአካባቢያቸው አሁንም ግጭቱ መቀጠሉን ለDW ተናግረዋል።

ከነቀምት ከተማ 42 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለች አንገር በተሰኘች አነስተኛ መንደር ነዋሪ እንደሆኑ የተናገሩት አቶ ኤርሚያስ አበራ ከአምስት ቀን በፊት የተኩስ #ድምጽ ሲሰሙ እና ቤቶች መቃጠል ሲጀምሩ ህይወታቸውን ለማትረፍ መሸሻቸውን ገልጸዋል። በአካባቢያቸው ከስምንት እስከ 10 ሰው እንደሞተ መስማታቸውን እና ደብዛቸው እስካሁን ያልታወቀ እንዳለም ጠቁመዋል።

በመኖሪያ መንደራቸው ያለው ሁኔታ መሻሻሉን ለማየት ዛሬ ወደ ስፍራው የሄዱት አቶ አበራ ቤቶች ሲቃጠሉ እንደተመለከቱ የዓይን እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። ። በአካባቢው የመከላከያ ሰራዊት ቢሰማራም ጥቃቱ አለመቆሙንም አስረድተዋል።

በአንገር እና አካባቢው ያለው ጥቃት አሁንም መቀጠሉን ያረጋገጡት አቶ ዘላለም ጉዳዩ ከክልሉ አቅም በላይ በመሆኑ ተጨማሪ የመከላከያ ኃይል ወደ ስፍራው እንዲገባ መጠየቁን #ገልጸዋል
ምንጭ ፦ DW
@yenetube @mycase27
11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ያለምንም የጸጥታ ችግር #ተጠናቋል-ፖሊስ

11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ያለምንም የጸጥታ ችግር መጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ዘይኑ ጀማል በሰጡት መግለጫ ለጉባዔው በስኬት መጠናቀቅ የሀዋሳ ህዝብ፣ የፌደራልና የክልል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ የብሄራዊ ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ወጣቶችንም ላደረጉት ትብብር ምስጋና #አቅርበዋል፡፡

በደቡብ ክልል #በሸካ ዞንና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ካሚሺ ዞን ያጋጠመውን የጸጥታ ችግር መከላከያና ፖሊስ ወደ ቦታው ገብቶ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ኮሚሽነር ዘይኑ #ገልጸዋል፡፡
©ebc
@yenetube @mycase27