YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ህወሓትን በመቃወም የትጥቅ ትግል ውስጥ የገቡት ብርጋዴር ጄነራል ገብረእግዚአብሄር በየነ፤ በ #አፋር እና በ #ትግራይ ክልሎች ውስጥ “አራት ክፍለ ጦር” ያለው የራሳቸውን ሠራዊት ማደራጀታቸውን ተናገሩ።

#ከትግራይ ኃይሎች በመለየት የራሳቸውን ሠራዊት እየገነቡ መሆናቸውን የጠቀሱት ብርጋዴር ጄነራል ገብረእግዚአብሄር፤ "አዲስ ነገር ለመፍጠር" ወደ በረሃ መውደረዳቸውን እና "ከፓርቲ ነጻ የሆነ ኃይል ለመፍጠር፣... ፓርቲ የማያዝዘው ሠራዊት ለመፍጠር" እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልፀዋል።

ጄነራሉ ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ ከትግራይ ሠራዊት አመራሮች ጋር የተለያዩት ከጥር 15/20017 ዓ.ም. ጀምሮ መሆኑን አስረድተዋል።

የትግራይ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ጥር 15 ተሰብስበው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ጊዜያዊ አስተዳደር ሲያወግዙ፣ ተቃውመው ስብሰባውን ረግጠው ከወጡ አመራሮች መካከል አንዱ ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ ናቸው።

ይህንንም ተከትሎ የሠራዊቱ አመራሮች ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነን እና ሌሎች የሠራዊቱን ውሳኔ የተቃወሙትን ማገዳቸው ይታወሳል።

ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር "ከፓርቲ ጋር ተጣብቆ ማህተም የሚነጥቅ፣ ከፓርቲ ጋር ተጣብቆ የሚሾም እና የሚሽር ኃይል ለወጣቱ ትውልድ ትተን መሄድ አንፈልግም። ወገንተኛ ያልሆነ ፍትሃዊ ኃይል ለመፍጠር እንጂ፣ የሆነ ፓርቲ አሽከርነት የለንም፤ አናደርገውም" ብለዋል።

ለተቃውሟቸው ጠመንጃ ማንሳትን መምረጣቸው በጦርነት ውስጥ የቆየውን የትግራይ ክልል ዳግም ወደ ግጭት አዙሪት አይከተውም ወይ ተብለው የተጠየቁት ጄነራሉ "እኔ ኢንተርናሽናል ጄነራል ነኝ። ይህንን ሆኜ የህወሓት ሚሊሻ መሆን አልፈልግም። ህወሓት ፓርቲያችን ነው የሚሉ የእርሱን ሚሊሻ እንደሆኑ ነው የሚቆጥረው። ሚሊሻነትን ደግሞ አልቀበልም" ብለዋል።

@Yenetube
43😁15👀1